#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ቀኑ ሰኞ ማታ ነው አየሩ ለሰስ ብሏል " ጨረቃ ፍንትው ብላ ወጥታለች "
እንዳይታይ ሠግቶ አንገቱን ደፍቶ ተገን እየመረጠ በእግሩ ከሚጓዘው ብቸኛ የሩቅ መንገደኛ ላይ የሚያበሩት ከዋክብትም ጥርት ብለው ደምቀዋል " ሰውየው የሥራ ካፖርቱን ለብሶ ሶሉ ምስማር የተጠቀጠቀበት ጫማ አድርጎ የጉልበት ሠራተኛ
ይመስላል " ረጅምና ጥቁር ሪዙ ታችኛውን ፊቱን ሲሸፍነው ክፈፈ ሰፊው ባርኔጣው ደግሞ ግንባሩን ዐልፎ ወርዷል " ወደ ሚስተር ሔር ቤት ተጠግቶ ግራና ቀኙን ደኅና አድርጎ ተመልክቶ በአጥር ተንጠልጥሎ ገብቶ ወደ አትክልቱ ቦታ መጣና ዛፎቹ መኻል ተጠግቶ ቆመ።
ሚስተር ሔር እቤት እንግዶች ካልመጡበት በቀር በዓመት ሁለት ቀን
እንኳን አድርጎት የማያውቅውን የዚያን ቀን ከቤቱ አምሽቷል ባርባራ የወንድሟን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአባቷ ከቤት ማምሸት በጣም አስጨንቋታል ካሁን አሁን በመጣ እያለች ስትመኝ እሱ ወንበሩን ወደ መስኮቱ አስጠግቶ ረጂም ፒፓውን ካፉ ሰክቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን ወደ አንድ በኩል
ገደድ አድርጎ በአትክልት ቦታውና በዐፀዱ ሙሉ ትይዩ ተቀምጦ ይመለከታል
“ ዛሬ አትወጣም እንዴ . . . ሪቻርድ '' አለችው ሚስዝ ሔር ፈራ ተባ እያለች
አልወጣም "
“ እማማ . . .የመስኮቱን መከለያዎች ላስዘጋቸው ? አለች ባርባራ "
“ ይዘጉ ?” ብሎ አጉረመረመ " “ ማነው ይህች ጨረቃ እያለች የሚዘጋው የኛ ቆንጆ ብትፈልጊ ፋኖሱ ከዚያ ጥግ አለልሽ ከዚያው ሔዶሽ ተቀመጭ ”
አባትው እንደዚያ በሚመለከትበት ጊዜ ሪቻርድ በድኑንም ይዘልቅና ያየው እንደሆን ብላ በጣም ሠጋች እንደ ፈራችው ምልክቱ መጣ ሲንቀሳቀስ ታያት "ባርባራ ተጨነቀች ነጭ ዐመዷ ቡን አለ » ከንፈሯ ደረቀ ።
አቤት በጣም ምቀኝ ! እኔስ በአትልቱ ቦታ ትንሽ ነፋስ ተቀብዬ ልምጣ መሰለኝ " አለች የመውጫ ምክንያት ፈልጋ "
ጠቆር ባለው የሐር ቀሚሷ ላይ ጠቆር ያለ መደረቢያ ጣል አድርጋ ሹልክ ብላ ወጣችና አባቷ አስተውሎ እንዳይመለከታት እየተጠነቀቀች ሪቻርድን ወዳየችበት ቦታ ሔዳ ተግናኙ ፊቱ ነጥቶ ከስቶ ስታየው በጣም አዘነች " ጸጉሩም እንዳለ
ሸበት መሆኑን ነገራት "
ሪቻርድ አሁን አላነጋግርህም " ዛሬ አባባ ያለ ወትሮው ከቤት አምሽቷል ስለዚሀ ነገ ማታ ተመለስ ”
ለሁለተኛ ምሽት ወደዚህ መምጣት ደስ አይለኝም ... ባርባራ የዚ አካባቢ ምድር በእያንዳንዱ ስንዝር ርቀት አደጋ አለበት
“መቆየትማ አለብህ ...
ሪቻርድ ! ያ ይህን ሁሉ ተንኮል የፈጸመው ቶርን
ዌስት ሊን መጥቷል” እሱ ሆነም አልሆነም ቶርን የሚባል ሰው እዚህ ይገኛል
እኔና ሚስተር ካርላይል
እሱ መሆኑን አምነንበታል
አንተም እንድታየው
እንፈልጋለን እንዴት አይተህ ልታረጋግጥ እንደምትችል ግን ሚስተር ካርላይል
ይነግረናል" ምንም እንኳን ሰውየው አንተ የምትለው ቶርን መሆኑ ስለ ተረጋገጠ
ብቻ አንተን ነፃ ለማድረግ በችኮላ የሚፈጸም ባይሆንም አንድ ትልቅ ነጥብ አጣርቶ መጠበቅም ቀላል ነገር አይደለም ግን አትረሳውም ? እንደምታውቀው እርግጠኛ ነኝ ትጠራጠራለህ?"
“አባቴን አላውቀውማ ! አንቺ አሁን ትጠፊኛለሻ ! አሱንም እንደዚሁ
እይው i ግን እንዴትና መቸ ነው ላየው የምችል ... ባርባራ ?
ሚስተር ካርላይልን እስክጠይቀው ድረስ ልነግርህ አልችልም አንተ ነገ
ማታ በጣም ሳይመሽብሀ እንደ ተመቸህ እዚሀ ድረስ እንድትመጣ " አባባም ከቤት አይኖርም ምናልባት.."
ነጎድጓድ የመሰለው የጀስቲስ ሔር ድምፅ በመስኮቱ አስተጋባ „ “
ባርባራ ብርድ እንዲመታሽ ነው እዚያ የምትንከለከይው አሁን ነይ ግቢ ነው የምልሽ.
“አዝናለሁ ሪቻርድ? . . . ልለይህ ነው” አለችውና በጆሮው “ ነገ ግን
አባባ ከቤት እንደማያመሽ አትጠራጠር ቢሞት አከታትሎ ሁለት ቀን ከቤት
አያመሽም " ደህና እደር ።
አሁን እንግዲህ መጣደፍ አስፈላጊ ሆነባት " የማንንም ሐሜትና ትችት ሳትፈራ ጧት ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ደረሰች " እንደዚያ እየተጣደፈች ?ስትደርስ ሚስተር ካርላይል አልገባም ። ጸሐፊዎቹም የሚገባበትን ሰዓት አላወቁም ።
"ሚስተር ዲል” አለች ባርባራ ሰውየው ሰላም ሊላት ወደሷ ሲመጣ“ ሚስተር ካርላይልን ማግኘት አለብኝ " በጣም እፈልገዋለሁ ”
“ ከሰዓት በኋላ ያውም ቆየት ብሎ ነው የሚገባው ከዚያ በፊት አይመጣም "
እኔ ልረዳሽ የምችለው ጉዳይ ነው?”
“ አይደለም ፣ አይደለም " አለችው በረጅሙ ተነፈሰችና
ሁለቱ ቁመው ሲነጋገሩ ሳቤላ ልጅዋን ትንሿ ሳቤላን ይዛ በሠረገላ ስታልፍ አየቻቸውና ለባርባራ ጅንን ብላ በንቀት እጅ ስትነሣት ለሚስተር ዲል ደግሞ ደመቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለችው "
ባርባራ ሚስተር ካርላይልን በዐሥር ሰዓት ላይ አገኘችውና የሪቻርድን መምጣት ነገረችው
ሚስተር ካርላይል ማንኛውንም ማታለልና ማጭበርበር በጣም ይጠላ ነበር አሁን ግን ቶርን በነበረበት ችግር አመካኝቶ ከቢሮው ማስጠራት እሱ ሳያውቅ ሪቻርድ እንዲያየው ማድረግ አማራጭ ያልነበረው ተገቢ ሥራ መሆኑን አመነበት"ስለዚህ ሪቻርድን በቀጠረችው ሰዓት ሲመጣ ወደሱ እንድትልከው ነገራት » እሱም በበኩሉ ጀፈርሰን ቤት የነበረበትን የራት ጥሪ ሰርዞ ካፔቴን ቶርን አማክሮት ስለ ነበረው ጉዳይ ማታ በሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ እንዲመጣ ላከበት ” እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ቀኑን ከቢሮ ባለመዋሉ አልላከበትም እንጂ ስለሱ ጉዳይ ጧቱን
አግባብ ካላቸው ጋር ተነጋግሮ መፍትሔ አግኝቶለት ነበር።
የሚስተር ካርላይልን አስቸኳይ ውሳኔ የሚጠይብቅ ብዙ ጉዳዮች ከቢሮ ይጠብቁት ነበር። ስለዚህ ወደ ቤቱ ከመሄዱ በፊት አስራ አንድ ሰአት ሆነ ከራት ጥሪው መገኘት አለመቻሉን ገና ለሚስቱ አልነገራትም " ስለዚህ ከቢሮው የነበረውን ውዝፍ ሥራ ሳይጨርስ ወደ ቤቱ መሔድ ግድ ሆነበት "
ሚስተር ካርላይል የግል ደስታውን ለወዳጅነትም ሆነ ለሥራ ለመሠዋት የማያወላውል ሰው ነበር ።
ከሰረገላው ተዘጋጅቶ ከበሩ ቁሞ ሳቤላም ልብሷን ለብሳ ከመልበሻ ክፍሏ ተቀምጣ ስትጠብቀው መጣ “ ጀፈርሰን ቤት ራት የሚጀመረው ባሥራ ሁለት ሰዓት መሆኑን ረሳኸው ? አለችው በሰላምታ ፈንታ
“ አልረሳሁትም. . .ሳቤላ ግን ከዚህ ቀድሜ መድረስ አልቻልኩም " አሁንም ቀደም ብዬ የደረስኩት አብሬሽ ለመሔድ ስለ አልተመቸኝ ሚስዝ ጀፈርሰንን ይቅርታ እንድትጠይቂልኝ ልነግርሽ ነው " ዛሬ ማታ ሌላ ሰው ሊሠራልኝ የማይችል ሥራ ስለ አጋጠመኝ አሁን ራት እንደ በላሁ ተመልሼ ወደ ቢሮ እሔዳለሁ " ሳቤላ
ሲላት ሳቤላ ፊቷ ተለዋወጠ " እሷን ወዝውዞ ሊገድላት የሆነው ልዩ ልዩ ሰበብ እየፈጠረ ጊዜውን ከባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ ስለሚፈልግ ነው የሚለው እምነቷ ነበር "
“ አትቆጭ . . . ሳቤላ እውነቴን ነው ወድጄ አይደለም ። ለሌላ ቀን የማይተላለፍ ዲልም ሊፈጽመው የማይችል ብርቱ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው በዚህ አጉል ሰዓት እንደዚህ ያለ ነገር በመፈጠሩ በጣም ነው የማዝነው።
"አለ ዛሬ ከመሸ በኋላ ወደ ቢሮ ተመልሰህ ገብተህ አታውቅም ”
“ እውነትሽን ነው " ምክንያቱም ማታ ወደ ቢሮ የሚያስገባ ነገር ቢፈጠርም
ዲል ሊሠራው የሚችል ነበር " የዛሬው ግን እኔ ራሴ መሥራት ያለብኝ ጉዳይ ስለ
ሆነ ነው ' '
ባይሆን ስትሠራ ቆይተህ ስትጨርስ አዛው ድረስ አትመጣም ?
በውነቱ የምደርስ አይመስለኝም ”

👍18👎1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ናንሲ ሌኔሃን ከማታውቀው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መተኛቷ
ሰላም ሳይነሳት አልቀረም:
ምንም እንኳን ክፍሉ የሙሽሮች ክፍል ቢሆንም አልጋዎቹ ተደራራቢ ናቸው፡፡ በሩ ክፍት እንዲሆን ቢፈልጉም በወጀቡ ምክንያት በሩ እየተወረወረ
ይዘጋል፡፡ ስለዚህ አስሬ ሲዘጋ እየተነሱ ከመክፈት ይልቅ አንድ ጊዜ ዘግቶ
መተዉ የሰውን ትኩረት አይስብም:፡
ናንሲ በጊዜ ላለመተኛት ብዙ ጥራለች። በዋናው ሳሎን ሄዳ ለመቀመጥ
ብትፈልግም ወንዶች ብቻ ናቸው የተሰባሰቡት፡፡ ቦታው በሲጋራ ጭስ ታፍኗል፧ በዊስኪ ሽታ ታውዷል፡ በተጨማሪም የካርታ ተጫዋቾች ስድብና
ጫጫታ ጆሮ ይሰነጥቃል፤ ቦታው ለሴት ልጅ የሚሆን አይደለም፤ ስለዚህ
‹መተኛት ሳይሻል አይቀርም› ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።
ስለዚህ መርቪንና ናንሲ መብራቱን አጠፉና በየአልጋቸው ላይ ሰፈሩ።
ናንሲ ዓይኖቿን ብትጨፍንም እንቅልፍ በአይኗ hልዞር አለ፡፡ ወጣቱ ሄሪ ማርክስ ያመጣላት አንድ መለኪያ ዊስኪ እንኳን ለመተኛት የረዳት ነገር
የለም፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም በዓይኗ እንቅልፍ አልኳል ብሏል፡
መርቪንም እንቅልፍ እንዳልያዘው አውቃለች፡ የላይኛው ቆጥ ላይ
ሰፍሮ ይገላበጣል፡፡ እንደ ሌሎች መኝታዎች የሙሽሮቹ አልጋዎች በመጋረጃ የተሸፈኑ ባለመሆናቸው ላለመታየት ያላት ምርጫ መብራቱን ማጥፋት ነው፡፡
እንቅልፍ አልመጣላት ሲል ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በሀሳቧ መጣች ማርጋሬት በጣም ወጣት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ የማይገባትና ወደፊት
ስለሚገጥማት ነገር ቅንጣት ታህል የማታውቅ ልጅ ናት። ከማርጋሬት
በጥርጣሬ የተሞላ ፊት ላይ ያነበበችው ግን ከፍተኛ ነፃ የመሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ወጣት በነበረችበት ጊዜ የገጠማት አይነት ችግር ነው፡፡ ናንሲም በዚያ ወቅት ከወላጆቿ ጋር አተካራ ውስጥ ገብታ ነበር፧
በተለይ ከእናቷ ጋር፡ እናቷ የተከበረ የቦስተን ቤተሰብ ልጅ እንድታገባ
ብትፈልግም እሷ ግን ገና አስራ ስድስት አመት ሲሞላት ሾን ሌኔሃን
ከሚባል የህክምና ትምህርት ከተማረ ከአባቷ ፋብሪካ ውስጥ ከሚሰራ ካቦ ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ እናትዬው ናንሲ ይህን ልጅ እንዳታገባው ልጁ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንደሚማግጥ፣ እናት አባቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ
እንደሚሳደብና በየጊዜው እንደሚያመው ሀሜት ብታስወራም ናንሲ ግን
የሚነዛውን ሀሜት እንዳልሰማች በማሳለፍ ሾንን አግብታ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አብራው ኖራለች፡፡
ማርጋሬት የእሷን ያህል ጥንካሬ ያላት ልጅ አትመስልም፡፡ ከአባቷ ጋር
ካልተስማማች ከቤታቸው መውጣት ትችላለች፡፡ ይቺ ልጅ በየጊዜው ችግር
እያነሳች እንዳታላዝንና ራሷን ለመቻል እንድትጥር የሚመክራት ሰው ያስፈልጋታል፡ እኔ በእሷ እድሜ የሁለት ህጻናት እናት ነበርኩ› አለች በሃሳቧ፡
ስለዚህ ማርጋሬት ራሷን እንድትችል ጠበቅ ያለ ምክር ለግሳታለች እሷም ቃሏን በመጠበቅ ስራ ልትሰጣት ተስፋ አድርጋለች፡፡
ይሄ ሁሉ ደግሞ የሚወሰነው ከወንድሟ ጋር ባላት ጠብ የሀይል
ሚዛኑን በጨበጠው በአጭበርባሪው ሽማግሌ በዳኒ ሪሌይ ነው፡፡ ናንሲ
እንደገና ወደ ጭንቀቷ ተመለሰች፡፡ ጠበቃዋ ማክ ዳኒ ሪሌይን ይኸኔ
አግኝቶት ይሆን? ከአገኘውስ ስለቀድሞው ወንጀሉ ሲነግረው ምን አለ? ይህ ሁሉ ሴራ እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ የተጠነሰሰ መሆኑን ጠርጥሮ ይሆን?›
እነዚህን ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ስታወጣ ስታወርድ እንቅልፍ አጥታ
አልጋዋ ላይ ትገላበጣለች፡፡
የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦትውድ ከተማ ነው፡፡ ኒውፋውንድ ስትደርስ ማክጋ ስልክ ደውላ ታረጋግጣለች፡፡በዚያ ጊዜ ሁሉ ነገር ይለይለታል፡
አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲንገጫገጭ ናንሲ መላ አካልዋ ተረበሸ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበታል፡ በአይሮፕላን በተደጋጋሚ ብትሄድም ከዚህ ቀደም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ግዙፉ አይሮፕላን በንፋሱና
በወጀቡ ሲወዛወዝ ስጋት ገብቷት ተወርውራ እንዳትወድቅ የአልጋውን ብረት አጥብቃ ያዘች፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ብዙ ችግር ገጥሟታል፤ ‹አሁን ጉልበቴ
በርታ በርታ› ማለት አለበት፤ ነገር ግን የአይሮፕላኑ መንዘፍዘፍ ክንፎቹን
ይገነጥል፣ ሞተሩን ሰብሮ ይጥለው ይሆን?› እያለች መፍራቷ አልቀረም፡፡
ፍርሃቷን ይቋቋምላት ይመስል ትራሷን በጥርሷ ነክሳ ያዘች፡፡ ድንገት
አይሮፕላኑ ቁልቁል ወረደ፡፡ ቁልቁል መውረዱ እንዲቆም በእጅጉ ብትመኝም
መውረዱን ቀጥሏል፡ ይህ ሁኔታ ክፉኛ አስደነገጣት፡፡ ከዚያም ዘጭ አለና
ቀጥ ብሎ መብረር ጀመረ፡
መርቪን እጁን ሰዶ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ንፋሱ የፈጠረው ወጀብ ነው አይሮፕላኑን እንዲህ የሚያደርገው›› አለ ‹‹ከዚህ የባሰ ሁኔታ እኔ ብዙ
ገጥሞኛል፤ አይዞሽ አትፍሪ›› ሲል አጽናናት፡፡
እጁን በእጇ ፈልጋ አጥብቃ ያዝ አደረገችው፡፡ ከአልጋው ወረደና እሷ አልጋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ ፀጉሯን ይደባብስ ገባ፡፡ አሁንም ፍርሃቷ ሙሉ በሙሉ ባይለቃትም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ መርቪን ያዝ ስላደረጋት በመጠኑ
ቀለል አላት፡፡
ምን ያህል ጊዜ እንደተያያዙ አላወቀችም:: ትንሽ ቆይቶ ወጀቡ ተነሳ፡፡በደምብ ስትረጋጋ የመርቪንን እጅ
ለቀቅ አደረገችው፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አላወቀችም።
ናንሲ መብራቱን አበራችና ከአልጋዋ ውስጥ ወጣች፡፡ ከላይ የሆነ ልብስ ደረብ አደረገችና መስታወቱ ፊት ቁጭ አለች፡፡ ሁልጊዜም
ጭንቀት ሲይዛት እንደምታደርገው ፀጉሯን አበጠረች፡፡ በጭንቀቷ ጊዜ የመርቪንን እጅ መያዟ አሳፈራት፡ በዚያ ጊዜ ክብሯን ሸጣ እጁን ለጥቂት ጊዜ በመያዟ በሆዷ
ብታመሰግነውም አሁን ፍርሃቷ ሲለቃት ግን ነገሩ አስፈራት፡፡ እሱም ስሜቷን በመረዳት እፍረቷ እንዲለቃት ብሎ ለጊዜው ክፍሉን ለቆላት ወጣ፡፡
መርቪን ትንሽ ቆይቶ ጠርሙስ ብራንዲ ከሁለት መለኪያ ጋር አመጣና
መጠጡን ቀድቶ አንዱን ሰጣት፡፡ አይሮፕላኑ ትንሽ ይወዛወዝ ስለነበር
በአንድ እጇ መለኪያውን በሌላ እጇ ደግሞ የአልጋውን ብረት ይዛለች:
የለበሰው አስቂኝ ልብስ ባያስቃት ኖሮ ድንጋጤው ቶሎ አይለቃትም አስቂኝ ቢሆንም ልክ ሱፍ ለብሶ
እንደሚንጎራደድ ሁሉ ምንም አልመሰለውም፡፡ ሰው ሞኝ ነው ቢለው ግድ
የለውም፡፡ ልበ ሙሉነቱ አስደስቷታል፡፡
ብራንዲዋን ስትጨልጥ በሰራ አካላቷ ሙቀት ስለፈጠረላት ደጋግማ
ተጎነጨች፡፡
መርቪን ወሬ ለመጀመር ብሎ ‹‹እዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ የሆነ
እንግዳ ነገር አየሁ›› አለ ‹‹እኔ ወደ መታጠቢያ ክፍል ስገባ አንድ በድንጋጤ
ቀልቡ የተገፈፈ ተሳፋሪ ሲወጣ አየሁ፡፡ የመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት ተሰብሯል የበረራ መሀንዲሱ ደግሞ ጥፋት ሲፈጸም የተያዘ ሰው መስሎ እዚያ ቆሟል፡፡ መስኮቱ የተሰበረው ከአይሮፕላኑ ውጭ ተወርውሮ በገባ
የበረዶ ቋጥኝ መሆኑን ሊታመን የማይችል ታሪክ ነገረኝ፡፡ እኔ ግን ሁለ±
ሲደባደቡ እንደነበር መገመት አላቃተኝም፡፡››
ናንሲ እዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚቀመጡ ታሪክ ስለነገራት በሆዷ
መርቪንን አመሰገነችው፡፡ ‹‹የትኛው የበረራ መሀንዲስ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹እንደ እኔ ቁመቱ ሎጋ የሆነና ፀጉሩ ቃጫ የመሰለ መልከ መልካም ወጣት››
‹‹መሀንዲሱን አወቅሁት፤ ተሳፋሪውስ ማን ነው?››
‹‹ስሙን አላውቀውም፤ ነጋዴ ይመስላል፤ አመድማ ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰውዬ ነው›› አለና መርቪን ተነስቶ ብራንዲ ብርጭቆዋ ውስጥ
ጨመረላት፡፡

👍20🥰1
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ከምን ያህል የጊዜ ደንዛዜ ውስጥ እንደቆየች አታውቅም .የሳሎኑ በራፍ ተበርግዶ ሲከፈት ነው ከሀሳቧ ውስጥ በመከራ የወጣችው…ጊፍቲ ከፊት መድህኔ ከኋላ እያለከለኩ ተከታትለው ገቡ
በመጠጥ ተዳክሞ በተቆላለፈ አንደበቷ ‹‹ነይ እንጂ ኑ ብያለሁ››አለቻት..ያልጠበቀችን እና ከነመፈጠሩም ጭሩሱኑ ረስታው የነበረውን መድሀኔን ስታየው ብሶቷ በእጥፍ ጨመረባት፡
ጊፊቲም በራሷ ድንጋጤ ላይ ስለሆነች እሷ የምትለውን እየሰማቻት አይደለም..ጥያቄዋን አዥጎደጎደችው‹‹እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው…?ቃልዬ የት አለ….?አመመው እንዴ….?››ተንደርድራ አልፋ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፈተችና ወደ ውስጥ አየች… ባዶ መሆኑን ስታይ ወደ ልዩ ተመለሰችና‹‹…ልዩ ንገሪኝ እንጂ…ተጣልታችሁ ነው….?አሁን እሱ የት ሄደ?››
ዝም ብላ አየቻት..ሆዷ ወደፊት እየገፋ ነው…በሶስት ወር ፣‹‹እንዲህ ያስታውቃል እንዴ…?››ስትል አሰበች ግራ ከመጋባቷ የተነሳ የማያሳስበው እያሳሰበት ነው፡፡መድህኔ እጁን በደረቱ ላይ አጣጥፎ ግራ በማጋባት ዝምብሎ ቁልቁል እያየት ነው፡፡አሳዝናዋለች.በጣም ነው ያሳዘነችው..ስሯ ተንበርክኮ ወደደረቱ አስጠግቶ እቅፍ አድርጎ ቢያፅናናት ደስ ይለዋል.ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም…
‹‹ልዩ አረ በፈጠረሽ …አናግሪኝ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው?››አለች ጊፊቲ
‹‹ቃል ከዛሬ ጀምሮ የለም››
‹‹የለም ማለት ምን ማለት ነው?››
‹‹መልሱ መኝታ ቤት ግቢና አልጋው ላይ አለልሽ››
ከተንበረከከችበት ተነስታ ተንደርድራ ወደመኝታ ቤት ስትገባ መድህኔ ‹‹ልጄን…›› አለ .አንድ ነገር እንዳይሆንበት የተሳቀቀ በሚመስል ሰውነቱን አሸማቆና ፊቱን አጨማዶ‹‹አረ ማሬ ቀስ በይ..ቀስ…..››
ፖስታውን በእጇ እያገላበጠች ተመልሳ መጣች፡፡‹‹የመጨረሻ ስንብት ማለት ምን ማለት ነው? ››ተንዘረዘረችባት
‹‹ወይዘሮ ጊፍቲ ብታነቢው እኮ የምትፈልጊውን መልስ ከውስጡ ታገኚያለሽ..››
ከፈተችውና ማንበብ እንደጀመረች እንደማዞር አደረጋት ፡፡ ተንገዳገደች….ተንደርድሮ ሄደና ክንዷን ያዛት …መድህኔ የልዩ የድሮ ፍቅር …ቃልን የማታገኝ መስሏት ለሌላ ሴት አሳልፋ የሸለመችው የልጅነት ጓደኛዋ …የረጅም ዘመን ፍቅረኛዋ… እየጎተተ ወሰዳትና ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ለማንኛውም ብሎ ልክ እንደባለስልጣን ጋርድ ከጎኗ በተጠንቀቅ ቆመ ..እንደምንም ብላ ማንበቧን ቀጠለች…ልዩም መጠጧን እየሳበች እየተከታተለቻት ነው፡፡ ጨረሰችና ደብዳቤውን ወደመሬት ጣለችው›
‹‹አንብቤያለሁ ግን ምንም አልገባኝም››
‹‹እኔም እኮ አልገባኝ ብሎ ነው የጠራሁሽ..አንቺ ምን አልባት የልጅነት ጓደኛው ስለሆንሽ ጠባዩንና ድርጊቱን ከኔ በተሻላ ትረጂያለሽ ብዬ ስለማስብ እንድታስረጂኝ ነበረ …አንቺ ግን መልሰሽ እኔን እየጠየቅሽ ነው፡፡››
‹‹ቀስ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና እየተጎተተች ሄዳ ከልዩ ጎን ተዘረፈጠች…..የውስኪውን ጠርሙስ አንስታ ልትጋተው ወደላይ ስታነሳ..ልክ አንደ እግር ኳስ በረኛ ካለበት ተንደረድሮ ሸርተቴ በመግባት ከእጇ ላይ ቀለበው…
‹‹ምን ነካሽ..?እርጉዝ እኮ ነሸ››
‹‹ይቅርታ መድህኔ …ግራ ስለተጋባሁ ነው..እንዴት ነው ቃል ህይወቱን ጥሎ፤ ስራውን ጥሎ፤ አባቱን ጥሎ፤ እኛን ጥሎ ገዳም የገባው…ገዳም መግባት ማለት ምን ማለት ነው…?››የመለሰላት የለም…..
መድህኔ ከሁለቱም ፊት ለፊት ቆሞ በጭንቀት እያፈራረቀ እያየቸው ነው..ምን እየተሰማው እንደሆን ልቡ ውስጥ ገብታ ማንበብ ብትችል ደስ ይለታል ..የድሮ ፍቅረኛውና የአሁኑ እጮኛው ሌላ ወንድ ጥሎን ገዳም ገባ በሚል ሰበብ ስብብርብር ብለው እንዲህ ሲነፈርቁ….በጣም ከባድ ነው……፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር በቃ አንተ ወደስራህ ሂድ…..››
‹‹እንዴ እንዲህ ጥያችሁ እንዴት…..››
‹‹ግድ የለህም ..ሂድ ..እኛ ምንም አንሆንም…››
‹‹እውነቷን ነው እንደውም ብቻችንን ብትተወን ውለታ እንደዋልክልን ነው የምቆጥረው…›.አለችው
‹‹በቃ..የሆነች አጭር ስብሰባ አለቺብኝ..እሷን እንደጨረስኩ ተመልሼ እመጣና ወሰድችሓለው…፡፡
‹‹ሚስትህን መጥተህ መውሰድ ትችላለህ ..እኔ ግን የማድረው እዚህ ነው….ባይሆን ለእማዬ ደውለህ የሆነ ምክንያት ስጣትና እንደማድር ንገርልኝ››
እኔም እሷን ጥያት ስለማልሄድ ..ለዛሬ ተወን..ከፈለግንህ እንደውልልሀለን…› አለችው…››ጊፍቲ
‹‹ካላችሁ እሺ…ስልክሽ ግን እንዳይዘጋ….ቻው›› ቅር እያለው ወጥቶ ሄደ
የእግሩ ኮቴ መራቁን አረጋግጠው ሁለቱም የተነጋሩ ይመስል እርስ በርስ ተቃቀፍና እየነፈረቁ ማልቀስ ቀጠሉ….ልክ የጋራ ቅርብ ዘመዳችው ሞቶ ተረድተው ነው የሚመስለው….
‹‹በጣም አፍቅሬው ነበር እኮ……››አለቻት
‹‹አዎ ጠርጥሬ ነበር…በጣም አዝናለሁ››
‹‹እሺ አሁንም ምን ይሻለኛል….?እንዴት ነው የማደርገው?››
‹‹እኔ አላውቅም የእኔ ማር..እኔም ያለእሱ ምክርና ማበረታቻ ህይወትን መኖር አለመድኩበትም…እንዴትም እንደሚዘለቅ አላውቅም….››>
ማኒቲሱ የሚባል ነፍሳት አለ፡፡ የፌንጣ ዝርያ ነው፡፡የፍቅር ታሪካቸው በጣም ልብ ሰባሪ ነወ፡፡ ሴቷ ወንድ ዙሪያውን በመሽከርከር ስትደንስና ክንፎቾን እያማታች ስታማልልው የወንዱ ስሜቱ ቀስ በቀስ ተነቃቅቶ በፈቅር ቅልጥልጥ ይላል..ከዛ እራሱን ከግንድና ካገኘው ጠንካራ ነገር ጋር ደጋግሞ ባማጋጨት ከሌላው ሰውነቱ በመለየት ቀንጥሶ ይጥለዋል..ምክንያም እንደዛ ሲያደርግ ብቻ ነው ከእሷ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ በማድረግ ከውጥረቱ መርካት ሚችለው…..እና እንዳሰበው ከፍቅር መቅደስ ገብቶ ወሲባዊ መዝምር ዘምሮ …ፍፅማዊ እርካታ ይረካል..ግን ወደህይወት መመለስ አይችልም….ዳግመኛ የተቀነጠሰ አንገቱን ለብቻው ከተዘረረ ሰውነቱ ጋ የማጣበቅ ምንም አይነት ተፈጥሮአዊ ችሎታ የለውም..በዚህም ምክንያት የህይወት ፍፃሜው ይሆናል፡፡
‹‹እና ምን ማለት ነው?››
እኔም እንደዛ ሆኜለሁ…እንደሴቷ ሳይሆን እንደወንዱ…ቃልን አገኛለሁ ብዬ በክንዱ እቅፍ ውስጥ ለአንድ ቀን እንኳን ለመግባትን በፍቅር ትንፋሹን ለመማግ ቋምጬ አንገቴን ከሌላው ሰውነቴ ቀንጥሼ ጥያለሁ..ግን የሚገርመው እንደ ፌንጣው እንኳን የአንድ ቅፅበት እድል አላገኘሁም…ከእነ ፍቅር አምሮቴ ሕይወቴ አከተመላት…ይህ ከበደል ሁሉ የከረፋ በደል ነው፡፡ይቅርታ ማያሰጥ ሀጥያት ነው የፈፀመብኝ››
‹‹ተይ ተይ ከእግዚያብሄር ጋር ለምን ታላትሚዋለሽ..››አለቻት ለቃል በመቆርቆር
‹‹እና ከሰይጣን ጋር ላድርገው..የሄደው እግዚያብሄርን ብሎ አይደል…?ታዲያ እግዚያብሄር ከእኔ ጋር የጀመረውን ጉዳይ አያውቅም ..እሱን ለማግኘት በመቋመጥ አንገቴን ከአከላቴ ቀንጥሼ መጣሌን አላየም..ተው ግዴለህም እዛው ቆይላት አይለውም ነበር፡፡››
✨ይቀጥላል✨

👍103😢36😁9❤5👎3🥰3
#ተአምረተ_ኬድሮነ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
ቀጥታ ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት በሀገሩ ህግ መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና እያመነ ሲሄድ አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡
ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡
እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ ተስማምታ የታማሚውን ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን መኪና ገዝታ ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና ድምቀት በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ አቅዳና ተከፍሏት ግድያ ፈፅማ ይቅርና እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር ይሆን እንዴ….….?››
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ ስቃዮ ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት በሽተኛ ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

👍88👎9❤7👏4😁1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ከ8 ሰዓት እራስን የመሳት ሂደት በኃላ ዶ/ር ሶፊያ ስትነቃ ከአንደበቷ ሾልኮ የወጣው የመጀመሪ ቃል <<ትንግርት››የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ አጠገቧ የነበረው ታዲዬስ ነበር፡፡ ግንባሯ በቀኝ በኩል በከፊል በፋሻ ተሸፍኗል፡፡ እንደምንም ተረጋግታ ያለችበትን ሁኔታ አጣራችና በደከመ ድምፅ << ታዲ >> ብላ ተጣራች ፡፡
‹‹አቤት…ምን ፈለግሽ?››
‹‹ትን..ግር ትስ?››
‹‹ሰላም ነች..አንቺ እራስሽን አረጋጊ፡።››
‹‹ንገረኝ ..የት ነው ያለችው..?ጥራልኝ በናትህ..ላገኛት እፈልጋለው፡፡››
‹‹አሁን እኮ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው..ነገ ታገኚያታለሽ››
‹‹አሁን ነው የምፈልጋት.. ታዲ በፈጠረህ ደውልላት፡፡››
‹‹ሞባይል ቁጥሯ የለኝም፡፡››
‹‹እኔ ሞባይል ውስጥ አለ፡፡››
ሊነግራት ባይፈልግም ስላስጨነቀችው ምንም ማድረግ አልቻለም ‹‹ታስራለች፡፡››አላት ፡፡
‹‹ወይኔ በጌታ ..!!!ማን አሰራ..ት?››አለች... ከተኛችበት ለመነሳት ብትጣጣርም ተራራ በጭንቅላተቷ የተሸከመች ይመስል የገዛ ራሷን ማነቃነቅ እንኳን አልተቻላትም፡፡
‹‹ህግ ነዋ ያሰራት...ልትገልሽ ሁሉ ትችል ነበር.::>>
‹‹ብትገድለኝም ይገባኛል..በፍፅም መታሰር የለባትም፡፡››
‹‹እሱ ያንቺ ፍላጎት ሊሆን ይችላል…ህግ ደግሞ እንደዛ አይልም፡፡››
‹‹ወይኔ ታዲ..አሁን ምን ይሻለናል?››
‹‹ስለምኑ?››
‹‹እንድትታሰር አልፈልግም፡፡››አለችው ደግማ፡፡
‹‹እንግዲ ሲነጋ የሚሆነውን እናያላን..ክስ ልትመሰርቺባት ካልፈለግሽ ምን አልባት በሽምግልና እንጨርሳለን ብለን ልናስፈታት እንችል ይሆናል፤አሁን ግን አንቺ ገና አላገገምሽም አረፍ በይ ፡፡››
‹‹ታዲ ...አንተ ግን ለምን ወደ ቤት ሳትሄድ…? ልጆችህስ?››
‹‹እንዲህ ሆነሽ እንዴት ጥዬሽ እሄዳለሁ…? ለልጆቹም ደውዬ ነግሬያቸዋለው፤ በጣም ነው ያዘኑት ፡፡ቶሎ እንድታገግሚ መልካም ምኞታቸው እንዳደርስላቸው ጠይቀውኛል፡፡ በገዛ እንግዳ እንዲህ በመሆንሽ አዝናለሁ፡፡››
‹‹ፍፅም ማዘን የለብህም...ይሄ የማንም ስህተት አይደለም፤ ለማንኛውም አብረኸኝ
ስለሆንክ ደስ ብሎኛል... አመሰግናለሁ፡፡››አለችውና አይኖቿን በድካም ከደነቻቸው.... እሱም የጀመረውን መጽሀፍ ማንበቡን ቀጠለ፡፡
ከለሊቱ 11 ሰአት ላይ ፎዚያ ተነስታ እየለባበሰች ሳለ ከውጭ የመኪና ጡሩንባ ጩኸት ሰማች... በጣም ነው የደነገጠችው፡፡ ‹‹በዚህን ሰዓት ማን ነው የመጠው..?››ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠባት፡፡‹‹የምን መርዶ ይዘውብኝ መጡ...?::>>
የመኝታ ቤቷን መስኮት ከፍታ ወደውጩ ስታማትር ዘበኛው የውጩን በር እየከፈተ ነበር፡፡ከዛ መኪናዋ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች .. የሰሎሞን መኪና ነች፡፡ሮጣ ወደ ውጭ ወጣች፡፡እሱ ሞተሩን አጥፍቶ ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እሷ ስሩ ደርሳ ‹‹ምን ተፈጠረ…? ምን ሆንክ..?ኤዲስ ደህና ነች…?››
‹‹አረ ተረጋጊ .…ሁሉም ሰላም ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ምነው በዚህን ሰዓት?››
‹‹አብሬሽ ሀዋሳ ልሄድ ነው፡፡››
«ለምን?»
‹‹ለሽርሽር፡፡››አሾፈባት፡፡
‹‹ማለቴ ማን ነገረህ?››
‹‹አንቺ ብትደብቂኝም ሁሴን ደወለልኝ..ይገርማል ሀገር ውስጥ የተሰራ ታሪክ በአሜሪካ ዞሮ ስሰማው››
‹‹እኔ እኮ ኤደን አሟታል ስትለኝ ላስጨንቅህ ስላልፈለኩ ነው፡፡››
‹‹ቢሆንም መስማት ነበረብኝ..አሁን በይ ተዘጋጂና እንሂድ፡፡››
‹‹እሺ ጨርሻለሁ ...አምስት ደቂቃ ብቻ፡፡››አለችውና ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች፡፡
ዝዋይ ሲደርሱ ከጥዋቱ 1፡4ዐ ነበር፡፡‹‹ቁርስ እንሞክር እንዴ?››አላት ሰሎሞን፡፡
‹‹ኧረ ገና ጥዋት ነው… እንቀጥል፡፡›› አለችው..ተስማማና ነዳው፡፡
‹‹ግን ኤደን ታማ እያለ ጥለሀት ስትመጣ አልከፋትም?›› ጠየቀችው... ፎዚያ ፡፡
‹‹ከፍቷታል... ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ሁሴን ሂድና እያት ብሎኝ ምክንያት ፈጥሬ እምቢ ልለው አልችልም፡፡ በዛ ላይ እኔ ኖርኩም አልኖርኩም ለውጥ የለውም፤ቤተሰቦቿ ዙሪያዋን ከበዋታል፡፡››
‹‹ቢሆንም.... ቤተሰብ ሌላ ባለቤት ሌላ፡፡››
‹‹ጉረኛ ...ስለባል ደግሞ ምን ታውቂያለሽ?››
‹‹ለምን አላውቅም፤ ስለባለትዳሮች ለማወቅ እኮ የግድ ባለትዳር መሆን የለብኝም፡፡››
‹‹መስሎሻል.. እኛም ሁለት ጊዜ ያገባነው እንኳን አሁንም ስለትዳር ምንም አልገባንም፡፡››
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ባክሽ ሴቶችን ማወቅ በጣም ነው እየከበደኝ ያለው፡፡››
‹‹ይህቺ ነገር..!!!!ምነው ከኤደን ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ባክሽ.. ከባለፉት ሁለት ወራቶች ወዲህ ንጭንጯን ልቋቋመው እየከበደኝ ነው....?»
‹‹መነሻውን አታውቅም? >>
‹‹ውሀ ቀጠነ ነው…ግን ቅዳሜ እና ዕሁድን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ ከጀመርኩ ወዲህ ይመስለኛል ነገሩ የጀመረው፡፡››
‹‹ከልጆቼ ጋር ስትል..ወደ ድሮ ሚስትህ እየሄድክ ማለት ነው?››
‹‹ኖ..ኖ ቅዳሜ እኔ ጋር ይመጣሉ. አብረውኝ አድረው እሁድ ማታ እመልሳቸዋለሁ.. ከእናታቸው ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም፡፡››
‹‹ታዲያ እሷን ምኑ ነው የደበራት?››
‹‹እኔም ያልገባኝ እሱ ነው፡፡እንግዲህ መጀመሪያም ልጆች እንዳሉኝ እያወቀች ነው ያገባችኝ...ከሚስቴ ተፋተው እንጂ ከልጆቼ አልተፋታውም፤ ምኑ ቅር እያሰኛት አንደሆነ አልገባኝም፡፡››
‹‹ቆይ ያልገባኝ...ልጆቹን መተው የሚያሳልፉት አብረዋችሁ ቤት አይደል..?››
‹‹በፊት ነበር…በኃላ ግን ቅዳሜና እሁድን መጥተው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ ቅር እያላት ፊቷን እያጠቆረችባቸው ስታሳቅቃቸው ..ነገርኳትና ውጭ ማለቴ ሶደሬ ፤ላንጋኖ ካልተቻለም ደግሞ እዛው አዲስ አበባ ሆቴል አብሬያቸው ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡
በነገራችን ላይ በሳምንት ሁለቱን ቀን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ እንዳለብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳሰበኝ ሁሴን ነው ፤ ከመሄዱ በፊት ሊሰናታቸው ቤት ሄዶ በናፍቆት በጣም ተጎድተውና ተሳቀው ስላገኛቸው እኔም ኤደንም ባለንበት ሁኔታውን በማስረዳት አሳምኖን ሄደ፡፡እኔም ሁኔታውን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ነበር የፀፀተኝ ‹‹እንዴት ልጆቼን ችላ ልል እንደቻልኩ ድንቅ ነበር ያለኝ….በአጠቃላይ ሁኔታው ሁሉ እንደዛ ነው እልሻለው፡፡››
‹‹አይ ቢሆንም ተነጋገሩበት…እሷም ነገሩን መቀበል መቻል አለባት፡፡ ቅሬታም ካላት በግልፅ ትንገርህና መፍትሄ ፈልጉለት፡፡››
‹‹እስቲ እሞክራለሁ....ምን አልባት የራሷን ልጅ ስትወልድ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ስለሚገባት ያን ጊዜ ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹እንድትረዳህ እመኝልሀለው...ካለበለዚያ ስታገባ ሰትትፈታ መኖርህ ነው፡፡››ብላ አሾፈችበት፡፡
‹‹እጣ ክፍሌ ከሆነ ምን አደርጋለሁ፡፡››
3 ሰዓት ሀዋሳ ደረሱ፡፡ኤልያስ ሲጠብቃቸው ስለነበረ ወዲያው ወደ ትንግርት ይዞቸው ሄደ፡፡
‹‹ተራማጆቹ ፀሀፊዎች በፖለቲካ በሚታሰሩበት ዘመን አንቺ በፈንካችነት ትቀላቀያቸዋለሽ..? ምነው ምነው?››አላት ሰሎሞን ገና ከፖሊሶቹ ፍቃድ አግኝተው ፊት ለፊት እንደተገናኙ፡፡
‹‹ምን ይደረግ ....ይህቺ ሀገር ፀሀፊ ሳይሆን ጀግና ነው ያጣችው ብዬ ነዋ!!››ብላ መለሰችለት፡፡
የሚነጋገሩት ፖሊሶቹ ጆሮ ይደርሳል... አይደርስም የሚለውን ለማጣራት ግራ ቀኙን ተገለማመጠ
‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡
‹‹ልጄ ለምን አልፈራ..በስህተት እንኳን አንድ ቀን እስር ቤት ባድር ፈንድቼ የምሞት ነው የሚመስለኝ፡፡››
‹‹ለመሆኑ እንዴት ነሽ…?ምን አሉሽ?›› አለቻት ፎዚያ በጭንቀትና በሀዘኔታ፡፡

👍82❤9😁4
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው።
‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ
"እውነቴን እኮ ነው"
""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።››
"ምንድነው ስራው?"
"ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ ወንድሜም እርግጠኛ ነኝ ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።››
"በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡"
"ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች።
ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡
ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል "
‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም"
"ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?"
"እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ ብር እናገኛለን፡፡ ከዛ አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡››
"መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር።
"የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።››
"እሱን ገና አልወሰንኩም...ይሄን አይነት ሀሳብ እራሱ ወደ አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።"
"አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?"
"የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት የህይወት አላማ የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ
እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።"
‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...››
‹‹ጠይቂኝ".
‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..."
የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?››
‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…››
‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?››
‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?"
የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን ..?ደሴ? ምን ለመስራት?"
"ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት መንገድ መሄድ የለብህም..እነሱ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ የሆኑ ሰዎች ናቸው።እንዳልከው እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ ብቻ አይመስለኝም?"
በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?"
"ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…"
"ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?"
"አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።"
‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.."
‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ… ይሄ ጓደኛዬ ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ ቅንጣት ሴሎች ነን፡፡ከመወለዳችን በፊት የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ ነው ያለን… ቦታችን እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…››
‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት በእግዚያብሄር ዘንድ ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ››
‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ"
‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?"
"እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ"
"ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት አደጋ ደርሷባቸው አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና ተሰናብተዋት ይሄዳሉ። እርግጥ ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር የሚሆኑ ሰዎችን ነው የያዘችው..እኔ አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች እግዚያብሄር ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ
አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡››
‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ መገናኘታችን እንዲሁ በዘፈቀደ የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡››
‹‹አልገባኝም››

👍106❤8👎1😁1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================
ቤቱ ቅልጥ ያለ ድግስ ላይ ነው፡፡ግቢ ውስጥ ግዙፍና ዘመናዊ ድንኳን ተደኩኖ በዲኮር አሸብርቋል፡፡በዝግጅቱ የሰሎሜ ፤ የእቴቴ የአላዛር እና የአለማየሁ አንድም ወዳጅና የስራ ባለደረቦች አልቀረም…ከ500 በላይ ሰው ነው የተጠራው፡፡እርግጥ ይሄ ድግስ እንዲደገስ ቀጠሮ የተያዘለት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን ከሰማች ከሳምንት በኃላ ነበር፡፡ግን ባልተጠበቀ ፕሮግራም ዜናው ከተሳማ ከሦስት ቀን በኃላ አለማየው ለአጭር ጊዜ ስለልጠና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪት እንዲሄድ በመስሪያ ቤቱ ስለታዘዘ ድግሱ በሁለት ወር እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
ይሄ ድግስ በዋናነት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን በማወቋ እና ዘመናት ለማወቅ ስታልመው የነበረው የአባቷን ማንነት በማወቋ የተፈጠረባትን ፈንጠዝያ ለማክበር ነበር..ሌላው ለህይወቷ በጣም አስጊ የሆነውን በሽታ ታክማ መዳን በመቻሏም ለተንከባከቧት ሰዎች ሆነ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ለሌላው ሶስተኛ ነገር ደግሞ ትዳር በያዘችባቸው ሶስት አመቷ ውስጥ ስትሰቃይበት የነበረችው ከአላዛር ላይ ተከስቶ የነበረው ስንፈተ ወሲብ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ልክ እንደአዲስ ሙሽራ ቀንና ለሊት ሳይለዩ በፊት ያበከኑትን ጊዜ ማካካስ በሚመስል መልኩ እልካቸውን እየተወጡበት ስለሆነ በዛ ጉዳይ የተፈጠረባቸውን ደስታ በይፋ ለማክበር ነው፡፡ያም መሆኑ ለሁለቱም ከፍተኛ ደስታና አዲስ የህይወት እርካታ አጎናፅፏቸዋል፡፡ከሁለቱም ልብ እየተበተነ ያለ ደስታ በዙሪያቸው ያለውን ሰው ላይ ሁሉ የሚጋባ አይነት ሆኗል፡፡ይሄም ድግሱ ደማቅና ሰፊ እንዲሆን አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ድግሱ ለሁለት ወር በመራዘሙ ምክንያት ሌላም ሊከበር የሚገባው ተደራራቢ ምክንያትና በረከት ተፈጥሮል፡፡
ድግሱ ላይ የታደሙት 500 ያህል የቅርብ ሰዎች ምሳ ከበሉ በኃላ ሰሎሜ የተፍለቀለቀ ፊቷን በፈገግታ አጅባ ወደመድረኩ ወጣች፡፡
ማይኩን ድግሱን በሙዚቃ እያደመቀ ካለው ዲጄ ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹ወዳጆቼ ዘመዶቼ ይሄ ድግስን አስመልክቶ ጥቂት ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡››ስትል ሁሉም የምትለውን ነገር ለመስማት የእርስ በርስ ወሬያቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ወደእሷ አዞሩ….ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ..እናቴ እቴቴ ..ባለቤቴ አላዛር….ወንድሜ አለማየሁ….ጓደኛዬ ሁሴን ..ሁላችሁም ወደዚህ መድረክ ኑና ከጎኔ ያለው የፊት ፊት መቀመጫ ላይ እንድትቀመጡ እፈልጋለው፡፡የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡
ሁሉም እየተያያዙ መጡና ፊታቸውን ወደእድምተኞች አዙረው መድረክ ላይ በተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተቀመጡ፡፡
ሰሎሜ ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንግዲህ እነዚህ አራት ሰዎች ወደእዚህ ምድር ከመጣሁበት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ከጎኔ ነበሩ…ሰሎሜ ሰሎሜ እንድትሆን ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡እኔ ማለት የእነሱ ውጤት ነኝ፡፡እናቴ እቴቴ … ከልጅነቴ ጀምሮ ያለአባት በጀግንነት አሳድጋኛለች፡፡ላደረግሺልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡በጣም ነው የምወድሽ፡፡
በህይወቴ ሁለት ጊዜ በከባድ በሽታ ሆስፒታል ገብቻለሁ፡፡ልጅ ሆኜ በታመምኩ ጊዜ ለህክምናው 70 ሺ ብር ተጠይቆ ነበር፡፡በወቅቱ እናቴ የነበራት ከ7ሺ ብር የማይበልጥ ብር ነበር፡፡ቀሪውን ብር በትምህርት ቤትና በየመንደሩ እየዞሩ ለምነው ያሳከሙኝ..እንዚህ ከፊት ለፊት ተቀምጠው የምታዬቸው የልጅነት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ከሶስት ወር በፊትም ተመሳሳይ አይነት ፈታኝ ህመም አሞኝ ነበር፡፡ ከአካሉ አካል ቆርሶ በመስጠት ደግመኛ ዛሬን እንደዚህ ከፊት ለፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ወንድሜ አለማየሁ ነው፡፡ይሄም ዝግጅት እንዲጋጅ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ‹‹ወንድሜም ስለሆንክ…ከህመሜም እንድፈወስ ስላደረከኝ››አመሰግናለው ለማለት ነው፡፡
ሌላው የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ ሁሴን በሁለቱም የህይወቴ ጨለማ ቀናቶች ከጎኔ ስለነበርክ አንተንም በጣም አመስገናለሁ፡፡በጣም እንደምትወደኝ አውቃለው….እኔም በጣም እወድሀለው….እናም ከሶስት ቀን በኃላ ተመልሰህ ወደውጭ እንደምትሄድ ስለማውቅ ዳግመኛ ሙሉ ጓዝህን ጠቅልለህ ወደሀገር እስክትመለስ እና አብረሀን መኖር አስክትጀምር ድረስ ይሄ እንደሽኝት ፕሮግራም እንዲታይልኝ እፈልጋለው፡፡
ከፍተኛ የሞቀ ጭብጨባ ተከተላት…ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ሌላው የእድሜ ልክ ጓደኛዬ እና አንድም አመት ቢሆን ከስሬ ተለይቶኝ የማያውቀው መከራዬንም ሆነ ደስታዬን አብሮኝ ያሳለፈው የምወደው ባለቤቴ አላዛር ..ስለተንከባከብከኝ. .ለአስቸጋሪው ፀባዬ ጠቅላላ ትዕግስት አድርገህ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ እስከአሁን አብሬህ እንድኖር ሚስትህ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግናለው..ለዚህም ድንቅ አበርክቶትህ ከእኔ ከሚስትህ በዚህ ሁሉ ወዳጅ ዘመድ ፊት አንድ ስጦታ ላበረክትልህ እፈልጋለው፡፡››አለችና ንግግሯን ገታ አደረገች…አላዛር ግራ ተጋባ..ሌሎችም የሽልማቱን ምንነት ለማወቅ ጉጉት አሳዩ፡፡
‹‹ውድ ባለቤቴ ወደእኔ ና››ስትል ጠየቀችው፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ….በእጆ የያዘችውን ፖስታ አቀበለችው፡፡ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቷት ዝም ብሎ እያገላበጠ ያየው ጀመር፡፡
ሁሴን እና አለማየሁ‹‹ይከፈት ይከፈት››አሉ..ሌሎችም እድምተኞች ተከተሏቸው፡፡አላዛር ምርጫ ስላሌለው በቀስታ ፖስታውን ሸረከተው፡፡አንድ ነጠላ ወረቀት ነው ውስጡ ያለው፡፡ አወጣውና ተመለከተው ፡፡ ምንም አልገባውም‹‹ምንድነው ፍቅር?››ሲል እሷኑ መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹አንብበዋ››አለችው፡፡
‹‹እንድምንም ትክረቱን ሰብስቦ ማንበብ ጀመረ…አይኑ ፈጠጠ…‹‹ምንድነው ፍቅር..? የማየው ነገር እውነት ነው…?››ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡ተንደረደረና ተጠጋት፡፡ዝቅ ብሎ ጉልበቷ አካባቢ በእጆቹ ያዛትና ወደላይ አንስቶ አሽከረከራት፡፡ሰው ሁሉ ሽልማቱ ምን ቢሆን ነው በሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ መወዛገብን ቀጠለ፡፡እንደምንም እንዲያወርዳት ካደረገች በኃላ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ማይክሮፎኑን ወደአፈዋ አስጠጋችና ‹አዎ እውነት ነው..ውድ ባለቤቴ ሽልማትህ ልጅ ነው..እኔ ሚስትህ የሁለት ወር እርጉዝ ነኝ፡፡››በማለት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ታዳሚው የምስራቹን አበሰረች፡፡መጀመሪያ እልልታዋን ያቀለጠችው እናቷ እቴቴ ነች….ከዛ ሙሉ ዱንኳኑ በእልልታና በጭብጨባ ተደበላለቀ፡፡.አለማየሁም ሆነ ሁሴን ከመጠን በላይ ተደሰቱና ተንደርድረው ባልና ሙስቶቹ ላይ ተጠመጠሙባቸው፡፡ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ልዩ አይነት ዝግጅት ሆኖ አለፈ…፡፡
እንግዶቹ ከተሸኙ በኋላ ቤተሰቡ ድግሱንና ፈንጠዝያውን ቀጠሉበት፡፡ሁሴን ወደመጣበት እንግሊዝ ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ ከዛ ቤት የሄደ ሰው አልነበረም፡፡.እቴቴ ለአመታት ቃል በገባችው መሰረት ብቸኛ ልጆን በእርግዝና ወቅቷ ለመንከባከብና ከወለደችም በኃላ የልጅ ልጆን ለማሳደግ ስትል የራሷን ቤት ዘግታ ሙሉ በሙሉ ባልና ሚስቱ ጋር ተጠቃላ ገባች፡፡አለማሁም ከእንግዳ ክፍሎቹ ውስጥ አንዱ ክፍል ተመርጧ የእሱ ቆሚ ክፍል ሆኖ እንዲደራጅ ተደረገና ቢያንስ በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን እየመጣ እነሱ ጋር ማደር ጀመረ፡፡እሱ እንቢ ብሎ እንጂ እነሱማ ቢያንስ የራስህን ሴት አግኝተህ ሚስት እስክታገባ ሙሉ በሙሉ የተከራየኸውን ቤት ልቀቅና እዚሁ እኛ ጋር ተጠቃለህ ግባ ና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንኑር ብለውት ነበር፡፡እሱ ግን ሙሉ በሙሉ በሚለው ሊስማማ አልቻለም፡፡በአጠቃላይ እንደዛ የጭቅጭቅ መናኸሪያ ሆኖ ቀዝቅዞ የነበረው ቤት አሁን ደምቆና በቤተሰብ

👍76❤15👏4🥰3👎1😱1