//ፍቺ በያይነቱ //
ካንድ ሰው ልብ በቅሎ ዘላለም መለምለም
ሊፈታ የማይችል ከባድ ህልም አይደለም ።
ምጡቅ የሰው አ'ምሮ ባለም ሲያበራ ፤
አንድ ሰው የኖራል ከሚሊዮን ጋራ።
ኃይሌን ባልጠቀም አንድ ሰው ባልሰራ፤
እንኳንስ ባንቺ ልብ በቅዬ ላፈራ፤
መኖሩ ከበደኝ አኔው ከኔው ጋራ ።
ደረጄ ደኜ (ጄጄ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ካንድ ሰው ልብ በቅሎ ዘላለም መለምለም
ሊፈታ የማይችል ከባድ ህልም አይደለም ።
ምጡቅ የሰው አ'ምሮ ባለም ሲያበራ ፤
አንድ ሰው የኖራል ከሚሊዮን ጋራ።
ኃይሌን ባልጠቀም አንድ ሰው ባልሰራ፤
እንኳንስ ባንቺ ልብ በቅዬ ላፈራ፤
መኖሩ ከበደኝ አኔው ከኔው ጋራ ።
ደረጄ ደኜ (ጄጄ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል Digital መፅሔት.pdf
4.3 MB
///////√ፍቅር/////////
.
ቀመር አታምጪብኝ
ፍቅር ሂሳብ መች ያውቃል?
ስሌቱን ካበዛን
ከ'ሩት' ውስጥ ሲወጣ መዋደድ ያበቃል
.
ያን ንፁህ ፍቅራችን
'ራዲካል' ውስጥ ገፍተን ውጤቱን ካሰላን
ያዋደደን ቃል ነው መልሶ ሚያጣላን
ለምሳሌ ስሪው….
√አጭሩን ቁመቴን አስቀያሚው መልኬን
√ባዶ ኪሴን' ይዘሽ 'ሩት' ውስጥ አስገቢያቸው
ፍቅርን አያመጡም
ጥላቻ ክህደት ነው የሂሳብ ውጤታቸው
ለምሳሌ ልስራው…
√ውበት የከለለው ነዝናዛ ዓመልሽን
√ቁመት የሸፈነው አጭሩ ሃሳብሽን
'ሩት' ውስጥ ካስገባሁት
ከዚህ ሁላ ውበት
ዓመልሽ ነው ሚቀር
ምኑን ኑሮ ኖርኩት?
.…
አምላክም ሲያስተምር
የፍቅርን እውነት
ለጠይም ለጥቁር
ለቀይ ብሎ አይደለም የተሰቀለለት
ከጥንትም ጀምሮ…
'ራዲካል' አልገባም የፍቅር ተመኑ
ለሁሉም ተሰጥቷል ሳያዩ ላመኑ
.…
እናትም ልጆቿን ፍቅር ስትሰጣቸው
'ሩት' ውስጥ መች ይገባል
መልክ ቀለማቸው?
.
ስለዚህ የኔ ውድ..
ብታምኚም ባታምኚም
ካንቺ ጋር አጣምሮ ያዘለቀን እውነት
ስላልቻልንበት ነው
የ'ራዲካል' ቀመር ሂሳብ ሚሉት ዕውቀት
ስለዚህ አፍርሺው...
ጅምር 'ራዲካልሽ' ሳይሰላ ይቅር
√ፍቅር…* √ፍቅር…= ፍቅር
(ልዑል ሀይሌ)
@lula_al_greeko
@getem
@getem
.
ቀመር አታምጪብኝ
ፍቅር ሂሳብ መች ያውቃል?
ስሌቱን ካበዛን
ከ'ሩት' ውስጥ ሲወጣ መዋደድ ያበቃል
.
ያን ንፁህ ፍቅራችን
'ራዲካል' ውስጥ ገፍተን ውጤቱን ካሰላን
ያዋደደን ቃል ነው መልሶ ሚያጣላን
ለምሳሌ ስሪው….
√አጭሩን ቁመቴን አስቀያሚው መልኬን
√ባዶ ኪሴን' ይዘሽ 'ሩት' ውስጥ አስገቢያቸው
ፍቅርን አያመጡም
ጥላቻ ክህደት ነው የሂሳብ ውጤታቸው
ለምሳሌ ልስራው…
√ውበት የከለለው ነዝናዛ ዓመልሽን
√ቁመት የሸፈነው አጭሩ ሃሳብሽን
'ሩት' ውስጥ ካስገባሁት
ከዚህ ሁላ ውበት
ዓመልሽ ነው ሚቀር
ምኑን ኑሮ ኖርኩት?
.…
አምላክም ሲያስተምር
የፍቅርን እውነት
ለጠይም ለጥቁር
ለቀይ ብሎ አይደለም የተሰቀለለት
ከጥንትም ጀምሮ…
'ራዲካል' አልገባም የፍቅር ተመኑ
ለሁሉም ተሰጥቷል ሳያዩ ላመኑ
.…
እናትም ልጆቿን ፍቅር ስትሰጣቸው
'ሩት' ውስጥ መች ይገባል
መልክ ቀለማቸው?
.
ስለዚህ የኔ ውድ..
ብታምኚም ባታምኚም
ካንቺ ጋር አጣምሮ ያዘለቀን እውነት
ስላልቻልንበት ነው
የ'ራዲካል' ቀመር ሂሳብ ሚሉት ዕውቀት
ስለዚህ አፍርሺው...
ጅምር 'ራዲካልሽ' ሳይሰላ ይቅር
√ፍቅር…* √ፍቅር…= ፍቅር
(ልዑል ሀይሌ)
@lula_al_greeko
@getem
@getem
" ሸገር ........"
( በአምባዬ ጌታነህ )
ጫኝ አውራጁ፣
መጭ ሀጁ፣
የያዘውን ለሰው ሰቶ፣
የሚመጣው ከመርካቶ፣
ፔስታል ሻንጣ አገልድሞ፣
መንገደኛው ትውኪያ ታሞ።
የመኪናው ግፊያ ልፊያ፣
ቦታ ታቶ ለማለፊያ፣
አንዱ ከአንዱ እንደ አዳል በግ፣
በመላተም ሲበረግግ፣
ይቅር ብሎ ፈጥኖ ሲሄድ፣
ከፒያሳ አራትኪሎ፣
ወገቧ እስር ተጠቅልሎ ፣
ታየኝ ከሩቅ ተረከዟ
ሎሚ መስሎ።
ለሲኒማ ተሰላፊው፣
ታክሲ ብሎ ተሰላፊው
በመንገድ ዳር አምፒር ጓሮ፣
እስከ ትሬን ታጥፎ ዞሮ፣
ከመስሪያቤት ከወደ ሱቅ፣
ሁሉም ሲሄድ ፀሀይ ስጠልቅ፣
ሳታናግር ሚያናግሩህ፣
የመንገድ ዳር ቋሚ ሴቶች፣
ሳይሰስቱ በፍራንካ
ገላቸውን ቸርቻሪወች።
በዛ ደግሞ በበረንዳው፣
አለ ምስኪን የበረደው፣
ከሌሎቹ ጓደኞቹ
አቡጀዴ እየቀማ፣
የሚታገል ለመተኛት
ለደቂቃ ማያቅማማ።
ሰካራሙ ሰካራሟ፣
እንደ እሱ አቅም
እንደ እሷ አቅም፣
አሰቡና ትራፊ አልኮል
ሲጠማቸው እንዲጠጡት፣
በቀጭቀጮ ቀድተው ያዙት።
ብርዱ ቁረን ያልገታቸው፣
የጎዳናው ዳር ጀብሎዎች፣
ባለ ላዳ ኮንትራቶች፣
ከዳንኪራ ጩኸት ቤቶች፣
ወተህ ማዶ ስታማትር
ከእሳት ጋራ የሚጣሉ፣
አሉ እንቁላል ሚቀቅሉ።
አየ ወልዶ መሀን መሆን፣
አጥንት መሳይ ያልሰራላት፣
ቂንቂኗ አፍላ ወጣት፣
በውል ሩጣ ያልጠገበች፣
ይሄው በሌት
ከቡና ቤት
ብድር ፀጉሯን ላያት ሁሉ
ከጥቅሻ ጋር ነሰነሰች።
ሸገር እናት ሆደ ሰፊ፣
የማትሰለች ሁሉ አቃፊ፣
የሁሉም ሰው የሁሉ እናት፣
ያም የእኔ ናት አይበላት፣
ለምን ሸገር ምን በወጣት
ለአንዱ ሆና የሚጨንቃት።
መልካም ቅዳሜ !!
ለሀሳብ አስተያየት @amba8
ለመቀላቀል @amba88
@getem
@getem
@gebriel_19
( በአምባዬ ጌታነህ )
ጫኝ አውራጁ፣
መጭ ሀጁ፣
የያዘውን ለሰው ሰቶ፣
የሚመጣው ከመርካቶ፣
ፔስታል ሻንጣ አገልድሞ፣
መንገደኛው ትውኪያ ታሞ።
የመኪናው ግፊያ ልፊያ፣
ቦታ ታቶ ለማለፊያ፣
አንዱ ከአንዱ እንደ አዳል በግ፣
በመላተም ሲበረግግ፣
ይቅር ብሎ ፈጥኖ ሲሄድ፣
ከፒያሳ አራትኪሎ፣
ወገቧ እስር ተጠቅልሎ ፣
ታየኝ ከሩቅ ተረከዟ
ሎሚ መስሎ።
ለሲኒማ ተሰላፊው፣
ታክሲ ብሎ ተሰላፊው
በመንገድ ዳር አምፒር ጓሮ፣
እስከ ትሬን ታጥፎ ዞሮ፣
ከመስሪያቤት ከወደ ሱቅ፣
ሁሉም ሲሄድ ፀሀይ ስጠልቅ፣
ሳታናግር ሚያናግሩህ፣
የመንገድ ዳር ቋሚ ሴቶች፣
ሳይሰስቱ በፍራንካ
ገላቸውን ቸርቻሪወች።
በዛ ደግሞ በበረንዳው፣
አለ ምስኪን የበረደው፣
ከሌሎቹ ጓደኞቹ
አቡጀዴ እየቀማ፣
የሚታገል ለመተኛት
ለደቂቃ ማያቅማማ።
ሰካራሙ ሰካራሟ፣
እንደ እሱ አቅም
እንደ እሷ አቅም፣
አሰቡና ትራፊ አልኮል
ሲጠማቸው እንዲጠጡት፣
በቀጭቀጮ ቀድተው ያዙት።
ብርዱ ቁረን ያልገታቸው፣
የጎዳናው ዳር ጀብሎዎች፣
ባለ ላዳ ኮንትራቶች፣
ከዳንኪራ ጩኸት ቤቶች፣
ወተህ ማዶ ስታማትር
ከእሳት ጋራ የሚጣሉ፣
አሉ እንቁላል ሚቀቅሉ።
አየ ወልዶ መሀን መሆን፣
አጥንት መሳይ ያልሰራላት፣
ቂንቂኗ አፍላ ወጣት፣
በውል ሩጣ ያልጠገበች፣
ይሄው በሌት
ከቡና ቤት
ብድር ፀጉሯን ላያት ሁሉ
ከጥቅሻ ጋር ነሰነሰች።
ሸገር እናት ሆደ ሰፊ፣
የማትሰለች ሁሉ አቃፊ፣
የሁሉም ሰው የሁሉ እናት፣
ያም የእኔ ናት አይበላት፣
ለምን ሸገር ምን በወጣት
ለአንዱ ሆና የሚጨንቃት።
መልካም ቅዳሜ !!
ለሀሳብ አስተያየት @amba8
ለመቀላቀል @amba88
@getem
@getem
@gebriel_19
Forwarded from SPACE COMPUTER
ለታራሚ የመታረምን መንገድ ያገኝበት ዘንድ መፅሐፍትን መለገስ ዓላማው አድርጎ የተነሳ ዝግጅት ሊካሄድ ቀናት ቀርተውታል። መግቢያ 2 መፅሐፍት እያዘጋጃችሁ ጠብቁማ...ደግሞም ሼር_share_ በማድረግ ይህ መልካም ሐሳብ ተደራሽ ይሆን ዘንድ የበኩልዎን ይወጡ!!...
ለበለጠ መረጃ ሠላም በለጠ 0912484072
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ለበለጠ መረጃ ሠላም በለጠ 0912484072
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
።።ረድኤት አሰፋ።።
እስኪ ልጠፍ ... ዘርጊ..
እጅሽ ከረዘመኝ፥ እስኪ ልየው ዘርጊ...
እጄን ብዘረጋ፥ ላልደርስበት ነገር
ይበላኛል አንዳች
'እከኩልኝ' ተብሎ፥ ለሰው 'ማይነገር።
እስኪ ዘርጊ አንችዬ
ብቻዬን ስቃጠል፥ ላልታገስ ችዬ
ወይም ላልደርስበት፥ ለምን ልንጠራራ?
ነገ ስም አውጥቶ፥
ባ'ሽሙር የሚገርፈኝ፥ ለምን የሩቅ ልጥራ?
ነይና ዘርጊበት፥
ታውቂዋለሽና፥ የበላኝን ስፍራ።
@getem
@getem
@gebriel_19
እስኪ ልጠፍ ... ዘርጊ..
እጅሽ ከረዘመኝ፥ እስኪ ልየው ዘርጊ...
እጄን ብዘረጋ፥ ላልደርስበት ነገር
ይበላኛል አንዳች
'እከኩልኝ' ተብሎ፥ ለሰው 'ማይነገር።
እስኪ ዘርጊ አንችዬ
ብቻዬን ስቃጠል፥ ላልታገስ ችዬ
ወይም ላልደርስበት፥ ለምን ልንጠራራ?
ነገ ስም አውጥቶ፥
ባ'ሽሙር የሚገርፈኝ፥ ለምን የሩቅ ልጥራ?
ነይና ዘርጊበት፥
ታውቂዋለሽና፥ የበላኝን ስፍራ።
@getem
@getem
@gebriel_19
የሰፋ ሀገር ይዘን ጠቦ መሞት ይብቃን
አይችለው የለ እንጂ የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው የፈሪ ሰው በትር የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትህ አይታለምም ሀቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ እስኪ መጀመርያ ይፈተሽ ፈታሹ።
አቀርቅራ ታዝግም ትጎናበስ እንጂ መሄድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ ምርኩዝ እንኪ ብለህ ደርሰህ አትደልላት።
በኔ ብቻ በሽታ ጥበት እየቀጣን፣
በእናታችን እርስት በአባታችን መሬት መደገፊያ እያጣን፣
ቁልቁል እያሰቡ ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደው ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ
መግፋት፣
ካብኩ እያሉ ማቅለል ሳምኩ እያሉ መትፋት፣
የበደል ላይ ጀግና እሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት የአሽቃባጭ አፍ መግዛት።
እየሸሹ ትግል እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቦና የነብር ዘመቻ።
የበላ እያሰረ የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ ያጠፋ ቢገርፈው፣
ጀግና ልማዱ ነው ባርያ ሆኖ ታሽቶ ንጉስ ሆኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ እየሞተ መብዛት።
ያ ሽንታም ላመሉ በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ ድል የጀግና ሞት ያምራል።
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን ጠቦ መሞት በቃን።
የጸደይ ወይን ሆኖ የሀቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
አይችለው የለ እንጂ የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው የፈሪ ሰው በትር የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትህ አይታለምም ሀቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ እስኪ መጀመርያ ይፈተሽ ፈታሹ።
አቀርቅራ ታዝግም ትጎናበስ እንጂ መሄድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ ምርኩዝ እንኪ ብለህ ደርሰህ አትደልላት።
በኔ ብቻ በሽታ ጥበት እየቀጣን፣
በእናታችን እርስት በአባታችን መሬት መደገፊያ እያጣን፣
ቁልቁል እያሰቡ ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደው ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ
መግፋት፣
ካብኩ እያሉ ማቅለል ሳምኩ እያሉ መትፋት፣
የበደል ላይ ጀግና እሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት የአሽቃባጭ አፍ መግዛት።
እየሸሹ ትግል እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቦና የነብር ዘመቻ።
የበላ እያሰረ የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ ያጠፋ ቢገርፈው፣
ጀግና ልማዱ ነው ባርያ ሆኖ ታሽቶ ንጉስ ሆኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ እየሞተ መብዛት።
ያ ሽንታም ላመሉ በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ ድል የጀግና ሞት ያምራል።
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን ጠቦ መሞት በቃን።
የጸደይ ወይን ሆኖ የሀቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ዘመናቶች ክፉ ናቸው!!
ከአምላክ ልደት ቀድመው፣
በ"ዓመተ-ዓለሙ" ይኖሩ የነበሩ፥
"ብሉይ-ኪዳናውያን"-
ዘመናቸው ከፍቶ፣
"ዘመኑ ክፉ ነው"ብለው ተናገሩ።
"አዲስ-ኪዳናውያን"-
የዘመናቸውን ካለፈው መሻሻል፣
ሰርክ ሊዘክሩ፥
የኋላውን ጥለው-
በአዳዲስ ህግጋት፣
በአዳዲስ አኗኗር፣ይመ'ሩ ጀምሩ።
ግና
ዘመን በዘመን ሲተካ ፣
ሰውና ዘመኑ ምን ቢቀያየሩም፥
ሁሉም ዘመናቶች"ዘመኑ ክፉ ነው"
ከመባል አልቀሩም።
ዘመንና ዘመን በሚተካኩበት፣
የመሻሻል ዓለም፥
የኑሮ ቢሆን እንጂ፣
የዘመን ጥሩ የለም።
የክፋቱ መጠን አንጻራዊ ቢሆንም ቅሉ የዘመን ክፋት ያለ፣የነበረና ለወደፊትም የሚኖር ነው።
ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
12/9/2011
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getEm
@gebriel_19
ከአምላክ ልደት ቀድመው፣
በ"ዓመተ-ዓለሙ" ይኖሩ የነበሩ፥
"ብሉይ-ኪዳናውያን"-
ዘመናቸው ከፍቶ፣
"ዘመኑ ክፉ ነው"ብለው ተናገሩ።
"አዲስ-ኪዳናውያን"-
የዘመናቸውን ካለፈው መሻሻል፣
ሰርክ ሊዘክሩ፥
የኋላውን ጥለው-
በአዳዲስ ህግጋት፣
በአዳዲስ አኗኗር፣ይመ'ሩ ጀምሩ።
ግና
ዘመን በዘመን ሲተካ ፣
ሰውና ዘመኑ ምን ቢቀያየሩም፥
ሁሉም ዘመናቶች"ዘመኑ ክፉ ነው"
ከመባል አልቀሩም።
ዘመንና ዘመን በሚተካኩበት፣
የመሻሻል ዓለም፥
የኑሮ ቢሆን እንጂ፣
የዘመን ጥሩ የለም።
የክፋቱ መጠን አንጻራዊ ቢሆንም ቅሉ የዘመን ክፋት ያለ፣የነበረና ለወደፊትም የሚኖር ነው።
ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
12/9/2011
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getEm
@gebriel_19
😇የገባኝ😇
___
ፊትሽን ስታዞሪ
እመልስሽ መስሎኝ
ሌላ ገላ ታቀፍኩ
አእላፍ ጭኖች ታከኩ
እራሴን በጭሶች
በሱሶቸ ደበኩ
ዳሩ
የገሎች መአዛ
የጭኖቹ ውበት
የጭሶቹ ሽታ
የሱሶቸ ብዛት
አንቺን መች መለሱ
ይልቁንስ ውዴ
በስምሽ ማእበል
በውስጠትሽ ምስል
ቅጥሮቼ ፈረሱ።
ስሟን ለማልጠቅሳት
ከ ✍ፀጋየ ግርማ (ሜሎስ)
17/9/2011
@getem
@getem
@gebriel_19
___
ፊትሽን ስታዞሪ
እመልስሽ መስሎኝ
ሌላ ገላ ታቀፍኩ
አእላፍ ጭኖች ታከኩ
እራሴን በጭሶች
በሱሶቸ ደበኩ
ዳሩ
የገሎች መአዛ
የጭኖቹ ውበት
የጭሶቹ ሽታ
የሱሶቸ ብዛት
አንቺን መች መለሱ
ይልቁንስ ውዴ
በስምሽ ማእበል
በውስጠትሽ ምስል
ቅጥሮቼ ፈረሱ።
ስሟን ለማልጠቅሳት
ከ ✍ፀጋየ ግርማ (ሜሎስ)
17/9/2011
@getem
@getem
@gebriel_19
"እንድትረጂኝ ነው "
( ✍️© እሱባለው ኢ. ✍️)
'ባትመጪም ቅጠሪኝ '
ብሎ እንደሚማፀን እንደ ጅል አፍቃሪ ፣
መያዣ ሳይኖረው
ሰው እንደሚያስቸግር የዋህ ተበዳሪ፣
ጠመኔውን ለብሶ
ሲጮህ እንደሚውል ታጋሽ አስተማሪ ፣
ተስፋና ትዝታ ተቀላቅለውበት
ኑሮ እንደከበደው ምስኪን ስደተኛ፣
ለራሷ ሳትሆን
ደክማ እንደምትውል የቤት ሰራተኛ፣
ካምላኩ ጋር ሁሌ
ቀርቦ እንደሚያወራ ትጉ ፀሎተኛ፣
ዋንጫ በህልሙ እንጂ
በአካል ለራቀው እንደ አርሴ ደጋፊ፣
እንደ ጎዳና ልጅ
ቡሌ እንደሚጠይቅ የሆቴል ትራፊ፣
ደበሎውን ለብሶ
ከብት እንደሚጠበቅ የቅኔ ዘራፊ፣
ሆስፒታል ሰልችቶ
ቤቱ እንደሚተኛ በፅኑ ታማሚ፣
ስብሰባ ተጠርቶ
ሁሉን እንደሚዘብ አስተዋይ ታዳሚ፣
ቃላት አልቀውበት
ሲያስብ እንደሚውል ብቸኛ ገጣሚ ፣
.........
ሆኜ የቀረብኩሽ ውስጤን ባዶ አድርጌ፣
ሌሎች ሳያውቁብኝ ፍቅርሽን ፈልጌ፣
እንድትረጂኝ ነው ይህንን ማድረጌ።
~~~~~~~~~~~~~~
እሱባለው ኢትዮጵያዊ (@esubalewbuze)
@getem
@getem
@gebriel_19
( ✍️© እሱባለው ኢ. ✍️)
'ባትመጪም ቅጠሪኝ '
ብሎ እንደሚማፀን እንደ ጅል አፍቃሪ ፣
መያዣ ሳይኖረው
ሰው እንደሚያስቸግር የዋህ ተበዳሪ፣
ጠመኔውን ለብሶ
ሲጮህ እንደሚውል ታጋሽ አስተማሪ ፣
ተስፋና ትዝታ ተቀላቅለውበት
ኑሮ እንደከበደው ምስኪን ስደተኛ፣
ለራሷ ሳትሆን
ደክማ እንደምትውል የቤት ሰራተኛ፣
ካምላኩ ጋር ሁሌ
ቀርቦ እንደሚያወራ ትጉ ፀሎተኛ፣
ዋንጫ በህልሙ እንጂ
በአካል ለራቀው እንደ አርሴ ደጋፊ፣
እንደ ጎዳና ልጅ
ቡሌ እንደሚጠይቅ የሆቴል ትራፊ፣
ደበሎውን ለብሶ
ከብት እንደሚጠበቅ የቅኔ ዘራፊ፣
ሆስፒታል ሰልችቶ
ቤቱ እንደሚተኛ በፅኑ ታማሚ፣
ስብሰባ ተጠርቶ
ሁሉን እንደሚዘብ አስተዋይ ታዳሚ፣
ቃላት አልቀውበት
ሲያስብ እንደሚውል ብቸኛ ገጣሚ ፣
.........
ሆኜ የቀረብኩሽ ውስጤን ባዶ አድርጌ፣
ሌሎች ሳያውቁብኝ ፍቅርሽን ፈልጌ፣
እንድትረጂኝ ነው ይህንን ማድረጌ።
~~~~~~~~~~~~~~
እሱባለው ኢትዮጵያዊ (@esubalewbuze)
@getem
@getem
@gebriel_19
#ያየልኝ
ትዝ ካለህ ያን ጊዜ እጣችን ተሳስቦ፣
በወቅቱ እማይታይ ሌላ አላማ አንግቦ፣
አላየሁም ነበር ማስተዋያ ቅሌ በሀሳብ ተከቦ፡፡
የህይወት ዉጣዉረድ ፤የልብ ምት መጥፋት፣
ያሳለፍኩት ታሪክ የሄደው ሞገዴ ሆኖብኝ እንቅፋት፣
ነገሩስ ጭንቀት ነው የሰው ስህተት ላርም ቀን ሌት እንቅልፍ ማጣት፡፡
ዉስጤ ሀር ሳለ ነስር አደፍርሶት፣
ከሀሳብ እንባየ ከቃል ዝምታየ እየቀደመብኝ ሲያመጣብኝ ብሶት፣
ተው አትፍረድ ውዴ ይሄ ሁሉ ሲሆን አላሰብኩም ክፋት፡፡
እውነቱ ይሄ ነው
በወደዱት መካድ ይሰብራል ይቆርሳል፣
እንኳንስ ከሀሳብ ከቀዬ ያሰድዳል፣
አምኖ ለታመኑት ምላሹ ሲከፋ እጂጉን ያስከፋል፡፡
የተሰበረ ልብ የዋለለ አዕምሮ፣
ቁስሉ ደርቆ እስኪድን ያበዛል ሮሮ፣
የፊቱን አይሻም ይመሽጋል ጓሮ፡፡
አንተም እንግዳየ ዝምታህ ጨምሮ ቤተሰብም ሆንከኝ፣
የውስጥ ውስጤን ጩኸት አንደበት አርገኸው ሳልነግርህ ሰማኸኝ፣
ምሽጌ ሳይርቅህ ጓዳየም ሳይቀፍህ መድሀኒት ሆንክልኝ፡፡
እርግጥ አጥፍቻለሁ ልኬትን ጥሻለሁ፣
የጎሳ ጭፈጨፋ አዳም ላይ ጥያለሁ፣
የአዳምም አዳም እንዳለዉ ስቻለሁ፡፡
ግና በመሀሉ ቁስሌ እየደረቀ ቀልቤ እያንዣበበ፣
በመልካሙ ሽቶ በፍቅርህ መዐዛ ከውስጡ ታጀበ፣
ውሃን ካልጨበጥኩኝ ነፋስ ካላፈስኩኝ ከሚሉ እብደቶች ሊታቀብ አሰበ፡፡
በአይኔ ሳላስተዉል ማዳመጫየንም ከዉል ሳላዉለው፣
ሚያቆመኝ ምሰሶ አንድ ብቻ መስሎኝ ወደቀብኝ ብየ ሂያጁን ስጠብቀው፣
እኔ ሳልችልበት ከኔ በላይ አሱ በእኔ እምነት የጣለው ፣
ትልቁ ምሰሶ ከመሰረቱ ጋር አብሮ የተከለኝ የልቤ ንጉሦ ነው፣
ደስታውን አብዝቶ ጤና እንዲሰጥልኝ ፀሎት አቅራቢ ነኝ ሁሌም ለላይኛው፡፡
#SElamawit
@getem
@getem
@gebreil_19
ትዝ ካለህ ያን ጊዜ እጣችን ተሳስቦ፣
በወቅቱ እማይታይ ሌላ አላማ አንግቦ፣
አላየሁም ነበር ማስተዋያ ቅሌ በሀሳብ ተከቦ፡፡
የህይወት ዉጣዉረድ ፤የልብ ምት መጥፋት፣
ያሳለፍኩት ታሪክ የሄደው ሞገዴ ሆኖብኝ እንቅፋት፣
ነገሩስ ጭንቀት ነው የሰው ስህተት ላርም ቀን ሌት እንቅልፍ ማጣት፡፡
ዉስጤ ሀር ሳለ ነስር አደፍርሶት፣
ከሀሳብ እንባየ ከቃል ዝምታየ እየቀደመብኝ ሲያመጣብኝ ብሶት፣
ተው አትፍረድ ውዴ ይሄ ሁሉ ሲሆን አላሰብኩም ክፋት፡፡
እውነቱ ይሄ ነው
በወደዱት መካድ ይሰብራል ይቆርሳል፣
እንኳንስ ከሀሳብ ከቀዬ ያሰድዳል፣
አምኖ ለታመኑት ምላሹ ሲከፋ እጂጉን ያስከፋል፡፡
የተሰበረ ልብ የዋለለ አዕምሮ፣
ቁስሉ ደርቆ እስኪድን ያበዛል ሮሮ፣
የፊቱን አይሻም ይመሽጋል ጓሮ፡፡
አንተም እንግዳየ ዝምታህ ጨምሮ ቤተሰብም ሆንከኝ፣
የውስጥ ውስጤን ጩኸት አንደበት አርገኸው ሳልነግርህ ሰማኸኝ፣
ምሽጌ ሳይርቅህ ጓዳየም ሳይቀፍህ መድሀኒት ሆንክልኝ፡፡
እርግጥ አጥፍቻለሁ ልኬትን ጥሻለሁ፣
የጎሳ ጭፈጨፋ አዳም ላይ ጥያለሁ፣
የአዳምም አዳም እንዳለዉ ስቻለሁ፡፡
ግና በመሀሉ ቁስሌ እየደረቀ ቀልቤ እያንዣበበ፣
በመልካሙ ሽቶ በፍቅርህ መዐዛ ከውስጡ ታጀበ፣
ውሃን ካልጨበጥኩኝ ነፋስ ካላፈስኩኝ ከሚሉ እብደቶች ሊታቀብ አሰበ፡፡
በአይኔ ሳላስተዉል ማዳመጫየንም ከዉል ሳላዉለው፣
ሚያቆመኝ ምሰሶ አንድ ብቻ መስሎኝ ወደቀብኝ ብየ ሂያጁን ስጠብቀው፣
እኔ ሳልችልበት ከኔ በላይ አሱ በእኔ እምነት የጣለው ፣
ትልቁ ምሰሶ ከመሰረቱ ጋር አብሮ የተከለኝ የልቤ ንጉሦ ነው፣
ደስታውን አብዝቶ ጤና እንዲሰጥልኝ ፀሎት አቅራቢ ነኝ ሁሌም ለላይኛው፡፡
#SElamawit
@getem
@getem
@gebreil_19
*መስኮት ላበጅልሽ*
በትንሿ ቤትሽ
በጠባብ ክፍልሽ
ሙቀቱ ሀይሎ መተንፈስ ሲያቅትሽ
ድፍኑን ግድግዳ ሸንቁሬ ቦርቡሬ
መስኮት ላበጅልሽ::
@mikiyas1177
@getem
@getem
በትንሿ ቤትሽ
በጠባብ ክፍልሽ
ሙቀቱ ሀይሎ መተንፈስ ሲያቅትሽ
ድፍኑን ግድግዳ ሸንቁሬ ቦርቡሬ
መስኮት ላበጅልሽ::
@mikiyas1177
@getem
@getem
የማያልፉት የለም ፣ ያ ሁሉ ታለፈ
ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣
ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ
በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ (ርዕሱ አይደለም )
።።
መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት
የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየት እንባ
ይተናነቃል ትካዜ ውስጥም ይከታል የታል በሬ ላይ የሚጣለው
ድንኳን ለማንኛውም እንኳን ለነፃነት ቀናችን ለግንቦት ሀያ
በሰላም አደረሳችሁ ።ዳይ የዛሬ ሁለት አመት ወደተፃፈው ፤ዛሬ ሪሚክስ
ወደተደረገው ከሰብልዬ ወደ ትብልዬ
(በላይ በቀለ ወያኔ )
።።።
፡
፡
የግንቦት ፍሬ ናቴ ፣ ትግል ያፈራት እጣን
ያሳደገችው ልጅ ፣ ሀክ ሲያደርጋት ስልጣን
ጥላኝ ወዴት ሔደች ፣ አልኩኝ ተማርሬ
ድንኳን በየቦታው ፣ ትጥል ነበር ማሬ፡ ፡
።።።
ምንሽሬ
አንቺ የትግል ፣ ዘመን ጓዴ
ተረሳሽ ወይ
የሳት ዙሪያው ፣ውጊያ ባንዴ
ምንሽሬ ፣አንቺ የልጅነቴ ቀለም
ምነው ዛሬ ፣በየቦታው ድንኳን የለም፡
።።።
ላሳደገኝ ትግል ፣ ያውም ፍሬ ሆኜ
አብይ እንዴት ይፍታኝ፣ ካንቺ እስር ድኜ
በጊዜ ተዋከብኩ፣ ቆሜ ከመንገዴ
የኔ ለውጥ ማምጣት ፣ ካንቺ አዳነኝ እንዴ?
"""
ሳዋህድ ከኖርኩት ፣ ቅኔን ከቀን ፀሐይ
ተሽሎ ተገኘ ፣ ኦነግ ዘረፋው ላይ
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በተቀኘው ቅኔ
ደግ ባትሆኚ ነው ፣ ደርግን ማመስገኔ
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በነፃ አውጪ ቁጣ
ደግ ጥሎን ሲሔድ ፣ ደርግ ሆኖ ከመጣ!
""""
ሀ ብለህ ተው ተኩስ ፣ ሲለኝ ህወሀቴ
ዋእ ብዬ ስተኩስ ፣ ያኔ ነው ጥፋቴ
ቀልሀ ወርቄ ቢሆን ፣ የቅርብ ዘመዴ
ወንድምን በመግደል ፣ ጀግንነት አለ እንዴ?
።።።
ታግላ ሸገር ገባች ፣ ተኩሳ ተኩሳ
ሸበጥና ቁምጣ ፣ አዩዋትማ ለብሳ፡፡
ማር ስትገባ ሸገር ፣ ያንን ቀን አስታውሳ
ታበላኝ ነበረ ፣ በሬ ላይ ደግሳ
።።፣
""አንቺ የግንቦት ፍሬ ፣ ውዴ ነሽ በጣሙን
የስልጣንሽን ልክ ፣ አላውቀውም ጣሙን
አዲስ ፍቅሬ መጣሽ ፣ ባንቺ ስል እፎየኹ
ደርግን ደግ የሚያስብል ፣ ጭካኔሽን አየኹ
።።
ማር ቋፍ ሆና
ማር ሬት ሆና
ማሬ ማሬ
ተቆፃፅራኝ ማሬ፡፡
"""
ማር ማር ብላ ፣ ገባች ሸገር
ሬት ሆነች ፣ በልቤ ሀገር
ቃሊቲ ወይ ቃሌን ክጄ
ነፃ ወጣሁ ፣ ተቀፍድጄ፡፡
"""
ከንግዲማ ፣ ቦንብ አስጥዬ
የሷን ስልጣን ተቀብዬ
በየቦታው ድንኳን ጥዬ
አንቺን ስል ተፈናቅዬ
ትብልዬ
ግንቦት ሀያዬ
ትብላለም
ድንኳንሽ የለም
ትብለፁ
ገፋሽ ወይ ለውፁ
አሆይይ
@getem
@getem
@gebriel_19
ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣
ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ
በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ (ርዕሱ አይደለም )
።።
መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት
የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየት እንባ
ይተናነቃል ትካዜ ውስጥም ይከታል የታል በሬ ላይ የሚጣለው
ድንኳን ለማንኛውም እንኳን ለነፃነት ቀናችን ለግንቦት ሀያ
በሰላም አደረሳችሁ ።ዳይ የዛሬ ሁለት አመት ወደተፃፈው ፤ዛሬ ሪሚክስ
ወደተደረገው ከሰብልዬ ወደ ትብልዬ
(በላይ በቀለ ወያኔ )
።።።
፡
፡
የግንቦት ፍሬ ናቴ ፣ ትግል ያፈራት እጣን
ያሳደገችው ልጅ ፣ ሀክ ሲያደርጋት ስልጣን
ጥላኝ ወዴት ሔደች ፣ አልኩኝ ተማርሬ
ድንኳን በየቦታው ፣ ትጥል ነበር ማሬ፡ ፡
።።።
ምንሽሬ
አንቺ የትግል ፣ ዘመን ጓዴ
ተረሳሽ ወይ
የሳት ዙሪያው ፣ውጊያ ባንዴ
ምንሽሬ ፣አንቺ የልጅነቴ ቀለም
ምነው ዛሬ ፣በየቦታው ድንኳን የለም፡
።።።
ላሳደገኝ ትግል ፣ ያውም ፍሬ ሆኜ
አብይ እንዴት ይፍታኝ፣ ካንቺ እስር ድኜ
በጊዜ ተዋከብኩ፣ ቆሜ ከመንገዴ
የኔ ለውጥ ማምጣት ፣ ካንቺ አዳነኝ እንዴ?
"""
ሳዋህድ ከኖርኩት ፣ ቅኔን ከቀን ፀሐይ
ተሽሎ ተገኘ ፣ ኦነግ ዘረፋው ላይ
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በተቀኘው ቅኔ
ደግ ባትሆኚ ነው ፣ ደርግን ማመስገኔ
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በነፃ አውጪ ቁጣ
ደግ ጥሎን ሲሔድ ፣ ደርግ ሆኖ ከመጣ!
""""
ሀ ብለህ ተው ተኩስ ፣ ሲለኝ ህወሀቴ
ዋእ ብዬ ስተኩስ ፣ ያኔ ነው ጥፋቴ
ቀልሀ ወርቄ ቢሆን ፣ የቅርብ ዘመዴ
ወንድምን በመግደል ፣ ጀግንነት አለ እንዴ?
።።።
ታግላ ሸገር ገባች ፣ ተኩሳ ተኩሳ
ሸበጥና ቁምጣ ፣ አዩዋትማ ለብሳ፡፡
ማር ስትገባ ሸገር ፣ ያንን ቀን አስታውሳ
ታበላኝ ነበረ ፣ በሬ ላይ ደግሳ
።።፣
""አንቺ የግንቦት ፍሬ ፣ ውዴ ነሽ በጣሙን
የስልጣንሽን ልክ ፣ አላውቀውም ጣሙን
አዲስ ፍቅሬ መጣሽ ፣ ባንቺ ስል እፎየኹ
ደርግን ደግ የሚያስብል ፣ ጭካኔሽን አየኹ
።።
ማር ቋፍ ሆና
ማር ሬት ሆና
ማሬ ማሬ
ተቆፃፅራኝ ማሬ፡፡
"""
ማር ማር ብላ ፣ ገባች ሸገር
ሬት ሆነች ፣ በልቤ ሀገር
ቃሊቲ ወይ ቃሌን ክጄ
ነፃ ወጣሁ ፣ ተቀፍድጄ፡፡
"""
ከንግዲማ ፣ ቦንብ አስጥዬ
የሷን ስልጣን ተቀብዬ
በየቦታው ድንኳን ጥዬ
አንቺን ስል ተፈናቅዬ
ትብልዬ
ግንቦት ሀያዬ
ትብላለም
ድንኳንሽ የለም
ትብለፁ
ገፋሽ ወይ ለውፁ
አሆይይ
@getem
@getem
@gebriel_19
የድል ቀን
""""""""""""
ትውልድ በራስ ትውልድ
አመፅ አስነስቶ ትውልድ ካኮላሸ
ማር ነው ያልነው ሁሉ
ሬት እየሆነ እያደር ከመሸ
ልንጨብጥ ስንለው ተስፋችን ከሸሸ....
ህመም ካገረሸ
ምኑ ነው የድል ቀን?
ሁል ጊዜ ሰቀቀን
እያነቡ እስክስታ ሁል ጊዜ ቀን በቀን
ጉንጭን ማልፋት ብቻ ጩኸት የበቀቀን..
እያደር ሲጨንቀን::
እቴ ስሚኝማ
ልንገርሽ አንድ ነገር...
መስከረም ሁለትም
ተብሎ ነበረ የነፃነት ቀንዲል
ደሞ እሱም ተረስቶ
ተተክቶ ነበር የግንቦት ሀያ ድል
ይሁና ግዴለም
ይከበር ይሁና በነጋ በጠባ
ለስራ ወዳድ ህዝብ
ለትምህርት ወዳዱ
ስራ አስፈትቶ ካላንደር ካዘጋ¿😜😳
እቴ ስሚኝማ
የቀልዴን አይደለም 'እምነግርሽ ነገር
እኔ ምን አቃለሁ
ላለቀሰ አዝኜ ለሳቀ እማጫፍር
እኔ ምን አቃለሁ
ይሄ ድል ነው ሲሉኝ
አዎ ድል ነው ብዬ ድንኳን የምተክል
ሆ.....ብዬ የኖርኩኝ
ለመስከረም ሁለት ለግንቦት ሃያ ድል!
እኔ የምልሽ ግን
ሌላ ድል መጣ እንዴ
ትውልድን ያጠፋ ህዝብን የገነዘ
ምነው የ'ግንቦት ፀሀይ
ደመንመን አለብኝ እየቀዘቀዘ
ዝንቡም ቀናነሰ!?
እንጃ ብቻ
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
""""""""""""
ትውልድ በራስ ትውልድ
አመፅ አስነስቶ ትውልድ ካኮላሸ
ማር ነው ያልነው ሁሉ
ሬት እየሆነ እያደር ከመሸ
ልንጨብጥ ስንለው ተስፋችን ከሸሸ....
ህመም ካገረሸ
ምኑ ነው የድል ቀን?
ሁል ጊዜ ሰቀቀን
እያነቡ እስክስታ ሁል ጊዜ ቀን በቀን
ጉንጭን ማልፋት ብቻ ጩኸት የበቀቀን..
እያደር ሲጨንቀን::
እቴ ስሚኝማ
ልንገርሽ አንድ ነገር...
መስከረም ሁለትም
ተብሎ ነበረ የነፃነት ቀንዲል
ደሞ እሱም ተረስቶ
ተተክቶ ነበር የግንቦት ሀያ ድል
ይሁና ግዴለም
ይከበር ይሁና በነጋ በጠባ
ለስራ ወዳድ ህዝብ
ለትምህርት ወዳዱ
ስራ አስፈትቶ ካላንደር ካዘጋ¿😜😳
እቴ ስሚኝማ
የቀልዴን አይደለም 'እምነግርሽ ነገር
እኔ ምን አቃለሁ
ላለቀሰ አዝኜ ለሳቀ እማጫፍር
እኔ ምን አቃለሁ
ይሄ ድል ነው ሲሉኝ
አዎ ድል ነው ብዬ ድንኳን የምተክል
ሆ.....ብዬ የኖርኩኝ
ለመስከረም ሁለት ለግንቦት ሃያ ድል!
እኔ የምልሽ ግን
ሌላ ድል መጣ እንዴ
ትውልድን ያጠፋ ህዝብን የገነዘ
ምነው የ'ግንቦት ፀሀይ
ደመንመን አለብኝ እየቀዘቀዘ
ዝንቡም ቀናነሰ!?
እንጃ ብቻ
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
እመነኝ ወዳጄ
ከዘንድሮ ፍቅርህ ያየችው ከሚያምራት
የትላንቷ ሚሚ
የቃቃነት ሚስትህ ሲበዛ ታማኝ ናት
ትዳር መያዝ ካሻህ
እሷኑ ፈልገህ እቤትህ አስገባት፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ)))
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ከዘንድሮ ፍቅርህ ያየችው ከሚያምራት
የትላንቷ ሚሚ
የቃቃነት ሚስትህ ሲበዛ ታማኝ ናት
ትዳር መያዝ ካሻህ
እሷኑ ፈልገህ እቤትህ አስገባት፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ)))
@getem
@getem
@lula_al_greeko