#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት።”
ጥላዬ፣ እምነቱንና ተስፋውን ጐንደር ላይ ጥሎ ሐሙስ ቀን እዚያች ብርቅየ ከተማ ገባ። ጨለማ የከተማዋን ሰማይ ለማልበስ በመጣደፍ ላይ
ነው። ጐንደሬዎች ቤታቸው ለመከተት ፈጠን ፈጠን እያሉ ሲራመዱ፣ጥላዬ፣ ብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ዓይነታቸው አስደነቀው። እንደ ግሪኮች፣ አርመኖች፣ ህንዶችና አረቦች የመሳሰሉ የውጭ ሃገር ዜጎች ሕዝቡ መሃል ውር ውር ሲሉ፣ የቆዳቸው፣ የመልካቸውና የአለባበሳቸው
መለየት አስደመመው።
ጭቃ ምርጎቹን ባለሳር ክዳን ጎጆዎች ትክ ብሎ አያቸው። ባዘቶ
የለበሱ የሚመስሉ ዋንዛ ዛፎች ስር ችምችም ማለታቸውና እንደ ቋራ ተሰባጥረው አለመቀመጣቸው ገረመው። በየቦታው ጣል ጣል ያሉት
የድንጋይ ግንቦችና ነገሥታት ብቻ የታደሉባቸው የኖራ ቅብ ቤቶች
የከተማዋ ጌጥ መስለው ታዩት። ያየው ሁሉ ከቋራ የተለየ ሆነበት።
ጐንደር ልዩ ስፍራ ሆነችበት፤ አስገረመችው።
ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው ቃል ኪዳን ገባችለት። እየተዘዋወረ ከተማዋን ማየት ፈልጎ ጨለማው በፍጥነት ማደሪያ እንዲፈልግ አስገደደው። ቤተክርስቲያን ፍለጋ ዐይኑን ሲያዘዋውር፣ አንድ የቆሎ ተማሪ በፍጥነት ሲራመድ አየና ሮጦ ደረሰበት።
“ከርመህ ነው? ላገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ነኝ። ማደሪያ ሚሆነኝ
ደጀሰላም ባገኝ ብየ” አለው።
“ኸደብረብርሃን ሥላሤ ማታድር? ምን የመሰለ ዛኒጋባ በቤተክሲያን
ዙሪያ እያለልህ። ወደዛው ነው ምኸድ፤ በል ና። አገርህ ወየት ነው?”
“እማር ብየ መጥቸ” አለ ጥላዬ፣ መናገር አልፈለገም።
“ጐንደር ደሞ ለትምርት። ኸየቦታው ሚመጡ ተማሮች፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና መምህሮች ሁሉ ኸዝሁ ማዶል ያሉት?” ብሎ ነጫጭ ጥርሶቹን አሳየው፣ ተማሪው።
ገራ ገር ፈገግታው ጥላዬን ማረከው። ዕድሜ ልኩን የሚያውቀው መስሎ ተሰማው። ቀደም ብሎ ማደሪያውን ሲያስብ ባይተዋርነት የተሰማውን ያህል፣ ከትከሻው ሸክም እንደወረደ ሁሉ ቀለል አለው።
“ቅኔ ልትማር ነው የመጣህ?”
“ሥዕል ልማር ብየ ነው የመጣሁ።”
“ዛዲያ ጐንደር ምን ገዷት! እደብረብርሃን ሥላሤ መምህሮቹም ተማሮቹም አሉልህ፡፡”
ጥላዬ ተደሰተ። ተማሪው ገዱ ሆኖ ተሰማው። ልባዊ ፈገግታው ደግ
ሰው እጅ ላይ እንደወደቀ ጠቆመው። “ምን እየተማርህ ነው?” ሲል ጠየቀው።
“ቅኔ እየተማርሁ ነው። መወድስ እያኸድሁ ነው።”
“ደሕና አኸደሀል።”
“አንተስ ሞካክረኻል?”
“ሥላሤ ደርሻለሁ። ማድርበት ደጀሰላም የት አገኝ ይሆን እያልሁ?”
“ጐንደር መጥተህ ነው ስጋት ሚያድርብህ? አንተስ አለማወቅህ ...እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት። ሴቶች ወጥ ሲሰሩ ኸደረስህ
ይሽተዋል ብለው ሳትበላ ማትኸድባት አገር እኮ ናት። ጐንደር የሁሉ ናት፤ ማንም ኸየት መጣ ኸየት ቤቴ፣ የኔ ብሎ ሚኖርባት። አልሰማህም
እንዴ፣
ቤተስኪያን ስሞ ለመኖር፣
መልካም አገር ነው ጐንደር።
ሲባልላት?” እያለ ግጥሙን በዜማ አወረደለት።
ጥላዬ ሳቅ አለና፣ “ገና መድረሴ፣ ምኔ ሰምቸ? ጐንደሬ ሁሉ እንዳንተ
ጥሩ ነው?” ሲል ጠየቀው።
“እኔስ ኸተምብየን ነው የመጣሁ። ዐራት ዓመት አርጌያለሁ ኸዝኸ።”
ተማሪው ከላይ የደረበውን ለምድ፣ ትከሻው ላይ ያንጠለጠለውን
አኮፋዳና ለውሻ መከላከያ የያዛቸውን ሁለት በትሮች ጥላዬ ትክ ብሎ ተመለከተና ከልመና እንደመጣ ገባው። ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርሱ
ደጀሰላሙን ተሳልመው ውስጥ ገቡ።
“እንዴት ያለ ቤተክሲያን ነው በል” አለው፣ ጥላዬ።
“አጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ መዠመሪያ አሠሩትና ተቃጠለ። ኸዚያ በኋላ፣ ልዣቸው... ሦስተኛው ሚባሉት አጤ ዳዊት እንደገና አሠሩት።
እሳቸው ግና ባባታቸው ስም እንዲጠራ ስለፈለጉ እኔ አሰራዋለሁ ስሙ ግን ባባቴ ይሁን አሉ።”
ጥላዬ ፈዞ ቆሞ የቤተክርስቲያኑን አሰራር ሲያደንቅ ተማሪው፣ “እኛ
ስንገባ ስንወጣ ለምደነዋል። እንግዲህ አንዱን ጥግ ይዘህ ተኛ። ኸኛ ዘንድ ምኝታ የለም ሁኖ ነው” ብሎት ሄደ።
ጥላዬ ቤተክርስቲያኑን እንደገና ተሳልሞ ዙርያውን ሲመለከት፣
እየጨለመ በመምጣቱ በወንዶቹ መግቢያ በኩል ጭንቅላቱን ጉልበቶቹ መሃል ቀብሮ ተቀመጠ። ግቢው ጭር ብሏል። መንገድ ሲመሽበት፣
“ቤት ያብርሃሙ ሥላሤ ነው” እያሉ ቁርበት ጣል፣ ትኩስ ሽሮ እንጀራ
ላይ ፈሰስ አድርገውለት፣ አለበለዚያ ቆሎ እንዲቆረጥም ወይ ቂጣ እንዲያላምጥ ሰጥተውት ያሳደሩት ሁሉ ትዝ አሉት። ከነጋ እህል አፉ አላደረገም። ሆዱ ከረሀብ ብዛት ዋይ ዋይ አለበት፤ ያለማቋረጥ
አዛጋው።
በዕድሜ ከእሱ ትንሽ ከፍ ስለሚለው ተማሪ አሰበና ባይለየው መረጠ። ስሙን እንኳ ሳይጠይቀው በመሄዱ ተቆጨ። አንገቱን እንደደፋ ሲያሰላስል ድምፅ ሰማ። ቀና ሲል ተማሪዎች ወደ መማሪያ ቦታቸው ወደ ቤተክርስቲያኑ ጀርባ ይሄዳሉ። ተማሪው ከእነሱ ነጠል ብሎ ወደእሱ ሲመጣ አየው። ሁለመናው ተበራታ።
“ራት ቢጤ አመጣሁልህ። የውሃ ቅሌን ልተውልህና ገሠሣ ሲያበቃ
መጥቸ ወስደዋለሁ። ስትተኛ ኸዚሁ ተወው። አነሳዋለሁ” ብሎት
መንገድ ሲጀምር ጥላዬ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣ “ሥላሤ ያክብሩልኝ።ስሜንም ሳልነግርህ... ጥላዬ እባላለሁ... ከቋራ ነው የዘለቅሁ” አለው::
ቀደም ብሎ አባቱ ፈልገው እንዳያገኙት ሲል ማንነቱን ደብቆ፣
አሁን የተማሪው ደግነት ምሥጢሩን አሟሸሸበት።
“በል ነገ ያገናኘን። አብርሃ ነው ስሜ። ገሠሣ እንዳያመልጠኝ
ብሎት ተማሪዎቹ ወደሄዱበት አቅጣጫ አመራ።
ጥላዬ፣ አብርሃ የሰጠውን ፍርፋሪ በልቶ፣ ውሃውን በላዩ ቸልሶና
አምላኩን አመስግኖ የመንገድ ድካም ስለተጫጫነው አንዱ ዛኒጋባ ጋ ተጠግቶ ጋደም እንዳለ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው።
ጠዋት ድምፅ ሲሰማ ብንን አለ። የት እንዳለ ለማወቅ ጥቂት ጊዜ
ወሰደበት። የሌሊቱ ብርድ፣ ልብሱን ውሃ የነካው አስመስሉታል። አንድ ጋቢ መኝታም ከላይ የሚለበስም ሆኖ አገልግሎታል። ከተቀመጠበት
ተነስቶ የቤተክርስቲያኑን መግቢያ በር ተሳለመና ወንዶቹ መግቢያ
ትይዩ ያለ አንድ ዋንዛ ዛፍ ስር ሄዶ ዳዊቱን አውጥቶ መድገም ጀመረ።
“አድረህ ነው?” የሚል ድምፅ ሲሰማ ቀና አለ። አብርሃ ነው ።
“ደሕና... ደሕና ... ይመስገነው።”
“አንደዜ ጠሎት ላድርስና ኸየንታ ሔኖክ ዘንድ ወስድሀለሁ” ብሎት
ሄደ።
ጥላዬ፣ በእሽታ ራሱን ነቀነቀለትና ወደ ዳዊቱ ተመለሰ። የዕለቱን
አድርሶ ሲጨርስ ዳዊቱን ማኅደሩ ውስጥ ጨምሮ፣ ስንጥር አንስቶ
መሬት ላይ መሞነጫጨር ጀመረ። እንደለመደው የወለተጊዮርጊስን ምስል ሊሥል ፈልጎ እዚያ ያደረሰው ምን እንደሆነ ትዝ ሲለው
ስንጥሩን ወረወረው።
ከቤት የወጣበት ምክንያት በመንገድ ድካምና በረሐብ በአእምሮው ውስጥ እየደበዘዘ መጥቶ ነበርና አሁን ቁጭ ሲል ሁሉ ነገር ፊቱ ላይ ድቅን አለበት። ወለተጊዮርጊስ ጐንደር መግባት ከለመግባቷን የማወቅ ፍላጎቱ ጸና። እሷ ሐር ቀሚስ ለብሳ ከቤት እንደወጣችው ሳይሆን፣ እሱ
እሑድ ቤተክርስቲያን ስትሳለም እንደሚያያት የዐዘቦት ልብሷን ለብሳ፣ ነጠላ ተከናንባ በበቅሎ ስትሰግር በዓይነ ኅሊናው ታየው፤ ሆዱ ባባ።
ያርባ ቀን ዕድሌ ነው እንግዲህ ምን አረጋለሁ? አለ፣ ለራሱ።
እናቱንና አባቱን አስታወሰ። በእሱ መጥፋት እናቱ እንዴት ጨርቃቸውን እንደሚጥሉ አሰበና ሆድ ባሰው። አባቱም ቢሆኑ አመል ሆኖባቸው ይነዛነዙ እንጂ፣ የእሱ ነገር እንደማይሆንላቸው ያውቃልና ጉዳታቸው ተሰምቶት ለመጀመሪያ ጊዜ አዘነላቸው። ሳያስበው ፊቱ በእንባ ርሷል። በጋቢው ፊቱን ጠራርጎ ቀና ሲል አብርሃ ፊቱ ቆሟል።

👍15❤2
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ሲልቪ
ውስጥ ውስጡን
በነጋታው ጧት የመኝታዬ በር በኃይል ሲንኳኳ ነቃሁ፡፡ ማነህ
ሳልል በሩን ከፈትኩ። ሲልቪ እየሳቀች ዘላ ተጠመጠመችብኝ፡፡
ተንገዳግደን አልጋዬ ላይ ወደቅን። የፀጉሯ ሽታ ደስ አለኝ
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«ፈተናዬን በማእረግ አለፍኩ። ተነስ እንሂድ»
«የት? »
«ፓሪስ። ቀጥሎ ጄኖቫ፣ ከዚያ ሮማ፣ ናፖሊ፣ ፊሬንዜ፣
ከዚያ ኒስ፣ ማርሰይ፣ ኤክስ፡፡ ፕላኑን በሙሉ አውጥቻለሁ፡፡ «ጎበዝ አደለሁም?»
«ጎበዝ ነሽ፡፡ መቼ ነው «ምንሄደው?»
«አሁኑኑ፡፡ ተነስ ተጣጠብ» አለችኝ፣ ሰሰፊ ኣፏ እየሳቀች
«ለባለሆቴሉ 'ምከፍለው ገንዘብ አልያዝኩማ»
«እኔ ይዣለሁ»
«በምንድነው የምንሄደው?»
«በባቡር። ባቡራችን ልክ ከዘጠና ሁለት ደቂቃ በኋላ ከማርሰይ
ይነሳል፡፡ ቶሎ በል»
እንደዚህ አጣድፋ፣ ማንንም ለመሰናበት ሳልችል ፓሪስ
ወሰደችኝ። ከሁሉ ቅር ያሰኘኝ አማንዳ ዱቤን ሳልሰናበት መሄዴ
ነበር በሚቀጥለው አስር ሳምንት
ውስጥ ስለባህራም በብዙም
አላሰብኩም፡፡ ስለ ምንም ነገር በብዙ አላሰብኩም፡፡ ሀሳቤን ሲልቪ ሞልታው ነበር
ባቡሩ ሞልቶ ቆይቶን አንድ ላይ ቦታ ለማግኘት ባለመቻላችን
ፊት ለፊቴ ተቀመጠች። ሁለታችንም መፅሀፍ ማንበብ ጀመርን።ትንሽ አነብና ሰርቄ አያታለሁ፡፡ ረዥም ፀጉሯ ውብ ነጭ ፈቷን እንደ ጥቁር ሀር ከቦታል። በጣም ቆንጆ ናት፣ የደስ ደስ አላት አንዳንድ ጊዜ ሳያት ትይዘኛለች። ትጠቅሰኝና ሳቅ ትላለች፡፡ መልሼ እጠቅሳታለሁ፡፡ ንባባችንን እንቀጥላለን። አልፎ አልፎ አንድ ያልገባኝን ቃል እጠይቃታለሁ:: ፈረንሳዮቹ
ብርቱካን ይበላሉ፣ ያወራሉ፣ ፖም ይበላሉ፣ ጋዜጣ ያነባሉ፣ ሳንድዊች ይበሳሉ፣ ወይን
ይጠጣሉ፣ ባቡሩን ያዝረከርኩታል፣ ያቆሽሹታል፣ ዝነኛውን «የፈረንሳይ ባቡር ግማት» ይሰጡታል
አቪኞን ስንደርስ አንዲት ኣሮጊት ከአጠገቤ ተነሳችና፣ ገና
ከመነሳቷ ቦታዋ ላይ እንድ ሰውዬ ተቀመጠ። ከኣቪኞን እንደወጣን
የሲልቪ አይኖች ደጋግመው እዚህ ሰውዬ ላይ ያርፉ ጀመር።
ሰውዬውን አየሁት። ፀጉሩ ላይ ነጭ ዘርቶበታል፣ ምናልባት ያርባ
አምስት አመት ሰው ይሆናል። አይኖቹ ንፁህ ሰማያዊ ሆነው፣
ቀጠን ያለ ፊቱ በጣም ቆንጆ ነው:: ሳየው ጠላሁት። ንባቤን ቀጠልኩ፣ ግን የማነበው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ስርቄ ሲልቪን አየኋት።
ሰውዬውን በሰማያዊ እይኖቿ ብርህን ታየዋለች። እሷ እሱን ስታይ፣እኔ እሷን ሳይ፣ ንዴቱ ውስጤ ሲጠራቀም፣ ብዙ ጊዜ ሄድን ሳያት ያዘችኝ። አይኖቿ ተርገበገቡ፣ ወደ ታች አየች፣ ጉንጮቿ ደም ለበሱ፡፡ ማማሯ የንዴቴን ጥቁር ደመና የፍትወት ብልጭታ ሲሰነጣጥቀው ተሰማኝ። «ድንገት ሳብ ኣድርጌ ቀሚሷን ገልቤ ጭኖቿን ፈልቅቄ..
በመስኮቱ ወደ ውጭ ማየት ጀመርኩ፡፡ ለጥ ያለ ሜዳ መሬት
ረዥም ቀጭን የቤተ ክርስቲያን ደወል ቤት ሰማዩን እንደ መርፌ
ወግቶታል፤ አንድ ቀጭን መንገድ ከሹሉ ደወል ቤት ስር ወጥቶ
እየተጠማዘዘ ሄዶ አድማሱ ውስጥ ገብቷል፣ ሰማይና ምድር
የተሰፉበት ክር ይመስላል፡፡ መንደሩ እንደ ልጅነት ቀስ እያለ ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ጠፋ
ዘወር ብዬ ሲልቪን አየኋት። ራሷን ወደ መፅሀፉ ደፍታለች፣
ፈቷ ደም እንደለበሰ ነው:: መፅሀፌን ማንበብ ጀመርኩ። አሁንም ቃላቱ አይኔን ዘልቆ እንጉሴ ውስጥ መግባት አቅቶት፣ አይኔ ብቻውን ያነባል። ሲልቪን አየኋት። አየችኝና ፈገግ አለች:: ሰማያዊ አይኖቿ ሳቂታ ናቸው፡ በጣም ቆንጆ ፈገግታ ኣሳየችው። እናቷን!
ንባቤን ቀጠልኩ። ከዚያ በኋላ እንደገና ደጋግማ ስታየው
አየኋት። አንድ ሶስት ጊዜ ያህል፣ ስታየው እንዳየኋት አይታ በጣም
አፈረች፥ አይኖቿ ተርገበገቡ፣ ጉንጮቿ ቀሉ፤ ንዴቴና ምኞቴ
ውስጤ እየታገለ አስጨነቁኝ
ሶስት ሰእት ያህል አለፈ
ከሊዮን በኋላ አንድ ሁለት ትንንሽ ከተማ እንዳለፍን ሰውየው
እግሮቹን የሚዘረጋ አስመስሎ የሲልቪን እግር ነካ፡፡ ቀና ብላ በውብ አይኖቿ በፈገግታ አየችው፡፡ በሰፊ እፏም ሳቅ አለችለት፡፡ ሰውዬው
በእግሩ እግሯን ማሻሸት ጀመረ። ቀላች። ውስጤ ስጋዊ ፍትወትና
ንዴት ታገለ፣ ንዴቱ አሸነፈ። እግሬን የምዘረጋ አስመስዬ የሰውዬውን ቅልጥም በኃይል መታሁትና፣ ዘወር ብዬ እያፈጠጥኩ
Pardon, monsieur» አልኩት (ይቅርታ መስዬ»)
ve vous en pries አለኝ («ኧረ ግድ የለም )
እግሩን ሰበሰበ። ፊቱ በንዴት ይሁን በእፍረት ደም ለብሷል።
ሲልቪን አየኋት። መፅሀፏን ታያለች፣ ፈገግታ ብጤ አፏ ዙሪያ
ይርበተበታል። ሰውየው የሲጋራ ፓኮ ከኪሱ አውጥቶ ወደ ሲልቪ
ዘረጋ፣ እየሳቀች ተቅበለችው:: አቀጣጠለላት ወደ ፓሪስ ነው : ሚሄዱት?» አለችው
«አዎን ማድሟዜል። እርስዎስ?» አላት ወሬ ጀመሩ። ብሽቅ አልኩ። ተነስቼ ትቻቸው ወጣሁ
መተላለፊያው ዘንድ አልፎ አልፎ የቆሙትን ፈረንሳዮች
እየገጨሁ Pardon! እያልኩ፣ አንድ አስር ሰረገላዎች እቋርጬ
ሂጂ ባቡሩ መጨረሻ ደረስኩ
ስመለስ ግማሽ መንገድ ላይ ቆምኩ። እቺ ንፍጣም!
ልታሰቃናኝ ፈልጋ አይደለም? እንደማልቀና ማወቅ አለባት። ግማሽ ሰአት እስኪያልፍ ወደሷ አልመለስም፡፡ ምን ያህል ግድ እንደሌለኝ ይግባት . .»
ግማሽ ሰአት እንዴት ረዥም ነው! ሰአቴን አስር ጊዜ አየኋት::
እሷ ታድያ አትንቀሳቀስም። አምስት ደቂቃ እንኳ ገና አላለፈም። ወደ ጆሮዬ አስጠጋኋት። ተኝታለች። የለም የለም፡ የባቡሩ ጩኸት
ድምፅዋን አላሰማ ስላለኝ ነው። . . . እኔና ሰአቷ ስንተያይ ሩብ ሰአት አለፈ። ከዚያ በኋላ ግን መቆየት አልቻልኩም፡፡ ሰዎቹን
እየገጨሁ «Partdom!» እያልኩ ወደነዚያ ውሾች መመለስ እንደ
ጀመርኩ፣ በመስኮቶቹ በኩል ቤቶች ብቅ እያሱ ወደኋላ ሽው ብለው ሲያልፉ ይታዩኝ ጀመር። አንድ ትንሽ ከተማ ደርሰናል፡፡ ባቡሩ በቆመልኝ! ማቆያ እንዲሆነኝ ጋዜጣ እገዛ ነበር. ጎሽ! ባቡሩ ቆመ፡፡ ወረድ ስል አንድ መለዮ የለበሰ የባቡሩ ኩባንያ ሰራተኛ አመስዬ፣ አይውረዱ፣ ሁለት ደቂቃ ብቻ ነው ያለን» አለኝ
«Je mn fous!» አልኩትና ወረድኩ («ደንታ የለኝም!»)
አንድ Le Monde ጋዜጣና ሁለት ሳንድዊች ገዝቼ እስክመለስ
ባቡሩ ተነሳ። ሮጬ ለትንሽ ደረስኩበት::
ጋዜጣውን ኣንብቤ ሳልጨርስ ወደሷ አልመለስም፡፡ ሳገኛት ደሞ ሳንድዊች እሰጣታለሁ፡፡
እየሳቅኩ። ጭራሽ አለመቅናቴ እንዲገባት የክሩስቼቭና የኬነዲ የቤንቤላ ስም አለ፤ የቪየትናም ሁከት ተጠቅሷል፣ ግን በደምብ አልገባኝም፡ የሲልቪ ፈገግታ፣ ለሌላ ያሰራችው ፈገግታ አንጎሌን በጥብጦታል። የሆነ ሆኖ፣ ያልኩት ግማሽ ሰአት አለፈልኝ። ኧረ ሰላሳ ሶስት ደቂቃ ነው ያለፈው! እኔ የሰውዬው ልጅ! ... ወደኛ ሰረገላ አመራሁ ሲልቪ የለችም። ሰውዬውም የለም፡፡
የታባታቸውን ሄዱ? እንደገና ፈረንሳዮቹን እየገጨሁ «Pardon!»
እያልኩ አንድ አምስት ሰረገላ ካቋረጥኩ በኋላ፣ ራሴን «የት ነው
ምትሄደው?» አልኩት፡፡
ቆምኩ «በቁላህ ሳይሆን በጭንቅላትህ አስብ» የሚል ሀሳብ ውስጡን አሳቀኝ። ለመሆኑ፣ ባገኛቸውስ ምን ላደርጋቸው ኖሯል ብዬ አሰብኩ። ተመልሼ ቦታዬ ቁጭ ብዬ ልጠብቃቸው ቆረጥኩ፡፡

👍20
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
መሴይ ማንደላይንን ባየ ቁጥር ከሃሳብ ጋር ሙግት መግጠሙን
ያስታውቅበታል፡፡.
ሰውዬው ኮስተርተር የሚል ዓይነት ስለነበር እንኳን በዓይነቁራኛ
ተከትሎ ለአንድ አፍታ ቢያይም «ይሄ ሰውዬ ከኔ ነገር አለው?» የሚያሰኝ ዓይነት ፊትና አመለካከት ያለው፧ ሳይወዱ በግድ ጭንቀትን ከልብ ውስጥ በማሳደር የሕሊና መረበሽን አንጎል ውስጥ የሚፈጥር ዓይነት ሰው ነበር::
ስሙ ዣቬር ይባላል፡፡ ፖሊስ ነው:: ተራ ፖሊስ ሳይሆን የከተማው
ፖሊስ አዛዥ ነው:: መሴይ ማንደላይን ወደ ከተማው ሲመጣ ከዚያ አልነበረም::
አንዳንድ የፖሊስ መኮንኖች የተለየ መልክ አላቸው:: አንዳንዴ
ደማቸው ውስጥ ከእልቅናቸው ጋር የተቆራኘ ክፋት ለመኖሩ ገጽታቸው ላይ ይታያል፡፡ ዣቬር የዚህ ዓይነት ገጽታ ቢኖረውም በውስጡ ግን ክፋት የተቀበረበት ዓይነት ሰው ነበር ለማለት አያስደፍርም:: እስር ቤት ነው
የተወለደው:: እናቱ ደግሞ ጠንቋይ ነበሩ፡፡ አባቱ የወህኒ ቤት ሠራተኛ ስለነበሩ ሁልጊዜም ሕብረተሰቡ የእነርሱን ቤተሰብ ከማኅበራዊ ኑሮ ያገለላ
ይመስላቸው ስለነበር ዣቬር ቀቢጸ ተስፋ ያዉቃዋል፡፡ የሰውን ልጅ ከሁለት ከፍሎ ነው የማያየው:: አንደኛው ወገን ሕብረተሰብን የሚያጠቃ ሲሆን
ሌላው ወገን ከዚህ ጥቃት የሚከላከልለት ክፍል ነው:: ዣቬር በሥነ ሥርዓትና በቅንነት በጣም ያምናል:: ጎሳውን ግን ይጠላል፡፡ ፖሊስ ለመሆን ፈልጎ ነው የፖሊስ ኃይል አባል የሆነው:: በሥራው ምስጉን ፖሊስ መሆን
ስለተረጋገጠ በአርባ ዓመቱ ከፍተኛ የማዕረግ እድገት አግኝቶ የክፍል አዛዥ ሆነ፡፡ በወጣትነት ዘመኑ ደቡብ ክፍለ ሀገራት ውስጥ ከሚገኝ ወህኒ
ቤት እንዲሠራ ይመደባል፡፡
አፍንጫው እንደ ቀትር እባብ ቀጥ ያለ ሲሆን ሪዘን ከግራና ከቀኝ
በጣም ኣሳድጎት ጉንጮቹን ሸፍኖበታል:: ዣቬር ድንገት የሳቀ እንደሆነ ስስ ከንፈሮቹ ተገልጠው ጥርሶቹን ብቻ ሳይሆን የሚያሳዩት ድዶቹንም ጭምር ነው:: ግን ብዙ ጊዜ መኮሳተርን እንጂ ሳቅ አያውቅም:: ከአፍንጫው ግራና
ቀኝ የተሸበሸበ ሥጋ ኣለው:: ይህም ሲቆጣ የአደን ውሻን፣ ሲስቅ ደግሞ ነብርን ያስመስለዋል፡፡ ከዚህ በተረፈ ጭንቅላቱ፡ ትንሽ፣ አገጩ ሰፊ፧ ፀጉሩን ወደፊት እያበጠረው ግምባሩ እስከ ቅንድቡ በፀጉር የተሸፈነ፤ ጨገጎ ፊት ያለው ፤ ፊቱ፡ የሚ.ያርበደብድና የኮስታራ አለቃ ሰውነት ያለው ሰው ነው።
ይህ ሰው በሁለት ዓይነት አመለካከቶች የተወጠረ ነበር፡፡ በመሠረቱ፡ሀሳቦቹ ምንም ዓይነት ስህተት የሌለባቸው ቀላል አመለካከቶች ሲሆን ዣቬር ግን በጣም ስላጋነናቸው እንደ ከባድ ነገር ነበር የሚያያቸው::
እነርሱም ባለሥልጣንን ማክበርና ሕግ የሚፃረሩትን መጥላት ናቸው:: በእርሱ አመለካከት ሌብነት፣ ግድያና ማንኛውም ወንጀል መፈጸም ማለት
ሕግን መፃረር ማለት ነው:: በማንኛውም የሥራ መስክ የተሰማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ማለት ከአገር መሪ ጀምሮ እስከ ተራ ወታደርና ተላላኪ. ድረስ የእርሱን እምነት መቀበል እንዳለባቸው ያምናል፡፡ በእርሱ
አመለካከት ሕግ የሚጥሱትን ሁሉ ተከታትሎ ማጥፋትና ማስወገድ ተገቢ እርምጃ ነው:: ሕግ የሚጥሱትን ከመጠን በላይ ያጠላል:: ማንንም ሳይለይ
ሕግን ማስከበር ለእርሱ ትልቅ ቁም ነገር ነው::
«በአንድ በኩል» ይላል ዣቬር፤ የመንግሥት ባለሥልጣንን ማታለል አይቻልም፧ ሕግ አስከባሪ ዳኛ ደግሞ ፈጽሞ አይሳሳትም:: በሌላ በኩል ደግሞ» ይላል፤ «መዳኛ ከሌለው አዘቅት ውስጥ ከተዘፈቁ ክፉ ሰዎች በጎ
ተግባር አይጠበቅም፡፡»
«ሰው የሠራው ሕግ መጣስ የለበትም» ብለው የሚያምኑ የአንዳንድ ወግ አጥባቂዎችን እምነት ይከተላል፡፡ ከተጠራጠረ እንደ ጦር የሚወጋውን ዓይነት ሰው ላይ እንዲተክል የማገፋፋው ይህ እምነቱ ነበር፡፡ ይህም
በመሆነ «ነቅቶ መጠበቅ› በሚል ፍልስፍና ሕይወቱን ያንፃል። በዚህም የተነሳ ሕሊናው ሕግን በማስከበር፧ እምነቱ የእለት ተግባሩን በመከታተል ላይ ያተኮረ ሲሆን ቄሶች ለቅዳሴ እንደሚራሯጡ ሁሉ እሱም ለስለላ ተግባር ይሯሯጣል፡፡
ይብላኝለት እርሱ መዳፍ ውስጥ ለሚወድቅ፡፡ አባቱ፡ ከእስር ቤት
ሲያመልጥ ቢያየው ሮጦ ሄዶ ያሲዘዋል:: እናቱ አንድ ጊዜ ቲኬት
ስታጭበረብር ስላገኛት አሳልፎ ሰጥቶአታል፡፡ ዣቬር ተመሳሳይ የሆነ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደፈጸመ ሰው መንፈሱ ይረካል::ሕይወቱ በብቸኝነትና በግላዊነት የተሞላ ሲሆን ከዓለማዊ ምቾት የራቀ
ነበር፡፡ የእርሱ ደስታ ወንጀለኞችን ተከታትሎ ማደን እንጂ ዳንኪራ መርገጥ ወይም መዚቃ ማዳመጥ አልነበረም::
ዣቬር ማለት ይህ ሲሆን አሁንም ዓይኑን ከመሴይ ማንደላይን
አላነሳም፤ በጣም ይጠራጠረዋል፡ግን የተጨበጠ ማስረጃ ሊያገኝ አልቻለም::በመጨረሻ በክፉ ዓይን እንደሚያየው መሴይ ማንደላይን ደረሰበት:: ሆኖም ከምንም አልቆጠረውም:: ዣቬር ማን እንደሆነ ለማወቅ ፈልጎ ጥያቄ
አልጠየቀውም:: ለማንኛውም ብዙም አላቀረበውም፤ ብዙም አልሸሸውም፡፡በየጊዜው ሲያፈጥበት እያየ እንዳላየ ሆኖ ያልፈዋል፡፡ ሌሎችን በሚያይበትና
ማንደላይን ሁናቴ ዣቬርን በይበልጥ ግራ አጋባው፡፡ ሆኖም አንድ ቀን የዣቬር ሁኔታ መሴይ ማንደላይንን ያስቆጣዋል:: ነገሩ እንዲህ ነበር፡፡
አንድ ቀን መሴይ ማንደላይን ከአንዲት መንደር ውስጥ ከወዲያ
ወዲህ እያለ ይንሸራሸራል፡፡ ጩኸት ሰምቶ ዞር ሲል ሰዎች ተሰብስበው ያያል፡፡ ወደ ሥፍራው ቢሄድ ደብተራ ፎሽለማ የተባሉ ሽማግሌ ወድቀው እቃ የጫነ ጋሪ ተጭኖአቸዋል፡፡ ፈረሱም ወድቆ እግሩ ስለተሰበረ መነቃነቅ
እንዳቃተው ሁሉ ሽማግሌውም ጋሪው ተጭኖአቸው ሊነቃነቁ አልቻሉም። ጋሪው ላይ መጠነኛ ጭነት ስለነበረ ሽማግሌው የጣር ያህል ነበር የተጨነቁት:: ሰዎች ተሰብስበው ጭነቱን ብድግ አድርገው ሊያላቅቋቸው
ቢሞክሩም አልሆነላቸውም:: ዋጋ የሌለው ሙከራ የአንዳንዱ አያያዝ
የአላዋቂ ሲሆን የአንዳንዱም አያያዝ ለማስመሰል ያህል ብቻ ነበር፡፡ ሽማግሌው ትንፋሽ አጥሯቸው ሊሞቱ ሆነ፡፡ መፍትሔው ከሥር ገብቶ ጋሪውን ብድ ማድረግ ነበር፡፡ ከጋሪው ላይ ወጥቶ የተጫነውን ጭነት ለማራገፍ ከሞከሩ የባሰውን ሊጫንዋቸው ሆነ፡፡ ከሥሩ ገብቶ በሸክም ብድግ ለማድረግ ለራስ
የሚያስፈራ ሆነ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተፋጠጡ፡፡ ዣቬር አደጋው እንደደረሰ መጥቶ ስለነበር የእቃ ማንሻ መሣሪያ እንዲመጣ ሰው ልኮአል::
መሴይ ማንደላይን ከሥፍራው ደረሰ፡፡ ሕዝቡ መንገድ ለቀቀለት
«እርዱኝ እባካችሁ» ብለው ሽማግሌው ጮኹ፡፡ «የማነው ሳምራዊ ይህን ሽማግሌ የሚያድን?» ሲል መሌይ ማንደላይን ጠየቀ፡፡
መሴይ ማንደላይን ዞር ዞር እያለ ተመለከተ፡፡
«የእቃ ማንሻ መሣሪያ ያለው የለም?»
«ሰዎች ሊያመጡ ሄደዋል» አለ አንድ ሰው::
«ቶሉ ይደርሳሉ?»
«ፍሉቮ ከተባለ ሥፍራ ወደሚገኝ አንጥረኛ ነው የሄዱት፡፡ መቼስ
ቢያንስ አንድ ሩብ ሰዓት ያህል ያቆያቸዋል፡፡›
«ሩብ ሰዓት!» ሲል ጮኸ፡፡
ሌሊቱን ሲዘንብ ስላደረ ኣካባቢው ጨቅይቶ ነበር፡፡ ፈረሰ ተንሸራትቶ
የወደቀበትም ሥፍራ እንደማጥ ዓይነት ስለነበር የጋሪው እግሮች በአንድ በኩል ከጭቃው ውስጥ እየዘለቁ ወደ ውስጥ ሰመጡ:: በዚህ ዓይነት በአምስት ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የሽማግሌው ወገብ ሊቀነጠስ ሆነ፡፡
«ሩብ ሰዓት መቆየት አንችልም» አላቸው መሴይ ማንደላይን እዚያ
የተሰበሰቡትን ሁሉ እያየ::

👍23😁3
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...ክፉ ያሳሰበኝን መንፈስ እከድከ ሰይጣን እያልሁ በልቤ ደጋግሜ ጸልዬ አስታገስሁት። ቀጥዬም ሰላም ለኪን ደገምሁበት እና ከሆስፒታል ወጣሁ። እንደ ወጣሁ የሆነብኝን ሁሉ የምነግረዉ ስፈልግ ከሁሉ ቀድሞ
ሐሳቤ ላይ የገባልኝ ሰዉ ባልቻ ነበር፡ እመዋን አቆይቼ ማለቴ ነዉ።ለእሷስ ያለፈዉ ይበቃታል፡ የሆስፒታሉንም ነግሬ ዳግመኛ ቅስሟን ልሰብረዉ አልፈልግም።
በእርግጥ እህትና ወንድሞቼም ነበሩልኝ። ጓደኞቼ ሁሉ አሉ። እሽቴም ቢሆን እኮ አለ የኖረዉ ቢኖርም፣ በተለይ አሁን ስላንጨዋለለኝ ፈታኝ ጉዳይ ለማማከር ግን፣ ከምድር ማንም እንደ ባልቻ የሚሆንልኝ ሰዉ
አይታየኝም: እሱ ብቻ ነዉ የጭንቄን መጠን ልክ እንደ ነገርሁት፣ እንዲያዉም ከነገርሁት አልፎ የሚገነዘብልኝ። ለማባበል
አይሸነግለኝም። ማባበል ከፈለገም እንደ'ሱ የሚያዉቅበት የለም። ጆሮዉ የተለየ ነዉ። ጭጭ ብሎ ሲያዳምጥ ብቻ ከጭንቅ ይፈዉሳል። እኔ ራሴ
እንኳን ስለ ራሴ የማላዉቀዉን ከእመዋ ቀጥሎ የሚያውቅልኝ ሌላ ሰዉ አላዉቅም: ባልቻ ብቻ:: እንዲያ ቢሆንም ግን፣ እሸቴም መስማት ስላለበት ኹለቱንም ወደማላጣበት ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሄድሁ።
“አባትዮ” አልሁት፣ ወደ ትልቁ የማኅበሩ ሕንጻ እየተቃረብሁ ሳለ ወደ ባልቻ ስልክ ደዉዬለት።
“አቤት ልጅየዋ”
“ለአንድ አፍታ ፈልጌህ ነበር”
“መቼ”
“አሁን”
“ዉይ፣ አሁን እንኳ አንዲት የጀመርኋት ሥራ አለችብኝ: ባይሆን ይቺን እንደ ጨረስሁ ልደዉልልሽ?”
“በማርያም! አሁኑኑ ነዉ የምፈልግህ፤ ይልቅ ቶሎ ናና ጉዴን ስማልኝ'
“እህ፤ እየነገርሁሽ?”
“ስሞትልህ! ከእሸቴ ጋር እዚሁ አንደኛ ፎቅ ባለዉ ምግብ ቤት
ብትመጡልኝ፣ የምጋብዛችሁ አታዉቁትም: አንተስ ምናለ ለአንዳንዴስ እንኳን ንፋስ ቢያገኝህ? ሁልጊዜ እዚያ ዉስጥ ተቀብረህ” አልሁት፣ ለግብዣዬ ያለዉን ከበሬታ ዘንግቶ ላለመምጣት ሲያቅማማ በዚያም ላይ ሰዓቱ የምሳ ስለሆነ ሦስታችን አብረን የምንበላበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ይሆንልናል። እንዳሰብሁት፣ ብዙም ሳያስጠብቁኝ ከእሸቴ ጋር ፊት እና
ኋላ ሆነዉ መጡልኝ፡
“አንቺ፤ ብለሽ ብለሽ ደግሞ እንዴት እንዴት ነዉ ያናገርሽኝ? እንደ ልጅ ና ከረሜላ ልግዛልህ ማለት እኮ ነዉ የቀረሽ አሁንማ አሁንማ” አለኝ በጨዋታ፣ ወንበር ስቦ ከአጠገቤ እየተቀመጠ፡ መልስ ከለከልሁት
“አንቺ? ምንድነዉ ደግሞ ለንቦጭሽ የታላቁን ንጉሥ አወዳደቅ ወድቋልሳ: ገና ለገና እርምሽን ልትጋብዥን ብትይ፣ ከአሁኑ ማኩረፍሽ ነዉ? አየህልኝ እሽቴ? ገና ከአሁኑ እንዲህ ከሆነች፣ ሂሳቡን ስትከፍልማ
እንደ ጨዉ ሟሙታ ወደ መሬት መስረጓ ነዉ በለኛ”
ወድጄ አይደለም ዝም ያልኋቸዉ ሆስፒታል የጀመሩኝ ክፉ ክፉ የሚባሉ ሐሳቦች ሁሉ አሁንም አሁንም ወደ ልቡናዬ እየመጡ ግብግብ ገጥመዉኛል፡ እንደ ምንም ጥርሴን ለመፈልቀቅ ሞከርሁ። የዉጤቱን ወሬ ከምሳ በኋላ መንገሩን ስለመረጥሁ፣ በግድ ፈገግ ለማለት እየታገልሁ
ነዉ፡ ብቻ የሆነ ያልሆነዉን እየቀላቀልሁ የጨዋታ ወሬ ለማምጣት ተዉሸለሸልሁ
“ምንድነዉ ልጄ?” አለ ባልቻ አዉቆብኝ ያልፈሰሰ እንባዬን እያበሰልኝ “ አሃ፤ ዛሬ ከነጋ አላየሁሽም ለካ? የት ዋልሽ?”
አስተናጋጁ እየተሸቆጠቆጠ መጥቶ የምንፈልገዉን ሊታዘዘን አጎበደደ፡ እሰይ! ገላገለኝ። በባዶ ሆዳቸዉ ሐቲታቸዉን ከምበላዉ፣
ምሳችንን በሰላም ብንበላ ለእነሱም ይሻላቸዋል። የቤቱን
የአገልግል ምግብ ከተጨማሪ ሱፍ ፍትፍት ጋር እንዲያመጣልን አዘዝን ሱፍ ፍትፍት የባልቻ የምንጊዜም ምርጫ መሆኑን
ከእሱ ጋር ለአንዴም
ቢሆን ማዕድ የተጋሩ ሁሉ ያዉቁለታል። የሚበላም የሚጣጠም ሲጠየቅ
ቀድሞ የሚመጣለት ነገር ሱፍ ነዉ። በሀገር ዉስጥ ምግብ ቤቶች ብቻም ሳይሆን፣ አንዴ ሩስያ አብረን የሄድን ጊዜ ሁሉ ቀዝቀዝ ያለ ሱፍ ፍትፍት ይኖራችኋል? ብሎ ሩስያዊቷን አስተናጋጅ ሲጠይቃት
ሰምቼዉ፣ የሳቅሁትን ሳቅ ሞቼም መርሳቴን እንጃልኝ! እስከ አሁን ትዝ ባለኝ ቁጥር ስቄ አይወጣልኝም: ሱፍ አዝዞ የለም ከተባለ፣ ለሆቴሉ የሚኖረዉ ግምት ሁሉ ወርዶ እንዴት እንደሚያደርገዉ አያድርስ ነዉ።
ይኼ ደግሞ ሆቴል ነዉ? ሱፍ ፍትፍት እንኳን የሌለበት ቤት! ብሎ
ሲያጣጥል ብዙ ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለእኔ ግን የሚበላ ይሁን እንጂ ምንም ቢሆን ያን ያህል አላማርጥም: በተለይ አሁን በኃይል ሞርሙሮኛል። ለወትሮዉ እንዲህ ድባቴ ዉስጥ ስሆን እንኳንስ ሊርበኝ ይቅርና የምግብ
ሽታ ሁሉ አይደርስብኝም ነበር አሁን ግን ምራቄ ኩችር ብሎ፣
ትንፋሼም ሳይቀር ሽታዉ እንደ ተለወጠ ለእኔም ታዉቆኛል።
“ችግር አለ እንዴ ዉቤ?” አለ እሸቴ፣ ከበላን በኋላ ከሁላችን በኋላ እጁን ታጥቦ ከመመለሱ፡
“ፊትሽ በፍጹም ልክ አይደለም” አለ፣ ባልቻም ተደርቦ፡
“ሆስፒታል ሄጄ ነበር''
“እ?” አሉ ኹለቱም፣ እኩል። የሆነዉን እና በሐኪሟ የተባልሁትን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኋቸዉ። በየመሀሉ በድንጋጤ ከአሁን አሁን
ራሳቸዉን ይስታሉ ብዬ ስጠባበቅ፣ እነሱ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ቀሩብኝ ጭራሽ ባልቻማ ሊስቅብኝ ምንም አልቀረዉ፡ እሸቴም ቢሆን የምጠብቅበትን ያህል ጸጸት ቀርቶ ሐዘኔታ እንኳን አላሳየኝም፡
“ለዚህ ነዉ እንዴ ፊትሽን እንዲህ የክረምት ሰማይ ያስመሰልሽዉ?
“ከዚህ በላይ ምን አለና አባታለም?”
“ኧረ ዝም በይ! ደም አርግቶ የፈጠረንን አምላክ ለምናመልክ ለኛ፤ ይኼንን ጉዳይ ብለሽ … ምን እና ምኑ ተገናኝቶ፣ ሰዉ ሆነን እንደ
ተፈጠርን ጠፍቶሽ ነዉ? ልጄ ሙች! ካንቺ ይኼን አልጠብቅም”
ድንገት የእጅ ስልኩ ጮኸ፡ ወዲያዉ ፈገግታዉንም ተግሳጹንም አቋርጦ ስልኩን አነሳና፣ ለቅጽበት ያህል ከወዲያ በኩል አዳመጠ። ወዲያዉም
የምግቡን ሂሳብ ለመክፈል ኪሱን መፈታተሽ ሲጀምር አስቸኳይ ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ገባኝ። ቀድሜዉ ሦስት ድፍን ድፍን መቶ ብሮች ጠረጴዛዉ ላይ አስቀመጥሁ።
“ምን ተፈጠረ?” አለ እሸቴ፣ እሱም እንደኔ ጥድፊያዉን በጥሞና እየተከታተለዉ ቆይቶ።
“ዕረፍት ያስፈልግሽ ነበር እዴ ዉቤ? አንድ መጥፎ ወሬ ደርሶኛል”
“ምነዉ ምን ተፈጠረ? ከየት ነዉ?”
“መስጊድ ላይ እሳት ተነስቷል ነዉ የሚሉኝ”
“የ..ት?” አለ እሸቴ፣ ልለዉ የነበረዉን ከአፌ ነጥቆኝ።
“ተከተሉኝ” ብሎ ከምግብ ቤቱ የመሮጥ ያህል ተራምዶ ወጣ፡ በእሱ ፍጥነት እግር በእግር ተከትለነዉ አሳንሠሩ ዉስጥ ገባንና ቁልፉን ተጭነን ወደ ላይኛዉ ፎቅ ጋለብን፡ በጠመዝማዛዉ መንገድ ገብተን
የለመድናቸዉን የደኅንነት ኬላዎች ሁሉ አልፈን በዚሁ ሕንጻ ወደ
ተሠወረዉ የሲራክ ፯ ማዕከል ስንደርስ፣ ሁሉም በየጥፍራቸዉ ቆመዉ አገኘናቸዉ እንኳንስ የጭንቅ ወሬ ተሰምቶበት፣ እንዲያዉም የዕረፍት
አልባዎች ቤት ነዉ ማዕከሉ
“እስኪ የታለ?” አለ ባልቻ፣ ከወገብ በላይ በግድግዳዉ ዙሪያ ወደ ተንጣለለዉ ዝርግ መከሰቻ ዓይኑን እያነጣጠረ፡
ደዉሎ የጠራዉ ልጅ የባልቻ ጥያቄ ስለገባዉ፣ የሚነካዉን ነካክቶ በርከት ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሰፊዉ መከሰቻ ከዳር እስከ ዳር ደረደረልን እስከ ሚናራዉ ድረስ በኃይለኛ እሳት ሲንቀለቀል የሚያሳዩ
የመስጊድ ምስሎች ናቸዉ። ወላፈኑ እዚህ ያለንበት ድረስ በሚለበልብ እሳት ሲነድ ይታያል። ብዙ ሰዎችም እሳቱን ለማጥፋት ዙሪያዉን ሲዋደቁ ይታያሉ እንደ እሳቱ አያያዝ ግን መስጊዱን ማትረፍ የሚቻል አይመስለኝም:: ባይሆን ዙሪያዉን ባልተዛመተ እና በአካባቢዉ ተጨማሪ ዉድመት ባልደረሰ ስል በልቤ ጸለይሁ

👍35❤2👎1
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
..የዌስት ሊን የቤተክርስቲያን ሰዓቶች ሁለት ሰዓት ሲሞላ ጮኹ ደወሎቹም እሑድ መሆኑን ለማብሠር ከሰዓቶቹ ተቀባብለው አስተጋቡ " ኮርነሊያ ልክ የደውሎቹን ድምፅ ስትሰማ እሑድ እሑድ ትለብሰው የነበረውን ዐይነት ሳይሆን ያዘቦት
ቀሚሷን አጥልቃ ከመኝታዋ ብድግ አለች „ ከወፍራም ዝንጉርጉር ጨርቅ የተሰፋ
እግር ጌጥና ባለጐፍላ ጉንጉን መቀነት ያለው አንድ የሌሊት ሰደዶ ቀሚስ ደርባ እስከ ቁርጭምጭሚቷ የሚደርስ ቀሚስ አጥልቃ እግር እግሩ ጥልፍልፍ የወፍ እግር "ጌጥና
ባለጎፍላ ጉንጉን መቀነት ያለው አንድ የለሊት ሰደዶ ቀሚስ ደርባለች " ይኸኛው በጥንቱ ጊዜ የናቷ የጧት ልብስ ነበር " ኮርነሊያ ዘመናዊውን አለባበስ በጣም ትንቅ ስለነበር ይኸን ልትጥለው አልፈለገችም ዘመናዊ ወይዛዝርት
በስፌቱ ዐይነት ሊሥቁ ይችሉ ይሆናል በጨርቁ ዐይነትና ጥራት ግን ሚስ ካርላይል በተለይ ትጠነቀቅበት ስለነበር ነውር ሊያወጡበት አይችሎም እሑድ እሑድ ጧት የእለቱን አለባበሷን አጠናቅቃ የመውጣት ልማድ ነበረባት ዛሬ ጧት ግን እንደ ልማዷ ለውሎዋ ጨርሳ ያለ መልበሷ ከቤት ውስጥ የሚሠራ ነገር እንደ ነበረባት ያመለክታል የራሷ መሸፈኛ ግን በቃላት ሊገለጽ አይችልም በልብስ የሞድ መጽሐፍም ሆነ ከዚያ ውጭ ተመሳሳይ አይገኝለትም " አንዳንድ ሰዎች የወንዶች ጥምጥም የሌሊት ቆብ ነው ሊሉት ይችላሉ ” ሌሎቹ ደግሞ ቅርጹ በጥንት ጊዜ በትምህርት ደካሞች የነበሩ ተማሪዎች ሲሣቅባቸው እንዲተጉ እየተባለ ከራሳቸው እንዲደፉት ይደረግ ከነበረው አፈ ሰፊና ራሰ ሾጣጣ ቆብና ከቤተ ክርስቲያን ደወል የተወሰደ ሊመስላቸው ይችላል " ያም ሆነ ይህ ቁመቱ ሾጠጥ ብሎ የወጣ ረጂምና ጎኑ ሰፊ ቀለሙ ነጭ የሆነ ግርማ ያለው ትልቅ ቁልል ነበር።
ሚስ ካርላይል መተላለፊያውን ተሻግራ ከራሷ መኝታ
ቤት ፊት ለፊት ወደ ነበረ መዝጊያ ሔደችና በቤቱ ውስጥ የተገኙትን ሰባቱንም ሰዎች በአንድ ጊዜ በቅሰቅስ ድምፅ እየደበደበች « †ነሥ አርኪባልድ ! ተነሥ ! » እያለች ጠራችው።
« ተነሥ ? ተነሥ ? » አለ እንቅልፍ የተጫጫነው አንድ ድምፅ ። «ለምንድነው የምነሣው ? ገና'ኮ ሁለት ሰዓት ነው »
« ገና ከጠዋቱ ዐሥራ ሁለትም ቢሆን መነሣት አለብህ » አለችው የሥልጣን ቃና ባለው አነጋገር " «ቁርስ ቀርቦ እየጠበቀ ነው " ሁላችንም የየራሳችን ጣጣ
አለብን ስለዚህ ቶሎ ተበልቶ እንዲያበቃ እፈልጋለሁ ።»
ሚስ ካርላይል ደረጃዎቹን ወረደችና ምግቡ ተዘጋጅቶ ወደሚጠብቅበት የቁርስ ክፍል ገባች » ምላሷ አንዳንድ ጊዜ ሁሉን ነገር ማየት የሚችለው
ሁልጊዜ ንቁና ስለታም ነበሩ " ክፍሉ በአውራ መንገዱ በኩል ነው። መስኮቶቹ ተከፍተዋል"" እንደ ሚስ ካርላይል ምንም ነቁጥ የማይገኝላቸው የሚያምሩት
ነጭ መጋረጃዎች በለስላሳው የበጋ ነፋስ ላመል ያህል ይወዛወዛሉ የክፍሉን
ዙሪያ አትኰራ ትመለከት ትንሽ ብናኝ ታያት ያየችውን ለጆይስ ልታበሥር ወደ ወጥ ቤት ተንደርድራ ሔደች ጆይስ ለቁርስ የሚዘጋጀው ሥጋ ሲጠበስ እየተቆጣጠረች ከእሳቱ ዳር ቁማ አገኘቻት
ይህን ያህል ሥራን ቸለል ማለት ምን የሚሉት ድፍረት ነው ጆይስ ? የሜግብ ቤቱ አቧራ ተወልውሎ አያውቅም»
« ተወልውሉ አያውቅም ?! ዐይኖችዎን ከምን ላይ ቢያሳርፏቸው ነው እንደዚህ የሚሉኝ ? »
አቧራው ላይ ነዋ ! » አለች ሚስ ካርላይል «በይ አሁን መወልወያ ያዥና ሔደሽ እይው » እኔ ከቁሻሻ ክፍል ውስጥ ግብቼ መቀመጥ አልችልም " ዛፊ ጠዋት
እርምሺን ትንሽ ተጨማሪ ሥራ ሠራሽና ነው እንዶዚህ እርግፍ አድርሽ የተውሺው ? »
« ኧረ እንዶሱም አይደለም ... እሜቴ እኔ ለራሴ በተጨማሪ ያዘዙኝን ሥራ ቶሎ ለመጨረስ ስል በዐሥራ አንድ ሰዓት ተነሣሁ አንድም ጉድለት እንዴይገኝ ተጠንቅቄ በተለይ ምግብ ቤቱን ተጨንቄ ነበር ያጸዳሁት " ግን እርስዎ መስኮቶቹ በጣም ይከፈቱ ስለሚሉ የውጭ አቧራ ሊበንበት ይችላል»
ጆይስ መወልወያ ይዛ ስትወጣ መጥሪያው ተደወለ " ወዲያው አንድ ቁመቱ መካከለኛ የሆነ ወፈር ያለ አሽከር ከማብሰያ ቤት ገባ "
« ምን ፈለግህ ፒተር ? » አለችው ሚስ ካርላይል "
« ለጌቶች የጢም ውሃ ብዬ ነው .. እሜቴ " »
« ጌቶች አሁን የጢም ውሃ" አያገኙም። ሒድና ንግረው ቁርስ ቀርቦ እየጠበቀ ስለሆነ ኋላ ይላጭ
ፒተር መልሶ መልእክቱን አለዝቦ ነገረው » ሚስተር ካርላይልም በቀዝቃዛ ውሃ ተላጭቶ ለባብሶ ወደቁርስ ቤት ሲገባ ኮርኒሊያ ከምግቡ ጠሬጴዛ ተቀምጣ
ስትጠብቀው አገኛት።
« ለምንድነው ዛሬ አለወትሮአችን በሁለት ሰዓት የምንበላው ? »
« ብዙ ሥራ አለብኝ » የቁርስን ጣጣ ቀደም ብዬ ካልገላልኩ ሌላ
ሥራዬን ሳላጠናቅቅ የቤተክርስቲያን ሰዓት ይደርስብኛል " ወጥ ቤቷ ሔዳለች»
« ሔዳለች ? » አለ ሚስተር ካርላይል የሷን ንግግር በመድገም
« አዎን አንተ ማምሻህን ከወጣህ በኋላ ነገር ተነሣ " ይኸን ለመንገር ብዬ ደሞ ተቀምጬ አልጠበቅሁሀም ለዛሬ ራት ዶሮ እንዲዘጋጅ ፈልጌ ነበር "
ዶሮቹ ብልታቸው ተለያይተው ታጥበው እንዲቀመጡ ያዘዝኳት ለትናንት ነበር "
ትናንት ብጠይቃት ተሰናድቶ አልቋል አለችኝ »

👍12
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የጣርያው ስር ክፍል
የጠዋቱ አራት ሰዓት መጣ፣ ሄደ፡
በየቀኑ ከሚመጣልን ምግብ የሚተርፈንን በቤቱ ውስጥ ቀዝቃዛ ሆኖ ባገኘነው በልብስ ማስቀመጫ መሳቢያው ስር አስቀመጥነው፡ በሌላኛው የህንፃው ክፍል አልጋ በማንጠፍ ላይ ያሉት ሠራተኞች ቀጥሎ ደግሞ ወደ ታችኛው ክፍል
መውረዳቸው ስለማይቀር ይህንን ክፍል ለሚቀጥሉት አራት ሰዓታት
አያዩትም፡
እኛም ክፍሉ ስለሰለቸንና የተመደበችልንን የተወሰነች ቦታ በደንብ ለማየት ስለጓጓን የመንትዮቹን እጆች ይዘን ልብሶቻችንን የያዙት ሻንጣዎች ወዳሉበት የልብስ ሳጥን በፀጥታ አመራን፡ እስካሁን ልብሶቻችንን ከሻንጣ አላወጣንም ነገ ብዙ የሚያማምሩ ክፍሎች ወዳሉበት ትልቁ ቤት ስንገባ፣ ልክ ፊልሞች
ላይ እንደምናየው እኛ ለመጫወት ወደ ውጪ ስንወጣ ሠራተኞቹ ደግሞ ሻንጣዎቻችንን ከፍተው ልብሶቻችንን ያስተካክሉልናል በወሩ መጨረሻ ላይ ባለው አርብ ሠራተኞቹ ለማፅዳት ሲመጡ በእርግጠኝነት እዚህ ክፍል ውስጥ አንኖርም።
በትልቁ ወንድሜ መሪነት ወደ ጨለማው፣ ጠባቡና ዳገታማው ደረጃ አመራን የመተላለፊያው ግድግዳዎች ጠባብ ከመሆናቸው የተነሳ በትከሻዎቻችን
እየታከክናቸው ማለፍ ነበረብን፡፡
“ያውና!”
ጣራ ስር የሚሰሩ ብዙ ክፍሎች አይተን የምናውቅ ቢሆንም ይሄኛው ግን በጣም የተለየ ነው በቆምንበት ተገትረን ዙሪያውን በጥርጣሬ ተመለከትን ክፍሉ ጨለም ያለ ሲሆን ቆሻሻና አቧራማ ነው ከአቧራው የተነሳ ሩቅ ያሉት ግድግዳዎቹን ማየት የማይቻል ነበር የሆነ ሞቶ ሳይቀበር የቀረ ነገር ሳይኖር አይቀርም መሰለኝ ሽታው ንፁህ አይደለም፡ ክፍሉ በአቧራ
በመሸፈኑ ምክንያት በተለይ ጨለም ባሉት ጥጋጥጎች ላይ ያለው ሁሉም ነገር የሚንቀሳቀስ
ይመስላል።
ከመግቢያው ባሻገር አራት መስኮቶች ከጀርባው ደግሞ ሌሎች አራት መስኮቶች ሲኖሩት ጎንና ጎኑ ግን መስኮት የለበትም በደንብ ካልተጠጉ በስተቀር ምን
እንዳለ ማየት አይቻልም ተራ በተራ
ከደረጃው ላይ ወረድን፡
ወለሉ ከእንጨት የተሰራ ሲሆን ለስላሳና የበሰበሰ ነው። በፍርሀት ስሜት እየተጠነቀቅን ቀስ እያልን ስንራመድ ወለሉ ላይ ያሉት ነፍሳት በሁሉም አቅጣጫ ተርመሰመሱ ክፍሉ ብዙ ቤቶችን ሊያሳምር የሚበቃ ቁሳቁስ ተቀምጦበታል ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ነገሮች የተሸፈኑበት ነጭ ጨርቅ
አቧራው ለብሶ ግራጫ ሆኗል፡ የተሸፈኑትን ዕቃዎች ዝም ብዬ ስመለከት የሚያንሾካሹኩ ጣዕረሞቶች ስለመሰሉኝ ጀርባዬን በረደኝ፡፡
ራቅ ያለውን ግድግዳ ተደግፈው በመደዳ የቆሙ ጌጠኛ ቁምሳጥኖች አየን ጠጋ ብለን ስንመለከት እያንዳንዳቸው በጥንታዊ ልብሶች የተሞሉ ሆነው
አገኘናቸው: እኔና ክሪስቶፈር በጥርጣሬ እየተመለከትናቸው ሳለን መንትዮቹ ደግሞ እኛ ላይ ተለጥፈው በትላልቅና በፈሩ አይኖቻቸው ዙሪያውን ያጤናሉ።
“እዚህ ይሞቃል ካቲ” አለች ኬሪ
“አዎ ይሞቃል”
“እዚህ መሆን አስጠልቶኛል!”
ወደ ኮሪ ስመለከት ትንሽ ፊቱ በፍርሀት ተውጧል ዙሪያውን እየተመለከተ ጎኔ ልጥፍ ብሏል በድሮ ሰዎች ልብሶችና አለባበሶች መመሰጤን አቁሜ የእሱንና የኬሪን እጆች ግራና ቀኝ ያዝኩና ሁላችንም ይህን ቦታ እንዴት
እንደምናደርገው ማሰብ ጀመርን፡ መታየት ያለበት ነው፡ በሺዎች የሚቆጠሩ አሮጌ መፃህፍት፣ ጥቋቁር የሂሳብ ሰነዶች፣ የቢሮ ጠረጴዛዎች ሁለት ትልልቅ ፒያኖዎች ሬዲዮኖች፣ በሁሉም መጠንና ቅርፅ ያሉ የቀሚስ
አይነቶች የወፍ ጎጆ ከነመስቀያው መጥረጊያ፣ አካፋዎች፣ በፍሬም ውስጥ የተቀመጡ የሞቱ ዘመዶቻችን ፎቶግራፎች ይታያሉ። ፎቶግራፉ ላይ ያሉት
ሰዎች አንዳንዶቹ ቀላ ያሉ አንዳንዶቹ ጥቁር ፀጉር ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም በሚባል አይነት የሚያስፈሩ፣ ጨካኝ፣ መራራ፣ ያዘኑ፣ ተስፋየለሾችና ባዶ
አይኖች ያሏቸው ናቸው እምላለሁ አንዳቸውም ደስተኛ አይኖች የሏቸውም።አንዳንዶቹ ፈገግ ብለዋል ብዙዎቹ ግን አላሉም አንድ በመጠኑ ፈገግ ያለች፣ እድሜዋ ምናልባት አስራስምንት አመት የሚሆናት ልጅ ፎቶ ቀልቤን
ሳበው ፈገግታዋ ሞናሊዛን አስታወሰኝ፡ ይቺ ግን የበለጠ ቆንጆ ናት።ጡቶቿ ተለቅ ያሉ ከመሆናቸው የተነሳ ክሪስቶፈር አንዱን ቀሚስ እያመለከተ
“የእሷ ነው!” አለ
“ቁንጅና ማለት ይሄ ነው” አለ በአድናቆት ተሞልቶ :: የተርብ የመሰለ ወገብ፣ ሞላ ያለ ዳሌ፣ ጎላ ያሉ ጡቶች: ካቲ… እንደዚህ አይነት ቅርፅ ቢኖርሽ ሀብታም ትሆኚ ነበር:"
“እውነት?” አልኩት በመሰላቸት፡ “ምንም አታውቅም ማለት ነው ይህ የሴት ተፈጥሯዊ ቅርፅ አይደለም ከውስጥ ኩርሲ ለብሳ ነው፡ ኩርሲው ወገቧን አጣብቆ ይይዛትና ከላይና ከታች ያለውን ጎላ አድርጎ እንዲታይ ያደርገዋል ''
“የሌለው ስለጨመቅሽው አይወጣም” አለ፡ ሌላ ቅርፅዋ የሚያምር ወጣት ሴት ተመለከተና “ታውቂያለሽ የሆነ ነገሯ እናታችንን ይመስላል፡ ፀጉር አሰራሯ ቢቀየርና ዘመናዊ ልብስ ብትለብስ ቁርጥ እሷን ነው የምትመስለው:"
“ይህቺ ልጅ ደስ ትላለች እናታችን ግን የበለጠ ውብ ናት” ብሎ አጠቃለለ
ይሄ ትልቅ ቦታ ፀጥታና ጭር ያለ ከመሆኑ የተነሳ የራስን የልብ ትርታ
መስማት ይቻላል ሆኖም ግን እያንዳንዱን ነገር መመርመር፣ እያንዳንዱ ሳጥን ውስጥ ያለውን መፈተሽ፣ እነዚያን ያረጁና የሚሸቱ ልብሶች መሞከርና እንደነሱ ማስመሰል ደስ የሚል ነገር ነበር ግን በጣም ይሞቃል። ያፍናል
ሳምባዬ ከሰበሰበው አቧራና ቆሻሻ አየር የተነሳ የተዘጋ መሰለኝ፡
ክሪስቶፈር መንትዮቹ ማማረር እንደጀመሩ ስለተመለከተ። “አሁን ተመልከቱ መስኮቶቹን በትንሹ እንከፍታቸዋለን፡ ከዚያ ንፁህ አየር በትንሹም ቢሆን ይገባል ማንም ሰው ከምድር ሆኖ የመስኮቶቹን መከፈት ማየት አይችልም::”
አለ፡፡ ከዚያ እጄን ለቀቀና ሳጥኖቹንና ዕቃዎቹን እየዘለለ ትቶኝ ወደ ፊት ሮጠ፡ ከዚያ የማይታይበት ቦታ ሆኖ ኑ ያገኘሁትን ተመልከቱ!” ሲል
ተጣራ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማል።
የሆነ ደስ የሚል አስገራሚ ነገር ለማየት ሮጥን፡ ያሳየን ግን አንድ ክፍል ነው ክፍሉ ቀለም አልተቀባም ግን ኮርኒስ ነበረው፡ ፊት ለፊት ያለውን መቀመጫ ስንመለከት ክፍሉ ለአምስት ልጆች የሚሆን የመማሪያ ክፍል
ይመስላል ክፍሉ ውስጥ ከተቀመጠው ባረጁ መፃህፍት ከተሞላው መደርደሪ? በላይ ጥቁር ሰሌዳ ተሰቅሏል፡ የእኔ ሁሉንም እውቀት ፈላጊ! ወዲያውኑ የመፅሀፍቱን ርዕሶች ጮክ ብሎ ማንበብ ጀመረ፡ መፃህፍቱ ስሜቱን ከፍ
ለማድረግ በቂ ነበሩ ወደ ሌላ አለማት የማምለጫ መንገድ እንዳገኘ አወቀ:
ወደ ትንንሾቹ መቀመጫዎች ቀረብ ብዬ ስመለከት ስሞችና ቀኖች ተፅፎባቸዋል:: ለምሳሌ ጆናታን፣ ዕድሜ 11፣ 1864: አዴል፣ ዕድሜ 9፣ 1879። ይህ ቤት እንዴት አሮጌ ነው! ይህን ጊዜ መቃብራቸው ሳይቀር በአፈር ተሸፍኗል እነሱ ግን በአንድ ወቅት እነሱም ወደዚህ ተልከው እንደነበረ ሊነግሩን ስማቸውን
ትተውልናል። ግን ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያጠኑ ብለው እንዴት ወደዚህ ይልኳቸዋል? ግን አያቶቻችን እንደሚጠየፉን እንደኛ አይነት ልጆች ሳይሆኑ የሚፈለጉ ልጆች ይመስሉኛል፡ ምናልባት ለእነሱ ጊዜ መስኮቶቹ በደንብ
ተከፍተው ይሆናል ወይም ሰራተኞቹ ጥጉ ላይ ባሉት ምድጃዎች ላይ ከሰልና
እንጨት ያነዱላቸው ይሆናል።

👍35🥰5👏1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ጀርመን በእንግሊዝ ላይ የምታወርደው የቦምብ ናዳ እስኪቆም ድረስ መንግስት ትያትር ቤቶችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ዳንስ ቤቶችን ቢዘጋም ዳንስ ቤቶች ግን ህጉን ተጋፍተው የሌሊት ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡ ሄሪም በአንድ ዳንስ ቤት ውስጥ ተወሽቆ የአሜሪካን ሙዚቃ በጆሮው እየተንቆረቆረ ውስኪውን ይጨልጣል፡ ሬቤካን እንዴት ሸውዶ ጥሏት እንደሄደ እያሰበ እያለ ወንድሟ ድንገት ከች አለበት፡፡
እዳውን ሳይከፍል ከምግብ ቤቱ በመውጣቱ የጅል ስራ ሰርቷል ሬቤካ ደግሞ ክብሯን ሽጣ ገንዘብ የምትከፍል ዓይነት ሴት አይደለችም፡ ትንሽ
ስታስቸግር የምግብ ቤቱ ኃላፊ ፖሊስ ጠራ፡ ቤተሰቦቿም ፖሊስ ጣቢያ
ተጎተቱ፡፡ እንዲህ አይነቱን ችግር ሄሪ ዘወትር ሲሸሽ ነው የኖረው፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰላሳ ያህል እስረኞች ጋር ጣቢያ ተዘግቶበታል፡፡ ክፍሉ
መስኮት የሚባል ነገር የሌለው ከመሆኑም በላይ በሲጋራ ጢስ ታፍኗል፡
ሬቤካ ሄሪ የቀረበበት ክስና ማስረጃ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ለመሰረተችበት ክስ የምግብ ቤቱ ኃላፊ ምስክር ሆኖ የሚቀርብ ሲሆን ጌታ ሞንክፎርድም የጠፋውን የሸሚዝ ማያያዣ በተመለከተ ከሰውታል፡ ከዚህም የከፋ ነገር አለ፡ በወንጀል ምርመራ መምሪያ ሲመረመር ነው የዋለው
ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመት ወዲህ ጌጣጌጥ ጠፍቶብናል የሚሉት
አመልካቾች በርክተዋል፡ አመልካቾቹ ጌጣጌጦቹ ተሰርቀዋል የሚል ግምት
የላቸውም ምክንያቱም ለመውሰድ ዕድሉ ያላቸው እንግዶቻቸው ብቻ ናቸው ለፖሊስ የሚያመለክቱትም እንዲያው ከተገኙ በማለት ነው፡፡
በምርመራው ወቅት ሄሪ አይናገር አይጋገር መልስ ለመስጠት አሻፈረ ብሏል፡፡ ሆዱ ግን ታምሷል፡፡ እስካሁን የፈጸመው ስርቆት እንዳልታወቀበት እርግጠኛ ቢሆንም በተቃራኒው የሰማው ነገር ፍርሃት ለቆበታል፡
መርማሪው አንድ የጠበደለ ዶሴ አውጥቶ እስካሁን ጠፉ የተባሉትን
ጌጣጌጦች ዘረዘረና ‹‹ይሄ ሰው ከፍተኛ የጌጣጌጥ ፍቅር የተጠናወተው ብቻ
ሳይሆን ጌጣጌጥም ያውቃል አለ። ፋይሉ እሱ በተለያዩ ጊዜያት የመነተፋቸውን ጌጣጌጦች ጉዳይ የያዘ ሳይሆን አይቀርም ሲል ገመተ።
ስርቆቶቹ በተፈጸሙበት ጊዜ ሄሪ በነዚህ ቦታዎች ላይ እንደነበር የሚመሰክ
ምስክሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱም በፖሊስ
መበርበሩ አይቀርም:
አብዛኛዎቹን ጌጣጌጦች ቢሸጣቸውም ጥቂቶቹን አስቀምጧቸዋል፡ የሽሚዝ
ማያያዣውን የሰረቀው አንድ ፓርቲ ላይ ሰክሮ ከሚያንቀላፋ ሰው ላይ ነው: እናቱ ያደረጉትን የአንገት ጌጥ ደግሞ የወሰደው አንድ ሰርግ ላይ ከአንዲት ሀብታም ሴት ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ስራህ ምንድነው ብለው ቢጠይቁት ምን ብሎ ሊመልስ ነው?
ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እስሩን አጠናቆ ሲወጣ ደግሞ ውትድርና ውስጥ ይከቱታል፡፡ ይሄ ደግሞ ከእስር ቤት አይሻልም።
ይህን ሲያስበው ብርድ ብርድ አለው።
መርማሪው የሸሚዙን ኮሌታ ጨምድዶ ከግድግዳ ጋር ቢያላጋውም ትንፍሽ አልል አለ፡፡ ዝምታው ግን የትም አያደርሰውም፡፡ሄሪ ነጻ
ለመውጣት ያለው አንድ እድል ብቻ ነው፤ ደኛው በዋስ እንደለቁት
ማድረግና ከአገር መጥፋት፡፡ ልክ በሰዓታት
ዳኛው በዋስ እንዲለቁት
ለዓመታት እንደታሰረ ሰው ያህል ነጻነቱን ተመኘ፡፡
ሀብታሞችን እየዘረፈ አኗኗራቸውን እየተላመደው መጥቷል፡፡ ጧት ዘግይቶ ከእንቅልፉ ይነሳል፤ የሚያማምሩ ልብሶች ይለብሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ደግሞ እንደ መሰሎቹ አነስተኛ ቡና ቤት ሄዶ ወይም እናቱን ይዞ
መዝናናቱንም አልተወም፡፡ ነገር ግን የእስር ቤት ኑሮ ለጠላቱ አይስጠው ቆሻሻ ልብስ፣ አሸር ባሽር ምግብ፣ መተፋፈጉ ከሁሉም በላይ ደግሞ ትርጉም የሌለው ኑሮ፡፡
በዋስ እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ማሰብ ጀመረ፡፡ ፖሊስ የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ባይፈልግም ዳኞቹ መወሰን አለባቸው፡፡ ሄሪ እስር ቤት ገብቶ
ባያውቅም ከየስዉ አፍ እንደሰማው የዋስ መብት የሚከለከለው ለግድያ
ወንጀል ብቻ ነው፡ ይሄን ደግሞ ሁሉም ሰው ያውቀዋል፡፡ ባብዛኛው ዳኞች ፖሊስ የጠየቀውን ነው የሚያደርጉት፡ ሁልጊዜም ባይሆን ተከሳሾች አሳዝነው ከነገሯቸው ሆዳቸው ሊራራ የሚችልበት አጋጣሚ ይኗራል አንዳንዴ ደግሞ ጋጠወጥ ፖሊስ ሲገጥማቸው የበላይነታቸውን ለማሳየት
ሲሉ ዋስ የሚፈቅዱበት ጊዜም አለ፡፡ የዋስ መብቱን ለማስከበር የሚያሲዘው
ገንዘብ አያጣም፡፡ ለዚህ ችግር የለበትም፡፡ ረብጣ ገንዘብ አለው፡፡ ስልክ
እንዲደውል ስለተፈቀደለት እናቱ ጋ ደውሎ ‹‹የዋስ መብቴን ሊያከብሩልኝ
ነው እማማ›› አለ ሄሪ
‹‹አውቃለሁ የኔ ልጅ›› አሉ ‹‹እናቱ አንተ ሁልጊዜ ዕድለኛ ነህ››
ብዙ ጊዜ ከችግር አምልጫለሁ አሁን ግን እንጃልኝ ሲል አሰበ፡፡
የእስር ቤት ዘበኛው ‹‹ማርክስ›› ሲል ተጣራ
ሄሪ ተነስቶ ቆመ ዳኞቹ ሲጠይቁት ምን እንደሚል ያቀደው ነገር የለም፡ እንደመጣለት የመናገር ችሎታ ያለው ቢሆንም ለዚህ ጊዜ ግን ተዘጋጅቶ ቢሆን በወደደ፡፡ ክራቫቱን አጠባብቆ ኮቱን ቆላለፈ፡ አገጩን አሻሽና ጢሙን እንዲላጭ ቢፈቅዱለት ተመኘ፡፡ በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለትና የሸሚዙን ማያያዣ አምባር ከክንዱ ላይ አንስቶ ኪሱ ከተተው፡፡
ችሎቱ ውስጥ ሲገባ ፊት ለፊት የዳኞቹ መንበር ጉብ ብሏል፡ ህዝብ የተቀመጠበትን ቦታ ሲያማትር እናቱ የክት ልብሳቸውን ለብሰው ራሳቸው ላይ ቆብ ደፍተው ተቀምጠዋል፡ የዋስ ገንዘብ እንዳለ ለማመልከት ይመስላል አስር ጊዜ ደረታቸውን ይደባብሳሉ፡ ከአንዷ ሀብታም ላይ የመነተፈውን የኮት ማያያዣ ጌጥ አድርገውት ሲያይ ፍርሃት ጨመደደው፡፡ እጁ
እንዳይንቀጠቀጥበት የተከሳሽ መቀመጫውን ፍርግርግ ለቀም አድርጎ ያዘ፡፡
አፍንጫው አለቅጥ የረዘመው አቃቤ ህግ ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት፣ ተከሳሹ
የሎርድ ሞንክፎርድ የሆነ ሃያ ፓውንድ ጥሬ ገንዘብና ጥንድ ከወርቅ የተሰሩ የሸሚዝ ማያያዣዎች ስርቆትና አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተመግቦ ሳይከፍሉ የመውጣት ጥፋት በመፈጸም ተከሷል፡ ፖሊስ የበርካታ ገንዘብ ስርቆት ጉዳይ እየመረመረ ስለሆነ ይህ ተከሳሽ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ይጠይቃል›› አለ፡፡
ሄሪ ዳኞቹን ሲመለከት ሁለቱም በንቀት ያዩታል፡ እነሱም ፊታቸው የቀረበ ሁሉ ጥፋተኛ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡ ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡እንግዲህ የመሃል ዳኛው ናቸው ወሳኙ፡፡ ሰውዬው ሪዛቸው የሸበተ ሲሆን ገፅታቸውን ላነበበ በስራ ዘመናቸው በርካታ የክስ ጉዳይ ሲዳኙ የኖሩ
መሆኑን ያሳያል፡፡ እሳቸውን ነው መጠንቀቅ ሲል አሰበ ሄሪ፡፡
የመሃል ዳኛውም ‹‹የዋስ መብት ትጠይቃለህ?›› አሉት
ሄሪ ግር አለው ‹‹ወይ አምላኬ፤ አዎ ጌታዬ›› አለ፡፡
የትልቅ ሰው ንግግሩን ሶስቱም ዳኞች አስተዋሉ፡
ሄሪም ይህን ተገንዝቧል፡፡ የሰዎችን ግምት ማስለወጥ በመቻሉ ይኮራል፡ የዳኞቹ ሁኔታ ስላበረታታው አሞኛቸዋለሁ ሲል አሰበ፡፡
‹‹ምን ትላለህ?›› ሲሉ ጠየቁት።
‹‹አንድ ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ጌታዬ›› ሲል ጀመረ፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ለመስማት በማቆብቆብ ወንበሮቻቸው ላይ ሲቁነጠነጡ ታዩ፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር በዚያ ምሽት ካርልተን ቡና ቤት
አንዳንዶቹ ሰዎች በጣም ጠጥተው ነበር›› አለና ዳኞቹን አማተረ፡
‹ካርልተን ክለብ ነው ያልከው?››
ሄሪ ከሚገባው በላይ የሄደ መሰለው፡፡ ምናልባትም የዚህ ክለብ አባል ነኝ ማለቱን ሊያምኑ ይችላሉ፡፡
ከዚያም ፈጠን ብሎ ‹‹በእውነት በጣም ያሳፍራል፡፡ ነገር ግን አሁኑኑ
እቦታው ድረስ ሄጄ ሁሉንም ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ልክ የምሽት
ልብስ መልበሱን ድንገት እንዳስታወሰ ለመምሰል ‹‹ይህን የለበስኩትን ልብስ
ለውጬ›› አለ።

👍18