ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
መልሱን በቀጥታ ለመመለስ ይህል በአንድ ጥያቄ እንጀምር የእመቤታች ጸሎት ማለትም "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ....የሚለው ጸሎት ማለት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #የለም ያለው ማነው ???በደንብ አለ እንጂ መጻሕፍ ቅዱስን በደንብ ሳንመለከት ይህ አለው ያለ የለውም ማለት ተገቢ አይደለም ስለዚህ አጠያየቁ ይታረም ::ይህ ጸሎት መጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ ተብሎ ይጠየቃል እንጂ የለም ብሎ መጀመር መጻሕፉን አለማወቅ ያስመስልብናልና::


#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶቾን በሙል ሥትሰራ በግለሰብና በማሕበረ ሰብ የሥጋ ሀሳብ ወይም በድምጽ ብልጫ አይደለም:: ንባብን ከትርጓሜ ትርጓሜን ከምስጢር አስማምታና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሁሉን ታሰናዳለች እንጂ: በዚህም ስንዱ እመቤት ለብላ ትጠራለች::

አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ከቁጥር 8ጀምሮ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው :: ሙሉ ያስተማረውን ጸሎት ቃል በቃል ለመመልከት ያክል "፤ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ "፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። " ....የሚል ነው (የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 8-13)

ታድያ ይህ ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ ካለ የእመቤታችንስ በየት ቦታ ነው ያለው ሊባል ይችላል ::ይህ የእመቤታችን ጸሎት ከሁለት የ መጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የተገኘ ነው የመጀመሪያው ከአብሳሪው መላእክ ከቅዱስ ገብኤልና ከቅድስት ኤልሳ ቤጥ የተገኘ የምስጋና ጸሎት ነው እስቲ ሁለቱንም ከግጥም እንመልከታችው

👉 የቅዱስ ገብርኤል ምሥጋና

"፤ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 28)

👉 የቅድስት ኤልሳቤጥ ምሥጋና

"፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 42)

አሁን ደግሞ እስቲ እኛ የምንጸልየውን እንመልከት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል አንቺ ከሴቶች ለተይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ(3)ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመዳኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን ለዘለዓለሙ አሜን
.....የሚል ነው
እስቲ ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ንግግር ውጪ የተጠቀምነው አዲስ የራሳችንን ምስጋና የቱ ጋር አለ?? በፍጽም የለም ሁሉንም ከእነርሱ ያገኘነው በመጻሕፍ ያነበብነው ነው
እመቤታችንም ፀጋን የተመላች ነችና ከተሰጣት ብዙ ፀጋዎች በአንዱ ነቢይት ነችና በአንዱ በቅዱስ ገብርኤልና በአንዱ በቅድስት ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል ስትል ከፈጣሪዋ ከልጇ ከወዳጆ ቀጥላ በአማኝ ትሁልዶች ሁሉ የምትመሰገን መሆኑን ነግራናለች ይህም ሐሰት የለውም የእውነት መንፈስ ሐሰት አያናግርምና እያመሰገናትም ነውና::

ሌላው አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ከፈጣሪ የተሰጠ ነው ቢሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የሚለውም ከፈጣሪ የተሰጠ ነው:: እንዴት ቢሉ ከላይ እንደ ተመለከትነው ጸሎቱን ያገኘነው ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ነው እነርሱን ልኮ ያናገረ ደግሞ እራሱ አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዮ ያለው እራሱ እግዚአብሔር ነውና ::

"፤ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ
(የሉቃስ ወንጌል 1÷ 26-27


"፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም #መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ " በታላቅ ድምፅም ጮኻ #እንዲህ አለች። #አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ #የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው አለቻት"

(የሉቃስ ወንጌል 1÷41-42


ስለዚህ ሁለቱም ሊነጣጠሉ የማይገቡ በአንድነት እንደየ ክብራቸው የተሰደሩ ሥርዓታዊ መጻሕፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ጸሎቶች ናቸው ...ይቆየን...
#የነገረ_ድኅነት ጥያቄ #መልሶች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ሐሰት
#ምክንያቱም :-ሰው ለመዳን ከማመን ያለፈ የተግባር ሰው (ምግባራትን እና ምሥጢራትን የሚፈጽም) መሆን አለበት:: ምግባራት የሚባሉትም በዋናነት #ጾም #ጸሎት #ስግደት #ምጽዋት ሲሆኑ ምሥጢራቱም #ምሥጢረ_ሜሮን #ቅዱስ_ጥምቀት እና #ቅዱስ_ቁርባን ይጠቀሳሉ #ሃይማኖት ያለ #ምግባራት ጥቅም አልባ የሞተ ነው::
"፤ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ #ከሥራ (ከምግባራት )የተለየ እምነት የሞተ ነው።" (የያዕቆብ መልእክት 2: 26)


#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :-በተለየ አካሉ #ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሶ ነፍስን ተስቶ በፍጽም ተዋህዶ #ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና:: #በምስጢረ ሥላሴ ትምህርታችን #አብ አባት #ወልድ ልጅ #መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ብለን ተምረናል እንዲህም እናምናለን:: ቅዱሳት መጻሕፍትም በተዋህዶ ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት ይነግሩናል:: ለምሳሌ "እግዚአብሔር አንድያ #ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶልና" ዮሐ3÷16

#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :- ምንም እንኳን ድኅነት በዕለተ አርብ በቀራኒዮ አደባባይ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ ለሰው ልጆች የተሰጠ ቢሆንም ከዚህ ከተሰጠው ድኅነት ግን ለመካፈል ሰው የራሱን ጥረት ማድረግ ይገባዋል። ድኅነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተፈጸመ ስለሆነ ብቻ ሰው ሁሉ ያመነውም ያላመነውም በግዴታ ይድናል ማለት አይደለም:: ለመዳን የወደደ ብቻ ከተፈፀመለት የድኅነት ሥራ በምግባራት ተሳትፎ ድኅነትን ያገኛል:: ስለዚህ በድኅነት ውስጥ ሰውም ሊፈጽመው የሚገባ ሂደት ነው::
"፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ #እንደ_ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ፤"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 12)

ልናስተውለው የሚገባን #የታዘዛችሁትን_በመፈጸም የምትለዋ እና #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ የምትለዋን ነው

በመሆኑም የእራሳችንን መዳን መፈጸም የምንችለው እና ከተሰራልን የድኅነት ሥራ የምንካፈለው የታዘዝነውን በመፈፀም ነው:: #የታዘዝነውም 10ቱ ትዕዛዛት 6ቱ ቃላተ ወንጌል ናቸው እነዚህን ለመፈፀም ደግሞ ጊዜ ዘመን ያስፈልገናል:: ይህ ደግሞ ድኅነት በሂደት የሚፈፀም እንጂ በአንድ ቀን በአንድ ቦታ በሰዓት ጌታን በመቀበል ብቻ አለመሆኑን ያስገነዝበናል:: በጥቅሉ ለመዳን ሰው የራሱ ድርሻን መወጣት ይገባዋል።

#ኛ እውነት

#ኛ ሐሰት
ምክንያቱም:-ያልተመለሰለት ጸጋ የለምና::
ፀጋ:-
ልጅነትን:- ከእንግዲ ወዲ ባሮች አትባሉም
ወራሽነትን:-
ገዢነትን(ሥልጣንን):- ግዛ ንዳ የተባለሁ ዓለምና በዓለም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ዛሬም ሰው ከትዕዛዙ ካልራቀ ሕጉን ከጠበቀ ከተፈጥሮ ሁሉ በላይ መግዛት መንዳት የሚችልና ሥልጣኑ ያለው መሆኑን በቅዱሳን ሕይወት መመልከት ይቻላል::


#በአጭሩ መልሱ

#ኛ #ስለ_ፍጽም_ፍቅሩ
#ለካሳ ለቤዛ
#የዲያብሎስ ጥበብ #በጥበቡ #ለመሻር
#ለምሳሌነት_ለአራያነት
#ድኅነት ሥርዓት ስላለው…

#ኛ #ማመን
#ሥራ (ምግባራት)
#ምሥጢራትን መፈጸም ማር 16:16 ዮሐ 6:54


#ኛ "፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ #በእርሱም ቍስል #እኛ ተፈወስን።"

(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 5)
"፤ #እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ #ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም #የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 6)

ነብዩ ስለ እኔ ብቻ አላለም #እኛ ብሎ አብዝቶ ተናገረ እንጂ:: እኛ ብሎ አብዝቶ መናገሩ የዓለምን ኃጢያት የተሸከመ የዓለም መድኀን መሆኑን ሲገልጥ ነው::

"እነሆ #የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1: 29)


#ኛ #መንግስቱን_ሲወርስ_ስሙን_ሲቀድስ


#ኛ ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው ማለት እንጂ ቅዱሳን አያድኑም ወይም መድኀኒት አይባሉም ለማለት አይደለም:: በቅዱስ መጽሐፍ ሰዎች ሆነው አዳኝ ተብለው የተጠሩ አሉ #ለምሳሌ "፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ #እግዚአብሔርም_የሚያድናቸውን_አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ #ጎቶንያልን_አስነሣላቸው።"
(መጽሐፈ መሳፍንት 3: 9) ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎችን አዳኝ መድኀኒት አድርጎ እንደሚያስነሳ ነው:: መዳን በሌላ በማንም የለም ማለቱ የቅዱሳን አዳኝነት (መድኀኒትነት) ጠፍቶት አይደለም:: ቅዱሳን የጸጋ አዳኝ ናቸው:: ጸጋ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፣የተቸረ ፣የተለገሰ ስጦታ ማለት ነው:: ስለዚህ ቅዱሳን መድኀኒት ቢባሉ በስጦታ ያገኙት ነው። "#እድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን #ሌላ ስም የለም" ማለቱ ደግሞ ቅዱሳን ሲያድኑም በእራሳቸው ኃይል ሳይሆን ማዳንን በሰጣቸው በፈጣሪያቸው ስም ነው ማለቱ ነው:: ቅዱሳን መላእክት አዳኝ (መድኅኒት )ናቸው። ስማቸው ስመ እግዚአብሔር ተሸክሞልና:: ስለሆነም ቅዱስ ሚካኤል አዳነ ማለት እግዚአብሔር አደነ ማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ (ቅዱሳን ሰዎችም) ቢያድኑ የፈጣሪን ስሙን ጠርተው ነው "፤ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ #በናዝሬቱ_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።"
(የሐዋርያት ሥራ 3: 6)
ከዚህም ባሻገር ቅዱሳን ወደ ቅድስና ሲጠሩ ስማቸው ይለወጣል ስመ እግዚአብሔርም ይሆናል:: በመሆኑ እነርሱም በስማቸው ማዳን ይቻላቸዋል "፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #በእኔ_የሚያምን_እኔ_የማደርገውን_ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ #ከዚህም_የሚበልጥ_ያደርጋል፥" (የዮሐንስ ወንጌል 14: 12)
ከእርሱ አብልጦ የሚሰራ የለም ነገር ግን በስሙ ላመኑ እርሱ ያደረገውን ሁሉ የማድረግ ሥልጣን አላቸው ማለቱ ነው።

ይቆየን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ዐውደ ምሕረት
Photo
#መንፈስ_ቅዱስ ወረደ ላይለ ሐዋርያት
ተመሲሎ(5) በነደ እሳት

#መንፈስ_ቅዱስ ወረደ በሐዋርያት ላይ
ተመስሎ (5) በሚነድ እሳት
"ይህ ቀን #የቤተ_ክርስቲያን_የልደት ቀን ነው"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ቤተ ክርስቲያ ሆይ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅጸነ ሐዋርያት እንኳን በዛሬዋ ዕለት ተወለድሽልን👏

ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሰኔ05/2014 ዓ.ምአ
አ.አ ኢትዮጵያ