‹‹አይ አመሰግናለው ..እኔው አደርጋዋለው፡፡››ብሎ በድንጋጤ ሀውልት ሆኖ ከቆመበት ተንቀሳቀሰና ኑሀሚ ወዳለችበት ጎጆ መጠጋት ጀመረ፡፡እነሱ እንዲገድሏት ማድረግ እችላለሁ ማለቱ ሰውነቱን በድንጋጤ ነው ያደነዘዘው…እነዛ ለአውሬ የቀረበ ባህሪ ያላቸው የእድሜ ዘመናቸውን በጫካ ሲሹለከለኩ የሚኖሩ ስለሆነ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሲያገኙ በተለይ ተገዳዮ ሴት ስትሆን ምን እንደሚያደርጉ ከልምድ ያውቀዋል፡፡‹‹መሞቷ ካልቀረማ ቢያንስ በክብር እንድትሞት ማድረግ አለብኝ›› ሲል አሰበ፡፡ሽጉጡን ከወገቡ አወጣና ውስጡ ስንት ጥይት እንዳለው አረጋገጠ…በትከሻው አንጠልጥሎት የነበረውን ጠመንጃ በቅርብ ርቀት ለሚገኝ ለአንድ አቀበለውና ልክ የገዛ ራስህን ግደል እንደተባለ ሰው እግሮቹን መሬት ላይ እየጎተተ ኑሀሚ ወዳለችበት ክፍል መራመድ ጀመረ..፡፡
‹‹ስማ…››ትዕዛዝ ሰጪው ድጋሚ አስቆመው፡፡
‹‹ተቀያሪ ትዕዛዝ ይኖር ይሆን በሚል ተስፋ በፍጥነት ዞረ…፡፡እዚህ እሷን መግደል የመንደሩን ኑዋሪዎች ትኩረት ይስባል…አንድ ሰው ጨምርና ወደጫካው ወስደችሁ በማስወገድ በስርአት ቅበሯት…ደግሞ እንዳትዝረከረኩ››
ምንም ሳይመልስለት ወደውስጥ ገባ፡፡ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞታል፡፡ተጠጋትና ስሯ ብርክክ ብሎ ተቀመጠ፡፡በትኩረት አያት ፡፡ይህቺን ሴት ካያት ቀን አንስቶ በልቡ ፈልጓታል.. በነፍሱ ተርቧታል..ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ተግባብተዋል፡፡በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደአጋችና ታጋች ሳይሆን የአማዞን ተፍጥሮዊ ውበትን ለማድነቅና በእግዜር ተአምራዊ የመፍጠር ብቃት ለመደነቅ ከሆነ የአለም ጥግ ተስማምተው በመምጣት አብረው እየተጓዙ እንዳሉ የልብ ጓደኛሞች ብዙ ብዙ ነገሮች ተጨዋውተዋል፡፡አብረውት ለአመታት ከቆዩት ከአንዳንድ ጓደኞቹ ይልቅ ስለእሷ የህይወት ታሪክ በተሻለ ጥልቀት ማወቅ ችሏል፡፡ኢትዬጵያዊ እንደሆነች፤በልጅነቷ እናትና አባቷ እራሳቸውን አጥፍተው እንደተገኙ..እሷ ግን በሰው እጅ ተገድለዋል ብላ እንደምታምን፤አንድ ከራሷ በላይ የምትወደው መንትያ ወንድም እንዳላት..ከወንድ ጋር የህፃናት ማሳደጊያ ገብተው እንደነበር..ከዛ ጎዳናም ወጥተው ለአመታት ኖረው እንደሚያውቁ ..ብዙ ብዙ ነገር ነግራዋለች፡፡፡አንድ የደበቀችው አንኳር ነገር ቢኖር ለኢትዬጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ሰላይ በመሆን ለአመታ መስሯቷንና የስለላም ሆነ የወታደራዊ እውቀት እንዳላት ነው፡፡
እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ ደግሞ ስለአንድ ሰው ታሪክ የበለጠ እያወቀን በሄደን ቁጥር በሰውዬው በተለየ መልኩ እየተሳብንና እየተመሰጥን እንሄዳለን፡፡በተለይ የሰውዬው ታሪክ አሳዛኝና በመከራና በአድቬንቸር የተሞላ ከሆነ በቃ በቀላሉ በሰውዬው ተፅዕኖ ስር መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡ከእንደዚህ አይነት ሰው ጋር ብዙ እየተቀራረብን በሄድን ቁጥር በፍቅሩ የመውደቃችን እድል ለመቶ ፐርሰንት የቀረበ ነው፡፡አሁን ካርሎስን ያጋጠመው ያ ነው፡፡
በሀዘን ልቡ እንደተኮማተረች ሚንቀጠቀጥ እጁን ትከሻዋ ላይ አሳረፈና ነቀነቃት፡፡ማራኪ ህልም ላይ ስለነበረች በርግጋ ተነሳች፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ..ተነሽ ፈልጌሽ ነው››አላት፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ›› ማለቱ ለራሱ አስገረመው፡፡ልክ ቀይ የፅጌረዳ አበባ አስታቅፎ ፍቅር ወደምትሰራበት ልዩ ሰገነት ላይ ይዞት እንደሚሄድ ነገር ነው ያስመሰለው..ለጊዜው ሊጠነቀቅላት ፈልጎ ቢዋሻትም ከደቂቀዎች በኃላ እንደምትገደል ስታውቅ በህይወቷ ከደነገጠችው ድንጋጤ የመጨረሻውን ድንጋጤ መደንገጦ የት ይቀራል፡፡
ቀልጠፍ ብላ ተነሳችና ቆመች‹‹ምነው ጉዞ ልንጀምር ነው አይደል?፡፡››
‹‹አይ እኛ ቀድመን መጓዝ ልንጀምር ነው..እነሱ ቀስ ብለው ይከተሉናል፡›› አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ባያውቅም ዋሻት፡፡ተያይዘው ሲወጡ ከእሱ ጋር የተመደበው ሰው መሳሪያውን በትከሻው አንጠልጥሎ የእሷን ቦርሳ በእጁ ይዞ እየጠበቃቸው ነው፡፡ዝም ብሎ እጇን ያዘና ከአማዞን ወንዙ በተቃራኒ ወደጥቅጥቁ ጫካ የምትወስደውን ቀጭን የእግር መንገድ ተያያዘው ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

🥰41👍37😢8❤7
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ይሄ መንገድ ግን ወደ መጣንበት አቅጣጫ የሚወስድ አይደል እንዴ?››በጥርጣሬ ጠየቀች፡፡
‹‹አይ አይደለም…..ትንሽ ከተጓዝን በኃላ እንታጠፋለን፡፡››ሲል ድጋሜ ዋሻት፡፡
ከዛ በኃላ ለ10 ደቂቃ ያህል ጫካውን ቁጥቆጦ እየገፉና እሾክና እንቅፋቶችን ከፊታቸው እያስወገድ ወደፊት ከመጓዝ ውጭ በሶስቱም መካከል ምንም ንግግር አልነበረም፡፡
ኑሀሚ የህይወቷ የመጨረሻ ጫፍ ላይ እንደደረሰች ተስምቷታል፡፡ከቡድኑ ነጥለው ወደጫካው እየነዷት ያለው ለሰላም እንዳልሆነ ወዲያው ነው የገባት፡፡ በተለይ የካርሎስ መርበትበትና በፊቱ ላይ እየተመለከተችው ያለው ሀዘን በጥርጣሬዋ እርግጠኛ እንደትሆን አድርጓታል፡፡ በዛ ላይ ከኃላ ሆኗ የሚከተላቸው ፊቱ የማፈታው ታጣቂ በጀርባው ባነገተው ቦርሳ አካፋም መቆፈሪያም ሆኖ የሚያገለግል ወታደሮች ምሽግ ለመስራት የሚጠቀሙበትን መሳሪያ ይዞ በማየቷ ሌላ እርግጠኛ እንድትሆን ያደረጋት ምልክት ነው፡፡
አካባቢን ማጥናት..ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል..ከዛ የይሆናል ትንበያዎችን አስቀምጦ ከቅርቃሩ ለመውጣት የሚያስችሉ አማራጮችን በፍጥነት ማስላት….በስለላ ህይወቷ የቀሰመችው ትምህርት ነው፡፡
እና ዝም ብላ መሞት እንደሌለባት እራሷን እያሳመነች ነው፡፡በህይወቷ እንዲህ መሰል በህይወትና በሞት ቅርቃር መካከል የመውደቅን አጋጣሚ ብዙ ጊዜ ገጥሞት ያውቃል፡፡ በአምስት ሰዎች ተከባ ልትገደል ብላ ግማሹን ገንድሳ ግማሹን ገድላ ነፃ የወጣችበትና ህይወቷን ያተረፈችበት አጋጣሚ ነበረ፡፡ከእዛ አንጻር ሲታይ ይሄ ቀላል ይመስላል..ምክንያቱም ከሁለት ታጣቂዎች ጋር ነው የምትፋለመው፡፡ ካላት ወታደራዊ እውቀትና ልምድ አንፃር አነሱን ገድላ ወይ ፌንት አስበልታ የማምለጥ እድሏ ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው ፡፡..ችግሩ ካመለጠች በኃላ ነው፡፡ፊቷ ያፈጠጠው ምኑንም የማታውቀው በየት ገብታ በየት መውጣት እንዳለባት ምንም እውቀት የሌላት የአማዞን ጫካ ነው፡፡ጫካ ውስጥ ያሉት አስፈሪና በስም እንኳን ለይታ የማታውቃቸው አውሬዎችና አንድ ጠብታ መርዛቸው እንኳን ሰውነት ላይ ሲያርፍ በሰከንድ ውስጥ የሚያደርቅ ተሳቢ እንስሳትና በራሪ ነፍሳት ጋር ነው፡፡ቢሆን በሰው ተቦጫጭቆ ከመበላት በአውሬ ጋር ለመፋለም ቁርጠኛ መሆን ይሻላል
፡፡በዚህ ቅፅበት አንድ ታሪክ ትዝ አላትና ለካርሎስ ልትተርክለት ፈለገች፡፡
‹‹አንድ ጣፍጭ ታርክ ልንገርህ?››
እንደ እሱ ግንዛቤ ሰዓቱ ታሪክ መንገሪያም ሆና ማዳመጪያ እንዳልሆነ ቢያምንም ለእሷ ግን ምን አልባት የመጨረሻ ቃሏ ሊሆንላት ይችላል ብሎ ስላሰበ እንድትነግረው ተስማማ፡፡
‹‹ጨቋኝ ገዢ ወይም የሰው ልጅ ከገዳይ ነብር የበለጠ አስፈሪ እንደሆነ የሚያስረዳ ታሪክ ነው፡፡
‹‹ገባኝ ንገሪኝ…››
ከአንድ የድሮ መፅሀፍ ላይ ያነበብኩት ታሪክ ነው፡፡በአንድ ወቅት በቻይና ግዛት ውስጥ በምትገኘው በታይ ተራራ ስር በሀዘን ተቆራምዳ እንባዋን እያዘራች የምትኖር ሴት ነበረች፡፡የዚህችን ሴት ታሪክ ኮንፌሽዬስ ሰማና አስጠራት፡፡ከዛም"አንቺ ሴት ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ሀዘን የበላሽ?"ሲል ጠየቃት።ሴቲቱም ‹‹በተራራው ላይ የሚኖረው ነብር ባሌን ፣የባሌን አባት እና ብቸኛ ልጄን በየተራ እየቀረጣጠፈ በላብኝ-በዛ ምክንያት ነው ሀዘኔ ጥልቅ የሆነው›› ብላ መለሰችለት።
እሱም መልሶ "ታዲያ መላ ቤተሠቦችሽን የበላው ነብር አሁንም በተራራው ላይ መኖን እያወቅሽ .እንዴት ከአካባቢው ሳትሸሺ?››ሲል በመገረም ጠየቃት።
ሴቲቱም‹‹ቦታውን ለቅቄ ያልተሠደድኩት ጨካኝ ገዢ የሌለበት ብቸኛ ስፍራ ስለሆነ ነው።"ስትል መለሠችለት
ኮንፌሽዬስም ወደ ደቀመዛሙርቱ ዞሮ" አያችሁ ጨቋኝ ገዢ ከገዳይ ነብር የበለጠ አስፈሪ እንደሆነ ከዚህች ሚስኪን ሴት ታሪክ ተማሩ፡፡›› አላቸው።
እኔም አሁን እዚህ አማዞን ደን ውስጥ ካሉት አውሬዎች በላይ ጨካኝ የሆኑ የሰው ልጆች ናቸው እያሰፈሩኝ ያሉት››ብላ ታሪኩን ደመደመች፡፡
‹‹አልተሳሳትሽም….የሰው ልጅ መጨከን ከጀመረ ወሰኑ አይደረስበትም…››
‹‹እኔ ምልህ ..አሁን ልትገድሉኝ ነው አይደል?››
ጥያቄዋ አስደነገጠው…ምን ብሎ እንደሚመልስላት ግራ ስለገባው…ዝም አለ…‹‹አትጨነቅ..ግን ያልገባኝ እንዲህ ልትገድሉኝ ይሄን ሁሉ ቀን እኔንም ማንከራተት እናንተም ከእኔ ጋር መንከራተት ለምን አስፈለገ?››
‹‹ትዕዛዙ የደረሰን አሁን ነው…››
‹‹ትዕዛዙን የሚሰጠው ማን ነው››
‹‹ሀለቃችን ነው…ካለበት ቦታ በሳተላይት መገናኛ ነው ከደቂቃዎች በፊት ትገደል ያለው፡፡››
‹‹ይገርማል…ቆይ ግን ከእኔ ጋር ያገኛችሁትን ሰውዬ ገድላችሁታል አይደል?››
ፈገግ አለ፡፡
የፊቱን ፈገግታ በቆረጣ እይታ አየችውና ተበሳጨችበት…‹‹ምነው? የሰው መገደል ያስቃል እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም … እንደውም በተቃራኒው ልቤን ነው የሚሰባብረው፡፡››
‹‹አይ ስትስቅ አየሁህ ብዬ ነው፡፡››
‹‹ጥያቄሽ ነው ያሳቀኝ …አንቺ እንድትገደይ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ሀለቃችን አሁን አንቺ የምትጨነቂለት ዳግላስ መሆኑን ሳስብ ነው ያሳቀኝ..አየሽ አለም በእንደዚህ ይነት ገራሚ ምፀቶች የተሞላች ነች፡፡››
እርምጃውን ገታችና ባለችበት ቆመች..ከኃላ እየተከተላቸው ታጣቂ አይኑን አጉረጠረጠ…የጓደኛውም ሆነ የተገዳዮ ነገረ ስራ ምንም አላማረውም…ጣልቃ ላለመግባት ነው እንጂ ወሬያቸውም አልተመቸውም.. ምክንያቱም እሱ ስፓኒሽኛ ተናጋሪ ሲሆን እንሱ እያወሩ ያሉት በእንግሊዘኛ ነው..እሱ ደግ እንግሊዘኛ ጆሮውን ቢቆርጡጥ አይሰማም፡፡
‹‹ማለት ከእኔ ጋር ያገታችሁት በሌላ ጀልባ ወደሌላ ስፍራ የወሰዳችሁት ዳግላስ የእናንተ ሀለቃ ነው?››ማመን ስላልቻለች ደግማ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን በሺ ሚቆጠሩ ሌሎች የታጣቂ ቡድኖች መሪ የጫካው ንጉስ እየተባለ የሚጠራ ከፍተኛ ቢሊዬን ዶላሮች የሚያንቀሳቅስ ከፔሩ፤ ኮሎምበያ፤ ፓናማ፤ ነካረጎ፤ ጉታማላ፤ ሚክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ እሱ የሚቆጣጠረው የንግድ መስመር ያለው በሶስት በአራት ሀገራት የደህንነት ሰዎች ሚፈለግ አለማ አቀፉ የኢንተርፖል የተፈላጊዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያው ገፅ ላይ የሰፈረ ተአምረኛ ሰው ነው፡፡››የሚላትና ማመን ነው እያቃታት፡፡‹‹እና እሱ እንደእዛ አይነት ሰው ከሆነ ለምን ከእኔ እኩል አፈናችሁት?፡፡››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹ሰውዬው መድሀኒቱን በጊዜ ካልወሰደ ከፍተኛ የመርሳት ችግር አለበት..ማለት እራሱንና ማንነቱን ሙሉ በሙሉ እስኪዘነጋ ድረስ ይደርሳል፡፡ከንቺ ጋር ሊማ አየር ማረፊያ ተገናኝታችሁ ኢኩቶስ እስክታርፉ ድረስ ከዛም ሆቴል ይዛችሁ ስታድሩ ሁሉ ያገጠማችሁ ያ ነው፡፡በወቅቱ ችግሩ እንደተፈጠረ ስናውቅ በግል ቻርተር አውሮፕላን እናንተ ወዳላችሁበት መጣን፡፡ ቀጥታ ሄደን ብናናግረው..አላውቃችሁም ሊለን ይችላል፡፡ ክርክር ብንገጥም ጭቅጭቅ ቢነሳ ደግሞ ትኩረት እንስባለን…እንዳልኩሽ በአለም አቀፍ ደረጀ የሚፈለግ ሰው ነው…ስለዚህ ሁኔታውን አመቻችተን ማፈን ነበረብን፡፡ለዛ ነው እንደዛ ያደረግነው፡፡››

👍68❤7👏2
‹‹ጥሩ እዚህ ሁሉ ውስጥ ታዲያ እኔ ምንድነው ያደረኩተት?፡፡››ስትል በአግሯሞት ጠየቀችው፡
‹‹ከእሱ ጋር አንድ ቀን አሳልፈሻል…. አንድ ቀን አብረሽው አድረሻል…ስለእሱ ምን መረጃ እንዳወቅሽ አይታወቅም…መጀመሪያውኑ ከእሱ ጋር ያንን ጊዜ ያሳለፍሽው ዝም ብለሽ በየዋህነት ነው..?በውበቱ ተማርከሽ ሴትነትሽን ልትሰጪው ነው..?ወይንስ የሆነ የደህንነት ተቋም ያሰማራሽ ሰላይ ነሽ…?ይሄ ነው ጥርጣሬችን››
‹‹ታዲያ ይሄንን የምታጣሩበት ዘዴ የላችሁም?፡፡››
‹‹አለን…እኔም እንደዛ እንደሚደረግ ነበር ተስፋ ያደረኩት…በተጨማሪም ከሰውዬው ጋር ባሳለፍሽው አንድ ቀን ጥሩ ጊዜ ካሳለፋችሁ ያንን ከግንዛቤ አስገብቶ የተሻለ ውሳኔ ይወስናል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር..ግን ሁሉ ነገር ካሰብኩት በተቃራኒ ነው የሆነው…ለነገሩ ሰውዬው ሁሌ እንደዚህ ነው..የመግደል ሱስ አለበት፡፡››
ጓደኛው በስፓኒሽኛ ያወራው ጀመር ..ትንሽ ተጨቃጨቁና ተስማሙ፡፡
‹‹ምንድነው የሚለው?››
‹‹አይ ይበቃናል..በቃ የምትቀበርበትን ጉድጓድ ትቆፍር ነው የሚለው፡፡›› ዝም አለች፡፡
‹‹እዛ ድንጋይ ላይ ተቀመጪ››አላት..ዝም ብላው ሄደችና እንዳላት ተቀመጠች፡፡
ካርሎስ አካፋውን ከጓደኛው ተቀበለውና የመቆፈሪያውን ክፍል አስተካክሎ እራሱ መቆፈር ጀመረ..መሬቱን በሚቆፍርበት መጠን የገዛ ልቡም እየተቆፈረበት ነው፡፡‹‹አሁን የእውነት ይህቺን የመሰለች ልጅ ተኩሼ ገድላታለው?፡፡››እራሱን ይጠይቃል፡፡አይ እንደዛማ ማድረግ አልችልም፡፡ለራሱ ይመልሳል፡፡ግን ደግሞ ትዕዛዙን ተግባራዊ አለማድረግ ከለምንም ምህረት ምን እንደሚያስከትልበት በደንብ ያውቃል፡፡በቃ ሞት ነው..ለዛውም ለሌሎቹ መቀጣጫ በሚሆንበት መንገድ አሰቃቂ የሆነ ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡
‹‹ለዚህች ለአራት ቀን ብቻ ለማውቃት ሴት ህልሜንም ህይወቴንም ልሰዋላት ዝግጁ ነኝ?››ሲል እራሱን ጠየቀ….መልሱ ቀላል እልሆነለትም፡፡
ጓደኛው ሊያግዘው ወደእሱ ተጠጋ፡፡ ከጉድጓዱ እንዲወጣ ጠየቀው ..መሳሪያውን ከትከሻው አነሳና አቀበለውና ወደጉድጓዱ ገባ…እየተፈራረቁ ጉድጓዱን ቆፍሮ ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃ ያህል ፈጀባቸው፡፡ከዛ የመጨረሻውን ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኑ፡፡ አነሱም ለመግደል እሷም ለመሞት …ድንገት ወደ እሷ ሄደና ‹‹በጣም አዝናለሁ….ላድንሽ ባለመቻሌ በራሴ አፍሬለሁ››አለና ጉንጮን ስሞ ብድግ አለና ፊቱን አዞረ ፡፡
ካርሎስ ‹‹በቃ አንተ አድርገው…….እኔ ወደእዛ ዞር ብዬ ላጭስ››ብሎ ለጓደኛው ነገረውና ወደግራው ዞር ብሎ ሶስት ያህል ርምጃ እንደተራመደ…ኑሀሚ ልክ እንደተናዳፊ ንብ ከተቀመጠችበት ተስፈነጠረችና የካርሎስን አንገት በእጆቾ ፈጥርቃ ይዛ በሌላ እጇ ወገቡ ላይ ያለውን ሽጉጥ መዘዘችና ግንባሩ ላይ ደቀነችበት‹‹አንተ ብቻ አይደለህም እኔም አንተን የመሰለ ቅን ፤መልካምና ፤ጀንትል ሰው ጋር የገዛ ህይወትን ለማትረፍ መፋለም በመገደዴ በጣም አዝናለው፡፡››አለችው
በዚህ ጊዜ ሁለተኛው ታጣቂ የያዘውን ዘመናዊ መሳሪያ በእሷ ትክክል ደቅኖ በማይገባት ቋንቋ ይለፈልፋ ጀመር፡፡
‹‹አይ አትዘኚ….ምን አለ በራሷ ተነሳሽነት የሆነ ነገር ማድረግ በቻለች እያልኩ ስፀልይ ነበር….የቻልሺውን አድርጊ ..በፀጋ እቀበላለው፡››አላት
‹‹እሺ ጓደኛህ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ ንገረው፡፡››
እንዳለችው በሚገባው የስፓኒሽ ቋንቋ ነገረው፡፡መለሰለት፡፡
‹‹ምን አለ?››ጠየቀችው፡፡
‹‹በተአምር የሀለቃዬን ትዕዛዝ እንዲከሽፍ ማድረግ አልችልም….››ነው ሚለው፡፡
‹‹እንዴ ….ካለስቀመጠ እኮ ተኩስብሀለው..ይሄንን አልነገርከውም?››
‹‹ነግሬዋለው..እሱም ገብቶታል፡፡ ግን እንደእሱ ውሳኔ እኔን ለማትረፍ በመጣር ነገሩን ከማበላሸት እኔን መስዋእት ማድረግን መርጧል፡፡››
‹‹እንደዛ የሚያደርግ ይመስልሀል?››
‹‹እንደአለመታደል ሆኖ ይመስለኛል….አንድም ቀን በመሀለከላችን መግባት ኖሮ አያውቅም….እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ለአመታት ሲጠብቅ እንደነበረ ነው የሚገባኝ፡፡››
እንግዲያው….አለችን በብርሀን ፍጥነት ሽጉጦን ከእሱ ግንባር አንስታ አቅጣጫውን ቀየረችና ተኮሰች …ደገመችው…ሰውዬው በቆመበት አይኑ እንዳፈጠጠ ተመለከታት..ከመሀል ግንባሩ ደም ቡልቅ ቡልቅ እያለ መውረድ ጀመረ ..ወዲያው ሽብርክ ብሎ ወደፊት ተደፋ፡፡ከዛ ለቀቀችውና ፈንጠር ብላ ቆመች፡፡
አንዴ መሬት ላይ ተዘርሮ በደም የታጠበው ጓደኛውን አንዴ እሷን እያፈራረቀ እያየ ግራ በመጋባት ደቂቃዎች አሳለፈ….ከዛ በርከክ ብሎ ጓደኛውን ገለበጠው…እጁን ወደ አንገቱ ልኮ በህይወት መኖር አለመኖሩን ተመለከተ፡፡
ሞቷል፡፡ኪሱን ፈተሸና የያዛቸውን እቃዎች አወጣ፡፡ እየጎተተ ለኑሀሚ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ወሰደውና ውስጥ ከተተው፡፡ከዛ በአካፋው አፈሩን መለሰና ደለደለው..ካዛ አዲስ የተቆፈረ መሆኑን እንዳያስታውቅ የደራረቁ ቅጠሎችና እንጨቶችን ከአካባቢው እየሰበሰበ አለበሰባትና በተቻላ መጠን ከአካባቢው መሬት ጋር በእይታ እንዲመሳሰል አደረገ፡፡መሳሪያውን ታጠቀ…ከኪሱ ያወጣቸውን እቃዎች የገዛ ኪሱ ውስጥ ጨመረ.. .ሟቹ ጓደኛ ይዞት የነበረውን የእሷን ቦርሳ አቀበላትና ….ከዛ ጎደኛው ጀርባ ላይ ከነበረው የመንገድ ሻንጣ ጠቃሚ ነው ያላቸውን እቃዎች…ባትሪ ከነተለዋጭ ድንጋዩ፤የተወሰኑ የታሸጉ ምግቦችን፤ሲቆፍሩበት ያነበረውን አካፋ መርጦ ወደረሱ ቦርሳ በመጨመር ‹‹በይ ፈጠን በይ እንሂድ›› አለትና ወደፊት መጓዝ ጀመረ፡፡
‹‹ወደየት ነው የምንሄደው?፡፡››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ…?በቃ እኮ አልቆልናል..ከተያዝን ሁለታችንም እንገደላለን..ስለዚህ ቢያንስ በተቻለን መጠን ለማምለጥ መሞከር አለብን፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነህ ራስህን የምታድንበት ሌላ መንገድ የለም?፡፡››
‹‹ነገርኩሽ..ይልቅ እያንዳንዷ ደቂቃ የህይወት ዋጋ አላት…ምንም ነገር መፈጠሩን ከማውቃቸው በፊት ከዚህ በጣም ርቀን መሄድ አለብን ››
..መጓዝ ጀመረች፡፡ተከተለችውና ደረሰችበት፡፡
‹‹እንካ…..››ሽጉጡን ወደእሱ ዘረጋች..ቀና ብሎ በትዝብት አያትና‹‹አሁንም ያንቺው ሆነ እኮ…ያዥው››አላት፡፡
‹‹ምንም ሳትከራከር…ሽጉጡን ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችና በትከሻዋ አንጠልጥላ ወደጥልቁ የአማዞን ሚስጥራዊና ትንግርተኛ ደን በደነዘዘ ስሜት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

❤51👍47👏8🤔1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ኮሎምቢያ/አማዞን ደን ውስጥ
ኑሀሚና ካርሎስ አምስት ሰዓት ያለምንም ረፍትና መንቀርፈፍ ነው የተጓዙት፡፡በቀንም ቢሆን እንኳን ፀሀይ የተንጣለሉትን የግዙፍ ዛፎችን ቅርንጫፍ ሰንጥቃ ወደመሬት መድረስ አይሆንላትም፤ ማታ ሲሆን ደግሞ ለጨረቃዋ በጣም ከባድ ስራ ነው የሚሆንባት፡፡ በዚህም ምክንያት በማታ አይደለም በቀንም ከፍተኛ ሀይል ያለው ባትሪ ሳይጠቀሙ መጓዝ አዳጋች እና በቀላሉ ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ ነው፡፡
‹‹አሁን ማረፍ ያለብን ይመስለኛል››አላት ካርሎስ
‹‹ይሻላል ብለህ ነው?››አለችው በዛለና በደከመ ድምጽ፡፡
‹‹አዎ አሁን የተወሰነ የራቅናቸው ይምስለኛል…ባይሆነ ለሊቱን አርፈን ንጊት ላይ በሙሉ አቅም ጉዞችንን እንቀጥላለን፡፡››አላትና ተስማሙ፡፡ቅጠል እየቆረጠች ግዘፉ ግንድ ስር መጓዝጎዝ ጀመረች፡፡
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?፡፡››
‹‹መሬት ላይ ከመቀመጥ ቅጠሉ ይሻለናል ብዬ ነዋ፡፡››
‹‹እዚህ የአማዞን እንብርት ላይ መሬት ላይ ተዝናተን መተኛት አንችልም…››
‹‹ለምን? ጃጓር ምናምን ፈርተህ ነው?››
‹‹እሱም አንድ ነገር ነው..ካዛ በላይ ግን ጥቃቅን መርዛማ ነፍሳቶች ናቸው የሚያስፈሩት…..ለምሳሌ የአማዞን ሸረሪት ሰውነትሽን ጥቂት ከጫረችሽ ወይ ከቦጨቀችሽ….በቀጥታ እራስሽን ለሞት ማዘጋጀት መጀመር ነው ያለብሽ፡፡በጣም ብርቱ ከሆንሽ አንድ ሰዓት ብቻ ነው የምትኖሪው፡፡መርዙን አርክሶ ከሞት የሚያድንሽ ምንም አይነት ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ መድሀኒት የለም፡፡እና ይህችን ሸረሪት በቁጥር አንድ ደረጃ ነው የምፈራት፡፡››
ፍራቻው ወደእሷም ተጋባበትና‹‹እና ምን እናድርግ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ሊያስተኛን የሚችል ዛፍ ነው መፈለግ ያለብን ..››ብሎ አይኖቹን በአካባቢው ወደሉት ግዙፍ ዛፎች ባትሪውና በማብራት መምረጥ ጀመረ…ከዛ ‹‹አዎ ይሄኛው የተሻለ ነው….፡፡››ስል ምራጫውን አሳወቃት፡፡
‹‹እንዴት አድርገን ነው እዚህ ላይ ምንወጣው?››
‹‹እንደምንም መውጣት ነዋ….መቼስ ቢከብድ ቢከብድ የሰው ህይወት ከማጥፋት በላይ አይከብድም፡፡››
በንግግሩ ድንግጥ አለች፡፡እስከአሁን እዛ ለእሷ በተቆፈረው መቃብር አካባቢ ስለሆነው ነገር አንሰተው አላወሩም‹‹ሰው መግደሉን ፈልጌው ወይም ቀላል ሆኖልኝ መሰለህ..?ጨንቆኝና የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩ…?ይሄም የህይወት እና የሞት ትግል ነው፡፡ከዚህ ደን በአውሬ ሳንበላ ወይም በነፍሳት ሳንነደፉ በሰላም ወጥተን የሆነ መንግስት የሚቆጣጠረው ትንሽዬም ቢሆን ከተማ ወይም መንደር እስክንገባ የህይወትና የሞት ሽረት ላይ እንደሆን እንዳትዘነጊ…. በይ ቦርሳሽን ለእኔ ስጪኝና ለመውጣት ተዘጋጂ …እኔ ከኃላ ሆኜ እደግፍሻለሁ፡፡››
የተወሰነ ጊዜ እንደማሰብ አለችና ትከሻዋ ላይ ያንጠለጠለችውን ቦርሳ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና ካንጠለጠለው ቦርሳ ጋር አንድ ላይ በቀኝ ትከሻው ደርቦ አንጠለጠለው፡፡በግራ ትከሻው ላይ ክላሽ አለ፡፡
እሷ በረጅሙ ትንፋሽ ወሰደችና ለመውጣት ዝግጁ ሆነች፡፡ቀኝ እግሯን አስቀደመች…ወገቧን ይዞ ደጋፋት፡፡ በእጆቿ ቅርብ ያለውን ቅርንጫፍ ተንጠራርታ ያዘችና ግራ እግሯን አስከተለች፡፡ እንዳዛ እያለች ወደ ላይ መንቀሳቀሷን ቀጠለች፡፡እሱ ከስር ሆኖ ትወድቅ ይሆን በሚል ስጋት በጭንቀት እየተከታተላት ነው፡፡እንደፈራው ሳይሆን እንደውም ይበልጥ አንድ ርምጃ ወደላይ ከፍ ባለች ቁጥር ይበልጥ እየፈጠነችና በራስ መተማመን እየታየባት መጣች፡፡ ለመተኛት ምቹ ነው ብሎ ያሰበበት ቦታ ስትደርስ ‹‹በቃሽ…እዛው ጠብቂኝ›› አላት፡፡እሱም በእፎይታ ወደላይ መውጣት ጀመረ፡፡እሱ ከልጅነቱ ጀምሮ የብዙ አመት ልምድ ስላለው ዛፍ መውጣት ለእሱ በምድር እንደመራመድ ቀላሉ እና ተራ ነገር ነው፡፡
ስሯ ደረሰና ከጎኗ ቁጭ ብሎ የእሷንም የእሱንም ቦርሳ ከአንደኛው ቅርንጫፍ ላይ አሰረው፡፡መሳሪያውንም እንደዛው አንጠለጠለውና በእፎይታ ደገፍ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ካልተመቸሽ እግርሽን በቅረንጫፉ መሀከል አድርጊና ጭንቅላትሽን እኔ ላይ አስደግፊ አላት፡፡››እንዳለት አደረገች፡፡ጭንቅላቷን ደረቱ ላይ ለጥፋ አረፍ ስትል የልብ ምቱ ድውድውታ ተሰማት፡፡
‹‹ልብህ በጣም ይመታል፡፡›› አለችው፡፡
‹‹አንቺን የመሰለች ፀይም መልዐክ ደረቴ ላይ ተኝታ የልብ ምቴ ባይጨምር ነበር የሚገርመው››አላት፡፡
‹‹አይገርምም …የዛሬን አያድረገውና አለቃህም በሰላሙ ቀን ፀይም መልአክ ብሎኝ ነበር››
‹‹እንደዘ በማለቱ እንኳን ተሳስቷል ማለት አልችልም…የእሱም ልብ እንደእኔው በውበትሽ ደንዝዛ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በዚህ ጣር ላይ ሆነህ ትቀልዳለህ አይደል?››
‹‹በጣር ላይ ሆንሽ በምቾት ላይ ልብሽ ጉዳዩ አይደለም እኮ …ከተነካ ተነካ ነው..በሲኦሉ ውስጥም ሆነ በገነት እጅ መስጠቱ አይቀርም፡፡››
‹‹ይሁንልህ…ውሀው አለቀች እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡ውሀ ጠምቷት ብቻ ሳይሆን የጀመሩትን የወሬ ርዕስ አቅጣጫ ማስቀየርም ስለፈለገች ነው፡፡የእሱን ልብ አታውቅም የእሷ ልብ ግን በዚህ ጊዜ ነፍሷን ለወንድሟ ስትል ከማትረፍ ውጭ ሌላ ተልዕኮ የላትም፡፡እጁን ወደተንጠለጠለው ቦርሳ ሰደደና ኮዳውን አውጥቶ ሰጣት፡፡ክዳኑን ከፈተችና ተጎነጨችለት፡፡መልሳ ከድና አቀበለችው፡፡ወደቦታው መለሰ፡፡
‹‹አሁን የት ነው ያለነው?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ነዋ፡፡››
‹‹እሱንእማ እያየሁት ነው…ሀገሩን ነው የጠየቅኩት፡፡
‹‹ብራዚል እና ኮሎምቢያ ድንበር ላይ ነን፡፡››
‹‹እንዴ …!ወደየት ነው እየሄድን ያለነው?››
‹‹ወደብራዚል ነው…››
‹‹ወደኮሎምቢያ ወይም ወደመጣንበት ወደፔሩ የምንሄድ ነበር የመሰለኝ፡፡››
‹‹አይ …ያንን ማድረግ አልመረጥኩም…ከፔሩ ፤ኮሎምቢያ ሜክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ ሰውዬው በብዙ ሺ የሚሆኑ ሰዎች አሉት…በየደረስንበት ሁለ ታዳኞች ነው የምንሆነው፡፡ይሄኔ ሁሉም እኛን በደረስንበት ቀጨም አድርጎ ወይ በህይወት ካለሆን ደግሞ እሬሳችንን ለእሱ በማስረከብ እና ደለብ ያለ ሽልማቱን ለመቀበል ቋምጠው እየጠበቁን ነው፡፡››
‹‹ብራዚልስ ሰው የለውም?››
‹‹አይ ብራዚል ተፅእኖው በጣም የሳሳ ነው፡፡በዛ ላይ አሁን እየተጓዝን ያለነው ወደግዙፍ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ነው..በቀደም እንደነገርኩሽ 60 ፐርሰንቱ የአማዞን ደን ያለው ብራዚል ውስጥ ነው፡፡ወደእዛ ጠልቀው ይገባሉ ብሎ ማንም አያስብም፡፡ገብተዋል ብለው ቢያስብ እንኳን ያን ሁሉ ደን ሰንጥቀን ከአውሬዎቹም ከተናዳፊ መራዛማ ነፍሳትም ተርፈን በህይወት የሆነ ቦታ እንደማንደርስ እርግጠኞች ናቸው..ስለዚህ ወደዚህ አይፈልጉንም፡፡ለዛ ነው በጣም ከባዱን መንገድ የመረጥኩት፡፡በህይወት እንዲሳካልሽ አንዳንዴ ቀላሉን መንገድ መምረጥ አዋጪ አይደለም…፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹አሳምነኸኛል..ግን አንተስ ከፊታችን እንደፓስፊክ ውቅያኖስ የተዘረጋውን አስፈሪ ጥቅጥቅ ደን ሰርቫይቭ አድረገን ሕይወታችንን እንደምናተርፍ እንዴት ልታምን ቻልክ?፡፡››
‹‹በቀደም በነገርሺኝ ታሪክ ነዋ››
‹‹የትኛው ታሪክ?፡፡››
‹‹የሴትዬዋ… ጨካኝ ንጉስ ያለበት ግዛት ውስጥ ከመኖር አዳኝ ነበር ያለበት ጫካ ውስጥ መኖር እንደሚሻል መምረጦን የነገርሺኝን…››
በጨለማ ውስጥ ፈገግ ብላ‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ፡፡››አለችው ፡፡
‹‹አዎ ጥሩ ተማሪ ነኝ..በዛ ላይ ሶስት ነገሮች ያግዙናል ብዬ አስባለው፡፡››
‹‹እስኪ ንገረኝ እነዚሀ ሶስት ነገሮች ምንድናቸው?፡፡››

👍79❤3👎1🥰1
‹‹አንደኛ እዚህ የአማዞን ደን ውስጥ ግማሽ እድሜዬን አሳልፌለሁ …ስለዕጽዋቱና እንስሳቱ ባህሪ ጥሩ የሚባል እውቀት አለኝ፡፡የትኛው እንስሳ አደገኛ እንደሆነ የትኛው ዕፅዋት ለየትኛው አይነት በሽታ መድሀኒት እንደሚሆን አውቃለሁ….››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛው…..ሰው ያለበት አካባቢ ስንደርስ ብራዚላዊ ስለሆንኩ በቃለሉ ከሀገሬ ሰዎች መግባባትና እርዳታ ማግኘት እንችላለን…በዛ ላይ ከሁለት የአገረቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ ፖርቹጊዝም እችላለሁ፡፡ታውቂያለሽ ብራዚል ብሄራዊ ቋንቋ እንደፔሩ ስፓንሽ አይደለም ፖርቹጊዝ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ ስንት ቋንቋ ነው የምትናገረው››
‹‹ሰባት››
‹‹ጥሩ… እሺ ሶስትኛውስ?››
‹‹ሶስተኛው ከዚህ አደገኛ ጉዞ በሕይወት ተርፎ ለመውጣት ዋናው አስፈላጊው አድቫንቴጃችን የአንቺ ጀግንነት፤ የመፋለም ብቃትና ቅልጥፍና ነው፡፡››
‹‹እየቀለድክ ነው?››
‹‹በፍፅም ….ስትፋለሚ እኮ ልክ እንደነብር ነው….ኢንተርፖል ነው ወይስ ሲአይ ኤ ነው የምትሰሪው?›› እንደቀልድ አስመስሎ በውስጡ ሲያብሰለስለው የቆየውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ዝም አለች….ለደቂቃ ትንፋሽ ወሰደችና..‹‹አንተም ሀለቃችሁን ለመሰለል በሆነ አካል ተቀጥሬ የተላኩ ሰላይ ነገር አድርገህ አምነኸል አይደል?››ስትል ጤቀችው፡፡
‹‹በፊት ፈጽሞ አላመንኩም ነበር…በህይወቴ ሁሉ ላሲዝ እችል ነበር፡፡ጥዋት እዛ የቆፈርነው ጉድጓድ ጋር እንዴት እኔን እንዳገትሺኝ.. እንዴት ሽጉጠን እንደነጠቅሽና ጓደኛዬንም የገደልሽበት ብቃትና ቅልጥፍናን ከየሁ በኃላ ግን እነሱ የጠረጠሩት ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜለው፡፡በጣም ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደና የረጅም ጊዜ የመስክ የፍልሚያ ልምድ የሌለው ሰው ካልሆነ በዛ ብቃት በመጨረሻው ሰዓት የሚፋለም ሰው የለም፡፡››
‹‹ስለወታደራዊ ስልጠናው ምናምን ትክክል ነህ…እኔ ግን ከኢንተርፖል ጋረም ሆነ ከምትላቸው ሲአይኤ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ..ሀለቃህን ያገኘሁት እንደማንኛውም ተራ ሰው በአጋጣሚ ነው፡፡››አለችው፡፡
ዝም አላት…የተናገረችውን እንዳላመናት ተሰምቷታል፡፡ ግን ደግሞ እሱን ለማሳመን ከዚህ በላይ ዝርዝር ጉዳዮችን ልትነግረው አልቻለችም….እሱን ከዚህ በላይ ትመነው ወይስ ይቅርባት መወሰን ተቸግራለች፡፡

👍66❤9🥰2
#ነገሩ_ገብቶኛል !
ጠዋት ቤትሽ መጣሁ
አንቺ ግን የለሽም፤ ቤተስኪያን ሄደሻል::
ያዉ፤ የገላገልሽዉ
የጉደሩ ጠርሙስ ባዶዉን ተኝቷል::
ስትንፈራገጪ ድንገት የረገጥሽዉ
ብርጭቆ ተሰብሮ፣ ወለሉን ሞልቶታል::
ብርድ ልብስሽ የለም
እንደአድፋጭ ዉሽማ፣ አልጋሽ ሥር መሽጓል::
አንሶላሽ ከፍቶታል
በሌሊቱ አበሳ ሽንሽን ቀሚስ መስሏል::
ግድየለሽም ፍቅሬ ነገሩ ገብቶኛል
በህልምሽ ከኔ ጋር፣ ተቃቅፈሽ አድረሻል::
እኔ አኩርፌሽ ብዬ፣ ጅሉ ልቤ ወልቋል::
አይ የልብሽ ጉዱ !
ዕምነትን መሻሩ፣ ልማድን መካዱ
ለብቻ እንዳደረ፣ ደሞ እንደጨዋ ልብ፣ ቤተስኪያን መሄዱ::
አይ የልብሽ ጉዱ !
ከስውር-ስፌት
🔘ነብይ መኮንን🔘
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ጠዋት ቤትሽ መጣሁ
አንቺ ግን የለሽም፤ ቤተስኪያን ሄደሻል::
ያዉ፤ የገላገልሽዉ
የጉደሩ ጠርሙስ ባዶዉን ተኝቷል::
ስትንፈራገጪ ድንገት የረገጥሽዉ
ብርጭቆ ተሰብሮ፣ ወለሉን ሞልቶታል::
ብርድ ልብስሽ የለም
እንደአድፋጭ ዉሽማ፣ አልጋሽ ሥር መሽጓል::
አንሶላሽ ከፍቶታል
በሌሊቱ አበሳ ሽንሽን ቀሚስ መስሏል::
ግድየለሽም ፍቅሬ ነገሩ ገብቶኛል
በህልምሽ ከኔ ጋር፣ ተቃቅፈሽ አድረሻል::
እኔ አኩርፌሽ ብዬ፣ ጅሉ ልቤ ወልቋል::
አይ የልብሽ ጉዱ !
ዕምነትን መሻሩ፣ ልማድን መካዱ
ለብቻ እንዳደረ፣ ደሞ እንደጨዋ ልብ፣ ቤተስኪያን መሄዱ::
አይ የልብሽ ጉዱ !
ከስውር-ስፌት
🔘ነብይ መኮንን🔘
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍27❤10😁4👏1
#አርምሞ.
.
.
ፍቅርና
ህብረት፥
አጥሩን ካልጣሰ
.
ንስሃና
ይቅርታ፥
ተበዳይ ካልካሰ
.
ፍርጠማና
ጡንቻ፥
ማዕበል ካልገታ
.
ጥበብና
ብስለት፥
ቋጠሮ ካልፈታ
.
ብትነቃም
ብታውቅም
አቅምህን
ሰብቀህ፥
እንደ ናዝሬት ጌታ
.
ሀቅህን
ባደራ
የምታኖርበት፥
የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ
.
ሽንፈት
እንዳይመስልህ
ቀን
ቆጥሮ
እሚያደባይ
አቅም ነው
ሃይል ነው
ጉልበት ነው #ዝምታ።
🔘ረድኤት አሰፋ🔘
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
.
.
ፍቅርና
ህብረት፥
አጥሩን ካልጣሰ
.
ንስሃና
ይቅርታ፥
ተበዳይ ካልካሰ
.
ፍርጠማና
ጡንቻ፥
ማዕበል ካልገታ
.
ጥበብና
ብስለት፥
ቋጠሮ ካልፈታ
.
ብትነቃም
ብታውቅም
አቅምህን
ሰብቀህ፥
እንደ ናዝሬት ጌታ
.
ሀቅህን
ባደራ
የምታኖርበት፥
የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ
.
ሽንፈት
እንዳይመስልህ
ቀን
ቆጥሮ
እሚያደባይ
አቅም ነው
ሃይል ነው
ጉልበት ነው #ዝምታ።
🔘ረድኤት አሰፋ🔘
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍28❤1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ደረቱ ላይ እንደተጋደመች..አይኖቾን ጨፍና ሀሳብ ውስጥ ገባች…በትዝታ ወደሚስኪን ሀገሯ ተመለሰች፡፡እንዴት ለጀመሪያ ጊዜ ከጓዳና ህይወት እራሳቸውን እንዳላቀቁ ነው ትዝ ያላት፡፡
ከ15 ዓመት በፊት /ኢትዬጵያ/አዲስ አበባ/
መንትዬዎቹ ከኩማደሩ ቢሮ እንደወጡ ቀጥታ ተንደርድረው ፊት ለፊት ያገኙት ካፌ ነበር የገቡት፡፡ሁለቱም ምሪንደ አዘው ውስጣቸውን እያቀዘቀዙ ለበርካታ ደቂቃዎች ያለንግግር በየራሳቸው እያወሩ አሳለፉ…
‹‹ወንድሜ ..ተይዘን ቢሆን ኖሮ የሆነ ነገር ያደርጉብኛል ብዬ በጣም ሰግቼ ነበር….››
‹‹እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ? ተይዘን ቢሆን ኖሮኮ ሁለታችንንም ነው የሆነ ነገር የሚያደርጉን..ወፌ ላላ ሁሉ ሊገርፉን ይችሉ ነበር…፡፡››ሲል መለሰላት
‹‹አውቃለሁ…ግን እኔ እችለዋለው..አንተን ግን በጣም ያምሀል››አለችው፡፡ አሁን የሆነ ይመስል በሰንበር የበላለዘ ጀርባውንና የቆሰለ ሰውነቱን በምናቧ እያይች ዝግንን አላት፡፡
‹‹አይ እህቴ ..አንዳንዴ እናቴ የሆንሽ ነው የሚመስለኝ..የ0 ደቂቃ ታላቅ ወንድምሽ መሆኔን ዘነጋሽው እንዴ?ለማንኛውም አሁን ስራችንን በስኬት አጠናቀናል፡፡ብዙ ገንዘብም አግኝተናል፡፡›
‹‹አዎ እሱ ጥሩ ነገር ነው….››
‹‹አዎ ..ጥሩ ነው ደጋግማ እንዲህ አይነት ስራዎችን እያሰራች እንዲህ ብዙ ብር ብትከፍለን በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹እስኪ መጀመሪያ የሰራንበትን ቀሪ ሂሳባችንን ትስጠን››
‹‹አረ ኑሀሚ…አሁንም ያቺን ልጅ ኣታምኚያትም ማለት ነው?››
‹‹ለምን ብዬ አምናታለው…ወላጆቼ ሰው በማመን ምን አተረፉ..ይገባሀል እኔ በዚህ ምድር ላይ ካንት በስተቀር ማንንም ሰው ማመን አልፈልግም››አለችው፡፡
‹‹በቃ አትቆጪ እንዳልሺ ይሁንልሽ..አሁን ሂሳብ ክፈይና እንውጣ፡፡››
‹‹ከብዙ ድፍን ብሮች መካከል አንድ ነጠላ መቶ ብር መዛ የሁለት ለስላሳ ሂሳብ ለአስተናጋጁ ሰጠችው፡፡ሂሳብን ቆረጠና መልሱን አመጣላት፡፡አምስት ብር ቲፕ አስቀመጠችለት..ናኦል ያደረገችውን አየና ፈገግ አለ…፡፡››
‹‹ምን ትገለፍጣለህ..እኛም ወግ ይድረሰን እንጂ፡፡ይሄን ያህል ብር ለሰው በቲፕ መልክ ስንሰጥ እኮ ይሄ የመጀመሪያ ቀን ታሪካችን ነው፡፡››አለችው፡፡
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ሳናስበው ታሪክ መስራት ጀመርን ማለት ነው?››በገረሜታ ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ..እየሰራን መሰለኝ፡፡››በዚህ ጊዜ ወደበረንዳቸው ተመልሰው ዘወትር የሚቀመጡበት ጥርብ ድንጋይ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል፡፡…ያንን ሁሉ ብር በኪሳቸው አጭቀው ይዘው ብዙ ብዙ ቦታ ሄደው ዘና ማለት እየቻሉ እዛ መቀመጥ አልነበረባቸውም፡፡ለምሳሌ ፊልም ቤት ገብተው ፊልም ማየት የሁለቱም ምርጫ ነበር፡፡ካልሆነም እናትና አባታችው መቃብር ጋር ሔደው ዛሬ የሰሩትን አስደናቂ ጀብዱም ሊነግሯቸው ይችሉ ነበር፤ግን አላደረጉትም ፡፡ ምክንያታቸው ምስራቅ እነሱን ፍለጋ ወደቋሚ ቦታቸው ስትመጣ እንዳታጣቸው ነው፡፡ግን በቀላሉ የምስራቅ ዱካ ሊሰማ አልቻለም፡፡ቦታው ላይ ስድስት ሰዓት የተቀመጡ እስከስምንት ሰዓት አልተንቀሳቀሱም ነበር፡፡
‹‹ወንድሜ ይህቺ ልጅ አብርታናለች መሰለኝ፡፡››
ኑሀሚ የተናገረችው እሱም በውስጡ እያሰላለስለ የነበረው ነገር ስለነበረ ለስለስ ባለ ቃል‹‹ለምን እንደዛ አልሺ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ይሄው እንደምታያት ቀረቻ….ጉዳዮ ከተፈፀመላት ለምን ብላ መጥታ ሁለት ሺ ብር ሙሉ ትሰጠናለች?››
‹‹ግድ የለሽም እንደዛ አታደርግም…ትንሽ እንጠብቃት፡፡››
‹‹አይ እኔ ደግሞ የምታደርገው ነው የሚመስለኝ…ጥዋት ሁለት ሺ ብር ብላን አልነበር..አይሆንም አራት አድርጊው ስላት…..አይሆንም ባይሆን ሶስት እንኳን ይሁን አላለችንም፡፡በአንዴ ነው የተስማማችው፡፡በወቅቱ እንደውም በውስጤ ምነው ስድስት ሺ ወይ ስምንት ሺ ባልኳት እያልኩ ነበር፡፡ግን ይሄው እሷ እኛን ለማበረታታት እና ስራዋን በሞራል እንድንሰራላት እንጂ እንደማትከፍለን ታውቅ ነበር፡፡
‹‹እና ተመልሳ አትመጣም እያልሺኝ ነው?››
‹‹አዎ እንደዛ ነበር ያሰብኩት ..ግን ተሳስቼያለሁ መሰለኝ››አለችው፡፡
ናኦል በእህቱ ንግግር ግራ ተጋባ..‹‹መቃዠት ጀመረች እንዴ?›› ሲል በውስጡ አልጎመጎመ፡፡
‹‹እህቴ አልገባኝም፡፡››
‹‹ያቹት መጣችልህ..››አለችው ከመንገድ ማዶ እየጠቆመችው፡፡
ናኦል በደስታ ፈንጥዞ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ…‹‹እውነትሽን ነው እህቴ? የታለች?››
ሱሪውን ያዘችና ወደታች እየጎተተች‹‹አረ ሼም ነው..ቁጭ በል፡፡ምንድነው እንዲህ መንሰፍሰፍ?እናትህ መሰለችህ እንዴ?››
ተመልሶ ቁጭ አለና.‹‹ነግሬሽ ነበር እኮ..እሷ እንደሌላው ሰው አይደለችም፡፡አትቀርም ብዬሽ ነበር…፡፡››
‹‹በቃ አፍህን ዝጋ እየቀረበች ነው፡፡››
ዝም አለና ሁለቱም አይኖቻቸውን እያቁለጨለጩ ስራቸው እስክትደርስ ይጠብቋት ነበር፡፡ምስራቅ እንደደረሰች በዝምታ መሀከላቸው ሰቅስቃ ገብታ ተቀመጠችና….‹‹እሺ ጩጬዎቹ እንዴት ሆነላችው?››ስትል ምንም ነገር እደማታውቅ ሆና ትጠይቃቸው ጀመር፡፡
‹‹አድርገናል…እንዳልሺን አስቀምጠናል፡፡››ሊያብራራላት ሞከረ፡፡
ኑሀሚ ኮስተር እንዳለች….‹‹ቀሪውን ብር ይዘሽ መተሻል››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹እህቴ ብሩ የት ይሄድብናል..?መጀመሪያ ስራውን በትክክል መስራታችንን ታረጋግጥና ቀስ ብላ ትሰጠናለች፡፡››በልምምጥ ሊያረጋጋት ሞከረ፡፡
‹‹አታርፍም እንዴ…በትክክል እንደሰራነውማ ገና ድሮ ነው ያወቀችው፡፡››በኑሀሚ ንግግር ምስራቅም ሆነች ወንድሟ ደነገጡ፡፡ናኦል..እነሱ ካልነገሯት እንዴት ታውቃለች ብላ ልታስብ እንደቻለች ስላልገባው ነው..ምስራቅ የደነገጠችው በልጅነቷ የአእምሮ ስልነት ስለተደመመች ነው፡፡
‹‹ማወቋን እንዴት አወቅሽ?››ሲል ጠየቀት፡፡
‹‹ነግረሺናል እኮ ..ዕቃውን እዛ ያስቀመጥነው አንቺ እዚ ሆነሽ ዛፓው የሚሰራውን ሁሉ ለመከታተል ነው፡፡አስቀምጠን እንደወጣን አንቺ ሰውዬውን መከታተል ጀምረሻል፡፡ያ ባይሆን ኖሮ ስትመጬ ፊትሽ ላይ ቁጣና ንዴት ይታይ ነበር፤አሁን ግን እርካታና ደስታ ነው የማነበው፡፡››አብራራችላት፡፡
ምስራቅ ኪሶ ገባችና የታጠፈ ብር በማውጣት ..‹‹ይሄው ሶስት ሺ ብር..አንድ ሺ ብሩ እንዳልሺው ስላስደሰታችሁኝ ቦነስ ነው፡፡››አለችና እጇ ላይ አስቀምጣላት…ከተቀመጠችበት ተነሳችና ናኦልን በፍቅር ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ቀጥ ብላ ተለይታቸው ሄደች፡፡
‹‹ምስራቅ…መች ነው የምትመጪው?››ጮክ ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹እዛ ቆቆር ቤት ወስደህ ቁርስ ምትጋብዘኝ ከሆነ ነገ ጥዋት እመጣለው፡፡››አለችው፡፡ ደስ ብሎት‹‹እጋብዝሻለሁ..እንዳትቀሪ፡፡››አላት ፡፡
‹‹እሺ አልቀርም፡፡››አለችውና ከእይታው ተሰወረች፡፡
ምስራቅን በአይኖቹ እስከመጨረሻው ሸኝቶ ወደ እህቱ ሲዞር የሰጠቻትን ብር እየቆጠረች ነበር፡፡በትዝብትና በገረሜታ ይከታተላት ጀመር፡፡
ጨረሰችና‹‹አዎ ትክክል ነች..ሶስት ሺ ብር ነው፡፡››
‹‹አይገርምም? ››አላት፡፡
ምን እንዳስገረመው ስላልገባት‹‹ምኑ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

👍65❤10👏1😁1
‹‹ቅድም እዛ ካፌ ለአስተናጋጁ 5 ብር ቲፕ ሰጠሸ…አሁን ደግሞ ለእኛ አንድ ሺ ብር ጭማሪ ተሰጠን፡፡››
‹‹እሱስ ይገርማል…እውነትህን ነው፡፡››
‹‹አሁን ምን እናድርግ?››
‹‹እስከዛሬ አድርገነው የማናውቀውን ሌላ አንድ ነገር እናድርግ፡፡››አለችው ..ሀሳቡ ድንገት ነው በአእምሮዋ ብልጭ ያለው፡፡እሱ ያሰበችውን ለመስማት በጉጉት ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹ምን እህቴ..?››
‹‹አልጋ ተከራይተን እንደር፡፡››
‹‹ምን?››ግራ ገባው ፡፡..እንዴት አሰበችው ሲል ተገረመ….?በቅፅበት በምታመጣቸው አስደንጋጭ ሀሳቦች ሁሌም እዳስደመሙት ነው፡፡ማብራራቷን ቀጠለች‹‹አዎ ይሄን ሁሉ ብር ይዘን ለምን እዚህ አፈር ላይ እንተኛለን፡፡ሻወር ወስደህ…ንፅህ አልጋ ላይ አንሶላ ገልጠህ ከላይ ንፅህ ብርድ ልብስና አልጋ ልብስ ደርበህ..ግድግዳና ጣሪያ ያለው ቤት ውስጥ መተኛት አልናፈቀህም..?››
‹‹በጣም እንጂ እህቴ በጣም ናፍቆኛል…ግን እውር ገና አይኑ እንደበራለት ምርኩዙን እንደሚጥል እኛም እንዳዛ መሰልን፡፡››አላት
‹‹ግድየለህም ይምሰል….በል ተነስ…..››ተያይዘው ሆቴሎች በርከት ብለው ወደሚገኙበት ሰፈር ሄዱ፡፡ መታወቂያ ስላልነበራቸው እና እድሜያቸውም ገና ጮርቃ በመሆኑ ምንም እንኳን ብሩ ቢኖራቸውም ቤርጎውን መከራየት ቀላል አልሆነላቸው፡፡ግን እነሱም በተለይ ኑሀሚ በቀላሉ ተስፋ የምትቆርጥ ልጅ ስላልሆነች ሌላ ዘዴ ዘየደች ፡፡ለአልጋ ክፍሏ ተጨማሪ 50 ብር ሰጥተው ያሰቡትን አልጋ አግኝተው በአሰቡት መንገድ ለማደር ቻሉ፡፡ያም ካሰቡት በላይ ጥልቅ ደስታና ለፍፁምነት የተጠጋ እርካታ አጎናፀፋቸው፡፡ናኦል በጥዋት ነበር ኑሀሚን አግለብልቦ ከቤርጎ ይዞት የወጣው፡፡ ሲቀሰቅሳት‹‹ወንድሜ ደግሞ ምን አለ ትንሽ ብንተኛ..?›ብላ ለምናው ነበር፡፡
‹‹ምነው ለሊቱን ሙሉ ተኝተሸ አይደል ያደርሽው ?አልጠገብሽም?››
‹‹እንዴ ትቀልዳል እንዴ ?እንዲህ እይነት ምቹ ክፍልና አልጋ ውስጥ ስልሳ ሶስት ቀን በተከታታይ ብተኛ እራሱ አልጠግብም፡፡››ስትል የእውነት የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን ችግር አለ? ብር አለን ዛሬ ማታም ደግመን እናድራለን..፡፡››ቃል ገባላት፡፡
‹‹አንተ ልጅ ይሄን ምቾት ለምደህ ወደጎዳናችን አልመለስም ብለህ እንዳታስቸግረኝ፡፡››ስጋቷን ተነፈሰች፡፡እንዲህ ልትናገር የቻለችው..በራሷ ሀሳብ ውስጥ እየበቀለ ያለው ተመሳሳይ ስሜት ስላለ ነው…ምን አለ ወደእዛ ጎዳና ባንመለስ የሚል…እሱም‹‹ባልመለስ ደስ ይለኛል.፡፡ለማንኛውም አሁን ቶሎ እንሂድ ምስራቅ መጥታ እንዳታጣን፡፡››አላት፡፡
‹‹ብታጣንስ ምን ችግር አለው?››በብስጭት ጠየቀችው፡፡
‹‹እንዴ ቁርስ ገዛልሻለሁ ብያትለሁ እኮ..አሁን ብታጣን ብሩን ሰስተን ነው የሚመስላት…ትቀየመናለች፡፡››
ሳቀችና‹‹ይሁንልህ፡፡››ብላ ክፍሉን ለቃ መንገድ ጀመረችለት፡፡ ..እሱም በደስታ ከኃላ ተከተላት፡፡ማደሪያቸው የነበረ ቦታ ሲደርሱ ገና አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር…ምስራቅን ለማግኘት ግን እስከሁለት ሰዓት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
‹‹ጩጬዎቹ ሰላም ናችሁ?››በተለመደ ሰላታዋ ተቀላቀለቻቸው፡፡
‹‹አለን..ሰላም ነን…ቆየሽ፡፡››አላት ናኦል፡፡
‹‹ባሌ አለቅ ብሎኝ ነው የቆየሁት››ስትል መለሰችለት፡፡፡
‹‹እንዴ..ባል አለሽ እንዴ?››በድንጋጤ እና በቅሬታ ጠየቃት፡፡፡
‹‹አለኝ ..ግን ፀባይ የለውም ..ሌላ ባል ካገኘው እፈታዋለሁ፡፡››አለችው፡፡
‹‹አዎ ብትፈቺው ይሻላል፡፡››አላት ናኦል
‹‹ፈታውስ ….አንተ ልታገባት ነው?››ኑሀሚ በንዴት ጠየቀችው፡፡
‹‹እስካድግ ከጠበቀቺኝ አገባታለሁ፡፡››
ምስራቅም‹‹አረ ጠብቅሀለው፡፡››አለችው በፈገግታ ተሞልታ፡፡
‹‹ብትጠብቅህስ ምን ዋጋ አለው…አንተ እስክታድግ እኮ እሷ ታረጃለች፡፡››ኑሀሚ ነች አብሻቂ ንግግር የተናገረችው፡፡
ናኦል እንደመበሳጨት ብሎ‹‹አንቺ ደግሞ ታርጃ ምን ችግር አለው…አሁን እንሂዳ ..ቁርስ እንብላ፡፡››አለ
‹‹..እኔም የመጣሁት ለቁሩሱ ነው፡፡››ብላ ተያይዘው ሄዱ፡፡እስከ 3 ሰዓት ድረስ እዛው ቁርስ ቤት ሲበሉና የባጥ የቆጡን እያወሩ ሲጫወቱ ነው የቆዩት፡፡
ከዛ ድንገት ‹‹የሆነ ቦታ አብራችሁኝ ትሄዳላችሁ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹የት?››ኑሀሚ በተለመደ ጥርጣሬዋ ጠየቀች፡፡
‹‹እሱ ሚስጥር ነው..ስንደርስ ታዩታላችሁ፡፡››
‹‹እሺ እንሂድ››ነኦል በግብዣው ተስማምቶ ከመቀመጫው ቀድሞ ተነሳ፡፡ምስራቅ እየፈገግች ኑሀሚ እየተነጫነጨች ከኃላው ተከትለው ተያይዘው ሄድ፡፡ቀጥታ ታክሲ ተራ ነበር ይዛቸው የሄደችው፡፡ከዛ ስታዲዬም ተሳፈሩ፡፡ከዛ ጎተራ ታክሲ ውስጥ ገቡ፡፡መጨረሻ ሲደርሱ ወረዱና ፡፡በእግር መጓዝ ጀመሩ፡፡በዝምታ ወደምትወስዳቸው እየተከተሏት ነው፡፡ቀጥታ ወደኮንደሚኒዬም ነው ይዛቸው የሄደችው፡፡አንዱ ኮንዲንዬም ውስጥ ይዛቸው ገባችና በደረጃው እየወጡ የመጨረሻ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል ይዛቸው ገባች ፡፡ቁልፍ ከኪሷ አወጣችና ከፈተቸ፡፡ቀድማ ገባችና ‹‹ግቡ›› አለቻቸው…ግራ በመጋባትና በመደነቅ ተከትለዋት ገቡ፡፡
የሚያምር ቤትና የሚያማማሩ እቃዎች ያሉበት ባለሁለት መኝታ ክፍል ቤት ነው፡፡ሳሎኑ መሀከል ወለል ላይ ቆመው በመገረምና በመደነቅ ዙሪያ ገባውን እየተቁለጨለጩ ማየት ቀጠሉ፡፡እለፉና ሶፋው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹በስመአብ ዘናጭ ቤት ነው…የድሮ ቤታችንን ይመስላል…ያንቺ ነው እንዴ?››ናኦል በአድናቆት እንደተሞላ ጠየቃት፡፡
‹‹አይ የወንድሜ ነው…ታስሮብኛል ያልኳችሁ ወንድሜ፡፡››
‹‹እ ነው… ታድሎ…››
‹‹ምን ታድሎ ትላለህ ..አምስት አመት እኮ ነው የተፈረደበት…ገና እስር ቤት ከገባ ስድስት ወሩ ነው..ቢያንስ ከሶስት አመት በላይ አዛ ይኖራል፡፡››
‹‹ያሳዝናል…››
‹‹አዎ ያሳዝናል..በሉ ዘና በሉ ፡፡ሱቅ ደርሼ መጣሁ፡፡›› ብላ ቴሌቪዢኑን ከፈተችላቸውና የፈለጉት ጣቢያ ላይ መቀያየር እንዲችሉ ሪሞቱን አቀብላቸው ወጥታ ሄደች፡፡
ኑሀሚም ኮቴዋ መራቁን እርግጠኛ ከሆነች በኃላ‹‹አልሰማ አልከኝ እንጂ ንግሬሀለው››አለችው፡፡
‹‹ምኑን ነው የነገርሺን?››
‹‹ይህቺ ሴት ማፍያ ነገር ነች…እያት እስኪ በየቀኑ እንድ አዲስ ነገር ታሳየናለች፡፡››
‹‹ቢሆን ግን ለእኛ እኮ ደግ ሆናልላለች፡፡››
‹‹የሸከከኝ እኮ እሱ ነው፡፡ለምን ደግ ሆነችልን….?ለምን አላማ ፈለገችን…?ብቻ ዝም ብለህ እትንሰፍሰፍላት፤በጥንቃቄ ተከታተላት፡፡››
በምትናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ ባያምንበትም ከእሷ ጋር ጨከን ብሎ መከራከሩን ሳላልፈለገ ‹‹እሺ እንዳልሽ፡፡››አላት፡፡
ወዲያው ምስራቅ በኩርቱ ፔስታል ሙሉ የቤት አስቤዛ ገዝታ መጣችና ፍሪጅ ውስጥ ትጠቀጥቀው ጀመር፡፡
../////
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባኖ ሲንሳቀስና ነበር እሷም ከጥልቅ ትዝታዋ ባና ከሀገር ቤት የቆየ ታሪኳ አሁን ወዳለችበት ነባራዊ ሁኔታ የተመለሰችው ፡፡በዛ ድቅድቅ ለሊት በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ማህፀን ውስጥ የተንጠለጠሉበት ግዙፍ ዛፍ ቀርንጫፍ ላይ ከአንድ ጎረምሳ ደረት ላይ ተለጥፋ መገኘቷን ስተስበው ተአምር የሚያስብል ሆኖ ነው ያገነችው፡፡

👍97❤23🥰5👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ደቡብ ኮሎምቢያ/የአማዞን ደን
ዳግላስ አንድ ወር ከራቀበት የግል ግዛቱ ሲመለስ ፍፁም የሆነ ደስታ ነው የተሰማው፡፡ከመኪናው ወረዶ የቅፅር ግቢውን አፈር እንደረገጠ በውስጡ ጎድሎ የነበረው ኀያልነቱ መልሶ ሲሰርግበት ተሰማው፡፡አፉን በደንብ ከፈተና አየሩን ወደውስጥ ምጎ በመሳብ በአፍንጫው አስወጣው፡፡.አሁን ያለበት የግል ግዛቱ የሆነው እንደቤተመንግስቱ የሚያየው ስፍራ አስር ሺ ካሬ ላይ ያረፈ ቅፅር ግቢ…ወደ ሰሜን አቅጣጨ ጠጋ ብሎ በአንድ ሺ ካሬ ሜር ላይ ያረፈ ግዙፍ ባለአንድ ፎቅ ህንፃ ሲኖር.. ህንፃው….ከመሬት በታች አንደርግራውንድ ቤት ሲኖረው ሙሉ በሙሉ መግቢያው በጀርበ በኩል ሚስጥራዊ መሹለኪ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ በውስጡ ሀያ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ከነረዳቶቻቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያለእረፍት ይሰሩባታል፡፡ ምን አልባትም በአለም ግዙፍ የተባለው የኮኬይን ቅመማ የሚካሄድበት የተሞላ የላባራቶሪ እቀዎች የተተከሉበት….በየወሩ አንድ 100 ኩንታል ኮኬይን ተቀምሞ፤ ተመርቶና በተለያየ መጠን በጥንቃቄ ታሽጎ በኮሎምቢያ …ፓናማና… ሚክሲኮን በመሸገር በአሜሪካ የሚገባበትና የሚሰራጭበት እስከአውሮፓ የሚዘልቅ ሰንሰለት ያለው ውስብስብ ስራ ነው፡፡
ኮኬይኑ እዛ ደርሶ ከተሰራጨ በኃላ ከሽያጩ ሚሰበሰበው ረብጣ ዶላል ለሁሉም ተወናዬች የየድርሻቸውን በማክፋፈል የቀረውን ዳጎስ የለ ድርሻ ለዳግላስ ተመልሶ የሚመጣበት አሰራር ነው ያለው፡፡ዳግለስ ለዚህ የኮከዬን ምርት ሚሆነውን የኮካ ዛፍ ምርት የሚያገኘው እዚሁ አሁን ካለበት ተያይዞ ካለ መቶ ሺ ካሬ ሜትር የእርሻ መሬት ነው፡፡ቀሪውን 60 ፐርሰንት ግን ከአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ በአማዘን ደን ወስጥ ሆነ ከዛ ውጭ ተበትነው በሚገኙ ከግለሰብ ሆነ ከብድን እምራቾች ጋር በፈጠረው የንግድ ስምምነት ይሰበስብና ጉድለቱን ያሟላል፡፡
ይሄን ጥሬ እቃውን ከእርሻ ቦታም ሆነ በክፍያ ከሚሰበሰብበት ቦታ የሚሰበበስቡ እንዲሁም የቢዝነሱን ሆነ የእሱን ድህነንት የሚጠብቁ…ግደሉ ሲላቸው የሚገድሉ፤ ሙቱልኝ ሲላቸው የሚሞቱላት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች አሉት፡፡የህንፃው ግራውንድ ላይ ደግሞ እታች ቤዝመንት ውስጥ ለሚሰሩት ሳይንቲቶችና ዋና ዋና የታጣቂ አዛዦች መኖሪያነት ያገለግለል፡፡ከላይ ያለው የመጀመሪያው ፍሎር ግን ለደግላስ የግል ቤተመንግስቱ ነው፡፡አንድ ግዙፍ ሳሎን፤30 የሚሆኑ መኝታ ቤቶች፤ከአምስት በላይ ቢሮዎችና በአጠቃላይ ከ50 በላይ ክፍሎች ከነቅንጡ እቀዎች ያሉበት ዘመናዊ ቤት ነው፡፡እዛው ቤት ውስጥ ደግላስና አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት አገልጋዬቹ ብቻ ናቸው የሚኖሩበት፡፡ከዛ ውጭ እሱ ኖረም አልኖረም ሳይፈቅለድት ወደ እዛ ህንፃ ለመውጣት የሚደፍር ሰው የለም፤ካለም በደግላስ ጥይት ወይ ግንባሩ ይፈረከሳል ወይ ደግሞ ደረቱ ይነዳላል፡፡
ሌላው የህንፃ ጣሪያ ከላይ እይታ እንዳይስብ አረንጓዴ ሳርና ቋጥኝ መሰል ተክሎች እንዲለብስ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ እይታው ከአማዞን ደን ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎል፡፡
የዳግላስን ወደቤቱ መምጡት አስመልክተው በስልፍ ሆነው የእንኳን በሳላም መጣህ አቀባበል ሊያደርጉለት እየጠበቅ ያሉትን ታጣቂዎችና ሌሎች ሰረተኞችን ቀላል እና አጭር ሰላምታ ሰጠና ቀጥታ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሔደ፡፡ከዛ ወደዋናኛ መኝታ ቤቱ ነው የገባው፡፡አሁንም ያቺ ጠፋች የተባለችው ኢትዬጵያዊት ሴት በአእምሮው እየተመላለሰች ነው፡፡እሷን እንዳገኞት እስክያበስሯት ድረስ ተረጋግቶ ስራውን በስርአት መስራት እንደማይችል ገብቶታል፡፡ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ስልኩን አወጣና መልሶ ላንቲኒያ ወደሚገኙ የእሱ ሰዎች ደወለ ‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹ሁሉንም ሰው አስማሪቼለው..እስከአሁን አዲስ ነገር አላገኘንም፡፡››
‹የልጅቷ እቃዎች አሉ?››ሲል ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡
‹‹የእጅ ቦርሰዋን ይዛ ነው የሄደችው… የልብስ ሻንጣዋ ግን አሁንም ከእኛ ጋር ነው፡፡››
‹‹ውስጡ ምን አለ?››
‹‹እኔ እንጀ! እስከአሁን ከፍተን አላየነውም፡፡››
‹‹ክፈተው››
‹‹እሺ…››
ከተወሰነ ደቂቃ ዝምታና መተረማመስ በኃላ…‹‹ሻንጣው ተቆልፏል እንዴት ላድርግ?››የሚል ቃል ተሰማ፡፡
‹‹አንተ ጀዝባ …ስረህ አልመሆኔ በጀህ እንጂ በዚህ ጥያቄህ ግንባርህን ነበር የመነድልልህ…በጩቤ ዘንጥለህ ክፈተው››አንቦረቀበት፡፡
እንዳለው ከጎኑ የሻጠውን ጩቤ አወጣና የኑሀሚ ሻንጣ ከጉን በኩል ቦትርፎ ከፈተው፡፡ ውስጥ ያለውን እቃ እንዳለ ወለሉ ላይ ዘረገፈ…ቀሚሶች..ጅንስ ሱሪ…ፓንቶች…ጡት ማስያዣ… ማስተወሻ ደብተር……በቀ ይሄው ነው ያለው፡፡››
‹‹በቃ..››በብስጭት ጠየቀ
‹‹አዎ ..ቆይ…ሌላ አንድ አይፓድ አለ፡››
‹‹አዎ እንደእሱ አይነት እቃ ነው የምፈልገው…ክፈተው፡፡››
‹‹እ››ብሎ ለመክፈት ማከረ..ግን አልሆነለትም፡
‹‹አበራሁት …ግን ልከፍተው አልቻልኩም… ፓስ ወርድ አለው››
‹‹በቃ..በቃ አሁኑኑ..ተነስና ለሊቱንም ተጉዘህ ወደእኔ ይዘኸው ና…..ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ አይፓዱን ካላገኘው..በቃ ሟች ነህ››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡
ታጣቂው ወዲያው ነበር ጊዜ ሳያባክን አይባዱን እና የቦተረፈውን ሻንጣ መልሶ ከፍቶ እቃዎችን ወደውስጥ በመመለስ ይዞ ከአካባቢ ገበሬ አንድ ፈረስ ተውሶ ዳግለስ ወደሚገኝበት ሳንቹዋሪ ሽምጥ መጋለብ የጀመረው፡፡
ዳግላስ ጥዋት በጠበቀው ሰዓት አይፓዱ ደረሰው፡፡ እዛው የእሱ ሰረተኛ በሆነ የኮምፒተር ባለሞያ ሀክ አስደርጎ ፓወርዱን ካሰበረ በኃላ ውስጡን ማየት ጀመረ፡፡
የፎቶ አይነት ..እርቃኗን የተናሳችውን ጭመር ..ቪዲዬዎች..፡፡አብዛኛዋቹ ፎቶዎቸና ቪዲዬዎቸ በእሷ አድሜ አካባቢ ካለ ወጣት ጋር አብራ ስትስቅ ..አልያም እላዩ ላይ ተንጠልጥላበት..አዝላው ወይም አዝሏት የተነሱት ወይም የተቀረፁት ነው፡፡ፍቅረኛዋ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ፡፡አይፓዱን ከኢተርኔት ጋር አገናኘና የተላኩላትን ብዙ መልእክቶች ተመለከተ፡፡ግን በማያውቀው ቋንቋ ስለሆነ መረዳት አልቻለም፡፡ወደጎግል ገበና የኢትዬጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ምን እንደሆነ ጠየቀ፡፡አማርኛ የሚል መልስ አገኘ፡፡አማርኛ የሚባል ቋንቋ መኖሩን እራሱ አያውቅም ነበር፡፡የሀገሬው ቋንቋ እንደሆነ ተረድቷል፡፡ በጣም ነው የተገረመው፡፡በደቡብ አሜሪካ ያሉትን ሀገሮች አሰበ…ፔሩ ፤ኮሎምብያ፤ አርጀንቲና ብሄራዊ ቋንቋቸው እስፓኒሽ ነው..ብራዚል በፖርቹጊዝ ቋንቋ ነው የምትገለገለው፤ኢጎና እንግሊዘኛ ነው ..እንደዛ እያለ ይቀጥላል፡፡ቢያስብ ቢያስብ አንድም ሀገር የራሱን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋው አድርጎ የሚጠቀም ሊያስታውስ አልቻም፡፡ሀሳቡን ተወና ጎግል ትራንስሌት ከፍቶ መልእክቶቹን ኮፒ ፔስት እያደረገ ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ በመቀየር ለመረዳት ሞከረ፡፡በጣም ነው የተገረመው፡፡ያ ሁሉ መልእክት ከወንድሟ እንደነበረ..እና እሷ በመጥፋቷና አድረሻዋን ሊያገኝ እንዳልቻለ በመጨነቅ በተደጋገሚ ጊዜ የላከላት መልእክት ነው፡፡…ፍቅረኛዋ ነው ብሎ ያሰበው ወንድሟ መሆኑን ሲያውቅ ደስ አለው፡፡በዚህ መጠን የሚተሳሰቡና የሚወደዱ ወንድም እና እህት መኖራቸውን ተጠራጠረ…የእሱን የራሱን ወንድምና እህቶች አሰበና በመሀከላቸው ያለውን መግባባትና ፍቅር መዝኖ ፈገግ አለ፡፡በዘ ቅፅበት ያላሰበው ተንኳል በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡ይህቺ ሴት አምልጣ የመንግስት ተቋም ያለበት አካባቢ በህይወት መድረስ ብትችል እንኳን

👍74❤15😁2🥰1
ስለእሱ ምንም እንዳትናገርና ከዛም አልፎ መልሳ በፍቀዷ እጁ እንድትገባ ማድረግ የሚያስችል ዘዴ ነው የመጣለት፡፡በጣም ደስ አለው፡፡በጥንቃቄ አስቦ ቆንጆ ኢሜል አዘጋጀ፡፡ኢትዬጵያ ለሚኖረው ለኑሀሚ ወንድም ኑሀሚ እሱ ጋር እንዳለች አስመስሎ ከፎቶ ጋር በማያያዝ ..እህቱን ማግኘተ ከፈገ ጉዳዩን ለማም ሳይናገር በሚስጥር ሹልክ ብሎ በአስቸኳይ ወደደቡብ አሜሪከ መምጣት እንዳለበት ገልፆ ላከለት፡፡ መልስ እስኪመለስለት የኬኬይን ቅመማውን እና የምርት ስራውን ለማየት ወደቤዝመንት ተጓዘ፡፡
አዲስ አበባ-ኢትዬጵያ
ናኦል የእህቱን መጥፋት በተመለከተ እስከአሁን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ መረጃ ከመስሪያ ቤቷም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያገኘ አይደለም፡፡ምስራቅም ሳምንቱን ሙሉ የሆነ ነገር ለማግኘት የተቻላትን ሁሉ እየጣረች ቢሆንም እስከአሁን ስለመሞቷም ሆነ በህይወት ስለመኖሯ ምንም አይነት ፍንጭ ልታገኝ አልቻለችም፡፡ዛሬ ግን እቤቱ ቁጭ ብሎ በእንባ እየታጠበ ማህራዊ ሚዲያዎቹን እያየ ባለበት ሰዓት በኢሜል አዲስ አይነት መረጃ ደረሰው፡፡መልክቱ ሲነበብ
እህትህን በህይወት ማግኘት ከፈለክ ለየትኛውም መንግስታዊ ተቋም መረጃ ሳትሰጥ ወደ ፔሩ ና …ወደ እህትህ የምትመጣበት 50 ሺ ዶላር በሳምንት ውስጥ ይላክልሀል፡፡ ማን ናቸው? ለምንድነው ይሄንን መልዕክት የላኩልኝ ?ብለህ ሌላ ምርምር ውስጥ እንዳትገባ…እንደዛ ከሆነ ግን እህትህን ታጣታለህ፡፡
ብሎ ከእህቱ ፎቶ ጋር አያይዞ ተልኮላታል፡፡
ወዲያው ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡ያው ወደመከረኛዋ ምስራቅ ጋር ነው የደወለው፡፡
‹‹ምስራቅ እህቴን››
‹‹ምን ሆነች? ምን ሰማህ?፡፡››በድንጋጤ ተውጣ ጠየቀችው፡
‹‹አሁኑኑ መገናኘት አለብን ..››
‹‹የት ነህ ?››
‹‹እቤት ነኝ…የት ልምጣ?››
‹‹አይ እኔ መጣሁ… እዛው ጠብቀኝ፡፡››ብላ ስልኩን ዘጋችበት፡፡
በተቀመጠበት ሆኖ እስክትመጣ መጠበቅ አልቻለም፡፡እቤቱን ለቆ ወጣና ግቢ ውስጥ መንጎራደድ ጀመረ….‹‹ማነው የሚቀልድብኝ?››ጥያቄውን ጠየቀ እንጂ መልስ ማግኘት አልቻለም፡፡
‹‹ደግሞ ቀልድ ነው እንደይባል ፎቶውን ከየት ሀገር ውስጥ የተነሳችው እንዳሆነ ያስታውቃል፤የለበሰችውን ልብስ እንኳን ከሚያውቃቸው የእሷ ልብሶች መካከል አይደሉም‹‹እዛ ከሄደች በኃላ የገዛችው መሆን አለበት›› ሲል አሰበ፡፡ከ20 ደቂቃ ጥበቃ በኃላ የውጭ በራፍ መጥሪያ ተንጣራራ፡፡ ሰራተኛዋ ለመክፈት ከሳሎን ስትወጣ ተንደርድሮ ቀደማትና ሄዶ ከፈተው፡፡ምስራቅ ነች፡፡፡በራፍን በደንብ ከፈተው፡፡ መኪናዋን ወደጊቢው አስገባች፡፡እንዳቆመችና ከመኪናው እንደወረደች ክንዷን ይዞ እየጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ይዞት ገባ፡፡ ሰራተኛዋ ሁኔታውን በገረሜታ እያየች በድንጋጤ እጇን በአፏ ከድና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡
መኝታ ቤት እንደገቡ ቀጥታ ላፕቶፑ ወዳለበት ቦታ ነበር ይዞት ነው የሄደው፡፡ላፕቶፑን ከፈተና ኢሜሉን እንድታነበው ዞር አለላት፡፡አንብባ እና ፎቶውንና አይታ እስክትጨርስ መኝታ ቤቱ ውስጥ እየተንጎራደደ በጭንቀት ተወጣጥሮ ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡››
‹‹አዎ ከመግረምም በላይ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው፤አሁን ምንድነው የምናደርገው?፡፡››
‹‹ቆይ እስኪ መጀመሪያ የመልዕክቱን ትክክለኝነት እናረጋግጥ፡፡››
‹‹እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?፡፡››
እንደማሰብ አለችና ከለበሰችው ጅንስ ሱሬ ኪስ ውስጥ እጇን ሰዳ አንድ ፍላሽ አወጣችና ላፕቶፖ ላይ ሰካች ፡፡››
‹‹ምን እያደረግሽ ነው?››
‹‹አንድ ዋናው መስሪያ ቤት የምንጠቀምበት ሶፍት ዌር አለ ፡፡ በትክክል ኢሜሉ ከየት እንደተላከ የሚያሳውቀን ሶፍትዌር ነው…››
‹‹ያማ ከተቻለ ጥሩ ነዋ..ኢሜሉ ከየት እንደተላከ ካረጋገጥን እህቴም የት እንዳለች የምናረጋግጥ ይሆናል››በደስታ ዘለለ፡፡
‹‹በጣም እድለኞች ከሆን አዎ…ግን አማተሮች ከሆኑ ነው እንደዛ የሚያደርጉት፡፡››
ሶፍት ዌሩን ጫነችና ኤሜሉን ከፈተች …አስሶ ውጤቱን እስኪያሳውቃት ለደቂቀዎች በዝምታ ስታሰላስል ቆየች፡፡
‹‹እ ምን አገኘሽ?››
‹‹ሁለት ነገር ነው ያገኘሁት..››
‹‹ምንና ምን?››
‹‹ኢሜሉ የተላከው ከዛው ኑሀሚ ካለችበት ደቡብ አሜሪካ ነው››
‹‹አሪፍ ነዋ…መልዕክቱ የእውነት ነው፡፡››
‹‹አዎ መሰለኝ፡፡››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››
ይሄ ሶፍትዌር አሁን እያሳየን ያለው ኢሜሉ የተላከበትን ቦታ ማለቴ ነጥቦችን ነው የሚያሳየው ፡፡ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ከሆነ ቀበሌውን ሳይቀር ያሳያል…ናይሮቢ ከሆነ እንዳዛው..››
‹‹እና አሁን ደቡብ አሜሪካ የትኛው ሀገር የትኛው ከተማ ነው ምልክቱ የሚያሳየው፡፡››
‹‹ችግሩ ያ ነው..ሰዎቹ ፕሮፌሽናል ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ነጥብ በአህጉሪቱ ባሉ ሶስት ሀገሮች ውስጥ ባለ የተለያዩ ሀያ ቦታዎች ላይ ነው የሚያመለክተው፡፡ብራዚል ፤ቤሩ፤ ኮሎምቢያ፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡ቆይ ከእህቴ ምንድነው የሚፈልጉት…የኢትዬጵያ መንግስትን አምርረው የሚቃወም አሸባሪ ቡድን እዛ አካባቢ ይንቀሳቀሳል እንዴ?ምን አልባት በእናንተ ስራ እህቴን የመስዋእት ጭዳ አድርጋችኋት ይሆን ?››ሲል ሰሞኑን በአእምሮ ሲጉላላበት የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹እስከአሁን ከእኛ መስሪያ ቤትም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዛም አልፎ በአካባቢው ሀገሮች ካሉን የእኛ ኢንባሲዎች ባጣራሁት መሰረት ከእኛ ስራ ጋር ሆነ ከሀገራችን ጋር ምንም የሚያገኛኘው ነገር የለም፡፡ .እንደውም አንድ ያለው ጥርጣሬ የአማዛን ደን ጥሬ ዕቃ የጎማ ተክል እየመነጠሩ ለፋብሪካቸው ጥሬ እቃ በማጋበስ ዶላር የሚዝቁ ኩባንያዎች ስብሰባውን ያዘጋጀው የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ እንቅስቃሴን ሴሚናሩ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲቀነቀን የነበረው እንዴት አድርገን በደኑ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱትን አውዳሚ ካማፓኒዎችን አደብ እሲዘን ከአካባቢው እስከወዲያኛው እንዴት እናስወግዳቸዋለን የሚል እንደሆነ ሰምቼለው፡፡እንደዛ አይነት ቅስቀሳና እንቅስቃሴ ደግሞ በዶላር ጡንቻቸው የፈረጠመውን እነዛን ከደኑ ተጠቃሚ የሆኑ ካማፓኒዎቹን ሳያስቆጣ አልቀረም፡፡እንደኔ ጥርጣሬ ምንአልባት ከካማፓኒዎች አንዱ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት በቅጥር ነፍሰ ገዳዬች ወይም አጋቾች ቀጥሮ ያስደረጉት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡››
‹‹ያልሽው ሊሆን ይችላል…ለጊዜው ግን እሷን ለመፈለግ እስካልረዳን ድረስ የተጠለፈችበት ምክንያት ምንም አይረባንም፡፡ለማንኛውም አሁን ሳስበው በኮምፒተሩ ላይ ኤሚሉ የተላኩባቸው ያልሻቸው ሀያ ቦታዎች እኮ ብዙ አይደሉም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበረን በአካባቢው ያሉ ኤምባሲዎቻችን የየሀገሩን መንግስት ትብብር ካገኙ ሀያ ቦታዎችን ፈልጎ ማረጋገጥ በሁለት በሶስት ቀን የሚሰራ ቀላል ተግባር ነው፡፡››
‹‹አዎ ባልከው እስማማለሁ፡፡እነዚህ ሀያ ቦታዎች ልክ እንደ አዲስአበባ፤ሀዋሳ ፤መቀሌ፤ድሬደዋ…ምናም አይነት ከተሞች ቢሆኑ ቀላል ነበር፡፡ግን እነዚህ ሀያ ቦታዎች በሶስት የተለያዩ መንግስታት በሚተዳደሩ ሶስት የተለያዩ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሰው ይኑርበት አይኑርበት በማይታወቁ ቦታዎች የተበተኑ ምልክቶች ናቸው፡፡እንዴት አድርገህ ነው ምስራቅ አፍሪካን ከሚያህል የደን ውስጥ አንድ ሰው ፍልጎ ማግኘት የሚቻለው››
ተስፋ ቆርጦ በቆመበት ግድግዳውን ተደገፈና ቀስ እያለ የተንሸራተተ …ወደወለሉ ወረደና በቂጡ ዝርፍጥ ብሎ ተቀመጠ፡፡

👍95❤11👏4😢3🤔2🥰1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ምስራቅ ኮስተር ብላ ‹‹አትልፈስፈስ…ጠንከር ብለህ መሆን ስለሚገባው ነገር ብቻ እንነጋር፡፡››አለችው፡፡
ናኦልም‹‹ምን የሚሆን ነገር አለና እንነጋራለን…በዚህ ምድር ላይ አንድ አለቺኝ የምላት እህቴን እንዲህ ባለ ሁኔታ አጥቼያት እኔስ በህይወት መኖሬን ቀጥላለው?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹አይዞህ ኑሀሚ እንደዚህ ካሉ ብዙ አደጋዎች ሰርቫይቭ የማድረግ ልምድ ያላት ልጅ ነች፤ደግሞ በምድር ላይ ያለችህ እሷ ብቻ አይደለችም..እኔም እኮ ስላለሁ መሰለኝ አሁን በዚህ የሀዘንህ ወቅት አጠገብህ ያለሁት፡፡
‹‹እሱማ እውነትሽን ነው፡፡››
‹‹እኮ ..በል ተነስና መልስ እንመልስለት፡፡››
ከተዘረፈጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ‹‹ምን ብለን?››
‹‹ያልከኸውን አደርጋለው..ለማንም ሳልናገር ያልከው ሀገር ድረስ እመጣለሁ..ግን እህቴ በህይወት መኖሯን በምን አውቃለሁ?አንድ ማረጋገጫ ስጠኝ፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ ብንለው ይሻላል አይደል…?ወይ ተጨማሪ ፎቶ ወይ ቪዲዬ ይልክልናል፡፡ወይ ደግሞ በስልክም ሊያገናኘን ይችላል፡፡››
‹‹በቃ ራስሽ ፃፊው››
እንደማሰብ አለችና ፃፈችና ላከች፡፡መልስ እስኪመጣ ለመጠበቅ ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ፡፡ለሁለቱም የሚጠጣ ቢራ አቀረበና እሱን እየጠጡ በትካዜ በስልኩ ከአሁን አሁን የሚላከውን ኢሜል መጠበቅ ቀጠለ፡፡
ከሶስት ሰዓት በኃላ ተጨማሪ ፎቶ ተላከላቸው፡፡እንሱ ያላወቁት እነዛ ፎቶዎች የተመረጡት ከኑሀሚ ስልክ ውስጥ በፔሩ ቆይታዋ በተያዩ ጊዜያቶች ከተነሳቸው ውስጥ የተመረጡትን ነው፡፡
ከፎቶ ጋር አጭር መልዕክት ተልዕኮል
‹‹ባቀረብንልህ ሀሳብ ከተስማማን አሁኑኑ አሳውቀን፡፡››ይላል፡፡
‹‹እ ምን አሰብሽ? ››አለት፡፡ ከምስራቅ የተሻለ ሀሳብ ለማግኘት እየተመኘ ጠየቃት.. ምርጫ የለንም ‹‹ተስማምቼያለሁ ብለህ ላክላቸው፡፡››እንዳለችው አደረገ፡፡
በል የጉዞ ሰነዶችህን አዘጋጅ…በሶስት ቀን ውስጥ አስፈላጊውን ገንዘብ ስለምንልክልህ ሙሉ ስምህን እና አስፈላጊ መረጃዎችን ላክልን፡፡እንደተነጋገርነው ግን ይሄንን ሚስጥር ሌላ ለሶስተኛ ወገን ለመንግስት አሳልፈህ ብትሰጥ ነገሮች ሁሉ ያከትምላቸዋል….ከዛ በኃላ
እህትህን በዚህ ምድር ላይ ዳግመኛ የማግኘት እድልህ ከዜሮ በታች ይሆናል…በል ፍጠን ይላል፡፡
‹‹አነበብሽው አይደል?››
‹‹አዎ ..አነበብኩት..››አለችና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
‹‹ምነው? ››
‹‹ልሄድ ነው፡፡››
‹‹ልሄድ ነው በእንደዚህ አይነት በተሰባበርኩበት ሁኔታ ላይ ሆኜ ጥለሺኝ ልትሄጂ ነው….፡፡››
‹‹ጎረምሳው ተረጋጋ እንጂ ..ይልቅ እራስህን ለረጅምና አስቸጋሪ ጉዞ አዘጋጅ፡፡እኔ ሄጄ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ፖስፖርትና ቢዛዎችን ላዘጋጅ፡፡ ታውቃለህ እነዚህን የጉዞ ሰነዶች በአሁኑ ጊዜ በስድስት ወር ውስጥም ማግኘት አይቻልም፡፡አኔ ደግሞ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማግኘት
አለብኝ፡፡ ለዚህ ደግሞ ደቂቃዎችን ሳላባክን ከአሁን ያለኝን ኃይልና መስመር ሁሉ ተጠቅሜ ማሳካት መቻል አለብኝ…እ ምን ትላለህ ጎረምሳው?››
ተንደረደረ ሄደና ተጠመጠመባት፡፡እሷም እጆቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመቻቸው… ጭምቅ አደረጋት፡፡
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ሁሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ዘላለም በእቅፍሽ ውስጥ መኖር ነው ምኞቴ…በጣም ነው የምወድሽ….››አላት
‹‹….ተራጋጋ፡፡ከዚህ በላይ ከወራን እንባዬ ያመልጠኛል፡፡››አለችና ከእቅፉ ወጥታ ፈዞ በቆመበት ፊቷን አዙራ ወጥታ ሄደች፡፡በቦዘዙ አይኖቹ በስስት እያያት በሀሳቡ ሸኛት፡፡..
///
ከሶስት ቀን በኃላ በአለምአቀፍ የሀዋላ አስተላላፊዎች አማካይነት 50 ሺ ዶላር ተላከለት፡፡ያልጠበቀው ነገር ነበር፡፡ብሩ ሲደርሰው ነገሩ ሲሪዬስ እንደሆነ እሱ ብቻ ሳይሆን ምስራቅም ተገነዘበች፡፡ሁለቱም መመለስ ያቃቸው ይሄ ሁሉ አጋቾቹ ይሄን ሁሉ ኢንቨስትመንትና ጥረት የሚያደርጉት ከእሷ ምን ፈልገው ነው? የሚለውን ነው ፤የእሱንስ ወደፔሩ መሄድ ለምን ፈለጉት?››በተለይ ይሄን ጥያቄ ከአንደበቷ አውጥታ ለእሱ አትንገረው እንጂ ምስራቅንም በጣም ነው ያሳሰባት፡፡
ናኦል ገንዘቡ እንደደረሰው ካወቀ በኃላ እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም፡፡ሰዓቱ ገፍቶ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኖኛል በተኛበት አልጋ ላይ እየተገላበጠ በትዝታ ወደኃላ ወደልጅነታቸው ተጓዘ፡፡ምስራቅ እሱና ተወዳጅ እህቱን ከጎዳና አንስታ እንዴት ሰላይ እዳደረገቻቸው በዝርዝር ትዝ አለው፡፡
ከ15 አመት በፊት ምስራቅ የወንድሜ ቤት ነው ብላ ከጓዳና አንስታ ጎተራ የሚገኝ ኮንደምንዬም ቤት ከወሰደቻቸው በኃላ ከአዛው ቤት ሳይወጡ ሁለት ወር ሙሉ ቆይተው
ነበር፡፡ በሶስተኛው ወር ግን ማታ እራት በልተው ቴሌቬዥን እያዩ እያለ ድንገት ሪሞቱን አንስታ ቴሌቪዝኑን አጠፋችና ፊት ለፊታቸው ቁጭ አለች፡፡
እህትና ወንድም እርስበር ተያዩ ፡፡የሆነ ነገር ልትነግራቸው እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡፡ግን የጠረጠሩት በቃ እስካሬ ለሁለት ወር በምቾትና በድሎት በወንድሜ ቤት አኑሬያችኋለው፤ ከአሁን በኃላ ግን ምትኖሩበት ቦታ ፈልጉ ›› ትለናለች ብለው ነበር የጠበቁት፡፡ይሄንን ጉዳይ እሷ ቤት በማትኖርበት ጊዜ እያነሱ ተወያይተውበታል..ለዛ ነው በፍጥነት ወደሁለቱም ምናብ ሀሳቡ የመጣው፡፡
‹‹ልጆች በጣም እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ አይደል?››
‹‹አዎ እናውቃለን፡፡ እኛም በጣም እንወድሻለን››ሲል የመለሰላት ናኦል ነበር፤ኑሀሚ ግን ይሄንን ቤት ለቀው ከወጡ በኃላ ምን ማድረግ እንዳለበባቸው ስታሰላስል ነበር፡፡ደግማኛ ወንድሟን ይዛ ወደበረናዳ ለመመለስ ፈፅሞ ፍቃደኛ አልነበረችም፡፡ትንሽም ቢሆን የራሳቸው ቤት ተከራተው መኖር እንዳለባቸው ከወሰነች ሰነባብታ ነበር፡፡ለዛ ኪራይ ቤት ክፍያ ሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ደግሞ ማንኛውንም ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ነበረች፡፡ ለወንድሟ ስትል ብትሰርቅም ብትገድልም ግድ አልነበራትም፡፡
ምስራቅ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ይሄውላችሁ ምን መሳላችሁ…አንደእኔ እንደእኔ ዘላለም እዚሁ አንድ ላይ እንዲህ እየተሳሰብን በፍቅርና በደስታ መኖር ብንችል ደስ ይለኝ ነበር… ግን ያው ታውቃላችሁ አይደል?››
ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባች‹‹ማለት የምትፈልገውን ፍርታ ማለት ባለመቻሏ ሁለቱም ላይ ጭንቀት ፈጠረች…ኑሀሚ ፈጠን አለችና‹‹ይገባናል..እስከዛሬ ስለተንከባከብሽንና በዚህ ሁኔታ እንድናገግምና ስለወደፊታችን እንድናስብ ስላደረግሽን የላለም ባለውለታችን ነሽ፤ግን ወንድሜን ይዤ ወደበረንዳ መውጣት አልፈልግም…ከቻልሽ ለእኛ ምትሆን ትንሽ ቤት
ተከራይተን መኖር እንድንችል አግዢን፡፡ማንኛውንም ያገኘነው ስራ በመስራት የቤት ኪራዩን በመክፈል እራሳችንን ማኖር አያቅተንም…እቤት ካገኘን ነገ ተነገ ወዲያ እንሄዳለን..አንቺ አታስቢ››
ምስራቅ ፈገግ አለች‹‹እንዳዛ ማለቴ አይደለም፡፡እኔ እንደምታዩት እዚህ የምኖረው ብቻዬን ነው፡፡ ቤቱም ሰፊና ለሁላችንም የሚበቃ ነው፡፡እዚህ ከእኔ ጋር በመኖራችሁ በጣም ተጠቃሚው እናናተ ሳትሆኑ እኔ ነኝ….ግን ለእናንተ የወደፊት ህይወት ሲባል የተለየ መንገድ መከተል አለብን፡፡››
ሁለቱም ስሜታቸው ይበልጥ ተናቃቃ፡፡የምትላቸው በፍፅም እየገባቸው አይደለም፡፡
‹‹አልገባንም›› አለች..ኑሀሚ፡፡

👍84❤7😱1
‹‹ያው አብረን በቆየንባቸው ጊዜቶች በተናጠልም ሆነ አንድ ላይ በተጫወትናቸው ጫወታዎች ወዲፊት ምኞታችሁንና ህልማችሁን ለመረዳት ችያለው፡፡ለምሳሌ የኑሀሚ ዋናው ህልም የወላጆቻችሁን በግፍ የተነጠቀ ቢላ ቤት በሆነ መንገድ ማስመለስ ነው.፡፡የናኦል ደግሞ ሀብታም ሆኖ እህቱን መንከባከብና ምንም አይነት ችግር እዳይገጥማት ማድረግ ነው..ተሳሳትኩ፡፡››
‹‹አረ ትክክል ነሽ፡፡››ሁለቱም በጋራ መለሱላት፡፡
‹‹ይሄንን ምኞታችሁን ለማሳካት ምን ያህል መስዋእትነት ለመክፈል ፍቃደኛ ናችሁ?››
‹‹እኔ ሙሉ አዲስአበባን ማቃጠል ካለብኝ አቃጥላለው››አለች ኑሀሚ፡፡
‹‹እኔም አደርገዋለው›› መለሰ ናኦል፡፡
‹‹አዲስ አበባን ማቃጠል አይጠበቅባችሁም…እናንተ ጠንካራ ፤ሚስጥር ጠባቂ፤ታታሪና ከሆናችሁ ይሄንን ህልማችሁን እውን ለማድረግ እንድትችሉ እኔ ልረዳችሁ እችላለሁ..››
‹‹እንዴ እህቴ እውነትሽን ነው…?ያልሺኝን እናደርጋለን፤ካንቺ ቃል ውልፍች አንልም፡፡››
ፊቷን ወደ ኑሀሚ አዞረችና የሆነ ነገር እንድትል ትጠብቃት ጀመር…..ኑሀሚ ረዘም ያለ ደቂቃ ስትተክዝ ቆየችና እንባዋን እያንጠባጠበች‹‹…ለእኔ ያንን የወላጆቼን ቤት መልሶ ማግኘት ገነት የመግባት ያህል ነው የምጓጓለት፡፡እሱን መልሰን የራሳችን እንድናደርግ ከረዳሺን ምንም ነገር ብትይን ምንም ያለማወላወል እንደምናደርገው እርግጠኛ ሁኚ፡፡››
‹‹ጥሩ ….እንደዛ ከሆነ የምትፈልጉት ነገር ለማግኘት በጣም ጠንካራ ተፋላሚና ባለስል አእምሮ ባለቤት መሆን አለባችሁ፡፡ለዚህ እንዲረዳችሁ የሆነ የመንግስት ተቋም ከ10-15 ዓመት እድሜ ያላቸውን ታዳጊዎችን ወስዶ ሚስጥራዊ በሆነ ስፋራ ሁለገብ የሆነ ስልጠና ይሰጣል፡፡ስልጠናው የሚወስደው ለ5 አመት ነው፡፡በ5 አመት ውስጥ መደበኛ ትምህርት ትማራላችሁ፤ቋንቋ ትማራላችሁ፤ወታደራዊ ስልጠና ትወስዳላችሁ፤ከዛ እንደብቃታችሁ በተለያየ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ትመደባላችሁ፡፡በተለይ ከ80 ሰልጣኞች መካከል ከ1- 20 ደረጃ ይዛችሁ ካጠናቀቃችሁ….በጣም ልዩ የተባለ እድል ነዋ የሚያጋጥማችሁ፡፡አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ግን ሰልጠናውን ለ5 አመት ከወሰደችሁ በኃላ ለአስር አመት የማገልገል ግዴታ አለባችሁ፡፡››
‹‹እህቴ የምትይው ነገር ያጓጓል….ግን የምንችለው ይመስልሻል?››ናኦል በጥርጣሬ ጠየቀ፡፡
‹‹ባይመስለኝማ ለዚህ ስራ አላጫችሁም ነበር››
‹‹እኔ ያልገባኝ…ይሄ ያልሽው የትምህርት ፤የቋንቋ ጥናት፤ ወታደራዊ ስልጠና…ስራ ለማግኘት ሊረዳን ይችላላል..?ማለት ፖሊስ ምናምን ልንሆን እንችላለን?እሺ እሱ ይሁን..ግን እንዴት አድርጎ ነው ቤታችንን የምናስመልሰው ?ሀብታምስ የምንሆነው?፡፡››ስትል ኑሀሚ እንደወትሮዋ ጠጠር ያለውን ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡
‹‹አይ ፖሊስ አትሆኑም…እንዳልኮችሁ ከ1-20 ከወጣችሁ ለሌላ የስለላ ስልጠና ወደውጭ ሀገር ትሄዱና ለተጨማሪ ሁለት ሶስት አመት የስለላ ትምህርት ትወስዱና ተመለሳችሁ፡፡በሀገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ሰላይ ሆናችሁ ታገለግላላችሁ፡፡ደረጃችሁ ከ20 በታችም ከሆነ ያው እደየችሎታችሁ ተመሳሳይ አይነት ሚስጥራዊ ስራዎችን ለሀገሪቱ ትሰራላችሁ…እቤቱን ባልሽው እመኚኝ በቀላሉ ይሳካል፡፡ ሰውዬው ላይ ሙሉ ምርመራ ይከፈታል ፤ መረጃዎች ከእንደገና ይታያሉ፤ፍርድ ቤትም ሳይሄድ ሰውዬው በፍላጎቱ ቤቱን አስረክቦ እንዲለቅ ማድረግ ይቻላል፡፡በተለይ እንዳልኳችሁ ቢያንስ ከሁለት አንዳችሁ ከ1-20 ውስጥ ከወጣችሁ የቤቱን ጉዳይ በእርግጠኝነት ይሳካል፡፡ሀብታም መሆኑን ያልኮችሁ ግን እንደእናንተ ብልጠትና ጥንካሬ የሚወሰን ነው፡፡ያንን እርግጠኛ ሆኜ ቃሌን ልሰጣችሁ አልችልም፡፡፡››
‹‹ገባኝ እሺ…ግን አንቺ ይሄንን እንዴት አወቅሽ?››
‹‹እኔም ተመሳሳይ ስልጠና ወስጄ ተመሳሳይ ስራ ምሰራ የስለላ ባለሞያ በመሆኔ ነው በእርግጠኝነት እየነገርኳችሁ ያለሁት››
ኑሀሚ እንጣጥ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳች..‹‹አውቄው ነበር፤የሆነ ነገር እንደደበቅሽን እርግጠኛ ነበርኩ..አየህ ወንድሜ ለወደፊቱ ትምህርት ይሁንህ …ዝም ብለህ ሰውን በቀላሉ አትመን፡፡››
ናኦል የእህቱ እንደ እብድ መሆንና ከአንደበቷ ምትሰነዝራቸው ንግግሮች ምስራቅን እንዳያስቀይም በመፍራት በተቀመጠበት ተቁነጠነጠ፡፡ምስራቅ መናገር ጀመረ..‹‹እኔም ለዚህ ስራ ፐርፌክት እንደምትሆኚ እርግጠኛ የሆንኩት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ነው፡፡ይሄ ተጣራጣሪነትሽ….ነገሮችን ከስር መሰረቱ አብጠርጥሮ ለመረዳት ያለሽ ተነሳሽነት፤አካባቢሽን ለመረዳት የምታደርጊው ጥረት….ወደፊት እንዲህ ቢሆን ብለሽ መተንበይና መተንተን ችሎታሽ ከእድሜሽ በጣም የራቀና የበሰለ በመሆኑ በተፈጥሮ ለዚህ ስራ የተሰጠሸ መሆንሽ ምልክት ነው፡፡እመኚኝ በጣም ነው ሚሳካልሽ፡፡››
‹‹እኔስ አይሳካልኝም ማለት ነው?፡፡››ቅሬታ ባዘለ የድምፅ ቃና ጥያቄውን ያቀረበው ናኦል ነበር፡፡
ምስራቅ ፈገግ አለች‹‹እውነት ለመናገር አንተም የራስ የሆኑ ኳሊቲዎች አሉህ…ታናሽ እህትህ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም የተለየች ነች ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ለማንኛው አሁን ክፍላችሁ ግቡና ተመካከሩ ፡፡ ከመተኛታችሁ በፊት ውሳኔያችሁን መጥታችሁ አሳውቁኝ፤እስከዛ ፊልም እያየሁ ጠብቃችኋለው፡፡
‹‹እንዴ…ዛሬውኑ?››
‹‹አዎ አሁን…አንድ ሰዓት ካሰባችሁበትና ከተማከራችሁበት በቂ ነው…ከተስማማችሁ በለሊት እወስድና አሰረክባችኋለው፡፡››
‹‹ምንድነው እንደዚህ ጥድፊያው?››ኑሀሚ ነች ጠያቂዋ፡፡
‹‹እንግዲህ አሰራሩ እንደዚህ ነው….በሉ ተነሱ ግቡ››
‹‹እህቴ ተስማምተን ከሄድን ግን አንቺም አብሪሽን ትሆኚያለሽ?››
ናሆም ምስራቅን በስስት እየተመለከተ ጠየቃት፡፡
ምስረቅ ፈገግ አለች‹‹አይ አልችልም…ጨርሳችሁ ስትወጡ ግን የምቀበላችሁ እኔው እራሴ ነኝ››ስትል ነበር ቃል የገባችላቸው፡፡
‹‹እኔ አምስት አመት ሙሉ አንቺን ሳላይ …እንዴት?››
‹‹ወረኛ ከአምስት ወራት በፊት እኮ ጭራሽ እስከመፈጠሯ አታውቃትም ነበር….በል ና እንግባ››ኑሀሚ አበሻቀጠችው፡፡ተያይዘው ገቡ፡፡መኝታ ቤታቸው ዘግተው አልጋው ጠርዝ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡ፡፡ለሀያ ደቂቃ ሁለቱም እርስ በርስ መነጋገር አልቻሉም ነበር፡፡
‹‹እህቴ ዝም አልሽ..የሆነ ነገር በያ››ናሆም በፍራቻ ውስጥ ሆኖ ጠየቃት፡፡
‹‹ምን እላለሁ….ነገሩ ምንም ግልፅ አይደለም፤የተወሳሰበ የማፊያ አይነት ስራ ነው የሚመስለው፡፡››
‹‹ግን እውነት ለመንግስት ምትሰራ ይመስልሻል?››
‹‹አንተም ተጠራጠርካት አይደል?ለመንግስትም ይሁን ለሌለ አላውቅም ግን ለሆነ ግብዳ ተቋም እንደምትሰራ እርግጥ ነው፡፡ህይወት እንድትበራልን ከፈለግን ጨከን ብለን እንዲህ አይነት ነገሮችን መሞከር አለብን፡፡ለመንግስትም ሆነ ለማፍዬዎች ለእኛ ምን ለውጥ አለው..?መንግስት ለእኛ ምን አድረጎልናል?››
‹‹አይ ማለት ለደህነነታችን ብዬ ነዋ፡፡››
‹‹ያው ነው ..ካበሳጨነው መንግስትም ይገድልኸል.. ማፊያዎቹም ይገድሉሀል…ዋናው እስማርት መሆንና የጨዌውን ህግ ጠንቅቆ በማወቅ በህጉ መሰረት መጫወት ነው፡፡››
‹‹እና እንሳማማ እያልሺኝ ነው?፡፡››
‹‹አዎ ሌላ ምርጫ እኮ የለንም…››
‹‹እንዴ ምን ማለትሽ ነው…?እምቢ ብለን እኮ እሷን አመስግነን እቤቷን ለቀን ወደምንሄድበት መሄድ እንችላለን፡፡››
‹‹አንችልም፡፡››

👍54❤6👏3
ናኦል በእህቱ መልስ ግራ ተጋባ፡፡እሷ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደመስኮት ሄደች፡፡ቀስ ብላ የመጋረጃውን አካፋይ ላይ ከፈት አደረገችና አይኖቾን አጨንቁራ ወደ ታች ተመለከተች…‹‹ና እስቲ››
ምን ልታሳየው እንደሆነ ባይገባውም ከተቀመጠበት ተነሳና ሄደ.. እሷ እንደምታደርገው አይኖቹን አጨንቁሮ ተመለከተ፡፡‹‹ ያቺን ጥቁር መኪና አየሀት…እኛን መከተል ከጀመረች ሳምንት ሆናት፤እንዳትፈራ ብዬ አልነገርኩህም እንጂ ወደከታማ ስንሄድ በሔድንበት ሁሉ እየሄዱ ሲከተሉን ነበር፡፡ወንድሜ የገባንበት ወጥመድ እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡ይህቺ ያንተ ተመራጭ ምስራቅም እንደምታያት ቀላል ሴት አይደለችም፡፡እኛ ደግሞ ስለእሷ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ነቄ ብለናል..አሁን ባቀረበችልን ሀሳብ አንስማማን ብለን እንንካው ብንላት…ዝም ብለው በቃ ቸው ብለው ሚሸኙን ይመስልሀል..አታስበው››
ናኦል እርግጠኝነት በማይነበብበት ስሜት ‹‹አረ እህቴ ምስራቅ በእኛ ላይ እንዲህ ታደርጋለች››በማለት ሊሞግታት ፈለገ፡፡
‹‹አይ ይሄ እኮ የስራው ፀባይ ነው፡፡የስጋ ወንድም እህቶቾም ብንሆን ተመሳሳዩን ነው የምታደርገው፡፡በል ተነስና አሁን የነገርኩህን ነገሮች በሆድህ አስቀምጠህ ባቀረበችልን ሀሳብ መስማማታችንን እንንገራትና ለሊት ወደሚወስዱን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ እንሁን፡፡››
ተስማሙና ወደሳሎን ሄደው መሳማማታቸው ነገሯት፡፡በደስታ ከተቀመጠችበት ተነሳታ አቀፈቻቸውና ሁለቱንማ ሳመቻቸው፡፡አንስማማም ቢሉ ስለሚሆነው ነገር እንደተጨነቀች ከሁኔታዋ ያሳታውቃል፡፡ እንደተባለውም ጥዋት ወስዳቸው ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ምን ልታሳየው እንደሆነ ባይገባውም ከተቀመጠበት ተነሳና ሄደ.. እሷ እንደምታደርገው አይኖቹን አጨንቁሮ ተመለከተ፡፡‹‹ ያቺን ጥቁር መኪና አየሀት…እኛን መከተል ከጀመረች ሳምንት ሆናት፤እንዳትፈራ ብዬ አልነገርኩህም እንጂ ወደከታማ ስንሄድ በሔድንበት ሁሉ እየሄዱ ሲከተሉን ነበር፡፡ወንድሜ የገባንበት ወጥመድ እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡ይህቺ ያንተ ተመራጭ ምስራቅም እንደምታያት ቀላል ሴት አይደለችም፡፡እኛ ደግሞ ስለእሷ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ነቄ ብለናል..አሁን ባቀረበችልን ሀሳብ አንስማማን ብለን እንንካው ብንላት…ዝም ብለው በቃ ቸው ብለው ሚሸኙን ይመስልሀል..አታስበው››
ናኦል እርግጠኝነት በማይነበብበት ስሜት ‹‹አረ እህቴ ምስራቅ በእኛ ላይ እንዲህ ታደርጋለች››በማለት ሊሞግታት ፈለገ፡፡
‹‹አይ ይሄ እኮ የስራው ፀባይ ነው፡፡የስጋ ወንድም እህቶቾም ብንሆን ተመሳሳዩን ነው የምታደርገው፡፡በል ተነስና አሁን የነገርኩህን ነገሮች በሆድህ አስቀምጠህ ባቀረበችልን ሀሳብ መስማማታችንን እንንገራትና ለሊት ወደሚወስዱን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ እንሁን፡፡››
ተስማሙና ወደሳሎን ሄደው መሳማማታቸው ነገሯት፡፡በደስታ ከተቀመጠችበት ተነሳታ አቀፈቻቸውና ሁለቱንማ ሳመቻቸው፡፡አንስማማም ቢሉ ስለሚሆነው ነገር እንደተጨነቀች ከሁኔታዋ ያሳታውቃል፡፡ እንደተባለውም ጥዋት ወስዳቸው ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍60🥰17❤6👏4🤔1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ከምስራቅ ካር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ይገጥመናል ከሉት በላይ በጣም የተወሳሰበ ነገር ነበር የገጠማቸው፡፡በመጀመሪያ የት እንደተወሰዱ ያለማወቃቸው ነበር ከባድ ነገር፡፡ መስታወቱ ድፍን ጥቁር ሆኖ ወደውጭ በማያሳይ መኪና ውስጥ ተከተው…ለአንድ ሰዓት ለበለጠ ጊዜ ሲጓዙ ከቆ በኃላ መኪናዋ ቆመችና ሲወርዱ አምስት የሚሆኑ ባለአምስት ፎቅ ዘመናው ህንፃዎች ያሉበት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፤ የመረብ ኳስ እና የመሳሰሉት ሜዳዎች ያሉበት ዙሪያውን በደን የተሸፈነ እና ቢያንስ 3 ሜትር ሚሆን ከኮንክሪትና ከብሎኬት የተሰራ አጥር ….በአጥሩ ጫፍ ላይ አደገኛ ሽቦ የተጠመጠመበት በጣም አስፈሪ ድባብ የተላበሰ ግዙፍ ስፍራ ነው፡፡በዛ ላይ .በተወሰነ ሜትር ርቀት በየሰዓቱ በሚቀያየሩ ቆፍጣና የጥበቃ ወታደሮች የሚታዩበት አስፈሪ ግቢ ውስጥ ነው ይዘዋቸው የገቡት፡፡
ይዞቸው ከመጡት መካከል አንድ ወደአንደኛው ፎቅ ይዟቸው ሄደና ወዳአንድ ቢሮ አስገባቸውና ምንነቱን ያለወቁት የሆነ ወረቀት አስፈርሞ በማስረከብ ቀሪውን ያዘና አነሱንም ልክ እንደወረቀቱ እዛው ጥሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዛ ከእነሱ ስለሚጠበቀው ነገር፤ ስለዋና ዋና የግቢው ህግ፤ማድረግ ስለሚገባቸው መድረግ ስለሌለባቸው ነገር የአንድ ሰዓት ገለፃ ከተሰጣቸው በኃላ ናኦል ወደ ወንዶች ህንፃ ኑሀሚም ወደ ሴቶች ህንጻ ተወሰድና ከሌላ ከአንድ ሰው ጋር የሚጋሩት የራሳቸው መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡በዚህ ሁኔታ አዲሱን ህይወታቸውን አህዱ ብለው ጀመሩ፡፡
ወደእዛ ግቢ ገብቶ በቃችሁ ውጡ ከመባሉ በፊት ለመውጣት መሞከር መጨረሻው ሞት ብቻ እንደሆነ ያወቁት ግቢውን በረገጡ በቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡እንደተባለውም ስልጠናው የተለየ እና በእነሱ ዕድሜ ደረጃ ላለ ወጣት ይቅርና ለሙሉ ወጣትም የማይሞከር ነበር….ግን ስልጠናውን በቃኝ አልቻልኩም ማለት እራስን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ሌላ የሚያሰገኘው ነገር የለም፡፡ስለዚህ የማይቻለን መቻል የግዳቸው ነበር፡፡ወታደራዊ ስልጠናው ብቻ ሳይሆን መደበኛ ትምህርቱ እራሱ በጣም ጥብቅ በሆነ ስነምግባር የሚሰጥ ነበር፡፡አንድ ልጅ እዛ ግቢ ሲገባ ሶስተኛ ክፍልም ይሁን ስድስታኛ ክፍል የ5 አመቱን የሥልጠና ጊዜ ጨርሷ ከዛ ጊቢ ተመርቆ ሲወጣ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ወስዶ መሆን አለበት ፡፡በዛ የተነሳ በአመት ሁለት ክፍሎችን መማር የግድ ይላል፡፡ደግነቱ የትምህርት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊና ሁሉ ነገር የተሞላለት አስተማሪዎቹ ልክ እንደእነሱ በልዩ ችሎታቸውና ብቃታቸው የተመረጡ ጂኒዬሶችና ነገሮችን በቀላሉ በማስረዳት ችሎታቸው የተመሰከረላቸውና ስለሆኑ ጫናዎቹ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይከብዳቸው ያግዛቸዋል፡፡በዛ ላይ እያንዳንዱ ሰልጣኝ እንደ ዝንባሌው በተለያዩ የስፖርት አይነቶቹ መሳተፍና የቋንቋ ስልጠናውም በተመሳሳይ ሁኔታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡በተለይ ከውጭ ቋንቋ እንግሊዘኛና አረብኛ ሲማሩ ከሀገር ውስጥ እንደየ ምርጫቸው ከሚያውቁት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
ይሄ በሀገሪቱ የደህነነት መስሪያ ቤት በልዩ ፕሮጀክት እቅድ ተነድፎለት በጀት ተይዞለት እየተካሄደው ያለው ልዩ ስልጠና ለመጀመሪያው አንድ አመት ለሁሉም ተማሪዎች በጣም ከባድ አካልንም መንፈስንም በእኩል ደረጃ የሚያዝል ነበር፡፡ለዚህም ማሳያ በተቀመጠው ክራይቴሪያ ከተለያ ቦታ በተለያየ ዘዴ ተሰብስበው ከገቡ 80 ተማሪዎች መካከል በአመቱ መጨረሻ 17 ቱ መቋቋም አቅቶቸው ሞተው ነበረ፡፡ናኦልም እህቱ ከጎኑ ኖራ በየጊዜው ብርታት ባትሰጠው ኖሮ ከሞቾቹ መካከል መሰለፉ አይቀርም ነበር፡፡ለዚህ ነው መጀመሪያውኑ ሰልጣኞቹ ሲመለመሉ አስፈላጊው ክራይቴሪያ ዘመድና ጠያቂ የሌላቸው እንዲሆኑ የሚፈለገው፡፡
ኑሀሚ ግን ከሶስት ወር በላይ አልተቸገረችም ነበር….ካዛ በኃላ በየዲሲፕሊኑ ከፉክከሩ መድረክ ከፊት የምትሰለፍ፤ ለሁሉም ሰልጣኞች ምሳሌና ብርታት ሆና ነበረ የቀጠለችው፡፡አመስት አመቱ አልቆ ሲመረቁ ከአንድ ወንድ ጋር በእኩል ነጥብ አንደኛ በመሆን የወርቅ ዋናጫውን ተቀበለች፡፡ወንድሟ ናኦል 53 ተኛ ወጥቶ ተመረቀ፡፡እና 5 አመት ከኖሩበት ከእዛ ማሳልጠኛ ውስጥ ልክ እንደአገባባቸው በጨለማ መኪና ውስጥ ተሳፍረው እንዲወጡ ተደረገ.፡፡ከሰዕታት ጉዞ በኃላ ግን ልክ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናዋ ቆማ ስታወርዳቸው የተቀበለቻቸው ምስራቅ ነበረች፡፡
በወቅቱ ሁለቱም ያለልዩነት ነበር የተጠመጠሙባት፡፡እሷም በደስታ እና በከፍተኛ እርካታ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡ስታያቸው ከበፊቱ በጣም አድገው ሙሉ ወጣት ሆነው ስላየቻቸው እጅግ ተደስታ ነበር፡፡ከዛ መኪና ውስጥ አስገባቻቸውና ቀጥታ ወደወላጆቻቸው ቤት ነበር የወሰደቻቸው፡፡ከመኪና ስትወርድ አብረዋት ወረዱ…ሰፈሩን ሲያዩና የቆሙበትን ሲረዳ ሁለቱም ደንዝዘው ነበር..ቀጥታ ሁለቱንም መሀከላቸው ገባችና ግራና ቀኝ እጃቸውን ይዛ ወደ ግቢው በራፍ ይዛቸው ሄደች…ሁለቱም በዝምታና በድንዛዜ ተከተሏት..ካዛ አንኳኩታ ሰውዬው ሲወጣ የሆነ ነገር ትለዋለች ብለው ሲጠብቁ..ኪሶ ገባችና ቁልፍ በማውጣት..‹‹ይሄው ቃል በገባሁት መሰረት የወላጆቻችሁ ቤት ቁልፍ ››ብላ ኑሀሚ እጅ ላይ አስቀመጠችላት፡፡ኑሀሚ አላመነችም፡፡ በድንዛዛ እጇን አንቀሳቀሰችና ቁልፉን ከፈተች.. አሸከረከረች… ተከፈተ.. ተንደርድራ ወደውስጥ ገባች፡፡ ወንድሟም ተከተላት፡፡ በረንዳው ላይ እስኪደርሱ አልቆሙም…የሳሎኑን በራፍ ስትገፋው ተዘግቷል፡፡ እጆ ላይ ባለው ቁልፍ ሞከረች ፤ተከፈተ……፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እነሱ ምንም ሳይለፉና ሳይጥሩ ነበር በምስራቅና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጥረት የወላጆቻቸው ቤት የተረከቡት፡፡
ከዛ ሁለት ወር ሰይቆይ ኑሀሚ በስልጠናዋ ባስመዘገበችው ብቃት ምክንያት ለተጨማሪ የሶስት አመት ስልጠና ወደ ራሺያ ተላከች፡፡
ናኦል ደግሞ ቤተሰቦቹ ቤት እየኖረ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን እየተማረ በተደራቢነት ከምስራቅ በሚሰጠው መመሪያና ተልዕኮ መሰረት የፊልድ ስረዎችን እንዲላመድ ተደረገ፡፡
ናኦል ከትዝታው ባኖ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ሰዓት ሲያይ በጣም ነበር የተገረመው….ከለሊቱ10፡20 ሆኗል …ላለፉት አራት ሰዓት በላይ ባለፈ ታሪኩ ውስጥ ሰምጦ በትዝታ ሲዋልል ነበረ፡፡አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ዝሏ ነበር ፡፡
/////
ኮሎምቢያ/አሞዞን ደን ውስጥ
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባነነ እና አይኖቹን ገለጠ፡፡በድቅድቁ ጨለማ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ግዙፍ ዛፍ ላይ ቆንጆና ወጣት ልጅ ደረቱ ላይ ተኝታ ነው ያገኘው…ያለበትን ሁኔታ አሰበና ፈገግ አለ፡፡ቀስ ብሎ ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ሲያስነሳት ነበር ከገባችበት ጥልቅ ትዝታ የነቃችው፡፡
‹‹ወይ ሀሳቤን ጥዬ ተንፈላሰስኩብህ አይደል?››አለችው፡፡
‹‹አይ የተፈጥሮ ጥሪ አጨናንቆኝ ነው››
‹‹ማለት?››
‹‹ሽንቴን…ኩላሊቴ ልትፈነዳ ነው››
‹‹እ ..ነው..ወርደህ ልትሸና ነው?፡፡
‹‹አይ ምን አስወረደኝ..ብወርድ ሽንት ቤት የለ ..ሜዳ ላይ ነው የምሸናው፡፡ ማይደብርሽ ከሆነ እዚሁ ሆኜ ልለቀው ነው፡፡››
በጨለማ ውስጥ የማይታየውን ፈገግታዋን እየለገሰችው‹‹ምን ቸገረኝ..ልቀቀው.››አለችው
‹‹አመሰግናለው ››አለና ቆመ፡፡ ዚፕን መክፈት ሲጀመር.
‹‹እንዴ…››ብላ አጉረመረመች
‹‹ምነው?››

👍63❤8