አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
576 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አንዳንዴ የጊዜ ማጠርና መርዘም በሰዎች የውስጥ ስሜት የሚለካ ይመስላል ለተጨነቀ ልብና መንፈስ አንዱ አመት በአስራ ቤት የሚቆጠር ሲመስል ለተደሰተ ደግሞ የአንድ ቀን ያህል አጭር ይሆናል እሱ ግን አሁንም ኡደቱን ሳያዛባ እየሄደ ነው። እየነጎደ ነው።የቀንና የለሊት ፍርርቅ መሰረት አድርጎ ሳምንቱን በሳምንት ወሩንም በወር እየተካ ተምዘገዘገ። ብሎ ብሎ አንድ አመት አለቀና ሌላው ተጋመሰ
እነሆ አስቻለው አስመራ ከሄደ ሁለት ዓመት ከሶስት ወሩ! ሔዋን ክበረ መንግስት ከሄደች እንኳ አንድ ዓመት ከአራት ወር ሞላት። ሔዋን በክብረ መንግስት ታፈሡ በልሁና መርዕድ ዲላ ውስጥ እየኖሩ ይህ ጊዜ ከአስቻለው ትዝታና ናፍቆት ጋር በተያያዘ በተመሳሳይ የስሜት አቆጣጠር
እያሰቡት በመከራና በስቃይ ነው ያሳለፉት። አዝግሞ፣ ተጎትቶና ተንፏቆ ነው እዚህ የደረሰው። አንድ ክፍለ ዘመን ያህል ርቆባቸዋል። ለመምህርት ሸዋዬ ደግሞ በሚያስገርም ሁኔታ አጅግ አጭር ነበር።
ሸዋዬ በአስቻለውና በሔዋን መለያየት ቀድሞ የነበረባት የመንፈስ ቁስልወደ መገረን ተቀይሮ ከቅናት ስቃይ እፎይ ብላለች፡፡ ዛሬ የሁለቱ ፍቅር የዕለት
ተዕለት ሃሳብና ጭንቋ አይደለምና ፀሎቷ በዚሁ እንዲቀጥል ብቻ ነው። በሰላም የህይወት አጋጣሚ ውስጥ ገብታለች። ኑሮዋ ሞቅ ደመቅ እያለ ነው፡፡ ማህበራዊ ግንኙነቷም እየተሻሻለ ነው፡፡ ነቃ ነቃ ብላለች። የመንፈስ መረጋጋትም ይታይባታል። የአሁኑ ይዞታዋ ዘለቄታ እንዲኖረው ደፋ ቀና ማለቷን ተያይዛዋለች።
ለዚህ ሁሉ ሰበቡ የእናቷ ከክብረ መንግስት መምጣትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሔዋንን ይዘው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ነበር። ያ አጋጣሚ በወቅቱ የእግር እሳት ሆኖ አንገብግቧት የነበረ ቢሆንም ለዛሬው ህይወቷ መሰረት ጥሉላት
ያለፈ በመሆኑ ግን በመልካም አጋጣሚነቱ እያስታወሰችው ትኖራለች።
የሔዋን እናት በሽዋዩ ቤት አድረው በነጋታው ወደ ሔዋን ጋ ከሄዱ በኋላ ከሸዋዬ ጋር ዳግም ሳይገናኙ ነበር ወደ ክብረ መንግስት የተመለሱት። በእርግጥ
መሄዴ ነውና ደህና ሁኚ' ሊሏት ከመሄዳቸው አንድ ቀን በፊት ወደ ቤቷ ጎራ ብለው ነበር፡፡ ግን አላገኟትም፡፡ ዕለቱ ባርናባስ ወየሶ በአንድ የሶሻሊስት አገር የውጭ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ሊሄድ ሞቅ ደመቅ ባለ ድግስ የሚሸኝበት ቀን ነበርና ሸዋዬም የድግሱ ታዳሚ በመሆን ከድግሱ ቦታ አምሽታለች። የሔዋን እናት
ቶሎ የምትመለስ መስሏቸው ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር እያወሩና እየተጫወቱ ቢጠብቋት
ቢቆዩም እሷ ግን እስከ ምሽት ድረስ ስለቆየችባቸው መልዕክቱ በወይዘሮ ዘነቡ በኩል እንዲደርሳት አድርገው ተመልሰዋል፡፡
ሽዋዬ የእናቷን ፈጥነው ወደ ክብረ መንግስት የመመለስ ጉዳይ ፈጽሞ ያሰበችው አልነበረም፡፡ በእሷ ግምት የሚሰነሳብቱና በዚያም አጋጣሚ የእሷንና
የሑዋንን ለየብቻ የመኖር ምክንያት ዋሽታም ቢሆን ቀጥፋ እውነታውን በመሽፈን
ልታወራላቸውና ራሷን ከተጠያቂነት ለማዳን የሚያስችሉ ብዙ መንገዶችን ፈጥራ ነበር፡፡ ግን ያ ካለመሆኑም በተጨማሪ እናቷ ከታፈሠ ጋር ውለው አድረው
እንዲሁም ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር ብዙ ተጫውተው የመመለሳቸው ነገር ክፉኛ ነበር ያስደነገጣት፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የአስቻለውንና የሔዋንን ግንኙነት እንዲሁም እሷ በሁለቱ ፍቅረኛሞች ላይ የነበራትን አቋም እንዴት አድርገው ለእናቷ እንደሚገልጹላት ታውቃለችና በተፈጠረባት መጥፎ
አጋጣሚም እጅጉን ተበሳጭታም ተናድዳም ነበር፡፡
የእናቷን ወደ ክብረ መንግስት መመለስ ጉዳይ በስማችበት ወቅት የነበራት ምርጫ አንድ ብቻ ነበር። የጉዟውን ሁኔታ ታውቃለች፡፡ ዲላ ተነስተው በአለታ ወንዶ በኩል ነው የሚጓዙት። አለታ ወንዶ ሲደርሱ ከዲላ መኪና ላይ ወርደው ከአዲስ አበባ ወደ ክብረ መንግስት የሚሄደውን አውቶብስ መጠበቅ አለባቸው፡፡
በመሀል ቢያንስ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓት ያህል አለታ ወንዶ ከተማ ይቆያሉ እናም ጠዋት ከዲላ ከተማ ተነስታ አብራቸው በመጓዝ አለታ ወንዶ
እስክሚደርሰብት ጊዜና በአለታ ወንዶ ከተማ በሚያደርጉት የቆይታ ጊዜ ውስጥ በወሬ ስትተከትካቸው ለመቆየት አስባ ይህንኑ ለመፈጸም ወስና አደረች::
በማግስቱ በጠዋት ተነሳች፡፡ እናቷን መሸንገያ የሚሆን ጥቂት ገንዘብ ቋጠረች። ወደ መናኸሪያው ገሰገሰች፡፡ ከእናቷ በፊት ቀድማ ከቦታው ደረሰች::
ሔዋን ከምትኖርበት አቅጣጫ ወደ መናኸሪያው በሚያመጣው መንገድ በርቀት ስትመለከት ስድስት ሰዎች ሲወጠ ታዩዋት። እየቀረቧት ሲሄዱ ማንነታቸውን
ለየች፡፡ እናቷ፥ ታፈሡ! በልሁ! መርዕድ፤ሔዋንና ትርፌ ናቸው፡፡ ዘንግታው እንጂ! ለካ እናቷ
መሸኘት ነበረባቸው:: ከተሸኙም በእነዚሁ ሰዎች ነው::ተበሳጨች፡፡ ከእናቷ ጋር በአንድ መኪና የመሳፈር ዕቅዷን ሰርዛ በተከታዩ ሎንችን ልትጓዝና እናቷን በአለታ ወንዶ ልትደርስባቸው፣ እዚያ በሚያደርጉት የቆይታ ጊዜ ብቻ ልታነጋግራቸውም ወሰነች፡፡ ለጊዜው በመናኻሪያው ውስጥ እንዳትታይ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታ በመቆም የእናቷንና የሸኝዎቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረች።

አሁንም የአላሰበችው ሁኔታ ተከሰተ፡፡ እሷ የምትጠብቀው የእናቷን መሄድ ብቻ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ሔዋንም መኪና ላይ ወጥታ በመስኮት አንገትና እጇቿን
አውጥታ አፏን ቧ እድርጋ ከፍታ ምርር ብላ ስታለቅስና እጆቿን እያርገበገበች ታፈሡን ስትሰናበት አየች:: እነሱም አስከሬን ወደ ቀብር ቦታ ሸኝተው የሚመለሱ
ሀዘንተኞችን ያህል ምርር ብለው ሲያለቅሱና እጀቻቸውን እያርገበገቡ ሲሰናበቷት አየች።
«እንዴ! እሷም ልትሄድ!» አለች ሽዋዬ ለብቻዋ እየተነጋገረች። ገረማትም ደነቃትም:: ግን ለዕለቱ እቅዷ ምንም ዓይነት እንቅፋት እንደማይፈጥርባት ገመተች፣ እሷ ለእናቷ ስለሆነ ነገር ብታወራ በትዝብት ታዳምጥ እንደሆነ እንጂ
ሔዋን ደፍራ ክርክር እንደማትገጥማት ታውቃታለችና።
እነ ሔዋንና እናቷ በአለታ ወንዶ በኩል በሚሄደው አውቶብስ ተሳፍረው ከሄዱና ሽኝዎቻቸውም ከመናኸሪያው ወጥተው ወደየአቅጣጫቸው ከተበታተኑ በኋላ ሸዋዬ በቀጣይ ወደ አለታ ወንዶ የሚሄደውን መኪና ፍለጋ ጀመረች:: በእርግጥም
አንድ የመኪና ላይ ሰራተኛ የአንዲት አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በር
ከፍቶ «ወንዶ! ወንዶ! አለታ ወንዶ!» የሚል ጥሪ አሰማ። ሽዋዬ ወደ መኪናዋ ሮጣ
በመግባት የጋቢና ወንበር ይዛ ቁጭ አለች፡፡
ከአንድ ሠዓት አለፍ አለ፡፡ ያቺ መኪና ግን ቶሎ አልሞላ አለች፡፡ በዚያው ልክ ሸዋዬ ተበሳጨች ቸኩላ ጋቢና ወስጥ ቁጭ ብላ ፊትለፊት ስትመለከት በርካታ መንገደኛ ወደ መናኸሪያው ሲገባ ታያለኝ። ግን እሷ ወዴለችባት መኪና የሚገባው ሰው ከቁጥር አይገባም፡፡ ረዳቱ አሁንም "ወንዶ ወንዶ" እያለ መንገደኛ ይጠራል
ሸዋዬ ወደ ኋላ ዞር ብላ ስታይ ግን በርካታ ወንበሮች ክፍት ሆነው
ትመለከታለች: በዚያው ልክ ቀልቧ እየቆመ ትቁነጠነጥ ጀመር፡፡
ከመኪናዋ ወንበሮች ግማሽ ያህሉ በሰው ከተያዙ በኋላ ሹፌሩ ወደ መኪናዋ ገብቶ ሞተር አስነሳ፡፡ ነገር ግን ሞቅ ሞቅ ከአደረገ በኃላ ተመልሶ ሊወርድ ሲዘጋጅ ሸዋዬ አየችውና «በእናትህ ሾፌር መንገድ ላይ ትሞላለህ፥ እንሂድ» አለችው፡፡
👍6👏1
እንሄዳለን፡፡ አላትና ከመኪናው ላይ ወረደ:: ቁልፎቹን እያቅጨለጨለ
በመኪናዋ አካባቢ ይንጎራደድ ጀመር።
ሾፌሩ ጥቁርና ጠብሰቅ ያለ ሰውነት ያለው ነው: ቁመቱዎ ዘለግ ያለና ዕድሜዉ በሰላሳዎቹ አጋማሽ ላይ የሚገኝ አፍላ ጎልማሳ ነዉ:: የሰማያዊ ቀለም እጅጌ ጉርድ ሸሚዝ ለብሶ ጨፈቃ የሚያህል እጁ ሲታይ ጡንቻው ያስፈራራል። አልፎ አልፎ ከመኪና ላይ ሰራተኞች ጋር እየተላፋ በዚያ ክንዱ ጥምዝዝ እድርጎ ሲያስጮሀቸው እያየች ሸዋዬ በልሁ ተገኔ ትዝ ይላታል፤ ከመልካቸው በቀር የሰውነታቸው አቋም ተመሳሳይ ነውና።
ሰዓቱ ወደ አንድ ተኩል ሲጠጋ እንደ ምንም ጉዞ ተጀመረ። ያ ሠዓት ሔዋንና እናቷ ወደ አለታ ወንዶ መዳረሻቸወ ነው፡፡ ያ መንገድ ደግሞ የትራፊክ
ቁጥጥር ስለሌለበት በተለይ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ሰው በሰው ላይ እየጫኑ ሴንተርያ ተፈሪ ኬላ፣ ቀባዶ በተባሉና በሌሎችም ትንንሽ ከተሞች ሲደርሱ ተሳፋሪ
በማውጣት በማውረድ ጊዜ ያባከናሉ፡፡ አታካችና አሰልቺ መንገድ ነው፡፡ ሸዋዩ የተሳፈረችባት መኪናም ይህን ድርጊት ዘልላው አላለፈችም፡፡ ትቆም ትገተር ጀመር። ሽዋዬ በወጪ ወራጅ ጭቅጭቅ ጊዜው እያለፈባት ስትበሽቅ ስትናደድ ልቧ
ሊፈነዳ ደርሶ እያለለክች ልክ ከጠዋቱ አራት ሠዓት አካባቢ በአለታ ወንዶ መናኸሪያ ውስጥ ደረሰች፡፡ ወዲያው ዓይኗን በመናኸሪያው ዙሪያ ብታንከራትት
ሔዋንና እናቷ በአካባቢው የሉም። በእርግጥ ከአዲስ አበባ ወደ ክብረ መንግስት የሚሄደው አውቶብስ እዚያ መድረሻው ሰዓት ገና ነውና። በዚህ አጋጣሚ ሄዋንና
እናቷ ሻይ ቡና ለማለት ሄደው ሊሆን እንደሚችል ገምታ በመናኸሪያው አካባቢ የሚገኙትን ቡና ቤቶች በሙሉ ማሰስ ጀመረች፡፡ ነገር ግን እናቷና ሔዋን
አልታገኙም:: አሁንም እየተናደደች ፍለጋዋን ቀጠለች፡፡ ቢቸግራት እሷ በየቡና ቤቶች ስትሯሯጥ እናቷና ሔዋን በሌላ መንገድ ወደ መናኸሪያው ተመልሰው ይሆናል ብላ በማሱስ እንደገና ወደ መናኸሪያው ሮጠች:: ወደ ውስጥ ገብታ የመናህሪያውን ዙሪያ በዓይኗ ስትቃኝ በነበረችበት ወቅት ከበስተ ግራዋ በኩል የአንድ ወንድና ሴት ጭቅጭቅ ድንገት ከጆሮዋ ጥልቅ አለ፡
«አንቺ ባትዘገይብኝ ኖሮ እኮ እስካሁን ሄደን ነበር፡» በማለት ወንዱ በሴትዋ ላይ ይጮሃል።
ከአሁን በፊት ክብረ መንገስት የሚሄድ መኪና ይገኛል ብዬ እንዴት ልገምት?» አለች ሴትዮዋ::
«እንዴ! አለች ሸዋዬ እንደ መደንገጥ ብላ፡፡ ወደ ሰውየው ጠጋ በማለት «በቅርቡ ወደ ክብረ መንግስት የሄደ መኪና ነበር እንዴ?» ስትል ጠየቀችው።
«ሰው አጥቶ ሲጮህ ቆይቶ ከዲላ የመጣው አውቶብስ የሰው መአት
ሲዘረግፋለተ ግጥግጥ አድርጎ ጭኖ ሄደ፡፡» አላት ሰውየው እግረ መንገዱን ቁጭቱን ቀድሞ ለሚያነጋግራት ሴትዮ በመግለጽ ዓይነት፡፡
«ኣ» አለኝ ሸዋዬ ድንግጥ ብላ።
«ሙች ስልሽ!» ሰውየው አሁንም::
ሸዋዬ አንጀቷ ቁርጥ አለ። ከንፈሯን ንክስ አድርጋ በቁጭት ስሜት ራሷን ወዘወዘች በቃ! እናቷ ወይዘሮ ዘነቡና ታፈሡ የነገሯቸውን ሁሉ ተሸክመው ክብረ መንግስት ገብተዋል:: የብስጭቷ ብዛት ወገቧን አርገድግዶ ከአጥር ጥግ ድንጋይ ላይ አስቀመጣት። ራሷን በሁለት እጆቿ በመያዝ ወደ መሬት አቀረቀረች። ሀሳብ አወጣች አወረደች። ግን ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡
በዚያው ቦታ ላይ እንደተቀመጠች ሳታውቀው ሰዓቱ ሂዶ ኖሯል፡፡ ወደ
ስድስት ሰዓት አካባቢ ከአዲስ አበባ ወደ ክብረ መንግስት የሚሄደው አውቶብስ ደረሰና ጡሩንባውን እየነፋ ወደ መናኸሪያ'ው ገባ፡፡ እንደው ለምናልባቱ ብላ ወደ
መናኸሪያው በር ብትመለከትም ሔዋንና እናቷ ብቅ አላሉም፡፡ አውቶብሱ የሚያወርደውን አውርዶ የሚጭነውን ጭኖ ወደ ክበረ መንግስት ጉዞውን ቀጠሉ፡፡
የሸዋዬ ተስፋም ተሟጠጠ። ወደ ቤቷ በመመለስ በቀር ምርጫ አልነበራትም?
ወደ ዲላ ስለ መመለሷ ማሰብ ስትጀምር ቀደም ሲል ይታያት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ትኩረት ወዳልሰጠችው ከቅጣጫ አተኮረች፡፡ ያቺ ከዲላ ይዛት
የመጣች ሊዮንችን እንደገና ወደ ዲላ ስትጭን ተመለከተች፡፡ ጠጋ ብላ ስትመለከት በመኪናዋ ውስጥ ሰው በሰው ላይ ተነባብሯል፡፡ የቆመው የተቀመጠው ተሳፋሪ አይተናነስም፡፡ ጨነቃት፡፡ ድንገት ወደ መናኸሪያው በር ዞር ብላ ስትመለከት ያን ወጠምሻ ሾፌር አየችው፡፡ አሁንም ቁልፎቹን እያቅጨለጨለ ከውጭ ወደ ውስጥ ይገባል። መኪናዋ አጠገብ እስከሚደርስ ጠበቀችና፡-
«የኔ ወንድም!» ስትል ጠራችው እንደ መሽኮርመም እያለች::
«አቤት!» እላት በጥቁር ፊቱ ላይ ወተት መስለው የሚታዩ ጥርሶቹን ፈገግ እያረገ፡፡
«መኪናህ በጣም ሞልቷል። እንዴት ይሻለኛል?» አለችው በመለማመጥ ዓይነት፡፡

«የመጣሽበት ጉዳይ አለቀ እንዴ?››
«ጨርሼ ነበር፡፡ መመለሻው ግን ጨነቀኝ::»
«እንደ ምንም ትሄጃለሻ!» አለና ሾፌሩ ወደ ረዳቱ ፊቱን መለስ አድርጎ
«እንዴት ነህ፣ ሞላ?» ሲል ረዳቱን ጠየቀው፡፡
«እየሞላ ነው::» አለው ረዳቱ የሚገባ ከተገኘ አሁንም ለመጫን የሚፈልግ መሆኑን በሚያመለክት አነጋገር፡፡
ሾፌሩ ሸዋዩንም ረዳቱንም ተውት አድርጎ ወደ ሌሉች ሰዎች ጠጋ ብሎ ያወራ ጀመር፡፡ ረዳቱ «ዲሳ ዲላ!» ማለቱን ቀጠለ፡፡ ሸዋዬ ግን ምናልባት ሾፌሩ ወንበር ፈልጎ ያስቀምጠኝ ይሆናል በማለት ቆማ ትጠባበቀው ጀመር። ከትንሽ
ቆይታ በኋላ ረዳቱ ሾፌሩን ተጣራ፡፡ ‹‹ማንዴ! ማንዴ! ግባና እንሂድ!» አለ፡፡
ሾፌሩ የረዳቱን ጥሪ በመቀበል ያወራቸው የነበሩትን ሰዎች ተሰናብቶ በመግቢያው በር በኩል ኸደ መኪናው ሲያመራ ሸዋዬ ከተል አለችና «ማንዴ እንዴት አረክልኝ ታድያ?» ስትል እንደ ማፈር እያለች ጠየቀችው ፡ የሾፌሩን ስም ከረዳቱ ጥሪ የወሰደችው ነው።
« አልገባሽም እንዴ?" አላት ሾፌሩ የራሱን መግቢያ በር ከፍቶ በእጁ ያዝ እያደረገ።
"መግቢያው ጨነቀኝ::»
ሾፌሩ ከመኪናወ ላይ ወጥቶ ከተቀመጠ በኋላ ወደ ኃላ ዞሮ ሲመስካት እውነትም መኪናው ሞልቶ ተጨናንቋል። መተንፈሻ የለም፡፡ ግን አንድ ነገር ትዝ አለው ሞተሩ ላይ ተቀምጠው ወደ ነበሩት ስዎች እየተመለከተ «እናንተ ተነሱ ሞተሩ ላይ መቀመጥ ክልከል ነው ወደ ኋላ! ወደ ኃላ ዳይ ዳይ» አላቸው፡፡
ሾፌሩ መሪ ይዞ የሚናገረው ሁሉ በተለይ በተቸገረ ተስፋሪ ዘንድ ተቀባይነት አለውና ሰዎቹ እያጉተመተሙ ቢሆን ተነሱ፡፡ ወዴኋላ እየተጋፋ ተሸጋሽገው
መቆማቸውን ከአረጋገጠ በኋላ ሾፈሩ ከመኪና ወርዶ ሸዋዬ
እንድትገባና ሞተር ላይ እንድትቀመጥ አደረጋት። ሸዋዬ ገባችና ፊቷን ወደ ሾፈሩ
አድርጋ እግሮቿን በማርሹ አጠገብ ኮርምታ በመቀመጥ ጉዞ ተጀመረ።
አስቸገርህ አይደል!» አለችው ሽዋዬ ሾፌሩ ማርሽ ሊቀይር ሲል እግሯ አወላክፎት የነበረ አጋጣሚን መነሻ በማድረግ።
«ምን ላድርግ፣ በሴት ልጅ አይጨክንም ብዬ ነዋ» አላት ሾፈሩ ቀና ብሎ በፈገግታ እያያት።
«ሁሉም እንዳተ በሆነ» አለች ሽዋዩ በመኪናው የፊት መስታወት ወዴፈት እያየችና ፈገግ እያለች፡፡ በዕለቱ ነጣ ያለ ሰማያዊ ኮትና ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች:: ከጉልበቷ ጀምሮ እስክ ጡቷ ድረስ ሞላ ያለ ሰውነቷ በቀሚሷ ተወጥሮ ትርፁ
ይታያል። በዚያ ላይ አፍንጫ የሚሰነፍጥ ልዩ መዓዛ ያለው ሽቶ ተቀብታለች።
👍5
« እንዴት?» አላት ሾፌሩ ሳቅ ብሎ አየት እያደረጋት።
«ለሴትየዋ ልጅ ማዘንህ ነዋ!»
«ግን እኮ እናንተ ሴቶች ለወንድ ልጅ አታዝነም፡፡»
«የሚታዘንለትም አለ።»
«ምን አይነት ወንድ ሲሆን ነው የሚታዘንለት?» ሲል እየሳቀ ጠየቃት።
«ልክ እንደ አንተ ተባባሪ ሲሆን ነዋ!» አለችና ሽዋዬ ኪ.ኪ.ኪ. ኪ ብላ ሳቀች።
«ኦ ወደሽኛል!»
«መውደድ ሲሉህ ታዲያ..»
«በቃ ገብቶኛል፣ ውድድድ! አደረኩህ ማለት ነው በማለት ለራሱ ስቆ ሸዋዬንም አሳቃት።
«ተጫዋች ቢጤ ሳትሆን አትቀርም!»
«በተለይ አጫዋች ካገኘሁ ማ»
«እ!»
«ማጫወትም እችልበታለሁ፡፡»
ሁለቱም ሳቁ። ፈገግታቸው ከፊታቸው ላይ ሳይጠፋ ለአፍታ ያህል ዝም ዝም ካሉ በኋላ ሾፌሩ ቀጠለ፡፡ «ለምን መጥተሽ ነው?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ሰዎች ፈልጌ ነበር፡፡ ግን እጥቻቸው ተመለስኩ፡፡ ሥራዬን ትቼ በከንቱ ለፋሁ።» አለችና ያ ቁጭቷ እንደገና ትዝ ብሏት ሳታውቀው ከንፈሯን ነከሰች፡፡
«የት ነው የምትሰሪው»
«መምህር ነኝ፡፡»
«ኦ! ምሁር ነሻ!»
«መባሌ ይሆን?ኪ ኪ ኪ ኪ!»
«ከአስተማሪ በሳይ ምሁር አለ እንዴ» አለና «እኛ ባለመማራችን አይደል የሰው መኪና ስንገፋ የምንኖረው አላት።
«ታዲያ የምትወፍሩት እናንተ» አለችው ሸዋዬ ያን መሪ የያዘ ጠብደል እጁን እየተመለከተች፡፡
«ሰርቀን ስለምንበላ እኮ ነው፡፡ አየሽ! እንዲህ እንደ አሁኑ ትርፍ ዕው ስንጭን ቦጨቅ የምናደርጋትን ገንዘብ አንሳሳላትም፤ ወዲያው ጉርስ ነው።አለበለዚያማ ይነቃብን ይመስለናል።»
«ለሚስቶቻችሁ ብትሰጧቸው እኮ…" ብላ ሳትጨርስ ሾፌሩ ቀደማት።
«ልብ ያላት ሴት የለችማ!»
«ባለቤትህ ገንዘብ መያዝ አትችልም'ን
«እሷማ ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን እሷም አብራ ጠፋች፡፡»
«ማለት»
«ነገሩ ብዘ ነው የኔ እህት! አሁን አወርቼ አልጨርሰውም፡» አላትና
ሾፌሩ ለአፍታ ያህል ወደ ትካዜ ውስጥ ገባ። ሾፌሩ ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር፡፡ በስራው ፀባይ ከቦታ ወደ ቦታ አዘውትሮ ሲዘዋዋር በመሀል ሚስቱ ከሌላ
ወንድ ጋር ስትማግጥ ቆይታ የኋላ ኋሳ እንዲያውም ጭራሽ ከድታው ተሰውራዐትታያለች:: ውላ ኣድራ ያንኑ ያማገጣትን ሰውዬ አግብታ ትኖራለች፡፡ ሾፌሩ ከዚያ ወዲህ በወንደላጤነት ብቻውን ይኖራል:: ይህን ታሪክ ለሽዋዬ ነገራትና
«አያሳዝንም?» ሲል ጠየቃት።
«በእውነት በጣም ያሳዝናል!»
«ይኸውልሽ ያልተማረ ሰው ትርፉ ይኸ ብቻ ነው::»
«መማር ብቻ አይምሰልህ፤ ልብም ይጠይቃል::»
«ጎሽ!» በማለት ሾፌሩ ሸዋዬን አደነቀና «አየሽ፤ ይህን እንኳ ማለትሽ የመማርሽ ውጤት ነው::» አላት ፈገግ ብሎ አየት እያረጋት::
«ሀሳቤን ወደድከው?»
«በእውነት አሁንስ አንቺንም ወደድኩሽ»
«ተቀደድና!»
«ነገሩ ሞቶ»
በራሳቸው ወሬና ንግግር ሁለቱም ተሳሳቁና ለአፍታ ያህል በዝምታ ተጓዙ::ቆየት ብሎ ግን ሾፌሩ ወሬውን ቀጠለ።
«የኔስ ታሪክ ተዘከዘከ ያንቺስ?» ሲል ጠየቃት ሽዋዬን በማሽኮርመም ዓይነት ፈገግ ብሎ በቅንድቡ ሥር አየት እያረጋት፡፡
«ምን ይመስልሃል?» አለችው በመሽኮርመም ዓይነት አየት እያደረገችው::
«ልጆች ያሉሽ ይመስለኛል።»
ሽዋዬ አንገቷን በመነቅነቅ፡ «የለኝም የሚል መልስ ስጠችው::
«እንዴ! እስከ አሁን ምን ትጠብቂያለሽ?»
«ባል » አለችና ሽዋዬ ኪ ኪ ኪ ኪ ብላ ለራሷ ሳቀች።
«እስካአሁን አላገባሽም?
”ዘገየሁ? ኪ ኪ ኪ ኪ ኪ»
«ለነገሩ ይደርሳል፡፡» አለና «ምናልባት ዛሬ አብሮ ያዋለን ጌታ አብሮ ሊያሳድረን ይሆን እንዴ?» ብሎ ፈገግ እያለ ፊትለፊት ያያት ጀመር።
«ጭራሽ! ኪ ኪ ኪ ኪ ኪ»
«ማን ያውቃል ቢያጋባንስ»
«ሾፌርና አስተማሪ ተጋቡ ብሎ የዓለም ጋዜጠኛ ሁሉ ይስብሰባ ካ ካ ካ ካ ካ»
ሾፌሩና ሸዋዬ እንዲህና እንዲያ እየተባባሉ ሲጫወቱ ሳያውቁት ዲላ መዳረሻ ከሆነችው አጎራባች ላይ ደረሱ መኪናዋ በመንገድ ላይ ባሉ የተለያዩ ትንንሽ ከተሞች እየቆመች ተሳፋሪ ስትጭን ስታወርድ ቆይታለች። ሾፌሩ ግን
ቁም ሲሉት መቆምን ሂድ የባሰ መሄድ እንጂ ስአት እንደወረደ ስንት እንደተሳፈረ አያስታውስም፡፡ ቀልቡ ሁሉ ሸዋዩና ከጫዋታቸው ጋር ብቻ ነበር።
«እንዴ !ዲላ ደረስን እኮ አንቺ» አላት ዲሳ ከተማን ቁልቁል እየተመለከተ።
«አልታወቀህም አይደል?
«ኧረ ስም ሳንለዋወጥ እንዳንለያይ!» አለና ዞር ብሎ በፈገግታ እያያት እኔ ማንደፍሮ ጌጠነህ እባላለሁ፡፡ ሲያቆላምጠኝ ደግሞ ማንዴ! ግንድዬ ማንድያዬ
አለና «አንቺስ?» ሲል ጠየቃት።
«ስምህ አልበዛም? ኪ ኪ ኪ…»
«ማን ያውቃል ገና አንቺ ትጨምሪልኝ ይሆናል።»
«በዚሁ ላይ!»
«በይ ንገሪኛ!»
ሽዋዬ ትንሽ ስትሽኮረመሃ' ቆየችና ስሟን በአንድ ጥቅል እድርጋ ሳይሆን እየቆራረጠችና እንደ ዜማ መነሻ የመኪናውን ስፖንዳ በእግሯ እየመታች፡-
«መምህርት-ሽዋዬ-ተስፋዬ-- እባላለሁ» አለችው::
«እኔ ደሞ የሽዋ እልሻለሁ፡፡»
እንዴ አለች ሽዋዬ በሆዷ፡ ባርናባስ ወየሶም ለመጀመሪያ ጊዜ
ሲተዋወቃት በዚሁ ሁኔታና ስም አወጣጥ ነበር፡፡ በሆዷ ባርኔ፤ ማንዴን ተክተክ ልትሄድ ይሆን እንዴ? አለች፡፡ ትናንት የሽኝቱን ድግስ በልታለችና ከእንግዲህ
ባርባናስ ላልተወሰነ ጊዜ ትዝታ ሆኖ እንደሚቀር ታውቃለችና።
«ይመችሻል?» ሲል ማንደፍሮ ስለ ስም ቁልምጫ ጠየቃት፡፡
«ድሮም እጠራበት የነበረ ነው፡፡» አለችው ሳቅ እያለች፡፡
«እንግዲህ ተወርሳችኋል ብለሽ ንገሪያቸው፡፡» ብሎ ማንደፍሮ ለራሱ ስቆ መኪናዋ ከዲላ መናኸሪያ ወስጥ ገባች፡፡ በየመንገዱ ታጭቆ የነበረ ተሳፋሪ
ሁሉ መውረድ ጀመረ። ሽዋዬ ሞተር ላይ ስለነበረች መተላለፊያ ስላልነበራት መጠበቅ ነበረባትና ለአፍታ ያህል በዚያው በተቀመጠችበት ላይ ተቀምጣ ሳለች ማንደፍሮ አናገራት።
«በቃ መውረድሽ ነው?» አላት እጇን ያዝ አድርጎ።
«መኪናህ ታዲያ መኝታም አለው እንዴ? ኪ ኪ ኪ ኪ ኪ..»
«ባይኖረውም መኝታ ካለበት ቦታ ያደርሳል::»
«ኧረ ከዜ እንዳታሳድረኝ ፈራሁ
ልቀቀኝ! አለችው እየሳቀች።
«ቢያንስ አድራሻችን፡፡»
«ምን ያደርግልሀል?»
«አንቺን ፈልጌ አገኝበታለሁ፡፡
«ሌላ ጊዜ፡፡»
«ሌላው ጊዜ ሌላ ይሰራበታል፡፡ እድራሻ ግን ዛሬ ማለቅ አለበት:: አላትና ማንደፍሮ ይጠበቅባቸዋል ሲያደርጋት ሸዋዬ ተረታች።
«እሺ ስልኬን ያዘው» ማንደፍሮ
ደስ እያለው ወረቀትና እስክርብቶ ከኪሱ እያወጣ የቤት ነው
የስራ ቦታ ሲል ጠየቃት።
«የመስሪያ ቤት፡፡»
ማንደፍሮ ሽዋዬን ከመኪና አውርዶ ከሸኛት በኋላ ወዲያው ወደ ስልክ መደውያዉ ቦታ አመራ፡ ገና ሸዋዬ ከዓይኑ ሳትጠፋ በሰችው ስልክ ደውሎ
«መምህርት ሸዋዬን ፈልጌ ነበር» ብሎ ሲጠይቅ ዛሬ ስራ አልገባችም» የሚል ምላሽ ተሰጠው። የሸዋዩን አድራሻ በትክክል ማግኘቱን አረጋገጠ። ብዙ አልቆየም በዚያው ሰሞን ሸዋዬን በስልክ አግኝቶ ቀጠሮ አሲያዛት፡፡ በቀጠሮ ሠዓትና ቦታ
ተገናኙ።በሉ ጠጡ ተጫወቱ:: ማንደፍሮ የማሳረጊያ ጥያቄ ሲያቀርብ በሸዋዬ ተቃውሞ ለሌላ ቀን ተላለፈበት፡፡ ያም ቀን ደረሰ፡፡ ደግመው ተገናኙ፡፡ ሸዋዬ
ማንደፍሮን በቤቷ አስተናገደችው ደገሙ። ደጋገሙ። ሽዋዬ ማንደፍሮን ውድድ ማደፍሮም
በዚያው ልምድ!! ቋሚ መኖሪያው አዋሳ ቢሆንም ወደ ዲላ ብቅ ባለ
ቁጥር እድራሻው የሸዋዬ ቤት ሆነ፡፡ ዉል ያልያዘው ባልና ሚስትነት ተጀመረ፡፡ እነሆ ከዓመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍15
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።”

“ትሰጥሻለች። ምን ይሳናታል? አሁን ስለሱ አታስቢ።”

ሆዷ እየገፋ ሲመጣ፣ ጭንቀቷ በረታ። ሴት በመውለዷ ባትከፋም፣ ወንድ አለመውለዷ ቤተመንግሥት ውስጥ ሊኖረኝ ይችላል ብላ ያሰበችውን ቦታ የሚያሳጣት መሰላት።
ይበልጡንም ደግሞ ወህኒ
አምባ ያሉ የነገሥታት ዘሮች የሚወለደው ወንድ ቢሆን ሐዘናቸውን፣ ሴት ብትሆን ደግሞ ደስታቸውንና የበካፋን ተስፋ መጨናገፍ እያሰበች መንፈሷ ተበጠበጠ። የጐንደርን ታቦታት ሁሉ ተማጸነች። የእሷ
ቋረኝነት ያብከነከናቸው መሣፍንትና መኳንንት ደግሞ በካፋ ሲሄዱ ቋረኛ አልጋው ላይ የመውጣቱ ጉዳይ ሲያሳስባቸው፣ ሲያነጋግራቸውና ልባቸውን ሲሰቅለው እሷ የበለጠ ጭንቀት ውስጥ ገባች።
የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ የበካፋ ደጋፊ መኳንንትና ሕዝቡ ግን
በእነሱ ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈች ለመጣችው፣ ለእሷ... ለምንትዋብ ወንድ ልጅ እንድትወልድ ተመኙላት።

ለወራት ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ፣ በየቤቱና በየመንደሩ ወሬው ተጋጋለ፤ ሞኝ መቆሚያ ላይ ተሟሟቀ፤ ጃን ተከል ላይ ተፋፋመ።የጃን ተከል ደንበኞች ወደ ሞኝ መቆሚያ ተጨማሪ ወሬ ለማሳደድ አሽቆለቆሉ። የሞኝ መቆሚያዎቹ ወደ ጃን ተከል በጥድፊያ አሻቀቡ።

መጽሐፍ ገላጩና ኮከብ ቆጣሪው ገሚሱ ወንድ፣ ሌላው ሴት ነው
ሲል ተነበየ። ገበሬው በየእርሻው፣ ነጋዴው በገበያው ላይ፣ ሴቶች ወንዝ ዳር፣ ሽማግሌና ወጣት በየጎጡ እሰጥ አገባ ያዙ፤ ተወራረዱ። የንግርት
ዓይነቶች ተወሱ። የቆራጣ ገዳም እመምኔቷ፣ የወለተጴጥሮስ ትንቢት ተወራ፣ የሰማው ላልሰማው አስተላለፈ። ወሬው ጐንደርን ተሻግሮ በየግዛቱ ተናፈሰ። ቀድሞ ስለነገሥታት የተነገሩ ሌሎች ንግርቶች
ሁሉ ለማመሳከሪያነት ቀረቡ፣ ተመረመሩ፣ ተተነተኑ።
ሃገር በወሬ ታመሰች። ወንድ ነው ሲሏት ጮቤ ስትረግጥ፣ ሴት ናት
ሲሏት ስትተክዝ ከረመች።

ምንትዋብ በበኩሏ ቀናቱ ሲያዘግሙባት፣ ወራቱ እንደ ገመድ ሲጎተቱባት ቆይታ አንድ ሌሊት ምጥ ያዛት። እናቷና አያቷ የነገሥታቱ አዋላጅ የሆኑትን ሴት በፍጥነት አስመጡ። ምንትዋብ ሌሊቱን በሙሉ ስታምጥ፣ ሴቱ “ማርያም”፣ “ማርያም” ሲል፣ በካፋ በጭንቀት ቁጭ
ብድግ ሲሉ፣ ሲጸልዩ፣ ካህናት ምህላ ሲያወርዱና የቤተመንግሥት ባለሟሎች ሲንቆራጠጡ ቆይተው ንጋት ላይ የመጀመሪያው ዕልልታ ተሰማ። በሰላም የመገላገሏ ዜና በመኾኑ ለአፄው የአፍታ እፎይታ
ቢሰጣቸውም የሕጻኑን ጸታ ለመለየት ዕልልታውን መቁጠር ጀመሩ።

ዕልልታው ተደገመ፤ የበካፋ ጭንቀትም ናረ፤ ሦስተኛውና የመጨረሻው ዕልልታ ይሰማና ወሽመጤን ይቆርጠው ይኾን ወይስ ይቀጥላል? የሚለው ጭንቀት በእያንዳንዱ ዕልልታ መሃል ያለችዋን ቅጽበት ዝንተዓለም እስክትመስል ድረስ ለጠጣት። ሦስተኛው ዕልልታ
ተሰማ። እዚኸ ላይ የበካፋ የልብ ትርታ ፀጥ አለ፤ ሌላ ዕልልታ ካልተሰማ አልቦ አልጋ ወራሽ የሚለው ሥጋት ሰቅዞ ይዟቸዋል። የጠላቶቻቸውን መደሰት፣ የወዳጆቻቸውን መሳቀቅ እየቃኙ ሳለ፣ አራተኛው የዕልልታ
ድምጽ መጣ። ወንድ ልጅ! አምስተኛውን፣ ስድስተኛውንና ሰባተኛውን ዕልልታ መስማት አላስፈለጋቸውም፤ ወንድ ልጅ ተወልዶላቸዋል! ዜናውን በመላ ቤተመንግሥቱ ግቢ ውስጥ ሲያስተጋቡት፣ ግቢው
ትርምስምሱ ወጣ።

ምንትዋብ ድካም ላይ ብትሆንም ደስታዋ ወሰን አጣ፣ በጭንቀት
የተኮማተረው ግንባሯ ተፍታታ፤ ቁስቋም ማርያምን አመሰገነች።
አፄ በካፋ በጭንቀት የሙጥኝ ይዘውት የነበረውን የጸሎት
መጽሐፋቸውን አስቀምጠው ከመኝታ ክፍላቸው ወጡ።

ምንትዋብ ወዳለችበት ገሰገሱ። ምንትዋብ እስክትጸዳዳ ጠብቀው
ሲገቡ፣ እየደጋገሙ፣ “እንኳን ማርያም ማረችሽ” አሏት። እንኰዬ
ህጻኑን ኣቅፈው ሲያሳይዋቸው የደስታ እንባ ተናነቃቸው። አልጋ ወራሽ በማግኘታቸው ሩፋኤልንና ከአንገርብ ወንዝ በስቲያ ደፈጫ የተከሏትን ኪዳነ ምሕረትን አመሰገኑ፤ ውለታቸውን በወርቅ እንደሚከፍሉ ቃል ገቡ።

ቤተመንግሥቱ ውስጥ ታላቅ ፈንጠዝያ ሆነ። ወዲያው ስፍር ቁጥር የሌለው የግባት ነፍጥ ወደላይ ተተኮሰ። የአካባቢው ሰው “ወንድ ነው!
ወንድ ነው!” እያለ ጃን ተከል ግልብጥ ብሎ ወጣ። ሴቶች ዕልልታቸውን አቀለጡት። ጐንደር የምሥራቹ ደረሳት፤ ፈነደቀች። ራቅ ካሉ ቦታዎች ሳይቀር ጐንደሬዎች እየከነፉ ጃን ተከል ደረሱ።

እቴጌ ወንድ ልዥ ተገላገሉ! ሰባት ግዝየ ሲተኮስ ቆጥሬያለሁ።
ወንድ ነው። ንጉሡ አልጋ ወራሽ አገኙ!” ይላል አንዱ።

“ሦስት ቆጥሬ ሴት ትሆን? ስል ዐራት ሲደገም እንግዲያማ ሰባት
ነው ሚሆን። ወንድ ነው ብየ ስሮጥ መጣሁ” ይላል ሌላው።
የዕጣና የውርርድ አሸናፊዎች የድል ዋጋቸውን ጠየቁ።

ንግርቶች ሁሉ እንደገና ተነገሩ። የቅድስት ወለተጴጥርስ ትንቢት
ተነሣ። “የሷ ንግርት መሬት አይወድቅም” ተባለ። በየደብሩ ካህናት ደወል አሰሙ። ዘመሩ፣ አሸበሸቡ። መነኮሳት ሕልማቸውን ተለወዋጡ: ደስታ በደስታ ሆኑ።

የበካፋ የሥልጣን ተቀናቃኞች ወሬውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ ተስፋቸው እንደ እንፋሎት ተነነ። የማስመሰል ካባ የደረቡ አንጀታቸው ያረረ፣ወንድ ልጅ በመወለዱ ከልብ የተደሰቱ መኳንንት፣ ካህናትና ሊቃውንት
ከቅርብና ከሩቅ ደስታቸውን ለመግለፅ ወደ ቤተመንግሥት ጎረፉ።

ለሕጻኑም መልካም ምኞታቸውን አዥጎደጎዱ። ሕጻኑ በአያቱ፣ በአፄ ኣድያም ሰገድ ኢያሱ ስም ተጠራ። ግብር በየቀኑ ገባ። ኢያሱ፣ በወጉ መሠረት በአርባ ቀኑ ክርስትና ተነሣ።

ኢያሱ ከተወለደ በኋላ፣ የመጀመሪያው መስቀል ነው። ለአፄ በካፋ ዓመታዊ ሠራዊት ግባት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው። እንደ ጎጃምና ትግራይ ካሉ ራቅ ካሉ ግዛቶች የሚመጡ አስተዳዳሪ መኳንንት
ክረምቱ ሳይገባ ግንቦት ወር ላይ እያንዳንዳቸው ሠራዊታቸውን
ይዘው ጐንደር ሲገቡ፣ እንደ ስሜንና ቤገምድር ካሉ ቅርብ ቦታዎች የሚመጡት ደግሞ ዐዲስ ዓመትን ቤታቸው ውለው ሠራዊታቸውን ይዘው ጐንደር ገብተዋል። ቤተመንግሥት ዙርያ ለየግላቸውና ይዘውት
ለመጡት ሠራዊት ድንኳን ተተክሎላቸው እዚያው አርፈዋል።

ምንትዋብና አያቷ ስለ ሠራዊት ግባቱ አስፈላጊነት ሲነጋገሩ
አያትየው፣ ነገሥታቱ እኼን በዓል ሚያደርጉት አንድም እንግዲህ
ወታደራዊ ጉልበታቸውን ለማሳየት...” ብለው ሲጀምሩ አቋረጠቻቸው።

“ለማን ነው ሚያሳዩት?”

“ለሁሉም። እሱ ብቻ ማዶል። የመኳንንቱን ታማኝነት ለማረጋገጥም ሲሉ ነው። ሌላ ደሞ... ደንብ ሲያወጡ ወይም አዋጅ ሲነግሩ መኳንንቱ
በየግዛታቸው ያነን ደንብና አዋጅ በተመሳሳይ መንገድ እንዲያስከብሩ ጭምር ነው። ሌላው ደሞ መቸም ንጉሡ መኳንንቱ እንዳያምጹባቸው...
ተቀይመዋቸው ከሆነ ደሞ ለማረጋጋትና ሰላም ለመፍጠር በጋብቻ ሚተሳሰሩበትም ግዝየ ነው። በዝኸ ግዝየ አንድ የተቀየመ መኰንን አሞኛል ብሎ ሊቀር ይችላል። እናም እኼ ግዝየ ጃንሆይ አለ ነገር ሚሉበት፣ ብዙ ነገር ሚያውቁበትና ሚስተካከል ኻለም ተሎ ብለው ሚያስተካክሉበትም ግዝየ ነው” አሏት።

የበዓሉ ዕለት፣ ምንትዋብ ከአፄ በካፋ ጎን ድባብ ተይዞላት አደባባይ ወጣች። ሥርዐቱን ለማየት እጅግ ጓግታለች። ከንጉሠ ነገሥቱ ጎን ተቀመች። ጐንደሬዎችም ይህን ታላቅ በዓል ለመታደም ሥራቸውን
ነቅለው ወጥተዋል። ፎካሪዎች በየተራ እየወጡ ወደላይ ወደታች እያሉ ፎከሩ፣ ሽለሉ። ንጉሠ ነገሥቱን አወደሱ፤ አመሰገኑ።ሽለላውና ፉከራው ሲቆም፣ በአጋፋሪ መሪነት ታላቁ ስልፍ ተጀመረ።
👍13
ባለነፍጡ እንዲሁም ባለጦሩ ጋሻውን አንግቦ ወጣ። የበግ ለምዱን ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ፣ ፀጉሩን አጎፍሮ በታላቅ ሥነ-ሥርዐትና ኩራት ጉልበቱንና ታማኝነቱን እያሳየ በንጉሠ ነገሥቱ፣ በመሣፍንቱ፣
በመኳንንቱና በሕዝቡ ፊት ተመመ። ሴቱ በዕልልታ ወንዱ በሆታ ተቀበላቸው፤ አከበራቸው፤ ተማመነባቸው፤ አድናቆቱን ገለፀላቸው።

ምንትዋብ፣ ከየቦታው በመጣው ጦር ብዛትና ሥርዐት ተደነቀች።
ንጉሠ ነገሥቱም የተሰማቸውን ደስታና ኩራት አስተዋለች።

ከሰልፉ በኋላ፣ በዓሉ ላይ የተገኘው ሁሉ ግብር ለመታደም ወደ ፋሲል ቤተመንግሥት ግቢ ግብር አዳራሽ አመራ። በሚቀጥሉት ቀናትም ንጉሠ ነገሥቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከመሣፍንቱና ከየግዛቱ ከመጡት መኳንንት ጋር ስለ ሃገር ደህንነት፣ ስለወሰን አጠባበቅ፣ ስለግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ። ከየግዛቱ የመጡት መኳንንትም መስቀልን አክብረው መስከረም መጨረሻ ላይ
ወደየመጡበት ተመለሱ።
እንደዚህ እያለም፣ ለምንትዋብ ዓለም ሙሉ ሆነችላት፣ ሕይወት
ዐዲስ ትርጉም ሰጠቻት። ተናግቶባት የነበረውን በራሷ መተማመንን መለሰችላት፤ ጥንካሬ አከለችላት። ቤተመንግሥት ውስጥ የሚኖራትን
ስፍራ እንድታመቻች በር ከፈተችላት። ቤተመንግሥትም ዓለምን በተለየ መልክ እንድትመለከት አደረጋት።

ውሉም እየሰፋላት መጣ።

የቤተመንግሥት ሕይወት በወግ የታጠረ፣ ያገር ጉዳይ የሚመከርበትና የሚወሰንበት፣ ጥሩም ክፉም የሚታለምበት፣ ሃይማኖታዊ ሆነ ሌላ
ወገናዊነት ጎልቶ የሚወጣበት፣ ለመሾም ለመሸለም ፉክክርና ሽኩቻ የበዛበት፣ በተለይም ደግሞ የቤተመንግሥቱ አንዱ ክፍል የሆነው መሠሪ የተባለው ድብቅ ቦታ ንጉሠ ነገሥቱ ከመሣፍንቱና ከመኳንንቱ ጋር እንደ ጦርነት ያለ ከፍተኛ የሃገር ጉዳይ የሚመክሩበት፣ ሤራ
የሚሸረብበትና የሚፈታበት፣ ውሳኔ የሚሰጥበትና ሹም ሽር የሚካሄድበት ቦታ መሆኑን አበጥራ አወቀች።

የቤተመንግሥት ወግና ውስብስብነት እንደበፊቱ ግራ ማጋባቱን ተወ።

ኢያሱን ከወለደች በኋላ፣ የቤተመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሃገር ጉዳይ ላይ መወያየትና ማን መሾም ማን ደግሞ መሻር እንዳለበት ሐሳብ መስጠት ጀመረች።

ንጉሠ ነገሥቱም ቢሆኑ በአስተዋይነቷ ተመኩ፤ የሰዎችን ባህርይ ጠንቅቃ ማወቅ በመቻሏም ተደነቁ። ማታ ማታ መኝታ ቤት ከመግባታቸው በፊት ማምሻ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ከእሷ ጋር መወያየት የሚያስደስታቸው ነገር ሆኖ አገኙት።

አንድ ምሽት ላይ እዛው ማምሻ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ሲያወጉ፡“ጃንሆይ እንዳየሁት ጠላቶች አሉዎ” አለቻቸው፣ ብዙ ናቸው ከማለት ተቆጥባ።

ንግሥና ማለት እኼው ማዶል? ጠላት ማፍራት? እኼው ነው።
አንዱን ሹሜ ሌላውን ስሽር የተሻረው ያኮርፋል... ያምጣል። ግብር መገበር ያለበት ሲያዘገይ ወይም አልገብርም ሲል ስትቀጭው ጦር አስከትሎ ይነሳል። ርስት ነጥቆ የያዘውን እነጥቀዋለሁ፤ ይቀየመኛል።
ነፍስ አጥፍቶ ይፈረድበትና ይግባኝ ብሎ ይመጣል፤ ፍትሑ ለሟች ተኾነ የዳኞቹን ፍርድ አጸናበታለሁ። ያንየ ተወላጆቹ ያኮርፉኛል።ስለዝኸ ዳኝነት ወይም ንግሥ የሚወደዱበት ሥራ ማዶል፤ አይግረምሽ እናቴዋ።”

“መቸም ኻጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ በኋላ፣ ኸነበሩት ጊዜያት ጋር ሲተያይ አሁን ይሻላል። ቢሆንም አንዳንዶች አይተኙልዎትም።
አመጠኛውን ሁሌ ኸመቅጣት በዘዴ መያዝ ጥሩ ነው።”
“ውነትሽ ነው። እኔም ሳልወድ በግድ ወደ ቅጣቱ አደላለሁ መሰል።ዛዲያ እኮ በጋብቻ እያስተሳሰርሁ፣ እየሾምሁ፣ አየሸለምሁ፣ መሬትና
ጉልት እየሰጠሁ ለማባበል ሞክራለሁ።”

“የኔም ዘመዶች እኮ ሊያግዙዎ ይችላሉ። የእሚታ ዮልያና ወንድም
ኒቆላዎስ የተማረና ብልህ ሰው ነው። በዕድሜም ብስል ነው። ቀኝ
እጅዎ... ኣማካሪዎ ሊሆን ይችላል። አጎቴ አርከሌድስም የተማረ ብቻ ሳይሆን ደፋርና ታማኝ ነው። ቤተመንግሥቱን ቀጥ አርጎ ይይዝልዎታል። ወንድሜ ወልደልዑልም ቢሆን ትምርት አለው። ላገር ሚበቃ ብርቱና አዋቂ ሰው ነው። እሽቴ፣ ነጮ፣ ጌታና አውሳቢዮስም ትምርት አላቸው ... ታዛዥ አገልጋይዎ እንጂ ሌላ አይሆኑም። እኒህ ሁሉ አጠገብዎ ኻሉ አለስጋት ሁሉን ማረግ ይችላሉ።”
“መልካም ብለሻል።”

“እንደማየው ካህናቱም አሁን ውስጥ ውስጡን ሽኩቻ ላይ ናቸው።እንደፊቶቹ ነገሥታት በአደባባይ ክርክር ቢያረጉ ያረጋጓቸው ነበር።ቅባቶቹ ክርክሩን ይፈልጉታል።”

“ቅባቶቹ ክርክሩን ይፈልጉታል” ስትል እሷ ወደቅባት ስለምታዘነብል አዝማሚያዋ ገባቸው።

“ክርክሩን ለማረግ አስቤያለሁ። ብቻ ቅባቶቹን አረጋጋለሁ ስል
ሌሎቹን ደሞ አስቀይማለሁ። ቅባቶቹን አረጋጋ ብየ አባቴ ያቆዩትን የተዋሕዶ ሃይማኖት እንዴት መጉዳት ይቻለኛል?”

“በክርክሩ ቅባቶች ኻቸነፉ መቸም... በወንድምዎ ባጤ ዳዊት ግዝየ አቸንፈው ማልነበር?”

“እሱ ብዙ ታሪክ አለው። ቅባቶች አቸነፉ ብየ ሃይማኖቴን መቀየር
አይቻለኝም። ቢስማሙልኝማ ሰላም አገኝ ነበር።”

“ውነትዎ ነው። ዋናው ነገር እኮ ሁሉም እንደ ሃይማኖቱ መሆኑ
ነው።”

“ሁሉ እንደሱ አያስብ ሁኖ ነው እንጂ እንደሱ ኻሰበማ ክርክር ምን ያረግ ኑሯል?”

ሁለቱም ዝም ብለው ቆዩና ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ።
ብዙም ሳይቆዩ፣ ስለፍቅሯና ስለአስተዋይነቷ ሲሉ በዕድሜ የገፋውን ኒቆላዎስን ግራዝማችነት፣ አርከሌድስን የአሪንጎ አስተዳዳሪ በኋላም
የእልፍኝ አዛዥ በማለት ማዕረግ ሰጧቸው። ወልደልዑልን፣ እሽቴንና
የአጎቶቿን ልጆች የቤተመንግሥት ባለሟሎች አድርገው ሾሟቸው።

ምንትዋብ ቋረኞችን ቤተመንግሥት ውስጥ አደላደለች።

ከሁሉ በላይ ግን ኢያሱን መንከባከብ ቀዳሚ ተግባሯ ሆነ። ኢያሱ ሦስተኛ ዓመቱን ሲይዝ ከሌሎች ነጋሢያን ልጆች ጋር ግቢ ውስጥ ጨዋታ ሲጀምር፣ በካፋ
“ልዤን እንዳይገድሉብኝ” ብለው ስጋት ገባቸው። ምንትዋብ እንደ ሌሎች ነጋሢያን ልጆች ዘመድጋ ይላክብኛል ብላ ፈራች። ሰንበት ብሎ ኢያሱ፣ አፄ በካፋ ከሌላ የወለዷት እህቱ ውቢት ዘንድ መሄዱ ሲረጋገጥ ጭንቅ ዋጣት።

እንደ እሷ ፈቃድ ቢሆን አጠገቧ አድርጋ አያቷ እሷን በዕውቀትና
በግብረገብ አንጸው እንዳሳደጓት፣ ልጇን ልታስተምር፣ በመልካም
ምግባር ልታንጽና በአካል ልትገነባ ፈልጋ፣ ተመኝታና ተዘጋጅታ
የነበረው ሁሉ መና ሆኖ መቅረቱ አሳሰባት።

አንድ ምሽት ከራት በኋላ ነው። ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ማምሻ ክፍል
ውስጥ ወንበሮቻቸው ላይ ቁጭ ብለው ይጫወታሉ። በካፋ ፈገግ አሉና፣
“ዛሬ ምንገድ ስኸድ አንዱ ደንጊያ ላይ ተቀምጦ ጠሐይ ይሞቃል። እኔ ስመጣ አልተነሣም” አሏት።

ወሬውን ለመንገር ካላቸው ጉጉት የተነሣ፣ ልቧ ከእሳቸው ጋር
እንዳልሆነና የወትሮው ፀሐይ የመሰለው ፊቷ ደመና እንደጣለበት አላስተዋሉም።

“ኒቆላዎስ ቆጣ ብሎ፣ “አንተ ንጉሥ ሲመጣ ማትነሳ?' ሲለው
ሰውየው፣ ንጉሥ መሆኑን በምን አውቃለሁ? ግንባሩ ላይ የለ። እኔ
ኸዝኸ ቁጭ ብየ ጠሐይ ስሞቅ ያከበርኩት የመሬቱን ሳይሆን የሰማዩን ንጉሥ ነው' ብሎ ሲመልስለት ተሳሳቅን...” ብለው አለመሳቋንና ፊቷ መለዋወጡን ልብ አሉና ደነገጡ።

“ምነው የኔ ዓለም የከፋሽ ትመስያለሽ? ላፍታ ስንኳ እንድትከፊብኝ አልሻም። የተከፋሽበት ነገር ካለ አዋዪኝ” አሏት።

“ጃንሆይ የኢያሱ ነገር ያሳስበኛል። እርሶ ውቢት ዘንድ ሽሬ
መስደድ ይፈልጋሉ። እኔ ደሞ ኸዝኸ ሁኖ ትምርቱን እንዲማር ነው እምሻ ። የቤተመንግሥትም ወግ እየተማረ ቢያድግ ነው ምመርጥ። ሌት ተቀን ሚያስጨንቀኝ፣ እንቅልፍ ሚነሳኝ እኼ ነው። ሌላ ቦታ ኸዶብኝ ተኝቼ ማደር አይሆንልኝም።”
👍151
የፊቷን መከስከስና የድምጿን መርበትበት አስተውለው ልባቸው
ተነካ።
“የኔ ዓለም...” ብለው እጇን ሳብ አድርገው እያሻሹ፣ምንትዋብ... ኻላንቺ መኖር እንደማልችለው ሁሉ ኸልዤ ተነጥዬ መኖር አይቻለኝም። ወድጄ ማዶል ኻይኔ ርቆ እንዲኸድ ምፈልገው። እንደምታቂው ብዙ ጠላቶች አሉኝ። እኔን ለመበቀል ሲሉ ይገድሉብኛል ብየ ሰግቸ ነው። ኸገደሉት እኮ አንቺም ብትሆኚ
ታዝኝብኛለሽ። ባክሽ ተረጂኝ። ትምርትም ቢሆን ኸዛው ይማራል።ኪዳነ ምሕረት ትርዳኝ፣ ተሎ እንዲመለስ አረጋለሁ” ብለው፣ የእሳቸው ጭንቀት ቢጨምርም የእሷን ሊያቃልሉ ሞከሩ።

ሊደብቁት ያልቻሉትን መጨነቅ ፊታቸው ላይ አየች። እሷን
በማስደሰትና የልጃቸውን ሕይወት ለማዳን በመፈለግ ልባቸው እንደተከፈለ ተረዳች። አንጀቷ ተላወሰ። የጠየቅሁትን ሁሉ
ይፈጥሙልኛል። እኼ ኢያሱን አደጋ ላይ ሚጥል ጉዳይ ስለሆነ
ልረዳቸው ይገባል አለች፣ ለራሷ።

ጭንቀታቸውን ለማቃለልም፣ “ውነትዎ ነው። ልዣችን አደጋ ላይ
ሲወድቅ ማየት አልፈልግም። ይኸድ ግድ የለም” አለቻቸው።

ኢያሱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እህቱጋ ሽሬ ተላከ። ምንትዋብ
እንባዋን ረጨች። በናፍቆት ባባች።ልጇ አጠገቧ ባለመኖሩና ያሰበችለትን ሁሉ ማድረግ ባለመቻሏ ቅር ተሰኘች። አያቷ ቋራ ሄደው ከእናቷ ጋር ተመልሰው መጥተው አጠገቧ ቢሆኑም፣ ከልጇ ጋር በመለያየቷ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍት ቦታ ሊሞሉ አቃታቸው። ቀደም ብሎ ከአፄ በካፋ የደጃዝማችነት
ማዕረግ አግኝተው የነበሩት አባቷ በቅርቡ አርፈው ስለነበር የእሳቸው
ሐዘን ተጨምሮበት ነገሩን አባባሰው። ከእናቷና ከአያቷ ጋር ስትሆን በአመዛኙ የምታወራው ስለ ልጇ በመሆኑ ጨርሰው ሊያጽናኗት አልሆንላቸው አለ።

አንድ ቀን፣ እናቷ ወሬ ለመቀየር ብለው ጥላዬ ከቤት ጠፍቶ በመሄዱ ባላምባራስ ሁነኝ፣ “ልጄን አማርሬ እንዲጠፋ አረግሁት” ብለው በሐዘን ብዛት እንደሞቱ ነገሯት።

“ጥላዬ የት ጠፋ?” አለቻቸው፣ ደንግጣ።

“ማን አወቀ። አንቺ ረቡዕ ወደዝኽ ልትነሺ ማክሰኞ ነው አሉ
የጠፋው። ጌጤ አንቺን ልትሰናበትሽ ስንኳ አልመጣችም፤ እቷጋ ይሆናል ብላ ልትፈልገው ኸዳ። መቸም ሰው ትሆናለች አላልንም ነበር፤ እኼው አለች። እንጃ ዐይኗ በልቅሶ ሳይጠፋም ኣይቀር። እኼው እስተዛሬ የት እንደደረሰ ማንም አላወቀ” አሏት።
ምንትዋብ፣ ደነገጠች፤ አዘነች፤ ልትናገር ፈልጋ ልሳኗ ተዘጋ።
የእሷን መሄድ ተከትሎ መጥፋቱ ገረማት። ለቀናት፣ “የት ኸዶ ይሆን?” የሚለው ጥያቄ ለልጇ ያላት ጭንቀት ላይ ተደምሮ ልቧን አስጨነቀው።......

ይቀጥላል
👍51
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።” “ትሰጥሻለች። ምን ይሳናታል? አሁን ስለሱ አታስቢ።” ሆዷ እየገፋ ሲመጣ፣ ጭንቀቷ በረታ። ሴት በመውለዷ ባትከፋም፣ ወንድ አለመውለዷ ቤተመንግሥት ውስጥ ሊኖረኝ ይችላል ብላ ያሰበችውን ቦታ የሚያሳጣት መሰላት። ይበልጡንም ደግሞ ወህኒ አምባ ያሉ የነገሥታት ዘሮች…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...በድሉ አሽናፊና ማንደፍሮ ጌጤነህ ቀድሞም ይተዋወቁ ነበር፡፡ መነሻው በድሉ የተሽከርካሪ ባለ ንብረት፣ ማንደፍሮ ሾፌር ስለሆነ ከህዝብ ማመላለስ ስራ
ጋር በተያያዘ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ስለሚገናኙ ነበር::ከቅርብ ቀናት ወዲህ ደግሞ የተለየ ግንኙነት ፈጥረው ሰንብተዋል ማንደፍሮ ቀድሞ ይዞቶ
የነበረውን ተሽከርካሪ ትቶ በሌላ መኪና ላይ ለመቀጠር ሲፈልግ፣ በድሉ ደግሞ የአንድ ተሸከርካሪን ነባር ሾፌር አባርሮ ሌላ ለመቅጠር በነበረው ፍላጎት መሰረት
በመጠያየቃቸው ነው፡፡ በመጨረሻም ሁለት በቀጣሪና በተቀጣሪነት ስምምነት ላይ
ደርሰው ውል የተፈራረሙ ዕለት እማኝ ምስክሮቻቸውን ሲጋብዙ በዋሉበት ቀን ወደ ማታ ላይ ደግሞ ብቻቸውን ከአንድ ቡና ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው ይጫወታሉ፡፡ በመሀል የደመወዝ ነገር ተነስቶ ቀድሞም ቢሆን ቅር ብሎት የነበረው ማንደፍሮ ስሜቱን ለበድሉ ማካፈል ጀመረ፡፡
የምትከፍለኝ ደመወዝ ከስራውና ከጣልክብኝ አደራ ጋር በፍጹም
አይጣጣምም::» አለው በድሉን፡፡
“ለዚህም እኔ ስለሆንኩ ነው ! አባቴ ቢሰማ 'ኡ ኡ' ነው የሚለውኑ ቀድሞ ስራው የታለና ከዚህ በላይ ደመወዝ ይከፈላል፡፡» ሲል በድሉ መለሰለት።
እውነቴን ነው በድሉ! እኔ ወደ ዲላ ጠጋ ለማለት የፈለኩበት ጉዳይ
ባይኖረኝ ኖሮ በዚህ ደሞዝ » ብሎ ሳይጨርስ በድሉ ቀደመው»
«ተጠቃለህ ብትገባማ ጥሩ»
«የሚቀር አልመሰለኝም፡፡»
«ቤት ልትሰራ አሰብክ?»
«መሰረቱን ጥያለሁ፡፡» አለ ማንደፍሮ ሳቅ እያለ በድሉን በማየት፡
«የት ቀበሌ»
«እዚህ ዜሮ አምስት ቀበሌ ስምንተኛ መንገድ አካባቢ
«እዚያ አካባቢ ክፍት ቦታ የታለና» አለና በድሉ የት ጋ ሊሆን
እንደሚችል ሲያሰላስል «ኪስ ቦታ አግኝቼ፡፡» በማለት ማንደፍሮ አሁንም ፈገግ እያለ በድለን ያየው ጀመር። በውስጡ ሌላ ምስጢር እንዳለ ከፊቱ ላይ ይነበባል።
«እኔ እንጃ!» አለና በድሉ ቢራውን ሊጎነጭ ብድግ እያረገ ገዝተህ እንደሆነ እንጂ በምሪት የሚሰጥ ቦታ እዚያ አካባቢ ስለመኖሩ ተጠራጠርኩ፡፡» አለው፡፡
«ለመሆኑ ያን አካባቢ በደንብ ታውቀዋለህ እንዴ?»
«ዲላ ውስጥ የማላውቀው ሰውና ቦታ የለም፡፡ አለና በድሉ ቢራውን
እየተጎነጨ «ግዛቴ አይደል?» በማለት ቀለደ፡፡
«እዚያ አካባቢ ማን ማን ታውቃለህ?»
«እኔ ከምዘረዝር አንተ እገሌ በለኛ»
«አንዲት መምህር ታውቃለህ?»
በድሉ ሽዋዬ ትዝ አለችው፡፡ ፈገግ ብሎ ማንደፍሮን ትኩር ብሎ
ከተመለከተ በኋላ ሽዋዬን እንዳይሆን?» አለው።
ማንደፍሮ እንደገና ድንግጥ አለና «እንዴ! እውነትም ታውቃታለህ እንዴ» ሲል ጠየቀው።
ሁለቱም በፈገግታ ተያዩና በተለይ በድሉ ሃሃሃሃ …ብሎ እየሳቀ «በደንብ አውቃታለሁ አለው።
«በምን ሁኔታ?» አለ ማንደፍሮም የባሰ እየደነገጠ።
«አይዞህ! ጉዳይ ካለህም አትደንግጥ። አንተ የጣልከውን መሰረት በማያነቃንቅ ሁኔታ ነው የማውቃት፡፡»
ሁስቱም ተሳሳቁ፡፡
«ለመሆኑ መቼ ጀምረህ ነው የምታውቃት?» ሲል በድሉ ማንደፍሮን ጠየቀው።
«ከዓመት አለፈኝ»
በድሉ በርናባስ ወደ ውጭ የሄደበትን ጊዜ አሰላስለና እሱ ከሄደ በኋላ፣ ግን ደግሞ ወዲያው እንደሄደ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ በመገረም ዓይነት ራሱን ወዘወዘ።

«ምነው በድሉ? ተደርቤ ይሆን ወይስ…» ብሎ ማንደፍሮ በድሉን ትኩር ብሎ ሲያየው በድሉ ቀጠለ፡፡
«አይ አይ! እሱንማ ነገርኩህ! እኔ የማውቀው ሌላ ነገር ስላለ ያ ትዝ
ብሎኝ ነው:: አለው አሁንም ቢራውን እየተጎነጨ።
«መጥፎ ነገር ካለ ንገረኝ፡፡»
"ምንም እንዲያውም ለኔም ለአንተም ጥሩ አጋጣሚ ሳይሆን አይቀርም፡፡
«ልቤን አንጠለጠልከው»
“እንዴያውም እንዲህ አድርግ» አለ በድሉ ፈገግ ብሎ እያየው
«እንዴት?»
«የኔንና የአንተን ግኑኝነት ሳትነግራት አንድን ይቀንሳል ከሰው ጋር አስተዋውቅሻለው ተዘጋጂ! ብለህ የእሷንም ልብ አንጠልጥላጠው፡፡ አብረን እንሂድና የሚሆነውን ታያለህ።»
«ተው አንተ ሰው ደግሞ ከገባህ በኋላ አልወጣም ያልክ እንደሆንስ?»በማለት ማንደፍሮ ራሱ ስቆ በድሉንም አሳቀው።
እንዲህ እንዲህ እያሉ ሲጨዋወቱ አመሹ፡፡ በድሉ ግን ለማንደፍሮ
አንዳች ምስጢር አውጥቶ አልነገረውም፡፡ በባርናባስ ምትክ ማንደፍሮ በሸዋዬ ቤት መግባቱ ለበድሉ ጉዳዩ አልነበረም። ምክንያቱ ባርናባስ ባለ ትዳር መሆንና ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ሊቆይ መቻሉ ሌላው ነው፡፡ ከዚያም በላይ ቀድሞ ነገር
በድሉና ባርናባስ ለረጅም ጊዜ የሚተዋወቁ የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ከመሆናቸው በቀር የተለየ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ ስለዚህም ከማንደፍሮ ጋር በሸዋዬ ቤት ከመገኘቱ ለእሶም ሆነ ለእሷ የሚጎረብጣቸው ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡
ማንደፍሮ የበድሉና የሸዋዬ መተዋወቅ መሰረቱ ምን ሊሆን እንደሚችልም ለማወቅ ሲጓጓ ሰንብቶ አንድ ቀን ከሄደበት አገር ዶሮ፣ ሽንኩርትና ቅቤ ገዝቶ በመምጣት ለሽዋዬ እያስረከበ በነገው ዕለት ትልቅ እንግዳ ጠርቻለሁ፡፡ ከአንቺም ጋር አስተዋውቃችኋለሁ :: ሴትነትሽ ይታይበታልና አስማምሪው፡፡» አላት፡፡
ማግስቱ ቅዳሜ ነው። ወደ አሥር ሠዓት አካባቢ ሸዋዬ በሁሉም ነገር ተዘጋጅታ የማንደፍርንና የትልቁን እንግዳ መምጣት ስትጠባበቅ ማንደፍሮ ከዲላ
ይርጋለም የነበረውን የደርሶ መልስ ምድብ ስራውን አጠናቆ ከበድሉ ጋር ለማምሻ የሚበቃ ጫት ገዝተው ከሸዋዬ ቤት ከች አሉ፡፡
«እንዴ!» አለች ሸዋዬ ደስታ አይሉት ድንጋጤ አንዳች የማታውቀው ስሜት መንፈሷን ልውጥውጥ እያደረገው። ቀጥላም «አንተ ነህ እንዴ ትልቁ እንግዳ!» አለችው በድሉን ልትስመው ጠጋ እያለች።
«በአንድ ወቅት ትልቅ ነበርን፡፡ እያደር ግን…» ብሎ በድሉ ሳቅ እያለ ሸዋዪን ሲስም ማንድፍሮ ጣልቃ ገባ::
«እንተዋወቅ ነበር እንዳትለ!»
«በአንተ ቤት ገና ማስተዋወቅህ ነው!» አለችና ሸዋዬ ሁለቱም ቁጭ እንዲሉ ጋበዘቻቸው::
«ተሽውደሀል ማንዴ።» አለው በድሉ ከተነጠፈው ፍራሽ ላይ ቁጭ እያለ::
«እንዴት?» አለ ማንደፍሮ የተገረመ በመምሰል።
«ቁጫ በልና በእርጋታ ይነገርሃል።» አለው በድሉ።
«ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም አሉ» እያለ ማንደፍሮም ወደ ፍራሻ
አለፍ ብሎ ተቀመጠና «የሸዋ፣ በይ ከጫት በፊት የሚበላ ነገር ቶሎ በይ!» አላት።
ሸዋዬም ግርምቷን ደጋግማ እየገለጸች ምግብ የማቅረብ ስራዋን ተያያዘችው:: በድሉ ከዚያ ቤት ከቀረ ከዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ በሽዋዬ ቤት ያየው
ለውጥ እስገረመው። የሽዋዬ ታጣፊ አልጋ ልዩ በሆነ ሞዝቦልድ አልጋ ተተክታለች፣ ለብቻ ቢተኙበት
'የሰው ያለህ' የሚያሰኝ፡፡ ከፊትለፊቱ ባለ መስታወት
ብፌ ግድግዳ ጥግ ይዞ ተሰይሟል። የጓዳው በር እንኳ መጋረጃው ዓይን ይስባል።
ቤቱ በሮዝ ቀለም ተቀብቶ ፍክት ብሏል። ሁሉመሰ ነገር ደስ ይላል። ይህን ሁሉ ሲያጤን ቆይቶ የሸዋዬን ጓዳ ውስጥ መሆን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ማንደፍሮ ጆሮ ጠጋ በማለት በሹክሹታ አነጋገር «ምን መሰረት ጥያለሁ ትላለህ ዋልታውንም
አቁምሃል እንጂ» አለና ለራሱ እየሳቀ ማንደፍሮንም አሳቀው።

ሽዋዬ እንጀራና ወጡን ለበድሉና ለማንደፍሮ አቅርባ እየጋበዘች እሷ ግን የቡና ማፍላቱን ስራ ቀጠለች፡፡ ግን ከእነሱ ይበልጥ እሷ ነበረች የምትበላው ሁለቱም እየተፈራረቁ በሚያጎርሷት ጉርሻ ጉንጯ እየሞላ ስራ ያለማቋረጧ ደግሞ ለቡናው
👍14
ቶሎ መድረስና ለጫት ቅሞሹ መጀመር አስተዋፅዎ አደረገ ።
«ማንዴ» ሲል ጠራው በድሉ ጫቱን አጎንብሶ እየቀነጣጠበ
«ወይ»
«አንተ እዚህ ቤት አባወራ ከመሆንህ በፊት እኔ ደግሞ አማች ነበርኩ።
«ማንን አግብተህ?» አለ ማንደፍሮ በድሉን ሸዋዬንም ተራ በተራ
እየተመለከተ፡፡ ከዚህ በኋላ ለሚወራው ሁሉ ማንደፍሮ አዲስ ስለሆነ ቀልቡ ይጓጓ ጀመር።
«ቀሪውን ሸዋዬ ትንገርህ»
«ቅልጥፍና ጎድሎህ ያጣኸውን ዕድል አሁን ለምን ታነሳሳለህ?» አለች ሸዋዬ ፈገግ ብላ በድሉንም ማንደፍሮንሃ" እያየች።
«እኔ በድሉ!?»
«እኔ ሽዋዬ ነኛ»
«አሪፍ ጨዋታ ልሰማ ነው፡፡» አለ ማንደፍሮ ሁለቱንም እያየ።
«ምን ዋጋ አለው! በወሬ ቀረ፡፡» ብሎ በድሉ በቁጭት ዓይነት ራሱን
ወዝወዝ ሲያደርግ ማንደፍሮ ቀጠለ፡፡ እንዴት? ለምን?
«በቃ! አቃተው፣ ቀረ፡፡» አለች ሽዋዬ።
«ልጃገረድ ነበረች?» ሲል ማንደፍሮ ጠየቀ በተለይ ሸዋዬን እየተመለከተ።
«ቀድሞ ማን ወንድ ሆኖ እዚያ ቦታ ደረሰና!» አለችና ሽዋዬ ኪ ኪ ኪ ኪ... ብላ ሳቀች።
«ወንድሜ ጉድ ሆነሃላ!» በማለት ማንደፍሮ በድሉን ቀለደበት
«ዝም በላት ትቀልድ፣ ቀስ እያልክ ምስጢሩን ታገኘው የለ» አለና በድሉ የተቀነጣጠበውን ጫት አፉ አደረገ።
«ልጅቱ አሁን የት ናት?» ሲል ጠየቀ ማንደፍሮ፡፡
«እህቷ ናትና አሷ ናት የምታውቀው::
«እንዴ!» ብሎ እንደ መደነቅ አለና ማንደፍሮ «ለዚያውም እህትሽ?» ሲል፣ በተለይ ሸዋዬን ጠየቃት።
«ባለ ጉዳይ ይፈልጋት እንጂ እኔ ምን አገባኝ፡፡»
« አቦ ልቤን አታንጠልጥሉት!» አለና ማንደፍሮ እንደ መናደድ ብሎ
«ትነግሩኝ እንደሆነ ንገሩኝ!» ብሎ ቀነጣጥቦ እጁ ላይ ያጠራቀመውን ጫት ቃመው።
«ሩቅ አገር ነው ያለችው፡፡»አለችው ሽዋዬ::
«መኪና አይገባውም?»
«ሄደህ ልታመጣለት? ኪ-ኪ-ኪ-ኪ ..»
ምን ችግር አለ? የምነዳው የአባቱን መኪና»
«ከመቼ ጀምሮ?» አለች ሸዋዬ በቁም ነገር። መኪና መቀየሩን አልሰማችም ማንደፍሮ ያልነገራት በድሉ ባሳሰበው መሰረት ነው። ያም የሆነው የዛሬውን የሸዋዬን ግርምት ለመፍጠር በማሰብ ነበር።
«ለነገሩ እንኳ ከሳምንት በላይ አይሆንም።» አላት ማንደፍሮ በመጠኑም ቢሆን እንደ እፍረት እየተሰማው።

«እንዴ!» አለች ሸዋዬ እውነትም ነገሩ ዱብ እዳ ሆኖባት። ሁለቱ ሰዎች እሷ የማታውቀው ምስጢር ይኖራቸው እንደሆነ ብላም ተጠራጠረችና ተራ በተራ ታያቸው ጀመር። ሁኔታዋ የገባቸው
በድሉና ማንደፍሮ የተገናኙበትን አጋጣሚ ዝርዝር አድርገው
ሲያስረዷት ወደ ማመኑ አዘነበለች። የተጀመረው ጨዋታ ቀጠለ።
«እውነት ግን ልጅቷ መምጣት አትችልም?» ሲል ማንደፍሮ ጠየቃቸው ሁለቱንም ተራበተራ እየተመለከታቸው።
እንዴት ነው የሸዋ ይኸ ነገር አላት ማንደፍሮም ሸዋዬን እየተመለከተ፡፡
«ይሆን አይመስለኝም" አለች ሸዋዬ፡፡ ግን ደግሞ ድንገት ፍዝዝ ትክዝ በማለት ከሃሳብ ውስጥ የገባች መሰለች። ሸዋዬ እውነትም ጭልጥ ብላ ከሀሳብ ውስጥ ገባች:: እንኳን በውኗ በህልሟ እንኳ ታይቷት የማያውቅ አዲስ ሀሳብ በአዕምሮዋ ተፈጠረ። እውነት ሔዋን በዚህ አጋጣሚ ወደ ዲላ ብትመጣስ የሚል
ሀሳብ በውስጧ ተመላለስ። መንገዱ እንደሆነ ክፍት ሆኗል፣ አስቻለው ከዘመቻ አልተመለሰም፡፡ ወደፊት ቢመጣ እንኳ ሁኔታዎች ሁሉ መሠረታቸው ከተለወጡ ምን ሊፈጠር ይችላል። እንዲያውም ሔዋንን ከበድሉ ጋር የማቆራኘት ምኞቷ ተሳክቶ የሔዋን ህይወት የተሻለ ቢሆን 'ይኸው የኔም አላማ ይኸ ነበር' እያለች ለሞፈከርና በተለይ ከእናቷ ጋር የሻከረባት ግኑኝነት ሊስተካከል እንደሚችል ይታያት ጀመር።
ምናልባት የሔዋንና የበድሉ ግንኙነት እሷም ከማንደፍሮ ጋር ያላትን ግንኙነት መሰረቱን እያጣበቀው ሊሄድ ይችላል፡፡ ሸዋዬ ደስ ደስ የሚል ስሜት ይሰማት ጀመር፡፡ ድንገት እፍን የሚያደርጋት ግን ሔዋንን የምታገኝበት መንገድ! በእርግጥ
ሔዋን እሷን ተማምና ወደ ዲላ ትመጣ ይሆን? እናቷስ እሷን አምነው ሔዋን ከክብረ መንግስት ትመጣ ዘንድ ይፈቅዱ ይሆን? አሳሳቢና አስጨናቂ ጉዳይ!
«አንድ ነገር በይ እንጂ የሽዋ ምነው ዝም አልሽ?» ሲል ማንደፍር ከሃሳቧ ቀሰቀሳት።

«እስቲ እየዋልን እያደርን»....

💫ይቀጥላል💫
👍101
#የራስ_ጥናት

አንባቢ አዋቂ ነው
ማንበብ ሰው ያደርጋል
ሲባል ሰማሁና
መፅሐፋን ብገልጠው
የሰው መሰረቱ የኑሮ ብልሃቱ
ራስን ማወቅ ነው ሲለኝ እያብራራ
መፅሐፉን ዘግቼ ሙከራ ጀመርኩኝ
ራሴን ላጠና.....
ራሴን ሳነበው...
አንቀፅም ምዕራፍም መግቢያም መደምደሚያም
ማውጫ ገፅ የሌለው
የምኞት ጋጋታ
የኑሮ ሁካታ ትልቅ ጎተራ ነው
ከዚህ ሁሉ መሃል
ለ ‹ማን ነኝ?ጥያቄ
ለራሴ ከራሴ መልሱን ስላጣሁት
የከፈትኩትን ራስ መልሼ ዘጋሁት።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍177👎1🔥1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንም እንኳን ልጇ ደሕና መሆኑንና ትምህርትና ዋናም እየተማረ እንደሆነ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ቀስት ውርወራ፣ ጉግስና አደን እንደሚማር ብትሰማም፣ ጭንቀቷ እምብዛም ሊቀንስላት አልቻለም። ሳታስበው ግን ሁኔታዎች ተቀየሩ። ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብ የሆነው ዐቃቤ ሰዐቱ ዲዮስቆሮስ ንጉሠ ነገሥቱን፣ “ኢያሱ መጥቶ የቤተመንግሥት ወግ፣
አስተዳደርና ትምርት በአግባቡ ይማር፤ ባባትዎ አጥንት ይዤዎታለሁ”እያለ አላስቆም አላስቀምጥ አላቸው።

ምንትዋብ አጋዥ ያገኘች መሰላት

አንድ ቀን ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። የስድስት ዓመቱ ኢያሱ ሲጫወት ድንገት በቀስት የሰው ጊደር ወጋ። የጊደሩን ባለቤት ፈርቶ ከዐይን ተሰወረ። ሲፈለግ በመጥፋቱ ክርስትና አባቱ፣ የእህቱ ባል
ደጃዝማች ባስልዮስና የአካባቢው ነዋሪ በጭንቀት አካባቢውን አሰሱ::ሰፈርተኛው ሁሉ በደቦ ተከፋፍሎ ቀየውን፣ ወንዙንና ጫካውን ፈተሽ::ኢያሱ የውሃ ሽታ ሆነ። ሰዉ ተደናገጠ፣ የሚያደርገው ጠፋው። ብሎም
ኡኡታ፣ ለቅሶና ጩኸት በረከተ። ለንጉሠ ነገሥቱና ለምንትዋብ
እንዴት እንደሚነገራቸው ተመከረ።

ኢያሱ ከተደበቀበት ሲወጣ ዕልልታና ደስታ ጩኸትንና ለቅሶን
ተኩ። ማንነቱ ተደብቆ የኖረው ልጅ በዚህ አጋጣሚ ማንነቱ ታወቀ።

ደጃዝማች ባስልዮስ ግን የኢያሱ ማንነት መታወቁ አደገኛና አሳሳቢ
መሆኑን ተረድቶ በሐሳብ ማሰነ። አፄ በካፋ ጉዳዩን እንዲሰሙ አደረገ።ኢያሱም በፍጥነት ጐንደር እንዲመለስ ተደረገ። ምንትዋብ፣ እናቷና አያቷ የደስታና የእፎይታ እንባ አነቡ።

ምንትዋብ ሳትውል ሳታድር፣ ኢያሱ በተመረጡ አስተማሪዎች
ትምህርት እንዲማር አደረገች። የመንፈስ፣ የግብረገብ፣ የአካል ግንባታና የቤተመንግሥት ወግ ትምህርትም ላይ አተኮረች።
አፄ በካፋ ጠላቶቼ ይገድሉብኛል ብለው ስጋት ቢገባቸውም፣ ዝምታን ፈቀዱ። በሌላ በኩል ግን ከእሷ፣ ከእመቤት እንኰዬ፣ ከእመቤት ዮልያናና ከግራዝማች ኒቆላዎስ ጋር ብዙ ጊዜ ቆይታ መያዝ አዘወተሩ።

በተለይ ምንትዋብን፣ “አንቺ ብልህና አስተዋይ ስለ ሆንሽ እኔ ሳልኖር ኸልዤ ጋር ሁነሽ አገሬን ባግባቡ እንድትመሪ፣ እንድታስተዳድሪ።
የባሕር ማዶ አረመኔዎች አገሬ ገብተው እንዳይበጠብጡ፤ ሕዝቤንም በሃይማኖት ሆነ በሌላ እንዳይበክሉ ዐደራ” ይሏታል።

በነገሡ በዘጠነኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ጥቅምት ወር ውስጥ ግን፣
“ወዳጅ ዘመዴን እለያለሁ” በሚል ታመምኩ ብለው ሲደበቁ ምንትዋብ
ምሥጢር ጠበቀች። ወዲያው፣ “ንጉሡ ሊሞቱ ነው”፣ “ንጉሡ ሙተዋል” የሚል ወሬ ጐንደርን አወዛገባት። የጐንደር ከንቲባ ብላቴን ጌታ ኩቾ ከወህኒ አምባ ንጋሢ አመጣለሁ' ብሎ ሠራዊት አዘጋጀ። ወህኒ አምባዎች በበኩላቸው ወሬውን ሲሰሙ እኔ ልንገሥ፣ አንተ ንገሥ፣ የለም እሱ ይንገሥ ተባባሉ፤ ተመራረጡ፤ ተፎካከሩ።

ጐንደር እንደ ልማዷ ልትታመስ ሆነ።

በካፋ ይህን ሲሰሙ አለመታመማቸውን ለማሳየት ሐሙስ ቀን ደብረብርሃን ሥላሤ ሲሄዱ፣ መኳንንቱ በርቀት ከጋሻ ጃግሬዎች ኋላ በፈረስ ተከተሏቸው። ሕዝቡም ከየቤቱ እንደ ጎርፍ ፍንቅል ብሎ
ወጣ፡፡

በካፋ፣ ሕዝቡን፣ “ታዩኛላችሁና ወደየቤታችሁ ግቡ” ብለው አሰናበቱ።ሊቃውንት ንጉሠ ነገሥቱን በሕይወት በማየታቸው መሬት ሳሙ፤ካህናት ዘመሩ፤ ሕዝቡ ተደሰተ። ከረብሻ ዳነ። በካፋ ግን ብዙ ታዘቡ።
ወዳጅ መሳይ ሁሉ ከበስተጀርባቸው ምን እንደሚያስብ ተረዱ።

መኳንንቱን ወርቅ ሰቀላ ጠርተው፣ በአፈ ንጉሥ በኩል፣ “ምነው
ባካችሁ እንዳው ጥቂት ቀን ታምሜ ብተኛ ሽብር ማስነሳታችሁ? ስለምን ከተማዬን አስደነገጣችኋት? ሞተ ብላችሁ እንደዝኸ መሆናችሁ ተገቢ ነውን?” ሲሉ ጠየቋቸው። እንደማይተኙላቸውም ተረዱ። ሆኖም፣“እነዝኸ በልባቸው ክፋት የለም” ብለው ይቅርታ አደረጉላቸው።መሣሪያ ያነሳው ኩቾ ግን ከነተከታዮቹ ተይዞ ጊዜያዊ እስር ቤት ገብቶ ለፍርድ እንዲቀርብ ተወስኖበት ፍርድ ሸንጎ ቀረበ።

የሃገር ክህደት ወይም ሌላ ከፍተኛ ወንጀል ካልሆነ በስተቀር የዙፋን
ችሎት የማይዙት ንጉሠ ነገሥት፡ ጃን ተከል ተገኝተው ከምንትዋብ ጋር እንደወትሯቸው ቀይ ድባብ ተይዞላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተቀመጡ።መሣፍንቱ፣ መኳንንቱና ሊቃውንቱ እንደየደረጃቸው ተሰየሙ። ፍትሐ ነገሥት ተርጓሚዎቹ፣ ፍርድ ሰጭዎቹና አዛዦቹ፣ ግራ ቀኝ ተችዎቹ
ሁሉ ተገኝተዋል። ዐራቱ ሊቃውንት ፍትሐ ነገሥት ይዘው ቦታቸው
ላይ ተቀመጡ። አቡኑ፣ ዐቃቤ ሰዐቱና መኳንንቱ የተለመደ ቦታቸው ላይ ሆኑ።

ኩቾና ተከታዮቹ እግራቸው በእግረ ሙቅ ታስሮ፣ ጋሻ ጃግሬዎች
ግራና ቀኝ እየጠበቋቸው በንጉሠ ነገሥቱ ትይዩ ቆሙ።ከአዛዦቹ አንደኛው፣ “ጠበቃ ኸፈለግህ ይፈቀድልኻል” አለው፣
ኩቾን።

“አያሻኝም።”

“እንግዲያማ ተጠየቅ።”

“ልጠየቅ!”

“አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ። ኸዝኽ
እንዳትዛነፍ በቅሎ ያግድህ። ጃንሆይ ትንሽ አሟቸው ሰንብተው
እንደነበር አልሰማህም?”

“ሰምቻለሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ጃንሆይን አደባባይ ባታያቸው ሊሞቱ ነው ብለህ አላወራህም?”

“አላወራሁም።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ያለ ጃንሆይ ፈቃድ ሠራዊትህን ማንቀሳቀስ እንደማትችል
ታውቃለህ አታውቅም?”

“አውቃለሁ ።"

“ተጠየቅ!"

“ልጠየቅ!”

“ዛዲያ ስለምን ሠራዊትህን አንቀሳቅሰህ ለአመጥ ተነሳህ?”

“ለአመጥ አልተነሳሁም።”

“ምስክር ይጠራብህ?”

“ሠራዊት...”

"አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ ያልኩህን አጣርሰኻል። ለበቅሎ ዋስ ጥራ።”

“አላጣረስሁም።”

“አጣርሰኻል። ምስክር ይጠራብኝ ወይንም አይጠራብኝ ነበር
መልሱ።”

“ኸጥያቄህ አልወጣሁም። እማኞች ይጠሩልኝ” እያለ ወደ ሰዉ ተመለከተ ኩቾ።

“አጣርሷል! አጣርሷል! በቅሎዋን ይክፈል!” አለ፣ ሰዉ።

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ለአመጥ መሣሪያ አላነሳህም?”

“ራስ ተስፋ ኢየሱስና ቢትወደድ ስኩት ጃንሆይ ያስሩኻል ቢሉኝ
መሣሪያ አነሳሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ምንም ሳታደርግ ጃንሆይ ስለምን ያስሩኻል? ሞተዋል ብለህ
ስላስወራህና ኸወህኒ ነጋሢ ልታመጣ ስለፈለግህ ነው እነራስ ተስፋ ኢየሱስ ያስሩኻል ያሉህ።”

ኩቾ ወደ እፄ በካፋ ተመለከተ። ሁለት እጆቹን ዘርግቶ፣ “ጃንሆይ
ይማሩኝ” ብሎ አጎነበሰ።

“ምትጠይቀው ጥያቄ አለ?” ሲል ጠየቀው አንደኛው አዛዥ ።

“የለኝም። ምሕረት ያርጉልኝ ጃንሆይ!” አለ፣ ኩቾ፣ አጎንብሶ።

ከአዛዦቹ አንደኛው ጋቢውን አስተካከለና ወደ ንጉሠ ነገሥቱ
ተመለከተ፣ “ጃንሆይ ኩቾ የቀረበበት ክስ ክህደት ነው። ክህደት ደሞ በሞት ያስቀጣል” አለ፣ ፍትሐ ነገሥቱን እያገላበጠ። “ፍታ ነገሥቱ ሚለው በንጉሥ ላይ ያመጠና ያሳመጠ በሞት ይቀጣ ነው።”

ይህን ዓይነቱ የሞት ብይን ይገባዋል አይገባውም፤ ወይንም ደግሞ ሌላ ቅጣት ይቀጣ ብለው ለመወሰን መኳንንት እንደየማዕረጋቸው እየቆሙ ከዝቅተኛው ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ አስተያየት ሰጡ።

“ክህደት ነውና ሞት ይገባዋል!” አሉ፣ አንደኛው መኰንን።

“ግዞት ይላክ!” አሉ፣ ሌላው።

“በግርፋት ይቀየርለት!” ብለው ተቀመጡ፣ አንደኛው
“ጃንሆይ መሐሪ ናቸውና ምህረት ይደረግለትና ሹመቱን ይገፈፍ”
አሉ፣ ሌላኛው።

እንደዚህ እያለ ሁሉም ተናግረው ከጨረሱ በኋላ፣ የማሳረጊያው
ንግግር የንጉሠ ነገሥቱ በመሆኑ፣ አፈ ንጉሡ አጎንብሶ ጆሮውን
ሲሰጣቸው ሁሉም ለመስማት ጆሯቸውን ሲያቀኑ ኩቾና ተከታዮቹ
ትንፋሻቸውን ውጠው ተጠባበቁ። ይህን ሁሉ በአንክሮ የምትመለከተው ምንትዋብም ተጠባበቀች።
👍20🤩1
አፈ ንጉሥ ቀና ብሎ ዐራቱን አዛዦች፣ “ጃንሆይ እናንተ ፈራጆቹ
እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት' ብለዋችኋል” አላቸው።

አዛዦቹ ሳያመነቱ ኩቾ ላይ ሞት ፈረዱበት።

ችሎት ተነሳ።

ንጉሠ ነገሥቱ ሲነሱ፣ ሁሉም ቆመው እጅ እየነሱ አሳለፏቸው።
ከፊት የሚመሩት ከፊት እየመሩ ለንጉሠ ነገሥቱና ለምንትዋብ ድባብ ተይዞላቸው፣ መኳንንት እንደየተራቸው አጅበው ወደ ቤተመንግሥት ግብር አዳራሽ አመሩ።

ኩቾና ግብረ አበሮቹ አደባባይ ላይ በሊጋባውና በረዳቶቹ አማካኘነት
ተሰቀሉ። አከታትሎ፣ ከኩቾ ጋር አምጸው የነበሩት የንጉሠ ነገሥቱ
ሁለት እህቶችም ታድነው ተይዘው አስከሬናቸው መሬት ተወርውሮ
ለቀናት ቀባሪ አጥቶ የጅብ ራት ሆነ።

አመጽ አስነስተዋል የተባሉትም ከፍተኛውን ቅጣት በመቀጣታቸው
ሃገር ሰላም ሆነች። ንጉሠ ነገሥቱ በመደበቃቸው “ሙተዋል” ተብሎ
የተናፈሰው ወሬ እውነትነት ባይኖረውም፣ ሕዝቡ ንጉሠ ነገሥቱ በራሳቸው ላይ ያሟረቱ ያህል ቆጠረባቸው።....

ይቀጥላል
👍72
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ....ምንም እንኳን ልጇ ደሕና መሆኑንና ትምህርትና ዋናም እየተማረ እንደሆነ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ቀስት ውርወራ፣ ጉግስና አደን እንደሚማር ብትሰማም፣ ጭንቀቷ እምብዛም ሊቀንስላት አልቻለም። ሳታስበው ግን ሁኔታዎች ተቀየሩ። ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብ የሆነው ዐቃቤ ሰዐቱ ዲዮስቆሮስ ንጉሠ ነገሥቱን፣ “ኢያሱ መጥቶ የቤተመንግሥት ወግ፣ አስተዳደርና…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ኑሮ በክበረ መንግስት ለሔዋን አልተመቸም፡፡ በእናት በአባቷ ቤት ደባል ብቸኛ ሆናለች፡፡ ተወልዳ ባደገችበት አገር ባይተዋር ሆናለች ዙርያዋን ብዙ ሰው እያለ ብቸኛ ሆናለች በሃሳብ እና በጭንቀት
ብዛት ራሷን ረስታለች፡፡ ብትበላ ብትጠጣ ሆዷ ይጥገብ እንደሆን እንጂ መንፈሷ ግን ረሀብተኛ ሆኗል።
ባህሪዋም ተለውጧል። ደስተኛ የነበረች ሔዋን ብስጩ ሆናለች። ፍልቅልቋ ሔዋን አኩራፊ ሆናለች፡፡ ታዛዥና ትሁት የነበረች ሔዋን ነጭናጫ ሆናለች።ተጨዋቿ ሔዋን በትካዜ ተውጣ በጭንቀት ተወርሳለች፡፡ ጤንነቷም ተጓደለ፡፡
ዘወትር 'ልቤን' ማለት አበዛች፡፡ ከመቆም ይልቅ መቀመጥን፣ ከመቀመጥም መተኛትን አዘወተረች።የምግብ ፍላጎት አጣች። ከምትብላው ምግብ ይልቅ የምትጠጣው ውሃ ያማራት ጀመር። ከቶም 'ብይ' ባትባል ደስታዋ ሆነ፡፡ - የግድ ብትበላም ብዙ አይስማማትም። እሷ ተቸግራ ቤተሰቦቿንም አስቸገረች፡፡ የህመሟ ጉዳይ
ቤተሰቦቿ በተለይ በአባትና እናቷ ዘንድ ሌላ ስጋት ፈጠረ፡፡ 'ያ የልጅነት ህመሟ ሊነሳባት እያሉ ይጨነቁ ጀመር።

ስጋታቸው መነሻ አለው፡፡ ሔዋን በህጻንነቷ እስከ ሁለት ዓምቷ ድረስ ፍፍት፣ ድንቡሽቡሽ ያለችና ፍልቅልቅ ነበረች። ከዚያ በኋላ ግን ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ሁለመናዋ ተለዋወጠ፡፡ ሰውነቷ እየከሳ ቆዳዋ እስከ መሸብሸብና እየጠቆረ መልኳ እስከ መቀየር ደረስ፡፡ በእግሯ መሄድ ከጀመረች በኋላ ወደ መዳህ! ቀጥሎም
ቁጭ ብላ ቀረች፡፡ ለቅሶ የማታውቀው ሔዋን መብሰክሰክ አብዝታ አልቃሻ ሆነች።
ወላጅ አባትና እናቷ ትሞትብናለች እያሉም መስጋት ጀመሩ።
የእሷን ህይወት ለማትረፍ ያልተደረገ ጥረት አልነበረም፡፡ በተለይ እናቷ ያልተሳለባት ቤተክርስቲያን ያልሄዱበት ጠበልና ያልጠየቁት ጠንቋይ አልነበረም።
ዘመናዊ ህክምናም እንዲሁ፡፡ የሔዋን ጤንነት ግን አንዳችም መሻሻል ሳያሳይ ድፍን ስድስት ዓመት ሞላት፡፡ እናቷ ሲፈጩም ሲጋግሩም፣ ሲያነፍሱም ሲቀቅሉም ገብያ ሲሄዱም እንኳ ልጃቸውን አቅፈው ወይ አዝለው መንከራተት ግድ ሆነባቸው።

የሔዋን እናት በዚሁ ሁኔታ በመልፋት ላይ ሳሉ ረንድ ቀን ያልታሰበ ሁኔታ ገጠማቸው:: ቤታቸው ከክብረ መንግስት ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ከከተማው
ወጣ ብሎ በሚገኝ ገጠራማ ሥፍራ ስለሆነ የሱቅ ዕቃ ሊገዙ ሔዋንን ታቅፈው መደ ከተማ ሄዱ፡፡ ከአንድ ሱቅ ደርሰው የግዢ ወረፋ ሲጠብቁ ሔዋንን በሱቁ
ባንኮኒ ላይ አስቀመጧት:: ሔዋን ምንም እንኳ በህመም ምክንያት ሰውነቷ ቢጥመለመልም ነፍስ እያወቀችና አፏን እየፈታች በመሄዷ በሱቁ መደርደሪያ ላይ
የሚታዩ የሸቀጥ ዓይነቶችን ለእናቷ እየጠቆመች “ያ ምንድነው እማ? ያስ? ያኛውስ?… እያለች ትጠይቃቸዋለች፡፡ እሳቸውም ያወቁትን ያህል ያስረዷታል።
በሰቁ ውስጥ ዕቃ ሊገዙ የገቡ አንዲት ዕድሜያቸው ወደ ስልሳ የሚጠጋ ሴት አዛውንት ሔዋንና እናቷ የሚመላለሱትን እያዳመጡ በተለይ ሔዋንን አየት ያደርጓት ኖሯል፡፡ ጤነኛ እንዳልሆነች ከሁኔታዋ እየተረዱ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ሲያዝኑላት ቆይተው የገዙትን ዕቃ በመቀነታቸው ላይ ከቆጣጠሩ በኋላ «ይቺ ልጅ ስንት ዓመቷ ነው የኔ እህት? ሲሉ የሔዋንን አናት ጠየቋቸው።
«እድሜዋ እንኳ ስድስት ዓመት ሞላት፡፡»
«ጤና የላትም?»
«የላትም የኔ እናት! በጣም ተቸግሪሃለው። ከሁለት ዓመቷ ጀምሮ ይኸው ተንገላታባኛለች።
ይኸው አራት ዓወት በሙሉ እሷን አዝዬ እኖራለሁ።
«እምም...ም» አሉና ሴትየዋ ቤትዎ የት ነው?» ሲሉ ጠየቋቸው
የሔዋን እናት በምልክት ሲነገራቸው። «እስቲ አንድ ቀን ብቅ ብዬ እጠይቆታለሁ ምናልባት መዳኒት ያገኘሁላት እንደሆን።» አሏዋቸው።
«ሆኖ ነው የኔ እናት!» ብለው፧ የሔዋን እናት ፍንድቅድቅ እያሉ «አገርዎ የት ነው?»ሲሉ ጠየቋቸው።
«ቅርብ ነው:: ተሲያት ላይ ብነሳ እርስዎ ቤት መድረስ እችላለሁ፡፡»
«አደራ የኔ እናት! እንደው አደራ እንደው አደሪ» በማለት የሔዋን እናት ሴትዮዋን አጥብቀው ተማፀኗቸው::»
«አላህ ከፈቀድ ሳምንት እመጣለሁ::"»
«እሺ የኔ እናት፤ እጠብቅዎታለሁ::»
እዛውንቷ ሴት ቀጠሮአቸውን አክብረው ከሔዋን ወላጆች ቤት መጡና የባህል ህክምናቸውን ጀመሩ ሔዋን አካላቷን እንድትታጠብ ከአደረጉ በኋላ
ራሳቸው ታቅፈው ቅባት መሰል በሆነ ነገር መላ አካላቷን እየቀሱ ያሿት ጀመር፡፡ ያን ሲጨርሱ ሌላ መድሃኒት በማር እየበጠበጡ ያጠጧታል። እምቢ ስትላቸው
የግድ ይግቷታል። በዚህ ዓይነት ለሰባት ቀናት እራሳቸው ከአከሟት በኋላ ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናትም እናቷ እንዲያደርጉላት መክረዋቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ።የሔዋን እናትም በተመከሩት መሰረትም ፈፀሙ።

ዘመናዊ የህክምና ጠበብቶች እንዴት ሆኖ? ምኑ ከምን ተገናኝቶ? ለሜን ዓይነት በሽታ ያ
ምን ዓይነት መድሃኒት? አወሳሰዱስ? መጠኑስ? ወዘተ እያሉ አመክኒየአቸውን እንደ ስጋ እየዘለዘሉ ሊጠያየቁ ይችሉ ይሆናል፤ የሔዋን ጤንነት
ግን ከዕለት ወደ ዕለት እየተሻሻለ ሄደ። የተሸበሸበ ቆዳዋ ወጠር፣ ፊቷ ፈካ፣ እያለ ከመምጣቱም በላይ መዳህ ጀመረች። ህክምና በተደረገላት በሁለተኛው ወር ቆማ
መሄድ ቻለች፡፡ ሦስት ወር ሲሞላት ሙሉ ጤነኛ ሆነች::
የሔዋን እናትና አባት የተሰማቸው ደስታ ወሰን አልነበረውም። ሔዋን
እንደገና እንደ ተፈጠረች ቆጠሯት፡፡ እየተመላለሱ የሚጠይቋትን ሀኪሟን ሴት
የሚያደርጉላቸውን አጡት ሰጥተዋቸው አልረካ አሉ፡፡ አመስግነዋቸው አልጠግብ
አሉ። ሁሉም ነገር ሳያረካቸው ቢቀር ቅድስት የነበረውን የሔዋን ስም 'ሀዋ" ብለው በአዛውንቷ ስም ቀየሩት። ነገር ግን በዘር ማንዘራቸው ክርስቲያን ስለሆኑ ከዚያው ሳይርቁ «ሔዋን» በሚል ተኩት፡፡ እነሆ ቋሚ ስሟ ሔዋን ሆኖ ቀረ::
ዛሬ ታዲያ 'ልቤን' እያለች ስትሰቃይባቸው፣ ድካም እየተሰማት ድፍት ብላ
ስትውልባቸው፣ ምግብ በአግባቡ መመገብ አቅቷት ሲያዩ፣ ፍዝዝ ትከዝ ስትል እየተመለከቱ እጅጉን ይሰጉ ጀመር፡፡ ወደ እመት ሐዋ አይሮጡ ነገር እመት ሐዋ
መሞታቸውን ከሰሙ ቆይተዋል። ወደ ዘመናዊ ሀኪም ቤት ወስደው
ሊያስመረምሯት ሀኪሞቹ የልብ ችግር እንዳለባት አረጋግጠው ክኒን ብቻ ሰጥተው የራሷ ሃኪም ራሷ ናት፡፡ ሃሳብና ጭንቀት ካለባት ያንን ትታ መንፈሷን ማረጋጋት እረፍት ማድረግ ይኖርባታል አሏቸው። ይሄ ደሞዝ በሔዋን በኩል የሚሞከር አልሆነም፡፡ ከሀሳብ " ከትካዜና ከጭንቀት ማን ጎትቶ ያውጣት?
ከህመሟ በተጨማሪ ያለባትን የውስጥ ችግር የሚያውቁላት እናቷ ግን ተስፋ አልቆረጡም' ሔዋንን የማረጋጋት ጥረታቸውን ቀጠሉ፡፡ መጀመሪያ ፍላጎቷን አጠኑ። ሔዋን ቤት ውስጥ ከሆነች መደብ ላይ ጋደም ማለት ነው ቤቱ ሲጨንቃት ወደ ጓሮ ሄዳ ከዛፍ ስር መቀመጥ ነው
ጓሮአቸወ ደግሞ ሰፊና በትላልቅ ዛፎች የተሞላ ነው። ሔዋን ከዛያ ውስጥ በአንዷ ዛፍ ስር መቀመጥ ታዘወትራለች ያንንም አጠኑ።
አቀማመጧ ይመቻት ዘንድ የዛችን ዛፍ ዙርያ በአፈር ደለደሉ፡፡ በፀሃይ ጊዜ አቧራ በዝናብ ጊዜ ጭቃ እንዳይሆንባት ሳር ተክለው ውሃ እያጠጡ አለመለሙላት ይበልጥ
👍91
እየተመቻት ሲሄድ ተሰማቸው።
በዚህ እላቆሙም፡፡ ሔዋን ወደዚያ አካባቢ የምትሄደው ብዙ ጊዜ ከሰዓት ከሰዓት መሆኑን ተከታተሉ። እሳቸውም የቤት ስራቸውን ሲጨርሱ በዛቺው ዛፍ
ስር ቡና እያፈሉ ያጨዋውቷት ጀመር። ሁኔታው ለብዙ ጊዜ በዚሁ ቀጠለ፡፡
እያደር እያደር ሔዋን እስኪርብቶና ወረቀት መያዝ ጀመረች፡፡ ብዙ ጊዜ ስትጽፍ ያዩዋታል:: ግን ደግሞ ስትጽፍ የዋለችውን ማታ ትቀደዋለች።በምታፅፍበት ጊዜ የሚያዩባት ሁኔታ ያሳዝናቸዋል፡፡ ሰማይ ሰማይ ታያለች።እንደገና ፍዝዝ ብላ መሬት መሬት፡፡ አንዳንዴ ብቻዋን የምታመራ ይመስል ከንፈርቿ ሲነቃነቁ፣ ሌላ ጊዜም ዓይኗ በእንባ ሊሞላ ያያሉ፡፡

የሔዋን እናት ይኸን ሁሉ ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በምትጽፈዎ ወረቀት ላይ ስሜቷን የሚያገኙት እየመሰላቸው ይጓጉ ጀመር። ያአስቸገራቸው ነገር ማታ ማታ መቅደዷ ነው፡፡ እንዴት አድርገው አግኝተው ሊያስነብቡት እንደሚችሉ ሲጨንቃቸው ቆይቶ ከመዋል ከማደር አንድ ብልሀት ታያቸው። ቢሳካም ባይሳካም
ብለው ሊሞክሩት አሰቡ ሙከራቸውን ሊያደርጉ ባሰቡበት እለት ወትሮ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከቀትር በኋላ እዚያው ሔዋን
በምትቀመጥባት ዛፍ ስር የቡና ማፍላት ስራቸውን ጀመሩ። የዕለቱ ዋና ዓላማቸው ግን የሔዋንን ስሜት በዘዴ ለመመርመርና የምትጽፈውን ወረቀት አቀማመጥ ልብ ብለው መመልከት ስለነበር በተለይ የወረቀቱን ጉዳይ በዓይናቸው ሰረቅ እያረጉ ሲከታተሉ ቆዩ።በኋላም ቡናው ፈልቶ እየጠጡ ባሉበት ሰዓት
«እሙዬ!» ሲሉ ጠሯት
«አቤት እማ!» አለቻቸው ሔዋን ዓይን ዓናቸውን እያየች::
«ምንድን ነው የምትፅፊው?»
«ምንም እማ! ዝም ብዬ ነው።» አለቻቸውና ሔዋን እስኪርቢቶና ወረቀቱን በማስደገፊያ ደብተሯ ውስጥ ከተት አድርጋ ከአጠገቧ መሬት ላይ አስቀመጠችው፡፡
እናቷ የደነገጠች መሰላቸውና «ጣፊ ጣፋ የኔ ልጅ! የተማርሽም
እንዳይጠፋብሽ ጣፊ!» አሏት እንደ ማባበል ዓይነት።
«መጻፍ የተማሩትን ያስታውሳል ብለሽ ነው እማ?»
«ቢሆንም፣ ቢሆንም! መጣፉ ይሻላል፡፡ ጣፊ!»
ሔዋን ግን ወዲያው ሀሳብ ውስጥ ገባች። ዓይኖ ሰማይ ላይ ተተከሉ ልቧ አድማስ ተሻግሮ ሄደ። አጠገቧ ያሉትን እናቷ ረሳቻቸው። በሆዷ እያወራች ከንፈሯቿም ይንቀሳቀሱ ጀመር።....

💫ይቀጥላል💫
👍81
#የኑሮ_ኳስ_ሜዳ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሃል ዳኛ የለም

በዚህች ከንቱ ዓለም...
ሁሉም ይሯሯጣል
የራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል

ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱን ያንዱን ሳይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ያገባል

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....

ሁሉም ሰው በራሱ 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል

በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም

በዚህች ከንቱ ዓስም.....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሃሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም
ውሽት እውነት እንጂ ሕውነት ውሽት የለም።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍10👎1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“ሺሕ ዓመት ንገሥ።"

ምንትዋብ፣ አፄ በካፋ ወደ መሠሪ እንድትመጣ ሲልኩባት፣ ሕይወቷ
ዳግም ተለወጠ። ለጥቂት ቀናት መሠሪ ሱባዔ ገብተው ስለነበር
ጨርሰው ነው ብላ አስባለች። ከእናቷና ከአያቷ ጋር መሠሪ ስትደርስ፣የበካፋ ታማኝ እልፍኝ አስከልካዮች ቴዎድሮስ፣ ገላስዮስና ድንጉዜ ዐይኖቻቸው ደም መስለዋል። እጅ ነስተዋት ስትገባ መሠሪ ከብዶታል፤
ጨላልሟል። ከወትሮው ጠባብ ሆኖባታል።

አፄ በካፋ ከተኙበት ኣልጋ ራስጌ የነፍስ አባታቸው አባ ዐደራ
መስቀላቸውን ይዘው ቆመዋል። ኒቆላዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ ግርጌ
አቀርቅሮ ቆሟል። ምንትዋብ ርምጃዋን ገታ አድርጋ ክፍሉንም
ሰዎቹንም ቃኘች።

ነገሩ አላምር አላት። መንፈሷ ተረበሸ። ሱባዔ ላይ የነበሩት ባሏ ምን እንደደረሰባቸው መገመት አቃታት። ወደ አልጋቸው መራመድ ፈልጋ እግሮቿ አልታዘዝ አሏት፤ ትንፋሽ አጠራት። ልቧ ደረቷን ሲደልቅ እንደ ማጥወልወል አላት። ሐውልት ይመስል ደርቃ ቀረች። ዐይኗ ኒቆላዎስን ኣልፎ ንጉሠ ነገሥቱ ላይ ሲያርፍ፣ ፊታቸው ተሸፍኗል።

ዕለቱ ማክሰኞ፣ ቀኑ መስከረም አስራ ስድስት ዓመተ ምህረቱ 1723 ነው። እኒያ ቅኔ የሚቀኙት፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን የሚፈትሹት፣ አደን የሚወዱት፣ ለሃገራቸው ፊደላት ጥብቅና ቆመው፣ “ፊደል አሳስቶ የጻፈ
እጁ ይቆረጣል” ብለው አዋጅ የጣሉት፣ ሥነ-ጥበብ እንዲዳብር፣ ቃላት እንዲበለፅጉ የጣሩት፣ በወባ ንዳድ ርደው እንደተራ ሰው ባላባት ቤት መደብ ላይ የተኙት፣ ላይ ታች እያሉ ያመጸውን ያስገበሩት፣ ያጠፋውን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት፣ እንደ ቀደምት ነገሥታት የሃይማኖት ክርክር
ያከራከሩትና አሻራቸውን ለመተው የራሳቸውን ግንብ የገነቡት አፄ
በካፋ በነገሠ በዘጠኝ ዓመት ከዐራት ወራቸው፣ ምንትዋብን ባገቡ በሰባት ዓመታቸውና በተወለዱ በሰላሳ ሰባት ዓመታቸው ሕይወታቸው
አልፏል።

“ምንድርነው? ጃንሆይ ምን ሁነዋል?” አለች፣ ምንትዋብ፣ ድምጾ ይርበተበታል ።
ተጠጋቻቸውና ቡሉኮውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረገችው።አፍንጫቸው ጫፍ ላይ ደም አየች፤ መላ ሰውነቷ ራደ። ኒቆላዎስ ላይ አፈጠጠች።

“ድንገት ነው የሆነው። ባፍ ባፍንጫቸው ደም ፈሰሰ... ምንም ያህል አልቆዩ ዐረፉ” አላት።

ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ “ኡኡኡኡ...” አለች። እናቷና አያቷ
ፈጠን ብለው ግራና ቀኝ ደገፏት።

“ምነው ሳትነግሩኝ? ስለምንስ ከፋችሁብኝ?” እያለች ጮኸች።
መሬት ላይ ተንከባለለች።

ያን ጊዜ እናቷና አያቷ አብረዋት ጮሁ። እንደ እሷ መሬት
ላይ ተንከባለሉ። መሠሪ ጩኸት በጩኸት ሆነ። ዋይታ በረከተ።
ምንትዋብ ለያዥ አስቸገረች። እነግራዝማች ኒቆላዎስ ተጨነቁ፡
ለቅሶው እንዳይሰማ። የቤተመንግሥት ባለሟሎች እንኳን እንዲሰሙ አልተፈለገም።

ምንትዋብ የምትሆነው ጠፋት። ከቶውንም የደረሰውን ማመን
አቃታት። አጎንብሳ፣ “ወዮ እኔ! ይብላኝ ለኔ” እያለች እንባዋን አዘራች።ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ግራና ቀኝ እጆቿን ይዘው እንድትቀመጥ ግድግዳ ተጠግቶ ወደ ተቀመጠ ወንበር ሊወስዷት ሞከሩ።

“ተዉኝ... ተዉኝ! ለባሌ ላልቅስ።
ተዉኝ!” እያለች እሪ አለች።

“እቴጌ ባክዎ ለቅሶዎ እንዳይሰማ” አሏት፣ አባ ዐደራ።

“ይሰማ ይሰማ! አገር ይስማ! እኔ አለባል ልዤ አላባት መቅረታችንን...አገር ይስማ... ወዮ እኔ...ወዮ ልዢ ።”

እነኒቆላዎስ እንደ ምንም አባብለው አስቀመጧት። አንዴ ንጉሠ ነገሥቱ የተኙበትን አልጋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጣራውን ደግሞም ወለሉን እያየች እንባዋ ረገፈ። ሐዘኗ መሪር ሆነ። የደረሰባትን ድንገተኛ ሐዘን
ጫንቃዋ መቋቋም የሚችል አልመስል አላት። ዓለም አስፈሪ ቦታ ሆነችባት። ሕይወቷ ላይ የሐዘን ጥላ አጠላችበት። የመኖር ተስፋዋን ሸረሽረችው። ትናንት ማሾ እያበራች ፈለጓን የተከተለችው መሬትም
ድንገት ጨለመችባት።

አልጋ ባልጋ የመጣው የሕይወቷ መንገድ ፍጻሜው የተቃረበ
መሰላት።

እንደገና ጩኸት ጀመረች። እነኒቆላዎስ ተደናገጡ። የእሷም
ሆነ የእናቷና የአያቷ ጩኸት እንዳይሰማ ፈሩ፤ ለማባበል ሞከሩ፤ አልሆነላቸውም። ምንትዋብን ብዙ ኃላፊነት እንደሚጠብቃት ኒቆላዎስ
ለማስረዳት ቢሞክር አልሰማ አለችው።

“ባሌ ኸሞቱ ገዳም ገብቸ መመንኮስ አለብኝ” አለችው።
እንባዋ ደረቷ ላይ ይወርዳል። ያቺ ፀዳል የመሰለች ሴት ፊቷ ድንገት
ጨለማ ለብሷል። ከመቅጽበት ዕድሜዋ ላይ ዓመታት የተጨመሩ
መስለዋል። ከዐይኗም ከአፍንጫዋም የሚወርደው ፈሳሽ አልቃሻ ሕፃን ልጅ አስመስሏታል።

ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ተረበሹ። እናቷና አያቷ ለቅሷቸውን አቋርጠው በድንጋጤ ተመለከቷት።

“አዎ... ኸዝኸ በኋላ ምን ዓለም አለኝ? እኔም እንደ ባለቤቴ መሬት
እስትገባ ዓለሜ ምናኔ ነው። እሳቸው ሙተው እኔ እንዴት ባለም
ኖራለሁ? ልዤን ይዤ ኸዳለሁ” እያለች ጮኸች።

ኒቆላዎስ፣ “የለም የለም፤ እኼማ አይሆንም” አላት፣ ተጠግቷት።
“ደሞስ ምናኔ ማን ያደርስሻል? የጃንሆይ ጠላቶች ወይም ወህኒ
አምባ ያሉ ደጋፊዎች ምንገድ ላይ ጠብቀው አንቺንም ልዥሽንም
ይገድሏችኋል። ባይገድሏችሁ ስንኳ መውጫና መውረጃ የሌለው ወህኒ አምባ ወስደው ያስሯችኋል። ገዳም ብትገቢም ጃንሆይ ቅባት ሃይማኖት
ተከታይ ነበሩ ተብለው ስለሚጠረጠሩ እዚያ ብዙ የተዋሕዶ መነኩሴ ጠላቶች አሏቸው፤ ይጣሉሻል” አላት።

እሷ ግን፣ “በቁስቋሟ ተዉኝ! ተዉኝ” እያለች እጆቿን እያርገበገበች ተማጸነቻቸው።

ያን ጊዜ አባ ዐደራ፣ “እቴጌ መቸም መቀበል እንጂ ምን ማረግ ይቻላል? ኸሞት ሚቀር የለ። አሁን እርስዎ እንደዝኸ ሲሆኑ ሳንዘጋጅ የጃንሆይ መሞት የተሰማ እንደሁ ሁከት ይነሳል። ወህኒ ያሉትም እግረ ሙቃቸውን ፈተው ይመጣሉ። ንጉሥ ሞተ ሲባል ሚሆነውን እናውቃለን። ባክዎ ይጠንክሩልን” እያሉ ተለማመኗት።

ዮልያናም፣ “የኔ ልዥ! ባክሽ ጠንክሪ። እንደዝህ መሆን ደግ ማዶል” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ጠራረጉላት፣ የራሳቸውን ለመግታት
እየታገሉ።

“ልጄ በጡቴ ይዤሻለሁ! በኢያሱ ይዠሻለሁ! በምትወጃት በቁስቋም ማርያም ይዠሻለሁ! በምትወጃቸው ባባትሽ አጥንት ይሻለሁ በርቺልኝ” እያሉ እንኰዬም ሙሾ እንደሚያወርዱ ሁሉ እጃቸውን ወደ ኋላ አድርገው እንባቸውን እያዘሩ ለመኗት።

እሷ ግን እንባዋን መግታት አቃታት፤ አልጽናና አለች።

ኒቆላዎስ አንዴ እንድታዳምጠው ለምኗት የንጉሠ ነገሥቱን ኑዛዜ
ቃል በቃል ነገራት።

“ምን እንደተሰማቸው አላወቅሁም ብቻ እኔን አስጠሩኝ። ኒቆላዎስ...
ዐደራ ምልህ ልዤን... አሉኝ፣ ድምጣቸው እየተቆራረጠ። ልዤን
ኢያሱን እንድታነግሥልኝ። ለነገሥታት ሚደረገውን ሥርዐት ሁሉ... ቅባዓ ንጉሡንም ዘውዱንም... አርገህ እንዲነግሥልኝ። እናቱ ምንትዋብ
ብልህ ናት ትርዳው፤ ኸጎኑ ትሁን። እሷ አገር መምራትና... ማስተዳደር
ትችላለች። አርቆ አስተዋይና እዝጊሃር የባረካት ሰው ናት። አገሬን... አገሬን ኸልዣችን ጋር ሁና፣ ተባህር እስተ ባህር ታስተዳድር። አገሬ.. ምንም ዓይነት በደል እንዳይፈጠምባት። እኔ የዠመርሁትን ሁሉ. አጠናክረሽ ቀጥይ፤ በዐጸደ ነፍስ ኹኜም አልለይሽም በልልኝ። ሁላችሁም ቃሌን ንገሩልኝ…. ዐደራ” ብለው አንቺን እንድንጠራላቸው
ሲጠይቁ፤ ደም ባፍ ባፍንጫቸው ያለማቋረጥ ወረደ። ግዝየም አላገኙ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።”

ምንትዋብ፣ ተናግሮ ሲጨርስ ሳግ እየተናነቃት ጣሪያውን፣
ግድግዳውን፣ ወለሉን፣ ሁሉንም በየተራ ተመለከተች። እነሱ ምን
እያሰበች እንደሆነ መገመት አቃታቸው። አንዴ እርስ በእርስ እየተያዩ ሌላ ጊዜ እሷን እያዩ ከአፉ የሚወጣውን ለመስማት ተጠባበቁ።
👍111
የተጣለባትን ኃላፊነት ስፋትና ጥልቀት ተረዳች። ኢያሱ ፊቷ
ድቅን አለ። ገዳም ብትገባ ባሏ የጣሉባትን ዐደራ አለመወጣት ብቻ ሳይሆን፣ እነኒቆላዎስ እንዳሉት የልጇንና የራሷን ሕይወት አደጋ ላይ መጣል መሆኑ ቁልጭ ብሎ ታያት።

የነገሩ ክብደት ታወቃት።አያቷ ስለ ወህኒ አምባ ያወሩላትን አስታወሰች። የአፄ በካፋን
መሞት ሲሰሙ ከነገሥታት ልጆች አንዱን ከወህኒ በመጫኛ አውርደው ሲያስኮበልሉትና ያም ነጋሢ ነኝ ባይ መጥቶ ልጁን ሲገድልባት፣አለበለዚያም እሷንም ልጇንም ወህኒ ሲወረውራቸው፣ ሃገር ሲበጠበጥ፣ሕዝብ ሲያልቅ በዐይነ ኅሊናዋ በፍጥነት አለፈ፤ ሰቀጠጣት። ከሁሉ በላይ ልጇን የማዳን ስሜት መላ ሰውነቷን ገዛው። ሄደሽ እቅፍሽ ውስጥ አስገቢው የሚል ስሜት አቅበጠበጣት።

አንዳች የእምቢተኝነት ስሜት ውስጧ ሰረፀ።
ለአፍታ ሁሉንም በየተራ ተመለከተቻቸው። የሁሉም ዐይን እሷ ላይ ተተክሏል። የእሷን መልስ ለመስማት እንደሚጠባበቁ ተረዳች።

“ባላችሁት ሁሉ እስማማለሁ” ስትላቸው እርስ በእርስ ተያዩ.
ማንኛቸውም አልተናገሩም፤ ይበልጥ ለመስማት አሰፍስፈው ተጠባበቁ. ነገሮችን ሳናመቻች የጃንሆይን ማረፍ ለማንም አንናገርም::በምሥጢር መያዝ አለበት። መዠመሪያ ልጄ ይንገሥ። የልጄን ዘውድ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም” አለች።
ሁሉም በእፎይታ ተነፈሱ። ታላቅ ሸክም ከትከሻቸው ላይ የወረደ
መሰላቸው። አባ ዐደራም፣ “ጃንሆይም እኼን ነበር ያሉት” አሏት፣ራሳቸውን በአዎንታ እየነቀነቁ።

ድንገት ጥድፊያ ውስጥ ገባች። ዐይኗን ከአባ ዐደራ አንስታ ወደ
ኒቆላዎስ አዞረችና፣ “አፈንጉሥ ኢዮብን ነገ መሣፍንቱንና መኳንንቱን እንዲጠራ ንገረው” አለችው። አሰብ አደረገችና፣ “እነቢትወደድ ላፍቶን፣
ፊታውራሪ ጊዮርጊስን፣ ባሻ ኤልያስን፣ ብላቴን ጌታ ዳዊትን፣ አዛዥ ጴጥሮስን...” እያለች የብዙ መኳንንት ስም ዝርዝር ሰጠችው።
ቀደም ብለው ያዩባትን ተስፋ መቁረጥና ከባድ ሐዘን ዋጥ አድርጋ ኃላፊነት መውሰዷና ሙሉ በሙሉ ተረጋግታ ውሳኔ መስጠትና ትዕዛዝ ማስተላለፍ መቻሏ አስደነቃቸው። አፄ በካፋ፣ “እሷ አገር መምራትና ማስተዳደር ትችላለች” ያሉት ያለነገር እንዳልሆነ ተረዱ።

ወደ እልፍኝ አስከልካዮቹ ፊቷን መለስ አድርጋ፣ “ኢያሱን
አምጡልኝ። አባቱን ይሰናበት” አለቻቸው። ባስልዮስ ተቻኩሎ ወጣ።ከጥቂት ደቂቃ በኋላ፣ ባስልዮስ ኢያሱን ይዞ ገባ። ምንትዋብ ብድግ ብላ አቀፈችው። እንባዋ እንደገና እንደ ጎርፍ መውረድ ጀመረ።
“ኢያሱ የኔ ልዥ አባትህን ተሰናበት” አለችው። እጁን ይዛ ወደ አባቱ ተጠጋች። የለበሱትን ቡልኮ ገለጥ አደረገችና መልሳ ፊታቸውን ሽፈነች፤ ዘገነናት። ነገሩ ያልገባው ኢያሱ ተደናገረ።
“አባባ ለምን ተኙ?” አላት።
“ነገ ነግርሃለሁ። አሁን ደሕና ሁኑ በላቸው።”
“ደሕና ሁኑ።” ይስሙት አይስሙት አላወቀም።
እሳቸው ያሉበት ክፍል እንዲዘጋ፣ ባለሟሎቹ ምሥጢር እንዲጠብቁ
ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥታ ከነኒቆላዎስ ጋር በሚቀጥለው ቀን ለመገናኘት
ተስማምተው ተለያዩ።....

ይቀጥላል
👍6🔥1😱1
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ “ሺሕ ዓመት ንገሥ።" ምንትዋብ፣ አፄ በካፋ ወደ መሠሪ እንድትመጣ ሲልኩባት፣ ሕይወቷ ዳግም ተለወጠ። ለጥቂት ቀናት መሠሪ ሱባዔ ገብተው ስለነበር ጨርሰው ነው ብላ አስባለች። ከእናቷና ከአያቷ ጋር መሠሪ ስትደርስ፣የበካፋ ታማኝ እልፍኝ አስከልካዮች ቴዎድሮስ፣ ገላስዮስና ድንጉዜ ዐይኖቻቸው ደም መስለዋል። እጅ ነስተዋት ስትገባ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ሔዋን ግን ወዲያው ሀሳብ ውስጥ ገባች። ዓይኖ ሰማይ ላይ ተተከሉ ልቧ አድማስ ተሻግሮ ሄደ። አጠገቧ ያሉትን እናቷ ረሳቻቸው። በሆዷ እያወራች ከንፈሯቿም ይንቀሳቀሱ ጀመር።

«እሙዬ» ሲሉ እናቷ አሁንም ከሃሳቧ ቀሰቀሷት::
«አቤት እማ»
«አኪሙ የነገረሽን ረሳሽው? ብዙ ማሰብና መጨነቅ እኮ ይቺን ልብሽን ታባብስብሻለች ብሎሽ ነበር። እኔም ስታስቢ ሳይሽ እሰጋለሁ። ታድያ አንዳንዴ እንኳን ቀልብሽን ሰብሰብ አድርገሽ ሀሳብሽን መርሳት ብትሞክሪ ምን አለበት የኔ ልጅ? አሏት በሀዘን አስተያየት መልከት እያሏት::

«አይዞሽ እማ! አትጨነቂ ብዙም አላስብ። አልጨነቅም!» አለቻቸው አንገቷን ወደ መሬት ደፋ አድርጋ።
«አየየ…እሙዬ! ሁኔታሽንማ እያየሁት አይደል! መጨነቄማ
ምን ይቀራል ብለሽ የኔ ልጅ?»
አሏት በትካዜ አነጋገር።
ተይ እማ፡ እንደዚህማ ከሆነ እኔም የባሰ እጨነቅብሻለሁ! ባይሆን እኔም ማሰቤን እተዋለሁ። አንቺም እትጨነቂብኝ፡፡» አለቻቸው ዓይን ዓይናቸውን እያየች።
«እባክሽ እሙዬ እባክሽ! እንደው በአጠባሁሽ ጡት ገዝቼሻለሁና ይህን ሃሳብና ትካዜ የሚባል ነገር እርግፍ አድርገሽ ተይልኝ! የኔ ልጅ እባክሽ» አሏት እናቷ አይናቸው እንባ እስኪአቀር ድረስ ጭንቅ እያላቸው።
«ተይ እማ! በጡትሽማ አትገዝችኝ ጡትሽ እኮ ለኔ የአንቺነትሽ መገለጫ ነው የእኔነቴ መሰረት ነው። ጡትሽ እኮ ስጋና ደሜ ነው ለዚያውም አስተዳደጌን እንደነገርሽኝ ለዚያን ያህል ዓመት የጠባሁት፡፡ ስለዚህ እማ! ግዝትሽን አወርጅልኝ ድንገት ተሳስቼ ሀሳብ ውስጥ የገባሁ እንደሆነ ግዝት መተላለፌ ሲሰማኝ ይበልጥኑ እጨነቅብሻለሁ እማ! አሁኑኑ ግዝትሽን አንሺልኝ እባክሽ የኔ እናት » ስትል እጆቿን እያርገበገበች ተማፀኘቻቸው።
«እሺ የኔ ልጅ፣አወርጄልሻለሁ ::" አሏት እንባቸው ከዓይናቸው ላይ እየወረደ።
«እወድሻለው እማ!» አለችና ሄዋንም እንባዋን ከዓይኗ ላይ
ትጠርግ ጀመር፡፡ ለአፍታ ያህል በመሀላቸው ፀጥታ ሰፈነ።
«ግን እሙዬ!» ሲሉ እንደገና ጠሯት።
«አቤት እማ!»
«እንደው ለዛ ልጅ ደብዳቤ ፅፈሽለት ታውቅያለሽ?» ሲሉ ጠየቋት ወደ ዛሬዋ ዋና ጉዳያቸው
ጠጋ ጠጋ ለማለት ፈልገው፡፡
«ለማን ለአስቻለው?»
«እ»
«የት ብዬ እማ! አድራሻውን ባውቅማ ኖሮ ደብዳቤ ከመጻፍ ይልቅ…» ብላ ንግግሯን ቆም ስታደርግ እናቷ ቀጠሉ።
«አዎ የኔ ልጅ! ሀሳብሽ ገብቶኛል፡፡ እንኳን አንቺ እኔ ራሴ ብርርር ብዬ
ሄጄ የሆነውን ነገር እጠይቀው ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፣ የሄደበት አገር አጉል አጉል ሆነ፣ ምን ማድረግ እችላላሁ የኔ ልጅ!?» አሏት በሀሳብ ከጎኗ መሆናቸውን ለማረጋገጥ።

«ኤርትራ ትሄጂ ነበር እማ?»
«ለምን አልሄድ እሙዬ ለምን አልለፋ ለምን አልንክራተስ እኔ
እኮ ነገሩኝ ሁሉን ገብቶኛል። ሁሉን ነገር በእነኛ ወርቆች ዓይን አደል ያየሁት» አሉ ታፈሡን በልሁንና መርእድን በማስታወስ። ቀጠሉና «ያየሁት የልጁ ወትግራፍስ ቢሆን በቀላሉ የሚረሳኝ ሆኖ ነው? ባልወልደውም ልጄ ይመስለኛል። እንደ ወለላ የረጋ መሆኑን አውቄዋለሁ!» አሏትና እንባቸውን ከዓይናቸው ላይ ጥርግ አረጉት፡፡

በዚህ ጊዜ ሔዋን ያ ሽዋዬ ለአባትና ለእናቷ የጻፈችባት ደብዳቤ አላት።በዚያ ምክንያት በእሷም ሆነ በአስቻለው ላይ አድሮ የነብረ ስጋት ታሰባትና
ዋይ ዋይ! አለች በሆዷ። ምነው ይኸን የእናቴን ሀሳብ አውቄው ቢሆን አስቹ።

ያኔ እንዲያ እየተጨነኩ ሳስጨንቅህ! እንዲያ እያለቀስኩ ሳስለቅስህ ያን ያህል ስለኔ ስትጨነቅና ስትጠበብ ኖረህ ዛሬ እናተረ ለአንተ ያላትን እምነትና ግምት አውቀኸው ቢሆን ኖሮ ምንኛ ደስ ባለህ ነበር? የቆሰለ መንፈስህ እንዴት በሻረልህ ነበር?
ግን ምን ዋጋ አለው? ያ ሁሉ ሲሆን ቆየና የዛሬው እድልህ እንዲህ ሆኖ ቀረ አስቹ?
የ'ኔ ሆድ ምን ላርግህ! የኔ ፍቅር እንዴት ልሁንልህ፡ በማለት ውስጥ
ውስጧን ስታስብና ስትብሰለሰል ቆየችና ድንገት ለቅሶ ፈንቅሏት እህህህ ….» በማለት ተንሰፈሰፈች።
«አንቺ እሙዬ» አሉና እናቷ ድንግጥ ብለው ከመቀመጬቸው በመነሳት ወደ እሷ ሮጡ።

«እማ ተይኝ!» አለች ሔዋን ፊቷን በጭኖቿ ላይ ድፍት አድርጋ እየተንሰቀሰቀች።

«እባክሽ እሙዬ እባክሽ የኔ ልጅ እባክሽ! አረ እንደው እባክሽ?» በማለት አንገቷን እቅፍ አድርገው እሳቸውም እያለቀሱ ይለምኗት ጀመር፡፡
ሔዋን ግን እሺ አላለችም። «እንቺ የማታውቂው ብዙ ነገር በሆዴ አለ እኮ እማ! » አለች አሁንም እያለቀሰች፡፡ በዚያው ቀጠለችና አስቻለው እኮ አብሮኝ የቆየው እያለቀሰ ነው እማ ትቶኝም የሄደው እያዘነ ነው እማ አስቻለው እኮ እኔን ሲል ያላየው መከራ የለም እማዬ! ያልቀመስዉ አበሳ የለም እኮ ወደ ኤርትራ እንዲሄድ ያደረኩት እኔ እራሴ ነኝ እማ! በዚያ ላይ የሄደበት አገር ጦርነት ነው።
የዋይታና የኡኡታ ምድር ነው፡፡ አስቻለው እኮ የሚታየኝ በዚህ ሀሉ የስው ልጅ አበሳና መከራ ውስጥ ሆኖ ነው።አስቻለው ሁል ጊዜ ሲደማ ይታየኛል ሁልጊዜ ሲቆስል ይሰማኛል፡፡ አንዳንዴማ ሞቶ ሬሳው በአውሬ ሲጎተት ይታየኛል፡፡
ስቃዩ መከራው ሁሉ በእዝነ-ልቦናዬ ውስጥ አልጠፋ አለ እማ! ታዲያ እንዴት ላድርግ እማ? እንዴት ልሁነው እማ እንዴትስ አይጨንቀኝ እንዴትስ አይጥበበኝ እማ!» አለችና እሁንም «እህህህ…» በማለት በለቅሶ ተንሰፈሰፈች።

«እሱን ማሪያም ትጠብቀዋለች የኔ ልጅ እመዬ እባክሽ አታልቅሽብኝ፤
እባክሽ በአጠባሁሽ ጡት! እሙዬ አሁን ዝም በይ በቃ ተይው የኔ ልጅ» በማለት እናቷ እየተርገበገቡ ለመኗት
ሔዋን ግን ለቅሶዋ ሊበርድ እንባዋ ሊቆም አልቻለም፤ አሁንም እያለቀሰች «እት አበባ እኮ፣ እት-አበባ እኮ..» ብላ ልትቀጥል ስትል ነገሩን ተወት አደረገችው፡፡ አንደበተ ቁጥቧ ሔዋን የቱንም ያህል ያስከፋቻት ቢሆን ሽዋዬን
በእናቷ ፊት መውቀስ አልፈለገችም፡፡ ብቻ እንጀቷ እስከሚሰፈሰፍ ድረስ አሁንም
በለቅሶ ተንሰቀሰቀች።
እናቷ ግን ገብቷቸዋል፡፡ «እሷን ተያት እውዬ! ያቺን አረመኔ ተያት የኔ ልጄ ያችን ጨካኝ ተያት እሙ
እኔ ገብቶኝ የለ! ተረድቼው የለ!
እባክሽ የን ልጅ ማልቀሱ አይጠቅምም።እባክሽ ዝም በይልኝ!» ሲሉ ተማፀኗት እሳቸውም እያለቀሱ።

«እ...እሺ እማ፣ ዝ..ዝም እላለሁ ቁጭ በይ!» አለቻቸው ድምጿ፤ በሲቃ እየተቆራረጠና በእንባ የራሰ ፊቷን በመጠራረግ።
የሔዋን እናት እያለቀሱ አጠገቧ ቁጭ አሉና ዓይን ዓይኗን ያዩት ጀመር። ከትንሽ ቆይታ በኋሳ ሔዋን በረድ እያላች መጣች። ለአፍታ ያህል ፀጥታ ሰፈነ ግን ደሞ ሔዋን ሀሳብ ውሰጥ ገባች ያን የሰሜን ኢትዮጽያ ክፍል በሃሳብ ትዳስሰው ጀመር ወደዚያ ለመሄድ እንዳታስብ እንኳ እንቅፋት የሆናትን ስለ አካባቢው ያላትን ግንዛቤ ሁሉ ታሰላስል ጀመር።
አዎ፤ ያ ሰሜን ኢትዮጵያ! የጥንት ስልጣኔ መነሻ፤ የውጭ ወራሪዎች መግቢያ መውጫ! በዘመናቱ አንገታቸውን ብቅ እያረጉ ሲሰልሱት የኖረና እያወደሙም ቢሆን የወደሙበት የዘመናት የጦር አውድማ! ያ ሰሜን ኢትዮጵያ፣የውጭ ወራሪዎች በፈጠሩት መዘዝ ወንድም ከወንድሙ እየተጋጨ አንተም ተው አንተም ተው' የሚል ጠፍቶ የእርስ በእርስ መጨራረሻ ሆኖ የቀረ የደም መሬት ያ
👍71