አትሮኖስ
268K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
433 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

          ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
           #ክፍል_1

ዱብዕዳ

ከተኛሁ በኋላ የተደወለውን ስልክ ማንሳት ሞት መስሎ ተሰማኝ: ዓይኔን እንደጨፈንኩ መብራት ለማብራት ግድግዳውን ዳበስኩት፡፡ ነገር ግን ማብሪያና ማጥፊያውን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ልማድ ሆኖብኝ ዓይኔን አንድ ጊዜ ከከፈትኩ በኋላ እንደገና እንቅልፍ ስለማይወስደኝ ብዙ ጊዜ እንቅልፌን ካልጨረስኩ ስልክ የማናግረው ዓይኔን እንደጨፈንኩ ነው፡፡ ኮመዲኖ ላይ የነበረውን ባትሪ አብርቼ ማብሪያና ማጥፊያውን ለመፈለግ ስል ዓይኔን ስከፍት ግን ያልጠበኩት ነገር ገጠመኝ፡፡ ምንም የተኛሁ ሳይመስለኝ ነግቶ ቤቱ በብርሀን ተሞልቶ ነበር፡፡ ለካስ ማታ ራሴን እስክስት ጠጥቼ ስለነበር ጫማዬንና ልብሴን ሳላወልቅ ወደ ግርጌ ዞሬ በመተኛቴ ነበር ማብሪያና ማጥፊያውን ማግኘት የተሳነኝ:: ወደ ራስጌ ዞሬ ስልኩን ኮመዲኖው ላይ ብፈልግም ላገኘው አልቻልኩም:: ሁሌ አምሽቼ ከመጣሁና የእረፍት ቀኔ ከሆነ ስልኩ እንዳይረብሽኝ ሳሎን ውስጥ ማስቀመጤ የተለመደ ስለሆነ ማታም እዚያው ወስጄው ኖሯል :: አማራጭ አልነበረኝምና ስልኩን እንድታቀብለኝ "ዓለሚቱ" እያልኩ ተጣራሁ፣ ግን መልስ የለም:: ረስቼው ነው እንጂ ለካስ ዘመድ ጥየቃ ብላ ሄዳለች፡፡ ዘመድ ያላት ሠራተኛ መቅጠር ጣጣ ነው፡፡ "ሴቶች ዘመዱን የጨረሰ ባል ስጠኝ" እንደሚሉት እኔ ደግሞ ዘመዶቿን የጨረሰች ሰራተኛ ስጠኝ እንዳልል ፈራሁ፡፡ ነጠላ ጫማ ፍለጋ አጎነበስኩ፡፡ ከሁሉ በላይ ጫማ መፈለግን የመሰለ ቦርጭን እንደሚያስተጣጥፍ ሥራ እጅግ የሚያስጠላኝ ነገር የለም፡፡ ላገኘው ስላልቻልኩ በባዶ እግሬ ሮጥ ሮጥ እያልኩ እንደምንም ብዬ ስልኩን ለማንሳት ወደ ሳሎን ለመሄድ ስደናበር ተበታትኖ የነበረው ወንበር አደናቅፎ ሊጥለኝ ሲል የመኝታ ቤቱን በር ተደግፌ ቆምኩ፡፡ እንደምንም ሄጄ የስልኩን እጄታ ወደ ጆሮዬ አስጠጋሁና፤ "ሀሎ" አልኩ፡፡ ምንም ድምፅ አልነበረም፡፡ ስደነባበር ደቂቃዎች ፈጅቼ ኖሮ ደዋዩ ሰው ተስፋ ቆርጦ ስልኩን ዘግቶት ነበር፡፡ ሶፋው ላይ ቁጭ ብዬ እንደመሳቅ ቃጣኝ፡፡ መሳቅ የቃጣኝ በሌላ ነገር ሳይሆን "እንዲህ አርበትብቶና አደናብሮ ያውም ለሚዘጋ ስልክ ምን አስሮጠኝ?" የሚለውን ሳስብ ነበር፡፡ እርግጥ በጠዋት የተደወለና ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ያስነሳኝ ስልክ ስለነበር ነገሮችን አሰባስቤ ለማስብ ፋታ ባለማግኘቴ፣ አሊያም ዓለሚቱ እደጅ በማደሯ "አንድ ነገር ሆና ይሆን ያለወትሮዋ ደጅ ያደረችው?'' እያልኩ ስጨነቅ

ስለነበር ይኸው ሳይሆን አይቀርም እንዲህ ያሯሯጠኝ፡፡ የራሴ ነገር እየገረመኝ ወደ አልጋዬ ለመሄድ ስነሳ ስልኩ ዳግም አቃጨለ፡፡ ስልኩን አነሳሁና፣ "ሀሎ" አልኩ፡፡ "አቶ አማረ?" አለ በስልክ የሚያናግረኝ ሰው፡፡ "አዎ ነኝ " አልኩ ተጣድፌ፡፡ "ከዚህ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው':: "ምነው በደህና?" "አይ በደህና ነው፡፡ወ/ሮ አልማዝ አስፋውን ያውቋታል?" ራሴ በአንዳች ነገር የተመታ ያህል አዞረኝና ሶፋው ላይ ተመልሼ ቁጭ አልኩ፡፡ አልማዝንና ፖሊስን ምን አገናኛቸው? አንድ ነገር እንደተፈጠረ ስለተስማኝ ተቻኩዬ እንደማውቃትና ምን እንደተፈጠረ እንዲነግረኝ ጠየቅሁ። እሱ ግን ለጥያቄዬ መልስ ሳይሰጠኝ "ለጥያቄ ስለምንፈልግዎ እባክዎን አዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ድረስ ቢመጡልን" አለኝ፡፡ "ምንድነው ችግሩ ለምን አትነግረኝም? " አልኩት፡፡ "ሲመጡ ይደርሳል'' ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋብኝ። መብረቅ እንደመታው ዛፍ እተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ ምን ተፈጥሮ ይሆን? በሕይወት ትኖር ይሆን ወይስ ሞታለች? ግን እኔ ለምን ተፈለግሁ? እንዴትስ እዚህ ልትመጣ ቻለች? ከሳኝ ይሆን? ሌላ ሌላም ጥያቄ ጭንቅላቴ ውስጥ መመላለስ ጀመረ። ሁሉንም ነገር ማውጣትና ማውረዱ ጥቅም ስለሌለው፣ የሆነው ነገር ሆኗልና ፈጥኜ መድረስ ስላለብኝ እየተንገዳገድኩ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ ያጣሁትን ጫማ ለመፈለግ እጄን አልጋው ሥር ሰድጄ ስደባብሰ ሽታው መራኝና አፍንጫዬ ሥር አገኘሁት:: ልብሶቼን ለመልበስ ስፈላልግ ከራስጌዬ አጠገብ ኮሞዲኖው ላይ ከተቀመጠው ከአልማዝ ፎቶ ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዓይኖቿ አሁንም ቦግ እንዳሉ ናቸው፡፡ ዘወትር የማይጠፋው ፈገግታዋ አሁንም አለ፡፡ እዚህ ግዑዝ አካል ላይም "ለዘላለም" ተጣብቆ ይኖራል፡፡ አሁን የሌለውና የማይሰማው ነገር ያ አሳዛኝ ድምዕዋ ብቻ ነበር፡፡

"ለምን ፈገግ አለች?" አልኩ፣ ትኩር ብዬ ፎቶዋን እያየሁ:: አስተያየቷንም ሳየው መሰለኝ፡፡ "አይ አንተ ምስኪን፣ አሁንም አለህ?" እያለች የምታፌዝብኝ አይ አልማዝ! አሁንም አይበቃትም? ለምን ሁሌ በእኔ ላይ እየሳቀች ታፌዛለች? በመውደዴ እንደጅል ቆጥራ ለምንስ ትጫወትብኛለች? ምን ይታወቃል፤ የበፊቱ አልበቃ ብሏት አሁን ደግሞ እንደገና እኔኑ ጥፋተኛ አድርጋ አሳኝ ሊሆን ይችላል አልኩ፡፡ ግን ለምን? ከእኔ ከምስኪኑ ምን ለማግኘት? ይኸ ሊሆን የሚችል አይደለም ፡፡ አንድ ነገር ሆና መሆን አለበት እያልኩ ወደ ጭንቀት ባሕር ሰጠምኩ፡፡ ፎቶዋን ደግሜ አየሁት፡፡ አይ አልማዝ! ሁሌ መሳቅ፣ ሲደሰቱም መሳቅ፣ ሲያሞኙም መሳቅ፣ ያኔም እንዲህ ነበረች፡፡ ጥንትም ገና ሳያት ያቀረበኝ ይኸው ሳቋ ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል፤ አለማያ ዩንቨርሲቲ እያለን እሷ ለምሳ የምትሰለፈው ከሀረሮች ጋር ነበር፡፡ ያኔ ሁሉም ተማሪ በተለይ በምሳ ሰዓት ድካምና ረሀቡ ፀንቶበት ቢያወራም በሹክሹክታ፣ ቢራመድም በቀስታ ነበር፡፡ የሀረር ልጆች ብቻ ሲከፋቸው አይታይም:: ሁሌ መሳቅ፣ ሁሌ መደሰት ነው፣ ጫት ብቻ አይጥፋ እንጂ! ጫት ተገዝቶ ከተቀመጠ ችኮላው ለሱ ነው፡፡ ሁሌ ቀደም ብለው ሰልፍ የሚይዙት እነሱ ናቸው፡፡ ሁሌ ከሰዓት በኋላ እነሱን ያየ ሰው ደስተኛ መሆናቸውን ያለጥርጥር መናገር ይችላል፡፡ ግን ምን ያደርጋል? ማታ ማታ ብቻ ከምርቃና በኋላ ድብርት ይይዛቸዋል፣ አንደበታቸውንም ይቆልፈዋል፡፡ በዚህ ሰዓት አላርፍ ብሎ ከእነሱ ጋር መቃለድ ወይም አፉን መክፈት የፈለገ ሰው ካለ የሚከተለው ሊሸከመው የማይችል ከእናት ጋር የተያያዘ ስድብ ነው:: መጀመሪያ አካባቢ በተለይ ከወደስሜን የመጣ ሰው እንዲህ ዓይነት ስድብ ሲሰደብ አንቄ ካልገደልኩ ይል ነበር። አንዴ ትዝ ይለኛል አንድ ጎንደሬ ተማሪ በዚህ ስድብ ተናዶ፣ “እኔው እራሴ እምዬን? እሱው ራሱ እንኳን ቢሆን ይሻል ነበር፣ እንዴት ያለ ነውር ነው እናንተ ሆዬ!" በማለት ካልገደልኩ ብሎ ግቢውን እንደበጠበጠ ትዝ ይለኛል፡፡ የአልሚና ጠባይ ግን እንደጫት ቃሚዎቹ ፀሐይ ስትወጣና ልትጠልቅ ስትል አብሮ ሲለዋወጥ አይታይም:: ሁሌ ከፊቷ ላይ ፈገግታ አይጠፋም፡፡ ከሷ ጋር በመልክ ቀለሟ ተቃራኒ ከሆነች የሴት ጓደኛዋ ጋር ማለቂያ የሌለው ወሬ እያወሩ መንከትከት የተለመደ ጠባያቸው ነው፡፡

አልሚና ቀላ ስትል ጓደኛዋ ግን ጠቆር ያለ ግን ውብ ቀለም ያለው ፊት አላት፡፡ የግቢው ሰው በዚሁ ማለቂያ በሌለው ወሬያቸው የተነሳ ቢቢሲ ይላቸዋል፡፡ እነርሱ ቤተመጻሐፍት ውስጥ ካሉ ጥናት የለም፡፡ ሲንሾካሾኩ ድምፃቸው አጠገባቸው የተቀመጠውን ሰው ሁሉ ይረብሻል፡፡ እኔ ግን በድምፃቸው ተረብሼ ካጠገባቸው አልጠፋም፡፡ ብዙውን ጊዜ የታፈነ ሳቃቸው ቀልቤን ስለሚስበው ምን እንደሚያወሩ ለማዳመጥ ጆሮዬን ሳሾል ጥናቴ መና ሆኖ ይቀራል፡፡ ብዙውን ጊዜ የትም ቦታ ቢሆን አልማዝና ኤልሳቤጥ ስለማይለያዩና አፍ ለአፍ ገጥመው እያወሩና እየተሳሳቁ ሲሄዱ ቀልብን ስለሚሰርቁ ግቢው ውስጥ እነሱን የማያውቅ ተማሪ አለ ማለት አያስደፍርም፡፡ አልፎ አልፎ የእርሻ ኢኮኖሚክስ ተማሪ የሆነው ተሾመ የሚባለው ልጅ አብሮ ከእነሱ ጋር