እስር ቤትና ጊዜ!!!
ያ አሳሪማ ሁሉማ ትግሉ ጊዜን ማሰር ነው ይላሉ
ግራ ነው አፈጣጠሩ የግርም ሊጥ ነው አመሉ
አሳሪ ማሰር ሲደክመው እራሱን ያብታል አሉ
የሚታሰር ያጣ ለታ ክፉ ራሱን ያስራል አሉ
እንጂ ጊዜን ማሰር ነበር ያ አሳሪማ ሁሉ ትግሉ
ለካስ ገዢዎች ጅል ናቸው ጊዜ የሚያጥር መስሎቸው
በጉጠት ሽቦ ያጥሩታል ቀን ባጭር ይቀጫል ብለው በረጅም ግንብ ይከቡታል
ወቅትም ይገታ መስሎዋቸው ዘበኛ ያቆሙለታል
ሰዐት ይታፈን መስሎዋቸው ድንጋይ ቤት ይዘጉበታል
ዘመን ይሰግድ መስሎአቸው የውስጥ እግሩን ይገርፉለታል
ጊዜግን ከቶ እጅ አይሰጥም ይረዝማል እንደ ዘላለም
ሞት ያህል ቁመት ያበቅላል እንኳን እሱ ራሱ ሊቆም እኛን እራሱ ይዞን ይሄዳል
እንኳን ለታሳሪው እና ለአሳሪም አሳር ነው ጊዜ
እንደ አዳል መጫኛ ረዝሞ ይፈጥራል ለሁሉ አባዜ
ጊዜን ማሰር አይቻልም ላፍታም ማገት አይከጀል
ይልቁንስ ጊዜ ራሱ ቀን ሞልቶለት ሲደላደል
አጥር ግንቡን ወህኒ ቤቱን ከናሳሪው ያፈርሰዋል
ደሞም ያው ደስ ያለው ለታ ከዘብጢያ ፈልቅቆ
ከፀሐይ ብርሃን ነፃ አየር ከተስፋ አድባር እምነት ጨምቆ
በወግ ያረገናል ከኑሮው ጋር አሳስቆ
ጊዜ እንደ ፀጥታ እኮ ነው ለአፍታ አይታሰርም ከቶ
ሰው እንኳንስ ጊዜን ሊያስር ሊኖር ጊዜ የት አጊንቶ
((( ነብይ መኮንን ))💚💛❤️
ሰኔ1993 ዓ.ም ( ለ እስር ቤት ጊዜአችን ))
የህይወቴ ከባድ ሚዛን ግጥሞች ውስጥ አንዱ!!!!!!
"ናካይታ"💚
@balmbaras
@getem
@getem
ያ አሳሪማ ሁሉማ ትግሉ ጊዜን ማሰር ነው ይላሉ
ግራ ነው አፈጣጠሩ የግርም ሊጥ ነው አመሉ
አሳሪ ማሰር ሲደክመው እራሱን ያብታል አሉ
የሚታሰር ያጣ ለታ ክፉ ራሱን ያስራል አሉ
እንጂ ጊዜን ማሰር ነበር ያ አሳሪማ ሁሉ ትግሉ
ለካስ ገዢዎች ጅል ናቸው ጊዜ የሚያጥር መስሎቸው
በጉጠት ሽቦ ያጥሩታል ቀን ባጭር ይቀጫል ብለው በረጅም ግንብ ይከቡታል
ወቅትም ይገታ መስሎዋቸው ዘበኛ ያቆሙለታል
ሰዐት ይታፈን መስሎዋቸው ድንጋይ ቤት ይዘጉበታል
ዘመን ይሰግድ መስሎአቸው የውስጥ እግሩን ይገርፉለታል
ጊዜግን ከቶ እጅ አይሰጥም ይረዝማል እንደ ዘላለም
ሞት ያህል ቁመት ያበቅላል እንኳን እሱ ራሱ ሊቆም እኛን እራሱ ይዞን ይሄዳል
እንኳን ለታሳሪው እና ለአሳሪም አሳር ነው ጊዜ
እንደ አዳል መጫኛ ረዝሞ ይፈጥራል ለሁሉ አባዜ
ጊዜን ማሰር አይቻልም ላፍታም ማገት አይከጀል
ይልቁንስ ጊዜ ራሱ ቀን ሞልቶለት ሲደላደል
አጥር ግንቡን ወህኒ ቤቱን ከናሳሪው ያፈርሰዋል
ደሞም ያው ደስ ያለው ለታ ከዘብጢያ ፈልቅቆ
ከፀሐይ ብርሃን ነፃ አየር ከተስፋ አድባር እምነት ጨምቆ
በወግ ያረገናል ከኑሮው ጋር አሳስቆ
ጊዜ እንደ ፀጥታ እኮ ነው ለአፍታ አይታሰርም ከቶ
ሰው እንኳንስ ጊዜን ሊያስር ሊኖር ጊዜ የት አጊንቶ
((( ነብይ መኮንን ))💚💛❤️
ሰኔ1993 ዓ.ም ( ለ እስር ቤት ጊዜአችን ))
የህይወቴ ከባድ ሚዛን ግጥሞች ውስጥ አንዱ!!!!!!
"ናካይታ"💚
@balmbaras
@getem
@getem
ለጁምኣችን
💚
#ዛሬ ከግጥም ወጣ ብለን ሸጋ የሆነች ወግ ብናወጋስ ማን ከልካይ አለን..? ማንም !!
ያው ጁመዐ አይደል ካነበብኩትና ከመሰጠኝ በኢራን የሚነገር ተረት ጀባ ልበላችሁ እነሆ
በረከት፦
አንድ ታላቁ መምህር የኢብን አል ሁሳይን ደቀ መዝሙር እንዲህ ሲል ጥያቄ ሰነዘረላቸው፦
በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ዓለምን ከቆሻሻዋ ለማንፃት ይነሳሳሉ?
እርሳቸው ይህንን መለሱለት፦
በአንድ ወቅት በደማስቆ ከተማ የሚኖር አቡ ሙሳ አል ቁማሲ የሚባል ሼህ ነበር።
ከጥልቅ እውቀቱና ከጠቢብነቱ የተነሳ ማንም ሰው በተለየ አክብሮት እና አድናቆት
ይመለከተው ነበር። መልካም ሰው ስለመሆኑም የሚያውቅ ግን ማንም አልነበረም ።
በአንድ ወቅት ታዲያ ሼሁ ከሚስቱ ጋር የሚኖርበት ቤት በግንባታ እክል ምክንያት ወድቆ
ፈራረሰ። ያልተጠበቀው አደጋ ያደናገጣቸው ጎረቤቶቹም ፍርስራሹ መቆፈር ተያያዙት።
በዚህ ጥረታቸውም የሼሁ ሚስት የምትገኝበትን ስፍራ ማመላከት ቻሉ።
ወዲያውኑ ሚስት "ስለ እኔ አትጨነቁ ይልቅ ባለቤቴን ፈልጉት። ፈልጋችሁም አድኑት።
ወደዚያ ተቀምጦ ስለነበር ከውስጥ አንዳች ቦታ ተቀብሮ መኖር አለበት። እያለች መወትወት
ጀመረች። ጎረቤቶቹ ሚስት የጠቆመቻቸው አካባቢ ያለውን ክምር ፍርስራሽ በሙሉ
አንስተው ሲገላልጡት እንደተባለውም ሼሁን አገኙት ወዲያው ለጎረቤቶቹ የተናገረውን
ይህንን ነበር።
"ስለ እኔ አትጨነቁ። ይልቅ ቅደሙ እና ባለቤቴን ፈልጓት ፈልጋችሁም አድኗት። እዚያም
አከባቢ ጋደም ብላ ነበርና ፍርስራሹን ስር ተቀብራ ይሆናል።"
መምህሩም ታሪካቸውን በሚከታተለው ዓረፍተ ነገር ደመደሙ፦
"ሰው ሁሉ እንደነዚህ ጥንዶች መሆን ሲችል ዓለምን በጠቅላላ ከህመሟ ሁሉ እያነፃት
እንዳለ ይውቅ።"
መልካም ጁመዓ💚 "ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
💚
#ዛሬ ከግጥም ወጣ ብለን ሸጋ የሆነች ወግ ብናወጋስ ማን ከልካይ አለን..? ማንም !!
ያው ጁመዐ አይደል ካነበብኩትና ከመሰጠኝ በኢራን የሚነገር ተረት ጀባ ልበላችሁ እነሆ
በረከት፦
አንድ ታላቁ መምህር የኢብን አል ሁሳይን ደቀ መዝሙር እንዲህ ሲል ጥያቄ ሰነዘረላቸው፦
በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ዓለምን ከቆሻሻዋ ለማንፃት ይነሳሳሉ?
እርሳቸው ይህንን መለሱለት፦
በአንድ ወቅት በደማስቆ ከተማ የሚኖር አቡ ሙሳ አል ቁማሲ የሚባል ሼህ ነበር።
ከጥልቅ እውቀቱና ከጠቢብነቱ የተነሳ ማንም ሰው በተለየ አክብሮት እና አድናቆት
ይመለከተው ነበር። መልካም ሰው ስለመሆኑም የሚያውቅ ግን ማንም አልነበረም ።
በአንድ ወቅት ታዲያ ሼሁ ከሚስቱ ጋር የሚኖርበት ቤት በግንባታ እክል ምክንያት ወድቆ
ፈራረሰ። ያልተጠበቀው አደጋ ያደናገጣቸው ጎረቤቶቹም ፍርስራሹ መቆፈር ተያያዙት።
በዚህ ጥረታቸውም የሼሁ ሚስት የምትገኝበትን ስፍራ ማመላከት ቻሉ።
ወዲያውኑ ሚስት "ስለ እኔ አትጨነቁ ይልቅ ባለቤቴን ፈልጉት። ፈልጋችሁም አድኑት።
ወደዚያ ተቀምጦ ስለነበር ከውስጥ አንዳች ቦታ ተቀብሮ መኖር አለበት። እያለች መወትወት
ጀመረች። ጎረቤቶቹ ሚስት የጠቆመቻቸው አካባቢ ያለውን ክምር ፍርስራሽ በሙሉ
አንስተው ሲገላልጡት እንደተባለውም ሼሁን አገኙት ወዲያው ለጎረቤቶቹ የተናገረውን
ይህንን ነበር።
"ስለ እኔ አትጨነቁ። ይልቅ ቅደሙ እና ባለቤቴን ፈልጓት ፈልጋችሁም አድኗት። እዚያም
አከባቢ ጋደም ብላ ነበርና ፍርስራሹን ስር ተቀብራ ይሆናል።"
መምህሩም ታሪካቸውን በሚከታተለው ዓረፍተ ነገር ደመደሙ፦
"ሰው ሁሉ እንደነዚህ ጥንዶች መሆን ሲችል ዓለምን በጠቅላላ ከህመሟ ሁሉ እያነፃት
እንዳለ ይውቅ።"
መልካም ጁመዓ💚 "ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
ሰማይ ጋር እናውጋ!!!!
አባ ይሰሙኛል፤
የሆችሚኒ ወግ፤
የስታሊን መፈክር፤
የነፃ አውጭ ፊደል፤
የአቢዮት ነጋሪት፤
ለዚች ምስኪን አገር ፤
ቢነገር ቢታወጅ ፤
ከደም ጅረት በቀር በጦቢያ ልጆች ፊት አላወጣም ዋጋ፤
ዛሬም ያው ነው መልኩ፤
ሃገር ላፍርስ ብሏል ጉም ጉም እያለ ጅረትና መንጋ፤
ተናጋሪው ትውልድ፤
የአባቶቹን ምክር፤
ምን ሊረባኝ ብሎ በሩን ስለዘጋ፤
እንባችንን ይዘን፤
እኔም በኪታቤ አንቱም በዳዊቱ ሰማይ ጋር እናውጋ፤
እዝነቱ ብዙ ነው፤
መዳኛው ብዙ ነው ድረስልኝ ብሎ እሱን የተጠጋ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት! "ናካይታ"
@getem
@getem
@balmbaras
አባ ይሰሙኛል፤
የሆችሚኒ ወግ፤
የስታሊን መፈክር፤
የነፃ አውጭ ፊደል፤
የአቢዮት ነጋሪት፤
ለዚች ምስኪን አገር ፤
ቢነገር ቢታወጅ ፤
ከደም ጅረት በቀር በጦቢያ ልጆች ፊት አላወጣም ዋጋ፤
ዛሬም ያው ነው መልኩ፤
ሃገር ላፍርስ ብሏል ጉም ጉም እያለ ጅረትና መንጋ፤
ተናጋሪው ትውልድ፤
የአባቶቹን ምክር፤
ምን ሊረባኝ ብሎ በሩን ስለዘጋ፤
እንባችንን ይዘን፤
እኔም በኪታቤ አንቱም በዳዊቱ ሰማይ ጋር እናውጋ፤
እዝነቱ ብዙ ነው፤
መዳኛው ብዙ ነው ድረስልኝ ብሎ እሱን የተጠጋ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት! "ናካይታ"
@getem
@getem
@balmbaras
እምወድሸዋ ቅዳሜዋ!
❤
የሃድራ ላይ መደድ!!!!
ይሉኛል ጓዶቼ፤
በጨለማው መሃል፤
በሸለቆው መሃል፤
የተደላደልከው፤
ምነው ሳትፈራ ፤ምነው ሳተክዝ፤
ጠየቁኝ አሁንም፤
በበረሃው መሃል፤
በንዳዱ መሃል፤
እንደምን ፈለቀ?
እንደምን ደመቀ፤የግንባርህ ወዝ?
ቁርጡን ነገርኳቸው፤
እንኳን የኔን ጅስም፤
ምድሩን የሚያጠራው፤ እንደ ሃምሌ ወንዝ፤
አልሃምዱ አይደለም ወይ፤
ሰማይ መወጣጫው፤ የዱኣው ምርኩዝ።
እናም ዘመዶቼ ፤
እንደአገሬ ጀማ፤
አሁንም አጥብቄ፤
አልሃምዱሊላሂ፤
ተመስገን ጌታየ፤ ሆኗል ንግግሬ፤
ለምንድን ካላችሁ፤
ያኔ በክፉ ቀን፤
በገራገር ዱኣ፤
በአልሃምዱ ጦር ጋሻ፤
ካውሬው ከእንጋግራው ተርፋለች አገሬ።
አጀብ እኔ!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሚት!❤
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
❤
የሃድራ ላይ መደድ!!!!
ይሉኛል ጓዶቼ፤
በጨለማው መሃል፤
በሸለቆው መሃል፤
የተደላደልከው፤
ምነው ሳትፈራ ፤ምነው ሳተክዝ፤
ጠየቁኝ አሁንም፤
በበረሃው መሃል፤
በንዳዱ መሃል፤
እንደምን ፈለቀ?
እንደምን ደመቀ፤የግንባርህ ወዝ?
ቁርጡን ነገርኳቸው፤
እንኳን የኔን ጅስም፤
ምድሩን የሚያጠራው፤ እንደ ሃምሌ ወንዝ፤
አልሃምዱ አይደለም ወይ፤
ሰማይ መወጣጫው፤ የዱኣው ምርኩዝ።
እናም ዘመዶቼ ፤
እንደአገሬ ጀማ፤
አሁንም አጥብቄ፤
አልሃምዱሊላሂ፤
ተመስገን ጌታየ፤ ሆኗል ንግግሬ፤
ለምንድን ካላችሁ፤
ያኔ በክፉ ቀን፤
በገራገር ዱኣ፤
በአልሃምዱ ጦር ጋሻ፤
ካውሬው ከእንጋግራው ተርፋለች አገሬ።
አጀብ እኔ!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሚት!❤
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
ያልተገናኘን ዕለት አልተገኘም ውበት
(ተፃፈ በ አቤነዘር ሽፈራው)
ሳንገናኝ ነጋ ሳንገናኝ መሸ
ፀሃይ አዘቅዝቃ ጨለማ አገረሸ
ቁሮችም በደስታ ስያዜሙ አደሩ
ውበትን እሚዘልፍ
መኖርን እሚገፍ
ሙታን እሚጣራ ዜማ ሲቀምሩ
ከዋክብት ደብዝዘው ጠፍቷል ቀለማቸው
ጠልሽቷል ወዛቸው
ፍቅር ተሸብሮ ገብቷል ከምሽጉ
ጥላቻና ክፋት አብረው ቢዋጉ
እናም
ሰማዩ ጥቀርሻ ፅልመት የወረሰው
አልጋዬ የሳማ ህልሜን ኮሰኮሰው
።።።።።።
ሳንገናኝ መሸ ሳንገናኝ ነጋ
ጀምበር አሎጣችም ጠፋች ተፈልጋ
ቅዠት ያባነኛል ህልሜን እየወጋ
በአእዋፍ ፋጨት ቦታ የጥሩምባ ቅኔ
በቅዳሴ ድምፅ ምትክ የመርዶ አርጂ ኮቴ
ጆረዬን ነረተው ፤ ሆዴን ባር ባር አለው
ለዕለት ባንገናኝ ሞተሻል ሊሉነው
ዘልቆል ከቀያችን ጨለማ ያለ ከልካይ
አልመጣች መሰል ከገባኦን ፀሃይ
እንዴት ነው ላልሽኝ መልስ
እንዲህ ነው አካሌ
እንዲህ ነው ዕለቱ
የእኔ እና ያንቺ ውበት
ያልተገናኘን ዕለት
@getem
@getem
@getem
(ተፃፈ በ አቤነዘር ሽፈራው)
ሳንገናኝ ነጋ ሳንገናኝ መሸ
ፀሃይ አዘቅዝቃ ጨለማ አገረሸ
ቁሮችም በደስታ ስያዜሙ አደሩ
ውበትን እሚዘልፍ
መኖርን እሚገፍ
ሙታን እሚጣራ ዜማ ሲቀምሩ
ከዋክብት ደብዝዘው ጠፍቷል ቀለማቸው
ጠልሽቷል ወዛቸው
ፍቅር ተሸብሮ ገብቷል ከምሽጉ
ጥላቻና ክፋት አብረው ቢዋጉ
እናም
ሰማዩ ጥቀርሻ ፅልመት የወረሰው
አልጋዬ የሳማ ህልሜን ኮሰኮሰው
።።።።።።
ሳንገናኝ መሸ ሳንገናኝ ነጋ
ጀምበር አሎጣችም ጠፋች ተፈልጋ
ቅዠት ያባነኛል ህልሜን እየወጋ
በአእዋፍ ፋጨት ቦታ የጥሩምባ ቅኔ
በቅዳሴ ድምፅ ምትክ የመርዶ አርጂ ኮቴ
ጆረዬን ነረተው ፤ ሆዴን ባር ባር አለው
ለዕለት ባንገናኝ ሞተሻል ሊሉነው
ዘልቆል ከቀያችን ጨለማ ያለ ከልካይ
አልመጣች መሰል ከገባኦን ፀሃይ
እንዴት ነው ላልሽኝ መልስ
እንዲህ ነው አካሌ
እንዲህ ነው ዕለቱ
የእኔ እና ያንቺ ውበት
ያልተገናኘን ዕለት
@getem
@getem
@getem
ይግባኝ
""""""""""
ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ ዶሴ፤
ማንንም የማላቅ
ያሉኝን የማምን ምስኪን ነኝ ለራሴ።
አትብላ ብትለኝ
እርኩሰት ያላትን ያቺን እፀ በለስ፤
ከጉያህ ወጥቼ በጥፋት እንዳል'ረክስ፤
ያጥንቴ ፍላጭ ናት የስህተቴ ምክንያት፤
በእሷም አልፈርድም
የራሷ የሆን እሷም ምክንያት አላት።
ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ መዝገብ፤
እኩል ፍርድ ተላልፏል
እንደ አንድ ተወስዶ ቅምሻና መመገብ።
እሷ በበኩላ ከፍሬው ቀንጥሳ፤
ከአንድም ሁለት ስትል
ከሁለትም ሶስቴ በልታ ስታገሳ፤
እኔ በበኩሌ
ከምላሴ ወርዶ ትዕዛዙም ቢረሳ፤
ሆዴን ቁልቁል አይቶ
ሳልበላው ሳይበላኝ ከአንገቴ ቀረሳ።
አልክድም እርግጥ ነው
ጥፋቴን በጉልህ በግልፅ አምኛለው፤
ነገር ግን ብይኑ ስህተት ነው እላለሁ፤
ይግባኝ አንተን ማለት
መልሶ መጠየቅ ያስፈራል አውቃለሁ፤
ፍርድ ያጣሁ ሲመስለኝ
መቼም ሰው ነኝና እንቆጠቆጣለሁ።
ግና እውቀልኝ
የድፍረት አይደለም ነፍሴን ብጠይቃት፤
አምናለሁ አያስቆጣም
ፈራጅን ለፍርዱ ፍርድህ ይግባኝ ማለት!
እናም ፈጣሪ ሆይ
ፈራጅ ፍትህ ይዞ ፍርድ ካላዘጋጀ
ቀማሹም በይውም እኩል ከፈረጀ
ውረዱ ወደመሬት ብሎ እንደታወጀ
ሚዛን ተጓደለች ቅጣቱም አልበጀ!
ያም ሆነ ይህም ሆነ
ግን ተርቤ ነበር ስትጥለኝ ከምድር፤
የበላሁት ፍሬ
እሆዴ ጋ ሳይደርስ አንገቴ ጋ ነበር..!
@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
""""""""""
ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ ዶሴ፤
ማንንም የማላቅ
ያሉኝን የማምን ምስኪን ነኝ ለራሴ።
አትብላ ብትለኝ
እርኩሰት ያላትን ያቺን እፀ በለስ፤
ከጉያህ ወጥቼ በጥፋት እንዳል'ረክስ፤
ያጥንቴ ፍላጭ ናት የስህተቴ ምክንያት፤
በእሷም አልፈርድም
የራሷ የሆን እሷም ምክንያት አላት።
ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ መዝገብ፤
እኩል ፍርድ ተላልፏል
እንደ አንድ ተወስዶ ቅምሻና መመገብ።
እሷ በበኩላ ከፍሬው ቀንጥሳ፤
ከአንድም ሁለት ስትል
ከሁለትም ሶስቴ በልታ ስታገሳ፤
እኔ በበኩሌ
ከምላሴ ወርዶ ትዕዛዙም ቢረሳ፤
ሆዴን ቁልቁል አይቶ
ሳልበላው ሳይበላኝ ከአንገቴ ቀረሳ።
አልክድም እርግጥ ነው
ጥፋቴን በጉልህ በግልፅ አምኛለው፤
ነገር ግን ብይኑ ስህተት ነው እላለሁ፤
ይግባኝ አንተን ማለት
መልሶ መጠየቅ ያስፈራል አውቃለሁ፤
ፍርድ ያጣሁ ሲመስለኝ
መቼም ሰው ነኝና እንቆጠቆጣለሁ።
ግና እውቀልኝ
የድፍረት አይደለም ነፍሴን ብጠይቃት፤
አምናለሁ አያስቆጣም
ፈራጅን ለፍርዱ ፍርድህ ይግባኝ ማለት!
እናም ፈጣሪ ሆይ
ፈራጅ ፍትህ ይዞ ፍርድ ካላዘጋጀ
ቀማሹም በይውም እኩል ከፈረጀ
ውረዱ ወደመሬት ብሎ እንደታወጀ
ሚዛን ተጓደለች ቅጣቱም አልበጀ!
ያም ሆነ ይህም ሆነ
ግን ተርቤ ነበር ስትጥለኝ ከምድር፤
የበላሁት ፍሬ
እሆዴ ጋ ሳይደርስ አንገቴ ጋ ነበር..!
@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
የፀሎት ፉክክር ፩(ልዑል ኃይሌ)
.
ለረጅም ዘመናት
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እየተባለበት፤
በእያንዳንዱ ሠው አፍ እግዜር ዕዳ አለበት፤
እያሉ ሠምቼ
ይኸው መጥቻለሁ
እሱ ይስጥህ እያሉ ሲልኩኝ ወዳንተ፤
በል እግዜር መፅውተኝ
ምሰፍርበት አጣሁ
ምድሩን ዘር ዘርተውት
እንኳን ለኔ ቀርቶ ቦታ የለም ላንተ፤
.
ብዛ ተባዛባት
ምድሪቱንም ሙላት ብለህ ስትልከኝ፤
ምን አስበህ ይሆን?
እንደሚታነቅ ሰው ባዶ ኪስ የላክከኝ?፤
.
ፍቃድ ትዕዛዝህን
ላከብር ልበዛ ኑሮ ልጀምር ስል፤
እንዳልከው አልሆነም
አብስትራክት ሆኗል የዚህች ምድር ምስል፤
.
ፈጣሪ ሆይ ፍረድ!
በደላቸው በዛ ትዕግስትህን አይተው፤
የገዛ መሬትህን
እየሸጡልኝ ነው በስንዝር ለክተው፤
.
ወይ ምድርህን ስጠኝ
ወይ ስንዝሩን ቀማ፤
መሬቴን ብቻ ሆኗል
የዚህች ምድር ዜማ፤
እኔ አላማረኝም
መሬትህን ውሰድ በሠው ሳትቀማ፤
19-01-2012 ዓ.ም.
@getem
@getem
@getem
.
ለረጅም ዘመናት
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እየተባለበት፤
በእያንዳንዱ ሠው አፍ እግዜር ዕዳ አለበት፤
እያሉ ሠምቼ
ይኸው መጥቻለሁ
እሱ ይስጥህ እያሉ ሲልኩኝ ወዳንተ፤
በል እግዜር መፅውተኝ
ምሰፍርበት አጣሁ
ምድሩን ዘር ዘርተውት
እንኳን ለኔ ቀርቶ ቦታ የለም ላንተ፤
.
ብዛ ተባዛባት
ምድሪቱንም ሙላት ብለህ ስትልከኝ፤
ምን አስበህ ይሆን?
እንደሚታነቅ ሰው ባዶ ኪስ የላክከኝ?፤
.
ፍቃድ ትዕዛዝህን
ላከብር ልበዛ ኑሮ ልጀምር ስል፤
እንዳልከው አልሆነም
አብስትራክት ሆኗል የዚህች ምድር ምስል፤
.
ፈጣሪ ሆይ ፍረድ!
በደላቸው በዛ ትዕግስትህን አይተው፤
የገዛ መሬትህን
እየሸጡልኝ ነው በስንዝር ለክተው፤
.
ወይ ምድርህን ስጠኝ
ወይ ስንዝሩን ቀማ፤
መሬቴን ብቻ ሆኗል
የዚህች ምድር ዜማ፤
እኔ አላማረኝም
መሬትህን ውሰድ በሠው ሳትቀማ፤
19-01-2012 ዓ.ም.
@getem
@getem
@getem
ለሰንበታችን
💚
ሙዚቃ የህይወታችን አንዱ ማጣፈጫ ቅመም ነች....!!
ደስታችን ፣ ሀዘናችን ፣ ፍቅራችንን፣አንድነታችን የምንገልፅባት የምንተነፍስባት...ሸጋ ጥበብ ነች !
እስቲ እኛም እንተፍስ ፣ እናጎራጉር ሀዘናችን ፣ መሻታችን ፣ ውስጣችን የሚርመሰመሰው በል በል የሚለንን አንድ ሁለቱን ሀሳብ እስቲ ከሙዚቀኞቻችን የሙዚቃ ማህደራቸው ወስደን #ብናጎራጉር ማን ከልካይ አለን...? ማንም..!!
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
💚
ሙዚቃ የህይወታችን አንዱ ማጣፈጫ ቅመም ነች....!!
ደስታችን ፣ ሀዘናችን ፣ ፍቅራችንን፣አንድነታችን የምንገልፅባት የምንተነፍስባት...ሸጋ ጥበብ ነች !
እስቲ እኛም እንተፍስ ፣ እናጎራጉር ሀዘናችን ፣ መሻታችን ፣ ውስጣችን የሚርመሰመሰው በል በል የሚለንን አንድ ሁለቱን ሀሳብ እስቲ ከሙዚቀኞቻችን የሙዚቃ ማህደራቸው ወስደን #ብናጎራጉር ማን ከልካይ አለን...? ማንም..!!
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
አማኝ ነሽ ሀገሬ
ጣድቅ አንቺነተሽ
ሀጣንን በሙሉ ደጁ ሚሰበስብ
እኛ ግን ጨቅይተን
ክብርሽን እረሳን
አንድነትን ጠልተን ስለ ጓጥ ስናስብ፡፡
፡
ቢገባን አውነቱ
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ ከሁሉ የበለጠ
ቃል ነበረን ድሮ
ሊያውም ከሰው ሳይሆን ከ'ግዜር የተሰጠ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
ጣድቅ አንቺነተሽ
ሀጣንን በሙሉ ደጁ ሚሰበስብ
እኛ ግን ጨቅይተን
ክብርሽን እረሳን
አንድነትን ጠልተን ስለ ጓጥ ስናስብ፡፡
፡
ቢገባን አውነቱ
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ ከሁሉ የበለጠ
ቃል ነበረን ድሮ
ሊያውም ከሰው ሳይሆን ከ'ግዜር የተሰጠ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
ተረትና ዘመን!
(ካልጨረስክ አትጀምር )
"እዮብ ዘ ማርያም"
-
ተረት ተረት ስልሽ፣
የ'ላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
ከዘመናት ባ'ንዱ...
ጎልያድ የሚሉት፣
ቋጥኝ የሚያህል ግዙፍ ሰው ነበረ
በዚህ ግዙፍ ሰው ላይ፣
ብላቴናው ዳዊት ጠጠር ወረወረ
በዚች ጠጠር ምክንያት ያ ሰው ወድቆ ቀረ
ብርቱ ነኝ የሚል ሰው፣
ገላውን አግዝፎ እንዲ'ሁ ቢዋትትም
መነሻው ያላማረ፣
ልክ እንደ ጎልያድ መድረሻው ነው የትም!
በዚች ግራ አለም፣
በሆነች ጣፋጭ በሆነች ከንቱ
ጌቶች ሲረግጡን፣
ሆነው እንዳ'ለቃ ሆነው እንደ ብርቱ
ሲረግጡን ቆዩና፣
እንቅፋት መቷቸው እንደ ዘበት ሞቱ!
በዚች ጣፋጭ አለም
በዚች መራራ አለም
ብርቱ ዘመን እንጂ ብርቱ ፍጡር የለም
ብርቱ ነኝ የሚልም፣
እርሱ ሰው ተሳስቷል እርሱ ብርቱ አይደለም!
የመቆም ጥበቡ፣
በምሁር ነን ባዮች በመላ ቢረቀቅ
የቆመ ሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ!
እናም አበባዬ አየሽልኝ አይደል
ባ'ንዲት ጠጠር ብቻ፣
እንዴት እን'ዶደቀ የማይወድቀው ወደል!
ይህ ፊኛ በከንቱ፣
ገላውን አግዝፎ እንዲ'ሁ ይነፋፋል
ስንጥር ያገኘው ዕለት...
ሟሽሾ ሟሽሾ ግዝፈቱ ይጠፋል
በአንዲት ቃል ብቻ ሰማይ ምድር ያልፋል!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ...
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
በሀበሻ ምድር በዚች ምስኪን ሀገር
"ነው"ነቱ ቀርቶ...
ሁሉም "ነበር"ሆኗል የሚታየው ነገር!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
ካ'መታት ድሮ አመት...
በኛ እናት ሀገር፣
ልክ እንደ ሚኒባስ ባውሎፕራን ውስጥም ወያላ ነበረ
ይህ ምስኪን ወያላ፣
ጣልያን ጣልያን ቢል የሚገባ ቢያጣ ብቻውን በረረ!
እናም አበባዬ አየሽልኝ አይደል፣
ድሮ ጦቢያውያን ክብራቸውን አልሸጡም
ጠላት አስወጡ እንጂ ከሀገር አልወጡም!
ይህን ስልሽ ደግሞ፣
መከራ ብሏቸው ካ'ገር ቤት በወጡ ከቶ እንዳትፈርጂ
በፈረድሽ ማግስት፣
አንቺም እንደ እነርሱ...
መከራ አንቆራጦሽ ይሆናል ትሄጂ!
እናልሽ አለሜ
ብጨቀጭቅሽም...
ወድጄሽ ነው እንጂ አይደለም ታምሜ!
ልክ እንደ ሰማይ ጫፍ፣
ጫፉን እያየነው ከቶ አላልቅ እንዳለ
ባለቀ ተረት ዉስጥ ጅምር ተረት አለ!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
@getem
@getem
@getem
(ካልጨረስክ አትጀምር )
"እዮብ ዘ ማርያም"
-
ተረት ተረት ስልሽ፣
የ'ላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
ከዘመናት ባ'ንዱ...
ጎልያድ የሚሉት፣
ቋጥኝ የሚያህል ግዙፍ ሰው ነበረ
በዚህ ግዙፍ ሰው ላይ፣
ብላቴናው ዳዊት ጠጠር ወረወረ
በዚች ጠጠር ምክንያት ያ ሰው ወድቆ ቀረ
ብርቱ ነኝ የሚል ሰው፣
ገላውን አግዝፎ እንዲ'ሁ ቢዋትትም
መነሻው ያላማረ፣
ልክ እንደ ጎልያድ መድረሻው ነው የትም!
በዚች ግራ አለም፣
በሆነች ጣፋጭ በሆነች ከንቱ
ጌቶች ሲረግጡን፣
ሆነው እንዳ'ለቃ ሆነው እንደ ብርቱ
ሲረግጡን ቆዩና፣
እንቅፋት መቷቸው እንደ ዘበት ሞቱ!
በዚች ጣፋጭ አለም
በዚች መራራ አለም
ብርቱ ዘመን እንጂ ብርቱ ፍጡር የለም
ብርቱ ነኝ የሚልም፣
እርሱ ሰው ተሳስቷል እርሱ ብርቱ አይደለም!
የመቆም ጥበቡ፣
በምሁር ነን ባዮች በመላ ቢረቀቅ
የቆመ ሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ!
እናም አበባዬ አየሽልኝ አይደል
ባ'ንዲት ጠጠር ብቻ፣
እንዴት እን'ዶደቀ የማይወድቀው ወደል!
ይህ ፊኛ በከንቱ፣
ገላውን አግዝፎ እንዲ'ሁ ይነፋፋል
ስንጥር ያገኘው ዕለት...
ሟሽሾ ሟሽሾ ግዝፈቱ ይጠፋል
በአንዲት ቃል ብቻ ሰማይ ምድር ያልፋል!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ...
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
በሀበሻ ምድር በዚች ምስኪን ሀገር
"ነው"ነቱ ቀርቶ...
ሁሉም "ነበር"ሆኗል የሚታየው ነገር!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
ካ'መታት ድሮ አመት...
በኛ እናት ሀገር፣
ልክ እንደ ሚኒባስ ባውሎፕራን ውስጥም ወያላ ነበረ
ይህ ምስኪን ወያላ፣
ጣልያን ጣልያን ቢል የሚገባ ቢያጣ ብቻውን በረረ!
እናም አበባዬ አየሽልኝ አይደል፣
ድሮ ጦቢያውያን ክብራቸውን አልሸጡም
ጠላት አስወጡ እንጂ ከሀገር አልወጡም!
ይህን ስልሽ ደግሞ፣
መከራ ብሏቸው ካ'ገር ቤት በወጡ ከቶ እንዳትፈርጂ
በፈረድሽ ማግስት፣
አንቺም እንደ እነርሱ...
መከራ አንቆራጦሽ ይሆናል ትሄጂ!
እናልሽ አለሜ
ብጨቀጭቅሽም...
ወድጄሽ ነው እንጂ አይደለም ታምሜ!
ልክ እንደ ሰማይ ጫፍ፣
ጫፉን እያየነው ከቶ አላልቅ እንዳለ
ባለቀ ተረት ዉስጥ ጅምር ተረት አለ!
ተረት ተረት ስልሽ፣
የላም በረት ብለሽ ተቀበዪኝ ውዴ
ምን ትልቅ ቢሆኑ፣
ተረት ተረት መስማት አይከፋም አንዳንዴ!
@getem
@getem
@getem
አትፅናኝ
።።።።።።
ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።
፣
አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።
፣
በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
፣
የሚገርም አይነት ጽሑፍ፣ ለዛውም የግጥም ጽሑፍ ማንበብ እንዲህ ከፍ ያደርጋል ለካ!
፣
#መዘክር_ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች: 2010 ዓ·ም)
@getem
@getem
@getem
።።።።።።
ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።
፣
አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።
፣
በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
፣
የሚገርም አይነት ጽሑፍ፣ ለዛውም የግጥም ጽሑፍ ማንበብ እንዲህ ከፍ ያደርጋል ለካ!
፣
#መዘክር_ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች: 2010 ዓ·ም)
@getem
@getem
@getem