አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ»
እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡
ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው ነበር:: ቆብ
ወይም ኮፍያ አላጠለቀም:: ሰውነቱ ገርጥቶአል፡፡ ትንሽ ከሳ ያለ ሰውነት ያለው ሲሆን የለበሰው ልብስ ጠቆር ያለ ነው፡፡ ፊቱ ጎልቶ ይታይ እንጂ አፍንጫው ሰልከክ ያለ ለመሆኑ ይታያል::

ኮዜት ብትደነግጥም የጩኸት ድምፅ ለማሰማት አልደፈረችም::
አንድ ነገር ወደፊት የሳባት ስለመሰላት ወደኋላ ሸሸት አለች:: ልጁ ከነበረበት አልተነቃነቀም:: ዐይኑን ለማየት ባትችልም በሀዘን መሞላቱን ገመተች::

ኮዜት ወደኋላ ስትሸሽ ከግንድ ጋር ስለተላተመች ያንኑ ግንድ ተደግፋ
ቀረች:: ዛፉን ተደግፋ ባትቆም ኖሮ እጅ እግርዋ ስለዛለባት ትወድቅ ነበር፡፡ዛፉን ተደግፋ እንደቆመች ድምፁን ሰማች:: ያን ድምፅ ከዚያ በፊት ሰምታው አታውቅም:: በጣም ዝግ ብሎ ነበር የሚናገረው::

«ይቅርታሽን፣ እዚህ ነው ያለሁት፡፡ ልቤ ሊፈነዳ ነው:: መኖር እየተሳነኝ ነው ከዚህ የመጣሁት፡፡ ከመቀመጫው ላይ የወረወርኩትን ፅሑፍ አንብበሽዋል? ለመሆኑ ማን እንደሆንኩ አውቀሽኛል? አትፍሪኝ::ጊዜው በጣም
ቆይቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያየንበት ቀን ታስታውሺዋለሽ?
ዘወትር ትሄጅበት የነበረው የሽርሽር ቦታ! በአጠገቤ ያለፍሽበት ቀንስ ቀኖቹ ሰኔ 16 እና ሐምሌ 2 ነበሩ፡፡ አሁንማ ዓመት ሊሞላው ምን ቀረው።
ዓይንሽን እንኳን ሳላይ ብዙ ጊዜ አለፈ፡፡ ማታ ማታ ከዚህ እመጣለሁ አትፍሪ፣ ግድ የለሽም፣ ከዚህ ማንም የለም:: ከዚህ የምመጣው የመኝታ ክፍልሽን መስኮት በሩቁ ለማየት ነው:: ከዚህ አካባቢ በምመጣበት ጊዜ
ደግሞ ድንገት በአካባቢው ካለሽ እንዳትደነግጪ እያልኩ ስራመድ
በዝግታ ነበር፡፡ አንድ ቀን ስትዘምሪ ሰምቼሽ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ከክፍልኝ ውስጥ ሆነሽ ስትዘምሪ መስማቴ ያስከፋሻል? ጉዳት ያለው አይመስለኝም። አየሽ፣ አንቺ እኮ ለእኔ መልአኬ ነሽ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እስቲ ከዚህ እንድቀመጥ
ፍቀጂልኝ፡፡ በቅርቡ እንደምሞት አውቃለሁ፡፡ ይህን ብታውቂ! እኔ እኮ እንደ አምላክ ነው የማመልክሽ! ይቅርታ አድርጊልኝ፤ ንግግር አላውቅም
ከአንቺ ጋር ማውራቴን ረስቼአለሁ፡፡ ምናልባት ሳላውቀው አናድጄሽ ወይ አበሳጭቼሽ ይሆናል፡፡ አዘንሽብኝ?

«ወይ እማዬ!» አለች፡፡ ልክ እንደሚሞት ሰው ተዝለፈለፈች፡፡

ከነበረበት ወደ እርስዋ ሮጠ፡፡ ከወደቀችበት እቅፍ አድርጎ አነሳት!
ምን እንደሚያደርግ ሳይታወቀው በጣም በመጭመቅ አቀፋት:: እየተንገዳገደ ወደ ላይ ብድግ አደረጋት፡፡ አካሉ በጭስ የተሞላ ይመስል ሰውነቱ ውስሳ
እየተነነ የሚሄድ ነገር እንዳለ ተሰማው:: መንፈሳዊ ተግባርም የሚያከናው መሰለው፡፡ ምንም እንኳን ከልቡ አስጠግቶ ቢያቅፋትም የፍቶተ ስሜት ጨርሶ አልተሰማውም፤ እውነተኛ ፍቅር የፍቶተ ሥጋ መርካት አይደለምና፡ ልጁ ከእውነተኛ ፍቅር ወጥመድ ውስጥ ለመግባቱ ምልክት
ነበር፡፡

እጁን ይዛ ወደ ልብዋ አስጠጋችው:: ወረቀት ከጡቶችዋ መኖሩን ተገነዘበ፡፡ ዝግ ባለ ድምፅ ተናገረ::

«እንግዲያውማ ትወጂኛለሽ ማለት ነዋ!»
ጆሮን በኃይል ካላቀኑ በማይሰማ በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ መልስ
ሰጠችው::

«እስቲ ዝም በል፤ እሱንማ የምታውቀው ነው::»

በሀፍረት የቀላው ፊትዋን ላለማሳየት ኩራት በተሰማውና በፍቅር በሰከረው ወጣት ብብት ስር ራስዋን ደበቀች::

ከድንጋዩ መቀመጫ ላይ ቁጭ ሲል እርሱዋም ከአጠገቡ
አለች:: ዝምታ ሰፈነ፡፡ ከዋክብት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: እንዴት ነው ከንፈሮቻቸው የተገናኙት? እንዴት ነው አእዋፍ በዚህ ሰዓት ማዜም
የጀመሩት? እንዴትስ አበቦች ሊፈኩ ቻሉ?
አለቀ! በቃ ! ሥሮቻቸው የተነቀሉ እስኪመስላቸው ተሳሳሙ::

የሁለቱም ሰውነት ነፋስ እንዳወዛወዘው ቅጠል ተንቀጠቀጠ፡፡ በጨለማ
የሁለቱም ዓይኖች ቦግ ስላሉ ተፋጠጡ፡፡ ብርዱ አልተሰማቸውም፤ ድንጋዩ
አልቆረቆራቸውም፤ መሬቱና ሳሩ አልቀዘቀዛቸውም:: አሁንም በመፋጠጥ እየተያዩ ነው፡፡ ልባቸው በአሳብ ተሞልቷል፡፡ ሳይታወቃቸው እጅ ለእጅ
ተጨባብጠዋል፡፡

ለማንኛውም እንዴት አድርጎ ከአጥር ግቢው ውስጥ እንደገባ
አልጠየቀችውም፤ ለመጠየቅም አልፈለገችም፡፡ የእርሱ ከዚያ መገኘት እንግዳ ነገር
አልሆነባትም::

አልፎ አልፎ የማሪየስ ጉልበት የኮዜትን ጉልበት ሲነካ ሁለቱም
በደስታ ይፈካሉ፡፡ ቆይታ ኮዜት አንዳንድ ቃል ትወረውራለች፡፡ ስትናገር ነፍስዋ ከከንፈርዋ ጫፍ ላይ እንደሆነች ከከንፈርዋ ጋር አብሮ ተንቀጠቀጠ ለማለት ይቻላል፡፡

ቀስ በቀስ ዝምታው ተወግዶ ማውራት ጀመሩ፡፡ እንደገና የፍቅር
ስበታቸው ሞልቶ ስለፈሰሰ ዝም ተባባሉ፡፡ ምድርም ዝም አለች፡፡ ነፋስ እንኳን «ዝም በል» ብለው ያዘዙት ይመስል ፀጥ አለ፡፡ እንደገና ጨዋታ ጀመሩት፡፡ እነዚህ ሁለት እንደ ጥቅምት ውሃ የጠሩ ፍጡሮች ስለነበሩ ስላለፈው ምኞታቸው፣ ወፈፍ አድርጎአቸው ስለፈጸሙት ተግባር፣ ስለደስታ
ዘመናቸውን ፣ ስለተከፉበት ጊዜ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ምን ያህል ይመኝ እንደነበር አንድም ነገር ሳይደባበቁ ተጫወቱ፡፡ አንዱ ስለሌላው ስለነበረው
ምኞትና አድናቆትም ተነጋገሩ፡: ሳይተያዩ ሲቀሩ ሁለቱም ምን ያህል ተስፋ ቆረጠው እንደነበር ተገላለጹ፡፡ ከሁለቱም ልብ ውስጥ የነበረው ሁሉ እንደ ውሃ ፈሰሰ፣ ተንቆረቆረ:: ስለዚህ ከአንድ ሰዓት በኋላ ወጣቱ የወጣትዋ፣
ወጣትዋ የወጣቱ ሕይወት ማለት እርሱ እርስዋን፣ እርስዋ እርሱን ሆኑ፡፡አንዱ ሌላው ልብ ወስጥ ዘልቆ ገባ፡፡ አንዱ የሌላው ጌታ ሆነ፡፡ አንዱ በሌላው ረካ፤ ፈካ፤ ተደሰተ፡፡

ልባቸው ውስጥ የነበረው ነገር ተሟጥጦ ሲያልቅ ጭንቅላትዋን
ከትከሻው ላይ አሳርፋ ጥያቄ ጠየቀችው::

«ስምህ ማነው?»

«ስሜ ማሪየስ ይባላል» አለ::

«የአንቺስ?»

«ኮዜት እባላለሁ፡፡››
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማምለጥ

ምንም እንኳን ቴናድዬ የታሠረው ከተለየ ክፍል ውስጥ ቢሆንም
እርሱና ሌሎች ሦስት ሽፍቶች የማምለጥ አድማ ይመታሉ፡፡ ሁለቱ ሽፍቶች ከምድር ቤት ውስጥ ሲሆኑ ቴናድዬ ብቻውን ፎቅ ላይ ነበር፡፡ ከአደሙ
መካከል አንደኛው አደገኛነቱ ታውቆ እንዲሁ ለብቻው ነበር የታስረው::

በምን ተአምር ጠርሙስ ቪኖ እንዴት ሊያስገባ እንደቻለ ባይታወቅም መጠጡ ቴናድዬ ክፍል ውስጥ ተገኝቷል ይህ መጠጥ በውስጡ ሱስ
የሚያሲዝ እንደ ሐሺሽ ያለ ቅመም እንደነበረበት ይነገራል

መቼስ በእያንዳንዱ እስር ቤት ውስጥ እስረኞች እንዲያመልጡ
የሚተባበሩና እምነታቸውንና መሐላቸውን ለገንዘብ የሚሰጡ ጉበኞች ወይም ሌቦች ወይም ቀጣፊዎች አይታጡም: እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ከደመወዛቸው
በላይ ገቢ አላቸው::

ሁለቱ ሽፍቶች አንድ ቀን ጠዋት ማምለጣቸውና ከመንገድ
የሚጠብቋቸው ለመሆኑ የሚያወቁ ሌሎች ሁለት ሽፍቶች ከውስጥ ይቀራሉ እነርሱም ለማምለጥ ዘዴ ይፈጥራሉ በአጋጣሚ በእለቱ በረዶ የተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ ይጥል ስለነበር በዚህ አጋጣሚ በመጠቀምና ጨለማን ተገን
በማድረግ እነዚያ ሁለት ሽፍቶች በፈጠሩት ዘዴ ተጠቅመው ለማምለጥ ችለዋል::
👍21👏21😁1
ከእስር ቤቱ እንዳመለጡ ቀደም ሲል አምልጠው የነበሩትን ሁለት
ጓደኞቻቸውን አገኙ ሰዎቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ቢታሰሩም እንዴት
አድርገው አቅድ እንዳወጡና እንደተመካከሩ አይታወቅም፡ ለምሳሌ ባመለጡበት ሌሊት ቴናድዬ ሳይተኛ ድምፅ እስኪሰማና ምልክት እስኪሰጥ
እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ አፍጥጦ ጠብቋል እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ እጅግ በጣም ይጠበቅ የነበረው ይኸው ሰው ማምለጡ ግራ የሚያጋባ ነው፡ ከነበረበት ክፍል ጠመንጃ የያዘ ዘብ ይቆም ነበር በከባድ የብረት ሰንሰለት ታስሮአል በየእለቱ በአሥር ሰዓት ፈታሽ እየገባ
ያየዋል: እግር ብረቱን ይመረምራል ይኸው መርማሪ ማታ ማታ እየመጣ በዓይነ ቁራኛ ይጠብቀዋል ለእስረኛው የተፈቀደለት ነገር ቢኖር የሚሰጠው ደረቅ ዳቦ አይጥ እንዳይበላበት ሰክቶ ከግድግዳ ላይ እንዲያንጠለጥልበ አንድ ሾል ያለ ብረት ነበር አንድ ቀን ከጠባቂዎቹ አንዱ የቴናድዬ
አደገኛነት በመገንዘብ ከብረት ይልቅ የሾለ እንጨት እንዲሰጠው
አሳስቦ ነበር።

ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት የጠባቂ ለውጥ ተደረገ: መርማሪው
ክፍሎቹን ጎበኘ፡፡ አዲስ ነገር አላየም አስር ሰዓት ላይ የጠባቂ ለውጥ ለማድረግ ሲመጡ ቀደም ሲል የተቀየረወ ጠባቂ ቴናድዬ ተኝቶበት ከነበረው ክፍል ውስጥ ለጥ ብሎ ተገኘ: ወደ ውስጥ ቢገባ ቴናድዬ አልነበረም:: እግሩ የታሰረበት ወደ 25 ኪሎ የሚመዝን የእግር ብረት
ወለሉ ላይ ወድቋል እርሱ የነበረበት ክፍል ጣራ ቆርቆሮ ተነቅሏል፡፡ከክፍሉ ውስጥ የተከፈተ ግማሽ ጠርሙስ ቪኖ ተቀምጧል:፡ ጠባቂው
እንቅልፍ የወሰደው ያንን ስለጠጣ እንደሆነ በኋላ ተደርሶበታል፡ የጠባቂው ጠመንጃ ከእጁ ላይ የለም።

ቴናድዬ የታሰረበት ክፍል ሦስተኛ ፎቅ ላይ ስለነበር ከዚያ እወርዳለሁ ብሎ ሲታገል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል ብለው ጠባቂዎቹ ጠረጠሩ ወደ
ጣራ ወጥተው ሲመለከቱ አንድ የተንጠለጠለ ገመድ አዩ ሆኖም ገመዱ አጭር ስለነበር ከመሬት የሚያደርሰው አልነበረም:: ነገር ግን ጣራ ለጣራ ጥቂት ከተራመዱ በኋላ ከእስር ቤቱ አጥር ውጭ አንድ የፈራረሰ ረጅም
አጥር ያለው ቤት አዩ ምናልባት ከጣራ ወደዚያ አጥር ዘልሎ ለመውጣት ይቻላል የሚል አሳብ ተቀረጸባቸው:: ግን ያም ቢሆን አደገኛ ነበር ቴናድዬ ከብዙ ትግልና ጥረት በኋላ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን በዚህ
ቤት በኩል ነበር ከመንገድ አጠገብ የደረሰው፡ ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ባንገባ ይሻላል እንጂ የደረሰበት ውጣ ውረድ ቀላል አልነበረም: ግን
ዝርዝሩን እንግለጽ ቢባልም ትክክለኛውን ለማወቅ አይቻልም:: ሆነም ቀረም ከነበረበት ለመድረስ ሰውነቱ በላብና በዝናብ መራሱ፣ ሰውነቱ መጋጋጡና መድማቱ፤ ልብሱ መቀዳደዱና መቦጫጨቁ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡

የያዘው ገመድ አጭር ነው፡፡ ለመዝለልም ፈራ፡፡ ከዘለለ ሞት
የሚጠብቀው መሰለው፡፡ ንጋት ስለተቃረበ ቶሎ ከዚያ ካልወጣ እንደሚያዝ ያውቃል፡፡ እንዲሁ ሲያመነታ አሥር ሰዓት ሆነ
ጠባቂዎቹ የቴናድዬ መጥፋት በደረሱበት ጊዜ ብዙ ድምፅ አሰሙ ቴናድዬ በፍርሃት ተዋጠ፣ ሰውነቱ ተርበተበተ፡፡ ከወደኋላ በር እየተከፈተ ሲዘጋና የእጅ መብራት ብርሃን ላይ ታች ሲል ከሩቁ አየ መብራቱ ጠባቂዎቹ ካደረጉት ቆብ ላይ አርፎ ንቅናቄያቸውን አመላከተው እርሱን
ፍለጋ እንደሆነ ታወቀው:
አሁንም ቴናድዬ ያለው ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ ነው ቢዘል ሞት
እንደሚጠብቀው፣ ቢቆይ እንደሚያዝ በሚገባ ያውቃል ታዲያ እንዴት ይሁን?
አሁንም ጊዜው እንደጨለመ ነው ሆኖም ሰዎች ከየጎራው ሲወጡ
ለመለየት ይቻላል አራት ሰዎች ከተለያየ አቅጣጫ መጥተው በሩቁ በመንገዱ ሲያልፉ ተመለከተ ግን እነማን እንደሆኑ ለመለየት አልተቻለውም:፡ ሰዎቹ ተሰባስበው እርሱ ወደነበረበት አመሩ፡፡ እየቀረቡ ስለሄዱ ጨዋታቸውን አዳመጠ፡፡ ድምፃቸውንና የሚጠቀሙባቸውን ቃላት በሰማ ጊዜ ጓደኞቹ እንደሆኑ አወቀ: የሚነጋገሩት በዱር አዳሪ ቋንቋ ነው ልቡ በተስፋ ተሞላ ሰዎቹ ንግግራቸውን ቀጠሉ
«እንሂድ፣ ከዚህ ምን እናደርጋለን» አለ አንዱ
«ዝናቡ ሳይቆም ከዚህ እንጥፋ: ይኸው እንደምታዩት ፖሊሶቹ
እየተንቀሳቀሱ ነው፡»

«ምን ማለታችሁ ነው፣ ከዚህ ደርሰው እንዲይዙን ነው እንዴ
የምንጠብቀው» አለ ሌላው::

«ምን ያስቸኩላችኋል፣ ጊዜው እንደሆነ ገና ነው: ትንሽ እንቆይ::
የእኛ እርዳታ አለመፈለጉን እንዴት እናውቃለን?» አለ ሦስተኛው:

አራቱም ሰዎች ሽፍቶች ጓደኞቹ እንደሆኑ ቴናድዬ አረጋገጠ:
ለመጣራት አልደፈረም:: ቢጣራ ድምፁ ይሰማል በእጁ የያዘውን የገመድ ቁራጭ ጠቅልሎ ወደ መንገዱ ወረወረው ገመዱ ከሰዎቹ እግር ስር
ወደቀ

‹‹የምን ገመድ ነው?» ሲል ባቤ የተባለ ሽፍታ

«ይሄማ እኔ እስር ቤት ሆኜ የገመድከት ነው» ሲል ብሩዦ የተባለው መለሰ::

‹‹የሆቴሉ ጌታ ከዚህ አካባቢ ነው ያለው ማለት ነው» አለ ሞንትፐርናሴ የተባለው ሽፍታ፡፡

ዓይኖቻቸውን ቀና አደረጉ፡፡ ቴናድዬ ተነቃነቀ

«በሉ ፍጠኑ» አለ ሞንትTርናሴ:: «ብሩዦ ገመድ ይዘሃል?»
«አዎን ይዤአለሁ:
«ሁለቱን ጫፎች ደህና አድርገህ ቋጥራቸወ:: ገመዱን
እንወረውርለታለን ከግምቡ ጫፍ ጋር አያይዞ መውረድ ይችላል፡»

«እንዴት አድርጎ?»

«እባክህ አንተ ብቻ የገመዱን ሁለት ጫፎች ደህና አድርገ
ቋጥራቸው»

«አልችልም»

«አንደኛችን እርሱ ካለበት እንውጣ» አለ ሞንትፐርናሴ፡፡

«ሦስት ፎቅ ነው የምንወጣው!» አለ ብሩዦ

ከእስር ቤቱ አጠገብ ከሚገኘው ፍርስራሽ ቤት የወደቀና ወደ እስር
ቤቱ ግድግዳ የተጋደመ አሮጌ የጭስ መውጫ ቱቦ ነበር፡፡ የጭስ መውጫው ቱቦ በጣም ረጅም ስለነበር ከሦስተኛው ፎቅ ወለል ለመድረስ ምንም ያህል
አይቀረውም፡፡ ይህ ከሲሚንቶ የተሠራው ቱቦ ቅጥልጥል የበዛበት ሲሆን አልፎ አልፎ ተሰነጣጥቋል ደግሞም የውስጡ ስፋት ጠባብ ነው፡

«በዚያች ቱቦ አማካይነት ልንወጣ እንችላለን» አለ ሞንትፐርናሴ፡

«በዚያች ቱቦ!» በማለት ባቤ አሽሟጠጠው፡፡ ‹‹በውስጡ ሰው ሊያልፍ! ጭራሽ አይደረግም: እንኳን ትልቅ ሰው ሕፃንም አያልፍ፡»

«ትንሽ ልጅ ብቻ ነው ከዚያ ቱቦ ውስጥ ሊያልፍ የሚችለው» አለ
ብሩዦ ::

«ታዲያ ልጅ ከየት ይገኛል?» ሲል ግዩለሜ ጠየቀ፡

«ቆዩ» አለ ሞንትፐርናሴ፣ ዘዴ አላጣም፡፡››

የዚያን የፈራረሰ ቤት የውጭ በር ቀስ ብሎ ከፍቶ ወደ ውጭ ወጣ:
ሰው አለመኖሩን ግራና ቀኝ ተመልክቶ በሩን መልሶ ዘጋው ከዚያም በሩጫ ፈረጠጠ፡፡

ሰባት ወይም ስምንት ደቂቃ አለፈ፡፡ ለቴናድዬ እንደ ስምንት ሺህ ዓመት ረዘመበት ባቤ፣ ብሩዦና ግዩለሜ ጥርሳቸውን ነክሰው ተገትረው ቀሩ በመጨረሻ በሩ እንደገና ተከፈተ ሞንትፐርናሴ ትንፋሽ አጥሮት ከጋቭሮች ጋር ብቅ አለ፡ አሁንም በኃይል ይዘንብ ስለነበር ማንም ደፍሮ
መንገድ ላይ አልወጣም፡፡
ትንሹ ጋቭሮች ከቱቦው ሥር ሆኖ ወደ ላይ ተመለከተ ሲያይ ውሃ
ጭንቅላቱ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
«እንዴት ነው አንተ ልጅ! የአባትህ ልጅ ነህ ወይስ የእናትህ» ሲል
ግዩለሜ ልጁን ጠየቀው

«እንዴ እኔ ያለውማ የአባቱ ልጅ ነው፤ እንደእናንተ ያለው ነው
እንጂ የእናቱ ልጅ» ሲል ልጁ ትከሻውን እየነቀነቀ ተናገረ
እንዴት ያለ የሾለ ምላስ ነው ያለው?» አለ ባቤ እየተገረመ
ፓሪሱ ወጣት ከገለባ የተሠራ ይመስላችኋል» በማለት በአገሩ የአራዳ ቋንቋ ባቤ ተናገረ::

«ምንድነው የምትፈልጉት?» ሲል ልጁ ጠየቀ፡፡

«በቱቦው አድርገህ ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ እንድትወጣ ነው
የምንፈልገው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ይህቺን ገመድ ይዘህ ነው የምትወጣው» አለ ባቤ::
👍22
ልጁ ገመዱን አገላብጦ አየው፡፡ የጭስ መውጫ ቱቦውንና ግድግዳውን አጤነ፡፡ ከዚያም «ለምንድነው የምወጣው?» ሲል ጠየቀ::

«ከሦስተኛው ፎቅ ጣራ ላይ አንድ ሰው አለ፡፡ የምትወጣው የእርሱን
ሕይወት ለማዳን ነው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ትወጣለህ?» ሲል ብሩገር በጉጉት ጠየቀው::

«ይቻላል» አለ ልጁ የተጠየቀውን ጥያቄ በማቃለል፡፡

ግዩለሜ ልጁን ተሸክሞ ከፈራረሰው ቤት ጣራ ላይ ወረወረው::

የበሰበሰው ጣራ ተንቋቋ፡፡፡ ብሩና ሁለቱን ጫፍ ከቋጠረ በኋላ ይዞት
የነበረውንም ገመድ ወረወረለት:: ልጁ ወደ ጭስ መውጫው አመራ፡፡ ልጁ እየተንፏቀቀ መውጣት እንደ ጀመረ ቴናድዬ አየው፡፡ ቴናድዩ ዝናብ እየዘነበበት ሳለ ውስጥ ውስጡን ከፍርሃት ብዛት እንዳላበው ታውቆታል።

ልጁ ገና ሲያየው ማን እንደሆነ አወቀው፡፡

«ቆዩ እስቲ! ይሄማ አባቴ ነው» ሲል ተናገረ፡፡ «ብቻ ይህም ቢሆን
ከመውጣት አያግደኝም» ብሎ ገመዱን በጥርሱ እንደያዘ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ልጁ እንዴት እንደወጣ በቃላት ለመግለጽ ያዳግታል፡፡ ዱር አዳሪ
ልጆች የሚሠሩት ሥራ ተአምር ነው ብሎ ከማለፍ በስተቀር ሌላ ለመናገር አይቻልም፡፡ ልጁ ቴናድዬ ከነበረበት ደርሶ ገመዱን በማጠላለፍ ረድቶት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዚያ አምልጠው ወረዱ፡፡ ልክ እነርሱ ከዚያ ወርደው መንገድ ሲጀምሩ ጎሕ እንደ መቅደድ አለ፡፡ ልጁ ምናልባት አባቱ ወደ እርሱ
ፍጡር መጥቶ ያነጋግረው እንደሆነ ጠበቀ፡፡ የጠበቀውን አላገኘም:: መንገድ ዳር
ከነበረው ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ከዚያም የተቀደደ ጫማውን ካጠለቀ በኋላ «አልቋል አይደል? ከአሁን በኋላ አትፈልገኝም? ችግራችሁ ተወግዶላችኋል፤ እንግዲህ እኔ ልሂድ?» ሲል ጠየቀ::

ይህን እንደተናገረ መንገዱን ቀጠለ፡፡ አምስቱ ሰዎች ግን ተራ በተራ ከፈራረሰው ቤት ወጥተው ሄዱ፡፡ ልጁ ራቅ ብለው እንደሄደ ባቤ ወደ ቴናድዬ ዞር ብሉ «ልጁን አየኸው?» ሲል ጠየቀው::

‹‹የምን ልጅ?››

«ገመዱን ከነበርክበት ያመጣልህ ልጅ ነዋ!»

«ልብም ብዬ አላየሁት::»

«ብቻ... እኔ እንጃ፣ ልጅህ ነው መሰለኝ::»

«ወይድ እባክህ» አለ ቴናድዬ ፣

«ይመስልሃል?»....

💫ይቀጥላል💫
👍28😁2
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ» እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው…»
#ሰው (አጭር ልቦለድ)


#በበእውቀቱ_ስዩም

ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”🙄
😁29👍18
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_አንድ

...ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

ጠዋት ዩኒፎርሚን ለብሼ ደብተሮቼን አዘጋጀሁና እየቀፈፈኝ ወደ ትልቁ ቤት ሄጀ አንኳኳሁ፡፡

“ማነው?” አለችኝ ዛፒ፡፡ ደነገጠኩ፡

እኔ ነኝ አልኩ እየፈራሁ፡፡

«ግባ ክፍት ነው»፡፡ ገፋ ሳደርገው የሚያብረቀርቀው የጣውላ ሰር ድምፅ ሳያሰማ ተከፈተ ክፍቱን ነው ያደረው ማለት ነው::
ዝርከርክ ያለው ሳሎን ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዛፒ ሶፋው ላይ
የአልጋ ልብስ ጣል አድርጋ ተኝታለች፡፡ ፊቷ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ብርጭቆ፣ የውሃ ጠርሙስ፡ ሩቡ ብቻ የተበላ ሰላጣ፣ ምንም ያልተነካ ዳቦ ዝርክርክ ብሏል፡፡ ብዙ ምግብ
ማቅረብና ምንም አለመብላት ልማዷ ነው ይገርመኛል፡፡

“ምንድነው በጠዋቱ“ አለች እየተነጫነጨች፡፡ ድምጿ የወንድ ይመስላል ጎርንኗል፡፡

"እ..ትምህርት ቤት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደኛ ወጣሁና ልንገርሽ ብዬ ነው"
ድምጼ ተንቀጠቀጠብኝ፡፡

ቀጥ ብላ ግራ በገባው ፊት እየችኝ፡፡ የሌሊት ልብሷን ትከሻዋና ትከሻዎ አካባቢ ይዛ አስተካከለች!
አቤት ደረቷ ቅላቱ ይንቦገቦጋል፡፡ ከኋላው ቢጫ መብራት የበራበት መስተዋት ይመስላል፡፡

"እኔ ምናገባኝ ታዲያ?!" የምትል መስሎኝ ነበር፡፡ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ፈገግ ብላ፤

"እና ሳመኛ! እንደዚህ ነው እንዴ የምስራች የሚነገረው? መርዶ አስመሰልከው እኮ!” አለችኝና
ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ ዘረጋቻቸው፤ ያውም በፈገግታ፡፡ ሁለት ጡቶቿ አፈጠጡብኝ፡፡

ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ፣ ና እንጂ ሳመኝ!” ብላ ጮኸትብኝ፡፡

በደመነፍስ እየተደነቃቀፍኩ ሄጄሄጄ ሄጄ ሄጄሄጀ.ሄጀ እጆቿ ሲጠመጠሙብኝ ሁሉ እርምጃዬን
ያቆምኩ አልመሰለኝም፡፡ ጥብቅ አድርጋ እቅፉኝ፣ “ጎበዝ የኔ ወንድም እኮራብሀለሁ!” አለችኝ፤
በለው ! ከሽ አለ የሻዩ ብርጭቆ ከጠረጴዛው ላይ ወድቆ፡፡ “ይሰበር ተወው!” አለቸኝና ጉንጬን
ስማ ለቀቀችኝ፡፡ ይሄ ቤት ለካ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ቤት ነው !!

ከዛፒ ጋር እንደወጣሁ በደስታ ሰከሬ መንገዱን ሁሉ፣ ሰውን ሁሉ አየሁት፡፡ መቼ ነው ይሄ ትልቅ
የመኪና ኪራይ ማስታወቂያ ነዳጅ ማደያው ፊትለፊት የተሰቀለው ? መቼ ነው ይሄንኛው ሕንፃ
ተሰርቶ ያለቀው? ወቸ ጉድ አዲስአበባ እንዴት ተለውጣላች? ከሆነ አገር የመጣሁ መሰለኝ፡፡
ደግም ደስ የሚል ነገር ይሸተኛል፡፡ አፍንጫዬም ዛሬ ገና የተከፈተ ይመስል።

ዮርዳኖስ ጋር ስንገናኝ፣ “ምነው?” አለችኝ፡፡

"እ" አልኳት፡፡

"አይ ቆመህ ሳገኝህ ነዋ” አለችኝ፡፡ ለካስ ዮርዳኖስን ቆሜ አልነበረም የምጠብቃት። ያልጠበቅኳት
መስዬ ነበር መጠበቅ የነበረብኝ፡፡ ሳመችኝ ጉንጬን፡፡ ዛፒና ዮርዳኖስ እኔ በምባል ኳስ
በከንፈራቸው እየተቀባበሉ ቮሊ ቦል የሚጫወቱ መሰለኝ፡፡ "ተስመህ ትወጣለህ፣ ሰመው
ይቀባሉሀል የሚል ትንቢት ከሰማይ የታወጀም መሰለኝ፡፡ ድፍን አዲስ አበባ እንደ ዳቦ፡ እንደ
ዘይት፣ እንደታክሲ እኔን ለመሳም የተሰለፈ መስሎ ተሰማኝ፡፡(ቀስ ትደርሳላችሁ አትጋፉ ሂሂሂሂ)

ዮርዳኖስ ፈገግ ብላ አፍንጫዋን በመቀሰር ጠጋ አለችኝና፣ ደሞ አሪፍ ሽቶ ፣ እፉፉፉፉፉፉ
ያደረጉብ ማነው?" አለችኝ:: አፈርኩ፡፡ ለካ የዛፒ ሽቶ ነው ሲከተለኝ የነበረው፡፡ የዛቲ ሽፋ
የዋዛ አልነበረም፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ እድሜ ልኬን ሲከተለኝ ነው የኖረው፡፡ ሲያሳድደኝ ሳይሆን
ሲከታለኝ፡፡ የሆነ ዙሪያዬን ከብቦ እንደ እናት አቅፎኝ፡፡

ሰው ወደ ውስጥ የሚስበው አየር እክስጅን፥ ወደ ውጭ የማያስወጣው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እያሉ ያስተማሩን ቅኔ ነበር ሳይንሳዊ ቅኔ !! አሁን አሸብር ወደ ውስጥ የሚስበው ፍቅር፣ መፈቀር፣ መከበር፣ መፈለግን ነው፡፡ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እርካታ፡፡ የአየር ብክለት ማለት ሌላ ትርጉም የለውም እኮ የተገፉ፣ የተገለሉ፣ የተናቁ፣ ሕዝቦች ጥላቻን ወደ ውስጣቸው ሰበው መልሰው ጥላቻን ወደ መላው ዓለም መተንፈሳቸው ነው:: መፍትሄው የፍቅር ችግኝ በልባቸው
መትከል ነው:: እነሆ ዮርዳኖስ የተከለችውን ዝግባ ዛፒ የምትባል ዝናብ ስታረሰርሰው ዘርፈፍ
ብሎ በቀለ፡፡ ሕያውነት ከስሩ አረፍ የሚልበት ጥላ ሆነ፡፡

እኔማ ዛፒ ጥቁር ደመና አዝላ እያጉረመረመች ሰማይ ላይ ተንጠልጥላ ሳያት፣ መሽቆጥቆጥና ጥላቻዬን እንደ ዥንጥላ ስዘረጋ ነበር የኖርኩት፡፡ ክፉትም ጉልበት የሚኖረው እንደክፋት ልንቀበለው በተዘጋጀነው መጠን ነው::

“አንተ ሴት ነህ እንዴ?” ብላ ዛፒ ሳቀችብኝ፡፡ አፈርኩ፡፡ አንደኛ መውጣቴን ምክንያት በማድረግ
ዛፒ ልብስ ልትገዛልኝ ወሰደችኝና ምረጥ! ስትላኝ መጀመሪያ እጄ አንድ ቀሚስ ላይ አረፈ፡፡
ለእቲዬ ልኳ የሚሆን ቀሚስ ነበረ፡፡ ለዛ ነበር የሳቃችው::ልብስና ጫማ ገዛችልኝ፡፡ የሱሪዬን ቁጥር ስጠየቅ አላውቅም ነበር፡፡ ሱሪ ገዝቼ አላውቅማ፤ የጫማ
ቁጥርም አላውቅም፡፡ የሀብታም ልጆች ልብስና ጫማቸው ከሱቅ የተገባ ሳይሆን አብሯቸው
የሚወለድ ይመስለኝ ነበረ፡፡
ሃሃሃ… ግን ይሄው ሁሉ ነገር ሱቅ ውስጥ አለ ሸቀጥ ነው፡፡ ያው እዛጋ ቶማስ የሚባለው
ሁልጊዜ በሴት የሚከስሰው የክፍላችን ልጅ ጫማ ይሄው የራሄል ቦርሳ ኧረ ጉድ የቲቸር
ተስፋ የጥቁር ባለ ብዙ ኪስ ጃኬትም ያውና፡፡ ትንሽ ብቆይ እነዛ ውድ ነን የሚሉ ልጆች
እዚህ ተደርድረው ሲሸጡ አገኛቸው ይሆናል፡፡
ሲገርም ሁለት ሱሪ፣ አንድ ጫማ፣ ሁሉት ሸሚዝና አንድ ሹራብ ነፍስ ካወቅኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ልብስ ከሱቅ ገዛሁ፡፡ ለካሁት፡፡ መስተዋቱ ፊት ስቆም ደነገጥኩ፡፡ ልብስ ማለት ተራ ድሪቶ ነው ምናምን የሚሱ ሰዎች እንዴት ጅሎች ናቸው እባካችሁ! ራሴን በመስተዋት ሳየው ታላቅ ፍንዳታ እዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠረ፡፡

እወራረዳለሁ ጥቁር አምበሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲሰ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆና ወንዳወንድ አቋም ያለኝ ልጅ እኔ ነኝ !! እፎይ! ከቤተክርስቲያን ሃጢያቱን ተናዞ እንደወጣ ሰው ሸክሜ ቀለለኝ አደግኩ ደግሞ !! የክፍሌን ልጆች በየቤታቸው እየሄድኩ እጄን ኪስና ኪሴ እስገብቼ “ሃይ!” ማለት አማረኝ፡፡

ዛፒ የለበስኩት አዲስ ሹራቡ ላይ የነበረውን ወረቀት ከኋላ ክሩን በጥርሷ በጥሳ አላቀቀችልኝና፣
አንተ ልጅ ቆንጆ እኮ ነህ አለችኝ፡፡ በሙቅ ውሃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ የመግባት ያህል ቓሏ ይሞቅ ነበር፡፡ ቆንጆ መሆን ማለት የአፍንጫ መሰልከከ፣ የዓይን መንከባለል፤ የጥርስ መደርደርና
ንጣት ማለት አልነበረም፡፡ ለኔ ቆንጆ ማለት በሰው ዓይን መሙላት ማለት ሆነልኝ፡፡

ዝም ብላችሁ የሕይወት መንገዳችሁኝ ዙሩና ተመልከቱ! አለቀ ያላችሁበት ቦታ ላይ የነበረውን የሚመጣውን የሚያያይዝ ድልድይ ይኖራል፡፡ ይሄን ድልድይ የሚያምኑ ፈጣሪ ነው ይሉታል የማያምኑ 'የስነሕይወት መርህ ነው' ይሉታል፡፡ ለእምነቱም ለሳይንሱም ግድ የማይሰጣቸው እድል ይሉታል፡፡ እኔ ግን ይሄ አንዴ በዛ አንዴ በዚህ የሕይወቴን ተራዳ አየደገፈ የሚያቆመው
ከአቲዬ ድፍን ሃምሳ ብር የተበደረው እግዚያብሔር ነው እላለሁ፡፡
👍3316
እንዲያ ነው የመቀጠላችን ስንከሳር ባማረ የሕይወት አትሮኖስ ላይ ተቀምጦ የሚገለጠው:: ዛፒ ልብስ ከገዛችልኝ ከሳምንት በኋላ ትምህርት ቤት ቁጭ ብዬ መቁረጫ የሌለው ሃሳብ ውስጥ
ተዘፈቅኩ። እንደ ቀልድ ነበር ሀሳቡን የጀመርኩት፡፡ ልብሴ የብዙዎች ፊት እንዲበራ አድርጓል፤ መንገድ ላይ ሴቶች ያዩኛል፡፡ እንዳንዴ ማፍጠጣቸው ሲበዛ፣ እነዚህ ሴቶች ግን ያልለበሰ
ሰው፣ ያላብረቀረቅ ነገር አብስትራክት ይሆንባቸዋል - ቶሎ አይታያቸውም” እያልኩ አስባለሁ፡፡

ዮርዳኖስ ክንዴን ጨምድዳ መሄድ ከጀመረች ቆየች፡፡ ጓደኞቿ “ኤክስሬይ ነገር ነሽ ይሄ ልጅ
ለካ ገና በፊት ውበቱ ታይቶሻል፡፡” እንዳሏት ነገረችኝ፡፡ እግረ መንገዷን፡ “ዛሬ ስለለበስክ ሳይሆን በፊት ከነድሪቶህ ሰው ሳያይህ በፊት ነው የቀረብኩህ መልዕክት ማስተላለፏም እንደሆነ አንጃ !!

እውነቱን ለመናገር ሰው ራሱን ወዳድ ነው:: በዚህ ሁሉ ሃሳቤ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳን ስለ አቲዬ አላሰብኩም፡፡ እኔነት ሲያደከመው የኖረ ሰው ሸክሙን ጣጥሎ ብቻውን የሚቆምበት ቀን አለ አይደል ጥፉታችንን ብቻችንን የምንጋፈጥበት!ራሳአችንን የምንወቅስበት፣ ደስታና ስኬታችንን በራሳችን ልፋት ያመጣነው ነው የምንልበት በቃ ራሳችንን ብቻ የምንሆንበት፣ የዛን ቀን እንደዛ ሆኜ ነበር፡፡

ታዲያ ውጤት ነበረው፡፡ በውስጤ የተትረማመሱ ሀሳቦች በስርዓት ተሰደሩ፡፡ “ሞተዋል" ያልኳቸው ጉዳዮች አፈራቸውን እያራገፉ በህሊናዬ አደባባይ በትንሳኤ ቆሙ፡፡ ፍቅር የሴት ይሁን የእናት አገር ይሁን የፈጣሪ ያልለየት ባለ ብዙ ዘርፍ ፍቅር ባዶውን የኖረ የልቤ መስቀል ላይ እንደገና የተሰቀለ መሰለኝ፡፡ እንደ ባንዲራ በሕይወት መዝሙር ታጅቦ ወደነፍሴ ከፍታ ቀስ እያለ የሚሳብ ፍቅር፡፡

እንደ ሰው ስንቆጠርና ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፡ መንደርተኛ፣ አገሬው ቦታ ሲሰጠን ወይም
የሰጠን ሲመስለን ከማሕበረሰብ ያፈነገጠ ውስጣዊም ውጪያዊም ስብዕናችንን ሰልፉን እንዲያሳምር ውስጣችን ራሱን ይመከራል፡፡ እንደዛ ነው የሆንኩት፡፡ እና ደግሞ ፈሪም ሆንኩኝ የሆነ ነገር መፍራት ጀመርኩ ፡፡

እንደ ሰው ከመቆጠር ስናልፍና እንፋሽ አከንፋሻችን ሲበዛ የሰልፉ መሪ የሆንን እየመሰለን እንደገና ያገኘንበት እንረግጣለን፡፡ መልካም መካሪ ካገኘን ወደ ሰልፉችን የመመለሳችን ነግር ያውም በጭብጨባ ታጅቦ ይደገማል፡፡ ካልሆነ ግን ማንነት፣ ስም፣ አላማ፣ ስብዕና “እብድ የበላው በሶ ሆኖ ይቀራል፡፡ የታዋቂ እውቅና መንኮታኮቱ፥ የእግር ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ በልክ እንዳልተሰፋ ቃሚስ መንዘላዘሉ፣ የትውልድ ሽሽት ከመጥበሻው ወደ እሳቱ የመሆኑም ነገር ሁሉ
የማንነትን ሰልፍ መሳት ነው፡፡
አጉል ወደድኩ ብሎ ሰልፍ ስትጥስ የሚያጨበጭብልህ፣ ጠላሁ ብሎ ጎትቶ ከሰልፍህ የሚያስወጣህ በሞላባት ምድር ጥላቻና ፍቅር እኩል የጥፋት መንገድ መሆናቸው የሚገባህ እንዲህ ራስህ ጋር ሃቅ ሃቁን ስትነጋር ነው፡፡

እናም ባነንኩ !! እኔ ማነኝ? እኔ አሸብር ነኝ፡፡ እናቴ አፀደ ትባላለች፡፡ በዚህች ምድር ላይ
የስጋ ዘመድ የምንለው የለንም፡፡ እናቴ በየሰዉ ቤት እንጀራ ትጋግራለች፣ ልብስ ታጥባለች፣
እንደ ሰው ተከብራ አታውቅም፡፡ ተስፋ የምታደርገው እኔን ብቻ ነው፡፡ ብቸኛ አላማዬ አገር፣
ሕዝብ፣ ወገን አይደለም እናቴ ናት !!

ማንም ስፖለቲካ አመለካከት ቢራኮት፣ ማንም ማንንም ቢከተል ስሜት አይሰጠኝም፡፡ የትኛውም
እምነት 'ወዮልህ! ቢል፡ በዚያ በዚህ ሲፈልግ በአምላኩ፡ ሲያሻው በፖለቲካው ተከልሎ ቢቧደን
(እችን ታህል አይገርመኝም፡፡ እናቴን ነፃ ለማውጣት የሕይወት ጦርነት ውስጥ ያለሁ ታጋይ
ነኝ፣ ሆቺ ሚኒ ነኝ ግዙፉን አምባገነን ሕዝብ ከትንሽ የእናትነት ግዛቴ የማባርር ቼጉቬራ ነኝ፤ በስግብግብና ራስ ወዳዶች ክንድ ስር በፅናት አልፌ የሚስኪን እናቴን ከፍታ የሚያረጋግጥ
አብዮት ምድርን የምንጥ እንጄላ ዴቪስ ነኝ፤ ፋራንት ፋኖን ነኝ፡፡

የእናቴ ጠላት ድህነት አይደለም 'ስለነፃነት የሚቀባጥረው ሕዝብ” እንጂ። የሕዝብ ልጅ የሚባል
ቀልድ አይገባኝም፡፡ የእናቴ ብቻ ልጅ ነኝ፡፡ ፅንፈኛ ነኝ፡ ዘረኛ ነኝ፣ አከራይ ነኝ - ከእናቴ ጋር
በጭፍን የተሰለፍኩ ሌላው የተረገመ ነው ብዬ የማምን ዘረኛ ነኝ፡፡ 'ከእናቴ ወዲያ ታጋሽ፣ ጨዋ፣
ለሰው ልጆች ኣሳቢ፣ አዋቂ ጀግና ዘር የለም የምል ! አክራሪ ነኝ፥ ከእኔ እናት ሊላ ሌላ እናት
እናት የማይመስለኝ፡፡ እናም ጠላቴ ሕዝብ ነው:: ሕዝብን መበቀል ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም
ጠላትህ የትም የሚገኝ እንደ ትቢያ እያፈስከ የትም የምትበትነው ገለባ ነው፡፡....

አላለቀም
22👍19
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


መማረክና መረሳሳት

ብረት በማግኔት እንደሚሳብ ፍቅረኛም ባፈቀረው ጠዋት ማታ
ይሳባል፤ ይጉተታል፡፡ ሮሚዮ በዡልየት ፍቅር ተጎትቶ በአትክልት ቦታ እንደ ተንሸራሸረ ሁሉ ማሪየስም ከኮዜት የአትክልት ሥፍራ ለመንሸራሸር ተመላለሰ፡፡ ሆኖም ማሪየስ የሮሚዮን ያህል አልተቸገረም:: ሮሚዮ ከዡልዬት
ግቢ ለመግባት ረጅም ግምብ መዝለል ነበረበት:: ማሪየስ ግን ይህ አላስፈለገውም:: የሽቦ አጥርን በቀላሉ ፈልቅቆ ነበር የሚገባው:: ቀጭን
ስለነበር ሰፊ ክፍት ቦታ አላስፈለገውም::

አካባቢውም ጭር ያለ ስለነበር ሰው ሳያየው በቀላሉ ሊገባ ቻለ፡፡
የሚመጣው ደግሞ ማታ ማታ ነው:: በዚያች በተባረከች ምሽት ከንፈር ለከንፈር ከተገናኙ ወዲህ በእየለቱ ነው የሚመጣው::

በ1832 ዓ.ም የግንቦት ወርን በሙሉ አንድ ቀን እንኳን ሳይጓደል
ማታ ማታ ተመላልሶ ከፍቅረኛው ጋር ተገናኘ:: እነዚህ ሁለት የዋህ
ፍጡሮች እንዳይገናኙ ጨለማ፣ ብርድ፣ ነፋስ አላገዳቸውም::

በየዕለቱ ሲገናኙ ምን ይሠራሉ? ምንም:: አንዱ ሌላውን በማድነቅ
ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ:: የሚረግጡትን መሬት እንደ ተቀደሰ ቦታ ነው የሚቆጥሩት:: ብዙ ጊዜ የሚያወሩት ስለፍቅር ነው:: ማሪየስ የሙት ልጅ
መሆኑን! ስሙ ማሪየስ ፓንትመርሲ እንደሚባልና የሕግ ባለሙያ እንደሆነ ገልጾላታል፡፡ ኑሮውን የሚያሸንፈው ለአሳታሚ ድርጅቶች አንዳንድ ጽሑፍ
እየጻፈ እንደሆነና አባቱ በአገሩ የታወቀ ጀግና እንደነበር ነገራት፡ እንዲሁም ከዲታው አያቱ ጋር መጣላቱንና የአባቱን ሹመት በመውረስ ባሮን እንደሆነም
ገልጾለታል። ባለማዕረግ ስለሆነ ኮዜት ላይ የተለየ ስሜት አላሳደረባትም::ለእርስዋ ምንም ይሁን ምን ማሪየስ ማሪየስ ነው:: በእርስዋም በኩል ገዳም ውስጥ ማደግዋን፣ እናትና አባትዋ መሞታቸውን፣ የእንጀራ አባትዋ ስም። መሴይ ፎሽለማ መሆኑን፣ ይህም ሰው ድሃን የሚወድ እጅግ ደግና ራሱም ምስኪን እንደሆነና እርስዋን ለማስደሰት ሲል ራሱን ረስቶ ያላደረገው ነገር
እንደሌላ ነገረችው፡፡ የእንጀራ አባትዋ ለእርስዋ ሲል ምቾቱን ሁሉ መሰዋቱንም አስረዳችው::

የሚገርመው ማሪየስ ኮዜትን ስላገኘና በምትነግረው ነገር ሁሉ
ስለረካ ሌላው ቀርቶ አንድ ቀን ሌሊት በቀዳዳ ከነቴናድዬ ቤት ውስጥ ያየውን እንኳን ረስቶ አባትዋ ላይ ደርሶ ስለነበረው ትርኢት አልነገራትም::
ሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ በአባትዋ ላይ ስላደረሱት በደልና አባትዋ እንዴት አድርጎ ከዚያ ወጥመድ እንዳመለጠ ለጊዜው አልታወሰውም:: ሌላው ቀርቶ ማታ ያደረገውን ጠዋት፣ ጠዋት የሠራውን ማታ ይረሳል፡፡ አንድ
ሰው ቀን ላይ ተገናኝቶ «ቁርስህን ምንድነው የበላኸው?» ብሎ ቢጠይቀው አያስታውስም፡፡ ጆሮውና ሕሊናው በኮዜት ትዝታ ስለተደፈነ የማስታወስ
ችሎታውን ቀንሶበታል፡፡ ከዚህም በላይ ከኮዜት ተለይቶ የሚያሳልፈው ጊዜ ዝም ብሎ የሚያልፍ እንጂ ኑሮን እየኖረ የሚያልፍ ስላልመሰለው በሌላ
ጊዜ የሚፈጽመው ተግባር ሁሉ እርባነቢስ በመሆነ ይረሳዋል:: ለማሪየስ ኑሮ ወይም ሕይወት ማለት ከኮዜት ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የእውነተኛ ፍቅር ባሕርይ ነው::

ኮዜት በጣም የተዋበች ልጅ ስትሆን ማሪየስ ነፍስዋንም ጭምር ለማየት ነው የሚፈልገው:: የአንድን ነገር ሁለንተና በጉልህ ለማየት
የሚቻለው ዓይን ሲጨፈን ስለሆነ ማሪየስ ዓይኑን ብዙ ጊዜ ይጨፍናል፡፡ ማሪየስና ኮዜት መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አንስተውና ተነጋግረውበት
አያውቁም፡፡ ማንኛውም ነገር እንደአመጣጡ ነው የሚቀበሉት፡-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዣን ቫልዣ ምንም አልጠረጠረም፡ኮዜት ዘወትር ደስ ብሉአት ስላየ
ከዚያ ወዲያ የሚፈልገው ነገር አልነበረምና ደስ እያለው ይኖራል፡፡ ኮዜትም ማሪየስን በማግኘትዋ መንፈስዋ ስለረካ ዘወትር የደስታ ምልክት ግንባርዋ ላይ ይነበባል:: በሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባባት ካለ አብረው መኖር
ይችላሉ:: በመካከላቸው ሰላም እስካለ ድሬስ የተለየ ጠባይ ስለማይታይባቸው ሦስተኛ ሰው አዲስ ነገር ሊያይባቸው አይችልም:: ጥቂት ጥንቃቄ በማድረግ ከፍቅረኛቸው ጋር መኖር ይችላሉ::

አባትዋ የፈለገውን ለማድረግ ሲፈልግ ተቃውሞ አላሳየችውም፡፡ ዞርዞር ብዬ ልምጣ? እሺ አባዬ:: ዛሬ ከቤት ልዋል መሰለኝ? እንደፈለግህ፡፡
አብረን እናምሽ፡፡ ደስታውን አልችለውም::አባትዋ ዘወትር አራት ሰዓት አካባቢ ይተኛል፡፡

ማሪየስ እንደሆነ ከኮዚት ጋር ለመጫወት የሚመጣው ከአራት ሰዓት በኋላ ነው:: ቀን ቀን
ተገናኝተው አያውቁም፡፡ ዣን ቫልዣ እንደሆነ የማሪየስ በሕይወት መኖር እንኳን ረስቷል፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ግን «ምነው ኮዜት፤ ከኋላሽ ኖራ ነክቶሻል ፤ ከየት መጣ?» ብሎ ይጠይቃታል፡፡ ያን እለት ማታ ከማሪየስ
ጋር ግድግዳ ተደግፋ ቆማ ኖሮ ልብስዋን ኖራ ነክቶባታል፡፡
አሮጊትዋ ቱሴይ በጊዜ ስለምትተኛ እርስዋም እንደ ዣን ቫልዣ ምንም ነገር አልጠረጠረችም:: ማሪየስ ደፍሮ ከቤትዋ ውስጥ ገብቶ
አያውቅም፡፡ አትክልቱ ውስጥ እንኳን ቢሆን አሳቻ ቦታ ይቀመጣሉ እንጂ ራሳቸውን አያጋልጡም:: ከአንድ ቦታ ከተቀመጡ አይነሱም:: ሁለቱም
አብረው በመሆናቸው ብቻ ረክተው ወሬም ባያወሩ ደንታ የላቸውም::ሌላው ቀርቶ በመንገድ የሚያልፍ እንኳን እንዳያያቸው ይጠነቀቃሉ፡፡
አብረው ተቀምጠው ሳለ ዓይን ለዓይን መተያየት፤ በየደቂቃው እጅ ለእጅ ተያይዞ ሃያ ጊዜ መጨማመቅ ደስታ ይሰጣቸዋል፡፡ በዚያች ሰዓት መብረቅ
ካጠገባቸወ: ቢወርድ እንኳን አይሰሙትም:: ይህን ያህል ነበር
ተመስጦአቸው::
ሆኖም ሁለቱ ፍቅረኞች በዚህ ሁኔታ እንዳሉ አንዳንድ ችግሮች
ደግሞ ፈር ቀድደው እየገቡ ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እንደ ለመደው ማሪየስ ወደ ቀጠሮው ቦታ ለመሄድ አቀርቅሮ ይጓዛል:: ከአንድ ኩርባ መንገድ ላይ
ደርሶ ሊጠመዘዝ ሲል ድምፅ ይሰማል::

‹‹ሚስተር ማሪየስ እንደምን አመሸህ!››

ቀና ብሎ ሲያይ ኢፓኒን ናት:: ደንገጥ አለ፡፡ የኮዜት ቤት ካሳየችው እለት ወዲህ ትዝ ብላው ወይም ተያይተው አያውቁም:: አሁን ላገኘው ደስታ ምክንያት ብትሆንም ጨርሶ ረስቷታል:: መርሳት ብቻ ሳይሆን እንደገና መገናኘታቸው አናደደው::

የተደላደለ ፍቅር አንድን ሰው ፍጹም ያደርገዋል ብንል ተሳስተናል:: በስሜት መዋጥ ዝንጉ እንደሚያደርግም መርሳት የለብንም:: በስሜት የተዋጠ ሰው ክፋትንና ደግነትን መለየት ይሳነዋል፡፡ ውለታን፣ የሥራ
ኃላፊነትንና፡ መቃወስ ያለባቸውን ጉዳዮች ሁሉ ሊያስረሳው ይችላል::

ምን! አንቺ ነሽ እንዴ ኢፓኒን?» ሲል ለሰጠችው ሰላምታ በጥያቄ
መልክ መለሰላት::

«ምነው፣ በጣም ተኮሳትረህ ነው የምታነጋግረኝ? የአጠፋሁት ነገር
አለ?»

«የለም» ሲል መለሰላት::

በእርግጥም የያዘባት ቂም አልነበረም:: ደግሞም የሚቀየምበትም ምክንያት አልነበረውም፡፡ ኮዜትን በሚያነጋግርበት አንደበት ኢፓኒንን በጥሞና ማነጋገሩ ስለከበደው ብቻ ነው እንደዚያ የሆነው:: እርሱ ዝም ሲላት
እርስዋ ጮክ ብላ ተናገረች::

«ንገረኝ እስቲ አሁን» ብላ የሚናገረው ነገር እንደጠፋው ሰው ዝም አለች:: ፈገግታ ለማሳየት ሞከረች፡፡ ግን አቃታት፤ እንደገና ለመናገር ሞከረች::

«እና….» ብላ ንግግርዋን እንደገና አቋርጣ አቀርቅራ ቀረች::

«ደህና አምሽ ማሪየስ» ብላ መንገድዋን ቀጠለች::
👍21
የሚቀጥለው ቀን ሰኔ 3 ቀን 1832 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ ቀን በፈረንሣይ ታሪክ ውስጥ የተለየ ትውስታ ያለው ቀን ሲሆን በእለቱ ማሪየስ እንደለመደው በተመሳሳይ ጎዳና አድርጎ ወደ ቀጠሮው ቦታ ይሄዳል:: ከዚያች በአለፈው
ቀን ከተገናኙበት ሥፍራ ኢፓኒን አጋጠመችው:: በተከታታይ ለሁለት ቀን ስላገኛት ትንሽ የበዛ መሰለው:: በሩቅ ሲያያት መንገዱን ቀይሮ ወደ ማዶ
ተሻገረና አሳብሮ ሄደ፡፡ ከዚያ በፊት አድርጋው ባታውቅም ኢፓኒን
ተከተለችው:: እስከዚያን እለት ድረስ በዚያ ሲያልፍ በዓይንዋ ካየችው ትረካ ነበር፡፡ በአለፈው ቀን ብቻ ነበር ለማነጋገር የደፈረችው::

እንደምትከተለው ማሪየስ አላወቀም:: በቀዳዳ ሾልኮ የት እንደሚገባ አየችው:: የአትክልቱን ቦታ ተመለከተች፡: አንጀት በሚበላ ድምፅ ዝግ ብላ
«ለምን!» ስትል ተናገረች:: «ወደ ቤት መግባቱ ነው::»

የሚሾልክበትን ቀዳዳ ጠጋ ብላ አየችው:: ማሪየስ የአጥሩን አንድ
ቋሚ ነቀል አድርጎ እንደሚገባ ተረዳች:: መግቢያውን ጠብቂ የተባለች ይመስል ከአጠገቡ ቁጭ አለች:: ቀዳዳው ከሚቀጥለው ቤት አጥር አጠገብ
ሲሆን ከሁለቱ ቤቶች አጥር መገናኛ ላይ እንደ ኩርባ ያለ ሰወር ያለ ሥፍራ ነበር፡፡ ኢፖኒን የተቀመጠችው ከዚያ ሰዋራ ቦታ ላይ ስለነበር ምሥጢር
ላላወቀ አትታይም::

ከአንድ ሰዓት በላይ ከዚያ ቁጭ አለች:: የአሳብ ተገዥ ሆና ቃል
ሳትተነፍስና ከወዲህ ወዲያ ሳትነቃነቅ ሀውልት መስላ ነበር የተቀመጠችው፡፡ከምሽቱ አራት ሰዓት አልፎአል፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በዚያ ብዙም
ሰው በማይተላለፍበት መንገድ ለማለፍ ሲመጡ ከሩቁ ይታያሉ፡፡ ሰዎቹ እየቀረቡ ሲሄዱ አንደኛው ሰውዬ ሲናገር ይሰማል፡፡

«እኔ እኮ በጣም የሚገርመኝ ሳያስታጉል በየቀኑ ማታ ማታ መምጣቱ ነው።

ዓይኑን አጥብቦ ወደ ውስጥ ለማየት ሞከረ:: ምንም ነገር ለማየት አልቻለም::
ኢፓኒንም የተቀመጠችበት ሥፍራ ጨለማ ስለነበር እርስዋንም አላያትም አካባቢው ጥቂት ያስፈራ ስለነበር እርምጃውን ጨምሮ ፈጠን በማለት ተራመደ:: በዚህ ጊዜ ማሪየስ ከኮዜት ጋር ነበር፡፡

ሰማዩ እንደዚያን እለት ጠርቶና ከዋክብት በዝተውበት አያውቅም፡፡ የዛፎቹ መዓዛና የነፋስ ሽውሽታም የተለየ ነበር፡፡ አእዋፍ ድምፃቸውን አጥፍተው ለጥ ብለዋል፡፡ አየሩ እጅግም አይሞቅም ወይም አይቀዘቅዝም፧
ለጤና ተስማሚ ነው:: የአየሩ ሁናቴ ሊሆን ይችላል፤ ያን እለት ምሽት ከሌላው ቀን ይበልጥ ማሪየስ ደስ ብሎታል፡፡ ኮዜት ግን ተክዛ ነው ያገኛት:: ከልቅሶ ብዛት ዓይኖችዋ ቀልተዋል:: በዚያ የሕልም ዓለም የመጀመሪያው
ጭጋግ መሆኑ ነው:: የማሪየስ የመጀመሪያዎቹ ቃላት «ምን ነካሽ?» የሚሉ ነበሩ::

«ተመልከት› ካለች በኋላ ከዚያም ከምናውቀው የድንጋይ መቀመጫ
ላይ ሄዳ ቁጭ አለች:: ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ከአጠገብዋ ሲቀመጥ እርስዋ ቀጠለች::

«ዛሬ ጠዋት አባዬ ዝግጅት እንዳደርግ ነገረኝ፡፡ ምናልባት ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ አገር ሳንሄድ አንቀርም፡፡»

ማሪየስ ነፍስ እንደተለየው ሥጋ ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር
ድርቅ ብሎ ቀረ ፤ በድን ሆነ፡፡ ከሕይወት መጨረሻ ስንደርስ መሞት ማለት መሄድ ሲሆን ከሕይወት መጀመሪያ ላይ ስንሆን ግን መሄድ ማለት መሞት ነው

ማሪየስ ለስድስት ሳምንታት ከኮዜት ጋር አብሮ በቆየበት ጊዜ ቀስ እያለ ደረጃ በደረጃ በየቀኑ የኮዜትን ልብ እየበላና አንጀትዋን እየሰረቀ ነበር፡፡ በፍጹም ልቦናዋ፤ በፍጹም አካልዋ ነበር የተገዛችለት:: ሥጋዋም ሆነ ነፍስዋ ከማሪየስ መዳፍ ስር ወድቋል፡፡ ለእርሱም ቢሆን ኮዜትን ማግኘት፣ ኮዜትን መጨበጥ ማለት እንደ እስትንፋስ መዋሀድ ማለት ነበር::ከዚህ ውህደት፣ ከዚህ አንድ የመሆን እምነት፣ ከዚህ ይነጣጠላሉ ተብሎ
ካልታሰበ የተጣመሩ ነፍሳት መካከል ወደ ውጭ አገር ሳንሄድ አንቀርም የሚል የመለያየት መልእክት መስማት ማለት የአንድን ሰው ልብ በቢላዋ
ከሁለት መክፈል ማለት ሆነ፡፡ ይህም ለማሪየስ «ኮዜት የአንተ አይደለችም» የሚል መልእክት መሰለው::

ቀደም ሲል እንዳልነው ማሪየስ ለስድስት ሳምንታት በሕይወት ኖረ፡፡
«መሄድ» የሚባለው ነገር ያንን ሕይወት ነው ያሳጣው:: የሚለውና የሚናገረው ነገር ጠፋው:: እንዲያው ዝም ሆነ፡፡ ቆየች ፣ ቆየችና እርስዋ በተራዋ «ምን ነካህ?» ስትል ጠየቀችው:: አጠገቡ ሆና ለመስማት
በሚያዳግታት ድምፅ «ያልሽው ነገር አልገባኝም» ሲላት እርስዋ ቀጠለች::

«እቃዬን እንዳዘጋጅ ዛሬ ጠዋት አባዬ ነገረኝ፡፡ የእርሱንም ልብስ
ሻንጣ ውስጥ በመልክ በመልኩ እንድከት አዝዞኛል፡፡ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ወደ ውጭ አገር መሄድ እንዳለበት ገልጾልኛል፡፡ ለእርሱ አንዲት አነስተኛ ሻንጣ፤ ለእኔ ግን ትልቅ ሻንጣ ሊገዛ ነው፧ ገዝቶም ይሆናል::ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልንሄድ ስለምንችል ሁሉንም እንዳዘጋጅ ነው
የነገረኝ፡፡ የምንሄደውም ወደ እንግሊዝ አገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ስለዚህ መለያየታችን ነው ማለት ነው:: »

‹‹ግን እኮ..» ብሎ ቀረ፡፡

ጥቂት ቆየና «መቼ መንገድ የምትጀምሩ ይመስልሻል?» ሲል ጠየቃት

«ቀኑን እንኳን ወስኖ አልነገረኝም::

ማሪየስ ከተቀመጠበት ተነሣ፡፡

«ኮዜት መልስ እንደመስጠት የማሪየስን እጅ ይዛ ጨመቀችው፡፡»

«ይህ ከሆነ እንግዲህ» አለ ማሪየስ፣ «እኔም ወደ አንድ ኣገር መሄድ ይኖርብኛል፡፡»

ምን ማለት እንደፈለገ ስለገባት ስሜትዋ ተለዋወጠ፡፡ የፊትዋ
መለዋወጥ በጨለማ እንኳን ታየ::

«ምን ማለትህ ነው?» ስትል ጠየቀችው::

ማሪየስ ትኩር ብሎ አያት:: ከዚያም ዓይኑን ቀስ እያለ ሽቅብ እየወረወረ

«ምንም» ሲል መለሰላት::

«ከሄድክ ሂድ! የት እንደምትሄድ ግን እኔ ነኝ የምነግርህ፡፡ እኔ
ከምሄድበት መጥተህ እዚያው እንገናኝ፡፡»

ማሪየስ ከእንቅልፉ በደምብ ነቃ፡፡ እውነታውን በደምብ ለማየት
ቻለ፡፡ ወደ ኮዜት ፊቱን አዙር ጮክ እያለ ተናገረ::

«ከአንቺ ጋር ነው የምሄደው? አብደሻል ልበል? ከአንቺ ጋር ለመሄድ እኮ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ ገንዘብ የለኝም::» ያውም እንግሊዝ አገር ለመሄድ! እህ! ሌላው ቀርቶ ፓስፖርት ሲወጣ የሚከፈል ገንዘብ እንኳን የለኝም።

አጠገቡ ከነበረው የዛፍ ግንድ ጋር ሳያውቀው ተጋጭቶ ኖሮ ግንዱን
ተደግፎ ቆመ:: በሁለት እጆቹ ጭንቅላቱን ይዞና ግንባሩን ከዛፉ ግንድ ላይ አሳርፎ ነው የቆመው:: የዛፉ ሸካራ ቅርፊትም ሆነ የሞቀው ሰውነቱ ትኩሳት አልተሰማውም፡፡ ተስፋ እንደቆረጠ ሰው እንደ ሐውልት ሳይነቃነቅ
እረጅም ጊዜ ተገትሮ ቀረ፡፡ በመጨረሻ ፊቱን አዞረ፡፡ ከአጠገቡ የሚንቀሳቀስ
ድምፅ ሰማ፡፡ ኮዜት እያነባችው ነበር፡፡ ማሪየስ በአሳብ ተውጦ ዛፉን ተደግፎ ሳለ ኮዜት ለረጅም ጊዜ አልቅሳለች፡፡

ማሪየስ ወደ ኮዜት ሄዶ ከጫማዋ ስር ተንበረከከ፡፡ ቀሚስዋን ገልጦ
አንድ እግርዋን ብድግ አድርጎ ሳመው::

«ስሚኝ» አለ፤ «ነገ ማታ አትጠብቂኝ፡፡»

«ምክንያቱን ንገረኝ!»

«ትደርሽበታለሽ፡፡»

«ቀኑን ሙሉ ሳላይህ ውዬ ላድር! እንዴት ተብሎ! ሊሆን አይችልም፡፡»

«የእድሜ ልክ ጊዜ ለማግኘት ሲባል አንድ ወይም ሁለት ቀን
መስዋዕት ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው::»

«ምኞትህ ከሆነ ይሁን፡፡»

«ኮዜት፣ ምኞቴ ብቻ ሳይሆን የምፈልገው ነው::»

በሁለት እጆችዋ ጉንጮቹን ያዘች፡፡ በቁመት ከእርሱ ጋር ለመስተካከል ከእግርዋ ጣቶች ጫፍ ላይ ቆመች፡፡ የጭንቅላቱን የውስጥ ኣካል ለማየት ትችል ይመስል ዓይን ዓይኑን አፍጥጣ አየችው:: ማሪየስ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
👍152
«አድራሻዬን ማወቅ አለብሽ መሰለኝ፡፡ ምን እንደሚሆን ለማወቅ አንችልም:: ኩርፌይራክ ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ነው የምኖረው:: መኖሪያችን
ከደ.ላ. ቫራ ጉዳና የቤት ቁጥር 16 ውስጥ ነው::

እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ሰንጢ አወጣ፡፡ በሰንጢው አድራሻውን
ካኣጥሩ ግድግዳ ላይ ጻፈ:: ነገራት ዓይን ዓይኑን ማየትዋን ቀጠለች::

ተነገ ወዲያ ባጊዜ ትመጣ የለ? እጠብቅሃለሁ:: ልክ ከምሽቱ አራት
ሰዓት ሲሆን ብትመጣ ይሻላል፡፡ ሰማኸኝ ፍቅሬ ቀኖቹ እንዲህ መርዘማቸው ያሳዝናል፡፡ ገባህ፣ እኔ ግን ከሦስት ሰዓት ጀምሮ ከአትክልቱ ቦታ ሆኜ
እጠብቅሃለሁ::

ቃል ሳይለዋወጡ በተመሳሳይ አሳብ በመዋጥና ከኮረንቲ ይበልጥ የስበት ኃይል ባለው የፍቅረኞች ግንኙነት በመሳብ አንዱ በሌላው ላይ በመወርወር ተቃቀፉ:: በፍቅር የሰከሩ ሁለት ሰዎች በሀዘን ጊዜ እንኳን
ምን እንደሚያደርጉ ሳይታወቃቸው ከንፈር ለከንፈር ይገናኛሉ፡፡ ዓይናቸው እምባ አቅርሮ አንዱ ሌላው ላይ ማፍጠጥ ሆነ፡፡ ማሪየስና ኮዜትም የፈጸሙት
ተግባር ይኸው ነበር፡፡


💫ይቀጥላል💫
👍24
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሁለት


...ጠላትህ የትም የሚገኝ እንደ ትቢያ እያፈስክ የትም የምትበትነው ገላባ ነው። አስተማሪ ብትሆን ከጠመኔህ ስር ጠላትህ አለ። ጥላቻ አእምሮው ውስጥ እየዘራህ ሰይጣን ታፈራለህ፡፡ ሹፌር ብትሆን የጠላትህ ነፍስ በእጅህ ነው፣ ይዘኸው ገደል ልትገባ ትችላለህ፡፡ ግንበኛ ወላ አናፂ ብትሆን
ምትሰራለት ቤት በላዩ ላይ ፈርሶ እንዲቀብረው የማድረግ ስልጣን በእጅህ ነው፡፡ ባለሰልጣን ከሆንክማ፥ እባቡም ከእግርህ፣ ዱላውም ከእጅህ ብትፈልግ ቀይሽብር ወንጀለኛ' ምናምን
ቅብርጥስ ብለህ በየመንገዱ ትደፋዋለህ፡፡ ካሻህ እድሜ ልኩን በድህነት እንዲማቅቅ ታደርገዋለህ፡፡

ደግሞ ለበቀልህ ማን ይተባበረኛል?' ብለህ አትሰጋም፣ ሕዝቡ ራሱ ለመባረክ ስትቆም ነጠላውን አጣፍቶ ከጎንህ ነው፡፡ ለማረድ ስትቆምም ቢላውን ስሎ ከጎንህ ነው፡፡ ከሌላ ዓለም ረዳት
መጥራት ሳያሻህ፤ ወንድሙ ላይ የሚጨከን ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ሕዝብ ጠላትህ ከሆነ
አደግድጎ ለበቀልህ ታዛዥ ነው

ደነዝ ሕዝብ፣ ደነዝ መሪ እንደሚወልድ እስኪገባው ትጫወትበታለህ፡፡ ጭራቅ ሕዝብ፣ ጭራቅ መሪዎች እንደሚፈለፍል እስኪያውቅ ታሸዋለህ፡፡ አዎ ጠላትህ ሕዝብ ከሆነ በቀልህ ቦታ እና ጊዜ ሳይመርጥ የትም ሊፈፀም ይችላል፡፡ ደግሞ ታዝበህ ከሆነ ከልብህ የሕዝብ ጠላት ከሆንክ ሕዝብ ይወድሃል፡፡ ስላንተ ይዘምራል፡፡ ጀግና! እያለ ሲያወሳህ ይኖራል፡፡ ለምን መሰለህ፤
ውስጡ ያለው ጭካኔ ነው በአደባባይ ያሳየኸው !

ወዳጁን እየካደና እየቀረጠፈ ውለታውን ትቢያ የሚያለብስ ሕዝብ የትናቴን ጉልበት እንደምስጥ መጥጦ እንጨቷን አስቀረ ብዪ አላዝንም፡፡ ሰው እሆናለሁ፡፡ በእኔ ሰው መሆን ትላንት ፍሬ የምትሰጥ ለምለም ዛፍ የነበረች ሕዝብ ያደረቃት እናት የምትባል እንጨት ከማገዶነት አፋፍ ተመልሳ እንደ እሴይ በትር ትለመልማለች፡፡

ያኔ በልጅ ልጆቿ ልብ ውስጥ ከቅዱስቅዱሳኑ ለዘላለም በከብር ትቀመጣላች፡፡ ቱ! አሸብር
አይደለሁማ !

አዎ ታጋይ ነኝ !! ታጋይ በሴት አይፈትንም፡፡ ሴቷ ቀይ እግር ቢኖራትም፤ አይኗ ቢያምርም፣
ተንጠራርታ ብትስምም፣ ስሟ ዮርዳኖስ ቢሆንም፣ ማታ ማታ ትዝ ብትልም፣ ከነድሪቶቹ
ብትቀርበኝም የጠላት ልጅ ያው ጠላት ነው !! ዮርዳኖስን ርግፍ አድርጌ ተውኳት !

ከባድ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ዐይኔን ስገልጥ ዮርዳኖስ ለእኔ ሸክም ነበረች፡፡

በብልጣ ብልጥ ሴትነት ነገን አሻግራ ያየች፣ መረቧን ተሽክማ ግራ በገባው አሳ ዙሪያ የምትሸከረከር ብልጥ ሴት፡፡ እሾሁን አራግፋ ልትቀረጥፈው !! ተውኳት፡፡

“ልብሱን ሲቀይር ተወኝ አለች ተባለ፤ እሷ የድሮ ልብሷን የሆነች ይመስል፡፡ ብዙ ፆታዊ
ግንኙነቶች ላይ ኣለመፈለግ ክህደት ተደርጎ ይታያል፡፡

አስራ ሁለተኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ዩኒቨርስቲ ሲገሱ ከትዘጋጁ ጥቂት ተማሪዎች
መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ አራት ነጥብ : አራት ነጥብ የሚባል አንድ ጠመንጃ ይዤ ለትጥቅ
ትግል ዩኒቨርስቲ ወደሚባል ጫካ ልዘምት ተዘጋጀሁ፡፡

ዛፒ እንጅ የናጠ የሃብታም ልጅ ሊኖረው ከሚችለው በላይ ልብስና ጫማ፣ ለሎችም ቁሳቁሶችን
ከአገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿም ጭምር አስመጥታ አምባሻበሻኝ፡፡ ምርር ያለ ቤተሰባዊ ፍቅር ውስጥ ገብተን ነበር፡፡ ዕይኗ ይወደኝ ነበረ ያስታውቃል፡፡ በተለይ አስራ ሁለተኛ ከፍል ተፈትኜ ውጤት ስጠብቅ ከዛፒ ጋር ያሳለፍነው ጊዜ የማይረሳ ነበረ፡፡
ያልዞርንበት መዝናኛ አልነበረም፡፡ የትም ስትሄድ ከ አለሁ፡፡ እኔን “ወንድሜ ብላ ማስተዋወቅ
እንዴት እንደሚያኮራት ዐይቼ ራሴን ለወንድምነት አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡ የእውነትም ደግሞ
ወንድሟ እመስል ነበረ፡፡ ዛፒ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአቲዬም ደግነቷ ተንሰራፍቶ ነበር፡፡ ማታ
ማታ ቡና ተፈልቶ በረንዳ ላይ ወይም ሳሎን ደስ የሚል ጊዜ ሦስታችንም እናሳልፋለን፡፡

ዛፒን ከምቾት ጋር ያገለለ ዓለም እኔና አቲዬንም ከጉስቁልና ጋር የተፋ ሕይወት በምን ሂሳብ
እንዳቀሳቀሰን ባይገባኝም ቅልቅሉ ግን ከልብ የሆነ ቤተሰባዊ ትስስርን ፈጥሮ ነበረ፡፡

አንድቀን “አቲዩ!አልኳት፣

“አቤት!”

“ምን ብሆን ደስ ይልሻል?”

“ኧረ እኔ ምን አውቄ፣ እኔ ትምርት የለኝ አላቀው“ ብላ ሳቀች፡፡

“ግዴለሽም ተምሬ እኔ ልጅሽ ምን ብሆንልሽ ደስ ይልሻል?”

“እሷን አማክራት እስቲ“ አለችኝ ዛፒን ማለቷ ነበር፡፡

“አቲ ዛሬ ካልነገርሽኝ አልለቅሽም ራስሽ ንገሪኝ"

ትንሽ አሰበችና፣ “ዶፍተር” አለችኝ በሳቅ፡፡ ሁለታችንም ባሳቅ ፍርስስስስ አልን።

አነጋገሯ በዕርግጥም ያስቅ ነበር፡፡ ህክምና የመማሬ ብቸኛ ምከንያት ይሄው ነው!! ሕዝቤንና
ውገኔን ከበሽታ ለመታደግ ምናምን በዬ አልነበረም!! እናቴ፣ የምወዳት እናቴ፡ የእዕምሮዋ ጥግ
የታላቅነት መጨረሻ የመሰላትን ነገር ለመሆን እንጂ!!

የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የደስታና የቅንጦት ነበረ፡፡ ዛፒ ውብ ሆና ግቢ ስትመጣ ዐይኑን የማይጥልባት ተማሪ አልነበረም፡፡ ብዙ ሰው እናቴ ያደርጋት ነበረ፡፡ ሴቶቹ የዛፒ ጫማና ልብስ ላይ ዐይናቸው ይጎለጎላል፡፡ ከዚህ የቆንጆ ዘር በረከቱን ሊካፈሉ የቋመጡ፣ በስልምልም ዐይን፣ በጨዋ መሳይ ፈገግታ ሲቀርቡኝ ሲዞሩኝ ነበር፡፡ 'ፀዳ ያለ ልጅ ይሉኛል፡፡ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ! አላልኳችሁም፣በድፍን ግምት ወደድን ብለው ከሰልፍ ሊያስወጡ መሞከር ይሄ ነው እኮ፣

የወደዱኝን ያከበሩኝን ሁሉ ቁምነገር ባለመቁጠር በቀሌን አንድ ብዬ ጀመርኩ፡፡ ኮተታሞቹ
የግቢ ልጆት ራሳቸውን ችለው መቆም ይፈራሉ፡፡ ሴቶቹ ወንድ ታዛ ስር ካልተጠለሉ ሰው የሆኑ
አይመስላቸውም፡፡ ወንዶቹ የተፈጥሮን ጾታዊ መፈላለግ
ሳይንስ ሊያደርጉት ጅራት ሲቆሉ፣ ግራ የገባቸው የከተማ ልጆች ጭልጥ ወዳለው ማሕበራዊ እንስሳነት ሲወርዱ፣ በግቢያችን ውስጥ እንደሰው መኖርን ያጣጣምኳት እኔ ከፍ ባለ ክብር እየተማርኩ ሁሉንም ተማሪ ፅንፍ በሌለውጥላቻና ንቀት እመለከት ነበረ፡፡

የናቀውን የሚወድ ሕዝብ ግን ከጎኔ ነበር! አሹዬ፣ እሹጎት፣ ሹ፣ .ሸቢ፣ ሹሹ፣ ከቤተሰቦቻቸው
የወረሱት እባብነት የስም ግንድ ላይ ሲጠመጠም ላለመነደፍ ልቤን ቆዳ አልብሼው ነበረ፡፡
ማቆላመጥ የሚወድ ሰው ጤነኛ አይመስለኝም፡፡ አጭበርባሪ ነጋዴ ነው የሚመስለኝ። በየስሙ ላይ ዬ' መለደፍ የፍቅር ሃዋሪያ መሆን ይመስላቸዋል፡፡

የቤተሰቦቻቸው መርዝ አልሰራ ሲል፣ (የተመረተበት ጊዜ አልፎ እንዳይሆን ሰግተው) ከፊልምም
ከመጽሄትም አዳዲስ መርዝ እየተሸከሙ ብቅ ይላሉ፡፡ በአነጋገር፣ በአለባበስ፣ በአስተያየት፣ በእግር፣ በዳሌ፣ በጣት፣ በፀጉር እናም በመጨረሻ በሃሜት፣ “ይሄ ልጅ ሴት አይመቸውም እንዴ? ማን ያውቃል? ዘመኑ ክፉ ነው እናትዬ፣ እንትን እንዳይሆን::

እነሱ ጋር ያልሆነ፣ እነሱን ያልፈለገ ጭራ አለው፤ ደብቆት ነው እንጂ፡፡ ቀንድ አለው፣ ጥፍር አለው፡፡ በዚህች ምድር ላይ እንደመናቅ የሚያም ነገር የለም፡፡ ንቀቴ አመማቸው !!

ቡምምምምምምምምም እውነት ፈነዳ !! “ይሄ ቀብራራ እዚህ ይኮፈሳል እናቱ እኝጀራ ጋጋሪ፣
ልብስ አጣቢ ነች አሉ”፡፡ ጮማ ወሬ ተገኘ፡፡ ዳሌያቸውን እየናጠጡ ፀጉራቸውን እየነሰነሱ፣ ጅራታቸውን ከሚቆሉላቸው ወንዶቻቸው ጋር አወሩ፡፡ ተሳለቁ፡፡ ሲያሸማቅቁኝ ሞከሩ፡ ራሳቸውን
ችለው መቆም ሲፈሩ፣ የእፉኝት ልጆች በልብስ አጣቢ ልጅ ሳቁ፡፡ የቤታቸውን አጠራቅመው
ለዘመን መለወጫ ቤታቸውን የሚያፀዱ ሁሉ፣ ሰው ሰራሽ ጠጉራቸው ራሳቸው ላይ ጀልቶ በጾም በጸሎት የሚፈታ ሁሉ፣ ተብረቅርቀው ሰው ነን ሊሉ፡፡ ልክ ለልክ ከተዋወቅን ቆየና ይሄም ጥይታቸው ከሸፈ፡፡
👍383👎1🥰1
ቢሆንም እኔ አሸብር ላይፍ' ሚሉት ጋጋታ ውስጥ ከሙታን ጋር ማኀበር አለመጠጣቴ
እንዳዷገናቸው ወደ ዱፍትርናው ተንደረደርኩ፡፡ ልማዴ ነው ስለኔ የሚንጫጩትን ትንሽ
እያደረግኩ ማለፍ፡፡ እንከን ፈላጊዎች ሚዛናቸው ከአሉባልታ ሌላ ምን ሊሰፍር...እፉፉፉፉ፣
ለማሸነፍ የተጠራሁ መሆኔ ሲገባኝ ተሸናፊ አቆላምጦም ይሁን ሳያቆላምጥ ሲጠራኝ አቤት
አልልም፡፡ እቤት ብትላቸው ቃላቸው እንድ ነው፡ “ኑ አብረን እንውደቅ!”.

የሕክምና ትምህርቴን ከጀመርኩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንዲት ሴት አስከሬን አየሁ፡፡ እድሜዋ
ሃምሳ የነበረ አሁን ግን ዘላለም የሆነ ጠይም ሴት። አስከሬኑ ለተማሪዎች የተግባር ልምምድ
ትምህርት የሚውል ነበር፡፡ ሁላችንም ለአስክሬን አዲስ ስለነበርን አንዳንዶቹ ደነገጡ፣ አንዳንዶቹ ተንቀጠቀጡ፣ አንዳንዶቹ ሊያስመልሳቸው ሞከረ (አንዲት ልጅ አስመልሷታል) እኔ
ግን እንባዬ መጣ፡፡

ሰው ሞቶ ሲያዩት እንዴት ያሳዝናል ኢትዮጵያዊ ሞቶ ሲያዩት እንዴት ያሳዝናል፡፡ የአንድ ምስኪን ኢትዮጵያዊ እስከሬን ማየት ከሞት ከራሱ የበለጠ ያሳዝናል ያስደነግጣል፡፡ ከዛ በሰራ አጋጣሚ በርካታ የፈረንጅ አስክሬን አይቻለሁ። ግን የፈረንጅ አስከሬን እንደ ኢትዮጵያዊ
አስከሬን አያስደነግጥም፡፡ ባዕድ ምድር ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ስትመለከቱ የሚሰማችሁ
የደመነፍስ ድንጋጤ ዓይነት፣ ግዑዝ ኢትዮጵያዊ አስከሬን ስታዩ ሕይወት ያለው ኢትዮጵያዊነት
ረብቦበት ይታያችኋል፡፡

ኢትዮጵያዊት እናት ሞታ ስትታይ እንዴት አንጀት ትበላለች መሰላችሁ፡፡ ዝም ይላል የሞተ ሰው፤ እጅና እግሩን አሳርፎ ዝም " ሰው እየጮኸ፣ እየተንጫጫ ወደ ዝምታው ነው የሚሮጠው::
እና ይህች ሴትዮ ዝምታዋ ላይ ደርሳ ነበረ፡፡ "ምነው ዘርፌ በሆነች፡፡

ከፉ ነገር እይቼ ለዘርፌ ያልተመኘሁበት፣ ለቀለመወርቅ ያላጨሁበት ብቸኛ ቀን ነበር፡፡ እንደውም 'ዘርፌንም ከዚህ ይሰውራት አልኩ፡፡ አንዳንድ ሰው በቁጣ፣ " ዝም በል!” ሲል “አፍህን ዝጋ ማለቱ ብቻ አይደለም፡፡ ከዛ ያለፈ እርግማን ነገር አለው፡፡ መምራት የምንፈልገው ሬሳን ነው
ካላሉ በስተቀር ለምንድን ነው መሪዎች ህዝባቸውን፡ “ዝም በል!” የሚሉት፡፡ ዝምታ ሰላም
አይደለም፣ አሁን ይህች ሴት ሰላማዊ ናት ? ዝምታ ኲርፊያ እይደለም፡፡ ይህቺ ሴት አኩርፋለች
? ዝምታ ትዕግስት አይደለም፤ ይህች ሴት ታጋሽ ናት ?
በምድርም የተመቻት ዓይነት ሴት ስላልነበረች ነው መሰል በጣም የተጎሳቆለ ሰውነት ነበረ ያላት፤ አስክሬን አንቱ አይባልም የተባለ ይመስል እንቺ ነበር ሁላችንም የምንላት፡፡ እንግዲህ
መፅሐፉ፣የብልሆች እግር ወደ ሀዘን ቤት ነው“ የሚለው ለምን እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው::
ሕክምና የምማረውም ለምን እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው፡፡

“ፍጠን አሽብር ሰዎች ዝምታቸው ላይ ሳይደርሱ” የሚል መልዕክት በውስጤ ያጣድፈኛል፡፡

ሰዎች ከፉም ይሁኑ ደግ፣ የሚጠቅምም ነገር ይናገሩ የማይጠቅም ዝባዝንኬ፡ ብቻ ዝምታቸው ላይ እንዳይወድቁ መሮጥ አለብኝ፡፡ ልቤ ታዲያ ደረቴን ፈጥርቆ የወጣ
እስኪመስለኝ ይመታል
ታፍኖ የኖረ ሚስኪን ሳያልፍለት እንዳይሞት ፡ በደሉን ሳይተነፍስ ዝም እንዳይል፥ የብዙ ብዙ
በደል መቃብር እንደሆነ ወደ መቃብር እንዳይወርድ እኔ አሸብር ዶከተር እሆናለሁ፡፡ ሰው ከቀኑ
እያልፍም ቢባልም ቅሉ፣ ቀኑን እስካላወቅነው ድረስ ቀን ለመጨመር እንሮጣለን ማምሻም እድሜ ነው።

ለእኔ ሰው በሁለት ይከፈላል፤ እናቴ አቲዬ እና ሌላው !! አቲዬ ትኑርልኝ፤ በቃ መኖር ያለባት
ሰው ናት፡፡ እኔ ልጇ ባልሆንም አቲዩ መኖር አለባት፡፡ ሌሎችም ይኑሩ አቲዬ መኖርዋን፣ ኖራም
ያንን አዘቅት መሻገሯን እንዲመሰከሩ !! እንግዲህ አንድ አስከሬን ነው ይሄን ሁሉ የሚያሳስበኝ፡፡

እኔኮ እስከሬን ሲባል የሚያብረቀርቅ ልብስ የሚለብስና ለአራት የሚሸከሙት አልጋ ነበር
የሚመስለኝ፡፡ ሞት እንዳለ አወቅኩ፣ ሰማሁ ሳይሆን አየሁት፡፡ ሞት ያፈረሰውን የሕይወት
ከተማ አየሁት፡፡ ያውም እናት የምትባል ዋና ከተማ፡፡ መምህራችን ረዳት ፕሮፌሰር ዘሩ ፊታችን ለተጋደመው አስከሬን የሚሰጡትን ትልቅ ክብር እና እንክብካቤ ሳይ ገረመኝ፡፡ አንዳንድ ዶክተሮች
በሕይወት ላለ በሽተኛ ከሚያደርጉት እንኮብካቤ በጣም የተሻለ ነበር፡፡ ይህ እስክሬን ከዛ በኋላ ያለ ሕይወቴን ቀይሯል፡፡ አስተሳሰቤን ቀይሯል፡፡ ሞት ማለት እርግማን መሆኑን አምኛለሁ
የሳይንሱ ባይልም፡፡) ዝምታ ጤናማ አይደለም፤ ከጭቆና ሁሉ የከፋው ጭቆና “ዝም በሉ!"
ማለት መሆኑን እስከሬኑ እየጮኸ ይመሰክራል፡፡

ለሰዎች ማዘን፣ በተለይ ዝም የሚሉ ሰዎች የጀመርኩትም ያኔ ሳይሆን አይቀርም። ቢሆንም
እስከምመረቅ ሲበዛ ዝምተኛ ነበርኩ፡፡ ውስጤ የሞተ ነገር ነበረ ትንሳኤ የሚያሻው፡፡ ትንሳኤው
በር ድረስ ታደርሰኝ ዘንድ የተሰጠችኝ ደግሞ ዛፒ ነበረች፡፡ የኔ ሚስኪን ዛፒ፣ ግራ የገባት ሙሴ፣ የድህነትን ባህር በፍቅር በትር እየከፈለች እኔና እናቴን ያሻገረች መሪ ነበረች፡፡

ዛፒ ምንም እንኳን በግል ሕይወቷ ደስተኛ ባትሆንም፣ ሙሉ የዩኒቨርስቲ ወጪዬን ልክ
በፍርድ ቤት እንደተወሰነበት ሰው ሳታስተጓጉል ትሽፍንልኝ ነበር። አደረገችልኝ ብዬ አይደለም
የማመሰግናት፣ ደግነቷ አያሸማቅቅም፣ ከርሷ ብር መውሰድ መብቴ እንዲመስለኝ አድርጋ ነው የምትረዳኝ፡፡ “አሹ እስኪ ዛሬ ጥናት ከሌለህ ራት ጋብዘኝ ትልና ራት ተጋብዘኛለች፡፡

በእኔና በዛፒ መካከል ለቁጥር የሚያዳግት የእድሜ ልዩነት አለ፣ ግን ጓደኛዋ የሆንኩ መስሎ
እንዲሰማኝ አድርጋኛለች:: የመጨረሻዋ ውብ ሴት ብትሆን እንኳን ከልዕልትነት ዙፋን ተምዘግዝጋ ታች የምትገኝበት የዝቅታ ዘመን አለ፡፡ ለሴት ልጅ ይሄ ከባድ ነው፡፡ ቢሆንም ሴቶች ከወንዶች በላይ ውድቀትን ዘንጠው እየሳቁ መቀበል ይችሉበታል፡፡ በእርግጥ ዛፒ እንዳንዴ በተጨናነቀ ሁኔታ ውስጥ ባለሁበት ሰዓት ከግቢ ትጠራኛለች፣ እንቢ ማለት አልችልም፡፡

እቤት እሄዳለሁ፡፡ ራሷን ጣል አድርጋ ደብሯት አገኛታለሁ፡፡ ከዚህ ድብርቷ ላወጣት እሞክራለሁ፡፡
በየቀኑ እደውልላታለሁ፤ ሲመቸኝ ወጣ ብለን እንዝናናለን፡፡

የአዲስ አበባ ወንድ እንደፈራ፣ ዛፒም እንደደበራት አምስት ዓመታት ነጎዱ፡፡ በዚህ ብቸኝነትና
ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆናም ግን ጀግነቷ ልክ አልነበረውም፡፡
ተመርቄ እስከምወጣ ሁለት ጊዜ ቤተሰቦቿ ጋር ውጭ ሄዳ ወደ አንድ ዓመት ስትቆይ እንኳን ጠቀም ያለ ገንዘብ ለእኔም ለአቲዬም መላኳን አቋርጣ አታውቅም ነበር፡፡ ይፈጥንብኛል ታሪኬ፡፡ በፍጥነት በሚበር መኪና መስኮት የምቃኘው እስኪመስለኝ ሁሉም ነገር ወደኋላዩ የሚፈተለከው በደንብ እንኳን ሳልመለከተው ነበር፡፡

አቲዩ ቀስ በቀስ የሰው ቤት ስራዋን እያቆመች የተወሰኑ ቤቶች ብቻ ለዛውም ሰርግ ሲኖር በኮንትራት ወጥ መሥራት የመሳስሉ ሥራ ላይ ብቻ ተወሰነች፡፡ ሰውነቷ ግን በጣም ተጎሳቁሎ ነበር፡፡ ድህነት የማይፋቅ ኣሻራውን ቆዳዎ ላይ አትሞ ቀርቷል፡፡ እጆቿ መሻከር የሚለው ቃል በማይገልፀው መልኩ ተፍረከርከዋል፡፡ ዐይኗ ለዘመናት በተጋፈጠችው የአሻሮና የማገዶ ጭስ እንዳያገገም ሆኖ ተጎድቷል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ግን አቲዩ ልክ ስሌለው ፍርሀት ውስጥ ተዘፍቃ ነበር፡፡ ከቀን ወደ ቀን ዝምታዋ እየከበደ ነበር የሚሄደው፡፡ ዝምታ እፈራለሁ፡፡ ዝምታዋ ፍርሃቷ በጣም ይብዛብኛል በተለይ ፍርሃቷ፡፡
👍264
አንዳንዴ በዚህ ባህሪዋ እበሳጭና እጮህባታለሁ፡፡ “ምን ላድርግ ብለህ ነው አሹዬ” ስትለኝ እንባዬ ይመጣል፡፡ የመንደሩ ትንንሽ ልጆች ጋር መንገድ ላይ ስትገናኝ ቆማ ልታሳልፋቸው
ትሞክራለች፡፡ ኳሳቸው ወደ ግቢ ቢገባባቸው በሁለት እጇ አንስታ ትሰጣቸዋለች፡፡ የሆነ ቦታ
ሄዳ እንደ ትልቅ ሰው ወንበር ላይ ከመቀመጥ ይልቅ እየፈራች ምንጣፍ ላይ ወይም ቁጢጥ ብላ
አንድ ጥግ ትቀመጣለች፡፡ ማንም ሲመጣ ወንበር ትለቃለች፡፡ ታክሲ ውስጥ ሳይቀር አንድ ቀን
ለአንዲት ልጅ ቦታ ልትለቅ ስትሞከር እጇን ይዤ በብስጭት አስቀምጫታለሁ፡፡ በቃ አዕምሮዋ
ውስጥ ትንሽ ነሽ” የሚል ክፉ መሀትም አኑረውበታል፡፡

ድህነት ገንዘብ የሚገዛውን ነገር ብቻ አይደለም የሚያሳጣው:: ለነገሮች ሁሉ ሰልፍህን ከኋላ
ያደርገዋል፡፡ አንዳንዴ ከአቲዬ በአስተሳሰብም በገንዘብም የሚያንሱ መንደርተኞች አቲዬን ሲያዩ ራሳቸውን ሊቆልሉ ሲሞክሩ እያየው ይገርመኛል፡፡ በቃ ይህቺ አዲስ አበባ ዝቅ ሲሉላት ሰው
አናት ላይ ቆማ ልትጨፍር ይዳዳታል ራሷ አናት ላይ ማንም ሲፈነጭባት አትነቃም እንጂ !...

ነገ ያልቃል
👍226
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ምን እንደሚያደርጉ ሳይታወቃቸው ከንፈር ለከንፈር ይገናኛሉ፡፡ ዓይናቸው እምባ አቅርሮ አንዱ ሌላው ላይ ማፍጠጥ ሆነ፡፡ ማሪየስና ኮዜትም የፈጸሙት ተግባር ይኸው ነበር፡፡

የማሪየስ አያት በዚህ ጊዜ ዘጠና አንድ ዓመት ሆኖአቸዋል፡፡ አሁንም
ከዚያ ትልቅ ቤታቸው ውስጥ ከሴት ልጃቸው ጋር ነው የሚኖሩት:: በዚህ እድሜያቸው ወገባቸው ሳይጎብጥና ሀዘን ፊታቸውን ሳይሰባብር ቀጥ ብለው
የሚጓዙና ለምሳሌነት ሊቀርቡ የሚችሉ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው::
ሽማግሌው ሠራተኞችን መደብደብና ምርኩዛቸውን ሳይዞ መንቀሳቀስ በተው ጊዜ ልጃቸው «አሁንስ አባቴ በእርግጥ አርጅቷል» እያለች ታስብ
ጀመር፡፡ በሐምሌ ወር የተጀመረው የፈረንሣይ አብዮት መጥፎ ስሜት
አሳድሮባቸዋል፡፡ ቢሆንም ሞራላቸው ብርቱ ስለነበር ለማንኛውም ነገር በቀላሉ አልተበገሩም፡፡ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን መጎዳታቸው ሳይሰማቸው አልቀረም:: ከአራት ዓመት በኋላ እንኳን አንድ ቀን ማሪየስ ከቤታቸው ተመልሶ ከጫማዬ ሥር ወድቆ ይቅርታ ይጠይቀኛል የሚል እምነት
ነበራቸው:: ማሪየስ ተመልሶ ከቤት ሳይወጣ እሞታለሁ የሚል ሀሳብ
ከሕሊናቸው ውስጥ ገብቶ አያውቅም:: እንዲያውም በቅርበ ማሪየስ ይመለሳል የሚለው እምነታቸው እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ ይህም ለውለታቢሱ የልጅ ልጃቸው የነበራቸው ፍቅር አጠነከረባቸው::

ይህ ልጅ ሰማይና ምድር ቀሚጨልምበት በክረምት ወራት ነበር ጥሎአቸው የሄደው:: ሽማግሌው በእርሳቸው በኩል ምንም ጥፋት እንደሌለና
ጥፋቱ የማሪየስ እንደሆነ በፍጹም ልቦናቸው ቢያምኑም ለልጁ የነበራቸው ፍቅር ግን አልተቀነሰም፡፡ በመጨረሻ ወደ ሞት መቃረባቸው ሲታወሳቸው
ለልጁ የነበራቸው ፍቅር ያይላል፡፡ ጥርሳቸው መርገፍ ጀምሯል:: ይህም ሀዘናቸውን ከፍ አደረገው::

አንድ ቀን ጉልበታቸውን አጣጥፈውና ዓይናቸውን በከፊል ጨፍነው ቁጭ ይላሉ፡፡ የተስፋ መቁረጥ ምልክት ከፊታቸው ላይ ይነበባል:: ሴት ልጃቸው ጥያቄ ጠየቀቻቸው:

"አባባ፣ አሁንም ልጁን እንደተቀየሙት ነው?»

ይህን ካለች በኋላ ለመቀጠል ስላልደፈረች ዝም አለች::

"ማንን ነው የምትዪው?» ሲሉ ጠየቅዋት::

«ያንን ምስኪን ማሪየስ፡፡»

የሽማግሌ ጭንቅላታቸውን ቀና አደረጉ:: ያንን የተሸበሸበወን
ክርናቸውን ከጠረጴዛ ላይ በማሳረፍ አገጫቸውን ደግፈው ያዙ፡፡ በጣም በተናደደና በተቆጣ አንደበት ተናገሩ፡፡

«ምስኪን ማሪየስ አልሽ? የማይረባ! እርሱ ብሎ ምስኪን፤ አጉራሹን የሚነክስ! የእኛ እልኸኛ! ልስቢስ፣ እንኳን ልብ ነፍስ የለውም::»

እምባ ያቀረረውን ዓይናቸው ልጃቸው እንዳታይ ከነበሩበት ፊታቸውን በማዞር ተነስተው ሄዱ:: ከሦስት ቀን በኋላ በዝምታ አራት ሰዓት ሙሉ ከአንድ ሥፍራ ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ ሽማግሌ ልጃቸውን በመገሰጽ ይናገራሉ::

«ስለዚያ ልጅ ሁለተኛ እንዳታነሽብኝ ብዬ አልነበረም?»

በዚያው ሰሞን መሴይ ጊልኖርማንድ እሳት እየሞቁ አምሽተው ስለደከማቸው በጊዜ ልጃቸውን ደህና እደሪ ብለው ወደ መኝታ ክፍላቸው ሄዱ:: ልጃቸው ከሚቀጥለው ክፍል ውስጥ በሩን ክፍት አድርጋ ልብስ እየሰፋች ነበር:: ሽማግሌው እሳት ይሞቁ የነበረው ብቻቸውን ሲሆን
መጽሐፍ ለስሙ በእጃቸው ይዘው ነበር እንጂ አያነቡትም::
እሳት እየሞቀ ሳለ የልጅ ልጃቸው ማሪየስን አስታወሱት:: አሁንም
ቢሆን ውስጥ ውስጡን ይናፍቃቸዋል:: ሊታረቁት ፈለጉ፡፡ ግን ልባቸው ውስጥ የገነነው ኩራትና እልህ መንገዱን ዘጋባቸው:: እንዲያውም ከነአካቴው የመታረቅ አሳብ ኅሊናቸው ውስጥ ስለገባ መላ ሰውነታቸውን አንገሸገሸው::

«ምን?» ሲሉ ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ ከአንገታቸው ቀና አሉ:: ከቤት
ውስጥ የገባ ስለመሰላቸው ተንገሸገሹ:: «ከዚህ ቤት ውስጥ ተመልሶ አይገባም» ሲሉ ለራሳቸው ቃል ገቡ:: ያ መላጣ ጭንቅላታቸው ነገር ስለከበደው ከደረታቸው ላይ ዘንበል ብሎ የወደቁ መሰላቸው:: ቀና ብለው
ከግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ስእል ላይ አፈጠጡ:: በአሳብ ተውጠው ሳለ ባስክ የተባለ የቤት አሽከራቸው ይገባል፡፡

«ጌታዬ ማሪየስን ያነጋግሩታል?» ሲል ጠየቃቸው:: ሽማግሌው ቀና ብለው ተመለከቱ:: ከአሳባቸው ባንነው ሲነቁ በጣም
ካመደንገጣቸው የተነሳ ጀርባቻው ቀዘቀዛቸው::
‹‹ምን አልክ?» ማሪየስን ነው ያልከው?
«እኔ እንጃ» ሲል ባስክ እየፈራ መልስ ሰጠ፡፡ «እኔ እንኳን በዓይኔ
አላየሁትም:: ሠራተኛዋ ናት የነገረችኝ፡፡ ውጭ ግን አንድ ወጣት መቆሙ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምናልባት ማሪየስ ሊሆን ይችላል፡፡»

«ግባ ግባ ግባ በለው» አሉ እየተንተባተቡ፡፡ ልባቸው እንደከበሮ እየመታ ዓይናቸውን በር ላይ ተክለው ቀሩ፡፡ በሩ ተከፈተ:: አንድ ወጣት በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ ማሪየስ ነበር፡፡

«ገባ በል እንጂ» በማለት እንዲጋበዝ የሚጠብቅ ይመስል ማሪየስ ከበሩ አጠገብ ቆም አለ፡፡ ጊዜው ጨልሞ ስለነበር የለበሰው አዳፋ ልብስ መቆሸሹ ብዙም አያስታውቅም፡፡ በሀዘን የተጨማለቀው ፊቱ ምንም እንኳን
ፀጥታ ቢሰፍንበትም መከፋቱን በግልጽ ያሳያል::

መሴይ ጊልኖርማንድ በደስታና በአድናቆት ልቡ እንደተነካ ሰው
ለጥቂት ጊዜ ዝም በማለት ሰማይ ሰማዩን አዩ፡፡ ማሪየስ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሠርቀው አዩት::

በመጨረሻ! ከአራት ዓመት በኋላ! ደስታ አንደበታቸውን ዘግቶ ሽባ
አደረጋቸው:: ባለፉት አራት ዓመታት እንዲያው ሲያስቡት ቆንጆ፣ ረጋ ያለና ምራቁን የዋጠ የጨዋ ልጅ እንደሚሆን ገምተዋል:: ቢመለስ ልባቸው |
በደስታ ፈክቶና ስሜታቸው በሕሊና ዕረፍት ረክቶ እጆቻቸውን ዘርግተው እንደሚቀበሉት ልቦናቸው ተመኝቶ እንደነበር ልቦናቸው ቢያውቁም ያ ሰዓት ሊመጣ ሳያወቁት የማይሆን ቃል አንደበታቸው ውስጥ ይገባል።

«ለምንድነው የመጣኸው?»

ማሪየስ ሀፍረት እየተሰማው መለሰ፡፡

«ጌቶች...»

መሴይ ጊልኖርማንድ ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ቢያቅፉት ደስ ባላቸው፤ ግን ማሪየስ አስቀይሞአቸዋል፡፡ በአንድ ወቅት ራሳቸውም ቢሆኑ
በወሰዱት እርምጃ ቅር መሰኘታቸው አልቀረም:: ማሪየስ ቢያስቀይማቸውም መታገስ እንደነበረባቸው ያውቃሉ፡፡ ደግና እልኸኛ ሰው የልቡን ደግነት
በእልህና በኃይለ ቃል እየሸፈነ ወስጥ ውስጡን ይሰቃያል:: ምሬቱ ትዝ ብሉአቸው እንዲናገር እድል ሳይሰጡት ጣልቃ ገቡበት::

‹‹ንገረኝ እኮ፣ ለምንድነው የመጣኸው?»

ጉልበቴን ለመሳም ወይም አቅፈህ ጉንጩን በመሳም ይቅርታ ለመጠየቅ ካልሆነ ለምንድነው የመጣኸው ማለታቸው ነበር፡፡ ማሪየስ አያቱን አተኩር
ሲመለከታቸው ሀሞታቸው መፍሰሱን ተገነዘበ፡፡

ሽማግሌው አሁንም በኃይለ ቃል አቋረጡት::

«ይቅርታ ለመጠየቅ ነው የመጣኸው? ተጸጽተህ ነው?»
ወደ እርሳቸው እንዲመለስ በር መክፈታቸው ነበር፡፡ እጁን የሚሰጥና የሚርበተበት መሰላቸው:: እውነትም ማሪየስ በድንጋጤ ሰውነቱ ተርበተበተ፡፡
ዓይኑን ወደ መሬት ሰበረ፡፡ ቢሆንም በድፍረት መልስ ሰጠ፡፡

«የለም ጌቶች::»

«እና ምንድነው የምትፈልገው?» ሲሉ ሽማግሌው ንዴትና ምሬት
እየተናነቃቸው ተናገሩ፡፡ «አሁን ከእኔ የምትፈልገው ምንድነው?»
ማሪየስ ሁለት እጆቹን በኃይል በመጨበጥ አጋጫቸው አንድ
እርምጃ ወደፊት ተራመደ፡፡

እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«አባባ ይዘኑልኝ::»
👍18🥰1
ይህ አነጋገር የሽማግሌውን አንጀት በላው:: ማሪየስ ይህን አባባል ቀደም ብሎ ቢናገር ኖሮ የመሴይ ጊልኖርማንድን ልብ ባለዘበው ነበር።
ትንሽ በመዘግየቱ ይህ ሊሆን አልቻለም:: ሽማግሌው ከተቀመጡበት ተነሱ::
ምርኩዛቸውን በሁለት እጃቸው ተደግፈው ቆሙ:: እንደማላብ ስላላቸው ግንባራቸው አቸፍችፎአል፡፡ ከንፈራቸው አሻቦ መሰለ፡በዚያ ግዙፍ ቁመናቸው ማሪየስን አቆልቁለው ሲያዩት ልቡን አሸበረው::

«የሚታዘንለት ጠፍቶ! ወጣቱ የዘጠና አንድ ሽማግሌ ይዘንለት!
የእኛ ሕግ አዋቂ፣ ጥሩ አነጋገር ትናገራለህ፡፡ እንኳን ደስ ያለህ::»
የፌዝ ንግግር ነበር፤ ቁጣም የታከለበት::

«እሺ ጠጋ በልና የምትፈልገውን ንገረኝ?»

«ጌቶች» አለ ማሪየስ፤ «እኔ ከዚህ መገኘት እንደሚያስከፋዎት
አውቃለሁ፡፡ ግን ስለቸገረኝ አንድ ነገር ላማክሮት ነው የመጣሁት:: ከዚያ በኋላ በቶሎ ከዚህ እጠፋለሁ::»

«ሞኝ ሰው ነህ» አሉ ሽማግሌው፤ «ማነው ከዚህ ጥፋ ያለህ?»

«ጌቶች» አለ ማሪየስ አሁንም ሲፈራና ሲቸር፤ «ትዳር ለመያዝ
ፈልጌ እንዲመርቁኝ ነው የመጣሁት::»

መሳይ ጊልኖርማንድ ደወል ደወሉ፡፡ ሠራተኛው በሩን በግማሽ
ከፍቶ ከበሩ ላይ ቆመ::

«ልጄን፣ አባትሽ ይፈልግሻል በላ

ከመቅጽበት ወዲያው በሩ እንደገና ተከፈተ፡፡ ልጃቸው ለመግባት ሳትደፍር መኖርዋን ለማሳወቅ ያህል ብቻ አንገትዋን በበሩ ብቅ አደረገች::
ማሪየስ እንደ ወንጀለኛ አንገቱን ደፍቶ ቆሞአል:: ቃል አይናገርም:: መሴይ ጊልኖርማንድ ከወዲያ ወዲህ ይንቆራጠጣሉ፡፡ ወደ ሴት ልጃቸው ዞር አሉ ሽማግሌው::

«ግቢ፣ ግቢ፧ ማሪየስ ነው:: ሰላም በዪዋ! ጌቶች ትዳር ለመያዝ
ይፈልጋሉ፡፡ ይኸው ነው ጉዳያቸው:: ሰላም ካልሽው በኋላ ልትሄጂ ትቺያለሽ፡፡»

አነጋገራቸው ጤነኛ አልነበረም፡፡ አክስቱ፡ በመገረም ማሪየስን ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉሩ ገረመመችው:: የምታወቀው ዓይነት አልመሰለችም::
«መሄድ ትቺያለሽ» የሚለውን ቃል ስትሰማ የለ ብላ ሰላምታ ሰጥታው አውሎ ነፋስ እንደሚያባርረው ደረቅ ቅጠል ሮጣ ሄደች::

የማሪየስ አያት ወደ እሳት ማንደጃው ተመልሰው ጀርባቸውን ለእሳት ሰጥተው ቆሙ::

«አንተ ነህ የምታገባው! በሃያ አንድ ዓመትህ! ዉሉን የጨረስከው አንተው ነህ! እና ልታገባ ትፈልጋለህ? ማንን? ለመሆኑ ግን ጥያቄ መጠየቅ
ይቻላል?»

ማሪየስ መልስ ለመስጠት አልቸኰለም:: ሽማግሌውም ለመልስ ፋታ አልሰጡትም::

‹ና ወደዚህ ጠጋ በል እስቲ: ፤ ጉዳይ አለህ አይደል እንዴ? ለመሆኑ የወር ገቢህ ምን ያህል ነው? ሥራ ትሠራ የለ?»

‹ሥራ የለኝም» አለ ማሪየስ ሳያወላውል::

«ሥራ የለኝም? እኔ ከምልክልህ ከአንድ ሽህ ሁለት መቶ ሊቫር ሌላ
ተጨማሪ ገቢ የለህም ማለት ነው? በእርሱው ነው የምትኖረው?»
ማሪየስ መልስ አልሰጣቸውም፡፡ መሴይ ጊልኖርማንድ ቀጠሉ፡፡
«እንግዲያውስ ልጅትዋ የሀብታም ልጅ መሆን አለባት:: »
«ከእኔም አትሻል፡፡›
«እንዴት! ጥሎሽ አታመጣማ!»
«አታመጣም::››
«ትንሽ እንኳን?»
«አይመስለኝም»
«ምንድነው የምትሠራው? አባትዋስ?
«እኔ እንጃ::»
«ማን ትባላለች?»
«መድምዋዜል ፎሽለማ»
«ፎሽ ምን?»
«ፎሽለማ»
«እትትት» አሉ ሽማግሌው::
«ጌቶች» አለ ማሪየስ በድንጋጤ፡፡
መሴይ ጊልኖርማንድ እርስ በራሳቸው ይነጋገሩ ይመስል ጣልቃ ገቡ

«አዎን፣ ሃያ አንድ ዓመት፣ ሥራ የለም፣ የዓመት ገቢ ሺህ ሁለት
መቶ ሊቭር፣ ባለቤቱ ሁለት ሱስ የሚያወጣ የወር ቀለብ ለመግዛት ገበያ ትወጣለች::»

«ጌቶች› አለ ማሪየስ ተስፋ በቆረጠ አነጋገር፤ ከጫማዎ ስር ተደፍቼ የምለውና ትህትና በተሞላበት አንደበት የምጠይቀው ልጅትዋን እንዳገባ
እንዲፈቅዱልኝና ቡራኬዎን እንዲሰጡኝ ነው::»

ሽማግሌው የፌዝ ሳቅ ሳቁ፡፡ ከዚያም ሳያስላቸው ያሳላቸው ይመስል የቀልድ ሳል ከሳሉ በኋላ የሚከተለውን በመሳለቅ ተናገሩ፡፡

«እህህህ! ምን እንደምትል ይገባሃል? ያልከው እኮ ምን አባትዋ ያቺን አሮጊት፣ ያቺን ደደብ አሁን ሄጄ እፈልጋታለሁ:: እኔን በማግኘትዋ ደስ ይላታል:: የእኔ ምኞት ሚስት ማግባት ብቻ ነው:: የማንም ልጅ ትሁን የማን፣ ደንታ የለኝም፡፡ እኔ እንደሆነ እግሬን ከሾህ የምከላከልበት፣ እርስዋም
እንደሆን ምንተ እፍረትዋን የምትሸፍንበት ቀሚስ የለንም:: ይህ ደግሞ ምንም አይደለም፡፡ የወደፊት እድሌን ከውሾች አፍ ላይ እንደተጣለ ቁራሽ
እንጀራ መጣሌ ነው፡፡ ታዲያ ምን ይጠበስ! ሚስቴን ከአንገቴ ላይ ጠምጥሜ መጨረሻ ከሌለው የችግር አዘቅት ውስጥ ብጥልቅስ! ይህ የእኔ ፍላጉት? የእኔ ምርጫ ነው፡፡ በዚህ ደግሞ መስማማት አለብህ:: ይህን ነው የምትጠይቀኝ፡፡ ውጣልኝ አንተ ልጅ፡፡ አንተ እንደፈለግህ እዚያው
ተጨማለቅ፡፡ ፑስለማን ወይስ ማን ናት ኩስለማህን እዚያው አግባ
ፈቃዴን ግን አትጠይቅ:: አይቻልም ጌታው.. አይቻልም ብያለሁ ፤
አይቻልም፡፡»

«አባባ!»

«በፍጹም!»

«በፍጹም» የሚለው ቃል የተናገሩት ጨርሶ ተስፋ በሚያስቆርጥ አባባል ስለነበር ማሪየስ ተስፋ ቆረጠ፡፡ ዝግ እያለ ወደፊት ሳይሆን ወደኋላ
ተራመደ፡፡ አሁንም እንዳቀረቀረ ነው:: መሴይ ጊልኖርማንድ በዓይናቸው ተከተሉት:: ማሪየስ ለመውጣት በሩን ከፈተ:: ሽማግሌው አንገቱን ከኋላ
አንቀው ይዘው ወደኋላ ሳቡት፡፡ ከበሩ አጠገብ ከነበረው መቀመጫ ወረወሩት::

«በል ዝርዝር ሁኔታውን ንገረኝ» ሲሉ ጠየቁት::
«አባባ» በማለት ማሪየስ የወረወረው አንድ ቃል ነው ይህን ለውጥ ያመጣው::

ማሪየስ በመገረም ቀና ብሎ አያቸው:: ከፊታቸው ላይ የእውነተኛ አያት አመለካከት ተንጸባረቀ፡፡ ለውጡ የሚያስገርም ነበር፡፡
«በል ቁጭ በልና ንገረኝ፡፡ አንድም ነገር አትደብቀኝ ስለ ፍቅረኛህ
ንገረኝ፡፡ ወይ አንተ ፈጣሪ! እነዚህ ወጣቶች እንዴት ይሳሳታሉ!»

«አባባ» በማለት ማሪየስ መናገር ጀመረ፡፡

የሽማግሌው ፊት እንደ ጠዋት ፀሐይ በራ፣ እንደ መስከረም አበባ
ፈካ፡:

«ኦው! ይኸው ነው የምፈልገው:: አባባ እያልክ ጥራኝ:: ከዚያ በኋላ
የሚሆነውን ታያለህ፡፡»

ከአሁኑ አነጋገራቸውና ሁኔታቸው ውስጥ የተቀበረ አንድ ዓይነት
ርህራሄና የሚጣፍጥ ግልጽነት የታከለበት አባታዊ ደግነት ነበር፡፡ ማሪየስ በዚህ ባልታሰበና ባልተጠበቀ ቅጽበታዊ ለውጥ በመገረም የሚናገረውን
አሳጣው:: ያንን አዳፋ ልብስ እንደለበሰ ከወንበሩ ላይ ቀረ:: አያቱ ከአዳፋው ልብስ ላይ ዓይናቸውን ተከሉ፡፡
«እንግዲህ አባባ» ብሎ ማሪየስ ንግግር ሲጀምር
«ብል ቀጥል» በማለት መሴይ ጊልኖርማንድ አቋረጡት:: «አሁንም»
ምንም ገንዘብ የለህም ማለት ነው? አለባበስህ የዱር አዳሪ ይመስላል፡፡»
ከኪሳቸው ውስጥ ቦርሳ አውጥተው ከማሪየስ አጠገብ ከነበረው ጠረጴዛ ላይ አኖሩት::
እስቲ እንካ ይህችን ውሰድና ልብስ ግዛባት» ብለው ጥቂት ገንዘብ ሰጡት

«አባባ» በማለት ማሪየስ ቀጠለ፡፡

አባዬ የልቤን ቢያውቁልኝ፤ እኔ እኮ እወዳታለሁ፡፡ ምናልባት አባባ
ወደኋላ ላይጥምዎት ይችላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት ሉክሰምበርግ ከተባለ ስፍራ ነው፡፡ በመጀመሪያ ይህን ያህል አልማረከችኝም ነበር፡፡ በኋላ ግን
👍12
ምን እንደነካኝ አላውቅም ፤ ከእርስዋ ጋር ፍቅር ያዘኝ:: በእርስዋ ምክንያት ምን ያህል እንደተሰቃየሁ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ አሁን እንኳን በየቀኑ
ቤትዋ እየሄድኩ እንገናኛለን፡፡ መገናኘታችንን ግን አባትዋ አያውቁም፡፡ የምንገናኘው ማታ ማታ ግቢያቸው ውስጥ ከሚገኘው የአትክልት ሥፍራ
ነው:: አባትዋ ይህን ባለማወቃቸው ወደ እንግሊዝ አገር ይዘዋት ሊሄዱ ነው:: የመጣሁት ይህን ልነግርዎት ነው:: መቼም ጥላኝ ከሄደች አብዳለሁ::
ማበድ ብቻ አይደለም፤ እሞታለሁ:: ራሴን ወንዝ ውስጥ ወርውሬ ነው ሕይወቴን የማጠፋው:: ስለዚህ ከማበድ ወይም ራሴን ከማጠፋ ባገባት
ይሻላል፡፡ ይህ ነው እውነታው፤ ከዚህ ሌላ የምጨምረው የለኝም::»

አያቱ ከደስታቸው ብዛት አጠገቡ ሄደው ቁጭ አሉ:: ታሪኩን እየሰሙና ትምባሆአቸውን እየማጉ የልጅ ልጃቸውን ድምፅ መስማቱ ከልብ አስደሰታቸው::

«ማሪየስ! እድሜ የሚያመጣው ነገር ስለሆነ በአንተ እድሜ ያለ
ወጣት ፍቅር ቢይዘው ትክክል ነው:: የተረገሙ ቆንጆ ሴቶች ናቸው:: ይህ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የምትላትን ልጅ እኔ አላውቃትም:: ይህ ደግሞ ከጉዳት ላይ የሚጥል አይደለም:: እኔም ያለፍኩበት ነገር ነው፤ ያውም ከአንዴ በላይ:: ያኔ ምን እናደርግ እንደነበር ታውቃለህ? እስከዚህም ከቁም
ነገር አንጥፈውም:: ወደ አሳዛኝ መጨረሻ አንሮጥም ነበር፡፡ የነገሮችን ቀኝና ግራ እናያለን እንጂ ለጋብቻ አንቸኩልም፡፡ ይህን ያህል ቀልባችን አልተገፈፈም::
በዚያን ጊዜ «አንተ፣ እስቲ የጅብ ችኩል አትሁን፤ ለጋብቻ አትሩጥ» እንላለን፡፡ ወደ አያቶቻችን ሮጠን ስንሄድ ደጉ አያታችን እጁን ዘርግቶ
ይቀበለናል፡፡ እኛም አባዬ ጉዳዩ እንዲህ ነው' እያልን እናጫውተዋለን፡፡
እርሱም ይህማ ደግ ነው ሲል ይመልስናል:: አንተም አንድ ቀን ሽማግሌ ባለፈበት ታልፋለህ፡፡ በተራህ ታረጃለህ፡፡ በአንድ ወቅት እኔም ወጣት ነበርኩ፡፡ እኔ አሁን የምመክርህን አንተም ለልጅ ልጅህ ትመክራለህ::
ይኸውልህ በዚህ ሁለት ፒስቶልስ ራስህን አስደስት፡፡ ከዚህ የተሻለ የለም፡፡
ቸኩለን ትዳር አንይዝም፡፡ ይህ ደግሞ ደስታና ፍስሐ አይነሳንም ፤ ገባህ?»
ማሪየስ ግራ ተጋብቶ ምን ብሎ እንደሚመልስ ስለተሳነው አንገቱን
ብቻ ነቀነቀ

ደጉ ሽማግሌ በሳቅ ፈነዱ፡፡ እንደመጥቀስ ብለው አንድ ዓይናቸውን ጨፈኑ፡፡ የማሪየስን ጉልበት መታ፣ መታ አደረጉ:: ቀጥ ብለው አዩትና ፍቅር በተሞላበት አንደበት ተናገሩት::

«አንተ ደደብ! በል እንግዲህ አሮጊትህ፣ እመቤትህ ትሁና!»

የማሪየስ ፊት ተለዋወጠ፡፡ አያቱ ከተናገሩት ንግግር አንዱንም
ኣልያዘም:: ሆኖም በመጨረሻ «አሮጊትህ፤ እመቤትህ ትሁና» ብለው የተናገሩት ቃል እንደ ጦር አጥንቱን ሰርስሮ ወጋው::
ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ቆቡን አነሳ፡፡ ቀጥ ብሎ ወደ በሩ ሄደ ::
ከበሩ ሲደርስ ፊቱን አዙሮ ለጥ ብሎ በማጎንበስ እጅ ነሳቸው፡፡ አያቱን እጅ ነስቶ ቀና ሲል «ከአምስት ዓመት በፊት አባቴን አስቀይመውት ነበር፡፡ ዛሬ
ደግሞ ሚስቴን አስቀየምዋት፣ ሰደብዋት፣ ከአሁን በኋላ ከእርስዎ የምጠይቀው ነገር አይኖርም፧ ደህና ይሁኑ» በማለት ተናገረ፡፡
አያቱ ደንግጠው ከነበሩበት ዞር ብለው እንዲያቅፉት ሁለት እጃቸውን ዘረጉለት:: ማሪየስ ግን ቶሎ ብሎ በሩን ከፍቶ ከወጣ በኋላ በሩን መልሶ ዘጋው::

ሽማግሌው ለጥቂት ጊዜ ከነበሩበት ሳይነቃነቁ እንደ ሐውልት ተገትረው ቀሩ፡፡ በመብረቅ እንደተመታ ሰው ሰውነታቸው ደነዘዘ፡፡
ለመናገር ቀርቶ መተንፈስ የተሳናቸወ መሰላቸወ:: በመጨረሻ ከተቀመጡበት ወንበር ራሳቸውን አላቅቀው የዘጠና አንድ ዓመት ሽማግሌ
ሊሮጥ በሚችልበት ፍጥነት ተራምደው በሩን ከከፈቱ በኋላ «እባካችሁ እርዱኝ» ሲሉ ተጣሩ፡፡

ልጃቸው ከተፍ አለች:: ከዚያም ሠራተኞች ከያለበት ብቅ ብቅ አሉ።

«ተከተሉት! ያዘት! እኔ ምን አደረግሁት! አብዷል! መጥፋቴ ነው የፈጣሪ ያለህ! ወይ አንተ አምላክ፣ ከአሁን በኋላስ አይመለስም» በማለት
ቀባጠሩ፡:

ወደ መስኮት ሄደው ግማሽ ሰውነታቸውን በመስኮት ብቅ አድርገው ወደ ውጭ ተመለከቱ፡፡ «ማሪየስ፣ አንተ ማሪየስ፣ ማሪየስ፣ ማሪየስ» ሲሉ ተጣሩ፡፡

ማሪየስ በጣም ርቆ ስለነበር አልሰማቸውም፡፡ ሽማግሌው በሁለት እጃቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ከወንበር ላይ ተቀመጡ:: ሰውነታቸው ተስፋ ቆርጦ፣ አንጀታቸው ተኮማትሮ፣ ልባቸው ደምቶና የወደፊት ኑሮኣቸው
እንደ ጨለማ ጠቁሮ በማየት ከተቀመጠበት ፈዝዘው ቀሩ፡፡

💫ይቀጥላል💫
👍24🥰1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሦስት

....ዩኒቨርስቲ ውስጥ የነበረኝ ሕይወት የአንድ መልካም ተረት ፍፃሜ ይመስል ነበር፡፡ ልክ
ከዛም በሰላምና በደስታ ይኖሩ ጀመር” ተብሎ እንዳለቀ ተረት፡፡ ብር አልቸገርም ነበር እድሜ
ለዛፒ፡፡ ጊዜ ባገኘሁበት ቀን ሁሉ አቲዬን አያታለሁ፡፡ በየቀኑም እደውላለሁ፡፡ አቲዬን በስልክ
ማውራት ከባድ ነው፡፡ በቃ ጥያቄዎቿ አንድ ዓይነት ናቸው፤ “
እንጀራው ጥሩ ነው ?”፣ “ልብስህ
አልቆሸሽም ?”፣ “ንባብ አታብዛ፣ በጊዜ ተኛ፤ ራስህን ያምህል፣ ማታ ማታ ጋቢ ልበስ፣ አሹ..
ደሞ እጅህን ወጣ ወጣ አታድርግ የሰው ዐይን ጥሩ አይደለም ሁሉንም በጥሞና አዳምጣታለሁ፥
ስለራሷ ስጠይቃት “እኔ ምን አለብኝ ብለህ” ብቻ ነው መልሷ፡፡ አቲዬ የሚያሰቃይ የወገብ ህመም
እንዳለባት እንኳን ያወቅኩት ከተመረቅኩ ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር፡፡ እንዳልጨነቅ ደብቃኝ፤
ፍፁም በተረጋጋ ሕይወት ውስጥ ትምህርቴ ላይ ብቻ መሉ ሐሳቤን ሰብስቤ እንዳጠና:: የሰው አፈጣጠሩ እየገረመኝ፣ የበሽታ መከሰቻው ምክንያት ብዛት እና መነገድ እያስደነቀኝ፣ ለዛውም የሰው ልጅ ምህረቱ ባይበዛለት በቀናት እድሜ ከምድር ተጠራርጎ የሚጠፋ ትበያ መሆኑ እያስደመመኝ፣ ሰው የምጠላው እኔ የሰው ጠላት የሆነ በሽታ ጋር ድብብቆሽ ስጫወት ወደ መመረቂያዬ ተቃረብኩ፡፡

ሴት አይቀርብም" ይሉኛል፡፡ ይሄም እንደ ጨዋነት ተቆጥሮልኝ ነበር፡፡ እኔ ባጠቃላይ ሰው
ነው የማልቀርበው፡፡ ለምን ለይተው፣ “ሴት አይቅርብም' እንደሚሉኝ ይገርመኛል፡፡ ሲጀመር
ማንም ጋር የሚያገናኘኝ የትምህርትና መሰል ጉዳዮች ከሴትም ይሁን ከወንድ ርቄ አላውቅም፡፡

ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለዛውም የሕክምና ትምህርት ላይ ብቸኛ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፡፡
ቢሆንም ከማይረባ መጠላለፍና በሕይወቴ አንድ እርምጃ እልፍ በማያደርገኝ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ
የመዳከር ፍላጎቱ አልነበረኝም፡፡ ለምሳሌ ፆታዊ ፍቅር !! ወንድ እና ሴት ቆመው ወይም አንድ
ጥግ ተቀምጠው ያንን ሁሉ ሰዓት ሲቆዩ ምን ጉድ እንደሚያውሩ ይገርመኛል፡፡ ፍቅር ለምን
አይይዘኝም ብዬ ያሰብኩት አንዲት ልጅ እንዳፈቀረችኝ የነገረችኝ ጊዜ ነው፡፡ ማህሌት ነው
ስሟ መጀመሪያ ስታፈጥብኝ አጋጣሚ መስሎኝ ነበር፣ ሲደጋጋም የሆነ ነገር ፈልጋ ይሆናል ብዬ ችላ አልኩት። ከዛ ከበበችኝ፡፡ አየር ሆነች፡፡ ላይብረሪ ካለሁ አለች፡፡ የሆነ ቦታ ከተቀመጥኩ ከሆነ ቦታው ፊትለፊት፣ ከኋላ ወይም ከጎን አለች። ባለፍኩበት ታጋጥመኛለች፡፡ ከሰላሳ መንታ
እህቶቿ ጋር ወደ ዩኒቨርስቲው አብራ የገባች እስኪመስለኝ በዛችብኝ፡፡ በመጨረሻ ወደድኩህ
አለችኝና እርፍ !!

እንደው አጋጣሚውን አልለፈው ምንስ ኣባቴ ቢክደኝ ባባቴ ወንድ አይደለሁ አልኩና ልሞክር
ወሰንኩ፡ ግን ልጅቱ በቀጣዩ ቀን ሰለቸችኝ !!

በቃ እግዚኣብሔርን ባፈቅር ይሻላል የሴት ፍቅር አያዋጣም' አልኩ፡፡ ሳይቆይ ግን ዓለም እግዜርን የሚያፈቅርበት አካሄድ እኔ ከማፈቅርበት ጋር አልገጥም አለኝ፡፡ አንድ እግዜርን በስንት መንገድ እንደሚያፈቅሩት ስመለከት አፈቃቀሬ የተሳሳተ ይሆን እንዴ ብዬ ፈራሁ፡፡

አንድ ቀን ከግቢ ወጥቼ የተማሪው ኪስ ሞላ ሲል የሚያዘወትራት ሬስቶራንት ሄድኩ፡፡ ምሳዬን
ኣዝዤ ስጠብቅ የዲፓርትመንቴ ልጆች መጡና ፊት ለፊት ተቀመጡ ሦስት ሴታች፡፡ ብዙ
ሴቶች ሲሰበሰቡ ኀብረተሰቡ የጫነባቸውን የፆታ ተፅእኖ ቀንበር የሰበሩት ይመስላቸዋል መሰል
ድፍረት ይጨምራሉ ጮክ ብለው ማውራት መሳቅ ምናምን…፡፡

ያዘዝኩት ምግብ ጭሱን እያግተለተለ መጣ፡፡ አስተናጋጇ ገነትን በስሀን ይዛልኝ የመጣች ነው የመሰለኝ፡፡ ርቦኝ ስለነበረ የምግቡ ሽታ የተለየ ሆንብኝ፡፡ አንገቴን ዝቅ እድርጌ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፣ጸሎት ይመስላል፡ ግን አልነበረም:: በጭራሽ ! መቼ እንደጀመርኩት ባላስታውስም፡ በተለይ ርቦኝ የሚበላ ነገር ሳገኝ፡ ደሰ የሚል ምግብ ሲቀርብልኝ ሁልጊዜም እንዲህ አደርጋለሁ፡፡ ጥልቅ የሆነ ስሜት ውስጤን ይሞላውና የሚያስገርም የአፍታ ዝምታ ውስጥ እገባለሁ፡፡ ለሞተው
የረሀብ ዘመኔ አጭር የህሊና ጸሎት !

ቀና ስል ሴቶቹ በግርምት አፋቸውን ከፍተው ያዩኛል፡፡ ፊታቸው ላይ ማክበር፡ መቀራረብ መፈለግ ነበር፡፡ ልክ እንደማላውቃቸው ሰዎች ችላ ብያቸው መብላት ጀመርኩ። በልቼ እንደጨረስኩ ቡና አዘዝኩ፡፡ እንዷ ወደኔ መጣች…ኤጭጭጭጭ !

“ሰላም ላንተ ይሁን፣ አሸብር!”

“ሃይ” አልኳት ባጭሩ፣ ስናገር ሊያገሳኝ ነበር፡፡

“መቀመጥ ይቻላል ?” አለች ለመቀመጥ መንገድ ጀምራ፡፡ ከዛም እንደ እኔ ቡና አዘዘችና ወሬ
ጀመረች፡፡ “ስታመሰግን አየንህ ክርስቲያን እንደሆክ አናውቅም ነበር” አለች ፈገግታዋ ፊቷ ላይ እየተንተገተግ፣
አልመሰስኩሳትም፡፡

“ፈሎሽፕ አለን ብንጋብዝህህህ ደስ ይለኛል፡፡ በቃ አብረን ጌታን ማምለክ ነው አላማው፡፡ ዕሮብና
ቅዳሜ ከሰዓት ነው ፕሮግራሙ” የሆነች ወረቀት ሰጠችኝና አመሰግናኝ ቡናዋን ሳታጋምሰው
ሄደች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር ተያይዘው ወጡ፡፡ ተመራርጠው ጓደኛ የሆኑ ይመስል ሦስቱም በቁመትም
በቅጥነትም አንድ ዓይነት ነበሩ፡፡

እንግዲህ ይሄ ምግብ ሲቀርብ ማቀርቀሬ ነው የአብረን እናምልክ!” ግብዣ ያመጣብኝ፣ ወላ ያመጣልኝ፡፡ ዝም ብዬ ሳስብ ከእነዚህ ልጆች ጋር እንዴት ነው በጋራ የምናመልከው?" ብዬ
ገረመኝ፤ እኔ ለየትኛውም እምነት፣ ለየትኛውም አምልኮ ግድ ያለኝ ሰው አይደለሁም፡፡ በሕይወቴ
ሙሉ የፀለይኩበት ቀን ኖሮ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር የእኔ ብቻ ስለሚመስለኝ ሌሎች ጋር
በጋራ ማምለኩም፣ መዘመሩም ምኑም ትዝ ብሎኝ አያውቅም፡፡
እግዚእብሔር እኔ ጋር በመተባበር አዲስ አበባን ድራሽዋን ለማጥፋት እስከመረቅ እየጠበቀኝ
አልያም እንደ ኖህና ቤተሰቡ እኔና አቲዬ ወደ መርከበ እንድንገባ ፈልጎ የጥፋት ውሀውን
ያዘገየው ስሰሚመስለኝ ማንም ጋር ማምለክ ፈልጌ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ቀተጋበዝኩበት ቀን
ቀረሁ፡፡ ንዝንዛቸው ግን መቆሚያ መቀመጫ ኣሳጣኝ፡፡ አንድ ቀን፣ “ይቅርታ የምትሉቀት ቦታ
መሄድ ስለማልፈልግ ካሁን በኋላ በዚሁ ብናቆም' አልኳት አንዷን በቁጣ፡፡

አዎ ተቆጥቼ ነበር " እግዚአብሄርን በምቾት የሚያውቁት ሞልቃቆች የቻፕስቲክ መግዣ ሲያጡ፣
“አግዚአብሔር ማነው?” የሚሉ..እግዚአብሄርን እንዲያስተዋውቁኝ አልፈልግም፡፡ አይቻቸዋለሁ በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ፣ ዶሮ ሦስት ጊዜ ሳይጮህ ጴጥሮስ ጌታን ሦስት ጊዜ እንደካደው የሚያትት መዝሙር እያንጎራጎሩ እነሱ ራሳቸው የሃብታም መኪና ጡሩንባ ባምባረቀ ቁጥር ከራሳቸው ሰላሳ ጊዜ ሲካካዱ፡፡ አይቻቸዋለሁ
የጌታ የማዳን ድንበር አቃቂና ኮተቤ ድረስ ብቻ ይመስል የአዲስ አበባ ልጆች ብቻ ተጠራርተው፤ “በጌታ ፍቅር” ምሳ ሲገባበዙ፣ ቸርች ሲሄዱ - የፅንፍየለሽ ከታማያዊ ዘረኝነት የሚነበብ ነገር ሲዋዋሱ፡፡አይቻቸዋለው በየእምነቱ ተቧድነው ሲናቆሩ ሲጠዛጠዙ፡፡ እኔ እና እናቴ እግዚእብሄርን ገደል ጫፍ ላይ እንደተንጠለጠለ ገመድ የሙጥኝ ብለን ሕዝብ ከዛ ከዚህ ሲገፋን፣ ድህነት እጃችንን እየቀጠቀጠ የመዳኛ ገመዳችንን ሊያስለቅቀን ሲታገል፣አንለቅም" ብለን የተረፍን ሚስኪኖች ነን፡፡ ሰው አትመልከት እግዜርን እንጂ” ይሉኛል፣
አብረን እናምልክ! ብሎ ጠርቶ 'ሰው አትመልከት፣ ማለት ምንድን ነው?
👍39
እግዚአብሄርን የማረፈያ ምቹ ሳሎን ሳይሆነን በፊት የውሽንፍርና የማዕበል መሻገሪያ ድልድያችን
ሆኖ እናውቀዋለን፡፡ መዝሙር በአፋችን የለም፣ እንጠቅሰው ምዕራፍ፣ እንመዘው ቁጥር የለንም ግን አንድ ነገር እናውቃለን፤ እግዚእብሄር ራሱን ያስተዋወቀን “አደርጋለሁ፣ እሰራለሁ” እያለ በሞፎከር ሳይሆን እየሰራና እያደረገ ነው፡፡ ፅኑ ክንዱን እያሳየ፡፡ ያስጨነቀንን ነገር ሁሉ እንደትቢያ ሲበታትነው እኔና እናቴ የዐይን ምስክሮች ነን፡፡ ሽባ ተተረተረ ቢሉን፣ እውር በራ ቢሉን፣ ሰማይ ቢከፈት፡ ምድር ቢናወጥ፣ ተዓምር ቢነግሩን መልሳችን አንድ ነው፣
አልሰሜን ግባ በለው፤ እግዚእብሄር ለእኛ ያደረገውን ነው ለሌሎች ያደረገው፡፡ ከራሱ ከፈጣሪ የተሰበክን ነን በስራው !!

ምግብ ፊቴ ሲቀርብ ውስጤ በመደነቅ ይሞላል. እነዚህ በመከራ ጩኸት እና በነፍስ ዋይታ
ሳይሆን በመዝሙር የተጠሩ ቆንጆዎት ይህን ብነግራቸው ያምናሉ ?…መሪር ትዝታ አለኝ፡፡
እንጀራ በቆረስኩ ቁጥር እንደወጥ የማጠቅሰው ፅልመት፡፡
ሕፃን ሆኜ ከአቲዬ ጋር ልብስ ቀምታጥብበት ቤት እንሄዳለን፡፡ አቲዬ የተቆሰለ ቆሻሻ ልብሳቸውን
ስታጥብ ባለቤቶቹ አጥንቱ ብቅ ጥልቅ እያለ የሚንተከተከ ቀይ ወጥ በረንዳቸው ላይ በትልቅ
ብረት ድስት ጥደው አያለሁ፡፡የሚንተከተክ ሽሮ አያለሁ፡፡ የሚጋገር ትኩስ እንጀራ አያለሁ፡፡
ደግሞ ሽታው አፌን በምራቅ ይሞላዋል ያቅለሸልሸኛል፡፡

እኔና አቲዬ ቁርስ ሳንበላ ነው የምንወጣው፡፡ አቤት ምሳ ሰዓት ኣራራቁ፡፡ የአቲዬ ኣሰሪዎች
ልጆቻቸውን ከሚጫወቱስት ለምሳ ይጠሯቸዋል፡፡ አቧራ የነካ የልጆቻቸውን ልብስ ከላያቸው
ላይ ገፍፈው ወደ አቲዬ የልብስ ቁልል ይጥሉና ይዘዋቸው ወደቤት ይገባሉ፡፡ በመቀነሻ ሰህን
ወጡን፣ አጥንቱን ጭምር ጨለፍ አድርገው ቀንሰው ይገባሉ፡፡ ከመጨለፉቸው በፊት በጭልፋው
አንድ ሁለቴ ማሰል ማሰል ያደርጉታል፤ አጥንቱና ወጡ ይደበላለቃል ፡፡ ይርበኛል !! በጣም ይርበኛል፡፡ ወጡ ሲንተከተከ ድምፁ እስከዛሬ ጆሮዬ ላይ አለ። የእነዛ ሰዎች ድምፃቸው
ይሰማኛል፡ “ብሉ እንጂ አጥንቱን ምነው ፈራችሁት እየተባባሉ፡፡ 'አልጫው አልጣፈጣችሁም
እንዴታ” እየተባባሉ፡፡ ትሪ፣ ጭልፋ ሲንኳኳ ይሰማኛል፡፡ ብቅ ብዬ ባያቸው እወዳለሁ፡፡

አባወራው፣ “እስቲ የአጥንት መቀጥቀጫ አምጪ ይላል ስጋውን የተገፈፈ ነጭ እንቢልታ
የሚያህል ቅልጥም ወድሮ ወደ በረንዳው እየወጣ፡፡ ከሽ ያደርገውና እንጋጥጦ መቅኒውን
ይስባል፡፡ ጉሮሮው ወደ ላይ ወደታች ይንቀሳቃላል፡፡ የእኔም ጕሮሮ ይንቀሳቀሳል፡፡ ምራቄን
ደጋግሜ እውጣለሁ።

የቅልጥም መርዘም እና ሰውዬው ወደ ሰማይ ወድሮ ጫፉን አፉ ውስጥ አስገብቶ ሲመጠው
ሰማይ ላይ ያለውን ደመና በቀሰም የሚመጠው ይመስላል፡፡

“አይይ…ወደቀ” ይላል ወደ መሬት እያየ፡፡ ሚስቱ ጉርሻ ጠቅልላ ወደ በረንዳ ትወጣላች፣ እችን ብቻ አፈር ስሆን!” እያለች በወጥ የረሰረሰ ጉርሻ፡፡ ውስጡ የተከተፈ ስጋ ወይም እንቁላል ሊኖረው ይችላልጎ እላለሁ በሆዴ፡፡ አንከርፍፉ ባሏን እንዲጎርስላት ትለምነዋለች፡፡ “ውይ ምኔ ላይ ይቀመጥ ሆዴ እኮ ሞላ” ይላል፡ “ለዚህች ቦታ አይጠፉም በሞቴ፡፡ አፉን ይከፍትና ጉርሻው እንዳይንጠባጠብ የግራ እጁን መዳፍ ከታችኛው ከንፈሩ ስር ይገድበዋል፡፡ ጉርሻውን
በሁለት ጉንጩ ሞልቶ እያላመጠ ተከታትለው ወደ ውስጥ ይገባሉ፡፡

“አሽብር!” ትለኛለች እቲዬ ድንገት:: ማፍጠጤ ሲበዛ፤ “እንካ ብስኩት ግዛና ና" ብላ አሮጌ መሀረቧን ፈትታ አንድ ብር ትሰጠኛለች፡፡ አንድ ብሩን ስታወጣ መሀረቡ ባዶ ይሆናል፡፡ ብስኩት ገዝቼ እመልሳለሁ፡፡ ዛሬ ላይ ሳስበው የሚቆጨኝ ለአቲዩ ብስኩት አልሰጣትም ነበር፡፡ ብቻዬን
እበላለሁ፡፡ በሩ ይከፈትና “አፀደ እቺን ለቅለቅ አድርጊያት ልጆቹ ሲንቀዝቀዡ ወጥ ደፉበት'፡፡
አንዳች የሚያከል የሰውየውን ኮት ትጨምራለች ባለቤቷ፡፡ ሁልጊዜም በሩ ሲከፈት ሰሃን ይዛ
የምትመጣና “ምሳችሁን ብሉ!” የምትል ይመስለኝ ነበር፥ ግን ብላን አታውቅም፡፡

ኣንዳንዱ ቤት ደግሞ ቁራሽ እንጀራ (ወጥ የነካካ) በሰሃን ይዘው ይመጡና፣ “እናትዬ እሷን
ለቅለቅ እድርጎሽ ስትጨርሺ እቺን ብይ” ትላለች አሰሪዋ፡፡ እሷን ለቅለቅ ያለቻት ቢደረደር
ሱቅ የሚሞላ ድርቶ ነው:: በነገራችን ላይ በራሴ ገጠመኝ እንዳየሁት ብዙ ሚስቶች ከፉዎች፣ ስስታሞችና ታላቅነታቸውን ለማሳየት ሠራተኛ የሚሰድቡ ናቸው፡፡ ባሎቻቸው ይሻላሉ፡፡ አቲዬ ታዲያ፣ "አሹ እችን ብላ” ትልና ፈገግ ብሳ ሰሃኑን ለኔ ሰጥታ ስራዋን ትቀጥላለች፡፡ አቲዬ ስትበላ አይቻት አላውቅም። ይገርመኛል፡፡ አቲዬ ካለምግብ መኖር የምትችል እየመሰለኝ በእርግጥም እገረም ነበር፡፡

ርሃብ እንደ ብርድ፣ እንደ ሙቀት እንደ ደስታ እንደ ሃዘን ሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠር ስሜት
ብቻ የሚመስላቸው ሞኞት አሉ፡፡ ርሃብ በሽታ ነው ፤ ቆሻሻ የሆነ በሽታ ነው፡፡ ዘመን ተሻግረው
ስለ ሰባ ሰባት ድርቅ ሲያወሩ፣ ስለ ስልሳ ስድስት ርሀብ ሲደሰኩሩ፧ እዚሁ በረንዳቸው ስር ከነእናቱ
የተቆራመድንብት ስንት አሰቃቂ ቀን አልፏል። ስንት ከፉ ቀናት ወደ ውስጥ አስለቅሰውናል፡፡
መሐል አዲስ ኣበባ በረሀብ የሚሞት የለም ሲሉኝ፣ ጥጋበኞች የምላቸው ዛሬ ስንቶች ናቸው?

ይሄ ልመናን ስራው ያደረገ ለማኝ ይመስሰናል የሚራበው:: አሉ ክብሩንም ይሉኝታውንም
ጥታ ሆዱን ሞልቶ፣ “የአዲሳባ ሕዝብ ውሎ ይግባ" እያለ ያድራል፡፡ መቀመጫዋን እያየህ፤ በዐይንህ የምትከተላት ዘናጭ ቆንጆ ሆዷ ሲፈተሽ ግን ማን ያውቃል፣ ሱፉን ለብሶ ላፕቶፑን
እንጠልጥሎ ከሥራ የሚወጣውን ጎልማሳ ብትመረምረው ግን ሙሉቀን እህል በአፉ አልዞረም
ይሆናል። ራበኝ ለማለት ይሉኝታ ያነቀው ባለዲግሪ ረሀብተኛ ነው አለ ስንለው እዚህ ግባ በማይባል በሽታ ክንብል የሚለው፡፡ በስራዩ የገጠሙኝ እልፍ ናቸው፡፡ ዘናጭ ረሀብተኞች፡፡በምግብ እጥረት እንዲሁ የቀሩ

ረሀብተኛው ርሃቡ እስኪጥለው የሚንጠራወት፣ በየበረንዳው ጃንቦውን ወዝቶ የምታየው ህዝብ
የበላውን እንዲያንሸራሽርለት የፈለገ ብቻ እንዳይመስልህ፣ ይሄ ፌርማታው ላይ ያልደረሰ ጅምር
ቢራ እራቱ ሊሆን ይችላል፡፡ ወዳጄ ፀጉራሙ በግ ነው አለ ሲባል የሚሞተው !

እናም እነዛ የርሃብ ዘመኖች አልፈው፣ ጭሱ የሚመዘዝ ሽፍንፍን ያላ ቋንጣ ፍርፍር ፊቴ
ሲቀርብ ሳልወድ ቀግድ አንገቴን ደፍቼ፣ አንዳንዴም እንባባዩ እየመጣ እግዚኣብሄርን እንዲህ
እለዋለሁ፤ እቤት ማጥገብ ስትችልበት” በቃ !! ምግብ ሲቀርብ ምንግዜም የምለው ይሄንን ነው::እንደውም ለእግዚአብሄር አይደለም ለራሴ ነው፣ ይሄ እግዚአብሄር ማጥገብ ሲችል የምለው:: ልቤ ታዲያ ያውቃል፣ “ቀላል ይችላል” ይለኛል ! ይሄንን የነፍስ ወግ ያዩት ሞልቃቆች ታዲያ፤ ጌታ ሆይ ይሄን ምግብ ባርከልን” የምል መስሏቸው፣ “አብረን እናምልክ” ይሉኛል፡፡

እግዚአብሄርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክ፣ መንፈስህን በደቆሰ የሕይወት ክንድ ስር እያለህ፣የእውነት መዳን፣ የእውነት ትንሳኤ፣ መኖሩን በመጀመሪያ እመን፡፡ በተመረጠ ቃል፣ የጣፈጠ
ዜማ መራር እውነትህን ለእግዚእብሄር አብረን እንንገረው! ብትለኝ እዛው የለመድክበት ነው
የምልህ : እዛው የለመድክበት !! ያውም ከተረት ጋር፡ “ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል::
👍20😢8
አንዳንዱ ሰው ዘመንን ተሻግሮ ታሪክን ተረማምዶ ከዓላማችሁ ሊያደናቅፋችሁ ፈታችሁ
ይጋረጣል፡፡ 'ቶሎ ተምሬ ይሄንን ህዝብ የምጫወትበት መቼ ነው” እያልኩ ሳስብ፧ የምበቀለው
እንዴት ነው?” እያልኩ ሳምሰለስል መመረቂያ ቀኔ ደረሰ፡፡ ያስተማሩን የተከበሩ ዶ/ሃ መምህራኖቻችን
መድረኩ ላይ በየመአረግ ልብሶቻቸው፡ ተቀምጠው፡፡ ወደ በኋላ ዶክተር የእኔ አምላክ ይነሱና፣
“ተመርቃችኋል ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ ይሄንን ሕዝብ ፍዳውን አብሉት” ማለታቸው አይቀርም
ባይሉም ለእኔ ትርጉሙ ያ ነው !! ይሄን ሁሉ ዓመት ስማር የህክምና ስነምግባር ከሕዝብ
ክፋት በልጦ ልቤን ሊያራራው አልቻለም፡፡

እኔ ግራ የገባኝ፣ ሕዝቡ ማነው?” የሚለው ጥያቁ ነው፡፡

ሕዝቡ የገፉቸው ብዙ አቲዬዎች አሉ፡፡ ገፊውን ከተገፊው ያልለየ በቀል ያን ያህል አያረካም፤
ሕዝቡ ማነው ? አንዳንዴ ደሃው ከፍ ሊል ሌላ ደሃ አየገፋ፥ የተገፋው ነፃ ሲወጣ የባሰ ገፊ
ሲሆን እያየ ሁሉንም በጅምላ ጠራርጌ አገር እንደሳር አዲስ ትውልድ ቢያቆጠቁጥባት ይሻላል
እላለሁ፡፡

የዚህ ህዝብ ዘርፌ የምትባል አመልካች ጣቱ፣ 'ቀለመወርቅ የሚባል አውራጣቱ ብቻ ጋንግሪን
እንደለከፈው እግር ተቆርጦ የሚጣል አይደለም፡፡ አገር በሙሉ፣ ሙሉ አካሉ ተበላሽቷል፣
በክፋት ደዌ ነፍርቋል፡፡

ምፅዓት እቃቃው ፈረሰ ዳቦው ተቆረሰ” ዓይነት የምድር እቃቃ ፍፃሜ አለመሆኑ የገባኝ
ያኒ ነው። የኖህ ውሀ፣ የሎጥ እሳት አንደምርቃት ቀኔ ይናፍቀኛል፡፡ በየሆቴሉ ሕዝቡ ሲበላ ሲጠጣ፣ ሆዱን የሞላበትን ሰሃን ጓዳ ውስጥ የምትፈትግ የእሱን ወጥ የምትቀቅል የራባት ወጥ ቤት ከኋላው በግፍ እንደምትገረድ እየታየኝ እበሳጫለሁ፡፡ እና ምን ይጠበስ ይልሀል” ሕዝቡ 'አንድ በአንድ ነበር ሜንጦ ላይ እያንጠለጠሉ መጥበስ እላለሁ እኔ፡፡

ሲፋቀር፣ ሲጋባና ሲወልድ ያበሳጨኛል፡፡ አንዱ ሞቶ ሌሎች ሊቀብሩ ሲሄዱ 'መሞት አልነበረበትም አይነት ጩኸታቸውና የአዞ እንባቸው ያስጠላኛል፡፡ ሰዎች ታምመው ደፋ ቀና ተብሎላቸው መሞታቸው ይቆጨኛል፡፡ የሎጥ እሳት…እሳት…እሳት.እሳት ! በየመንገዱ ይሄ ጨብራራ ፀጉራቸው በእሳት ተያይዞ ሲጮኹ ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ስሙ ራሱ ይማርከኛል፡፡ ይሄን በጅምላ ከፋትን
ባህሉ ያደረገ ክፉ ህዝብ በጅምላ ቡምምምምምምምም!! ጭጭ!!

ሽክ ብዬ የበቀል ደወል በሚደወልበት ቀን ወደ መመረቂያ አዳራሹ ገባሁ፡፡ ሁሉም ያየኛል
አውቃለሁ፡፡ ምክንያቱም ጎበዝ ነበርኩ፥ ጎበዝ ነኝ!! እዛጋ የተቀመጠው ዋንጫ የእኔ ነው፤
ይሄን ሕዝብ ኮሶ የማጠጣበት፡፡ ምድረ ኩታራ ሥራ ፈላጊ፣ “የክብር እና የሙያ ስም አሳዳጅ
ሁሉ ዕይናቸው እያየ የፈታቸው እንደምነግስ በመዐረግ ዛሬ እንደምቀባ ያውቃሉ፡፡ ለበቀል
እንደምቀባ አያውቁም፡፡ ዩኒቨርስቲ ሰይፏን ስላ ወደ ሕዝብ አንገት በመዓረግ ልታውዛገዝግ
ነው መጣሁልሽ አዲስ አበባ ሃሃሃሃሃ እያቃሰትሽ ከፊቴ ልትሰለፌ፣ ምጥ እያጣደፈሽ አድነኝ ልትይ፣ ደምሽ እየተንዠቀዠቀ አትርፈኝ ልትይ ሃሃሃሃ !!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አላችሁ! እልልልልልልልልል!
የበቀል ቀን እንዴት ፈጣን ነው፣ ይሄው ደረሰ !!

ተመልከቱ ከኋላ ወንበር ማን እንደተቀመጠ። ነጭ ፀጉር ጣል ጣል ያደረገባት፣ ያበሻ ቀሚስ
የለበሰች፣ ከዘመናት ጉስቁልናዋ አዲስ ልብስና ሹርባዋ ያልታደጋት ሚስኪን እናቴ አቲዬ እናቴ !! አቤት ሳያት ሰውነቴ እንዴት እልህ እንደሚሞላው ! አዳራሹ እንደዛሬ ሙሉ ሁኖ አያውቅም፤ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ታላላቅ ምሁራን የተገኙበት አራት አምስት ጊዜ ተገኝቼ አውቃለሁ ዛሬ ግን ሙሉ ነው አትዬ አለቻ።

የሕዝቡ ብዛት ግርግሩ ግራ እንዳጋባት ከዛፒ ጎን ተቀምጣለች፡ 'አልመጣም!' ብላ አስቸግራ ነበር ፈርታ። አቲዬኮ ይሄን ሁሉ ዘመን ሰው የዋለበት ውላ አታውቅም፡፡ እንግዳ እንኳ እነዛፒ ቤት ከመጣ ምግብ አቀራርባ ወደ ጓዳ ነው ሩጫዋ፡፡ ሰውን ፊት ለፊት ቀጥ ብላ አታይም፤ቀምተዋታል ሰብዓዊነቷን፡፡ ሰው ፊት እንዲህ አይቆምም እያሉ፣ እቃ እንዲህ አይያዝም እያሉ፡ ምን ትንከረፈፊያለሽ?” እያሉ፣ የእኔን እናት ካላሳነሱ ትልቅ መሆን የማይችሉ ይመስል ምድረ ገለባ አስኪበቃው እናቴ ላይ ተጨማልቋል።

ዛፒ እጇን አውለበለበችልኝ ! ደግሞ ፈገግታዋ፡፡ እንዴት ነው ደስ ያላት፡፡ ሳላስበው
አፍጥቼባቸው ነበር ለካ፡፡ አቲዬ በስስት እንደምታየኝ ከዚህ ርቀት አውቄያለሁ፡፡ የእርሷ መሲህ ጥቁር መጎናፀፊያ ለብሼ ሰላሳ
ስምንት አመት የተኛችበትን የድህነት አልጋ፣ የመገፋት
አልጋ የመከላፊትና የመናቅ አልጋ፣ “አንች ሴት ልጅሽ ደርሶልሻል ተሸከመሽ ሂጅ ልላት
ፊቷ ቆሜያለሁ፡፡ ሃሌሉያያያያያያያያ እኔ ዶክተር አሸብር ነኝ ! ዶክተር አሸብር በአምላክ !! የተገፋችው የተናቀችው የአፀደ ልጅ!!

እንኳን ደስ አላችሁ፣
እንኳን ደስ አላችሁ፤
እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

አንዳንዱ ሰው ዘመንን ተሻግሮ፣ ታሪክን ተረማምዶ ከዓላማችሁ ሊያደናቅፋችሁ ፊታችሁ
ይጋረጣል..ለምሳሌ ሂፖክራጥስ፡፡ ይሄ ሰው የዘርፌ የበኸር ልጅ እስኪመስለኝ፣ የቀለመወርቅ
የነፍስ ወዳጅ ነው ብዬ እስከጠረጥር ዛሬ ቅጥልልል ነው ያደረገኝ፡፡ በጓጓሁለት የምርቃት ቀኔ ፊቴ ተጋርጦ ማንም ሳያዘው ሽማግሌ ይሆናል ? (ወይስ የአዲስ አበባ ህዝብ ፈርቶ 'ከአሸብር ጋር አስታርቀኝ ብሎ ልኮት ነው?)

የሕክምና ዶክታር ሲመረቅ ቃለ መሀላ እንደሚፈፅም ባውቅም ረስቼው ነበር፡፡ በዚህች ቀን ግን
የሂፖከራጥስ መሃላ የሚባለውን አስመራቂው ዶክተር ቃል በቃል እያነበቡ ደግመን እንድንናገር
ሲያደርጉን፣ ሆን ተብሎ አሻጥር የተፈፀመብኝ እስኪመስለኝ ከፍቶኝ ነበር፡፡

እንዴት ነው፣ ሕዝብን ሙያዬን ተገን አድርጌ አልጎዳም ብዬ የምምለው ?

ለምንስ ሂሳብ ነው በጨዋነት የህመምተኛውን ክብርና ስብዕና በሚጎዳ መልኩ ምንም መጥፎ
ነገር ላላደርግ ብዩ የምምል የምገዝተው ? ይሄ ሕዝብ እናቴ ላይ በነፍሰ ስጋዋ ሲጫወትባት
ሂፖክራተስ ከነመሀላው የት ነበረ፡፡

አረ ቀልድ፡ ሕዝቡ ልጀ ኣይደለህም' ብሎ የወረወረኝ እኔ፣ ሕዝቡ ከአሜሪካ ላሙ እኩል
ሊያየኝ ያልፈለገ እኔ፣ “ሕዝቡን እንደ ቤተሰብ የሕዝቡን ልጅ እንደራሴ ልጅ ላይ” ብዬ እንድምል
ሂፖክራተስ ሽምግልና ፊቴ ቆመ፡፡ ይሄ “ዶክተር” ለመባል የቸኮለ ሁሉ የትባለውን በተመስጦ
ይደግማል፡፡

“በሕከምና ወቅት የምሰማውን የህመምተኛውን ሚስጥርም ሆነ የግል ጕዳይ በታማኝነት
ልጠብቅ" ወቸ ጉድ!

“ሕዝቤን ከልብ በመነጨ ፍቅር፣ ስብዓዊነት እና ሙያዊ ስነምግባር ላገለግል…” ካለፍኩበት
የትምህርት ውጣ ውረድ ይልቅ ይህን ታላቅ መሃላ ማለፍ ከባድ ነበረ፡፡ ያውም እኮ በእግዚአብሄር
ሰም፣ በእኔና በአቲዩ እግዚአብሄር ስም፡፡ ግን አንድ እውነት ልንገራችሁ መሃላው ልብን ያርዳል፡፡ ምንድን ነው የተማረን ሰው ፈሪ ማድረግ፣ ከውስጤ የፎከርኩበት በቀል ሲተን፣ እግዚአብሄር የበቀል በትሬን ከእጄ ላይ ፈልቅቆ ሲወስድ ይሰማኛል፡፡ ለምን እንባዬ በዐይኔ ሞልቶ ነበር፡፡

ግን ምን አደረገ የአዲስ አበባ ሕዝብ ?ሕይወት ሰለሜ ሰለሜ እያጫወተው ከከፉው ኋላ ክፉ
ተሰልፎ ማለቂያ በሌለው የከፋት ሰልፍ፣ አንድ አለንጋ ከኋላው እያራወጠው የሚኖር ሚስኪን
-ምን አደረገ ?? ልጆቻችን ተመረቁልን ብሎ አልጋው ላይ እያቃሰተ እየጠበቀን ይሆናል፡፡
ውጋቱን ችሎ፣ ቁርጠቱን ችሎ፧ ዘናጩ የአዲስ አበባ ሕዝብ ስንት ዓይነት ጉዳቱን በልብሱ
ሸፋፍኗታል ኤዲያ በቃ አፉ ብዬዋለሁ !
👍224
ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ራሴን ቀለለኝ፡፡ ስሜ ከመድረክ ሲጠራ አዳራሹ በጭብጨባ ሲናወጥ መድረክ
ላይ ቆሜ ተመለከትኩ፡፡ የማታጨበጭብ ብቸኛ ታዳሚ አቲዬ ነበረች፡፡ 'የሰው ዐይን ልጄን.." እያለች እኮ ነው መች አጣሁት፡፡ እናም አልኩ፣ እህቴ ዛፒ እወድሻለሁ" ሁሉም ወደሷ ዞሮ
አጨበጨበ፡፡ እንዴ፣ ዛፒ አለቀሰች !! አቲዬን አየኋት ዛሬ ድረስ ቪዲዮውን ሳየው አልቅስ
አልቅስ ይለኛል፡፡ አቲዬን ስሟን ብቻ እንደጠራሁ እንባዬ ተዘረገፈ በቃ!!

ሌሊቱን ሙሉ ምን ብዬ እንደማመሰግናት አጥንቼ ነበር እኮ !!

ሕይወት እንደ ሰዓት ናት።ፀ በሙላትና በጉድለት መሐል ይዛ የምትነጉድ፡፡ ሁልጊዜ ትቆጥራለች፡፡ ሩብ ጉዳይ፡ አስር ጕዳይ፣ አምስት ጉዳይ ትሞላለች ! ከአምስት፣ ከአስር፡ ከሩብ ትተርፋለች ! ውስጤ ፍፁም ሰላም ይሻል፡፡ ጥላቻና በቀል በመቀመር ያሳለፍኩትን መራር የወጣትነት ዘመኔን
ለማካካስ ስለ ሰላም ብቻ ማሰብ እሻለሁ፡፡ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ሰላም፡፡

እናም እንዲህ አሰብኩ፣ ድንገት የዘገየ የጸሎት ምላሽ ተልኮ ኒውክሌር ቦምብ እጄ ቢገባ ወስጄ
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት: “ያውላችሁ ለሰላማዊ ጉዳይ፣ ለኃይል ማመንጫ ምናምን
ማለት የለም! በሕግ አምላክ ውሰዱልኝ…፡ ይልቅ በጅምላ ሕዝብ የሚፈጁትን ወባና ኤችአይቪ እንዋጋቸው ዘንድ መከላከያውን በገፍ ላኩልንማ እላቸዋለሁ ! ፈገግታ ልቤ ውስጥ አለ፡፡ልቤ ፈገግታን እየተለማመደች ነው፡፡


አልቋል

በቅርብ በአዲስ ረጅም #ልብወለድ እመለሳለው።
👍2915👏13🥰2