#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ይሄ ሁሉ ሲሆን ባህራምን አልረሳሁትም ነበር ከምሳ በኋላ Le Monde የተባለውን ስመጥሩ የፈረንሳይ ጋዜጣ እገዛና፣ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ petit creme (ቡና በወተት በሲኒ)
አዝዤ ሀበሾቹ አጠገብ ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን ማንበብ እጀምራለሁ።
ጩኸት፣ ሳቅ፣ ወሬ፣ የሲጋራ ጪስ፣ የሴት ሽቶ ካፌውን
ይሞላዋል። በበጋው ሙቀት ምክንያት መስኮት ሁሉ ይከፈታል፡፡
ሰማያዊ ካኪ የስራ ልብስ የለበሱ የፋብሪካ ሰራተኞች የቡና ማፍያው መኪና የተቀመጠበትን ረዥም ባንኮኒ በክንዳቸው ተደግፈው በተርታ ቆመው ፓስቲስ (ነጭ አረቄ) እየጠጡ፣ የፋብሪካ ዘይት ምናምን ያቆሽሽውን ቀያይ ፀጉራም እጃቸውን በብዙ እያንቀሳቀሱ፣
በአስቂኝ የደቡብ ፈረንሳይኛቸው ያወራሉ። ከባንኮኒው ዳር፣ ከመስተዋት የተሰራው በር አጠገብ፣ የካፌው ባለቤት መስዬ ፖል የቂል ሳቁን እየሳቀ “Merc Bien morosiuro (እግዜር ይስጥልኝ ጌታዬ» እያለ የሚከፍሉትን ገንዘብ ይቀበላል፤ ቴምብርና ሲጋራ ይሸጣል
ከባንኮኒው ኋላ ቆንጆዋ የመስየ ፖል ሚስት ባጭሩ የተቆረጠ
ብጫ ብጤ ቀለም የተቀባ ፀጉሯ እያብለጨለጨ ለሰዎቹ ቡና ወይም ፓስቲስ እያቀበለች፣ ከወጣቶቹ ጋር ፈገግታና ቃላት ትቀባበላለች፣ ትሽኮረመማለች፣ በማርሰይ ዜማ ታወራለች። ሸርሞጥሞጥ የምትል ሴት ናት። ድምፅዋ፣ አስተያየቷ፣ አረማመዷ፣ ሁለመናዋ ወንድ ይጣራል። መስዬ ፖል በብስጭት ነው የሚኖረው ሲባል እሰማለሁ፡፡
ግን ተማሪ ውሽማ ያላትም ይላሉ። ተማሪዎቹ መስዬ ፖልን
ይወዱታል፣ ሚስቱን ሊነኩበት አይፈለጉም፡፡ እሷም ተማሪ
የምትፈልግ አትመስልም፡፡ ውሽሞቿ ጎረምሶችና የፋብሪካ ወይም የኩባ ሰራተኞች ናቸው በበጋው ሙቀት ኮታቸውን አውልቀው የሸሚዛቸውን ቁልፍ በሙሉ ፈተው፣ የደረታቸውን ፀጉርና ጡንቻ እያሳዩና እጅጌያቸውን ሰብስበው ጡንቸኛ ፀጉራም እጃቸውን እያወዛወዙ ካፌ ዶርቢቴል የሚመጡ ጎረምሶች
እጠረጴዛዎቹ መሀል ሁለቱ ሴት ቦዮች ቡና፣ መጠጥ፣ ሲጋራ እየያዙ ይዘዋወራሉ
ሀበሾቹና ባህራም ካንድ ሁለት አፍሪካውያን ወይም ፈረንሳዮች
ጋር ካርታ ሲጫወቱ፣ አጠገባቸው ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን አነባለሁ።
በካርታ የተሸነፉት ሁለት ልጆች፣ ሌሎች ሁለት ተሽንፈውሳቸው
ተራቸውን ለመጫወት እስኪችሉ ድረስ መጥተው ከኔ ጋር ያወራሉ
ተካ ይመጣና ጋዜጣዬን ሳነብ «የማታነበውን ገፅ ልመልከተው
ስቲ» ብሎ ጋዜጣዬን ነጥሎ ግማሹን ይወስድብኛል። የማነበውን ጨርሼ ወደሌላ ገፅ መሄዴ ሲሆን፣ ተካ «ቆይ እቺን ልጨርስና እሰጥሃለሁ» ይለኛል። «አምጣ እንጂ» ስለው «ጋዜጣው ካንተ ጋር ይውላል፣ ትንሽ ባነብ ምናለበት?» ይለኛል። ብሽቅ ብዬ አየዋለሁ፡፡
ጥፍሩን እየነከሰ ያነባል።ጋዜጣው ውስጥ ያሳቀውን ወይም
ያስገረመውን ነገር ያሳየኛል፤ በጭራሽ አያስቅም፣ አያስገርምም።አይ ተካ ብሽቁ! ግን ጥሩ ልጅ ነው፡፡ እሱ ራሱ ጋዜጣ ገዝቶ ያነብ እንደሆነ ጋዜጣውን ይሰጠኝና «የማታነበውን ገፅ ስጠኝ። ሌላውን ካንተ በኋላ ቀስ ብዪ አነበዋለሁ» ይለኛል
አንዳንዴ ሀበሾቹ ተሰብስበው ካርታ ሲጫወቱ ወዳጆቻቸው
ሴቶች አንድ ጠረጴዛ ይዘው እያወሩ ይጠብቁዋቸዋል፡፡ ሲያሰኘኝ ከነሱ ጋር ትንሽ አወራለሁ ከኒኮል ጋር ማውራት እሞክራለሁ፣ ያቅተኛል። በጣም
ታፍራለች፤ ያልለመደችውን ሰው ማናገር አይሆንላትም። ለጊዜው
በጭራሽ ላውቃት አልቻልኩም። ስለዚህ ባሀራም ምን አይቶባት
ይሆን? ለሚለው ጥያቄ የመልስ ጫፍ እንኳ አላገኘሁለትም፡፡
መልኳን አይቶ እንዳልሆነ ግን ግልፅ ነበር፡፡ ውሀ አረንጓዴ አይኖች፣ የተዘረዘሩ ጥቃቅን ጥርሶች፣ ትኩሳት እንደያዛቸው አይነት ቆዳቸው የደረቀ ከናፍር። ድምፅዋ ደስ ይላል። ባህራም ምን አይቶባት ይሆን? እውነት ለገንዘቧ ሲል ይሆን?
ከአማንዳ ጋር ግን ብዙ እናወራለን። ሀበሾቹ አማንዳ ዱቤ ነው የሚሏት፡፡ ሉልሰገድ ይዟት ሊሄድ ሲል ተካ «እንግዲህ ሂድና
ዱባህን አገላብጥ!» ይለዋል። ሉልሰገድ «አንተ ደሞ ከዱባ የተሻለች እስክታገላብጥ ድረስ ስለዱባ ባታወራ ጥሩ ነው!» ብሎት አማንዳን እቅፎ ይሄዳል፡፡ አማንዳ በእንግሊዝኛ «ምንድነው "ሚለው?»
ትለዋለች፡፡ «ተይው ዝም ብሎ ነው» ይላታል።
ጋዜጣዬን እንብቤ፣ ሰዉን አይቼ፣ ባህራምን ተመልክቼ፣ ስለራሱ ለማውራት ዝግጁ እንዳልሆነ ከተገነዘብኩ በኋላ፣ ከካፌው
ወጥቼ ወደ ኩር ሚራቦ በኩል ትንሽ እራመዳለሁ። ወደኋላ ዞሬ፣
ማንም ሀበሻ እንዳልተከተለኝ ካረጋገጥኩ በኋላ፣ እታጠፍና ወደ
ሲልቪ ቤት አመራለሁ
"አንድ ቀን ባህራምን ያዘክው?» አለችኝ
"የለም" አልኳት
"የምትይዘው ይመስልሀል?»
"እርግጠኛ ነኝ»
«የምስራቅ ሰው እንደሆንክ ያስታውቃል፡፡ ጊዜ የሚያመጣውን
ጊዜ እስኪያመጣው ትጠብቃለህ እንጂ ጊዜን ልታጣድፈው
አትሞክርም፡፡ የምእራብ ሰው ብትሆን ግን ባህራምን ሄደህ በብልሀት ታዋራው ታወጣጣው ነበር»
«እንደሱ ካረግኩማ እሱን ራሱን ላውቀው አልችልም፡፡ የማሰብና
የሰዋስው ችሎታውን ብቻ ነው ላውቅ የምችለው»
«ምን የሚል ይመስልሀል?»
«ምን እንደሚልማ ማወቅ ቀላል ነው»
«አንግዲያው ምንድነው የምትጠብቀው?»
«ያ ያልኩሽ ጊዜ ሲመጣ፣ ተጠንቅቄ ምሰማው ቃላቱን
አይደለም ኮ»
«ታድያስ?»
ድምፁን ነው:: ዜማውን፡፡ እጁ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ። ምን
ሲል ድምፁ እንደሚለሰልስ፣ ምን ሲናገር ግምባሩ እንደሚቋጠር።
አንዳንድ ጊዜ እኛ ሳናውቅ ፊታችን ላይ ፈገግታ ወይም ህዘን በገዛ
ራሱ ይጫወት የለ? ያንን ነው ምጠብቀው:: አንድን ሰው
የምናውቀው በሚናገረው ቃላት አይደለም፣ ያን ቃላት ሲናገር
በሚያሳየው ገፅ፣ በሚያሰማው ድምፅ ነው:: እሱን እሱን ለማየት
ነው ባህራምን አድፍጬ የምጠብቀው
ከሰአት በኋላውን ከሷ ጋር አሳልፈዋለሁ፡፡ እንቅልፍ ከወሰደን ወደ አስራ አንድ ላይ እንነቃለን። ወይ እናወራለን፣ ወይ እናነባለን!
ወይ ሙዚቃ እንሰማለን። ሰኞና አርብ በአስር ሰአት ላይ ክፍል
አለባት። አንዳንዴ ተኝቼ ትታኝ ሄዳ ስትመለስ ትቀሰቅሰኛለች።
አንዳንዴ ነቅቼ እንደ ሌላ ቀን ከአርት መፃህፍት አንዱን
እየተመለከትኩ፣ ወይም እያነበብኩ፣ ወይም ሙዚቃ እየሰማሁ አቆያታለሁ
ሲመሽ ተለይቻት እሄዳለሁ። A ጠdemain cheri» («እስከ ነገ
ደህና ሁንልኝ») ምግብ ቤት ሄጄ እራቴን በልቼ፣ ከዚያ ወጥቼ
የቴሌቪዥን ዜና አይቼ ሳበቃ፣ ሆቴሌ ሄጄ ስራ እጀምራለሁ።
(አሜሪካዊቷ መምጣት ትታለች) ወይም ሲኒማ እገባለሁ። ከሲኒማ
በኋላ ለመስራት እሞክራለሁ፡፡ እምቢ ካለኝ፣ የሌሊት ፀጥታ
የዋጣቸውን የኤክስን ጠባብ መንገዶች እዘዋወርባቸዋለሁ፡፡ ንጉሳቸው ነኝ
ጧት ተነስቼ፣ ቁርሴን ሁለት croissant በልቼ፣ ቡና በወተት
ጠጥቼ፣ ወደ ቤተመፃህፍት ሄጄ እስከምሳ ሰአት እሰራለሁ። (ክፍል
መግባት ከተውኩ መቸስ ዘመን የለኝም)
ከምሳ በኋላ ካፌ ዶርቢቴልን ጎብኝቼ ወደ ሲልቪ እሄዳለሁ፡፡
በሰፊ አፏ እየሳቀች ትቀበለኛለች
አያሌ ቀናት ካለፉ በኋላ፣ ተመስገንን እየሳቅኩ
«ሲልቪ እንደወጣች ቀረች?» አልኩት
«ቀረች!» አለኝ «አሁንማ ብትመለስም አልፈልጋት»
«ምነው?»

👍20❤1
«አንጎሏ ምላጭ የሆነ ሴት መቶ በመቶ ሴት አትመስለኝም፡፡
አሁን አንዲት ጅል ብጤ ፈረንሳይ ይዣለሁ:: በጣም ተስማምታ
ኛለች፡፡ እጄን ሰደድ ሳረግ መክፈት ነው። ዝብዝብ የለም፡፡
ፖለቲካ፣ ሊትሬቸር፣ ምናምን የለም። ያቺ ግን! ስለኢትዮጵያ
የምትጠይቀኝን ጥያቄ ለመመለስ ብቻ ስንትና ስንት አስፕሮ መዋጥ
ያስፈልገኝ ነበር፡፡ ያውም አብዛኛውን ለመመለስ አልችልም ነበር»
«እኔ ግን በጣም ደስ ትለኛለች ልጄ» አልኩት «እውነት
በጭራሽ አትፈልጋትም?»
«በጭራሽ። አንተ 'ምትወዳት አይነት ሴት ናት፡፡ ሞክራት»
«ብኋላ ይቆጭሀና መልስልኝ ትለኛለህ ልባርግ» አልኩት
«እርም ይሁንብኝ!»
«ተው!»
«ኦዎ! ይልቅ አንዱ ጭልፊት ፈረንሳይ ሳይሞጨልፋት ቶሉ
አብስላት»
«ታድያ አንተ የተጠቀምክበትን ዘዴ ንገረኛ፡ እንዲረዳኝ ያህል»
አልኩት
ነገረኝ መከረኝ፣ አብረን ፕላን አወጣን፡፡ በመጨረሻ
«አንድ ምክርና አንድ ማስጠንቀቅያ ልስጥህ መሰለኝ» አለኝ
«ምክሩ ይኸውና፣ ልጅቱን እንደፈለግካት ጌታው ተካ
እንዳያውቅብህ»
በዚህ ስቀን ስንጨርስ
«ማስጠንቀቂያውስ?» አልኩት
እቺ ሲልቪ አንዳንዴ ሌላ ሰው ትሆንብኛለች፡፡ አልጋ ውስጥ
ያለልማዷ እንደማበድ ትላለች፣ ወፈፍ ያረጋታል። እና በደስታ
ታሳብድሀለች፣ ታድያ--»
«ታድያ?»
ታድያ ነገሩ ካለቀ በኋላ ታኮርፋለች፡፡ ወደዚያ ፈንጠር ብላ
ራሷን እጂ ውስጥ ትደፋለች። አንዳንዴም ታለቅሳለች»
«ምን ሆንሽ ስትላትስ?»
«አትነግርህም፡፡ እና ግራ ያገባሀል። አውቀህ ብትገባበት ይሻላል ብዬ ነው»
«ይገባኛል» አልኩት
ተመስገን እንዳልዋሸ አውቄያለሁ። ግን ሳቂታዋ ሲልቪ አኩርፋ
ወይም ስታለቅስ - በጭራሽ ሊታየኝ አልቻለም
ካንድ ሳምንት በኋላ እኔና ሲልቪ በይፋ አብረን እንወጣ ጀመር፡፡ ሀበሾቹ «አልጋ ወራሽ» አሉኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልጋ
ወራሽነቴን ረሱት፤ ሰነሱ አይን ሲልቪ የኔ ሆነች
ተመስገን «የነገርኩህ ብልሀት ስራ መሰለኝ» አለኝ፡፡ የደስ ደስ
ቢራ ጋበዝኩትና ሲኒማ አስገባሁት። የያዛትን «ጅል ብጤ» ፈረንሳይ አስተዋወቀኝ። ብሎንድ ነጭ ፀጉራኝ እንደ ወንድ ተቆርጣለች።
በጣም ቆንጆ ናት። ይሄ ተመስገን ሴት አመራረጥ ያውቃል፡፡
ደሞ ሴቶች የሚወዱት ይመስላል። ታድያ የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ አዲስ አበባ በነበርንበት ጊዜ የምትጠጋው ሴት አልነበረችም.....
💫ይቀጥላል💫

👍19
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ባህራም
ከቅርብ
ማክሰኞ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ከምሳ በኋላ Le Monde ጋዜጣዬን ገዝቼ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ እንደ ልማዴ petit creme አዝዤ ካርታ የሚጫወቱት ሀበሾች አጠገብ ቁጭ አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ባህራም መጣ፡፡ ሳየው የተለወጠ መሰለኝ፡፡ ልማዱ በፍጥነት እርምጃው ከተፍ ብሎ ሲያበቃ፣ ሀበሾቹን «እናትክን! ሀለላሴ ሙት! Je veux jouer
aux cartes.» («ካርታ አጫውቱኝ») ብሎ ቁጭ ማለት ነበር፡፡ ዛሬ ግን በቀስታ እርምጃ መጣ። እንደ ድሮው አልቀለደም፡፡ እንደ አጋጣሚ ለካርታ ጨዋታው አንድ ሰው ጎድሏቸው ስለነበረ «ባህራም! ና ካርታ እንጫወት አሉት
«ካርታ ጨዋታ አላሰኘኝም» አለና ዝም ብሎ ቁጭ አለ።
የተበሳጨ ይመስላል
«ምን ሆነሀል?» አለው ሉልሰገድ
«በፈተና ወደቅኩ» አለ
ሁሉም የሚሉትን አጡ
እንግዲህ በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ደምብ፣ አንድ ተማሪ የሰኔ ወር ፈተናውን የወደቀ እንደሆነ በእረፍት ጊዜው ሲያጠና
ይከርምና፣ በጥቅምት (ትምህርት ቤት ሲከፈት) እንደገና
ይፈተናል። ስለዚህ ተመስገን
«አይዞህ በጥቅምት ፈተና ታልፋለህ» አለው ባህራም አልተፅናናም፡፡ ሁሉም ዝም አሉ። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ።
ባህራም «ዘላለም ካርታ ጨዋታ ምን ያረጋል? እንውጣ ትንሽ
እንንሽርሽር» አለ። ማንም መልስ አልሰጠውም፡፡አብረውት
መውጣት ፈርተዋል። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ ለጨዋታው
ብቻ ሳይሆን ከባህራም ብስጭት ለማምለጥም ጭምር። ገባው::
ተነስቶ ብቻውን ወጣ፡፡ ተከትዬው ወጣሁ። ወደ መናፈሻው በኩል
እያመለከትኩ
«ወደዚያ እንሂድ?» አልኩት፡፡ መልስ ሳይሰጠኝ ወደዚያው
አመራ። ትንሽ እንደተራመድን
«ያውና ተካ። ወደኛ በኩል ይመጣል» አለኝ «አደራህን አብሮን እንዳይመጣ። ዛሬ እሱ ሁለት ቃላት ቢያናግረኝ አብዳለሁ»
«አትስጋ» አልኩት
ተካ አቆመንና በፈረንሳይኛ
«ከየት ነው የምትመጡት?» አለን
«አሁን ከየትም ብንመጣ ደንታ የለህ። ለምንድነው የምትጠ
ይቀን?» አልኩት በአማርኛ
«ከዶርቢቴል ነው የምትመጡት?» አለኝ ባማርኛ
«አዎን» አልኩት ባህራም እጁን ኪሱ ከቶ ወደዚያ ይመለከታል
«ወዴት ነው የምትሄዱት?» አለኝ ተካ
«ወዴትም፡፡ ምን ያረግልሀል?»
«ወደ ሲቴ ነው የምትሄዱት?»
«ምነው? ከኛ ጋር ሲቴ መሄድ አማረህ?»
«አይ! እኔ ለራሴ ከዛ መምጣቴ ነው። ቡና አምሮኛል»
«እንግዲያው ሂድና ቡናህን ጠጣ»
«ጋዜጣህን አሁን አታነበው እንደሆነ ስጠኝ»
ጋዜጣዬን ሰጠሁትና መንገዳችንን ልንቀጥል ስንል
«ይሄ አቃጣሪ ገንዘብ እንዳያጭበረብርህ ተጠንቀቅ» አለኝ
«ሂድ ቡናህን ጠጣ» እልኩት። ሄደ
እኔና ባህራም አንድ ቃል ሳንነጋገር መናፈሻው ደረስን፡፡ ዛፎች
ጥላ ስር አንድ አግድም ወምበር ላይ ቁጭ አልን ፈተና መውደቅ የተለመደ ነገር ነው:: በጥቅምት ታልፋለህ» አልኩት
በተገማመደ ፈረንሳይኛው፣ በወፍራም ልዝብ ድምፁ መናገር
ጀመረ መውደቄ አይደለም የሚያበሳጨኝ፣ አወዳደቄ ነው።
ትምህርቱን በደምብ ይዤዋለሁ። በምን እንደጣሉኝ ታውቃለህ?
በፈረንሳይኛዬ ጉድለት: አያስቅህም? ፈተናውን የወደቅኩት እኔ ራሴ ባልሆን ያስቀኝ ነበር
«እኔንና ፈረንሳዮቹን የክፍሌን ልጆች አስተያየን እስቲ፡፡
ትምህርቱን እኩል እናጠናቀው። ፈተና እንግባና ጥያቄው ይሰጠን።
መልሱን እኔም እነሱም እኩል እንወቀው። እነሱ ምን ያረጋሉ?
መልሱን በፍጥነት ይፅፋሉ፡ አሰካኩንና አገባቡን ያማርጣሉ፡፡
ጥቃቅኗን ነገር ጭምር ያስገቧታል፡፡ ሀያ ሀያ አንድ ገፅ ፅፈው ይወጣሉ፡፡ ያልፋሉ፡፡ እኔም መልሱን ከነሱ እኩል አውቀዋለሁ፡፡
ታድያ ፈረንሳይኛው ከየት ይምጣ? ከሱ ጋር ስታገል የጊዜዬን
ግማሽ አጠፋለሁ:: ለዚያውም አምጩ የማመጣው ፈረንሳይኛ አንካሳ ሽባ ስለሆነ፣ በደምብ የማውቀውን መልስ ልክ እንደማላውቀውና
በግምት ወይም በነሲብ እንዳገኘሁት ያስመስልብኛል። ዘጠኝ አስር ገፅ ፅፌ እወጣለሁ፣ በመጥፎ ፈረንሳይኛ፡፡ ትምህርቱን እያወቅኩት ፈተናውን እወድቃለሁ
«ፈረንሳዮች ደሞ ታውቃቸዋለህ። በቋንቋቸው የመጣ በጣም
አንጎለ ጠባብ ናቸው። ለምሳሌ አስተውለህ እንደሆነ በፍጥነትና ያለ ስህተት ያነጋገርካቸው እንደሆነ ያከብሩሀል፣ «Intelligentይሉሀል።
እየተንተባተብክ ያነጋገርካቸው እንደሆነ ግን ምንም ቁም ነገር
ብትናገር መሃይም ነህ ማለት ነው። በቋንቋህ ብታናግራቸው እንደ ቂል አፋቸውን ከፍተው እንደሚቀሩና፣ የነሱም ቋንቋ ላንተ ያንን ያህል እንግዳ እንደነበረ፣ የሚሉት ሁሉ «ዠቨሹቪ» ይመስልህ እንደነበረ፣ በስንት ልፋት በመጠኑ ልታውቀው እንደቻልክ፣ በቋንቋቸው መንተባተብ ስለቻልክም ሊያመሰግኑህ እንጂ ሊንቁህ
እንደማይገባቸው፣ ይህን ለመገመት ያህል ሰፊ አንጎል የላቸውም።ተራውስ ሰው እንዲህ ቢሆን አልፈርድበትም፡፡ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮቹ እንዲህ ሲሆኑ ግን በጭራሽ አይገባኝም፡፡ እንግዲያውኑ የነሱ ትምህርት የታል? እቺን ያህል ቀላል ነገር ማመዛዘን ካልቻሉ አንጎላቸውስ ትምህርታቸውስ ምን ትርጉም ይኖረዋል?
«እማናውቀው አገር መጥተን፣ በማናውቀው ቋንቋ
የማናውቀውን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለመማር ስንታገል፣ ለምን
አስተያየት አያደርጉልንም?»
“ምን አይነት አስተያየት ሊያደርጉልን ይችላሉ?» አልኩት
«ፈረንሳይኛችን ትንሽ የተጣመመ እንደሆነ፣ የቋንቋውን መጣመም ችላ ብለው የፍሬ ነገሩን እዚያ መገኘት ለምን አያስቡልንም? አገራችን ስንመለስ በራሳችን ቋንቋ ነው የምንmቅመው፣ ስለዚህ ፈረንሳይኛውን አንደነሱ ቻልነው በመጠኑ ተንተባተብንበትስ ምን ያህል ልዩነት ያመጣል? እንግዳ ስንሆን፣ ፈረንሳይኛውን በሀያ ሶስት፣ በሀያ አራት፣ በሀያ አምስት
አመታችን ስንጀምረው፣ እንዴት ከናታቸው ጡት ጋር ሲጠቡት
ካደጉ ሰዎች እኩል ካልሆነ ተብለን እንቀጣበታለን? ቅጣት መሆኑ
ይታይሀል? ፍሬ ነገሩን እንደማውቀው ግልፅ ሳለ፣ የተጠቀምኩበት ፈረንሳይኛ የተቀመመ ፈረንሳይኛ ባለመሆኑ ፈተናዬን ስወድቅ፣አንድ አመት ሙሉ የለፋሁበትን ስከለከል፣ ይሄ ቅጣት ነው እንጂ ምንድነው? ፍትህ የሌለው ቅጣት
«አንድ አመት ምን ያህል እንደሆነ ይገባሀል? አስበው፡፡ የዘጠኝ
የአስር አመት ልጆች ሳለን ክፍል በመድገም አንድ አመት ብናጠፉ
ምንም አይደለም፡፡ በህያ ስድስት፣ በሀያ ሰባት አመታችን አንድ
አመት ማጥፋት ግን ሌላ ነገር ነው:: ምክንያቱም እነዚህ አመታት
ከሀያ አምስት እስከ ሰላሳ አምስት ሰፈር ያሉት አመታት የሌሎቹን አመታት ሶስት አራት እጥፍ ዋጋ አላቸው። አሁን ነው ህይወታችንን ለመጨረሻ የምንቀርፀው:: አሁን ነው ያለ የሌለንን ለሀገራችን ልናበረክትላት የሚገባን። አሁን ነው የኑሮ ስራችንን የምንመርጥበት የምንጀምርበት ጊዜ። አሁን ነው የኑሮ ጓደኛችንን
የምንመርጥበት፣ ትዳራችንን የምንቆረቁርበት ጊዜ፡፡ አሁን ነው።
አሁን! አሁን! አሁን ነው ልጅነትም የማያታልለን፣ እርጅናም የማይ
ጫጫነን፡፡ አሁን ነው ፍሬ ለመስጠት ዋጋ ለማስገኘት የምንችለው» ረጋ ባለ ድምፅ
«አሁን ነው ፈረንሳዮች "ለምን ቋንቋችንን ከኛ እኩል
አልቻላችሁም?' ብለው ወርቅማ አመታችንን የሚያጠፉብን

👍17❤5😁1
«ጠፋች በቃ እቺ አመት:: እኔም፣ ቤቶቼም፣ አገሬም አንድ ወርቃማ አመት ተነጠቅን። ታድያ የነጠቁን ሰዎች አልተጠቀሙበትም፡፡ እንደነጠቁንም ኣላወቁም፡፡ በጫካ ስታልፍ አንድ ትል ብትጨፈልቅ አይታወቅህም፣ የትሉ ሚስት ግን አለም ይጨልምባታል፡፡ ፈረንሳዮቹ አመቴን አጠፉብኝ። አንድ አመት ሙሉ!»
«ፈተናውን ባታልፍበትም እውቀቱን አግኝተህበታል» አልኩት
«እኛ አገር ምስክር ወረቀት የሌለው እውቀት ከእውቀት
አይቆጠርም፡፡ ስለዚህ ያገኘሁት እውቀት በምንም ሊጠቅመኝ
አይችልም። የህግ ትምህርት እንደ ፍልስፍና ወይም እንደ ስነ-ጽሁፍ
ትምህርት አይደለም። ጥቅሙ በስራ ሳይ ልታውለው ከቻልክ ብቻ
ነው። በስራ ላይ እንድታውለው ደሞ የምስክር ወረቀት
ያስፈልግሀል። የምስክር ወረቀት ለማግኘት የፈረንሳይኛ ቋንቋን
እንደ ፈረንሳዮቹ ማወቅ አለብህ:: በፈረንሳይኛ እርሳስ ተባእታይ
ፆታ ነው፣ ብእር ግን አንስታይ ፆታ ነው። ለምን? ምክንያት የለውም። መኪና፣ አውቶብስ፣ መፅሀፍ፣ ደብተር፣ ሰማይ፣ መሬት፣
ፀሀይ፣ ኮከብ፣ ደመና፣ ነፋስ እነዚህ ተባእታይ ይሁኑ እንስታይ
ፈረንሳይ ያልሆነ ሰው ቢያሳስት ይህን አሳሳትክ ተብሎ ፈተናውን
ይወድቃል? ይሄ የሚገባ ነገር ነው?»
እውነቱን ስለሆነ ምንም ልለው እልቻልኩም
«አይዞህ በጥቅምት ወር ተፈትነህ ታልፋለህ» አልኩት
«እንዴት አድርጌ?» አለኝ
«ትምህርቱ ቢሆን ያቃተኝ፣ ሌት
ተቀን አጥንቼ እፈተን ነበር። ፈረንሳይኛውን ግን በሶስት ወር ውስጥ ከምን ላደርሰው እችላለሁ? ከእንግዲህ ልጅ አይደለሁም፡፡ ሀያ አምስት አመቴ አልፏል፡፡ እስከ መቼስ ቢሆን ፈረንሳይኛውን ከነሱ እኩል ላውቀው እችላለሁ እንዴ?
“ጠፋች እቺ አመት። እንደ ሌሎቹ አመታት ጠፋች፣ ተከተለቻቸው»
«ሌሎቹ አመታት?» አልኩት
«በይሩት ነበር የምማረው፡፡ በህክምና ትምህርት ሁለተኛ
አመት እንደጨረስኩ ነው ወዲህ የመጣሁት»
(«ለምን መጣህ? መጥተህስ በህክምና ትምህርት እንደመቀጠል እንደገና ሀ ብለህ ህግን ለመማር ለምን ቆረጥክ?” ልለው ፈለግኩ፤ግን አሁን የመጠየቅ ጊዜ አልነበረም፡ ዝም ብሎ የመስማት ጊዜ ነበር)
ዝም ሲል ጊዜ ንግግራችን እንዲቀጥል ለመቆስቆስ ያህል
“አይዞህ በርታ፣ ሁሉም ሰው ችግር ያጋጥመዋል» አልኩት
ሳቅ አለ። አስተያየቱ በምቾት ቁጭ ብለህ በችግር
የሚፍጨረጨረውን ሰው 'አይዞህ፡ ረጋ በል ማለት ምንኛ ቀላል
ነው!» የሚል ይመስላል
ችግሩ ይህን ያህልም ከባድ አይደለም» አለ እንዲህ
የሚያስለፈልፈኝ ከሌላ ችግር ጋር ተጋግዞ ስለሚያጠቃኝ ነው።
በፈተና ስለወደቀ ያለቅሳል ብለህ እንዳትታዘበኝ
«ሌላ ችግር አለብህ?»
ቤቶቼ ናቸው ሌላው ችግር፡ አየህ፣ አባቴና ከሁሉ ታላቅ ወንድሜ ነጋዴዎች ናቸው:: አንዴ ገንዘብ ይተርፋቸዋል፣ አንዴ
ደሞ የተገዛው እቃ መሽጥ እስኪጀምር ጥሬ ገንዘብ ከእጃቸው ያጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት፣ በይሩት ስማር ሳለሁ በሶስት በአራት ወር ነበር ገንዘብ ሚልኩልኝ። ላኩልኝ ስላቸው ከጓደኞችሀ ተበደር በኋላ እንከፍላለን ይለኛል ..
እንግዲህ በይሩት ውስጥ መአት ሰው ያውቀዋል። ይበደራል። እሰከ ስድስት ሺ ፍራንክ ድረስ (3,000 ብር) ይበደር ነበር፡፡ ቤቶቹ ሲመቻቸው አንድ ስምንት ሺ ፍራንክ ይልኩለታል።
እዳውን ከፍሎ ሲጨርስ ሁለት ሺም ያህል ይተርፈዋል። እሷ
እስከታልቅ ካላኩለት እንደገና ሌላ ይበደራል፡፡ እንደዚህ ነብር
የሚኖረው
እዚህ ኤክስ እንደመጣ አድራሻውን ላከላቸው እንግዳ አገር ስለሆነብኝና የማውቃቸው ሰዎች ስለሌሉ እንድትልኩልኝ አደራ አላቸው፡፡ «እንደተመቸን እንልክልሀለን አሉት። መበደር ጀመረ፡፡ እንደገና ደብዳቤ ፃፈ። በቀን በቀን ደብዳቤ መጥቶልኝ እንደሆነ እያለ እየተንገበገበ ይጠብቃል። አራት ወር ሙሉ ምንም መልስ ሳይልኩለት ቆዩ። ብድሩ እየበዛ ሄደ።
ቴሌግራም ላከ «ምን ሆናችኋል? ሰግቻለሁ፣ እዳ ተጠራቅሞብኛል፣
ረሀብም አጥቅቶኛል» አላቸው:: መልስ ይጠብቅ ጀመር
ማታ ሲተኛ ስለነሱ ያስባል። ነገ ደብዳቢ ይደርሰኛል ይላል።
ጧት ሲነሳ ስለነሱ ያስባል። ዛሬስ ደብዳቤ አገኛለሁ ይላል። ደብዳቤ
ሳይደርሰው ቀኑ ሲመሽ ይገርመዋል። ይሰጋል፡፡ ምን ሆነው ይሆን? ይፈራል፡፡ ነገ ደብዳቤ ይደርሰኛል ይላል።
እዳው እየከበደው ሂደ
እንግዲህ የኤክስ ፖስታ በቀን ሁለቴ ነው የሚታደለው። የጧቱ
ባምስት ሰእት ሰፈር ይመጣል። ባህራም ከክፍል ወጥቶ ሲጣደፍ
ቤቱ ይሄዳል። ምንም ደብዳቤ አይጠብቀውም፡፡ ኩም ይላል። በአስር ተኩል ላይ ይመጣልኝ ይሆናል ይላል። እስከ አስር ተኩል ይጠብቃል። በአስር ተኩል ምንም ደብዳቤ አይመጣለትም፡፡ እነዚህን
ሰአቶች ይፈራቸው ጀመር። ተስፋ ልቡ ውስጥ እየተጠራቀመ
ይቆይና፣ ምንም ደብዳቤ እንዳልመጣለት ሲያይ፣ ነብሱ በኩምታ ሽምቅቅ ትላለች። በዛበት፡፡ ስለዚህ፣ ሁለቴ ኩም ከማለት ብሎ ከቤቱ ጧት የወጣ እስከ ማታ አይመለስም። ማታ ወደቤቱ ሲራመድ ጧት ደብዳቤ መጥቶልኝ ይሆናል፣ ወይም ከሰአት በኋላ መጥቶልኝ
ይሆናል፣ ከሁለቱ በአንዱ ሳይመጣልኝ አይቀርም» እያለ ያሰላስላል፡፡ታድያ ደብዳቤ የሚሏት የለችም። ተስፋና መንገብገቡ ድንገት አፈር
ይሆናል። ራሱን ማመን ያቅተዋል። እንዲህ ሊሆን አይችልም፣
ደብዳሲ ሳይኖረኝ አይችልም!» ይላል። «ነገ ይላል። እስከ ነገ በብዙ ይሰጋል። ቤቶቼን ምን ነክቷቸው ይሆን? አባቴና ወንድሜ ከስረው ይሆን? ግን ቢከስሩ ፅፈው አይነግሩኝም? መፃፍ አልቻሉ ይሆን?
ታስረው ይሆን? ሞተው ይሆን? ምን አግኝቷቸው ይሆን?»
ይሄ ሁሉ ሲሆን እዳው እየተካሃቸ ሄደ
«ከማውቃቸው ሰዎች ከአብዛኛዎቹ አምስት አስር፣ ሀያ ፍራንክ ተበድርያለሁ ይመስለኛል፡፡ አሁንማ ስንት ፍራንክ ከስንት ሰው
እንደተበደርኩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሰዎቹን በቀን በቀን
ኣገኛቸዋለ፡፡ በቅርቡ እመልስልሀለሁ እያልኩ ነበር የተበደርኳቸው::እና ሳያቸው አፍራለሁ። ሲያሳፍር የሰው አይን! አይተውህ ሲያልፉና፣ ካለፉህ በኋላ አይናቸው ውስጥ ያየኸውን ንቀት ስታስታውሰው ማሳፈሩ!»
የሚገባበት ይጨንቀዋል፡፡ ግን ምን ለማድረግ ይችላል?
እፍረቱና ስጋቱ ሲፈራረቁበት እያየ «ይሄ ሁሉ መጨረሻው ምን
ይሆን?» ማለት ብቻ ነበር
ከሁሉ የሚጎዳው ስለቤቶቹ ማሰብ ነበር። ማታ እንቅልፍ እምቢ እያለው ስለነሱ ሲያስብ፣ አንጎሉ እንደ ወሬኛ የመንደር ሴት ክፉ ክፉ ሀሳቦችን እየለቃቀመ የጭካኔ የጭቆና ትርኢቶችን ያሳየው ነበር ለጊዜው አንተን ችግር አያጥቃህ እንጂ፣ ቤቶችህስ ምንም አይሆኑም አይዞህ» አልኩት
«አንተ የኛን አገር አታውቀውም። ስንት ጭቦ እንደሚሰራ፣
ስንት በደል እንደሚፈፀም፤ እንኳን ልትገምት ልትጠረጥር
ኣትችልም»
ሌሊት ሲሆን የሚመጡብህ ሀሳቦች አሉ፡፡ ህልም አይደሉም፣ ምክንያቱም እንቅልፍ አይወስድህም። ግን ጤነኛ ሀሳቦች አይደሉም፧ የሌሊቱን ጭለማ ይለብሱና እንደ ጉንዳን ይወሩሀል ያስፈራሩሀል ቀን ቢመጡብህ ትስቅባቸዋለህ፤ እነሱም በቀን ደፍረው አይመጡብህም፡፡ ሌሊት ግን እውነት ይመስሉሀል። ብቻህን
በጭለማ በረሀ ውስጥ ስትፈራ እንደምታየው ቁጥቋጦ ናቸው።
በመጥፎ ህልምና በውን መካከል አንድ የሀሳባችን ጫካ አለ። ብቻህን ነህ፣ ጭለማ ውጦህል፣ የቁጥቋጦ መአት ከቦሀል.መሰረት
የሌለው ሀሳብ ሁሉ የመጨረሻ እውነት መስሎ ይመጣብሀል
እና በዚሀ ጊዜ ባህራም ስለቤቶቹ ሲያስብ፤ አንዴ ቤታቸው
ተቃጥሎ ሁለም ሞተው ይታየዋል፡ “አንዴ አባቱና ወንድሙ
ከስረው በእዳ ተይዘው ታስረው፣ ወንድሞቹና እህቶቹ መጠጊያ
አጥተው ሲጨነቁ ይታየዋል

👍22
በተለይ ከሁሉም አብልጦ
የሚወዳት እህት አለችው
የመጨረሻ ልጅ ናት። ቤቶቹ ሁሉም እሷን ነው የሚወዷት፡፡ ታድያ እሷ አልጋዋን ነው ምትወደው። ስታጠና አልጋዋ ላይ ሆና፤ ስትጫወት፣ ስታዝን፣ ስትደሰት የሚያገኙዋት፡፡ ይህን አልጋ ገረዶቹ እንዲያነጥፉት አይፈቀድላቸውም፤ ልጅቱ ራሷ ናት የምታነጥፈው በቀን ኣራት አምስት ጊዜ ይነጠፋል
«እህቴን ያመማት እንደሆነ እማማ ብቻ ናት እንድታነጥፈው
የሚፈቀድላት። ይሄ አልጋ በአመት ስድስት ሰባት አልጋ ልብስ
ይገዛለታል። ብቻ ምን ልበልህ፣ እህቴ ያለአልጋዋ መኖር
አትችልም፡፡ ታድያ በሀሳቤ ቤታችን ከነዕቃው ሲወረስ፣ የእህቴ
አልጋ በሀራጅ ሲሽጥና፣ እሷ ይህን ስትመለከት ይታየኛል። አይኖቿ ይታዩኛል። ሆዴን ያመኛል»
አንዳንዴ ደሞ አባቱ በፖለቲካ ምክንያት ተይዘው ወታደሮች
እያዳፉ ሲወስዷቸውና ሌሎቹ ወታደሮች ደሞ እህቶቹን
ሲደፍሩዋቸው፣ ወንድሞቹን በሰደፍ ራሳቸውን ሲፈነካክቷቸው
ይታየዋል። . «ይሄ ሁሉ እኛ አገር በየቀኑ የሚደረግ ስለሆነ፣
እነዚህ የሌሊት ሀሳቦች በጣም ያስፈሩኛል፣ ያስጨንቁኛል»
አንዳንዴ ስጋቱ ከመጠን በላይ ይበዛበትና፣ ተነስቼ አገሬ ልግባ
ይላል። ግን እንዴት ለመሄድ ይችላል? ባንድ በኩል ተስፋ የሚሉት አለ
«ይሄኔኮ ይህን ሁሉ ዝምታ የሚያስረዳ ደብዳቤና እዳዬን
በሙሉ ለመክፈል የሚያስችለኝ ገንዘብ መንገድ ላይ ይሆናል፣ ነገ
ወይ ተነገ ወድያ ይደርሰኝ ይሆናል» ይላል። በሌላ በኩል ለመሄድ ብቆርጥስ በምን እሄዳለሁ?» ብሎ ሲያስብ፣ በአሮፕላን፣ በመርከብ፣
በባቡር ወይም በአውቶብስ እንዳይሄድ፣ ምን ከፍሎ? በእግሩ እንዳይሂድ፣ አመት ወይም ሁለት አመት ይፈጅበታል፤ ለዚያውስ ስንቅ ከየት ይመጣል? ሲመሽስ የት ይተኛል? በሌላ በኩል ደሞ፣ የመሄጃ ዘዴ ቢያገኝስ እዳውን ሳይከፍል እንዴት አድርጎ ለመሄድ ይችላል?
እስረኛ ነኝ በቃ። በእዳና በተስፋ ታስሬ፣ በእፍረትና በስጋት
የምገረፍ እስረኛ ነኝ»
«እንዴት ጎበዝ ነህ!» አልኩት
እንዴት?» ለማለት ያህል አየኝ፡፡
ከቅንድቦቹ ጥቁር ጫካ ጥላ
ስር ቡናማ ትንንሽ አይኖቹ ያዩኛል፣ ሀዘን ሞልቷቸዋል፣ ግን ተስፋ
አልከዳቸውም፣ እንዲያውም ሳቁን የረሱ አይመስሉም
«እኔ አንተን ብሆን ድሮ ተስፋ ቆርጫለሁ» አልኩት።
አፍንጫው ትልቅና ሸካራ መሆኑን ገና አሁን አስተዋልኩ
በይሩት ሳለሁ እንዲህ አይነት ኑሮ የሚኖር ሰው አለ ቢሉኝ
ኖሮ፣ እኔም 'እንዴት ተስፋ አይቆርጥም!?' ብዬ ይገርመኝ ነበር።ስትገባበት ግን ሌላ ነው። አየህ፣ የሰው ልጅ በጣም ጠንካራ ነው፤ምንም ያህል መከራ ቢናድበት አይሸነፍም፣ መቸም ቢሆን ተስፋ አይቆርጥም
ዝም አልን። አፍንጫው ምን ያክላል!
«እኔ ተስፋ እንዳልቆርጥ የደገፈኝ ምን መሰለህ?» አለኝ
«ምን?»
«ሉልሰገድ፣ ተመስገንና፣ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን። እንደዚህ
ያሉ ሰዎች አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ፈረንሳዮችን ታውቃቸዋለህ
እግራቸው ስር ወድቀህ እየተንፈራገጥክ በራብ ሞትኩ ብትላቸው፣እጃቸውን ብድግ አርገው ትካሻቸውን እንቀሳቅሰው 'ኧእ! መስዬ፣ታድያ ይህ የኔ ጥፋት ነው? ለምን ወደ ኤምባሲዎ አያመለክቱም?ብለውህ መንገዳቸውን ይቀጥላሉ። ኤክስ ውስጥ ተበድሬ ተበድሬ፣
የማውቃቸውን ሰዎች ጨረስኩ። የቀረኝ ጥቅልል ብሎ በረሀብ
መሞት ነበር። ተመስገንና ሉልሰገድ አበሉኝ። ያገሬ ልጆች ማጣቴን አይተው ፊት በነሱኝ ሰአት፣ እንግዳ የሆኑ ሰዎች፣ ቋንቋቸውን ባህላቸውን የማላውቀው ሰዎች፣ ቆዳቸውና ፀጉራቸው ሳይቀር ከኔ
የተለየ ሰዎች ጠርተው አበሉኝ፡፡ በሀበሾች ጓደኞቼ ምክንያት፣ በሰው ልጅ ላይ ያልነበረኝ መተማመን አደረብኝ:: ምግብ ብቻ አይደለም የሰጡኝ። ስሙን እኔ እማላውቀው፣ ከምግብ የበለጠ ነገር ነው የሰጡኝ። ሌላ ሰው ሰጥቶኝ እማያውቀው ነገር ነው የሰጡኝ»
አይኖቹ ብርሀን ሙሉ
ብርህን አይደለም፣ እንባ ነው -
የሀዘን አምባ አይደለም፣ ሌላ አይነት እምባ ነው:: ወደዚያ አየ፡፡
እኔም ወደ ሌላ በኩል አየሁ
ሀበሾቹ እንደዚህ ጥሩ ሰዎች መስለው የታዩት ምንኛ የዋህ
ቢሆን ነው? ብዬ አሰብኩ
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ችግሬን ትከሻ ላይ ጫንኩብህ፣ ይቅርታ አርግልኝ አለኝ ዘወር ብዬ አየሁት። አይኖቹ ውስጥ እንባ የለም
«አታምነኝም ይሆናል» አልኩት «ግን ችግርህን ስላዋየህኝ ክብር
ይሰማኛል። ደሞ አይቼው የማላውቅ ጉብዝና ዛሬ አየሁ።
ሳቅ አለ
«አንድ ነገር ልንገርህ» አለኝ «ይሄ ስጋት፣ ፍርሀትና በእዳ ተይዞ ማፈር እየከበደኝ እያስጨነቀኝ ሲሄድ ጊዜ፤ ብቻዬን አልችለውም በማለት ለሰው ልናገረው ሞክሬ ነበር። ደጋግሜ ሞክሬ ነበር። ግን ልናገረው አልቻልኩም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰሚ አጣለሁ፡፡
የሚሰማኝ ሳገኝ ደሞ ልናገር እንደጀመርኩ እፍረት ይይዘኛል፡፡
መናገሩን እተወዋለሁ። ላንተ መናገር ግን በፍፁም አያሳፍርም፡፡
የማዳመጥ ስጦታ አለህ። ቄስ ለመሆን አስበህ ታውቃለህ?»
እፍረት ተሰማኝና ሳቅ ስል፣ እሱም ሳቅ እያለ
«ህለላሴ ሙት!» ብሎኝ ተነሳ። እኔም ተነሳሁ
«Vive l amitié frar Ethiopienne!» አለኝ:: ይስቃል።
(የኢራንና የኢትዮጵያ ጓደኝነት ለዘለአለም ይኑር») አሁን አሁን
ያን ሁሉ ችግሩን ሲያወራልኝ እንደነበረ ለማመን አመነታሁ
«Vive!» አልኩት « A bas les Yankees!» («ይኑር!
ያንኪዎች ይውደሙ!»)
«A bas!» አለኝ፡፡ (“ይውደሙ!»)
ወደ ካፌ ዶርቢቴል በኩል ስንራመድ መንገዳችን ላይ ምናምን ሲለቃቅሙ ከነበሩት ወፋፍራም እርግቦች አንዷን በእግሬ ቃጣሁባት:: አልበረረችም። እንዲያውም አልዘለለችም፡፡ እንደ ሞጃ
ወይዘሮ ደበልበል እያለች ከመንገዳችን ወጣ አለች። ባህራም
«የከይ ኮስሮ እርግብ ብትሆን ይህን ጊዜ በራ ጠፍታ ነበር»
አለ።
«ከይ ኮስሮ?»
«የጥንት የኢራን ሻህ፡፡ አየህ ከይ ኮስሮ በሰረገላ መሄድ ሰለቸው:: በአየር መሄድ አማረው:: የሌላ አገር ንጉስ ቢሆን መብረር
እንዳማረው ይቀር ነበር። ከይ ኮስሮ ግን የኢራን ሻህ-ን-ሻህ ነው::
መብረር ካሰኘው መብረሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ አንድ አምስት መቶ ወፎች ሰበሰበና ከአልጋው ጋር አስሯቸው ሲያበቃ፣ በማእረግ
አልጋው ላይ ወጥቶ ተጋደመና፣ አንዴ ጅራፉን ሲያስጮህባቸው
ጊዜ ተነስተው በረሩ። ከይ ኮስሮ አልጋው ላይ እንደ ተቀመጠ
ወደላይ ወጣ፣ ግን የልጓሙን ጉዳይ ሳያስብበት ቀርቶ ኖሮ፣ ወፎቹ ወደ ልዩ ልዩ ኣቅጣጫ መብረር ስለሞከሩ፣ ሩቅ ሳይሄዱ አልጋው ወደታች መዝኗቸው ወደቁ፡፡ ከይ ኮስሮ እግሩን
ተሰበረ። ከሚኒስትሮቹ አንድ አምስቱን አስገደለ»
«ለምን?»
«መጀመርያውኑ ተው እንዳትሰበር ብለው ስላልመከሩት። ግን
መጀመርያውኑ ተው እንዳትሰበር ቢሉት ኖሮ ደግሞ ያስገድላቸው
ነበር»
«ምክንያቱስ?»
መብረር ሲያምረኝ፣ ለምናባታችሁ ነጃሳ ቃል ትናገሩኛላችሁ? ብሎ ነዋ!»
«ግሩም ንጉስ ኖሯል!»
«እንዴታ! ተራ ንጉስ መስሎህ ኖሯል እንዴ? የኢራን ኻህ ን.
ሻህ ነው' ኮ።
እና ከዛስ?»
«ከዛ እግሩ ሲድንለት ለራዊቱን አስከተተና ወደ ህንድ ዘመተ።
«ከህንድ ጋር ጠብ ኖሯችኋል?»
«የምን ጠብ? ህንድ መቼ ጠብ ያውቃል?»

👍15
«እህ! እንግዲያው ከይ ኮስሮ ለምን ወደ ህንድ ዘመተ?»
«የደምቡን ለማድረስ ነዋ»
«በጭራሽ አልገባኝም»
ላስረዳህ፡፡ በዚያን ዘመን ማንም የኢራን ንጉስ ገንዘብ
ሲያስፈልገው ወይም ጉልበቱን ማሳየት ሲያምረው፣ ትንሽ ሰራዊት
ይሰበስብና ወደ ህንድ ብቅ ይላል፡፡ እንግዲህ ህንዶች ለቡድሀ ወይም ለሺቫ ይሁን፣ ለሌላ አምላክ ይሁን፤ ያለ የሌላቸውን አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ሉል፣ ምናምን ቤተ መቅደስ ውስጥ ያከማቻሉ።የኢራን ሰራዊት ይመጣና ለደምቡ ያህል ማለት ጦርነት አርገናል ለማለት ያህል ጥቂት የህንድ ወታደሮች ገድሎ፣ ሌሎቹን አባሮ
ሴቶቹን ትንሽ ተደስቶባቸው ሲያበቃ፣ ቤተ መቅደሱ ውስጥ
የተከማቸለትን ሀብት ተሸክሞ ወደ አገሩ በሰላም ይመለሳል
«ማንም ሻህ.ን.ሻህ በዘመነ መንግስቱ አንድ ጥያቄ ይገጥመዋል።ይኸውም፣ የኢራንን ህዝብ አዲስ ግብር ማስከፈል ይቀላል፣ ወይስ አንድ ሁለት ሺ ወታደር አስከትሎ ህንድ አገር ደርሶ መመለስ ይቀላል? የሚል ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንድ ነገስታት አሉ፤ የኢራን ታሪክ የሚያስታውሳቸው ህንድ አገር ባለመዝመታቸው ነው»
እንደዚህ እየቀለደ ካፌ ዶርቤቴል ደረስን። ሀበሾቹ አሁንም
ካርታ ጨዋታቸውን ይዘዋል፡፡ ባህራም እንደልማዱ
«አስቀያሚ! ሸርሙጣ! ሀሳለሴ ሙት! Je veix jouer aux cartes!»
እያለ መሀላቸው ቁጭ አለ። (ካርታ አጫውቱኝ)
እንደ ወጣት ረዥም ባህር ዛፍ ሆኖ ታየኝ . የመከራ ነፋስ
ይነፍሳል፣ ባህራም ይታጠፋል፤ መሬት እስኪነካ ይታጠፋል፤ ግን
አይሰበርም፣ ተመልሶ ቀጥ ይላል፤ እስከሚቀጥለው ነፋስ ድረስ ..
በስንት ጭቅጭቅ ጋዜጣዬን ከተካ ተቀብዬ ወደ ሲልቪ
ቤት ሄድኩ ባህራም የነገረኝን ሁሉ አጫወትኳት፡፡ ለረዥም ጊዜ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ
«ይገርምሀል፡፡ እኔ' ኮ gigolo ይመስለኝ ነበር» አለችኝ
«ዢጐሎ? ምንድነው እሱ?» አልኳት
«ዢጐሎ አታውቅም? ገና አልሰለጠንክማ!»
«እኮ ምንድነው እሱ?»
«ሴቶችን እያስደሰተ ገንዘብ የሚቀበል ወንድ ነው»
«ታድያ ባህራም ምኑ ያምራልና ዢጊሎ ይሆናል?» አልኳት
«አያምርም። ግን ከሚያምሩ ወንዶች ይበልጥ ደስ ይላል»
«አይ! እንግዲህ ወሬ እንለውጥ»
“እሺ። ግን እሱ የነገረህን ሁሉ ባታምን ይሻላል»
«ለምን?»
«ሰውዬው አሪፍ ውሸታም እንደሆነስ?»
«ይመስልሻል?»
«ይመስለኛል»
«እኔ ግን አይመስለኝም።
«እስቲ እናያለን» አለችኝ
እንዲህ በማለቷ በሸቅኩ፡፡ ግን መብሸቄን አላሳየኋትም፡፡...
✨ይቀጥላል✨

👍11
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል
፡
፡
#ስምንት (የመጨረሻ)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ
ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች።
ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት ልብሷን ከትራስጌ በኩል አንስታ ለበሰች፤ ተመልሳ ተኛች። ድንብርብሯ ወጥቶ ነበር። በብርድ ልብነስ በታፈነ ድምፅ ችግር የለውም” እለች እንደገና።..
“ሙና” አልኳት ጀርባዋን ሰጥታኝ ነበር የተኛችው። ልክ ሰይጣን የጠራት ይመስል ድንግጥ ብላ፣
“እ” አለችኝ። ድንጋጤዋ እኔንም አስደነገጠኝ።
“ይቅርታ እስካሁን ስላልነገርኩሽ"
“ችግር የለውም ! ይሄ ማንንም ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እንተኛ።” አነጋገሯ ምንም ለዛ የሌለው የሽሽት ይመስል ነበር፤ ዝም ላለማለት ያህል። ተኛች፤ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለኝ። ልነካት ፈራሁ።የሆነ አተኛኘቷ ራሱ ትንሽ ከሰውነቴ ራቅ የማለት ነገር ነበረበት። ይሰማኛል እባብ የሆነ ነፋስ በመሐላችን በተፈጠረ ሰርጥ መለያየት ሲሳብ …
ተነስቼ ከአልጋዬ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። ከፊቴ ትንሽ ጠረጴዛ አለች፤ መፃፍ ሲያምረኝ ከምኝታዬ ተነስቼ የምፅፍባት። ለምን ያህል ጊዜ እንደተቀመጥኩ እኔጃ፤ ሙና በእንቅልፉ ስትንቀሳቀስ ብርድ ልብሱ ተንሸራትቶ ግማሽ አካሏ .ተራቆተ። ህልም የሚመስል ቀይ ሰውነት፣ ከውስጡ ብርሃን የሚያመነጭ ሙልት ያለ ሰውነት፤ ውብ ሰውነት። በዚህች ቅፅበት ውስጤ በቅናት አረረ። የማላየው የወንድ እጅ እዚህ ሰውነት ላይ ሲያርፍ አሰብኩ። የሙና ሰውነት የደረቀ መሬት መስሎ ተሰማኝ። ውሃ የናፈቀ፡ የተቃጠለ፣ ማንም መቼም ሲዘንብበት ምጥጥ የሚያደርግ ምድረበዳ።
ዝም ብዬ አያታለሁ። ልቤ ታፍኗል። መረረኝ፣ ሕይውት አስጠላኝ። ሙና ስዕል ብትሆን ብዬ ተመኘሁ። የትም የማትሄድ፣ ለዘላለሙ እዚህ ተቀምጬ የማያት ስዕል፣ የምትታይ ብቻ። የስዕል፣የግጥም፣ የዘፈን የሁሉም ጥበብ መነሻ አለመቻል መሆኑ የገባኝ እዚህች ነጥብ ላይ ነው። ሰው አለመቻሉን ሲገልፅ መግለጫው መንገድ ላይ ይጠበብና ጥበበኛ ይባላል። ሰው በአካል ያልደረሰበትን ጥግ
ነው በጥበብ እጆቹ ተንጠራርቶ ለመንካት የሚፍገመገመው።
ሙና ተንቀሳቀሰች። ብርድ ልብሱ ሙሉ ለሙሉ ወደ እንድ ጎን ተሰበሰበ። በስስ የሌሊት ልብስ፣
ሰውነቷ ፍም መስሎ ቀልቷል። እዛጋ ሆና እዚህ ያለሁ እኔን ወላፈኗ ፈጀኝ። እንቁልልጭ የምታጣትን ልጅ ተመልከት.. እንዴት ውብ እንደሆነች እይ” የሚለኝ ሰይጣን ጭንቅላቴ ውስጥ የተቀመጠ መሰለኝ።
እየኋት …. ትክክከከ ብዬ አየኋት። ሕሊናዬ ትልቅ ሸራ ሆኖ መንፈሴ በማይጠፋ ቀለም ሙናን እየሳለ
ነበር። ልቤ ትልቅ ብራና ሆኖ ሙናን እየፃፋት ነበር። ከወንበሬ ተነስቼ የሙናን የእግር ጣቶች ተራ
በታራ ሳምኳቸው፤ አስሩንም። የተለኮሰ የሲጋራ ጫፍ የሳምኩ ይመስል የእግሮቿ ጣቶች ከንፈሬ ላይ ረመጥ ሙቀታቸውን አተሙት። ደግሞ የእግሯ ልስላሴ ! ወደ ቦታዩ ተመለስኩ። ብርድ ልብሱን አላለበስኳትም፤ ላያት ፈልጌያለሁ።
ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ ሙናን ስመለከታት የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ግጥም ልክ ጎረቤት እንደተከፈተ ዓይነት ከነድምፁ ጥርት ብሎ እንደ ጅረት ውኃ አዕምሮዬ ውስጥ ይፈስስ ጀመረ። ያውም በዓይኖቼ ሞልቶ በሚፈሰስ እንባዬ ታጅቦ። #ሶልያና የእኔ ኑዛዜ - የግጥም አልፋና ኦሜጋዬ … እያንዳንዱ ግጥም የኑሮ ዝባዝንኬ ድንጋዩን ቢጭንበትም አለ ጊዜ እንደ ከርሰ ምድር ውኃ የሚፈነዳበት። ገጣሚው እዚህ ተቀምጦ ሙናን እየተመለከተ የፃፈው እስኪመስለኝ፣ ሶሊያና የሙና የቤት ስሟ፣ የመኝታ ቤት
ስሟ እስኪመስለኝ … ገጣሚው የእኔን ሙሾ በደረቀ ሌሊት አወረደው ….
ሶ ሊ ያ ና
እኔን ከወንበር ላይ፤
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ፣
ወረቀት ላይ ወስዶኝ ….
እርሷን ካልጋችን ላይ፣
እንቅልፍ አሽኮርምሟት፣
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት፣
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ፣
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ፣
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ፣
ከደጋው ሐሳቤ በረሃ ስሰደድ፣
እንባን በፊደላት፣
ፊደልን በቃላት፣
ቃላትን በሐሳብ፣
ወረቀት ላይ ልወልድ፣
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ፣
"የኔ ነሽ” የምላት ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል
“ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋዬ ላይ፣
አንተን መናፈቅ በስሜት ስሰቃይ"
ቀና ብዬ ሳያት እውነት አለው ቃሏ፣
ፍም መስሏል አካሏ፣
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል፣
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል፣
እኔን በመጓጓት ደሟ ተቆጥቶ፣
ፍቅሯ ተሰውቶ፣
ስሜቷ ተጎድቶ፣
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ሕፃን፣
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉሯ ሲበታተን፣
ካልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን፣
ፍ ቅ ሬ ሶሊያና አወራችኝ መሰል በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ…
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰት ዓለም፣
የሰዎች ጥላ እንጂ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ፣
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ፧
ሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ፣
እኔ ውበቱ ነኝ ለፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም... ወዲህ እንዳትመጣ፣
በሌሊት ትጋትህ ሐዘን ሳይቀጣ፣
በኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ፣
ከየሰዉ ዓለም የሚመሳለሉ፣
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ፣
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፉ፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰዎችን እንባ
አትፃፍ ግዴለም፡
የፍጥረትን ሐዘን ስለህ አትዘልቅም፣
እውነት እለው ብለህ ሐዘንን አታልም፣
((ያለቀሱም ሰዎች ሐቀኞች እይደሉም}
ይልቅ የኔን ስሜት፤
ያንተንም እንባዎች ሁለቱን አሳየኝ፣
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ ! እኔን ብቻ ፃፈኝ !
“ያልተደሰተች ሴት” በሚል መጽሐፍህ
ዘ ላ ለ ም አሻግረኝ፣
ዘ ላ ለ ም ውሰደኝ፣
ዘ ላ ለ ም አኑረኝ !!”
“የኔ ነሽ” የምላት፣ “ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል።
ቁጭ ያልኩበት ወንበር ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ…
ሊነጋጋ ሲል….
“አብርሽ” የሙና ድምጽ እንደ ህልም ተሰማኝ። ዓይኖቼን ስገልጥ ፊቴ ቆማ ነበር። ልብሷን ለባብሳ፣አንድ እርምጃ የሚሆን ከእኔ ራቅ ብላ ቆማ ነበር። ሙና ስትቀሰቅሰኝ እንዲህ አልነበረም፡፡ ከተኛሁበት የምትቀሰቅሰኝ በከንፈሯ ነበር። በተኛሁበት ስትስመኝ ነበር የምነቃው። እና እዛጋ ምን አቆማት ፣
ሁሉን እንቅልፍ ባስረሳው በደበዘዘ አዕምሮ አያታለሁ።
“ተነስ ቁርስ ሰርቼልሃለሁ”
በዝምታ እንቁላል ፍርፍር በላን፣ ሻይ ጠጣን፤ (በዝምታ) ዕቃዎቹን አነሳስታ አጣጠበች እና መጥታ
ጎኔ ተቀመጠች። ሁለታችንም በአስፈሪ ዝምታ ውስጥ በዝምታ እንደተቀመጥን ድንገት የሙና እንባ ተዘረገፈ፤ እናም አቀፈችኝ። ከሙና እንዲህ ዓይነት ጉልበት ያለው አስተቃቀፍ አልጠበቅኩም ነበር።

👍25❤1🥰1
ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ጥብቅ ! አውቄያለሁ ሙና እየተለየችኝ ነው። ተነሳች .. ቦርሳዋን አነሳች ..
ቆም ብላ አይታኝ ወደ በሩ አመራች፤ ከፍታ ስትወጣ አላየኋትም።
እስከ ምሳ ሰዓት ከተቀመጥኩበት ሳልንቀሳቀስ ቁጭ ብዬ፣ ምንም ሳላስብ፣ ምንም ሳላይ ምንም ሆኜ ቆየሁ። የሆነ የመሬት ስበት የሌለበት ሕዋ ላይ እንደመንሳፈፍ ዓይነት ስሜት።
“ቻው ሙና” አልኩ ቁርስ ሰዓት ላይ የወጣችውን ልጅ ምሳ ሰዓት ላይ …. ቻው !
በሕዋ ላይ እየተንሳፈፍኩ ሥራ እሄዳለሁ፣ እመጣለሁ፤ እሄዳለሁ፣ እመጣለሁ … ከሙና ጋር ከተለያየን
2.3.45.67...
ወራት! “ግን ምክንያቱ ያለያይ ነበር እንዴ ?” እላለሁ አንዳንዴ። ሙና ቢያንስ የእኔ ችግር አለመሆኑን አውቃ፣ “እንዴት ሆንክ አይዞህ” አትለኝም እንዴ ? እላለሁ። ቅዳሜ ሁልጊዜ
የምትመጣ ይመስለኛል። ሁልጊዜ ከመኝታ ቤት ስወጣ ሳሎን ተቀምጣ የማገኛት ይመስለኛል። ሙና አለመደወሏ ይገርመኛል። ለድፍን ሰባት ወራት ስልኬ ሲጮህ ሙና እንደምትሆን እርግጠኛ ሆኜ አነሳው ነበር። ሙና ግን ተወችኝ !! (ተወችኝ ቃሉ እንዴት ያማል) ስልኳን ከሄደች ከሳምንቱ ጀምሮ እሞክር ነበር፤ አይሰራም ቁጥር ቀይራ ይሆናል።
ከሙና ጋር ከተለያየን ከዓመት ከምናምን በኋላ ሃኒባል እንዲህ አለኝ፣ “አብርሽ ከሌላ ሰው ሰምተህ ከምታዝን ራሴ ልንገርህ ብዬ ነው”
“ምንድን ነው”
ሙና ልታገባ ነው። ነገ እሁድ ነው ሰርጓ። አልደነገጥኩ፣ አልተከፋሁ፣ አልተደሰትኩ፣ አላዘንኩ !!
ድንዙዝ !!
እና ይሄ ምኑ ያሳዝናል” አልኩት ሃኒባልን።
( እ ? ሙና እኮ ነው ያልኩህ” አለ በግርምት እያየኝ።
“አይገርምም” ደገምኩለት ! የፍቅረኛ ሌላ ሰው ማግባት የመጨረሻው ጭካኔ የሚመስላቸው የመጨረሻ የዋህ ሰዎች አሉ። በፍቅር ውስጥ የመጨረሻው ህቅታ .. ጀርባን መስጠት ነው። ሙና ጀርባዋን ሰጥታኛለች። በእርግጥ እውነት አላት፤ ሙሉ ለሙሉ እኔ ችግር ውስጥ ነኝ። ሙና ደግሞ
ሰው ናት። ስለዚህ መሟዘዙ እድሜንም ስሜትንም ማባከን ነው፤ ደግ ሄደች ! እንኳንም ለቁም ነገር አበቃት። በቃ! ሙና ድል ባለ ሰርግ አገባች። የሰርጓ ቀን እዚህ ብሔራዊ መናፈሻ ውስጥ ተቀምጬ ዝም ብዬ ያንን የድንጋይ አንበሳ ሳየው ዋልኩ። “አንበሳው አንበሳ ባይመስልም የበላው ብር አንበሳ
ያስመስለዋል” አሉ አሉ ንጉሡ። ወንድነታችን ወንድ ባይሆንም ወንድ ለመምሰል ያቃጠልነው
ጊዜ ወንድ ያስመስለናል። ማሕበረሰቡ የከፈለልን የሞራልና የባሕል ዋጋ ወንድ ያደርገናል ... ቱ ! ቀፋፊ ቀን !! በሕይወት ውስጥ እንዲህ አፈር ድቤ በሚያስበላ ሽንፈት ያለህን ሁሉ ተነጥቀህ ባዶህን ሐውልት ሆነህ ሐውልት ፊት የምትቀመጥበት ጊዜ አለ። ያው ሐውልቱም የራሱ ታሪክ አለው፤ አገር የሚያውቀው። አንተም ታሪክ አለህ ማንም የማያውቀው፤ ብቻህን የሚያንገበግብህ። የእኔና የዚህ
የአንበሳ ሐውልት አንድነታችን ሁለታችንም የምንመስለውን አለመሆናችን ነው። እሱም አንበሳ፣ እኔም ወንድ አይደለሁም፤ መምሰል ብቻ።
አንዲት የሙና ጓደኛ አለች ሔዋን የምትባል። ከጥቁረቷ ብዛት የሙና ጥላ የምትመስል። ጀበና ሔዋን ጎን ቢቀመጥ ጠይም ይባላል። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የመሰለች። ድሮ እንኳን ብዙም አልቀርባትም ነበር፤ ከሙና ጋር ከተለያየን ጀምሮ ግን ሙና ስትናፍቀኝ አገኛታለሁ። እንዲሁ የጋራ ጉዳያችን ሙና ሆና።
“ሙና ደህና ነች ?” እላታለሁ።
“ደህና ነች”
“ፀሐይ ሲመታት ራሷን ያማት ነበር፤ አሁን እንዴት ነች ?”
“ደህና ናት ! ባሏ መኪና ገዝቶላታል፤ ፀሐይ የት ያገኛታል ብለህ ሃሃሃሃሃሃ
“ማንስትሬሽን ላይ ስትሆን በጣም ነበር የሚያማት አሁን እንዴት ሆና ይሆን ?”
አይ አብርሽ ! እሱማ ያው በየወሩ ነው አይቀየር ነገር፤ ስትወልድ ይተዋል ይባላል ባይ ዘ ዌይ
ሙና እርጉዝ ናት !” ልቤ ላይ የሆነ ነገር ሲሰካ ይሰማኛል። አገባች ሲባል ምንም ያልተሰማኝን፣ ልከ
እርምህን አውጣ ዓይነት መርዶ ይመስል ይሄንኛው አመመኝ፤ በጣም አመመኝ።
ከመቀሌ ወደዚህ ለመምጣት ቅያሬ ጠይቃ ነበር ተሳክቶላት ይሆን ?”
“ጠይቃ ነበር እንዴ ? እኔ ይሄንን አላወቅኩም ... አሁን ግን ሥራ አቁማለችኮ” አለችኝ በግርምት
(ምን አስገረማት)። በቃ ስለሙና ጥግብ እስከምል እጠይቃታለሁ፤ ሳትሰለች ታወራኛለች። መተንፈሻዬ
ሔዋን። በጣም ተቀራረብን፤ ቤቷ ሁሉ ወስዳኝ ቡና ታፈላልኛለች። መቼም መድረሻ ቢስ ሆኛለሁ።
ሙና ከሄደች በኋላ ለጎተተኝ የምጎተት ከርታታ ዘባተሎ ነገር ... የት ነበርክ ብባል እዚህ የማልል
የቱንም ያህል ጥብርር ያላችሁ ብትሆኑ፣ ሰው ለዓይኑ የሚናፍቃችሁ እንኳን ብትሆኑ፣ የሆነ ጊዜ አለ
እንደምናምንቴ የትም የምትገኙበት፣ ምነው በዛህ የምትባሉበት ...
አንድ ቀን ታዲያ ሔዋን ቤት ሄደን ከተደረደሩት ሲዲዎች አንዱ ላይ ዓይኔ አረፈ። የሙና የሰርግ
ቪዲዮ ! እንድትከፍትልኝ ሔዋንን ጠየቅኳት። አንገራግራ ተለምና በመከራ ከፈተችልኝ። ሙናዬ የኔ
ቆንጆ እንዴት ነው ያማረችው በእግዚአብሔር ! ባሏም ቆንጆ ኃብታም ነው። እንደኔ ኮሳሳ ሳይሆን የሆነ ግርማ ሞገስ ያለው፤ በጣም ነው የሚመጣጠኑት ! ቀናሁ፣ አደገኛ የበታችነት ስሜት ደቆሰኝ።
ቪዲዮውን እያየሁ ነው፤ ባሏ ለቤተዘመዱ ዲስኩር እያሰማ ሙና ከጎኑ ቆማ በእፍረት ትሽኮረመማለች
(ስትሽኮረመም ስታምር !)
እና የሙና ባል በኩራት እንዲህ አለ፣ (እጁን የሙና ትከሻ ላይ ጣል አድርጎ ... የእኔ ትከሻ ላይ እጁ
ያረፈ ያህል ከበደኝ)
ከሙና ጋር የዛሬ (ሦስት ዓመት) ፍቅር ስንጀምር፣ ለእኔ የከፈለችውን መስዋትነት ባትከፍል ኑሮ ለዚህቀን ባልበቃን ነበር። እኔ መቀሌ፣ እሷ አዲስ አበባ ሆነን((((ለእኔ ስትል ቅያሬ ጠይቃ መቀሌ ድረስ መጣች))))። የፍቅር ጀግና ናት ሙንዬ” ... ታዳሚው አጨበጨበ ቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿ
ቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿ
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አብርሾ ሞኙ ሰው አማኙ..እንደ እብድ ነው የሳቅኩት።
አስታወስኩ…አንድ ጊዜ መቀሌ ሄጄ የሙና ቤት አከራይ፣ “ደህና ዋልክ አክሊሉ” አሉኝ። ወደ እርሳቸው ስዞር፣ “የኔ ነገር ያንዱን ስም ከአንዱ ማጋጨት” ብለው ሳቁ። የሙና ባል አክሊሉ ነው ሥሙ!
ተቀበል አዝማሪ ...
ኧረ ሙና ሙና ሙና አቀበቲቱ፣
ስቃ ገደለችው ወንዱን ልጅ ሴቲቱ!
አሁን ሰሜን ደቡብ ምን ያሰኘዋል ሰው፣
አሁን ቆላ ደጋ ምን ያሰኘዋል ሰው፣
እንዴት ዞሮ ማያ አንገቱን ያጣል ሰው፣
እንዴት ማስተዋያ ዓይኑንስ ያጣል ሰው፣
ያጣል ሰው
ያጣል ሰው ሚሊየን ጊዜ እስከ ምፅዓት ድገመው!
አንድ ሰው አራት የሚሆንበት ምናይነት ዘመን መጣ ?! ይሄ የሰርግ ቪዲዮ አይደለም። ስምንተኛው ሺ በራችንን እያንኳኳ መሆኑን የሚያረዳ “ዶክመንተሪ” እንጂ !! ቱ ! አፈርኩ እግዚአብሔርን - አፈርኩ! ሐፍረቱ አሸማቀቀኝ። ቅናት ሳይሆን ሐፍረት ! የዛሬ ሦስት አመት ማለት እኮ ከሙና ጋር በፍቅር
ያበድንበት ጊዜ ነበር። አንዲት የባንክ ሰራተኛ ከመቀሌ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ስትመላለስ ብሩ ከየት መጣ እንዴት አላልኩም ... ! አፈርኩ በራሴ ! አንዲት የባንክ ሰራተኛ የወርቅ ሃብል ገዝታ ስትሰጠኝ እንዴት ብሩ ከየት መጣ አልልም፣ ይሄው አንገቴ ላይ የለማዳ ውሻ ሰንሰለት መስሎ- ቱ! አንዲት የባንክ
ሰራተኛ ከአዲስ አበባ መቀሌ ተቀይራ ስትሄድ፣ “ምንም እቃ አላንዘፋዝፍም እዛው የሚያስፈልገኝን እገዛለሁ” ስትል፣ ቤቷ በውድ ዕቃዎች ተሞልቶ ስመለከት እንዴት?' አላልኩም ...

👍30❤3😁2
ቱ! እኔ ደግሞ፣ “እንዳንተ የሚታገስ ወንድ አይቼ አላውቅም” ስትለኝ ካየችው ማወዳደሯን በምን አባቴ
ጠርጥሬ። ሰው ትንሽ እንኳን ምልክት ሳይታይበት ጣናን የሚያህል የፍቅር ሐይቅ ፍቅረኛው አፍንጫ
ስር ተደብቆ ይገድባል ? ኧረ ገረመኝ፤ ከምር ገረመኝ ! የሆነ ፀሐይ ወርዳ እዚህ አራት ኪሎ ላይ የተከሰከሰች ነገር መሰለኝ። ሙና የኔ ፍቅር ምንድነው ያደረግኳት .. እርሷኮ ነፍሴ ነበረች። አንድ ነፍስ
ለሁለት ወንድ ይካፈላል እንዴ። እሺ እኔ ያጎደልኩባት ነገር እንዲህ የበቀል ብትር የሚያሰነዝር ነበር ?
በቀል ይሁን ምናባቴ አውቃለሁ ? እንደው ምን እንደምለው ቸግሮኝ እንጂ ..
ሔዋን ቀስ ብላ መጥታ ጎኔ ተቀመጠች - ሔዋን የሙና ጓደኛ። እናም ትካሻዬ ላይ እጄን ጣል አድርጋ
እንዲህ አለች፣
አብርሽ በናትህ እንደሱ አትሁን” ዓይኗን አንከባለለችው። ያላት ውበት እሱ ብቻ ነው መቼም።
አንቺ ታውቂ ነበር ሙና ከእኔ ጋር ሆና ሌላ ወንድ ጋር ፍቅር እንደ ጀመረች ?”
በእውነት አላውቅም!እኔም ቪዲዮውን ሳየው ገርሞኛል”
ዓይኖቿ ተስለመለሙ። ሔዋን እጇ ትከሻዬ ላይ ነው። በጣም ተጠግታኛለች። እና ዝምታችን የሆነ ድባብ አለው። ሔዋን በጣም ተጠግታኛለች።
እንደውም አንዲት የቆመች ፀጉሯ በስሱ ጆሮዬን ስትነካኝ ተሰማኝ።
ምን ተፈጠረ ? ሔዋንን እያየኋት ወንድነቴ ነፍስ ሲዘራ ተሰማኝ። ማመን አልቻልኩም፤ ሱሪዬን
አውልቄ በዓይኔ ላየው ዳድቶኝ ነበር።ሔዋን ጎኔ ናት፤ እጄን አንስቼ ትከሻዋ ላይ አሳረፍኩት፤ ጠጋ
አለች እና እንዳቅፋት ተመቻቸችልኝ። እንደውም ራሷን ትከሻዬ ላይ ዘንበል አደረገችው። ወንድነቴ ዘራፍ ማለቱ እውን ሆነ።
ለሃኒባል ደውሉና ቆመ በሉልኝ !! አብሮኝ ተንከራትቷል። ቋሚ ይቆም ዘንድ አብሮኝ በችግሬ ለቆመ ቁም ነገረኛ ወዳጄ እመብርሃን በችግርህ ከጎንህ ትቁም በሉልኝ!ሙና ግን መንፈሷ የተኮላሸ ሴት ናት።
ልከስክስ !! መቶ ዓመት ለማይኖርባት ምድር ረክሶ ተልከስክሶ እና አስመስሎ መኖር ክብር መስሏት ቆይ ዘላለም ላይ እንገናኝ የለ!
፡፡፡፡፡፡፡፡።፡
የሔዋን መኝታ ቤት እንዴት ሰፊ ነው ? ሔዋን ደረቴ ላይ በእርካታ ተኝታ እንዲህ አለችኝ፣ “አንተ
የሚወራው ሁሉ ውሸት ነው ማለት ነው ...ውይ የሰው ወሬ"
"ምን ተወራ"
" እንትን አይችልም እየተባለ ነዋ የሚወራው”
“ማነው ያለው” አልኩ ታሪኬን ሐሰት ልል እየተንደረደርኩ።"
“የድሮ ሚስትህ ነቻ” ሙንዬ፣ ሙኒት፣ ሙንሻ የምትላት ጓደኛዋን “የድሮ ሚስትህ” ስትል አይቀፋትም ?
“ባክሽ እሷን ተያት” እቅፍ እቅፍቅፍ … እቅፍፍቅፍቅፍ !! ያልታቀፈበት ዘመናችንን ቀይ የሙና ገላ በጥቁር የሔዋን ገላ መቀያየሩ አልጋ ላይ የተዘረፈ ቅኔ ነገር ነው ... ይነጋል ይመሻል እንደማለት !
“አንተ አፈ ን ከ ኝ ሂሂሂ” ሔዋን የሙናን ፍቅረኛ በፍቅር አሸንፋ ራሷን የድል ማማ ላይ አስቀምጣ
ተፍነሽንሻለች። የሙና ባል እኔን አሸንፎ፣ሙናም እኔን አታልላ በብልጠት አልፋኝ እንደሄደች ሳይሰማት አልቀረም። እኔም ደስ አላለኝ አልከፋኝ፤ እንደው ደርበብ ባለ አብሮነት ዝምታን መረጥኩ። ለምን ደስ ይለኛል? ማፍቀር ተኮላሽቶ ወንድነት ስለቆመ? እንዲህ ዓይነቱን ደነዝ ወንድ የሚያመርተው፣ ደነዝ ክህደት ... ለሙና ሆነ!! መቼም ቢሆን አፉ አልላትም፤ ምክንያቱም አፈቅራታለሁ።
✨አለቀ✨

👍33👏3👎2
#ዓድዋ
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
#ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
#ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
#ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... #ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... #ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
#ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
#ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
#ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
#ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... #ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... #ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
#ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
👍13
‹‹ዓድዋ››
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ ዓድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሺባባው (ጂጂ)
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ ዓድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሺባባው (ጂጂ)
👍13❤5
#አታውቃት_እንደሆን
ሰው እንደ ሰው ቢቆም፥በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም፥ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት #ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
ሰው እንደ ሰው ቢቆም፥በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም፥ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት #ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
👍3
#አድዋ_ዛሬ_ናት_አድዋ_ትላንት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
(አንቀፅ 17 ፡ እኛም መስኮታችንን አንከፍትም፣ እናንተም ሚስቶቻችንን አትዩ ፡)
ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርራ አምስት ዓመት ፍዳዋን በልታ፣ ፍዳችንን ስታሰበላን አያቴ እሳት የላሰ
የውስጥና የውጭ አርበኛ ነበር። በጦር ሜዳ ብትሉ አንድ ባታሊዮን ጦር ጭጭ ምጭጭ ያደረገ
ጀግና ሲሉት፣ “ኤዲያ ምን አላት እቺ” ይላል !! በከተማ ብትሉ" ጠላት መኝታ ቤት ሳይቀር የተቀመጠ ሚስጥር ፈልፍሎ ሲያወጣ አጀብ ያስብል ነበር። ታዲያ በአያቴና በቆራጥ አርበኞች ትግል ፋሺስት ኢጣሊያንን ከሀገር ከተባረረ በኋላ፣ ለአገር በሠራው ታላቅ ጀብዱ፣ በድል አጥቢያ ጃንሆይ ራሳቸው አስጠርተው አሁን የጣልያን ኤምባሲ የሚባለው የተገነባበትን ቦታ በሙሉ ከታላቅ ክብርና ምስጋና
ጋር በሽልማት ለኢያቴ ሰጡት !
አያቴ እዚሁ በሽልማት የተሰጠው ቦታ ላይ ትንሽ ጎጆ ቀልሶና፣ የተረፈው ሜዳ ላይ የቆሎ ዘርቶ
ሲኖር፣ አንድ ቀን የጃንሆይ መልዕክተኞች ሲገሰግሱ ቤቱ ድረስ መጡና፣
“እዚህ በቆሎ የዘራህበት ቦታ ላይ የንባሲዮን ሊሰራሰት ነውና መድረሻህን ፈልግ ብለውሃል ጃንሆይ አሉት።
“ኧረ ውሰዱት ደሞ ለሞላ ቦታ አላቸው። ትንሽ ቆይቶ፣ “ይሄ ግን 'የንምባሲዮን' ያላችሁት ነገር መንግስት ነው ?” ሲል ጠየቀ።
“አይደለም !"
“አሃ ተማሪ ቤት መሆን አለበት :"
“አይደለም!”
ታዲያ ምንደን ነው ቤተስክያን ይሆን እንዴ ?" ሲል ግር ብሎት ጠየቀ።
"ኤማቢሲዎን ማለትንጉሥ የፈቀዱላቸው የውጭ አገር መኳንት እና መሳፍንት አገራቸውን
መስለው የሚቀመጡበት እና አንዳንድ የመንግሥት ሥራዎችን የሚከውኑበት ማረፊያ ነው" አሉት
ሳኔ ዕክተኞቹ አንዱ። ከመልክተኞቹ አንዱ።
"በቃ ?" ሲል ጠየቀ አያቴ በግርምት።
"በቃ!"
"እኮ ፈረንጆች ይሄን ሁሉ ቦታ አጥረው ቁጭ ሊሉ ነው” አለ እንደገና በታላቅ ግርምት።
"አዎ ! ይሄ የምባሲዮን ... የወከላቸው አገር የማይደፈር ግዛት ነው”
እንዲያ ድንበራችን ላይ ያባረርነውን ጠላት መናገሻችን ላይ አርደንለት ጋርደንለት ልናስቀምጠው ነው በለኛ አለ አያቴ በቁጭት።
መልዕከተኞቹ አያቴ ላይ ሳቁበት። ስለኤምባሲ ያለው እውቀት አነስተኛ መሆኑን በመገንዘባቸው
ድፍን ሁለት ሰዓት ስለኤምባሲ ተግባርና ለአጎራችን ስላለው ጠቀሜታ በዝርዝር አወሩት።
ተግባብተው ሊለያዩ ሲሉ ግን ነገር ተበላሽ።ጉድፈላ። አገር ተሸበረ።ድንገት ነው ነገሩ የተመሰቃቀለው
ከሆነስ ሆነና የማን አገር ኤምባሲዮን ነው ?" ሲል ጠየቀ አያቴ፣
“ጥልያን” ብለው መለሱለት።
"ጥልያን ጥሊያን ... እኮ ጥሊያን ይሄ ፋሽስት የነበረው" አለ አያቴ ማመን አቅቶት።
"እንዴታ አሁን በሰላም መጥተዋል”
አያቴ ሰይጣኑ ተነሳ። ተንደርድሮ ምንሽሩን መዥረጥ አደረገና ለግማሽ ሰዓት ያህል ፎክሮ ሲያበቃ፣
"ባንዳ ሁላ…” ብሎ የጃንሆይን መልዕክተኞች ማሳደድ ጀመረ !
ጥሎብን መከተል እንወዳለን። መንገድ ላይ ድንገት አያቴን ያዩ ሁሉ፡ ገና የአርበኝነት ስሜቱ
ያልበረደላቸው፣ እንዲሁም አርበኝነት ያመለጣቸው፣ እንደገና እድሉን አገኘን በማለት ምንሽራቸውን አፈፍ እያደረጉ፣ “ያዘው…" እያሉ ላይጠቅማቸው አያቴን ተቀላቅለው የንጉሱን መልእክተኞች ማሳደድ ጀመሩ። መቼስ አዲሳባ እንደዛን ቀን ተፎክሮባትም፣ ተሸልሎባትም አያውቅም ሲሉ ሁኔታውን የታዘቡ፡፡
አያቴ ቁጣው መለስ ሲል ዞሮ ቢመሰከት ድፍን የአዲስ አበባ ወንድ ተከትሎታል።
“ምን ሆናችሁ” ቢላቸው አያቴ፣ “አይ ሩጫው ወደ ቤተ መንግሥት መሆኑን ስንሰማ ነው
የተከተልኛችሁ” አሉ !!
አያቴ የተከታዩን ብዛት አየና በዛው ሸፈተ ! ስሙ የገነነ ሽፍታም ሆነ ! ስሙ ከተጠራ እንኳን ኢትዮጵያ
ምድር ያሉት ሮም የተቀጡትም ጥልያኖች ወባ እንደያዘው እየተንዘፈዘፉ ንሰሃ ይገባሉ ! ጭራሽ የኤምባሲው ግንባታ ሲጀመር በወርም በሳምንትም በል ሲለው በየሦስት ቀኑ ብቅ እያለ ይሄን ጣልያን ሁሉ ይፈጀው ጀመረ !!
ጃንሆይ በበኩላቸው አያቴን በዲፕሎማሲ ማሳመን መርጠው መልዕክት ላኩበት። በድፍረት ከነጎፈረ ጸገሩና ከነምንሽሩ ፊታቸው ቀርቦ፤ "ጃንሆይ ትላንት ይሄን ፋሽስት፣ እንኳን አሳረርከው' ብዬ የሸለሙኝን ቦታ ዛሬ ከኔ ነጥቀው ላባረርኩት ሰላቶ በመስጠትዎ ተቀይሜዎታለሁ !! እማምላክን ተቀይሜዎታለሁ። እንዴት እንዴት ነው ነገሩ ... እዚህች አገር አባራሪው ከተባራሪው ተደባለቀ እኮ
ዳር ላይ ያባረርነው ከመሐል እያባረረን ተቸገር?" አለ።
ጃንሆይ በጥሞና ሲያደምጡ ቆዩና፣ “ቅሬታህን ሰምተናል። ካንተ የሚበልጥብን የለም። ያው አንተ ዳር ላይ ልክ ያስገባሃቸው ናቸው ዛሬ ወዳጅነታችንን ፈልገው በእንብርክክ ደጅ የጠኑን
እንደምታውቀው ጀግና በጠብ የመጡበትን አንጂ በፍቅር የመጣን አይነኩም አሉና የአያቴን ቁጣ አበረዷት።
“በል አሁን በቃህ ለማን ብለህ ነው መሬትህን ጥለህ የምትሄደው፡፡ እነሱ እያዩህ ይሸማቀቁ እንጂ ብለው እዛው ኤምባሲው ጎን ለአያቴ ሰፊ ቦታ ሰጡት።
እርቅ ወረደ! ንጉሡ ብልህ ነበሩ። አንዳንዴ አያቴን ይጠሩትና፣ ጎረቤቶችህ ሰላም ናቸው ? ብለው
ይጠይቁታል። አያቴን ሰላይ አደረጉት እንግዲህ የአያቴ ጎጆ እና የጣሊያን ኤምባሲ በግንብ አጥር ብቻ ነበር የሚለያዩት። አያቴ ጣልያኖቹን ባያቸው ቁጥር ደሙ እየፈላ፣ "ወይ ነዶ የማንም ፋሽስት ጋር እንዲህ ትከሻ ለትካሻ እየተጋፋሁ ልኖር” እያለ በብስጭት ሲግል ሚስቱ ወይዘሮ በልጅጌ መኮንን (የፊታውራሪ መኮንን እጅጉ የመጀመሪያ
ልጅ እያባበለች ወደ መኝታ ቤታቸው ትወስደውና ከብስጭቱ አብርዳ በሌላ ጉዳይ ትለኩሰዋለች ! አቤት ማባበል ስታውቅበት …. ገና ስትታይ ነገር ታበርዳለች ... እሳት ፈገግታዋ እሳት ያጠፋል ... ይች ውብና አስተዋይ ሴት ሲበሳጭ ስታባብለው፣ ሲበሳጭ ስታባብለው .… አምስት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ ወለዱ። ይሄ ብቸኛ ወንድ ልጅ የእኔ አባት ነበር።
አያቴ ምንም እንኳን የልጆቹን አእምሮ በምክር አርሶና አለስልሶ የጣሊያንን ጥላቻ ቢዘራበትም
አልፀደቀም። በተለይ ሴት ልጆቹ ያማረ መኪና ይዘው የሚገቡና የሚወጡ የጣልያን ጎረምሶች ላይ
ልባቸው አልጨክን እያለ፣ ዓይናቸውም እየተንከራተተ አስቸገረው። ጭራሽ ይለይልህ
ብለው ከአባቴ በስተቀር ሁሉም ሶላቶ' አግብተው ቁጭ አሉ። በዚሁ ብስጭት ሙሉ ቦታውን ለአባቴ ብቻ አውርሶና ጥልያን ያገቡ ልጆቹን ሁሉ ክዶ ሚስኪን አያቴ በደም ግፊት ሞተ !! አባቴም፡ 'ሙሉ' የምትባል ውብ
ሴት አግብቶ እዚሁ ነገረኛ የወርስ ቦታ ላይ ቤት ሰርቶ መኖር ጀመረ (ሙሉ እናቴ ናት…)።
እናቴ ሙሉ መቼስ ወላ በቁንጅና፣ወላ ሰባሕሪ ቢባል ይሄ ቀረሽ የማትባል ውብ ናት። ስትገባ ስትመጣ ተመልካቹ በዛ፣ የሚመኛት እልፍ ነበር። አባቴ ታዲያ እናቴ ስትደነቅና ስትሞገስ ደስ ቢለውም፣ ከተመልካቹ ሁሉ ደሙን የሚያፈላው የጣልያኖቹ አስተያየት ነበረ። እንግዲህ ጣልያኖቹ እናቴ ስታልፍ ፊታቸው እንደ ቲማቲም ቀልቶ አፋቸውንም፣ ዓይናቸውንም በልጥጠው በአጥራቸው ላይ እየተንጠላጠሉ በአጉል ምኞት ሲመለከቷት አባቴ ይሰሳጫል፤ በላቸው በላቸው ይለዋል። (ደግሞ ለማለት፣ አያቴ እንደሆነ ምንሽሩን አውርሶታል- መታገስ ደግ ነው ብሎ እንጂ…)

👍15🥰1
ምድረ ሰላቶ ከዘበኛ እስከ አምባሳደር ማፍጠጣቸው ሳያንስ፣ “ለደህንነት” በሚል ሰበብ ፊታቸውን ወደ እኛ ግቢ ያዞሩ አራት ካሜራዎች ተከሉ። እናቴ ግቢ ውስጥ በተንቀሳቀሰች ቁጥር አራቱም ካሜራዎች ወደሄደችበት ተከትለዋት ይዞራሉ (የምታጠባቸው መንታ ልጆቿ ነበር የሚመስሉት)። ሌላ ሰው ሲንቀሳቀስ ካሜራዎቹ ግኡዝ ናቸው። ካሜራዎቹ የተተከሉት ለደህንነት ይሁን ላጉል ምኞት
አባቴ ግራ ገባው።
ጭራሽ ጥልያኖች ባሳተሙት አንድ ዓመታዊ መጽሔታቸው ላይ እናቴ አጎንብሳ አሮጌ የመኪና ጎማ
ላይ በተቀመጠ ጥሰት ልብስ ስታጥብ ከኋላዋ (ያውም አጭር የውስጥ ልብስ ብቻ ለብሳ) የሚያሳይ ባለቀለም ፎቶ ተካትቶ ነበር። ከእናቴ ፎቶ ጎን አንዲት ጥላ ቢስ፣ ሽርጥ ያሸረጠች ጣልያናዊት ኮረዳ ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ደገፍ ብላ የሚያሳይ ፎቶ አለ።
ከፎቶዎቹ ሥር፣ “ኢትዮጵያ ከጣልያን ስድስት ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ለእርዳታ አገኘች ይህም የኢትዮጵያዊያንን ሴቶች ድካም በመቀነስ ጊዜያቸውን ለሌላ ጉዳይ እንዲያውሉት ይረዳሉ የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። ሌላው ጉዳይ' ምንድን ነው ሲል አባቴ አሰበ።
እንዴት የሚስቴኝ ፎቶ ካለ እሷም ካለእኔም ፍቃድ መጽሔት ላይ ያትማሉ፣ ሲል ተብከነከነ፡
እንደውም አምባሳደሩን ራሱን ማብራሪያ እንዲሰጠው ሊጠይቀው ወሰነ። ሰውን ካለፍቃዱ፣ ያውም በገዛ ግቢው ውስጥ፣ እንዴት ፎቶ ያነሳሉ … ያውም በአጭር የውስጥ ልብስ ብቻ ይሄ ንቀት ነው
አባቴ በቀጥታ ወደ ኤምባሲው ዋና በር ሄደና እንደ ግለሰብ መኖሪያ ቤት አስፈሪውን የብረት በር አንኳኳ፣
ጓጓጓጓጓ
ዘበኛው አጨንቁሮ አባቴን ከተመለከተ በኋላ በሩን ከፍቶ ባለማመን እያየው፣
“ምን ፈለግክ ?” አለው እርዳታ የፈለገ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ብሎ፣
“ጌታህን ጥራው ! ባልቻ በርህ ላይ ይፈልግሃል አለው" አለ አባቴ ቆፍጠን ብሎ። ዘበኛው ግራ ተጋባና፣
“ማንን ነው የጥበቃ አልቃውን ነው ?” አለ።
“እሱ ምን ያደርግልኛል ?
አምባሳደሩን ነው ያልኩሆ
"እ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ … በል ሂድ ወደዛ ደፋር ብሎት እርፍ አባቴ ባልቻን !
መንደሩ የተከበረውን ኣባቴን እንደ ምጽዋት ፈላጊ የሶላቶዎቹ ዘበኞ፣ ሂድ ወደዛ አለው ! በዛችው
ቅፅበት ከአባቴ የተሰነዘረ ብርቱ ጥፊ ዘበኛውን አባቴ እግር ሥር ኩርምት አደረገው። የጥፊው ድምጽ ሮም ድረስ ስለተሰማ፣ የውቅቱ የጣሊያን መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ዓለማቀፉን የኤምባሲዮን ውል እና አሰራር በመተላለፍ የተከበረ ዜጋዬን በጥፊ በመደርገም በአድዋ ካደረሰችብኝ ውርደት የበለጠ
ውርደት አድርሳብናለች ሲል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቤት አለ።
ጃንሆይም በዚሁ ጕዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው፣ “በእርግጥ አፍሪቃ ኤሮፓዊያን ቅኝ ግዛት እየታመሰችበት ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ብዛሃን የአፍሪቃ ልጆች በቆዳቸው ቀለም ምክንያት በግፍ እየተገደሉ እና እየተገፉ ባሉበት ወቅት፣ በአንዲት ኤሮፓዊት አገር ኤምባሲ የጥበቃ ሰራተኛ ላይ፣ ያውም በራሱ ስህተት፣ በተሰነዘረ ጥፊ ዓለም ይህን ያህል መንጫጫቱ ገርሞናል። ይህ ጥፊ የኢትዮጵያ መንግሥትን የማይወክል፣ በዕለት ግጭት የተከሰተ ድንገተኛ ጥረቀማ በመሆኑ ግለሰቦቹ
በቀላል ሽምግልና ችግሩን እንዲፈቱት እናደርጋለን። አገራችንም ከጥፊው ባሻገር ለአፍሪቃ ብሎም ለዓለም ያበረከተችው ቀጎ ተግባር በዚህ ጥፊ ምክንያት ሊጠለሽ አይገባም” በማለት ዓለምን ያስደነቀ፣ አገሬውንም ያኮራ ንግግር አደረጉ።
በዚህ ንትርክ መሃል የእናቴ ፎቶ ጉዳይ ተድበሰሰሰ።
በጣልያኖች ተንኮል እልህ የተጋባው አባቴ፣ “ልጆቼ ስለበረከቱ ፎቅ ቤት እሰራለሁ…” አለና ማንንም ሳያስፈቅድ ባለ ሁለት ፎቅ ቪላ ወደ ኤምባሲው አጥር እስጠግቶ መሥራት ጀመረ።
ይሁንና ጣልያኖች ለደህንነታችን ያሰገናል በማለት ክስ አቀረቡ።
ኤምባሲ ጎን ፎቅ መሥራት ክልክል ነው ተብሎ አባቴ ታገደ
አገሬ ላይ እስከ ጨረቃስ ፎቅ ብሥራ ምን አገባችሁ ?” በማለት ጠየቀ።
“ለወዳጃችን የጣልያን መግሥት ስጋት ስለሚፈጥር፣ ለደህንነታቸውም ስለሚያሰጋ አይፈቀድልህም አቶ ሳልቻ”
አሄሄ እነሱን ለመግደል ማን ፎቅ ይሰራል … ውቤ በረሃ ሲያውደለድሉ አይደለም የሚውሉት…”
ሥርዓት ጌታው፣ እንግዶቻችንን ማክበር የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው”
ጉዳዩ በጣም ተጋነነና በአባትና በጣልያኑ አምባሳደር መካከል የሁለትዮሽ ድርድር ሲካሄድ የተሻለ
ነው በማለት በጃንሆይ ልዩ አማካሪዎች አስተባባሪነት በጣልያን መንግሥትና በአባቴ ባልቻ መካከል ታሪካዊ ድርድር ተካሄደ።
ይህ ድርድር በታሪክ፣ አንቀጽ 17 - እኛም መስኮታችንን አንከፍትም እናንተም ሚስቶቻችንን አትዩ”
በመባል ይታወቃል
የውሉ ዋና ዋና ነጥቦች!
አንቀፅ 1. አቶ ባልቻ ደመቀ ኤምባሲያችን ጎን የሚሰሩት ፎቅ መስኮቱ ወደ ጣልያን ኤምባሲ ላይ ላይዞር ከዞረም ላይከፈት።
አንቀፅ 2. ጣልያኖች ወደ ኤምባሲው ሲገቡና ሲወጡ አሁን ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚወለዱትን የአቶ ባልቻን ሴት ልጆች በቃልም ሆነ በድርጊት ላይተናኮሱ፧ በመኪናም ሆነ በእግር በር ላይ ላይንጎማለሉ
ሆን ብለው ስሜት ቀስቃሽ እና አማላይ ድርጊት ላይፈፅሙ።
.
.
.
.
.
.
አንቀጽ 17. ወደ አቶ ባልቻ ቤት የዞሩት የኤምባሲው የቪዲዮም ይሁኑ የፎቶ ካሜራዎች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ።
የዚህ ውል 17 ኛው አንቀጽ የጣልያኑ ትርጉም ግን እንዲህ ይል ነበረ፣
የኤምባሲያችን የቪዲዮም ይሁኑ የፎቶ ካሜራዎች፣ የሙሉን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ፎቶ ሊያነሳ ፈቃድ አላቸው ይላል።
ታሪክ ራሱን ይደግማል !!
እናቴ ሙሉ ታዲያ ከንፈሯን ሸምም አድርጋ የተንኮል ፈገግታ ፈገግ አለች። ማንም አላያት ከሰይጣን
እና ከእኔ በስተቀር። ትንሽ ወንድሜ አባቴን አለመምሰሉ እንደውም ፈረንጅ መምሰሉ እስቋት ይሆን.!

👍14🤔1
#አድዋ_በአፍ_አይገባም
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው ዛብ፣ የደም ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ አልጋ በእርግብ ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
🔘በነቢይ መኮንን🔘
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው ዛብ፣ የደም ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ አልጋ በእርግብ ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
🔘በነቢይ መኮንን🔘
👍4
“የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ”
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
🔘ተክለ ጻድቅ መኩሪያ🔘
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
🔘ተክለ ጻድቅ መኩሪያ🔘
👍8👏1