አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት

#ክፍል_ሶስት

#ሜርኮቲዎ
የሆነስ ሆነና ቀጠሮ ግን አለክ?

#ሮሜዎ
የወጣ ፡ ቃል ፡ የለም ፡ አፋችን ፡ ተናግሮ ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ ተያይተን ፡ ባይን ፡ ስንገናኝ ፡
ለኔ ፡ መፈጠሯ ፡ ለልቤ ፡ ተሰማኝ ።
እሷም ፡ እንደዚሁ ፡ በውስጣዊ ፡ ልቧ ፡
አይጠረጠርም ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማሰቧ ።
እጅግ ፡ የሚያስደንቅ ፡ ለብልኋ፡ አስተዋይ
እነሆ ፡ ይኸ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ፍቅር ፡ ጠባይ
አፍ ፡ ሳይንቀሳቀስ ፡ ታስሮ ፡ በዝምታ ፡
ልብ ፡ ከልብ ፡ ጋራ ፡ ያደርጋል ፡ ጨዋታ ፡
ተወኝ ፡ ልሂድበት ፡ እንግዲህ ፡ ደኅና ፡ እደር ፤
እኔን ፡ አየሁ ፡ ብለህ ፡ ለሰው ፡ አትናገር ።

(ሮሜዎ ፡ ሄደ) ።

#ሮሜዎ ፡ (በዡልዬት ፡ መኝታ ፡ ቤት ፡ አጠገብ • ማታ፡በጨረቃ ከውጭ ፡ ሆኖ)

የሚያፈቅራትን ፡ ልጅ ፡ የሚጠብቅ ፡ ወጣት ፡ ረዝሞ ፡ ይታየዋል ፡ ደቂቃ ፡ እንደ ሰዓት ፤ሰዓቱም ፡ እንደ ፡ ቀን ፥ ቀኑም ፡ እንደ ፡ ዘመን እኔስ ፡ መሞቴ ፡ ነው ፡ በፍቅሯ ፡ ሰመመን ።

(#ዡልዬት ፡ መስኮት ከፍታ'ብቅ'አለች "
አሳቤ ፡ ተነሣ 'ተከፈቱ'ዐይኖቼ፤
ደሜ ፡ ተንቀሳቀስ፡ተፍታቱ ፡ ሥሮቼ ።
ልቤ ፡ ተስፋ፡ ሲቈርጥ ፡ የማትወጣ ፡ መስሎት ፡ ያቻት፡ የኔ ፡ ሥራ ፡ ብቅ አለች ፡ በመስኮት ።
ልቤ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ መንፈሴ ተሸበር ፤
የዡልዬትን ፡ ውበት ፡ እንግዴህ 'ልናገር ፤
መስኮቷ ፡ ምሥራቅ ፡ ነው' ፊቷ' የጧት'ጀንበር ብርሃኗ' የለውም ፡ የሚያግደው ' ድንበር ።
ሰላም ፡ ላንቺ ፡ ይሁን ፡ ትልሻለች ፡ ነፍሴ ፤
ጮራሽ፡ ኣለበሰኝ ፡ ከእግር ፡ እስከ ፡ ራሴ ፡
እኔ ፡ እንደምወድሽ ፡ አታውቂውም ፡ ፍቅሬ ፤
አላጫወትኩሽም ፡ ባፌ ፡ ተናግሬ ፡
ካየሁሽ ፡ ይበቃል ፡ ቆሜ' ከሩቅ ፡ ቦታ፤
ያጠግበኛልና 'ያይኖችሽ ፡ ጨዋታ ፡
ዐይንሽ ፡ የሚመስለው ' የርግብ ፡ የሚዳቋ ፣
እኔ ፡ የማልጠግበው 'አለው ፡ ልዩ ፡ ቋንቋ
ዐይኔ ፡ እንደ ፡ ቀለበት ፡ ጣትሽ ፡ ላይ ፡ ተሰካ ፤
እዩት ፡ በቀኝ ፡ እጅዋ 'ጕንጮቿን ' ስትነካ ፡
የእጅ ፡ ሹራብ ፡ ሆኜ፡ ገላሽን ፡ ባለብሰው ፡
ፊትሽን ፡ ጕንጭሽን' ዡልዬት፡ብዳብሰው ፡
ደስታ፡ሕይወቴን'እንደ 'ምን' ባደሰው !

#ዡልዬት
ሮሜዎ፡ሮሜዎ'የልቤ'ወለላ '
እባክህ ፡ ለውጠው ፡ ስምህን ፡ በሌላ ፡
ፍቅራችንን 'ገደል ፡ ሆኖ ፡ የሚያግደው
ቂም ፡ በቀል ፡ ስላለ ፡ ኀጢአት ፡ የወለደው ,
እኔም ፡ ዘሬን ፡ ልካድ፤ አንተም'ዘርህን ፡
የኔ ፡ አባት ፡ ላንተ' አባት ፤ የናንተ ፡ ዘር ፡ ለኛ መሆኑን ' አትርሳ ፡ ባላንጣ 'ደመኛ ።

#ሮሜዎ
ይህን ፡ ኣልዘነጋም ፡ ዡልዬት ፡ ይሰማኛል
ነገር ፡ ግን 'ምን ፡ በቀል'ምንስ'ቂም ፡ ይገኛል ፡
ምንስ ' ጠላትነት ስታስቢው ፡ በሰው ፡
የፍቅር ፡ ማዕበል ፡ የማይደመስሰው ፡
የኔ ፡ አባት ፡ ላንች ፡ አባት' ቢሆንም ፡ ባላንጣ ፡
እኔ ፡ እወድሻለሁ ፡ ነፍሴ ፡ እስክትወጣ ።

#ዡልዬት
ሮሜዎ ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ዕድሜ ፡ ለሰው ፡ ክፋት !
በፍቅር ፡ መካከል ፡ አለ ፡ ብዙ፡ ዕንቅፋት ፡
የጌታ ፡ ልጅ'ድኻን 'አይውደድ' ይላሉ ፤
ብዙዎች ፡ ልጃቸውን ' በዚህ ' ይክዳሉ ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ የሰው ፡ ልብ ፡ በሰው ፡ አይመራም
የፍቅራችን ፡ መብራት፡በትእዛዝ አይበራም
ልጅ' ካባት 'አጣልቶ፡ብዙ፡ ሰው ፡ የጐዳ '
ይህን'የመሰለ'አለብን'ብዙ ዕዳ "
ቂም ፡ በቀል ፡ የሚሉት ፡ መከረኛ' ጣጣ'
ካያት ፡ ካባት ' ከናት ' ከዘር ፡ የሚመጣ
እኛ ፡ እንዳንፋቀር ፡ ማንንም ፡ ሳንፈራ ፡
ሆኖብን ፡ ተገኘ ፡ የፍቅር 'ደንቃራ ፤
ዳሩ ፡ ግን ፡ ይህ ፡ እክል ፡ ለሰው ፡ የማይራራ
እጅ ፡ እግር ፡ የሌለው ፡ እኛ፡ የማናውቀው፡
አይችልም ፡ ልብህን ፡ ከልቤ ፡ ሊያርቀው :
ሞንታግስ ምንድነው ፡ ፊደል አይደለም፡ ወይ ?
እኛን ፡ ሊለያየን'አይችልም ፡ ፍቅሬ ፡ ሆይ ፡
ስሟን 'ብንለውጠው ፡ እስቲ ፡ ጽጌ'ረዳ ፡
ይችላል ፡ ወይ ፡ መልኳ፡ ሊለወጥ ' ሊጐዳ
አይችልም ፡ ውሸት ፡ ነው ፡ በማዛ ፡ በውበት ፤
ጽጌ ረዳ'ያው ፡ ነች፡አይነካትም ፡ጕድለት ፡
ሮሜዎም ፡ እንዲሁ ፡ ስሙን ፡ ቢለውጠው ፡
ባሕርዩን 'ኣይችልም ፡ ከቶ ፡ ሊያናውጠው
ተወዳጅነቱ ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡
በጠባይ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በስሙ ።
ያንተ ፡ ስም ፡ ቢለወጥ፡ ዋጋህን ፡ አትርሳ ፡
እኔን ፡ ማግኘትህ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ትልቅ ፡ ካሳ ።

#ሮሜዎ
በመካከላችን ፡የተገኘው ፡ እክል ፡
ስሜ ፡ ከሆነማ ፡ የኛ ፡ መሰናክል ፡
አጭር ፡ ነው፡ ነገሩ፡ ዡልዬት፡ የኔ፡ ፋና ፡
አንቺን ፡ ደስ ፡ እንዲልሽ ፡ ለፍቅሬ ፡ ዋስትና ፡
ላደርገው ፡ የማልፈቅድ ፡ ነገር ፡ የለምና ፤
ቢያስፈልግ ፡ ልነሣ ፡ ዳግም ፡ ክርስትና ፡
ሲሰማ ፡ እንዳይቀፈው ፡ ስሜን ፡ ያንቺ ፡ ዦሮ ፡
ሮሜዎ ፡ኣይደለሁም ፡ ከዛሬ፡ ጀምሮ ፤
ፍቅርሽና ፡ ፍቅሬ ፡ በዘር ፡ ቂም ፡ ኣይፈርስም ፤
ከዛሬ ጀምሮ' ይለወጥ ፡ የኔ ፡ ስም ።

#ዡልዬት
ማነህ ፡ አንተ ፡ ከዚህ ፡ የቆምከው ፡ ከደጄ ?
ባይኔ ፡ የማላይህ ፡ የማልነካህ ፡ በእጄ ፡
ጨለማ ፡ የለበስክ ፡ የፍቅር ፡ ማዕበል ፡
የልቤ ፡ ነበልባል ፡ ስምህን ፡ ማ ፡ ልበል?

#ሮሜዎ
ባንቺ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ፡ የሚኖር ፡ ከርታታ፡
የቀን ፡ ብርሃን ፡ ሸሽቶ ፡ የመጣ ፡ በማታ ፡
አንቺን በመውደዱ ፡ ከራሱ'አብልጦ ፡
ያለ ፡ ስም ፡ የቀረ ፡ ስሙንም ፡ ለውጦ ።

#ዡልዬት
ያጥራችን ፡ ግንቡ ፡ ትልቅ ፡ አይበገር ፤ ..
እንዴት ፡ ነው ፡ የገባህ ፡ አንተም ሳትቸገር ? .
መች ፡አጥር ፡ብቻ ነው ፡ ትልቁን ፡ጉድ ትቼ
ደግሞም ፡ ይገድሉሃል ፡ቢያዩህ ፡ ዘመዶቼ

#ሮሜዎ
ፍቅር ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ ጕልበቴና ፡ ክንፌ ፡
ግንቡ ፡ ሳያግደኝ መጣሁኝ ፡ አልፌ ፡
ጨለማም ፡ አጥርም ፡ ሳያሰናክለኝ ፡
እንዴት ፡ ያለ ፡ ሰው ፡ ነው ፡የሚከለክለኝ ?

#ዡልዬት
ታዲያ ፡ እዚህ ፡ ቢያገኙህ፡ይገድሉህ ፡ የለም ፡ ወይ?

#ሮሜዎ
ለኔ ፡ ምንም ፡ አይዶል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ፍቅሬ ፡ ሆይ ፡
አጥር ፡ እጥሳለሁ ፡ ጦርም ፡ አያግደኝ ፤
ብርሃን ፡ የሞላበት ፡ እኔን ፡ ያሳበደኝ ፡
ጦሩስ ፡ ያንቺ ፡ ዐይን ፡ ነው ፡ የኔን ፡ ልብ ፡ የወጋ
በፍቅር ፡ ኣይተሽኝ ፡ መንፈሴ ፡ ቢረጋ ፤
ምንም ፡ ባላሠጋኝ ፡ የቀረው ፡ አደጋ ።

#ዡልዬት
ሳይህ ፡ በኛ ፡ ግቢ ፡ ይሰማኛል ፡ ሥጋት ፤
በሻምላ ፡ ወይ ፡ በጦር ፡ ልብህን ' ለመውጋት ፡
ስለማይመለስ ፡ ወገኔ ፡ አንተን ፡ አይቶ ፡
ቢያዩህ ፡ አልፈልግም ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ከቶ ።

#ሮሜዎ
ዥልዬት ፡ አታስቢ ፡ አትሥጊ ፡ለነፍሴ
ወዳንቺ' ስመጣ፡ ጨለማ ፡ ነው ፡ ልብሴ ፡
ትወጂኝ ፡ አትወጂኝ ፡ ባለመለየቴ ፡
ይህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ሕመሜና' ሞቴ ፤
ስለዚህ ፡ ንገሪኝ፡ ምንም ፡ አትደብቂ ፤
ሌላውን'አደጋ ፡ ግድ ፡ የለሽም ፡ ናቂ ።
አትወጂኝ' እንደሆን ፡ ሰፊ ፡ ነው፡ ሐዘኔ ፤
በዚህ ፡ ሕመም ፡ ብቻ ፡ እሞታለሁ ፡ እኔ ።

#ዡልዬት
እፍረት ፡ እንዳይዘኝ ፡ ጨለማ ፡ ለብሼ ፡
እንግዲያው ' ልንገርህ ፡ አሳቤን ፡ ጨርሼ
እፍረት'ደኅናሰንብት መግደርደር ደኅና ሁን
ሮሜዎ 'አንድ ፡ ነገር ፡ ልጠይቅህ ፡ አሁን ፡
ከፊቴ የቆምከው ፡ ወዳጄ ፡ ፍቅሬ 'ሆይ'
ካንጀትህ ' ከልብህ ፡ ትወደኛለህ ' ወይ ?
ማንንም ፡ አልወድም ፡ ብለህ ፡ካንቺ ፡ሌላ
ትናገራለህ ፡ ወይ ፡ አሁን ፡ በመሐላ ?
እኔ ፡ ባንተ ፡ ፍቅር በጣም ፡ ተጨንቄ '
ስለምወድህ ፡ ነው ይህን
#ሮሜዎና_ዡልዬት

#ክፍል_አራት

#ዡልዬት
ይቅርብኝ 'አትማል በውነትም ፡ በውሸት ፡
ደግሞም ፡ ልማል ፡ ብለህ፡አሳብህ ፡ ከጸና
ምን ጊዜም ፡ ጣዖቴ ፡ ፍቅሬ ፡ አንተ ፡ ነህና
በራስህ ፡ ማልልኝ ፡ የኔ ፡ ሁለንተና ።

#ሮሜዎ
እንግዲያውስ ፡ ስሚ ፡ እኔ ፡ አንቺን ፡ መውደዴ ፡

#ዡልዬት
ይቅር ፡ በቃ ፡ አትማል ፤ ተናወጠ ፡ ሆዴ ፡
ፈጥነህ ፡ ብትምልልኝ ፡ አሁን ፡ ዛሬ ፡ ማታ
ምንም ፡ አይሰማኝ ፡ ለልቤ ፡ ደስታ ፡
እንደዚህ ፡ በድንገት ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ፡
እንደዚህ ፡ በቶሎ ፡ የሆነ ፡ መሓላ ፡
መሠረት ፡ የለውም ፡ ይጠፋል ፡ ባንዳፍታ፤
አላፊ ፡ ነፋስ ፡ ነው ፡ የሰማይ ፡ ብልጭታ
የፍቅሩ፡ ቡቃያ ፡ ከዛሬ ፡ ጀምሮ ፡
ለምልሞ ፡ ይጠንክር ፡ በልባችን ፡ አድሮ ፡
እኛም ፡ እዚያ ፡ ድረስ ፡ሆነን ፡ ትዕግሥተኛ
ወደየቤታችን ፡ ገብተን ፡ እንተኛ ።

#ሮሜዎ
ልትሄጂ ፡ ነወይ ፡ ትተሽኝ ፡ በከንቱ ?

#ዥልየት
ይበቃል ፡ ለዛሬ ፡ መሽብን ፡ ሰዓቱ ።

#ሮሜዎ
ስጭኝ ፡ የሚያጠግብ፡አንድ ፡ ቃል ፡ የበቃ

#ዡልዬት
አንተ ፡ ሳትጠይቅ ፡ በፊት፡ዡልዬት ፡ዐውቃ
ሰጥታህ፡ወስደኸዋል፡የፍቅሯን፡ቃል ኪዳን
የተረፈው ፡ ይደር ፡ ለነገ ፡ እንዲረዳን ።

#ሮሜዎ
መልሰሽ ወስደሺው ፡'መልካሙን ፡ ስጦታ

#ዡልዬት
ቃሌን ፡ እሰጣለሁ ፡ ላንተ ፡ በችሮታ
የልቤ ፡ ደግነት ፡ ባሕር ፡ ነው ፡ ስፋቱ ፤
ፍቅሬም ፡ እንደዚሁ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ርቀቱ
መልካም ፡ ጠባዮቼ ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፡
ሰፊ ፡ ሀብት ፡ናቸው፡ ከሁሉም ፡ የላቁ ፤
ብሰጥህ ፡ ብሰጥህ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አያልቁ ።
(#ሞግዚቷ' #ጠራቻት ) ።
ጠሩኝ ፡ ድምፅ ፡ ሰማሁ ፡ በል ፡ ሄድኩኝ፡ደኅኖ፡እደር።
ሞግዚቴ ፡ እሺ ፡ መጣሁ ፤ ሮሜዎ ፡ አንድ ነገር ፡ አለ ፡ የምነግርህ፡አትሂድ፡ጠብቀኝ ፣ (ወደቤት'ግባች) »

#ሮሜዎ : (ብቻውን) "
የዛሬው ፡ ደስታ ፡ ምንኛ ፡ ደነቀኝ ።
ሕልም ፡ ነው ፡ ራእይ፡ ወይስ ' ደግሞ ቅዠት አልችልም ፡ ይህ ፡ ነገር ፡ ከቶ'ልደርስበት ፤
ፀሓዬ ፡ ጠለቀች ፡ ገባች ፡ ወደ ፡ ቤቷ ።
አሁን ፡ ተመልሳ ፡ ዳግም ፡ በመስኮቷ ፡
ብቅ ፡ እስክትል ፡ ድረስ ፡ ሆነብኝ ፡ ጨለማ ፡
ይኸው ፡ ተመለሰ ፡ የብርሃኗ ፡ ግርማ ።

#ዡልዬት ፡(ተመልሳ • መጣች
ሮሜዎ ፡ ልንገርህ ፡ የመጨረሻ ፡ ቃል ፤
እንደምታፈቅረኝ ፡ ዐወቅሁት ፡ ይበቃል ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ ፍቅራችን ፡ መሠረት ፡ አግኝቶ
በተክሊል ፡ ጋብቻ ፡ እንዲፈጸም ፡ ጸንቶ ፡
ትፈቅድ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ እልካለሁና ፥
ነገ ፡ ሰው ፡ ወዳንተ ፡ ጒዳዩን ፡ ካጠናህ ፡
ካሰበ ፡ በኋላ ፡ መንፈስህ ፡ መርምሮ ፡
የተክሊሉ ፡ ሰዓት ፡ ይሁን ፡ በቀጠር ።
ወስነህ ፡ ላክብኝ ፤ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ ግን ፡
ማመንታት ፡ ሳይኖረው ፡ ልቤ ፡ ሳይገነግን
ችግር ፡ ሳያግደኝ ፡ አደጋና ፡ ሞትም ፡
አንተን ፡ ተከትዬ ፡ እሄዳለሁ ፡ የትም ።
ነገር ግን ፡ ያንተ ፡አሳብ ከሌለው ፡ ንጽሕና
የማይሄድ ፡ ከሆነ ፡ እንደኔ ፡ ኅሊና ፡
አትምጣ፡ ወደኔ ፡ አትድከም ፡ በከንቱ
እንግዴህ ፡ ደኅና ፡ ሁን ፡ አለፈ ፡ ሰዓቱ '
ግባ ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ ፍጠን ፡ አታመንታ ፤
ሊነጋ ፡ ነውና ፡ ይታያል ፡ ወገግታ ፡
ጨለማ ፡ ለቀቀ ፡ ብርሃን ፡ ተከፈተ ፡
ስንት ፡ ሰዓት ፡ ሲሆን ፡ ሰው ፡ ልላክ ፡ ወዳንተ ?

#ሮሜዎ
ሦስት ፡ ሰዓት ሲሆን መልክተኛሽ ፡ ይምጣ

#ዡልዬት
እንግዴህ ፡ ደኅና ፡ ሁን ፡ ፀሓይ ፡ ሳትወጣ
እንግባ ፡ ቤታችን ። (ሄደች)•

#ሮሜዎ
ዡልዬት ፡ ደኅና ፡ ሁኝ፤
ልቤ ፡ ካንቺ ፡ ጋራ ፡ መቅረቱን ፡ እመኝ ። (ሄዴ) •

#ሮሜዎና #ኣባ_ሎራ ፡ (ባባ ' ሎራ' ቤት)

#ሮሜዎ
እንደምን ፡ አድረዋል፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ?

#አባ_ሎራ
ከምሥራቅ ፡ ሳይታይ ፡ የፀሓይዋ ፡ ሥራ ፡
ማነህ ፡ በማለዳ ፡ የመጣህ ፡ ከቤቴ ?
በጣፋጩ ፡ ድምፅህ ፡ የምትል ፡ አባቴ ።
እረግ ! አንተ ፡ ነህ ፡ ወይ ፡ሮሜዎ ፡ ጐበዙ
ዐይኔ ፡ ደከመና ፡ አላየም ፡ በብዙ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ አድረሃል ፡ የምወድህ ፡ ልጄ
ዐይንህ፡በጣም፡ቀልቷል፡ምን ነካህ ወዳጄ ?
አንድ ፡ ሰው ፡ እንደዚህ ፡ በጧት ፡ የሚነሣ
ነገር ፡ ሲያገኘው ፡ ነው ፡ እንቅልፍ ፡ የሚነሳ ፡
አሳብ ፡ የምንለው ፡ የሰላም ፡ መጋኛ ፡
መንፈሱን ፡ ሰፍሮበት ፡ እንቅልፍ ፡ የማይተኛ ፡
ሽማግሌ ፡ ሰው ፡ ነው ፤ ወጣት ፡ ግን ፡ በውኑ ፡
ከእንግዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፡ ነጻ ፡ በመሆኑ ፡
ተኝቶ ፡ ያነጋል ፡ እንቅልፉን ፡ በሰላም ፤
ስለዚህ ፡ ይህ ፡ ዐይንህ ፡ በደኅናው ፡ አልቀላም ፡
ሮሜዎ ፡ ምን ፡ ሆኖ ፡ ሳይተኛ ፡ ያደረ ?
አለመተኛቱን ፡ ዐይኑ ፡ መሰከረ ።

#ሮሜዎ
እውነት ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ግን ፡አርፌያለሁ ፡ በጣም

#አባ_ሎራ
ብታርፍማ ፡ ኖሮ ፡ በሌሊት ፡ አትመጣም ፡
ንገረኝ ፡ አትደብቅ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያደርከው ?

#ሮሜዎ
ድል ፡ አድራጊው : ፍቅሯ ፡ መንፈሴን ፡ ማረከው
አባቴ ፡ እጅዎ ፡ ተክሊሌን ፡ ይባርከው ።

#አባ_ሎራ
ያሰብከውን ፡ ነገር ፡ ንገረኝ ፡ አትፍራ ፤
ከመልካሟ ፡ እጮኛህ ፡ ከሮዛሊን ፡ ጋራ ፡
የተክሊል ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ ዛሬ ፡ ልትሞላ ፡
የመጣህ ፡ መሰለኝ ፡ ሳስበው ፡ በመላ ።

#ሮሜዎ
ሮዛሊን ፡ ቀርታለች ፡ አያንሷት ፡ አባቴ ፡
ትናንትና ፡ ማታ ፡ ተመታ ፡ ደረቴ ፡
ባዲስ ፡ የፍቅር ፡ ጦር ፡ በሰላ ፡ ጐራዴ ፤
ከመውደዷ ፡ ጋራ ፡ ገጠመ ፡ መውደዴ፡
ስሜታችን ፡ እኩል ፡ ፍቅራችን ፡ የጋራ ፡
ሆኖ ፡ ከተገኘ ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡
ተክሊሉን ፡ ይሙሉልን ፡ በሥልጣንዎ ፡ ባርከው ፡
እኛ ፡ ቂም ፡ የለንም ፤

#አባ_ሎራ
መንፈሴን ፡ ኣወከው
ምን ፡ አመጣህብኝ ፡ የማላውቀው ፡ ምስጢር ፥
መላ ፡ መትቶ ፡ ያውቃል ፡ ብለህ ፡ አትጠርጥር ፤
አልገባኝምና ፡ ያሁኑ ፡ ንግግር ።
ይህን ፡ እንቆቅልሽ ፡ እንደ ፡ ሾላ ፡ ድፍን ፡
ትተህ ፡ ፡ ግለጥልኝ ፡ ነገሩን ፡ ሳትሸፍን ።

#ሮሜዎ
አባቴ ፡ አልደብቅም ፡ ሁሉንም ፡ ገልጬ ፡
ለርስዎ ፡ ልነግር፡ ነው ፡ የመጣ ፡ ሮጬ፡
የነካፑሌን ፡ ልጅ ዡለየትን ፡ ወድጄ ፤
ራሴ ፡ እስቲጠፋ ፡ በፍቅር አብጄ ፡
እሷም ፡ በጣም ወዳኝ፡አድርገን ፡ መሐላ ፡
ተስማምተን ተዋደን ከቈረጥ ኋላ ፡
አሁን 'የሚቀረን'ተክሊል ፡ የሚሞላ ፡
ካህን ፡ ስለ ፡ ሆነ የሚሰጥ፡ ቡራኬ ፡
ከሷ ጋር ፡ መጥቼ ፈትዎ' ተንበርክኬ ፡
ሞልተው 'ያሰናብቱን የተክሊሉን ፡ ሥርዐት
ሰዓቱን 'ይንገሩኝ መቼ እንደምጠራት ።

#አባ_ሎራ
አይጣል፡ነው፡እናንተ፡ የወጣቶች ፡ ወረት፤
ፍቅራቸው ፡ ቃላቸው ፡ የለውም መሠረት፡
የቀድሞ ፡ እጮኛህ ፡ ሮዛሊን 'ተረስታ፡
ሌላ ፡ ልጅ ፡ አግኝተህ አሁን ትናንት ፡ ማታ
እንዴት ተለወጠ፡ ኣሳብህ ፡ ባንድ ፡ አፍታ፡
በሮዛሊን ፡ ፍቅር ፡ ልብህ ፡ እንዲያ፡ግሎ ፡
ዘላለም ፡ የማይበርድ፡እውነተኛ፡መስሎ ፡
ታጫውተኝ ፡ ነበር አሁን ፡ ይኸውና ፡
ያ ፡ ሁሉ ፡ መውደድህ 'ከመቼው 'ቀረና ፡
መጣህ ' ባዲስ ፡ ፍቅር ፡ ልብህ ፡ ተብረክርኮ ፡
ለምታያት፡ሁሉ፡መንፈስህ ፡ ተማርኮ፡

💫ይቀጥላል💫
👍1