አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ከሶስት አመት በኃላ.. እናትዬውን አሳምና ከደሎ ለቃ ስትወጣ  አንድ ሻንጣ ልብሷን ይዛ በትራንስፖርት ሳይሆን በንስሯ አማካይነት እየበረረች ነበር የተጓዘችው..በእጇ እናቷ ያስጨበጠቻትን 2000 ሺ ብር እና አጎቷ የሰጣትን 5 ሺ ብር .. በቃ ይሄንን ነው የያዘችው፡፡ግን ሻንጣዋ ውስጥ ከአመታት በፊት ኪኒማጀሮን ለመጓብኘት…»
#የተረታህ_ለታ

ተማር ከሽንብራ ፤ ተማር ከባቄላ
ከስንዴ ካተሩ
ተጥለው ነው ካፈር
የማታ የማታ ፍሬ የሚያፈሩ፡፡
👍61🔥12👏61
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

ኬድሮን ከዕንቅልፋ የነቃችው 11 ሰዓት አካበቢ ቢሆንም መኝታ ቤቷን ለቃ ወደ በረንዳው  የወጣችው 12 ሰዓት ተኩል ካለፈ በኋላ ነው፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ዘወትር እንደምታደርገው ዮጋ እየሰራች ነበር የቆየችው፡፡እቤቷን ለቃ ስትወጣ ንስሯ ተከትሏት ወጣ፡፡እሷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ማንበቧን ጀመረች ፡፡

ከ12 ሰዓት እስከሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ግቤዋ ውስጥ ባሉት ዛፎች ላይ የሰፈሩትን የተለያ አይነት የወፎች ህብረ ዝማሬ እየሰማች  ንፁህ በሆነ አዕምሮዋ ተረጋግታ በተመስጦ የምታነብበት ሰዓት ነው፡፡ከሀገሯ ወጥታ ለገጣፎ ከከተመች በኃላ ያዳበረችው አዲስ ልምድ ንባብ ነው፡፡ከመፅሀፍቶች ጋር ያላት ቁርኝት ለእሷም ለራሷ እስኪገርማት ድረስ በጣም የጠነከረ ሆኗል፡፡በአጠቃላይ ሱሰኛ ሆናለች ፡፡

አንድ ሰዓት አካባቢ  ከእሷ መኝታ ቤት ጎን ያለው የፕሮፌሰሩ በራፍ ተከፈተ ፡፡ያልጠበቀችው ክስተት ነበር፡፡ምክንያቱም  ደግሞ የፕሮፌሰሩ ባህሪ ከእሷ የተለየ ስለሆነ ነው፡፡እሳቸው እሰከ ለሊቱ አስር ሰዓት  ድረስ  ይቆዩና የተለየ ፕሮግራም  ከሌላቸው በስተቀር እስከ ጥዋቱ አራት ሰዓት ድረስ ይተኛሉ፡፡እና ስታነብ የነበረውን መጻሀፏን አጠፍ አድርጋ አይኗን ወደፕሮፌሰሩ በራፍ ላከች፡፡ከክፍሉ የወጡት ፕሮፌሰሩ ሳይሆኑ አንድ የ20 ዓመት አካባቢ ሚሆናት መልከ መልካም ሴት ነች፡፡ፈገግ አለች ፡፡
እኚ ሽማጊሌው ሙሁር ከአልማዝ የጠነከረ ጽናት እና የሚያስገርም ስብዕና ቢኖራቸውም ሴት ላይ ያላቸው አመል ግን የተለየ እና  የሚገርም ነው፡፡ካሉበት ዕድሜ ጋር የሚቃረን አይነት ነው፡፡እሳቸው ግን  ይሄንን ድክመታቸውን እንደድክመት ተመልክተውት አያውቁም፡፡ ለጤነኝነቴ እና በዚህ ዕድሜዬ ላይ ላለኝ ጥንካሬ ሚስጥሩ  ሁለት ነው ፤የመጀመሪያው ከእጽዋት ጋር ያለኝ ፍቅር እና ቁርኝት ሲሆን ሌላው ደግሞ  ለወሲብ ያለኝ ፍቅር ነው ብለው በድፍረት ለጠየቃቸው ሁሉ ይመልሳሉ፡፡ ጫን ብለው ለጠየቃቸውም ስለወሲብ ጥሩነት ዘርዘር አድርገው ለማስረዳት ይገደዳሉ‹‹…. የወሲብ ብቃት ቀጥታ ከጤነኝነት ጋር ትስስር አለው፣አንድ የወሲብ ብልቱ አልታዘዝ ያለው ሰው የሆነ የጓደለው ነገር አለው ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ ትልቅ ቢዝነስ ሚያንቀሳሰቅሱ ባለሀብቶች ወይም ትልቅ ድርጅት ሚያሰተዳድሩ የስራ መሪዎች የወሲብ ስሜታቸው ሚቀሰቀሰው ከእለታቶች በአንድ ቀን ፤ለዛውም በብዙ ድካምና የመድሀኒት እገዛ ነው ፡፡ይህ የሚሆነበት ዋናው ምክንያት በጭንቀት የተበረዘ አዕምሮ እና በስራ የዛለ አካል ስላላቸው ነው ለወሲብ ዝግጁ መሆን የማይችሉት:: አልያም ድባቴ ውስጥ ገብተው በጭንቀት በሽታ እየተሰቃዩ ነው፡፡

ጥናተቶች አንደሚያመለክቱት የአንድ ሰው ብልቱ ሲቆም ያለው ጥንካሬ እና የልብ ጥንካሬ ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው…ተገትሮ የሚሰነጥቅ ብልት ያለው ወንድ ልቡም እንደዛው የተደራረበ ጠንካራና ከብረት የደደረ ነው፡፡ በሳምንት 4 ቀን ወሲብ የሚፈጽም ሰው ከማይፈጽም ሰው በልብ ድካም የመያዝ  ዕድሉ 58 ፐርሰንት የበለጠ የተሻለ ነው ፡፡…..››እያሉ መሰል መረጃዎችን በመደርደር ያስረዳሉ፡፡

ስለእሳቸው ማሰቧን ገታ አድርጋ ፊት ለፊቷ ወዳለችው ልጅ ትኩረቷን መለሰች፡፡በዛ ተመሳሳይ ሰዓትም ንስሯ ፡፡ ከተቀመጠችበት ወንበር ትክክል ጣራው ላይ ሰፍሮ ዘና ብሎ ቁልቁል እሷንም ጊቢውንም እየቃኘ እና የጥዋቷን ፀሀይ አብሯት እየሞቀ እና የምትመለከታትን ልጅ እየተመለከተ ነው፡፡
ልጅቷ በራፉን መልሳ ዘጋችና ወደውጨኛው  በራፍ ለመሄድ እርምጃ ስትጀምር  አዕምሮዋን ሰረሰራት፡፡ቀና ብላ ወደ ንስሯ ስታይ እነዛ ሰርሰሪ አይኖቹን ልጅቷ ላይ ሰክቷል…‹‹ ነገር አለ›› አለችና እሷም ትኩረቷን በመሰብሰብ የሚያየየውን ለማየት ሞከረች…. የልጅቷ ልብ ጭልም ብሎ ነው እየታያት ያለው‹‹‹ ..በሀዘን ኩምትርትር ያለ….ደግሞ ግራ የተጋባ የተመሰቃቀለ  ነፍስ ነው ያላቻት ›ስትለ አጉረመረመች.. ..ወጣቷ ቆንጆ ለሚያያት ሁሉ በፈገግታ  የደመቀ ፊት ስለሚታየው በጨለማ የተሞላች  ነፍስ አላት ተብሎ ቢነገረው ማንም አያምንም ፡፡

‹‹የእኔ እህት ››ብላ ጠራቻት

‹‹አቤት››አለችና ባለችበት ቆማ ፊቷን ወደ እሷ አዞረች…

‹‹ደህና አደርሽ …?››

‹‹ደህና ››አለች ግራ በመጋባት

‹‹ምነው በለሊት…?››

በንግግሯ ግራ ተጋብታ በእጇ የያዘችውን ሞባይል አብርታ አየችና‹‹እንድ ሰዓት እኮ ሆኗል…?››አለቻት፡፡

‹‹ካልቸኮልሽ ቁርስ አብረን እንብላና ትሄጄያለሽ›› …..ይህን ስትላት ልጅቱ እንደማትቸኩል እርግጠኛ ነኝ ….በቃ እንደውም የምትሄድበትም ያላት አይነት እንዳልሆነች  ተረድታለች፡፡

እንደማቅማማት አለችና ፊቷን አዙራ ወደእሷ መጣች፤እንደዛ ያደረገችው ዝም ብላ አይደለም ….ውስጧ እንደዛ እንዳታደርግ ስለገፋፋት ነው…. ሁሌ ፕሮፌሰሩ የሚያመጧቸውን ሴቶች ወደ ክፍሏ በማስገባት ቁርስ እያበላች ትሸኛቸዋለች ማለት አይደለም፡፡በዛ ላይ እኮ ገና ቁርስም አልሰራችም፡፡ብቻ ይዛት ገባችና ቁጭ እንድትል ነገረቻት ..ያመለከተቻት ቦታ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ይቅርታ ቁርሱ አልተሰራም …ግን በፍጥነት ይደርሳል፡፡››ብላ እስቶቩን  ለኮሰች

‹‹አረ ችግር የለም…››

ወደ ፊሪጅ አመራችና ከፍታ አንድ  ብርጭቆ የማንጎ ጂውስ ሰጠቻት…… አመስግና ተቀበለቻትና መጠጣት ጀመረች ….እሷም  እያወራቻት ቁርሱን መስራት ጀመረች… 

‹‹እኔ ሶፊያ እባላለሁ…አንቺስ

…?››ሶፊያ የሚለውን ስም ለገጣፎ ከተመች ቡኃላ ደጋጋማ መጠቀም ጀምራለች፡፡ምንያቱም ከአዲስ ሰው ጋር ሁሉ ስትተዋወቅ ኬድሮን እባላለው ስትል‹‹ ኬድሮን ማለት ምን ማለት ነው?›› ብለው ሲጠየቋት እንዴት ብላ እንደምታስረዳ ግራ እየገባት ስለተቸገረች ነው፡ኬድሮን ማለት በማርስና በመሬት መካከል የሚገኝ ፕላኔት ነው ፤አባቴ የዛ ፕላኔት ኑዋሪ ነው…ትርጉሙ የዕውቀት ምድር ማለት ነው .እሱን ለማስታወስ ስትል እናቴ በፕላኔቷ ስም ስሜን ኬዴርን ብላ ሰየመችኝ ብላ ብታስረዳ‹‹እንዴ ኬድሮን የሚባል ፐላኔት መቼ ነው የተገኘው? ብለው ወደጎግል ይሮጣሉ… ምንም ሚጎለጎል መረጃ ሲያጡ እሷን እንደ እብድ ይመለከታቷል …ይሄ ነገር ሲደጋገምባት ሰለቻትና ለምን ሁለተኛ ስሜን አልጠቀምም አለችና ‹ሶፊያ› የሚል ስሞን አብዝታ መገልገል ጀመረች ፤እና ሁለቱንም ስሞቾን እንደአስፈላጊነቱ እየቀያየረች መጠቀም ጀመረች፡

‹‹አለም››

‹‹እሺ አለም….. አይዞሽ..ነገሮች ይስተካከላሉ››አለቻት፡፡

‹‹ ፍጥጥ ብላ አየቻት፡፡ምክንያቱም ስለታሪኳ ምንም አልነገረቻትም፡፡ እንዴት ልታውቅ ቻለች፤ ብላ ግራ ተጋብታ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም ››አለቻት፡፡

‹‹አይ አሁን ያለሽበት ችግር ይፈታል ማለቴ ነው››

በፍራቻም በጥርጣሬም እያየቻት ‹‹ነገርኩሽ እንዴ…? ››ጠየቀቻት …

‹‹አይ እንዲሁ ሳይሽ ውስጥሽ የተጨነቀ እንደሆነ ስለገባኝ ነው፡፡በጣም አዝነሻል፡፡››

እንባዋን መገደብ አቅቷት ዘረገፈችው፡፡

‹‹አዎ ከባድ ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡››
‹‹አይዞሽ..እስኪ ንገሪኝ››

‹‹እንደምታስቢው ሸርሙጣ አይደለሁም…ይሄንን ስራ ከጀመርኩ ሳምንትም አይሆነኝም…››

‹‹አይዞሽ ..ተረጋጊና አጫውቺኝ››
‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››

ይቀጥላል
👍15318👏1😁1
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ // ኬድሮን ከዕንቅልፋ የነቃችው 11 ሰዓት አካበቢ ቢሆንም መኝታ ቤቷን ለቃ ወደ በረንዳው  የወጣችው 12 ሰዓት ተኩል ካለፈ በኋላ ነው፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ዘወትር እንደምታደርገው ዮጋ እየሰራች ነበር የቆየችው፡፡እቤቷን ለቃ ስትወጣ ንስሯ ተከትሏት ወጣ፡፡እሷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ማንበቧን ጀመረች ፡፡ ከ12 ሰዓት እስከሁለት…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››

‹‹በባሏ ጠርጥራሽ ነው አይደል …?››ያው እኔ ሳላስበው ነው ቀደም ቀድም የምለው ….ምክንያቱም እሷ ታሪኳን በቃላት አቀናብራ ለሶፊ ከመናገሯ በፊት እሷ ቀድሞ ይታያታል…ንስሯ የበራፍ  በረንዳ ላይ ሶፊ ከለቀቀችበት ወንበር ላይ ተፈናጦ ክፍት በሆነው በራፍ ወደውስጥ አጨንቁሮል ….እርግጥ ልጅቷ ጀርባውና ስለሰጠችው እስከአሁን አላየችውም… እሷ ግን ፊት ለፊት ይታያታል ሁለቱም የልጅቷን ታሪክ ላይ አተኩረዋል …ለዛ ነው ቀደም ቀደም የምትለው….ያ ደግሞ ልጅቷን ግራ እያጋባት ስለሆነ መረጋጋት እንዳለባት ለራሷ እየነገረች ነው፡፡

‹‹አዎ ትክክል ነሽ…ብታይ ጭራቅ ሴት ነች፡፡ቅናቷ አያድረስ ነው፡፡በቃ ሰይጣናዊ የቅናት ዛር ነው የሰፈረባት፡፡ኑሮዬን ሁሉ ሲኦል ነው ያደረገችው፡፡››

‹‹ሙሉውን ሶስት አመት እዛው ነው የኖርሺው…?››

‹‹አዎ ሶስት አመት ሙሉ አንድ ቤት ነበርኩ…እርግጥ መጀመሪያውን  አንድ አመት አካባቢ ጥሩ ሴት ነበረች…ሁሉ ነገር መልካም ነበር… ደሞዜን በስርአቱ ትከፍለኛለች..እርግጥ እስከመጨረሻውም ደሞዜን ከልክላኝ ወይም አቋርጣብኝ አታውቅም…ለቤተሰቦቼ የምልከው ተጨማሪ ብር ሁሉ ትሰጠኝ ነበር፡፡ከዛ ድንገት ፀባይዋ ተቀያየረ….ለዓይኖቾ ተጠየፈችኝ….

‹‹ለምን ታዲያ አትለቂም ነበር..?ማለት ሌላ ማዳም ጋር ቀይረሽ መስራት ትቺይ ነበር…››

‹‹ያው እንደነገርኩሽ በህገወጥ መንገድ ነው የሄድኩት.. እንደልቤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሼ ስራ ማማረጥ አልችልም..ሌላው …››ብላ ዝም አለች ..ላውራ ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋ ሙግት የገጠመች መሆኑን አውቃባታለች…

‹‹ሌላው ምን…?››

‹‹ሰውዬው በጣም መልካም ሰው ነው…ልጆቹንም በጣም ነው የምወዳቸው….ለእነሱ ስል ነው ታግሼያት የኖርኩት››

ፈገግ አለች‹‹መጨረሻ ታዲያ እንዴት ሆነ?››

‹‹ቅናቷ ከቁጥጥር በላይ ሆነብኛ››
‹‹ያው  ምታደርጉትን እኮ ስለምታይ ነው››

‹‹ማለት…? እንዴት ታውቃለች……?›.
‹‹እርግጥ የእሷን አለመኖር  እየጠበቃችሁ ነው ፍቅራችሁን የምትወጡት… ግን እሷ በደንብ ታውቃለች ..እንደውም ጥሩ ሰው ነች››አለቻት
ልጅቷ ግራ ገባት ..ከድንጋጤዋ የተነሳም ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ሁሉ ለቃ  መውጣት ፈልጋለች..…

‹‹አይዞሽ አትደንግጪ …እሷን ለማስቀየም ወይም ለመበደል ብለሽ ሳይሆን ፍቅር ላይ ስለወደቅሽ ነው እንደዛ ያደረግሽው…ያ ደግሞ ከሰውዬው ቀረቤታ እና መልካምነት የተነሳ ነው..በዛ ላይ በጣም ቆንጆ እና ዘናጭ ነው…እንደምትወጂው አውቃለሁ  ፡፡እሱም በደንብ ነው የሚያፈቅርሽ፡፡በጣም የከፋው ነገር ግን ቅናተኛ ላልሻት ሴት ደግሞ ሰውዬው ሁለመናዋ ነው…እናንተ እርስ በርስ ከምትዋደዱት በላይ እሷ እሱን ትወደዋለች፡፡እና ሴትዬዋ በተፈጥሮዋ መጥፎ ሆና አንቺን በማሰቃየት የምትረካ ስለሆነች ሳይሆን ባሏን ላለማጣት የምታደረግው መፋለም እና ጥረት  ነበር፡፡እንደውም አንቺን ባሰቃየች ቁጥር እሱንም የምታስከፋው እና የምታጣው  መስሎ ስለሚሰማት በጣም ትጨናነቅ እና ትጠነቀቅ  ነበር…አንቺን ጎድታኛለች ብለሽ ከምታወሪው በላይ እሷ እራሷን አሰቃይታለች ….የጨጋራ በሽተኛ ሆናለች….››

‹‹ቆይ አንቺ ይሄን ሁሉ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…?››

እሱን ልታስረዳት አልቻለችም ‹‹..ትኩረት ከሰጠው  አንዳንድ ነገሮችን ማየት እችላለሁ፡፡

በውስጥሽ ይህቺ ልጅ ጠንቆይ ነች እንዴ…? እያልሽ እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ..እንደዛ በይው ችግር  የለውም››

‹‹አይ ማለቴ ….ልዋሽሽ አልችልም እንዳልሽው ነበር እያሰብኩ ያለሁት…ይገርማል ያልሻቸውን  ብዙውን ነገሮች ትክክል ነሽ››

‹‹ምንድነው ትክክል ያልሆንኩት…?››

‹‹እሷ ስለእኛ ግንኙነት በእርግጠኝነት ማወቋን እና..ከእኔ በላይ እሱን ማፍቀሯን››

‹‹ሁለታችሁ ፍቅር የምትሰሩት አንቺ ክፍል አይደል…?››

‹‹አዎ ግን እሷ ስራ በምትሆንበት እና ከቤት እርቃ በሄደችበት ጌዜ ጠብቀንና ተጠንቅቀን ነው››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ …በሁለታችሁ ያልተለመደ መቀራረብ ጥርጣሬ ካደረባት በኃላ ግን ክፍልሽ ውስጥ በስውር ካሜራ ስላስቀመጠች የተቀዳውን በፈለገችው ጌዜ ከፍታ ታየው ነበር፡፡››

‹‹ያማ አይሆንም..…?እንዴት ተደርጎ…?››

‹‹እንደዛ ነበር የሆነው…ከእኔ በላይ አታፈቅረውም ያልሺው ደግሞ ያው በራስሽ ሚዛን ስለምትመዝኚው ነው እንደዛ የምታስቢው እንጂ እንቺ በእሷ ቦታ ብትሆኚ እርግጠኛ ነኝ ወይ ጥለሺው ትሄጂያለሽ ..ወይ ሌላ እርምጃ ትወስጂያለሽ ….እሷ  ግን ካንቺ ጋር ብትጨቃጨቅም ….አንቺን ላይ ችግር ለመፍጠር ብትሞክርም አንድ ቀን እንኳን እሱ ላይ ተነጫንጫበት ወይንም  ጉዳዩን አንስታበትና ወቅሳው አታውቅም..ለእሷ እሱ ብቸኛው ፍቅሯ ነው..ለአንቺ ግን የመጀመሪያ ምርጫሽ አይደለም..ስለምታፈቅሪው ብቻ ሳይሆን ማዳሞ ከምታውቀው ሌላ ተጨማሪ ብር ስለሚሰጥሽ ነው  ..ፍቅርሽ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ምንጭሽም ስለሆነ ነው…ለእሷ ግን እንደዛ አልነበረም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው….የእውነት ካሜራው ኖሮ የምናደርገውን ሁሉ እያየች በትዕግስት አልፋን ከሆነ የሚገርም ነው…እኔ ብሆን ልገድለው ሁሉ እችላለሁ…አረ ሁለቱንም ነው በተቃቀፉበት የማጠፋቸው››

‹‹አየሽ..ሴትየዋ የምታስቢያትን ያህል ክፉ አልነበረችም….ከዚህም በላይ ልታሰቃይሽ ምክንያቱን ሰጥተሻት ነበር…ግን እሷ በተቻላት መጠን እራሷን ለመቆጣጠር ሞክራለች፡፡››

‹‹አዎ አንቺ ይገርማል… አሁን ሳስበው በህይወት ስላለውም እድለኛ ነኝ….››

‹‹እና እዚህ ስትመጪ ደግሞ ሌላ ታሪክ አጋጠመሽ››

‹‹አዎ በጣም የሚያንገበግበው እና ስብርብር ያደረገኝ ደግሞ ይሄኛው ነው›› አለች …..አሁን በፍራቻ እና በአድናቆት ነበር የምትመልስልኝ
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹መቼስ ታውቂዋለሽ…አንድ ቀን ወደ ሀገሬ ስመለስ ቤት ይኖረኛል….አገባዋለሁ..ልጅ ወልድለታለሁ ብዬ ደሞዜንም .ሰውዬው ይሰጠኝ የነበረውንም ብር እልክለት ነበር…ቤት እየሰራው ነው ይለኛል….የቤት ዕቃ እያሞለው ነው ይለኛል..ምን አለፋሽ ከሶስት መቶ ሺ ብር በላይ  ነው የላኩለት …..ግን ስደርስ ሌላ ሴት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዶ ጠበቀኝ…..ከዛ ምን ልንገርሽ ሁሉ ነገር አስጠላኝ …ክፍለሀገር ወደ ቤተሰቦቼም መሄድ አልፈለግኩም እንዴት ብዬ ምን ይዤ ሄዳለሁ…?……..  
‹‹አዎ ለእሱ ያልሽውን ሶስት መቶ ሺብር ስትልኪለት ለቤተሰቦችሽ የላክሺው ብር ሲደመር 50 ሺ ብርም አይሞላም..››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..የሚያንገበግበኝ እና ሞራሌን እንክትክት ያደረገው እና ዛሬ እዚህ ያስገኘኝ ይሄው  ነው….

አይዞሽ እናስተካክለዋለን ..በእኔ ተማመኚ..አልኳትና የደረሰውን ቁርስ አቅርቤ መብላት ጀመርን›…

ይቀጥላል
👍12622😁5👎3👏2😱2🔥1😢1
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ›› ‹‹በባሏ ጠርጥራሽ ነው አይደል …?››ያው እኔ ሳላስበው ነው ቀደም ቀድም የምለው…»
🔴👁በ'ነሱ ቤት👁🔴
👁🔴ክፍል አንድ🔴👁
🌻🔵🌻🔵🌻🔵🌻
አንዲት አነስተኛ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ ሦስት አብሮ አደግ ጓደኛሞች  የጦፈ ወሬ ይዘዋል ። ሦስቱም በአካባቢው ላይ አላቸው ከተባሉ አብታም ቤተሰቦች ነው የተገኙት ። ከችግር ከአሳብ ከጭንቀት ነፃ ሆነው ነው ያደጉት ። በእነሱ ቤት  አሳቢው ነገሮችን ማስተካከል ያለበት ወላጅ ብቻ ነው ።በቃ እነሱ እንደ እንቁላል ተጠንቅቀው ያሳደጓቸው የወላጆቻቸው ምርጦች ናቸው ። እነሱም የወላጆቻቸው ትምክህት ተጋብቶባቸው ነው መሰል ። በኑሮ እና እነሱ ባወጡት መስፈርት ደረጃቸው ካልመሰላቸው ሰው ጋር መገናኘት አይፈልጉም ።  ሰመረ  የጠይም ቆንጆ ቁመናው ያማረ ፈገግ ሲል ጥርሶቹ እንደፍሎረሰንት አንቦል ወገግ የሚሉ ቀኑን ሙሉ አብሬው በዋልኩ የሚያስብል የሃያ አመት ወጣት ነው  ። የስህል ችሎታም ስላለው  ትምህርቱንም የሚማረው በዚያው ዙሪያ ነው  ምንም እንኳ ቤተሰቦቹ ቢዝነስ እንዲያጠና ቢፈልጉም ።
ሌላው  ጌታ ሁን ነው  _ጌታሁን ከ ሰመረ አጠር ያለ እና ድንቡሽቡሽ ያለ ወጣት ነው  ትንሽ ከተናደደ ቀይ ፊቱ ቲማቲም ነው የሚመስለው  ኩርፊያውን መደበቅ አይችልም ። ትምህርቱን መደበኛውን እንደጨረሰ ነው ያቆመው ። 'ያው ተምሬ ገንዘብ ለማግኘት ነው አይደል በቃ እኔ እንደው ለዚ መልፋት አይጠበቅብኝም  ይልቅ እናቴን ድርጅቷ ውስጥ ያለባትን ጫና ላግዛት ይገባል  ለእውቀቱ ከሆነ መፀሐፍ አነባለው ' ብሎ ለጠየቀው ሁሉ መልስ ሰጥቶ አፍ አዘግቷል ።
ሦስተኛው  እንየው ነው  እንየው  ከሰመረ ጋር በቁመት እኩል  ነው  የቀይ ዳማ መልክ ያለው ሲሆን  መልከመልካም የሚባል አይነት ነው  በጣም ችኩል እና ተለዋዋጭ ስሜት አለው ። ለዚህም ይመስላል መደበኛ ትምህርቱን ከጨረሰ በዋላ የተለያየ ትምህርት እየጀመረ የሚያቆመው ። በቅርቡ ደሞ  ሞዴሊንግ እየሰለጠነ ነው  ። የመጀመሪያው ቀን ለሰመረ ሲነግረው ። የሚያማምሩ ጥርሶቹን መክደን አልቻለም እረጅም ሳቅ ነበር የሳቀው  ።
እንግዲ እነዚ ወጣቶች  የከተማችን ቱጃር ልጆች ናቸው ። የፈለጉበት ሄደው  በነፃነት መዝናናት በነፃነት የፈፈለጉትን ማድረግ የለመዱ ። ጮክብለው የሚያወሩ ጮክ ብለው የሚስቁ የከተማው ገዢ የሚመስሉ ። የፈለጓትን ሴት ነይ ሂጂ ማለት የለመዱ ። ሴቶቹላይ ያደረጉትን የሚይደባበቁ ። በምስኪን ሴቶች የሚሳለቁ  የሚያደርጉት ነገር ሌላው ላይ ምን እንደሚያስከትል እንኳ ለማሰብ ጊዜ የሌላቸው ። አንዳንዴ ሰመረ ነገሮችን ለማስተዋል ቢሞክር እንኳ ዳግም ተጎትቶ በነሱ ስር መከተቱ አይቀርም 👁

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍724👏3😢2🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡

‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡››

‹‹ፎቶው አለሽ?›› 

‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ‹‹ተከተይኝ ››አለቻት እና  ወደበረንዳው ወጡ…ንስሯ ተረጋግቶ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ስታየው እንደመፍራትም ግራ እንደመጋባትም አለችና፡፡

‹‹ምን አይነት አሞራ ነው..አይፈራም እንዴ? ››

‹‹የእኔ ነው››

‹‹አሞራው?››

‹‹አዎ…ግን አሞራ ሳይሆን  ንስር ነው…የእኔ ንሰር ፡፡››

‹‹ምን ያደርግልሻል?፡፡››

‹‹እሱማ ለእኔ ብዙ ነገሬ ነው… የፈለኩትን ነገር ያደርግልኛል..እኔ እንደውም የሚገርመኝ እኔ ለእሱ ምን አደርግለታለሁ ሚለውን ነው››

‹‹ይቅርታ ግን ያስፈራል…. .በተለይ አይኖቹ እና መንቁሩ…››እሷን ችላ አለቻትና ሞባይሏ ላይ ያለውን የልጅቷን ፍቅረኛ ፎቶ ለንስሯ እያሳየች ‹‹….እንርዳት መሰለኝ…እወነቱን ማወቅ መብት አላት››ስትለው ክንፎቹን አርገፈገፈና   መቀመጫውን ለቆ በአየር ላይ ተንሳፈፈ…እሷ  በርግጋ ወደኃላዋ አፈገፈገች….ወደላይ ተምዘግዝጎ አየሩን እየሰነጠቀ ከፍታውን ለአይን መታየት እሰከማይችል ድረስ ርቆ ተሰወረ፡

‹‹ቁጭ በይ› አለቻትና በረንዳው ላይ ካለው ወንበር አንዱን እያሳየቻት እሷ ንስሯ በለቀቀላት ወንበር ላይ እየተቀመጠች፡፡

‹‹ሄደብሽ እኮ …እንዲህ እርቆ ሄዶ አሁን አውቆ ተመልሶ ይመጣል?፡፡››

‹‹አዎ የእኔ እወቀት ዘጠና ፐርሰንቱ ከእሱ የማገኘው ነው…ንስሮች በተፈጥሮቸው በጣም ልዩ የሆኑ የአእዋፋት ዝርያዎች ናቸው፡፡እይታቸውም ጥልቅ አስተሳሰባቸውም ስል እና የተሞረደ  ነው፡፡ከዛም በላይ ግን የእኔ ንስር የተለየ ነው፡፡እንዴት የሚለውን ነገር ላብራራልሽ አልችልም..ግን አሁን የሚያደርገውን ታያለሽ ..ከዛ እራስሽ ትፈርጂያለሽ››

‹‹እንዴት?››

‹‹አሁን ፍቅረኛሽን ፎቶ እያሳየሁት ሳወራው አላየሽም?››

‹‹አይቻለው.ግን እናቴም ሲጨንቃት እና በሆዷ ነገር ሲገባ ከምታልባት ላም  ጋር ታወራ ነበር…እንደውም ለእሱ ስታወሪ እናቴ ነች ትዝ ያለችኝ፡፡››

‹‹አይ ይሄ ይለያል..አሁን ያንችን ችግር ማለት ስለፍቅረኛሽ ትክክለኛ ነገር እንዲያጣራልኝ ነው የላኩት››

‹‹እንዲት አድርጎ››

‹‹በቃ የተለየ ችሎታ አለው… ማንኛውም ነገር ካተኮረበት የውስጡን ሀሳብ እና ጠቅላላ ታሪኩን ማንበብ ይችላል…እኔ ደግሞ ከሱ አዕምሮ ማንበብ እችላለሁ..ወይም እንዳውቀው አዕምሮውን ይከፍትልኛል..ቅድም ያንቺን ታሪክ ላውቅ የቻልኩት ከእሱ ነው፡፡››

‹‹እኔ አላምንም ..ንስር ይሄን ሁሉ…. እንዴት  ተደርጎ?››

‹‹አየሽ እንዳልኩሽ የእኔ ንስር ልዩ ነው..ከእኔ  ጋር ያለውም ትስስር ከተፈጥሮ ክስተቶች እንደ አንድ ነው..ያም ሆኖ ግን እንዲሁ ንስር እና የሰው ልጅ ከጥንትም ጀመሮ የመንፈስ ትስስር እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡፡ሌላውን ተይና  በሀገራችን ጥንታዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ንስር የትንሳኤ ምልክት ነበር… በምጥቀት ማሰብ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር መንፈስ ተምሳሌ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡በግብጽ ደግሞ መቃብራቸውን ጋንኤል እንዳይደፍረው የንስር ምስል ከመቃብሩ በራፍ ላይ ያስቀምጡ ነበር…ያ የንስር ምስል የጋንኤሉ መንፈስ አልፎት ወደውስጥ ሊጋባ ስለማይችል እሬሳቸው ከጥቃት የተጠበቀ ይሆናል ብለው ያምናሉ..፡፡
የጲላጦስ ሀገር የሆነችው ግሪክ ደግሞ ከአመልክቶቾ ውስጥ አንድ የሆነው የአማልዕክቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው ዜዎስ በንስር ይመሰል እንደነበረ ይነገራል፡፡በጥንት ጊዜ አሜሪካኖች  ደግሞ እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው ያለቸውን ጥልቅ ፍቅር ሚገልጽት የንስር ላባ በመስጠት ነው፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ሲራክም  ሶስት እራስ እና አስራ ሁለት ክንፎች ሳላለው ንስር በህልሙ ራዕይ አይቶ ነበር….የራዕይው ፍቺ በየተራ ስለሚነግሱ ነገስታት ሲገለጽለት ነበር…ንስር የኃይልን እና የስልጣን ምልክት ነው፡፡…››ስብከት የመሰለ ንግግሯዋን ተናግራ ሳትጨርስ….ዶክተሩ በራፋቸውን ከፍተው ወጡና ወደእነሱ መጡ

…‹‹.ሶፊ ደህና ነሽ?››

‹‹እንዴት አደሩ ዶክተር?››
‹‹አለሁ….ዛሬ እንግዳ ከየት አገኘሽ ?››አለት እንግዳዋ ላይ በማተኮር፡፡

‹‹አያውቋትም?››

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት ግን ያየኋት ይመስለኛል››

‹‹አዎ ከባሌ የመጣች የአክስቴ ልጅ ነች…ከዚህ በፊትም መጥታ ስለነበረ.. ተገናኝታችኋል››
‹‹ለዛ ነዋ ፊቷ አዲስ ያልሆነብኝ….በሉ ተጫወቱ አንዲት ቀጠሮ አላለችብኝ ..ከሰዓት እንገናኛለን ..›ብለው ተሰናብተዋቸው ወደመኪናቸው ማቆሚያ ጥለዋቸው ሄዱ
ሶፊያ ሳቋ  አፍኗት  ስለነበር እንደራቁላት ለቀቀችው

…‹‹ሳያውቁኝ ቀርተው ነው ወይስ አውቀው ነው?››

‹‹አይ ተምታቶባቸዋል…ያው ማታ መጠጥም ስለሚወሳስዱ ነው ቅር አይበልሽ››

‹‹አረ ምን ቅር ይለኛል ነገራቸው ገርሞኝ እንጂ››ብትልም ቅር እንዳላት ግን በግልፅ ከንግግሯ ቃና በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እዚህ ቤት ከጥዋት ጀምሮ የሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ይገርማል አይደል?››

‹‹ምን መገረም ብቻ ከአዕምሮም በላይ ነው….እኔ እንዲህ….››ንግግሯን ሳትጨርስ  ንስሩ እየተምዘገዘገ መጣና ከእነሱ ፊት ለፊት በአምስት ሜትር ርቀት ያህል በሚገኝ የጽድ ዛፍ ላይ ሲያርፍ ስለተመለከተች  አቆረጠችና …ምን እንደሚከሰት ለማወቅ መጎጎቷን በሚያስታውቅባት መንፈስ‹‹መጣ ››አለቻት፡፡

‹‹ትንሽ ታገሺኝ ››አለቻትና አዕምሮዋን ሰብሰባ  ትኩረቷን በሙሉ  ከንስሯ ጋር በማቋራኘት እምሮውን  ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መምጣትሽን ፍቅረኛሽ አያውቅም አይደል?፡፡››

‹‹አዎ..አንዴ በእሱ ክህደትና ዘረፋ የሞትኩት አንሶኝ ጭራሽ መምጣቴን ነግሬው ስሩ ቆሜ ሁለተኛ ሞት ልሙት እንዴ? አላደርገውም ….ፍቅሬን መልስልኝ ብዬ ልማፀነው..?ወይስ ብሬን መልስልኝ ልበለው?››

በንስሯ አእምሮ አሻግራ እያየች ያለችው ታሪክ አሰገርሟት፡፡‹‹ቆይ ቆይ…በዚህ ሰዓት ፍቅረኛሽ ምን እየሰራ እንደሆነ ታውቂያለሽ…?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን እየሰራ ነው..?.ከሚስቱ እየተዳራ ወይም ልጁን እያጫወተ ይሆናል››ብስጭት እና ቅናት በተቀላቀለበት ድምፀት መለሰችላት፡፡

‹‹አይደለም …ትናንትና ወደ  ጊኒጪ ሄዶ እናትሽን  አምጥቶ ግሩም ጠቅላላ  ሆስፒታል እያሳከማቸው ነው…››

‹‹የእኔን እናት .. ?ምን ሆና ነው…?››በድንጋጤና በመገረም .እናም ደግሞ ባለማመን ጠየቀች፡፡

‹‹አትደንግጪ ያው የተለመደው በሽታዋ ነው….ድሮም ከፍተኛ የጨጎራ ቁስለት እንዳለባት ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹ግን እኔን እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ያሰጠጉታል …እናቴ ምንም የሚያስታምማት እና ሚያሳክማት ሰው ብታጣ እንዴት ልጇን ከከዳ ሰው ጋር ትተባበረለች…?እኔ ይሄን ማመን አልችልም …፡፡ሌላው ይቅር እናቴ እንኳን ለስላሳ እና የዋህ ስለሆነች  ይቅር ልትለው ትችላለች… እህቴ ግን እርግጠኛ ነኝ ይቅር አትለውም ፤ እርግጥ ሁሉም ለእሱ የላኩለትን ብር አያውቁም …ግን በጣም እንደማፈቅረውና ላገባውም  እንደምፈልግ ከዛም አልፎ ቃል እንደተግባባን ግን በደንብ ያውቃሉ፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ…በጣም ነው የሚያፈቅርሽ፡፡››
👍986👎2🥰2👏2🔥1😢1
​​‹‹ቢያፈቅረኝ ነዋ እንዲህ የከዳኝ..?ቢወደኝ ነው እንዲህ እራሴን ለማጥፋት እስክመኝ ደረስ ሙልጬን ያስቀረኝ?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ? ››

ይቀጥላል
😱32👍199
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ //// ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡ ‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡›› ‹‹ፎቶው አለሽ?››  ‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
""

‹‹ምን መሰለሽ ፍቅር በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከብረሀናማ ቀለማቶች የተሸመነ ጥልቁ ስሜት  ነው፡፡ፍቅር ወደ ወደድነው ሰው ልብ ውስጥ ሰተት ብለን የምንገባበትን በር  የምንከፍትበት ማስተር ኪይ ነው፡፡ፍቅር ስለእራሳችን በተለየ መልኩ እንድናስብ የሚያስገድደን የተቀደሰ የዕይታ ብሌናችን ነው፡፡በፍቅር የተነደፈ ደሀ  በውስጡ የሚሰማው አለም ሁሉ የእሱ ንብረት እንደሆነችና አውቆና ንቆ እንደተዋት ነው …የተናቀ እና መጠጊያ አልባው ሰው በፍቅር እቅፍ ውስጥ ሲወድቅ የንግስና ዙፋኑ የእሱ እንደሆነ እና አለም ጠቅላላ ወደእሱ አጎንብሳ እየሰገደችለት እንደሆነ ነው የሚሰማው፡፡

የስልጣን ማማ ላይ ተቆናጦ ልቡ በትዕቢት ያበጠ በፍቅር አዳልጦት ሲዘረጥጥ ..እንዴ ለካ እኔም ሰው ነኝ…?ለካ ማንበርከክ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለመንበርከክም እገደዳለሁ? ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል፡፡ ….ሰውን ሞት እና መቃብር ብቻ ሳይሆን ፍቅርም ወደ አንድ ተመሳሳይ ስሜት በመጎተት ያቀራርበዋል፡፡…..ግን አሳዛኙ ነገር ይሄ ቅዱሱ ፍቅር ብዙ ጊዜ ድምጥማጡ የሚጠፋው በማይረባ ትርኪ ሚርኪ  እውነትነታቸው ባልተረጋገጡ ጉዳዬች ነው…..ባለመደማመጥ እና ባልተጣራ ወሬ የተነሳ  ነው፡፡

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ፍቅረኛሽ እንዳገባ ማን ነው የነገረሽ……..? ››

‹‹ከእስር ቤት ወጥቼ ተጠርዥ ልመጣ ስል አንድ እዛ  የምትኖር ጓደኛዬ ከአሰሪዎቼ ቤት የነበረኝን ሻንጣዬን አውጥታ እሷ ጋር አድርጋልኝ ስለነበር…ስትሸኝ አቀብላኝ ነበር ፡፡ይቺ ጓደኛዬ ..በጣም ጥሩ ሰው ነች ለኪስ የሚሆነኝን ትንሽ ብር የሰጠችኝም እሷ ነበረች.. ወደ ኢትዬጵያ   የገባሁትም በለሊት ስለነበረ ሆቴል ነበር የያዝኩት እና በሰላም መግባቴን ለመናገር ለጓደኛዬ ስልክ ደወልኩላት፡፡ ፖስታ ከኢትዬጵያ መቶልኝ እንደነበረ እና ሻንጣ ኪስ ውስጥ ከታልኝ ሳትነገርኝ እንደረሳችው ነገረችኝ፤ስፈልገው አገኘሁት፡፡

‹‹ስልክ ባልደውልላት እና እሷም አስታውሳ ባትነግረኝ ኖሮ አላየውም ነበር…ቀጥታ ፍቅረኛዬ ቤት ሄጄ  ስርፕራይዝ ላደርገው ነበር እቅዴ..እሱ ጋር አንድ ሶስት ቀን አሳልፌ እና አገግሜ  ወደጊንጪ  ቤተሰቦቼ ጋር ልሄድ ነበር  ያሰብኩት..››
ፖስታውን ስከፍተው ግን በቃ የሲኦልን በር እንደመክፍት ቁጠሪው፣…ውስጡ ሲኦላዊ የክህደት እሳት ነበር ያለው..አገባዋለሁ ብዬ ሳልመው የነበረው ሰውዬ የአንድ አመት  ህጻን አቅፎ ሲያባብል የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ከመከራዬ አገግምበታላሁ  ከስባራቴ እጠገንበታላሁ ያልኩት ሰው ጭራሽ መከራዬን የሚጨምር.ስብራቴን የሚያባብስ ሆኖ ጠበቀኝ…..ከፎቶ ጀርባ ላይ…..  ናሆም ፍቃዱ እንኳንም ለአንደኛ አመት ልደት አደረሰህ ይላል፡፡ምድር ተሰንጥቃ ብትውጠኝ እወድ ነበር….ምን አይነት ክህደት ነው…?አላስቻለኝም እወነቱን ለማወቅ ጭለማን ተገን አድርጌ ሰፈሩ ሄድኩ….አድፍጬ በአጥር ቀዳዳ አጨንቁሬ ግቢውን ለሰዓታት ቃኘሁ…እውነት ነበረ ፤ልጅ አቅፎ ግቢ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያባብል እና ሲያጫውት አየሁት…በወለብታ ነው እንጂ ሚስቱንም በመጠኑ አይቼያታለሁ››

‹‹ማንነቷን ግን አላየሽም? ››

‹‹ማንነቷ  ምን ይሰራልኛል…ሮማንንም አገባ ቦንቱን ለእኔ ምንስ ሲጨምርልኝ ምንስ ሲቀንስልኝ?››

‹‹አይ ማንነቷን እስክታውቂ  በደንብ ብታጣሪ..ወይንም እሱን በአካል አግኝተሸ ለምን እንደዛ አደረግክ? ብለሽ ብትጠይቂው ጥሩ ነበረ ….ሁለት ሳምንት ሙሉ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነሽ አትሰቃይም ነበር..በማትፈልጊውን የህይወት መስመር አትጀምሪም ነበር.ብዙ ጊዜ አውነትን ለማደን ብለን እንደ ጀግና መንግድ እንጀምርና ገና የጫካው መግቢያ ጋር ስንደርስ ብርክ ይዞን  እንመለሳለን፤ ቀስታችንን እዛው ጨርሰን ወደኃላ እንመለሳለን.ኩልል እና ጥርት ያለውን እውነት ለማግኘት ግን የጫካው እንብርት ድረስ በእሾኩ እየተወጉ እና በፍርሀት እየራዱ መጓዝን ይጠይቃል  ››

‹‹አልገባኝም››አለቻት ኮስተር ብላ
‹‹ንብረትሽ..ማለት አንቺ ለፍቅረኛሽ የላክሽው ብር  በእጥፍ ጨምሮ አንቺኑ እየጠበቀሽ ነው››

‹‹እንዴት?››

‹‹በላክሽው 300 ሺ ብር ላይ የራሱን ብር ጨምሮ ሚኒባስ ገዝቶበታል››

‹‹እኮ እሱንማ ግቢው ውስጥ ቆማ አይቼያለሁ፡ግን አሁን ንብረትሽ ነው ብሎ የሚመልስልኝ ይመስልሻል…?ልመልስልሽስ ቢል ሚስቱ እሺ ትለዋለች..?እኔስ አሱ ፊት ቆሜ ብሬን ስጠኝ አትስጠየኝ ብዬ የመከራከሩ ጉልበት ይኖረኛል?፡፡›

‹‹ሚኒባሶ በቀን የምትሰራው ብር ያንቺ ድርሻ በስምሽ በተከፈተ የባንክ ደብተር እያስቀመጠልሽ ነው…በጥሬ ብር ደረጃ መቶ ሳላሳ ሺብር ባንክ ተቀምጦልሻል…..ሚኒባሶም ባንቺ ስም ነች፡፡››

‹‹እንዴት ተደርጎ?››

‹‹በቃ በጣም የሚያፈቅርሽ እና ላንቺም ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦችሽም የሚኖር  እና የሚጨነቅ መልካም ልጅ ነው››

‹‹አይ ያደረገው ነገር እወነት እንዳልሺው ከሆነ ዘራፊ አያሰኘው ይሆናል.. ነገር ግን  ፍቅሬን ትቶ ሌላ አግብቶ ሌላ ልጅ መውለዱ ግን  ከከዳተኛነት ውጭ ሌላ ስያሜ ሊሰጠው አይችልም ፡፡

‹‹አሁን ቀጥ ብለሽ ዛሬውኑ እቤቱ ሂጂ››

‹‹ምን ልፈጥር?››

‹‹ሂጂ አልኩሽ ሂጂ.››

‹‹ሄጄስ?››

‹‹በቃ ግቢውን አንኳኩተሸ ግቢ..ከዛ የሚሆነው ነገር ይሆናል…ይሄንን ካላደረግሽ ግን ህይወትሽን ሙሉ ምትፀፀችበትን ስህተት ነው የምትሰሪው››በብዙ ምክር እና ከማስፈራሪያ  በኃላ አሳምናት  ሸኘቻት….

….ከዚህ በላይ ልትነግራት አልፈለገችም..እራሷ በሂደቱ ውስጥ እንድታጣጥመው ነው የፈለገችው..ፍቅረኛዋ አሁንም አልወለደም ፤አላገባምም…እሱ በምንም አይነት እሷን አልከዳትም…ለአንድ ቀን እንኳን ወስልቶባት አያውቅም..እንደውም ከዳተኛ መባል ካለበት እራሷ ነች….፡፡
እርግጥ እንዳለችው እቤቱ ውስጥ ሴት አለች…አዎ እቤት ውስጥ ልጅም አለ..የሚወደድ ናሆም የሚባል የአንድ አመት ልጅ…ሴትዬዋ  ግን የገዛ እህቷ ነች….ታናሽ እህቷ ..ልጅም የእህቷ ልጅ፡፡ጊንጪ እቤተሰቦቾ ቤት ተቀምጣ የአስራሁለተኛ ክፍል ትምህርቷን በመማር ላይ እያለች አረገዘች….እሱ ሚስጥሩን ሰማ ፤ልጅቷም ህይወቷን እንዳታበላሽ ቤተሰቦቾም በኖሩበት ሀገር እንዳይሸማቀቁ ሁሉንም አሳመናቸውና ዞር አድርጎ አዲስአበባ ወደራሱ ቤት ወሰዳት….ለፍቅሩ ሲል…የእሷ ቤተሰቦች እንዳይሳቀቁ በማሰብ….. ..እሱ ጋር ተሸሽጋ ወለደች..አሁን ትምህርቷንም እየተማረች ነው፡፡››

ታዲያ ፎቶውን ማነው  የላከላት..?ማን ነው እንደዛ እንድታስብ የፈለገው›…?መልሱ የገዛ እህቷ ነች፡፡በእዛች ጭንቅ ጊዜዋ ያፈቀረችውና  ያረገዘችለት ሰው አፍንጫሽን ላሺ  ባላት ወቅት የእህቷ ፍቅረኛ ግን እንደዛ አይዞሽ ማለቱ፤ ሽሽጎ ተንከባክቦ ጭለማውን ጊዜ እንድታልፍ ማድረጉን ..እሷን መንከባከቡ ልጇን መውደዱ ሌላ ነገር እንድታስብ አደረጋት.. የሰው ሀገር በስደት ላይ ባለችው ታላቅ እህቷ እንድትቀና ..እንድታፈቅረው…የራሴ በሆነ ብላ እንድትመኝ …
👍9712👏2👎1
ስለዚህ እህቷ ተስፋ እንድትቆርጥ ተመልሳ እንዳትመጣና እሱም ጥበቃ ሲሰለቸው ስሩ ያለችውን እሷን እንዲያይ እና የራሱ እንዲያዳረጋት ተመኘች…የመጣላት ዘዴ  ፎቶውን  እንዲደርሳት ማድረግ ስለነበር ላከችላት..እንጂማ እሱ አሁንም ህልሙ እሷ ነች..አሁንም ረሀቡ እሷ ነች….እሷ እሱን ከምትፈልገው በብዙ እጥፍ በበለጠ ሁኔታ እሱ ያፈልጋታል፡፡እሷ ከምታፈቅረው በእጥፍ እሱ ያፈቅራታል….አሁን ሄዳ ስታገኘውና ስለሁኔታው በግልጽ ስትረዳ  ይቅርታ ትጠይቀውና እቅፉ ውስጥ ትገባለች ..ነገሮችም
ይስተካከሉላታል….የተሰባበረውም ልቧ ይጠገናል…..ግን አንድ ፈታና አለባት ፤ እህቷን ከህይወታቸው መሀል ዞር ማድረግ ቀላል ስራ አይሆንላትም.. ቢሆንም  ግን ትወጣዋለች፡፡አዎ ኬድሮን በንስሯ አማካይነት የተረዳችው ይሄንን ነው።

ይቀጥላል
👍85😢117👏3🔥2
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ "" ‹‹ምን መሰለሽ ፍቅር በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከብረሀናማ ቀለማቶች የተሸመነ ጥልቁ ስሜት  ነው፡፡ፍቅር ወደ ወደድነው ሰው ልብ ውስጥ ሰተት ብለን የምንገባበትን በር  የምንከፍትበት ማስተር ኪይ ነው፡፡ፍቅር ስለእራሳችን በተለየ መልኩ እንድናስብ የሚያስገድደን የተቀደሰ የዕይታ ብሌናችን ነው፡፡በፍቅር የተነደፈ ደሀ  በውስጡ የሚሰማው…»
🔵👁በ'ነሱ ቤት👁🔵
👁🔵ክፍል ሁለት🔵👁
💫💫💫💫💫💫💫💫
የሦስቱን ጓደኛሞች ወሬ በመገረም የሚሰማው አስተናጋጅ ጥጉን ይዞ መቅረቱን ያስተዋለው የስራ ባልደረባው " ሰሚር ኧረ ነቃ በል እዛጋር ከስተመር ገብቷል "ብሎት ሲያልፍ ነው ። ሰሚር በአስተናጋጅነት ብዙ ቦታ ቢረግጥም የተለያዩ ከስተመሮችን ቢያይም ቢያጋጥሙትም ። እንደነ ሰመረ ያለ ወጣት ግን ገጥሞት አያውቅም ። ሲያወሩ ሰው አለ የለም የማይሉ ወሬያቸው፣ ማህበረሰቡ ከለመደው ስርሃት ውጪ መሆኑ  ፣አለባበሳቸው  የጫማቸው በእጃቸው የሚያሽከረክሯት የመኪና ቁልፋቸው በአጠቃላይ ፅድት ካለ ውጫዊ ውበታቸው  ያለገደብ የሚወጣ ቃላቸው ልክ አለመሆን ተሰምቶት ፡ እነሱ በገቡ ቁጥር  በነሱ ዙሪያ ፈዞ መቅረቱን ተላምዷል ፡ከነሱ የሚወደው የሚሰጡት ቲፕ ብዛቱ ዋው  ,,,,,,
ሰሚር ባልደረባው ከጠቆመበት ቦታ ሊሄድ ሲዘጋጅ ጌታ ነህ ጠራው ....
"አቤት ምን ይምጣ "አለው እጁን ወደዋላ አድርጎ በክብር ። ጌታነህ ዝም ብሎ ወሬውን እያወራ አስጠበቀው  ሰሚር  በትህግስት ጠበቀው 
"እስኪ ልጁን አታቁመው ምን ፈልገህ ነው የጠራኽው "አለው ሰመረ የሰሚር ሁኔታ ትንሽ ነካ አርጎት
"እእ እ አስተናጋጅ ስምህ ማነው ?"አለው ጓደኞቹ እኩል ሳቁ
"እናንተ አታስካኩ "አለ እና ወደሰሚር መለስ ብሎ
"ስምህን መጠየቄ ክፋት አለው እንዴ "
"ኧረ የለውም  ፡ስሜ ሰሚር ጅላሉ ሚፍተሃ"ይባላል
"እ ሰሚር ብቻ ይበቃል ከዋላ ያሉትን ተዋቸው "አለ ጌታነህ ኮስተር ብሎ። ጓደኞቹ አኮሰታተሩ በቀልድ የታጀበ መሆኑን ስለሚያውቁ ተሳሳቁ
"ያው የዋላው ከሌለ የለም የፊቱ ብለን ነው "አለ ሰሚር እንደመቀለድ ብሎ
"እ እሱ መፈክር ላይ ነው !አሁን እሱን ተወውና ማነህ ሰሚር እዛ ፊት ለፊት ያለችው ኮስሞ ቤት ትታይሃለች "
አለው። እነሱ ከተቀመጡበት ሬስቶራንት አስባልት ተሻግሮ ያለች አነስተኛ ኮስሞ እየጠቆመው
"እ አዎ ትታየኛለች ሳሪና ኮስሞቲክስ አይደል "አለው
"አዎ እዛ ሱቅ በር ላይ ለተቀመጠችው ሴት ይሄን ስጣት "ብሎ ስልክ ቁጥሩን የያዘ ካርድ ሰጠው ሰሚር ትንሽ ግር አለው ስራዬ መልህክት ማመላለስ አይደለም ኤጭ አለ በሆዱ
"እ ስለላኩ ቅር አይልህም አይደል "
"እሺ ያው ማናጀሩ ካየ የት ነህ እንዳይል ነው እንጂ..."
"ችግር የለም ለሚፈጠርብህ ነገር ይሄም ስራነው ብሎ ካስቀየመህማ ከኔጋር ነው ፀቡ "አለው
"እሺ እሰጣታለው "
"ጎበዝ ልጅቷ ስለተመቸችኝ ነው እና መደወልሽን እንዳትረሺ ከቻልሽ አሁን ደውዩ በላት "አለው
ሰመረና እንየው እየተያዩ መሳቅ ጀመሩ
"ምንድነው የሚያስቃቹ !"
"አይ ከመቼው እዛማዶ አይተህ ነው እንዴዴዴዴዴ😀"
"ቆይቷል ካየዋት ሁሌም ፊትለፊት የምቀመጠው ለምን ይመስልሃል የሞዴሏን እንቅስቃሴ በትኩረት ተመልክቼ ተሳክቶልሻል ልላት ነው እና ዛሬ ትኬት ተቆርጦላታል ዌል ካም ቱ  ጌታነህ ተብላለች "አለ ወፈር ያለ ሰውነቱን ወደዋላ እየለጠጠ
"በጣም ጥሩ ግን ኤልሳ ምን ሆናብህ ነው ገና ሳምንት ሳይሞላቹ "አለ ሰመረ
"ኤልሳ ባክህ ስሟም አይመቸኝም በዛላይ አንድ ቦታ መቸከል መዛግ ነው ኪኪኪኪኪ አይመስልህም "
"ልክ ነህ ብሮ ይመችህ እዛጋር ያየኽውን አይተነው አሁን ገብቶኛል  የሆነ ቦታላይ የተከማቸ ሀብት አላት እሱን ልትቀራመት ነው ካካካካካካ ኧረ ምኑን ሰጣት ኧረምኑን ሰጣት ኪኪኪኪ"እንየው እየሳቀም እየዘፈነም ነበር
"የተረገምክ እኔ ኮ ከዚጋር ቁንጅናዋ ጎልቶ አይታይ እላለው ።ለካ የጎላ አይተ ነው "ብሎ ሰመረ አስባልቱን ተሻግሮ ለመሄድ የሚጣደፈውን ሰሚርን አየው ። ሰሚር መኪኖቹ ውር ውር ሲሉ እንደመቆም ብሎ አሳለፈ ከላይ አንዲት ገና አስራ ስድስት አመት መግቢያው ላይ የሆነች ልጅ መጥታ አጠገቡ ቆመች ለመሻገር ፈልጋ መኪኖቹ ማቆሚያም የላቸው ልጅቷ በጣም የተጣደፈች ትመስላለች አንዱን መኪና እንዳሳለፈች ለመሻገር ስትፈጥን ሰሚር ጮሆ ከመኪናው መንጭቆ አወጣት ልጅቷ ደነገጠች ሰሚር ተቆጣት ከስር ጫማዋ ግንጥል ማለቱን ስታይ ልጅቷ ተሳቀቀች ሁኔታዋ አንድ ቀጠሮ እንዳለበት ሰው ነው ባላት መጠን መልበሷ ያስታውቃል ያደረገችው ጫማ የጓደኛዋ ነው ትንሽ ተረከዝ አለው ይሄንን ጫማ እንድታውሳት መለመኗን ስታስታውስ ዕንባ በአይኗ ላይ ወረዛ  ጫማዋን አንስታ ወደዋላ ተመለሰች ፡ሰሚር መልህክቱን አድርሶ ሲመለስ ወደ ዋላ ተመልሳ ጫማዋን በአንድ እጇ እንደያዘች ያቀረቀረችውን ልጅ ተጠጋትና ። "እናት ምነው ጫማው ነው ያሳዘነሽ ሞተሽ እኮ ነበር "አላት
"ብሞት ይሻለኛል ከዚ ሁሉ "አለች
"እንዴ ይሄን ያህል ጫማ እኮ የሚገዛ ነገር ነው አንቺ ግን በሚሊዮኖች አትገኝም "አላት ለማፅናናት
"አሁን ምን ላደርግ ነው የቀጠሮ ሰአት እያለፈብኝ ነው"
"አይዞሽ ትንሽ ሄድ ብለሽ ጫማ የሚሠሩ ሰዎች ፈልጊ  "አላት እንዲ እያወሩ ሳለ ሰመረ መጥቶ ተቀላቀላቸው
ሁኔታሁን ሁሉ ከርቀት እየተመለከቱ ነበር እና በዚች ልጅ ሁኔታ የአለባበስ ስርሃት እየተሳለቁ ነበር ይባስ ብሎ ጨማዋ ሲገነጠል የሚገርም ትርሂት ብለው ሲስቁ ነበር ።ሰመረ እስኪ ላናግራት ብሎ እያሾፈ ነበር የመጣው ።
"ስሚ ሚጣ ምንድነው እሱ "አለ ሰመረ በማላገጥ
"ሚጣ አይደለም ስሜ አብ ላካት ነው ስሜ"አለች በብስጭት እሷ አድጌ አለው ከዚ በዋላ በብቸኝነት ያሳደገችኝን ጉሊት ቸርቻሪ እናቴን አሳርፋታለው ብላ የተነሳች ናት ፡ ዛሬም እራስሽን ጠብቀሽ ፅድት ብለሽ ነይ አንድ ቡቲክ ቤት አስቀጥርሻለው ያላትን በፌስቡክ የምታውቀውን ሰው ለማግኘት ነው ጫማ ተውሳ ያለቻትን ጉርድ ቀሚስ ማታ በድንብ አጥባ ከጥቁር ቀሚስ ጋር ነጣያለቲሸርት ያስፈልጋል ስላለቻት ጓደኛዋ እሱንም ከሷ ወስዳ ነው እንግዲ ወደ ቀጠሮዋ የተጣደፈችው ግን እየረፈደባት ነው በዚ ጫማ የተነሳ ስለዚ ሆድ ብሷታል
ሰመረ ከጠይም ትንሽዬ ፊቷ የሚፈልቀውን ውበት ለአፍታምቢሆን ልብ ብሏል  ግን ይበልጥ ትኩረቱን የሳበው ጫማው ነው በፍፁም ከሷጋር አይሄድም እንደተውሶ ጫማም ልኳ አይደለም ለሷ ግን ብርቋ ነው 
"እኔ ሰመረ እባላለው አብላካት ጫማሽ ተሰብሯል ስለዚ ሌላ መግዛት ሊኖርብሽ ነው "አለ ሰመረ ድንገት አንዳች አይል ማንነቱን የተቆጣጠረው መሰለ
"ሌላ ጫማ መግዛት እሱን ማድረግ አልችልም "አለች የያዘችውን የጓደኛዋን ጫማ እያየች ሰመረ መሳቅ ፈለገ ይሄ ጫማ የተጣለ ነው የሚመስለው ስለእህቱ ቬሮኒካ አሰበ የጫማዎቿ መደርደሪያ ተብሎ አንድ ክፍል ሙሉ ተለቆላታል እዛ መደርደሪያ ላይ ደሞ ሁሉም ማለት ይቻላል ከውጪ የመጡ ብራንድ ያላቸው ጫማዎች ናቸው ።እዚጋር ደሞ የተጣለ ጫማ ይዛ ታለቃቅሳለች ለሰመረ ይሄ አልተዋጠለትም ።እየደበረው ጫማዋን ከእጇ ላይ ነጥቆ ወረወረው
"ወይኔ ምን ሆነህ ነው "ብላ ጮኽች
"በቃ አየሽ አንቺን እዚጋር አስቁሞ ከሚያናድድሽ ቢርቅ ይሻላል ብዬ ነው በቃ አሁን የለም አየሽ "አላት እየሳቀ እሱን ትታ ሌላኛውን ጫማ አውልቃ በእጇ ይዛ የወረወረባትን ጫማ ላታመጣ ስትንቀሳቀስ ።ሌላኛውንም ተቀብሎ ወረወረው ።ጓደኞቹ ባሉበት ሆነው ዛሬደሞ ምን እየሰራ ነው ብለው ያሽካካሉ ።ሰሚር የልጅቷን ሁኔታ ሲያይ ችግርን ጠንቅቆ ያውቀዋላና እህቱን አስቦ ውስጡ አዘነ ፡ የሱ ዘይነብ የሆነቦታላይ ተቸግራ ልክ እንዲ በችግሯ ስትሸማቀቅ ድንገት ታስቦት አይኑ ዕንባ አቆረ ........



ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍13620😁8👏3👎1
🍓👁በ'ነሱ ቤት👁🍓
👁🍓ክፍል ሦስት🍓👁
🍓🔵🍓🔵🍓🔵🍓
አብላካት ቀጫጭን ጠይም እጆቿን በብስጭት እያወናጨፈች ሰመረን ተቃወመች ጮክብሎ መናገር አይሆንላትም እንደዛ ካደረገች እንኳ ዕንባዋ ይቀድማታል  እንደዛ እንዲሆን ደሞ አልፈለገችም በማንም ሰው ፊት እንደ ዕፃን ማልቀስን አትሻም ስታለቅስ የኖረችባቸው ጊዜያቶች እንዲያበቁ ብቻ ነው አሁን ላይ የምትፈልገው ። ከዚበፊት ስለ እናቷ መጠቀት አልቅሳለች ስለችግራቸው አልቅሳለች እንደሌሎች ልጆች የፈለገችውን ማግኘት እንደማትችል ባወቀች ጊዜ አልቅሳለች ። እርቧት የምትበላው ነገር በቤትውስጥ በማጣቷ አልቅሳለች ። ዛሬላይ ግን ሁሉ ነገር እንዲያበቃ ነው የምትፈልገው የወጣት አሮጊት የመሰለችባትን እናቷን ከችግር ማውጣት ያን ባትችል እንኳ ልታግዛት ፈልጋለች ፡ ለዚህም ነው በፌስቡክ ብቻ ካወቀችው ጥሩ ሰው ከመሰላት ሰው ጋር ቀጠሮ የያዘችው እናም ያሰው ብዙ ነገር ነው ቃል የገባላት ስራ እንደሚያስቀጥራት ሕይወቷ እንደሚቀየር የተሻለ ኑሮ እንደሚኖራት ጭንቅላቷን የሞላት ፡እናም ጓጉታ ነበር ይሄ የተረገመ ጫማ ሊያሰናክላት ነው በዛላይ ሰመረ ጫማዋን እየወረወረ አበሳጫት ።
አስተናጋጁ ሰሚር የልጅቷን ጫማ እየወረወረ በሚስቀው ሰመረ ላይ ከምር ተናደደበት ግን ንዴቱ ዋጥ አድርጎ ወደ እሬስቶራንቱ ከመመለስ ውጪ ምንም ማድረግ አልቻለም ።
ሰመረ ጫማዎቿን ለማምጣት የምትሯሯጠውን አብላካትን እጇን ይዞ በቁጣ አስቆማት ።አብላካት ጭራሽ ከሱም ብሶ ሲቆጣት ትላልቅ የሚያምሩ አይኖቿን አፍጣ በመገረም ታየው ጀመር ።
"ስሚ ሚጣ ከአሁን በዋላ ያጫማ አብቅቶለታል የምን ችክ ማለት ነው ።በቃ ሌላ ጫማ ሄደሽ ግዢ አለበለዚያ በጥፊ ነው የምልሽ እሺ"አላት ፊቱን እንዳኮሳተረ ።አብላካት ተገርማ
"ጭራሽ እንዴ ለምንድነው እንዲ የምታደርገው?"አለች ሰመረ እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ ብዙ የመቶብር ኖቶች ሲያወጣ አፋን ከፍታ ቀረች
"ለምን ምናምን ማለትሽን ትተሽ እንኪ ውሰጂና የምትፈልጊውን ጫማ ግዢ ለጊዜው የያዝኩት ይሄንን ነው የማይበቃሽ ከሆነ ነገ እዚው ስላለው መጥተሽ ውሰጂ ይሄን ጫማግን ደግመሽ እንዳታይው ሲያስጠላ "አለ ፊቱን አጨፍግጎ
"ግን ለምንድነው ይሄንን የምታደርግልኝ "አለች ድጋሚ
"ይኽውልሽ አጉል ክርክርሽን ተዪ ጫማው ተበላሽቶብሻል እኔ ደሞ ስላለኝ ነው የምትገዢበት የሰጠውሽ አሁን ሂጂ"አላት እጇላይ ያስቀመጠላት ብር ቡዙነው ለሷ እምቢ እንዳትል ችግሯን አሰበች እሺም እንዳትል ሒሉንታ ያዛት
"አንቺ ሚጣ ለምንድነው ሄደሽ የማትገዢው ያው እዛ ከኮስሞ አጠገብ የሴቶች ጫማ መሸጫ ይታየኛል እዛ ሄደሽ ግዢና ከዚ አካባቢ ሂጂ  "አለ ሰመረ
"ግን እኮ ጫማው የሰው ነው ማለቴ ጓደኛዬ አንድ ሰው ስራ ሊያስገባኝ ነው እና ጫማሽን አውሺኝ ብዬ ለምኛት ነው የሰጠችኝ ።እና እሷ እራሱ የታላቅ እህቷ ነው ጫማውን ወስጄ አሰርቼ ካልሰጠዋት ትጣላኛለች ።"አለችው ፈራ ተባ እያለች ።ሰመረ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨነቀ ።እንዴ ምን አይነት ነገር ነው አሁን ይሄም ጫማ ሆኖ ይዋዋሱታል ።አለ
"እሺ እንደፈለግሽ አድርጊ ሚጣ "አላት አዘን ብሎ
"ስሜ አብ ላካት ነው "አለች እና ስልኳ ሲጮኽ ሰምታ ከያዘቻት ትንሽዬ ያረጀች ቦርሳ ውስጥ ስልኳን አውጥታ "ሄሎ ሰላም ዋልክ ።አዎ አዎ ይቅርታ ግን አሁን መጥቻለው ።ትንሽ ጠብቀኝ ችግር ገጥሞኝ ነው እኮ ።አይ አይ አሁን ይሻላል ። እኮ ማማታማ እናቴ አትፈቅድልኝም ። እባክህ እንደዛ ማለቴ አይደለም ።እኔ ስራውን እፈልገዋለው ። እባክህ ቆይ አትዝጋው እኔ እኮ ማታ መውጣት ስለማልችል ነው ። ግን እኮ ስራው ያስፈልገኛል እናቴን መርዳት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ ።እሷ እየተጎዳችብኝ ነው  እባክህ ።ቆቆይ አትዝጋው ,,,,"ስልኩ ጆሮዋላይ ተዘጋ አብላካት የምትፈራው ዕንባዋ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ ።አጠገቧ ሰመረ መኖሩን እንኳ እረስታለች ,,,,,,,,,,

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍122🥰98👎1😁1
​​#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ  ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ  አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ  ወደ ዋና ጋንዳው አመራች ..ሰውነቷን  ጭፍግግ ስላለት  ዘና ማለት  ነው የፈለገችው….በዋና ሰውነቷን ማፍታታት……
የዋና ገንዳው አካባቢ እንደደረሰች ዘላ ውሀ ውስጥ ገብታ መንቦጫረቅ አልፈለገችም…የመዋኛ ገንዳውን ዙሪያ ከበው ወደ ተዘረጉ ዘመናዊ ወንበሮች ሄደችና ..ባዳውን ከሆነ አንድ ወንበር ላይ ዘና ብላ በመቀመጥ የሚዋኙትን ታዳሚዎች እያየችና  እየታዘበች መዝናናቷን ቀጠለች…..
…..አበሻም ፈረንጆችም…. ሴቶችም ወንዶችም… ህፃናትም፤ ወጣትና አሮጊቶችም በስብጥር  ሲዋኙ እና ሲንቦጫረቁ ይታያሉ….
ስሜቷ አንቀልቅሎ ወደ እዚህ ስፍራ ያመጣት ለምን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀላትም .. …?…..  ድንገት ግን ሳታስብ አንድ ወጣት ዕድሜው በግምት በ25 30 ዓመት መካከል የሚገኝ  ወንድ ላይ አይኗ አረፈ…ያምራል… በጣም ነው የሚያምረው..፡፡ ከደረቱ በላይ ያለው የሰውነት ቅርጽ ውጥርጥር ያለ እና ሚማርክ ነው…ፀጉሩ በውሀው አቅም ተሸንፎ በሚመስል ሁኔታ ዝልፍልፍ ብሎ ግንባሩ ላይ ተዘናፍሏል፡፡አይኖቹ ከጨረቃ የተዋሳቸው ይመስላሉ…ኪሊማንጀሮ ተራራ ጫፍ ላይ ያገኘችውን አንድሪውን አስታወሳት፡፡.
እሷ ደግሞ ካለ ችግሯ ወይም ድክመት ሊባልም ይችላል   ስድስት ወር ወይም አመት ምንም ወንድ ሳያምራት ወይም ከምንም አይነት ወንድ ጋር ሳትነካካ ትቆይና ድንገት በሰከንድ ውስጥ በእይታዋ ውስጥ የሆነ ወንድ ገብቶ ቀልቧን ከሰረቀት በቃ..ስግብግብ ነው የምትለው..፡፡በዛኑ ቀን ወይም ከተቻለም በዛኑ ደቂቃ ማግኘትና አምሮቷን መወጣት አለባት….(ያው የእሷ ፍቅር ከአንድ ጊዜ የወሲብ ፍላጎት አያልፍም ..ከዛ በላይ ፈልጋ አታውቅም ..ለእሷ በፍቅር መነሁለል እና . ወንድን እየተከተሉ መዞር ወይም ወንድ አፈቀርኩሽ እያለ ለሀጩን እያዝረበረበ በዙሪያዋ እንዲሽከረከርባት በፍፅም አትፈቅድም….)
.የእሷ ችግር ጊዜያዊ ነው ..ጊዜያዊም ብቻ ሳይሆን ቅፅበታዊም ጭምር ነው….በፈለገች ጊዜ ማግኘት አለባት… .ካለበለዛ እራሷን ሁሉ መቆጣጠር ስለሚያቅታት ጥፋት ታጠፋለች....የማይሰራ ስራ ትሰራለች…የወሲብ ጠኔም በቀላሉ አዙሮ እና አጥወልውሎ ሊደፋት ሁሉ ይችላል….እና አሁንም ይሄ ሻንቂላ ወንዳ ወንድ ወጣት እፊቷ ያለው ሰማያዊ መዋኛ  ገንዳ ውስጥ ጥበባዊ በሆነ ስልት እንደ ዓሳ ነባሪ ብቅ ጥልቅ በማለት እየዋኘ ቀልቧን ስልብልብ አድርጎታል..
‹‹ተይ ይቅርብሽ››እራሷን ለመገሰፅ ሞከረች…እራሷን መገደብ እንደማይሳካላት ግን ከልምድ ታውቃለች… …..ከለበሰችው የዋና ልብስ ስር እግሯ እና እግሯ መካከል ያሳክከት ጀመረ.. እጣቷን ወደ ጭኗ መካከል በመስደድ የሚበላትን አካባቢ አከክ…አከ…ክ አድርጋ ተንፈስ ለማለት አሰበችና   ዙሪያዋን በሰዎች መከበቧን  ሳታስተውል መልሳ ተወችው....ከተቀመጠችበት መቀመጫ ተነሳችና ወደዋናው ገንዳ ቀረበች…ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ነው…ድንገት በትይዩ አቅጣጫ በሰማዩ ላይ በሶስት መቶ ሜትር  ርቀት ….   ንስራ ሲያንጃብብ ተመለከተችና
‹‹…ወይ ከመቼው ተከትሎኝ መጣ….ግን እንኳን መጣህ.››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…. እሱን በአቅራቢያዋ በማየቷ ደስ አላት..አዎ ይሄ ቀልቧ ያረፈበትን ወጣት ከተቻለ አሁን ለመክሰስ..ካልሆነም ለእራት ለማድረስ የእሱ እርዳታ ያስፈልጋታል….ስለደካማ ጎኑ በእነዛ ሰርሳሪ አይኖቹ  በማየት  ካልነገረራትና በምን ሁኔታ ብትቀርበው የሀሳቧ ሊሳካ እንደሚችል መረጃውን ካላቀበላት ባሰበችው ፍጥነት ሊሰካላት አይችልም ፡፡

ደስታዋ ግን ሀሳቡን አስባ ሳትጨርስ ነው ከውስጧ በኖ የጠፋው….የንስሯን እርዳታ መጠቀም አትችልም…ምክንያቱም ይሄ ሰው ምን አልባት የማይሆን ታሪክ ካለው..ወይም አደጋኛ ሰው ከሆነ ንስሯ  የሆነ ተአምር ፈጥሮ ከእሱ ጋር በምንም አይነት ተአምር እንዳትገናኝ ያደርጋታል..በምኞቷ መካከል ጣልቃ ይገባና ያጨናግፍባታል…ያ እንዲሆን ደግሞ አትፈልግም...ስለዚህ እዚህ ታሪክ ውስጥ ንስሯን አታሳትፈውም፡፡እንደዛ ወሰነች፡፡

..እንዳዛ ከሆነ ደግሞ እየበላት ያለውን በገዛ ጣቶቾ  ስታክ ማደራ ነው…ፈርዶባት ደግሞ በአንዱ የተቀሰቀውን ስሜቷ  በሌላ ወንድ አካክሳ ልታበርደው  አትችልም…ይሄ የእሷ የሆነ ልዩ ባህሪ ነው……
ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በራሷ መወጣት አለባት….."ንስሯን ምንም እርዳታ አልጠይቀውም….እሱ በሚዋኝበት አካባቢ እስትራቴጂካል ቦታ መርጣ   ገንዳው ዳር ተቀመጠችና እግራን ብቻ ውሀ ውስጥ በማስገባት ልክ መዋኘት እንደሚፈልግ … ግን ዋና ስለማይችል መግባቱን እንደፈራ ሰው በመምሰል ማንቦጫረቅ እና በእጇ እየጨለፈች በውሀው መጫወት  ጀመረች….
አዎ  ልጁ እየዋኘ ወደስሯ ተጠጋ…ተመልሶ ሄደ ..ሶስት አራቴ በሰሯ ተመላለሰ…በአምስተኛው በአጠገቧ ሲያልፍና በጣም ሲጠጋት…

‹‹ታድለህ ››አለችው

‹‹ምን አልሺኝ…?››

‹‹ እንደ ዓሳ ነው የምትዋኘው…ታስቀናለህ…!!!  ››  

‹‹አመሰግናለሁ…››ብሏት ዋናውን ሊቀጥል ካለ በኃላ መልሶ ወደ እሷ  በመዞር..‹‹ለምን አትገቢም…? ››ሲል ጠየቀት

‹‹መግባት እፈልጋለሁ ..ግን ዋና አልችልም፤ ብሰምጥስ…?››

‹‹አይዞሽ እኔ እጠብቅሻለው ግቢ››

‹‹ኸረ ተው ይቅርብኝ››ተግደረደረች

‹‹ግቢ. በእኔ ተማመኚ››

የምትፈልገው  ሀሳብ ስለሆነ ቀሰ ብላ ገባችና ልክ እንደጀማሪ ዋናተኛ ተንደፋደፈች..በቅርቧ ስለነበረ ቶሎ ብሎ ከስር ገባና  ሰቅስቆ በክንዶቹ
መሀል አድርጎ ወደ ላይ አወጣት …
  

ይቀጥላል
👍10912👏1
አትሮኖስ pinned «​​#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ  ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ  አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ  ወደ ዋና ጋንዳው አመራች…»
⚫️🍄በ'ነሱ ቤት🍄⚫️
🍄👁ክፍል አራት👁🍄
🍓🍄🍓🍄🍓🍄🍓
ሰመረ እንደዚ አይነት መጨናነቅ የለመደ ልጅ አይደለም እና ሁኔታዋን አይቶ'ምነው እቺን ልጅ ላናድድ ብዬ ከተቀመጥኩበት ባልተነሳው በገዛ እጄ አባባይ ልሁን እኔ ሲጀመር ምን አገባኝ !ማድረግ ያለብኝን አድርጌላታለው  በቃ የራሷ ጉዳይ 'ብሎ ትቷት ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ ። ጓደኞቹ ገና ከመምጣቱ በተረብ አላስቀምጥ አሉት።
"እኔ የምልህ ከዚች አመዳም ጋር የዚን ያክል ክርክሩ ምንድነው ?ደሞ አይደብርህም እንዴ ያንን አስቀያሚ ጫማዋን ከእጇ እየነጠክ ትወረውራለህ ሃሃሃ በል በል አሁን ሂድና እጅህን ታጠብ ሆሆሆ ሳም ሙት! አንዳንዴ ምንም አትገባኝም በላይህ ላይ ጀርም ትጋብዛለህ ሃሃሃሃ"ብሎ ጌታነህ ሳቀበት ።እንየው ቀበል አድርጎ "እኔ እኮ የገረመኝ ገንዘብ አውጥተህ መስጠትህ ምን ፈልገህ ነው ግን ኪኪኪ ለነገሩ አጥበህ አስቆንጅተህ በትበላው የሚያስከፋ አይደለም በደንብ ከተያዘች ቆንጆ ነገር ናት ግን ጓደኞቼ እየወረዳቹ ነው ዛሬ 😀ወይ ከዚ በረንዳ ወደውስጥ እንግባ 😀"አለ ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ።
ሰመረ እነሱ የተናገሩት ነገር ምኑም ደስአላለውም ይብስ ተከፋ ሁለቱም ባሰቡት መንገድ እንዳላሰበ ደጋግሞ አስረዳ ። ከነሱ ጋር ክርክሩ አላዋጣ ሲለው አይኖቹን መልሶ ወደ መንገዱ ወርወር አደረገ አብላካት እየተወለጋገደች ሁለቱን ጫማወቿን አንጠልጥላ በተስፋመቁረጥ ስትራመድ አያት  ለምን እንደው ያላወቀው ስሜት ወረረው ልቡ አዘነ ይህቺ ልጅ ገና ታዳጊ ናት ለምንድነው የዚን ያክል መከፋት ያለባት ምን አይነት የተቸገረ ቤተሰብ ቢያሳድጋት ነው እንዲ የሆነችው አለ ለራሱ ፣ሰው በዚመጠን ደሃ ይሆናል ጫማ እስከመዋዋስ ለዛውም ጀየሚያስጠላ ጫማ ይገርማል ። በመንገዱላይ ብዙ ሰው አይታይም  አብላካት ያመንገድ አላልቅ ያላት ይመስላል በራሷ በጣም ተሸማቃለች ገና ከሳምንት ጀምሮ ስትዘጋጅበት የነበረ ቀጠሮ ነው የተበላሸባት ለሷ የመጀመሪያ ቀጠሮዋ ነው ለዛውም ከችግር የምትወጣበት ቀጠሮ ነገር ግን በገዛ እጇ አበላሸችው ምነው ታምራትን ከማስከፋው የራሴን ጫማ አድርጌ በመጣው ይሄኔ እኮ አግኝቼው የምሰራበትን ቦታ አሳይቶኝ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ እመለስ ነበር የተረገመ ጫማ ።ደሞስ ምን አጣደፈኝ ቀስ ብዬ አልሻገርም ነበር ።በራሴው ስህተት ነው ስራውን ያጣውት ።ዕድ ለቢስ ነኝ ሲጀመር  ብላ ስንጥቅ የበዛባትን የሞባይል ስልኳን አየች በተስፋ ታምራት የተባለው የፌስቡክ ጓደኛዋ ይደውል ይሆናል በሚል ምኞት ።ይህችን የሞባይል ስልክ ከሰው ላይ የገዛችላት እናቷ ነች  ከዘጠኝ ወደ አስር በጥሩ ውጤት ስላለፈችላት ደስታዋንና በሷ መኩራቷን ለማሳየት ።እና አብላካት የዛንቀን ከጓደኞቿ እኩል ሞባይል በመያዟ ደስታዋ ወደር አልነበረውም። ከዛን ጊዜጀምሮ ፌስቡክ ከፍታ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ታወራለች ከአንገት በላይ ተነስታ የምትለቃቸው ፎቶዎቿ የሚስቡ በመሆናቸው ብዙ ወንዶች ኢንቦክስ እየገቡ ያወሯታል የፍቅርጥያቄ ያቀርቡላታል አብላካት ለሁሉም በየዋህነት ገና ለዛ እንዳልደረሰች ትፅፍላቸዋለች ።ብዙዎቹ ያለምጡባታል ።ከነዛ ውስጥ ግን የታምራት አቀራረብ ይመቻታል ልጅነቷን ስትነግረው መገመቱን እና እሱ እህት እንዳለው ልክ በሷ ዕድሜ መሆኗን እየነገረ አግባባት ከዛ በዋላ ስለቤተሰብ ስለትምህርት እየጠየቀ ችግሯን ሁሉ ሳትደብቅእንድትነግረው አደረገ  ከዛም ነገረችው ።እናቷ እሷን በልጅነቷ ሰውቤት ሰራተኛ ሆና  ከአሰሪዋ ልጅ እንዳረገዘቻትና አሰሪዎቿ ይሄንን ሲያውቁ እንዳባረሯት ከዛም እሷን ጎዳናላይ እንደወለደቻት ከዛ በዋላም እናቷ እጅ ሳትሰጥ ጉሊት እየሰራች ፍራፍሬ አትክልት እየሸጠች እንዳሳደገቻት አወራችው ።በጣም የሚያሳዝን ታሪክ እንዳላት እና እሷን ለመርዳት ሲል የአክስቱን ልጅ እንደሚያናግራት እና እሷ ፑቲክ ውስጥ እንደሚያስቀጥራት ነገራት ።ይሄንን ያላት ቀን በደስታ ነበር የሰከረችው ። በተለይ እናቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እግሬን እየወጋኝ ነው እያለች ከምትሰራበት ጉሊት መመለሷ እየተለመደ መጥቷል እመም ይሰማታል ይሄን ስለምታውቅ ።እሱ ስለስራ ሲያወራት ቀጥታ የታያት እናቷን ማገዟ ነው ።አብላካት ስላረፈድሽ የማልቀርበት ጉዳይ ስላለኝ ሄጃለው ባይሆን ማታ ተገናኝተን ተጫውተሽ ትመለሻለ ሲላት አይመቸኝም ስትለው ድንገት ቅይር ብሎ ካልሆነ ይቅርብሻ ነበር ያላት በጣም ተናዳለች በፌስቡክ እንዳወራት አልሆነላትም  ።ሰው በአንድጊዜ ጥፋት እንዲ ይለወጣል ያሳዝናል ።'ወይኔ እናቴ መቼ ልደርስልሽ ነው 'እያለች በአዘን ተቆራምታ በባዶእግሯ ትጓዛለች ። ሰመረ የሰጣትን ብር ጨምቃ ይዛታለች ።
*ሰመረ ተነስቶ ቆመ ጓደኞቹ እኩል ወዴት ነው አሉት መጣው ብሎ በረንዳውን በፍጥነት መውረድ ጀመረ
ጓደኞቹ ግራ በመጋባት ተያዩ ሰመረወደ አብላካት አቅጣጫ ፈጠነ,,,,,,,

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉእዕ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11310🤔4👏2😁1
​​#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹አይዞሽ..አይዞሽ››

‹‹ያስፈራል..››

‹‹እኔ ደግፍሻለሁ… ቀስ ብለሽ ዋኚ..››እጆቹ ከስር ሲደግፈኝ በማወቅና ባለማወቅ መካከል ሆኖ  አንዴ ጡቶቼን ሲጨፈልቃት..አንዴ ወደጭኑ አካባቢ ሲንሸራተት..እሷም ደግሞ ልክ እንደፕሮፌሽናል ተዋናይ ፍጽም በማስመሰል … አንዴ የፈራች መስላ አንገቱ ላይ በመጠምጠም ከሰውነቱ ስትጣበቅ..አንዴ ከእጁ ሾልካ ውሀ ውስጥ እራሷን በመድፈቅ ስትንደፋደፍ…..በመጋል እና በመቃተት መካከል ሆና ግማሽ ሰዓት ያህል ካለማመዳት በኃላ

‹‹ለዛሬ ይብቃሽ ልወጣ ነው ››አለት…

ቅፅበታዊ ውሳኔው አበሳጫት

‹‹እንዴ ምነው …?በደንብ ሳልችል…?››ኮስተር ብላ..ኮስተር አባባሎን ለተመለከተ ገንዘብ ከፍላው የሚያስተምራትን ሰው የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡

መቼም የመልመድ ተስፋ የላትም የሚል  በሚመስል ስሜት ‹‹አረ ባክሽ..!!እኛ በስንት አመትና ልፋት የቻልነውን ዋና አንቺ በአንድ ቀን ..ለዛውም በግማሽ ሰዓት መልመድ ትልጊያለሽ……?.››አላት..
የሚያወሩት በጣም ጥልቅ ያልሆነ የገንዳው ጠርዝ አካባቢ ቆመው ነው..ውሀው እሷን ጡቷ አካባቢ እሱን ደግሞ እንብርቱን አካባቢ ድረስ ሸፍኖቸዋል…ከፊል እርቃናቸውን እየታያዩ ፊት ለፊት ተፋጠው ነው የምያወሩት..እሷ ለወሲብ እየጎመዣች..እሱ በትምክት እየጎረረባት 

‹‹አረ በናትህ ዋናን እኮ የተለየ ጥበብ አደረከው..›› አለችው..እወነቷን ነበር ያለችውት፡፡

እሷ የደሎ መና ልጅ ነኝ..ዋና እየተስገመገመ በሚጋልበው  የያዶት ወንዝ በ3 አመቷ በቀልድ ነው የለመደችው…በዕቃ ዕቃ ጫወታ…ያዶት መዋኘት ለለመደ ሰው  ደግሞ እዚህ የረጋ ወሃ  ላይ መዋኘት ቀልድ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ  ጥበብ ካልሆነ ያው ሜዳው…አሳይና››ብሎ አበሳጫት…የጀመረችውን የማጥመጃ ዘዴ በደቂቃ ውስጥ እረስታ ያልሸነፍ ባይነት እና የበላይነት መንፈሷ ከውስጧ ተንቀልቅሎ ገነፈለባት…በቆመችበት ቦታ ድንገት  ሰመጠችና  ውስጥ ለውስጥ መሹለክለክ ጀመረች … ካለችበት ጫፍ ወደሌላ ጫፍ ተወነጨፈችና በሰካንድ በዛኛው ጫፍ ስትወጣ እሱም እሷን ፍለጋ ሰምጦ ኖሮ በድንጋጤ ከመሀከል አካባቢ ከውሀ ውስጥ ሲወጣ ተመለከተችው..አይኑን ከወዲህ ወዲያ አማተረና እሱ ካለበት በብዙ እርቀት ተስፈንጥራ ከውሀ ውስጥ በሰላም እና በፈገግታ ታጅባ ብቅ ጥልቅ እያለች ሲያያት በመገረም  እና በንዴት አፈጠጠባት… በቄንጥና ቲያትራዊ በሆነ ትዕይንት  ከላይ እየተንሳፈፈች ፤ እየዋኛችና  እየተገለባበጠች ስሩ ደረሰች፡፡
‹‹እያሾፍሽብኝ ነበር..…?እኔ ደግሞ የሰመጥሽ መስሎኝ መደንገጤ››
‹‹ብሰምጥስ ምን ያስደነግጥሀል…?››

‹‹እንዴ ሰው አይደለሽ …? ለምን አልደነግጥ…?››

‹‹ስለተጨነክልኝ አመሰግናለሁ››

‹‹አረ ምስጋናሽን ቀቅለሽ ብይው..በአንቺ ቤት አራዳ ሆነሽ በዘዴ መጥበስሽ ነው?››

‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?››ንግግራቸውን በቅርባቸው የነበሩ ሁለት ሰዎች የሚዋኙ መስለው ግን ጆሮቸውን ወደ እነሱ ቀስረው  እያዳመጡ  ነው..ደንታም አልሰጣት፡፡

‹‹ሰምተሻል ባክሽ….እኔ ለእንደአንቺ አየነት ጩሉሌ ከምሸነፍ አራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…..

"እኔ ደግሞ በጥቂት ቀን አንተን መጥበስ ካልቻልኩ እራሴን አጠፋለሁ"

"አፍጥጦ አያትና ምንም ሳይናገር ጥሏት ሄደ
እሷም ከገንዳው ወጥታ ወደመኪናዋ ተንደረደረች...

ከፍታ ገባችና በውሀ የራሰውን የዋና ልብሷን አውልቃ ሌላ ልብሷን በመልበስ ከመኪናው ወጣች..ኮፈኑን ተደግፋ ንስሯ ፊት ለፊት ቆማ  ማሰብ ጀመረች …. በአካባቢው የሚያልፍ ሰዎች ከንስር ጋር ባልተለመደ ሁኔታ ፊት ለፊት ተፋጣ  ሲያዩት  በመገረም እየተገላመጡ ሲያልፍ አስተውላለች፡፡

‹‹የሆነውን አይተሀል አይደል…?በቃ ፈልገዋለሁ››የምታወራው ለንስሯ ነው

(ይቅርብሽ የሚል  ቃል ወደ አዕምሮዋ ላከላት)

‹‹ አታበሳጨኝ..በቃ ፈለኩት ማለት ፈለኩት ነው …አሁን የሆነ ነገር አድርግልኝ …ሆቴሉ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ቢራ እየተጎነጨው እጠብቅሀለሁ…››

ተነስቶ በረረ……..

እሷም እንዳለችው ወደሆቴሉ በረንዳ በመሄድ ወንበር ይዛ ተቀመጠችና ቢራ አዘዘች….እንግዲህ ያሰበችው እስኪሳካ ሌላነገር ማሰብም  አልቻለችም…ቀልቧን ሁሉ ጥቁሩ ልጅ ላይ እንደተጣበቀ ነው…….ጭኗ መካከል ይበላት የነበረው አሁንም እየበላት ነው…. ከመብላቱም አልፎ እያቁነጠነጣት ነው… አሁን እንደዚህ የሚያደርጋት የወሲብ ጥማት ነው…እንጂማ በቅጽበታዊ የፍቅር ፍላፃ ተመታ አይመስልም… ‹‹እንደዛ አይነት ደካማነትማ አይነካካኝም…መጀመሪያውኑስ ፍቅር  ምንድነው …...?የፍቅር መነሻውም መድረሻውም አይስማማኝም፡፡ማለቴ በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል ያለው የፍቅር ስሜት መነሻው የተለያየ ቢሆንም መዳረሻው ለምን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ሆነ….ሁል ጊዜ ለምን ፍቅር በወሲብ ልጥ ይታሰራል፡፡ልጡስ ለምን በጋብቻ ሰንሰለት እንዲቀየር ይጠበቃል?ለምን ፍቅር….ወሲብ..መለያት ወይም ፍቅር….ወሲብ ..ጋብቻ ..ልጅ መውለድ….፡፡ሌላስ አማራጭ ለምን  አይኖርም…ለምሳሌ ፍቅር …ጓደኝነት….በቃ፡፡እንደዛ ቢሆን ምንም ገደብ አያጨናግፈውም…አንድ ወንድ መቶ ሴት ቢያፈቅር ሚኮንነው ሰው የለም…ምክንያቱም ፍቅር  ከዛ ጓደኝነት ነው…ባል ይኑራቸው አይኑራቸው….ወደፊት ያግብ አያግቡ አያስጨንቀውም…፡፡ፍቅር ብቻ…ከልብ ማፍቀር ግን ደግሞ እንዳሻቸው ሲበሩና ሲከንፉ እያዩ መደሰት…ሲያገቡ መጨፈር..ሲወልዱ መሳም….ሲያለቅሱ ጉያ ውስጥ ሸጉጦ ማባበል፡፡ግን ይህ ህልም ብቻ ነው …አጉል ምኞት ፡፡ተፈጥሮም ማህበረሰብም አይፈቅድም፡፡ወንድ አንድን  ሴት አፍቅሮ እጆቾን ሲነካ  በሰውነቱ እሳተ ጎመራ ይንቀለቀላል…ከንፈሯን መገሽለጥ ጭኖቾን መፈልቀቅ ቀዳሚ ምኞቱ ይሆናል…በቃ ማህበረሰብም ተፋቀሩ ሲል ተኙ መከተል እንዳለበት ያምናል..ፍቅር እና አልጋ…ነገሩ ጥሩ ነው ጤነኝነትም ነው…ፍቅርም ወሲብም ለሰው ልጅ የተሰጡ ደስታቸውን የሚያመርቱባቸው ተፈጥሮአዊ የስሜት እርካታ ፍብሪካዎቻቸው ናቸው፡፡ግን ቢሆንስ ሁሉም ፍቅር ወደወሲብ  ሁሉም ወሲብ ደግሞ ወደ ጋብቻ መቀየር አለበት ወይ… ?….አይ  ምን እየቀባጠርኩ ነው …አትፍረዱብኝ ምን አልባት ይሄንን አይነት  ከሰው ልጅ  አስተሳሰብ ውጭ የሆነ ነገር ከአባቴ ዝርያ በደም የወረስኩት ይሆናል፡፡››በማለት ስትብሰለሰል ቆየች

ከ15 ደቂቃ በኋላ ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ንስሯ ተመልሷ መጣና በቅርብ ርቀት ጨለማውን እየሰነጠቃ በአየር ላይ ሲንሳፈፍ ተመለከተችው…ሀሳቧን  ሰበሰበችና  ከእሱ አእምሮው ጋር አገናኘችት… ያየችውን ወይም አሁን እያየች ያለውን ነገር ለማየት ….

ይቀጥላል
👍13016😁5😱4👎3🔥1🤔1