ትንግርት ታዲዬስን ለመጨበጥ በአየር ላይ የዘረጋችው እጇን እንዳንከረፈፈች ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ዶ/ር አዞረች፡፡በህይወቷ መቼም ፊት ለፊት አገኛታለሁ ብላ ለሰከንድ እንኳን አስባ የማታውቀውን ሰው ፊት ለፊት ስታይ አፏን ከፈተች.. ለደቂቃዎች ሁለቱም ደንዝዘው በፀጥታ ተፋጠጡ፡፡ ሶስት ወንዶች ግራ ገባቸው፡፡
በመጋባት ጠየቀ::
‹‹እጅግ በጣም እንተዋወቃለን ››ብላ ስትናገር እና ጠረጴዛ ላይ ያለውን የለስላሳ ጠርሙስ አንስታ ዶክተሯ ጭንቅላት ላይ ስትከሰክሰው አንድ ነበር፡፡በሰከንዶች ቅፅበት በአከባቢው ከፍተኛ ግርግርና ድንጋጤ ተከሰተ፡፡.ዶ/ር ሶፊያ መላ ፊቷ በደም ተሸፍኖ እራሷን ስታ ተቀምጣበት ከነበረበት ወንበር ወደ ኃላዋ ተገነደሰች፡፡
<< ምን ነካሽ አብደሻል እንዴ…?››ኤልያስ
‹‹እንዴ ምነካሽ ?እኛን እንኳን አታከብሪም?››ጋዜጠኛው አመነጫጨቃት፡፡ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በክንዶቹ አቅፎ ግራ በመጋባት ትንፋሿን ያዳምጣል፡፡
ከ5 ደቂቃ በኃላ ታዲዬስ እና ኤልያስ ዶ/ር ሶፊያን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በአፋጣኝ ደርሰው ወንጀለኛዋን ትንግርትን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ነው በጣም አመሰግናለው
አሁንም #Sebscribe ያለደረጋቹ እያደረጋቹ #ትንግርት እስከሚያልቅ 500 ##Sebscriber እጠብቃለሁ በቅድምያ ለሁላችሁሜ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍69❤15🤔6😱6
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ትንግርት ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ ከታሰረች ከአንድ ሰዓት በኃላ የዕለቱ ተረኛ መርማሪው ፖሊስ ዘንድ እንድትቀርብ ተደረገ፡፡
‹‹ሙሉ ስምሽን ብትነግሪኝ?››መርማሪው ብዕሩን መዝገቡ ላይ ቀስሮ ጠየቃት፤ነገረችው፡፡
‹‹በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋልሽ ታውቂያለሽ?››
‹‹አዎ አውቃለሁ፡፡››
‹‹እስቲ የተፈጠረውን በዝርዝር አስረጂኝ?››
ዝም አለች፡፡ትንግርት ዶ/ር ሶፊያ ጋር ባላሰበችው ቦታ ባልታሰበ አጋጣሚ ስትገናኝ እራሷን የመሳት ያህል ስሜቷ ጡዞ አቅሏን ስታ ነበር፡፡ በወቅቱ ምን እንደተከሰተ ምን እንዳደረገች በትክክል አታስታውስም፡፡.
‹‹ምንም የማስታውሰው ነገር የለም?››
‹‹የሰራሽውን ወንጀልማ ማስታወስ አለብሽ ፡፡››
‹‹ምንም ወንጀል አልሰራሁም አላልኩም፤እያንዳንዱን ድርጊት አስታውሼ ግን ልዘረዝርልህ አልችልም፡፡››
‹‹ግድ የለም የምታስታውሺውን ያህል ንገሪኝ፡፡ ዶ/ር ሶፊያ በምትባል ግለሰብ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰሺባታል ፡፡ግለሰቧ አሁን በህያወት እና በሞት መካከል ትገኛላች፡፡››
‹‹እኔም እሷ ከዓመታት በፊት ባደረሰችብኝ ጥቃት ለሦስት ጨለማ ዓመታት በህይወት እና በሞት መሀከል ተንጠልጥዬ ስቃትት ነበር፡፡ ስለዚህ ብትሞት እንኳን በእኔ ላይ የፈፀመችብኝን በደል በማካካስ ስርየት
አያስገኝላትም፡፡>>
‹‹እስቲ በደለችኝ የምትያቸውን ነገሮች ንገሪኝ?››
‹‹አልችልም::››
‹‹የምርመራ ስራዬን አስቸጋሪ እያደረግሺብኝ ነው፡፡››
‹‹ይገባኛል ...ግን አሁን ምንም ልነግርህ አልችልም ፤ጊዜ እፈልጋለሁ፡፡››
መርማሪው ፖሊስ ለተወሰነ ደቂቃዎች በዝምታ አሰላሰለና ‹‹እንግዲህ የተጠቂዋ ሁኔታ እስኪለይለት ማረፊያ ቤት ትቆያለሽ ፡፡ ዛሬ ቅዳሜ ነው ሰኞ ፍርድ ቤት እንድትቀርቢ እናደርጋለን፡፡ፍርድ ቤቱ ምን አልባት ዋስ ሊፈቅድልሽ ይችላል፡፡››በማለት ወደ ማረፊያ ቤቱ እንድትመለስ አደረገ፡፡
ኤልያስ የዶክተር ሶፊያን የህክምና ሁኔታ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ትንግርትን ሊያያት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡ፖሊሶቹን አስፈቅዶ ወደ እሷ ተጠጋ፤ከአጥሩ ወደዚያና ወደዚህ ሆነው መስኰት በመሰለች ክፍተት መነጋገር ጀመሩ፡፡
‹‹ሀይ ትንግርት ...እንዴት ነሽ?››
‹‹ሠላም ነኝ፡፡››
‹‹ፖሊሶቹ አናገሩሽ?››
‹‹አዎ ..…ማናገር አናግረውኛል፤አልተጋባባንም እንጂ፡፡››
‹‹አይዞሽ ..አንድ መቶ ሃለቃ ወዳጅ አለኝ፤ሁኔታውን ለእሱ አስረድቼዋለሁ፡፡ እንዲያናግራቸው አድርገን በዋስ ምትወጪበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡››
‹‹አይዞህ አትጨነቅ ምንም አልሆንም፡፡››
‹‹ቆይ ያልገባኝ... ምንድነው የተፈጠረው? ከልጅቷስ ጋር የት ነው ምትተዋወቁት?››
‹‹ኤልያስ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልፈልግምም…አልችልምም፡፡››
‹‹ተይ እነጂ ትንግርት፤ችግር ውስጥ እኮ ገብተሻል፤ ሁኔታውን ካላወቅን እንዴት ልንረዳሽ እንችላለን?››
‹‹ምንም ዓይነት እርዳታ አልፈልግም፡፡ እሷ ሞታ እኔ እዚሁ እስር ቤት ለዘላለም ብበሰብስ እንኳን ደስተኛ ነኝ፡፡››አለችው እየተንዘረዘረች፡፡
‹‹ያን ያህል?››
‹‹ከዚያም በላይ፡፡አሁን ከዚህ በዋስ ብታስፈተኝ እንኳን ቀጥታ ወዳለችበት ሆስፒታል ሄጄ እስትንፋሷን እስከመጨረሻው ማቋረጥ ነው ምፈልገው፤አዎ እንደዛ ነው የማደርገው፡፡››
‹‹ኤልያስ ግራ ገባው ፡፡ትንግርትን በእንዲህ ዓይነት የቂመኝነትና የክፋት ባህሪ ውስጥ ወድቃ አጋጥሞት አያውቅም፡፡እሷን በአዛኝነቷ፤በትእግስተኝነቷ፤ ለሰው ባላት ሀሳቢነት : የሰውን ልጅ ቀርቶ እቤቷ የገባች አይጥ በወጥመድ ተይዛ ብታገኛት በሀዘኔታ ከወጥመዱ አላቃ ከነ ህይወቷ ወደ ጐሬዋ እንድትመለስ የምትፈቅድላት ሰው እንደሆነች ነው የሚያውቀው፡፡ታዲያ እንዴት እንዲህ ልትቀየር ቻለች? ፡፡የዚህን ዓይነት የገዘፈ አውሬነት እንዴት በውስጧ ተሸሽጐ ሊኖር ቻለ? ያቺ ልጅስ ምን ያህል ብትበድላት ነው ይሄን ያህል ልታስቆጣት የቻለችው?››
‹‹እሺ ፎዚያን ምን ልበላት ...በስልክ እያጨናነቀቺኝ ነው?..
‹‹እንዴ!!! ነገርካት እንዴ?››
‹‹አዎ ነግሬያታለሁ... ስታጨናንቀኝ ምን ላድርግ?››
‹‹ሰላም ነች በላት፡፡››
‹‹እሱማ ብያታለሁ..ግን ካልመጣሁ እያለቺኝ ነው፡፡››
‹‹በቃ ከመጣች ከእኔ መኝታ ቤት ካለው ኮመዲኖ ታችኛው መሳቢያ ውስጥ ሁለት ጥቁር ልባስ ያላቸው ዲያሪዎች አሉ..እነሱን ይዛልኝ ትምጣ፡፡››
‹‹እሺ ነግራታለሁ፡፡››አላት፡፡
ብዙ ማውራት ቢፈልጉም ተረኛ ፖሊስቹ ከዛ በላይ ሊፈቅዱላቸው ስላልቻሉ እሷ ወደ ማረፊያዋ እሱ ደግሞ አንዳንድ ነገሮችን ለመመካከር መቶ ሃለቃ ጓደኛው ወዳለበት ቦጋ አመራ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው #subscribe ካደረገ ቀጣዩ ክፍል ማታ 3 ሰአት ላይ ይለቀቃል
#Share and #subscribe my #YouTube

👍87❤21👏4👎3🥰2