ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
//እንደ ምስጥ ከውስጥ//

ሰው ማወቅ አልቻልኩም እጅግ ተስኖኛል

የዛሬ ሰው መቼ ባዋሉት ይገኛል

ሁሉም ለራሱ ብልጥ

የሚያደማ የሰው ውስጥ

ጥሩ ብለው ቀርበው ያመኑት ከከዳ

ምንስ ወዳጅ አለ

ምንስ ዘመድ አለ

ኧረ ምንስ ኃደኛ አለ
.
.
.
በሬ ካራጁ ጋር ተታሎ እየዋለ።
(Adi adi)

@getem
@getem
ለመውሊዳችን ! ለቅዳሚታችን !



መውሊድና ዳና!!!!!


በየጁዎች ኪታብ፣
በወልዮቹ ቤት፣
ሃራ ጥጋ ጥጉን፣ ስንት ዱኣ ሞልቶ፣
ዳንዮል አወል ቤት፣
ኑ ብሉኝ እያለ፣
የቂሷው ሰደቃ፣ ኢልሙ ተፈትፍቶ፣
አደረ ይሉኛል፣
የሸሆቼን ኪታብ፣ የሚቀራው ጠፍቶ።
ሙሃባና ዚክር ፣ ኢልምና ደረሳ፣
ይሞሸር ነበረ፣
በላይኛው የጁ፣ በታችኛው መርሳ፣
ስንት አጀብ ነበረው፣
በሸሆቼ ዱኣ፣
እንኳን የታመመ፣ ሙት እየተነሳ።
ሞልቶ ከሚፈሰው፣
ከሃድራው ምርቃን፣ ከቱፍታው ወለላ፣
ይመጠጥ ነበረ፣
የአውገረድ ምርቃን፣ እንደከረሜላ።
እኒያ ደጋጎቹ፣
ልቡናቸው ፀሃይ፣
እንደዘምዘም ውሃ፣ ቀልባቸው ጡሃራ፣
ዘይሩኝ የሚያሰኝ፣
እንደ መዲና በር፣ እንደመካ ጎራ፣
አይናቸው ብርቅ ነው፣
አሻግሮ ይፈታል፣ የርዚቁን ኢሻራ፣
እነሱ አልነበሩ፣
የኒያው ባለሟል፣ የሂማው ሙሽራ።
መገን መደዱ ስር፣
እንደ በጋ ጅረት፣
ፍልቅልቅ እያለ፣ ፈሰሰ ስማቸው፣
አፌ ማር ያፈልቃል፣
ባንቱ ይሁን ብዬ፣እኔም ስጠራቸው።
ሸህ ዳውድ ማርዬ፣
ሚሌ ሸህ አቡዬ፣
መርሳ አባ ጌትዬ፣
መገን በጫልዬ፣
ይኸው ዛሬ መጣሁ፣ ባንቱ ይሁን ብዬ።
ኧረ ይኸ ልቤ፣
ሊበር ነው ደግሞ፣ ዛሬ ወደማታ፣
ና ድረስ ብሎኛል፣
የቃሉ መዘውር፣ አንቻሮና ገታ።
የሃድራው መኪና፣
ማይባርን ዘይሮ፣
ላይ ላዩን ተቃና፣ አልቡኮ ድረስ፣
ቀልቡን ሊታሸመው፣
በኢማኑ ማጀት፣ በጀማው ንጉስ።
የኢልሙ በረኛ፣
የመደዱ ሹፌር፣ ጀማ ንጉስ ሞልቶ፣
የቂርአቱ ዳኛ ፣
የተፍሲሩ ቀለም፣ ዳንዮል ቤት ሞልቶ፣
አጓጉል ደረሳ፣
ና ተማር ይለኛል፣
የተውሶ ኪታብ፣ ሜዳ ላይ ዘርግቶ።
መገን ሙፍቲ ራያ፣
የዞብሉ ሰንደቅ፣ የሜዳው ምስለኔ፣
እንደ ወለላ ማር፣
ፈሰሰስ እያሉ፣ ይመጣሉ በአይኔ።
ሸህ በድሬ መሃመድ፣
የኾርማት ዘብ አደር፣ የቁጥቡ በረኛ፣
አውቀዋለሁ እኔ፣
ያንቱን አፈሳሰር፣ ያንቱን አማርኛ፣
ይገንብረው በሉ፣
ይከንብለው በሉ፣እርዚቁን ወደኛ።
ሸህ ዳውድ ማርዬ፣
ዞብል በራ በሩ፣ ገደመዩ እንዴት ነው??
እንደ ኑር ሊጋባ፣
በሃድራው ጦሪቃ የተሽሞነሞነው፣
ባንቱ ቀዬ መስሎኝ፣
በመንዙማው እሳት፣ ኢልም የሚጋገረው፣
ኧረ በሸሆቼ፣
ደግሞ ዛሬ ደርሶ፣
ምንድን ነው ጀማውን፣ እንዲህ ያሳመረው???
ድቤው ሲመታ ነው፣
ጅስሜ የሚፈካው፣ ቀልቤ የሚሽረው።
ዳና ከበሩ ላይ፣
ከረም ዛውያው ላይ፣
የቢላል ምልክት፣ አዛኑ ሲሰማ፣
አሚን የሚባለው፣
የጁ ከበሩ ላይ፣ ወልዲያ ከተማ።
ታቹን በቦረና፣
እርም እርም አለ፣ ዘለለ መሬቱ ፣
የደገሩ ጌታ፣
ሱቢህና መቅሪብ፣ የሰገዱበቱ።
የሰሜኑ ሃያል፣ ሸህ ለጋስ ጎንደሬ፣
ዘርተውት ሂደዋል፣
የተውሂድን ቀለም፣ እንደ አውድማ ጥሬ፣
ላንብበው ቀለሙን፣ ስጡኝማ ዛሬ፣
የአሊሞቹን ነገር፣
ልክተብ በልቤ ላይ፣ ልቅራው በከንፈሬ።
ዳና ከጀማው ላይ፣
እያየሁት ባይኔ፣
በአንድ ቢስሚላሂ፣
በሶስት ቀን ቱፍታ፣ በሽታ እየሻረ፣
ምን ነካው ይኸ ሰው፣
አላየሁም ይላል፣
የአባቶቹን ኢማን፣ አውቆ እየቀበረ።
እያየሁት ባይኔ ፣
የሸሆቼን ከንፈር፣ ማር እያፈሰሰ፣
የዱኣው እንጀራ፣
በቱፍታ ወለላ እየተለወሰ፣
ዝንተ አለም ይጠግባል፣
አሚን ይሁን ብሎ፣ እሱን የቀመሰ።
የአበሻው አልሃዝሃር፣ ወሎ ማር ዘነቡ፣
አያወላውልም ፣
ለጦቢያ የሚበቃ፣ ሃቅ ነው ኪታቡ።
አራት አይናዎቹ፣
ሸሆቼ በሙሉ፣
በፊትና ገበያ፣ ሃያት የቀናቸው፣
አይቻለሁ ባይኔ፣
የቁርአን አርበኛ ፣ የእሱ ባሮች ናቸው፣
እንኳን ለማጀቱ፣
ላገር የሚበቃ፣ ኑር የከበባቸው።
ኧረ ተወኝ ጓዴ፣
ተወኝ ልሂድበት፣
አውቀዋለሁ እኔ፣ የኢልሙን ጎዳና፣
የሃያትን ሽቶ ፣ የኢማንን ጥፍጥና፣
ዳንዮል አወል ቤት፣
ዳና ከጀማው ስር፣ ቀምሻለሁና።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ የመውሊድ በዓል እንዲሁም ሸጋ ቅዳሜ! መውሊድን በማስመልከት ያውም በቅዳሜ በገምሻራዋ ቀን ሁለት ነሺዳዎችን ጀባ ብንላቹ ማን ከልካይ አለን .? ማንም!

@getem
@getem
@balmbaras
1👍1
*ገብረ ክርስቶስ ደስታ*
(4)ቀረሽ እንደዋዛ
---------------*
እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሀረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ˝
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
አይዞህ
።።።።።።።።።።።።

መኖርህ፣ መጥፋትህ የሚያስጭናቃቸው
ማጣት መከፋትህ የሚያሳስባቸው
የሚጨነቅልህ፣ ስላንተ የሚያስብ
በዙሪያ ከጠፋ፣
ማንም የለኝ ብለህ ከቶ እንዳትከፋ
መኖርክን ፈላጊ፣ ጠዋት ማታ አሳቢ
እንዲኖር በተስፋ፣
በርከት ያለ ገንዘብ ተበድረህ ጥፋ።

@getem
@getem
@paappii

#yonas kidane
👍2
አይዞህ
።።።።።።።።።።።።

መኖርህ፣ መጥፋትህ የሚያስጭናቃቸው
ማጣት መከፋትህ የሚያሳስባቸው
የሚጨነቅልህ፣ ስላንተ የሚያስብ
በዙሪያ ከጠፋ፣
ማንም የለኝ ብለህ ከቶ እንዳትከፋ
መኖርክን ፈላጊ፣ ጠዋት ማታ አሳቢ
እንዲኖር በተስፋ፣
በርከት ያለ ገንዘብ ተበድረህ ጥፋ።

@getem
@getem
@paappii

#yonas kidane
ኢልምና ከራማ ፤
በፊደል ጋጋታ ፤አይመጣም በአዋጅ፤
እንደ ሙፍቲ ኡመር፤
ሙሃባ እንዲከበኝ፤
በስጁድ በዝኪር ማረኝ ማረኝ ብየ እኔም ላልቅስ እንጅ።


ፊደል ያሰከረው፤
መፈክር ያዞረው ፤
የኔ ብቻ የሚል ሙሲበኛ ትውልድ ዛሬ ስለመጣ፤
እንባ ብቻ ሆኗል ይችን ምስኪን ሃገር ነጃ የሚያወጣ፤
ልክ እንደ አባቶቼ፤
እኔም በርከክ ብየ፤ በፈጣሪየ ፊት እንባየን ላዋጣ።


በልጆቹ ስካር፤ባገሩ ጨረባ በዙልመኛ ትውልድ የተነጀሰ ሰው፤
በእንባ ዲሞፍተር ነው የሾይጣንን ዳገት ዱቡን የሚያፈርሰው፤
እኔም እንደ ራሄል ፤
እኔም እንደ ሙፍቲ ሰብቅታኒ ብየ እንባየን ላፍስሰው።


በሰማይ ጌታ ፊት፤
በትሁት መንበርከክ ፤
በጡሃራ ጠሎት፤
የሚሆን ከሆነ፤
የእንባ ጅረት ፈሶ ጦቢያ ቀና ምትል ጎጆዋ የሚሰራ፤
ለጦቢያ ከሆነ፤
ባለቅስ ምን ገዶኝ፤ ማረን ማረን ብየ ሙፍቲ ኡመር ጋራ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
(5)ካንቺ ጋር
ገብረክርስቶስ ደስታ
-----------*
ካንቺ ጋር ሁሉም ነገር ሄዷል
ሰዓቱ ተረስቷል ቀኑም ሌላ ሆኗል
ዓመተ ምህረቱ
በጋና ጸሀዩ
የኖርሽበት ቤቱ
አልጋ ጠረጴዛው ስጋጃ ወንበሩ
መስኮቱና በሩ
ስዕሉ ግርግዳው
ካንቺ ጋራ ጠፍቷል
ሁሉም ተለውጠው
ዛሬ ነገ የለም
ቅናትና ፍቅሩ ሀዘኑ ጨዋታው
ደስታና መከራው
ፈጥሯል ሌላ ቀለም
ገርጥቶ ጠውልጎ መልኩ የነበዘ
ሞቷል መታሰቢያሽ ሆኗል የፈዘዘ
ፈራርሷል የካብሽው
ትዝታው የድሮው
ቀርተሸ ተረስተሻል
ጠፍተሻል ከልቤ
ወጥተሻል ከቤቴ
ወጥተሻል ካንጀቴ
ወጥተሻል ካጥንቴ
ሄደሻል ካሳቤ፡፡
የለሽም የለሽም
ሙዚቃ ድምጽሽን
እንደ ዱሮ አልሰማም
ቅዠት ዘፈንሽ ዜማሽ እንጉርጉሮሽ
ጭጋግ ነው ውበትሽ
የጊዜው መለወጥ
ገላሽን ደብቆ ጋርዶታል መልክሽን
ጥላሽ ነው የቀረው አካልሽ ተሰርቶ
ጨብጦ ቅርጽሽን
ሳቅና ፈገግታሽ ጨዋታና ቀልድሽ
ለዛና ወሬሽ
ቅንድብሽ ሽፋልሽ
የሚያበሩ አይኖችሽ
ጣፋጩ ከንፈርሽ
ለስላሳው ምላስሽ
በረዶ ጥርሶችሽ
ተለውጠው የሉም
ካሳቤ ጨለማ ገብተው አይታዩም
ያ ውብ ቆንጆ ባትሽ
የሚዋጋው ጡትሽ
የሚቆጣው ዳሌሽ
ካንቺ ጋር ሄዷል፡፡
………….//………….

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ሙሴ የ ገብረክርስቶስን ደስታን ቀረሽ እንደ ዋዛ ግጥም በዚህ መልኩ በደምፁ አቅርቦታል. እናመሰግናለን

@getem
@getem
@getem
👍1
እኔ እና አንቺ ማለት
ሲራክ
ገጣሚ እና አንባቢ ሲራክ


@getem
@getem
@siraaq
ገብረክርስቶስ ደስታ
(6)እኔ እወድሻለው
----------------*
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚልዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ፡፡
እኔ እወድሻለው
የሠማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ጽጌረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደሎሚ ሽታ፡፡
እንደ ከርቤ ብርጉድ
እንደ እጣን ጢስ እንጨት
ውዴ እወድሻለው አበባ እንዳየ ንብ፡፡
እንደቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ
በፍቅርሽ ልቅመሰው፡፡
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኳር
አማርኛ አይበቃ
ወይ ጉድ
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር
እኔ እወድሻለው
እንደማታ ጀንበር
እንደጨረቃ ጌጥ
እንደ ተወራርዋሪ ኮከብ
እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ ፤ስወድሽ፤ ስወድሽ ፤ስወድሽ ፡፡
ጡት እንዳየ ህጻን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው፡፡
ጣይ ላይ እንዳለ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው
አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
እኔ እወድሻለው
አይኖችሽን ባይኔ ደጋግሜ እያየው
ስወድሽ ሰወድሽ
ውድ እወድሻለው፡፡


@getem
@getem
@gebriel_19
#፪ ነፍስ ገዳዮች!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።

ይኸው ዛሬም ድረስ! 

የሰንበር ሀምሳያው ፥ ገመድ ተደራርቶ

አክሊለ እሾሁ ፦ 

ተምሳሌት እንዲሆን ፥ ለምስክር ወጥቶ

እየደበደቡ.. .. እየቀጠቀጡ 

ግጥም አሰናኝተው ዜማ የሚያወጡ

እስክስታ 'ሚወርዱ ...

ከበሮ አንጋቾች አሉ በመንገዱ።

ደግሞም ወዲህ ማዶ !

የሙት አካል ቆዳን 

እየረመረሙ እየረጋገጡ

ስልቻ አበጅተው ገበያ ሚወጡ

በካቻምና ዝናብ ...

ዛሬ አርሰናል ብለው ፥ መግለጫ ሚሰጡ 

አሉ ጎዳናው ላይ ፥

ሀቅታ ነው ብለው ፥  እብለት እየሸጡ ።

ይኸው ተመልከቺ.. .

ከነ መግላችን ፣ ከነ ሰንበራችን

እሳት  ባነፈረው ፥ ተበዳይ ገላችን

ሽቱ ሆነን ለሳሎን

ለእልፍኝ ለአዳራሽ...

እጣን ናቸው ብለው ቤታቸው ሲጫጫስ

እይ ተመልከቺ

ጌጥ ሆነን ለአያያዝ ፥ ቅንጦት ሆነን ለአማኝ

ክሩ ደምስራችን.. .ለመዝሙራት ሲቃኝ

እይ ተመልከቺ !

ከሙት አካላችን ...

ከፍራሽ ገላችን ፥ በሸለቱት ቆዳ 

ከበሮዋቸው ሆነን ፥ ዜማቸው ሲቀዳ

እይ ተመልከቺ !

እኛ በጨመቅነው ፥ በዘራነው እንባ

ውሀ ነው ተብሎ ...

ገዳያችን ሊፀድቅ ፥ ከጥምቀት ሲገባ

እይ ተመልከቺ!

ከስጋችን ማዶ ፥ መንፈሳችን ሲቀል

ባልዋልንበት ሜዳ ...

ኩበት ተሰብስቦ ፥ ዳቦዋቸው ሲበሰል።

@getem
@getem
@getem
\\__የህዳር ማዕጠንት__//
በታሪኩ ገላሼ(ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
።።።።።።።።።።።፨፨፨፨።።።።።።።።።።።።
በጥቅምት አንድ አጥንት
ያገኘም አገኘ
ያጣ እንደተመኘ፤
በሀገሬ ሰማይ በዚች በኔ መንደር፤
አጥንቱን ታቅፎ ለሚያሰምር አዳር፤
አጥንቱን ጋግጦ ለሚያቅድ ለትዳር፤
ለጥቅምት ገደቢስ ትርፍራፊ አጥንት
ለሚያስስ መንገድ ዳር፤
ለሁሉም ለሁሉም
ምድሯን ልታጠዳ
ጠብን ልታባርር ትጠባለች ህዳር።

ህዳር ስትጠባ
ሁሉ እየወጣ ብርድ ያስገለገለው ብርድልብስ አጠባ፤
ከመተቃቀፍ ጦስ የተዳደፉትን አንሶሎች አጠባ፤
እኛም እንዳቅሚቲ ለጥር ሰርግ እቅድ ጀመርን ቁጠባ።

ጭካኔ ያረረበበው ጥቅምት ጥቅም አልባ፤
አንገት እንደደፋ ሹልክ ብሎ ሄዶ ህዳር እንደገባ፤
ሌላው ልብስ አጠባ ሌላው ልብ አጠባ፤
ሁሉ ሰልፉን ትቶ ንሰሀ ሊገባ ሀገር ሊገነባ።

ከዘላለም እስከ
ዘንድሮዋ ጥቅምት
ያኔ ጥቅምት ሳለች፤
ህዝብን ለሰለፍ እና ለፀብ በመጀንጀን፤
ስንት እንዳላሰለፍን ስንት እንዳላስፈጀን፤
ህዳር እንጀገባች
በፍቅር ጧፍ ማዕጠንት ገርፋ ስትፈጀን፤
የሞት አዚም አጥፋ ብለን ባንተ መጀን፤
ሰልባጅ ሃሳብ ትተን ፈጣሪ ቤት ባጀን፤

በእኒያ ጥቅምቶች
በአጓጉል ሴራ ፤ ቀዬ ለመሸንሸን፤
መንገድ እንዳላሳትን ፤ ስንቱን እየዋሽን፤
ስንቱን በአረር ቆልተን ስንቱን እንዳልረሸን፤
ስንቱን የድሃ በግ ከጋጣ እንዳልነዳን
ካብት እንዳላሸሸን፤

በዚች ድሀ መንደር
ህዳር እንጀገባች
በአውጫጪኝ ቆሼ አጥና እያወጣጣችን እኛ እየዋሸን፤
በፍቅር ሳማ ቅብዓት ለስልሳ አለስልሳ በመላ ስታሸን፤
የሀኬት አዚም አውጡ በለን በርሶ ግሸን፤
ከፍቅርዎ አውደ ምህረት ዋልንና አመሸን፤

የውሸት አዚም አጥፉ ብለን በርሶ መጀን፤
ባጃጅ ሃሳብ ሸጠን ከርሶ ከአዋቂው ቤት
ባዶ እግር ባጀን።

ሰሜን ና ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ
ዞረን ልንበጠብጥ፤
ጥቅምት ሲሰራራን እንዳንድ ብልጣብልጥ፤
ያጫጫስነው ጎማ እና የያዝነው ፍልጣፍልጥ፤
በየመንገድ መሀል የኮለኮልናቸው
ድንጊያ እና ኮረኮንች፤
አጣና ና ማገር ጠርብ እና የፅድ ከንች፤
ህዳር እንደገባ
ሁሉም ተጠራርቶ ሄዷል ለድሃ ህዝብ ጎጆ ሊገነባ።

ጥቅምት የቆፈነው አውቆ-አባጅ በሞላ፤
በበረደኝ ምክኛት በሰበብ ባስባቡ የተቃቀፈ ሁላ፤
ወልዶ ልጅ ሊታቀፍ ወዳልጋ ሲፋጠን፤
አውቆ ማበድ ጠፍቶት ስላለ ቆፍጠንጠን፤
አጥንት ያላገኘው ቁፍጠናውን ትቶ ትርፌዎች ሲማጠን፤
ጥቅመኛዋ ጥቅምት ከኛ ተቀምታ
ህዳር ስትሰጠን፤
ህዳር ስትሰጠን፤
ዝሙት እና ክፋት ማፋሸግ ጀምሮ ቢያሴርም ሊውጠን፤
በወርሃ ጥቅሞች በወርሃ ጥቅምታት፤
ግጠን እና አኝከን የጣልናትን ሀገር እንደዶሮ አጥንት፤
ይኸው ፍታቷ ነው ከሞት ልትነሳ
በህዳር ማዕጥንት።

በሀገሬው በሞላ
ሞት ራሱ ተሰቅሎ የፍትህን መንፈስ
በርበሬ ሊታጠን፤
ውስጥ ውጩን አጥድቶ እድፉን አቃጥሎ በጪሱ ሊታጠን፤
ስለፍቅር ሲባል የተበደለ ሁሉ በዳይን ሊማጠን፤
ህዳር ቅዱስት ወር
አንድም ለንሰሃ
አንድም ለሱባኤ
አንድም ለጉባኤ
በቅዱስ ፈጣሪ በነፃ ህዳር ስትሰጠን።

ባለፈው በጥቅምት በሶ ተወደደ አገር በጠበጥን፤
ድሃዋ ሀገር አዝና ብብቻ ሰርስረን ካዝና ቦጠቦጥን፤
አውቀን እያበድን ልጃገረድ አገር
ስንቴ አስደነገጥን፤
ግና ህዳር መጥቶ
ቅዱሱ ወር ጠብቶ
በሀገሬው ሰማይ በየሰዉ ቀዬ
እውነት ሊሰለጥን፤
ይኸው ህዳር ገባ ሀገርን በእውነት በእምነት ልናጥን።
ጌታ ሆይ ተመስገን
ህዳር ለሰጠኸን።
አሜን!!!
ወሯን የእርቀሰላም የፍትህ ወር አርግልን
አሜን!!!

ህዳር 01, 2012 ዓ.ም
አዳማ,
ኢትዮጵያ

@getem
@getem
@getem
👍1
ወል የኪነ ጥበብ ምሽት አንድ ጀግና በሚል ህዳር 5 2012ዓ.ም በሶሊሽ ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል
ወል ለማንኛውም የኪነ ጥበብ ባለሙያ እና ለማንኛውም የኪነ ጥበብ አፍቃሪ የተዘጋጀ ልዩ ምሽት በእለቱ አንድ ፈርጥ ጀግናየ ያለውን የሚያመሰግንና የሚያከብር ይሆናል። እርስዎም ጀግናየ ያሉትን በመጋበዝ ጀግናዎን ያክብሪ። ያመስግኑ ፕሮግታሙ ለሁሉም በሚመጥንና ሁሉንም በሚጋብዝ መልኩ ተዘጋጅቷል። አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባልሙያዎች በድንቅ ስራዎቻቸው መድረኩን ያደምቁታል።
ወል የሁላችን ምሽት
ወል ጀግናዎን እንዲያከብሩና እንዲያመሰግኑ እድሉን የሚሰጥ ልዩ ምሽት
ወል የአንድነት ምሽት!

ህዳር 5 በሶሊሽ ኢንተርናሽናል ሆቴል እንገናኝ።
አድራሻ፦ ሜክሲኮ ከአርቂ ፋብሪካ ወደ ልደታ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ቢጂ አይ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፦ 0966712695
0940844145
0968568868

@getem
@getem
ገብረክርስቶስ ደስታ
(7)የፍቅር ፍልስፍና
-----------------*
ጅረቶች ከወንዞች ጋር
የሙጥን ብለው….. ተጣምረው
ወንዞችም ውቅያኖሶችን አቅፈው
የሰማየ ሰማያት ንፋስ
ጣፋጭ ስሜት ሲዋሃደው….
ተመልከችው
ከቶ አንድም ነገር
በአለም ላይ ያላቻ ጓደኛ
ሆኖ አይገኝም ብቸኛ
በውስጠ ሚስጥር ህላዌው
ይጣመራል ሁሉም በውል
በአንድ መንፈስ በአንድ ቃና
ስጋና ደሙን ሲያዋውል፡፡
እኔና አንቺስ ምን አለበት
አንድ ብንሆን ብናውቅበት
እንደመሶብ ከግጣሙ
ሰማያት ምድርን ሲስሙ…..
እይው ጣእሙ፡፡
ማዕበሎችን እያቸው
ባህር ላይ ሲሽኮረመሙ
ሲላላሱ አንዱ ባንዱ ውስጥ ሲሟሙ
አንዱ ማእበል አንደኛውን
አቅፎት ሲሄድ አቻውን….
እይው በሞቴ ጣእሙን፡፡
ደሞም የፍቅር ጡር ጣጣ
ሴቴ አበባ ያለወንዱ፤
አበባነቷ ቅጥ ሲያጣ
ወንዴ አበባም ያለሴቷ
በፀሀይ ሀሩር ሲቀጣ
እይው ቆንጅት እይውማ
ልቦና ፍቅር ሲጠማ
የፀሀይ ብርሀን ጠዋት የመሬትን ከንፈር ሲስም
በሙቀት እየዳበሰ ፈገግታዋን ሲያለመልም
ለዛው ሲፈካ ሲተም
የጨረቃ ጨረር ሞገድ
የባህርን ራቁት ገላ
በምሽት የእንቅልፍ ሰዓት
ይደበዝዛል እያጠላ
ስለዚህ አስተውይው
እኔን ሁኝ አንቺን ልሁን
በደም ስርሽ ደሜ ይፍሰስ፤
በደም ስርሽ ደሜ ይሁን፤
አንድ እንሁን፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
ጥቁር እና ነጭ ስካር(ልዑል ሀይሌ)
ባረቄ ሰከሩ
በዊስኪ ሰከርን፤
ቱቦ ስር ተገኙ
አልጋ ላይ አደርን፤
ብርድ ገረፋቸው
ሙቀቱ ገደለን፤
ግን ያለም ፈጣሪ አያዳላምና
አንድ እንቅልፍ አደለን፤
በእንቅልፋችን ዓለም
ሕልም አየን በጋራ፤
አረቄ የጠጡት
ውስኪ አውርደው ጠጡ፤
ባረቄ ወደሰከርን
ተንገዳግደው መጡ፤
ከባለፀግነት ከሕልም አመለጡ፤
እኛም ተንገዳግደን
የጠርሙስ አረቄ ባፍታ እየጨለጥን፤
ከድሕነት ዓለም ከሕልም አመለጥን፤
ጠዋት ከእንቅልፍ ነቃን ሕልማችንን ሽሽት፤
ቀኑን ልንገብረው ለሚመጣው ምሽት፤
በምሽት ተጋትነው የስካርን ዕጣ፤
ነፃነታችንን
ከተሸሸገበት ጠርሙስ ውስጥ አወጣ፤
ይመስገን ጠርሙሱ...
በዕውን ዓለም ውስኪ
በሕልማችን አረቄ ለምንጋትበት፤
ለዚህ ውለታው ነው
እየተለዋወጥን የምናነጋበት፤

(የሠካራም እኩልነት በጠርሙስ ሲገለጥ)
፳፬-፲፩-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@gebriel_19
Ethio-International Education consultant has made a special deal with Perm Medical University and where they have agreed to enrol Ethiopian students for Medicine and Dentistry with an extremely affordable yearly tution and Monthly Dormitory fee of 1800 USD and 6 USD accordingly. We need to register more students who are interested to study at Perm for the coming January to fill the quota we have been allocated. So to get considered  students are expected to send the following information and documents to @Coolrepublic Telegram account.

1.  Full Name
2.  Email Address
3.  Phone Number
4.  Address (Street,City,Region)
5.  Scan copy of Grade 12 result
6.  Scan copy of the passport
Mr. Neil International Director of ACE Online will discuss with applicants selected by Perm University when the offer letter arrives within two weeks.

Good Luck!
@EthiopiaEducation