አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ሲልቪ
ውስጥ ውስጡን


በነጋታው ጧት የመኝታዬ በር በኃይል ሲንኳኳ ነቃሁ፡፡ ማነህ
ሳልል በሩን ከፈትኩ። ሲልቪ እየሳቀች ዘላ ተጠመጠመችብኝ፡፡
ተንገዳግደን አልጋዬ ላይ ወደቅን። የፀጉሯ ሽታ ደስ አለኝ
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«ፈተናዬን በማእረግ አለፍኩ። ተነስ እንሂድ»
«የት? »
«ፓሪስ። ቀጥሎ ጄኖቫ፣ ከዚያ ሮማ፣ ናፖሊ፣ ፊሬንዜ፣
ከዚያ ኒስ፣ ማርሰይ፣ ኤክስ፡፡ ፕላኑን በሙሉ አውጥቻለሁ፡፡ «ጎበዝ አደለሁም?»
«ጎበዝ ነሽ፡፡ መቼ ነው «ምንሄደው?»
«አሁኑኑ፡፡ ተነስ ተጣጠብ» አለችኝ፣ ሰሰፊ ኣፏ እየሳቀች
«ለባለሆቴሉ 'ምከፍለው ገንዘብ አልያዝኩማ»
«እኔ ይዣለሁ»
«በምንድነው የምንሄደው?»
«በባቡር። ባቡራችን ልክ ከዘጠና ሁለት ደቂቃ በኋላ ከማርሰይ
ይነሳል፡፡ ቶሎ በል»
እንደዚህ አጣድፋ፣ ማንንም ለመሰናበት ሳልችል ፓሪስ
ወሰደችኝ። ከሁሉ ቅር ያሰኘኝ አማንዳ ዱቤን ሳልሰናበት መሄዴ
ነበር በሚቀጥለው አስር ሳምንት
ውስጥ ስለባህራም በብዙም
አላሰብኩም፡፡ ስለ ምንም ነገር በብዙ አላሰብኩም፡፡ ሀሳቤን ሲልቪ ሞልታው ነበር

ባቡሩ ሞልቶ ቆይቶን አንድ ላይ ቦታ ለማግኘት ባለመቻላችን
ፊት ለፊቴ ተቀመጠች። ሁለታችንም መፅሀፍ ማንበብ ጀመርን።ትንሽ አነብና ሰርቄ አያታለሁ፡፡ ረዥም ፀጉሯ ውብ ነጭ ፈቷን እንደ ጥቁር ሀር ከቦታል። በጣም ቆንጆ ናት፣ የደስ ደስ አላት አንዳንድ ጊዜ ሳያት ትይዘኛለች። ትጠቅሰኝና ሳቅ ትላለች፡፡ መልሼ እጠቅሳታለሁ፡፡ ንባባችንን እንቀጥላለን። አልፎ አልፎ አንድ ያልገባኝን ቃል እጠይቃታለሁ:: ፈረንሳዮቹ
ብርቱካን ይበላሉ፣ ያወራሉ፣ ፖም ይበላሉ፣ ጋዜጣ ያነባሉ፣ ሳንድዊች ይበሳሉ፣ ወይን
ይጠጣሉ፣ ባቡሩን ያዝረከርኩታል፣ ያቆሽሹታል፣ ዝነኛውን «የፈረንሳይ ባቡር ግማት» ይሰጡታል

አቪኞን ስንደርስ አንዲት ኣሮጊት ከአጠገቤ ተነሳችና፣ ገና
ከመነሳቷ ቦታዋ ላይ እንድ ሰውዬ ተቀመጠ። ከኣቪኞን እንደወጣን
የሲልቪ አይኖች ደጋግመው እዚህ ሰውዬ ላይ ያርፉ ጀመር።
ሰውዬውን አየሁት። ፀጉሩ ላይ ነጭ ዘርቶበታል፣ ምናልባት ያርባ
አምስት አመት ሰው ይሆናል። አይኖቹ ንፁህ ሰማያዊ ሆነው፣
ቀጠን ያለ ፊቱ በጣም ቆንጆ ነው:: ሳየው ጠላሁት። ንባቤን ቀጠልኩ፣ ግን የማነበው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ስርቄ ሲልቪን አየኋት።
ሰውዬውን በሰማያዊ እይኖቿ ብርህን ታየዋለች። እሷ እሱን ስታይ፣እኔ እሷን ሳይ፣ ንዴቱ ውስጤ ሲጠራቀም፣ ብዙ ጊዜ ሄድን ሳያት ያዘችኝ። አይኖቿ ተርገበገቡ፣ ወደ ታች አየች፣ ጉንጮቿ ደም ለበሱ፡፡ ማማሯ የንዴቴን ጥቁር ደመና የፍትወት ብልጭታ ሲሰነጣጥቀው ተሰማኝ። «ድንገት ሳብ ኣድርጌ ቀሚሷን ገልቤ ጭኖቿን ፈልቅቄ..

በመስኮቱ ወደ ውጭ ማየት ጀመርኩ፡፡ ለጥ ያለ ሜዳ መሬት
ረዥም ቀጭን የቤተ ክርስቲያን ደወል ቤት ሰማዩን እንደ መርፌ
ወግቶታል፤ አንድ ቀጭን መንገድ ከሹሉ ደወል ቤት ስር ወጥቶ
እየተጠማዘዘ ሄዶ አድማሱ ውስጥ ገብቷል፣ ሰማይና ምድር
የተሰፉበት ክር ይመስላል፡፡ መንደሩ እንደ ልጅነት ቀስ እያለ ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ጠፋ
ዘወር ብዬ ሲልቪን አየኋት። ራሷን ወደ መፅሀፉ ደፍታለች፣
ፈቷ ደም እንደለበሰ ነው:: መፅሀፌን ማንበብ ጀመርኩ። አሁንም ቃላቱ አይኔን ዘልቆ እንጉሴ ውስጥ መግባት አቅቶት፣ አይኔ ብቻውን ያነባል። ሲልቪን አየኋት። አየችኝና ፈገግ አለች:: ሰማያዊ አይኖቿ ሳቂታ ናቸው፡ በጣም ቆንጆ ፈገግታ ኣሳየችው። እናቷን!

ንባቤን ቀጠልኩ። ከዚያ በኋላ እንደገና ደጋግማ ስታየው
አየኋት። አንድ ሶስት ጊዜ ያህል፣ ስታየው እንዳየኋት አይታ በጣም
አፈረች፥ አይኖቿ ተርገበገቡ፣ ጉንጮቿ ቀሉ፤ ንዴቴና ምኞቴ
ውስጤ እየታገለ አስጨነቁኝ
ሶስት ሰእት ያህል አለፈ

ከሊዮን በኋላ አንድ ሁለት ትንንሽ ከተማ እንዳለፍን ሰውየው
እግሮቹን የሚዘረጋ አስመስሎ የሲልቪን እግር ነካ፡፡ ቀና ብላ በውብ አይኖቿ በፈገግታ አየችው፡፡ በሰፊ እፏም ሳቅ አለችለት፡፡ ሰውዬው
በእግሩ እግሯን ማሻሸት ጀመረ። ቀላች። ውስጤ ስጋዊ ፍትወትና
ንዴት ታገለ፣ ንዴቱ አሸነፈ። እግሬን የምዘረጋ አስመስዬ የሰውዬውን ቅልጥም በኃይል መታሁትና፣ ዘወር ብዬ እያፈጠጥኩ

Pardon, monsieur» አልኩት (ይቅርታ መስዬ»)

ve vous en pries አለኝ («ኧረ ግድ የለም )

እግሩን ሰበሰበ። ፊቱ በንዴት ይሁን በእፍረት ደም ለብሷል።
ሲልቪን አየኋት። መፅሀፏን ታያለች፣ ፈገግታ ብጤ አፏ ዙሪያ
ይርበተበታል። ሰውየው የሲጋራ ፓኮ ከኪሱ አውጥቶ ወደ ሲልቪ
ዘረጋ፣ እየሳቀች ተቅበለችው:: አቀጣጠለላት ወደ ፓሪስ ነው : ሚሄዱት?» አለችው
«አዎን ማድሟዜል። እርስዎስ?» አላት ወሬ ጀመሩ። ብሽቅ አልኩ። ተነስቼ ትቻቸው ወጣሁ
መተላለፊያው ዘንድ አልፎ አልፎ የቆሙትን ፈረንሳዮች
እየገጨሁ Pardon! እያልኩ፣ አንድ አስር ሰረገላዎች እቋርጬ
ሂጂ ባቡሩ መጨረሻ ደረስኩ
ስመለስ ግማሽ መንገድ ላይ ቆምኩ። እቺ ንፍጣም!

ልታሰቃናኝ ፈልጋ አይደለም? እንደማልቀና ማወቅ አለባት። ግማሽ ሰአት እስኪያልፍ ወደሷ አልመለስም፡፡ ምን ያህል ግድ እንደሌለኝ ይግባት . .»

ግማሽ ሰአት እንዴት ረዥም ነው! ሰአቴን አስር ጊዜ አየኋት::
እሷ ታድያ አትንቀሳቀስም። አምስት ደቂቃ እንኳ ገና አላለፈም። ወደ ጆሮዬ አስጠጋኋት። ተኝታለች። የለም የለም፡ የባቡሩ ጩኸት
ድምፅዋን አላሰማ ስላለኝ ነው። . . . እኔና ሰአቷ ስንተያይ ሩብ ሰአት አለፈ። ከዚያ በኋላ ግን መቆየት አልቻልኩም፡፡ ሰዎቹን
እየገጨሁ «Partdom!» እያልኩ ወደነዚያ ውሾች መመለስ እንደ
ጀመርኩ፣ በመስኮቶቹ በኩል ቤቶች ብቅ እያሱ ወደኋላ ሽው ብለው ሲያልፉ ይታዩኝ ጀመር። አንድ ትንሽ ከተማ ደርሰናል፡፡ ባቡሩ በቆመልኝ! ማቆያ እንዲሆነኝ ጋዜጣ እገዛ ነበር. ጎሽ! ባቡሩ ቆመ፡፡ ወረድ ስል አንድ መለዮ የለበሰ የባቡሩ ኩባንያ ሰራተኛ አመስዬ፣ አይውረዱ፣ ሁለት ደቂቃ ብቻ ነው ያለን» አለኝ
«Je mn fous!» አልኩትና ወረድኩ («ደንታ የለኝም!»)
አንድ Le Monde ጋዜጣና ሁለት ሳንድዊች ገዝቼ እስክመለስ
ባቡሩ ተነሳ። ሮጬ ለትንሽ ደረስኩበት::
ጋዜጣውን ኣንብቤ ሳልጨርስ ወደሷ አልመለስም፡፡ ሳገኛት ደሞ ሳንድዊች እሰጣታለሁ፡፡
እየሳቅኩ። ጭራሽ አለመቅናቴ እንዲገባት የክሩስቼቭና የኬነዲ የቤንቤላ ስም አለ፤ የቪየትናም ሁከት ተጠቅሷል፣ ግን በደምብ አልገባኝም፡ የሲልቪ ፈገግታ፣ ለሌላ ያሰራችው ፈገግታ አንጎሌን በጥብጦታል። የሆነ ሆኖ፣ ያልኩት ግማሽ ሰአት አለፈልኝ። ኧረ ሰላሳ ሶስት ደቂቃ ነው ያለፈው! እኔ የሰውዬው ልጅ! ... ወደኛ ሰረገላ አመራሁ ሲልቪ የለችም። ሰውዬውም የለም፡፡
የታባታቸውን ሄዱ? እንደገና ፈረንሳዮቹን እየገጨሁ «Pardon!»
እያልኩ አንድ አምስት ሰረገላ ካቋረጥኩ በኋላ፣ ራሴን «የት ነው
ምትሄደው?» አልኩት፡፡

ቆምኩ «በቁላህ ሳይሆን በጭንቅላትህ አስብ» የሚል ሀሳብ ውስጡን አሳቀኝ። ለመሆኑ፣ ባገኛቸውስ ምን ላደርጋቸው ኖሯል ብዬ አሰብኩ። ተመልሼ ቦታዬ ቁጭ ብዬ ልጠብቃቸው ቆረጥኩ፡፡
👍20
«እቺ ውሻ ከኤክስ አጣድፋ ያመጣችኝ ለዚህ ኖሯል? “ማን
መስያታለሁ'? ፈረንሳይ መስያታለሁ? አበሻ መሆኔን ማን በነገራት!ቆይ አሳያታለሁ ግን አልቸኩል። ዝግ ብዬ ረጋ ብዬ ሳስብ።እንደ ልጅ መጮህ መፍጨርጨር አያስፈልግም
እሷ አሁን አስቀናሁት ብላለች። እስቲ ማን ማንን እንደሚያስቀና እናያለን፡፡እቺ ቅሌታም ፈረንሳይ! ዋናው ነገር፣ እሁን እንዳልቀናሁ
ማሳየት ነው። ስትመጣ ልክ አንደ ድሮ አናግራታለሁ። ልክ
ባለሽበቱን ሰውዬ እንዳላየሁት መሆን አለብኝ፡፡ሌላ ቀን ታድያ፣ ከሁለት ወይ ሶስት ሳምንት በኋላ፣ መኖር እስኪያስጠላት
ድረስ አስቀናታለሁ። ያኔ እናያለን

እንዲህ የበቀል ሀሳብ እያሰላሰልኩ ወደ ቦታዬ በኩል ስራመድ፤መመላለሻው ዘንድ እያጨሱ፤ እያወሩ ወይም ፈዘው በመስኮቶቹ በኩል ወደ ውጭ እየተመለከቱ ከቆሙት ሰዎች አንዱ ከሩቅ ስመጣ
ጀምሮ ያየኛል ፀጉሩ ሳይ ሽብት ዘርቶበታል፤ ፊቱ ቀጭን ቆንጆ ብጤ ነው::አይኑ ሰማያዊ ባይሆንም ሽበቱና የቆንጆ ፊቱ መቅጠን አበሽቀኝ፡፡አጠገቡ እስክደርስ በብሩህ ቡናማ አይኖቹ ያየኛል። እየገላመጥኩት

«ምነው ያዩኛል?» አልኩት። እንደ መደንገጥ ብሎ

«ምንም መስየ» አለ

ፀጉርዎ አስር ጊዜ ሽበት ሲኖረው je men fous!» አልኩት።
(ደንታ የለኝም»)

ስለምን እንደማወራ አልገባውም፣ ግን ፈርቷል። ዝም አለ፡፡ሰውዬው ምንም እንዳልበደለኝና አሁን የማወርድበት ቁጣ ፈጽሞ
የማይገባ ጭቦ እንደሆነ ይሰማኛል፤ ግን ራሴን ለመግታት
አልቻልኩም፡፡ መልኩንና እድሜውን እያየሁ በንዴት ተቃጠልኩ

በሉ እንጂ ይንገሩኝ፡፡ ለምን ያፈጡብኛል? ሰው ሳንድዊች ይዞ
ሲሄድ አይተው አያውቁም? ወይስ ርቦዎታል? እንኩ ብሉት!»
አልኩና የያዝኩትን ሳንድዊች በድንገት አስጨብጨው ወደ ቦታዬ በኩል በንዴት ስራመድ፣ መተላለፊያው ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ በፀጥታ እኔን እንደሚመለከቱ ድንገት ታየኝ፡፡ ንዴቴ ወደ እፍረት ተለወጠ፤ ሽበታሙ ሰውዬ በጣም አሳዘነኝ፡፡ ይኸኔ'ኮ ወጣት ቢሆን
አይታገሰኝም ነበር፡ አሁን ወጣትነቱን በሀዘንና በናፍቆት ያስታውስ ይሆን? እረ ምን በደለኝና ነው ያዋረድኩት? መባለጌ በጣም ቆጫኝ፡፡ ቀኝ ኋላ ዞሬ ወደሱ ተራመድኩ። ሳንዲውቾቹ የተጠቀለሉበትን ወረቀት በሁለት እጁ እንደጨበጠ ይመለከተኛል። ፊቱ ላይ የመደናገር እንጂ የንዴት ስሜት አይታይም

መስዬ፡ እባክዎን ይቅርታ ያድርጉልኝ፡፡ ጤና አልያዘኝም
አልኩት። ታችኛ ከንፈሬ ሲንቀጠቀጥ ተሰማኝ ግን መንቀጥቀጡን አስተወው አልቻልኩም፡፡ ሲጨንቀኝ ጊዜ አፌን በእጄ ያዝኩት ረጋ ባለ ድምፅ “Ca ya jeune bornime. Yy perisons plus"
አለኝ። («ግድ የለም ጎበዝ። እንርሳው») “Merci, mossieur” ብዬው
ብሄድ ጥሩ ነበር፡፡ ግን አሁንም ራሲን ለመግታት ኣልቻልኩም፡፡
ሳልወድ በግድ ለፈለፍኩ
«ጤና ስላልያዘኝ ነው እንጂ ከገሬ ብሆን፣ እንኳን እኔው ራሴ ሽበት ያለው ሰው ልሰድብ፣ ማንም ወጣት እንዲህ ሲያደርግ ባየው
እጣላዋለሁ» አልኩት

«አውቃለሁ አለኝ»

«ያውቃሉ?»

የናንተን አገሮች ባህል በደምብ አውቀዋለሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ
ውስጥ የአንትሮፖሎጂ ፕሮፌሰር ነኝ፡፡ ደሞ፣ ካደጉበት አገር ወጥቶ
አንግዳ አገር ሄዶ፣ ባእድ ህዝብና ባይተዋር ባህል ሲያጋጥም፣
በመጠኑ ግር እንደሚል አውቃለሁ።ደጋግሜ ካገሬ ወጥቼ
አይቼዋለሁ። ስለዚህ አሁን እኔን ይቅርታ መጠየቅ በጭራሽ
አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይልቅ ቡና ልጋብዝዎትና ትንሽ እንጫወት-
ብሉ ቡና ወደሚጠጣበት ሰረገላ ወሰደኝ ሰውዬው ሊቅ ከመሆኑም በላይ ብልህና ደግ ነበር። ኮኛክ እየጠጣን ሳንድዊቾቹን በላናቸው
«ከኮኛክ ጋር እንኳ ሳንድዊች አይበላም፡ ብቻ ግድ የለም አሉ
ሰውዬው እየሳቀ:: ብዙ ብዙ ወሬ አወራን፡፡ በተለይም ስለአልጄሪያ
ጦርነት በሰፈው ነገረኝ፡፡ ጀኔራል ደጐል ባይኖር ኖሮ፣ ይህን ጊዜ
ፈረንሳዮች በአልጄሪያው ሁከት ምክንያት እርስ በራሳቸው
ተከፋፍለው ተዋግተው ትፋጅተው፣ ፍራንስ ራሷ ገደል ገብታ ነበር፤ አለኝ፡፡ እስከ ፓሪሰ እያወራን ብንሄድ ደስታዬ ነበር። ግን ፕሮፌሰሩ ዲዦን ወራጅ ነበር

ሲለየኝ፣ መውረጃው በር አጠገብ እንደቆምን፣ ሳላስበው እጆቹን
ትከሻዬ ላይ አሳረፈና፣ ደግነት በተሞሉ የአዋቂ አይኖቹ እያየኝ፣
አንቱ ማለቱን ትቶ ለመጀመሪያ ጊዜ አንተ እያለኝ

“ይገርማል፡ ጠቆርክ እንጂ ልክ የመጀመሪያ ልጄን ነው የምትመስለው፡፡ እንግዲህ ልጄ ትዝ ባለኝ ቁጥር አስታውስሀለሁ። ትናፍቀኛለክ Enfin, c'est la vie. Au revoire, jeune homme" (ይህ ነው የኑሮ ነገር፡ በል ደህና ሁን፣ ጐበዝ) አለና፡ ፈረንሳዮቹ የሚወዱትን ሰው ሲሰናበቱ አንደሚስሙት ጉንጭና ጉንጬን ሳመኝ። በእጁ ራቅ አድርጎ በናፍቆት አይን አየኝ። ፀጉሬን በእጁ በተን በተን አድርጎ፣ እንደገና ሳብ አድርጉ በኃይል እቅፍ አደረገኝና፣ ከባቡሩ ወረደ። ሻንጣውን ሳቀብለው፣ አይኑ ውስጥ እንባ አየሁ

ባቡሩ ቀስ ብሎ ተነሳ፡፡ «ልጄ ትዝ ባለኝ ቁጥር» እንዳለኝ አስታወስኩ

ከባቡሩ በላይ ጮኬ
ልጅዎ የት ነው? » አልኩት
«ሞቷል። አልጄሪያ» አለኝ፣ እጁን የስንብት እያራገበ
እጀን ሳወዛውዝለት፡ ተሰምቶኝ የማያውቅ አይነት ሀዘን ልቤን
ሞላው። አልቅስ አልቅስ አለኝ፡፡ እዚያ ቆሞ እጁን ሲያወዛውዝልኝ፣
እየራቀና እያነሰ ስሄድ፡ በሀይል እሳዘነኝ። በመጨረሻ ከአይኔ
ተሰወረ። ምን ያህል እንደወደድኩት ገና አሁን ገባኝ ..

መሬት መሬቱን እያየሁ፤ ማንንም ሳልገጭ፣ በዝግታ ወደ ቦታዬ ሄጄ ቁጭ ኣልኩ፡፡ በመስኮት ወደ ውጭ እያየሁ በብዙ አዘንኩ፡፡ ሲልቪ ደጋግማ ታወሰችኝ፡ ግን ንዴቱ ለቆኛል። ቅድም አሰላስል የነበረው የበቀል ህሳብ ከንቱ ሆኖ ታየኝ፡፡ ምስኪን ሲልቪ!
አሁን ምን አጠፋች? ካንዱ ጋር ስላወራች ነው? ታድያ ያገራቸው
ባህል ነው:: ደሞ ባህላቸው ባይሆንስ ምን አለበት? አሁን ባቡር ውስጥ ምን እንዳያደርጉ ነው?. .. ኧረ የፈለጉትንስ ቢያደርጉ ምን እንዳይቀርብኝ ነው?

ሰዎቹ ሻንጣቸውን ከተሰቀለበት ማውረድና መተራመስ ጀመሩ። ፓሪስ መድረሳችንም ነው። ሲልቪ ከሄደችበት ተመለሰች
ሰውዬው ግን አልመጣም) ሻንጣዋን አወረድኩላት። እንዴት እንደም ታናግረኝ ጨንቋታል። ምን አንደሆነ እንጃ፡ በጣም አሳዘነችኝ፡፡አቅፌ አይዞሽ ልላት ፈለግኩ፡፡ ግን ጊዜውም ቦታውም አይፈቅድም
«በለይል ርቦኛል። አልራበሽም?» አልኳት እየሳቅኩ። ያ ሳቅ ፊቴ ላይ ምን እንደሚመስል ብቻ እግዜር ይወቀው

«አዎን፣ በሀይል ርቦኛል» አለች

«ነይ፣ እራትሽን ላብላሽ” አልኳት

ከባቡር ጣብያው ትርምስምስ ወጥተን፣ እዚያው አጠገብ ኣንድ
ያረጀ ብጤ ሆቴል ውስጥ አንድ ክፍል ተከራይተን፣ ገላችንን
ታጥበን፣ እዚያው ሰፈር አንድ ርካሽ ብጤ ምግብ ቤት ውስጥ ጥሩ እራት በላን፡፡ ከሶስት ጠርሙስ ቀይ ወይንና፣ ከብዙ ብዙ ወሬ በኋላ፣ ሁለታችንም በጣም ሞቅ ብሎን ሳለ፣ እጄን ይዛ በቆንጆ ሰማያዊ አይኖቿ እያየችኝ

«ትፈልገኛለህ?» አለችኝ። የቀኑ ንዴት እሁንም ልቤ ውስጥ
አንድ ጊዜ ተገላበጠ፡፡ ግን በጭራሽ እንዳልተበሳጨሁ ማስመሰል አለብኝ በማለት፤ ጥቁር ፀጉሯን እየዳበስኩ

በሀይል በሀይል እፈልግሻለሁ» አልኳት። እውነቴን ነበር፡፡

«ና ቶሎ እንሂድ» አለችኝ.
👍151👏1
እንግዲህ እኔና ሲልቪ ስንተቃቀፍ በመብራት እየተያየን እያወራን፣ እየሳቅን ነው:: ዛሬ ግን ኣልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን
አጠፋችው፣ በጭለማው ስታቅፈኝ ያለልማዲ ቸኮለች፡ ተንገበገበች።
አንድ ቃል አልተናገረችም፡፡ በጭለማው እየሳመችኝ ማቃስት ብቻ ሆነ፡፡ ደስታው መሀል ላይ እንደደረስን፣ ያለልማዷ ከንፈሬን ነክሳ አሳበጠችኝ። ጠረኗ ብቻ የራሷ ሆነ እንጂ፣ እግር አነሳሷ ሳይቀር ተለወጠብኝ፤ በጠቅላላው ከሌላ ሴት ጋር እንደመተኛት ያህል ነበር።
መጨረሻ ላይ፣ በሀይል እየተንቀጠቀጠች፤ ፊቷን አንገቴ ውስጥ ቀብራ

«Oh piti monsieur! Pitié! Pitie!» እያለች አጉረመረመች።
(«አይ! ይማሩኝ፣ እባከዎን ይማሩኝ! ይማሩኝ!»)

ከጨረስን በኋላ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ከዚህ በፊት አልቅሳ
አታውቅም፡፡ ተመስገን ሲያስጠነቅቀኝ፣ አንዳንዴ ነገሩ ካለቀ በኋቁ አይዞሽ የኔ ቆንጆ፣ ምን ሆነሻል?» እያልኩ ሳቅፋት
በሹክሹክታ
«አሁን አንተ ነህ የተኛኸኝ በሀሳቤ ግን ሌላ ሰው ነበር የተኛኝ፡፡ በጭለማው አንተ እያቀፍከኝ፣ ሌላ ሰው ሲያቅፈኝና ሲስመኝ ነበር የሚታየኝ። ገላዬን የሰጠሁት ለሌላ ሰው ነበር»

ስካሬ ባንዳፍታ ጠፋ
«ለዚህ ነው መብራቱን ያጠፋሽው?» አልኳት፡፡
«አዎን»
«አሁን እናብራው?»
«የለም እፈራለሁ። አሁን አይንህን ማየት አልችልም» ብላ
ተጠመጠመችብኝ
«እሺ ይቅር። አይዞሽ፣ አይዞሽ. .. ግን እኔን ማፈርሽ ቂልነት
ነው። ይልቅ አስረጂኝ»
«እኔም ለራሴ አይገባኝማ!»
«ምስጢሩን አስረጂኝ ማለቴ አይደለም፡፡ አሁን ለምሳሌ
ስንተቃቀፍ ሳለን' በሀሳብሽ ውስጥ ምን ምን ተደረገ?. . . ንገሪኝ
አይዞሽ የኔ ሲልቪ»
«ያው ያደረግነው ነገር ነው የተደረገውስ፡ ብቻ. . .»
«ብቻ?»
«ሰውዬው አንተ አልነበርክም
«ማን ነበር?»
አፍራ ዝም አለች
«ያ ባቡር ውስጥ የነበረው ሽበታም ሰውዬ ነው?»
በሹክሹክታ አለችኝ። ምንም ቅናት አልተሰማኝም፡፡ ስጋዬ ስጋዋን ስለጠገበው ይሆን?

«አዎን። እባክህን ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ወድጄ አይደለም»
ይሆን? በጭለማው ከጐኔ አስነስቼ እላዬ ላይ አስተኛኋትና፣ ባንድ እጄ ጀርባዋን፣ በሌላው እጄ ፀጉሯንና አንገቷን እያሻሽሁና አይኗን እየሳምኩ

«አሁን ምን ይሰማሻል?» አልኳት
«እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል፡፡ እንግዲህ ይቅርታ ምናምኑን እርሺውና፣ ስለዚህ
ነገር የተቻለሽን ያህል ግለጪልኝ»

«እሺ። በመጀመሪያ ሰውዬን ሳየው ትንሽ ደስ አለኝ»
እየሳቅኩ፣
«ውሸታም! በሀይል ነው ደስ ያለሽ» አልኳት
እሷም እየሳቀችና በሀይል እያቀፈችኝ
«አቤት እንዴት ነው 'ምወድህ! እባክህን አግባኝ! አውቃለሁ
ከውቃለሁ፡፡ አገርህ እጮኛ አለችህ:: ደሞ ባትኖርህም ጥቁርና ነጭ ሲጋባ ትርፉ ብስጭት ነው:: አውቃለሁ። ጋብቻውን እንርሳው»
«ንገሪኝ»
«ሰውዬው ደስ አለኝ»
«ስጋዊ ምኞት አሳደረብሽ»
«አዎን። በሀይል ተመኘሁት። ግን. . .»
«ግን ምን?»
«እሱ ራሱ በስጋው እንዲገናኘኝ ኣልፈለግኩም»
«እንግዲያውስ?»
«አንተ እሱን ሆነህ እንድትተኛኝ ነው የፈልግኩት»
«ትንሽ አብራሪልኝ»
«እሱ ነው ያማረኝ፡፡ ግን እሱ ራሱ ሲገናኘኝ አልፈቅድም፡፡
ኣንተ ብትተኛኝ ነው 'ምፈቅደው:: ግን አንተ ስትተኛኝ አንተን
ሆነህ አይደለም፣ እሱን ሆነህ ነው፡፡ የሱ ገላ ነህ»
«እሱ በገላዬ እንዲያቅፍሽ ነው
'ምትፈልጊው?»
«አውቀሀል»
«ነገሩን ብናለዋውጠውስ?»
«እንዴት?»
«እሱ የኔ እንደራሴ ቢሆንና፣ የሱን ገላ እያቅፍሽ ስለኔ
ብታስቢት
«ብጭራሽ አይሆንም»
«እሺ ቀጥይ»
ቀጠለች። ግን ምንም ሌላ አዲስ ነገር አልነገረችኝም፡፡ ያው
ነበር። አንድ ወንድ ያማራት ጊዜ፡ እሱ ራሱ ከሚተኛት ይልቅ
ስለሱ አያሰሰች ሌላ ወንድ ቢተኛት ትመርጣለች ገረመኝ። ግን ሊገባኝ አልቻለም። ሁለት ሰአት ያህል ከተወያየንበት በኋላ እንደገና ሞቅ አለኝና ጭኗን ማሻሸት፣ ሰፊ አፏን መሳም ጀመርኩ። አሁንም ያለ ልማዷ ተንገበገበች፣ በብዙ አቃሰተች፣ ጀርባዬ እስኪደማ ድረስ ቧጨረችኝ፡ስትጨርስ እየተንቀጠቀጠች፣ Ah vous alors!Quel homme!»
እያለች እጉረመረመች። («አይ አንቱ! አይ ወንድ!»)

ከኔ ጋር እንዳልሆነች እያወቅኩ ውስጥ ውስጡን ተቃጠልኩ፡
የኔን ገላ ተውሶ ሌላ ሰው እንደተኛት እያወቅኩ ውስጥ ውስጡን ጦፍኩ፡፡ ግን የሴት ገላ እንደዚያን ቀን ልቤን አጥፍቶኝ አያውቅም።በነጋታው አያለሁ፡ ለካ ሳይታወቀኝ አንገቷን ሶስት ቦታ ነክሼያት ኖሯል። ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት ረዥም እንገቷ ዙሪያ ሻሽ ጠምጥማ መማር ግድ ሆነባት፡፡ ለጌጥ የለበሰችው ይመስል ነበር

በዚህ አኳኋን ከቅናት ጋር ተዋወቅኩ፡፡ ግን ቅናት ምን አይነት ግሩም ስሜት መሆኑን ለመገንዘብ ብዙ ሳምንት ወሰደብኝ. ..

በነጋታው ሲልቪ ቤቶቿ ዘንድ ዋለች፡ እኔ ፓሪስን በኦቶቡስና
በእግር ስዞር ዋልኩ። ማታ ሆቴላችን ተገናኘን። ሁለታችንም ደክሞን ስለነበረ፣ አልጋ ውስጥ እንደገባን እንቅልፍ ወሰደን፡፡ ሲነጋ ተነስተን ቁርስ በልተን ፓሪስን ዞርን። ምሳ በልተን ፓሪስን ዞርን፡፡ እራት በልተን ፓሪስን ዞርን። አያልቅም የፓሪስ ውበትና የሲልቪ ሳቅ ጨዋታ። ከሌሊቱ በስምንት ሰአት ሆቴላችን ተመለስን። ስንተኛ

«ፓሪስ እንዴት ቆንጆ ናት!» አልኳት
«ይገርምሀል፡፡ ባንተ አይን ሳየው ጊዜ ሌላ ፓሪስ አየሁ፡፡ ነገም
ስንዞር እንዋል?

«አመት ሙሉ እንዙር ብትይኝ ደስ ይለኛል።»

«አንድ ሳምንት ብቻ ነው ምንዞረው:: ከዚያ የት እንደምንሄድ ታውቃለህ?»
«የት?»
«ጄኖቫ፡፡ የክሪስቶፎ ኮሎምቦ ከተማ»
«እኔ አንድ ሺ ፍራንክ ብቻ ነው ያለኝ ልብ አርጊ»
«ግድ የለህም፡፡ እኔ ሁለት ሺ አምስት መቶ አለኝ»
«እሺ እንግዲያው»
«አሁን እቀፈኝ የድሮዋ ሳቂታ ሲልቪ ናት፡፡ ከትላንት ወዲያ ሌሊት የነበረውን ማቃሰት፣ ማልቀስና መናከስ አሁን ሳስበው ህልም መስሉ ተሰማኝ፡፡
እሷም ፈፅማ የረሳችው ትመስላለች። ብቻ ሳላውቅ አንገቷን የነካኋት እንደሆነ አይ!» ትላለች፡ ሁለታችንም እናስታውሳለን

ሮማ ከመሄዳችን በፊት ጄኖቫ ሶስት ቀን አደርን። ሁለተኛውን
ሌሊት በተለይ አስታውሳለሁ። እራት ከበላን በኋላ፣ አንድ ሲጋራ
የማይሽጥበት ቡና ቤት ገብተን ስናወራ ቆይተን፣ ሲጋራዋ ስላለቀባት ልገዛላት ወጣሁ
ስመለስ ከአንድ ረዥም ብሉንድ (ባለ ነጭ ፀጉር) ጎረምሳ ጋር
ትተያያለች፡፡ እሱ ቡና የሚቀዳበትን ባንኮኒ ተደግፎ ቆሞ ያያታል፡
ጥብቅ ያለ ጂንስ ሱሪና እጅጌው አጭር የሆነ ነጭ ሸሚዝ ለብሷል።እሷ ጠረጴዛችን ጋ ቁጭ እንዳለች ሽቅብ ታየዋለች፡ ውብ አይኖቿ ፊቱና ገላው ላይ ይንከራተታሉ። ትንሽ ከተያዩ በኋላ ሳቅ አለች፡
ጉልህ አይኖቿና ሰፊ አፏ የምኞት እስክስታ ይወርዳሉ ማማሯ
ኣይኔን አንዴ ወደ ጎረምሳው ጣል አደረግኩ፡ ጥርሱን ሳያሳይ ነው
ፈገግታ የሚልክላት። እሷን አየኋት፡ ቀያይ ከንፈሮቿን ለመግጠም ትሞክራለች፣ ፈገግታው ግን ሊፈለቅቃቸው ይፈልጋል፡ ታዲያ ከናፍሯ በሚያስጎመጅ አኳኋን ይርበተበታሉ፡፡ (ምኞቱ ሲያሳብጠኝ ተሰማኝ ታድያ ከፍርሀት ጋር ነው፤ ምክንያቱም የተመኘኋት ቀን ስለሆነች ብቻ ሳይሆን፣ ሰውየውን ስትመኘው ስላየኋትም ነው።
👍19👏1
ነው?)
ድንገት እጇ ወደ አንገቷ ሄደ። ያን ጊዜ የነከስኳትን አስታወስኩ። ፊቷ ቀስ ብሎ ደም ለበሰ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ የሰውየውን አይን ለመሸሽ ወደኔ በኩል አየች ከኔ ጋር አይን ለአይን ተጋጠምን!
ቅናቱ ደረቴን ያሳምመኛል፡ ግን ምንም እንዳላስተዋልኩ ያህል
(አሁን አሁን ከውጭ እንደመጣሁ አስመስዬ) ወደሷ ሄድኩና
ተቀመጥኩ። ሰውየው ወደ ኋላዬ ሆነ፡፡ ሲጋራ አያቀጣጠለች
«ስንት ሰአት ነው?» አለችኝ «አምስት ተኩል፡፡»
እንደ መድከም ብሉኛል፡፡ ሄደን አልጋ ውስጥ ተጋድመን
እናውራ?» አለችኝ፡፡ ገብቶኛል። እሺ አልኳት። ስንሄድ ቃል
አልተናገርንም፡፡ የከፍላችንን በር ቆለፍኩት፣ መብራቱን አጠፋችው።
በፀጥታ ልብሳችንን አወለቅን አልጋ ውስጥ ገባን፣ ተቃቀፍን። እንደ አንድ ቀኑ ሌሊት ተንገበገበች፡ ስስማት አፌ ውስጥ እያቃሰተች ጭኖቿን ከመጠን በላይ ፍርክክ አድርጋ አቀፈችኝ፣ ደምበኛው ፍቅር ሳይሆን፣ ቆሻሻ ብልግና የምንሰራ መስሎ ተሰማኝ። የባሰ ቆሻሻ
እንዲሆን አማረኝ፡ ጭኖቿን የባሰውን በለቀጥኳቸው። ወደ
መጨረሻው ልንደርስ ስንል ወፈፍ አደረጋት፤ በሚያስደነግጥ
ሰሚያስቀነዝር ሹክሹክታ «አፌ ውስጥ ይትፉ!» አለችና፡ መላ አፈ
ጎርሳ እስኪያመኝ ድረስ ጠባችው.
ነቃሁ ለካ እኔም ወፈፍ አርጐኝ ያለሁበትን ረስቼ፣ በሀይል እቅፌ
ይዤያት መተንፈስ ተስኗታል። ለቀቅ አደረግኳት። ቁና ቁና
መተንፈስ ጀመረች እኔም ቁና መተንፈስ ጀመርኩ፡ ሁለታችንም
በላብ ታጥበናል፡፡ በጭለማው ከግርጌ ፎጣ ሳብኩኛ ግምባሯን
መሀል ጡቶቿን፣ ብብቶቿንና ሆዷን አደረቅኩላት፡ «Merci.” ብላ
ፎጣውን ተቀበለችኝ፤ እኔንም አደረቀችኝ ያን ጊዜውኑ እንቅልፍ ወሰደን...

💫ይቀጥላል💫
👍111👎1
#የማያልቅ_ስጦታ

የካብኩት እየተናደ
የገመድኩትም ሲበጠስ
ያደመቅኩት እየፈዘዘ
ያነጽኩት ሁሉ ሲፈርስ
ደመናው ፀሐይ ሆኖብኝ
በመንገዴ እየተሰጣሁ
ከእንስራው ውሃ ጠፍቶ
ላቤን ከጉንጬ እየጠጣሁ
የበደሉኝን ይቅር ለማለት
ራሴን በራስ እየቀጣሁ
“ማነው?” ስባል “እኔ” የምል
የሰው ጥፋት የምሸከም
በኔ ይለፍ የምዘምር
እስክጠፋ የማልደክም
ሳይታሰብ እንደ መና
ከላይ ወርዶ የሚያወፍር
ስላለኝ ነው ታላቅ እውነት
ስላለኝ ነው አንዳች ክብር
ያንቺ ፍቅር...!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍105🔥1
#ልክ_በዛሬው_ቀን...

አበባ ባልሰጥሽ ለራት ባልቀጥርሽም
#የኔ_ወድሻለሁ
ባለሽበት ሆነሽ ባለሁበት ሆኜ
አብረን እንደሆንን ራሴን አሳምኜ
እራት እበላለሁ እራትሽን ብይ
ስጦታሽን እንቺ አበባሽን እይ

#የኔ_ወድሻለሁ...
ያለንበት ቦታ ለስላሳ ሙዚቃ
ሰማሽው አይደለ ላንቺ ይሁን በቃ
አውቃለሁ የኔ ሴት አውቃለሁ የኔ ዓለም
ቀይ መጸሀፍ እንጂ ቀይ ልብስ አትወጂም
ለራት የለበስሽው...
ሰማያዊ ቀሚስ ነጭ እስካርፍ ያለበት
ይሁን ደስ ብሎኛል ደምቀሽ እመሪበት

#የኔ_ወድሻለሁ...
ዘና በይ ፈገግ በይ
ባለሁበት ሆኜ ባለሽበት ሆነሽ
ብቸኝነት የለም የኔ ሆይ ልንገርሽ
ያሳቤን ስጦታ በይ አሁን ክፈቺው
አየሽው... ?
ወደድሽው... ?
የልቤ ትንፋሽ ነው በልብሽ ተንፍሺው

#የኔ_ወድሻለሁ!!!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍8
#ቦግ_እልም !!


#በአሌክስ_አብርሃም


አንዳንድ ታሪኮች አሉ፣የማያስደስቱ ግን ምን በወጣኝ ብቻዬን መሸከሜ ተብሎ ለሌሎች የሚነገሩ ልክ እንደዚህ.…

አንዳንጅ ታሪኮች ደግሞ አሉ፡ እንኳን ለግጥም፣ ለእግዜር ሰላምታ አፉ የማይፈታለትን ሰው በሐዘን ኮርኩረው ገጣሚ የሚያደርጉ፣ ልክ እንደዚህ….

ብቸኝነት ማለት …
ብዞዎች መካከል
አንድ ሆኖ መገኘት ?
ብቸኝነት ማለት …
ለሕዝብ እየታዩ ደምቀው እንዳበባ፧
በራስ ማንነት ውስጥ መቅለል ከገለባ ?
ብቸኝነት ማለት …
የብዙሀኑ ቀልብ ወዶን ሲንሰፈሰፍ፣
ራስን ረግጦ ወደ ምንም ማለፍ ?
ብቸኝነት ማለት ...
ዘላለም የሚያስንቅ ረዥም ጨለማ፣
በነገ አምላኪዎች በተስፈኞች መሐል፣
ከፍ ብሎ መቆም በሰቆቃ ማማ።
ለኩሰው ለብቻ የትዝታ ኩራዝ
በትላንት ሰንሰለት ተቀይዶ መያዝ ?
ብቸኝነት ማለት …
በዝምታ ጀልባ ከባሕር እእምሮ፣
ትላንት ላይ መቆም ዛሬን ወዲያ አባሮ …
ብቸኝነት ማለት ...

ይህ ታሪክ ያስጠላል። በተለይ እኔ ስጽፈው ያስጠላል። ምክንያቱም በተቻለኝ አቅም ሁሉ እንዲያስጠላ
አድርጌ ስለምጽፈው ነው። ለምን ? ትንሽ እንኳን ላሳምረው ብሞክር ሀጢያት የሠራሁ ስለሚመስለኝ ።

ከዓመት በፊት ነው፣ ጓደኛዬ ደወለና "አብርሽ 'ሚስ ክሪስመስ' ሞተችኮ” አለኝ። በቃ እንዲህ ነው
ያለኝ። እውነቱን ለመናገር አዞረኝ። ትንፋሽ ሁሉ ነው ያጠረኝ። ስልኬ ከእጄ ላይ ሊያመልጠኝ ነበር።
"ክሪስመስ” ያላት ስምረትን ነው። እኔ እንኳን እትዬ ስምረት ነበር የምላት።

“አትቀልድ ባክህ” አልኩት። ቀልድ አለመሆኑ ግን ገና ድሮ ተሰቶኝ ነበር።

“ማሪያምን ! አሁን ራሱ ፖሊሶች ቤቷ መጥተው በሩን ሰብረው ገቡ፡፡ ሬሳዋን ወደ ምርመራ ሊወስዱ እያዘገጃጁት ነው፤ እኛም እዛው ነን” አለኝ በተጋነነ ድምፅ። የድምፁ መጋነን ጦር ሜዳ መሀል ሆኖ ጦርነቱን የሚዘግብ ጋዜጠኛ እንጂ የአንዲትን ሚስኪን ሴት ሞት የሚያረዳ ጎረቤቷ አይመስልም።አንዳንዱ ሰው መርዶም ይሁን የምሥራች ቀድሞ ስለተናገረ ራሱን ጀግና አድርጎ ይቆጥራል ልበል?ግራ ታጋባሁ፡፡ እትዬ ስምረትን መቼ ለታ አንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የገና ዛፍ ገዝታ ስትወጣ አይቻት ነበር። እትዬ ስምረት…!!

መጀመሪያ ሥራ እንደያዝኩ አካባቢ ቤት ልከራይ ሳፈላልግ አንድ ቆንጆ ግቢ ውስጥ አንዲት ክፍል ቤት አገኘሁ። ደላላው አጣድፍ ካስገባኝ በኋላ ሒሳቡን ወስዶ ከዛ አካባቢ ጠፋ። በኋላ ስሰማ ባለቤቷ 'እብድ' ናት አሉኝ፡፡ እንደውም ከእኔ በፊት የነበረውን ሰው “ነገውኑ ቤቱን ለቀህ ውጣ ትለዋለች ሰውየው ችላ ይላታል፡፡ ማታ እንደተኛ የሆነ ጭስ ይሸተውና ከእንቅልፉ ሲነሳ ቤቱ በጭስ ታፍኖ እንደውም በሩ አካባቢ ነበልባል ይመለከታል። በርግጎ ከአልጋው ይነሳና መስኮቱን በርግዶ ከክፍሉ
ይወጣል፤ እርቃኑን። እትዬ ስምረት የጋዝ መያዣ ጀሪካን ይዛና በቀኝ እጇ ክብሪት እንደጨበጠች
የሚንቀለውን እሳት እየተመለከተች በስስ ፒጃማ መልአክ መስላ ቆማለች። ራሷ ናት ቤቱን እሳት የለቀቀችበት። እሳቱን በጎረቤት ትብብር አጥፍተው፣ ዕቃውን ሌሊቱኑ አውጥቶ፣ ሰውየው ጠፋ ጠፋ

ይኸው ከስንት ወር በኋላ ቤቱን አሳድሳ ለእኔ አከራየችኝ። ይሄን ታሪክ ስሰማ ደንግጬ ደላላውን
አፈላሰግኩና፣ “እንዴት እብድ ቤት ታስገባኛለህ አንተ?” ብዬ ጮኽኩበት።

“ባክህ ሰው ሲያጋንን ነው፤ ስምረት እብድ አይደለችም። በእርግጥ ትንሽ ወፈፍ ያደርጋታል። ምን ችግር አለው? ሰው ላይ አትደርስ” አለኝ።

“እንዴት ነው የተኛ ሰው ላይ ጋዝ አርከፍክፋ እሳት የምትለቅ ሴትዮ ሰው ላይ አትደርስም የምትለወ።

“እነሱን አትስማቸው፣ ሰዬው ተተናኮሏት ይሆናል…” ብሎ ብዙ ብዙ ነገር አወራኝና አሳመነኝ፡፡
ውይ ደላላ ሲባል ።

የግቢው ፀጥታ ያስፈራል። ዙሪያውን የበቀሉት ረዣዥም የፅድ ዛፍች ዕድሜ ጠገብ ስለሆኑ ቤቱ የቤተክርስቲያን ግቢ አስመስሎታል፡፡ ባለቤቷ እትዬ ስምረት ሲበዛ ውብ የሆነች እድሜዋ እስከ 40 የሚገመት ሴት ነበረች። ታዲያ ስትገባም ስትወጣም ሰው ሰላም አትልም። ምንንም ሰላም አትልም። ቤቷ እንግዳ አይመጣም። አንድ ግቢ እኔና እሷ ብቻ እየኖርን እኔንም ሰላም አትለኝም "ምን ያምበጣርራታል…” እያልኩ በውስጤ ስቦጭቃት ብዙ ወራት አለፉ። የቤት ኪራይ ካልሰጠኋት
አትጠይቀኝም ነበር። ማንንም ባስገባ ባስወጣ ግድ የላትም። ውኃ ፈሰሰ፣ መብራት በራ የለ ብቻ
መኖሬን የረሳች ሴት ነበረች። መኖሬን ስለረሳችው ነው መሰል እኔም አከራይ መኖሩን ረስቼ በነፃነት መኖሬን ተያያስኩት።

ግቢ ውስጥ ከእኔ ቤት ፊትለፊት ያለ አንድ የፅድ ዛፍ ከታች እስከ ላይ የገና መብራት ተጠምጥሞበታል ሁልጊዜ ማታ ማታ ይንቦገቦጋል። ለምን እንደዚህ እንደሚሆን ይገርመኛል። በዓልም ይሁን አዘቦት መብራቱ ከዛፉ ላይ አይነሳም። ዝናብና ፀሐይ እየተፈራረቀበት አለመቃጠሉም ይደንቀኛል። አንዳንዴ መበራቱ ቦግ እልም ሲል ግቢውን የአደጋ ቀጠና ቢያስመስለውም ለስላሳ ብርሃኑን ግን እወደው ነበር።

ሴትየዋ የምትኖርበት ግዙፍ ቪላ ሁልጊዜም በሩ ዝግ ነው፡፡ ሥራዋ ምን እንደሆነ እግዚአብሄር
ይወቅ። አንዳንዴ ዘንጣ ትወጣና በትልልቅ ፌስታሎች ብዙ ዕቃ ይዛ ትመለሳለች። ከዛ በሯ ይዘጋል።
ማታ ማታ በቤቷ መስኮት በኩል ከመጋረጃው ጀርባ ፈዘዝ ያለ የገና መብራት ዓይነት ረጋብሎ ሲበራና
ሲጠፋ ይታያል። ግቢ ውስጥ የቆመች አንዲት አዲስ መኪና አለች፣ ሰማያዊ፡ ሁልጊዜ ቅዳሜ ጧት ራሷ ታጥባታለች። መኪናዋን ግን ነድታትም አስነስታትም አታውቅም፡፡ እንደውም መኪናዋ ጎማ ሥር ሳር በቅሏል። ለአንድ ዓመት ያህል እዛ ቤት ስቆይ አንድ ቃል ተናግራኝ አታውቅም። አሁን ይሄን ማን ያምናል .…? ዝም ቄሱም ዝም፣ መጽሐፉም ዝም። ቤቱ፣ እርሷ እና ግቢው በአጠቃላይ ይጨንቃል።

አንድ ቀን ታዲያ አምሽቼ ወጀ ቤት ስገባ፣

"አብርሃም!” አለችኝ በረንዳ ላይ ቆማ እየጠበቀችኝ ነበር።

"አቤት….” ስሟ ጠፋብኝ። ደግሞ ልክ ጣረሞት እንደጠራኝ ነበር የደነገጥኩት።

"እንኳን መጣህልኝ፤ መብራት ተበላሽቶብኝ ነበር" አነጋገሯ በጭንቀት የተሞላ ስለነበር የሆነ ሰው የታመመባትና ድንገተኛ ክፍል ደውላ እባካችሁ ለነፍስ ድረሱልን” የምትል ያስመስላት ነበር።

"እሺ ምን ችግር አለው…" ብዬ ወደ ትልቁ እና ተዘግቶ ወደ ኖረው ቤቷ ገባሁ። ሁሌም ወደዚህ ቤት
ለመግባት እጓጓ ነበር። ከገባሁ በኋላ ግን ያየሁትን ነገር ማመን አልቻልኩም።

ሰፈው ሳሎን ውስጥ በትንሹ ሃያ የሚሆኑ ሰው ሠራሽ የገና ዛፎች ተደርድረዋል። ኮርኒሱን ሊነካ
ከደረስው ትልቅ ዛፍ፣ እስከ ትንንሽ ዛፎች ቤቱ ከዳር እስከዳር ተሞልቷል። ምን ይሄ ብቻ ግድግዳው እንደ ሸረሪት ድር የተወሳሰቡና የተለያየ መጠን ባላቸው የገና መብራቶች ተወርሯል። የቤቱ መብራት
በሙሉ እየበራ ስለነበር የተበላሸው የትኛው እንደሆነ ጠየቅኳት። ወደ መኝታ ቤቷ መራችኝ። ማመን አልቻልኩም። መኝታ ቤት ስፍር ቁጥር በሌላቸው የገና አባት አሻጉሊቶች ተሞልቷል። መልበሻዋ
ላይ የተቀመጠ የሚወዛወዝ ጌጥ ነገር በቀጭን የሚቅጨለጨል ድምፅ የገና መዝሙር ያወጣል።
ድምጹ ይጨንቃል።አንድ የገና መብራት ነበር የተበላሸባት። ስመለከተው ተቃጥሏል። ይህንኑ
ነገርኳት። ፊቷ ግርጥት ብሎ “
ሊሠራ አይችልም? እባክህ እርዳኝ አለችኝ። ስትናገር እንባ እየተናነቃት ነበር። ግራ ተጋባሁ። በጣም ርካሽ የሆነና ያን ያህል የሚያሳስብ የገና መብራት ይህን ያህል ለምን እንዳስጨነቃት ማወቅ አልቻልኩም።

“በቃ ተቃጥሏል … ባይሆን ያን ያህል የሚያስፈልግሽ ከሆነ ነገ ከስራ ስመለስ እገዛልሻለሁ አልኳት፡
👍18
“እሰይ የኔ ጌታ፣ እባክህ ጥሩውን መርጠህ ግዛልኝ፣ እጠብቅሀለው.…” ብላ ቦርሳዋን አነሳችና
ለማውጣት ስትከፋፍት እጆቿ ይንቀጠቀጡ ነበር። ሁኔታዋን ስመለከት እኔም ተረባበሸኩ። ቦርሳዋ ከእጇ ወደቀ። አነሳችው። ሦስት መቶ ብር አውጥታ ሰጠችኝ።

“ይበቃ ይሆን…?” አለችና አንድ መቶ ብር ጨመረችልኝ። ቦርሳዋ በጣም በብዙ ድፍን መቶ ብር፣
የተሞላ ነበር።

በቀጣዩ ቀን የተቃጠለውን የሚመስል ገዝቼላት መጣሁና ሰጠኋት። እየተጣደፈች ተቀብላኝ ወደ ውስጥ ገባች። አመሰግናለሁ እንኳን አላለችኝም። መልሱንም አልተቀበለችኝም፡፡ ክፍቱን በተወችልኝ በር ገብቼ መልሱን ጠረጴዛዋ ላይ አስቀምጬላት ወጣሁ፡፡

እዛው ጎረቤት ያለ ዓለማየሁ የሚባል ባለሱቅ ደንበኛዬ
አንድ ቀን አብረን ቆመን እያለ ይህቺ ሴት ትልቅ የገና ዛፍ ሊቆምጬ አሸክማ ስትገባ አየናትና በወሬ ወሬ ስለአከራዬ ታሪክ አወራልኝ።

“አከራይህ … ትንሽ አእምሮዋ ንፋስ ሰርቋል …” አለኝ።

“እንዴት… " አልኩት ለወሬ ጓጉቼ።

"እየውልህ፡እትዬ ስምረት በጣም አሪፍ ሴት ነበረች፡፡ገና መኪናዋ ብቅ ሲል የሰፈር ሕፃናት ይንጭጫሉ፥ደግ ናት፣ የደግ መጨረሻ። ሰውን ሁሉ ማብላት ማጠጣት ነበር ሥራዋ፤ የዛሬን አያድርገውና። ደግዋ ባልዋ ከሷ የባሰ መልአክ ነበር መላጣ ነው ረዥም ሳቁ ብቻ የሚያጠግብ ፍቅራቸው ለብቻው ነው። በቃ ሲገቡ ተቃቅፈህ፣ ሲወጡ ተቃቅፈው፣ ሁልጊዜ ሙሸራ ነበር የሚመስሉት።እሷም ቆንጆ ነበረች።

ባላሱቁ ነገር ያረዝማል…

"..እናልህ የዛሬ እስር፣ አስራ ሁለት ዓመት አካባቢ ይሆናል። እትዬ ስምረት እርጉዝ ነበረች በቃ
የእነሱን ልጅ አይተን የሁለት ቆንጆ ባልና ሚስት ልጆች እያለ ጎረቤቱ ሲያወራ፤ መቼም የሰው አፍ
ክፉ ነው፣ ምን እንደሆነ ሳይታውቅ ባለቤቷ ራሱን ሰቅሎ ተገኘ።”

“ምን…!” አልኩት ደንግጬ።

“አዎ…ግቢያቸው ውስጥ ያለ ዛፍ ላይ ራሱን ሰቅሎ ተገኘ። እንደውም እትዬ ስምረት አስካሁንም ዛፉ ላይ የገና መብራት አድርጋበታለች። አላየሁትም እንዳትል ብቻ እዛው እየኖርክ” አለና ጫቱን በጥርሱ
ቀረጣጥፎ ወሬውን ቀጠለ ..

"እትዬ ስምረት ራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች። ለቀብሩ እንኳን አልነቃችም ነበር። ያረገዘችውም ልጅ አስወረዳት። ከዛ በኋላ በቃ ይሄን ሁሉ ዓመት ሰው ሰላም አትል፤ ከሰው አትደባለቅ፣ የገና ዛፍ
እየሰበሰበች ግቢዋን ዘግታ መኖር ነው። ድንገት ከተነሳባት ከግቢዋም ልታባርርህ ትችላለች” አለና ፈገግ አለ።

"ዘመድ የላትም እንዴ” አልኩት።

“ሞልቷት ! ያውም የናጠጡ ሀብታሞች። እንትን ነዳጅ ማደያ የአባቷ ነው፣ ምንትስ ሱፐርማርኬት የወንድሟ ነው፣ ምንትስ አስመጪም የባሏ ነበር አሁን ቤተሰቦቿ እያስተዳደሩ ብር ለእሷ እንደፈለገች ይሰጧታል። ባይሰጧትም ስጡኝ አትልም። ሰው ስለማትፈልግ ማንም ቤቷን አይረግጥም። ብዙ ተጥሮላት ነበር። ፀበልም ወስደዋት ነበር። አማኑኤልም ወስደዋት ጤነኛ ናት ጊዜ እያለፈ ይሻላታል አሉ፤ ይሄው እሷ እንዳለች አለች ፤ አንዴ አለመለከፍ ነው አብርሾ …።" አለና ወደ ጫቱ ዞረ።

የነገረኝ ታሪh ወትሮም የሚቀፈኝን ግቢ እንዲከብደኝ አደረገኝ። እየቀፈፈኝ ወደ ቤት ስገባ ግቢው
ከነተለመደ ዝምታው ጋር ጣረሞት ሰፍሮበት ጠበቀኝ፡፡ ከቤቴ ፊት ለፊት ያ ቀፋፊ ዛፍ ዮገና መብራት
እንደ እባብ ተጠምጥሞበት ቦግ እልም ይልበታል። በጨለማው ውስጥ ዛፉ ላይ የተሰቀለ ሰው በቀስታ የሚወዛወዝ መስሎ ታየኝ ረዥም መላጣ ሰው…።

አንድ ሌሊት የስው ለቅሶ ሰምቼ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ስቅስቅ ብላ የምታለቅ ሴት ነበረች። ጆሮዬ
ቆመ። በእርግጥም የሴት ለቅሶ ነበር። ክረምት ነው፣ ስስ ካፊያ ነበር። ቀስ ብዩ ከአልጋዬ ተነሳሁና
መጋረጃዬን ገለጥ አድርጌ ተመለከትኩ። እትዬ ስምሪት ባሏ የተሰቀላሰት ዛፍ ስር ቆማ በዚያ
ባሚያንዘፈዝፍ ካፊያ ስስ የውስጥ ልብስ ብቻ ለብሳ ታለቅሳለች። ጨነቀኝ፡፡ ወጥቼ አይዞሽ ልላት
ፈለግኩ፤ ግን ደግሞ ፈራኋት። አለቃቀሷ አስፈሪ ነበር፤ ኡኡታ ! ኩርምት ብላና ጡቶቿን በእጆቿ
እቅፋ ካፊያው እየወረደባት ትንሰቀለቃለች። ሰዓት ተመለከትኩ፣ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት። ቦግ ኦልም ..ቦግ እልም ቀይ፣ አረንጓዴና ቢጫ ቀለማት ያሉት መብራቶች እቺን ሚስኪን ኮከብ በደረቅ ሌሊት ካፈያ ላይ የብርሃን መልኩን ይረጭባታል፡፡

እትዩ ስምረት ስታሰቅስ ካየኋት ከአራት ወር አካባቢ በኋላ ማታ ላይ በሬ ተንኳኳ። እሷ ነበረች።

"አብርሃም ደህና አመሸህ?”

“ደህና አመሸሽ እትዬ…"

“ቤት ፈልግና በዚህ ሳምንት ቤቴን ልቀቅ” ብላኝ ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች።

ምንም አልተቀየምኳትም።

እንዲያወም አዘንኩ።

ብጠቅምም ባልጠቅምም እዚህ አስፈሪ ግቢ ውስጥ እኔ መኖሬ ለእሷም ጥሩ ነበር። ዝም ብዬ ሳስበው፣ ብቻዋን በዚህ ግቢ ውስጥ…አሰቃቂ ነገር ነው። ለማንኛውም በዛው ሳምንት ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ። ቀስ በቀስም እትዬ ስምረት ከአእምሮዬ ደበዘዘች፡፡ ቤቱን ከለቀቅኩ ከአንድ ዓመት በኋላ እትዩ ስምረት መሞቷን ሰማሁ፡ ሞታ የተገኘችው ባለቤቷ የተሰቀለበት ዛፍ ስር ነበር - በስስ የውስጥ ልብስ ብቻ!አስከሬኗ ተመርምሮ ምንም ሕመም የለባትም፤ የሟቷ ምክንያት ግልፅ አይደለም ተባለ አሉ።

ቀብሯ ላይ ሄጄ ነበር። የተሰለፈ መኪና፣ ያልተያዘ የእትዬ ስምረት ፎቶ አልነበረም። የባሏም ፎቶ
ሲለቀስበት አይቻለሁ። ቤተሰቦቿ ከምር አሳዝነውኝ ነበረ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የገና ዛፍ፣ የገና መብራት
በተለይ የገና አባት የሚባሉትን አሻንጉሊቶች አልወዳቸወም !
ቦግ እልም ..ቦግ እልም ...ሰው ልጅ ገናው ፍቅር ነው። ቦግ ሲል መፋቀር በደስታና በተድላ መኖር።
ፍቅር እልም ሲል በቁም አልያም የማይቀረውን ሞት እንደወረደ መሞት። ቦግ..እልም፣ ቦግ እልም!!.....

አለቀ
👍173
አትሮኖስ pinned «#ቦግ_እልም !! ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም አንዳንድ ታሪኮች አሉ፣የማያስደስቱ ግን ምን በወጣኝ ብቻዬን መሸከሜ ተብሎ ለሌሎች የሚነገሩ ልክ እንደዚህ.… አንዳንጅ ታሪኮች ደግሞ አሉ፡ እንኳን ለግጥም፣ ለእግዜር ሰላምታ አፉ የማይፈታለትን ሰው በሐዘን ኮርኩረው ገጣሚ የሚያደርጉ፣ ልክ እንደዚህ…. ብቸኝነት ማለት … ብዞዎች መካከል አንድ ሆኖ መገኘት ? ብቸኝነት ማለት … ለሕዝብ እየታዩ ደምቀው እንዳበባ፧…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

..ፊሬንዜ ውብ ከተማ ናት፤ የነጻንቴ የነሚኪኤል አንጀሎ ከተማ!

አንዲት ትንሽ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ስንበላ ነበር፡፡ ሲልቪ
ምግቧን ረስታ ወደ ኋላዬ በኩል ትኩር ብላ ማየት ጀመረች።
ሳይታወቃት በግራ እጂ ፀጉሯን አስተካከለች ብቻ መስተካከል
አያስፈልገውም ነበር። ገባኝ። የምትጎመጀው ወንድ አይታ መሆን አለበት። ሹካና ቢላዋን ቁጭ አድርጋ ወይን አንስታ ፉት አለችና፣ ብርጭቆውን መልሳ እንደማስቀመጥ፣ በእጆቿ ውስጥ በዝግታ እያሽከረከረችው ወደዚያው ወደ ኋላዬ ማየቷን ቀጠለች። ቀይ ከንፈሮቿ ገርበብ፣ በወይን ረጠብ ብለው ያስጎመጃሉ

እሷ ወደዚያ ስታይ እኔ እሷን ስመለከት፣ ቆንጆ ፊቷ ቀስ ብሎ
ፈገግ አለ፤ ሰማያዊ ኣይኖቿ ስልምልም ማለት ጀመሩ። ምኞቱ
ውስጤ ሲያድግ ተሰማኝ፡፡ አይኖቿ ከአይኖቼ ጋር ተጋጠሙ፣ ፊቷ መቅላት ጀመረ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ። ሰውየው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ፡ ግን ወደኋላ ከተገላመጥኩ ነገሩ ይበላሻል፣ ስለዚህ ተውኩት

«ፍሬ ይምጣልሽ?» አልኳት
«የለም በቃኝ። አንተ ብላ »
«እኔም በቅቶኛል»
«እንግዲያው እንሂድ?» አለችኝ፣ ወደ ቅድሙ በኩል እያየች
ስንወጣ እሷ ታተኩርበት ወደነበረው በኩል ተመለከትኩ፡፡
በየጠረጴዛው የተበታተኑ አንድ አምስት ወንዶች አሉ፡ የትኛው
ፍላጎቷን እንደ ቀሰቀሰ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግን ፍላጐቷ በሀይል ተቀስቅሷል። አልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን አጠፋችው፣ እየተንገበገበች አቀፈችኝ፤ በመጨረሻ ላይ በእንግሊዝኛ ቃዥች

«Please, my lord! Please, have mercy!

ሌላ ሰው ሆኜ፣ ግን ማን እንደሆንኩ ሳላውቅ፣ በቅንዝርና
በቅናት እየተቃጠልኩ፣ ጥልቅ የሆነ ስጋዊ ደስታን ተደሰትኩ።
በነጋታው ቀኝ ጡቷን እያመማት ዋለ። ሳይታወቀኝ ጨፍልቄው
ኖሯል በሌላ ቀን፣ «ማን ሆኜ ነበር?» አልኳት። ስንበላ በስተኋላዬ አንድ ሰውዬ እይታ ኖሯል። «ልክ ስመ ጥሩውን ባለቅኔ ሎርድ ሳይረንን ይመስል ነበር አለችኝ እንደዚሀ ስንል፣ እሷ ደስ የሚላትን ወንድ ስታይ፤ እኔ በጭለማ እሱን እየሆንኩ ሳቅፋት እሷ ስትቃዥ፣ እኔ ስነክሳት ስጨፈልቃት፣ እንደዚህ ስንል፣ በሰማያዊ, አይኖቿ ብርሀንና በሰፊ አፏ ሳቅ እያሞቀችኝ፣ በውብ ወጣት ገላዋ እያቃጠለችኝ፡የጣልያንን ከተማዎች እያዞረችኝ «Je men fous» አያለች አያሳቀችኝ፣ እንደዚህ ስንል የበጋው እረፍት ወደ ማለቂያው ተቃረበ፡፡ ከፊሬንዜ ሮማ
ከሮማ ናፖሊ፤ ከናፖሊ ኒስ (ፈረንሳይ) ከኒስ ማርሰይ ተጓዝን።

ከማርሰይ እሷ ቤቶቿን ጥየቃ ፓሪስ ሄደች፡፡ ባቡር ጣቢያው
ሄጄ ስሸኛት ልክ የዛሬ ዘጠኝ ቀን ማክሰኞ ኤክስ እገባለሁ፤ ማታ
ቤቴ እጠብቅሀለሁ» አለችኝ
የሲልቪ ናፍቆት የሚገድለኝ መስሎኝ፤ ዘጠኝ ቀን ሙሉ
እንዴት ሊያልፍልኝ ነው? እያልኩ ስሰጋ ነበር፡፡ ግን ባቡሩ ይዟት
እንደሄደ፣ በሀዘን ፈንታ እፎይታ ተሰማኝ፡፡ ማታ አልጋ ውስጥ
ገብቼ ብቻዬን እንደ ልቤ ስገላበጥ፣ ብቸኝነት ሳይሆን ምቾት ተሰማኝ፡፡ ምቾቴ በደምብ እንዲታወቀኝ ስል በብዙ ተገላበጠኩ።ጧት ስነቃ ሲልቪ የለችም፡ ብቻዬን ነኝ፡፡ በናፍቆት ፈንታ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሲልቪ ሰልችታኝ ኖሯል? ወይስ ከሰው ጋር ለመኖር አልተፈጠርኩም? ሊገባኝ አልቻለም

ኤክስ ሄጄ ሲቴ (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አንድ የመኝታ ክፍል
ተቀበልኩ፡ ሁለተኛው አመት ወደ መጀመሩ ነበር ጧት ስነሳ በመስኮቱ ደማቅ ሰማያዊ የሆነ ንፁህ ሰማይ ታየኝ።ደስ አለኝ። ሳይታወቀኝ የኤክስ ውብ ሰማይ ናፍቆኝ ኖሯል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባህራም ከቅርብ

ኤክስ እንደተመለስኩ መጀመሪያ ያገኘሁት ተካን ነበር፡፡ ያው
እንደ ልማዱ ጥፍሩን እየነከሰ፣ የት ነበርክ? ከማን ጋር ነበርክ? ምን
አደረግክ? ምን አየህ? እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ፡፡ ግን ሳየው የጥርሱ መበለዝ የቀነሰ መሰለኝ፡፡ አፉም አልገማኝም፡፡ ጊዜው ከእራት በኋላ ነበር፤ ና ቡና ላጠጣህ ብሎ ወደ ክፍሉ ወሰደኝ፡፡ ቤቱ በጭራሽ
አይገማም!

እንግዲህ፣ የዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤቶች ባለ ሶስት ፎቅ
ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ለሚገኙት ሰላሳ ያህል ክፍሎች የጋራ የሆኑ አንድ የገላ መታጠቢያ ክፍልና፣ አጠገቡ ደግሞ (ልክ ደረጃው መጨረሻ ላይ) አንድ የቡና ማፍያ ምድጃ ያለው ክፍል አላቸው።ተካ ቡናውን ሊጥድ ወደ ማፍያው ክፍል ሲሄድ እኔ የሱን መኝታ ክፍል ተመለከትኩ፡፡ ንፁህ ነው። ፊት መታጠቢያው ዘንድ፡ ግማሹ ያለቀ ኮልጌት የጥርስ ሳሙናና አንድ የጥርስ ብሩሽ አለ። ተካ ጥርሱን ይቦርሻል! ምን ነካው?. ምን ይነካዋል? ያው
የተለመደው መሆን አለበታ! አንድን ጎረምሳ ጥርሱን ሊያስቦርሸው የሚችል ምንድነው? ሴት አይደለችም? ግምቴ ልክ ይሆን? ልክ
መሆን አለበት። አለዚያ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?

አንገቴን በበሩ ብቅ አድርጌ አየሁ። ጨለም ያለው ረዥም
መተላለፊያ ኮሪዶር ባዶውን ነው፡፡ ኮሪዶሩ መጨረሻ ላይ ያለው
የቡና ማፍያ ክፍል ተዘግቷል። ተካ ገና ቡናውን በመጣድ ላይ ነው
ማለት ነው። ጊዜ አለኝ፡፡ በሩን ዘጋሁ፡፡ ቶሎ ወደ አልጋው ራመድ
አልኩ፡፡ አንሶላውን ላመሉ ገለጥ ከደረግኩት። ጎምበስ ብዬ ትራሱን
አሸተተኩት፡፡ የሴት ጠረን። ያለጥርጥር። እንዴት ያለች ትሆን?
ቶሎ አልጋውን አስተካከልኩና፣ ቁጭ ብዬ ጋዜጣ እያነበብኩ
ቆየሁት ቡና ከጠጣን በኋላ ሊሎቹን ሀበሾች ፍለጋ ወጣን
ተካ «ተመስገንን ግን አታገኘውም» አለኝ «ወደ ፓሪስ
ተዛውሯል። ለምን እንደተዛወረ ታውቃለህ?»
«ለምንድነው?» አልኩት
«ነጭ ሴት ሰለቸኝ አለ።»
«ምን?
«ጥቁር ሴት ካላገኘሁ ልማር አልችልም አለ፡፡ እዚህ ኤክስ
ውስጥ ሁለት ጥቁር ሴት ብቻ ነው ያለው፡ ሁለቱም አስቀያሚ
ናቸው። ስለዚህ ፓሪስ መሄዴ ነው:: ቢሆን እግዜር ብሎ አንዲት
ሀበሻ ልጅ ታጋጥመኝ ይሆናል፡፡ ባይሆን ደሞ ሌላ ጥቁር ሴት
አላጣም፣ ብሎ ሄዴ»
ተመስገን እውነቱን ነው። ኤክስ ውስጥ ጥቁር ሴት አይገኝም
ሀበሻ ሴት ይናፍቃል። ያገራችን ሴቶች ትዝ ይሉናል፤
አነጋገራቸው፣ አሳሳቃቸው፣ መሽኮርመማቸው ይናፍቀናል፡ ጥቁር ቆዳቸው፣ ነጭ ጥርሳቸው እንቅልፍ ይነሳናል፡ በሀሳባችን
አረ ንሺ» ሲሉ ይሰማናል።

አንዳንድ ጊዜ ተሰብስበን ስለነሱ እናወራለን፡፡ ናፍቆት ሲበዛብን
እየሳቅን እየጮህን እንዘፍናለን
«አንቺ ጥቁር ድንጋይ ፍቅር አይገባሽ በሰው አገር ሆኜ ተቃጠልኩልሽ»
ሉልሰገድማ “ልጆችዬ፣ አብረን አንዲት እምስ የተቀረፀባት ሻማ ለቁልቢው እናብራለትና » አለን እምስ በፖስታ ላክልን፣
መጋረጃ እናስገባልሀለን፣ እንበለው፡፡ እውነቴን'ኮ ነው! ያገሩ ልጆች ነን፡ ይሰማናል። ኧረ እናታችሁን! ይሄ ምኑ ያስቃል?»

እኔና ተካ ሀበሾቹን ሉልሰገድ ቤት እገኘናቸው:: ባህራምና
አንድ ሌላ ኢራናዊ አብረዋቸው አሉ፡፡ ይህ ሌላ ኢራናዊ ጀምሺድ
ይባላል። ረዥም መልከ ቀና ወጣት። ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ
ከቢራቢሮ ክራቫት ጋር ለብሷል። ግብዣ ለመሄድ የተዘጋጀ
ይመስሳል። ረዘም ያላ ፈት፡ ቀጥ ያለ ረዥም አፍንጫ። ከሀር
መሳይ ውብ ቅንድቦቹ በታች ሰማያዊ ትንንሽ አይኖች ሁልጊዜ
ይጨፍራሉ፡፡ ብርሀን ሳቅ፣ ብልጠት የሚፈራረቅባቸው፣ ህይወት የሞላባቸው አይኖች ናቸው፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት፣ ጀምስድ ፈረንሳይ አገር ከመጣ አመት አልፎታል። ታድያ ቢበዛ ስምንት መቶ የፈረንሳይኛ ቃላት ቢያውቅ ነው (የቋንቋ ስጦታ የለውም) ግን እነዚህ ስምንት መቶ ቃላት ለንግግር ኮርተው ይበቁታል። ምክንያቱም ቀጭን ኮሚክ ድምፁና ትንንሽ ብልጮ አይኖቹ፣ ያለ ቃላትም ቢሆን የፈለገውን ይገልፁለታል
👍131
እኔና ተካ ስንገባ ጀምሺድ አንድ ታሪክ ጀምሮላቸው ኖሮ፣
ጨብጠናው ቁጭ ካልን በኋላ እንደገና ጀምርልን አሉት፡፡
ስብርብር እንቅሽቅሽ ባለ ፈረንሳይኛ ጀመረ። ሁለት አንካሳ አረፍተ ነገር ያህል እንደተናገረ ቃል ይጠፋዋል። በፋርስ ቋንቋ ባህራምን ይጠይቃል። ባህራም ፈረንሳይኛውን ቃል ይነግረዋል። ጀምስድ ታሪኩን ይቀጥላል።

«ከአስራ ሶስት ወር በፊት አለ ጀምሺድ «እኔና ሆዚ ከኢራን
እንመጣለን፡፡ ወደ ፓሪስ፡ ሆዚ ፈረንሳይኛ አይችል። አንዳች
በፍፁም እኔ ግን 'ዊ-ዊ' ማለት እችላለሁ። ደሞ 'ሜርሲ ቦኩ'
አውቃለሁ:: ግን ሜርሲ ቦኩ አልልም 'መርሳ ባኩ እላለሁ።
እኔና ሆዚ ሀሳብ፣ ሶርቦን ዩኒቨርሲቲ ለመማር፡፡ ለመማር
መመዝገብ። ለመመዝገብ ሶርቦን መሄድ። ሶርቦን ለመሄድ ሜትሮ
መግባት። (ሜትሮ ፓሪስ ውስጥ ከምድር ስር የሚሄድ የህዝብ
ማመላለሻ ባቡር ነው)

ጧት በሁለት ሰአት ሜትሮ ገባን። ሆዚ ፈረንሳይኛ አያውቅም፡፡
እኔ ግን ፈረንሳዮቹን፣ የትኛቸው ባቡር እንሳፈረው? ብዬ ጠየቅኩ፡፡
በቃላት አይደለም፤ በእጅ፣ በራስና በድምፅ። በምልክት፡፡ ዠ ቨ ቩ
ቪ! ቫም! ቩም!! » ይለናል።
ሆዚ ዝም ይላል። ፈረንሳይኛ
አያውቅ። እኔ ግን 'ዊ ዊ! መርስ ባኩ' ይላል እላለሁ ማለቱ
ማለቴ። እኔና ሆዚ አንድ ባቡር መሳፈር ሲቆም መውረድ። ሌላ
ባቡር መሳፈር። እንደዚህ በመሳፈር የምሳ ሰአት ማለፍ። ፈረንሳዮች እንጠይቃለን። ዥ ቨ ቩ ቪ ቫም! ቪም!” ይሉናል፡፡ ሆዚ ዝም እኔ 'ዊ ዊ! መርስ ባኩ!'። መሬት ውስጥ ገብተን መምሽት።
አሁን ወደ ሆቴላችን። ሌላ ባቡር። ሌላ ባቡር። ሌላ ባቡር። ሆዚ
ድካም፣ ራብ፣ ብስጭት እምባ እኔ የሆዚ እምባ ያሳዝነኛል። እኔ
እምባ! ሁለት ጎረምሶች ሜትሮ ውስጥ እምባ!!

«አንዲት አሮጊት መምጣት። ታየናለች። ዠ ቨ ቩ ቪ?
ትለናለች። ሆዚ ፈረንሳይኛ አያውቅ። ዝም፡፡ እምባ ብቻ። አኔ 'ዊ ማዳም፣ መርስ ባኩ!! አሮጊት ሆዚን ማቀፍ፣ ማልቀስ። ሶስታችን
ተቃቅፈን ማልቀስ፡፡ በኋላ እኔ አሮጊትን 'መርስ ባኩ ማዴም' ብሎ
መሳም፡፡ እሷ ሀዚን 'አሙር ቦኩ ብላ መሳም

እኔና ሆዚ ከሜትሮ መውጣት። በታክሲ ወደ ሆቴላችን። ዋጋ
አስራ ሰባት ፍራንክ

«በነገ በንጋት ከሌላ የኢራን ልጅ ጋር ወደ ሶርቦን። በሜትሮ ባንድ አፍታ ከተፍ!»

ጀምሺድና ሆዚ ሰትት ብለው ወደ አንድ ትልቅ ቢሮ ገቡ።የፕሬዚዳንቱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሲረግጡት ስምጥ የሚል ምንጣፍ ወለሉን በሞላ ሸፍኖታል። ከሰፊው ዴስክ በስተኋላ ተቀምጦ ፒፓ ያጨስ የነበረው መላጣ ባለትልቅ ሙስታሽ ሽማግሌ ዘሎ መጥቶ
እስኪቀመጡ እንኳ ሳይጠብቅ፣ ከጠረጴዛው ወደሰሩ፣ ከበሩ ወደ
ጨበጣቸውና፣ በእጁ መቀመጫ ሶፋ አመልክቷቸው ሲያበቃ፣
መስኮቱ፣ ከመስኮቱ ወደ ጠረጴዛው እየነጠረ መለፍለፍ ጀመረ።ይለፈልፍ ይለፈልፍና ቆም ይላል። Nest ce pas? (አይደለምን) ብሎ ፒፓውን እየማገ በመነፅሩ ሲያያቸው፣ ጀምሺድ ልክ ንግግሩኛ ቁም
ነገሩ እንደገባው ሰው ራሱን እየነቀነቀ

ዊ! ዊ!» ይለዋል

ሽማግሌው መነፅሩንና መላጣውን እያብለጨለጨ መለፍለፉንና እንደ ፈጣን ባቡር እየተዘዋወረ የፒፓውን ትምባሆ ቡልቅ ቡልቅ ማድረጉን ይቀጥላል። አልፎ ኣልፎ ቆም ይልና እያያቸው «Nest ce
pas?» ሲል፡ አሁንም ጀምሺድ ራሱን እየነቀነቀ «ዊ! ዊ!» ይለዋል፡፡አንድ እስር ደቂቃ ከተዘዋወረኛ ካለፈለፈ በኋላ፣ እሁንም «Nest ce pas?» ብሎ ፒፓውን እያቦነነ ሲያያቸው! ጀምሺድ እንደ ደምቡ
ዊ! ዊ!» አለው፡፡

«Comment oui?» («እንዴት ማለት አዎን?») ብሎ ጮኸበት
ኖ!» ማለት ነበረበት። ጄምስድ ተደናግጦ
ኖ! ዊ! ኖ! መርስ ባኩ! ዊ?» እያለ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣
ከኪሱ የሲጋራ ፓኮ አውጥቶ ጋበዘው። ሽማግሌው በሀይል እየጮኸ ፒፓውን ከአፉ አወጣና ጀምሺድ አፍንጫ ስር ደቀነው፡፡ ጀምሺድና ሆዚ ከዚያ የሮጡ፣ ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ሲወጡ ቆሙ

«ሩጫችንን ጨርሰን ቆመን፡፡ ያን ጊዜ ፒፓው ገማኝ» አለ
ጀምሺድ ለካ በድንጋጤው የሽማግሌውን ፒፓ መንጭቆ ይዞ ሽሽቶ ኖሯል። ፒፓውን ሊሰጡት ቢሮው ተመልሰው ሲገቡ፣ ሽማግሌው እንደ ቡድህ እግሮቹን ከስሩ አጣጥፎ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል።ፊቱ ወደ መስኮቱ በኩል ስለሆነ ሲገቡ አላያቸውም። ለጣኦት እንደሚቀርብ የሰለት ስጦታ ፒፓውን እግሮቹ አጠገብ
አስቀመጡለትና፣ እንዳይቀሰቅሱት በእግራቸው ጫፍ እየረገጡ ወጡ ሆዚ እገሩ ተመለሰ፡፡ ጀምሺድ ወደ ኤክስ መጣ ጀምሺድ ሌላ ብዙ የደረሰበትን ኮሚክ ነገር በኮሚክ ድምፁና በብልጮ ሰማያዊ አይኖቹ፣ በእጆቹና በእግሮቹ ትንሽ ትንሽ ደሞ በፈረንሳይኛው ሲያወራልን ስንስቅ ቆየን። ሶስት ሰአት ሲሆን
ኣብዛኛዎቹ ወደ ሲኒማ ሄዱ። እኔ ባህራምን ወደ ካፌ ሰንትራ
ወሰድኩት ከሰንትራ ፊት ለፊት ወዳለው «ሲኒማ ካዚኖ» ለመግባት ሰዎቹ ቲኬት ሲያስቆርጡ እያየናቸው ቀዝቃዛ ቢራ ካዘዝን በኋላ

“Alors, comment vas tu?» (ታዲያስ እንደምነህ?») አልኩት ያው እንደድሮው ቀልደኛ ነው፡ ቡናማ ትንንሽ አይኖቹ
ይስቃሉ፡፡ ግን ከስቷል፣ ጉንጮቹ ጎድጉደዋል፡ አፍንጫው ከድሮው
የባሰ ትልቅ መስሏል፡፡ በጣም ጥቁር ፀጉሩ ከጎንና ከጎኑ - አልፎ
አልፎ - አንዳንድ ሽበት ማውጣት ጀምሯል፡፡ ደህና ነኝ አለ ግን
እየለመደኝ ከሄደ በኋላና ሶስተኛ ጠርሙስ ቢራችንን ከጠጣን በኋላ
ሊነግረኝ ጀመረ

«ቤቶችህ ፃፉልሀ?» አልኩት
«የለም»
ታድያ የእረፍት ጊዜውን እንዴት አሳለፍከው?» አልኩት።
ሲልቪ ልብሷን ስታወልቅ ታየችኝ። በልዩ ጥንቃቄ የተቀረፁ ውብ
እግሮቿ ሀሳቤ ውስጥ ድቅን አለብኝ። ውስጤ ሙቀት ተሰማኝ::
እስክትመለስልኝ ቸኮልኩ። እንደት ያለ ግሩም የእረፍት ጊዜ
ነበር! የባህራም የእረፍት ጊዜ ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነበር
እኔ ሲልቪን ተከትዬ በሄድኩ በሳምንቱ፣ ኒኮል ለእረፍቱ ወደ
ቤቷ ስትሄድ (ቤቶቿ ሰሜን ፈረንሳይ ለሀቭር የተባለው ወደብ
ከተማ ውስጥ ነው የሚኖሩት) ጥቂት ፍራንክ ልትተውለት ፈለገች።ግድ የለም አያስፈልገኝም፤ ቤቶቹ ካሁን ካሁን ይልኩልኝ ይሆናል፣
ሳይልኩልኝም ስራ መያዜ ነው አላት፡፡ ስራውን እስከትይዝ ምን
ትበላለህ? ቤቶችህ ባይልኩልህስ? አለችው:: እምቢ በማለቱ አፈረ።ተቀበለ፡፡ በመቀበሉ የባሰውን አፈረ

ከኒኮል ቀጥሎ ሀበሾቹ ሄዱ፡፡ ብቻውን ቀረ፡፡ ስራ ፍለጋ
ጀመረ፡፡ ኒኮል የተወችለት ፍራንክ እንዳለቀ ከሷ ደብዳቤ ደረሰው።
አንድ መቶ ፍራንክ ልላክልህ ወይ አለችው:: አትላኪልኝ፡
አያስፈልገኝም ብሎ ፃፈላት
ይርበው ጀመር። ምግብ ቤቱ ሰፈር ይዞራል፡፡ ምናልባት
በሁለት በሶስት ቀን የሚያበላው ሰው ያገኛል። (በዚያውም ሲጋራ
ይጋብዙታል) ያን ጊዜ ከምግብ ቤቱ ዳቦ በኪሱ ይዞ ይወጣል። ዳቦው በበጋው ሙቀት ቶሎ ይደርቃል። ደረቁን ዳቦ በሻይ እየነከረ ይበላል። ያለስኳር፡ ስኳሩ አልቋል፡፡ ሻይ ቅጠሉም ወደ ማለቁ ነው።ያንኑ ቅጠል አምስት ስድስት ጊዜ ያፈላል። ቅጠሉ ይቀቀልና የሻይ ቃናው ጠፍቶ ሌላ አስቀያሚ ብረት ብረት የሚል ጣእም ይሰጣል

በምግብ ሰአት ባህራም ምግብ ቤቱ አጠገብ ይዞራል። በሶስት
👍191🔥1
ቀን አንድ ጊዜ ያህል አንዱ ምሳ ወይም እራት ይጋብዘዋል። በሶስት
ቀን አንድ ሙሉ ምግብ ማግኘቱም ድንገት ተቋረጠ። የምግብ ቤቱ ሰራተኛች የአመት እረፍታቸውን እንዲያገኙ ተብሎ ምግብ ቤቱ ለአንድ ወር ተዘጋ፡፡ እንግዲህ ወዴት ይሂድ?
አንድ የዘይት ፋብሪካ ውስጥ፣ እቃ መኪና ላይ መጫንና ማውረድ፣ እና ይህን የመሳሰለ የጉልበት ስራ አለ አሉት። ግን ስራው ካ'ንድ ሳምንት በፊት አይጀመርም፡፡ እስከዚያው ምን ይብላ?
ጨነቀው፡፡ የሲጋራ ጥምም በበኩሉ የመፍዘዝ ስሜት ያሳድርበታል።ብዙ ምግብ እንዳያስፈልገው በማለት አልጋው ላይ ተጋድሞ መዋል

ደረቅ ዳቦ በጠነዛ ሻይ ከበላ ሁለት ቀን አለፈው፡፡ ራብ
ሲገድለኝ እንዴት ዝም ብዬ ልተኛ? ብሎ ከቤቱ ወጣ። በተስፋ
ሳይሆን እንደዚሁ ወጣ: ትንሽ እንደሄደ ቆሻሻ መጣያ አጠገብ
የወደቀ የሰርዲን ቆርቆሮ አገኘ፡፡ በደህና ቀን ሰርዲን በጣም ይጠ
ላል፡፡ አሁን ግን ቤቱ ወስዶ እየተንገበገበ ከፈተው። ዘይቱ አላስበላ አለው። ዳቦ ቢያገኝ ዳቦ መግዣ ፍራንክ ፍለጋ ቤቱን ይበረብር ጀመር። አልጋው ስር፣ መፃህፍቱ መካከል፣ ኪሶቹ ውስጥ፤ የተወሻሽቁ የተረሱ ሳንቲሞች አገኘ። ለዳቦ መግዣ ሶስት ሳንቲም ጎደለው: ግን ሲበረብር አንድ እንደ ድንጋይ የደረቀ ቁራጭ ዳቦ አግኝቶ ነበር። እሱን ውሀ ውስጥ ነከረው:: ሲርስ ከውሀው አውጥቶ
ከሰርዲኑ ጋር ፈተፈተው፡፡ በላው፡፡
ትንሽ ቆይቶ ሆዱን አመመው። አቅሰሽለሸው፣ አስታወከው።
ላብ አጠመቀው:: የማስታወኩ ከፍና ዝቅ ያችን የተረፈችውን
ሀይሉን ጨረሰበት ድክም አለው፡፡ አቅሙ ውሀ ሆነ፣ ወደ አልጋው
ሲራመድ ጉልበቱ ከስር ታጠፈ፣ አልወደቀም፣ ቀስ ብሎ ወደ ወለሉ
ወርዶ ተዘረጋ። አይኑን ዘጋ። ትንሽ ቆይቶ ብርድ ብርድ አለው::
እየተንፏቀቀ አልጋው ደረሰ። አንሶሳው ውስጥ ገባ። አይኑን ዘጋ። እንደማዞር አለው:: ራቡ ብቻ አይደለም፡ ሲጋራ ማጣቱም ጭምር ነው። በረደው። በዚህ በጋ ሙቀት? ትኩሳት መሆን አለበት። እናቱ ትዝ አሉት፡፡ አመመህ» ብለው ግምባሩን ሲነኩት፣ አልጋው ዳር ሲያዩት፣ ትራሱን ሲያመቻቹለት፣አስታወሰ። ድንገት ብቸኝነት ተሰማው:: ውስጡ አንድ ድምፅ ብቻዬን ነኝ፣ ማንም የለኝ ማንም አይደርስልኝ!» ብሎ ጮኸ፡፡አሰፈራው። ከውስጡ፣ የድሮ የልጅነት ድምፁ «እማማ!» ብሎ ሲጣራ ተሰማው። «ወይኔ፣ ማበዴ ይሆን እንዴ? አሜሬካኖቹን
ሳላባርር?» ብሎ አሰበ፡፡ የባሰውን ፈራ። ብርድ አንቀጠቀጠው
ጥቅልል ብሎ ተኛ። በቅዠት ህልሙ እናቱ ትልልቅ ለስላሳ ትሬሳ
ላይ አስደግፈውት ሾርባ በማንኪያ ሲያጠጡት፡ አሜሪካኖችና የሻህ
ሰዎች መጥተው ሊያርዱት ሲሉ፣ ሲሸሽ፡ በጫካ በሸለቆ ሲያባርሩትን ሲሮጥ፣ ሲሮጥ፣ ሲሮጥ፣ አልጋው ውስጥ እያቃሰተ ሲገላበጥ፣ በላብ ሲታጠብ፤ በብርድ ሲንቀጠቀጥ አደረ
ጧት በማለዳ ነቃ። ጉልበቱ ትንሽ ተመልሶለታል፡፡ ተነስቶ ወጣ። ከቤቱ ትንሽ ሄድ እንዳለ፣ የወተት መኪኛ መጣና አንድ የምግብ ሽቀጥ ሱቅ ደጃፍ ላይ ሶስት ደርዘን የወተት ጠርሙስ
ኣስቀምጦ ሄደ። ባህራም ሁለቱን ጠርሙስ አንስቶ ወደ ቤቱ
ሲመለስ፣ መንገዱ ዳር አንድ ተገምጦ የተጣለ ፖም አገኘ፡፡
የተጎመጠውን በቢላ ቀርፍ ጥሎ፤ የቀረውን ግማሽ ፖም በውሀ
አጥቦ በልቶ ወተቱን እየጠጣ ዋለ

ሲመሽ ራብ አንገበገበው:: ኩራቱን ክብሩን ረሳ፡፡ አንድ የሚያውቀው ፈረንሳይ ቤት ሄደ። በቀጥታ «በራብ ልሞት ነው። አለው። ፈረንሳዩ ቤቱ አስገባና ጭቅና ከድንች ጥብስ ጋር፣ ስፓጌቲ፣ ሰላጣ፣ ቺዝ፣ ወይን አቀረበለት። ተንገብግቦ አምስት ጉርሻ
ያህል እንደ ጐረሰ ሆዱ ተዘጋ፡፡ እስኪጠግብ ከበላ ሳምንት
አልፎታል፡፡ ራቡ ሊገድለው ነው፣ ከዛሬ በኋላ መቼ ምግብ ሊያገኝ
እንደሚችል አያውቅም፡ አሁን ታዲያ ሆዱ እምቢ አልቀበልም
አለው:: በጣም ተበሳጨ፣ እምባ ተናነቀው፣ እዚያው ራሱን ደፍቶ
ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ፈረንሳዩን እግዜር ይስጥልኝ፣ ይቅርታ
ያድርጉልኝ» ብሎት ወጣና ቤቱ ተመለሰ። ተኛ በማለዳ ተነስቶ ከሌላ የምግብ ሱቅ ደጃፍ ሶስት ጠርሙስ ወተት አንስቶ ወሰደ። ተጋድሞ እሱን እየጠጣ ዋለ። ሌሊት ተቅማጥ ያዘው

ሲነጋ እንደምንም እየተጐተተ ዘይት ፋብሪካው ሄደ። ስራውን
ነገ ትጀምራለክ አሉቴ አለቃው አንዲት አርጀት ያለች ሴትዮ ናት
ሲያያት ፊቷ በጣም ርህሩህ መሰለው:: ችግሩን አጫወታት።
ከደመወዝህ ትከፍለኛለህ ብላ ሃምሳ ፍራንክ አበደረችው። ምግብ ገዝቶ ቤቱ ወሰድ፡፡ ትንሽ ቀማመሰ። ለመጀመሪያ ጊዜም ሲጋራ አጨሰ። ትልቅ እፎይታ ተሰማው፡፡ ተኛ። ነቅቶ እንደገና ትንሽ በላ፣ አንድ ሲጋራ አጨሰ፡፡ ተመልሶ ተኛ። ሲነጋ ደህና ቁርስ
በልቶ፣ አንድ ሲጋራ አጭሶ ወደ ስራው ሄደ፡፡

ከባድ እቃዎችን ከመኪና ማውረድና መኪና ላይ መጫን ነበር ስራው። ለመጀመሪያ ጊዜ እንድ መጠነኛ ሳጥን ከመኪናው አንስቶ ተሽክሞ ወደ ግምጃ ቤቱ ሲወስድ፣ ጥቂት እርምጃ እንደሄደ ጉልበቱ ከስሩ ታጠፈበት። ሳጥኑን ትከሻው ላይ እንደተሸከመ ተምበረከከና! በዚያው ቀስ ብሎ ቁጭ አለ

አሮጊት ብጤ አለቃው መጥታ ሳጥኑን ከላዩ ላይ አነሳችለት።
አፍሮ ቁጭ እንዳለ ቀረ። ውሀ አምጥታ አጠጣችው:: ብርጭቆውን ሲመልስላት፣ በርህሩህ ገፅዋ እስተያየት በጣም እንዳዘነችለት ታወቀው። ለሚቀጥለው አራት ቀን፣ ማለት ጉልበቱ እስኪመለስለት ድረስ፣ ጡንቻ የማያስፈልገው ስራ ሰጠችው፡፡ በኋላ ከባድ እቃዎችን
መሽከም ጀመረ። ትከሻውን ያመዋል፤ ወዝ የሚቆረጥ ይመስለዋል፣ መዳፉ ይላላጣል፣ በበጋው ሙቀት ከባድ እቃ መሸከሙ አንዳንዴ ራሱን
ያዞረዋል። ግን ማታ እራቱን ጥስቅ አርጎ ይበላል፣ ቡና ጠጥቶ
ሲጋራ ያጨሳል። አልጋው ውስጥ ይገባል። ከመቅፅበት እንቅልፍ
ይዞት ጥርግ ይላል

ልክ አራት ሳምንት እንደሰራ ስራው አለቀ። አሰናበቱት፡፡ቅዳሜ ነበር፡፡ ባለውለታ አለቃውን አመስግኖ ሲሰናበታት እራት ጋበዘችው:: ቤቷ አመሽ፡፡ ሲያያት፣ እርጅና አፈፍ ላይ ደርሳለች። ወንድ ካገኘች ብዙ ጊዜ ሳይሆናት አይቀርም፡፡ ከእንግዲህ ማግኘቷንም እንጃ፡ ሲያስብ ጊዜ፣ እሷ ደግ ባትውልለት ኖሮ ይህን ጊዜ በራብ ሞቶ ነበር። ሆን ብሎ ብዙ ወይን ጠጣና ሰከረ። አብሯት
አደረ ስራ ከተውኩ ይኸው ዛሬ አንድ ሳምንት ሆነኝ፡፡ ግን
የተሸከምኩበት አሁንም ትከሻዬን ወገቤን ያመኛል» አለ። ከዚህ
በፊት የጉልበት ስራ ሰርቶ አያውቅም ነበር

«ይሄ ሁሉ ሲሆን ጀምሺድ የት ነበር?» አልኩት

«ሞንቴ ካርሉ»

አታውቅም እንዴ? ቁማርተኛ ነውኮ። ቅዳሜ ቅዳሜ እዚህ
ካዚኖ ነው የሚያመሽው

ከተቀመጥንበት ካፌ ሰንትራ ፊት ለፊት መንገዱን ተሻግሮ
«ሲኒማ ካዚኖ» በብዙ መብራት አሸብርቆ ይታያል። የሲኒማ ህንፃው ቀኝ ጎን ቁማር ቤት ነው። ይኸኔ እዚያ ውስጥ ጥቁር ልብስ የለበሱ ወንዶችና ክቡር ጌጣጌጥ ባንገታቸውና በእጃቸው ያሰሩ ሴቶች የመጠጥ ብርጭቆ ወይም ሲጋራ እንደያዙ አይኖቻቸውን
የሚሽከረከረው ሩሌት ላይ ተክለዋል። የጀምሺድ አይኖችም ሩሌቱ ላይ ተተክለዋል። እንደ ቅድማቸው ሳቅና ቀልድ ይጨፍርባቸው ይሆን? ወይስ ፍዝዝ ብለው ይሆን?

«ባሀራምን ብዙ ይበላል?» አልኩት

«አዎን ይበላል። ግን የበላውን ወስዶ መልሶ ያስበላል። አንድ
ቀን ሰባት ሺ ፍራንክ ሲበላ አይቼዋለሁ። ታድያ እዚያው መልሶ ተበላ።.. እውነተኛ ቁማርተኛ ነው። ማለቴ፣ የሚጫወተው አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ለማድረግ አይደለም: ለቁማር ፍቅር ነው። ከሚያገኘው ገንዘብ የሚያጠፋው ይበልጣል። ከሁለት ወር በፊት ሲነግረኝ፣ ኤክስ ከመጣ ብቻ ሰላሳ ሰባት ሺ ፍራንክ ተበልቷል»

«ገንዘብ ከት ያመጣል?»
«ቤቶቹ በጣም ሀብታም ናቸው»
👍222👏1
ይህን ጊዜ ወደ ውጭ በኩል ስመለከት፣ ተካና አንዲት ግዙፍ
ብጤ ሴት እጅ ለእጅ ተቆላልፈው ሲሄዱ አየሁ። ባህራምን
«ተካ አገኘ እንዴ?» አልኩት
ሳቁን ለመቋጠር እየሞከረ «አዎ። ጀርመን» አለኝ
«እንዴት ያለች ናት?» አልኩት። ቡናማ አይኖቹ ያስቃሉ፣ ግን
ጥርሶቹን አንደምንም ከድኗል
«ከንፈሮቿ በጣም ውብ ናቸው:: እንደ ፅጌሬዳ ናቸው» አለ
«እና?»
አሁንስ ሳቁ እያመለጠው እና ከከንፈሯ በላይ ምን የመሰለ
ጥቁር ሙስታሽ አላት። ለምን እንደማትላጨው አይገባኝም አለ።
መሳቅ ጀመርኩ፡፡ ከኪሱ አንድ ወረቀት አውጥቶ አቀበለኝ፡፡
«ሉልሰገድ ነው ባማርኛ የፃፈልኝ፡፡ የናንተ አገር ምሳሌ ነው:: ጮክ
ብለህ አንብብልኝማ፡፡ ልሰማው እፈልጋለሁ» አለኝ፡፡ አነበብኩለት

«ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል»

እየሳቀ «ምን ማለት ነው? በደምብ አስረዳኝማ» አለኝ፡፡ሳስረዳው የባሰውን ሳቀ:: በመጨረሻ

«ምንድነው የሚያስቅህ?» አልኩት፡፡ እየተንከተከተ

«ምሳሌው ነው የሚያስቀኝ» አለ «በፊት ተካ አፉ ይሽትህ ነበር?»

«አዎን፡፡ ታድያ ይሄ ምኑ ያስቃል?» አልኩት

«ባለሙስታሿ ጀርመን ልጅ አፍንጫዋ አያሽትም!-- ድፍን
ነው!» አለኝ፡፡ ሁለታችንም በሳቅ ተንፈራፈርን፡፡

«እውነትክን ነው ግን?» አልኩት

«ሀለላሴ ሙት!»

ከዚያ እንግዲህ የኩምክና ወሬ መጣ፡፡ አብረን ስንስቅ አመሸን።

💫ይቀጥላል💫
👍151
#ሊሆን_ይችላል !!
:
:
#በአሌክስ_አብርሃም


ለሚስቴ ያለኝ ፍቅር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው የሚሄደው። ችግሩ ፍቅሩ የሚጨምረው
ብቻውን አልነበረም፤ እግር እጅ ከሌለው ቅናት ጋር እንጂ። በእኔ ልብ ውስጥ ፍቅርና ቅናት
እንደመንትያ ልጆች እኩል ነበር የሚያድጉት። እየቆየ ግን የፍቅር አቅም እየኮሰመነ፣ የቅናቴ ጡንቻ
እየፈረጠመ ሄደና ቅናቴ እንደ ምርቃት ቆብ ከነመነሳንሱ በፍቅሬ አናት ላይ በኩራት ጉብ አለ።

አያድርስ ነው! ርኩሳዊ ቅናት የሰይጣን አንዱ ሥራ ሳይሆን ሰይጣን ራሱ ሳይሆን አይቀርም። ሚስቴ መዓዛ ጨዋነቷን አገር ይመሰክርላታል። ግን ምን ዋጋ አለው። የእኔ የባሏ ሆድ ግልፅ ባልሆነ ምከንያት ሻክሯል።

“ምን ስታደርግ አይተሀት ቀናህ?” ብባል መልስ የለኝም። ግን እቀናለሁ። ስቀና እስሳጭባታለሁ።
አንዳንዴ እንደውም ከመሬት ተነስቼ ሁለት-ሦስት ቀን አኮርፋታለሁ፤ ግራ ይገባታል። የምትይዝ የምትጨብጠውን ታጣለች። አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ እየኖርን ስዘጋት የምታደርገውን ነገር ታጣለች። ..ደስ ይለኛል፡፡ ጭንቀቷ ነፍሴን ያረካታል፡፡ አንዳች የመበቀል እርካታ ይሰማኛል። ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠና ቀይ ጉንጯ በርበሬ መስሎ ግራ ተጋብታ ስመለከታት በኩራት ኩፍስ ብዬ በስቃይዋ
እዝናናለሁ!

ብዙ ጊዜ፣ በተለይ ወንዶች በፍቅረኝነት እያሉ ቅናት ያጠቃቸዋል። ያፈቀሯትን ሲያገቡ ግን በቁጥጥራቸው የዋለች መስሎ ስለሚሰማቸው አይቀኑም ሲባል ነበር የሰማሁት። የእኔ ቅናት ግን የተገላቢጦሽ ነው። በፍቅረኝነት እንደነበርንም ይሁን የተጋባን ሰምን አልቀናም ነበር። ለዛም ሳይሆን አይቀርም መዓዛን ብዙም ትኩረት ሰጥቼ የት ገባች፣ የት ወጣች የማልለው። የኋላ ኋላ ግን ቅናት ከነ የልጅ ልጁ ሰፈረብኝ።

የቅናት ትልቁ ችግር የሚቀናበት ሰው እንደሚያስቡት መሆን አለቀመሆኑ ላይ አይደለም። የሚቀናውን ሰው ራሱን በበታችነት ስሜት አጥለቅልቆ ያልሆነውን ማድረጉ እንጂ። መዓዛ ፊልም እየተመለከተች አንዱን የፊልም ተዋናይ ካደነቀች የጨጓራ ሕመሜ ይነሳል። በቃ ስለምቀና፣ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀውን ጎበዝ የፊልም ተዋናይ ማጣጣል እጀምራለሁ። መዓዛ ከተከራከረችኝማ በቃ ሰውነቴ ሁሉ
በብስጭት ይንገበገባል፤ እቀናለሁ !

“ምናባቱ ይሄ ሴታሴት ካሜራ ፊት ጀግና ይመስላል፣ ልክስክስ፣ እዚህ ካዛንችስ መጠጥ ቤት በመጠጥ ቤት፣ ጫት ቤት ለጫት ቤት ሲዞር አይደል የሚውለው!? እሱ ያልተኛቸው ሴተኛ አዳሪዎች የሉም።

“ኧረ አብርሽ በእግዚአብሔር፣ የተከበረ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው…” ትላለች መአዚ።

“አንቺ ስለ እሱ ሕያወት ስታጣሪ ነው የምትውይው? ምን ታውቂያለሽ…”

“እኔማ ምን አውቃለሁ ራሱ ነው በቲቪ ከነሚስቱ ቀርቦ ኢንተርቪው ሲሰጥ ያየሁት።” ትላለች
ጩኸቴ አስደንግጧት።

“እና በቴሌቪዥን ቀርቦ ጠጣለሁ፣ እቅማለሁ፣ ሴት አይተርፈኝም ይበል…?” እልና ሙዓዚ ላይ
አፈጥባታለሁ። መዓዚ በግርምት እየተመለከተችኝ ዝም ትላለች። ፊልም በተከፈተ ቁጥር መዓዛ
የምታደንቀውን ሰው ስዘልፍና ሳጣጥል ፊልሙን በቅጡ ሳናየው ስለሚያልፍ መዓዘ. ቀስ በቀስ
ማድነቋን አቆመች። እኔ ግን መቅናቴን አላቆምኩም። አንዱ ወንድ ተዋናይ በተናገረው ነገር ከሳቀች ወይም በመደነቅ ራሷን ከነቀነቀች ቅናቴ ያስለፈልፈኛል፤ እነዚህ የጠላ ቤትና የጫት ቤት ቀልድ እያመጡ ይቀባጥራሉ፤…አይ የኢትዮጵያ ፊልም እንዲህ የዱርዬ መናኸሪያ ሆኖ ይቅር…! ምን የፊልም ኢንዱስትሪ ነው፣ የዱርዬ፣ የሥራ ፈት ኢንዱስትሪ ቢሉት ይሻላል።”

ይሄ ባህሪዬ ሲያስመርራት መዓዚ ከእኔ ጋር ፊልም ማየት አቆመች፡፡ በፊት ፊልምሲከፈት ተንደርድራ
መጥታ ጎኔ ትቀመጥና ራሷን ትከሻዬ ላይ ዘንበል አድርጋ ነበር የምትመለከተው። የሚያስቅ ነገር
ስትመለከት አንገቴ ሥር ገብታ ፍርፍር ብላ ትስቅ ነበር። ዕድሜ ለቅናቴ! ይሄው ፊልም ከእኔ ጋር
ማየት አቆመችና አረፈችው። ፊልም ሲከፈት ወይ ጓዳ ገብታ ትንጎዳጉዳለች፣ ወይ መኝታ ቤት ትገባና ትተኛለች፣ ወይም ታነባለች፡፡

“ፊልም አታይም እንዴ?” እላታለሁ።

"ይቼዋለሁ።”

“የት አየሽሁ?”

"ባለፈው እማዬጋ የሄድኩ ጊዜ።"

"እማዬ ቴሌቪዥናቸው ተበላሸ አላልሽም…?”

“ሌላ ገዛች።”

“ማን "ገዛላቸው?”

"ኧረ አብርሽ በእግዚአብሔር አታጨናንቃኝ” ትልና በምሬት ታየኛለች። በቃ እናቷ ቤት አይደለም ያየችው …. የሆነ ወንድ ጋር ትክሻው ላይ ራሷን ጣል አድርጋ (በየመሀሉም እየተሳሳሙም ሊሆን ይችላል)፣
በቃ እንደዛ ነው ያየችው፣ … ልክስክስ ውይ ሴቶች ! እብሰለሰላለሁ፡፡ ትከሻውን የተደገፈችው ወንድ ማን ይሆን…? ምናልባት አብረውም ተኝተው ሊሆን ይችላል፤ አብራ ፌልም ለማየት ያልተመለሰች
እሺ ለእናቷ ማን ቴሌቪዥን ገዛላቸው? ይሄው ታሪኩ ሲገጣጠም መዓዛ ሀብታም ወንድ ጋር ሄደች…፣ ቤቱ ሄደው ፊልም አብረው አዩ፣ (ሶፋ ላይ አብረው ተቀምጠው፣ ጫማዋን አውልቃ፣ የሚያማምሩ እግሮቿን ሶፋው ላይ ሰብስባ አስቀምጣ፣ ልክ እንደ ቤቷ ዘና ብላ….)፣ ከዛ አብረው መኝታ ቤት ገቡ …፣ ኧረ ሶፋውን ማን ይዞባቸው ከዛ ነፍሳቸው መለስ ሲል አወሩ፣

ፊልም ትወጂያለሽ የኔ ቆንጆ ሊላት ይችላል፣ ግን “የኔ ማር" ነው የሚላት፣

“በ.ጣ.ም!!” ትለዋለች ደረቱ ላይ ተለጥፉ! ይቺ መዥገር። ሁለቱም መዥገር ናቸው እንጂ እሷም እሱ
ላይ እሱም ትዳራ ላይ የተጣበቁ መዥገሮች!!

"እና በየቀኑ ትመለክቻለ?”

"በፊት ነበር፤ አሁን ባሌ እየተነዛዘነዘ በየት በኩል ሊያሳየኝ ብለህ።”

"ኦ..ባልሽ ግን ምናይነት ደደብ ቅል ራስ ነው ባክሽ። ሙቪ እያያችሁ ይነዛነዛል ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አሜዚንግ !

በጣ…ም…! ምን ቅል ብቻ፡ ድንጋይ …! ባልጩት ራስ ነገር ነው እንጂ። ሲጋባ ሲዉጣ መነዛነዝ ነው።
እንዳልተሳካላት ተዋናይ ያየውን ተዋናይ ሁሉ ምዠመዝለፍ ነው ስራው” ትለዋለች::

እሷን ባፈቀርናት፣ ቤቴን ትዳሬን ባልኩ የማንም ዱርዬ ጋር ስታማኝ አያበሳጭም? (ውስጤ ይብከነክናል፤) ላብ ላብ ይለኛል! በላብ የጨቀየ መዳፌን በእልህ ጨብጬ ሶፋውን በቡጢ እነርተዋል መዓዛ በድንጋጤ ከራማዋ ተገፍፎ እያማተበች ትቀርበኝና ጭንቀት በወረረው ፊቷ ላይ እንባ በቋጠሩ ዓይኖቿ እየተመለከተቸኝ፣

“ምነው ፍቅር ምን ሆንክ? ከሰው ጋር ተጣላህ እንዴ? ላብ በላብ ሆንክ እኮ፧ አመመህ እንዴ የኔ
ፍቅር…?” ጉንጬ ላይ እጇን ልታሳርፍ ስትልክ እጇን ወደዛ አሽቀንጥሬ ተነስቼ ወደ መኝታ ቤቴ እገባና የቁም ቅዠቴን ተኝቼ እቀጥላለሁ፡ እሷም ግራ በመጋባት ወገቧን ይዛ መኝታ ቤት በር ላይ ቆማ ትቆያለች፣ “ምን እዳ ገባሁ!” እያለች።

እቀናለሁ…. እቀናለሁ ! እቀናለሁ ! አንዳንዴማ በህልሜ ሁሉ ስለምቃዥ መዓዛ ፀበል እንሂድ
ትለኛለች። ቢመቻት እብድ ነው ብላ አማኑኤል አሳሰራኝ ዓለሟን ከሌላ ወንድ ጋር ልትቀጭ
እንዳሰበች እጠረጥራለሁ… ተገኝቶ ነው ?አሁን ሌላ ወንድ ጋር ብትሄድ ሰው እያስቀምጣትም፣ እስኪ ምን አጥታ ጥጋብ ልክስክስነት እኝጂ ቱ ይሄን የመሰለ ሸበላ የጠገበ ደመውዝ የሚያበላ ባል ትታ …ወይ ጥጋብ ይላታል .. ካበድኩላት ግን እንዳሻት ትዘላለች ሰውም አይቃወማትም ምን ታድርግ
እብድ ጋር ትኑር እንዴ ታዲያ? ወጣት ናት! ቆንጆ ናት! ስንት ነገር ያምራታል! ምን አልባት…” ሊሉ
ይችላሉ። እኔ ደግሞ ለእልኳ አላብድ ሲያምራት ይቅር!!
👍45
ሌላ ቀን ደማቅ ሰማያዊ ሹራብ በቢጫ ሱሪ ለብሼ ልወጣ ስል፣ ኧረ አብርሽ አብሮ አይሄድም!
ሱሪውን ቀይረው የኔ ቆንጆ፤ ፊትህ ጥቁር ቢሆን እንኳን ያምርብህ ነበር፤ ካንተ ጋር ግን አይሄድም።”
ብላ በሳቅ ፍርስ አለች።ቆይ እሷ ስለወንድ አለባበስ እንዴት አወቀች? ይሄ ስለ ልብስ ቀለም ሳይሆን ስለእኔ ምርጫ አለማወቅ ለመናገር ሆነ ብላ የተናገረችው ነገር መሆን አለበት. እንዳልሰማ ሰው ትቻት ወጣሁ! እዛ ላስቀመጠችው ለእናቷ ቴሌቪዥን ለሚገዛው ደደብ ውሽማዋ ትንገረው … ምናልባት
ጥቁር ሊሆን ይችላል … ትቻት ወጣሁ። ለምን እንደሆነ እንጃ እንደማላከበራት ማሳየት እፈልጋለሁ።

አላለቀም
👍18👎31
#ሊሆን_ይችላል


#በአሌክስ_አብርሃም (መጨረሻው)

...ትቻት ወጣሁ። ለምን እንደሆነ እንጃ እንደማላከበራት ማሳየት እፈልጋለሁ።
በር ላይ አንድ የማልወደው ጎረቤቴ ደረቱን ገልብጦ በጠዋቱ በፓክ አውትና በቁምጣ ኮንዶሚኒየም ደረጃ ላይ እገኘሁት። እኔ ስወርድ እሱ ሲወጣ ነበር የተገናንነው፡፡ በእጁ የመዝለያ ገመድ ይዟል፤
ከስፖርት እየተመለሰ ነው።

“ሰላም አብርሽ!” አለኝ በፈገግታ።

"ሰላም ሰለሞን!” ብዬው ላልፍ ስል፣

“ምነው ይሄ አለባበስህ ትንሽ አልደመቀም…?” አለና ፈገግ አለ። ቀልዶ ምቷል ለዛ ቢስ ለካፌ ሁላ!!
እንዳልሰማሁ አለፍኩት። ጣሳ ራስ እሱ ስለኔ አለባበስ ምን አገባው!? ይሄ ቦዘኔ ጎረቤቴ ሥራው ምን እንደሆነ እንጃለት (ሥራ እንኳን ያለው አይመስለኝም) ሁልጊዜ የምንጋራው በረንዳ ላይ ወንበር
ያወጣና ዝሆኔ የያዘው የሚመስል (ፈርጣማ ይሉታል አንዳንዶች) ጠብደል ግንዲላ እግሩን ዘርግቶ
ጋዜጣ ያነባል። ኑሮው ዘና ያለ ነው።አንዳንዴ ውድ የሆነ ሙሉ ልብሱን ይለብስና ዲ ኤክስ መኪናውን አስነስቶ ይሄዳል … አፍታ ሳይቆይ ያመለሳል፡፡ ቤቱ ውስጥ የቀበረው ነገር ሳይኖር አይቀርም፤ ከቤቱ ርቆ አይሄድም፡፡ ይዞት ይሂድና! ቆይ ግን ቤት እየዋለ እንዲህ ተዝናንቶ የሚውልበትን ገንዘብ ከየት
አባቱ ነው የሚያመጣው። ሌባ ይሆን…? ወይንስ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ …?

ድንገት አንድ ሐሳብ እእምሮዬ ውስጥ ፈነዳና ቀጥ ብዬ ቆምኩ፤ ፋጭጭጭጭጭጭጭ እንደ
መኪና አቋቋሜ ድንገተኛ ስለነበር ከኋላዬ የነበረች ልጅ ልትጋጨኝ ለትንሽ ተረፈች። ቆይ ይሄ ጎረቤቴ
ቤት ሲወል ምን እያደረገ ይውላል? መደዳውን አራት ቤቶች አሉ። ጥግ ላይ የኔ ቤት። መዓዛ ሥራ ስለሌላት ቤት ነው የምትውለው። ቀጥሎ ሁልግዜ ዝግ የሆነው እንደኔ ከርታታው ጎረቤቴ (ፊልድ ነው ሥራው)፤ ቤቱ ሁልግዜ ዝግ ነው፤ የሸረሪት ድር ሁሉ በሩ ላይ ያደራል። ቀጥሎ ይሄ ቦዘኔ አለ። ቦዘኔው
መልኩ ጥቁር ነው፡፡ ልክ እንደ ፊልም የሚስቴ ንግግር በምልሰት ታየኝ፤ “ጥቁር እንኳን ብትሆን…”
ነው ያለችው አይደል?…ቢንጎ !!!

ቦዘኔው ቤት ነው የሚውለው። ምን ቤት እኔ ቤት ልበል እንጂ ! መቼስ በአንድ ዝግ ቤት ዳርና
ዳር ቦዘኔውና ሚስቴ ብቻቸውን ሲውሉ አይነጋገሩም ማለት ዘበት ነው። እንዴ አብረውም ፊልም
ሊመለከቱ ይችላሉ እንጂ። በእኔው ቴሌቪዥን፣ በእኔው ዲቪዲ፣ እኔው ሶፋ ላይ !...
ሊሆን ይችላል !!

ተመልሼ ወደ ቤቴ ሮጥኩ!

ጉድና ጅራት አሉ ! ወይ ድፍረት……!

በቤቴ … በራሴ ቤት … በራሴ አልጋ … በራሴ ብርድ ልብስ … በራሴ እንሶላ … በራሴ ፍራሽ … በራሴ ሚስት በራሴ … ! ባፍጢሜ እስከምደፋ ታጣደፍኩ። ምን ዋጋ አለው እስካሁን ነገር የተበላሸውን !አልጋውን እንደሆነ እኔ ሚስኪኑ እኔ ራሴ እንደ መኪና አሙቄ ትቼለት ወጥቻለሁ። መዓዛንም ቢሆን ሌሊቱን ልታቅፈኝ ስትሞክር በኩርፊያ እጇን እየገፋሁ ጀርባዬን ሰፕቻት በአምሮት አቃጥያት ነው
ትቻት የወጣሁት። በስስ ፒጃማ የሞቀ አልጋ ውስጥ እሳት ሆና ትጠብቀዋለች። በቃ ምን ቸገረው
ቁምጣውን ወለቅ አድርጎ በጠዋቱ ገነት መግባት ነው !!! ጉድ ጉድ ጉድ አሟሙቄ ለሰው። ወይ ነዶ
!! ሮጥኩ! ኮቴ እንደ ክንፍ እየተውለበለበ ወደ ቤቴ … ምን ቤት አለኝ ቤቴ ፈራርሶ ! ሱናሚ አውሎ ነፉስ ከሥር መሠረቱ ቤቴን ነቅሎ የሚጥል ጎርፍ ከጎረቤት አገር !

መንገዱ ረዘመብኝ። የመዓዛ ደረት የተላለጠ ሸንኩርት መስሎ ታየኝ። ጡቶቿ ስስ ፒጃማዋን ወጥረው
ጫፋቸው ባቄላ ባቄላ መስሎ… ቀይ ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ከሥር ተንጋልላ.. የሚያማምሩ እግሮቿ በጠረንገሎው ዙሪያ ተጠምጥመው ታየችኝ። እግሮቿማ ለምን አያምሩ፧ እሾህ አይወጋቸው ጋሬጣ ሎሚ መስለው እንደተቀመጡ ሳይወጡ ሳይወርዱ ቤታቸው። መኝታ ቤታቸው ድረስ ካንድ አይሉ ሁለት ባል ሲመጣላቸው …፤ ያ የገደል ስባሪ የሚያህል ቦዘኔ ጎረቤቴ ከነለቡ፣ ከነጠረኑ አልጋ
ላይ ታየኝ። ምናለ ሻወር እንኳን ቢወሰድ የሰው እልጋ መድፈሩ ካልቀረ ለወጉ ለሥርዓቱ ሰውነቱን
ለቅለቅ ብሎ ቢዳፈር ምናለ! ስራ ውዬ ደክሞኝ ነው የምገባው ለኔስ አያዝኑም? አንሶላ መጋፈፉን
ቢቀማኝ አንሳላ ለብሼ ኩርምት የምልባትን አልጋ ምናለ ቢተውልኝ? ወይ ጭካኔ ! ታየኝ ላቡ እንደማስቲሽ መዓዛ ውብ ሰውነት ላይ ታመርጎ አልለቅም ሲል። ማን ያውቃል የራሴ ሚስት በስሜት እየተስረቀረቀች የኔ ጌታ! ጠረንህ የናርዶስ ሽቶ ነው› እያለችው ይሆናል፤ ፍቅር እንኳን አፍንጫን እእምሮን ይዘጋ የለ!

ሲሆይችላል!!

ደግሞ እንደ አባወራ ቤት አለኝ ብዬ ሶፋ ላይ ተጎልቼ የማላውቀው አገር እሳተ ገሞራ ሲፈነዳ በሐዘን
ከንፈሬን እየመጠጥኩ ቢቢሲ አያለሁ…. የዋህ ኣባወራ እሳቱን ጎረቤት አስቀምጦ እሳተ ጎሞራ በዜና ያያል። እኔን ራሴን ዜና አደረጉኝ፤ ዕድሜ ለሚስቴ፣ እኔን ራሴን ዜና ! ያውም ሰበር ዜና …! ሞራሌንም ቅስሜንም የሚሰባብር የሚያነካካት ሰበር ዜና ! ሞኝ ጋዜጠኛ አለ እዚህ አገር …ቢኖርማ ካሜሬአቸውን ይዘው ከኋላዬ ተከትለውኝ በሮጡ ነበር ! ዝም ብለው ስለግድብ ያውሩ … እዚህ ስንት ሚሊዮን ሜጋ ዋት እሳት ከመኝታ ቤቴ ሲመነጭ መቼ በቁም ነገር ተመለከቱት…!!

ቤት ስደርስ ሰሩ ብርግድ ብሏል…!

እግዚኣ ድፍረት ! ያምናለ በሩን እንኳን መለስ ገርበብ ቢያደርጉት ሰው ባይፈሩ ነፉስ እንኳን አይፈሩም ወይስ የመኝታ ቤቱን በር ቆልፈው ሊሆን ይችላል !!

በተከፈተው በር ተወርውሬ ስገባ መዓዛ “አብርሽዬ ድረስ…" ብላ በእጇ የያዘችውን የዱቄት ሳሙና
በቁሟ ለቀቀችው፤ (ሳትለኝም ደርሼ ነበር እኔማ). ... ዱቄት መስሎ ሳሎኑ ምንጣፍ ላይ ተዘራ። ራቅ ብሎ ሊታጠብ የተዘጋጀ የእኔ የቆሸሸ ልብስ ተከምሯል! በዚህ ሌሊት ልብሴን ልታጥብ እየተዘጋጀች ነበር፤ መዓዛ ! የሐፍረቴን ወደ መኝታ ቤት ገብቼ ኮሜዲኖውን ከፈትኩና የረሳሁትን እቃ የወሰድኩ
መስዬ ተመልሼ ወደ ሥራዬ ሮጥኩ። ትንሽ ሐፍረት ቢሰማኝም አእምሮዬ ውስጥ ግን አንድ ሐሳብ
መጣብኝ ..

መዓዛ ልብስ አጥባ ካሰጣጥቻ በኋላ እስከሚደርቅ ምን ትሠራላች በተሰጣት ልብስ ውስጥ
ጠረንገሎ፤ ጎረቤቴ እየተሽሎከለከ ወደ ቤቴ ሲገባ … በሩ ሲዘጋ … ታየኝ !

ሊሆን ይችላል!

ከሰዓት ከምሠራበት አየር መንገድ ቢሮዬ ሆኜ ለመዓዛ ስልክ ደወልኩላት። አንዴ ጠራ …. 2 3 4
5. የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ አይመልስም? እባክዎ …”

ወይ እባክዎ … ምኑን ተከበርኩት … ምኑን ለአንቱታ በቃሁት… ኮት መልበስ ብቻውን አንቱ አያስብል
ቢሮ ያማረ ወንበር ላይ መጎለት አንቱ እያስብል … ጓዳዬ እየፈረሰ ቤቴ እየተገረሰሰ .… ሦስት ጉልቻ
ያልኩት ትዳሬ ስድስት ጉልቻ እየሆነ ወይ አንቱታ : ሰልኩ ያለው ሳሎን፤ ሚስቴ እሰካሁን መኝታ
ቤት ... ወይም የጠረንገሎው ጎረቤቴ ቤት ትሆናለች … ማን ያንሳው ስልኩን … ዘመድ እንደሌለው ሐዘንተኛ ብቻውን ያልቅስ አንጂ…፤ ብቻውን ስልኩ…!

ስብሰለሰል ስልኬ ጠራ …. መዓዛ ነበረች።

"የት ሄደሽ ነው ስልኩ ይሄን ያህል ሲጠራ…"
"ልብስ ሳጥብ ውዬ አሁን ገና ጨረስኩና ሻወር ገብቼ እኮ ነው…! ከነሳሙናዬ ራቁቴን ነው አሁን የቆምኩት ፍቅር ብታየኝ ሳስቅ…

"ማን አለ?”

“ማን አለ? የት አለች በግርምትና ግራ መጋባት። ያመለጠኝን ጥያቄ አልደገምኩትም፡ መዓዛም ከዛ
በኋላ አላነሳችውም።

ቅናቴ ሲጨምር ልፍስፍስና በራሴ የማልተማመን ሰው ሆንኩ። በፊት በቀላሉ የምሠራውን ነገር ሁሉ
መስራት አልቻልኩም። ቅናት አቅም ያሳጣል። አንድ የማይረባ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር በዙሪያችን ያሉ መልካም ነገሮችን ሁሉ ይጋርድብናል።
👍27
አንድ ቀን ከመዓዛ ጋር ሻይ ቡና እንበል ብለን ውጣንና አምሽተን ስንመለስ እኔ ይዢው የነበረው
የቤት ቁልፍ ጠፋ። ውጭ ቆመን አማራጭ መፈለግ ጀመርን። እኔ ሰብረን እንግባ ስል፣ መዓዚ
ሳይመሽና ታክሲ ሳናጣ እናቷ ቤት ሄደን እንድናድር ሐሳብ አቀረበች። ልሰማት አልፈለግኩም።
ቁልፉን ለመስበር መታገል ጀመርኩ፡፡ ታች አንደኛ ፎቅ ላይ ካሉ 'ጎረታች ቤት' (ለኮንዶሚኒየም የታች ጎረቤቶች የሰጠሁት ስም ነው… ላይ ያሉትን 'ጎረላይ ቤት … ጎን ሰው የለም እንጂ ጎረቤት ይሆን ነበር…) እና ከጎረታች ቤት ቢላዋ፣ ፒንሳ፣ መፍቻ ተውሼ መጣሁና መታገል ጀመርኩ - ወይ ፍንክች በሩ ! መዓዚ ረዥም ጫማ ስላደረገችና ወክ እያደረግን ስለመባን መቆም ደክሟት፣ የለበሰችውም ቀሚስ አጭር ስለነበር ብርጅ እያንሰፈሰፋት ከጎኔ ትንቆራጠጣለች።

አንድ ሰዓት የሚሆን ታግዬ ላብ በላብ ሆኜ እና እጄ ደም አርግዞ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር በሩ ሊከፈት
እንደማይችል ማረጋገጥ ነበር !

“በቃ አይከፈትም!” አልኳት፡፡

“ንግሬህ ነበር እኮ ፍቅር…! በቃ እማማ ጋር እንሂድ” አለችኝ እየተቻኮለች። በዚች ቅፅበት የጠረንገሎው 'ጎረቤት' በር ተከፈተ። በሩ ሲከፈት በበሩ ስፋት ልክ የብርሃን ምንጣፍ በሩ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ላይ ተነጠፈ፡፡ ጠረንገሎው የደረቱን እና የእጆቹን ጡንቻ አጉልቶ የሚያሳይ ጉርድ ቲ ሸርት ከቁምጤ ጋር ለብሶ ብቅ አለ።

የብርሃን ምንጣፉ ላይ ቆሞ ወደ እኛ አየት አደረገና፣

“ደህና አመሻችሁ አብርሽ፡” አለ። እሱን ሳይ እልሄ ከየት መጣ ሳልሰው ከንበል አለብኝ። ለሰላምታው መልስ ሳልሰጥ ኮቴን አውልቄ ያዥ.…. አልኳትና ቢላውን አንስቼ ቁልፉን መጎርጎር ጀመርኩ።

“ሰላም አመሸህ አቶ ሰለሞን፡፡ ቁልፍ፡ ጠፍቶብን ለመከፈት እየታገልን ነው ይሄውልህ” አለች መዓዛ።ምን አስለፈለፋት…።

እየተንጎራደደ መጥቶ አጠገባቻን ሲቆም ጥላው ከበደኝ።

አያያዜን ትንሽ ተመለከተና፣ “እስኪ መፍቻዋን ስጭኝ ...” ብሎ ከመዓዛ ተቀበለ።

እንዳቀረቀርኩ ገመትኩ ….

መፍቻውን ስትሰጠው እጆቻቸው ተነካክተዋል … ዓይኗን ዓይኑ ላይ ተከላ ፈገግ ብሳም ሊሆን
ይችላል። እጁ ሲነካት ብርድ ላይ ያመሸ ሰውነቷ በደስታ ተፍታትቶ ሙቀት በሙቀት ሆናም ሊሆን
ይችላል ... 'በዚህ ብርድ ይሄ ደፍዳፋ ባሌ ድራሹ ጠፍቶ አንተ ቤት ገብቼ እቅፍ ብታደርገኝ የሚል መልእክት በዓይኖቿ ልትነግረው ትችላለች፤ እሱም በጉርድ ቀሚስ ያልተሸፈኑትን ውብ እግሮቿን ተስገብግቦ እየተመለከተ ይሆናል ፤ እግሮቿን ሲስማቸው፦ እያለመስ እንደሆን ማን ያውቃል?

“አብርሽ አንዴ ልሞክረው እሰኪ…” አለኝ ወደ በሩ ጠጋ ብሎ።

“አይ አይከፈትም፤ ሞከርኩትኮ …፤በቃ ነገ በባለሞያ እናስከፍተዋለን። ቁልፉን ቢሮ ረስቼው ሊሆን ይችላል።" ብዬ ቀበጣጠርኩ።

ጠረንገሎው ግን እኔ ስናገር ወደ በሩ ጠጋ ብሎ ጀርባውን ሰጠኝና በሰከንዶች ዕድሜ … ምኑን
እንደነካው እንጃ ቀጭ ብሎ በሩ ተባረገደ። 'ካለበለቤቱ አይነድም እሳቱ' ባለቤት ሆኖበት የለ ቤቱን …ገና ሲነካው ተበረገደ!

ውስጤ በብስጭት፣ በመበለጥ ስሜት በቅናት ተንገበገበ፡፡

መዓዛ በሳቅ እና ደስታ በታጀበው ስርቅርቅ ድምፅ፣ “ኦ እግዚአብሔር ይስጥልን…” አለችው። ይሄ ድምጽዋ ከነፍሷ ስትደሰት ነው፦ ከውስጧ የሚወጣው። ለምሳሌ አግቢኝ ያልኳት ቀን “ኦ ማይ ጋድ ”
ብላለች፤ ከወሲብ በኋላም በጣም ስትደሰት “ኦ ማይ ጋድ ትላለች። አሁንም ይሄው ይሄ ጠረንገሎ
እኔ ያላላሁትን ስለከፈተ ደገመችው።

እባክህ ግባና ሻይ ጠጥተህ ትሄዳለህ' እያለች ትለምነው ጀመረ። ይሄ ጠረንገሎ በሩን ብቻ አይደለም፣የሚስቴንም ልብ ነው የበረገደው፤ ቀናሁ አመሰግናለሁ እንኳን ማለት አልቻልኩም። ገብቼ ወደ መኝታ ቤቴ አመራሁ። በዚህ አያያዛቸው ቀድመው መኝታ ቤቴን ሳይዙብኝ እረፍ ልበል ብዬ…

መዓዛ ሰውየዋን ሽኝታ ወደ መኝታ ቤት መጣችና ፈቷ ተቀያይሮ ፊቴ ቆመች፡፡ ያላየኋት መስዬ
ዓይኖቼን ጨፈንኩ!
“ስማ አብርሽ ! ለምን ይሄን ያህል ባለጌ ትሆናለህ። ሰው ጎረቤቱ ሲረዳው ማመስገኑ ቢቀር እንዲህ
መገላመጥ አለበት…? ለምን እኔንስ ታሳፍረኛለህ…?”

“ምንድነው የረዳን…? የሰው ቤት ቁልፍ ስለፈለቀቀ.? ወሮበላ !! ይሄ እንደውም ልምድ ያለው ቤት
ፈልቃቂ ሳይሆን እይቀርም።”

“ኧረ በእግዚአብሔር ኣብርሽ ሥርዓት ይኑርህ!"

“ሥርዓት አንቺ ነሽ የምታስተምሪኝ? መጀመሪያ ራሰሸ ሥርዓት ይኑርሽ። ሌላውን በሌለሁበት የምታደርጊውን ሁሉ ያላወቅኩ መስዬ ብችለው ጭራሽ የማንንም ቤት ሰርሳሪ እየጠራሽ ቤቴን ማሰበር ጀመርሽ…።”

መዓዛ ትክ ብላ እየተመለከተችኝ በተረጋጋና በሚያስፈራ ድምፅ፣ “ምንድነው በሌለህበት ያደረግኩት? አለችኝ

“አላውቅልሽም ! ልተኛበት !" ብዬ ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ።

“ምንድነው በሌለህበት ያደረግኩት?” ብላ ከበፊቱ ጠንከር ባለ ድምፅ ጠየቀችኝ።

“ቁልፍ ሰባሪ ጓደኛሽን ሂጅና ጠይቂው” አልኳት በእልህ።

በዚህች ቅፅበት በራችን ተንኳኳ። የጎለጎታችብኝ ዓይኗን እንደታጎለጎላ በሩን ልትከፍት ሄደች።

"ረስቼው መፍቻውን ይዤባችሁ ሄድኩ!” ሲል ሰማሁት ጠረንገሎውን።

ምን ትረሳዋለህ ... በየምክንያቱ ዓይንሽን ልይ አትልም !? እላለሁ በውስጤ።

"ውይ መጥቼ እወስደው አልነበር፣ ምን አመላለሰህ?" ስትል ሰማኋት፤ ከበፊቱ ሻከር ባለ ድምፅ፡፡
ይሄን የመዓዚን ድምፅ ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለሁለት ዓመት ትምህርት ሌላ አገር ልሄድ ስትሰናበተኝ እናቴ እንዳላገባት ፊቷ የነጎረችኝ ቀን። ይሄን ድምጿን እፈራዋለሁ። መኝታ ቤቴን ከውስጥ መቀርቀር ከጀለኝ። … ማንን ደስ ይበለው ብዬ!

መዓዛን ጠበቅኳት፤ ወደ መኝታ ቤት አልመጣችም። ቀስ ብዬ ወደ ሳሎን ሄድኩ። ሶፋ ላይ ቁጭ ብሳ
ባዶው ላይ አፍጥጣለች።

ተመልሼ ተኛሁ።

ሌሊት ወደ ዘጠኝ ሰዓት ከእንቅልፌ ስነቃ መዓዛ አሁንም ጎኔ የለችም።

ወደ ሳሎን ሄድኩ፤ ማታ እንዳየኋት ከነልብሷ ከነጫማዋ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ባዶው ላይ አፍጥጣለች።

ተመልሼ ተኛሁ።

ጠዋት ተነስቼ ወደ ሳሎን ሄድኩ። መዓዛ የተተኮሰ ልብስ ፤ ቁርስ አላዘጋጀትልኝም። እዛው ቦታ
በዛው ሁኔታ ተቀምጣ እንቅልፍ ወስዷታል።

እንደተኛች ወጣሁ።

ምን ሲያኮርፍ ፆሙን ያድራል አሉ .…ጠረንገሎው መኪና ማቆሚያው አካባቢ ገመድ ይዘላል።
ቁንጣን ያዘልለውና!

ማታ ወደ ቤት ስመለስ መዓዛ ቤቱን ትታልኝ ሄዳለች። አሁን ቅናት ሙሉ ሆነች። ማሰብ ጀመርኩ …
ሻንጣዋን ይዛ ስትሄድ የሆነ ባለ መኪና አገኛት ቆንጆ ወዴት ነው ልሸኝሽ?” ይላታል፤ ትግባለች፤ …
እያለቀሰች ታሪኳን ትነግረዋለች፣ አቅፎ ያባብላታል…።

መዓዛ ንፁህ አፍቃሪ መሆኗን ባውቅም ሁለት ሰው የሆንኩ እስኪመስለኝ አእምሮዬ የቅናት ቅዠቱን ሊያቆምልኝ አልቻለም።

ልቤ ይገስፀኛል ... ልቤን ገደል ግባ ስለው ነው ድሮም ራሴ ገደል የገባሁት።

መዓዛ አልተመለሰችም። እናቷ ቤት የለችም። ጓደኛም ከእኔ ውጭ አልነበራትምና ማን ጋር ሄጄ
ልጠይቅ …

ሌላ ሰው አግብታ ይሆን እንዴ…? ምናልባት ከእኔ ጋር እያለች ይገናኙ የነበረ ሀብታም ሊሆን ይችላል !
ከሦስት ዓመታት መለያየት በኋላ አየር መንገድ ሥራ ላይ እያለሁ ከሳኡዲ ታፍሰው ከተባረሩ
ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝር መካከል የመዓዛን ስም ተመለከትኩት። ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር ጀምሬ ነበርና ከዚህ በላይ ስለ መዓዛ ማሰብ አልፈለግኩም

ግን አዲሷ ፍቅረኛዬ ዛሬ እንዴት ሳትደውል ቀረች? ….ያ በጸሐፊነዠት የሚያሰራት አስቀያሚ ሀብታም ጋር ????

ሊሆን ይችላል !!

አለቀ
👍37
#ትኩሳት


#ክፍል_አስር


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ምጥ


ባህራም በሰኔ ወር የወደቀውን ፈተና እንደገና ለመፈተን
ማጥናት ጀመረ። የራሱ መኝታ ቤት ያረጀና የከረከሰ ሆኖ፣ ደምበኛ ጠረጴዛና ወምበር የለውም፡፡ እዚያ ማጥናት አልቻለም፡፡የዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍት እየሄደ እንዳያጠና፣ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ውር ውር እያሉ ሀሳቡን ይሰርቁታል። ከቀኙ፣ ከግራው፣ከፊቱ፣ ከኋላው ደሞ አስር፣ አስራ አምስት ፍራንክ ያበደሩት ሰዎች ያዩታል፣ ይከብዱታል። እነሉልሰገድ ቤት ሄዶ እንዳያጠና ወሬና
ጫጫታ ይበዛል። እኔ ቤት እየመጣ ያጠና ጀመር። ከሰአት በኋላ ሲኒማ እሄድለታለሁ፣ ሲያጠና ይውላል። ማታ እፅፋለሁ ወይም አነባለሁ፣ ሲያጠና ወይም የማኦ ትዜ ቱንግን መፃህፍት ሲያነብ ያመሻል፡፡ ጧት ግን ምንም ያህል አይሰራም፡፡ ወሬ እናበዛለን።

ጧት ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ መጥቶ፣ በቀስታ በሩን ከፍቶ
ገብቶ፣ ጠረጴዛው ዘንድ ተቀምጦ ሲሰራ ይቆያል። ስነቃ “Bon jour
እለዋለሁ። Bon jour ብሎኝ ቡና ይጥድና ስራውን ይቀጥላል።
አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ትላንት የፃፍኩትን እመለካከታለሁ፤
አርማለሁ፣ እሰርዛለሁ፣ እቀዳለሁ። ሙሉ ሰአት ሲሆን ባህራም «አንድ ጊዜ ዜና ብንሰማ ይረብሽሀል?» ይለኛል፡፡ (የፈረንሳይ ራዲዮ በየሰአቱ አጫጭር ዜና ያሰራጫል) ራስጌዬ ያለችውን ራዲዮ እከፍታታለሁ። ባህራም ያፈላውን ቡና በዱቄት ወተት እየጠጣን ስለቪየትናም ወሬ እንሰማለን። ቪየትኮንግ የደፈጣ አሜሪካኖቹን አጥቅተዋቸው እንደሆን ባህራም ደስ ይለውና ደስታው
አላስጠና ይለዋል። መናገር ይጀምራል።ቬየትኮጎቹ ድል
ማድረጋቸው አይቀርም ይላል፡፡ ንግግሩ ቀስ ብሎ ወደ ኢራን
ይወሳስደዋል።ስለኢራን ሊነግረኝ ይጀምራል። ስለኢራን፣
ስለኮሙኒዝም፣ ስለማኦ ትዜ ቱንግ፣ ስለአሜሪካን ወራሪነትና
አጥቂነት፣ ስለካፒታሊዝም ስናወራ እንቆይና፡ ሙሉ ሰአት ሲደርስ
እንደገና ራዲዮ እንከፍታለን፡፡ ዜናው ያስደስተዋል ወይም
ያበሳጨዋል። ወሬያችንን እንቀጥላለን። የምሳ ሰአት እስኪደርስ እናወራለን፣ እናወራለን ማለት፣ በአብዛኛው እሱ ሲያወራ እኔ አዳምጠዋለሁ፤ እንዳንድ ጊዜ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ፡፡ የነገረኝን
እያንዳንዱን ማታ ልተኛ ስል አንድ ትልቅዬ ደብተር ውስጥ አሰፍረው ነበር

አሁን ያንን ደብተር ሳነበው ባህራም ይታየኛል፡፡ እኔ አልጋ
ውስጥ ትራስ ተደግፌ ቁጭ ብዬ፡ እሱ በሽተኛ ሊጠይቅ የመጣ
ይመስል አጠገቤ ወምበር ላይ ተቀምጦ፣ በብልህ ቡናማ አይኖቹ
እያየኝ፣ ፀጉራም እጆቹን በብዙ እያንቀሳቀሰ፣ በወፍራም ልዝብ
ድምፁና በተሰባበረ ፈረንሳይኛው ሲያወራልኝ፣ ቁልጭ ብሎ
ይታየኛል

ወሬው አንድ መስመር ይዞ አይሄድም። ኢራን፣ ኒኮል፣
የባህራም ቤተሰብ፣ የባህራም ጓደኞች፣ ፈረንሳዮች፣ ጥቁሮች፣
ወጣት ኮሙኒስቶች የተባለ የኢራን አገር ማህበር፣ ትምህርት
ቤት፣ ሴቶች፣ ቡሽቲዎች፣ ጋዜጠኞች ብቻ ባህራም ያየውንና
የሰማውን ነገር፣ በህይወቱ የደረሰበትን ወይም በሌሎች ላይ
የደረሰባቸውን ነገር አሳዛኝ ነገር፣ አስደሳች ነገር፣ አስቂኝ ነገር፣
የሆነ ነገር ያወራልኝ ነበር፡፡ ስንቱን ብዬ ልናገረው እችላለሁ?
ጥቂቱን ብቻ ባጭሩ ላስፍረው፣ እንደ ባህራም ካንዱ ወደ ሌላው
እየዘለልኩ. እንደሚከተለው...

አሜሪካኖቹ ይወድቃሉ (ይላል ባህራም) ታያለህ፡፡ ስንቱን ህዝብ
ጨቁነው፣ ስንቱን አገር ፈትፍተው፣ ስንቱን መንግስት ገዝተው
ይችላሉ? አንድ ቀን ይወድቃሉ። እንኳን እንደነሱ ያለ ቂል ፈረስ
ይቅርና፣ እንደ እንግሊዝ ያለ ተንኮለኛ ቀበሮም ወድቋል። ተነስቶ ሌሎች ህዝቦችን
ጨቁኖ መውደቅ የሚቀርለት የለም፡፡ “አሜሪካኖችም ይወድቃሉ፡፡ ይወድቃሉ። ታይቶ የማይታወቅ አወዳደቅ ይወድቃሉ። ያን ጊዜ የአለም ህዝቦች እልል ይላሉ።
በአሜሪካ አግር ተረግጠው ደክመው እልል ለማለት ያህል አቅም ያነሳቸው ደሞ እፎይ ይላሉ

አሜሪካኖቹን መጀመሪያ
ሆ ቺ ሚን ከቪየትናም ያባርራቸዋል::ቀጥሎ እነ ማኦ ሴቱንግ ወይም ወራሾቹ ከሩቅ ምስራቅ ያስወጡዋቸዋል፡፡ ቀጥሎ እንግዲህ ማን ከየት እንደሚያስወጣቸው አላውቅም:: ብቻ እርግጠኛ ነኝ ያስወጡዋቸዋል። ይህን የሰው አገር ደም ጠጥቶ የወፈረ ቂጣቸውን በካልቾ እየመቱ “Yanked go home!
And stay honte!' (ያንኪ ወደ አገርህ ግባ እና እዚያው ቅር!»)
እያሉ ያስወጡዋቸዋል። ከሰው እድሜ በላይ በኖርኩ! አሜሪካ
ስትወድቅ ለማየት እንድችል ብቻ

ምን ማለትህ ነው? ለምን አልጠላቸውም? አሜሪካኖችን ያልጠላሁ ማንን ልጠላ ነው የነፃነትን ዋጋ እያወቅኩ፣ የተጨቆነ ህዝቤን እየወደድኩ፣ አሜሪካኖችን ካልጠላሁማ ሰው አይደለሁም ማለት ነው። ድንጋይ ነኝ ማለት ነው አሜሪካኖች አንድ የተቀደሰ ተግባር አላቸው:: ይኸውም፣ እባብ ያንዲትን ወፍ እንቁላል መጦ ጨርሶ ቅል ብቻ እንደሚያስቀርላት፣እነሱም ያንዲትን አገር ሀብት መጠው ጨርሰው፣ አፈርና ድንጋይ
ይተዉላታል። የኔን አገር ውሰድ። ዋና ሀብቷ ነዳጅ (ፔትሮል
ነው። ነዳጁን ከመሬት መጦ የሚወስደው አሜሪካ ነው

አንድ ቀን ሞሳዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ተነሳና የኢራን
ሀብት ለኢራን ህዝብ ነው አለ፡፡ አሜሪካኖቹ ተሳስተሀል አሉት፡፡
በቃል ሳይሆን በተግባር፣ የኢራን ሀብት ለአሚሪካ ነው፣ የኢራን
ሀብት ለኢራን ነው ካልክ ኮሙኒስት ነህ ማለት ነው አሉት።
ሲ.አይ.ኤ ልከው ገለበጡት። ሞሳዴግ ተይዞ ሞት ተፈረደበት። ግን ሽማግሌ በመሆኑ፣ የሞት ፍርዱ ወደ እስራት ተሻሻለለት። አሁንም ታስሯል፡፡ የኢራን ሀብት ለአሜሪካኖቹና ለሻህ ነው ያለ ሰው ግን ይሾማል ያሸለማል። ሻህ ማለት በነሲሩስ፣ በነዳርዩሽና በነኻሻር ያዥ ስመ ጥሩ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ኢራንን የሚጨቁን ጋንግስተር ማለት ነው:: አጋዦች አሉት። ህዝቡ ያረሰውን ለመንጠቅ የእርሻ ሚኒስትር ያግዘዋል። ህዝቡ ሲነግድ ከነጋዴው ለመቀማት የንግድ ሚኒስትር
ያግዘዋል። ለልዩ ልዩ አይነት ጭቆና ልዩ ልዩ ሚኒስትር አለው።
ህዝቡ በደስታ እንዲጨቆን፣ ማለትም ተጨቆንኩ ብሎ
እንዳያጉረምርም፣ ፀጥ የሚያሰኙ ያገር ግዛትና የፍርድ ሚኒስትሮች
አሉት

ያሻህን ሻህ ሚኒስትሮች፣ በተለይም የውጭ ጉዳይና ያገር ግዛት ሚኒስትሮቹ፣ ትእዛዛቸውን በቀጥታ ከዋሽንግተን ይቀበላሉ።
ምክንያቱም ኢራን የአሜሪካ የነዳጅ ማእድን ናት። ደሞ ኢራን
የሩሲያ ጎረቤት ስለሆነች፣ አሜሪካኖች በጣም ለኢራን
ይጠነቀቁላታል። አንድ ገበሬ ብዙ የምትታለብ ላም ብትኖረው
አይጠነቀቅላትም?

ሻህ ማለት ውሻ ነው፡፡ አሜሪካኖቹ ኢራንን አርደው ብልቷን ሲያወጡ እፉ ምራቅ እየሞላ በአይኑ ይከተላቸዋል፣ ሳምባ ወይም
ሌላ ቁራጭ ስጋ ጣል ያረጉለታል። እሱ ደሞ ህዝቡን ጨቁኖ
ይይዝላቸዋል። አየህ፣ ህዝቡ ተጨቁኖ ካልተያዘ፣ እንደ ሞሳዴግ
ተነስቶ የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች ይላል። ስለዚህ አሜሪካኖቹ
ለህዝቡ የማይቆረቆር፣ ጥቂት ሚልዮን ብር ቢሰጡት የሚበቃው፣ ህዝቡን ጨቁኖ የሚይዝላቸው ገዥ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ነው ዙፋኑን
የሚጠብቁለት በሞሳዴግ ጊዜ ረብሻ ተነሳ፡፡ ሽህ ሽሽቶ ከአገር ወጣ።አሚሪካኖች መጥተወ «የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች» የሚሉትን የሞሳዴግ ተከታዮች ፈጅተው፣ በዚያውም ያለ የሌለውን ኮሙኒስት አርደው ጨርሰው፣ አገሩን ጸት ካደረጉ በኋላ፣ ና ወደ ዙፋንህ
ተመለስ አሉት፡፡ ወደ ዙፋኑ ተመለሰ
👍22
ሻህ መሸሽ ልማዱ ነው:: ቴህራን ከተማ ውስጥ አራት ቤት
መንግስት አለው። እና ሁለቱ ውስጥ ለመብረር ዘወትር ዝግጁ የሆኑ ሁለት ኤሮፕላኖች አሉት፡፡ ትንሽ ረብሻ የተነሳ እንደሆነ፣ ወድያው ኤሮፕላኑ ውስጥ ይገባና ካገር ይጠፋል፡፡ ብቻ እሱ ያምልጥ እንጂ፣ ስዊስ፣ አሜሪካ፣ እና ምናልባት ኢንግላንድ ባንኮች ውስጥ ብዙ ሚልዮን ብር ስላለው፣ እንዴት እኖራለሁ ብሎ አይሰጋም እንግዲህ ፡ ይሽሻል። ረብሻው አልፎ ሰላም ሲመለስ፣ ወደ ውድ አገሩ ይመለሳል፣ ለውድ ህዝቡ ንግግር ያደርጋል
አንድ ቀን ግን የሚያስደንቅ ስራ ሰራ። ማለቴ፣ ረብሻ ሲነሳ
አልሸሽም፡፡ አይገርምም? አንተማ ምን ይገርምሀል? ሀለሳሴ ረብሻ
ሲነሳ ወደሀገሩ ይገሰግሳል እንጂ አይሸሽም። የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ
ሻ ሳይሽሽ የቀረ ጊዜ ለህዝቡ በሬዲዮ “ህዝቤ ሆይ! ዛሬም
እረኛችን ትቶን ይሄድ ይሆን? ብለህ አትስጋ:: ዛሬስ እዚችው
እሞታታለሁ እንጂ አልሄድም!» አለ

እዚህ አለም ላይ እንደ ኢራን ተራ ወታደር የመሰለ ጀግና አታገኝም። በጭራሽ አታገኝም። አየህ፣ ጦርነት የተፋፋመ ጊዜ ፣ የኢራን ተራ ወታደር ማንንም ኣይታዘዘ፡፡ በገዛ ራሱ እንዳሰኘው ይዋጋል፡፡ ጄኔራሉንም ሻለቃውም
አይታዘዝ። ምክንያቱም ጄኔራሉም የለ፣ ሻለቃውም የለ። በጦርነት
ጊዜ፣ የኢራን ሰራዊት ተራ ወታደር ብቻ ነው ሚዋጋው የኢራንን ጄኔራሎች የሚመስል የለም::

ከነመለዮዋቸው፤
ከነሊሻናቸው፣ ከነሙስታቸው፣ ከነአስተያየታቸው፣ አቤት ደስ
ማለታቸው! አረማመዳቸው ሲያኮራ! ግርማቸው ሲያስፈራ! እነሱም ይህን ያውቃሉ። መለዮዋቸውንና ሊሻናቸውን በሰላም ጊዜ ፈፅሞ
አያወልቁም፡፡ ጦርነት ሲመጣ
መለዮና ሊሻናቸ አውልቀው፣ የወታደር ሳይሆን የሰላማዊ ሰው ልብስ ይለብሳሉ። ይሄ
እንግዲህ የሴት ልብስ ያጡ እንደሆነ ነው:: የሴት ልብስ ካገኙ ግን፣ እሷን ይለብሱና እልም! ይጠፋሉ፣ በቃ፡፡ ተራው ወታደር ያለ አለቆቹ ይዋጋል ጦርነቱ አልቆ የሰላም ውል ከተፈረመ በኋላ፣ ጄኔራሎቹ መለዮአቸውን ለብሰው፣ ሊሻናቸውን ደርድረው፣ አንድ በአንድ ከተፍ ይላሉ፡፡ በየመፅሄቱ ስለጦርነቱ ይፅፋሉ፡፡ አንዳንዶቹም ሙሉ መፅሀፍ ይደርሳሉ፡፡ ጦርነቱ ላይ እንዴት እንደተዋጉ፣ እንዴት
እንደተከበቡ፣ እንዴት
በጣጥሰው እንደወጡ፣
ወታደራቸው ሁሉ አልቆ እንደተማረኩ፡ እንደታሰሩ፣ ስቃይ አንዳዩ ምናምን ይዘበዝባሉ። ሽህ ውሽታቸውን እንደሆነ ያውቃል። ግን የበለጠ ማእረግና ሊሻን ይሽልማቸዋል:: ሲሞቱ ብሄራዊ የቀብር ስርአት ያውጅላቸዋል፡፡ ይሄ ሁሉ ለምንድነው? ንጉሳቸው ሲሸሽ አርአያውን ተከትለው ስለሸሹ ነው

ግን ያልሸሹ፣ በጀግንነት ተዋግተው፣ ብዙ ተጋድሎን
አድርገው፣ ድልን ያስገኙ አንድ አራት ጀኔራሎች ይኖራሉ። እነሱ
ማእረግም፣ ክብርም፣ ሊሻንም አይጨመርላቸውም፡፡ ስማቸውም
አይጠራም፡፡ ስእላቸው በየጋዜጣው አይወጣም። ወደ ቤተመንግስትም አይጋበዙም። ምክንያቱም ሻ እነሱ እንደሚበልጡት ስለሚገነዘብ፣
እሱ ጋንግስተር ሆኖ እነሱ ግን እውነተኛ ኢራናውያን መሆናቸው
በጣም ስለሚከብደው፣ ሊያያቸው አይፈልግም እንግዲህ ሰላም መጣ፤ አይደለም? ጄኔራሉቹ መለዮዋቸውን ለብሰው፣ ሊሻናቸውን ደርድረውእንደ ውሀ በሚፈስ የአሜሪካን መኪና እየተዘዋወሩ ለህዝቡ ይታያሉ፡፡ ቀን ቀን። ሌሊት ሌሊት
ደሞ ሲበዱ ያድራሉ፡፡ የራሳቸውን ሚስቶች አብዛኛውን ጊዜ ሌላ
ሰው ነው የሚበዳቸው። እነሱ ሚበዱት የሌላ ሰው ሚስት ነው
እኛ ከተማ ውስጥ አንድ ጀኔራል ነበር። ከዋናው ፖሊስ አዛዥ
ጋር ሽርክ ነው:: ታድያ አንድ ግብዣ ላይ ደስ የምትለው ሴት
ሲያይ፣ ለፖሊስ አዛዡ ይነግረዋል፡፡ ፖሊስ አዛዡ የሴትዮዋን ባል ለምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይወስደውና፣ ባልየው ሲመረመር ያድራል። ጄኔራሉ ሂዶ ያችን ሴትዮ ሲበዳት ያድራል። ታዲያ አየህ ከቆሻሻነታቸው የተነሳ ሴትዮዋን እንኳ ወደ ጀኔራሉ ቤት
ወይም ወደ ሌላ ቦታ አይወስዷትም፡፡ እዚያው የባልየው አልጋ ላይ ጄኔራሉ ሲበዳት ያድራል። ምን ይሄ ብቻ? እዚያ ቤት የጄኔራሉ ዘብ ይቆማል። የጀኔራሉ ደስታ የሰው ሚስት በጉልበት መብዳት ብቻ ሳይሆን፣ የባልየውንም ክብር ማዋረድ ነው። ሰውየው ልጆች ይኖሩታል፤ ሽማግሌ ወላጆች ይኖሩታል፣ ከጄኔራል ጋር ለመጋጨት
ያህል ሀይል አይኖረውም። ውርደቱን ውጦ ዝም ይላል

አቤት ኢራን ውስጥ ስንት ሰው አለ ውርደቱን ውጦ ዝም ያለ!
ሞሳድግ እንደ ወደቁ የኢራን ፖሊስ ሰራዊት በሲ.አይ.ኤ ትእዛዝና እርዳታ ኮሚኒስቶችን መፍጀት ጀመረ። ዘዴው እንደዚህ ነበር

የጠረጠሩትን ሰው ይይዙና ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ኮሙኒስት
ነህ?» ይሉታል። አይደለሁም ይላል፡፡ ያሰቃዩታል፡፡ ውስጥ እግሩን በማስመሪያ ይጠፈጥፉታል፡ ጥፍሮቹን አንድ በአንድ ከስር ይነቅሉለታል። ቂጡ ውስጥ እንቁላል ይከቱበታል። ስቃዩ ሲበዛበት ኮሙኒስት ባይሆንም «አዎን፣ ኮሙኒስት ነኝ ይላል። በል አሁን የኮሙኒስት ጓዶችህን ስም ንገረን ይሉታል፡፡ ያሰቃዩታል። እንደ በረዶ የቀዘቀዘ ውሀ ውስጥ ይነከሩትና በአለንጋ ይገርፉታል። እጁን ጠምዝዘው ይሰብሩታል።ጥርሱን ቀጥቅጠው ያወላልቁታል።በመጨረሻ ስቃዩን አይችለውም። ስለዚህ ስም ይሰጣቸዋል።
ኮሙኒስት ከሆነ አውነተኛ ስም ሊነግራቸው ይችላል፡፡ ኮሙኒስት
ካልሆነ ግን የሆነ ስም ይነግራቸዋል፡፡ እነዚያ ስሞች መሀል ያንተ ስም ይገኛል፡፡ ትያዛለህ፡፡ ይሄኔ አንተ ኮሙኒስት አይደለህም እንዲያውም ኮሙኒስት ትጠላለህ። ግን ወስደው «ኮሙኒስት
እስከትል ያሰቃዩሀል። በኋላ፣ ስቃዩ ስለሚበዛብህ አንተም የመጣልህን ስም ትናገራለህ። በዚህ አኳኋን ኮሙኒስቶቹ አለቁ። ኮሙኒስት ያልሆኑም ብዙ ብዙ ታሰሩ፣ ተሰቃዩ፣ በስቃይ ላይ ሞቱ.
መንገድ ላይ አንዱ ሊላውን እየደበደበ «አንተ ውሻ ኮሙኒስት!
አንተ ነህ እኛን ፡ የምትሰድብ? ይለዋል። ሲደበደብ የነበረው
ፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳል። ኮሙኒስት ነኝ እስኪል የተለመደውን ስቃይ ይቀበላል

ግን ይሄ ሁሉ ስቃይ የሚደርስህ ገንዘብ ከሌለህ ብቻ ነው።
ገንዘብ ካለህ ኮሙኒስት ብትሆንም ትድናለህ። እንደታሰርክ አባትህ ወይም ወንድምህ ሄደው ጉቦ ይሰጡልሀል። ፋይልህ ላይ «በስህተት የተያቀ» ተብሎ ይፃፍና አንተ ነፃ ትለቀቃለህ፡፡ መጥፎነቱ፡
አብዛኛዎቹ ኮሙኒስቶች ድሀ ነበሩ
ታስረው ከተፈቱት ጥቂቶች ኣንዱ የደረሰበትን ነገረኝ።

መጀመሪያ ደበደቡት፣ ገረፉት:: ኮሙኒስት ነኝ አለ። በኋላ የሌሎች
ኮሙኒስቶች ስም ተናገር፣ አሉት፡፡ እምቢ አለ። ቀዝቃዛ ውሀ ውስጥ
ነክረው በእለንጋ ገረፉት፡፡ እምቢ አለ። ቂጡ ውስጥ እንቁላል
ጨመሩበት። እምቢ አለ፡፡ ልብሱን በሙሉ አስወለቁና ሁለት እጁን
በገመድ አስረው፣ እግሩ መሬት እንደማይነካ እድርገው ሰቀሉት።
ተንጠለጠለ። ሩብ ኪሎ ብረት አምጥተው ብረቱን በሲባጉ አስረው ከቆለጡ ላይ አንጠለጠሉት። ብረቱ በየደቂቃው ክብደት እየጨመረ
የሚሄድ ይመስል ስቃዩ እያደገ ሄደ። ሀሳቡን ለግማሽ ሰከንድ እንኳ ከቆለጡ ህመም ለማራቅ አልቻለም፡፡ ህይወቱ በሙሉ ቆለጡ ውስጥ ያለ መሰለው። ከግማሽ ሰአት በኋላ ተናገር» አሉት። ዝም አለ ክብደቱ ላይ አስር ግራም ብረት ጨመሩለት። ቀስ እያሉ አምስት አምስት ግራም እየጨመሩ፣ ስቃዩ እየበዛ ጩኸት የእብድ ሰው ይመስል እየቀጠለ፤ እስር ኩዊንታል ብረት ከቆለጡ የተንጠለጠለ እየመሰለው ሲጮህ፣ እነሱ ትንሽ በትንሽ ክብደቱ ላይ እየጨመሩ
👍19
«ተናገር» እያሉት፣ እሱ «አምቢ» ብሎ እየጮኸ፣ ድንገት ህመሙ
ተወው፣ ጭለማ ዋጠው።
ልቡ ሲመለስለት፣ እሱ አሁንም ተሰቅሏል፣ ግን ብሪቱን
ክቆለጡ ላይ አንስተውለታል። ትንሽ ቆየ። መጡ። «
ተናገር» አሉት፡፡ እምቢ አለ። በሲባጎ የታሰሩትን ብረቶች አመጡዋቸው።
ብረቶቹን በአይኑ ሲያይ ብቻ በሀይል ቆለጡን አመመውና ጮኸ «አታሳዩኝ! እናገራለሁ!» አለ፡፡ ፈትተው አወረዱትና ልብሱን
አልብሰው ወደ አለቃቸው በር ወሰዱት። አንጠልጥለው ወሰዱት።
ምክንያቱም ሲራመድ ቆለጡ ትንሽ ሲወዛወዝ ሊገድለው ሆነ። ቢሮ ሲደርስ ለመናገር ዝግጁ ነህ ወይ? ተባለ፡፡ አይደለሁም አለ። ምነው እናገራለሁ ብለህ? አሉት። ስቃዩን ፈርቼ ነው እንጂ፣ የማላውቀውን ከየት አምጥቼ ልናገር? አላቸው

ይህን ጊዜ አንድ ጓደኛው መጣ፡፡ የታሸገ ደብዳቢ ለፖሊስ
አለቃው ሰጠው። አለቅየው ደብዳቤውን አነበበ፡፡ ጓደኝየውን ወደ ልዩ ቢሮ ወሰደው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመለሱ። የፖሊሱ
አለቃ፣ እስረኛውን ወደ ስቃዩ ቦታ ሳይሆን፣ መኝታ ወዳለበት
ክፍል አስወሰደው:: በነጋታው ጓደኛው መጥቶ ወደ ቤት ወሰደው::ፋይሉ ውስጥ እንግዲህ በስህተት የታሰረ ወይም «
ተመርምሮ የተጣራ ኮምኒስት ኣይደለም» ተብሎ ተፅፏል፣ ማለት ነው ልጁ እንዴት ሊፈታ እንደቻለ ገርሞታል። ጓደኛው ድሀ ነው፣
ዘመዶቹ በሙሉ ድሀ ናቸ። ጉቦ ከየት ተገኘ?. . . ታድያ ልጁ
ድሀ ይሁን ኢንጂ፣ የከተማችን ኮሙኒስቶች ሶስተኛ አለቃ ነው።
ኮሙኒስት የሆንን ሁላችን አዋጥተን ነው ጉቦውን የከፈልንለት። ብቻ ካለቆቻችን አንዱን ለማስፈታት ገንዘብ አዋጡ ተባልን እንጂ፣ ማን እንደሆነ አናውቅም (እኔም ከብዙ አመታት በኋላ ነው ያወቅኩት)
አየህ፣ ኮሙኒዝም እንደ ወንጀል የሚቆጠርበት አገር ውስጥ፣
አለቆቻችንን እኛ ሌሎቹ ኮሙኒስቶች አናውቃቸውም፡፡

ሳስረዳህ ኮሙኒስት ፓርቲ በፍራ (cell) ነው ሚሰራው:: ከሁሉ በላይ አንድ «ፍሬ» አለ። ስድስት አባላት አሉት፡፡ ስድስቱ ሰዎች
እያንዳንዳቸው የአንድ ሌላ «ፍሬም አለቃ ናቸው:: የዚህ የሁለተኛው ፍሬ አምስቱም ሌሎች አባላት እያንዳንዳቸው የአንድ ፍሬ
አለቃ ናቸው:: እነዚያ ደሞ ተራቸውን አንዳንድ ፍሬ አላቸው።
አንተ የምታውቀው እንግዲህ ሁለት ፍሬ ብቻ ነው:: የአንድ ፍሬ
አባል ነህ፣ የፍሬው አለቃ ያንተ አለቃ ነው። ሌላው ፍሬ ደሞ
ኣለቃው አንተ ነህ:: አንተ አለቃቸው የሆንክ ሰዎች፣ እያንዳንዳቸው ካንተ በታች የአንድ ፍሬ አለቃ ናቸው። እንዲህ እያለ ይቀጥላል::ገባህ?

ደሞ ኮሙኒስቶቹ ሁሉም የኮድ ስም አላቸው። እርስ በራሳቸው
የሚጠራሩት በኮድ ስማቸው ብቻ ነው:: የእውነት ስማቸው ማን
እንደሆነ አይተዋወቁም። እንዲህ የሆነ እንደሆነ፣ አንተ ብትያዝ፣
እና ፈሪ ብትሆን፣ እና ስቃዩን ፈርተህ መናገር ብትፈልግ፣
ለፖሊሶቹ የምትነግራቸው የኮሙኒስቶቹን የኮድ ስም ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም የእውነት ስማቸውን አታውቅም፡፡ ይህም ሲሆን፣ የአንድ «ፍሬ»። አባሎች አንድ ሁለቱ ያንድ ሰፈር ወይም ያንድ ትምህርት ቤት ልጆች ስለሚሆኑ፣ የእውነት ስማቸውን ይተዋወቃሉ። ይህም
ፖሊሶቹን ይረዳቸዋል።

ኮሙኒስት ፓርቲ አንድ ነገር ለማድረግ ሲወስን፣ ውሳኔው
ከላይ ወደ ታች፣ ከፍሬ ወደ ፍሬ ይተሳለፋል። አንድ ሀሳብ ታች
ሲፈጠር፣ ከታች ወደ ላይ ከፍሬ ወደ ፍሬ ይተላለፋል

የኔ የፍሬ አለቃ ኣንድ ቀጭን፣ መነፅር የሚያደርግ ማኑ
የምንለው ልጅ ነበር። አምስታችንም የፍሬ አባሎች እንወደው ነበር። እኔ ግን በጣም በጣም ነበር የምወደው:: አደንቀው ነበር። አቤት
ሲፅፍ ስለሀገራችን አስተዳደር ጉድለት፣ ስለጭቦው፣ ስለከይሲነቱ ይፅፋል። ታድያ ሲፅፍ ልዩ አይነት ነው።
የፃፈውን ስታነበው ፡ ፍሬ ነገሩ በጣም እያናደደህ፣ አፃፃፉ በጣም
ያስቅሀል። በሳምንት በሳምንት አንድ ሙሉ ገፅ ይፅፋል
አንድ በከተማው የታወቀ፣ የማይጠረጠር ሀኪም አለ፡፡ ትልቅ
ቤት አለው:: ቤቱ ውስጥ ከመሰረቱ ስር የሚገኝ አንድ ክፍል አለ። እዚያ ውስጥ በስቴንስል የሚያባዛዐመኪና ኣለ። የከተማችን ኮሙኒስቶች ፅሁፋቸውን ሁሉ የሚያባዙት እዚያ ነው፡፡ ብዙ ሰው ለመታከም ስለሚመላለስ፣ ለመጠርጠር ያስቸግራል። እኔና ማኑ ያችን የፃፋትን ገፅ እናትማለን። ሁለት ሺ ኮፒ እናትምና፡ በየቡና ቤቱ፣ በየመንገዱ፣ በየአደባባዩ፣ ብቻ ምን ልበልሀ፣ ሰው ሊያያቸው
በሚችልበት ቦታ እንነዛቸዋለን:: በስርቆሽ፡፡ ሌሊት እየዞርን
በየግድግዳው እንለጥፋቸዋለን
አንድ ሌሊት በጭለማ እንደዚህ ስንለጥፍ፣ ሳናስበው ሁለት
ፖሊሶች ከተፍ አይሉም?! ደንግጨ ልሮጥ ስል' በወድያ በኩልም የመጡ መሰለኝ። ግን ጨለማ ነው፣ በደምብ አይታይም። ማኑ ድንገት አቀፈኝና በሹክሹክታ «ለጊዜው ማምለጫ የለም፡፡ እቀፈኝ!» አለኝ፡፡ ሁልጊዜ ስለሚያዘኝ በልማድ ታዘዝኩት እንጂ ነገሩ አልገባኝም፡፡ ተቃቀፍን። ፖሊሶቹ አጠገባችን ሲደርሱ፣ ማኑ በቀጭን
ድምፅ «እኔ ፈራሁ፣ ቤት ውሰደኝ አለኝ «አይዞሽ ምንም
አይደለም። ፖሊሶች ናቸው» አልኩት፡፡ «ዝም በል! እፈራለሁ!» አለ
«አይዞሽ እይዞሽ» እያልኩ ሳባብለው፣ ፖሊሶቹ ትንሽ ተለያይተው ቆመው ሲመለከቱን፣ ማኑ የሴት ድምፁን ትቶ በእውነት ድምፁ

«በለው!» አለኝ

ሁለታችንም ተወረወርን፡፡ በኔ በኩል ያለውን ፖሊስ በጭንቅላቴ
ሆዱን መታሁትና፣ ሲወድቅ ትቼው ተፈተለክኩ። ትንሽ እንደሮጥኩ
ማኑ እጠገቤ እንደሌለ ታወቀኝ፡፡ በሩጫ ተመልሼ አጠገቡ ስደርስ
«ሂድ መጣሁ» አለኝ፡፡ ፖሊሶቹ ተጋድመዋል፣ ግን በጭለማው
በደምብ ኣይታዩኝም፡፡ በቀስታ ስራመድ ማኑ በፍጥነት እርምጃ
ደረሰብኝ፡፡ ይስቃል
«ምነው ቆየህ?» አልኩት
«ቀበቶና ቁልፋቸውን ስበጥስ» አለኝ እየሳቀ። ብርሀን ጋ
ስንደርስ ከኪሱ ገንዘብ አወጣና ቆጠረ። ስምንት መቶ ቱማን (ብር
250.00):
«ከማን ነጥቀውት ይሆን?» አለ «ስምንት መቶ ቱማን።
የማተሚያ ቤታችን ወረቀት ወደማለቁ ተዳርሷል። ነገ ወረቀት
እንገዛለን የታተሙትን ወረቀቶች አሰራጭተን ከጨረስን በኋላ፣ የደስ ደስ ካፌ ገብተን ቡና ስንጠጣ ሳቅ እያለ፣
«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....

💫ይቀጥላል💫
👍34🥰1