😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ አስራ አራት (14)
ይህን ሐሳብ ግን ልትገፋበት አልደፈረችም ። ይህ ሀሳብ በፊቷ ላይ ሲዳምን ፒተር አይቷል ። ብዙ ጊዜ ይጠብቀዋል ። እንድ የተጐዳችበት ነገር . . . ያለፈ ሕይወቷ ቁስል...
ቢሆንም በጊዜ ብዛት ልትረሳው ትችላለች ተስፋ ያደርጋል።
«ፊልምስ ? ፊልም አላመጣሀልኝም ? »
«አምጥቻለሁ እንጄ !» አለና አነስ ያለች አራት ማዕዘን ጥቅል እየወረወረላት ፤ «ካሜራ አምጥቼ ፊልም ልርሳ ?» ሲል ጠየቃት ። «አንተ !! አንተ ምንም አትረሳ !» አለችና መጣደፍ ጀመረች ፤ ካሜራውን ፊልም ለመሙላት ። ወዲያው በተለያዩ አቅጣጫዎች ፤ በተለያየ መንገድ ጠቅ ጠቅ ፤ጠቅ ፎቶ ታነሳው ጀመር ። ይህን እያደረገች እያለ አነስ ያለ ቁጥር ያላቸው ወፎች ባጠገባቸው ሲበሩ ቶሎ ብላ አነሳቻቸው ። «ምናልባት ደህና ፎቶ ላይወጣ ይችላል ። ግን ለመነሻ ምንም አይልም» አለች ። እሱ ግን በጽሞና ይመለከታት ነበር ። ለረጅም ጊዜ በዚህ ሁኔታ ሲያጤናት ከቆየ በኋላ ብድግ ብሎ አጠገቧ ቆመና እጁን ጣል አደረገው እትከሻዋ ላይ ። ከዚያም «ናንሲ ዛሬ ላበረክትልሽ ያቀድኩት ሌላም ስጦታ አለኝ» አላት ። «ገባኝ አወቅኩት ፤ መርሰድስ ነው አይደል?» «የለም ናንሲ ፤ አሁን እውነቴን ነው» አለና በለስላሳ የጽሞና ፈገግታ ተመለከታት ፤ ካንዲት ጓደኛዬ ጋር ላስተዋውቅሽ እፈልጋለሁ ፤ የሁለታችንም ጓደኛ እንድትሆን ። ለየት ያለች እመቤት ነች»
አንዳንድ ቅጽበት አለች ። የምናስበውን በቅጡ መረዳ? የማንችልባት ። በዚያች ዓይነቲቱ ቅጽበት ናንሲን የሆነ ቅናት መላ አካሏን ሲወርራት ተሰማት ። ቢሆንም ከፒተር ሁኔታ/ ስሜት ሊሰማት እንደማይገባ ተረዳች ። «ፌ ትባላለች» አለ ፒተር ። «ሕክምና ያጠናነው ባንድ ነው ። ባሁኑ ጊዜ ፌ አሊሰን በምእራብ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙት ሳይኪያችሪሰቶች አንዷ ናት ።ምናልባትም በሀገሪቱ ሉ ከሚባሉት ታላላቅ የአዕምሮ ሐኪሞች አንዷ ልትሆንም ትችላለች ። በጓደኝነት መልክ ከሆነ ደግሞ ጓደኛ ሳይሆን ሁሉን ነገር የማለት ያህል ናት ።እንደምትወጂያት ተስፋ አለኝ ።»
«እና ?» አለች ናንሊ በመንፈሷ ውጥረትና የማወቅ ጉጉት ይታይባታል ።
«እናማ ብትተዋወቁ... ብታነጋግሪያት ደህና ይመስለኛል ። ማለት ነገሩን ከዚህ በፊት በመጠኑ ይሁን እንጂ ተነጋግረንበታል»
«ትንሽ የተዛባ ፤ ማለቴ መንፈሴ በቅጡ የተረጋጋ መስሎ አልታየህም ማለት ነው? » የመከፋት ድምጽ ነበር ። ይህን ስትጠይቀው ካሜራውን ወደ ጐን ቁጭ አደረገች ።
«አላልኩም ናንሲ ፤ በሁሉም በኩል ምንም እንከን የለብሽም ። ከቀን ወደ ቀን እየተረጋጋሽ ፤ ከቀን ወደ ቀን አዲስ እየሆንሽ እንደምትሄጂ አትጠራጠሪ ። ግን ደግሞ አስቢው ። ሌላው ቢቀር የሚያዋራሽ ፤ ከኔ ሌላ ሰው ያስፈልግሻል ። እኔ ፤ ሊሊና ግሬችን ብቻ በቂ አይደለንም ። ሌላ ሰው ያስፈልግሻል ወይስ አያስፈልግሽም ? » አለ ። መልሱን በልቧ ሰጠች ። አዎ አለች በልቧ ፤ያስፈልገኛል ። ያም ሌላ ሰው ማይክል፤ እሱ ብቻ ነው ።
«እንጃ ርግጠኛ አይደለሁም ። አስቤው አላውቅም» አለችው፡፡ «ከፌ ጋር ከተዋወቃችሁ በኋላ ለካ ታስፈልገኝ ኖሯል እንደምትይ ርግጠኛ ነኝ ። በጣም ደግና ሰው ወዳድ ፍጡር ናት። በዚያም ላይ ስላንቺ ሁልጊዜ ትጠይቀኛለች»
«ታውቃለች ማለት ነው? »
«ገና ነገሩ ሲወጠን ጀምሮ !» አለ ። ይህን ያለውም ናንሲን ለማግባባት አልነበረም ። እውነቱን ነበር ። ዶክተር ዊክፊልድና ማሪዮን ሂልያርድ ደውለው ያነጋገሩት ዕለት ፌ አሊሰን አብራው ነበረች ። ምክንያቱም ምንም እንኳ ናንሲ ይህን ማወቅ ባይኖርባት ፤ ፒተር ግራግሰንና ፌ አሊሰን በአካልም ግንኙነት አላቸው ። እንደ ፍቅረኞችም ናችው ጉዳዩ ግን በጣም የጠነከረ አልነበረም ። ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ያደርጉታል ። ከሱ ይልቅ ጓደኝነታቸው የጠነከረ ነው ። «ዛሬ ከቀትር በኋላ እመጣለሁ ብላኛለች ። ቡና እየጠጣን እንጫወታለን ። እንዴት ነው ! ቅር ይልሻል ?»
«አይ ቅር አይለኝም» አለች ፤ ምክንያቱም ቅር ይለኛል ብትልም ዋጋ አልነበረውም ። ያለቀለት ጉዳይ ነው ። ከዚያ በኋላ የወትሮዋ ናንሲን መሆን አልቻለችም ። ሁሉ ነገሯ ቁጥብ ሆነ ። የለም የሌላ ሰው በሷና በፒተር መካከል መገባት ምንም ደስታ ሊሰጣት አልቻለም ። ሦስተኛ ጓደኛ... ለዚያውም ሴት ፤ አልመስልሽም አላት ። የውድድርና የእምነት ማጣት ስሜት ዋጣት ።
ይህም የሆነው ከፌ ጋር እስኪተዋወቁ ፤ ፌን እስክታያት ነበር ። ፌ አሊሰን በተባለው ሰዓት መጣች ። አየቻት። ረጅም ፤ ቀጭን ፤ ነጣ ያለ ወርቅማ ፀጉር ያላት አጥንተ ሰፊ ሴት ነበረች ። ሆኖም ፊቷ ምንም ዓይነት ጭካኔ ወይም ክፋት አይታይበትም ። ይህም ሁሉ ሆኖ የናንሲ ልብ አላመነም። ጨዋታ ሲጀመር ፌ በቀላሉ ቀጠለች። ዓይኖቿ ሕያው ሲሆኑ ፈጥኖ የመገንዘብ ችሎታም ይታይባታል ። ቀልድ ሲመጣ ሰም ቀለድ ፤ ሲጠይቋት ለመመለስ ፤ የሳቅ ሰዓት ሲሆን ደግሞ ከት ብላ ለመሳቅ ተዘጋጅታ የምትጠብቅ ትመስላለች ። ልብ ብሎ ያያት ሰው ለቁምነገርና ጨዋታም ዝግጁ መሆኗን ሊገነዘብ ይችላል ። በቂ ቃላት ከተለዋወጡ በኋላ ፒተር ሹልክ ብሎ ወጣ ሁለቱ ይበልጥ እንዲጫወቱ ብቻቸውን እንዲሆኑ ። ያኔ ናንሲ ደስ ተሰኘች ። ከልብ ደስ ተሰኘች ።
ፌና ናንሲ ስለብዙ ነገር አወሩ ። ሺህ ጉዳዮችን አነሱ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በናንሲ ላይ ስለደረሰው አደጋ አላነሱም፡፡ ወዲያው ፌ ስላሳለፈቻቸው ነግሮች ቀስ እያለች ታጫውታት ጀመር ። ቁርጥራጭ አጋጣሚዎችን ከሕይወቷ ውጥንቅጥ እየመዘዘች ነገረቻት ። ናንሲም ሳታስበው ከሕይወቷ አካል ትንሽ ገለጥ እያደረገች በጨረፍታ አሳየቻት ። እየቆየች ከዚያ በፊት በተለይም ከማይክል ጋር ከመገናኘቷ በፊት ለማንም ሰው ነግራ የማታውቃቸውን ነገሮች ሁሉ ነገረቻት ። ስለ እጓለማውታን ማሳደጊያው አወጋቻት ። ይህም ለፒተር በነገረችው መንገድ ሳይሆን ፤ ማለት በቀልድ ሳይሆን የምር ይሰማት የነበረውን ትዘከዝክላት ጀመር ። ብቸኝነቱን ፤ ማን ነኝ ? ከየት መጣሁ ? ብላ ትጠይቀው የነበረውን ፤ ማን ለምን እዚያ ወስዶ ከተተኝ ? ትል የነበረውን ሁሉ ።

👍10😁1
ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዴት እንደተነሳ ሳታውቅ ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ታጫውታት ጀመር ። ፌ አሊስን ይህን ሁሉ የምታዳምጣት በጽሞና ነበር ፤ መገረም የለ፤መጨነቅ የለ ። በጽሞና ፤
«እኔንጃ ፤ ብቻ ስናገረው እንኳ ለራሴም እንግዳ መሆኑ ይታወቀኛል ። ግን…» አለችና ንግግሯን መቀጠል ተሳናት። ለምን ? ቂል የሆነች፤ ልጅ የሆነች መስሎ ተሰማት ። እና በጽሞና እምታዳምጠውን አዲስ ጓደኛዋን ቀና ብላ አይታ ለመቀጠል ሞከረች ። «ግን እየሽ እኔ . . . እንዳልኩሽ ያላባትና ያለናት ስላደግኩ» አሁን አፏ ፈታ እያለ ሄደ ። «ምንም ዘመድ አዝማድ የሚባል ነገር ኖሮኝ አያውቅም ነበር ። እናት ወደሚባለው ነገር ቀረብ ልትል የምትችለው ያው የሕፃናት ማሳደጊያው ዋና ነበረች ። አበምኔቷ ። እሷም ያው እንዶ እናት ሳይሆን ምናልባት እንደ ጋለሞታ አክስት ብትቆጠር ነው ። ስለማሪዮን ግን ያው መቼም ማይክልም ፤ ቤን የሚባለው የሱ ጓደኛም ሆነ ብለው ከነገሩኝ ወይም ድንገት ከምሰማው ብዙ ነገር እየሰማሁም ይህ ሁሉ እያለ ፤ ብንገናኝ ትወደኝ ነበር ፤ በተገናኘን ብቻ ! የሚለዉ ጅል ሐሳብ ልበልሽ ቅዝት ወይስ ሕልም ሁልጊዜ ይታየኝ ነበር ። መቼም ቢሆን ፤ ማሪዮንና እኔ ስምም ሆነን እንኖራለን የሚለውን ሐሳብ አምንበት ነበር» ድንገት ዓይኗ ላይ እንባ ግጥም አለ ። ላለማልቀስ እየታገ ለች ፊቷን ወደ ሌላ አዞረች ። «ምናልባትም እናቴ ትሆናለች ፤ ማለት እንደ እናት ትሆነ ኛለች ብለሽ ታስቢ ነበር ?» ናንሲ በአዎንታ ራቧሷን ነቀነቀች ። «እብደት አይደለም ይኸ ታዲያ ? »
«በፍጹም ። በፍጹም እብደት አይደለም ። ያለ ነገር ነው። ያለ እናት አደግሽ ።ማይክልን ወደድሽ ። የማይክልን እናት እንደ እናትሽ ለማየት ፤እናትሽ ለማድረግ ተመኘሽ። ያለ ነው። ምናልባት በዚህ ምክንያት ይሆን ፤ በመጨረሻ በውል መልክ ስትስማሙ በማሪዮን በጣም የተማረርሽባት ፤ አንችንም በጣም የከፋሽ ?»
«አዎ ። አየሽ እንዲያ ባለ ሁኔታ ቃል ስታስገባኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል እንደምትጠላኝ አረጋገጠችልኝ»
«እኔ ደሞ እንዲያ አይመስለኝም ። የሆነ ነገር ያላት ይመስለኛል ። ያ ባይሆን ይህን ሁሉ ነገር አታደርግልሽም ነበር ።ያ ሁሉ ገንዘብ ከፍላ አካልሽ እንዲመለስ ማድረጓ በጣም ስለምትጠላሽ አይመስለኝም» ይህን ሁሉ ምቾት ትተን አለች በልቧ ፌ አሊሰን ። «ግን ውሉን አስቢው። ይህን ሁሉ ያደረገችልኝ እኮ ማይክልን እንድተውላት ነው ። ከማይክል ጋር ግንኙነት ብፈጥር… እኔ ፈልጌ ዉሉ ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፡፡ ተቀብለሽ ከሱም ፊት ከኔም ፊት ጥፊ እንደማለት ነዉ ያኔ ስታነጋግረኝ ገባኝ ። ማሪዮን መቼም ቢሆን ልትቀበለኝ አትፈልግም ፤ ብዬ አሰብኩ ። ይህ ሐሳብ እንደተሰማኝ የሆንኩትን ልነግርሽ አልችልም ። በሕይወቴ ውስጥ ካጋጠሙኝ አስከፊ ነገሮች አንዱ ነበር» ይህን ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ። እንደገና መናገር ስትጀምር ድምጺ ለስለስ ብሎ ነበር ። «ግን ችግርም ፣ ስቃይም መከፋትም ለኔ ኦዲስ አይደሉም ። ደጋግመው ደርሰውብኝ ደጋግሜ አሳልፌአቸዋለሁ»
«ወላጆችሽ ሲሞቱ ነፍስ ታውቂ ነበር ?»
«ይህን ያህል የጐላ ትዝታ የለኝም» የምታስታውሰውን ያህል ነገረቻት ። ቀጥላም ፤ «ትዝ የሚለኝ የሚመስለኝ ምናልባት ብቻን መቅረት አለ አይደል እንደዚያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር መሰለኝ» አለች ። «ልክ አሁን እንደሚሰማሽ ዓይነት ስሜት?» ግምት ነበር ። ቢሆንም ባዶ ግምትም አልነበረም። «ምናልባት ሳይሆን አይቀርም ። የት እገባ ብሎ ማሰብ ። ልክ ሳይሆን አይቀርም ። ከዚህ በኋላ የት ነው እምገባ ? ማነው አይዞሽ የሚለኝ ? የሚል ስጋት ። አሁንም አልፎ አልፎ የዚህ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል» «ምናልባት ማይክል ? ማይክል ይፈልገኛል ፤ አይጥለኝም ብለሽ ትገግምቻልሽ ? »
«አዎ ፡፤ አንዳንዴ እንደሱ አስባለሁ። የለም አንዳንዴ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ።»
«በሌላ ጊዜስ ? ማለት ሁሌም አላልሽም»
«እሁን አሁን መጠራጠር ጀምሬአለሁ ። በፈት በፊት አየሽ ሳይመጣ ሲቀር ጊዜ ፊቴን ማየት ፈርቶ ነው ፤ ተሳቆ ነው እል ነበር ። አሁን አሁን ግን ስለሕክምናው ያውቃል ። ስለዚህ ምን ደረሰች ፤ እንዴት ነው ብሎ መጠየቅ ነበረበት ። ታዲያ እንዴት እንዲህ እልም ሊል በቃ ? እላለሁ»
«የግምት መልስ ሰጥተሽዋል ለጥያቄሽ ? »
«አዎ ። ግን በቂ መልስ የምትይው አይደለም ። አንዳንዴ ማሪዮን ያሳመነችው ይመስለኛል ። የሱ ዓይነቱን መልካም ስም ከሌለው ቤተሰብ የወጣች ሴት ጋር ማጋባት ለሙያህ ደግ አይደለም ብላ አሳምናው ይሆን እላለሁ ። ማሪዮን ቀላል ሰው እንዳትመስልሽ !»
«እሱ እንዲህ ዓይነቱን ሐሳብ ይቀበላል ትያለሽ ? »
«በፊት እንኳ ርግጠኛ ነኝ አይቀበልም ። አያምንበትም ፤ ነበር ... አሁን ግን እንጃ፤ምን ይታወቃል?»
«ሌላ ቢያገባ... ቢተውሽ ምን ያህል የምትጐጂ ይመስልሻል?» ናንሲ ኩምትር ስትል ታየች ። መልስ አልሰጠችም ። ግን መላ አካሏ መልሱን ሰጥቷል ። «የሆንሽውን ሲሰማ ደንግጦ ወይም እንዲያ ሆና ላያት አልፈልግም ብሎ እንደሆነስ ያልመጣው ? አየሽ ናንሲ ፤ አንዳንድ ወንዶች እኛ የምንፈልገውን ያህል ጠንካሮች አይደሉም»
« ይሆን ይሆናል »
«ታዲያ. . . በኋላ ከዳንሽ ከተስተካከልሽ በኋላ ቢመጣ ቅር አትሰኝበትም ?››
«ምናልባት ቅር ይለኝ ይሆናል ። ምኑም ግልጽ ሆኖ አይታወቀኝም ። አስባለሁ ፤ አስባለሁ ። ግን መልስ የለም»
«መልሱን መፈለግም አያሻም ። መቆየት ይመልሰዋል ጊዜ ይመልሰዋል ። ዋናው ነገር ግን ስሜትሽን መሸሽ የለብሽም ። ስሜትሽን በትክክል ለመረዳት መሞከር አለብሽ በቂ ነው ።ለመሆኑ ስላንቺ የሚሰማሽ ምንድነው ? ማለት ፊትሽ እንግዳ ነው እንግዳ ነሽ ለራስሽም ። ይህን ስታስቢ ትቅበጠበጫለሽ ? ትፈሪያለሽ ? ትደሰቻለሽ ? ትናደጃለሽ ?»
«ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ» አለች ። ሁለቱም ሳቁ «ግን አብዛኛውን ጊዜ በጣም እፈራለሁ ፤ እጨነቃለሁ ። አብሮ የኖረ ነነር ቀላል አይደለም ። ሀያ ሁለት ዓመት ሙሉ እኔ ያልኩት ሌላ ሲሆን አስቢው ፤ አያበሳጭም ብለሽ ነው?»
«እንዲያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶሽ ያውቃል?»
«አንዳንዴ. . . ግን አብዛኛውን ጊዜ ደፍሬ አላስብም ስለዚህ ጉዳይ»
«ብዙ ጊዜ እምታስቢው ስለምንድነው ?››
«እውነት ንገሪኝ ነው እምትይኝ ? »
«አዎና»
‹‹ማይክልን ። አንዳንድ ጊዜ ፒተር በሐሳቤ ይገባል ። አብዛኛውን ጊዜ ግን ስለማይክል ነው እማስበው»
«ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !»
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍23❤1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ስልሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሚስተር ካርላይል ከታወቀው ከባክስ ሔድ ሆቴል ሰገነት ወጥቶ ለተሰበሰበዉ ሕዝብ ንግግር ያደርግ ነበር " አረንጓዴ የተቀባው ስገነት ደጋፊቹን ሁሉ አሰባስቦ ለመያዝ በቂ ስፋት ነበረው ሚስተር ካርላይል አስቀድሞ ከነበረው መልካም
ስምና ተወዳጅነት ሌላ በንግግር ተስጥዎ የታደለ ስለ ነበሮ የዌስት ሊን ሕዝብ
ወደሱ እያደላ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን አገለለው።
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንም በበኩሉ ሬቨን ሆቴል ሆኖ ንግግር እያስማ ነበር "
ሆቴሎ ያማሩ መስኮቶች እንጂ ሰገነት አልነበረውም " ቦታው በደንብ ቁሞ ንግግር
ለማድረግ አይመችም " ስለዚህ ከአንደኛ ፎቅ ወደ ምድር ቤት ወርዶ በሳሎኑ ቅስት መስኮት ውጪኛ ጠርዝ ላይ ቁሞ ለመናገር ተገደደ " ያም ሆኖ ቦታው በጣም በመጥበቡ ክንዱን ማወወዝ እግሩን ማንቀሳቀስ ቢሞክር ሚዛኑን መጠበቅ ተቸገረ »
እሱን ሊያዳምጥ ከቆመው ሕዝብ ላይ በጭንቅላቱ እንዳይደፋ ስለ ፈራው ' ለመጀመሪያ ቀን ብቻ በአንድ በኩል ሚስተር ድሬክ በሌላው በኩል ጠበቃው ደግፈውት
ሊወጣው ቻለ ጠበቃው ግን ቁመቱ ከሁሉ ያጠረ ፡ ጐኑ ከሁሉ የሰፋ ወደል
በመሆኑ በንግግሩ መጨረሻ ተመልሶ ለመግባት ችግር ገጠመው " ሰር ፍራንሲዝ እየጎተተ ሚስተር ድሬክ እንደ መሰላል ተሸክሞት እየገፋ የተሰበሰበው ሕዝብ እየሳቀበት በስንት መከራ በደኅና ወረደ " ላቡን ከፊቱ እየጠረገ ዳግመኛ በመስኮት ላይ
በመንጠልጠል በልቡ ማለ
ሰር ፍራንሲዝ ሊቪሰን ሲናግር ያንቀጠቅጠዋል " አንድ ቀን ከቀትር በኋላ
ንግሩን በርቱዕ አንደበቱ ሲያንቆረቁረው ጓደኞቹ አብረውት ቁመዋል " የተሰበሰበው ሕዝብ መንገዱን ሙልት አድርጎ ዘግቶ ጥቂቱ ድጋፉን በመግለጽ እጅግ
የሚበልጠው ግን በማሾፍ ይሥቃል ያፋጫል ይጮኻል ያጨበጭባል " ሚስተር ካርላይል ንግግሩን ቀድም አድርጎ ስለጨረሰ ከሱ ዘንድ የነበረው ሕዝብ ግልብጥ
ብሎ ሰር ፍራንሲዝን ለማዳመጥ መጥቷል " ስለዚህ የነበረው ሕዝብ ብዛት ይህ ነው አይባልም » መተላለፊያ ጠፍቶ በክርኑ እየተጓሸመ • በትከሻው እየተጋፋ እግር ለእግር እየተራገጠ ይርመሰመሳል " ሕዝቡ እንደዚህ ሲተራመስ አንድ ባለ አራት እግር ግልጽ ሠረገላ እንደዚህ በሚተራመሰው ሕዝብ መኻል እየጣሰ በማለፍ ሊበትነው ሞከረ የሚስቡት ፈረሶች ደማቅ ቀይና ወይን ጠጅ ምልክት አሥረዋል " ከሠረገው አንዲት መልከ መልካም ወይዘሮ ተቀምጣለች ሚስዝ ካር
ላይል ።
ጥቅጥቅ ብሎ የምላው ሕዝብ ግን በቀላሉ የሚበተን አልሆነም " ሠረገላው በጣም እያዘገመ አንድ አንድ ጊዜም ቆም እያለ ለመጓዝ ተገደደ በዚህ ላይ ትርምሱና ጩኽት በረከተ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንም ሁኔታው ስክን እስኪልለት ንግግሩን ገታ አያረገ " ባርባራን ባጠገቡ ስታልፍ አይቷታል " ነገር ግን ሚስ ካርላይልን ሰላም በማለቱ የደረሰበትን ጣጣ በማስታወስ እጅ ሳይነሣት ዝም አለ " ወደ ባርባራም ሆነ ወደ ሌላ ትኩረት ሳያደርግ ሰው እስኪረጋጋለት ዝም ብሎ ይጠብቃል
ባርባራ ዳንተል ሥራ የሆነው ጃንጥላዋን ዘርግታ ዐይኖቿን ወደሱ በመለስ በወንፊቱ ተመለከተችው " በዚህ ጊዜ የቀኝ እጁን አነሣ" ራሱን ወደ ኋላው በቀስታ ነቀነቀ ጸጉሩን
ከግንባሩ ወደ ኋላ ምልስ አደረገ " የጣቱ ያልማዘ ቀለበት
በዙርያው አንጸባረቀ " ባርባራ ይኸንን ሁኔታውን እያየች ፊቷ ተለዋወጠ "
ስለ ሪቻርድ የተናገረቻችው ምልክቶችና ድርጊቶች አንዳሉ ናቸው ሪቻርድ ፍራንሲዝ ሌቪስንን ዐውቀዋለሁ ያለው ተሳስቶ ነው " ይህ ሰው ቶርን መሆን አለበት ብላ አሰበች።
በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሰላም ሲሏት አጸፋውን የምትመልስው ያለ ልቧ ነበር ሐሳቧ ተበጠበጠ „ “ ካርላይል ይኑር ! ምን ጊዜም ካርላይል! ብለው እየጮኹ
ባጠገቧ ሲያልፉ ባርባራ በግራም በቀኝም አጸፋውን እጅ በመንሣት ትመልስ እንጂ ሀሳቧ ከሌላ ነበር።
በመጨረሻ ሠረገላው መንገዱን ቀጠለ።
ንግግሩ አብቅቶ ሕዝቡ ሲበታተን ሚስተር ዲልና ሚስተር ኧበንዘር ተገናኙ ኧበንዘር ጀምዝ ለአሥራ ሁለትና ዐሥራ አምስት ዓመት በተለያዩ ሙያዎች በመሠማራት
የሚስተር ካርላይል ጸሐፊ ነበር ቀጠለና ሊንበራ ላይ ከነበረው ቲያትር ሮያል ከተባለው ገባ ከዚያ ሐራጅ ሻጭ ሆነ ያን ተወና ቄስ ሆነ።ከዚያ በኋላ የሕዝብ ማመላለሻ
ትልቅ ሠረገሳ ነጅ ሆነ ያ ደግሞ አላዋጣም ሲለው ቦልናትሬድማን ለተባሉ የዌስት ሊን ጠበቆች ጸሐፊ ሆነ ኧበንዘር ጀምዝ በቁም ነገር በኰል በዋልፈሰስ ቢሆንም ወግ
አዋቂ ለዛ ያለው ፈገግታ የማይለየው ጥሩ ሰው ነው " የሱ ክፋቱ ከችጋር አይወጣም " ኪሱ ባዶ ይሆናል አንዳንድ ጊዜም ከነሚላባብሰው ያጣል አባቱ በንግድ የተገኘ ብዙ ሀብት ያፈራ በሰው ዘንድ የተከበረ ነው " ነገር ግን'ሁለተኛ ሚስት አግብቶ የሁለት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሆነ " ስለዚህ ልጁም ገንዘብ ብሎ ወደባቱ
አይሔድም ቢሔድም ቁጣን እንጂ ገንዘብ አያገኝም "
“ ታዲያስ ኧበንዘር” አለው ሚስተር ዲል ሰላምታ ሲስጠው “ ዓለም እንዴት ይዛሃለች ?”
"አለች ታዘግማለች አንድም ቀን ሶምሶማ አትረግጥም ! ”
“ ትናንት ወደ
አባትህ ቤት ስትገባ አላየሁህም ?
ወዲያው ተባርሬ ወጣሁ ። እኔ እኮ እዚያ ቤት ከሔድኩ እንደ ውሻ ነው የምታው ቤሳ ከሚሰጠኝ ቢረግጠኝ ይወዳል ኧረ አሁን ዝም በል ! ሰዉ የውድድሩን ንግግር እንዳይሰማ እያስቸገርን ነው "
የተባለው ንግግር የስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው » ሚስተር ዲል ኮስተር ብሎ ሚስተር ኧበንር ደግሞ ሣቅ ሣቅ እያላቸው ሲያዳምጡ ከመኻል አንድ ዐይነት ግፊያና እንቅስቃሴ ወደ ዳር አወጣቸው ተናጋሪውን ማየት ከማይችሉበት ቦታ ደረሱ ንግግሩን ግን ይሰሙታል • እንደዚያ ተገፋፍተው ከቆሙበት ቦታ ሆነው መንገዱ ከሩቅ ድረስ ይታያቸዋል አንድ ሰው በኋላ እግሮቹ ቁሞ የሚሔድ የሩስያ ድብ የመሰለ ነገር ድንገት ከሩቅ ሲመጣ አየ
"
“ እኔስ ያ የሚመጣው ሰውዬ ቤቴል መሰለኝ ” አለ ኧበንዘር ጀምዝ "
· ቤቴል ! ” አለ ሚስተር ዲል ወዶ ሰውዬው እየተመለከተ ” “ ምን ሲያደርግ ከርሞ ብቅ አለ ?
ኦትዌይ ቤቴል ከድብ ቆዳ የተስፋ የመንገድ ልብስ ሳይቆረጥ ከነጅራቱ እንደ ለበሰና ጸጉራም ቆብ እንደ ደፋ ገና መድረሱ ነበር" የቆቡ ልብሱም ሆነ የፊቱ ጠጉር ሁሉ የተቆጣጠረና የተጠላለፈ ነበር እውነትም የዱር አውሬ ይመስል
ነበር ወደሱ ሲጠጋ ሚስተር ዲል የእውነት አውሬ ሆኖ ታየውና እንዳይበላ የፈራ ይመስል ወደ
ኋላው አፈገፈገ "
ስምህ ማን ይባላል ?
“ቤቴል እባል ነበራ ” አለ አስፈሪው ሰውዬ እጁን ወደዲል አየዘረጋ። “ጀምስ... እስካሁን ድረስ እተንፈረጋገጥህ በዚህ ዓለም አለህ ?”
“ ወደፊትም እንደዚሁ እየተፈራገጥሁ እንደምቆይ ተስፋ አለኝ... ኧረ አሁን ከየት ብቅ አልክ ? ከአንድ የሰሜን ዋልታ መንደር ነው ?”
እዚያ ድረስ እንኳን አልሔድኩም ... የምን ግርግር ነው የምሰማው?
“ መቸ መጣሀ ሚስተር ኦትዌይ ?” አለው ሽማግሌው ዲል ።
“ አሁን በዐሥሩ ሰዓት ባቡር መድረሴ ነው ። ምን ነገር ነው የምሰማውኮ ነው የምለው ?
ምርጫ ነው ” አለ ኧበንዘር “ አትሊ ተሸኘ ፤ አራት እግሩን በላ ”
“ ስለ ምርጫው አልጠየቅሁህም ስለሱ ከባቡር ጣቢያ ሰምቻለሁ” አለ ኦትዌይ ቤቴል” “ይህ ምንድነው ?” አለ መልሶ እጁን ወደ ሕዝቡ እየዘረጋ ።ደ
" ከተወዳደሪዎቹ አንዱ የሆነው ሌቪሰን ቃላትና ትንፋሽን እየዘራ ነው ''
“ እኔ የምልህ አሁን የሱ ከሚስተር ካርላይል ጋር መወዳደር በጣም አያስገሮምም ? አለ ቤቴል

👍17
“ ኃፍረት የሌለው ወራዳ ” አለ ዲል በንዴት ‥ “ ገና ምሱን ያገኛል አሁንም ጀምረውታል " ትናንትና ከሚስተር ጀስቲስ ሔር አረንጓዴ ኩሬ ውስጥ ደኅና አድርገው አስተናግደውታል
“ መቸም በመንገድ እየተጎተተ ሲሔድ በአካል ዲያብሎስን ይመስል ነበር” አለ ኧበንዘር እሣየቀ “ ወደ ሆቴሉ ወስደው ብርድ ልብስ ደራርበው ካለበሱት በኋላ የጎረና ብራንዲ ግተው ግተው ዛሬ ደግሞ ሰው መስሏል ”
“ እና አሁን ከካርላይል ጋር ተወዳድሮ ሊያሸንፍ ነው ?
“ ኧረ ባክሀ ወንድሜ ከካርላይል ጋር ተወዳድሮ ሊያሽንፍ!ምንም ተስፋ
የለውም " ደጋፊዎቹም የከብት መንጋ ቢሆኑ ነው የካርላይልን ተሰሚነት ያልተገነዘቡት ቤቴል . . .ሔደህበት የነበረው አገር ያለው ሕዝብ አለባበሱ እንደዚህ
ነው ?
“ ኪሳቸው ለመነመነባቸውና ብርድ ለጠናባቸው አሁን በግማሽ ዋጋ እሸዋልሃለሁ ጀምስ እስቲ ግን ይህን ሌቪሰን የሚባለውን እንየው ሰውዬውን አይቸው አላውቅም ”
ሌቪሰን ገና እየተናገረ ሳለ እንደገና ሌላ ትርምስ ተፈጠረ በዚህ አጋጣሚ
ተጠቅመው እነ ኧበንዘር ወደ ሌቪሰን ፊት ለፊት ተጠጉ ።
ይኸን ደሞ ከዚህ ምን አመጣው ? ምን እያደረገ ነው ? እንዴ
ማን?
“ ይኸ በእጁ ነጭ መሐረብ የያዘው” ብሎ በጣቱ አመለከተው "
“ እሱ እኮ ነው ስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን"
“ እንዴ ! እሱ ! ስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ! ?”
በዚያች ቅጽበት ፍራንሲዝ ሌቪሰንና ኦትዌይ ቤቴል ዐይን ለዐይን ግጥም አሉ
ቤቴል ጸጉራም ቆቡን ቢያነሣለት ሌቪሰን ድንግጥ አለ " ላንዳፍታ ብቻ የሚያደርገው ቅጡ ጠፍቶት ከቆየ በኋላ መነጽሩን ከዐይኑ ደንቅሮ፡ እንደዚህ የምትደፍረኝ ኧረ አንተ ደሞ ማነህ ? የሚል ይመስል በትዕቢት ዐይን ይመለከተው ጀመር ጕንጮቹና ከንፈሮቹ ግን እንደ ዕብነ በረድ እየነጡ ሄዱ "
“ ሌቪስንን ታውቀዋለህ
ኦትዌይ ቤቴል ? አለው ዲል
“ ዱሮ ትንሽ ትንሽ ዐውቀው ነበር "
“ ሌቪሰን ሳይሆን ሌላ የነበረ ጊዜ ” አለና ኧበንዘር ትንሽ ሳቅ ብሎ'“አይደለም ' ቤቴል ? አለው።
ቤቴል ደግሞ ልክ ሌቪሰን እሱን እንደ ገላመጠው አድርጎ ኤቤንዘርን ገልመጥ አደረገውና ምን ማለትህ ነው እባክህ ? ሥራም የለህ ?” አለው "
ኧበንዘርን ቸለል አለና ለዲል ራሱን ነቅነቅ አድርጎ ዞር እልም አለ ።
ሽማግሌው ኧበንዘርን ጠየቀው
ምንድነው የምትባባሉት ? አለው ዲል
“ ነገሩስ እስከዚህ አይደለም
አለ ኧበንዘር እየሣቀ“ ብቻ ” አለ ራሱን ወደ ሰር ፍራንሲዝ እየነቀነቅ “ዱሮ እንደ ዛሬው ታላቅ ሰው አልነበረም
“ እንዴት ?”
“ አይ .. .እኔ እንኳን ምናገባኝ በማለት ነገሩን ለማንም ተንፍሸው አላውቅም አንተ ግን ከምስጢሩ ባካፍልህም ግድ የለኝም። ዛሬ የዌስት ሊን እጩ እንደ ራሴ ሆኖ የቀረበው ይህ ታላቅ ባሮኒት ዱሮ በአቤይ ጫካ እየተሹለከለኩ ከአፊ ሆሊ
ጆን ጋር በፍቅር ይከንፍ እንደ ነበር ታምናለህ? ያን ጊዜ አለባበሱ ሺክ ያለ ጥሩ
ጥሩ ጌጥ ወዳጅ ነበር ከዌንሰን በኩል በፈረስ እየመጣ ፈረሱን ከጫካ አስሮ ከአፊ ጋር ያመሽ ነበር።ያ ሁሉ ሲሆን ቶርን እንጂ ሌቪሰን መሆኑን የሚያውቅ አልነበረም ።
“ አንተ ይህን ነገር እንዴት ልታውቅ ቻልክ ? አለው ሚስተር ዲል ።
“ ምን አንተ ደሞ
እኔስ ለራሴ እያልኩ ማታ ማታ እሷው ዘንድ እንከራተት አልነበር ? እንዲያውም እሱና ያ ነፍሰ ገዳዩ ሪቻርድ ባይኖሩ ኖሮ እኔ ላገባት ነበር " ሪቻርድን ይኸን ያህል ወዳው ሳይሆን ሁለቱም ያላቸው ሰዎች ልጆች ስለ ነበሩ ነው " እና ያን ጊዜ ዘወትር አየው ነበር
“ ግን ያን ጊዜ ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ዐውቀህ ነበር?”
ኧረ የለም እሱ ቶርን ነኝ ይል ስለ ነበር ቶርን እያልኩ ነበር የምጠራው ዛሬ ከካርይል ጋር ለመወዳዶር ብቅ ሲል ልክ እንደ ቤቴል እኔም ደነገጥኩና ወይ ጉድ ቶርን ሙቶ በምትኩ ሌቪሰን በቀለ ብዬ ለራሴ ገርሞኝ ዝም አልኩ …”
ኦትዌይ ቤተል ከሱ ጋር ምን ግንኙነት ነበረው ?
እኔ እስከማውቀው ድረስ ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም " ብቻ ቤተል
ለአፊ ሳይሆን ለሌላ አደን ጫካውን ያዘወትረው ስለ ነበር ቶርንን ደጋግሞ ሳያየው አልቀረም አሁን ባንድ ጊዜ ሲያስታውሰው ልብ ብለሃል "
“ ቶርን ኮ ... ሌቪሰን ማለቴ ነው መታወሱን የወደደው መስሎ አልታየኝም
"እሱ ባለበት ሁኔታ ያለ ከሆነ ማንስ ቢሆን መቸ ደስ ይለዋል?” አለ ኧበንዘር
ጀምስ እየሣቀ። “ እኔ እንኳ ራሴ ተራ ሰው ሁኜ የፈጸምኳቸውን የዱሮ ዕብደቶች ሁሉ ዛሬ ቢያወሱብኝ አልወድም " ስለዚህ ለቪሰን፡ “ቶርን እያለ አፊ ሆሊጆንን በወዳጅነት ይዞ እሷ ዘንድ ይመላለስ እንደ ነበር ቢወራበት ምኑ ደስ ይለዋል?”
“ ለምንድነው ራሱን ቶርን ብሎ የጠራው ? የገዛ ስሙን ለመደበቅ የፈለገው
ለምንድነሙ ? አለ ሚስተር ዲል "
“ እኔንጃ ግን ስሙ ሌቪሰን ነው ወይስ ቶርን ?”
አዬ አበንዘር .... አንተ ደሞ ዝም ብለህ ነው ”
ሚስተር ዲል በሰማው አዲስ ወሬ ተወጠረ " ለሚስተር ካርላይል ተንፍሶ
ለማረፍ ግጥም ብሎ የሞላው ሕዝብ ትንሽ ዘርዘር ሲልለት እየገፋና እየተሹለከለh ዐልፎ ከሚስተር ካርይል ልዩ ቢሮ ገባ " ሚስተር ካርላይልን ከጠረጴዛው ተቀምጦ ደብጻቤዎቹን ሲፈርም አገኘው "
"ምነው ዲል ? ትንፋሽ አጠረህሳ ?
“ አዎን ሚስተር ካርላይል... በጣም የሚደንቅ ነገር ስሰማ ቆይቸ ነው የመጣሁት የቶርንን ነገር ዐወቅሁት " ቶርን ማን ይመስልሃል ?”
ሚስተር ካርላይል ብዕሩን አኑሮ ሽማግሌውን ትክ ብሎ ተመለከተ " እንደዚያንለት መንፈሱ ግሎ አይቶት አያውቅም
“ ሌቪስን የሚባለው ሰውዬ እኮ ነው !
“ የምትለኝ አልግባኝም " አለው ሚስተር ካርላይል እውነትም አልገባኝም
ነበር " ነገሩ ግራ ሆነበት "
“ አፊ ሆሊጆንን ይከታተል የነበረው ቶርን የዛሬው ሌቪስን ያንተው ተወዳዳሪ
ነው ይኸው ነው ...
ሚስተር አርኪባልድ "
“ሊሆን አይችልም! አለ ሚስተር ካርላይል በሐሳብ ላይ ሐሳብ እየተከታተለበት „ “ ይኽን ወሬ ከየት ሰማኸው ?
ሚስተር ዲል ታሪኩን ነገረው " ኦትዌይ ቤቴል እንዳወቀው!ሰር ፍራንሲዝ
ሌሺስንን ዐመዱ ቡን ማለትና ሜስተር ኧበንዘርን አነጋር ሁሎ አብራርቶ አስረዳው።
“ቤቴል ቶርንን እንደሚያውቀው እንዲያውም እንደዚ ያለ ስም ከነመኖሩም እንደማያውቅ ደጋግሞ ክዶ ነበር ” አለ ሚስተር ካርላይል "
“ የካዶበት ምክንያት ይኖረዋል ” አለ ሚስተር ዲል “ ዛሬ እርስ በርሳቸው ሲተያዩ በደንብ ነበር የተዋወቁት ሌቪሰን ምንም እንኳን የማያውቀው ለመምሰል ቢሞክርም ቤቴልን በደንብ ለይቶታል " መቸም ሚስተር አርኪባልድ
በለቱ መኻል አንድ ምስጢር ባይኖር ምናለ በለኝ ”
የሚስዝ ሔር እምነትም ቤተል በግድያው እንዳለበት ነው " አለ ሚስተር ካርላይል ድምፁን ዝቅ አድርጎ "
“ምስጢራቸው ስለ ግድያው ከሆነ ቤቴል እንዳለበት አያጠራጥርም» አለ ሚስተር አርኪባልድ ...ሪቻርድን ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው
ግን በምን መነሻ እንጀምረው ? አለ ሚስተር ካርላይል "
ባሮባራ በበኩሏ ከሚስተር ካርላይል በሚበልጥ እንጂ በማያንስ ሁኔታ አምሮዋ ተረብሾ በሠረገላዋ ተሳፍራ ወደ ቤቷ መጣች እንደ ደረስች ወርዳ ወደ ቤት
ስትገባ ዊልያምና ማዳም ቬን ከመተላለፊያው አገኙዋት "
"ዶክተር ማርቲንን አይተነው መጣን እና ማማ እሱ
የሚለው
“ አሁን ያንተን ንግግር ለማዳመጥ መጠበቅ አልችልም •ዊልያም « ኋላ
አነጋግራችኋለሁ ብላቸው ተመለሰች "

👍11
ማዳም ቬን በቁጣ ዐይኗ እየተከተለቻት ወደ ፎቅ ወጣች „ “ምን ቸገራት” አለች ማዳም ቬን በሐሳቧ " የሷ ልጅ አይደል!”
ባርባራ ተንደርድራ አንደ ገባች ጃንጥላዋን hአንድ ወንበር የጅ ጓንቲዎቿን
ከሌላ ጣለችና ከጽሕፈት ጠረጴዛዋ ተቀመጠች "
“ እጽፍለታለሁ ለአንድ ሰዓትም ቢሆን እንዲመጣ እጠራዋለሁ " ሰውዬው
እሱ ነው " ከፋም ለማም 'እጠራዋለሁ " ደሞም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ አይከፋም አለችና አንድ ደብዳቤ በችኮላ ጻፈች።
“ የተወደድክ ሚስተር ስሚዝ እንድትመጣ እፈልግሃለሁ " ያንተን መምጣት የሚያስፈልግ አንድ ጉዳይ ተነሥቷል ቅዳሜ ደርሰህ ድንግዝግዝ ሲል ባትክልት በተጋረደው መንገድ ላይ እንገናኝ ምንጊዜም ያንተው ”
ደብዳቤው ሪቻርድ በስጣት አድራሻ መሠረት ለሚስተር ስሚዝ ሊቨርፑል ብላ አንድ የመንገድ ቁጥር ሞልታ አዘጋጀች » ከዚያም ምናልባት መምጫ እንዳይቸግረው ብላ በእጅዋ ስላልነበራትና ጆይስንም ጠይቃት ስለ አጣች ማዳም ቬንን
የአምስት ፓውንድ ኖት እንድታበድራት ጠየቀቻት "
ማዳም ቬን ገንዘቡን ልታመጣላት ስትሔድ ባርባራ ዊልያምን ሐኪሙ ምን እንዳለው ጠየቀችው "
ደረቴን መረመረኝ " ጎበዝ ልጅ መሆን እንዳለብኝ ዓሣ ዘይቱንም በደንብ
አንድጠጣ ሌላም ጥሩ የሆነውን ሁሉ እንደ ፈለግሁ እንድበላና እንድጠነክር ነገረኝ " ከዚህም ሌላ በሚመጣው ረቡዕ ከአባባ ቢሮ ወይም ከአክስት ኮርኒሊያ ቤት መጥቶ
እንደሚያየኝ ነግሮኛል " ማዳም ቬን ግን ከአባባ ጋርም ለመነጋገር እንዲችል አባባ ቢሮ ድረስ እንዲሆን አለችው ”
ምን ? አለችው ባርባራ "
ይች ማዳም ቬን ግን ከአሱ ጋር ከነተጋገረች ወዲህ ታለቅሳለች " ምን ያስለቅላታል ? ዐይኖቿን ከመነጽሯ ሥር ስታብስ የማላያት ይመስላታል" እኔ በጣም መታመሜን ዐውቀዋለሁ " እሷ በኔ ነገር ለምን ታለቅሳለች ?
"ማነው ደሞ በጣም ታመሃል ብሎ የነገረህ ?”
“ ማንምI እኔ ሳስበው የታመምኩ ይመስለኛል " አላት ቅዝዝ ብሎ “እስቲ
አሁን ጆይስ ወይም ሉሲ ቢያለቅሱ እንኳን ዕድሜ ልኬን ስለሚያውቁኝ ነው "
እሷ ግን የት ታውቀኛለችና ታለቅሳለች ?
ማዳም ቬን አንተ ስለ ታመምክ ማልቀሷ እንኳን የማይመስል ነገር ነው ”
ማዳም ቬን ገንዘቡን ይዛላት መጣች " ባርባራ ተቀብላ በፖስታ አሽጋ በሠረገላዋ
ሆና ራሷ ሔዳ ፖስታ ቤት አስገብታው እንደ ተመለሰች ወንዶቹም ለራት መጡ
እሷም ከመልበሻ ክፍሏ ገብታ ልብስ ስትለውጥ ሚስተር ካርይል ገባ
“ እኔስ አርኪባልድ ... አንድ ነገር የተሳሳትኩ እየመሰለኝ ፈራሁ
“ ሁላችንም አንዳንዴ እንሳሳታለን ... ባርባራ “ ለመሆኑ ምንድነው?
አላት "
“ነገሩ ከብዙ ዘመን ጀምሮ በአእምሮዬ እየተጉላላ የኖረ ነው " ነገር ግን ልነግርህ ደስ አልለኝ እያለ አፍኘ ይዠው ኖርኩ ”
“ ብዙ ዘመን ?”
“ አዎን፣እመቤት ሳቤላ ሌሊቱን ልትጠፋ ቀደም ብሎ ሪቻርድ ከኛ ተስናብቶ
በኋላ እንደግና ተመልሶ መጥቶ ቶርንን አየሁት ያለን ጊዜ ታስታውሳለህ ስለ ቶርን እጅና ቀለበት የነገረን ትዝ ይልሃል ?”
“ አዎን አስታውሳለሁ "
“እሱ የነግረን የእጅ እንቅስቃሴ በዚያን ጊዜ ኢስት ሊን ዐርፎ የነበረው ሰውዬ ሲደጋግም አየሁ " አንተ ግን እንዴት አንዳላስተዋልኩው ገረመኝ እኔ ከዚያች ሌሊት ጀምሮ ቶርንና ካፒቴን ሌቪሰን አንድ ሰው መሆናቸውን ማመን ጀምሬ ነበር ”
ታዲያ ለምን አልነገርሽኝም
“ እኔ በዚያን ጊዜ እንዴት አድርጌ የዚያን ሰውዬ ስም ከፊትህ ላንሣው? ከዚያ
በኋላም ሪቻርድ በዚያ በረዷማ ክረምት አልመጣም ያን ጊዜም ቶርንን ከሌቪስን
ጋር አየሁት ብሎ ሲነግረን መልሶ አጠራጠረኝ " ዛሬ ግን በሠረገላ ሁኜ በሬቨን
ሆቴል ሳልፍ ንግግር ሲያደርግ 0የው ልዩ ምልክቶቹን ልብ ብዬ አየኋቸው » ቶርንና ሌቪሰን አንድ ሰው መሆናቸውን በሚገባ አረጋገጥኩ "
“ አንድ ሰው መሆናቸውን ዐውቃለሁ ” አላት ሚስተር ካርላይል ምንም ሳያቆርጥ ካስጨረሳት በኋላ ከዚያም እንዴት እንዳወቀ ዲል በዐይኑ ያየውንና ከኧበን
ዘር የሰማውን ሁሉ ነገራት "
“ ይግርማል” አለች ባርባራ። “እማማ ስለ ሪቻርድ ስለ ቤቴልና ስለ አንድ ሌላ
ሰው ሕልም አይታ በዚህ ሰሞን ስለ ሆሊጆን አንድ ነገር እንደሚገለጽ ነግራኝ ነበር።
እንግዲህ ሪቻርድ ቅዳሜ እንዲመጣ ስለ ላክሁበት እሱ ራሱ ለይቶ ያውቀዋል "
ግን አርኪባልድ አሁን እሱን ነጻ ለማድረግ ምንድነው የሚደረግ ?”
“ መቸም እኔ የሌቪሰን ተቃዋሚ ሁኜ ብሟገት የቂም ስለሚመስልብኝ ልቆ
ምለት አልችልም "
ይሁን አንተስ አትቁምለት ግን ምን ይሻላል?”
“ ሪቻርድ እስኪደርስ እንጠብቅ ”
“ አንድ ባለ አምስት ፓውንድ ኖት በኪስህ ይኖርሃል ... አርኪባልድ ለሱ የምልክለት በጄ ስልነበረኝ ከማዳም ቬን ተበድሬ ነበር
ከቦርሳው አወጣና ገንዘቡን ሰጣት "
💫ይቀጥላል💫

👍22👏1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ አስራ አምስት (15)
«ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !»
«አይ ! አይመስለኝም ። ፒተርን እንዳባቴ ነው እማየው። አየሽ እንደማላውቀው አባቴ ። ስጦታ ሲሰጠኝ ሲያሞላቅቀኝ አባቴ ነው እሚመስለኝ ። ፍቅር ከማይክል ጋር ነው»
«እሱንም ስንቆይ እናያለን» አለችና ፌ አሊሰን ሰዓቷን አየች ። «ያምላክ ያለህ |! ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቂያለሽ ? » አለች ። ናንሲ ሰዓቷን አየች ። በጊዜው ያን ያህል መክነፍ በጣም ተደነቀች ። « ፒተር እንዳለው እውነትም የምትገርሚ ልዩ ዓይነት ሰው ነሽ ! ምን አድርገሸ ነው እንዲህ ጊዜውን ያስረሳሽኝ ፌ? እውነትም ልዩ ሰው ነሽ!»
«በመስማማታችን ደስ ይለኛል ። እንዲያውም ፒተር በተወሰነ ጊዜ ዘወትር መገናኘት እንዳለብን ነው የሚያስበው ምን ይመሰልሻል ናንሲ?»
«በጣም ደስ ይለኛል»
«ግን በየጊዜው ይህን ያህል አብረን ልንቆይ እንችላለን ማለት አይቻልም ። ጊዜ ላይኖረን ይችላል ። ስለዚህ በሳምንት ሦስት ቀን ብንገናኝ ምን ይመስልሻል ? በተረፈ ግን እንደጓደኛ በትርፍ ጊዜ መገናኘት ይቻላል። ይስማማሻል? »
«በጣም በጣም ይስማማኛል» ተጨባብጠው እንደተለያዩ ናንሲ ከሁለት ቀን በኋላ ሊገናኙ የወሰዱት ቀጠሮ ሩቅ መስሎ ታያት የራሷ ስሜት ራሷን አስገረማት ።
••••••••••••••
ናንሲ በክፍል ማሞቂያው ምድጃ አጠገብ በሚገኝ ምቹ ወንበረር ላይ ተዝናንታ ተቀመጠችና በረጅሙ እየተነፈሰች ራሷን ወንበሩ የራሰ መከዳ ላይ አሳረፈች ። ከፌ ጋር ባደረጉት ቀጠሮ መስረት፣ ነበር የመጣችው ። የቀጠሮው ሰዓት ገና አምስት ደቂቃ ያህል ቢቀረውም እሷ ግን ከዚያች ሴት ጋር ለመጨዋወት ቸኩላለች ። ወዲያው እሌላኛው ክፍል ውስጥ ቀጭ፣፤ ቋ የሚለው የፌ ኮቴ ተሰማት ። ናንሲ የተቀመጠችው ፌ የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በምታነጋግርበት በምትመረምርበትና ህክምና በምታደርግበት ክፍል ነበር ። የፌን ኮቴ እንደሰማች በደስታ ፈገግ ብላ ትስተካክላ ተቀመጠች ። ሁሉም ነገር ፌ እንደለመደችውና እንደምትፈልገው እንዲሆንላት ለማድረግ አስባበታለች ።
« እንደምን አደርሽ ፤ የንጋት ወፍ ። ይኸ ቀይ ልብስ እንዴት አድርጎ ተስማምቶሻል እባክሽ !» ፌ ይህን ብላ እበሩ ላይ እንደቆመች ፈገግ አለች ። ቀጥላም «ቀዩን ውብ ልብስ እንተወውና እስኪ አዲሱን ፊትሽን አሳይኝ » አለች ። ይህን ብላ ናንሲ ወዳለችበት ቀስ እያለች ተጠጋች ። ከፋሻ የተገለጠውን ፤ ከፊት አጥንቷ በታች የሚገኘውን ጉንጫን ካየች በኋላ እንኳን ደስ አለን የሚል ፈገግታ እፊቷ ላይ ነጋ። አይኖቻቸው ግጥምጥም አሉ ።
« እንዴት ነው ? ጥሩ ነው ? » እለች ናንሲ።
«ናንሲ ፤ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ሆንሽኮ ። ቆንጅዬ… በቃ አለች ፌ። ናንሲ እመነቻት ። ምክንያቱም የፌ ፊት በናንሲ መዳን ደስ መሰኘቷን ፤ በፒተር ስራ መደነቋን ቁልጭ እድርጉ ይናገር ነበር ።
ፌ ደግሞ እንዲያ ስትል ከልቧ ነበር ። ለግላጋ አንገቷ ከቅርጸ መልካም ትከሻዋ ላይ እንደ ባህር ሸንበቆ ተመዞ ፤ ልስልስ ጉንጯ ፤ ገርና ሳሙኝ የሚል አፏ ተገልጦ ያየ ሰው ቢደነቅ የማያስገርም ነገር ሊሆን እይችልም ። ሁሉም ከናንሲ የተፈጥሮ ጠባይ ጋር የሰመረ አካል ሆኖ ታያት ፤ ለፌ ። የፒትር ሁልቆ መስፈርት የሌለው የንድፍና የጥገና ፤ የሞዴል መቅረፅ ሥራ ፤በከንቱ እንዳልነበረ ግልፅ ሆኖ የታያት ፌ
« አስቀናሽን ፣ ዕውነት ቀናሁ ። እኔም እንዳንች ብሆን እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ ! » አለች ። ይህን የሰማችው ናንሲ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። ከጉንጪ በላይ ያለው ፊቷ ገና በፋሻ እንደታሰረ ሲሆን ፤ ባደረገችው ጥቁር ቡናማ ዘናጭ ባርኔጣ ጥላ ደብዘዝ ብሏል ። ይህን ባርኔጣ የገዛችው ከአሥራ አምስት ቀን በፊት ሲሆን በቀይ ቀሚስ ላይ ከሰበሰችው ቡና ዓይነት ሱፍ ኮትና ካደረገችው ቡናማ ቡት ጫማ ጋር ይሄዳል ። ናንሲ ድሮም ቅርጸ መልካም ልጅ ነች ። አዲሱ ፊቷ ሲጨመር ወንድን ሁሉ በያለበት የምትጥል ሴት ትሆናለች ስትል አሰበች ፤ ፌ ናንሲም ቢሆን ይህ ሊሰማት ጀምሯል ። ፒተር ቃሉን ለመጠበቅ የሚችል ሰው እንደሆነ አምናለችና ።
« ፌ በጣም ደስ ይለኛል ። አንዳንድ ጊዜማ ደስታ የሰራ አካላቴን ውጥር እስኪል ስለሚሞላው ጩሂ ! ጩሂና እፎጥ በይ ይለኛል » አለች ናንሲ።
«እንደሱ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ስላልሺኝ ደስ አለኝ ናንሲ ። ግን ይኽ ሌላ መሆኑስ ? ያልለመድሽው ገፅታ መሆኑስ ፣ ትንሽ አያስጨንቅሽም ?»
« የለም የፈራሁትን ያህል እይደለም ። ግን ሙሉ ፊቴን ስላላየሁት ሙሉውን ሳይ ምን እንደሚሰማኝ እንጃ ብቻ አየሽ ዱሮውንም ያን የአፌን ቅርፅ አልወደውም ነበር ብቻ ሲሆን ይታያል »
«ናንሲ… አንድ ነገር አለ››
« ምን? ምን ነገር»
« አየሽ ናንሲነትሽን ቀስ በቅስ እንድትረሺ ያስፈልጋል ግድ የለበትም ። አንች እንደተቻለሽ ። ስለዚህ ናንሲን ለመርሳት ናንሲን በደንብ ማስታወስ ያሻ ይሆናል ። ለምሳሌ እንበል የዱሮ አካሄድሽን ትወጂው ነበር ? » ይህ ነገር ለናንሲ ፈፅሞ አዲስ ነበር ፤ ተነስቶ ተወሰቶ የማያውቅ ።
« እኔ እንጃ ፣ ስላረማመዴ አስቤ እማውቅ ኢይመስለኝም » አለች ።« ለወያፊቱ በደንብ ታስቢበታለሽ። ድምፅሽን መስማት ትወጂ ነበር ? ለምሳሌ ድምፅሽን ለመገራት የዜማ አለማማጅ ቢቀጠርልሽ ምን ትያለሽ ? አየሽ በጣም ቆንጆ ድምፅ አለሽኮ ። ለምን መሰለሽ እንዲህ እምልሽ ? ከዚህ በፊት ያልሆንሽው ግን ልትሆኝው የምትችይውን ነገር እንድትለማመጅ ብናደርግስ ለማለት ነው ። ያን ስትሆኝ ያው አዲስ ሰው ሆንሽ ማለት ነውኮ ። ፒተር የተቻለውን እያደረገ ነው ። እኛስ ለምን አንሞክርም ? »

👍24
ሃሳቡ ቦግ ብሎ የታያትን ያህል በደስታ በራች፤ ናንሲ ።
‹‹ማለት ፒያኖ ብለማመድ ፤ አካሄዴን ብቅይር፣፤ አዲስ ሰዉ ሌላ ሰው ሆንኩ ማለት ነው ፤ አደል ? ከዚያ በኋላ እኮ ብፈልግ ስሜንም መቀየር እችላለሁ ?! » አለች ናንሲ ። «ያን ያህልም መቻኮል የለብንም ስም እስከመለወጥ ማለቴ ነው ። አንደኛሽን ራስሸን ያጣሽ መስሎ እንዲሰማሽ አያስፈልግም ። ራስሽን ማጣትሽ ሳይሆን መጨመርሽ ፤ ማደግሽ መሆኑን ማወቅ አለብሽ ። እስኪ እናስብበትና እንሞክረው ። ድንቅ ነገር ሳይገጥመን አይቅርም » አለች የአዕምሮ ህክምና ሊቋ ፌ «
« በመጀመሪያ ድምፄን… ሌላ ድምፅ እፈልጋለሁ» አለች ናንሲ እየሳቀች ። « እንደዚህ ዓይነት ድምፅ » አለች ድምጸን ቀነስ ወፈር አድርጋ ። ፌ ሳቀችእና « እሱን ድምፅ በደንብ ከተለማመድሽው ፒተር ሥራ ሊበዛበት ነው ማለት ነው » አለች። «እንዴት? » አለች ናንሲ በዚያው ጐርነን ባለው ድምፅ። «ጺም መሥራት ግድ ይሆንበታላ !»
« እንዲህ ነው ። እንኳን ነገርሺኝ !» ሁለቱም አንዴ በሳቅ መንከትከት ጀመሩ ። ተነስታ እንደትንሽ ልጅ መቅበጥበጥ ጀመረች ። ናንሲን እንዲያ ስትሆን ስታያት ፌ ሁልጊዜም ይገርማታል ። ሀያ ሶስት አመቷ ነው ። ናንሲ ግን ሃያ ሶስት ዘመን ቀርቶ ረጅም ዘመን የኖረም ሰው ቢሆን ያላየውን ብዙ ነገር እያየች ነው፡፡ እየሆነች ነው ። ውስጧ ግን ትንሽ ልጅ ናት ። ይኸው ስትቀብጥ ስትቅበጠበጥ !
« ግን አንድ ነገር አለ ፤ ናንሲ››
« ምን ነገር ?»
«ለምን ኦዲስ አንችን መፍጠር እንዳለብን ማወቅ አለብሽ ። ምክንያቱን ካወቅሽው ፤ ችግሩን ከተረዳሽው ነገሩ ቀላል ይሆናል ። እናትና አባትሽን አታውቂያቸውም ፤ እደለም ? ይኽ ደግሞ ምን እንደሚያስከትል ማወቅ አለብሽ ። እናትና አባት እኛ ራሳችንን ለመሆናችን ምስክር ናቸው ። ከየት መጣሁ ? እናትና አባቴ ወለዱኝ ። እውን ይሆናል ነገሩ ። ያ ጥያቄ ላንች ክፍት ቦታ ቢጤ ነው ። እሱን የምትሸሺ መምሰል የለበትም ። ሌላ ሰው ልችሆኝ እንደምትፈልጊ መሆን ነው ያለበት ። ያኔ መንገዱ ቀላል ይሆናል » አለች ፌ ።
ናንሲ ምንም ምን ሳትል ጸጥ ብላ ተቀመጠች ። ይህን ያየችው ፌ በፍቅር ፈገግ ብላ ከተመለከተቻት በኋላ ወደኋላዋ ተለጥጣ ተዝናንታ ተቀመጠች። ክፍሉ ምቾት የሚሰጥና መከፋትን ባንድ ጊዜ ከአዕምሮ ውስጥ እንደሚደመስስ ሆኖ የተዘጋጀ ይመስላል ። የግድግዳው ቀለም ፣ የዕቃዎቹ ዓይነት ፤ የዕቃዎቹ አቀማመጥ፤ ሁሉ ነገር የመንፈስ ሰላም የሚለግስ ነው ።
« እሺ እንግዲህ አሁን ያልኩሽን ቀስ እያልሽ አስቢበት። ለጊዜው ሌላ ነገር አለ ፤ ልንነጋገርበት የሚገባ። የእረፍት ጉዳይ፤ ያመትባል ጉዳይ »
« የመጪው አመትባል ምን እንዲሆን ? »
«ዘመን መለወጫ መምጣቱን ስታስቢ ምን ይሰማሻል ? ይጨንቅሻል ? ፍርሃት ፍርሃት ይልሻል ?››
«አይለኝም»
«ይከፋሻል ? »
‹‹በፍጹም »
«ደግ ናንሲ ። እኔ ከምገምትና ብዙ ከምሳሳት የሚሰማሽን አንች ብትነግሪኝስ ?»
«ምን እንደሚሰማኝ ለማወቅ ነው እምትፈልጊው ?» አለች፡፡
« በእርግጥ ማወቅ ትፈልጊያለሽ ?» ከተቀመጠችበት ተነሥታ እንዴ በክፍሉ ውስጥ በፍጥነት ወዲያ ደርሳ ወዲህ ከተመለሰች በኋላ ፣ «ምን እንደተሰማኝ ልንገርሽ ? » አለች «የተጣልኩ ፤እንደሽንት ተከፍዬ የተደፋሁ ይመስለኛል ፤ ስለዚህ ብሽቅ እላለሁ »
«እንደሽንት ? »
«አዎ ! ሽንቶ የደፋኝ መስሎ ይሰማኛል ፤ አናዶኛል ፤ አበሳጭቶኛል ፤ አብግኖኛል »
«ማን?››
«ማይክል…..

#ክፍል_ስልሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...አንድ ቀን በሚያዝያ ወር ውስጥ ሰዓቱ መሽቶ ለዐይን ሲይዝ ዊልምና ሳቤላ ሳሎን ውስጥ ተቀምጠዋል " ቀኑ ሞቃት ሆኖ ይዋል እንጂ እነዚያ የጸደይ ምሽቶች ግን ይባረዳሉ " የምድጃው እሳት ነዲድ ባይኖረውም ፍሙ ግማሹ ጠፍቶ ግማሹ ይጤሳል ማዳም ቬን እሳቱን ልብ አላለችውም ዊልያም ከሰፋው ተጋድም እሷም ዐይን ዐይኑን ታየዋለች " መነጽሯ በእንባ እየተነከረ አስቸገራት ልጆቹ እንዳያውቁት መሥጋቱንም ትታዋለች " ስለዚህ መጽሯን አወለቀች ልጁም ሊንበራ ደርሶ የተመለሰበት የሠረገላ ጉዞ ስላደከመው ዐይኖቹን ገጥሞ ተጋደመ እሷም የተኛ ሲመስላት ወዲያው መልሶ ገለጣቸው።
“ ከመሞቴ በፊት ስንት ቀን ይኖረኛል ?” አላት "
ያልጠበቀችው ጥያቄ ሆነባትና ናላዋ ዞረባት " “ ምን ማለትህ ነው
ዊልያም ስላንተ መሞት ማን አነሣ? አለችው "
“ ዐውቃለሁ እንጂ ስለኔ የሚወራውን እሰማ የለምእንዴ በቀደም ሐና
ያለችውን ሰምተሽ የለ ?
“ ምን? መቸ ?
“ እኔ ከምንጣፉ ላይ ተኝቼ ሻይ ይዛ የገባች ጊዜ " ለናንተ ቢመስላችሁም እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር " አንቺ እንኳ ልነቃ እንደምችል እንድትጠነቀቅ
ነግረሻት ነበር።
“እንጃ ልጄ እምብዛም አላስታውሰውም ሐና ምን የማትለፈልፈው አርቲ
ቡርቲ አላት ብለህ ነው ?”
“ ወደ መቃብሬ እየተጣደፍኩ መሆኔን ነበር የነገረችሽ " "
"አለች ? ሐና ኮ ማንም አይስማትም የምትናገረውን አታውቅም " ሞኝ ናት " አሁን ብርዳሙ ወቅት ዐልፎ የበጋው ሙቀት ሲገባ በጐ ትሆናለ "
“ ማዳም ቬን ”
“ ምነው የኔ ዓለም ”
“ ያንቺ እኔን ለማታለል መሞከርሽ ምን ይጠቅማል ? እያታለልሽኝ መሆኑን የማይገባኝ ይመስልሻል ? እኔ ሕፃን አይደለሁም አርኪባልድ ቢሆን ኖሮ ልታዋሸው ትችይ ነበር " ግን ምን ሁኘ ነው እንደዚህ የሆንኩት ?
ምንም አልሆንክም " ሰውነትህ ደካማ ከመሆኑ በስተቀር ምንም የለብህ እንደ ገና ስትጠነክር ደግሞ በጐ ትሆናለህ "
ዊልያም ራሱን ነቀነቀ " ልጁ ያስተሳሰቡ ፍጥነትና ጥልቀት ከዕድሜው የላቀ ነው ነገሮችን በማለባበስ ሊታለል የሚችል ልጅ አይደለም " ሲነግር በጀሮው
ያልሰማውን እንኳን ይደረግለት ከነበረው ጥንቃቄ በመነሣት የተሠጋለት መሆኑን በግምት የሚያውቅበት ችሎታ አለው “ እሱ ግን የሐናን አነጋገር የመሰለ ብዙ
ነገር በጆሮው ሰምቶ እንዲጠረጥር የሚያደርጉት ምክንያቶች አጠራቅሟል ስለዚህ ልጁ ሞት እየመጣ ለመሆኑ በደንብ አድርጎ ዐወቆታል "
“ታዲያ ምንም ነገር ከሌለብኝ ዶክተር ማርቲን ለምን ከኔፊት አላነጋገረሽም?
እሱ በሳቡ የነበረውን ሲነግርሽ ለምንድነው እኔን ከሌላ ክፍል አንድቆይ ያደረገኝ?
ማዳም ቬን . . . . እኔም እንዳንቺ ዐዋቂ ነኝ ”
“ አዎን የልጅ ዐዋቂ ነህ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ትሳሳታለህ ” አለችው ሁኔታው አንጀት አንጀቷን እየበላት "
“ እግዚአብሔር ከወደደን ኮ ሞት ምንም አይደለም ሎርድ ቬን እንደዚህ
ብሎኛል » እሱም አንድ ትንሽ ወንድም ሙቶበታል
እሱ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ተስፋ የተቆረጠበት በሽተኛ ነበር ” አለችው "
"እንዴ አንቺም ታውቂው ነበር ?
“ የሰማሁትን ነው የምነግርህ " አለችው ዝንጉነቷን በስልት አስተካክላ
“ አሁን እኔ እንደምሞት አታውቂም ?
“ አላውቅም "
" ታዲያ ከዶክተር ማርቲን ከተለየን ጀምሮ የምታዝኚው ለምንድነው ? እንዲ
ያውስ ከነጭራሹ ስለኔ ምን አሳዘነሽ ? እኔ ልጅሽ አይደለሁ ?
አነጋገሩና ሁኔታው ከምትችለው በላይ ሆነባት ከሶፋው ተንበረከከች እንባዋ ያለገደብ በአራት ማዕዘን ወረደ።
“ አየህ ዊልያም.....እኔ...እኔ አንድ ልጅ ነበረኝ የራሴ ልጅ አንተን ባየሁህ ቁጥር እሱ ይመጣብኛል " ስለዚህ ነው የማለቅለው "
“ ዐውቃለሁ ስለሱ ከዚህ በፊት ነግረሽኝ ነበር የሱም ስም ዊልያም ነበር
አይደለም?
ከላው ላይ ተደግፋ ትንፋሿን ከትንፋሹ እያቀላቀለች እጁን በእጅዋ ይዛ“ዊልያም ” አለችው " “ ፈጣሪ ከሁሉ አብልጦ የሚወዳቸውን አስቀድሞ እንደሚወስድ ታውቃለህ አንተም ብትሞት ኖሮ የዚህን ዓለም ሐሳብና ጣጣ እዚህ ትተህ መንግሥተ ሰማያት ትግባ ነበር። በሕፃንነታችን ብንሞት ኖሮ ለሁላችንም ደስታችን ነበር
“ ለአንቺም ደስ ይልሽ ነበር ?
“ አዎን ለደርሰብኝ ከሚገባኝ የበለጠ ኀዘንና መከራ ተቀብያለሁ " እንዲያው አንዳንድ ጊዜ ሳስበውስ የምችለውም አይመስለኝም"
“ አሁንም ኀዘንሽ አላለፈም ? አሁንም ብኀዘን ላይ ነሽ ?
“ሀዘኔ ሁልጊዜ ከኔ ጋር ነው " አስክሞትም አብሮኝ ይቆያል » በልጅነቴ
ሙቸ ቢሆን ኖሮ ግን ዊልያም አመልጠው ነበር " ዓለም በኀዘን የተሞላ ነው
“ ምን ዐይነት ኀዘን ?”
“ ሕመም በሽታ ሐሳብ ' ኃጢአት በደል ጸጸት ልፋት ” አለችና በሪጅሙ ተነፈሰች
“ ዓለም ከምታመጣብን መከራ ግማሹን እንኳን ልነግርህ አልችልም " በጣም ሲደክምህ ዊልያም .. ከትንሽ አልጋህ ላይ ጋደም ብለህ እንቅልፍ
እስኪወስድህ ስትጠብቅ ደስ አይልህም ?
“ አዎን እኔም እንደዚያ ድክም ይለኛል ”
“ ስለዚህ እኛም በዓለም ጣጣምች የደከምነው ተጋድመን የምናርፍበት መቃብራችንን እንናፍቃለን ቶሎ እንዲደርስ እንጸልያለን ግን አይገባህም ”
ከመቃብር ኮ አንጋደምም . ማዳም ቬን "
“ የለም የለም ሰውነታችን ከዚያ ያርፋል » በመጨረሻ ቀን በክብር በውበት ይነሣል ምነው!እንዲያው ምነው!አለች እየተኮማተረች ምነው አንተና እኔ
ሁለታችን እዚያ ብንገናኝ ! "
“ ዓለም የኀዘን ቦታ ናት ያለው ነው ... ማዳም ቬን ? እኔስ በተለይ በሙቀት ቀን ፀሐይ ስታበራ ቢራቢሮዎች ሲራወጡ ቆንጆ ትመስለኛለች " አሁን
ኢስትሊን በበጋ ብታይው በአግድመቶችና በቨርተቴዎች ሽቅብና ቁልቁል ስንሮጥ ዛፎች ከራሳችን በላይ ሲወዛወዙ • ሰማዩ ጠርቶ አበባ ሁሉ ፈንድቶ ስታይው የኅዘን ዓለም ነው አትይም ነበር "
“ እነዚያ አበቦች ኮ ከመንግሥተ ሰማያት ነው የምናያቸው »
“መቸ ጠፉኝ » ሥዕላቸውን አይቻለሁ ማርቲን ስለ ምጽአት የሳለቻቸውን ስዕሎች ለማየት ወደ ሊንበራ ሔደን ነበር የዶክተር ማርቲን አይደለም
" ነጭ ነጭ የለበሱ ብዙ ሰዎች አሉ አንድ ወንዝም አለ በወንዙ የሚያማምሩ ጀልባዎች ነፍሶችን ሲያመላልሱ ይታያሉ ከወንዙ ዳር ዳር በቅለው ሲታዩ የነበሩት አበባዎች ድምቀታቸ ደስ ይላል ”
"ሥዕሎቹን ለማየት ማን ወሰዳችሁ ?”
“ አባባ ' እኔ ሉሲ ' ሚስዝ ሔርና ባርባራ ሆነን ሔደን ነበር ባርባራ ያኔ እናታችን አልሆነችም ነበር ” አለና ድምፁን ድንገት ዝቅ በማድረግ '“ ሎሲ አባባን ምን ብላ ጠየቀችው መሰለሽ ?”
"ምን ብላ ጠየቀችው ? "
ከነዚያ ነጭ ነጭ ከለበሱት ብዙ ሰዎች ውስጥ እማማም አብራ ትኖር እንደ
ሆነ ወደ መንግሥተ ሰማያት ሒዳ እንደሆነ ጠየቀችው ያኔ በፊት እናታችን የነበረ
ችውንኮ ነው ወይዘሮ ሳቤላን ደሞ ስትጠይቀው ብዙ ሰው ነበር የሰማት
"አባትህ ምን መልስ ሰጣት ? ”
እንጃ " ምንም የመለሰላት አልመሰለኝም !ከባርባራ ጋር ወሬ ይዞ ነበር " እሷ አይገባትም ስለ ወይዘሮ ሳቤላ አባባ ፊት ምንም እንዳትናገር ዊልሰን ስንት
ጊዜ ነግራት ነበር መሰለሽ « ሚስ ማኒንግም እንደሱ ስትነግራት ነበር ከቤት እንደተመለስን ዊልሰን ሰማችና ትከሻና ትከሻዋን ይዛ አንዘፍዝፋ አንዘፍዝፋ ለቀቀቻት "
ለምንድነው የወይዘሮ ሳቤላ ስም ከፊቱ የማይነሣው ? አለችው »

👍14
“ እነግርሻለሁ " አባባን ጥላው ሔደች” አላት ዊልያም በክሹክታ “ ሉሲ
ተጠልፋ ሔደች የምትለው ነገር አላት። እሷ ግን ምንም አታውቅም" እነሱ አይመስላቸውም እንደሆነ እንጂ እኔ ነገሩን ዐውቀዋለሁ "
" አንድ ቀን እሷም ከዳኑት ጋር ትገኝ ይሆናል .. ዊልያም ... አንተም አብረሃት።"
ከሶፋው ትራስ ላይ እንደ ተንጋለለና የድካም አተነፋፈስ ተንፍሶ ዝም ብሎ
ቆየ ሳቤላም ፊቷን ጋርዳ ጸጥ ብላ ቆየችና እንደገና ከትካዜዋ ነቃች « ዊልያም
ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ "
“ እኔ ለመሞት አልፈልግም ለመሞት አልፈልግም ለምንድነው አባባንና
ሉሲን ትቼ የምሔደው? ”
ተነሳችና በላው ላይ ተደፋች በክንዶቿ ጥምጥም አድርጋ አቀፈችው " እንባው ከእንባዋ ኀዘኑን ሁሉ ከእንባው ጋር አውጥቶ ከደረቷ ዝርግፍ እንዲያደርገው አድርጋ አመቻችታ ያዘችው " ከጥቂት ጊዜ በኋላ እልፍ አለለት "
ከዋናው ምግብ ቤት ባለቤቶቹና ኧርል ማውንት እስቨርን ከነልጁ ራት በልተው ሲያበቁ ንግግርና ሣቅ ይሰማ ነበር ወንዶቹ የኮሚቴ ስብሰባ ስለነበራቸው ወደዚያ ሲሔዱ ባርባራ ወደ ግራጫው ሳሎን መጣች ማዳም ቬን ቶሎ ተነሥታ
መነጽሯን አድርጋ ኮስተር ብላ ከወንበር ላይ ተቀመጠች » ክፍሉ ጨልሞ ነበርና እሳቱን ራሷ ቆስቁሳ አነደደችው ዊልምን ሳይፈልግ ከሶፋው ተነሥቶ ወደ መኝታው እንዲሔድ አደረገችው ከዚያ በኋላ ዶክተር ማርቲን ምን ብሎ እንደ ሰደዳቸው ጠየቀቻት
፣ “በርግጥ ሳንባዎቹ መነካታቸን ነግሮኛል በተረፈ ይህም ነው ብሎ
የነገረኝ ቁርጥ ያለ ነገር የለም መቸም ሐኪሞች ሁሉ ልማዳቸው ሆኖ ነው እንጂ እሱ እንኳን ሁኔታውን እንደ ተረዳሁት አንድ ውሳኔ ላይ የደረሰ ይመስለኛል ”
“ደኅና እኔ ራሴ ወደ ዌስት ሊን እስደዋለሁ " እርግጠኛ ነኝ ሐኪሙ ለኔ ሳይሸሽግ ይነግረኛል » አሁን እንኳን የመጣሁት ያበደርሽኝን አምስት ፓውንድ ልከፍልሽ ነው " አለቻት የልጁን ነገር ትታ "
ሳቤላ ለመቀበል እጅዋን ዘረጋች "
“እንዲያው የገንዘብን ነገር ካነሣን ለልጆች ስጦታ እያልሽ ያን ያህል የምታመጪ ምን ሊተርፍሽ ነው ? አድራጎትሽን አኔም ሚስተር ካርላይልም አልወደድንልሽም " ባክሽ ማዳም ቬን ( ለወደፊቱ ተይ እኔ ገንዘብ የሚያስፈልገው ሰው የለኝም " ልጆች በጣም እወዳለሁ ” አለች
ማዳም ቬን በሷና በልጆች መኻል ጣልቃ ስለ ገባች የቀናች ይመስል
“ የለም እንደሱ አትበይ " ሌላ በይኖርሽ ለራስሽ ራስሽ አለሽ " ለማንኛው ነገር ትንሽ ተቀማጭ ገንዘብ ያስፈልግሻል " አንቺ ለራስሽ ማስብ ካልቻልሽ እኛ
እናስብልሻለን ስለዚህ የምንመክርሽን ካልሰማሽ ለልጆቹ ምንም ነገር እንዳትስጭ እንከክልሻለን "
“ ለፍቅር ምልክት ያህል ትንሽ ትንሽ ነገር እገዛላቸዋለሁ « ባይሆን የተቀረውን እቀንሳሰሁ ” አለች ሳቤላ "
እሱን ደና አንዳለፈሙ ውድ የሆኑ አሻንጕቶችን ሳይሆን ለምልክት ያህል አለቻትና አሁንም ወደ ሌላ ርእስ በመሻገር "ከሰር ፈሰራንሲስ ሊቪሰን ጋር ትውውቅ አላችሁ ? " አለቻት
" የለም ” አለች የውስጥ አካሏ እየተንቀጠቀጠ ጕንጮን እንደ እሳት እየፈጃት።
“ አኔ ኮ በቀደም ስለሱ ሳነሣ ጊዜ ሁኔታሺን ባየው የምታውቂው መሰለኝ
ጭራሽ አታውቂውም ?
“ አላውቀውም አለች ድምጿ, በግድ እየተሰማ ።
" በዚህ ቤት መጥፎ ነገር ያመጣው እሱ መሆኑን ታውቂ ኖሯል ማዳም
ሼን ?
“መጥፎ ነገር አለች ማዳም ቬን "
" አዎን እመቤት ሳቤላን ከቤቷ አስወጥቶ የወሰዳት እሱ ነበር። በርግጥ እሱ
ሊወስዳት እንደ ፈለጋት ሁሉ እሷም ፈልጋ ኖሮ ይሆናል "
የለም የለም! የሚል ተቃውሞ ሳታስበው ካፏ ነጥቆ ወጣ " እንዲያው
ባስበው ሊሆን የሚችል አይመስለኝም ለማለት ፈልጌ ነው " አለችና ለማቃናት ሞከረች "
“ እሱን በግምት እንጂ በትክክል ማወቅ አንችልም አንድ እርግጠኛ ነገር ነው የምንለው ባሏን ጥላ እሱን ተከትላ መሔዷ ነው " ሌላም የዚያኑ ያህል
ነገር አለ ይኸውም ያለፈቃዷ አልሔደችም " ዝርዝር ታሪኩን ሰምተሽዋል
"የለም "
እንዴት አድርጎ ከፈረንሳይ አምጥቶ ከቤቱ ደብቆ እንዳኖረው ከዘረዘረችላት
በኋላ በመጨረሻ ውለታ አድርው ሁለቱም ተመሳጥረው ሚስተር ካርላይልን ቤቱንና ልጆቹን አስታቅፈውት ተያይዘው መጥፋት ነበር " አለቻት "
ግን ሚስተር ካርላይል ስውዬውን ለምን ጠርተው አምጥተው ከቤታቸው
አስገቡት ?
እንዴ ለምን እንዲህ ትያለሽ ? ስውዬው እንደዚህ ርኩስ መሆኑን ሚስተር
ካርላይል ያውቅ ኖሯል ? ቢያውቅ ኖሮ ሚስቱን እመቤት ሳቤላን ትዋረድ መከራ ላይ ትውደቅ ብሎ ዝም ይል ኗሯል ሚስተር ካርላይል ኢስት ሊን ውስጥ አንድ መንጋ መጥፎ ሰዎችን ሊያጠራቅምበት ቢፈልግ አድራጎቱ አኔን ምን ያህል ይነካኛል ? በደኅንነቴ በጤንነቴ ለባሌ ስለ አለኝ ፍቅርና ቃል ኪዳን ምን ያህል እንደሚነካብኝ ማወቁ የኔ ፋንታ ነው”
ብቻ ይገርምሻል " አሁን ከሳሎን ብቻዬን ተቀምጬ ሰዎች ዕድል ስለሚሉት ነገር ሊሆን የሚችል ነው እያልኩ ሳስብ ነበር በሚስተር ካርላይል ቤተሰብ ላይ ችግርና ፈተና ያመጣባቸው ይኸ ሰው ነው ብየሻለሁ" የኔንም ቤተሰብ ከዚህ ያላሰ ፈተና ውስጥ የጣለ ይኸው ሰውዬ ለመሆኑ አሁን በቂ ምክንያት እንዳለኝ አምናለሁ " በወንጀል የተሰደደ ወንድም እንዳለኝ ታውቂያለሽ ?
ማወቋን አምና ለመናገር አልደፈረችም " የሪቻርድ ሔርን ታሪክ ማን ነገረኝ
ልትል ነው ?
አዳሜ ውርደት ነው ይለዋል”ቀጠለች ባርባራ ግን ሰው በሚያስበው
መንገድ ባይሆንም ነገሩ አሳፋሪ ነው ጥፋቱ ያለው ግን ኃፍረቱንና ውርደቱን በሪቻርድ ላይ ባላከከው በፍራንሲዝ ሌቪሰን ላይ ነው • ታሪኰ ሊነገር የሚገባው ስለ ሆነ አጫውትሻለሁ
ሳቤላ ከማዳመጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከሪቻርድ ሔር ጋር ምን እንዳገናኘው ገርሟት ነበር ".....

👍23❤5😁1🤔1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ናንሲ ሌኔሃን በትዕግስት ማጣት ስትቁነጠነጥ የመርቪን ላቭሴይ ትንሽ
አይሮፕላን ለበረራ ተዘጋጀች፡፡ ላቭሴይ ለፋብሪካው ካቦ መመሪያ እየሰጠ ነበር፡፡ መርቪን የፋብሪካው ወዛደሮች እንዳመጹና ሰሞኑንም የስራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ነገራት፡
‹‹አስራ ሰባት የመሳሪያ ቴክኒሻኖች ቀጥሬአለሁ አንዱ እንኳን ስለፋብሪካው ግድ የለውም፡፡››
‹‹ምንድነው የምታመርተው›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ቬንቲሌተር፣ የአይሮፕላን ሞተር ክፍሎች፣ የመርከብ መፍቻዎች፣ የመሳሰሉትን፡፡ ኢንጂነሪንግ ክፍሉ ችግር የለውም፡ እኔን ያስቸገረኝ ሰራተኛ ማስተዳደሩ ነው፡፡ አንቺ ግን የፋብሪካ ውዝግብ ምንሽም አይመስልም›› ሲል
ጨመረ።
‹‹እኔም ችግሬ እሱ ነው፡፡ እኔም የፋብሪካ ባለቤት ነኝ››
ላቭሴይ በአባባሏ ተገረመ
‹‹ምን አይነት ፋብሪካ?››
‹‹በቀን አምስት ሺ ሰባት መቶ ጥንድ ጫማዎች አመርታለሁ››
ተደነቀ፡፡ ሆኖም የተበለጠ ስለመሰለው ‹‹አንቺ ጎበዝ ነሽ›› አላት አድናቆትና ለበጣ በተቀላቀለበት ድምጽ ናንሲ የእሱ ድርጅት ከእሷ በጣም እንደሚያንስ ገምታለች፡
‹‹አሁንስ ፋብሪካ አለኝ ባልል ይሻላል›› አለች ምርር ብሏት ‹‹ወንድሜ እኔ ሳላውቅ ድርጅቱን ሊሸጥ እየተሯሯጠ ነው›› አለችና አይሮፕላኗን በስስት እያየች ‹‹ለዚህ ነው የሰማይ በራሪ ጀልባው ላይ ለመሳፈር
የቸኮልኩት›› አለች፡፡
‹‹አይዞሽ ትሳፈሪያለሽ›› አላት በፍጹም ልበ ሙሉነት ‹‹ይቺ ሚጢጢዬ
አይሮፕላኔ ከሰማይ በራሪው
ጀልባ መነሻ አንድ ሰዓት ቀድማ ታደርሰናለች፡››
‹‹እስቲ እግዜሄር ይሁነና!›› አለች፡፡
አይሮፕላኗን ሲጠጋግን የነበረው መካኒክ ዘሎ ወረደና ‹‹ሁሉም ዝግጁ
ሁሉም ሙሉ ሚስተር ላቭሴይ›› አለው፡
ላቭሴይ ናንሲን ተመለከተና ‹‹ሄልሜት አምጣላት ይህን ባርኔጣ አድርጋ መብረር አትችልም›› ሲል አዘዘው መካኒኩን ናንሲ ወደ ቀድሞው መደዴ ባህሪው ወዲያው ሲመለስ ስታይ
ገረማት፡ ምንም የሚሰራ በሌለበት ጊዜ ከእሷ ጋር ለመጨዋወት ደስተኛ
ነበር፡ ነገር ግን የሆነ ጠቃሚ ነገር ሲከሰት ጣል ጣል ያደርጋታል፡ በስራ
ቦታዋ እንደዚህ አይነት ባህሪ ከወንዶች አልለመደችም:: ምንም እንኳ ስትታይ የወሲብ አማላይ ባትመስልም በቀላሉ የወንዶች ዓይን ውስጥ ትገባለች፡ በስራ ቦታዋም ተገቢውን ክብር የሚነፍጋት የለም፡፡ ወንዶች እንደ ላቭሴይ ናቅ አያደርጓትም:: ሆኖም በዚህ ጊዜ ምንም ተቃውሞ ማሰማት አትችልም:፡ ወንድሟ ላይ እስክትደርስበት የሚደርስባትን ውርደት መቀበል ይኖርባታል፡፡
ስለ ትዳሩ ማወቅ ፈለገችና ጠየቀችው፤ ‹‹ጥላኝ የሄደችውን ሚስቴን
እያሳደድኩ ነው›› ሲል የሆዱን ነገራት፧ ወዲያውኑ ሚስቱ ለምን ጥላው
እንደሄደች ገባት፡፡ ሴትን የሚያማልል መልከ መልካም ቢሆንም ስራው ላይ ብቻ የሚያተኩርና ለሴት ግድ የለሽ ይመስላል፡ ሚስቱን ለመከታተል
መነሳቱ ደግሞ ሌላው ግራ የሚያጋባ ገጽታው ነው፡፡ መቼም በጣም ኩሩ
ሳይሆን አይቀርም፡፡ ናንሲ ስታየው ሚስቱን ገደል ትግባ የሚል አይነት መስሏት ነበር፡፡ ነገር ግን ተሳስታለች፡፡
ሚስቱ ምን እንደምትመስል ለማየት ጓጉታለች፡፡ ‹ቆንጆ ትሆን የአልጋ ላይ ንግስት፣ ራስ ወዳድ፣ ቅምጥል ወይስ እንደ ቆቅ የምትደነብር? በቅርቡ ታያታለች አይሮፕላኑ ሳይነሳ ከደረሱ፡፡
መካኒኩ የብረት ቆብ አመጣላትና ራሷ ላይ ደፋላት፡
ላቭሴይ አይሮፕላኗ ላይ ወጣና ‹‹ናንሲን እንድትወጣ አግዛት›› ሲል መካኒኩ ላይ ጮኸበት፡፡
መካኒኩ ከጌታው በተሻለ ትህትና ‹‹የኔ እመቤት እዚያ ላይ ጸሐይም ቢኖር ብርድ አለ አለና ኮቷን አለበሳት ከዚያ አወጣና ከላቭሴይ ኋላ ካለው ቦታ ላይ
አስቀመጣት፤ሻንጣዋንም እግሯ ስር አኖረላት፡
ሞተሩ ሲነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር አየር ላይ ልትወጣ እንደሆ ስታስበው ፍርሃት ጨመደዳት። መርቪን ላቭሴይ ብቃት የሌለው ፓይለት ወይም ደግሞ ነጭ ሴቶችን ለቱርክ ሴተኛ አዳሪ ቤቶች ወስዶ የሚሸጥ
ሊሆን ይችላል፤ ዕድሜዋ ለዚህ ያለፈ ቢሆንም፡፡ አይሮፕላኗ ደግሞ በደምብ
ያልተጠገነች ትሆን ይሆናል፡፡ ህይወቷን የሰጠችውን ላቭሴይን የምታምንበት ምንም ሁኔታ የለም፡፡ እንግሊዛዊና አይሮፕላን ያለው መሆኑን ብቻ ነው የምታውቀው:፡
ናንሲ ከዚህ ቀደም ሶስት ጊዜ በራለች፡ ሆኖም የበረረችባቸው አይሮፕላኖች ትልቅና ሽፍን ናቸው፡፡ ጊዜ ባለፈበት ባለ ድርብርብ የእንጨት ክንፍና በክፍት አይሮፕላን ስትሄድ
የመጀመሪያዋ ነው፡፡ ልክ በፈጣን ሽፍን ያልሆነ መኪና እንደመሄድ ይቆጠራል ሚጢጢዋ አይሮፕላን በአስፋልቱ ላይ ሮጣ እንደ ሰጋር በቅሎ እመር አለችና ወደ ሰማይ ተመነጠቀች ናንሲ በዚህ ጊዜ በፍርሃት ነፍሷ ውልቅ ልትል ምንም አልቀራት፡፡
የአብራሪነት ፈቃድ ይኖረው ይሆን?› አለች ለራሷ ደሞስ ከእንጨትና ከሸራ የተሰሩት የአይሮፕላኗ ክንፎች ቢቀነጠሱስ? ሞተሯ ቀጥ ቢልስ? ተሰብሮ መሬት ቢወድቅስ? ንፋሱ ወደ እነሱ አቅጣጫ ነፍሶ አይሮፕላኗ
ቢወዘውዛትስ? ጭጋግ ቢሆንስ? አቤት አምላኬ! እያለች ታስባለች ናንሲ¨
አይሮፕላኗ ግን አቅጣጫዋን ወደ አየርላንድ አድርጋ ሸመጠጠች¨
ጉዞው አስፈሪ ቢሆንም ደስ ይላል፡፡
ምዕራባዊ እንግሊዝን እንዳለፉ ናንሲ ውስጧ በድል አድራጊነት ሲሞቅ
ተሰማት፡ ፒተር ሆዬ ይሄኔ በሰማይ በራሪው ጀልባ ሊሳፈር እየተዘጋጀ ይሆናል፡፡ እዚያ ሲገባ ብልጧን እህቱን እንደሸወዳት ይረዳል፡፡ ነገር
ግን ደስታው የአጭር ጊዜ መሆኑን ስታውቅ ደግሞ አንጀቷ ቅቤ ጠጣ፡፡ ፎየንስ
መምጣቷን ሲያይ ምን ያህል እንደሚሸማቀቅ ለማየት ጓግታለች፡፡ ፒተር ላይ መድረስ ብቻ አይበቃም፡፡ ገና ከባድ ትልቅ ትግል ይጠብቃታል፡ በቦርድ ስብሰባው ላይ አክስቷ ቲሊንና ዳኒ ሪሌይን አክሲዮናቸውን
ከኩባንያው ጋር እንዲያቆዩና ከእሷ ጎን እንዲሰለፉ ማሳመን አለባት
ፒተር እህቱን እንዴት እንደዋሻትና ከእሷ ጀርባ ሲያሴር እንደነበር ለሁሉም ማሳወቅ ፈልጋለች፡፡ ምን አይነት እባብ እንደሆነ እንዲያውቁ ታደርጋለች፡ ነገር ግን ወዲያው ደግሞ አንድ ነገር ታሰባት፡፡ ንዴቷና በእሱ ላይ ያላት ጥላቻ በግልጽ ከታየ የኩባንያውን ውህደት የፈለገችው
በስሜታዊነት ነው ብለው ያስባሉ፡ ስለዚህ መጠንቀቅ አለባት፡ የፋብሪካው
የወደፊት መጻኢ እድል ምን እንደሆነና ከፒተር ጋር ያላቸው አለመግባባት
የስራ ብቻ እንደሆነ ቀዝቀዝ ብላ ማስረዳት አለባት፡፡ እሷ ከእሱ የተሻለ ድርጅቱን ማስተዳደር እንደምትችል ሁሉም ያውቃሉ፡፡
ክርክሯም በመጠኑ ስሜት ይሰጣል፡፡ለአክሲዮናቸው ሽያጭ የቀረበላቸው ዋጋ በኩባንያው አትራፊነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በፒተር
ደካማ አመራር ደግሞ ትርፉ አሽቆልቁሏል። ሌሎቹ የቦርድ አባላት ፋብሪካውን በመዝጋትና ሱቆቹን በመሸጥ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማግኘት
እንደሚፈልጉ ናንሲ ገምታለች፡፡ ነገር ግን እሷ የፋብሪካውን አሰራር
በማደራጀት ዳግም አትራፊ ለማድረግ አቅዳለች፡:
ሌላም ምክንያት አለ፡፡ ለጦር ሰራዊቱ ዕቃ የሚያቀርቡ እንደ ናንሲ ላሉ
ኩባንያዎች ጦርነት ጥሩ ነው፡፡ አሜሪካ ጦርነት ውስጥ አትገባም ይሆናል
ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል የጦሩን ትጥቅ ለማሟላት እንቅስቃሴ መደረጉ
አይቀርም፡፡ ስለዚህ ኩባንያቸው ትርፍ ማግበስበሱን ይጀምራል፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም
ናት ሪጅዌይ ብላክ ቡትስ ኩባንያን በእጁ ለማድረግ የቋመጠው።

👍27
ከራሷ ጋር ስታወራ የነበረው ነገር ሁሉ በሞተሩ ጩኸት ምክንያት መርቪን ላቭሴይ ጆሮ እንዳልደረሰ ገምታለች፡፡ ታዲያ ሞተሩ ችግር እንደገጠመው አላወቀችም፡፡ የሞተሩን መንተፋተፍና ድምጹ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ ማለቱን ስትሰማ ከሃሳቧ ባነነች፡፡ መርቪን አይሮፕላኑ እየከዳው ሲመጣ
አወቀች::
‹‹ምንድነው?›› ስትል ጮኸች ናንሲ ክው ብላ፡ መርቪን ወይ አልሰማትም ወይ በስራ ተጠምዷል፡፡ መልስ አልሰጣትም፡፡
"ኧረ ምን ተፈጠረ? አለች ለራሷ፡፡ የደረሰው ችግር ብርቱ ይሁን አይሁን መልስ የሚሰጣት ሰው አላገኘችም
ምክንያቱም መርቪን ወደፊት ብቻ ነው የሚያየው፡፡
ናንሲ ከዚህ በላይ መታገስ አልቻለችም፡፡ በጭንቀት እያለቀሰች ነው፡ አላስችላት ሲል ጊዜ የመቀመጫ ቀበቶዋን ፈታችና የላቭሴይን ጀርባ መታ
መታ አደረገችው:: መርቪንም አንገቱን ዞር አድርጎ ጆሮውን ሲሰጣት
‹ምንድነው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ ምን አውቄ›› አላት፡፡
‹‹ኧረ ምን ተፈጠረ?›› ስትል ደግማ ጠየቀችው:
‹‹አንዱ ሲሊንደር መሬት ሳይወድቅ አልቀረም›› አላት:
‹‹ስንት ሲሊንደር ነው ያለው?››
‹‹አራት››
አይሮፕላኗ አሁንም ወደ ታች ዘጭ አለች፡ ናንሲ በዚህ ጊዜ ተቁነጠነጠች፡፡ እሷም መኪና ትነዳለች፡፡ የእሷ መኪና አስራ ሁለት ሲሊንደር ነው ያላት፡፡ አንዱ ቢጠፋ በሌላው መሄድ ይችላል፡ ታዲያ አይሮፕላን
በሶስት ሲሊንደር መብረር ይችላል? የምታውቀው ነገር ስለሌለ በጭንቀት
በትር ተሸነቆጠች፡፡
አሁን አይሮፕላኗ በፍጥነት ወደመሬት እያሽቆለቆለች ነው፡፡ ናን አይሮፕላኗ በሶስት ሲሊንደር ትሄዳለች ነገር ግን ብዙ ርቀት መሄድ
አትችልም ይሆናል ስትል ገመተች፡፡ ከስንት ደቂቃ በኋላ ባህሩ ውስ
እንወድቅ ይሆን?
አሻግራ ስታይ መሬት በማየቷ በመጠኑ ቀለል አላት፡ አሁንም ትእግስቷ አልቆ የመቀመጫ ቀበቶዋን ፈታችና ላቭሴይን ‹‹መሬት በደህና እናርፍ ይሆን?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹አላውቅም›› ሲል ጮኸ፡፡
‹‹ምንም አታውቅም!›› ስትል ጮኸች፡፡ ድንጋጤዋ ሳታውቀው አስጮሃት፡፡ ለመረጋጋት ሞከረች፡ ‹‹ምንድነው ግምትህ?››
‹‹አፍሽን ዝጊና መንዳቱ ላይ ላተኩር››
ወንበሯ ላይ ደገፍ አለችና ‹መሞቴ ነው በቃ፡ ልጆቼ አድገዋል፡ የኔን እርዳታ የማይፈልጉበት ዕድሜ ላይ ደርሰዋል፡ በእርግጥ አባታቸውን በመኪና አደጋ ስላጡ እናታቸውንም በአይሮፕላን አደጋ ቢያጡ ሃዘናቸው ቀላል አይሆንም፡፡›
ቀጠል አድርጋ ደግሞ ‹አንድ ፍቅረኛ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር ስንት ጊዜ ሆነኝ. . . አስር ዓመት! አሁንስ ለመድኩት ብመለኩስ ይሻለኝ ነበር፧ ከናት ሪጅዌይ ጋር ብተኛ ኖሮ ጥሩ ነበር፧ እሱ ጥሩ ሰው ነው› ስትል አሰበች፡፡
አውሮፓ ከመምጣቷ በፊት ከአንድ አካውንታንት ጋር አንድ ሁለት ጊዜ ቀብጣ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሱ ጋር ወሲብ መፈጸሟን እንደ ስህተት ነበር የቆጠረችው፡ ሩህሩህ ቢሆንም ደካማ ነው ከዚህ በፊት የገጠሟት ሰዎች ጠንካራ ነች ብለው ስለሚያስቡ ሁሉም እንድትንከባከባቸው ይፈልጋሉ እኔ የምፈልገው እኔን የሚንከባከበኝ ወንድ ነው ስትል አሰበች፡፡
የምተርፍ ከሆነ ከመሞቴ በፊት አንድ ፍቅረኛ እንደሚኖረኝ እርግጠኛ
ነኝ አለች በሆዷ፡
ፒተር እንደረታት አውቃለች አሳዛኝ ነው፤ አባታቸው ትቶላቸው የሄደው ይህንኑ ፋብሪካ ብቻ ሲሆን በጄኔራል ቴክስታይልስ ሊዋጥ ነው አባታቸው እድሜያቸውን በሙሉ ይህን ፋብሪካ አሁን የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ ብዙ ቢለፉም አሁን ፒተር ኃላፊነቱን ከተረከበ አምስት አመት እንኳን ሳይሞላው ድምጥማጡን ሊያጠፋው ቆርጦ ተነስቷል፡
አንዳንድ ጊዜ አባቷ በአዕምሮዋ ድቅን ይሉባታል፤ ሲበዛ አዋቂ ነበሩ መላ ይፈልጉለታል፡፡ የእጅ እውቀት ስለነበራቸው የጫማ ማምረቻ ማሽን
ንግድ ስራ ሲቀዘቅዝ ወይም የሆነ የቤተሰብ ችግር ሲከሰት አባታቸው አንድ
አምራቾች ዲዛይናቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ያማክሯቸው ነበር፡፡ ናንሲ
የጫማ ምርት ሂደቱን ልቅም አድርጋ ታውቀዋለች የእሷ ልዩ ችሎታ ገበያው የሚፈልገውን ነገር አስቀድማ ማወቋ ነው፡፡ እሷ የፋብሪካው ኃላፊ
ከሆነች ወዲህ ብላክ የጫማ ፋብሪካ ከወንድ ጫማ ይልቅ በሴት ጫማ
ሽያጭ ነበር የበለጠ ትርፍ የሚያግበሰብሰው: አባታቸው በፒተር ላይ ጥላ
ያጠሉበትን ያህል በእሷ ላይ አላጠሉባትም ነበር፡፡
አሁን ደግሞ እሞታለሁ ብላ ማሰቧ ጅልነት እንደሆነ ተገነዘበች ለአፍታ ያህልም በራስ መተማመን ተሰማትና ውስጧን ደስ አላት ።
አይሮፕላኗ እንደገና ወደ ታች እየወረደች ሳለ የብላክ ቤተሰብ ከዚህ ምድር የፈለቀ መሆኑ ሲታሰባት ውስጧን ደስታ ወረረው፡፡
መርቪን ላቭሴይ ከአይሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ጋር ሲታገል ስታይ ፍርሃት ጨመደዳትና በልቧ መጸለይ ጀመረች፡፡ እድገቷ በካቶሊክ አማኝ ቤተሰብ ውስጥ ቢሆንም ባሏ ሾን ከሞተ ወዲህ ቤተክርስትያን ደጅ ደርሳ አታውቅም፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ቤተክርስቲያን የተገኘችው በባሏ ቀብር ላይ ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ማመንና አለማመኗን በቅጡ ባታውቅም መጸለዩ
የሚጎዳት ነገር ስለሌለው ጸሎት አደረሰች፤ ‹‹አባታችን ሆይ!›› ካለች በኋላ
የመጀመሪያ ልጇ ሂው አግብቶ የልጅ ልጅ እስኪያስታቅፋት ድረስ
እንዳይገላት አምላኳን ተማጸነች፡፡
አይሮፕላኗ ዝቅ እያለች ስትመጣ ማዕበሉ፤ ባህሩን የከበበው ተራራ፣ ገደላ ገደሉና ሜዳው ሁሉ እየጎላ መጣ፡፡ አይሮፕላኗ ባህሩ ላይ ብትወድቅ
እየዋኘች ወደ ዳር መውጣት መቻሏን ተጠራጠረች፡ ጥሩ ዋናተኛ ብትሆንም በመዋኛ ገንዳ እየዋኙ መዝናናትና እዚህ እዚያ ከሚያላጋ ማዕበል ውስጥ እየዋኙ መውጣት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ውሃው ደግሞ አጥንት
የሚሰብር ቀዝቃዛ ነው፤ ቦስተን ግሎብ የተባለው ያገሯ ጋዜጣ ሚስስ
ሌኒሃን የተሳፈረችበት አይሮፕላን ባህር ውስጥ በመግባቱ በቅዝቃዜ ሞተች
ብሎ ሲዘግብ ታያት፡፡
አይሮፕላኗ ባህር ላይ ከወደቀች ስለምትሞት ብርዱ አይሰማትም፡:
አይሮፕላኗ በምን ያህል ፍጥነት እንደምትበር አታውቅም፤ በሰዓት 90 ኪሎ ሜትር እንደምትበር ላቭሴይ ነግሯታል፤ አሁን ግን ፍጥነቷ እንደ ቀድሞው
ሳይሆን በሰዓት 50 ኪሎ ሜትር እየበረረች ነው፤ ሾን የተሳፈረበት አይሮፕላን በሰዓት 50 ኪሎ ሜትር እየበረረ እያለ ወድቆ ነው ህይወቱ ያለፈው::
አሁን ምን ያህል ዋኝታ ህይወቷን እንደምታተርፍ ማሰቡ አይረባትም፡:
ጸሎቷ ሰምሮላት አሁን
የባህሩ ዳርቻ ተቃርበዋል አይሮፕላኗ በቀድሞው ሁኔታ ሞተሯን እንደ ጢንዚዛ ጥዝዝዝ እያደረገች ትበራለች አይሮፕላን አሸዋ ወይም ጠጠር በተሞላበት የባህር ዳርቻ ያርፍ ይሆን?
እያለች ናንሲ ታስባለች፡:
አሁን ለባህሩ ዳርቻ ሩብ ኪሎ ሜትር ያህል ቢቀራቸውም አካባቢው
አለታማና በትልልቅ ቋጥኞች የተከበበ መሆኑን ስታይ ልቧ ስንጥቅ አለ፧
እታች በጎች ሳር ሲግጡ ይታያሉ፡፡
ቢጫ ቀለም የተቀባችው ሚጢጢ አይሮፕላን ቀስ በቀስ ዝቅ እያለች
ብትመጣም ቀጥ ብላ ለመብረር እየታገለች ነው ናንሲ የባህሩ መአዛ
አፍንጫዋጋ እየደረሰ ነው፡ ባህሩ ዳርቻ ላይ ከማረፍ ውሃው ላይ ማረፍ
ሳይሻል አይቀርም ስትል አሰበች አይሮፕላኗ ታች የሚታዩት እንደ ጦር
ሾል ሾል ያሉት አለቶች ላይ ለማረፍ ብትሞክር ብጥቅጥቋ ይወጣል
ናንሲም እንደዚሁ
ናንሲ ስቃይ የሌለው ሞት ተመኘች፡፡

👍14❤1
ላቭሴይ ምናልባት ከገደሉ በላይ ባለው መስክ ላይ አይሮፕላኗን ለማሳረፍ ሳያስብ አይቀርም፤ ያውም እዚያ መድረስ ከቻለ
የአይሮፕላኗ ሞተር እንደ ታመመ እንስሳ ቱፍ ቱፍ ማለቱን ተያይዞታል፤ ንፋሱ አይኗ ላይ የባህሩን ፍንጥቅጣቂ እየረጨው ነው‥ በጎቹ ላያቸው ላይ የምታንዣብባቸውን አይሮፕላን ሲያዩ ተበታተኑ፧ ናንሲ በስጋት የአይሮፕላኗን የፊት ክፍል ጨምድዳ የያዘችበት እጇ ደም አግቷል
አይሮፕላኗ ወደ ገደሉ ጫፍ ስትደርስ ጎማዎቿ ከገደሉ ጋር ሲጋጩ ላለማየት ዓይኗን ጨፈነች፡፡
ዓይኗን ስትከፍት ምንም ግጭት ባይኖርም አፍታም ሳይቆይ ግን አይሮፕላኗ ዘጭ ስትል ናንሲ ከመቀመጫዋ ተስፈነጠረች ትንሽ ቆይታ ደግሞ ወደ ላይ ወጣችº በመጨረሻ ተሳክቶላት መሬቱ ላይ አርፋ መስኩ ላይ እየተንገጫገጨች ሄደችና ላቭሴይ እንደምንም አቆማት
ናንሲ አይሮፕላኗ በደህና ማረፏን ስታይ ያ ሁሉ ፍርሃትና ጭንቀት
ከላይዋ ላይ ቢወርድም ሰውነቷ ይንዘፈዘፋል፤ ፍርሃቷ ለቋት ሰውነቷን
ስትገዛ አምላኳን አመሰገነች ላቭሴይ የእሷን በድንጋጤ መንዘፍዘፍ ሳያጤን የጥገና መሳሪያ የያዘውን ቦርሳውን ይዞ ከአይሮፕላኗ ወረደና
የሞተሩን በር ከፍቶ ይፈታትሽ ገባ፡፡ ናንሲም ተረፍሽ ወይ ብሎ
እንዲጠይቃት ብትጠብቅም እሱ ከምንም አልቆጠራትም፡፡
ናንሲ የላቭሴይ አድራጎት ጨዋነት የጎደለው ቢሆንም ተረጋግታለች አካባቢውን ስትቃኝ በጎቹም ሳሩን መጋጥ ጀምረዋል፤ ባህሩም እንደወትሮው እየተነሳ መፍረጡንና ከባህሩ ዳርቻ ጋር እየተላተመ መመለሱን አላቋረጠም ለተወሰነ ጊዜ ከመቀመጫዋ ሳትነቃነቅ ቆየችና እግሮቿ ሰውነቷን እንደ ሚሸከሙ ስታረጋግጥ በሩን ከፍታ ወጣች፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የአይሪሽ
መሬትን ስትረግጥ አይኖቿ በእምባ ተሞሉ፡ ይህ መሬት ነው አያቶቻችን የበቀሉበት፡፡ አያት ቅድም አያቶቻችን የእንግሊዝ ፕሮቴስታንቶች ባደረሱባቸው ግፍና ጭቆና እንዲሁም የድንች በሽታ ባስከተለባቸው ቸነፈር አገራቸውን ጥለው በመርከብ ታጭቀው ወዳዲሱ ዓለም አሜሪካ ተሰደዱ› ስትል አሰበች፡፡
የሆነ ሆኖ ተርፋለች፡፡ ስዓቷን ስታይ ስምንት ሰዓት ከሩብ ሆኗል፤ ወደ አሜሪካ የሚበረው የሰማይ በራሪ ጀልባ ይህን ጊዜ ከሳውዝ ሀምፕተን ተነስቷል፤ ይቺ አይሮፕላን መብረር ከቻለች ናንሲ ፎየንስ ከተማ በጊዜ
ትደርሳለች፤ ወደ ሞተሩ አካባቢ ሄዳ ስታይ ላቭሴይ ትልቅ መፍቻ ይዞ
ብሎን ሲያላላ አየችና ‹‹ይሆንልሃል?›› ስትል ጠየቀችው:
እሱም እንዳቀረቀረ ‹አላውቅም›› አላት፡፡
‹‹ምንድነው ችግሩ?››
‹‹እኔ እንጃ››
ላቭሴይ ወደ ተለመደው ዝግነቱ መመለሱን አየችና በስጨት ብላ
‹‹ኢንጂነር መስለኸኝ ነበር›› አለችው፡፡
ይህ አባባሏ ጠቅ አደረገውና ቀና ብሎ አይቷት ‹‹ያጠናሁት
ማቲማቲክስና ፊዚክስ ነው እንጂ የሞተር መካኒክነት አይደለም›› ሲል
መለሰላት ፈርጠም ብሎ፡፡
‹‹ካልቻልክ ከአየርላንድ መካኒክ እናስመጣ››
‹‹በድፍን አየርላንድ ውስጥ አንድም መካኒክ አታገኚም ይህ አገር አሁንም በድን
ዘመን ውስጥ ነው ያለው››
ይህ አገር ኋላ ቀር የሆነው በጨካኞቹ እንግሊዞች ለዘመናት ሲረገጥ
ስለኖረ ነው›› ስትል መለሰችለት፡፡
ራሱን ከሞተሩ ላይ ቀና አደረገና ‹‹ምን ሲደረግ ወደ ፖለቲካ ውስጥ ገባን?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ተረፍሽ ወይ ብለህ እንኳን አልጠየቅኸኝም››
‹‹ሳይሽ ደህና ነሽ››
‹‹ልትገለኝ ነበር››
‹‹አዳንኩሽ እንጂ››
‹‹ይህ ሰው ግራ ነው›› ስትል አሰበች ናንሲ ዙሪያ ገባውን ስትቃኝ ሩብ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ መንገድና ችምችም ያሉ ጎጆዎች አየች፡፡ ምናልባትም ወደ ፎየንስ የምትሄድበት መኪና ታገኝ እንደሆነ አሰበችና ‹‹አሁን የት ነው ያለነው?›› ስትል ጠየቀችው
‹‹አላውቅም እንዳትለኝ››
ፈገግ አለ፡፡አንዳንድ
ጊዜ ደህና ሲሆን ስታይ ይገርማታል፡
‹‹ምናልባትም ደብሊን ከተማ ልንደርስ ትንሽ ነው የቀረን›› አላት::
እጇን አጣጥፋ ቆማ ሞተሩን ሲጎረጉር ማየት እንደሌለባት ተገነዘበችና
‹‹እስቲ ሄጄ እርዳታ የሚሰጠኝ ሰው ልፈልግ››
አለች፡፡
እግሯን አየና ‹‹ይህን ጫማ አድርገሽ የትም አትደርሺም›› አላት:
በንዴት ‹‹አሳይሃለሁ›› አለችና ቀሚሷን ወደ ላይ ሰብስባ ስቶኪንጓን
ጠቅልላ ጫማዋን አወለቀች ወንድነቷን ልታሳየው መሆኑን ስታውቅ ልቧ በደስታ ሞቀ፡፡ ጫማዋን ኮቷ ኪስ ውስጥ ከተተችና ‹‹አልቆይም›› ብላው መንገዱን በእግሯ ተያያዘችው፡፡
ጀርባዋን ሰጥታው ትንሽ እንደተራመደች በድፍረት መንገድ መጀመመሯ
ፈገግ አሰኛት፡፡
በደስታዋ ግን አፍታም አልቆየች፡፡ እግሮቿ ጭቃ ውስጥ ተዘፈቁ፤
ቅዝቃዜውም እየተሰማት ነው፡፡ ጎጆ ቤቶቹ እንደገመተችው ሳይሆን ሩቅ ሆነውባታል፡፡ እዚያ ስትደርስም ምን እንደምትላቸው ግራ ገብቷታል፡ ወደ ደብሊን የሚወስዳት መኪናም ማግኘቷ አጠራጥሯታል፤ ላቭሴይ እዚህ ቦታ
መካኒክ አይገኝም ሲል የተናገረው ትክክል ሳይሆን አይቀርም:
ጎጆዎቹጋ ለመድረስ ሃያ ደቂቃ ፈጀባት፧ ከጎጆው ኋላ አንዲት ሴት የጓሮ አትክልቷን ስትቆፍር አየችና ‹‹እዚህ ቤቶች!›› ስትል ተጣራች፡፡
ከጎጆዋ የወጣችው ሴት ናንሲን ስታይ በድንጋጤ ‹‹ዋይ!›› አለች፡
‹‹የመጣሁበት አይሮፕላን ተበላሽቶብኝ መካኒክ ፈልጌ ነው የመጣሁት›› አለቻት ናንሲ፡፡
ሴትየዋ ናንሲ ልክ ከሌላ ዓለም የመጣች ይመስል አፈጠጠችባት፡፡ ናንሲ ጸጉራም ኮት ለብሳና ባዶ እግሯን ሆና ሰው ሲያያት ለየት እንደምትል ተገነዘበች፡፡ ሴትየዋ እጇን ቀስ ብላ ሰደደችና የናንሲን ጸጉራም ኮት ስትነካ ናንሲ አፈር አለች ሴትየዋ እንደ አምላክ ቆጠረቻት፡ ‹‹እኔ
አየርላንዳዊ ነኝ አለች ሰው መሆንዋን ለማስረገጥ፡ ‹‹ወደ አየርላንድ የሚወስደኝ መኪና አገኝ ይሆን?››
አሁን ሴትየዋ ገባት ‹‹ኦ መኪና ትፈልጊያለሽ?›› አለቻት፡
‹‹ምን ያህል ይርቃል ከዚህ?››
‹‹ጥሩ በቅሎ ካገኘሽ አንድ ሰዓት ተኩል ይፈጅብሻል››
ከፎየንስ ይነሳል፡፡ እዚህ አካባቢ መኪና ያለው የለም? ምን ዓይነት ጣጣ
‹‹ይህማ አይሆንም፧ የአየር በራሪው ጀልባ በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ
ነው!›› አለች ናንሲ፡፡
‹‹ስሚዝ ሞተር ሳይክል አለው›› አለቻት ሴትየዋ፡፡
‹‹ሞተር ሳይክልም ይሆናል›› አለች ናንሲ ደብሊን ከደረሰች ወደ
ፎየንስ የሚወስዳት መኪና አታጣም: ፎየንስ ምን ያህል እንደሚርቅና ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ የምታውቀው ነገር ባይኖርም ልትሞክር ቆርጣለች፡፡
ስሚዝ የት ነው የሚገኘው?››
‹‹እሱጋ እኔ እወስድሻለሁ›› አለችና አካፋዋን መሬቱ ላይ ሰክታ ተያይዘው ሄዱ።
መንገዱ ጭቃ በጭቃ በመሆኑ ሞተር ሳይክል ከበቅሎ በላይ ፈጥኖ
ሊሄድ እንደማይችል ስታውቅ ሆዷ በድንጋጤ ስንጥቅ አለ፡፡ አንድ ሌላ
ችግር ደግሞ ፊቷ ድቅን አለ፡ ሞተር ሳይክል ከነጂው ሌላ ማሳፈር የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው መኪና ካገኘች ደግሞ ተመልሳ ላቭሴይን ለመውሰድ አስባለች: በሞተር ሳይክል የሚኬድ ከሆነ ግን አንድ ላይ መሄድ አይችሉም፧ ባለቤቱ ሞተሩን ካልሽጣቸው በስተቀር፡፡ ከሸጠላቸው ደግሞ
ላቭሴይ እየነዳ እሷ ተፈናጣ ፎየንስ ገቡ ማለት ነው፡
ትንሽ እንደሄዱ አንድ እንደ ነገሩ የሆነ ጋራዥጋ ደርሰው፣ የሞተር ሳይክሉ ክፍሎች መሬት ላይ ተበታትነው፣ አንድ ባለሙያ ሲበይድ ስታይ ክፉኛ ተስፋ ቆረጠች፡፡ ሴትየዋ ስለ ናንሲ በአገሬው ቋንቋ ስትነግረው ቀና ብሎ ናንሲን በፈገግታ አየት አደረጋትና ‹‹አይሮፕላኑ የት ጋ ነው ያለው?›› ሲል ጠየቃት፡
‹‹ከዚህ ግማሽ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፡፡››
‹‹ልየው?››
‹‹ስለ አይሮፕላን ጥገና ታውቃለህ?›› ስትል ጠየቀችው ችሎታውን
ተጠራጥራ

ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹ሞተር ሞተር ነው›› አላት፡፡
ሞተር ሳይክል በታትኖ መገጣጠም ከቻለ አይሮፕላን እንደማያቅተው
ተገነዘበች፡
ባለሙያው ‹‹ትንሽ ሳንዘገይ አልቀረንም›› አላት፡፡ ምን እንዳለ ስላልገባት አባባሉ ትንሽ ግርታ ፈጠረባት፡፡ ትንሽ ቆይታ የአይሮፕላን ድምጽ ሰማች፡፡ ወደ ሰማይ ስታንጋጥጥ የላቭሴይ አይሮፕላን ዝቅ ብላ
ታንዣብባለች፡ ላቭሴይ አይሮፕላኗን ጠጋግኖ እሷን ሳይጠብቅ መብረር
ጀምሯል፡ ወደ ሰማይ እንዳንጋጠጠች ላቭሴይ እንዴት እንዲህ ያደርገኛል
ስትል ተብከነከነች: ሻንጣዋንም ይዞባት ሄዷል፡
ላቭሴይ እሷን ለማብሸቅ የፈለገ ይመስል እንደገና ዝቅ እያለ ሲበር ስታይ እጇን ቡጢ ጨብጣ እንደመዛት ስትል እጁን አውለበለበና
አይሮፕላኗን ሽቅብ ወደ ሰማይ አጎናት፡
ባለሙያው ይህን ሲያይ ‹‹አንቺን ትቶ ሊሄድ ነው›› አላት፡፡
‹‹ለሰው የማያዝን ርጉም ነው›› አለች፡፡
‹‹ባልሽ ነው?››
‹‹ኧረ አይደለም!›› አለች፡
ናንሲ ሆዲ በብስጭት ታመሰ እነዛ ሁለት ሰዎች አታለዋታል፡ ምን ባጠፋሁ ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡
አሁንስ ሁሉንም ነገር ‹ተይው ተይው› አሰኛት፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ
አሜሪካ የሚበረው አይሮፕላንጋ የምትደርስበት መንገድ ስለሌለ ፒተር ኩባንያውን ለናት ጅሪዌይ ሸጦ ሁሉ ነገር ያበቃለታል ስትል ክፉኛ ተንገበገበች:
ድንገት ሚጢጢዋ አይሮፕላን ወደ እነሱ አቅጣጫ ተጠመዘዘች:
ለምን ተመልሶ መጣ? አሁንም ሞተሩ እክል ገጠመው?› ስትል ከራሷ
ተሟገተች፡፡
አይሮፕላኗ ወረደችና ሶስቱ ሰዎች ያሉበት አካባቢ በጭቃው መንገድ
ላይ አረፈች፡
ናንሲ በደስታ ነፍሷን ልትስት ምንም አልቀራትም፡፡ ሊወስዳት ተመልሶ መጣ፡፡ መርቪን ላቭሴይ የሆነ ነገር እየተናገረ ነው፡፡
‹‹ምን?›› ስትል ጮኸች ምን እንዳለ ስላልተሰማት፡
ላቭሴይ እንዳልተሰማ ሲረዳ ወደ አይሮፕላኑ እንድትመጣ የጅ ምልክት አሳያት፡፡ ወደ እሱ ሮጠች፡፡
‹‹ምን ትጠብቂያለሽ? አትገቢም!››
ሰዓቷን ስትመለከት ለዘጠኝ ሩብ ጉዳይ ሆኗል፡ አሁን ከተነሱ ፎየንስ በሰዓቱ ይደርሳሉ፡፡ ይህም ተስፋዋን አለመለመውና ጥሎ አልጣለኝም አለች::
ወጣቱ ባለሙያ አይሮፕላኑ ላይ ስትወጣ አገዛትና ገብታ ወንበሩ ላይ ተቀመጠች፡፡ አይሮፕላኗም አፍታም ሳትቆይ ተነስታ በረረች፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍15🥰2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ስልሳ_ሦሥት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ሳቤላ ከማዳመጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከሪቻርድ ሔር ጋር ምን እንዳገናኘው ገርሟት ነበር
ድሮ በልጅነቴ በጣም ልጅም አልባልም ክፍ ብዬ ነበር ሪቻርድ አፊ ዘንድ እመላለስ ነበር እሷ ከአባቷ ከጆርጅ ሆሊጆን ጋር ነበር የምትኖር » ብዙ ወጣቶች እሷ ዘንድ አይጠፉም "እሷ ግን ቶርን የተባለው የትልቅ ሰው ልጅ በመሆኑ ከሁሉ አብልጣ ትወደው ነበር " ያ ሰው በአካባቢው የሚያውቀው አልነበረም
በምስጢር ሹልክ ብሎ ፈረስ አየጋለበ ይመጣና እንዳመጣጡ ሹልኮ ይመለሳል አንድ ቀን ማታ ሆሊጆን በጥይት ተገደለ ሪቻርድ ተሸሸገ " ምስክሩ በሱ ጠነከረበት « ፍርድ ቤትም ገዳይነቱን አምኖ ወሰነበት " ሁላችንም እሱ ስለ መግደሉ አልተጠራጠርንም አሁን እናቴ የልጅዋን ነገር እያነሳች በኅዘን ልትሞት ሆነ " ማንም ሊያጽናናት አልቻለም " በዚህ ዐይነት ያለ ምንም ለውጥ አራት ዓመት ያህል ቆየ።
ከዚያ በኋላ ሪቻርድ በምስጢር ለጥቂት ሰዓቶች ወደ ዌስት ሊን መጣና ወንጀለኛው እሱ ሳይሆን ቶርን የተባለ ሰው እንደ ነበር ነግሮን ሔደ ቶርንን ለማግኘት ብዙ ጥረት
ተደረገ " ነግር ግን ማን እንደ ነበረ የት እንደ ነበረ ከየት እንደ መጣ ወዴት እንደ ሔደ የሚያውቅ ሰው ሳይገኝ ጥቂት ዓመታት ዐለፉ " አንድ ጊዜ ቶርን የተባለ ካፒቲን
ወደ ዌስት ሊን መጣ። መልኩ ሁኔታው ሁሉ ሪቻርድ ከሰጠን ምልክት ጋር አንድ ሆነ " እኔም ሪቻርድ የነገረን ነፍሰ ገዳይ ቶርን እሱ መሆን አለበት ብዬ አመንኩ አሁን ምን መደረግ እንደሚገባው እንኳን ሳይታሰብበት ካፒቴን ቶርን ወደ መጣበት ሔደ አሁንም ከዚያ በኋላ ዓመቶች ዐለፉ ”
ባርባራ ዐረፍ አለች " ማዳም ቬን ፍዝዝ እንዳለች ቀረች " ያ ሁሉ ታሪክ ለሷ ምን እንደሚያደርግላትም አልገባትም "
“ኋላ ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኢስት ሊን እንግዳ ሆኖ በሰነበተበት ዘመን ካፒቴን ቶርን የሔርበርትን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ዌስት ሊን መጣ አሁን ሰውየው
እሱ መሆኑን ሚስተር ካርላይልና እኔ አመንበት " ቢሆንም ይበልጥ ለማረጋጥ እንሯሯጥ ጀመር። እማማ እንደ ልቧ ወዲያ ወዲህ ማለት ስለማትችልና አባባም የሪቻርድን ነገር ለመስማት ስለማይፈልግ እኔ ብቻ ነበርኩ ከሚስተር ካርላይል ጋር በየጊዜ መገናኘት የነበረብኝ " ያኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ኢስት ሊን ውስጥ ተደብቆ ስለ ተቀመጠ ለማንም ሌላ እንግዳ አይታይም ባለ
ዕዳዎቹ እንዳያገኙኝ ፈርቸ ነው ይል ነበር " አሁን ግን ውሸቱን ሳይሆን አይቀርም ብዬ መጠርጠር ጀመርኩ ሚስተር ካርላይልም በዚያ ጊዜ ዌስት ሊን ውስጥም ሆነ በአካባቢው በዕዳ የሚፈልገው ሰው የለም ያለውም ትዝ አለኝ » "
“ ታድያ በምን ምክንያት ነበር በግልጽ የማይወጣውና ከሰው የሚደበቀው?” አለች ወይዘሮ ሳቤላ አቋርጣ እሷም በበኩሏ ዘመኑ ይራቅ እንጂ ነገሩን በደንብ
ታስታውሳለች » የሚሹሎከሎከው ባለ ዕዳዎቹን በመፍራት መሆኑን ይነግራት ነበር » አንድ ጊዜ ብቻ በኢስት ሊን አካባቢ ፈላጊዎች እንደሌሉት አጫውቷታል
“ ከባለዕዳዎቹ የባሰ ፍራት ነበረበት " አለቻት ባርባራ “ እንዳጋጣሚ ሆነና
ካፒቴን ቶርን ከሔርበርት ቤተሰብ ዘንድ አንደ መጣ ከወንድሜ አንድ መልእክት
ደረሰን " መልእክቱም ለአጭር ጊዜ ወደ ዌስት ሊን መጥቸ ለመመለስ ፈልጌአለሁ የሚል ነው "ይኸንኑ ለሚስተር ካርላይል ነገርኩት " እማማ በጣም ተጨነቀችበት "
ሚስተር ካርላይልም የሪቻርድን ንጹሕነት ይፋ የሚሆንበትን መላ ለማግኘት ብዙ
ይጠበብበትና ይጓጓበት ነበር » ስለዚህ ከምን ጊዜውም የበለጠ ከሚስተር ካርላይል
ዘንድ እየተመላለስኩ መመካከር ግዴታ ሆነብኝ " አየሽ አባባና ሚስ ካርላይል ዘመዳሞች ናቸው " ስለዚህ የሪቻርድ መከራ የኛ ብቻ ሳይሆን የካርላይል ቤት ጭምር ነበር "
ሳቤላ ትዝታና መራራ ጸጸት ወደዚያ ዘመን ይዟት ተመለሰ " የሚስትር ካርይልና የባርባራ ቶሎ ቶሎ መግናኘት' በቅናት አመለካከት ሌላ ትርጕም መስጠቱን አስታወሰች " ለምንድነው ባልተረጋገጠ ነገር ከመከራ ላይ ለመውደቅ አእምሮን ያን ያህል ያስጨነቀችው ?
“ሪቻርድ መጣ " ጸሐፊዎቹ ወደ ቤታቸው ከሔዱ በኋላ እሱ ወደ ሚስተር ካርላይል ቢሮ ሹልክ ብሎ ሔዶ ከአንድ ክፍል እንደገባና ካፒቴን ቶርንን ተደብቆ
እንዲያው አስቸኳይ ዝግጅት ተደረገ " ካፒቴኑ ሚስተር ካርላይል የሚፈጽምለት አንድ ጕዳይ ነበረው " ሚስተር ካርላይልም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ
ቀጠረው » ስለዚህ ሁኔታውን ስለ ሪቻርድ ለማመቻቸት ምንም ችግር አልነበረውም የሚስተር ካርላይል ሚስት የኮበለለችው ያን ዕለት ሌሊት ስለ ነበር ምጊዜም ከአምሮው አይጠፋም
«ሳቤላ ድንግጥ አለችና ሽቅብ ተመለከተች »
" የሆነውን ኮ የምነግርሽ እመቤት ሳቤላና ሚስተር ካርላይል የራት ጥሪ ነበረባቸው " ሚስተር ካርላይል ከጥሪው ካልቀረ የሪቻድን ጉዳይ መፈጸም የማይቻለው ሆነ " መቸም ርኀሩጎና ለሰው አሳቢ ነው " ከራሱ ጥቅምና እርካታ ይልቅ ስለ ሌላው ደኅንነት ማሰብ ደስ ይለዋል " ስለዚህ ከጥሪው ቀረ " መቸም የሽብር ሌሊት ነበር " አባቴ ወጥቶ አምሽቷል ሪቻርድ በቀጠሮው መሠረት ወደ ዌስት ሊን በጨለማ በሚጓዝበት ጊዜ የመንገድ አደጋ ሊደርስበት ስለሚችል ተጨንቀናል " ስለዚህ እማማን እያረጋጋሁና እያጽናናሁ አብሬአት አመሸሁ " ሪቻርድ
ሚስተር ካርይል ጋር ያለውን ጉዳይ እንደ ጨረሰ ከእማማ ጋር ለመገናኘት
መምጣት ነበረበት ከተለያዩ ብዙ ዓመታቸው ሆኗቸው ነበርና።
ባርባራ ነገሯን ቆም አረገችና ሐሳብ ይዟት ጭልጥ አለ " ማዳም ቬንም ቃል ሳትተነፍስ ዝም አለች " ቢሆንም የሪቻርድ የካፒቴን ቶርንና የፍራንሲዝ ሌቪሰን ግንኙነት ምን እንደሆነ አላወቀችውም "
“በመስኮት ቁሜ ስጠብቃቸው ሚስተር ካርላይልና ሪቻርድ በአትክልቱ ቦታ በር ሲገቡ አየኋቸው ሰዓቱ ከምሽቱ ሦስትና በአራት መካከል ሳይሆን አይቀርም!
እንደ ተገናኘን ካፒቴን ቶርን ሪቻርድ ያለው ቶርን አለመሆኑን ሲነግሩኝ በጣም አዘንኩ ሚስተር ካርላይል ደግሞ' ' እንኳን እሱ አልሆነ ብሎ ደስ አለው
ሪቻርድ እማማ ዘንድ ገባ አባባ ካገኘው ይዞ ለፍርድ እንደሚያቀርበው ብዙጊዜ
ተናግሯል እሱ ተጫውቶ እስኪወጣ ድረስ እኔና ሚስተር ካርላይል ከግቢው ወዲያና ወዲህ እያልን የአባባን መምጣት አንድንጠባበቅ ተማከርን ከመጣ ሚስተር ካርላይል እያዝናጋው እንዲቆይና እኔ ሮጥ ብዪ ገብቼ ሪቻርድን እንዲሸሸግ እንዳስጠነቅቀው ከማማ ጋር ተነጋገርን ሚስተር ካርይልም የእማማን ልመና ተቀብሎ ሐሳቡ ተስማምቶ አብረን ከደጅ አመሽን " ሪቻርድም አልወጣም!ብዙ ቆየ አባባም አልመጣም " እኔና ሚስተር ካርላይልን ብዙ ጌዜ አስጠበቀን - ደስ የሚል የጨረቃ ሌሊት ነበር ።
ያልታደለችው ሳቤላ እጇን እስኪያማት እያፋተገች
አዳመጠች ባርባራ ምንም ሳትጠረጥር የሆነውን ሁሉ እያስታወሰች በቅንነቷ ስትነግራት ጸጸቱ እንደ እሳት ይፈጃት ጀመር ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲንጎራደዱ

👍13👏1🤔1
ያየቻቸው በሌላ ተልእኮ እንጂ በፍቅር ጉዳይ አንዳልነበር ዐወቀች" እውነተኛውንና ያ ደጉን ባሏን ለምን እንደ ጠረጠረችው ያንን ቀጣፊ ውሸታም ለምን እንዳመነችው ከአሳዛኙ ውሳኔ ለመድረስ ለምን እንደ ቸኮለች እያሰበች ሆድ ሆዷን ይበላት ጀመር!
መጨረሻ ሪቻርድ ወጥቶ እንደግና ወደ ስደቱ ሔደ ሚስተር ካርላይልም
ሔደ እኔ ግን አባባ ሲመጣ ለማየት ከበሩ ቆየሁ " ሆኖም ሚስተር ካርላይል ከቤቱ ሲደርስ ትንሽ ሲቀረው ከኛ ቤት አንድ ሰነድ መርሳቱን ትዝ ይለውና እንደገና ተመልሶ መቶ ሔደ ከሱ በኋላ ሪቻርድ ቁና ቁና እየተነፈሰ ተመልሶ መጣ "
“ ቶርንን ነፍሰ ገዳዩን ቶርን ማለቴ ነው ቢን ሌን ላይ አየሁት ብሎ ነገረኝ " ለጊዜው ጠረጠርኩት ነገር ግን ወዲያው ተያይዘን ከሚስተር ካርላይል
ለመድረስ ሮጥን " ሪቻርድ ቶርንን መልኩን 'የማታ ልብሱን 'ነጭ እጁን ያልማዝ ቀለበቱን በተለይም ጸጉሩን ወደኋላ ሲያስተኛ የእጁን እንቅስቃሴ ምን እንደ
ሚመስል አንድ ባንድ ዘረዘራቸው » በዚህ ጊዜ ይህ ቶርን የሚባለው ሰው ካፒቴን ሌቪሰን መሆን አለበት የሚል ሐሳብ መጣብኝ ገለጻው ከሌቪሰን ሁኔታ ጋር አንድ ነበር ሚስተር ካርላይል ግን ለምን እሱ ይሆናል ብሎ እንዳልጠረጠረ ብዙ ጊዜ
ሲገርመኝ ኖረ
ሳቤላ ነገሩ ግር ሲላት አፋን ከፍታ ዝም ብላ ተቀመጠች ኋላ ነገሩ ግልጽ ሲሆንላት አልተቀበለችውም ።
“ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነፍሰ ገዳይ ! አይደረግም " በርግጥ መጥፎ ሰው ነው
ነገር ግን ነፍስ ገዳይ አይደለም ” አለች »
“ ቆይ ” አለች ሚስዝ ካርላይል ስለዚህ ጉዳይ ምንም አልተናርኩም "
እንደዚያ የመሰለ የግፍ በደል የፈጸመበትን ሰው ስም እንዴት አድርጌ ለሚስተር ካርላይል ላንሣለት? ስለዚህ ሪቻርድም ወንጀለኛ ተብሎ እንደ ተሰደደ ቀረ - ዛሬ
በሠረገላ ሁኜ በዌስት ሊን ሳልፍ ፍራ ንሲዝ ሌቪሰን ለሕዝቡ ንግግር ያደርግ ነበር።ሪቻርድ የጠቀሳቸውን ምልክቶች ሁሉ በዐይኔ አየሁ ተፈላጊው ሰውዬ እሱ ነው የሚለው እምነቴ ከምን ጊዜውም የበለጠ እርግጠኛነቱ ተሰማኝ
ሊሆን አይችልም ” ብላ አጉረመረመች ሳቤላ ።
“ ቆይ “ ኮ ” አለች ባርባራ “ ይኸውልሽ ሚስተር ካርላይል ቅድም ለራት
ወደ ቤት ሲገባ ይህን ነገር ለመጀመሪ ጊዜ አነሣሁለት ነገሩ አዲስ አልሆነበትም
እሱ የቅስቀሳ ንግሩን ሲያዶርግ አፊ ሆሊጆንን ሲያባርር የነበረው ቶርን መሆኑን በሁለት ምስክሮች እንደ ተረጋገጠ ነገረኝ በጣም የሚዘገንን ነገር ነው ! ”
ሳቤላ " እንደ ተቀመጠች ሚስዝ ካርላይልን ትክ ብላ አየቻት " አሁንም ነገሩን ገና አላመነችም
“ በርግጥ በጣም የሚያሠቅቅ ነገር ነው » ይህ እርጉም ሆሊጆንን በገደለ የኔ ወንድም በስቃይና በውርደት ሲሠቃይ ኖረ " ያን ሌት ሪቻርድ ቢን ሌን ላይ ባገኘው ጊዜ ሳቤላን ይዞ የሚኮበልልበትን ሠረገላ ፍለጋ ዌስት ሊን ውስጥ ሲሽሎከሎክ ነበር " ሌሊት አባባ ሲገባ ባራት ፈረሶች የሚሳብ ሠረገላ በኛ በር አጠገብ ዐልፎት እንደ ሔዶ ነግሮን ነበር ምነው ያች ያልታደለች እመቤት ሳቤላ ከማን ጋር እንደምትኮበልል ዐውቃ ቢሆን ! ከዚያ ሁሉ መጥፎ ተግባሩ ላይ ደግሞ ነፍስ ገዳይ ሆኖ መገኘቱ ! በውነት ይኸን የመረጨሻ ጉድ ለማየት በይወሕት አለመኖሯ ለሷ ታላቅ ዕድል ነው " አሁን በሕይወት ብትኖር ኖሮ ምን ይሰማት ነበር ? ”
ማዳም ቬን ራሷን ለመግታት ስሜቷን ለመቈጣጠር ብዙ ብትታግልም የድንጋጤ ጩኽት አመለጣት " ፊቷ ዐመድ መስሎ ነጣ " ሚስዝ ካርላይል ገረማት "
ለምንድነው ታሪኰን ስትሰማ ማዳም ቬን እንደዚህ የምትሆነው ? ማዳም ቬን ስለ
ፍራንሲዝ ሴቪስን ከምትለው በላይ እንደምታውቅ ጠረጠረቻት
“ ማዳም ቬን ይህ ሰው ምንሽ ነው? አለቻት ወደሷ ጐንበስ ብላ "
ማዳም ቬን ከራሷ ጋር ታግላ ባይሆን አፍአዊ ስሜቷን አረጋጋችና''ይቅርታ
ሚዝ ካርይል ነገሩ እውነትም በጣም የሚዘንን ነው " አለቻት •
“ግን ምንሽም አይደለም ? ታውቂዋለሽ ? "
“ለኔ ምኔም አይደለም » ስለ ማቁ ግን ትናንት ከኩራው ሲከቱት አይቻለሁ!
ያን የመሰ ሰው ! ልጠጋው ይቀፈኛል ”
“በይ እንግህ ማዳም ቬን ይህን ሁሉ ታሪክ የነገርኩሽ አንቺን ከቤተሰባችን ቆጥሬ ስለ አመንኩሽ ነው …”
መልስ አልሰጠቻትም ፊቷ ጭው ብሎ እንደ ነጣ ተቀምጣለች
ነገሩ ተረት ይመስል ” አለች ባርባራ ጨዋታዋን በመቀጠል : “ አሁም
እሱ በመስቀል ላይ በተንጠለጠለና ታሪኩ በዚህ ቢፈጸም መልካም ነበር " ግን ተረቱ መስቀል ሳይ ሲንጠለጠል ይፈጸም ይሆናል " እስኪ አስቢው ማዳም ቬን እንዲያው ለራሱ ምን መስሎ እንደሚታየው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በነፍስ ገዳይ
ተፈርዶበት መስቀል ላይ ተንጠልጥሎ መታየት !
“ ባርባራ ' የኔ ፍቅር!”
የሚስተር ካርላይል ድምፅ ነበር እሷም ሳቤላን ትታት በፍቅር ክንፋ ወደ ባሏ በረረች " ያቺን ዱሮ በዘመኗ የመመለክ ያሀል ትወደድና ትከበር የነበረችውን 'ሚስት ' ብቻዋን ጥላት ወደምታመልከው ባሏ በረረች » ሳቤላም በጭንቀት ብዛት የታመመውን ልቧን በክንዷ እቅፍ አድርጋ ከሶፋው ውስጥ ሰጠመች ነፍሷንም የምትስት መሰላት እንድትሞትም ጸለየች » በእጅና በነፍሱ የግፍ ደም ያለበት ሰው ተከትላ ለመሔድ ስትል ኤርኪባልድ ካርላይልን የመሰለ ባል አሽቀንጥራ ጣለችው "....

ምዕራፍ አስራ ስድስት (16) «አዎ ! ሽንቶ የደፋኝ መስሎ ይሰማኛል ፤ አናዶኛል ፤ አበሳጭቶኛል ፤ አብግኖኛል »
«ማን?››
«ማይክል…..
አየሽ እስካሁን… ቢፈልግ እስካሁን ድረስ የት እንዳለሁ ማወቅ የሚቸገር አይመስለኝም ። ግን አልፈለገኝም። ወርውሮ ጥሎኛል »
«ሌላስ… ሌላስ ያናደደሽ ሰው አለ ? የበሸቅሽበት?»
«አዎ »
«ማ »
«እኔ ራሴ»
«ለምንድነው በራስሽ የበሸቅሽው? »
«ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ያደረግሁት ውል ልክ አልነበረም ። እሷ መቼም ደፋር ናት ። ድፍረቷ ይዘገንነኛል ከሷ ደግሞ የኔ ይብሳል ። ሸጥኩት አየሽ? ፍቅሬን ለሥጋዬ ሸጥኩት »
«በእውነት ፍቅሬን ሸጥኩት ብለሽ ታስቢያለሽ ? »
«ይመስለኛል ። ያውም በአዲስ ጉንጭ ! ፍቅርን ያህል ነገር በጉንጭ ፤! በመልክ››
«አይመስለኝም ፣ ናንሲ ። እኔ እንደምትይው አይመስለኝም « ለመልክ ሳይሆን ለመኖር ነው ። ነፍስሽን ለማቆየት ባንቺ ዕድሜ ምን አማራጭ እለሽ ? ሌላ ሴት ልጅ ባንች ዕድሜ ያለች ይህን አንች ያደረግሽውን ብታደርግ ምን ትያት ነበር?››
«እንጃ ! አላውቅም ። ምናልባት ችግሯን እረዳላት ይሆናል ወይም ንቄ እፈርድባት ይሆናል »
«ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት አዲስ ሕይወት መጀመር እንዳለብሽ ስንነጋገር ነበር ። አዲስ ድምጽ ፤ አዲስ አረማመድ አዲስ ገጽታ አዲስ ሁሉ ነገር ። ነገር ግን . . . ካንድ ነግር በስተቀር » አለች ፌ እና ዝም አለች ። ናንሲ ጠበቀቻት ። «ሁሉን ነገር እንድትቀይሪ ፤ የቀድሞውን እንድትረሺ ተነጋግረናል ። አንድ ነገሮ አላነሳንም » ዝም አሉ ሁለቱም ። «ማይክል… ስለማይክል አላነሳንም ። ናንሲ ማይክልን
ከሆድሽ አውጥተሽ ጥለሽ ማይክል የለም ብለሽ አዲስ ሕይወት መመሥረት የምትችይ ይመስልሻል ? »
«አልችልም… አልችልም» እንባዋ ቅርዝዝ አለ ። ሆኖም' ሁለቱም ይህ አባባል ውሸትም እንዳለበት ግብቷቸዋል ። «በፍጹም አትችይም ?››
«ፌ ፤ ሌላ ወንድ አስቤ አላውቅም ፤ ከማይክል ሌላ ። ግን ደግሞ አንዳንዴ ያለ ማይክል መኖር ይቻል ይሆንን አብሰለስላለሁ »
«እንዲያ ብለሽ ስታስቢ ምን ዓይነት ስሜት ይሰማሻል››
«ሞቴን እመኛለሁ››
«ለምን ናንሲ?... ለምሳሌ አሁን ከማይክል ጋር እይደለም እምትኖሪው ። ግን መከፋት የለብሽም ይመስለኛል አይደለም እንዴ?›› ናንሲ አዎንታዋን በአካል እንቅስቃሴ ገለጸች ።
«ናንሲ» አለች ፌ « ምናልባትም መድኃኒቱ የሚሠራዉ ይህንንም በደንብ ብታስቢበት ይመስለኛል »
«በቃ ! ማይክል ከአሁን በኋላ መጥቶ አይፈልጋትም ብለሽ አስበሻል ማለት ነው ?»
«ስለሱ ምንም እማውቀው ነገር የለም ፤ ናንሲ ። ይምጣ ይቅር ማንም ሊያውቀው አይችልም ከማይክል በስተቀር ማለቴ ነው »
«ልክ ነሽ ያ የውሻ ልጅ መልሱን እሱ ብቻ ነው የሚያውቀው !»
ናንሲ ይህን እያለች ከተቀመጠችበት ፈንጠር ብላ ተነሳች። አንዴ ካንዱ ዳር እስከ አንዱ ዳር ቤቱን በፍጥነት አካሔድ አዳረሰችው ። ከዚያም አካሔዱዋ ድንገት ቀነሰ ፤ ፍጥነቷ ኃይሏን የጨረሰው ይመስል ። ቆመች ። ባለችበት ላይ ። ስትቀመጥ ዕንባዋ በጉንጩዋ ላይ ፈስሶ ነበር ። «ፌ ! በጣም ፈራሁ ። በጣም በጣም ፈራሁ » አለች። «ምኑን ነው የፈራሽው፤ ናንሲ ? » ስትል ጠየቀች ፌ «ሁሉን ነገር» አለች ናንሲ «ሁሉን ነገር ። ብቸኛ መሆኔን ፣ ብቻዬን መሆኔን ፤ እራሴን ማጣቴን ፤ እኔን አለመሆኔን ። እንጃ… ምናልባት ያጠፋሁት ጥፋት ትልቅ በመሆኑ ቅጣቴ ሳይከብድ አይቀርም ይሆናል ። ፍቅርን ያህል ክቡር ነገር ለመልክ መለወጥ !››
«ግን ኮ ናንሲ ምርጫሽ ልክ ይመስለኛል ። ሙሉ አካል ከሌለ ፍቅርም እንደሌለ ተረዳሽ ። ቢያንስ የገጽታሽ መስተካከል የሚቻል ነው አሉሽ ። ተስማማሽ ። የለም ናንሲ፤ ወደፊትም ቢሆን በምርጫሽ የምትፀፀችበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም››
«ምናልባት ... ምናልባት » ናንሲን የለቅሶ ሳግ ይነትጋት ጀመር ።
«ገና፣ ዘመን መለወጫ ፤ አመትባል ። አመትባሉንም እንዴት እንደማሳልፈው ጨንቆኛል ። የዘንድሮውን አመትባል ሳስበው እጓለ ማውታን ማሳደጊያው ውስጥ ከነበረው ይበልጥ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ። ያኔ አየሽ ቢያንስ ሰው ነበረ ። ዘንድሮ ግን ብቻዬን ! አስቢው እስኪ ። ሊሊና ግሬቸን ካለፈው ወር ጀምሮ መሰናበታቸውን ታስታውሻለሽ ። አንች በበረዶ ሸርተቴ ለመዝናናት መሔድሽ ነው ። ፒተር ለሳምንት ያህልም ቢሆን ወደ አውሮፓ ይሔዳል ። እና....» ይህንን ሁሉ በእንባና በሳግ መካከል ነበር የተናገረችው ። ድንገት ንግግሯን አቋረጠች ። ምክንያቱም ፌንና ፒተርን አትሂዱ እንደማለት መሰላት ።
«ምናልባት ከሌሎች ሰዎች ጋር መተዋወቅ ያስፈልግሽ ይሆን ? ቢያንስ ለእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ» አለች ፌ። «እስኪ እይኝ ፌ » አለች ናንሲ ባርኔጣውን ከፍ እያደረገች ፊቷ በሙሉ እንዲታይ ፤ «እንዲህ ሆኜ ከማን ጋር ልተዋወቅ፤ፌ?!» .
«እንደሱ ብትሆኝ ምንድነው ። ባርኔጣውን ሳታነሽው የሚታየው ፋሻ ነው ። ፋሻ የአንድ ሰው ቆዳ እንዳልሆነ ፤ አደጋ ደርሶብሽ እንደነበረ ማንም ሰው ይገባዋል »
«ምናልባት ... ምናልባትም ይሆናል » አለች ። ሁለቱም ዝም አሉ ። ናንሲ በነገሩ ሙሉ በሙሉ እንዳላመነችበት ፌ ገብቷታል ። ያ ዓይነት ሐሳብ መኖሩን እንድታውቅ እንጂ ወዲያውኑ ልትቀበላት እንደማትችል ዱሮውንም ታውቃለች ። «ተቀበሉኝም ሸሹኝ ፤ አሁን እኔ ሰዎችን መተዋወቅ አልፈልግም ። እግዜር ይስጠው ፒተር የገዛልኝ ጓደኛ አለኝ ። ካሜራዬ ። ከሱ ጋር እጫወታለሁ ። በሱ ጊዜዬን አሳልፋለሁ አለች ። «ግሩም ፎቶግራፍ አንሺ ነሽኮ ። ካነሣሻቸው ፎቶዎች ጥቂቶቹን ባለፈው ጊዜ ፒተር ቢሮ ውስጥ አየኋቸው ። ድንቅ ናቸው ። ፒተር ደግሞ ቢሮው ለገባ ሁሉ ድንቅ ናቸው አይደሉም ? እያለ ሲያሳይ ነበር ። ድንቅ ፎቶግራፎች ናቸው »
« ስለወደድሽልኝ ደስ ይለኛል ፌ» አለችና እወንበሯ ላይ ተለጥጣ ተቀመጠች ። እግሯን አነባብራና ራሷን ይዛ «ፌ ምን ይሻለኛል ? እንዴት ፤ ምን ሆኜ ሰው ልሁን መኖር የምችል ይመስልሻል ? »
«እሱን ለማቀነባበር እየሞከርን አይደል እንዴ ፤ ናንሲ ። ላሁኑ ግን እስኪ የተማከርንባቸውን ነገሮች አስቢባቸው ። አዲስ የድምጽ ቃና አወጣጥን የሚያለማምድሽ ሰው ስለመቅጠር ፤ ደህና የሙዚቃ አስተማሪ ስለመፈለግ ፤ ባጠቃላይ አዲሷን አንችን ለመኖር ሀ ብለሽ ካሁኑ ሰዓት ለመጀመር ሞክሪ እስኪ» አለች ፌ ። ቀጥላም… « ሌላውን ተይው ። በጊዜው ይመጣል» የቤቱ አቀማመጥ ፤ የፌ ድምጽ ፤ የፌ ከንፈር መጠጣ የሌለበት ምክር ናንሲን አጽናኗት ። በልቧ ውስጥ ተጠራቅሞ የከበዳት ኀዘን ፍርሃት ፤ ጭንቀት ቀለል አለላት ። «ልክ ነሽ ፌ እንደሱ ማድረግ የሚሻለኝ ይመስለኛል በነገራችን ላይ መቼ ነው እረፍትሽን ጨርሰሽ እምትመለሽው!።»

👍19
«አሥራ አምስት ቀን ። በአሥራ አምስት ቀን ውስጥ እመለሳለሁ ። ከዚያ ወዲህ ባስፈልግሽ ደግሞ ችግር የለም ። አድራሻዬን እተውልሻለሁ ። ልትጠሪኝ ትችያለሽ » ፌ ለናንሲ ይህን የነገረቻት ረጋ ባለና ምንም ችግር እንደሌለ በሚነግር ድምጽ ቢሆንም በልቧ ግን ጨንቋት ነበር፡፡ ስለሷ ጉዞ ። ስለሷ ደስታ ሳይሆን ፤ ስለናንሲ ።መጭው ያመትባል ጊዜ መሆኑና እሷም ፒተርም ባንድ ጊዜ ትተዋት መሄዳቸውን ስታስብ ምን ዓይነት መጥፎ አጋጣሚ ነው ስትል አሰበች። ሌላ ጊዜ ቢሆን ደግ ዓመት ባል ግን ለየት ይላል፡፡ በጣም ለየት ይላል ። በዚህ ሁሉ መከራዋ ላይ አመትባሉን ያላንድ ሰው ብቻዋን ስትውል ናንሲ በጣም እንደምትደበር የተረጋገጠ ነው ዓመትባል ሲባል ደግሞ እንደለመዱት ካልዋሉት መከፋትን በልብ ውስጥ አጉልቶ የማስረጽ ባሕሪ አለው ።ሆኖም ይህን ለናንሲ መንገር አያስፈልግም ። እንደተሰማትም ማሳዬት የለባትም ። ስለዚህ ነገሩን ቀላል አድርጋ
«ለምን የዛሬ ሁለት ሳምንት ልንገናኝ አንቃጠርም ? እኔም ስለጉዞዬ ልነግርሽ ፤ አንችም ያነሳሻቸውን ፎቶግራፎች አትመሽ እንድትጠብቁቂኝ » አለች ። «ፖ ! የረሳሁትን ነገር አስታውስሽኝ » አለችና ናንሲ ከመቀመጫዋ ላይ እመር ብላ ተነሣች ። እና ከነበሩበት ክፍል ወጣች ። እንደተመለሰች በስጦታ መጠቅለያ ወረቀት የታሸገ ነገር እየሰጠቻት «መልካም የገና በዓል ይሁንልሽ ! » አለች ።
ፌ ከልብ በመነጨ ደስታ ፊቷ ፈገግ አለ ። እሽጉን ስትፈታውና ከውስጡ የወጣውን ነገር ስታይ ዓይኗን ማመን አቃታት ። የራሷ የፌ ፎቶግራፍ ነበር ። ናንሲ ያን ፎቶ መቼ እንዳነሣቻት ትዝ ባይላትም ፎቶውን ያዬ ማንም ሰው ግን «ፈገግ በይ ፤ እንደዚህ ሁኝ » እያለች ያነሣቻት ይመስለዋል ፤ በዝግጅት ። በፎቶው ላይ የምትታየዋ ፌ እናንሲ መኖሪያ ቤት ሰገንት ላይ ቆማለች ። ንፋሱ ፀጉሯን ያውለበልበዋል ። የለበሰችው ሐምራዊ ቀለም ሸሚዝ ከምትጠልቀዋ ፀሐይ ቀለም ጋር ተቀላቅሎ ሕብር ፈጥሯል ።
«መቼ ነው ያነሣሽኝ!? » አለች ፌ በአድናቆት እንደተሞላች ።
«ቀኑም ትዝ አይልሽ ?»
«ቀኑን አስታወስኩት… ግን…»
«ሳታይኝ ነው ያነሣሁሽ » ፌ ያን ያህል ደስ ሲላት ስታይ፤ ናንሲ በጣም ተደሰስተች። ይህንኑ ነበር የፈለገችው ። ፎቶግራፉን ያጠቆረችውም ያተመች ውም ራሷ ነበረች ። በጥንቃቄ ከዚያ ፍሬም አስገባችለት ሲያዩት የሥነጥበብ ሥራ መሆኑ ባያጠራጥርም ክፎቶ ይልቅ የእጅ ሥዕል ይመስል ነበር ። ወደዚያ የሚጠጋ ውበት ነበረው። «የማትታመኝ ጉድ ነሽኮ ናንሲ ። በጣም በጣም ውብ ነው ። በጣም ትልቅ ስጦታ ነው» አለች ፌ ። «ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሠሩት ሥራ ሁሉ ውብ ነው» አለች ናንሲ በደስታ እየተፍለቀለቀች ። ሁለቱ ሴቶች ተቃቅፈው ተሳሳሙ ። የፌን መሔድ ፤ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሊገናኙ እንደማይችሉ ስታስብ ናንሲ ኀዘን ተሰማት፡፡ «በይ እንግዲህ መልካም መዝናናት ይሁንልሽ» አለች ። «በይ በደህና ቆይኝ ። ስመሊስ ግግር በዶ ይዢልሽ እመጣለሁ » አለች ፌ ። «አትጃጃይ ፤ እሺ ? ! » አለችና እንደገና እቅፍ አደረገቻት ናንሲ ።
ናንሲና ፌ ተሰነባብተው ፤ መልካም አዲስ ዓመት መልካም የገና በዓል ተባብለው ተለያዩ ። ናንሲ ከሔደች በኋላ ሁሉ ፌ የምታስበው ስለናንሲ ነበር ናንሲ ጥሩ ልጅ ናት ። ባሕርይዋ ንጹሕ ነው። ሰው የሚባለው ደም ያ ነው ስትል አሰበች ። ይቀጥላል......

#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
የመርቪን ላቭሌይ ባለቤት ዳያና በደስታ ተፍነክንካለች በመጀመሪያ የሰማይ በራሪው ጀልባ መሬት ለቆ ሰማይ ላይ ሲወጣ ፈርታ ነበር አሁን ግን እየለመደችው መጣችና ደስ ይላት ጀመር ላቭሴይ በአይሮፕላኑ እንድትበር ዕድል ባይሰጣትም አይሮፕላኗን ብዙ ቀናት ፈጅታ ቀለም የቀባቻት እሷ ነች አንድ ጊዜ እስኪወጣ ነው እንጂ የሚያስፈራው እየተለመደ ሲመጣ ከሰማይ ሆኖ እርሻዎችን መንገዶችን የባቡር ሃዲዶችን፣ ቤተክርስ
ቲያኖችን፣ ፋብሪካዎችን ቁልቁል ሲያዩ የሚፈጥረው ደስታ ልክ የለውም
አሁን ነፃነት ተሰምቷታል፡፡ መርቪንን ጥላ ከማርክ ጋር ኮብልላለች፡፡
ትናንት ማታ ሳውዝሃምፕተን ከተማ በሳውዝ ዌስተርን ሆቴል ሚስተርና ሚስስ ማርክ አልደር በማለት ተመዝግበው የመጀመሪያውን
ሙሉ ምሽት አብረው
ሲፈጽሙ ያደሩት ወሲብ አልበቃ ብሏቸው ጧትም ደገሙት፡፡ ከዚህ ቀደም አዩኝ አላዩኝ እያሉ
እየተሳቀቁ ለአጭር ጊዜ ወሲብ ሲፈጽሙና ሲሳሳሙ ከነበረው ጋር ሲወዳደር
ይሄ ዓለም ነው በሰማይ በራሪው ጀልባ ሲበሩ ልክ ፊልም የሚያዩ ያህል
ነው የሚሰማው የአይሮፕላኑ የውስጥ ክፍል ያጌጠ፣ ተሳፋሪዎቹ ደግሞ
አለባበሳቸው የሚያምር ሲሆን ሁለቱ አስተናጋጆች ደግሞ ከአይን የቀደሙ ተፌዎች ናቸው ሁሉም እንቅስቃሴ በቅደም ተከተልና በቅልጥፍና
የሚካሄድ ሲሆን ዙሪያ ገባውን ታዋቂ ሰዎችም ይታያሉ፡ የይሁዲ ዝርያ ያለውና የጽዮናዊነት ንቅናቄ አራማጁ ባሮን ጋቦን አጠገባቸው ከተቀመጡ
ጎስቋላ ሰው ጋር በወሬ ተጠምደዋል ታዋቂው ፋሺስት የኦክስፎርዱ ባላባት ሎርድ ኦክሰንፎርድ ውቧን ሚስታቸውን አጠገባቸው ሻጥ አድርገው
ተኮፍሰዋል ልዕልት ላቪኒያ ባዛሮቭ ከዳያና ጋር ተቀምጠዋል
ከልዕልቷ ትይዩ ደግሞ በጥግ በኩል ታዋቂዋ የሆሊውድ ፊልም
ተዋናይ ሉሉ ቤል ቦታ ይዛለች፡፡ ዳያና በበርካታ ፊልሞች ላይ ያየቻት ሲሆን
ከማርክ ጋር እውቂያ አላት፡፡ ገና እንደተቀመጡ አንድ የአሜሪካዊያን አነጋገር ቅላጼ ያለው ድምጽ ‹‹ማርክ አልደር አንተ ነህ?! እኔ አላምንም››
ሲል ተሰማ፡፡ ዳያና ለማየት ዞር ከማለቷ አንዲት ከአፍ የወደቀች ፍሬ የምታክል ሴት ማርክ ላይ እንደ ጆፌ አሞራ ስትከመርበት ተመለከተች
በኋላ ታሪኩን እንዳጫወቷት ሉሉ እንደዚህ እንዳሁኑ ታዋቂ የፊልም አክተር ከመሆኗ በፊት ከማርክ ጋር የሬዲዮ ቶክ ሾው ላይ አብረው ሰርተዋል፡፡ ማርክም ዳያናንና ሉሉን አስተዋወቃቸው፡፡ ሉሉም ዳያና ቆንጆ መሆኗንና እሷን የመሰለች ማግኘት መቻሉ እድለኛ እንደሆነ ነገረችው፡፡
በእርግጥም ሉሉ ትኩረቷ ማርክ ላይ ስለነበር አይሮፕላኑ ከተነሳ ጀምሮ
ወጣት ሳሉ በችግር እንዴት እንዳሳለፉ እዚህ ግባ የማይባል ቤት ውስጥ
ሲኖሩ እንደነበሩና የመንደር አረቄ እየጠጡ ሌሊቱን ያሳለፉ እንደነበር
የጥንቱን አኗኗራቸውን እያነሱ ተጨዋወቱ፡፡
ዳያና ፊልሞቿ ላይ ረጅም ትምሰል እንጂ በእውን አጭር ናት፡ጸጉሯም በተፈጥሮ ቃጫ የመሰለ ሳይሆን ቀለም የተቀባ ነው፡፡ ሆኖም ፊልሟ ላይ እንደምትታየው እዚህም ያንኑ ፎልፏላነትና ልታይ ልታይ ባይነት ባህሪዋን ታንጸባርቃለች፡፡ ከማርክ ጋር እያወራች ሳለ ሁሉም እሷን
እሷን ይመለከታል፡፡
በሬዲዮ ድራማ ላይ አንድ ገጠመኝ አንስታ ስታወራ ሁሉም በሳቅ አውካካ፡፡ ‹‹አንድ ተዋናይ እሱ የሚናገረው የድራማው ክፍል አልቋል ብሎ በማሰብ ከስቱዲዮ ወጥቶ ሄዷል፡፡ መጨረሻ ላይ ግን የሚናገረው አንድ መስመር ንግግር ቀርቶታል፡፡ እኔም የፋሲጋውን ኬክ ማን በላው?
የሚለውን የራሴን ድርሻ ተናገርኩ፡ የኔን ድርሻ እንደገና ደግሜ ተናገርኩ፡፡
ዞር ብዬ ሳይ ተዋናዩ የለም፡፡ ቀጥሎ ያለውን የሚናገረው ሰው ሄዷል።አንድ ዘዴ በአእምሮዬ አውጠነጠንኩና በወንድ ድምጽ ድመቷ ናት
የበላችው በማለት ትርዒቱን አጠናቀቅኩ እላችኋለሁ›› ብላ አሳቀቻቸው::
ለማርክ ለመንገር ታሪኩን ስትጀምር አቋረጣትና ፊቱን ወደ ሉሉ አዙሮ ዳያናም አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ስትከታተል የሰማችውን
ከማርክ ጋር በቆየችባቸው ሶስት ወር ያህል ማርክ ፊት ነስቷት አያውቅም በኋላ ማርክን የብቻዋ ማድረግ የማትችል መሆንዋን
መረዳት ሊኖርባት ነው፡ አዳማጭ መሆንዋ ሰለቻትና ወደ ልዕልት ላቪኒያ ዞራ
‹ሬዲዮ ያዳምጣሉ ልዕልት?› ብላ ወሬ ጀመረች።
አሮጊቷ ራሻዊት አገጫቸውንና እንደ
አሞራ የተቆለመመ
አፍንጫቸውን በንቀት ከፍ አድርገው አቀራረባቸው ጨዋነት ይጎድለዋል›
አሉ፡፡
ዳያና ከዚህ ቀደም አመለ ቢስ አሮጊቶች ቢገጥሟትም እኚህኛዋ ግን የባሱ ናቸው፡ ‹‹ይደንቃል! ትናንት ግን የሰማነው የቤቶቨን ሙዚቃ ጥሩ ነው›› አለች ዳያና፡፡
‹‹የጀርመን ሙዚቃ ደረቅ ነው›› አሉ አሮጊቷ በማንቋሸሽ፡
እኚህን ሴት ምንም የሚያስደስታቸው ነገር የለም አለች ዳያና በሆዷ።
ልዕልቲቷ ከዚህ ቀደም እጅግ በጣም የተከበረ መደብ አባል የነበሩ ሲሆን
ይህንንም ዓለም በሙሉ እንዲያውቅላቸው ይፈልጋሉ የሚቀርብላቸው ነገር
ሁሉ ከዚህ ቀደም ሲቀርብላቸው ከነበረው ጋር ሲወዳደር እንደሳቸው
አስተሳሰብ እዚህ ግባ የሚባል ይደለም።
በኋለኛው የአይሮፕላኑ ክፍል የተመደበው አስተናጋጅ የሚፈልጉት
መጠጥ ካለ ለመታዘዝ ተሳፋሪዎቹ ፊት ቆሟል፡ ስሙ ዴቪ ሲሆን ሲራመድ ነጠር ነጠር የሚል የደስ ደስ ያለው ወጣት ነው፡፡ ዳያና ጠጥታው ባታውቅም የአሜሪካ ፊልሞች ላይ ሲጠጡት ስላየች ማርቲኒ አዘዘች፡
ከእሷ ቀጥሎ የተቀመጡትን ሁለት ሰዎች መልከት ስታደርግ በመስኮት ወደ ውጭ ያያሉ፡፡ ለጥቆ ደግሞ ረከስ ያለ ነገር ግን የሚያምር ልብስ የለበሰ ወጣት ሰው ተቀምጧል እንደ ስፖርተኛ ደልደል ያለ ትከሻ ያለው ሲሆን በርካታ ቀለበቶች አስሯል፡ ጠየም ያለ ፊቱ ደቡብ አሜሪካዊ መሆኑን
ይጠቁማል።
ከእሱ ትይዩ የተቀመጠው ሰው ደግሞ ለየት የሚል ሲሆን ኮሌታው የነተበ ሰፊ ኮት ለብሷል፡ በራው ደግሞ እንደ ስጋ ቤት አምፑል ዓይን
ያጥበረብራል፡ ሁለቱ ሰዎች ሲነጋገሩ ባይታዩም ዳያና አንድ ላይ እንደሆኑ
ገምታለች፡
መርቪን በአሁኑ ጊዜ ምን እየሰራ ይሆን? ስትል አሰበች፡፡ መቼም
ያስቀመጠችለትን ማስታወሻ ሳያነብ አይቀርም ያለቅስ ይሆናል አይ
አያደርገውም እሱ እንደዚህ አይነት ሰው አይደለም፡፡ መቼም በንዴት ጠጉሩን እየነጨ ይሆናል፡ በማን ላይ ይናደዳል ምናልባት በሰራተኞቹ ላይ? የጻፈችው ማስታወሻ ለስለስ ያለ ቢሆን ተመኘች ነገር ግን ከዚህ የተሻለ እንዳትጽፍ ሁኔታዎች አልፈቀዱም፡፡ እቤት ሲያጣት እህቷ ቲያ ጋ
ይደውልና አንቺጋ ናት? ብሎ ይጠይቅ ይሆናል የሄደችበትን መቼስ
ታውቃለች ብሎ፡ ወደ አሜሪካ እንደምትሄድ ስላልነገረቻት ቲያ ጠፋች
ሲባል ትደነግጣለች፡ የዳያናን አገር ጥሎ መጥፋት ለመንትያ ልጆቿ ምን ብላ ትነግራቸዋለች? ይህን ስታስበው ሆዷ ተምቦጫቦጨባት፡፡ የመንትዮቹን ልጆች ናፍቆት መቼም አትችለውም::
ዴቪ ያዘዙትን መጠጥ ይዞላቸው መጣ፡፡ ማርክ በመጀመሪያ ለሉሉ
ቀጥሎ ለዳያና ብርጭቆውን አነሳ በዚያው ቅጽበት ዳያና ማርቲኒውን
አንስታ ተጎነጨች፤ ስላንገፈገፋት ‹ህቅ› ብላ ተፋችና ‹‹ጂን ጂን ይላል››
ስትል ሁሉም አንዴ ሳቁባት፡፡ ማርክም ቀበል አድርጎ ‹‹ማርቲኒ እኮ ባብዛኛው ጂን ነው ከዚህ በፊት ጠጥተሽ አታውቂም ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ሰዎቹ ስለሳቁባት ዳያና በሃፍረት ተሸማቀቀች። ልክ ቡና ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደገባች ተማሪ የምታዘውን መጠጥ አታውቅም፡፡ እነዚህ
ከሰለጠነ ዓለም የመጡ ተሳፋሪዎች ደግሞ ፋራነቷን አወቁባት፡፡

👍17❤1