ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ በመጽሐፍ ቅዱስ #ሰዎች #መላእክትና #እንስሳት እንዲሁም ልዩ ልዩ #ስፍራዎች ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ስለተጠቀሱት ነገሮች #በተናጠል ብናያቸው የተሟላ #መረጃን አይሰጡም። ምክንያቱም #የመጽሐፍ ቅዱስ #ዓላማ #እግዚአብሔር እንጂ #ሰዎቹ፣ ልዩ ልዩ #ስፍራዎቹ ወይም #መላእክቱ አይደሉም።

▶️ በመሆኑም #መጽሐፍ #ቅዱስ #ማርያምን የሚያነሳበት #ዋና ምክንያት ስለሚመጣው #መሲህ #ከስር #መሠረቱ ለመናገር እንጂ #ማርያምን #ማዕከል ቢያደርግ ኖሮ አጠቃላይ #ውልደቷን#እድገቷን #የህይወት #ታሪኳን... ወ.ዘ.ተ #በተሟላና #በበቂ ሁኔታ ይገልጽ ነበር። ነገር ግን ያ አልነበረምና አልሆነም። #ማርያም #በሉቃ 1፥26 እና #በማቴ 1፥2 ላይ መጠቀሷ #ክርስቶስን #በድንግልና #እንደወለደችው፣ ይህም #ልጅ #ታላቅ እንደሚሆን ለማሳየት በመሆኑ እርሱ #ከተወለደ ቡኋላ #የክርስቶስን #ታሪክ #ተከትሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ #የእርሷን #ሁኔታ #ከወለደች #ቡኋላ ወደ ጎን ይተዋል።

▶️ ለምሳሌ #በማቴ 1፥18 <የኢየሱስ ክርስተስም ልደት እንዲህ ነበር> በማለት ይጀምርና #ለዮሴፍ #ታጭታ ከነበረችው #ድንግል #ሴት እንደተወለደ ያሳያል። እዚጋ ስናይ #ዋና #መልዕክቱ #የኢየሱስ #ክርስቶስን ልደት ማሳየት ስለሆነ #ድንግል #ማርያም እግረ መንገዷን እንደተጠቀሰች እናያለን። ምዕራፍ 2 ላይ ደግሞ #ለተወለደው #ህጻን (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የምስራቅ #ጠበብት #ሊሰግዱለት እንደመጡ ይናገርና <ህጻኑን ከእናቱ ጋር አዩት> በማለት #ድንግል #ማርያም #እግረ #መንገዷን ስትጠቀስ እናያለን። ከዛም <ወድቀውም ሰገዱላቸው> ሳይሆን <ወድቀውም ሰገዱለት> በማለት #ህጻኑን #ከእናቱ #ማርያም ጋር ቢያዩም #ለህጻኑ #ለክርስቶስ #ከእናቱ #ነጥለው #ስግደት ለእርሱ #ብቻ #አቀረቡ። በዚህም ሳያበቁ ሳጥኖቻቸውን ከፍተው #እጅ #መንሻ#ወርቅና #ዕጣን #ከርቤን አሁንም ከእናቱ #ነጥለው #አቀረቡለት
ከዚያም #ዩሐንስ #ወደቤቱ #እንደወሰዳት ይገልጽና ወደ ቤት #ተወስዳ ምን እንደሆነች፣ እንዴት እንደነበረች ወ.ዘ.ተ የሚጠቅስልን ምንም ነገር ሳይኖር #መጽሐፍ #ቅዱስ ወደ #ክርስቶስ #ሞት#መቀበርና #መነሳት ላይ #አንድ #በአንድ #ነጥብ #በነጥብ #አውጠንጥኖ ሰፊ ዘገባ ያቀርባል።

▶️ በሐዋ 1፤ 13-14 እንደ #አንድ #ምእመን #ማርያም #ከሐዋርያት ጋር በመሆን #በጸሎት #ትተጋ እንደነበር ይገልጽና ከዚያ #ስሟን እንኳ #ፈጽሞ አያነሳም።

▶️ ሐዋርያው #ጳውሎስ #አብ #ዘመኑ ሲደርስ #ልጁን እንደላከ #ለመግለጽ #ማርያምን #ስሟን እንኳ ሳይጠራ <ሴት> በማለት ብቻ ያውም #አንድ #ጊዜ #ጠቀሳት እንጂ #በ14 #የመልዕክት #መጻሕፍቱ ውስጥ #ታላቅ አድርጎ የሰበከው #ኢየሱስ #ክርስቶስን ብቻ ነበር። በመሆኑም #ማርያም #በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው #ለክርስቶስ #እግረ #መንገድነት እንጂ #የመጽሐፍ ቅዱስ #ዋና #ዓላማ ሆና አልነበረም። ስለሆነም #አንዳንድ #ሰዎች #ማርያምን #የሃይማኖታቸው #ማዕከል አድርገው ረጅም መንፈሳዊ #ፕሮግራማቸውን ማቃጠላቸው #ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ #ባህል ከመሆኑም በተጨማሪ #ለክርስቶስ የሰጡትን #ግምት #ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

(3.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
ይህ #ለከንፈርሽ#ለጉሮሮሽ#ለጡትሽ#ለሽንጥሽ#ለሆድሽ#ለኩላሊትሽ#ለአንጀትሽ#ለእንብርትሽ#ለማህፀንሽ#ለድንግልናሽ#ለተረከዝሽ#ለጫማዎችሽ#ለእግር ጥፍርሽ፣ #ለመቃብርሽ፣ የሚለው #መልክእ በየዕለቱ #በግልና #በጋራ በመከፋፈል #በቤተክርስቲያን ደረጃም፣ #በቃልም#በመጽሐፍም ይደገማል።

▶️ እንግዲህ ይህ #አይነቱ #ምስጋና እንኳንስ #ለማርያም #ለክርስቶስ እንኳ ብናረገው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ሁሉም ከዚህ #አለም ወደ እዛኛው #አለም #በነፍሳቸው የተሻገሩ #ሰዎች #በምድር በነበሩበት #በስጋዊ ዘመናቸው #ከልጅነት እድሜ #እውቀት ወደ #አዋቂ #ሲያድጉ#ሲበርዳቸው #ሲሞቃቸው#ሲያዝኑ#ሲደሰቱ#ጥፍራቸውና #ጸጉራቸው ሲያድግ፣ #ሲያጥር#ሰውነታቸው #ሲቆሽሽና ሲታጠብ.... ወዘተ እንደነበረው ሁሉ #በሰማይ እንደዛ አይታወቁም። #ሰማይ ሌላ #ስርዓት ነውና።

▶️ ስለዚህ #ድንግል ማርያም #በአጸደ ነፍስ ባለችበት #በሰማይ እንደ #ምድራዊ #ስጋ #አካል #ጥፍሯ በየቀኑ አያድግም፣ #ጡቶቿም ወተት #አያፈልቁም#አንጀቶቿም በሀዘን #አይቃጠሉም#ተረከዞቿም #ድጥ አያድጣቸውም፣ #እግሮቿም #ጫማ የላቸውም። <<ደግሞ ሰማያዊ አካል አለ፥ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር ልዩ ነው፥ የምድራዊም አካል ክብር ልዩ ነው።>> {1 ቆሮ 15፥40}። ስለሆነም #መልክዓ ማርያምና ተመሳሳይ #መጻሕፍት #ለአዕምሮ የማይመች #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ #አጸያፊ #ስነ ጽሁፍ እንጂ #ጸሎት ሊሆን በፍጹም አይችልም።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልፍ ክፍሌ ፤መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ መልክእ፤ ገጽ 566፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1948።