✍️✍️የጠንቋዩ ዋሻ✍️✍️
❀❀ክፍል 1 ❀✈️✈️✈️
☜☜☜☞☞☞☞☞
በድቅድቅ ጨለማ የተዋጠው ዋሻ ከማስፈራት አልፎ ያስጨንቃል ፡ ልብይስባል ፡ ፀጥታው ደሞ ይብስ ፡ሞትን ያስመኛል ፡ በዛ አስፈሪ ጎሬ ውስጥ ፡ በማያውቁት ፡ሰው በድንገት ታፍነው የመጡት ሦስት ፡ የደረሱ ጎረምሶች ፡ አይኖቻቸውን ፡በቀይ ጨርቅ ፡ቢሸፈኑም ፡ የገቡበት ፡ ጎሬ ፡አንዳች ብርሃን እንደሌለ ተውቋቸዋል ፡ ሦስቱም ፡በአካልም ሆነ በዕድሜ ተቀራራ ቢ ናቸው ፡ ገና በመፈርጠም ላይ ያለው ፡ ታዳጊ ሰውነታቸው ፡ የገቡበትን ፡ድንገተኛ ፡ወጥመድ ፡እንዴት ፡መቋቋም ፡እንደሚችል ፡ ምንም አልገባቸው ፡ ብቻ ከነሱ በገዘፈ ክንድ ውስጥ ፡በቁጥጥር ፡እንደዋሉ ካወቁ ሰአታት ተቆጥሯል ፡ ለወትሮው ፡ የሰፈር ውስጥ አይለኝነታቸውና የጎረምሳ ቲቢታቸው ፡ ልዩ ነበር ፡ ተወልደው ካደጉባት ፡ከተማ ፡አዲስ አበባ ፡ ወጥተው አያውቁም ፡ የነሱ ግዛት ፡ ከአብነት ፡እስከ ሜክሲኮ ፡ሲያልፍ ፡እስቴዴዬም ፡ድረስ ፡ብቻ ነው ፡ ዛሬን ፡ግን ፡ ከመጠን ፡ባለፈ ፡ ስካር ፡ውስጥ ፡ገብተው ፡ የሜክሲኮን ፡መንገድ ፡ይዘው በመምጣት ፡ሳሉ ፡ ባልታወቀ ፡ሰው ፡ ተጠልፈው ፡ ወደማያውቁትና ወዳልገባቸው ፡ስፍራ ፡እየተወሰዱ ነው ፡ * በመጀመሪያ ያፈርጣማ ና አስፈሪ ሰው ፡ በሚኒ ባስ ፡መኪናው ፡ከፊታቸው ፡ሲቆም ፡ በስካር ፡መንፈስ ፡ውስጥ ፡ሆነው ፡ ዕድላቸውን ፡በማመስገን ፡ቶሎ ፡ወደቤታቸው ፡እንዲያደርሳቸው ፡ ሰውየውን፡በጩኽትና ፡ በማስጠንቅቅ ፡እያደነቆሩት ፡ነበር ፡ ከቆይታ በዋላ ግን ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ በስካር ፡እብድ ፡ብለው ፡የሚለፈልፉትን ፡ ሦስቱን ጎረምሶች ፡አፋቸውን እንዲዘጉ በቁጣ ፡ሲጮህባቸው ፡ ከሱ የበለጠ በመናደድ ፡ መልሰው ፡ጮሁበት ፡ ያልታወቀው ፡ሰው መኪናውን ፡አቁሞ ፡በመውረድ ፡ ከዋላ የጫናቸውን ፡ጎረምሶች ፡አንድ ፡በአንድ ፡ከመኪናው ፡አውርዶ ፡ በፈርጣማ እጆቹ ፡ ደና አድርጎ ፡እየነረተ ፡መልሶ ፡ወደውስጥ ፡አስገባቸው ፡ እነሱም ፡በዚ ጊዜ ነበር ፡በተሳሳተ መስመር ላይ እንደሆኑ ያወቁት ፡ እናም ፡ሰውዬውን ፡ለመጀመሪያ ጊዜ ከስካር መንፈሳቸው ፡ተላቀው ፡ልብ ብለው ፡ አዩት በጣም ፡ከማስጠላቱም በላይ ፡ግዝፈቱ አነጋጋሪ የሚባል አይነት ፡ነው ፡ አንድ ፡አይኑ በጥቁር ፡ ጨርቅ መሰል ነገር ተሸፍኗል ፡ በዛ ሰፊና ፡አስጠሊ ፊቱ ላይ ፡ጉርጥርጥ የምትለ ብቸኛ እና ፡ቅልት ያለች ፡አይኑ ፡የበለጠ የልብን ፡ምት ታፈጥናለች ፡ ሦስቱም ፡እርስ ፡በእርስ ፡ተያይተው ፡አንድ ፡ዘዴ ፡ለማመንጨት ፡እና ፡ይህ ፡ሰው ፡በዚ ፍጥነቱ ፡ ሲሆል ፡ሳያደርሳቸው ፡በፊት ፡ለማምለጥ ፡አሰቡ ፡ ነገር ግን ያሰቡትን ፡ያወቀ ይመስል ፡ አንድ ፡ጨለማ ቦታ ሲደርስ ፡ መኪናውን ፡በማቆም ፡ ወደ እነሡው ፡መጥቶ ፡ ከአንድ ፡ ጥቁር ቦርሳ ውስጥ ፡ቀያይ ፡ጨርቅ ፡አውጥቶ ፡የሦስቱንም ፡አይን ፡አሰራቸው ፡ ቢፈራገጡም ምንም ፡ማድረግ ፡ሳይችሉ ቀሩ ምን እንዳስነካቸው ፡ሳያውቁ ፡ከቆይታ በዋላ ፡እራሳቸውን ፡ዝልፍልፍ ፡ አደረጋቸው ፡ ከዛ በዋላ ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡እረዥም ፡ሰአት ፡ነዳ ፡እነሱ ግን ፡ ወዴት ፡በየት ፡እንደሚነዳው ፡በጭራሽ ፡አላወቁም ፡ድንዝዝ ፡እንዳሉ ፡ነበር ፡ ከብዙ መደናዘዝ ፡በዋላ ነበር ፡የነቁት ፡ሲነቁ ፡በድቅ ድቅ ፡ጨለማ ፡በተዋጠ ጫካ ውስጥ ፡ተዘርረው ፡ነበር ፡ከመኪናው ፡ውስጥ ፡እንኳ ፡እንዴት ፡ብለው እንደወጡ የሚያስታውሱት ፡ነገር የለም ፡ እዛ ጨለማውስጥ ፡በትህግስት ፡እንዲነቁ ሲጠብቃቸው ፡የነበረው ፡ያልታወቀው ፡ሰው ድንገት ፡መንቀሳቀሳቸውን ፡ሲያውቅ ፡
"ተነሱ እናንተ ይበቃቹሃል ፡ አቢያራ ይጠብቃቹሃል " አላቸው ፡በሚያስፈራ ድምፅ ፡ ሦስቱም ፡ የሰሙትን ፡ስም ፡ ከዚ በፊት የትም ፡ቦታ ሰምተው ፡ስለማያውቁ ፡ግራ ተጋቡ ፡ ማነው ፡አቢያራ ፡ ምንድነው፡ከኛ የሚፈልገው ፡ ሁሉም ፡በየራሳቸው ፡አሰቡ ፡ መጠየቅ ፡እንዳይችሉ ግን ፡የሆነ ነገር ፡አንቆ ፡እንደያዛቸው፡አይነት ፡ሆኑ ፡ እናም ፡ያለምንም ፡ጥያቄ ፡ በፀጥታ እየተንቀጠቀጡ እና እየተደነቃቀፉ ፡ ያልታወቀውን ፡አስፈሪሰው ፡ተከተሉት ፡ እሱ መንገድ እየመራ ፡ወደግራ ታጠፉ ፡ደሞ ፡ወደቀኝ ፡እያለ ፡በድምፁ ሲመራቸው ፡እና፡አንዳንዴም ፡ሲገፈትራቸው ፡ ዕንባና ሳግ እየተናነቃቸው ፡ ስለማይጨክኑባቸው ፡ውድ ፡ቤተሰቦቻቸው ፡እያሰቡ ፡ሰውየውን ፡ተከትለው ፡ወደዋሻው ፡ገቡ ፡ ዋሻው ፡ውስጥ አይናቸው ፡ታስሮ ፡ምንም ፡ነገር ፡ለማየት ፡ ባይቻላቸውም ፡ግን ፡ አልፎ ፡አልፎ ፡ጪጪጪ የሚል ፡ልብ ፡የሚያሸብር ፡ድምፅ ፡ከተሰማ ፡በዋላ ፡ጭንቅላታቸውን ፡ገጭቷቸው ፡የሚያልፍ ፡ ወፍ ፡ይሁን ፡በውል ፡ያላወቁት ፡ነገር ፡አለ ፡የሰውዬው ፡ድምፅ ፡ የቁጣ መሆኑ ቀርቶ ፡በለሰለሰ ፡ድምፅ ፡"አባቴ ፡መጥቻለው ፡ክብር ፡ላንተ ይሁን ፡ ጌታዬ ፡በሰላም ፡ጠብቀህ ፡እዚ ላደረስከኝ፡ክብር ፡ላንተ ይገባል ፡ይላል" ጎረምሶቹ፡ይሰው ፡ የአንድ ፡አይለኛሰው ፡ ታዛዥ እንደ ሆነ ተሰምቷቸዋል ፡ ለማን አሳልፎ ፡እንደሚሰጣቸው ፡ ገና ያወቁት ነገር ባይኖርም ፡ ግን ያ እየጠበቃቸው ፡ያለው ፡ሰው ፡ቀላል ፡እንዳልሆነ ገብቷቸዋል ፡ በተሸፈኑት ፡ጨርቅ ላይ ፡የእንባ ፡ዘለላዎች ፡እየወረዱ ፡ ነበር ፡
"ደርሰናል ያአቢያራ ባሪያዎች "አለ ሰውዬው
"ምም ንድን ነው " አለ ከሦስቱ ጎረምሶች አንዱ ፡የሚያስፈራና ፡ እንደንፋስ አይነት ፡ሽውሽውታ ፡በአይል ፡ሲያዳምጥ ፡በፍርሃት ተውጦ ፡
"ድምፅ አታሰማ ተናገር ሳትባል ከአሁን በዋላ ፡እንዳትናገር ፡ ስትተነፍስ እንኳን ፡ መቆጠብ አለብህ ፡ ያአቢያራን ታስቆጣለህ "አለው በሹክሹክታ ፡ ሦስቱም ፡ተንቀጠቀጡ ፡ ሌላ ድምፅ ፡ሲያስገመግም ፡ተሰማ ፡ "አሆ አሆ አሆራራራራራ ያያአቢሃራራራ አሆያ አሆያ ሆሆሆሆሆ "የጩኽቱ መጠን ፡ልክ ፡የለውም የሚያጓራ ድምፅ አስጨናቂ ድምፅ ፡ በዛ ጨለማ ፡የሦስቱ ነብሶች ፡ ተስፋ ያበቃለት መሰለ
✍️✍️✍️ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ሙና መሐመድ
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️

👍57😱11👎6👏5❤1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
ቀኖቹን ሁላ ሰማያዊ ስትቀባ አንዱን ለጥቁር ተወው።
በማንኛውም ቀን ልንሄድ ነው፡፡ እናታችን በምሽት ወጣ እላለሁ እንዳለች፣
መጓጓዝ የሚችሉ ውድ ንብረቶቿም ከእሷ ይወጣሉ። ወደ ግላድስተን
አንመለስም እዚያ አሁን ክረምት ገብቷል። ገና እስከ ግንቦት ይቆያል።ሰርከስ የሚሰሩ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሳራሶታ እንሄዳለን፡ እዚያ ያሉ
ሰዎች ለየት ያለ የኋላ ታሪክ ላላቸው ሰዎች ደግነት በማሳየት የሚታወቁ
ናቸው ክሪስና እኔ ከፍ ያለ ቦታ ማለትም ጣራ ላይ ስለኖርን ምሰሶዎቹ
ላይ ብዙ ገመዶች የታሰሩበት በመሆኑ ለክሪስ “የዥዋዥዌ ትርኢት የምንሰራ እንሆናለን” አልኩት እየተፍለቀለቅኩ። በመጀመሪያ የሞኝ ሀሳብ እንደሆነ አስቦ ፈገግ አለ፤ ቀጥሎ ግን መንፈስን የሚቀሰቅስ ሀሳብ ብሎ ጠራው።
ኮሪ ጭንቅላቱን ቀና አደረገ፡፡ ሰማያዊ አይኖቹ በፍርሀት ፈጥጠዋል።
“አይሆንም!” አለች ኬሪ “እቅዳችሁን አልወደድነውም እንድትወድቁ አንፈልግም::”
“አንወድቅም” አለ ክሪስ፡ “እኔና ካቲ የማንቻል ቡድን ነን፡" አሻግሬ ወደ እሱ
እየተመለከትኩ መማሪያ ክፍሉ ውስጥ ከዚያም ጣሪያው ላይ ሆነን “ከአንቺ
በስተቀር ማንንም አላፈቅርም፣ ካቲ አውቀዋለሁ... እንደዚያ አይነት ስሜት ነው ያለኝ... ሁልጊዜ እኛ ብቻ:" ያለኝን አስታወስኩና በተለየ ሁኔታ ሳቅኩ። “ሞኝ አትሁን፣ በዚያ መንገድ እንደማትወደኝ ታውቃለህ፡ እና ጥፋተኝነት
ሊሰማህ ወይም ልታፍር አይገባም: የእኔም ጥፋት ነው: እንዳልተፈጠረ
ማስመሰልና በድጋሚ እንዳይፈጠር እርግጠኛ መሆን ነው ያለብን፡"
"ግን ካቲ....."
“አንቺና እኔ ሌሎች ሰዎች ሲኖሩን፣ በፍፁም… በፍፁም እርስ በርሳችን በዚህ መንገድ እንዲሰማን አይሆንም''
“እኔ ግን ስላንተ በዚህ መንገድ እንዲሰማኝ ነው የምፈልገው። እና ለእኔ ሌላ
ሰው ለማመንና ለመውደድ በጣም ዘግይቷል።”
ክሪስን መመልከት… ከዚያ መንትዮቹን. ለሁላችንም እቅድ ሳወጣና እንዴት
እንደምንሄድ ሳወራ ትልቅ የሆንኩ አይነት ስሜት ፈጠረብኝ፡ ለመኖር
የትኛውንም ነገር ለመስራት እንደምንገደድ ባውቅም እንኳን መንትዮቹ ሰላም
እንዲሰማቸው መፅናኛ ነገሮች አወራቸዋለሁ።
መስከረም አልፎ ጥቅምት ተተካ። በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል:
“ዛሬ ማታ” አለ ክሪስ፡ እናታችን በሩጋ ቆም ብላ ዞራ እንኳን ሳታየን
በግዴለሽነት ደህና ሁኑ ብላን ሄደች:: አሁን እኛን መመልከት እንኳን
መቋቋም አቅቷታል። አንዱን የትራስ ልብስ ሌላኛው ላይ ደርበን ጠንhር እንዲል አደረግን፡ በዚያ ትራስ ጨርቅ ውስጥ ክሪስ የእናታችንን ውድ
ጌጣጌጦች ሁሉ ከትቶ ያመጣል፡ እኔም ሁለት ሻንጣዎችን አሽጌ እናታችን
አሁን ወደዚያ ስለማትሄድ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ደብቄያለሁ።
ቀኑ መምሸት ሲጀምር ኮሪ ማስመለስ ጀመረ። እየደጋገመ ያስመልሰው
ጀመር። በመድኃኒት ማስቀመጫው ውስጥ ለሆድ የሚሆን መድኃኒት ነበረን የገረጣውን፣ የሚያንቀጠቅጠውን፣ የሚያስለቅሰውን አሰቃቂ ማስመለስ ያደረግነው ጥረት ሁሉ ሊያስቆመው አልቻለም ከዚያ ክንዶቹን በአንገቴ ዙሪያ ጠምጥሞ “እማዬ ደህና አይደለሁም::” ሲል አንሾካሾከ።
“እንዲሻልህ ምን ላድርግልህ ኮሪ?” ስል በጣም ልጅ መሆኔና ልምድ የሌለኝ መሆኔ እየተሰማኝ ጠየቅኩ።
“ሚኪ” አለ ያላመደውንና ጓደኛ ያደረገውን አይጥ በደካማ ድምፅ እየተጣራ
“ሚኪ እኔ ጋር እንዲተኛ እፈልጋለሁ”
“ግን ስትገለበጥ ላዩ ላይ ትተኛበትና ይሞትብሀል፡ እንዲሞትብህ አትፈልግም
አይደል?”
“አልፈልግም” አለ ሀሳቡ ራሱ ያስደነገጠው መሰለ፡ ከዚያ ያ አሰቃቂ መጓጠጥ
እንደገና ጀመረውና ክንዶቼ ላይ እንደያዝኩት እየቀዘቀዘ መጣ፡ በላብ የረጠበ
ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተለጥፏል ሰማያዊ አይኖቹ ፊቴ ላይ ተተክለው እየደጋገመ እናቱን ይጣራል። “እማዬ፣ እማዬ፣ አጥንቶቼን አሞኛል” “አይዞህ” አልኩት።
የተበላሸውን ፒጃማውን ለመቀየር ተሸክሜ ወደ አልጋው እየወሰድኩት ነው።
ሆዱ ውስጥ የቀረ ምንም ነገር ሳይኖር እንዴት ሊያስመልሰው ይችላል?
ክሪስ ይረዳሻል አትጨነቂ!” ሲለኝ ከጎኑ ጋደም ብዬ ደካማና የሚንቀጠቀጥ
ሰውነቱን በክንዶቼ አቀፍኩት::
ክሪስ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ የኮሪ የህመም ምልክቶች የሚያሳየውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያንዳንችንን ሊያጠቃን የሚችለውን ሚስጥራዊ በሽታ ለማወቅ
የሀክምና መፅሀፍ ላይ ተደፍቷል አሁን አስራ ስምንት አመት እየሆነው
ነው እኔንና ኬሪን ትታችሁን አትሂዱ! ሲል ለመነኝ፡ ጮክ ባለ ድምፅ “ክሪስ አትሂድ እዚህ ቆይ!” አለ።
ምን ማለቱ ነው? እንድናመልጥ አይፈልግም? ወይስ ለመስረቅ እንደገና
ወደ እናታችን ክፍል አትሂድ ማለቱ ይሆን? እኔና ክሪስ መንትዮቹ የምናደርጋቸውን ነገሮች በመረዳት ይመለከታሉ ብለን ያመንነው ለምንድነው?
በእርግጠኝነት እሱና ኬሪ ትተናቸው እንደማንሄድ ያውቃሉ ያንን ከማድረግ
ብንሞት ይሻለናል።
ኬሪ ነጭ ልብስ የለበሰች ትንሽ ጥላ መስላ ወደ አልጋው መጣችና በረጠቡት ትላልቅ ሰማያዊ አይኖቿ መንትያ ወንድሟን አተኩራ እየተመለከተች
ቆመች: ትንሽ ናት። በጨለማ ክፍል ውስጥ መንምና በአጭር ቀርታ ያደገች ትንሽዬ ተክል ናት።
“ከኮሪ ጋ መተኛት እችላለሁ? ምንም መጥፎ ወይም ክፉ ወይም ቅዱስ
ያልሆነ ነገር አንሰራም: እሱ አጠገብ መሆን ስለፈለግኩ ብቻ ነው” አለች።
አያትየው ትምጣና መጥፎ የምትለውን ነገር ታድርግ! ኬሪን ከኮሪ ጋር አስተኛኋት። ከዚያ እኔና ክሪስ ከትልቁ አልጋ ግራና ቀኝ ቆመን በሀዘን ተሞልተን ኮሪ ረፍት ባጣ ሁኔታ ሲቅበጠበጥና ለመተንፈስ ሲታገል እንዲሁም በቅዠት ሲጣራ እየተመለከትን ነው
እናቱንና አባቱን፣ ክሪስንና እኔን ይፈልጋል እምባዬ በሌሊት ልብሴ ኮሌታ
ላይ እየወረደ ነው ክሪስንም ስመለከተው ጉንጮቹ በእምባዬ ረጥበዋል። “ኬሪ
ኬሪ... ኬሪ የታለች?" ሲል በመደጋገም ጠየቀ እንቅልፍ ከወሰዳት ትንሽ
ቆይታለች: ፊቶቻቸው ተጠጋግተው ነበር። ቀጥታ ወደ እሷ እየተመለተ
ቢሆንም እያያት አይደለም
ቅጣት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ እግዚአብሔር እኔና ክሪስ ስለሰራነው ነገር እየቀጣን
ነው አያትየው አስጠንቅቃን ነበር. እስክተገረፍንበት ቀን ድረስ በየቀኑ
ታስጠነቅቀን ነበር ሌሊቱን ሙሉ እኔ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ፣ ክሪስ ደግሞ ከአንዱ የህክምና መፅሀፍ ወደ ሌላው እየሄደ ሲያነብ ነበር።
በመጨረሻ ደም የመሰሉ አይኖቹን ቀና አድርጎ “የምግብ መመረዝ ነው::
ወተቱ ተበላሽቷል ማለት ነው” አለ።
“ስቀምሰውም፣ ሳሸተውም ደህና ነበር” ስል መለስኩለት ሁልጊዜ የትኛውንም ምግብ ለክሪስና ለመንትዮቹ ከማቅረቤ በፊት በጥንቃቄ አሽትቼና ቀምሼ ነበር። በሆነ ምክንያት ሁሉንም ነገር ከሚወደውና ምንም ነገር ከሚበላው
ክሪስ የተሻለ የመቅመስ ችሎታ እንዳለኝ አስባለሁ።
“ሀምበርገሩ ይሆናል፡ ለየት ያለ ጣዕም ነበረው”
“አረ ጣዕሙ ለእኔ ደህና ነበር” አልኩት ለእሱም ደህና የነበረ ይመስለኛል::
ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ ኮሪ ምንም መብላት ስላልፈለገ የኬሪን ግማሽ ሀምበርገር ጨምሮ የኮሪንም ፋንታ ነበር የበላው ኮሪ ቀኑን ሙሉ ምንም መብላት አልፈለገም ነበር።
“ካቲ አንቺም ቀኑን ሙሉ ምንም እንዳልበላሽ አስተውያለሁ አንቺም እንደ
መንትዮቹ ያህል ከስተሻል፡ የምታመጣልን ምግብ በቂ ነው ራስሽን መበደል
አይጠበቅብሽም” አለኝ፡

👍34❤3🥰1
“ኮሪ የሚወደው ዶናቶቹን ነው፡ እኔም መብላት የምፈልገው እነሱን ብቻ
ነው እኔ ከምፈልጋቸው በላይ ለእሱ ያስፈልጉታል።”
ምሽቱ ቀጠለ፡፡ ክሪስ የህክምና መፃህፍቱን ማንበብ ቀጠለ፡ ለኮሪ የሚጠጣው ውሀ ስሰጠው ወዲያው አስመለሰው: ፊቱን ከደርዘን ጊዜ በላይ አጠብኩት ፒጃማውን ሶስት ጊዜ ቀየርኩለት᎓ ኬሪ መተኛቷን እንደቀጠለች ነው።
ነጋ።
ፀሐይዋ ወጣች፡ አያትየው የሽርሽር ቅርጫቱን ይዛ ስትገባ አሁንም ኮሪን
ዘግታ ቆለፈችና ቁልፉን ኪሷ ከታ ወደ ጠረጴዛው ተመለከተች። ከቅርጫቱ
ያሳመመው ምን እንደሆነ ለማወቅ እየሞከርን ነበር ቃል ሳትናገር በሩን
ውስጥ ወተት የያዘ ትልቅ ፔርሙዝ፣ ሾርባ ያለበት አነስ ያለ ፔርሙዝ፣
ሳንድዊቾች የያዘ የተጠቀለለ ወረቀት እና ሌሎቹንም አስቀመጠችና ለመውጣት ፊቷን አዞረች:
“አያቴ” አልኳት እያመነታሁ። ወደ ኮሪ አልተመለከተችም- አላየችውም:
“አላነጋገርኩሽም” አለች በቀዝቃዛ አነጋገር፡
“እስካነጋግርሽ ጠብቂ”
“መጠበቅ አልችልም” አልኩ ከተቀመጥኩበት የኮሪ አልጋ ጠርዝ ላይ
እየተነሳሁ እየተናደድኩ ነው “ኮሪ ታሟል! ሌሊቱን ሙሉ ሲያስመልሰው ነው ያደረው: ትናንትና ቀኑን ሙሉም እንደዚያው ዶክተርና እናቱን
ይፈልጋል።"
ወደ እኔም ሆነ ወደ ኮሪ አልተመለከተችም ከበሩ ወጣችና በሩን ቆለፈችው፡
ምንም አይነት የማፅናኛ ቃል አልተናገረችም: ለእናታችን እንደምትነግራትም
አልገለፀችም
በሩን ከፍቼ እናታችንን እፈልጋታለሁ:" አለ ክሪስ ትናንትና የለበሰውን
ልብስ እንደለበሰ ነበር። ስላልተኛ ልብሱን አልቀየረም
“ቁልፉ እንዳለን ያውቁብናል”
“ይወቁ!”
ልክ የዚህን ጊዜ በሩ ተከፍቶ እናታችን ገባች: አያትየው ከጀርባ አጅባት
ነበር። አብረው ወደ ኮሪ ተጠጉና የገረጣውን ቀዝቃዛ ፊቱን ዳስሰው አይን
ለአይን ተያዩ። ጥግ ላይ ሄደው በሹክሹክታ እየተነጋገሩ አሁንም አሁንም
ፀጥ ብሎ ወደተኛው የሞት አፋፍ ላይ ወዳለው ኮሪ ይመለከታሉ። ደረቱ
ብቻ ከፍና ዝቅ ይላል። ከጉሮሮው አየር ያጠረውና የታፈነ አይነት ድምፅ
ያወጣል ከቅንድቡ ላይ ላቡን ጠረግኩለት እንደዚያ ሰውነቱ ቀዝቅዞ እያዩ
ምን እንደሚያስቡ ይገርማል።
ኮሪ በፍጥነት ወደ ውስጥ፣ ወደውጪ… ወደ ውስጥ፣ ወደውጪ ይተነፍሳል።
እናታችን እዚህ አለች ግን ምንም አታደርግም መወሰን አልቻለችም! መኖር
የሌለባቸው ስለሆኑ አሁንም የሆነ ሰው ልጅ እንዳላት እንዳያውቅ ፈርታለች።
“ለምንድነው እዚያ ቆማችሁ የምትንሾካሾኩት?” ብዬ ጮህኩ። “ኮሪን ወደ
ሆስፒታል ወስዳችሁ የተገኘው ዶክተር ጋር ከማድረስ ሌላ ምን ምርጫ
አላችሁ?"
ሁለቱም አፈጠጡብኝ በተኮሳተረና በገረጣ ፊት እናታችን ሰማያዊ አይኖቿን
እኔ ላይ ተከለች፡ ከዚያ በሽብር ወደ ኮሪ አማተረች። አልጋው ላይ ያየችው
ነገር ከንፈሮቿ እንዲቀጠቀጡ፣ እጆቿ እንዲርበተበቱና ጡንቻዎቿ በሙሉ እንዲዝሉ አደረጋቸው እምባዋ እንዳይወርድ በሚመስል አይነት አይኖቿን
በተደጋጋሚ ታርገበግባለች:
እያንዳንዳቸውን የክህደት ምልክት የሆኑ በስሌት የተሰሩ ሀሳቦቿን በጠባቡ
ተመለከትኩ በኮሪ ልጇ መሆን መገለጥና ምድር ቤት ያለው ሽማግሌ አንድ
ቀን ሲሞት የምታጣው ውርስ መካከል እየመዘነች ነው መቼም አንድ ቀን
መሞቱ አይቀርም አይደል? ለዘለአለም አይኖርም:
ጮህኩኝ። “ምን ሆነሻል እማዬ? ትንሹ ልጅሽ እዚያ ተጋድሞ እየሞተ
አንቺ እዚያ ቆመሽ ስለራስሽና ስለምትወጂው ገንዘብ ታስቢያለሽ? ልትረጅው ይገባል! እሱ ላይ የሆነው ግድ አይሰጥሽም? እናቱ መሆንሽን ረስተሻል?
ካልረሳሽው እንደ እናት ሁኚ! ማመንታትሽን አቁሚና ትኩረት ስጪው! ነገ
ሳይሆን ዛሬ ያውም አሁኑኑ ትኩረት ያስፈልገዋል!”
የጭካኔ ቀለም ፊቷን አለበሰው አይኖቿን ወደ እኔ ዞር አደረገች። “አንቺ!”
ተናደደች። “ሁልጊዜም አንቺ ነሽ አለችና ቀለበት የተደረገበትን እጇን አንስታ
በሀይል በጥፊ አጮለችኝ! እንደገናም መታችኝ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ
ለዚያውም በእንደዚህ አይነት ምክንያት በጥፊ መታችኝ! በጣም ተናድጄ
ምንም ሳላስብ እኔም በጥፊ መታኋት... በኃይል!
አያትየው ቆማ እየተመለከተች ነው: በአስቀያሚው ስስ ከንፈሯ ላይ ግብዝ እርካታ ታየ። እናታችንን እንደገና ከመምታቴ በፊት ክሪስ ፈጥኖ እጄን ያዘኝ፡
ካቲ በዚህ አይነት ኮሪን አትረጂውም። ረጋ በይ: እናታችን ትክክለኛውን
ነገር ታደርጋለች” አለኝ።
የአባታችን ፊት አይኔ ላይ መጣ፡ ኮስተር ብሎ ለወለደችሽ ሴት ሁልጊዜ
ክብር ይኑርሽ ሲል በፀጥታ ነገረኝ፡ እንደዚያ እንደሚሰማው አውቃለሁ።
እንድመታት አይፈልግም
“ገሀነም ግቢ ኮሪን ፎክስወርዝ" እስከ መጨረሻው ጮህኩ። “ልጅሽን ሀኪም ቤት ካልወሰድሽ ገሀነም ግቢ! እኛ ላይ የምትፈልጊውን ነገር ማድረግ
እንደምትችይና ማንም እንደማያውቅ ታስቢያለሽ? ያንን የሚስጥር ብርድ
ልብስ መወርወር ትችያለሽ ግን የመበቀያ መንገድ አገኛለሁ አሁን የኮሪን
ህይወት ለማዳን ምንም ነገር ካላደረግሽ ህይወቴን በሙሉ ቢወስድብኝም እንኳን አስከፍልሻለሁ! በደንብ ትከፍያለሽ! ቀጥይ አይንሽን አፍጥጪብኝ አልቅሺ ለምኚ ስለገንዘብና ገንዘብ ስለሚገዛው ነገር ንገሪኝ ግን የምትይው ገንዘብ አንድ ጊዜ የሞተን ልጅ መልሶ መግዛት እንደማይችል እወቂ፡ አሁን አንድ ነገር ማድረግ ካልቻልሽ ወደ ባልሽ ሄጄ መጫወቻ ቦታቸው ጣሪያው ስር ያለው ክፍል የሆነ ለአመታት በተቆለፈ ክፍል ውስጥ ደብቀሽ ያስቀመጥሻቸው
አራት ልጆች እንዳሉሽ የምነግርበት መንገድ እንደማላገኝ ታስቢያለሽ? የዚያን ጊዜ ይወድሽ እንደሆነ ታያለሽ! የዚያን ጊዜ ፊቱን አይተሽ ለአንቺ ምን ያህል አክብሮትና አድናቆት እንደሚኖረው ጠብቂ: ተሸማቀቀች አይኖቿ ግን በሚገድል አይነት አስተያየት እየተመለከቱኝ ነው፡ “በተጨማሪ… ወደ ወንድ
አያትየው ሄጄ ለእሱም እነግረዋለሁ” የበለጠ ጮህኩ። “እና ሰባራ ሳንቲም አያወርስሽም:: ያ ሲሆን ደግሞ በጣም በጣም በጣም ደስ ይለኛል!”
ልትገለኝ ብትችል ደስ እንደሚላት ፊቷ ላይ ይታየኛል በሚገርም ሁኔታ
ያቺ የማትረባ አሮጊት ግን ረጋ ባለ መንገድ ተናገረች: “ልጅቷ ልክ ናት ኮሪን… ልጁ ሆስፒታል መሄድ አለበት!”
በዚያ ምሽት ተመልሰው መጡ፡ ሁለቱም ሠራተኞቹ ክፍላቸው ውስጥ ከተኙ
በኋላ መጡ አየሩ ድንገት ስለቀዘቀዘ በወፋፍራም ኮት ተጠቅልለዋል። የምሽቱ
ሰማይ ግራጫ ሆኗል። የክረምቱ መግቢያ ስለሆነ ይበርዳል በዛ ላይ በረዶ
ሊጥል ይመስላል። ሁለቱም ኮሪን ከእኔ ክንዶች ላይ ወስደው በአረንጓዴ
ብርድ ልብስ ጠቀለሉት። ያነሳችው እናታችን ነበረች። ኬሪ የጭንቀት ጩኸት
አሰማች። “ኮሪን አትውሰዱብኝ!" አለች። “አትውሰዱት… አትው...” አንድ ጊዜ እንኳን ተለይታው የማታውቀውን መንትያዋን ከመውሰድ እንዳስጥልላት
ራሷን ክንዶቼ ላይ ጥላ አምርራ አለቀሰች:
በዕንባ የራስ የገረጣ ፊቷ ላይ አተኩሬ “ኮሪ መሄዱ ጥሩ ነው" አልኳት።
ከእናታችን አይን ጋር ተጋጨን። “እኔም እሄዳለሁ ኮሪ ሆስፒታል ውስጥ
ሲሆን አብሬው እሆናለሁ። እኔ ካለሁ አይፈራም ነርሶቹ እሱን ለመጠበቅ ስራ ከበዛባቸው እኔ እዚያ እሆናለሁ። ያ ቶሎ እንዲሻለው ያደርገዋል። ኮሪ
እኔ ከእርሱ ጋር እንዳለሁ ሲያውቅ ጥሩ ይሰማዋል” አልኳት የተናገርኩት
እውነቴን ነበር፡ አሁን እሷን አይወዳትም፧ የሚፈልገው እኔን ነው: ልጆች
በተፈጥሮ አስተዋይ ናቸው: ማን በጣም እንደሚወዳቸውና ማን እያስመሰለ እንደሆነ ያውቃሉ።

👍19👏6😱1
'ካቲ ትክክል ናት እማዬ” አለ ክሪስ ያለምንም ስሜት ቀጥታ አይኖቹን
እየተመለከተ። “ኮሪ ካቲ ላይ ጥገኛ ነው: እባክሽ እንድትሄድ ፍቀጂ
እንዳለችው የሷ ከዛ መገኘት ቶሎ እንዲሻለው ያደርጋል በዚያ ላይ ከአንቺ
በተሻለ የበሽታውን ምልክቶች ለዶክተሩ በደንብ መግለፅ ትችላለች፡"
የእናታችን ባዶ ፍጥጫ ወደ እሱ ዞረ:: ልክ ምን ማለት እንደፈለገ ለመያዝ
የምትታገል ይመስል ነበር፡ የተምታታባት ትመስላለች… አይኖቿ ከኔ ወደ ክሪስ ከዚያ ወደ እናቷ ከዚያ ወደ ኬሪ ዘለሉና ተመልሰው ወደ ኮሪ መጡ።.....
✨ይቀጥላል✨

❤26👍18
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...የእናታችን ባዶ ፍጥጫ ወደ እሱ ዞረ:: ልክ ምን ማለት እንደፈለገ ለመያዝ የምትታገል ይመስል ነበር፡ የተምታታባት ትመስላለች… አይኖቿ ከኔ ወደ ክሪስ ከዚያ ወደ እናቷ ከዚያ ወደ ኬሪ ዘለሉና ተመልሰው ወደ ኮሪ መጡ።
“እማዬ” አለ ክሪስ ጥንክር አድርጎ፡ ካቲ አብራሽ ትሂድ ለኬሪ እኔ አለሁ
ምናልባት ያስጨነቀሽ ያ ከሆነ።"
እንድሄድ አልፈቀዱልኝም።
እናታችን ኮሪን ይዛ ወደ አዳራሹ ወጡ አያትየው ባገኘሁት ድል የጭካኔ
ፈገግታ ሰጥታኝ በሩን ቆለፈችው ኬሪ ወንድሟን በማጣቷ እየጮኸችና እምባዋ እየወረደ ትተዋት ሄዱ። ትንንሽ ደካማ ቡጢዎቿ ጥፋተኛዋ እኔ የሆንኩ ይመስል እኔ ላይ አረፉ፡ ካቲ እኔም
መሄድ እፈልጋለሁ! እንድሄድ እንዲፈቅዱልኝ አድርጊ! ኮሪ እኔ የማልሄድበት ቦታ መሄድ አይፈልግም... ጊታሩን ደግሞ ረስቶታል” አለች።
ከዚያ ቁጣዋ ሁሉ ሲበርድላት፣ ክንዶቼ ላይ ሆና ተንሰቀሰቀች: “ለምን ካቲ? ለምን?”
“ለምን?”
በህይወታችን ትልቁ ጥያቄ ነው።
በህይወታችን ከነበሩት አስቀያሚውና ረጅሙ ቀን ነበር። ኃጢአት ሰርተናል
እና እግዚአብሔር እንዴት በዚህ ፍጥነት ቅጣት ላከብን? ፈጠነም ዘገየም
አያትየው እንዳወቀችው ሁሉ ራሳችን ዋጋ ቢስ መሆናችንን እንደምናረጋግጥ
ያወቀ ይመስል፣ አይኖቹ እኛ ላይ ነበሩ ማለት ነው።
ቲቪ መጥቶ የቀኖቻችንን የተሻለ ክፍል ከመውሰዱ በፊት እንደነበረው እንደ
መጀመሪያው ቀን ቀኑን ሙሉ ቴሌቪዥን እንኳን ሳንከፍት በፀጥታ ቁጭ
ብለን ኮሪ እንዴት እንደሆነ ለመስማት እየጠበቅን ነው።
ክሪስ በሚወዛወዘው ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔና ኬሪ ጭኖቹ ላይ ተቀምጠን
በቀስታ ወደፊት ወደኋላ፣ ወደፊት ወደኋላ እየተወዛወዝን ነው።
ለረጅም ጊዜ ጭኖቹ ላይ ስንቀመጥበት የክሪስ እግሮች ለምን እንደማይደነዝዙ
አላውቅም ምግባችንን ለማሰናዳት ተነሳሁ። ጭራሽ አልነካነውም: የቀኑ
የመጨረሻ ምግብ ሲያበቃና ሳህኖቹ ታጥበው ከተቀመጡ በኋላ እኛም ገላችንን ተጣጥበን ለመተኛት ተዘጋጀን፡ ኮሪ አልጋ አጠገብ በመደዳ ተንበርክከን ፀሎታችንን አቀረብን “እባክህ፣ እባክህ ኮሪ እንዲሻለውና ወደ እኛ እንዲመለስ አድርግ አልን ሌላ ነገር ፀልየንም ከነበረ ምን እንደነበረ አላስታውስም ተኛን ወይም ለመተኛት ሞከርን ኬሪን በእኔና በክሪስ መካከል አድርገን ሶስታችንም አንድ አልጋ ላይ ተኛን በሁለታችን መካከል ድጋሚ ምንም
ነገር አይፈጠርም መቼም... መቼም እንደገና አይፈጠርም እግዚአብሔር
እኔና ክሪስን ለመጉዳት ብለህ ኮሪን አትቅጣው አስቀድመን ተጎድተናል
ልናደርገው ፈልገን አልነበረም ጌታ ሆይ አልነበረም በአጋጣሚ ነው
የሆነው ለዚያውም አንድ ጊዜ ብቻ በዚያ ላይ ምንም ደስታ አልነበረበትም።
እግዚአብሔር ሆይ በእውነት በእውነት ደስታ አልነበረበትም
አዲስ ቀን ነጋ ከመጋረጃዎቹ ጀርባ ውጪ ለሚኖሩት በእኛ ለማይታዩት
ህይወት ተጀመረ። ራሳችንን ዘና ለማድረግ፣ ሰዓታችንን ለመሙላትና ለመብላት ሞከርን ክሪስ እየረዳኝ የፍራሹን ልብስ ቀየርኩ ምክንያቱም በጣም ከባባድ በመሆናቸው ብቻዬን ላገባቸው አልችልም፡ በዚያ ላይ ኮሪ በአብዛኛው ሽንቱን ስለሚሸና በየጊዜው መቀየር ነበረበት፡ ክሪስና እኔ አልጋውን አንጥፈን ክፍሉን አፀዳድተን ጨርሰን ኬሪ የሚወዛወዘው ወንበር
ላይ ብቻዋን ተቀምጣ ባዶ አየር ላይ አፍጥጣለች።
አራት ስዓት ገደማ የምንሰራውን ሁሉ ጨርሰን ወደ አዳራሹ ቀረብ ወደሚለው አልጋ ላይ ተቀምጠን በሩ እጀታ ላይ አይኖቻችንን ተክለን ዜናውን ይዛልን የምትመጣልንን እናታችንን እንዲያስገባ እየጠበቅን ነው።
ጥቂት ቆይቶ እናታችን ከማልቀስ ብዛት አይኖቿ ቀልተው መጣች። ከእሷ
ጋር ባለብረት አይኗ አያታችን ረጅም፣ ድርቅ ያለችና እምባ የሌላት ሆና ተከትላታለች።
እናታችን እግሮቿ መቆም አቅቷቸው ወለሉ ላይ እንዳይጥሏት የፈራች
ይመስል በሩን ተደገፈች እኔና ክሪስ ከተቀመጥንበት ዘለን ተነስተን ቆምን፡
ኬሪ ግን እናታችን ባዶ አይን ላይ እንዳፈጠጠች ነው: “ኮሪን በመኪና ወደ
ሆስፒታል እየወሰድኩት ነበር ቅርብ ወዳለው ሆስፒታል ነበር በእውነት"
አለች እናታችን ውጥረት በተሞላበት ሻካራና አሁንም አሁንም እንቅ እንቅ
በሚል ድምፅ፡ “እና የወንድሜ ልጅ ነው ብዬ በውሸት አስመዘገብኩት"
“ውሸት! እማዬ ሁልጊዜ ውሸት እንዴት ነው?” ትዕግስት ባጣ ሁኔታ ጠየቅኳት። ሰማያዊ አይኖቿ ወደ እኛ ዞሩ፡፡ ባዶ ነገር ላይ ያፈጠጡ፣ የጠፋ፣የሆነ ለዘለአለም የጠፋ ነገር የሚፈልጉ አይኖች ሰብአዊነቷ እየፈለጉ
እንደሆነ ገምቻለሁ። “ኮሪ የያዘው የሳምባ ምች ነበር። ዶክተሮቹ የቻሉትን ሁሉ
አድርገው ነበር . . .ግን በጣም በጣም . . . በጣም ዘግይቶ ነበር”
“የሳምባ ምች ነበር?"
“የሚችሉትን አድርገው ነበር?”
“ዘግይቶ ነበር?”
“ነበር… ነበር!
ኮሪ ሞቷል እንደገና አናየውም!
ዜናው ክሪስን ልክ ወንድነቱ ላይ የተመታ አይነት ስሜት ነበር የፈጠረበት
እንደተረገጠ አይነት፡ ወደ ኋላ ተንጋሎና ፊቱን ለመደበቅ ዞሮ ትከሻዎቹ
እየተርገፈገፉ ሲንሰቀሰቅ አይቼዋለሁ።
በመጀመሪያ አላመንኳትም ነበር። ቆምኩ፣ አፈጠጥኩ፣ ተጠራጠርኩ፣ ፊቷ አሳመነኝ እና ልቤ ውስጥ የሆነ ትልቅና ባዶ ቦታ ሲሰፋ ተሰማኝ። ደንዝዤና
ሽባ ሆኜ አልጋው ላይ ወደቅኩ። ልብሶቼ ረጥበው እስክመለከት ድረስ
እያለቀስኩ እንደነበረ አላወቅኩም ነበር
ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ቢሆንም ኮሪ ከህይወታችን ወጥቶ መሄዱን ማመን
አልፈለግኩም ደግሞ ኬሪ፣ ምስኪን ኬሪ ጭንቅላቷን ቀና አደረገች። ወደ
ኋላ ወረወረችና አፏን ከፍታ እሪ... አለች።
ድምፅዋ ተዘግቶ መጮህ እስከማትችል ድረስ ጮኸች: ኮሪ ጊታሩን
ወደሚያስቀምጥበትና ትንንሽ ያለቁ የቴኒስ ጫማዎቹን ወደደረደረችበት
ጥግ ሄደች። መቀመጥ የፈለገችው እዚያ ከጫማዎቹና ከሙዚቃ መሳሪያው ጋር ነበር እና ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ አንዲት ቃል እንኳን ከከንፈሮቿ አልወጣም::
“ወደቀብሩ እንሄዳለን?” ክሪስ ጀርባውን እንዳዞረ ጠየቀ።
“ተቀብሯል” አለች እናታችን፡ “በመቃብሩ ላይ የውሸት ስም አፅፌያለሁ"አለችና ከጥያቄዎቻችንና ከክፍሉ ለማምለጥ በጣም በፍጥነት ወጣች
አያትየውም ተከተለቻት፡
በፈሩት አይኖቻችን ፊት ኬሪ በእያንዳንዱ ቀን የበለጠ እየጠወለገች ነው
እግዚአብሔር ኬሪንም ሊወስዳት እንደሚችል እና ሩቅ ቦታ ባለ የመቃብር
ስፍራ በሀሰት ስም ከኮሪ አጠገብ በቅርብ ርቀት የተቀበረ አባት እንኳን
በሌለበት እንደምትቀበር ተሰማኝ።
ማንኛችንም ብዙ መብላት አልቻልንም:: ፈዛዛና የደከመን ሁልጊዜ የደከመን
ሆነናል፡ ምንም ነገር ፍላጎታችንን አያነሳሳውም: ዕንባ ብቻ። ክሪስና እኔ
ውቅያኖስ የሚሞላ ያህል አለቀስን ወቀሳውን ሁሉ የእኛ አደረግነው: ከብዙ
ጊዜያት በፊት ማምለጥ ይገባን ነበር፡ ያንን የእንጨት ቁልፍ ተጠቅመን
ወጥተን እርዳታ መፈለግ እንችል ነበር። ኮሪ እንዲሞት አድርገናል: የእኛ
ሀላፊነት ነበር! ትንሹ ባለ ብዙ ተሰጥኦውና ፀጥተኛው ውድ ልጃችን እንዲሞት አደረግን አሁን ደግሞ ጥግ ላይ ተኮራምታ የምትቀመጥ በየቀኑ እየደከመች የምትሄድ ታናሽ እህት አለችን፡
ክሪስ ኬሪ እንዳትሰማ
ቀስ ባለ ድምፅ “ማምለጥ አለብን ካቲ! በፍጥነት።
አለዚያ ሁላችንም እንደ ኮሪ እንሞታለን፡ ሁላችንም የሆነ ነገር ሆነናል።ለረጅም ጊዜ ተዘግቶብናል፡ የምንኖረው ትክክለኛ ያልሆነ ህይወት ነው፡ ልክ ጀርሞች በሌሉበት አየር አልባ ቦታ እንደመኖር ነው።

👍46😢6❤3👎1🥰1
“በተለምዶ ልጆች የሚይዛቸው አይነት ኢንፌክሽኖች የሌሉበት ነው
የምንኖረው ስለዚህ እኛ ለኢንፌክሽን ምንም መከላከያ የሌለን ነን፡” አለ፡
“አልገባኝም” አልኩ።
“ማለቴ” አለ አንድ ወንበር ላይ እንደተቀመጥን በሹክሹክታ። “ልክ 'የአለማት ጦርነት' የሚለው መፅሀፍ ውስጥ እንዳሉት ከማርስ የመጡ ፍጡራን በአንድ የብርድ ጀርም ምክንያት ሁላችንም ልንሞት እንችላለን፡”
በፍርሃት እሱ ላይ ማፍጠጥ ብቻ ነው የቻልኩት እኔ ከማውቀው በላይ
ብዙ ነገሮች ያውቃል፡ እይታዬን ጥግ ላይ ወደ ተቀመጠችው ኬሪ መለስኩ።በሚያምር የልጅነት ፊቷ ላይ አይኖቿ ትላልቅ ሆነውና ከስራቸው ጠቁረው ባዶ ነገር ላይ አፍጥጣለች: ኮሪ ያለበት ዘለአለም ላይ ያተኮረ የራሷ እይታ እንዳላት አውቃለሁ ለኮሪ የሰጠሁትን ፍቅር ሁሉ አሁን ኬሪ ውስጥ
አድርጌያለሁ... ለሷ ፈርቼላታለሁ አካሏ ትንሽዬ አጥንት ብቻ ነው አንገቷ
ጭንቅላቷን መሸከም የሚችል አይመስልም የሁላችንም መጨረሻ በዚህ
መንገድ ይሆን?
ክሪስ. የምንሞት ቢሆንም እንኳን በወጥመድ እንደተያዘ አይጥ ሆነን
መሞት የለብንም: ጀርሞች ሊገድሉን ከቻሉ ይግደሉን ስለዚህ ዛሬ ማታ ትሰርቃለህ። ዋጋ ያለውና ልንይዘው የምንችለውን የትኛውንም ነገር ውሰድ!
ይዘን የምንሄደው ምሳ እቋጥራለሁ ከሻንጣው ውስጥ የኮሪን ልብሶች ስናወጣ በቂ ቦታ ይኖረናል ከመንጋቱ በፊት እንሄዳለን፡” አልኩት “አይሆንም!” አለ
በቀስታ: “ገንዘቡን ሁሉ ወስደን መሄድ የምንችለው ጌጣጌጦቹንም የምናገኘው
እናታችንና ባሏ ምሽቱን ከወጡ ብቻ ነው: በጣም የምንፈልጋቸውን ነገሮች
ብቻ ነው የምንወስደው ምንም አይነት አሻንጉሊት፣ መጫወቻ አንይዝም:
ችግሩ ግን ካቲ እናታችን ዛሬ አትወጣም ይሆናል በእርግጠኝነት በሀዘኗ
ወቅት የትኛውም ግብዣ ላይ አትገኝም:"
ባሏን ሁልጊዜ ጭለማ ውስጥ አስቀምጣ እንዴት ልታዝን ትችላለች? ምን
እንደተፈጠረ ለእኛ ለመንገር ከአያትየው በስተቀር ማንም አልመጣም: እኛን ለማነጋገርም ሆነ ለማየት አትፈልግም:: በጭንቅላቴ ውስጥ መንገድ ጀምረናል እና እሷን የማያት የድሮ ህይወታችን አንድ ክፍል እንደነበረች ብቻ አድርጌ ነው: የመለያያ ጊዜያችን በጣም ስለቀረበ ፍርሀት ተሰማኝ::ውጪው በጣም ትልቅ ነው: በራሳችን ነው የምንሆነው… አሁን አለም ስለኛ ምን ያስባል?
በፊት እንደነበርነው ያህል ቆንጆ አይደለንም: ረጅም ወደ ቢጫ የሚወስደው
ቀለም ያለው ፀጉር ያለን የጣራ ስር አይጦች… ውድ ግን በልካችን ያልሆኑ
ልብሶች ለብሰን እግሮቻችን ላይም ስኒከሮች አጥልቀናል።
እኔና ክሪስ ብዙ መፃህፍት በማንበብ ራሳችንን አስተምረናል። ነገር ግን እውነታውን ለመጋፈጥ የሚያስችል ጠቃሚና ተግባራዊ ነገር አልሰጠንም።
መዳን፡፡ ቴሌቭዥን ምንም የማያውቁ ልጆችን የሚያስተምራቸው ይህንን
ነው፡ ስለራሳቸው ብቻ እንጂ ስለማንም ሳይጨነቁ አንዳንዴ ስለራሳቸውም
ሳይጨነቁ አለም ላይ እንዴት እንደሚኖሩ ያስተምራል።
ገንዘብ፡፡ በእስር ዘመናችን የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር ገንዘብ መጀመሪያ
ላይ የሚመጣና ሌሎች ነገሮች ሁሉ ከእሱ በኋላ መሆናቸውን ነው᎓ እናታችን
ከብዙ ጊዜያት በፊት ተናግራው ነበር “አለምን የሚያሽከረክራት ገንዘብ እንጅ ፍቅር አይደለም”
የኮሪን ትንንሽ ልብሶች፣ በሁለተኛ ደረጃ የሚወደው ጫማውን፣ሁለት ጥንድ ፒጃማዎችን ከሻንጣው ውስጥ አወጣሁ፡ እናም ሁሉንም ጊዜ
እምባዬ እየረገፈና አፍንጫዬም እየረጠበ ነበር በሻንጣው የጎን ኪስ ውስጥ ያስቀመጠውን ሙዚቃ የተፃፈበት ወረቀት አገኘሁ። ማስመሪያ በመጠቀም ያሰመራቸውን መስመሮች፣ የፃፋቸውን ትናንሽ ጥቋቁር የሙዚቃ ኖቶች,ማየት በጣም ያሳዝናል።
ኮሪን በአእምሮዬ ውስጥ እንደያዝኩ ወደ መኝታ ሄድኩ። እንደ ሁልጊዜው
በጣም ስጨነቅ ህልም አየሁ በዚህ ጊዜ ግን እኔ ብቻ ነበርኩ፡ ራሴን ንፋስ
በበዛበት ዳርና ዳሩ የዱር አበቦች በበቀሉበትና በቀኝ በኩል ደግሞ ቢጫና
ነጭ የፈኩ አበቦች በለስላሳና ሞቃት የፀደይ ንፋስ ሲወዛወዙ ያሉበት ሰፊ
መንገድ ላይ አገኘሁት በእጄ ትንሽ ልጅ ይዣለሁ፡ ኬሪን ለማየት በመጠበቅ
አጎንብሼ ስመለከት ኮሪ ነው።
ሳቂታና ደስተኛ ነበር ከጎኔ ዘለል ዘለል እያለ በትንንሽ እግሮቹ ከእኔ ጋር እኩል ለመራመድ እየሞከረ ነበር፡ በእጁ እቅፍ አበቦች ይዟል ወደ እኔ እያየ ፈገግ አለና ሊናገር ሲል በጣም ብዙ ብሩህ ቀለማት ያላቸው ወፎች ከፊት ባሉ የጥላ ዛፎች ላይ ሆነው ሲንጫጩ ሰማን።
ወርቃማ ፀጉር ያለው፣ ቆዳው በፀሀይ የጠየመ፣ ነጭ የቴኒስ ልብሶች የለበሰ
ረጅም ቀጭን ሰውዬ ብዙ ዛፎች እንዲሁም የተለያዩ ቀለማት ያላቸውን
ፅጌረዳዎች ጨምሮ የሚያማምሩ አበቦች ካሉበት ባለ ግርማ የአትክልት ስፍራ
ወጥቶ በቀጥታ መጣ፡ ከእኛ ራቅ ብሎ ቆመና ለኮሪ ክንዶቹን ዘረጋለት።
ልቤ በህልሜ እንኳን በአድናቆትና በሀሴት ይደልቅ ነበር! አባታችን ነበር! ኮሪ የቀረውን መንገድ ብቻውን እንዳይሄድ አባታችን ሊያገኘው መጣ የኮሪን ትንሽዬ ሞቃት እጅ መልቀቅ እንደሚገባኝ ባውቅም ለዘለአለም ከእኔ ጋር ልይዘው ፈለግኩ።
አባታችን ወደኔ ተመለከተ በሀዘን ወይም በወቀሳ ሳይሆን በኩራትና
በአድናቆት ነበር። ከዚያ የኮሪን እጅ ለቅቄ በደስታ እየቦረቀ ወደ አባታችን
እቅፍ ሲገባ ቆሜ በደስታ ተመለከትኩት በአንድ ወቅት ሲይዙኝ አለም ሁሉ
በጣም ድንቅ እንደሆነ እንዲሰማኝ የሚያደርጉ ወደ ነበሩት ጠንካራ ክንዶች
ገባ፡ እኔም ወደ መንገዱ ገብቼ እነዚያን ክንዶች በድጋሚ አገኘኋቸውና አባቴ
የፈለገበት እንዲወስደኝ ፈቀድኩለት።
“ካቲ፣ ተነሺ!” አለኝ፡ ክሪስ አልጋው ላይ ተቀምጦ እየነቀነቀኝ ነው: “በእንቅልፍ
ልብሽ እያወራሽ ነበር፡ ትስቂያለሽ… ታለቅሺያለሽ ሰላም ትያለሽ ደህና ሁኑ
ትያለሽ ለምንድነው በጣም ህልም የምታይው?" እየፈጠንኩ ስናገር ቃላቶቼ
ተዛቡ ክሪስ ለማዳመጥ እንደነቃችው ኬሪ ተቀምጦ በትኩረት ይመለከተኝ
ነበር አባታችንን ለመጨረሻ ጊዜ ካየሁት ቆይቼ ነበር፡ ፊቱ ከአእምሮዬ
ውስጥ ደብዝዞ ነበር ክሪስን ስመለከተው ግን ግራ ተጋባሁ ወጣት ከመሆኑ
በስተቀር እጅግ በጣም አባታችንን ይመስላል።
ያ ህልም በቀን ብዙ ጊዜ ከሀሳቤ ውስጥ ተመላለሰ ደስ በሚል አይነት። ሰላም
ሰጠኝ፡ ከዚህ በፊት ያልነበረኝን እውቀት ሰጠኝ፡ ሰዎች ለካ አይሞቱም::
የሚወዷቸው ሰዎች መጥተው እስኪያገኟቸው ለጥቂት ጊዜ ሊጠብቁ ወደተሻለ ቦታ ነው የሚሄዱት ከዚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጡበት በተመሳሳይ መንገድ እንደገና ተመልሰው ወደ አለም ይመጣሉ፡....

👍29😢21❤5🥰2
✍✍የጠንቋዩ ዋሻ✍✍
♣♣♣ክፍል 2♣♣♣
❖✿❖✿❖✿❖✿❖✿
☞☞☞
"አባቴ ሆይ መጥቻለው ፡ ባሪያህ ሁሉ ባንተ ፍቃድ "አለ ያልታወቀው ሰው ፡ ከዋሻው ፡ውስጥ ፡ከምትገኘው ፡ እንደቤት ፡ተስተካክላ የተሰራች ፡ አንዲት ክፍል ፡ ጋር ፡ ከወገቡ እንደ ማጎንበስ ፡ብሎ ፡ ከጥቂት ፡ ማጓራት በዋላ ፀጥታ ሰፈነ ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ ወደሦስቱ ጎረምሶች ፡በመዞር ፡ማስጠንቀቃያ ሰጣቸው ፡ እዚ ዋሻ ውስጥ ፡ አቢያራ ፡ካልፈቀደ በስተቀር ፡ማንም፡ ድምፅ አያወጣም ፡አለበለዚያ ትቀሰፋላቹ ፡ አላቸው ፡ በሹክሹክታ ፡ ሦስቱም ፡ፍርሃታቸው ፡ጨመረ ፡ ነገርግን ፡ሦስቱም ፡በልባቸው ፡የፈጣሪያቸውን ፡ስም ፡ደጋግመው መጥራታቸውን ፡አልተውም ፡ አይናቸውን ፡እንደታሰሩ በመሆናቸው ፡ አካባቢውን ፡እስካሁን ፡አላዩትም ፡ሲገምቱ ግን ፡አስፈሪ መሆኑን ፡አውቀዋል ፡ ከቆይታ በዋላ ፡ ሲጢጢጢ የሚል ድምፅ ሰሙ ፡ እናም ፡ከውስጥ በኩል ፡የሚያስገመግምና ውፍረቱ ደሚከብድ ፡ድምፅ ፡" ግቡ ግልገሎቼ የጨለማው ፡ጌታ የቀዩ ቤት ፡አይል ፡ በናንተ ዙሪያ ነው "አለ ፡
"አሚን አባቴ ጠባቂዬ "አለ ያልታወቀው ፡ሰው ፡፡ ሦስቱም ፡ ፈጣሪያችን ፡ሆይ ፡ከዚ ጉድ ፡አውጣን ፡ እባክህ ፡ አሉ ፡
" ግለጣቸው ፡አይኖቻቸው ፡ውስጥ ፡ማየት ፡እፈልጋለው ፡ ኤዛ በሰአን ውሃ አፍልተሽ ይዘሽ ፡ነይ "አለ አስፈሪው ፡ድምፅ
"እሺ ጌታዬ "አለቺ አንዲት ሴት ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ጠጋብሎ ፡አይኖቻቸውን ፡ያሰረበትን ቀይ፡ጨርቅ ፡ ከሦስቱም ጎረምሶች ላይ ተራ በተራ ፈታ ፡ ጎረምሶቹ በዙሪያቸው ፡ባዩት ፡ነገር ፡ተርበተበቱ ፡ ሳያስቡት ፡በፍርሃት ፡ተጠጋጉ ፡ በመጀመሪያ ፡አይናቸው ፡ያረፈው ፡የፊቱ ገፅታ ሙሉ በሙሉ የማይታይ ፡ አንድ አንድ አስፈሪ ሰው ላይ ፡ነው ፡ እረጅም ፡ሰፊና ዝርክርክ ፡ያለ ጥቁር ፡ቀሚስ ፡ለብሷል ፡ በእጁ ቀይ ፡የተቀባ ፡ከዘራ ይዛል ፡ እረዘም ፡ያለው ፡ፀጉሩ ፡ሙሉ በሙሉ ሸብቷል ፡ የሚያስፈራ ፡ ግርማ ሞገስ ፡ነው ፡ያለው ፡ በክፍሉ ውስጥ ፡ ፀጥታ ቢሰፍንም ፡ ሰዎች ግን ፡ነበሩ ፡ አንዲት ሴት ፡በትልቅ ፡ረኮቦት ፡ብዙ ሲኒዎች ፡ደርድራ ፡ ትልቅ ፡ጀበና ፡ ይዛ ፡ ቡና እየቀዳች ፡ነበር ፡ በጣም ፡ታዳጊ የምትባል አይነት ፡ናት ፡ የለበሰችው ፡ቀይ ፡ቀሚስ ፡ ለእይታ ይከብዳል ፡ ሌሎች ፡ ሁለት ሴቶችም ፡ነበሩ አንድ ፡ጥግ ይዘው ፡ የተቀመጡ ፡ ቆንጆናቸው ፡ ረዘም ፡እረዘ ያሉ መሆናቸው ያስታውቃል ፡ እነሱም ፡ ቀይ የበዛበት ፡ልብስ ፡ለብሰዋል ፡ ዋሻው ፡ደሞ ፡በቀያይ ፡ጨርቅ ፡ዳበደ ነው ፡ አንድ ፡ጥግ ላይ ትልቅ ፡መጋረጃ ይታያል ፡ ቀይ፡ ነው ፡እሱም ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ አንድኛውን ጎረምሳ በመግፋት ፡ከጠንቋዩ አቢያራ አጠገብ ፡ አቆመው ፡ ልጁ ተንቀጠቀጠ፡ እዚ በቀይ ፡ጨርቅ ፡ያበደ ዋሻውስጥ ፡ቀይ ደሙ መሬቱን ሲያርሰው ፡ታየው ፡በቃ መስዋት ልንሆን ፡ነው ብሎ ፡አሰበ፡
" እራስህን አስተዋውቅ ፡ በርግጥ ፡ማነትህን ፡ጠንቅቄ አውቀዋለው ፡ ነገርግን ካንተም መስማት እፈልጋለው ፡ አንተ ውርንጭላ ኦሆሆሆይ አቢያራ "ብሎ ጮህ አለ ጠንቋዩ
"መመስፍን መስፍን ደስታ ፡ የእናቴ ስም ስምረት ፡የምኖረው ፡አብነት አዲሳባ ፡ አንዲት ታናሽ ፡እህት ፡አለችኝ ፡ሜሮን ፡ትባላለች ፡ የየ አስረኛ ክፍል ተተማሪ ነኝ ፡ ውጤት ፡ስላልመጣልኝ ፡ሰፈር ፡ነው ፡የምውለው ፡ እናቴ በምትሰጠኝ ፡ገንዘብ ፡አልፎ ፡አልፎ ፡ከገደኞቼ ጋር ፡እየወጣው ፡እዝ ,,,,,,,"
"በቃ ትርኪምርኪ ወሬህን ፡መስማት አልፈልግም ፡ እዛ መደብ ላይ ተቀመጥ ፡"አለ ጠንቋዩ ፡ የተሰላቸ ነው የሚመስለው ፡
"ቀጥል አንተ ቶሎ በል "አለ ያልታወቀው ፡ሰው
"እኔ ዳንኤል አሰፋ እና እእ,,,,,,"ብሎ ሁለተኛው ፡ጎረምሳ ሊቀጥል ሲል፡ እንዲቀመጥ ፡ምልክት ፡ተሰጠው ፡ሄዶ ፡ከጓደኛው ፡መስፍን ፡አጠገብ ፡ጥምልምል ፡ብሎ ፡ተቀመጠ
"አንተ ቶሎ ፡ስምህን ፡ተናገር "አለው ያልታወቀው ሰው
"መሳይ አበራ ፡ከ ,,,,,,,,"
"ቁጭ በል ፡ "ተባለ ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ምን ላድርጋቸው ፡በሚል ፡አስተያየት ፡ጠንቋዩን ፡ተመለከተው ፡ ጠንቋዩ ፡ ጸደ ቡናው ፡አየ ፡ የሆነ ነገር እያሰበ ይመስላል ,,,,, ,,
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል....

👍36
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ቀኑ ሰኞ ማታ ነው አየሩ ለሰስ ብሏል " ጨረቃ ፍንትው ብላ ወጥታለች "
እንዳይታይ ሠግቶ አንገቱን ደፍቶ ተገን እየመረጠ በእግሩ ከሚጓዘው ብቸኛ የሩቅ መንገደኛ ላይ የሚያበሩት ከዋክብትም ጥርት ብለው ደምቀዋል " ሰውየው የሥራ ካፖርቱን ለብሶ ሶሉ ምስማር የተጠቀጠቀበት ጫማ አድርጎ የጉልበት ሠራተኛ
ይመስላል " ረጅምና ጥቁር ሪዙ ታችኛውን ፊቱን ሲሸፍነው ክፈፈ ሰፊው ባርኔጣው ደግሞ ግንባሩን ዐልፎ ወርዷል " ወደ ሚስተር ሔር ቤት ተጠግቶ ግራና ቀኙን ደኅና አድርጎ ተመልክቶ በአጥር ተንጠልጥሎ ገብቶ ወደ አትክልቱ ቦታ መጣና ዛፎቹ መኻል ተጠግቶ ቆመ።
ሚስተር ሔር እቤት እንግዶች ካልመጡበት በቀር በዓመት ሁለት ቀን
እንኳን አድርጎት የማያውቅውን የዚያን ቀን ከቤቱ አምሽቷል ባርባራ የወንድሟን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአባቷ ከቤት ማምሸት በጣም አስጨንቋታል ካሁን አሁን በመጣ እያለች ስትመኝ እሱ ወንበሩን ወደ መስኮቱ አስጠግቶ ረጂም ፒፓውን ካፉ ሰክቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን ወደ አንድ በኩል
ገደድ አድርጎ በአትክልት ቦታውና በዐፀዱ ሙሉ ትይዩ ተቀምጦ ይመለከታል
“ ዛሬ አትወጣም እንዴ . . . ሪቻርድ '' አለችው ሚስዝ ሔር ፈራ ተባ እያለች
አልወጣም "
“ እማማ . . .የመስኮቱን መከለያዎች ላስዘጋቸው ? አለች ባርባራ "
“ ይዘጉ ?” ብሎ አጉረመረመ " “ ማነው ይህች ጨረቃ እያለች የሚዘጋው የኛ ቆንጆ ብትፈልጊ ፋኖሱ ከዚያ ጥግ አለልሽ ከዚያው ሔዶሽ ተቀመጭ ”
አባትው እንደዚያ በሚመለከትበት ጊዜ ሪቻርድ በድኑንም ይዘልቅና ያየው እንደሆን ብላ በጣም ሠጋች እንደ ፈራችው ምልክቱ መጣ ሲንቀሳቀስ ታያት "ባርባራ ተጨነቀች ነጭ ዐመዷ ቡን አለ » ከንፈሯ ደረቀ ።
አቤት በጣም ምቀኝ ! እኔስ በአትልቱ ቦታ ትንሽ ነፋስ ተቀብዬ ልምጣ መሰለኝ " አለች የመውጫ ምክንያት ፈልጋ "
ጠቆር ባለው የሐር ቀሚሷ ላይ ጠቆር ያለ መደረቢያ ጣል አድርጋ ሹልክ ብላ ወጣችና አባቷ አስተውሎ እንዳይመለከታት እየተጠነቀቀች ሪቻርድን ወዳየችበት ቦታ ሔዳ ተግናኙ ፊቱ ነጥቶ ከስቶ ስታየው በጣም አዘነች " ጸጉሩም እንዳለ
ሸበት መሆኑን ነገራት "
ሪቻርድ አሁን አላነጋግርህም " ዛሬ አባባ ያለ ወትሮው ከቤት አምሽቷል ስለዚሀ ነገ ማታ ተመለስ ”
ለሁለተኛ ምሽት ወደዚህ መምጣት ደስ አይለኝም ... ባርባራ የዚ አካባቢ ምድር በእያንዳንዱ ስንዝር ርቀት አደጋ አለበት
“መቆየትማ አለብህ ...
ሪቻርድ ! ያ ይህን ሁሉ ተንኮል የፈጸመው ቶርን
ዌስት ሊን መጥቷል” እሱ ሆነም አልሆነም ቶርን የሚባል ሰው እዚህ ይገኛል
እኔና ሚስተር ካርላይል
እሱ መሆኑን አምነንበታል
አንተም እንድታየው
እንፈልጋለን እንዴት አይተህ ልታረጋግጥ እንደምትችል ግን ሚስተር ካርላይል
ይነግረናል" ምንም እንኳን ሰውየው አንተ የምትለው ቶርን መሆኑ ስለ ተረጋገጠ
ብቻ አንተን ነፃ ለማድረግ በችኮላ የሚፈጸም ባይሆንም አንድ ትልቅ ነጥብ አጣርቶ መጠበቅም ቀላል ነገር አይደለም ግን አትረሳውም ? እንደምታውቀው እርግጠኛ ነኝ ትጠራጠራለህ?"
“አባቴን አላውቀውማ ! አንቺ አሁን ትጠፊኛለሻ ! አሱንም እንደዚሁ
እይው i ግን እንዴትና መቸ ነው ላየው የምችል ... ባርባራ ?
ሚስተር ካርላይልን እስክጠይቀው ድረስ ልነግርህ አልችልም አንተ ነገ
ማታ በጣም ሳይመሽብሀ እንደ ተመቸህ እዚሀ ድረስ እንድትመጣ " አባባም ከቤት አይኖርም ምናልባት.."
ነጎድጓድ የመሰለው የጀስቲስ ሔር ድምፅ በመስኮቱ አስተጋባ „ “
ባርባራ ብርድ እንዲመታሽ ነው እዚያ የምትንከለከይው አሁን ነይ ግቢ ነው የምልሽ.
“አዝናለሁ ሪቻርድ? . . . ልለይህ ነው” አለችውና በጆሮው “ ነገ ግን
አባባ ከቤት እንደማያመሽ አትጠራጠር ቢሞት አከታትሎ ሁለት ቀን ከቤት
አያመሽም " ደህና እደር ።
አሁን እንግዲህ መጣደፍ አስፈላጊ ሆነባት " የማንንም ሐሜትና ትችት ሳትፈራ ጧት ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ደረሰች " እንደዚያ እየተጣደፈች ?ስትደርስ ሚስተር ካርላይል አልገባም ። ጸሐፊዎቹም የሚገባበትን ሰዓት አላወቁም ።
"ሚስተር ዲል” አለች ባርባራ ሰውየው ሰላም ሊላት ወደሷ ሲመጣ“ ሚስተር ካርላይልን ማግኘት አለብኝ " በጣም እፈልገዋለሁ ”
“ ከሰዓት በኋላ ያውም ቆየት ብሎ ነው የሚገባው ከዚያ በፊት አይመጣም "
እኔ ልረዳሽ የምችለው ጉዳይ ነው?”
“ አይደለም ፣ አይደለም " አለችው በረጅሙ ተነፈሰችና
ሁለቱ ቁመው ሲነጋገሩ ሳቤላ ልጅዋን ትንሿ ሳቤላን ይዛ በሠረገላ ስታልፍ አየቻቸውና ለባርባራ ጅንን ብላ በንቀት እጅ ስትነሣት ለሚስተር ዲል ደግሞ ደመቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለችው "
ባርባራ ሚስተር ካርላይልን በዐሥር ሰዓት ላይ አገኘችውና የሪቻርድን መምጣት ነገረችው
ሚስተር ካርላይል ማንኛውንም ማታለልና ማጭበርበር በጣም ይጠላ ነበር አሁን ግን ቶርን በነበረበት ችግር አመካኝቶ ከቢሮው ማስጠራት እሱ ሳያውቅ ሪቻርድ እንዲያየው ማድረግ አማራጭ ያልነበረው ተገቢ ሥራ መሆኑን አመነበት"ስለዚህ ሪቻርድን በቀጠረችው ሰዓት ሲመጣ ወደሱ እንድትልከው ነገራት » እሱም በበኩሉ ጀፈርሰን ቤት የነበረበትን የራት ጥሪ ሰርዞ ካፔቴን ቶርን አማክሮት ስለ ነበረው ጉዳይ ማታ በሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ እንዲመጣ ላከበት ” እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ቀኑን ከቢሮ ባለመዋሉ አልላከበትም እንጂ ስለሱ ጉዳይ ጧቱን
አግባብ ካላቸው ጋር ተነጋግሮ መፍትሔ አግኝቶለት ነበር።
የሚስተር ካርላይልን አስቸኳይ ውሳኔ የሚጠይብቅ ብዙ ጉዳዮች ከቢሮ ይጠብቁት ነበር። ስለዚህ ወደ ቤቱ ከመሄዱ በፊት አስራ አንድ ሰአት ሆነ ከራት ጥሪው መገኘት አለመቻሉን ገና ለሚስቱ አልነገራትም " ስለዚህ ከቢሮው የነበረውን ውዝፍ ሥራ ሳይጨርስ ወደ ቤቱ መሔድ ግድ ሆነበት "
ሚስተር ካርላይል የግል ደስታውን ለወዳጅነትም ሆነ ለሥራ ለመሠዋት የማያወላውል ሰው ነበር ።
ከሰረገላው ተዘጋጅቶ ከበሩ ቁሞ ሳቤላም ልብሷን ለብሳ ከመልበሻ ክፍሏ ተቀምጣ ስትጠብቀው መጣ “ ጀፈርሰን ቤት ራት የሚጀመረው ባሥራ ሁለት ሰዓት መሆኑን ረሳኸው ? አለችው በሰላምታ ፈንታ
“ አልረሳሁትም. . .ሳቤላ ግን ከዚህ ቀድሜ መድረስ አልቻልኩም " አሁንም ቀደም ብዬ የደረስኩት አብሬሽ ለመሔድ ስለ አልተመቸኝ ሚስዝ ጀፈርሰንን ይቅርታ እንድትጠይቂልኝ ልነግርሽ ነው " ዛሬ ማታ ሌላ ሰው ሊሠራልኝ የማይችል ሥራ ስለ አጋጠመኝ አሁን ራት እንደ በላሁ ተመልሼ ወደ ቢሮ እሔዳለሁ " ሳቤላ
ሲላት ሳቤላ ፊቷ ተለዋወጠ " እሷን ወዝውዞ ሊገድላት የሆነው ልዩ ልዩ ሰበብ እየፈጠረ ጊዜውን ከባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ ስለሚፈልግ ነው የሚለው እምነቷ ነበር "
“ አትቆጭ . . . ሳቤላ እውነቴን ነው ወድጄ አይደለም ። ለሌላ ቀን የማይተላለፍ ዲልም ሊፈጽመው የማይችል ብርቱ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው በዚህ አጉል ሰዓት እንደዚህ ያለ ነገር በመፈጠሩ በጣም ነው የማዝነው።
"አለ ዛሬ ከመሸ በኋላ ወደ ቢሮ ተመልሰህ ገብተህ አታውቅም ”
“ እውነትሽን ነው " ምክንያቱም ማታ ወደ ቢሮ የሚያስገባ ነገር ቢፈጠርም
ዲል ሊሠራው የሚችል ነበር " የዛሬው ግን እኔ ራሴ መሥራት ያለብኝ ጉዳይ ስለ
ሆነ ነው ' '
ባይሆን ስትሠራ ቆይተህ ስትጨርስ አዛው ድረስ አትመጣም ?
በውነቱ የምደርስ አይመስለኝም ”

👍18👎1
ቀለል ያለ የአንገት ልብሷን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረገችና ደረጃዎቹን ስትወርድ
ሚስተር ካርላይል ደግፎ ከሠረገላው ሊያስገባት ተከተላት አስገብቷት ሲያበቃ ደኅና አምሺ ” ሲላት ምንም ሳትመልስለት እንደ ሐውልት ፍዝዝ ብላ ወደ ውጭ ትመለከት ጀመር "
"በስንት ልመለስ እሜቴ ” አለ ሠረገላ ነጂው ሚስዝ ጀፈርሰን ቤት አድርሷት ከሠረገላው እንደ ወረደች
ቀደም ብለህ ና በሦስት ሰዓት ኩል ”
ሪቻርድ ሔር አሳሳች ልብሱን ለብሶ የውሸት ጢሙን አድርጎ ከሁለት ሰዓት
ቀደም ብሎ ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ሲደርስ ብቻውን ስለ ነበር ወዲያው ከፈተለትና እጁን ይዞ አስገባው
“ ከመንገድ ላይ ብዙ የምታውቃቸው ሰዎች አገኘህ እንዴ ?
በመንገድ የማገኛቸውን ሰዎች ቀና ብዬ ከተመለከትኳቸው እነሱም አስተውለው ያዩኛል ብዬ ስለ ፈራሁ ፊት ፊቴን ብቻ እያየሁ ነው ቀጥ ብዬ የመጣሁት ቦታው ግን ብዙ ተለዋውጧል " ዱሮ የሽማግሌው የሞርጋን ሱቅ የነበረበት ቦታ አዲስ ሸክላ ቤት ተሠርቶበታል "
“እሱ አዲሱ ፖሊስ ጣቢያ ነው። ዌስትሊን እኮ በታላላቅ ሕንፃዎች ከፍተኛ
ዕድገት እየታየባት ነው ታዲያስ . . . ሪቻርድ ? እንደ ምን ነህ ? ኑሮህ እንደት ነው?
“ የኑሮማ ነገር በበሽታና በችጋር እንገላታለሁ ” አለው ሪቻርድ ሌላ ምን ዕድል አለኝና. . . ሚስተር ካርላይል?በተላከከብኝ የሐሰት ክስ እንደ ባሪያ
እየለፋሁ ኑሮዬን እገፋለሁ"
“ ይህን መልክ አጥፊ ባርኔጣህን አኑረው እዚህ ከሁለታችን በቀር ማንም
የለም" አለው ሚስተር ካርላይል ። ነገሩን በመቀጠል ፡ “ የፊቱ በር ተሰግቷል! ቢሮው አሁን ባዶ ነው ። እንግዲሀ ማንም ሊመጣ አይችልም ። ”
“ እኔ ኮ” አለ ሪቻርድ ባርኔጣውን አንሥቶ እያስቀመጠ "እንደምታውቀው የታየሁ እንደሆነ አሳደው ይዘው ይሰቅሉኛል ብዬ ነው " አሁን እውነት ቶርን እዚህ ድረስ ሊመጣ ነው ? ባርባራ ነገረችኝ …”
“አዎን የሆሊጆን አጥፊ መቶ አለቃ ቶርን ምን እንደሚመስል ከሰጠኸኝ ገለጻ ጋር ስናገናዝበው ' ይህ አሁን ያለው ቶርን እሱ ይሆናል ብለን ገምተናል” አለ ሚስተር ካርላይል “ መልኩ ቁርጥ አንተ እንዳልከው ነው። በተጨማሪም ከጥቂት ዓመት በፊት በስዌንሰን እንደ ነበርና አንድ አምባጓሮ †ፈጥሮበት እንዶ ነበረም አረጋግጫለሁ ። ክፍሉ ከጆ ሔርበት ረጂመንት ስለሆነ አሁን ለዕረፍት የመጣው ከሱ ጋር ነው "
“ ግን እንደዚያ ደፍሮ እዚህ ድረስ ከመጣ በውነቱ ከብት ነው በዚህ ሰፊ ዓለም ለሱ የሚሆን መሸሽጊያ ያጣል ?”
“እሱ ባለመታወቁ ይተማመናል እኔ እንደ ደረስኩበት እሱን በዚህ አካባቢ ካንተና ከእኔ በቀር የሚያውቀው የለም ። እንግዲህ ከሚስተር ዲል ቢሮ ካስገባሁህ በኋላ በትንሿ መስኮት በኩል ወደኔ ታያለህ " እኔ ደግሞ እሱ ገና ከቢሮዬ ሲገባ
ፊት ለፊት እንደምታየው አድርጌ አስቀምጠዋለሁ " አንተ ግን ሰውየውን ካየኸው ብዙ ጊዜ ስለሆነ አሁን ለይተህ ታውቀው ይመስልሃል ? አለው "
“ ከሃምሳ ዓመት በኋላም ቢሆንም አይጠፋኝም " እንደኔ መልኩን ለውጦ
አልባሌ ልብስ ለብሶ ሌላ ለመምሰል ሞክሮ ቢመጣም ለይቸ ዐውቀዋለሁ "
“ አሁን ወደ ዌስት ሊን እንደገና የመጣኸው ለምንድነው? ያጋጠመህ የተለየ ነገር አለ ?”
“ በርግጥ በተለይ ከታመምኩ ወዲህ እናቴና ባርባራ ናፍቀውኛል ነገር
ግን በአእምሮዬ ውስጥ ተንሰራፍቶ አልለቅም ያለኝ አጉል ተስፋ ነው ሒድሒድ
እያለ አላሳርፍ ያለኝ " ስለዚህ ለአንድ ቀን ብቅ ብዬ ለመመለስ ነው የመጣሁት ።
“ እኔ ዶግሞ እንደ በፊቱ ምናልባት የገንዘብ እርዳታ ፈልገህ መስሎኝ ነው"
ብዙ አይደለም እንጂ ገንዘብም እፈልጋለሁ ። በበሽታዬ ምክንያት እዳ
ገብቻለሁ » ስለዚህ እናቴ ትንሽ ገንዘብ ብታገኝልኝ በጣም ደስ ይለኛል ።”
“ ይስጡሃል ዛሬ ማታ ከኔ ትቀበላለህ ግን ምን ሆነህ ኖሯል ?”
መጀመሪያ ፈረስ ረግጦኝ "ስድስት ሳምንት ተኛሁ ። ከዚያ በጎ ሁኘ ሥራ
ስጀምር እንደገና ሰውነቴን አተኮሰኝና ታመምኩ ተመልሼ ሌላ ስድስት ሳምንት ተኛሁ ። ከዚያ ወዲህ ጤንነት አይሰማኝም
“ ታዲያ ምን ሆነህ ነው ያልጻፍክልኝ ወይም አድራሻህን ያልላክልኝ ''
“ ፈራሁ አንተን ሳይሆን ሚስተር ካርላይል ወረቀቱ
ከሌሎች እጅ እንዳይገባና
እንዳይታወቅ ፈራሁ።
ቶርን በቀጠሮው መጥቶ ሲደውል ሪቻርድ ከተነገረው ክፍል ገብቶ ተደበቀ
ሚስተር ካርላይል ቶርንን አስገብቶ ሪቻርድ ተጠግቶ ከተቀመጠበት ትንሽ መስኮት ፊት ለፊት ቁመው ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ አስቀመጠው "
“ ይቅርታ አድርግልኝ .. ሚስተር ካርላይል ከነገርከኝ ሰዓት ሠላሳ ደቂቃ አሳልፌአለሁ ከሔርበርት ቤት ለራት የተጠሩ ሦስት ያህል እንግዶች ስለ ነበሩ
ትቻቸው መነሣት አልቻልኩም " መቸም ዛሬ ማታ ለኔ ብቻ ስትል ከቢሮ እንዳልገባህ ተስፋ አደርጋለሁ ”
“ በሥራ ዋዛ የለም አለው እንደ ቀልድ አድርጎ። “ዛሬ ቀኑን ሙሉ ቢሮ አልገባሁም ነበር። ስለ አንተ ጉዳይ ዛሬ ጧት ከለንደን አንድ መልእክት ደርሶኛል ነገሩ
ደስ አይልም ። ለማቆየት አልፈለኩም ”
“ ግን በፍትህ ከሆነ የሚያስጠይቀኝ አይደለም .. ሚስተር ካርላይል ።
“ የምተነግረኝ እውነት ከሆነ አያስጠይቅህም " ግን አንዳንድ ጊዜ ሕግና
ፍትሕም እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ . . . ካፒቴን ቶርን
ግን አሁን የሚይዙኝ ይመስልሃል ?
ያለ ጥርጥር ይይዙህ ነበር። ነገር ግን ማንኛውም የኃይል እርምጃ ከመወሰዱ
በፊት መልስ እንዲላክ የሚል ደብዳቤ ጽፌአለሁ " መልሱ ከነገ ወዲያ ይመጣል ”
“ ታዲያ እኔ አሁን ምን ላድርግ ?”
“ የምትከራከርበት መንገድ እንኳን ሊኖር የሚችል ይመስለኛል ነገር ግን
ከዚህ በፊት የነገርኩህን የምታስታውስ እንደሆነ እኔ ይህን ጉዳይ ለመከታተል የምችል አይመስለኝም”
“ እኔ ደግሞ እምነቴም ተስፋዬም ባንተ ነው ”
እንደ ነገርኩህ ቃል ልገባልህ አልችልም "ለማንኛውም ምናልባት እኔ ባልችል ሌላ እንደኔ አድርጎ ሊረዳህ ወደሚችል እመራህ ይሆናል ፤ነገ እንድትመጣ” ብሎት ተሰነባበቱና እሱ እንደ ወጣ ሪቻርድን ከተዘጋበት ክፍል አስወጣው።
“ ታዲያስ ሪቻርድ . . . እሱ ነው ?”
“ ኧረ በጭራሽ ! በምንም አይመሳሰሉም ። ጥቂት በቁመትና በጸጉር ቀለም
ይቀራረባሉ ። ፊታቸውና አቋማቸው ግን የብርሃንና ጨለማ ያህል ነው ልዩነታቸው " ያኛው መልከ መልካም ሆኖ ሳለ ልዩ የሆነ ገጽታ አለው ”
ሚስተር ካርላይል ስለ ካፒቴን ቶርን ልዩ የሆነ እፎይታ ተሰማው " የስው
የውን ሁኔታ እንደ ገመገመው በነፍስ ግዳይ የሚጠረጠር ዐይነት አልመስል ብሎት ነበር " አሁን እንግዲህ ላለበት የሕግ ጥያቄም ሊከራከርለት ወሰነ "
አየህ ሚስተር ካርላይል. . . ያ ሆሊጆንን የገደለው እዚህ ላይ ልዩ የሆነ አመለካከት አለው።ሪቻርድ ጣቱን ወደፊቱ እያመለከተ "
ከምኑ ላይ ?”
ከምኑ ላይ እንደሆነ እንኳን በትክክል መናገር አልችልም ከቅንድቡ ይሁን ወይም ከዐይኑ ውስጥ ይሁን
ብቻ ከሁለቱ ባንደኛው ላይ ነበር ” እኔ እኮ የቶርን እዚህ መታየት ባርባራ ስትነግረኝ በጣም ገርሞኝ ነበር " ማመን አልቻልኩም ምክንያቱም ካላበዶ በቀር ወደዚህ ብቅ አይልም
በል እንግዲያው አሁን ወደ ዐፀዱ ሒድ » እናትህ ሊያዬህ በጣም ስለጓጉ በመዘግየትህ ይጨነቃሉ
ምን ያህል ገንዘብ ትፈልጋለህ?።
ኻያ አምስትም ፓውንድ ባገኝ ይበቃኛል " በርግጥ ሠላሳ ፓውንድ ባገኝ ችግሬን የበለጠ ያቀልልኛል።
« ደኅና ሠላሳ እሰጥሃለሁ " አሁን ከኔ ጋር ወይስ ብቻህን ብትሔድ ይሻልሃል?

👍14
ሚስተር ካርላይልን በመንገድ ያገኘው ሁሉ ስለሚያነጋግረው ሪቻርድ ፈራና ብቻውን መሔድ መረጠ " ከዚያ ሁለቱም ምንም ነገር ሳይገጥማቸው ከሚስተር ጀስቲስ ሔር ቤት ደረሱ " ያኔ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ዐልፎ ነበር "
በጣም አመሰግናለው ሚስተር ካርላይል " ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ ” አለው ሪቻርድ ከግቢው ደርሰው በእግሩ መንጀድ አብረው እየሔዱ "
“ ምነው ይህን እንቆቅልሽ መፍታት በቻልኩና ከዚህ የበለጠ : በረሁዳሁህ "
ለመሆኑ ባርባራ እየጠበቀች ነው ብለህ ? አዎን ያውና በሩ ቀስ ብሎ እየተከፈተ
ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል የራሱን ጥያቄ በመመለስ "
ሪቻርድ ሹልክ ብሎ ወደናቱ ገባ ባርባራ የካፒቴን ቶርንን ውጤት ለማወቅ
ከበረንዳው ቁማ ሚስተር ካርላይልን ትጠብቅ ነበር " መልሱን ለማወቅ
ስለ ነበር ድምጿም ተንቀጠቀጠ ።
“ እንዴት ነው ? ያው እኛ የምንፈልገው ቶርን ነው ? ” አለችው "
“ በሪቻርድ አባባል ምንም አይመሳሰሉም ። እንግዲህ የካፒቴን ቶርን ነገር በዚህ ያበቃል " እኛም ትኩረታችንን ሁሉ በዚህ ሰው ላይ ብቻ ስለ አደረግን ሌላ ፍለጋ አልሞከርንም ።
ሚስተር ካርላይልና ባርባራ ሲገቡ እናትና ልጅ ተጠማጥመው ሲላቀሱ አገኙዋቸው " ሚስዝ ሔር ወዲያው ሪቻርድን ለቀቀችና የካርላይልን እጅ ይዛ “ አንተ
ባትኖር ኖሮ ምን እሆን እንደ ነበር አላውቅም። የዋልክልኝ ውለታ ልክ የለውም "አሁን ደግሞ ደግነትህን በተጨማሪ ልጠቀምበት ፈልጌ ነበር " ነገሩን ባርባራ አንሥታልህ ነበር ?”
“ አሽከሮች እንዳይሰሙ ፈርቸ ከኮሪደሩ ልነግረው አልፈለግሁም ...እማማ”
ሚስተር ሔር ዛሬ ወደ በክስ ሔድ ሲሔድ አሞኛል ሲል ስለ ነበር ምናልባት እንደ ወትሮው እስከ አራት ሰዓት ማምሸት ካቃተው ቀደም ብሎ ይመጣ ይሆናል
ብዬ ፈራሁ " ስለዚህ ከሪቻርድ ጋር ያለሥጋት እንድጫወት ከባርባራ ጋር ሆናችሁ በአትክልቱ ውስጥ አየር እየተቀበላችሁ ጠብቁት " ምናልባት ከአራት ሰዓት በፊት
ከመጣ አንተ ከዚያው ቆም አድርገህ እስክታነጋግረው ድረስ ባርባራ መጥታ ልታስ
ጠነቅቀን ትችላለች " ከዚያ ሪቻርድ ከኮሪደሩ ካለው ቁም ሳጥን ገብቶ ካሳለፈው
በኋላ በደኅና ወጥቶ ሊሔድ ይችላል " ይኸን ለማድረግ ይመችሃል ... አርኪባልድ ? ” አለችው ሚስዝ ሔር
“ ምናለ ግድ የለም ” አለ ሚስተር ካርላይል "
“ አየህ አርኪባልድ” አለችው ሔር እጁን በምስጋና ጫን አድርጋ ይዛ “ ግድ ካልሆነብኝ በቀር ከአራት ሰዓት በፊት ከሱ ጋር ለመለያየት አልፈልግም
ሰባት ዓመት ሙሉ ጠፍቶ የኖረውን ልጅ ለአንድ ሰዓት ማነጋገር ማለት ምን
ማለት እንዶሆነ ላታውቀው ትችላለህ · · · በአራት ሰዓት እንሰነባበታለን “በሚስዝ ሔር ጥያቄ መሠረት ሚስተር ካርላይልና ባርባራ በበሩ አካባቢ ወዲያና ወዲህ እያሉ ይጠባበቁ ጀመር " ሚስተር ካርላይል ለአክብሮት ሲል ክንዱን
ሰጣት እሷም ተቀብላ ተያያዙና መጠበቅ ቀጠሉ » ጀስቲስ ሔር ግን ብቅ አላለም "
ልክ በሦስት ሰዓት ተኩል የወይዘሮ ሳቤላ ካርላይል ሠረግላ ሚስዝ ጀፈርስን
ቤት ሲደርስ ራስ ምታት አመካኝታ ወዲያውኑ ወጣች » ኢስትሊን በአቋራጭ መንገድ ሁለት ማይል ያህል ብቻ ይርቅ ስለነበር ለመድረስ ብዙ አያቆይም ሠረገላው
በጉዞ ላይ እንዳለ አንድ ሰው ለነጅው እጁን ሲያወዛውዝለት ቆመ " ሌላ ሰው ያስመሰለው ቆብ ደፍቶ ስለነበር ምንም እንኳን ደማቅ ጨረቃ ብትኖርም በደንብ እስኪጠጋ ድረስ ሳቤላ ሌቪሰን መሆኑን አላወቀችም ነበር " እሱ መሆኑን ስታውቅ መስ
ኮቱን ከፈተችለት "
“ ያንቺ ሠረገላ ይሆናል ብዬ አሰብኩ ምነው ቶሎ ተመለስሽ ? ሰለቸሽ?”
“ እመቤቴ በስንት ሰዓት እንደሚመለሱ ጠይቆኝ ዐውቆት ነበር አለ ሠረገላ ነጅው ለራሱ '' እኔስ ይኸ ሰው አታላይ መሰለኝ "
“ ነፋስ ልቀበል ብዬ ወጣሁና አሁን ድክም አለኝ ” አለና ነገሩን በመቀጠል
“አብሬሽ ልመጣ መቀመጫ ትፈቅጅልኛለሽ ?
ፈቀደችለትና ፍራንሲዝ ሌቪስን ከወይዘሮ ሳቤላ ጐን ተቀመጠ “ዋናውን
መንገድ ይዘህ ሒድ” አለ አንገቱን ወደ ነጂው አውጥቶ " ነጂውም በእሽታ ባርኔጣውን ነካ አደረገ " ዋናው መንገድ የሚወስደው በጀስቲስ ሔር በኩል ነበር "
“አላወቅሁህም ነበር እኮ” አለችው ራሷን መግዛትና ሐሳቧን መሰብሰብ ስትችል "የምን አሳሳች አስቀያሚ ቆብ ነው የደፋኸው ? ላለመታወቅ የፈለግህ ትመስላለህ ?”
ኧረ የለም : ለምን ብዬ ? በዚህ አካባቢ ባለ ዕዳዎች የሉኝም
“ ሚስተር ካርላይል ከቤት አለ ?
“ የለም”ብሎ ጥቂት ዝም ብሎ ቆየና ' “ እሱ ደኅና ደስ በሚል ሥራ የተያዛ መሰለኝ
በምን ሥራ ነው የተያዘው ?”
“ አሁን በጀስቲስ ሔር ደጅ ሳልፍ አንድ ጎበዝና አንዲት ቆንጆ በፍቅር ተጠማጥመው አፍ ላፍ ገጥመው ሲያወሩ በጨረቃው ብርሃን አየኋቸው እነሱም
ያንቺ ባልና ሚስ ሔር ነበሩ
ሳቤላ ጥርሶቿን ልታፋጭ ምንም አልቀራትም ማምሻውን ሁሉ ሆድ ሆዷን ሲያቃጥሏት ያመሹ የቅናት ጥርጣሬዎች ተረጋገጡ " ያ እንዲህ ያናደዳትና የጠላችው ሰውዬ አብሯት ወደ ተጠሩበት ግብዣ እንዳይሔድ አሳፋሪ ውሸት ደርድሮላት የቀረው!ጊዜውን ባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ እንደነበር ተረዳች ከሠረገላው ውስጥ
ብቻዋን ብትሆን ኖሮ የብሶቷን ያህል ትጮኸ ነበር "
ከጀስቲስ ሔር ቤት ፊት ለፊት ሲደርሱ ሥራዬ ብላ ወደ ውስጥ ስትመለከት
በጠራው ጨረቃ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ቀስ እያሉ ሲንጓራደዱ አየቻቸው
ልትቈጣጠረው ልትደብቀው ባልቻለችው የታፈነ እንቅስቃሴ እመቤት ሳቤላ
የኋሊት መቀመዋ መደገፊያ ላይ ተላትማ ቁጭ አለች "
ባለቤቷ ፍቅሩን ሲነፍጋት ደፋሩና ክፉሙ ሰው የሱ ፍቅር ያለላት መሆኑን
እያንሾካሾከ በክንዱ እቅፍ አድርጎ ወደሱ ጠጋ አደረጋት
የቀናች ሴት ዕብድ ናት የተናደደች ደግሞ እጥፍ ዕብድ ናትና ሳቤላም በባልና ሚስት መካከል ሊኖር በሚገባው ክቡር ስሜት ላይ ሚስተር ካርላይል
ክህደት የፈጸመ መሰላት
“ይህን እምነተ ቢስ ተበቀው ወትሮም አቻሽ አልነበረም !አሁንም የመከራ ኑሮሽን ትተሽ ወደ ደስታ ነይ ” እያለ ፍራንሲዝ ሊቪሰን ጣፋጭና አደገኛ በሆኑ ቃላት ያባብላት ጀመር.....
💫ይቀጥላል💫

👍17❤1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
ማምለጥ
ህዳር አስር… እዚህ እስር ቤት ውስጥ የምንቆይበት የመጨረሻ ቀናችን ነው
እግዚአብሔር አላዳነንም: ራሳችንን ማዳን አለብን።
ክሪስ ዛሬ ማታ ልክ አራት ሰዓት ሲያልፍ የመጨረሻውን ዝርፊያ ያከናውናል።እናታችን ለጥቂት ደቂቃዎች ለመቆየት መጥታ ነበር። አሁን ከእኛ ጋ መሆን
ብዙም እንደማይመቻት በግልፅ ይታያል። “ባርትና እኔ ዛሬ ማታ ወጣ እንላለን፡ እኔ አልፈለግኩም እሱ ግን ድርቅ አለ፡ አያችሁ፣ ለምን እንዳዘንኩ አይገባውም” ብላን ነበር።
እንደማይገባው እርግጠኛ ነኝ። ክሪስ ከበድ ያሉ ጌጣጌጦችን ይዞ ለመመለስ ሁለት የትራስ ልብሶችን ትከሻው ላይ አንጠለጠለ፡ የተከፈተው በር ጋ ቆመና ወጥቶ በሩን ከመቆለፉ በፊት ረዘም ላለ ጊዜ ቆም ብሎ ተመለከተን
በሩን ክፍት መተው አይችልም: ምክንያቱም አያትየው ድንገት ከመጣች
መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው ክሪስ ጨለማ በዋጠው በሰሜን አቅጣጫ
ካለው ኮሪደር ሲሰርቅ ልንሰማው አንችልም።
ምክንያቱም ግድግዳዎቹ በጣም ወፍራም ሲሆኑ አዳራሹ ውስጥ የተነጠፉት ምንጣፎች ደግሞ ወፍራምና ድምፅ የማያሳልፉ ናቸው።
ኬሪና እኔ ጎን ለጎን ተኝተን በክንዶቼ አቅፌያታለሁ።
ያ ህልም ኮሪ ደህና መሆኑን ባይነግረኝ ኖሮ፣ ቅርብ መሆኑ ስለማይሰማኝ
አሁንም አለቅስ ነበር። ታላቅ ወንድሙ እንደማይሰማን ባረጋገጠ ቁጥር
እማዬ ብሎ ይጠራኝ ለነበረው ትንሽ ልጅ መታመሙን ልረዳው አልቻልኩም ሁልጊዜ ክሪስ ምን ያህል እናቱን እንደናፈቀና እንደፈለገ ካወቀበት ሴታ ሴት
ብሎ ሊጠራው እንደሚችል ስለሚፈራ የሚነግረኝ ለእኔ ነበር እኔም ክሪስ
ራሱ እናቱን ስለሚፈልግ በጭራሽ እንደማይስቅበትና እንደማያሾፍበት
እነግረው ነበር በአንድ ወቅት ኮሪ በእሱ፣ በእኔና በኬሪ መካከል ሚስጥር
አድርጎት ነበር ወንዳወንድ ለመሆን እናትም አባትም ባይኖረው ምንም
እንዳልሆነ ራሱን ያሳመነ ይመስላል
ኬሪን ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና ልጅ ወይም ልጆች ሲኖሩኝ የማይሰማኝ
ወይም ለእነሱ ምላሽ የማልሰጥበት እኔን የመፈለግ ስሜት እንደማይኖራቸው
ማልኩ ምርጥ እናት እሆናለሁ ሰዓታት ልክ አመታት መሰሉ። ክሪስ
እስካሁን የእናታችንን ክፍል ለመጨረሻ ጊዜ ሊጎበኝ ከሄደበት አልተመለሰም
ዛሬ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ፈጀ? ንቅት ብዬና ተከፍቼ በፍርሀት ተሞላሁና
ሊያቆየው የሚችለውን ሁሉንም መሰናክሎች ማሰብ ጀመርኩ።
ባርት ዊንስሎ ... ተጠራጣሪው ባል ... ክሪስን ሊይዘው ይችላል! ከዚያ ፖሊስ ይጠራና እስር ቤት ይወስዱታል። እናታችን ድንጋጤዋን እየገለፀችና
የሆነ ሰው ሊሰርቃቸው በመድፈሩ እየተገረመች በእርጋታ ትቆማለች። እሷ
በፍፁም ልጅ የላትም
ሁሉም ሰው የሚያውቀው ልጅ እንደሌላት ነው በእግዚአብሔር! ከልጅ ጋር
ታይታ ታውቃለች? ያ ባለወርቃማ ፀጉርና ባለ ሰማያዊ አይን ልጅ በጣም የሷ ልጅ እንደሚመስል አታውቅም በዚያ ላይ ብዙ የተራራቁ የአክስትና የአጎት
ልጆች አሏት። እና የስጋ ዘመድም ቢሆን የሆነ አምስተኛ ወይም ስድስተኛ
ሩቅ የሆነ ዘመድ ያው ሌባ ነው።
ፀ እና ያቺ አያት ተብዬ ከያዘችው እጅግ መጥፎ የተባለው ቅጣት ያገኘዋል።
በዶሮ ጩኸት ንጋት እየመጣ መሆኑ ይሰማል።
ፀሀዩዋ በአድማስ ላይ እየመጣች ነው:: ትንሽ ከቆየ ለመሄድ በጣም የዘገየን እንሆናለን፡ የጠዋት ባቡር በጣቢያው በኩል ያልፋል፡ እና አያትየው በሩን
ከፍታ መሄዳችንን እስክታውቅ ድረስ ብዙ ሰዓታት ያስፈልጉናል። የሚፈልጉን ሰዎች ትልክብንም ይሆናል፡ ለፖሊስ ታስታውቃለች? ወይስ በመጨረሻ
ልታስወግደን ስለቻለች በመሄዳችን ትደሰታለች?
ተስፋ በመቁረጥ ውጪውን ለማየት በደረጃው ጣሪያው ስር ወዳለ ክፍል ወጣሁ: ጭጋጋማና ቀዝቃዛ ነው: ያለፈው ሳምንት የጣለው በረዶ ጣራው ላይ እዚህም እዚያም ይታያል፡ ደስታና ነፃነት ሊያመጣልን የማይችል ፈዛዛና
ክሪስ የትም ይሁን የት ወይም ምንም እየሰራ ይሁን እሱም እንደሚሰማውና
ሚስጥራዊ ቀን ነው እንደገና ዶሮ ሲጮህ ሰማሁ: በጣም ሩቅ ይመስላል።ክሪስ የትም ይሁን የት ወይም ምንም እየሰራ ይሁን እሱም እንደሚሰማውና እንዲፈጥን እንዲያደርገው ፀለይኩ ክሪስ ቀስ ብሎ ወደ ክፍላችን የሚገባበትን ያቺን ማለዳ አስታውሳታለሁ ኬሪ አጠገቤ ተኝታ እኔ ደግሞ የክፍላችን በር እንደተከፈተ ቶሎ እንድነቃ በሰመመን እንቅልፍ ላይ እሆናለሁ: ልብሶቼን ለባብሼ ለመሄድ ተዘጋጅቻለሁ። ክሪስ ተመልሶ መጥቶ እስኪያድነን ድረስ እጠብቃለሁ ድንገት ክሪስ እያመነታ ክፍሉ ውስጥ ገባ የፈዘዙ አይኖቹ ወደ እኔ እየተመለከቱ ነው፡ ከዚያ
ወደ እኔ አቅጣጫ መጣ: መፍጠን የሚገባውን ያህል እየቸኮለ አይደለም።
ወዲያው ይዞት ሄዶ የነበረውን የትራስ ልብስ ተመለከትኩ ባዶ ይመስላል።
“ጣጌጦቹ የታሉ?” ስል ጠየቅኩት። “ለምንድነው የቆየኸው!? በመስኮት
ተመልከት፣ ፀሀዩዋ እየወጣች ነው: ወደ ባቡር ጣቢያው በሰዓቱ አንደርስም”ድምፄ ጠንካራ፣ ከሳሽና የንዴት ነበር “እንደገና አዛኝ ሆንክ አይደል? ለዚያ
ነው የእናታችንን ጌጣጌጦች ሳትይዝ የመጣኸው!” አልኩት።
በዚህ ጊዜ አልጋው ጋ ደርሶ ባዶውን የትራስ ጨርቅ በእጁ እንዳንጠለጠለ
ቆሞ ነበር።
“የሉም… ሁሉም ጌጣጌጦች የሉም” አለ።
“የሉም?” አልኩት በቁጣ እየዋሸ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ። እየሸፈነላት
ነው እናታችን በጣም የምትወዳቸውን ነገሮች ሊወስድባት አልፈለገም።
ከዚያ አይኖቹን ተመለከትኩ፡ “የሉም? ክሪስ ጌጣጌጦቹ እኮ ሁሌም እዚያው ነው የሚሆኑት ግን ምን ሆነሀል? ለምንድነው እንግዳ ፀባይ ያሳየኸው?
አልጋው አጠገብ በጉልበቱ ተንበረከከ አጥንት የሌለው ይመስል ተልፈስፍሶ
ፊቱን ደረቴ ውስጥ ቀበረ፡ ከዚያ ይንሰቀሰቅ ጀመር: አምላኬ! ምንድነው
ነገሩ? ለምንድነው የሚያለቅሰው? ወንድ ልጅ ሲያለቅስ መስማት ይከብዳል።
በክንዶቼ ያዝኩት: በእጆቼ ፀጉሩን፣ ጉንጩን፣ ክንዶቹንና ጀርባውን
እየዳበስኩና እየሳምኩት ላባብለው ጥረት አደረግኩ የሆነ ከባድ ነገር
እንደተፈጠረ አውቄያለሁ: ሲከፋው እናታችን ስታደርግለት እመለከት
የነበረውን ነገሮች እያደረግኩለት ነው: እና ስሜቱ ተቀስቅሶ ልሰጠው
ከምፈቅደው በላይ እንደማይፈልግ ስለማውቅ አልፈራሁም እንዲናገር™
እንዲያብራራልኝ ማስገደድ ነበረብኝ፡
ሳጉ እየተናነቀው መዋጥ ነበረበት እምባውን ጠረገና ፊቱን በአንሶላው ጠርዝ
አደረቀ ከዚያ አይኖቹን ዞር አድርጎ ገሀነምና ቅጣቱን
ወደሚያሳየው አስፈሪ
ስዕል ተመለከተ። ንግግሩ በአብዛኛው እየተቆራረጠና ለቅሶውን ለመመለስ ሲሞክር እየቆመ ነበር።
በጉልበቱ አልጋው አጠገብ እንደተንበረከከ፣ የሚንቀጠቀጡ እጆቹን እንደያዝኩ አስጠንቅቆኝ መናገር ጀመረ: አስቀድሜ እንድጠነቀቅ የነገረኝ ቢሆንም ሰውነቱ እየራደና ሰማያዊ አይኖቹ ጠቁረው ሊያስደነግጠኝ እንደሚችል
ለሰማሁት ነገር ግን በጭራሽ አልተዘጋጀሁም ነበር።
በከባዱ ተነፈሰና ጀመረ። “ልክ ወደ ክፍሏ እንደገባሁ የሆነ የተለየ ነገር እንዳለ
አውቄያለሁ: የክፍሉን መብራት ሳላበራ የያዝኩትን ባትሪ ብቻ በመጠቀም
ዙሪያውን ስመለከት ማመን አልቻልኩም! መሄዳችንን የሚያዘገይ፣ የሚያጠፋ

👍30❤1🤔1
መጥፎ መራራ ነገር ነበር፡ ሄደዋል ካቲ። እናታችንና ባሏ ሄደዋል ጎረቤት
ወዳለ ድግስ አይደለም በቃ ሄደዋል! ክፍላቸው ውስጥ የነበራቸውን ነገሮች
በሙሉ ጠቅልለው ሄደዋል፡ ልብሶቿ፣ ቅባቶቿ፣ ሽቶዎቿ… ሁሉም ነገሮች የለም፡
“በጣም ስለተናደድኩ እንዳበደ ሰው እዚህ እዚያ እያልኩ የሆነ ዋጋ ያለው
ነገር አገኛለሁ በሚል ተስፋ ክፍሉን አተራመስኩት ምንም ነገር አላገኘሁም::
ጥሩ ስራ ነው የሰሩት: አንዲት ዋጋ የምታወጣ ነገር አልተውም። ከሷ
ለመስረቅ ባላሰብንበት ወቅት ላይ የነገረችንን ልዩ የሆነውን የታችኛውን
መሳቢያ ከፈትኩ ከዚያ ከውስጥ ያለችውን ቁልፍ ተጫንኳት። ታስታውሻለሽ
የሚስጥር ቁጥሩ የልደቷ ቀን ባይሆን ኖሮ ትረሳው እንደነበር ስትነግረን
እንዴት እየሳቀች እንደነበር? የሚስጥር ማስቀመጫው ሲከፈት አንድም
ቀለበት እንኳን አልነበራትም: ሽዋልያዎቹ፣ የአንገት ጌጦቹ ሁሉ የሉም᎓ ብዙ
ጊዜ አንዲት ትንሽ ቀለበት እንኳ እንድንወስድ ለምነሽኝ ነበር አላደረግኩትም
ምክንያቱም አምናት ነበርና:"
“አታልቅስ ክሪስ” እምባ አንቆት ፊቱን እንደገና ወደ ደረቴ ደፋ፡ “እንደምትሄድ
አላወቅክም ከኮሪ ሞት በኋላ ፈጥና ትሄዳለች ብለህ አላሰብክም አልኩት።
“አዎ በጣም አዝና ነበር፡ አይደለም እንዴ? ሲል ጠየቀኝ፡ “በእውነት ካቲ” ሲል ቀጠለ፡ “ከቁጥጥር ውጪ ሆኜ ከአንዱ ልብስ ማስቀመጫ ወደ
ሌላው እየተራወጥኩ የክረምት ልብሶቹን ስወረውር ሁሉም የበጋ ልብሶች እንደሌሉ ተመለከትኩ፡ ዝርዝር ሳንቲሞች ያስቀምጥበት የነበረውን ቆርቆሮ
ስፈልግ እሱንም ወስደውታል። ወይም የተሻለ ቦታ ደብቀውታል: አንድ ዋጋ የሚያወጣ ነገር ለማግኘት እጅግ ፈልጌ ነበር ምክንያቱም በቂ ገንዘብ
ሳይኖረን እንዴት እንሆናለን? ታውቂያለሽ… በዚያች ደቂቃ ክፍሏ መሀል ቆሜ ስላለንበት ሁኔታና ስለ ኬሪ አሳሳቢ ጤና ሳሰላስል ዶክተር ብሆን ለእኔ ምንም ማለት አለመሆኑ ገባኝ፡ የምፈልገው ብቸኛ ነገር ሁላችንም ከዚህ
እንድንወጣ ነው::
“hዚያ ምንም የምሰርቀው ነገር እንደማላገኝ ሳውቅ የኮመዲኖዋን የታችኛው
መሳቢያ ከፈትኩ። ያንን መሳቢያ አንድም ቀን ፈትሼው አላውቅም ነበር
ካቲ ውስጡ ብርማ ፍሬም ውስጥ የተቀመጠ የአባታችን ፎቶግራፍ፣ የጋብቻ ሰርተፍኬታቸው እና ትንሽዬ አረንጓዴ ሳጥን ነገር ነበረበት በአረንጓዴዋ
ሳጥን ውስጥ ደግሞ አባታችን የሰጣት የጋብቻና የቃል ኪዳን ቀለበት ነበሩበት ሁሉንም ነገሮች ስትወስድ ይህንን ፎቶግራፍና የሰጣትን ቀለበቶች ጥቅም
እንደሌላቸው ሁሉ ጥላ መሄዷ ይጎዳል።
ከዚያ እንግዳ የሆነ ሀሳብ ወደ አእምሮዬ መጣ፡ ምናልባት ከክፍሏ ውስጥ
የሚሰርቃት ማን እንደሆነ ስላወቀች ሆነ ብላ ትታው ቢሆንስ?”
“አይሆንም” አልኩ በማፌዝ: ያንን ሀሳብ አሽቀንጥሬ ጣልኩት አሁን ለእሱ ምንም ግድ ስለሌላት ነው . . . አሁን የሷ ባርት አለላት᎓ “የሆነው ሆኖ የሆነ
ነገር በማግኘቴ ደስ ብሎኛል ስለዚህ የትራስ ልብሱ እንደሚታየው ያህል
ባዶ አይደለም የአባታችን ፎቶግራፍና የእሷ ቀለበቶች አሉበት። ነገር ግን
እነዚህን ቀለበቶች ሽጦ መጠቀም መሸከም የማይቻል አሰቃቂ ቀውስ ነው:"
ድምፁ ውስጥ ማስጠንቀቂያ ይሰማኛል። ለሁሉም ጥሩ የሆነውን፣
የምተማመንበትን የበፊቱን ክሪስቶፈር ለመሆን እየተወነ ይመስል ነበር
"ንገረኝ፣ ቀጥሎ ምን ሆነ? አልኩት። ረዘም ላለ ጊዜ ዝም አለኝ። መቼም አሁን የነገረኝ ነገሮች ሙሉ ሌሊት አይፈጁም
“እናታችንን መዝረፍ አለመቻሌ ሲገባኝ አያትየው ክፍል ሄጄ ለመስረቅ
ወሰንኩ:” አለኝ።....

👍36👏4🥰2❤1🤔1
✍✍የጠንቋዩ ዋሻ✍✍
♣♣ክፍል ሦስት♣♣
♦♦♦♦°♦♦♦♦°♦♦♦♦°
ለለሦስቱም አብሮ አደግ ጓደኛማቾች ፡ ነገሩ ሁሉ አንደዘበት ፡የሚያዩት የነበረው ፡ የወረር ፊልም ፡በሁኑ ዓለም ፡የተከሰተባቸው ፡እስኪመስላቸው ፡ድረስ ፡ በፍርሃት የሚገቡበት ፡ጠፍቷቸዋል ፡ ጠንቋዩ ለደቂቃ አይኖቹን ፡ሲያጉረጠርጥባቸው ፡ቆይቶ ፡ ኤዛ ብሎ ፡የጠራት ፡ ቆንጅዬና ፡ማራኪ የሆነች ዋ ወጣት ፡ ያዘዛትን ፡የፈላ ውሃ ፡ይዛ ፊቱ ጎንበስ ፡ብላ ስትቀርብ ፡ በሌባ ጣቱ እረጅም ፡ሉጫ ፀጉሯ ፡ያረፈበትን ፡ አናቷን ፡ነካ ነካ አደረጋት ፡ እሱ በነካት ቁጥር ፡ከጭንቅላቷ ፡ዝቅ ፡ስትል ፡ መስፍን ፡የተባለው ፡ጎረምሳ ፡ ለጓደኛው ፡ ዳንኤል ፡ ' የሴጣን አለቃ ሳይሆን አይቀርም ፡ መዳንያለም ከዚብቻ በታምሩ ያውጣን 'አለው ፡በማንሾካሾክ ፡ ዳንኤል ማለት የሚፈልገው ፡ነገር ፡ቢኖርም ፡ ከንፈሮቹ በፍርሃት ፡አልላቀቅ አሉት ፡ ሦስተኛው ፡ጓደኛቸው ፡ መሳይ ፡ ቀጣዩን ፡የጠንቋዩን ፡እርምጃ ፡አይኑ ቁልጭልጭ ፡እያለ ይጠብቃል ፡ ፍርሃቱ ከሁለቱም ፡ጓደኞቹ ይብሳል ፡ አስተዳደጉም ፡ ፍቅርና ፡ማባበል ፡የበዛበት ፡ስለሆነ ፡ እንዲ አይነቱን ፡አስጨናቂ ሁኔታ ለመቋቋም ፡ አቅም አቷል ፡ ጠንቋዩ ፡በጣም ፡ቢጮህበት እንኳ ፡የሚሞት ነው የሚመስለው ፡ ከሁሉም በላይ ደሞ ፡ እነዛ ቀያይ የለበሱ ቀንጆ ሴቶች ፡ ድንገት ፡ ወደ ሴጣንነት ፡ተቀይረው ፡የሚያጠቋቸው ፡ነው የመሰለው ፡ የቫንባዬር ፊልም ታወሰው ፡ እናም ፡እነዚንም ፡ሴቶች ፡አላመናቸውም ፡ እዚ ጥቅጥቅ ፡ጫካውስጥ ፡ የሚያስፈራ ዋሻ ፡ውስጥ ፡ ከሚያስፈራራ ግዙፍ በለነጭ ፂም ሰውዬ ጋር ፡ምን ፡ሊያስደብቃቸው ፡የችላል የተለየ ነገር ከሌላቸው በቀር ፡ ,,,, ጠንቋዩ ፡ ኤዛ የተባለችው ልጅ በሰአን ያቀረበችው ፡የፈላ ውሃ ውስጥ ፡ ከጉያው ፡ውስጥ አንዲት ትንሽዬ ብልቃጥ ፡በማውጣት ፡ ከፈታትና ፡ ሦስት ጊዜ ፡ ቀይ ጠብታ ነገር ፡ወደውሃው ፡ጨመረ ፡ ቀጥሎ ፡ ሌላኛዋ ልጅ ፡በትንሽዬ ፡ ሙዳይ ፡አንዳች ነገር ይዛ መጣች ፡እናም አጠገቡ ስትደርስ ፡ጎንበስ ፡ብላ ጠይኖቹን ፡ሳታይ ፡ሙዳዩን ከፍታ አቀረበች ፡ጠንቋዩ በእጁ ቆንጠር አድርጎ ወደፈላውሃ ጨመረ ፡ከዛም በሌባ ጣቱ ቀላቀለው ፡ በነጩ ሰአን የነበረው ፡ውሃ ሙሉ በሙሉ ወፈር ያለ ቀይ ፈሳሽ ፡ሆነ ፡ ከዛም ፡ ሴቶቹን ፡" ውርንጭሎቼ እረፍት አድርጉ ፡ ወደጨለማው ፡ ክፍል ፡ሄዳቹ ተኙ አቢያራ ይጠብቃችዋል ፡ ከኔ አይጎልባችሁም "አላቸው ፡ በዋሻው ፡ክፍል ውስጥ የነበሩት አራት ቆነጃጂት ሴቶች ፡ በተራ በተራ ፡የጠንቋዩ አቢያራን ፡ እጅ ፡እየሳሙ አመሰገኑ ፡ ፡አቢያር ፡ በተራ እጁን እየሰጣቸው ፡ ስማቸውን ፡ እየጠራ ፡መረቃቸው " ኤዛ ያቢያራ መንፈስ ፡ይውረድብሽ ፡"አላት ጎንበስ ብላ
"ጌታዬ ምስጋና ይድረስህ "አለች
"ኤፍራ ፡የአቢያራ መንፈስ ካንቺ ይሁን "
"ምስጋና ላንተ "አለች ኤፍራ ብሎ የጠራት ሴት
"ኤልያታ ፡አቢያራ ካንቺ ይሁን"
"ሁሉ ባንተ ይሁን "አለች
" ኤፊ አቢያራ በሁሉ ነገርሽ ይግባ "
"ሁሌም ላንተ ነኝ አባቴ " አለች ፡ ነገሩ ግራ የገባቸው ፡ የታፈኑት ሦስቱ ጎረምሶች ፡ በየራሳቸው ፡ውስጥ የት ነው ያለነው ይሄ ነገር ህልም ነው እንዴ ፡ ይህ አስፈሪ ሰው ፡እራሱን እንዴት ነው እንደ አምላክ የቆጠረው ፡ እነዚንስ ፡ቀያይና ቆንጆ አማሪኛ የሚናገሩ የሌላ አገር ፡ሰው የሚመስሉ ሴቶች ፡ከወዴት ፡አመጣቸው ፡ ደሞስ ፡የስም አጠራራቸው ፡ የመጀመሪያ ፊደል መመሳሰል ፡ እንዴት ቻለ ፡ ነው ፡ለራሱ እንዲመቸው ፡አድርጎ ፡ሰይሟቸው ፡ነው ፡ የሆነስ ፡ሆነና ፡ ምንድነው ፡አላማው ፡ የሚያምኑትን ሰዎች ፡ማብዛት ፡ነው ፡ወይስ ፡ በተረት እንደሚነገረው ፡የሰው ፡ደም የሚጠጣ ጭራቅ ፡ይሆን ፡ ጎረምሶቹ ከአቢያራ ፡ይልቅ ፡አይኖቻቸውን ፡ይዟቸው ፡ወደመጣው ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡ ተክለዋል ፡ ከዚ ሴጣን ፡ከሚመስለው ፡አቢያራ ፡ ለምኖላቸው ፡በነሱላይ ፡ሊያደርግ ካሰበው ፡ነገር ፡እንዲያወጣቸው ፡ በአይናቸው ፡ተማፀኑ ፡ ሴቶቹ በአንዲት ፡ሸለቆ ፡ውስጥ ፡ገብተው ፡ተሰወሩ ፡ እነሱ ሲሄዱ ፡ ዋሻው ፡ የሞት መንፈስ ፡የሚጮህበት ፡መሰለ ፡ 'እሽሽሽሽሽ ሿሿሿሿሿ ፂፂፂፂፂፂ ስስስስስ ,,,,,,,' የልብን ትርታ የሚጨምር ፡ዝም ያለ ጩኽት ፡
አቢያራ "ና መስፍን "ሲል መስፍን ፡ልቡ በድንጋጤ ዘለለች ፡በስሜ ይጠራኛል ፡ብሎ ፡አላሰበም ፡እና ወደሱ ለመቅረብ ፡ዘገየ ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡ወደመስፍን በመጠጋት ፡ አባቴን ፡አታበሳጨው ፡ሲለው ፡መስፍን ፡ተንቀሳቀሰ ፡ እናም ፡አቢያራ ፡ፊት ቆመ አቢያራ የመስፍንን አይኖች ፡አፍጥጦ ሲያየው ፡ ቆይቶ ሳቅ ፡ብሎ ፡አፉን ፡እንዲ ከፍት ፡አዘዘው ፡ መስፍን ፡በፍርሃት እንደተዋጠ አፉን ከፈተ አቢያራ ከበጠበጠው ፡ቀይ ፈሳሽ ፡በእጁ ጨልፎ የመስፍን አፍ ውስጥ ጨመረው ፡ ከዛም ወደአልታወቀው ሰው ምልክት ፡ሲሰጠው ፡ያልታወቀው ሰው ፡የመስፍንን አፍ ፈሳሹ እንዳይወጣ ግጥም አድርጎ ያዘው ፡ መሰፍን እየተንገሸገሸ ዋጠው ፡ እና አይኑን ጨፍኖ ቀጣዩን ጠበቀ ፡ ምንም አይነት ለውጥ ፡ስላላሳየ ከሞት ተርፌያለው ብሎ አስቦ ፡ ተቀመጥ በተባለበት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ ፡ቦታው ጎድጎድ ያለ ልክ እንደ ሳፋ ያለ ድንጋይ ነገር ፡ስለሆነ ተሰበሰበ ፡ እግሩን እጥፍጥፍ አድርጎ ፡,,,,,ቀጥሎ ፡አቢያራ በሚያስገመግም ድምፁ " ዳንኤል ናወዲ "ሲል ፡የጓደኛውን ፡ምንም አለመሆን ያየው ፡ዳንኤል ፡ በርታ ብሎ ፡ቀረበ ፡ አቢያራ ፡ለሱም ፡ከፈሳሹ አጠጣው ፡ ፡ዳንኤል ፡ ፊቱን አጨፍግጎ የማይቀርለትን ተጎነጨው ፡ እሱንም ፡መጠጣቱን ካረጋገጡ በዋላ ፡ ወደ ጎድጓዳው ፡ቦታ እንዲሄድ አደረጉት ፡ ቀጥሎ ፡የመሳይ ፡ተራ ደረሰና አቢያራ "መሳይ ናወዲ "ሲለው ፡መሳይ ፡ ድንጋጤና መረበሹ ይበልጥ አይሎ ፡ በተቀመጠበት ተሰፍቶ ፡ቀረ "መሳይ ና ወዲ "መሳይ አልንቀሳቀስ አለ ፡አቢያራ ተቆጣ ፡በዚ ጊዜ ፡ ሰውዬው ፡ ወደመሳይ በመሄድ ፡"አንተ ትንሽዬ ደደብ ፡ ተንቀሳቀስ እንጂ አባቴን አታስቆጣው ፡ "አለው ፡መሳይ ፡በድን ፡ሆነ ሰውዬው ፡አቢያራ ከመናደዱ በፊት ፡ሊያስገድደው ፡ሞከረ ፡ አቢያራ "ተወው አድማስ መምጣቱ አይቀርም ፡ዞር በል ፡ካጠገቡ ፡"አለው ፡ በዚ አጋጣሚ ይዟቸው ፡የመጣው ፡ሰው ፡አድማስ ፡እንደሆነ ስሙ አወቁ ፡ አንተን ብሎ አድማስ ፡ብሎ ፡መስፍን ፡በውስጡ ሸረደደው ፡ የጓደኛው ፡ መሳይ ፡ሁኔታ ደሞ፡አስፈራው ፡ አንድነገር ፡እንዳያደርጉት በውስጡ ለአምላኩ ፀለየ ፡ ዳንኤልም መሳይን ፡እንዳይገሉት ፡ፈራ ፡ አቢያራ ድምፁ ወደ አስፈሪነት ይበልጥ ፡ተቀየረ "መ ሳ ይ ና ወደኔ አሆሆሆሆይ መሳ ይ "ጩኽቱ በፍርሃት ፡አራዳቸው ፡ መሳይ ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፡ ወባ እንደያዘው፡ ሰው አንዘፈዘፈው ፡ አደማስ ፡ ከኪሱ የሚያብረቀርቅ ፡ ስለት አውጥቶ ፡ ለመሳይ ፡አሳየው ፡ አቢያራ ፡ ማጓራትና መጮሁን ፡ቀጠለ ፡ ንዴት ፡ቀጣ ውስጥ ፡እንደገባ በግልፅ ፡ታየ ፡ መሳይ ፡አይኖቹ ብቻ መርገብገብ ፡እና መቁለጭለጭ ሆነ ሰውነቱ ለመንቀሳቀስ አልታዘዝ አለው ፡ ደጋግሞ የፈጣሪውን ፡ስም ፡በልቡ ጠራ ,,,,,,,,,,,,
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል

👍36❤1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ደቂቃዎች በረሩ ላራት ሰዓት ሩብ ጕዳይ አራት ተሩብ አሁንም ሪቻርድ ሔር ከእናቱ ጋር እንዳለ ነው " ሚስተር ካርላይልና ባርባራም በአትክልቱ ቦታ መኽል ባለዉ እግር መንገድ እስከዚያ ሰዓት ድረስ በትዕግሥት ይመላለሳሉ አራት ሰዓት ተሩብ ላይ ሪቻርድ ሔር ከናቱ ተሰናብቶ መጣ " ባርባራም ዕንባዋን እያወረደች ተሰናበተችው በመጣበት ለመሔድ ወደ ዐፀዱ ገባ "
“ በይ ባርባራ . . . ደኅና እደሪ " በጣም ስለመሸ ሚስዝ ሔርን አልተሰናበትኳቸውም " ሆኖም ሁሉ ነገር ደኅና በመሳካቱ የተሰማኝን ደስታ ንገሪልኝ ”ብሏት ሔደ እሱ በሰው እየተራመደ ወደ ቤቱ ሲገሠግሥ ባርባራ ብሶቷ በዕንባ እስኪወጣላት ድረስ ከበሩ ብረት ተደግፋ ማንም
ሳያቋርጣት እያነባች ዐሥር ደቂቃ ያህል ቆየች " እናቷም የራሷን የውስጥ ብሶት ስታስተነትን ፈጽማ ረስታት ኖሯል። ባርባራ ከዚያ እንደ ቆመች ፈጣን የእግር ዳና ስትሰማ በጣም ድንግጥ አለች ወዲያው ግን ሚስተር ካርላይል መሆኑን ዐወቀችው "
“ በውስጡ አንድ ብራና የያዘ ጥቅል ትቼ ነበር እባክሽ አምጭልኝ” ባርባራ
ስትበር ሔዳ አመጣችለት ሚስተር ካርላይልም ተቀበለና ባጭሩ አመስግኖ ወደ ቤቱ ገሠገሠ ። እሷም እንደ ነበረችው ከበሩ ተደግፋ በካርላይል መምጣት ተቋርጦ
የነበረውን ዕንባዋን ትለቀው ጀመር በወንድሟ ነገር አንጀቷ አሯል ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ካፒቴን ቶርን ሳይሆን በመቅረቱ የባሰውን በግናለች አሁንም ግና የአባቷ ዳና አልተሰማም እሷም ቁማ መጠበቋን ቀጠለች » ትንሽ ቆይታ በቁጥቋጦቹ ታኮ አንድ ስው ከሩቅ ታያት " እሷም የድንጋጤ ሀይኖቿን አፍጣ ተመለከተች " ልቧ ነጥሮ የሚወጣ እስኪመስል ይመታ ጀመር " ሪቻርድ መሆኑን ስታውቅ
ምን ጉዳይ አሳብዶ እንደ መለሰው ገረማት አሁንም ከደጅ ሲያገኛት ጊዜ ያባቱን
አለመግባት አረጋገጠና ያለ ሥጋት ተጠጋ " የሠራ አካላቱ እየተንቀጠቀጠ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ የሚሆነው ጠፍቶታል "
“ ባርባራ ! ባርባራ !.... ” አላት በኃይል እየቃተተ “ቶርንን አየሁት !
ራሱን ቶርንን በአካል አገኘሁት ”
ባርባራ እንግዳ ነገር ሆነባትና አፍጣ ታየው ጀመር
“ልክ ከዚህ እንደ ወጣሁ ሰው ስለማይበዛበት ከዚህኛው መንገድ ይሻላል
በማለት ወደ ቢን ሌን አቋርጨ ስሔድ አንድ ሰው ከሩቅ ሲመጣ አየሁ ምንም እንኳን ሌላ ለመምሰል ብሞክርም ማንም እንዲያገኘው ስለ አልፈለግሁ ወደ ዛፎቹ
ዘወር አልኩ እሱ መኻል መንገዱን ይዞ ወዶ ዌስትሊን ሲሔድ አየሁት ግና ከአጠገቤ ሳይደርስ ዐወቅሁት "
የሠራ አካላቴን ወረረኝ " እያንዳንዷ የደሜ ጠብታ የምትሯሯጥብኝ መሰለኝ" ዘለህ እነቀው የሆሊጆን ገዳይ ነው ብለህ አስይዘው የሚል ሐሳብ መጣብኝ
ሁኔታውን ገምግሜ ቀጥቅጦ እንዳይገለኝ ፈራሁና ተውኩት አየሽ... ደሞኮ አንድ ጊዜ ነፍስ ያጠፋ ሰው ሁለተኛ ለመድገም ወደ ኋላ አይልም አላት። "
«ሪቻርድ እርግጠኛ ነህ ? ስለ ቶርን ብዙ ስለምትናገር እንዲያው በሐሳብህ
መጥቶብህ እንዳይሆን ?አለችው "
ምን ነካሽ ... ባርባራ ሐሳብ? ከዚህ ተቀርጿል አላልኩሽም ? አላት ወደ
ልቡ እያመለከተ " በየጥላው ሥር ቶርንን አየሁ የምል ሰው በለበት ሰው የሚታየኝ ሕፃን መሰልኩሽ ወይንስ ዕብድ? በአንድ እጁ ባርኔጣውን ይዞ በሌላው ፀጉሩን ከግንባሩ የኋሊት እያስተኛ አሁንም አሁንም ጸጕሩን የኋሊት የመግፋት
ልምድ አለው በጣም እየተጣደፈ ይራመድ ነበር ጸጉሩን እንደዚያ ወደ ኋላ
በሚመልስበት ጊዜ የጣቱ አልማዝ በጨረቃው ብርሃን ይፈልቅ ነበር " ምንም አትጠራጠሪ።
ባርባራ በደንብ ካዳመጠችው በኋላ እሷም እንደሱ ስሜቷ ተቀሰቀሰ ድንጋጤዉ እንቅቃጤዉ ጥድፊያዉ ጉጉቱ እንዳለ ተጋባባት ። ማሰብ ማማዘን
ቦታ ለቀቁ።
በግብታዊ ስሜት ብቻ ተነዳች " የሪቻርድ አባባል ሙሉ በሙሉ እንዳመነችቐት
ምን እንደምታደርግ በማሰብ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም :
ምናልባት በዚያ ሰዓት ሰው ቢያገኛት ምን እንደሚላት በመዘንጋት አባቷ ከቤት ሲገባ ቢያጣት ምን እንደሚል በመርሳት ሪቻርድ ሔር ቀስ ብሎ ዙሪውን እያስተዋለ በሩቁ እየተከተላት ወደ ሚስተር ካርላይል እየሮጠች ሔዶች ገና ኢስትሊን በር ሊገባ ሲል ደረሰችበት "
“ባርባራ. . . ምን ነው በደኅናሽ ነው ?”
“ አርኪባልድ ! አርኪባልድ ! አለች ከትንፋሿ ጋር እየተናነቀች " እሱስ
ደኅና ነኝ' አንድ ጊዜ ሪቻርድን አነጋግረው ቶርንን አይቶታል ”
ሚስተር ካርላይል ምልስ አለና ወደ ቁጥቋጦች ዘወር ብለው ሪቻርድ ያየውን
ነገር ዝርዝር አድርጎ አጫወተው እሱም ምናልባት ሪቻርድን ላለማስከፋት ብሎ
እንደሆነም አይታወቅም : ልክ እንደ ባርባራ ሙሉ በሙሉ ሳይጠራጠር ያመነው መሰለ "
“ ሪቻርድ ... ዛሬ ማታ ከቢሮዬ ካየኸው ሰው በቀር በዚህ አካባቢ ቶርን የሚባል ሰው ጭራሽ የለም” አለው ካርላይል ትንሽ ካሰበ በኋላ “ የሚገርም ነገር ነው …”
“ አሁን ያገኘሁት ሰው ቶርን ለመሆኑ አልጠራጠርም ምናልባት እሱ እዚ
ያለው በሌላ ስም ሊሆን ይችላል።
አለባበሱ ምን ይመስል ነበር ? አለው ካርላይል።
እንደ ፈለገ ቢለብሰው ሰውየው አያሳስትም ” አለ ሪቻርድ “ የማታ ልብስ ለብሶ ቀጭን ካፖርት ብጤ ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ ነበር " ለባርባራ እንደነገርኳት ጸጉሩን ከግንባሩ ወደ ኋላው በመግፋት ልምዱ ብቻ በቀላሉ ዐውቀዋለሁ
በተጨማሪ ደግሞ ለስላሳ ነጭ የሆነው እጁና የሚያንጸባርቀው የአልማዝ
ቀለበቱ ዋና ምልክቶች ናቸው ”
"በል እንግዲያው ሪቻርድ ... እኔ አሁን የምመክርህ ከዚህ አንድ
ቀን ሰንብትና ይህን ሰውዬ ፈልገው » ድንገት ያየኸው እንዪሆነ የት እንደሚገባ
ተከታተለው ከተቻለ የዚህን ሰው ማንነት ማወቅ በጣም አስፌላጊ ነው አለው
በሚስተር ካርይል
"ብገኝ የሚጠብቀኝ አደጋሳ ?”
አንተ ደግሞ በጣም ስለ ተለዋወጥክ ቀን ለቀን በአደባባይ ብትሔድ እንኳን
የሚያውቅህ አይገኝም : "
ሪቻርድ በሚስተር ካርይል አነጋገር ሊተማመን ስለ አልቻለ ስለአየው ሰውዬ
ምልክት ዝርዝር አድርጎ ከገለጸላቸው በኋላ ለማንኛውም አስፈላጊ ነገር
የሎንዶን አድራሻውን ሰጥቶ ሔደ "
“ በይ እንግዲሀ ልሸኝሽ እንጂ .. ባርባራ ” አለ ሚስተር ካርላይል "
“ በጭራሽ አይሆንም ! እንደዚህ ጊዜው መሽቶ አንተ ደክሞህ እያለህ ሁለተኛ መንገድ አላስመታህም " አሁንም ስመጣ ብቻዬን ነበርኩ " ሪቻርድም እንኳን አብሮኝ አልነበረም ።
ስትመጭ ምንም ነገር ማድረግ ባልችልም አሁን ከሌሊቱ እምስት ሰዓት
ላይ በአውራ ጐዳና ብቻሽን ስትሔጅ ዝም ብዬ አላይሽም ” አለና ክንዱን ዘረጋላት " ተያይዘው ጉዞ ጀመሩ "
“አቤት ይህን ያህል አምሽተህ ስትገባ እቤት ሳቤላ ምን ትልህ ይሆን?”
“ እስካሁን ከግብዣው የምትመለስ አይመስለኝም ደሞም አንዴ ብቻ በአንድ ምክንያት ማምሸቴ ይህን ያህልም አይደለም ”
ከበሩ አድርሷት ተመለሰ እሷ ከቤት ስትገባ አባቷ አሁንም ገና አልመጣም
ነበር "
ሚስተር ካርይል ከቤቱ ሲደርስ ሳቤላ ከመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ተቀምጣ ስትጽፍ አገኛት " ስለ ግብዣው አንዳንድ ነገር ጠይቋት ባጭሩ ቁርጥ ቁርጥ እያደረገች
መለሰችለት " በመጨረሻም ለምን እንደማትተኛ ጠየቃት
“ እንቅልፌ አልመጣም ”
“ እኔ ግን ቶሎ መተኛት አለብኝ " ... ሳቤላ ሙትት ብዬ ደክሜአለሁ ”
" ትችላለህ ” አለችው "
ሊስማት ጐንበስ ሲል ፊቷን በዘዴ ዞር አደረገችበት ወደ ግብዣው አብሯት ባለመሔዱ የተቆጣች መሰለውና እጁን ከትከሻዋ ጣል አድርጎ ፈገግ አለ "

👍12
አንቺ የዋህ ሕፃን...አሁን በዚህ ትቆጫለሽ ?ወድጄ እንዳይመስልሽ የኔ ጥፋት አይደለም " አሁን ደክሞኛል " ሁሉንም ጧት እነግርሻለሁ አንቺም ቢበቃሽና ብትተኝ ይሻላል።
እሷ ግን ጽሕፈቷ ላይ
እንዳቀረቀረች ምንም አልመለሰችለትም "ሚስተር
ካርላይል ከመኝታ ቤቱ ገብቶ በሩን ዘጋ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሳቤላ ቀስ ብላ ወደ ጆይስ መኝታ ቤት ወጣች ጆይስ ድንገት ብንን ብላ ስትነቃ እመቤቷ ከፊቷ ቁማ አየቻት አይኗን አሻሽታ
ዙሪያውን አስተውላ ሀሳቧን
ተው " ላብን አረጋጋችኛ ከአልጋው ጠርዝ ተቀመጠች
"እሜቴ አመመዎት?"
"አዎን አሞኛል ' መሮኛል ” አለቻት ወይዘሮ ሳቤላ " እውነትም ፊቷ ወርዝቶ የታመመች ትመስል ነበር
“ጀይስ ቃል እንድትግቢልኝ እፈልጋለሁ በኔ ላይ አንድ ነገር ቢደርስ አንቺ ከልጆቼ ጋር ኢስት ሊን እንድትቀመጭ ከዚህ
በፊትም ቃል ገብተሽልኝ ነበር እንደገና ድገሚልኝ የመጣ ቢመጣ እኔ ከሌለሁ
አንቺ ከልጆቼ አንዳትለይ "
“እኔስ እሽ ከነሱ አልለይም " ግን ምን አገኘዎ ድንገተኛ በሽታ ታመሙ?
"ደኅና ሁኚ ጆይስ ” ብላት እንዳመጣጧ ቀስ ብላ ወጣች " ጆይስ ግራ እንደ
ተጋባች ለአንድ ሰዓት ስታስብ ከቆየች በኋላ እንቅልፍ ወሰዳት "
ሚስተር ካርይልም በበኩሉ ተኝቶ ቆየና ሲነቃ ሚስቱ ወደ አልጋው አለመምጣቷን አየ " ነገሩ ገረመውና ሰዓቱን ሲያይ ከሌሊቱ ዘጠኝ ተሩብ ሆኗል »
ተነሣና ወደ መልበሻ ክፍሏ ቢሔድ ጨለማ ሆነበት " ቢያዳምጥ ትንፋሽ እንኳን
አልነበረም " ስለዚህ ከዚያ ክፍል አለ መኖሯን ገመተ።
“ ሳቤላ ” ብሎ ጠራት ።
መልስ የለም " ጭልል ባለው ሌሊት የገዛ ድምፁ አያስተጋባ ነጥሮ ከመመለስ በቀር ምንም ምላሽ አጣ " ክብሪት ጭሮ ጧፍ አብሮቶ እንደ ነገሩ ለባበሰና ፍለጋ ወጣ " ታማ እንደሆነ ብሎ ሠጋ " ወይንም ደግሞ ከአንዱ ክፍል ተኝታ ይሆኖል
የሚል ሐሳብም መጣበት " ነገር ግን በየክፍሉ ፈልጎ አጣት ግራ ገባው ! የሚያደርገው ጠፋው ቢቸግረው ወደ እኅቱ መኝታ ቤት ሔዶ አንኳኳ ።
ሚስ ካርላይል ከእንቅልፋ ለመንቃት ትንሽ ምክንያት ነበር የሚበቃትና ወዟ
ዲያው ብድግ አለች "
“ ማነው ? "
“ እኔ ነኝ ...ኮርኒሊያ "”
“ አንተ ! ምን ሆንክ ? ግባ እስቲ „”
ሚስተር ካርላይል ከፍቶ ገባ " አንድ ክንድ የሚያህል የሌሊት ቆብ ደፍታ
ንቁ ዐይኖቿን እያቁለለጨች አገኛት "
“የታመመ ሰው አለ ?
" እኔ እንጃ ሳቤላ ታማለች መሰለኝ " ብፈልግ አጣኋት
“ አጣኋት ? እንዴት ?
ከመኝታዋ የለችም ? ስንት ሰዓት ነው ?” እያለች
ጮኸች "
“ አሁን ዘጠኝ ሰዓት" ከነ ጭራሹ ወደ መኝታ ቤት አልገባችም " ከክፍሎቹ
ሁሎም የለችም " ከልጆቹ ቤት ብሔድም አጣኋት "
“ እንግዲያውስ ልንገርህ አርኪባልድ የጆይስ ነገር አሳስቧት ልታያት ሔዳ ነው " ምናልባት አሁን ደግሞ አሟት ይሆናል " "
ሚስተር ካርላይል እንደ ተጠቆመው ወዶ ጆይስ ክፍል ሲንደረደር እህቱ ጠራችው
አርኪባልድ ” ጆይስ የሆነችው ነገር ካለ መጥተህ እንድትነግረኝ እኔም ሔጄ አያታለሁ " ምንም ቢሆን ልጂቱ ሚስትሀ ሳትወስዳት የኔ ገረድ ነበረች
ከጆይስ ክፍል ደረስና መብራት በርቶ ሚስቱ ከአልጋው ጐን ተቀምጋ እንደ ሚያገኛት በመተማመን በሩን ቀስ አድርጎ ከፈተው በጁ ከያዘው ጧፍ በቀር ምንም
መብራት አልበረም » የሚስቱ ምልክትም የለም ከምን ገባች ? ምናልባት ጆይስ ልትነግረው ትችል ይሆን? ቀረብ አለና ቀሰቀሳት....

👍15🤔2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...“እናታችንን መዝረፍ አለመቻሌ ሲገባኝ አያትየው ክፍል ሄጄ ለመስረቅ ወሰንኩ” አለኝ።
አምላኬ አይሆንም... ማድረግ አይችልም ግን ደግሞ በጣም ጥሩ በቀል ነው! ስል አሰብኩ። “ታውቂያለሽ… ጌጣጌጦች አሏት: ጣቶቿ ላይ ብዙ ቀለበቶች እና በዚያ ላይ የደንብ ልብሷ አንድ ክፍል እንደሆነ ሁሉ እድሜዋን
በሙሉ የምታደርገው የአልማዝ ጌጥ አላት እንደገናም በገና ግብዣው ላይ አድርጋቸው ያየናት እነዚያ አልማዞችም አሉ። እሷ የሚሰረቅ ብዙ ነገር እንዳላት አውቄያለሁ: በጨለማው መተላለፊያ አቋርጬ በጣቶቼ
እየተራመድኩ የአያትየው የተዘጋ ቢሮ ጋ ደረስኩ።”
ያንን ለማድረግ መድፈሩ እኔ መቼም በፍፁም . . .
“በበሩ ስር የሚታየው ቀጭን ቢጫ የብርሀን መስመር አሁንም እንቅልፍ
እንዳልተኛች እያስጠነቀቀኝ ነበር፡ ምርር አለኝ፡ መተኛት ነበረባት። ሁኔታዎቹ ያ ብርሀን እዛው እንድቆይና አሁን ካደረግኩት የባሰ አጉል ነገር እንዳላደርግ
አደረገኝ ወይም አሁን አንቺ የድርጊት ሰው ከሆንሽ በኋላ አንድ ቀን የቃልሽ ሰው ለመሆን እቅድ ስላለሽ “ድፍረት” ብለሽ ልትጠሪው ትችይ ይሆናል:"
“ክሪስ ከርዕሱ አትሽሽ! ቀጥል! ምን አይነት የእብደት ስራ እንደሰራህ ንገረኝ! አንተን ብሆን ኖሮ ፊቴን አዙሬ ቀጥታ ወደዚህ እመለስ ነበር!”
“እኔ አንቺን አይደለሁማ ካተሪን፣ እኔ እኔ ነኝ... ትንሽ ጥንቃቄ ተጠቅሜ
በቀስታ በሩን በትንሹ ከፈትኩ… በእያንዳንዷ ሰኮንድ ሲከፈት ድምፅ ያሰማል ብዬ ፈርቼ ነበር። ነገር ግን የሆነ ሰው መታጠፊያውን ዘይት አጥግቦታል:: እና እሷ ታየኛለች ብዬ ሳልፈራ በተከፈተው በር ወደ ውስጥ ተመለከትኩና ወደ ውስጥ ገባሁ:"
“እርቃኗን ሆና አየሀት?!” አቋረጥኩት።
“አይ!” ትዕግስት ባጣና በተናደደ አይነት መለሰልኝ፡ “እርቃኗን ሆና አላየኋትም እና በዚያም ደስ ብሎኛል፡ አልጋ ውስጥ ብርድ ልብሱ ስር ነበረች: እጅጌው ረጅም የምሽት ገዋን ለብሳ ተቀምጣ ነበር በትንሹ እርቃኗን ሆና አይቻታለሁ። ታውቂዋለሽ ያ የምንጠላው ብረት የሚመስለው ፀጉሯ
ጭንቅላቷ ላይ አልነበረም ሌሊት ድንገት አስቸኳይ ነገር ቢያጋጥም
አጠገቧ መሆኑን እርግጠኛ ለመሆን የፈለገች ይመስል ቅርብ ኮመዲኖ ላይ
ተቀምጧል"
“ዊግ ነው የምታደርገው?” ብዬ በመገረም ጠየቅኩት ግን ማወቅ ነበረብኝ
“አዎ ዊግ ታደርጋለች የክሪስማስ ግብዣው ዕለት ያደረገችውም ፀጉር ሳይሆን ዊግ ነበር። ጭንቅላቷ ላይ የቀረው ፀጉር የሳሳና ወደ ቢጫ የሚያደላ ነጭ ነው፡ እና ጭንቅላቷ ፀጉር የሌለባቸው ሰፋፊ ሮዝ ቦታዎች አሉት ረጅሙ አፍንጫዋ ጫፍ ላይ ጠርዝ የሌለው መነፅር ሰክታ ትልቅ ጥቁር መፅሀፍ ቅዱስ ታነባለች አሁን ከእሷ መስረቅ እንደማልችል ሳውቅ እየተመለከትኳት
መፅሀፍ ቅዱሱ ውስጥ ያቋረጠችበትን ቦታ በፖስት ካርድ ምልክት አድርጋ ኮመዲኖው ላይ አስቀመጠችና ከአልጋዋ ወርዳ ተንበረከከች ከዚያ አንገቷን አቀርቅራ እኛ እንደምናደርገው እጆቿን አገጯ ስር አደራርባ ረጅም ፀሎት ፀለየች:: ከዚያ ጮክ ብላ “ጌታ ሆይ ስለ ኃጢአቴ ይቅር በለኝ፡ ሁልጊዜ የምሰራው ጥሩ ነው ብዬ የማስበውን ነው እና ስህተቶች ከሰራሁ እባክህ ትክክል ለመስራት አስቤ እንደሆነ እመንልኝ በአንተ አይኖች ለዘለዓለም ፀጋ
ላግኝ አሜን ከተንበረከከችበት ተነስታ አልጋዋ ውስጥ ገባችና መብራቱን አጠፋች አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ምን እንደማደርግ አሰብኩ ባዶ እጄን ወዳንቺ ተመልሼ መምጣት አልቻልኩም:: ምክንያቱም አባታችን ለእናታችን የሰጣትን ቀለበቶች እንደማንሽጣቸው ተስፋ አድርጌያለሁ "
ቀጠለ. አሁን እጆቹ ፀጉሬ ላይ ናቸው፡ ጭንቅላቴን እየዳበሱኝ ነው። “ ወደ ዋናው ክፍል ሄድኩና የወንድ አያታችንን ክፍል አገኘሁት፡ በሩን ከፍቼ ያንን እዚያ ተጋድሞ ከአመት አመት ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው
የመጋፈጥ ድፍረት እንዳለኝ አላውቅም ነበር።
“ግን ይህ ብቸኛው እድሌ ነው: እጠቀምበታለሁ። የመጣው ይምጣ ብዬ
ልክ እንደ እውነተኛ ሌባ ድምፅ ሳላሰማ በደረጃው ወደ ታች ወረድኩ።ትልልቆቹን ውድ ክፍሎች አየሁ። በጣም ግዙፍና የሚያምሩ ነበሩ ልክ አንቺ እንደምታስቢው እኔም እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ ስለማደግ አሰብኩ
በብዙ ሰራተኞች ተከቦ ሁሉ ነገር በሰው ሲቀርብ ያለውን ስሜት አሰብኩ።
ኦ ካቲ፣ በጣም ቆንጆ ቤት ነው እቃዎቹ ከቤተመንግስት የመጡ መሆን አለባቸው: እናታችን ብዙ ጥያቄዎች ትጠይቂያት ስለነበር ወደ ቤተ መፃህፍት
የሚወስደውን መንገድ አውቄዋለሁ እና ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ካቲ?
ብዙ ጥያቄዎች በመጠየቅሽ በጣም ደስ ብሎኛል ባይሆን ኖሮ ከመሀሉ ተነስተው ወደ ግራና ወደቀኝ የሚታጠፉ ብዙ አዳራሾች ስለነበሩ ይጠፉብኝ ነበር:
“ግን ወደ ቤተመፃህፍቱ መሄድ በጣም ቀላል ነበር። ረጅም፣ ጨለማማ፣ በጣም ግዙፍ ክፍል ሆኖ ልክ እንደመቃብር ስፍራ ፀጥ ያለ ነው::"
ለመስማት የምናፍቀው የነበረውን ነገር እየነገረኝ ነው: በረጅሙ ተነፈስኩ።
መሳቢያዎቹ ውስጥ ገንዘብ እንደሚደበቅ ገምቻለሁ። ስለዚህ ባትሪዬን እያበራሁ
እያንዳንዱን መሳቢያ መፈተሽ ጀመርኩ አንዳቸውም አልተቆለፉም: እና ሁሉም ባዶ፣ ሙሉ በሙሉ ባዶ በመሆናቸው አለመቆለፋቸው አይገርምም እነዚያ ሁሉ ባዶ መሳቢያዎች፣ የወረቀት መያዣዎች፣ እርሳሶች፣
እስኪሪብቶዎች፣ ማስታወሻ ደብተሮች የመሳሰሉት ነገሮችን ለማስቀመጥ
ካልተጠቀሙባቸው መሳቢያው ለምን ይጠቅማል? ወደ ሀሳቤ የመጡት ጥርጣሬዎች ምን እንደሆነ አታውቂም: የዚያን ጊዜ ነው ከቤተመፃህፍቱ
ባሻገር ያለው የወንድ አያቴ ክፍል ለመግባት የወሰንኩት በመጨረሻ ላገኘው ነው... ከምጠላው አያቴ… እንዲሁም አጎቴ ጋር ፊት ለፊት ልገናኝ ነው:
“ግንኙነታችንን በሀሳቤ ሳልኩት እሱ አልጋ ላይ ነው ታሟል። ግን አሁንም
መብራቱን አበራዋለሁ: ከዚያ ያየኛል ትንፋሽ ያጥረዋል። ይለየኛል... ማን እንደሆንኩ ማወቅ አለበት: አንድ ጊዜ ሲያየኝ ወዲያውኑ ያውቃል፡ ከዚያ
እኔ “አያቴ… እንዲወለድ ያልፈለከው የልጅ ልጅህ እኔ ነኝ. እለዋለሁ:: ፎቁ ላይ በሰሜን በኩል ባለው የመኝታ ክፍል ውስጥ የተቆለፈባቸው ሁለት እህቶች አሉኝ በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድምም ነበረኝ፡ አሁን ግን ሟቷል እንዲገድሉት ረድተሀቸዋል” ይሄ ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ ነበር።ግን አንዳቸውንም ስለማለቴ ተጠራጥሬያለሁ። አንቺ ብትሆኚ ግን ጮኸሽ እንደምታወጪው ጥርጣሬ የለኝም:: ልክ ኬሪ ራሷን የምትገልፅበት ቃላት
ሲኖራት እንደምታደርው አይነት ማለቴ ነው አንቺ ግን ቃላቶቹ አሉሽ ምናልባት እናገረዋለሁ፣ ሲሸማቀቅ አይቼ እደሰት ይሆናል ወይም ምናልባት ሀዘኔታ ያሳይ ይሆናል ወይም በህይወት በመኖራችን የጋለ ብስጭት ያድርበት ይሆናል፡ ይህንን አውቃለሁ ከአሁን በኋላ ግን ለተጨማሪ አንድ ደቂቃ
እንኳን እስረኛ ሆኜ ኬሪም እንደ ኮሪ ስትሞት ማየትን መቋቋም አልችልም::
ትንፋሼን ዋጥኩ። አሁንም ሞቱን በሚጠብቅበት አልጋ ላይ ተጋድሞ፣ ያ ጠንካራ የመዳብ የሬሳ ሳጥን እስኪገባበት እየጠበቀው ቢሆንም የምንጠላውን

👍50❤2
አያታችንን ለመጋፈጥ ድፍረቱ ገርሞኛል: ቀጥሎ የሚመጣውን ነገር ትንፋሽ አጥሮኝ እየጠበቅኩ ነው:
“ላስገርመው በማቀድ የበሩን እጄታ በጥንቃቄ አዞርኩት በድፍረት እግሬን አንስቼ በሩን በርግጫ ብዬ እከፍተዋለሁ ብዬ አስቤ ስለነበረ ያንን ባለማድረጌ እፍረት ተሰማኝ፡ ውስጡ በጣም ጨለማ ስለነበር አንድም ነገር ማየት
አልቻልኩም: ባትሪዬንም መጠቀም አልፈለግኩም: ማብሪያ ማጥፊያ ፍለጋ ግድግዳውን ብዳስስም አንድም ማግኘት አልቻልኩም: ከዚያ የያዝኩትን ባትሪ
ሳበራ የሆስፒታሉ አልጋ ነጭ እንደተቀባ ተመለከትኩት።
ዝም ብዬ አፈጠጥኩ፡ ምክንያቱም ያየሁት ያልጠበቅኩትን ስለነበረ ነው ፍራሹ ታጥፏል። ባዶ አልጋ፣ ባዶ ክፍል እንጂ እየሞተ ያለ ለመተንፈስ የሚታገል፣ በህይወት ለመቆየት የሚያግዙት ብዙ ማሽኖች የተገጠሙለት
አያት እዚያ የለም ልክ ሆድ ላይ በጣም እንደመመታት ነበር፤ ላገኘው ራሴን ሳዘጋጅ እሱን ግን እዚያ ማየት አልቻልኩም
“ከአልጋው ብዙም ሳይርቅ ጥግ ላይ ከዘራ ተቀምጧል። ከከዘራው አጠገብ ደግሞ ቁጭ ብሎበት ያየነው የሚገፋ ወንበር ተቀምጧል። ብዙ ጊዜ አልተቀመጠበትም መሰለኝ አዲስ ይመስላል። ከሁለቱ ወንበሮች በተጨማሪ አንድ ዕቃ ብቻ ነው ያለው: እሱም ባለመስተዋት ኮመዲኖ ብቻ ነው ግን
ምንም ነገር አልነበረበትም: የፀጉር ቡሩሽ የለ፣ ማበጠሪያ የለ፣ ምንም
የለ ክፍሉ ልክ እናታችን ትታው እንደሄደቸው ክፍል ባዶ ነበር። የወንድ አያትየው ታሞ የተኛበት ክፍል ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ አይመስልም አየሩ የታፈገና እምክ እምክ የሚሸት ነው: ባለመስተዋቱ ኮመዲኖ ላይ አቧራ አለ በኋላ ልንጠቀምበት የምንችለው ዋጋ ያለው ነገር ፍለጋ ተጠግቼ አየሁ። ምንም... እንደገና ምንም የለም። በንዴት ተስፋ መቁረጥ ተሞልቼ ወደ ቤተመፃህፍቱ ተመለከትኩና እናታችን የነገረችንን ግድግዳው ላይ ያለውን ሚስጥራዊ የገንዘብ ካዝና የከለለውን ልዩ የመልክአ ምድር ስዕል መፈለግ ጀመርኩ።
“በቲቪ ሌቦች ካዝናዎችን ሲከፍቱ ስንት ጊዜ እንደተመለከትን ታውቂያለሽ እና በጣም ቀላል ይመስላል። ማድረግ ያለብሽ ጆሮሽን መክፈቻው ላይ አድርገሽ ቀስ ቀስ እያሉ ማዞርና በጥንቃቄ ማዳመጥ ከዚያ ቀጭ... የሚል ድምፅ ሲያሰማ ያንን መቁጠር. አሰብኩት። ከዚያ ቁጥሮቹ ይታወቃሉ። በትክክል መደርደር እና ቀጥሎ ብራቮ! ካዝናው ይከፈታል።"
አቋረጥኩት “ወንድ አያትየው ለምንድነው አልጋው ላይ የሌለው?”
ልክ እንዳልተናገርኩ ሁሉ ዝም ብሎ ቀጠለ “እያዳመጥኩ ቀጭ የሚል
ድምፅ እየሰማሁ ነው። እድለኛ ካልሆንኩ የብረት ካዝናው ሲከፈት ባዶ ሊሆን ይችላል። ምን እንደተፈጠረ ታውቂያለሽ ካቲ? ቁጥሮቹን የሚነግረኝ
ቀጭ የሚል ድምፅ እያዳመጥኩ ነው ግን በፍጥነት መቁጠር አልቻልኩም! የካዝናው መዝጊያ አልተከፈተም… ድምፁን ብሰማም በደንብ አልገባኝም።መፃህፍት እንዴት አሪፍ ሌባ እንደሚኮን ትምህርት አይሰጡም: በተፈጥሮ
የሚመጣ መሆን አለበት ከዚያ በመቆለፊያው በኩል አስገብቼ የምከፍትበት የሆነ ጠፍጣፋና ጠንካራ ነገር መፈለግ ጀመርኩ፡ የዚያን ጊዜ ነው የእግር
ኮቴ የሰማሁት:
”ለእሱ ደነገጥኩ..
“በፍጥነት ወደ አንዱ ሶፋ ጀርባ ሄጄ በሆዴ ተኛሁ ... የዚያን ጊዜ ባትሪዬን የወንድ አያትየው ክፍል ውስጥ መርሳቴን አስታወስኩ”
“አምላኬ!”
“ተጋለጥኩ ስል አስብኩ ግን ሳልንቀሳቀስ ፀጥ ብዬ ተጋደምኩ ከዚያ የሆኑ ወንድና ሴት ወደ ቤተመፃህፍቱ ገቡ፡፡ በመጀመሪያ የተናገረችው ሴቷ ነበረች::ደስ የሚል የሴት ድምፅ አላት
“ጆን” አለች “የሌለ ነገር ሰምቼ አይደለም እምላለሁ፡ ከዚህ ክፍል ውስጥ የመጣ ድምፅ ሰምቻለሁ"
“አንቺ ሁልጊዜ የሌለ ነገር ትሰሚያለሽ” ሲል ወንዱ በከባድ ድምፅ አጉረመረመ::
ከዚያ ሁለቱም በግማሽ ልብ ቤተመፃህፍቱን ማሰስ ጀመሩ ከዚያም ባሻገር ወዳለው የመኝታ ክፍል ገቡ ከአሁን አሁን ባትሪውን አገኙት እያልኩ ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ እየጠበቅኩ ነበር፡ ግን በሆነ ምክንያት አላገኙትም::
እንደምጠረጥረው ጆን ሴቷን እንጂ ሌላ ምንም ነገር ለማግኘት አልፈለገም::ከዚያ ተነስቼ ቤተመፃህፍቱን ለቅቄ ልወጣ ስል ተመልሰው መጡና ከጀርባው
የተደበቅኩበት ሶፋ ላይ ወደቁ!
“አየሽ…” አለ ጆን ወደ ቤተመፃህፍቱ መጥተው ሶፋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ።“እዚህም ሆነ እዚያ ማንም እንደሌለ ነግሬሽ አልነበር?” በራሱ የተደሰተ ይመስላል፡ “እውነቴን ነው ሁልጊዜ ጭንቀታም ነሽ ያ ደግሞ ደስታችንን ያጠፋብናል” አላት።
“ግን ጆን የሆነ ነገር ሰምቼያለሁ:"
“እንደነገርኩሽ አንቺ ብዙ የሌሉ ነገሮችን ትሰሚያለሽ: የገሀነምን ደውሎች ሳይቀር ትሰሚያለሽ፡ ዛሬ ጠዋት እንኳ ጣራው ስር ስላሉት አይጦች በድጋሚ
እያወራሽ ነበር። እንዴት እንደሚጮኹ ስትናገሪ ነበር:” “ከዚያ ያ ጆን አጉረመረመ:: ያቺ ውሻ አሮጊት ጣራው ስር ያለው ክፍል ያሉትን አይጦች
ሁሉ ገደለቻቸው በሽርሽር ቅርጫት ውስጥ . . . ሁሉንም አይጦች ሊፈጅ የሚችል ምግብ ይዛላቸው ትሄዳለች ”
ክሪስ ጉሮሮውን አፀዳና ቀጠለ። ሆዴ ውስጥ እንግዳ የሆነ ስሜት ተሰማኝና ልቤ ድምፅ ማሰማት ጀመረች: ሶፋው ላይ የነበሩት ጥንዶች በእርግጠኝነት
ይሰሙታል ብዬ አሰብኩ “አዎ እሷ ክፉና ሀይለኛ አሮጊት ናት᎓ እና እውነቱን ለመናገር ሽማግሌው ይሻላል። ቢያንስ ፈገግ ማለት ያውቃል፡ እሷ ግን እንዴት ፈገግ እንደሚባል እንኳ አታውቅም: በየጊዜው እዚህ ክፍል ላፀዳ
ስመጣ ሽማግሌው ክፍል ውስጥ አገኛታለሁ ... ዝም ብላ ትቆምና ባዶው አልጋ ላይ ታፈጣለች ከዚያ እሱ በመሞቱ እሷ ደግሞ ከሱ የበለጠ ረጅም በመኖሯና አሁን ነፃ በመሆኗ እንዲሁም ጀርባዋ ላይ ተቀምጦ ይህንን አድርጊ
ያንን አታድርጊ የሚላት፣ በተናገረ ቁጥር እንድትዘል የሚጠብቅ ሰው ባለመኖሩ የተደሰተች ይመስል የተመጠነ ፈገግታ ከንፈሯ ላይ ይታያል: አምላኬ ሆይ፣ አንዳንዴ እንዴት እንደምትታገሰውና እሱም እንዴት እንደሚታገሳት
ይገርመኛል አሁን ግን ሞቷል ገንዘቡን ታገኛለች ''
“አዎ ጥቂት ገንዘብ ታገኛለች” አለ ጆን: “ግን ቤተሰቦቿ የተውላት የራሷ
ገንዘብ አላት: ሽማግሌው ማልኮም ፎክስወርዝ የተወውን ሚሊዮኖች
የምታገኘው ልጇ ናት።”
“ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ተጨማሪ አትፈልግም ያለውን ንብረት በሙሉ ለልጁ ስለሰጠ ሽማግሌውን አትውቀሰው ከእሱ ብዙ ችግሮችን ተቀብላለች: ነርሶች የሆነ ነገር ሲሉት እሷ እዚያው እየጠበቀችው እንድታገለግለው ያደርጋት
ነበር እንደባሪያ ነበር የሚያያት፡ አሁን እሷም ነፃ ናት ያንን ቆንጆ ወጣት አግብታለች። አሁንም ወጣት፣ ቆንጆና ባለሀብት ናት። እሷን መሆን ምን ስሜት ይኖረው ይሆን? አንዳንድ ሰዎች ሁሉም እድል አላቸው: እኔ ግን
. . አንድም ኖሮኝ አያውቅም” አለች ልጅቷ።
“እኔስ ማሬ? እኔን አግኝተሻል። ቢያንስ የምትቀጥለዋ ቆንጆ እስክትመጣ ድረስ አለሁልሽ”

👍39❤2