#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#ክፍል_ሶስት
#ትንሣኤ
በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት የምርኮኞች ልውውጥ የሚጀመርበት የመጀመሪያው ምዕራፍ......
የድሬዳዋ ከተማ አሸብርቃለች፡፡ ገንደቆሬ፣ ገንደገራዳ፣ መጋላ፣ ከዚራ፣ ለገሀሬ፣ ..... መንደሮች በሙሉ በደስታ ስቀዋል፡፡
በየመንገዱ ግራና ቀኝ ተተክለው ቀዝቃዛና፤ ነፋሻማ አየርን የሚረጩት ዛፎች በደስታ ተውጠው የሚደንሱ ይመስላሉ፡፡ በዚያች ምድር ላይ የተካሄደው ቀውጢ ጦርነት አልፎ፤ ያንን የመሰለ የሰላም አየር መተንፈስ መቻል ዳግማዊ ልደት ነው፡፡
በሐረርጌ ምድር፡፡ በደገሀቡር፣ ቀብሪደሀር፣ መራራሌ፣ በሺላቦ፣
ደቦይን፣ በቆራሄ አሸዋማ ሜዳ፣ በኦጋዴን በረሃ፣ በካራማራ ተራሮችና በሌሎችም ሺህ ሌሊት ሺህ መአልት የፈሰሰው ደም፣ የተከሰከሰው አጥንት፣ያስገኘው ውጤት፡፡
በዚያን ቀውጢ ሰዓት ላይ ለዳር ድንበር ሲሉ ከጠላት ጋር እየተናነቁ አኩሪ ገድል የፈጸሙት፤ በደማቸው ማህተም፤ በአጥንታቸው ክስካሽ፤ ምድሪቱን ያቀሉት...የመስዋዕትነት ፈርጦች! የሚጠበቁበት ዕለት......
ሰማዩ በዚያን ቀውጢ የጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ አየር ሃይል የተሠራውን አስደናቂ ትርኢትና ተአምር አፍ አውጥቶ ሊናገር፣ የታሪክ ምስክርነቱን ሊሰጥ፣ የተዘጋጀ ይመስል አጉረመረመ፡፡ ለሚወዷት እናት አገራቸው ዳር ድንበር ሲሉ የተፋለሙና ልዩ ልዩ ጀብድ ከፈጸሙ በኋላ በጠላት እጅ ወድቀው በባእድ ሀገር በምርኮኝነትና፤ በእስረኝነት ለበርካታ
አመታት ከቆዩ በኋላ በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ዛሬ ወደሚያፈቅሯትና፤ ወደሚወዷት፤ እናት አገራቸው የሚመለሱበት እለት ስለሆነ፤ እነዚህን ውድ የሀገር አለኝታዎችና፤ ጀግኖች፤በልዩና፤ በደማቅ አቀባበል ፤ ሊቀበል ህዝቡ የአውሮፕላን
ማረፊያውን አካባቢ አጥለቅልቆታል....
ማርሽ የሚያሰማው ሠራዊት በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠባበቃል።ባንዲራዎች ይውለበለባሉ፡፡ ህዝቡ ይሯሯጣል፡፡ ይራወጣል። ሰማይ ሰማዩን እያንጋጠጠ ይመለከታል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ትላልቅ አሞራዎች ያሳስታሉ፡፡ የሁሉም ልብ ተንጠልጥሏል፡፡ እነማን ይሆኑ?! ሞቱ ተብለው ደረት
የተመታላቸው፣ ተዝካር የተበላላቸው፣ ማን ያውቃል? በህይወት ሊገኙ
ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ጦርነት በተካሄደባቸው ብዙ አገሮች በተደጋጋሚ
የታየ ክስተት ነው፡፡
ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ሰማዩ እንደገና በከፍተኛ ድምፅ አጉረመረመ፡፡አውሮፕላኗ በርቀት ታየች፡፡ ከዚያም እየጐላች ፤እየጐላች፤ መጣችና፤በማረፊያው ላይ እየዞረች፤ ማንዣባብ ጀመረች።
የሰው ጩኸት ሁካታ... ግርግር... ትርምሱ...ሌላ ሆኗል፡፡ማርሽ በረጅሙ ይሰማል፡፡ አውሮፕላኗ አዘቀዘቀች..... ከዚያም አኮበኮበችና አረፈች፡፡
ጀግኖች የታደሙባት አውሮፕላን! ለዳር ድንበሯ ሱሉ ደማቸውን ያፈሰሱላትን፣ በእስር የማቀቁላትን፣ ጥለው የወደቁላትን፣ ታስረው የተገረፉላትን፣ የጦር ምርኮኞችን ይዛ ይሄውና አውሮፕላኗ መሬት ላይ አረፈች....
የአውሮፕላኗ በር ተከፍቶ አንድ ረጅም፧ ቀጭን፤ መነጽር ያደረገና በአየር ኃይሉ ውስጥ በጦር ጄት የጠላትን ሃይል ድባቅ
በመምታት በደማቅ ቀለም ታሪክ ያስመዘገበ ምርኮኛ ብቅ አለ፡፡ማርሹ ይሰማል፡፡ እልልታው ቀለጠ!! ግማሹ በሲቃ ያለቅሳል፣ይፈነድቃል፡፡ ምርኮኞቹን ለማየት ሰው በሰው ላይ ይንጠላጠላል፣
ትዕይንቱ ብዙ ነው፡፡ ከዚያም የተዘጋጀውን እቅፍ አበባ ምርኮኛው ተቀበለ፡፡
ምርኮኞቹ ከአውሮፕላኗ እንደወረዱ መሬቷን ይስማሉ። አፈሯን ይልሳሉ፡፡ ያለቅሳሉ፣ ይንከባለላሉ፡፡ የደስታ እንባ... የናፍቆት እንባ... የትዝታ እንባ...
ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ከአገር፤ ከወገን፣ ከቤተሰብ ጋር ተለያይተው ፤ የብቸኝነትንና የመከራ ኑሮን ሲገፉ ከቆዩ በኋላ፤የሚወዱትንና፤ የሚያፈቅሩትን፤ ህዝብና አገር መቀላቀል ዳግም መወለድ
ነውና፤ ምርኮኞች ዳግም የተወለዱ ያህል በደስታ ሰከሩ። እንደዚያ ዳር ድንበርዋን ሊያስከብሩላት፤ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው፡ ሳንጃ ለሳንጃ ተሞዣልቀው፡ ጥለው የወደቁላት፡ የውድ ሀገራቸውን ለም አፈር ለማሽተት በመቻላቸው በደስታ የሚሆኑትን አጡ ...ህዝቡም በእልልታና በሆታ የጀግና አቀባበል አደረገላቸው፡፡ ደስ የሚል ከህሊና የማይጠፋ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት......
ለተወሰኑ ቀናቶች በድሬዳዋ ከተማ እረፍት አድርገው ከቆዩና መንፈሳቸው ከተረጋጋ በኋላ፣ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሊቀላቀሉ የቸኮሉት ቀድመው ተንቀሳቀሱ፡፡
እለተ ቅዳሜ! አዲስ አበባ!! የኢትዮጵያ ዋና ከተማ! ቀዝቃዛ ንፋስ ይነፍስባታል ። በተለይ የባህር ማዶው ዛፍ ለቅዝቃዜው የራሱን ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል፡፡
ባቡሩ መንገደኞቹን ጣቢያው አራገፈ፡፡ ግፊያው ለጉድ ነው፡፡ግማሹ ሲመጣ ግማሹ ሲሄድ... የገቢና ወጪ መንገደኞች ምልልስ የማያቋርጥበት አምባ......
ጊዜው ለዐይን ያዝ ማድረግ የጀመረበት ሰዓት ነው፡፡
አንድ ቁመቱ ረዘም ያለ፣ ሰውነቱ በበረሃ ግርፋትና በእስር ስቃይ ምክንያት የተለበለበ ግንድ ቢመስልም፤ በሰላሙ ጊዜ ማራኪ መልክና ቁመና እንደነበረው አሁንም በግልጽ የሚታየው ትክለ ሰውነቱ
ዐቢይ ምስክርነቱን የሚሰጥለት፤ ከሲታ ሰው ከባቡሩ ወረደ፡፡
ደረቱ ሰፋ ያለ፣ ፀጉረ ዞማና ዐይኖቹ ጐላ ጐላ ብለው የሚታዩ ረጅም ሰው ነው፡፡ ሻንጣ አንጠልጥሏል፡፡ ከተሰጠው የኪስ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ያዋለው ለሁለት ሴቶችና፤ ለአንድ ወንድ የሚሆኑ ልብሶችን በመግዛት ነው፡፡ ከባቡሩ ወርዶ፤ በአምባሳደር ቲያትር በኩል መጥቶ ፤ ወደ ኦርማ ጋራዥ አቀና፡፡ የሚራመደው በደመነፍስ ዐይነት ነው፡፡
በህልም ዓለም የሚራመድ ይመስላል፡፡
እሱ እራሱ የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን ተጠራጥሯል።ግራና ቀኙን በዓይኑ ያማትራል፡፡ ሰዎችን ይቃኛል፡፡ ምናልባት የማውቀው ሰው ካገኘሁ በሚል ግምት ነው፡፡ ግን ማንም የሚያውቀው ሰው አላገኘም፡፡ ድሮ የሚያውቁት ሲያዩት እንኳን፤ በቀላሉ ሊለዩት አይችሉም፡፡ ተለውጧል፡፡ ተጉሳቁሏል፡፡
መንገዶቹ የጠበቡ፣ ቤቶቹም ከምዕተ ዓመት በፊት የነበሩ መስለው ታዩት፡፡ በየመንገዱ ላይ ከሚያያቸው ሰዎች ውስጥ ሶስት ሰዎችን ለማግኘት በናፍቆትና በጉጉት ደጋግሞ ይቃኛል፡፡
የሱ ብርቅዬ፤ ድንቅዬዎች፡፡ ልዩ የህይወቱ ቅመሞች፡፡ የተዳፈነ የናፍቆቱ እምቅ ሊፈነዳ ተቃረበ፡፡ ልቡ ተሸበረ... እየተቃረበ ሲመጣ ልቡ ድው ድው የሚል ድምጽ ሰጠ፡፡ ትንፋሽ አጠረው፡፡
እጅግ አስገራሚ ነው! አስደናቂ
የማይጠበቀው ሰው ፤ እንደዚህ ባልተጠበቀ ሰዓት ከች! ሲል፤ እነሱ
ከአንጀቱ የሚያፈቅራቸው፣ የሚወዳቸው፣ የሚሞትላቸው ቤተሰቦቹ እንዴት ሆነው ይሆን? የሚወዳት ሚስቱ፣ የሚወዳቸው ልጆቹ እንዴት ሆነው ይሆን? ሲለያቸው በነበራቸው ዕድሜ ላይ አስራ አንድ ዓመት ሲጨመርበት የትየለሌ ነው፡፡ ምን መስለው ይሆን?
አቤቱ ፈጣሪ ያንተ ተአምር እንዴት ተወርቶ ያልቅ ይሆን? አደራህን ሁሉንም ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን ዐይናቸውን አይቼው
እንድሞት እርዳኝ፡፡ አንተ ታውቃለህ፡፡
ወባ እንደያዘው ሰው እየተቃረበ መጣ፡፡ ቤቱ ጋ ሲደርስ ሰውነቱ ተንዘፈዘፈበት :: ልቡ በፍጥነት ይመታ ጀመር፡፡
ግቢው ...ያ ...ግቢ የሚወደው ግቢ...እዚያ ውስጥ ያሉት እነ.. መራመድ አልቻለም፡፡ ቆመ፡፡ እንደሀውልት ተገትሮ ቀረ፡፡ ከዚያም ለዘመናት በወስጡ ሲንተከተክ የነበረው እንባ በድንገት ገንፍሉ ወጣ፡፡
ከደስታ ብዛት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ቤቱን አየው፡፡ ልጆቹን አቅፎ የሳመበትን፣ ከሚያፈቅራት ባለቤቱ ጋር ደስታን ያሳለፈበትን፣ በመጨረሻም ወደ ጦርነት ሲሄድ ከቤተሰቦቹ ጋር ተላቅሶ

👍2🔥1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
፡
፡
...የሴንቸሪ ሲቲ መንገዶች በሙሉ ውር ውር በሚሉ መኪናዎች ቢሞላም የእግረኛ መንገዶቹ ግን ጭር ያሉ ነበሩ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ሰዎች
በሎስ አንጀለስ በእግራቸው አይሄዱም፤ በተለይ ደግሞ በዝናብ ውስጥ መሄዱ የማይታሰብ ነገር ነው። እርግጥ የሚጠብቃት ሴት አንድ አንዴ
በእግር ትጓዛለች፡፡ “ዛሬስ ምናልባት በእግሯ ወደ ቤቷ መሄድ ብትችልስ?
“በይ ውጭ እኮ ውጭ የት ነው ያለሽው?” እያለ በውስጡ ሲያመላልስ
በድንገት ሴትየዋ ከህንፃው ስትወጣ ልቡ ደነገጠ፡፡ ምክንያቱም አልተዘጋጀም
ነበር፡፡ ልቡ በደንብ እየደለቀም እሷን መመልከት ጀመረ፡፡
ኮቷንም በቀበቶዋ ሸብ አድርጋ እና ራሷን አቀርቅራ በፍጥነት ወደ መንገዱ መሸጋገሪያ የምትሄደውን ሴት እየተመለከተ “እርዱኝ!” እያለ ጮኸ፡፡
በእርግጥ ድምፁ ያን ያክል ይሰማት አይሰማት እርግጠኛ አይደለም።
ቢሆንም ግን ዛሬ ይህቺ ሴት ልትሰማው ይገባል “ኧረ እርዱኝ!” አለ በድጋሚ፡፡
ይሄኔም ሊዛ ፍላንገን ወደ እሱ ዞር አለች ከቆሻሻው መጣያ አጠገብ አንድ ቀጭን ልጅ ይሁን ትልቅ ሰው መሆኑ የማይለይ ሰው አጎንብሶ ቁጢጥ ብሏል፡፡ ወደ እሱ ስትራመድ ስላያትም “እባክሽን 911 ደውይልኝ! ፖሊስ ጥሪልኝ፡፡ የሆነ ሰው በጩቤ ወግቶኛል።” አላት፡፡
እሷም “በእግዚአብሔር ስም” ብላ ስልኳን አወጣች እና እየደወለች ወደ
ልጁ ቀረበች፡፡ “ምን ሆነህ ነው? ደህና ነህ?” ብላ ጠየቀችው። ልጁ አጎንብሶ
ሆዱን በማጠፍ እጁን ሆዱ ላይ አስቀምጦታል፡፡ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነው
የለበሰው:: ሹራቡ ላይ የዘነበበት ዝናብም ፊቱን እና ፀጉሩን አርሶታል።
“የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ምን ነበር የፈለጉት?”
“ፖሊስ ይድረስልኝ፡፡” ብላ ሊዛ በማስከተል “ አምቡላንስም ጭምር” አለች እና አናቱን በእጇ እየነካች “አይዞህ እርዳታ እየመጣልን ነው። ምንህን ነው
የተጎዳኸው?” ብላ ጠየቀችው፡፡
ልጁም ፈገግ ብሎ ሲያያት ሊዛ የልጁን ፊት አይታ በጣም ቀፈፋት እና ለማስታወክ ዳዳት ከሹራብ ኮፍያው ሥር ያለው የልጁ ፊት የሰው አይመስልም፡፡ ፊቱ ፍፁም አረንጎዴ ከመሆኑም በላይ አጥንቱ ገጧል። ይባስ
ብሎም ተቆራርጠው የተንጠለጠሉ የበሰበሱ ነገሮች ከፊቱ ተንጠልጥለዋል። ልትጮህ አፍዋን ብትከፍትም አንድም
ሊወጣላት አልቻለም።
911 ላይ የሚያወራት ሰውም “የእኔ እመቤት የት እንዳለሽ ልትነግሪኝ
ትችያለሽ?” ብሎ ጠየቃት። ባለ አረንጎዴው ፊትም በድንጋጤ የተከፈተውን የሊዛን አፍ እየተመለከተ ከሆዱ ስር ስለታም ጩቤ አወጣ እና ሆዷ ላይ ሰመጠጠው። ይሄኔም አየሩን የሚሰነጥቅ የእሪታ ድምፅ ከሊዛ አፍ ሊወጣ በቃ። በድጋሚም ስለቱን ከሆዷ ነቅሎ በጣም በሀይል ሲሰመጥጥባት እጁ ከጩቤው ጋር ተያይዞ ወደ ውስጥ ስለገባ የሆነ የሚሞቅ ርጥበት እጁ ላይ
ተሰማው።
“እባኮትን ያናገሩኝ? ይሰማዎታል? ምንድን ነው የተከሰተው? የት ቦታ
እንደሚገኙ ሊነግሩኝ ይችላሉ?” መሬት ላይ ከእጇ አምልጦ ከወደቀው ስልክ
የሚወጣ የ911 ሰውዬዋ ድምፅ ነው። ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ የX ክላስ
መርሴዲስ መኪና የሌዘር ወንበር ላይ ተለጥጣ የገራጁ በር እስኪከፈት
እየጠበቀች ትገኛለች፡፡ መንገዱ ክፍት ከሆነ በሀያ ደቂቃ ውስጥ ብሬንትውድ
ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ትደርሳለች። ምንም እንኳን ረጅም እና
ባዶ የሆነ ህይወት ቤቷ ውስጥ ቢጠብቃትም ቴሌቪዥን በማየት በአንድ
ጠርሙስ አልኮል ባዶ ህይወቷን ትሞላለች:: እንኳን አንድ ምሽት፣ ሁሉ
ነገር ያልፍ አይደል?
ኒኪ መኪና ውስጥ እንዳለች የዛሬው ውሎዋ ላይ ሊዛን በሙሉ ልቧ ስላላደመጠቻት የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷታል። ታካሚዋን ብትወደውም
ሆነ ብትጠላው ስራዋን በአግባቡ ሰርታ ስላልወጣች በእውነትም ቅር ብሏታል። የገራዥ በር በቀስታ መከፈት እንደጀመረ ኒኪ ወደ በሩ ነዳች እና ከህንፃው ወጥታ ወደ ጠባቡ መንገድ ገባች።
ሊዛ የበሩን መከፈት እና መዘጋት ድምፅን እና የመኪና ሞተር ድምፅ ስትሰማ በነበረበት ጊዜ ከሆዷ እና ከደረቷ ደሟ እንደጎርፍ ይወርድ ነበር።
መሮጥም ሆነ መቆም አልቻለችም:: ማድረግ የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር
ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ ድረስ መጮህ ነበር። በስለት የወጋት ሰው በስለቱ
እጇን፣ ጡቷን እና ጭኗን ጭምር ደግሞ ደጋግሞ ይቆራርጣታል። ቶሎ
ሊገድላት አልፈለገም እና ልክ ድመት የያዘችውን አይጥ እያሰቃየች
እንደምትዝናና ሁሉ እሱም የሚያደርገው ያንን ነበር።
የመኪናው ሞተር ድምፅ እየጨመረ መምጣትን ስትሰማ ግን በተስፋ
ተሞልታ ትንፋሿን ሰበሰበች። ከዚያም በህይወቷ ጮሀ የማታውቀውን
ጩኸት ጮኸች። በጩኸቷ መሀል ላይ ደሟ ጉሮሮዋ ውስጥ ሲንተከተክ
ታውቋታል፡፡ አይኗም ተጎልጉሎ የሚወጣ ሁላ መስሏታል።
የመኪናው መብራት ወደ እነርሱ አቅጣጫ አበራ። ይሄኔም የሚወጋት ሰውዬ እሷን የመውጋት ስራውን አቆመ፡፡ የመኪናው ሞተርም ድምፁ ጠፋ።
ሊዛ ዶ/ር ሮበርትሰን አይታኛለች ከዚህ ነፍሰ ገዳይም ታተርፈኛለች ብላ
እረፍት ተሰማት። ነፍሰ ገዳዩም የያዘውን ጩቤ መሬቱ ላይ ጣለው፡፡ የልብ
ምቷ ቀስ እያለ ሲመታ ይሰማታል፡፡ ባለጩቤው ሰው ግን ጥሏት ሊሮጥ
አልቻለም። የመኪናው በርም ሲከፈት አልሰማችም::
ሁለት... አምስት... አስር ሰኮንዶች አለፉ፡፡ ምንም የተከሰተ ነገር ግን አልነበረም፡፡ “እንዴ... ምንድን ነው ነገሩ?”
የመኪናው ሞተር ድምፅ በድጋሚ ተሰማት፡፡ አይሆንም! ጠባቡን መታጠፊያ የመኪናው መብራት አጥለቀለቀው፡፡
“አይሆንም! አይሆንም! እባክሽን ድረሺልኝ! ስለእግዚአብሔር ብለሽ
ድረሺልኝ!!
የኒኪ ብርማ መርሴዲስ መኪና በጎን በኩል አለፋቸው እና ወደ ዋናው
መንገድ ውስጥ ገባ፡፡የበሰበሱ አጥንታማ እጆችም የሊዛ አንገት ላይ ተጠመጠሙ። ከፊት ለፊቷ አብረቅራቂው የገዳይ ጩቤ በእሷ ደም ጨቅይቶ ይታያታል።
ሊዛ “የት ነበር ያቆምነው?” ብሎ ገዳዩ ሰው እየገለፈጠ የተናገራት ንግግር እና አስቀያሚ ሳቁን ለመጨረሻ ጊዜ ነበር የሰማችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታች እንግዳ ማረፊያ ክፍሉ ስለሚጠብቁት ሁለቱ ታጣቂ የግል
ጠባቂዎች እያሰበ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ፈለገ። አልሰራም፡፡ ጥሩ ስሜት አልተሰማውም፡፡ በመቀጠል ደግሞ ቴራፒስቷን ራቁቷን አሰባት። ይሄ
ሳይሻል አይቀርም፡፡ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ስሜታዊ ሰው ነች ብሎ ያስባል።
ግራጫ አጭር ቀሚሷን ወደ ላይ ገፋ አድርጎ ዳሌዋን... አሰበ። ቦዲዋ
ተከፍቶ... “ኡፍ ደስ የሚል ነገር ነው...
ካርተር ከእኔ ጋር ነህ?” የሚለው ድምፅ ከሀሳቡ አነቃው። ድምፅዋን ሲሰማ ፊቱ ቀላበት፡፡ በመቀጠል ደግሞ ግራ ተጋባ፤ ለጥቆም ኮስተር አለ፡፡ስኬታማ የኢንቨስትመንት ባንከር፣ ወጣት የተማረ እና በጣም ሀብታም ሰው ነው። ሥራ ቦታው እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ሁሉ ካርተር ሰዎችን በትዕዛዝ ቁጭ ብድግ ያስደርጋቸዋል፡፡ የሚፈልገውን ነገርም ሊያሟሉለት የሚራኮቱለት አይነት ሰው ነው። በተለይ ደግሞ ሴቶችን በሙሉ ስልጣን ውስጥ ሆኖ ነው የሚያዛቸው፡፡ አሁን እዚህ ቦታ ላይ ግን ልክ እንደ አንድ
ረባሽ ተማሪ ስሙን ስትጠራው ምቾት አልተሰማውም።
“ትላንት ማታ ምን አየሁ ብለህ እንዳሰብክ ደግመህ ንገረኝ እስቲ” “ሀሳቤ አይደለም! እንዴ እኔ ያየሁትን ነገር አይቼያለሁ። እኔ እብድ አይደለሁም!”
ብሎ ተበሰጫጨ እና ጥቅጥቅ ቡናማ ፀጉሩን ሞነጫጨረው፡፡
“እኔ እንደዛ አላልኩም” ብላ ድምፅዋን በማለስለስ ቀጠለች እና “አንዳንዴ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ እንደዚህ አይነት ነገር ሊገጥማቸው ይችላል። እኔ እራሴ አንዳንዴ እንደዚያ

❤1👍1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....ዕለቱ የህዳር ወር የመጨረሻው ማክሰኞ ነው የአስቻለው ከንፈሮች ከሔዋን ከንፈሮች ጋር ከተገናኘ ሃምሳ ሁለተኛ ቀን። ሔዋን ቀጠሮ አክብራ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ከአስቻለው ቤት ደረሰች፡፡ አስቻለው ሔዋንን ከወስጥ አድርጎ ቤቱን ሲዘጋ ተሰምቶት የነበረ ደስታ አይረሳም።
በዚያ ዕለት ሔዋንን እንደ እንግዳ ወንበር ላይ ቁጭ በይ አላላትም፣
አንገቷን እቅፍ አድርጎ በቀጥታ ወደ አልጋ ወሰዳት፡፡ አልጋ ላይ ቁጭ ብለው ትንሽ ከተሟሟቁ በኋላ ስሜት በራሱ ሀይል ሲገፋቸው አንገት ለአንገት እንደተቃቀፋ፥ከንፈር ለከንፈር እንደተያያዙ ወደ ኋላ ከንብል አሉ፡፡ ጫማዎቻቸውን አወላልቀው
ወደ መሀል አልጋው ወጡና በሰፊው የፍቅር ሜዳ ላይ ሰፈሩ፡፡
ጉዞው ቀጠለ፡፡ ከንፈሮች በስራ ተጠመዱ፡፡ ዓይኖች ተስለመለሙ ትንፋሽ በረከተ፡፡ ገላጋይ የማያስፈልገው ትንቅንቅ ተጀመረ፣ የአስቻለው ቀኝ እጅ የሔዋንን
አንገት አቅፎ ግራው ደግሞ ሌላ ሥራ ያዘ። ከሔዋን ፀጉር ጀምሮ ማጅራቷን ይጎበኝና በወገቧ ላይ እየተስለክለክ ወደ ዳሌና ጭኖቿ ይወርዳል። ላይ ላዩን እንደ
ወረደ ሁሉ ወስጥ ውስጡን ለመመለስ በማሰብ ቀሚሷን ሰብሰብ እያደረገ ወደ
መሀል ጭኖቿ ጎራ ሊል ይቃጣዋል፡፡ ነገር ግን የሔዋን ጭኖች ወይ ፍንክች!!እንደገና ከላይ ይጀምራል፡፡ ይወርድ ይወርድና በአሰበው መንገድ ለመመሰስ ሲሞክር አሁንም ተቃውሞ ይገጥመዋል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ሞከረ:: የሔዋን ጭኖች ግን
አልበገር አሉ።
በአራተኛው ጊዜ ከንፈሮችም ድንገት ተላቀቁ:: ሔዋን ወደ ቀልቧ ተመልሳ ኖሮ ድንገት ፍንጥር ብላ በመነሳት አልጋው ላይ ቁጭ አለች። አስቻለውም አልዘገየም፣ ሔዋን በተነሳችበት ቅፅበት እሱም ፍንጥር ብሎ ጭራሽ ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወረደ:: ፊትለፊቷ ቆሞ በነጭ ካኒተራው ላይ ደረቱን እያሻሽ
"ስሜቱ አልገባሽም አይደል ሔዩ" አላት በስሜት ውስጥ ሆኖ
ቅልስልስ እያል፡፡
"ገብቶኛል"
"ታዲያ ለምን ታስጨንቂኛለሽ?"
"እኔም ስለጨነቀኝ፡፡
«እንዴት?"»
«የእናት እደራና የእህት ማስጠንቀቂያ ስላሉበኝ»
“አልገባኝም ሐዩ!
«ና ቁጭ በል ልንገርህ»
አስቻለው ፈጥኖ ከአጠገቧ ቁጭ አለ። በመሀል ሔዋን በሀሳብ ጭልጥ ብሳ ሄደች:: ያኔ በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ከሸዋዬ ጋር ጠዋት ከክብረ መንግሥት ወደ
ዲላ ሊመጡ ሲሉ ማታ በዝግጅት ላይ በነበሩበት ወቅት ሽዋዩ ሔዋንን እፊቷ ቁጭ አድርጋ ከእናቷ ጋር የተነጋገሩት ነገር።
ስሚ እማዬ » ብላ ነበር ሽዋዬ ወሬ የጀመረችው። «ይቺን ሔዋንን
ከአሁኑ ምክሪልኝ:: ዲላ የቡና አገር ነው ሀብታም ሁሉ ሰው በገንዘብ መግዛት ይፈልጋል:: እሷ ደሞ ቆንጆ ስለሆነች በገንዘብ እያታለሉ ትምህርቷን አስትተው ብልግና ሊያስተምሯት ይችላሉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ህይወቷ ሊበላሽ ይችላል። እኔም ብሆን እንኳን ብልግና ፈጽማ ፡ የወንድ እጅ ጨበጠች ያሉኝ ዕለት ባለጌሽን አምጥቼ አስረክብሻለሁ።» ብላቸው ነበር፡፡ እናቷ ከተል እንዲህ ዓይነት ብልግና ትፈጥማለች ብዬ አልገምትም::
ያን ያህል ለፍቼ አሳድጌታለሁና
ክብሯን ጠብቃ ወግ ማረግ ታሳየኛለች ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ ያ
ሳይሆን ቀርቶ ብልግና ፈጥማ አንቺ ወደኔ ብታመጫት እኔም የዚያኑ ዕለት ገደል ገደል ገብቼ እሞትና ቀብረሽኝ ትመለሻለሽ በማለት ተናግረው ነበር። ሔዋን ይህን የናቷን አደራና የእህቷን የማስጠንቀቂያ ቃል በሀሳቧ እያዳመጠች በነበረችበት ወቅት
«እስቲ ያስጨነቀሽን ነገር ንገሪኝ ሲል አስቻለሁ ከሀሳቧ ቀሰቀሳት፡፡
«ለመኑ ገርል መሆኔን ታውቃለህ?» አለችው ድንግል
መሆኗን ስትገልፅለት፡፡
«ኦ!» አለ አስቻለው ያላሰበው ነገር ሆኖበት።
«አትጠራጠር»። አለችውና ሔዋን እናቷ የጣለችባትን አደራና እህቷ ሸዋዬ የሰጠቻትን ማስጠንቀቂያ በዝርዝር አስረዳችው፡፡
ያ እንደ ብረት ግለ" የነበረ የአስቻለው ሰውነት ድንገት ቅዝትዝ ብርድ! ስንፍናና አለ።
«አደራ የምልህ አስቹ!» ስትል ቀጠለች ሔዋን። «ይህን የፍቅር ጉዳያችንን አንድ ቀን እታ አበባ የሰማች እንደሆነ መግቢያ ቀዳዳ የለኝም፡፡ ስለዚህ ሚስጥራችንን ከታፈሱና ጓደኞችህ" በቀር ሌላ ማንም ስለማያውቅ ሁሉም
በሚስጥር እንዲይዙልን አደራ እንድትላቸው ነው። እለችው::
አስቻለው በሁኔታው ተገርሞ ግንባሩን ይዞ መሬት መሬት ሲያይ ቆየና ድንገት ብድግ ብሎ ሔዋን ፊት በመቆም «እስቲ ወደኔ ነይ ሒዩ!» አላት፡፡
ሔዋንም ቡድግ ብላ በመቆም የአስቻለውን ዓይኖች ማየት ጀመረች፡፡
አስቻለው በሁለት እጆቹ የሔዋን ትክሻና ትክሻ ያዝ አድርጎ ቁልቁል
እየተመለከታት፡ ቃል ልገባ ነው ሐዩ፡»
«ምን ብለህ?»
የበሕይወት እስካለሁ ድረስ ፍጹም አልለይሽም። ከሠርጋችንም በፊት
ምንም አላደርግሽም» አላት፡፡
«እሺ» አለችው ሔዋን፡፡
አንገት ለአንገት ተቃተፉ። ምናልባት በሁለተኛው የህይወት ምዕራፍ ውስጥ እንደ ገቡ ታውቋቸው ሳይሆን አይቀርም ሆዳቸው ባብቶ ሁለቱም ተላቀሱ።
ይህ ዓይነቱ የፍቅር ከመሰራረት ሂደትና በውስጡ ያለው የሔዋን አደራ ነው ዛሬ አስቻለውን የከበደውና መንፈሱን ወጥሮ ነፍሱን ያስጨነቃት። አዎ
ተጨነቀ። ሔዋን በተፈጥሮ ፈሪና ሽቁጥቁጥ መሆኗን ያውቃል፡፡ ዛሬ በሸዋዬ ፊት እንደ ጭብጦ ጭርምትምት ብላ ታየችው:: ችግሩን በምን መላ ሊፈታው
እንደሚችል ግራ ገብቶት ፍዝዝ ትክዝ እንዳለ በዋርካው ምግብ ቤት ለብዙ ጊዜ የእራት ሠዓት ደርሶ ኖሯል። ድንገት ጓደኛው በልሁ በበር በኩል ወደ እሱ ሲያመራ አየወ፡፡ በልሁ ቁመቱ፡፡ ዘለግ ሰውነቱም ፈርጠምጠም ያለ ነው፡፡ ሰፋ ባለ የቀይ ዳማ ፊቱ ላይ በትር ወስሉ የተገተረው አፍንጫው ግርማ ሞገስ
አላብሶታል:: ዓይኑ ጎላ ጎላ ያለና ፈገግ ሲል ጥርሱ የሚያምር ነው:: ከውጭ ሲመጣ አስቻለው ትክዝ ብሉ በርቀት ዓይቶት ኖሮ ቀረብ ብሎ ሲያጤነውም ስሜቱ
መመሳቀሉን በመገንዘብ፡ ምነው ይክተር? ሰላም አይደለህም እንዴ?» አለና ሰላም ብሎት ከአጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ አስቻለው ነርስ ስለሆነ ጓደኞቹ ብዙ ጊዜ ይክተር አያሉ በመጥራት ያሾፉበታል፡፡......
💫ይቀጥላል💫

👍4