በቃል፣ «አዎን ትርጉም አለው ። ፎቶግራፎቹን ሳነሳኮ ሃሳቤ ወዳንተም እንዲደርስ ለማድረግ አስቤበት ነው » ስትል መለሰችለት። «እሱማ ለሁሉም ሰው ነው ። እኔ'ኮ ምልሽ… እንዴት ብዬ ላስረዳሽ ? ልክ አንዱን ፎቶ አየሁ ልበል። ያኔ. . .ምን ልበልሽ ያን ፎቶ በደንብ… አለ አይደለም… እማውቀው ይመስለኛል ። ብቻ ስናገረው ለራሴም የጅል ነገር ሆኖ ይሰማኛል » አለ ። ግን ማይክል እኔን አታውቀኝም ? ሌላው ይቅር እስኪ እኒህን ዓይኖች እያቸው ። አታውቃቸውም ? በልቧ ። እነዚህን ጥያቄዎች ልትጠይቀው አማራት ። ጸጥ ብለው ቡናቸውን ሲጠጡ «በቃ በእምቢታ ልትጸና ነው የሚል ደስ እማይል ስሜት ደርሶ ተሰማኝ » አላት በመከፋት ። ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች «ልክ ነህ አይቻልም » እያለች ።
«ችግሩ ምንድነው? ገንዘብ ይሆን? » አለ ።
«በፍጹም የገንዘብ ጉዳይ አይደለም »
«እኔም አልመሰለኝም »
እውነቱን ነበር « አልመሰለኝም » ያለው ። ቢመስለው ኖሮማ ገና ቅድም ያዘጋጀውን የሥራ ኮንትራት ውል አውጥቶ ያሳያት ነበር ። ውሉን አዘጋጅቶ ይዟል ። በዚያ ውል ብትስማማ እጅግ ብዙ ገንዘብ ታገኛለች ። ግን ሁኔታዋን ሲያይ የገንዘብና የውልን ነገር አለማንሳቱ የተሻለ ሆኖ አገኘው ። ይህን ጉዳይ ቢያነሳ ነገሩን ይበልጥ እንደሚያከረው ተገነዘበ ። « እንዲህ ምርር ብለሽ እምቢ እንድትይ ያደረገሽን ነገር ባወቅኩ » አለ «ምንም አይደለም ። አንዳንዴ ነካ ሲያደርገኝ እንዲሀ ነኝ ። ያለፈ ኑሮዬን የምበቀለው በዚህ ሁኔታ ነው ። ሌላ ምንም›› አለች ። የልቧን ስትናገር ደነገጠች ። እሱ ግን ምንም አድናቆት ወይም ትርጉም አላሳየም ። « እኔም የዚያ ዓይነት ነገር ሳይሆን አይቀርም እያልኩ ሳስብ ነበር» አለ። በመካከላቸው ሰላም ነበር ። ግን ደግሞ ማይክል አንድ ዓይነት መራራነት ያለው ጣፋጭ ስሜትም ይሰማዋል። ያ ስሜት ምን እንደሆነ ግን ሊገባው አልቻለም ። « እማዬ በሥራሽ እጅግ ተደስታለች ። ይህ ራሱም የሚገርም ነው ። ምክንያቱም ለሆነ ላልሆነው የምትንገበገብ ሰው አይደለችም » አለ ማይክል ። «እንዳልከው ነው እኔም እምሰማው ። እንድ ውል ስትዋዋል እንኳ ሁሉን ነገር እሳስራ ነው አሉ›› አለች ናንሲ ። «ነው…. ግን እንዲያ ማድረጓም ከንቱ እንዳይመስልሽ ። ኮተር ሂልያርድን እዚህ ያደረሰችው በዚህ ጥንካሬዋ ነዉ ። ዛሬ እኔ ምን ችግር ኣለብኝ? በሚገባ የተያዘች- መርከብ ካፒቴንነት እንደምረከብ ነው የሆነልኝ »
« እንዴት ታድለሃል » ይህን ሰትል ድምጺ ምሬት የተሞላ ነበር። ይህን ደግሞ ማይክል አጢኖታል ። ለምን? ግራ ተጋባ። ለምን ? ተቅበዘበዘ ። እና እጁን እነሳና እጉንጩ ላይ ያለች ትንሽ ጠባሳ መነካካት ጀመረ ይሄኔ ሜሪ ድንገች ሲኒዋን እጠረጴዛው ላይ እስቀምጣ ቀና ብላ እየችው ። እና «ምን ሆነህ ነው?» ስችል ጠየቆችው ። «ምኑ?» ሲል በጥያቄ መለሰላት ።
« ጠባሳው » እለችው ። ዓይኗን ከዚያች ጠባሳ ላይ ልትነቅል ኣልቻለችም ። ያች ጠባሳ ምን እንደሆነች በሚገባ ታውቃለች ። ያን እለት... «ምንም አይደለም ። አብሮኝ የቆየ ነው » ኣላት ። « የቆየ አይመስለኝም ፤ በቅርብ ጊዜ የሆነ ይመስላል » አለችው ።
«ሁለት ዓመት ያህል » አለ እያፈረ ። « ምንም አይደለም ቀላል ነገር ነው ። ከጓደኞቼ ጋር ቀላል አደጋ ደረሰብንና በቃ » ነገሩን አቃልሎ ሊያልፈው ሲፈልግ ስታይ ብልጭ እለባት ። ፊቱን በያዘችው ቡና ልታጠናፍረው አማራት ። የውሻ ልጅ ። ትንሽ አደጋ ይበል ! አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ ። አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆኖልኛል አለች በሀሳቧ ። እና... እና ቦርሳዋን አነሳች ። ተነሳች በክፉ ዓይን ቁልቁል ተመለከተችው። ልትጨብጠው እጅዋን ዘረጋችለት። « ጥሩ ጊዜ አብረን አሳለፍን ። አመሰግናለሁ ። እዚህ በምትቆይበት ጊዜ ሁሉ መልካም እንዲያጋጥምህ እመኝልሀለሁ›› አለች «ምን ? ልትሔጂ ነው ? ምን መጥፎ ነገር ተናገርኩ ?›› አለ ማይክል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ ሆኖበት ። አረ የክርስቶስ ያለህ ምናይነቷ አስቸጋሪ ፍጡር ናት ያጋጠመችኝ ! አሁን ደሞ እስኪ ምን ሆንኩ ነው እምትለው ? አሰበ ። ምን ብዬ ይሆን ? ቀና ብሎ አያት ። ዓይኗን ሲያይ እዚያ ውስጥ የሚንቀለቀለውን ቁጣ ሲመለከት ደነገጠ ። «ምን ? አጠፋሁ እንዴ ?» እለ ደግሞ ። «እንክት አርገህ እንጂ» አለችው ። ደንግጦ ዝም ብሎ ያያት ጀመር ።
«አየህ ፤ ስለዚህ ሰለደረሰብህ አደጋ አንብቤ ነበር ። ትዝ እንደሚለኝ ከሆነ እንዲህ ቀላል ተብሎ የሚጠራ አደጋም አልነበረም ። እነዚያ ያልካቸው ሁለት ጓደኞችህም እንደገመትኩት በጣም ነበር የተጐዱት ። ግን አንተ አነስተኛ አደጋ ትላለህ ። እንዲያው ለሰው ትንሽ እንኳ ልብ የለህም ? አታዝንም ማይክል ? ሁሉን ትተህ ሌትም ቀንም በቃ ስለዚህ እርጉም ሥራህ ብቻ ነው እምታስበው ማለቅ ነው!»
« ምናባሽ . . ምን ነካሽ ? ደሞስ በኔ ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገሽ !? »
« ሰው ነኝና ያገባኛል ። አንት ግን ሰው አይደለህም »
« እብድ ነሽ »
« አይይ !? ተሳሳትክ ጌታው ። እብድ አይደለሁም ። የለም አሁን እብድ አይደለሁም » ይህን ተናግራ እየተፈናጠረች ወጣች ። ማይክል ካለበት አፍጥጦ ተመለከታት ። ካይኑ ስትሰወር ድንገት ነቃ ። ተፈናጠረና ተነሳ ። የአምስት ዶላር ኖት እጠረጴዛው ላይ ወርውሮ እንዳበደ እየሮጠ ወጣ ። አዎ መንገር ይኖርበታል ። የለም ኣደጋው ቅላል አደጋ አልነበረም ። ሕይወቱን የለወጠ አደጋ ነበር ። በጣም የሚወዳት ፤ ሕይወቱን ፍቅሩን ያጣው በዚያ አደጋ የተነሳ ነው ። ይህን ሊነግራት ይገባል አሰበ ። ግን ይህን ለማወቅ ምን መብት አላት? ተናደደ ። ቢሆንም ... መንገድ ላይ ሲደርስ ታክሲው ይዟት ነጐደ።
አልነገራትም…. ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍28❤2
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ከሼዲያክ ወደ ቤይ ኦፍ ፈንዲ
አይሮፕላኑ ከካናዳ ወደ ኒውዮርክ ሲያቀና ማርጋሬት በጭንቀት ተወጥራለች ሄሪን ምን ዋጠው?› እያለች ታስባለች፡፡
ፖሊሶች ሄሪ በሃሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ አውቀዋል፡፡ ተሳፋሪዎቹም
ይህን ነው የተገነዘቡት፡ ፖሊሶቹ እንዴት እንደደረሱበት አልገባት ብሏታል ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ነው ያልታወቀው:: ምናልባትም ወደ እንግሊዝ አገር ይመልሱትና ጌጣጌጦቹን በመስረቁ እስር ቤት ይወረውሩት ይሆናል፤ ወይም ወደ ጦር ሰራዊት ውስጥ ይጨምሩታል። ታዲያ እንዴት ልታገኘው ነው?
እስካሁን እንዳልያዙት ግን አውቃለች፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ያየችው ሼዲያክ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ወደ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ነው፡ ታዲያ ያኔ ይሆን ያቀደው? ችግር እንደደረሰበት አውቋል ማለት ነው፡፡
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን በሙሉ ቢያስሱም አላገኙትም፡፡ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሾልኮ ጠፍቷል ማለት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? ምናልባትም
ከአይሮፕላኑ ወርዶ ጫካ ጫካውን እያሳበረና ሊፍት እየጠየቀ ሄዶ ይሆናል፡
ታዲያ ከዚህ በኋላ በዓይነ ስጋ ታየው ይሆን?
በዚህ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባት ተገንዝባለች፡፡ ሄሪን በማጣቷ ብትጎዳም ናንሲ አለችላት፡፡
አባቷ ዓላማዋን ከማሳካት አያግዷትም፡ ለራሳቸው ሁሉ ነገር የጠመመባቸውና ስደተኛ ስለሆኑ የማስገደድ ኃይላቸው ተዳክሟል፡ ሆኖም እንደ ቆሰለ አውሬ እንደገና አገርሽቶባቸው ዓላማዋን የሚያሰናክል ነገር ያደርጉ ይሆናል፡፡
አይሮፕላኑ ሽቅብ መጎኑን ጨርሶ የመቀመጫ ቀበቶዋን ፈትታ ናንሲን ለማነጋገር ሄደች።
አስተናጋጁ ለምሳ ጠረጴዛ እያዘጋጀ ነው፡፡ አባቷ ቦታቸው ላይ ቁጭ
ብለዋል ኦሊስ ፊልድ ከፍራንክ ጎርደን ጋር በካቴና ተጠፍሮ ቁጭ ብሏል፡
ማርጋሬት ወደ ሙሽሮቹ ክፍል ሄዳ ደጋግማ አንኳክታ ምላሽ ስታጣ በሩን
ከፈተች፤ ማንም የለም፡፡
በድንጋጤ ክው አለች፡፡
ምናልባትም ናንሲ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ እየተቆነጃጀች ይሆናል፡
መርቪን ላቭሴይ የት ሄደ? ወደ መታጠቢያ ክፍል የሄደ ከሆነ ታየው ነበር ክፍሉ ውስጥ አንድ ቦታ ተደብቀው እንደሆን ቃኘች፡፡ ነገር ግን ምንም መደበቂያ የለም፡፡
የናንሲ ወንድም ፒተርና ጓደኛው የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ተቀምጠዋል፡ ‹‹ሚስስ ሌኔሃን የት ነች?›› ስትል ጠየቀችው ፒተርን
‹‹ሼዲያክ ላይ ነው የወረደችው››
‹‹ምን አልክ?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹አንተ እንዴት አወቅህ?››
‹‹ነግራኛለች››
‹‹ለምን ግን?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹ለምንድነው የወረደችው?››
ፒተር የተሰደበ ያህል ተሰማው፡ ‹‹እኔ እንጃ›› ሲል መለሰላት፡ ‹‹ወደ ኒውዮርክ እንደማልሄድ ለፓይለቱ ንገርልኝ ነው ያለችኝ›› አላት ፊቱን አኮሳትሮ፡፡
ማርጋሬት ፒተርን በጥያቄ ማጣደፍ ነውር መሆኑን ብታውቅም አጥብቃ መጠየቁን አላቋረጠችም:፡ ‹‹ናንሲ የት ሄደች?››
ፒተር በዚህ ጊዜ አጠገቡ ያለውን ጋዜጣ አነሳና ‹‹እኔ የማውቀው ነገር የለም›› ሲል መልስ ሰጥቷት ማንበቡን ቀጠለ
ማርጋሬት ሆድ ባሳት፡ ናንሲ እንዴት እንዲህ ታደርጋለች አለች ምን ያህል በእሷ ላይ ተስፋዋን እንደጣለች ታውቃለች፡ ሆኖም
ነገር ሳይገጥማት ከመንገዷ አልተስተጎለችም መልእክት ትታ ይሆናል።
ከአስተያየቱ የነገራት ውሽቱን እንደሆነ ጠረጠረች ማርጋሬት እንደ ፖሊስ ስለመረመረችው ደስ አላለውም፡፡ በደመነፍስ ‹‹እውነቱን አይደለም
የነገርከኝ›› ስትል አፈጠጠችበት፡፡ አባባሏ ትክክል ባይሆንም ምላሹን ግን ትጠብቃለች፡፡
ፒተር ፊቱ በንዴት ቲማቲም መስሏል፡ ‹‹እንደ አባትሽ ጋጠወጥ ነሽ ከፊቴ ጥፊ!›› አላት፡
የፒተር ስድብ አንገቷን አስደፋት። ያባትሽን መጥፎ ባህሪ ይዘሻል ከሚል ስድብ በላይ የምትጠላው ነገር የለም፡፡ ምንም ሳትተነፍስ ውልቅ ብላ ሄደች፤ በዓይኗ እንባ እንደሞላ አልፋ ስትሄድ ውቧን የመርቪንን ሚስት ዳያና ላቭስሌይን አየቻት። አይሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተጓዥ በሙሉ ባሏን
ከድታ ከፍቅረኛዋ ጋር ስለኮበለለችው ሚስትና መልሶ በእጁ ለማስገባት አገር አቋርጦ ስለተከተላት ባሏና ቦታ አጥቶ ባሏ ከሞተባት ሴት ጋር በሙሽሮች ክፍል ውስጥ ለመዳበል የመገደዱን ወሬ በደስታ እየተቀባበለ ሲያወጋ ነው የሰነበተው፡፡ ማርጋሬት ባሏና ናንሲ የት እንደገቡ ዳያና ታውቅ እንደሆን መጠየቅ ፈለገች፡፡ በርግጥ ይህን ጥያቄ መጠየቅ የሚያሳፍር ቢሆንም መጥፋታቸው አሳስቧታል፡፡ ዳያና አጠገብ ተቀመጠችና ‹‹ይቅርታ መርቪንና ናንሲ የት እንደገቡ ታውቂ ይሆን?›› ስትል ጠየቀቻት፡ ዳያና ጥያቄው አስገርሟት ‹‹ምን ሆኑ? በሙሽሮች ክፍል ውስጥ የሉም እንዴ?››
‹‹ጭራሽ አይሮፕላኑ ውስጥ የሉም፡፡ እኛ ስንሳፈር እነሱ ቀርተዋል››
‹‹እውነት?›› ዳያና ደነገጠች አጠፋፋቸውም እንቆቅልሽ ሆኖባታል፡
‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል? አይሮፕላኑ አመለጣቸው እንዴ?››
‹‹የናንሲ ወንድም ጉዞውን ለማቋረጥ ወስነዋል ቢልም አላመንኩትም›› አለች ማርጋሬት፡፡
ሁለቱም ለኔ የነገሩኝ ነገር የለም›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹ብቻ ክፉ ነገር.አይድረስባቸው::››
‹‹ምን ማለትሽ ነው ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት ፍቅረኛዋ፡፡
‹‹ክፉ አይንካቸው ነው ያልኩት?››
ማርጋሬትም የዳያናን ሃሳብ መቀበሏን ራሷን በመነቅነቅ ገለጸች፡
‹‹ወንድምየውን ግን አላመንኩትም፡፡ የተናገረው ውሸት ይመስለኛል››
ማርክም ቀበል አደረገና ‹‹እኔም ይመስለኛል፡፡ አሁን አየር ላይ ስለሆንን የሚሆነውን ከመጠበቅ በስተቀር ማድረግ የምንችለው ነገር የለም››
‹‹ከዚህ በኋላ የሚያደርገው ነገር አያገባኝም›› አለች ዳያና መናደዷ በግልጽ እየታወቀባት፡፡ ‹‹የአምስት ዓመት ባሌ ስለሆነ ግን ክፉ እንዲያገኘው አልፈልግም፤ ያስጨነቀኝ ደግሞ ይኸው ነው››
‹‹አሜሪካ ስንደርስ ከእሱ መልእክት እናገኝ ይሆናል›› አለ ማርክ በማስተዛዘን አይነት፡፡
‹‹እስቲ እሱ ይሁነና›› አለች ዳያና፡፡
አስተናጋጁ የማርጋሬትን ክንድ ነካ አደረገና ‹‹ክብርት ማርጋሬት ምሳ ደርሷል፧ ቤተሰቦችሽ ለመብል ተሰይመዋል›› አላት
‹‹አመሰግናለሁ›› አለች ማርጋሬት ‹የምግብ አፒታይቴ ተዘግቷል፡፡››
ማርጋሬት ለመሄድ ስትነሳ ዳያና ‹‹ከናንሲ ጋር ወዳጅ ናችሁ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
በፋብሪካዋ ውስጥ ስራ ልትቀጥረኝ ቃል ገብታልኝ ነበር›› አለች ማርጋሬት በምሬት፡፡ ከንፈሯን እንደነከሰች ዞራ ሄደች፡፡
እናትና አባቷ እንዲሁም እንዲሁም ፔርሲ የመጀመርያው ዙር ምግብ
ቀርቦላቸዋል፡ ማርጋሬትም እንደተቀመጠች ‹‹ይቅርታ አባባ ስለዘገየሁ››
አለች፡፡ የቀረበላትንም ምግብ ትቆነጣጥራለች፡ አልቅሽ አልቅሽ አላት፡ ሄሪና
ናንሲ ሳይነግሯት እብስ ብለዋል፡ አሁን የሚረዳት የለም፡ እንደ እህቷ
ኤልሳቤት ለመኮብለል አስባ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር ተበላሽቶባታል፡
ሁለተኛው ዙር ምግብ ቀረበ፡፡ ሾርባ ነው፡፡ ሾርባውን አንድ ጊዜ ፉት
አደረገችና ተወችው: ድካምና ንዴት በአንድ ላይ ተሰማት አሟታል፡ የምግብ ፍላጎቷ ተዘግቷል፡ ምቹው አይሮፕላን እስር ቤት
ሆኖባታል፡ ለሃያ ሰባት ሰዓት ስለበረሩ ጉዞው ሰልችቷቸዋል፡ እናቷ

👍22
ፊታቸው ገርጥቷል፡፡ ድካም ይነበብባቸዋል፡ ድብርት ተጫጭኖአቸዋል።
ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ እጦት በርበሬ መስለዋል፡፡ ፔርሲ ቅዥቅዥ ያደርገዋል፡፡ አባቱን በክፉ ነው የሚያያቸው፡ ለጠብ ያሰፈሰፈ ይመስላል
ከፊት ለፊቷ ያሉትን ደባሪ ቀኖች አሰበች ማርጋሬት፡፡ በኒውዮርክ ሆቴል ከአባት ከእናቷ ጋር ነው የምትቆየው፡፡ ሄሪ ወደ መኝታ ክፍሏ አሸምቆ ሊመጣ አይችልም፡፡ እሱን እያሰበች ብቻዋን ትተኛለች፡፡ ከእናቷ ጋር ገበያ ለገበያ ትዞራለች፡ ከዚያ ወደ መኖሪያቸው ኮኔክቲከት ስቴት ይሄዳሉ።እሷን ሳያማክሯት የፈረስ መለማመጃና ቴኒስ ክለብ ያስመዘግቧታል፡
ፓርቲም እንድትሄድ ያዟታል፡፡ ከዚያ በኋላማ እናቷ ከከተማው ትላልቅ
ሰዎች ልጆች ጋር እንድትወዳጅ የሻይ ግብዣ በመጋበዝ ያስተዋውቋታል፡
አገሯ እንግሊዝ የጦርነት ወላፈን እየገረፋት እንዴት ነው እሷ እዚህ
የምትምነሸነሸው? ይሄን ባሰበችው ቁጥር ሀዘኗ ይበረታል፡፡
ማርጋሬት የቀረበላትን አይስክሬም ልሳ ጨረሰች፡፡
አባቷ ብራንዲና ቡናቸውን ጨልጠው ሲያበቁ ጉሮሯቸውን እህህ እህህ
በማለት አጸዱ፡ አንድ ነገር ማለት ፈልገዋል፡ መቼም ትናንትና ራት ላይ ለፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት ይቅርታ ሊጠይቁ እንዳልሆነ መገመት አያስቸግርም::
‹‹እናትሽና እኔ ስላንቺ ተነጋግረናል›› ሲሉ ንግግራቸውን ጀመሩ፡
‹‹ልክ ትዕዛዝ እንደማትቀበል ገረድ ቆጥራችሁኛል›› ስትል ማርጋሬት ጮኸች::
እናትም ቀበል አደረጉና ‹‹ሞገደኛ ልጅ ነሽ›› አሏት
«አስራ ዘጠኝ ዓመት ያለፈኝ ወጣት ነኝ እንዴት እኔን ልጅ
ትሉኛላችሁ?››
‹‹ዝም በይ!›› ሲሉ እናት ተቆጡ፡፡ አባባሏ አስደንግጧቸው ‹‹እንዲህ
አይነት የብልግና ቃል በአባትሽ ፊት ከተናገርሽ ገና ህጻን ልጅ ነሽ ማለት
ነው›› አሉ፡
‹‹በቃ ተዉኝ!›› አለች ማርጋሬት፡፡
አባትም ቀበል አደረጉና ‹‹የምታሳይው ጋጠወጥ ባህሪ የምንለው
እውነት መሆኑን ያመለክታል፡ በደህናው ህብረተሰብ መካከል ገብተሽ ትኖሪያለሽ ብለን አናምንም››
‹‹ለዚህ አምላክ ይመስገን!›› አለች ማርጋሬት፡
ፔርሲ ይህን ሲሰማ ከት ብሎ ሳቀ፤ አባት በፔርሲ አድራጎት ቢናደዱም
እሱን ናቅ አድርገው ማርጋሬትን ‹‹ብትበጠብጪም አንድ ብዙም ችግር
የማትፈጥሪበት ቦታ እንልክሻለን››
‹‹ገዳም ልትልኩኝ ነው?››
እንደዚህ የብልግና መልስ ሰጥታ ባታውቅም ንዴታቸውን እንደምንም
ዋጥ አድርገው ‹‹እንዲህ አይነት ንግግር አይረባሽም›› አሏት፡፡
‹‹አይረባሽም! ለመሆኑ ለእኔ ጥሩ የሆነው የቱ ነው:፡ የሚወዱኝ ወላጆቼ የእኔን ፍላጎት በማክበር የወደፊት ህይወቴን ይወስኑብኛል፣ ሌላ
ምን እፈልጋለሁ›› አለች በምሬት፡፡
‹‹ማርጋሬት አንቺ ጨካኝ ነሽ›› አሉና እናት ለቅሷቸውን ለቀቁት፡፡
ማርጋሬት በዚህ ጊዜ ልቧ ተነካ። እናቷ ሲያለቅሱ ስታይ ጉልበቷ ተብረከረከባት፡፡ ከዚያም ድምጿን አለሳልሳ ‹‹ታዲያ ምን ላድርግ እማማ?››
ስትል እናቷን ጠየቀች፡፡
‹‹አክስትሽ ክሌር ዘንድ ትኖሪያለሽ›› አሉ አባት፡ ‹‹ቬርሞንት ስቴት
ውስጥ ቤት አላት፡፡ የምትኖሪው ተራራ ስር እና ሩቅ ስለሆነ የምታሳፍሪው
ሰው አጠገብሽ የለም››
እናትም ጨመሩና ‹‹እህቴ ጥሩ ሴት ናት፡: ባል አላገባችም፡፡ የአካባቢው
ኤጵስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን ዋና አባል ናት፡፡››
ማርጋሬት እንደገና ብስጭት ቢወራትም ንዴቷን ዋጥ አድርጋ ‹‹አክስቴ ክሌር ስንት አመቷ ነው?›› ስትል ጠየቀች።
‹‹ከሃምሳ ዓመት በላይ ይሆናታል››
‹‹ብቻዋን ነው የምትኖረው?››
‹‹ገረዶች ካልተቀጠሩ አዎ››
ማርጋሬት በንዴት ተንዘፈዘፈች፡፡ ‹‹ለብቻዬ ልኑር ባልኩ ነው ይሄ
ሁሉ ቅጣት!›› አለች ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፤ ‹‹ምን ባጠፋሁ ነው ቆማ ከቀረች መበለቲት ጋር ተራራ ስር እንድኖር የተፈረደብኝ፤ ለመሆኑ ምን ያህል ጊዜ ነው እዚያ የምቆየው?››
‹‹አደብ እስክትገዥ ድረስ›› አሉ ‹‹አንድ አመት ያክል››
‹‹ዓመት!›› እድሜ ልክ መሰላት ማርጋሬት ‹‹ጅል አትሁኑ፤ ልታግቱኝ
አትችሉም ወይ አብዳለሁ ወይ ደግሞ እሞታለሁ ወይ ደግሞ አገር ጥዬ እጠፋለሁ›› አለች፡፡
‹‹ያለኛ ፈቃድ የትም ንቅንቅ አትይም፤ከፈቃዳችን ውጭ ብትሆኚ ደግሞ. . ›› አሉና ንግግራቸውን አቋረጡ፡፡
ማርጋሬት አባቷን ገረመመቻቸው ሊል ያሰበው ነገር አሳፍሮት
መናገር አቃተው› አለች በሆዷ፤ ምን ሊል ፈልጎ ነው?›
ከዚያም ከንፈራቸውን ሸርመም አድርገው ‹‹ከአክስትሽ ቤት ብትኮበልይ አዕምሮዋ በሽተኛ ናት ብለን የእብዶች ሃኪም ቤት እናዘጋብሻለን››
ማርጋሬት በንዴት ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀች መናገር አቃታት እንዲህ አይነት ጭካኔ አባቴ ይፈጽምብኛል ብላ አስባ አታውቅም፡ ወደ
እናቷ ፊቷን ስታዞር ዓይኗን ማየት አቃታቸው፡፡
ፔርሲ ከመቀመጫው ተነስቶ የአፍ መጥረጊያ ሶፍቱን ጣለና ‹‹አንተ
ጅል ሽማግሌ! አላበዛኸውም አሁንስ!›› አለና ጥሎ ሄደ፡ ፔርሲ ይህን ያለው ከሳምንት በፊት ቢሆን አልቆለት ነበር፡፡ ነገር ግን ስድቡን ናቅ አድርገው ምንም ሳይሉት ተዉት፡፡
ማርጋሬት አባቷ ላይ አፈጠጠች፡፡ ፊታቸው ላይ የሚነበበው የጸጸት
ስሜት ነው፡፡ የተናገሩት ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቁም ከአቋማቸው ንቅንቅ አላሉም፡፡
ከዚያም ስትረጋጋ ‹‹አባባ በቁሜ ቀብረኸኛል›› አለች፡፡
እናትም ድምጽ ሳያሰሙ አነቡ፡፡
ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡
✨ይቀጥላል✨

👍21😁1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ አጎት ቤት እንደ መጣች ፈጽሞ መንፈሷ ሊረጋጋላት ባለመቻሉ ካርለት የምታደርገውን አጣች" ጎይቲ ጽጕሯን ስትላጭ ካርለት ብቸኝነት እንዳይሰማት አብራት ተላጨች በከሰልና በቅቤ የተለወሰውንም ቅባት መላ ሰውነቷን ስትቀባ ካርለትም አብራት ተቀባች"
ጎይቲ አንተነህና ካርለት አልፈርድ ቆጥ ላይ ከተደበቁ በኋላ ካርለት ጎይቲን ለማጽናናትና ለማደፋፈር ብትጣጣርም አልሳካልሽ አላት ጎይቲ እንዲያውም ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረችባት
ካርለት ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ብታውቅም ሦስት ወር እስኪሞላቸው ድረስ ቆጡ ላይ መቆየት ነበረባቸውና እስከዚያ ድረስ
በመካከላቸው እርቀ ሰላም እንደሚወርድ ተመኘች"
ቀኑንና ምሽቱን ቆጥ ላይ ከቆዩ በኋላ ለአንድ አፍታ ወረድ ብለው ከሎ ከመምጣቱ በፊት ለመናፈስ ወጡ" ጎይቲ አነተነህ ቆጥ ላይ መውጣቱ አልዋጥልሽ ብሏታል።
«አሁን እሱ የወንድ ልብ አግኝቶ እኔን ሊመታኝ? በየትኛው ወኔውና ጀግንነቱ፤ ወይ ሲያየኝ እሱ ራሱ ባልተርበተበተ አይደል?
ወይኔ ጎይቲ የወንድ ልጅ ዱላም ይናፍቃል ለካ?» አለች ለካርለት ይሁን ለማን እንደተናገረች ሳይታወቅ።
ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከከሎ ሆራ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ" ከሎ ሆራ ሁለቱንም ሲያይ ደንገጥ ብሎ ቆመ!
ካርለት በዓይኗ ጠቅሳ እንዲመታት ልትነግረው ፈልጋ ነበር። ለእሱ
«ና ምታት» ብላ በዓይን ለማመልከት እንዴት እንደምታደርግ ስከታስብ ግን እሱ ከቆመበት ደረሱ። ከሎ ሆራ መንገዱን ለቆ
አሳለፋቸው። ካለፉ በኋላ ግን ተሰማው፤ በባህሉ መሠረት እንዳያት ደህና አድርጎ መግረፍ ነበረበት። ያን ሲያስብ የብሽቀት ስሜት ታየበት፤ ጎይቲ አንተነህን ይወዳታል፣ ባህሉንም ያከብራል
ቅሬታና ቂም የሚይዝ ከሆነ አካል በማይጎድልበት መንገድ መምታቱ
የሚያመጣው ችግር የለም።
«ወደፊት ግን ይህን ጥፋት መድገም የለብኝም" በመምታቴ ጎይቲ አንተነህን የሚሰማት ነገር የለም። እንዲያውም እሷን ባለመደብደቤ ቅሬታ ሊያድርባት ይችል ይሆናል» እያለ፣ ራሱን ወቅሷል"
ካርለትም በበኩሏ ትንሽ በሽቋታል። ከሎ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ፊት ለፊት ባገኛት ጊዜ ሁሉ እንዲገርፋት ተመካክረዋል። ጎይቲ
አንተነህ ደግሞ የከሎን የፍቅር ፍርሃት ባለመረዳት ሲርበተበት ስታየው ባሕርይው ያስጠላታል። ከሎ ወንድ ወንድ አልሸትሽ
ብሏታል። «ከሎ ትክክል አልሠራም። እሱ ጎይቲን ልክ ከተማ እንዳየው
ብዙ ሕይወቱን እንዳሳለፈበት በጠባይ ሊያግባባት፣ ሊያቀርባት
ፍቅሩን ሊገልጽላት ይፈልጋል" ጎይቲ ግን ወንድ ልጅ በቅድሚያ የምትፈልገው ኰስታራነት ነው ኵሩ ወንድ፣ ሸንቆጥ የሚያደርግ ወንድ፣ እሷን በፍቅር ገርቶ፣ በፍቅር አብሯት መጋለብ ይችላል
ሴት ልጅ ዱላ ሲያርፍባት የሴትነት ፍላጎቷ ከአሸለበበት ይቃል»
አምጭ አምጭ የሚላት፣ ፍቅር የሚናፍቃት፣ ድሪያ የሚታወሳት ያኔ ነው፤ ከሎ ደግሞ ይህን አልተረዳውም። እንግዳ ነገር ሆኖበታል ሕጉን እያወቀ በተግባር ግን አያከብርም። ይህ ደግሞ ስሕተቱ ነው ካርለት በእንግሊዝኛ ለጎይቲ ነገረቻት። ጎይቲ አንተነህ ግን ያለችው በጭራሽ አልገባትም እንግሊዝኛ ደግሞ የት አውቃ
ጎይቲ አንተነህ አጠገቧ ያለችው ቀውስ ብቻዋን ስትለፈልፍ ብትደነቅም፣ እሷም ተመሳሳዩን ፈጸመች።
«ይኸዋ ይህ ቦቅቧቃ! እንኳንስ ሲያየኝ እንደ ወንዶቹ ሊገርፈ
ይቅርና መንገድ ለቆ አሳለፈኝ" ባል እኔ ነኛ! እሱ ሚስት ነው እንዴት ሆኜ ከዚህ ሴት ጋር እኖራለሁ? ምነው ያን ቀን ደልቲ
ገልዲን ብዬ ባልሄድሁ ኖሮ፤ እሱን ብዬ በመሄዴ ቀናው እንጂ የታባቱ ያገኘኝ ነበር ይህ ሴት" ሴት ልጅ የባሏ ዱላ ሕይወቷ ፍቅሯ ነው" ታዲያ ይህ ሰው እኔንኮ ሕይወቴን እያጠፋ ነው" እሽ
የኔስ ነገር ይቅር ነገር ግን የሚወለዱት የሁለት ሴት ልጆች መባላቸው አይደል? ወይኔ ያልታደሉት" ወይኔ ወይኔ» እያለች፣ እንባዋ
ታወርደው ጀመር"
ካርለት ትንሿን ቴፕ ከፍታ የምትለውን እየቀዳች በማስታወሻ ደግሞ የሚሰማትን ትከትባለች» ካርለት በአንዳንድ ሁኔታ ላይ እሷም ራሷ እየተስማማች መጣች» በአገሯም፣ አንዳንድ እውቅ ሴቶች ስለ ወንድ ፍቅረኛቸውና ከእሱ ስለሚጠብቁት ባሕርይ ሲያወሱ ነካ አድርገው የሚያልፉት ነገር አለ፣ «ከፍቅረኛዩ ጋር ስንላፋ
ስንታገል፣ የፍቅር ዱላ ገላዬ ላይ ሲያርፍ ልቤ እስኪጠፋ ድረስ ራሴን እሰጠውና የሱን ደግሞ ለመውሰድ ሙሉ ፍላጎት አሳያለሁ ከዚያ በኋላ የምንሠራው የፍቅር ጨዋታ ሁሉ እንደ አይስhሬም እየጣፈጠኝ፣ መላ አካሌ ከጸጕር እስከ እግር ጥፍሬ በርካታ
ሲንበሸበሽ ይሰማኛል" እንደዚህ አድርገው ከኔ ጋር የተጫወቱ ወዶች የፍቅር ዙፋኑን ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም» ብለው
የተለያዩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ ሰምታለች።
እሷም ቢሆን አንዳንድ ልምዶችን አሳልፋለች" አንድ ጊዜ፣ ስሜ ጃክ ነው ብሎ የተዋወቃት አሜሪካዊ፣ ማንችስተር ውስጥ
ለጉዳይ መጥቶ አንድ የምሽት ዳንስ ላይ ይተዋወቃሉ“ ካርለት
በእርግጥ ወደ ዳንሱ ቦታ የሄደችው ከወንድ ጓደኛዋ ከዴቪድ ጋር ነው ታዲያ አሜሪካዊው አንድ ሁለት ጊዜ በትእዛዝ መልክ ዳንስ
ጋበዛትና ሰውነቷን በጠንካራ እጆቹ ጠበቅ አድርጎ እያሸ፣
አሳመማት። ቀደም ብላ ባሳለፈችው ሕይወቷ ወንዶች እንደዚያ ሰው
አድርገዋት አያውቁም" ሰውነቷን የሚደባብሱት ቀስና ላላ አድርገው
ነው። ሰውዬው ግን መሞረዱ አንሶ በረጅም እጁ መቀመጫዋን ደህና አድርጎ ቸብ ቸብ አደረገላት «ተው» ማለት እየፈለገች፣ ቃሉ ግን
ከጕሮሮዋ አልወጣልሽ አላት" በእርግጥ፣ ዴቪድም ከሌላ ሴት ጋር እየደነሰ ስለነበር እነሱን ልብ አላላቸውም።
አሜሪካዊው ፍጹም በማታውቀው መንገድ ሰውነቷን እየመታ፣ እየሞረደ፣ ልቧን ስልቱን አስቀየረው ከንፈሯን እንኳን
ሲስማት የንከሻ ያህል ሆኖባት እግሯን አንሥታ ለመጮህ ትንሽ ቀርቷት ነበር ግን አልጮኸችም" ዳንሱ አብቅቶ ሲለያዩ ካለልብ ወደ ቦታዋ ተመለሰች እንደ ምንም ታግሣ ሁለት ጨዋታዎችን
አሳልፋ ልቧን ወደ ቦታው ለመመለስ ወደ አሜሪካዊው ሰው ሄደች።
ቆንጅት እንደምትመጪ አውቅ ነበር...» ብሎ አሜሪካዊው ተመጻድቆባታል" ግን ፊቷን አዙራ አልተመለሰችም፤ ተመልሳ ካቴና እጆቹ መሃል ወደቀች ሞራርዶ፤ ቸባችቦ፤ ብድግ አድርጎ ተሸክሟት ወደ አንድ ክፍል ሲገባ፣ እግሮቿ አልተፈራገጡም"
እጆቿ አልተወራጩም፤ አፏም አልቀባጠረም።
ካርለት ይህንን አሜሪካዊ እስከ አሁን ድረስ በዚያች ለሰዓታት ብቻ በዘለቀች የፍቅር ጨዋታ የማትረሳው ትዝታ አስታቅፏት ነግዷላ" ያንን ሰው ለብዙ ጊዜ የተካው ወንድ አልነበረም። ኖራ ኖራ ግን ሐመር ላይ ተመሳሳዩን አገኘች" የሷም ብቻ ሳይሆን የጎይቲም የሆነው ሰው በእርግጥ ለየት ያለ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሌላ ወንድ ቢያስንቃቸው አይፈረድባቸውም"
ካርለት ቆጥ ላይ እንዳሉ እንዲህ በሐሳብ ተዘፍቃ ቆየችና እናቷ ትዝአሏት" ስለዚህ፣ ደብዳቤ ለመጻፍ ብዕርና ወረቀቷን
አስተካከለችና መጻፍ ጀመረች።
ውድ እናቴ፣
ምን ጊዜም እንደማፈቅርሽ፤ እንደማልምሽ የምትዘነጊ

👍23🤔1
አይመስለኝም። «እማ፣ አንቺን በማጣቴ እንዴት ጎደሎ እንደ ሆንኩ ልገልጽልሽ ይከብደኛል እኔና አንቺ አሁን ያለነው በተለያየ ዓለም ነው" የምትዪኝ ቢገባኝም፣ የምልሽ ግን ሊገባሽ አይችልም" ልጅሽ
አሁን ሌላ ሰው ነኝ" ከድሮው እኔነቴ የአሁኑ ሕይወቴ ትርጕም
ያለው ሆኖ ይሰማኛል እማ! እንዴት ብዬ አሁን ያለሁበትን
ሕይወት ልግለጽልሽ ይሆን? ከበደኝ" እማ! ይህ ልዩ ዓለም የራሱ የሆነ ተፈጥሯዊ ፍቅርና ደስታ ያለው ጣፋጭ ዓለም ነው" ገና ያልተበረዘ፣ ንጹሕ ዓለም ብክለት ያልደረሰበት ድንግል ምድር ነው" ማንም ከርቀት የሚመስለውን ሊል ይችላል። እኔ ያየሁትን ያየ
ግን መቼም ከዚህ የተሻለ ግሩም ዓለም ይኖራል ብሎ ማሰቡ ያጠራጥረኛል" ሰዎች የሚኖሩት በሕገ ልቦና ነው። ተካፍሎ
መብላት ተከባብሮ መኖር፤ መግባባት እውነተኛ መኖሪያቸው እዚህ
ነው። ሌላው ግን ውሸት የውሸት ውሸት ነው።
እማ! አሁን አሁን ምን እንደሚሰማኝ ታውቂያለሽ? የሌላው አካባቢ ብክለት ወደዚህ ሲገሰግስ እያየሁ እወራጫለሁ" ምን ልበልሽ? ለመሆኑ የምልሽ ይገባሻል?...
ካርለት
ካርለት ደብዳቤውን አጣጥፋ ከመክተቷ በፊት የእንባ ዘለላዎች
ዱብ ዱብ አሉባት" አሸገችው። ጎይቲ ሌሊት ስትነሣ፣ ካርለትም ከእንቅልፏ ነቃች" ጎይቲ
አንተነህ ከቤት ወጥታ ወደ ፍየሎች ጋጥ ስትሄድ ተከተለቻት። ጎይቲ
የፍየሎችን በጠጥ ማጽዳት ስትጀምር፣ ካርለትም እንደሷው ማጸዳዳት ጀመረች" ካርለት ጎይቲን እየተከተለች ወደ ከብቶች
በረትም ሄዳ የከብቶችን እበት ጠረገች ከዚያ ተመልሰው የሸፈሮ
ቡና ማፍያውን እንስራ ጎይቲ ስትጥድ፣ ካርለት እንጨቱን አቀራረበችላት" ጎይቲ አሁን አንድ ነገር መጠርጠር ጀመረች። ግን እንዴት
ሊሆን ይችላል? ከሆነም ግን የሚረዳት አገኘች ማለት ነው ጎይቲ
አንተነህ ካርለትን የከሎ ሆራ ሁለተኛ ሚስት እንደ ሆነች ገመተች" ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሥራ ተካፍለው
መሥራት አለባቸው ማለት
ነው። ጎይቲ አንተነህና ካርለት ሥራቸውን ጨርሰው ቡናውን ካፈሉ በኋላ ቆጣቸው ላይ ወጡ" ቆጥ ላይ እንዳሉ ጎይቲ አንዳንድ ነገሮችን ማውጣትና ማውረድ ጀመረች።
«ይህ ሰው ምን ያለ ሰው ነው? የኔን ሦስት አዲስ ጨረቃ ብቻ ገና እንደታየ ጥሎሹን ከፍሎ ጨረሰ። ሌላው ሐመር ግን ለቍጥር
የሚታክት አዳዲስ ጨረቃ ወጥቶ እንኳን ላይሳካለት ይችላል" ደግሞ ይህ አንሶ፣ በአንድ ጊዜ ሁለት ሚስት አምጥቷል። ለእኔ አባት
የከፈለውን ኮይታ ለዚችኛዋም ሴት አባት መቼም መክፈሉ
አይቀርም" በእርግጥ ሁለት፣ ሦስት ከዚያም በላይ ሚስት ያላቸው
ሐመሮችን አውቃለሁ። ሁለት ሚስት ባንድ ጊዜ ያገባ ግን እንኳን ላይ ሰምቼም አላውቅም" ደግሞኮ ይህች ሁለተኛ ሚስቱ አስባ በሐመር ባህል መሠረት አትሠራም" የምትሠራው እኔን እያየች ነው ስለዚህ፣ የመጀመሪያ ሚስት በመሆኔ ደስ ሊለኝ ይገባል" ለሷም
የማደርገውን ሁሉ እንድትፈጽም አደርጋታለሁ» ብላ ጎይቲ አሰበች።
ካርለት፣ ጎይቲ አንተነህ በባህሉ መሠረት የምታደርገውን ሁሉ
በማስታወሻዋ ትለቅማለች" ጎይቲ አንተነህም የምታሳያትን ትፈጽማለች። ካርለት፣ ጎይቲ ይህን እናድርግ፤ ያንን እናድርግ
ስትላት የተግባቡ እየመሰላት ሌላ ሌላ ጨዋታም ልታጫውታት
ስትፈልግ መልሳ ኩርፍ ትልባታለች" ጎይቲ አንተነህ እንዲያውም የከሎ ሚስት ስሙን የማታውቀውን ነገር ይዛ በነጭ ነገር ላይ
ስትጫጭር ስታያት፣ ምኒቱ የአዋቂ ጅል ናት በሉ! ገና መጫዎቻዋን ያልጣለች» ብላ አንድ ጊዜ ብዕርና ማስታወሻዋን ወርውራባታለች እንዲህ በመሆን ሁለት ሳምንት እንዳለፋቸው ግን ካርለትና ጎይቲ መግባባት ጀመሩ። እንዲያውም ጎይቲ ሐመርኛ ለካርለት ስታስተምራት፣ ካርለት ደግሞ የእንግሊዘኛ ፊደልና ቃላት ለጎይቲ
ማስተማር ጀመረች
ከሎ ፊት ለፊት ካገኛቸውም ሁለቱንም በተለይ ካርለትን ለኮፍ እያደረገ መምታቱን ስላልወደደችለት ጠበቅ አድርጎ እንዲመታት
ጠይቃዋለች
ጎይቲ አንተነህ እሷን የከሎ ሁለተኛ ሚስት አድርጋ መገመቷም በቀላሉ የጋብቻውን ሥነሥርዓት ለመከታተል አመቺ መሆን
አልተጠራጠረችም። ካርለትና ጎይቲ በወራቸው እጅግ በጣም የተግባቡ ሆኑ። መሣቅ፣ መጫወት፣ መላፋትም ቀጠሉ" ጎይቲ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቃላትን መጻፍና ማንበብ ጀመረች በዚህም ከካርለት
ጋር መግባባት ቀጠሉ ካርለትማ ሐመርኛውን የራሷ ቋንቋ አደረገችው።
ጎይቲ አንተነህ ዘጠና ቦታ የቋጠረችውን ቋጠሮ በቀን በቀን አንዳንዷን ፈትታ ጨረሰች" ይህ ማለት ደግሞ ሦስት ወር ሞላት ማለት ነው" ስለዚህ በቋጠሮው የተያዘው ቀጠሮ፣ ቋጠሮው ሲያልቅ አለቀ ልክ በሦስተኛው ወር ላይ ከሎ ሆራና ጎይቲ አንተነህ አካል ላካል
ከመገናኘታቸው በፊት ጎይቲ አንተነህ አንድ ቅል ወተትና አንድ ቅል አሸዋ ይዛ በና ማኅበረሰብ ክልል ሙቀጫ ከተባለው መንደር
ከካርለት ጋር ሄዱ" ሽማግሌው ሌሎችንም የዕድሜ እኩያዎቻቸውን
ጠርተው ሸፈሮ ቡና ሲጠጡ ቆዩና፣ «ችግርና ረሃብ ከእኛ ይራቅ ፍቅርና ሰላም አይለየን የሰማይ አፎች አይዘጉ ፀሐይ መውደቅ መነሣቷን አታቋርጥ ከብቶቻችን ይርቡ አንቺም ውለጅ ክበጅ»
ብለው የቡናውን ውሀ በራሷ ላይ አርከፈከፉባት ከዚያም ወተት የያዘውን ቅል ሰጥታ፣ አሸዋ የያዘውን ግን ተቀብላ እንደ ጨረሰች ካርለት ለሽማግሎቹ ያመጣችውን ሸፈሮ ቡናና አንድ ጀሪካን አረቄ ሰጥታ በመመረቅ የመልስ ጕዟቸውን ቀጠሉ።
ሻንቆ መንደር እንደ ደረሱ ጎይቲ አንተነህ አሸዋ የያዘውን ቅል ግርግም ላይ ሰቀለችና ከሎ ሆራ ከሚተኛበት ግርጌ በቆሎ በተን አደረገች" ይህ ማለት ደግሞ «ሰውነቴ አምሯል፣ አሁን አንተን ለማዝናናትና ለማስደሰት ዝግጁ ነኝ ከዛሬ ወዲያ በውቢቱ የግል ንብረትህ ኮርተህ የፈለገህን ልታዛት ትችላለህ» የማለት ምልክትና የሴቷን ግብረሥጋ ግንኙነት ፍላጎት የሚገልጽ መሆኑን ከሎ ሆራ ያውቃል"
ከሎ ሆራ፣ በተቻለው ሁሉ ሌሎች ወንድ ወገኖቹ የሚፈጽሙትን ለማድረግ ዝግጁ ስለ ነበረ ከጎይቲ በስተቀር ማንም ወደሌለበት የአጎቱ ጎጆ ሲሄዱ ልቡ ዳንኪራ መታበት"
ያችን የሚያፈቅራትን የሐመር ውብ ቀንበጥ ሰውነቷን ሊዳስሰው
ነው። ቀንና ሌሊት ያለማትን ቆንጆ ዛሬ ያላትን ሁሉ ለመፈጸም እየጠበቀችው ነው ወደ ጎጆው በተቃረበ ቁጥር እናቱን እንዳየ ሕፃን
ቦርቅ፣ ዝለል፣ ኧየሮጥክ ሄደህ ሳማት፣ እቀፋት፣ ይዘሃት መሬት ላይ
ዥዋ ብለህ ውደቅ አሰኘው።
ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ለማድረግ ባህሉ አይፈቅድለትም“ ስለዚህ ራሱን ለመቆጣጠር እየሞከረ ወደ ጎጆዋ ውስጥ ዘለቀ ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ ወደ ቤት ሲገባ አንገቷን ቀልበስ አድርጋ ፊቷን
ሳታዞር ቆማለች የአንድ ሰው ዓይን ብቻ የምታደርገውን በቀዳዳ ሆኖ ይከታተላታል።
ከሎ ፊቱን ዞር አድርጎ በተነጠፈው የከብት ቁርበት ላይ በጎኑ ተኛ ጎይቲ አንተነህ ቀስ ብላ ዞራ ስታየው፣ ፊቱን ዞሮ መጋደሙን አረጋገጠች" ከውጭ በኩል ሳታየው የሚከታተላት ዓይን ግን
አሁንም በጕጕት መከታተሉን አላቆመም"
ጎይቲ አንተነህ ቀስ ብላ መራመድ ቀጠለች። ከሎ ሆራ ልቡ እንደ ታምቡር እየደለቀ አስቸገረው" ለዓመታት ባለችበት ቆማ የቀረችምመሰለው። ስለዚህ፥ «ዞረህ እያት፣ ዞረህ ቃኛት፣ ዞረህ አምጣት» አሰኘው እንዲህም እንዲያደርግ ግን አይችልም።

👍15
ጎይቲ አንተነህ ቀስ ብላ እየተራመደች ሄዳ አጠገቡ እንደ ደረሰች ከወገቧ በታች የለበሰችውን ቆዳ ገለብ አደረገች ያ ከውጭ በኩል
ትርዒቱን የሚመለከተው ሰው ስሜቱ ቢወጣጠርበትም
ቀጠለ ፊቱን ማዞሪያው ጊዜ እንደ ተቃረበ አልጠፋውም።
ከሎ በጭንቀት ሊሞት ነው እነዚያ ግጥም ያሉ እግሮቿ፣ ኮራ ብሎ ነጠር ነጠር፣ ወዝወዝ የሚለው ዳሌዋ ወደሱ እየተጓዘ ነው
በሙሉ መብት ሊያቅፈው ተቃርቧልI ውብ ጥርሶቿና የሚያባብለው
ዓይኗ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እሱን እሱን ሊያዩት ነው። ስለዚህ ስሜቱ አካሉን ጥሎ ሰገረ አካሉን ሊያስከትል ሲል ግን ከጎኑ ጋደም ስትል
አዳመጠ" ገላዋ ገላውን ነካ አደረገው ንከኪው ከሎን ክፉኛ ናጠው ሁለቱም ግለል" የሱ ትኵሳት ለሷ፣ የሷ ለሱ ፈውስ
እንደሚሰጣቸው ያ በጉጉት የሚከታተላቸው ሰው እየገመተ ነው" ከሎ ሆራ ፊቱን ዘወር ሲል የጎይቲ አንተነህን ዓይን ለአመል
ያህል ተመለከተው" እንደ ንጋት ኮከብ ጠይም ፊቷ ላይ ይንቦገቦጋል። እጁን ሰደድ አድርጎ አቀፋት፣ እሷም አቀፈችው"
ከንፈሩ ወደ ከንፈሯ፣ ከንፈሯ ወደ ከንፈሩ ተጓዙ" የጎይቲ የንብ አውራ መሳይ ወገብ ወደፊት ተለጥጦ ከከሎ የፍየል ቀንድ ጋር
ፍልሚያ ገጠመ” አንዱ ወደ ኋላ ሲያፈገፍግ ሁለተኛው ተንደርድሮ ሄዶ ሲወጋ፣ እንደገና ሲያፈገፍግ ሌላው ሲንደረደር፣ ከላይ አንዱ
ሌላውን ሲጎርስ ትንሽ ቆዩና ጎይቲ አንተነህ ፊቷን ዞራ ጀርባዋንና መቀመጫዋን ለከሎ አዞረችለት በዚህ ጊዜ ከሎ ሆራ እየተመቻቹ
ሲጠጋ፣ ቁርበቱ ዝማሬውን ቀጠለ።
ካርለት በሕይወቷ እንዲህ የሚማርክ ሕይወት አይታ
አታውቅም ያየችውን ሁሉ ልክ እሷ የምታደርገው ይመስል ሳይታወቃት ወገቧን ሰብቃለችI መጨረሻ ላይ ግን ሌሎች ወደ
ማራኪው ዓለም ሲነጠቁ እሷ ግን ተመልካች ኖራ ደረቅ መሬት ላይ
እንደ ቆመች ስትቀር፣ «አምላኬ!» ብላ ዓይኗን ጨፈነች"
ከሎ ሆራና ጎይቲ አንተነህ አካል ለአካል ተገናኝተው ከተጫወቱ በኋላ የፍትወት ስሜታቸው ረግቦ ትንሽ ተንፈስ እንዳሉ ዕድሜዋ
አጭር የሆነ እንቅልፍ ሸለብ አረገቻቸው ጎይቲ ከተኛችበት ስትነሣ
የታጠፈውን ቆዳዋን ወደ ታች ስትለው እንደ ፍየል ጅራት ግራና ቀኝ ውን ውን አለ"
ከሎ ሆራ ሳዳጎራውን በአጭሩ አገልድሞ ሲነሣ ጎይቲ በእጇ መዳፍ የያዘችውን ትንባሆ ለመስጠት ተንበርክካ እጇን ዘረጋችለት ከሎ በደንቡ መሠረት እሷን ሳያይ ትንባሆውን ተቀብሎ መሄድ
ነበረበት" እሱ ግን አልቻለም ዓይኖቿን እያቁለጨለጨች አንጋጣ በአክብሮት ትንባሆ የምታቀብለውን ሴት ከልቡ ያፈቅራታልI ፍቅሯ ረቶት ልብሱን ጥሎላታልI ሐሳቡ እየባዘነ እንደ ኢንሹ ቁጥቋጦ ለቁጥቋጦ ተሽሎከሉኮላታል።
ከሎ ሆራ ጎይቲን ለአፍታ ትክ ብሎ አያት ጭኖቿ ግጥም ብለው መሃል ለመሃል አጭር ቆዳ ተንጠልጥሎበታል በቆሙት
ጡቶቿ መሃል እንብርቷ ተሰርጉዷል፣ በትከሻና በትከሻዋ እንደ ሸለቆ እየጠበበ ወርዶ ዳጐስ ያለው ዳሌዋ የዓይኑን አቅጣጫ አስቀረው
ጎይቲ አንገቷን አቀርቅራ ቆይታ ቀና ስትል ደሟ ሞልቶ እንደገና አማረባት ከንፈሮቿ የንቡጥ ፅጌረዳ ቅላት ያ" ጎይቲ የከሎ ሁኔታ ገባት አባቷ የመከራትንም አስታወሰች፣ «ሴት ልጅ ሣቂታ፣ ወንድ ኮስታራ ነው» ብሏታል፣ እሷም ዕድሜ ልኳን በዚህ ስታምን ኖራለች።ስለዚህ ሣቅ አለች-
ከሎ ግን ፈገግታዋን ሲያይ ልቡ ስንጥቅ አለ። በሽተኛ
ሆነ ስለዚህ አስታማሚውን ይዞ እንደገና ቁርበቱ ላይ ወጣ።
ጎይቲ ሌላ ትንባሆ ይዛ ለመምጣት የታጠፈ ቆዳዋን ዘርጋ ዘርጋ አደረገችI ከሎም አንድ ጊዜ በጥፊ መቶ የተቀበላትን ትንባሆ ይዞ ወጣ ጎይቲ አንተነህ፣ ከሎ በጣም ይመታኛል ብላ ጠብቃ ነበር እሱ ግን ለአንዱም አንጀቱ አልቻለለትም ነበር።
ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ ሥራው ሁሉ እንደ ናቀችው ሆኖ አላገኘችውም" አስተቃቀፉ የላላ ቢሆንም፣ ልቧ እስኪጠፋ ድረስ
"በደንብ አድርጎ ስሟታልl የወንድነት ጥንካሬውም እንደ ደልቲ አንጀት አርስ ባይሆንም የሚያስከፋ ሆኖ አላገኘችውም።
ከጎይቲና ከሎ የፍቅር ጨዋታ በኋላ ጎይቲና ካርለት ሲጨዋወቱ
ካርለት ጎይቲን አንዳንድ ነገር ጠየቀቻት።
«ጎይቲ ምነው ደስ ያለሽ ትመስያለሽ?» ካርለት ጎይቲን ጠየቀቻት"
«ይእ! ተቃበጥኳ» አለች፣ ጎይቲ ፈርጠም ያለች።
«ከማን፣ ከከሎ ጋር?» ካርለት ጕሮሮዋ የጮኸባትን ጨዋታቸውን አስታውሳ የተሰማትን ስሜት እያፈነች
«አዎን» አለች፣ አገጯን ወደ ላይ እየለጠጠች፣ አናቷን ወደ ኋላ በማስተኛት።
ከሎን ወደድሽው? »
«ይእ! ወድጄ ነው» ጎይቲ የሚያማምሩ ጥርሶቿን በሙሉ እያሳየች ሣቋን ለቀቀች።
«የግብረሥጋ ግንኙነት አደረጋችሁ?» ጎይቲ አንተነህ ካርለት
ቂል ሆና እሷንም የተደጋገመና የቂል መልስ እንድትመልስ በመጠየቋ፣ የካርለትን ትከሻ በቀኝ እጇ መታ በማድረግ፣ «ቅድም
ነግሬሽ–አዎን ተቃበጥን» አለች» ካርለት እንደ ነገረቻት
አስታወሰች በመርሳቷ ግን እራሷን ታዘበች።
«ከከሎ ሆራ ጋር በስሜት ግንኙነት አደረግሽ? »
«ይእ! ድሮስ–ከእንግዲህ ወዲያ ስሜቴን ለማን እሰጣለሁ?
እሱኮ ከአሁን በኋላ የእኔ ጌታ ነው። ስለዚህ ሁለመናዬን በፍላጎቴ
መስጠቴ አይቀርም።»
«..አርጋችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከሎን ወደድሽው ማለቴ ስሜትሽ ረካ?»
«አዎ ግን ሳይደጋግም ተወኝ» ብላ፣ ሁለት ጠጠር ከመሬት አንሥታ አሳየቻት፤ ሁለት ጊዜ አረግን ለማለት።
«ለምን አንቺ እንዲደጋግም አትነግሪውም ነበር?»
«ይእ! ልጃገረድ ብሆን ኖሮ እንዳልሽው የፈለኩትን ጠይቄ ወንዶች እንዲፈጽሙ አደርግ ነበር" የሐመር ወንዶች ልጃገረድ
ያለቻቸውን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይሉም" አሁን ግን ልጃገረድ አይደለሁም፣ ባል አግብቻለሁ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ «እንዲህ
አድርጊ» ስባል ማድረግ እንጂ «እንዲህ አድርግ» ብዬ ባሌን መጠየቅ አልችልም።» ጎይቲ አንገቷን ደፍታ ለካርለት መለሰችላት"
«ከሎ ሆራ፣ አይዞሽ አትፍሪI የምትፈልጊውን ሳትሳቀቂ
ጠይቂኝ ቢልሽ እሽ ትያለሽ?» አለቻት ካርለት
«ይእ! ከባህሉ ውጭ? አሁን አንቺስ ይህን አጥተሽው ነው? አንችስ ሴት መስለሽኝ?» አለች ጎይቲ፣ ኰስተር ብላ"
«ጎይቲ እኔ የከሎ ሚስት መስየሽ ነበር?»
«አዎ! የዛኔ ቆጥ ላይ አብረሽኝ እያለሽ ሁኔታው ግር ቢለኝም፣
የሱ ሚስት መስለሽኝ እኮ ነው ሥራ አብረሽኝ ስትሠሪ ዝም ያልኩት"
አሁን ግን አለመሆንሽን አወቅሁ" ምነው የሱ ሚስት በሆንሽ ኖሮ፣ጉልበት ቢያንስሽም አዛባና እበት ለመዛቁ ንገሩኝ ብለሽ ልብ
አታወልቂም» አለቻት ጎይቲ፣ በሣቅ እየተንከተከተች”
ከሎን ለምንድነው እሱ የምትይው፣ በስሙ አትጠሪውም? »
ይእ! ገና አንድ እንኳን ሳልወልድ መጥራቱን እፈራለሁ»አለች ጎይቲ ፈርጠም ብላ።
ካርለት ስለ ጎይቲ አንተነህ ባሕርይና ድርጊት ብዙ ነገር
ተከታተለች" ስለዚህ ስለሷ የምታውቀው ብዙ ነው" እሷ ደግሞ የሐመር ልጃገረዶችንና የአገቡ ሴቶችን ባሕርይ የምትወክል ናት።
“ጎይቲ፣ ደልቲ ገልዲን ትወጂው ነበር?» ካርለት ጎይቲን ጠየቀቻት
«ይእ ነፍሴ እስኪጠፋ ነዋ!» አለች ጎይቲ።
«ለምንድነው ከሌሎች ወንዶች ሁሉ እሱን ነፍስሽ እስኪወጣ የምትወጂው? »
«ይእ! ጀግና ነዋ፤ ጐበዝ ነውI በፍቅር ጨዋታም ጠንካራ ነዋI ኧረ እሱ ምን የማይሆነው አለቴ" እሱ ሲይዘኝ ልቤ በደስታ
ይሞላል" በዚያ ጠንካራ እጁ ወደ ደረቱ እየሳበ ሲለጥፈኝ፣ እኔም ጀግና የሆንሁ ይመስለኛል» አለች ጎይቲ፣ አሁን የምታደርገው
ይመስል ዓይኖቿ እየቦዙና እንባዋ ዓይኗ ላይ እየተንጣለለ።
«ጎይቲ እኔና ደልቲ ገልዲኮ ተቃብጠናል፤ እኔም እንዳንች ሳልወደው የምቀር አይመስለኝም» አለች ካርለት በቅናት ገፅታዋ
ይቀ'ር ይሆን ብላ ጎይቲ አንተነህን እያስተዋለች።

👍33😁3👎1
«ይእ! እንግዲያው እኔን ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ አንችም ከእሱ ጋር ተቃብጠሻል ለካ!» አለች ጎይቲ"
«ጎይቲ ከፍቅረኛሽ ጋር ግንኙነት በማድረጌ አትቀየሚኝም? »
ካርለት ጎይቲን ስትጠይቃት፣ ጎይቲ አልገባት አለ። ስለዚህ ካርለት እንደገና፣ «ከደልቲ ጋር በመቃበጤ አትናደጅም?»
“ይእ! ለምን? ልጃገረድ አይደለሽም እንዴ? ካሰኘሽ ጋር ብትቃበጭ ደሞ ጥላቻውና ንዴቱ ምንድን ነው? እሱም ወንድ ነውI
ከፈለጋት ሴት ጋር ቢቃበጥ ጠያቂ የለውም" ልጃገረድና ወንድ ደግሞ ለመቃበጡ ማን ከልካይ አለበት?
እንዴት እንዴት ጠየቅሽኝ
ደግሞ? »
ካርለት በሐመር ማኅበረሰብ የአባለዘር በሽታ ችግር እንደሌለ
አረጋግጣለች" በሐመር ውስጥ ትልቁ ገዳይ በሽታ ወባ ነው ሐመሮች ለብዙ በሽታ እንደ መድኃኒት የሚጠቀሙበት ላት
ቆርጠው፣ ጨው ይጨምሩበትና አሥረው ጥቂት ጊዜ በማቆየት
ጠጣሩ ላት ሲሟሟ ያኔ በቀሰም እየሳቡ ይጠጡታል" ለቁርጠትም
የጨፌ ሣር ሥር እንደሚጠቀሙ አይታለች”
ካርለት በጎይቲ መልስ እጅግ ተመስጣ፣ ባህላዊ የግብረሥጋ ግንኙነት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለውን ጠንቅ ስታስብ ጎይቲ ደግሞ በተራዋ ጠየቀቻት፣
«ለምንድነው ገላሽ የነጣ?»
«የፀሐይ ቃጠሎ ከማይበዛበት አገር ስለመጣሁ።»
«የመጣሽበት ከኮንሶ ይርቃል?»
«ጎይቲ ኮንሶማ እዚህ እናንተ ጥግ፣ እናንተ አገር እኮ ነው ያለው እኔ ግን ብዙ አገር አቋርጬ፣ በአውሮፕላን ሰማይ ላይ ሲበር ድምፁ በሚሰማው ነው የመጣሁት"»
«ይእ! አንቺ ደግሞ ቀልደኛ ነሽ እኔ የእውነቴን ጠየኩሽi
አንቺ ግን ትቀልጃለሽ» አለች ጎይቲ"
«ጎይቲ እውነቴን እኮ ነው።»
ጎይቲ አንተነህ ካርለት ያለቻትን እውነት ነው ብላ መቼም መቀበል አትችልም።
«ሰው በሰማይ በሚበረው ይሄዳል ብዬ ባምን አገር በኔ ዓመት አይሥቅም?»
ጎይቲ ትንሽ ቀየም አለችና ካርለትም ጎይቲ አንተነህን ለማስረዳት መጣሩ የማይሳካ ስለሆነባት፣ «አሁን ባታምኝኝም፣ ወደፊት ወስጄ ሳሳይሽ ያኔ ታምኝኛለሽ» አለቻት ጎይቲ ግን ከአጠገቧ ኵርፍ ብላ
ሄደች"....
💫ይቀጥላል💫

👍28🥰6
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡
አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ።
ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡
ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር አይሮፕላኑ ሰላማዊ መንገዱን ይጓዝ ነበር
አሁን ግን ምንም ሆነ ምን ችግሩ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጦ መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደተሳፋሪ መብረር ካልሆነ በስተቀር የበረራ መሀንዲስ መሆን አይችልም፡፡ አልቆለታል። በንዴት ስህተት እንዳይሰራ
መጠንቀቅ አለበት፡ ይህን ዕቅድ በርጋት መከወን አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ
ህይወቱን ያመሰቃቀሉበት ርጉሞች ላይ ይዘምታል።
አይሮፕላኑ በድንገት ባህር ላይ ማረፍ ሊገደድ ነው: ሚስቱን ያገቱበት ወሮበሎች አይሮፕላኑ ላይ ይወጡና ፍራንክ ጎርዲኖን ያስፈታሉ፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነው አይታወቅም:፡ ካሮል አን ደህና ስለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወሮበሎቹ ወደ አይሮፕላኑ ሲመጡ የጠረፍ ጠባቂ
ፖሊሶች አደጋ ይጥሉባቸው ይሆናል፡፡ ኤዲ በዚህ ስራ ውስጥ ለፈጸመው እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እሱ እጣ ፈንታው ሆኖ እዚህ ውስጥ በመግባቱ ነው
ለእስር የሚበቃው።ካሮል አንን በደህና እጁ እንዳስገባ ሌላ የሚፈልገው ነገር የለም::
የአይሮፕላኑ ሞተሮች ቀጥ ካሉ ከአፍታ በኋላ የካፒቴን ቤከር ድምጽ በጆሮ ማዳመጫው መጣና ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡
ኤዲ በድንጋጤ አፉ ስለደረቀበት ከመናገሩ በፊት ሁለት ጊዜ ምራቁን ዋጥ አደረገ ‹‹ገና አላወቅሁትም›› አለና መለሰ፤ ነገር ግን መልሱን ያውቃል፡ ሞተሮቹ መስራት ያቆሙት ነዳጅ ስላለቀ ነው፡፡ እሱ ነው ነዳጅ
ወደ ሞተሮቹ እንዳይደርስ ሆን ብሎ ያደረገው። አይሮፕላኑ ስድስት የነዳጅ
ታንከሮች ያሉት ሲሆን ነዳጅ ወደ ሞተሮቹ የሚያደርሰው ክንፉ ላይ ባሉት
ታንከሮች አማካይነት ነው፡፡ ወደ ሞተሮቹ ነዳጅ
የሚያመጡትን ፓምፖች ሆን ብሎ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ሌላ ኢንጂነር
ቢያየው ሆን ብሎ እንዳይሰሩ እንደተደረጉ ያውቅበታል፡
ረዳት ኢንጂነሩ ሚኪ ፊን ተራው ባይደርስም ድንገት ሊመጣ ይችላል ብሎ ተጨንቋል፡ ነገር ግን ሚኪ እንቅልፉን እየለጠጠ ይሆናል ይህን ጊዜ፡
በረራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ ውጭ ያሉ
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ይተኛሉ፡
ሼዲያክ ላይ ሁለት ጊዜ አስፈሪ የፖሊስ ምርመራዎች ነበሩ፡
የመጀመሪያው ፖሊሶች አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረውን የፍራንኪ ጎርዲኖ
ግብረ አበር ስም ማወቃቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ኤዲ ሉተርን ማለታቸውን
ገምቷል በዚህም ምክንያት ሉተር አልቆለታል ብሎ ካሮል አንን የሚያስለቅቅበትን ሌላ ስልት ማውጠንጠን ጀምሮ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ
ፖሊሶቹ ሄሪ ቫንዴርፖስትን እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ኤዲ ጮቤ ረገጠ፡፡ከድንጋጤው መለስ ሲል ከሃብታም ቤተሰብ የተወለደ የሚመስለው ቫንዴርፖስት ለምን በሀሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ ገርሞታል፡የፖሊሶችን ትኩረት ከሉተር ወደ ራሱ እንዲዞር በማድረጉ ቫንዴርፖስትን በሆዱ እግዚአብሔር ይስጥህ ብሎታል፡።
ፖሊሶችም በምርመራው ብዙም ሳይገፉበት ርግፍ አድርገው ተዉት፡ ስለዚህ ሉተር ተረዳና በዕቅዱ መሰረት እነ ኤዲ የጀመሩትን ሊያከናውኑ ተነሱ፡፡
የፖሊሶችን
ለካፒቴን ቤከር ግን የተፈጸመው ሁሉ ጥርጣሬን የሚቀሰቅስ ሆኖበታል፡፡ ኤዲ ገና ከድንጋጤው ሳያገግም አንድ ድንገተኛ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ላይ ጎርዲኖ
ተባባሪ አለው ማለት እሱን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ሰው አለ ሲል ደመደመ፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖን ከአይሮፕላኑ ላይ ማስወረድ ፈለገ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤዲ እቅድ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡
ህግ እንዳይከበር በማድረጉ በህግ እንደሚጠይቀው የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድ ካፒቴን ቤከር ላይ ዝቶ ነበር፡፡ በመጨረሻ ካፒቴኑ ኒውዮርክ ለሚገኘው ለፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ስልክ ደውሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ አየር መንገዱም ጎርዲኖ በአይሮፕላኑ
መጓዙን እንዲቀጥል ሲፈቅድለት ኤዲም በእፎይታ ተነፈሰ፡፡
ሼዲያክ ላይ አንድ አስደሳች መልዕክት ደረሰው፡፡ የመጣው የኮድ
መልዕክት ከጓደኛው ስቲቭ አፕል ባይ መሆኑ አያጠራጥርም፡ መልዕክቱም አንድ የባህር ኃይል ጀልባ አይሮፕላኑ የሚያርፍበት አካባቢ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንና እንዳይታወቅ ከእይታ ውጭ ሆኖ ወደ አይሮፕላኑ የሚጠጋ ማንኛውንም ጀልባ ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡
ይሄ ለኤዲ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በኋላ ወሮበሎቹ ከህግ እንደማያመልጡ
ማረጋገጫ ቢሰጠውም ዕቅዱ ግን ያለምንም እንከን ባሰበው መልኩ
እንዲጠናቀቅ እንቅፋት እንዳይፈጠር ምኞቱ ነው፡፡
ካፒቴን ቤከር ወደ ኤዲ መጣ፡፡ ኤዲ እጁ እየተንቀጠቀጠ ለሞተሩ ነዳጅ የሚመግበውን ፓምፕ ከፈተውና ‹‹ታንከሩ ባዶ ስለሆነ ሞተሩ አልነሳ አለ›› አለው::
‹‹ለምን?›› ሲል ካፒቴኑ ተቆጣ፡፡
ኤዲ መልስ አልነበረውም፡፡
የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች በመጠባበቂያ ነዳጅና በመጋቢ ቧንቧዎቹ
መካከል የነዳጅ እንቅስቃሴ ወይም ግፊት መኖሩን አያሳዩም፡ ፓይለቶቹ ጋ
ግን የነዳጅ ሁኔታን የሚያሳዩ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች አሉ ካፒቴኑ ሁሉንም በየተራ አየና ‹‹ምንም ነዳጅ የለም›› አለ፡፡ ‹‹በክንፉ ላይ ባለው
ታንከር ውስጥ ምን ያህል ነዳጅ አለን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ትንሽ ነው የቀረው - የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ብቻ የሚያስኬድ››
‹‹እንዴት ነው ይህን ያላስተዋልከው?›› ሲል ጠየቀ በቁጣ፡
‹‹እኔ ፓምፕ እያደረገ ነው የመሰለኝ›› አለ ኤዲ በተቆራረጠ ድምጽ
ይህ መልስ ግን ካፒቴኑን አላጠገበውም፡፡
‹‹ሶስቱም ፓምፖች እንዴት ባንድ ጊዜ ስራ ሊያቆሙ እንደቻሉ አልገባኝም›› አለ ካፒቴኑ።
‹‹ቶሎ ባህር ላይ ካላረፍን የቀረው ነዳጅ ተንጠፍጥፎ አይሮፕላኑ ሊወድቅ ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡
‹‹ባህር ላይ ልናርፍ ስለሆነ ሁላችሁም ተዘጋጁ›› አለ ቤከር፡፡ ጣቱንም ኤዲ ላይ እያወዛወዘ ‹‹አንተ አታስፈልገኝም አላምንህም›› አለው፡
ኤዲ ሞቱን ተመኘ፡፡ ካፒቴኑ ላይ ክህደት ለመፈጸም በቂ ምክንያት እንዳለው ቢያውቅም የፈጸመውን ድርጊት አልወደደውም፡ ህይወቱን በሙሉ
ሃቀኛ ሆኖ ነው የኖረው:: አጭበርባሪዎችንና አታላዮችን አጥብቆ ይጠላ
ነበር፡፡ አሁን ግን የሚጠላውን ነገር ለማድረግ ተገዷል፡
ካፒቴኑ ናቪጌተሩ ጋ በመሄድ ቻርቱ ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ኤዲን በግርምታ ገረመመውና ‹‹አሁን ያለነው እዚህ ላይ ነው››
ብሎ ቻርቱ ላይ በመጠቆም ለካፒቴኑ አሳየው፡፡
የኤዲ ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው አይሮፕላኑ እሱ ባሰበው ቦታ ከወረደ
ነው፡፡ ወሮበሎቹ እዚህ ቦታ ላይ ነው የሚጠብቁት፡፡ ነገር ግን ድንገት
የሚፈጠር ነገር ካለ ከታሰበው ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ካፒቴኑ ሌላ ቦታ
ከመረጠ ግን ኤዲ እሱ ያለው ቦታ የተሻለ ስለሆነ እዚያ ማረፍ እንዳለበት
ካፒቴኑን ማሳሰቡ አይቀርም፡፡ ካፒቴኑ ሊጠረጥር ቢችልም እዚህ ቦታ ከማረፍ የተሻለ ነገር እንደሌለ በሎጂክ መቀበል ይኖርበታል፡ ሌላ ቦታ
እንዲያርፍ የሚያደርግ ከሆነ ግን ትክክል የማይሆነው እሱ ነው፡፡ ስለዚህ የእሱ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹እዚህ ጋ ነው የምናርፈው›› አለ ካፒቴኑ፡

👍19
ኤዲ በተቀዳጀው ድል መደሰቱን ካፒቴኑ እንዳያውቅበት ዞር አለ፡፡
ለካሮል አን እየደረሰላት መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ኤዲ በመስኮት ወደ ታች ባህሩን ሲቃኝ አንድ ነጭ መርከብ ውሃ ላይ እንደተጣለ ኳስ ሲዋልል አየ፡፡ ባህሩ ማዕበል አዘል ስለሆነ ለአይሮፕላን አይመችም፡፡
ልቡን ቀጥ ሊያደርግ የሚችል ድምጽ ከአንድ አቅጣጫ መጣ::
‹‹አይሮፕላኑ በድንገት ሊያርፍ ነው›› አለ ሚኪ ፊን፡፡
ኤዲ ሚኪ ፊን ላይ በፍርሃት አፈጠጠ፡ ሚኪ የእጅ ፓምፑ ላይ ያለው ቫልቭ እንደማይሰራ አውቋል፡፡ ስለዚህ እሱን ከዚህ ቦታ ማራቅ ይኖርበታል፡ ካፒቴን ቤከር ደረሰለት፡ ‹‹ሚኪ ከዚህ ጥፋ!›› ሲል ተቆጣ
ፈረቃቸው ያልሆኑ ሰራተኞች አይሮፕላኑ ድንገት ሲያርፍ የመቀመጫ
ቀበቷቸውን አስረው ነው መቀመጥ ያለባቸው እንጂ የማይረባ ጥያቄ
ለመጠየቅ እዚህ እዚያ አይሉም: ሚኪ ከአካባቢው በሮ ሲጠፋ ኤዲ እፎይ አለ፡፡
አይሮፕላኑ ወደ መሬት ማዘቅዘቅ ጀመረ፡ ነዳጁ ከተጠበቀው ጊዜ
በፊት አልቆ አይሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ማረፍ የተሻለ ነው ብሎ አምኗል፡፡
ደሴቷን አልፎ ላለመሄድ ሲሉ ወደ ምዕራብ አጠመዘዙ፡፡ ነዳጅ
አልቆባቸው አይሮፕላኑ መሬት ላይ ከወደቀ ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ አንድም
ሰው አይኖርም ባህሩ ላይ አራት ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ከባድ ማዕበል ይታያል በዚህ ሁኔታ አይሮፕላኑን ማሳረፍ አስቸጋሪ ነው፡፡ ኤዲ በፍርሃት ጥርሱ ተፋጨ
ኤዲ ለህይወቱ ፈራ፡
አይሮፕላኑ አየር ላይ ቢሆንም የሞተሩ አለመስራት ፍጥነቱን
በመቀነሱ ከፍታውን ጠብቆ መብረር አልቻለም፡፡ በተቃራኒው የመሬት ስበት
ወደ ታች ይስበዋል፡፡ ስለዚህ ሲያርፍ መንሸራተት ሳይሆን ውሃው ላይ
በሆዱ ይወድቃል፡ የአይሮፕላኑ ሆድ በስስ አሉሙኒየም የተሰራ በመሆኑ እንደ ካርቶን ሊበጫጨቅ ይችላል፡
እስኪያርፍ በጭንቀት ጠበቀ፡፡ አይሮፕላኑ ወርዶ ከውሃው ጋር ሲላተም ሰቀጠጠው፡፡ የአይሮፕላኑ መስኮቶች በውሃ ተሸፈኑ። ወደ አንድ ጎን ሲያዘነብል ወምበሩ ላይ በቀበቶ ባይታሰር ኖሮ ይጋጭ ነበር፡
ውሃው ላይ ለማረፍ ሲነሳ ሲወድቅ በፍርሃት የተዋጠው የተሳፋሪዎች
ጩኸት በረታ፡
ትንሽ ቆየና አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ቀጥ ብሎ መሄድ ጀመረ፡ በኋላም
ባህሩ ላይ ቆሞ ላይ ታች ማለት ያዘ፡፡ ሞተሮቹ እያጓሩ ነው፡፡ ትንሽ በትንሽ
ኤዲ ፍርሃቱ እየለቀቀው መጣ፡፡
ኤዲ ጀልባ ይኖር እንደሆን ለማየት በመስኮቱ አሻግሮ ተመለከተ ጸሃይ የወጣ ቢሆንም ደመና እያንዣበበ ነው፡፡ በአካባቢው ጀልባ አይታይም ወደ መቀመጫው ተመለሰና ሞተሮቹን አጠፋቸው፡፡ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ
የድረሱልኝ ጥሪውን እያሰማ ነው፡፡ ‹‹እስቲ ልሂድና ተሳፋሪውን ላረጋጋ››
አለ ካፒቴኑ፡
የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ለድረሱልኝ ጥሪው ምላሽ ያገኘ ሲሆን ኤዲ ምላሽ የሰጡት የጎርዲኖ ሰዎች እንዲሆኑ ተመኘ፡
ለማወቅ ጓጓ፡፡ ኤዲ የአይሮፕላኑን በር ከፈተ፡፡ የባህር ሞገዱ የሚረጨው ውሃ ጫማውን እያራሰው ነው፡፡ ጀምበር ከደመናው ኋላ ገባች፡ አይሮፕላኑን ቃኘው ምንም አልሆነም፤ ጭረት እንኳን የለበትም፡፡
ኤዲ መልህቁን ባህሩ ላይ ጣለና ዙሪያ ገባውን ቃኘ - የሆነ ጀልባ አይ ይሆን ብሎ፡፡ የሉተር ሰዎች የት ደረሱ? የሆነ እክል ተፈጥሮ ይሆን?ካልመጡስ ምንድነው የሚደረገው? ሲል ተጨነቀ፡፡ ትንሽ ቆይቶ አንድ የሞተር ጀልባ በሩቅ ታየች፡፡ ልቡ ደለቀ፡፡ ይሄ ይሆን ጀልባው? ካሮል አን
ውስጡ ትኖር ይሆን? በድንገት የወረደውን አይሮፕላን ሊታደግ የመጣ
ጀልባ ሊሆን ይችላል ሲል ተጨነቀ ውጥኑን ሊያበላሽ የመጣ፡፡
ጀልባው ወደ እነሱ መጣ በማዕበሉ ላይ ታች እያለ እየቀረበ ሲመጣ
ትልቅ ጀልባ መሆኑን አየ፡ ጀልባው ላይ አራት ለዎች ይታያሉ፡ ሶስት ወንዶችና አንዲት ሴት ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ካሮል አን ደግሞ
ሰማያዊ ቀሚስ አላት፡፡
እሷ ናት ብሎ ገምቷል፡፡ ነገር ግን ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ሴትየዋ
ጸጉሯ ነጣ ሰውነቷ ቀጠን ያለ ነው፡፡ እሷም እንዲሁ ናት፡፡ ከወንዶቹ ፈንጠር ብላ ነው የቆመችው፡፡ ጸሃይ እንደገና ስትመጣ ሴትየዋ እጇን ወደ ወታደር ሰላምታ ሰጪ ግምባሯ ላይ አደረገች፡፡ ጀልባው እየተጠጋ ሲመጣ
ሚስቱ መሆኗን አወቀ፡
‹‹ካሮል አን›› ሲል ተጣራ፡፡
ደስታ ወረረው፡፡ የገቡበትን አደጋ ለጊዜው ረስቶ ዳግም ሲያገኛት ደስታው ወደር አጣ፡፡ ምድር ጠበበችው፡፡ ‹ሮል አን›› ‹ሓሮል አን›› ሲል
ደጋግሞ ተጣራ::
ድምጹን ስትሰማ ለየችው፡፡ እሱ ይሆን አይሆን እያለች በመጠራጠር እጇን ቀስ እያለች ነበር የምታውለበልበው፡፡ በኋላ እሱ መሆኑን ስታውቅ
ግን ክንዷ እስኪገነጠል እጇን አወናጨፈች፡፡
‹እጇን ማወናጨፍ የቻለችው ደህና ብትሆን ነው የኔ ካሮል› አለ በሆዱ
ደስታው ሆዱን እያሞቀው፡፡
ሆኖም ገና ነገሩ እንዳላለቀ ተረዳ፡ ብዙ የሚሰራው ነገር ስላለ እጁን እንደገና አውለበለበና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡ደ
ወደ ውስጥ ሲገባ ከካፒቴን ቤከር ተገናኙና ‹‹አይሮፕላኑ ጉዳት ደርሶበታል?›› ሲል ጠየቀው ቤከር፡
‹‹ምንም አልሆነም››
ካፒቴኑ ወደ ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ሲዞር ‹‹የድረሱልኝ ጥሪያችንን ሰምተው
ብዙ መርከቦች እየመጡልን ነው፡፡ አንድ ጀልባ ግን አይሮፕላናችን ጋ
እየቀረበች ነው፤ እያቸው›› አለ ኦፕሬተሩ፡፡ ቀጠለና ‹‹ጀልባዋ ላይ ያሉት
ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ እንግባ እያሉ ነው›› አለ፡፡
‹‹አይሆንም›› አለ ካፒቴኑ፡ በዚህ ጊዜ ኤዲ ተበሳጨ፡ ‹መግባት አለባቸው አለ ኤዲ በሆዱ፡፡ ቤከርም ቀጠለና ‹‹ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር እንዳታስሩት፤ የአይሮፕላኑ ውጫዊ ክፍል ይጎዳል፡፡ በዚህ ማዕበል ውስጥ
ከአይሮፕላኑ ወደ ጀልባው ሰው ስናዛውር ባህሩ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ
ልትረዱን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን፤ ነገር ግን እርዳታችሁ አያስፈልገንም
በላቸው›› አለው፡
ኤዲ ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ፡ ጭንቀቱንም ለመደበቅ ሲል ምንም
ያልመሰለው ለመምሰል ሞከረ፡ አይሮፕላኑ ከፈለገ ግንጥልጥሉ ሊወጣ
ይችላል፡ የሉተር ወዳጆች አይሮፕላኑ ላይ መውጣት አለባቸው ይህ ሊሆን
የሚችለው ግን አይሮፕላኑ ውስጥ የሚረዳቸው ሰው ካለ ነው፡፡ አንድ ሰው
ገመድ ወጥሮ ካልያዘላቸው ሊገቡ አይችሉም ታዲያ እንዴት ብለው አይሮፕላኑ ውስጥ ይግቡ› አለ በሆዱ፡፡
ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹መግባት እንደማይችሉ ብነግራቸው በጀ አላሉም›› አለ ለካፒቴኑ
ኤዲ ወደ ውጭ ሲመለከት ጀልባዋ አይሮፕላኑን ትዞራለች፡
‹‹ከምንም አትቁጠራቸው›› አለ ካፒቴኑ፡
ኤዲ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲሄድ የት ነው የምትሄደው?› ሲል ተቆጣ
ካፕቴኑ።
መልህቁን በትክክል ጥዬው መሆኑን ላረጋግጥ ነው አለና ከካፒቴ መልስ ሳይጠብቅ ከአይሮፕላኑ ወጣ፡፡
‹ይሄ ሰው በቅቶኛል›› አለ ቤከር፡፡
እኔም አውቄዋለሁ ይህን አስቀድሜ አለ ኤዲ በሆዱ፡ ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ብዙም አትርቅም፤ ካሮል አን በደምብ ትታየዋለች፡፡ ስራ
ስትሰራ የምትለብሰውን አሮጌ ቀሚስና ጫማ ለብሳለች ሊወስዷት ሲመጡ በስራ ልብሷ ላይ አለኝ የምትለውን ኮት ደርባለች ፊቷ ገርጥቷል፤ ኤዲ በዚህ ጊዜ ደሙ ፈላ፤ አልለቃቸውም! አለ በሆዱ። ከዚያም እጁን ጀልባዋ
አሳያቸው:፡ ሰዎቹ የሚያደርገው እስኪገባቸው ድረስ ብዙ ጊዜ ገመዱን

👍14
ላይ ላሉት ሰዎች አውለበለበና ገመዱን እንዲወረውሩለት በምልክት
አወዛወዘ ልምድ የሌላቸው መርከበኞች መሆናቸው ወዲያው ነው የገባው፡
የለበሱት ሙሉ ልብስና ንፋሱ ኮፍያዎቻቸውን እንዳይወስድባቸው በእጃቸው ተጭነው መያዛቸው ለአካባቢ እንግዳ እንደሆኑ ያሳያል፡ የጀልባው ነጂ በባህር ሞገዱ ምክንያት ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር እንዳትጋጭ ለማድረግ
ስራ በዝቶበት ይታያል፡፡ በመጨረሻ ከሰዎቹ አንዱ የኤዲ ገመድ የማወዛወዝ
ምልክት ገባውና ገመዱን አነሳ፡፡ ልምድ የሌለው ገመድ ወርዋሪ በመሆኑ
ኤዲ ገመዱን የቀለበው ከአራት የውርወራ ሙከራ በኋላ ነው፡፡
ኤዲ ገመዱን ቀለበው፡ የጀልባው ነጂ ጀልባዋን ወደ አይሮፕላኑ ለማስጠጋት እየሞከረ ነው:፡ ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር ስትነፃፀር ትንሽ በመሆኗ በማዕበሉ ውዝዋዜ ምክንያት በጣም ላይና ታች ትል ነበር፡ ስለዚህ ከአይሮፕላኑ ጋር ማሰር ከባድ ስራ ሆኖ ነበር፡
ኤዲ ገመዱን ለማሰር ሲታገል ሚኪ ፊን አየውና
‹‹ኧረ ለመሆኑ ምን
እያደረግህ ነው?›› ሲል ጠየቀው፡፡
ኤዲም ዞር አለና ‹‹አያገባህም ሚኪ ተጠንቀቅ ጣልቃ እገባለሁ ብትል አይሮፕላኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ይጎዳሉ›› አለው፡፡
ሚኪ ፈራ ‹‹እሺ እንዳልክ›› አለና ተመለሰ ኤዲ አብዷል ብሎ እያሰበ፡፡ ጀልባዋ አይሮፕላኑን ተጠግታለች፡፡ ሶስቱን ሰዎች አያቸው: አንዱ ዕድሜው ከአስራ ስምንት አይበልጥም፡፡ ሌላው ደግሞ አርጀት ብሎ ቀጨጭ ያለ ሲሆን አፉ ላይ ያለው ሲጋራ ማዕበሉን ተከትሎ ይወዛወዛል፡፡ ሶስተኛው ሰው ባለመስመር ሙሉ ልብስ የለበሰ ሲሆን አዛዣቸው ይመስላል፡፡
ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር በደንብ ለመጠፈር ሁለተኛ ገመድ እንደሚያስፈልግ ኤዲ ተረዳ፡፡ ‹‹ሌላ ገመድ ወርውሩልኝ›› ሲል እጁን አፉ ላይ ደቅኖ ተናገረ ድምጹ በደንብ እንዲሰማቸው፡፡
ባለ መስመር ልብስ የለበሰው ሰው ሌላ ገመድ አነሳና ለኤዲ አሳየው፡
‹‹ኤዲ እሱ አይሆንም! ሌላ ጠንካራ ገመድ ወርውርልኝ›› አለ፡፡
ሰውዬው ኤዲ ያለው ገባውና ሌላ ገመድ ሲወረውር ኤዲ ቀለብ አድርጎ ጀልባውን አይሮፕላኑ ጋር ጠፈረው፡፡ ጀልባዋ ቀስ እያለች ወደ አይሮፕላኑ
ተጠጋች፡፡ ከዚያም የጀልባዋ ሞተር ጠፋና ቱታ የለበሰ ጀልባ ነጂ ገመዱን
ወጥሮ ያዘ፡፡ ይህ ሰው በእርግጥም መርከበኛ ነው፡፡
ኤዲ ከወደ አይሮፕላኑ ድምጽ ሰማ፡፡ ድምጹ የካፒቴን ቤከር ነው፡፡
‹‹ቀጥታ ትዕዛዝ ጥሰሃል›› አለው ኤዲን፡፡
ኤዲ የካፒቴኑን ትዕዛዝ ከምንም አልቆጠረውም፡፡ ለተወሰነ ጊዜም
ጣልቃ እንዳይገባ ነው ፍላጎቱ፡
ቤከር ኤዲን ‹‹ና አሁኑኑ›› ሲል ጮኸ፡፡
ባለመስመር ሙሉ ልብስ የለበሰው የወሮበሎቹ መሪ ዘሎ ወደ አይሮፕላኑ ለመግባት ሲዘጋጅ ከኋላው የቆመው ቤከር ጃኬቱን ሲጎትት ወሮበላው ሽጉጡን ለመምዘዝ ኪሱን ደባበሰ፡፡
ኤዲ ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች መካከል አንዱ ነሽጦት ወሮበሎቹን እተናነቃለሁ ቢል ሊሞት ይችላል ብሎ ነው የሚፈራው፡፡
ወዳጁ ስቲቭ አፕልባይ የባህር ኃይል ጀልባ ይዞ እየመጣ መሆኑን
ቢነግራቸው በወደደ፤ ነገር ግን አይሮፕላኑ ላይ ያለው የወሮበሎቹ ግብረ
አበር ሰዎቹን ሊያስጠነቅቅ ይችላል ብሎ ገምቷል፡ ወደ ቤከር ዞር አለና
‹ካፒቴን ዞር በል ከዚህ እነዚህ ሰዎች መሳሪያ ይዘዋል››
ቤከር ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡ ወሮበላውን አየና ወደ ኋላ አፈገፈገ፡
ሰውየው ቤከር ወደ ኋላ መመለሱን ሲያውቅ ሽጉጡን መልሶ ኪሱ
ከተተው፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋር አታካራ ብገጥም ተሳፋሪዎቹ ሊሞቱ
ይችላሉ› ሲል አሰበ፡፡
የወሮበሎቹ መሪ ኤዲ የያዘለትን ገመድ ይዞ ወደ አይሮፕላኑ መግቢያ
ዘለለ፤ ኤዲም ሰውየው እንዳይወድቅ ያዝ አደረገው፡፡
‹‹አንተ ነህ ኤዲ?›› ሲል ጠየቀ፡፡
ኤዲ ይህን ድምጽ ወዲያው ለየው። በስልክ የሰማው ድምጽ ነው፡፡
‹‹ቪንቺኒ›› ብሎ ጠበቅ አድርጎ ተናገረ የስድብ ያህል፡ በኋላ ግን በአባባሉ
ተፀፀተ፡፡ ይህ ሰው ሚስቱን በማዳን በኩል እንዲተባበረው በእጅጉ
ይፈልጋል፡፡ ‹‹ሁሉ ነገር እንዳሰብነው ያለ እንከን እንዲፈፀም መተባበር
አለብን››
ቪንቺኒ ፊቱን እንዳኮሳተረ ‹‹እሺ ነገር ግን ሌላ ነገር አደርጋለሁ ብለህ
የምትሞክር ከሆነ ህይወትህን ታጣለህ›› አለ አነጋገሩ ቀጥተኛ ሲሆን
ድምጹም አስፈሪ ነው፡፡
‹‹ጓደኞችህን እስካስገባ ድረስ ውስጥ ቆየኝ›› አለው ኤዲ ቪንቺኒን፡፡
‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡

👍16❤1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ አርባ ሁለት (42)
ልክ እወደቡ ደርሳ የካሜራ መትከያውን ባለሶስት እግር መቋሚያ እንዳስተካከለች አንድ ሰዉ ቀጥ ብሎ ወደ እሷ ሲመጣ ታያት ። አማመዱ ወደሷ መሆኑ አጠያየቃት፡፡ ማን እንደሆ አወቀች፤ ቆይታ ።
ማይክል !ጣጣ ነው ፤አለች በሀሳቧ።
«አንድ ነገር ልነግርሽ ነው የመጣሁት» አለ እፊቷ ተገትሮ። «መስማት አልፈልግም» አለችው ቀና ሳትል። «እሱ እንኳ ያስቸግራል ። ምክንያቱም ፈቀድሽም ቀረ እነግርሻለሁ ። እና ብታስቢበት ይሻላል ስለግል ሕይወቴ የሆነ ያልሆነ ነገር እየጎረጎርሽ ሀሳብ የመስጠት መብት የለሽም ። እንዲህ ያለህ ሰው ነህ እንዲህ አይነት ፍጡር ነህ ልትይኝ አትችይም። አታውቂኝም ፤ አላውቅሽም ። ይህን ለማለት ምን መብት አለሽ !?» አለ።
ትናንት የተናገረችው ቃል ሌሊቱን ሙሉ እንደጥርስ ህመም ሲጠዘጥዘው ነው ያደረው። «ስለኔ ስነምግባር አስተያየትም ሆነ ፍርድ ለመስጠት የሾመሽ ማን ይሆን ? የኛ ዳኛ ምን መብትስ አለሽ» ጦፈ ። «ምንም» አለች ረጋ እንዳለች ። « ግን ደግሞ የማየው ነገር ደስ አላለኝም » ይህን ስትል ቀና ብላ አላየችውም ። የካሜራ ሌንስ ትቀይር ነበር ። «ያየሽው ነገር ምን ይሆን እባክሽ ?»
«ዛጎል ። ቀንዳውጣው የሞተ በድን ቅርፊት ። ልቡ ፍቅርን የተራቆተ፤ ስራ ስራ ብቻ የሚል ሰው። ስለማንም ደንታ የሌለው ማንንም የማይወድ፤ ምንም የማይሰጥ ፤ ምንም ያልሆነ ባዶ ሰዉ ይህንን ነው ያየሁት ። »
«አንች ውሻ |! አንች ማን ሆነሽ፤ ምን አውቀሽ ነው ደሞ ስለኔ የውስጥ ስሜት ይህን ያህል እምታወሪው ! ለመሆኑ አንችን ሁሉን አዋቂ ያደረገሽ ማነው በይ!» አለ። ዝም ብላ ካሜራዋን አዙራ የአሸዋ ኮረብታ ላይ አነጣጠረች። «አንችን እኮ ነው እማናግረው! ሰሚኝ !» አለ ካሜራዋን ሊይዝ እየሞከረ ። ቀደም ብላ ፊት ለፊቱ ቆመችና አፈጠጠችበት። ከዚያም እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ «ለምን አትተወኝም ። ለምን እሰው ኑሮ ውስጥ ገብተህ የሰው ሰላም ትነሳለህ ?» አለችው ። «ማ ? እኔ ? እኔ አንች ኑሮ ውስጥ አልገባሁም ። እኔ ጥቂት ፎቶግራፎችን መግዛት ብቻ ነው እምፈልገው በቃ ። በተረፈ ያንቺን ኑሮም ፤ያንችን አስተያዬት አልሻም ። ፎቶግራፍ ! በቃ!» በንዴት መንቀጥቀጥ ጀመረ። እሷ ግን አልመለሰችለትም ። እንደቆመ ትታው ሄደች። አንድ ብርድ ልብስ ላይ የተቀመጠ የወረቀት መያዣ ቦርሳ አነሳች ፤ ዚፑን ከፍታ ከውስጡ አንድ የታጠበ ፎቶግራፍ አወጣች እና ፎቶ ግራፍ ነው የምትፈልገው አደል? ይኽውልህ ። ይኽን ወስደህ የፈለገህን ነገር አድርገው ። እኔን ግን ተወት አርገኝ። እሺ» ብላ ሰጠችው ። ተቀበላት ። አላነጋገራትም ። ሄደ ዞራ አላየችውም። ስራዋን ቀጠለች። ስራ ፤ ስራ ፤ሰራ። ጸሐይ ብርሃኗን ስትነሳ ካሜራው መስራት ሲሳነው ስራዋን አቆመች።
እቤቷ እንደደረሰች እንቁላል ጠብሳ በልታ ቡና አፍልታ ጠጣች በኋላ ወደ ፎቶግራፍ ማጠቢያ ክፍሏ ገባች። ያንለት የተኛችው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ሲሆን ነበር ። ጧት በሁለት ሰዓት ለመነሳት ወስና ባለዶወል ሰዓቷን አስተካክላ ተኛች። ባለችው ሰዓት ነቃች። ደወሉ ቀሰቀሳት ። ሰውነቷን ታጥባ ፣ ልብሷን ለባብሳ፤ ቡናዋን እየጠጣች ጋዜጣዋን እንብባ ከቤቷ ስትወጣ ልክ ማታ ባቀደችው መሰረት ለሶስት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ይቀር ነበር ። ደረጃውን ስትወርድ ሁሉ የምታስበው ስለቀኑ ስራዋ ነበር። ፍሬድ ኋላ ኋላዋ ቱስ ቱስ እያለ እሷ እያሰበች ከቤት ወጡ፡፡ የውጪውን ደረጃ በመውረድ ላይ እንዳለች አንድ ደረጃ ሲቅራት ቀና ብላ ተመለከተች ። ከመንገድ ማዶ ማይክል ሂልያርድን ቆሞ አየችው። እጁን አውለበለበላት ። አጠገቡ ባለው የጭነት መኪና ላይ በትልቅ ሰሌዳ የተለጠፈ ስእል አየች ። ተመለከተችው ። ትናንት ጧት የሰጠችው ፎቶ ግራፍ ነበር ። ወስዶ በትልቁ ኦጉልቶ አሳጥቦ አንዳች በሚያህል ሰሌዳ ላይ ለጥፎ ይዞት መጥቷል ። ድንገት ሳቋ መጣ ። እደረጃው ላይ ቁጭ ብላ ትንከተከት ጀመር ። ፊቱ በፈገግታ በርቶ ሰውነቱ በደስታ ተሞልቶ ወደ ተቀመጠችበት መጣ፡። አጠገቧ ሲደርስ በፈገግታ እንደበራ በደስታ እንደተሞላ እደረጃው ላይ እጎኗ ተቀመጠ። «ቆንጆ ነው? ወደደሺው ?» ሲል ጠየቃት። «አንተ ግን የምትገርም ሰው ነህ!» አለችው ። «ልክ ብለሻል ። ግን እንዴት ነው? ደስ አይልም?» ሲል አሁንም ደግሞ ጠየቃት። ደስ ይላል ብትለው እንዴት አድርጎ ይደሰት። «እይው እስኪ፤ አሪፍ አሪፎቹን ፎቶግራፎች መርጠን ከፊሉን እንዲህ በትልቁ አሳጥበን እህክምና ማእከሉ አናት ላይ ብንሰቅላቸው ጉድ አይደለም ? » አላት ። ጉድስ ራስህ ነህ… ስትል አሰበች።፡ ደስ እንዳላት ሲያይ በጣም ደስ አለው ። ስለዚህም ነፃ ሆነ «አሁን እዚህ ምን ጎለተን? ተነሺና አንድ ቦታ ሄደን ቁርሳችንን እንብላ» አላት ።
ዛሬ ቆርጦ ተነስቷል ። እሺ ሳያስኛት ይች ቀን አታልፍም። ለዚህ ሲል ከሰዓት በፊት ያለውን ጊዜ በጠቅላላ ምንም ቀጠሮ አልያዘበትም ። እሷም ብትሆን ይህንን ውሳኔውን ከሁኔታው ተረድታለች። ውሣኔው ልቧን ነክቷታል ፤ አስደንቋታል ። በዚህም ላይ ጭቅጭቅ መፍጠሩን ስሜቷ አልተቀበለውም ። «እንሂድ» አላት ። «እምቢ ማለት ነበሪብኝ። ግን አልልህም» አለች፡፡ «ጥሩ ዘይደሻል ። አብረን እንሂድ?» ሲል ጠየቃት ። «በምን? በዚያ?» አለችው የጭነት መኪናውን እያሳየችው። ነገሩ አስቂኝ ሆነባት ። «ምናለበት ይሄዳል እኮ » አስተስማማች ።
አሳ አጥማጆች ወደሚመገቡት ሆቴል አመሩ ። መኪናውን እበሩ ላይ አቆሙት ። በዚያ አካባቢ የጭነት መኪና አዲስ አልነበረምና ማንም ጉዳዬ ብሎ አላያቸውም ። ገትረውት ወደቁርስ ገቡ። ማንም ያን ያህል ፎቶግራፍ አንስቶ ይወስዳል የሚል ፍርሀት አልነበረባቸውምና ጠባቂ አልፈለጉም ። ያንለት ቁርሱ ሳይቀር በሚያስገርም ሁኔታ ድንቅ ሆነላቸው። ቡናቸውን ጠጥተው እስኪጨርሱ ድረስ በመካከላቸፅ- ጭቅጭት አልተነሳም ። ያኔ… «አሁን ተስማማሽ አይደለም?» ሲል ጠየቀ ። ነገሩን በጥያቄ ያቅርበው እንጂ በፊቱ ላይ የሚታየው ፈገግታ ርግጠኛነትና ኩራት አረፍተ ነገሩን «አሸነፍኩሽ» የሚል ስሜት ስጥተውት ነበር ። «በፍጹም አልተስማማሁም። ሆኖም ደስ የሜል ቁርስ በላሁ ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩ» አለችው ። «ትንሽ ውለታ ሲውሉልኝ ውለታ አነሰ ብዬ በጥፊ የምመታ ሰው አደለሁም ። ሆኖም ያ ሙሉ መንገዴ አይደለም»
«ሙሉው ምንድ ነው? እስኪ ንገረኝ»
«አሃ! ስለኔ አንች መናገርሽን ፤ መፍረድሽን አቁመሽ እኔ ራሴ እንድናገር ፈቀድሽልኝ ማለት ነው?» ነገሩን እንደቀልድ ቢለውም በውስጡ ሽሙጥ ነበረበት ። «ባለፈው ቀን ያልሽው በመጠኑም ቢሆን እውነትነት አለው ። ለስራዬ ብዙ እጨነቃለሁ» አላት ። «ሌሳ የምታስብለት ምንም ነገር የለህም? ።»
«በእውነት ከሆነ ሌሳው ነገር ለኔ ይህን ያህልም አደለም። ምናልባትም ብዙዎቹ በኑሮ ተስተካክለዋል የምንላቸው ሰዎች ካለስራ ሌላ ሕይወት የላቸው ይሆናል ። ጊዜም ቦታም አይገኝ ?››

👍18🥰1
«ታዲያ ይኸ ጅልነት ነው። በጣም ትልቅ ጅልነት ። ስራህን ለማሳካት ኑሮህን መስዋእት ማድረግ የለብህም ። ካልካቸው ትልልቅ ሰዎች መካከል ደግሞ ኑሮንም እየኖሩ ስራቸውን በሚገባ የሚያካሂዱ ይኖራሉ»
«ካንቿ እንነሳ። ሁለቱንም አጣምረሽ ማድረግ ትችያለሽ ?»
«አሁን አልችልም ። ወደፊት ግን አይቀርም። ቻልኩም፤ቀረም ቢያንስ እንደሚቻል ግን አውቃለሁ»
«ምናልባትም እንዳልሺው ይሆን ይሆናል ። እኔም ዱሮ እንደማስበው አላስብ ይሆናል » ይህን ሲላት አዘነች። ልቧ ለሰለሰ
«ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ሕይወቴ እጅጉን ተለውጧል ። በፊት ያቀድኩት ነገር ሁሉ ከልቡናዬ ጠፍቷል፡፡ መልሼ ያን ለማሰብ ደግሞ አቅም የለኝም። አልሞክርም። በጭራሽ የሆነ ሆኖ አልተጎዳሁም ። መተኪያ የሚሆን መላ አግኝቻለሁ›› አለ፡፡ ለምሣሌ የኮተር ሂልያርድ ፕሬዚዳንት መሆንን የመሰለ ሲል በሀሳቡ ጨመረ ። ለመናገር ግን እፈረ ። «አሃ ገባኝ። አላገባህም ማለት ነው» አለች፡፡ «እንዲያውም ። ጊዜም የለኝ ፤ ፍላጎትም » አለ ። እንዲያ ነው? አለች በሀሳቧ። እንዲያ ከሆነ ባደጋ ተመካኝቶ የቀረው ጋብቻ እንኳን የቀረ ። «ኑሮን ተቆርጦ የደረቀ ቅጠል አደረግከው ኮ» አለች ። «ለጊዜው ለኔ እንዲያ ንው። አንችስ እንዴት ነው ?»
«እኔም አላገባሁም››
«ይገርምሻል ፤ እንዲያው የኔን የአኗኗር ዘዬ ታረካክሽዋለሽ እንጂ ያንችንም ሕይወት ከኔ በምንም ሁኔታ የተለዬ ሆኖ አላገኘሁትም ። እንደኔ በስራ የተጠመድሽ ነሽ ። እንደእኔ ብቸኛ ነሽ ። እንደ እኔ በግልሽ ትንሽ አለም ውስጥ ተቀብረሽ ነው የምትኖሪው፤ ያው ነሽ ። ታዲያ እንዲህ ሆነሽ ሳለ አጉል ፍርድ ትሰነዝሪብኛለሽ? ደግ ነገር አይመስለኝም» ይህን ሲናገር ድምፁ ለስላሳ ቢሆንም ወቀሳ ያዘለም ነበር ። ስለዚህም ተሰማት ። «ይቅርታ አድርግልኝ ። ምናልባትም ልክ አይደለሁም ይሆናል» እለች።
ይህን ብላ ቀና አለች እየችው ። ማይክል ነው ። የተሰበረው ማይክል ። የተሰበረች እሷ ። የተጣጡ ሁለት ። ያኔ ደስ እሚላት ማልቀስ ብትችል ፣ ብታነባ ፣ እሪ ብትል ነበር አየችው ። ተለያይተዋል ። መንገዳቸው ለየብቻ ሆኗል፡፡ በሕይወት እያለህ አልለይህም ፣ ደህና ሁን. . . አልለይህም… ቃል ኪዳናቸው ትዝ አላት ። ይህ ግን ፤ መለያየታቸውን ፣ መንገዳቸው ለየብቻ መሆኑን ማወቋ ግን ፣ ደህና ሁን እንደማለት ነው ። «ብሄድ ይሻላል መሰለኝ… ወደ ሥራ» አለች ሰዓቷን አየት አድርጋ ። «ወደ ይቻላል ተቃረብኩ ይሆን… ለድርጅታችን ትሠሪያለሽ ለሚለው ጥያቄዬ? »
«አይመስለኝም… አይቻልም» አለች ።
ይህን ሲሰማ ካሁን በኋላ የፈለገውን ቢያደርግ እሺ ሊያሰኛት እንደማይችል ገባው ። እስከዛሬ የለፋው ልፋት ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበ ። በጣም ጠንካራ የሆነች ሴት ናት ። ግን ደግሞ ወዷታል ። ሁሉን ነገር ትታ ሰው ስትሆን ፤ ስትሸነፍ ምን ዓይነት ልብ እንዳላት ሲያስብ ተደነቀ ። የልቧን ንጽሕና፤ ገርነትዋን ፤ ውስጡዋን ሲያይ ይህን ያህል ጊዜ ማንም ሰው መስጦት ስቦት የማያውቀውን ያህል እንዳቀረበችው ተገነዘበ ።»
«አንድ ቀን ራት አብረን እንድንበላ ብጠይቅሽ እሺ የምትይ ይመስልሻል ሜሪ ? ማለት እንዳሸነፍሽኝ ተረድቻለሁ ። ለማጽናናት ያህል እሺ አትይኝም?» አለ ። ፊቱ ላይ የነበረውን ነገር አይታ በለሆሳስ ሳቀች ። ከዚያም እጁን በአይዞህ አትዘን ማጽናናት መንገድ ቸብ ቸብ ካደረገችው በኋላ «እኔም ደስ ይለኛል ። ግን አሁን አይሆንም ። በቅርብ ከከተማ መውጣቴ አይቀርም» አለች፡፡ ምን ዓይነት የተገረመ ነገር ነው አሁንም አልቻለም ። ዙሪያ ገባውን መሸነፍ በመሸነፍ ሆነ ማለት ነው አሰበ ።
«ወዴት ነው ለመሄድ ያሰብሽው? »
«ወደ ምሥራቅ ልመለስ አስቤአለሁ ። ለጥቂት ቀን ለግል ጉዳዬ » ይህን የወሰነችው ድንገት ነበር ። ከማይክል ጋር እየተነጋገሩ ሳለ ። ከግማሽ ሰዓት ባፊት ። ቀድሞ ማድረግ እንደሚገባት አልወሰነችም ። አሁን ግን ወስናለች ። ፒተር እንዳላት ለማድረግ አስባለች ። ያለፈውን ቁስል መሸፋፈን ሳይሆን ገልጦ ምን ያህል እንዳመረቀዘ ፤ እንደተመረዘ ማዬት ። ፒተር ልክ ነው ባንድ በኩል ስትል ነበር ። አሁን ግን ልክ እንደነበረ በሚገባ አረጋግጣለች ። ገልጣ ማዳን አለባት ። ገልጣ አይታ ማከም ይገባታል ። እሱ ፒተር እንዳለው ። «በሚቀጥለው ጊዜ ሳንፍራንሲስኮ ስመጣ ስልክ እደውልልሻለሁ ወይም መጥቼ እጠይቅሻለሁ ። ያኔ ከዚህ የተሻለ ዕድል እንደሚገጥመኝ ተስፋ አደርጋለሁ » ምናልባት አለች በሐሳቧ ። ምናልባትም ያኔ የፒተር ግሬግስን ባለቤት ሆኜ ታገኘኝ ይሆናል ። ምናልባትም ያኔ ከበሸታዬ ተፈውሼ አልፈልግህ ይሆናል ።
ጸጥ ብለው መኪናው ወደቆመበት ሄዱ ፤ ጐን ለጐን ። ቤቷ በር ላይ አወረዳት ። ያኔም ሆነ እመንገድ ላይ ብዙ ንግግር አልተለዋወጡም ። ከመኪናው ስትወርድም ብዙ አልተናገረችም ። ቁርስ ስለጋበዛት አመሰገነችው ጨበጠችው ሄደች ። አለቀለት ተሸነፈ ። ይህን እያሰበ ወደ ቤቷ ስትሄድ አያት ። መጠን የሌለው ኀዘን ሲወድቅበት ፤ ልቡን ሲያስጨንቃት ተሰማው ። አንድ ልዩ የሆነ ፤ ካለው ነገር ሁሉ የላቀ ነገር እንዳጣ ፤ እንደጠፋበት ሆኖ ተሰማው ። ምን እንደሆነ ግን ፈጽሞ አላወቀውም ። የሥራ ውል? ተወዳጅ ሴት ወይስ ጥሩ ጓደኛ ? እንጃ ። አንድ ነገር ግን ከእጁ ሾልኮ ጠፍቶበታል ። በዚህ በረጅም ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ መጠንህ የማይባል ብቸኝነት ተጫነው ። መኪናውን አስነስቶ ወደ ሆቴሉ ፈረጠጠ ።
ይቀጥላል......

👍41❤3🔥2
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡
ኤዲም ካፒቴን እንደሚልህ አድርግ እባክህ እነዚህ ሰዎች ቀልድ አያውቁም›› አለ ቤከር ባለበት ቆመና እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡
ጆ የተባለው ወሮበላ ‹‹እዚህ ውስጥ ብወድቅ መዋኘት አልችልም›› አለ
ከጀልባው ወደ አይሮፕላኑ መዝለል ፈርቶ፡፡
‹‹መዋኘት አያስፈልግም›› አለ ኤዲ እጁን ዘረጋለት፡፡
ጆም እንደምንም ዘለለና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡
ከእሱ በፊት ሁለት ሰዎች በደህና መዝለላቸውን አይቶ ትንሹ ልጅ ኮራ ብሎ ዘለለ፤ ነገር ግን ሲዘል ሚዛኑን ሳተና ወደኋላው ሊወድቅ ሲል ኤዲ የልጁን ቀበቶ ይዞ አዳነው ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡፡
አሁን የካሮል አን ተራ ደረሰ ለመዝለል ፈርታ የኤዲን አይን አይን ታያለች በተፈጥሮዋ ፈሪ ሆና ሳይሆን ከእሷ በፊት ትንሹ ልጅ ተንገዳግዶ ባህር ውስጥ ሊገባ ሲል ስላየች ነው የፈራችው፡፡ ኤዲም ፈገግ አለና
‹‹እንደነሱ ዝለይ ማርዬ›› አለ ‹‹አይዞሽ ውሃ ውስጥ አትወድቂም::››
ኤዲ በፍርሃት ልቡ እየደለቀ በጉጉት ጠበቀ ሚስቱ እስክትዘል፡፡ ካሮል
አን መዝለል መቻሏን ተጠራጠረች፡፡ ‹‹ተዘጋጂና ዝለይ!›› አላት እሱም የእሷ
ፍርሃት ተጋብቶበት፡፡
ካሮል አን ጥርሷን ነክሳ እንደ ምንም ዘለለች፤ ነገር ግን ግማሽ አካሏ ባህሩ ውስጥ ሆኖ ገመዱን ለመያዝ ተፍጨረጨረች፤ ‹‹ገመዱን አጥብቀሽ
ያዥ አይዞሽ›› አለ ወደ ባህሩ የምትወድቅ ከሆነ ለመዝለል ተዘጋጅቶ
ኤዲ ተንበረከከና እጇን ለመያዝ እጁን ሰደደ፤ ሆኖም ሚዛኑን ሳተና ወደ
ባህሩ ሲወድቅ እጇን መያዝ አልቻለም፤ የባህሩ ሞገድ ጎትቶ ውሃ ውስጥ
ሲያስቀራት በተስፋ መቁረጥ ጮኸች፡፡
ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ወደ ኤዲ እየዋኘች ተጠጋች፤ ኤዲ ጥርሷ
ሊንገጫገጭ አየ፧ እንደ ምንም ብሎ እግሯን ያዘ፤ ሆኖም የባህሩ ሞገድ
ሃይለኛ በመሆኑ ከእጁ አፈተለከችና እንደገና ባህሩ ላይ ወደቀች፤ ካሮል አን
እየሰመጠች ነው እሱም እጁን ሰደደና ወገቧን ያዘ፡፡
‹‹አይዞሽ የኔ ማር ይዤሻለሁ›› አለና እንደምንም ተሸክሞ ወደ
አይሮፕላኑ አስገባት፡፡ ካሮል አን ባሏ እቅፍ ውስጥ ገብታ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ እምባ ቢተናነቀውም እንደምንም ዋጥ አደረገው፡፡የምትንቀጠቀጠውን
ሚስቱን ለማረጋጋት አጥብቆ ደረቱ ላይ ለጠፋት
‹‹ደህና ነሽ የኔ ማር? እነዚህ ሰዎች አንገላቱሽ?›› ሲል ጠየቃት
‹‹ደህና ነኝ›› አለች ጥርሷ እየተንገጫገጨ፡፡
የካፒቴኑን ዓይን ለማየት ፈርቶ እየሰረቀ ያየዋል፡፡ ቤከር ወደ ካሮል
አን አማተረና
‹‹ያደረግኸው ሁሉ ለምን እንደሆነ አሁን እየገባኝ መጣ›› አለ፡፡
‹‹ይበቃል የምንሰራው ስራ አለን›› አለ ቪንቺኒም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን ለቀቃትና ‹‹እሺ ወደምትፈልጉት ሰው እወስዳችኋለሁ››
‹‹እሺ›› አለ የወሮበሎቹ መሪ፡
‹‹ተከተሉኝ›› አላቸውና ወደ ውስጥ ገቡ፡ ሰራተኞቹ ምንም ነገር ለማድረግ እንዳይሞክሩ ኤዲ አስጠነቀቃቸው:
‹‹ሁላችሁም አደብ ግዙ፡፡ እነዚህ ሰዎች አድርጉ የሚሏችሁን ማድረግ
ብቻ ነው ያለባችሁ አለበለዚያ በጥይት ከመግደል ወደ ኋላ የሚሉ ሰዎች አይደሉም፡ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም፡ ካፒቴኑም ይህንኑ ነው የሚላችሁ አለ ኤዲ፡
‹‹ትክክል ነው›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ጎበዝ! እነዚህ ሰዎች መሳሪያ የያዙ ናቸው፤ ብትወራጩ በጥይት ነው የሚሏችሁ ››
ኤዲ ወደ ቪንቺኒ ዞረና ‹‹እንሂድ እንግዲህ፤ ካፒቴን ተሳፋሪዎቹን ማረጋጋት ይኖርብሃል›› አለ፡፡
ቪንቺኒ በኤዲ አባባል መስማማቱን በራሱ ንቅናቄ አሳየ፡
‹‹ካሮል አን ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር ሁኚ፧ እሺ›› አላት፡፡
ኤዲ ሚስቱ ከወሮበሎቹ ጥይት መራቋን ወዶታል፡ በተጨማሪም ባሏ
ለምን እነዚህን ሰዎች ሊተባበር እንደወሰነ ለተሳፋሪዎቹ ታስረዳለታለች፡
ኤዲ ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ጠመንጃህን ከተሳፋሪዎች ብታርቅልኝ፧ ይፈራሉ››
‹‹ተነፋ!›› አለ ቪንቺኒ ‹‹እንሂድ›› ሲል አዘዘ ጓደኞቹን፡ ኤዲ ትከሻውን
በንዴት ነቀነቀ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታቸው ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ሁለቱ አስተናጋጆች ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
ኤዲ አይሮፕላኑ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያይ መብል ክፍሉ ትርምስምስ
ብሏል፡፡ ወለሉ በሸክላ እና በብርጭቆ ስብርባሪ ተሸፍኗል። ምግብ ተበልቶ
ስላለቀና ተሳፋሪዎች እየጠጡ ስለሆነ የተደፋፋ ነገር አይታይም፡:
ተሳፋሪዎቹ የቪንቺኒን ሽጉጥ ሲያዩ በፍርሃት ድምጻቸውን አጠፉ፡፡ ካፒቴን
ቤከር ወደ ፊት መጣና ‹‹ክቡራንና ክቡራት ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡ ከመቀመጫችሁ እንዳትነሱ፡ አሁን ያለው ችግር ከተወሰነ
ደቂቃ በኋላ መፍትሄ ያገኛል›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድና ፍራንኪ ጎርዲኖ አብረው ቁጭ ብለዋል አሁን ነፍሰ
ገዳይ እንዲያመልጥ ላደርግ ነው አለ ኤዲ ለራሱ፡ ወደ ጎርዲኖም ጣቱን እየጠቆመ ‹‹ያውልህ ሰውዬህ ውሰደው›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድ ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹ይሄ የኤፍ ቢ አይ መርማሪ ቶሚ ማክ አርድል ነው›› አለ ‹‹ፍራንኪ ጎርዲኖ ትላንት በመርከብ ኒውዮርክ ደርሶ ወህኒ ገብቷል››
‹‹የአምላክ ያለህ!›› ሲል ኤዲ በግርምት ጮኸ፡፡ ይህን ሁሉ እኩይ ተግባር ሲፈጽም የነበረው ለአስመሳይ ሰው ነው?!
‹‹እኛ ከፍራንኪ ጉዳይ የለንም፡፡ ጀርመናዊው ሳይንቲስት የታለ?›› አለ ቬኒቺኒ
ኤዲ ተገርሞ ቪንቺኒ ላይ አፈጠጠ፡፡ ጎርዲኖን አይፈልጉትም፡፡ ታዲያ
ማንን ነው የሚፈልጉት?ተ
የቶም ሉተር ድምፅ ተሰማ ‹‹እዚህ ነው ያለው፤ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው›› አለ ሉተር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን እየደገነ፡፡ተ
ኤዲ የበለጠ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ የፓትሪያርካ ማፊያ ቡድን ለምንድን ነው ካርል ሃርትማንን ማገት የፈለገው?› ‹‹ሳይንቲስቱን ለምንድን ነው የምትፈልጉት?› ሲል ጠየቀ፡፡
ቀበል አድርጎ ‹‹ተራ ሳይንቲስት እንዳይመስልህ የኒኩሊየር ፊዚስት
ነው›› አለ ሉተር፡
‹‹እናንተ ናዚ ናችሁ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡
‹‹አይደለንም፧ እኛ ዲሞክራቶች ነን፡፡ እነሱ ሳይንቲስቱን አግተን
እንድንሰጣቸው ስራ አዘውን ነው፡ ረብጣ ገንዘብ ይከፍሉናል›› አለና ቪንቺኒ
ተንከተከተ፡
ሉተርም ‹‹እኔ ዲሞክራት አይደለሁም፡፡ የጀርመን አሜሪካን ትብብር
ማህበር አባል ነኝ፡፡ ይህ ማህበር በናዚ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ
የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ሂትለር ራሱ ነው ከአገር አምልጦ የወጣውን
ሳይንቲስት አፍኜ ወደ ጀርመን እንዳመጣው ያዘዘኝ›› አለ፡፡ ሉተር ይህን
ሲናገር በኩራት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከፍዬ የማሰራቸው እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዶክተር ፕሮፌሰር ሃርትማንን ወደ ጀርመን መልሼ እወስደዋለሁ፡
ሳይንቲስቱ እዚያ በጣም ይፈለጋል›› አለ፡
ኤዲ ከሃርትማን ጋር ዓይን ላይን ግጥም አለ፡፡ ሰውዬው ፍርሃት
ጨምድዷቸዋል፡ ኤዲ ወዲያው ፀፀት ገባው፡፡ ሳይንቲስቱ ወደ ጀርመን
ሊመለሱ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የኤዲ ጥፋት ነው፡፡
‹‹ምን ላድርግ ባለቤቴን ስላገቱብኝ ነው የተባበርኳቸው›› አለ፡፡
የሃርትማን አስተያየት ተለወጠ ‹‹ይገባኛል›› አሉ ሳይንቲስቱ ‹‹እንደዚህ
አይነት ክህደቶችን ጀርመን ውስጥ ለምደናቸዋል፡ አንዱን ለማዳን ስትል
ሌላውን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡ ምንም ምርጫ አልነበረህም፡፡ በዚህ ራስህን አትውቀስ›› አሉት፡፡

👍12
ኤዲ ሳይንቲስቱ በዚህ ወቅት ሊያጽናኑት በመሞከራቸው ተገርሟል፡
ኤዲ ወደ ኦሊስ ፊልድ ዞሮ ‹‹ለምንድነው አስመሳይ ሰው አይሮፕላን ውስጥ ያሳፈራችሁት?››
‹‹ጎርዲኖ ለፖሊስ መረጃ እንዳይሰጥ ሊገድሉት እንደሆነ መረጃ ደረሰን፡፡ አሜሪካ እንደደረሰ ይመቱታል፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን
እንደሚሄድ የሀሰት መረጃ ለማፊያዎቹ አቀበልናቸውና እሱን አስቀድመን
በመርከብ ላክነው፡፡ ጎርዲኖ እስር ቤት መግባቱን የማፊያ ቡድኑ ሲሰማ
መሸወዱን ያውቃል››
‹ለምንድን ነው ለካርል ሃርትማን ጥበቃ ያላደረጋችሁላቸው?,,
እሳቸው በዚህ አይሮፕላን ላይ እንደሚሳፈሩ አናውቅም፡፡ የነገረን
ሰው የለም፡፡››
ጆ የሚባለው ወሮበላ በአንድ እጁ ሽጉጡን በሌላ እጁ የሻምፓኝ ጠርሙስ ይዞ ‹‹እዚህ ያሉት ተሳፋሪዎች በፍርሃት ረጭ ብለዋል፡ ስለዚህ
ትንሹ ልጅ እነሱን መቆጣጠር ይችላል›› አለው ቪንቺኒን፡፡
ቪንቺኒም ‹‹የታለ የባህር ጠላቂው መርከብ?›› ሲል ሉተርን ጠየቀው፡
‹‹በጥቂት ጊዜ ውስጥ እዚህ ይደርሳል›› አለ ሉተር፡
‹‹በል እንግዲህ ሉተር ስራችንን ጨርሰናል ገንዘቡን ስጠን›› አለ ቪንቺኒ፡፡
ሉተር ሳምሶናይት ቦርሳ አወጣና ለቪንቺኒ አቀበለው: ቪንቺኒ
ቦርሳውን ሲከፍተው ረብጣ ገንዘብ አለበት፡፡
‹‹አንድ መቶ ሺህ ዶላር ነው›› አለው ሉተር፡፡
‹‹እስቲ ቼክ ላድርግ›› አለና ቪንቺኒ ሽጉጡን አስቀምጦ ቦርሳውን ጉልበቱ ላይ አኖረና ገንዘቡን መቁጠር ጀመረ፡፡ ሉተርም ሲቆጥር አይቶ
‹‹ይሄን ሁሉ ለመቁጠር ብዙ ሰዓት ይወስድብሃል›› አለው
ሁሉም ሰው ቪንቺኒን ገንዘቡን ሲቆጥር አፍጦ ያየዋል፡፡ ጆ ተዋናይዋን
ሉሉ ቤልን አወቃትና ‹‹አንቺ የፊልም ተዋናይ አይደለሽም?›› ሲል
ጠየቃት፡፡ ሉሉ ፊቷን አዞረች፡፡ ጆ ከጠርሙሱ ላይ መጠጡን ተጎነጨና
ዳያና ላቭሴይን ‹‹ጠጪ›› ብሎ ጠርሙሱን አቀረበላት፡፡ እሷ በጥላቻ ፈንጠር አለች፡፡ ‹‹አዎ ይሄ ያሰክርሻል›› ብሎ ቀሚሷ ላይ መጠጡን ሲደፋው ዳያና ጮኸችና እጁን ገፋ አደረገች፡፡ በመጠጥ የራሰው ቀሚሷ ሰውነቷ ላይ
ተጣብቆ ገላዋን በግልጽ ያሳያል፡፡
እንዲህ አይነት ነገር ጠብ ሊያጭር መቻሉን ኤዲ ተገነዘበና ‹‹ተው››
ሲል ተቆጣ፡፡ ወሮበላው የኤዲ ቁጣ ምንም አልመሰለውም፡፡ ጠርሙሱን
ጣለና ጡቷን ያዝ ሲያደርገው ዳያና ጮኸች፡፡
ወዳጇ ማርክ ‹‹ተዋት አንተ ወንበዴ!›› ሲል ተሳደበ በመቀመጫ ቀበቶው ታስሮ እንደተቀመጠ፡ ወሮበላው ታዲያ ቀልጠፍ አለና ማርክን በሽጉጡ አፉን ሲለው ደሙ ተንፎለፎለ፡፡
ኤዲም ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ተው በላቸው›› ሲል ለመነው፡፡
‹‹እንደዚህ ያለች ሴት ከዚህ ቀደም ጡቷን አልተዳሰሰች ከሆነ የመዳበሻ ጊዜዋ አሁን ነው›› አለ ቪንቺኒ፡፡
ጆ በዳያና ቀሚስ ስር እጁን ሲሰድ እጁን ለማስጣል ታገለች፡፡ ነገር ግን
እሷም ወንበሯ ላይ በመቀመጫ ቀበቶ ታስራ ስለነበር እጁን ማስጣል
አልቻለችም::
ማርክ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈታና ሲነሳ ሰውዬው እንደገና አይኑን
መታው፡፡ ቀጠለና ሆዱንና ፊቱን በሽጉጡ እጀታ እየደጋገመ ሲመታው
ማርክም በሚፈሰው ደም ዓይኑ ስለተጋረደ ማየት አቃተው፡፡ ሴቶቹ
ይጮሃሉ፡
ኤዲ የደረሰው ሁኔታ አስደንግጦታል፡ ምንም ደም ሳይፈስ የእገታው
ድራማ እንዲጠናቀቅ ነው የሚፈልገው፡፡ ከዚህ በላይ ግን መታገስ አልቻለም: ጆ እንደገና ማርክን ሊመታ ሲል ኤዲ ህይወቱን ሸጦ
ወሮበላውን እጁን ለቀም አድርጎ ያዘው፡፡
ጆ ራሱን ለማስለቀቅና ሽጉጡን ኤዲ ላይ ለመደገን ቢሞክርም ኤዲ አጥብቆ እጁን ስለያዘው መፈናፈን አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ ጆ የሽጉጡን ምላጭ ሳበው የጥይቱ ጨኸት ጆሮ ይሰነጥቃል፡ ነገር ግን ሽጉጡ የያዘውን
የጆን እጅ ታግሎ ወደ ታች ስለያዘው የወጣው ጥይት ወለሉን በሳው የመጀመሪያ ጥይት ሲተኮስ ሁኔታው ከእጅ እየወጣ መሆኑ ኤዲ
ታወቀው፡፡ እዚህ ላይ ካልቆመ ደም መፋሰስ ይከተላል በመጨረሻም ቪንቺኒ ጣልቃ መግባት ግድ ሆነበትና ‹‹ጆ ይበቃሃል
አቁም!›› ሲል ጮኸ፡
ጆ ትግሉን ሲያቆም ኤዲም ለቀቀው፡
ጆ በጥላቻ ኤዲን አየው ነገር ግን ምንም አላለም፡
ቪንቺኒም ‹‹መሄድ እንችላለን ገንዘቡን ተቀብለናል›› አለ፡፡
ኤዲ ተስፋው ለመለመ:፡ አሁን ከሄዱ ደም መፋሰስ አይኖርም› አለ
በሆዱ፡ቪንቺኒ ቀጠለና ‹‹ጆ ሴትዬዋን ከፈለካት አምጣት እኔም ልነፋት እፈልጋለሁ፡፡ ከኢንጂነሩ ሰናና ሚስት እሷ ትሻላለች›› አለና ተነሳ፡፡
ዳያና ጮኸች ‹‹እባካችሁ ተዉኝ!››
ጆ የዳያናን የመቀመጫ ቀበቶ ፈታና ፀጉሯን ጎትቶ አነሳት፡ ዳያና የአቅሟን ያህል ታገለች ማርክ ደሙን ከዓይኑ ላይ እየጠራረገ ለጠብ ሲነሳ ኤዲ አየና ‹‹ይገሉሃል›› አለው በለሆሳስ፡፡ ‹‹አይዞ ችግር አይኖርም፡››የባህር ኃይሉ መርከብ እየመጣ መሆኑን እንደሚደርስላቸው ሊነግረው ፈልጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቪንቺኒ ሊሰማ ይችላል ብሎ ተወው፡
ጆም ቀጠለና ማርክ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ዳያናን ‹‹አንቺን እንወስድሻለን፧ አለበለዚያ ወዳጅሽ ዓይን ላይ ጥይት እንለቅበታለን›› አለ ዳያና በድንጋጤ ቆመችና ማልቀስ ጀመረች፡
‹‹እኔ ከእናንተ ጋር እመጣለሁ፡፡ የባህር ጠላቂው መርከብ መምጣት ያስቸግረዋል››
አለ ሉተር
ቪንቺኒ ስለ ጠላቂ መርከብ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ምናልባትም ጠላቂው መርከብ ያልመጣው የስቲቭ አፕልባይን የጦር መርከብ አይቶ ሊሆን ይችላል፡ ስለዚህ ጀልባው ራቅ ብሎ እስኪሄድ ሊጠብቅ ይችላል፡
‹‹አንሂድ›› አለ ቪንቺኒ፡፡ ‹‹በመጀመሪያ እኔ እወጣለሁ፡፡ ቀጥሎ ኤዲ፡፡
በመጨረሻ ጆ ከቆንጆዋ ጋር ትወጣለህ፡፡››
ማርክ ኦልደር ከኤዲ እጅ ለማምለጥ ይታገላል፡፡ ቪንቺኒም ቀጠለና
ሌላውን መርማሪ ‹‹ይህን ሰው አደብ እንዲገዛ
ኦሊስ ፊልድንና ታደርጉታላችሁ ወይስ ጆ በጥይት ይበለው?›› ሲል ጠየቀ፡፡ እነሱም ማርክን
እንዳይንቀሳቀስ አድርገው አጥብቀው ያዙት
ኤዲ ቪንቺኒን ተከትሎ ሲሄድ ሚስተር መምበሪ ሽጉጡን መዞ
‹‹ቁም!›› አለና ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡ ‹‹ወሮበላ ሁሉ ጸጥ በይ!
አለበለዚያ አለቃሽን በጥይት እደፋዋለሁ›› አለ፡ ቪንቺኒም ይህን ሲያይ
ደንግጦ ‹‹ሁላችሁም እንዳትንቀሳቀሱ!›› ሲል ጓደኞቹን አዘዘ፡፡ ነገር ግን
ትንሹ ልጅ የሚባለው ሰውዬ ፈንጠር አለና ሁለት ጊዜ ሲተኩስ መምበሪ
ወደቀ፡ ቪንቺኒም ትንሹ ላይ ጮኸ ‹‹አንተ የማትረባ! ሰውዬው ሊገለኝ
ይችል ነበር እኮ!›› አለው፡
‹‹አነጋገሩን አልሰማኸውም?›› ሲል ትንሹ ልጅ መለሰ ‹‹እንግሊዛዊ እኮ
ነው››
‹‹ታዲያ ቢሆንስ?›› ሲል ቪንቺኒ አምባረቀ፡፡
‹‹በርካታ ፊልም አይቻለሁ ነገር ግን በእንግሊዛዊ ጥይት የተመታ ሰው
የለም፡፡››
ኤዲ መምበሪ አጠገብ ተምበርክኮ ሲያይ ጥይቶቹ ደረቱን በስተው
ገብተዋል፡፡ ደሙ እየተንፎለፎለ ነው ‹‹ማነህ አንተ?›› ሲል ጠየቀው
መምበሪን፡፡
‹‹የእንግሊዝ ልዩ ፖሊስ አባል ነኝ›› አለ መምበሪ በደከመ ድምፅ፡፡‹‹ሳይንቲስቱን ሃርትማንን ለመጠበቅ ነው የተመደብኩት አልሆነልኝም››
አለና አይኑን ዘጋ፤ ትንፋሹም ቆመ:፡
ኤዲ አንድ ሰው ሳይሞት ወሮበሎቹ ከአይሮፕላኑ እንዲወጡ ፈልጎ
ነበር፡ ያሰበው ሊሳካለትም ትንሽ ነበር የቀረው፡፡ ነገር ግን ይሄው አንድ ፖሊስ ተገደለ፡ በትዕግስት ሊታለፍ ይችል ነበር፡፡ ለሰው ህይወት መጥፊያ
የሆነው ደግሞ እሱ ነው፡፡
የእነ ቪንቺኒ ጀልባ ነጂ ሲሮጥ መጣና ‹‹የሬዲዮ መልእክት መጥቷል››
አለው፡:
የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ለአስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ መገናኛ እንዳይጠቀም
ነግሬው አልነበረም?›› አለ ቪንቺኒ፡፡
‹ይሄ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡ አንድ የባህር ኃይል መርከብ እየመጣ ነው።

የኤዲ ልብ ሊቆም ምንም አልቀረውም፡፡ የወሮበላው ቡድን መልዕክት አስተላለፊ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቪንቺኒ ወጥመድ ውስጥ እንደወደቁ አውቋል፡
‹‹ከዳኸኝ›› አለ ቪንቺኒ ኤዲን፡፡ ‹‹ለዚህ ክህደትህ ደግሞ እገልሃለሁ››
ኤዲ የካፒቴኑን ዓይን ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ካፒቴኑ ጥረቱን እንደተረዳለትና ባደረገው አክብሮት እንዳለው ከካፒቴኑ አይን ላይ አነበበ፡
ቪንቺኒ ኤዲ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡
‹‹የቻልኩትን ያህል እንዳደረኩ ሁሉም አውቆልኛል፡ አሁን ብሞትም
አይቆጨኝም›› አለ ኤዲ፡
ሉተርም ለጠቀና ቪንቺኒን ‹‹አንድ ድምጽ አይሰማህም?›› ሲል
ጠየቀው፡
ሁሉም ጸጥ አለ፡፡ የሌላ አይሮፕላን ድምጽ ነው፡፡
ሉተር በመስኮቱ አሻግሮ ሲመለከት ባህር ላይ የሚያርፍ አይሮፕላን
መሆኑን አወቀ፡ አጠገባቸው ሊያርፍ ነው፡
ቪንቺኒ ሽጉጡን ወደ ታች አደረገ፤ ኤዲ ጉልበቱ ተብረከረከ፡፡ ‹‹ቢሆንስ
አናስኬድም ካሉን በጥይት ነው የምንረፈርፋቸው›› አለ ቪንቺኒ፡፡
‹‹ሌላ ነገር አይታይም›› አለ ሉተር በደስታ በዚህ አይሮፕላን ከባህር ሀይሉ መርከብ በላይ በረን እናመልጣለን›› አለ፡፡
ቪንቺኒ በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ጥሩ አስበሃል እንደዚያ ነው የምናደርገው›› አለ፡

👍10❤4
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ አርባ ሶስት (43)
ሜሪ ስልክ በመደወል ላይ ነበረች፡፡ ለፒተር ግሬግሰን ። «መቼ አልሺኝ? ዛሬ» አለ ፒተር ግሬግሰን ‹‹ውዴ ዛሬ ስብሰባ አለብኝ »
«እንዲያ ከሆነ ስብሰባውን እንደጨረስክ እፈልግሃለሁ ። በጣም እፈልግሃለሁ ። ነገ መሄዴ ነው»
«የት ? ወዴት ? ለስንት ጊዜ!»
«ስትመጣ እነግርሃለሁ ። ዛሬውኑ ና ። ማታ»
«እሺ...ይሁን ። እሺ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ። ግን ስብሰባውን… የቂል ሥራ መሰለኝ ። ሊዘገይ አይችልም»
«በፍጹም አይቻልም» አለች ። ሁለት ዓመት ሙሉ ቆይቷል ። ያን ያህል ጊዜ ማቆየቱም ራሱን የቻለ ቂልነት ነበር እብደት አለች በሐሳቧ ። «እሺ እንግዲህ እመጣለሁ » ዘጋ ። ወዲያው ወደ አየር መንገድ ቢሮ ደወለች ፤ቲኬት እንዲይዙላት ። ቀጥላም ወደ እንስሳት ሐኪም ደወለች ፤ ለፍሬድ ማቆያ እንዲያዘጋጅላት...
ያንለት ከሰዓት በኋላ ሜሪ ፌ አሊሰንን ለማነጋገር መደ መሥሪያ ቤቷ ሄደች ። ሜሪ ወደ ፌ መሥሪያ ቤት ከሄደች ወራት አልፈው ነበረና ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ስትገባ ምንም እንዳልተቀየረና እንደ ተለመደው ምቹ እንደሆነ ተገነዘበች። እምቹው ወንበር ላይ ተቀምጣ እግሯን ፊት ለፊት ዘርግታ ጣቶቿን እየተመለከተች ቀስ በቀስ ሐሳብ ውስጥ ገባች ። ሐሳቡ ጭልጥ አድርጐ ወሰዷት ነበርና ፌ ስትግባ አልሰማቻትም ። «እንቅልፍ እየታገለሽ ነው ወይስ እጸጥታ ቁዘማ ላይ ነሽ ?» የፌ አሊሰን ድምጽ ከሐሳቧ የመለሳት ሜሪ ፈገግ ብላ ፊት ለፊቷ በሚገኘው ወንበር ላይ የምትቀመጠው ፌን በጸጥታ ተመለከተቻት ። «እንቅልፍም ቁዘማም አይደለም። ዝም ብሎ ሐሳብ ነው» አለች ሜሪ ። ፌ «ደግ» በሚል አስተያየት እያየቻት ፈገግታዋን መለሰችላት ። ሜሪ ፌን ስታይ ደስ አላት ይህንንም፡፡ «ናፍቀሽኝ ኖሯል ባክሽ ፤ ሳይሽ በጣም ደስ አለኝ» ስትል ገለጸችላት ። «ድንቅ ነገር ሆነሻል ልበልሽ ወይስ ከዚያም ከዚያም ስለምትሰሚው ሰልችቶሻል ?» አለች ፌ አሊሰን በፈገግታ በርታ። በፌ አሊሰን ፊት ላይ ያየችው ደስታ ተጋባባትና ሜሪም መሳቅ ጀመረች ። ቀጥላም «ድንቅ ነሽ መባል ምኑ ይሰለቻል ብለሽ» ስትል ተናገረች ። ይህን ስትል ደስ አላት ። ለፌ አሊሰን ባይሆን ይህን እውነት እንኳ ለመናገር አስቸጋሪ እንደነበር ታውቀዋለች ። «ዛሬ ደርሼ ዱብ ስል ለምን መጣች ? የሚል ጥያቄ እንደሚመጣብሽ መቼም የታወቀ ነው» አለች ሜሪ አዳምሰን ። «ጥያቄው ብልጭ ብሎብኝ ነበር» ፌ ግምቷን አረጋገጠችላት ። ፊት ለፊት ፤ ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ ። ቦግ ድርግም ፈገግታ ተለዋወጡ ። ከዚያም ሜሪን ሐሳብ ጠለፋትና ወደ ቁዘማዋ ገባች ። ስለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። ከዚያም ሜሪ ድንገት ቀና ብላ በቦዛዛ ድምጽ ማይክልን አገኘሁት'ኮ» ስትል ተናገረች ። «ሊፈልግሽ መጣ ? »
«መልሱ አዎም ሊሆን ይችላል አልመጣምም ሊሆን ይችላል ። ነገሩንኳ የፈለገው ያገኘውም ሜሪ አዳምሰንን ነው» ቀጥላም ማይክል ለምን እንደፈለጋት ባጭሩ ነገረቻት ። «ሦስቱም ሰዎች ይህን ያህል ለመኑሽ »
«ሽንጣቸውን ገትረው»
«ደህና ምልክት ይመስላል ። በነገራችን ላይ. . . ከሦስቱ አንዱም እንኳ ማን መሆንሽን አላጤነም'!? »
«ሁለቱ ወንዶች አላወቁም ። ማሪዮን ግን አውቃለች ። እንዲያውም ማይክልን የላከችውም አውቃ ነው የሚል ግምት አለኝ» ለተወሰነ ጊዜ ጸጥ አሉ
‹‹ስትገናኙ ምን ስሜት ተሰማሽ ? »
«ከማን ጋር ? »
«ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር»
«አስቀያሚ ፤ አስቀያሚ ስሜት ነበረ የተሰማኝ ። ልክ እንዳየኋት ያደረሰችብኝ ስቃይ ሁሉ ፍንትው ብሎ ታየኝ ። ጦላኋት››
‹‹እሺ››
«ምን ልበልሽ ? ያላሰብኩት ነገር አልነበረም የናቴ ምትክ እንድትሆን የተመኘኋት ፤ ብትወደኝ ብዬ ያለምኩዋት የማይክል ሚስት ለመሆን እምበቃ መሆኔን እንድትቀበል የጓጓሁት ። ያ ሁሉ ነገር ትዝ አለኝ»
«አሁንም የማይክል ሚስት ለመሆን አትበቂም እምትል ይመስልሻል ?»
«ያሁኑን አላውቅም ። ብቻ እንጃ ። አየሽ ያንለት እንዳየኋት ብዙው ነገሯ ተለውጦአል ። እንደመሰለኝ የፈጸመችው በደል ከብዷታል ። የተጸጸተችበት ይመስለኛል ። ለኔ ሳይሆ ለልጅዋ ይሆናል ። እንደገመትኩት ከሆነ ማይክልም የሚመስለውን ያህል ደስተኛ አይደለም»
«ደስተኛ አሊመሆኑ ሲሰማሽ ልብሽ ምን አለ ?»
«ቀለል አለኛ»
ሆኖም ለማጋነን የፈለገችውን ያህል አላጋነነላችም ቀለል ማለቱ ። እንዲያውም በኀዘን የተሰበረ ድምጽ ነበረ። ለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። «ቆይቼ ሳስበው ግን» አለች ሜሪ ጸጥታውን እየገሰሰች ፤ «ቆይቼ ሳስበው ግን ፤ እሱን ደላው ከፋው ለኔ ያው እንደሆነ ገባኝ ። የኔና የሱ ነገር ያበቃ ነገር ነው ፌ። ዛሬ እሱም አያውቀኝ እኔም አላውቀው ። ሁለታችንም በጣም ተለውጠናል ። ማን መሆኔን ቢያውቅ ሥራዬ ብሎንኳ ሊያነጋግረኝ አይፈልግ ይሆናል ። እኔ ናንሲ ማክአሊስተር ያልሆንኩትን ያህል እሱም ማይክል ሂልያርድ አይደለም »
«ያን ያህል እንደተለወጠ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ!»
«አየሁታ ! መራራ ፤ ጥድፍድፍ ሰው ሆኗል ። ልቡ ቀዝቅዞ ሰብአዊ ስሜቱ ሞቷል ።እዚሀ ሁሉ ውስጥ ምን እንዳለ እንጃ…. ያየሁት ባህርይ ግን አብዛኛው አዲስ ነው»
«የፈለጉት የማጣት ፤ ተስፋ የመቁረጥ ፤ የጥልቅ ሀዘን ስሜት አይታይበትም ?››
«የለም አልታየኝም ። ይልቅ እኔን ስለመክዳቱ ፣ ስለመምጣቱስ ምን ይሰማሻል ? ልትይኝ የፈለግሽ መሰለኝ ። ቁም ነገሩ ይህ አይመስልሽም ?››
«እኔ እንጃ ። እኔ እንኳ ይህን አላሰብኩም። ግን እስካሁን ይህ አይነቱ ስሜት አለብሽ ማለት ነው? በትለይም እንደከዳሽ ነው እሁንም የቆጠርሽው ? »
‹‹እንደከዳኝ እንጂ እንደሌላ ልቆጥረው እችላለሁ ? » አለች ከረር በለ ድምፅ « ፌ፣ ማይክልን እንዴት መሰለሽ እምጠላው ! ››
ያን የህል እጠላዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ አሁንም ሀሳብሽ ሙሉ በሙሉ እሱ ላይ ነው ማለት ነው»
ናንሲ ይህ እውነት እንዳልሆነ ሽንጧን ገትራ ትከራከረች ። ምን ያህል እንደምትጠላው እምርራ ተናገረች ። ይህን እያደረገች ሳለችተም እንባዋ ተናነቃት ። አለቀሰች። ፌ አሊሰን ይህን ስታይ ነገሩን ለማለስለስ ፣ ሜሪን ላማፅናናት አልሞከረችም ። ይልቁንም የተነሳውን ነገር ፍርጥ ለማድረግ «ናንሲ ፤ ንገሪኝ ። ማይክልን ታፈቅሪዋለሽ ወይስ ፍቅርሽን ጨርሰሻል ? » ስትል ጠየቀቻች ። ናንሲ ብላ የጠራቻት አውቃ ነበር ። ናንሲ የፌ አሊሰንን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ፈጀባት ። ስትመልስም ጣራ ጣራውን እያየች ሲሆን ድምጺም ደከም ያለ ነበረ ። « ናንሲ አሁንም ታፈቅረው ይሁናል ። መቼም የናንሲ ርዝራዥ ከውሰጧ አይጠፋም ። እሷ ትወደው ይሆናል ። ሜሪ ግን ማይክልን አትወደውም ። ሜሪ ማለት እኔ ነኝ ፣ፌ ። አዲስ ህይወት፤ አዲስ ዓለም ያለኝ ሰው ነኝ ። ልወደው አልችልም ማይክልን!»
«ለምን እትችይም ?››
«ምክንያቱም እይወደኝም ። እርሉን መርሳት ኣለብኝ፣ ፌ ፈጽሞ መርሳት አለብኝ ።ይህን ወስኛለሁ ፣ አውቀዋለሁ ። ስለዚህ ይህን ላማክርሽ ፣፡ ስለማይክል ፍቅር አንስቼ ኣንገትሽ ስር ተወሽቄ ላለቅስ አይደለም የዛሬው አመጣጤ ። የተሰማኝን ነገር ላንድ ስው መንገር እንዳለብኝ በመግመት ነው። ለፒትር ብነግረው ጥሩ ነበር፡፡ ግን ይህን ለሱ መንገር ደግሞ የማይቻል መስሎ ታየኝ ። መንፈሱን ይረብሻዋል ብዬ ገመትኩ ። ለለዚህ ቀለል እንዲለኝ ላንቺ መንገር እንዳለብኝ ገባኝ ። ሙጣሁ»

👍16
‹‹መምጣትሽም ፤ መንገርሽም ጥሩ ነው። ደለ ብሎኛል ግን እልብ ውስጥ የሰረፀን ነገር እንዲህ በቀላሉ በቃኝ ፤ ተውኩት በማለት ብቻ ማራገፍ የሚቻል እይመስለኝም።. . . ያን ያህል ቀላል እይደለም»
«የተራገፈውኮ የዛሬ ሁለት አመት ነው ። እኔ ሙጭጭ ብዬ ነው እንጂ ። ሙጭጭ ማለቴን ደግሞ ስክድ ነበር ። አሁን ግን ግልፅ ሆኖልኛል ። እና….. ›› ንግግሯን ድንገት አቋረጠችና ቆና ብላ ተቀመጠች ። ከዚያም ፌ አሊሰንን እየተመለከተች…. «ነገ ለጉዳይ ወደ ቦስተን መሄዴ ነው» ስትል ተናገረች
«ለምን ጉዳይ ?»
«ሁሉን ነገር የማራገፍ ጉዳይ ። እኔና ማይክ ኣንድ ላይ በነበርንበት ጊዜ በጋራ የአደረግናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ ። እስከዛሬ ድረስ ማይክል ይመለሳል ፣ ያስበኛል ፤፣ ይፈልገኛል እያልኩ የተውኳቸውን ነገሮች ማለቴ ነው ። ለፍቅራችን ሀውልት እንዲሆኑ ብዬ ነበር የተውኳቸው ። አሁን በቃ ። ሄጄ አንድ ነገር ላደርግ ወስኛለሁ»
«እምትችይ ይመስልሻል ?»
«በሚገባ» አለች ፌ እሊሰንን እንኳ ቆራጥ መስሎ በተሰማት ድምፅ።
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
«የተራገፈውኮ የዛሬ ሁለት አመት ነው ። እኔ ሙጭጭ ብዬ ነው እንጂ ። ሙጭጭ ማለቴን ደግሞ ስክድ ነበር ። አሁን ግን ግልፅ ሆኖልኛል ። እና….. ›› ንግግሯን ድንገት አቋረጠችና ቆና ብላ ተቀመጠች ። ከዚያም ፌ አሊሰንን እየተመለከተች…. «ነገ ለጉዳይ ወደ ቦስተን መሄዴ ነው» ስትል ተናገረች
«ለምን ጉዳይ ?»
«ሁሉን ነገር የማራገፍ ጉዳይ ። እኔና ማይክ ኣንድ ላይ በነበርንበት ጊዜ በጋራ የአደረግናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ ። እስከዛሬ ድረስ ማይክል ይመለሳል ፣ ያስበኛል ፤፣ ይፈልገኛል እያልኩ የተውኳቸውን ነገሮች ማለቴ ነው ። ለፍቅራችን ሀውልት እንዲሆኑ ብዬ ነበር የተውኳቸው ። አሁን በቃ ። ሄጄ አንድ ነገር ላደርግ ወስኛለሁ»
«እምትችይ ይመስልሻል ?»
«በሚገባ» አለች ፌ እሊሰንን እንኳ ቆራጥ መስሎ በተሰማት ድምፅ።
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍14🥰1
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ ሶስት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ሰዓቱ ዘጠኝ ሰኣት ከ20 ሆኗል..ፕሮፌሰሩ ሳሎን ውስጥ ከወዲህ-ወዲያ እየተወራጨ ይሽከረከራል….ግማሽ መላጣው ፊቱን ጨምሮ በላብ ተዝፍቋል…በዚህ ቀዝቃና ነፋሻማ ለሊት እንዲህ አይነት ላብ ከከፍተኝ ንዳድ ካለበት በሽታ እንጂ ከጭንቀትና ንዴት የተነሳ ሆነ ቢባል ማን ያምናል፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ
‹‹እ..እስከአሁን አላገኛችሆትም….?››በቁጣ ድምፅ ጠየቀ
‹‹አላገኘሁትም….በሶስት የተለያየ መኪና በከተማዋ መንገዶች እያሰስናት ነው፡፡››
‹‹ግን ምን አይነት ዝርክርኮች ናችሁ በፈጣሪ….ፕሮፌሽናል ነን ..ምንጥቅርሴ እያላችሁ ያንን ሁሉ ብር ስትጠይቁ እኮ እንኳን አንድ እራሷን በቅጡ መከላከል የማትችል ሴት ይቅርና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን እኮ ከቤተመንግስት ገብታችሁ መግደል የምትችሉ ነው ምታስመስሉት››
ወቀሳውን መከላከል በሚያስችል ጠንከር ያለ ንግግር፡፡‹‹ፕሮፌሰር …ችሎታችንን በተመለከተ እስከምን ጥግ እደሚሄድ በዚህ ከተማ ከአንተ በላይ ምስክር ያለ አይመስለኝም…እንግዲህ በማንኛውም ስራ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ስሀትት ይፈጠራል››ሲል መለሰለት
‹‹ስለትናንት ጀብዶችሁ ማውራት ምን ይረባል…?ትሰማኛለህ..አንዳንድ ስራዎች ፍፅምናን ይጠይቃሉ….እንደእዚህ አይነት ስራዎች ለስህተት ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆን አለባቸው….ከስህተታቸው ጀርባ እኮ ታላቅ ውድቀትነው የሚያስከትሉት…ድምጥማጥን የሚያጠፋ ውርድት….ወለል ብሎ የተከፈተ እስርቤት…አሁን ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ አመልክታስ ከሆነ ማን አወቀ?››
‹‹አይ እሱን በአካባቢውና በቅርብ ርቀት ባሉ ፖሊስ ጣያዎች ሁሉ ዝር እንዳላለች በየጣቢያው ባሉ የእኛ ሰዎች አማካይነት አረጋግጠናል››
‹‹እሺ እሱም አንድ ነገር ነው….ለመሆኑ ያንን ኤሌያስ ተብዬውንስ ሄዳችሁ አረጋገጣችሁ?››
‹‹‹አዎ መልሰን ሰው ልከን ነበር….እንደውም ሰለእሱ ጉዳይ ልደውልልህ ስል ነው ቀድመህ የደወልክልኝ..››
‹‹ምን አዲስ ነገር አለ እንዴ?›› በስጋትና ጥርጣሬ ጠየቀ
‹‹እራሱን ስቶ ቤተሰቦቹ አግኝተውት ወደ ሆስፒታል ወስደውታል››
ጭንቅላቱን ያዘ‹‹ወደሆስፒታል? ያንተ ያለህ..አልቆልናል በለኛ››
‹‹አይ አላለቀልንም..ቤተሰቦቹም ይመስለኛል ምንም የጠረጠሩት ነገር ስለሌለ ወደእናንተው ሆስፒታል ነው የወሰድት››
‹እሱም አንድ ነገር ነው….ግን እስከአሁን ለሆነ ሰው የሆነ ነገር ብሎ ከሆነስ?››
‹‹አይመስለኝም….አሁን ሆሰፒታል ደውዬ ማጣራት እንደቻልኩት ሰውዬው እራሱን ስቷል፡፡ አሁን ቀዶ ጥገና ሊያደርጉለት ማደንዘዣ ሰጥተውታል…..እንደሰማሁት ከሆነ ቀዶ ጥገናው ቢያንስ ሶስት ሰአት ይፈጃል..ስለዚህ አስበን የሆነ ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ ያለን ይመስለኛ፡፡››
‹‹በቃ እሺ ..ደግሞ በየደረሳችሁበት አሻራ ምናምን እንዳታዝረከርኩ…ምን ላድርግ ይሄንንን ልንገራችሁ እንጂ..በል አሁን ከፈለክ ሳማይ ውጣ..ከልሆነም መቀመቅ ግባ..ይቺ ለሊት ከመንጋቷ በፊት ያቺን ሴት አግኝተህ አጥፋልኝ…፡፡ይህንን ካሳካችሁ ከተነጋገረንው እጥፍ ክፍያ ይጠብቃችሆል..ካልተሳካላችሁ ግን አብረን እንጠፋታለን፡፡የኤልያስን ጉዳይ ምን ማድረግ እንደምችል አስብበት እና ደውልላችሆለው››
‹‹እሺ ጌታዬ››
ስልኩን ዘጋውና ወደጠረጳዛው ሄደ፡፡ ውስኪ ያያዘውን ጠርሙስ አነሳ ፡፡አፉ ላይ ደቅኖ ገርገጭ ገርገጭ አድርጎ ጠጣለት….፡፡አዎ ስሜቱን ቢያስተካክልለት …አይኖቹን ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ገዝፎ ከሚታየው ከእጮኛው ፎቶ ላይ ሰካ…..ዶ/ር ሰጲራ…በጣም ነው የማፈቅርሽ..በጣም..››አለና በእጁ ይዞ የነበረው ጠርሙስ ልክ እንደ ዲስከስ ፉር አድርጎ ወረወረው ….ተምዘግዝጎ ከፎቶ በታች ካለ ግድግዳ ጋር ተላተመና ፍርክስስ ብሎ ተበተነ…በአቅራቢያው ያለ የሳሎን ወለል በጠርሙስ ስብርባሪ እና በውስኪ ፈሳሽ ፍንጥቅጣቂ ተሞላ
ድጋሚ ስልኩን ካስቀመጠበት ጠረጳዛ አነሳና ደወለ….ጥሪው ሰልችቶት ሊዘጋ ሲል ተነሳለት
‹‹ሄሎ ….ሼኪ ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል…››ጎርናና...ያልተሞሸ የለሊት ድምጽ
‹‹ጭራሽ ማን ልበል?››እሱ ለሊቱን ሙሉ ነፍስ ግቢ ነፍስውጪ መከራውን ያያል የሆስፒታሉ ትልቁ ባለድርሻ ሀገር ሰላም ብለው እንቅልፋቸውን መለጠጣቸው አበሳጭቶታል፡፡
‹‹እ..ፕሮፌሰር..ምነው በለሊት?
‹‹በለሊት…አስር ሰዓት እየተቃረበ እኮ ነው››
‹‹ለ85 ዓመት ሽማግሌ 10 ሰዓት ለሊት አይመስልህም?››
‹‹አይመስለኝም ..ለ85 ዓመት ሽማጊሌ ቢያንስ ሌላው ይቅር ለፀሎት በዚህን ሰዓት ንቁ መሆን የለበትም…?››
‹‹ፕሮፌሰር ምነው እንደምታስተምራቸው ተማሪዎች ወረድክብኝ..በሰላም ነው?››
‹‹ምን ሰላም አለ…ነገሮች ምስቅልቅላቸው ወጥቷል…››
‹‹ተረጋጋ የነገሮች መመሰቃቀል ሳይሆን አደገኛው የገዛ አይምሮህ መመሰቃቀል መሆኑን መቼም ለአንተ አልነግህም…መጀመሪያ የተመሰቃቀለውን አዕምሮህን አረጋጋው …ከዛ ሌላውን ለማስተካከል መንገዱ ይገለጽልሀል››
‹‹ወይ እርሶ …ነገሩ እንዲህ ቀላል አደረጉት እንዴ?››
‹‹ቀላል እዳልሆነማ በዚህ ሰዓት ደውለህ መአት ስታወራ መገመት ችያለሁ››
ያንን በቀደም ያማከርኮትን ነገር ዛሬ ማታ ለማድረግ ተንቀሳቅሰን ነበር.. አንደኛውን ማድረግ ብንሞክርም ሁለተኛው ግን እስከአሁን ማሳካት አልቻልንም….፡፡››
‹‹እስኪ ልገምት..ያንተዋን ነው አይደል ያለተሳካላችሁ?››
‹‹አዎ በምን አወቁ ?ኤልያስ ልክ እንደተመታ እራሱን ከመሳቱ በፊት ደውሎ አስጠንቅቋት ስለነበረ በለሊት ከቤቷ ወጥታ ተሰውራለች.እስከአሁን ልጆቹ እያሰሶት ቢሆንም እልተሳካላቸውም፡፡››
‹‹አይ.. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ…መጀመሪያ በዲፕሎማሲ እስከመጨረሻ ሞክር ብዬህ ነበር እኮ››
‹‹ያልሞከርኩ ይመስሎታል ..እምቢ አለች …ደጋሜ ሞከርኩ ለመንኳት አስፈራራዋት እምቢ አለች››
‹‹ምነው ወደፊት ይህችን ሀገር መምራት ፈልጋለሁ ትል የለ እንዴ? ታዲያ የገዛ ፍቅረኛህን ማሳማን ሳትችል ይሄንን ውስብስብና ሙልጭልጭ ህዝብ እንዴት አድርገህ ልታሳምን ነው?››
‹‹እርሶ ደግሞ…አሁን ለዚህ አይነት ተራባ አሁን ጊዜው ነው››
‹‹አይደለም አፉ በለኝ..ለመሆኑ ያኛውስ በትክክል ተጠናቋል..ማለት የኤልያስ?››
‹‹ያበሳጨኝ እሱ አይደል…እሱም ክፍኛ ቆስሎ እራሱን ቢስትም እስከአሁን አልሞተም›››
‹‹እና››
‹‹እናማ..ቤተሰቦቹ ወደ ሆስፒታል አምጥተውት ዶክተሮች ቀዶ ጥገና እያደረጉለት ነው››
‹‹አይ ፕሮፌሰር..ዛሬ ሁሉን ነገር አጨመላልቀኸዋል››
‹‹አውቃለው..እሱን እራሴ እንደምንም አስተካክለዋለሁ…..አሁን የደወልኩሎት አንድ ሰዓት ቢሮ እንድንገናኝ ነው….ለአቶ ንገሩት››
‹‹አንድ ሰዓት ቢሮ..ትቀልዳለህ….?ከባለደረባችን አንዱ በቤቱ ተተኩሶበት ለህይወቱ እያጣጣረ ሌላዋ ያለችበት ሳይታወቅ እኛ በግልጽ ሰው እያየን ቢሮ ለዛውም ባልተመደ ሰዓት…?››
‹‹እና የተለየ ሀሳብ አሎት?፡፡››
‹‹መልሼ እደውልልሀለው…እከዛው እራስህን አረጋጋ››
ስልኩን ዘጋና የኤልያስን ጉዳይ ከኮማው ከመንቃቱ በፊት እንዴት አድርጎ እልባት እንዲሚያበጅለት ማሰላሰል ጀመረ….
//////
ዶክተር ሰጵራ የገባችበትን ክፍል ዙሪያ ገባ በደንብ ካተመለከተች ቡኃላ አጠገቧ ያገኘችው የፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀመጠች….

👍27
አጋቾ በራፍን ዘግቶ ከዛው አካባቢ ሳይንቀሳቀስ ግድግዳውን ተደግፎ ቆሟል…..ሲጋራውን እና ላይተሩን ከቀኝ ኪሱ አወጣ… ለኮሰ…ጪሱን በጥልቀት ወደውስጡ እየሳበ ለሰከንዶች አቆይቶ ይለቀዋል..እየተትጎለጎለና ክብ እየሰራ አየሩን ይሞላዋል… በዛ ክብ ውስጥ አሻግሮ እሷን ይመለከታታል… ያለብዥታ..ያለምንም የአይን እርግብግብታ….፡፡‹.ይህቺ ሴት ከእሱ ሴት ጋር በጣም ትመሳሰላለች….››ሲል አሰበ በውስጡ፡፡ከከዳችውና እያፈቀራት ጥላው ከተሰደደችው ፍቅረኛው ጋር..የገዛ ጓደኛውን ተከትላ ከሄደችው ፍቅሩ ጋር.. ከውስጡ ሊቆጣጠረው የማይችለው ቁጣ ሲቀጣጠል ይታወቀዋል‹‹….አብዬት እቺ እሷ አደለችም..እራስህን ተቆጣጠር…እንዳትጎዳት፡፡››እራሱን ለመገሰፅ የሚቻለውን መጣር ጀመረ….እጁን ወደግራ ኪሱ ሰደደና የአረቄ ብልቃጥ ይዞ ወጣ.. አንደቀደቀው፡፡
ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ዶክተር በጣም ፈራችው..እያየችው ስሜቱ እየተቀያየረ ነው….ዛሬ በቃ ሙቺ ተብሎ ከእግዚያብሄር ትዕዛዝ ተላልፎብኛል እያለች በማሰላሰል ላይ ሳለች…በእጁ የቀረችውን የሲጋራ ትርኮሽ የጣውላ ወለል ላይ ጥሎ በእግሩ ጭፍልቅልቅ አደረጋትና ከአረቄው አንዴ ተጎንጭቶ ብልቃጦን በግራ እጁ እንዳንጠለጠለ ወደ እሷ ተጠጋ …፡፡በተቀመጠችበት መነሳት ባትችልም እራሷን ወደኃላ ለጥጣ ከፕላስቲክ ወንበሩ ጋር በመለጠፍ ለመሸሽ የማይሆን ሙከራ ሞከረች ፡፡ ጨምድዶ ያዛትና ወደ ላይ ጎትቶ አስነሳት….አረቄ የያዘ እጁ በወጋቧ አዙሮ ያዛትና ወደ እሱ ስቦ ከሰፊ ደረቱ ጋር አጣበቃት…፡፡ጡቶቹ ከጠናካራ ደረቱ ጋር ሲጋጩ የመጨፍለቅና የህመም ስሜት ተሰማት….ከእሱ ትንፋሽ ወደእሷ የሚደርሰው ሽታ ከቅድሙ በላይ አስጠሊታ ሆነባት…
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹ምነው ትንፋሼ አንገሸገሸሽ..እንቺ ይሄን ስትጠጪ ይተውሻል›› ብሎ በግድ ህጻን ልጅ ጡጦ እደሚግት አፏን ፈልቅቆ አረቄውን በጉሮሮዋ አንደቀደቀው….፡፡
እንዳዛ ያደረገው ሳትዘጋጅ ስለሆነ ሁለቴ ወደውስጥ እንዳስገባች ትን አላት..ከአፎ አላቀቀውና ብልቃጡን ወረወረው….ከዛ ነፃ በሆኑ ሁለት እጆቹ ሙሉ በሙሉ ተሸከማትና አልጋው ላይ ወረወራት…
‹‹ምን እያደረክ ነው..?እጮሀለው….ተወኝ›››
‹‹አምቦርቂው…..ግን ልንገርሽ ጉሮሮሽ ይሰነጠቃል እንጂ ማንም ደፍሮ ወደእዚህ አይመጣልሽም..ምን አልባት አሳዳጆችሽ ሰምተው ሊመጡ ይችሉ ይሆናል ››
‹‹በፈጠረህ….በምትወደው››
‹‹ምንም የምወደው የለም›› አለና….ከላይ ለብሳው ነበረውን ካፖርት ጫፍን ያዘና ሞሽልቆ ከላዬ ላይ አወለቀው…፡፡እጇ የተገነጠለባት መሳለትና ድምፅ አውጥታ ጮኸች፡፡ አፎን በአስፈሪ መዳፉ አፈናት በቀኝ እጁ የለበሰችውን የጨርቅ ሱሪ ከላይ ይዞ ወደላይ ጎተተው….እግሮቾን አንድ ላይ አጣምራ ያሰበውን እዳያደርግ ለመከላከል ሞከረች…አፎ ላይ የከደነውን እጁን አነሳና በሁለት እጆቹ የሱሪዋን ጠርዝ ግራና ቀኝ ይዞ ወደታች ሸረከተው……በግራ በኩል ተመሳሳዩን አደረገ..ከዛ ሞሽልቆ ከላዬ ላይ ሙሉ በሙሉ አንሰቶ ጣለው..፡፡
በዚህ ጊዜ ወሰነች….ተስፋ ከመቁረጥ ተመዘዘ ውሳኔ.. በቃ ከዚህ በላይ መታገል ይበልጥ ለመጎዳትና በራስ ላይ ስቃይን መጨመር ነው እንጂ ሌላ የምታተርፈው ነገር እንደሌለ አሰበች..ይኅን የህክምና ሰው ስለሆነች በልምድ ታውቀዋለች….ቡዙ ግዚ ሴቶች በመደፈር ታሪክ ውስጥ በጣም ጉዳት የሚደርስባቸው ከግንኙነቱ በላይ በትግልና እራሳቸውን ለማትረፍ በሚያደርጉት መፋተግ ነው..እርግጥ ለራሳቸው ክብር ሲሉ እስከመጨረሻው ህቅታ ለሚፋለሙ ሴቷች ክብር አላት…አሁን ግን እሷ ያንን ማድረግ አትችልም…አራሷን ከትግል ሙሉ በሙሉ አላቀቀች…፡፡ከላይ የለበሰችውን ልብስ ወደ ላይ ሞሽልቆ ሲያወጣ በፍቃደኝነት ተባበረችው……ጡት ማስያዣዋን ሳይቀር አወለቀ…እሷ እየለዘበች ስትመጣ የእሱም የንዴትና የእልህ ስሜቱ እየረገበ መጣ፡፡
እንዳጋጣሚ ከቤት ስትወጣ ፓንት አላደረገችም ነበርና፡፡እንዳጋጣሚ ማታ ስትተኛ ፓንት አውልቆ ቢጃማ ብቻ አድርጎ የመተኛት ልምድ ነበራት …እና ለሊት ኤልያስ ሲደውልላት ከመደናገጧ የተነሳ ቢጃማዋን አውልቃ ሱሪዋን ከመልበስ ውጭ ስለፓንት አስፈላጊነት በወቅቱ አልተገለፀላትም ነበር…እና አሁን ሱሪዋን ቀዳዶ ሲጥለው..ቀጥታ እርቃኖን ነበር ቀረችው...እርቃኖን ካስቀራት ቡኃላ ወለሉ ላይ በሁለተ እግሮች ቆሞ ቁልቁል ያያት ጀመር..እሷ አይኖቾን ጨፍና በቀጣይ የሚሆነውን እየጠበቀች ነው….አዎ አሁን ልብሱን አውልቆ መጥቶ ሊጫወተብኝ ነው……ግን ምን ምርጫ አለኝ…አምላኬ ሆይ አንተ ካልክ ይሁን ››ብላ ስታሰላስል
.እሱ ጎንበስ ብሎ አንደ እጅን እግሯን በሌላ እጁ አንገቷ አካባቢ በመያዝ ሰቅስቆ እንደህፃን ልጅ ወደላይ አቀፈት…..
‹‹‹አረ..እሺ በስርአቱ አድርገው..በፈጠረህ››መልሳ መወራጨት ጀመረች ፡፡እሷ ያሰበችው ወዳ ላይ ሲያቅፋትና ሰያነሳት በፊልም የወሲብ ፊልም ሚሰሩ ፈረንጆች እንደሚፈፅሙት አይነት እሷም ያለመደችውን አይነት ወሲብ ሊፈፅምና ሊያበለሻሻት መስሎት ነበር፡፡ እሱ ግን እንዳቀፋት ጎንበስ አለና አልጋ ልብሱንና ብርደልብሱን ገፎ ከውስጥ አንሶላው ላይ አስተኛት..ከዛ እንሶላውንና ብርድ ልብሱን አልብሶት አልጋ ልብሱን ከላይ ገፈፈና ወደፊት ለፊት ተራመደ …ከዛ አይኖቾን በስሱ ገልጣ እያየችው በራፉን ከፍቶ ወጣና መልሶ ዘጋው..፡፡ባዶ ከፍል ብቻዋን ስትቀር ቅድም ከፈራችው በላይ አሁን ይበልጥ ፈራች…..፡፡
ሊያደርግ የፈለገውን ሳያደርግ ሀሳቡን ቀይሮ መልሶ መውጣቱን አሁንም አላመነችም..አሁንም መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..አረ ውስጧም ጭምር እየተንዘፈዘፈ ነው..፡፡‹‹ገና የእውነት ሀሳቡን ቀይሮ ነው ወይስ የቡድን ወሲብ እንደሚሉት ጎደኞቹን ጠርቶ ሊመጣ ይሆን?›› የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ተፈበረከ፡፡ ብድግ ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃኖን ወለሉ ላይ ቆመች.. ካፖርቷን ከመሬት አነሳችና ለበሰች….ቅስ ብላ ወደ በራፉ ሄደችና ቆለፈችው…. ከዛ ደግሞ ሀሳቧን ቀይራ ከፈተችው..እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ከፈተችው ..እንገቷን አስግጋ ወደ ውጭ ስትመለከት እዛው በራፍ ስር በረንዳ ላይ እልጋ ልብሱን ተከናንቦ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ አይቹን ሰማይ ላይ የተሰቀለችው ጨረቃ ላይ ተክሎ ሲጋራውን እያቧነነ ነበር፡፡መልሳ ወደ ውስጥ ገባች..፡፡
‹‹አሁን ዝም ብዬ ሳልቀረቅረው ልተኛ.?...ለሊት ላይ የወንድነት ስሜቱ ዳግም አገርሽቶበት መጥቶ ቢከመርብኝስ?አይ መቆለፍ አለብኝ..››አለችና ቆለፈችው፡፡ ሁለት እርምጃ ከሄደች ቡኃላ ደግሞ ሌላ ተቀያሪ ሀሳብ መጣባት..‹‹እንዴ የሰው ሰው በገዛ ቤቱ ውጭ አሳድርሬ እንዴት ይሆናል…ምን አልባት ለሊት ላይ ብርዱን መቋቋም አቅቶት ወደ ውስጥ መግባት ቢፈልግስ….?የራሱ ጉዳይ›› አለችና ተመልሳ የቆለፈችውን ቁልፍ ከፋታ ወደመኝታዋ ሄዳ ተኛች…እንቅልፍ የወሰዳት ግን ምን አልባት ከሳዕታት መገለባበጥ ቡኃላ ነው… ለዛውም በቅዠትና የተሞላ አስጠሊታ እንቅልፍ፡፡

👍24❤1