ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ተውበሽ በቀላል !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
በተውሶ ፀጉር ...
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው!
ያዩት ከሆናቸው...
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
.
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
.
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
.
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
ያንቺ ወዳጅ ልቤ
ርጋታ ተስኖት ... በስጋት በራደ !
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#አስቢው.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉም አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
ታድያ ...
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. .
እኔ ያንቺው ፈቺ ፥ በወርቅ ልደምቅ ነው።

@getem
@getem
@paappii
👍41