ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ለምን_ነው_የተውኸኝ ?
.
በሰደድ እሳት ውስጥ እንደ መራመዴ
እንዴት አይሞቀኝም? ይቅርና መንደዴ፣
ግግር በረዶ ላይ በባዶ እግሬ ቆሜ
ለምን ያተኩሳል? ሥጋዬና ደሜ፣
ሁሉን እንደ ጉሊት ክበህ ስታፈርሰው
በምን ሃጥያቴ ነው የነጠልኸኝ ከሰው?
ምነው እኔ ብቻ? ያለሁ በእርጋታ
ልድን እወዳለሁ ማረኝ የኔ ጌታ!!!
-------------------//--------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
#ለምን_እንዳትይኝ

የሚያምር ስብእና
እንደ ውብ አበባ የሚማርክ ገላ
የሰው ውሃ ልኩ
ሁለመናሽ ሙሉ ሌላን የሚያስጠላ
አንቺን ባየሁ ቁጥር
ውስጤ ቢከብደውም ራሴን ተጠይፌ
ስተክዝ ውላለሁ
አይንሽን ለማየት ዘወትር ከደጃፌ
ግና ምንም ያህል
ከራሴ አስበልጬ አንቺን ብወድሽም
ካየሁሽ በቂ ነው
ሺ ዘመን ላፍቅርሽ እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሳላይሽ አልደር
አይምሽብኝ ቀኑ አይንጋ ለሊቱ
እጆችሽን ይዤ
ዶፍ በላዬ ውረድ አትውጣ ጠሃይቱ
አየሽልኝ አይደል
የመውደዴን ልኬት የፍቅሬን መስፈርያ
ሕይወቴ የምልሽ
ያድርግሽ የምለው የሴት መጀመሪያ
እኔ አንቺን ያወቁት
ትላንት ወይም ዛሬ ቀኑን ባልነግርሽም
ስወድሽ ስወድሽ
የድሜ ጀምበር ትጥለቅ አኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሳላገኝሽ በፊት
ድምጽሽን ሳልሰማ ሳትሆኝ አጠገቤ
አቅሜን አውቀዋለሁ
ምግብ እያላመጥኩ ይጠናል ረሃቤ
ብቻ እኔ አላውቀውም
ምንሽን እንደሆን የወደደው ነፍሴ
ከአጠገቤ አትራቂ
ያሻሽን አድርጊኝ አልጣሽ ከራሴ
ይሄን ሁሉ ብዬ
እያሞጋገስኩኝ አለሜ ብልሽም
ለፍቅሬ አይመጥንም
ምን አባቴ ላድርግ እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ገንዘብ ሃብት ዝና
አለማዊ ነገር ካንቺ ዘንድ ሳይጠፋ
ነፍስሽን የሰጠሽ
ታትረሽ የምትኖሪ በፈጣሪሽ ተስፋ
ማንም ያልተቸረው
እውቀት እና ጥበብ ከአካልሽ ውበት ጋር
ልብሽ ፍቅር ያዘንባል
ጌታ ባረፈበት በመስቀሉ ችንካር
ይሄ ቢሆን እንኳን
በመውደዴ መስፈርት ንግስት ብትሆኚም
ሳከብርሽ ልኑረው
አንቺ ብትወጂኝም እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሰው በዙሪያሽ ሳለ
በሄድሽበት ሚሄድ አጃቢሽ ቢበዛ
ከራሱ አስበልጦ
ስላንቺ ቢለፍፍ ወሬውን ቢነዛ
ፍቅርን የሚያስተምር
ሺ መፅሃፍ ቢገለጥ ቢኖረው ሰባኪ
እኔን አይገባኝም
ቃላት አይገልፅሽም አንቺ ተባለኪ
ጉዳዬ አይደለም
ስጋዬ እና ነፍሴ አንቺን ቢያፈቅሩሽም
ብቻ ከአቅሜ በላይ
ሳፈቅርሽ ልኑረው እኔ አላገባሽም ፡፡
ለምን እንዳትይኝ !

#እንደራሴ

(Kibrom G Mariam)


@getem
@getem
@getem
👍1
#ከፋኝ

ንቄም ከፋኝ ስቄም ከፋኝ
አክብሬ ስናቅ ደስታ ከዳኝ
እውነት አጣኝ
በገባኝ ልክ እየኖርኩ በሰማውት ልክ ሳላወራ
የሌለኝን የለኝ ብዬ በያዝኩትም ሳልኩራራ

ጥርሴን ወገግ
አይኔን ገርበብ
ለሚያወሩት እኔ እያፈርኩ
ጆሮዬን ግን ክፍት እያረኩ
ሳላምንበት እሺ ብዬ ሳልረዳ ብቀበልም
ውስጥ ውስጤ ግን አይገኝም

#ለምን?????
ለምን ላለኝ ለምን ጥሩ
ከፋኝ ያልኩት ከጅምሩ
ማጣት አይደለም ሚስጥሩ
በኔ አይደለም ክፍት ያለኝ
በኔ አይደለም መረበሼ
ይልቅስ እማዝነው ምድሪቱ ላይ ለሰፈረው
ጥዋት ማታ ለሚበክነው
ላሁን ዘመን ላሁን ሰው ነው።

ሀ በል ሲባል ፊደል ትቶ አፉን ሚከፍት
ለ በል ሲባል ሰውን ረግጦ ለኔ ለኔ እሚጋፋ
ለበላዩ አሸርግዶ በታቹ ላይ ሚደነፋ

እኔስ ማዝነው ላሁን ዘመን ለዚህ ሰዎ ነው።

ግና የኔ ማዘን ምን ሊጠቅም
ለዚህ ሁሉ መልስ አይሆንም
እናም በማስበው ባቅሜ ልክ
የገባኝን መፍትሄ ልስጥ.......

ሀ ተብሎ ምን ቢበላ ቢጠገብም
ርሀብን አያስቀርም
ለኔ ለኔ ምን ቢባልም
ከሰው በላይ የራስ ስጋ የራስ ምቾት ቢወደድም
በቀን መሀል ለሚመጣው ለክፉ ቀን ስንቅ አይሆንም
ስለዚህ......
ሀ በሉ ሲባል ከ ሀ እስከ ሆ
ለ በሉ ሲባል ከ ለ እስከ ሎ
እንደያኔው ህፃንነት
ፊደል ጠርተን ተማምረን
እንለፋት እቺን ዘመን
ምህረቱን እስኪያድለን
ቸርነትን እስኪቸረን። 🙏🙏🙏🙏

@getem
@getem

#nata
👍1
#ለምን_ነው_የተውኸኝ ?
[በርናባስ ከበደ]
-
በሰደድ እሳት ውስጥ : እንደ መራመዴ
እንዴት አይሞቀኝም? ይቅርና መንደዴ።
ግግር በረዶ ላይ : በባዶ እግሬ ቆሜ
ለምን ያተኩሳል? ሥጋዬ እና ደሜ ።
ሁሉም በወረፋው : ወር ተራ ሲደርሰው
እንደ ጉሊት ሸቀጥ ፡ ክበህ ስታፈርሰው
በምን ሃጥያቴ ነው : የነጠልኸኝ ከሰው??
ምነው እኔ ብቻ? ያለሁ በእርጋታ
ልድን እወዳለሁ : ማረኝ የኔ ጌታ።
____________________________

@getem
@getem
@getem
👍1
ለውብ ቀን!
💚

#ለምን ዛሬ ውብ ቀናችንን ለየት አናረገውም.....#ቅኔ ያለው ትውልድ የሚል እዚሁ ቴሌግራም መንደር የሚገኝ ቻናል እና የመወያያ ግሩፕ አለ .....ሁለቱም ጋር ብትገቡ በብዙ ታተርፋላቹ ነብስ ያላቸው ሀሳቦች ይነሱበታል.....እናም ለውይይት በሚነሱ ሀሳቦች ላይ እኔም መሳተፍ እፈልጋለው ፣ እኔም የዚህ ቤተሰብ አባል መሆን እሻለው ፣ ማን እንደዚህ አይነት እድል ገጥሞት እንቢ ይላል .....ይኼ አይደለም ወይ የተጠፋው የምትሉ ከሆነ ደስ ደስ እያላቸው ያስተናግዳሉ።

# የናንተን ምርጥ ምርጥ ሀሳቦች ይፈልጋሉ እና አካፍሏቸው።

#ከዚህ በታች ወደ ቴሌግራም ቤቱ የሚያደርሰውን ሊንክ ጀባ እላለሁኝ....መሄድና መግባት ለፈለገ ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው.....

ውብ ቀን!💚
👇👇👇👇
#ለምን ነው ? ስትይኝ.. .

።።።።።።

ፍቅርህ ቀዘቀዘ ... ሆነብኝ በረዶ

መውደድህ ጠለሸ.. . ከእሳት ዳር ተማግዶ

ዛሬ ግጥም ፅፈህ.. .ነፍሴን ላታሞቃት

ውበቴን ሸምነህ ... ኩታ አርገህ ላትለብሳት

ወረት ወርሶህ ጠፋህ ታጠፈች ብዕርህ

ድሮ የነበረ...

 ዜማህ ስድ ሆኖ ... ደረቀ ዘፈንህ

ብለሽ አትበይኝ! ከፍቶሽ አትቆዝሚ

ይልቅ ጆሮ ሰጥተሽ ምክንያቴን ስሚ...

እቴ! 

ድሮ.. .

ያንቺን ድምፅ መስማት ዜማ ነው የመቅደስ

ከንፈርሽን  መቅመስ ጣፋጭ እንደ በለስ 

ካንቺ ጋር መራመድ አብሮ መንገድ መውጣት

ከነፍስ አልፎ ለከርስ ... ይሆነኛል ራት 

ብዬ የጣፍኩልሽ ጊዜን አስታውሼ

ውበትሽን በስንኝ በቃላት ከሽኜ 

መሆኑን ሳስታውስ የዛን ደግ ዘመን 

ከተቀመጥሁበት ብርኩማ ላይ ሳለሁ ይወርሰኛል ሀዘን ...

ዛሬ !

እንደ መቅደስ ዜማ ጣፍጦኝ የነበረው...

የሚያባብል ድምፅሽ.. .

ዛሬ እንዳይሰማኝ ተኩስ አለ በደጅሽ!

እንዴት ግጥም ልፃፍ ስለ አይንሽ ጉልላት?

ከስጋዬ የነሳ ወገኔ ተቀጥፎ ወርዶበታል መዓት!

ከየት ይምጣ ስንኝ የቃላት ቋጠሮ?

ሁሉ ወዝ አልባ ነው አይደል እንደድሮ!

ዛሬ ...

ብዕሬን ሳነሳ ላንቺ ውበት ምስጋና

ሰቆቃን ያዘለ ይደርሰኛል ዜና 

እከሊት ሞተች ነው ... እከሌ ታሰረ 

በዚህ ሰንኮፍ መሀል ግጥም ላንቺ ቀረ

ምኔ ነው ከንፈርሽ ? ምኔ ነው ያንቺ ጣዕም?

ዛሬ ላይ ብስመው.. .

ነገ አያስደግም ... መንገድ አያስመጣም !

ሁሉ ዝግ ነው ዛሬ ... ሳለ ነፃ አውጪ

ነፃነት ግን የለም አንቺም እንዳትመጪ

ከየት ይምጣ ግጥም?.. . ድሮ ቀረ ዜማ 

ድሮ ቀረ ማድነቅ ... የውበትሽን ግርማ

ድሮ ቀረ አርምሞ.. . ማሳው ተሞሽሮ 

ዛሬ ሰብሉ ረግፏል.. .በአንበጣ ተወሮ ።

ከየት ይምጣ ግጥም.. .?

በሰላም አየር ላይ.. . ተንሳፎ የኖረ

ይኸው መሬት ወድቋል ክንፉ ተሰበረ ...

ዛሬ !

ውበትን አወዳሽ ... ተፈጥሮን ዘካሪ 

ምጥን ያለች ቅኔ.. . ነገር አሳማሪ 

ጥዑም አሰላሳይ ... ጆሮ ገብ ዝማሬ

ሀሴት የሚያቀዳጅ.. . የሚጣፍጥ ወሬ

ሳይኖር በሰፈሩ ... ሳይኖር ኸኸተማ

ምን ያለው ቧልት ነው...

ግጥም ቀረ ብሎ.. . ኩርፊያና ቁዘማ ?

በጠበበ ሀገር ...

ጥበብ ጌጥሽ...  ሆኖ አያደምቅሽማ።

...(ሚካኤል አስጨናቂ)....

@getem
@getem
@getem
👍2
(አሌክስ አብርሃም)
#ለምን_ታምሪኛለሽ ?

ትላንተና ሌሊት ስትናፍቂኝ አደርኩ …..ሳስብሽ አነጋሁ
ሸለብ ሲያደርገኝ በቅዠቴ መሃል ስምሽን አነሳሁ
‹‹ነግቶ ልርሳት›› እያልኩ ነግቶ ራሴን እረሳሁ !!
ኧረ በጌታ እናት በመብርሃን እርጅኝ
በተከበርኩበት አገር አታዋርጅኝ !
‹‹ይሄ አስመሳይ ፍጥረት ‹ስለሴት ዘፈኑ ›
ስለሴት አወሩ ብሎ የዘለፈ
ይሄው በማለዳው ስላንዲት ሴት ዳሌ መዝገብ ሙሉ ፃፈ››
ብለው የሚወቅሱኝ የሰሉ አሽሟጣጮች ሲዞሩኝ እያየሽ
እንቅልፌን እስክጥል ብእር እስካነሳ ለምን ታምሪኛለሽ ?
ይሄው ትላንትና ‹‹ያየ አመነዘረ ›› ብየ ሰብኪያለሁ
ዛሬ በተራየ እንኳን ፊቴ ቁመሽ በሌሊት ምናቤ
ከጥፍር እስከ ፀጉርሽ ሳይሽ አነጋለሁ…
ሸለብ ሲያደርገኝ በቅዠቴ መሃል ስምሽን አነሳሁ
በመኪኖቹ ጭስ በቆሻሻው ሽታ
በሽቶው ጥረና ባ,የሩ ሁካታ
ነፍስያየ መርጦ አንችን ማነፍነፉ
ላ,በቦች መአዛ ለቡናው ላይ እጣን አፍንጫ መስነፉ
እኮ ለምንድነው አፍጫየ መርጦ አንችን ያሸተተው
የአገሬ ነፋስ በአየር ጡቶቹ ጠረንሽን ያጋተው?
ኧረ ምን መዓት ነው?
ሳላይ ከመኖሬ ከ,ለት ምናኒየ ልታቆራርጭኝ
በአምሮት መንጠቆ ከጥሞና ባህር ጠልፈሽ ልታስወጭኝ
የሲኦሉን እሳት ….የእግዜሩን ቁጣ
የበደሉን ምላሽ ….የእምነቱን ጣጣ
ከየደብሩ ስብከት ከየመፅሃፉ ትዛዙን እያወቅሽ
ለምን ታምሪኛለሽ……
ኧረ በጌታ እናት በመብርሃን እርጅኝ
በተከበርኩበት አገር አታዋርጅኝ !
ኧረ በፈጠረሽ ወይ ነብሴን ተረጃት
ከመኮፈሻዋ በሃቂቃ ፍቅር ጎትተሸ አውርጃት !!

@getem
@getem
👍2
#ተውበሽ በቀላል !
.
#በተውሶ ፀጉር ... በተውሶ ጥፍር
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው👌
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#እንጂማ.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉ አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. . በወርቅ ልደምቅ ነው።
....
ሚካኤል አስጨናቂ ....

@getem
@getem
@getem
#ተውበሽ በቀላል !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
በተውሶ ፀጉር ...
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው!
ያዩት ከሆናቸው...
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
.
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
.
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
.
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
ያንቺ ወዳጅ ልቤ
ርጋታ ተስኖት ... በስጋት በራደ !
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#አስቢው.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉም አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
ታድያ ...
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. .
እኔ ያንቺው ፈቺ ፥ በወርቅ ልደምቅ ነው።

@getem
@getem
@paappii
👍41
#ለምን እንደረከስኩ.. . !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
በቀልዴ ስትስቂ.. . ፈገግታሽ ሲገለጥ
ለኔ ደስታ የለም ከዚህ ገኖ 'ሚበልጥ
ስትስቂ ግን ድንገት
ሄጄ በሀሳብ ዥረት.. .
ተመልሼ ድሮ.. . አምናና ካቻምና
ከሌላ ወንድ ጋር አብረሽ ነበርሽና
ለሱም ስቃ ነበር ...በቀልዱ ተገርማ
ብዬ አኮርፋለሁ ... ደስታዬ ሲቀማ ።
.
እንዲሁ እንደ ዘበት
አንዳንድ ቀን ድንገት
በአልጋ ላይ ጨዋታ
ነፍሳችን ተረታ ...
አንገትሽ ስር ባለች.. . መዓዛ ሰክሬ
ሸሽቼ ከቅጥሬ.. .
ስቤ በምምገው ... ቃናሽ ሳልረካ
ሌላም ሰው ደርሶታል ይሄ ሽታም ለካ !
የሚል ሞጋች ሀሳብ እያንገበገበኝ
አንቺን አቅፎ ማደር ገላዬን ሸከከኝ።
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ማሽን ያተኮሰው
እኔ የምወደው.. .
የፀጉርሽ ሽታ
ደርሷል ሌላ ቦታ ...
.
ከፍቶሽ ስታነቢ እንባሽ ሲወርድ ቁልቁል
ሌላም ሰው እንደኔ አፅናንቶሻል እኩል
.
መስታወት ፊት ቆመን
የተንጋደደው የሸሚዝ ኮሌታ
ሲቃና በጣትሽ
ትናንት የሌላ ወንድ ኮሌታ ላይ አርፏል
ይሄ የጣት ፍቅርሽ
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ወይን እየጠጣን የተጨዋወትንበት
ይሄ ቦታ ድንገት
ከሌላ ወንድ ጋር በፊት ነበርሽበት ...
.
መውደድን ያየሁት ባንተ ነው ፍቅሬ
የሚል አፅናኝ ወሬ ...
አይደለም የዛሬ
.
ፅጌረዳ መሳይ አበባው ከንፈርሽ
እንቡጥ ሳለ ድሮ ተስሟል ባፍቃሪሽ
.
ይህን ጊዜ ታድያ ...
ካንቺ ኋላ መጥታ ላወኳት ሌላ ሴት
በቅናት በንዴት ...
ቀልዱን አጋርቻት አየሁ የሷን ሀሴት
አንገቷ ስር ገባሁ... ሳብኩት መዓዛዋን
የተከዘች ጊዜ ክንዴ ስር አቅፌ አበስኩኝ እንባዋን
.
ማሽን ያተኮሰው ጡገሯን አሸተትኩኝ
(ሽታሽ ይብልጣታል .. )
ሸሚዜን ላቃና ከሷ ፊት ዘንድ ቆምኩኝ
ጠጣን አብረን ወይን በኔና አንቺ ቦታ
ከንፈሯን ጎረስኩት ካላንዳንች ይሉኝታ
.
ረከስኩ
ረከስኩ
ለሌላ ሴት ወደኩ!
ከክብር ተናነስኩ!
.
ከዛ ግን ተቃናሁ ... በገላዬ ርኩሰት
ዛሬ አንቺን አቅፌ ... እንዲሁ በድንገት
"ሌላ ወንድ አቅፏታል" የሚል ክፉ ሀሳብ
ውስጤን ሲሞግተኝ...
"እኔ ማን ሆኜ ነው የሌላ ሰው ሀጥያት
ቀድሞ የሚታየኝ ?"
የሚል ምላሽ አለኝ!

@getem
@getem
@paappii

#Mikael aschenaki
👍1
#ለምን_ይሆን?
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ፣
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ፣
ማልቀሴን ምረሳው ለምን ይሆን ውዴ፣
አስተናግር ቅጠል አቀመስሺኝ እንዴ?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
48👍37😁21
#ለምን እንደረከስኩ.. . !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
በቀልዴ ስትስቂ.. . ፈገግታሽ ሲገለጥ
ለኔ ደስታ የለም ከዚህ ገኖ 'ሚበልጥ
ስትስቂ ግን ድንገት
ሄጄ በሀሳብ ዥረት.. .
ተመልሼ ድሮ.. . አምናና ካቻምና
ከሌላ ወንድ ጋር አብረሽ ነበርሽና
ለሱም ስቃ ነበር ...በቀልዱ ተገርማ
ብዬ አኮርፋለሁ ... ደስታዬ ሲቀማ ።
.
እንዲሁ እንደ ዘበት
አንዳንድ ቀን ድንገት
በአልጋ ላይ ጨዋታ
ነፍሳችን ተረታ ...
አንገትሽ ስር ባለች.. . መዓዛ ሰክሬ
ሸሽቼ ከቅጥሬ.. .
ስቤ በምምገው ... ቃናሽ ሳልረካ
ሌላም ሰው ደርሶታል ይሄ ሽታም ለካ !
የሚል ሞጋች ሀሳብ እያንገበገበኝ
አንቺን አቅፎ ማደር ገላዬን ሸከከኝ።
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ማሽን ያተኮሰው
እኔ የምወደው.. .
የፀጉርሽ ሽታ
ደርሷል ሌላ ቦታ ...
.
ከፍቶሽ ስታነቢ እንባሽ ሲወርድ ቁልቁል
ሌላም ሰው እንደኔ አፅናንቶሻል እኩል
.
መስታወት ፊት ቆመን
የተንጋደደው የሸሚዝ ኮሌታ
ሲቃና በጣትሽ
ትናንት የሌላ ወንድ ኮሌታ ላይ አርፏል
ይሄ የጣት ፍቅርሽ
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ወይን እየጠጣን የተጨዋወትንበት
ይሄ ቦታ ድንገት
ከሌላ ወንድ ጋር በፊት ነበርሽበት ...
.
"መውደድን ያየሁት ባንተ ነው ፍቅሬ"
የሚል አፅናኝ ወሬ ...
አይደለም የዛሬ
.
ፅጌረዳ መሳይ አበባው ከንፈርሽ
እንቡጥ ሳለ ድሮ ተስሟል ባፍቃሪሽ
.
ይህን ጊዜ ታድያ ...
ካንቺ ኋላ መጥታ ላወኳት ሌላ ሴት
በቅናት በንዴት ...
ቀልዱን አጋርቻት አየሁ የሷን ሀሴት
አንገቷ ስር ገባሁ... ሳብኩት መዓዛዋን
የተከዘች ጊዜ ክንዴ ስር አቅፌ አበስኩኝ እንባዋን
.
ማሽን ያተኮሰው ጡገሯን አሸተትኩኝ
(ሽታሽ ይበልጣታል .. )
ሸሚዜን ላቃና ከሷ ፊት ዘንድ ቆምኩኝ
ጠጣን አብረን ወይን በኔና አንቺ ቦታ
ከንፈሯን ጎረስኩት ካላንዳንች ይሉኝታ
.
ረከስኩ
ረከስኩ
ለሌላ ሴት ወደኩ!
ከክብር ተናነስኩ!
.
ከዛ ግን ተቃናሁ ... በገላዬ ርኩሰት
ዛሬ አንቺን አቅፌ ... እንዲሁ በድንገት
"ሌላ ወንድ አቅፏታል" የሚል ክፉ ሀሳብ
ውስጤን ሲሞግተኝ...
"እኔ ማን ሆኜ ነው የሌላ ሰው ሀጥያት
ቀድሞ የሚታየኝ ?"
የሚል ምላሽ አለኝ!

@getem
@getem
@getem
👍8238😱7🤩7🔥2
#ለምን_ይሆን?
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ፣
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ፣
ማልቀሴን ምረሳው ለምን ይሆን ውዴ፣
አስተናግር ቅጠል አቀመስሺኝ እንዴ?

#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@getem
@getem
@getem
33👍24😁24👎5