አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሚዮና_ዡልየት

እስቲ #በትያትር ደግሞ ዘና በሉ

#ክፍል_አንድ

ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ ሁለት ፡ ባላባቶች ፡
ሆነው ፡ የሚኖሩ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ጠላቶች ፡
የእነሱም ፡ ወገኖች ፡ ባገረ ፡ ቬሮና ፡
ድንገት ፡ ሲገናኙ ፡ ሲያልፉ ፡ በጐዳና ፡
ጠብ ፡ እያበቀሉ ፡ በተንኰል ፡ በዘዴ ፡
ይተላለቃሉ ፡ በሰይፍ ፡ በጐራዴ ።
ሮሜዎና ዡልዬት ፡ ሁለት ፡ ልጆቻቸው ፡
በጣም ፡ ተዋደዱ ፡ ፍቅር ፡ አድሮባቸው፡
ግን ፡ አባቶቻቸው ፡ በነሱ ፡ መካከል ፡
ብርቱ ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ የነበረው ፡ በቀል ፡
ዕርቅን ፡ እንቢ ፡ ብለው ፡ ከቂም ፡ ስላልወጡ ፡በእነሱ ፡ ኀጢአት ፡ ልጆቹ ፡ ተቀጡ ።
ሆኖ ፡ የተገኘ ፡ ባገረ ፡ ቬሮና፡
እጅግ ፡ የሚያሳዝን ፡ የሚያስለቅስ ፡ ዜና ፡
አንባቢ፡ ተመልከት ፥ እንግዲህ፡ አስተውለው፤የምናቀርብልህ ፡ ታሪኩ ፡ ይኸ ፡ ነው ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
#በቤሮና_ከተማ_አውራ_መንገድ_ላይ

#ሶምሶንና#ጎርጎርዮስ

#ሶምሶን
ዛሬ ፡ ሣር ፡ ቅጠሉ ፡ ዐፈርና ፡ ሙጃ ፡
ደም ፡ ደም ፡ ይሸተኛል ፡ ምክንያቱን ፡ እንጃ ።

#ጎርጎርዮስ
የሞንታግ ፡ ወገኖች ፡ ሸተውህ ፡ ይሆናል

#ሶምሶን
የነሱማ ፡ ጠረን ፡ በሩቅ ፡ ይቀረናል ።

#ጎርጎርዮስ
ምን ፡ ታደርግ ፡ ኖሯል ፡ አሁን ፡ ብቅ ፡ ቢሉ ?

#ሶምሶን
ኣይዞህ ፥ በኔ ፡ በኩል ፡ አይነሣም ፡ ጥሉ ፡
ግን ፡ እኔ ፡ በሰላም ፡ ብሄድም ፡ ዐርፌ ፡
ሳይጣላ ፡ አይቀርም ፡ ዐመለኛው ፡ ሰይፌ

#ጎርጎርዮስ
አይጠረጠርም ፤ መቼም ፡ ካየናቸው ፤
እነሱም ፡ አይለቁን ፥ እኛም አንተዋቸው ።

#ሶምሶን
እኔማ ፡ እንኳንስ ፡ እነሱን ፡ አይቼ ፡
ውሻቸውን ፡ ሳየው ፡ በድንገት ፡ አግኝቼ ፡
ያንቀጠቅጠኛል ፡ ደሜ ፡ እየተቈጣ ።

#ጎርጎርዮስ
ከሞንታግ ፡ አሽከሮች ፡ ያው ፡ አንደኛው ፡ መጣ ፡አንዱም፡ተከተለ ፡ ብቅ፡አሉ፡ሁለቱ ።

#ሶምሶን
ይንቀሳቀስ ፡ ጀመር ፡ የሰይፌ፡ ስለቱ ።

#ጎርጎርዮስ
እንግዲህ ፡ ተጠንቀቅ ፡ ሶምሶን ፡ ተሰናዳ

#ሶምሶን
ብቻ ፡ እንዳያገኘን ፡ የዳኝነት ፡ ዕዳ ፡
አንድ፡ ዘዴ ፡ እናምጣ ፡ ጠቡን ፡ እንዲያነሡ ፡እዚህ ፡ ከኛ ፡ አጠገብ ፡ ጠብቄ ፡ ሲደርሱ ፡ ፊቴን ፡ ወደ ፡ እነሱ ፡ እንዲያዩኝ ፡ መልሼ ፡
አስቆጣቸዋለሁ ፡ ከንፈሬን ፡ ነክሼ ።

( #አብርሃምና #ቤልሻጥር #መጡ ) ።
👇👇

#አብርሃም
አንተ ፡ በኛ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ከንፈር ፡ የምትነክሰው ፤

#ሶምሶን
እኔን ፡ አይጠይቅም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሰው ።

#አብርሃም
በኛ፡ ላይ ፡ እንደሆን ፡ ንገረኝ ፡ በፍጥነት ፡

#ሶምሶን
መጠየቅ ፡ አያሻም፡ ከኖረህ ፡ ወንድነት ።

#አብርሃም
ሁሉም ፡ በጃቸው ፡ ነው ፡ ሻምላ ፡ ሆነ ፡ ሰይፉም ፤
#የሞንታግ ፡ ወገኖች ፡ ተሰድበው ፡ አያልፉም ።

#ሶምሶን
የት ፡ አይተሃል ፡ ቀርተው ፡መዋጋት ፡ ሳያውቁ ፤
#የካፑሌ ፡ አሽከሮች ፡ በናንተ ፡ ሲጠቁ ?

#አብርሃም
ሊታይ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ የናንተ ፡ ጕብዝና ፤

#ሶምሶን
መች፡ አጣህ ፡ መሆኑን ፡ የኛ ፡ ወገን ፡ ጀግና ።

( #ውግያ' #ይገጥማሉ )

#ቤንቮሊዎ ። (ይመጣል) ።

ያላንድ ፡ ምክንያት ፡ በከንቱ ፡ ሳይቸግር ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ የናንተ ፡ ግርግር ።
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ጧት ፡ ማታ ፡ ስታልፉ፡ በመንገድ ፡ልማድ ፡ ሆነባችሁ ፡ ደርሶ ፡ ማንገራበድ ።
ለማምጣት ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በናንት ፡ የተነሣ
በጌቶቻችሁ ፡ ላይ ፡ የዳኛ ፡ ወቀሣ።

#ቲባልት ፡ (ሻምላውን መዞ እያወዛወዘ ' መጣ )

እየው ፡ ቤንቮሊዎ ፡ ጥላውን ፡ ዘርግቶ
ሞት ፡ የያዘ ፡ ሻሞላ ' በራስህ ፡ ላይ፡ መጥቶ ፡ ተመልከት ፡ ሲያንዣብብ ፡ እንደ ፡ ጆፌ አሞራ

#ቤንቮሊዎ
መንፋትህ ፡ ይቅርና ፡ የማይረባ ፡ ጉራ
እንገላግላቸው ፡ ይልቅ ፡ ተረዳድተን ።

#ቲባልት
ልገጥምህ ፡ ነውና ፡ የመጣሁት ፡ አንተን ፡
ይልቅ ፡ ተሰናዳ ፡ ሻምላህን ፡ ምዘዘው ፤
ሳትዋጋ ፡ እንዳትሞት ፡ ቶሎ ፡ በጅህ 'ያዘው "

ቲባልት ፡ ሻምላ ፡ መዞ ፡ እጁን ፡ ከዘረጋ ፡
ሊመለስ ፡ አይችልም ፡ ጠላቱን ፡ ሳይወጋ
ወይም ፡ ደግሞ ፡ ራሱ ፡ ቀድሞ ፡ ካልወደቀ ።
#ቤንቮሊዎ
ፉከራህ ፡ ከንቱ ፡ ነው፡ በጣም ፡ የተናቀ ።

(#ውጊያ #ይገጥማሉ) ።

#ሞንታግ ፡ (መጣ)
ወገኖቼ ፡ ሁሉ ፡ ድረሱ ፡ በፍጥነት ፤
እነሆ ፡ ሰዎቼን ፡ ፈጁዋቸው ፡ በድንገት ።

💫ይቀጥላል💫
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ስድስት


አሁንም ፡ ፡ ይሻላል ፡ ብታየው ፡ አስተውለህ ፤

የደረቀ፡ደም፡ነው፡ዝገት፡የመሰለህ

#ቲባልት
ኧረግ ፡ እንዲህ ፡ነው ፡ ወይ ! የበግ ፡ ነው ፡ የዶሮ ?

#ቤንቮሊዎ
ፈሶ : የተገኘ ፡ ካንገቱ ፡ ጕረሮ ፡
የወገንህ ፡ ደም ፡ ነው ፡ ከበግ ፡ የማይሻል

#ቲባልት
በመሳደብ ፡ ብቻ ፡ ጊዜያችን ፡ ይመሻል ፡
እንግዲህ፡ ይቀጥል ፡ የወንዶቹ ፡ ሥራ ።
(#ሻምላ#መዘዘ)።

#ሜርኩቲዎ
ዘወትር፡ዝግጁ፡ነኝ፡ማንንም፡አልፈራ፤(#ሜርኩቲዎም #መዘዘ)
(ሮሜዎ ፡ መጣ) ።

#ቲባልት
ከናንተ ፡ ኣልዋጋም ፡ መጣ ፡ የኔ ፡ እኩያ ፤
ስማኝ ፡ ሮሜዎ ፡ ወጥቼ ፡ ገበያ ፡
አቃተኝ ፡ ለማግኘት ፡ ፈልጌ ፡ ክፉኛ ፡
አንተን ፡ የመሰለ ፡ የወንድ ፡ መናኛ ።

#ሮሜዎ
ተፍቋል ፡ ጨርሶ ፡ ቂም ፡ በቀል ፡ ከልቤ ፤
በመጥፎ ፡ ንግግር ፡ ሮሜዎን ፡ ሰድቤ ፡
ላስቈጣው ፡ በማለት ፡ ቂሙን ፡ ልቁስቀሰው ፡ ማለት በከንቱ ፡ ይደክማል ፡ የተጣጣረ ፡ ሰው' .
የፍቅሬ ፡ ምክንያት ፡ ሆኗልና ፡ ብርቱ ፡
ቲባልት ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ አትድከም ፡ በከንቱ

#ቲባልት
ኀይለኛው ፡ ቂማችን ፡ ያከማቸው ፡ ዕዳ ፡
መች ፡ እንዲህ 'ይፋቃል ፡ ይልቅ ፡ ተሰናዳ

#ሮሜዎ
ቲባልት ፡ ስማኝ ፡ እኔ ፡ ንጹሕ ፡ ነኝ፡ ከቂሙ
ካፑሌ ፡ የሚሉት ፡ የዘራችሁ ፡ ስሙ ፡
እንደ ማር፡ ጣፋጭ ነው፡አይመረኝም ለኔ
ጠባችሁ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በውነቱ ፡ ሐዘኔ ።
የፍቅሬን ፡ ምክንያት ፡ ሳታውቀው ፡ መርምረህ ፤
አትድከም ፡ በከንቱ ፡ ክፉ ቃል ፡ተናግረህ፡
ቲባልት ፡ እኔና ፡ አንተ መቼም : አንጣላም
ደኅና ፡ ዋል ፡ ወዳጄ ፡ እንሂድ ፡ በሰላም ፡
ደግሞም ፡ ከዚህ በቀር ፡ የሕጉን ፡ ወቀሣ
የመስፍኑን ፡ ዐዋጅ ፡ ልብህ ፡ እንዳይረሳ ።

#ሜርኩቲዎ
ዦሮዬ ፡ አይሰማም እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍራት
ቲባልት ፡ እይ ፡ ሻምላዬ ፡ ሲያበራ ፡ እንደ ፡ መብራት ። (መዘዘ)።
ተመልሶ ፡ እንግዴህ ፡ ኣይገባም ፡ ካፎቱ ፡
በደም ፡ ካልታጠበ ፡ የዛገው ፡ ስለቱ ።
(አቲባልት'ጋራ ውጊያ'ገጠሙ)•

#ሮሜዎ
ፍጠን ፡ ቤንቮሊዎ ፡ እንገላግላቸው ፤
ሁለቱም አይረቡ በውነት እብዶች ፡ ናቸው
ቲባልት ! ሜርኩቲዎ ! አስቡት ፥ አትርሱ ፤
ልዑል ፡ በቀደም ፡ ለት ፡ ደም ፡ እንዳታፈሱ
ብለው ፡ የሰጡትን ፡ ዐዋጁን ፡ አስታውሱ
(ገላገላቸወ፡ ቲባልት' ከወገኖቹ'ጋራ'ሄደ)

#ሜርኩቲዎ
ቈስያለሁ ፡ እኮ ፡ በቃ ፡ የኔ ፡ ነገር ፤
ተበላሸሁ ፡ እኔ ፡ ወይ ፡ አለመመከር ።
ቤንቮሊዎ ፡(ቁስሉን'ያያል)"
ለካ ፡ ቁስለሃል ፡ ወይ ? አላየሁም ፡ እኮ !

#ሜርኩቲዎ
ሐኪም ፡ ይጠራልኝ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ተልኮ
(የልፍኝ' አሽከር መሄዴ) "

#ቤንቮሊዎ
አይዞህ ፡ የኔ ፡ ወንድም፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ቍስሉ ፤

#ሜርኩቲዎ
ምንም ፡ ትንሽ ፡ ቢሆን ፡ አይቀርም ፡ መግደሉ'ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ ትውልዳቸው ፡ ይጥፋ፤
በነሱ፡ ምክንያት ፡ ስንት ፡ ሰው ፡ ተደፋ፡
በምን ፡ ኀጢአታችን ፡ እንሞታለን ፡ እኛ ፡
ለማይረባ፡ ነገር ፡ ተሳድቦ ፡ እንደ እረኛ ፡
በሰው፡እጅ፡ መሞት ፡ በሆነ ፡ ባልሆነው '
ከንቱ ፡ ሞት ይሉሃል ፡ እንደዚህ ፡ ያለ ነው
ተመቸውና ፡ ነው ፡ ይኸ ፡ ፈሪ፡ መጥፎ ፡
በሮሜዎ ፡ እጅ ፡ ሥር ፡ ታቹን ፡ አሳልፎ ፡
በድንገት ፡ የወጋኝ ፡ በቃ ፡ የኔ ፡ ነገር ፤
ባትገላግሉኝ ፡ አይነካኝም ፡ ነበር ።
(ሜርኩቲዎን'ቤንሾሊዎ 'ደግፎት ፡ አብረው ሄዱ)”

#ሮሜዎ ፡ (ወቻውን)
ወዳጄ ፡ ሜርኩቲዎ ፡ የመስፍኑ፡ ዘመድ ፡
አባቴን ፡ ወገኔን ፡ እኔንም ፡ በመውደድ
እንሆ ፡ቈሰለ ፡ ለኛ ፡ ሲል ፡ ተጣልቶ ፤
ቲባልት ፡ አዋረደኝ ፡ ከመሬት' ተነሥቶ
ዡልዬትን • ወድጄ ፡ ፍቅር ፡ መፈለጌ ፡
ስድቡንም ፡ ሸሽቼ ፡ ከጠብ ፡ ማፈግፈጌ፡
ወደ 'መለማመጥ ወገኖቼን ' መሪ
ወንድነት 'ያነሰኝ'አስመሰለኝ ' ፈሪ ።
(ቤንቮሊዎ መጣ)

#ቤንቮሊዎ
አልቅስ ፡ሮሜዎ ' እንባህን 'አፍስሰው
ሜርኩቲዎ ፡ ሞተ፡ መልካሙ 'ደጉ' ሰው ።
መልካሙ ፡ ወዳጄ ፡ ሜርኩቲዎ ' ከሞተ '
እንግዴህ ፡ መታረቅ ፡ ሰላም ፡ ተከተተ ፥
ጠባችን ፡ ነደደ ፡ በሉ ፡ የተነሣ ፤
ወደ ፡ ፊት ፡ ይወድቃል ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ ሬሳ
(ቲባልት' ተመልሶ ፡ መጣ)

#ቤንቮሊዎ
ቲባልት ፡ ይኸ ሰይጣን መጥፎ ፡ ጥጋበኛ
እየው ተመልሶ ፡ ሲመጣ ፡ ወደ ፡ እኛ ።

#ሮሜዎ ፡ ለብቻው' ይናገራል) "
ወይ ፡ ጥሎኝ ወይ ፡ ጥዬው አንጀቴን ላርሰው ፤
ቆይ ፡ ይምጣ ፡ ግድ ፡ የለም ፡ ደም ፡ ነው፡ የመለሰው።
ዡልዬት ፡ ደግነቷ ፡ ፍቅሯ ፡ ሰላም ፡ ሆኖ ፡
ይዞህ ፡ የነበርከው ፡ በትዕግሥት ፡ ሸፍኖ ፡
በልቤ ፡ ያለኸው ፡ የቂሜ ፡ ትኵሳት ፡
ለብልበኝ ፥ ጠበሰኝ ፡ አቃጥለኝ ፡ እንደ ፡ እሳት ።
(ለቲባልት • ይናገራል) "
ቲባልት ፡ በል ስደበኝ፡ አሁን እንደ ቅድም
የሜርኩቲዎ ፡ ነፍስ ፡ ብቻዋን ፡ አትሄድም
ወይ ፡ እኔን ፡ ወይ ፡ አንተን ፡ አንዱን ፡ ሳያስተክትል፤
ሻሞላህን ፡ ምዘዘው ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ ሳትል ፡
የምትሻው ፡ ቂሜ ፡ የነደደ ፡ ይሁን ።

#ቲባልት ። ..
አንተም፡ ከሱ ፡ ጋራ ፡ ትሞታለህ ፡አሁን ።
(ይዋጉና'ቲባልት 'ይወድቃል )

#ቤንቮሊዎ
ሮሜዎ ፡ አትቁም ፡ ቶሎ ፡ ከዚህ ፡ ጥፋ ፤
ቲባልት ፡ ከሞተ ፡ ምንም ፡ የለህ ፡ ተስፋ፡
መስፍኑ ፡ ሲያገኝህ ይህን ፡ነገር ፡ ሰምቶት
ዕወቅ ፡ አይምርህም ፡ ይቀጣሃል ፡ በሞት
(ሮሜዎ 'ሸሸ ፡ ሰዎች፡ መጡ)

#ወታደር
እንዴህ ፡ ያለ ነገር ዘለዓለም ፡ የማይበርድ
ነጋ ፡ ጠባ ፡ ሬሳ ፡ በየዋናው ፡ መንገድ ፡
ጠብ መሆኑን፡ሰምተው ይኸው፡ልዑል መጡ፤
ማነው ፡ የገደለው ? አሁን ፡ በቶሎ ፡ አውጡ ።

#መስፍን
አወይ ፡ ዘመዴ ፡ ሆይ፡ ሜርኩቲዎ ፡ ሞተ፤
ማነው ፡ ጠብ ፡ ሲጀመር 'የተመለከተ?

#ቤንቮሊዎ
ልዑል ሆይ፡እኔ ነኝ'ያየሁ፡ሁሉንም ፡ ነገር !
ፈቃድዎ ፡ ቢሆን' ፈጥኝ፡ ልናገር ።

#መስፍን
ንገረኝ ፡ ሁሉንም ፡ ከምንጩ ፡ ጀምሮ፤

💫ይቀጥላል💫