አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከምሽቱ 5 ሰዓት ስንዱ ስራዋን ጨርሳ ለመተኛት ወደመኝታዋ መጥታ ከውጭ ቀርቅራ የሄደችውን መኝታ ቤት ስትከፍት ነበር..ሳባ 14 ዓመት ወደ ኋላ የተጓዘችበትን ረጅም የትዝታ ጉዞ አቋርጣ የተመለሰችው፡፡ስንዱ ቀስ ብላ ከፍታ ገባች ስታያት ጭብጥብጥ ብላ በተኛችበት አይኗን ቁልጭ ቁልጭ ታደርጋለች፡

‹‹ውይ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?››

‹‹አይ አረ አልተኛሁም ነበር?››

‹‹ምነው እስከአሁን?አመመሽ እንዴ?››

‹‹አይ ምንም አልል..እንዲሁ የባጥ የቆጡን ሳስብ ነው?››

‹‹ካልተኛሽማ እራት ላምጣልሽ?››

‹‹አረ እኔ ነገም አልበላ..ቅድም እኮ ጠቀጠቅሸብኝ.ይልቅ. ስትደክሚ ነው የዋልሽው ነይና ተኚ›› ‹‹ካልሽ እሺ››
አለችና..ወደቁምሳጥኑ.ሄዳ ከፈተችና ለብሳ ስትሰራበት የቆየችውን ቀሚስ አውልቃ ሌላ ፒጃማ ከውስጥ አውጥታ ስትለብስ ከተደረደሩት ልብሶች መካከል የሆነ ቢጫ ልብስ ከቁምሳጥኑ ተንሸራቶ አልጋው ጠርዝ ላይ ወደቀ…ሳባ ጨርቁ ሳታስበው ትኩረቷን ሳበውና እጇን ዘረጋች…ወደራሷ ጎተተችው፡፡

‹‹እንዴ ስንድ ይሄ ምንድነው?››

‹‹የመነኩሴ ልብስ ነዋ››

‹‹የመነኩሴ?…እትዬ ልትመለኩስ ነው.እንዴ?››እትዬ ያለችው የስንዱን እናት ነው፡፡

‹‹አይ እሷ ገና ሌላ ለማግባት ሁሉ ሳታስብ አትቀርም››ስትል ቀለደች

‹‹እና የማን ነው?››

‹‹የእኔ?››

ሳባ ቆሌዋ ነው ተገፈፈው

‹‹ምን?›ከተኛችበት  ብርግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምነው ?ይሄን ያህል ያስጨንቃል እንዴ?››

‹‹እኔ እኮ ደረቅነትሽን ስለማውቅ ነው እስከዛሬ ዝም ያልኩሽ…ሰባት አመቱ ካለፈ ግን ግድ አናግራታለሁ ብዬ እቅድ ነበረኝ››
ስንዱ ፒጃማውን ለብሳ ጨርሳ ወደአልጋው ወጣችና ከጎኗ ቁጭ ብላ‹ምን የምታናግሪኝ ነገር አለ.?ምንም እኮ የለም›አለቻት
‹ለምን የለም…?ገና እኮ 34 አመትሽ ነው….ሰላሳ አራት አመት ማለት ደግሞ ገና ሙሉ ወጣት ነሽ ማለት ነው.አብዛኛው የአዲስ አበባ ሴት በዚህ እድሜዋ ከእናቷ እቅፍም አትወጣም..ገና በዚህ እድሜያቸው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ስለማግባት ራሱ የሚያስቡት››

‹‹እና ታዲያ እኔ ስለምን ላስብ..በህይወቴ በጣም የማፈቅረውን ሰው አግብቼ ልዩ የሆነ የትዳር ጊዜ አሳልፌያለሁ፤በህይወቴ በጣም የምወዳቸው አንድ ሴትና አንድ ጎረምሳ ወንድ ልጅ አለኝ…እና ከዚህ በላይ ምን ለማግኘት ብዬ ስለዚህ ጉዳይ አስባለሁ?›

‹‹ተይ እንጂ ስንዱ..አባዬስ በዚህ ውሳኔሽ  ደስ  የሚለው ይመስልሻል?  በዛ  ላይ እኔም እህት ራጂም ወንድም ይፈልጋል፡››

‹‹አይ እንደዛ ከሆነ አንቺ የምትወልጂውን ልጅ ወንድም አድርጎ መቀበል ይችላል አንቺም እንደዛው.እኔ ባሌን ሳገባው በህይወት እስካለህ ድረስ ሳይሆን በህይወት እስካለሁ ድረስ ለአንተ ታምኜ ያንተ ሚስት ሆኜ እኖራለሁ ብዬ  ነው ቃል የገባሁለት… ይሄንን ቃሌን ከማጥፍ ደግሞ ዛሬውኑ ብሞት  ይሻለኛል..በይ አሁን ተኚ›› ብላ ከጭንቅላቷ በላይ ያለውን ማብሪያ  ማጥፊያ  ተጭና  አጠፋችና ትራሷን አስተካክላ ተኛች…ሳባም  እሷ  እንዳደረገችው  አደረገችና  እቅፍ አደረገቻት…፡፡

‹‹ስንድ››

‹‹ወይ ሳባ››

‹‹ከድሮም ጀምሮ ባንቺ የማፍቀር ፀጋ እንደቀናሁ ነው..እኔም በህይወቴ ያንቺ አይነት ፍቅር ማፍቀር ብችል አንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ?››

‹‹ትቺያለሽ አንድ ቀን እንደዛ የምታፈቅሪውን ሰው አምላክ ይሸልምሽ ይሆናል፡፡››

‹‹ያ ቀን ሳይመጣ አረጀሁ እኮ ››

‹‹ሳቢ እኔ ካንቺ ባላውቅም እስትንፋስሽ በውስጥሽ እስካለ ድረስ ለምንም ነገር አይረፍድም…እንደውም አንዴ የነፍስ አባቴ የነገሩኝን አጭር ታሪክ ልንገርሽ››

‹‹እሺ ንገሪኝ››

‹‹ሰውዬው ነፍስ ካወቀ ጀምሮ በራዕይ አንድ ዛፍ ስር የተቀመጡ አዛውንት መምህር ሲያገኝና የእሳቸው ደቀ መዝሙር በመሆን ጥበብንና እውቀትን ሲያስተምሩት በተደጋጋሚ ያያል።ከዛም እድሜው ሲጎለብትና ሙሉ ወጣት ሲሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ቆርጦ ይነሳል።ሰውዬው እኛን እድሜውን ሙሉ በራዕይ ሲመለከታቸው የኖረውን መምህር ፍለጋ አለምን ለመዞር ቁርጠኛ ነበር።ከዛም ስንቁን ሸክፎ ጉዞ ጀመረ።ከመንደሩ ወጣ እንዳለ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ተገናኘ።ሽማግሌው በሚያስደነግጥ ግርማ ሞገስና በፍፁማዊ ፀጥታ ዛፍ ስር ቁጭ ብለዋል።

ወደእሳቸው ጠጋ አለና"ሲታዩ ተጓዠ ይመስላሉ?"ሲል ጠየቃቸው

"አዎ:-እኔ ተጓዥ ነኝ፡፡ በዚህ እድሜዬ ሙሉ ዓለምን በጠቅላላ ዞሬያለሁ ማለት ይቻላል።"ሲሉ መለሱለት።

"እርሷ ትክክለኛው ሰው ኖት...እኔ ፍፁማዊ ለሆነ መምህር ደቀመዝሙር መሆን ታላቁ ምኞቴ ነው።ቤቴንና መንደሬን ለቅቄ የህልሜ ሰው የሆነውን
በዕውቀት የበሰለና በጥበብ የመጠቀ መምህር ፍለጋ እየወጣሁ ነው።እባክዎ በየት ብሄድ የምፈልገውን አይነት መምህር  ላገኝ  እና  የእሱ የዘላለም ደቀመዝሙር መሆን እንደምችል ሊጠቁሙኝ ይችላሉ?"ሲል ጠየቃቸው። ሽማግሌውም የተወሰነ አድራሻዎች ሰጡት...ወጣቱም አመስግኖ ተለያቸውና በጉጉትና በተስፋ ጉዞውን ቀጠለ።
ወጣቱ እንዳሰበው ሳይሆን ከአንድ መምህር ወደሌላው እየዞረ  ለ30  አመት ምድርን ካሰሳት በኃላ የሚፈልገውን አይነት ጥበብና እውቀት  ኖሮት  ልብን ሊያሸንፍ የሚችል መምህር  ሊያገኝ  ስላልቻለ  ተስፋ ቆርጦ አዝኖና  በጣም ተከፍቶ ወደመንደሩ የመልስ ጉዞ ጀመረ፤በሚገርም አጋጣሚ ወደመንደሩ ሲቃረብ ከሰላሳ አመት በፊት አግኝቶና አውርቷቸው የነበሩት አዛውንት ሰውዬ ይበልጥ አርጅተው እዛው ዛፍ ስር እንደተቀመጡ አገኛቸው።ወዲያው  እንዳያቸው ተገለፀለት፤ግማሽ እድሜውን ፈጅቶ ሲፈልጋቸው የነበሩት መምህር እራሳቸው እንደሆኑ አመነ፤ የተቀመጡበትም ዛፍ ልጅ ሆኖ በተደጋጋሚ በህልሙ ሲያየው የነበረው እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ። እናም ተንደርድሮ ወደ እሳቸው ቀረበ።እግራቸው ስር ተደፋና"ከሰላሳ አመት በፊት ስጠይቆት ለምን እርሶ እንደሆኑ አልነገሩኝም?"ሲል ጠየቃቸው

"ልጄ በወቅቱ ለአንተ ጊዜው አልነበረም።ለዛ ነው ሊገለፅልህና ልትለየኝ ያልቻልከው።አለምን በመዞር የተወሰነ ልምድ ማግኘት እና  የተወሰነ መብሰል ነበረብህ።አሁን በብስለት ማየት ችለሀል።ከሰላሳ አመት በፊት ግን እንዲህ አልነበርክም።አግኝተኸኝ ነበር ግን ልታየኝ አልቻልክም።አውርተኸኝ ነበር ግን እያዳመጥከኝ አልነበረም።እና በጠየቅከኝ መሠረት የተወሰኑ አድራሻዎችን ሰጠሁህ ፡፡ አድራሻዎቹ የተሳሳቱ ቢሆንም ግን ተምረህባቸዋል...እኔም ይሄው.ሰላሳ አመት ሙሉ ከዚህ ዛፍ ስር አልተንቀሳቀስኩም ፡፡አንተን ተመልሰህ እስክትመጣ እየጠበቅኩህ ነበር አሉት።

‹‹እሺ ምን ለማለት ነው?››አለቻት ሳባ

‹‹ምን አልባት እስከዛሬ ፍለጋሽ የራቀ ቦታ ሆኖ እየኳተንሽ ይሆናል የኖርሽው…ለአንቺ የሚሆነው ነገር በእግዜር ተዘጋጅቶልሽ  በቅርብሽ  በቀላሉ  በምታገኚበት ቦታ ተቀምጦ ሳለ ሳታይው ቀርተሸ እንዳይሆን ብዬ እሰጋለሁ፡፡እና ቀኑ ደርሶ በማስተዋል አይንሽ ተገልጦ ያንቺ  የሆነውን  አንድምታይ  እርግጠኛ ነኝ …በይ አሁን ደህና እደሪ ለሊት መነሳት አለብን፡፡››
ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍11317🔥2👎1👏1😁1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለ ኮፍያ ጀኬት አወጣና ሰጣት፡፡በፈገግታ አመሰገነችውና እርምጃዋና ሳታቆም ለበሰች፡፡

ፊት ለፊታቸውም ያሉት እራቅ ብለዋል ኋላም ያሉት ቢያንስ በ20 እርምጃ ወደኃላ ቀርተዋል፡፡፡ስለዚህ በምቾት ታወራው ጀመረ፡፡

‹‹ቁራኛዬ..ስለመልካምነትህ አመሰግናለሁ››አለችው፡፡
‹‹ቁራኛዬ ማለት ምን ማለት ነው?››ጠየቃት፡፡
‹‹በሀገራችን የጥንት ጊዜ ቁራኛዬ የሚባል ባህላዊ የፍርድ ስርዓት ነበር፡፡ በዳይና ተበዳይ፤ሰራቂና ተሰራቂ ፤ገዳይና የተገደለበት ፍርድ የሚሰጥበት ቦታ እስኪደርሱ ድረስ እንዲህ እንደእኔና እንደአንተ በአካባቢው ሽማግሌ ሸማቸውን አንድ ላይ ይቋጥርሩትና እርስ በርስ አቆራኝተው ይልኳቸዋል፡፡በጉዞቸው ታዲያ አንድ ሌላውን በመንከባከብ..ከአደጋ በመጠበቅ ፍርድ እስከሚያገኙበት ቦታ ድረስ በሰላም የመድረስ ግዴታ አለባቸው፡፡ከዛ ተከራክረውና ማስረጃቸውና አቅርበው የተወሰነው ከተወሰነ በኃላ ነገሩ ይደመደማል ፡፡
‹‹የሚገርም ባህል ነው፡፡››
‹‹አዎ ነው..ለመሆኑ ትክክለኛ ስምህ ማን ነው?፡፡››
‹‹ካርሎስ››
‹‹የእኔ ኑሀሚ ነው ..ኢትዬጵያዊ ነኝ፡፡››
‹‹ኢትዬጵያ የት ነች..?ኢስያ አህጉር ውስጥ ነች?››
‹‹አይ አፍሪካ ነች….ምስራቅ አፍሪካ፡፡››
‹‹እ አዎ አስታወስኩ…ታዲያ እዚህ እንዴት ተገኘሽ?››
‹‹በናንተ ተጠለፍኩ እንጂ… የተባበሩት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ ፅ/ቤት ባዘጋጀው አለምአቀፍ ሴሚናር ላይ ለመካፈል ነበር አመጣጤ፡፡››
‹‹እ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ነው የምትሰሪው?››በአድናቆት ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ …ነበር፡፡››
‹‹እድለኛ ነሽ…የተፈጥሮ ጥበቃ ወታደር መሆን ከምንም በላይ የሚያኮራ ስራ ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ በከፍተኛ ትጋትና ጥረት ምድርን ለማውደም እየሰራ ነው….ያ በጣም አሳሳቢ እና አደገኛ ጉዳይ ነው..ግን ደግሞ ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያደርገን እንደአንቺ አይነት ጀግኖች ያንን ጥፋት ለማክሰም ሲለፉና ሲጥሩ ስለምናይ ነው፡፡ ››
እሷ ለተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ እሱ በሚያስበው ልክ ቁርጠኝነቱ ሆነ ፍላጎቱ እንደሌላት ብታውቅም ያንን በግልፅ ልትነግረው አልፈለገችም፡፡ስለእሷ አሁን እየተሰማው ባለው አድናቆትና ክብር እንዲቀጥል ፈልጋለች..ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ ሊጠቅማት አንደሚችል አሰበች፡፡
‹‹ተፈጥሮ ላይ ያለህ ፍላጎት ጥልቅ ይመስላል?፡፡››

‹‹አዎ እዚህ በምታይው መልኩ ለመኖሬ ምክንያቴ ለተፈጥሮ ካለኝ ቀናኢነት የተነሳ ነው፡፡ከአማዞን ጫካም ሆነ ከአማዞን ወንዝ ፍቅር ይዞኛል፡፡ይሄው እዚህ ከገባሁ አምስት አመት አለፈኝ…በተቻለኝ አቅምና ዕውቀት የዚህ ደን ውስጠ ሚስጥሩን በርብሬ እያጠናሁ ነው፡፡እስከአሁን ሁለት መፅሀፍ አሳትሜያለሁ….አሁን ደግሞ ሶስተኛውን እየሰራው ነው፡፡››ብሎ አስደመማት፡፡
‹‹የእውነትህን ነው የምታወራኝ?››
‹‹አዎ እውነቴን ነው፡፡››
‹‹እስኪ ስለአማዞን ጥቂት ንገረኝ፡፡››አለችው
‹‹ምን ልንገርሽ…?››
‹‹ስለአጠቃላይና መሰረታዊ ነገሮች፡፡››
 
‹‹እሺ …አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡ የአማዞን ጥቅጥቅ ደን 9 ሀገራት ላይ የረፈ በዓለም ላይ ትልቁ ሞቃታማ ደን ሲሆን የሚያካትታቸው ሀገሮችም ብራዚልን  60% ፣ ፔሩ  13% የደን ሽፋን ፣ ኮሎምቢያ 10% እና ቀሪው 17% ቬንዙዌላ ፣ ኢኳዶር ፣ ቦሊቪያ ፣ ጉያና ፣ ሱሪናሜ እና የፈረንሳይ ጓያና የአማዞን ደን የጋራ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የአማዞን ስፋት የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡ያ ማለት አማዞን አንድ ላይ ተካሎ እራሱን የቻለ አንድ ሀገር ይሁን ቢባል ከ30ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉት የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹ይገርማል፡፡››ብላ አድናቆቷን ገለፀችለት፡፡
በዛ ተበረታቶ ማብራሪያውን ቀጠለ‹‹ሌላው በአማዞን ደን ከ350 በላይ ነበር ጎሳዎች በውስጡ ተበታትነው ሲኖሩበት ከእነዛ ጎሳዎች መካከል ከ75 በላይ የሚሆኑት ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው የማያውቁ እራሳቸውን ከሌላው ማህበረሰብ፤ከመንግስትም ሆነ ከማንኛውም ቴክኖሎጂ ያራቁ ናቸው፡፡ ስለእንስሳቱ ንገረኝ ካልሺኝ ደግሞ አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡በዛ ጥቅጥቅ ደን 400 ቢሊዮን ዛፎች፤40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡››
በገለፃው የእውነት ከልቧ ተደምማበት‹‹እውነትም ከዚህ ደን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ይዞሀል››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡
‹‹አዎ…በትክክል ገልጸሸዋል፡፡››

ንግግሩን ያቋረጠው ከኃላቸው የፉጨት ድምፅ ሲሰማ ነው፡፡ፈጠን አለና ክንዷን ጨምድዶ እየሄድበት ካለው ጠባብ መንገድ ዞር አድርጎ በመውሰድ አንድ ግዙፍ ዛፍ ጋር አጣብቋት በሰውነቱ ጋርዷትና ቆመ ፡፡እሷን በግንዱና በራስ መካከል አድርጎ ስላቆማት ትንፋሽ አጠራት፡፡ቢሆንም እንደምንም ችላው ‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
በእጅ ላይ ያለውን ሽጉጥ እንዳቀባበለ ወደፊት ደቅኖ የሚሆነውን እየጠበቀ ነው….እጁን አፉ ላይ በመጫን ዝም እንድትልና ድምፅ እንዳታሰማ ጠየቃት ፡፡ወዲያው ሰቅጣጭ የሚያጎራ አይነት የሰው ድምፅ ተሰማ …እሱን ተከትሎ…ሶስት ተከታታይ ፉጨት ተሰማ፡፡
የሆነ አደጋ ተፈጥሮል፡፡እርዳታ እየጠየቁ ነው፡፡ከጀርባዬ ተከልለሽ በጥንቃቄ ተከተይኝ አለና ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ…በአንድ እጇ ትከሻውን ይዛ ከወጋቧ ወደታች አጎንብሳ ልክ እንደእሱ እየተሹለከለከች ወደኃላ መጎዝ ጀመሩ፡፡ ከሶስት ደቂቃ በኃላ ተፈላጊው ቦታ ሲደርሱ የሚዘገንን ነገር ገጠማቸው…የሆነ ኩሬ መሳይ እረግረግ ቦታ ላይ ስድስት ሚሆኑት አጋቾቾ ክብ ሰርተው መሳሪያቸውን አቀባብለውና ደቅነው እንተኩስ አትኩሱ እየተባባሉ ይጨቃጨቃሉ፡፡መሀከል ላይ ያ ሲነሱ ከቤት ክንዷን ጨምድዶ ያወጣት አውሬ መሳየ ሰው ተዘርሯል፡፡ እሱ መሆኑን ያወቀችው በተንጨፈረረ ፀጉሩ እና በለበሰው ጃኬት ነው፡፡በሙሉ ሰውነቱ አንኮንዳ ዘንዶ ልክ እንደጥምዝ ቀለበት ተጠምጥሞበት ወደረግረጉ ጉድጓድ እያሰመጠው ነው፡፡እዲህ አይነት ነገር እንኳን በአካል በፊልም አንኳን አይታ አታውቅም፡፡ዝግንን አላት፡፡አረ በፈጣሪ የሆነ ነገር አድርጉና አድኑት››ጮኸች፡፡
ሁሉም ዞር ዞር እያሉ አዮት››መናገሯን እንጂ ምን እንዳለች የገባው የለም፡፡››ለካ ያወራችው በአማርኛ ነው፡፡ሁል ጊዜ ከልክ በላይ ስትደነግጥና ስትናደድ ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ በአንደበቷ ለምን ሌላ ቋንቋ እንደማይገባ ሁሌ እንደገረማት ነው፡፡ትዝ ሲላት ወዲያው ስህተቷን አረመችና በእንግሊዘኛ ደገመችላቸው፡፡እነሱ በእስፓኒሽ ተነጋገሩና መተኮስ ጀመሩ …ደም እየተንኮለለ መፍሰስ ጀመረ ..የሰውዬው ይሁን የአናኮንዳው አላወቀችም፡፡ሁለቱም ኩሬ መሳይ እረግረግ ውሀ ውስጥ ሰመጡና ከእይታቸው ተሰወሩ፡፡ከተወሰነ ደቂቃዎች መደናገጥ እና ቁዘማ በኃላ ሁሉም እንደቀድሟቸው በሰልፍ ገብተው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
👍694👎1😢1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞን ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው
‹‹ምንድነው መስራት ያለብኝ?ምን አይነት ዕውቀት ነው ያለኝ?ምን አይነት ጥሪትስ አለኝ?ህብረተሠብስ ምን አይነት ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ነው መግዛት የሚፈልገው?። መልሶቹ ቀላል አልነበሩም...ወደ አእምሮው የሚመጣው መልስ ወደግል ስራ የሚያስገባው ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው የሚያርቀ ነው የሆነበት።

1/ይሄ የምኖርበት ህብረተሠብ በዚህ ሰአት ግዙፍ ችግሩ ምንድነው...?ወረቀትና እስኪሪብቶ ያዘና ዘርዝሮ መፅፍ ጀመረ

1/ኑሮ ውድነት
2/የሠላም እጦት
3/የፍቅር እጦት
4/ቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት
5/...!!የአየር ፀባይ መዛባት
የፃፈውን መለስ ብሎ አየው ...ለደቂቃዎች ብቻውን ተንከትክቶ ሳቅ ። ዝርዝሩን አንድ አነስተኛ የግል ቢዝነስ ለመክፈት ሳይሆን አዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ ተሹሞ በሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጡ የፓሊሲ አማራጮችን ለማርቀቅ መነሻ ሀሳቧችን እያሰላ ያለ ፓለቲከኛ ነው  የሚመስለው።

‹‹እስቲ የህብረተሠብም የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ምን አይነት ቢዝነስ ነው የሚኖረው...?ኑሮ ውድነቱ እንኳን ግለሠብ መንግስትስ ለማስተካከል አቅም አለው...?የመለኮት ጣልቃ ገብነት ከሌለስ  መፍትሄ ይኖረዋል?።››ሲል አሰበና በራሱ ድርጊት ዳግመኛ ሳቀ፡፡ ከዘረዘራቸው ሀሳቦች የ3 ተኛው ሀሳቡን ገዛው።‹‹ፍቅር እጦት የእኔም የማህበረሰብም የጋራ ችግር ነው።የፍቅር እጦት ደግሞ የሌሎች ችግሮች ሁሉ መነሻ ምክንያት ነው።ደግሞ በሙሉ አቅሜ መስራት የምችለው ስራ እሱን ነው …ሞያዬም ችሎታዬም እሱ ላይ ነው››ሲል አሰበና ወሰነ፡፡

አሜሪካ እያለ ተቀጥሮ የሚሰረባትን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ድርጅት እዚህ ሀገሩ መሀል አዲስ አበባ ላይ በራሱ ለመክፍት ወሰነ…‹‹የራስህን ቢዝነስ ጀምር›› ብላ ስትጨቀጭቀው ለነበረችው አስቴር ነገራት፡፡፡አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመች በሀሳብ በጣም መደሰቷንና በማንኛውም ነገር ከጓኑ እንደሆነች አበሰረችው…እሷ የተደሰተችበት ነገር ደግሞ በእሱ ህይወት ትልቅ ቦታ ስላለው ወዲያውኑ በደስታ ወደእንቅስቃሴ ገባ……ፍቃድ ለማውጣት ቢሮ ለመከራየትና አስፈላጊ የቢሮ እቃዎችን አሞልቶ ለመክፈት 40 ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ያህል በሰአት ቢሮ እየገባ በሰዓት ቢወጣም አንድም ደንበኛ ማግኘት አልቻለም…ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት፡፡ግራ ገባው ፣በመጀመሪያውም ዝግና ድብቅ ባህል ባለበት ሀገር የጋብቻና የፍቅር አማካሪ ድርጅት ከፍቶ ውጤታማ ሆናለው ብሎ በማሰብ በራሱ ጅልነት ተበሳጨ…የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ባይከፍልና ለፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎችን ለማሟላት ከመቶ ሺ ብሮች በላይ ባያወጣ ኖሮ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ዘጋግቶ ሌላ የቅጥር ስራ ይፈልግ ነበር..ግን ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አይችልም…‹‹አዎ ለአስቴር ምን እላታለሁ….?እንድታፍርብኝማ አላደርግም…እሷ ከምታፍርብኝ አለም ጠቅላላ ብትገለባበጥ እመርጣለሁ….ስለዚህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››በማለት ወሰነና ቀኑን ሙሉ ሲያሰላስል ዋለ… የሆነ ነገር ብልጭ አለለት፡ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡
ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ ወንድሜ….›››የሚል ድምፅ በስልኩ እስፒከር አቆርጦ ጆሮው ውስጥ ተሰነቀረ…

‹‹አለሁልሽ››

‹‹ምነው ድምፅህ?››

‹‹ደህና ነኝ….የሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር?››

‹‹ይቻላል..ግን ስራ አሪፍ ነው እንዴ?….››

‹‹አሪፍ ነው …አሁን አንድ ደምበኛዬን ወደትዳር ከመግባቷ በፊት ማድረግ ስለሚገባት ቅድመ ዝግጅት ማወቅ ፈልጋ ነበር.. እሷን እንደሸኘሁ ነው የደወልኩልሽ››ዋሻት፡፡

‹‹ደስ ይላል ወንድሜ …ህልምህን መኖር ጀምረሀል ማለት ነው….››

‹‹አንቺ ከጎኔ ሆነሽ እስከደገፍሺኝ ድረስ ምንም ማላሳከው ነገር የለም…..አሁን ለምን መሰለሽ የደወልኩልሽ…ፀሀፊ ብቀጥር ብዬ አሰብኩ…››ያሰበውን ነገራት፡፡

‹‹አዎ አንተ ….እስከዛሬ እንዴት አላሰብንበትም…?ለፕሮቶኮሉ እራሱ አስፈጊ ነው…ባለጉዳዬች እንደመጡ አንተን ማግኘት የለባቸውም በፀሀፊህ በኩል ቀጠሮ ይዘውና ተገቢውን ቅድመ ማሟላት ያለባቸውን ነገር አሟልተው መሆን አለነበት…አሪፍ ነው…››

‹‹እና እንዴት ላደርርግ ?ማስታወቂያ ላውጣ….?››

‹‹አይ እኔ በሶስት ቀን ውስጥ ምርጥ ፀሀፊህ ቀጥርልሀለው….አንተ በዚህ ጉዳይ ምንም አትጨነቅ…..ሶስት ቀን ብቻ ስጠኝ››

‹‹እሺ ማታ እቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ..ወንድሜ››

‹‹ቻው..››

ወንድሜ የሚለው ቃል ከአንደበቷ በወጣ ቁጥር በአንገቱ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት ነው የሚታየው….ሆነ ብላ እሱን ለማጥቃት አስባ ከአንደበቷ የምታወጣው ነው የሚመስለው….‹‹አደራ እኔ እህትህ ባልሆንም ልክ እንደእህትህ ነኝና ሌላ ነገር በአእምሮህ እንዳይበቅል››የሚል ማስጠንቀቂያ ነው የሚመስለው፡፡
የእናትና አባቱ ልጆች የሆኑት እህቱ ወንድሜ የሚለውን ስም በአመት አንዴ እንኳን ሲጠቀሙ አልሰማም….ትዝም የሚላቸው አይመስለውም…እሷ ግን ልክ እንደዘወትር ፀሎት እንደውዳሴ ማርዬም ነው በየእለቱ የምትደግመው፡፡
///.....////...../////

በፀሎት ጥዋት ከእንቅልፏ ስትባንን እቤት ውስጥ ከወ.ሮ እልፍነሽ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም፡፡

‹‹እማዬ ሰው ሁሉ የት ሄደ?››እማዬ ብላ መጣራቷን ለራሷም እየገረማት ነው…ደግሞ አፏ ላይ አልከበዳትም…ወላጅ እናቷ…ሌላ ሴት እናቴ እያለች መጥራት መጀመሯን ብትሰማ ልብ ድካም ይዟት ፀጥ እንደምትል እርግጠኛ ነች፡፡

‹‹ወይ ልጄ… ነቃሽ…ልቀስቅሳት ወይስ ትንሽ ትተኛ እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር፡፡ በረሀብ ሞትሽ እኮ››ብለው  ወደ ጓዲያ ገብና የእጅ  ማስታጠቢያ  ይዘው መጥተው,ሊያስታጥቧት ጎንበስ አሉ…እንደምንም ከአንገቷ ቀና ብላ ተነሳችና ‹‹ያስቀምጡት እኔ እታጠባለው››

‹‹አረ ችግር የለውም ልጄ ..ችግር የለውም››

‹‹ግድ የሎትም….››.

‹‹እንግዲያው ታጠቢ …ቁርስሽን ላቅርብ ›› ብለው ማስታጠቢያው ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላትና ተመልሰው ወደ ጓዲያ ሔድ

…….እግሯ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ጥዝጣዜው ነፍሶ ድረስ ይሰማታል…..ፊቷ ላይ አሁንም ተራራ የሚያህል ቁስል የተሸከመች እየመሰላት ነው…እንደምንም ተንፏቀቀችና እጇን ታጥባ የሚመጣላትን ቁርስ መጠበቅ ጀመረች…ጩኮ ከእርጎ ጋር ነበር የመጣላት…ጩኮ መች በልታ እንደምታውቅ አታስታውስም….ቤቷ ቁርስ ሲቀርብ አስር …አስራአምስት አይነት ምግብ ጠረጴዛ ሞልቶ ነው….ከዛ ውስጥ ሶስት ወይም አራት አይነቱን አፕታይቷ የፈቀደላትን መርጣ በልታ ሌላውን ትተዋለች..አሁን የቀረበላት ምግብ ይህን ያህል ግን አስደሳች አልነበረም…….እርቧት ስለነበረ እየተስገበገበች በላች…
ያጋባችውን ሰሀንና ብርጭቆ መልሳ…እጇን ታጠበችና…..‹‹እማዬ ማንም የለም እንዴ?››ስትል ደግማ ጠየቀች፡፡

‹‹ልጄ ለሊሴ ስራ ፍለጋ ብላ ወጥታለች…ፊራኦል ስራ ነው ..አባትሽም እንደዛው››መለሱላት፡፡

‹‹ለሊሴ ምን አይነት ስራ ነው የምትፈልገው?››
👍5513
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


እጅግ በጣም ይቅርታ ስልኬ ስለጠፋ እረጅም ጊዜ ታሪኩን ሳለቅ ቀረሁ ወደኋላ መለስ ብለቹ ታሪኩን በማስታወስ ቀጥሉ እንደእግዚአብሔር ፍቃድ ከነገ ጀምሮ ሁለት ክፍል እለቃለሁ እንዲሁም ነገ ማታ ሁለት ሰአት ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን የተከፋችሁብኝ አሁንም በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏

ያሬድ

ከገበያ መጥቶ ደክሞታል፡፡ ገና ሳይመሽ ከመኝታው ላይ ጋደም እንደማለት ብሏል፡፡

"ተመስገንን አብረን እንሄዳለን ብለኸው ነበር እንዴ"? አለች ፤ ባለቤቱ አበበች፡፡

"አዎ ፤ ብዬው ነበር፡፡ ገንዘብ እንዳዘጋጀ ነገረሽ እንዴ"?

"ትላንት አንተን ፈልጎ መጥቶ ነበር፡፡ ሳያገኝህ ሲቀር ለእኔ አጫውቶኛል፡፡ እንሂድ እስከምትለው ነው የሚጠብቀው" ፡፡

"ታዲያ ምን ችግር አለ፡፡ የመነገድ ፍላጎት ካለው አሁን ደግሞ ውሎ ገባ ስለሆነ የምንመጣው ቀን እንኳን ቢመሽም ሁለት መሆኑ አይከፋም፡፡ ከነገ ወዲያ ይዠው እሄዳለሁ"፡፡

ገና በደንብ አልነጋም፡፡ ያሬድም ከመኝታው አልተነሳም፡፡ አበበች አለ ፡፡ ሳይደጋግም በአንዴ የሚሰማ መስሎት፡፡ ነገር ግን የሚሰማው አላገኘም፡፡ አቤት የሚለው አጣ፡፡ ደግሞ ተጣራ፡፡ ያሬድ…..ያሬድ አለ፡፡ አቤት አለች አበበች፡፡ ብቅበይ አለ፡፡ በጥዋት ወደ ያሬድ ጋር የመጣው ተመስገን፡፡

ማነው በጥዋት ብቅበይ የሚለው ብላ ብቅ አለች፡፡

"ደህና አደርሽ አበበች ? አለ" ተመስገን፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርህ ተመስገን፡፡ አትገባም እንዴ ከብርድ ላይ ፡፡

"ይሁን አልገባም፡፡ ያሬድ የለም እንዴ ? ፡፡

"አለ ፤ ከመኝታውም አልተነሳም፡፡ ምነው ደህና አይደለህም እንዴ ?

"ኧረ ደህናነኝ፡፡ ለዛ ላጫወትኩሽ ጉዳይ ነበር የመጣሁት ፡፡

"አይ! እሱንማ ከሆነ እኔም ማታ አጫውቸዋለሁ፡፡ ለመነገድ ፍላጎት ካለው ይዠው እሄዳለሁ ብሏል፡፡ ለማንኛውም ግባና አነጋግረው ፡፡

ተመስገን የመጣበትን ጉዳይ እንደተሳካለት አሰበ፡፡ ያሬድን ለማነጋገር ወደ ቤት ገባ፡፡

"ደህና አደርህ ያሬድ? ፣ ደሞ ዛሬ በጥዋት አልተነሳህም፡፡ እንቅልፍ ነው ወይስ ድካም ነው?፡፡ ያስተኛህ ፡፡

"ሰላም አደርህ ተመስገን፡፡ ምን የትናንት ገበያ ውልቅልቅ አድርጎኛል፡፡ አሁን በደንብ ነግቷል ማለት ነው እንዴ? አለ፡፡ ከተኛበት መኝታ ተነስቶ እየተንጠራራ፡፡

"ስድስት ሰዓት ሆኖ ነግቷል ትላለህ እንዴ ፤ ለነገሩ ከተማ ለከተማ ስትመላለስ የከተማ ሰው ሆነሃል፡፡ እነኝህ ከተመኞች ሰዓት አስረው ቢይዙም ፤ የሚቆጥሩ መሆናቸውን እንጃ ፤ በየሰዓቱ ነው የሚበሉ

አለ፡፡ ተመስገን እንደማሾፍ ብሎ፡፡

"አይ! ተመስገን እነሱማ በሰዓት የማይበሉበት ጊዜ ስለሌላቸው ነው፡፡ ያለመቁጠር አይደለም፡፡ እንዲያውም እኛ ነን አንዴ ቁርስሠ ፣ አንዴ ምሳ ሰዓት ፣ ደረሰ እያልን ሰዓት የሚቃወመን ይመስል በቀን ሶስቴ ሳይበቃን አራተኛ መክሰስ እያልን የምንመገበው፡

"አይ! መልካም ነው" ብሎ "ለባለፈው ጉዳይ ነበር የመጣሁት" አለ ተመስገን ፡፡

"አበበች ማታ በጨዋታ አንስተን ነግራኛለች፡፡ እና ለመነገድ ፈልገሃል ማለት ነው?፡፡

"የመነገድ ፍላጎት እንኳን ብዙም የለኝም፡፡ እንዴው የዛችን የእህቴ ነገር አንጄቴ አልቆርጥ ብሎኝ ነው፡፡ መቼም እቤት ከመቀመጥ አካባቢንና አገርን ማወቅ አይከፋም፡፡ የእግዚአብሔር ስራም አይታወቅም፡፡ በዛውም እናገኛት ይሆናል"፡፡

"ጥሩ ነው ለማንኛውም ሃሳብህ አይከፋም፡፡ ነገ አብረን ማለድ ብለህ በጥዋት ና፡፡ ውሎ ገባ ስለምንመለስ እንዳይረፍድብን"፡፡

"እሽ በጥዋት እመጣለሁ፡፡ ብሎት ተሰነባብተው ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

"በነጋታው በጥዋት ቡና ፈልቶ ተመስገን እየተጠበቀ ነው፡፡ ግን ቶሎ ሊመጣ አልቻለም፡፡ በቃ ቀርቶ ነው ብላ አበበች ቁርስ ልታቀርብ ስትል ተመስገን መጣ፡፡ ሰላምታ ተለዋውጠው ተቀመጠ፡፡

"ምነው አረፈድህ" አለው ያሬድ
"ምን ሌሊቱን እንቅልፍ ሳይወሰደኝ አድሮ ሊነጋጋ አካባቢ ሸለብ አላደረገኝ መሰለህ ፡፡

"አይ! አንተ ሌሊቱን ሙሉ በሃሳብ ስትሄድ አድረህ ነዋ፡፡ ጥዋት በመነሻህ ሰዓት እንቅልፍ የጣለህ፡፡ በል አሁን የቡና ቁርሱን ያዝና ቡናውን ጠጥተን ቶሎ እንውጣ፡፡ የባልጪ መኪና ሳያመልጠን እንድረስበት፡፡ አንዴ ካመለጠን መመለስ ካልሆነ ሌላ መኪና አናገኝም፡፡

ባለቤቱን በይ እንግዴህ ከብት ሳይበዛ ከብቶቹን ውሃ አጠጫቸው ብሏት ተነስተው ከተመስገን ጋር ጉዞዋቸውን ወደ አዳማ ቀጠሉ፡፡

መኪና እንዳያመልጣቸው እየተጣደፉ ነው፡፡ ከመንገድ ላይ አንድ ጥቁር ሰው ከፊት ለፊታቸው ገጠማቸው፡፡

"ዛሬ ላይቀናን ነው መሰለኝ አለ ተመስገን፡፡ ውስጡ እንደመረበሽ እያለበት፡፡

"ምነው ምን አየህ አለው? ያሬድ፡፡

"ተመስገን የፍጥነት እርምጃውን ገታ አድርጎ ፤ መንገድ ስትሄድ አንድ ሰው ከገጠመህ የምትሄድበት አይቀናህም፡፡ አባቴ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ አሁንም እኛ አንድ ሰው ሰለገጠመን ብዬ ነው፡፡

ባያምንበትም ግን ሆዱ እንደመፍራት ብሏል፡፡ "ተው! እባክ ይህ የአንዳንድ ሰው አባባል ነው፡፡ አንተ ደግሞ ያባትህን አትከተል እግዚአብሔር እንደፈቀደ ያድርገን እንግዴህ አለ፡፡ በፍራቻ ንግግርም ቢሆን፡፡

"እሱማ እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ እንዴው የሚባለውንና ነው እንጅ ያልኩህ፡፡

ያሬድ ነገሩን ተወት አድርጎ ፤ አሁን ቶሎ ቶሎ ራመድ ራመድ በል፡፡ ያ አቶ ላንቻ ብቻ ሳይቀድመን እንድንደርስበት፡፡

"የማነው አቶ ላንቻ? አለ ተመስገን፡፡

"ለእኔ ከድሬ አዳማ ድረስ አልባሳ የሚያመጡልኝ ናቸው፡፡ መቼም ብታያቸው የተባረኩ እና ደግ ሰው ናቸው፡፡

አሁንም ከሳቸው ተረክበን ነው፡፡ የምንመለሰው ከቀናን"፡፡

"እኔ እኮ ውሎ ገባ ስትመጣ በአየር መምጣት ጀመረ እንዴ ብየ ነበር፡፡ ለካስ አንተ አዳማ ድረስ የሚያመጣልህ ደንበኛ አግኝተህ ኖሯል፡፡እየከነፍህ የምትመጣው"፡፡

"መኪናው ሞልቶ አንድ ሰው ብቻ ቀርቶት ይጠባበቃል፡፡ እየተጣደፉ ደረሱ፡፡ ግን እረዳቱ ከአንድ ሰው ውጭ አልጭንም አላቸው፡፡ ጫነን አልጭንም ፤ ሲከራከሩ አንድ ረፍዶበት የነበር ሰው ረዳቱንም ሳይጠይቅ አልፎ መኪናው ውስጥ ገባ፡፡ ያሬድ ቢለምንም ፣ ቢማፀንም ሳያሳፍራቸው ጥሏቸው ሄደ፡፡

አላልኩህም፡፡ አንድ ሰው ጥሩ አይደለም ብየህ ነበር አለው ተመስገን፡፡

ጸያሬድ ተመስገን ያለውን የሰማው አይመስልም፡፡ ልቡ ያለው አቶ ላንቻ ጋር ነው፡፡ አንድ የጭነት መኪና ወደ አዳማ ልትወጣ ከመንገድ ላይ ቆማለች፡፡

"ይችን መኪና እንጠይቃት እስቲ ፤ ትጭነን እንደ ሆነ አለ ተመስገን፡፡

"እህል ጭና እያየሃት እንዴት እሽ ብለው ይጭኑናል፡፡ ያጠፋነው እኛ ነን፡፡ በጥዋት መምጣት ሲገባን አርፍደን፡፡ አሁን ያለን አማራጭ ወደ ቤት መመለስ ነው፡፡ ነገ ተመልሰን እንመጣለን፡፡ እንደው
የሚያነድደኝ እምነት ማጉደሌ ነው፡፡ መቼም መኪና አጥቶ ቀረ አይሉኝም፡፡ ሆነ ብሎ ነው እንጅ የሚሉኝ፡፡ እህል ወደ ጫነችው አይሱዚ ተጠጉ፡፡

ፈራ ተባ እያለ ማነህ ወንድም ወደ አዳማ እንደሆነ የምትሄደው መኪና ጥሎን ስለሄደ ነው፡፡ እባክህ ተባበረን ብሎ ሹፌሩን ጠየቀው ያሬድ፡፡

የመኪናው ሹፌር አላመነታም፡፡ "ስንት ናችሁ"? አለ፡፡

"ሁለት ነን አለ፤ ያሬድ፡፡

"ሁለት ሰው ከሆነ አልጭንም"፡፡ አንድ ሰው ከሆነ ጋቢና ግባ አለ፡፡ ባጭር ቃል ሹፌሩ፡፡

"እባክህን ወንድም ተባበረን ስለማንነጣጠል ነው፡፡ የምንሔደውም የታመመ ሰው ለማምጣት ነው፡፡

እንደምንም ተቸገርልን፡፡ ከላይም ቢሆን ተጭነን እንሄዳለን እያለ ሹፌሩን ተማፀነው፡፡
👍8511👎2🥰1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁ ከተማውን ለቆ በሄደ በ15ተኛው ቀን ለአላዛር  አንድ በስራ ምክንያት የሚያውቀው ሰው የደወለለት፡፡ለረጂም ጊዜ ተደዋውለው ስለማያውቁ ግራ በመጋባት ነበር ስልኩን ያነሳው፡፡
‹‹ሄሎ ሙሳ…በህይወት አለህ እንዴ?››ሲል ጠየቀው አላዛር፡

‹‹አለሁ ባክህ…››

‹‹ከእኛ ሰፈር ከለቀቀክ በኋላ እኮ ተደዋውለን አናውቅም…ውጭ ውጭ ስለምትል የሸመጠጥክ መስሎኝ ነበር››

‹‹አይ እዚሁ ነኝ››

ግራ ገባው ንግግሩ ቀዝቀዝ አለበት…ድሮ ቢሆን ነገሮችን ማግለብለብና ማዳነቅ ይወድ ነበር…የሆነ ነገር እንደሆነ ገባው፡፡

‹‹ሙሳ ሰላም ነው…?እሺ ምን ልታዘዝ?፡፡››

‹‹ባክህ አሁን በአባትህ ሰፈር  እያለፍኩ ነበር…››

የበለጠ ግራ ተጋባ…አባት የሚለውን ቃል  ከእሱ አንደበት አልጠበቀም ነበር‹‹እሺ››

‹‹እኔ እንጃ አባትህ የሆነ ነገር የሆኑ ይመስለኛል…››

‹‹የሆነ ነገር ስትል..?››

‹‹ምን አልባት ተፈንክተው መሰለኝ….ከግንባራቸው ደም እየፈሰሰ ሸሚዛቸው ላይ  ተረጫጭቷል…ከቤታቸው ወጥተው እየሄዱ ነበር..አስቁሜያቸው ላናግራቸው ብል ስለማያውቁኝ መሰለኝ አመናጭቀውኝ ጥለውኝ ሄዱ፡፡››

‹‹ማንም አብሮት የለም?››

‹‹አዎ ብቻቸውን ናቸው …ያ ነው ያሳሰበኝ…ከቻልክ እስኪ ደውልላቸው፡፡››

‹‹እሺ ሙሳ አመሰግናለው…ደውልልሀለው ቻው››ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡በደቂቃ ውስጥ ውስጡ እርብሽብሽ አለበት፡፡‹‹የዚህ ሰውዬ ጣጣ መቼ ነው የሚለቀኝ?››ሲል ተበሳጨ..ስልኩን አወጣና አባቱ ጋር ደወለ…ይጠራል አይነሳም፤መልሶ ደወለ ፤አሁንም አይነሳም…ሶስተኛ ሲሞክር ተዘግቷል፡፡ይሄ ደግሞ ይበልጥ አሳሰበው…፡፡.እቤት የእንጀራ እናቱ ጋር ደውሎ እንዳይጠይቅ ስልክ የላትም…፡፡.በአካል ሄዶ ከማረጋገጥ ውጭ ምንም ምርጫ የለውም፡፡ለአሌክስ ደውሎ ሊነግረውና አብረው እንዲሄዱ ሊጠይቀው አሰበና ስልኩን አንስቶ ለመደወል ከተዘጋጀ በኃላ በራሱ ፈገግ በማለት መልሶ ተወው‹‹አሌክስ ጥሏቸው ከሄደ ሰነባብቷል …ግን ደግሞ እስከአሁን እንደዛ ማድረጉን አምኖ መቀበል አልቻለም፡፡

ዝም ብሎ ተነሳና ላዳ ተከራይቶ ብቻውን ወደአባቱ ቤት ሄደ…ፈራ ተባ እያለ የውጩን በራፍ ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት፡፡አልፎ ወደውስጥ ገባ፡፡በረንዳ ላይ ደረሰ፡፡በስሱ አንኳኳ..መልስ የለም፡፡…አንኳኳ መልስ የለም…፡፡የበለጠ እየፈራና እየተረበሸ መጣ…፡፡በራፉን ገፋ አደረገው፤ ተበርግዶ ተከፈተለት…፡፡ወደውስጥ ገባ….፡፡የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም…፡፡ዛር እንደወረደበት ባለውቃቢ ሰውነቱ ይንዘፈዘፍበት ጀመር…፡፡አረ እንደውም እያቅለሸለሸው ነው….፡፡ተንደርድሮ መልሶ ወደውጭ ወጣ፡፡ በረንዳው ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ…፡፡ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የበላው እራት አንድም ሳይቀር ተዘርግፎ ወጣ….፡፡.እዛው በተንበረከከበት ደንዝዞ ደቂቃዎች አሳለፈ፡፡‹‹እየቃዠው ነው? ወይስ ያየሁት ነገር በእውነት የሆነ ነገር ነው?››በማለት እንደምንም እየተንበረከከ ወደውስጥ ተመልሶ ገባ.፡፡.አዎ ቅዠትም ህልምም አልነበረም…በትክክል ደግሞ እያየው ነው..፡፡ሳሎኑ እንዳለ በደም ፍንጥቅጣቂ ተጨመላለልቋል፡፡እንጀራ እናቱ መሀከል ወለል ላይ እርቃኗን ዝርግትግት ብላ ተኝታላች…ግማሽ ገላዋ ከእንብርቷ በታች ያለው አካሎ በሙሉ በደም ተበክሏል…፡፡.አንጀቷ  ዝርግፍ ብሎ ወጥቷል…፡፡ከአንጀቷ ጋር ደም መሰለ ህጻን ልጅ ይታያል…፡፡ከዛም በታች ያለው አካሏ ተደጋግሞ በጩቤ ይሁን በቢላዋ ተጨቅጭቋል፡፡
እየተንሸራተተ ወደኃላ ተመለሰና ቤቱን ለቆ ወጣ….፡፡ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብም ሆነ መወሰን አልቻለም፡፡ዝም ብሎ ግቢውን ለቆ ወጣ….፡፡ቀጥታ አካባቢው ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ነው የሄደው…፡፡.አዎ ገና ህይወትን በቅጡ ያልኖረችውን ያቺን ምስኪን ነፍሰ ጡር ሴት እንደዛ ብልሽትሽት ያደረጋት አባትዬው ነው፡፡ደግሞ ህይወቱን ያጣው ጮርቃው ህፃን ወንድሙ እንደሆነ ሲያስብ የበለጠ ልቡ ደከመ፡፡ስለዚህ መቀጣት አለበት ሲል ወሰነ …፡፡ለህግ አሳልፎ ይሰጠዋል፡፡ቀሪ ዘመኑን በእስር ቤት ያሳልፋል፡፡አዎ አሁን ለፖሊስ ማመልከትና የተፈጠረውን አሰቃቂ ወንጀል ሄዶ ማሳየት አለበት…፡፡ፖሊስ ጣቢያው ጋር ደረሰ…፡፡አልፎ ወደውስጥ መግባት ግን አልቻለም፡፡እግሩን ካቆመበት መሬት ጋር የማያውቀው ኃይል አስሮ ይዞታል፡፡ፊቱን ወደኃላ ዞረና መራመድ ጀመረ…፡፡ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 5፡00 ሰዓት ያለማቆረጥ በደመነፍስ በእግሩ ሲዞር ነበር፡፡ጭው ያለ አስቀያሚ ስሜት እየተሰማው ነው፡፡አሁን አባቱን አይደለም እየወቀሰና እየረገመ ያለው..እራሱንም ጭምር ነው፡፡
‹‹ይህቺ ያለጊዜዋ የተቀጠፈች ሴት እናቴ ወይም እህቴ ብትሆን ምንድነበር የማደርገው…?እዛው  ሬሳዋን ባየሁበት ቅፅበት ጭንቅላቴን ይዤ ኡኡ ብዬ በመጮህ የሰፈሩ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብና ገዳዩም ወዲያው በቁጥጥር ስር እንዲውል አላደርግም ነበር?››እራሱን ጠየቀ…፡፡‹‹አሁን እንዲህ እግሬ እስኪዝል የምኳትነው አባቴን አሳልፎ ላለመስጠጥት ካለኝ ውስጣዊ ፍላጎት የተነሳ ነው…፡፡አዎ ያ ብሽቅ የሆነ አውሬ ሰውዬን ለመከላከል…አዎ ‹‹አባቱን አሳልፎ ፤ለህግ ሰጠ ላለመባል››እርግጥ አባቱን ለፖሊስ አሳልፎ ቢሰጥ እህቶቹ እንደማይደሰቱበት ያውቃል..ግን ደግሞ ተገቢውና ትክክለኛው ነገር ያ ነበር፡፡የሆነ ነገር በአእምሮ ብልጭ አለበት‹‹ቆይ እሱ ግን የት ሄዶ ነው…?ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ወደፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ከሆነስ…?መቼስ ትንሽ ሽራፊ አእምሮ ያለው ሰው በደም ፍላትና በንዴት ምንም አይነት ወንጀል ከሰራ በኃላ ትንሽ ሲረጋጋና ደሙ ዚቀዘቅዝ በመጀመሪያ የሚያደርገው ነገር  ቀጥታ ወደህግ ሄዶ የሰራውን ወንጀል አብራርቶ ተናዞ እጅ መስጠት ነው..፡፡እና አባቱም እንደዛ አድርጎ  ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ እንደሆነ ተስፋ አደረገ እና ወደ አባቱ ቤት ተመልሶ መራመድ ጀመረ…፡፡ደረሰ…፡፡ተስፋ እንዳደረግ ግቢው በሰው ተሞልቶ በአካባቢው ፖሊሶች እየተተረማመሱ  አይደለም…በተቃራኒው ዝምና ፀጥ እንዳለ ነው..፡፡እንደዛ በመሆኑ ደግሞ መላ ሰውነቱ በፍራቻ ተናወፀ….‹‹ብን ብሎ ሀገሩን ለቆ ጠፍቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበ…፡፡
‹‹እንደዛ ካደረገ ምንድነው የሚሆነው?›፡፡ቶሎ ብሎ ገብቶ አረጋግጦ ወደደም ጠላም ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ አለበት… ‹‹እስኪጣራ ብለው እኔን እስር ቤት ቢወረውሩኝስ…?አሻራዬ እንደሆነ የውጩም ሆነ የቤቱ በራፍ ላይ ተዝረክርኳል….‹‹አባዬ እድሜ ልኬን ስጠላህ ነው የኖርኩት..አሁንም አምርሬ ጠላሀለው››አለ.

.‹‹ግን እኮ  ሙሳ ደውሎ ነው የጠራኝ..አባቴ በደም የቀለመ ልብስ ለብሶ ከቤቱ ወጥቶ ሲሄድ እንዳየው በስልክ ስለነገረኝ ነው የመጣሁት… ያንን ህግ ፊት ቀርቦ ማስረዳት ይችላል፡፡››ሲል አሰበና ቀላል አለው፡፡ወደ ውስጥ ገባ…የቤቱን  በራፍ ከፍቶ ገባ ፡፡ሌላ የሚያደንዘዝዝ ነገር፡፡‹‹ዛሬ ምን እየተከሰተ ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ዘለለና መኝታ ቤት ገባ….ማንም የለም፡፡ወደሳሎን ተመለሰ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነው..፡፡ወለሉም ንፅህና ፅዱ ነው፡፡ምንም አይነት የተዘረረ እርቃን የሴት ገላ የተዘረገፍ አንጀትና ለአቅመ መወለድ ያልደረሰ ህፃን አይታይም…፡፡‹‹ሰውዬው እንዴት እንዴት አድርጎ ነው እንዲህ ያፀዳው?››ተገርሞ ጠየቀ..፡‹‹፡ሬሳውን የት አደረገው?››ምንም መገመት አልቻለም…፡፡ በፍራቻ የሚንዘፈዘፍ ሰውነቱን እንደምንም ብሎ በራፍ አካባቢ ባለ ደረቅ ወንበር ላይ አሳረፈ፡፡ለምን ቁጭ ማለት እንደፈለገ አያውቅም፡፡ግን ቤቱን ለቆ መውጣት አልቻለም፡፡ከ20 ደቂቃ በኃላ
👍532
#አላገባህም


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
‹‹ነይ እስኪ ቁጭ እንበል›› አለና ክንዷን ይዞ እየጎተተ አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀመጣት፡፡

‹‹እሺ ንገረኝ…ምንድነው ያሳቀህ?››

‹‹በጣም ነው እንጂ የሚያስቀው…ማንም ሴት እንዲህ አይነት መደራደሪያ አቅርባልኝ አታውቅም››

‹‹እኔ እኔ ነኝ ..ስለሌሎች ሴቶች አላውቅም፡፡››

‹‹ባል ወይም ፍቅረኛ አለሽ እንዴ?››በአእምሮ ሲያብሰለስል የነበረው ጥያቄ ጠየቃት፡፡

አፈጠጠችበት..ደነገጠም ..ግራ ተጋባም

‹‹እንዴ …ምን መጥፎ ነገር ተናገርኩ?››

‹‹ባል ወይም ፍቅረኛ ቢኖረኝ እዚህ ከአንተ ጋር ምን ያንዘላዝለኛል?፡፡››

ወደራሱ ጎተተና ከንፈሯ ላይ ተጠጣበቀባት…ተቃውሞ አላሰማችም..እንደውም ቀስ ብላ እጆቾን አነሳችና በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመች…አልጋውን ለቃ እየተንሳፈፈች እንደሆነ አይነት ምትሀታዊ አይነት ስሜት እየተሳማት ነው፡፡

የልቧን ምት ፍጥነት መቆጣጠር ስላልቻለችና መተንፈስም ስለከበዳት እየፈለገች ግን ከንፈሯን ከከንፈሩ አላቀቀችና

፣‹‹የሚጠጣ ነገር ይኖራል?››
ስትል ጠየቀችው፡፡መጠጥ የጠየቀችው በወሲብ ወቅት ድፍረት ይሰጣል ሲባል ስለሰማች ነው፡፡

‹‹አዎ አለ፡፡››አለና ከተቀመጠበት ተነሳ… ለእሱም ለእሷም መጠጥ ይዞ መጣና ጠረጴዛውን ወደ አልጋው አስጠግቶ ከጎኗ ተመልሶ ቁጭ አለ፡፡

‹‹ምነው ይሄን ያህል አስፈራለሁ እንዴ?››

‹‹አይ በፍፅም…..ግን ››ንግግሯን አቋረጠችና ስልኳን ካስቀመጠችበት ኮመዲኖ ተንጠራርታ አነሳችና..ከፍታ  ሰጠችው፡፡

‹‹ምንድነው?››

ተቀበላትና ተመለከተ..ውብ ቆንጅዬ የምታምር ልጅ ፎቶ ይታያል፡፡ግራ ገባውና ቀና ብሎ በትኩረት አያት‹‹ልጄ ነች…ስድስት አመቷ ነው፡፡››

‹‹ምን …?››ከተቀመጠበት ተነሳ…አፍጥጦ ፎቶውን መመለክት ጀመረ፡፡

በሁኔታው ተበሳጨች….‹‹… ዝም ብዬ እንድታውቀው ስለፈለኩ ነው እንጂ ይሄን ያህል ምን ያስደነግጥሀል…?አታገባኝ ወይ አትወሽመኝ ..አንድ ልጅ ኖረኝ አምስት ምን አጨናነቀህ…?››

በቆመበት አፍጥጦ በዝምታ ያያት ጀመር፡፡ያ ደግሞ የበለጠ ንዴቷን እንዲጨምር አደረገ…‹‹እንደውም ሁሉ  ነገር እዚህ ላይ ያብቃ ወደቤቴ ልሂድ››ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ተንደርድሮ መጥቶ ትከሻዋን ይዞ አስቀመጣትና ግንባሯን ሳማት፡፡

‹‹በጣም ነጭናጫ ሴት መሆንሽን ታውቂያለሽ?››

‹‹እንኳን››

‹‹እኔ ይህቺን የመሰለች ልጅ ስላለሽ ቀናሁብሽ እንጂ አልተበሳጨሁበሽም…በጣም እኮ ነው የምታምረው…..ደግሞ በስንት አመትሽ ብትወልጂያት ነው እንዲህ ያደገችው?››

‹‹በ17››

‹‹እና የት ነው ያለችው ..ከአንቺ ጋር ወይስ አባቷ ጋር?››

‹‹አባቷ መፀናሷን እንዳወቀ ነው ሸሽቶ ውትድርና ተቀጥሮ የጠፋው..እስከአሁን ይኑር ይሙት አላውቅም…እሷ ከእኔ ጋር ነው ያለችው፡፡››

‹‹እና አሁን እቤት ነው ያለቻ ?ብንሄድ እናገኛታለን?››

በመገረም አፍጥጣ ተመለከተችው‹‹የእውነት አሁን እንሂድ ብልህ ትሄዳለህ?››

‹‹አዎ..››ሞባይሉን አወጣና ሰዓቱን ተመለከተ …‹‹ሰዓቱ ገና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከ10 ነው …ተነሽ እንደውም….የሆነ ነገር ገዝተንላት እንሂድ እና እናስደስታት፡፡››

እሱ ጃኬቱን ሲለብስ እሷ ከተቀመጠችበት ሳትንቀሳቀስ በገረሜታ አፏን ከፈተችና በፍዘት ታየው ነበር፡፡

‹‹አልሰማሺኝም እንዴ? ተነሽ እንሂድ››

‹‹ልጅ ማትወድ መስሎኝ ነበር››

በተራው ደነገጠ…‹‹እንዴ ምን ማለት ነው…?እንዴት እንደዛ ልታስቢ ቻልሽ?››

‹‹ቅድም የወንድምህን ልጅ ወደአንተ ይዤ መጥቼ ሳስተዋውቅህ..ከእቅፌ ወስደህ አቅፈህ የምትስመው መስሎኝ ነበር…ግን እንደዛ አላደረክም..ጉንጩን አንኳን አልሳምክም››

ወደእሷ መጣና ከጎኗ ተቀመጠ‹‹ያን ያህል ስትታዘቢኝ ነበር ማለት ነው…?ላቅፈውና ልስመው በጣም ነበር የፈለኩት….አጎትህ ነኝ ብዬ እሽኮኮ በማድረግ ከሆቴሉ ይዤው ወጥቼ ላዝናናው ሁሉ ፈልጌ ነበር..ግን አልቻልኩም…ምክንያቱም የወንድሜ ልጅ ነው ፤ስለወንድሜ ሳስብ ደግሞ በደረቷ ቢላዋ ተሰክቶባት ወለል ላይ የተዘረጋች እናቴና በገመድ የተንጠለጠለች እህቴ ነች ወደአእምሮዬ የምትመጣው…በዛን ወቅት አሰብ የነበረው ስለእነሱ ነበር …እንባዬ እንዳያመልጠኝና በሰርግ እድምተኞች ፊት እንዳልዋረድ እየጣርኩ ነበር››እንባው ከአይኖቹ እየተዘረገፈ መውረድ ጀመረ፡፡ ደነገጠችና ከተቀመጠችበት ተነሳች በእጇቾ እንባውን እበሰችና ግንበሩን ጉንጮቹን እያገላበጠች እየሰማች‹‹ይቅርታ…በጣም ይቅርታ…እኔ እንዲህ አይነት ቀሽም ሴት ነኝ…ሶሪ ወንዶችን ሰላማላምን ሁሉን ነገር ነው የምጠራጠረው…ከልጄ አባት ውጭ ሌላ ወንድ አላውቅም…ከአንተ ጋር በእንደዚህ አይነት መጠን መቀራረብና በአንድ ክፍል ውስጥ መሆን በጣም ቢያስደስተኝም በዛው መጠን አስፈርቶኛል….ለዛ ነው ያልሆነ ነገር የምቀባጥረው፡፡››

‹‹ችግር የለውም… ተረድቼሻለው››

‹‹በቃ በፈጣሪ ያልኩህን  ሁሉ እርሳው…››ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት..በጠንካራ እጆቹን በቀጭን ወገቧ ዙሪያ ጠመጠመና ከሰውነት ጋር ለጥፎ ትንፋሽ እስኪያጥራት መጠጣት…..ከዛ ለቀቃትና..‹‹በይ አታረሳሺኝ ተነሽ እንሂድ››

‹‹በእውነት ቢሆንና ብታይህ በጣም ነበር የምትደሰተው…ሙዚቀዎችህን በጣም ነው የምትወዳቸው…ግን አሁን የለችም››

‹‹የለችም ማለት?››

‹‹አሁን ክረምት አይደል..ትምህርት ስለተዘጋ አያቶቾ ወስደዋታል….የሚቀጥለውን አንድ ወር እነሱ ጋር ነው የምታሳለፈው….››

‹‹እ ያሳዝናል…እንግዲህ ምን ማድረግ ይቻላል ስትመለስ ታስተዋውቂኛለሽ››

‹ስትመለስ?››አለችና ሳቀች፡፡

‹‹ምን ያስቅሻል?››

‹‹የዛሬ ወር እኮ ነው ያልኩህ…››

‹‹ምነው የዛሬ ወር የለሁም እንዴ..?አለሁ እኮ ፤ማለቴ በፍቅርሽ አሟሙተሸ ካላጠፋሺኝ አለው..››

‹‹ይሁን እስኪ…..ለማንኛውም አስገርመሀኛል››አለችና የመጠጡን ብርጭቆ አነስታ ተጎነጨች፡፡

‹‹እድሉን እስከሰጠሺን ድረስ ገና ብዙ አሰግርምሻለው፡፡››

ከዛ ቀልል ያለ ወሬ እያወሩ ከመጠጡ መጎንጨታቸውን ቀጠሉ….

‹‹ይሞቃል አይደል?››አለችው የእውነትም በጣም እየሞቃት ነው…ያላወቀችው የሙቀቱ ምንጭ ከምትጠጣው መጠጥ ይመንጭ ወይም ከጎኗ ካለው ሸበላ ወይም ከአየር ፀባዩ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም፡፡

‹‹እኔም ሞቋኛል …››አለና ጃኬቱን አወለቀ፡፡

‹‹እኔስ ቀሚሴን ላውልቅ?››አለችውና ሳቀች፡፡

‹‹ይቻላል..ቆይ እንደውም..›› አለና ከተቀመጠበት ተነሳና ወደሻንጣው በመሄድ ከፈተው፡፡ምን ሊያደርግ ነው ብላ በትኩረት እየተከታተለችው ነው፡፡

ስስ ቁምጣ እና ቲሸርት አወጣና…እንቺ  ቀሚሱን አውልቂና ይሄን ልበሺ አለና ለራሱ ሌላ ቢጃማ በማውጠት  ሱሪውን ለማውለቅ ቀበቷውን መፍታት ጀመረ፡፡

‹‹ምን እያደረክ ነው?››

‹‹ሱሬዬን ልቀይር ነዋ….››

ሱሪውን ወደታች አወለቀ..ከዛ ከላይ የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀ..በነጭ ፓካውትና በሰማያዊ ፓንት ብቻ በሁለት ሜትር ርቀት ቆሞ ስትመለከት ሰውነቷን ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ ነገር አንዘረዘራት፡፡በልብስ ከሚታየው ይልቅ እርቃኑን ያምራል…ደግሞ ከፊል ሰውነቱ በተለያዩ ማራኪ ንቅሳቶች የተዥጎረጎረ ነው፡፡

‹‹ምነው ፈዘዝሽ?››ብሎ አሳፈራት፡፡

‹‹ምን ፈዛለው…እንደ ሸራ በስእል ተዥጎርጉረህ የለ እንዴ?››

የሚቀይረውን ቢጃማ ሱሪ አነሳና በእጁ እንደያዘ‹‹ያምራል አይደል…?እስኪ በደንብ ተመልከቺው ››አለና ይበልጥ ወደእሷ ተጠጋና ስሯ ቆመ፡፡

ዝም አለች ..ጎትቶ አስነሳት‹‹እንዴ ምን እያደረክ ነው?››
👍6513🥰1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ራሄልም እህቷን ይዛ እቤት እንደገባች ጓደኛዋ  ሜሮን ቤት እየጠበቀቻት ነው፡፡መጀመሪያ ቀጠሮውን ለመሰረዝ ፈልጋ ነበር…በኋላ ስታስበው ግን ሴትዬዋ ለስብሰባው ትኩረት እንዳልሰጠች አድርጋ ልትረዳት እንደምትችል ስላሰበች ለመሄድ ወሰነች፡፡ ከሆስፒታል እንደተነሳች ነበር ደውላ ቤት እንድትጠብቃት የጠየቀቻት፡፡፡‹‹ቀጠሮው በጣም ወሳኝ ስለሆነ  ነው ያስቸገርኩሽ፡፡››

‹‹አረ ችግር የለውም..ያንቺ እህት ማለት እኮ የእኔ እህት ነች››አለች ሜሮን፡፡

‹‹እሱስ እውነት ነው››

‹‹አዎ ደግሞም አሪፍ የምስራች አለኝ…››

‹‹እባክሽ ንገሪኝ ቀኑን ሙሉ ስጨናነቅ ነው የዋልኩት…ፈገግ ማለት አምሮኛል››

‹‹አንድ እምቅ ችሎታ ያላት እና በነርሲንግ የሰለጠነች ሞግዚት አግኝቼልሻለው›› አለቻት….ከሁለት ቀን በፊት ለሁሉም ጓደኞቾ  ስለፀጋ ነግራቸው የሰለጠነች ሞግዚት እንዲፈልጉላት አደራ ብላቸው  ነበር፡፡

‹‹አንቺ እኮ ሕይወት አድን ነሽ›› አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጯን ሳመቻት፡፡

ወደቀጠሮ ቦታ ይዛ የምትሄደቸውን ወረቀቶች ወደ ቦርሳዋ አስገባች።

‹‹ሞግዚት ማግኘት ከቻልኩ የፀጋ ዶ/ር የሰጠውን መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ እንዲተገበር ማድረግ እችላለው። ውዴ  ለአሁን ፀጋን ልትጠብቂልኝ ስለወሰንሽ  ደስተኛ ነኝ። ነገሮች ሁሉ ሰላም  እንደሚሆኑ አምናለው?››

‹‹ሄይ. ታውቂያለሽ እኔ  በጣም ጥሩ ጓደኛሽ  ነኝ.››

‹‹ብቃት ያለው ሞግዚት አግኝተሸልኝማ ያንን መካድ አልችልም…  በጣም ጥሩ ጓደኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ህይወት አድንም ነሽ።››

‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ እስኪ በመጠኑ ዘና ለማለት ሞክሪ….››

ራሄል  ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ላላት ቀጠሮ የምትጠቀምባቸውን መረጀጃዎች የያዙ ወረቀቶች እየለየች ‹‹ዘና ማለት እንኳን የምችል አይመስለኝም…ደክሞኛል… በአእምሮዬ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ,››ስትል መለሰችላት፡፡ቀጥላም‹‹‹‹በፋውንዴሽን ውስጥ ነገሮች በጥሩ መንገድ እየሄዱ አይደለም ፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ለጋሾችን አጥቻለሁ አሁን የምሄድባትን ሴትዬ ከዋና ለጋሾቻችን የመጀመሪያዋ ነች….እሷን የግድ ማሳመን አለብኝ ››

‹‹ለምን ሎዛ እንድትሰራው  አታደርጊም?››

ራሄል ነገሩን በማሰብ ትንሽ ቆም ብላ ራሷን በአሉታ ነቀነቀች።‹‹ይህን ከባድ ኃላፊነት በእሷ ትከሻ ላይ መጣል አልችልም››

‹‹ስለዚህ በራስሽ ላይ ትጥያለሽ ..እሱ ችግር የለውም ማለት ነው?››

‹‹ትከሻዬ ከሷ የበለጠ ልምድ ያለው ነው›› አለች ፡፡

‹‹ጓደኛዬ ጥቂት ስራዎችን ለሌላ ሰው  ብታስተላልፊ አለም አትገለባበጥም።እና ደግሞ የህይወት ሸክማችንን የሚያቀልልን ክርስቶስ ነው….በእሱ መታመን ችግራቸንን ያቀልልናል፡፡››

‹‹እና ለምን ያቺን አሁን በስቃይ የምታለቅሰውን  ትንሽ ልጅ  እንዲህ አጎጉል አደረጋት? በኢየሱስ አላምንም ብላ ይሆን ?››በራሄል ንግግር ሜሮን  በጣም ደነገጠች፣

‹‹ራሄል .. አንቺ እኮ ከዚህ የበለጠ አስተዋይ ነሽ ››ራሄል እጇን ወደ ላይ ዘረጋች።

‹‹አዝናለሁ ስለ ኃጢአት እና ክፋት ሁሉን ነገር አውቃለሁ እናም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር እንደሆነም አምናለው, ስለዚህ ስብከት አንዳትጀምሪኝ››

ሜሮን  የጓደኛዋን ትከሻው በፍቅር እየዳበሰች‹‹ታውቂያለሽ አይደል …?ማመን ስለማትፈልጊ ብቻ ነው. እንዲህ የምትይው…ግን እወቂ አሁንም በኢየሱስ ጥበቃ ውስጥ ነሽ …አዎ፣ በግንኙነቶች ውስጥ ህመም አለ…በሆነ ግንኙነት ተሰብረን ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም  ልባችንን ሁሌ ለፍቅር ክፍት መሆን አለበት ››

‹‹ደህና፣ አሁን ለልብ ጉዳዬች ጊዜ የለኝም።ደግሞ እስከአሁን ለእኔ የሚሆን ሰው አላጋጠመኝም።›› መስታወት አወጣች እና ሜካፕ እና ፀጉሯን በፍጥነት አስተካከለች።

ሜሮን ‹‹ዶ/ሩ በጣም የሚስብ ይመስለኛል››ስትል አዲስ ድንገተኛ ርዕስ ከፈተች፡፡

ራሄል የጓደኛዋን ሹፈት ችላ በማለት ቦርሳዋን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች ፡፡

‹‹እሱ ማራኪ ነው…እንዳልኩሽ  ግን ለጊዜው ለማንም ጊዜ የለኝም ።››በማለት መለሰችላት፡፡

ራሄል ወደ በሩ ስትሄድ ሜሮን ‹‹መልካም ጊዜ ይሁንልሽ›› ብላ ጮኸች።

////
ራሄል ከሴትዬዋ ጋር እያካሄደች ያለውን ስብሰባ አንድ ሰዓት በላይ ብታሳልፍም..እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ልታሳምናት አልቻለችም፡፡

‹‹ባለቤቴ በዚህ ገንዘብ በጣም ነው የሚያምነኝ… እናም ይህን  በትክክለኛው መንገድ ማድረግ  ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹ይገባኛል››አለች ራሄል። ነገር ግን የባለቤቷትን  እምነትን ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ገንዘቡን ለትክክለኛው ዓላማ ብቻ ለሚጠቀም በጎ አድራጎት መስጠት ነው።››
ወ.ሮ ላምሮት ፈገግ አለችላት፡፡

ወ.ሮ ላምሮት ራሄልን በትኩረት አየቻትና ‹‹አባትሽን ትመስያለሽ›› አለቻት። ‹‹እሱ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚሰራ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜ ምሳሌ ነው.››ስትል አከለችበት፡፡

ራሄል መራራ ህመም ተሰማት። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአምላክ ጋር ብዙ ጊዜ አላጠፋችም። የወ.ሮዋ  ቃላት አብዝታ ወደ ጸለየችበት፣ መጽሐፍ ቅዱሷን በሰፊው ታንብበት  ወደ ነበረችበት ጊዜ አመጣት። ቤተክርስቲያን እና እምነት የመተንፈስ ያህል የእርሷ አካል ነበር። እምነቷን መልሶ ለማግኘት እና በአምላክ ላይ መታመን ለምን እንደሚያስፈልጓት አሰበች። ››

በወ.ሮ ላምሮት ፈገግ ብላ ሰዓቷን በጥበብ ተመለከተች። ለመውጣት ጊዜው ነበር፡፡

‹‹እኔ እንዳልኩት፣ እባኮት ይህን በትክክለኛው መንገድ  ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ..ያንን ብቻ ነው የምጠይቀው››አለች ራሄል፣

ወ.ሮ ላምሮት ከግዙፉ መኖሪያ ቤቷ ስትሸኛት ራሄል የመጨረሻ የማሳመኛ ንግግሯን ተናገረች‹‹እርግጠኛ ነኝ .. ባለቤቷት በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲቸኩሉ አይፈልግም ››

ነገር ግን ከወ.ሮዋ ፊት ምንም ነገር ማንበብ አልቻለችም  ፡፡ሴትዬዋን ለማሳመን የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች..ግን ይሳካላት አይሳካላት መገመት ስላልቻለች በጣም ተበሳጨች ፣ መኪናውን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው…መኪናዋን አቁማ ወደአፓርታማዋ ተጠጋች… የአሳንሰሩን ቁልፍ ተጫነች እና ገባች፤ውስጥ ያልጠበቀችውን ሰው አገኘች፡፡የቆዳ ጃኬት ለብሶ ነበር። የሞተር ሳይክል ሄልሜት በእጁ ይዟል።

‹‹ሰላም. እዚህ ምን እየሰራህ ነው?››ብላ ጠየቀችው፣ እስትንፋሶ ተቆራረጠባት፡፡

‹‹በቃ ጎራ  ብዬ ከፀጋ ጋር እንዴት እየተለማመድሽ እንዳለሽ ለማየት አስቤ ነበር።››

‹‹ጥሩ አደረክ››አለችው

‹‹ወደ ውጭ ወጥተሽ ነበር?››

‹‹አዎ ጠቃሚ ስብሰባ ነበረኝ›

‹‹እንደ ሁሉም ስብሰባዎችሽ››አለ

‹‹አይዞህ አታስብ ጓደኛዬ በጣም ብቃት ያለት ሞግዚት ነች።እርግጠኛ ነኝ እሷ ከእኔ በተሻለ  ከፀጋ ጋር ትግባባለች።››ሊፍት ሲቆም ወደ ኋላ ዞር አለላት።ራሄል ቀድማ ወጣች..ተከተላት፡፡ ኮሪደሩን እንደረገጡ  የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሁለቱም ጆሮ ገባ። የመጣው ከራሷ ቤት  ነው።ሁለቱም ርምጃቸውን አፈጠኑና ተከታትለው ወደቤት ገቡ ፡፡ሜሮን የምትጮኸውን ፀጋን  ተሸክማ እቤት ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትሽከረከራለች፣ የልጁቷ ክንዶች በሜሮን  ጀርባ ላይ ተዝለፍልፋው ይታያሉ፡፡

ራሄል ቦርሳዋን ጥላ ወደ ጓደኛዋ ሮጣ ሄደች። ጸጋ ራሄልን እንዳየች ከሜሮን እቅፍ ውስጥ ተስፈንጥራ  እጇን ዘረጋች። እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለሉ በመርገፍ ላይ ናቸው፡፡
55👍3🥰1👏1😢1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ከዛ ጉሮሮውን አሟሸና መናገር ጀመረ"ከእድሜሽ በላይ ለማሸነፍ ስጥር ነው የኖርኩት…እናም ቡዙ ነገር አግኝቼ .. ብዙ ነገር አጥቻለሁ፣ ወጣቷ ሴት…ኪሳራ አያስደነግጠኝም። ሀብታም መሆን የበለጠ አስደሳች ነገር ነው፣ ግን ኪሳራም የበለጠ አስደሳች ነው። እራስን የሚያንፁና የሚገነቡ ጥቅሞች  አሉት። ››

‹‹ከከተማዋም አልፎ በሀገሪቱም የተሳካልህ የቢዝነስ ሰው መሆንህን አውቃለው፡፡ገንዘብ ስላለህም የፈለከውን ነገር በፈለከው ሰዓት ማድረግ እንደምትችል እንደምታምንም አውቃለው፡፡››አለችው በልበሙሉነት፡፡

"ታዲያ ካወቅሽ ይህን አስቂኝ ምርመራ ለምን አትተይውም?"ሲል ቀጥታ ወደሚፈልገው ርዕስ ገባ፡፡

"ይህ መቼም የሚሆን አይመስለኝም ..አላደርገውም››

"እናትሽን የገደልኩት እኔ እንደሆንኩ እንዴት ታስቢያለሽ? እሷ ከጁኒየር ምርጥ ጓደኞች መካከል አንዷ ነበረች:: በየእለቱ ከዚህ ቤት ትወጣና ትገባ ነበር::እርግጥ ካገባች በኋላ ብዙም አትመጣም ነበር… እናትሽን ለመጉዳት ጣቴን አንስቼ አላውቅም።››

አለም እሱን ማመን ፈለገች። በወንጀል ጉዳይ ተጠርጣሪ ቢሆንም እሷ ግን በጣም ታደንቀው ነበር። በውይይታቸው ከተገነዘበችው እና ለምርመራዋ ስትል ከሰበሰበችው መራጃ እንደተረዳችው ከምንም ነገር ተነስቶ ኢምፓየር መገንባት ችሏል።በማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር. አሳማኝ ባህሪ ነበረው። ነገር ግን በቀለማት ያሸበረቀ ስብዕናው ከጀርባ ሚሰራቸውን ቆሻሻ ድርጊቷች በቀላሉ እንዳይገለፁ ምክንያት እንደሆኑ በደንብ ታውቃለች።ቢሆንም ግን ለፍሰሀ ያላት አድናቆት እንደፍላጎቷ ሙሉና ጠንካራ አልነበረም..፡፡

ደገመችና ‹‹ምንም ቢሆን ምንም ምርመራውን ማቋረጥ አልችልም" አለች ።

‹‹ለምን ?››

" ብፈልግ እንኳን ዋና አቃቢ ህጉን በስንት መከራ ካሳመንኩት በኃላ ወደኃላ እንድመለስ መጠየቅ ያሳፍራል ፡፡"

"ስሚ" አለና አይኖቾን በትኩረት እያየ " ስህተት እንደሰራሽ ንገሪው፣ እናም ነገ በዚህ ሰአት እዚህ የመጣሽበትን ጉዳይ እንኳን እንደማያስታውስ ዋስትና እሰጥሻለሁ..ስራውንም ለቀሽ ወደአዲስአበባ መመለስና ቆንጆ የጥብቅና ቢሮ ማቋቋም ትችያለሽ….እናትሽ የልጄ የልብ ጓደኛ ነች…አንቺን ለማቋቋም የሆነ ነገር ማድረግ ለእኔ ያን ያህል የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ።"

" አላደርገውም "

"እሺ፣ እንግዲያውስ ዋና አቃቢ ህጉን ለእኔ ተይልኝ..እኔ አናግረዋለው።"

"አቶ ፍሰሀ… ››ጮክ ብላ ተናገረች "የኔ ሀሳብ አልተረዳህልኝም"ትኩረቱን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን "ልጅህ በምርጫ ያለውን ተሳትፎ የሚጎዳ ምንም ነገር ለማድረግ እቅድ የለኝም…ያ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደማደርግና እያንዳንዱን እንቅስቃሴዬንና ምርመራዬን በከፍተኛ ሚስጥር እንደማከናውን ቃል እገባለው…ማድረግ የምችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››

"የአንድ ሙሉ ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ቢሆንም ሀሳብሽን አትቀይሪም ማለት ነው?"

"ከተራቡ ህፃናት ዳቦ እየወሰድኩ ነው የሚመስልህ…?ነው ወይስ ያንተ ልጅ ይህቺን ከተማ ወክሎ የተወካዬች ምክር ቤት ከገባ በኩልፎ ወንዝ ወተት እንደሚንዠቀዘቅ እና ህዝቡ በቁንጣን እንደሚሰቃይ ነው የምታስበው?"

" ተይ እንጂ ..እኔ እንደዛ አላልኩም "

" እንግዲያው አቋሜን በግልፅ አሳውቂያለው..እኔ ሁላችሁንም በግል ለማጥቃትና ለማውደም ምንም እቅድ የለኝም…ግን ደግሞ የእናቴን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ ህይወቴንም የሚያስከፍለኝ ቢሆን ግድ የለኝም..እስትንፋሴ እስካለች ድረስ ወደፊት እቀጥላለው››

‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?"

‹‹አዎ..እኔን ማስቆሚያ ብቸኛው መንገድ እኔንም እንደእናቴ ማስወገድ ነው….በዛ ጉዳይ ላይ ልታስብበት ትችላላችሁ፡፡››

‹‹ንግግርሽ በጣም….››አቶ ፍሰሀ ንግግሩን አቋረጠ..እንደዛ ያደረገው ልጁ ጂኒዬር በራፉን ከፍቶ ስለገባ ነው፡፡

ጁኒየር በሩን በድንገት ከፍቶ አንገቱን ወደ ውስጥ አሰገገና"ሄይ, በሰላም ነው ..በጣም መሸ እኮ…እራት ሊቀርብ ነው" ፡፡

"በጣም ጥሩ ….ውይይታችን ጨርሰናል…..ግን እራቱ ይቅርብኝ ….ቀጥታ ወደቤቴ ነው መሄድ የምፈልገው››አለች አለም።

አቶ ፍሰሀ ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው "እዚህ በቁም ነገር እየተነጋገርን ነበር። ዳግመኛ በግል ቢሮዬ ውስጥ ከሰው ጋር እያለው አንዳታቋርጠኝ፣ ።››
ጁኒየር "ንግግራችሁ በጣም ግላዊ ወይም በጣም ከባድ እንደሆነ አላውቅም ነበር።"ሲል ለአባቱ ቅሬታ ምላሽ ሰጠ፡፡

"አቶ ፍሰሀ.. እባክህ, ምንም አይደለም…በበቂ መጠን ተጋግረናል እኮ..የቀረም ነገር ካለ ሁለተችንም እዚሁ ከተማ ውስጥ ነን..ደጋግመን መገናኘታችን አይቀርም በእውነቱን ለመናገር፣ ጁኒየር ስላቋረጠን ደስተኛ ነኝ። ምን ያህል እንደመሸ አሁን ነው ያስተዋልኩት… አሁን መሄድ አለብኝ።"

ሁሉም ተያይዘው ወደሳሎን ተመለሱ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነበር፡፡ገመዶም ሆነ ሳራ አልነበሩም፡፡

‹‹ለራት ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል››አቶ ፍሰሀ ናቸው ተናጋሪው

‹‹አይ ይቅርብኝ..ደህና እደሩ››

ጁኒየር  ኮቷን ከያዘላት በኋላ መኪናዋ ድረስ ሸኛት ..ወደ እሱ ዘወር አለችና ።"ጁኒየር አመሰግናለው …ደህና እደር።"አለችው
" እጇን ያዘና ጎንበስ ብሎ ሳመው… ከዛ መዳፏን ወደ ላይ አዙሮ ሳመው። "የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ እንደዚህ ታሽኮረምማለህ?"

የማይገባ ፈገግታ ፈገግ አለላት ፡፡

"ለፍቅር በቀላሉ ተጋላጭ ነህ እንዴ?"ሌላ ጥያቄ አስከተለች፡፡ "እንደዛ ነኝ እንዴ..?አይ አይደለሁም."ፈገግታው እየሰፋ ሄዶ ፡፡
‹‹ለማንኛም መልካም ምሽት››አለችና መኪና ውስጥ ገብታ አካባቢውን ለቃ ተፈተለከች ጁኒዬር ወደቤት ተመለሰና ቀጥታ ወደእናቱ መኝታ ክፈል አመራ እና በስሱ አንኳኳ
‹‹እማዬ ፣ ልግባ?››

" ውዴ እባክህ ግባ" ሳራ ፈቀደችለት… በልጇ ጉብኝት በጣም እንደተደሰተች ግልጽ ነው። ርካሽ የንባብ መነፅሯን አውልቃ እያነበበች የነበረውን መፅሃፉ ከጎኗ አስቀመጠች፡፡

‹‹አትቀመጥም››

‹‹አይ  ይሁን››  አለና  አልጋው  ጎን  በመቆም፡፡ 

"መጽሐፉ  እንዴት  ነው?"  ሲል ጠየቃት፡፡መፅሀፉን ገዝቶ ያመጣላት እሱ ነበር፡፡

"በጣም አስደሳች ነው።››ስትል በአጭሩ መለሰችለት፡፡ "ጥሩ፣ ስለተደሰትሽበት ደስ ብሎኛል"

ሳራ እናቱ እንደመኆኗ መጠን በውስጡ የሚገላበጠውን ጭንቀት ተረዳችና። "ምንድነው ችግሩ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

"ምንም።"

"አንድ የተሳሳተ ነገር ሲኖር ማወቅ እችላለሁ."
"ከተለመደው የተለየ ነገር የለም ከአሌክስ..ማለቴ ከአለም ጋር የነበራቸውን ውይይት በማቋረጤ አባቴን አበሳጭቼዋለው››

"አባትህ የጋራችን በሆነው መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ሲኖር ራሱን እንዴት መምራት እንዳለበት እስካሁን አልተማረም። በቤታችን የጋራ እንግዳችን ሆና የመጣችን ሴት ለግል ውይይት ብሎ ክፍል ውስጥ በማስገባት ማዋራት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ስለሆነ አንተም ፣ ውይይቱን በማቋረጥ ባለጌ የመሆን መብት አለህ።››አለችው

‹‹እማዬ…››

"ለማንኛውም በግል ምን እየተወያዩ ነበር?"

"ስለ እናቷ ሞት ይመስለኛል….ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም."

"እርግጠኛ ነህ? ዛሬ ማታ ሁሉም ሰው በጣም የተጨናነቀ ስሜት ላይ እንዳለ መረዳት ችያለው።"

" ችግርም ካለ አባዬ ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው ይቆጣጠረዋል። በእርግጠኝነት ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም።››
38👍4