አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሚስቴ_ማነች?


#ክፍል_አንድ


#በጥላሁን

የጫካ ስሜ ፍልፈሉ ይባላል ። አሁን ካለሁበት የሰው ጫካ ከሞላበት ከተማ ውስጥ መኖር ከመጀመሬ በፊት በየዱራዱሩ እና ጫካ ውስጥ ባሉ የተያዩ ዋሻዎች ከ ስምንት እመት በላይ ኖሪያለሁ። ጫካ የምኖረው አውሬ አልያም ከሰው ተቀላቅሎ መኖር የማይችል ልዩ ፍጡር ስለሆንኩ
አልነበረም ።

በግዜውና በነሱ ምልከታ ትክክል የመሰላቸውን እኔም በግዜው ትክክል የመሰለኝን ፈፅሜ ልፈፅም እንጂ።
አስተሳሰብ የሚያቀና እውቀትን አልያም ሀብትና መሬትን ሳይሆን ከፊቱ አደራ የታከለበት በቀልን አውርሰውኝ ከሞተው አባቴ የተቀበልኩትን ገሎ የመበቀል ውርስ ለመፈፀም ባጠፋሁት ነብስ ምክንያት ከሚደርስብኝ የበቀል ዱላና ቅጣት ለመደበቅ መኖሪያዬን በዱር እንዳደርግ ግድ ሆኖብኝ እንጂ ።

ገና አስራ ስምንት አመት ሳይሞላኝ ከሁለት አመት በፊት ከተለየኝ አባቴ የተሰጠኝን ነገር ቢኖር የምበቀለው እነማንን እንደሆነና የት አከባቢ ሊኖሩ እንደሚችሉ እና መሳርያ ብቻ ነበር።

18 አመት እንደሞላኝ ካባቴ የተሰጠችኝን መሳሪያ ጠራርጌ እናቴን ተሰናብቼ ከቤት ወጣሁ ለስድስት ወራት በአከባቢው ካለ ጫካ ውስጥ ተደብቄ የበቀል ኢላማዬ የሚያርፍባቸውን ካባቴ ዘር ነብስ አጥፍተው የተሸሸጉ ሁለት ሰዎችን መውጫያ መግቢያ ሳጠና እና አመቺ ግዜ ስጠብቅ ቆየሁ።

በሶስተኛው አመት መገባደጃ ላይ ግዳጄን እንደፈፀምኩ ከሶስት ቀን በላይ በግር ተጉዤ ከነበርኩበት ራቅ ወዳለ ሌላ ጫካ ገባሁ።
እልፎ እልፎ ከምኖርባት የጫካ ዋሻ በቅርብ ርቀት ባለች አንዲት ተራራማ መንደር እየሄድኩ የሚያስፈልገኝን ይዤ እመለሳለሁ ።

በአምስት አመት ውስጥ በአሳቻ ሰአት እራሴን ቀይሬ ሁለት ግዜ ብቻ እናቴን ጠይቂያታለሁ።
ወደዚች ከተሸሸኩበት ጫካ በቅርብ ርቀት ወዳለች የገጠር መንደር ግን በሳምት ውስጥ ከሁለት ግዜ ብላይ መሄድ ጀመርኩ።

በ አንድ የገና አውዳ አመት እለት ወደ መንደሯ ጎራ ብዬ በግሬ ሳዘግም አንድ ጠላ ቤት በር ላይ እንደደረስኩ ሽታው አወደኝ የሚያውቀኝ ሰው እንዳይኖር ፈራ ተባ እያልኩ ዘው ብዬ ስገባ አመት በአል ስለነበር ከሶስት ጎረምሶችና ካንድ በድሜ ጠና ካለ ሽማግሌ ውጪ ብዙም ሰው አልነበረም። ጥጌን ይዤ እንደተቀመጥኩ አንድ እድሚያቸው በሀምሳዎቹ አፋፍ ላይ የሚሆናቸው ባልቴት ጠላውን ፊት ለፊቴ ባለችው ትንሽ ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጡ ደና ዋልህ ልጄ አሉኝ።

ለሰላምታው ምላሽ ሰጥቼ ጠላውን አንስቼ ጎንጨት አልኩት አላወረድኩትም ግሩም ነበርና ባንድ ትንፋሽ ግማሽ አደረስኩት።
እቤቱ ውስጥ ያሉት ሶስት ጎረምሶች ስለ ባለጠላ ቤቷ ሴትዬ ልጅ ቁንጁና ከሚገባው በላይ እያደነቁ ያወራሉ ።

ያን ያመሰለ ውበት ይዛ እስካሁን ባለማግባታ ይደመማሉ። እሷ እዛ የገጠር መንደር ውስጥ ዘናጭ የሆነ ቤት ሰርታ ለብቻዋ እየኖረች የሳቸው ጠላ መሸጥ አይገርምም እያሉ ያሽማጥጣሉ። ሴትዬዋ ጠላውን ሊቀዱላቸው ጠጋ ሲሉ ወሬያቸውን ያቋርጣሉ። ልጅቷን የማየት ጉጉቴ ጨመረ ።አልፎ አልፎ ወደዛ ጠላ ቤት እንድምትመጣ ስለሰማሁ ላይን ያዝ እስኪያደርግ ጠላውን እየደጋገምኩ ብጠብቅም እሷ ሳትመጣ እኔ ሰከርኩ።
ጠላው በሳምት ውስጥ ማክሰኛ እና ቅዳሜ ብቻ ነው የሚኖረው ። የኔም የማክሰኛና ቅዳሜ ውሎ ጫካ ሳይሆን እዛ ቤት ሆነ ከሶስት ሳምንት የማክሰኛና ቅዳሜ ምልልስ ቡሀላ በአራተኛው ሳምንት ቅዳሜ ቁጭ ብዬ ጠላዬን ሳጣጥም ድንገት ዘው ብላ የገባችውን ሴት ስመለከት የተሰማኝ ስሜት ከዛ በፊትም ከዛ ቡኋላም እስከዛሬ ድረስ ተሰምቶኝ አያውቅም።

ምድር ላይ ካሉ ሴቶች ሁሉ ውበት ቀምቶ ለሷ የሰጣት ነው የምትመስለው አይኖቿ ልብ ያሸብራሉ።
ሀር የመሰለው ቀጭን ወገባ ላይ የሚንከባለለው ጥቁር አንፀባራቂ ፀጉሯ ለካ እስከዛሬ ፀጉር አይቼ አላውቅም ያስብላል።

ወደ ውስጥ ስትዘልቅ ከቀጭን ወገባ ቁልቁል ግዛቱን እያሰፋ የሄደው ዳሌዋ ሲውረገረግ ቁጭ ብድግ ያሰኛል። ጥርት ያለው ጠይምነቷ እንኳንም ነጫጭባ ፈረንጅ አልሆንኩ እንኳንም ኢትዬጲያዊ ሆንኩ ያሰኛል ።
ፈገግታዋ ልብ ላይ የተተኮሰ ጥይት ይመስል ልብ ይንዳል ። አንድ ባል አይደለም አንድ ክፍለጦር በውበት አንበርክኮ የሚያስከትል ይሄን ሁሉ ውበት ይዛ ያላገባችበት ምስጢር ምን ይሆን አልኩ ለራሴ።

ተወልጄ ባደግኩበትም ይሁን በሄድኩበት ሁሉ እስከዛሬ ይችን የመሰለች የውበት ሚስጥሩን የገለጠባት ከ
ኮረዳ ተመልክቼ አላውቅም።
ወይ ጣጣ ከፊቴ ተቀምጣ አይኔን እንዴት ከሷ ላይ ልንቀልና ልጠጣ ።

የምትኖርበት መንደር በመሀላቸው ጫካ እርሻ እና ተራራ ያራራቃቸው እዚህም እዛም ተራርቀው ካሉት ውስን ቤቶች በቀር ብዙም ነዋሪ የለም ።
ለመንደሩ አዲስ እንደሆንኩ ታውቋታል መሰለኝ ከናቷ ጋር እያወጋች አልፎ አልፎ እነኛን ውብ እይኖቿ ከብለል እያረገች ትመለከተኛለች ።
እንደተቆጡት ህጣን ልጅ እርበተበታለሁ።
አለባበሷ ግን ከተሜ ቀመስ ትመስላለች እንደው ወደ ከተማ ባል ይኖራት ይሆን? ካላት ታድያ እዚህ ለምን ትኖራለች ?።
ስፈራ ስቸር ቆይቼ አንድ ቃል ካፌ ወጣ።
እናት አለም ጠላ እንጠጣ?
"አባት አለም አልጠጣም! ክክክ"
ደነገጥኩ ስደነግጥ አይታ ይባስበት ይደንብር ብላ ነው መሰል ሳቋን ለቀቀችው።

ስትስቅብኝ ወንድነቴ ኬት እንደመጣ እንጃ ፍርሀቱን ትቼ ደፈር ብዬ አጫውታት ጀመር በስም ብቻ እማውቀው ፍቅር እኔን ለመቆጣጠር ቀጠሮም አላስፈለገው አልቻልኩም ከማክሰኛና ከቅዳሜ ውጪ ጠላ ኖረም አልኖረም ከተደበቅሁበት ዋሻ ወደሷ መሮጥ የየለት ተግባሬ ሆነ እኔ ቀድሜ በፍቅሯ ብወድቅም እሷ ቀስ በቀስ ለምዳኝ ይሁን ወዳኝ እርግጠኛ ባልሆንም ስንለያይ " ነገ ትመጣለህ ?" ማለት ጀመረች።

ማን እንደሆንኩ አንድም ቀን ሳትጠይቀኝ ለምን እስካሁን እንዳላገባች እንድጠይቃት ሳትፈቅድልኝ ከሶስት ወር ምልልስ ቡሀላ ጠቅልዬ ቤቷ ገባሁ። ተጋባን ።

ተጋብተን በሁለተኛው ቀን ግራ የሚያጋባ ነገር ገጠመኝ ማታ አጠገቤ የተኛችው ፍቅሬ እኩለ ለሊት ካለፈ ቡሀሏ ድንገት ስነቃ አጠገቤ የለችም •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#ሚስቴ_ማነች?


#ክፍል_ሁለት


#በጥላሁን

ተጋብተን በሁለተኛው ቀን ግራ የሚያጋባ ነገር ገጠመኝ ማታ አጠገቤ የተኛችው ፍቅሬ እኩለ ለሊት ካለፈ ቡሀሏ ድንገት ስነቃ አጠገቤ የለችም።

ደነገጥኩ ቤቱ ሁለት ክፍል ነው ከተኛሁበት ክፍል ተነስቼ ሌላኛው ክፍል ውስጥ መኖር አለመኖሯን ለማረጋገጥ ባስብም ከማሰብ ውጪ ካልጋው ላይ መውረድ አቃተኝ አልቻልኩም።
በተፈጥሮ ከንቅልፍ ነቅተን ለመነሳት ከሚጫጫነን ስሜት እጅግ በላቀ ሁኔታ እንዳልነሳ ተጫጫነኝ ቀና ማለት እየፈለኩ ቀና ማለት ተሳነኝ እስርስር ድብት የሚያረግ መንፈስ ወረሰኝ። መነሳት እየፈለኩ መልሶ እንቅልፍ ጣለኝ።ወፍ ጭጭጭጭ ሲል ነቃሁ። አጠገቤ ተኝታለች። ግራ ተጋባሁ ለሊት ካጠገቤ ያጧኋት በህልሜ ይሁን በውኔ መለየት ፈተና እንደሆነብኝ መምሸቱ አይቀርም ዳግም መሸ።

ትናንት በነቃሁበት በተመሳሳይ ሰአት እኩለ ለሊት እንደተሻገረ ነቃሁ አጠገቤ ተኝታለች። ያን ቀን ደግሞ ከትናንቱ በተቃራኒ አንዴ ከነቃሁ ቡሀላ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ስገላበጥ ነጋ ።
አራተኛው ምሽት መጣ ስንጨዋወት አምሽተን እራት በልተን ተኛን። በተለመደው ሰአት በር ሲከፈት ይሁን ሲዘጋ እንጃ ብቻ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝና ብንን አልኩ። ኧእምሬዬ ከተኛበት ቢነቃም አይኔ አልተገለጠም ነበርና እጄን ወደ ጎን ልኬ ዳበስ ዳሰስ ሳደርግ ከፍራሹ ካንሶላ እና ከብርድልብሱ ውጪ ማታ አጠገቤ የተኛችው ሚስቴ የለችም ።ፈራሁ። አይኔን መግለጥ ፈራሁ።

በትግል የገለጥኩት አይኔ በፋኖሱ ብርሀን የኔዋ ጉድ አጠገቤም የተኛሁበት ክፍል ውስጥም ያለመኖሯን አረጋገጠልኝ። እቤቱ ውስጥ ምንም ድምፅ የለም ፀጥ ረጭ ብሏል። መነሳት እየፈለኩ አልነሳም መጣራት እየፈለኩ አልጣራም።ጭራሽ ከመነሳት ሀሳቤ ጋር ያልተናበበው አይኔ ካልተከደንኩ እያለ ይታገለኝ ጀመረ ። አይኔ እየተከደነ እንቅልፍ ሊጥለኝ ሲሞክር ላለመተኛት ያደረኩት ትግል ከውስን ደቂቃዎች መሻገር አልቻለም። መሸነፌ የገባኝ ጥዋት ስነቃ ነው ለሊት ያልነበረችው ሚስቴ አጠገቤ ጧ ብላ ተኝታ እራሷን አታውቅም ።

የኔ ፍቅር ማነሽ አቅሌን እስካጣ በፍቅርሽ መውደቄ ይሆን እያቃዥኝ ያለው ።
የፍቅሬ ደረጃ ይሆን ጥለሽኝ የወጣሽ ካጠገቤ የራቅሽ እየመሰለኝ እንድጨነቅ የሚያደርገኝ ነው ወይስ የእውነት ነቅቼ ካጠገቤ እያጣሁሽ ነው ።
እንደዛ ከሆነስ በውድቅት ለሊት የት እየሄድሽ ነው ? መቼስ ባዛ የሰይጣን ሰአት መብራት በሌለበት በዚህ የገጠር መንደር ውስጥ ከቤት መውጣት እንኳን ለሴት ለወንድም ያስፈራል ። ታድያ ምን እየሆንኩ ነው የእውነት ነቅቼ ካጠገቤ አጥቼሽ ከሆነስ ለምንድን ነው ተነስቼ ሁለተኛው ክፍል ውስጥም አለመኖርሽን እና ቤቱ ቤት በኩል እንደተዘጋ ከውጪ ይሁን ከውስጥ ማረጋገጥ ያቃተኝ ።

በለሊት ካጠገቤ ተነስተሽ የት ሄደሽ ነው አልነበርሽም ብዬ እንዳልጠይቅሽ ችግሩ ከኔ ከሆነ እንዳላስቀይምሽ ሰጋሁ። አልኩኝ በውስጤ ብርድልብስም አንሶላም ሳትለብስ ተዘረጋግታ በተኛችው ሚስቴ ላይ እንደጥዋት ፀሀይ ሰውነት የሚያሞቀውን የውበት መአት የፈሰሰበትን ገላ ከታች እስከ ላይ እያየሁ። ምን ዋጋ አለው የትዳር ጣእም የላይ ውበት ሳይሆን የውስጥ ሰላም መሆኑ አሁን ነው የገባኝ።

እሄ ነገር አንድ ቀን እየዘለለ በተመሳሳይ ሁኔታ ቀጠለ። ተአምር የሆነብኝ ነገር ለሊት ስነቃ አጠገቤ ካለች ከነቃሁ ቡሀላ በጭራሽ እንቅልፍ አይወስደኝም ። በሚቀጥለው ቀን ስነቃ ደግሞ አጠገቤ አትኖርም ግን መነሳትም አልችልም በዛ ላይ ወድያው እንቅልፍ ይጥለኛል።ጭንቀቴን ለማን ላዋየው ያለሁት ከሷ ውጪ ማንንም በማላውቅበት ሀገር ነው ።
ጭንቀቴ እና ፍርሀቴ ለሊቱን ብቻ ሳይሆን ቀኑኑም አጨለመብኝ።
እሄን ግዜ ነበር እናቴ ያለችኝ ነገር ትዝ ያለኝ ።
ያባቴን የበቀል ውርስ ልፈፅም ስነሳ ብቻ ብርክክ አለችና ጉልበቶቼን ይዛ "ተው ልጄ የሰው ደም ደግ አይደለም በምድርም በሰማይም ሰላም አይሰጥም ።የሰው ነብስ ያጠፋ የሰላም እንቅልፍ የለውም።የገደለው ሰው ነብስ ታስጨንቀዋለች። አንድ ሰው ስትገድል በህይወት ዘመኑ የሰራው ሀጥያት በሙሉ ወዳንተ ይዞርና እሱ ይፀድቃል አንተ ትኮነናለህ ።
በምድርም በሰማይም ብኩን ሆነህ ትቀራለህ። እሄን ባለማድረግህ አባትህን እንደከዳኸው ቃሉን እንዳላከበርክ አይሰማህ። ይልቅ የነሱን ስተት አትድገመው ካለፈ ነገር ማስቀጠል ያለብን ደግ ደጉንና የሚጠቅመንን እንጂ ክፋቱንና የሚያጠፋንን መሆን የለበትም። ይህን የበቀል መንገድ አንተ ካላቆምከው ማን ያቆመዋል። ሰው በመግደል ጀግንነት ነው ብሎ ማሰብ ሗላ ቀር አመለካከት ነው ። ልጄ ተለመነኝ አትሂድ!"
ልመናዋን መቀበል ፈሪ መሆን ከወንድነት ዝቅ ማለት መስሎ ተሰማኝ ።
እማምዬን ከጉልበቴ ላይ አነሳሗትና ጥያት ወጣሁ። ታድያ አግብቼ ወር ሳይሞላኝ መቋጠሪያውም መፍቻውም የማይታወቅ ፈተና ሲገጥመኝ ። እማማ እንዳለችው ያ ያጠፋሁት ነብስ በቁሜ እያቃዥኝ እንጂ የኔ ንግስት በለሊት የምትወጣበት ምንም ምክንያት ሊኖራት አይችልም ብዬ እራሴን ለማፅናናትም ለመኮነንም ሞከርኩ።

ከብዙ አስጨናቂ ቀናት ቡሀላ አንድ ቀን ወደ ጫካ ወርጄ ለብዙ ሰአት ተቀምጬ ያሳለፍኳት እያንዳንዷን አስጨናቂ ቀን ስፈትሽ ሚስቴ ማታ ማታ ከምታደርጋቸው ነገሮች እስካሁን የተጋረደብኝ እና ያላስተዋልኩት አንድ ነገር ብልጭ አለልኝ።
በድንጋጤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቆምኩ በለሊት ከአጠገቤ የሄደች በመሰሉኝ ቀናት በሙሉ ማታ ማታ ወደ ምኝታዬ ልሄድ ስል በንድ ከቀንድ በተሰራ የጠላ መጠጫ ቀላስ ሙሉ ጠላ ትሰጠኝ ነበር አጠገቤ በነበረችባቸው ለሊቶች ምሽት ግን ያ ጠላ ተሰጥቶኝ እንደማያውቅ ተገለጠልኝ ። ከምኝታዬ እንዳልነሳ ጠፍንጎ የሚይዘኝ ሚስጥር ከጠላው ጋር የተያያዘ መሆን አለበት አልኩ።

ከሩጫ በማይተናነስ እርምጃ ወደ ቤት አመራሁም። ያን ቀን ማታ ጠላው አልተሰጠኝም። እሳም ለሊት አጠገቤ ነበረች።
በሚቀጥለው ቀን ማታ ከራት ቡሀላ ልተኛ ስል "እንካ ጠጣ ለንቅልፍ ይሆንሀል"እያለች ጠላውን በዛው መጣጫ ይዛልኝ መጣች። ተቀብያት ወደ ውስጥ ገባሁና ሳታዬኝ ደፋሁት።
ምኝታዬ ውስጥ ገብቼ የተኛሁ በመምሰል እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር እየተጠባበኩ እኩለ ለሊት አለፈ። በግምት ከለሊቱ ስምንት ሰአት አከባቢ ድምፁ ቀጭን የሰው ሳቅ የሚመስል ጅብ ወደ አለንበት ግቢ ተጠግቶ ማስካካት ጀመረ ። ትንሽ ቆይቶ የማስካካቱ ድምፅ እየቀረበ የሚያሽካኩትም ጅቦች እየበዙ መጡ።
ድምፁን በሰማሁ በሰከንዶች ውስጥ ጉደኛዋ ሚስቴ ድንገት ብድግ አለች። ፊቴን አዙሬ በተኛሁበት በድንጋጤ ላብ አዘፈቀኝ ። ፋኖሱን ይዛ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ስትገባ በቀስታ ተነስቾ በመሀለኛው በር ጠርዝ አጮልቄ መመልከት ጀመርኩ። ከመቅፅበት መሶብ ወርቅ ከሚባለው የመሶብ አይነት ውስጥ ቅጠል የመሰለ ነገር አንስታ አፏ ውስጥ ከተተችና ትርጉሙ ባልገባኝ ቋንቋ በጣም በፍጥነት እየለፈለፈች ከግንባሯ በላይ ያለውን የራስ ቅሏን ልክ እንደኮፍያ ከነፀጉራ አውልቃ መሶብ ወርቁን ከፍታ አስቀመጠችው። ወንድነቴ ተፈተነ እግሮቼ መቆም ተሳናቸው በሩን ከፍታ ስትወጣ ከቆምኩበት መንቀሳቀስ አቃተኝ•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ሚስቴ_ማነች?


#ክፍል_ሶስት


#በጥላሁን

የራስቅሏን ከነፀጉራ አውልቃ መሶብ ወርቁን ከፍታ አስቀመጠችው። ወንድነቴ ፈተነኝ እግሮቼ መቆም ተሳናቸው በሩን ከፍታ ስትወጣ ከቆምኩበት መንቀሳቀስ አቃተኝ•••

እዛው የተደገፍኩትን ግድግዳ ተደግፌ ቁልቁል ተንሸራተትኩ። ቁጭ አልኩ። ማን ነች? ምንድን ነች? ምን ላድርግ? ሳትመለስ ውልቅ ብዬ ልጥፋ? ያን ሁሉ አይቼ የማላውቀውን ልቤ ላይ የተቆለለውን የፍቅር ክምር ባንድ ግዜ መናድ ባንድ ግዜ መጥላት እችል ይሆን? ኧረ ፈራሁ! ጫካ ውስጥ ወይ ለመግደል ወይ ለመሞት ወስኜ ካባቴ ጠላቶች ጋር ልፋለም ስወጣ ከነሱ ጋር ፊት ለፊት ስጋፈጥ ቅንጣት ታክል ፍርሀት ስላልተሰማኝ ጀግና ነኝ ብዬ አስብ ነበር።ታድያ አሁን ያ ሁሉ ወኔዬ ወዴት ሄደ። ፍቅር ፈሪ ያደርገል እንዴ? ፍቅር ለካ ከጥይት በላይ ያስፈራል! ፍቅር ለካ ከሞትም በላይ ያስፈራል! ሞት ቢያስፈራኝማ ያኔ በፈራሁ ።አሁን የፈራሁት ሞትን አይደለም ማለት ነው? የፈራሁት በሆነው ምክንያት ያፈቀርኳትን ላጣት ግድ ሊሂንብኝ መሆኑ ነው።
ያስፈራኝ ካሁን ቡሀላ ያን ደስ የሚል የፍቅር ስሜት ቀስ በቀስ ከልቤ ተኖ ሊጠፋ መሆኑ ነው ።

ጨነቀኝ። በሂወቴ እንደዝች ቅፅበት ያስጨነቀኝ ነገር ኖሮ አያውቅም።
እሺ አሁን ምን ላድርግ? ! እዛ መሶብ ወርቅ ውስጥ ያስቀመጠችውን ነገር ላየው ፈለኩ ። ተነስቼ ወደ መሶብ ወርቁ ተጠጋሁ እንዴት ልክፈተው እጄ አልታዘዝ አለኝ። ወንድ ልጁ መሬት የጣለው ክንዴ መሶብ ወርቁን ለመክፈት ጉልበት አጣ። እራሴን አረጋግቼ እሷን ለመጥላትም ማድረግ ያለብኝንም ለመወሰን ግዜ እንደሚያስፈልገኝ አሰብኩ ።
ለብዙ ደቂቃ ግራ ተጋብቼ በቆምኩበት ከውጪ የሆነ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ። በፍጥነት ወደ ምኝታዬ ተመለሼ የሚሆነውን ስጠባበቅ መልሶ ፀጥ ረጭ አለ ።
ከቆይታ ቡሀላ በሩ ሲከፈት ሰማሁ። በኮቴዋ ድምፅ ወደ መሶብ ወርቁ እንደሄደች ተረዳሁ። ወድያው ስትታጠብ ተሰማኝ ። ፍቴን ወደ ግድግዳው አዙሬ ወጪ ገቢ ትንፋሼን የተኛሁ እንዲመስል አደረኩት።
መጥታ አንሶላና ብርድ ልብሱን ገልጣ አጠገቤ ስትተኛ ያቺ የማፈቅራት ቆንጆ ሴት ሳትሆን የሆነ አውሬ አብሮኝ የተኛ መሰለኝ ። ቀፈፈኝ። ገላዩ ከገላዋ እንዳይነካካ ወደ ግድግዳው ተለጠፍኩ። ለደቂቃዎች ቁና ቁና እየተነፈሰች ቆየችና
"ለምንድን ነው ፊትህን አዙረህ ምተኛው ብላ ጎትታ በመገልበጥ በጀርባይ አንጋለለችኝ ።
ብድግ ብላ እላዬ ላይ ጉብ አለች ። ሆዴ ላይ ቁጭ አለች። አይኔን ለግለጥ ድፍረት አጣሁ ። ጎንበስ ብላ ከንፈሬን ጎረሰችው ትንፋሽ አጠረኝ። ከንፈሬን ደምደም እለኝ ከሄዴ ውስጥ አንዳች ነገር ሲገላበጥ ተሰማኝ ። ጥውልውል አደረገኝ። እንደፈለገች ስታደርገኝ እስክትጨርስ አይኔን ጨፍኜ መዝለቁ ከባድ የሚሆንበት ግዜ ላይ ደረስኩኝ።አይኔን ገለጥኩ። እላዬ ላይ የምትጨፍረውን ሴት ሽቅብ ተመለከትኳት ። እራሷ ነች ። ፀጉሯ ፍቷን ሸፍኗት ቁልቁል ይዘናፈላል አቤት ውበት! አቤት ጭንቀት! ወርዳ ተዘረረች ። በተኛችበት ጥያት ልጠፋ አሰብኩ። አሰብኩ እንጂ አላደረኩትም ነጋ ተነስቼ ቁርስ ሳልበላ ወደ ዋሻዬ ወደ ጫካ ሄድኩ ከራሴ ጋር ስማከር ከራሴ ጋር ስከራከር ከራሴ ጋር ስጣላ ቀኑ ተጋመሰ።

ወደ ቤት ተመለስኩ በጥዋት ተነስቼ መጥፋቴ አስቆጣት። ዝምታዬ አስጨነቃት " ምን ሆነሀል? እያለች በተደጋጋሚ ብትጠይቀይኝ መልሴ ምንም ብቻ ነበር። ሁለት የምጥ ቀናት አለፍ
ባፈቀርኳት የመጀመሪያው የፍቅር ሂይወቴ ላይ የተጫወተችውን ፍቅሬን በንጭጩ አምክና ልቤን የሰበረችውን ይቺን ሴት ማንነቷን አጋልጬ በኖረችበት መንደር ላሸማቅቃት ወስኜ ነበር ከጫካ የተመለስኩት። ያን ካደረኩ ቡሀላ ስፍራውን ለቅቄ እግሬ ወደወሰደኝ ልሰደድ ዝግጅቴን አጠናቀኩ።
እንደተለመደው በመጀመሪያው ቀን ያልተሰጠኝ ጠላ በሁለተኛው ቀን ማታ ልተኛ ስል ጠብቃ ሰጠችኝ። ሳታየኝ ደፋቼው ተጠቅልዬ ተኛሁ። እኩለ ለሊት እንዳለፈ ልክ እንደከትናንት ወድያው ጅቦቹ የጥሪ ድምፅ አሰሙ ቤቷን ከበው በጩኸት አነቃነቋት። ብድግ አለች አይኔን ገለጥኩ ። ተነስታ ወረደች ። ወደ ሚቀጥለው ክፍል ስትሄድ ተነሳሁና ተደብቄ ማየት ጀመርኩ። ቅጠሏን በልታ እየለፈለፈች የራስ ቅሏን ከቅንድቧ በላይ እንደ ጀሪካን ክዳን ከፍታ ፀጉሯን ጠቅለል አደረገችና መሶብ ወርቋ ውስጥ አስቀምጣ ወጣች ።

ውስጤ ፍርሀት የሚባል ነገር ሳይሰማኝ ፈጠን ብዬ ፋኖሱን አጠፋሀትና የቤቷን መስኮት በትንሹ ከፍቼ ወደ ውጪ ተመለከትኩ ከ ስድስት በላይ የሚሆኑ ነጭና ጥቁር መልክ ያላቸው ጅቦች ግቢው ውስጥ ተመለከትኩ ። እንደወጣች አንደኛው ጅብ ጀርባ ላይ ቂብ አለች ።

እየጋለበችው ቤቱን ሶስት ግዜ ከዞረች ቡሀላ ከወገቡ ላይ ስትወርድ ባለ ሁለት እግሯ ሴት ባለ አራት እግር ጅብ ሆነች። አይኔን ማመን አቃተኝ ጠፍቶ የነበረው ፍርሀቴ መልሶ ተቆጣጠረኝ።

እሷ ፊት ፊት ሌሎቹ ከጀርባ እየተከተሏት የስሪያ ድምፅ እያሰሙ ከግቢው ወጥተው ተፈተለኩ። እቤት ውስጥ ጥቁር ፌስታል ፈልጌ እንዳገኘሁ ቀጥታ ወደ መሶብ ወርቁ ሄጄ አይኔን ጨፍኜ ውስጥ ያስቀመጠችውን እንደኮፍያ የሚመስል የራስ ቅል ከነ ፀጉሩ አውጥቼ ፌስታሉ ውስጥ ከተትኩት ።
በሩን ከውጪ ስለዘጋችው ይዤው በመስኮት ወጣሁ ። ግቢ ውስጥ ወዳለው ማድ ቤት ገብቼ በፌስታል የያዝኩትን እዛው ማድ ቤት ውስጥ ጥግ ላይ ካለ አንድ ማዳበሪያ ውስጥ ደብቄ ቀድሜ ማድ ቤት ያስቀመጥኩትን መሳሪያዬን ይዤ ቁጭ አልኩ። ፍቅሯን ከነሰንኮፉ ከውስጤ ነቅዬ ለመጣል መጨረሻዋን ለማየት ቁጭ ብልም የተፈጠረው ያልጠበኩት ነበርና ክፉኛ አስደነገጠኝ ።

እንደመጣች ። ገብቷ ፀጉሯን እና እኔን ከነበርንበት ስታጣን በሯን ዘግታ እሪታዋን አቀለጠችው "እርርርይ ጉድ ሆኛለሁ እርርርይ ያዙልኝ እንዳያመልጥ እርርርይ !" በዛ በውድቅት ለሊት መንደሯን በጩኸት አናወጠቻት።

የመንደሩ ሰው ዱላ ያለው ድላውን መሳሪያ ያለው መሳሪያውን እየያዘ ግቢውን ወረረው ተጠግተው "ምን ሆነሻል ? ምን ተፈጠረ?" እያሉ በሩን ሊከፍቱ ሲሞክሩ እንደዛ ሆና እንዳይመለከቷት "በሬን እንዳትትነኩ ! እንዳትገነጥሉ ! ይልቅ ሂዱና ሰውየውን ካለበት ይዛችሁ አምጥሉኝ " ትላለች ዘመዷ ነው መሰለኝ ሁኔታው ገብቶት ይሁን አይሁን ባላውቅም በሯ ላይ ቆሞ በሩ እንዳይከፈት መከላከል ጀመረ ።
የተወሰኑ ሰዎች እኔን መፈለግ ጀመሩ ። አማራጭ ስላልነበረኝ መሳሪያዬን አቀባብዬ አንድ ሰው እንዳይጠጋኝ እያልኩ ከተደበቅሁበት ማድ ቤት ወጣሁ።

ድርጊቴ የማልወጣው ወጥመድ ውስጥ እንደከተትኝ የተረዳሁት እርርርይ ስትል ሰምቶ የተሰበበሰበው የመንደሩ ነዋሪ በሷ ማንነት ከመደነቅ ይልቅ ለኔ ህይወት ማዘናቸውን ሲገልፁልኝ ነው ። ግራ ገባኝ ፍርሀት መላ እኔነቴን እየናጠው ምንም አታረገኝም እኔ ለሷ አንሼ ነው ጭራሽ ለኔ የምታዝኑት እያልኩ ስጮህ
አንድ ፊቱን ስመለከተው ያዘነልኝ የሚመስል ሰው ጠጋ አለኝና •••

" እስቲ ና ወዳጄ ምን አይነት የማትወጣው ጉዱ ውስጥ እራስህን እንዳስገባህ የገባህ አልመሰለኝም ይልቅ ድምፅህን አጥፋና ፀጉሯን የት እንደደበከው ተናግረህ የምታመልጥበትን መንገድ ፈልግ።

ባንተ ቤት ስለነሱ መንደሩ የማያውቅ መስሎህ ጉዳቸውን አጋልጠህ በድንጋይ ተወግሯ የምትሞት መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል ወዳጄ እዚህ መንደር ውስጥ ዘር ማንዘሮቿ እንዳለ እኮ እንደዛ ናቸው ሰፈሩን ጥለህ ካልጠፋህ ከልብስህ በስተቀር ለቀብር እንኳን የሚተርፍ ነገር እንዳይኖርህ በጫጭቀው ደብዛህን ያጠፍቷል!

እየውልህ ቀስ ብለህ ወደዛ ተመልከት እነዛ እዛጋ አይናቸው ደም እንደለበሰ የቆሙት ሶ
👍2
#ሚስቴ_ማነች?


#ክፍል_አራት(የመጨረሻ ክፍል)


#በጥላሁን

ዛፍ ላይ ወጥቼ ለመተኛት ጫካ እስካገኝ ስጓዝ ለሊቱ ተጋመሰ ጫካው ሳይገኝ አጉል ቦታ ላይ አውላላ ሜዳ ላይ ከርቀት ድምፅ ሰምቼ ዘወር ስል ጥቁርና ነጭ መልክ ያላቸው አይናቸው የሚያበራ ከአምስት በላይ የሚሆኑ ጅቦች በከባድ ፍጥነት እየጮሁ ወደኔ አቅጣጫ ሲመጡ ተመለከትኩ መሮጥ ብፈልግም እግሬ አልላወስ አለኝ•••

በዛች በመጨረሻዋ የጭንቀትና የሞት ሽረት ሰአት እራሴን ማረጋግትና የቻልኩትን በሙሉ ማድረግ እንዳለብኝ ለማሰብ ግዜ አላጠፋሁም።
እየቀረቡ ሲመጡ እኔን ፍለጋ እንደመጡ ከሁኔታቸው እርግጠኛ ሆንኩ። ወደ ላይ ቀና ብዬ ፈጣሪዬን ለመለመን ብፈልግም በሰው ነፍስ : በሰው ደም የጎደፈውን ማንነቴን አስቤ ፀሎት እና ልመናዬ የመጀመሪያውን ሰማይ የማይሻገር መስሎ ተሰማኝ ቢሆንም ጨንቆኛልና ፈጣሪዬ እንዲረዳኝ ለመንኩት።

ሮጬ እንደማላመልጥ ስለገባኝ ለመሮጥ አልሞከርኩም። ከጀርባዬ ላይ ያጋደምኩትን መሳሪያ አውርጄ በማቀባበል በተጠንቀቅ ቆምኩ። ብዙ አመት ጫካ ኖሪያለሁ ጅቦች በባህሪያቸው መሬት ሳይጥሉ እንደማይበሉኝ አውቃለሁ። ላለመውደቅ የቻልኩትን አደርጋለሁ በዚህ መሀል የመሳሪያውን ድምፅ ሰምቶ የሚደርስልኝ አላጣም።

ከኔ በቅርብ ርቀት ላይ እንደደረሱ ቆሙ አንደኛው ወጣ አላና ከሁሉም ፊት ቆመ ይቺ የኔዋ ትሆን እንዴ አልኩ። ከፊት የቆመው ጅብ የሆነ ለየት ያለ ድምፅ ሲያወጣ ባንድ ላይ የነበሩት ስድስት ጅቦች ብትንትን ብለው ከበቡኝ።
ሁለቱ ከጀርባዬ ሁለቱ ከፊቴ አንዱ በስተግራዬ አንዱ ደግሞ በስተቀኜ ሆነው ከኔ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ቆሙ።
ይህን ተንኮላቸውን ስመለከት "የሰው ጅብ እንደሰው ያስብ ይሆን እንዴ አልኩ ደንግጬ።

ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ ግራና ቀኝ ያሉት ከቆሙበት ሳይንቀሳቀሱ ከፊቴ እና ከጀርባዬ ያሉት በተመሳይ ግዜና ፍጥነት ወደኔ ሲወረወሩ እንኳን አልሞ ለመተኮስ ለማሰብ እንኳን ግዜ አላገኘሁም።
በንፋስ ፍጥነት ታከውኝ ሲተላለፉ ተንገዳግጄ ቆምኩ። አስደንግጠው ሊጥሉኝ ማሰባቸው ገባኝ። ወድያው በነዚህኛቹ ክው ያለውን ቀልቤን ሳላረጋጋ በስተግራና በስተቀኝ ያሉት በተራቸው ወደኔ ተምዘገዘጉ። በደመነፍስ ዝም ብዬ በስተቀኝ በኩል ወደ መጣው ፊቴን አዙሬ መተኮስ ጀመርኩ ሁለቴ እንደተኮስኩ በስተግራ የነበረው ደርሶ ገፍትሮኝ አለፈ አይወድቁ አወዳደቅ ወደኩ ተንደባለልኩ መሳሪያዬም ከጄ ወጣ ከመቅስፈት በወደኩበት ከበቡኝ ። ሁለቱ አልተጠጉኝም።

እሷ የትኛዋ እንደሆነች ባላውቅም አራቱ ዙርያዬን ከበው ቁልቁል ሲመለከቱኝ ነብስ ያዘኝ።ተስፋ ቆረጥኩ።
መግደል ምድራዊ ታሪኬን መደምደም በምትችልባት ቅስፅበት በዛች ውድቅት ለሊት እስትንፋሴን መቋጨት ስትችል እስከምሞት በስቃይ እንድኖር ስለፈለገች ነው መሰለኝ ሁለቱ ግራና ቀኝ እግሬን እያሰቃዩ ዘንጥለው ይዘው ሄዱ ።
አንዱ ግራ እጄን ገንጥሎ እንደሄደ። አንደኛው ግን ብዙም አጥብቆ ያልነከሰውን ቀኝ እጄ ተወልኝ።
እራሴን ከመሳቴ ከሰከንዶች በፊት ሁሉም ጅቦች ወደ መጡበት ሲመለሱ ቀኝ እጄን የተወልኝ ጅብ ተለይቶ በመቅረት ፊት ለፊቴ ቆሞ ሲመለከተኝ ትዝ ይለኛል ምናልባት እሷ ትሆናለች።
ከዛ ቡሀላ ከተማ ወጥተው መንገድ የመሸባቸ ገበሬዎች አግኝተውኝ የሚፈሰውን ደሜን አስረው እቤታቸው እንዳሳደሩኝና በአከባቢው ከነበረ ከአንድ የሀብታም ገበሬ የህል መጋዘን ውስጥ እህል ሊጭን ለመጣ የአይሱዙ ሹፌር ሁኔታውን ነግረው ወደዚህ ይዞኝ እንዲመጣ እንዳደረጉና ሆስፒታል አድርሶኝ እንደሄደ ወደ ራሴ ስመለስ ያገኘኋቸው ዶክተሮች ነገሩኝ ።

ከዛን ግዜ ጀምሮ ለነብሱ ባደረ አንድ ደግ ሰው በተሰጠችኝ በዚች ነገር እየተንቀሳቀስኩ እድሜዬን በልመና አሳለፍኩ።

ለምኜ ሳንቲም የምቀበልባትን
ቆርሼ የምጎርስባትን መቀመጫዬን የምገፋባትን እቺን እጄን ባትተውልኝ እንዴት እሆን ነበር እላለሁ አንዳንዴ።
ዛሬም እዛው የተለመደው ቦታዬ ላይ ስለምን አገኛችሁኝ። ከልመና ያውጣችሁ ልጆቼ ።

ከኔ ታሪክ ከተማራችሁ•••
መርጣችሁ ስሙ ልጆቼ !። መርጣችሁ እሺ በሉ!።
አሉ ፍለፍታቸው የተቀመጥነው እኔ እና እህቴ ፍታችን በእንባ ታጥቧል
ይህን ታሪክ ያጫወቱን ነገ በምንዘክረው የአባታችን ሰባተኛ ሙት አመት ወይም ተስካር ላይ እናቴ የኔቢጤዋችን ብቻ ለማብላት በመወሰኗ ከዛሬ ከዋዜማው ጀምረን እኔ እና እህቴ አዲስ አበባ ውስጥ በየቦታው የወደቁ የኔቢጤዋችን ወደ ቤት ይዘን እንድንመጣ ስላዘዘችን ። አቅማችን የፈቀደውን ያህል የኔቢጤዋች ወደ ሰፊው የመኖሩያችን ግቢ ስናመጣ መሀል ሚክሲኮ አከባቢ ዊልቸር ላይ ተቀምጠው ሲለምኑ ያገኘናቸው ሁለት እግርና አንድ እጅ የለላቸው እድሚያቸው ወደ ሰማንያዎቹ የሚጠጋ ጋሽ ፍልፍሉ ናቸው ።

ፈጣሪ እሄን ታሪክ ለኛ መማሪያ ይሆን ዘንድ እስኪነግሩን ያቆያቸው ይመስል እኔና ታናሽ እህቴ በአባ ፍልፍሉ ታሪክ ልባችንን እንዳዘነ እምባችንን ከፊታችን ላይ ጠራርገን ከጠላውም ከምግቡም ግቢ ውስጥ ላሉት የኔ ብጤዋች አባ ፍልፈሉን ጨምር ስናበላ ስናጠጣ አምሽተን ወደ ቤት ገባን ይህ በሆነ ከሰአታት ቡሀላ ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ ጠላ እየጠጡ በመሀል ትን አላቸው አባባ ፍልፍሉን ።

ትንታቸው እየባሰ ሲርርርር ሲርር ሲሉ አጠገባቸው የነበረ ሌላ የኔብጤ "ኧረ የሰው ያለህ " ጮኸ እኔና እህቴን ጨምሮ እቤት ውስጥ የነበርነው ተሯሩጠን አጠገባቸው ስንደርስ አባባ ፍልፈሉ እንዲህ አሉ •••

" ጠላው አይደለም ትን ያለኝ ልጆቼ እሷ ነች ያነቀችኝ ! አልተርፍም ልጆቼ! አልተርፍም ! ያልኳችሁን አትርሱ
ከኔ ታሪክ ከተማራችሁ•••
መርጣችሁ ስሙ ልጆቼ! መርጣችሁ እሺ በሉ!!።
አባቴን ከምሰማ እናቴን ሰምቻት ቢሆን ይሻለኝ ነበር!"
የአባ ፍልፈሉ የመጨረሻ እስትንፋሳቸው ንግግር።

💫ተፈፀመ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4