ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንዳንድ ገፅ
"""""""'''''''''''''''""

የኔነቴ ምዕራፍ
ልክ እንደ መፅሀፍ
ጠፍተው የተረፉ ሰባት ገፆች አሉት፤
የኔና አንቺን ህይወት በግልፁ የሚያትት።

ማውጫ የለው መግቢያ
ጥራዝ የለው ሽፋን
ወና ....ቤት አልባ ገፅ፤
እንዲህ ይነበባል
በባለ ታሪኩ ታሪኩ ሲገለ'ፅ።

(ገፅ አንድ)

በሰፈሬ መንገድ ቁልቁለቱን ስወርድ፤
አንቺ ደሞ ወደላይ ስትወጪ አቀበት፤
እንቅፋት ሳይነካኝ ልቤ አለ ሸርተት፤
አልገባኝም ነበር?
ከየት አመጣጡ? ደርሶ ይሄ ስሜት።

አቀበት ሆኖብሽ
ደካክሞሻል አንቺ ያለሽበት መንገድ፤
ድካም ነው ቁንጅናሽ?
አልገባኝም ከቶ ደርሶ የልቤ መራድ።

መንገዱ ሲወስደኝ የልቤ መረበሽ፤
መንገዱ ሲይለፋሽ እንዲያ ተደካክመሽ፤
ድጋሚ አልገባኝም?
ጎን ለጎን ስንደርስ
ለምን ተሽኮረመምሽ? ለምን ስቀሽ አለፍሽ?

(ገፅ ሁለት)

እኔ እንቅልፋሙ
የሞትኩ የምመስለው ጎኔ ሲነካ አልጋ፤
አልገባኝም ዛሬም?
አልጋው ኮሰኮሰኝ ስገላበጥ ነጋ።

ውሎዬ አላማረ
እንዲሁ ስነጫነጭ ባህሪዬ ከፍቶ፤
"ምን ሆነሀል?" ሲለኝ
መጤ ባህሪዬን ሰዉ ተመልክቶ።
አላውቅም ምንድነው?
ልገልፀው አልቻልኩም ያናደደኝ ነገር፤
ቆይቼ ሲገባኝ
ገፅ አንድ ላይ ያለው አሳሳቅሽ ነበር!

(ገፅ ሶስት)

ድንገት ያየሁሽ ቀን
በደስታ ባህር ውስጥ ልቤ ሲረግጥ ጮቤ፤
ያላየሁሽ ለታ
ተከፍቼ ስገኝ ሀዘኔን ደርቤ፤
ለተመልካች ሁሉ
እኔ አንቺን መውደዴ አሳበቀ ቀልቤ፤
ልቀርብሽ ፈለኩኝ
የወንድነት ወኔ ድፍረቴን ሰብስቤ።

(ገፅ አራት)

ሰላም ተባባልን
ትንሽ ተንተባተብኩ አንቺም ተዋወቅሽኝ፤
ፍርሃቴም ቀነሰ
ተለማመድንና ቀርቤሽ ቀርበሽኝ፤
ግን ሌላ ምጥ ያዘኝ
እንደ ጓደኛ እንጂ በፍቅር አላየሽኝ፤
ድጋሚ አማጥኩኝ
ትንሽ ጉድጓድ ስዘል ትልቅ ገደል ሆንሽኝ።

(ገፅ አምስት)

ምንም አይገባሽም
ላሳይሽ ብሞክር ፍቅሬን በተግባር፤
የፍቅር አኩኩሉ
እየተጫወትኩኝ ተደብቄ ነበር፤
ደንታም አልነበረሽ
በስስት ማየቴ ለማሳይሽ ነገር፤
ግን ስፈራ ስቸር
ልነግርሽ ወሰንኩኝ በቃል የኔን ፍቅር።

(ገፅ ስድስት)

የነገርኩሽ ለታ
እንደ መሳቅ እያልሽ
"እንዴት ነው ያየከኝ?" የሚል ወጣ ካፍሽ
"ስሜት የለኝ ላንተ"
በምትለዋ ቃል በሰቀቀን ጥለሽ መንፈሴን አደማሽ
ታዲያ ገፅ አንድ ላይ
ምን አሽኮረመመሽ?...ለምን ስቀሽ አለፍሽ?

(ገፅ ሰባት)

ገብቶሻል ስሜቴ
አትምሰይ እባክሽ ይሄ የማይገባሽ፤
ጨንቆኝ የቀረብኩሽ
እህት ፈልጌ አይደል
ያልገባው አትምሰይ ገብቶሻል እባክሽ።

አሁን በይምሰልሽ አውቀሽ ልትመልሽኝ፤
ሳቅሽ ቀመር ነበር
ዳገቱም ነው ቀመር
አካሄድሽ ቀመር አውቀሽ ነው የታየሽኝ።

(ገፅ ስምንት)

ገፅ ስምንት ላይ
"አውቀሽ ነው የታየሽኝ..." በከፊሉ ይላል.....

የወረቀቱ ገፅ በግማሽ ተቀዷል
.
.
.
.
ውድቆ ቀርቷል እንጂ ታሪኩ ይቀጥላል

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
👍1
#ንፅፅር
( #አብርሀም_ተክሉ)

አንቺና ሀገሬን ሳመሳስላችሁ
የመጣውን ሁሉ !!
እንዳልክ.....እያላችሁ
ጥርስ የደረደረ ፥ ደባ እያደባችሁ
ባላዋቂ ጮሌ
በዘመን ወፍጮ ላይ ፥ ነገረ አፈጃችሁ ።
ታውቂያለሽ?
ምስኪኗ የኔ አገር
ባንድ መቀመጫ ፥ ሁለት ባል ሲገርፋት
ከፋፍላ ሰጠችው ፥ በጉብታው ስፋት
#አንቺ_ደሞ
ልክ እንደሀገሬ ፥ ነገር ስትዋጂ
የባልሽን አልጋ ፥ ከእልፍኝ ሞገሱ
ለሎሌሽ ማረፊያ ፥ ክብሩ ስታወርጂ
የተንቆራቆዘ
አልጋሽ ወድቆ ከደጅ
የተገላቢጦሽ
አሽሙርሽ ሲበጃጅ
ባንቺው ተንገላትቶ ፥ በግብርሽ ላረጀ
በሰበርከው ምፀት
አይጡ በበላ ፥ ዳዋውን አስፈጀ።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem
3ኛው ዳሪክ የጥበብ ምሽት
ሐሙስ ጥቅምት 27 /2012 ዓ/ም
ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ
በዳሪክ ቡና አዳማ
አዳማ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት
በምሽቱ
ግጥም
☞ ገጣሚ አደም ሁሴን
☞ ገጣሚ ተስፋሁን ከበደ(ፍራሽ አዳሽ)
☞ ገጣሚ ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ)
☞ ገጣሚት ኑሐሚን ዮናታን
☞ ገጣሚ ምህረቱ በላቸው
☞ ገጣሚት ቢታንያ ሽመልስ
☞ ገጣሚ ዳግም ደጀኔ (ሔራን)
☞ ገጣሚ ሡራፌል ተስፋዬ
☞ ገጣሚ ሚኪያስ ሽፈራው
የተገለጠ ገፅ
☞ ዮናስ መሐመድ (ዮኒ ሞህ)
ወግ
☞እሡቤ ኮብላዩ
ዲስኩር
☞እንዳሻው ጌታቸው
ጨዋታ( ፎክሎራዊ ወግ)
☞ያዳም አንዱዓለም

@getem
@getem
#በክፍት የበር መቃን ...!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።
በትር ዱላ አይቆርጥም እግዚሀር ሲቆጣ
አመፅ አቅሉን ነስቶት መፋቀርን ላጣ
ለአልገዛም ባይ ህዝብ ይልካል አንበጣ
ብዬ እንደነገርኩሽ ከጥያቄሽ ማግስት
ዘር ብሄርን ሳይለይ እህል የሚያነክት
ርግማን ተነስቷል በይ ክንድሽ ይመክት
ስሚኝ እታለሜ!
ተመልከች ማሳውን.. .
ተመልከችው መስኩን ...
ጥላቻ አዝሞት ምሰሶው ሳይፀና
የጎጆዋችን ክዳን ከመሬት ሳይቃና
መደማመጥ ጠፍቶን ፍቅር ሲሆን ኦና
ፍሬያችን ረግፏል የዘራነው አምና
እንግዲያስ ምን በጀን?
ምን ምድር ይዋጠን?
ጠግበን ስንላፋ ርሀብ ሊቀድመን
አፉን ከፍቶ ከደጅ.. .ከደፍ ቆሟልና
ለድል መራኮቱ ግጥሚያው ይቆይና
የፉክክሩ ቤት በሩ እንዳይከፈት
ጎተራችን ጎድሎ አየር ሳይሞላበት
አንቺም ለኔ ቁሚ እኔም ልቁም ላንቺ
ጥላቻ ያራቀው...
ልግመኛው ልብሽን ለህብረት አበርቺ
ተነሺ ልነሳ
ልነሳ ተነሺ
ክንዶቼ ስር ሰምጠሽ
አንድ የሆንበትን ፥ ትናንትን አስታውሺ
ልጠጋ ተጠጊ
ተጠጊ ልጠጋ
መፎካከር ቀድሞን ፥
በዱር አውሬ ቀንዶች ፥ ገላችን ሳይወጋ
ተረኛ ነን ስንል ፦
ተራችን ደርሶብን ፥ ሳንከፍል ዋጋ
የተከፈተው በር ፥ አንድ ሆነን ይዘጋ።
(ግድ የለም ቅረቢኝ....!)

@getem
@getem
@getem
ሞት አያምም!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

@getem
@getem
ለውብ ቀን!
💚

እነሆ አንድ ውብ ግጥም ልጋብዛችሁ ወደድኩ። ገጣሚው ወሰንሰገድ ገብረኪዳን ነው።
ይህ ግጥሙ ሰሞነኛውን ስሜታችንን የሚጋራ፣ ግራ መጋባታችንን የሚያብራራ ነው። የዛሬ
ሦስት ዓመትም ፌስ ቡክ ላይ ለጥፎት ነበር። እናም አንብቡት - ትደመማላችሁ።

በነገራችን ላይ ይህን ግጥም ከማግኘቴ ከሰዓታት በፊት ለረጅም ጊዜያት
ስንቀጣጠር ቆይተን የፈጣሪ መሻት ሆኖ ዛሬ ካገኘሁት ወዳጄ ጋር ካወጋናቸው ጉዳዮች
አንዱ ነው - ልክ እንደዚህች መከረኛ ሀገራችን ተጨባጭ ሁነት፣ ነገሮች ሲሳከሩ፣ የነበረው
እንዳልነበረ ሲሆን የሚፈጠር የስሜት መጎሽ።
"ሀገር ላይ ሆኖ ሀገርን ማጣት"። "ሀገር ላይም ተሁኖ ሀገርን መናፈቅ"። "ሀገር ላይም ሁኖ
ሀገርን መግለፅ አለመቻል። አበሳ ነው - አቦ!
-- -- --

ሀገሬን_ሳሚልኝ !
------------------------
(ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን)
.
“እንዴት ነህ - እንዴት ነህ - እንዴት ነህ በአያሌው
ኑሮ እንዴት ይዞሃል? - አማን ነው ወይ ቀዬው?”
ብለሽ የጠየቅሺኝ - የእናቴ ልጅ ውዴ
እንደው በደፈናው - “አለሁ!” እልሻለሁ - የአፍ ሆኖ ልማዴ፡፡
.
እንጂ መኖር አይደል - ሁሉም ነገር ከፍቷል
ወገኔ ምትይው - ኩሩ ሀበሻ ሁሉ - ወገን አልባ ሆኗል፡፡
እንዴት? እንዳትይኝ - እንዴት እንደሆነ - እኔንም ጨንቆኛል
ሰው # ስዋስው ሆኗል - ሰውነቱን ትቷል፤
እምነቱን ረስቷል!
.
ግን ለወጉ ያህል - ቤተስኪያን ይሄዳል
የአዛን ሠዓት ቆጥሮ - መስገዱን ይሰግዳል
ሆኖም እንደእምነቱ - መቆም አቅቶታል
ማጎብደድን ባህል - ዘዬው አድርጎታል
ታዲያ ይሄ መኖር - መኖር ነው ይባላል!?

ይኸው አሁን እንኳ - እንዴት ነህ? ስትይኝ፣
እንዲህ ነኝ እንዳልል - ማንነቴ ጠፍቶኝ
ነፍስያዬን ስቼ - በሥጋት ተውጬ
ማልቀስ ይቃጣኛል - በግፍ ተረግጬ፡፡

ይህ የምልሽ ሁሉ - የቀልድ እንዳይመስልሽ - አጉል እንቶ ፈንቶ
በአበሻ ምድር ላይ - እውነትና እምነት - ቃሉ ብቻ ቀርቶ
ተፈጥፍጦልሻል - የሚያነሳው አጥቶ፡፡

ያቺ የምታውቂያት - በኔም ባንቺም ልብ ውስጥ የተቀረፀችው
ኢትዮጵያችን ያልናት - ሥም ብቻ ሆናለች - በሥም ነው
ያለችው፡፡
ባይገርምሽ ውዴ ሆይ፣
አዋቂ ሚባለው - የተማረው ሁሉ - የተመራመረው
ለካስ ሆኖ ኖሮ - እውነት የመረረው - ሐቅ የጎፈነነው
አጎንባሽ አከንፋሽ - ብኩን ሆኖሻል
ህሊናውን ትቶ - ከራሱ ተጣልቷል
ግን ለወጉ ያህል - “አለሁ!” “አለን!” ይላል፡፡
ምን ምኑን ልንገርሽ፣
ሊቅ አይባል ደቂቅ - ትንሹም ትልቁ
“ወየው” ብቻ ሆኗል - ወየው ብቻ ስንቁ፡፡
.
“ዋ!….” ባይ ነው አዳሜ - “ዋ!” ባይ ነው ሹመኛው
“ዋ!” ሆኗል ገንዘቡ - “ዋ!” ሆኗል አዱኛው፡፡
ሁሉንም ዘርዝሬ - አልነግርሽም ይቅር
ሽምግልና ረክሷል - ሽበት አጥቷል ክብር፤
እርቅ የሚባል ነገር - ተረስቷል ተጥሏል
ተበዳይ ሲያለቅስ
ከበዳይ ጋር መዝፈን - ማጨብጨብ ወግ ሆኗል፡፡

አዬ የኔ ነገር - ምኑን ከምን ብዬ - ልንገርሽ ዘርዝሬ
ስሟ ብቻ ቀርቷል - ተሰዳለች መሰል - ምስኪን ይቺ አገሬ፡፡
.
እስቲ ፈልጊልኝ - ትገኝ እንደሆነ - ምናልባት አንቺ ዘንድ
ውለታ ዋይልኝ - ለመቼ ነው ዘመድ!
ድንገት ካገኘሻት - በእውነት አፋልገሽኝ፣
ባይደላውም እንኳ - ያፈቅርሻል ብለሽ - ሃገሬን ሳሚልኝ!!
.

ውብ ቀን! "ናካይታ"💚

@getem
@getem
@balmbaras
የገብረ ክርስቶስ ደስታ አስሩ (ዘመን አይሽሬ) የፍቅር ግጥሞች!!!

(1)የመጀመሪያ ቀን
----------------*
አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ፡፡
.
.
.
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የገብረ ክርስቶስ ደስታ አስሩ የፍቅር ግጥሞች!!!
(2)ያገረሸ ፍቅር
---------------*
የሰማይ አሞራ
ላዋይህ ችግሬን
ብረር ሂድ ንገራት
ከትልቁ ዛፍ ሥር
ድሮ በልጅነት
ከተጨዋትንበት
ከትልቁ ዛፍ ሥር አታጣትም ፍቅሬን
ብረር ሂድ ንገራት ንገር መናፈቄን፡፡
……//………..
@getem
@getem
@gebriel_19
ግጥም ብቻ 📘
ለውብ ቀን! 💚 እነሆ አንድ ውብ ግጥም ልጋብዛችሁ ወደድኩ። ገጣሚው ወሰንሰገድ ገብረኪዳን ነው። ይህ ግጥሙ ሰሞነኛውን ስሜታችንን የሚጋራ፣ ግራ መጋባታችንን የሚያብራራ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመትም ፌስ ቡክ ላይ ለጥፎት ነበር። እናም አንብቡት - ትደመማላችሁ። በነገራችን ላይ ይህን ግጥም ከማግኘቴ ከሰዓታት በፊት ለረጅም ጊዜያት ስንቀጣጠር ቆይተን የፈጣሪ መሻት ሆኖ ዛሬ ካገኘሁት ወዳጄ ጋር ካወጋናቸው…
#ክፍል 2

ባለፈው ደብዳቤ - ግራ መጋባትሽ - እኔን አይደንቀኝም
ከችግር ተላምደን - ደንዝዘን ገርዝዘን - እያለን የለንም፡፡
“አለን!” የምንለው - ነፍስና ሥጋችን - ባይላቀቅ እንጂ
ሞተናል በቁሙ - እውነቱን ልንገርሽ - የጆሮን በአዋጅ፡፡
ስለዚህ እኮ ነው፡-
ፈልገሽ አፋልገሽ - አገሬን ሳሚልኝ - ብዬሽ የነበረ
ምን የማይለው አለ - መላ ቅጥ ሲጠፋው - ሰው ከተቸገረ!?
አቤት ነው አቤቱ!!
የአገር ልጅ ጭንቀቱ! - ብዛትና ዓይነቱ
ፍትህ መታረዙ - ርትዕ ማጣቱ - ኑሮ ውድነቱ!
ኧረ ስንቱ ስንቱ!!?
በስንቱ መከራ - የአገሩ ሰው ሁሉ - ታስሮ ተጠፍሮ
አንገት ደፊ ሆኗል - መብሰልሰልን መርጧል - መኖር አቀርቅሮ፡፡
/
ደረትን ነፋ አር'ጎ - ቀና ብሎ መሄድ
በአበሻ ምድር ላይ - የህልም ዓለም ሆኗል - የትዝታ መንገድ፡፡
እንዲህ ነው እንግዲህ - ወገኔ 'ምትይው - ኑሮና ህይወቱ
በአካል ይኑር እንጂ - በመንፈስ ተሰዷል - ከአገሩ ከ“ቤቱ”፡፡
/
ስለዚህ እኮ ነው - ተሰዳለች መሰል - ሃገሬ የምልሽ
አንቺ ባለሽበት- ትገኝ እንደሆነ - ሳሚልኝ እባክሽ
.
(ክፍል 3 ይቀጥላል )

@getem
@getem
@balmbaras
ጥቅምት29/2012 በ ጎንደር ከተማ በሀይሌ ሪዞርት እና ስፓ ሽ ዝንቦች አንድ ሆነው የንጉስን ማእድን እንደማይከፍቱ ሁሉ ሽ መጥፎ አመለካከቶችም ኢትዬጵያን እያፈርሱም በሚልመሪቃል የንጉስ ማእድ የተሰኘ ታላቅ የስነ ፅሁፍ ምሽት ተዘጋጅቷል።በፕሮግራሙ
ግጥም
መነባንብ
ወግ
ድስኩር
ፉከራ
ቀረርቶ እና ሌሎችም እዝናኝ ዝግጅቶች በታዋቂ እና አንጋፋ ደራሲያን እና ገጣሚያን ይቀርባል ጥቅምት 29 ከ 11:ሰአት ጀምሮ በሀይሌ ሪዞርት እንዳይቀሩ መግቢያ ትኬቱን በ አቢሲኒያ እና በአባይ ባንኮዝ ሁሉም ቅርንጫፎች እና በተለያዩ 20 የሚሆኑ ኤጀንቶች ያገኙታል።

አዘጋጅ ቢራቢሮ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

@getem
@getem
@getem
ለጁምኣችን!
💚

በጣም ከሚገርሙኝ የነሺዳ ስንኞች
አንዱ...

"አላህ አደራህን በዝነትህ ፈልገን

ባለንበት ዘመን የሌለን አታርገን"

አሚን!💚
ሸጋ ጁምኣ!💚
"ናካይታ"!💚

@getem
@getem
@balmbaras
🎉1
አሁን 8:25
ቀጠሯችን 9:30
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አሁንም አሁንም ሰዓቴን አያለሁ
ይሄ ዘጠኝ ሰዓት ደረሰ እንዴ? እላለሁ
እንዲህ ያሳሰበኝ ውዴ ያንቺ መምጫ
ጊዜ እንዳያጥረኝ ነው
አብራኝ ያለችውን ከቤቴ ማስወጫ። 😁

@getem
@getem
@paappii

#yonas kidane
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
(3)ፍቅር ጥላ ሲጥል
-------------------*
በገና ቢቀኙ
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ…..
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ምነው ቢናፍቁ
አገር ቢያቋርጡ
ቢሄዱ ቢርቁ
አመት ቢጠብቁ
ለሚወዱት ምነው?
……….//………….

@getem
@getem
@gebriel_19
ፊደል ነሽ

ተፃፈ በአኑ


ሄዳለች ይሉኛል
አትመጣም ይላሉ እኔ አለች እላለሁ
በግጥሞቼ ውስጥ
በፊደሎች መሀል ውብ መልኳን እያየሁ
"ሀ" በፃፍኩ ጊዜ
"ለ"በፃፍኩ ጊዜ
መሠረ እያልኩኝ ቤት በመታው ቁጥር
ትዝታ ያፈርሰዋል
ናፍቆት ያፈርሰዋል ተርቦ የሷን ፍቅር
እኔ ገጣሚ ነኝ
አንቺ ደሞ ፊደል የግጥም ቤት መድፊያ
የግጥሜ እውነት
የግጥሜ ይዘት የሀሳቡ ማረፊያ
እፅፋለሁ ላንቺ
ባንቺ ይመታል ቤቴ
ቢያፈርስብኝም የገዛ ናፍቆቴ
እስቲ አስቢው ውዴ
ናፍቆት አፍርሶበት
ቤት መምታት ያቃተው የኔ አይነት አፍቃሪ
በፊደላት መሀል
ፍቅሩን እየሳለ የሚማር ተማሪ
ፊደል የጠፋ ለት
ቃላት የሞቱ ለት ምንድነው እጣ ፈንታው?
ምን ሊሆን ትዝታው?
የቱ ገጣሚ ነው
ያለ ፊደላቶች ቤቱን የሚመታው?

@getem
@getem
@gebriel_19
#ዳና_ከጎራው_ላይ
#የመውሊዱ_ዱኣ ፤ ምንጭ_ያፈልቃል አሉ፤
#የአንበጣውን ክምር፤
#ጎርፍ አርገህ ውሰደው ፤ እባክህ ጀሊሉ።

((( ጃ ኖ))💚💛❤️

"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
ጎረቤቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።

ወጉን ለመሰለቅ ከሰው ተቀላቅሎ
ትንሽ አፍ ማሟሻ ወሬ ባገኝ ብሎ
ፊቱ የሚፈካው ያ ሁሉ ጎሮቤት
ለቡና ሲጠራ
ጆሮው ላይ ይተኛል "ና" ሲባል ለስራ

@getem
@getem
@paappii

#yonas kidane