አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ሳይሆን የሥነ ምግባሩን ሥርዓት ያወቀ ከራግቤ ትምህርት ቤት ከጨረሰ በኋላ ኦክስፎርድ ዩኒቬርስቲ ተምሮ በድግሪ የተመረቀ ምሑር ነው ።

«ሚስተር ካርላይል » አለ የቤቱ ጌታ እንደ ተቀመጠ እጁን እየዘረጋ ። « መቼም
ለመነሣት ብሞክር በብዙ ችግር ካልሆነ በቀር እንደማይሆንልኝ ሁኔታዬን የምታየው ነው። ያ የተረገመ እሪህ ዛሬ ደግሞ እንደገና ተነሣብኝና አመመኝ ። ተቀመጥ እስቲ ። ከከተማ መጥተህ ሰንብተሃል እንዴ ? »

« ክቡርነትዎን ማነጋገር ስለፈለግሁ አሁን ከዌስት ሊን መምጣቴ ነው ። »

« ምንድነው የመጣህበት ? » አለው ዊልያም ቬን ምናልባት ሚስተር ካርላይል ከነዚያ ብዙ ነዝናዞች ባለዕዳዎች ለአንዱ ገንዘቡን ለማስመለስ ሊከራከርለት ተቀጥሮ እንደሆነ የሚል የጥርጣሬ ሐሳብ ስለ መጣበት እየቀፈፈው ።

ሚስተር ካርላይል ፡ ወንበሩን ወደ በሽተኛው አስጠግቶ ድምፁን ዝቅ በማድ
ረግ « አመጣጤማ ጌታዬ ፡ ኤስት ስንን ሊሸጡት ነው የሚል ወሬ ሰምቼ ነው ። »

« ቆይ እስቲ ጌታዬ » አለው ቀደም ሲል የመጣበት ጥርጣሬ ይበልጥ ግልጽ መስሎ ተሰማውና ። « ሁለታችንም እውነተኞች ሆነን ፡ ተማምነን ምስጢር መጫወት እንችላለን ?ወይስ ይህ ጥያቄህ የሚያስከትለው ሌላ ነገር አለው? »

« ምን ለማለት እንደ ፈለጉ አልገባኝም » አለው ሚስተር ካርላይል ።

« ስማኝ ! ......... በግልጽ ስናገር እንዳይከፋህ ። መጠርጠር አለብኝ ። እነዚያ ነገረኞች አበዳሪዎቼ ራሳቸው ሞክረው ያቃታቸውን መረጃ አንተ ከኔ መግምገህ እንድትወስድላቸው ልከውህ እንደሆነስ ? »

« በርግጥ » አለ እንግዳው « አንድ ጠበቃ ስለ ክብሩ እምብዛም ሳያስብ ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጥር ዐውቃለሁ። እኔን ግን ያውም በእርስዎ ላይ ሥውር ተንኮል ይወራብኛል ብለው አይጠራጠሩ ። እስከ ዛሬ አንድም አሳፋሪ ሥራ መፈጸሜን አላስታውም ። ለወደፊትም የሚቃጣኝ አይመስለኝም ።

« ይቅርታ አድርግልኝ በል ....ሚስተር ካርላይል ። ከተፈጸመብኝ ብዙ
ተንኮል ውስጥ እኩሌታውን እንኳን ብታውቀው ኖሮ ፡ ማንንም በመጠርጠሬ
አትፈርድብኝም ነበር ። በል እስቲ የመጣህበትን ንገረኝ ። »

“ ኢስት ሊንን ሊሸጡት እንደሚያስቡ ወኪልዎ እንዲያውም በደፈናው እንደ
ዘበት አድርጐ ነግሮኛል ። በእርግጥ የሚሸጡት ከሆነ እኔ ላስቀረው አስቤ ነው ።

« ለማን ? »

« ለራሴ ። »

« ላንተ ለራስህ ! » አለና ሣቀ ። « ሆ! ሆ! ጥብቅና እኮ ......... ደኅና ሥራ ነው።

« እንዴታ » አለ ሚስተር ካርላይል ። « በተለይ እንደኛ ብዙ ከፍተኛ ጉዳዮችን ለሚከታተሉ ። ከዚህ ሌላም ከአጎቴና ከአባቴ ጠቀም ያለ ውርስ ማግኘቱን
ያስታውሳሉ ። »

«እሱን ዐውቃለሁ ። በዚህ ላይ ደግሞ የጥብቅናህ ገቢ አለ ። »

« ይኸ ብቻ ሳይሆን እናቴም በጋብቻዋ ጊዜ ብዙ ገንዘብ ይዛ መጥታ ነበር ።
አባቴም ያን ገንዘብ ደኅና አድርጎ በማንቀሳቅስ አበራከተው ። እኔም ገንዘቡን ከአንድ ቁም ነገር ለማዋል ሳስብ የኢስት ሊንን የመሸጥ ወሬ ሰማሁ ። የተወራው እውነት ከሆነና በዋጋም ከተስማማን እኔ አስቀረዋለሁ ። »

ዊልያም ቬን ጥቂት አሰበና፡ « ሚስተር ካርላይል እኔ በጣም በሚያሳስብ ሁኔታ
ላይ ነው ያለሁት ። ጥሬ ገንዘብ በጣም ያስፈልገኛል ። ኢስትሊን ከማንኛውም
የውርስ ግዴታ ነጻ ነው ። ከዋጋው ጋር የሚመጣጠን የወለድ አግድ ዕዳም የለበትም ። የዛሬ ዐሥራ ስምንት ዓመት በደኅና ዋጋ የገዛሁት ጊዜ የሻጮቹ ጉዳይ ፈጻሚ እንደ ነበርክ ትዝ ይለኛል ።

« አባቴ ነበር » አለ ሚስተር ካርላይል ሣቅ ብሎ ። « እኔማ ያን ጊዜ ገና
ልጅ ነበርኩ ። »

« አዎን አባትህ ማለት ነበረብኝ ። እንግዲህ ኢስት ሊንን ሸጩ ዕዳዬን ከከፈ
ልኩ በኋላ ፡ ለኔ የሚቀሩኝ ጥቂት ሺ ብሮች ብቻ ቢሆኑም ፡ ችግሬን የማቃልልበት ሌላ መንገድ ስለአጣሁ ኢስት ሊንን በመሸጡ ቆርጫለሁ። ግን ልብ በል ! የኢስት ሊን መሸጥ በይፋ ከተወራ ባለዕዳዎቹ እንደ ተርብ እንደሚወሩኝ ዕወቀው ። ስለዚህ አደራህን ፡ ሁሉን ነገር በምስጢር መያዝ አለብህ ። ገባህ ? »

« አዎን ገብቶኛል ፡ ለመሆኑ ስንት ይሉታል ? »

« ስለዝርዝሩ ነገር ከወኪሎቼ ከዋርበርትንና ከዌር ጋር ተነጋገር ። ቢሆንም ከሰባ ሺ ፓውንድ አይወርድም ።

« ይኸማ በጣም በዛ ...... .. ጌታዬ » አለ ሚስተር ካርላይል ።

« ኧረ ይኸም ሲሆን ዋጋው አልነበረም !!»

« የግፊት ሺያጮች ምን ጊዜም የሚገባቸውን ያህል ዋጋ አያወጡም »

አለና ግልጹ ጠበቃ ነገሩን በመቀጠል
« እኔ ደግሞ ከሚስተር ቦሻም ጭምጭምታውን ከመስማቴ በፊት ኢስት ሊን ለሴት ልጅዎ በውርስ የተሰጠ ይመስለኝ ነበር ።»

« ይገርምሃል ለሷ የተላለፈ ምንም ነገር አልተያዘም » አለ ዊልያም ቬን የግንባሩ መኮማተር በግልጽ እየታየበት ። « ለዚህ ሁሉም ምክንያት ነገሩን አዙሬ ሳላይ የፈጸምኩት የጠለፋ ጋብቻ ነው ። ከጄኔራል ኮንዌይ ልጅ ጋር ፍቅር ይዞኝ
ነበር። እሷም ተከትላኝ ኮበለለች ። በርግጥ እኔም እሷም ተሳሳትን ። አባቷ እኔ የልጅነት ዕብደቴን ካልተውኩ ልጃቸውን ' ሜሪን እንዳገባ እንደማይፈቅዱልኝ ቁርጡን ነገሩኝ ። እኔም ልጅቱን ወደ ጌሬትና ግሪን አስኮብልዬ ያለ ምንም ውል አገባኋት ። እኔ የማውንት እስቨርን ኧርል ተብዬ ስለ ነበር እሷንም እመቤት ማውንት
እስቨርን አልኳት ። ጀኔራሉ ልጃቸው መኮብለሏን ሲሰሙ ንዴት ገደላቸው ። »

« ገደላቸው ? » አለ ሚስተር ካርላይል

« እዎን ገደላቸው " ሰውየው ቀድሞውንም ልበ በሽተኛ ነበሩ ። ኋላ ደግሞ ይኸ በጣም ያናደዳቸው ምክንያት ተፈጠረና በሺታቸው ጠናባቸው ! በመዉረሻም ወሰዳቸው " ያቺ ምስኪን ሚስቴ ደግሞ የአባቷን መሞት ከሰማችበት ጊዜ ጀምሮ ለመሞታቸው ምክንያት እሷ መሆኗን በማሰብ አንድ ቀን እንኳን ደስ ሳይላት
ሕይወቷ ለማለፍ በቃ ። አባቷን ንዴት እንደ ገደላቸው እሷንም የገደላት ጸጸት መሰለኝ ብዙ ዓመት ታመመች ።

« ሐኪሞች የሳንባ በሽታ ነው ቢሉም ይዞታው ግን የጠቅላላ ሰውነት ማለቅ
ነበር ። እዚህ ያመኛል ፡ እንደዚህ ይሰማኛል ሳትል እልቅ ብላ መነመነች ። በቤታቸው ደግሞ የሳንባ በሽታ አልነበረባቸውም ። ብቻ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ሲደርስ እንዳየሁት የጠለፋ ጋብቻ ሲባል እንከን አያጣውም ። ምን ጊዜም ቢሆን አንድ መጥፎ ነገር
ይከተለዋል » አለና ሐሳብ ይዞት ጭልጥ አለ ። « ከጋባችሁ በኋላ የተፈጸመ
አንድ የስምምነት ውል ሊኖር ይችላል » አለው ሚስተር ካርላይል ። ዊልያም ቬን ከያዘው ሐሳብ ምልስ አለና፡ «ሊኖር ይችል እንደ ነበር ዐውቃለሁ ። ግን አልተፈጸመም ። እሷ ሀብት የሚባል ነገር አልነበራትም ። እኔ ደግሞ በገንዘብ መርጨት ዕብደት ተጠመድኩ ። ስለዚህ ሁለታችንም ወደፊት ስለሚወለዱት ልጆቻችን ቅርስ ያለ ጉዳይ አላሰብንበትም ብናስበውም እንኳን አልፈጸምነውም ። አየህ................
ሚስተር ካርላይል ፡ በማንኛውም ጊዜ ሊሠራ የሚችል ነገር፡ ምን ጊዜም ሳይሠራ ይቅራል የሚባል ያባቶች ምሳሌ አለ ። »
👍231
ሚስተር ካርላይል ፡ ነገሩ የገባው መሆኑን ለመግለጽ እጅ ነሣ ። « ስለዚህ» አለ ዊልያም ቬን ንግግሩን በመቀጠል
« ልጄ ምንም ድርሻ የላትም ። ለኑሮዋ ከሚያስተማምን አንድ ቦታ ሳሳስጠጋት የሞትኩባት እንደሆነ ምን ያህል እንደምትቸገር ሳስበው ጭንቅ ይለኛል።በርግጥ ያቺ ከኔ ጋር ከመኮብለል በቀር ፡ ምንም እንከን ያልነበራት እናቷ በደንብ አድርጋ ስላሳደገቻት የመብለጭለጭና የልታይ ባይነት ቅብጠት አታውቅም ። እናቷ ዐሥራ ሁለት ዓመቷን ስትጨርስ እንደ ሞተችባት ጥሩ
ሞግዚት ተገኘችላት ። በመልኳም ይህ ቀረሽ የማትባል ቆንጆ ናት ።

« ሥነ ሥርዓትን ተምራ ያደገችና መልክ የታደለች ስለሆነች ፡ ጥሩ ትዳር ሳትይዝ እንደማትቀር አምናለሁ ። መቸም እንደ እናቷ ወደ ግሬትና ግሪን ትኮበልላለች ብዬ አልሠጋም ። »

« እኔም ትዝ ትለኛለች » አለ ካርላይል በጣም የምታምር ልጅ ነበረች ። »
« አዎን ፤ እናቷ በሕይወት በነበረች ጊዜ ኢስት ሊን ሳለን አይተሃት ነበር ።
በል ወደ ዋናው ነገራችን እንመለስና፡ ኢስት ሊንን ከገዛህ የወለድ አግድ ዕዳ እንደተከፈለ ቀሪውን ገንዘብ በእጄ ተቀብዬ ለችግሬ ማዋል አለብኝ ። እንደምታውቀው እነዚያ የተረገሙ አበዳሪዎቼ ስለሺያጩ ፍንጭ ከሰሙ አንዲት ቤሳ እንኳን አላገኝም ። ስለዚህ ጉዳዩ በምስጢር ተጠብቆ ኢስት ሊን የሎርድ ዊልያም ቬን ንብረት መሆኑ ብቻ እንደሚታወቅ ሆኖ ለትንሽ ጊዜ ይቆያል ። አንተም በዚህ ቅር እንደ ማይልህ ተስፋ አለኝ ።»

ሚስተር ካርላይል መልስ ከመስጠቱ በፊት ጥቂት አሰበና ጭውውታቸውን
ቀጠሉ ። ከዊልያም ቬን ጠበቆች ከዋርበርተንና ዌር ጋር በበነጋው ጧት ተገናኝቶ እንዲነገጋር ተስማሙ ። ካርላይል ለመሔድ ሲነሣ ጊዜው መሽቶ ነበር ።

« ቆይና ራት በልተህ ሒድ እንጂ » አለው

ሚስተር ካርላይል አመነታ ። የገዛ ልብሱን አስተውሎ አየ ። ተራ የቀን ልብስ ነበር። ሎርድ ዊልያም ቬንን ከሚያህል ታላቅ ሰው ራት ግብዣ ላይ የሚለበስ ዐይነት አልነበረም ።.......

💫ይቀጥላል💫


ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
11👍6🥰2👏1🤩1
Forwarded from Yared😊 buttons

📌 በሀዘን😔
በደስታ😀
💻 በስራ ቦታ
💺 የእረፍት ጊዜ ለይ

የሚደመጡ ዝማሬዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
👏7👍4😁1
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በታደለ_አያሌው


...እንደ ክራሞቴ ቢሆን፣ ይኼን ስሰማ ጸጥ ብዬ መሞት ነበረብኝ፡ ያን ያህል ግን ከብዶ አልታየኝም፡ ብሎ ብሎ ድንጋጤ ሁሉ ከዉስጤ
ተሟጥጦ አለቀ መሰለኝ፣ የሐኪሜን ያህል ቀርቶ እንዲች ብዬ አልደነገጥሁም ጭራሽ እሷን ለማበረታታት ሁሉ ምንም አልቀረኝም

“ዉብዬ፣ መገናኛ አካባቢ ዶክተር ሙደያን ሻምሩን የሚባል አንድ ስመ ጥሩ ሐኪም አለ: he is a senior neurosurgeon. ለሰባት ዓመታት ያህል በሙያዉ ላይ ቆይቶበታል። እሱ ዘንድ እልክሻለሁ። ያዉ እዚህም
ሌሎች ታካሚዎች ስለቀጠርሁ ነዉ እንጂ፣ አብሬሽ መሄድ ነበረብኝ: ቢሆንም ግን በዶክተር ሙደያን ፊት ያን ያህል እንግድነት አይሰማሽም፣ እንደኔ ልትቆጥሪዉ ትችያለሽ”

ከሁኔታዋ አንጻር የተለየ ቀረቤታ እንዳላቸዉ ከመጠራጠር ባለፈ፣ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ግን አልጠየቅኋትም
“ያም ሆኖ ግን ታዲያ፣ ከዚያ የምናገኘዉን ምክርም ሆነ ዉጤት እንደ ተጨማሪ ግብአት እንጠቀምበታለን እንጂ፣ዉሳኔዉን የምንወስነዉ እኛዉ ነን። እኔ፣ አንቺ እና እሸቴ ብቻ” አለችኝ፣ እኔ ሥጋት እንዳይገባኝ ራሷ ሰግታ

ከተባለዉ ዶክተር ዉጤቱን እንዳገኘሁ ወደ እሷ እንድመለስ ለነገ ተቀጣጥረን ተለያየን፡

ከሆስፒታሉ ስወጣ፣ መጨላለም ጀምሯል፡በምሳ ሰዓት እመዋን ካገኘኋት ጀምሮ የነበረኝ በጎ ስሜት እስከ አሁንም ድረስ ባለመቀዝቀዙ እየተደነቅሁ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ በፈገግታ ተሞልቼ ለባልቻ ደወልሁለት። ከደወልሁለት፣ በተለይም በዚህ ስሜት
ሆኜ ካናገርሁት ሰንበት ብያለሁ።

“አባትዮዉ”

“ልጅዮዋ”

“ማግኘት ይቻላል?”

“ክራርሽን ይዘሽ ከመጣሽ?”

“በደስታ ነዋ ያዉም!”

“እንደሱ በይኛ! በይ ነይ: እንግዲህ አንቺ ከቢሮዬ እስከምትደርሽ ድረስ
ዓይኔን ከበሩ እንደማላነሳዉ ልባርጊ። ነዪልኝ ቶሎ” ከእሱ ይልቅ እኔ ራሴ እያንጎራጎርሁ ክራሬን መግረፍ፣ የዉሃ ጥም ያህል ቢያሰኘኝም፣ የእመዋን ነገር አንስቼለት በሚያወራልኝ ተጨማሪ ምስጢር ለመደመም ካለኝ ጉጉት አንጻር ግን ምኑም ላይ አይደርስም፡ ምን እና ምን! የእሷን ነገር ባሰብሁት ቁጥር አግራሞት ከደሜ ጋር በሠራ አካላቴ
ይዘዋወርብኛል ቅድም እንኳን ከሐኪሜ ጋር እንዲያ ሆነን ሁሉ፣
በየመሀሉ ትዉስ እያለኝ እንዲሁ ሲያደርገኝ ነበር

ወይ ጉድ!

ከእሱ አፍ እስከምሰማዉ እንደ ቸኮልሁ፣ በፊቴ ያገኘሁትን ታክሲ
ተኮናትሬ አቋራጭ አቋራጭ ቅያሶችን ለሾፌሩ እየጠቆምሁት ወደ ዋናዉ የማኅበሩ ሕንጻ አንከብክቦ አደረሰኝ፡፡ ወደ ሕንጻዉ ከገባሁ በኋላ፣ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ለመዉረስ ከሚያልፉበት መከራ ትንሽ መለስ ያለ ፍዳ የሚያቀምሰዉን ጠባቡን የሲራክ፯ መግቢያ እንደ ወትሮዬ በጥንቃቄ
አለፍሁበት፡

“አባትዮዉ” አልሁ ለራሴ፣ ወደ ባልቻ ቢሮ መሬቱን በኃይል እየረገጥሁ ብደርስም ቢሮዉ ዉስጥ አጥቼዉ ስቅቅ እያልሁ። ልመለስ ስል፣ ከኋላዬ
መጥቶ አቀፈኝ፡

“አባትዮዉ፣ ቀጥረኸኝ የት ገብተህ ነዉ?”

“መንገድ ላይ እኮ ባጠገቤ ነዉ ያለፍሽዉ: ብጠራሽ ብጠራሽ ልትሰሚ„ ነዉ አንቺ?”

“ባክህ ነፍሴንም አላዉቀዉ: ይልቅ ከየት ልጀምርልህ?”

“ምኑን?”

“የእመዋን ነገር ነዋ”

“ቆይ: ቆዪኝ እሺ እመለሳለሁ: እዚሁ እኔ ቢሮ ጠብቂኝ: ከእሸቴ ጋ
አንዲት ጊዜ የማትሰጥ ሥራ ላይ ነበርን። እሷን ከዉነን ቶሎ
እንመጣለን: እምጷ!” ብሎኝ በአንድ ትንፋሽ፣ hፊቴ አጣሁት
በጉጉቴ ነበልባል ላይ እንትፍ ብሎበት እንደሄደ ግን ይወቀዉ!
ከቢሮዉ ገብቼ ብዙ ጠበቅሁት ለብቻዬ እየተቁለጨለጭሁ፣ ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይኼኛዉ ጉጉቴ እየቀነሰ፣ ወንድሜ በሐሳቤ እየሞላ መጣ:ወንድሜ ጃሪም: እንደ ዋንጫ ጠላ እህትነትሽ በቅቶኛል እያለ የሚግደረደርብኝ ወንድሜ፡ በሚያዉቀንም በማያዉቀንም ሰዉ ዘንድ
እህቱ አይደለችም ተብዬ የታማሁበት፣ ጃሪም

የዛሬ ኹለት ወር ገደማ፣ ዐመጸኞችን እየመራ የቅዱስ ዑራኤልን ካቴዴራል ለማቃጠል ሲመጣ፣ በዓይኔ በብረቱ ያየሁትን የማይታመን ነገርስ ለማን ነገርሁት? ያን ጊዜ የጃሪምን ምስሎች ለሲራክ ፯ ብልክም፣
የኔ ወንድም ስለመሆኑ ግን እስካሁንም የታወቀ አይመስለኝም: እኛ በዋናነት ከምንላፋቸዉ አካላት መካከል የኔ ወንድም ጃሪም እንዳለበት
ከእኛ ማን ያዉቃል? ባልቻ? እመዋ? ኧረ አይመስለኝም:

ይብላኝላት ለእመዋ፤ ከገዛ ልጇ ጋር ለምትዋጋዉ!

ታዉቅ ይሆን ግን ይኼን ጉዷን? ጃሪም ራሱስ ሲራክ ፯ን ያዉቀዋል? የእመዋን እና የኔን ምስጢርስ? የሲራክ ፯ አባል መሆናችንንስ?

ማለቂያ የሌላቸዉን ጥያቄዎቼን ተከትሎ፣ ደዉይ ደዉይ የሚል ስሜትዐተጠናወተኝ፡ ከመሬት ተነስቶ ወይ ደግሞ ሐሜተኞችን ሰምቶ፣ የእናቴ ልጅ አይደለሽም, ብሎ የገዛ ሰማዩን ሳይቀር ከነቀነቀዉ በኋላ እኮ ፊት
ፊት ተገጣጥመን አናውቅም: እንኳንስ እንደ እህትና ወንድም
ልንደዋወል ቀርቶ፣ በመንገድ ላይ እንኳን ላለመተያየት ያልበላነዉ ፍዳ የለም

ለምሳሌ ባለፈዉ ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲያን እየሄድሁ ነበር ከርቀት
በመንገዴ ላይ እሱ ሲመጣ አየሁት: መንገዷ ደግሞ ቀጭን በመንደር መካከል መሿለኪያ ስለሆነች፣ ግንባር ለግንባር መገጣጠማችን የማይቀር
ነበር። ካየሁት በኋላ፣ ልክ አንድ ርምጃ በተራመድሁ ቁጥር ልቤ
መዉደቅ መነሳት ጀመረች: በዚያች ቅጽበት ስንቱን እንዳሰብሁት!ከልጅነታችን ጀምሮ ያሳለፍነዉ ጊዜ ሁሉ አንድ በአንድ እንደ ነፋስ ሽዉ እያለ አለፈብኝ፡ ከከተማ ከተማ፣ ከገዳም ገዳም፣ ከቤት ቤት፣ ከጨዋታ ጨዋታ እየተፍነከነክን የተሽከረhርነዉ ሁሉ መጣብኝ፡፡ ይኼንን
ለሚያህል ትልቅ ቤተሰብ የአንድ ሰዉ ያዉም የአንድ ካህን ደሞዝ
በቂያችን ሆና፣ ከእኛ አልፈን ወላጆቻችንን ጭምር የኑሮዉ ጫና እንዳይሰማቸዉ ማድረግ ችለን ነበር፡ ከሌሎች እህቶቼና ወንድሞቼ ጋር ክብ እየተቃቀፍን ጨለማዉን ቀን፣ ቀኑን ደግሞ ምርጥ ቀን አድርገን ያሳለፍነዉ ሳይቀር ትዝ አለኝ፡፡ ቀና ብዬ አየሁት እየተደራረስን ነዉ፡
እሱም እርምጃዎች ወደኔ ሲመጣ፣ እኔም ያን ያህል በተጠጋሁት ቁጥር፤
አሁን ግን ምን እንባባል ይሆን? የሚል ጭንቅ ዉስጥ ወደቅሁ።
መቼም ከአንዴም ኹለት ሦስት ጊዜ አፍ አዉጥቶ እህቴ አይደለሽም ብሎኛል። ካቴዴራል ሊያቃጥል ሲል ዓይኔ በብረቱ አይቶታል፣ ተፈራርተን ወር ሆኖናል፡ ታዲያ አሁን እንዲህ ብቻ ለብቻ ስንገናኝ፣ ምን ሊዉጠን ነዉ? ቆይ ምን ከመባባልስ ነዉ የምንጀምረዉ? በበኩሌ ለሰላምታ ራሴን እያረጋጋሁ ሳለ፣ እሱ አየኝ፡፡ ለካንስ እስከ አሁን አላየኝም ኖሯል፡ ልክ ሲያየኝ በምን ቅጽበት እንደ ተሸበለለ! ጥቅልል ብሎ ዞሮ ወደ መጣበት ፈረጠጠ፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ ስንትና ስንት ጊዜ
ተመላልጠናል፡ በዚህ ሁኔታ መሆናችንን ሆዴ እያወቀዉም፣ ደዉይ ደዉይ የሚለዉ
ስሜት ለምን አሁን እንደ ተጠናወተኝ አልገባኝም: ብቻ ጸንቶብኛል ለነገሩማ ምንስ ቢሆን ወንድሜ አይደል? ያዉም ከፍ ዝቁን አብሮኝ ያየ የእናቴ ልጅ!

ደወልሁለት

አያነሳም

ደግሜ ብሞክርም፣ አያነሳም: ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ በስልክ
የማግኘቱ ጉዳይ እንዳልሆነልኝ ሳዉቅ፣ ሌላ አማራጭ አጣበርሁ በአካል መፈለግ አማራጭ ሆኖ መጣልኝ፡፡ ነገር ግን፣ በዚህ ባሕር በሆነ ከተማ አንድ እሱን በእግር በፈረስ ፈልጎ ማግኘቱ፣ ባሕር ዉስጥ የወደቀችን ጠጠር ፈልጎ እንደ ማግኘት የማይሞከር ነገር ነዉ፡ ስለዚህ ከሲራክ ቢያንስ አንድ የሚረዳኝ ሰዉ ያስፈልገኛል፡
👍27👏4
ይኼን ሐሳብ ይዤ በነፍሰ ጡር ጉልበቴ መሬቱን በኃይል እየረገጥሁ፣ ከባልቻ ቢሮ ወጣሁ በሲራክ ፯ ማዕከላዊ መዋቅር ዘንድ ታህታይ የሆኑት፣ ዋና ዋናዉን ሥራ ግን የሚከዉኑት ባለሙያዎች ወደሚገኙበት
ሰፊ ክፍል ገባሁ፡ ይኼ ክፍል፣ የመረጃ ቅበላ እና ትንተና ጣጣ ሁሉ እንደሚሆን እንደሚሆን የሚደረግበት ሲሆን፣ በቁጥርም ደረጃ ቢሆን ከመስክ ሠራተኞች ቀጥሎ ብዙ የማዕከሉ አባላት ያሉበት በጉርድ መስታዎቶች የተሸነሸነ በጣም ሰፊ አዳራሽ ነዉ። የአሁኑ አመጣጤ ከእነዚህ አባላት መካከል አሁን በአካል ያለዉን እና ሊረዳኝ የሚችለዉን
ሰዉ አይቼ ልመርጥ ነዉ። ከበሩ ላይ ቆሜ የተሻለ ቀረቤታ ያለኝን አባል ለመምረጥ ግራ ቀኝ በዓይኔ ስቃብዝ፣ ዓይኔ ዉስጥ እሸቴ ጥልቅ አለ

“አንተ፤ እዚህ ነህ እንዴ?” አልሁት፣ እዚህ ይሆናል ብዬ ስላልጠበቅሁ።
“ከእሸቴ ጋር ሥራ ይዘናል ብሎኝ አልነበረም ባልቻ?” ከንፈሮቹን አሞጥሙጦ ወደ ኮምፒዉተሩ ጠቆመኝ <ታዲያ አሁንስ ምን
እያደረግሁ መሰለሽ? ማለቱ እንደሆነ ከገጽታዉ ላይ አነበብሁበት።ጆሮዉ ላይ የተሰካዉን ማዳመጫ ስመለከት ደግሞ፣ እዉነትም ባልቻ
ከዉጪ እሱ ደግሞ ከዚህ ሆነዉ የሚከዉኑት አንዳች ሥራ እንዳላቸዉ ገባኝ፡፡ ሥራዉ ምን እንደሆነ ማወቅ ግን አይጠበቅብኝም: ስለዚህ
ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅም አልፈለግሁም ብፈልግም አልችልም: ክልክል ነዉ

“አንዲት የግል ጉዳይ ላስቸግርህ?” የሚል ጽሑፍ ጽፌ፣ ወደ ፊቱ ገፋሁለት፡ እንደ ዉስጠ ሕጋችን ከሆነ፣ መረጃን ጨምሮ ማንኛዉንም የሲራክ ፯ ንብረት ለግል ጉዳይ መጠቀም የተከለከለ እና የሚያስቀጣ ነዉ
ሕግ እየተላለፍሁ መሆኔን ባላጣዉም፣ ወንድሜን ላገኘዉ የምችለዉ ግን ወይ አጋጣሚ መልሶ ካገናኘን፣ ወይ ደግሞ በሲራክ ፯ አሁናዊ የአድራሻ
ማሰሻ በመታገዝ ነዉ: ባይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ሕግ መተላለፌን
በምስጢር እንዲይዝልኝ፣ የራሴን ሰዉ እሸቴን ማግኘቴ ሕግ መተላለፉንዐእንድገፋበት የልብ ልብ ሰጠኝ፡ እሸቴም አላሳፈረኝም እሺ የሚል ፊቱን አሳየኝ፡

“ይኼ ሰዉ አሁን የት አካባቢ እዳለ ፈልግልኝ እስኪ” ከሚል ልመና ጋር የጃሪምን ቁጥር ጽፌ ወረቀቱን እንደገና ገፋሁለት።

አንድ አፍታ ቆይቶ፣ ወደ ኮምፒዉተሩ እንድመለከት ፈቀደልኝ፡ ቁጥሩን ወስዶ ሲያስስ የነበረዉ መተግበሪያ፣ የባለቤቱን ሙሉ ስም እና ምስል ነበር ቀድሞ ያሳየኝ፡፡ የምፈልገዉ ሰዉ ይኼ በምስሉ ላይ የሚያሳየኝ
ሰዉ ራሱ መሆኑን በምልክት ካረጋገጥሁለት በኋላ፣ አሁናዊ መገኛዉን ደግሞ ይፈልግልኝ ጀመር። ነገር ግን ባሁኑ ሰዓት ስልኩን ለምንም ዓይነት የቴሌኮም አገልግሎት እየተጠቀመበት ስላልሆነ፣ አሁን በትክክል
የት እንዳለ ማግኘት ተቸገረ፡ ለማንኛዉም የመጨረሻ ግንኙነቱ ከየት አካባባቢ እንደሆነ እንዲያዪልኝ ከንፈሬን ነክሼ በቀስታ ጠየቅሁት የፍለጋዉን ዉጤት በአመልካች ቀለም አቅልሞ፣ ራሴ እንዳነበዉ
ጠቆመኝ፡

"ፍል ውሃ"

"መቼ"

"1:02 ላይ"

ሰዓቴን ተመለከትሁ ከአራት ደቂቃዎች በፊት ማለት ነዉ፡ ስለዚህ አሁንም እዚያዉ ፍል ዉሃ ብሄድ እንደማላጣዉ ገመትሁ። የእሸቴን ጉንጮች ሳምሁና፣ ልክ እንዳገባቤ መሬቱን በኃይል እየረገጥሁ ልወጣ ስል፣
መኪናዬን እንዳልያዝኋት ትዉስ አለኝ፡ ኮንትራት እንዳልጠራ፣ ታክሲዉ ራሱ እዚህ እስከሚደርስ ድረስ ብቻ ጊዜዬን ይፈጅብኛል። ደግነቱ አማራጭ ቸግሮ አልቸገረኝም: የባልታ መኪና
በዓይነ ልቡናዬ ክትት አለልኝ፡ በዚሁ የነፍስ ጡር ጉልበቴ እየተራመድሁ ወደ ቢሮዉ ሄጄ ልክ በሩን ስበረግድ፣ ፊት ለፊቴ የወንበሩ የኋላ መደገፌ
ላይ ስክት ያለ ኮቱን አየሁት ምንም ጠብታ ጊዜ ሳላባክን ኪሶቹን መፈታተሸ እንደ ጀመርሁ፣ አንደኛዉ ኪሱ ላይ የምፈልገዉን የመኪ ቁልፍ ግማሹ ብቻ ከቀረለት ማስቲካ ጋር አገኘሁት፡ ደስ ሲል! ምናለበት የፈለጉት ነገር ሁሉ፣ ይገኛል ብለዉ በገመቱበት ቦታ እንዲህ ቢገኝ?

የማስቲካዋን ጣዕም እያጣጣምሁ፣ በባልቻ መኪና ከአራት ኪሎ በርሬ ፍልዉሃ ስደርስ፣ አምስት ደቂቃዎች እንኳን አልፈጀሁም፡ ግን ምን ዋጋ አለዉ? ፍልዉሃ ብደርስም፣ ፍልዉሃ ግን ሳጥን አይደለችም፡ ሰፈር ናት፡ ያዉም ባለ ብዙ ቅያስ፣ ባለ ብዙ የአገልግሎት ጣቢያ፣ ባለ ብዙ እንግዳ ናት ብዙ መታጠቢያ ቤቶች፣ ብዙ መጠጥ ቤቶች፣ ብዙ ሱቆች አሉ በፍል ዉሃ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ እና አሁን ባለኝ መረጃ ብቻ፧ ጃሪምን ማግኘት የሚሆን ነወይ? ከባድ ነዉ

ወደ እሸቴ ስልክ ደወልሁ።

“አልጨረሳችሁም?” አልሁት፣ ዘዉ ብዬ ወደ ጉዳዬ ላለመግባት ያህል

“መመመመ.መጨረስ እንኳን አልጨረስንም:: አአአ..አንቺ ማዋራት ግን እችላለሁ። እሺ፤ ወንድምሽን አገኘሽዉ?”

“ምን? ምንሽ ?”

“ወንድምሽን፤ ጃሪምን አገኘሽዉ
ወይ?''

“ጃሪምን ታዉቀዉ ኖሯል እንዴ? ጭራሽ ወንድሜ መሆኑንም ጭምር ? ''

“ ይገርማል?”

“በጣም እንጂ”

“እኔ ግን ከቤተሰብሽ የማላዉቀዉ ያለ አይመስለኝም”

“ጉድ ፈላ”

“እንዴ ዉቤ፤ ከገረመስ ወንድምሽን ባላዉቀዉ ነበር እንጂ፣ ማወቄ ምኑ
ይገር ማል ?»

እዉነቱን እኮ ነዉ ምኑ ነዉ የገረመኝ? መቼም ማንም አያዉቀኝም ያልሁበትን ሳይቀር አዉቆብኝ ልጅ አርግዤለት ሳበቃ፣ ጃሪም ወንድሜ መሆኑን አወቀ ብዬ በእሸቴ ልደነቅ አልችልም: እንዲያዉ ሌላዉ ቢቀር፣
ቅድም በስልክ ቁጥሩ ሲፈልገዉ የወጣለት ስም፣ ከእኔ ስም ጋር በአባትም በአያትም አንድ መሆኑን አይቷል፡ እና ምኑ ነዉ የገረመኝ?
“ለማንኛዉም…” አለኝ እሸቴ፣ ጥያቄዉን በዝምታ ያለፍሁበት
መስሎት። “ለማንኛዉም ፊንፊኔ የባህል ሆቴል የት እንዳለ ታዉቂ የለ?''

“አዎና:: ፍልዉሃ ግቢ ዉስጥ ያለዉ ማለትህ አይደል?”

“በቃ፤ እዚያ ብትሄጂ ታገኝዋለሽ''

“ማንን?”

“ጃሪምን”

“እንዴት አወቅህ?”

“እኔ አይደለሁም፣ ባልቻ ነዉ የነገረኝ''

“ማለት? እኮ ምስጢር አዉጥተህ!?” ደሜ ከምኔዉ እንደ ፈላ

“እርሜን አንድ ዉለታ ዋልልኝ ብልህ እሱንም ወስደህ አሻዉከሃል?!”

“ለባልቻ እኮ ነዉ የነገርሁት: ከባልቻ የሚደበቅ ነገር አለ እንዴ?”

“ጅል!”

ያለ ቅጥ አበሻቀጥሁት

“ …አንዴ ስሚኝ፤ ባልቻ ነኝ እኔ: ቆይ እኔን አዳምጪኛ” እያለ
ከማወርደዉ የስድብ መዐት ሊያስታግሰኝ ሞከረ፣ ባልቻ ስልኩን ከእሸቴ ነጥቆ። “ቆይ እስኪ ስሚኝ እኔን”

“አቤት” አልሁት፣ ጊዜ ወስጄ እንደ ምንም ወደ ልቡናዬ ከተመለስሁ
በኋላ፡

“እሽቴ ባይነግረኝም እኮ ማወቄ አይቀርም ነበር። መኪናዬን ሳታስፈቅጂ መዉሰድሽ ሳያንስ፣ ምነዉ ‹የፈሲታ ተቆጢታ> ሆሽሳ። እህ! እኔ እንኳን ያንቺን ያህል አልተቆጣሁም: ሆሆ! ይልቁን ስለሄድሽበት ጉዳይ
ብንመካከር አይሻልም? ስለ ጃሪም?”

“የጃሪም ጉዳይ የእኔ ጉዳይ ነዉ። የቤተሰብ ጉዳይ ስለሆነ፣ ራሴ
እወጣዋለሁ”

“ አ ይ ደ ለ ም” አለ ባልቻ፣ ፊደሎቹን አንጠባጥቦ:: “ጃሪም ያንቺ ጉዳይ ብቻ ነዉ ብለሽ ነዉ? በጭራሽ ልክ አትመስዪም”

“እሱማ ልክ ነህ” አልሁት፣ ከእሱ የምሸሽገዉ የግል ጉዳይ እንደ ሌለኝ አስታዉሼ ሐፍረት እየሸነቆጠኝ፡፡ “ልክ ነህ የኔ ጉዳይ ያተም ጉዳይ ነዉ። ቢሆንም ግን…”

“የለም፣ እንደሱ ብቻ አይደለም: ጃሪም ካንቺ አልፎ የሲራክ
ከዚያም አልፎ የቤተ ክርስቲያን እንዲያዉም የሀገር አጀንዳ ሆኗል:
ስለዚህ ቀጥለሽ የምትወስጃቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ጥንቃቄ
ያስፈልጋቸዋል”

ከንግግሮቹ በተረዳሁት ስጋቱ ተነስቼ የቅዱስ ዑራኤልን ካቴዴራል ሊያቃጥሉ ከመጡት ወጣቶች መካከል ጃሪም እንደ ነበረበት ደርሶበት ሊሆን እንደሚችል አሰብሁ
👍30
“ሳታማክሪኝ ባትሄጂ መልካም ነበር። ከሆነ አይቀር ግን አሁን አንቺ ፍልዉሃ ያለሽዉ በግልሽ እንደ ዉብርስት ብቻ ሳይሆን፣ የሲራክን ተልእኮ ይዘሽ መሆኑን ልብ እንድታደጊልኝ እፈልጋለሁ"

“እሺ”

“ጥሩ” አሁኑኑ ወደ ፊንፊኔ የባህል ሆቴል መሄድ ትችያለሽ: በዚያ ያሉ
የእኛ ሰዎች ሽፋን እንዲሰጡሽ ተነግሮልሻል። ከመግቢያዉ በር ገባ ብሎ (ቀለወ) ብሎ ሰላምታ የሚያቀርብልሽ አስተናጋጅ ተከተዪዉ: አደራሽን ቸኩለሽ ነገር እንዳታበላሺ። ጃሪም አንቺ እዚያ ካየሽ መደንበሩ ነዉ። በፍጹም ሊያይሽ አይገባም”

“ገብቶኛል”....

ይቀጥላል
👍24
#ሳቤላ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

« እረ እባክህ ምንም አይደለም » አለ ጌትዮው ። « ማን አለ መሰለህ ?ከልጄና
ከማርሊንግ ከመጣችው ከሚሲስ ቬን በቀር ሌላ የለብንም።ሚሲስ ቬንል ወደ ግብዣው ይዛት ለመሔድ ነበር የመጣችው። እሷም ብትሆን ከውጭ ራት አለባት ሲሉ የሰማው መስሎኛል እንደተባለው ከሌለች እኛ ብቻችንን እንበላለን እስኪ እሱን ደወል ነካ አድርገው ሚስተር ካርላይል ፡ ይህ መከረኛ እግሬ እኮ አልንቀሳቀስ አለኝ " ደውል ተደወለ። አሽከር ገባ።

« እስኪ ሚሲዝ ቬን ከኛ ጋር ራት ትበላ እንደሆነ ጠይቅ ። »
« ከውጭ ነው የሚበሉት. ...ጌታዬ ። የሚሔዱበት ሰረገላ ከደጅ እየጠበቃቸው ነው።

« መልካም ......... ሚስተር ካርላይል ፡ እንግዲህ እኛው ብቻ ነን ያለን ! አለ የቤቱ ጌታ።

ራት በአንድ ሰዓት ቀረበ ። ዊልያም ቬን በተሽከርካሪ ወንበሩ ሆኖ ወደ ምግብ
ቤት እየተገፋ ሔደ ። ከእንግዳው ጋር በአንዱ በር ሲገቡ ከፊት ለፊታቸው በነበረው በር ደግሞ ሌላ ሰው ገባ ። ለሚስተር ካርላይል የታየው ሰው ይሁን መልእክ ተጠራጠረና ልብ ብሎ ተመለከተ።

በሠዓሊዎች ሐሳብ ከሚታየው በቀር እጅግ ጥቂቶች ብቻ የታደሉት ቁንጅና
ከምንለው የላቀ መልክ ያላት ልጅ ነበረች። ከጫፉ እንደ ቀለበት ጥቅልል ጥቅል ያለው ጥቁር ጸጉሯ ከአንገቷና ከግራ ቀኝ ትከሻዋ ላይ ወርዶ ተቆልሏል ከለስላሳ የልጅ ክንዶቿ ላይ የሉል ጌጥ አስራ ውድ የሆነ ነጭ የዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ ከፊት ለፊታቸው ብቅ ስትልበት መልአክ ትሁን ሰው ለመለየት ተጠራጠረ።

« ልጄ ናት ሚስተር ካርላይል ። እመቤት ሳቤላ ቬን» ብሎ አስተዋወቀው ። ሁሉም ከምግቡ ገበታ ዙሪያ ተቀመጡ ። ዊልያም ቬን የተለመደ የክብር ቦታውን ያዘ ። ልጅቱና ሚስተር ካርላይል ፊት ለፊት ሆነው ቁጭ አሉ ።

ሚስተር ካርላያል ለሴት ልጅ መልክ እደነግጣለሁ ብሎ አያስብም ነበር ።
የዚያች ቆንጆ ልዩ ውበት ግን ጠቅላላ መንፈሱን ማረከው ። ራሱን መቈጣጠር
እስኪሳነው ድረስ አፈዘዘው ። ከሁሉ የበለጠ ያስደሰተው ደግሞ ቅርፆ መልካም ፊቷ ወይም ትከሻዋ ላይ የተኛው ጸጉሯ ወይም የጽጌረዳ አበባ የመሰሉት ለስላሳ ጉንጮቿ ሳይሆኑ የዐይኖቿ አገላለጥ ነበር ። ከዚያ በፊት ያን የመሰለ አጋጣሚ አይቶ ስለማያውቅ ዐይኖቹን ከገጿ ላይ ሊነቅል አልቻለም ።

"ሳቤላ.... ለብሰሻል' አይደለም? » አላት አባቷ ።

« አዎን.....አባባ ። ባልቴቷን ሚሲዝ ሌቪሰን ለሻይ ብዙ እንዳይጠብቁኝ ልሔድላቸው ነው ። እሳቸው ለራሳቸው ሻያቸውን በጊዜ መጠጣት ነው የሚፈልጉ። ቢያመሹ አይወዱም ። ሚሲስ ቬንም ከዚህ ስትነሣ ዐሥራ ሁለት
ሰዓት ዐልፎ ስለነበር ለራት ሳታስጠብቃቸው አትቀርም ። »

« ብዙ እንደማታመሺ ተስፋ አለኝ ሳቤላ » አለ አባቷ ።

« እንደ ሚሲዝ ቬን ሁኔታ ነዋ አባባ እሷ ካላመሸች አላመሽም ። »

"አየ እንግዲያውስ ማምሸትሽ አይቀርም መቼም በዚ በኛ ዘመን ቆነጃጂቱ ሌሊቱን ወደ ቀን እየለወጡት ነው ። ይኸ ደግሞ ለለጋው ዕድሜያቸው ደግ አይደለም ። አንተስ ምን ይመስልሃል ሚስተር ካርላይል ? »

ሚስተር ካርላይል ቀና ብሎ ወደ እሷ ተመለከተ። ጉንጮቿ በበለጠ ደምቀው በቀላሉ የማይጠወልጉ ጽጌ ረዳዎች መስለው ታዩት ።

ራት ተበልቶ እንዳበቃ አንዲት የቤት ሠራተኛ ከሱፍ የተሠራ መደረቢያ ይዛ
ገብታ ከወጣቲቱ እመቤት ትከሻ ላይ ጣል አደረገችላት ። ልጂቱም ወደ አባቷ ቀረብ ብላ «ደኅና አምሽ ......... አባባ » አለችው

"ደና አምሺ........ የኔ ዓለም » አላት ወደሱ ሳብ አድርጎ የሚያምረው ጉንጯን ሳመና « እስኪነጋ ድረስ ውጭ መቆየትሽን እንደማልፈልግ ለሚሲዝ ቪን ንገሪያት " አንቺ ለራስሽ ገና ልጅ ነሽ እስኪ መጥሪያውን ንካው ሚስተር ካርላይል ። ልጄን ከሠረገላው ድረስ መሸኘት እንኳን አቃተኝ። »

« የእርስዎ ፈቃድ ከሆነና እመቤት ሳቤላም ወጣት ሴቶች አስተናግዶ የማያ
ውቅ እንደኔ ያለ ሰው እንዲሽኛት ከተስማማች አሳፍሪያት ብመጣ ደስ ይለኛል »አለ ትንሽ እንደ መደናገጥ ብሎ መጥሪያውን እየደወለ ።

ዊልያም ቬን አመሰገነው ። ወጣቷ እመቤትም ፈገግታ አሳየችው ። ሚስተር
ካርላይልም መብራቱ በተንጣለለበት ደረጃ እየመራ ይዟት ወረደና ከሚያምረው ምቹ ሠረገላ ውስጥ ደግፎ አስገባት ። እጅዋን ዘርግታ ሰላምታ ሰጠችውና ሠረገላው መሽከርከር ሲጀምር ካርላይልም ወደ ዊልያም ቬን ተመልሶ ገባ ።

« ታድያስ ቆንጆ ልጅ አይደለችም : ሚስተር ካርላይል ? »

« ቁንጅና የሚለው ቃል ያንሳታል ። የሷን ያህል ቆንጆ አይቼ አላውቅም ። »

« ባለፈው ሳምንት ከአንድ ግብዣ ሔዳ ነበር ። ሕዝበ አዳም አዳራሹ ውስጥ
ሲያያት ጊዜ ልዩ ስሜት ተፈጥሮ ነበር አሉ እኔማ መቼም ይህ ክፉ ቁራኛ በሽታ
ኮድኩዶ ከቤት አዋለኝና ያንን እንኳን ለማየት ሳልታደል ቀረሁ ። ልጂቱ ልቧም
እንደ መልኳ ነው ፤ እንዲህ አትምሰልህ ፤ ጥሩ ሰው ናት ። »

አባትየው የተናገረው ፡ ልጁ በመሆኗ ለማስወደድ ብሎ ሳይሆን ከልቡ ነበር ።
ሳቤላ ፡ በአስታሳሰብና በትክለ ሰውነትዋ ብቻ ሳይሆን በደግነቷም መስል አልነበራትም ።

ታርማና ተመክራ ነው ያደገችው ። ከቤት ውጭ ምንም ነገር አይታ አታውቅም ። እንደ ዘመኑ ልጆች ቅብጥብጥና ቅንጦት ወዳድ ሳትሆን ፡ ረጋ ያለች ጨዋ ልጅ ነበረች ። እናቷ በሕይወት በነበረች ጊዜ አንዳንዴ ኢስት ሊን፡ አብዛኛው ጊዜ ግን ማውንት እስቨርን ነበር የምትቀመጥ ። ከእናቷ ሞት በኋላ ከአንዲት አስተማሪ ጋር ወደ ማውንት እስቨርን ጠቅላ ገባች ። አባትየው አንድ የሟላ ትንሽ ቤት ሰጥቶ ዐልፎ ዐልፎ ያያቸው ነበር ። ሳቤላ ዐይነ አፋርና በመጠኑም ስሜት ንቁ አደብ የገዛች፡ ለሁሉ አሳቢና ተጨናቂ ነበረች ። አባቷም በጣም ስለሚወዳት መከራ ላይ ወድቃ ከሚያያት እሱ ራሱ ቢገድላት ይመርጥ ነበር ።

የወይዘሮ ሳቤላ ቬን ሠረገላ ጉዞውን ቀጥሎ ከሚስዝ ሌቪሰን መኖሪያ ቤት
አወረዳት ። ሚስዝ ሌቪሰን ጠባይዋ ልዝብ' አንደበቷ ስትር ያለ ሰማኒያ ዓመት
የሚሆናት ባልቴት ነበረች ። ሚሲዝ ቬን እንደ ተፈራው ዘግይታ ደረሰች ባልቴቷ
ለራት ብዙ ስለጠበቀች ተበሳጭታ ኖሮ ፡ ኋላ ደግሞ ሳቤላም የሻይ ሰዓት እስኪያ
ልፍ ስትቆይባት ጊዜ በመናደድ ቆቧን እንጋድዳ ደፍታ ኩፍስ ብላ ተቀምጣ አገኘቻት እውነትም እንደዚህ የመሰለ አሠራር ለአረጋውያን ጤንነትም ሆነ ጠባይ አይስማማም ።

« አስጠበቅሁዎ መሰለኝ » አለች ሳቤላ ወደ ሚስዝ ሌቪሰን እየተጠጋች ,
« ከአባባ ጋር ራት የሚበላ አንድ እንግዳ ስለ ነበረ ነው ትንሽ የቆየሁት »

« ኻያ ኣምስት ደቂቃ አሳልፈሻል » አለች ባልቴቷ ቆጣ ብላ ።

«አሁን ሻይ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ ።
ኤማ ......... ቶሎ እዘዥልኝ ። »ሚስዝ ቬን ደወለችና እንደ ታዘዘችው ተናገረች ። ይህች ወይዘሮ በመልክ በኩል እንደ ነገሩ ብትሆንም ተክለ ቁመናዋ ያማረ ፡ እና ዕቡይ ከቁመቷ መለስ ያለች የኻያ ስድስት ዓመት ቆንጆ ነበረች ። እናቷ የባልቴቷ የሚሲዝ ሌቪሰን ልጅ ነበረች ፣ ቀደም ብላ ሞታለች ። ሎርድ ( ጌታ)ዊልያም ሼን ወንድ ልጅ አልነበረውምና።ባገሩና በዘመኑ ሕግ መሠረት በወርስ ላገኘው የማወንት እስቨርንን ጉልት ማዕረግና ሀብት ሕጋዊ ወራሽ' የቅርብ ዘመዱ የሆነው ፣ ወንድ ልጅ የርሷ ባል ሬይሞንድ ቬን ብቻ ነበር ።
👍20
« ኧረ ሻዩ ገና አልፈላም ...... እምዬ ! » አለች ሚስዝ ቬን ሠራተኞቹ ማቅረቢያና ከብር የተሠራ ማፍያ ይዘው ሲዘልቁ አይታ በመገረም ። « መቸም እማማ ፡ እዚህ ክፍል ውስ

ጥ እንደ

ማታስፈሊው እርግጠኛ ነኝ ። »

« ታዲያ የት ላስፈላው ኖሯል ? » አለቻት አያቲቱ ።

« እንዴ ከማብሰያ ቤት አስፈልቶ ማስወጣቱ ይቀላል ። እኔ እሱን ለማፍላት
ጐንበስ ቀና ማለቱ በጣም ነው የሚያስጠላኝ » አለች ሚስዝ ቬን

« ነው እንጂ ! » አለች ባልቴቷ በማሾፍ ። «ከዚያ በኋላ እንደ ወተት ቀዝቅዞ የመጣውን ሻይ እየቀዱ መጠጣት ! አንቺኮ.......ኤማ ከልጅነትሽ ጀምረሽ ሰነፍ ነበርሽ ። »

« ለመሆኑ ሁል ጊዜ ሻይ የሚያፈላልሽ ማነው ? » አለቻት ሚስዝ ቬን ፡ ካሮጊቷ በስተጀርባ ቁማ ወደ ነበረችው ወደ ሳቤላ ቬን የንቀት ግልምጫዋን ወርወር
አደረገችና ።

እመቤት ሳቤላ ግን እንገቷን ደፋች ። ጉንጮቿ ልውጥ አሉ ። በአንድ ወገን
ያባቷ እንግዳ ሆና ከመጣችውና በዕድሜም ታላቋ ከሆነችው ከሚስዝ ኤማ ቬን ጋር የሐሳብ ልዩነት መፍጠሩን ጠላችው። በሌላ በኩል ደግሞ በሸመገለ ወላጅ ላይ ያንል ውለታ ቢስነትና ፌዝ ታይባት አላስችላት አለ።

« ሐሪየት እየመጣች ታፈላልኛለች ፣ ብዙ ጊዚ ብቻዬን ስሆንም ተቀምጣ ታጣጣኛለች ። አንቺሳ ከኩራትሽ ጋር ምን ልትይ ይሆን ......... እመቤት ኤማ? »

« ኧረ እኔስ ላንቺ ደስ እንደሚልሽ ይሁንልሽ ......... እማማ ። »

« በይ አሁንም ዛሬ ማታ፡ይኸን ሻይ የምንጠጣው ከሆነ የሻይ ቅጠሉ ዕቃ ካጠገብሽ አለልሽና ውሃውም እየተንተከተከ ሳያልቅ ተዘጋጅቶ ቶሎ ይቅረብ ። »

« እኔስ ምን ያህል የሻይ ቅጠል እንደሚጨመርበትም አላውቅም » አለች
ሚስዝ ቬን ። እሷ ለራሷ የእጅ ሹራቧንም ሆነ እጅዋን አንድም ነገር እንዳይነካባት
ሁሉን የምትጠየፍ ኩራተኛ ነበረች ።

« እኔ ላፍላው ......... እማማ » አለች ሳቤላ ቶሎ ብድግ ብላ ። « ማውንት
እስቨርን ሳለሁ ብዙ ጊዜ አዘጋጅ ነበር ። ላባባም የማፈላለት እኔ ነኝ ። »

« እስቲ እንግዲያማ በይ ልጄ ! ከሷ ዐሥር እጅ ትችያለሽ » አለቻት ። ሳቤላ
ደስ ደስ ፡ ሣቅ ሣቅ እያላት የእጅ ሹራቧን አወለቀችና ሥራ ልትጀምር ስትቀመጥ'
አንድ ጥሩ ጥሩ ልብስ የለበሰ ወጣት ገባ ። ቁልጭ ያለው የፊቱ ቅርጽ ' ጥቋቁር ዐይኖቹ ' ሐር የመሰለው ጥቁር ጸጉሩና ነጫጭ ጥርሶቹ በአንድነት ሲታዩ ፡ መልከ መልካም ሰው ሆኖ እያለ መልከ መልካምነቱ ለልብ ባይ አይስብም ነበር ። ደስ የማይል መልከኛ ። ከአንድ ሰው ጋር ሲነጋገር ጥቋቁር ዐይኖቹ ወዲያ ወዲህ የመቀላመጥ ልማድ ነበራቸው ። ሰውየው ካፒቴን ፍራንሲዝ ሌቪዞን ይባል ነበር ።

እሱም የሚስዝ ሌቪሰን የልጅ ልጅ በመሆኑ' ከሚሲዝ ቬን ጋር የአንድ አያት
ልጆች ነበሩ ። በአነጋገሩ ለዛ ፡ በፊቱ ውበትና በቁመናው ማማር የሱን ያህል የሚማርኩ ስሜቶቻቸውን በቀላሉ የሚስቡና የሚያሳምኑ ጥቂት በጣም ጥቂት ናቸው ። ምንም እንኳን እልም ያለ ገንዘብ አባካኝ ቢሆንም'የሽማግሌው ባለጸጋ የሰር ፒተር ሌቪሰን ተስፈኛ ወራሽ መሆኑን ማንም ያውቀው ስለ ነበር' አገር ያከብረወና ያደገድግለት ነበር ።

« ካፒቴን ሌቪሰን ተዋወቁ ፡ እመቤት ሳቤላ ቬን ትባላለች » አለች ባልቴቷ ። እነሱም ሰላምታ ተሰጣጥተው ተዋወቁ ። ስለ ዓለም ጣጣ ገና እንግዳ የነበረችው ሳቤላ የወጣቱን መኮንን ገጽታና አመለካከት ስታይ ፊቷ ፍም መሰለ ።

« እንዴት የሚያምር መስቀል ነው ......... ልጄ » አለች ሚስዝ ሌቪሰን ሳቤላ ፡ አጠር ቀጠን ባለ ሐብል ካንገቷ አስራው የነበረውን ባለ ሰባት ብሩህ አረንጓዴ የዕንቁ ፈርጦች መስቀል እየተመለከተች

« ያምራል ' አይደለም ? » አለች ሳቤላ ። « እማምዬ ከመሞቷ ጥቂት ቀደም
ብላ የሰጠችኝ እኮ ነው ። ይቆዩ አውልቄ ላሳይዎ ። ልዩ ክበረ በዓል ቀን ሲሆን
ብቻ ነው የማስረው ። »

ከአንድ መስፍን ቤት ግብዣ ስትገኝ የመጀመሪያዋ በመሆኑ' ለዚች ብዙ ላላየችና ከቤት ውስጥ ላደገች ልጅ እንደ ትልቅ ነገር ሆኖ ታያት ፡ የሃብሉን መያያዣ ፈለቀቀችና ከነመስቀሉ ለሚስዝ ሌቪሰን ሰጠቻት ።

« ከዚህ መስቀልና ከጥቂት የመናኛ ፈርጥ አምባሮች በቀር ምናምን የለሽም
ማለት ነው ? እኔ እኮ እስካሁን አስተውዬ አላየሁሽም ነበር » አለቻት ሚሲዝ ቬን ።.
ሁለቱንም እናቴ ነበረች የሰጠችኝ ። አምባሮቹን ሁል ጊዜ ታደርጋቸው ነበር።

« ምን ያለሽ መና ነሽ ! እና ገና እናትሽ ጥንት ያደረጉዋቸው ስለ ነበር ዛሬ ይህን ዘመን ያለፈበትን ጌጥ ብለሽ አሁን ታደርጊዋለሽ ? ለምን አልማዞችሽን አታደርጊም ነበር ? » ብላ ሚስዝ ቬን ጮኸችባት ።

እነሱንም እኮ አጥልቄያቸው ነበር፤ ግን መልሼ አወለቅኋቸው» አለች ሳቢላ

« ይህችን ቀጭን የወርቅ ክር ብቻ አድርገሽ ምናምን ሳትጨምሪበት

« እኮ ለምን ? »

« እኔ በጣም ማሸብረቁ ደስ አላለኝም » አለች ፊቷ እየቀላ ሣቅ አለችና

« በጣም ስለሚያብረቀርቁ እነሱን አስሬ ለመታየት ያደረግኋቸው እንዳይመስልልብኝ ፈራሁ።

« ነው እንዴ ! ገባኝ ጌጥን እየወደዱት የሚንቁት መስለው ለመታየት ከሚሞክሩት አስመሳዮች አንዷ ነሻ እመቤት ሳቤላ » አለቻት ሚሲዝ ቪን በማንቋሸሽ ፣ « የተራቀቀ አስመሳይነት ነው። »

ሳቤላ በስድቡ አልተቆጣችም ። ሚስ ቬንን እንደዚያ ያነጫነጫት አንድ ነገር መኖር አለበት ብላ አሰበች ። በርግጥም ነበር ። ያም ነገር ካፒቴን ሌቪን እሷን ቸል ብሎ ለሳቤላ የወጣትነት ውበት የተሰማውን አድናቆት በግልጽ በማሳየቱ ነበር ።

« እንቺ መስቀልሽን ልጄ » አለች ሚስዝ ሌቪሰን ። « በጣም ቆንጆ ነው ፡
በአንገትሽ ስታደርጊውማ ፡ ከአልማዞች ሁሉ የበለጠ ነው የሚያምርብሽ። አሁንምብዙ መብለጭለጭ እንዳያምርሽ ኤማ የምትለውን አትስሚያት ። »

ፍራንስዝ ሌቪሰን ፡ መስቀሉን ከነሐብሉ ለሳቤላ ለማቀበል ከአያቱ እጅ ተቀ
በለ።ሳቤላ የጅ ሹራቦቿን መሐረቧንና መደረቢያዋን ይዛ ነበር ። አሁን ከሱ
አለመጠንቀቅ ይሁን ወይም ሳቤላ እጅዋ በመሙላቱ አልይዝላት ብሎ ይሁን አልታ
ወቀም ሁለቱ ሲቀባበሉ ከመኻላቸው ወደቀ ። መኮንኑ ድንግጥ ብሎ ለማንሣት
ሲሞክር የባሰውን በእግሩ ቆመበትና መስቀሉ እንክት ብሎ ለሁለት ተከፈለ ።

« አረግ ! ማነው እንዲህ የሚሠራ ? » ብላ ጮኸች ሚሲዝ ሌቪሰን " ሳቤላ
ምንም አልመለሰችም ። ልቧ በኀዘን ተዋጠ ። የተሰበረውን መስቀል በምታነሣ
በት ጊዜ ዕንባዋ ገንፍሎ ሲወርድ ልትገታው አልቻለችም ።

« እንዴ ! ለዚህ መናኛ ውዳቂ መስቀልሽ ነው ለቅሶው ! » አለቻት ኤግ ስለ ጥፋቱ ይቅርታ ሊጠይቅ የነበረውን መኮንን ቀድማ ።

« ልታስቀጥይው ትችያለሽ » አለቻት ሚስዝ ሌቪሰን ደግሞ " እመቤት
ሳቤላ እንደ ምንም ብላ ዕንባዋን አደራረቀችና ወደ ካፒቴን ሌቪሰን በፈገግታ ዞር ብላ ' « እባክህ አትዘን » አለችው በቅን አስተሳሰቧ፡« ጥፋቱ የሁለታችንም ነው ! ያም ቢሆን እማማ እንደሚሉት ሊቀጠል ይችላል ። »

ሐብሉን ላዩ ላይ ከቀረ ስባሪ አላቅቃ ባንገቷ አጠለቀችው ።

« ይህችን ቀጭን የወርቅ ክር ብቻ አድርገሽ ምናምን ሳትጨምሪበት አትሒጂም አለቻት ሚሲስ ቬን......

💫ይቀጥላል💫

አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍24👎1
አትሮኖስ pinned «#ገረገራ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #በታደለ_አያሌው ...እንደ ክራሞቴ ቢሆን፣ ይኼን ስሰማ ጸጥ ብዬ መሞት ነበረብኝ፡ ያን ያህል ግን ከብዶ አልታየኝም፡ ብሎ ብሎ ድንጋጤ ሁሉ ከዉስጤ ተሟጥጦ አለቀ መሰለኝ፣ የሐኪሜን ያህል ቀርቶ እንዲች ብዬ አልደነገጥሁም ጭራሽ እሷን ለማበረታታት ሁሉ ምንም አልቀረኝም “ዉብዬ፣ መገናኛ አካባቢ ዶክተር ሙደያን ሻምሩን የሚባል አንድ ስመ ጥሩ ሐኪም አለ:…»
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በታደለ_አያሌው


...“ጥሩ” አሁኑኑ ወደ ፊንፊኔ የባህል ሆቴል መሄድ ትችያለሽ: በዚያ ያሉ
የእኛ ሰዎች ሽፋን እንዲሰጡሽ ተነግሮልሻል። ከመግቢያዉ በር ገባ ብሎ (ቀለወ) ብሎ ሰላምታ የሚያቀርብልሽ አስተናጋጅ ተከተዪዉ: አደራሽን ቸኩለሽ ነገር እንዳታበላሺ። ጃሪም አንቺ እዚያ ካየሽ መደንበሩ ነዉ። በፍጹም ሊያይሽ አይገባም”

“ገብቶኛል”

በይ እንግዲህ ልጅ ወልደሽ እስከምንስማት ድረስ፣ ይኼኛዉ
የመጨረሻ ተልእኮሽ ይሆናል”

“እሺ”

“መልካም ዕድል”

“ለማኅበራች!” ብዬ ስልኩን ዘጋሁት፣ ሁልጊዜም ተልእኮ ስንቀበል እንደ አመቺነቱ እንደምናደርገዉ ሁሉ ማተቤን እየጨበጥሁ፡

ባልቻ እንዳለኝ ልክ ከባህል ሆቴሉ የዉጪ በር ገባ እንዳልሁ፣ አንድ
ወጣት አስተናጋጅ መጥቶ ንግሥት እንደሚያገለግል ሰዉ ተሽቆጥቁጦዐበፊቴ እጅ ነሳ ቀጥሎ ምንም ፋታ ሳይሰጠኝ፣ “የባህሎች ሁሉ መታያ
ወደ ሆነዉ ሆቴላችን እንኳንም በደህና መጡልን ቀለዘ እባላለሁ፤
ምሽትዎ እንደ ፈቃድዎ ለማድረግ እጅግ ጓጉቻለሁ” አለኝ፣ ነፍስ
በሚያረካ ፈገግታ እና ትሕትና

“እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ አመሰግናለሁ ወንድሜ” ስል ፈገግታዉን ተጋራሁት።

“ይከተሉኝ እባክዎ”

“በደስታ” ብዬ ተከተልሁት እንግዳ መቀበያዉ ያለበትን በግራ በኩል
ትቶ ወደ ጀርባ በር መራኝ ትኩረት ላለመሳብ የሚያደርገዉን ጥንቃቄ
ሳይ አደነቅሁት
“በዚች በኩል ይምጡ እባክዎ። የመጡት የባህል ቤት ነዉ: በባህላችን ደግሞ ንግሥት እና ነፍሰ ጡር የፈቃዳቸዉ ልናሟላላቸዉ ግዳችን ነዉ።
እኔ በበኩሌ፣ እርስዎ የሚፈልጉትን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለማሟላት
የማልሰንፍ መሆኔን ይወቁልኝ እመቤቴ”

“እዉቃለሁ: ግን እኮ፣ ለቤታችሁ ያን ያህል እንግዳ አይደለሁም

“አይደል?”

“አዎ አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ”

“ልክ ነዉ፤ አንድ ጊዜ ቤታችንን ያዩ ሁሉ አዘዉትረዉ እንደሚመለሱ እናዉቃለ። ስለ ደበኝነትዎ ሞልቶልን ሽልማት ባናዘጋጅልዎ፣ ቢያንስ
ደህና መስተግዶ ግን ይገባዎታል እንኳስ ንጉሥ ይሁን ንግሥት
በሆድዎ ይዘዉ!”

ለብ ያለ ሳቅ ሳቅሁለት በጀርባ በር ከወጣን በኋላ፣ ትንሽ እንደ ሄድን
በተለየ ክፍያ የተለየ መስተንግዶ የሚሰጥበት ልዩ (VIP) ቤት ይዞኝ ገባ:: የገጠሩን ድባብ ለመፍጠር ይመስላል፣ ክፍሉ ጭልጭል የሚሉ ኹለት ፋኖሶች በግራና በቀኝ በኩል ባለዉ ግድግዳ ላይ ተለኩሰዉበታል፡ ያም ሆኖ ግን በቤቱ ያሉትን ሰዎች ቀርቶ፣ ራሳቸዉን ፋኖሶቹን ለማየት የጅብ
ዓይን ሳይቀር ይፈትናሉ በቤቱ አማካይ የሆነ ቦታ ላይ በተሠራዉ
መድረክ፣ ኹለት ወጣቶች ከዘፋኟ እና ከሙዚቀኞች ጋር እየተናበቡ
ቅልቅል ባህላዊ ጭፈራ እያቀረቡ ናቸዉ፡ እነሱ ብቻ እንደ ልብ ይታያሉ ከእነሱ በቀር ጥላ የሚመስል ነገር ነዉ የሚታየኝ፡፡ በዚያ ላይ የመድረኩ አሸሸ ገዳሜ ድምፅ ስለዋጠዉ፣ ጥላ የሚመስሉት የቤቱ ተስተናጋጆች
የሚያወሩትን አንዱንም መስማት አልቻልሁም

መጀመሪያ እንዲያዉም ትርኢት ለመመልከት ወደ ብሔራዊ ቴአትር አርፍጄ የገባሁ ነበር የመሰለኝ፡ ቴአትር ከተጀመረ በኋላ የመድረኩ መብራት ብቻ ስለሚቀር፣ ቴአትር ቤት አርፍጄ ስገባ መቀመጫ ለማግኘት የማየዉን ፍዳ አስታወሰኝ፡፡

ከበር ጀምሮ ያመጣኝ አስተናጋጅ፣ ወደ ወንበር ባይመራኝ ኖሮ ስደናበር የሆነ ተስተናጋጅ ላይ መከመሬ አይቀርም ነበር፡ ደግነቱ እሱ የቤቱን ዐመል በዳበሳ ያዉቀዋል፡ በመሆኑም እጄን ይዞ እየጎተተ ወሰደኝና ክብ ሠርተዉ ለተቀመጡ ጥላዎች ጀርባዬን እንድሰጥ አድርጎ አስቀመጠኝ።
ጨለማዉን እየለመድሁት ስመጣ ከአጠገቤ ክብ ሠርተዉ ተቀምጠዉ የሚነጋገሩት ሰዎች ጥላ እንደ መድመቅ እያለልኝ መጣ፡፡ በመጠኑም ቢሆን ወገግ አለልኝ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ እየተቀባበሉ የሚናገሩትን ማዳመጥ ስጀምር፣ አንደኛዉ በድንገት የጃሪምን ስም ጠርቶ የሠራ አካላቴን አቀለጠብኝ

“ጃሪም ካነሳቸዉ ነጥቦች ላይ” ብሎ ጀመረ፡ ጀርባዬን እንደ ሰጠሁ
በተወዛዋዦቹ ላይ ጥዬ፣ ቁጭ
ብዬ፣ የመድረኩን ትዕይንት እንደሚከታተል ሰዉ ዓይኖቼን
ከተወዛዋዦች ላይ ጥዬ ተናጋሪዎችን ማዳመጡን ተያያዝሁት ጃሪም አነሳቸዉ የተባሉት ነጥቦች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመስማት ቸኮልሁ

ጀሪም ካነሳቸዉ ነጥች ላይ ምንም የሚወድቅ ነገ አላገኘሁም: ነገ ዛሬ ሳንል፣ ነገሮችን ማዕከላዊ እና መስመራዊ ማድረግ አለብን ያለበዚያ እንዲህ እያቦጫረቅን ከማደፍረስ ያለፈ የትም ማድረስ አንችልም። አዛዥ ያስፈልገናል። መስመር መያዝ አለብን። ለምንወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ግብ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል ኪሳራዎቻች ዜሮ ማድረስ ባንችልም፣ መቀነስ ግን አያቅተንም ለዚያ ደግሞ ለሁሉም
መግቢያዎቻችን መዉጫ የሚያበጅልን አካል ያስፈልገናል። ሕመም እና ሕልማችንን የሚጋሩን ብዙ እንደሆኑ ባዉቅም፣ ተበታትነን ስለምታገል ጉዟችንን አርዝሞብናል: ስለዚህ በአንድ እዝ ሥር የሚያደርገን አካል
ያስፈልገናል። ያለበዚያ መድረሻችን አንድ ሆኖ ሳለ፣ ባለመተዋወቅ እና የጋራ መሪ በማጣት ብቻ ራሳችን የራሳችን እንቅፋት እየሆንን መቀጠላችን ነዉ: አንድ አካል ያስፈልገናል። ያን አካል ደግሞ አሁኑኑ መሠየም አለብን በበኩሌ ሙሉ ሆነን እስከምንመርጥ ድረስ፣ ጃሪም
ጊዚያዊ አዛዥ ቢሆነን…

“ቆይ ቆይ!” አለች ሌላኛዋ፣ የቀደማትን ተናጋሪ ከአፉ ቀምታ
“ቆይ እንጂ! መጀመሪያ ሐሳቡን እንስማማበት እና ምርጫዉን
እንደርስበታለን” አለ ሌላኛዉም፣ ተቀብሏት “በእርግጥ እንደተባለዉ
ነዉ። እስከ አሁን ግብ አልነበረንም ማለት ሳይሆን፣ የነጠረ ለማድረግ እና
እርስ በእርስ ለመናበብ ግን የተደራጀን መሆን እንዳለብን እኔም አምንበታለሁ”

“ከዚያ በፊት” ሲል ተቀበለ ሌላኛዉ፣ ምን እንደሆነ ያላየሁትን መጠጥ ገርገጭ አድርጎ ተጎንጭቶለት: ጉሮሮዉ ፏፏቴነት አለዉ እንዴ ብያለሁ በልቤ፣ የተጎነጨዉን ሲዉጥ ያወጣዉ ድምፅ አስገርሞኝ፡ “ከዚያ በፊት
ስለ እህቱ አንድ ነገር ማለት የለብንም ወይ?”

እህቱ? ስለ ማን እህት? ስለ ጃሪም እህት፣ ስለ እኔ እንዳይሆን ብቻ!

“እ..ህ..ቴ አይደለችም!” አለ ጃሪም፣ እጅግ በተቆጣ እርጋታ፡ እፍን ባለ ንዴት… “ዉብርስት የሚባል እህት አላውቅም ብያችኋለሁ: እኔ እህት የለኝም! ማንም ሰዉ እህትህ እንዲለኝ አልፈልግም ከዚህ በኋላ::
ማንም!”

“ከልብህ መሆኑን አሳየና”

“ምን አድርጌ ነዉ የማሳይህ በል? አትመና ከፈለግህ! ምን ይላል ይኼ?” አለ ንዴቱ እየተገለጠበት፡ እንዲያዉም ለድብድብ የሚነሱ ነበር
የመሰለኝ፡ “ና ሆዴ ዉስጥ ግባ: ግባና በልቤ ዉስጥ እሷን እህት፣ እናቷ ደግሞ እናቴ ሆና ካገኘኻት ፈልጋታ! ና በላ!”

ከእሱ በኋላ ደፍሮ የተናገረ የለም፡

ረዥም ዝምታ ሆነ፡

“ቀን ነዉ የምጠብቅላት: አንተ እንድታምን ስል ግን የማደርገዉ ነገር የሚኖር እንዳይመስልህ! አንድ የሚያጠራጥር ነገር ስላየሁባት እሱን እያጣራሁ ነዉ: የሆነ ቡድን ከጀርባዋ ያለ ይመስለኛል: ወጣ ወረደ
ከዚህ በኋላ የእናት የአባቴ ቤት ላይ እንዳሻቸዉ እንዲሆኑ
አልፈቅድላቸዉም: አፈር ነዉ የማገባት! አለብሳታለሁ!”

የሆንሁትን አላዉቀዉም፡ ብቻ ግን፣ ጭዉ የሚል ድምፅ ይሰመኛል።
👍42🤔2
ለመጨረሻ ጊዜ በቅጡ የሰማሁት ቃል፣ “አለብሳታለሁ” የሚለዉን
የጃሪምን ዛቻ ነበር፡ ከዚያ በኋላ ጉሮሮዉን እንደ ታነቀ ሰዉ ትንፋሽ
ሳይቀር እምቢ አለኝ፡ ህዉ እና ጭዉ ብሎብኛል፡ አጉል ነገር እንዳላደርግ የረዳኝም፣ ቀድሞ ከባህል ሆቴሉ በር ላይ ቀለዘ ብሎ ተዋዉቆኝ ከዚያ ጀምሮ ያስተናገደኝ ሰዉ ነዉ፡ እሱ ደጋግፎ ማዉጣቱን እና በዉጪ
የነበረ ሌላ ሰዉ ደግሞ ወደ መኪና እንዳስገባኝ እንደ ሕልም እንደ ሕልም ሆኖ ይታወሰኛል

ከዚያ በኋላ የሠራ አካላቴ እንደ መሸከብኝ እንዲችዉ ሌሊቱ አለፈ። ራሴን ጨርሼ ባልስትም፣ ከሆነዉ ግን የማስታዉሰዉ ምንም የለም: ብቻ እንዲሁ ክርችም እንዳልሁ፣ በሲራክ ፯ ማዕከል ዉስጥ በሚገኝ ማረፊያ
ቤት ዉስጥ ነጋልኝ ከነጋ በኋላ እንደ ምንም ወደ ልቡናዬ ስመለስ፣ባልቻ እና እሸቴ በግራ እና በቀኝ ቆመዉ የኔን መንቃት ይጠባበቃሉ።

“ግዚአብሔርይመስገን፣ ነቃሽ?” አሉኝ፣ እኩል እጃቸዉን ለድጋፍ
እየሰደዱልኝ፡ ተኝቼ ነበር እንዴ? እጆቻቸዉን ተመርኩዤ፣ ከአልጋዉ
ወረድሁና ተራ በተራ አየኋቸዉ: ልክ ከሞት እንደ ተመለስሁላቸዉ
ቆጥረዉ፣ እንደ ተአምር በስስት ያዩኛል፡ ሆዴን ዳበስሁት። በሆዴ የነበረዉን ሁሉ እንደ ነበረዉ ስላገኘሁት በእፎይታ ተነፈስሁ

“ወደ ሆስፒታል መሄድ አለብሽ” አለ ባልቻ፣ እሱም ሆዴን እንደኔ
እየዳበሰ፡፡

“ነግቷል አይደል?”

ሞባይሉን አዉጥቶ ሰዓቱን አሳየኝ፡ ከመንጋትም አልፎ ረፍዷል:

“ምንድነዉ የሆንሁት?”

«ለረዥም መንገድ አይሮጥ፣ ለረዥም ነገር አይደነገጥ» መባሉን ከማን እንደ ሰማሁ ታዉቂያለሽ? ከእሽቴ: እሽቴ ደግሞ ከየት እንደሰማ ልንገርሽ? ከእመዋ”

“ቆይ”

“የጃሪም ነገር እንግዲህ ረዥም ነዉ። እንኳን ተደንግጦለት፣ ጸንተው ቀጥቅጠዉትም የማይወድቅ እባብ ሆኗል አሁን”

“የገዛ ወንድሜ እስከ ግድያ ድረስ ከፈለገኝ፣ እንግዲህ እኔስ ማነኝ?”

“ነገርኩሽ እኮ እሱ…”

“ለእኔ እኮ እሱ ወንድም ብቻ አይደለም። እናንተ ራሳችሁ ቁም ነገረኛ ነሽ ትሉኝ የለ? ከዕድሜዬ በላይ ቁም ነገረኛ የሁንኩት እኮ በእሱ ነዉ"

ዝም ብለዉ አዳመጡኝ፡

“አባታችን ካህን አልነበረ? እሱ ለአገልግሎት ከደብር ወደ ሌላ ደብር፣ ከሀገረ ስብከት ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት እያስከተለ ሲዘዋወር ነዉ የኖርነዉ። እና፤ የሆነ ዓመትም እደዚሁ ሱራሎ ወደ ምትባል ቆላ ሄድን¨ወንዝ ዳር ያለች ትንሽዬ የገጠር ከተማ ብትሆንም ታዋቂ ናት። የሱራሎ
ጎርፍ ሲባል በዘፈን እንኳ ን አልሰማችሁም?

"ሱራሎች ከቆላ ቅመሱልኝ ባልን ፀ የማር እንጀራዉን ፣
ደገኛ አያልቅበት መበጥበጫ እያለ ጎርፍ ሰደደል"

ተብሎላታል እኮ። ከደጋ የመጣ ጎርፍ የሱራሎን ሰዉ ባጠቃዉ ጊዜ፣ እንድ ወጣት ነዉ እ ዲህ የዘፈነዉ። ታዲያ በዚያ ጊዜ እኛም እዚያ ስንኖር፣ በአንደኛዉ ማለዳ እመዋ ለእኛ ለልጆቿ ቁርስ እያቀራረበችልን ነበር
አባታችን ደግሞ ለማያስታጉለዉ አገልግሎቱ ወደ ደብር ቀደም ብሎ ወጥቷል። በድገት እንዲህ ነዉ ብለዉ የማይገልጹት ኃይለኛ ጎርፍ እየጠረገ መጣ። መኖሪያችንም በወዙ አቅራቢያ ስለነበር ቤታችንን ልክ እንደ አብዛኛዉ የከተማዋ ቤቶች ጎርፉ እንዳትሆን እንዳትሆን አድርጎ
ነቀነቃት።ወለሉና ማጀቱ ሁሉ በዉሃ ተጥለቅልቋል።ምሰሶዉ እና
ወጋግራዎች ሲቀሩ፣ ቤታችን ዉልቅልቋ ወጥቷል: ምንም እቃ
አልተረፈም፣ እንዳለ ጎርፍ ጠረገዉ። እኛ ትረፉ ሲለን፣ እንዲሁ በደመ ነፍስ በየወጋግራዎቹ ላይ ተንጠላጠልን። ከዚያ፣ በየወጋግራዉ ላይ
እንደተንጠለጠል ባለበት ‹እሰይ ተረፍን ተባብለን እርስ በእርስ በዓይ ስንፈላለግ፣ እምዋን አጣናት: ዝቅ ብለ ወደ ታች ስንመለከት፣ እስከ አንገቷ ድረስ በጎርፉ ተዉጣ ምሰሶዉን ብቻ ይዛ ታጣጥራለች። በአፍ በአፍንጫዋ ጎርፍ እየገባ ቡልቅ ቡልቅ ይላል። ትንፋሽ አጥሯታል። ያን ጊዜ ከሁላችን ቀድሞ ማን እንደ ወረደላት ታዉቃላችሁ? ጃሪም!
ከተንጠለጠለበት ወጋግራ ላይ ዘሎ ወረደና እመዋን አቅፎ ከፍ አደረጋት።እሱን ተከትለን ሁላችንም እየዘለልን ወረድን እና እርስ በእርስ ተያይዘን ጎርፉን አሳለፍነዉ። ያሁሉ አልፎ ዛሬ፣ እመዋን እመዋ አይደለሽም እኔንም እገድላታለሁ ሲል ልስማዉ ጃሪምን? አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር ባልቻ? እሽቴ አንተስ እኔን ብትሆን? ''

ፍጥጥ ብለዉ ቀሩብኝ፡፡ ምን ይበሉኝ? ምንም:

“ይገርማል” አለ ባልቻ፣ ግንባሩን መዳፉ ላይ አስደገፎ ሲያዳምጠኝ
ቆይቶ፡ “ታዲያ እንዴት እዚህ ደረሰ? ሌላ ሌላዉስ ይሁን እሺ። ሰዉ ዉሎዉን ይመስላልና፣ ዐመሉ ተለወጠ እንበል። ግን የፈለገ ምን
ቢለወጥ፣ ከአንድ እናትና አባት እንዳልተወልዳችሁ፣ እንዴት እህቴ
አይደለችም ይልሻል?''

“እኔስ ምኑ ደነቀኝ?''

“ግድየለም፣ የእሱ ጉዳይ አያስቸኩለም”

“ምን ማለት ነዉ አያስቸኩለም ማለት!?”

“አሃ፣ ሲጀመር ራስሽ እኮ ነሽ ነገሩን ሁሉ ያበላሸሽዉ”

“እኔ?”

“ኋላ እኔ ነኝ!? ትናትና የሠራሽዉ በፍጹም ትክክል አይደለም: ሲጀመር ሳታማክሪኝ መሄድ አልነበረብሽም: ከሄድሽም በኋላ ገና ጫፏን ሰምተሽ እንደዚያ መሆን አልነበረብሽም: አደራ እንዳያይሽ እያልሁሽ፣ ተቻኩለሽ
ነገሩ አበለሻሽዉ”

“ቆይ ቆይ፤ አይቶኛል እንዴ?”

“አይቶሻል”

“ጃሪም አይቶኛል? እንዴት?”

“እሁን የሆነዉ ሆኗል አንዴ። የእሱ ጉዳይ ለእኔ ተዪልኝ። ይልቅ ነይ
እንዉጣ” አለኝ ባልቻ፣ ወደ በሩ እየተራመደ።

“ወዴት?”

“ቀጠሮ አለሽ አይደል?”

“የምን ቀጠሮ?” አልሁት፣ በሐሳብ እንደ ተዋጥሁ

“ሐኪምሽ አልቀጠረችሽም ወይ?”

“ቀጥራኛለች”

“እኮ ነይ እንሂዳ”

“መሄድ አለብኝ?”

“እርፍ! በነፍስ ማደርሽም እኮ ተመስገን ነዉ በይ ይልቅ እንዉጣ”

“የሚከርመዉም የማይከርመዉም እግዜርን እኩል ዝናብ ለመኑት አሉ:
የእናቴ ልጅ ሊገድለኝ እንደሚፈልግ እያወቅሁት፣ ምን የሚጓጓ ኖሮ ነዉ ሆስፒታል የምሄደዉ? ባልሄድስ ምን እንዳልሆን ከዚህ ሌላ?''

የተሰበረዉ ልቤ፣ ቃል በተነፈስሁ ቁጥር የባሰ ድቅቅ ሲል ይታወቀኛል:
እንደ ትናንትናዉ ዕቅድ ቢሆንማ፣ ዛሬ በጠዋት ተነስቼ ወደ መገናኛ
ልሄድ ነበር፡ ከዚያም ሐኪሜ የጠቆመችኝ ሌላ ባለሙያ አይቶኝ የሚሰጠኝን ምክር ይዤ፣ ስመለስ ከእሷ ጋር አንዳች ዉሳኔ ልንወስን ነበር ቀጠሯችን፡

“ንገሩኝ ባልሄድስ?”

“ነገርሁሽ፤ መሄድ አለብን” አለኝ ባልቻ፣ ተኝቼበት የነበረዉን አንሶላ
እያሳየኝ፡ ቀጭን የተልባ ብጥብጥ የሚመስል ፈሳሽ ተንጠባጥቦበታል፡
አዝግሜ ሄጄ በጣቶቼ ስነካዉ፣ ልክ እንደ ቅባት ለሰለሰኝ፡ የእንሽርት
ዉሃ መሆኑን ለማወቅ ከዚህ በላይ ማስተዋል አያስፈልገኝም: አዉቄዋለሁ፣ ነዉ፡፡ ምንም የምጥ ስሜት ግን የለኝም፡፡
“እሱ እኮ ነዉ የምልሽ: መፍጠን አለብን”

“ጉድ ፈላ! በሰባት ወር ልወልድ ነዉ ጭራሽ?” አልሁኝ፣ እርር ያለ ሳቅ እየተናናቀኝ፡፡ ይኼም ሳቅ ሆኖ ሳልጨርሰዉ፣ እየደከመኝ እና
እየተዝለፈለፍሁ መጣሁ፡ ራሴን ችዬ መቆም እንዳቃተኝ ሲያዩ፣ እሸቴ እና ባልቻ አቅፈዉ ወለሉ ላይ እንደ ዉሃ ከመፍሰስ አተረፉኝ፡
በተሸከርካሪ አልጋ ላይ አስተኝተዉ ልባቸዉ እስኪጠፋ እየተሯሯጡ ምድር ቤት ወዳለዉ የማዕከሉ መኪና ማቆሚያ ወሰዱኝ፡ እኔ ግን የእንሽርት ዉሃ ከመፍሰሱ እና ድካም ድካም ከማለቱ ዉጪ፣ አሁንም
👍28😁1
የምጥ ስሜት አይሰማኝም:: ምንም ሆስፒታል ደርሼም ያዉ ነኝ፡፡ ማዋለጃ ክፍል ገብቼ እንዳምጥ ስጠበቅም፣
ያዉ እንዲያዉ ነርሶቹ የፅንሱን ነባራዊ ሁኔታ ባለማወቅ ለምጥ ጠበቁኝ እንጂ፣ የሚሆን አልነበረም: ጭንቅላቷ ላይ የበዛዉ የዉሃ መጠን የራስ
ቅሏን ያለቅጥ ስላሳደገዉ፣ ቱናትን በመደበኛዉ መንገድ መዉለድ
የሚቻለኝ አይደለም:፡ እንኳንስ እንደዚህ ጭራሽ ምጥ እንኳን ባልመጣበት ሁኔታ ይቅርና፣ በጊዜዉ ቢሆንም ኖሮ የመጣዉ፣ ምጥ መሞከር ለእኔ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ እንደ መሞከር ነዉ፡ እህ ብዬ አልወልድም እኔ።
ብዙም ሳልቆይ መምጣቴን ለዶክተር ነገሯት፡ የቀድሞዋ ወዳጄ፣ የአሁኗ ሐኪሜ ጉዴን ሰምታ መጣችልኝ፡ ዶክተር ሸዊት ቀድማም የጠበቀችዉ ስለነበረ መሰለኝ፣ እንዲያዉም አልደነገጠችም: የፅንሱን ነገር
ካወቀች ጀምሮ አስተዉልባት የነበረዉ መደነጋገጥም አሁን እንጥፍጣፊዉ አይታይባትም፡፡ ምናልባት አዳሩን ሙሉ ስታስብበት አድራ ወጥቶላትም
ሊሆን ይችላል፡ ብቻ ግን እጅግ ተበራታለች: አሁን ገና የዶክተርነት
መልኳን አየሁላት እስከ አሁን ድረስ ወዳጅነቷን ነበር አብልጣ
ያሳየችኝ፡፡

ፈገግ ብላ መጣችልኝ፡

ፈገግታዋ ሆዴን አላወሰዉ፡ የገጽታዋም ፍካት የሚጋባ ብርታት አለው: እንደዋዛ፣ ወልዶ የመሳም ጉጉት ልቤን ነክቶት አለፈ ዉለጅ ዉለጅ የሚል ነገር ሽዉ አለብኝ፡፡ ዓይን ለዓይን ተያይተን ብቻ ነገሩን ጨረስነዉ፡፡

በኦፕራሲዮን ለመዉለድ ተስማማሁ፤ ተስማማን

“እንግባ?” አለችኝ፣ ከመጣች ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍ አዉጥታ።

ዓይኔን ጨፍኜ ገለጥሁላት፡ እሺ› ማለቴ ነዉ፡

ዶክተሯ ወደ ቀዶ ማዋለጃዉ ክፍል ለመሄድ በተለየ ልበ ሙሉነት ቀድማን ወጣች: ቀልጣፎቹ ነርሶች ደግሞ ጋለል ያልሁበትን አልጋ እያሽከረከሩልኝ እግር በእግር ተከተልናት፡ በሰባት ወር፣ ያዉም ጤናማ ያልሆነ ልጅ፣ ያዉም በቀዶ ሕክምና ለመዉለድ እየገባሁ መሆኔን ለመጨረሻ ጊዜ ለልቤ ሹክ አልሁት.....


ይቀጥላል
👍137
#ሳቤላ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

« ለምን አልሔድም ? ሰዎች ሲጠይቁኝ አጋጣሚ መሰበሩን እንግራቸዋለሁ።

ሚስዝ ቬን ከት ብላ ሣቀችባትና
«ሰዎች ቢጠይቁኝ!» አለች በማፌዝ ድምፅ የሳቤላን አባባል በመድገም «እነሱማ የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ የጌጥ
ችግረኛ ናት ብለው ከማሽሟጠጥ አልፈው ምን ሊሉ ኖረዋል ብላ አሾፈችባት።

ሳቤላ ሣቅ ብላ ራሷን ነቀነቀችና «አልማዞቹን ባለፈው የዳንስ ምሽት አይተዋቸዋል » አለቻት ።

« ይኽን በደል በኔ ላይ አድርሰሽው ቢሆን ኖሮ ፍራንሲዝ ሌቪሰን» አለችው ባልቴቷ «ለአንድ ወር ሙሉ ከቤቴ አላስደርስህም ነበር ። ምንድነው ነገሩ …...…… ኤማ? የምትሔዱ ከሆነ አሁን ሒዱ ። ዳንሱ የሚጀመረው በአራት ሰዓት ነው " በኔ ዘመን በአንድ ሰዓት ነበር የምንሔድ ፡ ዛሬ ደግሞ ሌሊቱን ወደ ቀን መለወጥ ልማድ ሆኗል ። »

« ሣልሳዊ ጆርጅ ራቱን የበግና ያትክልት ቅቅል በአንድ ሰዓት ይበላበት በነበረበት ጊዜ አለ ለአያቱ ከሚሲዝ ቬን የተሻለ አክብሮት ያልነበረው ካፒቴን ። ይኽን እየተናገሩ ደረጃዎቹን ደግፎ ሊያሳፍራት ስለፈለገ ወደ ሳቤላ ዞር አለ እንዳሰበው ይዞ ወርዶ ከሠረገላው ሲያሳፍራት ሚሲዝ ቬን ግን ብቻዋን ወርደች። በዚህ ጊዜ ይባሱን ብግን ብላ ተናደደች ።

« ደኅና እደር » አለችው ።
«ደኅና እደሩ አልላችሁም እኔም እናንተ እንደ ደረሳችሁ ተከትዬ እደርሳለሁ» አላት "

« አልመጣም ብለኸኝም አልነበር?የወንደላጤዎች ድግስ ያላችሁ መስሎኝ »

« ብዬ ነበር ግን ሐሳቤን ለወጥኩ " በይ ለአሁኑ ደኅና ሁኝ ወይዘሮ ሳቤላ "»

« እስኪ አሁን አንዲት ብጣሽ የተማሪ ሐብል አድርገሽ ያየሽ ሁሎ ምን ትመስይው ይሆን ? » አለች ሚሲዝ ቬን መነዝነዟን በመቀጠል "

« እሱስ ምንም አልነበረም ሚስዝ ቬን ? እኔን ያሳዘነኝ የመስቀሌ
መሰበር ነው ። እናቴ ልትሞት ስትል ነበር ይህን መስቀል የሰጠችኝ " ጉዳት ከማይዶርስበት ቦታ በደንብ አስቀምጬ አንዳች ችግር ሲደርስብኝ ወይም የሒሳብ እርዳታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ሲገጥመኝ እሱን እያየሁ የእናቴን ምክር ለማስታወስ በመሞከር እንድከተላቸው ነግራኝ ነበር " አሁን ግን ተሰበረብኝ ነገሩ ደስ አላለኝም " ገዱ አላማረኝም " »

በሠረገላው ውስጥ እንዳሉ የመንገዱ የጋዝ መብራት ሳቤላ ፊት ላይ ቦግ ብሎ ሲበራ ፊቷ በዕንባ እንደ ታጠበ ሚስዝ ቬን አየቻት » «አሁንም እንደገና ማልቀስ ጀመርሽ ? እኔ ልንገርሽ ! በለቅሶ ደም የለበሱ ዐይኖችሽን እያየሁ አንቺን ይዤ ከዳርት ፎርድ መስፍን ዘንድ መቅረብ አልችልም " ስለዚህ ለቅሶን የማታቆሚ ከሆነ
ሠረገላው ወደ ቤት ይዞሽ እንዲመለስ አድርጌ እኔ ብቻዬን እሔዳለሁ »

ሳቤላ በረጂሙ ተነፈሰችና ዐይኖችዋን አብሳ ዕንባዋን አደረቀች » « ስባሪዎቹን ማስቀጠል እችላለሁ " ለኔ ግን እንግዲህ ተመልሶ እንደ ዱሮው ሊሆንልኝ አይችልም»

«ለመሆኑ ስባሪዎቹንስ ከምን አዶረግሻቸው ? » አለቻት ሚስዝ ቬን በቁጣ «ይዣቸዋለሁ እኒህውና ኪስ ስለሌለኝ ነው» አለቻትና ከምኗ ላይ እንዳኖረችው
በእጅዋ አሳየቻት "

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከግብዣው ቦታ ደረሱ ሳቤላም ንዴቷን ረሳችጡ ፀሐይ መስለው የበሩት ክፍሎች ልብን የሚሰውር የሕልም ዓለም መስለው ታዩአት
ምክንያቱም ልቧ ግና በአፍለኝነቱ ነበርና የመርካት ልምድ አልነበራትም የገባችበት ቦታና ሁኔታ ብርቅና ድንቅ ሆነባት ከዚያ በድምቀቱና በውበቱ ከሰወረው አዳራሽ እንደ ገባች ይቀርብላት የነበረው የአክብሮት ሰላምታ ስታይ እጅ ስትነሣ በጆሮዋ ይንቆረቆሩ የነበሩትን የውዳሴ ቃላት ስትሰማ የተሰበረውን
መስቀል እንዴት አድርጋ ታስታውሰው !

« ታዲያስ » አለ አንድ የኦክስፎርድ ተማሪ ለቫልስ ተጨዋቾች ቦታ ለቆ ወደ
ግድግዳው እየተጠጋ «እንደዚህ ወደ መሰሉ ቦታዎች መምጣት ያቆምክ መስሎኝ ነበር " »

« አዎን ትቸው ነበር » አለ ሁለተኛዉ «አሁን ግን በማፈላለግ ላይ ስለሆንኩ ሳልወድ ተመለስኩባቸው እኔ መቸም እንደ. ዳንስ አዳራሽ የሚሰለች ነገር ያለ አይመስለኝም " »

« ምንድነው የምታፈላልገው ? »

« ሚስት ነዋ ! አባቴ እስካልተሻሻልኩና እስካልታረምኩ ድረስ ዕዳ የሚባል ነገር እንደማይከፍልልኝ ለኔም አንዲት ሽልንግ እንኳን እንደማይጥልልኝ ምሎ ተገዝቶ ገንዘብ ከልክሎኛል " አሁን ለመስተካከል የመጀመሪያ ደረጃ ብሎ ያመነበት
ሚስት ማግባት ስለሆነ የምትመስለኝን መምረጥ ይዣለሁ እንዳልተወው ማንም ከሚያስበው በላይ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቄአለሁ ።

« ታዲያ አዲሲቱን ቆንጆ አታበም እንዴ ! »

« ማናት እሷ ? »

« ሳቤላ ሼን " »

« ለጥቆማህ በጣም አመሰግናለሁ» አለው «ግን ማንም ሰው ቢሆን ክብሩን የሚጠብቅ አማት እንዲኖረው ይፈልጋል " ሎርድ ዊልያምና እኔ ተመሳሳይ አመል ስለ አለን ከዜ ብዛት ልንጋጭ እንችላለን " »

« ሁሉ ነገር እኮ ተሟልቶ አይገኝም ልጂቱ በመልኳ መሰል የላትም ።
ያ ቀጣፊ ሌቪሰን ወደ አሷ ጠጋ ጠጋ ሲል አይቸዋለሁ እሱ ዶግሞ ሴቶችን በሚመለከት ረገድ የሚያቅተው ነገር ያለ አይመስለውም" »

« ታዲያ እኮ ብዙ ጊዜ እንዳሰበ ይሆንለታል " »

« እኔ አሱን ሰውዬ አጠላዋለሁ " ጫፉን ጥቅልል እያደረገ የያበጥረሙ ጸጉሩን የሚብለጨለት ጥርሶቹንና ነጫጭ እጆቹን እያየ ያለሱ ሰው ያለ አይመስለውም » ስለ ሰው ጉዳት ምንም ስሜት የለውም ለመሆኑ ያ ተዳፍኖ የቀረ
የሚስተር ቻርተሪዝ ጉዳይ ነገሩ እንዴት ሆነ ? »

« ማን ያውቀዋል ? ሌቪሰን ከነገሩ እንዶ ዐሣ ተሙለጭልጮ ወጣ " ሴቶቹም እሱ ከፈጸመው ጥፋት በሱ የደረሰበት በደል ይበልጣል ብለው ተከራከሩለት » ከሕዝቡም ሦስት አራተኛው አመናቸው " ይኸውልህ መጣ I የዊልያም ቬን ልጅም አብራው አለች " »

ሳቤላና ሌቬሰን እየቀረቡ መጡ " ስለ መስቀሉ በድንገት መሰበር እየደጋገመ ፀፀቱን ይገልጽላት ነበር " « እንግዲህ ተመልሶ እንደ ነበረው የሚሆን አይመስለኝም» አላት ቀስ ብሎ በጆሮዋ « መቼም uመኔን በሙሎ ልባL ኀን ስልጽ
ብኖር የምተካው አይመስለኝም "

መንፈስን እያነቃቃ የደስታ ስሜትን እየነካካ ከአእምሮ የሚገባው ረጋ ያለው ሥልተኛ አነጋገሩ ጆርን የሚያስደስት ልብን የሚያሳስት አደገኛ ነበር "
ሳቤላ ቀና ብላ ስትመለከተው ዐይኖቹ ከሷ ላይ ተተክለው ሲስለመለሙ አየቻቸው እንደዚያ ያለ ቋንቋ አጋጥሟት አያውቅም ነበርና እሶም ጉንጮቿ ተለዋወጡ
ዐይኖቿ ክድን አሉ ልትናገራቸው የነበሩት ቃላት ከከንፈሯ ደርሰው ጠፉባት "

« ሰውየው አጭበርባሪ ይመስላል» አለ መኮንኑ "

« ነውና " እኔ እንኳን ስለሱ አንድ ሁለት ነገሮች ዐውቃለሁ " አሁንም ይች ልጅ ቆንጆ ስለሆነች ለዝና ሲል ልቧን ያጠፋዋል " ከሷ ለሚቀበለው ስጦታ ግን ለመመለስና የሚያስበው ውለታ የለውም».....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዌስት ሊን የፋብሪካ ወይም የአንድ ካቴድራል ከተማ ወይም የክልሉ አስተዳደር ዋና ከተማ አይደለችም" ነገር ግን ምንም እንኳን በጥንታዊ ልማዱና ባህሏ ወደ ኋላ ቀረት ያለች ብትሆንም ራሷን በተለይ ደህና ከተማ አድርጋ ትቆጥራለች ለፓርላማ ሁለት እንደራሴዎችን ትወክላለች
👍21👎1
ከተማይቱ በጣም የምትመካበት
ከላይ ከፀሐይና ከዝናም የተጋረደ አንድ ገበያ አላት " ከገበያዉ ከፍ ብሎ ደግሞ «የከተማ አዳራሽ » እያሉ የሚጠሩት አንድ ትልቅ ክፍል አለ “ በዚህ ክፍል ያካባቢው የሕግ ባለሥልጣኖች እየተገናኙ ይሠሩበታል ከዌስት ሊን ከተማ ወጥቶ ወደ ምሥራቅ ሲኬድ ፈንጠር ፈንጠር እያሉ የተሠሩ ብዙ የትልልቅ ሰዎች ቤቶች ይታያሉ በነዚህ ቤቶች አካባቢ ደግሞ ከሌሎች አድባራት የተለያዩ የመኳንትና የወዛዝርት ምእመናን የሚበዙበት የቅዱስ ይሁዳ ቤተክርስቲያን ይገኛል ቤተ ክርስቲያኑ ደመቅ ወዳለው የከተማው ክፍል ሲገኝ
ወደ አንድ ማይል ያህል ወጣ ብሎ ነው እነዚያ ተበታትነው የተሠሩት ቤቶች የሚገኙት ። ቤቶቹን ዐልፎ ደግሞ
ከአንድ ማይል ርቀት በኋላ ኢስት ሊን እየተባለ የሚጠራው አንድ በጣም የሚያምር ክልል መሬትና ቤት ይኛል " በሠረገላ ተሳፍሮ አውራውን መንገድ ተከትሎ ለሚያልፍ ሸጥና ተረተር የበዛበት
በለምለም አፅድ የተሞላ አግድመት ማየት ይቻላል ለእግረኛ ግን በጣም ከፍተኛ የሆነው የግምብ አጥር ስለሚጋርደው አይታየውም " በዐፀዱ ውስጥ በቁመት ዘልቀው በጐን ሰፍተው በሚታዩት ትልልቅና
የሚያማምሩ ዛፎቹ የበጋው ጋበን ሲበረታ ሰዎቹም አጋዘኖችም ሳይቀሩ ይጠሉባቸዋል " ከዋናው መንገድ ወደ ቀኝ ጠምዘዝ ሲሉ በግራና በቀኝ የዘብ መቆሚያ
ቤቶች ያሉት አንድ ትልቅ በር ይገኛል ። በሩን እንዳለፉ 'መንገዱን ይዞ ቀጥታ
በመሔድ ዋናው ቤት ወዳለበት ይደረሳል " ከአንዳንድ የገጠር መኖሪያዎች ጋር
ሲነጻጸር ትልቅ ቤት ለመባል ባይችልም በቪላ መልክ የተሠራ በጣም የሚያምር ነጭ ቅብ ሆኖ ባጠቃላይ ቤቱም ቦታውም ለዐይን ደስ የሚል አካባቢ ነው።

ቀደም ብለው የተጠቀሱትንና ተበታትነው የተሠሩትን ቤቶች ዐልፎ አራት መቶ ሜትር ያህል እንደ ሔዱ ወይም ኢስት ሊን ለመድረስ አንድ ኪሎ ሜትር ተሩብ የሚሆን መንገድ ሲቀር አንድ ቤት ይኛል " ከዚያ ቤት አንሥቶ እስክ ኢስት ሊን
ድረስ ደን የለበሰና ጭር ያለ መንገድ እንጂ ምንም ቤት አይገኝም ። ይህ ከሌሎች
ቤቶች አራት መቶ ሜትር ያህል ዐልፎ የሚኀኘው ቤት የቆመው ከመንገዱ በስተ ግራ ጥቂት ገባ ብሎ ነው " የአራቱም ማዕዘን ጎኖች ቁመት እኩል የሆነና በቀይ
ሸከላ የተሠራ ሲሆን እምብዛም ለዐይን ደስ የሚል ቤት አይደለም ከጉልላቱ ላይ የአየርን ሁኔታ የሚያመለክት የአውራ ዶሮ ምስል ያለበት መኖረያ ይታያል " ከበስተፊቱ ደልደል ያለ የግቢ ጨፌ አለው " ግቢውን ከዋናው መንገድ ከሚያካልለው የገራገር
አጥር ጥግ የጥቂት ሜትሮች ጥልቀት ያለው አንድ ቸብ ያለ ትንሽ ዱር ይገኛል " እንግዲህ ከዋናው መንገድ በአንድ ጠባብ የብረት በር ተገብቶ ያንን የግቢ
ጨፌ ለሁለት እኩል ሰንጥቆ በሚያልፈው ጠባብ የጠጠር መንገድ በመሔድ ያገር
ቤት ሥራ ከሆነ የቤቱ በረንዳ ይዶርሳል " በረንዳውን ዐልፎ ሲገባ በግራና በቀኝ በኩል አንዳንድ የእንግዳ መቀበያ ክፍሎች ያሉት አንድ ድንጋይ ንጥፍ የሆነ ትልቅ መተላለፊያ ሲገኝ ከፊት ለፊቱ ደሞ አንድ ሰፊ ደረጃ ይታያል በደረጃው በስተ ጎን ዐለፍ ብሎ ደግሞ ያሽከሮች ቤትና ቢሮዎች አሉ ከገረገራው አጥር ውጪ ችምችም ባለው ትንሽ ዱር ምክንያት በልማድ ዐፀዱ ወይም ደኑ አየተባለ የሚጠራው ይህ ቦታ የሚስተር ሪቻርድ ሔር ቤትና ግቢ ነው " ይህ ሰው ሕዝቡ በተለምዶ ጀስቲስ ፡ ዳኛው ሔር እያለ ይጠረዋል።

በበሩ ሲገቡ በስተግራ ያለው ክፍል የዘወትር ሳሎን ሲሆን የበስተቀኙ ግን ጥሩ ጥሩ መዓዛ የሚሰጡ ነገሮች ይዶረጉበትና ከፍተኛ ጉዳይ ሲኖር ብቻ እየተከፈተ ከሚሠራበት በቀር ተዘግቶ ነው የሚኖር " ሚስተር ሪቻርድ ሔርና ባለቤቱ ሚስዝ ሔር አንድ ወንድና ሁለት ሴት ልጆች አሏቸው አን የምትባለው ትልቂቱ
በልጅነቷ ተድራ ባለትዳር ሆና ተቀምጣለች » የሷ ተከታይ ባርባራ ደግሞ ዐሥራ ዘጠኝ ዓመቷ ነው " የሁለቱም ታላቅ ስለሆነው ስለ ሪቻርድ ሔር ግን ኋላ እንመለስበታለን።

አንድ ቀን ማታ ብርዱ በሚያንስፈስፍበት በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ሚስተር ካርይል ከዊልያም ቬን ጋር ከተነጋገረ ከጥቂት ቀኖች በኋላ መሆኑ ነው ሚሲዝ ሔር ስልበል ግርጥት ብላ መጐናጸፊያዎቿን ደራርባ በመከዳዎች ተደግፋ ተቀምጣ
ነበር " የተቀመጠችበት ባለ መከዳ ወንበር ወደ ምድጃው ይጠጋ እንጂ ምድጃው
እሳት አልነበረውም " ምሽቱ በጣም ቀዝቃዛ ቢሆንም ቀኑ ሞቃት ሆኖ ውሎ ነበር"
ከመስኮቱ አጠገብ ጸጉሯ ቀላ' አፍንጫዋ ቀና ያለ አንዲት ቀለመ ደማቅ ልጅ ተቀምጣ ፍዝዝ እንዳለች ያለ ልቧ የአንዱን መጽሐፍ ቅጠሎች ታግላብጣለች "ባርባራ...መቼም አሁን የሻይ ሰዓት መድረስ እንዳለበት እርግጠኛ ነኝ" ጊዜው አልገፋልሽ አለ ......... እማማ " ገና ዐሥራ ሁለት ካሥር ነው ካልኩሽ
ወዲህ እንኳን ሩብ ሰዓት አልሞላም ።»
« በሻይ አምሮት ሞትኩ እንጂ » አለች ምስኪኗ በሽተኛ «ኧረ አባክሽን ሒጂና ሰዓቱን እንደገና እይው »
ባርባራ እየከፋት ሳትወድ ተነሣችና በሩን ከፍታ ከመተላለፊያው ግድግዳ
የተሰቀለውን ትልቅ ሰዓት ተመልክታ ተመለለች » «ለአንድ ሰዓት ኻያ ዘጠኝ ደቂቃ ጉዳይ ነው እማማ ኧረ እንዲያው አሁንስ ሰዓትሽን ለንድ ቀን እንኳን
ብታስሪው ምነው?ይኸው ከራት ወዲህ ሰዓት ለማየት አራት ጊዜ ላክሺኝ »

« ኧረ በጣም አሰኘኝ » አለች ሚሲዝ ሔር መልሳ ልቅሶ እየተናነቃት » « ኧሪ ምነው አሁንስ አንድ ሰዓት በተደወለ ! በሻይ አምሮት መሞቴ ነው»

“ሚሲዝ ሔር የቤቱ ባለቤት እመቤት ሆና ሰዓት ደረሰ አልደረሰ ተዶወለ አልተደወለ ብላ የምትጨነቀው ለምንድነው ? አንድ ሲኒ ሻይ አስፈልታ ለመጠጣት ችግሯ ምንድነው ? የሚል ጥያቄ በሁሎም አእምሮ ሊደቀን ይችላል ። ሚሲዝ ሔር ዘንድ እንዲህ ያለ ነገር የለም " ባሏ አግብቶ ወዶዚህ ቤት ካመጣት ከኸያ አራት ዓመት በፊት ጀምራ ፍላጐቷን ለመግለጽ በሷ ኃላፊነት ሊፈጸሙ በሚችሉ ጉዳዮች
ትእዛዝ ለመስጠት ደፍራ አታውቅም " ዳኛው ሔር ግንባሩ የማይፈታ ፈላጭ ቆራጭ ግትርና ራስ ወዳድ ሰው የነበረ ሰው ሲሆን ሚስቲቱ ደግሞ ድንጉጥ የዋህና ደካማ ነበረች " ከዚህም ሌላ ባሏን በጣም ትወድ ስለነበር ፍላጐቷን ሁሉ በሱ ፈቃድ ብቻ እንዲሰጣት ስታደርግ ብትኖርም የጭቆናው ቀንበር ግን ተሰምቷት አያውቅም " የአንዳንዱ ተፈጥሮ እንዲህ ነው " እሱም ቢሆን ያን ያህል ያምባገነንነት ጠባይ ሲያሳይ ዐመል ሆኖበት አንጂ በሚስቱ ለመጨከን ፈልጎ አልነበረም " ከሦስት ልጆቹ ካባቷ ጠባይ በመጠኑ የወረሰች ባርባራ ብቻ ነበረች " እባክሽን ልክ አንድ ሰዓት ሲሞላ ወዲያውኑ ሻዬን እንዲያቀርቡልኝ ደውይና ተዘጅተው እንዲጠብቁ ንግሪያቸው " »

"ሁልግዜ ተዘጋጅቶ እንደሚጠብቅ ታውቂያለሽ እማማ ግን አባባም በሰዓቱ ላይደርስ ስለሚችል የሚያስቸኩል አይደለም » አለቻትና አሁንም እየከፋት ተነሥታ ሠራተኛዉን በደወል ጠርታ ሻይ ቀዶም ብሎ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ አዘዘችው "

«አዬ ልጄ !ጐሮሮዬ ምን ያህል እንደ ደረቀ አፌ እንዴት እንደ ተቃጠለ ብታውቂልኝ ኖሮ እንደዚህ አትሰለቕኝም ነበር » አለቻት »

ባርባራ መጽሐፉን ዘግታ ባሳየችው መሰልቸት እየተጸጸተች እናቷን ሳመችና አሁንም በመስኮቱ ዘልቃ ወዶ ውጭ እየተመለከተች ትተክዝ ጀመር « እንዲያውም አባባም መጣ » አለቻት "
👍16
ዳኛው ሔር ገባ " ቁመቱ መካከለኛ ሲራመድ ጅንን የሚል ፊቱም የማይፈታ ሰው ነው ከጫፉ ቁልቁል ቁልምም ያለው አፍንጫው ስብስብ ያሉት ከንፈሮቹንና ሾጠጥ ያሉት አገጩን ሲያዩት ትንሽ ባርባራን ሊመስል ሲል ' ባጠቃላይ መልክ ግን እሷ በጣም ትበልጠው ነበር "
« ሪቻርድ» አለች ሚሲዝ ሔር በደራረበቻቸው ልብሶች እንደ ተሸፋፈነች ገና በሩን ከፍቶ ሲገባ "

« ምነው ? » አላት

« ሻይ አምሮኛል ዛሬ ከወትሮው ጥቂት ቀደም ብለን ብንጠጣስ ? ይሽውልህ ሰውነቴን እንደገና አተኮሰኝ ምላሴ ቅጥል ብሎ አሯል " አሁንስ ከነመናገሩም
ሊከለክለኝ ምንም አልቀረው " »

« አይ አሁን እኮ ለአንድ ስዓት ምንም ያህል አልቀረውም " እስከዚያ ታገሽ » አላትና • ለዚያች ያልጋ ቁራኛ በሽተኛ ሚስቱ 'ይህን የመሰለ ከልክ ያለፈ ከበሬታና አዘኔታ የተመላበት መልስ ሰጥቶ ክፉ ነገር ሳይናገር መጊያውን ግው አድርጎ በመዝጋት ወጥቶ ሄደ። "

ሚሲዝ ሔር ጨርሳ ባላሰበችሙ ተስፋ አስቆራጭ መልስ የተሰማት ኀዘን ግና ሳይወጣላት ተመልሶ ገባና: «እንዲያውም ዛሬ ጥሩ ጨረቃ ስላለች ከፒነር ጋር ሆነን
ቦሻ ዘንድ ትምባሆ ስናጤስ ለማምሸት የተመቸ ነው " ስለዚህ አሁን ብጠጣም ግድ የለኝም » በይ ባርባራ... ሻዩን አስመጪልን » አላት ሻይ ተጠጥቶ እንዳበቃ የሚስተር ቦሻ የርስት ሹም ሚስተር ስፒነር ከደጅ ሆኖ ተጣራና ከዳኛው ሔር ጋር ተያይዘው ሔዱ " hኢስት ሊን ማዶ ከነበረው አፋፍ ላይ ይኖር የነበረው ሚስተር ቦሻም ብዙ መሬት የሚያሳርስና ለዊልያም ቬንም የኢስት ሊን ወኪሉ የነበረ ሰው ነው «ባርባራ · በረደኝ » አለች ሚስዝ ሔር እየተንቀጠቀጠችና ባሏም በጠጠሩ መንገድ ዘቅዝቆ ሲሔድ እየተመለከተች « እሳት ባስነድድ አባትሽ ይቆጣኝ ይሆን ? »

« ከፌለግሽ አስነድጂ » አለቻት
ባርባራ መጥሪያውን እየደወለች » « አባባ የሚመለሰው ከተኛን በኋላ ስለሆነ ምንም ሊያውቅ አይችልም " ጃስፐር …....
እማማን ስለ በረዳት እሳት ትፈልጋለች " »

« አዴራህን ጃስፐር...ቶሎ እንዲያያዝና በደንብ እንዲነድ ከዕንጨቱ በርከትከት አድርግበት» አለችው ሚሲዝ ሔር ዕንጨቱ የሷም መሆኑ ቀርቶ የጃስፐር እንደሆነ ሁሉ በሚያሳዝን የልመና ድምፅ ....

💫ይቀጥላል💫
👍112
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው



“ምንድነዉ እመ?”

እየቆየ ፍርሐት እየለቀቀብኝ፣ ላብ እያጠመቀኝ መጣ፡ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ድምፅዋን እንኳን አልሰማሁትም? ለምን አላለቀሰችም? “ኧረ ልጄስ? ልጄ አታመጡልኝም?” አልሁኝ ከአሁን አሁን ቱናትን አምጥተዉ ያስታቅፉኛል ብዬ ብጠብቅ ዝም ስላሉኝ፡ አጭር ጊዜ በፈጀ
ቀዶ ሕክምና ቢሆንም የወለድሁት፣ የእናት ወጉ ደርሶኝ ገና ጡቴን ለልጄ አላጠባኋትም ጡት ማጥባት ቀርቶ ለዓይኔ እንኳን አላሳዩኝም፡

“አይ፣ ለትንሽ ጊዜማ ማሞቂያ ክፍል አትቆይም ብለሽ ነዉ? እንግዲህ ዶክተርሽ ያለችን እንደዚያ ነዉ” አለች እመዋ፣ ከእሸቴና ባልቻ ጋር የያዘችዉን ሞቅ ያለ ጨዋታ አቋርጣ ትኩረት እየሰጠችኝ፡

“እኮ ባይሆን አሳዩኛ። ላያት እፈልጋለሁ”

“ቆይ ትንሽ ተብለሽ እኮ ነዉ: አንቺም ትንሽ አረፍ በይ እስኪ ፊት”

“እመዋ፤ ወይ ወደ ልጄ ዉሰጅኝ ወይ ደሞ ልጄን አምጭልኝ” አልሁኝ፣ ከአልጋዬ ላይ ለመነሳት እየተገለገልሁ አቅም አጣሁ እንጂ ማንም አይመልሰኝም ነበር ለምንም ነገር እንዲህ ሆኜ አላዉቅም ለካ እንዲህ ነዉ የሚያደርገዉ? አሁን በአሁን እናት ሆኜ እርፍ! የእናት ሆድ ኖሮኝ
ቁጭ! ጭራሹን ያላየኋት ልጄ በዓይን በዓይኔ ዞረች᎓᎓ ናፈቀችኝ፡ ራበችኝ፡ ደግሞ ልቤ እንዴት ነዉ የሚደልቀዉ? ልጄን እንጂ የፍርድ ቤት ዳኛ አይደል የምተያየዉ፡

የናፍቆቱስ እሺ ይገባኛል፤ ፍርሃቱን ግን ምን አመጣዉ?
የልቤ መንቀጥቀጥ ቆዳዬ ላይ እስከሚታወቅ ድረስ በጣም ፈርቻለሁ ጭንቅላቷን ማየት ነዉ ፤ያስፈራኝ: ትልቅነቱ ምን አህሎ ይሆን? ራሷስ ምን ታህል ይሆን? ኹለት ኪሎ እንኳን መሙላቷን እንጃ አተነፋፈሷ ልክ ነዉ? በቅድመ ወሊድ እንደ ተፈራዉ፣ የጀርባዋ ነርቭ ክፍተት ፈጥሮ ይሆን? ቢያንስ እግሮቿን ማንቀሳቀስ ትችልም እንደሆነ
እኮ ገና የነገረኝ የለም: ዓይኖቿም በትክክል ማየታቸዉን አላወቅሁም
ወይስ እግዚአብሔር ተአምር ሠራ? ባልቻ እና እመዋ እንደ ተማመበት ድንቅ ሥራዉን አሳይቷቸዉ ይሆን? በተአምሩ የሰዉ መልክ፣ የሰዉ ጤና፣ የሰዉ ትንፋሽ ሰጥቷትስ ቢሆን! እሱንስ ቢሆን ማን ነገረኝ?
እግዚአብሔር እኮ ሥራዉ የሚታወቀዉ አንድም በጨቅላዎች ነዉ ይባላል፡፡ ከማሕጸን እንደ ወጡ ገና የጡትን ቦታ እና ጥቅም አጥተዉት
አያዉቁም: ልጄንስ ጡት አያምራት ይሆን? ካላየኋትማ መሞቴ ነዉ፡

እንደገና ፈራኋት ፡ እንደገና ናፈቅኋት።

“አንቺ ግን አየሻት ወይ እመ?” አልኋት፣ እጆቼን ከጡቶቼ ላይ ሳላነሳ።

“ማንን፣ ቱናትን?”

“አሃ፤ ስምም አዉጥታችሁላታላ?” አለ ባልቻ፣ ከእመዋ አፍ ተቃምቶ።

“ቱናት ብያታለሁ በበኩሌ” አለች፣ እመዋ:

“እመዋ” ስል ጠራኋት ቆጣ ብዬ፣ የባልቻ አጠያየቅ ወሬ ለመለወጥ
መሆኑ ስለ ገባኝ፡

“ዉብዬዋ” አለችኝ፣ የእናት እጇን ጭምር እየሰጠችኝ ይኼዋ እንዴት
እንደምታቆለማምጠኝ! ቁልምጫዋንስ ማቆላመጥ ታዉቅበት የለ? እሷ እናትነቷን እንዲህ ባጠጣችኝ ቁጥር፣ የእኔም ጉጉት ሰማይ ይደርሳል
እሷ ለእኔ እንደምትሆነዉ፣ እኔም ለልጄ ለመሆን ቋምጫለሁ

“እመዋ”

“እመት ዓለሜዋ”

“ስሞትልሽ! ስሞትልሽ ልጄን አምጭልኝ'

“ኧረ ቀስ! ምነዉ ልጄ? ወዲያዉስ የሐኪምሽ ወዳጅነት ላንቺ መስሎኝ! እንዲህ ሆነሽ ትወስድሽ ሆይ ወይ ደግሞ ቱናትን እንዲያ እዳለች ታመጣልሽ እንደሆነ፤ ሐኪምሽን ራስሽ የማትጠይቂያት”

"እኮ ጥሪልኛ እመዋ ዶክተሯን ጥሪልኝ እሺ”

እንደማልለቃቸዉ ሲያዉቁ ዶክተሯን ማስፈለግ ጀመሩ፡ ነገር ግን ሌላ ተረኛ ነፍሰ ጡር ለማዋለድ፣ ወደ ማዋለጃ ክፍል ቅርብ ጊዜ እንደ ገባች ከነርሶቹ መስማታቸዉን ነገሩኝ፡
አላመንኋቸዉም በይበልጥ
እየፈራሁላት፣ በይበልጥ እየተጠራጠርኋቸዉ መጣሁ ቅጽበት በቆየሁ ቁጥር ክፉ ክፉዉን ለሚያሳስበኝ መንፈስ መረታት ያዝሁ፡ ጭራሽ በሕይወት ባትኖር ይሆናል እንጂ፣ ቢያንስ እንዴት ድምፁዋን እንኳን
አያሰሙኝም?

“አአአ..አንድ ሐሳብ መመመመ..መጣልኝ” ሲል ሰማሁት እሸቴን፣ እስከ
አሁን ዓይኖቹን ከማንከራተት በቀር ትንፍሽ ሳይል ቆይቶ፡ “ዉዉዉ..
ዉቤ? ”

“እየሰማሁህ ነዉ”

ሐሳቡን አንድ ብሎ ሊነግረኝ ሲጀምር ገና፣ ልታዋልድ ኦፕራሲዮን ክፍል ገብታለች የተባለችዋ ዶክተር የክፍሉን በር ከፍታ ገባች፡

“ኦንኳን ማርያም ማረችሽ” አለችኝ፡

“ማርያም ታኑርሽ” አለች እመዋ ቀድማኝ ወዲያዉም ከጎኔ ቁጭ
ካለችበት የአልጋዉ ጫፍ ብድግ ብላ፡ ዶክተር ሸዊት ያ ብዙም
የማይለያትን ፈገግታዋን
ሳትቀንስ ሁሉንም እያቀፈች ሰላምታ ከተለዋወጠች በኋላ፣ እኔንም ጎንብስ ብላ ሳመችኝ፡፡ ግንባሬን አንገቴን እና እጆቼን እየደባበሰችኝ ሳለ፣ ለምን ልጄን እንደማያመጡልኝ ልጠይቃት ስል ቀልቧን ወደ እመዋ አደረገችብኝ፡፡

“እመዋ? እንኳን ደስ አለዎ”

“በአምላክሽ!”

“መቼስ ረስተዉኝ አይሆንም፤ ረሱኝ እንዴ ? "

“ተይ እንጂ! ምን ብረሳ ብረሳ፣ አንቺን እረሳ ብለሽኝ ነዉ? ምነው
አንድዜ እንኳ ከዉብዬ ጋ ለክረምቱ ይሁን ለገናዉ ዕረፍት
መጥታችሁ አብረንም አልሰነበትን?”

“አልረሱኝማ”

“ አንቺን? እንዲያዉ ያቺን ጨዋታሽ የምረሳልሽ መስሎሻል?”

“የቷን?” አለች፣ ለመፍካት ችኩል የሆኑ ጥርሶቿን እየገለጠች

“ምነዉ እንኳን አንድዜ፣ የሩስያ ምንቴስ ነዉ ያልሽኝ ሰዉ በዉብርስቴ ደም ግባት የሆነዉን ሁሉ አጫዉተሽኝ?”

“ስለ እሱ ጉድ ነግሬሽ ነበር ወይ እመዋ?”

“እህሳ”

“ለእኛም ንገሪን እንጂ ዶክተር” አለ ባልቻ፣ ያለ ወትሮዉ ለወሬ ሰፍ ብሎ፡ የእሸቴም ጆሮ ከምኔዉ ቀጥ እንዳለ! የእሸቴ እና የባልቻስ ይሁን እሺ፣ እመዋ እንኳን እንደ አዲስ ለመስማት በዓይኖቿ ደጅ ስትጠናት ሳይ እኔም የልጄ ናፍቆት በረድ አለልኝ፡፡

“ጉዷ ያልቅ መስሏችኋል?” ብላ ጀመረች፡ “ይቺ ጉደኛ! የተመረቅን
ሰሞን ነዉ ነገሩ። ቀድሞዉንም ቢሆን በዉጤት እንደ ምንም እቀራረባት እንደሆነ እንጂ ደርሼባት አላውቅም:: በተለይ የመመረቂያ ጥናቷን ያዩላት ሰዎች ሁሉ እዴት ይደነቁባት እንደነበር አትጠይቁኝ። እና እንደ አጋጣሚ፣ በዚያ ሰሞን የሩስያ አምባሳደር ከሀገራቸዉ የመጡ በጎ ፈቃደኛ
ሀኪሞችን እየመሩ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተዋል። ጠሪዉ ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ነዉ: የዚያን ዕለት ታዲያ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት ራሱ ስልክ ደዉሎላት ኹለት ሁነኛ ሰዎች እንድትመርጥ እና በጎ ፈቃደኛ ሩስያዊ ሀኪሞችን እንድታግዝ ያዝዟታል”

“ማንን?”

“ይቺን ነዋ፤ ዉብርስትን''

“እሺ”

"እሷ ደግሞ እኔን እና አንድ ሌላ ሐኪም ስትጠይቀን፣ እናግዛለን ብለን ሳይሆን እንጠቀማለን ብለን ወደ ተባሉት በጎ አድራጊዎች በጠዋት †ነስተን ተከተልናት።
በዚያች አንድ ቀን ታዲያ፣ ሩስያዉያኑ ያልደረሱበት የጎንደር ዙሪያ ጤና ጣቢያ የለም። እኛም አብረናቸዉ እየዞርን እነሱ ለጤና ጣቢያዎቹ ያመጡልን መድኃኒት ስናድል እና ለጥቂት አበሻ ሕመምተኞች ደግሞ መጠነኛ ሕክምና ሲሰጡ ስናይ ዋልን
ማታዉኑ፣ ዩኒቨርስቲዉ እንግዶቹን እራት ካልጋበዝሁ አለ። አምባሳደሩ ግን አመሻሹ ላይ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ቢሆንም ዕቅዳቸዉ፣ ከስንት መለመን በኋላ የበረራ ሰዓታቸዉ እንዲዘገይ ተስማምተዉ በግብዣዉ ላይ
ተገኙ። እኛም እንደ እንግዶች በክብር ተጠርተን፣ መጥሪያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ተገኝተናል። የከተማዉ ከንቲባ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት፣ምክትሎቻቸዉ እና ዘመዶቻቸዉ ጭምር
መጥተዉ ሳይሆን አይቀርም፣ ያን የሚያህል አዳራሽ ጢም ብሏል።
የጎንደር መታወቂያ የሚባሉ አዝማሪዎችም መድረኩን ሞልተዉታል።ብርቆዎች፣ ጨዋታዎች፣ ሳቆች ድብልቅልቅ አድር ገዉታል”
👍33
“እዚህ ላይ አይደል ጉዱ?” አለች እመዋ፣
እየደረደረች፡ ሸዊት ቀጠለች፡፡

“መቼም አዝማሪዎች የታወቁ ናቸዉ በዚህ በዚህ: አሽሙሩንም፣
ሙገሳዉንም፣ ትንቢቱንም፣ ታሪኩንም እየቀላቀሉ ያመጡታል። ቋንቋዉ ባይገባቸዉም፣ ሩስያዉያኑ እንግዶች እጃቸዉን አፋቸዉ ላይ ጭነው
በአድናቆት ይመለከቷቸዋል። የእነሱ ነገረ ሥራ ደንቆኝ፣ ወደ ዉቤ ዞር ስል ትቁነጠነጣለች። የአዝማሪዎቹ የዜማ አወራረድ እና የግጥም አካሄድ በኃይል ነሽጧት
ኖሮ፣ ብቻ እንዴት እንዴት አትጠይቁኝ። ምን ሊያደርጋት ነዉ ስል ድጓገት ተስፈጥራ ከአጠገቤ ተነሳች። በዚያ ጊዜ ራሷንም ማወቋን እንጃ ብቻ፣ ቀጥ ብላ ወደ መድረኩ ሄደች። እኔ ሰዉ እንደሷ ሲሆን ያየሁት፣ ዲማ ቅኔ ቤት የጎበኘሁ ጊዜ ነዉ። የቅኔ ተማሪዎችን ብቻ ነዉ እንደሷ እየዘለሉ እልም ብለዉ ስሜት
ዉስጥ ሲገቡ ያየኋቸዉ: አንዱ አዱን ነጥቆ ሲዘርፍ ያሁት እነሱ
ነበር። ያኔ ግን ኋደኛዬ በቅጡ እደማላዉቃት ገባኝ። በእሷ የሚደርስ ማንም የለም ኖሯል ለካ: እየተንደረደረች ሄደችና
ከአዝማሪዎ መካከል ቆሞ የሚያዜመዉን ሰዉ ክራር ነጠቀችዉ: ደግነቱ እሱም
አልከላከላትም: ይልቁስ እሱ ጀምሮት ከነበረዉ ሐረግ ላይ ተነስታ እስካሁንም ድረስ ፍቺዉ ያልገባኝ ቅኔ ስትቀኝ በአድናቆት ተመለከታት:መመልከት ብቻም ሳይሆን እጁ እስኪዝል ድረስ ቆሞ አጨበጨበላት::አዳራሹ ዉስጥ ተቀምጬ የቀረሁት እኔ ብቻ ነበሁ ብላችሁ ታምኑኛላችሁ? በስመአብ!ሩስያዉያኑ እንግዶች ሳይቀር ትርጉሙ የገባቸዉ ይመስል፣ አፋቸዉን ከፍተዉ ቀሩ: አምባሳደሩም እንዲያ ወደ
አዲስ አበባ ለመሄድ ቸኩለዉ የበረራ ሰዓታቸዉ ትንሽ በመራዘሙ ለንቦጫቸዉ ጥለዉ እዳልነበር ፣ አሁን ግን ተለዉጠዉ ጉድ አላመጡም?”

“የምን ጉድ?” አለ ባልቻ፣ እሱም እንደ እመዋ እና እንደ እሸቴ ቁጭ
ብድግ እያለ ሲያዳምጣት ቆይቶ፡
አይ እሷ! አቤት አገላለጽ! በምታወራዉ ላይ ዉሸት ባላገኝበትም፣ አገላለጽዋ ላይ የምትጨማምራቸዉ ነገሮች ግን፣ የምትለዉ ዉሸት እንኳን ቢሆን ኖሮ ከማመን አያተርፈኝም ነበር፡ እንኳንስ እነ ባልቻን እኔን ባለ ታሪኳን ሁሉ ስሚኝ ስሚኝ አስብለኛለች ያዉም በልጄ ናፍቆት
ክፉና ደጉን ከማሰብ አዉጥታኝ፡

“አምባሳደሩ?” አለ እሸቴ፣ እሱም ጉጉት እንደ ባልቻ እና እንደ እመዋ
እያደረገዉ፡

“አምባሳደሩ ጉድ አመጡ: (በስመ አብ! አሉበአማርኛ: እዉነትም
አዝማሪዎቹ እንደ ከዋክብት፣ ዉብዬ ግን እንደ ጨረቃ ሆነዋል። የዉበት ዳርቻ እኮ ናት ጓደኛዬ! አንዳንዱማ እንዲያዉም (በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ፀሐይ ከየት ወጣች እስከ ማለት ነበር የደረሰዉ። መድረኩ ላይ ብቻ
ሳይሆን በአዳራሹ ሙሉ፣ በአዳራሹም ብቻ ሳይሆን በመላ ከተማዉ፣ በዚያም ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሩ እሷን የሚተካከል ቆጓጆ አለመኖሩን እየማለ ተወራረደ። ለቆንጆ ሰዉ ቆንጆ ጭንቅላት እና ቆንጆ ድምፅ ሰጥቶ
የፈጠራትን አምላክ፣ሁሉም ቀና እያለ አደነቀ። ‹ኧረረረረ አሉ
አምባሳደሩ እንደገና፣ በጎንደርኛ: ይኼ ሲገርመ እኔ፣ ሰተት ብለዉ ወደ መድረኩ ወጧ''

“ምን ሊሆኑ?”

“ሊስሟት”

“ምን?” አሉ ሁሉም እኩል፣ ግርምም ቅፍፍም እያላቸዉ፡
“ካልሳምሁሽ አሉ። አምባሳደሩ ለመሳም፣ ዉብዬ ላለመሳም የሆኑትን መሆን እያየ የሆቴሉ ታዳሚ ዝንታለም ተስቆ የማያዉቅ ሳቅ ሳቀባቸዉ”

“እእእ እሰይ! ማን ቅለል ብሎታል? የት አባቱ!” አለ እሸቴ፣ በአሸናፊነት

“እንጃለት!” አለ ባልቻም፣ ቀበል አድርጎ፡ “አምባሳደር ሆኖ ሲያበቃ፣ ባህላችንን ማወቅ አልነበረበትም? ሮጦ ወደ ሀገራች ከመምጣቱ አስቀድሞ፤ እንኳንስ የሰዉ ሰዉ የገዛ ሚስቱን እንኳን በአደባባይ መሳም ነዉር መሆኑን አያውቅም ኖሯል? ይበለዉ!''

ሸዊት እኔን ስትጠቅሰኝ ባላጅባትም፣ በኹለቱም ፍርስ ብላ ሳቀችባቸዉ

“እንደሱ እኮ አይደለም:: ሌላ ነገር ፈልጎ መስሏችኋል?

“ኧረ ባክሽi እና እዴት ኖሯል በይ?”

“ለካንስ፣ በሩስያዉያን ባህል መሠረት አድናቆት የሚገለጸዉ ወይ ጉንጭን ግጥም አድርጎ በመሳም ወይ ደግሞ አንድ ሸክም አበባ በማስታቀፍ ኖሯል። በሱ ቤት እንግዲህ አድናቆቱን፣ መግለጹ ነዉ''

“በሩስያ ባህል?” አለ ባልቻ፣ እሱ ስለ ሩስያዊያን ከሚያዉቀዉ የተለየ ሆኖበት ባልቻ ሩስያን በደንብ እንደሚያዉቃት፣ የማዉቀዉ እኔ ብቻ ሳልሆን አልቀርም ሩስያዉያን በተዘዋዋሪ፣ የሩስያ መንግሥት ደግሞ
በቀጥታ የሲራክ ፯ ወደር የለሽ አጋር በመሆናቸዉ፣ ቋንቋቸዉን ሳይቀር አቀላጥፎ ይነጋገርበታል
“እርፍ!” አለች ዶክተር፣ አጠገቧ ያለዉ ሰዉ ባልቻ መሆኑን አሁን ገና ልብ አድርጋ እያየችዉ: “አንቺ” አለችኝ፣ ከንፈሯን ነክሳ ወደኔ
እያንሾካሾከች። “ይኼ ሰዉ ባልቻ ነዉ እንዳትዪኝ ብቻ!”

“አልተዋወቃችሁም እንዴ እስከ አሁን? ኋደኛዬን ሳትተዋወቅ ነዉ እንዴ እስከ አሁን የምታስለፈልፋት አባትዮዉ ?” አልሁት ባልቻን፣ ቀብረር ብዬ በመጽሐፍቱ የተነሳ፣ ከድሮም ጀምሮ ለባልቻ እጅግ ከፍ ያለ ከበሬታ እንዳላት ስለማዉቅ እና በእኔ የተነሳ ልትተዋወቀዉ መሆኑ ኩራት እንደ ለቀቀብኝ ግንባሬ ላይ እያሳየኋት፡

“ባልቻ እባላለሁ”

“ኧረ አዉቅሃለሁ: አንተን የማያዉቅ ሐበሻ ይኖራል ብለህ ነዉ? ያላወቅሁትስ በምን ተአምር የዉብርስት ቤተሰብ ሆነህ እንደ ተገኘህ ብቻ ነዉ'

“እሱስ ቢሆን ምኑ ይገርማል?”
“ይገርማል እንጂ! በእርግጥ ግቢ እያለንም ያንተ መጻሕፍት
አልፈዉን አያዉቁም: ያንጊዜ ለእነም ለዉብርስትም ያዉ ነበርህ
እኔም እሷም እናውቅህ የነበረዉ ወይ በቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ስታደርግ ነዉ፣ ያለበዚያም በጽሑፎችህ ብቻ ነበር። አሁን ግን የእሷ አስታማሚ ሆነህ ከመጣህ፣ በመሀሉ ያለፈኝ ሌላ ታሪክ አለ ማለትም አይደል?''

“የሥራ ባልደረባዬ ነዉ” አልኋት፣ ነገሩን በአጭር ያስቀረሁ መስሎኝ፡፡መቼስ አንቺ የማታዉቂዉ ሲራክ-፯ የሚባል የደኅንነት ማዕከል አለ፡
እኔና ባልቻ የተዋወቅነዉ እዚያ ነዉ አልላት ነገር። “የሥራ ባልደረባዬ ነዉ” አልኋት፣ በደፈናዉ:

“ሥራ?”

“አዎ፣ አብረን ነዉ የምንሠራዉ”
ተይ እንጂ ! ሌላዉ ቢቀር ትናትና እኮ፣ሥራ እንደ ሌለሽ ነበር
የነገርሽኝ። ታዲያ ዛሬ ደግሞ የሥራ ባልደረባነቱን ከየት አመጣሽዉ በይ? አንድ የደበቅሽኝ ነገርማ አለች። የሆነዉሆኖ፣ እንዲህ ገጽ ለገጽ ስላሁህ በጣም ደስ ብሎኛል። በሀገራችን ልዩ ሥፍራ ከምሰጣቸዉ
አሳቢዎች መካከል፣ አንተን የሚያህልልኝ የለም”

እግዜር ያክብርልኝ” አለ ባልቻ፣ በትክክለኛ ትሕትና

ባልቻን በአካል አገኘሁት? ላምን አልችልም: እኔ አላምንም” አለች፣
እንዳዲስ ጥርስ በጥርስ እየሆነች፡ ወደ እኔ እየዞረች፣ በዓይኖቿ ሳይቀር ተፍነከነከች እኔም ከባልቻ ጋር ባለን ቀረቤታ ተኩራራሁባት የዋዛ ሰዉ መስየሽ ኖሯል? በሚል ትከሻዬን ነቀነቅሁባት

ቀናችብኝ፡

“እኔ ምልሽ” አላት ባልቻ፣ እሷ ገና ተገርማ ሳትጠግብ፡፡

“አቤት”

“ዉብርስት የሩስያዉን አምባሳደር ሳይቀር ምን ብላ እንዳስደነቀችዉ እኮ አልነገር ሽንም: መቼስ እሷ አያልቅባት፣ ለመሆኑ ምን ብትልላችሁ ነዉ ያን ያህል?”

“አይ እሱን እንኳን… ”

“እባክሽ እባክሽ”

“ከራሷ አፍ ይሻላችኋል ብዬ ነዉ። ራሷ እያለች? እሺ ካለችስ፣ ከዚያ
ክራሯ ጋር በዚያ ድምፁዋ ለኔም ብትደግምልኝ ደስታዉን አልችለዉም::ደግሞ አለቃትም፣ ማርያም በሽልም ታዉጣልን ብቻ!” አለች፣ የሙቀት መጠኔን ለመገመት መዳፏን ግንባሬ
ላይ እያኖረችብኝ፡ “ቃል
አትገቢልንም ዉቤ?”
👍29
መልስ አልሰጠኋትም፡ በሽልም ስለመዉጣት ስታነሳ፣ ልጄ በሐሳቤ መጣችብኝና፣ የቅድሙ ናፍቆት እና ፍርሃቴ እንደገና መጣብኝ፡ የፊቴን መለዋወጥ አይተዉ ኖሯል፣ ሁላቸዉም ትንፋሻቸዉን ዉጠዉ ወዲያ
ወዲህ ተቁለጨለጩ።

“እስኪ…” አለች ዶክተር ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ ወደ በሩ እያመለከተቻቸዉ። “እስኪ አድ አፍታ ላስቸግራችሁ፣ ዉጪ ጠብቁ ያለ ምንም ጥያቄ ሁሉም ምሰስ እያሉ ሲወጡ፣ በክፍሉ እኔና እሷ ብቻ ቀረንበት....

ይቀጥላል
👍175
#ሳቤላ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

... ሚሲዝ ሔር እሳቷን አስነድዳ ወንበሯን አስጠጋችና አግሮቿን ከምድጃውጠርዝ ዘርግታ ስትሞቅ ባርባራ ግን አሁንም ሐሳቧ እንደ ተበተነ ልቧ እንደ ተሰቀለ ነበር " በመጨረሻ ከልብስ መስቀያው አንድ የሱፍ ያንገት ልብስ አውርዳ ከትከሻዋ ደረበችና ወጥታ ሔደች የግቢውን የአግር መንገድ ይዛ በቀጥታ ሔዳ ከብረቱ በር ስትደርስ ቆም ብላ ወደ ሕዝቡ ጐዳና ትመለከት ጀመር " ነገር ግን ያ ጐዳና በዚያ ሰዓትና ቦታ፡እንደ ሌላው ጊዜ ሕዝብ አልነበረበትም!ጸጥ ብሎ ነበር
የግንቦት መጀመሪያ ላይ ስለ ነበረ በጣም ቀዝቃዛ ይሁን እንጂ ጸጥ ያለ አስደሳች የጨረቃ ምሽት ነበር።

“ ከቶ መቸ....ይመለስ ይሆን ? አለች ባርባራ ከበሩ ተደግፋ ብቻዋን ስታወራ (እሱ የሌለበት ሕይወት ምን ሕይወት ነው ! አሁን በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ ምን ያህል ተጨነቅሁ ? እንደ ኮርኒሊያ አባባል ከሆነ ለአንድ ቀን ብቻ ነበር የሔደው " ለመሆኑ ወደዚያ ምን ጉዳይ ቢኖረው ነው የሔደው ?

የእግር ዳና ከጆሮዋ ጥልቅ አለ በዚያ ሰዓትና ቦታ ማንም መንገደኛ እንዲያያት አልፈለገችም ስለዚህ ወደ ኋላዋ ምልስ ብላ ከዛፎቹ ጥላ ሥር ተከለለች "
የኮቴው ድምፅ እየቀረበ ሲመጣ ከዚያ በፊት የምታውቀው አረጋጥ መሆኑን ለየችው ስሜቷ ተለዋወጠ ዐይኖቿ በሩ ጉንጮቿ ፍም መሰሉየደም ሥሮቿ
ከደስታዋ ብዛት ነዘሩ እንዳትታይ ተጠንቅቃ በበሩ ቁልቁል ስትመለከት አንድ ረጅም ሰውዬ ከወደ ዌስት ሊን ሲመጣ አየች " የኋሊት ሽሽት አለች እውነተኛ
ፍቅር ድንጉጥ ነው " የባርባራ ሔር ሌሎች ተስጥዎች ያፈቀደውን ቢባሉም ፍቅሯ
ግን ልባዊና ጥልቅ ነበር ከበሩ ሲደርስ ይገባል ብላ ስትጠብቀው ዐልፎ የሚሔድ ይመስል ወደ በሩ እንኳን ዞር ብሎ አላየም " ባርባራ ሐሞቷ ፍስስ አለ እንደገና
ወደበሩ ተጠግታ ፍዝዝ ብላ በጕጒት መመልከት ጀመረች።

በርግጥም ስለሷ ምንም ሳያስብ ወደሷ ዘወር ሳይል ዐልፎ ወደፊቱ ሲገሠግሥ ስታይ በዚያች ቅጽበት በመጣበት የስሜት ግፊት «አርኪባልድ» ብላ ጠራችው።
« ባርባራ ... ሌቦችና ሕገ ወጥ አዳኞች እንዳይቡ እየጠበቅሽ ነው እንዴ ? እንደምነሽ ? » አለ

«እንደምነህ?» አለችው በአንድ በኩል በሩን ከፍታ ይዛ ስታስገባው በሌላ በኩል ደግሞ ከሱ ጋር እጅ ለእጅ ስትጨባበጥ እየገነፈለ ያስጨነቃትን ስሜት ለማመቅ ከራሷ ጋር እየተናነቀች » « መቸ መጣህ ? » አለችው " « አሁን በሁለት ሰዓቱ ባቡር መድረሴ ነው " ላንዳፍታ ከቢሮ ገባሁና አሁን ደግሞ ሚስተር ቦሻምን ለአንድ ጉዳይ ስለምፈልገው ወደሱ እየሔድኩ ነው " በይ ስመለስ እገባ ይሆናል " አሁን ግን ቸኩያለሁ አመሰግናለሁ " »

አዬ አባባና ሚስተር ስፒርነርም ከዚያ ስለአሉ ' ከነሱ ጋር ቆይተው ወደዚህ ለመምጣት በጣም ይመሽብሃል “ እነሱ እንዶሆኑ ከአምስትና ከስድስት ሰዓት በፊት
አይላቀቁም " »

« እነሱ እዚያ ካሉስ ከሚስተር ቦሻም ጋር ያለኝ ጉዳይ የግል ስለሆነ ለነገ ማስተላለፌ ነው » የያዘችውን በር ተቀብሎ ዘጋውና ክንዷን በክንዱ ይዞ ወደቤት
አመሩ እሱ ይህን ያህል የሚቀርባትና የሚይዛት በምንም ስሜታዊ ግፊት ሳይሆን
ከልማዳዊው ትሕትና በመነሣት ማክበሩ ነበር ባርባራ ሔር ግን ክንዷን ከክንዱ አቆላልፋ ጐን ለጐን ሆነው እያነጋገራት ሲሔዱ ኤደን ገነት ውስጥ እንደ ገባች ሆና ሀይሰማት ነበር "

«ታዲያስ ባርባራ ... ... ... በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ እንዴት ሰነበታችሁ?
« መሔድህን ሳንሰማ ምን ነገር ነው ድንገት ብድግ አድርጎ የወሰደህ ? »
« ተናርሺው እኮ ባርባራ!...... ... አንድ ያልታሰበ የሥራ ጉዳይ ተፈጠረ ሔድኩ »
« ኮርኒሊያ ግን ለአንድ ቀን ብቻ መሔድን ነበር የነገረችኝ»

« አለችሽ እንዴ ? ለንደን ከደረስኰ በኋላ ብዙ የምፈጽማቸው ነገሮች
ገጠሙኝና ቆየሁ " ሚስዝ ሔር እንደምን ስነበቱ ? »

« እሷ ያው ናት እኔስ ግማሾቹ በሽታዎቿን በሐሳቧ የፈጠረቻቸው ይመስሉኛል " አሁን በግድ እየተነሣች ብትንቀሳቀስ ይሻላት ነበር " ምንድነው ከሱ ጠቅለህ የያዝከው ? »

« ሚሲዝ ሔርን እንጂ አንቺን ስለማይመለከት አትጠይቂኝ " »
« ለእማማ ያመጣህላት ነገር ነው ማለት ነው አርኪባልድ ? »

« አዎን ' አንድ ገጠሬ ለንደን ከደረሰ ለወዳጆቹ ምን ስጦታ ይዞላቸው እንደሚመለስ ነው የሚያስበው " የጥንት ወጉ ይኸ ነበር " »

« እና አሁን በርግጥ ለእማማ ያመጣህላት ነው? »

« ምነው እየነገርኩሽ …. ባርባራ ላንቺም እንድ ነገር አምጥቼልሻለሁ»

« ምን አመጣልኝ ? » አለችው ፊቷ እንዳመሉ እየቀላ ቀልዱን ይሁን እውነቱን እስክታውቅ ድረስ ሐሳቧ በጕጒት እየተንጓለለ "

« ቀስ በይ እኮ አትቸኩይ !ምን እንደሆነማ ልታይው አይደል » አላትና የያዘውን ጥቅል አጠገባቸው ከነበረ ከአንድ ያትክልት ቦታ ወንበር ላይ አስቀመጠና ኪሶቹን ሁሉ ቢዳብስ አጣ "

« ባርባራ ... ካንዱ ሳልጥለው ቀረሁ ብለሽ ? » አለና እንደገና
ኪሶቹን ሁሉ ፈለገ አራገፈ " በመጨረሻ አንድ ያልታሰበ ኪስ ውስጥ አንድ ነገር ጐረበጠው
«አይ እዚህ አለ መሰለኝ ። ግን እዚህ ምን አመጣው ? » አለና አንዲት ትንሽ ሣጥን አውጥቶ በመክፈት ከውስጧ አንድ ረጂም የወርቅ ሐብል አንሥቶ ባንገቷ አጠለቀላት ከሐብሉ ጋር ባንድ በኰል ጌጥ በሌላ በኩል የጥቃቅን መታስቢያዎች ለመያዣ የሚያገለግል ትንሽ የወርቅ ሙዳይ ተያይዞ ነበር ።

ልቧ በኃይል ሲመታ የፊቷ ቅላት እንደ ልቧ አመታት ቦግ እልም ይል ጀመር አንዲት የምስጋና ቃል እንኳን መተንፈስ አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ያኖረውን ጥቅል አንሥቶ ወደ ሚስዝ ሔር ዘንድ ገባ። ሻማ ባይያያዝም በክፍሉ ሲነድ የነበረው እሳት ቦግ ብሎ በርቶ ነበርዠ።

« መቸም እንዳይሥቁብኝ» አለ ያመጣውን ጥቅል እየፈታ እስከዚህም የረባ ስጦታ አይደለም ብቻ ብዙ ጊዜ ሲመኙት እሰማ ስለ ነበር ከአንድ ሱቅ መስኮት ላይ አይቼ በአየር የሚሞላ መከዳ ነው ያመጣሁለዎ » ብሎ ሰጣት » በመጋደምና በመቀመጥ ሰውነቷ ያለቀው ሚሲዝ ሔር እንደዚያ ያለ ዕቃ ለንደን እንደሚገኝ
ከመስማቷ በቀር ከነማየቷም አታስታውሰውም እንደ ጓጓች ተቀበለችውና በምስጋና ትክ ብላ ተመለከተችው "

« አንዴት ብዬ ነው የማመሰግንህ? » አለችው የደስታ ዕንባ እየተናነቃት
« አስበህ ስለ አመጣሀልኝ አመሰግንሃለሁ»

« አሁን ለባርባራ ስነግራት ነበር " ወደ ለንደን ከሔድን ለወዳጆቻችን ምን ይዘን መመለስ እንደሚገባን ማሰብ እንጀምራለን ባርባራንስ እንዴት እንዳሳመርኳት አዩዋት አይደል ? » አላት ሚስተር ካርላይል "

ባርባራ ሐብሉን ካንገቷ ቶሎ አወለቀችና ከናቷ ፊት አኖረችው "
«አቤት እንዴት ያምራል ልጄ!መቸም ለዚህ ያወጣኸው ገንዘብ ልክ አይኖረውም»

« ኧረ እሱስ ጥቂት ነው ፍሬም የለው» አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሳቅ ብሎ " « እንዴት እንደገዛሁት ላጫውታችሁ የጅ ስዓቴ ማሰሪያ እየተፊታ አስ
ቸገረኝና ወደ አንድ ወርቅ ሠሪ ዘንድ ጎራ ብዬ ነበር በዚያ ብዙ አይነት ሐብሎች ተሰቅለው ሳይ ኮርነሊያና ባርባራ አብረውኝወደ ሊንቦራ ሔደው በነበረ ጊዜ ባርባራ የጠፋባትን ሐብል አስታወሱኝ " ስለዚህ ለባርባራ አንገት የሚስማማውን መርጬ
👍23
ገዛሁ ባለሱቁ ደግሞ ከሐብሉ ጋር ሊያያዙ የሚችሉ የተለዩ ዘመድም ሆነ የፍ ቅረኛ ጸጉር በማስታወሻነት የሚይዙ ትንንሽ የወርቅ ሙዳዮችን አሳየኝ እኔም
ከሁሉ አብልጠሽ የምትወጂውን ሰው አንዲት ዘለላ ጸጉር ታስቀምጭበት ይሆናል
ብዬ አንዱን መርጩ ከሐብሉ ጋር እንዲያያይዝልኝ ነገኩት»

« የምን ጸጉር ? » አለች ሚሲስ ሔር "

ሚስተር ካርላይል ግድግዳዎቹም እንዳይሰሙት የፈራቸው ይመስል ዙሪያውን ካስተዋለ በኋላ ቀስ ብሎ «የሪቻርድ » አላት « አንድ ቀን ጠረጴዛዋን ስታስናዳ ሪቻርድ ታሞ የነበረ ጊዜ የተቆረጠ ነው ብላ ጸጉር አሳይታኝ ነበር »
ሚስዝ ሔር ከወንበሯ እንዶ ተቀመጠች ቁልቁል የሰጠመች መሰለች: እጥፍጥፍ አለችና ፊቷን በእጆቿ መኻል ደፍታ ንዳድ እንዶ ያዘው ተንቀጠቀጠች የሚስተር ካርላይል ቃሎች ለአንድ ከባድ ኀዘን ምክንያት የሆነ ትዝታ ቀስቀሰባት «ወይ ልጄ !ልጄ ! ያልታደልከው ልጄ ! ሚስተር ሔር ስለኔ በሽታ ይገርማል "
አየህ አርኪባልድ ..... ባርባራም ትቀልድብኛለች " ግን ይህ ሁሉ የአካልና የመንፈስ ጭንቀት የሚደርስብኝና የምሰቃየው በልጄ ምክንያት ነው ። ልጄ ሪቻርድ ልጄ ! » እያለች ትንሰቀሰቅ ጀመር

ይነጋገሩበት የነበረው ርዕስ ለምትጨነቀው እናት ተስፋም
ማጽናኛም የሚሰጥ ሳይሆን የተለየ ስለነበር ሁሉም ለጊዜው ትንሽ ጸጥ ብለው ቆዩ » « ባርባራ
ሐብልሺን አጥልቂው » አላትና ሚስተር ካርላይል ጥቂት ቆይቶ « ባንገትሽ አስረሽ ትጠግቢው ዘንድ ጤንነትን እመኝልሻለሁ ። ጤንነትና የመንፈስ ተሐድሶ ላንቺ ይሁኑ ቆንጂት »

ባርባራ የሚያምሩት ዐይኖቿን እያንከባለለች ፈገግ ብላ በሰመመን ዐይን 0ይኑን እያየች ለኮርነሊያስ ምን አመጣህላት ? » አለችው « አንድ ጥሩ ያንገት ልበስ አመጣሁላት ሻጩ እውነተኛ የፋርስ ሱፍ መሆኑን ነግሮኛል " እኔም ተራው ያገራችን የማንቸስተር ሥራ እንደማይሆን አምኜ ገዛሁት " »

« ያግር ውስጥም ቢሆን እኮ ኮርነሊያ ልዩነቱን አታውቀውም » አለችሙ ባርባራ "

« እኔ እንጃ በበኩሌ ግን የውጭ አገር ሸቀጥ ካገራችን የሚበልጥበት ምክንያት አይገባኝም " እኔ ያንገት ልብስ የምለብስ ብሆን ምርጥ ከተባለው የፈረንሳይ ሥራ ይልቅ ከራሳችን ፋብሪካዎች የተሠሩትን እመርጥ ነበር » አላት ሚስተር ካርላይል "

ሚስዝ ሔር እጆቿን ከጠወለገው ፊቷ አንሥታ ቀና አለችና«ለመሆኑ ያንገት ልብሱስ ምን ያህል ዋጋ ወሰደ? » አለችው "

« ብነግርዎ ለኮርነሊያ እንደማይነግሯት ቃል እንዲገቡልኝ እፈልጋለሁ ያወቀችው እንዴሆነ ገንዘቡን በከንቱ እንደ ጣልኩት ቆጥራ እኔንም ቁም ስቅሌን
ታሳኛለች " ልብሱንም ጠቅልላ ከሳጥን ከታ ሁሌተኛ አትነካውም " ዐሥራ ስምንት ፓውንድ ነው የከፈልኩበት " »

« አቤት ! ብዙ ነው ። በጣም ጥሩ ዕቃ መሆን አለበት እኔ ግን እስከ ዛሬ ላንገት ልብስ ከስድስት ፓውንድ በላይ ከፍዬ አላውቅም » አለች ሚስዝ ሔር ።

« ኮርነሊያ ደግሞ » አለ ሚስተር ካርላይል እየሣቀ « ከሦስት ፓውንድ በላይ ከፍላ አታውቅም " በሉ ደኅና አምሹ ከውጭ ከለንደን ተመልሼ ከቤት ሳልገባ
ይህን ያህል እዚህ መቆየቴን ካወቀች ትወርድብኛላች » አለና የእጅ ሰላምታ ሰጥቷቸው ሲወጣ ባርባራ ልትሸኘው ተከተለችው

« ብርድ እንዳይመታሽ "ባርባራ " ያንገት ልብስሽን እንኳን አልዶረ
ብሽም " »

« አይነካኝም " ግን እንዴት ቸኮልክ ዐሥር ደቂቃ እንኳን አልቆየህም»

« ከመጣሁ ከቤት አለመድረሴን ረስተሽዋል መሰለኝ»

« ወደ ቦሻም ቤት ልትሔድ አልነበረም ? ሒደህ ቢሆን ኖሮ እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ አትመለስም ነበር ። »

« ይህ ሌላ ነገር ነው " ለሥራ ጉዳይ ከሆነ እኮ ኮርነሊያም ደስ ይላታል እንጂ አይከፋትም ። በሥራ ጉዳይ ባልሆነ ካጠገቧ ከጠፋሁ ግን መሬት አይበቃትም
አሁን እንኳን ስለ ለንደን አምስት መቶ ጥያቄ በምላሷ ጫፍ ይዛ እንዶምትጠብቀኝ አትጠራጠሪ » በነገራችን ላይ ባርባራ …….….. እናትሽ ያመማቸው ይመስላሉ »

« እሷ በትንሹ ነገር ሁሌ ራሷን እንደምትበጠብጥ ታውቃለህ። ትናንት ሌሊት ደግሞ አንድ ሕልም አየሁ ብላ እንደ ተመለከትካት እስካሁን ትንቀጠቀጣለች
እሷ እንደምትለው ሕልም አንድ መጥፎ ነገር ሊደርስ ሲል የሚታይ ማስጠንቀቂያ ነው" ስለዚህ የሚሆን ነገር አለ እያለች በሐሳብ ስትወዘወዝ ትኩሳቷ ሁሉ ተነሥቶ
እንደ ነደዶች ዋለች " ለአባባ ደግሞ ስለ ሕልሙ ደፍሮ የነገረው የለም » ሰውነቷ እንደዚህ ሆኖ የመነመነው ተጨብጣ ስለምትውል ስለሆነ ለምን አትንቀሳቀስም እያለ ይቆጣል »

« ስለ ሕልሙ ያልነገራችኋቸው ሕልሙ ስለ....»

ሚስተር ካርላይል ነገሩን አቋርጦ ዝም አለ አሁን እንደ በፊቱ ክንዱን አልሰጣትም " ባርባራ ዙሪያዋን አስተውላ ወደሱ ጠጋ አለችና «አዎን ስለ ግድያው ስለሆነ ነው " እማማ በግድያው ወንጀል ቤተልም አለበት እያለች እንደምትለፈልፍ ታውቃለህ » ለዚህ ሌላ መረጃ ባታገኝ እንኳን ሕልሟ እንዳረጋገጠላት ታምናለች "ሁልጊዜ በሕልሟ
ገባህ ? ከ....ጋር በሕልሟ እንደምታየው ትናገራለች " »

« ከሃሊዮን ? » አለ ሚስተር ካርላይል

« ከሃሊዮን ጋር » ብላ አረጋገጠችለት ባርባራ አየተንቀጠቀጠች « ሃሊዮን
ከወለሉ እንደ ተዘረረ ቤተል ከላዩ ላይ ቆሞ ታይቷታል ያቺ አፊ ደግሞ ከማድ ቤት አጠገብ ቆማ ስትመለከት ትታያታለች " »

« እሳቸው እኮ ሕልም ሰላም እንዲነሣቸው ማድረግ አይገባቸውም ቁመውም
ተቀምጠውም ስለ ግድያው ስለሚያስቡ ስለሱ ሕልም ቢያዩ አያስግርምም " ነገር ግን የሕልሙ ሐሳብ ከሌሊቱ ጋር ለቋቸው እንዲሔድ መጣር አለባቸው "

« አዬ አንተ........... የእማማን ነገር እያወቅኸው " በርግጥ እንደሱ ማድረግ ነበረባት " ነገር
ግን አልቻለችም አባባም ጧት ጧት ብሶባት ሲያይ ለምን እንደ
ሆነ እየገረመው ሲጠይቃት የማትሰጠው ምክንያት የላትም ምክንያቱም ስለ ግድያው ምንም ነገር ለሱ መተንፈስ አይቻልም »

ሚስተር ካርላይል እያዘነ ራሱን ነቀነቀ።

« እማማ ቤተልን ነው እየደጋገመች በሕልሟ የምታየው ትናንትና በበሩ ሲያልፍ አየችው " ሌሊት በሕልሟ መጣባት " እሷ የምትለው ቤተል ገደለው ሳይሆን የሱም እጅ በነገሩ አለበት ነው እና ሁልጊዜ በሕልሟ ይመጣል "

ካርላይል 'ምንም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ" የሚመልሰውም አልነበረውም ከሚስቴር ሔር ቤት እንዲህ ያለ ዳመና ማንዣበቡ አሳዛኝ ነገር ነበር ባርባራ ንግግሯን ቀጠለች "

« እማማ ይህን ሕልም ስለ አየች የሚደርስ ክፉ ነገር አለ እያለች ራሷን ይህን ያህል ማስጨነቋ ትልቅ የዋሀነት ነው » እኔ ቢቸግረኝ አኩርፊያት ዋልኩ አየህ
አርኪባልድ ባሁኑ በሥልጣኔ ዘመን ሕልሞች ወዶፊት ስለሚሆነው ነገር ይናገራሉ ብሎ ማመን ሞኝነት ነው »

« የናትሽ ችግር ከባድ ነው ሰውነታቸውም እየደከመ ሔደ» አላትና ስለዚሁ እየተወያዩ ከበር ደርሰው ሚስተር ካርላይል ሊወጣ ሲል ክንዱን ያዝ አድርጋ በማቆም ድምጿን ልስልስ አድርጋ : « አርኪባልድ ......... » አለችው

« ምነው ? »

« ለዚህ እኮ ምስጋና እንኳን አላቀረብኩልህም » አለችው ሐብሉን ከነሙዳዩ እያሳየችው «ምስጋና ቢስ አድርገህ እንዳትገምተኝ »

« ኤዲያ ለዚህ ደግሞ ምን ምስጋና ያስፈልጋል ? በይ ይልቅ ደኅና እደሪ » አለና ጐንበስ ብሎ ጉንጯን ስሞ ሲያበቃ ዞር ብሎ አይቷት ለሁለተኛ ጊዜ ደኅና
እደሪ ብሏት ሔደ
👍17🥰2😁1