ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
*ከዘመን ጥል*
መላ አካሌን ቆፈን ወርሶት ካንዲት ጥጋት ተጠልዬ
ከረጠበው አካሌ ላይ የልጅነት ትዝታዬን አንጠልጥዬ
...........................
'ኳትናለሁ ላልመልሠው ከዘመን ጋር ተሟግቼ
ንፁህ ነፍሴ ካቤን ንዷት ከጉድፌ ተጋብቼ
.............................
ይኸው አለሁ ልቤ ናፍቆት ውብ ፈገግታ
ከእውነት ጋር የተጋባ የተቃኘ በዝምታ
.............................
ይኸው ዛሬን ዘልቂያለሁ ከትዝታ ተጣልቼ
ከልቤ ላይ የማይጠፋ ያልነቀዘ ፍቅሬን ሽቼ
............................
ይኸው...
ዛሬ ያልነው ትላንታችን ከቀንህ ላይ ቀኔን ሠርቆ
አኩኩሉ ይጫወታል በይነጋል ተስፋ ስሌት ከልቤ ላይ ተደብቆ
..........................
ዘራፊዬ አኩኩሉ ይጫወታል
ምስኪን ልቤ ይነጋልን ይናፍቃል
..........................
በይነጋል ተሸሽጎ የመሸበት
ማን ሊያድነው ያለመንጋት
............................
መላ አካሌን ቆፈን ወርሶት ካንዲት ጥጋት ተጠልዬ
ከረጠበው አካሌ ላይ የልጅነት ትዝታዬን አንጠልጥዬ
............................
'ኳትናለሁ ላልመልሰው ከዘመን ጋር ተሟግቼ
ንፁህ ነፍሴን ካቤን ንዷት ከጉድፌ ተጋብቼ
..........................
ይኸው አለሁ ብጀ ፣ ብቀ ፣ ሠላሽ ናፍቆኝ
ልዮ አንዳይነት ተጣጥለን የረታሁህ የረታኸኝ
......................... ....
ይኸው አለሁ ከካፊያው ጋር ተደባልቃ የምትወጣ ፀሀይ ናፍቃኝ
ጅብ ወለደች የሚል ዜና አስጨንቆ አስደስቶኝ
............................
ይኸው አለሁ በጣቶችህ የዳበስከው መሃረቤ እንደጠፋ
አላየሁም በበዛበት መላ አካሌ ለመፈለግ እየለፋ
...........................
ይኸው አለሁ የልጅነት ትዝታዬን አንተን ሽቼ
ከምኞቴ እደርስ እንደሁ በማሪያም ጣት ተመርቼ
........................
ይኸው አለሁ
ከዘመንህ ተጣልቼ
ከዘመኔ ተሟግቼ
.................//.............
ተፃፈ በሔለን ፋንታሁን

@getem
@getem
@lula_al_greeko
📌 የምክርና የንግግር ህክምና (Counseling and Therapy) በ Online Chat ፣ በ Video Call ወይም በ Phone Call በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ላይ ሆኖ በነፃ ማግኘት ይችላሉ ።

🔖 100% ሚስጥሮት ተጠብቆ የሚፈልጉትን እርዳታ አሁን ያግኙ !

🔎 ለህክምና እርዳታ ለማግኘት አሁኑኑ የ ሳይክ ኢንፎ ቤተሰብ ይሁኑ

በተጨማሪም ስለ ሰው ባህርይ ፣ አስተሳሰብ፣ የአዕምሮ ጤና ፣ የአዕምሮ በሽታዎች እና ምልክቶች ትኩስ መረጃ ያግኙ!!

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE-6H4qqKyDyXr8oGA
...ተሰፋ አንቆርጥም...(ሳሙኤል አዳነ)

ውሀ በፈረቃ ፣
መብራት በፈረቃ፣
ስልጣን በፈረቃ ፣
     ላገር ሲታደሉ ፣
      ውሀ አጣጭ ፈለጋ
    መብራት ጠፋ ብለሽ ፣
     ከባለ ስልጣን ጋር
      ትዞሪያለሽ አሉ ።

ይሁና ..
ውሀ የመጣለት ...
     ገላዬን ታጥቤ፣
ልብሴን አሳጥቤ ፣
     ስልጣንም ካገኘሁ ፣
እሱን ተረክቤ
    መብራትም ይመጣና፣
በግዙፍ አዳራሽ
ሰርጌን አከብራለሁ ፣
    ብትመጭ አታጭኝም ፣
     ግን አታገቢኝም ፣
ካሁኑ ሄጃለሁ ።

  እናም የዛንለት ...
በእጣ ፈንታችን
       መንግስት እንወቅሳለን ፣
       ሀገር እንከሳለን፣
ቆይቶ..ቆይቶ..ቆይቶ..
ጩህታችን ሰምሮ ፣
በሌላ ፈረቃ እንገናኛለን ።

ተሰፋ አንቆርጥም

12/09/2011
ከጧቱ 12:00 ሰአት
መብራት ሳይጠፋ
    

    
@gebriel_19
@getem
@getem      
   
ለወዳጄ ኑሮ!!

አልነበርክም እንጅ ፡ ብትኖርማ ኑሮ፣
የባዶነት ድንኳን፡
ባልተከደነብን ፡ እንደ ቅርጫት ዶሮ፡፡
ብትኖርማ …..ኑሮ!፡
ጥርጊያው በተነሳ : በተደላደለች፡ ባማረች ተፈጥሮ፡፡
ቸነፈር እርዛት፡ ለኬት ባጣ ቱጃር፣
በስምህ ሲነገድ፡ በስምህ ሲዘከር፣
ብትኖርማ …..ኑሮ!
ይህንን እያየህ ዝም .. !! ጭጭ ..!! ጸጥ..!! አትልም ነበር፡፡
አይኖቼን ገርብቤ፡ በሽንፍላየ ጭራ፣
በተዋጠ ልሳን ፡ ስምህን ስጠራ፣
እጆቼን ግራ ቀኝ፡ ላገኝህ ስዳብስ፣
ዳናህ ጠፍቶብኛል ፡ ጋርዶሀል ክፉ አድማስ፡፡
ብትሰማኝ ..ኑሮ፣
ብታየኝም …ኑሮ፣
ብትኖርማ ኑሮ፣
የማይጨክን ልብህ፡ አንጀትህ ተቋጥሮ፣
ነጭ ሜዳ አውርሰህ ፡ ጥለኸኝ….ሸሽተኸኝ ፣
እቅፍ ትቢያ አስታቅፈህ፡ ባዶነት ችረኸኝ፣
የምኞት እንጀራ፡ በተስፋ አጓጉተህ ፡ ወኔ አስታጠከኝ፡፡
ሽንገላው በዛና፡ ስታለል የሰማ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሲሉኝ ፡ መልሱን ባልተቸገርኩ ፡
ኑረህ ቢሆንማ፡፡
ዙሮ ዙሮ ከቤት፡ ኑሮ ኑሮ ከሞት፣
ድንገት ቢታወሰኝ ፡ የእነ ማማ ተረት፣
ሳይገለጥልኝ ፡ሳይገባኝ ሚስጥሩ፣
ለካስ ከጥንት ነው፡ አንተም ኑረህ ኑረህ ፡
የጠፋህ ካገሩ፡፡
የጊዜየን ቋጥኝ ፡ ዕፍኝ ተመልክቶ፣
ከኔ መራቅህን፡ ጠረኑን አሽትቶ፣
ከቶ ማን ጠየቀኝ ፡ ከሰውነት ቆጥሮ፣
ዝም አትልም ነበር፡ ብትኖርማ …..ኑሮ!፡፡
የለህም!! ..የለህም!! ፡ አለሁ እንዳትለኝ፣
ባንተ የተራብኩኝ ፡ ኑሮ ዕያጎበጠኝ፣
ኑሮ የተጠማሁ ፡ የጎዳና ልጅ ነኝ፡፡
አለሁ እንዳትለኝ፣
የመጎሳቆሌን ፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ወዳጅህ እልፍ ነው..፣
ደጋፊህ መንጋ ነው፣
ጠያቂህ ብዙ ነው ፣
ረጋሚህ ድርብ ፡ ስፍር ቁጥር አልባ፣
ኑሮ የጠፋበት ፡ ኑሮ እንዴት ነው ይላል፡
ያገኘው ይመስል ፡ በሌሎች አንቀልባ፡፡
ስላንተ ተጨንቆ ፡ ዘወትር ጧት ማታ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሁኗል ፡ የግዚሄር ሰላምታ፡፡
የመጎሳቆሌን፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ኑሮ እንደት ነው ላለኝ!፣
እሱማ ምን ጎሎት፡
ይመስገን ደህና ነው! በጎ ነው እላለሁ፡፡


#Gizatu_Amare

@getem
@getem
የዕድሜ ገደብ


በሚጠምቀው ቢራ ፣
ከወቀሳ ሊደን፣ጻድቅ መልኩን ሳለ፥
ለገዛው ሊሸጠው፣
ዕድሜውን ላይጠይቅ፣
የ ዕድሜ ገደብ ጣለ።


ምን ይሉት ሰዓሊ ነው ፣
በጠመቀው ቢራ ፣
የዕድሜን ገደብ ሚስል፥
በጠርሙሶች ቁጥር፣
የሚከበር ልደት ይለያይ ይመስል።
የሰካራም ዕድሜ፣
ያንዱ ከሌላኛው ይለያይ ይመስል።

ጠጣ ትንሽዬው!!
የምን ገደብ ማክበር፣
የ"አትጠጡ"ገደብ ፣
ከምንስ ሊያድነን፥
የሰከርን ለታ፣
ባስተሳሰብ እንጂ፣
በ ዕድሜያችን አንድ ነን።


ማነሽ ለኔና ለዚህ 18 ላልሞላው
ልጅ ሁለት ቢራ እስኪ!!!!


ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)

ግንቦት 10/2011
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ



@getem
@getem
@Ezihbetsanaddis
የ ሃሳቤ ጥያቄ...
.
.
.
ጭንቅ በሞላበት በዚች ጠባብ ምድር
የ ግድ ከሆነ የ እኔ መፈጠር
ለምንስ መጣሁኝ...🤔
ለምን ተፈጠርኩኝ ተግባሬ ምንድነዉ..?
መወለዴ ካልቀረ መኖሬስ ለማነዉ...?
እንዲ እንዲ አይነት ሀሳብ እያሰብኩኝ
ለ ጥያቄዬ የሚሆን መልስ እየፈለኩኝ
የሚመልስልኝ አንድ ሰዉ አጣሁኝ😔
እንደዚ አይነት ሃሳብ በሃሳቤ እያሰብኩኝ
ከእንዲ አይነት ሃሳብ ጋር ሃሳቤ ኣጋጨኝ
ደግሞ እየመለሰኝ
የኔዉ ሃሳብ ለኔ
ለ እኔዉ ጥያቄ መልሱን መለሰልኝ
እንዲ ሲል ጀመረ...
.
ኣዏን ትክክል ነክ
ያንተ ወደዚ መምጣት በርግጥ ግድ ነዉ
በእዚች አለም ላይም የ አንተ መፈጠር
ስህተት የለዉም ሁሉም ትክክል ነዉ
ተግባርህም ቢሆን ልንገርክ ይሄ ነዉ
.
ያልኖሩ ህይወቶችን በዉስጥ ማኖር ነዉ

F.D.N
05/09/2011

አንድ ሰዉ ኖረ የምንለዉ በራሱ ኑሮ ዉስጥ ሌሎችን ማኖር ሲጀምር ነዉ
ስለዚህ...እኔም አንቺም አንተም ከዚች ሰአት ጀምረን መኖር አንጀምር።

@getem
@getem
@gebriel_19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተኩስ!!!!!!🔫🔫🔫

በ እጅህ ላይ ያለው
ከ እጅ የተሰራ፣
የጭካኔ ቀንዲል
የ እሳት አዝመራ።
እሳት የጎረሰ
እሳት የሚተፋ፣
ለምስኪኑ ጩኸት
ላጥፊው 'ሚሰጥ ተስፋ።
በፍቅር መርታትን
ባልለመደው ጎራ፣
ለኔ አዲስ አይደለም
በጠብ መንጃ
ረትቶ በሙታን በድን ላይ
ማሳየት ጭፈራ።
ስማ‼️
ምንም ኃይል ቢኖርህ
ምንም ብትታጠቅ፣
የወንድሜን ህይወት
ከኔ ህይወት በፊት
አትችልም መንጠቅ።
በጨቅላነቴ ዉስጥ
ትልቅ ወጣት አለ፣
ካንተ እንጭጭ እሳቤ
በእጥፍ የበሰለ።
በስስ አካሌ ዉስጥ
ጠንካራ ልብ አለ፣
ጥይት የማይፈራ
ፍቅርን የታደለ።
ለእንዳንተ አይነቱ
ጨካኝ አረመኔ፣
ወንድሜን አልሰጥም
በህይወት ሳለሁ እኔ።
ተኩስ ቃታውን ሳብ
አነጣጥረው ከእኔ፣
ከወንድሜ በፊት
ጽዋውን ልጎንጨው
እንዲሆነው ወኔ።
ቤተሰብ ላጣ ሰው
ህዝብ ላጣ ዓለም፣
የሞት ጽዋን ልፎ
ካጣው ወገኑ ጋር
እንደመቀላቀል የሚያስደስት የለም።
ተኩስ!!!!!!!!🔫🔫🔫


😞😞መኖርን ሲሹ ገዳይ ለበዛባቸው፤ሞተው እንኳን ቀባሪ ላጡ፤የዓለም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን የሚሉት ሰብአዊ መብታቸውን ለነሷቸው፤ኃያላን ነን የሚሉ ሃገሮች የጉልበታቸውን መጠን ያሳዪባቸው፤ የወደቀ መርፌን እንኳን አጉልተው የሚያሳዩት የዓለም መገናኛ ብዙሃኖች እንኳን ጆሮ ዳባ ልበሱ ላሏቸው፨፨፨ ምስኪን የ palestine ዜጎች ልባዊ የሃዘን ማብቂያ ጊዜ ተመኘሁ!😔😔😔

አብዱ



@getem
@getem
@tubelightbyabdu
............ተመስገን..........

የቀረበ ሲርቅ፣ ያጀበ ሲበተን
ቀና ብዬ ሳይህ፣ አላጣህም አንተን ።

@getem
@getem
@paappii

#izana
መቁንኗ መኩሪታ ተጋግሮ ዳጉሳ፣
ትበላለች ሁሌም
ከፀለየች ኋላ ሀገሬ መንኩሳ።

እሷ ስትፀልይ እኛ አንድ እንድንሆን፣
እኛ እንድንለያይ ሴራ ስንጎነጉን፣
ተለያይተን ባሳብ በጎጥኛ ግብር
ሀገር አልባ ሆንን።

(አምባዬ ጌታነህ )

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
አስተያየት
@amba8
T.me/amba88



@getem
@getem
@gebriel_19
ገለባ አይደለሁም !

አውሎ ነፋስ ደርሶ ~ የሚያርገበግበኝ

ወንጭፍም አይደለሁ

ማንም እያሾረ ~ የሚወዘውዘኝ

እኔ ደራሽ ውሀ

የመንፈስ አምሀ

እሳቱን የሀሜት ~ ምላስ የማከስም

ድኩማኗን ነፍሴን ~ በፊደል የማክም

ወጀቡን ነፋሱን ~ የማልፋቸው ጥዬ

አጎንብሼ 'ማልቀር ~ መንፈሴን አ..ዝዬ

ገለባ ነው ሲሉኝ ~ ፍሬ የማፈራ

ሊከስም ነው ሲሉኝ ~ ከርሞ 'ምጎመራ

የርግማን ውርጅብኝ ~ ከቶ የማልፈራ

በጭብጨባ ብዛት ~ ደንቆኝ የማልኮራ

የዝምታው ዳኛ...

በሸክላ ገላና ~ ብረት ልብ ያነፀኝ

በጩኸት የማልወድቅ የእጆቹ ስራ ነኝ።

#ሚካኤል አስጨናቂ

@getem
@getem
@gebriel_19
📌 ሳይክ-ኢንፎ

የምክርና የንግግር ህክምና (Counseling and Therapy) በ Online Chat ፣ በ Video Call ወይም በ Phone Call በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ላይ ሆነው በነፃ ማግኘት ይችላሉ ። 100% ሚስጥሮት ተጠብቆ የሚፈልጉትን እርዳታ አሁን ያግኙ !
።።።ውርሰ-ውበት።።።።
(ልዑል ሀይሌ)


ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
.
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው
..
.
ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ
..
.
ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ
..
.
ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት
..
.
ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ
..
.
ፀባይሽ ግን ውዴ...
.
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
..
.
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
.
ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ


እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸው

8-1-2009



@lula_al_greeko
@getem
@getem
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትንቢት

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል 👇
@burukassahunc


@getem
@getem
የምርቃና ግፉ !

( በረከት በላይነህ )

..

የሙዚቃ ሊቁ..
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ፤
ጠባቧ እስቱዲዮ ጫት ሞልቷት ነበረ ።

..

ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ ፥
ሊቅም ቁርሱን በላ።

..

ሹማምንቶቻችን ፥..
ገንቢ አፍራሾቻችን ዕቅዱን ሲፅፉ ፤
በትዕዛዝ ያደገ አወዳይ ቀጠፉ።

..

ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ ፤
ደብዳቤ ፃፈልሽ...
ከገራባ መሐል ምርቅን ቃላት ለቅሞ !!

..

እናስ!

መሪ ከተከታይ ፤
ፍትሕ ከተበዳይ፤
ጥበብ ከአድናቂው ፤
ምላሽ ከጠያቂው ፤
የነቃ ከእውኑ ፤
የተኛ ከሕልሙ ፤
ውበት ከቀለሙ ፤
እኮ በምን ስሌት ፣ እንደምን ይስማማ ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ !!!

@getem
@getem
@gebriel_19
ከግንዷ ልወለድ
ከነጎደጎደው ከጨሰው ሰማይ ስር ፤
በደላላማው ጎርፍ ከረጠበው ምድር፤
በአውሎንፋሱ በመብረቁ ጩኧት፤
አለም ጭር ባለበት ጎራ በለየበት፤
ጫካው ነጭ ሲሆን ክሎሪን ሲታጠን፤
ህይወት እንደዋዛ እንደጤዛ ሲተን፤
በቀለም መገፋት በቀለም መገረፍ፤
በቀለም መደፋት ለምትማስነው ዛፍ፤
በአረጓዴ ቅጠል በቢጫ አበባ፤
በቀላ ፍሬዋ ለምታማልለው፤
ልፍለቅ ከደግንዷ ላይ ከማበገረው፡፡
ቀለሟን አጥፍተው የቀለሟት እለታ፤
ረቂቅ ሚስጥሯ ካላግባብ ሲፈታ፤
በትዕቢት መትረው ሊቆርጧት ሲመጡ፤
ቅጠሏን ቅርፊቷን ሸንሸነው ሊሸጡ፤
ልወለድ ከግንዷ ውድቀት ከማይወደው፤
የሰው ካባ ለብሶ ሀሩር ከሚበርደው፡፡
አንድም ከቅጠሏ ከአበባው ሳይቀጥፉ፤
ቅርፊት ከግንዱ የሚያስተሳስረው ሀረግ ሳያጠፉ፤
ልወለድ ከግንዷ በመቦረቂያዬ፤
መጫውቱን ይቅር ልጥፋ ልሰወረው ከሚወደኝ ቄዬ፡፡

እድሜዬ ባይመጥን መባዘን በዱሩ፤
የአባቴ አባት የአባቱም አባት ያኔ ከጅምሩ፤
ዛፏ ስትተከል በባዶ እግራቸውቸ ችለው አመኬላ፤
ለወራት ተጉዘው ያኖሩልኝ ተክል ያኖሩልኝ መላ፤
ልጠብቀው እኔ በአፍላ እድሜዬ፤
ልወለድ ከግንዷ ላርብ ለብቻዬ፡፡

ኬሎ እዳይፈልገኝ ወንዙን ልሻገረው፤
ልራቅ ከመደሬ ከጫካው ልኖረው፤
ዛፏ ስትናወጥ ክፉ ቀን ሲመጣ፤
ባባቶቼ ብልሀት ባባቶቼ ወኔ፤
ከሰው በታች መሆን ገፈቱን ላልጠጣ፤
ይቅርብኝ መቦረቅ ታገስ አፍላነቴ፤
ወጣትነት ስማኝ ላሳይ ማንነቴ፤
ታሪክ ይዘክረኝ ዝናዬ ይሰማ ፤
ትውልድ ይመርከኝ ይበል እደ ጃገማ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!
ረቂቅ ሚሰጥር ነው!
ጃንሆይ በአንድ ወቅት…..
ጉብኝት ላይ ሳሉ ፤
የኢትዮጵያዊነት ሚስጥሩ ምን ይሆን ቢባሉ ፤
‹‹ኢትዮጵያዊ ዘንድ ብቴድ እንግድነት ፤
አጥቦ ስሞ ያስተኛል የዛለው ሰውነት ፤
የእርሱ አልጋ ለቆ ይተኛል ከመሬት ፡፡
ሆኖም ግን…….
በሚወዳት ሚሰቱ፣
በሀገር እናቱ፣
የመጣህ እነደሆን ፤
መርገም መፈጠርን ፤
ከእርሱ ትማራለህ ፤
የጥይቶች ናዳ አንተው ተቆጥራለህ ፡፡
ለነገሩ ሰዉ ይህን ለመረዳት ፤
ኢትዮጵያዊ መሆን ይጠይቃል መስፈርት::”
ብለው መለሱለት….
ሆኖም ይህ ረቂቅ ሚስጥር ፤
ተሳሰሮ የቆየው ጠነካራው የደም ክር ፤
እነዲህ በቀላሉ እንዲህ እነደዋዛ ፤
ፈርሶ መቀጠሉ በዋዛ ፈዛዛ ፤
ተስፋችን ጨልሞ ደርቆዋል እንደ ጤዛ፡፡

ስም፡- አሰፋ ጋሚኒ

@getem
@getem
@getem
#የጊዜሽ እውነታ! !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።

የፎቶ ዓለም ነው!

የብልጭታ ዘመን...
ታይታ የሞላው ፥ መታበይ የሰራው

አዋቂው ብዙ ነው !

በራሱ ዛቢያ ላይ ፥ መንገድ 'ሚያቀናው።

ጎዳናው አንድ ነው!

የለም የተለየ...

ጠርጣሪው እልፍ ነው!

ገለባ ሸንትሮ ፥ ሽንብራ ያለየ።

መቅረዝ ተሸካሚው.. .

አትሮኖሱን ዘርጊው...

ባለ ጧፉ ብዙ

ባለ መጣፍ ብዙ

መድረኩ ላይ ቆሞ ፥ እኔን ስሙ 'ሚለው

እሪያው አሸን ነው!

ያሉትን አድምጦ ፥ በመንጋ 'ሚጎርፈው

#ይኸው ተመልከቺ!

ስንደዶው መች ጠፋ?

አክርማው መች ጠፋ?

ባለሙያው ብዙ

ባለ ወስፌው ብዙ

እንዴት ቢሰፋ ነው?

መሶቡ ሳያምር ፥ የሚታይ ሰበዙ?

#አየሽ!

በዚህች በጉድ ሀገር...

ቱባውን አፍታቶ ፥ ክሮቹን ወድሮ

ጋቢ ልስፋ 'ሚለው ፥ ሸማኔው ቢበዛም

ሁሉም እርቃኑን ነው!

የሞቀው ሰው የለም ፥ ውርጩም አልተረታም።


@getem
@getem
@gebriel_19
......ንገረኝ....(ሳሙኤል አዳነ)

ወድሻለሀው ብለህ
ሞልተህኝ በተስፋ
ወዴየት ተሰወርክ
ምነው ኮቴህ ጠፋ ።
.
እንዲህ ነው ወይ ፍቅር?
ሞትኩኝ አበድኩልሽ
የተባለን መውደድ
መድረሻውን ሳናይ
የያዝነውን መንገድ
ምን ይሉት ብሂል ነው
ልብ እየሰበሩ
ፍቅርን ገደል መስደድ ።
ገደብ የለው ፍቅር
ዙሪያው አይለካ
የቱ ተፈጽሞ
የትኛው ተነካ ።
እንዲህ ነው ወይ መውደድ
የነጠላ ዜማ የፍቅር ኑዛዜ:
ሆድን ቆርጦ መሄድ በፈለጉት ጊዜ ::

.

በል እስኪ ንገረኝ
ትተህኝ ከሄድክ
ቆየህ ሰንብተሀል :
የትኛው ጎሎብህ
የትኛው ቀንቶሀል :
ፍቅርን አሳምመህ
ምንን አድነሀል ?
መውደድን ሰባብረህ
የቱን ጠግነሀል ።
የትኛው ትክክል
የትኛው ስህተት ነው
ብለህ ወስነሀል ።

በል እስኪ ንገረኝ
ወዳጅ ትቶ መሄድ
ቆይ እንዴት ያደርጋል
ምሽቱ ሰምሮልህ
ሌሊቱስ ይነጋል ።
አንተባለህበት
አሮጌው ቀን አልፎ
አድሱ ይነግሳል ?
በአራቱ አቅጣጫ
ንፋሱስ ይነፍሳል ?
የወንዙ ጅረትስ
ድምጹን እያሰማ
አሁንም ይፈሳል?
......................
ህህህ
እኔ ባለሁበት
ይህ ሁሉ ከሆነ ቆይቷል ሰንብቷል
ወይ ፍቅርህ ሸፍኖኝ
ወይ ፈጣሪ አዳልቷል ።
..
ታዘብኩህ
አንችስ አትለኝም
እኔማ በሀሳብ
ደክሜልሀለሁ
በትናንትና ውስጥ
መኖር ጀምሬያለሁ ።
ይምሽ ይንጋ አላውቅም
ከሀሳቤ ጋራ መታገል ነው እንጂ
ቀን መቁጠር ትቻለሁ ።

.
ባክህ ነገረኝ
ወይ ተመለስና ፍቅራችን ይቃና
ካልሆነ እንድተውህ
መርሳት አስተምረኝ
እኔም ደጅ አልጥና ።
ልብህ በሌለበት
ልብን ትቶ መሄድ
አያዘልቅምና ።


27/01/2011
5:00pm A.A

@getem
@getem
@gebriel_19
ኦሮሞ ነኝ፣ ያውም አማራ
በትግረኛ የምናገር፣ ጉራግኛ የማወራ
እንደውም ሁሉን ብሔር ነኝ፣ ሰው ተብዬ የምጠራ
ዘር እንዳልቆጥር ዘሬ ሰው ነው፣ በሰውነት የምኮራ
በሰው ደስታ የምደሰት ፣ የሚያስከፋኝ የሰው ሲቃ
ኢትዮጵያዊ ሰው ነኝ በቃ!!!!

(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem