#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ወረቀቱን ፍለጋ ወደ ዉስጥ ተመለሰ
ፍቃዱ ወረቀቱን እያነሳ ድል እንዳረገ ሰው ኮራ እና ጀነን እያለ
"አገኘኋችሁ"
ሲል አጉተምትሞ የወረቀቱን አቅጣጫ ተከትሎ መሄድ ጀመረ።
እማማ ስንቅነሽ ቁርስ ሰራርተዉ ዉጪ ተገትራ የቆመችዉን ቤዛዊትን ወደ ቤት ዉስጥ ገብታ
እንድትበላ ጠሯት አልሰማቻቸዉም ልቧ ከአሁን አሁን መጣ አልመጣም ብላ የምትጠብቀዉ ፍፁም ላይ ነዉ።
ቀረብ ብለዉ እየነኳት
"ልጄ የምትጠብቂዉ ሰዉ አለ እንዴ"
እማማ ስንቅነሽ በሁኔታዋ ተጠራጥረዉ ጠየቋት
"አዎ ግን አሁን አልነግሮትም"
ፈጠን ፈጠን እያለች እያወራች
የእማማን ልብ ለማንጠልጠል አስባ
ነገር ግን እማማ ስንቅነሽ ምንም አልመሰላቸዉም እንደሚያማት ስለሚያዉቁ አብዳ ለይቶላት
ጨርቋን ጥላ ሳይፀየፉ ሰዉ ናት ብለዉ ስላቀረቧት አሁን አሟት ቢሆን እንኳ ሰዉ የምትጠብቀዉ ሊጫኗት አልፈለጉም።
እዉነተኛ ወዳጅም እንደዚህ ነዉ ጥፋትህን ስህተትህን ካወቀ በስህተት በጥፋትህ ተጠቅሞ
ሊጎዳህ አይሞክርም
ያግዝሀል ያበረታሀል እንጂ
እማማ ስንቅነሽም የቤዛዊትን እጅ በፍቅር ይዘዉ ሳብ እያረጉዋት
"በይ ነይና ቁርስሽን በልተሽ ትጠብቂዋለሽ"
ለእሳቸዉ የእሷ ቁርስ መብላት እንጂ ታማ ዉጪ መገተሯ ወይ በጤነኛ አይምሮዋ ሰዉ ቀጥራ
እየጠበቀች መሆኑ ብዙም ትኩረት አይሰጣቸዉም
ቤዛዊት የቀጠረችዉ ሰዓት ሳይደርስ መጨነቋ እየገረማት እና ፍፁምን ምን ያክል እንደምትወደዉ እያሰበች ወደ ቤቱ ዉስጥ ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ተከታትለዉ ገቡ።
እጇ ላይ ያሰረችዉ ሰዓት ይቆጥራል እርግጠኛ ስላልመሰላትም በእማማ ስንቅነሽ በር በኩል
የሚያልፉ እና የሚያገድሙ ሰወችን
"ይቅርታ ሰዓት ስንት ነዉ?"
በሚያሳዝን አስተያየት ትጠይቃለች
"ሶስት ተኩል፣አራት ስዓት .."
እያሉዋት የጠየቀቻቸዉ ሰወች ያልፉሉ
እሷም ያሰረችዉ ሰዓት ግን ትክክል ነበር የሚሰራዉ።
ቤዛዊት ስልኳን ይዛ ባለመዉጣቷ ተበሳጨች ይዛዉ ብትጠፋ ቤተሰቦቿ እየደወሉ የሚጨቀጭቋት ስለመሰላት ነበር ትታዉ የወጣችዉ አሁን ግን ብይዘዉ ኖሮ ስትል
ተመኘች የፍፁም መዘግየት እያሳሰባት ስድስት ስዓት ሊሆን ተቃርቧል።
እማማ ስንቅነሽ በጠራራ ፀሐይ ዉጪ የቆመችዉን ቤዛዊትን ቤት እንድትገባ ለመለመን ከጉዋዳቸዉ ወጡ
"አይ ልጄ ፀሀዩ በረታብሽ እንዳያምሽ ወይ ወደ ቤት ግቢ አልያም በረንዳ ላይ ጥላ ቦታ ተቀመጪ"
"ቀረብኝ እኮ ሶስት ሰዓት ተባብለን ስድስት ሰዓት ሞላ"
"እኮ ይመጣል ብቻ ከፀሐይዋ ራቅ በይ"
እንደዚህ ሲልዋት ቤዛዊት በደስታ ፈገግ እያለች
"የሚመጣዉ ማን እንደሆነ ልንገሮት?"
በእሺታ እማማ ስንቅነሽ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁ
"ጉዋደኛዬ ፍቅረኛዬ ባሌ"
ቀጠል አድርጋም
"ፍፁም ይባላል ሲመጣ አስተዋዉቃችሁዋለሁ"
እማማ በእሷ ደስተኛ መሆን እየተደሰቱ እና እያዋሩ ቤዛዊትን ከፀሀዩ ወደ ጥላ ወስደዋት ነበር።
(ከሰዓታት በፊት)
ፍፁም ሁለት ስዓት ተኩል አካባቢ ከተባለዉ አድራሻ በታክሲ ተሳፍሮ እንደወረደ እና ባለችዉ አቅጣጫ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ቦታዉን ለማረጋገጥ ፈልጎ ቤዛዊት የሰጠችዉን ወረቀት ኪሶቹ ዉስጥ ሲፈልግ ስላጣዉ እየተበሳጨ
የት ሊጥለዉ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ።
ቤቱ እየወጣ ለአከራዩ ብር ሲሰጥ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ የቦታዉን እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ
ጭንቅላቱን መጠየቅ ተያያዘ
አልተሳሳተም ያለችዉ ቦታ ላይ ደርሷል ነገር ግን እሱ ከቆመበት መንገድ ተሻግሮ ነበር
አንገቱን ቀና አርጎ ለማየት ሞከረ ቤዛዊትን በርቀት አያት
በእድሜ ገፋ ካሉ ሴትዮ ጋር ቆማ ታወራለች
ስላያት እየተደሰተ ግዜ ሳያጠፋ መንገዱን ሊሻገር ሲል በቅርብ እርቀት ከቅድም ጀምሮ ከጀርባዉ
የነበረ የመሰለዉ ሰዉ ስላየ መሻገሩን ተቶ የሰዉየዉን ፊት ለማየት በቀስታ ዞሮ በጨረፍታ አይቶት
መሻገሩን ወደ ቤዛዊት መቅረቡን ትቶ ቀጥታዉን መንገድ ይዞ እየተናደደ እያጉተመተመ መራመድ ጀመረ።
"ከቤት ጀምሮ ሲከተለኝ ነበር ወይስ እንዴት እዚህ ድረስ ሊመጣ ቻለ"
ፍፁም እራሱን እየጠየቀ ከኋላዉ የሚከተለዉን ሰዉዬ ለማምለጥ እየሞከረ ነዉ
"አይ ፍቃዱ ምን አርግ ነዉ ግን የሚለኝ ምን በደልኩት ምን አሰቀየምኩት
ይሄን ያህል የጎን ዉጋት የሆነብኝ"
ፍፁም ከፊት ሲራመድ ፍቃዱ አድፍጦ ከኋላው እየተከተለዉ ነዉ ፍፁም እሮጦ ማምለጥ
ተመኘ ነገር ግን እግሮቹ ለመሮጥ ብቁ አደሉም
ፍፁም እያነከሰ ፍቃዱን ለማምለጥ ክራንቹን ተጠቅሞ ፈጠን ፈጠን ለማለት እየታገለ ነዉ
ከጀርባዉ ያለዉ ፍቃዱ ግን ዘና ብሎ እየተራመደ በፍፁም አረማመድ አነካከስ እየሳቀ እየተከተለዉ ነበር።
አንዳንዴ በህይወት መስመራችን ዉስጥም ከእኛ በብዙ እጥፍ የሚበልጡን በብዙ እጥፍ
የተሻሉ ሰወች አሉ
ነገር ግን አብዛኞቹ ስለበለጡን የሚኮፈሱ ስላነስን የሚንቁን ናቸዉ
ህየወትንም ከባድ የመያረጋት መሮጥ የሚችል ሰዉን በታመመ እግር በክራንች ታግዘዉ ማምለጥ መቻል ነዉ።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

❤2👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
..“ይሸጣል እንዴ?” ከመካከላቸው አንዱ፡፡
“አሉልህ እኮ አሁን ወጣ ብለን ብንፈልግ ደማቸውን እንደ ጭማቂ ለመሸጥ የሚንጐራደዱ አይታጡም" ”ሌላው፡፡ ይሄ ደግሞ የገንዘብ መስዋዕትነትን ጠየቀ፡፡ አሁንም ተፋጠጡ፡፡
“አቦ ትጠራ ምን ትሆናለች” ባዩ በዛና ትህትና ይሄንን መርዶ በጠዋቱ እንድትረዳ ፈረዱባት፡፡ ከዚያም ልጁ ሊጠራት እየበረረ ከሆስፒታሉ ወጣ፡፡
እሷ በዚያን ሰዓት አገር ሠላም ነው ብላ ለእናቷ የምትወስደውን ምግብ እያዘጋጀች ነበር፡፡ ወንድሟ ለሷ ለሚወዳት እህቱ ብሎ በዚህች
ስዓት በሕይወትና በሞት መካከል ይገኛል፡፡
በጠዋቱ የተንኳኳውን በር ሄዳ ከፈተች፡፡ ለምን እንደሆነ አላወቀችም ልቧ ሽብር ሽብር አለባት፡፡
“አንዱአለም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብቷል” አላት ጭክን ብሎ።
“ኡ ይ!” ምን ሆኖ!” ጮኸች።
“ሰው ደብድቦት፡፡ አሁን በአስቸኳይ ደም ተጠይቋል” ቁርጡን ነገራት። ከዚያ በኋላ ያደረገችውን አታውቅም፡፡ የሞተ ነው የመሰላት፡፡
የውጭውን በር በርግዳ....
“ኡኡ.... አንዱዬ ...! አንዱዬ....! ወንድሜን!... ወንድሜን!”
ሩጫዋን ቀጠለች። ልጁም ከኋላ ከኋላዋ እየተከተለ ተያይዘው ቁልቁል ይሮጡ ጀመር፡፡ እንደዚያ ራሷን ስታ እየጮኸች ስትሮጥ የሚያያት ሰው በጣም ነበር ያዘነላት፡፡ እንባዋ እንደጉድ ይፈሳል፡፡
ከጥቁር አንበሳ ት/ቤት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመሻገር ከላይም ከታችም መኪና ማየት ሲገባት፤ እንደዚሁ ግብኗን እየበረረች ግማሹን አስፋልት ተሻግራ ደሴቱን አቋረጠችና ወደ ሁለተኛው አስፋልት ጥልቅ ብላ ገባች፡፡
ከዚያ ከላይ ከቴዎድሮስ አደባባይ ቁልቁል እየበረረች የምትመጣው ውይይት ታክሲ በድንገት ጥልቅ ብላ የገባችውን ልጅ ለማዳን ሹፌሩ ፍሬኑን በሃይል ሲረግጠው፤ መኪናዋ ወደጐን ዞረችና ደሴቱ መሐል ገብታ ተቀረቀረች፡፡
እዚያ ታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በድንጋጤ ውሃ ሆነዋል፡፡ ትህትና የዚህ ሁሉ መንስኤ እሷ መሆኗን አታውቅም፡፡
ሩጫዋን አላቆመችም፡፡ ልጁ በተፈጠረው አደጋ ተደናግጦ ጭንቅላቱን
በሁለት እጆቹ ይዞ ቀረ፡፡ ከዚያም ሮጦ ደረሰባትና! እጇን ይዞ ይማፀናት
ጀመር፡፡ አልሰማ አለችው፡፡ ያለው አማራጭ ከኋላ ከኋላዋ መሮጥ ብቻ
ነበር፡፡ ተያይዘው ሆስፒታል እንደ ደረሱ፤ እነዚያ የሆያ ሆዬ ጓደኞቹ ተሰባስበው! ተቀበሏት፡፡
“የት ነው ያለው? ወንድሜ የት ነው? አንዱዬ የታለ? ሞቶ እንደሆን ንገሩኝ” ትለፈልፋለች፡፡ ከስንት ልመና በኋላ እንደምንም ብለው ሊያረጋጓት ሞከሩ፡፡ ከዚያም ሀኪሞች “አይዞሽ ደህና ነው” ብለው ካጽናኗት በኋላ ደም እንድትሰጥ ተደረገ፡፡
“ወንድሜን ዐይኑን ልየው እባካችሁ?” እያለች ፤ እያለቀሰች ብትለምንም “ሪከቨሪ” ስለሆነ መግባት አይቻልም ተባለች፡፡
ቀስ በቀስ ነፍሷን መግዛት ስትጀምር፤
ለአዜብ ስልክ አስደወለችላትና አዜብ መጣች፡፡ አዜብ ሁኔታውን እንዳረጋገጠች...
“ምን መዘዘኛ ነኝ?” የሚል መጥፎ ስሜት ተሰማት፡፡ ሚስጥሩን ስትነግረው በፍፁም የዚህ አይነቱ አደጋ ይደርስበታል ብላ አልገመተችም ነበር። ትንሽ እዚያ አካባቢ ዞር፤ ዞር፤ እያለች ከቆየች በኋላ፤ ሹልክ ብላ ሳትነግራት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
ትህትና ጨንቋት፤ አጽናኝ በምትፈልግበት ሰዓት ላይ ጓደኛዋን ብትፈልግ አጣቻት፡፡ ወዲያና ወዲህ ተዘዋወረች፡፡ ተዟዟረች፡፡ አዜብ ግን የለችም፡፡ በመጨረሻ ላይ እቤት ስልክ ደወለች፡፡ “የለችም” አስባለች፡፡ እየመሸ መጣ፡፡ እንደገና ስልክ ደወለች፡፡ አሁንም የለችም ተባለች፡፡
ክው ብላ ደነገጠች፡፡ “ምነው? ምን አደረኳት አዜቢናን?” ሽምቅቅ ብላ፤ ስልኩን አስቀምጣ፤ ብቻዋን ጭር ያለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠችና፤ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ እናቷ የካቲት አስራ ሁለት
ሆስፒታል፣ ወንድሟ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ምን ዓይነት ስቃይ
ነው? እንደተመኘችው ሳታየው መሸ፡፡ በማግስቱ እናቷን ጠይቃ፤ ወደ
ወንድሟ መጣች፡፡ ልታየው አልቻለችም፡፡ ፀጉሯን እንኳን ማበጠር አቁማለች፡፡ እንደዚያ የምታምረው ልጅ ነገሮች ተደራርበውባት፧ ማስፈራሪያ እየመሰለች ነው፡፡ እንደዚህ ሆና መከራዋን ካየች በኋላ ወንድሟን ያገኘችው፤ በሶስተኛው ቀኑ ነው፡፡
አንዱአለም ድንበሩ ከሞት ድንበር ደርሶ ተመለሰ፡፡ በሶስተኛው ቀን፤ በሶስተኛ ማዕረግ ከቀዶ ጥገና በሽተኞች ጋር ተቀላቀለ፡፡ እንደዚያ ፊቱ አብጦና፤ ጠቁሮ፤ ስታየው የምትሆነውን ነበር ያጣችው፡፡
“አንዱዬ ምንድነው የሆንከው?” ቀስ ብላ ጠየቀችው። ከትንፋሹ
ጋር እየታገለ....
“እንደሻው... አስደበደበኝ” ብሉ ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ አዜብ የሸሸችበት ሚስጥር አሁን ገና ወለል ብሎ ታያት፡፡ ሰውነቷን የሆነ ነገር ውርር አደረጋት :: እንደሻው
በግንባሩ ላይ ብዙ ጠመዝማዛ ቀንዶች አብቅሎ፣ ጥርሶቹ ተስለውና፤
አንደመጋዝ ሾለው፣ ጥፍሮቹ እንደ ጃርት እሾህ ተንጨፍርረው፣ ታይዋት፡፡ .
እንደሻው ... እንደሻው ... እንደሻው ... አእምሮዋን እንድትስት አድርጉ ከመታት በኋላ ሊከመርባት፤ በሀሳብዋ መጣባት፡፡ ሰውነቷ እንደሻው ምን ያላደረጋት ነገር አለ? የምትወደው ሻምበል ብሩክን ያጣችው በእንደሻው ምክንያት ነው፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያ ውሻ አድርጐ የሰደባት፤ በኋላም ስለእናቷ ክፉ ንግግር የተናገራት፤ እንደሻው በፈጸመባት ወንጀል ምክንያት ነው፡፡ ስራዋንም ያጣችው በሱ
ድርጊት የተነሳ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ግፍ ምንም የበቀል እርምጃ አልወሰደችም፡፡ እሷ ብትተወውም ግን እሱ ሊተዋት አልፈለገም፡፡
ይሄውና አሁን ደግሞ እንደ ዐይኗ ብሌን የምትሳሳለት፤ አንድና ብቸኛ ወንድሟን እንዳይሞት እንዳይድን፣ አድርጉ! አስደበደበው፡፡ ግን ለምን ይሄን ያክል ጨከነባት?
“የሰው ልጅ አይደለሁም እንዴ? ምነው ምን አደረኩት?” በሚል ጭንቀት ተውጣ ራሷን ጠየቀች፡፡ በሷ እምነት ምንም
አላደረገችውም።የፈጸመችበት በደል አልነበረም፡፡ የማፈቅረው ሰው ስላለኝ
ይቅርታ አድርግልኝ ብላ ለምና ተለማምጣ ልታግባባው ሞከረች እንጂ
አንዳችም ክፉ ነገር አልወጣትም፡፡እሱ ግን ያንን እንደ ጥቃት ቆጥሮ፤ በጭካኔ ደብድቦ፧ ክብረ ንጽህናዋን መድፈሩ ሳያንሰው አሁን ደግሞ እንደገና ,በወንድሟ ላይ የጭካኔ በትሩን አሳረፈ፡፡ግን ለምን?... ለምን?...ለምን?... ለዚህ ጥያቄዋ መልሱ ብዙም ሳይቆይ ወደ አእምሮዋ መጣላት፡፡ አላንገራገረችም፡፡ ይሄ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ስትል ወሰነች፡፡ የሆነውን ሁሉ በተቆራረጠ ድምጽ ነገራት፡፡
አሁን ሁሉንም ነገር ሰምታ ከጨረሰች በኋላ አዜብ አሳዘነቻት፡፡ እሷን ጠልታ ሳይሆን፤ በሷ ላይ በተደጋጋሚ ለሚደርሰው አስጠሊታ አጋጣሚ ሁሉ እጂ ስላለበት፤ መጥፎ ስሜት ተሰምቷት እንደሆነ ስታውቅ፤ “ጓደኛዬን አስጨነኳት፡፡ ጭንቀቴ እንጂ አንድም ቀን ደስታዬ
ተርፏት አያውቅም፡፡ በዚያው ለሷም ግልግል ነው፡፡” የሚል ስሜት
አደረባት፡፡
ታሪኩን በሙሉ አንድ በአንድ ሰምታ ስታበቃም፤ አሞቷ ኮስተር አለ፡፡ ለሁሉም ገደብ አለው፡፡ ትዕግሥትም ልክ አለው፡፡ እንኳንስ በደል፤ ማርም ሲበዛ ይመራል። በደል ሲደጋገም ደግሞ ከምሬት በላይ ነው፡፡ በቃ! እንደሻውን ልትበቀለው ስመ እግዚአብሔርን ጠርታ በልቧ መሀላ
ፈጸመች፡፡
አንዱዓለም የምትወደው ታናሽ ወንድሟ፤ የተፈጸመባት ግፍ አንገብግቦት ሊበቀልላት ሄዶ ጉድ ሆኗል፡፡ እሷ ደግሞ በታናሽ ወንድሟ ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ምላሽ መስጠት አያቅታትም፡የመጨረሻው የአባቷ ቅርስ ታያት፡፡ በክብር ተሸፍኖ በሣጥን ውስጥ በድብቅ
የተቀመጠውን፣ እሷና እናቷ ብቻ የሚያውቁትን፣ መቶ አለቃ

👍2
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ናትናኤል ለጥያቄው መልስ ሲያገኝ ይበልጥ ተበሳጨ፡፡ ለዚህ ቀላል ጥያቄ፣ ለዚህ ቀላል መልስ ይህን ያህል ከተቸገረ እንግዲያው ማስተዋል ቀንሷል ማለት ነው ከሚገባው በላይ ተወናብዷል ማለት ነው፡፡ ፈርቷል ማለት ነው፡፡
እራሱን ገሰጸወ፡፡
ረጋ ማለት አለበት፡፡ አለበለዚያ በማይረባ ስህተት እራሱን አጋልጦ ይሰጣል፡፡
ስሟን እስካወቀ፤ የስልክ ቁጥሯን እስካወቀ፤ የአባቷንና የአያቷን ስም ከማንኛውም የስልክ ደብተር ላይ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡
ሌሊቱን በሙሉ በሃሳብ ሲታመስ ሳያሸልበው ፀሐይ ሥፍራዋን
ተረከበች::
ናትናኤል ከአልጋው ተነስቶ ማታ አለቅልቆና በእርጥብ መሃረቡ
ጠራርጎ ከግርጌ ካለ ወንበር ላይ ያሰጣቸውን ሸሚዙንና ኮቱን አንስቶ
ለባበሰና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ በተቻለው መጠን ረጋ ብሎ ተጣጥቦ
ያለፈውን ሌሊት አሻራ ሙልጭ አድርጎ ካፀዳ በኋላ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ብቅ
አለ፡፡
ጥግ ላይ ተቀምጦ ሁለት ስኒ ቡና ጠጣና ፈጠን ብሎ ከሆቴሉ ወጣ፡፡ ሌላቱን ያለእንቅልፍ ቢያሳልፈውም የድካም ስሜት አልተሰማውም፡፡ምናልባት ድንጋጤው ይሆናል፧ ምናልባት ፍርሃት፣ ምናልባት ሥጋት፡፡
ደሙ በሰውነቱ ውስጥ ሲሽቀዳደምና ሲራወጥ ለራሱ ይሰማዋል፡፡ መፍጠኝና
መሮጥ አለበት!
ታክሲ ተሳፈረና ወደ መርካቶ ሸሸ፡፡
መርካቶ ባህር ነው ውቅያኖስ፤ መርካቶ ጫካ ነው ደን፡፡መርካቶ ቤቱ ነው የዘውድዬ፡፡
መሀል መርካቶ ከታክሲ እንደወረደ ወደ አንድ ቡና ቤት ገባ፡፡ገንዘብ ተቀባይዋን ተጠግቶ ሠላምታ ከሰጣት በኋሳ የስልክ ማውጫ ጠየቃት፡፡
“ጩኒ ቁልፍ፡፡” አለች ረጅም ወንበር ላይ የተቀመጠችው ወጣት ሴት ወደኋላ ዞራ፡፡
“ በእድሜ የሚመጣጠናት ወንድ ልጅ በቀጭን ሰንሰለት ውስጥ የተሰገሰጉ አስር የሚሆን ቁልፎች አቀበላት፡፡ ከቁልፎቹ ውስጥ አንዷን መርጣ አወጣችና አጠገቧ ያለ መሳቢያ ስባ የስልኩን ደብተር አውጥታ
አቀበለችው::
"እግዜር ይስጥልኝ” አላት ማውጫውን ተቀብሏት እየከፈተው፡፡
'የምሥራች ይልማ መጀመሪያ የምሥራችን ስም ፈለገ፡፡ በርካታ የምሥራች ይልማዎች የተደረደሩትን ገፅ እንዳገኘ የስልክ ቁጥሯን ፈለገው:: ቁጥሩን እንዳገኘ ወደኋላ ተመልሶ በትይዩ የተፃፈውን የምሥራችን ስም እስከ አያቷ ስም አነበበው የምሥራች ይልማ ገዛኽኝ::
“እቶ ይልማ ገዛኸኝ ድጋሚ የስልክ ማውጫውን እያገለባበጠ
ይፈልግ ጀመር አቶ ያልማ ገዛኸኝ... ይ.… ይ. ይ.. ያልማ አዳሙ... ይልማ መብራቱ
ይልማ ገብረማርያም…ያልማ ገዛኽኝ
የስልክ ቁጥሩን በወረቀት ላይ ገለበጠና የቡና ቤቱን ገንዘብ ተቀባይ አመስግኖ ወጣ፡፡ እዚያው አካባቢ የሕዝብ ስልክ ፈልጎ ኣቶ ይልማ ገዛኸኝ መኖሪያ ቤት ደወለ፡፡“
ከቤት” አለው ቀጠን ያለ የሴት ድምፅ፡፡
“እባኮት አቶ ይልማን ነበር”
“ሥራ ናቸው” አለች ሴትየዋ በተሰላቸ ድምዕ::
“እባኮት ችግር ገጥሞኝ ነው የሥራ ቦታቸውን ስልክ ቢሰጡኝ፡፡
“የሱቁን ነው?”
“አዎ ላገኛቸው የምችልበትን ቦታ፡፡”
ነገረችው:: ቀልጠፍ ብሎ ቁጥሩን ጻፍ ጻፍ አደረገና አመስግኗት ስልኩን ዘጋ:: ወዲያው የሰጠችውን ቁጥር ደወለ፡፡
ሃሎ” አለ ውፍረት የደፈነወ፣ ስጋ የዘጋው፣ እርስ በእርስ የሚተሻሽ ድምፅ::
“እባኮት አቶ ያልማ ይኖራሉ?”
“ነኝ:: ማን ልበል?”
“እንደምን ዋላ፡፡ የምሥራች ነበረች የላከችኝ..." ናትናኤል የሰውየውን ስሜት ለማጥናት ለአንድ አፍታ ዝም አለ፡፡
“ማን አሉኝ?” አለ ሰውየው መልሰው፡፡
“የምሥራች… የምሥራች ይልማ፡፡”
“ከየት ነው? ማንን ነው የሚፈልጉት?” ሰውየው ግራ የተጋቡ መሰሉ፡፡
“የምሥራች... የምሥራች የእርሶ ልጅ::”
“የማን ልጅ? ” ሰውየው ያበልጥ ተደነጋገራቸው፡፡
““ካዛንቺስ ሆቴል ያላት የእርሶ ልጅ::የምሥራች ይልማ ባለሆቴሏ...
“የምን ሆቴል ነው የሚሉኝ?”
ይቐርታ ጠይቋቸው ስልኩን ዘጋ፡፡
ሌላ ይልማ ገዛኽኝ በአዲስ አበባ ስልክ ማውጫ ደብተር ውስጥ የተመዘገበ የለም፡፡ ያለው አማራጭ ወደ ድሬዳዋ መንጎድ ብቻ ነው፡፡ድሬዳዋን አያውቃትም:: እዚያም ሄዶ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ ግን የተሻለ
ምርጫ የለም::
መፍጠን አለበት፡፡ ምንም ጠባብ ቢሆን በተከፈተለት በር ሁሉ መሮጥ አለበት፡፡
ወደ ካልቨርት መጠጋት አለበት::
ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ ወደ ባቡር ጣቢያ ሄዶ በማግስቱ ምሽት ላይ ወደ ድሬዳዋ በሚሄድ ባቡር ላይ የሁለተኛ ማዕረግ ትኬት ከቆረጠ በኋላ አውቶቡስ ተራ ወደ ዘውዲቱ ቤት ወደ ጎሬው በረረ፡፡
ምሳውን ከዘውዲቱ ጋር ከበላ በኋላ አሰዓት ወደ ገበያ ወጣ፡፡መርካቶ የዘመን መለወጫ በዓልን መስከረም አንድን ለመቀበል በሚዘገጃጅ ገብያተኛ ተጣባለች፡፡
ወደ ድሬዳዋ ሲሄድ ሊለብስ ያሰበውን ጀለቢያና ሽርጥ ነጠላ ጫማ እንዲሁም አንድ አነስተኛ የሸራ ሻንጣ ገዛ፡፡ አዲስ አበባ እስካለ ድረስ ደግሞ አጥልቆት የሚዘዋወረውን ወራጅ የጋራዥ ቱታና ፊቱን ጥሩ እድርጋ የምትሸፍንለት አንድ የተልፈሰፈሰች ባርኔጣ ጨመረ፡፡መንገድ ላይ ከኣንድ ጋራዥ ገባ ብሎ ለዘበኛወ ሁለት ብር ሰጠና በትንሽ ቆርቆሮ የተቃጠለ ዘያት ይዞ ወደ ጎሬው ሲመለስ ከእንድ ሱቅ ጎብቶ አንድ ጥሩ ሽቶና የሴት
ነጠላ ጫማ ሾመተ:: ከዘውዲቱ ቤት ሲደርስ ባይመሽም ቀኑ ገፍቶ ነበር።
ልብሱን አወላልቆ ዘወዲቱ እልጋ ወስጥ ገብቶ ጥቅልል አለ፡፡ የዘውዲቱን ቤት ተከራይቶ ከገባ ጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ዘውዲቱ፡ አብሯት የሚያድር ደንበኛ አጥታ እንድትመጣ ተመኘ፡፡
ያን ሌሊት በውዲቱ ቀንቷት ደንበኛ አገኘች አልተመለሰችም፡፡አልጋዊ ላይ ብቻዉን ሲገላበጥ ሲያቃዠው አደረ፡፡አንዱን ቅዠት ሳያገባድድ ሌላ ቅዠት እያቋረጠው ያባረረው ውሻ ሳያዘው ጭልጥ ካለ ገደል እየገባ ከገደሉ ወለል ደርሶ አናቱ እንደ እንቁላል ሳይፈርጥ አየር ላይ ጭልፊቶች
ገላውን እየገመጡ አይኖቹን እየጓጎጡት ሲወራጭ አደረ፡፡
ጠዋት በሩ ሲከፈት በርግጎ ሲነሳ ጭንቅላቱን በፋስ ሲወቅረው ተሰማው እራስ ምታት ነፍስ ዘርቶ፡፡
“እንደምን አደርክ?” አለችው ዘውዲቱ ወደ ውስጥ ገብታ በሩን እየዘጋች፡፡ እስካሁን አልተነሳህም? ሁለት ሰዓት አልፏልኮ::” የያዘችውን የላስቲክ ከረጢት ወንበር ላይ ጣል ኣድርጋ ኣልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለችና ኩንታል ስትሸከም እንዳደረች “
ኡፍ.....ፍ፡!” አለች፡፡ “እንዴ ለምን እራትህን ሳትበላ አደርክ?” አለች ሳይከፈት ያደረውን የምግብ ሳህን ከራስጌ ስታይ ዞራ እየተመለከተችው::
“አላየሁትም ነበር፡፡” አላት ናትናኤል እራቁት ደረቱን እያከከ ዞር ከራስጌ የተቀመጠውን ሳህን እየተመለከተ::
“እና ጾምን አደርክ ማለት ነው? ደግሞ ከትላንት ወዲያ የት ነበር ያደርከው?” ጥያቄ አከታተለችበት፡፡
ሳይመልስላት ከአልጋው ተነስቶ ከወገቡ በላይ ለመለቃለቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ሰወነቱን ተለቃልቆ ሲመለስ ዘውዲቱ ከራስጌ ያደረውን ሳህን ከፍታ በግራ እጇ ይዛ እየተንጎራደደች በላይ በላዩ ስትጎርስ አገኛት::
“ቡዳ የሆነ ሰውዬ ራቴን ሳያበላኝ ቤቱ ወስዶ እንደቅሪላ ሲያለፋኝ አደረ::” አለች እየሳቀች፡፡ “ላጉርስህ? ”
ራሱን ነቀነቀ፡፡ ናትናኤል ምግብ አላሰኘውም፡፡
“ምን ሆነሃል? ቤት ደህና አይደሉም እንዴ? ”
“ደህና ናቸው እነሱስ...” የጀመረውን አንጠልጥሎ ተወው፡፡
“ታዲያ ምን ሆነሃል? "
“ሰውየው ተያዘ::”
የቱ ሰውዬ?” መንጎራደዷን አቁማ በተቀመጠበት ቁልቁል ተመለከተችው፡፡
“አለቃዬ። የመሥሪያ ቤታችንን ገንዘህ ያጠፋው፡፡”
“አትለኝም!” የያዘችውን የምግብ ሳህን ከራስጌ አስቀምጣ በወጥ የተጨማለቀ እጇን አንከርፋ ኣልጋው ላይ ከጎኑ

👍1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን የክንዱን ቆዳ ቀይ እስኪሆን ድረስ እያከከ
በዴንከር ጎዳና ላይ ከሚገኘው የትሬይቮን ሬይሞንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በር ላይ ቆሟል፡፡ ገና ከመኪናው እንደወጣ ነበር እንግዲህ ክንዱን ማሳከክ የጀመረው። ምናልባትም ለዚህ አስቀያሚ እና “ቴስቲሞንት” የሚባለው ሰፈር በመጣ ቁጥር አለርጂኩ ይነሳበታል፡፡ በእርግጥም ደግሞ ይኼ ትሬይ
ሬይሞንድ ያደገበት መንገድ ላይ አሰቃቂ ወንጀሎች፣ አመጸኛ ድርጊቶች፣
አደንዛዝ ዕፆች፣ ሙስናዎች እና ግማቶችን ሲያስተናግድ የኖረ መንገድ
ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ሚክ ጆንሰንን ዘረኛ ነው ይሉታል፡፡ ይህንን በእሱ ላይ በዚህ
ጉዳይ የሚደርሰውን ወቀሳ ሲቃወም ኖሯል። ግን እዚህ ሰፈር ሲመጣ
በዘረኝነቱ ዙሪያ የሚቀርቡበትን ወቀሳዎች ልክ ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ለምን ቢባል ሁለት በጣም የሚቀርባቸው የሥራ ባልደረባዎቹ እና ጓደኞቹን
በተጨማሪም ባለፈው ጊዜ ከእሱ ጋር አጋሩ ሆኖ ይሠራ የነበረው ዴቭ
ማሎንም ጨምሮ እዚሁ መንገድ ላይ ነው እንግዲህ በወጣት ጥቁር የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በጥይት የተገደሉት። ግድያዎቹ የተፈጸሙት በጠራራ ፀሐይ ቢሆንም አንድም ሰው ቢሆን ጥይቱን ተኩሰው የገደሉትን ሰዎች አይተናል ብሎ ምስክርነት አልሰጠም፡፡ ብቻ ዴቭ ዳሽ ቦርዱ ላይ ከሚያስቀምጠው ካሜራ ላይ የገዳዮቹ ማንነት ስለታወቀ እነዚህ ሁለት
ጥቁሮች በሳን ኮንቲን እስር ቤት የሞት ፍርዳቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ
ተራቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ጓደኞችህን የገደሉብህንና የዋሽህ ህብረተሰብ ላይ ምንም ዓይነት ቂም
አለመያዝ በራሱ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ በደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሎስ አንጀለስ
ላይ ሁልጊዜም ጦርነት አለ፡፡ በትሬቨን ሬይሞንድ እድሜ ላይ የሚገኙት
የአደንዛዝ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ጠላቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ
ዶውግ እና ኒክ ሮበርትስ ያሉ ነፃ አሳቢ እና ለዘብተኛ ልብ አውልቅ ሰዎች
ደግሞ ከአደንዛዥ ዕፅ የማገገሚያ ክሊኒኮች ሃሳብ መልሶ መክሰስ አለበት፡፡
ጥቁሮቹ በጣም ድህነት ውስጥ ስለሆኑም ነው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ
ገብተው አደንዛዝ ዕፆችን የሚጠቀሙት፡፡ በሀገሪቱ ሲስተም ደካማነት የተነሳ
ወጣት ጥቁር አሜሪካውያንን እዚህ ችግር ውስጥ ለመክተት ችሏል እያሉ
ይበጠረቃሉ፡፡ እነርሱ እኮ እንደ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ. ፖሊሶች ምሽግ ውስጥ ሆነው ጦርነቱን እየተዋጉ አይደለም፡፡ ደግሞም ሲስተሙ አይደለም ዴቭ ማሎንን የተኮሰበት እና ደሙን ሲያዘራም እያየ ቆሞ የሳቀበት፡፡
ጆንሰን ሬይሞንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤትን በር በኃይል እየደበደበደ ማንኳኳት ጀመረ።
“ክፈቱ! ይህን የተረገመ በር ክፈቱ! ፖሊስ ነኝ” ብሎ በጣም ቁጣ በሚነበብበት ድምፅ ተቆጥቶ አዘዘ፡፡
ከውስጥ በኩልም ቀጭን የሴት ድምፅ “እሺ እየመጣሁ ነው! እየመጣሁ
ነው!”
“ቶሎ ነይ እና በሩን ክፈቺ!” አላት ጆንሰን በትዕዛዝ ድምጽ፡፡
በዚሁ መንገድ ላይ በመቶ ያርድ ርቀት ላይ በኒሳን አልቲማ መኪናው ውስጥ ቁጭ ያለው ዴሪክ ዊሊያምስ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን የሚያደርገውን ነገር ሲመለከት ተበሳጨ፡፡ ቀጭን እና ትንሽ ሰውነት ያላት አሮጊት ሴት
(ምናልባትም የትሬቮን አያት) ልትሆን የምትችል ናት በሩን ከፍታ ቆማ
በጆንሰን የሚደርስባትን ማመናጨቅ በፀጋ እየተቀበለች ያለችው፡፡ ችላ ዝም
ማለቷም አሳዝኖታል፡፡ እነዚህ የሟች ቤተሰቦች ምንም ዓይነት ወንጀል
ሳይፈጽሙ እንኳን እንደ ወንጀለኛ ነው እየተቆጠሩ ያሉት ለዚያውም በገዛ
ቤታቸው ውስጥ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በቆዳቸው ቀለም እና በመርማሪ
ፖሊስ ጆንሰን ዘረኝነት የተነሳ ነው፡፡ ይህንን ነው እንግዲህ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ
“ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ብሎ የሚደሰኩርበት፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የዚህ ሰፈር ነዋሪዎች ኤል.ኤ.ፒ.ዲን በሙሉ የሚጠሉት፡፡
ዴሪክ ዊሊያምስም ቢሆን ኤል.ኤ.ፒ.ዲን ይጠላዋል፡፡ የጥላቻው ምክንያቱ ግን ከጥቁሮቹ ጋር አይመሳሰልም፡፡ ዴሪክ በድምሩ ለሦስት ጊዜያት ያህል የኤል.ኤ.ፒ.ዲ አባል ለመሆን ማመልከቻ አስገብቶ ነበር፡፡ የአካል ብቃት ፈተናዎቹን በጥሩ ውጤት አልፎ የነበረ ቢሆንም እንኳን ፊታቸውን በማያውቃቸው ቅጥሩን በሚወስኑ ሰዎች አልተቀበልንህም የሚል
መልስን የያዘ ደብዳቤ ለሦስት ጊዜ ያህል ተጽፎለታል፡፡
ይኼ እንግዲህ ከ20 ዓመታት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ቢሆንም እስከአሁን
ድረስ ነገሩን ሲያስበው ያንገበግበዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የተዛባ ሃሳብ ያላቸውን
እንደሚክ ጆንሰን እና እንደ አጋሩ ጉድማን ያሉ ቀሽም የመሃይም መርማሪዎችን ሲመለከት በጣም ይበሳጫል፡፡
ጄንሰን ሬይሞንድ ቤተሰብ ቤት ውስጥ ለአርባ ደቂቃ ያህል ቆይቶ ሲወጣ ፊቱ ቀልቶ እና ወደቤቱ ከመግባቱ በፊት ከነበረበት የንዴት ስሜት በላቀ ንዴት ውስጥ ሆኖ ነበር ከቤቱ የወጣው፡፡ ዊሊያም ጆንሰን መኪናውን አስነስቶ ከአካባቢው በራቀ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመኪናው ወርዶ ወደ ሬይሞድ ቤተሰብ ቤት አመራ፡፡ የቤቱ በርንም ክብርን በማያሳይ መልኩ አንኳኳ።
“አሁን ደግሞ ምን ቀረህ?” አለ የቅሬታ ድምጸት የሚሰማበት የሴት ድምጽ እኛ የምናውቀውን ነገር ሁሉ ነገርንህ አይደል! ለምንድነው የማትተወን ብላ ደስ የምትል ጥቁር በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ
ሴት በሩን ከፈተችለት፡፡ ድምጹን ልታወጣ የቻለችውም መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን ተመልሶ የመጣ ስለመሰላት ነበር፡፡ በሩ ላይ የቆመው ሰው መሆኑን ስታይም የቅሬታ ፊቷ ወደቁጣ ተቀየረ፡፡ ዓይኗን አጥብባ እየተመለከተችውም
“አንተ ሌላኛው መርማሪ ነህ? ጓደኛህ አሁን ነው ከዚህ የወጣው፡፡ እዚህ
መጥታችሁ ከወንጀል ነፃ የሆኑ ሁለት ሴቶችን ከምታበሻቅጡ ለምንድነው
ይኼንን ገዳይ ይዛችሁ ለፍርድ የማታቀርቡት” ብላ በቁጣ ጠየቀችው::
“እኔ ፖሊስ አይደለሁም” ብሎ የቢዝነስ ካርዱን አውጥቶ እየሰጣትም “እኔ የግል መርማሪ ነኝ ሚስስ ሬይሞንድ፡፡ እኔ የትሬይን ገዳይ አድኜ ለማግኘት ነው በኒክ ሮበርትስ የተቀጠርኩት፡፡ ወደ ውስጥ መግባት እችላለሁ?” አላት ዊሊያምስ፡፡
ቤቱ ውስጥ ከገባ ከአስር ደቂቃ በኋላ ዊሊያምስ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ
ኩባያው ውስጥ የሚገኘውን ቡና ፉት እያለ ነው፡፡ ከእሱ በተቃራኒ ደግሞ
ሁለት መደገፊያ ባላቸው ወንበሮች ላይ የሬይሞንድ እናት እና አያት ቁጭ
እንዳሉ በትህትና እያናገሩት ነው፡፡
“ስለዚህ አንተን የቀጠረችህ ደ/ር ሮበርትስ ናት?” ብላ የሬይሞንድ እናት
ጠየቀችው እና “በጣም ጥሩ ሰው ናት፡፡ ምንም እንኳን ቀለል ያለች እና ልታዋራት የምትችል ሴት ብትሆንም በእውነት ጥሩ ናት፡፡ ሟች ባሏ ደግሞ በጣም ቅዱስ ሰው ነበር”
“አዎን ቅዱስ ነበር” ብላ የሬይሞንድ አያት ተናገረች፡፡
“ለትሬይ ሥራ ሰጠችው፡፡ ሁሌም ደግሞ ለእሱ ደግ ነበረች፡፡ እናመሰግናታለን፡፡ እና እሷ ናት የቀጠረችህ?”
ዊሊያምስም ራሱን በአዎንታ ከነቀነቀ በኋላ “ፖሊሶቹ የትሬይን ገዳይ
ለመያዝ በበቂ ሁኔታ እየሠሩ እንዳልሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡ እሷም ላይ የግድያ ማስፈራሪያ ደርሶባታል፡፡” አላት ዊሊያምስ፡፡
ሁለቱ ሴቶችም እርስ በርስ ከተያዩ በኋላ “ይህንን ነገር አላወቅንም ነበር፡፡ በእውነት እንደርሱ ከሆነ መጥፎ ነገር ነው፡፡”
“ሊዛ ፍላንገን የተባለች ሌላ የተገደለች ወጣት ነበረች”
ይኼኔም የትሬይ እናት መሃረቧን አውጥታ ዓይኗን እየጨመቀች
“ይህቺን ሴት ትሬይ ይወዳት ነበር፡፡ የዶክተር ሮበርትስ ታካሚ ነበረች
አይደል? ምስኪን ሴት በተለይ ደግሞ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ስላላት ግንኙነት
በጋዜጦች ላይ የሚፃፉት ነገሮች ትክክል

#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...እናቴ ደረጃው ላይ ቆማ «አደራ በጊዜ እንድትመለሺ... ይኽ ወጣ ወጣ..» አለቻትና ተመልሳ ገባች። የቀኑ ሞቃት አየር እንደ ብረት ምጣድ ያሰማትን መኪና ከፍተን በቀጥታ ጉዞ ጀመርን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከቤቴ አጥር በር አጠገብ ስንደርስ በደከሙ ዓይኖቹ ትናንሽ ፊደሉች እንደሚያነብ ዓይነ ደካማ ሽማግሌ፣ የውብነሽ በድንጋጤና በመገረም ዐይኗን ተክላ አየችኝ፡፡
«ያንተ ነገር እኮ አይታወቅም፡ ደረስን ልትለኝ እኮ ይሆናል» ብላ ወረቱ እንደ ረከሰበት ነጋደ ዐይኗ ቃበዘ፡፡ እጆቿ ተወራጩ፡፡ ቁልቁልም ሽቅብም
ወሰደቻቸው:: መጨረሻዋን ለማየት በጸጥታ ተቀመጥኩ፡፡ ቃላቷ በድንጋጤ
እየተቆራረጡ «እንዴት ብዩ ዐይኗን አየዋለሁ? ስንገናኝ ምን ምን ልበላት? በዚያ በሥቃይና መከራዋ ጊዜ ሳልጠይቃትና የት ገባች ሳልላት ኖሬ አሁን እንዲህ ብቅ ስል ምን ትለኛለች? ወይኔ ዛሬ 0ፈር በበላሁት!» አለችና ያንን ምድረ በዳ የሆነ ዐይኗን አቁለጨለጨችው::
«ይልቅ ነይ እንሒድ! እንዳንድ ጊዜ እዚህ ድረስ እየመጣች
ስለምትቀበለኝ አጉል ቦታ ላይ እንዳታገኝኽና ይብሱን እንዳትርበተበቺ ብዩ ከመናገሬ ጋሻዬነህ ከወደ ቤት «እባብዪ መጣ አባባ መጣ! » እያለ ሲጮህ ተሰማ፡፡ እናቱ ደግሞ በዚያች ቀጠን ብላ ቃናዋ በሚማርክ ድምጺ ና! ና
ተመለስ! ተው ትወድቃለህ! » እያለች ስትጣራና ስታስጠነቅቅ ሰማን። የውብነሽ
ማንቁርቱን እንቀው ዐይኑን እንዳስፈጠጡት ሰው አይኗ ፈጠጠ። የየወዲያነሽን ድምፅ ከሰማች ድፍን ስድስት ዓመት ኣልፏል። የውብነሽን ለማበረታታት ያህል
«አይዞሽ አትፍሪ! » ባለቤቴ እኮ ክፉ ሰው አይደለችም፡፡ ገና ገባ ስንል አንገቷ
ላይ ተጠምጥመሽ ሳሚያትና ኃፍረትሽን አስወግጂ፡፡ እንደገና ደግሞ ሳሚያት።
በእርሷ በኩል ሁሉንም ነገር በይቅርታ ትታዋለች፡፡ ከትናንት ጀምራ በጉጉት ነው
የምትጠባበቅሽ» አልኩና ከዚህም ከዚያም እምታትቼ እበረታታኋት፡፡ መለስ
ያለውን የአጥር በር ከፍተን ገባን።
ጋሻዬነህ ሰብሰቡ ሳይ ዝንጉርጉር ኳስ እያንከባለለ ይጫወት ነበር፡፡ ኳሱን
ጥሉ እየሮጠ መጥቶ አጠገቤ እንደደረሰ እጁን ዘረጋ፡፡ ቅብል ብዬ ታቀፍኩት፡፡
የየውብነሽ አእምሮ ያለ የሌለ ኃይሉን ፍርሃትን ለመቋቋሚያ አዋለው:: ዐይኖቿ
እንኳ በሚገባ ማየት የሚችሉ አይመስሉም ነበር፡፡ ቀይ ዳማ ፊቷ ከረመጥ የወጣ ካራ መስሎ ለሥቃይ መግለጫ ትሆን ዘንድ የተቀረፀች የመብ ሐውልት መሰለች፡፡ ወደ ቤት ገባ እንዳልን የወዲያነሽ ከወደ ጓዳ ወጣች፡፡ ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ሽንሽን ቀሚስና ብሩህ እረንጓዴ እጀ ጉርድ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ጸጉሯን በቀላሉ ጐንጉናና የቤት ውስጥ ቀላል ጫማ እድርጋ ወደ እኔ ስትመጣ
ከበስተጀርባዬ ያለችውን የውብነሽን ከወደ ጎኔ በኩል ኣየቻት። «እውይ የውብነሽ! አቤት የውቧ !» ብላ እጅዋን እስከ ትከሸዋ ከፍ ኣድርጋ ተንደርድራ
አንገቷ ላይ ተጠመጠመች። የየውብነሽ ኮሮጆ በድንጋጤም ይሁን ከደስታ ብዛት
አምልጧት ወደቀ፡፡ እንስቼ ወንበር ላይ አስቀመጥኩት። ተቃቅፈው ሲሳሳሙ
ልክየለሽ ደስታ አጥለቀለቀኝ፡፡ የምሆነው መላቅጡ ጠፋኝ፡፡ የየወዲያነሽ አለባበስ
እንደ ነገሩ ቢሆንም ደስ አለኝ እንጂ አልተከፋሁም። ጎን ለጎን ተቀምጠው
«ደኅና ነሽ ወይ?» እየተባባሉ በሣቅና በፈግታ ሲጠያየቁ ምንጊዜም በቃላት
እቀናብሬ ልገልጸው የማይቻለኝ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ጋሻዬነህ ጭኔ ላይ አስቀምጬ
ፊት ለፊታቸው ጉብ አልኩ፡፡ ደቂቃዎች እየፈነጠዙ ተግተለተሉ፡፡ የየውብነሽ
ፍርሃትና ድንጋጤ ሙልጭ ብሎ ከላይዋ ላይ በመጥፋቱ ያለቻትን ፈገግታ ሁሉ
ሞጣጥጣ አወጣቻት። ጋሻዬነህ ከጭኔ ላይ ወርዶ ወደ እናቱ ሲሔድ የውብነሽ
አገላብጣ ሳመችው። ዐይን ዐይኑን እያየች «እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እኔንም
እንኳን ይህን ለማየት አበቃኝ» ብላ ኣንስታ አቀፈችው::
የወዲያነሽን፡ ስለ የውብነሽ እንግድነት ይህን ይህን እንድታዘጋጂ ብዬ አልነገርኳትም። ደስ የሚያሰኘውንና መቅረብ የሚገባውን ነገር ሁሉ
ስለምታውቀው ይህን እንድትሠሪ ያንን እንዳትረሺ ማለት አላስፈለገኝም፡፡
የወዲያነሽ ንብ ነች! የውብነሽ አሁንም
አሁንም የማርያምን ጽዋ እያስቆሙ
እንደሚስሙ ሕፃናት የጋሻዬነህን ጉንጭ ደጋግማ ሳመች። ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ
እውነተኛ ድል ከድሉች ሁሉ የበለጠ ድል ነው። የወዲያነሽ ግልጽና ቅን ከመሆኗ
የተነሣ ከየውብነሽ ጋር በምትነጋገርበት ጊዜ ሁሉ ካንጀቷ ስለምትሥቅና ፈገግ
ስለምትል አኳኋኗና አቀራረቧ ሁሉ የየውብነሽን ልብ ማረከው፡፡ ቀድሞም ቢሆን የውብነሽና የወዲያነሽ በጣም ይዋደዱ ስለነበር አሁን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሲገናኙ ፍቅራቸው ከትዝታቸው ሰታቴ ገንፍሎ ወጣ፡፡ የሁለቱ መግባባትና አዲስ ግንኙነት መጀመር ለእኔ አንድ ታላቅ የትግል ምርት ነበር። በእኅቴና በባለቤቴ መካከል ያለው ጋሻዬነህም በሁለት የሚያማምሩ አበቦች ዙሪያ እንደምትዞር የመስቀል ወፍ ይማርካል። የወዲያነሽ ከሁለታችን ተለይታ ወደ ጓዳ ገባች፡፡
በጋሻዬነህና በአክስቱ እንዲሁም በእኔ መካከል ውብ ትዝታው እስከ መቼም የማይረሳ ወሬ ቀጠለ፡፡ ጊዜ እንደ አበደ ውሻ ተክለፈለፈች። መሰለኝ እንጂ አትረዝም አታጥር! የወዲያነሽ ከሠራተኛይቱ ጋር በመረዳዳት ምግብና
መጠጥ አቀረቡ። ከግምቴ በላይ ሆኖ በማግኘቴ በአቀራረቧ ረክቼ ባይኔ ጠገብኩ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ እኔ፤ ባለቤቴና እኅቴ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ቀረብን፡፡ ድሉ ግን የእኔና የየወዲያዩ ነበር፡፡ ምንም እንኳ የውብነሽን ያ በአእምሮዋ ውስጥ
ተዳፍኖ በመጥፎ ትዝታ የሚጫረው ያንድ ቀን ስሕተቷ እያጸጸተ አንገቷን
እንድትደፋ ቢታገላትም እጅግም ስላላጠቃት ጨዋታው ደራ፡፡ የወዲያነሽ
በተደጋጋሚ ስታጎርሳት ቀጥ ያለ ዓቀበት ዘልቆ እፎይ እንዳለ መንገደኛ ተደሰትኩ፡፡ የውብነሽም በሌላ በኩል ብድር የምትመልስ ይመስል «ይቺን ብቻ
ጋሻው» እያለች ለጋሻዬነህ ታጎርሳለች፡፡
የማዕዱ ጣጣ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ እንደ ልብ
እንዲጠያየቁና እንዲጫወቱ ነጻነት መስጠቴ ነበር፡፡ ተቆርጦ እንደ ወደቀ የጥድ ዕንጨት ተዘረርኩ እንጂ እንቅልፍስ በዐይኔም አልተኳለ፡፡
የፈለግኸውን ነገር ብትጠይቀኝና አድርጊልኝ ብትለኝ እፈጽምልሃለሁ፡
የፈለግሁትን ሰው አምጥቼ ታረቁልኝ ብል እታረቅልሃለሁ ብለሽኛልና በይ
እንግዲህ እንደ መሐላሽና እንደ ቃልሽ ፈፅሚልኝ ብዬ እናቴን ሳስገድዳት እሺ
ብላ የወዲያነሽ ጋር ትታረቅልኛለች ወይ?» የሚለው ሓሳብ አንጎሌን በሥጋት
ሹል ወስፌ ዉቀዉቀው። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ደረደርኩ፡፡
እናቴ በአስገዳጅ ምክንያቶችና ሁኔታዎች ተገፋፍታ እሺ ብትለኝና ከባለቤቴ ጋር ብትታረቅልኝ የአባቴን ጉዳይ እንዴት ልወጣው እችላለሁ? የሚለው ሐሳብ ደግሞ የባሕር ላይ ኩበት አደረገኝ። ይህ ጉዳይ በእናቴ በኩል ቢደርሰው ይቀላል ወይስ በቀጥታ በእኔ አማካይነት? ይሁን ፈጽሞ ያላወቀውንና ይደርሳል ብሎ ያልጠረጠረውን ነገር ከሥር ከመሠረቱ አብራርቶ ለማስረዳት ቀላሉ ዘዴ ምንድነው? እያልኩ ራስን በራሲ በሐሳብ ቢላዋ ዘለከልኩት።
በቀላል ሐሳብም ሆነ በጊዜያዊ መግባባት ከአባቴ ይልቅ እናቴ ቅረብ
ስለምትለኝ በመጀመሪያ በእናቴ በኩል ያለውን ወደ ፍጻሚ ማድረስ አለብኝ
የሚለው ሐሳብ አመዘነ፡፡ በሐሳብ አዞሪት ውስጥ ተዘፍቄ ብቅ ጥልቅ በማለት ላይ
እንዳለው የውብነሽ ጋሻዬነህን
ስትገባ ከአሳቢ ተናጠብኩ፡፡
አልተንቀሳቀስኩም፡፡ ጎንበስ ብላ ጫማውን ካወለቀችለት በኋላ በላዩ ሳይ አሻግሬ አልጋው ላይ አስቀመችው::
ትንሽ ጎበጥ ብላ በሁለት እጅዋ አልጋውን በመመርኮዝ

👍3🥰1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ቅድመ ዝግጅቱ በእነ ጃኖ በኩል ተጠናቀቀ። ሁሉም ነገር መስመር
መስመር ያዘ፡፡ እንዳሰቡት ሊያሳኩ ጭው...እልም..ብለው ሊጠፉ ከሀሳብና ጭንቀት ነፃ በሆነ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ሊጀምሩ የቀረቻቸው አንዲት ጀምበር የዛሬዋ ዕለት ብቻ ነበረችና ራታቸውን ከበሉ በኋላ ሌቱናን በፍቅር ዐይን ዐይኗን ትኩር ብሎ እያየ "ሌቱ!" አላት። "አቤት
ጃኖዬ” አለችው። እንደ እውነቱ ቢሆን ኖሮ እኔ እሱን ሸሽቼ ቤት ንብረቴን ሸጬ መጥፋት የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፡፡ ተበዳይ እኔ፣ ወንጀል የተፈፀመብኝ እኔው ሆኜ ሳለ እንደጥፋተኛ የተወለድኩበት፣ ያደግኩበትን መንደር ጥዬ መኮብለሌ በጣም የሚያሳዝን ነው" አላት።
እሱማ ምን ጥያቄ አለው ጃኖዬ? ከበደልም በደል ከግፍም ግፍ እንጂ”አለች በፀፀት፡፡ የበደሉ ድልየግፍ ግፍ በእጁ እያጎረሰ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ከብቶቹን በሙሉ ሽጦ ከገበረ በኋላ የልጃገረድ ሚስቱ መሆኗ በወላጆቿ አንደበት ተረጋግጦ በተስፋ ሲጠባበቅ ቱሬ በአቋራጭ መጣና እፍታውን ወሰደው... አቦሉን ላፈው….ይሄም አነሰና ከአገር ሊጠፉ ሊኮበለሉ መዘጋጀታቸው ተበዳይነታቸውን አባብሶት ታያትና ከበደልም
በደል ከግፍም ግፍ ስትል የጃኖን ሃሳብ ደገፈች።
“እንደዚያም ሆኖ የባላባት ጃዊሳ የወገናችንን ጎሳ አገር ደፍሮ መጥቶ ጦርነት ሊያነሳ ፀብ ሊፈጥር የሚከጅል አይመስለኝም፡፡ እስከ አሁን
ድረስ የቆየው ይሄንኑ ፈርቶ እንደሆነ ይሰማኛል። እኔ ግን በሱ ትምክህት ሳይሆን በእውነተኛ ተበዳይነቴ ሰው ቢፈርድብኝ ሰው ቢያጠቃኝ እግዚአብሔር ይክሰኛልና ብዙ አልጨነቅም፡፡ አይመስልሽም ሌቱ?" አላት
የፍቅር ዐይኖቹን ከዐይኖቿ ላይ ሳይነቅል።
“ይመስለኛል እንጂ ጃኖዬ እንዴት አይመስለኝም? የተወለድንባትን፣
ጭቃ እያቦካን ያደግንባትን፣ ፍቅራችንን የተከልንባት ቀዬአችንን ጥለን የምንሰደደው በደል አድርሰን ሳይሆን በደል ደርሶብን ተገፍተን አይደለም እንዴ? የተገፋን የተበደልን በመሆናችን ደግሞ መጪው ጊዜ የሰላምና የደስታ እንደሚሆን አትጠራጠር ብላ ጉንጩን ሳም አደረገችው።
"አባትሽም እናትሽም ቂም እንደያዙ አንድ ቀን እንኳ ዐይንሽን ሳያዩት መለያየታችን ነው አይደል?"አላት ምሽቱ እየተቃረበ ሲመጣ በዚያች በመጨረሻዋ ለሊት እንኳ ተሰናብታቸው ብትመጣ የሚል ስሜት ተሰምቶት፡፡
ነግሬሃለሁኮ ጃኖ! እኔ ወላጆች የሉኝም፡፡ ወላጆች ወላጅነታቸው የሚለካው ለልጃቸው በሚሰጡት የፍቅር ስሜት እንጂ የወለዱትን መልሰው ለመብላት ባላቸው የረሃብ ስሜት አይደለም። የወላጅነት ትርጉም መውለድ ብቻ ከሆነ እበት ትል ይወልዳል። የወለደቻቸው ልጆችዋን መልሳ የምትበላ ድመትም አምጣ ትወልዳለች። ድመት ልጆቿን መልሳ የምትብላቸው በጥላቻ ይሁን በፍቅር ምክንያቱን አላውቅም። በምንም ይሁን በምን እሷ እንስሳ ናት፣ የማመዛዘንና የማስተዋል ችሎታ የላትምና ለጥጋብ ብላ ብትበላቸው እንኳ የወንጀሏ ክብደት እንደኔ ወላጆች
ከብዶ አይታይባትም፡፡የኔ ወላጆች ግን እንስሶች ሳይሆኑ ስዎች ናቸው።የማመዛዘንና የማስተዋል ችሎታ አላቸው፡፡ ይህን እያወቁ የራሳቸውን ኑሮ ለማደላደል፣ ለራሳቸው እንዲጠግቡ የቀረቻቸውን አጭር ህይወት
በደስታ ለመምራት ሲሉ የኔን ሰፊ ዕድል ያጨለሙ በኔ ስቃይ ለመጥገብ የፈለጉ ሆዳሞች ናቸውና ዳግም የነሱን ስም አታንሳብኝ” ስትል በምሬት ተናገረች፡፡
"ይሁን ሌቱ! ይሁን... ስለነሱ የምትነግሪኝ ሁሉ ከምርሽ መሆኑን ለማረጋገጥ ብዬ እንጂ፣ ተለይተሻቸው ከሄድሽ በኋላ ናፈቁኝ ብለሽ እንዳታስቸግሪኝ ፈርቼ ነው እንጂ፣ እውነትም ይሄንን ያክል የተማረርሽባቸው
ከሆነ እውነቱን ልንገርሽ ሌቱ? ያንቺ ወላጆች ምትክ የማይገኝላቸው ጨካኞች ናቸውና ዳግም ስማቸውን በፊትሽ አላነሳም" አላት።
እናቴም አባቴም አንተው ነህ ጃኖ! እነሱ ባጨለሙት ህይወቴ ላይ
ብርሃን ያበራህልኝ፣ወላጆቼ እንድሸከም የፈረዱብኝን የባርነት ቀንበር ከላዬ ላይ አሽቀንጥረህ የወረወርክልኝና አዲስ የህይወት ተስፋ የፈነጠክልኝ ከሞት አፋፍ መልሰህ የህይወትን ጣፋጭ ትርጉም እንዳጣጥም ያደረከኝ አንተ ብቻ ነህና አንተን ተከትዬ የትም እሄዳለሁ።ገደል እንግባ
ብትለኝ እንኳ በደስታ እከተልሃለሁ" አለችው፡፡
“እውነቴን ነው ሌቱ አንችን ያጣሁ ቀን የተሰማኝን ስሜት ይህ ነው
ብዬ በቃላት ልገልፅልሽ የምችለው አልነበረም፡፡ መጠለፍሽን ስሰማ ህይወቴን ሳትኩ፣ ራሴን ጠላሁ አንዲት ለሊት እንኳ እንቅልፍ አግኝቼ ማደር ተሳነኝ፡፡ ለኔ የተፈጠርሽው አንቺ ብቻ ነሽ፡፡ የትም ቢሆን የት ካንቺ ውጪ ደልቶኝ ከምኖር አንቺ የኔ ሆነሽ ቆሎ እየቆረጠምን በፍቅር
ለመኖር ነው የምፈልገው፡፡ ተስፋዬ አንቺው ነሽ"አለና ጭምቅ አድርጎ
እንደ ሎሚ መጠጣት... እንደዚህ እየተጨዋወቱ አመሹና የነገ መንገ
ደኞቹ የሌሊት ተጓገዦቹ የሚወዷትን የትውልድ መንደራቸውን ጥለው ሰው ሳያያቸው በለሊት ሊጠፉ ወስነው ማልደው ለመነሳት በጊዜ ተቃ
ቅፈው ተኙ፡፡
በፍቅር ክንዱን አንተርሷት ደረቱ ላይ ለጥፏት ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ድብን ያለ ከሞት ያልተናነሰ እንቅልፍ ይዟቸው ጥርግ.…አለ።
በዚያ እነሱ በፍቅር ተቃቅፈው የሰላም እንቅልፍ በሚለጥጡባት የመጨረሻ ምሽት አንድ ፍጡር ወደ እነሱ በመገስገስ ላይ ነበር፡፡ በትረ መቅሰፍቱን የታጠቀ የድቅድቁ ጨለማ ንጉሥ፣ የሽብር አለቃው ጎንቻ!! ከወረወረ የማይስተው ጎንቻ! ፎክሮ ከወጣ የማይመለሰው ጎንቻ! በገባው
ቃል መሰረት የውሸቱን ባላባት ሚስኪኑን ገበሬ ጃኖን ሊያስቃይ በዚያ በውድቅት ለሊት ከተፍ!! ብሏል፡፡ ምፅአተ መርገምቱን አርግዞ፣ የሞትና የስቃይ ሰይፉን መዝዞ... ከምሽቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ በጃኖ ጎጆ ላይ ወርዷል... ጠቋሚዎች ቤቱን በርቀት አሳዩና ፈረሶቻቸውን ይዘው ሰዋራ
ስፍራ ላይ ቆሙ::
ሁለቱ ጀሌዎቹ ቱሲና ጊርቦ ጎንቻን ተከትለው ወደ ጃኖ ቤት ተጠጉ...
ጎንቻ በሆዱ ሳቀ፡፡ "እንዴት ያለ ደሃ የስም ባላባት ነው?” ብሎ ተገረመ።
"የባላባት ቤት ቀርቶ የሀብታም ገበሬ ቤት እንኳ አያክልም" አለ፡፡ የድሃው ገበሬ የጃኖ ቤት መሆኑን ሲያውቅ ግን ጃኖን ባደነቀው ነበር፡፡ ጎንቻ በግራ ክንዱ ላይ የአውሬ ስጋ ግጥም አድርጎ አስሮበታል። ተናካሽ ውሻ ካጋጠ
መው የሚከላከልበት ጋሻ መሆኑ ነው። እንደተለመደው ግራ ጎኑ ላይ ከሁለቱም ጎኑ የተሳለ ካራ ሰክቷል፡፡ ከደረቱ የማይነጥላት አጭር ምንሽሩን ከሙሉ ዝናር ጥይት ጋር ታጥቆ በዚያ በቅቤ በረበረሰውና ቁልቁል በተንዠረገገው ጎፈሬው፣ በአስፈሪ ተክለ ቁመናውና በቀል ባረገዘ ክፉ ልቦናው በጭካኔ ተደራጅቶ ወደ ሚስኪኑ ጃኖ ቤት እየተቃረበ መጣ...ጃኖ እሱ የሚበላውን እያበላ ወተት እያጠጣ ያሳደገው አንበሳ የመሰላ አዳኝ ውሻው ተኝቷል። ጠረን ሸተተው፡፡ ተቅበጠበጠ፡፡ ዋህ! ዋህ! ጠረኑ እየተጠጋው ሲመጣ “ጌታዬ ንቃ! ጌታዬ ጠላት መጥቶብናል ተነስ!!" ማለቱ ነበር፡፡ ጃኖ ግን እንኳንስ የውሻ ጩኸት ቢወጉት የማያስነቃ ድብት የሚያደርግ እንቅልፍ ነበር የወሰደው። የጃኖ ውሻ ጎንቻ አጥሩን ዘሉ እስከሚ ገባ ድረስ አልጠበቀውም። በከፊል ከድንጋይና በከፊል ከአፈር ጓል የተገነባውን በላዩ ላይ እሾህ የታጠረበትን አጥር እመር! አለና ዘሎ ወጣ፡፡ በጣም የሚያስፈራ መልኩ ዳለቻ የሆነ ትልቅ ውሻ ነበር። ጎንቻ ልቡ ትንሽም
አልደነገጠ። ሁለቱ ጀሌዎቹ ግን ሽንት ቀረሽ ድንጋጤ ነበር የደነገጡት።

👍5