አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

« ለምን አልሔድም ? ሰዎች ሲጠይቁኝ አጋጣሚ መሰበሩን እንግራቸዋለሁ።

ሚስዝ ቬን ከት ብላ ሣቀችባትና
«ሰዎች ቢጠይቁኝ!» አለች በማፌዝ ድምፅ የሳቤላን አባባል በመድገም «እነሱማ የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ የጌጥ
ችግረኛ ናት ብለው ከማሽሟጠጥ አልፈው ምን ሊሉ ኖረዋል ብላ አሾፈችባት።

ሳቤላ ሣቅ ብላ ራሷን ነቀነቀችና «አልማዞቹን ባለፈው የዳንስ ምሽት አይተዋቸዋል » አለቻት ።

« ይኽን በደል በኔ ላይ አድርሰሽው ቢሆን ኖሮ ፍራንሲዝ ሌቪሰን» አለችው ባልቴቷ «ለአንድ ወር ሙሉ ከቤቴ አላስደርስህም ነበር ። ምንድነው ነገሩ …...…… ኤማ? የምትሔዱ ከሆነ አሁን ሒዱ ። ዳንሱ የሚጀመረው በአራት ሰዓት ነው " በኔ ዘመን በአንድ ሰዓት ነበር የምንሔድ ፡ ዛሬ ደግሞ ሌሊቱን ወደ ቀን መለወጥ ልማድ ሆኗል ። »

« ሣልሳዊ ጆርጅ ራቱን የበግና ያትክልት ቅቅል በአንድ ሰዓት ይበላበት በነበረበት ጊዜ አለ ለአያቱ ከሚሲዝ ቬን የተሻለ አክብሮት ያልነበረው ካፒቴን ። ይኽን እየተናገሩ ደረጃዎቹን ደግፎ ሊያሳፍራት ስለፈለገ ወደ ሳቤላ ዞር አለ እንዳሰበው ይዞ ወርዶ ከሠረገላው ሲያሳፍራት ሚሲዝ ቬን ግን ብቻዋን ወርደች። በዚህ ጊዜ ይባሱን ብግን ብላ ተናደደች ።

« ደኅና እደር » አለችው ።
«ደኅና እደሩ አልላችሁም እኔም እናንተ እንደ ደረሳችሁ ተከትዬ እደርሳለሁ» አላት "

« አልመጣም ብለኸኝም አልነበር?የወንደላጤዎች ድግስ ያላችሁ መስሎኝ »

« ብዬ ነበር ግን ሐሳቤን ለወጥኩ " በይ ለአሁኑ ደኅና ሁኝ ወይዘሮ ሳቤላ "»

« እስኪ አሁን አንዲት ብጣሽ የተማሪ ሐብል አድርገሽ ያየሽ ሁሎ ምን ትመስይው ይሆን ? » አለች ሚሲዝ ቬን መነዝነዟን በመቀጠል "

« እሱስ ምንም አልነበረም ሚስዝ ቬን ? እኔን ያሳዘነኝ የመስቀሌ
መሰበር ነው ። እናቴ ልትሞት ስትል ነበር ይህን መስቀል የሰጠችኝ " ጉዳት ከማይዶርስበት ቦታ በደንብ አስቀምጬ አንዳች ችግር ሲደርስብኝ ወይም የሒሳብ እርዳታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ሲገጥመኝ እሱን እያየሁ የእናቴን ምክር ለማስታወስ በመሞከር እንድከተላቸው ነግራኝ ነበር " አሁን ግን ተሰበረብኝ ነገሩ ደስ አላለኝም " ገዱ አላማረኝም " »

በሠረገላው ውስጥ እንዳሉ የመንገዱ የጋዝ መብራት ሳቤላ ፊት ላይ ቦግ ብሎ ሲበራ ፊቷ በዕንባ እንደ ታጠበ ሚስዝ ቬን አየቻት » «አሁንም እንደገና ማልቀስ ጀመርሽ ? እኔ ልንገርሽ ! በለቅሶ ደም የለበሱ ዐይኖችሽን እያየሁ አንቺን ይዤ ከዳርት ፎርድ መስፍን ዘንድ መቅረብ አልችልም " ስለዚህ ለቅሶን የማታቆሚ ከሆነ
ሠረገላው ወደ ቤት ይዞሽ እንዲመለስ አድርጌ እኔ ብቻዬን እሔዳለሁ »

ሳቤላ በረጂሙ ተነፈሰችና ዐይኖችዋን አብሳ ዕንባዋን አደረቀች » « ስባሪዎቹን ማስቀጠል እችላለሁ " ለኔ ግን እንግዲህ ተመልሶ እንደ ዱሮው ሊሆንልኝ አይችልም»

«ለመሆኑ ስባሪዎቹንስ ከምን አዶረግሻቸው ? » አለቻት ሚስዝ ቬን በቁጣ «ይዣቸዋለሁ እኒህውና ኪስ ስለሌለኝ ነው» አለቻትና ከምኗ ላይ እንዳኖረችው
በእጅዋ አሳየቻት "

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከግብዣው ቦታ ደረሱ ሳቤላም ንዴቷን ረሳችጡ ፀሐይ መስለው የበሩት ክፍሎች ልብን የሚሰውር የሕልም ዓለም መስለው ታዩአት
ምክንያቱም ልቧ ግና በአፍለኝነቱ ነበርና የመርካት ልምድ አልነበራትም የገባችበት ቦታና ሁኔታ ብርቅና ድንቅ ሆነባት ከዚያ በድምቀቱና በውበቱ ከሰወረው አዳራሽ እንደ ገባች ይቀርብላት የነበረው የአክብሮት ሰላምታ ስታይ እጅ ስትነሣ በጆሮዋ ይንቆረቆሩ የነበሩትን የውዳሴ ቃላት ስትሰማ የተሰበረውን
መስቀል እንዴት አድርጋ ታስታውሰው !

« ታዲያስ » አለ አንድ የኦክስፎርድ ተማሪ ለቫልስ ተጨዋቾች ቦታ ለቆ ወደ
ግድግዳው እየተጠጋ «እንደዚህ ወደ መሰሉ ቦታዎች መምጣት ያቆምክ መስሎኝ ነበር " »

« አዎን ትቸው ነበር » አለ ሁለተኛዉ «አሁን ግን በማፈላለግ ላይ ስለሆንኩ ሳልወድ ተመለስኩባቸው እኔ መቸም እንደ. ዳንስ አዳራሽ የሚሰለች ነገር ያለ አይመስለኝም " »

« ምንድነው የምታፈላልገው ? »

« ሚስት ነዋ ! አባቴ እስካልተሻሻልኩና እስካልታረምኩ ድረስ ዕዳ የሚባል ነገር እንደማይከፍልልኝ ለኔም አንዲት ሽልንግ እንኳን እንደማይጥልልኝ ምሎ ተገዝቶ ገንዘብ ከልክሎኛል " አሁን ለመስተካከል የመጀመሪያ ደረጃ ብሎ ያመነበት
ሚስት ማግባት ስለሆነ የምትመስለኝን መምረጥ ይዣለሁ እንዳልተወው ማንም ከሚያስበው በላይ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቄአለሁ ።

« ታዲያ አዲሲቱን ቆንጆ አታበም እንዴ ! »

« ማናት እሷ ? »

« ሳቤላ ሼን " »

« ለጥቆማህ በጣም አመሰግናለሁ» አለው «ግን ማንም ሰው ቢሆን ክብሩን የሚጠብቅ አማት እንዲኖረው ይፈልጋል " ሎርድ ዊልያምና እኔ ተመሳሳይ አመል ስለ አለን ከዜ ብዛት ልንጋጭ እንችላለን " »

« ሁሉ ነገር እኮ ተሟልቶ አይገኝም ልጂቱ በመልኳ መሰል የላትም ።
ያ ቀጣፊ ሌቪሰን ወደ አሷ ጠጋ ጠጋ ሲል አይቸዋለሁ እሱ ዶግሞ ሴቶችን በሚመለከት ረገድ የሚያቅተው ነገር ያለ አይመስለውም" »

« ታዲያ እኮ ብዙ ጊዜ እንዳሰበ ይሆንለታል " »

« እኔ አሱን ሰውዬ አጠላዋለሁ " ጫፉን ጥቅልል እያደረገ የያበጥረሙ ጸጉሩን የሚብለጨለት ጥርሶቹንና ነጫጭ እጆቹን እያየ ያለሱ ሰው ያለ አይመስለውም » ስለ ሰው ጉዳት ምንም ስሜት የለውም ለመሆኑ ያ ተዳፍኖ የቀረ
የሚስተር ቻርተሪዝ ጉዳይ ነገሩ እንዴት ሆነ ? »

« ማን ያውቀዋል ? ሌቪሰን ከነገሩ እንዶ ዐሣ ተሙለጭልጮ ወጣ " ሴቶቹም እሱ ከፈጸመው ጥፋት በሱ የደረሰበት በደል ይበልጣል ብለው ተከራከሩለት » ከሕዝቡም ሦስት አራተኛው አመናቸው " ይኸውልህ መጣ I የዊልያም ቬን ልጅም አብራው አለች " »

ሳቤላና ሌቬሰን እየቀረቡ መጡ " ስለ መስቀሉ በድንገት መሰበር እየደጋገመ ፀፀቱን ይገልጽላት ነበር " « እንግዲህ ተመልሶ እንደ ነበረው የሚሆን አይመስለኝም» አላት ቀስ ብሎ በጆሮዋ « መቼም uመኔን በሙሎ ልባL ኀን ስልጽ
ብኖር የምተካው አይመስለኝም "

መንፈስን እያነቃቃ የደስታ ስሜትን እየነካካ ከአእምሮ የሚገባው ረጋ ያለው ሥልተኛ አነጋገሩ ጆርን የሚያስደስት ልብን የሚያሳስት አደገኛ ነበር "
ሳቤላ ቀና ብላ ስትመለከተው ዐይኖቹ ከሷ ላይ ተተክለው ሲስለመለሙ አየቻቸው እንደዚያ ያለ ቋንቋ አጋጥሟት አያውቅም ነበርና እሶም ጉንጮቿ ተለዋወጡ
ዐይኖቿ ክድን አሉ ልትናገራቸው የነበሩት ቃላት ከከንፈሯ ደርሰው ጠፉባት "

« ሰውየው አጭበርባሪ ይመስላል» አለ መኮንኑ "

« ነውና " እኔ እንኳን ስለሱ አንድ ሁለት ነገሮች ዐውቃለሁ " አሁንም ይች ልጅ ቆንጆ ስለሆነች ለዝና ሲል ልቧን ያጠፋዋል " ከሷ ለሚቀበለው ስጦታ ግን ለመመለስና የሚያስበው ውለታ የለውም».....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዌስት ሊን የፋብሪካ ወይም የአንድ ካቴድራል ከተማ ወይም የክልሉ አስተዳደር ዋና ከተማ አይደለችም" ነገር ግን ምንም እንኳን በጥንታዊ ልማዱና ባህሏ ወደ ኋላ ቀረት ያለች ብትሆንም ራሷን በተለይ ደህና ከተማ አድርጋ ትቆጥራለች ለፓርላማ ሁለት እንደራሴዎችን ትወክላለች
👍21👎1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሁለት ሳምንት አለፈው ካርለትና ከሎ የየራሳቸውን የጕዞ ዝግጅት ሲያደርጉ ሰነበቱ። ከሎ ሐመር ሲሄድ የሚያነባቸው ልብወለድና
ታሪክ ነክ የአማርኛ መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ
ልብወለድና የሳይንስ መጻሕፍትን እየገዛ ከፊሉንም እየተዋሰ
አዘጋጀ"

በተለይም ካርለት ኮተቷ በዛ" በማስታወሻዋ በዝርዝር ከያዘችው
አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶች የታሸገ የዓሣ፣ የአሳማ፣ የከብት ሥጋ የድንች የዱባ፣ ያጃ ሾርባI የፓፓያ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ
ጭማቂ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር የበዛበት ብስኩት ደረቅ ብስኩት የቆርቆሮ ቢራ ወዘተ ከመድኃኒ ዓይነትም ክሎሮኪን፣ ፓልዱሪን፣ ኒቫኩይን ለወባ መከላከያI ሌሎች፣ «አንቲባዮቲክስ» መድኃኒቶችንና የመጀመሪያ ሕክምና ኪት ኮዳክ ፊልሞችI ባትሪ
ድንጋዮችI ሶፍቶች ወዘተ. በአራት የፕላስቲh ሣጥኖች ደረደረች" ካኖንና ፔንታክስ ካሜራዋንና የተለያየ መጠን ያላቸውን ሌንሶች
በእጅ በሚንጠለጠለው ቦርሳዋ ካኪ ሱሪዎች፣ ካኔትራ፣ ውስጥ
ሱሪ ፎጣ፣ ጡት ማስያዣ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ ግራጫ  መልክ ያለው ሹራብ በአየር የሚሞላና ሌላ ተጣጣፊ ፍራሽ፣ ሳሙና፣ ኦሞ፣
ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበሩ የፒያኖ ሶናታና የፒያኖ ኮንቸቶ የቤቶቪን ሲንፎኒ ከሦስት ጊዜ በላይ
የወርቅ ዲስክ አሸናፊው ድምፃዊ የቢሊ ጆይል፤ ከሦስት መቶ ዓመት
በፊት የነበረውና የሲንፎኒ አባቱ የሃይደን እንዲሁም ሌሎቹን የባሮክ
ክላሲካል፣ ሮማንቲክና ዘመናዊ የሙዚቃ ካሴቶችን፣ ማስታወሻ፣
ብዕር መጻሕፍትና መጽሔቶች በአራት ማዕዘኑ የብረት ሣጥን
ውስጥ ከተተች" ለሽፍን ላንድ ክሩሰር ቶዮታ መኪናዋም በሁለቱም
ታንከር ነዳጅ ሞላች“ አምስት ጀሪካን ናፍጣም ለመጠባበቂያ ያዘች
ካርለት ለሦስት ወራት የሚያስፈልጋትን ቁሳቁስ ካሟላች በኋላ
ቀሪውን ዕቃዋንና ገንዘቧን ስቲቭ በሰጣት ክፍል ውስጥ
አስቀመጠች» ለአንዳንድ ወጪ ብላ የያዘችውን ሦስት ሺህ አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብርም በሹራቧ ውስጥ በሰፋችው ስውር ኪስ፣
አንገቷ ላይ በምታንጠለጥለው የጨርቅ ቦርሳና ብረት ሣጥኑ ውስጥ
አhፋፍላ ያዘች
ሰኞ ጠዋት ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ሞቢሉ
ጎን ካለው ሱቅ በር ላይ በቀጠሯቸው ተገናኙu ካርለት ልጥፍ የኋላ
ኪስ ያለው ካኪ ሱሪ፣ ተረከዙ ፕላስቲክ የሆነ ሽፍን ባለማሰሪያ
ማ፣ ቡና ዓይነት ቲ–ሸርት ለብሳ፣ አንገቷ ላይ አነስ ያለ ነጭ ፎጣ
ጣል አድርጋ፣ ከመኪናው በመውረድ የከሎን «ዩኤስኤ» የሚል
ወስፋት የነፋው የሕፃን ሆድ መስሎ የተወጠረ ቦርሳ የኋላ በሩን ከፍታ
በዕቃ ከሞላው መኪና ውስጥ በአንድ በኩል ባለው ክፍት ቦታ
አስገባችና ወደ መኪናው ውስጥ ገቡ" ካርለት የውኃ ኮዳዋን፣ ዳቦ
የያዘ ላስቲኳን አቀረበችና ከከሎና እሷ መካከል ካለው የካሴት ሣጥን
የሞዛርትን ፒያኖ ሶናታ ወደ መኪናው ቴፕ አስገብታ ማስታወሻዋን
በማውጣት የተነሡበትን ሰዓት መዘገበች" ከዚያም ፈገግ ብላ
«መሄድ እንችላለን?» አለችው።

«ኢ ህ» አላት ከሎ፣ ዝግጁ መሆኑን አንገቱን በማወዛወዝ እየገለጸ። ካርለት፣ ቀኝ እጇን ማርሹ ላይ በማስቀመጥ፣ በግራ እግሯ ፍሪሲዮኑን እረግጣ፣ የመኪናውን መስተዋት አየትየት በማድረግ
በአራት ኪሎው የድል ሐውልት ወደ ቀኝ ታጥፈው፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት አድርገው ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ወረዱ።
ከዚያም በደብረ ዘይት መንገድ ወደ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ዱከም ተጕዘው ደብረ ዘይት ከተማ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፈው ሁለት ኪሎ ሜትር በመጓዝ ዠመኪናዋን ሆራ ሆቴል አቁመው ለቁርስ ወደ ውስጥ ገቡ" በስተጀርባ፣ ከሐይቁ ትይዩ የመርከብ ላይ መናፈሻ ከሚመስለው ስፍራ ሆነው የተለያዩና ቱር ቱር እያሉ በመዘመር
የሚበሩ አዕዋፍን እያዩ ቁርሳቸውን ተመግበው ወጡ" ካርለትና ከሎ
ሆራ በሞጆ ታጥፈው፣ ወደ ሻሸመኔ ጕዟቸውን ተያያዙ“ ካርለት፣በመንገዱ ግራና ቀኝ የግራር፣ የጥድ፣ የኮሶ፣ የዝግባ...ዛፎችንና
የተለያዩ ቀለም ያላቸውን እፅዋት እያየች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚኙት ከሃያ በላይ አዕዋፋት ውስጥ የምታያቸውን በመልክና
በቅርፃቸው ለማወቅ በጆን ጂ ዊሊያምስና በኖርማን አርሎት የተጻፈውን የአዕዋፍ ምስል፣ ቀለም ባሕርይና የሚገኙበትን አካባቢ እያየች ተጓዙና ለምሳ በስምጥ ሸለቆ ካሉት ሐይቆችና የመናፈሻ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ወደ ላንጋኖ ከመንገዱ ወደ ግራ ታጥፈው ገቡ"

ላንጋኖ ሆቴል ምግብ ቤት ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች፣ አፍሪቃውያንና ኢትዮጵያውያን ክብ እየሠሩ በመጫወት ይመገባሉ። ከሆቴሉ ውጪ በቀላል ድንኳን ጥግ፣ በዋና ውስጥ ሱሪና ጡት ማስያዣ
ሆነው የፀሐይ ክሬም ሰውነታቸውን የሚቀቡና ሐይቁ ዳር ለዳር
የሚዋኙ ሴትና ወንዶች ይታያሉ" ጥቁርና ነጭ ሕፃናትም በመዋኛ
ፕላስቲክ ውኃውን በማንቦራጨቅ እየተንጫጩ ይጫወታሉ ከሎና ካርለት ከምግብ ቤቱ ትይዩ የፀሐይ ጃንጥላው ውስጥ
ተቀምጠው ቡናቸውን ሲጎነጩ ቆዩና ካርለት የሐይቁን ዳር ትርምስ
አሸጋግራ ስትቃኝ ቆይታ፣ «ሐይቅ ዳር ስሆን እረካለሁI አገሬ ውስጥ ከጓደኞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ያለሁ ስለሚመስለኝ የደስታ ስሜት ይሰማኛል" በአውሮፓ፣ ብዙዎች መዝናኛዎች የሚገኙት ባሕር ዳርቻ ነው" ብቻ...» ካርለት ከሎ ሆራን በጎን ተመለከተችው“


«ኢ ህ» አላት እግሮቹን ወደፊት በመዘርጋት ሰውነቱን ለጥጦ" ካርለት የከሎ ሆራ ጠባይ ደንቋታል ግን አልከፋትም" በቀላሉ ከምትግባባቸው ሰዎች ይልቅ አስቸጋሪ ባሕርይ ያላቸውን ታከብራለች" ሁሉም ሰው ሊረዳው የሚችል ባሕርይ ያላቸው ሰዎች ለሷ አያረኳትም" እረቀቅ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ግን አእምሮዋን
አስደንሳ መላ ፈጥራ፣ የተለያየ ስልት በመጠቀም እንደ ግል ሬዲዮና መከፈት መዝጋት እንደ መቻል
የምትረካበት ነገር የለም።
ለዚህም ካርለት «ዘመናችን የሚርጠው ልዩና ውስብስብ አስተሳሰብ ያላቸውን ነው" ምክንያቱም የነገው ፈጠራና ብሩህ
ሕልም ህላዊነት በመዳፋቸው መሃል ያለው ከእነዚህ ዓይነት ግራ
አጋቢ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ነው» ብላ ታምናለች።

ከሎ ቅንና ተባባሪ ሰው መሆኑን፣ ነገር ግን ይህን ባሕሪውን የሚገልጽ የቃላት ድርደራ ችሎታ የሚጎድለው መሆኑን ተገንዝባለች" ካርለት ከሎን የተለያዩ ነገሮችን እያወራች
እየጠየቀች የቱ እንደሚያስደስተው፣ የቱ አፍንጫውን እንደሚ
ያስነፋውና ጥንካሬውን ከደካማ ጎኑ ለመለየት ምርምሯን ስለ ቀጠለች
አንድ ወጥ በሆነው የሥውር ባሕርይው ዋሻ ለመግባት ትልቁ
የድንጋይ መዝጊያ ማንቀሳቀስ ጀምራለች።

«አዎ የከሎ ባሕርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው" እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ ማዘጋጀት አለብኝ» አለች
ካርለት፣ ከሻሸመኔ ከተማ ወጥታ የአርባ ምንጭን መንገድ ስትይዝ"
ከሻሸመኔ ትንሽ ራቅ ብለው የአስፋልቱ ጐዳና አልቆ ኮረኮንቹን መንገድ ሲጀምሩ ግን መኪናዋ እየተገጨች ስትንሰጠሰጥና ከፊት
ለፊቷ ያሉትን መኪናዎች ስታልፍና ከእሷ ተቃራኒ የሚያልፉት መኪናዎች የሚያነሡት አቧራ መኪናዋ ውስጥ እየገባ ማፈን
ሲጀምር፣ ካርለት መኪናዋን አቁማ፣ ጸጕሯን በመሸብለል፣ ቆብ
ደፋችበትና መኪናዋን በማንቀሳቀስ ከመሪው ጋር መታገል ጀመረች"
👍20🔥1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ፀጥታውን አዳመጠው፡ ይንጫጫል: ስልቱ ግን ጣፈጠው።እንደገና ጆሮውን አቁሞ ሰማ... “በዚህ ትርምስ በሞላበት ዓለም
ምናለ ፀጥታም በካሴት ታትሞ ቢሸጥ?“ ተፈላሰፈ።

ኤርቦሬ ማሕበረሰብ ውስጥ እያለ ህይወቱ ቀለል ያለ
ይመስላል። በእርግጥ ይበላል: ልብስ ግን አልነበረውም:

...ይህን ግዙልኝ መጫወቻ አምጡልኝ ኬክ ቤት
ውሰዱኝ..." ብሎ አላስቸገረም ወይንም አልተቸገረም:: እራሱን
ከጓደኞቹ ጋር በዚያ የእንቦቀቅላነት ዘመኑ አላወዳደረም: ሕይወት
ተመሳሳይ ነበረች። ራቁት ሆኖ አፈር ረጭቶ አቧራ አቡኖ ከበግና ፍየል ግልገሉች ጋር ሮጦ ነበር የኖረው።

“ተማር ህይወትህን ለውጥ ለወገንሀ ጠቃሚ ዜጋ ሁን..." ብለው ከባሕሩ አስወጡት: ያኔ እንደ ዓሣ ጨነቀው:: ግን መኖር ቻለ አዲስ ንድፈ ሃሳብን አወቀ።
አወቀ።ህልሙ ግን እውነት
አልሆነለትም ማወቅና መተግበር አራምባና ቆቦ ' መሆናቸውን ተረዳ። ተቀምጦ ታሪክ በሚያወራ ተማርሁ' ብሎ ብርጭቆ
ጨብጦ የካምፓስ ሕይወት" እያለ ከሚቦተልከው ራሱን አርቆ
ለሃገሩ ለአፍሪካ ለዓለም ለዚች ፕላኔት ቤዛ የመሆን ህልሙ አስኳሉ እንደወጣ እንቁላል ኮፈኑ ብቻ ቀረ። ኮፈኑ ይለብሳል ኮፈኑ
ያጌጣል ኮፈኑ ያዝናናል... ህሊናው ግን አፍሮ ተደብቋል።

የልመና እጆች ሲበራከቱ ማጣት ሲንሰራፋ ጥላቻና በቀል ለዚህ ማዳበሪያ እየሆነ አለመግባባትን ሲያበቅሉ እያዬ ሀዝቡን
እሚያስተምረው ስለ አተሞች በአይን ስለማይታዩት ሕዋሳት ነው::
የወገኑን ህይወት ለማይቀይረው ትምህርት ለዘመናት ባዘነ  ትምህርት ግን ማውራትን እንጂ ጥጃ መጠበቅን በጦር መሬት
ወግቶ በቆሉ መዝራትን አስረሳው። እውቀት ፈጠራ የነጮቹ ወሬ መናቆር የእኛ መሆኑን አምኖ እነሱ ሰርተው ላመጡት ግኝት ዜማ ይሰጡትና ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እያጨበጨበ እንዲዘምር ይነግሩታል።
እና! የወር ደመወዝ የሚያገኝበትን ሲዘምር ይውላል። ከዚያ ብርጭቆ
ውስጥ ተጠቅልሉ ያመሻል። ሲሞቀው እንደ ህፃን እየተወለጋገደ
ሲኮላተፍ ይተኛል።

ነገ ግን ያው ነች:: እሱም ነገን ለውጥ እንደሌላት ያውቃል፡ በትናንት የተዘራ በዛሬ የተኮተኮተ... የለም፡ እና ከነገ እንዴት ፍሬ
ይጠበቅ!

በእርግጥ በህፃንነት ዘመኑ ማንም ሳያስተምረው ያወቀው ማልቀስን ነው: ከዚያ መሰል ተፈጥሯዊ ክስተቶች ተጨማሪ ግን
ሁሉንም ነገር ለማወቅ ህሊናው ሲፈልግ እጆቹ ሲወራጩ እግሩ ሲኳትን... የእንቦቀቅላነት ዘመኑን ያሳለፈው በደስታ ነበር። ከሁለት በላይ በሆነ ባህል ውስጥ ተሰንቅሮ ይህን አትይ ያንን አትንካ እንደዚህ አትናገር ያ መጥፎ ነው ያስቀጣል ያሳስራል... እየተባለ በአዳዲስ ሃሣቦች ሲኮረኮም ሲገሰፅ ሲቆነጠጥ ኖረ:

ህሊናን የሚያዞር የህይወት ፈተና! የመፈቀርና የመጠላት እጣ የማግኘትና የማጣት የተንኮልና የጥላቻ... አንዱ እያጣደፈ
ሲያስቀምጠው ሌላው ሲያስኮፍሰው እንደ ፊኛ ሲነፋ ቱሽ ተደርጎ ሲጎድል ሕይወት ስትጥመው ስትመረው ያዝኩሽ ሲላት
ስትርቀው ራቅሽ ሲላት ቅርብ ነኝ እያለች ስትሸነግለው ኖረ።
ዛሬና ትናንት እንዲሁ በተስፋና ቅዠት አለፉ። ነገ ደግሞ አካሉ ያረጃል መንፈሱ ይደክማል ውበቱ ይረግፋል... ያኔ ይቆዝማል
ህይወት ግን ማዕበል አሳሯን እንደሚያሳያት ጀልባ እየዋዠቀች እንኳ የምትጥም ትሆንበታለች ህሊናው ሁሉም ያልፋል በሚል እምነት ቢታጨቅም የሚተማመንበት ያጣል መኖሩን ማሪጋገጥ
አይችልም ልቡ በፍቅር ቢጠማም ጥም መቁረጫውን አያገኝም።
መስታዋት የማያ ሰበቡ ይጠፋል... ከስዎች ጋር እንዳልናረ ሁሉ ያለፈ ህይወቱን ሲከልሰው ብቻውን ጡል ጡል እያለ መኖሩን ይረዳል። ይህን ሲያስብ ያሳላፈው ህይወት ጣምናው ይጠፋዋል።
ስለዚህ “መጥኔ... አይ ህይወት...” እያለ እየተትከነከነ ወደዚያ አቀበት
ይኳትናል  ወደ ሞት ሲረግጣት የኖረችው ምድር ስትውጠው እስትንፋሉ ሲቆም. ያኔ “...ይብላኝ ለቋሚ ( ሟችስ ጣጣውን ጨርሶ ወደ እውነተኛው ዓለም ሄዴ.. ተገላገለ” ይባላል። ይህም ግን
“ይባላል" ነው። ተዚያ ወዲያ ሕይወት የግል ሚስጥር ነች ለተጓዦች!

ሶራም ይህን ተራራ መውጣቱን ተያይዞታል: ጫፉ ዳመና  ውስጥ የገባው ተራራ ግን መንገድ አልባ እሾህ የበዛበት
የሚያንሸራትተው የበረከተ... አስፈሪ ነው:: ያለፉበትን ሲያዩት ያስፈራል
ገና የሚወጡት ደግሞ ከማስፈራራትም ያስጨንቃል: በዚያ ላይ የሚፈራረቀው ብርሐንና ጨለማ ቆፈንና ሙቀት. ያታከታል።

መፅናኛው ግን ብዙ ነው: ጠኔ ያስቸገረው አካለ ስንኩሉ የእለት ጉርሱ ያጣው በሽተኛው ያን ሲያዘይ የሙከራ ጥረቱ
ይጨምራል... ካሰበው ቦታ ስለመድረሱ ግን ማረጋገጫ ያለው የለም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ህሊናው አካሉን እየቧጨረ እየታገለ... እረፍት ሲነሳው
እንደቆየ የቤቱ በር ተንኳኳ።

“ይግቡ...” አለ በታከተ ድምፅ ቅላፄ። ደሞ ማን ይሆን እንደ መርዶ ነጋሪ በጠዋቱ የመጣብኝ' እያለ በር በሩን እያዬ በሩ በዝግታ ሲጢጥ…” ብሉ ሲከፈት ተረከዘ ሎሚ ከበሩ ግርጌ
ተመለከተ።

ማናት...?” አለ ግራ እየገባው ከዚያ ከተጋደመበት ቀና
ብሎ አይኑን እንደ አበያ በሬ አፍጥጦ ጆሮውን እንደ ጥንቸል ቀሰረ:

ግቢ... ማን ልበል?"  ያላሰበውን ዓረፍተ  ነገር ከራሱ አንደበት ሲወጣ ተስማው። እንግዳዋ ረጋ ብላ ወደ ውስጥ ዘለቀች።

“ይቅርታ!... ካለቀጠሮ በመምጣቴ...” አለችው የቤቱ ብርሃን ደብዘዝ ስላለባት አይኖችዋን ፈጠጥ አድርጋ፡

"ምንም አይደለም” ብሎ ፈገግ አለ፡ ማንነቷን ለማወቅ ህሊናውን ውለዳት ቢለውም ሊያገኛት ሊያውቃት አልቻለም።
ከመቀመጫው ተነሳና ወንበር ቀረብ አድርጎላት! “እዚህ ላይ አረፍ በያ! እያለ እሁንም ሊያስታውሳት ሞከረ: መልኳን ከዚህ በፊት
ያየው መሰለው። የት ነው የማውቃት?' ጠየቀ ራሱን።

"ካለቀጠሮ በመምጣቴ ይቅርታ" አለችውና አንገቷን ደፋች፡፡ “ለነገሩ  ቀጠሮ  አስፈላጊ ነበር ለማለትም ይከብደኛል" ቀና ብላ
አይታው አሁንም ሃሳቧን ገታችበት።
በሃሳቡ! ቀጠሮ የምን ቀጠሮ?' ብሎ እንዳሰበ በመላምት ህሊናውን አገለባበጠና ሃሳቡን ማጠቃለያ ላይ ለጊዜው ደረሰ: ልቡን ደስ አለው፡ ሴት ልጅ አፈቀርሁህ ብላው አታውቅም እሱ ግን ብዙ
ሌሊት ኮርኒሱን በአይኑ ሲቧጥጥ ቀን ላይ እንደ ክምር ፈጅ ገመሬ
ዝንጀሮ በአይኑ መሬት ሲያርስ ኖሯል፡

“ለጊዜው የኔም ቤት  የተከራየሁት ማለቴ ነው ከዚህ ብዙም አይቀርም። የማልኮራበትም ስራ አለኝ አለችና አሁንም በስርቆሽ ተመለከተችው።

ላቡ ግንባሩ ላይ ተንቸረፈፈ: ተቀጥቶ አፍህን ያዝ
እንደተባለ ህፃንም የፍርሃቱ ሳግ ላይ ላይ ሲያቃትተው

“ምን ነካኝ?” ብሎ
ተወራጨ። እግሮቹን እየቀያየረ አነባበራቸው፡ እጆቹን እንደ ሙሾ አውራጅ አወዛወዛቸው:

“ተናኘ... ተናኘ ወርቅ
እባላለሁ። ቶምም ይሉኛል
የሚቀርቡኝ:: ብዙ ጊዜ እንደ ቶማስ ሳላይ አላምንም ስለምል: ስለ ቶማስ ታውቃለህ መቼም? ቀና ብላ አየችው:

“አዎ! እየሱስ ሞትን ነስቶ ወደ ደቀመዝሙሮቹ መጥቶ
“እኔ ነኝ' ሲላቸው ካላየሁ አላምንም' ያለውን ነው" አላት። ፈገግ ብላ ትክክል መሆኑን አረጋገጠችለት “ሻይ ቡና” ምርጫ አቀረበላት:

“ኡፍ አንተም የሞቀ ውሃ ሰጥተህ የሚተናነቀኝን ቁልቁል ልታወርደው ትፈልጋለህ?" ነብር ሆነችበት አራስ ነብር::
👍26😁3
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሦስት

አስተናጋጅ ሆኜ ከተቀጠርኩ አንድ አመት  አለፈኝ።በሲቪዬ ላይ የስራ ልምድ በሚለው ርዕስ ስር የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እና የሆቴል አስተናጋጅነት የአንድ አመት የስራ ልምድ የሚለውን አስገብቼ መፃፍ እችላለሁ፤አዎ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም።እያንዳንዱን የሠው ትዕዛዝ በትሪ ይዤ አቀርብና በዛው ትሪ ባህሪያቸውን  ያስረክቡኛል። ትሁቱ... ቁጡ.. ጉረኛ... ጋግርታም... እርብትብት... ለጋስ...ንፉግና ተነጫናጭ...በየቀኑ ፀባዩ የሚገለባበጥ ሙልጭልጭ በቃ እኔ ትምህርት ሚኒስቴርን ብሆን ኖሮ ሳይኮሎጂ እና ሶሾሎጂ ለሚያጠኑ  ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ቢያንስ ለስድስት ወር እንደዚህ አይነት ቦታ አፓረንት እንዲወጡ አደርጋቸው ነበር..ሆቴል ማለት የሠው ባህሪ በብፌ መልክ የሚቀርብበት ቦታ እኮ   ነው።

አሁን ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል ፡፡ባሩ ውስጥ አንድ ተስተናጋጅ ብቻ ነው ያለው፡፡ ለዛውም ሴት ደንበኛ...፡፡ይሄንን ብላክ ሌብል  ትጋተዋለች ።አሁን አሷ ብትወጣልን ሌላ የቀረን ስራ ስለሌለን ወደየቤታችን እንሄድና አረፍ እንል  ነበር ስል አሰብኩ ስናስተናግድ ከነበረነው  ስምንት ሴትና አራት ወንድ አስተናጋጆች መካከል አምስቱ ሴት ቀድመው መውጫ ቆርጠው ሄደዋል?ምን? መውጫ ምንድነው ?አላችሁኝ... መውጫ ማለት አንድ ሴት አብሯት የሚያድር ሰው አግኝታ የስራ ሰዓቷ ከመጠናቀቁ በፊት መውጣትና ከደንበኛዋ ጋር መሄድ ከፈለገች እንደሰዓቱ እየታየ ከምታገኘው ላይ እንድትከፍል ይደረጋል...ያው ግብር በሉት ።
ብዙውን ጊዜ በኢትዬጵያ የቡና ቤት ሴቶች ግብር አይከፍሉም ይባላል..እኔም እንደዛ አምን ነበር፡፡ አሁን ግን እንዲህ ተጠግቼ ሳይ አመት እስከ አመት እንደውም እንደእነሱ የሚከፍል የለም? ያው ግብር ማለት ከደሀው  መቀነት  ተቀንሶ  ለኃያላኑ ጡንቻ ማፈርጠሚያ  በግዳጅም ይሁን በይሁንታ የሚሰጥ መባ ነው።ኃያሉ መንግስት ሊሆን ይችላል..ባለሀብት ሊሆን ይችላል...የሠፈር አስተዳዳሪ ባለጡንቻ ሊሆን ይችላል...፡፡  ሁሉም በሚስኪኑ ደሀ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ ከርሱን የሚሞላ  ብልጉ አውሬ ነው...ውይ በማሪያም አለቃዬን ነው ከሌላው ባለጉልበት ጨምሬ እንዲህ የጨፈጨፍኩት .አምላክ ሰምቶ ውለታ ቢስ ብሎ እንዳይቀየመኝ፡፡

አሁን ሆቴል ውስጥ የቀረነው ሁለት ወንድ  አስተናጋጆች እና አንድ ሴት አስተናጋጅ እና ደግሞ የእለቱን የተሰራ ሂሳብ ተረክቦ   እየደመረ ያለው ባሉካ ብቻ ነኝ...ሽኩክ ብዬ ወደእሱ ሄድኩና ፡፡
"ጋሼ እንዴት ነው?"

"ስለምኑ ነው የምትጠይቀኝ ጎረምሳው?"

‹‹ስድስት ሰዓት ሊሆን ነው...ተስተናጋጇን ልንዘጋ ነው ልበላት እንዴ?"

"አይ አይሆንም...ትልቅ ደንበኛችን ነች ..ቅር እንዲላት አልፈልግም.."

"አይ ለእሷም ቢሆን ይመሽባታል ብዬ እኮ ነው፡፡"

"የእኔ አሳቢ አይመሽባትም... ከተቀመጠችበት ተነስትታ አስር እርምጃ ከተራመደች የተከራየችበት ቤርጎ ትደርሳለች"

"ኦ ረስቼው… ለካ እዚህ ነው አልጋ የያዘችው"

"አዎ ባይሆን ልጇቹ ይግቡ ..ንገራቸው፡፡"

"እሺ ግን ጋሼ እሷ እስክትሄድ ብቻህን ልትሆን ነው?"

"አይ እኔ አይደለሁም ቀርቼ የማስተናግዳት ...አንተነህ.፡፡..በራሷ  ጊዜ በቅቷት ስትሄድ ቆላልፍና ሂድ...እኔ ሚስቴ ትጠብቀኛለች ...አንተ ከአይጥ ጋር ድብብቆሽ ለመጫወት ምን አስቸኮለህ?››

‹‹እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር የማወራው ነገር ተደብቆ ይሰማል እንዴ...?"ስል በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ከሶስት ቀን በፊት ነበር ለሴቶቹ አንድ አይጥ አላስተኛ እንዳለቺኝና ልክ ስተኛ ጆሮዬን እየቀረጠፈች፤ ከንፈሬን እየነከሰች  አስቸገረችኝ ብዬ ያወራኋቸው...እነሱ ደግሞ አፍቅራህ ነው እያሉ ሲያሾፍብኝ ነበር..ይሄው አሁን ጋሼም ተቀላቀላቸው...
ጋሼ ሂሳቡን ሰርቶ ጨርሶ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"ጋሼ ለመቆየቱ ግን ካሌብ አይሻልም?"

"ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?...መልካም አዳር"ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ...፡፡እኔም ሌሎቹ እንዲሄዱ ተናግሬ በዛ ውድቅት ለሊት ከአንድ እንስት ተስተናጋጅ ጋር ተፋጥጬ ተቀመጥኩ...፡፡
እኔም እንደሌሎች በዚህ ሰአት ክፍሌ ገብቼ አረፍ ባለማለቴ ከፍቶኛል ..ግን ደግሞ ጋሼ የተናገራት ነገር ልቤ ላይ አሪፍ  ደስታና ኩራትን አርከፋክፋብኛለች "ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?ነበር ያለኝ አይደል?፡፡ "በእውነት መታመን ያስደስታል" ለዛውም አንድ አመት ባልበለጠው ጊዜ ውስጥ ይህን መሳይ ክብር ማግኘት ተስፋው ለፈረሰበት ሰውም ቢሆን  በህይወቱ ጥቂት መነቃቃትን ይፈጥራል፡፡

ጠረጴዛው ተንኳኳ ከነበርኩበት ባንኮኒ ውስጥ ፡ሮጬ ወጣሁና  ወደ ተጠራሁበት ቀርቤ፤ እጇቼን ወደኃላዬ አጣምሬ፤ ከጉልበቴ ሸብረክ ፤ ከአንገቴ ጎንበስ ብዬ"አቤት ምን ጎደለ ? ምን ላምጣ?"አልኩ፡፡

"እ ..ምንድነበር..?."በፈጣሪ ሰክራለች መሠለኝ ..?ለምን እንደጠራችኝ እንኳን  አታውቅም፡፡
"አዎ..ሙዚቃውን በጣም ቀንሰው እናም አንድ ብርጭቆ አምጣልኝ"
ወይ ፈጣሪዬ ሴትዬዋ ገና መጠጣት ልትጀምር ነው..ለዛውም በሁለት ብርጭቆ…. እንዳለችኝ የሙዚቃውን ድምፅ  ቀነስኩና ብርጭቆውን አጣጥቤ ይዤላት ሄጄ ጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጥኩላትና ልመለስ ስል "ተቀመጥ"አለችኝ...
ተቀመጥ በሚለው ቃሏ ውስጥ ምንም አይነት ትህትናም ሆነ ሀዘኔታ አይነበብም፡፡.

"ምን አልሺኝ እመቤቴ?"

"ቁጭ በል..ንግግሬ አይሰማም እንዴ?"

"ኸረ በደንብ ይሰማል"ብዬ ትዕዛዟን በማክበር ሽኩክ ብዬ ቁጭ አልኩ..ፊቷ የተቀመጠውን  የተጋመሰ ብላክ ሌብል ጠርሙስ አነሳችና አዲስ ያመጣሁት ብርጭቆ ውስጥ አንደቀደቀችው፤ስትጨርስ  ወደፊት ለፊቴ አሽከርክራ አሰጠጋችው።

"ኸረ ይሄ ነገር ለእኔ አይሆንም?"

"ባክህ አትንጠባረር ..ዝም ብለህ ጠጣ "ብላኝ እርፍ...
አሁን ይሄ ግብዠ ነው አስገድዷ ደፈራ፡፡ፈራኋት መሠለኝ አነስሁና አንዴ ጎንጨት አልኩለት...
.፡፡‹‹እራት መቼ ነበር የበላሁት?›› ስል እራሴን ጠየቅኩ፡፡ አዎ 12፡30 አካባቢ....‹‹ምንድ ነበር የበላሁት?›› ዳቦ በሙዝ ...፡፡.ሶስት ሙዝና ሁለት ዶቦ....፡፡‹‹አሁን ከስድስት ሰዓት በኃላ ምን እየጠጣሁ ነው›› ውስኪ፡፡...‹‹ይህቺ ጋባዤ አራት ሰዓት አካባቢ ምንድነበር ያዘዘችው..?››ለማስታወስ ሞከርኩ...አዎ ክትፎ ነበረ ያዘዘችው እናም ግማሹን በልታ ግማሹ እንደተመለሠ አይቼያለሁ....አሁን ኪችን ብገባ ግማሹን ትራፊ አገኝ ይሆን?

"እዚህ ሀገር ለስራ መጥተሽ ነው?"ጥያቄውን መጠየቅ ፈልጌ ሳይሆን ዝም ብሎ መቀመጥ ስለጨነቀኝ ነው የቀባጠርኩት። ቢዝነስ የሚሰሩ ሴት  አስተናጋጆች ግን  እንዴት ብለው ነው ከማያውቁት ሰው ፊት ለፊት ተቀምጠው ዘና ብለው የሚጠጡት...ከዛም አልፎ የሚስቁት፤ የሚጫወቱት?ለዛውም በየቀኑ…፡፡ጥያቄዬን ሰምታ ሲጋራዋን ለኮሰች ...እናም ጭሱን አትጎልጉላ እላዬ ላይ በተነችብኝ ፡፡...ልክ እንደቤተመቅደስ ማዕጠንት ዝም ብዬ በፀጋ ተቀበልኩና ወደውስጤ ማግኩት?

"ምሽቱ ደስ ይላል..."ሌላ የማይረባ አስተያየት ከአንደበቴ ድንገት ሾለከ፡፡

"ምሽቱ አንተን ነው የሚመስለው?"አለችኝ፡፡
👍522👎1👏1
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሦስት

ካርለት መሳተፍ የማትችለውን የሽማግሎች ስብሰባ በርቀት
እየተመለከተች አልፎ አልፎም የካሜራ ችፕስ  በተደረገበት ባለዙም ካሜራዋ ፎቶ ስታነሳ ቆይታ ጎይቲን ፍለጋ ወደ መንደር
ተመለሰች

"ካርለት ነጋያ ... ነጋያ ... ያ ፈያው" አሉ ህፃናት የካርለትን ነጭ እጅ ለመያዝ እየተሽቀዳደሙ "ነጋያኒ  ጎይቲ ዳ! ደህና ነኝ
ጎይቲ አለች ብላ ጠየቀቻቸው በሐመርኛ

"እእ  ዳኒ" አለች አንዷ ህፃን ራሷን ዝቅ አድርጋ ሽቅብ
በመናጥ አለች ለማለት ካርለት  መዝጊያ ወደሌለው መግቢያ ጎንበስ ብላ በጠባቧ በር ወደ ውስጥ ስታይ ምርግ በሌለው የእንጨት መከታ መሐል ለመሐል በሚገባው ብርሃን ጎይቲ በርከክ ብላ እጆችደ
ከወፍጮው መጅ ላይ ሳይነሱ ራሷን ብቻ ወደ በሩ መልሳ አየቻትደ ካርለት የጎይቲን ማራኪ ፈገግታና የምትወደውን ጥርሷን ስታይ የደስታ ስሜት ውርር አድርጓት እሷም ሳቀች  ተሳሳቁ"

"አርዳ?" አለች ጎይቲ በአንገቷ እንደምትስባት ሁሉ አገጯን ወደ ታች እየሰበቀች ካርለት ፈገግ እንዳለች እሷን፥ ከኋላዋ
የተንጠለጠሉትን የቁርበት ልብሶች ግርግሙ ላይ የተንጠለጠሉትን
ዶላዎች (የወተት መያዣዎች) ግልጥጥ ያለውን የምድጃ ፍም:
በቀበቶው ጉጥ ላይ ቁልቁል የተንጠለጠለውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ
ልጆች አመዱን በውሃ በጥብጠው መግቢያው ጥግ ባለው የግድግዳ
ልጥፍ ላይ ያዩትን ለመሳል ያደረጉትን ጥረት ... በዐይኗ ስትቃኝ.

"አርዳ!" አለች ጎይቲ ደግማ አትገቢም! ለማለት ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

"ፈያኔ" ብላ ካርለት እንደ ጅራት ከኋላዋ የተንጠለጠለውን
የፍዬል ቆዳዋን በግራ እጅዋ ወደ እግሮችዋ መሐል አስገብታ ቀኝ
እግሯን በማስቀደም በጠባቧ በር ሹልክ ብላ ገባች የሐመር ቤት
መዝጊያ የለውም  ቀንም ሆነ ማታ እንግዳ የአባት ሙት መንፈስ ከመጣ ሁሌም ሳይጠብቅ: ደጅ ሳይጠና ሰተት ብሎ መግባት አለበት ትንሽዋ በር ደፍዋ ከፍ ያለ በመሆኑ ለከብትም ሆነ ለአውሬ
ለመግባት አታመችም ቤት ለሐመሮች መቀመጫና መተኛ እንጂ መቆሚያ  አይደለም"  ሁሉም ነገር ትርጉም  ሊኖረው ይገባል
ስለሆነም ካለ ህፃናት በስተቀር በጣም አጭር ሰው እንኳ ጎንበስ ብሎ
ካልሆነ መቆም አይችልም ይህ የሆነው ደግሞ እንጨት ጠፍቶ ቦታ
ጠቦ ሳይሆን ለትርጉሙ ነው"

"ጎይቲ?"

"ዬ!"

ምነው ዛሬስ ስትፈጭ መዝፈን: ማንጎራጎሩን ተውሽው?" ብላ ጠይቃት ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን ሳመቻት እንደ
ሐመር ሴቶች የልብ ሰላምታ ጎይቲ ካርለት ለጠየቀቻት መልስ  ሳትሰጥ አንገቷን ደፍታ እጅዋ ወፍጮው
መጅ ላይ እንዳለ በተመስጦ ስታስብ ቆይታ በቀኝ እጅዋ ማሽላውን ግራና ቀኝ ሰብስባ  ወደ ወፍጮው ጥርስ አስገብታ
ወገቧን ወደ ኋላና ወደ ፊት
እያረገረገች "ሸርደም: ሸርደም አድርጋ ፈጨችውና ብርኩማዋ ላይ ተቀመጠች
ከዚያ እኒያን ሐጫ በረዶ የመሳሰሉ ጥርሶችዋን
ገልጣ ለዓመል ያህል ፈርጠም አለችና

"ይእ!ካርለቴ ኧረ አሁን ሳንጎራጉር ነበር መቼ
እንጉርጉሮዬን እንደ አቆምኩት ግን እንጃ! አዝኜ እንኳን ቢሆን ሁልጊዜ መፍጨት ስጀምር እህሉ ከታች ሲደቅ እኔ ከላይ ትዝታዬን እየጨመርሁ እንጉርጉሮዬን አቀልጠው ነበር አሁን እኮ ኮቶ እግሯ
ወጣ ከማለቱ ነው አንች የመጣሽ ከኮቶ ጋር እየተከራከርን ሁላ እዘፍን ነበር  በኋላ ግን ኮቶ ለመሄድ ስትቁነጠነጥ እያወራች እንድትቆይ ብዙ
ክርክር ገጠምኋት
ታውቂያታለሽ ተከራክራ ተከራክራ ካልረታች እንደ ፍየል ልዋጋ ስትል ታስቀኛለች ስለዚህ ጥላኝ ከምትሄድ ብዬ ነገር ጀመርኋት

"ኮቶ ከተማ አትሄጅም?" ስላት

"ይእ! ኧረ ምን አልሁሽ እቴ እኔስ ያገሬ ጅብ ይብላኝ
አለችኝ ትንሽ ላስለፍልፋት ብዬ እኔ ግን መበላቴ ታልቀረ የጅብ ዘመድ አልመርጥም አልኋት አይምሰልሽ ጅሊት! ያገርሽ ጅብ ገሎ ነው የሚበላሽ  የሰው አገር ጅብ ግን እየበላ ነው የሚገልሽ ስትለኝ ይእ! አንች ምነው ታልጠፋ አውሬ ጅብን እንዲህ ዘመድ
አዋቂ አደረግሽው?
አልኳት‥ ይሄ እንኳ ምሳሌ ነው ስትለኝ ሞጥሟጤ  ምሳሌሽን ቀይሪያ!ታለበለዚያ ካለ
ጥንባቸው ሌላ
የማያውቁትን ጅቦች ካለስማቸው
ስም ሰጥተሽ ቅዱስ አድርገሽ ታውሬው ሁሉ አታቀያይሚያቸው" ብላት ወገቤን ደቅታኝ ሹልክ ብላ ሄደች ከዚያ ማንጎራጎር ጀምሬ ነበር ወዲያው ግን ድምፄ ለከት የለሽ ሆኖ ልቤ ግንድ የሚያመሽክ ምስጥ ይርመሰመስበት ጀመር

"ምን ሆነሽ ነው ጎይቲ የምን ጭንቀት ነው?"

"ወደው አይስቁ አለ ያገሬ ሰው ..." ብላ ጎይቲ ከትከት ብላ ስቃ።

"ይእ! ምነው እንዳንች ጅል ሆኜ እድሜ ልኬን ስጠይቅ
በኖርሁ" ስትላት ተያይዘው እንደገና ተሳሳቁ

"ካርለቴ! እውን ሴት ልጅ እግርና እጅዋ የሚያጥረው፥
ቀትረ ቀላል ሆና ድምጿ የሚሰለው ... ለምን እንደሆን አታውቂም?

"አላውቅም ጎይቲ ለምንድን ነው?"

"ይእ! እንግዲያ ዝናብ እንደበዛበት ማሽላ ታለ ፍሬ መለል ብለሽ ያደግሽ አገዳ ነሻ! ሙች አንችስ ተህፃን አትሻይም አንቺ እኮ! ተንግዲህ ወዲያ ትልቅ ሰው ነሽ! ጉያሽና ልብሽ ላይ የትዝታ ምሰሶ የተተከለ
ፈጭተሽ የምታበይ ጭሮሽ ውሃ ቀድተሽ ለጥም
መቁረጫ የምታጠጭ
የወንድ ልብ ሲጎመራ ጫካ መሃል ገብተሽ የምትካፈይ
ፍቅርሽን እንደ ህፃን ልጅሽ የምትግች ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?" ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?"

"ጎይቲ የባሰ ግራ ገባኝ?"

"ይእ! እንዲያ ይሻላል! ቁም ነገር አታውቂም ብዬ ተመንገር ሌላ እህ ላሳይሽ?"  ብላ ጎይቲ በአድናቆት ጨብጨብ ጨብጨብ አድርጋ በሣቅ ተፍለቀለቀች

ካርለት ከተቀመጠችበት
ፈገግ ብላ ተነስታ ጎይቲን ገፋ አድርጋት የወፍጮውን መጅ በግራ እጅዋ ይዛ ከሾርቃው በቀኝ
እጅዋ ማሽላውን አፍሳ ጨምራ

"እሽ እኔ እፈጫለሁ አንች ንገሪኝ?" አለቻት

"ይእ! እውነት ታላወቅሽውማ እነግርሻለሁ  እንጂ ብላ እግሯን ዘርግታ ቁርበቱ ላይ ቁጭ አለች ጎይቲ ወደ ቁምነገር
ስትመለስ የሚያስጨንቃትን
ለመናገር ስትዘጋጅ ውስጧን የሚጎማምደው ችግሯ የፈገግታ ፀዳሏን እየቸለሰ አከሰመው ደሟ
እንደቀትር ማዕበል ደረቱን ገልብጦ እየዘለለ በመፍረጥ አረፋ ደፈቀ
ታወከ
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ የግል ችግር የለባትም እምትበላውን መሬቷ እምትጠጣውን ላሞች: ፍቅርን ደግሞ የሐመር ወንዶች እንደ ማሽላ ገንፎ እያድበለበሉ ያውጧታል ሴት ልጅ ወንዝ
ብትሄድ እንጨት ለቀማ ጫካ ብትገባ እህል ልታቀና ገበያ ብትወጣ ብቻዋን አትሆንም ሰው ከብቶች: ዛፎች አሉላት ሴት ብቻዋን ችግር የሚገጥማት የማትወልድ ስትሆን ነው መሐንነት ትታይሻለች ያች ፀሐይ " ዝቅ ብላ በግርግዳው ቀዳዳ ጮራዋን ፈንጥቃ የምትንቦገቦገውን የረፋድ ፀሐይ እያሳየቻት

"ይኸውልሽ መሐንነት ያችን በሙቀት የምትነድ እሳት ዘላለም እንደ ጨቅላ ህፃን ደረትሽ ላይ ታቅፈሽ መኖር: ታቅፈሽ መሞት ነው" ተዚያ እድሜ ልክሽን መቃጠል: መንደድ ነው"

"መሐንነቱ የመጣብሽ ሳታስቢው የሴት ብልትሽን ውሃ ነክቶት ይሆናል ሆን ብለሽ ባታደርጊውም ትዕዛዝ ነውና ቅጣቱ ቃጠሎው ወደ ገለብ ብትሮጭም አታመልጭውም ስትቃጠይ ደግሞ ሰው የሻጉራ እያዬ ይሸሽሻል ባይሆን ከቃጠሎሽ  ባይጠቅምሽም
ለእነሱም ባይጠቅማቸውም ለአባትሽ ለእናትሽ ለእህትሽ
ለዘመዶችሽ ታካፍያቸዋለሽ የተረገመ ቤተሰብ እያሰኘሽ" ብላ ዝም አለች ጎይቲ  እንደተላጠ ጣውላ ሰውነቷ ሟሾ

ግዙፍነት ለካ በአጥንትና ስጋ ብቻ አይደለምና  መጠንም በህሊና ይወሰናል ውበትና ቁመና ህሊና በሚፈጥረው መተማመን ተገዥ ነውና! እያለች ካርለት ጎይቲን እያየች ስታስብ
👍19👎1