አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹ሞተር ሞተር ነው›› አላት፡፡
ሞተር ሳይክል በታትኖ መገጣጠም ከቻለ አይሮፕላን እንደማያቅተው
ተገነዘበች፡

ባለሙያው ‹‹ትንሽ ሳንዘገይ አልቀረንም›› አላት፡፡ ምን እንዳለ ስላልገባት አባባሉ ትንሽ ግርታ ፈጠረባት፡፡ ትንሽ ቆይታ የአይሮፕላን ድምጽ ሰማች፡፡ ወደ ሰማይ ስታንጋጥጥ የላቭሴይ አይሮፕላን ዝቅ ብላ
ታንዣብባለች፡ ላቭሴይ አይሮፕላኗን ጠጋግኖ እሷን ሳይጠብቅ መብረር
ጀምሯል፡ ወደ ሰማይ እንዳንጋጠጠች ላቭሴይ እንዴት እንዲህ ያደርገኛል
ስትል ተብከነከነች: ሻንጣዋንም ይዞባት ሄዷል፡

ላቭሴይ እሷን ለማብሸቅ የፈለገ ይመስል እንደገና ዝቅ እያለ ሲበር ስታይ እጇን ቡጢ ጨብጣ እንደመዛት ስትል እጁን አውለበለበና
አይሮፕላኗን ሽቅብ ወደ ሰማይ አጎናት፡

ባለሙያው ይህን ሲያይ ‹‹አንቺን ትቶ ሊሄድ ነው›› አላት፡፡

‹‹ለሰው የማያዝን ርጉም ነው›› አለች፡፡

‹‹ባልሽ ነው?››
‹‹ኧረ አይደለም!›› አለች፡
ናንሲ ሆዲ በብስጭት ታመሰ እነዛ ሁለት ሰዎች አታለዋታል፡ ምን ባጠፋሁ ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡

አሁንስ ሁሉንም ነገር ‹ተይው ተይው› አሰኛት፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ
አሜሪካ የሚበረው አይሮፕላንጋ የምትደርስበት መንገድ ስለሌለ ፒተር ኩባንያውን ለናት ጅሪዌይ ሸጦ ሁሉ ነገር ያበቃለታል ስትል ክፉኛ ተንገበገበች:
ድንገት ሚጢጢዋ አይሮፕላን ወደ እነሱ አቅጣጫ ተጠመዘዘች:
ለምን ተመልሶ መጣ? አሁንም ሞተሩ እክል ገጠመው?› ስትል ከራሷ
ተሟገተች፡፡

አይሮፕላኗ ወረደችና ሶስቱ ሰዎች ያሉበት አካባቢ በጭቃው መንገድ
ላይ አረፈች፡

ናንሲ በደስታ ነፍሷን ልትስት ምንም አልቀራትም፡፡ ሊወስዳት ተመልሶ መጣ፡፡ መርቪን ላቭሴይ የሆነ ነገር እየተናገረ ነው፡፡

‹‹ምን?›› ስትል ጮኸች ምን እንዳለ ስላልተሰማት፡

ላቭሴይ እንዳልተሰማ ሲረዳ ወደ አይሮፕላኑ እንድትመጣ የጅ ምልክት አሳያት፡፡ ወደ እሱ ሮጠች፡፡

‹‹ምን ትጠብቂያለሽ? አትገቢም!››

ሰዓቷን ስትመለከት ለዘጠኝ ሩብ ጉዳይ ሆኗል፡ አሁን ከተነሱ ፎየንስ በሰዓቱ ይደርሳሉ፡፡ ይህም ተስፋዋን አለመለመውና ጥሎ አልጣለኝም አለች::

ወጣቱ ባለሙያ አይሮፕላኑ ላይ ስትወጣ አገዛትና ገብታ ወንበሩ ላይ ተቀመጠች፡፡ አይሮፕላኗም አፍታም ሳትቆይ ተነስታ በረረች፡፡

ይቀጥላል
👍15🥰2
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ናንሲ ሌኔሃን በትዕግስት ማጣት ስትቁነጠነጥ የመርቪን ላቭሴይ ትንሽ አይሮፕላን ለበረራ ተዘጋጀች፡፡ ላቭሴይ ለፋብሪካው ካቦ መመሪያ እየሰጠ ነበር፡፡ መርቪን የፋብሪካው ወዛደሮች እንዳመጹና ሰሞኑንም የስራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ነገራት፡ ‹‹አስራ ሰባት የመሳሪያ ቴክኒሻኖች ቀጥሬአለሁ አንዱ እንኳን ስለፋብሪካው…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሦሥት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ሳቤላ ከማዳመጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከሪቻርድ ሔር ጋር ምን እንዳገናኘው ገርሟት ነበር

ድሮ በልጅነቴ በጣም ልጅም አልባልም ክፍ ብዬ ነበር ሪቻርድ አፊ ዘንድ እመላለስ ነበር እሷ ከአባቷ ከጆርጅ ሆሊጆን ጋር ነበር የምትኖር » ብዙ ወጣቶች እሷ ዘንድ አይጠፉም "እሷ ግን ቶርን የተባለው የትልቅ ሰው ልጅ በመሆኑ ከሁሉ አብልጣ ትወደው ነበር " ያ ሰው በአካባቢው የሚያውቀው አልነበረም
በምስጢር ሹልክ ብሎ ፈረስ አየጋለበ ይመጣና እንዳመጣጡ ሹልኮ ይመለሳል አንድ ቀን ማታ ሆሊጆን በጥይት ተገደለ ሪቻርድ ተሸሸገ " ምስክሩ በሱ ጠነከረበት « ፍርድ ቤትም ገዳይነቱን አምኖ ወሰነበት " ሁላችንም እሱ ስለ መግደሉ አልተጠራጠርንም አሁን እናቴ የልጅዋን ነገር እያነሳች በኅዘን ልትሞት ሆነ " ማንም ሊያጽናናት አልቻለም " በዚህ ዐይነት ያለ ምንም ለውጥ አራት ዓመት ያህል ቆየ።
ከዚያ በኋላ ሪቻርድ በምስጢር ለጥቂት ሰዓቶች ወደ ዌስት ሊን መጣና ወንጀለኛው እሱ ሳይሆን ቶርን የተባለ ሰው እንደ ነበር ነግሮን ሔደ ቶርንን ለማግኘት ብዙ ጥረት
ተደረገ " ነግር ግን ማን እንደ ነበረ የት እንደ ነበረ ከየት እንደ መጣ ወዴት እንደ ሔደ የሚያውቅ ሰው ሳይገኝ ጥቂት ዓመታት ዐለፉ " አንድ ጊዜ ቶርን የተባለ ካፒቲን
ወደ ዌስት ሊን መጣ። መልኩ ሁኔታው ሁሉ ሪቻርድ ከሰጠን ምልክት ጋር አንድ ሆነ " እኔም ሪቻርድ የነገረን ነፍሰ ገዳይ ቶርን እሱ መሆን አለበት ብዬ አመንኩ አሁን ምን መደረግ እንደሚገባው እንኳን ሳይታሰብበት ካፒቴን ቶርን ወደ መጣበት ሔደ አሁንም ከዚያ በኋላ ዓመቶች ዐለፉ ”

ባርባራ ዐረፍ አለች " ማዳም ቬን ፍዝዝ እንዳለች ቀረች " ያ ሁሉ ታሪክ ለሷ ምን እንደሚያደርግላትም አልገባትም "

“ኋላ ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኢስት ሊን እንግዳ ሆኖ በሰነበተበት ዘመን ካፒቴን ቶርን የሔርበርትን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ዌስት ሊን መጣ አሁን ሰውየው
እሱ መሆኑን ሚስተር ካርላይልና እኔ አመንበት " ቢሆንም ይበልጥ ለማረጋጥ እንሯሯጥ ጀመር። እማማ እንደ ልቧ ወዲያ ወዲህ ማለት ስለማትችልና አባባም የሪቻርድን ነገር ለመስማት ስለማይፈልግ እኔ ብቻ ነበርኩ ከሚስተር ካርላይል ጋር በየጊዜ መገናኘት የነበረብኝ " ያኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ኢስት ሊን ውስጥ ተደብቆ ስለ ተቀመጠ ለማንም ሌላ እንግዳ አይታይም ባለ
ዕዳዎቹ እንዳያገኙኝ ፈርቸ ነው ይል ነበር " አሁን ግን ውሸቱን ሳይሆን አይቀርም ብዬ መጠርጠር ጀመርኩ ሚስተር ካርላይልም በዚያ ጊዜ ዌስት ሊን ውስጥም ሆነ በአካባቢው በዕዳ የሚፈልገው ሰው የለም ያለውም ትዝ አለኝ » "

“ ታድያ በምን ምክንያት ነበር በግልጽ የማይወጣውና ከሰው የሚደበቀው?” አለች ወይዘሮ ሳቤላ አቋርጣ እሷም በበኩሏ ዘመኑ ይራቅ እንጂ ነገሩን በደንብ
ታስታውሳለች » የሚሹሎከሎከው ባለ ዕዳዎቹን በመፍራት መሆኑን ይነግራት ነበር » አንድ ጊዜ ብቻ በኢስት ሊን አካባቢ ፈላጊዎች እንደሌሉት አጫውቷታል

“ ከባለዕዳዎቹ የባሰ ፍራት ነበረበት " አለቻት ባርባራ “ እንዳጋጣሚ ሆነና
ካፒቴን ቶርን ከሔርበርት ቤተሰብ ዘንድ አንደ መጣ ከወንድሜ አንድ መልእክት
ደረሰን " መልእክቱም ለአጭር ጊዜ ወደ ዌስት ሊን መጥቸ ለመመለስ ፈልጌአለሁ የሚል ነው "ይኸንኑ ለሚስተር ካርላይል ነገርኩት " እማማ በጣም ተጨነቀችበት "
ሚስተር ካርላይልም የሪቻርድን ንጹሕነት ይፋ የሚሆንበትን መላ ለማግኘት ብዙ
ይጠበብበትና ይጓጓበት ነበር » ስለዚህ ከምን ጊዜውም የበለጠ ከሚስተር ካርላይል
ዘንድ እየተመላለስኩ መመካከር ግዴታ ሆነብኝ " አየሽ አባባና ሚስ ካርላይል ዘመዳሞች ናቸው " ስለዚህ የሪቻርድ መከራ የኛ ብቻ ሳይሆን የካርላይል ቤት ጭምር ነበር "

ሳቤላ ትዝታና መራራ ጸጸት ወደዚያ ዘመን ይዟት ተመለሰ " የሚስትር ካርይልና የባርባራ ቶሎ ቶሎ መግናኘት' በቅናት አመለካከት ሌላ ትርጕም መስጠቱን አስታወሰች " ለምንድነው ባልተረጋገጠ ነገር ከመከራ ላይ ለመውደቅ አእምሮን ያን ያህል ያስጨነቀችው ?

“ሪቻርድ መጣ " ጸሐፊዎቹ ወደ ቤታቸው ከሔዱ በኋላ እሱ ወደ ሚስተር ካርላይል ቢሮ ሹልክ ብሎ ሔዶ ከአንድ ክፍል እንደገባና ካፒቴን ቶርንን ተደብቆ
እንዲያው አስቸኳይ ዝግጅት ተደረገ " ካፒቴኑ ሚስተር ካርላይል የሚፈጽምለት አንድ ጕዳይ ነበረው " ሚስተር ካርላይልም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ
ቀጠረው » ስለዚህ ሁኔታውን ስለ ሪቻርድ ለማመቻቸት ምንም ችግር አልነበረውም የሚስተር ካርላይል ሚስት የኮበለለችው ያን ዕለት ሌሊት ስለ ነበር ምጊዜም ከአምሮው አይጠፋም

«ሳቤላ ድንግጥ አለችና ሽቅብ ተመለከተች »

" የሆነውን ኮ የምነግርሽ እመቤት ሳቤላና ሚስተር ካርላይል የራት ጥሪ ነበረባቸው " ሚስተር ካርላይል ከጥሪው ካልቀረ የሪቻድን ጉዳይ መፈጸም የማይቻለው ሆነ " መቸም ርኀሩጎና ለሰው አሳቢ ነው " ከራሱ ጥቅምና እርካታ ይልቅ ስለ ሌላው ደኅንነት ማሰብ ደስ ይለዋል " ስለዚህ ከጥሪው ቀረ " መቸም የሽብር ሌሊት ነበር " አባቴ ወጥቶ አምሽቷል ሪቻርድ በቀጠሮው መሠረት ወደ ዌስት ሊን በጨለማ በሚጓዝበት ጊዜ የመንገድ አደጋ ሊደርስበት ስለሚችል ተጨንቀናል " ስለዚህ እማማን እያረጋጋሁና እያጽናናሁ አብሬአት አመሸሁ " ሪቻርድ
ሚስተር ካርይል ጋር ያለውን ጉዳይ እንደ ጨረሰ ከእማማ ጋር ለመገናኘት
መምጣት ነበረበት ከተለያዩ ብዙ ዓመታቸው ሆኗቸው ነበርና።

ባርባራ ነገሯን ቆም አረገችና ሐሳብ ይዟት ጭልጥ አለ " ማዳም ቬንም ቃል ሳትተነፍስ ዝም አለች " ቢሆንም የሪቻርድ የካፒቴን ቶርንና የፍራንሲዝ ሌቪሰን ግንኙነት ምን እንደሆነ አላወቀችውም "

“በመስኮት ቁሜ ስጠብቃቸው ሚስተር ካርላይልና ሪቻርድ በአትክልቱ ቦታ በር ሲገቡ አየኋቸው ሰዓቱ ከምሽቱ ሦስትና በአራት መካከል ሳይሆን አይቀርም!
እንደ ተገናኘን ካፒቴን ቶርን ሪቻርድ ያለው ቶርን አለመሆኑን ሲነግሩኝ በጣም አዘንኩ ሚስተር ካርላይል ደግሞ' ' እንኳን እሱ አልሆነ ብሎ ደስ አለው
ሪቻርድ እማማ ዘንድ ገባ አባባ ካገኘው ይዞ ለፍርድ እንደሚያቀርበው ብዙጊዜ
ተናግሯል እሱ ተጫውቶ እስኪወጣ ድረስ እኔና ሚስተር ካርላይል ከግቢው ወዲያና ወዲህ እያልን የአባባን መምጣት አንድንጠባበቅ ተማከርን ከመጣ ሚስተር ካርላይል እያዝናጋው እንዲቆይና እኔ ሮጥ ብዪ ገብቼ ሪቻርድን እንዲሸሸግ እንዳስጠነቅቀው ከማማ ጋር ተነጋገርን ሚስተር ካርይልም የእማማን ልመና ተቀብሎ ሐሳቡ ተስማምቶ አብረን ከደጅ አመሽን " ሪቻርድም አልወጣም!ብዙ ቆየ አባባም አልመጣም " እኔና ሚስተር ካርላይልን ብዙ ጌዜ አስጠበቀን - ደስ የሚል የጨረቃ ሌሊት ነበር ።

ያልታደለችው ሳቤላ እጇን እስኪያማት እያፋተገች
አዳመጠች ባርባራ ምንም ሳትጠረጥር የሆነውን ሁሉ እያስታወሰች በቅንነቷ ስትነግራት ጸጸቱ እንደ እሳት ይፈጃት ጀመር ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲንጎራደዱ
👍13👏1🤔1
ያየቻቸው በሌላ ተልእኮ እንጂ በፍቅር ጉዳይ አንዳልነበር ዐወቀች" እውነተኛውንና ያ ደጉን ባሏን ለምን እንደ ጠረጠረችው ያንን ቀጣፊ ውሸታም ለምን እንዳመነችው ከአሳዛኙ ውሳኔ ለመድረስ ለምን እንደ ቸኮለች እያሰበች ሆድ ሆዷን ይበላት ጀመር!
መጨረሻ ሪቻርድ ወጥቶ እንደግና ወደ ስደቱ ሔደ ሚስተር ካርላይልም
ሔደ እኔ ግን አባባ ሲመጣ ለማየት ከበሩ ቆየሁ " ሆኖም ሚስተር ካርላይል ከቤቱ ሲደርስ ትንሽ ሲቀረው ከኛ ቤት አንድ ሰነድ መርሳቱን ትዝ ይለውና እንደገና ተመልሶ መቶ ሔደ ከሱ በኋላ ሪቻርድ ቁና ቁና እየተነፈሰ ተመልሶ መጣ "
“ ቶርንን ነፍሰ ገዳዩን ቶርን ማለቴ ነው ቢን ሌን ላይ አየሁት ብሎ ነገረኝ " ለጊዜው ጠረጠርኩት ነገር ግን ወዲያው ተያይዘን ከሚስተር ካርላይል
ለመድረስ ሮጥን " ሪቻርድ ቶርንን መልኩን 'የማታ ልብሱን 'ነጭ እጁን ያልማዝ ቀለበቱን በተለይም ጸጉሩን ወደኋላ ሲያስተኛ የእጁን እንቅስቃሴ ምን እንደ
ሚመስል አንድ ባንድ ዘረዘራቸው » በዚህ ጊዜ ይህ ቶርን የሚባለው ሰው ካፒቴን ሌቪሰን መሆን አለበት የሚል ሐሳብ መጣብኝ ገለጻው ከሌቪሰን ሁኔታ ጋር አንድ ነበር ሚስተር ካርላይል ግን ለምን እሱ ይሆናል ብሎ እንዳልጠረጠረ ብዙ ጊዜ
ሲገርመኝ ኖረ

ሳቤላ ነገሩ ግር ሲላት አፋን ከፍታ ዝም ብላ ተቀመጠች ኋላ ነገሩ ግልጽ ሲሆንላት አልተቀበለችውም ።

“ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነፍሰ ገዳይ ! አይደረግም " በርግጥ መጥፎ ሰው ነው
ነገር ግን ነፍስ ገዳይ አይደለም ” አለች »

“ ቆይ ” አለች ሚስዝ ካርላይል ስለዚህ ጉዳይ ምንም አልተናርኩም "
እንደዚያ የመሰለ የግፍ በደል የፈጸመበትን ሰው ስም እንዴት አድርጌ ለሚስተር ካርላይል ላንሣለት? ስለዚህ ሪቻርድም ወንጀለኛ ተብሎ እንደ ተሰደደ ቀረ - ዛሬ
በሠረገላ ሁኜ በዌስት ሊን ሳልፍ ፍራ ንሲዝ ሌቪሰን ለሕዝቡ ንግግር ያደርግ ነበር።ሪቻርድ የጠቀሳቸውን ምልክቶች ሁሉ በዐይኔ አየሁ ተፈላጊው ሰውዬ እሱ ነው የሚለው እምነቴ ከምን ጊዜውም የበለጠ እርግጠኛነቱ ተሰማኝ

ሊሆን አይችልም ” ብላ አጉረመረመች ሳቤላ ።

“ ቆይ “ ኮ ” አለች ባርባራ “ ይኸውልሽ ሚስተር ካርላይል ቅድም ለራት
ወደ ቤት ሲገባ ይህን ነገር ለመጀመሪ ጊዜ አነሣሁለት ነገሩ አዲስ አልሆነበትም
እሱ የቅስቀሳ ንግሩን ሲያዶርግ አፊ ሆሊጆንን ሲያባርር የነበረው ቶርን መሆኑን በሁለት ምስክሮች እንደ ተረጋገጠ ነገረኝ በጣም የሚዘገንን ነገር ነው ! ”

ሳቤላ " እንደ ተቀመጠች ሚስዝ ካርላይልን ትክ ብላ አየቻት " አሁንም ነገሩን ገና አላመነችም

“ በርግጥ በጣም የሚያሠቅቅ ነገር ነው » ይህ እርጉም ሆሊጆንን በገደለ የኔ ወንድም በስቃይና በውርደት ሲሠቃይ ኖረ " ያን ሌት ሪቻርድ ቢን ሌን ላይ ባገኘው ጊዜ ሳቤላን ይዞ የሚኮበልልበትን ሠረገላ ፍለጋ ዌስት ሊን ውስጥ ሲሽሎከሎክ ነበር " ሌሊት አባባ ሲገባ ባራት ፈረሶች የሚሳብ ሠረገላ በኛ በር አጠገብ ዐልፎት እንደ ሔዶ ነግሮን ነበር ምነው ያች ያልታደለች እመቤት ሳቤላ ከማን ጋር እንደምትኮበልል ዐውቃ ቢሆን ! ከዚያ ሁሉ መጥፎ ተግባሩ ላይ ደግሞ ነፍስ ገዳይ ሆኖ መገኘቱ ! በውነት ይኸን የመረጨሻ ጉድ ለማየት በይወሕት አለመኖሯ ለሷ ታላቅ ዕድል ነው " አሁን በሕይወት ብትኖር ኖሮ ምን ይሰማት ነበር ? ”

ማዳም ቬን ራሷን ለመግታት ስሜቷን ለመቈጣጠር ብዙ ብትታግልም የድንጋጤ ጩኽት አመለጣት " ፊቷ ዐመድ መስሎ ነጣ " ሚስዝ ካርላይል ገረማት "
ለምንድነው ታሪኰን ስትሰማ ማዳም ቬን እንደዚህ የምትሆነው ? ማዳም ቬን ስለ
ፍራንሲዝ ሴቪስን ከምትለው በላይ እንደምታውቅ ጠረጠረቻት

“ ማዳም ቬን ይህ ሰው ምንሽ ነው? አለቻት ወደሷ ጐንበስ ብላ "

ማዳም ቬን ከራሷ ጋር ታግላ ባይሆን አፍአዊ ስሜቷን አረጋጋችና''ይቅርታ
ሚዝ ካርይል ነገሩ እውነትም በጣም የሚዘንን ነው " አለቻት •

“ግን ምንሽም አይደለም ? ታውቂዋለሽ ? "

“ለኔ ምኔም አይደለም » ስለ ማቁ ግን ትናንት ከኩራው ሲከቱት አይቻለሁ!
ያን የመሰ ሰው ! ልጠጋው ይቀፈኛል ”

“በይ እንግህ ማዳም ቬን ይህን ሁሉ ታሪክ የነገርኩሽ አንቺን ከቤተሰባችን ቆጥሬ ስለ አመንኩሽ ነው …”

መልስ አልሰጠቻትም ፊቷ ጭው ብሎ እንደ ነጣ ተቀምጣለች

ነገሩ ተረት ይመስል ” አለች ባርባራ ጨዋታዋን በመቀጠል : “ አሁም
እሱ በመስቀል ላይ በተንጠለጠለና ታሪኩ በዚህ ቢፈጸም መልካም ነበር " ግን ተረቱ መስቀል ሳይ ሲንጠለጠል ይፈጸም ይሆናል " እስኪ አስቢው ማዳም ቬን እንዲያው ለራሱ ምን መስሎ እንደሚታየው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በነፍስ ገዳይ
ተፈርዶበት መስቀል ላይ ተንጠልጥሎ መታየት !

“ ባርባራ ' የኔ ፍቅር!”

የሚስተር ካርላይል ድምፅ ነበር እሷም ሳቤላን ትታት በፍቅር ክንፋ ወደ ባሏ በረረች " ያቺን ዱሮ በዘመኗ የመመለክ ያሀል ትወደድና ትከበር የነበረችውን 'ሚስት ' ብቻዋን ጥላት ወደምታመልከው ባሏ በረረች » ሳቤላም በጭንቀት ብዛት የታመመውን ልቧን በክንዷ እቅፍ አድርጋ ከሶፋው ውስጥ ሰጠመች ነፍሷንም የምትስት መሰላት እንድትሞትም ጸለየች » በእጅና በነፍሱ የግፍ ደም ያለበት ሰው ተከትላ ለመሔድ ስትል ኤርኪባልድ ካርላይልን የመሰለ ባል አሽቀንጥራ ጣለችው "....

💫ይቀጥላል💫
👍24
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ስድስት (16) «አዎ ! ሽንቶ የደፋኝ መስሎ ይሰማኛል ፤ አናዶኛል ፤ አበሳጭቶኛል ፤ አብግኖኛል »
«ማን?››
«ማይክል…..
አየሽ እስካሁን… ቢፈልግ እስካሁን ድረስ የት እንዳለሁ ማወቅ የሚቸገር አይመስለኝም ። ግን አልፈለገኝም። ወርውሮ ጥሎኛል »
«ሌላስ… ሌላስ ያናደደሽ ሰው አለ ? የበሸቅሽበት?»
«አዎ »
«ማ »
«እኔ ራሴ»
«ለምንድነው በራስሽ የበሸቅሽው? »
«ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ያደረግሁት ውል ልክ አልነበረም ። እሷ መቼም ደፋር ናት ። ድፍረቷ ይዘገንነኛል ከሷ ደግሞ የኔ ይብሳል ። ሸጥኩት አየሽ? ፍቅሬን ለሥጋዬ ሸጥኩት »
«በእውነት ፍቅሬን ሸጥኩት ብለሽ ታስቢያለሽ ? »
«ይመስለኛል ። ያውም በአዲስ ጉንጭ ! ፍቅርን ያህል ነገር በጉንጭ ፤! በመልክ››
«አይመስለኝም ፣ ናንሲ ። እኔ እንደምትይው አይመስለኝም « ለመልክ ሳይሆን ለመኖር ነው ። ነፍስሽን ለማቆየት ባንቺ ዕድሜ ምን አማራጭ እለሽ ? ሌላ ሴት ልጅ ባንች ዕድሜ ያለች ይህን አንች ያደረግሽውን ብታደርግ ምን ትያት ነበር?››
«እንጃ ! አላውቅም ። ምናልባት ችግሯን እረዳላት ይሆናል ወይም ንቄ እፈርድባት ይሆናል »
«ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት አዲስ ሕይወት መጀመር እንዳለብሽ ስንነጋገር ነበር ። አዲስ ድምጽ ፤ አዲስ አረማመድ አዲስ ገጽታ አዲስ ሁሉ ነገር ። ነገር ግን . . . ካንድ ነግር በስተቀር » አለች ፌ እና ዝም አለች ። ናንሲ ጠበቀቻት ። «ሁሉን ነገር እንድትቀይሪ ፤ የቀድሞውን እንድትረሺ ተነጋግረናል ። አንድ ነገሮ አላነሳንም » ዝም አሉ ሁለቱም ። «ማይክል… ስለማይክል አላነሳንም ። ናንሲ ማይክልን
ከሆድሽ አውጥተሽ ጥለሽ ማይክል የለም ብለሽ አዲስ ሕይወት መመሥረት የምትችይ ይመስልሻል ? »

«አልችልም… አልችልም» እንባዋ ቅርዝዝ አለ ። ሆኖም' ሁለቱም ይህ አባባል ውሸትም እንዳለበት ግብቷቸዋል ። «በፍጹም አትችይም ?››
«ፌ ፤ ሌላ ወንድ አስቤ አላውቅም ፤ ከማይክል ሌላ ። ግን ደግሞ አንዳንዴ ያለ ማይክል መኖር ይቻል ይሆንን አብሰለስላለሁ »
«እንዲያ ብለሽ ስታስቢ ምን ዓይነት ስሜት ይሰማሻል››
«ሞቴን እመኛለሁ››
«ለምን ናንሲ?... ለምሳሌ አሁን ከማይክል ጋር እይደለም እምትኖሪው ። ግን መከፋት የለብሽም ይመስለኛል አይደለም እንዴ?›› ናንሲ አዎንታዋን በአካል እንቅስቃሴ ገለጸች ።

«ናንሲ» አለች ፌ « ምናልባትም መድኃኒቱ የሚሠራዉ ይህንንም በደንብ ብታስቢበት ይመስለኛል »
«በቃ ! ማይክል ከአሁን በኋላ መጥቶ አይፈልጋትም ብለሽ አስበሻል ማለት ነው ?»
«ስለሱ ምንም እማውቀው ነገር የለም ፤ ናንሲ ። ይምጣ ይቅር ማንም ሊያውቀው አይችልም ከማይክል በስተቀር ማለቴ ነው »
«ልክ ነሽ ያ የውሻ ልጅ መልሱን እሱ ብቻ ነው የሚያውቀው !»

ናንሲ ይህን እያለች ከተቀመጠችበት ፈንጠር ብላ ተነሳች። አንዴ ካንዱ ዳር እስከ አንዱ ዳር ቤቱን በፍጥነት አካሔድ አዳረሰችው ። ከዚያም አካሔዱዋ ድንገት ቀነሰ ፤ ፍጥነቷ ኃይሏን የጨረሰው ይመስል ። ቆመች ። ባለችበት ላይ ። ስትቀመጥ ዕንባዋ በጉንጩዋ ላይ ፈስሶ ነበር ። «ፌ ! በጣም ፈራሁ ። በጣም በጣም ፈራሁ » አለች። «ምኑን ነው የፈራሽው፤ ናንሲ ? » ስትል ጠየቀች ፌ «ሁሉን ነገር» አለች ናንሲ «ሁሉን ነገር ። ብቸኛ መሆኔን ፣ ብቻዬን መሆኔን ፤ እራሴን ማጣቴን ፤ እኔን አለመሆኔን ። እንጃ… ምናልባት ያጠፋሁት ጥፋት ትልቅ በመሆኑ ቅጣቴ ሳይከብድ አይቀርም ይሆናል ። ፍቅርን ያህል ክቡር ነገር ለመልክ መለወጥ !››
«ግን ኮ ናንሲ ምርጫሽ ልክ ይመስለኛል ። ሙሉ አካል ከሌለ ፍቅርም እንደሌለ ተረዳሽ ። ቢያንስ የገጽታሽ መስተካከል የሚቻል ነው አሉሽ ። ተስማማሽ ። የለም ናንሲ፤ ወደፊትም ቢሆን በምርጫሽ የምትፀፀችበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም››
«ምናልባት ... ምናልባት » ናንሲን የለቅሶ ሳግ ይነትጋት ጀመር ።
«ገና፣ ዘመን መለወጫ ፤ አመትባል ። አመትባሉንም እንዴት እንደማሳልፈው ጨንቆኛል ። የዘንድሮውን አመትባል ሳስበው እጓለ ማውታን ማሳደጊያው ውስጥ ከነበረው ይበልጥ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ። ያኔ አየሽ ቢያንስ ሰው ነበረ ። ዘንድሮ ግን ብቻዬን ! አስቢው እስኪ ። ሊሊና ግሬቸን ካለፈው ወር ጀምሮ መሰናበታቸውን ታስታውሻለሽ ። አንች በበረዶ ሸርተቴ ለመዝናናት መሔድሽ ነው ። ፒተር ለሳምንት ያህልም ቢሆን ወደ አውሮፓ ይሔዳል ። እና....» ይህንን ሁሉ በእንባና በሳግ መካከል ነበር የተናገረችው ። ድንገት ንግግሯን አቋረጠች ። ምክንያቱም ፌንና ፒተርን አትሂዱ እንደማለት መሰላት ።

«ምናልባት ከሌሎች ሰዎች ጋር መተዋወቅ ያስፈልግሽ ይሆን ? ቢያንስ ለእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ» አለች ፌ። «እስኪ እይኝ ፌ » አለች ናንሲ ባርኔጣውን ከፍ እያደረገች ፊቷ በሙሉ እንዲታይ ፤ «እንዲህ ሆኜ ከማን ጋር ልተዋወቅ፤ፌ?!» .
«እንደሱ ብትሆኝ ምንድነው ። ባርኔጣውን ሳታነሽው የሚታየው ፋሻ ነው ። ፋሻ የአንድ ሰው ቆዳ እንዳልሆነ ፤ አደጋ ደርሶብሽ እንደነበረ ማንም ሰው ይገባዋል »
«ምናልባት ... ምናልባትም ይሆናል » አለች ። ሁለቱም ዝም አሉ ። ናንሲ በነገሩ ሙሉ በሙሉ እንዳላመነችበት ፌ ገብቷታል ። ያ ዓይነት ሐሳብ መኖሩን እንድታውቅ እንጂ ወዲያውኑ ልትቀበላት እንደማትችል ዱሮውንም ታውቃለች ። «ተቀበሉኝም ሸሹኝ ፤ አሁን እኔ ሰዎችን መተዋወቅ አልፈልግም ። እግዜር ይስጠው ፒተር የገዛልኝ ጓደኛ አለኝ ። ካሜራዬ ። ከሱ ጋር እጫወታለሁ ። በሱ ጊዜዬን አሳልፋለሁ አለች ። «ግሩም ፎቶግራፍ አንሺ ነሽኮ ። ካነሣሻቸው ፎቶዎች ጥቂቶቹን ባለፈው ጊዜ ፒተር ቢሮ ውስጥ አየኋቸው ። ድንቅ ናቸው ። ፒተር ደግሞ ቢሮው ለገባ ሁሉ ድንቅ ናቸው አይደሉም ? እያለ ሲያሳይ ነበር ። ድንቅ ፎቶግራፎች ናቸው »
« ስለወደድሽልኝ ደስ ይለኛል ፌ» አለችና እወንበሯ ላይ ተለጥጣ ተቀመጠች ። እግሯን አነባብራና ራሷን ይዛ «ፌ ምን ይሻለኛል ? እንዴት ፤ ምን ሆኜ ሰው ልሁን መኖር የምችል ይመስልሻል ? »
«እሱን ለማቀነባበር እየሞከርን አይደል እንዴ ፤ ናንሲ ። ላሁኑ ግን እስኪ የተማከርንባቸውን ነገሮች አስቢባቸው ። አዲስ የድምጽ ቃና አወጣጥን የሚያለማምድሽ ሰው ስለመቅጠር ፤ ደህና የሙዚቃ አስተማሪ ስለመፈለግ ፤ ባጠቃላይ አዲሷን አንችን ለመኖር ሀ ብለሽ ካሁኑ ሰዓት ለመጀመር ሞክሪ እስኪ» አለች ፌ ። ቀጥላም… « ሌላውን ተይው ። በጊዜው ይመጣል» የቤቱ አቀማመጥ ፤ የፌ ድምጽ ፤ የፌ ከንፈር መጠጣ የሌለበት ምክር ናንሲን አጽናኗት ። በልቧ ውስጥ ተጠራቅሞ የከበዳት ኀዘን ፍርሃት ፤ ጭንቀት ቀለል አለላት ። «ልክ ነሽ ፌ እንደሱ ማድረግ የሚሻለኝ ይመስለኛል በነገራችን ላይ መቼ ነው እረፍትሽን ጨርሰሽ እምትመለሽው!።»
👍19
«አሥራ አምስት ቀን ። በአሥራ አምስት ቀን ውስጥ እመለሳለሁ ። ከዚያ ወዲህ ባስፈልግሽ ደግሞ ችግር የለም ። አድራሻዬን እተውልሻለሁ ። ልትጠሪኝ ትችያለሽ » ፌ ለናንሲ ይህን የነገረቻት ረጋ ባለና ምንም ችግር እንደሌለ በሚነግር ድምጽ ቢሆንም በልቧ ግን ጨንቋት ነበር፡፡ ስለሷ ጉዞ ። ስለሷ ደስታ ሳይሆን ፤ ስለናንሲ ።መጭው ያመትባል ጊዜ መሆኑና እሷም ፒተርም ባንድ ጊዜ ትተዋት መሄዳቸውን ስታስብ ምን ዓይነት መጥፎ አጋጣሚ ነው ስትል አሰበች። ሌላ ጊዜ ቢሆን ደግ ዓመት ባል ግን ለየት ይላል፡፡ በጣም ለየት ይላል ። በዚህ ሁሉ መከራዋ ላይ አመትባሉን ያላንድ ሰው ብቻዋን ስትውል ናንሲ በጣም እንደምትደበር የተረጋገጠ ነው ዓመትባል ሲባል ደግሞ እንደለመዱት ካልዋሉት መከፋትን በልብ ውስጥ አጉልቶ የማስረጽ ባሕሪ አለው ።ሆኖም ይህን ለናንሲ መንገር አያስፈልግም ። እንደተሰማትም ማሳዬት የለባትም ። ስለዚህ ነገሩን ቀላል አድርጋ

«ለምን የዛሬ ሁለት ሳምንት ልንገናኝ አንቃጠርም ? እኔም ስለጉዞዬ ልነግርሽ ፤ አንችም ያነሳሻቸውን ፎቶግራፎች አትመሽ እንድትጠብቁቂኝ » አለች ። «ፖ ! የረሳሁትን ነገር አስታውስሽኝ » አለችና ናንሲ ከመቀመጫዋ ላይ እመር ብላ ተነሣች ። እና ከነበሩበት ክፍል ወጣች ። እንደተመለሰች በስጦታ መጠቅለያ ወረቀት የታሸገ ነገር እየሰጠቻት «መልካም የገና በዓል ይሁንልሽ ! » አለች ።

ፌ ከልብ በመነጨ ደስታ ፊቷ ፈገግ አለ ። እሽጉን ስትፈታውና ከውስጡ የወጣውን ነገር ስታይ ዓይኗን ማመን አቃታት ። የራሷ የፌ ፎቶግራፍ ነበር ። ናንሲ ያን ፎቶ መቼ እንዳነሣቻት ትዝ ባይላትም ፎቶውን ያዬ ማንም ሰው ግን «ፈገግ በይ ፤ እንደዚህ ሁኝ » እያለች ያነሣቻት ይመስለዋል ፤ በዝግጅት ። በፎቶው ላይ የምትታየዋ ፌ እናንሲ መኖሪያ ቤት ሰገንት ላይ ቆማለች ። ንፋሱ ፀጉሯን ያውለበልበዋል ። የለበሰችው ሐምራዊ ቀለም ሸሚዝ ከምትጠልቀዋ ፀሐይ ቀለም ጋር ተቀላቅሎ ሕብር ፈጥሯል ።
«መቼ ነው ያነሣሽኝ!? » አለች ፌ በአድናቆት እንደተሞላች ።
«ቀኑም ትዝ አይልሽ ?»
«ቀኑን አስታወስኩት… ግን…»
«ሳታይኝ ነው ያነሣሁሽ » ፌ ያን ያህል ደስ ሲላት ስታይ፤ ናንሲ በጣም ተደሰስተች። ይህንኑ ነበር የፈለገችው ። ፎቶግራፉን ያጠቆረችውም ያተመች ውም ራሷ ነበረች ። በጥንቃቄ ከዚያ ፍሬም አስገባችለት ሲያዩት የሥነጥበብ ሥራ መሆኑ ባያጠራጥርም ክፎቶ ይልቅ የእጅ ሥዕል ይመስል ነበር ። ወደዚያ የሚጠጋ ውበት ነበረው። «የማትታመኝ ጉድ ነሽኮ ናንሲ ። በጣም በጣም ውብ ነው ። በጣም ትልቅ ስጦታ ነው» አለች ፌ ። «ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሠሩት ሥራ ሁሉ ውብ ነው» አለች ናንሲ በደስታ እየተፍለቀለቀች ። ሁለቱ ሴቶች ተቃቅፈው ተሳሳሙ ። የፌን መሔድ ፤ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሊገናኙ እንደማይችሉ ስታስብ ናንሲ ኀዘን ተሰማት፡፡ «በይ እንግዲህ መልካም መዝናናት ይሁንልሽ» አለች ። «በይ በደህና ቆይኝ ። ስመሊስ ግግር በዶ ይዢልሽ እመጣለሁ » አለች ፌ ። «አትጃጃይ ፤ እሺ ? ! » አለችና እንደገና እቅፍ አደረገቻት ናንሲ ።

ናንሲና ፌ ተሰነባብተው ፤ መልካም አዲስ ዓመት መልካም የገና በዓል ተባብለው ተለያዩ ። ናንሲ ከሔደች በኋላ ሁሉ ፌ የምታስበው ስለናንሲ ነበር ናንሲ ጥሩ ልጅ ናት ። ባሕርይዋ ንጹሕ ነው። ሰው የሚባለው ደም ያ ነው ስትል አሰበች ። ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍19
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


የመርቪን ላቭሌይ ባለቤት ዳያና በደስታ ተፍነክንካለች በመጀመሪያ የሰማይ በራሪው ጀልባ መሬት ለቆ ሰማይ ላይ ሲወጣ ፈርታ ነበር አሁን ግን እየለመደችው መጣችና ደስ ይላት ጀመር ላቭሴይ በአይሮፕላኑ እንድትበር ዕድል ባይሰጣትም አይሮፕላኗን ብዙ ቀናት ፈጅታ ቀለም የቀባቻት እሷ ነች አንድ ጊዜ እስኪወጣ ነው እንጂ የሚያስፈራው እየተለመደ ሲመጣ ከሰማይ ሆኖ እርሻዎችን መንገዶችን የባቡር ሃዲዶችን፣ ቤተክርስ
ቲያኖችን፣ ፋብሪካዎችን ቁልቁል ሲያዩ የሚፈጥረው ደስታ ልክ የለውም
አሁን ነፃነት ተሰምቷታል፡፡ መርቪንን ጥላ ከማርክ ጋር ኮብልላለች፡፡
ትናንት ማታ ሳውዝሃምፕተን ከተማ በሳውዝ ዌስተርን ሆቴል ሚስተርና ሚስስ ማርክ አልደር በማለት ተመዝግበው የመጀመሪያውን
ሙሉ ምሽት አብረው
ሲፈጽሙ ያደሩት ወሲብ አልበቃ ብሏቸው ጧትም ደገሙት፡፡ ከዚህ ቀደም አዩኝ አላዩኝ እያሉ
እየተሳቀቁ ለአጭር ጊዜ ወሲብ ሲፈጽሙና ሲሳሳሙ ከነበረው ጋር ሲወዳደር
ይሄ ዓለም ነው በሰማይ በራሪው ጀልባ ሲበሩ ልክ ፊልም የሚያዩ ያህል
ነው የሚሰማው የአይሮፕላኑ የውስጥ ክፍል ያጌጠ፣ ተሳፋሪዎቹ ደግሞ
አለባበሳቸው የሚያምር ሲሆን ሁለቱ አስተናጋጆች ደግሞ ከአይን የቀደሙ ተፌዎች ናቸው ሁሉም እንቅስቃሴ በቅደም ተከተልና በቅልጥፍና
የሚካሄድ ሲሆን ዙሪያ ገባውን ታዋቂ ሰዎችም ይታያሉ፡ የይሁዲ ዝርያ ያለውና የጽዮናዊነት ንቅናቄ አራማጁ ባሮን ጋቦን አጠገባቸው ከተቀመጡ
ጎስቋላ ሰው ጋር በወሬ ተጠምደዋል ታዋቂው ፋሺስት የኦክስፎርዱ ባላባት ሎርድ ኦክሰንፎርድ ውቧን ሚስታቸውን አጠገባቸው ሻጥ አድርገው
ተኮፍሰዋል ልዕልት ላቪኒያ ባዛሮቭ ከዳያና ጋር ተቀምጠዋል

ከልዕልቷ ትይዩ ደግሞ በጥግ በኩል ታዋቂዋ የሆሊውድ ፊልም
ተዋናይ ሉሉ ቤል ቦታ ይዛለች፡፡ ዳያና በበርካታ ፊልሞች ላይ ያየቻት ሲሆን
ከማርክ ጋር እውቂያ አላት፡፡ ገና እንደተቀመጡ አንድ የአሜሪካዊያን አነጋገር ቅላጼ ያለው ድምጽ ‹‹ማርክ አልደር አንተ ነህ?! እኔ አላምንም››
ሲል ተሰማ፡፡ ዳያና ለማየት ዞር ከማለቷ አንዲት ከአፍ የወደቀች ፍሬ የምታክል ሴት ማርክ ላይ እንደ ጆፌ አሞራ ስትከመርበት ተመለከተች
በኋላ ታሪኩን እንዳጫወቷት ሉሉ እንደዚህ እንዳሁኑ ታዋቂ የፊልም አክተር ከመሆኗ በፊት ከማርክ ጋር የሬዲዮ ቶክ ሾው ላይ አብረው ሰርተዋል፡፡ ማርክም ዳያናንና ሉሉን አስተዋወቃቸው፡፡ ሉሉም ዳያና ቆንጆ መሆኗንና እሷን የመሰለች ማግኘት መቻሉ እድለኛ እንደሆነ ነገረችው፡፡
በእርግጥም ሉሉ ትኩረቷ ማርክ ላይ ስለነበር አይሮፕላኑ ከተነሳ ጀምሮ
ወጣት ሳሉ በችግር እንዴት እንዳሳለፉ እዚህ ግባ የማይባል ቤት ውስጥ
ሲኖሩ እንደነበሩና የመንደር አረቄ እየጠጡ ሌሊቱን ያሳለፉ እንደነበር
የጥንቱን አኗኗራቸውን እያነሱ ተጨዋወቱ፡፡

ዳያና ፊልሞቿ ላይ ረጅም ትምሰል እንጂ በእውን አጭር ናት፡ጸጉሯም በተፈጥሮ ቃጫ የመሰለ ሳይሆን ቀለም የተቀባ ነው፡፡ ሆኖም ፊልሟ ላይ እንደምትታየው እዚህም ያንኑ ፎልፏላነትና ልታይ ልታይ ባይነት ባህሪዋን ታንጸባርቃለች፡፡ ከማርክ ጋር እያወራች ሳለ ሁሉም እሷን
እሷን ይመለከታል፡፡

በሬዲዮ ድራማ ላይ አንድ ገጠመኝ አንስታ ስታወራ ሁሉም በሳቅ አውካካ፡፡ ‹‹አንድ ተዋናይ እሱ የሚናገረው የድራማው ክፍል አልቋል ብሎ በማሰብ ከስቱዲዮ ወጥቶ ሄዷል፡፡ መጨረሻ ላይ ግን የሚናገረው አንድ መስመር ንግግር ቀርቶታል፡፡ እኔም የፋሲጋውን ኬክ ማን በላው?
የሚለውን የራሴን ድርሻ ተናገርኩ፡ የኔን ድርሻ እንደገና ደግሜ ተናገርኩ፡፡

ዞር ብዬ ሳይ ተዋናዩ የለም፡፡ ቀጥሎ ያለውን የሚናገረው ሰው ሄዷል።አንድ ዘዴ በአእምሮዬ አውጠነጠንኩና በወንድ ድምጽ ድመቷ ናት
የበላችው በማለት ትርዒቱን አጠናቀቅኩ እላችኋለሁ›› ብላ አሳቀቻቸው::

ለማርክ ለመንገር ታሪኩን ስትጀምር አቋረጣትና ፊቱን ወደ ሉሉ አዙሮ ዳያናም አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ስትከታተል የሰማችውን
ከማርክ ጋር በቆየችባቸው ሶስት ወር ያህል ማርክ ፊት ነስቷት አያውቅም በኋላ ማርክን የብቻዋ ማድረግ የማትችል መሆንዋን
መረዳት ሊኖርባት ነው፡ አዳማጭ መሆንዋ ሰለቻትና ወደ ልዕልት ላቪኒያ ዞራ

‹ሬዲዮ ያዳምጣሉ ልዕልት?› ብላ ወሬ ጀመረች።

አሮጊቷ ራሻዊት አገጫቸውንና እንደ
አሞራ የተቆለመመ
አፍንጫቸውን በንቀት ከፍ አድርገው አቀራረባቸው ጨዋነት ይጎድለዋል›
አሉ፡፡

ዳያና ከዚህ ቀደም አመለ ቢስ አሮጊቶች ቢገጥሟትም እኚህኛዋ ግን የባሱ ናቸው፡ ‹‹ይደንቃል! ትናንት ግን የሰማነው የቤቶቨን ሙዚቃ ጥሩ ነው›› አለች ዳያና፡፡

‹‹የጀርመን ሙዚቃ ደረቅ ነው›› አሉ አሮጊቷ በማንቋሸሽ፡
እኚህን ሴት ምንም የሚያስደስታቸው ነገር የለም አለች ዳያና በሆዷ።
ልዕልቲቷ ከዚህ ቀደም እጅግ በጣም የተከበረ መደብ አባል የነበሩ ሲሆን
ይህንንም ዓለም በሙሉ እንዲያውቅላቸው ይፈልጋሉ የሚቀርብላቸው ነገር
ሁሉ ከዚህ ቀደም ሲቀርብላቸው ከነበረው ጋር ሲወዳደር እንደሳቸው
አስተሳሰብ እዚህ ግባ የሚባል ይደለም።

በኋለኛው የአይሮፕላኑ ክፍል የተመደበው አስተናጋጅ የሚፈልጉት
መጠጥ ካለ ለመታዘዝ ተሳፋሪዎቹ ፊት ቆሟል፡ ስሙ ዴቪ ሲሆን ሲራመድ ነጠር ነጠር የሚል የደስ ደስ ያለው ወጣት ነው፡፡ ዳያና ጠጥታው ባታውቅም የአሜሪካ ፊልሞች ላይ ሲጠጡት ስላየች ማርቲኒ አዘዘች፡

ከእሷ ቀጥሎ የተቀመጡትን ሁለት ሰዎች መልከት ስታደርግ በመስኮት ወደ ውጭ ያያሉ፡፡ ለጥቆ ደግሞ ረከስ ያለ ነገር ግን የሚያምር ልብስ የለበሰ ወጣት ሰው ተቀምጧል እንደ ስፖርተኛ ደልደል ያለ ትከሻ ያለው ሲሆን በርካታ ቀለበቶች አስሯል፡ ጠየም ያለ ፊቱ ደቡብ አሜሪካዊ መሆኑን
ይጠቁማል።

ከእሱ ትይዩ የተቀመጠው ሰው ደግሞ ለየት የሚል ሲሆን ኮሌታው የነተበ ሰፊ ኮት ለብሷል፡ በራው ደግሞ እንደ ስጋ ቤት አምፑል ዓይን
ያጥበረብራል፡ ሁለቱ ሰዎች ሲነጋገሩ ባይታዩም ዳያና አንድ ላይ እንደሆኑ
ገምታለች፡

መርቪን በአሁኑ ጊዜ ምን እየሰራ ይሆን? ስትል አሰበች፡፡ መቼም
ያስቀመጠችለትን ማስታወሻ ሳያነብ አይቀርም ያለቅስ ይሆናል አይ
አያደርገውም እሱ እንደዚህ አይነት ሰው አይደለም፡፡ መቼም በንዴት ጠጉሩን እየነጨ ይሆናል፡ በማን ላይ ይናደዳል ምናልባት በሰራተኞቹ ላይ? የጻፈችው ማስታወሻ ለስለስ ያለ ቢሆን ተመኘች ነገር ግን ከዚህ የተሻለ እንዳትጽፍ ሁኔታዎች አልፈቀዱም፡፡ እቤት ሲያጣት እህቷ ቲያ ጋ
ይደውልና አንቺጋ ናት? ብሎ ይጠይቅ ይሆናል የሄደችበትን መቼስ
ታውቃለች ብሎ፡ ወደ አሜሪካ እንደምትሄድ ስላልነገረቻት ቲያ ጠፋች
ሲባል ትደነግጣለች፡ የዳያናን አገር ጥሎ መጥፋት ለመንትያ ልጆቿ ምን ብላ ትነግራቸዋለች? ይህን ስታስበው ሆዷ ተምቦጫቦጨባት፡፡ የመንትዮቹን ልጆች ናፍቆት መቼም አትችለውም::

ዴቪ ያዘዙትን መጠጥ ይዞላቸው መጣ፡፡ ማርክ በመጀመሪያ ለሉሉ
ቀጥሎ ለዳያና ብርጭቆውን አነሳ በዚያው ቅጽበት ዳያና ማርቲኒውን
አንስታ ተጎነጨች፤ ስላንገፈገፋት ‹ህቅ› ብላ ተፋችና ‹‹ጂን ጂን ይላል››
ስትል ሁሉም አንዴ ሳቁባት፡፡ ማርክም ቀበል አድርጎ ‹‹ማርቲኒ እኮ ባብዛኛው ጂን ነው ከዚህ በፊት ጠጥተሽ አታውቂም ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

ሰዎቹ ስለሳቁባት ዳያና በሃፍረት ተሸማቀቀች። ልክ ቡና ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደገባች ተማሪ የምታዘውን መጠጥ አታውቅም፡፡ እነዚህ
ከሰለጠነ ዓለም የመጡ ተሳፋሪዎች ደግሞ ፋራነቷን አወቁባት፡፡
👍171
ዴቪም ቀልጠፍ ብሎ ‹‹እመቤት ሌላ መጠጥ ላምጣልሽ?›› አላት፡
‹‹እንግዲያው ሻምፓኝ ይሁንልኝ›› አለች ለምቦጯን ጥላ፡፡
‹‹እሺ እመቤቴ››
‹‹ከዚህ ቀደም ማርቲኒ ጠጥቼ ስለማላውቅ ልሞክረው ብዬ ነው
ያዘዝኩት፡፡ ታዲያ መሞከሩ ክፋት አለው?›› ስትል ማርክ ላይ አፈጠጠች፡፡
‹‹ኧረ የለበትም የኔ ማር›› አለና ጭኗን ዳበስ ዳበስ አደረጋት፡፡
‹‹አሁን ይሄ ብራንዲ ነው ንሳማ አንተ ልጅ በዚህ ፋንታ ሻይ አምጣልኝ›› አሉ ልዕልት ላቪኒያ እየተቆናጠሩ፡

‹‹እሺ እመቤቴ›› ብሎ ተፍ ተፍ እያለ ሄደ ዴቭ፡፡
ዳያና ይቅርታ ጠየቀችና አይሮፕላኑ የኋላ ክፍል ጋ የሚገኘው መጸዳጃ ቤት ሄደች፡፡ ከመጸዳጃ ቤት መልስ ቀጥሎ የሚገኘው የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች፡

የመዋቢያ ክፍሉ ዘና አደረጋት፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት በሚያምር
ጨርቅ የተለበጡ ተሽከርካሪ ወንበሮችና ኮሞዲኖ ያሉ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ
የመዋቢያ ቁሳቁሶች ተደርድረዋል፡፡ ዳያና መስታወቱ ፊት ለፊት ተሰየመች፡፡

መስታወት ስታይ የተከፋ ፊት አፈጠጠባት፡ ሉሉ ቤል ልክ ጸሃይ እንደሚጋርድ ደመና ሆናባታለች፡ የማርክን ልብ መውሰዷ ሳያንስ እሷን
እንደ ዕቃ ቆጥረው ፊት ነስተዋታል የሉሉ ዕድሜ ከማርክ ጋር
የሚቀራረብ ሲሆን ሉሉ አርባ ዓመት ያለፋት ትመስላለች ማርክ ሰላሳ
ዘጠኝ ዓመቱ ሲሆን ዳያና ገና ሰላሳ አራት ዓመቷ ነው፡ ማርክ የሉሉፀዘፀአት
ሁለቱም በፊልሙ ዓለም ይሰራሉ፣ አሜሪካውያን ናቸው፣ ሁለቱም በዲ
ጥረት አያደርጉም፡፡ ችግሩ ማርክና ሉሉ ብዙ የሚጋሩት ነር አላቸው:
ዕድሜ ያውቅ ይሆን? ወንዶች እንደዚህ አይነቱን ነገር ለማወቅ ብዙም
ድርጅት በአቅራቢነት ሰርተዋል፡፡ ዳያና ደግሞ እንደዚህ ያለውን ስራ ሰርታ
አታውቅም፡፡ እሷ የምታውቀው የአንድ የገጠር ከተማ ህብረተስብ አኗS
ሁልጊዜ እንደዚህ ነው ማለት ነው የሚኖረው
የምትሄደው እሱ አገር ነው፡፡ እሱ ሁሉንም ነገር ያውቃል ለእሷ ደግሞ
ሁሉ ነገር አዲስ ነው፡፡ ጓደኞቹን መቀላቀሏ አይቀርም፡፡ እሷ ደግሞ ከማርክ
በስተቀር የምታውቀው ሰው የለም፡ ሌሎች የሚያውቁትን ባለማወቋ ስንት
ጊዜ ይሳቅባት ይሆን? ትታው የመጣችው ህይወት ይናፍቃት ይሆን?
ከአዕምሮዋ
ማውጣት አለባት::
ነው፡፡ ከማርክ ጋር
ነገር አሁን
የነበርኩበት ዓለም አንገፍግፎኛል፤ ነፃነትና አዲስ ህይወትማ ስመኝ
እንደዚህ ያለውን
ኖርያለሁ: አሁን አግኝቸዋለሁ› ስትል አሰበች፡:
የማርክን ልብ ለማሸነፍ ጥረት ለማድረግ ወሰነች፡፡ ምን ልታደርግ ነው
ታዲያ? የምታሳየውን ባህሪ አልወደድኩትም ብላ ፊት ለፊት ልትጋፈጠው
አትደፍርም፡፡ ይህማ ደካማ ነች› ያስብላታል፡

እሱ እንዳደረገው ማድረግ ይኖርባታል፡፡ እሱ እሷን ዘግቶ ከሉሉ ጋ እንዳወራ ሁሉ እሷም ከሌላ ሰው ጋር ማውራት ይኖርባታል ቅናት ቢጤ ጠቅ ቢያደርገው፡፡ ታዲያ ያ ሰው ማን ይሁን?› ከመተላለፊያው ትይዩ
የተቀመጠው መልከ መልካም ወጣት ተስማሚ ይመስላል፡ በዕድሜ ከማርክ የሚያንስ ሲሆን ፈርጠም ያለ ነው፡፡ ይህን ሲያይ ማርክ ይንጨረጨራል።

በጆሮዎቿና በጡቶቿ ስር ሽቶ አርከፈከፈችና ከመዋቢያው ክፍል
ወጣች፡ ከንፈሮቿን ወሲብ ቀስቃሽ በሆነ ሁኔታ ከፈት አድርጋ የወንዶቹ የቀነዘረ፣ የሴቶቹ ደግሞ በቅናት ያበደ ዓይን እየገረፋት ዳሌዋን አለቅጥ እያውረገረገች አለፈች፡ አይሮፕላኑ ላይ እንደኔ ዓይነት ቆንጆ ሴት
የለችም፤ ሉሉ ቤል ደግሞ ይህን ታውቃለች› ስትል አሰበች።

መቀመጫዋን ትታ ወጣቱ ሰው ወደ ተቀመጠበት አምርታ በመስኮት አሻግራ ስትመለከት ወጣቱ አይቷት ፈገግ አለ፡፡

እሷም ፈገግ አለችና ‹‹ደስ አይልም?›› ስትል ወጣቱን ጠየቀችው፡

‹‹ደስ ይላል እንጂ›› አለና ልክ ፊት ለፊቱ ካለው ሰው ተግሳጽ የሚጠብቅ ይመስል ሰውየውን በፍርሃት አየት አደረገው፡፡

ዳያና ለጠቅ አርጋ ‹‹ሁለታችሁ አንድ ላይ ናችሁ?›› ብላ ጠየቀችው፡

ከወጣቱ ፊት ለፊት የተቀመጠው ራሰ በራ ሰው ‹‹አብረን ነው የምንሰራው›› በማለት አጠር ያለ መልስ ሰጠና እጁን ለሰላምታ ዘርግቶ
‹‹ኦሊስ ፊልድ እባላለሁ›› በማለት ራሱን አስተዋወቀ፡፡
‹‹ዳያና ላቭሴይ›› አለች ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ስትጨብጥ እየቀፈፋት ጥፍሮቹ ቆሽሸዋል፡ ፊቷን ወደ ወጣቱ አዞረች ‹‹ፍራንክ
ጎርደን እባላለሁ›› አላት፡

ሁለቱም አሜሪካውያን ናቸው፡ ፍራንክ ጎርደን ያማረ ሱፍ የለበሰ ሲሆን የኮቱ የላይኛው ኪስ ላይ የሃር ጨርቅ ሻጥ አድርጓል፡፡ አፉ ኮሎኝ ኮሎኝ ይሸታል፤ ሉጫ ጸጉሩ ደግሞ በቅባት ርሷል፡ ‹‹ታች የሚታየው አገር
ምን ይባላል?››

ዳያናም ሆነ ብላ ወጣቱ ሰው ላይ ደገፍ ብላ ሽቶዋን እያሸተተችው በመስኮት አየት አደረገችና ‹‹ዲቮን የሚባል ቦታ ሳይሆን አይቀርም›› አለችው:፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እሷም አገሩን አታውቀውም፡፡

‹‹አንቺስ ከየት ነው የመጣሽው ቆንጂት?›› ሲል ጠየቃት፡

ዳያና አጠገቡ ተቀመጠችና ‹‹ማንቼስተር›› አለችው፡፡

ወደ ማርክ አየት ስታደርግ ማርክ አይኑ ላይ የቅናት አስተያየት አየች፡ ፊቷን ቶሎ ወደ ጎርደን መልሳም ‹‹ማንቼስተር በሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ የምትገኝ ከተማ ናት›› አለችው:

ፊት ለፊት የተቀመጠው ኦሊስ ፊልድ ፊቱ ላይ መከፋቱ እየታወቀበት
ሲጋራ ሲለኩስ ዳያና ይባስ ብላ አንድ እግሯን ሌላው እግሯ ላይ ደረበችና
ተመቻችታ ቁጭ አለች፡

‹‹ወላጆቼ ከጣሊያን አገር የፈለሱ ናቸው›› አለ ጎርደን፡፡

‹‹አሁን ስልጣን ላይ ያለው የኢጣሊያ መንግስት ፋሺስት ነው›› አለች
ዳያና በፍጹም ገርነት ‹‹ኢጣልያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ
የምትገባ ይመስልሃል?›› ስትል ጠየቀችው:፡

ፍራንክ ጎርደን ራሱን በአሉታ ነቀነቀና ‹‹የኢጣሊያ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም›› አላት፡

‹‹ማን ጦርነት ይፈልጋል›› አለች ዳያና፡፡

‹‹እዚህም እዚያም ጦርነት የሆነው ለምንድነው ታዲያ?››

ዳያና ከዚህ ሰው ጋር መግባባት የምትችል አልመሰላትም፡ ሲያዩት
ሃብታም ቢመስልም ትምህርት የቀሰመ አይመስልም፡፡ ብዙ ወንዶች
ፈለገችም አልፈለገችም ዕውቀታቸውን ለእሷ ለማሳየት ሲጥሩ ይታያሉ፡
ይህ ሰው ግን እንደዚህ አይነት ሰው አይመስልም፡፡ ወደ ጓደኛው ዞረችና
‹‹ምን ይመስልሃል ሚስተር ፊልድ?›› ብላ ጠየቀች፡፡

‹‹ምንም የምሰጠው አስተያየት የለኝም›› ሲል የኩርፊያ መልስ ሰጠ፡፡

እንደገና ወደ ወጣቱ ሰው ፊቷን አዞረችና ፋሺስት መሪዎች ህዝባቸውን ጠፍሮ ለማቆየት ጦርነትን እንደመፍትሄ ሳይጠቀሙበት
አይቀርም›› አለች ወሬ ለማራዘም፡፡

እንደገና ወደ ማርክ ስትመለከት ከሉሉ ጋር ሞቅ ያለ ወሬ ይዘው እንደ
ልጃገረድ ተማሪዎች ያሽካካሉ፡፡ ብቸኝነት ተሰማት፡፡ ምን ነካው ማርክ?መርቪን ቢሆን ይህን ጊዜ ‹‹ተደፈርኩ›› ብሎ የፍራንክ ጎርደንን አፍንጫ
በቡጢ ያወልቀው ነበር› አለች በሆዷ።

አሁንም ወደ ጎርደን ፊቷን አዙራ ‹‹እስቲ ስለ ራስህ አውራኝ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡ ወዲያው ደግሞ የሱን ደባሪ መልስ መስማት አልፈለገችም:
ዴቭ ሻምፓኝና የተጠበሰ ዶሮ ይዞላት መጥቶ ገላገላት።

ለጥቂት ጊዜ የማርክንና የሉሉን ወሬ በምሬት ስታዳምጥ ቆይታ በሀሳብ
ጭልጥ ብላ ሄደች፡፡ ማርክ እንደሚወዳት እያወቀች በሉሉ መናደዷ ጅልነት
ነው፡፡ አሁን እነሱ የድሮውን ትዝታቸውን እያነሱ በመዝናናት ላይ ናቸው::
👍22😁1
በአሁኑ ሰዓት መርቪን የጻፈችለትን ማስታወሻ መቼም ሳያነብ አይቀርም፡፡ ይቺ አርባ አምስት ዓመት ሴት ማርክን ትነጥቀኛለች ብሎ ማሰብ ተላላነት ነው፡፡ በቅርቡ የአሜሪካውያንን አኗኗር ዘይቤ፣ የሚጠጡትን መጠጥ፣ የሬዲዮ ፕሮግራሞቻቸውንና ባህሪያቸውን ትላበሳለች፡፡ አፍታም ሳትቆይ ከማርክ የበለጡ ብዙ ጓደኞች ታፈራለች፤ ወንዶችን የሚስብ አንዳች
መስህብ አላት፡፡

አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የሚደረገውን ረጅም የአየር በረራ በጉጉት ጠብቃለች፡፡ ባየር በራሪው ጀልባ የሚደረገው ጉዞ በጣም አስደሳች መሆኑን
የሚገልጸውን የማንቼስተር ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገባ አንብባለች፡፡ ከአየርላንድ
ኒውፋውንድ ላንድ ካናዳ በአየር ለመጓዝ አስራ ሰባት ሰዓት ይፈጃል፡ በአየር
ላይ ራት እንደሚበላና ሌሊቱን በሙሉ እንደሚተኛ ሰምታለች፡፡ በአይሮፕላኑ
ላይ ብዙ የተወራለት የሙሽሮች ክፍል ውስጥ እንኳን ጥንድ አልጋ የለም::
የተሳፋሪዎች አልጋ ተደራራቢ መሆኑን አይታለች፡ ብዙ መቶ ሜትር
ከፍታ ላይ ከውቅያኖስ በላይ በሰማይ ላይ ተኝቶ መሄድ አስደሳች የሆነውን
ያህል አስፈሪም ነው፡፡ ከነአካቴው እንቅልፍ ይወስዳት እንደሆን እርግጠኛ አይደለችም: የአይሮፕላኑ ሞተሮች እሷ ተኛች አልተኛች መስራታቸው አይቀርም ወይም ደግሞ ተኝታ ሳለ ሊበላሹም ይችላሉ፡

በአይሮፕላኑ መስኮት ስታይ ከባህር በላይ እንደሚበሩ አወቀች አየርላንድ አካባቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡

አይሮፕላኑ ደመና ውስጥ ሲገባ ምንም ነገር አይታይም። አይሮፕላኑ
መንቀጥቀጥ ሲጀምር ተሳፋሪው በሙሉ በፍርሃት ተያየ፡፡ አስተናጋጆች
በየወንበሩ እየሄዱ የመቀመጫ ቀበቶአቸውን እንዲያስሩ ነገሩ፡፡ ዳያና
በደመናው ምክንያት መሬት አልታይ ሲላት ጭንቀት ውስጥ ገባች፡ ልዕልት
ላቪኒያ የወንበራቸውን ጫፍ የሙጢኝ አሉ፡ ማርክና ሉሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሁሉ ወሬያቸውን ይሰልቃሉ፡ ፍራንክ ጎርደንና ኦሊስ ፊልድ ሲጋራቸውን ይምጋሉ፡፡

ማርክ ‹‹ሙሬል ፌርፊልድ የት ደረሰች?›› ብሎ ሉሉን ሲጠይቅ አይሮፕላኑ እንደሚወድቅ ሁሉ ወደ ታች ዘጭ አለ፡፡ ዳያና ልክ ሆዷ
ጉሮሮዋጋ የተወተፈ መሰላት፡፡ በሌላኛው የአይሮፕላኑ ክፍለ አንድ ሰው ሲጮሀ ይሰማል፡፡ ትንሽ ቆየና መሬት ያረፈ እስኪመስል ድረስ አይሮፕላኑ ተስተካከለ፡

ሉሉም ‹‹ሙሬል ፌርፊልድማ ሚሊየነር አገባች፡፡››

‹‹አትቀልጂ›› አለ ማርክ ‹‹እሷ እኮ አስቀያሚ ናት እንዴት ቀናት ባክሽ ዳያና በዚህ ጊዜ ‹‹ፈራሁ ማርክ›› አለችው፡

ማርክ ወደ ዳያና ዞረና ‹‹አይዞሽ አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ይሆናል፡
የተለመደ ነው›› አላት፡

‹‹ ይሮፕላኑ የሚወድቅ ይመስላል›› አለች ዳያና
‹‹አይወድቅም››
ማርክ ወደ ሉሉ ዞረ፡ ሉሉ ዳያና አንድ ነገር ትላለች ብላ ብትጠብቅም ዳያና በንዴት ፊቷን አዞረች፡፡

ማርክም ቀጠለና ‹‹ሙሬል እንዴት ሚሊየነር ባል አገኘች ባክሽ?›› ሲል
ጠየቀ

‹‹እኔ እንጃ፧ ሰውየው ፊልም ላይ ኢንቨስት ያደርጋል፡፡››
ዳያና የማርክ ግድ የለሽነት አስፈራት፡፡ ምሽት ላይ አየርላንድን አልፈው አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ይበራሉ፡ መቼም አትላንቲክ ውቅያኖስ ቢሄዱት ቢሄዱት የማያልቅና ቀዝቀዛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በማንቼስተር
ጋርዲያን ጋዜጣ ላይ ባህሩ ላይ የሚታየው የበረዶ ቋጥኝ ብቻ እንደሆነ
አንብባለች፡ ደሴት ወይም ትንሽ መሬት ብታይ ምንኛ በወደደች የሚታየው አይሮፕላኑ፣ ጨረቃና ባህር ብቻ ነው።

ሁኔታው በሙሉ ጭንቀት ውስጥ ከቷታል፡፡ በአዕምሮዋ ሌላም ነገር
አሰበች አሜሪካ ደርሳ ግሩም ምግብ መብላት ተመኘች፡፡ ተደራራቢ አልጋ
ላይ መተኛት የልጅ ጨዋታ ሆኖባታል በሌላኛው የዓለም ጫፍ
ሲያይዋቸው የሚያፈዙት
የኒውዮርክ ህንፃዎች ይጠብቋታል፡፡ ወደ
ማታውቀው ዓለም የምታደርገው ጉዞ ግን አስፈሪ ሆኖባታል፡፡ ሻምፓኙን በአንድ ትንፋሽ ጨልጣ ሌላ ብትደግምም አልተረጋጋችም፡፡ ማርክና ሉሉ ስታያቸው አሁንም የእሷን በጭንቀት መወጠር ከምንም ሳይቆጥሩ
ቀደዳቸውን ቀጥለዋል፡ አልቅሽ አልቅሽ ቢላትም ከእምባዋ ጋር እየታገለች
ንዴቷን ቻል አደረገች፡፡ ትንሽ ቆይቶ አይሮፕላኑ ፎየንስ ያርፍና መሬት ላይ በእግሯ ትሄዳለች፡፡ ከዚያም እንደገና አይሮፕላኑ ላይ ይሳፈሩና አትላንቲክን አቋራጭ ጉዞ ያደርጋሉ፡

ብዚህ ሁኔታ አንድ ሰዓት እንኳን መታገስ አልችልም ሌሊቱን በሙሉ እንዴት ልሆን ነው ታዲያ? ጭንቀት ይገለኛል፤ ታዲያ ከዚህ ሌላ
ምን ማድረግ ይቻላል› ስትል አሰበች፡፡ፎየንስ ላይ ማንም ሰው አይሮፕላኑ ላይ እንድትወጣ ሊያስገድዳት
እንደማይችል ታውቃለች፡ ግን ላለመውጣት መፈለጓን
እርግጠኛ አይደለችም::

ማርክ በዚህች በጸጉር ቀለምና በሜክ አፕ እርጅናዋን ለመደበቅ
በምትሞክር ያጠረች ሴት አይኗ ስር በቁሙ ሲበላ ማየት አትሻም።

የማደርገውን አውቃለሁ፤ ለመርቪን እደውልለትና ይቅርታ አድርግልኝ
መርቪን ይቅር እንደሚላት እርግጠኛ በመሆኗ እፍረት ተሰማት ብታቆስለውም መመለሷን ሲያይ እቅፉ ውስጥ እንደሚጥላት ተማምናለች::
ሌላው ሀሳቧ ደግሞ ይህ እንዲሆን እንደማትፈልግ፣ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ የምትወደውን ማርክን አግብታ መኖር እንዳለባት ይሞግታታል።

ደግሞ ሌላው ሃሳቧ ይህን ማሰቧ ጅልነት እንደሆነ፣ እሷ የመርቪን ላቭሴይ የህግ ሚስት፣ የቲያ እህትና የሁለቱ ልጆቿ አክስት እንደሆነችና አገሯም ማንቼስተር ኢንግላንድ እንደሆነ፣ ከእሷ ይልቅ ለስራው ቅድሚያ የሚሰጥ አናዳጅ ግን ታማኝ ባል እንዳላት፣ብዙ ሴቶችም ትዳራቸው እንደዚሁ ዓይነት እንደሆነና ይህም የተለመደ መሆኑን፣ ሁሉም ሚስቶች
በኑሯቸው ብስጩ ቢሆኑም ከአንዳንድ ሰካራምና የማይረቡ ባሎች ካገቡ
ሴቶች እንደምትሻል፣ እርስ በእርሳቸው እንደሚተዛዘኑና በየሱፐርማርኬቱ
እየዞሩ እቃ መግዛትና ጸጉር ቤት መሄድ ብቻ እጣ ፈንታቸው እንደሆነ
የተቀበሉ ስለሆነ አሜሪካ መሄድ የግድ እንዳልሆነ ራሷን ለማሳመን
ሞከረች፡፡.....

ይቀጥላል
👍26🥰2
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ የመርቪን ላቭሌይ ባለቤት ዳያና በደስታ ተፍነክንካለች በመጀመሪያ የሰማይ በራሪው ጀልባ መሬት ለቆ ሰማይ ላይ ሲወጣ ፈርታ ነበር አሁን ግን እየለመደችው መጣችና ደስ ይላት ጀመር ላቭሴይ በአይሮፕላኑ እንድትበር ዕድል ባይሰጣትም አይሮፕላኗን ብዙ ቀናት ፈጅታ ቀለም የቀባቻት እሷ ነች አንድ ጊዜ እስኪወጣ ነው እንጂ የሚያስፈራው…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ሰባት (17)

የውስጥ ስልክ ተደውሎ ጆርጅ ኮሎዌ የውጭ ስልክ እንደሚፈልገው ነገረው ። የቴሌፎኑ ጭርርታ እስኪቀሰቅሰው ድረስ በስራው ላይ ስለተመሰጠ ምንም ነገር አይሰማውም ነበር ፣፤ ማይክል ሂልያርድ ። ለአምስት ወይም ለስድስት ሰዓት ያህል ያለማቋረጥ የወረደው በረዶ በቀለጠ በረዶ ድጥ የተጥለቀለቁትን መንገዶች ይበልጥ እያጥለቀለቀ ሲወርድ እንኳ ማይክል ሂልያርድ ወላ ሀንቲ ነገር አልሰማም ። ስራ የገባው ከንጋቱ አስራ ሁለት ስዓት ላይ ቢሆንም ፡ ስልኩ የተደወለለት ከሰዓት በኋላ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ቢሆንም ፡ ማይክል ግን ከቢሮውም አልወጣ ፤ ከስራውም ላይ ንቅንቅ አላለም ነበር ። የውጭ ጥሪ መቀበያውን ስልክ በግራ እጁ ሲያነሳ እንኳ ቀኝ እጁ ስራ አልፈታም ። በፖስታ የሚላኩ ደብዳቤዎች ተቆልለው ነበረና እየፈረመ ነበር ስልኩን ያነሳው። የስራ ብዛት። የስራ ብዛት ። የስራ ብዛት… ማይክል ሂልያርድ ትንፋሹን አስተካክሎ የሚተነፍስበት ጊዜ አልነበረውም። ያአንድ ሰሞን ቁም ስቅሉን አሳጥቶት የነበረው የካንሳስ ሲቲ ፕሮጀክት አሁን አያስቸግረውም ። ከሱ ትከሻ ላይ ወርዷል። አሁን ደግሞ የሀውስተኑ ፕሮጀክት ነው የሚያባዝነው ። ይኸ ሲያልቅ ደግሞ ያ የሳንፍራንሲስኮ የሕክምና ማእከል ይተካና ራስ ምታት ይሆንበታል ። ግን ስራ ጥሩ ነው፡፡ አለመቦዘኑ ነው እስከ ዛሬ ቆሞ እንዲሄድ የረዳው ። አምላክ ምስጋና ይግባው ።

«ጆርጅ ነህ ? ማይክል ነኝ ። ምን ነገር ተፈጠረ ?››
« እናትህ ይደውልልኝ ስላለችኝ ነው » አለ የጆርጅ ኮሎዌ
«ስብሰባው ተፈፀመ?»
«አላለቀም። እሷ አሁንም እስብሰባው ላይ ነች »
«እሺ»
«በረዶው ጋብ ካለ ዛሬውኑ ከቦስተን እንመለሳለን፤ጋብ ካላለ ግን ነገ እንመጣለን ብለህ ንገረው ስላለችኝ ነው የደወልኩልህ»
«በረዶ እየጣለ ነው እንዴ ቦስተን?»
«ቦስተን ምንም በረዶ የለም። ግን ኒውዮርክ ዶፉን እያወረደው ነው ብለው ነገሩን… ውሽት ነው እንዴ?» ማይክል ገርገብ ብሎ ወደውጭ ተመለከተ፤ በመስኮት በኩል። ያወርደዋል ፤ ዶፉን ። የመገረም ፈገግታ ለመናገሪያው እያሳዬ… «እውነትም ዶፋን እያወረደው ነው። አልተሰማኝም ነበር። ቀና አላልኩም… ይቅርታ» ጆርጅ ኮሎዌ ይህን ሲሰማ ይህ ልጅ በዚህ ሁኔታ እየሰራ ምኑን ሰው ሆነው? ያው እንደ እናቱ በስራ ብዛት ሰውነቱንም ጤናውንም ሊጨርስ ነው እንጂ ሲል አሰበ ። ከዚያም በመገረም ባጭሩ ስቆ «እንግዲህ እንዲያ ከሆነ ነገ ያው ገና አይደለም ? ራት አብረን ስለምንበላ እንድትገኝ ብላሃለች ። ሌሎች እንግዶችም እንዳሉ ነግራኛለች፡፡ እንዳትቀር አደራ በለው ብላ አጥብቃ ነው የነገረችኝ። ሌሎች ጥቂት ሰዎች አሉ ማይክል ትንፋሹን ውጦ በረጅሙ እያስወጣ ፤ ይኸኔ ሰላሳ ወይም አርባ ሰዎች ይሆናሉ።
«ጀርጅ ይቅርታ ትጠይቅልኛለህ።ቀደም ያለ ቀጠሮ አለኝ» አለ ማይክል፤ለስልኩ መናገሪያ ። «አለህ?» አለ ጀርጅ በአድናቆት በተዋጠ ድምፅ። «ይገርምሀል ከሣምንት በፊት የተያዝ ቀጠሮ ነው። ባለፈው ሳምንት ልነግራት አስቤ ረሳሁት ። ይኸ የሀውስተን ማዕከል ጉዳይ አያፈናፍንም እንደምታየው ። አሁንም ግዴለም ኣንተ ንገራት… ይገባታል»

የሀውስተንን ማዕከል ጉዳይ እንዴት ቀጥ አድርጎ እንደያዘላት ታውቃለች። ቢያንስ በስራው ላይ ከገመተችው በላይ የሆኑ ነገሮችን በመፈፀምና በማድረግ ደስ እንዳሰኛት ርግጠኛ ነው «ሌላው እንግዲህ ሌላ ነው። ሌላውም ሊገባት ይገባል፣ አለ በሀሳቡ። «መቼም ቅር እንደሚላት የታወቀ ነው» አለ ጆርጅ «ሆኖም ቀጠሮ እንዳለህ ማወቁ ራሱ የሚያስደስታትም ይመስለኛል ። ቀጠሮውስ እንዴት ነው? መቼም ደስ የሚል መሆን አለበት… ይመስለኛል»
«በጣም በጣም ሀሪፍ ነው»
«እንዴት ነው… ከልብ የሆነ ነገር ነው?»

በጆርጅ ድምፅ ውስጥ መጨነቁን ሰማበት ። በቃ እኮ ምንም ነገር ቢመጣ ማፍተልተላቸው አይቀርም አለ በሀሳቡ። «አይ! አይ! ይህን ያህል የሚያሳስበን ነገር አይደለም ። አለ አይደል ጊዜያዊ ሆይ ሆይ የዚያ አይነት ነገር ነው» አለ ማይክል። «እንዲያ ከሆነ ማለፊያ በል እንግዲህ በአሉን የደስታና የፈንጠዝያ ያድርግልህ ማይክ»
«ላንተም እንደዚያው ። እማዬን ሳምልኝ ። ነገ እደውልልሻለሁ በላት »
«ይሁን ። እነግራታለሁ » ስልኩን እንደዘጋ የጆርጅ ኮልዌ ገፅታ በፈገግታ አበባ አጌጠ። በቃ አሁን ሊመለስ ነው ማለት ነው፤የሚል ሀሳብ መጣበት ።

ከናንሲ ጋር ባለፈው የመፀው ወራት የደረሰበት አደጋ፤ የሚወዳትን ልጅ ማጣቱን ሲሰማ ያደረበት የመንፈስ መናወፅና መዳከም፤ እንዲህ በቀላሉ የሚሽር አይመስልም ነበረና ሁኔታውን ባዬ ቁጥር ጆርጅ ይከፋው ነበር። እንዲሀ ወጣ ወጣ ካለ የመንፈስ ስብራቱ ቀስ በቀስ ሊሽርለት ይችላል ። ስለገና እለት የራት ግብዣ ምንም አትልም ። ለጊዜው ቡራ ከረዩ ማለቷ አይቀርም ይሆናል ። ግን ደግሞ ይህ እሱ ያየው ነገር ለሷም ተስፋ ይሰጣታል። ምንስ ቢሆን ወጣት አደል ፤ አፍለኛ ወጣት ጊዜው ነው ። እንደተመቸው መጨፈርን ሊነፈግ አይገባውም ። ይህን ማሪዮንም አታጣው ። ትዝ አለው ያ እድሜ ። ሐሳቡም ምን ጊዜም ያን እድሜ ሲያስብ ወደ ሚፈስበት አቅጣጫ ሄደ ። ወደ ኋላ ፤ ወደ ማሪዮን ሂልያርድ ።

እማይክል ቢሮ ውስጥ ስልኩ ተንጫረረ ። ቤን አቭሪ ነበር የደወለው ። ያንለት ጉዳይ ይኑረው ወይም አይኑረው ለማወቅ ነበረ የደወለው። ማይክል እናቱ ዘንድ መድረስ እንዳለበት ነገረው። አሰልቺ ቢሆንም ያው ስለሚጠበቅበት ማድረግ ያለበት ጉዳይ እንደሆነ አስረዳው። ከዚያ ቀጥሎ ባለጉዳዮች ይደውሉለት ጀመር ። እያከታተሉ ። አንዱ እንኳን አደረሰህ ይላል ፤ ሌላው ቅሬታውን ያወርደዋል ። ሌላው ምስጋናውን ያዥጐደጉደዋል ። ስልኩን አስቀምጦ… ሁልህም እንጦሮጦስ ውረድ !? አለና ስራውን ሊቀጥል ሲል አንድ እንግዳ ድምፅ ሰማና ቀና አለ። የህንፃዎች የውስጥ አሰራር ንድፍ ባለሙያ የሆነችው የድርጅቱ ሰራተኛ ነበረች እቢሮው በር ላይ ቆማ የምትስቀው ።ይህች ልጅ የምትሰራው በቤን አቭሪ ስር ሲሆን የቀጠራትም ራሱ ቤን ነበር፡፡ የዳማ ጭራ የመሰለው ጸጉሯ ንፋስ እንደሚያስሮጠው የዘረዘረ ጤፍ አባጣ ጎባጣ ሰርቶ ይወርድና እትከሻዋ ላይ ይረፈረፋል ። ልስልስ ያለ ቆዳዋና ሰማያዊ ቀለም ያለው አይና የሚደነቁ ናቸው።ይህ ሁሉ ቢባልም ለማይክል ሂልያርድ ሰራተኛ መሆኗ እንጃ ውበቷ ታይቶት አያውቅም ። ውሳኔ የሚሰጥበት ወይም ሊፈርምበት የሚገባው ነገር ካልሆነና እጠረጴዛው ላይ ካልተቀመጠ በስተቀር ምንም ነገር አይታየውም ፡ ውበትም ።
👍161
«ሰዎችን ሁሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ የምትላቸው በዚህ እይነት ሁኔታ ነው?» አለች በፊቱ ላይ ያለውን አድናቆት በመጠቆም።
« አዎ አንዳንድ ሰዎችን» አለ ። ምንድነው እምትፈልገው? ይህን ያህል እውቂያ የላቸውም ። በስራም ቢሆን በቀጥታ እሚያገናኛቸው ነገር የለም ። «ምን ልታዘዝ ሚስ» አለና አቋረጠ ። ይኸ የተረገመ አንጎል እሚሉት ነገር !ስሟ ጠፋበት ። ይህ የገባት ቆንጆ ፤ «ዌንዲ… ዌንዲ ታውንሴንድ» ብላ ስሟን ነገረችው ። «ለማዘዝ መታዘዝ ሳይሆን ፤ ለብርሃነ ልደቱ እንኳን አደረሰህ ልልህ ነው የመጣሁት »
«ነው ? አሃ ተጠምቆ እማይነጻ የተዋጣለት ገብጋባ ነው አላሉሽም? ደቡር ነው ብለው አልነገሩሽም ?»
«ባይነግሩኝም ሳይገባኝ አልቀረም ። ለምሳሌ ባለፈው ጊዜ ሠራተኞች ባዘጋጁት ፓርቲ ላይ አልተገኘህም። የገናን በአል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የራት ምሽት ላይም አልነበርክም ። ከሰው የምስማው ሌላ ነው ፤ ይሰራል፡ ይሰራል፤ ይሰራል ነው »
«ሥራ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል ቢሉኝ ነዋ»
«ይሆናል ፤ግን ሌሎች ነገሮችም ያው ናቸው»

በዚህ ጊዜ እቢሮው ገብታ እፊት ለፊቱ ባለው ወንበር ላይ ተቀምጣ ነበር፡፡ ቀና ሲል አንደኛውን እግሯን አንስታ እሌላኛው ላይ አነባበረችው ። እግሮቿ በጣም ያምራሉ ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍7
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ው

በፉጨት የሚጋልብ ከባድ ንፋስ መለል ያሉትን ረጃጅም ዛፎች እየለመጠ ሰፋፊ ቅርንፎቻቸውን አያወዛወዘ ቅርንጫፍን ከቅርንጫፍ እያላተመ
አዋከበው » ቅጠል ከቅጠል እያማታ ኢስት ሊንና አካባቢውን አዋከበ

ድምፁ የሚያሳዝን አመጣጡ የሚያስፈራ ቅጽበታዊ ነፋስ ተለዋወጠ " ዝናብ አዘል ዳመናዎች ተጠረቃቀሙ » በዚያ ቅዳሜ ምሽት ብቻውን
ይጓዝ የነበረ አንድ የሩቅ መንገደኛ ዝናቡ ከመንገድ እንዳይዘው እያሰበ › በእግሩ
ይኳትናል ሰውየው የመርከበኛ ልብስ ለብሷል " ከሰማያዊው አንገትያው በላይ ያለውን አንገቱንና ፊቱን ቸምቸም ያለው ጢሙ ሸፍኖታል " ከግንባሩ ዝቅ አድርጎ የደፋው ባርኔጣው ለጢሙ ተጨማሪ ሆኖ ጋርዶታል ሰፊና ሸካራው ሱሪውን በቀበቶ አጥብቆ ታጥቆ አጭር ሰፊና ወፍራም የመርከበኛ ሱፍ ካፖርት ደርቦ እየተወዛወዘ ቢን ሌን ደረሰ » ቀደም ሲልም በዚህ ታሪክ የተወሳው ቢን ሌን ስላች
መንገድ ነው ። ከዚያ ቀጥሎ እግር በማይበዛበት በአንድ ትንሽ በር ዐልፎ ከኢስት ሊን ምድረ ግቢ
ገባ ።

የገባበትን በር መልሶ ዘጋው መወርወርያውን ቀረቀረው ከዚያ በየት በኩል
መሔድ እንደሚገባው ቆም ብሎ አሰላሰለ "ቆይ እስቲ” አለ ለራሱ » “ በዛፎቹ
የተሸፈነ መንገድ ያለችኝ በግራሮቹ አጠገብ ሳይሆን አይቀርም ስለዚህ ወደ ቀኝ
መታጠፍ አለብኝ " ለመሆኑ ከሁለቱ አንዱ እየጠበቁኝ ይሆን ?”"

አውነትም ባርባራን የምሽት አየር ለመቀበል የወጣች መስላ ስትንጐራደድ
አገኛት " የናፍቆታቸውን ተናንቀው ተሳሳሙ " ሁለቱንም ሲቃ ተናነቃቸው "
ባርባራ እንደ ትንሽ ልጅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች " እንቅ አድርጎ ይዟት የነበረውን ለቀቃትና ትክ ብሉ አያት "

“ ታዲያስ ባርባራ ! በቃ አሁን አግብተሽ ትዳር ይዘሽ ተቀምጠሻል !”

“ አዎን በትዳሬም ደስተኛ ነኝ " ያንተ ነገር እየተደቀነብኝ ከማዘኔ በቀር
ምንም የጐደለብኝ የለም " ብታየው በጣም የሚያሳሳ ልጅ ወልጃለሁ እሱም
አሁን አንድ ዓመት ሊሞላው ነው " በቅርቡ ደግሞ ሁለተኛ ልጄን እወልዳለሁ ”

ሰዎቻችንሳ እንደ ምን ናቸው ?”

“ ደኅና ናቸው » እማማም ከቅርብ ጊዜ ወዲሀ በጎ ናት

" ዛሬ ግን ያንተን መምጣት አላወቀችም "

“ዛሬስ እሷን ማየት አለብኝ ከዚህ ቀደም ሳላያት መሔዴን ታስታውሻለሽ የለ?”

“ ሁሉም በጊዜው ይሆናል " የሊቨርፑል ኑሮስ እንዴት ይዞሃል ? እዚያ ምን
ትሠራለህ ?”

“ አጥብቀሽ አትጠይቂኝ ባርባራ " የተወሰነ ሥራ የለኝም " ያገኘሁትን
እሠራለሁ " ከዚህ በምትሰጡኝ እየተደገፍኩ እኖራለሁ " ግን ለምንድነ© ወደዚህ የጠራሽኝ ? ምን አዲስ ነገር ተገኘ ?”

“ እውን ቶርን እዚህ ብታየው ግን ታውቀዋለህ ?

“ ታውቀዋለህ ወይ ! ምኑ ይጠየቃል ? ”

“ ዌስት ሊን ላይ የሕዝብ እንደራሴነት ምርጫ በመካሔድ ላይ መሆኑን ታውቃለህ?

“ አዎን ሚስተር ካርላይልና ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን እንደሚወዳደሩ ከጋዜጣ አንብቢያለሁ።

“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን እንዴት ልታውቀው እንደ ቻልክ ልትነግረኝ ትችላለህ
· ሪቻርድ ? ”

“ እሱንማ ዐውዋዋለሁ ከቶርን ጋር ሁለት ጊዜ አይቸዋለሁ „ “

“ እኔ የምልህ እንዴት ልታውቀው ቻልክ ? ”🍾

“ ቶርንን ከአንድ ሰው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አየሁትና አጠገቤ የነበረውን
አንድ ታንኳ ቀዛፊ በእጄ እያሳየሁ ያውቀው እንደሆነ ጠየቅሁት " እኔ ያመለከትኩትን ሰውዬ እንደሚያውቀውና ካጠገቡ የነበረውን ግን ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ነገረኝ

“ እንግዲያውስ ሪቻርድ አንተና ታንኳኛው አንድ የሆነ ስሕተት አድርጋችኋል " ወይ አንተ ስታሳየው ወይ ደግሞ እሱ ያልጠየቅኸውን ሰው ሲያሳይህ አስተውለህ አላየኽውም እንጂ ' ቶርን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ራሱ ነው

“ ምን ማለትሽ ነው ... ባርባራ ” አላት ዐይኖቹን አፍጥጦ እያያት

"ነው አለችና ራሱ ሪቻርድ ቢን ሌን ላይ አየሁት ካለበት ጊዜ ጀምሮ ስትጠረጥረው እንደ ኖረችና፡ ከዚያም በመጨረሻ ይፈለግ የነበረው ቶርን ራሱ ፍራንሲዝ ሌቪስን ለመሆኑ ኦትዌይ ቤቴልና ኧበንዘር ጄምስ ለይተው እንዳወቁት አብራርታ ነገረችው

ሁለቱም ሊያወቁት ይችላሉ ” አለ ሪቻርድ " ጄምስ ራሱ ሆልጆን ዘን ይሹለከለክ ስለ ነበር ቶርንን ብዙ ጊዜ አይቶታል" ኦትዌይ ቤቴልም በፊት ቢክድም አይቶት ሊሆን ይችላል - ”

ሪቻርድ ከሩቅ አንድ ሰው ሲመጣ ሲያይ ጊዜ ጥሏት ሮጠና ከአንዱ ቁጥቋጦ
ውስጥ ድርግም አለ » ባርባራ ሣቅ አለች " ለካስ ሚስተር ካርይል ኖሯል "

“ ዛሬም ትፈራለህ ሪቻርድ ? ” አለው ሲጨብጠው „ “ ዛሬስ የመንገድ ልብስህን ለውጠሃል።

በፊት ስለብሰው የነበረው ስለ ታወቀብኝ ለብሸው ለመምጣት ፈራሁ "
ስለዚህ ይህን በሁለት ፓውንድ ገዛሁ ”

ጸጉሩንም ጢሙንም ጭምር ነው ?

ጸጉሩማ እንዳዲስ ተበጥሮና ዘይት ተቀብቶ ነው እንጂ የድሮው ነው
ጸጉር አስተካካዩም የውሸት ጢሙን አበጃጅቶ የራሱንም ጸጉር ከርክሞ አንድ ሽልንግ አስከፈለኝ ሚስተር ካርላይል ... ባርባራ አረመኔው ቶርን ሌቪሰን ሆኖተገኘ ትለኛለች "

" አዝማሚያ ይመስላል ቢሆንም አንዳች ነገር ከመደረጉ በፊት አንተም
ሊቪስንን በዐይንህ አይተህ ማረጋግጥ አለብህ " ወደ ቨን ሆቴል ብቅ ብትል ሲገባ
ሲወጣ በቀላሉ ታየዋለህ ደሞ ዛሬ ሰው ሁሉ ልቡን ወደ ምርጫው ስለ አደረገ
የሚያውቅህም የሚያስብህም አይኖርም " ስለዚህ በጥንቃቄ አስተውለህ አረጋግጠህ ና አለው ሚስተር ካርላይል "
“ ቶርን መሆኑን ካረጋጥኩ በኋላ ምን እርምጃዎች ይወሰዳሉ ?

"ችግሩ እዚህ ላይ ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ ክሱን የሚመሠርተው ከዚያም ጉዳዬን የሚከታተለው ማን ነው ?

“ እሱንማ አንተ ራስህ ነህ... ሪቻርድ " እኔ በዚህ ነገር በጣም አስቤበታለሁ
የምትከታተለው አንተው ነህ
“ አንተ ልትይዘው አትችልም
ሚስተር ካርላይል ? ''

“አልችልም !ሌቪሰን ከሆነ እንዴት አድርጌ ?” አለው "
ዐፈር ይብላ ይህ ርኩስ ” አለ ሬቻርድ በንዴት " ግን እሱ ቢሆን ምን ቸገረህ
ሚስተር ካርላይል ? ብዙ የተበደሉ ሰዎች ጠላታቸው በአጃቸው ሲገባ ለመበቀል ሲጣደፉ አይተሃል "

“ በሆሊጆን በተፈጸመው ወንጀል ፍርዱ እስከሚፈጸምበት ሰገነት ድረስ ልክታተለው እችላለሁ ስለ ራሴ በደል ግን አልሞክረውም" ወደ ዌስት ሊን ከመጣበት ጀምሮ ራሴን ለመቁጣጠርና ለመታገሥ ኃይለኛና አስቸጋሪ ትግል ባላደርግ ኖሮ ነፍሱ እስኪ ወጣ አስገርፈው ነበር "

“ ታዲያ ነፍሱ እስኪወጣ ብታስገፈው ዋጋውን አገኘ ኮ ነው የሚባለው ” አለው ሪቻርድ "

ለግድያው ተጠያቂ መሆኑን አምናለሁ ነገር ግን እኔ እጄን አንሥቸበት ወደ አሳፋሪ ሞት ከምሰደው ያነሣሁትን እጄን ቆርጦ ብጥለው እመርጣለሁ።ምክንያቱም የሰውዬውን የነፍስ ማጥፋት ወንጀል በኔ ላይ ከፈጸመው በደል ልለየው
አልችልምና " በሆሊጆን ሕይወት ብከታተለውም የሌላም ሕይወት ያጠፋ ለመሆኑ ሊሰወር አይችልም ሁልጊዜ አዛኝ የሆነው ዓለምም ለሚስተር ካርላይል ደስታውን
የሚገልጽበት በሚስተር ሆሊጆን ገጻይ ሳላስፈረደበት ሳይሆን ለተዋለበት ግፍ ብድሩን ስለ መለስ ይሆናል" ስለዚህ ነው በዚህ ነገር አልገባም
ሪቻርድ....

“ እሺ አንተስ ተወው ባርባራ ልትከታተልልኝ አትችልም ? " አላው "
ባርባራ ክንዶቿን ከባሏ ክንዶች ጋር አቆላልፋ ቁማ ትሰማለች "
“ ባርባራማ የኔ ሚስት ናት "
“ እንግዲህ ነገሩ ለመገለጽ ተስፋ የለውም " እኔም ተስፋ ቆርጬ ልሒድ ”
👍6
“ የለም” አለው ሚስተር ካርላይል : “ ጉዳይህን ሊከታተሉልህ የሚገባቸው
አባትህ ነበሩ " ግን እንደማያደርጉት እናውቃለን " እናትህም ጤናም ጉልበትም የላቸውም » ከባላቸው ፈቃድ ወጥተው ሊያደርጉልህ አይችሉም " እኔም እጆቼ ታስረዋል " ባርባራም የኔ አካል ስለ ሆነች ቁጥሯ ከኔ ነው ስለዚህ አንተ ብቻ ነህ የቀረህ " ይህን አጉል ፍራትህን ወዲያ ጥለህ ለጥቂት ቀኖች በዚህ አካባቢ መሰንበት አለብህ " ከዚህ አንድ ሁለት ማይል ወጣ ብሎ የምትገባበት ቤት እንዳለህ ነግረህኝ ነበር "

“ እሱስ አለ እኔ ግን ሙሉ ደኅንነት የሚሰማኝ ከዚህ አገር ጨርሸ ስርቅ ነው "
“ ስለዚህ ሁለት ሦስት ቀን ከዚያው ሰንብተህ ነገሩን እንዲከታተሉት ለቦልና ትፊድማን ታመለክታለህ ”
የምትለው ነገር አልገባኝም
ሚስተር ካርላይል ሰተት ብለህ ሔደህ እጅህን ለፍርድ ቤት ስጥ ብትለኝ አይሻልም ቦልና ትሬድማን ገና ሲያዩኝ ነው አንጠልጥለው ለፍርድ የሚያቀርቡኝ "

“እንደሱ አይደለም አንተ እንደ ማንም በግልጽ ወደ ቢሮአቸው አትሔድም" መጀመሪያ ከሚስተር ቦል ጋር ተወዳጅ እሱ ቀና ሰው ለመሆን ከፈለገ ቀና መሆን
ይችላል " ታሪክህን በሙሉ ንገረውና ሊከታተልልህ ይችል እንደሆነ ጠይቀው "
የአንተን ንጹሕነት የዚያኛውን ሰው ጥፋተኝነት ከምታስጨብጠው መረጃ በመረዳት ካመነበት ጥያቄህን ይቀበልሃል ለመጀመሪያ ጊዜ ትሬድማን ነገሩን ማወቅ አያስፈልገውም " ቦል ነግሮቹን ሲያንቀሳቅስም ያለህበትን ማወቅ አያስፈልውም"

“ቦልን እንኳን አልጠላውም አንድ ጊዜ ቃሉን ከሰጠ ይፈጽመዋል " ችግሩ ግን” አለ ሪቻርድ “
ማነው ቃል የሚያስገባው ?”

«እኔ አስገባዋለሁ ” አለ ሚስተር ካርላይል “ እስከሱ ድረስ ያለውን መንገድ እጠርግልሃለሁ " ከዚያ በኋላ የኔ ጣልቃ መግባት ያቆማል

“አሁን እንግዲህ በጀመሪያ የማደርገው ምንድነው?”
አለ ሪቻርድ "

« አሁን ወደምትደበቅበት ቦታሀ ሒድና እስከ ሰኞ ቆይ "ሰኞ ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ወደዚህ ትመጣለህ " እኔ ደግሞ አስከዚያ ድረስ ሚስተር ቦልን አነጋግረዋለ " ግን አየህ ከቦል ጋር ከመነጋገሬ በፊት ቶርንና ሌቪሰን አንድ ሰው
መሆናቸውን ካንተ ለመስማት እፈልጋለሁ "

“ እሺ አሁን ወደ ሬቨን ሔጄ እንዳየሁት ወዲያውኑ እመለሳለሁ ” አለና ሊሔድ ሲጀምር ባርባራ አቆመችው "

“ አይደክምህም ... ሪቻርድ ?” አለችው "

“ቶርን ለመታወቅ ቁሞ ይጠብቃል ካሉኝ አንድ መቶ ማይል በእግሬ ብሔድም አልደክምም "

“ መቸም ከቤት ልናስገባህም አልደፈርንም ባይሆን የምትበላውና የምትጠጣው እዚህ ድረስ ላምጣልህ …”

“ከዌስት ሊን ቀጥሎ ካለው ባቡር ጣቢያ ወረድኩና ካንድ ምግብ ቤት ገብቼ ደኅና ራት አግኝቼ በላሁ ስለዚህ ተይኝ ልሒድ ”

ሪቻርድ ሬቨን ደርሶ ገና ቆም ከማለቱ ሁለት ሰዎች እጅ ለእጅ ተያይዘው ወጡ • • • የሌሺሰን ማረፊያና አካባቢው በዘዋሪዎችና በወሬ አናፋሾች ተሞልተው ነበር " ሪቻርድ ሔርም ባርጣውን ዝቅ አድርጎ ከነሱ ተቀላቀለ እነዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው የወጡት ሁለት ሰዎች ሰዉ ወደ በረከተበት ሲጠጉ ደጋፊዎቹ ምን ጊዜም ሌቪሰን የሚል ድምፅ ያስሟቸው ጀመር "
ሪቻርድ አብሮ አልጮኸም " ጭንቅ ጭንቅ አለው " ልቡ በጣም መታ የትኛው መሆኑ ቢምታታበትም ከነዚያ ሁለት ሰዎች አንዱ ቶርን እንደ ነበር ዐውቋል "
ሁለተኛው ደግሞ ለንደን ''ሰር ፍራንሲሰ ሊቪሰን ነው ተብሎ የተጠቆመለት ሰውዬ ነው

“ ከነዚህ ሁለቱ ሌቪስን የትኛው ነው ? አለው ባጠግቡ ቆሞ የነበረውን አንዱን ሰውዬ

አታውቀውም ?ባርኔጣውን አንሥቶ እጅ በመንሣት ያመሰገነን ነው እኮ ”
ከዚህ በላይ መጠየቅ አላስፈለገውም እሱ የሚያውቀው ቶርን መሆኑን አረጋገጠ "

ሁለተኛውስ ማነው ? ” አለ ሪቻርድ "
ከለንደን አብሮት የመጣ መኮንን ነው " ድሬክ ይባላል" ግን አንተ መርከበኛ ... ብጫ ነህ ወይስ ቀይና ወይን ጠጅ ? '' አለው "

“ ከሁሉም የለሁም። በከተማው ዐልፌ የምሔድ መንግደኛ ነኝ” አለ ሪቻርድ
“ ዱርዬ ነህ ? "
" ዱርዬ ! አይደለሁም ” አለና ያየውን ለሚስተር ካርላይል ለመንገር ወደ ኢስት ሊን አመራ "

ሳቤላ ከሐሳብ ብዛት ከጸጸት ጥናት የተነሣ የመንፈስ ዕረፍት አጣች " ከቤት ተቀምጣ ጭንቅንቅ አላት " ልጆቹ ወደ መኝታቸው ከሔዱ በኋላ ከቤት ቁጭ ማለቴ
አልቻላት አለና ሆድ ሆዷን ሲፊጃት የነበረውን እሳት ያበርድላት ይመስል ሹልክ ብላ ወጥታ በዚያ አቅል በሚያጠፋ ኃይለኛ ነፋስ መኻል በምድረ ግቢው ትንሸራሸር ጀመር አንዱን መንገድ ተከትላ ልትጠመዘዝ ስትል አንድ መርከበኛ ልብስ የለበሰ ሰው ኘየች " እሷም ለራሷ ልትታይ ስለ አልፈለገች ሰውየው እንዳለፈ ተመልሳ መንገዷን እስክትይዝ ድረስ ዛፎቹ መኻል ገብታ ተገን ያዘች » ማን እንደሆነ ምን ጉዳይ እንዳመጣው እያሰበች በመገረም ትመለከተዋለች "

እሱ ግን ሳቤላ እንዳሰበችው አላለፈም " ከዚያው ትንሽ እንደቆየ ሚስዝ ካርላይል መጣችና ተቃቅፈው ሲሳሳሙ አየቻቸው

ሌላ ሰው መሳም ! ሚስዝ ካርላይል ! አለችና ሳቤላ ደሟ ፈልቶ እስከ ጭንቅላቷ ወረራት " " ሁለተኛ ሚስቱም በሱ ላይ ልትወሰልትበት ነው ? እሷም እንደገና ተዋርዳ ከኢስት ሊን ልትወጣ ነው ? እያለች ተገረመች “ ዳሩ ምን ቸገረኝ ለኔ ምኔ ነው? ከእንግዲህ የኔን ዕድል አንዲት ቅንጣት ያህል እንኳን ፈቀቅ አያደርገውም " እያለች ' በገዛ ጥፋቷ ' ከእጅዋ አውጥታ ካንገቷ ፈትታ የጣለችውን የባሏን ፍቅር ፍቅር እንደማይመስላት አስባ ተወችው።

መርከበኛዉ ወገቧን ይዞ በመንገዱ መንጐራደድ ጀመሩ " ትንሽ ቆይቶ ሚስተር ካርላይል መጣና ተቀላቀለ መርከበኛዉና ባርባራ እንደ ተያያዙ ወግ ጀመሩ ሳቤላ የነበረውንና ያየችውን ነገር እያገናዘበች ስታስበው በራሷ ነገር ገረማት ጥቂት ከተጨዋወቱ በኋላ መርከበኛዉ ተሰናብቷቸ ሔደ " የሚስተር ካርላይል እጅ የሰውየው እጅ በነበረበት ሽንጥ ተተክቶና ወደ ራሱ አስጠግቶ ተያይዘው ሔዱ " ሳቤላ የባርባራ ወንድም ትዝ አላትና ነገሩ ገባት "

“ድሮስ አብጀ ኖሯል ? እሷ በሱ ላይ ልትወሰልት ማለት ዘበት ነው ! የለም ! የለም ! ያ መጥፎ ዕድል ለኔ ብቻ የተሰጠ ነው '

ቦልና ትሬድማን ከቢሮአቸው በር የተለጠፈው ነሐስ እንደሚያመለክተ
የሕግ ጠበቆችና የንብረት ማስተላለፍ የሕግ በለሙያዎች ነበሩ " አብዛኛውን ጊዜ
የማስተላለፉን ጉዳይ ይከታተል የነበረው ሚስተር ትሬድማን ከቤተሰቡ ጋር የኖረው ከቢሮው ሲሆን ዐርባ አምስትና በሃምሳ ዓመት መካከል የሚገመተው
ወንደላጤዉ ቦል ግን የሚኖረው ከውጭ ነበር " ፊቱ ንቁ ዐይኖቹ አረንጓዴ
የሆኑ አጭርና ብርቱ ሰው ነበር" ሚስተር ካርላይል ሰኞ ጧት ቀደም ብሎ ከቤቱ ሔደ " ሚስተር ቦል ለሚስተር ካርላይል ከፍተኛ አክብሮት ነበረው ከሱ በፊትም ቢሆን ለአባቱ ለትልቁ ካርላይል ተመሳሳይ አክብሮት ነበረው ሁለቱ ካርላይሎች ለነዚህ ሰዎች ብዙ የሙያ ውለታ ውለውላቸዋል

ሚስተር ካርላይል ሲገባ' ሚስተር ቦል ቁርስ ላይ ነበር "

“ደህና ነህ ሚስተር ካርላይል ? ምነው በጧት መጣህ?”

ተው ተው ቁጭ በል አትቸገር እኔ እንደሆንክ ቁርስ አድርጌ ነው የመጣሁት።

“ይኸ የተለየ ነው እንዲህ አይምሰልህ ! ከስትራበርግ በቀጥታ የማስመጣው ነው።

ሚስተር ካርላይል አመስግኖ ምግቡን እምቢ አለና "የመጣሁት ለጉዳይ ነው ሆኖም ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት ምናልባት
ልትከታተለው ያልቻልክ
እንደ ሆነ የምነግርህን ነገር ምስጢር አድርገህ እንድትይዘው እፈልጋለው”
👍10
ግድ የለም እጠብቃለሁ አታስብ...ምን ዐይነት ጕዳይ ነው እሱ ?

“እኔ ልቆምለት የማልችል ባለ ጉዳይ ገጠመኝ ነገሩ የሆሊጆን ግድያ የሚመለከት ነው” አለው ሚስተር ካርላይል ራሱን ወደሱ ጠጋ ድምፁን ዝቅ አድርጎ

“ እንዴ እሱማ ዱሮ አይደለም ተወስኖ አልቆለት የተዘጋው ?

“ አላለቀለትም ሪቻርድ ሔር በነገሩ አንደሌለበትና ግድያውን የፈጸመው
ሌላ ሰው መሆኑን የሚያመለክቱ አንዳንድ ነገሮች ተገኝተዋል

“ ከሱ ጋር በመተባበር ነው ? አለው ቦል "

“ የለም ብቻውን እንጂ ! ሪቻርድ ሔር ከግድያው ጋር ምንም ግንኙነት አልነበረውም ሰውዬው ሲገደል እንኳን ከዚያ ቦታ አልነበረም "

“ አንተ ታምንበታለህ ? ”

“ እኔ ካመንኩበት ብዙ ዘመን ዐልፏል።

ታዲያ ግድያውን ማን ፈጸመው ? ”

“ ገዳዩ ቶርን የተባለ ሰው ነው ይላል ሪቻርድ " ከብዙ ዓመት በፊት ሪቻርድ ሔርን አግኝቸው ነበር " ትክክለኛ ሆነው ከተገኙ የሪቻርድ ሔርን ከወንጀሉ ንጹሕ መሆን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አንዳንድ ጭብጦች ገለጸልኝ ከዚያ ጊዜ ወዲህ ይህ ስሜት ቀስ በቀስ ትንሽ ነገር በትንሹ ላይ እየታከለ ከአጣራጣሪነት ወደ ተጨባጭነት እያመዘነ መጣ " በመጨረሻ ለማረጋገጥ ከሚቻልበት ደረጃ ስለ ደረስኩ ዛሬ ስለ ንጹሕነቱ አልጠራጠርም " ቶርን የተባለው ማን እንደሆነ የት እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ብችል ኖሮ ቢሳካም ባይሳካም ገና ዱሮ ነበር ለሕግ የማቀርበው " ነገር ግን የሰውየውን ደብዛ ማግኘት አልተቻለም " አሁን ግን ቶርን የተባለው ስም እውነተኛ ሳይሆን የውሸት ስም መሆኑን ደርስንበታል "

"እና አሁንስ ሰዉየው ይገኛል ?

ተገኝቷል። እዚሁ ዌስት ሊን አለ “ ልብ በል እኔ አልከሰውም ስለ ጥፋተኛነቱም ምንም ሐሳብ አላቀርብም" እኔ አሪጋግጬ የምገልጸው ስለ ሪቻርድ ንጹሕነት ብቻ ነው ነገሩ ግልጽ እንደሆነልኝ የሪቻርድን ጉዳይ እኔ ራሴ ልከታተለው ነበር » አሁን ግን ልከታተልለት የማልችልበት ሁኔታ ተፈጠረና ተውኩት ”

ምን አስተወህ ? ” አለው ቦል "

ስለዚህ ወደ አንተ መጣሁ ” አለ ሚስተር ካርላይል የተጠየቀውን ወደ ጎን በመተሙ „ “ የመጣሁት በሪቻርድ ሔር ስም ነሙ " ለምን እኔ ልቆምለት እንዳልቻልኩ አስረድቸ • ላንተ ቀርቦ እንዲያመለክት መክሬ እኔም ቀደም ብዬ ጕዳዩን ላንተ እንደምገልጽልህ ቃል ገብቸ ሸኝቸዋለሁ » አሁን ሪቻርድ አንተ ዘንድ እንዲመጣና ታሪኩን ራሱ ገልጾ እንዲነግርህ ትፈቅዳለህ

“ግድ የለም ደስ እያለኝ አስተናግደዋለሁ ምስኪኑን ሪቻርድ ሔርን ለመጉዳት እልፈልግም " ስለ ንጹሕነቱ ሊያሳምንኝ ከቻለም ክሱን ለመመሥረት የሚቻለኝን አደርጋለሁ ስለዚህ ያለ ምንም ስጋት መጥቶ እንዲያስረዳኝ ንገረው አንተ ልትቆምለት ያልፈለኽው ለምድነው ?

" ሪቻርድ ጥፋተኛ ነው የሚለውን ስው መክሰስ ስለ አልፈለግሁ ነው
ሁሉንም ነገር ከሪቻርድ ታገኘዋለህ

“ እንተ ልትከራከረው የማትፈልገው ሰው ደሞ ዌስት ሊን ውስጥ ማን ይገኛል ሪቻርድ ሔር አባቱን ነው እንዴ የhሰሰ ?”

“ በል እንግዲU ” አለው ሚስተር ካርላይል ሲነሣ ' “ የትና እንዴት ነው
የምትገናኙት ?

“ እሱ አሁን ዌስት ሊን ነው ያለው ?
“ የለም " ግን ስልክበት ሊመጣ ይችላል " ዛሬ ማታ ቢመጣ ይመችሃል ?

“ እንግዲያው እዚህ ቤት ድረስ ይምጣ " ምንም የሚያስፈራው ነገር አይኖርም።

ደግ ይሁን ከአንግዲህ የኔ ድርሻ ያበቃል " አለወና ጥቂት ቃላት ከተለዋወጡ በኋላ ተለያዩ "

ሚስተር ቦል ቁሞ ሚስተር ካርላይልን እስኪርቅ ድረስ ሲመለከተው ቆየ "
“በጣም እንግዳ የሆነ ነገር ነው ሪቻርድ አንዷን የሚስተር ካርላይልን ፍቅረኛ የከስስ ይመስላል » ደፍሮ ሊሞግታት የጨነቀው አንዲት ወይዘሮ ትሆናለች....

💫ይቀጥላል💫
👍18👎1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

የበረራ መሃንዲሱ ኤዲ ዲከን የስማይ በራሪ ጀልባውን የሚያየው
ጥንቃቄ የሚፈልግ ነገር አድርጎ ነው፡፡ የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች ገና በቅጡ
ያልዳበሩ መሆናቸውንና በአትላንቲክ ውቅያኖስ በምሽት በሚደረገው በረራ
ወቅት ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ተሳፋሪዎቹ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡ ሆኖም ኤዲ የካፒቴኑ የመሾፈር ብቃት፣ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ከልብ መስራትና የአሜሪካ ኢንጂነሪንግ የደረሰበት ደረጃ ተዳምረው አይሮፕላኑን በሰላም አሜሪካ እንደሚያደርሱት ይተማመናል።

ይህ ጉዞም እስካሁን ካደረጋቸው ጉዞዎች ሁሉ አስፈሪ ሆኖበታል፡በተሳፋሪዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ቶም ሉተር የሚባል ሰው መኖሩን አይቷል፡፡ ተሳፋሪዎቹ አንድ በአንድ አይሮፕላኑ ላይ ሲሳፈሩ ከእነዚህ ውስጥ ካሮል አንን ያገታት ቶም ሉተር የቱ ይሆን? አለ በሆዱ¨
አዕምሮውን ወጥሮ የያዘውን የካሮል አንን ጉዳይ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ትቶ አይሮፕላኑን ለበረራ ለማዘጋጀት ተነሳ፡፡ የአይሮፕላኑ የተለያዩ መሳሪያዎች የሚሰሩና የማይሰሩ መሆናቸውን መፈተሽ፣ አራቱን ግዙፍ ሞተሮች መቆጣጠር ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ናቸው፡ አይሮፕላኑ ተነስቶ በጥሩ ሁኔታ መብረር ከጀመረ በኋላ ብዙም የሚሰራው ነገር አይኖርም፡፡ በዚህ ጊዜ የአይሮፕላኑ ፍጥነትና
የሞተሮቹ ሙቀት መጠን
በትክክል መስራቱንና ነዳጁን መቆጣጠር
ይሆናል። ሆኖም አዕምሮው እንደገና ወደ ካሮል አን እየሄደበት ተቸገረ፡፡
ካሮል አን በሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ በእነዚህ አረመኔዎች እጅ በተለይም ከጠጡ ምን ሊደርስባት እንደሚችል አይታወቅም:

እነዚህ ሰዎች ምንድነው
ከእሱ የሚፈልጉት? የስራ ጓደኞቹ የተቸገረበትን ነገር እንዳያውቁበት መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሁሉም ግዴታውን
ለመወጣት ተፍ ተፍ ስለሚል ላያውቁበት ይችላሉ፡ ካፒቴን ቤከርና ረዳት ካፒቴን ጆኒ ዶት የአይሮፕላኑ ጋቢና ውስጥ ተመቻችተው ተቀምጠዋል
ከተሳፋሪዎች ክፍል የሚመጣው ብርሃን ፓይለቶቹን እንዳያስቸግራቸው
ማታ ማታ ወፍራም መጋረጃ ይጋረዳል፡ ማፖችንና መሳሪያዎች በመጠቀም
አይሮፕላኑን ትክክለኛውን አቅጣጫ እንዲይዝ የሚያደርገው ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ማፑ ላይ አፍጥጧል፡

ይህን አይሮፕላን ከሌሎች አይሮፕላኖች የሚለየው አይሮፕላኑ መሬት
ሳይወርድ ዘይት የሚያፈስን የሞተር ክፍል ጥገናን የመሳሰሉ ቀላል የጥገና
ስራዎችን መስራት ማስቻሉ ነው፡፡ ቀጥሎ የሚገኘው ቦታ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ
የቤን ቶምሰን ሲሆን ከእሱ ኋላ ደግሞ የኤዲ የስራ ቦታ ይገኛል።

ኤዲ ጀርባቸውን ለእሱ ሰጥተው በተመስጦ የሚሰሩ ጓደኖቹ የእሱን
ጭንቀትና ፍርሃት ባለማስተዋላቸው ተረጋጋ:: ለጊዜው ማንነቱ ያልታወቀው ሚስተር ሉተር እኔ ነኝ እንዲል ለማድረግ ፍላጎት አደረበት፡፡
በተሳፋሪዎች ክፍል መተላለፊያ መንጎራደድ ፈለገና ከመቀመጫው ተነስቶ ‹‹እስቲ አንድ ቼክ የማደርገው ነገር አለ›› ብሎ ለናቪጌተሩ ነገረና ደረጃውን
ወርዶ ሄደ፡፡ የሆነ ሰው ለምን ቼክ ማድረግ እንደፈለገ ቢጠይቀው ዝም ብሎ እንደሚያልፍ ወስኗል፡፡

ኤዲ በመተላለፊያው ላይ ቀስ ብሎ ተራመደ፡ ኒክና ዴቪ ለተሳፋሪዎች ምግብና መጠጥ እያደሉ ነው፡፡ ተሳፋሪዎቹ በተለያዩ ቋንቋዎች ያወራሉ፡፡
የተወሰኑ ሰዎች ካርታ ጨዋታ አጧጡፈዋል፡ ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታዋቂ ሰዎች ቢያይም ሃሳቡ ስለተበታተነበት እነማን እንደሆኑ መለየት አልቻለም፡፡እያንዳንዱ ሰው ላይ ተራ በተራ ቢያፈጥም ማንም ሰው ‹ቶም ሉተር እኔ
ነኝ›› አላለውም፡፡ ማየት የፈለገውን ነገር እንደነገሩ አይቶ በሩን ሲዘጋ አንድ
አስራ አራት አመት የሚሆነው ልጅ የሚሰራውን በተመስጦ ሲመለከት አየና
ፈገግ አለ፡፡

የፓይለቶቹን ጋቢና ማየት ይቻላል?›› ሲል ጠየቀው ልጁ፡
‹‹ይቻላል›› አለ ኤዲ፡ በዚህ ሰዓት ማንም እንዲያስቸግረው ባይፈልግም ተሳፋሪውን በትህትና ማናገር አለበት፡
‹በጣም አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡
‹‹ወደ መቀመጫህ ተመለስና ጥቂት ጊዜ ቆይቼ እጠራሃለሁ›› አለው
ልጁ በኤዲ መልስ ግራ ቢጋባም ራሱን በእሺታ ነቀነቀና ፈጠን ብሎ
ሄደ፡፡

ኤዲ በመተላለፊያው ላይ እየተንጎራደደ አንድ ሰው እንዲያናግረው ጠበቀ፡፡ የሚያናግረው ሰው አለመኖሩን ሲረዳ ሰውየው ሰው የማይኖርበትን
አጋጣሚ እየጠበቀ መሆኑን ገመተ፡ አስተናጋጁን ሉተር የተባለው ሰው የቱጋ እንደተቀመጠ መጠየቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን ለምንህ ነው የምትጠይቀው?› ብሎ ቢለው ምን መልስ እንደሚሰጥ አያውቅም በዚህ ጊዜ የስራ ባልደረቦቹ በእሱ ላይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዲያድርባቸ
የሚያደርግ ነገር ማድረግ የለበትም፡፡

ልጁ ከአባትና ከእናቱ ጋር ነው የተቀመጠው፡፡ ኤዲም ‹‹ማሙሽ አሁን ና›› ሲል ተጣራ፡ አባትና እናቱም በመቀበል ራሳቸውን ነቀነቁ። አንዲት ጸጉረ ረጅም ልጅ የልጁ እህት ሳትሆን አትቀርም ሞቅ ያለ ፈገግታ
ስትመግበው ልቡ ደንገጥ አለ፡፡ ልጅቷ ስትስቅ ታምራለች፡

‹‹ማነው ስምህ ማሙሽ?›› አለው፡

‹‹ፔርሲ ኦክሰንፎርድ›› አለ፡
‹‹እኔ ኤዲ ዲኪን እባላለሁ፡፡ የበረራ መሀንዲስ ነኝ፡፡ ሞተሮቹን በትክክል መስራታቸውን መከታተል ነው ስራዬ››

የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደረሱ፡ ‹‹ይሄ ሁሉ ደውልና መሳሪያ ምን ያደርጋል?››

‹‹የሽክርክሪቱን ፍጥነት፣ የሞተሩን የሙቀት መጠን እና የነዳጁን ቅልቅል ይቆጣጠራል፡፡›› ለልጁ በይበልጥ እንዲገባው ‹‹እዚህ ወንበር ላይ
ቁጭ በል›› አለው፡ ፔርሲም ቁጭ አለ፡፡ ‹‹ይሄ ደውል የቁጥር ሁለት ሞተርን የሙቀት መጠን ያሳያል፡ አሁን ሙቀቱ ከፍ ብሏል፡ ትንሽ ማቀዝቀዝ ያስፈልጋል፡››

‹‹እንዴት ነው ይሄን የምታደርገው?››

‹‹እጀታውን ያዝና ትንሽ ወደታች ግፋው ይህን ያህል ይበቃል፡ አሁን ተጨማሪ አየር እየገባ ነው ከትንሽ ደቂቃ በኋላ የሙቀት መጠኑ ሲወርድ
ታያለህ፡፡ ፊዚክስ ተምረሃል?›› ሲል ጠየቀው ኤዲ፡፡

‹‹እኔ የምማረው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ውስጥ አይደለም›› አለ ፔርሲ፣ ‹‹ትምህርት ቤቱ ላቲንና ግሪክ ቋንቋዎች ላይ ነው በይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው፡፡ ሳይንስ ላይ እስከዚህም ነው፡፡››
‹‹ሌሎቹ የስራ ባልደረቦችህስ ምንድነው ስራቸው?››
‹ዋናው ትልቅ ስራ ያለበት ናቪጌተሩ ነው፤ ቻርቱ ላይ ያፈጠጠው ጃክ አሽፎርድ ይባላል አይሮፕላኑ የት እንዳለ የሚቆጣጠረው እሱ ነው! በተለይ መሃል አትላንቲክ ላይ ስንበር፡፡››

ጃክ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ፈገግ አለ፡፡ ‹‹አይሮፕላኑ እየበረረ የሚገኝበትን ቦታ የሚጠቁመንን መሳሪያ የሚቆጣጠረው ጃክ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ከባህር በላይ ሲበር ቦታውን ማወቅ አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡››

ጃክም ስለስራው ሲናገር ‹‹ብመጀመሪያ መሳሪያውን በመጠቀም በመስታወት እያየህ አንድ ኮከብ ፈልገህ ኮከቡ በአድማስ ላይ ትክክል እስኪመጣ ጠብቀህ የመስታወቱን አንግል ታስተካክላለህ›› አለ፡

‹‹ይሄማ ቀላል ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹ይሄ በቲዮሪ ደረጃ ነው›› አለ ጃክ እየሳቀ ‹‹የዚህ የጉዞ መስመር ችግር ጠቅላላ በረራውን ድፍን ባለ ደመና ልንጓዝ የምንችልበት አጋጣሚ
የሚፈጠርበት ጊዜ መኖሩ ነው፡፡ የተነሳህበትን ነጥብ ካወቅህና በተመሳሳይ
አቅጣጫ የምትጓዝ ከሆንክ ልትሳሳትበት የምትችልበት አጋጣሚ ባይኖርም
ይሄ የሚሆነው ግን ነፋስ በሌለበት ጊዜ ነው፡፡ሀይለኛ ንፋስ በሚኖርበት ጊዜ
አይሮፕላኑን ወዲህና ወዲያ የሚያላጋው ስለሆነ መስመር ጠብቆ መጓዝ
አስቸጋሪ ነው:፡
👍20🥰1😁1
ኤዲ የፔርሲን ሁሉን ለማወቅ መጓጓት አየና ‹እኔም አንድ ቀን ለልጄ
እንደዚህ ማስረዳት የምችልበት ጊዜ ይመጣ ይሆናል ሲል አሰበ፡፡ ይህም
ካሮል አንን አስታወሰውና ንዴት ውስጡን ጠቅ አደረገው፡፡ ሚስተር ሉተር
የተባለው ሰው እኔ ነኝ ብሎ ራሱን ቢያስተዋውቀውና ከእሱ የሚፈልገውን
ነገር ቢያሳውቀው ቀለል ይለው ነበር፡፡

የፔርሲ ጥያቄም አላበቃም ‹‹የአይሮፕላኑን ክንፍ ማየት እችላለሁ?›› ሲል ጠየቀ
‹‹በሚገባ›› አለና ኤዲ ወደ ክንፉ የሚያስገባውን ፉካ ከፈተለት፡፡ ፉካው ሲከፈት የአይሮፕላኑ ሞተር አስገምጋሚ ድምጽና የነዳጅ ሽታ ተቀበለው፡፡
በክንፉ ውስጥ በእንፉቅቅ መተላለፍ የሚያስችል መንገድ አለ፡፡ ከሞተሮቹ
በስተጀርባ የጥገና ስራ ቆሞ መስራት የሚያስችል ቦታ ያለ ሲሆን ቦታው
በሙሉ በኤሌክትሪክ ገመዶች፣ በትንንሽ ቧንቧዎችና በብሎኖች የተሞላ ነው: ‹‹ሁሉም አይሮፕላኖች እንደዚሁ ናቸው›› ሲል ጮኾ ተናገረ ኤዲ፡፡

‹‹ልግባና ልየው?›› ሲል ጠየቀ ፔርሲ

‹‹አይሆንም፡፡ ተሳፋሪዎች እዚህ ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም››
አለና በሩን ዘጋው፡፡ ኤዲም የስራ ቦታው ጋ በመሄድ መሳሪያዎቹ የሚሰሩ
መሆናቸውን አረጋገጠ፡፡
የመገናኛ ባለሙያው ቤን ቶምሰን ፎየንስ ላይ ያለው የአየር ሁኔታ ንፋሳማ ባህሩም ሞገዳማ መሆኑን ተናገረ፡፡ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኤዲ በሚቆጣጠረው ሰሌዳ ላይ ‹‹ማረፍ ይቻላል
የሚል መልእክት ሲመጣ አየና ‹ሞተሩ አይሮፕላኑን ለማሳረፍ ዝግጁ ነው አለ ጃክም ‹አይሮፕላኑ ሊያርፍ ስለሆነ ወደ ቦታህ ሄደህ ተቀመጥ አለው ፔርሲን፡፡ ፔርሲም የተሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ወደ ቦታው ሄደ፡

አውሮፕላኑ ለማረፍ በሚያደርገው እንቅስቃሴ
የሞተሩ ድምፅ ተለወጠ፡፡ ቀስ በቀስም ወደ ታች ዝቅ ዝቅ ማለት ጀመረ፡ በዚህ ወቀተ ኤዲ ብቸኝነት ተሰማው፡፡ በሆዱ የሚያብሰለስለውን ነገር አውጥቶ ቢናገር በወደደ፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጓደኞቹ ናቸው፡ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ አብረው በረዋል፡፡ ችግሩን ነግሯቸው ምክራቸውን ማግኘት ቢፈልግም ይህን መንገር ግን ከጥቅሙ ይልቅ አደጋው የከፋ ሆነበት፡፡

ከመቀመጫው ብድግ አለና በመስኮት ተመለከተ፡ አንድ ትንሽ ከተማ ትታየዋለች፡፡ ባሻገር የአይሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እየተካሄደ ነው፡፡ ዋናው አብራሪ ካፒቴን ቤከር የአይሮፕላኑን አፍንጫ ወደ ማረፊያው አዞረ፡ እታች ባህሩ ላይ ነዳጅ ጫኝ ጀልባ ይጠብቃቸዋል፡ ወደቡ በሰማይ የሚበረውን
ጀልባ ለማየት በተሰበሰቡ ሰዎች ተጨናንቋል፡

ቤን ቶምሰን በሬዲዮ ማይክሮፎኑ እየተነጋገረ ነው፡፡ ቤን የሚለው
ባይሰማውም እንዳነጋገሩ ከሆነ ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፡፡

አሁን አይሮፕላኑ እየወረደ ነው፡፡ ባህሩ ጸጥ ያለ ከሆነ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ማረፉ የሚታወቀው ቆይቶ ነው፡፡ ዛሬ ግን ባህሩ ሞገደኛ ነው።

አይሮፕላኑ ዝቅ እያለ ሄዶ ባህሩ ላይ አረፈና እንደ ጀልባ መሄድ ጀመረ፡ ከውጭ ነጭ ቤትና ሳር የሚግጡ በጎች ይታያሉ፡፡ ፎየንስ ከተማ ደርሰዋል፡

አንድ ጀልባ ወደ አይሮፕላኑ ስትከንፍ መጣች፡ ጀልባው ላይ ያለው ሰው እጁን ለኤዲ አውለበለበለትና ማሰሪያ ገመድ ወረወረለት፡፡
ተሳፋሪዎቹን የሚወስድ ሌላ ጀልባ መጣ፡፡ ኤዲ የአይሮፕላኑን ሞተር
አጠፋ፡፡ ሁሉ ነገር እንደተጠናቀቀ ዩኒፎርሙን ለበሰና ኮፍያውን አድርጎ
ወጣ።

ኤዲ ጀልባው ላይ የተሳፈሩትን ተሳፋሪዎች ቃኛቸው፡፡ የትኛው ይሆን
ቶም ሉተር? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ከዚህ ቀደም ባየው ፊልም ላይ የተወነችውን ሉሉ ቤልን አወቃት፡ካንድ ሰው ጋር ታወራለች፡፡ ‹ቶም ሉተር ይሆን?› ሲል ራሱን ጠየቀ፡ ከነሱ ጋር አንዲት ነጠብጣብ ያለበት ልብስ የለበሰች ቆንጆ ሴት አየ፡፡ ከዚህ በፊት የሚያውቃቸው ሰዎች ጀልባ ውስጥ ያሉ
ሲሆን ብዙዎቹን ግን አያውቃቸውም።

ሉተር ራሱ መጥቶ እኔ ነኝ ሉተር› ካላለ ኤዲ ራሱ ለመጠየቅ ወሰነ፡ እጁን አጣጥፎ መጠበቁ እልህ አስጨራሽ ሆኖበታል፡ ሚስቱ ትዝ አለችው
ሰዎቹ በሩን በርግደው ሲገቡ በዓይነ ህሊናው ታየው፡ ካሮል አን እየበላች
ወይም ቡና እየጠጣች ወይም ወደ ስራ ለመሄድ እየተዘጋጀች ወይም የገላ
መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ሆናም ይሆናል ሰዎቹ በርግደው የገቡት፡ ኤዲ
ገላዋን ስትታጠብ እርቃኗን ማየት ደስ ይለዋል፡ ጸጉሯን በጸጉር ማስያዣ ታስይዝና ገንዳው ውስጥ ጋደም ብላ መቃ አንገቷን ብቅ አድርጋ ገላዋን በሳሙና ትቀባለች፤ እሱ ዳር ቁጭ ብሎ ያጫውታታል፡ እሷን ከመተዋወቁ በፊት እንዲህ ዓይነት ነገር የሚኖረው በልብ ወለድ መጽሐፍ ውስጥ ብቻ ይመስለው ነበር አሁን የሆኑ ሰዎች በሩን በርግደው ገብተው ሰላሟን ነስተዋት ታየችው:፡

ሰዎቹ ሲመጡባት
ያጋጠማት ፍርሃትና
ድንጋጤ ሲታሰበው
ሊያሳብደው ይደርሳል፡፡ ራሱን ያመዋል፡ ደግሞ ምንም ማድረግ አለመቻሉ
ያንገበግበዋል።

ሰዎቹን የሚወስደው ጀልባ የሰማይ በራሪው ጀልባ ጋ ደረሰና ተሳፋሪዎቹንና የአይሮፕላኑን ሰራተኞች ወደ ህንጻው ወሰዳቸው፡ ወደ
ህንጻው ሲገቡ ይህ ነው የሚባል ቁጥጥር አልነበረም፡፡ ተሳፋሪዎቹ ወደ መንደሯ ዘለቁና ብቸኛዋ ቡና ቤት ውስጥ ገቡ፡፡

ኤዲ ነው መጨረሻ ከጀልባው የወጣው፡ ገና ህንጻው ጋ ከመድረሱ
አንድ ሰው ወደ እሱ መጥቶ ‹‹አንተ ነህ የበረራ መሀንዲሱ?›› ሲል
ጠየቀው: ኤዲ በዚህ ጊዜ ደም ስሩ ተገታተረ፡፡ የሚያናግረው ሰው
ሰላሳ አምስት ዓመት የሚሆነው ሲሆን ከእሱ አጠር፣ ወፈር ያለና ጡንቻው ፈርጣማ ነው፡ አመድማ ሱፍ ልብስ ለብሷል፤ ክራቫት አስሯል፡፡ ኮፍያም አናቱ ላይ ደፍቷል፡

‹‹ስሜ ቶም ሉተር ይባላል›› አለው ሰውየው፡

ኤዲ ከመቅጽበት በንዴት መንቀጥቀጥ ጀመረ፡ ሉተርን አንገቱን አንቆ
ከግድግዳው ጋር አላጋው፡፡ ‹ሮሌን ምንድነው ካሮሌን ምንድን ነው ያደረጋችኋት?›› አለና
ምራቁን ተፋበት፡ ሉተር ድንገት በሆነው ነገር ተደናገጠ፡ የጠበቀው
በፍርሃት የሚርድ እጅ የሰጠ ሰው ነበር፡፡ ኤዲ የሉተር ጥርስ እስከሚንገጫገጭ ድረስ የሸሚዙን ክሳድ ይዞ ወዘወዘው፡፡ ‹‹አንተ
እግዚአብሔርን የካድክ ሸርሙጣ! ሚስቴን የት ነው ያደረስካት?›› አለው፡፡

ሉተር ድንጋጤው ሲለቀው ራሱን ከኤዲ ባለ በሌለ ኃይሉ አላቀቀና
ቡጢ ሰነዘረ፡፡ ኤዲ ቡጢ ስንዘራውን በአንድ እጁ መከተና ሉተርን ሁለቴ
በቡጢ ነረተው፡ ሉተር እንደ ተነፈሰ ፊኛ አየር አስወጣ፡፡ ሉተር ጠንካራ ቢሆንም ድንገት የመጣበትን ውርጅብኝ መቋቋም አልቻለም፡፡ ኤዲ በዚህ
ብቻ ሳያበቃ ጉሮሮውን ፈጥርቆ ያዘው፡፡ አያያዙን እያጠበቀ ሲመጣ የሉተር
ዓይን ተጎልጉሎ ሊወጣ ምንም አልቀረም፡፡ ነገር ግን ኤዲ ሰውየው በእጁ
ሊጠፋ መሆኑን ሲገነዘብ እጁን እያላላ መጣና ለቀቀው፡፡ ሉተርም
ግድግዳውን ተደግፎ አንገቱን እያሻሽ አየር መሳብ ጀመረ፡፡
አየርላንዳዊው የጉምሩክ ሰራተኛ ኤዲ ሉተርን ከግድግዳው ሲያላጋው
አየና ‹‹ምን ሆናችሁ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ሉተር እንደምንም ቀና አለና ‹‹ራሴን ስቼ ነው፤ አሁን ተሽሎኛል››

የጉምሩኩ ሰራተኛ ጎንበስ አለና የሉተርን ኮፍያ አንስቶ ሰጠው::ሁለቱንም አንዴ አየት አድርጎ ምንም ሳይናገር ጥሏቸው ሄደ፡

ኤዲ አካባቢውን ቃኘና ግብግባቸውን ከጉምሩክ ሰራተኛው በስተቀር ያየ
እንደሌለ አረጋገጠ፡፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞችና ተሳፋሪዎች በየፊናቸው
ተበታትነዋል፡፡
👍14🔥2🥰1😁1
ሉተር ኮፍያውን አናቱ ላይ ደፋና በታፈነ ድምጽ ‹‹ይህን ጉዳይ በሰላም ካልያዝከው እኔና አንተ እንዲሁም ያቺ ጦሰኛ ሚስትህ ሟች ነን›› አለው ሉተር የካሮል አንን ስም ሲያነሳ ኤዲ እንደገና ንዴቱ አገረሸበትና በቡጢ
ሊለው ሲሰነዝር ሉተር መከተና ‹‹አደብ ግዛ ሰውዬ፤ በዚህ ዓይነት የሚስትህን ዓይን ዳግም አታይም፧ እኔ እንደማስፈልግህ አይገባህም?›› አለው፡
ኤዲ ሉተር ምን እንዳለ በሚገባ ገብቶታል። ስለተናደደ የሚሰራውን
አያውቅም፡፡ ወደኋላ ፈቀቅ አለና ሰውየውን አየው ሉተር ሲያዩት ንግግሩ የደህና ሰው ይመስላል፤ የለበሰውም ልብስ ደህና ገንዘብ የወጣበት ነው፡ ሪዙ
የጎፈረ ሲሆን ዓይኖቹ ጥላቻ ይፈነጥቃሉ፡ ኤዲ ሉተርን በቦክስ በማጣደፉ
ምንም ቅሬታ አልተሰማውም፡፡ ለንዴቱ መወጫ አንድ ነገር መምታት ፈልጎ ነበር፧ ሉተር ደግሞ ጥሩ ዒላማ ሆኖለታል፡

‹‹ከኔ ምንድነው የምትፈልጉት?›› ሲል ጠየቀው ሉተርን

ሉተር እጁን ደረት ኪሱ ውስጥ ከተተ፡ ኤዲ ሽጉጥ ሊያወጣ ነው ብሎ
ሲያስብ የሉተር እጅ አንድ ፖስት ካርድ ይዞ ወጣና ለኤዲ ሰጠው፡፡ በፖስት
ካርዱ ላይ በአሜሪካ በሜይን ስቴት ውስጥ የሚገኘው ባንጎር ከተማ
ይታያል።

ሉተር ‹‹የፎቶግራፉን ጀርባ ተመልከት›› አለው፡

ፎቶግራፉ ጀርባ ላይ 44.70N 67.00W የሚል ተፅፏል፡፡

‹‹እነዚህ በካርታ ላይ ቦታ ማመልከቻ ቁጥሮች ምን ላድርጋቸው?››

ሲል ጠየቀው ኤዲ፡፡

‹‹አይሮፕላኑን በ44.70 ዲግሪ ሰሜንና በ67 ዲግሪ ምዕራብ› ቦታ ላይ
ታሳርፈዋለህ፡››

‹‹አይሮፕላኑን አሳርፍ ነው ያልከኝ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ ግራ ተጋብቶ

‹‹አዎ›› አለው ሉተር፡፡
‹‹ይህን ነው ከኔ የምትፈልጉት ሚስቴን ያፈናችኋት ለዚህ ነው?››
‹‹አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ ላይ ማሳረፍ አለብህ››

‹ግን ለምን?››
‹ምክንያቱም ውቧን ሚስትህን መልሰህ እጅህ
ማስገባት ስለምትፈልግ››

ይህ ቦታ የት ነው?››

‹‹ሜይን ስቴት ባህር ዳርቻ ላይ›› ሲል መለሰ ሉተር፡

ሰዎች ባህር ላይ የሚያርፍ አይሮፕላን ባህር ላይ የትም ቦታ የሚያርፍ ይመስላቸዋል፡ አይሮፕላኑ
ለማረፍ በጣም የረጋ ባህር
ይፈልጋል፡ ለደህንነት ሲባል ፓን አሜሪካን አየር መንገድ ከአንድ ሜትር የባህሩ ሞገድ በጠነከረበት ባህር ላይ አይሮፕላን ለማረፍ ቢሞክር ስብርብሩ
ነው የሚወጣው፡:

ኤዲም ‹‹አይሮፕላኑን ገላጣ ባህር ላይ ማሳረፍ አይቻልም›› አለው
ሉተርን፡፡

እሱን እናውቃለን፡፡ ቦታው በጉብታ የተከለለ ነው›› አለ ሉተር፡፡

ቢሆንም ማሳረፍ አስቸጋሪ ነው››

ቼክ አድርገው፤ እዚያ ላይ ማሳረፍ አያቅትህም፤ እኔም ይህን አረጋግጫለሁ፡››

ሰውየው እዚያ ቦታ ላይ ማሳረፍ እንደሚቻል እርግጠኛ ሆኖ ነው
የሚናገረው፡

‹‹ነገር ግን ሌላ ችግር አለ፡፡ እኔ እንዴት ነው አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ ላይ ማሳረፍ የምችለው፧ ፓይለቱ እኔ አይደለሁ›› አለ ኤዲ፡
‹‹ይህን ነገር በደንብ አጥንቼዋለሁ፡ ካፒቴኑ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ
የሰማይ በራሪ ጀልባውን ማሳረፍ ይችላል፡ ነገር ግን እዚያ ቦታ ለማሳረፍ
በቂ ምክንያት ይፈልጋል፡ አንተ ግን የበረራ መሀንዲስ ነህ፡፡ አንድ የሆነ
የአይሮፕላኑ ክፍል እንዲበላሽ ማድረግ የምትችለው አንተ ነህ›› አለው ሉተር፡

‹‹አይሮፕላኑን ባህሩ ላይ እንድጥለው ትፈልጋለህ?››
‹‹እንደዚያማ ማድረግ አትችልምº እኔ አይሮፕላኑ ውስጥ አለሁ
ፓይለቱ እዚያ ቦታ ላይ በድንገት እንዲያርፍ የሚያስገድደው አንድ ችግር ፍጠር›› አለው በሚገባ በተከረከመ ጥፍሩ ፖስት ካርዱ ላይ ያለውን ቦታ እያመለከተው፡፡
የበረራ መሃንዲሱ ፓይለቱ በድንገት አይሮፕላኑን ለማሳረፍ የሚያስገድደው ችግር መፍጠር አያቅተውም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍ ችግር መፍጠር ለጊዜው ኤዲ አልከሰትልህ አለው፡፡

‹‹ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን የማይሆን ነገር ግን አይደለም
እኔም ይህን ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጫለሁ››
‹‹ማነው ይህን የነገረህ? እናንተስ እነማን ናችሁ? አለ ኤዲ ንዴቱ ተቀስቅሶ፡

‹‹ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ መጠየቅ አትችልም›› አለው ሉተር::....

ይቀጥላል
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ስምንት (18)

በዚህ ጊዜ እቢሮው ገብታ እፊት ለፊቱ ባለው ወንበር ላይ ተቀምጣ ነበር፡፡ ቀና ሲል አንደኛውን እግሯን አንስታ እሌላኛው ላይ አነባበረችው ። እግሮቿ በጣም ያምራሉ ።
ማይክል ሂልያርድ ግን ይህን አሳጤነም ።
«በዚያም ላይ» አለች ። «ባለፈው ጊዜ ለተደረገልኝ እድገት ምስጋናዬን ለማቅረብም ነው»
« በእሱ እንኳ እኔ አልመሰገንም ።እድገቱን እንድታገኚ ያደረገው ቤን አቭሪ ነው ።እሱኑ ነው ማመስገን ያለብሽ»
« ገባኝ »
በደንብ ነበር የገባት ።የትም እማያደርስ ወሬ ነበር የጀመሩት። ባደረገችው ነገር እየተፀፀተች ከመቀመጫዋ ተነሳችና በመስኮት ወደ ውጭ እያዬች «የዘንድሮው ገና በበረዶ ያሸበረቀ ነጭ ገና ሊሆን ነው ማለት ነው። እሚገርመው ነገር ዛሬ እንዴት ተሁኖ ነው ወደ ቤት የሚደረሰው?» አለች። «እሱን ያዥልኝ ። በበኩሌ አልሞክረውም ። ሲጀመርም ያን መኝታ እዚህ ቢሮ ውስጥ ያስቀመጡት ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም። የቢሮዬ ቁራኛ ሆኜ እንድኖር » ዌንዲ ይህን ስትሰማ በልቧ ተቃውሞ አሰማች። የለም ።አያ እንቶኔ ፤እራስህን መቅጣት ትችላለህ። ሌላ ሰው ግን ... በኦፏ ግን ፈገግ ብላ «በል መልካም የገና በአል» አለችውና ወጣች ። ያንለት እንዳለውም እቢሮው ውስጥ አደረ ።

የገና በአል ዋዜማ ለትም ፤ የገና የለቱ እለትም ፤ ማይክል ከቢሮው አልወጣም ። ለበአሉ ሲባል እና እንዳጋጣሚ በአሉ የዋለው እሑድ ቅዳሜን ተንተርሶ ስለነበረ ፅዳት ሰራተኞችና ዘበኞች እንኳ አላዩትም። ከሌሊቱ ዘበኛ በስተቀር ያየው አልነበረም። እዚያች ቤት ውስጥ፤ እዚያች የናንሲ ማክአሊስተርን መኖሪያ ትመስላለች ብሎ እመረጣት አፓርታማ ውስጥ ሆኖ ብቻውን የገናን በአል ሊያሳልፍ ከቶም ከቶ ድፍረት አልነበረውም። እሱ ግን ይህን ፍርሃቱን እንዳህ ጥርት አርጎ አላሰበውም ። ማይክል የዜያን ዓመት የገና በአል ከነትዝታው ከነአኬራው፤ ከነድቅስቃሱ ነበረና የፈራው ወደ ቤቱ አልገባም ። ገና ድቅስቃሱን፤ አኬራውን ፤ ትዝታውን ይዞ ሲያልፍ እቤቱ ሄደ ። እባዶዋ፤ወናዋ ቤቱ። የተላከ አበባ እበሩ ላይ በስተውጭ ተቀምጦ ጠበቀው ። ይህ የሆነው ኒውዮርክ ነበር

በሳንፍራንሲስኮ ከተማ ናንሲ አመትባሉን ያሳለፈችው ከዚህ በተሻለ ምቾት ነበረ ፤ብቸኝነቱ ግን ያው ። ዶሮ ሰርታ ለብቻዋ የገና መዝሙሮችን በመዘመር የበአሉን ዋዜማ አከበረች በማግስቱ ፤ ማለትም የገና የለቱ ለት አስከረፋድ ድረስ ካልጋዋ ላይ አልተነሳችም። እረፋዱ ላይ ካልጋዋ ተነስታ ውጭውን ስትመለከት ነገሩ ሁሉ የገና በአል አልመስልሽ አላት። ምንም እንኳ የገና ዛፉ ፤ ተርኪናውና ሌላው ሌላው ሁሉ ሲሸጥ ፡ ሲጓጓዝ ያየች ቢሆንም ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ስትኖር የምታከብረውን አይነት ገና አልመስል አላት ። የሳንፍራንሲስኮ የአየር ጠባይ ካደገችበት ምስራቃዊ ግዛት የተለየ ነው። የገናን በአል ያለ በረዶ ፤ ይህን በአል ያለዚያ አየር ጠባይ ላስብህ ብትለው የማይሆን ሆነ ። በዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎች ገናን አከበርን ለማለት የሚሞክሩ ፤ የሚያስመስሉ መሰላት እንጂ ገናን ኢያከበሩ መሆኑ ከቶም እውን ሊሆንላት አልቻለም ። ይህ ግን ሀዘኗንና ጭንቀቷን ቀላል አደረገላት ።

የሰራችውን ዶሮና ሌላም ሌላም ነገር ቀማምሳ ስታበቃ ፌ ለገና በአል የሰጠቻትን የቀልዶች መጽሐፍ ማንበብ ጀመረች። በዘንድሮው በአል ያገኘችው ሁለት ስጦታ ብቻ ነበረ ። አንደኛው ፒተር ግሬግሰን (የቀዶ ሕክምና ሊቁ እና ሀኪሟ ) የሰጣት ውድም ውብም የሆነ የእጅ ቦርሳና ይህ ከላይ የተባለው ፌ የሰጠቻት የቀልዶች መጽሐፍ። እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ ስታነብ ዋለች ። ከዚያ በኋላ ተነስታ ካሜራዋን አዘጋጀች ። ጉምም ሆነ ጭጋግ የማይታይበት ብሩህ ምሽት ፎቶግራፎች ለማንሳት አመቺ ነው።

ከቤቷ ስትወጣ መንገዱን ሁሉ ጭር ብሎ አገኘችው። ሰዉ ለአመት ባሉ የበላው ምግብ ከብዶት በየቤቱና በየጓሮው ያናውዛል ማለት ነው። አንዳንዱ ይኸኔ ቲቪ ከፍቶ ደፋ ቀና እያለ ይመለከት ይሆናል ። ይህን ስታስብ የራሷ አስተሳሰብ ገረማትና ለብቻዋም ቢሆን ፈገግ አለች ። በዚህ ጊዜ አንድ ነገር አደናቀፋት ። ልትወድቅ ስትንደረደር ፒተር ያስጠነቀቃት ትዝ አላት። መውደቅ የለባትም ። በዚህ የሕክምና ወቅት ውስጥ ። በዚህም የተነሳ ነው ከፌ ጋር ወደ በረዶ ሸርተቴ መጫወቻ ቀበሌዎች እንዳትሄድ የተከለከለችው ። እጂዋ ቀድሞ መሬት ይዞ ባይደግፋት አወዳደቋ አደገኛና አሰቃቂ ይሆን ነበር ። ያ ነገር ሲያደናቅፋት በድንጋጤ ጮሃ ነበር። እሷ ብቻ ሳትሆን ሌላም ነገር ጮሆ ነበር አጠገቧ አገኘችው፤ ኩስምን ያለ አቁስጣ መልክ ያለው ውሻ ያኔ ደንግጦ ይጩህ እንጂ አልሸሸም እንዲያውም ጭራውን እያወዛወዘ፣ መለማመጫ ድምፅ እያሰማ እይን አይኗን ያያታል ። «ይቅርታ አጋጣሚ ነው ሳላይዎት ነው ። እርስዎም ነፍሴ ጥላኝ ብን እስክትል እንዳስደነገጡኝ እንዳይረሱ ግን » አለችው ለውሻው ፤ እየሳቀች ። ጎንበስ ብላ ዳበስ ዳበስ ስታደርገው ጭራውን እያወዛወዘ ሀይል በሌለው ሁኔታ «ዉዉ!» አለ። በጣም አስቂኝ የሆነ ትንሽ ውሻ ነበር ።ከመጨረሻው ድንክዬ ውሻ እምብዛም አይበልጥም። ናንሲ ይህን ውሻ ስትመለከት አዘነች እንደራበው በደንብ ያስታውቃል ። የሆነ ሆኖ ምንም ማድረግ አይቻልም አሁን አንስቼ ልውሰድ ብትል አንዱ ውሻየን አስኮበለለች ብሎ ሊከስሳት ይችላል ።

ልትሄድ ስትል በዚያው በሚለማመጥ ሁኔታው ፤ በዚያው ሀይል በሌለው ድምፅ «ውዉዉ ! አለ
«ገባኝ ደህና ይሁኑ ። ባይ ባይ» አለች ፈገግ ብላ እጅዋን ለሰንብት እያወዛወዘች ። ጉዞዋን ቀጠለች ።፡ ውሻውም በጎን በጎኗ ቱስ ቱስ እያለ ይከተላት ጀመር። ስለዚህ መንገደን አቋርጣ ውሻውን ቁልቁል እየተ መለከተች እንዲህ አለችው ። «ስሙ ጌታዬ ! ወስላታ መሆን አይገባም ።፡ ወደ ቤትዎ ይሂዱ በቀጥታ ወደ ቤት፡፡›› ይህ ተደጋገመ። ምክንያቱም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ከሷ መለየት የማይፈልግ ይመስላል ፤ ስትሄድ በጎን በጎኗ ቱስ ቱስ እያለ ይከተላታል ። ስትቆም ይቆምና ሽቅብ ያያታል ጭራውን እያወዛወዘ ፣ በአይኑ እየተለማመጠ ፤ ወይም ቁጢጥ ብሎ። በመጨረሻ ቆማ ቁልቁል ከተመለከተችው በኋላ በነገሩ ከት ብላ ስቃ ጎንበስ አለችና ደባበሰችው የማን ውሻ እንደሆነ የሚገልፅ ዘለበት አንገቱ ላይ ፈለገች ።ግን አልነበረውም። ምንም ምን የሌለው ውሻ ስትል አሰበች። ምን ይሻላል ? ካሜራዋን አስታወሰች ። ፎቶግራፍ ልታነሳው አሰበች ። ገና አንዴ እንዳነሳችው ፎቶ መነሳቱን ያወቀ ይመስል በተለያየ ሁኔታ ይስተካከልላት ጀመር ። መቼም በሷ አስተያየት እነዚያን ሁኔታዎች ስለወደደቻቸው ሊሆን ይችላል እንጂ ውሻው ይህን አውቆ አደረገው ለማለት ያስቸግር ይሆናል ። ለሷ ግን የሚገርም አጋጣሚ ሆኖ ታያት ።
👍26
በመጀመሪያ ሲሄዱ ሲቆሙ ቀጥሎ ፎቶ ስታነሳው ቁጢጥ ሲል ፤ ሲፈነጥዝ ፤ የቀልድ ሊናከስ ሲፈልግ ፤ ከዚያም ሄድ ስትል ከኋላዋ ቱስ ቱስ እያለ ሲከተላት በዚህ ሁኔታ ግማሽ ሰዓት አለፈ ። በዚህ ጊዜ «እሺ እንግዲህ አብረን እንሂድ» አለች ። አብረው ሄዱ። መርከቦች እቃ ወደሚጭኑበትና እሚያራግፉበት ወደብ ። እዚያም የትያትር መድረክ በመሰለው ዋቅራ ላይ ወጥታ የተለያዩ ፎቶግራፎችን አነሳች ። የጐርምጥ ማጠራቀሚያዎችን፣ የሸርጣን ማጥመጃዎችን፣ ቱሪስቶችን ፤ የሰከሩ የገና አባቶችን ፤ ጀልባዎችን ፤፣የባህር ላይ ወፎችን አነሳች። በዚህ መሀል ውሻውንም አንስታው ነበር … ሳይበዛ ። ያንለት ያሰበችውን ያህል ፤ የፈራችውን ያህል የገናን በአል ሳይከፋት ዋለች ። በተለይ ከቤቷ ከወጣች በኋላ ሁሉም ነገር ደስ የሚል ነበር ።ውሻውም ይበልጥ እየለመዳት እየተጠጋት ሄደ እንጂ ከቶም ካጠገቧ አልተለያትም ። ትንሽ እንደመድከም አላት ። በዚህ ጊዜም ካሜራዋን ወደ ማህደሩ መልሳ ቡና ለመጠጣት ወደ አንዲት ትንሽ ቁርስ ቤት ጎራ አለች ። ወደ ቡና ቤትና ትናንሽ ቁርስ ቤቶች መግባት ቀደም ብላ የተለማመደችው ነገር ሆኗል ። ይህን ያህልም ፊቷ አያሳፍራትም ። ማለትም ከባርኔጣዋ ተርፎ በዘለቀው ፀጉሯ ፊቷን ሸፈን ታደርግና የምትፈልገውን ነገር ታዛለች። ለምዳዋለች ዛሬማ የታችኛው የፊቷ ክፍል ስለተገለጠ «አመሰግናለሁ»ብላ ፈገግ ማለትም ትችላለች ። ፊቷን በመስታወት ያየችው ትዝ አላት» አዲሱን ፈገግታዋን ወዳዋለች ። ፒተር ሕክምናውን ሲጨርስ ትመስል ይሆን? ሁኔታውን ስታየው የሚያልማትን ሴት ፊት ሊያለብሳት የሚፈልግ ይመስላል ። እንዲያውም አንዴ በሀሳቤ ውስጥ የማልማትን ሴት ልሰራ እፈልጋለሁ ብሏት እንደነበር ታስታውሳለች። ሰው የሰራው ፊት ለራስ ስሜት ይጎረብጣል ። ሆኖም ይሀን ሰው የሰራውን ፈገግታዋን ወዳዋለች ።

ቡና አዘዘች ፤ ጥቁር ቡና ለራሷ ። ለውሻው ደግሞ የአሳማ ስጋ ሳንድዊች ። እመተላለፊያው ላይ በወረቀት ሳህኑ የመጣለትን ሳንዱች አስቀመጠችለት ። ያው በውሻ እበላል ፤ ያውም የራበው ውሻ !ስልጥቅ አደረገና ቀና ብሎ ያችን ገር «ዉዉ»ውን አሰማት። ‹‹አመሰግናለሁ ማለት ብቻ ነው ወይስ ሌላ ተጨማሪ ነገር አለበት» ስትል ጠየቀችው ። «ዉዉ ! » አላት ደግሞ ። ሳቀች ። አንድ ሰው መጣና ጎንበስ ብሎ ደባበስበው ። እና ‹‹ማነው ስሙ» ሲል ጠየቃት ። ‹‹እኔ እንጃ ፤ በመንገድ ላይ ተገናኝተን እሞታለሁ እንጂ ካንች አልለይም ብሎ ጥብቅ አለብኝ» ስትል መለሰችለት፡፡ «ለፖሊስ ወይም በእንስሳት ላይ የሚደረገውን ጭካኔ ማሰወገጃ ማኅበር ለሚባለው ብታስታውቂ አይከፋም» አለ ሰውየው «ጥሩ! እስካሁን ትዝ አላለኝም ነበር »

እቤቷ ከደረሰች በኋላ ለተባሉት ድርጅቶች አመለከተች ። ያን የመሰለ ውሻ ጠፋብኝ ብሎ ያመለከተ ሰው እንደሌለና ከፈለገች ውሻውን ማቆየት እንደምትችል ካልፈለገች ደግሞ ባካባቢው ወደሚገኘው የጠፉ ውሾች መጠለያ እንድትወስደው ነገሯት ።መጠለያ የሚለውን ነገር ስትሰማ ተናደደች ። ትንሹን፤ ውድ ጓደኛዋን ወደ መጠለያ! ሆሆይ! «እውን ይህ ነገር ደግ ነው?» አለች። «ዉውዉ!» ሲል መሰሰላት ።

ስቃ ታሻሻው ጀመር ። ብዙ ቀን ሲንከራተት እንደቆየና ታጥቦ እንደማያውቅ ሲገባት «ገላዎትን ቢታጠቡ ምን ይመስልዎታል?›» ስትል በፌዝ መልክ ጠየቀችው ። ምላሱንና ጭራውን ባንዴ እያወዛወዘ ተቅበጠበጠ ። አቅፋ ወደ መታጠቢያ ቤት ይዛው ሄደች። አጠበችው። በእውነቱ ይህን ማድረግ አልነበረባትም ። ምክንያቱም ውሻው ደርሶ ሰውነቱን ቢያራግፍ ወይም ቢዘል ውሀው ተሞቦራጭቆ ፊቷ ላይ ያለውን ፋሻ ቢያረጥበው የስንት ጊዜ ልፋት ብላሽ ሊሆን ይችል ነበር። በእርግጥ ተጠንቅቃ ነበር ይህን ያደረገችው።ግን… አጥባ በፎጣ አድርቃ ስትመለከተው ሌላ ውሻ ሆኖ ታያት ። አቁስጣ ሳይሆን ነጭና ቡናማ መልክ ያለው ዝንጉርጉር ሆኖ አገኘችው፡፡ ለድርጅቶቹ በትክክል እንዳላስታወቀች ቢገባትም ውሻዋን መስጠት አልፈለገችም ። ከልጅነቷ ጀምሮ ትመኛለች ። ውሻ የማግኘት እድል ግን አልነበራትም ። «ዋናው ነገር አሁን ስም ነው። ስምዎን ማን ብንል ይፈቅዳሉ?» ጭራውን እያወዛወዘ ተመለከታት ። አንድ ስም አስታወሰች ። ያን ስም ማይክል ነበረ የነገራት አንዴ በጣም የሚወደው ውሻ እንደነበረው ሲያጫውታት። «ፍሬድ የሚለው ስም ይሰማማዎታል ፤ትንሹ ወዳጃችን ? » ስትል ጠየቀችው ውሻውን።«ዉዉ!-ዉዉ! አለ። በጣም በጣም ! ማለቱ ነው ስትል ተረጎመችው ።

••••••••••••••••••

ናንሲ የተዘጋውን በር በቀስታ ከፍታ አንገቷን ብቻ ወደ ክፍሉ ውስጥ አሰግጋ ስትመለከት ፌ አሊሰን (የአእምሮ ሐኪም የሆነችው ጓደኛዋ) እሳቱ አጠገብ ተመቻችታ ተቀምጣ አየች። ፌ ናንሲን ስታይ በደስታ ፈገግታ በራች ። «ምነው ያጮልቃሎ? ምን ያሰቡት ተንኮል አለ ፤እመቤቲቱ?» አለች ፌ አሊሰን ፣ ፈገግ ብላ ። ፈገግ ያደረጋት የናንሲ አመጣጥ ብቻ ሳይሆን ናንሲ ብቻዋን ያሳለፈቻቸውን ሁለት ሳምንቶች ስታስብና ሁኔታውን ስትመለከት ብዙ ለውጥ እንዳላየች ስለገባት ነበር። «አንድ ጓደኛዬ አብሮኝ መጥቷል » አለች ናንሲ፡፡ « አትይኝም ! በሁለት ሳምንት ውስጥ ከዳሽኝና ሌላ ጓደኛ አበጀሽ ?ምናለ ብትጠብቂኝ ? ለመሆኑ እንዴት ቀናሽ ፤ በይ?»

ፌ አሊሰን ይህን ስትል ናንሲ በሩን ከፈት አደረገችው ። በዚህ ጊዜ ፍሬድ እየፈነጠዘ ወደ ክፍሉ ውስጥ ገባ ። ፍሬድ አንገቱ ላይ በተደረገለት አዲስ ቀይ ዘለበት ኩራት የተሰማው መሆኑ በግልዕ ይታወቅበታል ። ናንሲ ፍሬድን ስታጥበው ሌላ መልክ እንዳመጣ ባለፈው ምዕራፍ ተናግረን ነበር ። ይህንን መልኩን ጠቅሳ ለሚሜመለከተው አስታወቀች ቆይታ ። አሁንም የዚያ ዓይነት ውሻ ጠፋብኝ የሚል ብቅ ሳይል ቀረ ። ስለዚህም ፍሬድ የናንሲ ንብረት ሆኗል፡፡ በሷ ስም ተመዝግቧል ። ጤንነቱ ተመርምሮ « ነፃ » የሚል ምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል። ዛሬ ፍሬድ የግሉ መኝታ የግሉ መመገቢያ ገንዳ በርከት ያሉ መጫወቻ አሻንጉሊቶች አሉት የኮራ ውሻ ነው። ናንሲ ደግሞ ትወደዋለች ። « ፌ ፤ከፍሬድ ጋር ተዋወቁ » አለች ናንሲ ውሻውን በፍቅር ዓይን እየተመለከተች ። « ድንቅ ውሻ ነው። የት አገኘሽው ልጄ ?»
«የገና ለት ማታ እመንገድ ላይ በድንገት ተገናኘን ። የጉዲፈቻ ልጅሽ ነኝ ብሎ ተጣበቀብኝ»
«አንቺም ተቀበልሽው ፤ አደል?»
«ምንም ማድረግ አይቻልም ። ስሙን ኖየል (ልደቱ) ብለው ነበር ልክ እሚመጣው ። ሆኖም ፍሬድን መረጥኩለት፡፡ ለምን ፍሬድ አልሽው ብትለኝ ማይክል ፍሬድ የሚባል ቡችላ ስለነበረው ብላት እያለች ስትጨነቅ ፌ አሊሰን ግን ያን ጥያቄ ሳታነሳው ዘግዬት አለች ስለዚህም ናንሲ «ደሞ ይህ ምን ይመስልሻል? ይህ የፎቶ ግራፎች ቅርቅብ ነው። እንድችመለከቻቸው ነው ያመጣሁልሽ»
« አረ በስላሴ ንብ ሆነሽ ነው የከረምሸው ማለትኮ ነው። እንዲህ ከሆነ አሁንም ወደ ሌላ ቦታ ዘወር ብልልሽ ሳይሻል እይቀርም»
«ፌ፤ አንድ ነገር ልለምንሽ የትም የት አትሒጂ አብረን እንድንሆን እፈልጋለሁ»

ናንሲ ይህን ስትል ፌ አሊሰን በመጠኑ ቢሰማትም ሁኔታዋን ላየው ግን ናንሲ ልትገልጸው የፈለገችውን ያህል ብቸኝነቱ እንዳልተሰማትም ግልፅ ሆኖ ገብቷታል ። «ደሞ ሌላ ነገር…» አለች ናንሲ በኩራት።
«ምን?»
«ደሞ ሌላ ነገር የድምፅ አወጣጥ ልምምድ ለማድረግ ይህ ሙያ ካለው ሰው ወር ተዋውዬ ጨርሻለሁ» ፌ አሊሰን በአድናቆት ተመለከተቻት።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍25