👉የ ማስቲካ ቅሬታ...
.
በክብር ተቀምጬ..
ካለሁበት ልጣጭ
አዉጥተዉ ሲያኝኩኝ..
እንዳልሰጠሁ ጣፋጭ
ጥፍጥናዬ ሲያልቅ...
እ ን ት ፍ...ብለዉ ተፉኝ😔
ለ ኣፋቸዉ ጠረን...
ደስ የሚል መኣዛ...
ቃና እንዳልሰጠሁኝ።😏
____/____
/
F.D.N
07/09/2011
@getem
@getem
@gebriel_19
.
በክብር ተቀምጬ..
ካለሁበት ልጣጭ
አዉጥተዉ ሲያኝኩኝ..
እንዳልሰጠሁ ጣፋጭ
ጥፍጥናዬ ሲያልቅ...
እ ን ት ፍ...ብለዉ ተፉኝ😔
ለ ኣፋቸዉ ጠረን...
ደስ የሚል መኣዛ...
ቃና እንዳልሰጠሁኝ።😏
____/____
/
F.D.N
07/09/2011
@getem
@getem
@gebriel_19
🏿"በጭስ ተደብቄ"
መሄጃ ቢጠፋኝ ካንቺ ምርቅበት
አንቺን ሳላስጨንቅ እኔም ሳልጨነቅ
ዝም ከምልበት
ጭስን ምርጫዬ አረኩ
መደበቅን ወሰንኩ
ቀንም ሌትም በጭስና ሀሳብ
ስብሰለሰል ዉዬ
ሰውነቴ አልቆ በማሽን የላጉት
ጣዉላ መስዬ
ሰው ሁሉ በዓይኑ እየሳተ ያልፈኛል
ምን ብዬ ልንገርሽ ሰማይና ምድሩ
ገደል ሆኖብኛል
እየሄድኩ ቃዣለዉ እለፈልፋለው
አሁን አሁንማ ድምፄ ተለዉጦ
ጃዟ ያለቀባት ቴፕ መስያለው
በጭስ ዉስጥ ስደበቅ
ሰላም ይሰማኛል
አንቺን አንቺን ያየው
ከቅፌ የገባሽ መስሎ ይሰማኛል
አዎ እራሴን ልጣ ሰዉነቴም ይለቅ
ሱሪዬም ይካደኝ
መቀመጥ አቅቶት ከላዬላይ ወልቆ
እርቃኔን ያስቀረኝ
አንቺን ማጣት ለኔ ከዚህም በላይ ነው
ከገነት ተጥሎ ወደሲኦል ገብቶ
መቃጠል ያክል ነው
አዎ አጨሳለው በደምብ አጨሳለው
በጭስ ተከብቤ ሳልምሽ ኖራለው
አንቺ ማለት ለኔ ከምንም በላይ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ የፍቅር መማርያዬ
ልዩ ብዕሬ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ ፍቅርን ያየሁብሽ
ልዬ ብሌኔ ነሽ
በዓይኖቼ ያላየሁሽ እየሸሸው የወደድኩሽ
አንቺ ለኔ ልዬ ሴት ነሽ
@AtiTaAdi
@getem
@getem
መሄጃ ቢጠፋኝ ካንቺ ምርቅበት
አንቺን ሳላስጨንቅ እኔም ሳልጨነቅ
ዝም ከምልበት
ጭስን ምርጫዬ አረኩ
መደበቅን ወሰንኩ
ቀንም ሌትም በጭስና ሀሳብ
ስብሰለሰል ዉዬ
ሰውነቴ አልቆ በማሽን የላጉት
ጣዉላ መስዬ
ሰው ሁሉ በዓይኑ እየሳተ ያልፈኛል
ምን ብዬ ልንገርሽ ሰማይና ምድሩ
ገደል ሆኖብኛል
እየሄድኩ ቃዣለዉ እለፈልፋለው
አሁን አሁንማ ድምፄ ተለዉጦ
ጃዟ ያለቀባት ቴፕ መስያለው
በጭስ ዉስጥ ስደበቅ
ሰላም ይሰማኛል
አንቺን አንቺን ያየው
ከቅፌ የገባሽ መስሎ ይሰማኛል
አዎ እራሴን ልጣ ሰዉነቴም ይለቅ
ሱሪዬም ይካደኝ
መቀመጥ አቅቶት ከላዬላይ ወልቆ
እርቃኔን ያስቀረኝ
አንቺን ማጣት ለኔ ከዚህም በላይ ነው
ከገነት ተጥሎ ወደሲኦል ገብቶ
መቃጠል ያክል ነው
አዎ አጨሳለው በደምብ አጨሳለው
በጭስ ተከብቤ ሳልምሽ ኖራለው
አንቺ ማለት ለኔ ከምንም በላይ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ የፍቅር መማርያዬ
ልዩ ብዕሬ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ ፍቅርን ያየሁብሽ
ልዬ ብሌኔ ነሽ
በዓይኖቼ ያላየሁሽ እየሸሸው የወደድኩሽ
አንቺ ለኔ ልዬ ሴት ነሽ
@AtiTaAdi
@getem
@getem
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰካራሙ ሴራ
ሴራ በዚህ አገባብ ተንኮል የሚለውን አቻ ፍቺ ይዞ የሚገኝ ሳይሆን ይልቁንም በልብ-ወለድ፣ በፊልም ድርሰትና በመሳሰሉት አላባ ሆኖ ምናገኘውን ‹ሴራ› ማለትም ምክንያትንና ውጤትን በአንድ ላይ በመያዝ የታሪኩን ቅጥጥል የሚፈጥርልን እንደ ማለት ነው፡፡
ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc
@getem
@getem
ሴራ በዚህ አገባብ ተንኮል የሚለውን አቻ ፍቺ ይዞ የሚገኝ ሳይሆን ይልቁንም በልብ-ወለድ፣ በፊልም ድርሰትና በመሳሰሉት አላባ ሆኖ ምናገኘውን ‹ሴራ› ማለትም ምክንያትንና ውጤትን በአንድ ላይ በመያዝ የታሪኩን ቅጥጥል የሚፈጥርልን እንደ ማለት ነው፡፡
ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc
@getem
@getem
#ረድኤት_አሰፋ
ከዛኛው መደዳ ፥
"ፍሬ ነሳኝ" ብላ፥ ባምላኳ ያቄመች፤
ሰልፏን አመናቅራ፥
ከዚኛው መደዳ ፥መጥታ ተሰለፈች፤
ልጁን የሰጣትን፥
የሰልፏን ፈጣሪ፥ በልጇ ቀየረች።
ከዚኛው መደዳ፥
ፍሬው የከበበው ፥ምንዱብ መፃተኛ፤
የጨቅላ ጉሮሮ፥
ለመድፈን ሲዳክር ፥ይነጋል ሳይተኛ።
ምሬት አስረግዞ፥
ልጅና ማጣቱን፤ ማዘል ያደከመው
ከዚህ ሰልፉን ትቶ፥
ከዛ ለመሰለፍ፥ የለም የቀደመው።
ፍላጎት ሲነግስ፥
ጥማት ልክ ሲያጣ፥ መሻት መርን ሲለቅ፤
በራስ እየለኩ፥
ፈጣሪን መቅረጽ ነው፥ የዘመኑ ማወቅ።
@getem
@getem
@gebriel_19
ከዛኛው መደዳ ፥
"ፍሬ ነሳኝ" ብላ፥ ባምላኳ ያቄመች፤
ሰልፏን አመናቅራ፥
ከዚኛው መደዳ ፥መጥታ ተሰለፈች፤
ልጁን የሰጣትን፥
የሰልፏን ፈጣሪ፥ በልጇ ቀየረች።
ከዚኛው መደዳ፥
ፍሬው የከበበው ፥ምንዱብ መፃተኛ፤
የጨቅላ ጉሮሮ፥
ለመድፈን ሲዳክር ፥ይነጋል ሳይተኛ።
ምሬት አስረግዞ፥
ልጅና ማጣቱን፤ ማዘል ያደከመው
ከዚህ ሰልፉን ትቶ፥
ከዛ ለመሰለፍ፥ የለም የቀደመው።
ፍላጎት ሲነግስ፥
ጥማት ልክ ሲያጣ፥ መሻት መርን ሲለቅ፤
በራስ እየለኩ፥
ፈጣሪን መቅረጽ ነው፥ የዘመኑ ማወቅ።
@getem
@getem
@gebriel_19
[#ፋሲል_ስዩም]
.
ጥፎ ለባሽ!
...///...
ደጋን ጨባጭ መዳፍ፣ቀስትን አስፈንጣሪ፣
የንድ አሳብ ዐውድ፣የፊደል ቃራሚ፣
አጁ 'የሻከረ፣
ጣቱ የተቃማ፣
ልባሱ ተቀዶ፣ገላው የደማማ፣
ሱሪው የወለቀ፣ሳያብድ ያበደ፣
የሰው'ነቱን ልኬት፣አስሮ ያነደ፣
በምናብ የሚነጉድ፣
በምናብ የሚነድ፣
ለምናብ የሚሰግድ፣
'ራቁታም ጫሪ፣
ራቁት ሰዐሊ፣
ራቁት ደራሲ፣
ራቁት አንባቢ፣
የሲቃውን ንባል በብዕሩ አርካሽ፣
ቅዳዱ ልባቡን ዳግ ጥፎ ለባሽ!
...///...
@getem
@getem
@gebriel_19
.
ጥፎ ለባሽ!
...///...
ደጋን ጨባጭ መዳፍ፣ቀስትን አስፈንጣሪ፣
የንድ አሳብ ዐውድ፣የፊደል ቃራሚ፣
አጁ 'የሻከረ፣
ጣቱ የተቃማ፣
ልባሱ ተቀዶ፣ገላው የደማማ፣
ሱሪው የወለቀ፣ሳያብድ ያበደ፣
የሰው'ነቱን ልኬት፣አስሮ ያነደ፣
በምናብ የሚነጉድ፣
በምናብ የሚነድ፣
ለምናብ የሚሰግድ፣
'ራቁታም ጫሪ፣
ራቁት ሰዐሊ፣
ራቁት ደራሲ፣
ራቁት አንባቢ፣
የሲቃውን ንባል በብዕሩ አርካሽ፣
ቅዳዱ ልባቡን ዳግ ጥፎ ለባሽ!
...///...
@getem
@getem
@gebriel_19
ስም ኣጣሁልሽ..
የ ቋንቋዎች ሚስጥር
የ ፈጣሪ ድንቅ ስራ
የ አምላኬ ልዩ ቀመር
እማ...
ኣንቺ ማለት እናትነት
እናትነት ፈጣሪነት...
ተፈጥረሽ የምትፈጥሪ
የፈጣሪ ድንቅ ስሌት
ኣንቺነትን ዪገልፅ ዪመስል
ስም ሰይመዉ በ ሁለት ፊደል
እማ...ቢሉሽ ምን ሊፈይድ
ስምሽ ከ አንቺ ሳዪዋሃድ
እማ የሚለዉ ጠባቡ ቃል
ተግባርሽን ላያሰላዉ
ላይገልፅልኝ የፍቅሬን ጥግ
ላንቺ የሚሆን ስም ፍለጋ
ከ ስሞች መሃል ስም ስምግ
ስም ባጣ እንኳን ስም አልፈልግ
ላወጣልሽ ኣልኳትንም
ለ አንቺ የሚሆን ስምፍለጋ
ካል ገጥሜ ስም አልሰራም፡፡
===/===
ቀን፡21/03/2011 በ፡ፊራኦል ደሰታ✍
@getem
@getem
@gebriel_19
የ ቋንቋዎች ሚስጥር
የ ፈጣሪ ድንቅ ስራ
የ አምላኬ ልዩ ቀመር
እማ...
ኣንቺ ማለት እናትነት
እናትነት ፈጣሪነት...
ተፈጥረሽ የምትፈጥሪ
የፈጣሪ ድንቅ ስሌት
ኣንቺነትን ዪገልፅ ዪመስል
ስም ሰይመዉ በ ሁለት ፊደል
እማ...ቢሉሽ ምን ሊፈይድ
ስምሽ ከ አንቺ ሳዪዋሃድ
እማ የሚለዉ ጠባቡ ቃል
ተግባርሽን ላያሰላዉ
ላይገልፅልኝ የፍቅሬን ጥግ
ላንቺ የሚሆን ስም ፍለጋ
ከ ስሞች መሃል ስም ስምግ
ስም ባጣ እንኳን ስም አልፈልግ
ላወጣልሽ ኣልኳትንም
ለ አንቺ የሚሆን ስምፍለጋ
ካል ገጥሜ ስም አልሰራም፡፡
===/===
ቀን፡21/03/2011 በ፡ፊራኦል ደሰታ✍
@getem
@getem
@gebriel_19
ቀጥሮኝ ጠፋ ብለሽ
ስልኩ ዝግ ነው ብለሽ ፣እንዳትናደጂ
ፓወር ባንክ ያላት ጋር
ቻርጅ እያደረኩ ፣ አድሬ ነው እንጂ
በሌላ አትጠርጥሪኝ
ሲነጋ ደውዬ ፣ መጣለሁ ሳትቀጥሪኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ስልኩ ዝግ ነው ብለሽ ፣እንዳትናደጂ
ፓወር ባንክ ያላት ጋር
ቻርጅ እያደረኩ ፣ አድሬ ነው እንጂ
በሌላ አትጠርጥሪኝ
ሲነጋ ደውዬ ፣ መጣለሁ ሳትቀጥሪኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ለ'ሷ
1ኛ
ይቺ...
አይሉዋት ነገር
ከብረት ጠጥራ ከድር የሀየለች
ከነብር አኩርፋ ከሠደድ የሞቀች
ከአጥቢያ ውበት ነጥቆ ውበት እሱዋን አርጎ
ነጎድጉዋዱ በርዶ
አለማቱ ላይኑዋ ከነአንገቱ ሠግዶ
እንዴት አንቺ ትባል?
ካጥንቴ ተፈጥራ
ከጎኔ እንደወጣች ቀዳማዊት ሄዋን ሥያሜዋ ይቅለል?
2ኛ
አንተም....
እንዳትባል
ከእ'ርግብ ለሥልሣ ከንብ የወዘነች
እንደአሮን ብትር ታጥፋ የተቃናች
እኩይ ፈገግተዋ........
ከሰማይ ክዋክብት ከጨርቃ ደምቆ ከፀሀየ የላቀች
ካናት እንደወጣ አደንዛዥ ቅራሬ ከደም የወፈረች
እንዴት አንተ ትባል?
ቅጠልን በእግዜሄር ቀይሮ በሚያብል
3ኛ
ስያሜ ማጣቴ.....
ለሥርንቅ ደረቷ
ፍቅር ነው መክሊቷ
@getem
@getem
1ኛ
ይቺ...
አይሉዋት ነገር
ከብረት ጠጥራ ከድር የሀየለች
ከነብር አኩርፋ ከሠደድ የሞቀች
ከአጥቢያ ውበት ነጥቆ ውበት እሱዋን አርጎ
ነጎድጉዋዱ በርዶ
አለማቱ ላይኑዋ ከነአንገቱ ሠግዶ
እንዴት አንቺ ትባል?
ካጥንቴ ተፈጥራ
ከጎኔ እንደወጣች ቀዳማዊት ሄዋን ሥያሜዋ ይቅለል?
2ኛ
አንተም....
እንዳትባል
ከእ'ርግብ ለሥልሣ ከንብ የወዘነች
እንደአሮን ብትር ታጥፋ የተቃናች
እኩይ ፈገግተዋ........
ከሰማይ ክዋክብት ከጨርቃ ደምቆ ከፀሀየ የላቀች
ካናት እንደወጣ አደንዛዥ ቅራሬ ከደም የወፈረች
እንዴት አንተ ትባል?
ቅጠልን በእግዜሄር ቀይሮ በሚያብል
3ኛ
ስያሜ ማጣቴ.....
ለሥርንቅ ደረቷ
ፍቅር ነው መክሊቷ
@getem
@getem
ለማይበራ መብራት ፣ ቀብድ እየከፈልኩኝ
ለማይሰራ ኔትወርክ ፣ ካርድ እየገበርኩኝ
ሁሉ ነይ የሚላት፣ ቆንጆ ሴት አፍቅሬ
የማትመጣ ውሃ
የማትመጣ መብራት
የማትመጣ ሴትን ፣ አንድ ላይ ቀጥሬ
ዘልአለም ሳልሰለች ፣ ስኖር በጥበቃ
ብትቀሪ ምን ግዴ
ቢፈራረቁብኝ ፣ ጠሐይና ጨረቃ
ትመጣለች የሚል
ግጥም እየፃፍኩ ፣ ልጠብቅሽ በቃ
(በላይ በቀለ ወያ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ለማይሰራ ኔትወርክ ፣ ካርድ እየገበርኩኝ
ሁሉ ነይ የሚላት፣ ቆንጆ ሴት አፍቅሬ
የማትመጣ ውሃ
የማትመጣ መብራት
የማትመጣ ሴትን ፣ አንድ ላይ ቀጥሬ
ዘልአለም ሳልሰለች ፣ ስኖር በጥበቃ
ብትቀሪ ምን ግዴ
ቢፈራረቁብኝ ፣ ጠሐይና ጨረቃ
ትመጣለች የሚል
ግጥም እየፃፍኩ ፣ ልጠብቅሽ በቃ
(በላይ በቀለ ወያ)
@getem
@getem
@gebriel_19
እጠብቅሻለው(be tsega(melos))
………………………
ጥለሽኝ ብትሄጂ
ፍቅሬን ሳትርጂ
መውደዴን ሳታውቂ
ውስጤን ሳጠይቂ
ህመሜ ሳይገባሽ
ድህነቴን አይተሽ
ጥለሽኝ ብትሄጂ
ሌላ ገላ ለምደሽ
ሌላ ጠረን ናፍቀሽ
ነገን ሳታስቢ
በዛሬ ተታለሽ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
ንዋይ አሳውሮሽ
ገንዘብ አደንቁሮሽ
ውሸት እውነት ሆኖ
ባንቺ ላይ ቆንኖ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
አልተቀየምኩሽም
አላዘንኩብሽም
እንዲያውም እንዲያውም
ደጀሰላም ሄጄ ስላንች ለመንኩኝ
ስላንች ማለድኩኝ
አደራ ጠብቃት ብየ ተማፀንኩኝ
እንዲያውም አለሜ እውነቱን ልንገርሽ
እጠብቅሻለው
እድሜየን በሙሉ አንቺን አስባለው
እናፍቅሻለው
ገብቶሽ ከመጣሽም
ያልኖርኩትን ቀን ያልኖርኩትን እድሜ ።
፩ ብየ እጀምራለው ዘመኑን አቁሜ
@getem
@getem
@gebriel_19
………………………
ጥለሽኝ ብትሄጂ
ፍቅሬን ሳትርጂ
መውደዴን ሳታውቂ
ውስጤን ሳጠይቂ
ህመሜ ሳይገባሽ
ድህነቴን አይተሽ
ጥለሽኝ ብትሄጂ
ሌላ ገላ ለምደሽ
ሌላ ጠረን ናፍቀሽ
ነገን ሳታስቢ
በዛሬ ተታለሽ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
ንዋይ አሳውሮሽ
ገንዘብ አደንቁሮሽ
ውሸት እውነት ሆኖ
ባንቺ ላይ ቆንኖ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
አልተቀየምኩሽም
አላዘንኩብሽም
እንዲያውም እንዲያውም
ደጀሰላም ሄጄ ስላንች ለመንኩኝ
ስላንች ማለድኩኝ
አደራ ጠብቃት ብየ ተማፀንኩኝ
እንዲያውም አለሜ እውነቱን ልንገርሽ
እጠብቅሻለው
እድሜየን በሙሉ አንቺን አስባለው
እናፍቅሻለው
ገብቶሽ ከመጣሽም
ያልኖርኩትን ቀን ያልኖርኩትን እድሜ ።
፩ ብየ እጀምራለው ዘመኑን አቁሜ
@getem
@getem
@gebriel_19
የሰንበት ውሎ (ወግ ግጥም)
(ቡሩክ ካሳሁን)
እሁድ እረፋድ ላይ በለተ ሰንበት
ደውላ ጠራችን ከተኛሁበት
‹‹ውዴ ፍቅሬ ሆዴ
ካላንተኮ አትደምቅም አንዲቷ እሁዴ
ምነው አልደወልክም ጠፋህብኝ ዛሬ››
ብላ ብጠይቀኝ በእጆቿ መካከል እጄን አዟዙሬ
‹‹ምንስ አለኝና ካንቺ እለያለሁ
ብርሀኔ እኮ ነሽ ጨለማ እፈራለሁ
ካንቺ ከምነጠል ሞቴን እመርጣለሁ››
በማለት ነግሬያት ከአፌ ሳልጨርስ
‹‹አባቢ አስተዋውቂኝ ስላለኝ ተነስ
ቶሎ ሳይረፋፍድ እቤት እንድረስ››
ብላ እየጎተተች ከቤቷ አድርሳኝ
የአባቷ ሰላምታ ሰላም እየነሳኝ
‹‹በሉ ተጫወቱ›› ብላ ስትነሳ
የአባቷም ምላስ ለነገር ተነሳ፡፡
‹‹እኔ ምልህ ወዳጄ
ለልጄ ባል ልትሆን መተሃል ከደጄ
አንተም በሌጣ እጅህ እኔም በባዶ እጄ
ይልቁን የኔን ልጅ ለማግባት ስትወስን
ታመክ ነበር እንዴ በጽኑ ራስህን?
የኔን ልጅ ለማግባት ምን ያህል ሃብት አለህ?
ቋሚ ተንቀሳቃሽ በራስህ ስም ያለ››
ብለው ቢጠይቁኝ ድምጼን ሞረድኩና
ነገሬን ጀመርኩኝ እንደዚ አልኩና
‹‹እኔ ምለው ልጆት ምን ያህል ብር ናት
ከየትኛው ባንክስ ነው ብድር የጠየኳት?
ይህን ያሉኝ መስፈርት ሰው የሚጠየቀው
ባንክ ቤት በመሄድ ብድር ሲጠይቅ ነው፡፡
ቋሚ ተንቀሳቃሽ አሁን የጠሯቸው
ለኔ እንግዳ ናቸው
በህልም አለም እንጂ በውን ማላውቃቸው››
ይህንን ስላቸው በንቀት ፈገግታ
‹‹እንደ ንግግርህ ሳቄም አይገታ
ተጫዋች ነህ ባክህ እንዲሁም አላጋጭ
ባዶ እጅህን መጥተህ ከኔ ብዙ ነዋይ የምትል እናጋጭ
ከመሳሪያ ይልቅ ለደረሰኝ ደንጋጭ››
ሲሉኝ
‹‹አሾፉበት እንጂ የኔ ድህነቴ
ከቶውን አያንስም ለኔና ለቤቴ
ተምሬያለሁና ነገ በእውቀቴ
ሀብት እራሱ ይመጣል በፅኑ ጥረቴ››
ስላቸው
‹‹እስኪ አትንዛብኝ የማይመስል ተረት
ለወደፊት እንጂ ለአሁን የሌለበት
በቸገረህ ጊዜ ማትጠቀምበት
ይልቁን አትልፋ ብለህ እሷን አገኝ
ላጤ ቱጃር በዝቶ ተርፎ ስለሚገኝ
ለአንዱ ከበርቴ ድሬ እጠራሀለሁ
ታዲያ እንዳትቀር አሳስብሀለሁ››
ሲሉኝ ተናድጄ
በነገሩ አብጄ
‹‹ለምን በአክሲዮን ለብዙ ሀብታሞች ከፋፍለው አይሸጧትም
ወይንም በይፋ አያጫርቷትም
እሷ ስታልቅቦት ሌላ ሴት የሎትም
በዚ አኳኳኖ ፈራው ለሚስቶትም››
ይህን ተናግሬ በጣም አዘንኩና
ደ በሌለው ደመና
ሽ በሌለው ሽመና
ሁሉም ሲቀር ሆኖ መና
ይህን ሳሰላስል ጎንበስ ሳልል ቀና
ጀርባዬ ደቀቀ በግዙፍ አጠና፡፡
እንኳንስ መናገር መተንፈስ አቆምኩኝ
እንደ እባብ በመሬት እየተጎተትኩኝ
‹‹ውጣልኝ እኮ አልኩህ›› ሚል ድምፅ አዳመጥኩኝ፡፡
የነፍስ ነፍስ ይዞኝ ከዛ ተነስቼ
ራሴን አገኝሁት በራሴው አላጋ ላይ ስባንን ተኝቼ
ህልም እልም ህልም እልም አልኩኝ ደጋግሜ
እንዳይደርስ ፈርቼ የረፋዱ ህልሜ
እሷስ ምን አቃዥቷት ምንስ አልማለች
እንደ ረፋዱ ህልሜ በረፋድ ደወለች፡፡
ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc
@getem
@getem
@gebriel_19
(ቡሩክ ካሳሁን)
እሁድ እረፋድ ላይ በለተ ሰንበት
ደውላ ጠራችን ከተኛሁበት
‹‹ውዴ ፍቅሬ ሆዴ
ካላንተኮ አትደምቅም አንዲቷ እሁዴ
ምነው አልደወልክም ጠፋህብኝ ዛሬ››
ብላ ብጠይቀኝ በእጆቿ መካከል እጄን አዟዙሬ
‹‹ምንስ አለኝና ካንቺ እለያለሁ
ብርሀኔ እኮ ነሽ ጨለማ እፈራለሁ
ካንቺ ከምነጠል ሞቴን እመርጣለሁ››
በማለት ነግሬያት ከአፌ ሳልጨርስ
‹‹አባቢ አስተዋውቂኝ ስላለኝ ተነስ
ቶሎ ሳይረፋፍድ እቤት እንድረስ››
ብላ እየጎተተች ከቤቷ አድርሳኝ
የአባቷ ሰላምታ ሰላም እየነሳኝ
‹‹በሉ ተጫወቱ›› ብላ ስትነሳ
የአባቷም ምላስ ለነገር ተነሳ፡፡
‹‹እኔ ምልህ ወዳጄ
ለልጄ ባል ልትሆን መተሃል ከደጄ
አንተም በሌጣ እጅህ እኔም በባዶ እጄ
ይልቁን የኔን ልጅ ለማግባት ስትወስን
ታመክ ነበር እንዴ በጽኑ ራስህን?
የኔን ልጅ ለማግባት ምን ያህል ሃብት አለህ?
ቋሚ ተንቀሳቃሽ በራስህ ስም ያለ››
ብለው ቢጠይቁኝ ድምጼን ሞረድኩና
ነገሬን ጀመርኩኝ እንደዚ አልኩና
‹‹እኔ ምለው ልጆት ምን ያህል ብር ናት
ከየትኛው ባንክስ ነው ብድር የጠየኳት?
ይህን ያሉኝ መስፈርት ሰው የሚጠየቀው
ባንክ ቤት በመሄድ ብድር ሲጠይቅ ነው፡፡
ቋሚ ተንቀሳቃሽ አሁን የጠሯቸው
ለኔ እንግዳ ናቸው
በህልም አለም እንጂ በውን ማላውቃቸው››
ይህንን ስላቸው በንቀት ፈገግታ
‹‹እንደ ንግግርህ ሳቄም አይገታ
ተጫዋች ነህ ባክህ እንዲሁም አላጋጭ
ባዶ እጅህን መጥተህ ከኔ ብዙ ነዋይ የምትል እናጋጭ
ከመሳሪያ ይልቅ ለደረሰኝ ደንጋጭ››
ሲሉኝ
‹‹አሾፉበት እንጂ የኔ ድህነቴ
ከቶውን አያንስም ለኔና ለቤቴ
ተምሬያለሁና ነገ በእውቀቴ
ሀብት እራሱ ይመጣል በፅኑ ጥረቴ››
ስላቸው
‹‹እስኪ አትንዛብኝ የማይመስል ተረት
ለወደፊት እንጂ ለአሁን የሌለበት
በቸገረህ ጊዜ ማትጠቀምበት
ይልቁን አትልፋ ብለህ እሷን አገኝ
ላጤ ቱጃር በዝቶ ተርፎ ስለሚገኝ
ለአንዱ ከበርቴ ድሬ እጠራሀለሁ
ታዲያ እንዳትቀር አሳስብሀለሁ››
ሲሉኝ ተናድጄ
በነገሩ አብጄ
‹‹ለምን በአክሲዮን ለብዙ ሀብታሞች ከፋፍለው አይሸጧትም
ወይንም በይፋ አያጫርቷትም
እሷ ስታልቅቦት ሌላ ሴት የሎትም
በዚ አኳኳኖ ፈራው ለሚስቶትም››
ይህን ተናግሬ በጣም አዘንኩና
ደ በሌለው ደመና
ሽ በሌለው ሽመና
ሁሉም ሲቀር ሆኖ መና
ይህን ሳሰላስል ጎንበስ ሳልል ቀና
ጀርባዬ ደቀቀ በግዙፍ አጠና፡፡
እንኳንስ መናገር መተንፈስ አቆምኩኝ
እንደ እባብ በመሬት እየተጎተትኩኝ
‹‹ውጣልኝ እኮ አልኩህ›› ሚል ድምፅ አዳመጥኩኝ፡፡
የነፍስ ነፍስ ይዞኝ ከዛ ተነስቼ
ራሴን አገኝሁት በራሴው አላጋ ላይ ስባንን ተኝቼ
ህልም እልም ህልም እልም አልኩኝ ደጋግሜ
እንዳይደርስ ፈርቼ የረፋዱ ህልሜ
እሷስ ምን አቃዥቷት ምንስ አልማለች
እንደ ረፋዱ ህልሜ በረፋድ ደወለች፡፡
ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc
@getem
@getem
@gebriel_19
___
አእላፍ ስሞች
___
ቢለያይም ስረው ቃሉ
ባይገባንም ውስጠ ውሉ
አንደ ነው ወርቁ ቅኔው
ታትሟል ላንለያየው
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ
እስር ነው ትርጉሙ ማይፈታ
ሀገር ማለት እናት
እናት ማለት ፍቅር
ፍቅር ማለት ሚስጥር
ሚስጥር ማለት እኛ
እነዲሁ በየቦታው
ከቶ ማንነገር
ከቶ ማንዘከር
የሺዎች ደም ፍላፃ
አትመው ያቆሟት በማይናድ ህንፃ
የፍቅር ሁሉ ጥግ የመዋደድ ሸማ
ሀገር ማለትማ
የሰላም ምልክት የአንድነት አርማ
ሀገር ማለትማ
እናት ማለትማ
ፍቅር ማለትማ
ሚስጥር ማለትማ
እኛ ማለትማ
የአንድ መፅሐፍ እልፍ ገፆች
የአንድ ሀገር እልፍ ስሞች
ምንም ቢለያይም ስረው ቃሉ
ባይገባንም ውስጠ ውሉ
አንደ ነው ወርቁ ቅኔው
ታትሟል ላንለያየው
ታድያ ምን ያረጋል
ዛሬዛሬ
አጥንት ስንበረብር
አያቴ ቅድመ አያቴ ቅምቅም አያቴ
እያልን ስንቆጥር የዚህ ዘር ነኝ በምንዥላቴ
የዘር ዛር አንደፍድፎን
የቆምን መስሎን ሳንቆም ቁመን
የዘጠኝ ወር የስቃይ ጣር
ልናረዝም የምንታትር
የተማርነው ሳይገባን ገብቶን
እየተናጥን በደም እቶን
ኤጭ ድንቄም መማር መመራመር
ሳናውቀው የሰው መሆንን ሚስጢር
ኤጭ ብርቄም ማወቅ መራቀቅ
ላይቆሙ ለእልፍ ዘመን መንፏቀቅ
ብቻ ብቻ
ሰሚ ካለ ይስማ
ላልሰማም ያሰማ
ሀገር ማለት እናት
እናት ማለት ፍቅር
ፍቅር ማለት ሚስጥር
ሚስጥር ማለት እኛ
እነዲሁ በየቦታው
ከቶ ማንነገር
ከቶ ማንዘከር።
ፀጋዬ ግርማ(ሜሎስ)
@getem
@getem
@gebriel_19
አእላፍ ስሞች
___
ቢለያይም ስረው ቃሉ
ባይገባንም ውስጠ ውሉ
አንደ ነው ወርቁ ቅኔው
ታትሟል ላንለያየው
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ
እስር ነው ትርጉሙ ማይፈታ
ሀገር ማለት እናት
እናት ማለት ፍቅር
ፍቅር ማለት ሚስጥር
ሚስጥር ማለት እኛ
እነዲሁ በየቦታው
ከቶ ማንነገር
ከቶ ማንዘከር
የሺዎች ደም ፍላፃ
አትመው ያቆሟት በማይናድ ህንፃ
የፍቅር ሁሉ ጥግ የመዋደድ ሸማ
ሀገር ማለትማ
የሰላም ምልክት የአንድነት አርማ
ሀገር ማለትማ
እናት ማለትማ
ፍቅር ማለትማ
ሚስጥር ማለትማ
እኛ ማለትማ
የአንድ መፅሐፍ እልፍ ገፆች
የአንድ ሀገር እልፍ ስሞች
ምንም ቢለያይም ስረው ቃሉ
ባይገባንም ውስጠ ውሉ
አንደ ነው ወርቁ ቅኔው
ታትሟል ላንለያየው
ታድያ ምን ያረጋል
ዛሬዛሬ
አጥንት ስንበረብር
አያቴ ቅድመ አያቴ ቅምቅም አያቴ
እያልን ስንቆጥር የዚህ ዘር ነኝ በምንዥላቴ
የዘር ዛር አንደፍድፎን
የቆምን መስሎን ሳንቆም ቁመን
የዘጠኝ ወር የስቃይ ጣር
ልናረዝም የምንታትር
የተማርነው ሳይገባን ገብቶን
እየተናጥን በደም እቶን
ኤጭ ድንቄም መማር መመራመር
ሳናውቀው የሰው መሆንን ሚስጢር
ኤጭ ብርቄም ማወቅ መራቀቅ
ላይቆሙ ለእልፍ ዘመን መንፏቀቅ
ብቻ ብቻ
ሰሚ ካለ ይስማ
ላልሰማም ያሰማ
ሀገር ማለት እናት
እናት ማለት ፍቅር
ፍቅር ማለት ሚስጥር
ሚስጥር ማለት እኛ
እነዲሁ በየቦታው
ከቶ ማንነገር
ከቶ ማንዘከር።
ፀጋዬ ግርማ(ሜሎስ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ስኬት በፈተና
ህይወት እንደዚህ ናት ፈተናም እንደዛው
በአንዱ ልሂድ ሥትይ ሌላው የሚዘጋው
አማራጭ በበዛው መንገድ እራሥን ከማቁሠል
ጠንካራ መሆን ደርሦ በማብሠልሠል
ይልቁን ልምከርሽ ብሰሚኝ ይሻላል
ተሥፋ በመቁረጥ ውሥጥ መጥፎው ይከተላል
ህይወት አላፊ ናት አላፊም ህይወት ናት
ዛሬ ላይ ቆመሽ ትላንት የምትያት
ኑሮም እንደዛው ነው ብዙ ጣጣ ያመጣል
ሥለዚህ ታገሺ ይህም ሁሉ ያልፋል
በመስራት ያለመከፋት በመልፋት
ህይወትን ቀይሪያት
ለአላፊው ምድር ስኬት ስጦታ ናት
በራሱ ላመነ ድርብ ሽልማት ናት
አይቻልም ያልሽውን ብታይው ሞክረሽ
በውድቀት ውስጥ ሁሉ ስኬት ታገኛለሽ
@getem
@getem
@gebriel_19
ህይወት እንደዚህ ናት ፈተናም እንደዛው
በአንዱ ልሂድ ሥትይ ሌላው የሚዘጋው
አማራጭ በበዛው መንገድ እራሥን ከማቁሠል
ጠንካራ መሆን ደርሦ በማብሠልሠል
ይልቁን ልምከርሽ ብሰሚኝ ይሻላል
ተሥፋ በመቁረጥ ውሥጥ መጥፎው ይከተላል
ህይወት አላፊ ናት አላፊም ህይወት ናት
ዛሬ ላይ ቆመሽ ትላንት የምትያት
ኑሮም እንደዛው ነው ብዙ ጣጣ ያመጣል
ሥለዚህ ታገሺ ይህም ሁሉ ያልፋል
በመስራት ያለመከፋት በመልፋት
ህይወትን ቀይሪያት
ለአላፊው ምድር ስኬት ስጦታ ናት
በራሱ ላመነ ድርብ ሽልማት ናት
አይቻልም ያልሽውን ብታይው ሞክረሽ
በውድቀት ውስጥ ሁሉ ስኬት ታገኛለሽ
@getem
@getem
@gebriel_19
Forwarded from Studio Anaya
መቋደሻ
ከዶሮ ብልት ላይ
ካስራ ሁለት ውስጥ
አንዲት ብልት ሳትኖር
ጠፍታ በድንገት
አባትም ተናዶ
ሲቆጣ ሲዝት
"የት ሄደ?" እያለ
ሲወተውታት....
እናትም ደንግጣ
ሲጠፋት መሸሻ
ለአባት ጥርጣሬ
ስትሆን መጠንሰሻ
የት አባቷ ገባች አወይ መቋደሻ?
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
ከዶሮ ብልት ላይ
ካስራ ሁለት ውስጥ
አንዲት ብልት ሳትኖር
ጠፍታ በድንገት
አባትም ተናዶ
ሲቆጣ ሲዝት
"የት ሄደ?" እያለ
ሲወተውታት....
እናትም ደንግጣ
ሲጠፋት መሸሻ
ለአባት ጥርጣሬ
ስትሆን መጠንሰሻ
የት አባቷ ገባች አወይ መቋደሻ?
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
# በፍቅር፦ስም
----///------------
(ከናሆም አየለ)
--------;;;;;;;---------
ውዴ
እኔ'ና አንቺ በፍቅር ስም
እኔ'ና አንቺ በእውነት ስም
የምኖረው እውነት
የሠራነው ጓደኝነት
የገነባነው የሞቀ ቤት
በፍቅር ስም
ቆሞቀር ከመሆን ደም የቆረጠባት
ብቸኛ ከመሆን ዘመን ያለፈባት
አልያ ደግሞ በመጓጓት
የአልጋ ገድሌን በመመኘት
አዲስ ወዳጅ ፍለጋ ከመንከራተት
በፍቅር ስም ስታጠምጂኝ
በእውነት ስም ስትዋሺኝ
የማላውቅ መስሎሻል?
ይሀውልሽ አለሜ
እኔ ያንቺ አፍቃሪ
የቀደም ሀጥያቴን ባንቺ አስቀያሚነት
የትላንት ማጣቴን ካንቺ ብቸኝነት
አገኘው ይመስል
በእውነት ስም---ዋሸውሽ
በፍቅር ስም----ወደድኩሽ፡፡
@getem
@getem
@lula_al_greeko
----///------------
(ከናሆም አየለ)
--------;;;;;;;---------
ውዴ
እኔ'ና አንቺ በፍቅር ስም
እኔ'ና አንቺ በእውነት ስም
የምኖረው እውነት
የሠራነው ጓደኝነት
የገነባነው የሞቀ ቤት
በፍቅር ስም
ቆሞቀር ከመሆን ደም የቆረጠባት
ብቸኛ ከመሆን ዘመን ያለፈባት
አልያ ደግሞ በመጓጓት
የአልጋ ገድሌን በመመኘት
አዲስ ወዳጅ ፍለጋ ከመንከራተት
በፍቅር ስም ስታጠምጂኝ
በእውነት ስም ስትዋሺኝ
የማላውቅ መስሎሻል?
ይሀውልሽ አለሜ
እኔ ያንቺ አፍቃሪ
የቀደም ሀጥያቴን ባንቺ አስቀያሚነት
የትላንት ማጣቴን ካንቺ ብቸኝነት
አገኘው ይመስል
በእውነት ስም---ዋሸውሽ
በፍቅር ስም----ወደድኩሽ፡፡
@getem
@getem
@lula_al_greeko