🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_2
"አዎ! በስልክ እዚህ እንድመጣ ቀጥረውኝ ነበር፡፡ አልማዝ አስፋውን በተመለከተ ተፈልጌ ነው" አልኩኝ። የረሳውን ነገር ያስታወሰ በሚመስል ሁኔታ፤ በፊት፤ "እ! አቶ አማረ አንተ ነህ ? ተቀመጥ" አለኝ፡፡ እኔ ግን ከመቀመጤ "ምነው ለምን ፈለጋችሁኝ? በደህና ነው? አልማዝ ደህና አይደለችም እንዴ?" በማለት አከታትዬ ጠየቅሁት፡፡ ሃምሳ አለቃው በተረጋጋ መንገድ! "ይቀመጡ አቶ አማረ፤ ስለአልማዝ ሁኔታማ ከእኛ በላይ እርስዎ የሚያውቁ መስሎኝ በማለት አንዴ አንተ አንዴ አንቱ እያለ ጥያቄ አቀረበልኝ፡ እንደተቀመጥኩ፤ “አቶ አማረ፣ ሃምሳ አለቃ አደፍርስ አባላለሁ፡፡ አሁን የፈለግንዎት አልማዝን በተመለከተ ከእርሶ የምንፈልገው መረጃ ስላለ ነው::" “አልገባኝም የምን መረጃ ነው ከእኔ የምትፈልገው?" "መጨረሻ ላይ ስለነበረው ሁኔታ ነዋ"፡፡ "አልገባኝም ሃምሳ አለቃ፤ ግልፅ ብታደርግልኝ'። "እንዴት አልገባዎትም? የሚያውቁትን ነገር እኮ ነው የጠየቅሁዎት ማለትም ስለአልማዝ የሚያውቁትን ነገር ሁሉ አንድባንድ፣ በዝርዝርና በግልጽ እንዲነግሩን እንፈልጋለን፡፡ ይኸውም የት እንደተዋወቃችሁ፣ ግንኙነታችሁ ምን ዓይነት እንደነበርና በኋላም እንዴት እንደተለያያችሁ እያለ ያልጠበቅሁትን ጥያቄ ይጠይቀኝ ጀመር፡፡ እኔም መልስ በመስጠት ፋንታ አልማዝ የት እንዳለችና ምን አዲስ ነገር እንደተፈጠረ መጀመሪያ እንዲነግረኝ ወተወትኩት፡፡ ነገር ግን ይህንን የሚነግረኝ የሚጠይቀኝን ጥያቄ ሁሉ ከመለስኩ በኋላ መሆኑን ነገረኝ፡፡ አማራጭ አልነበረኝምና መልስ ለመስጠት ዓመታት ያስቆጠሩ ትዝታዎቼን ማሰባሰብ ጀመርኩ፡፡ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የነበረውን የመጀመሪያ ትውውቃችንን ቆጠብ ባለ ሁኔታ ነገሬው መልስ እንዲሰጠኝ ብጠብቅም፣ ከእኔ ገና በጣም ብዙ መስማት የሚፈልግ መሆኑን ዳግመኛ ስለነገረኝ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና ትረካዬን ልቀጥል ስል፤
“አንድ ነገር ግልጽ ላድርግልዎት ታሪኩ መቀነጫጨብና የምንፈልገውን ቁምነገር የሚያሳጣን መሆን ስለሌለበት፤ ይህ አያስፈልግም ከምልዎት ውጪ ሁሉንም ይግለጹልን፡፡" አለኝ በአጽንኦት፤ "አዎ! ቤተመጻሕፍት ውስጥ በፈገግታ የተጀመረው ትውውቃችን በደጅም ቀጠለ፡፡ ቤተመጻሕፍት እንደተዘጋ እነሱ ፊት ለፊት እኔ ከኋላ ተከታትለን ወጣን፡፡ ተማሪው ሁሉ ወደ ማደሪያው አምርቶ ስለነበር የቀረነው እኛ ብቻ ነበርን፡፡ ከቤተመጻሕፍት ፊት ለፊት በአጫጭሩ ተከምከመው በግራና ቀኝ በተተከሉ ዕዶች የተከበበችውን "ላቭ ስትሪት" ወይም "የፍቅር ጎዳና" ተብላ የምትጠራውን ጠባብ መንገድ ለሁለት ዘግተው እየተሳሳቁ በዝግታ ይሄዱ ስለነበር ከኋላቸው ስደርስ ዝግ ለማለት ተገደድሁ፡፡ ለማለፍ ይቅርታ መጠየቅና መንገድ ማስከፈት ስለነበረብኝ እየፈራሁ በጥግ በኩል "ይቅርታ" ብዬ ለማለፍ ስሞክር ይብስ ተብሎ እሱም ተዘጋብኝ:: በሌላው ዳርቻ ለማለፍ ስሞክርም ለካስ ሆን ብለው የሚያደርጉት ድርጊት ኖሮ ያችንም መልሰው ዘጓት፡፡ ግር ብሎኝ ቆም እንደማለት ስል" "የት ለመሄድ ነው ችኮላው? ለጥናት ከሆነ ያጠናኸው ይበቃሃል። ጥናት ሲበዛ ጥሩ አይደለም፣ ያሳብዳል ይባላል፡፡ ስለዚህ አንዳንዴ እረፍትም ጠቃሚ መሆኑን አትዘንጋ" አለችኝ የኔ መካሪ፡፡ የምመልሰው ጠፍቶኝ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡ ሁል ጊዜ እንዴት እንደማናግራት ሳወጣና ሳወርድ እውላለሁ፡፡አንዳንዴም በሕልሜ አገኛትና ከማውራት አልፌ አቅፌ ስስማት ይታየኛል፡፡ ግን አንድም ቀን ደፍሬ በውኔ አንዲት ቃል ትንፍሽ ብዬ አላውቅም፡፡ ከየት የመጣ ትንፍሽ ማለት! ቀና ብዬ እንኳን የማያት ብዙ ርቃ ከሄደች በኋላ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ "ዛሬስ የመጣው ይመጣል እንጂ ሳላናግራትማ አልመጣም" ብዬ ቆርጬ እወጣና በምታልፍበት መንገድ ላይ ስጠብቃት እውልና አጠገቤ ስትደርስ፣ "ኤጭ! ከጓደኞችዋ ጋር ነች፣ ያ ሴታ ሴት ተሾመ አጠገቧ አለ፣ ወይም ወደ ሆነ ቦታ ለመሄድ ስለቸኮለች አሁን ቀልቧን ሰብስባ አታናግረኝም™ እያልኩ ሰበብ ፈጥሬ እመለሳለሁ:: አንዳንዴ ደግሞ ብቻዋን ከወጣች እንደነገሩ ከተል እልና ባጋጣሚ ዞር ካለች አቅጣጫዬን ለውጬ እሄዳለሁ፡፡ ዛሬ ግን እሷው ቀድማ ስታናግረኝና መንገዱ ወለል ብሎ ሲከፈትልኝ የምናገረውና የማደርገው ጠፍቶኝ ፈዝዤ መቆሜ ምን ይባላል? አሁን ወደድኩም ጠላሁም ልወጣው ከማልችለው እውነታ ጋር ተፋጥጫለሁና መልስ መስጠት ስለነበረብኝ፣ "እ... እ.... አልቸኮልኩም " ብዬ በነበርኩበት ፈዝዤ ቆሜ ቀረሁ።
መፍራቴን እንዳወቁና እንዳዩ በሳቅ መንከትከት ጀመሩ፡፡ ሳቃቸውን ስሰማማ መላ ሰውነቱን ድንጋጤ ወረረው ::ይባስ ብሎም ጉልበቴ መብረክረክ፣ ላቤም በፊቴ ላይ ችፍፍ ማለት ጀመረ፡፡ አይገርምም! ላብ በጭለማ ያውም በብርድ ወቅት፡፡ እፍረቴን ለማስወገድ በሚመስል መልኩ እጇን ዘርግታ፣ "እንተዋወቅ፤ አልማዝ እባላለሁ፣ እሷ ደግሞ ኤልሳቤጥ ትባላለች" አለችኝ፡፡ አልማዝ ስልክክ ያለች ቆንጆ ነች ማለት ባይቻልም የደስ ደስ ያላትና ያያት ሁሉ የሚወዳት፣ ፊቷ የሚማርክ የቀይ ዳማ ነች፡፡ ኤልሳቤጥ ጠቆር ስለምትል የእሷን ቅላት ታጎላዋለች እንጂ ቀይ የምትባል አልነበረችም:: ከሁለመናዋ እኔን የሚስቡኝ ግን ጎላ ጎላ ያሉት ዓይኖችዋ እና ከፍልቅልቅ ሳቅዋ ጀርባ የተደበቁት ሳቅ አድማቂዎቹ ነጭ ሰልፈኛ የሚመስሉት ጥርሶቿ እንዲሁም ውብና ተመጥኖ የተሰራው ከንፈሯ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀጠንና ረዘም ያለች ሆና ከወደ ዳሌዋ ሰፋ ያለች ናት፡፡ አልማዝ ምንም እንኳን ለውበትዋ ብዙም የማትጨነቅ፤ መኳኳልና መሽቀርቀር የማታበዛ ብትሆንም፣ እንደነገሩ እንኳን ለባብሳ ስትወጣ መላ ሰውነቷ ውበትን ይላበሳል፡፡ እኔ በተለይ እሁድ እሁድ ልብስ ለማጠብ እንደነገሩ ሆና ስትወጣ ማለትም ለአለባበስዋም ሆነ ለመልኳ ብዙም ሳትጨነቅ ሳያት በጣም ታምረኛለች፡፡ ፀጉርዋ ዞማ ሆኖ ጀርባዋ ላይ አይተኛ እንጂ ሉጫ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሌላው እኔን የሳበኝ የድምፅዋ ቃና ነው፡፡ ቤተመጻሕፍት ውስጥ ስትንሾካሾክም ሆነ መንገድ ላይ ስታወራ ስሰማት የሙዚቃ ቃና ያለው ድምፅዋንና አወራሯን ተከትለው ወደ ላይና ወደ ታች የሚንከባለሉት ዓይኖችዋ ማንንም የማማለል ችሎታ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ባጠቃላይ ከግቢው ተወዳጅ ሴቶች ውስጥ ብቸኛዋ ባትሆንም ከዋናዎቹ ቆንጆዎች ጎራ የምትመደብ ነበረች፡፡ለእኔ ግን ከሁሉም በላይ የቆንጆ ቆንጆ ነበረች::" ሃምሳ አለቃው ለዛ ቢስ ፈገግታውን እያሳየኝ፤ "የሚገርም ነው! ለምን ሰዓሊ ወይም ደራሲ አልሆንክም? በጣም ጥሩ ገለፃ ነው፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ እንዴት እንደተዋወቃችሁ በዝርዝር ንገረን" አለኝ በትዕዛዛዊ ስሜት፡፡ አነጋገሩ የለበጣ ቢመስልም አማራጭ አልነበረኝምና ትረካውን ቀጠልኩ፡፡ "እዚያ የፍቅር ጎዳና ላይ ቆሜ ፈራ ተባ እያልኩ ስሜን ተናገርኩ፡፡ ጊዜው ቢርቅም ትክክለኛ ስሜን የተናገርኩ ይመስለኛል፡፡ ድንጋጤውም ቀስ በቀስ እየለቀቀኝ በመሄዱ በእነሱ ጨዋታ አምጪነት የቆጥ የባጡን መቀባጠር ጀመርን፡፡ እኔም ብዙም ቁም ነገር ያለው ጨዋታ ባላመጣም የተቻለኝን ያህል አወጋሁ፡፡ በመጨረሻም ወደ ፊት አብረን ለማጥናት ተነጋግረን ተለያየን፡፡