አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ልክ ዐይታው እንደማታውቅ ሰው እጆቿን ስትዘረጋለት ተመለከትኩ፡፡

ረጅም፣ ጠይም፣ ደልዳላና ዱባ ከንፈር ያለው ቢገፋ ቢገፋ ከሠላሳ
ሦስት የማይዘል ሰው ነው፡፡በሳምኳት ቁጥር ሥሥ ከንፈሮቼን መንከስ የጀመረችው ይሄን ዱባ ከንፈሮቹን ያገኘች እየመሰላት ይሆን?

እንዲህ አቅርባ የምታወራውን
ለሁሉም እንደምታደርገው በማቀፍና መሳም ፈንታ እጆቿን ለመጨባበጥ
ስትዘረጋለት፤ ቤቴ፣ ቤቴ ሳይሆን የብሄራዊ ቲያትር መድረክ፣
እነሱም ሊተውት የመጡ የኪነት ሰዎች ሆነው ታዩኝ፡፡

“በረከት ባሌን ተዋወቀው...” አለችና ቀድማው ወደ እኔ መጣች፡፡
ስትሰናዳበት እንደቆየችው ቂጡዋን በእሱ የዕይታ ማእቀፍ ውስጥ
አድርጋ እየተወዘወዘች ስትመጣ፣ እንደማፈር ብሎ እያያት ሲከተላት ተመለከትኩ፡፡

“ሙሉጌታ...” አልኩት፣

የጨበጠኝ እጁን ጭምቅ አድርጌ
ጨብጬ... የገዛ ስሜ አፌ ውስጥ ዝገት ዝገት እያለኝ...

ቤታችን ከሚፈቅደው በላይ የተነጋገሩ በሚመስል ሁኔታ ተራርቀው ተቀመጡ፡፡(በዚህ ጊዜ ቢሆን #ኮረና ይባል ነበር) አልፎ አልፎ ካልሆነ አይተያዩም፡፡

ዐየኋት፡፡

ዐይቶና ነክቷት እንደማያውቅ ሁሉ እጆቹን ባፈረ ሰው አኳኋን አጣምሮ ሷፏው ላይ እየተቁነጠነጠ ተቀምጧል።

ቀሽም ተዋናዮች!

የግብዣውን ቡፌ አጋምሶ ሆዱ ጢቅ እስኪል ከበላ በኋላም የጠገበ
አልመሰላትም መሰለኝ...

“በረከት ይኼ ዳቦ እኮ ልክ አንተ እንደምትወደው ነው... ያዝ እንጂ...”

“ኧረ ጎመን በስጋውን መች ነካኸው በረከት...”

“ላዛኛው ከውጪ የመጣ መስሎህ ነው.? በረከት ሙት... እኔው
ራሴ ነኝ እኮ የሠራሁት... ባለሙያ እኮ ነኝ ሃሃ”

ምሳው አብቅቶ ለቡና ስንቀመጥ እንደገና ዐየኋቸው፡፡

በዐይኑ ይነካታል፡፡

በዐይኑ ልብሷን ያወልቃል፡፡

በዐይኑ ይተኛታል፡፡

በዐይኖቿ ትስመዋለች፡፡

በዐይኖቿ ትዳራዋለች፡፡

በዐይኖቿ የአልጋ ላይ ጨዋታ እንደሰመረላት ሴት
እየተስለመለመች ትሞትለታለች፡፡

ያለ ቃል፣ ያለ አልጋ፣ ፊት ለፊቴ ሲዳሩ ደሜ ከፍ አለ፡፡ ሲጋራ ላጭስ ብዬ ወጣሁ፡፡

አርባ አራት ሲጋራ ይመስለኛል አጭሼ ስመለስ ጭኮ ቀርቧል፡፡ ይሄ ሰው ሚስቴን ብቻ ሳይሆን ጓዳዬንም ሊዘርፍ ነው የመጣው?

“ብላ በናትህ... እንደ ወለጋ ጭኮ ባይሆንም አሪፍ ነው....”
አለችው፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብዬ ስቀመጥ፣

“ስቃኝ ሳምሪ....” ተግደረደረ፡፡

“እስቲ እሱን ነገር ለእኔ ስጪኝ...” አልኩ ንዴቴ ጢም ብሎ ሲሞላ፡፡ ዐየችኝ፡፡

“ምነው...ጭኮ እንደምወድ ታውቂያለሽ... ስጪኝ እንጂ?” አልኩ
መልሼ፡፡

“እኔ እኮ ለበረከት የገዛሁት 'ደምቢዶሎ የምበላው የእናቴ ጭኮ እያለ ሲያወራ ሰምቼ አሳዝኖኝ ነው፡፡

አንተማ አይፈቀድልህም.... ሃሃ” ሣቀች፡፡

ጥርስሽ ይርገፍ፡፡

“ተይ እንጂ... በቤቱ አትከልክይው...” አለች ቃል ከዳን፣ ተነስታ ሰሀኑን እያመጣች፡፡ መምጣቷን ብቻ ሳይሆን መፈጠሯንም ረስቼው ነበር፡፡

“ተይ ቃል.... ወድጄ እኮ አይደለም የከለከልኩት.. ቦርጩን
አታይም...? ያወፍረዋል... በረከት እኮ ቢያንስ ጂም ይሠራል... የኔ ባል ግን ሰነፍ ነው... ለእሱ አስቤ እኮ ነው...”

አላበዛችውም?
*
ከአንድ ሳምንት በኋላ...
የበረከት ስም በድንገት ሊባል በሚችል ሁናቴ ከሚስቴ አፍም፧ከቤታችንም ተለየ፡፡ ፈጽሞ አትጠራውም፡፡ ጨርሶ አታነሳውም፡፡በነገሩ ስገረምም ስብሰለሰልም ከረምኩና፣ አንዱን ማታ የመጣው ይምጣ ብዬ፣

“እኔ የምልሽ...” አልኳት፡፡

“አንተ የምትለኝ...?”

“ያ በረከት ደህና ነው...? ምነው ስለእሱ ስታወሪ አልሰማም - ይህን
ሰሞን?” አልቆዘመችም፡፡ ለማሰብ ጊዜ አልወሰደችም፡፡

ለጥያቄው እንደተዘጋጀች ሁሉ፣

“ኡፍ... እሱ ልጅ እንዳስጠላኝ...” አለችኝ፡፡

“ምነው ምን አደረገ?” እያቁነጠነጠኝ ጠየቅኩ፡፡

“አይ... ምንም.... ማለት እኔን ምንም አላደረገኝም ....ግን አንዳንድ
ሰው ደህና ይመስልና ስታውቀው ይደብርሃል... አይደል? እንደዛ
ነው.... በቃ አለ አይደል...”

ወሬዋን ሳትቋጭ አቀርቅራ ወደ ማእድ ቤት ሄደች፡፡ ስታውቀው ይደብርሃል?

ምን ተፈጥሮ ነው? ተኝቷት ዐይንሽን ላፈር አላት?

ሌላ ዐየባት? ተደብሮባት ወደ ዩኤን ሄደ? እጁን ስመው ተቀበሉት?

ሲያዝንባትና ሲጠየፋት የከረመ ገላዬ
ተኮማተረ፡፡ የበጠሰችው አንጀቴ ደነደነ፡፡

በነጋታው እንቅልፍ ያላየ ዐይኔን እያሻሽሁ ሳሎን ሆኜ ፤ ንግስቴን፣
“ከልቤ ዙፋን ተባረሻል” ብዬ ለመንገር እሰናዳለሁ፡፡ ለምን እንደበቃኝ
ላስረዳት እዘጋጃለሁ፡፡
ሐሳቤን ሳልቋጭ መጣች፡፡
ጸጉሯን በቅድመ በረከት ዘመን እንደነበረው ፤ ጨብራራ ፍሪዝ
አድርጋ፣ የምወደውን ዘልዛላ ሰፊ ሱሪዋን እና ታኮ የለሽ ክፍት ጫማዋን ተጫምታ ሜክአፕ ያልዞረበትን የምወደውን ፊቷን ይዛ ከመኝታ ቤት መጣች፡፡

ዐየኋት፡፡

.ልቤ አንገራገረ፡፡

የጎዳችው ልቤ አንገራገረ፡፡

አንገራገረ።

አንገራገረ።

በኛ በኩል አልቋል እናንተ ከፈለጋቹ ቀጥሉበት😃

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ #ፍክት ያለ ቅዳሜ ይሁንላቹ ደሞ #Share አድርጉ እንጂ 🙏
👍3