#የጊዜሽ እውነታ! !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
የፎቶ ዓለም ነው!
የብልጭታ ዘመን...
ታይታ የሞላው ፥ መታበይ የሰራው
አዋቂው ብዙ ነው !
በራሱ ዛቢያ ላይ ፥ መንገድ 'ሚያቀናው።
ጎዳናው አንድ ነው!
የለም የተለየ...
ጠርጣሪው እልፍ ነው!
ገለባ ሸንትሮ ፥ ሽንብራ ያለየ።
መቅረዝ ተሸካሚው.. .
አትሮኖሱን ዘርጊው...
ባለ ጧፉ ብዙ
ባለ መጣፍ ብዙ
መድረኩ ላይ ቆሞ ፥ እኔን ስሙ 'ሚለው
እሪያው አሸን ነው!
ያሉትን አድምጦ ፥ በመንጋ 'ሚጎርፈው
#ይኸው ተመልከቺ!
ስንደዶው መች ጠፋ?
አክርማው መች ጠፋ?
ባለሙያው ብዙ
ባለ ወስፌው ብዙ
እንዴት ቢሰፋ ነው?
መሶቡ ሳያምር ፥ የሚታይ ሰበዙ?
#አየሽ!
በዚህች በጉድ ሀገር...
ቱባውን አፍታቶ ፥ ክሮቹን ወድሮ
ጋቢ ልስፋ 'ሚለው ፥ ሸማኔው ቢበዛም
ሁሉም እርቃኑን ነው!
የሞቀው ሰው የለም ፥ ውርጩም አልተረታም።
@getem
@getem
@gebriel_19
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
የፎቶ ዓለም ነው!
የብልጭታ ዘመን...
ታይታ የሞላው ፥ መታበይ የሰራው
አዋቂው ብዙ ነው !
በራሱ ዛቢያ ላይ ፥ መንገድ 'ሚያቀናው።
ጎዳናው አንድ ነው!
የለም የተለየ...
ጠርጣሪው እልፍ ነው!
ገለባ ሸንትሮ ፥ ሽንብራ ያለየ።
መቅረዝ ተሸካሚው.. .
አትሮኖሱን ዘርጊው...
ባለ ጧፉ ብዙ
ባለ መጣፍ ብዙ
መድረኩ ላይ ቆሞ ፥ እኔን ስሙ 'ሚለው
እሪያው አሸን ነው!
ያሉትን አድምጦ ፥ በመንጋ 'ሚጎርፈው
#ይኸው ተመልከቺ!
ስንደዶው መች ጠፋ?
አክርማው መች ጠፋ?
ባለሙያው ብዙ
ባለ ወስፌው ብዙ
እንዴት ቢሰፋ ነው?
መሶቡ ሳያምር ፥ የሚታይ ሰበዙ?
#አየሽ!
በዚህች በጉድ ሀገር...
ቱባውን አፍታቶ ፥ ክሮቹን ወድሮ
ጋቢ ልስፋ 'ሚለው ፥ ሸማኔው ቢበዛም
ሁሉም እርቃኑን ነው!
የሞቀው ሰው የለም ፥ ውርጩም አልተረታም።
@getem
@getem
@gebriel_19