ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ዋኖቻችሁን አስቡ። ዕብ 13:7

ይህን ኃይለ ቃል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች በላከው መልዕክቱ ያሰፈረው ሲሆን ፍጻሜው ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለኛ ለምዕመናን ሁሉ ነው።

ዋኖቻችን እነማን ናቸው? በአጭር ቃል ሐዋርያው «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁ» በማለት መልሶልናል። እነርሱም ከቀደምት አበው ጀምሮ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ቅዱሳን ናቸው።

ቅዱሳንን ማሰብ ለምን ይጠቅማል?

1 ከሀሳብ ኃጢአት እንጠበቃለን። ኃጢአት በሀሳብ ይጸነሳል። በነቢብ (በመናገር) ደግሞ ይወለዳል ኋላም በተግባር ሲፈጸም ይጎለብታል ከእግዚአብሔር ይጣላል። ሰው ቅዱሳንን በማሰብ ጊዜውን የሚያሳልፍ ከሆነ ኃጢአትን ለማሰብ ጊዜ አይኖረውም።

2 ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት እናገኛለን። ጠቢቡ ሰለሞን በምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 7 ላይ «የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።» እንዲል ።

3 ቅዱሳንን አርአያችን በማድረግ እነርሱን ለመምሰል እንጥራለን። ፈጣሪያችን በኦሪቱ «እኔ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።» እና በሐዲስ ኪዳንም «የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ ፍጹማን ሁኑ።» በማለት የቅድስና ጥሪን ለሰው ልጆች አቅርቧል። ሰው ቅዱስ መሆን የማይችል ቢሆን ይህንን ጥሪ አምላካችን ባላቀረበ ነበር። ነገር ግን ሰዎች ይህንን የቅድስና ጥሪ ተቀብለው በጽድቅ በቅድስናና በንጽሕና መኖር እንደሚቻል ያሳዩን ቅዱሳን ናቸው። ይህንን የቅድስና ጥሪን ተቀብለው በኑሮአቸው ቅዱሳን የሆኑትን ስንመልከት ለጽድቅ ለትሩፋት እንነሳለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «እኔ ክርስቶስን እንድመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።» 1ቆሮ 11:1 ላይ እንዳለን እነርሱን በማሰብ የበምግባር በሃይማኖት እነርሱን ለመምሰለል እንጥራለን። ጥረታችንም ተሳክቶ ለቅድስና እንበቃለን። ኋላም እነርሱ የገቡበት እንገባለን። እነርሱ የወረሱትን እንወርሳለን።

4 በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነትና ተስፋ እንዲጠነክር ያደርጋል። ለምሳሌ ልጅ ባለመውለድ እየተፈተኑ ያሉ ሰዎች አብርሃምና ሳራን በማሰብ እነርሱን ያልተወ በእርጅናቸው ወራት ልጅ የሰጠ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በእምነት ይጸናሉ።

እንዴት እናስብ?

1 ገድላቸውንና ዜና ሕይወታቸውን በማንበብ። “ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ።” ኢሳ 51፥2 እነርሱ በሥጋ ከተለዩን ብዙ ዓመታት ነውና እንደምን ልናያቸው እንችላለን? አብርሃምን በእምነት መነጽር ለማየት ገድለ አብርሃምን ማንበብ ያስፈልጋል።

2 በዓላቸው በማክበር በስማቸው ለመታሰቢያ በታነጸ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ማስቀደስ፣ መሳለም፣ ጠበል መጠጣት፣ እጣንና ጧፍ በመስጠት ማሰብ ያስፈልጋል።

3 በስማቸው ዝክርን በመዘከር (መታሰቢያን በማድረግ) ነድያንን ማብላትና ማጠጣት። ማቴ 10:41

በመጨረሻም ሐዋርያው እንዳለ ቅዱሳኑን አስበን የነሱን አሰረ ፍኖት ተከትለን በምግባር በሃይማኖት እንድንመስላቸው አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ፍቅሯን በልባችን ጧሟን በአንደበታችን ታኑርልን። ቅዱስ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤታቸውን በረከታቸውን ያሳድሩብን።

ይቆየን።

(አቤኔዘር ወልደ ተክለሃይማኖት)

ሰኔ 04 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሥርዓተ ቅዳሴ01
<unknown>
ሥርዓተ ቅዳሴ ክፍል አንድ

በቀሲስ #አስተርአየ ጌጤ

ይዘት
👉ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

"ወናስተብቑአክሙ አሐዊነ
ገስጾሙ ለዝሉፋነ" ....

፤ ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5: 14)

👉 @awedimeherit
👉 @awedimeherit
👉 @awedimeherit
"ይትዓየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል #ያድናቸውማል።" መዝ 33:7

👉 ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ልበ አምላክ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው። በግልጽ እንደነገረን የእግዚአብሔር የሆኑት ቅዱሳን መላእክት የሚያድኑ አዳኞች ናቸው። እነርሱን ከሚፈሯቸውና ከሚያምኗቸው ሰዎች አይለዩም። ከሚደርስባቸው መከራ እና ችግር ፈተና ሁሉ ያድኗቸዋል ይታደጓቸዋል። ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን የሚያድኑ አዳኞች መሆናቸውን ቅዱስ ያዕቆብ ዮሴፍንና ልጆቹን በባረከ ጊዜም እንዲህ ሲል መስክሯል። "ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ #ያዳነኝ_መልአክ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ።" ዘፍ 48:15

👉 እሱም ብቻ አይደለም የሰው ልጅ አምላክ በፈጸመለት የማዳን ተግባር ውስጥ የቅዱሳን መላእክት ሱታፌ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገልገል የሚላኩ የሚያግዙ መናፍስት አይደሉምን?" ብሎ የሰው ልጅ እንዲድን የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት እና እገዛ የግድ እንደሚያስፈልገው ተናግሯል። ዕብ 1:14 እንዲሁም የሰው ልጅ የመዳኑ ነገር ለቅዱሳን መላእክት ታላቅ ደስታ መሆኑን ጌታ በወንጌል እንዲህ በማለት ተናግሯል። "እላችኋለሁ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።" ሉቃ 15: 7

👉 ቅዱሳን መላእክት በተጨነቅን እና በተቸገርን ጊዜ በጸሎት ስንጠራቸው መጥተው ያበረቱናል ያረጋጉናል። ጌታችን በመዋለ ሥጋዌው ለእኛ አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ በምሴተ ሐሙስ መከራን ከመቀበሉ በፊት ሲጸልይ "ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው።" ይላል። ሉቃ 22:43 የመላእክት ፈጣሪያቸው እርሱ ሆኖ ሳለ የሚያበረታው መልአክ ታየው መባሉ ስለምንድን ነው ቢሉ እናንተም በጨነቃችሁ በጠበባችሁ መከራ ውስጥ በገባችሁ ጊዜ ብትጸልዩ ቅዱሳን መላእክት እናንተን ለማበርታት ይላካሉ ሲለን ነው።

👉 ቅዱሳን መላእክት ስለ ሰው ልጆች ዘውትር በአምላክ ፊት ያማልዳሉ። እግዚአብሔርም ምልጃቸውን ቸል አይልም። ዘካ 1:12–13 "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ። እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።" እንዲል። መልአኩ እግዚአብሔርን አሳዝነው 70 ዓመት ለተቆጡት እስራኤል ዘሥጋ ከለመነ፤ በቅዱሳን መላእክት ለታመንን እስራኤል ዘነፍስ ለሆንን ለኛ እንዴት አይማልዱልንም? እነርሱም ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ፣ የእግዚአብሔርንም ፊት ያያሉ። ማቴ 18:10 ኢዮ 1:7 ሉቃ 1:9 "የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።" እንዲል የቅዱሳን መልአክትንም ምልጃቸውን ይቀበላል። መዝ 33(34):15

በተጨማሪም #ቅዱሳን_መልአክት

👉 አጽናኞቻችን ናቸው። ዳን 10:20
👉 ይረዱናል። ዳን 10:13
👉 ይጠብቁናል። መዝ 90:1
👉 እንሰግድላቸው ዘንድ ይገባል። ኢያ 5:14 ዘፍ 19:1 ራዕ 19:10 ራዕ 22:8

በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ባህራንን ደግሞ ከሞት ያዳነበት ዕለት ነው። ከመልአኩ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

ይቆየን።

አዘጋጅ ወንድማችን #አቤኔዘር

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ከእናንተው በእናንተው #ለእናንተው

መክሊትህን የት አረከው?
አምላክ የሰጠህን!
መክሊትሽን የት አረግሽው ?
አምላክ የሰጠሽን!
ማቴ25፥14-31

👉መንፈሳዊ ግጥም 👉ዝማሬ
👉መነባንብ 👉መጣጥፍ
👉አጫጭር ትረካዎችን አዘጋጅተው የሚልኩ የዓውደ ምህረት ቤተሰቦችን በየ ዘርፉ አወዳድሮ መሸለም እና ጸጋችሁን እንድታውቁትና እንድታወጡት ይፈልጋል::

በመሆኑም የነዚህ ጸጋዎች ባለቤት የሆናችሁ በመልእክት አድራሻችን በመላክ ጸጋችሁን እያዳበራችሁ ከበረከት ሽልማቶቻችን ተሳታፊዎች መሆን ትችላላችሁ::
#የመላኪያ_አድራሻዎቻችን
@Midyam
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
@Yotor24

#ማስታወሻ :- የሚቀርቡ ማንኛውም ሥራዎች የእርሶ ቢሆኑ ይመረጣል ከልዮ ልዮ ቦታ ያገኙት ከሆነ ደግሞ ምንጭ መጥቀስዎን መርሳት የለብዎትም::

#ከእናንተው በእናንተው #ለእናንተው
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ዓውደ ምህረት የእርስዎ
#ከእናንተው በእናንተው #ለእናንተው

መክሊትህን የት አረከው?
አምላክ የሰጠህን!
መክሊትሽን የት አረግሽው ?
አምላክ የሰጠሽን!
ማቴ25፥14-31

👉መንፈሳዊ ግጥም 👉ዝማሬ
👉መነባንብ 👉መጣጥፍ
👉አጫጭር ትረካዎችን አዘጋጅተው የሚልኩ የዓውደ ምህረት ቤተሰቦችን በየ ዘርፉ አወዳድሮ መሸለም እና ጸጋችሁን እንድታውቁትና እንድታወጡት ይፈልጋል::

በመሆኑም የነዚህ ጸጋዎች ባለቤት የሆናችሁ በመልእክት አድራሻችን በመላክ ጸጋችሁን እያዳበራችሁ ከበረከት ሽልማቶቻችን ተሳታፊዎች መሆን ትችላላችሁ::
#የመላኪያ_አድራሻዎቻችን
@Midyam
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
@Yotor24

#ማስታወሻ :- የሚቀርቡ ማንኛውም ሥራዎች የእርሶ ቢሆኑ ይመረጣል ከልዮ ልዮ ቦታ ያገኙት ከሆነ ደግሞ ምንጭ መጥቀስዎን መርሳት የለብዎትም::

#ከእናንተው በእናንተው #ለእናንተው
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ዓውደ ምህረት የእርስዎ
Audio
👉መንፈሳዊ ውይይት

ርዕስ:- #ቅዱሳን_ሐዋርያትና_ጾማቸው
#በወንድማችን ብሩክ መልሳቸው እና
#በወንድማችን ተርቢኖስ ሰብስቤ የተዘጋጀ
መዝሙር :-በዘማሪት #ሰብለ ስፍር
#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#መላእከ ውቃቢ

.......ካለፈው የለጠቀ.........

ሰኔ 12የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ምክንያት በማድረግ በዚሁ ርዕስ ሥር መላከ ውቃቢ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ነገደ መላእክትን ከነ አለቆቻቸው መዳሰስ ጀምረን ነበር ዛሬም ቀጣዮንና የመጨረሻውን ክፍል ሰኔ 19 የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ምክንያት አድርገን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ዛሬ
.........................
#ውቃቢ የሚለው ገላጭ ግሥ ለምን በብዛት ከጥንቁልና ጋር ተያይዞ ይነሳል? መላእክትስ እራሳቸው ስለዚህ (ስለ ጥንቁልና) ምን ይላሉ? የሚለውን እንቃኛለን አብራቹን ቆዮ ::
..........................

ውቃቢ የሚለው ቃል አቃቢ ጠባቂ የሚል ትርጉም ያለው በመሆኑ ሰዎች ያድነናል ከክፉሁ ነገር ይጠብቀናል ብለው ስለሚያምኑ የሚያመልኩትን አካል ውቃቢዬ (ጠባቂዬ )ብለው ሲጠሩ ይስተዋላል ጠንቆይ ከሰዎች በግ ፍየል በሬ ገንዘብ ወዘተ ነገሮች የሚጠብቅ(የሚሻ)እንጂ ሰዎችን የሚጠብቅ አይደለም ስለዚህ ውቃቢ የሚለው ስም አይገባውም ከዛይልቅ አውዳሚ የሚለው ስመ ስያሜ ይስማማዋል ::ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጠንቋይ የሚለውስ መጠሪያ ስትተረጉመው እራሱ ጠንቋይ ማለት #ጠ_ን_ቀ_ነ_ዋ_ይ (የገንዘብ ጠንቅ ) ማለት ነው ብላ አርቃ ትተረጉማለት:: እውነት ነው የተባረከ ሥራ እንድሰጥህ ውድ ሽቶ አምጣ የተባረከ ትዳር እንድሰጥህ መካደሚያ የሚሆን ቪላ ቤት ሰርተህ ስጠኝ የተባረከ ልጅ እንድሰጥህ ሰንጋ በሬ ጣልልኝ የሚሉ ጠንቀ ነዋዮች (ጠንቋዮች) ብዙ ናቸው:: ለሰዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጠባቂ አቃቢ መላክ አላቸው አንዱ በቀን ሌላኛው በሌሊት የቀኑ ከጠዋቱ 12ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ይጠብቅና ለሌላኛው መላክ ይሰጠዋል ያም መላክ ይህ ሰው ደገኛ ነውን ይለዋል ደገኛ ከሆነ አዎን እጁ ከምጽዋት እግሩ ከቤተ እግዚአብሔር ጆሮው ከቃለ እግዚአብሔር ሰውነቱ ከጦም አይተለየኝ ይለዋል ተረኛው መላክም ደስ እያለው ከምሽቱ 12ሰዓት እስከ ንጋቱ 12ሰዓት ይጠብቀዋል ሰውየው ደገኛ ካልሆነ ግን ማለትም እጁ ከምጽዋት እግሩ ከቤተ እግዚአብሔር ሰውነቱ ከጦም ከራቀ ግን ተረካቢው መላክ ያዝናል ምነው አምላኬ ይህን ከምታስጠብቀኝ እንሰሳ ብታስጠብቀኝ ይሻላል ይላል ይጠየፈዋል ::ጠንቋዮች ጠንቀኞች ናቸው :: በማሳያ ጠቀስን እንጂ ጠንቀኝነታቸውም በገንዘብ ብቻ የሚቆም አይደለም የእግሬን እጣቢ ጠጣ የሚሉ ጠንቀ ጤና ፣ ያገባአት ሴት ዕጣ ክፍልህ አይደለችም የሚሉ ጠንቀ ፍቅር ፣ ግደል ግደል የሚሉጨጠንቀ ሠላም ፣ አሁን ምን ቀረህ እራስህን አጥፋ አጥፋ የሚያሰኙ ጠንቀ ተስፋ ፣ አምጣ አምጣ የሚሉ በዝባዦች ጠንቀ ብልጥግና፣ የሚያጠራጥሩ ከእምነት ጎዳና የሚያወጡ ጠንቀ እምነትቶች ጭምር ናቸው:: እግዚአብሔር ግን እነዚህ መሠል ሰዎች ጋር እንዳንገኝ አስጠንቅቆናል “አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።” ዘዳግም 18፥11 ባንተ ዘንድ አይገኝ ማለት አንተ እራስህ ጠንቁል ጠንቁል የሚል ሰሜት አይሰማህ እንደዚህም የሚያደርጉ ቤተሰቦች ወንድሞች ወይም እህቶች ጓደኞች የሥራ ባልደረቦች አይኑሩህ ማለቱ ጭምር ነው ጠንቋዮች እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር ሰዎችን የሚገዳደሩ ደፋሮችም ናቸው:: ለምሳሌ ላይ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ነቢዮ ሙሴን የተገዳደሩትን ሁለቱን ጠንቋዮች መመልከት እንችላለን መገዳደራቸው ግን በተአምራት ሳይሆን በምትዐት በቅድስና ብቃት ሳይሆን በእርኩሰት ብቃት በማድረግ ሳይሆን ያደረጉ በማስመሰል በቅዱሱ በእግዚአብሔር መንፈስ ሳይሆን በእርኩሱ በሰይጣን መንፈስ በመሰራት ነው :: “ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነች።” ዘጸአት 7፥10 ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።” ዘጸአት 7፥12 እነዚህ ሙሴና አሮንን የተገዳደሩ ሁለቱ ጠንቋዮች ምንም እንኳን በምተአት በትሮቻቸውን ወደ እባብነት ቢለውጡም ከጠንቋዮች ምትዐት ይልቅ የእግዚአብሔር ሰዎች ተአምራት እንደሚበልጥ ሲያስገነዝበን የጠንቋዮቹ እባቦች በነ ሙሴ እባቦች ተመዋጡ ብሎናል:: ዛሬም ይመላቸው እንጂ የኃላ የኃላ ሥር ማሽ፣ ቅጠል በጣሽ ፣ ሙት ሳቢ፣ ጋኔን ጠሪ፣ ሞራ ገላጭ ውቃቢ አምላኪ ሙአርተኛ እና መተተኛ በገሃነም እሳት መዋጣቸው አይቀርም :: “የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።”1ኛ ቆሮንቶስ 3፥19-20 በመጽሐፍ ዲቢሎስ እባብ ተብሎ ተጠርቷል“የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥” ራእይ 20፥2 ታዲያ የእባቡን የዲያቢሎስን ጥበብ (መርዝ) በጥበቡ ለመሻር ሲል መድኃኒተ ዓለም ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ተገለጠ ለመርዘኛው መድኃኒት መርዙ ነውና ዲያቢሎስ በመድኃኒት የሞተ የተሸነፈ የመጀመሪያ ፍጡር ሆነ “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ ዮሐንስ 3፥9 :: ጥንቆላ ጠንቀኝነት ነውና በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተጠየፈ ነው ኢት አምልክ (ሌሎች አማልክትን አታምልክ የሚል ትዕዛዝም አስቀድሞ መስጠቱ ለዚሁ ነው:: ዘጸ20፥1- ፍቅረ ጣዖት ያደረባቸው እሥራኤል ዘሥጋም ሙሴ በሥጋ በተለያቸው ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ከእሥራኤል ፊት ቅዱሱን የሙሴን ሥጋ ሰውሮባቸው ነበር ::ለምን ያልን እንደሆነ ሙሴን አብዝተው ይወዱት ስለነበረ ሥጋውን ሳይቀብሩ እናምልከው ይሉ ነበርና ነው:: ሰው ለሚወደው ነገር ባሪያ ነው :: ክፋት የክፋት ልጅ ዲያቢሎስ ታዲያ የተሠወረውን የውሴን ሥጋ ካለበት አድርሶ ለእስራኤል ገልጦላቸው ሊያሰመልካቸው ወደደ በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር ተከራከረ:: ዛሬ ብዙዎች በቅዱሳን አማላጅነትና ተራዳይነት መማጠናችንን እያነሱ ይኮኑኑናል ቅድስ ኦርቶዶክስ ግን ሙሴን ሳይሆን የሙሴ አምላክ ክርስቶስን ታመልካለች ለሙሴ የጸጋ ለክርስቶስ የባህሪ የአምልኮ ስግደት ታቀርባለች ሙሴን አማላጅ ክርስቶስን ደግሞ ፈራጅ ብላ ታከብራቸዋለች:: ሰይጣን ዲያቢሎስ ግን እስራኤል የሙሴን ሥጋ አግኝተው እንዲያመልኩት እንዲጠነቁሉበት ለማድረግ ካልገለጥኩ ሲል ተጋ ቅዱስ ሚካኤል ግን ገሰጸው ሲገስጸውም አልተሳደበም፣ አልተራገመምም :: “የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።” ይሁዳ 1፥9 ዛሬም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በፍርሃትም ይሁን በድፍረት የሚጠነቁሉና የሚያስጠነቁሉ ሰዎችን መሳደብ ሳይሆን መገሰጽ ማንቋሸሽ ሳይሆን ማስተማር እና ከዚህ ሕይወት በቸርነቱ ነጻ ያወጣቸው ዘንድ መለመን እንደሚገባን አስተምሮናል::
..........ይቆየን..........ተፈጸመ...... ዝንቱ ጡሁማር::
ከአቃቢያነ መላክ ከቅዱስ ሚካኤል ወገብርኤል እረድኤትን ይክፈለይ::

አዘጋጅ:- #ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
@YEAWEDIMERITE
ሰኔ 19/2012ዓ.ም
👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#ዓውደ ምህረት የእናንተ
#አዲስ_ልጅነት_አዲስ_እናትነት_ቤቢ_ሻወር

በህንድ semantham ወይም Pumsavana santham (Valaikaappu) በመባልም የሚታወቅ ፣ በደቡብ ሕንድ የአራራ ፕራህ ፣ ተለጊና ፣ ካናታካ እና ታሚል ኑዱ በሴቶች 6 ኛ ፣ በ 7 ኛው ወይም በ 8 ኛው ወር ውስጥ የሚታወቅ የህንድ ባህል ነው። ምንም እንኳን በጥንት ዘመን ሰመታም የተደረገው በእያንዳንዱ ልጅ መወለድ ላይ ቢሆንም ዛሬ ግን ለመጀመሪያ ልጅ እንዲደረግ የተወሰነ ይመስላል። ይህ ሥነ-ሥርዓት በምዕራባውያን ባህሎች ከሚከናወነው የሕፃን ገላ መታጠብ ጋር ይመሳሰላል ፡፡ “ሴሜንትሃም” የሚለው ቃል ሲሪል ማላሻክሚ በሚኖርበት ከዐይን ዐይን በላይ ያለውን ፀጉር መከፋፈልን ያመለክታል ፡፡ ይህ የሆነች ሴት ልጅን ስትወልድ እራሷ የአምላኬ Lakshmi አካል እንደሆነች ተደርጋ ትቆጠራለች ፡፡
ከክርስትና አንፃር ማድረግ ተገቢ ነው አይደለም የሚለውን ለመመለስ ሳይሆን ባለንበት ዘመን አብዛኛው ወጣት ክርስቲያን በዚህ ወጥምድ ስር መገኘቱ የቤቢ ሻወር ቅድመ ወሊድ የሚደረግ ዝግጅት እንደ ወረርሽኝ በየቤቱ መግባቱ የባህል ወረራም በመሆኑ የቱ ጋር ነን ወዴትስ እየሄድነው የሚል ስጋት ስላጫረ በአጭሩ ለማስቀመጥ ነው፡፡
ይህ ሥነ-ሥርዓት በምዕራባውያን ባህሎች ከሚከናወነው የሕፃን ገላ መታጠብ ጋር ይመሳሰላል ጥንት ግን እንዲህ አልነበረም የጥንት ግሪኮች እና ግብፃውያን አዲሱን ሕፃን እናቱን ለማክበር የአምልኮ ሥነ-ሥርዓትን ያካሂዱ ነበር ፡፡ በእነዚህ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይም ለተለያዩ አማልክት እና ጣኦቶች ስጦታን እና መልካም ምኞቶችን ያቀርባሉ ፡፡ በመካከለኛው ዘመን የሕፃኑ መታጠብ ለአዲሶቹ ወላጆች ስጦታን በመስጠት ያከብሩት ነበር ፡፡ ስጦታዎች የሃይማኖታዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ይደረግም ስለነበር ፣ እና አማልክት ብዙውን ጊዜ የሚሰጡት ተአምር አለ ተብሎ ይታመናል ፡፡ በኋላ ፣ በመካከለኛው ዘመን እናቶች ህጻን ሲወለድ የከበሩ ስጦታዎች ከቅርብ ጓደኞችና በቤተሰቦች ተሰጡ ፡፡ አስቀድሞ ግን አውሮፓውያኑም እሩቅ ምስራቃውያንም ልጆቻቸውን ለጣዖታት ይገብሩ እንደነበርና የአምልኮም ስርዓት ሲያከናውኑ መቆየታቸው ወደዚህ ባህል እንዳደረሳቸው ይታመናል ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ልጆቻቸውን ለጣዖት እንዴት ሲገብሩ እንደነበር በብዙ ቦታ ተጽፏል ፡፡ በጥቂቱ ሊያስረዱን የሚችሉ የመጽፍ ክፍሎች ውስጥ ኩፋሌ 1:10 ፣ መ.ጥበብ 14:22 ፣ ሕዝ16:36 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ለጣዖት ልጆቻቸውን የሚሰው ወላጆች እንደነበሩ አስረግጦ ይነግረናል፡፡ እነዚህ የተወለዱ ልጆች ቀጥታ ለመስዋዕትነት ይቀርባሉ በኀላ ግን በስጦታ መልክ በመስጠት የመገበሩን አካሄድ በሌላ አምልኮ ቀይረውታል ፡፡ ምዕራባዊያን ጥንትም ቢሆን ከጣዖታት ጋር ጥብቅ ቅሩኝነት ስለነበራቸው ሲያደርጉት ቆይተዋል በኀላ በ2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስትናው እየተስፋፋ በመሄዱ በዚያን ጊዜ የነበራቸውን ለጣዖት የመገበር ሥርአት እንደባህል ይዘውት ቀርተዋል፡፡ግሪኮች ህንዶች ግብፆች በአብዛኛው ከሴት ጣዖት ጋር በማገናኘት ያመልኩ ስለነበር ከጣዖት አምልኮ ሲላቀቁ ባህሉን ግን እንደያዙት ቀጥለው የተወሰኑ የቀናት ማሻሻያ በማድረግ ቅድመ ወሊድ አዲስ እናትነትን ከአዲስ ልጅነት አገኘን በማለት ሴቶቹ በስፋት ያከብሩታል father shower በአንዳንድ አገራት ጨምረው ያከብራሉ ፡፡

በሀገራችን አስቀድሞ የኦሪት ስርዓት በመኖሩ በእርግዝና ወቅት በሃይማኖት ደረጃ ጎልተው የሚከበሩ ዝግጅቶች ባይኖርም ከወሊድ በኋላ ግን እስከ ክርስትናው ድረስ ሊዘልቁ የቻሉ ስርዓቶች ነበሩ፡፡ በአገራችን በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ ያለው ከወሊድጋር በተያያዘ የሚሰጠው የማህበረሰብ አዘገጃጀት ይለያያል ባህል እንደ አካባቢው በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ግን የእመቤታችን የፅንሰቷ ዘመን የ የቅዱሳን አንስት የጽንሰት ዘመን ልጆቿ እንዲማሩ የቅዱሳንን ታሪካቸውን ተጋድሎዋቸውን ባጠቃላይ ህይወታቸውን ታሰተምራለች ፡፡ በአዲስ ኪዳኗ ቤተክርስቲያን በእርግዝና ወቅት ፈተኄ ማህፀን ሩፋኤል መልአክ ድርሳኑ እንዲደገም ይደረጋል ይህም የሚደረገው በማህፀን ላይ፡የተሾመ በመሆኑ ነው፡፡ የቅዱሳን ታምራቸው ገድላቸው አቅም በፈቀደ ይነበባል፡፡

ይቆየን።

#አዘጋጅ #_ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
«አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።» መኃ 4፥7

እንተ ተሐንጸት በስሙ ወተቀደሳት በደሙ። በዚህች ቀን የእናታችን .
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴዋ የከበረበት ታላቅ የተቀደሰ ቀን ነው።

አንድም ለእመቤታችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን የሰጠበት ቀን ነው። (ሰኔ ጎልጎታ)

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ አማላጅነቷ ወሰን የሌለው ፍቅርና ጣዕሟ በሁላችን ላይ ይደር። ለዘላለሙ አሜን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
“.. የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? "
ዮሐንስ ፳፩÷፲፮
ተናጋሪው ወልደአብ ወልደማርያም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠየቀው ሊቀ ካህናት ስምዖን ጴጥሮስ የጻፈው ወንጌላዊው የጌታ ወንድም የተባለው ፍቁረ እግዚዕ ቁፁረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ጌታ ሞትን ድል አደርጎ ከተነሳ በኀላ በጥብሪያዶስ ወንዝ ለሐዋርያት እንደገና በተገለጠበት ወቅት ነበር ቅዱሱ ሊቀ ካልኑ ጴጥርስ የተጠየቀው እንግዲህ ከጥያቄው እንደምንረዳው ጌታ በድጋሚ ከተገለጠላቸው በኀላ ሊያሰማራቸው ትዛዝ ሊያክልላቸው ወደዚህ አለም የመጣበት አላማ አንዱ በጎቹን ወደ ቀደመው አዳም ክብር ከፍ ማድረግ እና ከተኩላው ዲያብሎስ መጠበቅ ስለሆነ ለእነ ቅዱስ ጴጥሮስ ትዛዝን ሊሰጥ ግድ ስለሆነ ምዕመናንን በሦስት ደረጃ በመክፈል ለዮና ልጅ ለስምዖን ጴጥሮስ ከወደደው በጎቹን ፡ ከወደደው ጠቦቶቹን ከወደደው ግልገሎቹን እንዴት መያዝ እንዳለበት ጌታ ሲነግረው ቅዱስ ጴጥሮስም ለተጠየቀው ትወደኛለኸን ጥያቄ ጌታ እንደምወድህ አንተ ታውቃለኽ በማለት ጌታ እርሱን መውደዱን እንደሚያውቅ ቅዱስ ጴጥሮስ መልስ ሰጥቷል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሁሉንም ጳጳሳት ሸክም ተሸከመ ቅዱስ ጴጥሮስ የሁሉንም ቀሳውስት የክህነት ኃላፊነት ተሸከመ ቅዱስ ጴጥሮስ የሁሉንም መምህራን ዲያቆናት ሸክም ተሸከመ በእርሱ ዓለትነት ቤ/ክ ተመስርታለችና የጳጳሳት፡የካህናት የመምህራን ዲያቆናት ሥልጣን ቁልፍ በእጁ ሆነለት በእርሱ በኩል ለሁሉ ተሰጠ እርሱም በዛሬዋ ዕለት ለበጎቹ፡ለጠቦቶቹ እንዲሁም ለግልገሎቹ ክርስቶስ ለቤ/ክ እራሱን አሳልፉ እንደሰጠ እርሱም ከወንድሙ ቅዱስ ጳውሎስ ጋር አብሮ እራሱን አሳልፎ ሰጠ በጎች ጠቦቶች እንዲሁም ግልገሎች በእርሱ ሞት አሸነፉ እርሱን ለመሆንም በመንገዱ ቆሙ በዛም ስለመንግስተ ሠማያት መራራ ሞትን ታግሰው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው እነርሱን መሰሉ ለቤተክርስቲያን ብርታት ድል ሆነ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ታትማለችና፡፡የኢትዮጵያ ቤ/ክ ዛሬም ለበጎቿ ለጥቦቶቿ እንዲሁም ለግልገሎቿ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቶስን መውደድ የሚመሰክሩ አባቶች ወንድሞች ያስፈልጓቷል ዛሬም በክርስቶስ ጥያቄ ጴጥሮሳዊ መልስ እንጠይቃለን መልስም እንፈልጋለን
ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ክርስቶስን እንወደዋለን ? ካህናት መምህራንን ክርስቶስን እንወደዋለን ? ወጣት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ክርስቶስን እንወደዋለን? ከወደድነው በጎቹን ጠቦቶቹን ግልገሎቹን በመጠበቅ በማሠማራት ከክፉ ሁሉ ቀድመናቸው እየተሰዋን እየወደቅን የቤተ/ክ ጌጦች ምዕመናንን በመጠበቅ በማሠማራት ቅዱስ ጴጥሮስ " አዎን ጌታ ሆይ፥ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ ።” እንዳለው እኛም ከሊቅ እስከ ደቂቅ
እንደምንወድህ አንተ ታውቃለህ አዎን ጌታሆይ እንሆድሃለን እንለው ዘንድ ጊዜው ወቅቱ ያስገድዳል ምክንያቱም አንድሰው ተገደለ በተባለ ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠሩ የተዋሕዶ ምዕመናን እየገደሉ አብያተክርስቲያናት እየተቃጠሉ ነውና ምዕመናን መጠበቅ ስለ እነርሱ መጮህ ጊዜው የሚጠይቀው ግዴታ የተሰጠን ወንጌላዊ አገልግሎት አላማም ነው፡፡
እንኳን አደረሰን
ሐምሌ ፭/፳፻፲፪ ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit