አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
577 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ምንትዋብም በበኩሏ የሰዉን ደስታና ጭፈራ ስታይ እንዳው በከንቱ እንዳልጨፈሩ ገባት። ተስፋቸውን እሷ ላይ ጥለው፣ ሌሎች ያልሰጧቸውን ትሰጠናለች ብለው አምነው እንደሆነ ተረዳች። የኃላፊነት ስሜት ልቧ ውስጥ ዘልቆ ገባ፤ እንባ ተናነቃት። በባሏ ሞት ማግስት ጠዋት፣ ላይ ቆማ ለሕዝቡና ለሃገሯ የገባችውን ቃል አስታወሰች።

ልትክሳቸው፣ እንባቸውን ልታብስላቸው ፈለገች፤ ቆረጠች።

ቤተመንግሥት ስትመለስ ሕዝቡ አደናግር በር ድረስ በዘፈን፣
በጭፈራ፣ በዕልልታና በሆታ ሸኛት። እልፍኝ ገብታ በወርቅ የተለበጠ ወንበር ላይ ስትቀመጥ ጽራግ ማሰሬ ማሞ ዘውዷን ከራሷ ላይ አነሱላት።እንደየማዕረጉ የገባውም እንግዳ ግብር ተካፈለ።

ዐጅቦ የመጣውም ሕዝብ በተራ እየገባ ከታላቁ ግብር ተቋደሰ።
ምግብ፣ መጠጥ፣ አሞሌ ጨው፣ ልብስ፣ ጌጣ ጌጥ፣ ፈረስና በቅሎ
ታደለው። ጠጅ በጉሮሮው አንቆረቆረ። ለነገሥታቱ ያለውን ምስጋና መሬት እየሳመ አበረከተ። ረጅም ዕድሜም ተመኝቶላቸው እጅ እየነሳ ወደየቤቱ ተመለሰ።

ምንትዋብና ዳግማዊ ኢያሱ ራሳቸው ተደስተው ሁሉን አስደስተው፣ ምርቃታቸውን ደርበው ወደ ማረፊያ ቦታቸው አመሩ።

በንጉሠ ነገሥቱ ሕልፈት ምክንያት ጐንደር ሰማይ ላይ አረብቦ የነበረው የፍራቻ ግርዶሽም ከምንትዋብ ንግሥ በኋላ ተገለጠ። ጸሎትና ተማፅኖ
በምስጋና ተቀየሩ። ልባቸው ተሰቅሎ የነበሩት ጐንደሬዎች “እፎይ” አሉ። ጐንደርም ሃገርም ከረብሻ ዳኑ። ጐንደር እንደገና ፍርሐቷንና ጭንቀቷን ከጉያዋ ወሽቃ የዕለት ተዕለት ተግባሯን ለማከናወን ወጣ ገባ አለች። አጣሪዎች ገበያውን አደሩት። አረቄ ቤቱ ከጣሪያው ላይ ጭስ ታየ። ካህናት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በየደብሩ ሃሌ ሉያ
አሰሙ።

ምንትዋብም በነገሠች በወሩ ታላቅ በዓል ሆነና ብርሃን ሞገሳ
የሚል የንግሥና ስም ተሰጣት። እውነትም የግዛት ዘመኗ ላይ ብርሃን ፈነጠቀች።.....

ይቀጥላል
👍81😱1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...አስራ ስድስት ወራትን በክብረ መንግስት አሳልፋ ወዴ ዲላ የተመስሰችው ሔዋን ብዙ አካባቢያዊ ለውጥ ሊገጥማት እንደሚችል ገምታ ነበር፡፡ነገር ግን ከሽዋዬ ቤት በዘመናዊ የቤት እቃዎች መሞላትና ወንድ ወንድ ከመሽተት በቀር ሁሉም ነገር ያው ነው።በሸዋዬ ቤት የወንድ ኮትና ጃኬት ግድግዳ ላይ ተሰቅለው የወንድ ጫማ በአልጋ ሥር ተቀምጦና ትልቅ የወንድ ፎቶ ግራፍ ብፌ ላይ ስታይ ሸዋዬ ባል ያገባች መስሎ ተሰማት። በእርግጥም “ማንዴፍሮን ገና የገባች እለት ተዋወቀችው።
ማንደፍሮ መልኩ ጥቁር ፊቱ ጉሩድረድ ያለና አካሉ ግዙፍ
ከመሆኑ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጨብጣት የእጁ አከባበድ የሚያስፈራ ሆኖባት ቢሆንም እያደር ስትግባባው ግን ባህሪው ቀላል የሆነ ሰው ነው። ይስቃል
ይጫወታል። ቀልዶቹ ይጥማሉ፡፡ እየሰነበተች ስታየው እንዲያውም በእሱ መኖር ቤቱ ድምቅ ሲል መንፈሷም ዘና እያለ መጣ፡፡ «የኔ ፍልቅልቅ» በማለት እያጫወተም ይበልጥ ያፍለቀልቃት ጀመር።
ዲላ እንደገባች በአፍንጫዋ የገባው አየር በአስቻለው የሰቀቀን ትዝታ የተለወሰው ነበር፡፡ ሆዷን ባር ባር እያለው እንባዋም ያለ ገደብ ፈስሷል። ያም ሆኖም
በተለይ ታፈሡን፣ በልሁን መርዕድንና ትርፌን አግኝታቸው በጋራ አልቅሰውና አንብተው እፎይ ካሉ ወዲህ ከፊል የመንፈስ መረጋጋትም እያደረባት ሄደ። ሸዋዬም ለአባትና ለእናቷ የገባችውን ቃል ያከበረች መሰለች! ሔዋን በማንኛውም ሰዓት ወደ
ታፈሡ ቤት ሄዳ የቱንም ያህል ጊዜ ቆይታ ብትመለስ የት ነበርሽ ምን አስቆየሽ?” አትላትም፡፡ ለሔዋን ከምንም በላይ የተመቻት ይህ የሸዋዬ ቃል ማከበር ነው።

ለአንድ አስራ አምስት ቀናት ያህል በዚህ አይነት እንፃራዊ የመንፈስ
መራጋጋት ውስጥ የሰነበተችው ሔዋን ሦስተኛው ሳምንት ሲጀመር ግን ያ በሸዋዬ ቤት የመኖር ሥጋቷ የልቧን ግድግዳ ማንኳኳት ጀመረ፣ በድሉ አሸናፊ ማንደፍሮን እየተከተለ በዚያ ቤት ውስጥ ገባ ወጣ ማለት ጀመረ፡፡ ማንደፍሮ ስለ ሔዋን ብዙ ነገር ሲነገረው ከርሟል። ከአስቻለው ጋር የነበራት ግንኙነት፣ በድሉ ሔዋንን ለመቅረብ ያደረገዉ ጥረትና የሰጠችው ምላሽ፣ በአሁኑ ወቅት አስቻለው ስለሚገኝበት ሁኔታና ሌሎችም ሁኔታዎች በዝርዝር ተገልፀውለታል፡፡ ወደፈት
የበድሉንና የሔዋንን ጉዳይ እንዲጨርስም አደራ ተጥሎበታል፡፡
ምንም እንኳ በአስቻለውና በሔዋን መካከል የነበረው ግንኙነት በተዛባ ሁኔታ የተነገረው የተሳሳተ መንገድ እንዲከተል የተገፋፋ ቢሆንም ማንደፍሮ ግን
ሆዱን ፍርሃት ፍርሃት ይለው ነበር። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን አንድ ነገር ተገንዝቧል። ሔዋን የምታፈቅረው ሰው አላት። ያ ሰው ለጊዜው በአካባቢው ባይኖረም በተስፋ እየጠበቀችው እንደሆነ ልብ ብሏል። የተጣለበት አደራ ደግሞ ይህን ተስፋ በጥሶ ሌላ እንዲቀጥል ነው። እናም ለህሊናው እየከበደው ውስጥ ውስጡን ይጨነቃል።
በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩ የበድሉ ነው፣ የሥራ ዋስትናው። እንዲሁም የሸዋዬም ጭምር ነው፤ የአፍላ ፍቅረኛው፡፡ በዚህና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እየተገፋፋ የተጣለበትን አደራ መወጣት የሚያስችሉ መላዎችን ሲፈጥር ሰንብቷል።አንድ ቀን በተለመደው
ሁኔታ በድሉና ማንደፍሮ በሽዋዬ ቤት ጫት ለመቃም አቅደው ከሸዋዬ ጋር በተደረገ ምክክር ቤቱ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ሲደርሱ ማንደፍሮ ከቤቱ ወለል ላይ ቆሞ ለየት ያለ ሀሳብ አቀረበ
«ዛሬ ከምንም ነገር በፊት አንድን ነገር መፈፀም አለበት።» አለ በዚያ ሰዓት ጓዳ ውስጥ ለነበረችው ሔዋን በሚሰማ ሁኔታ ድምፁን ከፍ በማድረግ።
«ምን?» አለች ሽዋዩ እንደማታውቅ ሆና፡፡
«ሔዋን የለችም እንዴ?» ሲል ማንደፍሮ እንደገና ጠየቃት፡፡
«አለች። ጓዳ ውስጥ ናት፡፡»
«ኑ ሁላችንም ወደ እሷ እንሂድ፡፡» አለና ማንደፍሮ ቀድሞ ወደ ጓዳ
ተራመደ። በድሉና ሸዋዬም ተከተሉት::
«የኔ ፍልቅልቅ» ሲል ጠራት ማንደፍሮ ሔዋንን፡፡
«አቤት» አለች ሔዋን ድንግጥ እያለች፡፡ የዚያን ዕለት ደግሞ የልብ
ህመሟ ዘወር ብሎባት ፍራሽ ላይ ጋደም ብላለች፡፡
«አንድ ጊዜ ብድግ ብትይ!»
ሔዋን በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ እንዳለ ተነስታ በዚያው ፍራሻ ላይ
ቆመችና ከፊት ለፊቷ የተኮለኮሉትን ሁሉ ተራ በተራ ታያቸው ጀመር፡፡
«ዛሬ ዛሬ ሁሉም ነገር ገብቶኛል፡፡» አለ ማንደፍሮ ሳቅ ብሎ። “ይህ ሰውዬ!» ሲል ቀጠለ ወደ በድሉ እያመለከተ ወደዚህ ቤት በመጣ ቁጥር ስሜትሽ ለምን እንደሚቀያየር ተረድቻለሁ። ያለ ፍላጎትሽ እየጎነተለ ሲያስቀይምሽ እንደቆየ ገብቶኛል።አሁን አሁን ጥፋት መሆኑን አምኖ ተቀብሏል፡፡ ይቅርታም ሊጠይቅሽ ተዘጋጅቷል።ይቅርታውን ተቀብለሽ እንድትታረቁና ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ እየተያየን እንድንኖር ፈልጌለሁ።» አላት።
ሔዋን ያላሰበችውና ያልጠበቀችው አቀራረብ ነበር። ለጊዜው ግን ድንግጥ ተብላ ወደ መሬት ከማቀርቀር በቀር ያለችው ነገር አልነበረም። ማንደፍር ወደ በድሉ ዞር አለና ቆጣ ባለ አነጋገር «በል እግሯ ላይ ውደቅ!» ሲል አዘዘው፡፡ በድሉ ኮቱን ወደ ኋላ መለስ አድርጎ በሔዋን እግር ላይ ወደቀ፡፡
«እልልልል» አለች ሽዋዬ። ማንደፍሮም ብቻውን አጨበጨበ። ለሔዋን ግን ትልቅ የእረብሻና የግርግር ጩኸት ወስጥ የገባች መሰላት፡፡ በድሉ በእግሯ ላይ ወድቆ ለአፍታ ሲቆይ ለመግደርደር ያህል እንኳ በቃ ተነስ አላለችውም። ሲበቃው ራሱ ተነሳ::
«ቀጥል!» አለ ማንደፍሮ ነገሩን በማሟሟቅ ዓይነት ፈንደቅ እያለ፡፡
በድሉ ቀኝ እጁን በኮቱ ኪስ አስገብቶ አንዲት በብልጭልጭ ወረቀት የተጠቀለለች ነገር አወጣ፡፡ ወረቀቱን ቀዶ ጣለ፡፡ ከማይካ የተስራች ነጭ ሙዳይ
ብቅ አለች፡፡ እሷንም ከፈታት። በቅድሚያ ጥጥ መሳይ ነገር ታየ። ቀጠለና በግምት አሥራ አራት ግራም የሚሆን የክርስቶስ የስቅለት ተምሳሌት ማጫዎች
የተንጠለጠለበት የወርቅ ሀብል አወጣና በአንገት ውስጥ ለማስገባት የተዘጋጀ በሚመስል ሁኔታ ከያዘ በኋላ ፈገግ እያለ ማንደፍርን አየት አደረገው::
«ቀጥላ! ምን ታየኛለህ?» አለ ማንደፍሮ፡፡ በድሉ እነዚያን አራት ገጣጣ ጥርሶቹን ገልፈጥ አድርጎ ወደ ሔዋን ጠጋ ሲል ሔዋን ግን ድንገት ጮኸች::
«አልፈልግም!»
«ተይ እንጂ የኔ ፍልቅልቅ አለ ማንደፍሮ እሱም ደንግጥ አያለ፡፡
«እምቢ! አልፈልግም» ሔዋን አሁንም፡፡ ፊቷን ክስክስ አድርጋ በድሉን በጥላቻ ዓይን ታየው ጀመር።
«አይ እንግዲህ!" አለና ማንደፍሮ ሔዋንን ወደ ራሱ ጎተት አደረገና ሁለት እጆቿን ያዝ በማድረግ «አጥልቅላት » አለው በድሉን።
በድሉ የሔዋን እጆቿ እንደተያዙለት ሀብሉን በአንገቷ ላይ የመጣል ያህል አስገብቶ ወደ ኋላው ፈግፈግ አለ።ማንደፍሮና ሸዋዬ አጨበጨቡ፡፡ ማንደፍሮ በሔዋን አንገት ላይ ያረፊቱን ሀብል በእጁ ያዝ አድርጎ ወርቁንም ሔዋንንም
ተራ በተራ እየተመለከተ«አንቺን ለመሰለች ቆንጆ የሚገባ ልዩ ስጦታ!» አላት።
ሔዋን ግን ዓይኖቿ በእንባ ሞሉ፡፡ ግንባሯን በከንዷ ጋርዳ ወደ መሬት
በማቀርቀር ታለቅስ ጀመር።
«ሔዋን እንዳንቀያየም» አላት ማንደፍሮ። ሔዋን መልስ አልሰጠችውም፡፡አሁንም አጎንብሳ ታለቅስ ጀመር፡፡
👍8😱1
ጉዳያቸው እንዳልሞላ ፣ዓላማቸው እንዳልተሳካ በውል የተረዱትና ማንደፍሮ፡ በድሉና ሽዋዩ ወደ ሳሎን ተመልሰው ፍራሻቸው ላይ ተኮስኮሉ፡፡ ሸዋዬ ተናዳለች፡፡ በድሉ አኩርፏል። ማንደፍሮም ቅስሙ ተሰብሯል።
በዝምታ የተጀመረው ጫት በኩርፊያ ጥቂት ተቃመ፡፡ አልፎ አልፎ አንዱ ወሬ ቢጀምርም እንኳ የሌላውን የሞቀ ምላሽ ሲያጣ ቶሎ ይቆርጠዋል በየሆዳቸው ነገር ያስላስሳሉ፡፡ ሽዋዬ ንዴቷን እንዴት እንደምትወጣ በድሉ በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበትና ማንደፍሮ ደግሞ የተሰማውን ፀፀት እንዴት አድርጎ ከልቡ ሊያነፃ እንደሚችል ያስባሉ።
ሔዋንን ጓዳ ውስጥ ሆና በሌላ ሀሳብ ተውጣለች፡፡ ያን አንገቷ ላይ
የተጣለባትን ሀብል አውልቃ ፍራሹ ላይ አስቀምጣ በጥላቻ ዓይን ታየዋለች::ወርቅ መሆኑ ቀርቶ ተገድሎ የተጣለ አውሬ
ይመስላታል ( የኤርትራ የሄደ ይመለሳል ብለሽ...) በማለት
መንፈሷን ባቆሰለ ሰው የተገዛ ነውና እርም ሆኖባታል:: በዚያው ሰበብ አስቻለውን አስታወሰችው፡፡ ያኔ ለዝውውር ጥያቄ ወደ
አዲስ ኣበባ ሊሄድ ሲል …ምን ገዝቼልሽ ልምጣ?” ብሎ የጠየቃት ከእእምሮዋ ድቅን አለ፣ የሰጠችውም ምላሽ እንዲሁ፡፡ የመኪናው አደጋ ሰቀቀን ትዝ አላት፡፡ወደ ኤርትራ አካሄዱም በትዝታ መጣባት። 'አልሄድም' ብሎ የተከራከራትንም፣
ይሄድ ዘንድ ያባበለችበትንም ቃሎች አስታወሰቻቸው፡፡ ከአሁኑ የአስቻለው መቅረት አያገናዘበች በፀፀት እሳት ተቃጠለች፡፡ ተንገበገበች፡፡ አለቀሰችም። ሁሉም ነገር ተደማረና ለአንድ ርምጃ አነሳሳት፡፡ ድንገት ከፍራሿ ላይ ብድግ አለችና ያንን
የወርቅ ሀብል ይዛ ወደ ሳሎን ወጣች:: ሁለም ቀና ቀና ብለው ሲያዩዋት ሀብሉን ማንደፍሮ ጭኖች ላይ ውርውር አድርጋ ወደ ውጭ ገሰገሰች::
ሦስቱም በድንጋጤ ይተያዩ ጀመር፡፡ በየአፋቸው ውስጥ ያስገቡት ጫት እስከሚታይ ድረስ አፋቸው ተከፈተ፡፡ ዝም ዝም። ክው፣ ድርቅ በያሉበት፡፡
“ምን መሆኗ ነው?» አለ ማንደፍሮ ከአፍታ ቆይታ በኋላ፡፡
ማንዴ፡ ዝም ትላለህ?» አለችው ሽዋዬ፡፡ ማንደፍሮ ጥቂት አሰበና አንድ ነገር በአዕምሮ ብልጭ ሲልበት ብድግ ብሎ በፍጥነት እየተራመደ ከቤት ወጣ፡፡
ከግቢም ወጥቶ ግራና ቀኝ ሲመለከት ሔዋንን ከሩቅ አያትና «ሔዩ!» ሲል ጠራት።
እሷ ግን ዘወር አላለችም፣ ርምጃዋን ቀጠለች። ማንደፍሮ ሮጦ ደረሰባት፡፡

ከፊትለፊቷ በረከክ ብሎ ተቀምጦ ቀና ብሎ እየተመለከታት «የኔ ፍልቅልቅ በእናትሽ» አላት።
«ተወኝ ጋሽ ማንደፍሮ» አለች ሔዋን እያለቀሰች፡፡
«ለራሴ ነው የምለምንሽ የኔ ቆንጆ፤ አንዴ አዳምጭኝ!»
«ምን ላድርግልህ?»
«ለሰራሁት ጥፋት ይቅርታ አድርጊልኝ ሁለተኛ አልደግመውም፡፡»
«ይኸ ሰውዬ ዳግመኛ እዚህ ቤት እንዳይመጣ ታደርግልኛለህ?»
«ቢያንስ እኔን ተክትሎ እንዳይወጣ አደርጋለሁ፡፡ ስለ እንቺ ቢያወራል መልስ አልሰጠውም:: አንቺ የምታከብሪውን ሰው እኔም አከብራለሁ::
«እሺ ጋሽ ማንደፍሮ! አሁን ልቀቀኝና ልሂድ»
ማንደፍሮ ቀሪውን የይቅርታ ልመና ወደፊት እንደሚቀጥል ተስፋ በማድረግ ከተንበረከከበት ብድግ ብሎ ሔዋንን ግንባሯ ላይ ሳመሰ አድርጎ ለቀቃት እሷም ወደ ታፈሡ ቤት ገሰገሰች። እሱም ወደ፤ ጫቱ ተመለሰ።
«እምቢ አለችህ?» አስችው ሸዋዩ ዓይኗን ብልጥጥ አድርጋ እያየችው::
«ተዋት:: ትረጋጋ!» አለ ማንደፍሮ የልቡን አድርሷልና ለራሱ ተረጋግቶ ወደ ፍሬሹ አልፎ እየተቀመጠ።
«ምን ልሁን እያለች ነው?» አለ በድሉ ሽዎዬንም ማንደፍርንም አየት አየት እያረገ።
«ፈርታ ይመስለኛል?» አለች ሸዋዬ።
«ማንን?" ሲል ጠየቃት በድሉ፡፡
«ታስታውሰው የለም ያን በልሁ ተገኔ የሚባል ቀፈታም!» አለችና ያለ እሱ በዚች ልጅ ህይወት ላይ ችግር የፈጠረ የለም፡፡ እሱ እያለ ከየት አመጣሁት ብላ ይህን ሀብል አንገቷ ላይ ታውለው?» ብላ በቁጭት ዓይነት ራሷን ወዘዘች።
«በልሁ የሚባለው ምኗ ነው?» ሲል ጠየቀ ማንደፍሮ።
«የዚያ የአሥመራ ስውየዋ ጓደኛ ነኝ ባይ!» አለች ሽዋዬ አሁንም ውጭ ውጭ እያየች:: በድሉ አንገቱን ነቅነቅ ነቅነቅ አድርጎ «የዘነጋሁት ነገር ገና አሁን
ትዝ አለኝ፡፡» አለ በተለይ ሽዋዬን ትኩር ብሎ እየተመለክተ።
«እኔ ድሮም አውቀዋለሁ:: ለአንተ ግልፅ ባደርግልህ አጉል በእልህ
ተነሳስተህ አንድ ነገር ላድርግ ትላለህ ብዬ ፈርቼ ነው እንጂ!» አለችው፡፡በድሉ ድንገት ብድግ አለና ጫማውን አጠለቀ፡፡ አፉን ተጉመጥምጦ ኮቱንም ለበስ፡፡ የዕለቱ የጫት ቅሞሽ ከራማው ተገፏልና ማንደፍሮም ተከተለ
ሁለቱም ከቤት ሊወጡ ሲዘጋጁ «ወጣ አንልም የሸዋ!?» ሲል ማንደፍሮ ሸዋዩን ጠየቃት።
«አይ አይ! የዛሬው ይለፈኝ፤ እናንተ ሂዱ፡፡»
«ምነው? ደበረሽ?»
«ዛሬ ብርቱ ጉዳይ አለኝ፤ ከዚህ ቤት መውጣት አልፈልግም፡፡» አለችው።
ማንደፍሮ የሸዋዬ ስሜት ገብቶት በሔዋን ላይ አንድ ነገር ልትፈፅምባት ይሆናል በማለት ልቡ እየሰጋ በድሉን ተከትሎ ከቤት ወጥቶ ሄደ።
ጊዜው መሸ፡፡ ከአሥራ ሁለት ሰዓት አልፎ ዓይን መያዝ ጀመረ፡፡ ሔዋን ወትሮ እንደምታደርገው ሁሉ ከታፈሡ ቤት አመሻሽታ ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ከቤቷ ከች አለች፡፡ ሽዋዬ ግን ዓይኗን አፍጣ ጥርሷን አግጥ ጠበቀቻት፡፡
በዚያ ሰዓት የሸዋዬን ቤት ውስጥ መኖር ሔዋን ያልጠበቀችው ሁኔታ ነበር፡፡
«ስሚ አንቺ!” አለቻት ሽዋዬ ሔዋን ገና እግሯ ወደ ቤት ገባ እንዳለ፡፡
«አቤት!» አለች ሔዋን።
«እስቲ ቁጭ በይና እንነጋገር።» አለቻት በዓይኗ ከፊት ለፊቷ ያለችውን ዱካ እያሳየቻት።
ሔዋን ቁጭ ስትል ሸዋዬ ራሷ
«የት ነበር የሄድሽው?» አለቻት።
«እታፈሡ ጋ»
«ዳግም ወደዚያ ቤት እንደማትሄጂ ታውቂያለሽ!? »
«ለምን እት-አበባ? ለእማዬ የገባሽውን ቃል እረሳሺው?»
«አንቺ በሰው ሞራል ላይ ምን እየሰራሽ እንደሆነ እያየሁ እኔ ያረጀ ያፈጀ አደራ ላከብርልሽ ትፈልጊያለሽ?» አለቻት።
«የእናት አደራ አያረጅም፡፡»
«ለመሆኑ ቅድም ሰርተሽ የሄድሽው ነገር ትዝ ይልሻል?»
«የሰው ንብረት መለስኩ እንጂ ሌላ ምን አደረኩ?»
«የሰው ንብረት?» ስትል ሽዋዬ ቃሉን ደገመች።
«የኔ ያልሆነ ነገር ሁሉ የሰው ነው::
«ትንሽ አታፍሪም?።»
«ምንም እት አበባ!»
«ገልቱ የሰው ገልቱ!!»
«ሔዋን ወደ መሬት አቀረቀረች። እጆቿን በጡቶቿ ሥር አቆላልፋ መሬት መሬት ታይ ጀመር።
«ከወርቅ የበለጠ ምን እንዲሰጥሽ ትፈልጊያሰች?» አለቻት ሽዋዬ አሁንሃም በቁጣና በረቀቀ አነጋገር።
«ላጌጥበት ወይስ ልሸከመው?»
«ጤነኛ ነሽ ግን?»
«ሕመሜንማ ታውቂው የለ እት አበባ!! »
«ይዞሽ ይሂድ!»
ሔዋን እንባዋ በዓይኗ ሙሉ ግጥም አለ፡፡ ብድግ ብላ ወደ ጓዳ ገባችና ፍራሿ ላይ ድፍት አለች፡፡ ሸዋዬ ተፈናጥራ ተከተለቻትና ከፊቷ በመቶም ትሰሚያለሽ? ለአንቺ ይብላኝልሽ እንጂ በድሉ እሽናፊ እንደሆነ ስንቶች ስንት ነገር
እናድርግልህ የሚሉት የተከበረ ልጅ ነው።» አለቻት።
«ታዲያ የሚሰጡት ካሉ መስጠት ለምን አስፈሰገው? አለቻት ሔዋን ፍራሿ ላይ ድፍት እንዳለች::
«የኛ ፈላስፋ!»
«እት አበባ! በእናታችን ጡት ይዝሻለሁ፣ እያመመኝ ነው ተይኝ::»
«ለምን አያምሽ አንቺ እንደሆንሽ ዲላ እየኖርሽ ሀሳብሽ ያለው ኤርትራ!» አለችና «አሁን ያን ሀብል ትወስጃለሽ ወይስ አትወስጂም?» ስትል ጠየቀቻት።
👍8
«እኔ የሰው ገንዘብ አልፈልግም::»
«ኧረ ወዲያ! ለካ አትፈልጊም?» በማለት ሽዋዬ ሔዋንን ካላገጠችባት በኋላ ወዲያው ደግሞ «ለመሆኑ የለበስሽውን ቀሚስና ያስርሽውን ሰዓት የገዛችው ሽዋዬ መሰለችሽ በድሉ እኮ ነው ሰው መስለሽው ሰው ሊያረግሽ አስቦ ያሽሞነሞነሽ ካለቻት በኋላ «ደንቆሮ»ብላት እየተፈናጠረች ወደ ሳሎን ሄዳ ፍራሿ ላይ ቁጭ አለች በእርግጥም ሔዋን በእለቱ የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ባለፈው ጊዜ ክብረ መንግስት ሳለች በሸዋዬ የቀረበላት ስጦታ ነው።
እንደገና አየት አደረገችው ወዲያው ሁለመናዋን ቀነቀናት። ቶሎ አወለቀችና በሌላ ቀየረችው። ሰአቱንም ከእጇ ላይ ፈታች በትንሽ ፌስታል ውስጥ ሁሉንም አስገባችና ወደ ሳሎን በመሄድ «እንቺ እታ አበባ ለባለቤቱ መልሽለት» ብላ ከሸዋዬ ጎን አስቀምጣ ወደ ጓደዋ ተመለሰች።
«አንቺ» አለች ሸዋዬ አሁንም በቁጣ፡፡ «ምን እያረግሽ ነው?»
«ተይኝ እት አበባ አሞኛል።»
«ሐኪምሽ ያለው እኮ ኤርትራ ነው ለምን ተጠቅልለሽ ሄደሽ አታርፊም
ኪ ኪ ኪ ኪ ኪ...የንዴት ሳቅ የብሽሽቀት ኳኳታ።
ሔዋን ግን ዝም ብላ ጥቅልል ብላ ተኛች። የልብ ህመሟም ይጫጫናት ጀመር። እየጨነቃት ሄደ።
«መልስ የለሽም?» አለች ሸዋዬ አሁንም ጮክ ባለ ድምጽ።
«የሚሰማ ጆሮ የለማ!».....

💫ይቀጥላል💫
👍61🔥1
₀₀₀₀₀₀₀₀₀ አታውቂም! ₀₀₀₀₀₀₀₀₀₀
ከጠረንሽ ጋራ ፣ ሱባኤ እንደገባሁ፤
አታውቂም!
"ወንድ አይደለህም እንዴ"
እስከሚሉኝ ድረስ ፣ ቁጭ ብዬ እንዳነባሁ፡፡
አታውቂም!
ባገኘሁት ዘፈን ፣ ሆድ እንደሚብሰኝ፤
አታውቂም!
ስላንቺ ለማሰብ ፣ ዘመን እንደማያንሰኝ፡፡
አታውቂም!
ከለበስሽው ጋራ ፣ መቀመጥ ማሞሸቴን፤
አታውቂም!
እኩያ እስከማጣ ፣ ብቻዬን መቅረቴን፡፡
አታውቂም!

አታውቂም!

ብታውቂም አትመጪም፤
አትመጪሞ ፤ አታውቂም፤
ሞን ብዬ ልጸልይ ፣ ከሕይወት ይዤ ቂም።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
14👍6
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

"በእግዝሃር ፍጥረት ሴት ልሁን እንጂ ምን ይጎለኛል?”

ምንትዋብ ለራሷ፣ ለሃገሯና ለጐንደር በገባችው ቃል መሠረት
በቅድሚያ ሰላም ማስፈንንና ሃገር ማረጋጋትን መረጠች። ለዚህም
እንዲበጅና የልጇን መንግሥት ለማደላደልና ለማጠናከር ንጉሥ
ሲነግሥ እንደሚደረገው ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር ሆና መኳንንቱን
አሸዋ ግንብ ሰብስባ ሹመት ሰጠች። ሕዝቡ የወደደውን ሹመቱ እንዲጸና አደረገች፤ የሚሻረውን ሻረች።

የልጇን መንግሥት ይበልጥ ለማጠናከር ግራዝማች ኒቆላዎስን፣ አዛዥ አርከሌድስንና ወልደልዑልን ደጃዝማች ብላ ሾመቻቸው።

በደንቡ መሠረት ግብር አገባች፣ ብላም ከመኳንንቱ ጋር ምክክር
አደረገች።በምክክሩ መሠረት ደጃዝማች ኮንቤን የጃዊና የዳሞት ገዢ ኣድርጋ በመሾሟ ቀድሞውንም አፄ በካፋ ላይ ሲያምጹ የነበሩት ጃዊዎች
ኮንቤን አንፈልግም ሲሉ እሷም ላይ አመጹባት። ለምን ሹመቱን
እንደተቃወሙ ስትጠይቅ፣ “ኸራሳችን የወጣ፣ ወግ ልማዳችንን ሚያቅ ኸራሳችን የተወለደ ይሾምልን” አሏት።

መኳንንቱን እንደገና ወርቅ ሰቀላ ውስጥ ሰብስባ መከረች።
መጽሐፉም ወኩሎ በዘትገብር ተማከር ምስለ ሰብእ፡ እስመ ዘእንበለ ምክርሰ ገቢር ዕበድ ውእቱ ማንኛውንም ስራ ስትሠራ ከሰዎች ጋር ተማከር፤ አለበለዚያ የሰነፍ ሥራ ይሆንብሀል ነው የሚለው።
መኳንንቱም፣ “እንደ ልማዳቸው እናርግላቸው” አሉ። ምንትዋብ
ተቀበለች። ሻለቃ ወረኛን ብትልክላቸው ጃዊዎች ፈነጠዙ፤ ተረጋጉ።እሷም የመጀመሪያውን የአስተዳደር ትምህርት ገበየች። እንደገናም ከኢያሱ ጋር ሆና ሃገር ላረጋጉት ሹመት ሰጠች።

ሕዝቡን አስደስታ፣ እሷም ተደሰተች፣ ሃገርም ተረጋጋች:

ደስታውና መረጋጋቱ ግን በአስተዳደር በኩል ሊገጥማት ከሚችለው ችግር ለረጅም ጊዜ ሊያድናት አለመቻሉን በመገንዘብ፣ ከመኳንንቱ ጋር ከምታደርገው ምክክር ውጭ ብዙውን ጊዜዋን ከኒቆላዎስ፣ከወልደልዑል፣ ከአርከሌድስ፣ ከአያቷ፣ ከእናቷ፣ ከአጎቷና ከአጎቷ ልጆች
ጋር እየተሰበሰበች ስለአስተዳደር መወያየትን ልማድ አደረገች።

እንደሁልጊዜያቸው አንድ ቀን እልፍኝ ውስጥ ተሰብስበው ሳለ፣
“እኔ ስንኳ” አለቻቸው። “እኔ ስንኳ ሌት ተቀን ማስበው እንዴት
ላስተዳድር እያልሁ ነው። የነገሥሁ ዕለት ድኻው ምንኛ ተስፋ
እንደጣለብኝ አይቻለሁ። ኸነሱ ተስፋ አንሼ ልገኝ አልሻም። ምኞቴ
ሁሉ ላገሬ መልካም ማረግ ነው። ሌላው ደሞ ኸመኳንንቱ መኻልም
ቋረኛ ሊገዛን?'፣ ብሎ ብሎ ቋረኛ ይንገሥ?” ሚሉ እንዳሉ አውቃለሁ።ቋረኛ ብሆን ኸነሱ እንደማላንስ ማሳየት ፈልጋለሁ። በናንተ ድጋፍ መዠመሪያ መጠናከር አለብኝ። እኔ ዋናው አገር እንዲረጋጋና የኢያሱ
አልጋ እንዲደላደል ነው ምፈልግ። የኢያሱ አልጋ እንዲደላደል ደሞ
አገር መረጋጋት አለበት።”

እንደ ባሏ የግዛት ዘመኗን አመጽ እያበረዱ ማሳለፍ አልፈቀደችም።
ይህን ስታሰላስል ወልደልዑል ሲናገር፣ ከእንቅልፏ እንደባነነች ሁሉ ራሷን ነቅነቅ ዐይኗን እርግብግብ እያደረገች አየችው።

ስሜቷን ተረድቶ ሐሳቧንም እንደሚጋራ ሊያሳያት፣ “ምታስቢው ሁሉ ይገባኛል” አላት። “ልክ ነው። ድኻው ተስፋውን ኻንቺ አኑሯልና
ቢከብድሽ አያስገርምም። ሁሉን እንደምትወጪ ግን እንተማመንብሻለን።
እንዳልሽውም ደሞ ኸቋራ ስለመጣሽ ንቀትና ጥርጣሬ አላቸው። ቋረኛ የፍየልም እረኛ ማዶል ሚሉን? ቋራን እንደዝኸ ንቀው እኼው አንቺን አፈራ። አንቺም ደሞ ማን እንደ ሆንሽ ማሳየት አለብሽ። እንዳው ነው እንጂ ኸየትም ነይ ኸየትም ሥራሽ ነው ሚያስመሰግንሽ። አሁንም
ጠንክረሽ ማስተዳደር ነው ያለብሽ። እንዳልሽው የአጤ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ አልጋ እንዲደላደል አገር መረጋጋት አለበት። አገር እንዲረጋጋ
ደሞ አንዱ ኸመኳንንቱ ጋር ስምም መሆን ነው። እነሱ ማዶሉ ለሰዉ ሚቀርቡ? ኻለነሱ የት ይሆናል ። ባለፈው የዳሞት ገዢ የነበረው ተንሴ ማሞ ብዙ ግዝየ፣ “እኒህ ቋረኞች” ሲል ተሰምቷል ። ግዝየውን ጠብቆ ማመጡ አይቀርም። ወህኒ አምባን ደሞ በሚገባ ማስጠበቅ አለብን።
እኔም ሁሉን ባይነቁራኛ እመለከታለሁ” አለና እነአርከሌድስን መልከት
አድርጎ፣ “እኛ እስታለን ድረስ ጥቃት አይደርስብሽም። አንቺም
በተፈጥሮሽ ጠንካራና አስተዋይ ነሽ” አላት።

“ላለፉት ሰባት ዓመታት ስለቤተመንግሥት ብዙ ነገር ተምሬያለሁ”አለቻቸው፣ እጆቿን ደረቷ ላይ አስቀምጣ። “እኼ ይመጣል ብየም ባይሆን ማን ምን እንደ ሆነ ሳጠና ነው የቆየሁ። ቋራ ሳለሁ እንዳው ንጉሥ አዛዥ ናዛዥ ይመስለኝ ነበር...”

ኒቆላዎስ ጣልቃ ገባ፣ “ንጉሥ በርግጥም አዛዥ ናዛዥ ነው። መኳንንቱ ብዙውን ግዝየ ኸንጉሡ በዝምድናም ይሁን በጋብቻ የተሳሰሩ ቢሆኑም ንጉሡ የፈለጉትን መኰንን በፈለጉ ግዘየ ያለ ማስጠንቀቂያ ኸማረጉ
ሊያነሱት፣ ይዞታውን ሁሉ ሊነጥቁት ይችላሉ። አይተሽ የለ እንዴ አንድ መኰንን ያለ ንጉሡ ፈቃድ መዘዋወር ስንኳ እንደማይችል? ግና ያለ መኳንንቱ መንግሥት አይጠናም። አማካሮቹ፣ የቤተመንግሥት
ምሰሶዎቹ እነሱኮ ናቸው። እነሱን በጅ ማረግና ኸነሱ መምከር ግዴታ ነው። ፍታ ነገሥቱም ያዛል። ፈላስፋውም ቢሆን 'በገዛ ራሱ ምክር ብቻ ሚኸድ ሰው ይደክመዋል፣ ኻልሆነም ነገር ወድቆ ይቀራል ይል የለ?
ደሞስ ግብር ሰብሳቢዎቹ፣ ጦርነት ሲኖር ተዋጊዎቹና አዋጊዎቹ እነሱ
ማዶሉ? ፍርድ ሸንጎ ሚቀመጡ፣ ዳኛ ሚሆኑም እነሱ ናቸው። ንጉሡ ነው ሚፈርዱ። የግዛቶቹ ሁሉ አስተዳዳሪዎችም እነሱው ናቸው። አንድ ሲፈልጉ የራሳቸውን ፍርድ ቢሰጡም፣ የነሱን ሰምተውና አመዛዝነው
መኰንን አመጸብሽ ማለት አንድ ግዛት ይዞብሽ ኸደ ማለት ነው።
ያኔ ለማስገበር ጦርነት ትገጥሚያለሽ። በመጨረሻም ኸወህኒ አንዱን አምጥተው ያነግሡብሻል።ኻንች ከሆኑ አመጥ ቢነሳ ስንኳ ሚያዳፍኑልሽ
እነሱም ናቸው። ሚያቀጣጥሉብሽም እነሱ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዝኸ አብረሽ እየመከርሽ፣ እየሾምሽና እየሸለምሽ ይዞታቸውን እየጠበቅሽና እየጨመርሽ ነው መያዝ ያለብሽ። እንካ በእንካ ነው ነገሩ። ስትሾሚ ደሞ ባለፈው እንዳረግሽው ጥሩ ሚያስተዳድረውን ትሾሚያለሽ፤
ማይጠቅመውን ታማኝ ቢሆንም ስንኳ ትሽሪያለሽ።”

“እኔ አሳቤ ያው ጃንሆይ እንደሚያረጉት ኸጥንትም ቢሆን ያለ ማዶል? የመኻሉን ጠበቅ አርጌ ይዤ የሩቁን ግዛታቸውን እንደ ልማዳቸው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ነው.. ያው አሁን ለጃዊዎች እንዳረግነው። ዋናው ዓላማየ አገር ማረጋጋትና መንግሥት ማደላደልነው።”

“አንገብርም ብለው ኻላመጡና ድኻውን ኻልበደሉ በቀር ጣልቃ
ሳትገቢ” አላት፣ ኒቆላዎስ።

“አዎ ጣልቃ ሳልገባባቸው። መኳንንቱ ብዙ ግዝየ ኸዝኸ ይመጡ የለ? ቤታቸው ራሱ እዝሁ ቤተመንግሥት አጠገብ ነው። ምማከረውም ኸነሱ ነው። ማነንም ጦር እያነሱ ማስገበር አልፈልግም። በሰላም አንድ
ሁነን እነሱም ግብር እያገቡ፣ ድኻውን በደንቡ እያስተዳደሩ መኖርን ነው ምመርጥ። እነሱም ሆኑ ድኻው እኔ ላይ እምነት እንዲጥሉ ፈቃዴ ነው። እምነት ኻልጣሉብኝ እንዴት ማስተዳደር እችላለሁ? ጥሩ ታስተዳደርሁ ደሞ እምነት እንደሚጥሉብኝ አውቃለሁ።”

“ትክክል” አሉ፣ ዮልያና።
👍5
“ደሞም አቡኑን፣ ዐቃቤ ሰዐቱን፣ ጸሐፊ ትዛዙን፣ አፈ ንጉሡን፣
ሊጋባውንና አዛዦቹን በደንቡ መሠረት መያዝ አለብሽ” አላት
ወልደልዑል። “ዋናዎቹ ደሞ እነሱ ጭምር ማዶሉ? ወታደሮችሽንም
በጥንቃቄ መያዝና ያንቺ ዘበኞች እንዲሆኑ ማረግ ነው። ቅባት ስለሆንሽ ደሞ ጠንቀቅ ማለት አለብሽ። ተዋሕዶዎቹ ዝም ብለው ሚያዩሽ እንዳይመስልሽ። እነሱ ኻመጡብሽ ደሞ ድኻውን ሆነ መኳንንቱን እንደሚያሳምጹብሽ ማወቅ አለብሽ። ሙያሽን በልብ ይዘሽ ማስተዳደር ነው። ለምሳሌ እኝህ አለቃ ማነው ሚሏቸው፣ ቅባት ናት፣ ሃይማኖት ልታጠፋ፣ ጃንሆይንም ተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን አግባብታ አስቀይራ ቅባት ልታደርጋቸው የነበረው እሷ ናት ሲሉ ተሰምተዋል። በቅርቡ
ለተፈጠረው የሃይማኖት ውዝግብ የሷም እጅ አለበት ብለዋል። እኼንን ሁሉ ኸግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።”

“ኸተዋሕዶም ቢሆን ስንት መልካም ሰው አለ?” አለችው፣ ፊቷን ወደ እሱ መልሳ። “ስንትስ ወዳጅ አለኝ? ኸቅባትስ ቢሆን ስንት ሤራ ጠንሳሽ አለ? ቅባቶቹስ ቢሆኑ ሊያሳምጹብህ ኸፈለጉ ባይብሱ አያንሱም። ምናቀው ማዶል? እኔኮ ቢሆንልኝ ሁለቱን ማስታረቅ ነው ምኞቴ። አጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ የቤተመንግሥት ዋና ዋና
ቦታውን ለመኳንንት ሰጥተው የካህናቱን ቁጥር ኸቤተመንግሥት እንዲቀነስ አርገዋል። እኔም ያንኑ ነው ማረግ ማስበው። በሳቸው ግዝየ
የሥራ ተዋረድ ስንኳ ደንብ ነበረው። ትዛዝ ኻንድ ሹም ወደሚቀጥለው እያለ ነበር ሚፈጸም። ምክር ቤት ለማቋቋምም ጥረዋል። ያስቸገረውን ሲችሉ እየተደራደሩ እምቢየው ያለውን እያስገበሩ፣ ለድኻው ሰላም ሰጡ። ኻልባሰባቸው በቀር ሁሉን በሰላም ነበር ሚፈቱ። ርኅሩሕና
መሐሪ ነበሯ!”

ወልደልዑል ተደነቀ። ያቺ ትንሿ ወለቴ፣ ያቺ የሚሳሳላት ትንሿ
እህቱ ዛሬ እንዲህ ታሪክ ማወቋና ሃገር ለመምራት ታጥቃ መነሳቷ
አስገረመው።

“አሁን ከሁሉ ሚያሰጋሽ ራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ነው” አላት።

ከንፈሯን በጥርሷ ነከሰችና በግራ ሌባ ጣትዋ መታ መታ አደረገችው
ሐሳብ ሲገባት ወይ በስጨት ስትል እንደምታደርገው።

“አዎ... ጃንሆይ “ኸጐንደር ውጣልኝ ብለው ግዞት የላኩት ወደው መሰለሽ?” ሲል ቀጠለ፤ የእህቱን ስሜት ተረድቶ። ነገሩ ሊያሳስባት እንደሚገባ አምኗል። “እሳቸው አይነግሡም፣ ወንድማቸው ኣቤቶ ወልደ ጊዮርጊስ ነው መንገሥ ያለበት ብሎ ስለአመጸ ማዶል እንዴ
ኸጐንደር ውጣልኝ ያሉት? አሁንም እሳቸው ሞቱ ብሎ አዘናግቶም
ቢሆን ማመጹ ማይቀር ነው። ሥልጣን ይፈልጋላ! ኸጐንደርም የሱ አባሪ አይጠፋም። የሳቸውን መንግሥት ያዳከሙ እንዲህ ያሉ አመጸች ናቸው። ሲሾሙና ሲሸለሙ፣ ጉልት ሲጎለቱ፣ ርስት ሲተከሉ፣ ባረቄና በጠጅ ጉሮሯቸውን ሲያጥቡ የከረሙ ሁሉ ግዝየ አይተው መክዳታቸው
አይቀሬ ነው። ሁሉን ባይነቁራኛ መጠባበቅ ያስፈልጋል። ሰዉም
ቢሆን ጦር ሲያነሱበት ኃይለኛው ጋር ነው ሚወግን። ስለሚፈራ
ለሱ ይነጠፋል። ሲወድም ሲጠላም የዛን ያህል ነው። እኼን ኸውስጥ ሚዶልተውንና ሤራ ሚጠነስሰውን በዝኽ ነው ምትቋቋሚው። እኛም
መሰናክል እንዳይገጥምሽ ጆሯችንን አንቅተን ዐይናችንን ከፍተን እንጠብቃለን፤ ኸጎንሽ ነነ።”

“ጌታዬ ላገሬ ያሰብሁትን ሁሉ እንዲያሳካልኝ ምኞቴ ነው።
የጃንሆይም ዐደራ አለብኝ። ወልድየ ዛሬ ነገ ሳትል ወህኒ ዝለቃ።”
ነገ ማልጄ እነሳለሁ” አለ፣ ደጃዝማች ወልደልዑል።ሁሉም ምሳ ለመብላት ወደ እልፍኝ አደራሽ ሄደው ከምሳ በኋላ
እሷም፣ እልፍኟ ገባች። ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ከራሷ ጋር መነጋገር
ፈለገች። የቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ጉዳይ ግን ትንሽ አሳሰባት። ኸቁስቋም ጋር ተዘጋጅቸ ጠብቀዋለሁ፤ አልረታለትም አለች።

ወልደልዑል፣ “ከሁሉ ሚያሰጋሽ ራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ነው”
እንዳላት ሁሉ፣ ራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ የአፄ በካፋን ወንድም አቤቶ ወልደጊዮርጊስን “ነግሧል” ብሎ አሳወጀ። ጦር ይዞ ተነሳ። ከወልደልዑል ጋር ወህኒ አምባ ተገጣጠሙ።

ወልደልዑል ከተራራው ግርጌ ዘጊዮርጊስ ከላይ ሆነው ባደረጉት
ውጊያ ወልደልዑል ሲሸነፍ ምንትዋብ ኒቆላዎስን ከተጨማሪ ኃይል ጋር ስትልክለት ተጠናክሮ በመዋጋቱ ከሁለት ቀን ውጊያ በኋላ፣ዘጊዮርጊስ ተሸነፈ። አቤቶ ወልደጊዮርጊስ ለፍርድ ቀርቦ ፈራጆች ሞት ቢፈርዱበት፣ ምንትዋብ የንጉሥ ዘር በሞት አይቀጣም የሚለውን ሕግ በማክበር እዛው ወህኒ አምባው እንዲጋዝ አደረገች። ቢትወደድ
ዘጊዮርጊስ እንደገና ግዞት ተላከ።.

ይቀጥላል
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ጥቂት ቀናት አለፉ። አንድ ቀን ምሽት ላይ በልሁና መርዕድ በምህጻረ ቃል አምሆ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ ከውጭ ወደ ቡና ቤቱ ሲገቡ በስተቀኝ በኩል በምትገኝ ብቸኛ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብለው ከአንዲት የቡና ቤቱ እስተናጋጅ
ጋር እየተቃለዱ ይጠጣሉ። ከጠረጴዛው ፊትለፊት ያለው ባንኮኒና የቡና ማሽን ብቻ
ስለሆነ ቦታው እንደ ልብ ለመጫወት አመቺ ነው። የቀልዳቸውና የጭውውታቸው
ማዕከልም የመርዕድ ዓይን አፋርነት ነው:: አስተናጋጇ ባህሪውን ቀደም ብላ ስለምታውቅ በነገር እየነካካች ታሳፍረው ይዛለች፡፡መቼም የአንተን ድንግል የምወስደው እኔ ነኝ፡፡» ትለዋለች ጉልበቱንና ጭኖቹን እያሻሸች።
«እስቲ እንደ ምንም ብለሽ ገላግይው::» በልሁ እየሳቀ፡፡
«አቦ ተይኝና ሌላ ወሬ አምጪ!» ይላል መርዕድ የአስተናጋጇን እጅ ከላዩ ላይ ለማንሳት እየሞከረ።
አይዞህ! ቦታውን እንደሆነ እኔው ራሴ አሳይሃለሁ፡፡» አስተናጋጇ አሁንም።
«እንዲህ ከመባል ሞት ይሻላል መርዕድ!» እያለ በልሁ ይስቃል::
እንዲህና እንዲያ እያሉ በመጫወት ላይ ሳሉ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ሁለት ሰዎች ተከታትለው ወደ ቡና ቤቱ ገቡና ግራ ቀኝ ተመለከቱ፡፡ ከበሩ
በስተግራ በኩል ያለው ዋናው ሳሎን በሰው ተሞልቷል። በቀኝ በኩል ያለችው ጠረጴዛ ደግሞ በእነበልሁ ተይዛለች። በቀጥታ ወደ ባንኮኒው በመጠጋት ጀርባቸውን ለእነበልሁ ሰጥተው ቆሙ:: ወዲያው ደግሞ በድሉ አሸናፊ ከውጭ መጥቶ
ተቀላቀላቸው:: እሱ ከመሀል ሌሎቹ ግራና ቀኝ በመሆን ፈንጠር ፈጠር ብለው ተደረደሩና የሚጠጡትን አዘዙ፡፡ ለሁሉም አረቄ ቀረበላቸው ::
በልሁ ግን ቅፍፍ ይለው ጀመር፡፡ እሱና በድሉ ቀድሞም ተዳፍጠው ነበር የኖሩት. ዜሬ ደግሞ ገና ሲገባ ገልመጥ አድርጎት ነበርና
እንዲሁም ከተማ ውስጥ አይቷቸው ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ገጥሟልና ጥርጣሬ ገባው መጠጥ አወሳሰዳቸውም አላምር አለው ግልብጥ ግልብጥ ያደርጉታል። በሹክሹክታም ሲወያዩ ያያቸዋል። ወደ ኋላቸው ዞር እያሉ ሲገላምጡት ያይ ጀመር
መርዕድና አስተናጋጇ የሚያወሩትን ትቶ እነ በድለን መከታተል ቀጠለ፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አለፈ። የመደመጥ እድሉን እዚያው የተፈጠረበት አገር ረስቶ የመጣው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቡና ቤቱ ውስጥ ተከፍቶ ያለ ምንም አድማጭ ለራሱ ይጮሀል። ዜና እወጃውን ጨርሶ የግብርና ፕሮግራም ማስተላለፍ ጀምሯል።የመስኖ ስራ እንቅስቃሴ እያሳየ ገበሬዎች ያገኙትን ጠቀሜታ ይዘረዝራል።
በድለና ጓደኞቹ ከቴሌቪዥኑ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ወሬ ማውራት ጀመሩ። ያም ቢሆን ከበልሁ ጀሮ ደረሰና እሱም በጥንቃቄ ያዳምጥ ጀመር፡፡ከበድሉ በስተቀኝ በኩል ከቡና ማሽኑ አጠገብ ቆሞ የሚጠጣው የበድሎ ጓደኛ "ስሚ አንቺ"
ሲል ጨራት ከባንኮኒ ውስጥ ቆማ የነበረችውን አስተናጋጅ።
«አቤት» አለችው።
የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቴሌቪዥን ገዙ ወይስ እኔና አንቺን ገበሬ ለማድረግ ተፈልጎ ነው ይኸ ፕሮግራም የሚተላለፈው ? ሲል ጮክ ባለ ድምፅ ጠየቃት።
«እኔ ምን አወቄ?» አልች አስተናጋጇ።
«የከተማ ገበሬ ሞልቷሌ አትይውም!» አላት ሌላው የበድሉ ጓደኛ ከግራ በኩል ሆኖ ወደ ኋላ
ዞር ብሎ በልሁንም አየት አደረገው፡፡
«ይኽ ከየጓሮው ወፍ ዘራሽ ቡና የሚለቅመው?» ሲል የመጀመሪያው ተናጋሪ ጠየቀ።
«ሞፈርና ቀንበራቸውን ሰቅለው ወደ ከተማ የገቡ ገበሬዎች ስላሉ
ጎምዥተው እንዲመለሱ ይሆናል፡፡ አለና በድሉ ወደ ኋላው ዞር ብሎ በልሁን ገልመጥ ሲያደርገው ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ፡፡

«አሃ» አለ በልሁ፡፡ ነገሮች ሁሉ ይበልጥ እየገቡት ሄዱ። ሁኔታው የበለጠ ጆሮውን ጥሎ እንዲያዳምጥ አደረገው።
ከተማ ውስጥ ገብቶ ማውደልደል የጀመለ ገበሬ ምንም ቢሉት ምን
ቢያደርጉት ተመልሶ ገጠር አይገባም፡፡» አለ የመጀመሪያው ተናጋሪ የበድሉ ጓደኛ፡፡
እሱም በልሁን ዞር ብሎ ሲያየው አሁንም ከበልሁ ጋር ተገጣጠሙ::
«ወዶ ነው! ተጎዶ ይመለሳል፡፡» በማለት በድሉ ሲጨምር በልሁ
ሁለመናውን ይነዝረው ጀመር፡፡ በልሁ ጠብ ጠብ ሲሸተው ትንፋሽ ያጥረዋል፡፡እስኪጀምር ድረስ መላ ሰውነቱ ይንዘፈዘፋል። ዓይኑ ይፈጣል፡፡ ያ በሽታው ተነሳበት:: በዚያው ስሜት ውስጥ ሆኖ ምልልሳቸውን ማዳመጡን ቀጠለ፡፡
«ስሚ አንቺ!» ሲል ተጣራ በድሉ አሁንም እስተናጋጇን፡፡
«አቤት»
«ይህን ቴሌቪዥን ዝጊና «ቆይ ብቻ» የሚለውን ካሴት ክፈች፡፡ ይኸ ሴት አውል ሁሉ ልብ ቢገዘ» አለና አሁንም ዞር ብሎ በልሁን ገላመጠው ።
በዚህ ጊዜ በልሁ ለየለት፡፡ ተዘጋጅተው እንደመጡብትም በትክክል ተረዳ፡፡
ወዲያው በግራ ጣቱ ላይ ያጠለቃትን ባለ ፈርጥ ቀለበት ወደ ቀኝ ጣቱ አዛወራት፡፡
ጡንቻውን ማጠባበቅ ጀመረ። አንዲት የትንኮሳ ቃልና ግልምጫ ብቻ ቀረችው። ይጠባበቃትም ጀመር።
በድሉ አሁንም ቀጠለ፡፡ እንኳን የግብርና ወሬ መስማት የግብርና ባለሙያ ነኝ ባይ በከተማው ውስጥ ማየት አስጠልቶናል። አለና ብርጭቆዉን ብድግ አድርጎ
አረቄውን ጨለጠና ከመጠን በላይ ባንኮኒ እያንኳኳ «ቶሎ በይ ነዳጅ ጨምሪ ዛሬ የማነደው አለኝ» አለና አሁንም ወደ በልሁ ዞር አለ።
«ስማ አንተ» አለው በልሁ መርእድን
«ወይ» አለ መርእድ። መሰከረ እየሆነ ያለውን ነገርም ይከታተል ነበርና ደንግጦ መግቢያ ቀዳዳ አቷል
«ከተቀመጥክበት ንቅንቅ እንዳትል እሺ»
«ለምን ወጥተን አንሄድም?» አለ መርዕድ፡፡
«ጉዳዩን እስከምፈፅም" ጠብቀኝ» አለና በልሁ ከወንበሩ ላይ ተነስቶ
በቀጥታ ወደ ባንኒው አመራ፡፡ በበድሉ እና በቀኙ በኩል ባለው ጓድኛው መካከል ባንኮኒ ተደግፎ ቆመና «ጎበዝ» አላቸው ሦስቱንም ተራ በተራ እየተመለከተ፡፡
«የጨዋታችሁ ደስ አለኝና መጣሁ።» እያጋበዛችሁኝ ወይ እየጋበዝኳችሁ እንጫወት
ብዬ ነው::» አላቸው ዓይኑን ፈጠጥ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ፈገግ ብሎ
«ታውቀናለህ?» አለው በድሉ በቁመት የሚበልጠውን በልሁን አንጋጦ እየተመለከተ፡፡
«ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ግን እንደማንተዋወቅ ገባኝ፡፡ ግን ደግሞ ሳንተዋወቅ እንለያይም።» ሲል መለሰለት በልሁ ረጋ ብሎ። «ተገድጄ ወደ አገሬ ልመለስ ነውና የወጪ ልበልህ፤ ጠጣ!» አለው አሁንም እያፌዘ።እስከዚህ ወቅት
ድረስ የበድሉ ጓደኞች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ ግን በልሁን በግርምት ዓይን ይመለከቱታል።
«ነገር ፈልገሃል እንዴ?» አለ በድሉ አሁንም በልሁን እየተመለከተ::»
«ራሱ ፈልጎኝ ነው የመጣሁት።
አሁን ጠጣ! ካልጠጣህ ግን
እመታሀለሁ፡፡»
«ኣ?» ብሎ በድሉ ቀስቀስ ሊል ሲል በልሁ ድንገት አንገቱን አነቀወ። ገበሬ አይደለሁ ፊትህን ላርሰው ነው» አለና በመሀል ፊቱ ላይ ሀይለኛ ቡጢ አሳረፈበት፡፡ በፍጥነት ደገመው ከቀኙ በኩል ያለውን የበድለን ጓደኛ እንቅስቃሴ
ይከታተል ነበርና እውነትም ሲንቀሳቀስ አይቶት ኖሮ በቃሪያ ጥፊ ዓይነት በሀይል ሲሰነዝርበት ጆሮ ግንዱን አገኘው። ሰውየው ባላሰበው ሁኔታና ሀይል ስለተመታ
ከመርዕድ እግር ስር ወድቆ ጥቅልል አለ። መርዕድ በዚያው ጀመረው። በወደቀበት
👍12
በእርግጫ ፊት ፊቱን ይለው ጀመር። ከበድሉ በስተግራ የነበረው ስውዬ በልሁን
ሊመታ ሲሞክር በልሁ ግን የበድሉን አንገት ይዞ ወዲያ ወዲህ እያሽከረከረ መመከቻ አደረገው፡፡ በዚህ አላበቃም፣ አዘናግቶ በበድሉ ትከሻ ላይ አሻግሮ
በመስንዘር ከፌቱ ላይ ከባድ ቡጢ አሳረፈበት። ቀጠለና በድሉን ለሦስተኛ ጊዜ ከደገመው በኋላ አንገቱን ሲለቀው በድሉ ተዝለፍልፎ መሬት ላይ ተዘረጋ። በዚህ ጊዜ በልሁ ወደ ሰውዬው ሲሮጥ ስውየው ግን ወደ ኋላው ዞሮ በቡና ቤቱ በር በኩል እግሬ አወጪኝ አለ። አመለጠው::
በልሁ የሮጠውን ሰውዬ ትቶ ወደ ቤት ምልስ በማለት በድሉን በወደቀበት ፊቱ ላይ አንዴ በእርግጫ ብሎት መጀመሪያ ወደ ጣለው ሰውዬ አለፈ። ሰውዬውና
መርዕድ እየታገሉ ናቸው። እንደውም ሰውዬው መርዕድን አሽንፎ ሊነሳ ትንሽ ቀርቶት ነበር፡፡ ነገር ግን በልሁ ደርሶ በክርኑ ወገቡ ላይ በሀይል ሲመታው
ተመልሶ መሬት ላይ ተነጠፈ። ቀጥሎም በእርግጫ እንደ አልቻሉም ያለፋው ጀመር።
እሪታና ጩኸት ቀለጠ፤ ቤቱ ተተረማመሰ፡፡ የበልሁን አሰናዘር ያየ ማንም ወጪ ሊይዘው ወይም ሊጋበዘው አልሞከረም፡፡ ሁሉም አንገቱን ወደ ትከሻው ቀብሮ
አቤት ገደለው! ገደላቸው! ጨረሳቸው እያሉ ከመሸማቀቅ በቀር ማንም ምንም አልሞከረም። የአስተናጋጆቹ ጩኸት ግን ምድሪቱን ቀውጢ አደረጋት፡፡
አብዛኛው ጠጪ ምስክርነት ፈርቶ እየተፈተለከ ከቡና ቤቱ ወጣ።
ጥሎ ገንድሶ ያለ ገላጋይ የተገላገለው በልሁ ግን ድንገት ሳይታሰብ ባንኮኒውን በቡጢ እየመታ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ!» ካለ በኋላ ቀጥሎም ወንድሜ
አስቻለው! ኧረ ምን በላህ? ኧረ ምን ዋጠህ ወንድሜ? ትዝ አልከኝ እኮ ትዝ አልከኝ
እኮ ወንድሜ?!» እያለ ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ጀመር፡፡ በዚያ ሰዓት ምን ትዝ እንዳለው ከእሱ በቀር ማንም ያወቀ አልነበረም፡፡ ወዲያው ግማሾቹ አስተናጋጆች የወደቁትን ሰዎች ደም በውሃ ሲያጥቡ ሌሎቹ ደግሞ ከመርዕድ ጋር በመተባበር በልሁን ገፋፍተው
በጓዳ በር በኩል ከቡና ቤቱ ውጪ ወሰዱት።......

💫ይቀጥላል💫
👍10
ደስ ባለሽ ቀን ነይ ፤ ነይ ደስ ባለሽ ቀን፤
ተፈጥሮ ይሰበር ፤ ዶፍ ሠኔ ይሙቀን።
አቦ
ነይልኝ ዝሞ እንዳልሽ ፤ ወረኛን ስበሪው፤
ዙፋን ሰልችቶታል፣ አፍቃሪሽን ምሪው።
አቦ
ነይ ደስ ባለሽ ቀን ፤ በፈለግሽው ሰዓት፤
አንቺ የኔ ጸሎት ፣ የጠላቴ መዓት።
ከየትሞ አልሄድኩሞ ፣ መጠበቅ አርቆኝ፤
በተፋቀርንበት ጊዜ ቀርቻለሁ፤ ናፍቆትሽ አጣብቆኝ፤
ወገን ተሰብስቦ፣ ሂድ ቢለኝም እንኳ፣ አልሄድሞ የምለው
ድንገት የሄድኩ ቀን ፣ብትመጪስ ብዬ ነው።
ነይ ደስ ባለሽ ቀን!

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍61
በሣቅሽልኝ ቁጥር ፣ ወደደችኝ ያልከት፣
ሣቅሽን በፍቅር ፣ እየተረጎምኩት፣
የምወቃቀሰው፣
የምቀዋወሰው፣
እስኪታዘበኝ ሰው።
ጅል አይደለሁ? መቼም
በሣቅሽልኝ ቁጥር ፣ ልቤን ስታሞኚ
ወንድ አይደለሁ? መቼም
ቀልዴን ጨረስኩብሽ ፣ ቤቴ ሳትኮኚ፤
ቀልዱን ለጨረሰ ፣ በወደደሽኝ ተስፋ
በእንባ ላይበተን ፣ከሣቅ የተሰፋ
ቆይ ምን ምን ሆኜ ጃል
በሴት ሣቅ መጃጃል?
የጥርስሽ ዘብ ሆኜ ፣ ሞቴ ተወጠነ፤
ቀልዴን መጨረሴም ፣ ራሱ ቀልድ ሆነ፤
ቀልድ የጠፋው አዳም፣
ቀልድ ያለቀበት ወንድ፣
ከታዘብሽ ከሰማሽ ፣ ውርደትን ሸክፎ
አትፍረጅ ግድ የለም
ለሴት ጨርሶት ነው ፣ በጥርሷ ተለክፎ፤


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍84
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ከራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ መሸነፍ በኋላ፣ ሰላም ቀስ በቀስ በሃገሪቱ መልሶ ሰፈነ። ምንትዋብ በነገሠች በዓመቱ እንደ ቀድሞ ነገሥታት የራሷ የሆነ ቤተመንግሥት ለማሠራት ያደረባትን ጽኑ ፍቅርና ፍላጎት
ለማርካት ከባለቤቷ ከአፄ በካፋ ግንብ ጎን ቆማ ያሠራችው የተዋበውና የረቀቀው ፣ እንደ ሌሎቹ ግንቦች ሁሉ ባለ ሰቀሰቁና ባለ ሁለት ደርቡ ቤተመንግሥት የተደነቀ ሆነላት።

አፄ በካፋ በሞቱ በሁለተኛ ዓመታቸው ላይ ያሳደጓት፣ ያስተማሯት፣ በቤተመንግሥት ሥርዐት ሆነ በአስተዳደር ታንጻ እንድትወጣ የረዷት፣ አንደበተ ርቱዕዋ፣ የቤተክህነት ትምህርትና የቤተመንግሥት ወግ አዋቂዋ አያቷ ወይዘሮ ዮልያና ይህችን ምድር ጥለው ሄዱ። እሷ
ሆነች እናቷ መሪር ሐዘን ገባቸው። ዮልያና ታላቅ የቀብር ሥርዐት
ተደርጎላቸው ተቀባሩ። ምንትዋብ ተዝካራቸውንም ታላቅ ድግስ ደግሳ አወጣች።

ዮልያና በሞቱ በስድስተኛ ወራቸው ታናሽ ወንድማቸው ኒቆላዎስ ዐረፈ። ምንትዋብ ተጎዳች። ሆኖም ኒቆላዎስ በታላቅ ለቅሶና ሐዘን ተገቢው ሥርዐት ተደርጎለት ተቀበረ። ቀድሞውንም ቢሆን ለአፄ በካፋ ሁነኛ የነበረና በኋላም፣ ከእሷ ቀጥሎ ትልቁ ባለሥልጣን የነበረ፣አጋሯና በማንኛውም መንገድ ሲያግዛት፣ ሲያማክራትና ትዕዛዞቿን ሁሉ በተገቢው መንገድ ሲያስፈጽምላትና ሲፈጽምላት የቆየ ቀኝ እጇ በመሆኑ፣ የእሱ መሞት በቤተመንግሥት ውስጥ ትልቅ ክፍተት ፈጠረ።

ኒቆላዎስ ከሞተ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ምንትዋብና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዐዲሱ ቤተመንግሥት እልፍኝ ውስጥ እጅ የሚነሱትን መሣፍንትና መኳንንት አሰናብተው ጨርሰው፣ ኢያሱ ከአጃቢዎቹ ጋር ወጥቷል።
ምንትዋብም እልፍኟ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነች፡፡ ደጃዝማች
ወልደልዑል ጫማውን ሳያወልቅ እልፍኝ ዘው ሲል ከአረማመዱ የሆነ ነገር እንደገጠመው አወቀች። ዛሬ ወልድየ ምንን ሁኖ ነው አለወትሮው በችኮላ ሚራመደው አለች፣ ትኩር ብላ እያየችው።

“ችግር አለ” አላት፣ የችኮላ ሰላምታ ከሰጣት በኋላ።

“የምን ችግር ወልድየ?” ከተቀመጠችበት ተነሳች።

“የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ ለውጊያ ታጥቋል።”

“ምን ይሁን ብሎ?” ፊቷ ጥላ ጣለበት። “ምን ይሁን ብሎ ነው አሁን ጦር ይዞ ሚነሳ?”

“ኸኢያሱ ክፍል የለኝም ብሎ። ያው ፊት እንደሰማነው፣ እኒህ
ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ።”

ከቋራ ስለመምጣቷ ከአያቷ ጋር ሲያወሩ፣ “ንቀታቸው... ወደ ፊት
ታቂዋለሽ” ያሉት ትዝ አላትና ራሷን በትዝብት ነቀነቀች። “እኒህ

ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ?” አለችና ከት ብላ የምጸት ሳቅ ሳቀች።

“አዎ እስተመቸ ነው ሚገዙን እያለ ሲቆጭ ቆይቷል” አላትና
እንድትቀመጥ በእጁ ዙፋኗን አመለከታት።

ቀጥል በሚል እጇን አወዛወዘችለት።

“አንዱም ኸተሰጠው የዳሞት ገዥነት ስለወረደ በልቡ ቂም ኣሳድሮ ነው እኼን ሊያረግ የተነሳው። ጥላቻውና እብሪቱ መጠን አጥቶ እዋጋለሁ ብሎ ነገሩን ኻዘጋጀ ሰንብቷል። “
እኼን የኩበት ካብ ሳላፈርስ
ሰው አልባልም ብሏል አሉ።”

“የኩበት ካብ?”

“የንጉሥ ኢያሱንና ያንቺን መንግሥት ማለቱ ነዋ!”

“ዛዲያማ ይጠብቀና” አለች፣ ሌባ ጣቷን እያወዛወዘች።

“ኸመጣሽ ዠምሮ ቋረኞች ላይ ያለው ግምት ምን እንደሁ
ታውቂያለሽ። አንቺም ብትሆኚ አልተሸነፍሽላቸውም፤ ወደፊትም
ታሸንፊያቸዋለሽ። ስሰማ ተንሴ ማሞ ኸዝኸ ሁሉ መጥቶ ግቢውን
አይቶ ነው አሉ የኸደው። ተመልሸ መጣለሁ ብሎ ዝቷል።”

“እንዴት ልቡ አብጧል በል? ይምጣ... ይምጣ... እስቲ እናያለን
የኩበት ካቡን ሲያፈርስ። የልዢን አልጋ ኻላስከበርሁማ እኔ ምንትዋብ ሰው ማዶለሁ” አለች።

ሰውነቷ ጋለ።

“አሳቡ አንቺንና ንጉሥ ኢያሱን መግደል ነው። መንገስ ሚፈልገውን ጠይቆ ሊመጣ ወህኒ ኸዷል። ወንድሙ ተስፋ ማሞም
ኸሱ ጋር አምጿል። ኸጎዣምም ብዙ ሠራዊት ሰብስቧል አሉ። እኛም መዘጋጀት አለብን።”
ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ አየችውና፣ “ሚነግሠውን ያምጣ። የትኛው
አልጋ ላይ እንደሚያስቀምጠው እናያለን። ይልቅስ አሁን ኸመሣፍንቱ፣ ኸመኳንንቱና ኸጦር አበጋዞቹ ጋር እንምከር። ለወሎና ለጎዣም ባላባትም ስለሁኔታው እናመላክታቸው። ዛሬውኑ መልክተኛ እንላክ።ጠንካራ ጦር ስላላቸው ኸነሱ ጋር ተባብረን ነው እኒህን ሰዎች መቋቋም
ምንችለው። ዛሬውኑ ሁነኛ ሰው ላክና እንዲደርሱልን አርግ::”

“በጀ፤ እንደሱ አረጋለሁ” ብሏት እጅ ነስቶ ወጣ።

የእልፍኝ አስከልካዩን ቴዎድሮስን አስጠራች።መኳንንቱና የጦር አበጋዞቹ በአስቸኳይ መሠሪ
እንዲነግራቸው ነገረችው። ኢያሱም ከግቢ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ሰጠች።ቴዎድሮስ እጅ ነስቶ በፍጥነት ወጣ።

ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። “የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ
ለውጊያ ታጥቋል” የሚሉት የወንድሟ ቃላት ጆሮዋ ላይ አቃጨሉ::እሷንና ኢያሱን መግደል መፈለጉ አስገረማት። ኢያሱን መግደል የሚለው ቃል ዘገነናት። ልጄን በደንብ ማስጠበቅ አለብኝ አለች።

አምላኬ ልዤን ዐደራህን አለች፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ
መስኮቱ እየሄደች። በስተቀኝ በኩል በባሏ ግንብና በፈረስ ቤቱ መሃል ያለው ሰፊ ቦታ ላይ ኢያሱ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ባልደራሱ ያነጋግረዋል።ወደ ግቢው በር እየጠቆመ ሌባ ጣቱን ያወዛውዛል። አትውጣ ተብለሀል
ነው ሚለው አለች፣ ምንትዋብ።

በፈረሱ ዙርያ በርካታ የመሣፍንት ልጆች እየተሯሯጡ ይጫወታሉ።
አሁን እስቲ እኼ ትንሽ ልዥ ምን አረገው? ለአልጋ ብሎ ትንሽ ልዥ
ይገድላል? እሱ እንደሆን አይቀመጥበት። ደሞ ማነም ሆነ ማን ኸወህኒ አምባ ቢመጣ የኢያሱን አልጋ አይወስድም. ቁሜ ነው ሙቼ።ልዤንም አልጋውንም እከላከላለሁ አለች። ኢያሱን እያየች፣ እንደነዝኸ ልዥች በመጫወቻው ሰዐት ለሞት ሊዳርግብኝ ባሏ ያስገነቡትን
ግንብ አየችና አስታወሰቻቸው። ለካንስ እንደዝኸ እያመጡ ነው ሰላም ሲነሷቸው የከረሙት.

ኧረ ደሞ ተንሴ ማሞ ተሹሞ ኸነበረ ላይሻር ኑሯል? ስንቱ ይሻር
የለ? ሹም ሽረት ያለ ነው። ደሞ ሰነባበተ እኮ። እንዴት ያለ በቀለኛ
እያሰበችበት ስትመጣ የጋለ ስሜት በመላ አካላቷ ተሰራጨ። ጉንጫፍም መሰለ።

እኔ ምንትዋብ ምን መስየዋለሁ? ቁጭ ብየ ምጠብቀው ይመስለዋል? ይኼ ኸመጣማ አልመለስለትም፡፡ እስቲ ልዤን እንድች ብሎ ንክች ያርግ ያየኛል፣ ብላ ቀኝ እጇን ጨብጣ የመስኮቱን ደፍ መታ መታ አደረገችው። እስቲ አሁን ሰላም ሆንን ስል... ስንት ነገር ላገሬ ሳስብ እንደዝኸ ያለው ይምጣ ላገሬ ያሰብሁትን ሳላረግማ እሱ አይቀድመኝም ኸመንገዴ ላይማ አይቆምም፤ እፋለመዋለሁ። ግድ የለም መልሸ ሰላም አመጣለሁ። አንዴ የሱን ነገር ልወጣ።

ተመልሳ ሄዳ ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። አሁን ብናደድ ምንም ጥቅም የለው። ይልቅስ ማረግ ያለብኝን ባስብ ነው ሚሻል። በመዠመሪያ የግቢውን በሮች እንዲዘጉ ማረግ አለብኝ መጠለያ እንዳይሆናቸው ደሞ ኸግቢ ውጭ ያሉትን ዛፎች ቅርንጫፍ ሁሉ ማስቆረጥ። አሁን
ይልቅ መሣፍንቱን፣ የጦር አበጋዞቹንና መኳንንቱን ተሎ ላነጋግር።ወልድየም ተሎ ብሎ ወሎና ጎዣም መልክት ይላክ፡
👍12
አንድ ሰዐት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከኢያሱ ጋር መሠሪ ስትገባ፣
መሣፍንቱ፣ መኳንንቱና የጦር አበጋዞቹ ተሰብስበዋል። ምንትዋብ ዘንድ የተለመደውና ትጥቃቸውን የሚያስፈታቸው ፈገግታዋ የለም።ምን እንደተፈጠረ ለመገመት እንኳን ዕድል ሳትሰጣቸው የተጠሩበትን
ጉዳይ ነገረቻቸው። ከዝቅተኛው ጀምሮ እስከ ከፍተኛው መኰንን ድረስ ከተቀመጡበት እየተነሡ ሐሳብ ሰጡ። የተንሴ ማሞንና የራሳቸውን ጦር ጥንካሬና ድክመት አመዛዘኑ። ተንሴ ማሞ ቀድሞ በመደራጀቱ ከጐንደር ውጭ ያለ ጦራቸውን እስኪያሰባስቡ ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል በሽምግልና ዕርቅ እንፍጠር ኣሏት።

ጉንጮቿ ደም አዘሉ። ዐይኖቿ እስከ መጨረሻው ተከፈቱ። ከንፈሯን በጥርሷ ነክሳ በግራ ሌባ ጣቷ ተመተመችው።

ሴት ናት ጦር መቋቋም አትችልም ብለው ነው እንዲህ ሚሉ? እቴጌ
ሰብለወንጌል ባላቸው አጤ ልብነድንግል ሲሞቱ፣ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ሲያዋጉ የነበሩ እሳቸው ማልነበሩ? እኔ ኸማን አንሸ ነው? አለች፤ ለራሷ።

ስሜቷን ለመቆጣጠር ቁና ቁና ተነፈሰች። ጣራ ጣራውን ተመለከተች አልሆነላትም። ድንገት ብድግ አለችና፣ “ዕርቅና ሽምግልና አያሻኝም ብላ ጮኸች፤ ድምጿ አስገመገመ። ከንፈሯን ደግማ ነከሰችው።

መኳንንቱ ስንቱን አመጸኛ እንዳላርበደበዱ፣ ፊት ለፊት ጦር
ገጥመው እንዳልረቱ ሁሉ ተደናገጡ። እርስ በእርስ ተያዩ።
ከመሃላቸው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ።
“የመጣው ይምጣ። ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ። ያበጠው ይፈንዳ”
አለቻቸው። ወደ ጎን ሄድ ብላ ተመልሳ የነበረችበት ቆመች። ድምጿን ለዘብ አድርጋ፣ “ሰዌን አልበደልሁም። ሰዉም ቢሆን ለነዝኸ ራስ ወዳድ ወንበዴዎች አሳልፎ አይሰጠኝም።”

ፀጥታ ሰፍኗል። መርፌ ቢወድቅ ይሰማል።

ቀጠለች፣ “እኔ ምንትዋብ ስታዩኝ ምን መስላለሁ? በተፈጥሮ ሕግ
ሴት ብሆንም፣ ባለኝ ተሰጦና ሀብት ኸወንዶች እበልጥ እንደሁ እንጂ ማንስ አደለሁም። ኸፈጣሪ የተሰጠኝ ሀብት ኸወንዶችም ወንዶች ሚሰጡት ሀብት ነው። በምንም አያንስም። በእዝጊሃር ፍጥረት ሴት ልሁን እንጂ ምን ይጎለኛል? ማንን ፈራለሁ? ግድ የለም። እኼን ታያላችሁ። ለዘውድ ቀንተው የሜጫ፣ የይልማና ዴንሳ፣ የጃዊ፣ የዳሞትና
የማቻከል እንዲሁም አጠቃላይ የጎዣም ሰዎች ቢመጡ አልፈራም።ገሚሱ የጎዣም ሕዝብ ደሞ ሥጋዬ ነው። እነሸበል በረንታ፣ እነእነማይ ያጤ ሚናስ ወገኖች ናቸው። ያጤ ሚናስ እናት እቴጌ ሰብለወንጌል የእናቴ ወገን ናቸው። ይልቅስ ኩርዓት ሥርዐቱ ይምጣልኝ።”

መኳንንቱ በአንደበተ ስልነቷና በቆራጥ መንፈሷ ተደመሙ። በአንድ ድምፅ፣ “ይበጅ! ይበጅ!” አሉ።..........

ይቀጥላል
😱2👍1
ሚስት ስጠኝ ስለው፣ እናት እየሰጠኝ
እናት ስጠኝ ስለው፣ ለትዳር ቢያሮጠኝ፣
ትዳር ስጠኝ ስለው፣ዐዳርን ቢሰጠኝ፣
ልክ አንቺን ሳገኝሽ.....
ዘግይቶ ገባልኝ ፣ሁሉ እንዳመለጠን፡፡

ምኔ ነሽ?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
6
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..ሔዋን የልብ ህመሟ ከመቼውም ጊዜ ብሶባት ፍራሽ ላይ ድፍት ብላ
መዋል አዘውትራለች።በበልሁ በጢ ፊቱ የተጠረማመሰው በድሉ አሸናፊ አልጋ ላይ ከዋለ አስራ አንድ ቀን ሆኖታል፡፡ እዚሁ ቀን ላይ ሆኖ ሲቆጠር “ማንደፍሮ በአንድ ሳምንት ያህል ተረኛ ሆኖ በተመደበበት ከአዋሳ ይርጋለም መስመር ላይ ለመስራት ከቤቱ ከወጣ ሶስት ቀናት አልፎታል።
እለቱ እሁድ ነው፣ ከሰአት በኋላ፡፡ ሸዋዬ ቤትዋ ውስጥ ለብቻዋ ቁጭ ብላ ጫት ትቅማለች።
ነገር ግን የጎረሰችውን ጫት ማላመጥ እስከምትረሳ ድረስ
በሃሳብ ተውጣ ፍዝዝ ትክዝ ትላለች። በበድሉ ላይ የደረሰው ውርደት ከእሱ ይበልጥ እሷን አሳፍሯታል። ዛሬ በማውጠንጠን ላይ ያለችው ሃሳብም ይህንኑ
ሀፍረትና ውርደት ስለምታካክስበት መንገድና ሁኔታ ነው።
መነሻ ያደረገችው ከራሱ ከበድሉ የመነጨ ሀሳብ ነው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተኛበት አልጋ አጠገብ ቁጭ ብላ ስታፅናናው በነበረችብት ወቅት በድሉ
አንድ ነገር ተናግሯታል ሸዋዬ! በእህትሽ ምክንያት ደሜ ፈስሷል፡፡ ቅሌት ደርሶብኛል። መካሻዬም እሷው ናት:: የመጣው ይመጣል እንጂ አልተዋትም። ወይ
እንደኔ ትዋረዳለች። አለያም እስከ መጨረሻው በእጄ ትገባለች። ለዚህ ደግሞ የአንቺን የአላሰለሰ ጥረት እጠብቃለሁ የሚል፡፡ የዛሬው ህሳብና ትካዜዋም በዚሁ
ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ከበድሉ የዛቻ ቃሎች በተግባር ተፈጽሞ ማየት የምትፈልገው ሔዋን ጥቅልል ብላ በእሱ እጅ መግባቷን ብቻ ነው::
ሸዋዬ ያለማወላወል በአንድ ሀሳብ ፀንታለች። ሔዋን ከበድሉ እጅ እስከ ወዲያኛው ትገባ ዘንድ አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ከእሱ መፀነስ ይኖርባታል። ይህ ከሆነ መንገዶች ሁሉ ያጥራሉ፡፡ ሔዋን አስቻለውን በተስፋ የመጠበቅ ሀሳቧ ይቀየራል ቢመጣ እንኳን መሸሹን ትመርጣለች። አስቻለው ራሱም ዘወር ብሎ ሊያያት አይሞክርም አንዴ ከወለደች የልጅ አባት ያስፈልጋታልና በድሉን መራቅ አትፈልግም ምርጫዋም እሱና ብቻ ይሆናል። ማርገዟ ያሳፍራትና ከነታፈሡና ከነበልሁም ትርቃለች እንዲያውም ጭራሽ እንዳያውቁባት ወደ ቤተሰቦቿ ወደ ክብረ መንግስት ልሂድ ከሰል ትችላለች ያኔ በድሉም ወደዛው መመላለስ ይጀምራል በዚያው ከቤተሰቦቿ ይተዋወቅና እጁንም መዘርጋት ይጀምራል። ይሄ ደግሞ ለሸዋዬ ድርብ ድል ይሆናል "እኔም ለዚህ ብዬ ነበር" ለማለት ያበቃታል ይህንም ወርቃማው መላ ብላ ሰይመዋለች።

ይህን ወርቃማ መላ ለፍሬ ለማብቃት ግን በድሉ ከሔዋን ጋር
የሚፈፅመው የወሲብ ግኑኝነት
በተጠና ወቅትና ሰዓት መሆን እንዳለበት ታምናለች ለዚህ መሰረት የሆናት ደግሞ በወር አበባ አቆጣጠር የሚታወቅ
የእርግዝና ወቅት ነው። እንደ ሔዋን ለመውለድ ሳይሆን ላለመውለድ ስትል ራሷ
ስትጠቀምበት ኖራለችና እውቀቱ አይቸግራትም የሚያስፈልጋት የሔዋንን የወር አበባ ዙር ማወቅ ብቻ ነው በየስንት ቀን እንደማታየት ካወቅች በየትኛው ቀን ግኑኝነት ብትፈፅም መፀነስ እንደምትችል ታውቀዋለች።በዚህ ሰአት ሔዋን ይፈፀምባት ዘንድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ወስናለች። ሔዋን ጩኸት ብታሰማ
እንኳ በተያያዥ ሊነሳባት የሚችለውን ውግወት ጆሮ ዳባ ልበስ ልትለው ቆርጣለች።
የሔዋንን የወር አበባ ዙር ለማወቅ ግን ተቸግራለች፡፡ እሷን እራሷን
አትጠይቃት ነገር ሰሞኑን ተኳርፈዋል። በሌላ በኩል በትክክል ላትነግራት ትችልና
ጥረቷ ሊመክን ይችላል። አስተማማኝ እንዲሆንላት ሐኪም ማማከር እንደሚሻል ታይቷታል። ለዚህ ስኬት ደግሞ የሔዋንን የልብ ህመም መነሻ ማድረግ ፈለገች ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባርናባስ ወይሶ ታወሳት። እሱ ደግሞ የውጭ ሀገር ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ሥራው ከተመለሰ
ሰምብቷል። ከመጣም ተገናኝተዋል፡፡ ባል ማግባቷን ሰምቶ ተነጋግረውበታል፡፡ ባርኔ አልተከፋም እንዲያውም እንኳን ደስ ያለሽ ብሏታል በተገናኙ ቁጥር መቃለዳቸውን አልተውም። እናም የሔዋንን የልብ ህመም በማስመርመር ሂደት ምናልባት የወር አበባሽ ጋር ግንኙነት ካለው በሚል ሰበብ በሚቀርበው ሀኪም በኩል የወር አበባ ቀን መምጫ ዙር ሊያስጠናላት እንደሚችል ገመተች። ይህን ዘዴ ለራሱ ለበድሉ ብታካፍለው ከእሷ በተሻለ
ከባርናባስ ጋር ተመካክሮ ሲያሳካው እንደሚችል አሰበች፡፡ የዚያን ዕለት ልትነግረው ወሰነች።
ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ከቤቷ ወጣች፡፡ በቀበሌ ዜሮ ሦስት የመጨረሻ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው የበድሉ መኖሪያ ቤት ማምራት ጀመረት:
ቀኑ መሽት ብሎ ለዓይን መያዝ ጀምሯል፡፡ ወደ በድሉ ቤት በመሄድ ላይ ሳለች ልክ አስፋልቱ ላይ ስትደርስ ድንገት ሳታስበው ባርናባስን ከሩቅ አየችው
አስፋልቱን ይዞ ከታች ወደ ላይ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን እሷ ወደነበረችበት አቅጣጫ ይመጣል:: ከበድሉ በፊት ለእሱ ስለ ውስጥ አሳቧ በዚያ አጋጣሚ ትንሽ ፍንጭ ልትሰጠው ወደደች፡፡ መንገድ ዳር ቆማ ጠበቀችው። ባርናባስ ልክ አጠገቧ ሲደርስ ከሰዎቹ ነጠል ብሎ ወደ እሷ እንዲመጣ በእጇ ጠቀሰችው፡፡ ባርናባስም ጥሪዋን ተቀበሎ ወደ እሷ ጠጋ እያለ
«የሽዋ፣ በጨለማ መንገድ ዳር ምን አቆመሽ?» ሲል ጠየቃት እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ።
ቸግሮኝ::» አለችው እንደመሽኮርመም እያለች።
«ምነው? ምን ገጠመሽ? አላት ባርናባስ። ሞቅ ስላለው አፉ ተያይዟል።
«ከቸገረኝ እንኳ ቆይቷል፡፡ ድንገት በሩቅ ሳይህ ግን ላማክርህ ፈልጌ ነው፡፡
«ምንድነው ችግሩ?።»
«ባክህ ያቺን እህቴን ልቧን እያመማት ተቸግሬአለሁ።» ምናልባት በደንብ ሊከታተላት የሚችል አንተ በተለይ የምትቀርበው ሀኪም ካለ አደራ ትልልኝ እንደሆነ ብዬ ነው።»
«እሱ ምን ይቸግራል ይዘሻት ነያ»
«ቢሮህ ውስጥ ምን ጊዜም ትኖራላህ እያደል?»
«የት እሄዳለሁ፡፡» ካለ በኋላ
ባርናባስ እጇን ያዝ አድርጎ «ድሮ እንኳ ወደ ዜሮ አምስት ቀበሌ ጎራ እል ነበር! ዛሬ ግን ማንዴ አስለቀቀኝ» በማለት ሳቅ ብሎ ሸዋዬንም አሳቃት።
«ሁሉም በጊዜው ሆኗል በቃ!» አለች ሸዋዬ እንደ መሽኮርመም እያለች።
«በቃ ! በቃ? አላት ባርናባስ አሁንም ወልገድገድ እያለ፡፡
«አብቅቶ»
«ታዲያ ያቺን ቆንጆ እህትሽን እንዴት አድርጌ ልጠይቃት?»
«እንዴ እሷን መጠየቅ ማን ይከለክልሀል?»
«አሁን እችላለሁ? ወይስ ስውየሽ ይኖር እንደሆን ብሎ ነገሩን ተወት
ሲያደርግ ሸዋዬ ቀጠለች።
«አሁን መሸ ጓደኞችህም ጥለውህ ሂዱ»
«እነሱን ተያቸው እባክሽ!» አለና እውነት ሰውየሽ ከሌለ ልጠይቃት
በጣም በጣም ናፍቃኛለች፡፡» ሸዋዬ የበርናባስሀሳብ አልከበዳትም ማንደፍሮ የለምና ዓይን ለዓይን አይጋጩባትም። በሌላ በኩል እግረ መንገዷን
ሔዋን ወደ ሐኪም ቤት እንድትሄድ ሊገፋፋት እንደሚችል ታያት፡፡
«ከበረታህ እንሂድ፡፡ እንደውም ቀኑን ሙሉ እንደተኛች ነው የዋለችው»
«ሰውየው ግን አይኖርም? አየሽ ምናልባት» ብሎ አፍ አፏን ሲጠባበቅ ሸዋዬ ቀጠለች፡፡ ለነገሩ ሰሞኑን አይኖርም የስራ ተራው ይርጋለም አዋሳ መስመር ሳይ ነው።» አለችና ግን ቢኖርም የኔና የአንተን ጉዳይ የት ያውቃልና
ይጠራጠራል ብለህ ሰጋህ?»
«አለመኖሩ ጥሩ!»
👍13
ተያይዘው ሄዱ፡፡
በግምት ለአስር ደቂቃ ያህል ተጉዘው ከቤት ሲደርሱ ቤቱ ተቆልፎ አገኙት፡፡ ሐዋን የለችም ። የሄደችበትን ቦታ በመገመት ሸዋዬ ወስጧ እርር ድብን አለ። ሔዋን ሰሞኑን ወደ ታፈሡ ቤት ብቅ ብላ ስሰማታውቅ ይቺን አጋጣሚ
ተጠቅማ ወደዚያው እንደሾለከች ገባት። ውስጧ ብግን አለና በሆዷ ቆይ አባቷ ትመጣታላች» እያለች ባርናባስ ይቀመጥ ዘንድ ጋበዘችው፡፡
ባርናባስ ወደ ውጭ አገር ለትምህርት ከሄደና ከተመለሰም ወዲህ በሽዋዬ ቤት ሲገባ የመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ የቤቷ መለዋወጥ ገረመው ከሁሉም በላይ ያ ሳሎን ውስጥ የተዘረጋ አልጋ አማለለው፡፡
«እውነትም ባል አግብተሻል የሸዋ፡አላት እንደ አዲስ።
«እይደል? ኪ-ኪ ኪ.....»
ባርናባስ ከሞቅታ ጋር ተቀላቅሎበት ሳይሆን አይቀርም ከቁጥጥሩ ውጭ በሆነ ስሜት አልጋው ላይ ቁጭ አለና ከፊቱ የቆመችውን ሸዋዬ አንጋጦ
ይመለከታት ጀመር።
«እንዴ! ምን ነካህ?» አለች ሸዋዬ እንደመሽኮርመም እያለች፡፡ ባርናባስ ግን እንዲያውም ቀሚሷን ይዞ ጎተት ሲያደርጋት ኧረ በህግ እምሳክ?» አለችው፡፡
ባርናባስ ጠንከር አለ፡፡ አልጋው ላይ ጎትቶ እስቀመጣትና «በህግ አምላክ መባል ያለበት ሌላ! እኔ እኮ የቀድሞ ባለይዞታ ነኝ፡፡ አላት ደበስበስ እያደረገ፡፡
«ያ እኮ ቀረ።»
«ያ እኮ የሚቀረው እኔና አንቺ ስንቀር ብቻ ነው::» እያለ ትከሻዋን ይዞ ወደ አልጋው ጋለል አደረጋት፡፡ በዚያው ቀጠሉ። ሄዱ፤ ነጎዱ። ባሉበት መንገድ ጅውውው!።
አጋጣሚ ሆኖ ማንደፍሮ ከሸዋዬ ቤት ሊደርስ ከአስር ደቂቃ ያልበለጠ ጊዜ የሚወስድ መንገድ ብቻ ቀርቶታል አስቦበት አልነበረም፤ ጠዋት ሰዎችን አሳፍሮ ከይርጋለም ወደ አዋሳ ሲሄድ ወደ አፖስቶ ኬላ ብቅ መበያ ዳገት ላይ መኪና ተበላሽቶበት ለመጠገን ሲለፋ ውሏል። የብልሽቱ መጠን ከባድ በመሆኑ ዕቃ ለውጦ መገጣጠም የሚችል ባለሙያ አስፈላጊ መሆኑን አምኖ ጉዳዩን
ለተሸከርካሪው ባለቤቶች ሊያስረዳ ምሽቱን ዲላ ጉበቷል፡፡ ዲላ ከተማ ከገባ በኋላ ቶሎ ወደ ቤቱ አልሄደም፡፡ ለውሃ ጥም መቁረጫ ያህል ሲጠጣ ቆይቷል፡፡ ከዚያም በኋላ በቅድሚያ ወደ በድሉ ነበር የሄደው። የገጠመውን ችግር አስረድቶ አስፈላጊውን ሁሉ ጠዋት ለመፈጸም ቀጠሮ ይዞ ወደ ቤቱ እየተመለሰ ነው፡፡
ማንደፍሮ እቤቱ ሲደርስ ቤት ውስጥ መብራት ሲበራ ከሩቅ ታየው በር ከፍቶ ሊገባ እጁን ከመዝጊያው ላይ ጣል ሊያደርግ ሲል ድንገት አንድ ደምፅ ጆሮው ውስጥ ጥልቅ አለ፡፡ በሩን መግፋት ወይም መቆርቆር ትቶ ጆሮውን ወደ ውስጥ ጣል ሲያደርግ ያንን ድምጽ ደግሞ ሰማው። የሸዋዬ ድምጽ ነው፡፡ ሸዋዪ ወሲብ በምትፈጽምበት ጊዜ መለፍለፍ ትወዳለች። የወሲብ አጋሯን ስም ደጋግማ
ካልጠራች አይሆንላትም፡፡ ይህን አመሏን ማንደፍሮም ያውቀዋልና አሁንም ሲያዳምጥ ባርኔ! አንተ ባርኔ፣ እንዴት ነው እሱ? እኮ! አዎ... !» ስትል ሰማት።
«ኣ! » አለ ማንደፍሮ ድንግጥ ብሎ። ጆሮውን አሾልኮ ከአፏ ላይ ያደርሰው ይመስል በቀዳዳው ላይ ለተመው:: ሸዋዬ ልፍለፋዋን አሁንም ቀጠለች::እንዲያውም የወንድ ወሲባዊ ድምፅ ጎረምረምረም ሲል ተሰማው፡፡ በዚህ እየሆነ ያለው ነገር በትክክል ገባው።
ማንደፍሮ ልክ ከርቀት የሚጣራ ይመስል ድምፁን ከፍ አድርጎ «አንቺ» ሲል ጮኸ፡፡ «ምን እየሰራሽ ነው በይ!?» አለና በዚያ በፈረጠመ ክንዱ ያን መዝጊያ
ጓ! ! ጓ! ... ጓ...ጓ..ያደርገው ጀመር፡፡ ወዲያው ድምፁ ቆመ፡፡ መብራትም ጠፋ። ማንደፍሮ አሁንም በጩኸት ድምፅ «የትም አታመልጪ! እንደ መብራቱ አንችም ትጠፊያለሽ በማንዴ ምትክ ያመጣሽው ባርኔም ዛሬ ይለይለታል!!» ካለ በኋላ
እሁንም በሩን ጓ! ! ጓ! እያደረገ «ክፈች! ክፈች! ክፈች!» እያለ ይጮኽ ጀመር፡፡
መልስ አጣ:: መዝጊያውን ለመስበር ከማጠፊያው በኩል በእግሩም በእጁም መውገሩን ቀጠለ:: ምናልባት ለእሱ አይታወቀው እንደሆነ እንጂ ድምፁም ሆነ የበሩ ምት ጩኸት እስከ ውጭ ድረስ ይሰማል፡፡ ወይዘሮ ዘነቡና ሠራተኛቸው በጓሮ በር በኩል ብቅ ብቅ ብለው
ሁኔታውን ይመለከታሉ ድምፅ ግን ቶሉ አላሰሙም እየቆየ ግን በተለይ ወይዘሮ ዘነቡ የቤታቸውም ደህንነት አስግቷቸው ሰራተኛቸው እሪ እንድትል ሳያዛዟት አልቀሩም ፋንታዬም ድምጿን ከፍ አድርጋ «እሪሪሪሪ» ስትል ጮህች።
ማንደፍሮ በር መውገሩን ቀጥሏል ከተደጋጋሚ ምት በኋላ የመዝጊያ ማጠፊያዎች ሁለቱም ተነቀሉ። አልከፈት ወይም አልወድቅ አለው ለካ ባርናባስ ከውስጥ ወደ ውጭ
ገትሮ ይዞበት ኖሯል ለማንደፍሮም ሚስጥሩ ገባው ብቻ ግፊያውን ቀጠለ፡፡ ያ መዝጊያ ከውስጥና ከወጭ እየተገፋ ወዲያ ወዲህ በመዋለል መከራውን አየ። ሁለቱም ሀይላቸውን ለማጠናከር «እምምም..» እያሉን ይፍረመረማሉ። ባርናባስ ከውስጥ «ምምም ..» ማንደፍር ከውጭ «እምምም..» ትግሉ
ቀጠለ። ማንደፍሮ ለመግደል! ባርናባስ ለመትረፍ።
የኋላ ኋላ ግን ባርናባስ ደክሞ ኖሯል፡፡ የጀርባው ላብ በመቀመጫው ፍንክት መሀል ሲንቆረቆር ተሰምቶታል በትንፋሹም ብዛት ልቡም ልትፈነዳ
ደርሳለች። ሽንቱም አምልጦታል። በዚህ ጊዜ መረታቱን አውቆ መዝጊያውን ትቶ ወደ አንድ በኩል ሽሸት ሲል ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ይገፋ የነበረው ማንደፍሮ ወደ ውስጥ ተወርውሮ መሀል ወለሉ ላይ በደረቱ እርርርብ አለ።ቀአፍጢሙ ተደፋ። እሱ ቀድሞ ወለሉ ላይ ከተዘረጋ በኋላ በሀይል ሚዛን መዛባት ምክንያት ተንሳፎ የነበረው መዝጊያ ከላዩ ላይ ዞሮ ተጫነው።ባርናባስ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ማንደፍሮን በተኛበት ላይ ለማዳከም
አልቃጣም። ፓንትና ካኒትራውን እንዲሁም ጫማውን ጨምሮ ወንበር ላይ አስቀምጦት የነበረ ልብሱን በሙሉ በአንድ ላይ በሁለት እጆቹ እፍስ አድርጎ ደረቱ
ላይ በመታቀፍ ማንደፍሮንና መዝጊያውን ተራምዶ ከላይ እስከ ታች እርቃኑን እንደሆነ ወደ ውጭ ሮጠ፡፡ ከመሉ ጨረቃ በሚፈልቀው ብርሃን ያን ቀይ ሰውነቱን እያንቦገቦገ ሲሮጥ
ጩኸትና እሪታውን ሰምቶ ወደ ወይዘሮ ዘነቡ ግቢ ይጎርፍ
የነበረው ሕዝብ «እብድ! እብድ! እብድ' እያለ መንገድ ለቀቀለት፡፡ በርካቶች ከኋላ ሲመለከቱት ቁልቁል ወደ እሬሣ ቀበሌ ገበሬ ማህብር ሽመጠጠ፡፡
ማንደፍሮ ከወደቀበት እንደ ምንም ተነስቶ መብራት ሲያበራ መጀመሪያ ያየው የተመሰቃቀለ አልጋውን ነው፡፡ ቆጨው፡፡ ወደ ውጭ ያመለጠ ሰው እንዳለ
ተሰምቶታል። ግን ሊደርስበት እንደማይችል ገመተና ወደ ጓዳ አየት ሲያደርግ ሸዋዬ እርቃኗን እንስራ መስላ ከዕቃ መደርደሪያው ሥር ሽጉጥ ብላ አገኛት::
«ባርኔ?» አለችው ሽዋዬ በልመና ዓይነት እጆቿን በደረቷ ላይ ልጥፍ
አድርጋ በመኮራመት። በእሷ ቤት 'ማንዴ ማለቷ ነበር። ደንግጣለችና ተሳሳተች።
«አይደለሁም!» አላት ማንደፍሮ በፌዝ አነጋገር፡፡
«በእናትህ ይዤሀለው»
«ባርኒ ሆኖ ቢሆን ይምርሽ ነበር!»
እኔ ግን ማንዴ ነኝ» አለና
«እንዳትንቀሳቀሽ!» ሲል አስጠነቀቃትና ከኋላዋ በኩል ዞረና ቅልጥሟን፣ ጭኗንና
ወገቧን አንድ ጋር አጣብቆሰ በመታቀፍ ብድግ አድርጎ እንደገና ወደ መሬት ወርውሮ እን...ዘጭ! አደረጋት፡፡ አደረጋት
ሸዋዬ ለአንዴ «ኣኣኣ.» ብላ ጮኸችና ማንዴ ልተረተር እኮ ነው» አለችው። «የእኔስ ልፋት ለምንድን ነው? እንድትሰነጣጠቂ እይደል » አለና እንደገና ብድግ አድርጎ በሀይል ወረወረና ከግድግዳው ጋር ሲያላትማት አጠቃላይ ቤቱ ግውው የሚል ድምፅ አሰማ። ያቺ ሰርቪስ ቤት ዳር እስዳር ተነቃነቀች
👍10😁1
ማንደፍሮ ደገመና ሸዋዬን ከወደቀችበት አንስቶ እንደገና ዕቃ መደርደሪያው ላይ ወርውሮ ሲያላትማት ራሷ የገዛቸው ብርጭቆዎችና ኸካላ ሳህኖች
ከሽሽሽ...አሉና አመድ ሆኑ፡፡ ቤቱም እንደገና ተነቃነቀ፡፡
«አረ ቤቱን! አረ ቤቱን! ያገር ያለህ!» የሚል ድምፅ ከውጭ ተሰማ የወይዘሮ ዘነቡ ድምፅ ሰው ሁሉ በር ላይ ተኮለኮሎ ይመለከታል አንዳንዱ ይጮሀል።
ገብቶ ለመገላገል ግን ሁሉም ፈርቷል ብቻ ገደላት! ገደላት! ገደላት! ይላል ማንደፍሮ ሁሉንም ከቁብ አይቆጥረውም፡፡ የሽዋዬን እጅ ጥምዝዝ አደረገና ወገቧን
ወደ ላይ አዙሮ በክርኑ ሲደስቃት «ኣኣኣ ………» አለችና መሬት ላይ ተዘረጋች።
ከዚያ በኋላ ግን አልነሳ አለችው ታግላ አሸንፋው አይደለም ከመድከሟ የተነሳ ሰውነቷ ስለተዝለፈለፈ ክብደቷ ጨመረበት፡፡ የእልሁን ያህል ወለል ላይ የተጋደመ ፊቷን በጫማው ረግጦ ድፍጥጥ ካደረጋት በኋላ እዚያው እንደተዘረረች ትቷት ወደ በር አመራ።......

💫ይቀጥላል💫
👍10
. . . #አዜሙ_ዘፈኑ . . .

ዘፈን ነው መፍትሔ? . . .
በተቃርኖ ስሌት ሲኾን ሱሪ ባ'ንገት
ዳቦ የበላና . . .
ቆሎ የሚናፍቅ ሲወድቅ በድንገት
በድንገቴ ሐሳብ የድንገቴ ኹነት
የዳቦ እሥረኛ ቆሎ ዕላሚ ኑረት !
መሠረት የሌለው ቤቱ ዐጥር አልባ ፣
በገል ምንነቱ . . .
ማዕበል ተማምኖ የሚዋዥቅ ጀልባ፡፡

የ'ንእሜቴ ጎጆ . .
እንዲኽ ባ'ንድ ጊዜ ገብስ ጠፋ ሲሉ
የ'ነማሞ ፍቅር መፍረስ ነው ዐመሉ።
በጥሬ ሕይወቱ . .
ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ፣ ዳቦ እየናፈቀ
ከሥጋ መደብ ላይ በሆዱ ወደቀ
ከግብሩ ሲራራቅ ዘፈኑ ደመቀ።

‹‹ማሞና ማሚቱ ገዙ ዳቦ ቆሎ
ሮጠው ወደቁ ተነሡ በቶሎ!››

በየወደቁበት እየተዋወቁ
በየቦረቁበት እየተዋደቁ
በየዘገኑበት እየተሣለቁ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ .
ከግዙፉ ማሳ መደቡ ተለቀ ፤
ዳቦቆሎ ኾኖ . . .
የጥንዶች ቅኔ በዘፈን ዐለቀ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
4👍2🔥1
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ከስብሰባው እንደወጣች የክተት አዋጅ ጃን ተከል ላይ በሊጋባው አማካኝነት አስነገረች። ጐንደር አካባቢ ያለው ሠራዊት በአጣዳፊ እንዲሰለፍ አደረገች። ከሰዐት በኋላ፣ ጐንደር ያለ ሠራዊት ተሰበሰበ። ኩርዓት ሥርዐቱ መጥቶ ሠራዊቱ ለዘውዱ ሲል መሐላ እንዲገባ ጠየቀች። ሠራዊቱም፣ “አብረን ባንቆም፣ አብረን ባንታገል፣ እዝጊሃር
ይደምስሰን፤ ኸቴጌይቱና ኸንጉሡ በረከት አያሳትፈን” እያለ ማለ።

ምንትዋብ፣ ምግብ በተፋጠነ ሁኔታ ከቤተመንግሥት ቀህ በር
ለተሰበሰበው ሠራዊት እንዲታደል አደረገች። በቤተመንግሥቱ ዙርያ
ያሉት የዋርካ ቅርንጫፎች ተቆረጡ። የገባም እንዳይወጣ የወጣም እንዳይገባ አስራ ሁለቱም የቤተመንግሥት በሮች ተዘጉ።

በሁሉም በሮች መኳንንት ሠራዊት ይዘው እንዲቆሙ አስደረገች።
በተለይም ደግሞ ለጠላት መግቢያ ይሆናሉ ብላ በገመተቻቸው በሮች ላይ ጀግና የምትላቸውን መኳንንትና የጦር አበጋዞች አሰለፈች። የጦር
አበጋዞቹም ከቋራ፣ ከወገራ፣ ከከምከምና ከቃሮዳ በየቀኑ የሚገባውን ሠራዊት በሁሉም በሮች እንዲያስቆሙ አደረገች።
ልጇን ይዛ ከባለሟሎች ጋር በተዘክሮ በር ስትቆም፣ ታቦታትም
ከእነሱ ጎን ቆሙ። በጀግንነታቸውና በብልህነታቸው የተመሰገኑት ጦረኞች የዮልያና ልጅ ደጃዝማች አርከሌድስ፣ ብላቴን ጌታ ኤፍሬም፣
ፊታውራሪ ጎለም የመሳሰሉት ከጎኗ ተሰለፉ። ደጃዝማች ወልደልዑል ለውጊያ እንዲመቹ በየበሮቹ ላይ መስኮት መውጣት አለበት ብሎ በማሳሰቡ በሁሉም በሮች መስኮቶች ተከፈቱ።

የወህኒ ጠባቂው ቄርሎስ ከእነተንሴ ማሞ ጋር ተዋውሎና ለእነምንትዋብ የገባውን መሐላ ክዶ “ኢያሱ ሙቷል። መኳንንት ተመካክረው ሕዝቅያስ
ወረኛን አምጣ ተብያለሁ” ብሎ፣ ሕዝቅያስ ወረኛ የተባለውን የነጋሢ
ወገን ከወህኒ አውጥቶ፣ ለእነተንሴ ማሞ መስጠቱን ምንትዋብ ሰማች።ተንሴ ማሞ ሕዝቅያስን ይዞና በርካታ ጦር አስከትሎ በፍጥነት ጐንደር
መድረሱና ሠራዊቱ ቀሀ ወንዝ አጠገብ የጥምቀተ ባሕር ግቢ ውስጥ የመስፈሩ ዜና ደረሳት።

በቅርቡ ተሾመው የነበሩትና አፄ በካፋ በሞቱ ጊዜ ምንትዋብ
ለምክክር የጠራቻቸው እንደ እነቢትወደድ ላፍቶና ባሻ ኤልያስ
የመሳሰሉ መኳንንት ከተንሴ ማሞ ጋር ወገኑ። ምንትዋብ ስትሰማ
አዘነች። ወልደልዑል፣ “ሲሾሙና ሲሸለሙ፣ ጉልት ሲጎለቱ፣ ርስት
ሲተከሉ፣ ባረቄና በጠጅ ጉሮሯቸውን ሲያጥቡ የከረሙ ሁሉ ጊዜ አይተው መክዳታቸው አይቀርም” ያለውን አስታወሰች።

ትምህርት ተማረች።

የቀድሞው መኰንን ተንሴ ማሞ ጃን ተከል ወጥቶ፣ “ሕዝቅያስ
ነግሣል” ብሎ አሳወጀ። ሕዝቡ፣ መኳንንትና ወይዛዝርት ሳይቀሩ ከፍራቻ የተነሳ ለዐዲሱ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እየወጡ ሰገዱ። ምንትዋብ ስትሰማ ወንድሟ ወልደልዑል፣ “ሰዉም ቢሆን ጦር ሲያነሱበት ኃይለኛው ጋር
ነው ሚወግን። ስለሚፈራ ለሱ ይነጠፋል” ያላት ትዝ አላትና ገረማት።
ካህናቱም ዐዲሱን ንጉሥ በማሕሌት ተቀበሉ።
ሠራዊቱንም ተከትለው እነምንትዋብ ባሉበት በተዘክሮ በር መጡ። ጦሩን አደራጅቶ
በተጠንቀቅ ይጠብቅ የነበረው ወልደልዑል የመጣውን ጦር በውጊያ አሸነፈ። በሌሎች በሮችም እንደዚሁ በተደረገው ውጊያ የምንትዋብ ጦር አሸነፈ።

እነተንሴ ማሞ ግን የበለጠ እየተጠናከሩ መጡ። በየበሩ እየተመለሱ ውጊያውን አፋፋሙት። በተዘክሮና በአደናግር በሮች በተለይ ውጊያ ተጧጧፈ። ደጃዝማች አርከሌድስ በሚዋጋበት በር ስለተሸነፈ፣ ዐማጽያን በሩን ሰብረው ገቡ። ያገኙትን መዘበሩ። ወርቅ ሰቀላን፣ አደናግርን፣ ርግብና ዙፋን ቤቶችን አቃጠሉ። አረቄና ጠላ እየጠጡ ተሳክረው በየቦታው ወድቀው ተሸነፉና፣ ከግቢ ተባረሩ።

ከውጭ ሴቶች ከማጀት ወጥተው እነተንሴ ማሞን ወግነው ለውጊያ
ታጠቁ። ወንዶቹንም በዜማና በፉከራ አነሳሱ። አዝማሪዎችም

አንተ ሰው

አንተ ሰው

ግንቡን ጣሰው፣ እያሉ የእነተንሴ ማሞን ሠራዊት አበረታቱ።
ለጊዜውም ቢሆን የጦርነቱ ዕጣና አቅጣጫ ወዴት እንደሚያዘነብል
ለማወቅ አስቸገረ።

የተንሴ ማሞ ሠራዊት እነምንትዋብን ለመግደል ተዘክሮ በርን ሰብሮ ሲገባ፣ የእነምንትዋብ ሠራዊት ሲሸበር ወልደልዑል ተበሳጨ። “የት ትሸሻለህ? ባለህበት ቁም” አላቸው፣ መሬቱን በሌባ ጣቱ እየጠቆመ።
ወደጎን፣ ወደፊት፣ ወደኋላ እየተንጎራደደ፣ እጁን እያወናጨፈ፣ “ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር ይሁንብኝ። አንቺ ኸእግሬ ስር ኻልሸሸሽ እኔ አልሸሽም” አለ፣ መሬቱን እያየ። ፊት ለፊት፣ ጠመንጃ ለጠመንጃ፤
ሠይፍ ለሠይፍ፣ ጦር ለጦር፣ ጋሻ ለጋሻ ጠላቶቹን ገጠመ።
ተዘክሮ በር ድብልቅልቁ ወጣ። የስቃይ ጩኸት በቤተመንግሥት
ዙርያ አስተጋባ። ክፉኛ የቆሰለ ጓደኛውን፣ ወንድሙንና አጋሩን
ትከሻው ላይ አንጠልጥሎ ሊሸሽ ሲሞክር ከኋላው በጦር ሲወጋ ወይንም ሠይፍ ሲሻጥበት ከተሸከመው ጋር አብሮ ሲወድቅ፣ አካባቢው ደም ለበሰ፤ ሬሳ በሬሳ ሆነ፤ ቀውጢ ሆነ።

የሰው ልጅ ጭካኔ፣ በውስጡ ያለ ያልተገራ ፍጥረቱ ይፋ ወጣ ::

በጩቤ የተወጋው፣ በሠይፍ እጁ ወይ እግሩ የተጎመደው እጁን ወደ
ሰማይ ሰቅሎ “ድረሱልኝ!” “አድኑኝ!” “ልጅን ዐደራ! “ምሽቴን ዕደራ!”
“እናቴን ዐደራ” “ውሃ!” “አምላኬ ነፍሴን ተቀበላት!” ሲል ተማጸነ።

መሬት ላይ ወድቆ ነፍስያ የያዘውን ሁሉ ሞት እየዞረ ጎበኘ ::

በሁለቱም ወገን ብዙ ሰው አለቀ። ወልደልዑል፣ ተዘክሮን ሰብሮ
ለገባው የጠላት ጦር ክንዱን አሳየ፤ አሸነፈ። ነፍሱ የተረፈች የጠላት ጦር ፈረጠጠ። አፄ በካፋ የተከሉትን ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ግን አቃጠለ። ሌሎችን ቦታዎችንም እንዲሁ።

ጐንደር ይበልጡንም በማታ ጋየች፤ ቤቶች ተቃጠሉ። ንብረትና
ከብቶች ተዘረፉ፤ ሴቶች ተደፈሩ። እነተንሴ ማሞ ቀሀ ወንዝ አካባቢን
በመያዛቸው ውሃ ጠፋ። ጐንደር ለውሃ ጥምና ለሰቆቃ ተጋለጠች።
ሰዉ “ውሃ” እያለ ጮኸ። ሰዉም እንስሳውም እጁን ለሞት ሰጠ።
በቤተመንግሥቱ በሮች እንደገና ውጊያ አየለ። ብዙ ሰው አለቀ፤ ሬሳ
በየመንገዱ ወደቀ፤ የወደቀ ቁስለኛ የሚያነሳው አጣ። ከቤተመንግሥት ውጭ ያለውን የእህል ጉድጓድ የተንሴ ማሞ ጦር በመያዙ፣ ግቢው ውስጥ የምግብ እጥረት ተፈጠረ።

ጐንደር ፍዳዋን ኣየች።

እነተንሴ ማሞ አቡኑን፣ ዕጨጌውንና ካህናቱን ሰብስበው፣ “እቴጌንና ንጉሡን አውግዙልን፣ ኮተሊክ ቄሶች መጥተው ቤተመንግሥት ውስጥ
ኸንጉሡና ኸቴጌይቱ ጋር ተዘግቶባቸዋል” አሏቸው።

እነሱም፣ “ለቴጌይቱና ለንጉሡ እንጨት የሰበረ፣ ውሃ የቀዳ፣ የታዘዘ ሁሉ ቃለ ሐዋርያት ይሁንበት። ከንጉሡ ጎን ሁነህ ሕዝቅያስን የወጋህ ሁሉ ገዝተንሃል” ሲሉ ገዘቱ።
ሊቃውንቱ ግን ተቃወሙ። “እኼ ግዝት የሕገ ወጦች ግዝት ነው።
ወፈ ገዝት ነው” ብለው አወገዙ። ምንትዋብ ስትሰማ “የሆዳሞች ግዝት” አለችው።

የጃዊ አዛዥ ሆኖ ተሾሞ የነበረው ሻለቃ ወረኛና የሜጫው አዛዥ
ጊዮርጊስም ዘንድ “ተከበናል ፍጠኑ” ስትል መልዕክት ላከች። ተንሴ ማሞ ይህን ሲሰማ አፍዞ አደንግዞ ያስቀረው ዘንድ ሻለቃ ወረኛ ላይ አስማተኛ ላከበት። ወረኛ የመጣውን አስማተኛና ዐጃቢዎቹን በጦር አለችው።
ወግቶ ገደላቸው።

ተንሴ ማሞ ዓላማው እንዳልተሳካለት ሲሰማ ተበሳጭቶ ለወረኛ፣ እነምንትዋብ ሙተዋል። ሕዝቅያስ ነግዟል። በዚያው ባለህበት ሹመትህን አጥንተናል፤ አትምጣ። ኸጊዜው ሁን” ሲል ላከበት።

ሻለቃ ወረኛና አዛዥ ጊዮርጊስ ግን የጃዊና የሜጫን ቀስተኛ፣ ፈረሰኛ፣
ነፍጠኛ፣ እግረኛና ወንጭፈኛ ሠራዊት ይዘው ፈጥነው ጐንደር ገቡ።የተንሴ ማሞን ጦር ከበቡ። የእነምንትዋብ ጦር ሲያይል አቡኑ፣ “ስለ ንጉሡ ብላችሁ ብትሞቱ የሰማዕታት ክብር ታገኛላችሁ” ብለው ሰበኩ።
👍14🔥2
በመጨረሻው ቀን ውጊያው ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ተፋፋመ።በሁለቱም ወገን ብዙ ነፍስ ወደቀ። ታህሳስ የተጀመረው ውጊያ ከሁለት ሳምንት በኋላ፣ ጥር ውስጥ እነተንሴ ማሞ የድል አቅጣጫ ወደ እነምንትዋብ ማዘንበሉን ሲያረጋግጡ፣ ሕዝቅያስን ይዘው ሊሸሹ ሞከሩ።
እነደጃዝማች ወረኛ ግን ሕዝቅያስን አሳደው ጀርባውን ወግተውና አስረውት፣ ነጋሪት እየጎሰሙ፣ መለከት እየነፉ፣ ሰንደቅ እያውለበለቡ
ጐንደር ይዘውት ገቡ።

ተንሴ ማሞና ግብረ አበሮቹ ድል ሆኑ።

የድሉ ዜና ለምንትዋብና ለብርሃን ሰገድ ኢያሱ ቤተመንግሥት ድረስ መጣ። የዘጠኝ ዓመቱ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ኢያሱ
“እዝጊሃር ይመስገን” አለና ጐንደሬዎች የሚወዷቸውንና ካለእሳቸው የማይሆንላቸውን አቡነ ተክለሃይማኖትን ጠርቶ፣ “እኼ ሁሉ በአቡነ ተክለሃይማኖት ነው የሆነው” አለ። ምንትዋብም ለፈጣሪዋ ምስጋና አቀረበች። ታላቅ ደስታ ሆነ። ነጋሪት ተመታ፣ እምቢልታ ተነፋ ሰንደቅ ዓላማ ተውለበለበ።

ጐንደር ዕልል አለች።

እነምንትዋብ ወደ ጃን ተከል አቀኑ። ሠራዊቱ ጎራዴውን እየወዘወዘ፣
“እኔ የኢያሱ አሽከር፣ እኔ የምንትዋብ ሎሌ” እያለ አቅራራ፤ ሸለለ፤ ፎከረ።

ሕዝቅያስ ተከሶ ለፍርድ ቀረበ። ሊቃውንቱና የጦር አዛዥ
መክረው፣ “ይሙት” ሲሉ ፈረዱበት። ምንትዋብ ግን በሕጉ መሠረት፣
“የንጉሥ ልዥ አይገደልም። እወህኒ ይመለስ” አለች።

የሕዝቧን ደም ያፈሰሰውን፣ ሰላማቸውን የሰረቀባቸውን፣ ሠርተው እንዳይበሉ ያደረጋቸውን፣ እፎይታ የነፈጋቸውንና ሲሸሽ ታድኖ የተያዘውን ተንሴ ማሞን ግን ለፍርድ አቀረበችው። ፈራጆች ከእነግብረ አበሮቹ በስቅላት እንዲቀጣ ወስኑበት።

ምንትዋብ ሁለት ጊዜ የከዷቸውን አቡነ ክርስቶዶለንና ዕጨጌውን
ደግሞ አደባባይ አቆመቻቸው። ለራሷ እንዴት ነው መስቀል ይዘው
በሁለት ቢላ ሚበሉ? አለችና ትክ ብላ ተመለከተቻቸው። እነሱንም፣
“በምን ምክኛት ነው እኛን ገዝታችሁ ኸሽፍቶች ጋር ሁናችሁ ትወጉን የነበረው? ለምንስ ነው ያወገዛችሁን? ለመሆኑ ምን አርጌያችሁ ነው?
ምን በድያችሁ ነው እሷን እሷን ስትሉ ከርማችሁ አሁን እንደዝኸ
የሆናችሁት? ኸኢያሱ ክፍል የለንም' ብላችሁ የተነሳችሁት? ዘውዱ ምን በደላችሁ?” ስትል ጠየቀቻቸው።ጽንሃህ ይዘው፣ “በሃይማኖታችሁ ይዘናችኋል ማሩነ። ያሳቱነ ዓማጽያን ናቸው። ደሞም ድሜጥሮስና ጓደኞቹ ኮተሊክ ናቸው፣ ንጉሡ
ግቢ ገብተው ተቀምጠዋል፣ ሲለነ ግዝየ በዝኸ ተቀይምነ። እናንተም
ይቅርታ አድርጉልነ። እኛም ግዝታችንን እናንሳ” ብለው ተማጸኑ፣ ግዝታቸውን ፈቱ።

ምንትዋብ ዕርቅና ምሕረትን መረጠች።በጦርነቱ ወደ ኋላ ሳይሉ የተዋጉትን መሪዎች፣ መንፈሰ ጠንካራዎቹን፣ ሃገራቸውንና ዘውዱን ለማስከበር የተዋደቁትን ጀግኖች በምስጋና
ካበቻቸው፤ ሸለመቻቸው። ሹመት፣ ጉልት፣ መሬትና ካባ ሰጠቻቸው።
ሻለቃ ወረኛም ደጃዝማች ዘዳሞት ሆነ።

ሊጋባው፣ ተንሴ ማሞን ገበያ ወስዶ ሰቀለው።

ጐንደር እንቅልፍ ተኝታ አደረች። ከጅብና ከአሞራ የተረፉትን
ራሳዎች ከመንገድ በማንሳት በወግ ቀበረች። ቀስ በቀስ ወደ ዕለት ተግባሯ ተመለሰች።
ሃገር ተረጋጋ።.....

ይቀጥላል
👍7