አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
⚫️🎈የእናቴ ልጅ🎈⚫️
🎈ክፍል ሃያ አራት🎈
⚫️🎈⚫️🎈⚫️🎈⚫️
አንዳንድ ጊዜ አለ ልብህ አስቀድሞ አንዳች አደጋ እንደመጣ እና አስቀድመህ እንድትጠነቀቅ  የሚያሳስብህ ጊዜ ። ጭንቅ ጭንቅ ይልሃል፣ ፍርሃት ይወርሃል፣ ያቁነጠንጥሃል ፣ ብቻ እንዲ አይነት አጋጣሚ አለ ።
አቤል ከወጣ ጀምሮ አይምሮዬ አላረፈም ማን ይሆን የጠራው ፣ምን ሊፈጠር ይሆን እያልኩ ማሰቤን አልተውኩም ። እናቴ ከነደግነሽ ጋር እየተጫወተች አልፎ አልፎ ወደኔ አየት ታደርጋለች  በግንባሬ ወደ ውጭ ባሳያትም ኮስተር እያለች አርፈህ ተቀመጥ አይነት ምልክት ትሰጠኛለች ፡  ባዩሽ እላዩዋላይ እንደተጣበቀች እንቅልፍ የጣላትን ማማን ፀጉር እያሻሸች በደግነሽ ወሬ ተመስጣ ታዳምጣለች ፡  እኔ ግን የጫወታቸው እርዕስ እንኳ ምን እንደው በቅጡ አላዳመጥኩም ፡ ከረጅም ቆይታ በዋላ ስልኬ እሪ ብላ ስትጮህ እንዴት ከቂጤ ብድግ እንዳልኩ ፡እንዲ ደንግጬ አላውቅም ። እናቴ የኔ ድንጋጤ ተጋብቶባት
"ውይ ናቲዬ ልጄ እኔ ልደንግጥ "አለች የሷ ድንጋጤ እራሱ እያሳበቀባት ። ስልኬን ከጩኽቷ ለመገላገል አነሳዋት "ሃሉ "አልኩኝ ። በስልኩ ውስጥ የሚንሾካሸክ ድምፅ መጣ
"ናታኒየም ነህ"አለኝ
"አዎ ነኝ ማን ልበል "አልኩት የልቤን ምት ለመቆጣጠር እየሞከርኩ
"እኔን አታውቀኝም እባክህ መምጣት ትችላለህ ወንድምህን ይዘውታል  "አለኝ ። አይኖቼ ፈጠጡ
"መጣው ስልኩን እንዳትዘጋው "አልኩት ፡የማላውቀውን ሰው ። ይህን ያደረኩት እናቴን ላለማስጨነቅ ነበር  ሁሉም ወደኔ ሲያፈጡ ።
"ተረጋጉ የአቤልን መሄድ ድንገት የሰማ ጓደኛው ነው እኔንም ስለሚያውቀኝ ፡ወቀሳ ሊያቀርብልኝ ነው ለማንኛውም መጣው በሩ ላይ እየጠበቀኝ ነው እንደውም አቤልን በዛውም ይዘነው እንመለሳለን አታስቡ "ብያቸው ወጣው እናቴ ለማመን የተቸገረች ይመስላል በቀላሉ የምትሸወድአደለችም በእርግጥ ።
ከግቢ እንደወጣው ያልተዘጋውን ስልኬን ወደጆሮዬ አስጠግቼ "እሺ ማነህ አንተ ተናገር አሁን ከቤት ወጥቻለው  በግልፅ ምንድነው የሆነው "አልኩት ማነው እንዲ የተዳፈረኝ እኔ እኮ ናታኒየም ግዛው ነኝ ፡እንዴት ወንድሜን ይይዙታል ለዛውም በዚ ቀን እንዴት በንዴት ጦፍኩ
"እኔ ማንነታቸውን አላወቅኩም እኔና አቤል ተገናኝተን ነበር ሰላም ብሎኝ እንዳለፈ ጩኽት ሰማው ወደዋላዬ ስመለስ ሦስት ሰዎች ናቸው ይዘው ሲያዋክቡት አየው  በጣም ስለደነገጥኩ ጥጌን ይዤ ዝም አልኩ "አለ የሚያወራውን ለመመርመር ጊዜ አልነበረኝም እንዳለ ጭንቅላቴ ወንድሜጋር ነው አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት ልደርስለት ብቻ ነው ያሰብኩት
"እና ወዴት ነው የወሰዱት በጋሽ ከድር ሱቅ በኩል ወደታች እየገፈታተሩ ነው የወሰዱት በፍቃደኝነት እየሄደ ስላልሆነ ልትደርስባቸው ትችላለህ ፍጠን እኔም  እዛው አካባቢ ነኝ "አለኝ ።ልቤ ፍጠን በሚል ምቱን ጨመረ ደሞ ለክፋቱ የመንገድ መብራት ጠፍቷል ፡ እየተወለካከፍኩ እሮጥኩ  ። ስሮጥ ከዋላዬ ሰው የተከተለኝ መሰለኝ እና ለአፍታ ዞር አልኩ ስዞር ቀስብሎ የሚራመድ ተለቅያለሰው ያየው መሰለኝ ።ችላ ብያቸው እሮጥኩ በስልክ የተጠቆምኩቀት አካባቢ ደረስኩ ጨለማው ከማየሉ ውጪ ምንም ነገር አይታይም  ። እጠብቅሃለው ያለው በስልክ ያናገረኝም ሰው የለም ፡ ነር ግን በጨለማው ውስጥ ዝምብዬ እሮጥኩ ወንድሜን በደስታው ቀን ምን ሊያደርጉብኝ ነው ። እያልኩ  ብዙ ከደከምኩ በዋላ ለምን ስልክ አልደውልም ብዬ ስልኬን ከኪሴ ለማውጣት ቆም አልኩ ። በዛው ቅስበት አንዳች ነገር አናቴ ላይ አረፈ ምቱ አይለኛ ስለነቀረ መቋቋም አልቻልኩም ተንገዳግጄ መሬት ላይ አረፍኩ ፡ ከተኛውበት ሆኜ ለማየት ሞከርኩ ፡ሁለት ወጣቶች ናቸው በግልፅ አልታዩኝም ፡ ጠጋ ብለው ። ካዩኝ በዋላ በቃ በትክክል መጨረስህን እርግጠኛ ሆነህ ደውልልኝ እኔ መሄድ አለብኝ ፡ አለው አንደኛው እየተንሾካሸከ ቢሆንም ድምፁ አልጠፋኝም ፡ መናገር ግን አቃተኝ ዕንባዬ ወረደ አለቀስኩ ከምር .......


,ደራሲ Unknown


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍93😢285👏3🔥1🤔1
#ህያብ


#ክፍል_ሶስት


#ድርስት_ኤርሚ

እና ሁሉም ነገር እንደዚህ ሊቀጥል ነው? አይሆንም! እናቴም እኔም አንገታችንን ከምንደፋ የሆነ ሀሳብ በውስጤ መጣልኝ። እንደማደርገው እርግጠኛ ሆንኩ....
ቤት እንደደረስን ቁጭ አድርጋ የምክር ናዳ አወረደችብኝ ግን አንዱንም ከልቤ ሆኜ አልሰማኋትም..... እንዴት እንደማደርገው እቅድ እያወጣሁ ነበር።

ሁሌም ማክሰኞ ቀን እናቴ ገበያ ትሄዳለች። ያሰብኩትን ለማድረግ ከዚህ ቀን ውጪ የተመቸ እንደሌለ አውቃለሁ ስለዚህ ማክሰኞን መጠበቅ አለብኝ።
....
የምጥ ቀን እሁድ አለፈና ሰኞ መጣ.... ብርድ ልብሴን ክንብንብ ብዬ የተኛሁ መሰልኩ። እማዬ ቤት ውስጥ ውዲህ ወዲያ ስትል እንቅስቃሴዋ ይሰማኛል። አጠገቤ መጣችና
"አንቺ ሚጣ.... ሚጣዬ..... ሚጣ" ብላ ጠራችኝ። ባልሰማ ዝም ብያት የተኛሁ እንዲመስል ጣርኩ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤት መሄድ በጓደኞቼ እና በሌሎች ተማሪዎች መዋረድ አልፈልግም።

እኛ ላለንበት ማህበረሰብ ይሄ ከባድ ነገር ነው። መደፈሬን የሚያውቀው ሳይቀር
"የወይንሸት ልጅ ዲቃላ አረገዘች.... ድሮም ሴት ያሳደገው" ብለው እኔን ብቻ ሳይሆን ብርቱዋን እናቴንም ጭምር ነው የሚሰብሩብኝ

"አንቺ ሚጣ... ተነሽ እንቅልፍ እንዳልወሰደሽ አውቃለሁ..." አለችኝ። ምንም ማምለጫ የለኝም ፊቴን ቀስ ብዬ ገለጥኩና አጠገቤ የቆመችውን ድንቅ ሴት ከታች ወደላይ አየኋት..... እምዬን.... እናቴን። ጎንበስ ብላ በስስት እያየችኝ ነው። ከተኛሁበት ቀና ብዬ ቁጭ እንዳልኩ አጠገቤ መጣችና ጥምጥም ብላ አቀፈችኝ።

"ልጄ የኔ ስስት.... አለሜ እኮ አንቺ ብቻ ነሽ.... በዚህ እድሜሽ እንደዚ ስብር አትበይብኝ። ምን ያክል እንደሚያም ካንቺ በላይ ይገባኛል። ህመምሽ ካንቺ የበለጠ እኔን ያመኛል። ነገር ግን ቁጭ ብለን በእንባ እና ያለፈውን መራር ጊዜ በማሰብ ነጋችንን አናጨልመውም ልጄ ትማሪያለሽ ልክ እንደምትመኝው ዶክተር ትሆኛለሽ..."

"እማ እኔ ትምህርት ቤት አልሄድም" እንባዬ ከአይኔ ክልብስ አለ። እየተንሰቀሰኩ አለቅስ ጀመር።
"አይ እንግዲህ የምን ለቅሶ ነው" አለችኝ ቆጣ ብላ ይሄን ቁጣዋን አውቀዋለው ምናባሽ.... የታባሽ..... የሚባለው አይነት ቁጣ አይደለም። ቃሏ እና ፊቷ ላይ "መፍትሄ አለው" ከሚል መልዕክት ጋር ነው የምትናገረው። ለቅሶዬን አቁሜ የምትለውን ለመስማት ተመቻቸሁ።

"ልብ ብለሽ ስሚኝ የኔ ልጅ...."
በሚገባኝ ቋንቋ አስረዳችኝ።

ሙሉ ለሙሉ ነው ሀሳቤን ያስቀየረችኝ የኔ እቅድ የነበረው ገበያ ስትሄድልኝ የገዛሁትን የአይጥ መርዝ ጠጥቼ ይህችን አለም መሰናበት ነበር። ንቁዋ እናቴ ግን እቅዴን ሁሉ ቀድማ ደረሰችበት። አዲሱን እቅዷን ከነገረችኝ በኋላ እንዲህ አለችኝ።

" ያቀድሽውን ሁሉ ደርሼበታለሁ ሚጣ.... መርዝ ልትጠጭ ነበር አይደል" ክው ብዬ ነው የደነገጥኩት
........

"እንዴት ሆኖ ከኔና ባለሱቁ ውጪ እኮ መግዛቴን የሚያውቅ አልነበረም" አልኳት ምን ያክል እንደምትደነግጥና ልታዝንብኝ እንደምትችል እያሰብኩ... ፊት ለፊቴ ያለችው ሴት ግን ፍፁም መረጋጋት ነው የሚታይባት

"ባለሱቁ ባንዴ ሶስት ስትገዢው ተጠራጥሮ ነው። በመንገድ ሳልፍ ጠርቶ የነገረኝ አልዋሽሽም እንደሰማሁ ምድር ነበር የከዳችኝ... ቶሎ ብዬ ቤት ሰመጣ በረንዳ ቁጭ ብለሽ አገኘሁሽ ያኔ ወደቤት ገብቼ ከደበቅሽበት ፈልጌ አገኘሁትና ወሰድኩት....."

"ይቅርታ እማዬ ሁሉም ነገር ጨለመብኝ ከኔ ብሶ አንቺም አንገትሽን ደፋሽ..."

"ይገባኛል ሚጣዬ አሁን ስለ እቅዱ ምን ትያለሽ...." ብላ ሀሳቤን ጠየቀችኝ። እናቴ ለኔ እንዲህ ናት አስፈላጊ ያለችው ነገር ላይ ምን ታስቢያለሽ ብላ ታማክረኛለች። ምንም እንኳን ከልቤ ባልሰማት............
..........ወይም እሷ እያወራች ለጨዋታ ጓደኞቼ ሲጠሩኝ ሳላስጨርሳት ሮጬ ብሄድ..........
....... ወይም ደግሞ የልጅ ሀሳቤን ነግሪያት ሆዷን ይዛ ፍርፍር ብላ ብትስቅ... እናቴ ልጅ ናት ብላ ልትነግረኝ እንደሚገባ ያሰበችውን ለኔ ከመንገር ወደ ኋላ አትልም። በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ስሄድባት

" ምን ትያለሽ እያልኩሽ ነው ሚጣዬ" አለችኝ ዘልዬ ጥምጥም አልኩባትና

"እጅግ በጣም ምርጥ ሀሳብ ነው ቶሎ ብለን እናድርገው አልኳት

"ኦ ኦ ልጄ እስከምትወልጂ ድረስ እንደፈለግሽ መዝለልና መንፈራገጥ የለም። በይ አሁን ተነሽ ቁርስ እንብላና ያልኩሽን እናደርጋለን።

ለብቻዬ ሌላ ጀንበር የወጣችልኝ መሰለኝ ...... ብሩህ ተስፋ.....

የተሳፈርንበትን አውቶብስ መስኮት በትንሹ ከፈትኩት፤ በመስኮቱ የሚገባው ቀዝቃዛ አየር ከነፋስ ጋር ተቀላቅሎ በጆሮዬ ላይ ቢያፏጭም ምቾት አልነሳኝም። በመስታወት ውስጥ አሻግሬ ሰማዩን ስመለከት ፀሀይ ደም የተነከረ ሸማ መስላ ከወደ ምስራቅ ብቅ ማለት ጀምራለች። በፎቶግራፍ መቅረት ያለበት ድንቅ የተፈጥሮ ውበት። አይኔን እድማሱ ላይ ሰክቼ በራሴ ከቀናት በፊት የነበረውን ነገር ማስታወስ ጀመርኩኝ።
................

ልክ እንደዛ ስብር እንክትክት ብዬ በነበረበት ሰዓት...... ራሴን ላጠፋ ጫፍ በደረስኩበት ሰዓት..... ሀሳቤን አስቀይሮ በደስታ ያስፈነጠዘኝ የእናቴ እቅድ ይህ ነበር።

" ሁሉም ሰው የሚያውቀው የአባትሽ ወንድም አጎትሽ ያለው አዲስ አበባ እንደሆነ......." አላስጨረስኳትም

"አዎ ግን የሱ እዛ መሆን ለምን ይጠቅመናል"

"እዛ የምንሄደው እሱ አንቺን ለማስተማር ጠርቶሽ እኔ ደግሞ ካንቺ አልለይም ብዬ ነው አሉ.... ይህን ለሚጠይቀን ሁሉ እንነግራለን"

"እሺ ግን መቼም አጎቴ ጋ እንሂድ አትይኝም አይደል" አይን አይኗን እያየሁ ጠየኳት

"ለጊዜው የምናርፈው እሱ ጋር ነው ትላንትና ማታ ሱቅ ሄጄ ደውዬለት ነበር ባይዋጥለትም ሁሉንም በዝርዝር ነግሬዋለሁ"

"ምን እያልሽ ነው እማ... የወንድሜ ልጅ ብሎ አንድ ቀን እንኳን ዞር ብሎ ላላየኝ.... አንቺን ሳይቀር ወንድሙን እንደገደልሽበት ለሚቆጥረው.... ለሚጠላን ሰው ነገርሽው"
አልኳት ያልጠበኩት ነገር ነው

"አዎ እኔም አንቺም ይህን ተፅዕኖ መቋቋም አንችልም። ይሁን ብንል እንኳን የኔ ችግር የለውም አንቺ ግን ይከብድሻል ለህክምና ክትትሉም ሆነ ለትምህርትሽ አዲስ አበባ ይሻልሻል...."

"ግን እዛ ሄደንስ ምን ሰርተን እንዴት ሆነን ልንኖር..." ግራ ግብት አለኝ

" እሱ እያሳስብሽ እኔ እናትሽ ላንቺ አላንስም አንቺንም ልጅሽንም ማኖር አይከብደኝም ዳገት ወጥቼም ሆነ ቁልቁለት ወርጄ ህልምሽን እንድታሳኪ አደርግሻለሁ። ታዲያ ለዚህ ያንቺ ጥንካሬ ወሳኝ ነው። በይ አሁን ለጠየቀሽ ሁሉ ካልኩት ውጪ እንዳትናገሪ ነገሮችን ላስተካክልና በጥቂት ቀን ውስጥ እንሄዳለን።

ከሀሳቤ ስመለስ እናቴን ዞር ብዬ አየኋት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ናት።
መስኮቱን ተደግፌ አይኔን አድማሱ ላይ ተከልኩ

፧፧
ከኔ አካል ቅጥነት ጋር ሲነፃፀር ሆዴ ትልቅ ሆኖ ላየው ይሰቀጥጣል። ምጤ መቶ ሆስፒታል ገብቻለሁ
"አይዞሽ በርቺ..... ግፊ.... አይዞሽ እንደሱ..... በርቺ..... ግፊ" ብዙ ጊዜ ደጋግመው ቢሉኝም ያለኝን አቅም አሟጥጬ ባምጥም ልጄ ሊወለድ አልቻለም። እኔ ግን እቅት ድክም አለኝ የሚሉት በሰመመን ይሰማኛል...

"የልብ ምቷ በጣም እየወረደ ነው ባስቸኳይ ዶክተር ፋሲልን ጥሪ" ልሞት ነው ማለት ነው። የሰዎች መሯሯጥ ድምፅ ተሰማኝ ትንሽ ቆየት ብሎ

"በአስቸኳይ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል አስገቧት ይህቺን የምታክል ትንሽ ልጅ እንዴት በምጥ እንድትወልድ ታደርጋላችሁ..."
👍568🥰2🤔1😢1
"ይቅርታ ዶክተር ፋሲል እናቷ ልትፈቅድልን አልቻለችም"
በሆስፒታል አልጋ እየገፉኝ እየወሰዱኝ እያለ አይኔን ለመግለጥ ሞከርኩ እናቴን በጭላንጭል አየሁዋት የአልጋውን ጠርዝ ይዛ በለቅሶ እየተከተለችን ነው የሆነ ክፍል አስገቡኝና በሩን ዘጉት ለመጨረሻ ጊዜ የሰማሁት የእናቴ ድምፅ

"ልጄን አድኑልኝ.....ልጄን"

እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ ይሰማኛል
"ከሁለት አንዳቸው አይተርፉም ካልፈጠንን ግን ልጅቷንም በሆዷ ያለውንም ነው የምናጣው... ፍጠኑ.... "

በጭንቅ ግራ ቀኝ ስወዛወዝ ከፊት ለፊቴ ያለው የተሳፋሪ ወንበር ላይ ተደፋሁ። ግንባሬን የመታኝ ወንበር ካለሁበት አስፈሪ ህልም ቀሰቀሰኝ.....ተመስገን በህይወት አለሁ።

እጄን ሰድጄ ሆዴን ዳበስኩት አሁንም ያቺ ትንሽዬ እብጠት ነው ያለችው።

ረዳቱ ጮክ ብሎ"ለምሳ ሀያ ደቂቃ ከዚህ በላይ መቆዬት አይቻልም" እለ። እናቴን ዞር ብዬ ሳያት ወደኋላ ለጠጥ ብላ ተኝታለች። እሷም እንደኔ አስፈሪ ህልም እያየች ይሆን? ትከሻዋን ይዤ ወዝወዝ ሳደርጋት ነቃች።

አውቶብሳችን ሲቆም ወርደን ምሳ በልተን እና የሚያስፈልገንን ሸማምተን ተመለስን። ከኔ በላይ እናቴ ፊት ላይ የማየው ተስፋ እና ደስታ አቅሌን ሊያስተኝ ደርሷል። ወንበሩ ላይ እንደተቀመጠን አንገቴን ወደሷ ስባ እቅፍ አደረገችኝ..... ልብ ሰርስሮ የሚገባውን የእናት ጠረኗን አሸተትኩት። "አሁን ማን ሊያቆመኝ ይችላል" አልኩ በውስጤ.... ከፊቴ ደጀን ሆና ወኔ ብርታት የምትሰጠኝ.... ሀዘኔ ከኔ በላይ የሚያሳዝናት በደስታዬ የምትደሰት ችግሮቼን ቀድማ የምትጋፈጥልኝ እናት እያለችኝ..... እኮ ማን?

፧፧፧፧፧

ከወራት በኋላ

አጎቴ ያሰብኩትን ያክል አልጨከነብንም። የራሳችንን ቤት ተከራይተን እስክንወጣ አንድ ክፍል ቤትና ምግባችንን ሰጥቶን ነበር። እኛም ብዙ ጊዜ ሳናስቸግረው ገጠር ያለውን የአባቴ ቤተሰብ ማለትም የአያቶቼ ውርስ የሆነውን የእርሻ መሬት ብዙ አመት መከራዬት ለፈለገ ሰው አከራየንውና ጥሩ ገንዘብ አገኘን። እማዬ ጊዜ ሳታጠፋ ነው በብሩ ከጀበና ቡና ጋር ጠዋት ቂንጬ ጨጨብሳ እና አንዳንድ ለቁርስ የሚሆኑ ምግቦችን ማታ ደግሞ ድንች እየቀቀለች መሸጥ የጀመረችው። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ብዙ ደንበኞችን ማፍራት ቻለች። ስራው ትርፋማ እየሆነ ሲመጣ የራሳችን ቤት ተከራይተን ከአጎቴ ቤት በሰላም ወጣን።

፧፧፧፧፧፧
በቀጫጫ እና ባልጠነከረ ሰውነቴ ላይ የሆዴ ትልቅነት ሲታይ ልክ በህልሜ እንዳየሁት ያስፈራል "አምላክ ሆይ ህልሜን እውን አታድርግብኝ" በልቤ ፀለይኩ

በምጥ መውለድ አትችልም ተብሎ ስለተወሰነ በቀዶ ጥገና ልጄን ወለድኩ። እነሱ ባይሉም እንኳን በምጥ አልወልድም ብዬ ኡ ኡ ነበር የምለው። ህልሜማ እውን አይሆንም

ሆዴ ውስጥ እያለ እንደ እንቅፋት እያሰብኩ እጠላው የነበረን ልጅ አምጥተው ክንዴ ላይ ሲያስቀምጡልኝ ስፍስፍ የሚያደርግ ስሜት ተሰማኝ። ሴት ልጅ ናት እናቴ ሀዘናችንን የምንረሳብሽ ስትል ስሟን ምናሴ አለቻት። ልጄ ትንሽ ጠንከር ስትልልኝ ትምህርቴን ካቆምኩበት ሰባተኛ ክፍል ቀጠልኩ። ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራትም አመታትን እየወለዱ የአስራ ሁለተኛ ክፍል(የዩንቨርስቲ መግቢያ) ፈተናን ተፈተንኩ።

ልጄም ልክ እንደ እኔ እሳት የላሰች ጎበዝ ተማሪ ሆናልኛለች። ከሷ ጋር ስሆን ቦርቄ ያልጨረስኩት ልጅነቴ ይመጣብኛል እና ሁሌም ቢሆን ከልጄ ጋር ልጅ ነኝ። ያለፈኝን ህይወት በሷ እየካስኩ እንዳለሁ ይሰማኛል።

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ..

ይቀጥላል...
👍66😁32
🎈💰የእናቴ ልጅ💰🎈
💰ክፍል ሃያ አምስት💰
🎈💰🎈💰🎈💰🎈
ጨለማውን ፈራውት አፉን ከፍቶ ሊበላኝ የተዘጋጀ መሰለኝ ፡ ለማንም የማይመለሰው ልቤ ተልፈሰፈሰብኝ ፡ እናቴን ሳስባት ደሞ ይበልጥ ሆዴ ባባ ።አቅም አጥቼ በተዘረርኩበት መሬት ላይ ሆኜ ስለሷ አዘንኩ ። ደጋግማ አስጠንቅቃኝ ነበር 'ወንድምህን መውደድ ትችላለህ ግን እንዳታምነው ተጠንቀቅ ከኔ ከእናቱ የበለጠ ወዳጅ የለውም ነገር ግን ለኔም አይመለስም' የሚለው የናቴ ንግግር ጆሮዬላይ አቃጨለ ፡ እራሴን ለማበረታታትና ለመነሳት ሞከርኩ  ነገርግን ተህዛዝ የተቀበለው ልጅ በርግጫ ብሎ አስተኛኝ ምቱ አይለኛ ነው  በጣም አመመኝ ጥርሴ ተናጋ ከአፌ ደም ሲፈስ ይሰማኛል ።
"አዝናለው እኔ እንዲ እንዲሆን አልፈለኩም ፡የወንድምህ ትህዛዝ ነው ፡ እንዲ ካላደረኩ ደሞ የማጣው ነገር አለ "አለኝ ።ድምፁን አወኩት ፡በስልክ ወንድምህን ይዘውታል ያለኝ ሰው ነው ። በራሴ ተናደድኩ እንዴት የእናቴን ማስጠንቀቂያ ችላ አልኩ ፡ይህ ሰው ስልኬን ከየት አምጥቶ ሊደውል ይችላል ።አቤል እስካልሰጠው ድረስ ፡እንዴት አልመረመርኩም ።
"ይኽውልህ ወንድም በፍፁም ወደውጪ የመሄድ እቅድ የለውም እሱ የሚፈልገው እዚሁ ቀርቶ ለብቻው የእናቱ ወራሽ መሆን ብቻ ነው  ያደሞ አንተ እስካለህ አይሆንም ስለዚህ አንተ ዞር ማለት አለብህ ለዚ ደሞ ከኔ ጋር ስምምነት ደርሰናል ፡ ከሚያገኘው ውርስ አንድ ሦስተኛው የኔ ነው የሚሆነው ፡ ይህን ስምምነት  እውን ለማድረግ ደሞ እኔ ስራዬን መጨረስ አለብኝ ፡እና በጣም ይቅርታ አድርግልኝ በሰላም ልሸኝህ እገደዳለው "ብሎ ከለበሰው ኮት ኪስ ውስጥ በጨለማውስጥ የሚያብለጨልጭ ስለት አወጣ ፡እናም በአይል ወደኔ ሲሰነዝር አይኔን ጨፈንኩ ፡ ስለቱ ግን ሲወድቅ ተሰማኝ እሱም ከፍተኛ ድምፅ አሰማ ፡በፍጥነት አይኔን ገለጥኩ ፡ለማመን በሚከብድ ሁኔታ ፡ባለጩቤው የአቤል ቅጥረኛ መሬት ወድቋል ፡በሱ ፈንታ ሌላ ሰው ወፍራም ዱላ ይዞ ወደኔ አጎንብሶ እየነካካኝ ቁና ቁና ሲተነፍስ አየው ፡ ሰውዬው ከወደቀው ሰው የሞባይል ስልኩን ወሰዱና ፊቴላይ አበሩብኝ እና "ልጄ የኔ ልጅ ናቲ ደና ነህ ደርሼልሃለው ለትንሽ ነው እኮ የቀደሙኝ  አብሬህ መሮጥ ባለመቻሌ ነው ወይኔ "አሉ ።አወቅኳቸው ቤታችን የሚመጡት ሽማግሌ አቶ መብራቱ ። በጣም ተደነቅኩ በዚ ሰአት እሳቸውእዚ ምን ይሰራሉ ።እጃቸውን ሰጡኝ እጃቸውን ለመያዝ ሞከርኩ አቅም አጣው "የኔ ልጅ ለእናትህ ስትል በርታ እባክህ "ብለው እጄን ይዘው ሊያቆሙኝ ታገሉ ፡ እናም ተሳክቶላቸው አነሱኝ ፡እሳቸው እራሳቸው ቆፍጠን ብለዋል እንዲ ጠንካራ አይመስሉም ነበር ፡ እኔን እንደምንም ወደ እራሴ እንድመለስ ጥረት አደረጉ ፡ ብዥ ቢልብኝም እራሴን ችዬ ቆምኩ ፡
"መራመድ የምትችል ይመስልሃል "አሉኝ
"እእኔጃ እየዞረብኝ ነው"አልኳቸው
"እኔን ለኔ ይዙርብኝ ልጄ "አሉኝና በዱላ ያጋደሙትን ቅጥረኛ ጎንበስ ብለው በፊትለፊቱ ገለቀጡት እናም የለበሰውን ሸሚዝ ይዞት በነበረው ስለት ቀደው ካወለቁት በዋላ ጭንቅላቴን ጥምጥም አድርገው አሰሩኝ እንዲ ካደረጉልኝ በዋላ ጠንከር አልኩ ከአፌ የሚወርደው ደምም ቀንሷል ፡
"አሁን መጠንከር አለብህ ወንጀለኛውን ፊትለፊት ለማጋፈጥ ፡መጎበዝ አለብህ ፡ይህንን የማይረባ ነብሰገዳይ ፡የምንደብቅበት ቦታ ብናገኝ ጥሩ ነበር  ምክንያቱም በወንድምህ ላይ የሚመሰክረው ብቸኛው ተባባሪ ነው "አሉኝ ይሄንን ስሰማ ለማመን ከበደኝ እሳቸው ወንድሜ እንዳለበት በምን አወቁ ።አፍጥጬ ሳያቸው
"ይገባኛል ደና ስትሆን ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልሱን እሰጥሃለው ፡አሁን ግን ይህ ልጅ ከመንቃቱ በፊት ወስደን የምናቆይበት ቦታ ቢኖር ጥሩ ነበር "አሉኝ
"እእሺ ወወደቤት ይይዘነው እንሂድ "አልኳቸው እንደምንም ቃላቶቼን እየጎተትኩ ፡በዛላይ መንፈሴ የሌለ ነው ስብር ያለው ፡
"እንዴ ቤት እናንተ ጋር "አሉኝ በመጠራጠር
"አዎ"አልኳቸው እሳቸው እንዳሉት ልጁ እንዲያመልጠኝ አልፈለኩም ፡ በጭራሽ አቅም አጥቼ እንጂ እዚው ቦጫጭቄ ብጥለው እወድ ነበር ነገር ግን ሰውነቴ ሁሉ ዝሏል ብዙ ደም ሳይፈሰኝ አልቀረም
"ግን እንዴት "አሉኝ
"በመጀመሪያ እኔ ወደ ቤት እሄዳለው እርሶ ከዋላዋላ ተከተሉኝ ምን አልባት ሊፈልጉኝ ወጣ ካሉ ለመጠንቀቅ ነው በር አካባቢ ማንም ከሌለ ወደጊቢ ይዘነው ገብተን ሰርቢስ ቤት እንቆልፍበታለን "አልኳቸው  በአሳቤ ተስማሙ እና ገዳዬን አንስተው እየጎተቱ መራመድ ጀመሩ ፡የጥንካሬ አቸው ሁኔታ አስገረመኝ ፡ ገዳዬን የመቱበት ዱላ ምንኛ አይለኛ እንደሆነ ያስታውቃል እኔ ተደግፌበት እየሄድኩ ነው ከባድ ነው እሱም እንደኔ ደሙ እየወረደ ነው ፡ ቤት አካባቢ ስንደርስ ገዳዬ ነቃ ፡እናም ሽማግሌውን ታገላቸው ፡እሳቸውም የዋዛ አይደሉም ዝም የማይል ከሆነ ጉሮሮውን እንደሚበጥሱለት ተናገሩ ድምፃቸው እንኳን ለሱ ለኔም አስፈራኝ ፡ ፀጥ አለ ጩቤውን ጎኑላይ ሻጥ እንዳደረጉት"ምንም አይነት ድምፅ ሳታሰማ ተንቀሳቀስ ፡ቀጥል ፡አለበለዚያ ያው ልጄን ታውቀዋለህ አሁን ጠንከር ብሎ ቆሟል እድሜለኔ በል ቅድም ገና መሬት ሰትወድቅ ተነስቶ ይገልህ ነበር "አሉት ወደኔ እያሳዩት ፡አይኑ ወደ እኔ ተቁለጨለጩ ፡ፈራኝ ፡ የጊቢያችን በርላይ ደርሰን ቆም አልን ማንም አልወጣም ፡ ደስ አለኝ ለነገሩ አቤል አንድ ነገር ፈጥሮ ነው እንዳይወጡ ያደረጋቸው ፡ይሄ ከይሲ ልቤ የመጨረሻ ጠላው ፡ለሱ የነበረኝ ነገር እንዳለ ተቆርጦ ሲወድቅ ተሰማኝ ።ጊቢ ገቡ ተን በቀስታ ከዚበፊት አቤልን ካሰርኩበት ሰርፒስ ቤት አስገባነው ከነ ማስጠንቀቂያው ።አርፎ ከተቀመጠ ከሱጋር ምንም ፀብ እንደማይኖረኝ ነገርኩት ፡ በፍርሃት አንገቱን ወዘወዘ ፡።
ከዛ ወደ ትልቁ ቤት ከሽማግሌው ጋር ሄድን በመጀመሪያ ሽማግሌው በሩን ሲያንኳኩ
"ጭራሽ ታንኳኳለህ እንዲ አስጨንቀኽኝ ናግባ አሁን ሆሆ"አለች እናቴ ሽማግሌው
"እኔ ነኝ "ብለው ሲገቡ
"ምን እርሶ እንዴት ገቡ ቁልፍ ከየት አመጡ"በጭንቀት ተናግራ ሳጨርስ
"አንተ ለማኝ በዚ ሰአት ደሞ ምን ትሰራለህ "አለ አቤል በድንፋታ
"እኔም አለው እናቴ "ብዬ በደም የተበከለ ሰውነቴን ይዤ ስገባ እናቴ ኡኡ ታዋን አቀለጠችው ደግነሽም ተከተለች ባዩሽም አልቀረች ። ሽማግሌው ሰው እንዳይሰማ እያሉ ተከላከሏቸው እንደምንም እንዲረጋጉ አድርገው ይልቅ ደሙን እንጠበው ።አሉ እናቴ ዱርዬዎች ናቸው ልጄን ያጠቁት ብላ ሽማግሌውን በጥያቄ አጣደፈች እሳቸው መልሰሰ ከመስጠት ይልቅ አቤል ላይ በቁጣ እንዳፈጠጡ ቀሩ አቤል እኔን በማየቱ እራሱን ሊስት ምንም አልቀረውም ፡ ..............

Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍12329👏6😁1
#ህያብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በኤርሚ

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ.. ትምህርቴን መተው እናቴን እንደመቅበር ነው። ሁላችንም ቢከብደንም ግዴታ ሄጄ መማር አለብኝ።
.....
ስራ ቦታዋ ሄጄ ለእናቴ ስነግራት እልልታዋን አቀለጠችው። ደንበኞቿ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው እንኳን ደስ ያለሽ እያሉ እናቴን አቀፏት..... ከሁኔታቸው እኔ ሳልሆን እናቴ ውጤት የመጣላት ነበር የሚመስለው....
......
ቤት ውስጥ ጎረቤቶቻችንና አንዳንድ የእናቴ ወዳጆች በተገኙበት መጠነኛ የሽኝት ዝግጅት ተደረገልኝ። ልለያት እንደሆነ ያላወቀችው ልጄም ከኔ እኩል ፍንድቅድቅ ብላለች። እንግዶች በልተው ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እናቴ ወደ መሀል ወጣችና
"አንዴ ፀጥታ...." ብላ ጨብጨብ ስታደርግ ሁሉም ሰው ባንዴ ዝምምም አለ።

"በህይወቴ እንደዛሬ የተደሰትኩበት ቀን የለም ... ልጄ ዩንቨርስቲ ገባችልኝ። ይሄ ከምንም በላይ ትልቁ ህልሜ ነው። እዛ ሄዳ በስኬት እንደምትመለስ እተማመንባታለሁ። ትልቅ ነገርም ባይሆን ይሄን ስጦታ በእናንተ ፊት እሰጣታለሁ" ወደኔ መጥታ ጉንጬን አገላብጣ ከሳመችኝ በኋላ የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠችኝና"ክፈቺው..." አለችኝ። የተጠቀለለበትን ወረቀት ስከፍተው ሞባይል ከነ ቻርጀሩ ብቅ አለ። አላመንኩም እናቴ ለኔ የእጅ ስልክ ገዛችልኝ... በዚያን ጊዜ አብዛኛው ሰው ባለ ሞባይል እየሆነ ቢሆንም እኔ ይኖረኛል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"አመሰግናለሁ እናቴ.... ደግሞ ቃል እገባልሻለሁ... አኮራሻለሁ"

"እተማመንብሻለሁ የኔ ጀግና.... ሳትሳቀቂ በናፈቅሺን ሰዓት መደወል ብቻ ነው...."ወደ ደረቷ ወስዳ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ይሄን እቅፍ እኮ ስወደው..............
ቃል ባትናገር እንኳን በእቅፏ ብቻ ብዙ መልዕክት የምታስተላልፍልኝ ይመስለኛል።
"በርቺ....
ባንቺ እተማመናለሁ....
እኔ አለሁልሽ...
እወድሻለሁ......." ብቻ ስታቅፈኝ ከዚህም በላይ ብዙ የምትለኝ ይመስለኛል።
..............

የምወዳት ልጄን እና እናቴን ተሰናብቼ ወደ አፄ ፋሲል ሀገር ጥንታዊቷ ጎንደር ተጓዝኩ ።
..........

ምዝገባ እና ሌሎች ፕሮሰሶች አልቀው ትምህርት የምንጀምርበት ቀን ደረሰ...... የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ቀድሞ ክፍል ተገኝቷል ከነኛ መሀል አንዷ እኔ ነኝ።
.....
ከደቂቃዎች በኋላ
"ይሄ ሸበላ ብቻ እንዳይሆን የሚያስተምረን" ከኋላዬ ያለችው ልጅ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ አንሾካሾከችልኝ። ከንግግሯ እኩል ቀና ብዬ ወደ ፊት ለፊቴ አየሁ..... " ዋው ውበት ..... ዋው ቁመና.... ዋው ደረት...." ብዙ ዋው የሚያስብሉ ነገሮችን ያሟላ ሸበላ ሰው.....
......
"እሺ ዛሬ ብዙም የምንማረው ነገር አይኖረንም እርስ በርሳችን እንተዋወቅና ኮርስ አውትላይን እሰጣችኋለሁ...... እምም ከፊት ልጀምር ስምሽን አስተዋውቂን እስኪ...." ምኑ ነው ምን አለ እስከምረጋጋ እንኳን ሌላ ሰው ቢጠይቅ

"ህያብ በዛብህ እባላለሁ የመጣሁት ከአዲስ አበባ" ጣቱን ከኔ ቀጥሎ ወዳለችው ልጅ ጠቆመ

"መቅደስ ገዛህኝ..... ከሀዋሳ
ተፈሪ ይልማ...... ከደሴ
አብሳላት አበበ.... ከአዳማ
የትናዬት ዘመረ..... ከአዲስ አበባ......" ሁሉም ስማቸውን እና የመጡበትን ከተማ ተናገሩ ሁላችንንም ከሰማ በኋላ

" የኔ ስም ደግሞ ዮናታን ይባላል የ...." ከዚህ በኋላ ያለውን አልሰማሁትም .... ዮናታን.... ዮኒ ስሙ ደስ ይላል መልኩም ደስ ይላል። ሳላውቀው ስለሱ ብዙ አሰብኩ.... እጄ ላይ ያረፈ ወረቀት ከሀሳቤ አነቃኝ

"ያልኩትን ሰምተሽኛል ህያብ" ድንብርብሬ ወቶ አይን አይኑን አየው ጀመር እሱም ትንሽ ካየኝ በኋላ

" ተወካይ እስክትመርጡ ድረስ አንቺ ተወካይ ሆነሽ እነኝህን ወረቀቶች ለሁሉም አዳርሺ...." መልሴን ሳይጠብቅ ክፍሉን ለቆ ወጣ። እንዴ ቆይ ደግሞ ስሜን እንዴት ባንዴ ያዘው..... ይገርማል
........
" እና እኔንም አፈዘዘኝ እያልሽኝ ነው" አለችኝ ከፊት ለፊቴ መጥታ

"ይቅርታ እህቴ ምን......"

."ቅድም አልሰማሽኝም የትናየት.... የትናዬት ነው ስሜ"

"እሺ የትናዬት የምትይው አልገባኝም"

"ቀስ ብሎ ይገባሻል ለማንኛውም የራሴን ልውሰድ." አንዱን ወረቀት አንስታ እየተቆናጠረች ከክፍሉ ወጣች።

"ወይ አምላኬ ስንት አይነት ሰው አለ" ብዬ ስዞር ሁሉም አፍጠው የሚያዩኝ እኔን ነው።

ህይወት ልክ በምኞታችን ውስጥ እንዳሰብናት ቀላልና ጣፋጭ አይደለችም። ልንመራት ያወጣነውን እቅድ አስጥላ በራሷ ምህዋር ላይ ታሽከረክረናለች። እምቢ ብለን ብናስቸግራት እንኳን ወይ ከራሳችን እቅድ ወይም ሽክርክሪቱ ከሚያመጣው ነገር ሳንቋደስ ሜዳ ላይ እንቀራለን።

ዩንቨርስቲ መግባትን ሳስብ የሚታየኝ ጠንክሮ መማርና መማር ብቻ ነበር። ግቢ ውስጥ ሆኜ ከትምህርቴ የበለጠ ቦታ እሰጠዋለሁ ብዬ የማስበው ምንም ነገር አልነበረም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ ሰው መጥቶ ይህን ጥያቄ ቢጠይቀኝ በመጠየቁ ልናደድበት እችል ነበር። ዛሬ ግን ያን እምነቴን የትላንት እቅዴን ሊያከሽፍ የሚችል ፍቅር ያዘኝ። ያውም ውድድር የበዛበት ፍቅር.....
አብሬው ልሁን ብዬ ባስብ እንኳን ከሱ እኔን አለማፍቀር ውጪ ከደርዘን በላይ ሴቶች ጋር መጋፈጥ ይኖርብኛል..... ያውም እኔ የማውቃቸው ብቻ።

ያለኝ አማራጭ አንድ ብቻ ነው ቢከብደኝም ስሜቴን አምቄ መያዝ እና በሰላም ትምህርቴን መቀጠል። ምንም ሳይተነፍሱ ሁሉንም በልብ መያዝ ከምንም በላይ ህመም ነው.... በተለይ ደግሞ ፍቅር ሲሆን...

ብዙ ጊዜ ይሄን አስባለሁ ለእናቴ ይሄ አይገባትም አይደል? ... ስኬቴን ለምትናፍቅ እናቴ ስል ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን መርጫለሁ። የምሸሽበት ምክንያት ዋናው ቁም ነገሩ እኮ ማፍቀሬ አይደለም ፍቅር በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ስሜት ነው። ችግሩ ለዚህ ፍቅር ስል ብፋለም ለትምህርት የሚሆን ነፃ አይምሮ ላገኝ እችላለው ወይ? የበለጠው ችግር ደግሞ ያፈቀርኩት ሰው ሁሉንም ቀማሽ መሆኑ ነው።
፧፧፧፧፧፧
ከዛን ቀን ጀምሮ ማለትም ከመጀመሪያ የትምህርት ቀናችን ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፊያለሁ። ፍቅር እንደያዘኝ እንኳን እያወኩ ላለማመን ከራሴ ጋር ለወራት ተከራክሪያለሁ። የትናዬት በየቀኑ እኔን ማስበርገግ ስራዬ ብላ ከያዘች ቆይታለች። በተለይ ዮናታን አስተምሮን ሲወጣ ወይ ከጎኔ ናት ወይም ከፊት ለፊቴ.... እልፍ ጊዜ እኮ አብረው አይቻቸዋለሁ... ብዙ ጊዜ ቢሮው ስትገባ ያዩዋት ነግረውኛል...... እኔ ደግሞ በተቃራኒው ከሱ ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ሁላ ላፈርስ የምሞክር ሰው ነኝ። ለምን ይሄን ያክል የቤት ስራ እንደሆንኩባት አላውቅም። አሁን ግን መሮኛል ፀብ ላለመፍጠር እያልኩ እንደፈሪ መታየት መሮኛል።

ዛሬም እንደለመደችው ከጥሩ ትወና ጋር የአሽሙር ንግግሯን ተናግራኝ ከክፍሉ ወጣች። ብሽቅ ብዬ ወረቀቶቼን ሰብስቤ ተከትያት እየወጣሁ እያለ አንድ ሰው ከኋላዬ ያዘኝ። ዞር ስል ቢኒ ነው ከተማሪዎች ሁሉ የተለየው ዝምተኛ ልጅ።

"አቤት ቢኒ" አልኩት ኮስተር ብዬ... ግንባሬን አይቶ እጁን ከክንዴ ላይ አነሳ እና

"ይቅርታ ህያብ.... ጣልቃ ልገባ ፈልጌ አይደለም ግን እኔ የታየኝን አንድ ነገር ልበልሽ..."

"ምን"
👍4910👏3🥰1🤔1
"የትናየት ካንቺ የምትፈልገው ይህንን ነው... ማለትም ፀብ.... ከሷ የተሻልኩ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ እቅዷን ቀድመሽ አክሽፊባት...."

"ማለት..... እንዴት አድርጌ"

"እኔ አግዝሻለሁ..." እንስማማ አይነት እጁን ዘረጋልኝ። ሳላወላውል ጨበጥኩት.... ተገኝቶ ነው ይቺን የሰው ቆንጥር ከአጠገቤ የሚያርቅልኝ

ወደ መነሻ

አስታወሳችሁ መነሻዬን እንጂ መድረሻዬን ሳላውቅ እግሬ ወደመራኝ እየሄድኩ ነው ብያችሁ ነበር። አዎ መንገዴንቨ አላቋረጥኩም። ከእርምጃዬ እኩል ትዝታዬ በልቤ ውስጥ ይፈሳል በአይምሮዬም ውስጥ ይመላለሳል።

ከተማውን ሙሉ ለሙሉ መልቀቄን ያስተዋልኩት ከፊት ለፊቴ ያለው ሰፊ የግጦሽ ሜዳ ላይ የእረኛዎችን ድምፅ ስሰማ ነው።

ድንገት እኔን አልፎ ሲጥጥ ብሎ የቆመ መኪና ከሀሳቤ አንቅቶ አስበረገገኝ። ቅድም ሳይገጨኝ ያለፈው መኪና.... ከውስጡ አንድ ሰው ወረደና ወደኔ መጣ። በድንጋጤ ደርቄ ነው የቀረሁት

"ህያብ በዚህ መልኩ አገኝሻለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር" አጠገቤ መጥቶ ክንዴን ያዘኝ ልክ እንደመጀመሪያው ቀን ልዩነቱ ያኔ ከኋላ አሁን ግን ከፊት ለፊት መሆኑ ነው

"ቅድም አንተ ነበርክ"

"አዎ ግን አንቺ መሆንሽን ለመለየት ጊዜ ወሰደብኝ ህያቤ በጣም ተጎሳቁለሻል አንቺ እንደሆንሽ ያወኩት "ዞር በሉልኝ አስማሳዮች" ብለሽ ስትናገሪ በሰማውት ድምፅሽ ነው አረማመድሽ ደግሞ አረጋገጠለኝ። እናም ተከተልኩሽ.... የምትሄጅበትን መድረሻሽን ለማወቅ ተከተልኩሽ ግን እንደማየው.......

"ቢኒ እኔ...." ቃላቶቼ አፌ ላይ ተንገዋለሉ። ወደራሱ አስጠግቶ እቅፍ አደረገኝ።

"እሽሽሽሽሽሽሽ ይገባኛል ምንም አታስረጂኝ"

በህይወት መንገድ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኘን..... እኔና ቢኒ

ይቀጥላል
38👍33👎3
🔵💘የእናቴ ልጅ💘🔵
🏮ክፍል ሃያ ስድስት🏮
🔵💘🔵💘🔵💘🔵
ሰውን ከልብህ ስትጠላው ድምፁንም ሆነ አይኑን ለማየት ትጠላለህ ልክ የማይስማማህን ምግብ በግዴታ ብላ እንደመባል ነው የሚሆንብህ ። በሰአቱ የተሰማኝ ነገር  ለመናገር የማይቻል አስቸጋሪ ነበር ።
ወንድሜ ነብሰ ገዳይ ቀጥሮ ሊያስገድለኝ ተደራደረ በኔ በእናቱ ልጅ ላይ ።ለምን ብቻውን ወራሽ ለመሆን ለገንዘብ ብሎ ።'ምን አይነት ጊዜነው ክፉ ዘመን 'ብለው እናቶች አንዳንዴ የሚያማርሩት ያለነገር አይደለም ለካ ።እንደዚ አይነት የበዛ እራስ ወዳድነትእና ጥቅመኝነት ስላለ ነው ። ሰው እንዴት በሌላው ላይ ተረማምዶ ሕይወት ለመመስረት ይጥራል ። ሲሆን አቅምና ጉልበቱን አይምሮውን ተጠቅሞ እራሱን መለወጥ ሲኖርበት ባለፋበት ሀብት ላይ አይኑን ጥሎ  ሰውን እስከማጥፋት መድረስ ተገቢነው።  እውነትም ከባድ ጊዜ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚነሳበት መሰሪነት የበዛበት ።
💘እናቴ ሽማግሌውን በጥያቄ ማጠደፉን አላቆም አለች እሳቸውም ዝም ብለው አቤልን ማየት ሆነ  ባዩሽ እያለቀሰች በመዘፍዘፊያ ውሃ አምጥታ ደሜን በጨርቅ እያረጠበች ትጠራርጋለች  ደግነሽ እልልልታዋ ወደኡኡታ ተቀይሮባታል
"ኡኡኡኡ እኔን አፈር ልብላ እኔን አክስትህን የኔሸበላ እንዲሁ ጠርተው ከመንገድ ሊያስቀሩህ ?የስራቸውን ይስጣቸው መዳኒዓለም ። እኔማ መጀመሪያም ሰትወጣ ደስ አላለኝም ነበር"እያለች ታለቅሳለች
"እባክዎት ማነው እንዲ ያደረገው ይንገሩኝ አባቴ "አለች እናቴ  ድምጿ ፍርሐት ያዘለ ነው ።ሽማግሌው እንዲነግሯት አልፈለኩም ለነገሩ እሳቸውም ዝም ብለዋት ነበር  ።እናቴ የልጇን የመጨረሻ አውሬነት ስታውቅ ምንልትሆን ትችላለች ፡ይህንን ነው የፈራውት ።እንጂማ አቤልን አንቄ ብገድለው እንኳ አሁን ላይ ቅር አይለኝም ነበር  ። ሽማግሌው ፡ያጎነበሰ ሰውነታቸው ቀጥ ብሎ መቆሙ በራሱ ገርሞኛል እኛ ድቅቅ ያሉ ሰውዬ በሳምንቱ ውስጥ ምን አግኝተው ነው እንዲ ቆፍጠን ያሉት ከክሳታቸው በቀር ተለውጠዋሉ  ። እናቴ ውትወታዋን አላቋረጠችም ሽማግሌው ደሞ ቃላት ያጡ ይመስል አቤል ላይ እንዳረፉ ነው ።አቤል ምንም ነገር ሳይተነፍስ ቆይቶ ድንገት የባነነ ይመስል ።
"አንቺ ባዩሽ ጓደኛውን ሊያገኝ ነው የወጣው አላልሽም ነበር እንዴ "አላት ባዩሽ አቀረቀረች
"እንዴ እሱማ እሱ የነገረንን ነው የሆነሰው በስልክ ጠርቶት ነው እንደውም ያንተው ጓደኛ እንደሆነነው ናቲ የነገረን አይደልእንዴ ናቲ ? ደሞስ የሆነ ሆነና ወጥተን እንፈልገው ስልህ ይመጣል ምን ይሆናል እያልክ ያዘናጋኽን አንተ አይደለህ "አለች አክስቴ ደግነሽ ቆጣ ብላ ።
እናቴ በጥርጣሬ ወደ አቤል ዞረች አይኗን ለመሸሽ ይመስል ተንቀሳቀሰ ፡  እናቴ ወደ አቤል ተጠግታ
"አንተ አንድ ነገር አድርገሃል እንዴ?"አለች ድምጿ እየተንቀጠቀጠ
"ኧረ እማዬ እኔ እኔ መቼ አአገኘውት እዚሁ ካካንቺ ጋር አአልነበርኩም "አለ እየተንተባተበ ።
"ባትሆን ይሻላል ከሆነ መቼም ይቅር አልልህም "ከማለቷ ።የሽማግሌው ቁጣ ገንፍሎ ወጣ ፍፁም ሌላ ሰው ሆኑ በፍጥነት እናቴን ከአቤል ዞር አድርገዋት ፊትለፊት አቤልን ተጋፈጡት  ከኪሳቸው የሚያብለጨልጭ ስለት አውጥተው የአቤል አንገት ላይ ቀሰሩት ፡አቤል እንዲ አይነት ነገር ገጥሞት ስለማያውቅ በድንጋጤ ፡ የእናታችንን ስም ጠራ ሽማግሌው በቁጣ "አንተ ነህ ወንድምህን ልታስገድል የነበረው አንተ ሳታየኝ በጨለማውስጥ ከዛ ከይሲ ነብሰ ገዳይ ጋር ስትደራደር አይቼሃለው ፡እዛ የቆማችሁበት ጨለማ ውስጥ ተደብቄ ሰምቻችዋለው ።ከዛ ምን እንዳደረኩ ታውቃለህ በፍጥነት እዚ መጣው ናቲ ከቤት ወጥቶ እናንተ የጠራችሁት ቦታ እንዳይመጣ ፀልዬ ነበር ነገር ግን መጣ ስለዚ እሱ አንተ የተጎዳህ መስሎት ሲሮጥ ከመንገድ ያገኘውትን ዱላ ይዤ ተከተልኩት ግን የሱንያክል መፍጠን አልቻልኩም ። እዛ ስደርስ የመጨረሻ እስትንፋሱን ሊዘጋው ቅጥረኛህ በዚ ስለት ሊሰነዝርበት ሲል የሞት ሞቴን በዱላ አናቱን አልኩና ጣልኩት ። ለትንሽ ልጄን አጥቼው ነበር ።አንተ አቤል መባል አልነበረብህም አንተ ቃዬል ነህ "ብለው አቤልን በጥፊ አጮሉት አቤል ሶፋውላይ በቁሙ ወደቀ ። እናቴ አበደች የምትይዝ የምትጨብጠው ጠፋት ። ደግነሽ የቤቴ ጉድ ብላ ለቅሶዋን አባሰችው ።ባዩሽ አፏን በሁለት እጆቿ ይዛ በድንጋጤ ቆማለች ።እኔ የሽማግሌው ከኔም በላይ ሆነው ተበሳጭተው እንደዛ ሲሆኑ ሳይ ተገርሜአለው በዚች ጥቂት ጊዜ ምን ያክል ቢወዱኝ ነው የኔ ተቆርቋሪ የሆኑት ።
"አንተ አንተ በቃ መቼም አታርፍም ደሞአሁን ምንድነው  ያልከኝን ሁሉ አድርጌ ጉዞህን አስተካከልኩ አሁን እሺ ምንድነው ከሱ ጋር የሚያጣላህ "ብላ ቁጭ ብላ እናታችን አለቀሰች አቤል ምን ያክል እንደሚሰባብራት አውቃለው እናቴ አሳዘነችኝ እናት ናትና ።
"አንተ መቼም ወደውጪ አትሄድም መቀጣት አለብህ ባለጌ እኔ ነበርኩ አቤል ያልኩህ ስትወለድ አንተ ግን የአቤልነት ጫፍ የለህም ሴጣን "አሉ ሽማግሌው ስሜታዊ ሆነው ።እሳቸው በቁጣውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር አምልጦአቸው ቢወጣም ፡እኛ በቤት ውስጥ ያለነው ሰዎች ሁሉ በአንድነት ምን ብለን ድምፅ አወጣን ። በተለይእናቴ አይኗም ሳይቀር ፈጠጠ ።በዚ ጊዜ ግን እኔ የሌለኝን ብርታት ከየት እንዳመጣሁት አላውቅም ተነስቼ ከፊትለፊታቸው ቆምኩ ።
"እርሶ ማን ነዎት ለሱ ስም ያወጡለት "አልኳቸው።መናገራቸውን ያወቁ አይመስልም ደነገጡ
"ይንገሩኝ እርሶ ማን ነዎት"ጮውኩ
"እኔ ምን አልኩ እባክህ ናቲ ተው "አሉ ተጨንቀው ወደ እናቴ እያዩ
"አንዴ ተናግረዋል እኔነኝ ስም ያወጣውለት ብለዋል "አልኳቸው ።እናቴ እንደመንገዳገድ እያረጋት መጣችና ሽማግሌውን በትኩረት አየቻቸው ። ድንጋጤዋ ጨመረ የለበሱትን ቲሸርት በጎን በኩል ገለፅ አድርጋ አንድ ምልክት አየች ከዛ በዋላ "ግዛው !!!!!!"ብላ ጮሃ ወደመሬት ወረደች መሬት ከመንካቷ በፊት ሽማግሌው ፈጥነው ያዟት ..........

Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍14129😱10👎4🥰4👏1
#ህያብ
:
:
#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በኤርሚ


አንዳንዶች ለወደዱት ብቻ ጥሩ ይሆናሉ.... አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በተፈጥሯቸው ጥሩነትን ይታደሉታል። ቢኒ እንደዛ ነው መልካምነትን የታደለ ጥሩ ልብ ያለው ልጅ ነው። ድሀ ወይም ሀብታም፣ ክርስቲያን  ሙስሊም ወይም ሌላ እምነት፣ ቆንጆ ወይም መልከ ጥፉ፣ ቢኒ ጋር መስፈርት አይደሉም። ለሁሉም እኩል ፍቅርና እንክብካቤ ሲሰጥ ታዩታላችሁ..... ግቢ ውስጥም ሆነ ከተማ ውስጥ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች አያመልጡትም.....

"ቢኒዬ ግን እርግጠኛ ነህ እዚህ ብሆን አረብሽህም.." እረጅም ሰዓት ተጨቃጭቀን እስከፈለኩ ድረስ ቤቱ እንድኖር ከነገረኝ በኋላ ሀሳቡን ቢቀይር ብዬ ጠየኩት

አጠገቤ መጣና ቁጭ አለ.... እጆቹን ልኮ ሁለት እጆቼን ያዘና አይን አይኔን እያዬ "ህዩ አንቺ ጓደኛዬ ነሽ... ጓደኝነት ውስጥ ደግሞ እኔ የሚባል ነገር የለም በተለይ እኔ ካንቺ እኔን ላስቀድም አልችልም ምክንያቱም......" ከንፈሮቹ ተንቀጠቀጡ።

"ምክንያቱም ምን ቢኒዬ" እጄን ለቆ ተነሳና ጀርባውን ሰቶኝ ከመስኮት ዳር ቆመ።

"ህያብ ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው ብዬ አምናለሁ... እናም ሁሉም በጊዜው ሲሆን ደስ ይላል። አሁን ከኔ ምክንያት በላይ ያንቺ ሁኔታዎች ናቸው መስተካከል ያለባቸው...." ክትክት ብዬ ሳቅሁ... የእብደት ሳቅ
ከሳቄ በኋላ

" እስኪ ንገረኝ ምኑን ነው የምታስተካክለው.... እናቴን ልጄን ወይስ ከሀዲው ባሌን ማንን መልሰህ ልታመጣልኝ የምትችል ይመስልሀል..." ድጋሚ አመመኝ... መቋቋም አቃተኝ... በሁለት እጄ ጭንቅላቴን ጥፍንግ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ሽክርክሪት ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል ዥውውውውውውውው.... ሳቅ ከዛ ደግሞ ዝምምምምታ.... ከዛ ደግሞ ሌላ ሳቅ.... ይሄኛው አለም የተሻለ ይመስለኛል።

የሆነ ሰው አፌ ውስጥ የሆነ ነገር ለማስገባት ታገለኝ አልከለከልኩትም ዋጥኩት ከዛ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።

ምን ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም ራሴን ጋቢ ለብሼ ሶፋ ላይ ተኝቼ አገኘሁት። ቀና ብዬ ተስተካክዬ ቁጭ ስል ቢኒን ከእግሬ ስር ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ሲያነብ አየሁት።

"ይቅርታ ቢኒ ረበሽኩህ መሰለኝ.." መፅሀፍ ቅዱሱን ዘግቶ ከሳመ በኋላ የኔንም ግንባር ነካ አደረገበትና ተነስቶ አስቀምጦ ተመለሰ።

"ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትይኝ ማስቸገር ገለመሌ የሚባል ታሪክ የለም ያራቅሺኝ ነው የሚመስለኝ..."

"እሺ በቃ አይለመደኝም..... ይልቅ እስኪ ንገረኝ የውጪ ቆይታህ እንዴት ነበር የተመለስከውስ መች ነው"

"ቆይታዬን በደፈናው ጥሩ ነበር ልበልሽ መሰለኝ። የተመለስኩት ሁለት ወር አካባቢ ሆነኝ ግን ቀጥታ ቤተሰብ ጋር ክፍለ ሀገር ነው የሄድኩት ከተመለስኩ ገና ሳምንትም አልሞላኝ"

"እና ለምን ልትፈልገኝ ወደ ቤት አልመጣህም..." ክፍት ነው ያለኝ ምንም እንኳን የሱን ስም ሲሰማ ባሌ ቢናደድም ቢኒ ላጣው የማልፈልገው ጓደኛዬ ነው እና እንዴት...

"ወዳንቺ ጋር እየመጣሁ እያለ እኮ ነው መኪና ውስጥ የገባሽብኝ"

"ኦ እሺ እንደዛ ከሆነ"

"አልተዋጠልሽም አይደል ህያቤ ብዙ ጊዜ እንዳልደወልኩልሽ አውቃ..." አቋረጥኩት

"ምን ብዙ ጊዜ ትላለህ ከሄድክ ጀምሮ ሁለቴ ብቻ እኮ ነው የደወልከው.... እናም አልዋሽህም ተቀይሜሀለሁ"

"ምክንያቴን ስታውቂ እንደምትረጂኝ ስለማውቅ ችግር የለውም.... የሆነ ነገር መብላት አለብን ምን ትፈልጊያለሽ..." አለኝ ወደ ኪቺን እየገባ

"ፍላጎትሽን አትናገሪም ካለዛ ዱባ ወጥ ነው የምሰራው ሀ ሀ ሀ" ሽርጡን አገልድሞ ብቅ አለ

" ዱባ ስራና ሶስት ቀን ውጪ አሳድሬ ነው የማበላህ.... አንተ ደግሞ ሼፍ መስለህ የለም እንዴ"

"ነይ አሁን ተነሺ ቢያንስ ዱባውን እንኳን በመክተፍ አግዢኝ" ከስሙ ጭምር እንደምጠላው ስለሚያውቅ እኮ ነው ...ዱባን....

"ሀ ሀ ሀ አንተ እብድ ትቀልድብኛለህ አ" ከረጅም ጊዜ በኋላ ሳቅሁ
......

፨፨፨ ፨፨፨፨ ፨፨፨፨
ጎንደር ዩንቨርስቲ ሁለተኛ አመት

"ቢኒ ዮናታንን እወደዋለሁ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም እናም እነግረዋለሁ"

"ህያብ ዮናታንን ታውቂዋለሽ.... እሺ አለሽ እንበል ከዛ እነኝህን ሁሉ ሴቶች ትቶ ካንቺ ጋር ብቻ የሚሆን ይመስልሻል"

"አላውቅም ግን እድሌን ልሞክር.."

"ተይ ህያብ ይቅርብሽ"

"አይሆንም ቢኒ እድሌን እሞክራለሁ" ይሄን ሁሉ የምንጨቃጨቀው ዮናታን የሚያመሽበት ጭፈራ ቤት በር ላይ ሆነን ነው። ወደ ውስጥ ገባሁ... አይኔን ዞር ዞር እያደረኩ ፈለኩት ጥግ ሶፋ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር የተሰፋ ያክል ተጣብቋል.... በደንብ ቀረብኳቸው... አንገቱ ስር ስማው ቀና ስትል አይን ለአይን ተገጣጠምን... የትናዬት....

ደንዝዤ አንደቆምኩ የሆነ ሰው እጅ ትከሻዬ ላይ አረፈ "የኔ ቆንጆ በዛኛው በኩል ቦታ አግኝቻለሁ.... እንሂድ አይደል"  ውጪ ቆይ አላልኩትም ነበር.... ቢሆንም ግን ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው የደረሰው።

"አየሽ አይደል በራስሽ ላይ ምን እያመጣሽ እንደሆነ"

ሲጀመር እሱን ብቻውን አገኘዋለሁ ብዬ ማሰቤ ነው የኔ ጥፋት እርር ድብን ብሽቅቅቅቅ ብያለሁ እኮ

"አረጋጊው እንጂ ውዷ ጉበትሽን መትፋት አማረሽ እንዴ"

"ተወኝ ባክህ ልጠጣበ" ከነ ጠርሙሱ አንስቼ ለመጠጣት ስሞክር ከእጄ ቀማኝና

"ነይ በቃ እንሂድ ግቢ ይዘጋል" አለኝ

"የትም አልሄድም ተወኝ"

"ይሄንን ነው መፍራት... ኧረ ህያብ በፈጠረሽ..." ጠርሙሱን ተቀብዬው እየተንገዳገድኩ እነሱ ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ....

"ህያብ አንቺ ህያብ" የእናቴ ድምፅ መሰለኝ.... እየጠራችኝ ነው።

"አቤት እማ መጣሁ" ብዬ ከተኛሁበት ለመነሳት ስሞክር ሀይለኛ ራስ ምታት አናቴን ይዞ እየፈለጠኝ ነው። ጭንቅላቴን በሁለት እጄ ጥፍንግ አድርጌ ይዤው ከቆየሁ በኋላ አይኔን በደንብ ከፍቼ ሳይ ያለሁት እናቴ ቤት አይደለም....

ከፊት ለፊቴ ቢኒ ተቀምጦ የማደርገውን ነገር ያያል።

"ኡፍፍፍፍ የት ነው ያለሁት ምን ተፈጥሮ ነው.... ቆይ እማዬ የጠራችኝ አልመሰለኝም.."

"ባክሽ እኔ ነኝ የጠራሁሽ ክፍል ልቀቁ እየተባልን ነው ተነሺ..." ቢኒ እንደዚህ አውርቶኝ አያውቅም....

"ምንድነው ቢኒ ችግር አለ እየተነጫነጭክ እኮ ነው ምነው ማታ አስቀየምኩህ እንዴ.... ማታ....ቆይ ቆይ እንዴት ወደዚህ ልመጣ ቻልኩ? ማነው ያመጣኝ? ማለት ምን ተፈጥሮ ነው?..." የጥያቄ መአት አከታተልኩበት

"በመጀመሪያ ተነሽና ታጠቢ ከዛ ወደ ግቢ እንመለስና ዶርም ገብተሽ እረፍት አድርጊ ከዛ ተገናኝተን ጥያቄዎችሽን እመልስልሻለሁ እስከዛው ትዝ የሚልሽ ነገር ካለ ራስሽ ጥያቄሽን መመለስ ትችያለሽ" እንዴ ምንድነው ጉዱ ቢኒ እንደዚ ከረር ብሎ አይቼው አላውቅም ጭራሽ የማላውቀው ሰው ነው የሆነብኝ። ተጨማሪ ጥያቄ ሳልጠይቅ ጭንቅላቴን ደግፌ እየተጎተትኩ መታጠቢያ ቤት ገባሁ።
ሰውነቴ ስብርብር ያለ ያክል እየተሰማኝ ታጥቤ ጨረስኩ

፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨

"አንተ ቢኒ ግን አልተኛህም እንዴ አይንህ እኮ በርበሬ ነው የሚመስለው" ወደ ግቢ እየሄድን ጠየኩት
👍448😁1
"ህያብ ፊቴን አንብበሽ መረዳት ከቻልሽ እባክሽ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም.... እና ካወራሁም በጣም አስከፋሻለሁ ስለዚህ እኔም ተረጋግቼ አንቺም እረፍት አድርገሽ የተለመደው ቦታ ዘጠኝ ሰዓት እንገናኝ... ቻው" መልሴን ሳይጠብቅ ትቶኝ ሄደ። ግራ እንደተጋባሁ ዶርም ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ግን እንቅልፍ ከየት አባቱ ወደ ግራ ወደቀኝ እየተገላበጥኩ አሰብኩ.... አሰብኩ.... አሰብኩ... ግን ትላንትና ማታ ምን እንደተፈጠረ ማስታወስ አቃተኝ

ከቀጠሯችን አስር ደቂቃ ቀድሜ ተገኘሁ... ብዙም አላስጠበቀኝም። እንደመጣ

"በናትህ ቢኒ እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የቀጠሯችን ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ሳልተኛ ብዙ አሰብኩ ግን ምንም ትዝ አይለኝም"

"የእውነት ምንም አታስታውሺም"

" እነሱን አይቼ ተናድጄ ካንተ ጋር እየጠጣሁ ነበር ከዛ እነሱ ወደተቀመጡበት እንደሄድኩ ትዝ ይለኛል ከዛ ውጪ አዎ ምንም አላስታውስም"

"እሺ ጥሩ እንደዛ ከሆነ እኔ ላስታውስሻ....
በጣም ሰክረሽ ነበር ጠርሙሱን ቀምቼሽ ወደ ዶርም እንሂድ ስልሽ  አልሰማሺኝም ተቀብለሽኝ እየተንገዳገድሽ ዮናታንና የትናዬት ወደተቀመጡበት ቦታ ሄድሽ። ሁኔታሽ ስላላማረኝ ተከተልኩሽ... ከዮናታን ውጪ ማንም አልነበረም እናም አንዴ እየሳቅሽ ሲልሽ እያለቀሽ እንዴት እንደምትወጂው ለእናትሽና ለአላማሽ ብለሽ ከሱ እንደራቅሽ ነግረሽው የየትናዬትን ተንኮል እየነገርሺው እያለ ከየት መጣች ሳትባል ፀጉርሺን ጨምድዳ ይዛ በጥፊ መሬት አነጠፈችሽ..."

"ምን ጭራሽ ተደባድቤም ነበር" አሁን የተመታሁ ይመስል ጉንጬን በእጄ ዳበስኩት

"አዎ.... ያም ብቻ ሳይሆን በወደቅሽበት ትንሽ መታሻለች... ብዙም ሳይቆይ ሰዎች አገላገሏችሁ እና እኔ አንቺን ይዤሽ ከዛ ወጣን እና አልጋ ፈልጌ ያዝኩ አንቺን አስተኝቼሽ ትንሽ ቆዬት እንዳልኩ የክፍሉ በር ተንኳኳ ሄጄ ስከፍት ዮናታን በር ላይ ቆሟል..."

"ምን...... ማለት ለምን ነበር የመጣው" ወይኔ ነገሩን ሀሉ በአንድ ቀን ስካር አበላሸሁት ማለት ነው። ቢኒ ለመናገር ሲታሽ አየሁት

"ምንድነው እሱ ቢኒ ንገረኝ እንጂ..."

"ይሄ እኔን ይጎዳኝ ይሆናል አንቺን ስለሚጠቅምሽ ግን ልንገርሽ"ለአፍታ ዝምምም አለ

"ምን ቢኒ" ልቤ ስቅል አለ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

ይቀጥላል
👍2720🔥2
💰🎈የእናቴ ልጅ🎈💰
  🎈ክፍል ሃያ ሰባት🎈
💰🎈💰🎈💰🎈💰
ያልጠበኩት ነገር ነበር የተፈጠረው ነገሩሁሉ ተምታታብኝ እናቴ የነገረችኝ የአባቴ ሁነታ እና እያየው ያለውት የተለየ ነው ።ሽማግሌው የኔ አባት ?ለማመን ተቸገርኩ ፡ እኛን ለማግኘት ያን ያክል ከባድ አልነበረም እንዴት ለሃያ ሦስት አመት ሳያየን ቆየ?
የት ነበር እስከዛሬ ለምን ሕይወቱን በዚ መልኩ ለመኖር ወሰነ የተሻለ ነገር ለማሰብ ለምን አልሞከረም ? አብታምና ምንም ነገር እንደማይሳነው አድርጋ ነበር እናቴ ስለ አባቴ የነገረችኝ ።አሁን የማየው ሰው ግን የተጎሳቆለ እና መንገድ ላይ ላስቲክ ወጥሮ የሚኖር የዋህ ሽማግሌ ነው ። ለምን አይምታታብኝ !
🎈እናቴ በስንት ማባበል ጩኽቷንና ለቅሶዋን አቆመች እነባዩሽ አብረዋት አንብተው ዝም ስትል አብረው ዝም አሉ እኔግን ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ ለዛውም ቁጣን ያዘሉ ጥያቄዎች ። አቤል የሚገባበት ቀዳዳ የሚፈልግ ነው የሚመስለው ፡ሽማግሌው አባታችን መሆኑን ካወቀ ሰአት አንስቶ ምንም አይነት ነገር አልተናገረም ነገርግን ለአንዴ እንኳ ቀና አላለም አንገቱን እንደደፋ ነው ፊቱላይ ያለውን ለውጥ ለማየት እንኳ አልቻልኩም ።  እናቴ በቀስታ "ለምን?"ስትል ሰማዋት ።የኔም ጥያቄ ስለነበር ወደ ሽማግሌው አባቴ ዞርኩ
"ለምን ?ለምንድነው እስከዛሬ ድረስ በሕይወት እያለህ አንዴ እንኳን ተሳስተህ መጥተህ ያላየኽን ? እኛ ለማግኘት እንደማይከብድህ እርግጠኛ ነኝ !እንኳን አንተ ቀርቶ አክስቴ ደግነሽ እንኳ የቀድሞ ሰራተኛህን አግኝታ ያለንበትን አውቃ መጥታለች ። እና አንተስ ? "ብዬ ዝም አልኩ ።እናቴም ቀና ብላ መልሱን ጠበቀች ።
"ይቅርታ አድርጉልኝ እኔ ለእናንተ የምገባ ሰው አይደለውም ጥሩ ሰው አልነበርኩም ።በተለይ ለባለቤቴ ዘውድነሽ አልገባትም ነበር እሷ የዋሕና ገና ታዳጊ ልጅ ነበረች በዛች ትንሽዬ ልጅ ላይ የሕይወትን ሸክም አሸክሜያታለው።  ግን እንደዛ መሆን ነበረበት እንደሱ ባላደርግ ኖሮ ሁላችሁንም በኔ የተነሳ ያጠፏቹ ነበር ። ጓደኞቼ ካልኳቸው ሰዎች ጋር በድንገት በተፈጠረ አለመግባባት ተቃቅረን ነበር ሲያጣላን የነበረው ደሞ በጋራ የሰራነው ስራ ነበር ስራው እገወጥ ነው  ስራውን ሰርተን ስንጨርስ በምንከፋፈለው ድርሻ ምክንያት አለመስማማት ተፈጠረ  እቃውን ያስገባውት እኔነኝ  ነገርግን በስራው ላይ አነስተኛ ድርሻ የነበራቸው ሰዎች እኩል ክፍፍል ሲፈልጉ አይገባችሁም አልኳቸው ፡በወቅቱ የኔን አቅም ስለሚያውቁ የተስማሙ መሰሉ ።በዋላ ላይ ግን በሴራ ጠልፈው ሊጥሉኝ ተስማሙ ፡ከዛ ባላደረኩት ነገር እንድከሰስ አደረጉኝ ፡  ከዛ ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳላገኝ አዋከቡኝ ይህን ልቋቋም አልቻልኩም ክሴን እየተከታተልኩ ። እነሱን ደሞ በሌላ መልኩ ልበቀላቸው ወጥመድ መዘርጋት ጀመርኩ ፡ እና ይህን ፍላጎቴን ለማሳካት ደሞ እናታችሁን እና እናንተን እንዳይነኩብኝ ማራቅ ነበረብኝ ።እናንተ እንዳትቸገሩ ያለኝን በሙሉ ለዘውድነሽ አስተላለፍኩ ቤት ገዛው  ።ምክንያቱም እናንተ ለኔ አይኖቼ ነበራቹ ስጦታዎቼ ....."ብለው ዝም አሉ እኔ ደሞ እገወጥ ስራ ስላሉ ደስ የሚል ስሜት አልተሰማኝም ፡በዛላይ እነዛን ጓደኞቻቸውን ምን አድርገዋቸው ነው ብዬ ተሰቀቅኩ ።የወንጀለኛ ልጅ መሆን ይከብዳል
"እሺ አሳጥረው የት እንደነበሩ ይንገሩን "አልኩ
"ከዛማ እነሱን ለመበቀል የኔን ሰዎች አሰማራው ነገር ግን ሳይሆን ቀረ እኔ አንድ ጉዳት ከማድረሴ በፊት ከኔ የሆነሰው ለነሱ የሚወግን ሆኖ ተገኝቶ እኔን ከዳኝ እናም  ። በላሰብኩት ሁኔታ አሳልፎ ሰጠኝ እነሱም ያልሰራውትን ሁሉ እንደሰራው አድርገው ከሰሱኝ በወቅቱ የነበሩት ከፍተኛ ቦታላይ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በገንዘብ ገዝተው ኖሮ ።በጮህ ብለፈልፍ ሰሚ አጣው እና በቁጥጥር ስር አዋሉኝ ። ከዛ በዋላ እስርቤት ወረወሩኝ ያለምንም ፍርድ ለሃያ አመት እዛው ነበርኩ ፡ልጄ ቅስሜ ሁሉ ተሰባብሮ ።ሰው መሆኔን እስክጠላ ነበር ጉዳዩ  ።ብቻ እንደው ስለጠየከኝ እንጂ ማውራትም አልፈልግም ነበር ባጭሩ ግን ለሃያ አመት ያለፍርድ ታስሬ አለው ስፈታ ወደ እናንተ ነበር የመጣውት ግን ከፍለጋ በዋላ የዘውድነሽን አድራሻ ባውቅም ግን ወደእናንተ መቅረብ አቃተኝ ለምን እንደው ፈራው  "አሉ አይናቸውን ሰበር አድርገው ። ድጋሚ ሌላ ጥያቄ ልጠይቃቸው ልናገርስል ስልኬ ጮኽ ብሌን ነበረች
"ሃሉ "አልኩኝ ለምን በፍጥነትእንዳነሳውት ለራሴም ገረመኝ ምን አልባት ዛሬ የሕይወቴ ፍፃሜ ሊሆን ስለነበር ከሷ መለየቴን ፈርቼው ነበር
"ናቲ የኔውድ ሰላም ነህ በጣም ፈርቻለው"አለች
"ምነው ብሌኔ ደና ነኝ ለምንፈራሽ "አልኳት
"እኔ እንጃ ብቻ በጊዜ ነበር የተኛውት እና ደስ የማይል ህልም አየው ስለ አንተ ደና ነህ አይደል እኔ በህልም ምናምን አላምንም ግን ይሄ ያስፈራል "አለች
"ደና ነኝ ብሌኔ ህልም ህልም በይ በቃ "አልኳት ሳላስበው አቃሰትኩ ። ጭንቅላቴን አመም አደረገኝ
"ምንድነው እየዋሸህ ነው አይደል አንድ ነገር ሆነሃል ?መጣው በቃ "አለች ።
"አይ አይ እኔ ....."ስል ስልኩን ዘጋችብኝ ደግሜ ስደውል ይዘጋል ስልኩ ።ተናደድኩ እንዲ ሆኜ እንድታየኝ አልፈለኩም ።በዛ ላይ የአባቴን ታሪክ እውነተኛውን በትክክል ለመስማት ፈልጌያለው ገና የአቤልም ጉዳይ አልተቋጨም ።ብሌን ተጨማሪ ጭንቀት እንድትሆንብኝ አልፈለኩም ።እሷን ደሞ ንነዲነው እንዲያነው እያሉ ለማስረዳት ተጨማሪ አቅም ከየት ላምጣ ።ጭንቅንቅ ስል እናቴ አይታ ።ወደአቤል በመዞር ወደመኝታ ክፍል እንዲገባ ጠቆመችው ፍፁም ተኮሳትራ ነበር ።አባታችን ግን የትም አይሄድም ብሎ ያዘው .......
የአቤል አይን ተቁለጨለጨ ወደሄትም ማምለጥ እንደማይችል ገባው ከአባታችን ጋር ተፋጠጠ.......


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍8413👎2🥰2🔥1👏1
#ህያብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በኤርሚ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"
👍488🥰2👏1
"ልጅ ያላትን ሴት ማን ሊፈልጋት ይችላል እና በዚህ ምክንያት እሱን ላጣው ነው" እንባዬ ከየት መጣ ሳልለው ዱብ ዱብ አለ።

"እና የእውነትም ልጅ አለሽ ማለት ነው"

"አዎ አለችኝ"

"የት?.... እንዴት?... ማለቴ..." አይን አይኔን እያየ ቀበጣጠረ

ከውስጤ አንዳች ነገር ፈንቅሎ የወጣ እስከሚመስለኝ በሀይል ተናገርኩ"ዝርዝሩን አይደለም ላንተ ለራሴም ደግሜ አልነግረውም እና ለዮናታንም ቢሆን ንገረው በጣም የምወዳት ልጅ አለችኝ ግን ስለ ልጄ የት? እንዴት? ከማን ወለድሻት? የሚል ጥያቄ የሚጠይቀኝ ከሆነ አጠገቤ እንዳይደርስ ንገረው.... አንተም ብትሆን እንደዛው" በተቀመጠበት ትቼው እያለቀስኩ ወደ ዶርም ሄድኩ። በር ላይ ስደርስ የዶርም አጋሮቼ እንዳያውቁ እንባዬን ጠራርጌ ገባሁ። የለበስኩትን ቱታ በቀሚስ ቀይሬ ነጠላዬን አንስቼ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። ገና የውጨኛው በር ላይ እንደደረስኩ እንባዬን ዘረገፍኩት

"ለምን አምላኬ...? ያለፈው ህመሜን ለምን እንድረሳው አታደርገኝም? ለምን ዛሬ እንደሆነ ሁሉ እንደፊልም አየዋለሁ? ዛሬም ከእንቅልፌ በርግጌ መነሳት ዛሬም ስለልጄ ሲጠይቁኝ ደስተኛ ሆኜ ስለሷ ከማውራት ይልቅ እሷ የተፈጠረችበትን አጋጣሚ መርገም..... አምላኬ እኔ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ... እንዴት ባደርግ ነው ትላንትናን ረስቼ ዛሬን መኖር የምችለው...." ረጅም ሰዓት በእንባ እና በእልህ ነገርኩት።

ብዙ አመታቶች ቢቆጠሩም ደስተኛ ቤተሰብ ቢኖረኝም ህልሜ የነበረውን ህክምና እየተማርኩ ቢሆንም የህይወቴ ግማሽ ስኬት ትላንቴን ሊያስረሳኝ አልቻለም። ልክ ዛሬ እንደሆነ ሁሉ ያስፈራኛል.... እንዴት ወንድ የተባለ ፍጡር ላፈቅር እንደቻልኩ ለኔ ጥያቄ ነው። ቢያንስ ግን ውስጤ ያለውን የትዝታ አውሬ እስካልቀሰቀሱብኝ ለሰዎች ሰላማዊና የተረጋጋሁ ሰው ነኝ።

ክላስ ረፍዶብኝ በፍጥነት እየተራመድኩ
"እንኳን ደስ አለሽ ህያብ በዛብህ.... እንኳን ደስ አለሽ" እርምጃዬን ገትቼ ወደኋላ ዞርኩ.... የትናዬት

"እባክሽ ክላስ ረፍዶብኛል" ፊቴን አዙሬ ልሄድ ስል

"ዮናታን ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረ ሰማሽ"አለችኝ። ክው ብዬ ቀረሁ

"ምን እያልሽ ነው" ይሄን ሁሉ ቀን ሊያገኘኝም ሆነ ሊያወራኝ ያልፈለገው ልጅ አላት ስለተባለ እንደሆነ ቢገባኝም እሱ የኔ እንደማይሆን ባስብም ከአይኔ እንዲርቅ ግን አልፈልግም

"ህያብ ዮኒ እንደሚወድሽ ከኔ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም። የኔ ይሆናል ብዬ ባንቺም ላይ በሌሎችም ላይ ብዙ ተንኮል ሰርቻለሁ... " ከአይኗ እንባ ኮለል ብሎ ወረደ

"ይቅርታ አድርጊልኝ ህያብ ከልቤ ነው ብዙ ነገር አድርጌሻለሁ። አንቺ እንኳን ለይተሽ ያላወቅሽውን ብዙ ነገር.... መምህር ውጤትሽን እንዲያበላሽ አልጋው ላይ ወድቂያለሁ... የዶርምሽን ልጆች ገንዘብ እየከፈልኩ እዚህ መሆንሽን እንድትጠይ አድርጊያለሁ... ይሄን ይሄን ብልሽ ጊዜ አይበቃኝም። እኔን ይቅር ባትይኝም ችግር የለውም ስለሚገባኝ ነው። እነሱን ግን ይቅር በያቸው ሁሉንም በደካማ ጎናቸው ይዣቸው ነው" ወደ ጎን ስታይ ከሷ እኩል ዞር ብዬ አየሁ ሁሉም ተደርድረው ቆመው ያዩኛል... አንደኛዋ መጥታ እግሬ ላይ ወደቀች ሌሎቹም ተከተሏት እነሱን አንስቼ ዞር ስል የትናዬት የለችም።

ኦ የትናዬት አልኩ ለራሴ አንደኛ አመት ላይ ሰርቻለሁ ያልኩት ኮርስ ውጤት ተበላሽቶብኝ ያየሁት መከራ ትዝ አለኝ።

ዶርሜ ውስጥስ ቢሆን አንዳቸው እንኳን ጓደኛ ሊያደርጉኝ ፈቃደኛ አልነበሩም በማደርገው በእያንዳንዱ ነገር ይሳለቁብኝ ነበር። ትንሽ ህይወት የምትባለው ትሻላለች። ትዝታ፣ ቤዛዊት እና ዝናሽ የነሱ ይለይ ነበር። እንደ ድንገት ተስቶኝ ከሎከር ውጪ እቃ ካስቀመጥኩ ወይም ሳልቆልፍ ከረሳሁ ወይ የሆነ ነገር ይጠፋል ወይም ደግሞ ቅባትና ሎሺኔ ግማሽ ደርሶ ነው የማገኘው... ኧረ ብዙ ብዙ ለመተኛት ካልሆነ ወደ ዶርም አልሄድም ነበር። የነሱ ይህን ያክል እኔን መግፋት ቢኒ ላይ እንድጣበቅ አደረገኝ። ቢኒ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ጓደኛዬ ወንድሜ አማካሪዬ አስጠኝዬ... ቃል ከሚገልፀው በላይ እወደዋለሁ። ለሴት ጓደኛ እንኳን ለመንገር የሚከብዱ ነገሮችን ነግረዋለሁ አማክረዋለሁ። ከ1 ነገር በስተቀር ስለኔ ሁሉንም ያውቃል ከ1 ውሸት በስተቀር ምንም ዋሽቼው አላውቅም እሱም የትውልድ ሀገሬ አዲስ አበባ እንደሆነ ነው የነገርኩት ሁሉም ቢሆን የሚያውቁት ይህን ነው። በአጠቃላይ ቢኒ የማላውቀውን የወንድም ፍቅር ያወኩበት ልጅ ነው። ይሄን ሰሞን እሱም ጥፍት ብሏል ምናልባት ተቀይሞኝ ይሆናል ቢሆንም አልፈርድበትም ካለን ቅርበት አንፃር እንዴት አልነገረችኝም ሊል ይችላል።

"ይቅርታ ህያብ ከራሴ ጋር ትንሽ ግጭት ውስጥ ነበርኩ ለዛ ነው ካንቺም ከክላስም የጠፋሁት" የእውነት አናዶኝ ነበር

"አንተ ሰው ያስባል ይጨነቃል እንኳን አትልም ግቢውን ለቀህ የት ሄደህ ነው" ትንሽ ካቅማማ በኋላ

"ቤተሰብ ጋ" አለኝ

"የት ድሬዳዋ.... እዛ ነበርክ"

"አዎ"

"ምነው ቤት ሰላም አይደሉም እንዴ"

"አይ ሰላም ናቸው። አሁን ለጠፋሁበት ራት በመጋበዝ እቀጣለሁ" ፈገግ እያለ እጁን ዘረጋልኝ

"ቅጣቱንማ የምወስነው እኔ ነኝ" ተንደርድሬ እቅፉ ውስጥ ገባሁ "የምር ናፍቀኸኝ ነበር ቢኒ ወንድሜ"

"እኔም ናፍቀሽኝ ነበር...
ተማሪማ ከዚህ የበለጠ ሊቀጣ አይችልም ሀሀሀሀ"

ቶሎ ቶሎ ለባብሼ ከዶርም ልወጣ ስል
"እንዲህ አምሮብሽ ወዴት ነው" አለችኝ ቤዛ። ዝም ብያት ልሄድ አልኩና እንደታረቅን ትዝ ሲለኝ "እራት ቀጠሮ አለብኝ ከተባልኩት ሰዓት አርፍጃለሁ" ፊቴን አዙሬ ልወጣ ስል

"ቆይ ቆይ እና እራት ተጋብዘሽ ነው እንደዚህ የለበሽው ነይ ሂዊ እኛ እናልብሳት" ወደኔ መጣችና ቦርሳዬን ተቀብላ ካስቀመጠችው በኋላ ልብስ እያነሰች ማማረጥ ጀመረች "ኧረ ቤዚ ረፍዶብኛል ደግሞኮ ፍቅረኛዬን ላገኝ አልሄድ ቢኒ እኮ ነው" ችኩል ብያለሁ ምክንያቱም ቢኒ ሲያስጠብቁት አይወድም

"ቢሆንም ፏ ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ" በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌላ ሰው አስመሰሉኝ ራሴን በመስታወት ውስጥ ሳየው አምሮብኛል።

"አሁን መሄድ ትችያለሽ ሰላም ተመለሽ" ህይወት ጉንጬን ሳም አደረገችኝና በር ከፍታ አስወጣችኝ። ለኔ አዲስ ሰዎች ነው የሆኑብኝ ግን ከልባቸው እንደሆነ በደንብ ያስታውቃል።

"ይቅርታ ቢኒ ከወጣሁ በኋላ እኮ እነ ህይወት እንደዚ ለብሰሽ አትሄጂም ብለውኝ"

"ችግር የለውም ውዷ ብዙም አላስጠበቅሽኝም" ተያይዘን ከግቢ ወጣን በየጥጋጥጉ እንዲሁም በደንበኞች ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡት የሻማ መብራቶች ለሆቴሉ ልዩ ውበት አጎናፅፈውታል። በአድናቆት ዙሪያ ገባውን እያየሁ አንድ አስተናጋጅ ወደኛ መጣና ለየት ብሎ ወደተዘጋጀ ጠረጴዛ እየመራ ወሰደን.... ከተቀመጥን በኋላ

"አንተ ምንድነው ነገሩን ሁሉ ሮማንስ አደረከው እኮ የምር ግራ እያጋባህኝ ነው ትልቅ ሆቴል መግባታችን ሲያስገርመኝ ጭራሽ.." የማወራውን ነገር ችላ ብሎ

"እባክህን ሜኑ አምጣልን" ግራ ገብቶኝ ዝም ብዬ አያየሁት ሜኑ እጄ ላይ አረፈ ተቀብዬ ስገልጠው የምታምር ትንሽዬ ቀይ አበባ ውስጡ ቁጭ ብላለች። ቀና ብዬ አስተናጋጁን አየሁት ቅልቅ ድንጋጤ.... አበባዋን አንስቶ አጠገቤ ብርክክ አለ

"ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"

"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው.....

ይቀጥላል
👍8417👏4🥰3
⚫️🎈የእናቴ ልጅ🎈⚫️
ክፍል ሃያ ስምንት
💰💰💰💰💰💰💰
አባታችን አቤል ላይ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁላችንም ማፍጠጣችን አልቀረም ። አቤል ፍርሐቱ እንዳለ ሆኖ የአባታችንን ሁኔታ ለመጋፈጥ አይል ለማሰባሰብ ሲሞክር አየውት እጆቹን እንደማወራጨት ብሎ  ወደክፍሉ ለመግባት አባታችንን ዘወርበልልኝ በሚል አስተያየት አየው ።
"እስካሁን ምንም አይነት የጥፋተኝነት ስሜት አላየውብህም ።ከዛ ይልቅ ስላወቅንብህ የቆጨኽ ነው የምትመስለው ፡እንዴት በአንድ ወንድምህ ላይ የዚህን ያክል በደል አድርሰህበት ምንም አይመስልህም ፡እውነት አንተ የኔ ልጅ ነህ ምን አይነት ጉድ ነህ ፡ አንተ ዛሬ አንድኛውን ልጄን አሳጥተኽኝ ነበር  አዎ እዛቦታላይ ደርሼ ነገሩን ባላስቆመው ኖሮ በጭካኔ አስገድለኽው ነበር እና ስለዚ አንተ የሚገባህ በሰላም ወደ ክፍልህ ገብተኽ መተኛት ሳይሆን መቀጣት ነው ያለብህ ፡እና የትም እንዳትሄድ እዚሁ ቁም የወንድምህን ውሳኔ እስክትሰማ "አሉት ።እናቴ በድጋሚ አለቀሰች ።እናቴ ምናልባት ዛሬ ባለቤቷን በዛ መልኩ በማግኘቷም ጭምር ግራ መጋባት ውስጥ ሳቶን አትቀርም ፡ብዙ አዘኖች ተደራርበው እየሰባበሯት ነው ምን እንደምትወስን ገና አላወቀችም ፡አቤልን ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷታል ። እኔ ደሞ አሳቤ ሁሉ ተምታቶብኛል ፡ የአባታችን በዚመጠን እራሱን ዝቅ አድርጎ ከኛ መደበቁንና ፡አኗኗራችንን ሲከታተል መቆየቱ በጣም ነው ያሳዘነኝ ።ጠጋብሎ ያለበትን ሁኔታ ቢነግረን ምን አለ ፡ ይሁሉ ላይፈጠር ይችል ነበር ፡እናታችን ያለአጋዥ ያሳለፈችውን ሕይወት በግልፅ ቢመጣ ያቀልላት ነበር  ።መቼም እናቴ በግልፅ ነገሮችን ስትረዳ ለይቅርታ አትሰስትም ።  ግን ያሳዝናል። እንግዲ አባታችን በራሱመንገድ እራሱን እየቀጣ ነበረ ። አቤል በአባታችን ቆፍጠን ያለ ንግግር የተደናገጠ መሰለ እናም እየተርበተበተ "እኔ ስለምትሉት ነገር አአላውቅም ሆነ ብለው እኔንና ወንድሜን ለማለያየት ያደረጉት ነው ፡ "አለ ።እኔ በጣም ተናደድኩ መናገር ግን አቃተኝ ።
"ተው ተው ቢያንስ እንኳ ከዚ በዋላ እንኳ ለመፀፀት ልብ ይኑርህ"አለው አባታችን ተቆጥቶ
"ለምን ባላረኩት ነገር እፀፀታለው ፡"አለ አቤል በድርቅና
"አንተ የማትረባ ልጅ እናትህ እንዴት አድርጋ እንዳሳደገችህ አላውቅም ፡ በጣም አስመሳይ እና ከሃዲ ነህ አንተ ልጄ አይደለህም አፈር ብላ "አለው አባታችን በንዴት ጦፎ
"እኔም ድንገት አንድ የጎዳና ሰው መጥቶ አባትህ ነኝ ቢለኝ የምቀበል ሰው አይደለውም "ሲል ለመነሳት ሞከርኩ አቅም አጣው ።እናቴ ግን ከመቅስበት ተነስታ እኔ ያሰብኩትን ፈፀመች ።አቤልን ሄዳ በጥፊ ስታጮለው ቤቱውስጥ ፍንዳታ የተከሰተ መሰለ ።ደስ ነው ያለኝ ።እራሴን ግን አልቻልኩም ፡ ህመሙ እየበረታብኝ ነው አይኖቼ ብዥዥ እያሉብኝ ነው ።የአባታችን ቁጣ ወደ አይል ተለወጠ እናቴ ከዚ በፊት የአባቱ ልጅ ብላ በስድብ መልክ የተናገረችኝ ትዝ አለኝ ፡ አባቴ የመጨረሻ ትህግስቱን ሲያጣ ማንም አይችለውም ፡ልክ እንደኔ ፡ አቤልን አንቆ ያዘው ።
"አንተ ደደብ እያናገርኩህ ያለውት ስለኔ አይደለም ስለ ምስኪኑ መልካሙ ወንድምህ ነው ፡እና እኔን ልትዋሸኝ ነው ና እንደውም ከአጋርህ ጋር ነው የምትቆየው ።እዚህማ በሰላም አታድርም እውነቱን ከሱጋር ታወራላቹ !!"ብሎ አባታችን አቤልን እየጎተተው ከትልቁቤት ይዞት ወጣ ። አቤል ለመከላከል ሲሞክር ደና ጥፊ አቀመሰው ። እናቴ ወደ እኔ አየች
"እናቴ በአቤል ተቀጥሮ ሊገለኝ የነበረው ልጅ እዚ ነው ያለው ይዘነው መጥተን ሰርፒስ ቤት ቆልፈንበታል እዛ ነው የሚወስዱት "አልኳት ።አፏን ያዘች ። ደግነሽ "ጉድ ነው ኧረዋ ጭካኔ ፡እኔ አፈር ይብላኝ ናቲዬ ወንድሜ ወንድሜ ስትል ለሱ ስትለፋ ፀባዩ ተስተካክሏል ስትል ድፍት አድርጎ ሊያስቀርህ ነበር ፡ናቲዬ መቼም አንተን ገሎ አያቆምም ነበር እናትህም አይቀርላት ፡መቼም ገንዘብ አይን ያሳውራል አብዝቶ መውደድ አያስፈልግም ኧረ ኧረ"አለች ።ባዩሽ አንገቷን ነቀነቀች ።
🎈የጊቢያችን መጥሪያ ስታቃጭል ተሰማ  ደግነሽ "አሁን ደሞ ምንድነው "አለች
"ተረጋጊ ብሌን ትሆናለች "አልኳት
"እሺ እኔ ከፍታለው "ብላ ወጣች እናቴ ወደኔ ቀረብ ብላ"ደና ነህ ግን ልጄ አኪም ቢያይህ አይሻልም ፡ከሱጋር ስንጨቃጨቅ አንተን እረሳንህ ።"አለችኝ
"አይ ደና ነኝ እናቴ አታስቢ ትንሽ እራስምታት ነው "አልኳት እንደ እውነቱ ከሆነ ከባድ ነው  ።ብሌን ስትገባ ድንገት ተነስታ እንደመጣች ያስታውቅባታል ቢጃማዋ ላይ የሴት ካቦርት ነገር ጣል አድርጋ ነጠላ ጫማ ተጫምታ እረጅም ፀጉራ ላይ ሻሽ ሸብ አድርጋ ለች ።ሁኔታውን ወደድኩት ሁሉም ነገር የሚያምርባት ልጅ !!!!    ስታየኝ በድንጋጤ ወከክ አለች ስፍስፍ ብላ ስትነካካኝ "ደና ነኝ አትጨነቂ "አልኳት
"አይ አይ ደና አይደለህም ምንድነው እሱ በፈጣሪ "አለች አናቴላይ የተጠቀለለውን ጨርቅ በፍርሃት ነበር የምታየው
"ደና ነኝ ሳላስበውከዋላ አጠቁኝ  ሁኔታው ያስፈራ ነበር አሁን ግን ደና ነኝ "አልኳት
"ታውቆኝ ነበር እንዲ አይነት የተጨናነቀ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም በጣም አስፈሪ የሚያስደነግጥ ስላንተ ብቻ ነበር የኔ ውድ በጣም ጎድተውሃል "አለችኝ ዕንባዋን እየታገለች
"እእ አዎ በእርግጥ ቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ ነበር አመጣጡ ሊገለኝ ነበር "አልኳት ሳወራ እራሱ አቅም እያጣው ነበር
"በቃ በቃ ዝም በል ።ተነስ አሁኔ አኪም ሊያይህ ይገባል እንዳየሁት ከሆነ ደም ፈሶሃል ተነስ "አለቼ
"ብሌን የኔ ውድ አትጨነቂ ደና እሆናለው "አልኳት
"አይ እንደሱ አይደለም ስታድር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ግድ ነው ተነስ መሰፋት ያለበት ቦታ ሊኖር ይችላል "አለች ።እናቴ አሳቧን የሚጋራት በማግኘቷ ደስ ያላት ይመስላል ቀብሌን አሳብ ተስማማች እሷም ግፊት አድርጋ ።በመጨረሻ ተስማማው ።ስንወጣ አባታችን ከሰርፒስ ቤቱ ወጥተው ሲመጡ አይታ ብሌን በጥያቄ አስተዋለችኝ።
"እሳቸው ናቸው ያዳኑኝ ታሪኩን ሌላ ጊዜ እነግርሻለው "አልኳት
"እሺ "አለች ።አባታችን ወደ አኪም ቤት መሄዳችንን ስንነግረው ተስማማ ።እናቴ እና ብሌን ከኔጋር አብረን ውጪ የቆመችዋ የብሌን መኪና ውስጥ ገባን ። ቀስበቀስ አቅሜ እየተዳከመ መጣ ወደ እናቴ ዘንበል አልኩ እናቴ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ።እጇን በትኩሳት ያበደ ጭንቅላቴ ላይ ጣል አድርጋ ታሻሸኝ ጀመር ....
ብሌን መኪናዋን በፍጥነት እየነዳች ስቅ የሚል ድምፅ ስታወጣ ይሰማኛል ፡የኔ ፍቅር የኔ እብድ ዛሬ በኔ እየተፈተነች ነው ምንም እንዳልሆንባት ነው የምትፈልገው ...........


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍13826😁6👏5👎2🔥1
#ህያብ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በኤርሚ


"ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"

"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው። ፈገግታው ውስጥ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የሚል መልዕክት ያነበብኩ መሰለኝ••• አበባውን ተቀበልኩ

ከዮኒ ጋር ህልም የሚመስሉ ሁለት ሳምንታትን አሳለፍን። ሁሉም ነገር በጣም ደስ የሚል ነበር እያንዳንዷን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍናት።

ጎንደርን ለቆ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድበት ቀን ደረሰ እኔና ቢን ቀድመን ለመሰናበት አገኘነው።
ካፌ ተገናኝተን ሞቅ ያለ ወሬ እያወራን በመሀል ቢኒ
"ይህን ሁሉ ጊዜ አስለፍተሀት አንድ ወርም ሳይቆይ ልትሄድ ነው?" አለው።

"በልፋት እንኳን ከኔ የበለጠ የለፋች አይመስለኝም ሀሀሀሀ ስቀልድ ነው። ይሄን የመሰለ ፍቅር ትቼ መሄዴ ሳያስከፋኝ ቀርቶ መሰለህ በእርግጥ መጀመሪያ ወድጄና ፈቅጄ እንደውም በጣም ፈልጌው ነበር ዝውውር የጠየኩት" ያልሰማሁት አዲስ ነገር ሆነብኝ

"አንተ ጠይቀህ ነው እንዴ የተዘዋወርከው" ግርም ብሎኝ ጠየኩት

"አዎ ለዚህ ዝውውር እስከ ጥግ ለፍቻለሁ አሁን ግን አልፈልገውም ነበር ግን ምንም ማድረግ አልችልም" እዝን ብሎ አንገቱን ደፋ

"ለምን ነበር ዝውውሩን የጠየከው" ቢኒ ጣልቃ ገባ

"በሷ ምክንያት ነዋ" እጄን በእጁ እያጠላለፈ "ያን ሁሉ ነገር ሰማሁ ምንም ብሰማ እንኳን ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሊቀንስ አልቻለም ጭራሽ የማላውቀው ስበት ወዳንቺ ይገፋኛል። መቋቋም አቃተኝ ስራዬ ላይ ሳይቀር ተፅዕኖ ፈጠረብኝ እናም መሸሽን መረጥኩ እና ዝውውር ጠየኩ"

"የዚህ አመት ትምህርት ሲያልቅ እመጣ አይደል ከእናቴ ውጪ የሚቀበለኝ ሰው አለ ማለት ነው" መሄዱ ሀዘን እንዳይለቅብኝ መልካም መልካም ነገሮችን ለማውራትና ለማሰብ ሞከርኩ

"እስከዛው አደራ የምለው ላንተ ነው ቢኒያም.... ናፍቆት ናፍቆት እያለች ትምህርት ላይ እንዳትዘናጋ ደግሞ በስልክም እናወራለን" ቢኒ በአንገት ንቅናቄ እሽታውን ገለፀ።

ፍቅሬን ሞቅ ባለ ስንብት ወደ አዲስ አበባ ሸኘነው።

እኔ ልሁን እሱ ይሁን ማን እንደተቀየረ ባይገባኝም ከቢኒ ጋር እንደድሯችን ልንሆን አልቻልንም ሳገኘው ሳወራው  የሆነ ክፍተት እንዳለ ይሰማኛል። መጥፎ ስሜቶች አብረውኝ እንዲቆዩ አልፋግም እሱን ለማውራት ወሰንኩ

"ቢን ግን የተፈጠረ ችግር አለ ማለቴ ምንም እንደድሮው ልንሆን አልቻልንም እኮ ያጠፋሁት ጥፋት አለ እንዴ"

"ኖ ህያብ ምንም አላጠፋሽም እኔ ነኝ በራሴ ችግር ምክንያት ነው አንቺም ለይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ አላወኩም.... "

"እና ችግሩን ንገራታ መፍትሄው እኮ በሷ እጅ ነው" የቢኒ ጓደኛ ሀብታሙ ከየት መጣ ሳይባል አጠገባችን ተገኝቷል

"እየውልሽ ህያብ ቢኒ ባንቺ ምክንያት ሀገ..." ንግግሩን ሳይጨርስ የቢኒ እጅ አፉ ላይ አረፈ እና እንቅ አድርጎ ያዘው ትንሽ ከታገሉ በኋላ ለቀቀው

"ባለፈው እንደነገርኩህ ነው ወይ ንገራት ካለዛ እኔ እነግራታለሁ"

" ቢኒ ምንድነው ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ" ቢኒ ግራ ገብቶት አንዴ እሱን አንዴ እኔን ያያል።

"አቦ ዝም ብለህ እኮ ነው የምታካብደው" ሀብታሙ በንዴት እየተወናጨፈ ትቶን ሄደ

"ቢን ንገረኝ ምንድነው ከኔ የምትደብቀው ነገር አለ እንዴ"

"አይ ህያብ ለመደበቅ አይደለም እነግርሻለሁ ምን መሰለሽ ግን.... እ...እ....እ ማለቴ እኔ ካንቺ..... ማለቴ ....አንቺን.... "

እኔ ቢኒያም ነኝ ልተርክላቹ

ከመጀመሪያ ጀምሮ ምን እንደተፈጠረ ልንገራችሁ። ህያብን አፈቅራታለሁ አጠገቤ እያለች የማንም ሳትሆን በየቀኑ አብሪያት ስሆን ስንተቃቀፍ ስናወራ አብረን ስንበላና ስንጠጣ ጭንቅላቴ የሚያስበው ጓደኛዬ እንደሆነች ቢሆንም ይህ ልቤ ግን ሁሉን ነገር ፍቅር ብሎ ይወስደው ነበር። ሁሉም ነገር የገባኝ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ሳያት ነው። መቋቋም አቃተኝ

ከዮኒ ጋር ካወራን በኋላ እሷ ያለምንም ጥርጥር የሱ እንደምትሆን አመንኩ በዛው ልክ ደግሞ ህያብን ላጣት እንደሆነ እና መቼም የኔ እንደማትሆን ተረዳሁ....  አለ አይደል በቃ ሳስብ የኖርኩት የዮኒ ብልግና የሆነ ቀን አንገሽግሿት እሱን መፈለጓን ለማቆም የምትወስን..... ከዛ የኔ የምትሆንበት ሰፊ እድል.....
በነዛ ሁሉ ጊዜያቶች ለራሴ ስነግረው የነበረው ህያብ መቼም ቢሆን ከዛ ባለጌ ዮኒ ጋር ልትሆን እንደማትችል እና የኔ እና የኔ ብቻ እንደምትሆን ነበር። ሁኔታዎች ግን ባላሰብኩት መንገድ ድብልቅልቃቸው ወጣ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ላያት ሆነ።

ለዶርም ጓደኞቼ ህያብም ሆነ ማንም ቢጠይቃቸው ቤተሰብ ጋ እንደሄድኩ እንዲነግሩ አስጠንቅቄ ከሀብታሙ ጋር አዲስ አበባ አክስቱ ቤት ሄድን። ሀብታሙ ከስር ከመሰረቱ ለሷ ያለኝን ፍቅር ያውቃል እንድቀርባትም ያደፋፈረኝ እሱ ነበር ለዛም ነው ብቻዬን ልሂድ ስለው አይሆንም ብሎኝ አክስቱ ጋር በነፃነት መሆን እንደምንችል አሳምኖኝ አብሮኝ የመጣው

ለቀናት ጠጣሁ ሰከርኩ በእብደት አለም ውስጥ ዋዠኩ። መርጋጋት የሚባለው ነገር ከኔ በእጥፍ እራቀ። ሁኔታዬ ያሳሰበው ሀብትሽ ከቀናት በኋላ መጠጥ ከሚባል ቦታ እንዳልደርስ በግድ ከለከለኝ

ወደምጠጣበት ቦታ ለመሄድ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ጫማዬን እያሰርኩ ፊት ለፊቴ መጥቶ ቆመና "ምን እየሆንክ ነው በዚህ ሁኔታህ ህያብን የምታገኛት ይመስልሀል። ቢኒያም እንደዚህ እየሆነ መሆኑን የምታውቅ መሰለህ.... እሷማ የምታውቀው ቢኒ እንደታላቅ ወንድም የምታየው ጓደኛዋ እንደሆነ ነው። ንገረኝ እስኪ በማን ላይ ነው የተናደድከው ህያብ ላይ ነው?"

"አይደለም" አልኩት አንገቴን እንደደፋሁ

"በፍቅር ነው?"

"አይደለም እሷን በማፍቀሬማ ደስተኛ ነኝ"

"በራስህ ነው?"

"አዎ ምክንያቱም እስከዛሬ ያመንኩበት ሁሉ ገደል ገባ"

"ይህ እንዳይሆን ማድረግ የምትችለው ነገር ነበር?"

"አላውቅም ምን ላደርግ እችላለሁ መጀመሪያ ነግሪያት ቢሆን የምትወደው ጓደኛዋ ለመሆን አልችልም ነበር። መሀል ላይ ደግሞ ያመንኩት የሱ ነገር ስልችቷት እኔን እንደምታይ ነበር። አሁን ደግሞ ረፍዷል እና በራሴ የትኛውን ነገር አላደረክም ብዬ ልናደድበት?"

"ጥያቄዬን በጥያቄ ሳይሆን በቀጥታ መልስልኝ በራስህ ነው የተናደድከው?"

"አይደለም" አልኩት

"በዮኒ ነው?"

"አይደለም"?

" እና በማን ነው"?

"አላውቅም" አልኩት እውነት ግን በማን ነው የተናደድኩት

"እሺ ለምንድነው እንደዚ እየሆንክ ያለኸው"

"ትቀልዳለህ እንዴ ህያብ የኔ ስለማትሆን ነዋ! በናትህ አሁን መጠጣት ነው የምፈልገው" አልኩት ወሬውን ጨርሶ ዞር እንዲልልኝ በማሰብ

"እንደዚህ መሆንህ ህያብን ያንተ እንድትሆን ያደርጋታል?"

"አያደርጋትም" ከፊት ለፊቴ ዞር አለና ከኮመዲኖ ላይ ቁልፍ እነሳ ከዛ ቀጥታ ወደበሩ አመራ እና ቁልፉን እያሳየኝ

"ስለዚህ በማን እንደተናደድክ አታውቅም ግን ምስኪኑን ጨጓራህን በመጠጥ እያነደድከው ነው ቢያንስ ለጨጓራህ በጠዋት እየተነሳሁ እስከማታ በመጠጥ የማነድህ በዚህ ሰው ተናድጄ ነው ብለህ አንድ ምክንያት ንገረው። ህያብ ደግሞ ከእጅህ ወጥታለች ስለዚህ ሁኔታዎችን አምነህ ተቀበል ወይም ያንተ የምትሆን ከሆነ ያንን ጊዜ ጠብቅ.... ወደራስህ ተመልሰህ ጠብቀኝ ምግብ ይዤ እመጣለሁ" በሩን ቆልፎብኝ ሄደ

ያለሁበት አንድ ክፍል ቤት ሌላ መውጫ የለውም ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና አልጋ ላይ ወጥቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ።
👍9611👏4🔥2🤩1
ምን ያክል ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም የቀናት እንቅልፍ ማጣትና ድካሜ በትንሹ ቀለል ብሎኝ ሆዴን ደግሞ ከባድ ረሀብ እየሞረሞረኝ ነበር። ተነሳሁና የሚበላ ነገር ስፈልግ ጠረጴዛ ላይ ተከድኖ የተቀመጠ ምግብ አገኘሁ። እየበላሁ እያለ ሀብትሽ ገባ

"እሺ አፍቃሪው እኔማ ይሄ ልጅ ሳር እንዳይበቅልበት እያልኩ ነበር" አጠገቤ መጥቶ እየተቀመጠ

"ብዙ ተኛሁ እንዴ"

"ለስድስት ሰዓት ያክል ነው የተኛኸው ያውም ምግቡን ካመጣሁልክ ጀምሮ ያለውን ብቻ ቆጥሬው" አለኝ እየሳቀ "አሁን ማውራት ይኖርብናል እየውልክ እዛ ትተን የመጣነው ትምህርት ነው... ነጋችንን ነው.... ሁሉንም ነገር ለጊዜ ስጠው 'ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው' ስትል ሰምቼህ አውቃለሁ። ይህን ጉዳይም ለጊዜ ስጠው ፈጣሪ ያንተ ካላት ከማንም ጋር ብትሆን ተመልሳ ያንተ ትሆናለች ያንተ ካላላት ግን የቱንም ያክል ብትለፋ ያንተ አትሆንም። የሆነች ቢመስልህና በፍቅር አመታቶችን ብታሳልፉ እንኳን ፈጣሪ ወዳለላት ትሄዳለች እንጂ ያንተ አትሆንም ስለዚህ ለፈጣሪ እና ለጊዜ ሁሉንም ተወው። እሷን ማፍቀርህን አቁም አልልህም ብልህም ሊሆን የማይችል እንደሆነ ይገባኛል ግን ለሷ ያለህ ፍቅር ዛሬ ማድረግ ያለብህን ነገሮች እንዳታደርግ አድርጎ ነገህን ሊያጨልምብህ አይገባም" ለኔ ምን ያክል እንደተጨነቀልኝ ገባኝ እኔን ብቻ ሳይሆን እሱንም ከትምህርቱ አስተጓጉየዋለሁ

"ትኬት ቆርጠን ነገ በሌሊት እንሄዳለን" አልኩት። በደስታ አቀፈኝ

ከተመለስን በኋላ ልክ እንደመጀመሪያው ለመቀጠል ሞከርኩ ህያብና ዮኒን ለማገናኘት... አደረኩትም አገናኝኋቸው።

ህያብ በሄደችበት እንደሴት ጓደኛዋ እኔን ይዛ መሄድ ነው የለመደችው ዮኒ ጋ በምትወስደኝ ጊዜ ግን
የሚሰማኝን ስሜት መግታት አቃተኝ በቦታው እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ዶርም ስገባ ግን ሌላ ሰው ሆንኩ። ማንበብ የሚባለውን ነገር እርግፍ አድርጌ ተውኩ በድጋሚ ጠጥቼ መስከር ጀመርኩ
ነጭናጫ እና ሆደ ባሻ ሆንኩ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ሀብትሽ አብሮኝ ተሰቃዬ

"ትነግራታለህ ካለዛ እኔ እነግራታለሁ" አለኝ ክላስ ቀጥቼ በተኛሁበት አጠገቤ መጥቶ እየተቀመጠ። ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁና

"ያምሃል እንዴ ጭራሽ ጓደኝነታችንንም ልጣው" አልኩት

"ህያብ ከማውቃቸው ሁሉ እስተዋይ ልጅ ናት ምን ያክል እንደተሰቃይህ ስታውቅ ታዝንልህ ይሆናል ምናልባት የሚፈጠረውን ማን ያውቃል" አለኝ

"እንድታዝንልኝ ሳይሆን እንድታፈቅረኝ ነው የምፈልገው" አልኩት ጮክ ብዬ

"ፍቅር ከሀዘኔታም ይመነጫል ይህንም ያልከኝ አንተ ነህ የኔ ፈላስፋ" አለኝ እየሳቀ

"ህያብ እኮ የሌላ ሰው ሆናለች ማንም አብሯት ባይሆን እሺ እድል ይኖረኛል አሁን ግን...." አላስጨረሰኝም

"ዮናታንን ነው.... አሁን እኮ አጠገቧ አይደለም አዲስ አበባ ሄዷል። ከአይን የራቀ ደግሞ ከልብም ሊርቅ ይችላል። አይኗ ስር ያለኸው አንተ ነህ እድልህን ሞክር። የእውነቴን ነው የምልህ ካለዛ እንደዚ እየሆንኩ እቀጥላለሁ ብትል ሁለም ነገር... ከስር መሰረቱ ጀምሮ የተፈጠረውን እኔ እነግራታለሁ ምርጫው ያንተ ነው ከኔ አፍ ወይስ ካንተ ትስማው" ኮስተር ብሎ ነው የተናገረው ሊያደርገውም ይችላል።

"ከኔም ካንተም አፍ አትሰማም እኔ ለመስተካከልና እንደድሮዬ ለመሆን እሞክራለሁ" እልኩት ይህን ልበለው እንጂ ቀጣይ ቀናትም በዛው ሁኔታዬ ነበር የቀጠልኩት

የሆነኛው ቀን ላይ እያነበበ ያለውን መፅሀፍ ድንገት ዘጋና

"ህያብ ጋር ልሄድ ነው" አለኝ

"ለምን"

"ሁሉንም ነገር ልነግራት አንተ ካልቻልክ እኔ እነግራታለሁ" ሀብትሽ ትእግስተኛ ሰው አይደለም በዛ ላይ ደፋርና ቁጡ ነው። እንደሚያደርገው ቅንጣት አልተጠራጠርኩም

"እንድናወራ ቀጥራኛለች እኔ እነግራታለሁ" አልኩት እንደምነግራት ግን እርግጠኛ አልነበርኩም

ወደ ዋናው ሀሳባችን ስመለስ

"ቢን ግን የተፈጠረ ችግር አለ ማለቴ ምንም እንደድሮው ልንሆን አልቻልንም እኮ ያጠፋሁት ጥፋት አለ እንዴ" ንግግሯ አንጀት ይበላል የምር አሳዘነችኝ

"ኖ ህያብ ምንም አላጠፋሽም እኔ ነኝ በራሴ ችግር ምክንያት ነው አንቺም ለይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ አላወኩም.... " ምን መናገር እንዳለብኝ ግራ ግብት ብሎኝ ከዬት መጣ ሳልለው ሀብታሙ

"እና ችግሩን ንገራታ መፍትሄው እኮ በሷ እጅ ነው" አለኝ። እንደማልነግራት ስላወቀ ነው ተከትሎኝ የመጣው

"እየውልሽ ህያብ ቢኒ ባንቺ ምክንያት ሀገ..." ንግግሩን ሳይጨርስ ዘልዬ እፉን ያዝኩት ከለቀቅሁት በኋላ

"ባለፈው እንደነገርኩህ ነው ወይ ንገራት ካለዛ እኔ እነግራታለሁ" ብሎኝ ሄደ ያደርገዋል። ስለዚህ እኔ እነግራታለሁ ግን እንዴት???

"ቢን ንገረኝ ምንድነው ከኔ የምትደብቀው ነገር አለ እንዴ" አለችኝ በተማፅኖ አይን እያየችኝ

"አይ ህያብ ለመደበቅ አይደለም እነግርሻለሁ ምን መሰለሽ ግን.... እ...እ....እ ማለቴ እኔ ካንቺ..... ማለቴ ....አንቺን.... " ተንተባተብኩ

"እኔን አንተ ምን? ቢኒ ምንድነው ንገረኝ?" አይሆንም አልኩ በውስጤ.... በፍፁም አይሆንም.... ወደራሴ መመለስ፣ ከህያብ ጋር እንደድሮዬ መቀጠል፣ ሀብታሙንም ማሳመን ነው ያለብኝ። የኔ ላትሆን ነገር የምትወደውን ታላቅ ወንድሟን አፈቅርሻለሁ ብዬ ላሳጣት አልፈልግም። በሀሳብ ተውጬ ስቀርባት እጇን ፊቴ ላይ እያውለበለበች

"እኔን እዚህ አስቀምጠህ የት ሄድክ። አየጠበኩህ ነው ቢኒ ንገረኝ ታውቀኝ አይደል አስተዋይ እኮ አይደለሁም በነገሮች መሀል አስከፍቼህ ይሆናል" እንዲህ ናት ህያብ በድለዋት እንኳን በዛ ውስጥ ያንን ሰው ይቅር ለማለት የራሷን ጥፋት የምትፈልግ...
እንደዚ የሆነው ይህን ስላረኩ ነው ብላ ይቅርታ ሳይጠይቋት እንኳን ይቅር የምትል.... ንፁህ ልብ ያላት ልጅ ይህን ልቧን ደግሞ ከዮኒም ሆነ ከማንም በላይ የማውቀው እኔ ነኝ።

"ማለቴ እኔ አንቺን ዋሽቼሻለሁ" ድንገት የመጣልኝን ነው የተናገርኩት

"ለዚህ ነው ይሄ ሁሉ ጭንቅ ብትዋሽ እንኳን ያለምክንያት እንደማትዋሸኝ አውቃለሁ ግን ምንድነው የዋሸኸኝ ልስማው እስኪ"

"ባለፈው እኮ ድሬደዋ ሳይሆን አዲስ አበባ ነው የሄድኩት ማለቴ የሀብትሽ አክስት ጋር ግን እዛ ሆኜ ትንሽ አሞኝ" ቀበጣጠርኩ

"ምንህን? ምን ሆነክ?" ህመሜን ፊቴ ላይ የምታይ ይመስል ፊቴን ግራ ቀኝ እያዟዟረች አየችኝ

"አይ ብዙም ከባድ አይደለም እኮ የኩላሊት ጠጠር ብለውኝ"

"ድሮም እኮ ሰው የሚልህን አትሰማም ራስህን አትንከባከብም የከፋ ደርጇ ደርሷል ወይስ"

"አይ ብዙም አይደለም"

" በል ከነገ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን እየሄድን ፀበል ትጠጣለህ ከዛ መልስ ደግሞ ውሃ ትጠጣለህ በትንሹ እስከ አምስት ሌትር" ምነው ካልጠፋ በሽታ የኩላሊት ጠጠር ባልልስ በየሰዓቱ እየጠጣሁ ስሸና ታየኝ እኮ ኡፍፍፍ....

እንደማታሸንፍ እያወክ መታገል ትርፉ መጋጋጥ ነው ብዬ አስባለሁ እኔም እንደዛ እየሆንኩ መሰለኝ እና አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ወይ በትግሌ ቀጥዬ ራሴን ማጣት ወይም እንደተመከርኩት ለጊዜ ሰጥቼ ራሴን ማረጋጋት። መረጋጋትን መርጫለሁ

ሀብትሽ እንዳልነገርኳት ሲያውቅ ዶርሙን ቀውጢ አድርጎት ነበር ግን እንደምንም አረጋግቼው ሀሳቤን ነገርኩት

"አቦ ሀብትሽ ደግሞ አታካብዳ በቃ ከልቤ ነው አልኩህ አይደል እመነኝ"

"እስኪ እናቴን በለኝ እንደዛ ካልክ አምንሀለሁ" እናቴን ብዬ ብዙ ጊዜ አልምልም ከማልኩም በጣም ሳመር እንደሆነ ያውቃሉ።
👍667🥰3👏3
"እናቴን ሀብትሽ! በቃ ጓደኝነታችንን አጥቼው መሰቃዬት አልፈልግም። ትምህርቴንም እንደድሮዬ እሆናለሁ ባጠቃላይ እንደነገርኩህ ነው የእውነት እስተካከላለሁ"

"እሺ ቢኒ እተማመንብሀለሁ"  ወዳጃዊ በሆነ ፈገግታ እያዬኝ

ሰለ ሀብትሽ ሳስብ ይገርመኛል ባንዴ ብዙ ገፀ ባህሪዎችን የተላበሰ ድንቅ ልጅ.... ተጫዋች... ደስ ሲለው ኮስታራ..... በጣም ሰቃይ ተማሪ.....  ደግና ለሰው አዛኝ ደግሞም ቁጡና ሀይለኛ.... የሚገርም ትዕግስት አለው ብላችሁ ሳትጨርሱ ግልፍተኝነቱን ታዩታላችሁ....bእኔ ከሀብትሽ ጋር ስሆን ከብዙ ሰው ጋር የሆንኩ ነው የሚመስለኝ። ሀብትሽ ለወደደው ሟች ነው ልክ እንደታላቅ ወንድም መንገድ ስስት ካዬኝ ምክር ቁጣ ከዛ ካለፈም ስድብ ይኖራል። በህያብ ጉዳይ እንደዚ ስሆን እሱ ካጠገቤ ባይኖርልኝ ኖሮ ምን እንደምሆን ሁሉ መገመት አልችልም....

ቀላል ባይሆንም እንዳልኩት ነገሮች እየቀጠሉ ነው። ከህያብ ጋር ሰላማዊ ግንኙነታችንን መልሼ ትምህርቴም ላይ ትኩረቴን አድርጊያለሁ

#ህያብ_ነኝ

ቢኒን ካወራሁት በኋላ ምክንያቱን ነግሮኝ እንደድሯችን ቀጥለናል.... ከዮኒም ጋር በየቀኑ እንደዋወላለን። ከዶርም አጋሮቼም ጋር የሚያስቀና እና ሰላማዊ ግንኙነት ኖሮናል።

የትናዬትን ይቅርታ ከጠየቀችኝ በኋላ አይቻት አላውቅም ጓደኛዋን ስጠይቃት አሜሪካ አጎቷ ጋ እንደሄደች ነገረችኝ። የእውነት ከልቤ አግኝቻት ባወራትና ከልቤ ይቅር እንዳልኳት ብነግራት ደስ ይለኝ ነበር ብቻ ባለችበት ሰላም ትሁን።

ፋይናል ፈተና ተፈትነን ወደ ቤት ተመልሻለሁ ወደ ናፍቆቶቼ። በመጣሁ ማግስት ከዮኒ ጋር ተገናኘን በጣም ተነፋፍቀን ነበር ሰው ጉድ እስከሚል ጥምጥም ብዬበት ወገቤን ይዞ አሽከረከረኝ "የኔ ናፍቆት እንኳን መጣሽልኝ ደና ነሽ አይደል" ከተቀመጥን በኋላ እጄን ይዞ አይን አይኔን እያየ

"ደና ነኝ ፍቅር አንተስ"

"ካንቺ ናፍቆት በስተቀር እንደምታይኝ በጣም ደህና ነኝ" ከብዙ የናፍቆት ወሬዎች በኋላ

"ቤተሰቦቼን ላስተዋውቅህ እፈልጋለሁ ምን ይመስልሀል" አልኩት

"በጣም ደስ ይለኛል"

ለእናቴ ስነግራት የተደሰተችው ደስታ እኔ እንኳን የሷን ያክል የተደሰትኩ አልመሰለኝም። በተደጋጋሚ "ተመስገን ፈጣሪ ፀሎቴን ሰማህ" ትላለች። ያለፈውን ላናወራ ቃል ስለተገባባን እንጂ በምን ምክንያት እንደዚ እንደምትሆን ገብቶኛል ። በወንድ ምክንያት ያንን ህይወት አሳልፌ ወንድ አጠገቤ የማስደርስ አይመስላትም ነበር ለነገሩ እንኳን እሷ እኔም አይመስለኝም ነበር።

"እና መች ይዤው ልምጣ እማ"

"እሁድ ይዘሽው ነይ" እንዴት ደስ እንዳለኝ

"ግባ እንኳን ደህና መጣህ" እናቴን ጎንበስ ብሎ ጉልበቷን ሊስም ሲል ቀና አደረገችውና

"አይገባም ልጄ" ብላ ሰላም ካለችው በኋላ "ወይንሸት እባላለሁ የልጄን ልብ የወሰደ ጀግና ማን ነው?" አለችው በፈገግታ እያየችው

"ዮናታን እባላለሁ" አለ ከአንገቱ ቀርቀር ብሎ

"ይቺ ደግሞ ልጄ ናት ምናሴ ትባላለች እኔ እንኳን እንቁ ነው የምላት የኔ እንቁ ሂጂ ሰላም በይው" አልኳት።

"ዮኒ እሷን ዞር ብሎ ካዬ በኋላ ፍዝዝ ብሎ የነቃው ሄዳ ሰላም ስትለው ነው" ከትውውቁ በኋላ ግብዣና ጨዋታው ቀጠለ።

ከቤት ወጥተን እየሸኘሁት እያለ "ልጅሽ ግን" አለኝ

"ልጄ ሁሉ ነገሬ ነች ዮኒ..... ልጄ ነገዬ.... ማያዬ.... የኔ ተስፋ ናት። በዛ ላይ እኮ እንዴት ጎበዝ ተማሪ እንደሆነች ብታያት" ስለሷ ብዙ ካወራሁለት በኋላ ቀና ብዬ ሳየው ሀሳቡ ከኔ ጋር አይደለም

"እኔ ብቻዬን ስለፈልፍ የት ጠለኸኝ ሄድክ" ድንግጥ አለና

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም"

ይቀጥላል
👍8410😱6🥰2
አትሮኖስ pinned «#ህያብ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በኤርሚ "ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?" "ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው። ፈገግታው ውስጥ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የሚል መልዕክት ያነበብኩ መሰለኝ••• አበባውን ተቀበልኩ ከዮኒ ጋር ህልም የሚመስሉ ሁለት ሳምንታትን አሳለፍን። ሁሉም…»
#ህያብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በኤርሚ

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም" ሸኝቸው ከተመለስኩ በኋላ ለደቂቃዎች ሁኔታውን አሰብኩትና ለምን እንቁን ሲያያት እንደዚህ ፈዘዘ ለሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘሁ መሰለኝ ስለሷ ምንም ስላልነገርኩትና ቢጠይቀኝም እንደማልነግረው ስለሚያውቅ ነው።

ከዚህ በኋላ ያሉት ጥቂት አመታቶች ተመሳሳይ ነበሩ። ለእረፍት መምጣት፣ ከዮኒ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ጊቢ መሄድ፣ ከቢኒ እና ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር የነበረንን ግንኙነት መቀጠል፣ መማር፣ ማንበብ፣ የተለያዩ ሆስፒታሎች አፓረንት መውጣት.... ባጠቃላይ ብዙም አዲስ ነገር የሌለበት ተመሳሳይ ጡዘት ነበር።

የመጨረሻ አመት ላይ ውጥረቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ነበር። ዩንቨርስቲያችን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አስር ልጆችን ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ ያወቅንበት ጊዜ ነበር። ጥቂት ቢ እና ኤ ማይነስ ውጤቶች ቢኖሩኝም እድሉን አገኛለሁ ብዬ እየተፍጨረጨርኩ ነበር። ቢኒ እና ሀብትሽ እንኳን በእርግጠኝነት ከአስሮቹ መሀል ይሆናሉ። ሀብታሙ እስካሁን ያለው ውጤቱ ኤ እና ኤ ፕላስ እንደሆነ ነው የምናውቀው። ቢኒ ደግሞ ሁለት ቢ ሌላው ኤ በአጠቃላይ የግቢያችን ሰቃዮች የእስኮላሩም ባለ እድሎች ይሆናሉ ብዬ ከምጠብቃቸው መሀል ናቸው።

ውጥረቱ እንዳለ ቀጥሎ ፋይናል ፈተና ተፈተንን እና እፎይ አልን። ምርቃታችን አንድ ሳምንት ሲቀረው ሂዊ እና ቤዛ ወጣ ብለን ፈታ እንበል ብለው ሲጨቀጭቁኝ እሺ አልኳቸው። ሌላ ፕሮግራም ያለብን ይመስል ከግራ ቀኝ እየተቀባበሉ አስዋቡኝ።

"ለቢኒ ልደውልለት እንዴ ከተመቸው አብሮን ቢሆን ደስ ይለኛል" ስላቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ቤዛ

"ትችያለሽ" አለችኝ። እሺ ብዬ ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ሁለቴ እንደጠራ አነሳውና

"ሀሎ ዶክተር ህያብ እንደምን አሉ" አለኝ ድምፁን እንደ ሽማግሌ እያደረገ ሳቅሁና በምላሹ

"አለን እግዚአብሔር ይመስገን እርሶስ እንዴት ኖት ዶክተር ቢኒያም" አልኩት።

"አለን ክብሩ ይስፋ ይገርሞታል አሁን ከባድ ቀዶ ጥገና አለብኝ እና ወደዛ ልገባ" አቋረጥኩትና

"እንደዛ ከሆነማ አብረን ቀደን እንጠግነዋለን ሀ ሀ ሀ ሀ የት ነህ ከነ ቤዚ ጋር ልንወጣ ነው ከቻልክ ተቀላቀለን" አልኩት።

"ደስ ይለኛል እንደውም ብቻዬን ደብሮኝ ነበር"

"ሀብትሽስ" አልኩት

"ሀብትሽማ አክስቱ ከአዲስ አበባ መጥታ ረስቶኛል ያው አትፍረጅበት የመዓረግ ተመራቂ ነገር "በል አሁን ወሬውን ተውና ውጣ እኛ ወተናል" ስልኩን ዘጋሁና ቦርሳዬን አንስቼ ከዶርም ወጣን።

በኮንትራት ራቅ ወዳለ ቦታ ሄድንና አንድ ውስጡም ውጪውም ውብ ወደሆነ ሆቴል ገባን።

"እናንተ ፈታ እንበል ብላችሁ ሆቴል ኧረ ፌር አይደለም" አለ ቢኒ ወደነሂዊ እያየ እኔም ሀሳቡን ተጋርቼው በጥያቄ መልክ አይን አይናቸውን እያየሁ እያለ ሂዊ

"ህያብ ሰርፕራይዝ አለሽ" አለችና ሳታስፈቅደኝ አይኔን በጨርቅ አሰረችው። እጄን ይዛኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ፎቅ ደረጃ ወጣንና በድጋሚ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ቆምን

"አይንሽን መግለጥ አይቻልም" አለችኝ ቤዚ

"እኔንም ግራ እያጋባችሁኝ ነው ምንድነው ነገሩ" ቢኒ ተናገረ። የበር መከፈት ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ተዘጋ።

"ሰፕራይዝ" ብለው ባንዴ ጮሁና አይኔ ላይ ያለውን ጨርቅ ሲያነሱት እኔ ደግሞ በተራዬ ጮህሁ። አንዴ ወደግራ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ደግሞ ፊት ለፊቴ ወደተንበረከከው ዮኒ እያየሁ ነው። ከመደንገጤ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል። ቤዚን ሳያት ጭንቅላቷን በአዎንታ ነቀነቀችልኝ ሂዊም እንደዛው ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ድንዝዝ ብሎ ቆሟል።

"ታገቢኛለሽ የኔ ቆኝጆ" ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመልኝ

"አዎ የኔ ፍቅር አዎ አገባሀለሁ" የደስታ እንባ ከአይኔ ኮለል ብሎ ወረደ። ግራ እጄን ዘረጋሁለትና የቀለበት ጣቴ ላይ የሚያምር ቀለበት አድርጎልኝ ሳም ካረገው በኋላ ጥምጥም ብሎ አቀፈኝ.... እኔም ልጥፍ አልኩበት...

ወዲያው በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ሰማሁ ከእቅፉ ወጥቼ ዞር ስል ቢኒ የለም። ምን ሆኖ ነው ግራ ተጋባሁ...
የቢኒን ነገር በይደር ያዝኩትና ወደ ደስታችን ተመለስኩ። እነ ሂዊ ትንሽ አብረውን ከቆዩ በኋላ ቻው ብለውን ሄዱ እነሱን አስወጥቼ በሩን ዘግቼ ስዞር ዮኒ አጠገቤ መጥቶ ቆሟል። ጊዜ እንኳን ሳይሰጠኝ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀ።

ሁሉም ነገር በስሜት ጡዘት ውስጥ እየሆነ ነበር ማንም መመሪያ ሳይሰጥ እያንዳንዱን ምዕራፍ ገለጥነው ከምዕራፎቹ መሀል አንደኛው ላይ ግን ነገር ተበላሸ። ከምትወደው ዮናታን ጋር በስሜት አለም የምትቃትተው ህያብ ጠፋችና የአስራ ሶስት አመቷ ህያብ ተከሰተች።

"እባክህን ተወኝ.... ሳግ... እንባ... እባክህን አትንካኝ.... ብዙ ትንቅንቅ..... ለእናቴ መድኋኒት ልገዛ ነው.....እናቴን አሟታል..... እባክህን ተወኝ ልሂድ....." ከላዬ ላይ ምንጭቅ ብሎ ተነሳና እየወዘወዘኝ ህያብ ህያብ ብሎ መጣራት ጀመረ ድምፁ ከሩቅ ቢሰማኝም ካለሁበት የህልም አለም ግን መንቃት አልቻልኩም

"እባክህ ተወኝ" ግራ ሲገባው መሰለኝ በተኛሁበት ውሃ አምጥቶ ፊቴ ላይ አርከፈከፈብኝ የውሃው ቅዝቃዜ ካለሁበት መጥፎ አለም መንጭቆ አወጣኝና ተነስቼ ቁጭ አልኩ። የሆነው ሁሉ ስለገባኝ አይኑን ማየት ፈራሁ እንገቴን ባቀረቀርኩበት ከጀርባዬ መጣና ጥምጥም ብሎ አቀፈኝና

"የኔ ፍቅር" አለኝ ሀዘኔታ በተሞላበት ቅላፄ

"ወዬ ውዴ ይቅርታ እሺ በጣም አዝናለሁ እንደዚ የምሆን አልመሰለኝም ነበር" ምላሴ ተሳሰረ ጫፉን እንኳን ስለማያውቀው እንዲያውቅም ስለማልፈልገው ታሪክ ምን ብዬ አስረዳዋለሁ።

"ተደፍረሽ ነበር አይደል" አለኝ። ረጅም ደቂቃ መልስ ሳልመልስለት ዝምም አልኩት

"ይገባኛል ህያብ ማውራት የማትፈልጊው ርዕስና ቁስልሽ እንደሆነ ግን እኔ ባልሽ ልሆን ነው ህመምሽም መካፈል ሀዘንሽን መጋራት እፈልጋለሁ። ሚስቴ ብቻዋን ስትሰቃይ ማየት የበለጠ ነው የሚያሳምመኝ" ንግግሩ አንጄቴን በላው ግን ምን ብዬ ልንገረው ምክንያቱም እኔም እናቴም የነገርነው አዲስ አበባ ተወልጄ እንዳደኩ ነው። ለእናቴ ደግሞ ቃል ገብቼላታለሁ
ማንም ቢጠይቀኝ የአዲስ አበባ ልጅ እንደሆንኩ እንድናገር ነግራኛለች። ምክንያቷ የትውልድ መንደሬን ስም በተናገርኩ ቀጥር ያንን መጥፎ አጋጣሚ በየጊዜ እንዳላስበው ብላ ነው። ይህም የሆነው ሰለዛ ሀገር ከሷ ጋር እንኳን ባወራንበት አጋጣሚ ከሷ ዞር ብዬ ሳለቅስና ሁኔታዎቼ ሲቀያየሩ ስላየች ነበር። እሷም ስለዛ ላታወራ እኔም ማንም ቢጠይቀኝ የተወለድኩት አዲስ አበባ እንደሆነ ልናገር ቃል ያስገባችኝ።

ከጊዜ በኋላ ሁኔታውን ለመድኩትና እውነትም አዲስ አበባ የተወለድኩ እስከሚመስለኝ የምናገረው ውሸት እውነት ሆነልኝ።

"አዎ ልክ ነህ ተደፍሪያለሁ ግን እንዴት? የት? ምናምን ብለህ አትጠይቀኝ ምክንያቱም ድጋሚ በዝርዝር ካሰብኩት እታመምብሀለሁ። ብቻ እመነኝ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እወጣለሁ እንደዚ የምሆን ስላልመሰለኝ ነው እኮ ችላ ብዬው የነበረው"

"ይገባኛል አትጨነቂ የስነ ልቦና አማካሪ ትፈልጊያለሽ"

"አዎ ግን አንተ አትቸገር በራሴ አደርገዋለሁ የማውቃቸው ጎበዝ ሳይካትሪስቶች አሉ" ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ እቅፍ አድርጎኝ ተኛን ወዲያው ወደ እንቅልፍ አለም ተሸጋገርኩ
👍726🤔1
የዛን እለት ነው የደወልኩለት አዲስ አበባ እንደሆነ ሲነግረኝ ዛሬውኑ እንገናኝ አልኩት ደስ እያለው እሺ አለኝ። ከአንድ ብዙም ሰው ከማይበዛበት መናፈሻ ተቀጣጠርን ቀድሞኝ ነበር የደረሰው እኔን ሲያይ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ ሮጬ ተጠመጠምኩበት

"ናፍቄህ ነበር "

"እኔም ናፍቄሽ ነበር በጣም" ሳሩ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጥን

"ብናፍቅህማ እንደዚህ አትጨክንብኝም ነበር የምር ግን ጨካኝ ነህ እሺ" አልኩት ከልቤ እንዳልሆነ ያውቃል

"እሱንማ ብዙ ጊዜ ትነግሪኛለሽ ይልቅ አዲስ ስም ፈልጊልኝ አሁን ከፈለግሽ አፍቃሪ ነህ ማለት ትችያለሽ" ለደቂቃዎች ዝምም አልኩና ነገሮችን በውስጤ ማመላለስ ጀመርኩ ከዛ

"እንዴት ግን ቢኒ እስኪ የማላውቀውን ንገረኝ" ተስተካክሎ ተቀመጠና

"የመጀመሪያ ክላሳችን ቀን ነው ከሀብትሽ ጋር ቀድመን ክላስ ቁጭ ብለናል ብዙም ሳንቆይ ረጅም ቀሚስ የለበሰች ቁመቷ ረጅም ቆንጆ ልጅ ወደ ክፍላችን ገባች። በእያንዳንዱ እርምጃዋ የኔን ልብ የረገጠችው ይመስል ልቤን በእጄ ይዤ የመጀመሪያውን የፍቅር ህመም ታመምኩላት። ልክ ገብታ ወንበር አየት አድርጋ ስትቀመጥ እጄም ከልቤ ላይ ተነሳ። ሀብትሽ እኔንም አንቺንም እያየ በሁኔታዬ ግራ ተጋብቶ

'ቢኒያም ችግር አለ ምን ሆነህ ነው?' አለኝ
ለሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ሌሎች ተማሪዎች ግርርር ብለው ገቡ ብዙም ሳይቆይ ዮናታን ገባ። ከክላስ ከወጣን በኋላ የሀብትሽ ምን ሆነህ ነው ጭቅጭቅ አላስቀምጥ ሲለኝ 'ተወኝ ባክህ እኔም ምን እንደሆንኩ አላውቀውም። ልጅቷ ግን...''በል ወዳጄ እዚህ ብዙ ቆንጆ የዛኑ ያክል ብዙ መልከ ጥፉ ልታይ ትችላለህ ለቆንጆዎቹ ሁሉ ልብህን ይዘህ እና አይንህን አፍዘህ አትችለውም ትኩረትህን ትምህርትህ ላይ አድርግ' ብሎ የመጀመሪያ ምክሩን መከረኝ።

ከዛማ ህያቤ ምን ልበልሽ ቀናቶች በሄዱ ቁጥር የበለጠ እየወደድኩሽ መጣሁ። ሳይሽ ደግሞ ብቸኛ እና ከማንም ጋር ቅርበት ለመፍጠር የማትሞክሪ ነበርሽ። የትናዬትም አንቺን በእያንዳንዷ ነገር ልታጠቃ ስትሞክር አየሁ። ሀብትሽም ከኔ እኩል ነገሮችን ያይ ነበር። አንድ ቀን ካፌ ቁጭ ብለን ሻይ እየጠጣን በአጠገባችን አልፈሽ ጥግ ካለ ወንበር ላይ ብቻሽን ቁጭ አልሽ። ስትገቢ ጀምሮ እስከምትቀመጪ አይኔ አንቺ ላይ ነበር። ሀብትሽ ወዳንቺ የዞረውን ፊቴን በእጁ ከመለሰ በኋላ 'ይቺን ልጅ አፍቅረሀታል' አለኝ መካድ አልቻልኩም።

'እንደዛ ከሆነ ሳትቀደም ቅረባት'

'እንዴት አድርጌ'

'እሱን ለኔ ተወው የሆነ መንገድ አይጠፋም' ከዛ በኋላ ባሉት እያንዳንዱ ቀን የሱ ግፊት ነበር 'ቅረባት ወይ ከዚህ የበለጠ ትወዳታለህ ወይም ደግሞ መጥፎ ባህሪ ካላት ስታውቃት ትጠላታለህ እንደዚህ በሩቁ ወደሀት ብቻህን አትሰቃይ' በስተመጨረሻ ተሳካልኝና በምታውቂው መንገድ ቀረብኩሽ። እሱ እንዳለው ስቀርብሽ እጥፍ እጥፍ ወደድኩሽ

አንቺ ደግሞ ዮናታንን የዛኑ ያክል እንደምትወጂው አወቅሁ። ከዛ በኋላ ያለውን እንደምታውቂው ነው። ያንቺን ደስታ ብቻ ነበር የምፈልገው" በረጅሙ ተነፈሰና ፊቱን ወደኔ አዙሮ አይን አይኔን ያይ ጀመር አንገቴን ሰበርኩ

"ለምን ግን ቢኒ ለምን ብቻህን ተሰቃየህ? ለምን እስከዛሬ አልነገርከኝም?"

"ፈራሁ ህያቤ የኔ ላትሆኚ እንደማፈቅርሽ ብነግርሽ ጓደኝነታችንን አጣዋለሁ ብዬ ፈራሁ። ለአንድ ቀን እንኳን አኩርፈሽ ብትርቂኝ ብዬ ሳስበው ምድር የምትደፋብኝ መሰለኝ"

እንዴት ይሄን ያክል ጊዜ ሁኔታውን አይቼ መረዳት አቃተኝ እኔን ብሎ ዶክተር አልኩ ለራሴ

"ይሄ ካንተ ሊያርቀኝ አይችልም አንተ ከኔ መራቅ እስካልፈለግህ ድረስ እኔ በፍፁም አርቅህም። ቢኒዬ ወንድሜ ነህ እልሀለሁ ግን አንተ እኔን እህትህ የማድረግ ግዴታ የለብህም። ለምን አፈቀርከኝ አልልህም... አይደለም የኛን ያክል እስከ ጥግ የተቀራረበ ሰው ይቅርና ብዙም ሳይተዋወቁ በፍቅር የሚወድቁ ሰዎች አሉ። እኔ እድለኛ ሰው ነኝ... የእውነቴን ነው የምልህ እድለኛ ሰው ነኝ። ባንተ በመፈቀሬ እድለኛ ነኝ። ቆንጆ፣ ጎበዝ፣ ጠንካራ፣ ሰዎችን የምትረዳ መልካም ልብ ያለህ ሰው ነህ.... እንዳንተ አይነቱን ወንድ ማንም ሴት ቀርባ አይደለም አይታ ትመኘዋለች። የኔን ግን እንደምታውቀው ነው ከመጀመሪያ ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፌ ነበር...... አንተን በፍቅር አስቤህ አላውቅም። እንደምታውቀውም አሁን ባለትዳር ሆኛለሁ ቢሆንም ግን አፍቅረህኛል ብዬ ልርቅህ አልፈልግም ለኔ አሁንም የድሮው ቢኒ ነህ.... ወንድሜ ነህ እዛም ሄደህ ቢሆን ደውልልኝ። አንተ ልራቃት ካላልክ እኔ አርቅህም" ወደኔ ጠጋ ብሎ አቀፈኝ

"ዋው..... ዋው.... ዋው.... የሁለቱ ጓደኛሞች አስገራሚ የፍቅር ጊዜ እንበለው ወይስ በስተመጨረሻ የተጋለጠው የሁለቱ ወጣቶች ፍቅር እንበለው የትኛው ይሻላል" ዮኒ.... ከቢኒ እቅፍ ወጣሁና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ደብዳቤውን በእጁ ይዞ ፊት ለፊቴ ቆሟል....

ይቀጥላል
👍5913😢3😁2
🔮⚫️የእናቴ ልጅ⚫️🔮
⚫️ክፍል ሃያ ዘጠኝ⚫️
🔮⚫️🔮⚫️🔮⚫️🔮
ከቀናት በዋላ ነበር በአንድ ከፍተኛ እክምና መስጫ ክፍል ውስጥ እራሴን ያገኘውት ፡ዙሪያዬን እንደ እንግዳ ሰው ስቃኝ ቆይቼ ወደ እግርጌዬ ጎንበስ ስል ብሌንን አንገቷን ደፍታ እንደተኛች ልብ አልኩ ፡ ወይ ብሌኔ የኔ ልዩ ስለኔ ተጨነቀች ስለእኔ አነባች አንገቷን ደፍታ ባልተመቻቸ ሁኔታ ከአጠገቤ ተኝታለች ፡ፈጣሪ የውስጤን አይቶ የሰጠኝ በረከቴ ነች አልኩ ለራሴ ፍቅሬ ጨመረ ፡ የወንድም የእናት ልጅ ፍቅር ቢነሳኝም የባዳ ወኪል መከታ አፍቃሪ አሳምር ሰጥቶኛል አመሰገንኩ። እናቴን ባለማየቴ ግን ቅር አለኝ ።
ከሰአታት ቆይታ በዋላ ብሌን ነቅታ ወደኔ ተመለከተች ።አይኖቼን ገልጬ ስታይ መጀመሪያ ፍዝዝ አለች ቀጥላ ጠጋ ብላኝ እየተርበተበተች ግንባሬን ሳመችኝ ።ፈገግ ብዬ ደንነቴን አሳየዋት።
"የኔ ውድ ነቃህልኝ ?"
"አዎ ብሌኔ"
"ሁለተኛ እንደዚ እረጅም እንቅልፍ እንዳትተኛ እሺ"
"ይቅርታ ውዴ"
"አስፈራራኽኝ እኮ ጭልጥ ብለህ ወደ ሄድክበት ሰመመን በተሃምር መግባትና አብሬህ መሆን ተመኝቼ ነበር እኮ "አለች ዕንባዋን ጉንጬ ላይ እያንጠባጠበች፡ እያንዳንዷ የዕንባ ዘለላዋ ጉንጬላይ ሲያርፉ ልዩ የሆነ ስሜት ተሰማኝ ፡ከንፈሯን ልስም ተንጠራራው ፡ አሳቤን ተረድታ ከንፈሯን አቀበለችኝ ፡ምጥጥ አድርጌ ሳምኳት ፡ሁኔታዬ ፡እራሴጋር እስከመጨረሻው ላስቀራት ይመስላል ፡ ትንፋሿ ቁርጥርጥ ሲልብኝ ለቀኳትና አይኖቿ ውስጥ አየዋት ፡ ፍዝዝ ያለው እይታዋ ቅኔ አለው እዛው ቅልጥ አልኩ .....በሩ ተከፍቶ ሰው ሲገባ ነበር ወደ እራሳችን የተመለስነው ። እናትና አባቴ ነበሩ ።ሁለቱን አንድ ላይ ማየት እንዴት ደስ ይላል ፡በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉነት ተሰማኝ ፡ አባቴ ፍፁም ተቀይሮ ፡አምሯል አለባበሱ ፅድት ማለቱ ከዕድሜው አስር አመት ያስቀነሰው ይመስላል ።እናቴ ትንሽ ገርጣ ብላለች ፡በጭንቀት እንደሰነበተች ያስታውቅባታል ። ሁለቱም መጥተው በደስታ ቁልቁል ሲመለከቱኝ ፡ደስታ ተሰማኝ እፎይ አልኩ ፡ሌላ ችግር አለመፈጠሩን ሁኔታቸው ስለነገረኝ ።እናቴ ቀና ብዬ ስቀመጥ ጠብቃ ወደውስጧ የመክተት ያክል አቀፈችኝ ፡ አባቴ እጆቹን ፀጉሬ ላይ አድርጎ እየደባበሰኝ ተመስገን አለ ። ደስ አለኝ አልጋዬን ከበው ሲያወሩኝ ሲያጫውቱኝ ቆዩ እናቴ ስለብሌን አድንቃ ነገረችኝ ፡እንደወደደቻት ገባኝ አባቴም እድለኝነቴን አወራ ፡በዚጊዜ አብሮ የሚታመም ወዳጅ ብርቅ በሆነበት ሰአት አንተግን ብሌን አለችህ ፡የፈጣሪ ስጦታህ ናት እንዳታስቀይማት ፡ አደራ አለኝ ።ውስጤ በሀሴት ተሞላ ።
ከቆይታ በዋላ አኪሙን አናግረው ነገ መውጣት ይችላል ተብለው ።ወደቤት መሄዳቸው ግድ ሆነ ፡ሊወጡ ሲሉ ስለ አቤል ጠየኩ እየደበረኝ ቢሆንም ማወቅ ስላለብኝ ፡ አባቴ ነገ ሁሉንም እንነግርሃለን አለ ፡አሁን መስማት እፈልጋለው አልኩት ፡ለመጨረሻ ጊዜ ማታላይ አባቴ አቤልን ከቀጠረው ነብሰ ገዳይ ጋር አብሮ ሲቀላቅላቸው አስታውሳለው ፡እና አንድ ላይ አድርጓቸው ምን ተፈጠረ ፣ የአቤል ጉዞስ የነብሰ ገዳይ ጓደኛውስ መጨረሻ መስማት ፈልጌያለው ፡አባቴ ነገ ብሎ ዘጋብኝ ፡ብሌን እሺ እንድል ምልክት ሰጠችኝ ። ሳልወድ በግድ ዝም አልኩ ፡የሚያድር ነገር ችግር አለው ብዬ አሰብኩ ፡እናቴ ላይ ያየውት ጭንቀት ደሞ አስፈራኝ አቤል ምን ሆኖ ነው? እኔ እራሴን ስቼ ከተኛው አራት ቀኔ እንደሆነ ነግረውኛል ፡ አቤል ደሞ የተመታው ቀን ማግስት ከአገር የሚወጣበት ቀን ነበር ፡ እና ለምንድነው ያዘኑት ፡ፈራው አንዳች ነገር ጠረጠርኩ ........

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍9218👎6🥰1