ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
መልሱን በቀጥታ ለመመለስ ይህል በአንድ ጥያቄ እንጀምር የእመቤታች ጸሎት ማለትም "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ....የሚለው ጸሎት ማለት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #የለም ያለው ማነው ???በደንብ አለ እንጂ መጻሕፍ ቅዱስን በደንብ ሳንመለከት ይህ አለው ያለ የለውም ማለት ተገቢ አይደለም ስለዚህ አጠያየቁ ይታረም ::ይህ ጸሎት መጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ ተብሎ ይጠየቃል እንጂ የለም ብሎ መጀመር መጻሕፉን አለማወቅ ያስመስልብናልና::


#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶቾን በሙል ሥትሰራ በግለሰብና በማሕበረ ሰብ የሥጋ ሀሳብ ወይም በድምጽ ብልጫ አይደለም:: ንባብን ከትርጓሜ ትርጓሜን ከምስጢር አስማምታና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሁሉን ታሰናዳለች እንጂ: በዚህም ስንዱ እመቤት ለብላ ትጠራለች::

አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ከቁጥር 8ጀምሮ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው :: ሙሉ ያስተማረውን ጸሎት ቃል በቃል ለመመልከት ያክል "፤ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ "፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። " ....የሚል ነው (የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 8-13)

ታድያ ይህ ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ ካለ የእመቤታችንስ በየት ቦታ ነው ያለው ሊባል ይችላል ::ይህ የእመቤታችን ጸሎት ከሁለት የ መጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የተገኘ ነው የመጀመሪያው ከአብሳሪው መላእክ ከቅዱስ ገብኤልና ከቅድስት ኤልሳ ቤጥ የተገኘ የምስጋና ጸሎት ነው እስቲ ሁለቱንም ከግጥም እንመልከታችው

👉 የቅዱስ ገብርኤል ምሥጋና

"፤ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 28)

👉 የቅድስት ኤልሳቤጥ ምሥጋና

"፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 42)

አሁን ደግሞ እስቲ እኛ የምንጸልየውን እንመልከት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል አንቺ ከሴቶች ለተይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ(3)ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመዳኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን ለዘለዓለሙ አሜን
.....የሚል ነው
እስቲ ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ንግግር ውጪ የተጠቀምነው አዲስ የራሳችንን ምስጋና የቱ ጋር አለ?? በፍጽም የለም ሁሉንም ከእነርሱ ያገኘነው በመጻሕፍ ያነበብነው ነው
እመቤታችንም ፀጋን የተመላች ነችና ከተሰጣት ብዙ ፀጋዎች በአንዱ ነቢይት ነችና በአንዱ በቅዱስ ገብርኤልና በአንዱ በቅድስት ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል ስትል ከፈጣሪዋ ከልጇ ከወዳጆ ቀጥላ በአማኝ ትሁልዶች ሁሉ የምትመሰገን መሆኑን ነግራናለች ይህም ሐሰት የለውም የእውነት መንፈስ ሐሰት አያናግርምና እያመሰገናትም ነውና::

ሌላው አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ከፈጣሪ የተሰጠ ነው ቢሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የሚለውም ከፈጣሪ የተሰጠ ነው:: እንዴት ቢሉ ከላይ እንደ ተመለከትነው ጸሎቱን ያገኘነው ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ነው እነርሱን ልኮ ያናገረ ደግሞ እራሱ አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዮ ያለው እራሱ እግዚአብሔር ነውና ::

"፤ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ
(የሉቃስ ወንጌል 1÷ 26-27


"፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም #መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ " በታላቅ ድምፅም ጮኻ #እንዲህ አለች። #አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ #የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው አለቻት"

(የሉቃስ ወንጌል 1÷41-42


ስለዚህ ሁለቱም ሊነጣጠሉ የማይገቡ በአንድነት እንደየ ክብራቸው የተሰደሩ ሥርዓታዊ መጻሕፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ጸሎቶች ናቸው ...ይቆየን...