ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ በመጽሐፍ ቅዱስ #ሰዎች #መላእክትና #እንስሳት እንዲሁም ልዩ ልዩ #ስፍራዎች ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ስለተጠቀሱት ነገሮች #በተናጠል ብናያቸው የተሟላ #መረጃን አይሰጡም። ምክንያቱም #የመጽሐፍ ቅዱስ #ዓላማ #እግዚአብሔር እንጂ #ሰዎቹ፣ ልዩ ልዩ #ስፍራዎቹ ወይም #መላእክቱ አይደሉም።

▶️ በመሆኑም #መጽሐፍ #ቅዱስ #ማርያምን የሚያነሳበት #ዋና ምክንያት ስለሚመጣው #መሲህ #ከስር #መሠረቱ ለመናገር እንጂ #ማርያምን #ማዕከል ቢያደርግ ኖሮ አጠቃላይ #ውልደቷን#እድገቷን #የህይወት #ታሪኳን... ወ.ዘ.ተ #በተሟላና #በበቂ ሁኔታ ይገልጽ ነበር። ነገር ግን ያ አልነበረምና አልሆነም። #ማርያም #በሉቃ 1፥26 እና #በማቴ 1፥2 ላይ መጠቀሷ #ክርስቶስን #በድንግልና #እንደወለደችው፣ ይህም #ልጅ #ታላቅ እንደሚሆን ለማሳየት በመሆኑ እርሱ #ከተወለደ ቡኋላ #የክርስቶስን #ታሪክ #ተከትሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ #የእርሷን #ሁኔታ #ከወለደች #ቡኋላ ወደ ጎን ይተዋል።

▶️ ለምሳሌ #በማቴ 1፥18 <የኢየሱስ ክርስተስም ልደት እንዲህ ነበር> በማለት ይጀምርና #ለዮሴፍ #ታጭታ ከነበረችው #ድንግል #ሴት እንደተወለደ ያሳያል። እዚጋ ስናይ #ዋና #መልዕክቱ #የኢየሱስ #ክርስቶስን ልደት ማሳየት ስለሆነ #ድንግል #ማርያም እግረ መንገዷን እንደተጠቀሰች እናያለን። ምዕራፍ 2 ላይ ደግሞ #ለተወለደው #ህጻን (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የምስራቅ #ጠበብት #ሊሰግዱለት እንደመጡ ይናገርና <ህጻኑን ከእናቱ ጋር አዩት> በማለት #ድንግል #ማርያም #እግረ #መንገዷን ስትጠቀስ እናያለን። ከዛም <ወድቀውም ሰገዱላቸው> ሳይሆን <ወድቀውም ሰገዱለት> በማለት #ህጻኑን #ከእናቱ #ማርያም ጋር ቢያዩም #ለህጻኑ #ለክርስቶስ #ከእናቱ #ነጥለው #ስግደት ለእርሱ #ብቻ #አቀረቡ። በዚህም ሳያበቁ ሳጥኖቻቸውን ከፍተው #እጅ #መንሻ#ወርቅና #ዕጣን #ከርቤን አሁንም ከእናቱ #ነጥለው #አቀረቡለት
ሰብዓ ሰገል በኮከቡ መሪነት ጌታችንን ካገኙ በኋላ ይዘውት የመጡትን ስጦታ ከመስጠት በተጨማሪ እኛ ሁላችን በሙሉ ደስታ ለምንሰግድለት ጌታ ሰግደውለታል።

እነዚህ ሰዎች ለሕጻኑ ሲሰግዱ በወቅቱ በዚያ ሥፍራ ላይ ስግደት የሚገባቸው ሌሎች ሰዎች ስላልነበሩ ለማንም አልሰገዱም።

ምናልባት በወቅቱ ከነበሩት ሰዎች ስግደት የሚገባው አካል ኖሮ እነርሱ ግን ሳይሰግዱ የቀሩ ከሆነ የመጀመሪያዎቹ መናፍቃን እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

መጽሐፉ እንደሚነግረን የሰገዱት ለእርሱ ብቻ ነው። በእርግጥም ስግደት የሚገባው እርሱ ብቻ ነውና ለእርሱ ብቻ ለመስገድ የወሰናችሁ እውነተኛውን አምልኮ እየፈፀማችሁ ነውና በርቱ!!


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 2)
----------
9፤ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

10፤ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።

11፤ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ #ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም #ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም #አቀረቡለት

@gedlatnadersanat
@gedlatnadersanat