#የአራዳ_ልጅ_ሽለላ
ጎራው...ና...ጎራው...ና...ጎራው...ና
ጎራው...ና...ጎራው...ና....ጎራው...ና
ጎራው...ና እያለ ማነዉ የሚጣራ
ጎራው...ና እያለ ማነዉ የሚጣራ በሉ እናተ ሂዱ
እኔስ ፀብን ፈራሁ ተዉኝ
ጎራው.. ተወኝ ጎራው
ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ ! ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ !
ቢገርፈኝ እንኳን ሱስ እንዳለጋ ኑሮ እንደ ጅራፍ ማልደራደር ባንዲት አገሬ
እንደ ፕሪም ዛፍ እንደ ፖም ፍሬ
መንግስትን ላወርድ ድንጋይ ወርዉሬ
አልሳካ ሲል ከሀዘኔ ላይ ሳቅ የምቀጥል
የመንግስትን ስም ባሽሙር በነገር የማብጠለጥል
ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ ! ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ !
አልሞ ተኳሽ አነጣጣሪ
የሚጨማደድ ሸሚዝ ወይ ሱሪ
በወፍ ወስፈንጥር ሰዉ አባራሪ
#ዘራፍ
በሰዉ ካዉያ በሰዉ እሳት
እንዴት መተኮስ አወቀበት
ብለዉ ለሚሉ አራዳ መልሱ
ሲለብስ ይታያል አተኳኮሱ
#ዘራፍ
በል በለዉና ይምጣ የመጣዉ
ከሀገር ቀድሞ ትግል የወጣዉ
በባዶ እጁ ታንክ የማረከ
ወያኔ ሌባ የሚለውን ስድብ የፈበረከ
ፀረ ዘረኛ ስመ ቅምጥል
በኮብል ስቶን ጠመንጃ የሚያስጥል
የቀበሌ አጥር የሚገነጥል
ከቻይና ጫማ ፍቅሩ የሚያቃጥል
#ዘራፍ
ቄሮና ፋኖ ዘርማ ሳይኖሩ
ተነስ እያለ ላንዲት አገሩ
ላንዲት ባንዲራ ሁሉ አንዲታገል
የቀሰቀሰክ ሳትመነገል
መሪ ኮከብክ ለሰባ ሰገል
ያዲሳባ ልጅ ስሙ ያራዳ
ቀለም ያልቀባ በመኪና አሰፋልት በሰዉ ግድግዳ
በመንጋ ስሜት የማይነዳ
ሰዉ ሀገር ነዉ ባይ ሰዉ የማይጎዳ
#ዘራፍ
ያዲሳባ ልጅ ያራዳ ልቡ ሰውን ከፍ አድርጎ ልክ አንደ ሰንደቅ የሚያዉለበልብ ቢያገኝ አካፋይ ቢያጣ የሚያዝን
ከሚዛን በላይ የሚያመዛዝን
ራሱን የማያኖር ሰዎችን ቀብሮ
ብይ የሚጫወት ጉድጓድ ቆፍሮ
ቀስት ባይኖረዉ ቀልዱን ወርዉሮ
ሺህ መሳይ ገዳይ በሙቀት ጥላ በብርድ ፀሀይ
መሆን የሚቻለዉ እንደ ሁኔታዉ
በሰዎች ቋንቋ አፉን የፈታዉ
ቃል የማይወጣዉ አፍ ለሚከፍቱ
አፍ የሚያዘጋ በመሀል ጣቱ
ቢያፈገፍግም ፈርቶ የማይሮጠዉ
ሲጨፍር ብቻ የሚንቀጠቀጠዉ
#ዘራፍ
🔘ከ በላይ 🔘

❤1
#እኔ_ደግሞ …."
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
#እኔ_ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
#እኔ_ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
🔘አሌክስ አብርሃም 🔘
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
#እኔ_ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
#እኔ_ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
🔘አሌክስ አብርሃም 🔘
#ውርሰ_ውበት
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው
ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ
ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ
ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት
ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ
ፀባይሽ ግን ውዴ...
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ
🔘ልዑል ሀይሌ🔘
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው
ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ
ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ
ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት
ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ
ፀባይሽ ግን ውዴ...
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ
🔘ልዑል ሀይሌ🔘
#ያሳፈርኩህ_እንዳታፍር_በመፈለጌ_ነው
‹‹ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ያምሻል?›› ስል እናቴ ላይ በብስጭት ጮህኩባት ... አንድ ጥግ ላይ ኩርምት ብላ እና አንገቷን ደፍታ በቁጣ የምደነፋባትን ንግግር ሁሉ ስታዳምጠኝ ትልቅ ወንጀል ሰርቶ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ እንጅ የሰባት አመት ልጇ የሚጮህባት እናት አትመስልም ነበር !
ብስጭቴ ልክ አልነበረውም እንዲያውም ከንዴቴና ከቁጣየ የተነሳ እናቴ አስጠላችኝ ‹‹አሁኑ ብትሞች ግልግል ነበር›› ስል ጮህኩባት እውነቴን ነበር እንዲህ ከምታሳፍረኝ ብትሞት እና ብገላገል በሰላም እኖር ነበር ! እንዴት እንዳስጠላችኝ እንደቀፈፈችኝ ! ደምስሬ ተገታትሯል እንባየ በአይኖቸ ሞልቶ በእልህና በጥላቻ አስቀያሚዋ እናቴ ፊት እየተንቀጠቀጥኩ ነበር ! አርሷ ግን አንገቷን ደፍታ አሮጌ ጫማወቿን አቀርቅራ እየተመለከተች በዝምታ የምላትን ሁሉ ታደምጥ ነበር !
እናቴ ካለአባት ብቻዋን ነበረ ያሳደገችኝ ….እኔን ለማሳደግ ብቸኛ የገቢ ምንጯ የነበረው በምማርበት ት/ቤት ውስጥ ለመምህራንና ተማሪወች ምግብ በማዘጋጀት የሚከፈላት አነስተኛ ክፍያ ነበር ! እንዲህም ሁኖ የምማርበት ትምህርት ቤት የሃብታም ልጆች መማሪያ ስለነበርና እኔም በልብስም ሆነ በመማሪያ ቁሳቁሶቸ ከማንም ስለማላንስ ስለእናቴ ማንነት ማንም አያዉቅም ነበር እኔም ስለእናቴ ተናግሬ አላውቅም !
በእናቴ የማፍረው ደሃ ስለሆነች ብቻ አልነበረም አንድ አይን ብቻ የነበራት ሴት ስለነበረች እንጅ ! በእውነትም እናቴ አስቀያሚ መልክ ነበራት ! የግራ አይኗ የነበረበት ቦታ ባዶ ጉድጓዱ ብቻ ቀርቶ አንዲት ትንሽ አይኗ ብቻ እየተቁለጨች ድንገት ለተመለከታት ከማስቀየም አልፎ ትቀፍ ነበር ! የብዙ ጓደኞቸ እናቶች አይኖቻቸው በኩል ተከበውና አምረው ስመለከት የእናቴ አንድ አይን ያሳፍረኛል ! ምንም ማድረግ አልችልም ‹‹ምንም ቢሆን እናቴ ናት ›› እያልኩ ነገሩን ለመቀበል ብሞክርም አልቻልኩም ! በእናቴ መልክ በጣም እሳቀቅና አፍር ነበር! በእርግጥም የእናቴ አንድ አይናነት ለእኔ የማልቋቋመው የሃፍረት ምንጭ ነበር !
ቢሆንም እናቴን ማንም ስለማያውቃትና ስለዚህም ጉዳይ ተናግሮኝ የሚያውቅ ተማሪ ስላልነበር እናቴን ሳያት ካልሆነ በስተቀር ትዝ አትለኝም ነበር ! በአንድ የተረገመ ቀን ታዲያ እማርበት ወደነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወች ብቻ ወደሚገኙበት አጥር ውስጥ እናቴ ስትመጣ አየኋት ! ራሴን ልስት ምንም አልቀረኝም ... ተማሪወቹ የእናቴን አይን ሲመለከቱ በሳቅ አውካኩ አሾፉባት የእማማ ፊት ላይ ግን ምንም መከፋት ሳይታይ ወደእኔ ትራመድ ነበር …..ድንገት ወደኋላየ ሮጥኩ ‹አላውቃትም እችን ሴት ወዲያ በሉልኝ ›› እያልኩ ሮጥኩ ! ይሁንና ተማሪ ጓደኞቸ መዘባበቻ አደረጉኝ
‹‹አንተ እናትህ አይኗ የት ሂዶ ነው? ››
‹‹እናትህ 'ሆረር' ፊልም የምትሰራ ነው የምትመስለው ››
‹‹እናትህ በአንድ አይኗ ሽንኩርት ስትከትፍ እጇን አብራ አትከትፍም ?ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ›› ተማሪው አሽካካ ተውካካ ለዘላለሙ ልቤን የሚሰብር የእናቴ ድርጊት ሁኖ ተሰማኝ ! ከዛን ቀን በኋላ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ የነበሩ ህፃናት የሚስቁት የማሾፍ ሳቅና የሚወረውሩብኝ ቃል የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነበር ! እድሜ ላሳፈረችኝ እናቴ ! እጠላታለሁ ! እቤቴ ማታ ስመለከታት እንኳ የጓደኞቸ ሳቅ ነው የሚታወሰኝ !
በዚህ ሁኔታ አብሪያት ልኖር ስላልቻልኩ ትንሽ ከፍ ስልና ነብስ ሳውቅ እናቴን ትቻት ወደሌላ ሩቅ አገር ትምህርት ቤቱ ባመቻቸው እድል ተጠቅሜ ተሰደድኩ ! እዛም ማንነቴን በማያውቁ ሰወች መሃል በደስታና በኩራት እኖር ጀመረ ! አድጌ ዩኒቨርስቲ ስገባ ስራ ስይዝ እና ሚስት አግብቸ ልጆች ስወልድ ሁሉ እናቴን አይቻትም ስለእርሷም ወሬ ሰምቸ አላውቅም ነበር ! ትልቅና የሚያምር የግሌ መኖሪያ ቤት ቆንጆ ሚስትና የሚያማምሩና ጎበዝ ልጆች አሉኝ !
ሚስቴም ሆነች ልጆቸ ትክክለኛውን ነገር አያውቁም ነበር ! ስለእናቴ ሲጠይቁኝ እንዲህ እላቸው ነበር ‹‹ እናቴ ውብ ነበረች... በተለይ አይኖቿ ጨረቃን የሚያስንቁ ከውስጣቸው ብርሃን የሚረጩ ውቦች ነበሩ የእናቴን አይን ተመልክቶ በፍቅሯ የማይማረክ የለም ግን ከብዙ አመታት በፊት ሙታለች ›› በቃ!! በዚህም የውሸት ታሪክ ታላቅ ኩራት ሰማኛል !
አንድ ቀን ግን ይህ ውብ ኑሮየን የሚያደፈረስ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ ! የቤቴ በር ተንኳኳ ….ትልቁ ልጀ በጉጉት በሩን ከከፈተው በኋላ በድንጋጤ እየጮኸ ወደቤት ተመለሰ ….ሁላችንም ያስደነገጠውን ነገር ለመመልከት በእኔ መሪነት ክፍቱን ወደተተወው በር ተንጋጋን ይህች አሰቃቂ እናቴ በር ላይ ቁማ ነበር ! ከበፊቱ የበለጠ ተጎሳቁላና የፊቷ አጥንት ቀርቶ የአይኗ ጉድጓድ የባሰ ሰፍቶ ይታያል አንድ አይኗ ሲቁለጨለጭ አንዳች አስፈሪ አውሬ ትመስል ነበር !
ድንጋጠየን ተቋቁሜ ‹‹ምን ልርዳሽ ሴትዮ›› አልኳት አጠያየቄ ግልምጫ የታከለበትና ፍፁም የማላውቃት ሴት መሆኗን የሚያሳይ ነበር
‹‹ የኔ ልጅ ላይህ ጓጉቸ ነበር ….›› ብላ መናገር ከጀመረች በኋላ ወደሚስቴና በድንጋጤ የእናታቸውን ቀሚስ ጨምድደው ወደቆሙት ልጆቸ በዛቹ አንድ አይኗ ተመልክታ እንዲህ አለች ‹‹ ይቅርታ አድራሻ ተሳስቶብኝ ነው ›› ከዛም ተመልሳ መንገድ ጀመረች ጀርባዋ ጎበጥ ብሏል ፀጉሯም ግማሽ በግማሽ ነጭ ሁኗል ! እውነቱን ለመናገር ምንም አላዘንኩም እንደውም በየሄድኩበት እየተከተለች ኑሮየን መበጥበጧ አበሳጨችኝ !!
ከአንድ አመት በኋላ ድሮ እማርበት የነበረው ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ተማሪወች ጠርቶ የምስረታ በአሉን ሲያከብር የክብር እንግዳ አድርጎ ስለጠራኝ ወደጥንት መንደሬ በአሉ ላይ ለመገኘት ሄድኩ ! እናቴ የነበረችበት የጥንት መንደር ምንም ሳይሻሻል ከነ ደሳሳ ቤቶቹ እዛው ነበር !
በአሉን ተሳትፌ ልመለስ ስዘጋጅ አንድ እንደእናቴ የተጎሳቆለ ሰው ወደእኔ እየተጣደፈ መጣና እንዲህ አለኝ
‹‹ እናትህ ሙታለች … !! ›› እውነት እላችኋለሁ ትልቅ እረፍት ተሰማኝ ካሁን በኋላ መሳቀቄ ሃፍረቴ ሁሉ አብሮ ሞተ ! የማፍርበት የኋላ ታሪኬ መቃብር ወረደ ! እፎይይይይይይይይይ! ይሄ መርዶ ሳይሆን ‹‹የምስራች›› ነበር!!
ይሁንና ‹የምስራቹን › ያበሰረኝ ሰው አንድ አሮጌ ፖስታ ከአሮጌ ኮቱ ኪስ አውጥቶ ሰጠኝና ‹‹እናትህ አደራ ስጥልኝ ብላኝ ነው ›› ብሎ ፖስታው ጋር ትቶኝ እየተጣደፈ ሄደ !ፊቱን ሲያዞርና ከእኔ ለመራቅ ሲጣደፍ አንዳች ቆሻሻ ነገር የሚሸሽ ነበር የሚመስለው ! ፖስታውን ከፍቸ ድሮ የማስታውሰው የእናቴ የእጅ ፅሁፍ ጋር ተፋጠጥኩ አጭር እና ግልፅ መልእክት ነበር !
‹‹ የምወድህ ልጀ እድሜ ልክህን ሳሳፍርህ እና ሳሳቅቅህ በመኖሬ ይቅር በለኝ …. ለትልቅ ደረጃ መድረስህን እቤትህ ድረስ መጥቸ በአንድ አይኔ በማየቴ ደስ ብሎኝ ቀሪ እድሜየን ኑሪያለሁ ! ውድ ልጀ ያሳፈርኩህ እንዳታፍር በመፈለጌ ነው ….በልጅነትህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህ ጠፍቶ ነበር እድሜ ልክህን በአንድ አይን እንድትኖር የእናት አንጀቴ ስላልቻለ የራሴን አንድ አይን ልለግስህና በቀሪው አንድ አይኔ ደስታህን ልመለከት ስለፈለኩ ይሄንኑ አድርጊያለሁ !! በዚህም እኮራለሁ ልጄ ! ………እናትህ ››
ከውስጥ የማይወጣ ፀፀት ተሰማኝ ያን ፊት እንደገና ማየት ተመኘሁ ግን😢😢

👍6
#ለግዜር_የተፃፈ_ደብዳቤ
,,,,,,,,,,
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሁሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሾመው ሁሉ "ፀሃይ ነኝ " እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል "ዝናብ" ሁኖ እንደመፈጠር ........
ኧረ እግዜር በናትህ ...
በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርበዋ
ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን
ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና.......!

#በፍቅር_እንኑር
መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል ትንፋሽ መውሰጃ ጊዜ የለም፡፡ምን አልባትም ማይክሮሰከንድ አይኖርም ይሆናል፡፡ነገር ግን ሽርፍራፊዋም ብትሆን ያው የኛ ዕድሜ ነች፡፡በዚህ ዓለም አረፍ የምንልባት(የምንኖርባት እንዳልል ከመጣንበት ዝንት ዓለም እና ከምንሄድበት ዘላለም አንፃር የዕድሜያችን ርዝማኔ መለኪያው ስለማይነፃፀር እና ከዓይን ጥቅሻ ያነሰ በመሆኑ ነው)አንዳአንዴ ያንኑው የጥቅሻ ዕድሜ ያሰለቸናል፡፡ያነጫንጨናል፡፡ምክንያቱም እንደማረፊያ ሳይሆን እንደ ቋሚ መኖሪያ እናስባታለን፡፡እናም ቋም ነገሮችን ለመገንባት እንጣጣራለን...ወደ ውስጥ የሳብነውን አየር መልሰን ወደ ውጭ ሳንበትን የረፍት ጊዜያችን ይገባደድ እና እረጂም..በጣም እረጂም የፀጥታ እና የማይታወቅ ጉዦችንን እንጀምራለን፡፡
እና የዘላለም ተገጓዦች ነን፡፡በምድር ምንገነባው ህንፃ ማረፊያ ድንኳን እንጂ ቋሚ ሀውልት አይደለም፡፡ዘና ብሎ መሳቅ ...በፈገግታ መደሰት እንጂ ፊታችንን አጨማደን… ልባችንን አኮማትረን ..ስለ ኒዩኪሌር ቦንብ መጠበብ በህይወት ስለት ትርጉመ ቢስ ነው
ህይወት እኮ ምትሰለቸን እረፍታችን ምቸት ስለሌለው ነው...ለዚህ ነው የሚቀነቅነን፡፡የአብዛኞቻችን ኑሮ በችግር የታጠረበት ዋናው ምክንያት የጥቂተች ስግብግብነት ነው፡፡መቶ ሺ ዓመት በዚህች ምድር እንደሚኖር ..አንድ ሺ ሰዎች እድሜ ልክ ማኖር የሚችን ንብረት ብቻውን ታቅፎ እና ቀብሮ...እሱ በምቾት እና በስግብግብነት ቅዠት ውስጥ እየኖረ ..ሌሎች ሺ ዋችን በችግር እና በሰቀቀን ቅዠት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ትርፉ ምንድነው፡፡
እና እስቲ እንተሳሰብ፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡ ጠብታ ጊዜያችንን በክፋት አናጨማልቃት፡፡በፈገግታ ጀምረን...በሳቅ አዋዝተን....በዜማ አጅበን...በደስታ ዘለን...በፍቅር ሰክረን..በእርካታ እንሰናበታት፡፤መጨረሻችን መድረሻ የሌለው ዘላለም አይደል፡፡
ስለዚህ መልካም አልመን ...መልካም ተግብረን...በመልካም ሁኔታ ኖረን..ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ፀፀት አልባ ሆነን እንድንገጓዝ ከፀለምተኛ አስተሳሰባችን...ከስግብግብ ባህሪያችን...ከመጠላለፍ ምግባራችን እንላቀቅ፡፡ትናንትን አክባሪ...ዛሬን አፍቃሪ...ነገን ናፋቂ እንደሆን ህይወትን ሳንሰለች ሩጫችንን በጥሩ አነሳስ ጀጀምረን በድንቅ አጨራረስ ማጠናቀቅ ይገባናል
#መልካም_ቀን
🔘ከዘሪሁን🔘

👍3
#ከኢንጅነር_ናዝራዊት_የተላከ
😥😥እናንተዉ ውለዱኝ😢
"በቅን አስተሳሰብ በገራገር ልቤ
የታሸገ ሻንጣ በስሜ አስመዝግቤ
እኔም እንደባሕራን የሞቴን ደብዳቤ
መልክቴን ለማድረስ ሳላየው አንብቤ
ተሰናበትኩና የሀገሬን ጓዳ
በእምነት ገሰገስኩ ወጣሁ በማለዳ
ከኢትዮጵያ አየር ከአፈሯ ስርቅ
ባየር ተሳፍሬ ስሔድ እሩቅ ምስራቅ
ምኞቴ ሊሳካ በደስታ ስቦርቅ
አውሮፕላን ወርዶ ከሀገረ ቻይና
በፍቅር ደርሼ በሰላም በጤና
ሀገሩን አፈሩን ባይኔ ሳላይ ገና
በኋላ በፊቴ ከበቡኝ መጡና
እጀግ ደነገጥኩኝ ሆዴም ተሸበረ
ከቶ ምን ወረደ ምንስ ተፈጠረ
በሴትነት መንፈስ በሰፍሳፋ አንጄቴ
ጨለማ ሲውጠኝ ጠፋኝ እኔነቴ
እራሴን ስፈልግ ራሴ ጠርጥሬ
ራሴን ስጠይቅ ራሴን መርምሬ
ናዝራዊት አይደለሁ ሌላ ሴት ነኝ እኔ
አደንዛዥ ዕፅ ሰቶ የላከኝ ወገኔ
መሞት መገደልን ካገሬ ሳላጣው
እንዴት ሞት ፍለጋ ወደቻይና መጣሁ?
እኔ ለመሆኔ ባይኖርም መረጃ
ለካስ እኔ ሳላውቅ ያገሬ ምድጃ
ውጭ ውጭ ብሎ ሸኝቶ የላከኝ
በሞት ብያኔ ነው ካገር ያሾለከኝ
እናማ ወገኔ የሀገሬ ዜጋ
እኔም ሳልሰቀል እንደ ፍየል ሥጋ
የታነቀችን ነብስ በብርቱ ፈልጉ
ድምጻችሁን ስጡኝ ሳትሳሱ ሳትነፍጉ
እኔ እንደባሕራን ነኝ ሞቴን ተሸካሚ
መላኩን ላኩልኝ ለህይወቴ ቋሚ
መላክ ፈልጉልኝ የሚታመን ቃሉ
ጦማር የሚለውጥ እፍ ብሎ በቃሉ
ሚካኤልን ጥሩት ገብርኤልን ላኩልኝ
የሞቴን ደብዳቤ የሠርግ ያድርጉልኝ
ዳንኤልን ጥሩት ባንድ ድምጽ ሁኑና
በረበናት ቅጣት እንዳትሞት ሶስና
ወገን ድምጽ ሰጠኝ ናፍቆቱ ከብዶኛል
ድምጽ ደምጽ የሚያሰኝ ስስት አድሮብኛል
እናቴ ብትወልደኝ ዘጠኝ ወር አርግዛ
ከናቴ ማሕጸን ወጥቼ እንደዋዛ
እንዳትቀር እናቴ ፎቶ ብቻ ይዛ
አዋቂ በእውቀቱ አማኝ በጸሎቱ
ሰው የሚፈጥርበት አሁን ነው ሰዐቱ
የሞት የልደቴን ቀን እየጠበኩኝ
ደግሞኛ ጽንስ ሁኜ ስለተረገዝኩኝ
ነብሴን ሳያጠፉት በጽንሴ ሳይጎዱኝ
እናንተ አምጣችሁ እናንተ ወለዱኝ"
15/7/2011
🔘በመምህር ኤፍሬም ተስፋ🔘
http://chng.it/YPY2Z4ZMfg
😥😥እናንተዉ ውለዱኝ😢
"በቅን አስተሳሰብ በገራገር ልቤ
የታሸገ ሻንጣ በስሜ አስመዝግቤ
እኔም እንደባሕራን የሞቴን ደብዳቤ
መልክቴን ለማድረስ ሳላየው አንብቤ
ተሰናበትኩና የሀገሬን ጓዳ
በእምነት ገሰገስኩ ወጣሁ በማለዳ
ከኢትዮጵያ አየር ከአፈሯ ስርቅ
ባየር ተሳፍሬ ስሔድ እሩቅ ምስራቅ
ምኞቴ ሊሳካ በደስታ ስቦርቅ
አውሮፕላን ወርዶ ከሀገረ ቻይና
በፍቅር ደርሼ በሰላም በጤና
ሀገሩን አፈሩን ባይኔ ሳላይ ገና
በኋላ በፊቴ ከበቡኝ መጡና
እጀግ ደነገጥኩኝ ሆዴም ተሸበረ
ከቶ ምን ወረደ ምንስ ተፈጠረ
በሴትነት መንፈስ በሰፍሳፋ አንጄቴ
ጨለማ ሲውጠኝ ጠፋኝ እኔነቴ
እራሴን ስፈልግ ራሴ ጠርጥሬ
ራሴን ስጠይቅ ራሴን መርምሬ
ናዝራዊት አይደለሁ ሌላ ሴት ነኝ እኔ
አደንዛዥ ዕፅ ሰቶ የላከኝ ወገኔ
መሞት መገደልን ካገሬ ሳላጣው
እንዴት ሞት ፍለጋ ወደቻይና መጣሁ?
እኔ ለመሆኔ ባይኖርም መረጃ
ለካስ እኔ ሳላውቅ ያገሬ ምድጃ
ውጭ ውጭ ብሎ ሸኝቶ የላከኝ
በሞት ብያኔ ነው ካገር ያሾለከኝ
እናማ ወገኔ የሀገሬ ዜጋ
እኔም ሳልሰቀል እንደ ፍየል ሥጋ
የታነቀችን ነብስ በብርቱ ፈልጉ
ድምጻችሁን ስጡኝ ሳትሳሱ ሳትነፍጉ
እኔ እንደባሕራን ነኝ ሞቴን ተሸካሚ
መላኩን ላኩልኝ ለህይወቴ ቋሚ
መላክ ፈልጉልኝ የሚታመን ቃሉ
ጦማር የሚለውጥ እፍ ብሎ በቃሉ
ሚካኤልን ጥሩት ገብርኤልን ላኩልኝ
የሞቴን ደብዳቤ የሠርግ ያድርጉልኝ
ዳንኤልን ጥሩት ባንድ ድምጽ ሁኑና
በረበናት ቅጣት እንዳትሞት ሶስና
ወገን ድምጽ ሰጠኝ ናፍቆቱ ከብዶኛል
ድምጽ ደምጽ የሚያሰኝ ስስት አድሮብኛል
እናቴ ብትወልደኝ ዘጠኝ ወር አርግዛ
ከናቴ ማሕጸን ወጥቼ እንደዋዛ
እንዳትቀር እናቴ ፎቶ ብቻ ይዛ
አዋቂ በእውቀቱ አማኝ በጸሎቱ
ሰው የሚፈጥርበት አሁን ነው ሰዐቱ
የሞት የልደቴን ቀን እየጠበኩኝ
ደግሞኛ ጽንስ ሁኜ ስለተረገዝኩኝ
ነብሴን ሳያጠፉት በጽንሴ ሳይጎዱኝ
እናንተ አምጣችሁ እናንተ ወለዱኝ"
15/7/2011
🔘በመምህር ኤፍሬም ተስፋ🔘
http://chng.it/YPY2Z4ZMfg
Change.org
Sign the Petition
Free Nazrawit Abera from Guangzhou Prison
👍2
#የሕይወት_አዙሪት
ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመ
ርክበት ነው፡፡ ልብ በል!
.
• ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡
• በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።
• የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ፡፡
.......
ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡
መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት!
.
መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡
.
ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል! የዓለም # ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም፤ ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ እዚህ ትመጣለህ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም፡፡››
ከመርበብት መጽሐፍ የተወሰደ

ጉዳዩ #ልምድን_ስለመጻፍ
ይድረስ ለማፈቅርሽ..ይድረስ ለምወድሽ
ጠልተሽ ላባረርሽኝ..በገዛ ፈቃድሽ::
ቀድሞ ለነበርሽው..የፍቅር አቻዬ
በቅጡ ይጤንልኝ..ይህ ማመልከቻዬ::-
ጥረቴን..ልፋቴን..ድካሜን..ትጋቴን..
ለፍቅር እንደገበርኩ..ቀንና ሌሊቴን..
ችዬ ያካበትኩትን..የዘመናት ልምዴን..
ከልብ ማፍቀሬን..አጥብቄ መውደዴን..
...ንፁህ ሆኜ መኖሬን..
ፈጣሪን መፍራቴን..
...ፍጥረቱን ማክበሬን..
ልዩ ሐሴትእንዳለኝ..ማንም እማይቀማኝ..
እንደሆንኩኝ ታማኝ..እንደነበርኩ አማኝ..
ካሻሽ ወንጀለኛ..
ወይም ኃጢኃተኛ..
ሁሉንም ዘርዝረሽ..በይፋ አውጂልኝ
የሔዋን ዘር በሙሉ..ልምዴን እንዲያውቅልኝ
"ለሚመለከተው ሁሉ"
በሚል ዐብይ ርዕስ..ማስረጃ ጻፊልኝ::
ከሰላምታ ጋር
ያንቺው የፍቅር አጋር!!
ይድረስ ለማፈቅርሽ..ይድረስ ለምወድሽ
ጠልተሽ ላባረርሽኝ..በገዛ ፈቃድሽ::
ቀድሞ ለነበርሽው..የፍቅር አቻዬ
በቅጡ ይጤንልኝ..ይህ ማመልከቻዬ::-
ጥረቴን..ልፋቴን..ድካሜን..ትጋቴን..
ለፍቅር እንደገበርኩ..ቀንና ሌሊቴን..
ችዬ ያካበትኩትን..የዘመናት ልምዴን..
ከልብ ማፍቀሬን..አጥብቄ መውደዴን..
...ንፁህ ሆኜ መኖሬን..
ፈጣሪን መፍራቴን..
...ፍጥረቱን ማክበሬን..
ልዩ ሐሴትእንዳለኝ..ማንም እማይቀማኝ..
እንደሆንኩኝ ታማኝ..እንደነበርኩ አማኝ..
ካሻሽ ወንጀለኛ..
ወይም ኃጢኃተኛ..
ሁሉንም ዘርዝረሽ..በይፋ አውጂልኝ
የሔዋን ዘር በሙሉ..ልምዴን እንዲያውቅልኝ
"ለሚመለከተው ሁሉ"
በሚል ዐብይ ርዕስ..ማስረጃ ጻፊልኝ::
ከሰላምታ ጋር
ያንቺው የፍቅር አጋር!!
#ፍቅር ፤ #ከፍቅር_እስከ_መቃብር
ፍቅር የአየር ንብረት አይደለም፡፡ ሳይተነብዩት መጥቶ፥ ሳይተነብዩት ይሄዳል፡፡ የደምሴ እና የሰላም ፍቅርም እንዲሁ ሳይተነበይ መጥቶ ነው የሄደው:: ሲመጣ፥ ለሁለቱም መጣ፡፡ አካሔዱ ግን እንዳመጣጡ ቀላል አልነበረም፡፡
ደምሴ ቆፍጣና የፍልስፍና መምህር ነው፡፡ ሰላም ደግሞ ቀልቃላ ቢጤ የውበት ባለሙያ፡፡ ነገረ ሥራቸው ሁሉ እሱን ወንዳወንድ እሷን ሴታሴት ያደርጋቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ሰሞን ‹‹በፊዚክስ ሕግ ተቃራኒዎች ይሳሳባባሉ›› ይላት ነበር ፍቅራቸውን ሲገልጸው፡፡ ኋላስ?!
ደምሴ እና ሰላም የተዋወቁት የሰው ሠርግ ላይ ነው፡፡ አጋጣሚ ጎን ለጎን አስቀመጣቸው፣ አጋጣሚ እሷን መኪና አሳጣት እና ወደፎቶ ፕሮግራም በእሱ መኪና ሄደች፡፡ ሁሉም በአጋጣሚ ፈጠነ፡፡ ደምሴ ሲያወሩት የሚያወራ፣ ሲዘጉት የሚዘጋ ዓይነት ሰው በመሆኑ ከሰላም ተጫዋችነት ጋር በጊዜው ሰምሮ ነበር፡፡
ሲመሽ ወደ ቤቷ ሸኛት፡፡ መኪና ውስጥ ትንሽ አወጉ፡፡ ‹‹በነገራችን ላይ ሰላም እባላለሁ›› አለችው፡፡
‹‹ኦው!›› አለ፤ ለካስ እስካሁን ስማቸውን አልተለዋወጡም፡፡
‹‹ደምሴ እባላለሁ፤›› አላት፡፡
‹‹ደምሴ?›› አለችው፡፡ ‹‹አዎ›› አላት፤ የገረማት ትመስላለች፡፡ ለምን እንደገረማት ግን እራሷም አልገባትም፡፡ ምናልባት ጨዋታው እንዲቀጥል ፈልጋ ይሆናል፡፡
‹‹ደምሴ ማለት ደምስሴ ማለት ነው፤›› የፍልስፍና ማብራሪያውን ሳያስበው ማዥጎድጎድ ሊጀምር ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያውያን ምኞቶቻቸውን በልጆቻቸው ማሳካት ይፈልጋሉ፡፡ ምናልባት የኔ ወላጆች አድጌ እንድደመስስላቸው የሚፈልጉት ጠላት ሳይኖራቸው አይቀርም ነበር፡፡ ያለዚያ ደምሴ አይሉኝም ነበር፡፡››
ሰላም ፈገግ አለች፡፡
‹‹እውነቴን ነው የምልሽ፤ በኢትዮጵያውያን ባሕል የልጅ ድርሻ ዘርን መተካት ብቻ አይደለም፡፡ እልህ መወጫ፣ መበቀያ ወይም ሕይወትን መቀየሪያ ነው፡፡ ወንድ ልጅ ሲሆን ደግሞ ጫናው ይበዛል፡፡ ደብድቦም፣ ገድሎም ቤቱን የሚያስከብር እንዲሆን ከስሙ ጀምሮ እስከአስተዳደጉ ጥረት አይለየውም፡፡››
‹‹እሺ እኔስ ለምን ሰላም ተባልኩ?›› አለችው፡፡
አሰብ አደረገና ‹‹ምናልባት እናትና አባትሽ በልጅ እጦት እየተጣሉ ከነበረ ሰላም የወረደላቸው ባንቺ ይሆናል….›› ግምቱን ሰነዘረ፤ ግምቱ ትክክል ስለነበር ከትከት ብላ ሳቀች፡፡
ሲተዋወቁ የመጀመሪያ ቀናቸው አይመስልም፡፡ በጣም ቅልል የሚል ሰው ሆነላት፡፡ ስልክ ተለዋወጡ፡፡ ከመኪናው ስትወርድ ከንፈሩን ስማው እንደወረደች እንኳን አልታወቃትም ነበር፡፡
ሁሉም ነገር የሆነው በጣም በፍጥነት እና በጣም ደስ በሚል ሁኔታ በመሆኑ ሳይጠያየቁ በጀመሩት ፍቅር ልባቸው ጦዟል፡፡ ለወትሮው ‹‹ፍቅርና ገንዘብ እንደመንዛሪው ነው›› እያለ የሚተርተው ደምሴ የሰላምን ፍቅር ያልቅብሻል ብሎ ሳይሰስት በየቀኑ ይመነዝረው ጀመር፡፡ እሷም ሁለመናዋን ሳትሰስት እንደሰጠችሁ ሁሉ!
አንድ ቀን፥ ፍቅር ሰርተው ሲጨርሱ፤ ‹‹ታውቂያለሽ?›› አላት፡፡ ‹‹ታውቂያለሽ፤ የፍቅር ግንኙነት የፍቅርን ጣዕም ያጠፋዋል ብዬ አምን ነበር፡፡ አሁን ግን ሲገባኝ፤ የፍቅር ጣዕሙ የሚያልቀው፥ ከትክክለኛዋ ሴት ጋር ካልሆነ ነው፤›› ብሏት መልሷን እንኳን ሳይጠብቅ ‹በአፉ መሳም› ይስማት ቀጠል፡፡
የደምሴና ሰላም ሦስት ወራት በፍቅር አለፉ፡፡ ወሬያቸው፣ ምግባራቸው እና ምኞታቸው ሁሉ ፍቅር ነበር፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ ግን የደምሴ ፍልስፍና እውነት እየሆነ የመጣ መሰለ፡፡ ፍቅራቸው ተመንዝሮ ወደማለቁ ተጠጋ፡፡
ፍቅር ሰርተው ሲጨርሱ፥ በጋራ ሻወር ይወስዳሉ፡፡ ከዚያም፣ እንደተለመደው ሰላም ገላዋን በሎሽን፣ ከንፈሯን በቀለም፣ ዓይኗን በኩል ስታሰማምር ቁጭ ብሎ ይመለከታታል፡፡ በፊት፣ በፊት ውበቷን በማድነቅ ስሜት ነበር የሚያያት አሁን፣ አሁን ግን ‹መቼ ትጨርስ ይሆን?› እያለ ነው፡፡ አልፎ፣ አልፎ ‹‹ዝም ብዬ ሳይሽ እኮ - ተኳኩለሽ ስትጨርሺ እግዜር የሰራት ሰላም ቀርታ ሌላ ሰላም የተፈጠረች ይመስለኛ›› ይላት ጀምሯል፡፡
‹‹ምን?.... በሜካፕ ብዛት ነው የምታምሪው ልትለኝ ነው?››
‹‹አልወጣኝም›› ይላታል፡፡
እየቆዩ፣ እየቆዩ ከፍቅራቸው ይልቅ ንትርካቸው በዛ፡፡ መንስኤው እሱ ‹‹እሷ ማንነቴን ልትለውጥ መፈለጓ ነው›› ብሎ ሲያስብ፤ እሷ ደግሞ ‹‹እሱ የማይለወጥ ሰው ስለሆነ ነው›› ትላለች፡፡
ሌላው ቀርቶ የጎፈረው ጺሙ ያጣላቸዋል፡፡ ይጣላሉ፣ ይታረቃሉ፡፡ ሲጣሉ ይነፋፈቃሉ፣ ሲታረቁ ለአንድ ሳምንት ይጣጣማሉ፣ መልሰው ይጣላሉ፡፡ ይሄ ዑደት ሲደጋገም ሰላምን አሰለቻት፡፡ ሰላም ከዚህ ሰንሰለታዊ ሕይወት መውጣት የምትችለው ሌላ ወንድ በማግኘት እንደሆነ አሰበች - በሐሳቧ ተጓዘች፡፡
ደምሴና ሰላም እንደተለመደው በትንሽ ንትርክ ተከራክረው በተለያዩ ሳምንታቸው ገደማ ሰላም ከአንድ ሰው ጋር መቀጣጠር ጀመረች፡፡ መቀጣጠር በጀመረች በጥቂት ቀናት ውስጥ ደምሴ እንደገና ደወለ፤ ኩርፊያው አልፎለታል ማለት ነው፡፡ ግን ረፍዷል፡፡ የሰላም ልብ ላዲሱ ሰውዬ መቅለጥ ጀምሯል፡፡ በዚያ ላይ ከደምሴ እስር የምትላቀቀው በዚህ ውስጥ እንደሆነ ተሰምቷታል፡፡
ችግሩ ለደምሴ ይሄንን ለመንገር ድፍረቱ ከየት ይምጣ የሚለው ነው፡፡ እንዳኮረፈ ሰው አናግራው ስልኩን ዘጋችበት፤ በማግስቱ ደግሞ ደወለ ሳታነሳው ቀረች፡፡ ደጋግሞ ደወለ፥ በሐሳቧ ቁርጡን ልትነግረው ወስና ቀጠረችው ሲገናኙ ግን ይህንን ማድረግ አቅሙ አልነበራትም፡፡ እንዲያውም ወደቤቷ ሸኝቷት ከመኪናው ልትወርድ ስትል ሲስማት መልሳ ስማዋለች፡፡
ሕይወቷ ሐዲዱን ሳተ፡፡ አዲሱ ሰው ጠዋት የሳማት እንደሁ ደምሴ ማታ ይስማታል፡፡ አፍቃሪዋ ሰላም አስመሳይ ተዋናይት ሆነች፡፡ ከዚያኛው ጋር ሁና የደምሴን፣ ከደምሴ ጋር ሁና የዚያኛውን ሰው ስልክ እንዳመሉ ማስተናገዱን ተጠበበችበት፡፡ ጊዜው ነጎደ፡፡ ሰላም ለውጥ ፈላጊ አፍቃሪ መሆኗ ቀርቶ ጥፋቷን ለመሸፈን ስትል፣ ወይም መውጫው መንገድ ጠፍቷት የምትንከራተት ‹‹እንዳሻችሁ ጋልቡኝ›› ባይ ሴት ሆና አረፈችው፡፡
ሰላም በጊዜ ሒደት ውስጥ ሁለቱንም ወንዶች የምትወዳቸው ሁነው አገኘቻቸው፡፡ ሁለቱንም ማጣት ቀላል ሊሆንላት አልቻለም፡፡ ሁለቱንም አብሮ ማስኬድም የድብብቆሽ ስቃይ አለው፡፡ በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ ሁና መፍትሄ እስኪመጣላት የያዘችው፥ ‹‹በሁለት እግር ሁለት ዛፍ የመውጣት›› ሙከራዋ አላዛለቃትም፡፡ ሁለቱም ወንዶች ነቅተውባት የሆዳቸውን በሆዳቸው አብተዋል፡፡
ውድ አንባቢያን፡-
የዚህ ታሪክ መጨረሻ ሁለት አማራጮች አሉት፡፡ አንዱን መምረጥ የእናንተ ድርሻ ነው፡፡
#አማራጭ_አንድ
አዲሱ የሰላም ፍቅረኛ ዛሬ አብሯት ሊያድር እንደሚፈልግ ነግሯታል እሱ ትንሽ የሚያቆየው ሥራ ስላለው ከከተማው አንድ ዳርቻ የሚገኝ ፔንሲዮን ጠቁሟት እዚያ ክፍል በጊዜ እንድትይዝና እንድትጠብቀው ነግሯታል፡፡
ይህንን ያደረገው ሆነ ብሎ ነው፡፡ የፔንሲዮኑ አከራዮች የሷን አድራሻ ብቻ ነው የሚይዙት፥ እሱ ሹልክ ብሎ ይገባና ገድሏት እንዳገባቡ ይወጣል - ዕቅዱ ይኸው ነው፡፡
ደምሴ በበኩሉ በዚሁ ቀን ደውሎ እንዲገናኙ ሲጠይቃት፥ ሰላም ‹‹አይመቸኝም›› በማለቷ ለብዙ ጊዜ የተዘጋጀበትን ድግስ ደግሶላታል፡፡ ከቢሮዋ ስትወጣ ጀምሮ በተከራየው መኪና ይከታተላት ጀመር፡ የገባችበትን ፔንሲዮን አየ፤ ሰውየው አብሯት አልመጣም እዚያው አካባቢ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ሰውየውን እየተገላመጠ ሲገባ አየው ቀድሞ ባጠናው አጥር ተንጠልጥሎ ገብቶ ተከተለው በኮሊደሩ ተከልሎ ሰውየው የሚገባበትን ክፍል አስተዋለሰውየው ሲገባ፥ ደምሴ በዝግታ ወደክፍሉ አመራ በሩ ላይ ጆሮውን ለጥፎ አደመጠ የመሳሳም የሚመስል ድምጽ ተሰማው ደጋግሞ አዳመጠ

ብስጭቱ በረታ፣ ደሙ ፈላ፡፡ የሷ ድምጽ በከፊል ይሰማ ጀመር፤ ከምኔው ጀመሩ? የቅናት ስሜቱን መግራት አልቻለም፡፡ ራሱን ለመግዛት እና እርምጃ ለመውሰድ ደቂቃዎች ፈጀበት፡፡ በሩን በርግዶት ገባ፡፡ ሰውየው በድንጋጤ ፊቱን ወደደምሴ አዞረ፡፡
ደምሴ በሚመለከተው ነገር ግራ ተጋብቷል፡፡ ሰውየው በትራስ አፍኖ ሰላምን ጨርሷታል፡፡ ምን እየተካሔደ እንደሆነ ለማሰብ ጊዜ የለውም፡፡ ያቀባበለውን ሽጉጥ በሰውየው ደረት ላይ አነጣጥሮ ቃታውን ሳበ፡፡
#አማራጭ_ሁለት
አዲሱ የሰላም ፍቅረኛ ዛሬ አብሯት ሊያድር እንደሚፈልግ ነግሯታል፡፡ ሆኖም ሊዘገይ ስለሚችል እስከዛሬ የሚገናኙበት ሆቴል ውስጥ ክፍል ይዛ እንድትጠብቀው ነግሯታል፡፡
ሰላም አንዱ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ፍቅረኛዋን እየጠበቀችው ነው፡፡ ደምሴ እንዳይደውልባት ስልኳን አጥፍታዋለች፡፡ በሩ ተንኳኳ፡፡ ከፊል ራቁቷን ነች፡፡ ፍቅረኛዋ ሰዐት አክባሪ ነው፡፡ ልክ በነገራት ሰዓት ከች በማለቱ ተደስታ በሙሉ ፈገግታ በሩን ከፈተችለት፡፡
አዲሱ ፍቅረኛዋ ብቻውን አልነበረም፤ ደምሴ አብሮት አለ፡፡ ከፊት ለፊቷ የምታየው ነገር ሰውነቷን አራደው፡፡ ከፊል እርቃኗን እንዳያዩባት ለመደበቅም የፈለገች መሰለች፡፡ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ እንጂ መናገር አልቻለችም፡፡ እንግዶቿ ያለግብዣዋ ገብተው በሩን ዘጉት፡፡ ምክንያቷን ሳያዳምጡ፣ ለስሜቷም ሆነ ለምላሽዋ ሳይጨነቁ ሰማይ በሚበሳ ድምጽ እየተፈራረቁ አምባረቁባትና ሲበቃቸው ወጡ፡፡
ሁለቱንም ማጣት ያልፈለገችው ሰላም ከሁለት አንዱንም ከማጣት የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማት፡፡
ወድ አንባብያን፡-
ምርጫችሁ የቱ ነው? የቱንም ብትመርጡ የምርጫችሁ ቅጣት ግዞተኛ መሆናችሁ እንደማይቀር ጸሃፊው ያስባል፤ ምርጫችሁ ያውጣችሁ!!!
እስቲ ምርጫችሁን 👉 @atronosebot ላይ አሳዉቁኝ

#ስትናፍቂኝ
:
ናፍቆት ያደመነው
የናፋቂሽ ውብ ፊት
ከ...ዝርጉ ሸራ ላይ .. በ'ሰማይ ተሰቅሎ
እንደ ሐምሌ ሠማይ
የ'ጭጋግን አድባር
ሲያላዝን ውሎ ያድራል .. በጉም ተከልሎ
ያ .. .. የ'ሐምሌ ሠማይ
በመብረቅ ብልጭታ
በ'ቅፅበት ድን'ፋታ
ፍጥረታቱን ሚያርድ .. ሚያርበደብደው
ስነግረው የነበር
የ'ትዝታዬን ጥግ
የናፍቆቴን መጠን .. መሸከም ከብዶት ነው
ብዬሽም አልነበር .. ?
.
(ደግሞሳ ..!)
.
ያው .. የ'ሐምሌ ሠማይ
.
በፅኑ ታመመ .. ህመሙም በረታ
ሀዘኑ ቅጥ ኣጣ .. ከ'ደስታ ተፋታ
ናፍቆት አጠላበት .. ጉጉት አደከመው
የ'ጨረቃ ፍካት
የፀሐይም ድምቀት ~ እያደረ ሸሸው
ብዬሽስ አልነበር .. ?
.
.
.
አይተሻል ሰማዩን
አይተሻል ስሜቱን
በ'ተሳለ ናፍቆት ~ ተወግቶ መውደቁን?
.
.
አይተሻል ህመሙን
አይተሻል አለሙን
ከ'ጀምበር ተፋቶ .. ፅልመቷን መውረሱን
.
(ታድያ ምነው ውዴ ..!)
.
ናፍቆትህ እስከ ምነው
ምን ያህል ይገዝፋል
ምን ያህል ይርቃል ..?
ብለሽ መጠየቅሽ
በ'ነገርኳት ብቻ
የሠማይዋ ጀምበር .. ስትጠልቅ እያየሽ
.
(ኣዬሽ!
በ'መናፈቅ አለም .. በ'መናፈቅ ምድር
የናፍቆትን ህመም
ማንም አያውቀውም .. ከ'ናፋቂው በቀር)
:
:
እናም ..
:
:
እገልፅበት ቃላት
አወራበት ሀሳብ .. ያጥረኛል ያጥረኛል
ብቻ ስትናፍቂኝ
እንደ ሐምሌ ሠማይ .. ያነጫንጨኛል
:
ናፍቆት ያደመነው
የናፋቂሽ ውብ ፊት
ከ...ዝርጉ ሸራ ላይ .. በ'ሰማይ ተሰቅሎ
እንደ ሐምሌ ሠማይ
የ'ጭጋግን አድባር
ሲያላዝን ውሎ ያድራል .. በጉም ተከልሎ
ያ .. .. የ'ሐምሌ ሠማይ
በመብረቅ ብልጭታ
በ'ቅፅበት ድን'ፋታ
ፍጥረታቱን ሚያርድ .. ሚያርበደብደው
ስነግረው የነበር
የ'ትዝታዬን ጥግ
የናፍቆቴን መጠን .. መሸከም ከብዶት ነው
ብዬሽም አልነበር .. ?
.
(ደግሞሳ ..!)
.
ያው .. የ'ሐምሌ ሠማይ
.
በፅኑ ታመመ .. ህመሙም በረታ
ሀዘኑ ቅጥ ኣጣ .. ከ'ደስታ ተፋታ
ናፍቆት አጠላበት .. ጉጉት አደከመው
የ'ጨረቃ ፍካት
የፀሐይም ድምቀት ~ እያደረ ሸሸው
ብዬሽስ አልነበር .. ?
.
.
.
አይተሻል ሰማዩን
አይተሻል ስሜቱን
በ'ተሳለ ናፍቆት ~ ተወግቶ መውደቁን?
.
.
አይተሻል ህመሙን
አይተሻል አለሙን
ከ'ጀምበር ተፋቶ .. ፅልመቷን መውረሱን
.
(ታድያ ምነው ውዴ ..!)
.
ናፍቆትህ እስከ ምነው
ምን ያህል ይገዝፋል
ምን ያህል ይርቃል ..?
ብለሽ መጠየቅሽ
በ'ነገርኳት ብቻ
የሠማይዋ ጀምበር .. ስትጠልቅ እያየሽ
.
(ኣዬሽ!
በ'መናፈቅ አለም .. በ'መናፈቅ ምድር
የናፍቆትን ህመም
ማንም አያውቀውም .. ከ'ናፋቂው በቀር)
:
:
እናም ..
:
:
እገልፅበት ቃላት
አወራበት ሀሳብ .. ያጥረኛል ያጥረኛል
ብቻ ስትናፍቂኝ
እንደ ሐምሌ ሠማይ .. ያነጫንጨኛል
👍1
#ለማበድ_አካባቢ አጭር ❤️ ወለድ
“ስሟ ግን ማነው?” አልኩት አቡሽን
“እብድ ደግሞ ስም አለው? አንተ ልጅ ዛሬ ምን ሆነሃል? ልታብድ ነው እንዴ?” መለሰልኝ።
ላብድ መሆኔን እኔም ጠርጥሪያለሁ። ማታ ሰክሬ ነው ብዬ ያባበልኩት ቅዠቴ አድሮ ከህሊናዬ ካልጠፋ ለማበድ እየተቃረብኩ መሆን አለበት።ባለፈ ለሊት ሰማይ ተቀዶ በሚወርደው ዶፍ እየታጠብኩ፣ በውሃ መያዣ ፕላስቲክ በያዝኳት አረቄ ጉሮሮዬን እያጠብኩ፣ በስካር እዚህና እዚያ እየረገጥኩ ወደቤቴ ልገባ ስል ነበር ያየኋት። እርቃኗን መንገዱ ዳር ቆማ ዝናብ ትመታለች። ፍፁም እርቃኗን!! ከላይ ወደታች አስተዋልኳት።
ፀጉሯ የዝናቡን ውሃ እያዘለ አሁንም አሁንም በረዣዥም የእጅ ጣቶቿ ስትሞዥቀው ውሃው በየአቅጣጫው ይረጫል። ከፊቷ የሚወርደው ዝናብ በረዥም አንገቷ ተንደርድሮ የተሰደሩ ጡቶቿ ላይ ይደርስና በሾሉት የጡቷ ጫፎች ጠብ……ጠብ…… እያለ ይወርዳል። እንደዘበት ከፈት ያደረገቻቸው ረዣዥም ውብ እግሮቿ፣ ውሃውን ከአካሏ ስታራግፍ የምትንጠው ቀጭን ወገቧ፣ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ላይ ታች የሚለው ተለቅ ያለ መቀመጫዋ … አይኔ በሰውነቷ ውበት ፈዞ የሚያርፍበት ቦታ ጠፍቶት ገላዋ ላይ ሲንከራተት አየችኝ። ደነገጠች። ግን አልሮጠችም። አቅጣጫ ቀይራ የቀድሞ ጨዋታዋን ከዝናቡ ጋር ቀጠለች። ጀርባዋን ሰጠችኝ። እሷ ስለማታየኝ የተደበቀች መስሏት ይሆን? ዓይኔ ላይ የበራ የመኪና መብራት ነበር አይኔን ከሷ እንድነቅል ያደረገኝ። ከመሃል መንገድ ፈንጠር ብዬ ጥግ ያዝኩ። መኪናው ካለፈ በኋላ ወደነበረችበት አቅጣጫ ዞርኩ። አልነበረችም።
—እሷ—
እሷ እብድ ናት። ድፍን አውቶቢስ ተራ የሚያውቃት እና የሚፈራት እብድ። እብድ ምን ታሪክ አለው? በቃ እብድ ናታ!!
“እሺ የት እንደምታድርስ ታውቃለህ?” አልኩት አቡሽን
“ማን?” ብሎ መልሶ ሲጠይቀኝ እየሰማኝ ባለመሆኑ ተናደድኩበት። አልፈርድበትም። የማወራውን ለራሴ እንኳን ሳደምጠው የእብደት ወሬ ነው። ገላዋ ከዝናቡ ጋር የፈጠረውን ውብ መስተጋብር ያላየ እንዴት ብሎ ቅዠቴን ሊረዳው ይችላል?
አቡሽ ጓደኛዬ ነው። የክፍለ ሃገር አውቶቢስ መነሃሪያ ውስጥ ውድ የሆነውን የተራ ማስከበር ስራ አብረን ነው የምንሰራው። መንገድ ዳር ያለች ለእግር መዘርጊያ የማትመች ኮንቴነር በርካሽ ተከራይተን አብረን ነው የምንኖረው።
—ትናንትን ለመድገም—
አንዱን ጥግ ተከልዬ እየጠበቅኳት ነው። ከእትዬ ሸዋረገድ አረቄ ቤት ያለወትሮዬ ሸካክፌ በጊዜ የወጣሁት እንዳታመልጠኝ ነው። አሁንም አሁንም አረቄዬን ፉት እያልኩ ለማላውቀው ሰዓት ያህል ከራሴ እያወራሁ ጠበቅኳት። ብትመጣ ምንድነው የምላት? ማንስ ብዬ እጠራታለሁ? ኸረ ለመሆኑ ለምንድነው እየጠበቅኳት ያለሁትስ?
እርቃኗን እየተጎተተች ትናንት የነበረችበት ቦታ ቆመች። ዝናብ የለም። እሷ ግን ራቁቷን ናት። ያለዝናቡ ውበቷ ጎዶሎ ሆነብኝ። በደመነፍስ እግሮቼ ወደሷ ሲራመዱ ይታወቀኛል። እጆቼ ሊነኳት ወደፊት ተዘረጉ። ዝም ያለ ስሜት አልባ ፊት ነው ያላት። ጠይም ቆዳዋ እያየሁት ጠቆረብኝ። ጥቋቁር ጥቅጥቅ ያሉ ፀጉሮች አበቀለ። ሰውነቷ እንደመለጠጥ አለ። አፍጥጬ አየኋት። ‘እሷ’መሆኗ ቀርቶ ጥቁር ላም ሆነችብኝ። ላም!! ግን ደግሞ በአራት እግሮቿ ምትክ አራት የመኪና ጎማ ያላት ላም! ሁለቱ ዓይኖቿ የመኪና መብራት መሰሉ። ወደኋላዬ ሸሸኋት። እንደመኪና እያጓራች ‘ላሚቷ’ ጎማዋን እያሽከረከረች ስትርቅ የ‘እሷ’ ድምፅ የሰመመን ያህል ይሰማኛል።
“ልጆቼን በሏቸው። ቀርጥፈው!! በሚጥሚጣ አጥቅሰው ነፏቸው።”
ግድግዳውን እንደተደገፍኩ፣ በእጄ በውሃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ያለ አረቄዬን እንዳነቅኩ ነቃሁ። ሊነጋ እያቅላላ ነበር።ፊቴ ቆማለች።
“ልጆቼን በሏቸው። ቀርጥፈው። በሚጥሚጣ አጥቅሰው ነፏቸው።” አለችኝ ኮስተር ብላ።
ያወቀችኝም የሚመስል ፣ ያወቀችብኝም የሚመስል፣ አውቃ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰችኝም የሚመስል ዓይነት ብልጭታ ፈገግታ ፈገግ ብላ ጥላኝ ሄደች። ሰው እንዳላየኝ አረጋግጬ ልብሴን እያራገፍኩ ወደቤቴ አቀናሁ። እየራቀች ስትሄድ ድምፅዋ ይሰማኛል።
“ልጆቼን በሏቸው…………… ”
—ልጆቿ—
ከሀገሬ የመጣሁ ሰሞን አውቶቢስ ተራው አካባቢ ውር ውር ስል ግርግር አይቼ ተጠጋሁ። የተሰበሰበውን ሰው አቋርጬ ወደ መሃል ስጠጋ የቀናት አራስ ህፃን ልጅ በእራፊ ጨርቅ ተጠቅልሎ ይዛ አንዲት አዳፋ የለበሰች ሴት ‘ኡ ኡ ኡ…’ ትላለች። የሚያውቋትና ድርጊቱ የለመዱት ዓይነት ከሚመስሉ ሰዎች ጉርምርምታ ሴቲቱ እብድ መሆኗን እናየወለደችውን ልጅ በሁለተኛ ቀኑ ዳቦ አጉርሳ አፍና እንደገደለችው ሰማሁ። ‘እሷ’ ናት!!
‘እሷን’ እዛ አካባቢ ማየት የአውቶቢስ መነሃሪያ ጊቢውን እንደምልክት እየቆጠርኩ ከመንቀሳቀስ እኩል የለመድኩት ነገር ሆነ። ትጮሃለች፣ በድንጋይ ያገኘችውን ሰው ታባርራለች፣ የትም ያገኘችውን ትበላለች …………
ከተሜነቴን ተላምጄ ‘የት ሰፈር ነህ?‘ ሲሉኝ ‘አውቶቢስ ተራ!‘ ማለት የጀመርኩ ሰሞን እብደቷ በረደላትና ‘አደብ ገዛች።’ ‘አርግዛ ነው በቃ!‘ እያሉ ሲያወሩ ሰማሁ።
ከክረምቱ ጠዋቶቼ በአንደኛው ጉርሴን ላበሳስል በወጣሁበት የውሃ መውረጃ ቱቦ አካባቢ ሰዎች ሰብሰብ ብለው አየሁ። ጠጋ ብዬ የሰዎቹ መሰባሰብ ስለምን እንደሆነ አጣራሁ። በቱቦው በሚወርደው ውሃ ውስጥ ህፃኗን አቅፋ ታለቅሳለች። ‘ከወለደችው ድፍን አንድ ቀን አልሞላም።’ ሲሉ ሰማሁ። ቱቦው ውስጥ ህፃኑን ደብቃው ሄዳ ስትመለስ ውሃው አፍኖ ነው የገደለው። ‘ለራሱ ምግብ ላመጣለት ነው የሄድኩት።‘ ትላለች ከእንባዋ ጋር እየታገለች። ጡት እንጂ ምግብ እንደማያስፈልገው የማታውቅ እብድ መሞቱን እንዴት አወቀች? እብድ አይደለች? ስል ተገረምኩ። ‘እሷ’ ናት!!
“እንዴት ማሰብ የማይችል ቢሆን ነው? ሰው እንዴት በጤነኛ ጭንቅላቱ ከዝህች እብድ ጋር ይተኛል? አብሯት የተኛው፣ ያረገዘችለት ሰው እሱም እብድ መሆን አለበት።” ብዬ ራሴን በአመዛዛኝ ሂሳብ መዳኘቴ ያለፈ ስህተቴ ነው። የአሁን እርማቴ ደግሞ “እብድ ሊሆን አይችልም። ያበደ ሰው የገላዋ የውበት ቀመር ሊገባው አይችልም። እንደኔ እርቃኗን ከዝናብ ስትጫወት አይቶ የፈዘዘ መሆን አለበት።”
—ከትናንት በስቲያን ለመድገም—
እየጠበቅኳት ነው። እርቃኗን ሆና ለማየት ዝናቡን እንዲያወርድ የሀገሬን ታቦት እለማመናለሁ። የምትደራርባቸው ድሪቶዎቿ አስቀያሚና ቆሻሻ ስለሚያደርጓት ቀን ቀን ለብሳ ሳያት እናደድ ጀምሪያለሁ። እየጠበቅኳት ነው። ……… እንደትናንቱ እንቅልፍ ወሰደኝ። እንደትናንቱ ሁሉ ያ ቅዠቴ መጣብኝ። አራት ጎማ ያላት ጥቁር ላም ሆና መጣችብኝ። እንደትናንቱ ሊነጋ ሲል በጩኸት ቀሰቀሰችኝ።
“ልጆቼን በሏቸው። ቀርጥፈው!! በሚጥሚጣ አጥቅሰው ነፏቸው።”
—ያን ቀን ለመድገም—
በየእለቱ ለሊት እጠብቃታለሁ። በየእለቱ እንቅልፍ ይጥለኛል። በየእለቱ ያ ቅዠቴ ይመጣብኛል። በየእለቱ ሊነጋ ሲል በጩኸቷ ትቀሰቅሰኛለች። ያን ማድረጓን ታውቀው ይመስል ፈገግ ብላ አይታኝ እያንባረቀች ትሄዳለች።…… አስር ቀን ሆነ። እያበድኩ መሰለኝ።ላያት እየጓጓሁ በጠበቅኳት ቁጥር ጭራሽ ያየሁት ውበትም ምስሉ እየደበዘዘ በላሟ እየተተካብኝ መጣ።ተውኩት። መጠበቄን ተውኩት። ባልረሳውም ምስሏን ልረሳው ሞከርኩ። እቤት ከጓደኛዬ ጋር አደርኩ። ቅዠቴ መጣብኝ። ጥቁሯን ላም ሆነች። ግን እንደሌላው ቀን እያጓራች አልሄደችም።
ላሚቷ የደከመች መሰለች። ጎማዎቿ መሄድ ያቃታቸው።‘ላሚቷ አደብ ገዛች!’ አደብ ለመግዛቷ ምክንያት እኔ እንአሆንኩ እየተሰማኝ እፀፀታለሁ። … እንዳለፉት አስር ቀናት በሷ ጩኸት ሳይሆን ከአቡሽ ጋር በምናድርባት ኮንቴነር

👍6❤1
መንኳኳት ነቃሁ። እየተደናበርኩ በቀዳዳ አጮለቅኩ።
“ማነው እሱ?” አለ አቡሽ
“ማንም አይታይም። ገና ለሊት ነው።” አልኩት ማጮለቄን ሳላቆም። በመንገዱ መብራት መንገዱ ግልፅ ብሎ ይታያል። ዝናብ እየዘነበ ነው። ……… አየኋት!!
“ሽንቴን ልሽና!” ብዬ ከፍቼ ወጣሁ።
መውጣቴን ስታይ ፈገግ ብላ መሄድ ጀመረች። የምኖርበትን ታውቃለች? ማደሪያዬን ያንኳኳችው እሷ ናት? እየጠበቅኳት እንደነበር ታውቅ ነበር ማለት ነው? ዛሬ ከቦታዬ ስታጣኝ ነው የመጣችው? ኸረ ለመሆኑ ይህቺ ሴት እብድ ናት ጤነኛ? ራሴስ ጤነኛ ነኝ? ራሴን እየጠየቅኩ ዝናቡ እየመታኝ ትንሽ ወደሷ ራመድ እንዳልኩ ቆምኩ። ተራ በተራ የለበሰቻቸውን ድሪቶዎች እያወለቀች መጓዟን ቀጠለች። እየተከተልኳት እንደሆነ ለማወቅ መሰለኝ ዘወር እያለች ታየኛለች። የማደርገው ሳይገባኝ ተከተልኳት። ከሰው አይን ሰወር ያለ ቦታ ስትደርስ ፍፁም እርቃኗን ሆነች። ……
ይሄ ከሆነ ከወራት በኋላ ‘እሷም’ በቅዠቴ እንዳባተተችኝ ጥቁር ላም ‘አደብ ገዛች!!’ ……
🔘በሜሪ ፈለቀ🔘
🔘🔘🔘 ጨርሰናል። 🔘🔘🔘

👍5
#ከዘፈኖች_ጀርባ_የሚዘፈን_ዘፈን
:
ዘፈን ከሙሾ አነሰ፣
ትርጉሙ ተዛባ፣ ረከሰ ውሉ
ነጠላ ዜማና፣ ነጠላ ጫማ ነው፣ መንገዱ በሙሉ
፡
ልክ እንደቶምቦላ ፣ልክ እንደሎተሪ
በዘፈን ውስጥ ያልፋል፣ እንጀራ ሞካሪ
፡
ተሰጥኦ አፈር በላ
ገደል ገባ መክሊት፣ ኳኳታ ገነነ
ድምፅ ሞራጅ በዛ
ድምፅ ያወጣ ሁሉ ፣ዘፋኝ እየሆነ
፡
ታዲያ ይህን ስናይ ፣ቧልታችን ገዘፈ
የሳቃችን ምንጩ፣ ከንዴት ባሕራችን፣ እየተጨለፈ
፡
ቧልት አንድ
እኔ ደሃ ማለት ፣የፈራ አቀንቃኝ
የኖረውን እውነት
ከፍቅሩ አጣብቆ
የኔ ደሃ ይላል
እንዳይፈናፈን፣ በማጣቱ ታንቆ
ግርም ነው ሚለው
በጋራ ባዶነት ፣አብራ ካልማቀቀች
ፍቅርን ያሕል ነገር
ወደኋላ ገፍታ ፣እንዴት ተሰደደች?
የኔ ደሃ ይላል ፣የድሆች የበላይ
ኖሮት እንደሸኘ ፣ነፍሱን አስሯት ስቃይ!!
:
ቧልት ሁለት
፡
በማጣቴ ምክንያት ፣ፍቅሬ ጥላኝ ሔደች
ገንዘብ አሸነፋት ፣ለንዋይ ተረታች
ብሎ እየጮኸ
ችግር በሚሰብኩ፣ ሽንፈታም ስንኞች፣
ማዘን ሲጀምረን
በምስል ቀረፃው
አዲስ ንድፍ መኪና ፣'ሚያስገርም ቪላ ቤት
እንዳለው ሲያሳየን
የእሱ አይነት ድህነት ፣ቢሰጠን ተመኘን!!
:
ቧልት ሦስት
፡
መናኛ ሰባኪ
ነጋችንን ሊነጥቅ፣ ከዛሬ አጣብቆ
በርካሽ ሊገዛን
የእድሜ እረፍታችንን፣ በጫጫታ ጠምቆ
ዛሬ ትኖር፣ ነገ አታውቀው
ለምንድን ነው ፣ምትጨነቀው
፡
አትጨናነቅ
አትጨናነቅ
አትጨናነቅ
፡
ባለህ ተደሰት
፡
የምናባቱ ቁጠባ ፣የምናባቱ ማስቀመጥ
እጅህን ወደላይ ፣ይጨፈር ይቀወጥ
፡
ብሎ እየዘፈነ
እኛ ስንራገፍ ፣ስንቱ ሃብታም ሆነ!!
:
ቧልት አራት
፡
ወገን ተሰብሰብ፣ ተሰብሰብ
ባገሬ ምድር ላይ ፣እንዲሆን ዓለም
፡
ወዳ'ገርህ ግባ፣ ተሰብሰብ ባላገር
፡
ኑ…… ኑ
፡
አላስቀምጥ ብላው፣ ስደተኛ ነብሱ
ወዴት ነው 'ሚጠራን? የት ነው እሱ እራሱ?
፡
የዚህ አይነት ዘፈኖች
እንሰማ እንሰማና ፣ዘፋኞቹን እዚህ ፣ፈልገን ብናጣ
ሌላ ኢትዮጵያ አለች
በሚል ይመስለኛል
በባህር በድንበር፣ ካ'ገር የምንወጣ!!
:
ቧልት አምስት
፡
የመኳኳል ብዛት
አብዝቶ ፈሶባት
በዚህች ባንዲት ዘፈን
ብዙ የልብስ አይነት፣ እየቀያየረች
ከዘፈኗ በላይ፣ በልብሷ እየጮኸች
አንዴ መኝታ ቤት
አንዴ ደረጃ ላይ
ሳሎን ውስጥ
ጊቢ ውስጥ
እ~ያ~ው~ረ~ገ~ረ~ጋ~ት
ጊዜ ስንቷን ዘፋኝ
የልብስ አከራዮች፣ ደንበኛ አደረጋት
እምፅፅፅፅ
እሷን ከነልብሱ
አንድጊዜ ጠቅልሎ
ማነው ሚያሳርፈን? ማን ይሆን ሚገዛት?
፡
ቧልት ስድስት
፡
ብርሃን ፈሪ ፍቅር ፣ከቀን የተፋታ
ከፀሐይ ያሸሹት ፣የሰፉት ከማታ
፡
ነይልኝ ማታ ማታ
፡
ማታ ማታ
፡
ይሄም መጥቶ ማታ
ያቺም መጥታ ማታ
ኳኳታ
ቱማታ
፡
በመልክ የሚያፍር ነው፣ ወይደግሞ አተራማሽ
ውዱንና ፍቅሩን፣ የሚያስሰው ሲመሽ
፡
ማቀፍስ በቀን ነው~ ማቀፍ ባደባባይ
ፀሐይ አይደብቅም
አበባ አያረግፍም
ያፈቀረ ሰማይ!!
:
ቧልት ሰባት
፡
እንቺ እንካ
እንካ
ባደባባዩ
እንካ
፡
ማታ ማታ ያምረኛል
፡
ነይ እንመቻች
፡
እሰይ ሰለጠንን ፣ነውር ገሃድ ወጣች
፡
ዋናው መዝፈን ነው ጎበዝ
ያው ብልግናም ቢሆን ፣ትንሽ እናጣመው
ጫጫታ ሲነግስ
በሁሉም ጆሮ ላይ፣ እሱ ነው ሚጥመው
፡
ፈሪሃ ሰው እግዜር፣ ከምድራችን ይብቀል
ስክነት ደህና ሰንብች፣ በደቦ እንቀልቀል
ታዛቢ አጥተን እንጂ
ጭራ ነው ሚቀረን~ ጭራ ለማስበቀል!!
:
:
:
ኧረ ብዙ ብዙ~ ብዙ የሳቅ ቋንቋ
እንፈበርካለን፣ እድሜ ለሙዚቃ
፡
መረጋጋትን ሸኘናት
እሰየው መስከን ራቀ
በየጥጋጥጉ
የኳኳታ ሕጋችን፣ ባርምሞ ፀደቀ
፡
ማዳመጥ ተረሳ፣ መስማት ለመለመ
አይምሮም ኳኳታን፣ እየተረጎመ
፡
ኳ
እንቺ እንካ
፡
ከሽ
ማታ ነይ እባክሽ
፡
ድዝ
ደሞ የምን መፍዘዝ
፡
ድም
ዛሬ አንላቀቅም
፡
ቃ
ጆሯችን ተሰዋ
እድሜ ያለትርጉም፣ ለሚጮህ ሙዚቃ
፡
እግዚሃር ይመስገን
ይህን ሁሉ ጯሂ
በአጭር ዓመታት፣ እንደቀልድ አፍርተን
ከቁም ነገር በላይ፣ ቧልት ነው የተረፈን
፡
እግዚሃር ይመስገን
ብርዝ ዘፈንና ፣በራዥ ሙዚቀኛ
የለት ሳቃችንን ፣ጋብዞን ነው ምንተኛ!!!!!
:
🔘በፍቃዱ ጌታቸው🔘
:
ዘፈን ከሙሾ አነሰ፣
ትርጉሙ ተዛባ፣ ረከሰ ውሉ
ነጠላ ዜማና፣ ነጠላ ጫማ ነው፣ መንገዱ በሙሉ
፡
ልክ እንደቶምቦላ ፣ልክ እንደሎተሪ
በዘፈን ውስጥ ያልፋል፣ እንጀራ ሞካሪ
፡
ተሰጥኦ አፈር በላ
ገደል ገባ መክሊት፣ ኳኳታ ገነነ
ድምፅ ሞራጅ በዛ
ድምፅ ያወጣ ሁሉ ፣ዘፋኝ እየሆነ
፡
ታዲያ ይህን ስናይ ፣ቧልታችን ገዘፈ
የሳቃችን ምንጩ፣ ከንዴት ባሕራችን፣ እየተጨለፈ
፡
ቧልት አንድ
እኔ ደሃ ማለት ፣የፈራ አቀንቃኝ
የኖረውን እውነት
ከፍቅሩ አጣብቆ
የኔ ደሃ ይላል
እንዳይፈናፈን፣ በማጣቱ ታንቆ
ግርም ነው ሚለው
በጋራ ባዶነት ፣አብራ ካልማቀቀች
ፍቅርን ያሕል ነገር
ወደኋላ ገፍታ ፣እንዴት ተሰደደች?
የኔ ደሃ ይላል ፣የድሆች የበላይ
ኖሮት እንደሸኘ ፣ነፍሱን አስሯት ስቃይ!!
:
ቧልት ሁለት
፡
በማጣቴ ምክንያት ፣ፍቅሬ ጥላኝ ሔደች
ገንዘብ አሸነፋት ፣ለንዋይ ተረታች
ብሎ እየጮኸ
ችግር በሚሰብኩ፣ ሽንፈታም ስንኞች፣
ማዘን ሲጀምረን
በምስል ቀረፃው
አዲስ ንድፍ መኪና ፣'ሚያስገርም ቪላ ቤት
እንዳለው ሲያሳየን
የእሱ አይነት ድህነት ፣ቢሰጠን ተመኘን!!
:
ቧልት ሦስት
፡
መናኛ ሰባኪ
ነጋችንን ሊነጥቅ፣ ከዛሬ አጣብቆ
በርካሽ ሊገዛን
የእድሜ እረፍታችንን፣ በጫጫታ ጠምቆ
ዛሬ ትኖር፣ ነገ አታውቀው
ለምንድን ነው ፣ምትጨነቀው
፡
አትጨናነቅ
አትጨናነቅ
አትጨናነቅ
፡
ባለህ ተደሰት
፡
የምናባቱ ቁጠባ ፣የምናባቱ ማስቀመጥ
እጅህን ወደላይ ፣ይጨፈር ይቀወጥ
፡
ብሎ እየዘፈነ
እኛ ስንራገፍ ፣ስንቱ ሃብታም ሆነ!!
:
ቧልት አራት
፡
ወገን ተሰብሰብ፣ ተሰብሰብ
ባገሬ ምድር ላይ ፣እንዲሆን ዓለም
፡
ወዳ'ገርህ ግባ፣ ተሰብሰብ ባላገር
፡
ኑ…… ኑ
፡
አላስቀምጥ ብላው፣ ስደተኛ ነብሱ
ወዴት ነው 'ሚጠራን? የት ነው እሱ እራሱ?
፡
የዚህ አይነት ዘፈኖች
እንሰማ እንሰማና ፣ዘፋኞቹን እዚህ ፣ፈልገን ብናጣ
ሌላ ኢትዮጵያ አለች
በሚል ይመስለኛል
በባህር በድንበር፣ ካ'ገር የምንወጣ!!
:
ቧልት አምስት
፡
የመኳኳል ብዛት
አብዝቶ ፈሶባት
በዚህች ባንዲት ዘፈን
ብዙ የልብስ አይነት፣ እየቀያየረች
ከዘፈኗ በላይ፣ በልብሷ እየጮኸች
አንዴ መኝታ ቤት
አንዴ ደረጃ ላይ
ሳሎን ውስጥ
ጊቢ ውስጥ
እ~ያ~ው~ረ~ገ~ረ~ጋ~ት
ጊዜ ስንቷን ዘፋኝ
የልብስ አከራዮች፣ ደንበኛ አደረጋት
እምፅፅፅፅ
እሷን ከነልብሱ
አንድጊዜ ጠቅልሎ
ማነው ሚያሳርፈን? ማን ይሆን ሚገዛት?
፡
ቧልት ስድስት
፡
ብርሃን ፈሪ ፍቅር ፣ከቀን የተፋታ
ከፀሐይ ያሸሹት ፣የሰፉት ከማታ
፡
ነይልኝ ማታ ማታ
፡
ማታ ማታ
፡
ይሄም መጥቶ ማታ
ያቺም መጥታ ማታ
ኳኳታ
ቱማታ
፡
በመልክ የሚያፍር ነው፣ ወይደግሞ አተራማሽ
ውዱንና ፍቅሩን፣ የሚያስሰው ሲመሽ
፡
ማቀፍስ በቀን ነው~ ማቀፍ ባደባባይ
ፀሐይ አይደብቅም
አበባ አያረግፍም
ያፈቀረ ሰማይ!!
:
ቧልት ሰባት
፡
እንቺ እንካ
እንካ
ባደባባዩ
እንካ
፡
ማታ ማታ ያምረኛል
፡
ነይ እንመቻች
፡
እሰይ ሰለጠንን ፣ነውር ገሃድ ወጣች
፡
ዋናው መዝፈን ነው ጎበዝ
ያው ብልግናም ቢሆን ፣ትንሽ እናጣመው
ጫጫታ ሲነግስ
በሁሉም ጆሮ ላይ፣ እሱ ነው ሚጥመው
፡
ፈሪሃ ሰው እግዜር፣ ከምድራችን ይብቀል
ስክነት ደህና ሰንብች፣ በደቦ እንቀልቀል
ታዛቢ አጥተን እንጂ
ጭራ ነው ሚቀረን~ ጭራ ለማስበቀል!!
:
:
:
ኧረ ብዙ ብዙ~ ብዙ የሳቅ ቋንቋ
እንፈበርካለን፣ እድሜ ለሙዚቃ
፡
መረጋጋትን ሸኘናት
እሰየው መስከን ራቀ
በየጥጋጥጉ
የኳኳታ ሕጋችን፣ ባርምሞ ፀደቀ
፡
ማዳመጥ ተረሳ፣ መስማት ለመለመ
አይምሮም ኳኳታን፣ እየተረጎመ
፡
ኳ
እንቺ እንካ
፡
ከሽ
ማታ ነይ እባክሽ
፡
ድዝ
ደሞ የምን መፍዘዝ
፡
ድም
ዛሬ አንላቀቅም
፡
ቃ
ጆሯችን ተሰዋ
እድሜ ያለትርጉም፣ ለሚጮህ ሙዚቃ
፡
እግዚሃር ይመስገን
ይህን ሁሉ ጯሂ
በአጭር ዓመታት፣ እንደቀልድ አፍርተን
ከቁም ነገር በላይ፣ ቧልት ነው የተረፈን
፡
እግዚሃር ይመስገን
ብርዝ ዘፈንና ፣በራዥ ሙዚቀኛ
የለት ሳቃችንን ፣ጋብዞን ነው ምንተኛ!!!!!
:
🔘በፍቃዱ ጌታቸው🔘
👍1
#ሀርሜ_ኮ
ክፍል-1
✍
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ
አንድ ሰው በጣም እድለኛ ከሆነ እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ሁለት ነገሮች ይኖሩታል፡፡እናት እና ሀገር፡፡በከፋን ቀን በእናት ጉያ መሸጎጥ ደስ ባለን ቀን በራስ ሀገር ሰማይ ስር መቦረቅ በብር ልንገዛው የማንችል ከመታደል የሚገኝ በረከት ነው፡፡ለዚህ ነው ለእናት ጤንነት እና ለሀግር ሰላም ሁሉም የሚጨነቀው፡፡እናትና ሀገርን ማጣት ማለት እኛነታችንን ማጣት ስለሆነ የእኛ ማንነት እና ሙሉ ታሪክ እናትና ሀገራችን ጉያ ውስጥ ስለሚገኝ….እኛ አስኳል ብንሆን እናትና ሀገራችን አስኳሉን ሸፍነውና ከልለው ከአደጋ የሚጠብቁት እና በህይወት የሚያቆዩት ከመንፈሳዊ ብልፅግና እና ከጥልቅ ፍቅር የተሰሩ ቅርፊቶቹ ናቸው..(ከለላዎች)፡፡ቅርፊቱ ከተሸነቆረ አስኳሉም የለ….አዎ እናት ስትሞት እና ሀገር ስትፈርስ በእቅፋቸው ውስጥ የነበረው ህይወት አብሮ ይከስማል፡፡ህልወና ያከትማል።
……. ቤታችን ሶስት መኝታ ክፍል ከአንድ ሳሎን ጋር ኩሽናንና መታጠቢያ ቤትን አጠቃሎ የያዘ መለሰተኛ ቢላ ቤት ነው፡፡እዚህ ውስጥ መኖር ከጀመርን 25 ዓመታትን አስቆጥረናል …. የቤቱ ኑዋሪዎች የመጀመሪያው መኝታ ቤት ሁለት እህቶቼ እና አንድ የእህቴ ልጅ ሌላው ክፍል ወንድሜ ለብቻው ሶስተኛው መኝታ ክፍል እኔ እና እናቴ እንተኛበታለን..በነገራችን ላይ ከእኔ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደር የሚችል አንድ ብቸኛ ሰው ብትኖር እናቴ ብቻ ነች..ምክንያቱም ያው እዛው አልጋዬ መሀከል ላይ ተቀዶ በተሰራልኝ ልዩ መፀዳጃ ስለምፀዳዳ፡፡ ምንም እንኳን እናቴ ተከታትላ ሳትሰለች በየቀበኑ ብታፀዳውም….ሰንደሉንም እጣኑንም ብታጫጭስበትም ጠረን ማምጣቱ አይቀርም…ስለዚህ ማንም እዛ ክፍል ከደቂቃዎች በላይ መቆየት አይችልም..ወንድሜና እህቶቼ እንኳን ስሬ ቁጭ ብለው የሚያወሩኝ እና የሚያጫውቱኝ ተፀዳድቼ መኝታ ቤቴን ለቅቄ ሳሎን በዊልቸሬ ላይ ወይም ሶፋ ላይ ተዘርሬ ሲያገኙኝ ብቻ ነው የሚያዩኝ..እናቴ ግን ይሄው 22 ዓመት ከጎኔ ተለይታኝ ተኝታ አታውቅም…ግን እንዴት አይሰለቻትም..?ለመሆኑ የእናትነት ፀጋ ማለት ከምን አይነት ጽናት ጋር ይሆን ሚሰጠው…?እኔ እንጃ… ይሄ ከእኔ የማሰብ አቅም በላይ ነው፡፡
ይቅርታ አንድ ተጨማሪ ሰው ዘንግቼያለው ባለፍት 5 ዓመታት አብራን የምትኖር ትርሲት የምትባል ሰራተኛ አለች፡፡
እስቲ ሰለቤተሰባችን አባል ዘርዘር ያለ መረጃ ልስጣችሁ… ..ከማን ልጀምር ከእናቴ ጀመርኩ…..?እናቴ ዕድሜዋ 49 ዓመት አካባቢ ይሆናል፡፡በ23 ዓመቷ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ በባይሎጂ ተመርቃ ሃይስኩል ውስጥ ማስተማር ከጀመረች 26 ዓመት አልፎታል ፡፡ያው ከእኔ ዕድሜ 4 ዓመት በፊት ጀምሮ ማለት ነው ፡፡ብዙ ሙሁሮችንም ብዙ ብኩኖችንም ለዚህች ሀገር አበርክታለች፡፡
ይሄ እናቴ የምታስተምርበት ሀይስኩል ከቤታችን ከተንቀራፈፉ 5 ደቂቃ ከፈጠኑ ሁለት ደቂቃ ነው የሚርቀው፡፡ያ ማለት … እናቴ መኖሪያዋ እና የስራ ቦታዋ አንድ ቦታ እንደሆነ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡እናቴ ይሄን ሁሉ አመት እንዴት አንድ ትምህርት ቤት አንድ አይነት ትምህርት ስታስተምር ኖረች..? እንዴት ትምህርቷን ሳትቀጥል..? እንዴት ስራ ሳትቀይር..?እንዴት ሳታገባ…? የእነዚህ ሁሉ መልስ ከእኔ ማንነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡
እናቴ አስተማሪ ሆና ትምህርት ቤቷ ውስጥ እና እናት ሆና ቤት ውስጥ ሁለት የተለያየች ሴት እንደሆነች ነው ሚሰማኝ….እናቴ ውብ ምትባል አይነት ሴት ነች፡፡ወደ ቀይነት ያደላ የሰውነት ቀለም ፤ ደርበብ እና ሞላ ያለ ሰውነት፤ ባለ ስልካካ አፍንጫ እና ቦግ ቦግ ያሉ አይኖች ያሏት ሜትር ከ79 የምትረዝም ዘለግ ያለች ሴት ነች፡፡
ስለፀባይዋ ልንገራችሁ… ልስልስ አመል ያላት ምትገርም ሴት ነች…ለማንም ሰው ቢሆን ሊጣሏት የምታስቸግር አይነት ሰው ነች፡የጋለውን ማብረድ፤የሞቀውን ማቀዝቀዝ፤የተወጠረውን ማስተንፈስ ትችልበታለች፡፡ነገሮችን በተረጋጋ እና ባልተዋከበ እርጋታ መከወን የተካነችበት ስጦታዋ ነው፡፡ያው የዚህ ታሪክ ዋና ምሰሶ እሷ ስለሆነች በየክፍሉ ስለእሷ ምነግራችሁ ብዙ ነገሮች ስለሚኖሩ ይበልጥ እያወቃችኃት እና እየወደዳችኃት ትመጣላችሁ፡፡ …ለአሁኑ ግን ወደሌሎቹ ልሂድ….፡፡ቆይ ስሟን አልነገራኮችሁም ለካ…መገርቱ ትባላለች፡፡
መሀሪ ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡የዓለም ቁጥር አንድ ዝርክርክ እና ግድ የለሽ ሰው እሱ ይመስለኛል…ተራሮች ወደ ሸለቆነት ቢቀየሩ ፤ምድር እንደኖህ ዘመን በጥፋት ውሀ ብትጥለቀለቅ፤ፀሀይ በጠለቀችበት በዛው ቀርታ ይህቺ ምድር በጨለማ ብትዋጥ ለእሱ ደንታው አይደለም…፡፡ለዚህ ወንድሜ በህይወት ለመኖር ሶስት ነገሮች በቂው ናቸው… የሚያነበው መጽሀፍ ፤የሚቅመው ጫት እና የሚጎነጨው አረቄ…በቃ ፡፡ከዛ የተረፈው የዓለም ትርምስ ሁሉ ለእሱ ትርፍ ነው፡፡እቤት ሲገባና ሲወጣ እራሱ ማን አለ… ማን የለም.? ዞር ብሎም አያይም…፡፡ደህና ዋሉ ሳይል ይወጣል… ደህና ቆያችሁ ሳይል ይቀላቀላል…፡፡
ከእህቶቹ ጋር ቃላት እንኳን የሚለዋወጠው በወር ወይም በሁለት ወር አንድ ቀን ሊሆን ይችላል..ከእናቴ ጋር ግን የተሻለ ያወራል..ቢያንስ ማውራት ቢያስጠላው እንኳን ግንባሯን ስሞ ገብቶ ግንባሯን ስሞ መውጣቱ የማይዛነፍ ተግባሩ ነው፡፡ከእኔ ጋ ያለው ግንኙነት ግን የተለየ ነው፡፡እኔ ለወንድሜ ሚስጥረኛው ነኝ፡፡ሰው ሁሉ ከቤት ተጠራርጎ ወጥቶ ብቻችንን በምንሆንበት ሰአት የማያወራኝ ነገር የለም… ከግል ሚስጥሩ አንስቶ ስለጠቅላላ ሀገር አቀፍ ሆነ አለም አቀገፍ ወቅታዊ እወነቶች፡ ስላነበባቸው መጽሀፎች፡ ስለሰማቸው ዜናዎች.. ከኢንተርኔት ላይ ስላገኛቸውና ስላስደነቁት ተአምሮች ያለመሰልቸት ያወራኛል፡፡ በጽሞና አደምጠዋለው..፡፡
አንዳንዴም በእኔ ላይ ያለውን ቅሬታ...የህይወቱን አቅጣጫ እንዲህ ዝብርቅርቅ ያደረግኩት እኔ መሆኔን…በዚህም ምክንያት እንደሚበሳጭብኝ በምሬት ይነግረኛል..እኔም እሰማዋለው›..ምክንያቱም ወቀሳው እውነትነት እንዳለው እኔም አምናለው…፡፡
እንዲያም ሆኖ ግን ወንድሜ መሀሪ ባለሞያ ነው.. ጎበዝ የኮምፒተር ባለሞያ…በኮምፒተር ሳይንስ ዲፕሎማ አለው…ግን ከዛ በላይ የተፈጥሮ ስጦታው ይበልጣል…ተለምኖ፤ በስልክ ተጨቅጭቆ ነው የሚሰራው፡፡በቀን ውስጥ በጣም ሰራ ከተባለ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓት ነው..ግን እንደዛም ሆኖ ተጠቅሞ ከሚጨርሰው ብር የበለጠ ገቢ ያገኛል ….
ቀጥሎ ወደእህቶቼ ልሂድላችሁ …እኚ እህቶቼ መንትዬች ናቸው…ለእኔ ታላቆቼ ናቸው፡፡ፌናን እና ሮማን ይባላሉ ፡፡ስማቸውን ለአንደኛዋ አባቴ ለሌለኛዋ ደግሞ እናቴ ነች ያወጣችላት፡፡አንደኛዋን ከአንደኛዋ በመልክ ለመለየት ለማንም ሰው ከባድ ፈተና ነው..እኔና እናቴ ግን በቀላሉ እንለያቸዋለን፡፡ሁለቱም ቀይ ቀጭን መካከለኛ ቁመት ከግብዴ መቀመጫ ጋር ያላቸው ቆንጆ እና ጎረምሳው ሁሉ ለሀጩን የሚያዝረከርክባቸው ቀሽት ሚባሉ ጉብሎች ናቸው፡፡
እህቶቼን በተመለከተ በጣም የሚማርከኝ ነገር ቢኖር ጫወታቸው ነው፡፡እነሱ እቤት ውሥጥ ካሉ በቃ የእኛ ቤት ኮመዲያን የተሰባሰቡበት ኮንሰርት ነው የሚመስላችሁ…. ..እርስ በርስ ጫወታቸው፤መተራረባቸው፤ከእናቴ ጋር የሚያወሩት ወሬ….ሁለ ነገራቸው ድምቀት አለው፡፡እኚህ እህቶቼ ለማንኛውም ሰው እንደመልካቸው ሁሉ ፀባያቸውም አንድ ይመስለዋል ..ግን በጥልቀት ሲመረመር በጣም ይለያያሉ፡፡
ለምሳሌ ሮማን..እቤት ውስጥ ሮሚ ነው የሚሏት… ትምህርት በጣም ስትወድ ፌናን ደግሞ ቶሎ ብላ በዚህም በዛም ብላ ሀብታም መሆን ነው ፍላጎቷ… ሀብታም ለመሆን የመጀመሪያዋ ምርጫዋ ነጋዴ መሆን ነው....አሁን ጀመራዋለች ፡፡ያ ካልተሳካላት

👍11🥰2❤1
ግን መዝረፍ እና ማጅራት መምታት ሁሉ ልትጀምር እንደምትችል በቀልድ እያስመሰለችም ቢሆን ታወራለች..ይህ ሁሉ ካልተሳካላት የመጨረሻ ምርጫዋ ግን ሀብታም ባል አግብታ ሀብታም መሆን ነው፡፡ በአቋራጭ መክበር ይሏችሆል እንዲህ ነው፡፡
ሮሚ ያው እንደነገሪኮችሁ ቀለሜዋ ነች ..አሁን የህክምና የ5ኛ ዓመት ተማሪ ነች፡፡ ለዛውም የእውነት ሰቃይ ተማሪ፡፡እርግጥ እንደአጀማመሯ አሁን ስድስተኛ አመቷ ላይ መሆን ነበረባት፡፡ግን ሶስተኛ አመት እያለች ዊዝድሮዋል ለመሙላት እና አንድ አመት ለማቋረጥ ተገዳ ነበር ..ለምን ብትሉ….? አርግዛ፡፡ምክንያቱም እሷ ወንድን ማመን እና በቅጽበት ለፍቅር ዝልፍልፍ ማለት ዋና ድክመቷ ነው… ፡፡እናም አሁን የሦስት አመት ልጅ አላት….ማክዳ እንላታለን፡፡በዚህ ጉዳይም ከፌናን ጋር ይላያያሉ ያቺኛዋ ቆቅ ነች …ከዛም ከዛም ጋር ስቃና ፎግራ ዞር ማለቱን ተክናበታለች፡፡
ማክዳ ያው እንደነገርኮችሁ የእህቴ የሮማን ልጅ ናት፡፡ቤታችንን እና አለማችንን ከተቀላቀለች ገና ሶስት አመቷ ቢሆንም ታሪካዊ ለነበረው ቤተሰብ ሌላ ታሪክ ጨምራበታለች…..ሌላ ድምቀት ሌላ ደስታ..ሌላ ፍንደቃ..በተለይ ለእናቴ...ምንም ቢሆን የመጀመሪያዋ የልጅ ልጇ አይደለች፡፡
አሁን የቀረውት እኔ ነኝ ፡፡ቆይ ስለእኔ ማውራት ከመጀመሬ በፊት ለካ አባት የሚባል ነገር አለ ፡፡የሁላችንም አባት አንድ ሰው ነው፡፡ከእናቴ ጋር በትዳር 8 ዓመት ከቆየ ቡኋላ ተፋተዋል..የፍቺያቸው መንስኤ እኔ ነኝ…፡፡በእኔ ጉዳይ ላይ መስማማት ስላቃታቸው ለመለያየት በቅተዋል…አሁን የት እንዳለ በትክክል አላውቅም ..ማወቅም አልፈልግም …ቢሞት ሁሉ ግድ ያለኝ አይመስለኝም…፡፡…በነገራችን ላይ አንዳንዴ ሳስብ እናቴን ያለ ባል ወንድምና እህቶቼን ያለአባት ስላስቀረዋቸው ውስጤን ይደማል፡፡….መላ ቤተሰቡ ለእኔ ሲል የከፈለውን መስዋዕትነት ሳስብ ምነው ባልተፈጠርኩ ኖሮ ምልባቸው ቀናቶች ብዙናቸው…በጣም ብዙ፡፡
እስቲ ስለራሴ እንዲሁ ለትውውቅ ያህል ጥቂት ላውራችሁ፡፡ስሜ ብዙ ነው፡፡እዬብ፣በእሱ ፍቃድ ፤ፀጋ፤ ኪያ እኚ ሁሉ ስሞች ከኪያ በስተቀር የወጡልኝ በእናቴ ነው…ኪያ እህቴ ፌናን ያወጣችልኝ ስም ሲሆን አሁን እቤት ውስጥ አብዛኛው ሰው አዘውትሮ የሚጠቀመው ይሄንን ስም ነው፡፡አሁን 22 ዓመቴ እንደሆነ የነገርኳችሁ መሰለኝ፡፡ትምህርት አልተማርኩም..እንዳይደናገራችሁ አልተማርኩም ስላችሁ መሀይም ነኝ ማለቴ አይደለም፡፡ግን መደበኛውን የትምህርት ስርዓትና ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ አንደኛ ሁለተኛ እያልኩና ትምህርት ቤት እየተመላለስኩ የመማሩን እድል አላገኘውም፡፡ግን አሁን የጠቅላላ ዕውቀት ፈተና ብፈተን አንድ ጎበዝ ከሚባል ዲግሪ ምሩቅ ጋር የተመጣጠነ ክህሎት እንደሚኖረኝ እተማመናለው፡፡ይሄ ክህሎት በቀልድ የተገኘ አልነበረም እናቴ ያለፉትን አስራ አምስት አመት ለፍታ አስተምራኛለች፡፡ማለቴ ለብቻዬ..እቤት ውስጥ….ግራ ተጋባችሁ አይደል…..?፡፡
አሁን በዚህን ወቅት ሰማያዊ ቀለም ያለው ለስለስ ያለ ሙሉ ቢጃማ ለብሼ ከቤታችን ጓሮ ካለው ጽዱና በአበቦች በተከበበው አፀድ ውስጥ ዊልቸር ላይ ተቀምጬ የጥዋት ፀሀይ በተመስጦ እየሞቅኩ ነው …፡፡እግሮቼ የዊልቸሩ እግር ተደግፈው ልፍስፍስ ብለው ይታዩኛል…. ቀኝ እጄ እናቴ ቅድም እዚህ ቦታ ስታመጣኝ የዊልቸሩ እጀታ ላይ አስተካክላ እንዳስቀመጠችው እዛው ባታ እንደዛው ተልፈስፍሶ ተቀምጧል፡፡ደካማው አንገቴ ጭንቅላቴን ሙሉ ለሙሉ መሸከም ስለማይችል ዝንብል ወደለበት ወደግራ በኩል ለሱ ተብሎ በተሰራለት መደገፊያ ላይ ደገፍ ብሏል …የተከፈተ አፌን መክደን ተስኖኝ ለሀጬ መዝረክረኩ ለእኔው እየታየኝ በራሴው ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ ነው፡፡
ከሰውነት ክፍሎቼ ያለማንም እርዳታ በነፃነት መንቀሳቀስ የሚችሉት ዓይኖቼ እና ግራ እጄ ብቻ ነው፡፡በግራ እጄ እበላለው…. በግራ እጄ ዊልቸሬን በመጠኑ ማንቀሳቀስ እችላለው..በግራ እጄ እጽፋለው…በግራ እጄ በምልክት ከቤተሰቦቼ ጋር ለመግባባት እሞክራለው…እናም ደስታኛ ነኝ፡፡መቼስ ደስተኛ ነኝ ስላችሁ ምፀት ይመስላችኃል አይደል...?እውነቴን ነው፡፡ለዚህ ማንነቴ የበቃውት በተአምር እና በእናቴ የዘመናት ትጋት ነው፡፡ቢያንስ እኮ የምጠቀምበት አንድ እጅ አለኝ ..ይሄ እጄ ደግሞ መንቀሳቀስ ከጀመረ ገና ሶስተኛ አመቱ ነው…አይኖቼ ከበፊቱም በደንብ አጥርተው ያዩልኛል..ጆሮዎቼ ከብዙ ርቀት አጥርተው ይሰሙልኛል..አዕምሮዬ ጥርት አድርጎ ነገሮችን ማገናዘብና መመራመር ይችላል…፡፡
እዚህ ላይ ከሁሉም በላይ እኔ ማሰብ እንደምችል አካባቢዬ ያሉ ሰዎች ሁሉ ማመን ከጀመሩ ገና አምስት ስድስት አመታት ቢሆነው ነው፡፡ከዛ በፊት ለሁሉም ሰው አዕምሮዬም እንደአካሌ የበደነ እንደሆነ ነበር የሚገምቱት… ከእናቴ በስተቀር..፡፡
እንደነገርኳችሁ ከአምስት አመቴ ጀምሮ እናቴ ጭኗ ላይ አስተኝታ ፀጉሬን እያሻሻች መፅሀፍ ታነብልኝ ነበር… ያንን የሚያስተውሉ ዘመድ ወዳጆች ግን እሷም ማበዷ ነው ይሏት ነበር..እና በትራስ ደራርባ በማስደገፍ ከፊቴ ጥቁር ብላክ ቦርድ ሰቅላ ከአምስት አመቴ ጀምሮ ሀ..ሁ..ሂ እያለች ያለመታከት ስታስጠናኛ…A,B.C….ስታለማምደኝ 1..2..3..እያለች ስትደጋግምልኝ..ሁሉም ሰው የሚያስበው ጋንኤል እንደለከፋት ነበር
…እኔ እንደዛሬ ግራ እጄን እንኳን ማንቀሳቀስ አልችልም ስለነበር… በምልክት እንኳን ገብቶኛል አልገባኝም ብዬ አላረጋግጥላት አልችልም ነበር..አንገቴንም› እንኳን ሙሉ በሙሉ ለማዘዝ አልችልም ነበር…..ከእነዛ አይኖቼ የሚወጡት የብርሀን ጨረሮች ግን ከእናቴ ጋር ለመግባት በቂ ነበሩ…የምትለውን እንደምሰማትም እንደምረዳትም ከአይኖቼ ውስጥ አንብባ ታውቅ ነበር…እናቴ ትምህርት ቤት ባይሎጂ እንደምታስተምር ነግሬያችሁ ነበር… እቤት ግን እኔን ሁሉንም ትምህርት ደራጃውን በጠበቀ ጥራት ታስተምራኛለች….አሁንም ድረስ መናገር አልችልም፡፡ግን ሶስት ቋንቋ በደንብ አጥረቼ ሰማለው..እፅፋለው፡፡እድሜ ለእናቴ…
እንግዲህ ወደ ዋናው የቤተሰባችን ታሪክ ለመግባት ከእናቴ የወጣትነት ጊዜ ጀምራለው…. የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለች ጀምሮ ያለውን…...
💫💫ይቀጥላል💫💫
አብሮነታችሁ ያበረታናል Like 👍 በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን
ማንኛውንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍8😁1
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-2
✍
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
...ይሄ ታሪክ እናቴ እና አባቴ እንዴት እንደተዋወቁ የሚያትት ነው፡፡ታሪኩን የነገረችኝ እናቴ ነች፡፡እርግጥ ታሪኩን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በስድስት ወር እና በዓመት ልዩነት አቀራረብን ለወጥ እያደረገች የተወሰነውን እየቀነሰች እና በፊት ነግራኝ ከነበረው ውስጥ ያልተካተተ አዲስ ታሪክ እየጨመረችበት ነግራኛለች፡፡እናቴ ስለአባቴ የምታወራኝ ብሶት ሲሰማት ነው..ውስጧን ሀዘን ሲቦረቡረው ነው…ልቧ ውስጥ ያለ ጥልቅ ባዶ ሽንቁር ሲረብሻት ነው፡፡የዛን ጊዜ ትናንቷን ታስታውሳለች፤የድሮ ፍቅሯ ትዝ ይላታል፡፡የዛን ጊዜ አባቴን ታስታውሳለች፤የዛን ጊዜ የሚያዳምጣትን ሰው ትፈልጋለች፤ለማዳመጥ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ከእኔ ከልጇ በላይ ችሎታ ያለው ሰው የለም..ድንቅ የተባልኩ አድማጭ ነኝ የማንንም ንግግር አላቋርጥም ደግሞም ሚስጥር ጠባቂ ነኝ ..ማንም የፈለገውን ነገር ለእኔ ቢነግረኝ በቃ ለአምላኩ በሽኩሽኩታ እንደነገረው መቁጠር አለበት.ስለዚህ የቤታችን አባል መተንፈስ እና እፎይ ማለት ሲያስፈልጋቸው ወደ እኔ ነው የሚሮጡት..ይህ እናቴንም ያጠቃልላል፡፡
እና ይሄንን ከአባቴ ጋር የነበራትን የፍቅር ታሪክ ደጋግማ ስለነገረችኝ ልክ በእያንዳንዷ ግንኙነታቸው ወቅት አብሬያቸው የነበርኩ መስሎ ነው ሚሰማኝ …ሁሉ ነገር ልክ አሪፍ ደራሲ እንደደረሰው መሳጭ የፍቅር ድርሰት ፍንትው ብሎ ይታወሰኛል፡፡
የተገናኙት ሁለቱም የአዲስ አበባ የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው፡፡እሱ የኬሚስትሪ እሷ የባይሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ ነበሩ …ያው ፍረሽ ማን ላይ ሁለቱም የሚወስዱት ተመሳሳይ አይነት ኮርስ ነበረ እና የገና ማዕበል ለማምለጥ ሁሉም ተማሪ በፍራቻ ተውጦ፤በስጋት እየተናጠ አንገቱን አቀርቅሮ በየዩኒቨርሲቲው ጥጋ ጥግ እና በላይብረሪው ከወረቀት ጋር እራሱን አጣብቆ ፍዳውን በሚያበት ወቅት ነበር..በተለይ መምህሩ አንብቡ ብሎ የጠቆማቸውን መጽሀፍና፤ሲኒየር ሚባሉት ተማሪዎች ለፈተና ያንን መጽሀፍ አንብቡት ብለው የጠቆሙትን መጽሀፍ ለማግኘት ላይብረሪ ውስጥ ያለው መራኮት እና መሻማት ያስቃልም .ያስተዛዝባልም፡፡ በተለይ የፈተናው ወቅት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ውጥረቶቹ በዛው ልክ እየከረሩ ይሄድ ነበር፡፡
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ሞጋስ ባሴ የተባለው ከጎንደር አርማጭኦ አካባቢ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የመጣው ወጣት በዚህ መራኮት ውስጥ በመደነጋገርም ቢሆን መፋለም ጀምሮ የነበረው..ግን ሁሌ ተሸናፊ ነበር…፡፡ካደገበት ማህበረሰብ የወረሰው ይሉኝታ ለተሸናፊ እንዲዳረግ አመቻችቶታል፤ከመናጠቅ ይልቅ መካፈልን ነበር የሚያውቀው ጓደኛን ወደ ኃላ ስቦ በማስቀረት ወደ ፊት ከመሸምጠጥ ይልቅ አንተ ቅደም ወንድሜ ብሎ ከመንገድ ገለል ብሎ ሌላውን የማሰቀደም ስነ ልቦና ነበር የነበረው፡፡ንጽህ የዋህነት፤የጠራ ሰባዊነት የግል ንብረቶቹ ነበሩ…፡፡ግን አዲስ አበባ ሌላ ነው፡፡እርግጥ ከእሱ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ የክፍለሀገር ልጆች ነበሩ..ግን በተለይ በመጀመሪያው አመት የሚደምቁትና ፈካ ብለው የሚታዩት የትላልቅ ከተማ ውልዶቹ ናቸው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ..በምዕራባዊውና በምሰራቃዊው ፍልስፍና መካከል የሚዋልል ከተሜን በውስጧ የያዘች መንጠቅ እንደብልጠት፣መቅደም እንደአራዳነት የሚታይባት የተለየች ቦታ ..እና አንድ መጽሀፍ ለማግኘት ለ5 ቀን የላይብረሪውን ደጅ ፀንቶ ነበር..አልቀናውም እንጂ..፡፡
‹‹አረ ወዲያ….›› እያለ ላይብረሪውን ለቆ በቅሬታ ሲወጣ ..ያንን የሰሙ ሌሎች እኩዬቹ ሲገለፍጡበት ለሶስት ቀን የታዘበችው እናቴ ታዝባ ቅር ብሎት ነበር…በአራተኛው ቀን ግን ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ሳትንቀሳቀስ በምልክት ጠራችው..እሷ ወደ ተቀመጠችበት መቀመጫ ግራ በተጋባ እይታ ተገትሮ ሲያማትር መልሳ በእጇ ምልክት ጠራችው…፡፡በንዴቱ ውስጥ ቢሆንም…ወደ እሷ ተጠጋ..ስሯ ደረሰ….
‹‹ተቀመጥ አለችው…››በሹክሹክታ
‹‹ምን ይሁነኝ ብዬ….?.››መለሰላት ከእሷ ትንሽ ከፍ ባለ ድምጽ ሌሎችን የላይብረሪ ተጠቃሚዎችን እንዳይረብሹ በመስጋት ግራና ቀኝ በመሳቀቅ ተመለከተችና‹‹ ቁጭ በል›› ብላ ልክ ከዚህ በፊት በደንብ እንደምታውቀው የቅርብ ጓደኛዋ እጁን በመያዝ ስባ አስቀመጠችውና‹‹ይሄን አይደል የፈለከው …እንካ አንብብ››ብላ ስታነበው የነበረውን መጻሀፍ ወደ እሱ ፊት አስጠጋችለት ….ማመን አልቻለም..አንዴ መፅሀፉን ..አንዴ ልጅቷን እያፈራረቀ ማየት ጀመረ
‹‹አጥና እንጂ… ለዚህ መጽሀፍ አይደል ሳምንቱን ሙሉ ስትበሰጭ የሰነበትከው…..?እኔ በቂ ቀን አግኝቼ ማየት ያለብኝን ያህል አይቼዋለው ዛሬ ደብተሬን ነው የማነበው…››
‹‹ታዲያ እማታነቢው ከሆነ ለምን ታቀፍሺው.? ››በብስጭት
‹‹ለአንተ ብዬ.››
‹‹አረገኝ…..?.›.›
‹‹ባክህ ታጠና እንደሆነ አጥና …ካልፈለግክ መጽሀፍን አምጣው..››ለራሷም ባልታወቃት ስሜትም በቁጣ መለሰችለት፡፡…. እንግዲህ የመጀመሪያ ትውውቃቸው እንዲህ ነበር የጀመረው፡፡
እርግጥ ሁለቱም ኢትዬጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተለያየ አካባቢ እና ባህል ውስጥ ነው ያደጉት ፡፡ ቢሆንም ይሄ ልዩነታቸው ለግንኙነታቸው እንቅፋት አልሆነባቸውም..እናቴ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው አዲስ አለም ከተማ ተወልዳ ያደገችና ሀይስኩል ስትደርስ ወደአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ገብታ ተምህርቷን የጨረሰች በመሆኗ ከተሜነት ሲያጠቃት አባቴ ግን ከአነስተኛ የገጠር ከተማ በመውጣቱ በተቃራኒ ስሜት ውስጥ ያለ ነበር..
ከዛን ቀን ወዲህ ለሁለተኛ ጌዜ የተገናኙት አንደኛ ሴሚስተር ፈተና ተጠናቆ የፈተና ውጤቱ ታውቆ ውጤቱም ቦርድ ላይ ተለጥፎ ተማሪ እየተተረማመሰ በሚያበት ጊዜ ሁለቱም ከትርምሱ ውስጥ የየራሳቸውን አይተው ሲወጡ እርስ በርስ በመላተማቸው ነበር…ዞር ብላ ስታየው ማንነቱ ትዝ ስላላት ‹‹…አንተ››አለቸ
‹‹አንቺው…አለሽ ኖሮል.? ››
‹‹ምነው ፈልገሀኝ ነበር እንዴ.?››ይሄንን የሚያወሩት ከተማሪዎቹ አጀቡ ተገንጥለው በመውጣት ብቻቸውን ጎን ለጎን እየተራመዱ ነበር
‹‹እሱማ አልፈለግኩሽም…በሀሳቤ ተሰንቅረሺብኝ እንጂ››
‹‹ምን ተሰንቅረሽብኝ..ማ.. እኔ .?››እናቴ በመገረም
‹‹እንደእሱም ማለቴ እማየደል.?››
‹‹እና እንዴት ማለት ነው.?››
‹‹በቃ ተይው…ለመሆኑ ፈተናይቱን እንዴት ሆንሽ…..?››
‹‹አሪፍ ነው...አንተስ….?››
‹‹እኔማ ጥሩ ነው.. እንዲሁ ባልፈራ ኖሮ የተሸለ አመጣ ነበር…ወይኔ ወንድ በሀገሬ መውዜር እና ምንሽር ቢደቀንብኝ ማልበረግግ ዠግና እዚ በወረቀት ተለቅልቆ ለሚመለስ የፈረንጄ ወሬ ልንቦቅቦቅ…...?››
ከዚህ ቡኃላ ግንኙነታቸው በጓደኝነት ይቀጥላል …ሁለተኛ አመት ግምሽ ድረስ ተመሳሳይ ይሆናል…አብረው ያጠናሉ…አብረው ከተማውን ይዞራሉ…ሚስጥር ይጋራሉ፡፡
ነገሮች የተቀየሩበት ቅጽበት አባቴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሁለት አመት ሲማር ከዕውቀቱ ይልቅ አራዳነቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷ ነበር .ከንግግሩ ቀልጠፍ፤ከአለባበሱ ዘነጥ፤ካረማመዱ ጀነን ማለቱ ለሌላ ሰው አይደለም ለሱ ለራሱ ይታወቀው ነበር…አሁን ከየዋህነት ይልቅ ብልጠትን፤ከመበለጥ ይልቅ መሸወድን፤ከመግደርደር ይልቅ አይን አውጣነትን፤ተጎትቶ ከመቅረት ይልቅ ጎትቶ ማለፍን እለት ከእለት ከመደበኛ ትምህር እኩል እንደውም ከእዛም በላይ እየተለማመዳቸው የህይወቱ አንድ ክፍል አድርጎቸው አድርጓቸው ነበር የእኛ ስልጣኔ እንዲህ አይደል?እና እናቴንም በተመለከተ ሳይቀደም ሊቀድም ወሰነ በአንድ እለተ እሁድ የረፍት ቀን በወቅቱ ዝነኛ ወደ ነበረው እና ዘፋኞች ሁሉ የቪዲዬ ክሊፓቸወንን ወደሚያስቀሩጽበት ብሄረ-ጽጌ መናፈሻ ሳታስብ ወሰዳት

👍14😁1