አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

አቤል ወላጆቹን ትቶ ወደ ትዕግሥት በሐሳቡ መጓዝ ስለጀመረ ዐይኑን ቦዘዝ እንዳደረገ ዝም አለ ።

ምነው ? ”አሉ ዮናታን ፥ አንዳች ስሜቴን የሚጎዳ ነገር የተናገሩ መስሎአቸው ተደናግጠው ። ሐሳባቸው ዘሎ
ያረፈው እናቱ ወይም አባቱ ሞተዋል ከሚል ግምት ላይ ነበር ። ይህን ደግሞ ከአሁን በፊት አልነገራቸውም ፡ ግራ ተጋቡ።

“ ምንም አይደለም ”አላቸው ከሐሳቡ ባነነና ። እርስዎ ለእኔ ያለዎት ክብርና ፍቅር እየታሰበኝ ነው ።ለእኔ መድከምዎ አንሶ ወላጆቼን ሊረዱልኝ ሲያስቡ ... ”

“ ይህ ውለታ ሆኖ ካሳሰበህ ተሳስተሃል ” አሉት ዮናታን “ይህ ማንኛውም ዜጋ ሊያደርገው የሚገባ ነገርም ነው ። ማስተማር ለእኔ ግዴታ ሳይሆን ፥ የመንፈስ ክብርና ኩራት የሚሰጠኝ መስክ ነው ። እናም ጥሩ ተማሪዬን ጥሩ
ቦታ ወይም የሙያ ዘርፍ ላይ ለማየት እንጂ የማስተማር ግዴታዩን ለመወጣት ብቻ አይደለም የማስተምረው ። መረዳዳት ያስፈልጋል ። ደግሞም አጥብቀን አናስበውም እንጂ
ከመረዳዳት ውጪ የሆነ እንቅስቃሴ ምን ታገኛለህ ? ሁሉም የግል ጎጆ ቢቀልስም፡ የሕይወት እንቅስቃሴው የጋራ ነው። ማኅ
በረሰብ ከሌለ ግለሰብ የሚባል ነገር የለም " ምኑን ከምን አርጎ ሊንቀሳቀስ ? ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ ከግል ኑሮአችን በመነሳት የምናደርገው፥ ማኅበራዊ ግንኙነት ከመረዳዳት እንጻር
አጉልተን አናየውም እንጂ ኑሮአችን በመረዳዳት የተሳሰረ ነው።

ዮናታን ከልባቸው እየተመሰጡ ንግግራቸው እየጎላና እየረቀቁ ሲሔድ ፥ የአቤልን እንባ አደረቀው ። አፉን ከፍቶ
ነበር የሚያዳምጣቸው ።

“እሺ እንግዲህ 'እንዳሉት 'አሁን ያለኝ ምርጫ ትምህርቴን ማቋረጥ ነው ። እናም አቋርጠዋለሁ ” አለ የሜዝት
በሚመስል ጉልህ ድምፅ "

«« አዎ ! ቆራጥነት ያስፈልጋል አሉ ዮናታን
“ቆራጥ ካልሆንክና ውሳኔ መውሰድ ካልቻልክ ሕይወትህ የተመሰቃቀለ ይሆንብሃል ። አብዛኛውን ጊዜ ሕይወት የባለ ቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች የቆራጥነትና ወሳኝነት ትርጉም የሚገባህ ውጤቱን ካየህ በሁዋላ ነው ። አይዞህ
በአንተም ሆነ በወላጆችህ ላይ የሚደርስ ጊዜያዊ ችግር ቢኖር በጋራ እንወጣዋለን አንተም ነገ ትልቅ ሰው እንደምትሆን
አትጠራጠር ። ”

በፊት ያንዣብብ የነበረው የጭንቀት ደመና ከአቤል ፊት ሳይ እየጠፋ መሔዱን ሲመለከቱ ዮናታን ደስታ ተሰማቸው
ጥረታቸው ዋጋ እንዳገኘ እድርገው ገመቱ።

“ እሺ ፤ ለማቋረጥ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች ላሟላ ”ብሎ አቤል ከተቀመጠበት ተነሣ ።

“ ግሩም ! ” አሉ ዮናታን ሐሳቡን በመደግፍ ለማቋረጡ ተግባር የምረዳህ ነገር ካለ ብቅ ብለህ አማክረኝ ፡

አቤል እጅ ነሥቶ ሲወጣ በቆራጥነት ስሜት ግንባሩን አኮማትሮ ነበር ። በሐሳቡ የታየው ነገር ይህን “ የሥቃይ
ግቢ ” በአስቸኳይ ለቅቆ መውጣት ብቻ ነበር ። አንድ የሆነ ተቃራኒ ስሜት ጭንቅላቱን ቢከብደውም እስኪወጣ ድረስ ቀውል አልተከሠተለትም ።

ዮናታን ከደስታቸው ብዛት የሚይዙ የሚለቁትን አትተው ፊታቸው የተቀመጡትን ወረቀቶች ያለ ምንም ዓላማ ወዲያ ወዲህ ያገላብጡ ጀመር ፡ አቤል ሐሳባቸውን መቀበሉን የመጀመሪያው ደረጃ አድርገው ወሰዱት የዕቅዳቸው መጀመሪያ እንደ ተሳካ አድርገው በመገመት በጥረታቸው ረኩ ።

“ እሺ እንግዲህ ፡ ትምህርቱን አቋረጠ ። ከዚያ በኋላስ ምን መደረግ አለበት?” በማለት ዮናታን ፥ አቤልን ከተጠመደበት የዐይን ፍቅር ሕመም ለማዳን የሚቀጥለው ደረጃ ምን መሆን እንዳለበት ማሰብ ጀመሩ ። ይህን ሐሳብ በማውጣትና በማውረድ ላይ እንዳሉ በሩ ተከፈተ ።

ቀና ሲሉ አቤል ነው ፊቱ ከስሏል ዐይኖቹ ቀልተዋል በሆነ ስሜት ከራሱ ጋር የተጣላ ይመስላል ከኋላ እንደ ተባረረ ሰው እየቻኮለ ነበር በሩን የከፈተው።

ይቅርታ ያድርጉልኝ ለምን እንደ ዋሸሆዎት አላውቅም። ምናልባት ፈርቼዎት ይሆናል ትምህርቴን ማቋረጥ የለብኝም ብሞክርም አልችልም አላቸው ወደ ውስጥ ሳይገባ በሩ ላይ ቆሞ።

ዮናታን ግር አላቸው ምን ሰይጣን ነው በአንዴ ሐሳቡን ያስቀለበሰው ለጊዜው
የሚመልሱትም ሆነ የሚጠይቁት ነገር እልነበራቸውም።

አቤል ሐሳቡን የቀየረው በሩን ወጥቶ ገና ጥቂት እንኳን ሳይራመድ ነው ። ክፍል ውስጥ ሆኖ ከዮናታን ጋር ሲስማማ ከውስጡ ሲጫጫነውና ሲከብደው የነበረው ተቃራኒ ስሜት ገና ከመውጣ እውነት አሁን ትምህርትህን አቋርጠክ ይህን ትእግስት ያለችበትን ግቢ ልትለቅ ነው? እውነት ከትእግስት ጋር ሳትተያይ ውለህ ማደር የምትችል ይመስልሃል?
የዐይን ፍቅረኛህን ትተህ የት ልትደርስ? እያለ እንደ ጥላ ተከተለው ። አቋርጣለሁ እያለ ቀድሞ ሲፎክር የነበረው ሁሉ ባዶ ጩህት ሆኖ አገኘው ትእግሥትን ጥሎ
ወዴት ?

ለዮናታን ቃል መግባታ አሳዝነው ። እንዴት እንደሚያስተባብላቸወ በማሸበ ቆሞ ተጨነቀ። ሆኖም ዮናታን ያቋርጣል በሚል ተስፋ ልባቸውን ሞልተው እንዳይቀመጡ ቶሎ ተመልሶ ማስተባበል
ነበረበት እራሱን እየረገመ ነው የተመለሰው ምነው? ተስማምተን አልሔድክም እንዴ? ምን ነካህ? ” አሉት ዮናታን በተደናገጠ ስሜት።

አዎ በሃሳቦዎ ተስማምቼ ነበር የወጣሁት ነገር ግን አርቄ ሳስባት ፈተና ተፈትኜ ዕድሌን መሞከር አለብኝ ?” አላቸውና መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ሔደ።

«ስማኝ እንጂ አቤል ! ቆይ እስቲ ?” አሉት ዮናታን ከተቀመጡበት ተነስተው ሊከተሉት እየሞከሩ ዝም ብሏቸው ካጠገባቸው መጭ አለ።

ዮናታን በብስጭት ፈዘው ቀሩ ለሰም ሰው እኔ ምን አስጨነቀኝ ? ” የሚል ተፈታታኝ ሐሳብ መጣባቸው
ተስፋ የመቁረረጥ ስሜት ተስማቸው አኳኋኑ አናደዳቸው ግን ሁኔታን ባስታወሱ ጊዜ ልባቸው ሊጨክን አልቻለም ። እድራጎቱ አንድም የልጅነት አሊያም የፍቅር ቡሶት ነው ደመደሙ።

ቢሮእቸውን ቆልፈው ቀጥታ ወደ አቶ ቢልልኝ ቢሮ አመሩ አረማመዳቸው የሩጫ ያህል ነበር ። በመንገዳቸው
ላይ ሦስት ያህል የሚያውቋቸው ሰዎች ሰላምታ ሳይሰጡ ማለፋቸው አልታወቃቸውም።

ከከባቢልልኝ ቢሮ እንደ ደረሱ ሰላምታ እንኳን ሳይለዋወጡ አረእስተ ጉዳያቸውን አነሱ።

«ቢልልኝ የዚያን ልጅ ጉዳይ ሁላችሁም ቸል ማለታችሁ ነው ?

አቶ ቢልልኝ ! የዮናታን አርእስቱ ስለ አቤል ጉዳይ መሆኑ ለመገመት ጊዜ አልወሰደባቸውም።

የአቤልን ነገር ነው ?...ችላ ማለት አይደለም ኮ እኔ በበኩሌ የዐቅሜን እየመበከርኩ ነው። ሆኖም የልጁ ሁንታ
አስቸኳይ መፍትሔ የሚገኝለት አልሆነም።

"እንዴት ? ” አሉ ዮናታን ፡ ለመቀመጥ ወንበሩን እየሳቡ።

እስቸኳይ መፍትሔ ለማግኘት ልጁ ምቹ አይደለም ቢልልኝ ወደ ጉዳዩ ጠልቀው ሲገቡ ፊታቸው እየተለዋወጠ አዎ አቤል ግልጽ አይደለም ። አንዳንዱ ሰው ሰላፈቀራት ሴት ላገኘው ሰው ሁሉ በየደቂቃው ካላወራ አይሆንለትም ፤ ሌላ አርዕስት የለውም ። ሁሌ ሰው ለሰ
ፍቅር መፍትሔ የሚፈልግለት ይመስለዋል አንዳንዴ ደግሞ ለማንም ሳያዋይ ፍቅሩን ራሱ ዋጥ አርጎ ውስጥ ውስጡን
መቃጠል ይመርጣል ። ሌላ ሰው ለሱ ፍቅር ጤናማ አመለካከት ያለው አይመስለውም የአቤል በደረጃ ከመለየቱ በቀር ይሄኛውን ይመስላል ሁሉም አይነት ግን አስተዳደግና አካባቢን የተመረኮዘ መሠረት ይኖረዋል።

"ታዲያ አሁን የአቤል ነገር እንዴት ይሻላል ?” አሉ ዮናታን ፥ በተጨነቀና በተቻኮለ ስሜት ።

“ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ መፍትሔ ያገኛል ” አሉ ቢልልኝ፡ “ ጊዜ ! ጊዜ ይወስዳል ። የሥነ ልቡና ጥናት
ሥራ ዘዴና ትዕግሥት ይጠይቃል አቤል ፥ ሌላው ቀርቶ የግል የሕይወት ታሪኩን ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም
ስለዚህ ሥራችን
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....ሻምበል ብሩክ ይመስላታል፡፡
የሆነ ደስ የሚል መናፈሻ ውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ሲንሸራሸሩ ከቆዩ በኋላ፤ ወደ ኣንድ ጥላው ቀዝቀዝ ያለ፣ ንፁህ አየር ወደሚነፍስበት የወይን ዛፍ ሥር
ይመጡና ከሥሩ ካለው ለምለም ሣር ላይ ጋደም ይላሉ::

በዚህ ጊዜ እሷ እሱን ትራስ አድርጋ፣ ፀጥ ያለውን ኣካባቢ እየቃኙ የተፈጥሮ ውበትን ሲያደንቁ፤ የሁለቱም ዐይኖች ከፊት
ለፊታቸው በሚያዩዋት የጽጌዳ ቅርንጫፍ ላይ ባለችው እንቡጥ ጽጌረዳ አበባ ተማርኮ፤ ጽጌረዳዋን ሲመለከቱ ከቆዩ በኋላ፤ ስለዚያች ጽጌረዳ ለመናገር በአንድ ጊዜ “ እንዴ ” ብለው ይጀምራሉ፡፡

"ምን ልትል ነበር?” ትለዋለች እየሣቀች::
“አንቺስ ምን ልትይ ነበር?” ይላታል እሱም እየሳቀ::

“እንዴት ታምራለች ልል ነበር” ስትለው..
“እኔም እንደሱ ልል ነበር:: ከማማሯም በላይ ደግሞ ልክ የሁለታችንን ፍቅር ትመስላለች ልልሽ ነበር” ይልና ቁልቁል ወርዶ ከንፈሯን ይስማታል፡፡

“ማማሯስ እሺ የሁለታችንን ፍቅር እንዴት ነው የምትመስለው?” ትለዋለች:: ስለፍቅራቸው የበለጠ እንዲያወራላት
ጓጉታ::

“ያልፈነዳ እንቡጥ ጽጌረዳ በአበባነት ደረጃ ላይ ካለው ፍቅራችን ጋር ይመሳሰላል” ይላታል፡፡

“አበባው ፍሬ የሚሆነው መቼ ነው ብሩኬ?” አይን፤ ዐይኑን ሽቅብ እያየች ትጠይቀዋለች::
ወፎች የሚዘምሩ ይመስላታል፡፡ ንፋሱ ሽውው ይላል፡፡ዛፎች ይደንሣሉ፡፡ሰማዩ የጠራ ነው፡፡ሌላ ዓለም፡: ልዩ ዓለም.....
“የሠርጋችን ዕለት በዚያ በጫጉላ ቤት ውስጥ አሀዱ ብለን ትዳርን ስንቀድሰው፡፡ አይመስልሽም ትሁቲና? ቆይ እንዲያውም ይህችን ጽጌረዳ ስለፍቅራችን ገፀበረከት ላቅርብልሽ” ይልና ብድግ ብሎ ያቺን የምታምር እንቡጥ ጽጌረዳ አበባ ቀጥፎ ያመጣና
ይሰጣታል::

“በሠርጋችን ዕለት? .... በጫጉላ ቤት? .... አሀዱ ብለን?... ስንቀድሰው?
ምን ዐይነት ጣጣ ነው? የሆነውን ሁሉ
ብነግረውስ? የጫጉላ ቤቱ ዕቅዳችን መፍረሱን፣ እንደሻው አስገድዶ ክብረ ንፅህናዬን መድፈሩን፤ ብገልጽለትስ?
አያምነኝ ይሆን?
በቃሽኝ አታላይ ነሽ ይለኝ ይሆን? ልንገረው? እያለቀስኩ ልግለጽለት
ወይንስ ልተወው? ወይኔ አምላኬ ምን ጣጣ ውስጥ ከተትከኝ? ወይኔ
ብሩኬ በዚህ ምክንያት እንለያይ ይሆን?...” በስጋት ተዋጠች፡፡
ይህንን ፍርሃቷን በልቧ አምቃ በጭንቀት እንደተዋጠች፤
ሻምበል ብሩክ ቀጥፎ የሰጣትን ጽጌረዳ እንባ በጋረዳቸው ዐይኖቿ ትኩር ብላ መመልከቷን ቀጠለች::
ያቺ የምታምር ጽጌረዳ፣ ያንን የመሰለ ማራኪ ውበት የተላበሰች ለምለም እንቡጥ አባባ፣ ቀስ በቀስ እየጠወለገች፣
እየጠወለገች፣እየደረቀች ሄደችና፣ በእጇ ላይ እንዳለች እርር ብላ ተንኮሻኩሻ ደቀቀች::
በዚህ ጊዜ ትህትና በድንጋጤ ተወራጭታ ከገባችበት አስደንጋጭ የህልም ዓለም ስትወጣ፤ ሰውነቷ ሁሉ በላብ ተዘፍቆ
መንቀጥቀጥ ጀመረች::
ቀስ ብላ ያየችውን ህልም ስትመረምር ፍርሃት ነገሰባትና፤ ሆድ ብሷት “በቃ ልክ ነው:: ህልሜ ትክክል ነው:: ብሩኬን አጣሁት ማለት ነው፡፡ ወይኔ ወይኔ” እያለች ስቅስቅ ብላ ዐይኖቿ
እስከሚያብጡ ድረስ አለቀሰች፡፡
ሻምበል ብሩክ ልጃገረድ ያለመህኗን ሲያውቅ፤ ውሸታም ባለጌ አድርጐ እንደሚገምታት፤ በቃሽኝ እንደሚላት፤ ጠርጥራ ልቧ በሀዘን ተሰበረ::
በዚህ መጥፎ ስሜት ውስጥ ገብታ በሃሣብ ስትዋዥቅ ከቆየች በኋላ፤ ሻምበል ብሩክን የራሷ አድርጋ ለማስቀረት የሚያስችላትን ዘዴ ማውጠንጠን ጀመረች፡፡ በመጨረሻም የሆነ ሃሣብ መጣላት::
“ማን ያውቃል? ዛሬም እንደበፊቱ ሁሉ ልጃገረድ የመሆኔ ምልክቱ ሙሉ ለሙሉ ላይጠፋ ይችላልና የማያስታውቅ ከሆነ ለምን አንድ ሙከራ አላደርግም?” ስትል አሰበች። በመጨረሻም ከሻምበል
ብሩክ ጋር ከመገናኘቷ በፊት ራሷን በዶክተር ልትፈትሽ ወሰነች::
አንዴ ላይታፈስ የፈሰሰ ውሃ፤ በድጋሚ የሚገኝ መስሏት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ቀጠሮ ያዘች::
ከመቸኮሏ የተነሳ አርብ ዕለት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር በያዘችው ቀጠሮ መሠረት
ወደ ቤት እንደደረሱ ተያይዘው ወደ ቤት እንደደረሱ ሠራተኛዋን አገላብጣ ሣመቻት::
ምነው ፍቅርሽ በዛ?” አለቻት ሠራተኛዋ በልቧ፡፡ ትህትና ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ካሳለፈችው ጊዜ ሁሉ ለየት ያለው የዛሬው ነው:: ለዛሬው ግንኙነታቸው የራሷ ምክንያት ስለአላት፤ የሚሆነውን ቶሎ ለማወቅ፤ ቶሎ ወደ አልጋ ለመሄድ
ቸኮለች፡፡
ቢሆንም ግን ይህንን መቸኮሏን
ዶክተር እንዲያውቅባት አላደረገችም::
እንደተለመደው ሁሉ ዶክተር እራሱን ሊፈትሽ፤ እሷም የልጃገረድነት ሚስጥሯን ልትፈትሽ፤ ተፈላልገውና፤ ተግባብተው፤
ተያይዘው፤ ወደ መኝታ ክፍል ገቡ::
ዶክተር በዚያ ረገድ በራሱ ላይ እምነት እያጣ ስለሄደ በውስጡ የነበረው ጉጉት ቀዝቅዟል፡፡ ሆኖም እንደተለመደው የማይጠገብ ውብ የልጅነት ገላዋ የሚያመነጨውን ሙቀት ለመቋደስ ያህል ብቻ መፍጨርጨሩን ቀጠለ፡፡
......
እሷ ደግሞ በሥጋት እንደተዋጠች ከአሁን አሁን
“ምን ዐይነት ሁኔታ ይፈጠር ይሆን? ልጃገረድ በመሆንና ባለመሆን መካከል ያለው ልዩነት ምን ይመስል ይሆን? በማለት ቁርጧን ለማወቅ ልቧ ትር፤
ትር፤ እያለች የሚያደርገውን
እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በንቃት ትከታተላለች፡፡

ቀስ በቀስ አካሉ ከአካሏ ጋር እየተሟሟቀ ፤እየተዋሀደ፣ እየተግባባ፤ መጣና የሷ ገላ እሾህ አመኬላውን አስወግዶ ሊያስተናግደው ዝግጁ መሆኑን ሳያውቅ፣ በሀይል ሲታገላት፤ባልጠበቀው መንገድ ተቀብሎ ያስተናግደው ጀመር፡፡
ትህትና ያንን ሁኔታ ስትመለከት ቅስሟ ስብር ብሎ፤ በሃሣብ ጭልጥ ብላ ሄዳ ሌላ ዓለም ውስጥ ገባች፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ደግሞ በዚያ ባጋጠመው አዲስ ሁኔታ ተደንቆ ጉድ ነው!” አለና ለጊዜው ከገባበት ስሜታዊ ረመጥ ወጥቶ እፎይታ ለማግኘት ያህል ጉልበቱን
እንደድሮው እንደአፍላ የጉርምስና ዘመኑ አድርጐ መጫወቱን ቀጠለ፡፡
በቀላሉ ሊበርድ አልቻለም፡፡ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዶ ተጫወተ፡፡
ይህቺ ሰው ጨው አላት መሰለኝ” እያለ በሚያደርገው ነገር ሁሉ እየተደነቀ ነበር፡፡
ነበር፡፡
እሱ እንደዚያ በደስታ ሲቃ ተውጦ ሲቦርቅ ፣እሷ ግን በድን አካሏን ከሥሩ አጋድማ ዐይኖቿ በከፈቱት ቧንቧዎች እየታጠበች
ዶክተር የልቡ ሲደርስ ቀስ በቀስ ከዚያ ከሚናጥበት የስሜት ማዕበል ወጥቶ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ ያስበው ጀመር፡፡
በዚህ ጊዜ የሆነ የቅናት ስሜት ተለኮሰበትና ገላው በንዴት እየተቃጠለ ይጨስ ጀመር፡፡በወሲብ በኩል እርካታን ቢያገኝም፣ ልቡ በዚያው ልክ የምሬት
ደም ሲረጭ ተሰማው::
የልቡ ከደረሰ በኋላ ንጽህናዋን የወሰደው እሱ ባለመሆኑ፤የሆነ የቅናትና የዝቅተኝነት ስሜት አእምሮውን ሰርስሮት ገባ፡፡
መጀመሪያ ካገኛት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያደረገው ድካሙ ሁሉ ከንቱ መቅረቱን ሲያስታውሰው፤ ያንን ውብ ገላዋን ለሌላ ሰው አሳልፋ መስጠቷን ሲያሰላስለው፣ በንዴት እያረረ፣ ጨጓራው ተቀቅሎ እንደገነተረ ሥጋ ሲገነትር ተሰማው:: የተናቀ የተተፋ መሰለው፡፡
የዚያን ጊዜ የልቡን በልቡ አድርጐ.....
“ትህትና እንደዚህ የማደርገው እኮ ስለምጠብቅሽ ነው” ያላት ቀን
“ይገባኛል ዶክተር” ነበር ያለችው:: ግን ዋሸችው:: እሱ ሲጠብቃት እሷ ከዳችው።

እሱ ተንከባክቦ ያቆየውን ውድ ነገር ለሌላ አስረክባቸው መጣች:: ዶክተር ሁሉም ነገር እንደሰንሰለት ተያይዞ በሃሣቡ
መጣበት:: ደካማነቱ የራሱ ሆኖ ሳለ ራሷን አሳልፋ የሰጠችውን ልጅ ሞራሏን
ሊነካው ፈለገ፡፡የሱ ሞራል ተነክቷል፤ ቅስሙ ተሰብሯልና፤ አጥንት በሌለው ምላሱ አጥንት የሚሰብር ንግግር ሊናገራት ፈልጎ ... ጠጋ አላትና
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

......ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀጭን አጭር ሰው መንገዱን ተሻግሮ ወደ ቢጫዋ ቁርስ ቤት ሲጣደፍ ተመለከተ፡፡ኮቱን ትከሻው ላይ እንጠልጥሎታል፡፡ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ካለው የላይቤርያ ኤምባሲ እስከ ቁርስ ቤቷ ለመድረስ ብዙ ባያስኬድም ወደፊት ደፋ
ደፋ የሚለው ሰው ረዥም መንገድ የተጓዘ ይመስላል፡፡ ሰውየው ከቁርስ ቤቷ እንደደረስ ወደውስጥ ከመግባቱ በፊት ቆም ብሎ ዙሪያውን ተገላምጦ
ተመለከተ፡፡ ወዲያው ዘው ብሎ ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ሰውየው ወደ ውስጥ ሲገባ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ከጥግ ወዳለ
የህዝብ ስልክ አመራና አንብቦ በጭንቅላቱ የያዘውን የቢጫዋን ቁርስ ቤት ቁጥር ደወለ፡፡

“አ.ቤት::” አለ የሴት ወይዘሮ ድምፅ፡፡
ያ ክምር ጡታቸው መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት ናትናኤል፡፡

“እንደምን ዋሉ...ደህና ኖት?” ሴትየዋ መልስ ከመስጠታቸው በፊት አጣደፋቸው “ገብረየሱስ ነኝ..እንደምን ኖት?!” አለ እንደሚያውቃቸው ተዝናንቶ፡፡ “እባኮት ስዩም ጋር ቀጠሮ ነበረን እርሶ ቤት
ያገናኙኝ…ስዩም ይበሉልኝ…እቤትዎ ውስጥ ነው ያለው…ደህና ኖት ግን
እርስዎ..በሉ ስዩምን ያገናኙኝ..” በላይ ቀላይ አጣደፋቸው፡፡

“የማን ስዩምን? አሉ ሴትየዋ ፋታ ሲያገኙ፡፡

“እንዴ!.. ረሱን እንዴ? እቤትዎ በልተን ጠጥተን? አይ የርሶ ነገር! ይብሉ ስዩም ይበሉልኝ፡፡ አይ የርሶ ነገር! ደንበኞቾንም ይረሱ ጀመር?” አጣደፋቸው፡፡

“ኧረ ንሽቴ! የምን መርሳት አመጣህብኝ::!” አሉ ሴትየዋ ድፍረት
አሰባስበው:: “ደሞ እናንተን ደንበኞቼን ልርሳ? ሄ! ሄ! ሄ! ገና ሳላረጅ ምነው
ባክህ! ደህና ነህ ግን አንተ ጠፋህሳ?”
ሴትየዋ ሲጣሩ “ስዩም የሚባል! ስልክ?” ሲሉ በስልኩ ውስጥ ተሰማው፡፡ ነፍሱ መለስ አለችለት:: ስልኩን ጆሮው ላይ እንዳይጠራቅምበት ሰግቶ ነበር፡፡

“ሀሎ… ” አለው ያው ነፍናፋ ድምፅ፡፡
“ስዩም? ” ናትናኤል ቆፍጠን ባለ ድምፅ ጠየቀ፡፡
“ነኝ.የት…?”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ::ቁርስ ቤቷ ውስጥ ይጠብቀኛል ብለህ አስበህ
ከሆነ ሞኝ ነህ፡፡ መልዕክቱን ብቻ እሰጥሀለሁ፡፡ ትስማማለህ?” አለ ናትናኤል ጥድፊያ በተቀላቀለው ድምፅ፡፡

“አዎ አዎ፡: ቀጥል፡፡”

“ጥሩ…. እንዳልኩህ ካልቨርት ለአንተ የማደርስለትን መልዕክትና፡ በርከት ያለ ገንዘብ ሰጥቶኛል፡፡ መልእክቱን ከመስጠቴ በፊት ግን አንተነትህን ማረጋገጥ አለብኝ፡፡”

“ነኝ..ነኝ ግድ የለም:: ስዩም ነኝ፡፡”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ! ለምጠይቅህ ጥያቄ ብቻ ኣጫጭር መልስ ነው የምፈልገው፡፡” አለ ናትናኤል ሰውየውን ይበልጥ ለማደናገር ቱግ ብሎ:: “ካልቨርት በየትኛው ጣቱ ላይ ነው ቀለበት የሚያደርገው?” ያዘጋጃትን ማስመሰያ ጥያቄ አስቀደሙ:: በአውራጣቱ፡ ላያ ቢለውም ግድ አልነበ
ረውም፡፡ ነገር ግን ወደ ዋናዎቹ ጥያቄዎች ከመግባቱ በፊት የሰውየውን
ጭንቅላት ማሟሸት አለበት፡፡
“ቀለበት አያደርግም ካልቨርት::” አለ ሰውየው በሚያስደንቅ ፍጥነት::

“ጥሩ፡፡ አሁንም ፈጣን መልስ እፈልጋለሁ:: ተጠንቀቅ ብትሳሳት
ወይ ብትጠራጠር፡፡ ብትዘገይ ስልኩን ዘግቼ ነው የምሄደው:: የምፈልገው
ትክክለኛውን ስዩም ነው:: የያዝኩትን በርካታ ገንዘብ ላልሆነ ሰው ማስታቀፍ፣
አልፈልግም:: አድምጥ:: የካዛንቺሷ ሴት ስም ማነው?” ናትናኤል በጭንቀት
ትንፋሹን ያዘ፡፡

“የምሥራች ይልማ!” አለ ሰውየው ሌላ ሰው እንዳይቀድመው የፈራ ይመስል በጥድፊያ፡፡
“የስልክ ቁጥሯስ?” አከታትሉ ጠየቀው፡፡
“ትዝ አይለኝም::?”
“እንግዳው ስዩም አያደለህም፡፡ደህና ዋል።”
“ቆይ! ቆይ አለ ነፍናፋው ድምፅ በጭንቀት ተወጥሮ፡፡ቆይ
ስልኩን እንዳትዘጋው። ”
ማስታወሻዬን ልይ… ቆይ አንዴ. እ…ኤ… አዎ ...ይኸው..”

ናትናኤል ስልኩን በጆርውና በትከሻው መሃል ይዞ ሰውየው የነገረውን የስልክ ቁጥር በወረቀት ላይ ይጽፍ ጀመር፡፡ ድንገት ላይ ከሜክሲኮ አደባባይ አቅጣጫ ኣንድ ነጭ ፎርድ መኪና በከፍተኛ ፍጥነት መጥታ ከቢጫዋ ቁርስ ቤት በር ላይ ቆመች:: ወዲያው ከውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች በሮቻቸውን እየከፈቱ፡ ወረዱ። ሁለቱም የመኪናዋን በሮች
ለመቆለፍ አንኳን ሳይሞክሩ. እየተጣደፉ ወደ ቁርስ ቤቷ አመሩ። ጥቋቁር ኮትና ሱሪ ለብስው የኮታቸውን ቁልፎች ቆልፈዋቸዋል። ናትናኤል ፈሊጡ ገባው:: ቶሎ ዘዴ መቀየስ እንዳለበት ተረዳ፡፡

“ጥሩ፡፡” አለ ድምፁን ሳይቀይር ረጋ ባለ መንፈስ፡፡ “ስዩም ያለሁት ናዝሬት ነው:: ነገ ከጠዋቱ ልክ በአራት ሰዓት ናዝሬት ከቴሌመኒኬሽን ሕንፃ ፊት ለፊት 'ግሪር ሆቴል' የሚል ቤት አለ እዛ እጠብቅሃለሁ:: ነጭ ኮትና ጥቁር መነጸር አደርጋለሁ፡፡ ፒፓ አጨሳለሁ፡፡ ኣደራ ያወራነውን በምሥጢር ያዘው ናትናኤል ስልኩን ዘግቶ እራቅ ብሎ ይጠባበቅ ጀመር፡፡

ወንዲያው ከቢጫዋ ቁርስ ቤት የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ሁለቱን
ስዎች አስከትሎ ብቅ አለ፡፡ ሦስቱ" ተከታትለው ወደ መኪናዋ ገቡ፡፡
መኪናዋ ግን አልተንቀሳቀሰችም፡፡ ከኋላ የተቀመጠው የላይቤርያው ኤምባሲ
ሾፌር እጆቹን እያወናጨፈ ሲያወራ ሁለቱ ሰዎች ፊታቸውን ወደኋላ መልሰው ሲያዳምጡት ቆዩ፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች ሰኋላ ስዩም ከመኪናዋ ዕርዶ ለብቻው መንገዱን ተሻግሮ ወደ መሥሪያ ቤቱ አቅጣጫ ሲያመራ ነጯ ፎርድ ተጠምዝዛ ሽቅብ በሜክስኮ አደባባይ አቅጣጫ ተፈተለከች፡፡
ፈገግ አለ ናትናኤል፡፡ “ነገ ናዝሬት እንገናኝ” አለ ከራሱ ጋር፡፡ ወዲያው ኪሱ ከቷት የነበረችውን ወረቀት አወጥቶ አነበባት፡፡ ካዛንቺስ የምሥራች ይልማ
የፈለገውን ይኸን ነበር፡፡ስሟንና የስልክ ቁጥሯን፡፡የፈለገውን ሁሉ አግኝቷል።

የላይቤርያው ሾፌር ያለጥርጥር ለበላይ አለቆቹ አስታውቋል፤ ለአብርሃም አለቆች:: ቢሆንም ለጊዜው አትኩሮታቸው ናዝሬት ከተማ ውስጥ ስለሚሆን እዛው ነው የሚሄዱት፡፡ የአውሬውም ጆሮ በአካባቢው ካለ የእውሬውም አይን ናዝሬት ላይ ነው የሚያፈጥ:: ሁሉም ናዝሬት ነው የሚንጋጉት፡፡ አሁን ነው ጊዜው:: አሁን ነው መነቃነቅ ያለባት፡፡

ሃሎ። “ የህዝብ ስልኩ ውስጥ ሳንቲም ጨምሮ ደወለ፡፡
ሃ..ሎው” ሙልቅቅ ያለ የሴት ድምፅ ጆሮው ውስጥ ዥረር አለበት፡፡

“እ... የምሥራች ይልማ ሆቴል ነው. እባኮት…”
“አዎ ነው፡፡ ማንን ላቅርብሎት?” ሙልቅቅቅ አለችበት፡፡

“እንደምንዋልሽ የኔ እመቤት፡፡ እ...ከባህር ዳር ነበር የመጣሁት፡፡
ባልንጀራዬ መስተንግዷችሁን አድንቆ እናንተጋ እንዳርፍ የስልክ ቁጥራችሁን
ሰጥቶኝ ነበር፡፡ እ... ለባለቤቲቱም ደብዳቤ ይዤ ነበር፡፡ ግን ቤታችሁን
ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ባክሽ..
“እይውሎት…. " አቋረጠችው:: “ሞቢል ነዳጅ ማደያው አለ አይደል ካዛንቺስ?” የልጅቷ ድምፅ ሲወርድ እንደ ተልባ ነው፡፡
“ያውቁታል...? በቃ በሱጋ ቀጥታ ሲሄዱ እንደዚህ በስተቀኝ ወደ ላይ ወደግራ የሚታጠፍ መንገድ አለ.. አ..ዎ! እሱን ትተው በስተቀኝ ትንሽ እንደሄዱ በትልቁ
'የምሥራች ሆቴል' የሚል ማስታወቂያ አለ፡፡ አጥሩ ሮዝ ቀለም የተቀባ..”
እቅጣጫውን ከነምልክቱ ጥርት አድርጋ ነገረችው::

ናትናኤል ወዲያውነ ታክሲ ተሳፍሮ ወደ ካዛንቺስ በረረ፡፡ እዚያ ሲደርስ ምን እንደሚያደርግ ግን ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም:: በሁለት ታክሲ አሳብሮ የምሥራች ሆቴልን ደጃፍ አለፍ እንዳለ የታክሲውን ሂሣብ ከፍሎ ወረደና ጋቢውን ትከሻው ላይ ቆልሎ ዘውዲቱ የገባችለትን አዲሱን ምርኩዙን እያስቀደመ እሱ እየተክተለ መንገድ ባሻገር ያለውን ሆቴል
እያጠና አለፈ፡፡ እራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ ከአንድ የአውቶቡስ ፌርማታ ከለላ
አድርጎ ተቀምጦ
👍2
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ከዘጠኝ ዓመታት በፊት

ዴሪክ ዊልያምስ ሙሉ መስታወት በሆነው የቢሮ በር አሻግሮ ከእንግዳ
ማረፊያ ክፍል ውስጥ የተቀመጡትን ባል እና ሚስቶችን እየተመለከታቸው
ነው፡፡

ቢሮው ትልቅ እና ውድ በሆኑ እቃዎች የተሞላ ነው፡፡ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሉም ቢሆን ኮርኒሱ ከፍ ብሎ የተሰራ ከመሆኑም በላይ በጥሩ የዲዛይን ባለሙያ እና በደንብ ባጌጡ ሶፋዎች የተሞላ ነው፡፡
ጠረጴዛዎቹ ላይም ላይፍ ስታይል መፅሄቶች ሞልተውታል፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገችው ደግሞ የዴሪክ ዊልያምስ አዲሱ ሚስቱ ሎርያን ነች፡፡

“ማሬ ገንዘብ ለማግኘት እኮ ገንዘብ ማውጣት ይኖርብናል” የሚለው
ምክርዋ ዋነኛው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ “ሰዎችን መጀመሪያ ባገኘሃቸው
ጊዜ ነው ልታስደስታቸው የምትችለው ሌላ እድል የለህም” የሚለው ነው።
ዴሪክ የሎርያንን ምክር ተግባራዊ ያደርግ የነበረው ስለምወዳት ነው ብሎ
ያስባል ወይንም ደግሞ ምርጥ ጡቶችና ያበደ መቀመጫ ስላላት እና ሌሎች
ሰዎችን ትታ እሱን በመምረጥዋ ሊሆን ይችላል ብሎ አንዳንዴ ይፈላሰፋል።
ለማንኛውም ይሄ “ገንዘብ ለማግኘት እኮ ገንዘብ ማውጣት ይኖርብናል የሚለው ፍልስፍና ሲሰራ ተመልክቷል። ምክንያቱም አዲሱ ቢሮው ከተሰራ
በኋላ የእሱ ተፈላጊነት በስልሳ ፐርሰንት ጨምሯል። ገቢውም ቢሆን በሶስት
እጥፍ ለማደግ ችሏል፡፡ ምናልባትም ይሄ
ሊሆን የቻለው ሰዎች ለሚያገኙት
አገልግሎት ብዙ ገንዘብ ሲያወጡ ነገሩ እንደሚከናወንላቸው ስለሚያምኑ ሊሆን ይችላል፡፡ ማንም ሰው ደግሞ እርካሽ የሆነ አገልግሎት አይፈልግም ብላ ሚስቱ የምትነግረው ነገር ትክክል ስለሆነም ሊሆን ይችላል፡፡

የዛሬዎቹ ጥንዶች ግን ለዴሪክ አገልግሎት የከፈሉት ክፍያ ትንሽ
ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊትም ለሰራላቸው የተለያዩ ምርመራዎች
ያልከፈሉት ብዙ ዕዳዎች አለባቸው፡፡ ለምን እንደሆነ አያውቀውም ብቻ
ለእነርሱ ከልብ የመነጨ የሃዘኔታ ስሜት ይሰማዋል። ለምንስ ዛሬ ሊያገኙት
እንደመጡ ሲያስብ ደግሞ ልቡን ፍርሃት ፍርሃት ብሎታል። እነሱ ግን እጅ
ለእጅ ተያይዘው እና ጣቶቻቸውን አቆላልፈው ጎን ለጎን ተቀምጠዋል።

ሰውዬው ተከር ክላንሲ ይባላል፡፡ ጥቅጥቅ ያለ በደንብ የተገነባ ሰውነት
አለው፡፡ ደንዳና አንገቱን ጥብቅ አድርጎ በሸሚዙ ስለቆለፈው የታነቀ ይመስላል፡፡ ካኪ ሱሪ እና ጂንስ ሱሪ ለብሷል፡፡ ወግ አጥባቂ ነገርም ስለሆነ ምናልባት ልብሱን ሲያወልቅ ሰውነቱ ላይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ምልክት የሆነውን ዝሆን ተነቅሶት ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉ ነገሩን በጥንቃቄ እና
በስርአቱ የሚከውን ሰው መሆኑን ፊቱን በማየት ብቻ ማወቅ ይቻላል። ያም
ቢሆን ግን የደረሰበት ከፍተኛ ሀዘን እና ውስጣዊ ሀዘኑን ከፊቱ ላይ ማንበብ
ይቻላል። ዕድሜው በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ ቢገኝም ሲታይ ግን የስልሳ
አመት ሽማግሌ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ልጅን በሞት ማጣትን የሚመስል
ከባድ ሀዘን አይገኝም፡፡ ነገር ግን ይህቺን አንድ ልጅህን ጠፍታ ሳትገኝ መቅረትዋ በወላጅ የዋህ ልብም የጠፋችው ልጅ የሆነ ቀን ላይ ተገኝታ ወደ ቤትዋ በመመለስ የወላጆችዋን ስቃይ እንዲያበቃ ታደርጋለች ብሎ መጠበቅን
የመሰለ እጅግ በጣም ስሜትን የሚጎዳ ነገር እንደሌለ ዴሪክ ዊልያምስ በደንብ
ይገባዋል፡፡

ባለቤቱ ሜሪ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ ትመስላለች። እርግጥ ነው
እሷም ብትሆን ይደክማታል፤ ያም ሆኖ ግን የልጅዋን ዕጣ ፈንታ ከባሏ በታቃራኒ መልኩ ተቀብላ ነገረ አለሙን ሁሉ ረስታ የተቀመጠች ሴት ሆናለች፡፡ ለዚህም ሊሆን ይችላል በውስጧ የሚገኘውን ስቃይዋን ፊቷ ላይ ማንበብ የማይቻለው፡፡ ይሄ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከሁለቱ አንዱ እውነታውን ተቀብለውታል ብሎ ዊልያምስ አሰበ፡፡
ለሶስት ሳምንት ያህል ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ዊሊያምስ የክላንሲን ልጅ
ቻርሎቴን ለመፈለግ ሲኳትን ነበር፡፡
ከመጥፋትዋ በፊት ያሉትን የቻርሎቴ
ውሎዎችን አና ያገኘቻቸውን ሰዎች በማግኘትም ዱካዋን ለመፈለግ ጥረት
ሲያደርግ ቆየ፡፡ ቆንጅየዋ ቻርሎቴ ክላንሲ ረጅም ናት፤ በተለይ ደግሞ ከሃገሬው የሜክሲኮ ሴቶች አንጻር በቀላሉ በምትኖርበት አካባቢ የምትለይ
ቢሆንም ከጠፋችበት ምሽት በኋላ ማንም ሰው አይቷት እንደማያውቅ ነበር
የነገሩት፡፡

በመጀመሪያ ጊዜ ባል እና ሚስቱ የቻርሎቴ ወላጆች ስለ ቻርሎቴ የፍለጋ
ሁኔታ በደንብ አልነገሩትም ነበር፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አባቷ ተከር አላንሲ የውጭ ሀገር ፖሊሶች በተለይ ደግሞ የሜክሲኮ ፖሊሶች በሙሉ የማይረቡ ናቸው ብሎ ስለሚያምን ነበር፡፡ ስለዚህም በፍለጋው ላይ ምናልባትም ኤፍ.ቢ.አይ እና በሜክሲኮ የአሜሪካ ቆንስላ በጉዳዩ ላይ ቢገቡበት ልጁ የምትገኝ መስሎት ነበር፡፡ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ከሜክሲኮ ፖሊሶች በባሰ መልኩ የልጁን ጉዳይ ችላ ስላሉት ንዴቱን በዚህ
መልኩ ነበር የገለጸለት፡፡

“ስለ ቻርሊ እኮ ምንም ደንታ የላቸውም” ብሎ በመጮህ ነበር ተከር ክላንሲ በሁሉም ነገር ተስፋ ቆርጦ እሱን ለመቅጠር በመጣ ጊዜ የተናገረው
እሷ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሴት አይደለችም እንዴ? ታዲያ ለምንድነው
በየጥሻው ውስጥ የማይፈልጓት?”

ዊልያምስ የተከር ክላንሲ ንዴት ይገባዋል ግን ደግሞ በኤፍ.ቢ.አይ እና በቆንጽላው ጽ/ቤት አልተገረመም፡፡ “አሳዛኙ ነገር ግን ምን መሰላችሁ ቻርሎቴን በደንብ ሊፈልጓት የሚችሉት እሷ የሀብታም ልጅ ወይንም የባለስልጣን ልጅ ብትሆን ነበር፡፡ ስለሆነም የኤፍ ቢ አይ ሰዎች እሷን ለመፈለግ ጊዜያቸውን እና ሀብታቸውን ማውጣት አይፈልጉም፡፡ እሷ
ለመጨረሻ ጊዜ ወደ እናንተ ስትደውልላችሁ እድሜዋ ከ18 አመት በላይ ነበር፡፡ ብዙ ልጆች ደግሞ በዚህ እድሜያቸው ላይ ለወላጆቻቸው ሳይናገሩ
ከሆነ ሰው ጋር ሊጠፉ ይችላሉ፡፡”

ቻርሊ በፍፁም እንደዚህ ያለ ነገር አታደርግም” አለ ተከር ክላንሲ፡፡በዚያ ላይ ደግሞ ለአመታት ያህል በእኛ ላይ ጨክና ሳታናግረን አትተወንም፡፡” ሲል ሚስቱም ቀጠል አድርጋ “ሚስተር ዊልያምስ የሆነ ነገር ልጃችን ላይ እንደደረሰባት ይታወቀናል” ብላ እምባዋን ታግላ አስቀረችው እና ወይዘሮ ባደን እንደነገረችንኸውን ሜክሲኮ ውስጥ በየአመቱ ቱሪስቶች እና ሌሎች ሰዎች እንደሚታገቱ ነው፡፡”

“ምን አልሽኝ?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቀ፡፡

“ቫለንቲና ባደን ናት፡፡ የዊሊ ባደን ሚስት ናት፡፡ የጠፉ ሰዎችን የሚያፈላልጉ የበጎ አድራጎት ድርጅት የከፈተች ናት።ከማንም በላይ ቻርሎቴን ለመፈለግ እገዛ አድርጋልናለች አለው ተከር ክላንሲ፡፡”

ይህንን ሲሰማ በድንገት አንድ ነገር ትዝ አለው ተከር፡፡ የሆነ ማታ ላይ ሁለት ታላላቅ ክለቦች እየተጫወቱ በነበሩበት የእራት ሰዓት ላይ ልጆቻቸውን እንዲያፈላልጉላቸው ሲማጸኑ እንደነበር አስታወሰ፡፡ ያኔ በዚህ የእረፍት ሰዓት ላይ ለሚተላለፉ ማንኛውም ነገሮች በጣም ውድ የሆነ ዋጋ ለቲቪ ጣቢያዎች ተከፍሎ ነው፡፡ ስለዚህም ይህንን የማስታውቂያ ክፍያ የከፈለችው
የዊሊ ባደን ሚስት ቫለንቲና ባደን መሆንዋን ተረዳ፡፡

“በፍፁም ወደዚያ እንድትሄድ ልፈቅድላት አይገባኝም ነበር፡፡” አለ ተከር ክላንሲ በቁጭት፡፡

“ምን መሰለህ ሚስ ባደን በእገታ የተወሰዱ ሰዎችን በማፈላለግና
ለአጋቾቹ የማስለቀቂያ ክፍያ እየከፈለች ታጋቾችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር
እንደምታገኛኝ ነው የምናውቀው፡፡ ይሄው እንግዲህ ስለልጃችን ግን አንድም
ሰው እስካሁን ድረስ የደወለልን የለም፡፡ ይሄ ነገር ጥሩ ይሁን መጥፎ ሊገባን
አልቻለም” አለችው ሜሪ ክላንሲ፡፡

መጥፎ ነው እንጂ ብሎ አሰበ ዊልያምስ ደግሞም ይህቺ ቫለንቲና
ባደን ለቻርሎቴ
👍2🔥1
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


እናቴም የአባቴን አኳኋንና ለዘብተኛ አነጋገር በመከተል እንደ ወትሮዋ አልተቆጣችኝም

ከየውብነሽ ጋር መገናኘቴን ቀጠልኩ። አባቴ ስለ እኔ ያለውን አስተያየት እምብዛም እንዳልለወጠው አጣራሁ፡፡ እናቴም የእኔን ደጅ ደጅ ማየት ችላ እንዳለችውና እንኳን ከዚያች ከመናጢ ገረድ ጋር አብሮ ያልታየና ስማችንን ያላስጠፋው እንጂ የኋላ ኋላ መመለሱና ልብ መግዛቱ አይቀርም፡፡ እኔም ለጊዜው ንድድ ያለኝ ከገረድ ጋር መዋልና መልከስከሱ ነበር፣ ሌላ ሌላውስ ግድ የለም” ማለቷን የዋህ ተመስዩ ከየውብነሽ ሰማሁ፡፡

ያም ሆነ ይህ አንድ ቀን የእኔንና የየወዲያነሽን ጉዳይ ይፋ ለማውጣት ቆርጬ በምነሣበት ጊዜ ንትርክና ከባድ የቤተሰብ ውዝግብ እንደሚያጋጥመኝ በእርግጠኝነት ወለል ብሎ ታየኝ፡፡ ካለፈ አገደም ከሥራ መልስ በምሳ ሰዓት ወደ ወላጆቼ ቤት እየሄድኩ የሻከረ ሆዳቸውንና
አስተያየታቸውን ደረጃ በደረጃ ለመለወጥ ጥሩ ጥረት አደረግሁ፡፡ ተደጋጋሚ
ሙከራዩ ትንሽ የለውጥ ፍሬ አሳየ፡፡ በተለይም ከእናቴ ጋር የማደርገው ወሬና
ጨዋታ ሁሉ አስደሳች ቅርርብ ፈጠረ፡፡ ትንሽም ፊቷ በኀዘን የሚጠወልግና
የጠራራ ቅጠል የምትመስለው ደህና እደሪ ብዬ ለመሄድ በምነሣበት ጊዜ
ነበር።

አንድ ቀን ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከየውብነሽ ጋር መኝታ ቤቷ ውስጥ
ተቀምጠን ሞቅ ደመቅ ያለ መሬ ስናወራ «አንተ ጌታነህ» አለችኝ፡፡ ዐይኖቿ
የትዝታዋን ክብደት ለማስረዳት እየቦዙ ያነዩ ዱሮ ከዚያች ከገረዳችን ጋር
እንዲያ ስትሆን አባባ ያየኛል፣ ይሰማብኛል ብለሀ አልፈራህም?» ብላ
ታላቅነቴን በማክበር የኃፍረት ሣቅ ሣቀች። ምናልባት አንዳንድ ያልሰማሁትን
ነገር ታሰማኝ ይሆናል በማለት ልበ ግልጽ
ተመስዩ «እንዳልታይና እንዳይሰማብኝ ያልሠራሁትና ያልፈጸምኩት ዘድ አልነበረም። አንቺንም በጣም እፈራሽና እጠራጠርሽ ነበር» አልኩና አልጋዋ ላይ ጣል ያደረገችውን የሰነበተ ጋዜጣ ማገላበጥ ጀመርኩ። አንገቷን ወደ ቀኝ ሰበር አድርጋ የማገላብጠውን
ጋዜጣ እየተመለከተች ግን እኮ እያደር እንዳፈቀርካትና ከወዲያ ወዲህ
እየተመላለሰች በምትሠራበት ጊዜ ዐይኖችህ አብረዋት እንደሚዋትቱ ኣሳምሬ ዐውቅ ነበር፡፡ ከእንጀራ አቅም እንኳ ሌላ ሰው ሲያቀርብልህ ደስ አይልህም ነበር። እሷም የዋዛ ሾላካ አልነበረችም ! ኋላማ ልናባርራት አቅራቢያ
አረማመዷና አነጋገሯ፣ ጸጉር አሠራሯና አለባበሷ ሁሉ በጣም ተሻሽሉ ነበር፡፡
እኔ ከሁሉም ከሁሉም የማይረሳኝ ጠባይዋና ሲያዝዋት እሺ ባይነቷ ነው፡፡ ምን ይሆናል፣ ያ መሳይ መልክ ያለ ቦታው ቀረ፡፡ እሷ የተማረች ሆና ውጪ
ውጪውን ብናገኛት ኖሮ... እኔ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ስለ እሷ አንዳችም ወሬ
ሰምቼ አላውቅም» ብላ አጠናቀቀች። የወሬ ከረጢቷን መፍታቷ ስለ ታወቀኝ
ለጊዜው ውስጣዊ ብስጭቴን ኣፍኜ ባናነሣው ይሻላል ያለፈው አልፏል እንጂ
ብሳሳትም ባልሳሳትም ከዚህ ቤት ስታባርሯት እርጉዝ ነበረች። ቀስ ብላችሁ
ሹክ ብትሉኝ ኖሮ እንደምንም አንዱ ጋ አስጠጋትና ትወልድ ነበር፡፡

ይኸንዬ እኔን አባብዬ” ሲል አንቺን ደግሞ ”እቴቴ' እቴ ሸንኮሬ 'እት -አይገኝ” ይልሽ ነበር» አልኳት፡፡ የአሁኑን የ'ወዲያነሽን ሕይወትና ኑሮ የማታውቀዋ እኅቴ ከሁሉም ከሁሉም በጣም የሚያሳዝነኝ» ብላ ቀጠለች፣
«ያነዪ አንተ ወደ ሥራ ወጣ ከማለትu እማዬ በአባባ ከዘራ ታፋ ታፋዋን'
ጀርባ ጀርባዋን ስትደበድባት ኩርምት ብላ ስትደበደብ የወረደባት የዱላ መዓት ነው፡፡ በመጨረሻ የተሰነዘረው ዱላ መኻል እናቷ ላይ በማረፉ ደሟ በጸጉሯ ውስጥ እየተንጀረጀረ ትከሻዋ ላይ ተንጠፈጠፈ፡፡ ነፍስ ይዟትም ይሁን ያሰበችውን እንጃ ከዘራውን ይዛ እለቅም በማለቷ እኔም እናቴን የተዳፈረችብኝና ግብግብ የምትገጥማት ስለመሰለኝ ሁለት ጊዜ በጥፊ አላስኳት።

«እሷ ግን ቀና ብላ አይታ፣ አንቺም? አንቺም? ጨክነሽ ትመቺኝ የውብነሽ? ኣይ ድኃ መሆን!” ያለችኝ ዛሬም አንጀት አንጀቴን ይበላኛል፡፡»
«እሷ ግን በጣም የተንገበገበችውና ያለቀሰችው ከቤት በመባረሯና
በመደብደቧ ሳይሆን እንተን ሳትሰናበትሀና ሳታይህ በመሔዷ ነበር። ከሥራ ስትመለስ መንገድ ላይ ጠብቃ እንዳታግባባሀና በሴት እንባዋ እንዳታታልልህ ከዚህ አካባቢ ያባረርናት በዘበኛ ነበር» ብላ ያን ዚያ ቀደም አሳርሮ
ያከሰለኝን መራራ ነገር እንደገና ጋተችኝ፡፡ የየወዲያነሽ መከራና እንግልት
ሁሉ ከተቀበረበት የትዝብት መቃብር ወጥቶ ነጭ ዓፅሙ ፊት ለፊቴ ተገተረ፡፡ ሌላ ተጨማሪ ነገር በመስማት አንጎሌን ማጥመልመል ስላልፈለግሁ
«ነገ አራት ሰዓት ላይ ዕጓለ ማውታ ስለምሔድ አብረን እንሂድ። ከዚያ በኋላ
ደግሞ ሌላ የማማክርሽ ጉዳይ ስላለ ቀደም ብለሽ ቀበና ድልድይ አጠገብ
ጠብቂኝ ብያት ወጣሁ፡፡

በማግሥቱ እሑድ እኅቴና ባለቤቴ ዕጓለ ማውታ እንዳይገናኙብኝ፡ የወዲያነሽን «እንግዳ ይዤ እመጣለሁና ተዘጋጅተሽ እንድትጠብቂኝ፡ ከዚያ በኋላ እንሔዳለን» ብያት ከቤት ወጣሁ፡፡ መኪና መግዛቴን መላ ቤተሰቦቼ ስላልሰሙ የውብነሽ የምትጠብቀኝ በእግር እንጂ በመኪና ይመጣል ብላ አልነበረም፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ዘግየት ብዬ ቀጠሮእችን ቦታ ስደርስ የውብነሽ ተረከዘ ሹል ጫማ አድርጋ ከጉልበቷ ትንሽ ከፍ ያለ ቀለመ ብዙ የፈረንጅ ቅድ ቀሚስና ነጭ ሸሚዝ ለብሳ ቡናማ ኮረጆዋን አንግታ ድልድዩ አካባቢ ስትጠብቀኝ አገኘኋት። መኪና አጠገቧ ደርሳ በመቆሟ ባለ መኪናውም እኔ መሆኔን ባለማወቋ ፊቷን በቁጣ ከሰከሰች፡፡ እንዳንድ የጎዳና ሴቶች
ለመግደርደር ሲሉ የሚያሳዩት አኳኋን ትዝ አለኝና የየውብነሽ አድራጎት አሣቀኝ፡፡ ወዲያው ወጣ ብዬ ወደ እርሷ ተራመድኩ። ከመኪና ወጥቶ ወደ
እርሷ የሚራመደው ሰው ታላቅ ወንድሟ መሆኑን ስታውቅ የአድናቆት ሣቅ
ሣቀች፡፡

«መኪና ገዛሁ እንዳትለኝ አለችኝ፡፡ «አዎ ገዛሁ እኔም ወጉ ይድረሰኝ ብዬ ገና ሁለተኛ ወሯን መያዟ ነው» አልኩና እየተሣሣቅን ተጨባበጥን፡፡
«የውቤ፣ ይቺንም ታድያ ቤተሰብ እንዳይሰማ፣ እንድ ቀን ሁሉንም ነገር
አጠራቅሜ አቀርበዋለሁ፡፡» «ሌላ ደግሞ ምን የሚነገር አለህ?» ብላ አየችኝ፡፡
«እኔ ገና ብዙ የሚነገር ነገር አለኝ» ብያት መኪና ውስጥ ገብተን መንገድ
ቀጠልን፡፡ በአሥራ አምስት ደቂቃ ውስጥ አግድመት ቁልቁለቱን ጨርሰን
ሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ደረስን፡፡ ለምለሙ መስክ ላይ ትላልቅና ትናንሽ
ልጆች እንደ ጥሬ ፈስሰው ልዩ ልዩ ጨዋታዎች ይጫወታሉ። ከትንንሾቹ
ልጆች መኻል አንድ የግራ ዐይኑ የጠፋችና በዐይን አር የተጨማለቀች
ሰማያዊ ቁምጣና ትከሻው ላይ የተጣፈች እሷኑ መሰል ኮት የለበሰ ልጅ
በሩጫ መጥቶ ጨበጠኝ፡፡ የጋሻዬነህ ጓደኛ ነው:: ከኪሴ ከረሜላ ኣውጥቼ ሰጠሁት። የውብነሽ በድንጋጤ አፏን ከፍታ «ምነው ምን ሆነ? ዐይኑን ምን ነካው? ደኅና አልነበረም እንዴ !?» አለችኝ፡፡
«ይህ እኮ ያ ከዚህ ቀደም ያየሽው የጓደኛዬ ልጅ አይደለም፣ ይኸ ጓደኛዉ ነው:: አሁን ሮጦ ይጠራልናል» አልኩና የደነገጠውን ስሜቷን በደስታ
አደስኩት:: ከረሜላውን ልጦ ጎረሰና ተለይቶን ሔደ። እምብዛም ሳይቆይ
ጋሻነህን ይዞት መጣ፡፡ አንዲት በጣም የጠወለገች ነጭ አበባ ይዞ ነበረ።
እጆቼን ከብብቱ ሥር አስገብቼ በማንሣት ጉንጮቹን ስስም ሁሉም ነገር
ጥሉኝ ጠፋ፡፡ የውብነሽ ቀበል ብላ አገላብጣ ሳመችው:: ቀድሞውንም የሙት ልጅ ነው ብዬ ነግሬያት ስለ ነበር በርኅራኄ ተመለከተችው:: አላስችል ስላላት ዕንባ ተናነቃት። መሐረቧን አውጥቃ ዐይኖቿን አበሰች። «ለመሆኑ ያባቱ ዘመዶች እየመጡ ይጠይቁታል እንዴ?» አለችኝ፡፡ ልጅ ያለው መሆኑን የሰማ አንድም
👍2