ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
የአገራችን ቅዱሳን እውን መንፈሳዊ ናቸው ?? #በአገራችን ቅዱሳን ተብለው ታቦት ተቀርጾ -ቀን ተሰይሞ -ገድል ተጽፎላቸው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል እየተባሉ ከወር እስከወር የሰው ልብ ላይ ነግሰው የአምላክ ገንዘብ የሆነውን ስግደትና ዝማሬ መስዋእትም በጸጋ ስም የሚኮመኩሙ የቡልጋ የትግራይና የጎጃም ተወላጅ የሆኑ አፈጣጠራቸው አኑዋኑዋራቸውና ትምህርታቸው አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያልተሰማ #ክንፍ…


ቅዱስ እውነት ???

#ገድለ ተክለሃይማኖት፥ 48:1- 4

" አንድ ቀን በባሕር ዳር ተቀምጦ ሳለ፥ ሰይጣን ከባሕሩ ወጣ። የአባታችንንም ደቀመዝሙር ያዘው። አንተ ርኩስ መንፈስ ከልጄ ውጣ እያለ በመስቀል ምልክት አማተበ። ሰይጣኑም ዛሩም ደቀመዝሙሩን ትቶ ፈጥኖ ሸሸ። ሊያመልጥም ወደደ። ብፁዕ አባታችንም አማተበበት። ወደ ባሕሩ ሊገባ ባይቻለው በጥልቁ ባሕር ወደብ ቆመ። ብፁዕ አባታችንም ሄዶ #በእጁ #ያዘው። ያን ጊዜ ዕጡ ወደቀና ኃይሉም ደከመና ለሁሉም በግልጥ ታየ።
“...ስምህ ማን ነው?” አለው።
"ባሕረ አልቅም።"
"እንግዲህ #ከእኔ ጋር #ትሄዳለህን ወይስ ወደ ማደሪያህ #ትመለሳለህ?” አለ።
"ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ማደሪያዬ መመለስ አይቻለኝም። #በማማተብህ ስልጣኔን ሽረኸዋልና።" አለው።
አባታችን ተክለሃይማኖትም ወስዶ #ገረዘው፥ ወደ ፍፁም #ክርስቲያንነትም ለወጠው። ስሙንም #ክርስቶስ ኃረዮ ማለትም #ክርስቶስ የመረጠው ብሎ ጠራው። ብፁዕ አባታችንን ሲያገለግለው ኖረ። ከጥቂትም ቀን በኋላም የምንኩስናውን ልብስ አልብሶ ወደ ባዕቱ አገባው። ይህችውም ደብረ አሰቦ ናት። ሰይጣን #ሞቶ #መንግስተ ሰማያት እስኪገባ ድረስ በተረፈው ዘመኑ ሁሉ #መነኮሳትን #ደስ #የሚያሰኝ#እግዚአብሔርንም #የሚወድ ሆነ።
********

በኦርቶዶክስ ቤተ እምነት ውስጥ ያሉ #ድርሳናት#ገድላት#ሰይፈ ሥላሴ፥ #ክርስቶስ ሳምራ፥ #ገድለ ክርስቶስ፥ #ተዓምረ ማርያም፥ #መልክዓ መላዕክታት፥ #ውዳሴ ማርያም እንዲሁም በስድሳ ስድስቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መፃሕፍት ላይ #የተጨመሩ ሌሎች መፅሐፍት መፅሐፍ ቅዱስን እጅግ የሚፃረሩ #ፀረ ክርስቶስ፣ #የደብተራ ሥጋዊና አጋንንታዊ ውጤት ናቸው።
#አጋንንት ሳቢ #ደብተራዎች የጻፉት የረከሱ ገድላት መካከል #ገድለ ተክለሃይማኖት አንዱ ነው።

እስከ መቼ ጌታ እግዚአብሔርን ነው የማመልከው እያልክ #በተክለሃይማኖት ስም የአጋንንትን ጽዋ ትጠጣለህ። እርም ባለበት መርገም አይርቅም። ልብህን ወደ እውነተኛው #የእግዚአብሔር ቃል ወደ #መፅሐፍ ቅዱስ እና ወደ ነፍስህ አዳኝ ወደ #ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ለፍሬ በሆነ ንስሐ ተመልስ።
********

"እሁድና ሐሙስ እባብ የገደለ የክርስቲያን ወገን ሁሉ ኃጢያቱ ይሰረይለታል፤ ብለህ ለልጆችህ ንገራቸው።" ብሎ ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ የነገረኝን አሁንም እነግራችኋለሁ። በልባችሁ ጠብቁት።
#ገድለተክለሃይማኖት፥51፥6
********
🕇 የከበረውን የሕያው እግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል #መፅሐፍ ቅዱስን ገለባ ከሆነውና ከረከሰው ስጋዊና አጋንንታዊ መልዕክት ጋር ምን አንድ አደረገው???
#ሰይጣንን ይዤ #ገረዝኩት#አጠመኩት#ቅስና አስተምሬ #የኦርቶዶክስ #መነኩሳትን #አገልግሎ #ሰይጣን ወደ #መንግስተ ሰማያት ገብቶዋል ብሎ እራሱ በፃፈው በገድለ ተክለሃይማኖት.48:1-4 ላይ መስክሯል።
********
#ገድለ ተክለሃይማኖት፥ 48:1- 4 :- አንድ ቀን በባሕር ዳር ተቀምጦ ሳለ፥ ሰይጣን ከባሕሩ ወጣ። ......
********
ይህ የአጋንንት ጎታቾች ክፉ ግብር እንጂ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል ጨርሶ አይደለም። #ሰይጣን መንግስተ ሰማያት ገብቶማ ቢሆን ኖሮ ምድር የንፁሐንና የጻድቃን ደም ባልፈሰሰባት ነበር። ዋይታና ልቅሶ፥ ረሃብና ጥማት፥ ጦርነትና ሞት ባልተገኘባት ነበር።
የተረገመው ሰይጣን ግን ኦርቶዶክስ እንደምትከተለው የተክለ ሃይማኖት የሐሰት ትምህርት በመንግሥተ ሰማያት ሳይሆን በምድርና በአየር በጥልቁም ሆኖ የአመፅ፥ የክፋት፥ የጭካኔ፥ የእርኩስት፥ የማታለልና የሐሰት ክፉ ጨካኝ ደም አፍሳሽ ስራውን በምድር ሁሉ ላይ እያደረገ ነው።
ለሰይጣን መንግስተ ሰማያት ቦታ እንደሌለ አላነበቡም ይሆን..👇

የማቴዎስ ወንጌል 25:41

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ #ለሰይጣንና ለመላእክቱ #ወደ #ተዘጋጀ ወደ #ዘላለም #እሳት ከእኔ ሂዱ።

ከዚህ በላይ #ለሰይጣን #ጠበቃና #አገልጋይ ማን ነው?
ከዚህ በላይ ምን #የተረገመና እርም ምን አለ?
ከዚህ በላይ #መናፍቅ ማን ነው?
ከዚህ በላይ #ፀረ ክርስቶስ ማን ነው?

ኦርቶዶክስ #ገድላትን#ድርሳናትን#ውዳሴያትን#መልክዓ #መላዕክትንና#ሰይፈ ሥላሴ፥ #ክርስቶስ ሳምራ፥ #ገድለ ክርስቶስ፥ #ተዓምረ ማርያም፥ ሌሎችንም #ፀረ #ክርስቶስ መጻሕፍቶቿን አቃጥላና ጥላ ልብን በትህትና በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመከተል ተሐድሶ ማድረጓ በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ የእምነት ተከታዮቿ የዘላለም ሕይወትና ክብር ነው። ልብን እልከኛ ማድረግ ግን ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እንደሰቀሉት ለአይሁድ ፈሪሳውያኖችም አልሆነም።

@gedlatnadersanat
👇👇
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ታሪኩ ሲጀምር መጽሐፉ “ #ቅምር” በሚባል አገር አንድ ሰው ነበር “ #ወኢየበልዕ እክለ ወኢ ሥጋ ላሕም ወኢ ካልአ እንሥሣ አላ ይበልዕ ሥጋ ሰብእ” ትርጉም:- እህል፥ የላም፥ ሥጋ የሌሎችንም እንሥሳ ሥጋ አይበላም ነበር የሰው ሥጋ ይበላ ነበር እንጂ” #ቁ 68።) « #ወዘበልዖሙሰ ሰብእ የአክሉ ፸ወ፰ተ ነፍሳተ ወኀልቁ ወተወድኡ ዓርካኒሁ ወፍቁራኒሁ ወአዝማዲሁ ወመገብቱ» ትርጉም:- «የበላቸውም…


በጣም የገረመኝ ግን ሚዛኑ #78 የሰው #ነፍስና #ጥሪኝ ውሃ #ከእግዚአብሔረ #እውቅና #ውጪ #ማድረጉ። ጉድ ሳይሰማ አሉ። እኛ ሰዎች ስንባል ደካማነታችንን ከምናውቅበት አንዱ የተሸከምነውን ስጋ ስንት እንደሚመዝን እንኳ የክብደት መለኪያ ካልነገረን አናውቅም። እግዚአብሔር እኔ ራሴን ከማውቀው በላይ የሚያውቀኝ አምላክ ነው #ስሙ #ይቀደስ
የደራሲው #ድፍረት ግን ይገርማል። #እግዚአብሔርን ከእውቀት ውጪ ማድረጉ። እሱ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ደራሲው #ጨካኝና #ሁሉን ወደ #ሲኦል #የሚጥል አምላክ አድርጎ ነው ያቀረበው። በተጨማሪም የእግዚአብሄር ፍርድ #በሚዛን #የሚለካና #በክርክርም ቢሆን እግዚአብሔር በማርያም የሚሸነፍና #አስቀድሞ #የሰጠውን ብይን #የሚቀለብስ ዳኛ ተደርጎ ነው የተሣለው።
ብቻ ምን አለፋችሁ ይህ #ጉደኛና #ነውረኛ መፅሐፍ ከመጀመሪያ ፊደሉ እስከ መጨረሻው ቃል ድረስ #አመፅና #ስድብ #የያዘ ነው።
ታዲያ ይህንን #ነውረኛና #ውሸታም #መፅሐፍ የሚቃወም ጳጳስ የጠፋ መሰላችሁ። አይደለም ይልቅ በተፅህኖ ውስጥ ወድቀው ክርስትና #በእጅ #ብልጫ #ሆኖባቸው ጊዜ ሲጠብቁ ነበረ። አሁን ግን እግዚአብሔር #የማብቂያ #ደውል ካሰማን ሰንበትበት ብለናል። እውነተኛውን ወንጌል የተረዱ አባቶች ብቅ በማለታቸው የተነሳ #ታምረ ማርያም ሲኖዶሱን አውኮታል። መላው የሲኖዶስ አባላት በዚህ ጉዳይ ቢስማሙም ይህንን መፅሐፍ ዋጋ ቢስ ነው ቢባል ማንም የኣርቶዶክስ ምዕመን አይለቀንም በሚል ፍራቻ ተውጠው ይገኛሉ። ነገር ግን የክርስቶስን መከራ ለመካፈል ቆርጠው የተነሱ #ጳጳሳት አላፊነቱን በመውሰድ #የበላዓ ሰብና #የታምረ ማርያም ዝምድና ሊያበቃለት ቀርቧል።

#ተሀድሶ ለኦርቶዶክስ

#ምንጭ:- ተአምረ ማርያም
(ተአምር 12 ቁጥር 68 ጀምሮ..)

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል(ዩሀ 8፥32)

@gedlatnadersanat @teeod