አትሮኖስ
266K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
424 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ካራማራ ኢትዮጵያዊው የድል ቀን

ይህ ነው ምኞቴ እኔ በሕይወቴ
ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ...

የካቲት 26 1970 ዓ.ም 🇪🇹
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ቤቱ ቅልጥ ያለ ድግስ ላይ ነው፡፡ግቢ ውስጥ ግዙፍና ዘመናዊ ድንኳን ተደኩኖ በዲኮር አሸብርቋል፡፡በዝግጅቱ የሰሎሜ ፤ የእቴቴ የአላዛር እና የአለማየሁ አንድም ወዳጅና የስራ ባለደረቦች አልቀረም…ከ500 በላይ ሰው ነው የተጠራው፡፡እርግጥ ይሄ ድግስ እንዲደገስ ቀጠሮ የተያዘለት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን ከሰማች ከሳምንት በኃላ ነበር፡፡ግን ባልተጠበቀ ፕሮግራም ዜናው ከተሳማ ከሦስት ቀን በኃላ አለማየው ለአጭር ጊዜ ስለልጠና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪት እንዲሄድ በመስሪያ ቤቱ ስለታዘዘ ድግሱ በሁለት ወር እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

ይሄ ድግስ በዋናነት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን በማወቋ እና ዘመናት ለማወቅ ስታልመው የነበረው የአባቷን ማንነት በማወቋ የተፈጠረባትን ፈንጠዝያ ለማክበር ነበር..ሌላው ለህይወቷ በጣም አስጊ የሆነውን በሽታ ታክማ መዳን በመቻሏም ለተንከባከቧት ሰዎች ሆነ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ለሌላው ሶስተኛ ነገር ደግሞ ትዳር በያዘችባቸው ሶስት አመቷ ውስጥ ስትሰቃይበት የነበረችው ከአላዛር ላይ ተከስቶ የነበረው ስንፈተ ወሲብ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ  ልክ እንደአዲስ ሙሽራ ቀንና ለሊት ሳይለዩ በፊት ያበከኑትን ጊዜ ማካካስ በሚመስል መልኩ እልካቸውን እየተወጡበት ስለሆነ በዛ ጉዳይ የተፈጠረባቸውን ደስታ በይፋ ለማክበር ነው፡፡ያም መሆኑ ለሁለቱም ከፍተኛ ደስታና አዲስ የህይወት እርካታ አጎናፅፏቸዋል፡፡ከሁለቱም ልብ እየተበተነ ያለ ደስታ በዙሪያቸው ያለውን ሰው ላይ ሁሉ የሚጋባ አይነት ሆኗል፡፡ይሄም ድግሱ ደማቅና ሰፊ እንዲሆን አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ድግሱ ለሁለት ወር በመራዘሙ ምክንያት ሌላም ሊከበር የሚገባው ተደራራቢ ምክንያትና በረከት ተፈጥሮል፡፡

ድግሱ ላይ የታደሙት 500  ያህል የቅርብ ሰዎች ምሳ ከበሉ በኃላ ሰሎሜ የተፍለቀለቀ ፊቷን በፈገግታ አጅባ ወደመድረኩ ወጣች፡፡

ማይኩን ድግሱን በሙዚቃ እያደመቀ ካለው ዲጄ  ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹ወዳጆቼ ዘመዶቼ ይሄ ድግስን አስመልክቶ ጥቂት ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡››ስትል ሁሉም የምትለውን ነገር ለመስማት የእርስ በርስ ወሬያቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ወደእሷ አዞሩ….ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ..እናቴ እቴቴ ..ባለቤቴ አላዛር….ወንድሜ አለማየሁ….ጓደኛዬ ሁሴን ..ሁላችሁም ወደዚህ መድረክ ኑና ከጎኔ ያለው የፊት ፊት መቀመጫ ላይ እንድትቀመጡ እፈልጋለው፡፡የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡

ሁሉም እየተያያዙ መጡና ፊታቸውን ወደእድምተኞች አዙረው መድረክ ላይ በተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተቀመጡ፡፡

ሰሎሜ ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንግዲህ እነዚህ አራት ሰዎች ወደእዚህ ምድር ከመጣሁበት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ከጎኔ ነበሩ…ሰሎሜ ሰሎሜ እንድትሆን ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡እኔ ማለት የእነሱ ውጤት ነኝ፡፡እናቴ እቴቴ … ከልጅነቴ ጀምሮ ያለአባት  በጀግንነት አሳድጋኛለች፡፡ላደረግሺልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡በጣም ነው የምወድሽ፡፡
በህይወቴ ሁለት ጊዜ በከባድ በሽታ ሆስፒታል ገብቻለሁ፡፡ልጅ ሆኜ በታመምኩ ጊዜ ለህክምናው 70 ሺ ብር ተጠይቆ ነበር፡፡በወቅቱ እናቴ የነበራት ከ7ሺ ብር የማይበልጥ ብር ነበር፡፡ቀሪውን ብር በትምህርት ቤትና በየመንደሩ እየዞሩ ለምነው ያሳከሙኝ..እንዚህ ከፊት ለፊት ተቀምጠው የምታዬቸው የልጅነት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ከሶስት ወር በፊትም ተመሳሳይ አይነት ፈታኝ ህመም አሞኝ ነበር፡፡ ከአካሉ አካል ቆርሶ በመስጠት ደግመኛ ዛሬን እንደዚህ ከፊት ለፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ወንድሜ አለማየሁ ነው፡፡ይሄም ዝግጅት እንዲጋጅ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ‹‹ወንድሜም ስለሆንክ…ከህመሜም እንድፈወስ ስላደረከኝ››አመሰግናለው ለማለት ነው፡፡

ሌላው የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ  ሁሴን በሁለቱም የህይወቴ ጨለማ ቀናቶች ከጎኔ ስለነበርክ አንተንም በጣም አመስገናለሁ፡፡በጣም እንደምትወደኝ አውቃለው….እኔም በጣም እወድሀለው….እናም ከሶስት ቀን በኃላ ተመልሰህ ወደውጭ እንደምትሄድ ስለማውቅ ዳግመኛ ሙሉ ጓዝህን ጠቅልለህ ወደሀገር እስክትመለስ እና አብረሀን መኖር አስክትጀምር ድረስ  ይሄ እንደሽኝት ፕሮግራም እንዲታይልኝ እፈልጋለው፡፡
ከፍተኛ የሞቀ ጭብጨባ ተከተላት…ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ሌላው የእድሜ ልክ ጓደኛዬ እና አንድም አመት ቢሆን ከስሬ ተለይቶኝ የማያውቀው መከራዬንም ሆነ ደስታዬን አብሮኝ ያሳለፈው የምወደው ባለቤቴ  አላዛር  ..ስለተንከባከብከኝ. .ለአስቸጋሪው ፀባዬ ጠቅላላ ትዕግስት አድርገህ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ እስከአሁን አብሬህ እንድኖር ሚስትህ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግናለው..ለዚህም ድንቅ አበርክቶትህ ከእኔ ከሚስትህ በዚህ ሁሉ ወዳጅ ዘመድ ፊት አንድ ስጦታ ላበረክትልህ እፈልጋለው፡፡››አለችና ንግግሯን ገታ አደረገች…አላዛር ግራ ተጋባ..ሌሎችም የሽልማቱን ምንነት ለማወቅ ጉጉት አሳዩ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ ወደእኔ ና››ስትል ጠየቀችው፡፡

ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ….በእጆ የያዘችውን ፖስታ አቀበለችው፡፡ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቷት ዝም ብሎ እያገላበጠ ያየው ጀመር፡፡

ሁሴን እና አለማየሁ‹‹ይከፈት ይከፈት››አሉ..ሌሎችም እድምተኞች ተከተሏቸው፡፡አላዛር ምርጫ ስላሌለው በቀስታ ፖስታውን ሸረከተው፡፡አንድ ነጠላ ወረቀት ነው ውስጡ ያለው፡፡ አወጣውና  ተመለከተው ፡፡ ምንም አልገባውም‹‹ምንድነው ፍቅር?››ሲል እሷኑ መልሶ ጠየቃት፡፡

‹‹አንብበዋ››አለችው፡፡

‹‹እንድምንም ትክረቱን ሰብስቦ ማንበብ ጀመረ…አይኑ ፈጠጠ…‹‹ምንድነው ፍቅር..? የማየው ነገር እውነት ነው…?››ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡ተንደረደረና ተጠጋት፡፡ዝቅ ብሎ ጉልበቷ አካባቢ በእጆቹ ያዛትና ወደላይ አንስቶ አሽከረከራት፡፡ሰው ሁሉ ሽልማቱ ምን ቢሆን ነው በሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ መወዛገብን ቀጠለ፡፡እንደምንም እንዲያወርዳት ካደረገች በኃላ ጠረጴዛ ላይ ያለውን  ማይክሮፎኑን ወደአፈዋ አስጠጋችና ‹አዎ እውነት ነው..ውድ ባለቤቴ ሽልማትህ ልጅ ነው..እኔ ሚስትህ የሁለት ወር እርጉዝ ነኝ፡፡››በማለት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ታዳሚው የምስራቹን አበሰረች፡፡መጀመሪያ እልልታዋን ያቀለጠችው እናቷ እቴቴ ነች….ከዛ ሙሉ ዱንኳኑ በእልልታና በጭብጨባ ተደበላለቀ፡፡.አለማየሁም ሆነ ሁሴን ከመጠን በላይ ተደሰቱና ተንደርድረው ባልና ሙስቶቹ ላይ ተጠመጠሙባቸው፡፡ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ልዩ አይነት ዝግጅት ሆኖ አለፈ…፡፡

እንግዶቹ ከተሸኙ በኋላ ቤተሰቡ ድግሱንና ፈንጠዝያውን ቀጠሉበት፡፡ሁሴን ወደመጣበት እንግሊዝ ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ ከዛ ቤት የሄደ ሰው አልነበረም፡፡.እቴቴ ለአመታት ቃል በገባችው መሰረት ብቸኛ ልጆን በእርግዝና ወቅቷ ለመንከባከብና ከወለደችም በኃላ የልጅ ልጆን ለማሳደግ ስትል የራሷን ቤት ዘግታ ሙሉ በሙሉ ባልና ሚስቱ ጋር ተጠቃላ ገባች፡፡አለማሁም ከእንግዳ ክፍሎቹ ውስጥ አንዱ ክፍል ተመርጧ የእሱ ቆሚ ክፍል ሆኖ እንዲደራጅ ተደረገና ቢያንስ በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን እየመጣ እነሱ ጋር ማደር ጀመረ፡፡እሱ እንቢ ብሎ እንጂ እነሱማ ቢያንስ የራስህን ሴት አግኝተህ ሚስት እስክታገባ ሙሉ በሙሉ የተከራየኸውን ቤት ልቀቅና  እዚሁ እኛ ጋር ተጠቃለህ ግባ ና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንኑር ብለውት ነበር፡፡እሱ ግን ሙሉ በሙሉ በሚለው ሊስማማ አልቻለም፡፡በአጠቃላይ እንደዛ የጭቅጭቅ መናኸሪያ ሆኖ ቀዝቅዞ የነበረው ቤት አሁን ደምቆና በቤተሰብ
ተሞልተ ሳቅና ደስታ የሚመረትበት..የተስፋና የብስራት መቅደስ ሆኗል…..በሁሉም ላይ ደግሞ ይሄ ደስታ ቀጣይ እንደሚሆን ልባዊ ምኞት አለ፡፡

💫ተፈፀመ💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem
#የሴትነት_ክብር

ከእውነታው ድግስ በሀቅ እንዲታደም
ከሴቶች ቀን በፊት ሴትን ማክበር ይቅደም።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
#የሴት_ልጅ

የሴት ልጅ ነው በሉኝ ስሜን ተውትና፣ ከፍ ከፍ አድርጉኝ ኩራቴ ናትና። ክብሬ ስለሆነ መጠራት በእናቴ፣ እሷ ስለሆነች ስጋ ደም አጥንቴ፣ ለኔ ልዕልና ነው የሷን ስም ማግኘቴ።

🔘ሀይደር🔘
#የሴት_ልጅ

የሴት ልጅ ይለኛል ያዋረደኝ መስሎት
ስድብ እና ሙገሳ መለየት ተስኖት
አው የሴት ልጅ ነኝ ያውም የጀግናዋ
ጉንበስ ቀና ብላ ለልጅዋ ኗሪዋ
ዘጠኝ ወር ሳልከፍል በሆድዋ ተኝቼ
በጀርባዋ አዝላኝ እሰክሄድ በእግሮቼ
ተደፍታ ስታነድ ምግቡን ለማብሰል
እንጀራ ስትጋግር ፊትዋ መስሎ ከሰል
ሳጠፋ ገስፃ እንዳልኩራ መክራ
በርታ እያለችኝ ሁሌም እንዳልፈራ
አይዞህ አልከፋም ሴት ያሳደገኝ ነኝ
ስድብ ከመሰለህ ደጋግመህ ስደበኝ
አልቀየምህም በስምዋ ስትጠራኝ
እውነቱን ልንገርህ አዎ የሴት ልጅ ነኝ

"መታሰቢያነቱ እናቱን ለሚወድ በሙሉ።"

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን🔘
#ንግድና_መሐላ

እጅን ለመሀላ

ከፍ አርጎ ዘርግቶ

በድለላ ቋንቋ

አግባብቶና ዋሽቶ

ለመሸጥ ሲታሰብ

የሁለቱን በሃያ፤

የአሥሩን በመቶ

በቀማኞች ጉሊት

በሌቦች ገበያ

ወላሂና እዝጌርን

ወጥ ሆኑ ማባያ ፡፡

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem
አሁን በቀደም'ለት..!

መጣች ተቀበልኳት አወጋች አመንኳት ብዙ ብዙ አለችኝ፣ የትም ከርማ መጥታ የሄደችበትን ምክንያት ነገረችኝ፣

ትክክል ነሽ አልኳት ባትሆንም ግድ የለኝ፣ ከመመለሷ እንጂ፣ ከመሄድ ምን አለኝ!?

🔘ሰሎሞን ሽፈራው🔘
"ቢደርስብህ ሀዘን ቢደርስብህ በደል ተሸሽገህ አልቅስ ወንድ ልጅ ነህ አይደል?

ሚሉህን አትስማ ተረቱን አፍርሰው
አልቅስ አልቅስ ካለህ፤
መሀል አደባባይ ዕንባህን አፍስሰው።

ግድ የለም ተንሰቅሰቅ፤
በልብህ እያነባህ ስቃይ አታስታምም ይህንን አስታውስ ፤

ውስጥህ ሲፈስ ነው የሚገድለው ደም

🔘እዮብ🔘
#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ጫማ ሽታ

ልክ እንደ በሽታ

ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ

#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ረጅም መንገድ

ለሀብታም እንደ መስገድ

ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ

#እኔ_ጠላሻለሁ

ገንዘብ እንደ ማጣት

ዳገት እንደ መውጣት

ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት

#እኔ_ጠላሻለሁ

ልክ እንደ መልከስከስ

እምነት እንደ ማርከስ

ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ

እኔ ጠላሻለሁ . . . (ወዘተ )

አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል ጠላሁሽ ያበዛሁ #ወድጄሽ ነው መሰል፡፡

🔘እዮብ🔘
#አንቺ. . .

እንደዘመኑ ሴት፤
መኪና ላለው ወንድ ጭንሽን ማትከፍቺ ኑሮን ለማሸንፍ፣
የምትታትሪ የምትሟሟቺ
አንቺ. . !

በአቋራጭ ሄደሽ ቁማር ሳትቆምሪ በጉልበት በላብሽ፤
የራስሽን ህይወት ምታስተዳድሪ ቤተክርስቲያን ብለሽ፤
ከቦርጫም ሰውዬ ጋ ክለብ የማታድሪ
አንቺ .. !

የሄዋን ምሳሌ የሴትነት ልኩ
መልካም ፀባይ ያለሽ የጨዋነት መልኩ

ዘመንሽ ይለምለም ...
በበረከትና በፀጋ ተከቦ
መልካሙ ፈጣሪ ፤
መልካሙን በሙሉ ጀባ ይበልሽ አቦ! ! !

🔘እዮብ🔘
አልወድክም በይኝ

   ልቤ ተጨነቀ....

መጥላትም ፍቅር ነው

  ቁርጡ ከታወቀ።😔
እንገናኝ ስልሽ ደስ ይለኛል'' ያልሽው፣
የት ይሻላል?' ስልሽ ቦታ ያልመረጠጥሽው፣

ፒያሳም ይርቀኛል ቦሌም አልተመቸኝ    ጎተራና ሳሪስ ቄራም ደስ አላለኝ፣

ሜክሲኮ ፍልውሃ ካዛንቺስ አልመጣም፣ አንቺን ለማዝናናት ከተማዋ አትበቃም።

ነፍሴ ተጨነቀች ቦታ አላውቅም ውዴ፣ አልጋዬ ስፊ ነው ይመችሻል እንዴ?
እ.........
#አታጭኝም

የረታኝ ቁመናሽ ወይ መልክሽ አይደለም ተፈጥሮሽ ስቦኝ ነው ከብልጭልጩ ዓለም
ልብሽ ነው የገዛኝ ገራገርነትሽ ተለይቶ ቢታየኝ...

ከአስመሳዮች መሀል እወነተኛነትሽ ውበትሽም ቢጠፋ እርጅና ተጭኖት
እኔ አንቺን ማፍቀሬ አይቆምም እስከሞት ይሄው ቃሌን እንኪ...

ደስታን ልፈጥርልሽ፣ ሰላም ስትፈልጊ ልሆንሽ ማረፊያ

አንቺ እሳት ስትሆኚ እኔ መሬት ልሆን
ንዴት ማራገፊያ
ቃሌ ነው እመኝኝ...

በሀዘን በህመምሽ ደንቀፍም ሲያደርግሽ አታጭኝም እኔን አጠገብሽ ሆኜ
ሁሌም እኔን ስልሽ።

🔘ቴድ ሀበሻ🔘
''ቱ በል ልምታልህ'' አለችው
ሲያለቅስ አቀፈችው።

''ቱ" አለ
በእጇ መታችለት በጥፊ መሬቱን
ማልቀሱ አበቃ አቆመ ምሬቱን!

አደገ
ትልቅ ሆነ

ህይወትን ቢቀየም
ለብቻው አዘነ በዕንባ ላይወጣለት


ዛሬ ሰው የለውም
ጊዜን ማን ይምታለት ?


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#የምትመስለው

የኔ ልዕልት ...

ጸዳል ክብሯ ከሴት መሐል አቻ የሌለው
በማለዳ ደምቃ የፈካች
ውብ ጸሐይ ነው የምትመስለው

ብዬሸ ነበር ያኔ ድሮ ልጅ እያለው

ግና ዛሬ አደግሁና
ሁሉን በጥልቅ ሳስተውለው
ይቅር በይኝ ማሪኝ ውዴ አጥፍቻለው

ለካ ጸሐይ ራሷ ናት
ቁር'ጥ አንቺን የምትመስለው !
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_10

ለመቀንጠስ እጁን ሲያሾል ነበር ያቆምኩት:: ንባቤም ቀጠልኩ። የኔቶ ቀባጣሪም መቀባጠሯን ቀጠለች፣ "ጊዜ በጊዜ እየተተካ በሄደ ቁጥር እኔም ንዴቴ ቀስ በቀስ እየበረደ መጣ። እርግጥ በደሱ ሊረሳ የሚችል አልነበረም። ማንኛውም የሰው ፍጡር የህይወቴ ጎዳና ይህ ይሆናል፣ ሀይወቴንም በዚህ መንገድ፣ እንዲህ አድርጊ! እመራዋለሁ ብሎ የወጠነው ሁሉ ተመሰቃቅሎ ከፊት ለፊቱ የሚያየውና ሊጓዝበት ያሰበው ለስለሳና ደልዳላ መንገድ በእሾህና በጋሬጣ ታጥሮ መውጪያውና መግቢያው ወደማይለይ አባጣና ጎርባጣ መንገድ በቅጽበት ሲለወጥበትና ተስፋ ለተስፋቢስነት ቦታ ሲለቅ ሲያይ መበሳጨት እንዴት ይበዛበታል:: የኔ ሁኔታ ከዚህ የተለየ አልነበረም:: ከአማረ ጋር ሆኜ በደስታና በፍቅር አሳልፈዋለሁ ያልኩት ህይወት የማይጨበጥ ህልም ሆኖ ሲቀር የምመካበትና አንድ አለኝ የምለው ሰው ሲከዳኝና በአንድ ጊዜ ተስፋዬ ተሟጦ የወደፊት ህይወቴ ምን ሊሆን እንደሚችል ልገምት በማልችልበት ሁኔታ ላይ ሆኜ እያለሁ ደስታ ይኖረኛል ብሎ መገመት የዋህነት ነው:: ይሁን እንጂ ዶ/ር አድማሱ በጭንቅት ቀን ከእግዜር የተላከ መልአክ ተመስሎ ባጠገቤ በመገኘቱ ብዙውን ነገር ቀስ በቀስ ባልረሳው እንኳን ለመርሳት እንድሞክር ረድቶኛል:: አብዛኛውን ከትምህርት ውጪ ያለውን ጊዜዬን የማሳልፈው ከእሱ ጋር ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜ በትምህርቴ እንድጠነክርና ሁሉንም ነገር እንደ ተራ ነገር እንድረሳው ይመክረኛል፡፡ እኔም አብዛኛውን ጊዜ የግቢውን ወሬ ሳልፈራና ለማንም ቁብ ሳልሰጥ እሱ ቤት እያመሸሁ ጥናቴን ተያያዝኩት፡፡ የሚቸግረኝን እየረዳኝ ከጎኔ ሳይለይ የሚያፅናናኝም እሱ ብቻ ነበር፡፡ ከእሱ ጋር ያለኝ ግንኙነት እየጠነከረ የመሄዱን ያህል የትምህርት ቤት ጎደኞቼ ደግሞ ይበልጥ በጥላቻ ይመለከቱኝ ጀመር። አብዛኛው ተማሪ ከዶ/ር አድማሱ ጋር የነበረኝን ግንኙነት አማረን በጥቅም _ ለውጬ የፈጠርኩት ግንኙነት አድርጎ የተሳሳተ ግንዛቤ ፈጥሮ ስለነበር ቢጠሉኝም በእነሱ አልፈረድኩም:: በተለይ ጓደኞቹ እኔን ጠይቀው በመረዳት ፈንታ እኔን አኩርፈው ወሬውን በመሰላቸው መንገድ ያናፍሱት ስለነበር ተማሪዎቹ የሰሙትን የተሳሳተ ወሬ ሰምተው ቢጠሉኝ አያስገርምም፡፡ ከሃዲዋ እኔ ላልሆን ከሀዲው አማረ መሆኑንና ከዶክተር አድማሱም ጋር ያለኝ ግንኝነት የወንድምና የእህትነት ዓይነት እንደሆነ ለጓደኞቼ ብናገርም የሚያምኑኝ አልነበሩም። ስለዚህም እኔ ይህንኑ ተንትኜ ለማስረዳት እቅሙም ሆነ ችሎታው ስላልነበረኝ እንደመፍትሄ የወሰድኩት ለማንም ሳልጨነቅ ይበልጥ ከተማሪዎች በመራቅ አብዛኛውን ጊዜዬን ከዶክተር አድማሱ ጋር ማሳለፍ ብቻ ነበር።

ጥር 30 ቀን 1978 ዓ.ም

ተሾመ ለእኔ ያለው የፍቅር ስሜት የእብደት እንጂ የጤንነት ነው ማለት ያዳግታል፡፡ አማረ ግቢ ውስጥ በነበረበት ወቅት ምን ያህል እንደምንዋደድና በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር መደባደቡን እያወቀ፣ ከዚህም አልፎ ተርፎ እኔ ለእሱ ፍቅር እንደሌለኝ ደግሜና ደጋግሜ ብነግረውም በፍጹም ሊተወኝ አልቻለም፡፡ እንዲያውም ቀስ በቀስ በሰላማዊ መንገድ እንደማያገኘኝ ስለተረዳ ማስፈራራትና መማታቱን ቀጠለ፡፡ ሌላ የማገባ ከሆነ እኔን፣ የማገባውን ሰውና የራሱን ህይወት ጭምር እንደሚያጠፋ መዛት የዘወትር ተግባሩ ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ይህንን ለአማረ መናገር ማለት ተጋደሉ ማለት ስለመሰለኝ ለመናገር አልፈለኩም ነበር። አማረ ግቢውን ከለቀቀ በኋላም ተሾመ ይህንኑ ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠሉ ለመክሰስ እንደወሰንኩ ለኤልሳ ነገርኳት፡፡ ኤልሳ ግን ከከሰስኩት ከዩንቨርስቲ _ ስለሚያባርሩት እሷ እንዲያርፍ እንደምትነግረውና ነገር ግን ምክሯን ሰምቶ ካላረፈ ለወላጆቹ ደውላ እንደምትነግር ቃል ስለገባችልኝ ክሱን ተውኩት፡፡ የነገርኳትን ነግሬዋለሁ ካለች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ መተናኮሉን ቢያቆምም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ዶ/ር አድማሱ ቤት አዘውትሬ መሄዴን በማወቁ ተመልሶ አገረሸበት፡፡ ኤልሳ ይህንኑ ጉዳይ ለወላጆቹ ነግሬአለሁ ትበል እንጂ እሱ ግን በፍፁም ሊታገስ አልቻለም፡፡ በተለይ ሁሌ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ማታ ማታ እየጠበቀ የሚያስፈራራኝና የሚመታኝ ባጋጣሚ ከኤልሳ ተለይቼ በምሄድበት ጊዜ ስለነበር ሆን ብላ ከእሱ ጋር እየተነጋገረች ምክንያት ፈጥራ ከእኔ የምትለይ እየመሰለኝ መጣ፡፡ በወንድምነት ይሁን ወይም በጾታዊ ፍቅር መሆኑ በግልጽ ባይገባኝም፤ ኤልሳ እንደምትወደው ግን አውቃለሁ፡፡ እሱ ግን ለእሷ አንዳችም ፍቅር የለውም.፡፡ እኔ እንዲያውም አንዳንዴ ብገላገል በማለት እስኪ እንደምትወጂው ልንገረው ካልኳት፤ ይህንን ከነገርኩት እንደምንጣላ ከመናገር ውጪ እሱን የእሷ ለማድረግ የምታደርገው ጥረት ግን የለም፡፡ ተሾመ ከእኔ ጋር የሚፈጠረውን አምባጓሮ እያየች ምንም የቅናት ስሜት ስለማላይባት ሆን ብላ እኔና እሱን ለማፋቀር የምታደርገው ምክንያት እንጂ ከእሱ ጋር ፍቅር የላትም ብዬ እንድጠረጥር አደረገኝ፡፡ በመጨረሻም ማስቸገሩ ሲበዛብኝ ሁኔታውን ለዶ/ር አድማሱ ነገርኩት፤ ልከሰው ስላሰብኩም ምን እንደሚመክረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱ ግን መፍትሄ እንድሚፈልግልኝ ቃል ገብቶ እንዳልከሰው ከለከለኝ፡፡ ዛሬ የመጀመሪያውን ሴሚስተር _ ፈተና ጨርስን ውጤት ተለጥፎ በነበረበት ምሽት ወደ ራት ስሄድ ተሾመን እንደተለመደው ከራት ስመለስ ብቻውን አገኘሁት፡፡ ገና እንደደረሰ በጥፊ ካጮለኝ በኋላ፤

"አንቺንም፣ ያን ዶክተርሽንም ካልደፋኂችሁ እኔ ተሾመ አይደለሁም፡ ብሎ ዝቶብኝ ሄደ። አጥፊው በላይ ፊቱ ላይ የነበረውን ንዴቱን ሳይ ክፉኛ ደነገጥኩ፣ ተናደድኩም፡፡ ወዲያው ዶ/ር አድማሱ ጋ ሄድኩና፤ "አንተ ነህ እንዲህ እምትጫወትብኝ፣ ልክሰስ ስልህ እኔ አስታግሰዋለሁ እያልክ ልታስገድለኝ ነው፡፡ ከአሁን ወዲያ የፈለከውን ብትል አላምንህም፣ ቢፈልጉ እንኳን ከዩንቨርስቲ ማባረር _ ቀርቶ እንጦሮጦስም ይክተቱት እንጂ እኔ እንደሆነ ነገ መክሰሴ አይቀርም" እያልኩ ጮህኩበት፡፡ እሱ ግን በተራጋጋ መንፈስ በጥፊ የቀላውን ፊቴን በእጁ እያሻሸ፤ “በቃ ተይ አትናደጂ፣ ከአሁን በኋላ መክሰስ ትችያለሽ፣ እኔ አያገባኝም፡፡ እኔ ይሰማኛል በማለት አንድ ሁለት ጊዜ መካክሬው ነበር፡፡ እሱ ግን ብመክረውም ተመልሶ እዛው ስለሆነ ከአሁን በኋላ አያገባኝም፤ ነገውኑ ክሰሺው" አለኝ፡፡ ጠዋት እሱን ለመክሰስ ወስኜ ከቤት ብወጣም፣ ኤልሳ ቁርስ እየበላን ሳለ ተሾመ በዶ/ር አድማሱ ሁለት ኮርሶች ኤፍ (F) ማግኘቱንና ከዩንቨርስቲ መባረሩን ነገረችኝ፡፡ ይህንን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ፡፡ እንደተለያየን በጥድፊያ ወደ ዶ/ር አድማሱ ቢሮ አመራሁ፡፡ እንደገባሁም በሩን ከኋላዬ ዘግቼ! "ዶ/ር፣ ለእኔ ብለህ ነው እንዴ ለተሾመ ኤፍ (F) ሰጥተህ ከትምህርት ቤት እንዲባረር ያደረከው" ብዬ አፈጠጥኩበት?' እሱ ግን ምንም እንደማያውቅ በሚመስል ሁኔታ፤ "ተሾመ ኤፍ አምጥቶ ተባረረ ነው የምትዪኝ? እኔ የሰማሁት አሁን ገና ከአንቺ አፍ ነው፡፡ ለመሆኑ በምን ትምህርት ነው ኤፍ ያመጣው?" ብሎ እኔኑ መልሶ ጠየቀኝ፡ "አንተ በምትሰጣቸው ሁለት ትምህርቶች ነው ወድቆ የተባረረው። ይህንን አታውቅም ማለት ነው?' አልኩት በንዴት፡፡ "ማወቅ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ልጁ ሰነፍ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ እሱ ትምህርቱን ትቶ አንቺን አፈቀርኩ እያለ ሲሟዘዝ ስለሚውል ቢወድቅ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እርግጥ በእኔ ትምህርት ኤፍ ያገኙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ እኔ ሁሌ ፈተና ሳርም እንዳላዳላ (Bias እንዳልሆን) በማለት ስም ስለማላይ ኤፍ ያገኘው እሱ ይሁን ሌላ ሰው የማውቀው
ነገር የለም፡፡ ያም ሆነ ይህ አንቺ ምን አስጨነቀሽ? እንዲያውም አንቺ ከስሰሺው ለእሱ መባረር ምክንያት ከመሆን ድነሻል" ብሎ በተረጋጋ መንፈስ አባብሎ ሸኘኝ።

ከተሾመ መባረር በኋላ የግቢው ሰው በእኔ ላይ ያለው ጥላቻ እየተባባሰ መጣ። እርግጥ ተሸመ ከእኔ ጋር ባለው ጠብ የተነሳ ሆን ተብሎ በዶ/ር አድማሱ እንደተባረረ ለአካዳሚክ ኮሚሽን ከሶ በተደረገው ምርመራ ይህንን የሚደግፍ ወይም የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ ክሱ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ ይሁን እንጂ እኔን ራሴን ጨምሮ አብዛኛው ተማሪ ዶ/ር አድማሱ ሆን ብሎ ያደረገው ነው በማለት በመጠርጠራቸው በዚህ የተነሳ ቢጠሉኝ አያስደንቅም፡፡ ያም ሆነ ይህ እያዘንኩም ቢሆን ተሾመ ግቢውን ለቆ በመሄዱ ሰላም አገኘሁ፡፡ ነገር ግን ኤልሳ በዚሁ የተነሳ ውስጥ ውስጡን ተቀይማኝ ስለነበር ጓደኝነታችን ቢቀጥልም እንደድሮው ግን ሊሆን አልቻለም፡፡ ሰኔ 4 ቀን 1978 ዓ.ም "እግዚአብሄር ሳይደግስ አይጣላም እንደሚባለው ሁሉ፣ በዚህ ግቢ ውስጥ የተለያየ ችግርና መከራ ቢፈራረቅብኝም በዶ/ር አድማሱ እርዳታ የመመረቂያ ፕሮጀክቴን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቲ ለማቅረብ ዝግጅቲን ጨረስኩ:: የምመረቀው በእርሻ ምህንድስና ሲሆን የመመረቂያ ፕሮጄክቴ ጥቃቅን የመስኖ ቴክኖሎጂ (Micro-Irrigation) በሚባለው ላይ ነበር። እነዚህ በቀላሉ በሰው ጉልበት ወይም በእንስሳት ኃይል ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ የህ ፓምፖች ሲሆኑ ወንዞችን፣ በጉድጓድ ወይም በኩሬዎች የተከማቸ ውሀን በመጠቀም ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የሚጠቅም የመስኖ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ እንደ ዛምቢያና ናይጄሪያ በመሳሰሉ አገሮች በስፋት የሚጠቀሙበት ሲሆን “አርፈሽ ተኚ” እያሉ ይጠሩታል:: ይህ ስያሜ የተሰጠው ወንዱ ቀን ቀን በዚህ ፓምፕ ውሀ ለማውጣት በእግሩ ወይም በእጁ ፓምፑን ሲያሽከረክር ውሎ ደክሞት ወደ ቤት ስለሚገባና ለወሲብ የሚሆን አቅም ስለሌለው ሚስቱ እንዳትረብሸው የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማሳየት የሚጠቀሙበት ብሂል ነው:: ለፕሮጄክት የተጠቀምኩበት ቴክኖሎጂ በአገራችን እምብዛም የተለመደ ስላልነበር ተግባር ላይ ቢውል ጠቀሚታው የጎላ ነው በሚል የመረጥኩት ሲሆን፤ በአነስተኛ ወጪ ከአካባቢ ቁሳቁስ ሊሰራ የሚችልና ማንኛውም ሰው በቀላሉ ተረድቶ ሊተገብረው የሚችል ተስማሚ ቴክኖሎጂ ነው:: ፕሮጄክቱን በዓለማያ አካባቢ ካሉ አርሶ አደሮች ጋር በጋራ ያከናወንነው ሲሆን ገበሬዎቹ ይህንን ፓምፕ በአካባቢያቸው ከሚገኝ ቁሳቁስ _ ሰርተው ውሀ ለማውጣትና ሰብላቸውን ለማጠጣት ተጠቅመውበታል፡፡ በዚህም ከፍተኛ ምርት ሊያገኙ ችለዋል፡፡ የመመረቂያዬ ቀን ተቃርቦ ፕሮጄክቴን የማቀርብበት ቀን ሲደርስ የተደባለቀ ስሜት ፈጠረብኝ፡፡ በአንድ በኩል ይኸን ለእኔ ገነትም ገሀነምም የነበረውን ዩንቨርስቲ ለቅቄ የምወጣበት ቀን በመድረሱ ሁሉንም ነገር በቶሎ

አጠናቆ መውጣት ደስታን ሲፈጥርብኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፍቅርን ከነፈጉኝ ተማሪዎች ፊት ቆሜ ፕሮጄክቴን ማቅረብ ፍርሀት ነዛብኝ: ዶ/ር አድማሱ ቀደም ሲል ፕሮጀክቴ አድናቆት ማግኘቱን፣ አብሬ ከምሰራው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የአምስት ሺ ብር ሽልማት ያስገኘልኝና በዩንቨርስቲውም ተደናቂነትን ያተረፈ መሆኑን ያውቅ ስለነበር፤ ያለፈውን ነገር ሁሉ ትቼ ዛሬ ፕሮጄክቴን በተዋጣለት መልኩ በማቅረብ ላይ እንዳተኩር ደጋግሞ መክሮኛል:: ለእኔም ከሐሳብ የመውጪያ ብቸኛው መንገድ ይኸው በመሆኑና ብዙ ደክሜበት ስለነበር የተዋጣለት እንደሚሆን እርግጠኛ ነበርኩ:: ቀኑ ደርሶ ፕሮጄክቴን ለማቅረብ ስወጣ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም አቅቶት ተብረከረከ፡፡ እንደምንም ወጥቼ የመጀመሪያውን ቃል ለመናገር አፌን ከከፈትኩ በኋላ ግን ፍርሀቴ ጠፍቶ ሁለመናዬ ፕሮጄክቴ ውስጥ ገባ:: የፈራሁት የተማሪዎች ዓይን ብዙም ተፅዕኖ ሳያሳድርብኝ ሁሉም ነገር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ጥሩና ስኬታማ ነገር በማቅረቤ ተማሪው እጅግ ከመደነቁ የተነሳ ባልጠበቁት ሁኔታ ወደ መቀመጪያ ቦታዬ እስከምደርስ ድረስ ቆመው አጨበጨቡልኝ፡፡ የጠበቅሁትን ሳይሆን ያልጠበቅሁትን በማየቴ እጅግ ተደሰትኩ፡፡ እነዚያ ይጠሉኛል ብዬ የምገምታቸው ተማሪዎች ሁሉ ቆሞው ሲያጨበጭቡልኝ ሥራዬ በእርግጠኝነት የተዋጣለት መሆኑ ተሰምቶኛል፡፡ ከእኔ በፊትም ሆነ በኋላ እንደ እኔ የተጨበጨበለት ተማሪም አልነበረም:: ወደ ወንበሬ እንደተመለስኩ መጀመሪያ መመልከት የፈለኩት ዶክተር አድማሱን ነበር፡፡ እንደእኔ የደከመበት ፕሮጄክት ስለነበር ምን እንደተሰማው ለማወቅ መጓጓቴ አግባብነት ነበረው:: መድረኩ ላይ ቁጭ ብሉ ተማሪዎቹ ሁሉ የእኔንና የእሱን ሁኔታ እንደሚከታተሉ ቢያውቅም፣ ለዚህ ምንም ቁብ ሳይሰጠው ከሌሎች አስተማሪዎች በተለየ ሁኔታ እያጨበጨበ ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ በአድናቆት ራሱን ሲነቀንቅ በማየቴ ዓይኔ በእምባ ተሞላ፡፡ ስሜቴን መቆጣጠር ተስኖኝ የደስታ እምባ በጉንጮቼ ላይ ወረደ:: እርግጥ ደስታና ሐዘን የተፈራረቀበት የዩንቨርስቲ ህይወቴ ባልጠበቁት አኳኋን እንዲህ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ በደስታ ብዛት ባነባ የሚገርም አልነበረም። እነሆ እኔና ዶ/ር አድማሱ የለፋንበትና የደከምንበት ፕሮጄክት በውጤታማነት ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የረዳኝን አምላኬንም እዚያው እተቀመጥኩበት ዓይኔን ጨፍኜ ምስጋና አቀረብኩለት፡፡ ለእኔ የዚህ ፕሮጄክት መሳካት ለትልቅ ግምት የሚሰጠው ነበር፡፡ ምክንያቱም በሁሉም ውጤቶቼ ከተማሪው በሙሉ የተሻለ ከፍተኛ ውጤት ያመጣሁ በመሆኔና ፕሮጄክቴም በጠበቅሁት ሁኔታ ከተጠናቀቀ የሽልማቱ ወርቅ የእኔው እንደሚሆን የማረጋግጥበት ወቅት በመሆኑ ነው:: ይህንንም ዛሬ ማረጋገጥ ስለቻልኩ በደስታ ባለቅስ የሚበዛብኝ አልነበረም:: ተማሪው ይህንኑ

ስለሚያውቁ፣ እኔን ቢጠሉኝም ሥራዬን ግን በመውደዳቸው አልባቸው አጨብጭበውልኛል:: ተማሪዎቹ ሁሉ ይጠሉኛል ብዬ የማስብ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ግን "ማን ያውቃል ብዙ የሚወዱኝ ሊኖሩ ይችላሉ ብዬም ማሰብ ጀመርኩ:: ሰኔ 25 ቀን 1978 ዓ.ም ዛሬ የመመረቂያችን ቀን በመሆኑ ግቢው ጥቁር ገዋን በለበሱ ተማሪዎች፣ የአበሻ ቀሚስና ሱፍ ልብስ በለበሱና ልጆቻችውን ለማስመረቅ ተጋጊጠው በመጡ ወላጆች አሸብርቋል። ይህ ቀን ለእኔ እንደአለፈው ሕይውቴ ሁሉ ሁለት ገፅታ አለው፡፡ በአንድ በኩል የተማሪዎች ቁንጮ መሆኔ የሚበሰርበት የብስራት ቀን ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ውጣ ውረድ የበዛበት የታሪኬ ምዕራፍ የሚዘጋበት ዕለት ነበር:: አባቴ በወቅቱ በመታመሙ ምክንያት ባይመጣም እናቴ ግን መጥታ ነበር፡፡ የምፀልየው ግን እናቴ የሳንቲሙን አንድ ገፅታ ብቻ ሰምታና አይታ እንድትመለስ ነበር፡፡ ይህም ደክማና ለፍታ ያሳደገቻት ልጅ የተማሪዎች ቁንጮ ሆና ስትመረቅ ማየት ነው:: ይህንንም ሳስብ ልቤ በደስታ ይሞላል:: እንደጠበቅሁትም ሆነ፡፡ የሽልማቱን ወርቅ አጥልቄ እንዳየች እናቴ ማልቀስ ብቻ ሳይሆን በእምባ ታጥባ ነበር፡፡ ተቃቅፈን ተላቀስን፡፡ ዶ/ር አድማሱም ዛሬ ደስታውን መቆጣጠር _ አልቻለም:: _ ከአዳራሹ ስንወጣ የተማሪዎቹ ዓይን ሳይፈራ አቅፎ ሳመኝና፤ “አንቺ ገና ብዙ ትላልቅ ነገር ሊሰራ የሚችል ጭንቀላት ያለሽ ነሽ፡፡ አደራ በማይረባ ነገር እንዳታበላሺው" አለኝ፡፡ ለራሴም ከአሁን በኋላ ይህንን ጭንቅላት ላላበላሸውና ትላልቅ ረቂቅ ነገሮችን የሚያብሰለስል እንጂ ግለሰቦችንና የእነሱን ዝባዝንኬ ታሪክ በማውጣትና በማውረድ እንዲላሽቅ እንደማላደርገው ቃል ገባሁ፡፡ ከምረቃው አዳራሽ እንደወጣን ፎቶግራፍ ለመንሳት ወደ አትክልቱ ቦታ አመራን፡፡ አማረን ለማስታወስ
በማለት በእነዚያ በአጭሩ በተከመከሙና በመንገዱ ግራና ቀኝ በተተከሉ ፅዶች በተዋበው "የፍቅር ጎዳና" ላይ እስከሚበቃኝ ድረስ ከእናቴ፣ ከዶ/ር አድማሱና ከብዙ አድናቂ ተማሪዎች ጋር ፎቶ ተነሳሁ፡፡ እያንዳንዷ ከሰዎች ጋር ተቃቅፌ የምነሳት ፎቶ፣ ከአማረ ጋር ከላይብረሪ ወጥተን በዚህ መንገድ ላይ ተቃቅፈን የሄድንበት ጊዜ የሚያስታውሰኝ በመሆኑ ከደስታዬ ባሻግር አንዳች ነገር እንደቀረብኝ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ አፍ አውጥቼ ባልናገርም፤

"ምናለ ዛሬ አጠገቤ በነበርና ደስታዬ እጥፍ ድርብ በሆነ˚ አልኩ፡፡ ምረቃው ካበቃ በኋላ ግቢውን ለቅቄ የምሄድበት ቀን ቁርጥ እየሆነ ሲመጣ ደግሞ ፍርሀት ወረረኝ:: ግን ለምን? ከዚህ በኋላ እዚህ ምን ቀረኝ? ለምንስ ፈራሁ? ራሴን ጠየቅሁ:: አዎ! እርግጥ ነው የእኔ ለእዚህ መብቃት ምሥጋናው መድረስ ያለበት ለዶ/ር አድማሱ ነው:: ይህንን ሁሉ መከራ አልፌ ለዚህ እንድደርስ ያበቃኝ እሱ ነው:: የቀረኝ አንድ ጓደኛም እሱ ብቻ ነበር:: ዛሬ ደግሞ በተራው እሱንም ላጣው ነው። ከእሱ መለየቴን ሳስብ ልቤ በፍርሀት ራደ:: ለዚህ ሁሉ ውለታው ምን ሊከፈለው ይቻላል? ይህን ምንም ስጦታ ሊተካው የማይችለውን ውለታውን እኔ ከፍዬ ልወጣው ስለማልችል አምላኬ ሁሉንም ጥሩ ጥሩ ነገር እንዲያደርግለት ተመኘሁ:: እናቴን ግቢውን እያዞርኩ ሳስጎበኛት በመዋሌ በጣም ደክሟት ስለነበር በጊዜ መተኛት በመፈለጓ አልጋዬን ለቅቄላት እኔ ግን ከጎደኞቼ ጋር እንደማድር ነግሬያት ተሰናብቼያት ወጣሁ፡፡ ይህንን ሁሉ ጊዜ አጠገቤ ሆኖ ሲያፅናናኝና ሲረዳኝ የነበረውን ዶክተር አድማሱን ቀኑን ሙሉ ስላላገኘሁትና የዋለልኝን ውለታ ሁሉ ልመልሰው የማልችል ቢሆን እንኳ ቢያንስ አቅሜ የቻለውን ስጦታ መስጠት አለብኝ ብዬ በመወሰኔ ስጦታዬን ይዤ ወደ ቤቲ አመራሁ:: ወደ ቤቱ እንደምመጣ ያወቀ ይመስል ቤቱን አሰማምሮ ጠበቀኝ:: ጠረጴዛው በምግብና በተለያዩ መጠጦች በመሞላቱ ሌላ እንግዳ ይኖራል ብዬ ገመትኩ፡፡ እንደገባሁ እቅፎና ጉንጬን ስሞ ወንበር ስቦ አስቀመጠኝ:: ብቻችንን እንድንሆን ፈልጌ ብሄድም የዶክተር አድማሱ ዝግጅት ሲታይ ግን እንግዳ እንዳለበት ያመላክታል፡፡ ከዚህ ቀደም ሰው ሲጋብዝ አይቼው ስለማላውቅ፤ “እንግዶች ጋብዘሃል እንዴ?'' አልኩት፡፡ “አዎን ትልቅ እንግዳ፣ ከእንግዶች ሁሉ የላቀና የማከብረው'' አለኝ:: "ማንን?" አልኩት ግራ ተጋብቼ፡፡ "አንቺን” አለኝ ጉንጬን እየሳመ፡፡ ፍላጎቴ ይህ ስለነበር ደስ አለኝ፡፡ ጠረጴዛው ላይ _ ለስላሳና አልኮል መጠጦች እንዲሁም የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ተደርድረዋል:: በሕይወቴ ከአማረ ጋር ከጠጣሁት ቢራ ውጪ ሌላ አልኮል መጠጥ ጠጥቼ አላውቅም፡፡ ዶ/ር አድማሱ አልፎ አልፎ ወደ ቤቱ ስሄድ ቢጋብዘኝም፤ ያቺ የመጀመሪያዋ መጠጥ ያስከተለችውን መዘዝ ስለማውቅ፣ መልሴ ሁሌ "አልወድም ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ የተለያዩ የአልኮል መጠጦችንም ደርድሮ ሲጠብቀኝ ገረመኝ፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ደስ

ስላለኝና ቀኑንም ለየት ላደርገው ስለፈለግሁ እንካንስ መጠጥ የሚያስደስት ከሆነና ካልገደለኝ መርዝም ቢቀርብልኝ እንደምጠጣው እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ የማላውቀውን የመጠጥ ዓይነት ሲያስመርጠኝም አልጠጣም የሚል ቃል ትንፍሽ አላልኩም:: “የቱ ይሻልሻል? ውስኪ፣ ቢራ ወይስ ወይን?” አስመረጠኝ፡፡ “አንተ የምትጠጣውን፣ ደስ ያለህን ቅዳልኝ' አልኩት፡፡ "እንግዲያውስ ውስኪ ይሻልሻል፡፡ ዛሬ የደስታ ቀን ስለሆነ በመጠኑ ብትጠጪ አይጎዳሽም ብሎ ቀዳልኝ፡፡ በሆዴም ቢጎዳስ፣ ለአንድ የደስታ ቀን ያልሆነ ጨጎራ ወይም ጉበት ይበጣጠስ አልኩ፡፡ (የሚጎዳውን ባላውቅም መቼም ከእነዚህ አንዱን ይሆናል ብዬ ጠርጥሬ)። ራት ከበላን በኋላ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ትንሽ ፓኮ አምጥቶ ስጠኝ፡፡ ክፈቺው ብሎ ስከፍተው ውስጡ የወርቅ ሀብልና ፖስት ካርድ ነበረበት:: ሀብሉን አንስቶ አንገቴ ላይ አጠለቀልኝና ፖስት ካርዱን "አንብቢው" አለኝ። “የእኔ በመሆንሽ ኮራሁብሽ፣ እንኳን ደስ አለን፡፡ ለእኔ የመጀመሪያዬና የመጨረሻዬ እንደምትሆኚ ቃል እገባለሁ" ይላል፡፡ ደነገጥኩ፡፡ የደነገጥኩት ስጦታ ልሰጠው መጥቼ ስለቀደመኝ ሳይሆን እኔ እሱ ለሚመኘው ጉዳይ መብቃቴ ላይ እርግጠኛ ስላልነበርኩ ነው፡፡ ከስጦታው በኋላ መጠጡን እየቀማመስን መዝናናቱን ተያያዝነው:: በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ሙዚቃ ተከፍቷል። ከቴፑ የሚወጣው ድምፅ እንኳንስ ህያው ሰብዓዊ ፍጥረትን ቀርቶ ዛፍንም ቢሆን ማንቀሳቀሱ አይቀርም ያሰኛል:: ዶክተር አድማሱ መለያየታችን ተሰምቶታል፡፡ ከወትሮው ለየት ባለና በሚያሳዝን ሁኔታ ስለመለያየታችን አስከፊነት እየደጋገመ ያወራኛል:: በመሀሉ ፈራ ተባ እያለ “እንደንስ አለኝ" “አልችልም" አልኩት “ምን መቻል ያስፈልጋል፣ ነይ እኔ አሳይሻለሁ" ብሎ እንድንደንስ እጁን ሰጠኝ፡፡ በቀዝቃዛ ሙዚቃ ታጅበን ቯልስ መደነስ ጀመርን:: ከአንገቱ ስር ውሽቅ ብዬና ደረቱ ላይ ተለጥፌ ስደንስ ሰውነታችን ብቻ ሳይሆን ልባችንም ሲደንስ ምቱ ይሰማ ጀመር:: የሰውነታችን ሙቀት ከእኔ ወደ እሱ ከእሱ ወደእኔ ሲመጣ በግልፅ ታወቀኝ::

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
''ምነው?'' አላት ዝም አለች
ለቅሶ ከየት ይምጣ ዕንባ ጨርሳለች

    ''ንገሪኝ'' ብሎ ዓይኗን ሲያየው
        ቆይቷል ሰው ካወያየው።

          አቀፋት ዝም እንዳለች
          ለዘላለም ቀዝቅዛለች

             "ደና ነሽ" አላት
          እንደምንም እየጣረ

      አንድ ቃል አወጣች
                ''ደና ምን ነበረ?''

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘