ለወዳጄ ኑሮ!!
አልነበርክም እንጅ ፡ ብትኖርማ ኑሮ፣
የባዶነት ድንኳን፡
ባልተከደነብን ፡ እንደ ቅርጫት ዶሮ፡፡
ብትኖርማ …..ኑሮ!፡
ጥርጊያው በተነሳ : በተደላደለች፡ ባማረች ተፈጥሮ፡፡
ቸነፈር እርዛት፡ ለኬት ባጣ ቱጃር፣
በስምህ ሲነገድ፡ በስምህ ሲዘከር፣
ብትኖርማ …..ኑሮ!
ይህንን እያየህ ዝም .. !! ጭጭ ..!! ጸጥ..!! አትልም ነበር፡፡
አይኖቼን ገርብቤ፡ በሽንፍላየ ጭራ፣
በተዋጠ ልሳን ፡ ስምህን ስጠራ፣
እጆቼን ግራ ቀኝ፡ ላገኝህ ስዳብስ፣
ዳናህ ጠፍቶብኛል ፡ ጋርዶሀል ክፉ አድማስ፡፡
ብትሰማኝ ..ኑሮ፣
ብታየኝም …ኑሮ፣
ብትኖርማ ኑሮ፣
የማይጨክን ልብህ፡ አንጀትህ ተቋጥሮ፣
ነጭ ሜዳ አውርሰህ ፡ ጥለኸኝ….ሸሽተኸኝ ፣
እቅፍ ትቢያ አስታቅፈህ፡ ባዶነት ችረኸኝ፣
የምኞት እንጀራ፡ በተስፋ አጓጉተህ ፡ ወኔ አስታጠከኝ፡፡
ሽንገላው በዛና፡ ስታለል የሰማ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሲሉኝ ፡ መልሱን ባልተቸገርኩ ፡
ኑረህ ቢሆንማ፡፡
ዙሮ ዙሮ ከቤት፡ ኑሮ ኑሮ ከሞት፣
ድንገት ቢታወሰኝ ፡ የእነ ማማ ተረት፣
ሳይገለጥልኝ ፡ሳይገባኝ ሚስጥሩ፣
ለካስ ከጥንት ነው፡ አንተም ኑረህ ኑረህ ፡
የጠፋህ ካገሩ፡፡
የጊዜየን ቋጥኝ ፡ ዕፍኝ ተመልክቶ፣
ከኔ መራቅህን፡ ጠረኑን አሽትቶ፣
ከቶ ማን ጠየቀኝ ፡ ከሰውነት ቆጥሮ፣
ዝም አትልም ነበር፡ ብትኖርማ …..ኑሮ!፡፡
የለህም!! ..የለህም!! ፡ አለሁ እንዳትለኝ፣
ባንተ የተራብኩኝ ፡ ኑሮ ዕያጎበጠኝ፣
ኑሮ የተጠማሁ ፡ የጎዳና ልጅ ነኝ፡፡
አለሁ እንዳትለኝ፣
የመጎሳቆሌን ፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ወዳጅህ እልፍ ነው..፣
ደጋፊህ መንጋ ነው፣
ጠያቂህ ብዙ ነው ፣
ረጋሚህ ድርብ ፡ ስፍር ቁጥር አልባ፣
ኑሮ የጠፋበት ፡ ኑሮ እንዴት ነው ይላል፡
ያገኘው ይመስል ፡ በሌሎች አንቀልባ፡፡
ስላንተ ተጨንቆ ፡ ዘወትር ጧት ማታ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሁኗል ፡ የግዚሄር ሰላምታ፡፡
የመጎሳቆሌን፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ኑሮ እንደት ነው ላለኝ!፣
እሱማ ምን ጎሎት፡
ይመስገን ደህና ነው! በጎ ነው እላለሁ፡፡
#Gizatu_Amare
@getem
@getem
አልነበርክም እንጅ ፡ ብትኖርማ ኑሮ፣
የባዶነት ድንኳን፡
ባልተከደነብን ፡ እንደ ቅርጫት ዶሮ፡፡
ብትኖርማ …..ኑሮ!፡
ጥርጊያው በተነሳ : በተደላደለች፡ ባማረች ተፈጥሮ፡፡
ቸነፈር እርዛት፡ ለኬት ባጣ ቱጃር፣
በስምህ ሲነገድ፡ በስምህ ሲዘከር፣
ብትኖርማ …..ኑሮ!
ይህንን እያየህ ዝም .. !! ጭጭ ..!! ጸጥ..!! አትልም ነበር፡፡
አይኖቼን ገርብቤ፡ በሽንፍላየ ጭራ፣
በተዋጠ ልሳን ፡ ስምህን ስጠራ፣
እጆቼን ግራ ቀኝ፡ ላገኝህ ስዳብስ፣
ዳናህ ጠፍቶብኛል ፡ ጋርዶሀል ክፉ አድማስ፡፡
ብትሰማኝ ..ኑሮ፣
ብታየኝም …ኑሮ፣
ብትኖርማ ኑሮ፣
የማይጨክን ልብህ፡ አንጀትህ ተቋጥሮ፣
ነጭ ሜዳ አውርሰህ ፡ ጥለኸኝ….ሸሽተኸኝ ፣
እቅፍ ትቢያ አስታቅፈህ፡ ባዶነት ችረኸኝ፣
የምኞት እንጀራ፡ በተስፋ አጓጉተህ ፡ ወኔ አስታጠከኝ፡፡
ሽንገላው በዛና፡ ስታለል የሰማ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሲሉኝ ፡ መልሱን ባልተቸገርኩ ፡
ኑረህ ቢሆንማ፡፡
ዙሮ ዙሮ ከቤት፡ ኑሮ ኑሮ ከሞት፣
ድንገት ቢታወሰኝ ፡ የእነ ማማ ተረት፣
ሳይገለጥልኝ ፡ሳይገባኝ ሚስጥሩ፣
ለካስ ከጥንት ነው፡ አንተም ኑረህ ኑረህ ፡
የጠፋህ ካገሩ፡፡
የጊዜየን ቋጥኝ ፡ ዕፍኝ ተመልክቶ፣
ከኔ መራቅህን፡ ጠረኑን አሽትቶ፣
ከቶ ማን ጠየቀኝ ፡ ከሰውነት ቆጥሮ፣
ዝም አትልም ነበር፡ ብትኖርማ …..ኑሮ!፡፡
የለህም!! ..የለህም!! ፡ አለሁ እንዳትለኝ፣
ባንተ የተራብኩኝ ፡ ኑሮ ዕያጎበጠኝ፣
ኑሮ የተጠማሁ ፡ የጎዳና ልጅ ነኝ፡፡
አለሁ እንዳትለኝ፣
የመጎሳቆሌን ፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ወዳጅህ እልፍ ነው..፣
ደጋፊህ መንጋ ነው፣
ጠያቂህ ብዙ ነው ፣
ረጋሚህ ድርብ ፡ ስፍር ቁጥር አልባ፣
ኑሮ የጠፋበት ፡ ኑሮ እንዴት ነው ይላል፡
ያገኘው ይመስል ፡ በሌሎች አንቀልባ፡፡
ስላንተ ተጨንቆ ፡ ዘወትር ጧት ማታ፣
ኑሮ እንዴት ነው ሁኗል ፡ የግዚሄር ሰላምታ፡፡
የመጎሳቆሌን፡ የቱጃሬን እጣ፣
ታስራለች ህይወቴ ፡ ከእቅፍህ እንዳትወጣ፡፡
ኑሮ እንደት ነው ላለኝ!፣
እሱማ ምን ጎሎት፡
ይመስገን ደህና ነው! በጎ ነው እላለሁ፡፡
#Gizatu_Amare
@getem
@getem