አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"ለማንኛውም መቃብሩን አስከፍቼ ሬሳውን ለማስወጣት አስቤ ነበር ። የፎረንሲክ ምርመራ በማድረግ የእናቴን ገዳይ ምንነትን በተመለከተ የተወሰነ ፍንጭ ይሰጠኛል ብዬ አስቤ ነበር።››ለተወሰነ ሰከንድ ድምጿ ጠፋ።የአቶ ፍሰሀ ማብራሪያ የማያሳምን አይነት ነው የሆነባት ። ሁሉንም የቀብር ወጪዎችን መክፈል፣ ሁሉንም ዝግጅት ማድረግ፣ የሴት አያቷን ሃላፊነት መሸከምና እና የገንዘብ ስጦታ መስጠት። እርግጥ ያደረገው ነገር እንደ ሰሎሜ ልጅ ሆና ስትመለከተው ውስጧን ጥሩ ስሜት እንዲሰማት አድርጎታል። እንደ አቃቤ ህግ ግን የበለጠ እንድትጠራጠር አድርጓታል።

ለጊዜው ከዛ በላይ ምንም የሚታናግራቸው ነገር ስላልነበራት ተሰናብታቸው ወጣች

…ጁኒዬር ልሸኝሽ ብሏት ሲነሳ ..‹‹ቆይ እኔ ልሸኛት›› ብሎ አቶ ፍሰሀ ተነሳ እና ከኋላዋ ተከተላት፡፡

‹‹አረ ችግር የለውም ነበር እኮ››

"ግድ የለም፡በዛውም እግሬን ላፍታታ ብዬ ነው…የሽማግሌ ሰውነት በቀላሉ ነው የሚተሳሰረው››

‹‹አረ አንተ ሽማግሌ..?ከልጅህ የተሻለ ሞቃት ደምና የጋለ ፍላጎት የሚንተከተክብህ ጎረምሳ ነህ››አለችው፡፡

በንግግሯ ከት ብሎ ሳቀና"ለአነቃቂው አስተያየትሽ አመሰግናለው››አላት፡፡

‹‹ምንም አይደል?››

"ስለ አያትሽ መረጃ አለሽ?"ሲል ሌላ ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡

"በየቀኑ  ወደ  ሀኪም  ቤት  ስልክ  እደውላለሁ  …ምንም  ለውጥ  እንደሌለ  ነው የሚነግሩኝ….ሰሞኑን ብቅ ብዬ አያታለው ብያለው"

"እግዚያብሄር ቀላሉን እንዲያደርግላቸው ምኞቴ ነው… የሆነ ነገር ከፈለግሽ ምንም ሳታቅማሚ ንገሪኝ?"በዚህ ጊዜ ህንፃውን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡

አለም በመገረም  በትኩረት ተመለከተችውና ‹‹አቶ ፍሰሀ… ለምን ለእኔ እንደዚህ  ደግ ልትሆንልኝ ትሞክራለህ ?"ስትልየገረማትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

"ስለምወድሽ  እና  በዋናነት  በእናትሽ  ምክንያት  ነው  ።ማወቅ  ያለብሽ  እኛ  ከአንቺ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም።"

‹‹ለማንኛውም አመሰግናለው…››ብላ ለመሰናበት እጇን ዘረጋች.. ሲጨብጣት ተንጠራራችና ጉንጩን ስማ ፈዞ በቆመበት ወደመኪናዋ ሄደች……ወደቢሮው ሲመለስ ልጁ ጁኒዬር አሁንም ከመቀመጫው አልተንቀሳቀሰም ነበር…ቀጥታ ወደወንበሩ ሄደና ተቀመጠ፡፡

ጁኒየር ከተቀመጠበት ተነሳና የቢሮውን በር ከውስጥ ዘጋውና ወደውስጠኛው ክፍል ገብቶ የመጠጥ ጠርሙስና ብርጭቆ ይዞ መጣና  "ቦድካ ለመጠጣት ዝግጁ ነህ አባ?"ሲል ጠየቀ፡፡

አባትዬውም  በልጁ  ሁኔታ  ግራ  እየተጋባ"እስካሁን  አይደለሁም  ….ጠንካራ  መጠጥ ለመጠጣት ቀኑ በጣም ገና ነው።"ሲል መለሰለት፡፡

"ከመቼ ጀምሮ ነው መጠጥ ለመጠጣት ጊዜውን ከግምት ውስጥ ማስገባት የጀመርከው? "ከዛሬ"
ዝም ብሎ በራሱ ፍላጎት መጠጡን በሁለት ብርጭቆ ቀዳና አንዱን አባቱ ፊት ሌላውን ለራሱ ይዞ ቁጭ አለና ‹‹አባዬ…ላናግርህ እፈልጋለሁ።" አለው፡፡

"ስለምንድን ነው? ስለስራ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ ። ›› "ስለአለም ነው ."

" ስለአለም ምን?››

‹‹ወዴት እያመራች ነው….?ይሄንን ጉዳይ እስከምን ድረስ ነው የምትቆፍረው? ››

"የወንጀሉ ፍንጭ ላይ ለመድረስ በቁርጠኝነት እየሰራች ያለች ሴት ነች። ቆንጆ ሴት ብትሆንም ችኮ ነገር ነች። ለስላሳ ትመስላለች ነገር ግን አይደለችም። እሷ ጭቃ ሰብስቦ እንደያዘ ቦት ጫማ ከባድ ነች። ››አለው

ጁኒየር በቁጭት "ይህን አውቃለሁ" አለ።

" ታውቃለህ ግን ደግሞ እሷን ለማስቆም ምንም ነገር ስትሰራ አላየሁም።" "ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ?››

‹‹በፍቅር አንበርክካት››

‹‹እንዴት አድርጌ? ልክ እንደ ጎረምሳ አፍቃሪ ወደፍርድ ቤት የምትሄድበትን መንገድ በአበቦች …የቢሮዋን ጠረጴዛ በቸኮሌት ልሸፍነው…ለዛውም ገደብ ያለበት ፍቅር እንዴትነው የሚሰራው?"

"አዎ …ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ .. ትሰማለህ የእኔ ልጅ ። ጥሩ ሕይወት አለህ። በየዓመቱ አዲስ ሞዴል መኪና ትነዳለህ፣ ትልቅ በአልማዝ ያሸበረቀ ሮሌክስ ሰዓት ታስራለህ። ረብጣ ብር እያሲያዝክ ቁማር ትጫወታለህ።ግን ህይወት ማለት ያ ብቻ አይደለም..አሁን ትልቅ ሰው ሆነሀል…..እያንዳንዱ እንቅስቃሴህም የተለካ መሆን አለበት..አስብ… ለምርጫውም ከአንድአመት ብዙም ያልበለጠ ጊዜ ነው የቀረህ››

‹‹ግን ዝም ብንላት …..የት ድረስ ትጓዛለች?››

"ምንም በተጨባጭ ልታቀርበው የምትችለው ማስረጃ የላትም። ይህን የምታውቅ ይመስለኛል። ወደ ጨለማ ቀስቷን እየወረወረች በአጋጣሚ አንዱን አህያ ልመታው እችላለው ብላ እድሏን እየሞከረች ነው ያለችው። ይዋል ይደር እንጂ፣ ክንዷ ይደክማል። ቢሆንም ግን ገና ለገና እንደዛ ይሆናል በሚል ተስፋ እጅና እግራችንን አጣጥፈን ቁጭ ማለት የለብንም፡፡››

"ስለዚህ ምን እንደሚሰማኝ ታውቃለህ አባዬ። እንደዚህ አይነት ጩኸት አልወድም። ሴቶች በፍርድ ቤት ውስጥ ባይገቡ ጥሩ ነበር።"

"ወዴት ታስቀምጣቸዋለህ? በመኝታ ክፍልህ?"ተሳለቀበት፡፡

ጁኒየር ሳቀ። "እንደዛ ቢሆን ምንም ስህተት የለውም."

"ስለ ዋናው አቃቢ ህግ ግርማ በደንብ ነው የማውቀው….እሱ ለሀቅ እሞታው የሚል አደገኛ ሰው ነው፣ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፍርድ ማግኘት እንዲችል ነው ወንበሬ ላይ የተቀመጥኩት ብሎ የሚመፃደቅ ሰው ነው..እናም ይህቺ የእሱ ምክትል የሆነች አማላይ ወጣት ምንም ነገር ብታደርግ ከጓኗ ሆኖ ያግዛታል እንጂ አድቢ አይላትም››

"ሁሉንም ነገር ላይ በጥልቀት እያሰብክበት እንደሆነ አይቻለሁ" ሲል ጁኒየር በደረቅ አስተያየት ተናገረ።

"ምክንያቱም ካንተ በተለየ መልኩ ነገሮችን ለአጋጣሚ አልተዋቸውም።የማጣራት ስራ ሰርቼያለው፣እሷን በዙረያዋ ያሉትን ሰዎች ታሪክ በጥልቀት ፈትሻለው።››
ጁኒየር በሹክሹክታ "አባዬ አንተ እኮ ሁሌ እንዳስገረምከኝ ነው"አለው በአድናቆት ።

"ሁሌ ሊያጠቃህ የሚፈልገው ሰው ምን አይነት ካርዶች እንደያዘ ማወቅ አለብህ።ልጄ ሆይ አሸናፊ እጅ መያዝህ ምንም አይጠቅምህም።ይህቺን ልጅ በፍጥነት ተቆጣጠራት..ግን ደግሜ አስጠነቅቅሀለው በምንም አይነት ተአምር አልጋ ላይ ይዛሀት እንዳትወድቅ..”

‹‹ ይህ እኮ ነው የማይገባኝ አባዬ….ካፈቀርኳት ለምን አይሆንም..እንደውም ለምን አላገባትም፡፡››

አቶ ፍሰሀ የጁኒየርን ጉልበት መታ መታ አደረገና "እንደዛ ከሆነ በጣም መጥፎ ችግር ነው ሚያጋጥምህ….ምን አልባትም እድሜ ልክህን እስር ቤት እንድታሳለፍ ነው የማደርግህ?"አለው

ጁኒዬር በአባቱ ማስጠንቀቂያ ፍርሀት ተሰማው፡፡

‹‹ሰሎሜ ባሏ ከሞተባት በኃላ… ‹ ለእኔ ተስማሚ ሚስት ነሽ ..አፈቅርሻለው …እንጋባ›› ብዬት ነበር….ግን መልሷ የሚያሳምም ነበር….እናትዬውን በዛ ወቅት ማሳመን ያልቻልኩ አሁን እንዴት ብዬ ነው  ልጅዬውን ማሳመን የምችለው…ላድርገው ብልም አይሳካልኝም፡፡››

‹‹ ያኔ የአሥራ ስምንት አመት አፍላ ጎረምሳ ነበርክ ልጄ!..ሰሎሜ ደግሞ ሕፃን ያላት መበለት ነበረች።ባለፈው ነገር አትዘን….አሁን ግን የምልህን ስማ ››

‹‹ሰሎሜ ባታበላሸው …ዛሬ አለም የእንጀራ ልጄ ልትሆን ትችል ነበር "
28👍5
"ሌሎች ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ነበሩ."
ጁኒየር ዙሪያውን ዞረ። "እንደ ምን አይነት?"
"ያ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር፣ሌላ ጊዜ፤ሌላ ሰው. አለምን እንደ እናቷ አይደለችም. የበለጠ ውብ ነች ,…የማሰብ ብቃቷም በጣም የተሻለ ነው ፡፡ አንተ መሆን ካለብህ ሰው ግማሹን ከሆንክ  በህይወትህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልብህ ይልቅ በጭንቅላትህ ማሰብ ከቻልክ ያሳብከውን ታሳከዋለህ….እሷም ካንተ ፍቅር ከያዛት በኃላ የእናቷን ገዳይ ማሳደድ ትረሳውና አንተን ማሳደድ ትጀምራለች››

" እንደዛ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለው። ከእሷ ጋር የፍቅር ጫወታ ከመጀመሬ በፊት እርግጠኛ ለመሆን ፈልጌ ነበር ።አመንክም አላመንክም ሰሎሜን በጣም እወደት ነበር። እና ምን አልባትም ልጇንም ልክ እንደእሷ መውደድ እችል ይሆናል። ››

"አትተኛት እንጂ… በፈለከው መጠን ልትወዳት ትችላለህ?"

በቃ አባዬ ከዚህ በላይ ካንተ ጋር ማውራት አልችልም..በጣም እየተጨናነቅኩ ነው….››በማለት መቀመጫውን ለቀቀና ወደበሩ መራመድ ጀመረ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3921
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራታ ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// ስርጉት ወደአባቷ የጥናት ክፍል ስትገባ ። አባቷ ጠረጴዛው ላይ አቀርቅሮ አንድ ፋይል እያነበበ ነበር ›› "ዛሬ እረፍት የሆንክ መስሎኝ ነበር›› " አዎ ነበርኩ ግን አንዱ ማየት የሚገባኝ ጉዳይ ስለነበረ ይሄው እንደምታይኝ ፋይል እያገላበጥኩ ነው፡፡›› "በቅርብ በጣም ጠንክረህ እየሰራህ ነው.. ግን ደግሞ በጣም መጨናነቅ…»
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
አለም ወደ አፓርታማዋ  እደገባች የእጅ ቦርሳዋን እና ካፖርትዋን ወንበር ላይ አስቀመጠች
ዛሬ ከሰአት በኋላ ለዋናው አቃቢ ህጉ ደውላለት ነበር። እስካሁን እጇ ላይ ባስገባችው ግኝት ደስተኛ ሆኖ አላገኘችውም፡፡ ስራውና እርግፍ አድርጋ ወደ አዲስ አበባዋ እንድትመለስ ወይም እራሷን ካለፈው ታሪኳ ጋር እንድታስታርቅ ምርጫ አቀረበላት።እስከአሁን በሚጠበቀው ልክ ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ያለመቻሏ የሱ ቅሬታ አንዱ ምክንያት ነበር። ዛሬ ማታ ባላት ቀጠሮ መሰረት ለዋናው አቃቢ ህግጉ የአይን እማኙን አግኝታ ያገኘችውን መረጃ ስታቀርብለት ስሜቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነች።
ወደ መጠጥ ቤቱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በገባችበትን ቅጽበት ብዙም ተስፋ እንደማይሰጥ ማወቅ ነበረባት። አምፖሎቹ ቦግ ብልጭ ድርግም ከሚለው የሸዋ በር መጠጥ ቤቶች መካከል በአንዱ ነው የቀጠራት ። ከደረሰች በላ ወደ ውስጥ አልፋ ለመግባት በጣም አመንትታ ነበር።ግን ይሄ የያዘችውን ምርመራ ከስኬት ለማድረስ መክፈል ከሚገባት መስዋዕትነት መካከል አንዱ እንደሆነ ራሷን በራሷ አሳመነችና እግሮቾን እየጎተተች ወደውስጥ ገባች፡፡በክፍሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ትኩስ ስጋ እንዳየ ጥንብ አንሳ ወደ እሷ ተመለከቷት፡። የተወሰኑ ሴቶች ቢኖርም የእነሱ እይታ እንደውም ከወንዶቹ በተቃራኒ ሻካራ መስሎ ነው የተሰማት ፡፡ወደኋላ ዞራ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ትታ መሮጥ ፈለገች ..ግን ያደረገችው ወደግራዋ ታጥፋ ኮርነር አካባቢ ወንበር ስባ መቀመጥ ነበር፡፡

አስተናጋጆ መጥታ

‹‹ ምን ልታዘዝ ስትላት"

‹‹እባክሽ ነጭ ወይን "ስትል አዘዘች፡፡
በስልክ ያናገራት እና ድምፁን ብቻ የሰማችው ሰው የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ዓይኗን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው በማወናጨፍ ለመገመት ሞከረች ።ግን ….አይኗ ሲንከራተት እየተካታተሉ የነበሩ አንዳንድ ወንዶች ሁኔታዋን በተለየ መንገድ ትርጉም ሰጥተውት አስፀያፊ ምልክት ሲሰጦት ነው ያወቀችው። ከዛ በኋላ አይኖቾን አደብ አስገዛችና መጠጧን እየተጎነጨች አቀርቅራ ማሰላሰሏን ቀጠለች፡፡ የምትፈልገው ሰው እዛ ሆቴል ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ከሆነ የምትወደው አይነት ሰው ሊሆን እንደማይችል አሰበችና ተረበሸች፡፡

እያጨሰች ባትሆንም በዙሪያዋ ብዙ ሰዎች የተለያየ አይነት ሲጋር እያጬሱ ስለሆነ በጭስ ደመና ታፍናለች። እና አሁንም ብቻዋን እንደተቀመጠች ነው።በመጨረሻ፣ እሷ ስትመጣ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ የተጎሳቆለ አይነት ሰው ከመቀመጫው ተነሳና ወደ እሷ አቅጣጫ መጣ። ከእሷ ጠረጴዛ ጋር ከመድረሱ በፊት ካለው ሌለኛው ጠረጴዛ ላይ ወንበር ስቦ ተቀመጠና ይዞ የመጣውን ቢራ ከፊት ለፊቱ አስቀመጠ…የሁለቱ ወንበር መደገፊያ የተደጋገፈ ስለሆነ ጅርባቸው ተጋጥሟል ማለት ይቻላል..በዛ ላይ ሰውዬው ጥቁር ኮፍያ አድርጎ ፊቱን በከፍል ስለሸፈነ ምን እንደሚመስል በትክክል ልትለየው አልቻለችም፡፡፡

አንገቱን ወደኋላ ለጥጦ"ሰው እየጠበቅሽ ነው?"ሲል ተናገረ…ድምፁ የተለየ ይመስላል፣
"እኔ መሆኔን በምን አወቅክ ?ደግሞስ ይህን ያህል ጊዜ የፈጀብህ ለምንድን ነው?"ብላ በቀዝቃዛ ድምጽ መለሰችለት።

"ድፍረቴን እያሰባሰብኩ ነበር" አለ ከቢራው እየተጎነጨለት።

‹‹ጥሩ….ከእኔ ጋር አንድ ጠረጴዛ ለመጋራት ይሄን ያህል ትፈራለህ እንዴ?››

‹‹ህይወት እኮ ነው የያዝኩት… ለምን አልፈራም?››

"ይሁን እሺ…የምትነግረኝ ነገር እንዳለህ ገምታለው…ምንድነው ?።"

"የምትፈልጊውን ሁሉ ማውራት እንችላለን " የቢራ ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ከኪሱ ብር አወጣና አስቀምጦ ‹‹..ግን መጀመሪያ ከዚህ መውጣት አለብን›› አላት፡፡

‹‹ ጥሩ የእኔ መኪና ውጭ ነው …ነጭ ቪታራ ነች"
‹‹አውቃታለው››

‹‹ሂሳብ ከፍዬ መጣሁ.. እዛ ጠብቀኝ››
ቀድሞ መራመድ ጀመረ፡፡ሹክክ ብሎ ሆቴሉን ለቆ ተሰወረ….እሷም አስተናጋጁን ጠርታ ሂሳብን ዘጋችና ግማሽ የቀረውን የወይን ጠርሙስ ባለበት ጥላ ቦርሳዋን ይዛ ወደውጭ ወጣች ..ወደ መኪናዋ ቀረበች ….ምንም ሰው በአካባቢው አይታያትም…..ወደመኪናዋ ውስጥ ገባችና ..የውስጥ መብረቱን አብርታ መጠበቅ ጀመረች…….ምንም ብቅ የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ግራ ተጋባች…ተበሳጨች…ሰሞኑን ይደውልላት በነበረው ስልክ ደወለችለት…እንደተለመደው ይጠራል አይነሳም፡፡ማልቀስ ሁሉ አማራት..እዛው መኪናዋ ውስጥ ኩርምት እንዳለች ከአንድ ሰዓት በላይ አሳለፈች..በመጨረሻ ተስፋ ቆረጠችና አዲስ ወደ ተከራየችው አፓርታማ ነዳችው፡፡ከሀሳቧ ያባነናት የስልክ ጥሪ ድምፅ ነው… ከብስጭቷ ሳትወጣ ከአልጋዋ ተፈናጥራ ተነሳችና አነሳችው።

"ሀሎ።"

"እብድ ነው እንዴ ብለሽ አስበሻል አይደል ?"
የምታውቀውና የምትጠብቀው ድምፅ ነው።

"አንተ የት ነበርክ? ከእኔ ጋር ምን አይነት ጫወታ ነው አየተጫወትክ ያለኸው?መኪናዬ ውስጥ ተጎልቼ አንድ ሰዓት ያህል ስጠብቅህ ነበር.."

"ካንቺ ጋር ድብብቆሽ መጫወት ብፈልግ ኖሮ መልኬን እንድታይው አልፈቅድልሽም ነበር….ኩማንደሩ እዛው ነበር?"

"ምንድን ነው የምታወራው? ገማዶ እዚያ አልነበረም"

"የእኔ እመቤት ነበረ፣ በትክክል ነው ያየሁት። በቀጠሯችን መሰረት በቦታው ተገኝቻለሁ ግን ኩማንደር ገመዶ ከጀርባሽ በቅርብ ርቀት ተቀምጦ እያየሁት በአካባቢው መቆየት እና ከአንቺ ጋር ማውራቱን መቀጠል አልችልም… ፡፡››

‹‹ኩማንደሩ እየተከተለህ ነበር እንዴ?"

"እንዴት እንደዛ ያደርጋል….እኔ ምንም አይነት ህግ እልጣስኩም,…በተለይም ከፍሰሀ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች አንገቴ ስር ሲተነፍሱ. ደስ አይለኝም…ኩማንደሩ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍሰሀ ጋር ያበረ ወፍራም ሌባ ነው. የእሱ ዋነኛ ቀኝ እጁ ነው..ለማንኛውም አንቺን ተከትሎ የመጣ ይመስለኛል!!››

"ኩማንደሩ በአካባቢዬ እንዳለ አላውቅም ነበር. ሌላ ቦታ እንገናኛለን. በሚቀጥለው ጊዜ እሱ እንዳልተከተለኝ እርግጠኛ እሆናለሁ."ስትል ቃል ገባችለት፡፡

" እስቲ እናያለን።"

‹‹እናያለን ማለት ምንድነው…?ነው ወይስ የምትነግረኝ ነገር ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም፡፡.››

"ወንጀሉን ማን እንደፈፀመው አይቻለሁ እመቤት"

ተፈላጊነቱን ስታሳንስበት ተበሳጨ፡፡

"ታዲያ የት ነው የምንገናኘው?

እና መቼ?"

‹‹አሁን ህዝብ የተሰበሰበበት ቦታ አይደለም መገናኘት ያለብን ….ከቶታል ማደያ በቀኝ በኩል በምታስገባው መንገድ አንድ ሰማያዊ ቀለም የተቀባ ህንጻ አለ…. ከእሱ ፊት ለፊት
አንድ አሮጌ ሰማያዊ ባጃጅ ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለው። እኔ ከኃላ ውስጥ አለሁ..ዝም ብለሽ ትገቢያለሽ።"

‹‹ባጃጁ ያንተ ነው ማለት ነው››

‹‹ከየት አባቴ አምጥቼ…የጓደኛዬ ነው..ሰሞኑን ስለታመመ እኔ ደግሞ ስራ ፈት ስለሆንኩ እየሰራሁለት ነው፡፡››

"በቃ በሰዓቱ እገኛለሁ- ግን እስከዛው ቢያንስ ስምህን ልትነግረኝ አትችልም?"

"አይ አልችልም" ስልኩን ዘጋው። አለም ተሳደበች። ከአልጋው ወርዳ ወደ መስኮቱ ሄደች ፣ መጋረጃዎችን ገለጠችና ወደውጭ ተመለከተች…የጠቆረው እና ኮከቦች የተበተሉበት ሰማይን በትኩረት አየች፡፡መጋረጃዎቹን ዘጋች፣ ወደ ስልኩ ተመለሰች፣ እና በቁጣ ውስጥ እንዳለች ሌላ ቁጥር ላይ ደወለች። የዓይን እማኝን በማስፈራራቱ በኩማንደሩ ላይ በጣም ተናደደች፣ እየተንቀጠቀጠች ነበር።ቀጥታ እሱ ላይ ነበር መደወል የፈለገችው…ግን ደግሞ ቁጥሩን አታውቅም…..የሰዓቱ መምሸት ግድ አልሰጣትም ፡፡ስልኩ ተነሳ፡፡
49👍2🥰2
"ፖሊስ ጣቢያ ነው ."

‹‹አዎ..ምን ልታዘዝ?››ጎርናና የወንድ ድምፅ፡፡

"ኩማንደር ገመዶን  ፈልጌ ነበር."

"ይቅርታ በዚህን ሰዓት አይገኙም" ተባለች።

"አስቸኳይ ነው?"

" ምንም ልረዳሽ አልችልም የእኔ እህት….ችግር ላይ ከሆንሽ ከተረኛ ፖሊስ ጋር ላገናኝሽ?"

‹‹አይ ቀጥታ ኩማንደሩን ነው የፈለኩት››
"እንግዲያው መኖሪያ ቤቱ ነው..በግል ስልኩ ደውይለት፡፡." "እባክህ የቤቱን ቁጥር ትሰጠኛለህ ?"

"እኛ የግል ስልኩን ለመስጠት ፈቃድ የለንም ."

"እኔ የዞኑ  ረዳት አቃቢ ህግ  አለም ጎበና  ነኝ … ። አሁኑኑ  ከኩማንደሩ  ጋር መነጋገር አለብኝ። በጣም አስፈላጊ ነው። ››

ማብራሪያዋን ተከትሎ ያለምንም ማቅማማት ስልክ ቁጥሩ ተሰጣት። ኩማንደሩ በእሷ ላይ እያደረገ ያለውን ድብቅ ክትትል ወዲያውኑ ለማስቆም አስባ ነበር።ስልኩን አንስቶ ድምፁን ስትሰማ ግን የሷ ውሳኔ ጠፋ።

"አለም ነኝ."

"ምን ፈለግሽ?"

"ዛሬ ማታ ለምን ስትከተለኝ እንደነበር ማወቅ እፈልጋለሁ?." "እየተከታተልኩሽ እንደሆነ እንዴት አወቅሽ?"

".. አየሁህ።"

"አይ፣ አላየሺኝም። በዚያ ሆቴል ውስጥ ከሙስጠፋ ጋር ምን ታደርጊ ነበር?" "ከማንም ጋር አልነበርኩም..እኔ ብቻዬን እየጠጣሁ ነበር."

" አረባክሽ..ካልጠፋ ቦታ የዞኑ አቃቢ ህግ የሆነች ሴት የወንጀለኞች መገናኛ የሆነ ሆቴል ዘና ብላ መጠጥ እየጠጣች ማየት የሚገርም ነገር ነው››በማለት በፌዝ ጠየቀ።

"ለስራ ጉዳይ እዛ ተገኝቼ ቢሆንስ ምን ታውቃለህ ?ለማንኛውም እየተከታተልከኝ እንደነበረ አመንክ ማለት ነው?"
ኩማደሩ በግትርነት ዝም አለ።

"ይህ  ነገ ጥዋት ከምንወያይባቸው  በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው..መብቴን በህግ እንዳስጠብቅ አትገፋፋኝ።""

‹‹ይቅርታ.. ነገ የዕረፍት ቀኔ ነው።›› "መገናኘታችን የግድ ነው"

"ያ የአንቺ  አስተያየት ነው."

"እሺ እርፍትህን የት ነው የምታሳልፈው?"

" ነገ በእንስሰታ እርባታው ቦታ ፈረሶቼን እየተንከባከብኩ ነው የምውለው ።" " ቀኑን ሙሉ ።"

‹‹አዲስ ነገር ካልተፈጠረ ከ3 ሰዓት 9 ሰዓት እዛው ነኝ››

‹‹ጥሩ.. ደህና እደር ›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
////
ወደእሱ ከመቅረቧ በፊት ባለችበት ቆማ ስለሁኔታው በትዝብት ማየቷን ቀጠለች፡፡ የለበሰው ጂንስ ሱሪ ንፁህ ቢሆንም ፣ ከወደ ጫፎቹ ተቀዳዷል፣ ቢጫ ቀለም ያለው ቦት ጫማ ተጫምቷ.. በጭንቅላቱ ላይ ከሰሌን የተሰራ ሰፊ ኮፍያ አድርጓ ደንበኛ ገበሬ መስሏል፡፡ጓንት ያጠለቀው እጅን በፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ በፍቅር ያሻሸዋል…‹‹እርግጠኛ ነኝ ሰውን እንኳን በዚህ መጠን አይንከባከብም››ስትል በውስጧ አማችው፡፡

አንደኛውን እጁን በላይኛው የአጥር አግዳሚ እንጨት ላይ ተደግፎ ነበር፡፡ባለፈው ምሽት ቤቷ በመጣ ጊዜ ከሰውነቱ አጣብቆ አቅፎ ሲያስለቅሳት ነበር ። አካሏ ላይ ያሳረፋቸው እጆቹን ከእርቃን ሰውነቷ በቀጥታ እንዳይገናኝ በሰዓቱ ከሻወር ቤት ስትወጣ የለበሰችው ጋወን ነበር የከለከለው፡፡ በወቅቱ በጀርባዋ ላይ ጣቶቹን እያንቀሳቀሰ ስሜቷን ሲቆሰቁስ እንደነበረ ትዝ አለት ፡፡ልክ አሁን እየሆነ እንዳሆነ አሰበችና በሰውነቷ ሙቀት ሲፈስበት ተሰማት፡፡
"እረፍ ..አደብ ግዛ" ብሎ ፈረሱ ላይ ጮኸበት።

ድምፁ ልክ እንደ ባህሪያቱ ሁሉ ወንዳ ወንድ ነው።በአቅራቢያው የሚገኙ ፈረሶች ወደ አራት አካባቢ  ተከፋፍለው ይታያሉ፣

ሁሉም ሸኮናቸው መሬቱን እየቆፈሩ ስራቸው ፦፦፦ከቀረበላቸው የሳር ክምር ላይ እያነሱ ይበላሉ። የሚንቀጠቀጡት የፈረሶቹ የአፍንጫ ቀዳዳዎች የእንፋሎት መሰል ጭስ ያወጣል
።ኩማንደሩ አንዱን ፈረስ በተለይ ወደእሱ ስቦ መዳበሱን ቀጥሏል፡፡ ወደእሱ ቀረበችና ‹‹ስሙ ማን ይባላል››አለችው፡፡

የኩማንደሩ ጭንቅላቱን ቀና ብሎ ተመለከታት፡፡ "ሴት ነች።"ሲል መለሰላት፡፡

"ኦ. ነው እንዴ…ወንድ መስላኝ ነው "አለችና ጀርባዋን መዳበስ ጀመረች፡፡" ያንተ ነች?" "አዎ"
‹‹ይገርማል.. አንድ የፖሊስ መኮንን የራሱ ፈረሶች ኖረውት ሲንከባከብ››

‹‹ምን ይገርማል…ፖሊስ ከመሆኔ በፊት በልጅነቴ ጀምሮ እዚህ እሰራ ነበር…የራሴ የሆኑ ከብቶችና ፈረሶች ይኖሩኝ የጀመረው የፖሊስ መኮንን ከመሆኔ በፊት ነው…እንደውም ፖሊስ ባልሆን ኖሮ አሁን ካሉኝ ነገሮች በጣም በበለጠ ይኖረኝ ነበር››

‹‹አዎ..ትክክል ነህ…እኔም እንደዛ ነው የማምነው…ግን ታዲያ ለምን ፖሊስ ለመሆን ፈለክ?››

‹‹ምክንያቴን ለአንቺ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለሁም››አለና ከወንዶቹ ፈረሶች መካከል ነጭ እና ጥቁር ቀለም ኖሮት ቡራቡሬ ገፅ ያለውን ውብ ፈረስ ሉጋሙን በአፉ ከቶ ከመሀከል ጎትቶ አወጣው፡፡ፈረሱም እንዳደረገው ሲሆንለት አየችና ተገረመች፡፡

"ከእሱ ጋር እውነተኛ ግንኙነት ያለህ ይመስላል." አለችው አለም።

"ሲወለድ ስሩ ነበርኩ ..ሙሉ እድሜውን በፍቅር ተንከባክቤዋለው….ስለዚህ ቢወደኝ አይገርምም፡፡››

‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኃላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
50👍12
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ /// አለም ወደ አፓርታማዋ  እደገባች የእጅ ቦርሳዋን እና ካፖርትዋን ወንበር ላይ አስቀመጠች ዛሬ ከሰአት በኋላ ለዋናው አቃቢ ህጉ ደውላለት ነበር። እስካሁን እጇ ላይ ባስገባችው ግኝት ደስተኛ ሆኖ አላገኘችውም፡፡ ስራውና እርግፍ አድርጋ ወደ አዲስ አበባዋ እንድትመለስ ወይም እራሷን ካለፈው ታሪኳ ጋር እንድታስታርቅ ምርጫ…»
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኋላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››

የምፀት ፈገግታ ፈገግ አለና‹‹ለፈረሶችም ሆነ ለሰዎች የሚገባቸውን ነው ማደርገው….››አለና አጥሩ ላይ የተንጠለጠለውን ኮርቻ በማንሳት ፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ አሳሰረውና የፈረሱን ሉጋም ይዞ ወደመውጫው መሄድ ጀመረ፡፡
ግራ ተጋብታ

"ወዴት ትሄዳለህ?"ስትል ጠየቀችው

" ትንሽ መጋለብ ፈልጋለው"

ከንዴቷ አንፃር ማልቀስ አማራት ‹‹ላናግርህ እፈልጋለሁ..ለምን እንደመጣሁ እያወቅክ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው..?›› አለችው

ፈረሱ ላይ ወጣና ወደእሷ ቀረበ…እጁን ዘረጋላት….ግራ ተጋብትና በቆመችበት አይኖቾን አቁለጨለጨች….

‹‹እጅሽን ስጪኝ››አላት…..ዝምብላ ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቀለችለት.. አጥብቆ ያዛትና ወደላይ ጎተታት…ጥንካሬው አስገረማት….እርካብ ላይ እግሯና አኖረችና እንጣጥ ብላ በመውጣት ከጀርባው ፈረሱ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ከዛ ለፈረሱ ሉጋሙን ለቀቅ ሲያደርግለት ፈረሱ እየሰገረ ወደፊት ተስፈነጠረ ፡፡በፍራቻ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው….የኮረኮንች መንገዱን ይዞ ወደ ከተማዋ መውጫ ሽምጥ መጋለብ ጀመሩ….፡፡
"ትላንትና ማታ በቡና ቤት ውስጥ ከማን ጋር ነበር የተገናኘሽው?"

"ይሄ የኔ ጉዳይ ነው ኩማንደር …ለምን ተከተልከኝ?"ልትጠይቀው የምትፈልገው ብዙ ጥያቄዎች ነበራት፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ የፈረስ እንቅስቃሴ ከተቀመጠችበት እንጣጥ ብላ ጀርባው ላይ ስትለጠፍበት ስለነበር አእምሮዋን በጀመረው ሀሳብ ላይ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ ከባድ ሆነባት። እንደምንም ወደ አእምሯዋ የመጣውን የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቀችው።

"አንተ እና እናቴ እንዴት የቅርብ ጓደኛሞች ሆናችሁ?"

"አብረን ነው ያደግነው" አለ በንቀት። ተንፋሽ ወሰደና ቀጠለ"ት/ቤት መጫወቻ ሜዳ ላይ ተጀምሮ በእድሜ እየገፋን ስንሄድ ተሻሻለ"

"አስቸጋሪ ሆኖ አያውቅም?"

"አይ አንዳችን ከሌላችን የምደብቀው ምንም ምስጢር አልነበረንም. እንዲያውም ያንቺን ካሳየሺኝ የእኔንም አሳይሻለው እያልን እንጫወት ነበር."አለና ፈገግ አለ።‹‹በአጠቃላይ በእኔ እና እሷ መካከል አይነኬ የተባለ የውይይት ርዕስ አልነበረም ።››ሲል አከለበት፡፡

"ያ አንድ ሴት ልጅ ከሌላ ሴት ጋር የሚኖራት አይነት ግንኙነት አይደለምን?"

‹‹ብዙውን ጊዜ ግን ሰሎሜ ብዙ የሴት ጓደኞች አልነበራትም, አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በእሷ ይቀኑ ነበር."

"ለምን፧"

አለም መልሱን ቀድሞውንም ብታውቅም ከእሱ አንደበት መስማት ፈለገች፡፡ "በአንተ ምክንያት ነበር አይደል? ካንተ ጋር የነበራት ወዳጅነት?"
"ምናልባት ሊሆን ይችላል, ዋናው ጉዳይ ግን እሷ በጣም ቆንጆ ነበረች…በዙሪያዋ ያሉ አብዛኞቹ ልጃገረዶች እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ተቀናቃኝ ነበር የሚቆጥሯት፡፡….ቆይ አንዴ።›› ፈረሱን አቅጣጫ ከመቀየሩ በፊት አስጠነቀቃት እና ፈረሱ ጓድጓዳ አካባቢ ሲረግጥ ወደ ፊት ገፋት፣ እሱ ላይ ተለጠፈች። በደመ ነፍስ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው።

"ፈረስ ቁልቁል ሲወርድ ወደፊት መንሸራተቱ የሚጠበቅ ነው….››
ስትረጋጋ“እናቴ ሁሉንም ሚስጥሮቾን እያመጣች ለአንተ ትዘረግፍ እንደነበረ እየነገርከኝ ነው?›› ብላ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ, እንደዛ ነበር የምታደርገው…እሷ እንደአንቺ አይነት ውስብስብ ሴት አልበረችም…ለምሳሌ አንድ ቀን ምንም ሳትነግረኝ ከትምህር ቤት ቀረች እና የሆነ ችግር እንዳለ አውቄ ነበር...ተጨንቄ ስለነበር በእረፍት ወደ ቤቷ ሄድኩ. አያትሽ በሥራ ላይ ስለነበሩ ሰሎሜን ብቻዋን እያለቀሰች ነበር ያገኘዋት…ፈርቼ ምን እንደሆነች እስክትነግረኝ ድረስ ጨቀጨቅኳት።"

‹‹ጉዳዩ ምን ነበር?"

‹‹ የወር አበባዋን ለመጀመሪያ ጊዜ መቶባት ነበር….አያትሽ የወር አበባን በተመለከተ የሀጥያት ፍሬ እና እርግማን እንደሆነ የሚተርኩ አስፈሪ ታሪኮች ነግረዋት ስለነበር በጣም አዝና ነበር ያገኘኋት ፡፡ እንዴት ነው አያትሽ ለአንቺም እንደዛ አይነት አስፈሪ ታሪኮችን ይነግሩሽ ነበር?››
አለም ወገቡን ሳትለቅ አንገቷን እንደምንም ቀና አደረገችና‹‹ያን ያህል የሚረብሹ አይነት ታሪኮችን ነግራኝ አታውቀኝም… ምናልባት አያቴ እኔን ማሳደግ በጀመረችበት ጊዜ ተሻሽላ ሊሆን ይችላል።ለአቅመ አዳም በደረስኩበት ጊዜ በቀላሉ ነው የተቀበልኩት።››

ፈረሱ ግልቢያውን እስኪያቆም ድረስ አለም ያሉበትን ቦታ አላስተዋለችም ነበር፡፡መኖሪያ ቤቱ ደርሶ ነበር ያቆመው፡፡

" ከዛስ እንዴት ሆነ?"

‹‹አፅናናኋት እና የወርአበባ ማለት ሴትነቷ በይፋ የታወጀበት ድንቅ ቀን እንደሆነ እና መደስት እንጂ ማልቀስ እንደማይገባት ነገርኳት።››

"ሰራ ታዲያ?"

"እንደምገምተው አዎ። ማልቀሷን አቆመች"
'እና...?'' አለም የታሪኩን በጣም አስፈላጊ ክፍል እንዳልነገራ ስላወቀች  እንዲቀጥል አነሳሳችው።
"ከዛማ.. በቃ ።››አለና ቀድሞ ከፈረሱ ላይ በቀላሉ በመውረድ ‹‹ እግርሽን አንሺው።" አለና እሷን ለማውረድ እጁን ዘርግቶ በጠንካራ እጁ ወገቡ ላይ አቀፋትና ወደ መሬት አወረዳት።

ከእናቷ ጋር ሲሳሳም ሚያሳየውን ፎቶ መመልከቷን አስታወሰች ። "ለቅሶዋን ካቆመች በኃላ ሳምካት አይደል?"

በትከሻው የማይመች እንቅስቃሴ አደረገ። "ከዚያን ቀን በፊትም ስሜያት ነበር።" "ግን ያ የመጀመሪያው እውነተኛ መሳም ነበር አይደል?"
እሷን በጥልቀት ተመለከታትና ወደ ቤቱ  በረንዳ ወጥቶ በሩን ገፋው ። ወደኃላ ዞር አለና

‹‹መግባትም ሆነ አለመግባት የአንቺ ጉዳይ ነው።››አለና ክፍት አድርጎ ተወው… ወደ ውስጥ ገብቶ ጠፋ, ተስፋ የቆረጠች ቢሆንም ግን ደግሞ ተጫማሪ የማወቅ ጉጉት ስላላት ተከተለችው።
መየፊት ለፊት በር በቀጥታ ወደ ሳሎን ተከፈተ። በግራዋ በኩል ባለው በር በኩል የመመገቢያ ቦታ እና ኩሽና ማየት ችላለች። በተቃራኒው በኩል ያለው የመተላለፊያ መንገድ ወደ መኝታ ክፍል ይወስዳል፣ እሱም ሲያወራ ትሰማለች። የሳሎኑን በር ዘጋች፣ መነጽርዋን አውልቃ ዙሪያዋን ተመለከተች።ቤቱ የወንደላጤነት ወዝ ነበረው …ፈሪኒቸሮቹ መጠነኛና ቅልብጭ ያሉ ናቸው፡፡በግራ ግድግዳ ያለው መደርደሪያ ላይ ያሉት መጻሕፍቶች የተዘበራረቁ ነበሩ፣ ፡፡

"ቡና ትፈልጊያለሽ?"

"ባገኝ ደስ ይለኛል።››

ወደ ኩሽና ገባ። የቀዘቀዙ እግሮቿ የደም ዝውውር እንዲስተካከል እያፍታታች በክፍሉ ውስጥ መዞሯን ቀጠለች። ከመጽሐፍ መደርደሪያው በላይ ወደተቀመጠው አንድ ረጅም ዋንጫ ቀልቧ ተሳበ። በላዩ ላይ የኩማንዱሩ ስም እና ቀኑ በግልፅ ፊደላት ተቀርጾበታል።
"ይህ ትክክለኛው ቀለም ነው?" ዘወር ስትል አንድ ኩባያ ቡና ይዞላት ወደ እሷ እየቀረበ ነበር።

"አመሰግናለሁ።" ብላ ተቀበለችውና …ጭንቅላቷን ወደ ዋንጫው በማዘንበል "ይሄ ያንተ ምርጡ አመት አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"ምን አልባት"

"ምነው ?እርግጠኛ አይደለህም?"

ወደ ወንበሩ ሄደና ተቀመጠ ፡፡ "ያኔ እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር እና አሁንም ድረስ በወቅቱ የሚደግፈኝ ጥሩ ቡድን እንደነበረኝ ይሰማኛል።ሌሎች በእጩነት የቀረቡት ተጫዋቾችም እንደኔ ዋጋ ያላቸው ነበሩ።"

"ለምሳሌ ጁኒየር?"

"አዎ እሱም ከነሱ አንዱ ነበር " ሲል መለሰ፣

‹‹ሽልማቱን ያሸነፍከው አንተ እንጂ ጁኒየር አይደለም።››ዓይኖቹ ወደሷ አፍጠጠ፡፡
"ውድ አቃቢህግ ከእኔ ጋር የጀመርሽውን ጫወታ አቁሚ እና በአእምሮሽ ያለውን ነገር ቀጥታ ተናገሪ።"
40👍4🔥1
እሺ በተሸፈነው የዋንጫ ክንድ ላይ ተደግፋ በጥንቃቄ ተመለከተችው፣ “በወቅቱ ኮከብ ግብ አግቢም ኮኮብ ተጫዋችም መሆን ያለብህ አንተ ነበርክ…..ግን ጁኒየር ኮከብ ተጫዋች ሆኖ እንዲመረጥ አሻጥር ሰራህ.. እንደዛ ለምን አደረክ ?›› ስትል ጠየቀችው።

"እሱን ጠይቂው"

"ምናልባት ጠይቀው ይሆናል… ፍላጎት ካለው አባትዬውንም እጠይቀዋለሁ።ግን የሽልማት ግብዣው በተካሄደበት ምሽት አቶ ፍሰሀ የበለጠ ኩራት ተሰምቶት ነበር አይደል?ለእሱ ኮኮብ ተጫዋች ተብሎ መሸለም ያንተ ሚና ምን ነበር…ለዛ ውለታህ ምን ተከፈለህ

?እርግጠኛ ነኝ ሽልማቱ ለአንተ ነበር የሚገባው."

"የፈለግሽውን እመኚ። ለእኔ ምንም ለውጥ አያመጣም።" የቡናውን ኩባያ ባዶ አድርጎ ከፊቱ ባለው ትሪ ላይ አስቀምጦ ቆመ።

"ለመሄድ ዝግጁ ነሽ?"ሲል ጠየቃት፡፡

እሷም ቡናዋን አስቀመጠች፤ነገር ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረገችም.

"ይህ ጉዳይ መነሳቱ ለምንድነው የሚረብሽህ ?"አለችው፡፡

"መረበሽ አይደለም፤አሰልቺ ነው." ፊቱን ወደ እሷ አስጠጋ ።… "ያ ዋንጫ ሃያ አምስት አመት  ያስቆጠረ የተበላሸ ቆሻሻ ነው… አቧራ ከመሰብሰብ በቀር ምንም የማይጠቅም"

"ታዲያ እነደዚህን ከሆነ ይህን ሁሉ ዓመታት ለምን በክብር አስቀመጥከው?" "አየሽ አሁን ምንም አይነት ዋጋ የለውም.፡፡››

"ግን ያኔ ዋጋ ነበረው።"

‹‹አዎ ..ኮሌጅ ለመግባት የሚያስችለኝን ገንዘብ የማገኝበት መንገድን ለማመቻቸት ይረዳኛል ብዬ አስቢ ነበር፡፡››

‹‹እና እንዴት ሆነ?››

‹‹ያገኘሁት ገንዘብ ለዛ በቂ አልነበረም››

"ምን አረግክ…ኮሌጅ ገብቶ መማሩን ተውከው፧"

‹‹አይ ተማርኩ››

"ክፍያውን እንዴት ሟሞላት ቻልክ፧"

"ብድር"

"የመንግስት ብድር?"

"የለም የግል" ሲል መለሰ። "ገንዘቡን ማን አበደረህ አቶ ፍሰሀ ?"

"አዎ ? ግን ለሶስት አመት ወጪያ ያበደረኝን እያንዳንዱን ሳንቲም መልሼለታለው›› "ለሱ በመስራት?"

"አዎ …ፖለስ ማሰልጠኛ እስክገባ ድረስ ለእሱ ነበር የምሰራው›› "ፖሊስ ቤት የተቀጠርከው..ከእሱ ስር ራስህን ነፃ ለማውጣት ነው?›› መስመር በለቀቁ ጥያቄዎቾ ተገርሞ ዝም አላት፡፡

‹‹መልስልኝ እንጂ?››

‹‹አይ መጀመሪያ ወታደር ቤት ነው የተቀጠርኩት…በባድመ  ጦርነት ለአንድ አመት ተሳትፌለው…ጦርነቱ አብቅቶ እድሉን ሳገኝ ወደፖሊስ ቤት ቀየርኩ፡፡››

‹‹ለዛ ነዋ የፖሊስ ሳይሆን የወታደር ፈርጣማ ሰውነት ያለህ …?ጁኒየርስ እንደ አንተ ወታደር ቤት አገልግሏል?"

"ጁኒዬር ወታደር ? ይህን በዓይነ ሕሊናሽ ማየት ትችያለሽ ?" ብሎ በሀሳቧ ሳቅ ።

"ለምን ታዲያ ዩኒፎርም የለበሱ ፎቶዎች  የሉህም?" ግድግዳው ላይ የተሰቀሉትን ስዕል እየተመለከተች ጠየቀችው፡፡

" የጦርነት ጊዜ ምንም ትውስታ እንዲኖረኝ አልፈልግም።"አለና ከእርሷ ወደ ኋላ ተመለሰ፣ ኮፍያውን፣ ኮቱን አነሳ፣ ከዚያም ወደ መግቢያው በር ሄዶ ከፈተው።አለም ባለችበት ቀረች።

"አንተ እና ጁኒየር የጋራ ፎቶ አላችሁ? ››

"ስለ እኔ ምንም አታውቂውም። ››አላት በንዴት

‹‹ምን ያበሳጭሀል..ቀላል ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩህ… ብዙ ሰዎች ያለፈ ጊዜያቸውን በማስታወስ ደስ ይላቸዋል."

" እኔ ደግሞ እደዛ አይደለሁም… ያለፈውን ትቼ ወደፊት መሄድ እፈልጋለሁ." "ምክንያቱም ያለፈውን ማስታወስ ይጎዳሀል?"

" አንዳንዶቹን ታሪኮቼን ማስታወስ …አዎ ይጎዳኛል..."

"ለምሳሌ እናቴን ለመጀመሪያ ጊዜ የሳምክበትን ጊዜ ማስታወስ ይጎዳሀል?"

ወደ ወስጥ ተመልሶ ተራመደ..ወደእሷ ተጠጋ  … ወገቧን በእጆቹ ያዘ.. እና ከሰውነቱ ለጠፋት" አንቺን ብስምሽ በጣም እንደሚያስደስትሽ  እርግጠኛ ነኝ፣ አይደል አቃቢት ህግ?"
ምንም ማለት አልቻለችም።"እንግዲህ፣ እናትሽ እንዴት እንደሳምኳት ለማወቅ የምትጓጊ ከሆነ ምናልባት አንቺ በራስሽ ልታጣጥሚው ትችያለሽ። ››አለና አንገቱን ወደታች ዝቅ አደረገና ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ አጣበቀ፡፡ በአፍንጫዋ መተንፈስ ጀመረች።  እየሆነ ያለውን ነገር ስትረዳ ሁለቱንም እጆቿን ደረቱ ላይ አጥብቃ ያዘች። ጭንቅላቷን ወደ ጎን ልታዞር ብትሞክርም በአንድ እጁ መንጋጋዋን አጥብቆ ያዘው። ከንፈሮቹ በልዩ ሁኔታ አሻሸው፣ ከዚያም ምላሱን በመካከላቸው ሰነቀረው። በደንብ ሳማት፣ ትንሽ የመገረም እና የመደነቅ ጩኸት አሰምታ ሊሆን ይችላል። ሰውነቷ ከሱ ጋር ለመስማማት ተንጠልጥሎ ሊሆን ይችላል።.ነገር ግን በጭኖቿ መካከል ያለውን ስሜት፣ ወይም የጡቶቿ መንቀጥቀጥ፣ መቆጣጠር አልቻለችም። ብርቅዬ እና  አስደናቂውን  የአፉ  ጣዕም፣  በህይወቷ  ዘመን  የምትረሳው  አይነት  አይደለም።በተከታታይ ለስላሳ እና ርጥበታማ ከንፈሯን ሳማት… የከንፈሮቿን ጥግ በምላሱ ጫፍ ዳበሳቸው፣ እንደምንም ለቀቃት እና አንገቱን ቀና በማድረግ የደነዘዙ አይኖቿን ተመለከተ።ራሷ ግራ ተጋባችባት። በድጋሚ ወራሪ ምላሱ ወደአፏ ውስጥ አስገባው….ሰውነቷን ንዝረት መቋቋም ስላልቻለች በጥፍሯ ቆመች…..በአንገቷ ዙሪያ የሉትን እጇቾን ይበልጥ ጨመቀችውና ይበልጥ ተለጠፈችበት…። ጡቶቾ ሲጨፈለቁ ከዚህ በፊት ተሰምቷት የማያውቀው ጣፋጭ ህመም ተሰማት ፣ ነገሮች ከዚህ በላይ እዲያድጉ ፈለገች…. እሱ ግን ድንገት ከእንቅልፉ እደነቃ ሰው አይነኖቹን ገለጠና ለቀቃት እና ሰውነቱን ከሰውነቷ አላቆ ወደ ኃላው ጠጋ  አለ …በመሀከላቸው ክፍተት ፈጠረ፡፡
"ልክ እንዳታለልኩሽ እንዳይሰማሽ፣ክብርት አቃቢ ህግ.. ከአሁን በኋላ ፣ ያሉሽን ጥያቄዎች በፍርድ ቤት በኩል እንድታቀርቢ እመክርሻለሁ።ያ ለአንቺ የበለጠ አስተማማኝ ነው።"አላት
ምንም ሳትናገር ቤቱን ለቃ ወጣችና መኪናዋን አስነስታ አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡ከእሱ ለመለየት ስለፈገች ብቻ ሳይሆን እናትሽን ማን እንደገደላት አውቃለው… ካላት ሰውዬ ጋርም ለመገናኘት ቀጠሮ ስለላት ነበር፡፡

ቦታው ላይ እንደደረሰች በሩቅ የነገራትን አሮጌ ባጃጅ መኪና ተመለከተች….ውስጡም አንድ ሰው እንዳለ እየታያት ነው፡፡አሁን የእናቷን ትክክለኛ ገዳይ ማን እንደሆነ የምታውቅበት ደቂቃ መቃረብን አሰበችና፣ደስታም ፍርሀትም ተሰማት…፡፡

‹‹የእናቴ ገዳይ ከደቂቃዎች በፊት እላዩ ላይ ተጣብቄ ስስመው የነበረው ሰው ቢሆንስ…?ምንድነው የማደርገው?››ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡መልሱን የመገመት ድፍረት እኳን አልነበራትም፡፡መኪናዋን ለቃ ወረደችና አካባቢውን በጥንቃቄ ቃኘች፣ከዛ ወደ ባጇጅ ተራመደች….ሰውዬው ከጀርባ ተቀምጦ ማየት ትችላለች ፣ ጫማዎቿ መሬቱን ሲረግጡ የሚያሰሙት ድምጽ በጇሮዋ ያንቃጭላል ። አካባቢው በጨለማ እንደተዋጠ ነበር… ሌላ ምንም አይነት መኪና በአቅራቢያ አልቆመም።አለም ባጇጆ አጠገብ ስትደርስ ድንጋጤን ተሰማት። ወደውስጥ ገባች…።የአይን ምስክሯ አስቀያሚ ትንፋሽ ወደውስጦ ገባ ። እሱ ደንዝዞ ነበር፣ ።‹‹በተደጋጋሚ ገላውን መታጠብ አለበት››ስትል አሰበች…. አትኩራ አየችው…በጣም ደነገጠች..አንገቱ ወደኃላ ታጥፎ ይታያል…አይኖቹ ፈጠው ያስፈራሉ በአንገቱ ዙሪያ ያለው ገመድ አንገቱ ስር ጠልቆ ገብቷል …እሱ ሞቷል።
ደንዝዛ ለተወሰነ ጊዜ ባለችበት ተቀመጠች….ከዛ በደመነፍስ ባጇጆን ለቃ ወጣች። እግሯ መሬት ላይ ቢያርፍም መንቀሳቀስ ግን አልቻለችም፡፡እየተንቀጠቀጠች ነው…በፍርሃት
33👍6
ጮኸች እና. …ጨለማው ውስጥ ሆና ቃተተች…ድንገት ሁለት የፊት መብራቶች ግንባሯ ላይ በራ ፣በሁለት እጆቾ ፊቷን ለመከለል ሞከረች .. መሮጥ ፈለገች.. ምንም ነገር ከማድረጓ በፊት አንድ ሰው ከኃላዋ ተንደርድሮ መጣና ክንዷን ያዛት… ዞር ብላ ስታየው ያልጠበቀችው ሰው  ነው "ገመዶ!" እፎይታ እና ሽብር በተቀላቀለበት ስሜት አለቀሰች፡፡

"እዚህ ምን ታደርጊያለሽ?"
"ተመሳሳይ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር። ያ ሰውዬ…ሞቷል" አለች፣ የሚወዛወዝ ጣት ወደ ባጇጆ እየጠቆመች፣

"አዎ አውቃለሁ።"

"ታውቃለህ?"

"ስሙ ሙስጠፋ ደደፎ ይባላል። ለአቶ ፍሰሀ ይሰራ የነበረ ሰው ነው።››

"በኢየሱስ…ምን አይነት ውጥንቅጥ ነው?"

"አይ በነፍስ ግድያ ተጠርጥሪነት የማልወስድሽ ምክንያት ሰውዬው ጉሮሮው ታንቆ መገደሉን ደውሎ የነገረን ምስክር አንቺ ከሞተ በኃላ ወደ ባጇጆ እንደገባሽ ስለነገረን ነው."

"ሲገደል ያየ ሰው አለ?"

"ትክክል"

"ገዳዩ እኔ እሱን ለማግኘት ወደዚህ እንደምመጣ  የሚያውቅ ይመስለኛል …አንተ እንዴት በፍጥነት እዚህ ደረስክ?"

"እሱን አንገቱ ላይ ገመድ ጠምጥሜ ያነቅኩት ይመስልሻል?" ብሎ ሳቅ ፡፡ከዛ አንድ ምክትሉን ጠራና። ‹‹ሳጂን አቃቢት ህጓን ወደ ቤቷ መልሷት" ሲል አዘዘው፡" ወደ ቤቷ መግባቷን እርግጠኛ ሁን››ሲል አከለበት፡፡

"እሺ ጌታዪ።"

"እስኪ ነጋ ድረስ በአካባቢው ሆኖ የሚጠብቃት ሰው መድብ የትም እንደማትሄድ እርግጠኛ ሁን."

ምክትሉ ወደ መኪናዋ እንድትመለስ ከመፍቀዷ በፊት አለም እና ኩማንደሩ የጥላቻ እይታ ተለዋወጡ

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3312🤔5
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ነጋ አልነጋ ብላ ጥዋት ወደቢሮዋ ከመግባቷ በፊት ቀጥታ ወደኩማንደሩ ቢሮ ነው የሄደችው፡፡እንዳጋጣሚ እሱም በማለዳ እንደገባ ነገሯት፡፡ቀጥታ ወደቢሮ መራመድ ጀመረች፡፡
ኩማንደር ወደቢሮ በጥዋት ቢገባም ከጥቂት ሰኮንዶች በላይ በአንድ ሀሳቡ ላይ ትኩረት አድርጎ ማሰብ አልቻለም። የአለም ምስል በምናቡ ብልጭ ድርግም እያለ እየረበሸው ነው፡፡ወንበሩን ትቶ ወደ መስኮቱ ሄደ። መጋረጃውን ገልጦ ወደ ውጭ መመልከት ጀመረ፣የጥዋቷ ፀሐይ ደማቅና ብሩህ ነች። ትላንትን ከአለም ጋር ያሳለፈውን ጊዜ አስታወሰ
.. እሷን ጎትቶ ፈረስ ላይ ሲያወጣት እና ተፈናጥራ በእጇቾ ወገቡን ጨምድዳ ስትይዝ… ጀርባዋ ላይ ስትለጠፍበት …አናዳጅና አብሻቂ ጥያቄዎቾን ስታዥጎደጉድበት በወቅቱ ያየባት ብልሀትና ብልጠት አስገርሞታል….በተቃራኒው ደግሞ ማታ የሙስጠፋ ሬሳ ጋር በዛ በጭለማ ቦታ ሲያገኛት በጣም የፈራች ፤የምትንቀጠቀጥና ፈሪ ሴት ሆና ነው ያገኛት፡፡

‹‹ምናልባት የሙስጠፋ አሰቃቂ ግድያ ስለእናቷ ግድያ የምታደርገውን ምርመራ ፈርታ እንድታቆም ያስገድዳት ይሆናል። ምናልባት ሻሸመኔን ትታ ወደ ኋላ ላትመለስ ወደ አዲስአባዋ ትመለስ ይሆናል።››ሲል አሰበ፡፡ይህ አጋጣሚ ሊያስደስተው በተገባ ነበር። ግን አላስደሰተውም። በእሷ እና በራሱ ላይ የበለጠ ተናደደ።ትላንትን ከእሷ ጋር መሳሳሙ የደደብ ሰው ተግባር እንደፈፀመ ነው የተሰማው፡፡በወቅቱ ራሱን መቆጣጠር ፈልጎ ነበር። ግን ለስሜቱ ተገዢ ሆኖ ማድረግ የሌለበትን ነገር አድርጎል፡፡በህይወቱ እንዲህ እንዲያደርግ ያስቸለው አንድ ሌላ ሴት ብቻ ነበረች እሷም ሰሎሜ ነች። ገረመው። ለዓመታት አላሰበውም ነበር ፣ ግን አሁን በአእምሮው ውስጥ ግልፅ ሆኖ እየታየው ነው።

ሰሎሜ ትወደው ነበር።እሱም ወዷት ነበር። አንድ ቀን ሊጋቡ ተስማምተው ነበር….ፍቅራቸውን የሚያጨነግፍ ምንም አይነት እንቅፋት በመሀከላቸው እንደማይፈጠር እርግጠኞች ነበሩ….ገመዶ አይኑን በድካም እያሻሸ ወደ ጠረጴዛው ተመለሰ እና ወንበር ላይ
ተቀመጠ ። አለም ለዓመታት ውስጡ የቀበረውን  ትዝታ እየቆሰቆሰች እንዲያስታውስ እየደረገችው ስለሆነ ተበሳጨባት ፡፡ትናንት እሷን ሲስማት  ሊቀጣት እና ሊያበሳጫት ነበር አላማው ። ነገር ግን ውጤቱ ተገላቢጦሽ ነበር የሆነበት… ።ከንፈሯ ልክ እንደእናቷ በዛ መጠን  ይጣፍጣል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ያ ጣፋጭነት አሁንም በምላሱ ላይ ቀርቷል. ድድር ጡቶቿ በዛ ልክ ስሜት ቀስቃሽ እና ለስላሳ እንደሚሆኑ እንዴት ሊገምት ይችላል? ለወደፊቱ ሁሉንም እቅዶቹን ማበላሸቷ እንደማይቀር ገመተ። ህልሙን እውን ለማድረግ በጣም ቅርቦ ነበር። ሊደርስ  ጥቂት ነበር የቀረው….።ህይወቱን በሙሉ በትጋት የሰራበት ቦታ ለመሆን አንድ የመጨረሻ እርምጃ ነበር የቀረው።በዚህ መጥፎ ጊዜ ነው እንቅፋት ሆና ከፊቱ የተገተረችው፡፡‹እና ምን ያድርግ አንቆ ይግደላት ?›ስለማነቅ ሲያስብ ዘገነነው፡፡ ሀሳቡን ሳያገባድድ የበራፍ መቆርቆር ሰማ….

‹‹ይግቡ››

በራፉን  ከፈተችና  ገባች  እና  "  እንደገባህ  ነግረውኝ  ነው  ቀጥታ  ወደእዚህ የመጣሁት››አለችው፡፡

እሷን በማያቱ እንዳልተደሰተ በሚያሳብ የድምፅ ቃና‹‹እ …ዛሬ ደግሞ ምንድነው?››ሲል ጠየቃት ፡፡አለም በሩን ዘጋችና ወደውስጥ ዘልቃ በመግባት ወንበር ይዛ ተቀመጠች፡፡

"ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ፍርድ ቤት እንደምሄድ አልነገሩሽም? ››

‹‹አይ…አልነገሩኝም››አለችው ፈገግ ብላ…ከትናንት ማታው ሁኔታ ያገገመች ትመስላለች፡፡ " እሺ ምንድነው ጉዳይሽ?"በመሰላቸት ጠየቃት፡፡

"ስለተገደለው  ሰው  ልትጠይቁኝ  ትፈልጋላችሁ  ብዬ  ስላሰብኩ  ነው…ቃል  ልሰጥ የመጣሁት››

"በእርግጥ ተጠርጣሪ አይደለሽም። የተሳሳተ ጊዜ ላይ በተሳሳተ ቦታ ተገኝተሸ ነው ፡፡ይሄ ድግሞ ያንቺ መጥፎ ልማድ ነው።"አላት፡፡

"በእኔ እና በእሱ ግድያ መካከል ግንኙነት ያለ አይመስላችሁም?" "አይ አይመስለንም ››አላት ፍርጥም ብሎ፡፡

‹‹እኔ ደግሞ ይመስለኛል››

"ከሆነ እንስማው" አለ።

"አስቀድመህ የምታውቀው ይመስለኛል። ሙስጠፋ የሰሎሜን ግድያን አይቷል…የአይን እማኝ ምስክር ነበር።"

በበደነ እና በቀዘቀዘ ስሜት "እንዴት አወቅሽ?"ሲል ጠየቃት፡፡

"በስልክ ደውሎ ነገረኝ።"

"እሱ እኮ  ውሸታም ሰው እንደሆነ ማንም ያውቃል….ስለባህሪው የሚያውቁትን ሰዎች መጠየቅ ትችያለሽ "

"እኔ አምኜዋለሁ። በጣም የተደናገጠ እና በጣም የፈራ ይመስላል ነበር። በመጨረሻ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘን ነበር፣ አንተ ስትከተለኝ እንደነበረ የነገረኝ እሱ ነው…በዛን ቀን እዛ ሆቴል ባትገኝ ኖሮ የእናቴን ገዳይ በዝርዝር ይነግረኝ ነበር።"

"ታዲያ ይሄ ዝርዝር.. የሰሎሜ ገዳይ ያደርገኛል?"

"ገዳይ ባትሆን አንኳን ለገደለው ሰው እየሸፈንክለት ሊሆን ይችላል ››

"በንድፈ ሀሳብሽ ላይ ምን ችግር እንዳለ ልንገርሽ?አቶ ፍሰሀ ከስራ ካባረረው ቀን አንስቶ እሱ የበቀል ጉዞ ላይ ነበር፣ ድንገት አንቺ የእናትሽን ገዳይ እያነፈነፍሽ እንዳለ ሲሰማ በዛ ተንኮለኛ ጭንቅላቱ ነገሮችን አገጣጠመና ጥሩ ድረሰት በአእምሮ ቀምሞ ሊያጃጅልሽ ሞከረ…››

" ያ እውነት አይደለም..ሰውዬው የተገደለው. ስለእናቴ አሟሟት ለእኔ እንዳይነግረኝ አፉን ለማዘጋት ነው ፡፡ይህ ሰውዬ የእናቴን መገደል ለማየት የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ ነው…እንደሚታወቀው እናቴ የሞተችው በእርባታ ድርጅት ውስጥ በከብቶቹ በረት አካባቢ ነው..እሱ ደግሞ የከብቶቹ ተንከባካቢ ስለሆነ አብዛኛውን ጊዜ ከአካባቢው አይጠፋም፣››

‹‹የፈለግሽውን ማመን ትችያለሽ…ለማንኛውም የእሱን መገደል የተመለከተ የአይን እማኝ እንዳገኘን ነግሬሽ ነበር..እድሜ ለእሱ አሁን የሰውዬውን ገዳይ ይዘነዋል…››

ደነገጠች‹‹ይዘነዋል…..እና አመነ?››

‹‹ትንሽ ቢያቅማማም አምኗል››

‹ለምን ገደልኩት አለ?››

‹‹ሚስቴን አማግጦብኛል ..የሚል ምክንያት ነው የሰጠው…የሰውዬውን ሚስትም አግኝተን አናግረናታል…ከሟቹ ጋር የድብቅ የፍቅር ግንኙነት እንዳላት አልካደችም…..››

‹‹ይገርማል…ለሊቱን ሙሉ አልተኛህም አይደል….?በእውነት በአንድ ለሊት ይሄን ሁሉ አቀናብራችሁና አደራጅታችሁ ማደር በመቻላችሁ በራሳችሁ ልትኮሩ ይገባል….››

‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?››የደፈረሱ አይኖቹን አጉረጠረጠባት፡፡

‹‹አንዲት ሴት የደፈረ ወንጀለኛ ለመያዝ ስድስት ወር የማይበቃችሁ በ12 ሰዓት ውስጥ ለዛውም በለሊት ገዳዩን ይዛችሁ …ምስክር አጠናቅራችሁ እንዲህ ጥንቅቅ ብላችሁ ሳያችሁ ባልደነቅ ነው የሚገርመው…..እርግጠኛ ነኝ በጥዋት መጥቼ እንደማፋጥጥህ እርግጠኛ ስለሆንክ መደረግ ያለበትን ነገር ሁሉ አድርገሀል…አድናቂህ ነኝ፡፡››

ሚመልስላት ስላልነበረው ዝም አላት..

"ሁሉንም ፕሮፌሽናል ሴቶች ትጠላለህ ወይስ በተለይ እኔ ነው የምትጠላው?"ስትል ሌላ ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹በተለይ አንቺ ነው የምጠላው።"አላት ፡፡ድፍረቱ አስነዋሪ ነበር። የትናንት መሳሳማቸውን እንዳልወደደው የሚያሳይ ነገር አላነበበችበትም ፡፡በመሀከላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ሞከረች፡፡ ግን መርሳት አልቻለችም። ንግግሩ በጣም ጎድቷታል።

"ለምንድነው ማትወደኝ?"ስትል ጠየቀችው

"ምክንያቱም አንቺ ጣልቃ ገብ ነሽ። በሌሎች ሰዎች ህይወት ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ ሰዎችን አልወድም።"

"ይህ ጣልቃ መግባት አይደለም… የእኔ ጉዳይ የእናቴን ገዳይ መፈለግ  ነው."
31👍5
"እንዴት ሊሆን ይችላል? ሰሎሜ ስትገደል አንቺ በዳይፐር ውስጥ ነበርሽ…ምንም የምታውቂው ነገር የለም" ሲል ጮኸ።

"ይህን በማንሳትህ ደስ ብሎኛል:: ያኔ ገና የሁለት ወር ልጅ ስለነበርኩ ነው…እናቴ በዛ ምሽት በእርባታው ቦታ ምን ትሰራ ነበር?"

ለጥያቄው የሰጠው አስደንጋጭ ምላሽ ።" አላሳታውስም ››የሚል ነበር፡፡
"ልትረሳው አትችልም ። እዛ ምን ታደርግ ነበር? እባክህ ንገረኝ"ተነሳ። አለምም እንዲሁ።

"ከጁኒየር ጋር ቀጠሮ ነበራት መሰለኝ ..አልፎ አልፎ እዛ እርባታ ቦታ ባለው ሰፊ ሜዳ ላይ በጨረቃዋ ድምቀት እሳት አቀጣጥለን…ስጋ እየጠበስንና መጠጥ እየጠጣን የመዝናናት ልምድ ነበረን….በእለቱም ለተመሳሳይ ጉዳይ ነበር የተገኘችው..።"

" በቃ ለዚህ ብቻ ነው የተገኛኙት?"

"ሌላ ነገር አለ ምትይ ከሆነ እሱን ጠይቀው"
"እጠይቅሃለሁ፡ ዝግጅቱ ምን ነበር? የተለየ ትርጉም ነበረው ?።" "ምናልባት አዘኖላት መሰለኝ"

"ይቅርታ? ለምን ያዝንላታል?"

" ካለእድሜዋ ስለወለደች ነዋ!!አንቺን ስትወልድ አስራ ስምንት አመት ብቻ ነበረች፣በዛ ላይ ባሏ ወዲያው ነው ጥሎት ውትድርና የሄደው….በጣም ከፍቷት ነበር።"

‹‹ በዚያ ምሽት እራት ላይ እዚያ ነበርክ? ” "አዎ እዚያ ነበርኩ" እጁን ነጻ አወጣ

"ምሽቱን ሙሉ?"

"አይ  ..ከዚህ  በፊትም  እኮ  ይህን  ጥያቄ  ጠይቀሽኝ  መልሼልሻለሁ  ….ከእራት  በኋላ ተለይቻቸው ሄድኩ."

"ለምን?፧" ዝም አለት

መልስልኝ ገመዶ፣ ‹‹የት ነው የሄድከው?"

‹‹የፍቅር ቀጠሮ ነበረኝ"

"ከማን ጋር? አሁንም እዚህ ከተማ ውስጥ ትኖራለች?" "ኖረች አልኖረች ልዩነት ምንድነው?"
" ላናግራት እፈልጋለሁ።"
" እሷን ወደዚህ ጉዳይ በፍጹም ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም።" ". ያን ምሽት ወደ እርባታ ቦታው አልተመለስክም?"

"አይ አልተመለስኩም።ነገርኩሽ የፍቅር ቀጠሮ ነበረኝ" ትንፋሹ  እስኪሰማት ድረስ ፊቱን ወደ እሷ አስጠጋ።
///
"እራት እና ጭፈራ ላይ እንዴት ነሽ?››ሲል ጠየቃት ጁኒየር "እንደ ተረት ተረት"

" አይ አይመስለኝም.ሲያዩሽ ደናሽ ነው የምትመስይው››

"እራት እና ጭፈራ እየጋበዝከኝ ነው እንዴ?"
"አዎ ..ዛሬ አመታዊ የነጋዴዎች ህብረት ክብረበዓል የሚከበርበት ቀን ነው…ዛሬ በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና ሀብታሞች ከነ ሚስቶቻቸውና ከነልጆቻቸው ይገኙበታለል….እና እባክሽ ከእኔ ጋር ትሄጂያለሽ… ?ካልሆነ ግን እንደ ገሃነም አሰልቺ ይሆንብኛል።››አላት፡፡

አለም ሳቀች። "ጁኒየር፣ እንደእዚህ አይነት ቦታ ለአንተ መቼም አሰልቺ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም ፡፡ በተለይ ሴቶች በዙሪያህ ባሉበት ጊዜ የሚታሰብ አይደለም…አብዛኛዎቹ በአንተ ውበት ይወድቃሉ?"

" ዛሬ ማታ አንቺ አብረሽኝ ከሄድሽ ያለ ምንም ልዩነት ማለት ይቻላል., " "ዛሬ ማታ?"

‹‹አዎ ዛሬ ማታ ››፥

"በእርግጥ አልችልም. ደክሞኛል. ትናንት ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አላገኘሁም - "
"አዎ፣ ሙሰጠፋ በዚያ መንገድ ሞቶ እንዳገኘሽው  ሰምቼያለሁ።በጣም አስከፊ  ምሽት እንዳሳለፍሽ መገመት እችላሁ፡፡ አእምሮሽን ከዛ እንድታወጪ መርዳትና እፈልጋለሁ።"
"አስተያየትህን አደንቃለሁ ግን መሄድ አልችልም." "ተቃውሞ አልቀበልም"
"ጁኒየር በእውነት መሄድ አልችልም።"

"ለምን?"

"ሁሉም የእራት ልብሶቼ ላውንደሪ ሊታጠቡ ሄደዋል ። የምለብሰው የለኝም።"
"እሱ አሳማኝ ምክንያት አይደለም….አንቺን የመሰለች ዘናጭና ሽቅርቅር ሴት አንድ የእራት ልብስ ቤቷ ታጣለች…?ለምሳሌ ትናንት ለብሰሽ የነበረው ሌዘር ቀሚስ..በጣም እኮ ነው የሚያምርብሽ"

አስተያየቱ አሞቃት ‹‹እባክህ ተወኝ..ይቅርብኝ››

"ለምን ?

ምክንያቱም በቅርቡ የእስር ቤት ነዋሪ እንደምሆን ተስፋ ስላደረግሽ?"

"አይ!"

"ታዲያ ምን?"

"ወደ እስር ቤት ልልክህ አልፈልግም… ነገር ግን አንተ በግድያ ጉዳይ ላይ አንዱ ተጠርጣሪ ነህ።"

‹‹አሌክስ ስለ እኔ የሆነ ግንዛቤ ለማግኘት በቂ ጊዜ ያገኘሽ ይመስለኛል …እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል እንደምሰራ በእውነት ታምኛለሽ?"
ገመዶን ጁኒየር ወታደር ሆኖ ያውቃል ወይ ብላ ስትጠይቀው  እንዴት እንደሳቀባት አስታውሰች።
"አይ፣  አላደርገውም"  ስትል  ለስለስ  ብላ  መለሰችለት፡፡  "ግን  አሁንም  ተጠርጣሪ ነህ።ጓደኛሞች መሆናችንን አያዋጣንም።››

"ይህን ቃል ወድጄዋለሁ" አላት፡፡

"ምን?"

"ዛሬ ማታ ከእኔ ጋር ትሄጃለሽ…ማታ አንድ ሰዓት ላይ እወስድሻለሁ።"

"አልችልም።"

“አሌክስ፣ አሌክስ፣” ሲል በሚያስገርም ሁኔታ አቃሰተ፣ “

በዚህ መንገድ ተመልከቺው። ዝግጅቱ ላይ እኔ ሁለት ወይም ሶስት ጠርሙስ እጠጣለሁ፣ ምናልባትም ከዛም በላይ ልጠጣ እችላለው ።ከዛ አንቺ ስለምትፈልጊያቸው መረጃዎች ማስታወስ ልጀምር እችላለሁ፣ ምን አልባትም በውስጤ የቀበርኩትን ሚስጥር ልናገር እችል ይሆናል።ስለዚህ አንቺ በቦታው ተገኝተሸ እድልሽን ብትሞክሪ ጥሩ ይመስለኛል። ምን አይነት አስደናቂ ኑዛዜዎች እንደማሰማሽ ማን ያውቃል? በዛ ላይ በዝግጅቱ ብዛት ያላቸው የአባቴ ወዳጆችና የእኔም ጎደኞች ይገኛሉ…ከብዙ ሰዎች የመተዋወቅ እድል ይኖርሻል፡፡››

እንደገና፣ በአስደናቂ ሁኔታ አቃሰተች። "በቃ እሺ…አንድ  ሰዓት."ስትል መስማማቷን ነገረችው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3129
#ፍቅር_ሙጀሌ

እየነዘነዘ እንቅልፍ ቢነሳም ፣
ንክሻ ፣ ስቃዩ ፣ረብሻው ይጥማል፣
ፍቅር ሙጀሌ ነው፣
በትዝታ ጥፍር ሲያኩት ደስ ደስ ይላል።

🔘ኑረዲን ዒሳ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍84😁4
ከዛ ምግብ የሚበላበት ሰዓት ደረሰና ሳራ ወደ ፍሰሀ ስትሄድ ጁኒዬር ደግሞ ወደአላም መጣና ቢፌ አነስትው በየጠረጴዛቸው ላይ ተቀመጡ፡፡
ከፊት ለፊታቸው ያለችው የዳኛው ሴት ልጅ ጁኒዬር ላይ አይኖቾን እንደተከለች ታዘበች…ድንገት ቀና ሲል አይን ለአይንት ተገጣጠሙ….እንደመደንገጥ አለና "ሄይ ስርጉት" በማለት በወዳጅዊ መንፈስ እጁን አነሳ።በሴቲቱ ፊት ላይ አንፀባራቂ ፈገግታ ታየ። እጇን አንስታ እንደማውለብላብ አለችለትና እንደመሽኮርመም ብላ መልሳ አቀረቀረች፡፡ ሁኔታውን በትኩረት ስትከታተል የነበረችው አለም ስለእሷ ማወቅ ጉጉት አደረባት፡፡

የጁኒየር ጥያቄ የአለም ጭንቅላት አዞረ። " የጎድን አጥንት ትወጂያለሽ?"

" በጣም" ብላ ሳቀች ..የምትፈልገውን ምግብ መርጣ ያመጣች ቢሆንም የመብላት ፍላጎት ግን አልነበራትም፡

"አልተመቸሽም እንዴ ሌላ ነገር ላስመጣልሽ?"

‹‹አይ ..አያስፈልግም››

ከበሉ በኋላ ወደመጠጣቸው  እና ጫወታቸው ተመለሱ "ገመዶ የክለብ አባል ነው?" ብላ ድንገት ጂኒዬርን ጠየቀች ።

" አይ አይደለም..አልፎ አልፎ ግን በክብር እንግድነት እየተጋበዘ ይገኛል…..››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ዛሬ ታዲያ ለምን አልተገኘም..አልተጋበዘም እንዴ?››

‹ምነው መገኘት ነበረበት….?ማለት ፈልገሽው ነበር?››

‹‹አይ እንዲሁ ትዝ ስላለኝ ነው..ለማንኛውም ሽንት ቤት ደርሼ ልምጣ››ብላ ወንበሯን ገፋ አድርጋ ተነሳች፡፡

‹‹ልከተልሽ እንዴ?››

‹‹አይ ..ትልቅ ሰው ነኝ እኮ …ራሴን መጠበቅ እችላለሁ››አለችውና ወደሽንት ቤት ሄደች፡፡ ተጠቅማ ስትወጣ የዳኛዋ ሴት ልጅ በመስታወቱ ፊት ቆማ.. ውስጥ የገዛ ራሷን ነፀብራቅ እያየች ልብሷን ስታስተካከል አገኘቻት። ዘወር ብላ አለም ስታያት ፈገግ አለች ፡፡

"ሃይ።"አለም ድንገት ነው ከአፏ ያመለጣት!!

"ሀይ..ሰላም ነው?።"

አለም  ወደ  ማታጠቢያ  ገንዳ  ሄደች  እና  እጆቿን  ታጠበች።  "ቅድም  በትክክል አልተዋወቅንም። እኔ አለም ጎበና እባላለሁ››

"አውቃለሁ።

"የዳኛ ዋልልኝ ሴት ልጅ ነሽ አይደል?."

‹‹አዎ የዳኛ ዋልልኝ ሴት ልጅ ነኝ ..በተጨማሪም..››

‹‹በተጨማሪም ምን?››አለም በጉጉት ጠየቀች፡፡
‹‹የጁኒዬር የመጀመሪያ ሚስቱ ነኝ…›› አለም…ከመደንገጧ የተነሳ አይኖቾ ፈጠጡ

"ይህ ለአንቺ የሚገርም  ዜና እንደሆነብሽ መረዳት ችያለው" አለቻት….. ስርጉት በአለም መደንዘዝ እየሳቀች፡፡

"አዎ..በጣም አስገርሞኛል" ብላ መለሰች። "ይህን ማንም አልነገረኝም"

"ይሄው  አሁን  እኔ  እየነገርኩሽ  ነው….እያደረስሽ  ያለውን  ጥፋት  የምታውቂው አይመስለኝም?"አለቻት ከፈገግታ ወደቁጣ ተቀየረ፡፡

"በማን ላይ ነው ጥፋት ያደረስኩት?"

"በእኔ ላይ " ብላ ደረቷን እየመታች ጮኸች። ለአፍታ አይኖቿን ጨፈነች። ስትከፍታቸው በጥላቻ ተሞልተው ነበር፣ ትንሽ ቆይቶ ግን ራሷን የተቆጣጠረች መሰለች።

"ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ጁኒየር ከእናትሽ በተመለሰ ጊዜ አገባኝ ››
አለም ምንም ነገር አልተናገረችም ፣ ግን በጥፋተኝነት አይኖቿን ዝቅ አደረገች።"አንቺ በእኔ ላይ የተሳሳተ እምነት እንደያዝሽ አይቻለሁ።ይቅርታ ወይዘሮ ስርጉት ፡ በምርመራዬ ስላስጨነቀኳችሁ አዝናለሁ።"

" ያንቺ ሀዘኔታ ምን ያደርግልናል ? የባሌንና የአባቴን ስም በሀሰት በማጥቆር በአየር ላይ እየበተንሽው ነው።"

"የጁኒየር የመጀመሪያ ሚስት ማን እንደሆነች ወይም በዚህ በሻሸመኔ ከተማ ውስጥ እንደምትኖር አላውቅም ነበር.››

‹‹ብታውቂ ኖሮ ችግር ይፈጥር ነበር?››

‹‹ምናልባት ላይሆን ይችላል" ስትል መለሰችላት ፡፡

‹‹ስለ አባቴስ?"

‹‹ስለ እሱ ምን?"

‹‹ይህ ያንቺ ትንሽ ምርመራ ህይወቱን እያመሰቃቀለው  ነው።››

"የእናቴን ገዳይ በተመለከተ መጀመሪያ የተሰጠውን ፍርዱ ስለምጠራጠር ነው።"

‹‹አዝናለሁ። እኔ ይህን መረዳት አልችልም።››ስትል እጆቿን ወደ ጎን ዘርግታ በንዴት ተንቀጠቀጠች።
"ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሌሎችን መልካም ስም የሚቆሽሹ ሰዎችን እጸየፋለሁ።"

አለም እየተናነቃት ጠየቀች። "ይህን ምርመራ የስራ እድገት ለማግኘት ወይም ዝነኛ ለመሆን ፈልጌ የጀመርኩት ይመስልሻል?"

"እና ታዲያ ለምንድነው?"

"እናቴ የተገደለችው እዚያ በረት ውስጥ ነው። እሷን በመግደል የተከሰሰው ሰው ያንን ወንጀል ሊፈጽም ይችላል ብዬ አላምንም። የምር የሆነውን ማወቅ እፈልጋለው ። ወላጅ አልባ ላደረገኝ ሰው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ እፈልጋለው …ምክንያቴ ያ ብቻ ነው"

"ጥርጣሬሽ ውሀ ሚቆጥር አይደለም.. የፈለግሽው በቀል ብቻ ነው ››

"በቀል ሳይሆን ፍትህ ነው የምፈልገው።"

‹‹ሌሎች ሰዎች የሚያስከፍላቸው ዋጋ ምንም ይሁን ምንም?" "ለሚያስከፍላቸው ማንኛውም ዋጋ አስቀድሜ ይቅርታ ጠይቃለው.››
ስርጉት የምፀት ድምፅ አሰማች። "አባቴን በአደባባይ ልታሰቅይው  ትፈልጊያለሽ? ቢያንስ ቢያንስ በፍርድ ላይ ከባድ ስህተት ሰርቷል ብለሽ እየወቀስሺው ነው።››

‹‹ያንን መካድ አልችልም …አዎ፣ ሊቁ የተባለውን እብድ እናቴን እንደገደለ አድርጎ በመወሰን ስህተት እንደሰራ አምናለው…ያንንም ለማረጋገጥ ጠንክሬ እሰራለው፡፡››

"አባዬ ለፍትህ በታማኝት አርባ አመት አሳልፎል…በፍርዱ አደበባይ ላይ እንከን የለሽ ሰው ነው››

" እንግዲያው እንደምትይው የአባትሽ የአርባ አመት ፍርድ እንከን የለሽ ከሆነ የእኔ መንፈራገጥ ይሄን ያህል ሊያሳስባችሁና ሊያስቆጣችሁ አይገባም…››በማለት በቆመችበት ጥላት መራመድ ጀመረች…ስርጉት ከኋላ እያወራች ተከተለቻት ፡፡

‹‹የአባቴን የአርባ አመት ስኬታማ የስራ ህይወት ለማበላሸት የምትሞክሪ ከሆነ እጄን አጣጥፌ አላይሽም…. ››

"ስርጉት የአባትሽ የስራ ህይወት ማጨለም ምንም ፍላጎት የለኝም ። የማንንም ስሜት መጉዳት ወይም ንፁህ የሆነን ሰው ሀዘን ወይም ውርደት ላይ መጣል አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ፍትሃዊ ስራ ሲሰራ ማየት ብቻ ነው።ለዛ ደግሞ አይደለም ብቻሽን ጦር
አሰልፈሽ ብትመጪ ወደኋላ አንድ ስንዝር አታስቆሚኝም "ጠባቡን ኮርደር አለፉና ወደግራ ታጥፈው በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ፊት ለፊት ተቀምጠው ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ

"ያ የፍትህ ጉዳይ ነው"

ስርጉት ተሳለቀች፣ "ያንን ቃል የመናገር መብት የለሽም። ልክ እንደ እናትሽ ቆንጆ ነሽ… ነገር ግን ራስ ወዳድ ነሽ። ለሌሎች ሰዎች ስሜት ግድ የለሽም። ከራስሽ ምኞት በላይ ማየት አትችይም።››

"እናቴን በጣም እንደማትወጂያት እየነገርሽኝ ነው? ስትል…በአሽሙር ጠየቀቻት። ስርጉት ጥያቄዋን በቁም ነገር ወሰዳ‹‹አዎ ጠላታለው።››ስትል ሀቁን ነገረቻት፡፡

"ለምን? ››

‹‹ጁኒየር እሷን በጣም ያፈቅራት  ነበር?"

"ስርጉት፣ እናቴ ከተገደለች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጁኒየርን እንዳገባሽ አውቃለሁ። ይህ ለእኔ ምን ያህል እንግዳ ነገር እንደሆነ ልደብቅሽ አልፈልግም።"
"እንዳልሺው ድንገተኛ ሊመስል ይችላል… ነገር ግን ለዓመታት አብረን ነበርን ›› ይህም አለምን አስገረማት፡፡

"የእውነት..አብራችሁ ነበራችሁ?"

‹‹አዎ። እና አብዛኛውን ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበርን"
አለም አሁን ሙሉ ምስል አግኝታለች፡፡ ከምትወደው መልከ መልካም የእግር ኳስ ጀግና ከነበረ ወጣት ጋር ፍቅር የያዛት ሴት እሱን ለማግኘት ስትል ማንኛውንም ነገር ለመሰዋት ፈቃደኛ እንደነበረች ገባት፡፡ የእሱን ቅንጣት ትኩረት እንኳን ለማግኘት ማንኛውንም ነገር ታደርግ ነበር።››

"እውነታው ምንድን ነው ስርጉት?"
27👍9👏2
"ሰሎሜን በተመለከተ ጁኒዬር ተሳስቶ ነበር፡፡ እሷም ያለማቋረጥ ከገመዶ ጋር ታወዳድረው ነበር. ጁኒየር ሁልጊዜ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነበር….እኔ ግን እሱ በማንም እንዴት እንደሚለካ ግድ አልነበረኝም. በሆነው ነገር ሁሉ እወደው ነበር. እሱ ግን ቀልቡ እኔ ጋር አልነበረም፡፡››

" ያንን ማመን አልፈልግም ››

‹‹ ግን እናትሽ ….አባትሽ እና አንቺ ብትኖሩም ሰሎሜ ሁል ጊዜ ገመዶን ትወደው ነበር።››

" በጣም የምትወደው ከሆነ ለምን አባቴን አገባችው?" ይህ ጥያቄ አለምን ለረጅም ጊዜ እያስጨነቃት ነበር።

"ሰሎሜ ከአስራአንደኛ ክፍል ወደ አሰራሁለት እንዳለፈች ክረምት ላይ አጎቶቾ ጋር ወደኮፈሌ ሄዳ ነበር...ሁለቱን ወር እዛ ነበር ያሳለፈችው…ከአባትሽ ጋር እዛ ነው የተገናኙት፡፡ከዛ ብዙም ሳይቆይ ተጋቡ…ብቻ እንደዛ ይመስለኛል ..ዝርዝሩን አላውቅም…. ››

"አባቴን ያገኘችው እዚያ ነው"

"አዎ …

በእንደተጋቡ ስድስት ወርም ሳይቆይ ወታደር ቤት ተቀጠረና ሄደ ፡፡እሷም ከኮፈሌ ወደሻሸመኔ ተመለሰችና ከአያትሽ ጋር መኖር ጀመረች…ከነጁኒዬር ጋር ያላትን ግንኙነትም ካቆመችበት ቀጠለች…ስትመጣ አንቺን እርጉዝ ነበረች፡፡…ወልዳሽ ብዙም ሳይቆይ አባትሽ በባድሜው ጦርነት መሞቱን ሰማች፡፡እና እሱ ከሞተ በኋላ፣ ከገመዶ ጋር እንደገና ለመቀጠል ፈለገች፣ ነገር ግን እሱ ፍቃደኛ ስላልሆነ የጁኒየርን ተስፋ ቀሰቀሰችው። እሱ ሁል ጊዜ እንደሚፈልጋት ታውቃለች፣ ግን እሱ በገመዶ ምክንያት በጭራሽ ፍቅሩን አይገልፅላትም ነበር፣ አየሽ በሁለት ጓደኛሞች መሀከል እንዴት እንደተጫወተች እና ከእርግዝናዋ ጋር በማያያዝ እርሱን የማግባት ሀሳብ እደነበራት ማወቅ ችያለው ፣ ግን ጋሽ ፍሰሀ ገማዶ እስካልሆነ ድረስ በጭራሽ ጁኒዬርና ማግባት እንደማትችል ያስብ ነበር፡፡ ››

‹‹የሚገርም ታሪክ ነው እየነገርሽኝ ያለሽው››

"እናትሽ ጁኒየርን በተስፋ ክር ስታንጠለጥለው ነው የኖረችው፣ ህይወቱን አሳዛኝ እንዲሆን አድርገዋለች። በሕይወት ብትቆይ ኖሮ ደግሞ ይብልጥ ትጎዳው ነበር ፡፡››

"ሰሎሜና ስትሞት ደስ ብሎሽ ነበር?."

የጥርጣሬ ብልጭታ በአለም አይኖች ውስጥ ዘለለ፣ ‹‹አልዋሽሽም…የሆነ ተራራ ከጭንቅላቴ እንደወረደ እፎይታ ነው የተሰማኝ ››የሚል አስደንጋጭ መልስ መለሰችላት፡፡
////

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3511
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት__በዘሪሁን_ገመቹ
……

ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ

///
ዝግጅቱ በተዘጋጀበት የከተማዋ ግዙፉ ሆቴል የጁኒዬርን እጅ ይዛ ስትገባ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማት፡፡ ለስለስ ያለ ምርጥ ሙዚቃ እና እዚህማ እዛም በፈገግታ የታጀበ ሳቅ ይሰማ ነበር፡ከበርካታ ሰዎች ጋር አስተዋወቃት…ከብዙ ሰዎች ጋር የማውራት እድል አገኘች፡፡ አንዳቸውም ውይይቶች በእናቷ ግድያ ዙሪያ ያተኮሩ አልነበሩም። ያ በራሱ መንፈስን የሚያድስ ለውጥ ነበር። እረፍት ላይ እንዳለች መስሎ ተሰማት። ጁኒየር በመጠጥ ተፅዕኖ ውስጥ ገብቶ ሚስጥሩን ለእሷ አሳልፎ እንደሚሰጣት ቀድሞውንም አላመነችም። እሷ ምንም አስገራሚ ኑዛዜዎችን የመስማት ዕድል እንደሌለት ገምታ ነበር።ቢሆን ከምሽቱ አንድ ጠቃሚ ነገር ሊወጣ ይችላል የሚል ተስፋ መሰነቋ ግን አልቀረም. ፡፡
ከሁሉም በላይ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከአቶ ፍሰሀ እና ከኩማደሩ ጋር በደንብ ከሚተዋወቁ እና ባህሪያቸውንና ድብቅ ተግባራቸው ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የመቀላቀል እድል አላት፡፡
እንደተለመደው "ነጭ ወይን"ይዛ እየጠጣች ነው ጁኒዬር ከጎኗ አለ፡፡

"ሙዚቃው የእኔ ጣዕም አይደለም ነገር ግን መደነስ ከፈለግሽ እኔ ታዛዥ ነኝ.››አላት

ጭንቅላቷን በአሉታ ነቀነቀች። "አመሰግናለሁ …እኔ ከመደነስ ይልቅ ማየት እመርጣለሁ።››

ከጥቂት ዘፈኖች በኋላ ጁኒየር ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ፣"እናትና አባቴ እዛ ጋር ናቸው….ሰላም እንበላቸው›› አለና..እየጎተተ ይዟት ሄደ፡፡
አለም በዳንስ ወለል ዙሪያ ለመመገቢያ ወደተዘጋጁት የጠረጴዛዎች ስብስብ አብሮት ሄደ። ሳራ ጆ እና አቶ ፍሰሀ በአንድ ላይ ተቀምጠዋል። ደረሱና

"ጤና ይስጥልኝ ወይዘሮ ሳራ ዛሬ ማታ ቆንጆ ሆነሻል።››አለቻት አለም

‹‹አንቺም እንደዛው ….እንኳን በሰላም መጣሽ››ስትል መለሰችላት፡፡

ሰላምታ  ተለዋውጠው  አንድ  ጠረጴዛ  ከበው  የየግላቸውን  መጠጥ  በመጠጣት ጫወታቸውን ጀመሩ፡፡

‹‹የሙስጠፋን የሞተ  አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሽው አንቺ  እንደሆንሽ  ሰማሁ››።ሲል ኮስተር ባለ ነገር ጫወታውን የጀመረው አቶ ፍሰሀ ነበር፡፡

"አባዬ  ይህ  ፓርቲ  ነው…አለም  ስለ  እንደዚህ  አይነት  መጥፎ  ነገር  ማውራት አትይፈልግም."አለ ጁኒየር።

"አይ፣ ምንም አይደለም፣ ጁኒየር፣ ይዋል ይደር እንጂ እኔ ራሴ አነሳው ነበር።››

"ጥሩ ..ከሱ ጋር የተገናኘሽው በአጋጣሚ ነው ብዬ አላስብም።ያንን ደደብ ሽማግሌ ለምን ነበር ልታገኚ የፈለግሽው?"

"አይ….።››በማለት ከሙስጠፋ ጋር የነበራትን የስልክ ውይይት በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡

‹‹ያ ውሸታም ሽማግሌ ሊያታልልሽና አንቺን አጓጉቶ ገንዘብ ሊቀበልሽና ..እግረ መንገዱንም እኔን ለመበቀል ሲያደባ ነበር…ግን ፈጣሪ የልቡን ተንኮል አይቶ ለሌላ ወንጀለኛ አሳልፎ ሰጠው፡፡››
"ኦህ፣ እንዴት በእርግጠኝነት እንደዛ ደመደምክ..?››

‹‹ ሙስጠፋ ከሰሎሜ ጋር ወደዚያ በረት ውስጥ የገባው ማን እንደሆነ አይቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን የእውነት እንደሚለው ሰው አይቶ ከሆነ ሊያይ የሚችለው ሊቁን ነው።››ሲል ጁኒዬር አከለበት፡፡
አለም ..ለመናገር የፈለገውን ከተናገረ በኋላ …እንዲከራከር እድል አልሰጠችውም ፣ የሙስጠፋ ርዕስ ለጊዜው ባለበት እንዲቆም አደረገች ።መጠጣቸውን እንደጨረሱ፣ አቶ ፍሰሀ እና ጁኒየር ሴቶቹን ባሉበት ጥለው ሌሎች የቢዝነስ ሰዎችና ለማነጋገር ተያይዘው ሄዱ፡፡
ከሳራ ጆ ጋር ለረጅም ደቂቃዎች መቆየት ከባድ ነው ..ከእሷ ጋር ማውራትም ቀላል እንደማይሆን አሰበች፣ቢሆንም እንደምንም እራሷን አጀግና "ለረጅም ጊዜ የዚህ ማህበር አባል ናችሁ?"የሚል ጥያቄ ሰነዘረችላት፡፡

"ፍሰሀ ከመስራች አባላት አንዱ ነበር" ስትል ሳራ ግድ በሌለው ሁኔታ መለሰችላት ።
በመድረኩ ላይ በርካንታ ጥንዶች እየደነሱ እና እየተጎነታተሉ ይታያሉ፡፡አለም"አቶ ፍሰሀ በእያንዳንዱ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እጁ ያለበት ይመስላል " ስትል አስተያየት ሰጠች.
"ትክክል ነሽ…የከተማዋ ጠባቂ እንደሆነ ነው የሚያስበው… እየሆነ ያለውን ሁሉ ማወቅ ይፈልጋል….በዛ ምክንያት ..ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ሲል ሁሉም ነገር ውስጥ ይገባል››ሳራ በረጅሙ ተነፈሰች እና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች "አየሽ ፍሰሀ በእያንዳዱ የከተማው ኑዋሪ …በባለስልጣናቱም ዘንድ ሆነ በነጋዴዎች ክበብ የመወደድ ፍላጎት አለው
፤ እሱ ሁል ጊዜ ፖለቲከኛ ነው ፣ ››
አለም እጆቿን ከአገጯ በታች አጣጥፋ በክርኖቿ ጠረጴዛው ላይ ተደግፋ። "አንቺ ያ.. አስፈላጊ ነው ብለሽ ታምኚያለሽ?"

"አይ አላንም።" አለችና ለመጀመሪያ ጊዜ አለምን በትኩረት  ተመለከተች።

"ጁኒየር ለአንቺ የሚያሳይሽን እንክብካቤ ብዙም ትርጉም አትስጪው››በማለት አዲስ ርዕስ ከፈተች፡፡

"አቤት…ምን ማለት ነው?"

"ልጄ የሚያገኛት ሴት ሁሉ የማሽኮርመም ልክፍት አለበት እያልኩሽ ነው ››

አለም ቀስ ብላ እጆቿን ወደ ታች አወረደች። ንዴቷ ወደ ውስጥ ገባ፣ ነገር ግን ድምጿን ዝቅ አድርጋና እራሷን እንደምንም ተቆጣጥራ “ወ/ሮ ሳራ አንድምታይው ተናድጃለሁ።››

ሳራ ጆ በግዴለሽነት አንድ ትከሻ ከፍ ዝቅ አደረገች‹‹ግድ የለኝም ››የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ ፈልጋ እንደሆነ አለም በግልፅ ገብቷታል፡፡

"ሁለቱም ወንዶቼ ቆንጆዎች ናቸው እና እነሱም ያንን ስለሚያውቁ አላግባብ ይጠቀሙበታል..አብዛኛዎቹ ሴቶች ደግሞ የእነሱ ማሽኮርመም ትርጉም የለሽ እንደሆነ አይገባቸውም."

" እርግጠኛ ነኝ ፍሰሀን በተመለከተ ያልሽው እውነት ነው፣ ስለ ጁኒየር ግን አይመስለኝም።
ሶስት የቀድሞ ሚስቶች ስለ እሱ ማሽኮርመም ከአንቺ ጋር ላይስማሙ ይችላሉ።››

"ሁሉም እሱን በተመለከተ ተሳስተው ነበር።"

"እናቴስ? እሷም እሱን በተመለከተ ታሳስታ  ነበር?"ሳራ ባዶ አይኗን አሌክስ ላይ በድጋሚ ተከለች።

"አዎ ተሳስታለች ፤አንቺም እንደሷ  ነሽ ….ታውቂያለሽ አይደል?።"

"እኔ?"

" አዎ!!አለመግባባት መፍጠር ያስደስትሻል። እናትሽ አስጨናቂ ነገሮችን በመፍጠር እርካታ አልነበራትም። ልዩነቱ አንቺ ከሷ በላይ ችግር እና መጥፎ ስሜትን በመፍጠር የተሻልሽ መሆንሽ ብቻ ነው። ብዙውን ጊዜ ብልሀት የሚጎድልሽ ቀጥተኛ ሴት ነሽ።››ዓይኖቿን ከአለም ጀርባ አሻግራ አንድ ሰው ትመለከት ጀመረ፡፡

"ደህና አመሻሽ ሳራ "

"ዳኛ ዋልልኝ" ጣፋጭ ፈገግታ በሳራ ጆ ፊት ላይ ታየ።በዛ ቅፅበት የሚመለከታት አንድ ሰው ከሴኮንዶች ቀደም ብሎ ከፍተኛ ንዴት ላይ እንደነበረች በጭራሽ መገመት አይችልም

‹‹… ሰላም ስርጉት።››አለም በሳራ ያልተጠበቀ ትችት የተናደደ ፊቷን ወደኋላ አዞረች። ዳኛው የእሷን እዛ መገኘት እንደትልቅ ጥፋት የቆጠረ እንደሆነ በሚያሳብቅ ስሜት ትኩር ብሎ ያያት ጀመር።

" ክብርት አቃቢት ህግ "

"ጤና ይስጥልኝ ክቡር ዳኛ " ከሳቸው ጎን የቆመችው ሴት አለምን ከሱ ጋር የሚዛመድ ተግሳፅ ተመለከተች ፣ ዳኛው የሴትየዋን ክንድ ነካ አድርገው ወደ ሌላ ጠረጴዛ ሄዱ

"ሚስቱ ናት?" አለም ለሳራ ጥያቄ አቀረበች ፡፡

ሳራ በመደነቅ "በእግዚያብሄር ስም….አረ አይደለችም..የሱ ሴት ልጅ ነች ስርጉት…የመጀመሪያ እና ብቸኛ  ሴት ልጁ ነች፡››

ከላይ የለጠፍነው ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ ነው።

#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

"ሰሎሜና ስትሞት ደስ ብሎኝ ነበር."

የጥርጣሬ ብልጭታ በአለም አይኖች ውስጥ ዘለለ፣ ‹‹አልዋሽሽም…የሆነ ተራራ ከጭንቅላቴ እንደወረደ እፎይታ ነው የተሰማኝ ››
56👍3👎1
‹‹አንቺ በዚያ ምሽት.እዚያ ነበርሽ?"

‹‹ብኖር ባልኖር ምን ያርግልሻል…ብቻ ጁኒየርን ወዲያውኑ አገባኝ። ፣ ሁል ጊዜ የሚፈልገው ሰሎሜን መሆኑን ባውቅም ከሞተች በኃላ ግን ከሐዘኑ እንዲያገግም እንድረዳው እንደፈለገኝ አውቄ ነበር፡፡ከሀዘኑ ለማገገም ቢጠቀምብኝ ግድ አልነበረኝም። ለእሱ በሆነ ነገር ጠቃሚ ሆኖ መገኘት ፍላጎቴ ነበር ፡፡ ምግብ አበስልለታለው…ልብሱን አጥብለታለው…ሲፈልግ ደግሞ ወደ አልጋው ላይ እወጣለታለው፡፡ ከተጋባን በኋላም ለእኔ ታማኝ አልነበረም … ። ከቤት በምንወጣበት ጊዜ ሁሉም ሴቶች ወደ እሱ ሲሳብ እመለከት ነበር። የትኛውም ወንድ ያን የመሰለ ጠንካራ ፈተና መቋቋም ይችላል ?ብዬ እራሴን ጠየቅኩ ፡፡ከእኔ ጋር እንደተጋባ ቢቀጥል ኖሮ ፍቅረኛዎቹን ሁሉ በታገሥኳቸው ነበር።ነገር ግን ፍቺ ጠየቀኝ፣ መጀመሪያ ላይ እምቢ አልኩት፣ ቀጠለና እኔን መጉዳት መቀጠሉ ምቾት እንደነሳው ነገረኝ፣ ምንም አማራጭ ሳጣ ለእሱ የአእምሮ ሰላም ስል በፍቺው ተስማማው..
፣ ልቤ ተሰበረ፣ ቢሆንም ግን ስለምወደው የሚፈልገውን ሰጠሁት፣ እኔ እሱን እስከጥግ ድረስ በማፍቀሬ በሚደርስብኝ ስቃይ የምሞት ሁሉ ይመስለኝ ነበር…እንደማስበው እኔ የምረዳውን ያህል ማንም ሌላ ሴት እንደማትረዳው አውቃለው ››ንግግሯን ገታ አደረገችና አይኖቾን አለም ላይ አንከባለለቻቸው….ከዛ ቀጠለች"እና አሁንም ከጎኑ ቆሜ ከሴት ወደ ሴት ሲዘል እያየሁት ነው ፡፡ ሁል ጊዜ የሚፈልገውን ልሰጠው እፈልጋለሁ…ዛሬ ማታ እንኳን ሲጨፍር እና አንቺን ሲያሽኮረምም ለማየት ተገድጄያለው…ኦ አምላኬ!!!›› አለች እና አለቀሰች፣ ፊቷን ወደ ኮርኒሱ ቀና አደረገች…..አምላኳም ብሶቷን እንዲያዳምጥላት የፈለገች ትመስላለች፡፡

" አሁን አንቺም እሱን ልታጠፊው ትፈልጊያለሽ..እሱ ግን ከአንቺ ቁንጅና ባሻገር ያለውን ተንኮለኛ እቅድሽን ማየት አልቻለም››እጇን ዝቅ አድርጋ አለም ላይ ትኩር ብላ ተመለከተች

"አንቺ መርዝ ነሽ። ወ .ሪት አለም .. እኔ ዛሬ ማታ ስለአንቺ የተሰማኝ ስሜት ከሀያአምስት አመት በፊት እናትሽ ላይ ከሚሰማኝ ስሜት ጋር ተመሳሳይ ነው››በመካከላቸው ያለውን ርቀት አጥብባ ወደእሷ ተጠጋች እና

"ፈጽሞ ባትወለጂ እመኛለሁ...››አለቻትና መቀመጫዋን ለቃ በተቀመጠችበት ጥላት ሄደች፡፡

አለም ስርጉት ጥላት ከሄደች በኋላ እራሷን ለመሰብሰብ ያደረገችው ሙከራ ከንቱ ነበር። ፊቷ ገርጥቷል እና እየተንቀጠቀጠች ነው፡፡ ከበረንዳው ተነሳችና ወደአዳርሹ ገባች።" ጁኒየር እየጠበቃት ነበር።

"አሌክስ?ምንድነው ቆየሽ..?ልፈልግሽ መጥቼ ነበር..በረንዳው ላይ ከስርጉት ጋር እያወራችሁ ስለነበረ ልረብሻችሁ አልፈለኩም››
ዝም ብላ በተቋጠረ ፊት ታየው ጀመር፡፡ጨነቀው‹‹ ምንድነው ችግር አለ እንዴ?"

‹‹አሁን ወደቤቴ መሄድ እፈልጋለሁ." አለችው፡፡

"ታመሻል ? ምንድን ነው የተፈጠረው-"

"እባክዎ በመንገድ ላይ እንነጋገራለን››
.ጁኒየር ያለ ተጨማሪ ክርክር እጇን ይዞ ወደ ውጭ መራመድ ጀመረ.. ሆቴሉን ለቀው ወጡና ወደ ራሱ ቀይ ጃጓር ውስጥ አስገባት። መኪናዋ ተንቀሳቀሰች ፡፡ከአካባቢው የተወሰነ ከራቁ በኃላ

"እሺ ምን ሆናሻል?"ሲል ጠየቃት፡፡

"ስርጉት  ባለቤትህ እንደነበረች ለምን አልነገርከኝም?"

የሚነዳውን መኪና መሪ መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ ደንግጦ አፈጠጠባትና አንገቱን አዙሮ መንገድ ላይ አተኩሮ። "

አልጠየቅሽም።"ሲል መለሰላት፡፡

አሁንም የሚንቀለቀል ንዴትና ቁጣ ላይ ነች…ምን ብላ እንደምትመልስለት አልገባትም፡፡የስርጉት የእሱ ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን የዳኛው ሴት ልጅ መሆኗም ጭምር ነው ያበሸቃት፡፡ዳኛው ከሶስቱ የእናቷ ገዳይ ተጠራጣሪዎች ጋር በጋብቻ የተሳሰሩ የአንድ ግሩፕ አባሎች መሆናቸውን ስታስበው..የጀመረችው ነገር ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ የበለጠ ገባት፡፡

"ግን ይህ ንዴት አስፈላጊ ነው?"ሲል ጁኒየር ጠየቀ።

"አላውቅም።"

" ነው የከነከነሽ ሌላ ጉዳይ አለ….?እስኪ ንገሪኝ?"
‹‹አይ ምንም የምነግርህ ጉዳይ የለም››

‹‹የእኔና የስርጉት ጋብቻ እኮ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ነው የቆየው። ከዛ በኃላ ጓደኛሞች ነን፡፡››
ንግግሩ የበለጠ አበሳጫት"

በፈጣሪ ጁኒዬር…ጓደኞሞች ነን ትላለህ እንዴ …?ሴትዬዋ እኮ አሁንም ከአንተ ጋር የጋለ ፍቅር ላይ ነች."

"በእኔ እና እሷ መካከል ያለው ዋናው  ችግርም  ይህ ነበር። ስርጉት ግትር  አፍቃሪ ነች
…ፋታ አትሰጥም… መተንፈስ ስላልቻልኩ ነው ልፈታት የተገደድኩት ››

"ፍቅሯ ቁንጣን ሆነብኝ እያልከኝ ነው …?በእውነት ግድ የለኝም ..ምንም አይነት ማብራሪያ እንድትሰጠኝ አልፈልግም››

"ታዲያ ቀድመሽ ለምን አነሳሽው?"

ምክንያቱም መፀዳጀ ክፍል ድረስ ተከትላ ስላፋጠጠችኝ… እና በዚህ ምርመራ የአባቷን ህይወት እያመሰቃቀልኩት እንደሆነ እና ከድርጊቴ ካልታቀብኩ እርምጃ እንደምትወስድብኝ ስለዛተችብኝ ነው››

"አሌክስ, ዳኛው አልቃሻ ነገር ነው፡፡ምን አልባት ስለ አንቺ ስርጉት ፊቷ አንድ አንድ አስከፊ ነገር ተናግሮ ለአንቺ አሉታዊ አመለካከት እንዲያድርባት ማድረጉን ለደቂቃ አልጠራጠርም. እሷ እንድታዝንለት ያደረገው ዘዴ ነው. አባትና ልጅ የተለየ አይነት ግንኙነት ነው ያላቸው፡ለተናገረችው ነገር ያን ያህል ትኩረት አትስጪው››

አለም ጁኒየር ላይ ያላት አመለካከት በጣም ነው የተዘበራረቀባት፡፡ ለሴት ያለው አመለካከት ፈጽሞ አልተመቻትም - ። ልክ ስርጉት እንደገለፀችው ዛሬ ማታ ከአንዷ ሴት ወደ ሌላ ሴት ሲዘዋወር ስትታዘበው ነበር። ወጣቱ እና በእድሜ የፀኑት ፣ ማራኪ እና ሽቅርቅሮች፣ ያገቡ እና ያላገቡ ፣ ከሁሉም ጋር ሲያሽካካ እና ሲጨዋት ነበር ። እሱ ህዝቡ እንደሚያገለግል የገበያ ማዕከል ሰራተኛ መስሎነው የተሰማት፣ ጁኒየር የሚያናግራቸው ሴቶች ሁሉ የሚፈልገውን ምላሽ እንደሚሰጡት እርግጠኛ እንደሆነ ታዝባለች ። ማንኛውንም የፈለጋትን ሴት ማሽኮርመም ለእሱ እንደ መተንፈስ ተፈጥሯዊ ነው። አንድ
ሰው ሃሳቡን በተሳሳተ መንገድ ተርጎሞ የስሜት ሥቃይ ሊደርስበት እንደሚችል እንኳን አያስብም..።ምናልባት እሷ ከስርጉት ጋር ባትወያይ ኖሮ እንደሌሎቹ ሴቶች በፈገግታው ወጥመድ ገብታ ተመሳሳይ ፈገግታ ትሰጠው ነበር ። አሁን በእሱ ላይ ተናድዳለች ፡፡

" ስርጉት ለዳኛው አባቷ ብቻ አይደለም የተከራከረችው።ካንተ ጋር ስለነበራት የትዳር ትዝታ እያነሳሳች ነበር ። የቀድሞ ጓደኛህ ልጅ መሆኔ ለእሷ እውነተኛ ፈተና እንደሆንኩ እንድታስብ ምክንያት ሆኗታል ። ያ የኔ ችግር አይደለም አይደል?››

"ምናልባት መሆን አለበት."ጠንከር ያለ ምላሽዋ አስገረመው።

" ተናደድሽብኝ አይደል?። ግን ለምን?"

"አላውቅም።" የንዴቷ ነበልባል አጭር እና ጣፋጭ ነበር። አሁን የድካም ስሜት ተሰማት።

"አዝናለሁ… ምናልባት ሁልጊዜ ትኩረት ለተነፈጋችው ሰዎች ስለምማረክ ሊሆን ይችላል ››

ቀኝ እጁን አነሳና የተራቆተ ጉልበቷ ላይ አሳረፈው ፡፡ አለም በዝግታ እጁን ከጉልበቷ ላይ አነሳችና በመካከላቸው ባለው የመኪናው የቆዳ መቀመጫ ላይ አሳረፈችው።

"ስርጉትን ለምን አገባሀት?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"በእርግጥ መጠየቅ የምትፈልጊው ይህ ነው?" አለና መኪናውን ፍጥነት ጨምሮ ያግለበልበው ጀመር››

"አዎ።"

ፊቱን ወደ እርሷ አዞረና"

በወቅቱ መደረግ ያለበት ነገር ስለነበር››

"አትወዳትም።"

ዝም አለ..
"ከ ስርጉት ጋር ከማግባታችሁ በፊት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች እንደሆናችሁ ነገረችኝ." "ፍቅረኛሞች አይደለንም አሌክስ። ግን ብዙ ጊዜ አወጣት ነበር።"

"ለምን ያህል ጊዜ?"
47👍6
"በግልጽ ማወቅ ትፈልጊያለሽ?"

"አዎ ንገረኝ››

"ባሰኘኝ ጊዜ ሁሉ››

"በዋነኛነት ከስርጉት  ጋር ፍቅር እየሰራህ  በምናብ ግን  የምትዘሙተው ከእናቴ ጋር እንደነበረ ታውቃለች?።››

"በኢየሱስ ስም..ንግግርሽ እንዴት ነው?››

‹‹እውነት ነው?"

"ሰሎሜ ሁልጊዜ ከገመዶ ጋር ነበረች…, ልክ እንደዚያ የህይወት እውነታ ነበር."

‹‹ ምንም እንኳን እሷ የቅርብ ጓደኛህ ብትሆንም ግን እሷን ትፈልጋት ነበር፣!" ዝም አለ

"ስርጉት አንድ ነገር ነግራኝ ነበር …እናቴን በተመለከተ"

"ምን?"

‹‹እናቴን ማግባት ፈልገህ ነበር።››

ለአንድ ሰከንድ ያህል አንገቱን አቀርቅሮ ከቆየ በኃላ “አዎ” ሲል መለሰ፡፡

"አግብታ እኔን ከወለደችን በኋላ ነው?"

"ከማግባቷ በፊትም ሆነ አግብታ ከወለደች በኃላ ላገባት እፈልግ ነበር."

ግራ መጋባቷን ሲያይ፣ “አንድ ወንድ ሰሎሜን አይቶ ለራሱ ሊያደርጋት መመኘቱ የሚቀር አይመስለኝም። ቆንጆ እና አስቂኝ ነበረች እና ለእሷ ልዩ እንደሆንሽ እንድታስቢ የምታደርግበት ጥበብ አላት ፤….የሆነ ነገር" ብሎ በቡጢ የመኪናውን ዳሽ ቦርድ በቁጭት ነረተው፡፡

"ከእናቴ ጋር ተኝተህ ታውቃለህ?"

"አይ … በጭራሽ ››

‹‹ሞክረህ አታውቅም? ››

‹‹ አይመስለኝም. በጭራሽ አልሞከርኩም. ቢያንስ ጠንከር ያለ ሙከራ ሞክሬ አላውቅም››

‹‹ በጣም የምትፈልጋት ከሆነ፣ለምን አልሞከርክም?"

"ምክንያቱም… ገመዶ ይገድለን ነበር."

በድንጋጤ ተመለከተችው።

‹‹የእውነት መሰለሽ እንዴ.. ለአገላለፅ ያህል ነው፡፡››

አለም ግን በማስተባበያው እርግጠኛ አልነበረችም፡፡ጣቶቹን በእሷ በኩል ወደ ላይ አንሸራትቶ አውራ ጣቱን አንገቷ ላይ አሳርፎ ደበሳት
"ይህ ..አስፈሪ ርዕሰ ጉዳይ ነው።››
‹‹እንለውጠው" በማለት በሹክሹክታ ተናገረ፣ ፡፡

እሷ ቤት ፊት ለፊት ደርሰው ስለነበረ መኪናውን አቁመው ወሪያቸውን ቀጠሉ፡፡

"ያለፈውን ለጥቂት ጊዜ ትተን ስለአሁኑ ብናስብ እንዴት ነው?›› ዓይኖቹ ፊቷ ላይ ተቅበዘበዙ

‹‹ስለአሁን ምን?››በለሆሳሳ ጠየቀችው፡፡

ድንገት " አሌክስ ካንቺ ጋር በፍቅር መጣመር እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጥያቄው አስደናጋጭና ቅፅበታዊ ነው፡፡ለአፍታ ያህል አፍጥጣ ተመለከተችው፣ መናገር እስኪያቅታት ድረስ በጣም ደነገጠች።

"ቁምነገር አይደለም አይደል?"

"አረ ከምሬ ነው?"በማለት ፊቱን ወደእሷ አስጠጋ …ጭንቅላቱን በማዘንበል..ከንፈሮቹን በእሷ ከንፈሮች ላይ አሳረፈ…ምላሽ ባትሰጥም አልተቃወመችውም… ወደ ኋላ አፈገፈገ እና ግራ የተጋባ እይታን አያት።

"አይ።"

"ለምን አይሆንም?"

"እኔ ሳልነግርህ ታውቃዋለህ። ይህ ስህተት ነው።"

"ከዚህ በላይ ያበዱ ነገሮችን ሠርቻለሁ።" እጁን ወደ ሹራቧ ልኮ ለስላሳ ቲሸርቶን አልፎ ወደጡቶቾ ጣቶቹን ሰደደ…..

‹‹ይህ ፍፁም ስህተት ነው››

"አንድ ላይ ብንሆን ጥሩ ጥንድ ይወጣን ነበር ።"

"ጥሩ እንደሚሆን በፍፁም አናውቅም።››አዝጋሚ ግስጋሴውን በአይኑ እየተከታተለ አውራ ጣቱን በታችኛው ከንፈሯ ላይ አሳረፈ ።

"የማይሆን የለም።"

ራሱን ወደእሱ አስጠጋችና እና እንደገና በፍቅር ሳመችው፣ ከዛ የገቢናውን በራፍ ከፍታ ወረደች … በሩን መልሳ ዘጋችለትና

‹‹ደህና እደር›› አለችው፡፡ አገላለጹ አስደሳች ነበር። አለም በጣም ጨዋ ሆነችለት…እንደዚህም በመሆኗ እሷን ማግኘት የጊዜ ጉዳይ እንደሆነ እንደሚያስብ ታውቅ ነበር።

ቤቷን ከፍታ እንደገባች ነበር የዘጋችውን ሞባይል የከፈተችው…መልእክት ተልኳላት ነበር፡፡አያቷን ይከታተላት የነበረው ሀኪም ነው፡፡ይህንን መልእክት እንዳነበብሽ ደውይልኝ..አስቸኳይ  ነው››ይላል..በጣም  ከመደንገጧ  የተነሳ  ሰውነቷ  ተንዘፈዘፈ
…እንደምንም እራሷን አጠንክራ ደወለችለት፡፡

‹‹ሄሎ ዶክተር…አለም ነኝ››

‹‹እሺ አለም ..እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ዶክተር..ደውለህልኝ ነበር መሰለኝ?››

‹‹አዎ በጣም አዝናለሁ፣ አያትሽ ከአንድ ሰዓት በፊት አርፋለች… ከገባችበት ኮማ ሳትነቃ ነው በዛው የሞተችው፡፡››

ስልኩን እንደዘጋች ወዲያው ነበር ሻንጣዋን ማዘጋጀት የጀመረችው፡፡ለማንም ሳትናገር መኪናዋን እራሷ እያሽከረከረች ለሊቱን ሙሉ ነድታ ሊነጋጋ ሲል አዲስ አበባ አያቷ የሞተችበት ሆስፒታል ደርሳ መኪናዋን አቆመች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
55👍15
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

አለም የቢሮውን በራፍ አንኳኳች… የኩማንደሩን ‹ይግቡ› የሚል ሻካራ ቃል እስክትሰማ ድረስ ጠበቀች እና ወደውስጥ ገባች፡፡

"እንደምን አደርክ። ልታገኘኝ ስለፈቀድክ  አመሰግናለሁ።››በማለት ከጠረጴዛው ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ ተቀመጠች ፡፡
ሳይጠይቃት አንድ ኩባያ ቡና ቀዳላትና ከፊት ለፊቷ አስቀመጠ።ስለቡናው አመሰገነችው። ተሸከርካሪ ወንበሩ ላይ ተቀመጦ፡

"ስለ አያትሽ አዝናለሁ ..አለም" አላት፡፡

"አመሰግናለሁ።"አለች፡፡

አለም የአያቷን የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈፅምና ተያያዝ ጉዳዬችን መስመር ለማስያዝ ለአንድ ሳምንት አዲስአበባ ቆይታ ከመጣች ገና ሁለተኛ ቀኗ ነው ። በቀብሩ ላይ ጥቂት የድሮ ጓደኞቾ እና ከመቅዶኒያ የመጡ አያቷን በቅርበት የሚያውቁ ጥቂት ሰዎች ነበር የተገኙት፡፡… ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ አለም ወደአረጋዊ ማእከሉ ሄዳ የአያቷን እቃዎች መሰብሰብ ነበረባት…አብዛኛውን እቃዎች እዛው ለሚስፈልጋቸው ሰዎች በመስጠት ነበር ያስወገደችው፡፡
ከዛ ጥልቅ የሆነ ትካዜ ውስጥ ገባችው፡፡ ዳግመኛ ወደ ሻሸመኔ ከተማ መሄድ ይኑርባት ወይም እዛው አዲስአባ ትቅር ግራ ገብቷት ነበር፡፡አሁን አያቷ ሞተዋል….‹‹የእናትሽ ጋዳይ ነሽ››ብሎ እጣቱን የሚጠቁምባት ሰው የለም….ታዲያ ምን አሰቃያታል?፡፡በኋላ ግን ስታስበው እንደዛ ብታደርግ ፈፅሞ የመንፈስ እረፍት እንደማታገኝ ገባት …እንደውም ከበፊቱ በበለጠ እራሷን አጠንክራ ወደሻሸመኔ መመለስ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ከህግ አንፃር፣ አሁንም ጉዳዩ በጣም ደካማ ነው…በዛም ምክንያት ፍርድ ቤት መቆም አልቻለችም። ከመካከላቸው የትኛው ለእናቷ ግድያ ተጠያቂ መሆን አለመሆኗቸውን ማወቅ አለባት። በዚህም ምክንያት ወደሻሸመኔ ተመልሳ መጣች።

ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ"እንደምትመለሺ እርግጠኛ አልነበርኩም" ብሎ በግልፅ ነገራት።

‹‹ተስፋ አልቆርጥም አልኩህ እኮ።››

‹‹ አዎ አስታውሳለሁ" አለ በብስጭት፡

"አዲስአበባ ከመሄድሽ በፊት የነጋዴዎች ማህበር አመታዊ ክብረ በአል ላይ ያሳለፍሽው ምሽት እንዴት ነበር?"በማለት ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡

በመገረም "እዛ ዝግጅት ላይ መሄዴን እንዴት አወቅክ?" ስትል ጠየቀችው፡፡ ዝም አላት፡፡

" ጁኒየር ነው የነገረህ?"

‹‹አይ።"

‹‹እና››

‹‹ምክትሌ በዛን ቀን ማታ …በአውራ ጎዳናው ላይ ከሱ ጋር በመኪናው ውስጥ አይቶሻል።ከፍጥነት በላይ ይነዳ ስለነበረ ቀልቡን ስቦት ነበር››

‹‹አዎ ነበርኩ…. ጁኒዬር ጋብዞኝ ሄጄ ነበር››

‹‹እንዴት ነው ጥሩ ጊዜ አሳለፍሽ?››

"ቆይ ስርጉት የጁኒየር ሚስት እንደነበረች ማንም ያልነገረኝ ለምንድን ነው?"

" አልጠየቅሽም።ደግሞስ ስላልተሳካ የድሮ ትዳር ማወቅ ለአንቺ ምን ይፈይድልሻል ?"

‹‹ሙሽራይቱ የዳኛው ልጅ ሆና መገኘቷ እንግዳ ነገር አይመስልህም? ።" "ይህ በፍፁም እንግዳ ነገር አይደለም."
"የአጋጣሚ ጉዳይ ነው እያልከኝ ነው?."

"አይ አይደለም:: ስርጉት ለመጀመሪያ ጊዜ ጂኒዬርን ካየችበት ቀን ጀምሮ በፍቅር ወይም በፍትወት ውስጥ ነበረች። ሁሉም ያንን ያውቅ ነበር። እሷም ምንም አይነት በደል በማንም ላይ አልፈፀመችም። ሰሎሜ ስትሞት. እድሏን ተጠቀመችበት።››

‹‹እንደዛ ነው የምታስበው››
"በግልፅ…ጁኒየር እንዲወዳት ማድረግ አልቻለችም።ምክንያቱም በየሄደበት እየተንሸራተተ የሚከፈተውን የሱን የሱሪ ዚፕ መዝጋት ለማንም ሴት ቢሆን የሚከብድ ፈታኝ ስራ ነበር።››

"ገመዶ፣ ጥድፊያው ምን ነበር? ጁኒየር ከስርጉት ጋር ፍቅር አልያዘውም ነበር። ታዲያ ለምን ተጋቡ?ነው ወይስ የቤተሰብ ግፊት ነበረባቸው?"

‹‹እነሱኑ ብትጠይቂያቸው አይሻልም?›› ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ መስኮቱ አመራች፡፡

‹‹ያው አንተም ቤተሰብ ነህ ብዬ እኮ ነው ››

‹‹አዎ…ቤተሰቦቼ ናቸው..ሁል ጊዜ አብረውኝ ነበሩ …››

ወደ እሱ ዞር አለች፣ እሱ ግን ምንም እያያት አልነበረም። ‹‹አባቴ ሲሞት ከመላው የሻሸመኔ ኑዋሪ ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ የመጡት አቶ ፍሰሀ እና ጁኒየር ብቻ ነበሩ ። ከቀብር በኃላ አቶ ፍሰሀ  ወደ ሥራ ተመለሰ። ጁኒየር ደግሞ ወደ ትምህርት ቤት ኄደ። እኔ ወደ ቤት ሄድኩ።ብዙም ሳይቆይ ሰሎሜ ወደ ቤቴ መጣች። ትምህርቷን አቋርጣ ነበር የመጣችው። አባቴን በህይወት እያለ ብጠላውም በመሞቱ ግን ብቸኝነት እንደሚሰማኝ ታውቅ ነበር። አልጋዬ ላይ አብረን ተኛን እና እስኪመሽ ድረስ እዚያ ቆየን። ወደ ቤቷ የሄደችው እናቷ እንደምትጨነቅ ስለሰጋች ነበር። ››
ንግግሩን ሲያቆም በክፍሉ ውስጥ ስሜታዊ ፀጥታ ሰፈነ። አለም ምንም እንቅስቃሴ ሳታደርግ በታሪኩ ተመስጣ .. በመስኮቱ አጠገብ ቆማ ነበር። በብቸኝነት የነበረውን ያንን ሚስኪን ወጣት አሰበችና ደረቷ ላይ ህመም ተሰማት።

"ከእናቴ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር የያዘህ በዛን ቀን ነበር?"ስትል ጠየቀችው፡፡

በቀጥታ ወደእሷ ተመለከተ… እና ከወንበሩን ለቆ ወደ እሷ ቀረበ። "የፍቅር ጉዳይ ካነሳሽ… ያንቺ እንዴት ነው?"

‹‹የእኔ ምን?››በንዴት ጠየቀችው

"ከጂኒዬር ጋር…..?ማለቴ….››ሆነ ብሎ ንግግሩን አንጠልጥሎ ተወው

"አንተ ባለጌ ነህ"አለችው

"እንደሞከረ እርግጠኛ ነኝ። እሱ ሁልጊዜም ይሞክራል።››ሲል አከለበት፡፡

"ገሃነም ግባ።"

በእሷን በጁኒዬር መሀከል ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ለምን አጥብቆ ፈለገ ?‹‹… አሁን ፊቱ ላይ የሚነበብበት ስሜት ምንድነው ?ምናልባትም ንቀት፣ ወይስ ቅናት….››አሰላሰለች፡፡

"ለምንድነው  ክረምት እናቴ ወደኮፈሌ ስትሄድ የፈቀድክላት…ወደዛ ባትሄድ ኖሮ ከአባቴ ጋር አትገናኝም ነበር….ከአንተ ጋር የነበራችሁ ፍቅርም እክል አያጋጥመውም ነበር››
"ምናልባት  የመልክአ  ምድር  ለውጥ  አስፈልጎት  ይሆናል….ወይንም  ደግሞ  ዘመዶቾ ስለናፈቋት…" ሲል በቁጭት ተናግሯል።

‹‹የቅርብ ጓደኛህ ምን ያህል ይወዳት እንደነበረ ታውቃለህ አይደል?።››
"በትምህርት ቤት ያሉ ሁሉም ወንዶች እናትሽን ያፈቅሯት እንደነበረ አውቃለው እና ደግሞ የከበርቴው ልጅ ከሆነው ጁኒዬር ጋር ስለ ፍቅር ጉዳይ አላወራም ነበር››.

"ጁኒየር እሷ ላይ ባለው ፍቅር ምን እንደተሰማው ታውቃለህ?"

‹‹ነገርኩሽ እኩ…ስለፍቅር ከእሱ ጋር አውርተን አናውቅም››

"እሷን ለማግኘት ምንም ነገር ቢሞክር ትገድለው እንደነበረ ነው የነገረኝ:: የእውነት ሁለቱም ቢከዱህ ትገድላቸው ነበር ?"

"እርግጠኛ ነኝ እንደዛ ያለሽ ንግግሩን ለማሳመር ፈልጎ ነው."አላት፡፡

"ጁኒየርም መልሼ ስጠይቀው የተናገረው ይህንኑ ነው፣ ግን አይመስለኝም" አለች
"ብዙ የሚቀሰቅሱ ስሜቶች ነበሩ። እርስ በርስ ያላችሁ ግንኙነት ተደራራቢ እና ውስብስብ ነው።"

"የምን ግንኙነቶች?"

"አንተ እና እናቴ ትዋደዳላችሁ፣ነገር ግን ሁለታችሁም ጁኒየርን ትወዱታላችሁ።››

"ምንድን ነው የምታወሪው? ከጁኒየር ጋር ፣አልወዳደርም."

"ምናልባት እያወቅክ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሌሎች ሰዎች እርስ በእርሳችሁ ያወዳድራችኋል። እና ከመካከላችሁ የትኛው ነው ሁልጊዜ ወደላይ የሚወጣው? አንተ። ያ ያስጨንቅሀል?። ››
"ይሄ የአንቺ የስነ ልቦናህ ጫወታ ነው"

"የእኔ አስተያየት ብቻ አይደለም። ስርጉት በቀደም ይሄንኑ ነገር ነግራኛለች፡፡። ሰዎች ሁል ጊዜ ሁለታችሁን እንደሚያነፃፅሩና ጁኒየር ሁል ጊዜ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ነግራኛለች።"
42👍6
"ሰዎች ምን እንደሚያስቡ መርዳትም መቆጣጠርም አልችልም."
"ጁኒየር የሰሎሜ ፍቅረኛ መሆን ፈልጎ ነበር ነገር ግን አንተን ፈርቶ ተወው ››

በመሀከላቸው ረጅም ጸጥታ ሰፈነ፡፡"አለም ጥሩ እየሞከርሽ ነው፣ ግን ከእኔ ለምርመራሽ የሚጠቅምሽ ምንም ነገር አታገኚም " አላት።
"እሺ ፍቅረኛዋ አልነበርክም? አሁን ነገሩን ማድበስበስ ምን ለውጥ ያመጣል?" የፀሐይ ብርሃን እያረፈባት ያለውን ከንፈሯን እንዲሰማት ፈለገች ....ወደእሷ ተጠጋ …በድንገት፣ እጁን  ጀርባ ላይ በማሳረፍ ወደ እሱ ጎትቶ፣ ፊቷን  በቀጥታ ወደፊቱ አዞረና ዓይኖቹን ዓይኖቿ ውስጥ ተከላቸው፡፡

"የአንቺ ቆንጆ ልዕልት… እኔን ለመፈታተን አትሞክሪ…እኔ የወንጀል ጉዳዮችን በመከታተል እና ፍርድ ቤት በመመላለስ አስራ ስምንት አመታትን አሳልፌለሁ እና በዛ ላይ እንደምታይኝ በተፈጥሮ ብልህ ነኝ ፡፡››እጁን ይበልጥ አጠበቃና ከራሱ ጋር ለጠፋት፡፡የ ትንፋሿ ሙቀት ተሰማው እና በፍጥነት ወደ ፊቷ ተጠጋ። "በእኔና በጁኒየር መካከል ስንጥቅ ለማግኘት አትሞክሪ.. ሰማሽ? ››ዓይኖቹ ጠበቡ። "እናትሽ በሁለቱ ጫፎች መሃል ላይ የመጫወት መጥፎ ልማድ ነበራት ። እንደእዚህ አይነት ጫወታ አግባብ እንዳልሆነ ትምህርት ከማግኘቷ በፊት ገደሏት። እንደዚህ አይነት ነገር በአንቺ ላይ ከመድረስ በፊት ብትማሪ ጥሩ ነው።"

በንዴት መነጨቀችውና ከእቅፉ ወጥታ ቢሮውን ለቃ ወጣች…በፍርድ ቤቱ ህንጻ ላይ ወደአለው የራሷ ቢሮ ተመልሳ ያልተረጋጉ ሀሳቦችን እያሰላሰለች እና ነገሮችን በመቀጣጠል የተወሰኑ መላምቶችን እየገመገመች ቆየች። ግን አንድ ሀሳብ እሷን እያስጨነቃት ነው። በእናቷ ሞት እና በጁኒየር ፈጣን ጋብቻ መካከል የሆነ ግንኙነት ያለ መስሎ እየተሰማት ነው፡፡የዳኛው ሴት ልጅ ስርጉትን በቀላሉ ከአእምሮዋ ልታወጣት አልቻለችም፡፡እስካሁን ከመረመረቻቸው ሰዎች ሁሉ እናቷን ለመግደል በቂ የሆነ ጥላቻ እና ምክንያት ያላት እሷ ሆና ነው ያገኘችው፡፡ከመሞቷም ቢያንስ ለጊዜው ትልቁን ትርፍ ያገኘችው እሷ ነች፡፡ወዲያው ጂኒዬርን አሳምና ልታገባው ችላለች፡፡እና ከጀርባ አድብታ የገደለቻት ወይም ያስገደለቻት እሷ ብትሆንስ?በአእምሮዋ ያሰላሰለችውን በጠቅላላ በማስታወሻ ደብተሯ ላይ አሰፈረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3418
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ገመዶ እኩለ ለሊት ላይ ስልኩ ጮኸ….

"ምንድን ነው ነገሩ" በማለት እየተነጫነጨ በተኛበት እጁን ዘረጋና ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አንስቶ ጆሮው ላይ ለጠፈና ‹‹ሄሎ››አለ፡፡

‹‹ኮማንደር መስማት አለብህ ብዬ ነው…ድንገተኛ ነገር ተከስቷል."ምክትሉ ነበር፡፡ ከመኝታው ተነሳና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡

"…ምንድነው የተፈጠረው?"

"ከእርባታ. ቦታው …ማለቴ የቤተሰቦችህ እርባታ ቦታ፣ከዛ ነው የተደወለልን"አለው…

ከአልጋው ወርዶ ጂንስ ሱሪውን መልበስ ጀምሮ ነበር፡፡ጭንቅላቱ የፍርሀት ቅዝቃዜ ሲፈስ ታወቀው፡፡

"ምን አይነት ድንገተኛ አደጋ ነው?"
‹‹ገና አልተረጋገጠም..ኃይል ወደእዛው ልከናል፡፡›› ያልተቆለፈ ሸሚዙን ከቆለፈ በኋላ ቆሞ ጫማውን አደረገ፡፡

‹‹በቃ ቶሎ አጣርተህ ደውልልኝ…ወደእዛው እሄዳለው፣ይሄው እየወጣሁ ነው… ››ስልኩን ዘጋና ኮቱንና ኮፍያውን አድርጎ ወደ ኮሪደሩ ሮጠ።
/////

አለም በከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበረች፣ ለዚህም ነው የበሯን መንኳኳት በህልሟ መስሎ የተሰማት…።ህልም ውስጥ ነበረች….በመጨረሻ ተከታታይ የሆነው የጥሪ ድምፅ ከእንቅልፏ ቀስቅሷት።

"ተነሺ እና በሩን ክፈቺ."በቁጣ እየጮኸባት ነው፣ ቁጭ አለችና አልጋው ዳር ያለውን መብራት አበራችው… መብራቱ ሲበራ …. ብርሃኑ ዓይኗን አጭበረበራት።

"ገመዶ ነኝ… ክፈቺ?" ጮኸ ። ዝም አለችው፡፡

"በአስር ሰከንድ ውስጥ ካልተነሳህሽ በሩን ሰብረዋለው››

የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች። ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ገደማ ነበር።

‹‹ኩማንደሩ ወይ ሰክሯል ወይም አብዷል።››ስትል አሰበች፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ባለበት ሁኔታ በሯን ልትከፍትለት አልፈለገችም።

"ምን ፈለክ?"

ከእሱ መልስ ስትጠብቅ በራፉ ላይ ፈንጅ የተጣለበት ይመስል ጎጎጎጎ አለና ተከፈተ….ተንደረደረና መኝታ ቤቷ ገባ፡፡በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠች አልጋዋ ላይ ቆመች "ምን እየሰራህ ነው?"ብላ ጮኸችበት በቆመችበት አልጋ ልብሱን እየሰበሰበች እርቃኗን ለመሸፈን እየጣረች ነው››

"አንቺን ለማግኘት ነው የመጣሁ ‹‹
ከአልጋው ላይ ጎተተና ወለሉ ላይ አቆማት፣የተጠቀለለችበትን አልጋ ልብስ ከላዬ ላይ ገፎ ወረወረው፣እርቃኗን በፓንት ብቻ ፊት ለፊቱ ቆመች፣ምን ሊያደርጋት እንደሆነ መገመት ሁሉ አልቻለችም፡፡

"ኩማንደር በሬን ገንጥለህ መኝታ ቤቴ ለመግባትህ በቂ ምክንያት እንዳለህ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ማብራሪያ አለኝ።" አለና መሳቢያውን ከፈተ እና ውስጡ ያሉትን ልብሶች ማተረማመስ ጀመረ።

"ንገረኝ ምን እየፈለክ ነው?."አለችና እርቃኗን ወደእሱ ሄዳ ሚያተራምሰውን  የቁምሳጥን በራፍ በዳሌዋ ገፋችና ዘጋችበት ፡፡

"ምን ፈልገህ ነው?"ዳግመኛ ጠየቀችው፡፡
"ልብስ። እንደዚህ እርቃንሽን  መውጣት ካልመረጥሽ በስተቀር  ምትለብሺው ልብስ ያስፈልግሻል››

‹‹ወደየትም አልሄድም››

" ጂንስሽ የት ነው ያለው?›› በ ወፍራም ድምፁ ጠየቀ ። "የትም አልሄድም። ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቃለህ?››

ድንገት ቀና ሲል ከአልጋው አጠገብ ባለው ግድግዳ ልብሷ ተሰቅሎ አየው፡፡ ጂንሱን ከተሰቀለበት ላይ አወረደና ወረወረላት፣ መያዝ ስላልቻለች ወደ ወለሉ ወደቀ።
ከጫማዋቾ ውስጥ አንዱን መረጠና ወደእግሯቾ አቀረበላት፡፡ ዝም ብላ ፈዛ ታየው ጀመር፡፡ "እሺ.. እንዳለብስሽ ትፈልጊያለሽ?"

እሱን ለማስቆጣት ምን እንዳደረገች መገመት አልቻለችም። እርቃኗን እሱ ፊት ቆማ መከራከሩ ስለደከማት ጆንሱን አነሳችና አጠለቀች ፡፡ከላይ ሹራብ ለበሰች….ከኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ አንድ ካልሲ አወጣችና አራግፋ አጠለቀችና ጫማዋን አደረገች፡፡ በመጨረሻም ዞር ብላ አየችው።

"እሺ ይሄው ልብስ ለብሻለሁ …አሁን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ንገረኝ ?"

"እየሄድን  እነግርሻለው  ››አለና  እጆቿን  በመያዝ  እየጎተተ  ይዞት  ወጣ  ፡፡በንዴት እየተንቀጠቀጠች ነበር።

‹‹እንዲህ እንድታደርገኝ ማን ነው የፈቀደልህ?››

"አንገትሽን መስበር አለብኝ…..አላደረገውም››በማለት ወደእሷ ተጠጋና ከንፈሯን ሳማት።ያለተቃውሞ ተሳመችለት፡፡ምላሱን ወደ አፏ ውስጥ አስገባ። በዚህ ጊዜ በቁጣ ስሜት መነጨቀችውና እራሷን አላቀቀች፡፡

ኮትዋን ከሳሎን በራፍ አካባቢ ካለው ማንጠልጠያ አነሳችና ያዘች፡፡ ከቤት ይዞት ወጣ " በሩስ?"ብላ ጠየቀችው ።
"የሚጠግን ሰው እልካለሁ።"

"በዚህ ለሊት?"

"በፈጣሪ … በሩን እርሺው..በአካባቢው ቤትሽን በንቃት የሚጠብቁ ፖሊሶች አሉ" ብሎ ጮኸ።

‹‹የሚጠብቁ ነው ሚሰልሉኝ?››

እጇን ጨምድዶ እንደያዛት ስትጠብቀው ወደነበረ ታክሲ ውስጥ ይዞት ገባ፡፡

"በፈጣሪ ገመዶ…ምን እየተፈጠረ ነው……?ነው ወይስ እያሰርከኝ ነው?››

‹‹እያሰርከኝ ..አንቺን……?ምነው ወንጀል ሰርተሸል እንዴ?›› ፡፡

‹‹እና ምንድነው ንገረኛ….?ወደየት እንደምሄድና ለምን እንደምሄድ የማወቅ መብት አለኝ›› ።

"የእርባታ ቦታው እየተቃጠለ ነው."

‹‹የእርባታ ቦታው.?.የነጁኒዬር?››

‹‹አዎ››

‹‹ወይ..ፈረሶችህ ተረፉ?››

ፈረሶቹን ምን ያህል ይወዳቸውና በምን ያህል መጠን ይንከባከባቸው እንደነበረ ስለምታውቅ ነው ቀድማ ስለፈረሶቹ የጠየቀችው፡፡

‹‹አላውቅም…የወደመውንና የተረፈውን ስንደርስ ነው የምናውቀው፡፡››
////
ሲደርሱ እሳቱ ከፈረሶቹ ጋጣ አካባቢ እየተንቀለቀለ ነው…በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሚገኘው የእንጨት ፋብሪካው ከአደጋ ውጭ ነው፡፡ቢሆንም በንፋስ ታግዞ ወይም በሆነ ምክንያት እሳቱ እዛ ቢደርስ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው፡፡

እንደደረሱ መኪናዋ ስትቆም ኩማንደሩ ከመኪናው ወረደና ወደእሳቱ አቅጣጫ ተንቀሳቀሰ…አለም ከኋላው ተከተለችው፡፡ከአንዱ የፈረስ ጋጣ ጭስ ሲትጎለጎል ይታያል…አለም ሆዷ ተገለባበጠባት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነበር።ብዛት ያላቸው የእርባታው ሰራተኞችና የአካባቢው ኑዋሪዎች ቅጠለም አፈርም እየተጠቀሙ እሳቱ እንዳይዛመት ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ነው፡፡
አንድ ሰው ወደኩማንደሩ ቀርቦ"በጣም ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ደርሰውበታል" ሲል ነገረው፡፡

‹‹ሰውስ አልተጎዳም?››

‹‹አንድ የተጎዳ ሰው አለ…››የሚል ድምፅ ሰማ፡፡

"ማንው የተጎድቷል?"

‹‹በጣም አሰቃቂ ትዕይንት ነበር።ከፈረስ ተንከባካቢዎች አንዱ ነው… በቂ አየር ወደ ሳምባዋ መሳብ አልቻለችም። ፈረሶችን ለማዳን ሲሯሯት አንድ እግሩም ተሰብሯል››

በዛ ቅፅበት አንድ ፈረስ እየጮኸ ነበር፣ በግልጽ ህመም ላይ እንዳለ ያስታውቃል። አለም እስካሁን ሰምታ የማያውቀው እጅግ አሳቃቂ ድምፅ ነበር የሰማችው። ገመዶ በፍጥነት ወደእዛው አመራ…ከኃላው ተከተለችው….የአቶ ፍሰሀ ቤተሰቦች በጠቅላላ በለሊት ቢጃማቸው በአካባቢው ነበሩ ፡፡መኖሪያ ቤታቸው ከእርባታው ድርጅት ብዙም ሰላማይርቅ እንደሰሙ በእግራቸው ነው ሮጠው ወዲያው ነው የደረሱት፡፡ ሳራ እያለቀሰች ነበር። ፍሰሀ

እራሱን ተቆጣጥሮ በፅናት ቆሞ ይታያል…ጁኒዬር እናቱን አቅፎ ያፅናናል፡፡ ገመዶ ወደ ጎን ገፋቸው እና እሳቱ ጠፍቶ ጭሱ ብቻ ከሚታይበት ጋጣ ውስጥ ገባ ፡፡
48👍4🔥1