አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በክፍለማርያም

..ፍቃዱ የሚወጣዉን ሰዉ ተመለከተዉ
ፍፁም የጀመረዉን አጋምሶ ፍቃዱ እስካሁን ስለጠፋሁበት ተመልሶ ይሆናል በማለት ለጥቂት ደቂቃ ስለተቀመጠ እግሩን እያስነከሰዉ በክራንቹ እየተመረኮዘ ሰበር ሰካ እያለ ሲወጣ
ፍቃዱ ከቅድሙ ሰዉዬ ጋር ቆሞ እያወራ ፊት ለፊት ተፋጠጡ።

ቤዛዊት በሽታዋ እያገረሸ እየተብከነከነች ብቻዋን እያወራች ወደ ፍፁም ቤት አምርታ አለመኖሩ ስታረጋግጥ አከራዩ ጋር ሄዳ

"የት ነዉ የሄደዉ?"

ለእሳቸዉ የማይጠየቅ ጥያቄ አይኖቿን እያጉረጠረጠች ጠየቀቻቸዉ
"እኔ ምን አዉቃለዉ የሚሄድበትን ነግሮኝ አይሄድ"
ሲሉ አኩዋሀኗ ያላማራቸዉ የፍፁም አከራይ መለሱላት
"እሺ እኔን የምትመስል ቁመት ብቻ የምትበልጠኝ ሴት መጥታ ነበር"
አጉረጠረጠችባቸዉ
የፍፁም ቤት አከራይ በልባቸዉ ምኗ ለካፊ ናት እያሉ
"የኔ እመቤት ማንም የመጣ ሰዉ አላየሁም አቶ ፍፁም ግን ብቻዉን ጠዋት ሲወጣ ተገናኝተን ነበር"
ይህን ሲሏት ትንሽ ተረጋጋች ከእህቴ ጋር ነዉ ስትል የነበረዉን ትታ እየከነፈች ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት አመራች።

ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ደርሳ ከመግባቷ በፊት ለአፍታ ፍፁምን አሰበችዉ
"የት ሄዶ ይሆን ምን ገጠመዉ"
አይምሮዋ ግን አልተረጋጋም በቆመችበት ቦታ አንፑላንስ ድምፁን እያሰማ በአጠገቧ ሲያልፍ ጩሀቱ ስለቀፈፋት በእጆቿ ጆሮወቿን ደፍና ለደቂቃ ቆመች
መኪናዉ አልፎ ጩሀቱ እየቀነሰ ሲመጣ ተስፋ በመቁረጥ ስሜት አስፓልቱ ዳር ዝርፍጥ ብላ ተቀምጣ በአይኖቿ የፍፁምን መምጣት ትጠባበቃለች።

እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊት መጣሁ ብላ መጥፋት አሳስቧቸዉ ወደ ዉጪ ወጣ ሲሉ መንገድ ዳር ተቀምጣ አይኖቿ ሲንከራተቱ ስላዩዋት ደረታቸዉን እየደቁ እየደገፉ ወደ ቤት ለማስገባት የቤዛዊትን ሰዉነት መጎተት ጀመሩ።

"አይመጣም ቀረ..."

እያለቻቸዉ እየተሳበች እየተጎተተች ተነስታ የእማማ ስንቅነሽን ቀሚስ ጨምድዳ ይዛ እየቆመች
በታመመ አይምሮዋ የቅድሙን ቃል ደገመችላቸዉ

"አይመጣም ቀረ..."

እማማ ስንቅነሽም በዝምታ ወደ ቤት እንድትገባላቸዉ እየጎተቷት
ቅድም ያለፈዉ አንፑላንስ ተመልሶ እየጮሀ አለፈ በአሁኑ ግን ጆሮወቿን አልያዘችም በድንገት ግትር ብላ ቆማ
"ያ ዉ ያዉና መጣ"
የቀኝ እጇን የመጠቆምያ ጣት ወደ ታች ወደሚወርዱ ብዛት ያላቸዉ ሰወች ቀስራ
ፍፁም እያነከሰ በሁለት ፖሊሶች ተከቦ ከጀርባቸዉ ወሬ አድማቂ ሰዉ አጅቦት አንገቱን ደፍቶ እየተራመደ ነዉ መሬት መሬቱን እያየ ሸንከል ሸግከል እያለ ይራመዳል ፖሊሶቹ እንዲፈጥን ኮሌታዉን ይዘዉ ይጎትቱታል
ፍፁምን ካጀቡት ሰወች መሀከል
"ገድሎታል አረ አልሞተም"
እየተባባሉ ይከራከራሉ
ቤዛዊት እማማ ስንቅነሽ እጅ ላይ አይኖቿ ፍዝዝ ብለዉ በድን ሆና ቆማለች መናገር አቁማለች የምትሰማም አትመስልም የአይኖቿ ብሌኖች ብቻ በቀስታ ይንከዋለላሉ።

(ከደቂቃወች በፊት)
ፍፁም ፊት ለፊቱ የቆመዉን ፍቃዱን ሲያየዉ እያዘነ አይቶ እንዳላየዉ መስሎ ሊያልፈዉ ሲል ፍቃዱ ከጀርባዉ ደርሶበት
"የት ለመድረስ ነዉ የምታነክሰዉ"
ይለዋል በንቀት እግር እግሩን እያየ
ፍፁም መልስ ሳይሰጠዉ መራመዱን ሲቀጥል ፍቃዱ ደግሞ ደርሶበት እየሳቀ
"ቤዛዊትን መቼም አታገኛትም የኔ ናት አንተ ዉሻ እያዋራሁክ ደሞ የምን ንቀት ነዉ ጥለሀኝ የምትሄደዉ..."
ፍፁም መታገስ አልቻለም ክራንቹን ወደ ሰማይ አንስቶ ፍቃዱ ላይ ሳያቋርጥ ማሳረፍ ጀመረ።

ሳያስበዉ በእልህ ፍቃዱን ክፉኛ ስለመታዉ መቆም ያቃተዉ ፍቃዱ ተዝለፍልፎ ወደቀ።

💫ይቀጥላል💫

ምዕራፍ #1 በዚህ ተጠናቋል ምዕራፍ #2 በቅርቡ እንጀምራለን እስከዛው በሌሎች ጣፋጭ ድርሰቶች እንቀጥላለን እስካሁን በሄደው ድርሰት ላይ ያሎትን አስተያየት አድርሱን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...“ እንዲያው ምን ምን ይላት ይሆን?እኔ እሱ ለሴት ልጅ የሚያወራውን ነገር ለመስማት እጓጓለሁ " ግን አንተ ባል
ከው ዐይነት አገጣጥሞኝ አያውቅም ። ”

“አጅሬ ምኑ ሞኝ ነው ላንተ የሚታየው ?!እሷን ሲያገኛት ቦታው ጭር የሚልበትን ጊዜ ጠብቆ ነው ።

“ ወይ ጉድ ! መቼም ፍቅር የማያሸንፈው ልብ የለም ”አለ እስክንድር በልቡ ። ስለ ድብርት የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ ነበር ። ሆኖም ጨዋታው በተዘዋዋሪም ቢሆን አንዳንድ የአቤልን ድርጊቶች እንደሚንካ ስለ ገመተ አርዕስቱን ለመለወጥ ፈለገ ሳምሶንም ይህንን ሁሉ ልብ ሳይል እንደ መጣለት ነበር የሚጫወተው ። እስክንድር ግን የአቤል ስሜት
እየተለዋወጠ እንደ መጣ በሥርቆት ከገጽታው ላይ አንብቦአል ድብርት የሴት ጓደኛውን ለማግኘት ጭር ያለ ጊዜ
መጠበቁ የአቤልን ስሜት ክፉኛ ነክቶታል እሱም ትዕግሥትን ለማየት የሚጠቀምባቸውን ጊዜያቶች ያውቃል ።

ስማኝ ላምሶን ! ግን ለምንድነው አንተ ብዙ ጊዜ ድብርትን የምትለክፈው ? ” በማለት እስክንድር አርዕስቱን አሸጋገረው
“ ለተንኮል አይደለም ። ግን የሚነፋነፍ ሰው መልከፍ እንዲሁ ደስ ይለኛል ። እንዴት ብዬ ላስረዳህ ? ለምሳሌ
ቀርቦ መናከስ የማይደፍር ውሻ በሩቁ እያፈገፈገ ሲጮህብህ እልሁን ለማስጨራረስ በዱላ እንደምትተናኮለው ዐይነት ነው ። ብቻ እንዲሁ ስለክፈው ደስ ይለኛል እንጂ ለድብርት መጥፎ አመለካከት የለኝም ለየት ያለ ተፈጥሮ ስላለው ያስገርመኛል ” አለና አሳላፊዋን ለመጥራት ጠረጴዛውን ጠበጠበ።

“ አቤት ! ምን ልታዘዝ? ” እያለች አንገቷ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ሴት ከፊታቸው መጥታ ቆመች ።

“ ቢራ ድገሚን ሦስት ቢራ ! ” አላት ሳምሶን በዚያው ቁጡ ድምፁ

“ እኔ ይብቃኝ ! ” አለ አቤል "

“ አትቀልድ እባክህ ። አንቺ እኔ የማዝሽን አምጪ!” አለና ሳምሶን አሳላፊዋ ላይ ጮኸባት ።

"ጥርስሽን እንዳያወልቅ ” አለና እስክንድር በልቡ ሳቀ ።

“ እኔኮ ያንተም ተፈጥሮ ያስገርመኛል ” አለው እስክንድር ሳምሶንን
“ እንዴት ?”
“ አሁን ሚስተር ሆርስ ከአቤል ጋር ከታረቀ በኋላ ለምን ትዝትበታለህ ?”

“ አዎ ! የማታውቀው ነገር አለ እስክንድር እየዛትክ የምትተው ከሆነ ዛቻው ሲደጋገም ሰው ይንቅሃል ።ወንድ ከሆንክ አንዴ ማቅመስ አለብህ ። እንዲያውም አንተን ብዬ ነው እንጂ እሱን ልጅ አንድቀን ብሰብረው ደስይለኛል ። ከፈለገ የገዛ ጥርሱን ከመሬት አሰለቅመዋለሁ ።

“ጡንቻህን ፈትነኝ እያለ ያስቸግሃል መሰለኝ” አለና እስክንድር እየሣቀ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ ፡ “ ብቻ ያለንበትንም ጊዜ አትዘንጋ : ሀያኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነን ” አለው ።

“ እና ? ” የብሽቀት ድምፅ ነበር ።

“ እናማ ስፖርተኝነትህን እወድልሃለሁ ። ይህችን በጡንቻ መመካትህን ግን ...

“ እንግዲህ አትልከፈኝ ፡ ልጠጣበት ! ” አለና ቢራውን ተጎነጨ

ሳምሶን ሌላ ሰው እንዲህ ቢናገረውም ካልተደባደበ በዋዛ እይላቀቁም ነበር ። ለእስክንድር ያለው ክብር ግን ብዙ ዓመት ከቆየ የልጅነት የአስተሳሰብ ተጽዕኖ የመጣ ነው ። የሠፈር ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን ሳምሶን ስለ እስክንድር ብዙ ነገር ያውቃል ። እሱ ገና ልጅነቱን ሳይጨርስ እስክንድር በሠፈራቸው ውስጥ ስመ ጥር ጎረምሳ
ነበር ። እንዲህ እንዳሁኑ ከመስከኑ በፊት እናቱ በእስክንድር ያላዩት አበሳ የለም ። ከለውጡ በፊት ጸብ አሽትቶ ነበር
የሚፈልገው ። እስር ቤትን ቤቱ አድርጎት ነበር ። አንዴ ጸበኞቹ በቡድን ሆነው ከደበደቡት በኋላ ሆዱ ላይ በጩቤ
ወግተውት ለጥቂት ነው ከምት የተረፈው ከለውጡ በኋላ ደግሞ በወቅቱ በተፈጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ሳቢያ
ያልቀመሰው፡ አበሳ የለም ። ችኩል ነበር ። ሰው አይገራውም ፣ ያየሁት አይለፈኝ የሚል ስሜት ያሸንፈዋል ።
የጀብደኝነት ስሜት ያጠቃዋል ። ትኩስ ኃያልነቱ፡ መንፈሱን ያቅበጠብጠዋል ። አሁን ግን በዕድሜም በብስለትም ሰክኖ
እንኳን ለራሰ ሌሎችንም ይመክራል ። ከአፍላነት ቅብጥብጥነት ጊዜው ይዞ የመጣውና አሁንም ያልተወው ነገር ቢኖር
የሲጋራ ሱስ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ በሳምሶን ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። በፀጉሩ ኪንኪነት እየለከፈው ከእስክንድር ጋር መቃለድ የጀመረው እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው።

አቤል እባክህ ተጫወት ይሄንን ተወው
አለ ሳምሶን እስክንድርን በመንቀፍ አይነት

“ እየሰማኋችሁ “ኮ ነው ? ” አለ አቤል በጨዋታቸው ውስጥ የቆየ ለመምሰል ጥርሱን በውሸት ብልጭ አደረገ።

ሐሳቡ በከፌል ወደ እነ ትእግስት ዘምቶ ነበረ። ፈተና ከጨረሰች በኋሳ ወዴት ትሔድ ይሆን ? አርፎ መተኛት ወይስ
ዙረት መውጣት ? እያለ ሲያሰላስል ነው የቆየው።ሁለተኛውን ጠርሙስ ቢራ ግማሽ አድርሶታል ። ከቻቻታው ጋር
ቢራው ሞቅ አድርጎት ውስጥ ውስጡን እየሰከረ መምጣቱ ይሰማው ነበር። የመጠጣት ልምድ ስለሌለው ጭንቅላቱ ቶሎ መረታት ጀምሯል ። ድፍረትም ተሰማው ማንንም ያለመፍራት ሃይነት ስሜት !

“ ለምን ሙዚቃውን አይቀይሩልንም ? ” ሲል ድምፁን አሰማ ። የእንግሊዝኛ ሙዚቃ ነበር አዳራሹን የሚነቀንቀው፤“ ማስቀየር እንችላለን ። የማን ክር ይደረግ ? ” አሉ እስክንድርና ሳምሶን በአንድ ድምፅ አቤል ከዝምታ ወደ
ተሳትፎ መምጣቱ ደስ አሰኝቶአቸው ነበር

•የ... የመልካሙ ተበጀ ክር ቢሆን
ይሻላል” አለ አቤል በተሰባበረ ድምፅ

እስክንድርም ሆነ ሳምሶን በፍጥነት የጠረጠሩት ነገር አልነበረም ። አሳላፊዋን ጠርተው ክሩ እንዲቀየር አዘዟዋት።

ባለቤትየዋ እሷ የመረጠችው ዘፈን ካልሆን እሺ አትልም ግን ልሞክርላችሁ ” አለች አሳላፊዋ ።

“ ንገሪያት ! ለምን እሺ አትልም ? ” አለና ሳምሶን አፈጠጠበት እሷ ዘፈኑን ልታዝዝ ስትሔድ አቤል ቀድሞ በልቡ
ያንጐራጉር ጀመር።

አረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናፋር ሆኛለሁ ፡ ዐይናፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት።

ልቡ ይህን እያዜመ፥ ጆሮው የሚሰማው ግን ሌላ ሙዚቃ ነበር ቢጠብቅ ፥ ቢጠብቅ የተለወጠ ነገር የለም ጥቂት
ቆይታ አሳላፊዋ ተመልሳ መጣች።

የመልካሙ ክር የለም ብላለች ባለቤትየዋ ! ”

አቤል በሽቆ “ ገደል ግቢ በያት ! ” ከማለቱ ዐይኑ እንባ አቀረረ ። የሰው ስሜት የማይጠበቅበት ዓለም ! ባለቡና ቤቶች ፍቅረኛውን የሚያስታውስበትን ዘፈን አይከፍቱለትም "መምህራን ትምህርት ምን ያህል እንዳስጠላው አይረዱለትም ። ወላጆቹ ልጃቸው ከድህነት ቀንበር እንዲያላቅቃቸው
ይመኛሉ እንጂ እሱ ያለበትን ችግር አያውቁለትም ። ጓደኞቹ ብቸኝነቱን አይፈቅዱለትም ።

“ እሷ ከሙዚቃዋ ጋር ገደል ትግባ ! አንቺ ቢራ ድግሚን ” አላት ሳምሶን በሽቆ ።

“ኧረ ይብቃን ! ሰዓቱም መሽቷል የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም ” አለ እንክንርድ ኪሱን እየዳበሰ ።

አምጪልን እባክሽ እንጠጣው ዛሬ ካምፓስ ማን ይገባል? ” አለ ሳምሶን በሞቅታ ስሜት ።

“በይ እንግዲያው አንቺንም እንጋብዝሽ የምትጠጪውን ነገር ይዘሽ ነይ ” አላትና እስክንድር ፡ ወደ ሳምሶን ዘወር ብሎ ፥ “ ከጠጣን አይቀር መሐላችን አንዲት አንስታይ ስትኖር ይሻላል” አለው ። ከሳምሶን ሁኔታ ገንዘብ እንደያዘ
ገምቶ ነበር "

እቤል ምንም አስተያየት አልሰጠም ። የያዘውን ቢራም አልጨረሰም ። ከዚያ በላይ መጠጣት አልፈለገም ። ሆኖም
አልተከላከለም ። ሕይወትን የመሰልቸት ዐይነት ነበር የሚሰማው ። ለምንም ነገር ያለመጨነቅ ። ስካር ማለት ይሄ ይሆን እንዴ?
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ትህትና ዛሬ ትንሽ ደሟ መለስ ብሎ ስትመለከት እናቷ ደስ አላት፡፡ ሰሞኑን ጥውልግልግ ብላ አስደንግጣት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሰውነቷን ተጣጥባ፣ ፊቷን ተቀባብታ፣ ምርጥ ለብሳ፣ ትህትናን መስላ ስታያት፤“ተመስገን” አለች በልቧ።
ያንን ምሽት እንደ አስታማሚ ልጅ ሳይሆን፤ እንደ ጥሩ አፍቃሪ ባል ፡ እቅፍ አድርጋት አደረች። ናፍቆቷን ሙሉውን ሌሊት አቅፋት በመተኛት ተወጣች፡፡
አሁን ሁሉንም ጣጣዋን ጨርሳለች፡፡ ዕቅዷን ልትፈጽም ሰዓቱ እየደረሰ ነው፡፡ በሌሊት ተነስታ ልብሷን ለባብሳ ጨረሰችና፣ ከፔርሙስ ትንሽ አጥሚት ቀድታ ካጠጣቻት በኋላ፤ “ወደ ቤት ልሂድ እማ!” ብላ ለመሄደ ተነሳች፡፡
ደግማ፤ ደጋግማ፤ ጉንጮቿን አገላብጣ ሳመቻትና፤ ወጣች፡፡ስትወጣ መንፈሷ ሁሉ ጠንካራ ነበር፡፡ ፍርሀት ጓዙን ጠቅልሎ ነው የሄደው፡፡ ቤት ደርሳ ያንን ትናንትና በፍቅር ስታሽሞነሙነው የዋለችውን የአባቷን ቅርስ ሸፋፍና፤ በቦርሳዋ ይዛ፤ ወደ መርካቶ ገሰገሰች፡፡
እዚያ እፍልሚያው ቦታ ስትደርስ ከታክሲ ወረደችና ራቅ ብላ ዓይኖቿን በሱቁ ላይ ተክላ ትጠባበቅ ጀመር፡፡
ልቧ ድው! ድው፤ ይላል፡፡ እልህና ሲቃ ይተናነቋታል፡፡ እንዷ ደቂቃ አቤት ርዝመቷ! አውሬው ወጥመዱ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ በንቃት መጠባበቋን ቀጠለች፡፡
አንዳንድ ሱቆች መከፈት ጀምረዋል፡፡ እምብዛም ሰው አይታይም፡፡ መርካቶ ትንሽ ሞቅ ሲል እንደዚያ እንደማይተራመስ ሁሉ አሁን ያለው ሁኔታ የሚያስገርም ነው፡፡
ነጠላዋን ተሸፋፍና፣ መንገደኛ መስላ፧ አንድ ጥግ ላይ ተቀመጠችና፤ ግዳይዋን መጠባበቁን ተያያዘችው፡፡ በእርግጥም ስለቸኮለች ነው መሰል በጣም ቀድማ ነበር የመጣችው፡፡
ገንዘብ በገፍ እየገባለት የመጣው ጎረምሳ በንግዱ ላይ ትኩረቱን እየጣለ ሄዶ ነበር፡፡ አበራን ወደዚያ ካባረረ በኋላ ትርፉን ለግሉ ማግበስበስ ጀምሯል።
ገንዘብ ሲቀምሱት ይጣፍጣል፡፡ በላይ በላዩ ያስመኛል። እህል ሲጠግቡት ያስገሳል፡፡ሲበዛም ያስጠላል፡፡ ገንዘብ የሚጠግብ ሆድ ግን የለም፡፡ ግሳትም የለው፡፡ በላይ በላዩ ጨምሩልኝ፣ ጨምሩልኝ፣ የሚያሰኝ፣ እየበሉት የሚርብ ነገር ቢኖር ገንዘብ ነው፡፡
እንደሻው የራሱ የሆነውን፤ እንደፈለገው የሚያዝበትን ገንዘብ ሲያገኝ፤ እንደጠላት ገንዘብ ማውደም ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ ሱቁን በማደራጀት ሀብታም መሆን ስለፈለገ፣ ቆጣቢና ትጉህ ሠራተኛ ሆኗል።
ዛሬ ከሌሎቹ ሁሉ ቀደም ብሎ ገበያ ሊሻማ መጣና የሱቁን በር ከፈተ፡፡ ሙሉ ጂንስ ለብሷል፡፡ ከላይ ጥቁር ክብ ባርኔጣ አድርጓል፡፡
አንገቱ ላይ አጠር ያለች ወፍራም ሻርፕ ጠምጥሞ ነበር፡፡
የሱቁን በር ከፍቶ ወደ ውስጥ መዝለቁን ስታይ ትህትና ተዘጋጀች፡፡ እሷም ጂንስ ሱሪ ነው የለበሰችው፡፡
ቀስ ብላ ቀኝ እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰደደችና፣ ማጥበቂያውን አላላች፡፡ ሽጉጡ ላግዳጁ ዝግጁ ሆነ፡፡ አሁንም ቀስ ብላ ጨበጠቸው፡፡ እጇ የተንቀጠቀጠ መሰላት፡፡
“አይዞሽ ትህትና ጠንከር በይ” አለች ለራሷ፡፡ “የመጨረሻው ሰዓት የድል ሰዓት ደርሷል፡፡ የመጨረሻውን የድል ሰዓት ባትወጪው አበቃልሽ!” አለችና ራሷን አደፋፈረች፡፡
ይህ የመጨረሻው መክሸፍ የሌለበት እርምጃ ነው፡፡ በእውነትም ጠንከር አለች፡፡ ልቧ በትክክል መምታት ጀመረ፡፡ ሰውነቷ መራራ ደም ሲረጭ ተሰማት፡፡ የቀድሞ ባህሪዋ ከውስጧ ጥርግርግ ብሎ ወጣና፤ አዲስ የቆራጥነት፣ የደፋርነትና፤ የጭካኔ ባህሪይ ተላበሰች፡፡
“አምላኬ በደሌን አንተ ይቅር በለኝ፡፡ ነፍሴን ተቀበላት!” አለችና የሽጉጡን ምላጭ እንደያዘች እየተንደረደረች ወደ ሱቁ ሩጫዋን ቀጠለች፡፡
ሱቁ በር ላይ ስትደርስ እንደሻው በሚያየው ነገር ተደናግጦ፣ ዐይኖቹ ተበልጥጠው፣ አፉ ተከፍቶ እንደቀረ ትንፋሽ ከማውጣቱ በፊት
ሽጉጡን ላጥ አድርጋ አወጣችው፡፡
ንግግር የለ፣ ግርግር የለ፣ ፋታ ሳትሰጠው በቀጥታ እርምጃውን ወሰደች፡፡
ዷ! ዷ! ዷ! ዷ! አምስት የቆጠረች መሰላት፡፡ አራንቱን ጥይቶች ካንጣጣችበት በኋላ፣ ተንገዳግዶ መውደቁን ስታረጋግጥ፧ ሽጉጡን
ወደራሷ አዙራ አፍዋ ውስጥ አስገባቸው፡፡
ሰው መሯሯጥ ጀመረ፡፡ ለሚተራመሰው ሰው ቦታ ሳትሰጥ፤
እርምጃዋን በራሷ ላይ ወሰደች፡፡ ምላጩን ሳበቸው፡፡ ዷ! ዷ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ የተባዘተ ጥጥ በመሰለው ደመና ተዥጐርጉሯል።
ጨረሯን የፈነጠቀችው ፀሐይ ያንን የደመና ቁልል እየናደችው ስትመጣ፤
ሰዓሊው በሸራ ላይ በብሩሹ የፈነጠቀው ንድፍ እየመሰለ ሄደ፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ደመናው ተገፈፈና፤ ጥርት ያለ ሰማይ ታየ፡፡
የሰው ልጅ የውስጥ ስሜቱ ሲጐዳ፣ ሲከፋው፣ ሲጨንቀው፤ ልክ ሰማዩ በደመና እንደሚያኮርፈው ሁሉ፤ ይህንን መጥፎ የውስጥ ስሜቱን በጨፈገገ ገጽታው ይገልጸዋል፡፡ በሆነ ባልሆነው ሆደ ባሻነት ያጠቃዋል፡፡
እነሆ ልቡ ከአምስት ዓመታት በላይ ከፍቅር ተገልሎ የቆየው ሻምበል ብሩክ ትህትናን ካገኘበት እለት ጀምሮ መንፈሱ ታድሶ!
የወደፊት የትዳር ህይወቱን በቅርብ ርቀት አሻግሮ መመልከት ሲጀምር፤ በእንጭጩ ተቀጨ፡፡
ትህትና ፍቅሯን ብቻ ሳይሆን፤ ያንን ደስተኛነቱን ጭምር በልቡ ውስጥ ገድላበት ነው የሄደችው፡፡
ድምጿን ለመስማት ይፈልጋል፣ ወዲያውኑ ደግሞ ከነመፈጠሯ እንዲረሳት ይመኛል፡፡ ትናፍቀዋለች፤ የሠራችው በደል ፊቱ ላይ ድቅን
ይልበታል፡፡ በቅናት ይቃጠላል፡፡ ወዲያውኑ ደግሞ ብሩኬ.... ብሩኬ....
ብሩኬ.... የሚለው ያ ለስላሳ ድምጿ፣ ያ ለስላሳ ሰውነቷ ያ ለስላሳ ባህሪዋ፤ ይታወሰዋል፡፡
በፊት የነበረችው ትህትና እንዴት የምትወደድ ልጅ ነበረች? ለምን ፈጣሪ አሳይቶ ነሳው? ምነው እሱ ለፍቅር አልታደለ? ሁል ጊዜ መጨነቅ?
“ምነው የዚያን ዕለት ባልተገናኘን ኖሮ” የሚል ሃሣብ መጣበት፡፡ ሆኖም በመገናኘታቸው አንድ መልካም ሥራ መስራቱ ያስደስተዋል፡፡
አጋር ያልነበራት እናቷን መርዳት መቻሉ እርካታን ይሰጠዋል።
ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም፡፡ እንዲሉ፣ እሷ ትበድለው እንጂ፤ እሱ ከበደል ይልቅ መልካም ሥራን የሠራ ተበዳይ መሆኑ ሲታወሰው፤ “ይሁን እስቲ ሁሉ ነገር ከፈጣሪ ይገኛል” ይልና
ይጽናናል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የሰሞኑ ሁኔታው የተለየ ነበር፡፡ ናፍቆቷ ነፍሱን ሊያወጣው ደርሷል፡፡
በውስጡ ፍቅርና ጥላቻ ነግሰውበታል፡፡ እንዳይጠላት ይወዳታል፣ እንዳይወዳት ደግሞ የሠራችው ሥራ...እንዳንድ ጊዜ ያ አለቃቀሷ፤ እዚያ እላዩ ላይ ተጠምጥማ እየተንሰቀሰቀች የተናገረችው ንግግር፣ ትዝ ይለውና፤ “ምን ነበረበት ይቅር ብላት ኖሮ? ግብዝ ነኝ” በማለት እራሱን
ይኮንናል፡፡ ወዲያው ደግሞ የሻክረና ጥርጣሬ የገባው ልብ ተመልሶ ልብ
ላይሆን፡፡ የነቃ ብርሌ ተመልሶ ዕቃ ላይሆን፣ አጉል ሙጥኝ አለማለቱን
ይወደውና..
እንኳንም በጊዜ አቋረጥን” የሚል ስሜት ይሰማዋል፡፡በጠዋቱ መ/ቤቱ እንደደረሰ ወደ ቢሮ ከመግባቱ በፊት ጫማውን
ሊያስጠርግ ሄደ፡፡ሰማዩን አየው፡፡ ከቤት ሲወጣ በደመና የተሸፈነ ነበር፡፡ አሁን
ግን ጥርት ብሏል፡፡ የሱ ስሜት ግን እንደሰማዩ አልጠራም፡፡ ፊቱ ጨፍግጓል፡፡ ጫማውን አስጠርጐ ወደ መሥሪያ ቤቱ ግቢ ሲዘልቅ......
“እንደምን አደርክ ሻምበል መልዕክት አለህ” አዳሪው ፖሊስ ከኪሱ ውስጥ ያስቀመጠውን ፖስታ አቀበለው፡፡
ሻምበል ፖስታውን ተቀብሎ ተመለከተው፡፡ የላኪው ሥም
የለበትም፡፡
የአደራ ደብዳቤነቱን እንጂ ከማን እንደተላከ አይገልጽም፡፡
“ማን ነው የሰጠህ?” ሲል ፖሊሱን ጠየቀው፡፡ ስሟን እንዳልነገረችው ገለፀለት፡፡ በቀጥታ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
የቢሮውን መስኮት ከፈተው፡፡ ንፁህ አየር ገባ፡፡ ከዚያም
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....አፓርትመንቷ ጋ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ እጥፍ ብሎ ከአንድ ትንሽ ሻይ ቤት ገባና በሩ አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሻይ አዘዘ፡፡ ጥንቃቄ ያስፈልጋል እርጋታ፡፡ ባሻገር የሚታየው የአፓርትመንቱ ቅጥር ግቢ አለቅጥ ጭር ብሏል፡፡ የወትሮው ግርግር ወጪና ገቢ አይታይም፡፡ ከአፓርትመንቱ ስር መኪናዎች በስርኣት ተደርድረው ቆመዋል፡፡ ለወትሮው ሲሯሯጠ የሚታዩ ሲጫወቱ የሚገኙ የአፓርትመንቱ ነዋሪዎች ልጆች በግቢው አይታዩም፡፡በር ላይ ብቻ እኛው የድሮው ሽማግሌ ዘበኛ አፈርማ ካፖርታቸውን ደርበው ከዘበኛዋ ቤት ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ያንጎላጃሉ፡፡

ይህ ነው ብሎ ምክንያት ሳይሰጠውም ፍርሃት ገባው፡፡ ፀጥታ ተራ ነገር አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሙሉ ፀጥታ አደጋ ከመድረሱ በፊት የሚያንዣብብ ማዘናጊያና አደጋው ከደረሰ በኋላ ድንጋጤን ደርቦ የሚንጠለጠል ግግርት ነው፡፡ ጥፍሩን መቆረጣጠም ጀመረ። ጭንቅላቱ ግራና ቀኝ ቆሞ ይሟገት ጀመር፡፡

ሰዓቱን ተመለከተ አሥራ ሁለት ከሃያ፡፡

ዝም ብዬ ነውኮ ይልቅ ብሎ ገብቼ እይቻት ብወጣ ይሻላል...ግን በአካባቢው የአውሬው አይን ቢኖርስ ስገባ ቢያየኝስ?ወዲያው ቢከቡኝስ ታዲያ እስከመቼ እዚህ ተቀምጨ እቆያለሁ?! ስልክ ደውዩ
ወንድሟን «ውጣ» ብለውስ ከአፓርትመንቱ እራቅ እንዲል ነግሬው
ባነጋግረውስ ምን ዋጋ አለው? ገብቼ ካላየኋትማ ለምንስ መጣሁ? ብገባ
ይሻላል... አዎ አይቻት ቶሉ እወጣለሁ… በአካባቢው ካሉ ግን ያለጥርጥር
እንደ ጅግራ ነው ክንፌን ብለው የሚጥሉኝ…ምን ዘዴ መፍጠር ይሻላል?

ጭንቅላቱን አፋጨው፡፡ አካባቢው እየጨለመ መጣ፡፡ የመንገድ
መብራቶች ቦግ ቦግ ቢሉም ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይበልጥ የሚደምቀውን
ጨለማ መታገል ማሸነፍ መግፈፍ እያቃታቸው መጠ፡፡ ናትናኤል ያለበትን
ክፍል ቃኘው፡፡ ትንሿ የሻይ ቤት ንጽህና የሌላት ናት፡፡ . በውስጧ የተሰበሰቡትም ሰዎች እሱው?እንዳጠለቀው በህይት የተጨማለቀ የጋራዥ ቱታ ቆሻሻ ልብስ የለበሱ ቀዝቅተኛ ኑሮ የሚገፉ፤ የሚጎትቱ እንደሆነ “ ያስታውቃሉ፡፡ ሰዓቱን ድጋሚ ተመለከተ፡፡ አስራ ሁለት ተኩል፡፡
በተቀመጠበት እንዳለ አሻግሮ የአፓርትመቱን መግቢያ በር ቃኘው፡፡ በሩቅ በድንግዝግዝ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ የበሩን አንድ ወገን መቃን ተደግፎ ቆሟል ሰውየወ:: ናትናኤል አትካር ተመለከተው፤ ካፖርት ለብሶ
አንገተዬውን ቀልብሶ የቆመውን ሰው ግን ሊለየው አልቻለም፡፡

'ብስራት ይሆን? መሆን አለበት። አሰበ፡፡
ተነስቶ ወደ አፓርትመንቱ መሄድ ግን ፈራ፡፡ ድጋሚ ዞር አለና እሱ ከተቀመጠበት ስፍራ ፈንጠር ብሎ ሁለት ክንዶቹን ጠረጴዛ ላይ ተክሎ
ጉንጭጮቹን በሁለት መዳፎቹ ደግፎ የተቀመጠ ጎረምሳ ላይ አተኮረ፡፡ አንድ
ዘዴ መጣለት:: ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ወጣቱ ተጠጋ፡፡

“ሰላም...ልቀመጥ?” አለ ከወጣቱ ጠረጴዛ ዙሪያ ከተደረደሩት ሦስት
ወንበሮች አንዱን ያዝ ኣድርጎ፡፡

ወጣቱ ጉንጮቹን ዘሁለት መዳፎቹ ውስጥ ሳያወጣ አይኑን ብቻ
አቅንቶ ተመለከተው::

“ተቀመጥ:: አለ ወጣቱ ግድ እንደሌለው ለማሳየት ትከሻውን ከፍ ዝቅ አድርጎ፡፡

“እንድ የምትሰራልኝ ስራ ነበር፡፡ በቂ ገንዘብ እከፍልሃለሁ፡፡” አለ ናትናኤል ከኪሱ ቦርሳወን አውጥቶ ሁለት የአስር ብር ኖቶች እየመዘዘ፡፡

ከፊት ለፊቱ የተቀመጠው ወጣት ቀያዮቹን ኖቶች ሲመለከት ጉንጮቹን ለቀቅ አደረገና ቀና አለ፡፡ የደረበው ረጅም አሮጌ ኮት አንገትዬው ነትቧል፤ ከውስጥ ሸሚዞ በሽቅጧል፡፡

“ትስማማለህ?”
“ምንድነው የምሰራልህ? የሚደበደብ ሰው ከሆነ እርሳው፡፡” አለ ወጣቱ አገጩ ላይ ችፍርግ ብሎ የበቀለውን የቆሽሽ ጺም እያከከ፡፡

“አይደለም፡፡” አለ ናትናኤል ወደፊት ጠጋ ብሎ “እየው ያ ፎቅ ይታይሃል? በሩ ላይ የቆመው ሰውዬ ይታይሃል?”
ወጣቱ በ'አዎንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡

“…ቀጥ ብለህ ወደ ሰውየው ትሄድና አጠገቡ ልትደርስ ጥቂት
እርምጃዎች ሲቀርህ ናትናኤል ይፈልግሃል። ተከተለኝ በለውና ድንገት
ፊትህን መልሰህ እየሮጥክ ከግቢው ወጥተህ ትመጣለህ፡፡”

“እናስ.. ከዛ በኋላስ?”
“በቃ::”
“እንዴት በቃ? እለ ወጣቱ ፊቱ ጥርጣሬ ለብሶ:: “እዛች ደርሼ ስለተመለስኩ ነው ይህን የምትሰጠኝ?” ወጣቱ፡፡ ዓይኖቹን በሁለቱ፡ የአስር ብር ኖቶች ላይ አነጣጠራቸው፡፡

“አዎ::"
“ምንም ሳልሰራ?”
“አዎ፡፡”
“አትቀልድ፡፡ ነገር አለው፡፡” አለ ጎረምሳው ወደ አንድ ወገን እየሳቀ፡፡

“ምንም ነገር የለውም፡፡”

ወጣቱ ኣይኖቸን አጥብቦ ናትናኤልን ሊያጠናው ሞከረ::
“ለምን እራስህ አትሄድም?"
“ትፈልጋለህ አትፈልግም?” አለ ናትናኤል ሁለቱን የአስር ብር ኖቶች ወደፊት እየገፋ::

ወጣቱ፡ ከራሱ ጋር ክርክር የገጠመ መሰለ፡፡ ናትናኤል ድንገት ትቶት ሲነሳ ፈጠን ብሎ አብሮት ተነሳ፡፡

“እሺ አምጣ፡፡ ፀጥ ብዬ ገብቼ ናትናኤል ያጠራሃል ብዬው ፀጥ ብዬ መወጣት ነው… እይደል?”

“እየሮጥክ ነው የምትወጣው፤ ፀጥ ብለህ አያደለም:: ልክ ከሰውየው እንደምትሸሽ ዓይነት እየሮጥክ፡፡” ናትናኤል ቆፍጠን አለ ሃያ ብር
የያዘውን ቀኝ እጁን ወደኋላ ሰብስቦ፡፡

“እሺ ኣምጣ…. እሮጣለሁ፡፡” አለ ወጣቱ እጁን ወደ ብሩ ዘርግቶ፡፡
“ደርስህ ስትመለስ…. መሮጥሀን ካየሁ በኋላ፡፡” ናትናኤል ፈርጠም አላ::

“እሺ ግማሹን ስጠኝ::”
“ደርሰህ ስትመለስ መሉው ያንተ ነው፡፡”
ወጣቱ ከሻይ ቤቷ ወጥቶ ወደ አፓርትመንቱ ሲያመራ ናትናኤል
ተከትሎት ወጣና የመኪና መንገዱን ተሻግሮ ከለላ ይዞ የሚሆነውን
ይከታተል ጀመር፡፡

የሚጠባበቁት ሰዎች ካሉ ወደ አፓርትመንቱ ሲገባ ሊይዘት ወጥመድ ያጠመዱ ካሉ። ወጥመዳቸው በወጣቱ ላይ እንደሚወነጨፍ እርግጠኛ ነበር፡፡

ወጣቱ የአፓርትመንቱን የአጥር ግቢ በር አልፎ ሲገባ ሽማግሌው ዘበኛ ከእንቅልፋቸው አልነቁም:: ወጣቱ እጆቹን የኮት ከሶቹ ውስጥ ከትቶ በእርጋታ አፓርትመንቱ በር ላይ ወደቆመው ሰው አመራ፡፡ ሰውዬውጋ ለመድረስ በግምት አአስር እርምጃዎች ሲቀሩት ድንገት ቆም አለና ናትናኤል እንዳዘዘው መልዕክቱን ተንፍሶ ፊቱን መልሶ ሮጥ ከማለቱ፡ ግራና ቀኝ ቆመው የነበሩ መኪናዎች በሮች እየተበረገዱ አራት ሰዎች ዱብ ዱብ አሉ፡፡
ናትናኤል አይኖቹን አፍጥጦ ቀረ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ወጣት
ለማምለጥ ቢሞክርም ከአጥር ግቢው በር ከመድረሱ በፊት ይዘው እፍስፍጥ
አድርገው ከአንደኛዋ መኪና ውስጥ ከተቱት፡፡

ለደቂቃዎች ናትናኤል ካለበት ሳይንቀሳቀስ ተጠባበቀ፡፡ ወዲያው
የመኪናዋ በር ተከፈተና በሁለት በኩል የወጣቱን ክንዶች የልጨመደዱ ሁለት
ሰዎችና ሌሎች ተጨጨማሪ ሶስት ሰዎች ወደ አፓርትመንቱ፡ ግቢ በር ያጣደፉ ጀመር፡፡ ከአፓርትመንቱ፡ ግቢ ሲወጡ ናትናኤል ወደ ኋላ አፈገፈገና ጥሩ ከለላ ይዞ በሩቁ በአይኑ ያስተውላቸው ጀመር::

አምስቱ ሰዎች ወጣቱን ከበው ወደ ሻይ ቤቷ ተጣደፉ፡፡ ከሻይ ቤቷ ደጃፍ፡ እንደደረሱ ሀለቱ ልጁን አስቀድመን ከተል ብለው ሲገቡ ሁለቱ፡፡ በሻይ ቤቷ ጓሮ ዞሩ፡፡ የተቀረው አምስተኛው እፊት ለፊት ጀርባውን ግድግዳው ላያ ለጥፎ ቀኝ እጁን ከኮቱ፡ ስር ብብቱ ስር ከቶ ቆመ::

ናትናኤል ሰውየው ከኮቱ ስር የጨበጠው ምን እንደሆነ ሲረዳ አብርሃም ታወሰው፡፡ ሻይ ቤቷ ውስጥ የቡት ሰዎች ከውስጥ ሲያጡት ወጥተው አካበቢውን ሊያስሱ እንደሚችሉ ሲረዳ ፈጠን ብሎ ከተደበቀበት ወጣና ሽቅብ በሩጫ ተፈተለኩ ታክሲ ተራ ደርሶ ለገሃር ብሎ ታክሲው ወንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሁሉ ሁለት ሦስቴ እየተገላመጠ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው የተከተለው ሰው ግን አልነበረም፡፡ ወደኋላ መመለስ
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ኪም ቾይ ላና ግሬይ ከዶክተር ሮበርትስ ቢሮ ስትወጣ እንዳየቻት ኮምፒውተሯ ላይ እየተየበች እንደሆነ ማስመሰል ጀመረች።

በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በኒሮ ሳይንስ ዲግሪዋን የያዘችው ኪም ቾይ የኒኪ ረዳት ሆና የትሬይን ቦታ ተክታ በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ ኪም በጣም ጎበዝ እና ቆንጆ ናት፡፡ ለስላሳ የእስያ ቆዳ፣ ጎላ ጎላ ያሉ ዓይኖች እና ጥቁር ሀር የመሰለ ፀጉር አላት፡፡

ወግ አጥባቂ በሆነ የቻይና ቤተሰብ ውስጥ ስላደገችም የቀድሞ ታዋቂ
የቴሌቪዥን ተዋናይዋን ስታያት በጣም ነው የደነገጠችው።

“ሚሲስ ግሬይ ሌላ የቀጠሮ ጊዜ ልያዝልሽ?” ብላም ኪም ልቧ በጣም
እየመታባት ጠየቀቻት፡፡ ከዚህ በፊት ከታዋቂ ሰው ጋር በአካል ተገናኝታ
ስለማታውቅ ነበር ልቧ መምታቱ። ይኼ የትርፍ ጊዜ ስራዋ ብዙ ታዋቂ
ሰዎችን በአካል እንድታይ አድርጓታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ላይብረሪ ውስጥ
ከመንቀዋለል እዚህ መዋሏ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው የሚፈጥርላት።

ላና ዞር ብላ ከዴስኩ ጀርባ የምትገኘውን ቀጭን ቆንጆ የእስያ ደም ያላትን ልጅም ስትመለከት ኃይለኛ ቅናት ጉሮሮዋን አነቃት፡፡ የራሷ የዶክተሯ አልበቃ ብሏት በየሳምንቱ ዶክተሯን ስታገኛት በእሷ ሕይወት እና ቁንጅና ማስቀናቷ አልበቃ አላት እና አሁን ደግሞ በጣም ቆንጆ ወጣትን ለቢሮዋ ቀጠረች።

'ይህን ነገር አውቃ ነው የምታደርገው?' ብላ ላና እያሰበች 'ለራሴ ያለኝን
ግምት ልታንኮታኩተው ትፈልጋለች ፤ ስለዚህም ይህንን የወደቀውን ለራሴ
ያለኝን ግምት ለማስተካከል ብዬ ወደ እሷ ስመላለስ እንግዲህ እሷ 300
ዶላሯን ላጥ ታደርጋለች ማለት ነው፡፡ ማን ይታመናል በዚህ ጊዜ ዶክተሯ ይህን አታደርግም አይባልም፡፡

ላናም ወደ ኪም ዴስክ ቀረበች እና ጎንበስ ብላ በተቆጣ ድምፅ “እኔ ሌላ ቀጠሮ መያዝ ብፈልግ እነግርሽ አልነበር እንዴ?” ብላ ጠየቀቻት፡፡

ኪምም በላና ምላሽ በጣም ደንግጣ ግራ ተጋባች፡፡ “ምናልባት የሐኪሟ ደምበኞች ሳይናገሩኝ ማናገር አይጠበቅብኝ ይሆን? ብላም አሰበች እኛ
“ይቅርታ ሚስስ ግሬይ እኔ ያሰብኩት...” አለቻት፡፡

ላናም በጣም ተናድዳ ወደ ዴስኩ ሄደችና ኪም ላይ አይኗን አጉረጥርጣ
“እኔ ቀጠሮ ስፈልግ እጠይቅሻለሁ። እንዲያውም ከዚህ በኋላ እዚህ አልመጣም” ብላት እየተቆናጠረች በሩን በሀይል ዘግታ ከእንግዳ መቀበያው
ክፍል ወጣች፡፡

የበሩን በሀይል መዘጋትን የሰማችው ኒኪም ከቢሮዋ ወጥታ የእንግዳ
መቀበያ ክፍሉ ውስጥ ስትገባ ረዳቷ ኪም ቾይን አይኗ እምባ አቅርሮ ተመለከተቻት፡፡

“ይቅርታ ዶክተር እኔ ላናን ሳላበሳጫት አልቀርም። ግን እኮ ቀጠሮ ልያዝልሽ ነው እንጂ ሌላ ምንም ነገር አላልኳትም፡፡”

“አይዞሽ እሷ ሁሌም እንደዚህ ናት” ብላ ኒኪ አፅናናቻት።

“ግን እኮ ሁለተኛ እዚህ አልመጣም ብላለች። ይቅርታ ሥራሽን አበላሽሁብሽ መሰለኝ” ብላ ኪም ቾይ ማልቀስ ጀመረች፡፡

“ኧረ አታልቅሺ፡፡ ታያለሽ በሚቀጥለው ሳምንት እራሷ ትመጣለች። አሁን ተረጋጊ፡ ሌላው ደግሞ ካርተር በርክሌይ እንደመጣ አስገቢው” አለቻት፡፡

ኒኪ ወደ ቢሮዋ ተመልሳ ወንበር ላይ ቁጭ ካለች በኋላ ባሏ በሕይወት
እያለ ያለማመዳትን የትንፋሽ ልምምድ ማድረግ ጀመረች።

አየር በኃይል ወደ ውስጥ ሳቢ የሚለው የባሏ ድምፅ በውስጧ ይሰማታል፡፡ ከዚያም ወረቀቶችሽን እየነጠልሽ እንደምታስቀምጪ ሁሉ
ሃሳቦችሽንም አንድ በአንድ በየተራ እየነጠልሽ አስቀምጪያቸው።

አየር በኃይል ወደ ውስጥ ሳበች እና የመጀመሪያውን ሃሳቧን ማሰብ ጀመረች ላናን ላግዛት አልቻልኩም፡፡ እሷ ሁሌም ወጣት ሴቶችን ባየች ቁጥር ንዴቷ እየጨመረ ነው የሚመጣው፡፡ ምናልባት ወደ ሌላ ቴራፒስት ልልካት ይገባል፡፡ ቴራፒስት ብቻ ሳይሆን ሳይካትሪስትም ሳያስፈልጋት አይቀርም፡፡ ግን እንዴት ልልካት እችላለሁ?'

ለሁለተኛ ጊዜ አየር በጣም ወደ ውስጥ ሳበች እና ስለእሷ ማሰብ ጀመረች፡፡ እኔ ጥሩ ቴራፒስትም ጥሩ ሚስትም አይደለሁም፡፡ ምክንያቱም ጥሩ ሚስት ብሆን ኖሮ ለባሌ አርግዤለት ልጅ እወልድለት ነበር፡፡ እሱም ሌላ ሰው ጋር ባልሄደ ነበር፡፡' ብላ አሰበች፡፡ በመቀጠልም “አሁን ስለራሴ
ሳይሆን ስለታካሚዎቼ ነው ማሰብ የሚገባኝ እያለች ሃሳቧን ልትጀምር
ስትል ቢሮዋ ግርግዳ ላይ ያለው የተረኛ ታካሚውን መምጣት የሚገልጸው
መብራት ብልጭ ድርግም ሲል ካርተር እንደመጣ አወቀች፡፡ ከወንበሯ
ተነስታም የቢሮዋን በር ከፈተች::

ኮሪደሩ ላይ ካርተር አንድ እግሩ በጀሶ ታስሮ እና በአንደኛው ወንበር መደገፊያም ላይም ሁለት ክራንቾቹን አስቀምጧል፡፡ የቢሮውን መከፈት እንዳየም በፍጥነት ሁለቱን ክራንቾቹን በግራና በቀኝ በኩል እየተደገፈ ወደ ቢሮው ውስጥ ገባ፡፡ ኒኪ በሩን ዘግታ ካርተር ወንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ ምን ሆነህ ነው?” ብላ አስባለት ጠየቀችው፡፡

ፊቱ ላይ ላቡ ችፍ ብሎ ጠብታዎች ግንባሩ ላይ ሠርቷል፡፡ ጥርሱም
እየተንቀጫቀጨ ነው።

“በጥይት መተውኝ ነው!” አላት እና በፍርሃት ዓይን ያያት ጀመር፡፡

“በእግዚአብሔር ስም ማን ነው የመታህ? መቼ ነው ይኼ ነገር የተከሰተው?”

“ምናልባት አላማርኳቸው ይሆናል፡፡ ግን እነዚያ ሁሌም ስነግርሽ የነበሩት የሜክሲኮ ወሮበሎች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም ቤቴ ገብተው የማስፈራሪያ ነገር መኝታ ቤቴ ውስጥ አስቀምጠው ነበር፡፡”

“ይህንን ደግሞ ፖሊሶች ጋር አመልክቼ ነበር፡፡ እነርሱ ግን እኔ ፈጥሬ የተናገርኩት ይመስል አላመኑኝም” አላት፡፡

ኒኪ ይህንን ስትሰማ ደነገጠች፡፡ ምክንያቱም እሷ ቤትም የሆነ ሰው
ከመኝታ ቤቷ ውስጥ የሚገኘውን የእሷና የባሏን የሠርግ ፎቶ እንደተወሰደባት ለፖሊሶች ብትነግርም እነርሱ ግን ችላ ያሉትን ነገር አስታወሰች፡፡

“እነርሱ እንደዚህ ቢያስቡም አያገባኝም፡፡ እናታቸውን... እኔ እውነታውን በደንብ ነው የማውቀው፡፡ በጥይት የተመታሁት ባለፈው ቅዳሜ ከክለብ ስወጣ ሌሊት ላይ ነው፡፡ በግምት ከሌሊቱ 7፡30 ላይ፡፡ ምናልባትም ይከታተሉን ስለነበር ያለሁበትን ቦታ አውቀውታል፡፡ እኔ ከክለቡ ወጥቼ መኪናዬን ፓርክ ያደረገው ሰው መኪናዬን እስኪያመጣልኝ ድረስ
እየጠበቅሁት ነበር፡፡ ይኼኔም አንድ መኪና ከአጠገቤ ቆመ እና ሁለት ሰዎች
ወጡ፡፡ አንደኛው ቅልጥሜ ላይ በጥይት ከመታኝ በኋላ መኪና ውስጥ
ገብተው መሬት ላይ ጥለውኝ ሄዱ፡፡”
ካርተር የደረሰበትን ነገር በፍጥነት ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ አሁንም
የደረሰበትን ነገር እያስታወሰ ጥርሱን ሲያንቀጫቅጭ ኒኪ ተመለከተችው፡፡

“በጥይት ሲመቱህ በአካባቢው ላይ ማንም አልነበረም?” ብላ ጠየቀችው፡፡
ካርተርም ጭንቅላቱን በአሉታ ወዝውዞ “ማንም አልነበረም ብቻዬን ነበርኩኝ፡ መኪናዬን ያቆመው ልጅም መኪናዬን ካቆመበት ቦታ ሊያመጣ ሄዶ ነበር፡፡ እሱ መኪናዬን ይዞ በመጣ ጊዜ እኔ መሬት ላይ ወድቄ ደሜን እያዘራሁ ከመሆኔም በላይ ራሴንም በመሳት ላይ ነበርኩኝ”

“መልካም” አለች ኒኪ፡፡ እንደሰው የነገራትን ነገር ማመን ይኖርባታል።
ምክንያቱም እሷን ለማሳመን ብሎ እግሩን በጀሶ እንደማያጅል ይገባታል፡፡
ምናልባት እንኳን የነገራት ነገር ውሽት ቢሆን እንኳን የራሱን ቅልጥም
በሽጉጥ መትቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ይህንን ለምን ያደርጋል? አትኩሮት
ፍለጋ ነው? ካርተር ደግሞ በዚህ መልኩ በሽታው ብሶበታል ብላ ኒኪ አታምንም፡፡ ምክንያቱም የባንክ ሥራውን በአግባቡ እየሰራ መሆኑን ታውቃለች

ስለሜክሲካኖቹ የወሮበሎች ቡድን በየጊዜው የሚያወራትን ነገር
ተጨባጭነት ባለው ምክንያት ሳያረጋግጥላት በጥይት ቅልጥሙን መቱት የሚለውን
👍2