አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስር


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
ዛሬ ላይ..
ለሊት 11 ሰዓት ተነስተው ቤተክርስቲያን ሄዱ፤ለአባትየው ሰባት ዓመት ፍትሀተ-ፀሎት ከመደረጉ በተጨማሪ የስንዱም የምንኩስና ስርዓት ፀሎት ተደርጎ እማሆይ አፀደማርያ ተብላ ቆብ ደፋች.ይሄ ድርጊት በአብዛኛው  ሰው  ዘንድ መደነቅን ለጥቂቱ ደግሞ ለሀሜት አሳልፎ ሰጣት…ከቅዳሴ በኋላ ከቤት ተዘጋጅቶ የመጣውን ፀበል ፃዲቅ ሰንበቴ ቤት በመታደም ከተቋደሱ በኋላ ቤት ላለው ዝግጅት ተመለሱ ቀኑን  ሙሉ ባለፉት 6  ዓመታት እንደተደረገው  ችግረኞችና  የኔ ቢጤዎች ሲመላለሱበት ዋሉ…ሳባ በዕለቱ አብዛኛውን ፕሮግራምና ሽር ጉዱን ብትሳተፍም ከአስር ሰዓት በኃላ ግን ደከማት፡፡  ተዝለፍልፋ ሰው መሀል ከመውደቋ በፊት እየተጎተተች ወደመኝታ ቤት ገባችና አልጋ ላይ ወጥታ ተዘረረች..ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት…እንቅልፏ ግን እጅግ  ሰቅጣጭ  የሆነ ቅዠት የሞላበት ነፍስ አስጨናቂ ነበር…ደግሞ የሚገርመው  ሕልሙ  እንደ ሆረር ፊልም ከአንዱ አሰቃቂ ትዕይንት ወደሌላ በተሸጋገረ ቁጥር ጭንቀላቷ ውጥርጥር እያለ ሲለጠጥ በትክክል ይታወቃታል…በተለጠጠ ቁጥር ደግሞ ውጥረቱ የሆኑ ነርቮቿን እንደሚበጣጥስ ይሰማትና ከህመሙ ራሷን ለማዳን ከእንቅልፏ ለመንቃት እየጣረች ነው.. አዎ ይታወቃታል..በደንብ ከልቧ እየጣረች ነው…ግን አልቻለችም፡፡ ስንዱ እቃ ለመውሰድ ወደመኝታ ቤት ስትገባ ሳባ በላብ ተደፍቃ ስትወራጭ በማየቷ ወዝውዛ ነበር ከእንቅልፏ ያነቃቻት..

‹‹ወይ ስንድ..ገላገልሺኝ.. እመሰግናለሁ›አለችና ተጠመጠመችባት፡፡
ስንዱም ጭንቅላቷን እያሻሸቻት‹‹ምንድነው ይሄ ሁሉ ላብ? አሞሻል እንዴ አንቺ ልጅ?›ስትል ጠየቀቻት፡

‹‹አይ ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ የታዘዘልኝ መድሀኒት ነበር..ስመጣ ግን  ረስቼው መጣሁ››

‹‹ታዲያ ለምን ከዚህ አይገዛልሽም?››
‹‹አይ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይነት አይደለም..ማዘዣው ስለሌለኝ አይሸጡልኝም፡፡ግዴለሽም አሁን ትንሽ ስለተኛሁበት ይሻለኛል..ወደ እንግዶችሽ ተመለሺ››

‹‹እሺ በቃ መለስ መለስ እያልኩ አይሻለሁ..››ብላ ግንባሯን ሳመችና በራፉን ዘግታላት ወጥታ ሔደች፡፡
ሳባም መልሶ እንቅልፍ እንዳይወስዳትና ወደተመሳሳይ ቅዠት ገብታ ስቃይ ውስጥ ላለመግባት ስትል ወደሀሳብ ውስጥ ገባች ወደ ትናንቷ ተመለሰች፡፡ትዝ ይላታል የዛን ሰሞን አሰላ ሄዳ ቤተሰቦቿን ጠይቃ ከተመለሰች በኋላ እና አባቷ ደብቆ ሻንጣዋ ውስጥ ያስቀመጠላትን 3ሺብር ካገኘች በኋላ ምንም ሰላም ማግኘት አልቻለችም ነበር፡፡ ቀንና ለሊት ሕይወቷን እንዴት ማስተካከል እንደምትችልና ከቤተሰቧ ድጎማ እራሷን አላቃ በተራዋ ለቤተሰቦቿ ተገቢውን ድጋፍ እንዴት ልታደርግ እንደምትችል ማሰብ ነበር ቋሚ ስራዋ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን ተዓምር ተከሰተ፡፡፡:

ትዝ ይላታል ማክሰኞ ቀን ነው፡፡ ስራ ገበታዋ ላይ ሆና  በተለመደ  መልኩ ባለጉዳዬችን እያስተናገደች ሳለ ረፋድ ላይ አንድ እጅግ ዘመናዊ ጥራት ያላቸው ብራንድ ልብሶች የለበሰች፤ውድ የሆኑ አብረቅራቂ ጌጣጌጦችን ጆሮዎቿና እጆቿ ላይ የደረደረች ሴት ወደ ቢሮዋ የገባችው፡፡ልክ እንዳየቻት ነው  ልቧ የደነገጠላት..በሁለመናዋ ነው የቀናችባት….አየሩን ሞልቶ ወደ አፍንጫዋ ሰርጎ በገባው ውድ ሽቶዋ ሳይቀር ቀናችባት፡፡እናም ሳታስበው ከወትሮ በተለየ አይነት ፈግታና ቅልጥፍና ሴትዬዋን ማስተናገድ ጀመረች፡፡ እሷ የምትጨርሳቸውን ስራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቢሮዎች የሚሰሩ እና የሚፈረሙ ፊርማዎችን  ሳይቀር ሴትዬዋን  የራሷ  ቢሮ አስቀምጣ እሷ (ልክ ጉቦ ይሰጥሀል እንደተባለ ኤክስፐርት) ተዟዙራ አስጨረሰችላትና ሰጠቻት፡፡
ከዛም ሴትዬዋ..ወረቀቷን ተቀብላ ትሄዳለች ብላ  ስትጠብቅ  ተመቻችታ  ፊት ለፊቷ ተቀመጠችና….‹‹ስሜን መቼስ ከሰነዱ አንብበሻል…ትብለጥ እባለለሁ…››

‹‹እኔ ደግሞ ሳባ››ስትል የራሷንም ነገረቻት፡፡

‹‹ሳባ ዋው…ስምሽም እንደመልክሽያምራል››አለቻት፡፡የሴትዬዋ ንግግር ቀጥታ ልቧ ላይ አርፎ ነበር ቅልጥ ያደረጋት፡፡ አንድ ጎረምሳ ወንድ እንኳን እንደዛ አይነት አስተያየት ቢሰጣት የዛን አይነት ስሜት በውስጧ አያጭርባትም፡

‹‹አመሰግናለሁ….›› አለች ሌላ ምትለው ነገር ስለጠፋት፡፡

ሴትዬዋ ቀጠለች‹‹ስራ እንዴት ነው?››

‹‹ያው እንደምታይው ነው…ምንም አይልም››

‹‹ምንም አይልም ነው ወይስ ጥሩ ነው ነው?›

‹‹አይ ምንም አይልም…ጥሩ የሚባል ስራ እንዲህ በቀላሉ ይኖራል ብለሽ ነው?›› አለቻት ሰሞኑን ስላለችበት ብሶት እያሰላሰለች፡

‹‹እንደ አንቺ ቆንጆ፤መለሎ ቁመና የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅ ያላትና በዛ ላይ የተማረች ሴትማ በጣም ጥሩ የተባለ ስራ ሊኖራት የግድ ነው…››አለችና እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰዳ የቢዝነስ ካርዷን አወጣችና ጠረጴዛዋ ላይ እያስቀመጠችላት
‹‹ይሄውልሽ ሳባ ለምን እንደሆነ አላውቅም ወድጄሻለሁ ምን አልባት ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በምትፈልጊበት ቀን ደውይልኝ….በይ ቻው  ለመስተንግዶሽ አመሰግናለሁ፡፡››ብላ ጉንጯን ሳመችና ቢሮዋን ለቃ ወጣች፡፡ ሳባም በተቀመጠችበት መቀመጫ ደንዝዛ በፈዘዙ አይኖቿ ከኋላዋ ተከተለቻት ሴትዬዋ እየተሞናደለች ቢሮውን ለቃ ስትወጣ በራፍ ላይ ሁለት ወጠምሻና ባለጡንቻ ወጣቶች እየጠበቋት.ነበር….መሀከል አስገብተዋት ይዘዋት ሄዱ…፡፡

‹‹ይህቺ ባለስልጣን ነች ወይስ የባለስልጣን ሚስት?› ስትል ራሷን ጠየቀች….ብንን እንደማለት አለችና ትታላት የሄደችውን ቢዝነስ ካርድ አነሳችና…አየችው..
ትብለጥ ግዛው፡፡

‹‹ቤርሙዳ ማሳጅ ቤት›› ይላል፡፡

‹‹እንዴ ባለማሳጅ ቤት ነች ግን አስመጪና ላኪ  ነው  የምትመስለው›› ስትል የስራዋ አይነት ከግምቷ ውጭ ሰለመሆኑ አብሰለሰለች፡፡ሌላ ባለጉዳይ ገባባት፡፡ሳትወድ.በግዷ.ሀሳቡን ለጊዜው በልቧ ሸሸገችውና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት። እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9913😱2👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ በጀመረች ሶስት ወርም ሳይሞላት በፊት ነበር፡፡ምክንያቱም ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ትክክለኛ ያልበተበረዘና ያልተከለሰ ማሳጅ 25 ፐርሰንትም አይሆንም...አሱ ሽፋን ነው፡፡
ወደስራው ጠልቃ ከገባች በኃላ ብዙ ብዙ ገራሚ ገጠመኞችን አስትናግዳለች… አንዳንዶቹ እስከህይወቷ ፍፃሜ የማትዘነጋቸው አይነት ናቸው፡፡
ከበርካታ ያልተለመዱ አይነት ገጠመኞቾ መካከል  አንድን ለምሳሌ ያህል ለማየት ብንችል ነገሮችን ግልፅ ያደርግልናል፡፡ስራ በጀመረች በአራተኛው አመት ነው፡፡ደምበኛ እንዳላት ተነግሯት በሰዓቷ ስራ ቦታዋ ተገኝታ እየጠበቀች ነው፡፡ እንደተባለውም በሰዓቱ በራፍ ተንኳኳ… ከፈተች፡፡በራፍ ላይ በመግባትና ተመልሶ ሮጦ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ውዝግብ ውስጥ የገባ ስሜት ላይ ያለ ጎልማሳ  ሰው  ቆሟል..ሰውዬውን  ታውቀዋለች… በአካል አይደለም..ታዋቂ ሰው ነው..ግን ምንድነው?  ተዋናይ  ነው?  ፖለቲከኛ ነው…? ግልፅ ብሎ ሊታወሳት አልቻለም፡፡‹‹ጌታዬ እንኳን ደህና መጡ ይግቡ.›› አለችና በራፉን በሰፊው ከፈተችለት..የመዝለል ያህል ፍንጥር አለና ወደ ውስጥ ገባ…እሷም በራፉን ዘጋችና  ተከተለችው…እቤቱ  ውስጥ  ከወዲህ  ወዲያ መንጎራደድ ጀመረ‹‹…ጌታይ ችግር አለ? ››ጠየቀችው፡፡

‹‹እዚህ መምጣቴ ትክክል ነው ወይስ ስህተት አላውቅም››

‹‹ጌታዬ ስህትም  ሆነ  ትክክል  አንዴ  መጥተዋል..አረፍ  ይበሉና  ትንሽ ይረጋጉ..እዚህ መምጣቶት ስህተትም ቢሆን የሆነ ጥቅም አይጠፋውም….ደግሞ ነገሮች እንደአጠቃቀማችን ይወሰናሉ…የህይወት ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ዳካሮ መውጣት የብርሀኗን ውበት የበለጠ እንድናጣጥም  ግንዛቤያችንን ይጨምርልናል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡››ብሎ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ፡፡ሳባም ወደፍሪጁ ሄደችና የታሸገ ውሀ በማምጣት ከጎኑ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለት..ከፈተና ገርገጭ.ገርገጭ አድርጎ ግማሽ ያህሉን ከጠጣለት በኃላ ከደነና መልሶ አስቀመጠው፡፡ለእኔ እዚህ ቦታ መምጣት ቀላል አይደለም…እዚህ እንድመጣ የጠቆመኝ አንድ ወዳጄ ነው….

‹‹ጥሩ ነው…ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚፈልጉት…ሙሉ ማሳጅ ..የእግር ማሳጅ አለ…ከአንገት በላይ ማሳጅ አለን…ሌሎች አገልግሎቶቹም አሉን.መጠጥና
…››
‹‹አይ እንዳዛ አይደለም…የዘረዘርሻቸውንም ሁሉ አንዳቸውንም አልፈልግም…እኔ የምፈልገው እንድታዳምጪኝ ብቻ ነው…ቆይ አሉና እጃቸውን ወደ ኮት ኪሳቸው በመክተት አንድ መለስተኛ ጥራዝ ያለው መፅሀፍ  አወጡና  ዘረጉላት፡፡ግራ በመጋባት ተቀበለችና አነበበችው›

‹‹የኢየሱስ ተአምራዊ የማዳን ስራ››የሚል ርዕስ አለው፡፡ጀርባውን ገልብጣ አየችው ፀሀፊ-ፓስተር ጴጥሮስ ዳንሳ ይላል፡፡ ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ፎቶ ገጭ ብሎበታል…እንደአዲስ ደነገጠች..ሰውዬው በደንብ ታውቀዋለች..በፕሮቴሰታንቱ መንደር በጣም ታዋቂና ዝነኘ ፓስተር ነው…በዛ ላይ የራሱ ሆነ ቴሌቬዥን ጣቢያ ስላለው.በተደጋጋሚ ስብከቱን በቴሌቪዥን መስኮት አዳምጣለች፤አሷ  ጋር መምጣቱ ለምን እንደዚህ እንደከበደው ወዲያው ነበር ግልፅ  የሆነላት..ኸረ መምጣቱ ለእሷ ለራሷ በጣም ገርሟታል..››

‹‹ፓስተር.በእውነት የአርሷ እዚህ  መምጣት  ለእኔ  ትልቅ  ክብር  ነው….እና እንዳሉኝ የሚፈልጉት እንዳዳምጧት ከሆነ በሙሉ ነፍሴ  የለምንም  ፍርድና ትዝብት እንደማዳምጧት እርግጠኛ ይሁኑ››

‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ .ማወራሽ ስለመፅሀፉ ነው፡፡በእጅሽ ስለያዝሺው መፅሀፍ ፡፡ መፅሀፉ እውነተኛ የህይወት ገጠመኜ የሰፈረበት ነው፡ይሄ ገጠመኝ ምንም ማጣፈጫ ያልተጨመረበት ንፅህ እውነት ነው ብዬ  አምን  ነበር።ላለፍት  9 ዓመታት ሰፋ ያለ ህዝብ በታደመበት አውደ ምህረት ላይ  ያለመሰልቸት ተርኬዋለሁ። ምዕመኑም አንዳንድ ሶስቴ ሌላውም 13ቴ ደጋግሞ ሰምተውታል። ግን አይ ሰልችቶኛል የሚል የለም፡፡ ከእልልታው ጥቂት ዝንጣፊ የሚቀንስ የለም።በጌታ ሰው አንደበት የሚነገር የጌታ ተአምር እንዴት ሰለቸኝ ማለት ይቻላል...?መታሰብስ።

የዛሬ 14 አመት ለአገልግሎት ደቡብ ኢትዬጰያና ሱዳን ድንበር  አካባቢ  ወደሉ ጎሳዎች እሄዳለሁ።እርግጥ ብቻዬን ሳይሆን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ነበር።እና ጉዞችን ጥቅጥቅ ደን የምናቋርጥበት ከአውሬ ጋር ድብብቆሽ የምንጫወትበት አስደናቂና አስፈሪ ነበር..ግን ደግሞ ጌታ ከእኛ ጋር ስለነበር በዝምታ ሳይሆን በዝማሬ ነበር የተጓዝነው። መንገድ ከሚገኝበት የሁለት ቀን የእግር መንገድ ተሂዶ ነው የሚደረሰው። ጌታ ይመስገን በሰላም ደረስን።ጌታን አገለገልን በሶስት ወር ቆይታችን 10 ብቻ የነበሩትን አማኞች ወደ ሶስት መቶ አሳድገን በመንደሩና በአካባቢው  የጌታ  አገልጋዬች  አድርገን  ጉባኤ  አደራጅተን  ቤተክርስቲያን መስርተን አንደኛውን ጓደኛችንን እዛው  እንዲያገለግል  ትተን  የመልስ  ጉዞ ጀመርን።

በመሀል ደረቀ ጉሮሮውን ለማርጠብ ከጎኑ ካለው ጠረጴዛ ውሀውን አነሳና ላይ የተቀመጠለትን ሀይላደንድ ውሀ በመክፈት እየተጎነጨ በተመስጦና በስሜት ትረካውን ቀጥሏል…፡
…በሁለተኛው ቀን ከጓደኞቼ ነጥለው ጠለፍኝ።አንድ መፅሀፍ ቅድስ ብቻ ነበር በእጄ የያዝኩት፡፡ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀኝ አልኩ።የጠለፍኝ ሰዎች ቋንቋቸው የማይገባ እጅግ ከሰው ተነጥለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የሚኖሩ 2መቶ የማይሞላ ቁጥር ያላቸው አባላት ያላቸው ጎሳዎች ናቸው።
ከወሰዱኝ በኃላ አንድ ጠባብ ጎጆ ውስጥ ጠርቅመውብኝ በራፍን ገንጥዬ እንዳላመልጥ ሁለት ጦር የቀሰሩ ጠባቂዎች በራፍ  ላይ  አስቀመጡ።መፅሀፍ ቁዱሴን ደረቴ ላይ ለጥፌ እኔ ፀልያለሁ...ያለማቆረጥ ከጌታ ጋር አወራለሁ።ሶስታ ቀንና ሶስት ለሊት  እዛች  ጠባብ ጎጆ  ውስጥ  አሳደሩኝ፡፡  በአራተኛው ቀን የተለየ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ውጭ ታላቅ  ክብረ  በዓል  ለማዘጋጀት  ትርምስ  ላይ እንደሆኑ ይታየኛል።‹‹ጌታ ሆይ  ተአምራትህን  በዚህ  ዝግጅት  ላይ  አድርግ›› እያልኩ ፀሎቴን ቀጠልኩ.. ሲጨልም ምቀምሰውን ምግብ አንድ ልጃገረድ ይዛልኝ መጣች፡፡ ጠባቂዎቹ ወደውስጥ እንድታልፍ ፈቀድላት...:: ጎምበስ ብላ ምግብን እያቀረበችልኝ
"አይዞህ"አለችኝ፡፡

‹‹ እንዴ ጌታ ስራውን መስራት ጀመረ ››አልኩ...አማርኛ ትችላለች..

"ለምንድነው የያዙኝ...?ከእኔ ምን ፈልገው ነው ?"ከእሷ ባነሰ ደካማ ድምፅ ጠየቅኳት።
"ለመስዎእትነት..ለአማልዕክቱ ሊያቀርብህ ነው" አለችኝ... ያልጠበቅኩትን መልስ ነበር ያገኘሁት…የጌታ ጥበቃ በዙሪያዬ እንዳለ ባምንም..የልጅቷ በዛን ሰዓት

ከአማርኛ  ችሎታ  ጋር  ስሬ  መከሰት  አንድ  ምልክት  እንደሆነ  ባልጠራጠርም
...ሰውነቴ በፍራቻ መራድ፤አፌም በድንጋጤ መድረቁ አልቀረም ነበር።"
👍795🥰4👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሷ እየተንደረደረች ወደቤቷ ገባችና ፎቁን ወጣች መኝታ ቤት ገባች፡፡ የሆነ ነገር አደናቅፎት እንዳትወድቅ እንኳን  መብራቱን  ማብራት  አልፈለገችም።በዳበሳ ከልጋዋ ላይ ወጣችና ጠርዙን ያዘች፡፡ ወደ ኮመዲኖ ተንጠራራች ቀን በጅምር ያቆመችውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ክዳኑን ከፍታ አንደቀደቀችው።

"እስኪ ይሄ ምስኪን ልጅ ምን አደረገኝ?"እራሷን እረገመች። ምነው እግሬን በሠበረው በማለቱ ወደእሱ በመሄዶ እራሷን ወቀሰች፡፡
….////…
ሳባ አሁን በዚህን ሰዓት 80ሺ ብር የተገዛ ባለ 2 ሜትር የተንጣለለ ግዙፍ አልጋ ጠርዝ ላይ ተኝታ  ያቺን ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበረችዋን  የዋህ  ንፅህ  ጉጉ ተስፈኛ ወጣት አብዝታ እየናፈቀቻት ነው፡፡አሁን ያላትን  ሀብትና  ንብረት  ሁሉ ከፍላ ይቺን ሚስኪን ወጣት ከነሙሉ ክብሯ፤ ንፅህናዋና፤ የዋህነቷ እንዲውም ከሙሉ ተስፋዋ ጋር ቢመልሱላት ዓይኗን ሳታሽ ነበር የምትስማማው፤ ግን ያንን ማድረግ እንደማይቻል ስታውቅት ተስፋ ቆርጣ ይበልጥ አንገት ያስደፋታል፡፡
ደግሞ ይህ ተስፋ መቁረጧ ጫፍ ላይ አድርሶ እርሷን እንድታጠፋ እና ካለችበት ቅዠት እንድትገላገል ቢያግዛት  ደሰተኛ  ትሆን  ነበር፡፡ግን  ህይወትን  በአዲስ መንፈስ አድሳ ከድባቴ እራሷን አላቃ ከሚወቅራት እራስ ምታትና ከሚያኮረማምታት የመንፈስ መሰበር ተላቃ አዲስ ህይወት ለመጀመር የሚያስችላት አቅም ለማግኘት ሆነ እስከዛሬ ባለፈችበት የሀጥያት  መንገድና የተበላሸ የህይወት መስመር የተነሳ እራሷን ተጠይፋ ከህይወት መዝገብ  ላይ በፍቃዷ እራሷን ለማሰናበት የሚያስችል ብቃትና ፅናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ያ ደግሞ በአየር ላይ አንገትን በገመድ ታንቆ እንደመንጠንጠል አይነት የሚያቃትት ስሜት ነው እንዲሰማት እያደረጋት ያለው፡፡
አሁን እንደዚህ ምስቅልቅል ባለ ህይወት ላይ ሆና ለሚያያት ሰው ምን ሆነሽ ነው
?ብለው ቢጠይቋት እንዲህ ሆኜ ነው ብላ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ የምትመልሰው ለሰሚው ሚዛን የሚደፋና ለእሷም እንዲያዝኑላት የሚያደርግ ምንም ምክንያት የላትም… ምክንያቱም ትክክለኛ ምክንያቷን(ነፍስ ገዳይነተዋን)መናገር አትችልም…ብትናገር ማረፊያዋ እስር ቤት ነው፡፡
እነዛን ሚስጥሮች የማያውቁ  ሰዎች ደግሞ‹‹ባፈቀረችውና ልቧን አሳልፋ በሰጠችው ሰው የመከዳት ችግር አልገጠማትም ..የገንዘብ እጥረት ወይም ኪሳራ ፍፅም የለባትም..የሆነ ወንጀል ሰርታ የተከሰሰችበት ጉዳይ ፈፅሞ የለም..የህክምና ምርመራ አድርጋ እንዲህ አይነት ቋሚ የጤና ችግረ አለብሽ ተብሎ አልተነገራት…ታዲያ ምንድነው እንዲህ የሚሰባብራት?›› ብሎ ቢያስብና ቅብጠት ነው ብሎ ፍርድ ቢሰጥ አይገርምም፡፡
እውነታው ግን አሁን በዚህ ወቅት የሳባ መንፈሶ ተሰብሯል ፤የመኖር ጉጉቷ ተንቆሻቁሾል፤በውስጧ ምንም አይነት  የደስታ  ቅመም  መመረት  ካቆመ ሰነባብቷል፡፡ የመኖርም  ሆነ  የመሞት  ፍላጎቷን  አጥታለች፡፡ማፍቀርም  ሆነ መፈቀር ሳይቀር ትርጉመ ቢስ ሆኖባታል፡፡በአጠቃላይ ስሜተ ቢስ እየሆነች ነው፡፡እንደሚታወቀው ስሜት ማለት የሠው  ልጅ  መንፈሳዊ  ወዝ  ነው።  የሰው ልጅ ህይወትን ጣፍጭና ወዝ ያለው የሚያደርገው የስሜቱ ውጣ  ውረድ ነው ። ሰው ሲከፍው ከላለቀሰና ሲደሰት ካልሳቀ ከፍተኛ የስሜት መሠበር እንዳለበትና ጠንካራ ህክምና እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።ጠንካራ ስሜት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው ደማቅና ከሩቅ ትኩረት የሚስብ ናቸው።ግን ደግሞ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲሰበሩም በትልቁና በቀላሉ ነው፧፡ለዚህ  ነው  የሠውን ስሜት መስበር አስጠሊታ ሀጥያት የሚባለው።
እለቱ ማክሰኞ እኩለቀን አካባቢ ነው።ሰራተኛዋ አለም የምትሰራውን ሰርታ ወደቤት ለመሄድ ስትወጣ ቀናውን በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ እንደወትሮው ሲያነብ አገኘችው፡፡ኮቴዋን ሲሰማ ቀና ብሎ ‹‹ልትሂጂ ነው?››አላት፡፡
‹‹አዎ ልሄድ ነው….ግን አንድ ነገር ላማክርህ ነበር፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ‹‹ምንድነበር?››ጠየቃት፡፡
‹‹የዚህች ልጅ ነገር በጣም አሳስቦኛል…ይሄው መኝታ ቤቷ ከተሸሸገች ሁለት ወር ሊደፍናት ነው..ምግብ አትበላ፤ መጠጣትና ..መተኛት ብቻ ነው ስራዋ…፡፡አሁንማ ሰውነቷ አልቆ አልቆ ስንጥር አክላለች..በዚሁ ከቀጠለች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መሞቷ አይቀርም፡››
‹‹የእሷ ነገር እኔንም አሳስቦኛል…..አንቺ ምን አሰብሽ?››
‹‹እንዴ ግራ ገባኝ ..ከቤት መውጣት እምቢ ካለች፤ ህክምናዋና ካቆረጠች፤ መብላትና መጠጣት ካቆመች..እራሷን ቀስ በቀስ እየገደለች እኮ ነው….አንድ ነገር ከሆነች ደግሞ እኔና አንተ መጠየቃችን አይቀርም.. በተለይ እኔ……በጣም አሳስቦኛል፡፡››
‹‹ቆይ ዘመዶች የሏትም እንዴ?››
‹‹አላት …አሰላ ናቸው እንጂ  ዘመዶች  አሏት  ፡፡እሷ  ግን  ያለችበትን  ሁኔታ ለማንም እንዳንናገር በጥብቅ ነው ያስጠነቀቀችኝ…ግን አሁን አሁን ምርጫ የለኝም..ግፋ ቢል ስራውን መልቀቅ ነው፣ እስር ቤት ከመግባት ስራዬን ባጣ ይሻለኛል…እንደምንም የእንጀራ እናቷን ስልክ አግኝቼያለሁ…ልደወልላት ነው፡፡››
‹‹እኔ የሆነ ነገር አስቤ ነበር››አላት ቀናው፡፡

‹‹ምን?››
‹‹አሁን አልነግርሽም…ግን አንድ ሳምንት ይፈጅብኛል..እንደምንም አንድ ሳምንት ጊዜ ስጪኝና ልሞክር… እስከዛ ምንም ለውጥ ካላሳየች እንዳልሺውም ትደውይላቸዋለሽ፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ እንደማሰብ አለችና‹‹..እሺ  ካልክ…እስከዛሬ  ያልሞተች  መቼስ በአንድ ሳምንት ውስጥ አትሞትም ››ብላ ተሰናበተችውና  ወጥታ  ሄደች፡፡ቀናው ወደ ነበረበት መቀመጫ ተመልሶ ተቀመጠና ማሰላሰል ጀመረ..ምን  አድርጎ ቀጣሪው ከገባችበት የመደበት ስሜት ሊያወጣት እንደሚችል አሰበ …ቢያንስ የተወሰነ ቀና ብላ ወደህክምና ክትትሏ እንድትመለስ ማድረግ እንዳለበት ወሰነና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ግቢውን ቆላለፈና   አነስተኛ ምንጣፋና አንድ መፅሀፍ ይዛ ወደ ትልቁ ቤት ገባ።
የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ውስጡ እየገፋፋው ነበር የከረመው ዛሬ  ደግሞ የአለም ንግግር በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አስገደደው…እርግጥ ከእሷ የሚያጋጥመውን መልስ ምን እንደሚሆን አያውቅም ግን ምንም ሆነ ምንም ለመጋፈጥ ወስኗል......ሳሎኑን አልፎ ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ ተያያዘው... መኝታ ቤቷን ቀስ ብሎ ገፍው፡፡ አንገቱን  አሰገገና  ወደ  ውስጥ  ተመለከተ... እንደዚህ ባለ ቅርበት ካያት  ብዙ  ቀናት  አልፈዋል....ፀጉሯ  ተንጨፍርሮና  እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ አስፈሪ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ሆዷ ከጀርባዋ የተጣበቀ ነው የሚመስለው ፤በጣም ከስታለች፤ አይኖቾ ኮርኒሱ ላይ እንደተሰካ ነው ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባና መልሶ ዘጋው።በዚህ ጊዜ አይኖቾን አንከባለለችና ወደእሱ ተመለከተች
..የሆነ ነገር እንድትለው ፈልጎ ባለበት ተገትሮ ቆመ...፡፡
ምንም አላለችውም..ወደጥግ ሄደና ግድግዳውን አስጠግቶ ምንጣፉን አነጠፈ... እንደብዲስት መነኩሴ እግሩን አጣምሮ ቁጭ አለ።መፅሀፍን ከፊት ለፊቱ አስቀመጣና እጇቹን አቆላለፈ...ከዛ ልክ እንደእሷ ፀጥ አለ...ልዩነቱ የእሷ ፀጥታ በድንዛዜ ሲሆን የእሱ ፀጥታ በንቃት ነበረ...
👍559🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ  ላይ  ረገጠችው…መላ  እሷነቷን  በፅሞና  ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ  የነበረው  የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና  ወደ  ውስጥ  ጎድጉደው  ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት  ግን  የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ  ለወራት  ችላ  የተባለው  የብልቷ  ፀጉር  በአስፈሪ  ሁኔታ   አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን  ዘረጋችና  አንገቷን  ጠምዝዛ  ብብቷን  ተመለከተች  ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡  ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ  እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና  ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና  የፀጉር  መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን  ታጥባና  ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት  ብንን  አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››

‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ  ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››

‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ  ማሳየት  ቢሆን  ምንም  አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም  ጋር  በገዛ  ምርመራ  ክፍሉ  የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን  ሰወርሽ….?እንዴት  እዲህ  ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር  ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››

ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ  እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››

‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››

‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››

‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡

ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና   ሲጨነቅ   የከረመው   ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን  ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››

‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›

‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…

‹‹እኔ  እንጃ  ማለት  ምን  ማለት  ነው…ህክምናው  ቢቀር  አንኳን  ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››

‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››

ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር  የለም….እንገናኛለን…››

‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››
👍697👏4🥰2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡

‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት

‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››

‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››

‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››

‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››

‹‹እንዴ…ከእናትና  አባትሽም  ቤት  የተሻለ  ቦታ  ነኝ  ነው  የምትይኝ…ይሄንን  ማመን አልችልም፡ ››

‹‹ነገርኩህ እኮ…››

‹‹‹እ ..ገባኝ››

‹‹ምኑ ነው የገባህ?››

‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሁለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››

‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››

‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ  ፎቶዎ ተጨናንቆል  ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››

‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››

‹‹አይ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ነኝ እድለኛ….ምንም ባላደርግላቸው እንኳን ማንም ፊት በኩራት አባዬ ብለው ይጠሩኛል፡፡በቀደም ለሊሴ ይሄ ፌስቡክ ነው ምን በምትሉት ነገር ላይ በተንዠረገገ ፂሜንና በጎፈረ ፀጉሬ የተነሳሁትን የተጎሳቆለ ፎቶ ለጥፋ አባዬ መልካም
👍8415🥰4👏4
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
:
:
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰሎሞን ሁለቱን ባለትዳሮች ፊት ለፊት አስቀምጦ እያወራ ነው፡፡‹‹የፈለገ ጥረት ብናደርግ ለእያንዳንዱ ብሎን የራሱን ትክክለኛ መፍቻ ካልተጠቀምን ልንፈታው አንችልም!! በህይወታችንም ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን ተረጋግተን ለችግሩ ትክክለኛ የመፍትሄ ሀሳብ ማስቀመጥና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ካልቻልን እንዲሁ ስንባክን እና በችግሩ ውስጥ ስንዳክር ነው የምንኖረው፡፡ይሄንን በስራ አለም በትክክል እየተገበራችሁ ውጤታማ እንደሆናችሁ አውቃለው…በትዳር ህይወታችሁስ?ዋናው ጥያቄ እሱ ነው፡፡››
አቶ ኃይለልኡል ተቀበሉት‹‹ገብቶናል…እንደምንም ብለን በመሀከላችንን የተፈጠረውን ክፍተት በማስወገድ እና ፍቅራችንን መመለስ እንዳለብን በደንብ ተረድተናል…አዎ እንደምታየውም ጥሩ መሻሻል እያሳየን ይመስለኛል፡፡››
ሰለሞን ቀጠለ‹‹ጥሩ ግን ፍቅር ብቻውን በሰላም ለመኖር በቂ አይደለም፡፡በመሀከላችው ምንም አይነት ጥል የሌለ ጥንዶች በመሀከላቸው ፍቅር እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም…እንደዛውም ዘወትር በነጋ በጣባ የሚጣሉና የሚጨቃጨቁ ጥንዶችም በመሀከላቸው ያለው ፍቅር አልቋል ወይም ቀዝቅዞል ማለት አይደለም….ከዛ ይልቅ እንዴት እርስ በርስ እንደሚግባቡ እና አንዱ የአንዱን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዳ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡ስለዚህ አሁን መልሳችሁ ማደስ የሚገባችሁ ፍቅራችሁን ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችሁንም ጭምር ነው፡፡አንዳችሁ ሌላችሁን በጥልቀት ለመረዳት እስከምን ድረስ ለመጓዝ ትፈቅዳላችሁ?ይሄ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡››

ወ.ሮ ስንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ‹‹ትክክል ነህ ልጄ… ለፍቀራችን መበላሸት ዋናው ምክንያት እንደውም እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችን ስለተበላሸ ነው….እሱም እኔን እኔም እሱን ለመረዳት ምንም የምናደርገው ጥረት አልነበረም…ሁለታችንም እርስ በርስ እንከን ነበር የምፈላለገው….ያንን በደንብ ተረድቼለው፡፡››
‹‹አዎ ይሄ ችግር የእናንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ባለትዳር ችግር ነው…አንድ ሰው በፍቅር ሲወድቅ በመጀመሪያ ስለራሱ ምቾና ደስታ እንጂ ስላፈቀረው ሰው ደህንነት አይደለም የሚጨነቀው…ሁለቱም ተጣማሪዎች በጋብቻ ጥምረት ውስጥ ለእነሱ የሚመች ሰፋ ያለ ግዛት ቶሎ ብሎ ለመያዝ ይጣጣራሉ…ሁለቱም ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው ፍትጊያ ይፈጠራል…አንዱ የሌለኛውን ድምበር ማለፍ…ይሄኛው የዛኛውን ቀይ መስመር መደፍጠጥ ይጀምራል……ከሁለት አንዱ በፍጥነት ነቅቶ ወደኃላ በመመለስ መረጋጋት ውስጥ ካልገባ ችግሩ መስመር ይስታል፡፡
እኔ 25፡50፡25 የሚል ፕሪንስፕል አለኝ፡፡በትዳር ውስጥ እሷ(ሚስትዬው) እሱ(ባልዬው) እና እነሱ (ባልና ሚስቶቹ)አሉ፡፡እና ስሜታቸው፤ፍላጎታቸው፤የህይወት አላማቸው ወ.ዘ.ተ ተጠቅልሎ መቶ ፐርሰን ቢሰጠው፡፡እሷ የግሏ ፍላጎት በግሏ የሚያስደስታት ነገር፤ መዝናኛ ቦታ፤ጓደኞች፤ 25 ፐርሰንት ትይዛለች….እሱም ለብቻው 25 ፐርሰንት ይይዛል፡፡50 ፐርሰንቱ ግን የጋራቸው ነው፡፡በጋራ የሚያቅዱበት፤በጋራ የሚሰሩበትና የሚለፉበት ቤት መስራት፤ልጆች መውለድና ማሳደግ…ወዘተ፡፡ሁል ግዜ ተሰፍሮ 25፤50፤25 ላይሆን ይችላል፡፡በተለይ ሴቶች ከእነሱ 25ፐርሰንት 10ሩን ወይም 15 ቱን ቆርሰው ለጋራቸው ያውሉታል…ወንዶች ደግሞ ከሞላ ጎደል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከጋራቸው ላይ ቆረስ አደርገው የእነሱን 25 ፐርሰንት 30 እና 40 አንዳንዴም ከ50 በላይ ያደርሱታል..የዛን ጊዜ የጋብቻው ባላንስ ይናጋል፡፡ምሰሶው መነቃነቅ ይጀምራል..እርማት ካልተደረገለት ጋብቸውን እያከሳ ይሄድና መጨረሻ ያከትምለታል፡፡…የምናገረው ግልፅ ነው አይደል››
‹‹አዎ..በጣም ግልፅ ነው፡፡››
‹‹በምሳሌ ይበልጥ ለማስረዳት አንድ ገጠር የምትኖር አክስቴ ከአስር በላይ ባሎች አግብታለች፡፡ግማሹን እነሱ ናቸው የፈቷት ግማሾቹን እራሷ ነች ያደረገችው፡፡ከሁሉም ግን የሳበኝን አንደኛውን ልንገራችሁ፡፡አገባሁት አለች..በጣም ሰላማዊ ..ምንም አይነት ክፉ ነገር ማይናገር…የጠየቅኩትን ሁሉ የሚያሞላልኝ ሰላማዊ ሰው ነበር አለች፡፡በፊት ከለመደቻቸው ተደባባዳቢ እና ተጨቃጫቂ ባሎች ጋር የትኛውም ፀባዩ የሚገጥም

አልነበረም፡፡ግን ብዙም ሳይቆይ ሰለቻት….ሁሉ ነገር ዝም እና ጭጭ ያለ ሆነባት…በቃ ግንኙነታቸው ውስጥ ነፍስ አጣችበት ፡፡አንድ ቀን በለሊት ተነሳና በሬዎቹንና ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ወደማሳ ወጣ …ሲሄድ ቁርስም አልሰጠችውም..ምሳም ይዛ መሄድ ቢገባትም አልወሰደችለትም..ጭራሽም አልሰራችም…በጣም የባሰው ነገር ደግሞ የቤቱን እቃ ብረትድስት ፤ሰሀን ፤ብርጭቆ አንድም ሳታስቀር ከቤት ጀምራ የቤቱን መግቢያ ደጃፍ…ወለሉን ጠቅላላ አዝረክርካ እና ሞልታ ኩርሲ ላይ ቀጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር ፡፡.
ከዛ መጣ…ከውጭ ጀምሮ ያዝረከረከችውን እቃ አንድ በአንድ ጎንበስ ብሎ እየለቀመ…‹‹እታዋቡ …ሰላም ነሽ….?ምንም አልሆንሺብኝም አይደል….?››እያለ ሁሉንም እቃ ወደመደርደሪያ መልሶ ስሯ ቁጭ ብሎ በልምምጥ ጭንቅላቷን መዳበስ ጀመረ..
ከዛ ይህቺ አክስቴ ምን ብታደርግ ጥሩ ነው‹‹ ብድግ አለችና ሻንጣዋን ይዛ‹‹እንዴት ቁርስ አላበላሁህ ..ምሳ አለመጣሁልህ….ቤቱን እዲህ አዝረክርኬ ነው የጠበቅኩህ..ምን እስካደርግህ ነው የምትጠብቀው…?ምንም አይነት የወንድነት ወኔ የለህም እንዴ…?ሁለት ሴት አንድ ቤት አይኖርም… ነውር ነው››ብላ ጥላው ወጣች..በዛው ፈታችው ፡፡አያችሁ ትዳር በጣም ውስብስብ ግንኙነት ነው፡፡የበዛ ጭቅጭና ጥል ብቻ ሳይሆን የበዛ ሰላምና ፀጥታም ሊያፈርሰው ይችላል፡፡፡ዋናው በሁሉም ነገር ሚዛን ጠብቆ መጓዝን መልመድ ነው፡፡››
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደና ፊትለፊቱ ካለ የታሸገ ውሀ በማንሳት አንዴ ተጎንጭቶለት ከንፈሩን አረጣጠበና ንግግሩን ቀጠለ፣እነሱም ልክ በቅርብ ፈተና እንደደረሰበት ቸካይ ታማሪ በጥሞናና በትኩረት እየተከታተሉት ነው‹‹አሁን ልብ በሉ፣ ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደለም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቅ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው.. በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ነገር ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር ለብንም፡፡እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት

በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራችን ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ጋና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት
👍7912
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..

የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ  መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ

እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡
👍735👎2