#በክፍት የበር መቃን ...!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።
በትር ዱላ አይቆርጥም እግዚሀር ሲቆጣ
አመፅ አቅሉን ነስቶት መፋቀርን ላጣ
ለአልገዛም ባይ ህዝብ ይልካል አንበጣ
ብዬ እንደነገርኩሽ ከጥያቄሽ ማግስት
ዘር ብሄርን ሳይለይ እህል የሚያነክት
ርግማን ተነስቷል በይ ክንድሽ ይመክት
ስሚኝ እታለሜ!
ተመልከች ማሳውን.. .
ተመልከችው መስኩን ...
ጥላቻ አዝሞት ምሰሶው ሳይፀና
የጎጆዋችን ክዳን ከመሬት ሳይቃና
መደማመጥ ጠፍቶን ፍቅር ሲሆን ኦና
ፍሬያችን ረግፏል የዘራነው አምና
እንግዲያስ ምን በጀን?
ምን ምድር ይዋጠን?
ጠግበን ስንላፋ ርሀብ ሊቀድመን
አፉን ከፍቶ ከደጅ.. .ከደፍ ቆሟልና
ለድል መራኮቱ ግጥሚያው ይቆይና
የፉክክሩ ቤት በሩ እንዳይከፈት
ጎተራችን ጎድሎ አየር ሳይሞላበት
አንቺም ለኔ ቁሚ እኔም ልቁም ላንቺ
ጥላቻ ያራቀው...
ልግመኛው ልብሽን ለህብረት አበርቺ
ተነሺ ልነሳ
ልነሳ ተነሺ
ክንዶቼ ስር ሰምጠሽ
አንድ የሆንበትን ፥ ትናንትን አስታውሺ
ልጠጋ ተጠጊ
ተጠጊ ልጠጋ
መፎካከር ቀድሞን ፥
በዱር አውሬ ቀንዶች ፥ ገላችን ሳይወጋ
ተረኛ ነን ስንል ፦
ተራችን ደርሶብን ፥ ሳንከፍል ዋጋ
የተከፈተው በር ፥ አንድ ሆነን ይዘጋ።
(ግድ የለም ቅረቢኝ....!)
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።
በትር ዱላ አይቆርጥም እግዚሀር ሲቆጣ
አመፅ አቅሉን ነስቶት መፋቀርን ላጣ
ለአልገዛም ባይ ህዝብ ይልካል አንበጣ
ብዬ እንደነገርኩሽ ከጥያቄሽ ማግስት
ዘር ብሄርን ሳይለይ እህል የሚያነክት
ርግማን ተነስቷል በይ ክንድሽ ይመክት
ስሚኝ እታለሜ!
ተመልከች ማሳውን.. .
ተመልከችው መስኩን ...
ጥላቻ አዝሞት ምሰሶው ሳይፀና
የጎጆዋችን ክዳን ከመሬት ሳይቃና
መደማመጥ ጠፍቶን ፍቅር ሲሆን ኦና
ፍሬያችን ረግፏል የዘራነው አምና
እንግዲያስ ምን በጀን?
ምን ምድር ይዋጠን?
ጠግበን ስንላፋ ርሀብ ሊቀድመን
አፉን ከፍቶ ከደጅ.. .ከደፍ ቆሟልና
ለድል መራኮቱ ግጥሚያው ይቆይና
የፉክክሩ ቤት በሩ እንዳይከፈት
ጎተራችን ጎድሎ አየር ሳይሞላበት
አንቺም ለኔ ቁሚ እኔም ልቁም ላንቺ
ጥላቻ ያራቀው...
ልግመኛው ልብሽን ለህብረት አበርቺ
ተነሺ ልነሳ
ልነሳ ተነሺ
ክንዶቼ ስር ሰምጠሽ
አንድ የሆንበትን ፥ ትናንትን አስታውሺ
ልጠጋ ተጠጊ
ተጠጊ ልጠጋ
መፎካከር ቀድሞን ፥
በዱር አውሬ ቀንዶች ፥ ገላችን ሳይወጋ
ተረኛ ነን ስንል ፦
ተራችን ደርሶብን ፥ ሳንከፍል ዋጋ
የተከፈተው በር ፥ አንድ ሆነን ይዘጋ።
(ግድ የለም ቅረቢኝ....!)
@getem
@getem
@getem