አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሀርሜ_ኮ

ክፍል-1

:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ

አንድ ሰው በጣም እድለኛ ከሆነ እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ሁለት ነገሮች ይኖሩታል፡፡እናት እና ሀገር፡፡በከፋን ቀን በእናት ጉያ መሸጎጥ ደስ ባለን ቀን በራስ ሀገር ሰማይ ስር መቦረቅ በብር ልንገዛው የማንችል ከመታደል የሚገኝ በረከት ነው፡፡ለዚህ ነው ለእናት ጤንነት እና ለሀግር ሰላም ሁሉም የሚጨነቀው፡፡እናትና ሀገርን ማጣት ማለት እኛነታችንን ማጣት ስለሆነ የእኛ ማንነት እና ሙሉ ታሪክ እናትና ሀገራችን ጉያ ውስጥ ስለሚገኝ….እኛ አስኳል ብንሆን እናትና ሀገራችን አስኳሉን ሸፍነውና ከልለው ከአደጋ የሚጠብቁት እና በህይወት የሚያቆዩት ከመንፈሳዊ ብልፅግና እና ከጥልቅ ፍቅር የተሰሩ ቅርፊቶቹ ናቸው..(ከለላዎች)፡፡ቅርፊቱ ከተሸነቆረ አስኳሉም የለ….አዎ እናት ስትሞት እና ሀገር ስትፈርስ በእቅፋቸው ውስጥ የነበረው ህይወት አብሮ ይከስማል፡፡ህልወና ያከትማል።
……. ቤታችን ሶስት መኝታ ክፍል ከአንድ ሳሎን ጋር ኩሽናንና መታጠቢያ ቤትን አጠቃሎ የያዘ መለሰተኛ ቢላ ቤት ነው፡፡እዚህ ውስጥ መኖር ከጀመርን 25 ዓመታትን አስቆጥረናል …. የቤቱ ኑዋሪዎች የመጀመሪያው መኝታ ቤት ሁለት እህቶቼ እና አንድ የእህቴ ልጅ ሌላው ክፍል ወንድሜ ለብቻው ሶስተኛው መኝታ ክፍል እኔ እና እናቴ እንተኛበታለን..በነገራችን ላይ ከእኔ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደር የሚችል አንድ ብቸኛ ሰው ብትኖር እናቴ ብቻ ነች..ምክንያቱም ያው እዛው አልጋዬ መሀከል ላይ ተቀዶ በተሰራልኝ ልዩ መፀዳጃ ስለምፀዳዳ፡፡ ምንም እንኳን እናቴ ተከታትላ ሳትሰለች በየቀበኑ ብታፀዳውም….ሰንደሉንም እጣኑንም ብታጫጭስበትም ጠረን ማምጣቱ አይቀርም…ስለዚህ ማንም እዛ ክፍል ከደቂቃዎች በላይ መቆየት አይችልም..ወንድሜና እህቶቼ እንኳን ስሬ ቁጭ ብለው የሚያወሩኝ እና የሚያጫውቱኝ ተፀዳድቼ መኝታ ቤቴን ለቅቄ ሳሎን በዊልቸሬ ላይ ወይም ሶፋ ላይ ተዘርሬ ሲያገኙኝ ብቻ ነው የሚያዩኝ..እናቴ ግን ይሄው 22 ዓመት ከጎኔ ተለይታኝ ተኝታ አታውቅም…ግን እንዴት አይሰለቻትም..?ለመሆኑ የእናትነት ፀጋ ማለት ከምን አይነት ጽናት ጋር ይሆን ሚሰጠው…?እኔ እንጃ… ይሄ ከእኔ የማሰብ አቅም በላይ ነው፡፡
ይቅርታ አንድ ተጨማሪ ሰው ዘንግቼያለው ባለፍት 5 ዓመታት አብራን የምትኖር ትርሲት የምትባል ሰራተኛ አለች፡፡
እስቲ ሰለቤተሰባችን አባል ዘርዘር ያለ መረጃ ልስጣችሁ… ..ከማን ልጀምር ከእናቴ ጀመርኩ…..?እናቴ ዕድሜዋ 49 ዓመት አካባቢ ይሆናል፡፡በ23 ዓመቷ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ በባይሎጂ ተመርቃ ሃይስኩል ውስጥ ማስተማር ከጀመረች 26 ዓመት አልፎታል ፡፡ያው ከእኔ ዕድሜ 4 ዓመት በፊት ጀምሮ ማለት ነው ፡፡ብዙ ሙሁሮችንም ብዙ ብኩኖችንም ለዚህች ሀገር አበርክታለች፡፡
ይሄ እናቴ የምታስተምርበት ሀይስኩል ከቤታችን ከተንቀራፈፉ 5 ደቂቃ ከፈጠኑ ሁለት ደቂቃ ነው የሚርቀው፡፡ያ ማለት … እናቴ መኖሪያዋ እና የስራ ቦታዋ አንድ ቦታ እንደሆነ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡እናቴ ይሄን ሁሉ አመት እንዴት አንድ ትምህርት ቤት አንድ አይነት ትምህርት ስታስተምር ኖረች..? እንዴት ትምህርቷን ሳትቀጥል..? እንዴት ስራ ሳትቀይር..?እንዴት ሳታገባ…? የእነዚህ ሁሉ መልስ ከእኔ ማንነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡
እናቴ አስተማሪ ሆና ትምህርት ቤቷ ውስጥ እና እናት ሆና ቤት ውስጥ ሁለት የተለያየች ሴት እንደሆነች ነው ሚሰማኝ….እናቴ ውብ ምትባል አይነት ሴት ነች፡፡ወደ ቀይነት ያደላ የሰውነት ቀለም ፤ ደርበብ እና ሞላ ያለ ሰውነት፤ ባለ ስልካካ አፍንጫ እና ቦግ ቦግ ያሉ አይኖች ያሏት ሜትር ከ79 የምትረዝም ዘለግ ያለች ሴት ነች፡፡
ስለፀባይዋ ልንገራችሁ… ልስልስ አመል ያላት ምትገርም ሴት ነች…ለማንም ሰው ቢሆን ሊጣሏት የምታስቸግር አይነት ሰው ነች፡የጋለውን ማብረድ፤የሞቀውን ማቀዝቀዝ፤የተወጠረውን ማስተንፈስ ትችልበታለች፡፡ነገሮችን በተረጋጋ እና ባልተዋከበ እርጋታ መከወን የተካነችበት ስጦታዋ ነው፡፡ያው የዚህ ታሪክ ዋና ምሰሶ እሷ ስለሆነች በየክፍሉ ስለእሷ ምነግራችሁ ብዙ ነገሮች ስለሚኖሩ ይበልጥ እያወቃችኃት እና እየወደዳችኃት ትመጣላችሁ፡፡ …ለአሁኑ ግን ወደሌሎቹ ልሂድ….፡፡ቆይ ስሟን አልነገራኮችሁም ለካ…መገርቱ ትባላለች፡፡
መሀሪ ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡የዓለም ቁጥር አንድ ዝርክርክ እና ግድ የለሽ ሰው እሱ ይመስለኛል…ተራሮች ወደ ሸለቆነት ቢቀየሩ ፤ምድር እንደኖህ ዘመን በጥፋት ውሀ ብትጥለቀለቅ፤ፀሀይ በጠለቀችበት በዛው ቀርታ ይህቺ ምድር በጨለማ ብትዋጥ ለእሱ ደንታው አይደለም…፡፡ለዚህ ወንድሜ በህይወት ለመኖር ሶስት ነገሮች በቂው ናቸው… የሚያነበው መጽሀፍ ፤የሚቅመው ጫት እና የሚጎነጨው አረቄ…በቃ ፡፡ከዛ የተረፈው የዓለም ትርምስ ሁሉ ለእሱ ትርፍ ነው፡፡እቤት ሲገባና ሲወጣ እራሱ ማን አለ… ማን የለም.? ዞር ብሎም አያይም…፡፡ደህና ዋሉ ሳይል ይወጣል… ደህና ቆያችሁ ሳይል ይቀላቀላል…፡፡
ከእህቶቹ ጋር ቃላት እንኳን የሚለዋወጠው በወር ወይም በሁለት ወር አንድ ቀን ሊሆን ይችላል..ከእናቴ ጋር ግን የተሻለ ያወራል..ቢያንስ ማውራት ቢያስጠላው እንኳን ግንባሯን ስሞ ገብቶ ግንባሯን ስሞ መውጣቱ የማይዛነፍ ተግባሩ ነው፡፡ከእኔ ጋ ያለው ግንኙነት ግን የተለየ ነው፡፡እኔ ለወንድሜ ሚስጥረኛው ነኝ፡፡ሰው ሁሉ ከቤት ተጠራርጎ ወጥቶ ብቻችንን በምንሆንበት ሰአት የማያወራኝ ነገር የለም… ከግል ሚስጥሩ አንስቶ ስለጠቅላላ ሀገር አቀፍ ሆነ አለም አቀገፍ ወቅታዊ እወነቶች፡ ስላነበባቸው መጽሀፎች፡ ስለሰማቸው ዜናዎች.. ከኢንተርኔት ላይ ስላገኛቸውና ስላስደነቁት ተአምሮች ያለመሰልቸት ያወራኛል፡፡ በጽሞና አደምጠዋለው..፡፡
አንዳንዴም በእኔ ላይ ያለውን ቅሬታ...የህይወቱን አቅጣጫ እንዲህ ዝብርቅርቅ ያደረግኩት እኔ መሆኔን…በዚህም ምክንያት እንደሚበሳጭብኝ በምሬት ይነግረኛል..እኔም እሰማዋለው›..ምክንያቱም ወቀሳው እውነትነት እንዳለው እኔም አምናለው…፡፡
እንዲያም ሆኖ ግን ወንድሜ መሀሪ ባለሞያ ነው.. ጎበዝ የኮምፒተር ባለሞያ…በኮምፒተር ሳይንስ ዲፕሎማ አለው…ግን ከዛ በላይ የተፈጥሮ ስጦታው ይበልጣል…ተለምኖ፤ በስልክ ተጨቅጭቆ ነው የሚሰራው፡፡በቀን ውስጥ በጣም ሰራ ከተባለ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓት ነው..ግን እንደዛም ሆኖ ተጠቅሞ ከሚጨርሰው ብር የበለጠ ገቢ ያገኛል ….
ቀጥሎ ወደእህቶቼ ልሂድላችሁ …እኚ እህቶቼ መንትዬች ናቸው…ለእኔ ታላቆቼ ናቸው፡፡ፌናን እና ሮማን ይባላሉ ፡፡ስማቸውን ለአንደኛዋ አባቴ ለሌለኛዋ ደግሞ እናቴ ነች ያወጣችላት፡፡አንደኛዋን ከአንደኛዋ በመልክ ለመለየት ለማንም ሰው ከባድ ፈተና ነው..እኔና እናቴ ግን በቀላሉ እንለያቸዋለን፡፡ሁለቱም ቀይ ቀጭን መካከለኛ ቁመት ከግብዴ መቀመጫ ጋር ያላቸው ቆንጆ እና ጎረምሳው ሁሉ ለሀጩን የሚያዝረከርክባቸው ቀሽት ሚባሉ ጉብሎች ናቸው፡፡
እህቶቼን በተመለከተ በጣም የሚማርከኝ ነገር ቢኖር ጫወታቸው ነው፡፡እነሱ እቤት ውሥጥ ካሉ በቃ የእኛ ቤት ኮመዲያን የተሰባሰቡበት ኮንሰርት ነው የሚመስላችሁ…. ..እርስ በርስ ጫወታቸው፤መተራረባቸው፤ከእናቴ ጋር የሚያወሩት ወሬ….ሁለ ነገራቸው ድምቀት አለው፡፡እኚህ እህቶቼ ለማንኛውም ሰው እንደመልካቸው ሁሉ ፀባያቸውም አንድ ይመስለዋል ..ግን በጥልቀት ሲመረመር በጣም ይለያያሉ፡፡
ለምሳሌ ሮማን..እቤት ውስጥ ሮሚ ነው የሚሏት… ትምህርት በጣም ስትወድ ፌናን ደግሞ ቶሎ ብላ በዚህም በዛም ብላ ሀብታም መሆን ነው ፍላጎቷ… ሀብታም ለመሆን የመጀመሪያዋ ምርጫዋ ነጋዴ መሆን ነው....አሁን ጀመራዋለች ፡፡ያ ካልተሳካላት
👍11🥰21
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-2

:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ይሄ ታሪክ እናቴ እና አባቴ እንዴት እንደተዋወቁ የሚያትት ነው፡፡ታሪኩን የነገረችኝ እናቴ ነች፡፡እርግጥ ታሪኩን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በስድስት ወር እና በዓመት ልዩነት አቀራረብን ለወጥ እያደረገች የተወሰነውን እየቀነሰች እና በፊት ነግራኝ ከነበረው ውስጥ ያልተካተተ አዲስ ታሪክ እየጨመረችበት ነግራኛለች፡፡እናቴ ስለአባቴ የምታወራኝ ብሶት ሲሰማት ነው..ውስጧን ሀዘን ሲቦረቡረው ነው…ልቧ ውስጥ ያለ ጥልቅ ባዶ ሽንቁር ሲረብሻት ነው፡፡የዛን ጊዜ ትናንቷን ታስታውሳለች፤የድሮ ፍቅሯ ትዝ ይላታል፡፡የዛን ጊዜ አባቴን ታስታውሳለች፤የዛን ጊዜ የሚያዳምጣትን ሰው ትፈልጋለች፤ለማዳመጥ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ከእኔ ከልጇ በላይ ችሎታ ያለው ሰው የለም..ድንቅ የተባልኩ አድማጭ ነኝ የማንንም ንግግር አላቋርጥም ደግሞም ሚስጥር ጠባቂ ነኝ ..ማንም የፈለገውን ነገር ለእኔ ቢነግረኝ በቃ ለአምላኩ በሽኩሽኩታ እንደነገረው መቁጠር አለበት.ስለዚህ የቤታችን አባል መተንፈስ እና እፎይ ማለት ሲያስፈልጋቸው ወደ እኔ ነው የሚሮጡት..ይህ እናቴንም ያጠቃልላል፡፡
እና ይሄንን ከአባቴ ጋር የነበራትን የፍቅር ታሪክ ደጋግማ ስለነገረችኝ ልክ በእያንዳንዷ ግንኙነታቸው ወቅት አብሬያቸው የነበርኩ መስሎ ነው ሚሰማኝ …ሁሉ ነገር ልክ አሪፍ ደራሲ እንደደረሰው መሳጭ የፍቅር ድርሰት ፍንትው ብሎ ይታወሰኛል፡፡
የተገናኙት ሁለቱም የአዲስ አበባ የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው፡፡እሱ የኬሚስትሪ እሷ የባይሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ ነበሩ …ያው ፍረሽ ማን ላይ ሁለቱም የሚወስዱት ተመሳሳይ አይነት ኮርስ ነበረ እና የገና ማዕበል ለማምለጥ ሁሉም ተማሪ በፍራቻ ተውጦ፤በስጋት እየተናጠ አንገቱን አቀርቅሮ በየዩኒቨርሲቲው ጥጋ ጥግ እና በላይብረሪው ከወረቀት ጋር እራሱን አጣብቆ ፍዳውን በሚያበት ወቅት ነበር..በተለይ መምህሩ አንብቡ ብሎ የጠቆማቸውን መጽሀፍና፤ሲኒየር ሚባሉት ተማሪዎች ለፈተና ያንን መጽሀፍ አንብቡት ብለው የጠቆሙትን መጽሀፍ ለማግኘት ላይብረሪ ውስጥ ያለው መራኮት እና መሻማት ያስቃልም .ያስተዛዝባልም፡፡ በተለይ የፈተናው ወቅት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ውጥረቶቹ በዛው ልክ እየከረሩ ይሄድ ነበር፡፡
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ሞጋስ ባሴ የተባለው ከጎንደር አርማጭኦ አካባቢ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የመጣው ወጣት በዚህ መራኮት ውስጥ በመደነጋገርም ቢሆን መፋለም ጀምሮ የነበረው..ግን ሁሌ ተሸናፊ ነበር…፡፡ካደገበት ማህበረሰብ የወረሰው ይሉኝታ ለተሸናፊ እንዲዳረግ አመቻችቶታል፤ከመናጠቅ ይልቅ መካፈልን ነበር የሚያውቀው ጓደኛን ወደ ኃላ ስቦ በማስቀረት ወደ ፊት ከመሸምጠጥ ይልቅ አንተ ቅደም ወንድሜ ብሎ ከመንገድ ገለል ብሎ ሌላውን የማሰቀደም ስነ ልቦና ነበር የነበረው፡፡ንጽህ የዋህነት፤የጠራ ሰባዊነት የግል ንብረቶቹ ነበሩ…፡፡ግን አዲስ አበባ ሌላ ነው፡፡እርግጥ ከእሱ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ የክፍለሀገር ልጆች ነበሩ..ግን በተለይ በመጀመሪያው አመት የሚደምቁትና ፈካ ብለው የሚታዩት የትላልቅ ከተማ ውልዶቹ ናቸው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ..በምዕራባዊውና በምሰራቃዊው ፍልስፍና መካከል የሚዋልል ከተሜን በውስጧ የያዘች መንጠቅ እንደብልጠት፣መቅደም እንደአራዳነት የሚታይባት የተለየች ቦታ ..እና አንድ መጽሀፍ ለማግኘት ለ5 ቀን የላይብረሪውን ደጅ ፀንቶ ነበር..አልቀናውም እንጂ..፡፡
‹‹አረ ወዲያ….›› እያለ ላይብረሪውን ለቆ በቅሬታ ሲወጣ ..ያንን የሰሙ ሌሎች እኩዬቹ ሲገለፍጡበት ለሶስት ቀን የታዘበችው እናቴ ታዝባ ቅር ብሎት ነበር…በአራተኛው ቀን ግን ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ሳትንቀሳቀስ በምልክት ጠራችው..እሷ ወደ ተቀመጠችበት መቀመጫ ግራ በተጋባ እይታ ተገትሮ ሲያማትር መልሳ በእጇ ምልክት ጠራችው…፡፡በንዴቱ ውስጥ ቢሆንም…ወደ እሷ ተጠጋ..ስሯ ደረሰ….
‹‹ተቀመጥ አለችው…››በሹክሹክታ
‹‹ምን ይሁነኝ ብዬ….?.››መለሰላት ከእሷ ትንሽ ከፍ ባለ ድምጽ ሌሎችን የላይብረሪ ተጠቃሚዎችን እንዳይረብሹ በመስጋት ግራና ቀኝ በመሳቀቅ ተመለከተችና‹‹ ቁጭ በል›› ብላ ልክ ከዚህ በፊት በደንብ እንደምታውቀው የቅርብ ጓደኛዋ እጁን በመያዝ ስባ አስቀመጠችውና‹‹ይሄን አይደል የፈለከው …እንካ አንብብ››ብላ ስታነበው የነበረውን መጻሀፍ ወደ እሱ ፊት አስጠጋችለት ….ማመን አልቻለም..አንዴ መፅሀፉን ..አንዴ ልጅቷን እያፈራረቀ ማየት ጀመረ
‹‹አጥና እንጂ… ለዚህ መጽሀፍ አይደል ሳምንቱን ሙሉ ስትበሰጭ የሰነበትከው…..?እኔ በቂ ቀን አግኝቼ ማየት ያለብኝን ያህል አይቼዋለው ዛሬ ደብተሬን ነው የማነበው…››
‹‹ታዲያ እማታነቢው ከሆነ ለምን ታቀፍሺው.? ››በብስጭት
‹‹ለአንተ ብዬ.››
‹‹አረገኝ…..?.›.›
‹‹ባክህ ታጠና እንደሆነ አጥና …ካልፈለግክ መጽሀፍን አምጣው..››ለራሷም ባልታወቃት ስሜትም በቁጣ መለሰችለት፡፡…. እንግዲህ የመጀመሪያ ትውውቃቸው እንዲህ ነበር የጀመረው፡፡
እርግጥ ሁለቱም ኢትዬጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተለያየ አካባቢ እና ባህል ውስጥ ነው ያደጉት ፡፡ ቢሆንም ይሄ ልዩነታቸው ለግንኙነታቸው እንቅፋት አልሆነባቸውም..እናቴ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው አዲስ አለም ከተማ ተወልዳ ያደገችና ሀይስኩል ስትደርስ ወደአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ገብታ ተምህርቷን የጨረሰች በመሆኗ ከተሜነት ሲያጠቃት አባቴ ግን ከአነስተኛ የገጠር ከተማ በመውጣቱ በተቃራኒ ስሜት ውስጥ ያለ ነበር..
ከዛን ቀን ወዲህ ለሁለተኛ ጌዜ የተገናኙት አንደኛ ሴሚስተር ፈተና ተጠናቆ የፈተና ውጤቱ ታውቆ ውጤቱም ቦርድ ላይ ተለጥፎ ተማሪ እየተተረማመሰ በሚያበት ጊዜ ሁለቱም ከትርምሱ ውስጥ የየራሳቸውን አይተው ሲወጡ እርስ በርስ በመላተማቸው ነበር…ዞር ብላ ስታየው ማንነቱ ትዝ ስላላት ‹‹…አንተ››አለቸ
‹‹አንቺው…አለሽ ኖሮል.? ››
‹‹ምነው ፈልገሀኝ ነበር እንዴ.?››ይሄንን የሚያወሩት ከተማሪዎቹ አጀቡ ተገንጥለው በመውጣት ብቻቸውን ጎን ለጎን እየተራመዱ ነበር
‹‹እሱማ አልፈለግኩሽም…በሀሳቤ ተሰንቅረሺብኝ እንጂ››
‹‹ምን ተሰንቅረሽብኝ..ማ.. እኔ .?››እናቴ በመገረም
‹‹እንደእሱም ማለቴ እማየደል.?››
‹‹እና እንዴት ማለት ነው.?››
‹‹በቃ ተይው…ለመሆኑ ፈተናይቱን እንዴት ሆንሽ…..?››
‹‹አሪፍ ነው...አንተስ….?››
‹‹እኔማ ጥሩ ነው.. እንዲሁ ባልፈራ ኖሮ የተሸለ አመጣ ነበር…ወይኔ ወንድ በሀገሬ መውዜር እና ምንሽር ቢደቀንብኝ ማልበረግግ ዠግና እዚ በወረቀት ተለቅልቆ ለሚመለስ የፈረንጄ ወሬ ልንቦቅቦቅ…...?››
ከዚህ ቡኃላ ግንኙነታቸው በጓደኝነት ይቀጥላል …ሁለተኛ አመት ግምሽ ድረስ ተመሳሳይ ይሆናል…አብረው ያጠናሉ…አብረው ከተማውን ይዞራሉ…ሚስጥር ይጋራሉ፡፡
ነገሮች የተቀየሩበት ቅጽበት አባቴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሁለት አመት ሲማር ከዕውቀቱ ይልቅ አራዳነቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷ ነበር .ከንግግሩ ቀልጠፍ፤ከአለባበሱ ዘነጥ፤ካረማመዱ ጀነን ማለቱ ለሌላ ሰው አይደለም ለሱ ለራሱ ይታወቀው ነበር…አሁን ከየዋህነት ይልቅ ብልጠትን፤ከመበለጥ ይልቅ መሸወድን፤ከመግደርደር ይልቅ አይን አውጣነትን፤ተጎትቶ ከመቅረት ይልቅ ጎትቶ ማለፍን እለት ከእለት ከመደበኛ ትምህር እኩል እንደውም ከእዛም በላይ እየተለማመዳቸው የህይወቱ አንድ ክፍል አድርጎቸው አድርጓቸው ነበር የእኛ ስልጣኔ እንዲህ አይደል?እና እናቴንም በተመለከተ ሳይቀደም ሊቀድም ወሰነ በአንድ እለተ እሁድ የረፍት ቀን በወቅቱ ዝነኛ ወደ ነበረው እና ዘፋኞች ሁሉ የቪዲዬ ክሊፓቸወንን ወደሚያስቀሩጽበት ብሄረ-ጽጌ መናፈሻ ሳታስብ ወሰዳት
👍14😁1
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-3

:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

....‹‹ያን የመሰለ ደስተኛ ኑሮችን እንዲህ ምስቅልቅሉ የወጣው…ይሄ ልጅ ከተወለደ ቡኃላ ነው››
‹‹አረ ተው ጡር አትናገር….ምንም ቢሆን ልጃችን አይደል››አለችው ኮስተር እና ቆፍጠን ብላ..
‹‹አይ ይሄ ልጃችን አይደለም….ይሄ ሳቃችንን የነጠቀን እና ፈገግታችንን የሰረቀን ለቤታችን የተላከ መቅሰፍት ነው››
‹‹ልጄንማ እንዲህ እንድትለው አልፈቅድልህም…..››
ቁጣዋን ችላ ብሎ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት ‹‹ታፈቅሪኛለሽ አይደል.?››
‹‹ምን የሚሉት ጥያቄ ነው ….?በደንብ አፈቅርሀለው››መለሰችለት፡፡
‹‹እንደዱሮችን በሳቅ በተሞላ ኑሮ በደስታ እየቧረቅን ልጆቻችንን አብረን እንድናሳድግ ትፈልጊያለሽ አይደል.?››
‹‹አዎ እፈልጋለው..በጣም እፈልጋለው››የተቋጠረ ፊቷን አላቀ የተከደነ ጥርሷን ከፈት አድርጋ በተስፋ መለሰችለት
‹‹እንግዲያው ለእሱም ለእኛም ስንል..ይሄንን ልጅ ለእርዳታ ድርጅት እናስረክበው..እዛ የተሸለ ህክምና ያገኛል..ከእኛ በተሻለ…..››የእናቴ ተስፋ መልሶ ጨለመ...እሱ ለተናገረው እሷ ተሳቀቀች
‹‹እንዳትጨርሰው….ልጄን በህይወት እያለው ለማንም አልሰጥም..እንኳን ለእርዳታ ድርጅት ለገዛ እናቴም አልሰጥ..እንደው አቅም አንሶኝ ለማሳደግ ብቸገር እንኳን ሌሎቹን ልጆቼን አሳዳጊ ልሰጥ እችል ይሆናል እንጂ እሱን አላደርገውም፡፡ምክንያቱም ማንም እንደእኔ ሊረዳው አይችልም..፡፡ ማንም እንደእኔ ሊንከባከበው አይችልም..፡፡ለእኔ ከእግዜር የተሰጠኝ የህይወት ዘመን ፀጋዬ ነው፡፡አንድም ቀን መከራዬ ሆኖ ተሰምቶኝ አያውቅም..ለዛም ነው ፀጋዬ ብዬ የምጠራው››
‹‹እኔ ግን አልችልም..አካሉም አዕምሮውም በድን የሆነ ልጅ ጥዋት ማታ እያየውና እየተሳቀቅኩ ቀሪ ዘመኔን መቀጠል አልችልም…..ያቅማችንን ሞክረናል..ያለንን ገንዘብ ጌጣችንን እና ንብረታችንን ሁሉ እሱን ደህና ለማድረግ ስንል በትነናል…. ከዛም አልፎ እዳ ውስጥ ገብተናል..እንደዛም ሆኖ ግን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም…አዕምሮው የተበላሸ ልጅ ምንም ልናደርገው አንችልም……››
‹‹የእኔ ልጅ አካሉ የማይንቀሳቀስ ሊሆን ይችላል…አዕምሮው ግን ጤነኛ ከሆኑት ልጆችህ በተሸለ ያስባል…. ይሰራል››
‹‹እሱ የእናትነት ልብሽ የሚያስበው ነው…ምኞት፡፡አዕምሮውም ልክ እንደመላ አካሉ አንድ ቦታ ረግቶ የተቀመጠ መስራት ያቆመ..በቃ ምን ልበልሽ… የነከሰ ሞተር ማለት ነው፡፡››
‹‹ተሳስተሀል››እየተንዘረዘረች፡፡
‹‹አልተሳሳትኩም…ያልኩሽን እንድርጊና የቀድሞ ህይወታችንን እንኑር ..አንቺም ወደስራሽ ተመለሺ..የቻልነውን ሞክረናል..እግዜሩም ሰውም በዚህ ውሳኔችን ይደግፉናል እንጂ የሚያዝንብን የለም››
‹‹አልችልም ..በህይወት እያለው.ከልጄ መነጠል አልችልም››
‹‹እንግዲያው የሶስት ቀን ማሰቢያ ጊዜ ሰጥሻለው …እሱ ባለበት እንዲህ በሀዘን የተጨመላለቀ አሳቃቂ ኑሮ ውስጥ መኖር አልችልንም›› ብሎ ፈታኝ ጥያቄ ላይ ጥሏት ወደ ስራ ይሄዳል
እናቴ ለአንድ ቀን ሙሉ በነገሩ ላይ አሰበችበት..አወጣች አወረደች ይሻላል ያለችውን በሁለተኛው ቀን ወሰነች…ወደትምህርት ሚኒስቴር ሄደችና ወደስራዋ አንዲመልሳት ማመልከቻዋን አስገባች..ልጄን ቢያምብኝ ብላ ለክፉ ቀን ያስቀመጠቻትን ሽርፍራፊ ገንዘብ አውጥታ ቤት ተከራየች..በሶስተኛው ቀን አባቴ ስራ ሲሄድ ጠብቃ….አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ የእኔን እና የእሷን እቃዎች..መተኛ አልጋችንን..ማብሰያ ዕቃዎችን የመሳሰሉትን አዲስ ወደ ተከራየችው ቤት አጋዘች..ተክሲ ተኮናትራ እኔን ይዛ እቤቱንም ልጆቾንም ጥላ ወጣች….
አንደተለመደው አባቴ አምሽቶ እና ወሳስዶ እቤት ሲመጣ ሶስቱ ልጆች በግራ በመጋባት እና በፍራቻ ውስጥ ሆነው ጎን ለጎን ተኮልኩለው ነበር ያገኛቸው፡፡
‹‹ምን ሆናችሁ.?››
‹‹እማዬ››ከመንታዎቹ አንዷ
‹‹እማዬ ምን.?››
‹‹ሄደች››
‹‹ሄደች ማለት.?››
‹‹ሄደች …ጥላን ፀግሽን በታክሲ ይዛው ሔደች››ግራ ተጋባ
‹‹አመመው እንዴ...?ሀኪም ቤት ነው የወሰደችው.?››
‹‹አይ አይደለም… ይሄን ስጡት ብላለች››ብለው ወረቀቱን አቀበሉት… ገለበጠው፡፡ ለእሱ የተጻፈ ደብዳቤ ነበር፡፡በቆመበት በሚንቀጠቀጥ እጅ ጨምድዶ ይዞ በሚርገበገቡ አይኖቹ ማነበቡን ቀጠለ፡፡
……..ይህቺ ቀን ትመጣለች ብዬ መቼም አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ካየውህና ካወቅኩህ ቀን ጀምሮ አፈቅርህ ነበር ..እርግጥ አሁንም አፈቅርሀለው ….. የመጀመሪያ ፍቅሬ ነህ..ሴት ያደረግከኝ አንተ ነህ…ልቤ ካንተ ውጭ ሌላ ሰው ለሽርፍራፊ ሰከንዶች ቢሆን እንኳን ጎራ ብሎበት አያውቅም..ሳገባህ ገነት የገባው አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር…አብሬህ ስኖር በሙሉ ልቤና ነፍሴም ጭምር ነበር..፡፡እመነኝ ከአንተ ጋር ህይወቴን ሙሉ ለመኖር ህይወቴንም ቢሆን በክፍያ ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ… ልጅን ግን አላደርገውም፡፡ለወደፊትህም አንድ ምክር ልስጥህ አንድን እናት በምንም አይነት ከልጅሽ አስበልጪኝ የሚል ፈታኝ ምርጫ አታቅርብላት ከዛ ይልቅ ሙቺልኝ ብትላት የተሻለ ትክክለኛ እና ፍትሀዊ ጥያቄ ይሆናል…ካፈቀረችህ ያለማቅማማት ልትሞትልህ ትችላለች ..ልጆን ግን…..በፍፅም፡፡
እርግጥ ይገባኛል..ለአንተም ልጅህ እንደመሆኑ መጠን ጫናው ከብዶህ እንጂ ጠልተሀው እንዳልሆነ አውቃለው..እኔ ግን እናት ነኝ መቼም መቼም ቢሆን በልጄ ተስፋ ልቆርጥ አልችልም…ይሄንን ስሜቴን ምን አልባት እመብርሀንም ልጅ ስለነበራት ትረዳኝ ይሆናል..ለእናንተ ስል ልጄን ከምተው ..ለልጄ ስል ሁላችሁንም ባሌንም… ልጆቼንም…ቤቴን ብተው እመርጣለው….እዚህ ላይ ንፅፅር እንዳታደርግ ..ጥለሻቸውስ የሄድሽው ልጆችሽ አይደሉም ወይ ብለህ እንዳትጠይቀኝ..፡፡ከሶስት ጤነኛ ልጆች እንዴት አንድ መላ አካሉን ማዘዝ የማይችል ልጅ ልትመርጪ ቻልሽ እንዳትለኝ...? የዚህን መልስ ለመመለስ ለእኔ ቀላል አይደለም…ግን ቢያንስ እነሱን ማንም ተቀብሎ ሊያሳድጋቸው ይችላል…..የፈለጉትን መጠየቅ የተበደሉትን መናገር ይችላሉ፡፡እቤት ከአንዱ ክፍል እሳት ቢነሳ በጎሮ በር ወይም በመስኮት ዘለው ለማምለጥ ለእነሱ ቀላል ነው፡፡ቢርባቸው እንኳን ማድቤት ገብተው ምግብ ፈልገው ለመጉረስ አይሰንፉም፡፡ሽንታቸውን ቢወጥራቸው ወደ ሽንት ቤት ሄደው ለመሽናት ውሃ ቢጠማቸው ወደ ፍሪጅ ሄደው አልያም ከቧንቧ ቀድተው ደቅነው ለመጠጣት ለእነሱ በጣም ቀላል ነው….አየህ የእኔ ሚስኪን ልጅ ግን ይሄን ሁኑ ማድረግ አይችልም…ምን እንደፈለገ እንኳን መናገር ስለማይችል ከእኔ ከእናቱ ውጭ ማንም ሊረዳው አይችልም…ግን ደግሞ እሱም እንደእነሱ በህይወት አለ..እሱም እንደነሱ ይራባል…፤እሱም እንደነሱ መጸዳዳት አለበት.ያን ሁሉ ማድረግ የሚችለው ግን በእኔ በእናቱ እርዳታ ነው እናም እኔ ለእናንተ ከማስፈልገው በላይ በብዙ ሺ እጥፍ ለእሱ አስፈልገዋለው ስለዚህ አንተንም ላለመረበሽ ስል ቤቱን ለቅቄ ልጄን ይዤ ወጥቼያለው፡፡አይዞህ እንዴት ይኖራሉ ብለህ አታስብ ወደ ስራዬ ለመመለስ ስለወሰንኩ ማመልከቻ አስገብቼያለው አንተም ልጆችህን ጥሩ አባት ሆነህ እንደምታሳድግ ምራጫውን ለአንተ ትቼዋለው ከፈለግክ ሰራተኛ ቅጠር …ከፈለክም ማግባት ትችላልህ፡፡ በዚህ ምንም ቅሬታ አይሰማኝም…..ፍቺያችንንም ዝግጁ ስትሆን ንገረኝና በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲያልቅ አደርጋለው፡፡ብቻ አደራ ምልህ እቅፍ ውስጥ ላሉት ሶስት ጤነኛ ልጆቸች ጥሩ አባት ሁናቸው፡፡ያንተው አክባሪህ
ፈጽሞ ያልጠበቀው ዱብ እዳ ነው ያጋጠመው..መቼም እንዲህ አይት ውሳኔ ላይ ትደርሳለች ቡሎ ገምቶም ጠርጥሮም አያውቅ ነበር .፡፡በእሱ የምትጨክን
👍6🔥1🥰1
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-አራት

:
:
ደራሲ.ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...እቤት ውስጥ ማንም የለም …..እኔ ሳሎን ሶፋው ላይ ተመቻችቼ ተሰትሬ ተኝቼያለው…አንገቴ ከፍ የሚያደርግ ልዩ አይነት ትራስ ከስር ተደርጎልኝ ቀና ብያለው…ፊት ለሰፊቴ ግድግዳ ላይ ለእኔ እይታ እንዲመች ተስተካክሎ የተለጠፈ 32” ሶኔ ፍላት ቴሌቬዝን ላይ አፍጥጬ…. ‹‹ብሬኪንግ ባድ›› የሚል ርዕስ ያለው ተከታታይ ፊልም እያየው ነው…፡፡ያው ከመጽሀፍ ቀጥሎ ፊልም ማየት በጣም የምወደው እና የሚያዝናናኝ የእየ እለት ድርጊቴ ነው..
ስለአለም ያለኝን ግንዛቤ በጣም ያሰፋልኝ የማያቸው የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፊልሞች ናቸው..፡፡በቀን ቢያንስ 5 ፊልም አያለው..ቢያንስ ነው..እሰከ አስር እና ከዛም በላይ የማይበት ቀን አለ…፡፡ከሁሉም በላይ ግን በእናቴ እና አልፎ አልፎ በወንድሜ የሚነበብልኝ መጽሀፍት ለእኔ ሱሴ ናቸው..
በዚህ ውስብስብ የህይወት ቆይታዬ የተረዳውት አንድ ዋና ፌሬ ነገር ቢኖር መጻሀፍን የሚተካ ምንም ነገር አለመኖሩን ነው…ፊልም፤ኢንተርኔት ምንም ቢሆን ምንም፡፡ መጽሀፍ አዕምሮን እንደሚያዳብር አምናለው….ማንበብ የማሰብ ብቃትን የሚያጠነክር የአእምሮ ስፖርት ነው፡፡መፅሀፍ ስናነብ ቃሉን ወደ አዕምሮችን ልከን ምስሉንና እያንዳንዱን ድርጊት በራሳችን የአዕምሮ ግንዛቤ እና ፍላጎት መጠን አስልተን በራሳችን ዳሬክተርነት አክረተሮችን በምናባችን ፈጥረን ፊልሙን በመስራት የታሪኩን ሙሉ ጭብጥ ለመረዳ እንጥራለን፡፡ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ ታዲያ የማሰብ ብቃታችንን በጊዜ ሂደት ውስጥ ሚያፈረጥምልን የአዕምሮ ቅልጥፍና ማበልፀጊያ ጅምናስቲክ ማለት ነው…..፡፡
ለማንኛውም ሰው ካረዳኝ በራሴ መጽሀፍ ማንበቡ ስለሚከብደኝ አሁን ፊልሙን እያየው ነው እንዲህ አሁን ባለውበት ሁኔታ ሁሉን ነገር አስተካክላልኝ የሄደችው እናቴ ነች…ቤቱ ባዶ ከሆነ ሁለት ሰዓት በላይ ሆኖታል.የቤታችን ተንከባካቢ ትርሲትም እንኳን አስቤዛ ልትሸምት ወደ መርካቶ ከሄደች ቆየች…
አሁን ግን በሩ ሲከፈት ሰማው…ማን እንደሆነ አንገቴን ጠምዝዤ በአይኖቼ ማየት አልችልም…፡፡
ግን በበር አከፋፈቱ እና በእርምጃው ማንነቱን ወዴያው ነው ያወቅኩት…ወንድሜ መሀሪ ነው፡፡አዎ መጥቶ ፊት ለፊቴ ተገተረ..ያው እንደወትሮው ጭብርር እንዳለ ነው….በጥቁር ፔስታል የታጨቀ ዕቃ ተሸክሞ በመምጣት አጠገቤ ካለው ጠረጵዛ ላይ ጎንበስ ብሎ አስቀመጠውና እሱም አጠገቤ ቁጭ በማለት
‹‹ሀይ ወንድሜ?›› አለኝ እንደሁልጊዜው አይኖቼን በማርገብገብ ለሰላምታው ምላሽ ሰጠውት
‹‹ማንም የለም እንዴ?››የግራ እጄን የማሀል ጣት በማወዛወዝ ቤቱ ባዶ እንደሆነ ነገርኩት ፡፡እጁን ወደ ፔስታሉ ሰደደና በፕላስቲክ የታሸገ የመንጎ ጭማቂ አወጣ…ከፈተውና እስትሮ አደረገበት..ከዛ ወደ እኔ አፍ አስጠጋና ጭማቂውን በግራ እጁ ይዞ በቀኝ እጁ እስትሮውን አፌላይ ሰካው ‹‹…በል እንግዲህ እድሜ ለወንድሜ እያልክ ምጠጥ ››አለና ከእስትሮው በተነሳ እጁ ሪሞቱን በማንሳት እያየውት የነበረውን ፊልም ዘጋው‹‹ይቅርታ…አሁን ፊልም ማየት አትችልም …ወይ መጽሀፍ እናነባለን ..ወይም እናወራለን›› አለኝ
ፈገግ አልኩና በሀሳቡ እንደተስማማው ገለጽኩልት..ግማሽ ሊትር የሆነችውን ጅውስ ለመጠጣት ግማሽ ሰዓት ያህል ፈጀበኝ…ያን ሁሉ ጊዜ ወንድሜ ያለምንም መቻኮልና መሰልቸት በቀልድ እያዋዛ ነበር ጅውሱን የመገበኝ፡፡
‹‹በል እንግዲህ አሁን ደግሞ ያራሴን ጅውስ ልጠጣ›› አለና እኔ የጠጣውበትን ባዶ የጅውስ ፕላስቲክ ወርውሮ እጅን ወደ ፔስታሉ ከተተና በለጬ ጫቱን መዞ በማውጣት ጠረጵዛው ላይ አስቀመጠው…አሁንም እጁን በድጋሜ ሰደደና የፕላስቲክ እሽግ ኮካና በወረቀት የታሸገ ለውዝ አውጥቶ እዛው ጠረጵዛ ላይ በመደዳ ደረደራቸው፤ የጫቱን ፔስታል ከፍቶ የጫቱን እስር ፈቶ አንድ ሁለት ቅጠል አወጣና በቄንጥና በፍቅር እየቀነጣጠሰ ወደ አፉ በመውሰድ ይጠቀጥቀው ጀመር…ከዛ ኮካውን ከፈተና ተጎነጨለትና መልሶ አስቀመጠው…ሌላ ጫት መዘዘ ቀነጠሰና ጎረሰው…ለውዙን ፈለፈለእና ወደ አፉ ጨመረ…….ከዛ ከለበሰው ግብዴ ጃኬት ሰፊ ኪስ ውስጥ መፃፍና አወጣና ገለጦ ማንበብ ጀመረ..ሁሌ እስኪግል እንዲህ ነው የሚያደርገው…ለሀያ ደቂቃ ያህል በፅሞና ካነበበ ብኃላ አጣጥፎ አስቀመጠውና ወደ እኔ ዞረ.
‹‹አንድ ነገር ላውራህ እስኪ›› ሲል ጀመረ..ለመስማት ተዘገጀው…ያው ተዘጋጀው ስል ስሜቴን አነቀቃው ማለቴ ነው…ታናሽ ወንድሜ ቀጠለ ‹‹ምን አልባት የምትወደውን ወሬ ላይሆን ይችላል ላወራልህ የተዘጋጀውት..ግን ይሄንን ወሬ ካንተ ጋር ካልሆነ ከሌላ ከማንም ሰው ጋር ላወራው አልችልም..ከእህቶቼም ጋር.. ከእናቴም ጋር..፡፡ለምን? ብትለኝ እኔ እንጃ ነው መልሴ….፡፡ ከእነሱ ጋር ማውራት ከአንተ ጋር እንደማውራ አይቀለኝም..፡፡ምን አልባት አንተ ጥሩ አድማጭ ስለሆንክ ሊሆን ይችላል..ምን አልባት ሁለታችንም ወንድም አማቾች ብቻ ሳንሆን የቤቱም ብቸኛ ወንዶች ስለሆን ሊሆን ይችላል….››አለና ንግግሩን አቆርጦ ፔስታሉን ወደ ራሱ ጎተት አደረገና ጫቱን ከውስጡ መዝዞ ቀነጣጥሶ በመጉረስ በላዩ ላይ ኮካ ተጎነጨለትና ጠርሙሱን አስቀምጦ ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ…‹‹ላወራህ የፈለግኩት ስለአባቴ ነው….ማለት ስለአባታችን…ያው ስለእሱ መስማት እንደማትፈልግ እና እንደማትወደው አውቃለው…እኔም ስለእሱ ሳስብ ግራ የሚያጋባ ስሜት ነው የሚሰማኝ….እርግጥ አልዋሽህም አንዳንዴ ምን አለ አጠገቤ ቢኖር ብዬ እመኛለው....እርግጥ ለእዚህ ቤተሰብ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት አልከፈለም…..ያ ትልቅ ድክመቱ ነው…ግን ያው ምንም ቢሆን አባቴ ነው….ዝም ብዬ እንዳልተፈጠረ ሰው ልቆጥረውና ልረሳው አልችልም …
አሁን ስለእሱ ላወራህ የቻልኩት አንድ ጽሁፉን ፌስ ብክ ገጹ ላይ አንብቤ ነው..ያው እንግሊዝ ከገባ ቡኃላ ሀይለኛ ፖለቲከኛ ሆኗል….፡፡ ስለዲያስፖር ፖለቲካ ደጋግሜ አውርቼሀለው…አባታችን ከነዛ ተዋናዬች ውስጥ ዋናው ሆኗል..ይግርምሀል ስለአባቴ ብዙ ነገሮቸ ለማወቅ ሞክሬያለው..ማለት ያው ጥሎን ሲሄድ ህጻን ስለነበርኩ እንደ ህልም ነው ሚታወሰኝ..ግን እዚህ ሳለ እንዴት አይነት ሰው ነበር…?ምን አይነት አባት…እንዴት አይነት አስተማሪ…?እንደነበር ከተለያ ሰዎች ለማጣራት ሞክሬያለው…፡፡
እዚህ አገር ሳለ የነበረውን የፖለቲካ ተሳትፎም ለማወቅ ጥሬያለው…..እርግጥ እዚህ እያለ የሆነ ፓለቲካ ድርጅት ውስጥ አባል ነበር..ግን ማንም የማየውቀውና እዚህ ግባ የማይባል ተሳትፎ የነበረው ተራ አባል ነበር…. አሁን በገጹ ላይ የሚጽፋቸው ጽሁፎችን ሳነብ ልክ ከዚህ ሀገር የወጣው የፖለቲከኛ ስደተኛ ሆኖ ከኢህአዲግ የእስር መንጋጋ ሾልኮ በሱዳን በኩል ኮብልሎ በስቃይ አሁን ያለበት ሀገር እንደደረሰ ነው፡፡
እኔም አንተም እንደምናውቀው ሀቁ ግን አባታችን የፖለቲካ ስደተኛ ሳይሆን የኑሮ ስደተኛ እንደሆነ ነው…፡፡ያው ታውቀወለህ ለምን ጥሎን እንደሄደ..እሱ ግን በዲያስፖራው አለም ያለውን ተቀባይነት ለማግዘፍ ‹‹…ስራዬን ለቅቄ ቤተሰቤን በትኜ በስደት አለም ከ15 አመት በላይ የእየባከንኩ ያለውት በዘረኛው መንግስት ምክንያት ነው…››ብሎ የጻፈውን አንብቤ ምን አይነት ውሸታም አባት ነው ያለን ?ብዬ ልታዘበው ችያለው…ግን እንደዛም ሆኖ በሆነ ተአምር ወደ ሀገር ተመልሶ ለአንዴም ሰከንድ ቢሆን ፊት ለፊት በአካል ባየው ደስ ይለኛል..ይገርምሀል እኔ ብቻ አልምሰልህ እናቴም በጣም ትናፍቀዋለች..መአት ቀን ፎቶውን በተመስጦ እየተመለከተች እንባዋን ስታንጠባጥብ ደርሼባታለው …ግን እውነቱን ለመናገር የእናቴ እንባ ለእሱ
👍12
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-አምስት

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ከልደቴ ከ5 ቀናት ቡኃላ ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ተኝቼያለው፡፡እንቅ
ልፍ ግን አልወሰደኝም....ቢሆንም ግን አይኖቼ ተጨፍነዋል፡፡እናቴ መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ ወደ ውስጥ ስትገባ ይሰማኛል‹‹…ወይ ልጄ እንቅልፍ ወሰደህ?›› አለችና ግንባሬን ስማ አልጋው ላይ ስትቀመጥ ይታወቀኛል…ወዲያው ግን ትርሲት‹‹ እቴቴ…እቴቴ›› እያለች ወደውስጥ ስትገባ ሰማዋት…
‹‹ምነው… ?ምን ፈለግሽ..?››
‹‹ፀግሸ ተኛ እንዴ?››
‹‹እዚህ ፊልም ላይ ሲፈዝ ውሎ ደክሞታል መሰለኝ በጊዜ ተኝቷል››
‹‹አይ ጥዋት ቁርስ ምን ልስራልሽ ልልሽ ነው?››
‹‹አይ ..ምንም.. ነገር እኮ አርብ ነው ..ፆም ነው..ቁርስ አልፈልግም››
‹‹ውይ… አይ የእኔ ነገር!! ረስቼው››
‹‹እሺ በይ ደህና እደሪ››
‹‹ደህና እደሪ…ግን ነገ ከትምህርት ቤት እንደመጣው ፀግሽን ይዤ ከከተማ እወጣለው፡፡››
‹‹እወጣለው ስትይ?››
‹‹ልጄን ይዤ ቅዳሜ ና እሁድ ሶደሬ ነው የማሳልፈው››
‹‹መኪና አገኘሽ እንዴ…?››
‹‹ወንድም ጥላ ከሹፌር ጋ ልክልሻለው ብሎኛል›› ወንድም ጥላ የምትለው ታለቅ ወንድሞን ነው….አጎቴን፡፡
‹‹አሪፍ ነዋ..ግን እኔንም ይዛችሁኝ ብትሄዱ አሪፍ ነበር››
‹‹አይ ከልጄ ጋር ለብቻዬ መሆን ነው የምፈልገው››ይሄን ሁሉ ንግግራቸውን አድፍጬ እየሰማዋቸው ነው..፡፡
‹‹በቃ እንደፈለግሽ…ስለዚህ በአንድ ሻንጣ ቅያሬ ልብስ ላዘጋጅላችሁ አይደል?›››
‹‹አዎ ..ፀግሽንም ሰውነቱን አጥበሽ ብትጠብቂኝ ደስ ይለኛል››
‹‹ሰውነቱን!!!››አለች ልክ አዲስ ነገር እንደሰማ ሰው በመደነቅ
‹‹ምነው አዎ ሰውነቱን››
‹‹ግን እኮ እቴቴ…››በሰለለ ድምፅ
‹‹እንዴ !!ሰላምነሽ ግን..?ምነው ችግር አለ?››
‹‹አይ!! እንደው ነግርሻለው እያልኩ…››
‹‹ምኑን ነው የምትነግሪኝ?››
‹‹ማለት ትንሽ ያሳፍራል››
‹‹ኦ ሴትዬ በውድቅት ለሊት አታድርቂኝ…በቃ ማጠቡ ከከበደሽ ተይው እኔ ስመጣ አጥበዋለው››በተከፋ የድምጽ ቀና ተነጫነጨችባት
‹‹አይ እኔማ አጥበዋለው…እሱን መንከባከብ በጣም ደስ እንደሚለኝ ታውቂያለሽ..በጣም የምወደው እና የምሳሳለት ወንድሜ ነው..ግን በቀደም የልደቱ ቀን ሰወነቱን ሳጥበው…››
‹‹ሰውነቱን ስታጥቢው ምን….?››
‹‹ሰውነቱን ሳጥበው እንትኑ ቆመ..ለረጅም ደቂቃ ግትር ብሎ ቆመ ..እንዲህ ሲሆን አይቼው አላውቅም››
‹‹ምኑ ቆመ .. ?ምን ንገሪኝ..?››
‹‹እንዴ እቴቴ ደግሞ…. እንትኑ ነዋ..ለምን ታሳፍሪኛለሽ?››ይሄንን ስሰማ ባደፈጥኩበት ሆኜ እንዴት እንደተሸማቀቅኩ አትጠይቁኝ …በራሴ አስቤበትና አቅጄ የሆነ ወንጀል የሰራው ነው የመሰለኝ…..እናቴ እንዴት እንደምትደነግጥ እና እንዴት እንደምትበሳጭብኝ ስገምት ትንፋሽ አጠረኝ..ግን የሆነው ካሰብኩት በተቃራኒው ነው … አናቴ ከተቀመጠችበት አልጋ ተስፈንጥራ በመነሳት ወለሉ መሀከል ተገትራ በመሳቀቅ ስታወራ የነበረችው ትርሲት ላይ ስትጠመጠምባት አይኔን አጨንቁሬ ተመለከትኩ..ጨምቃ ስታቅፋት…አገላብጣ ስትስማት
‹‹እንዴ እቴቴ ምንድነው……?የነገርኩሽን ሰምተሸል?››
‹‹አዎ ሰምቼያለው..ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ..ልጄ ተአምራዊ በሆነ መልኩ ቀስ በቀስ የመዳን ተስፋው እየለመለመ መሆኑን ነው››
‹‹እንዴት… ?ይሄ ደግሞ ከመዳን ጋር ምን አገናኘው››እኔም በውስጤ ሥጠይቅ የነበረውን ጥያቄ ነው ትርሲት እናቴን የጠየቀችልኝ ..ከስንት ዓመት አሰልቺ ጥበቃ ቡሃላ ግራ እጁን ማንቀሳቀስ እና በመጠኑም ቢሆን መጠቀም ጀመረ…አሁን ደግሞ ውጫዊው የመራቢያ አካሉ ለውስጣዊው ስሜቱ መልስ መስጠት ጀመረ…የምለውን በቀላሉ ልትረጂኝ አትቺይም..ግን ይሄ ትልቅ የምስራች ነው…ብዙ የህክምና ፕሮፌሰሮች ማድረግ ያልቻሉትን ነው አንቺ በየዋህነት እና በንጽህ ፍቅርሽ ማድረግ የቻልሽው…እንዴት ይሄንን የመሰለ ዜና እስከዛሬ ትደብቂኛለሽ?››
‹‹እንዴ እቴቴ …ምን ብዬ እንደምነግርሽ እኮ ጨንቆኝ ነው….እኔ ጥፋት የሰራው መስሎኝ ፀፀት ላይ ነበርኩ››
‹‹የምን ጥፋት ..የምን ፀፀት››
‹‹አይ እቴቴ የዛን ቀን ሳጥበው ልብሴ እንዳይበሰብስ ስለፈለኩ በዛውም እኔም ገላዬን ልታጠብ ፈልጌ ስለነበር እራቁቴን ሆኜ ነበር …የነበረው..ማለቴ በፓንት ብቻ….እርግጥ የዛን ጊዜ አይደለም ያልኩሽ ነገር የተከሰተው…ሰውነቱን በማሸው ጊዜ ነው….. ››
ደግማ ስባ ወደ ደረቷ አስጠግታ ..በማቀፍ ግንባሯን ሳመቻት‹‹..ምን አይነት ውለታ እንደዋልሺልኝ አታውቂም..እንኳንም እንደዛ አደረግሽ..ምን አልባት የልጄ ድህነት ቁልፍ በዚህ መንገድ የሚገኝ ሊሆን ይችላል….፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹አይ ተይው …እንዲሁ ነው..በይ አሁን ሂጂ ደህና እደሪ››
‹‹እሺ እቴቴ..አንቺም ደህና እደሪ››
‹‹እሺ ደህና እደሪ...ግን ከመሄድሽ በፊት ነገ ሰውነቱን ታጥቢልኛለሽ አይደል?››
‹‹እጠቢው ካልሽ እሺ..ደስ ይለኛል››
‹‹አዎ በደንብ እጠቢው…..እና ደግሞ ስታጥቢው ልብስሽ እንዳይረጥብብሽ አውልቂው…››
‹‹እንደዛ ይሻላል…››በፈገግታ እና በእፍረት
‹‹አዎ አንቺም እየታጠብሽ ብታጥቢው በጣም ደስ ይለዋል….››
‹‹እሺ እቴቴ››
‹‹..እና ደግሞ ሰውነቱ ዘና እንዲልለት ማሸቱንም እንዳትዘነጊ››
‹‹አልዘነጋም እቴቴ…››ብላ መኝታ ቤታችንን ለመጨረሻ ጊዜ ለቃ ወጣች፡፡አሁንም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ያለው አስመስዬ አይኖቼን ጨፍኜ ግን ደግሜ በስሱ አጨንቁሬ መከታተሌን ቀጥያለው…. እናቴ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከውስጥ ቀረቀረችና ግድግዳው ላይ በተሰቀለው የመድሀኒአለም ስዕል ፊት ለፊት ወለሉ ላይ ተንበረከከች..ዓይኖቾን ስዕሉ ላይ የእጆቾን መዳፎችን ደግሞ አንድ ላይ አጣምራ ወደ ግንባሯ አካባቢ አንከርፍፋ ፀሎቷን ማነብነብ ጀመረች
‹‹…..አምላክ ምንም እንኳን ዝምታህ ለእኛ ለደካሞቹ የዘላለም መስሎን ተስፋ ቢያስቆርጠንም አንተ ግን በትክክለኛው ቀን ትክክለኛውን መልስ መመለሱን ታውቅበታለህ…ይሄንን የመሰለ ተዓምራዊ ዜና ስላሰማሀኝ አመሰግናለው..ጌታ ሆይ ደግሞ አምናለው ልጄ በቅርቡ በሁለት እግሮቹ ይቆማል…ልጄ በእጆቹ ይመገባል…ልጄ አፍቅሮ የሴት ልጅ ከንፈር ይስማል… ከቆንጆ ጉብል ጋር ፍቅር ይጋራል…..አምናለው ልጄ የህይወትን ተአምራዊ በረከት የሚዘንብለት ሰው ይሆናል…ጌታ ሆይ ክብር ላንተ ይሆን ››በማለት ፀሎቷን አጠናቃ ወደ እኔ ስትመጣ አይኖቼ ፈጠው አንባዬ በግራ ጉንጬ ላይ ወደ ታች ሲንጠባጠቡ ነበር ያገኘቺኝ
‹‹ወይ!!! የእኔ ፀጋ… ነቅተሀል እንዴ ?ለምን ታለቅሳለህ….የሀዘን ዘመናችን እኮ እያከተመለት ነው..››በማለት አንሶላውን ገልጣ ከውስጥ ገባችና እቅፍ አድርጋኝ በእጆቾ እንባዬን እያበሰችልኝ…ፀጉሬን እያሻሸችልኝ…የእውነት በደስታ በተሞላ ሰላማዊ እንቅልፍ እንድዋጥ አደረገችኝ፡፡የማንነቴ ፈጣሪ ሀርሜ …..

💫ይቀጥላል💫

Like👍 ማድረግ እንዳይረሳ

አስተያየታችሁን በ @atronosebot አድርሱን
👍81
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-ስድስት

:
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ሶደሬ ደርሰናል …….ከአዲስ አበባ ሶደሬ ድረስ ያሳለፍነውን የጉዞ ታሪክ ልተርክላችሁ አልፈልግም ..ምክንያም ብዙም የተለየ ትዕይንት የለውም….እንደደረስን ሶስት የተለያየ ማረፊያ አልጋ ተከራየን…በአንዱ ክፍል ትርሲት ልብሶን አስቀመጠችበት …. በሌላው ክፍል የሶስታችን ዕቃዎች ተቀመጡበት..ሹፌሩ ከእኛ እራቅ ያለ ሌላ ክፍል ተያዘለት….፡፡
የተወሰነ እረፍት አድረግንና ተሰባስበን ወጣን… ዘና ለማለት …፡፡እራታችን በልተን ሁሉን ነገር ጨርሰን ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ወደ ማረፊያችን ተመለስን…ዊልቸሬን እየገፋች ያለችው ትርሲት ነች…..ልክ ጎን ለጎን የሚገኘው መኝታ ክፍላችን በራፍ ጋር ስንደርስ
..እኔን ለማስረከብ ዊልቸሬን ወደ እናቴ እየገፋች‹‹መኝታው አይበቃችሁም ማክዳ ከእኔ ጋር ትተኛ››አለች ትርሲት
‹‹አይ ይበቃናል››እናቴ ፍርጥም ብላ መለሰችላት
‹‹አረ እቴቴ… እኔም ብቻዬን መተኛት እፈራለው..?››
‹‹ለሊት ታስቸግርሻለች..ባይሆን ፀግሽ ካንቺ ጋር ይተኛ››
‹‹ምን..?››አለች በድንጋጤ ወደ እናቴ ስትገፋ የነበረውን እኔ የተቀመጥኩበትን ዊልቸር መልሳ ወደ ራሷ እየሳበች
‹‹እንዴ ምን አስደነገጠሸ....?ብቻዬን መተኛት እፈራለው የምትይ ከሆነ ፀግሽን ወሰጂው››
አይደለም እሷ እኔም በጣም ነው የደነገጥኩትም የተደነጋገርኩትም…..እናቴ ምን ማለቷ ነው....?እንዴት ከእኔ ይልቅ ማክዳ አብራት እንድትተኛ ፈለገች…...?ውስጤ የተፈጠረ ጥያቄ ነበር…ቅር ያለኝ መሰለኝ ..ግን ደግሞ ከቅሬታዬ ባሻገር ጎላ ያለ የደስታ ስሜት እየተሰማኝ ነው…ከትርሲት ጋር ለመተኛት አጋጣሚውን በማግኘቴ የመጣ ደስታ
‹‹እ ምን ወሰንሽ..?››
‹‹አረ እሺ›› ብላ ስትገፋው የነበረውን ዊልቸሬን ጠምዝዛ እየገፋች የእሷ ዕቃዎች ወደ አሉበት ወደ አንደኛው ክፍል ይዛኝ ከገባች ቡኃላ…‹‹ደኅና እደሩ››አለቻት
‹ደህና እደሩ..ፀግሽ ደህና እደር››እናቴ ነች
ትርሲት በራፍን ዘጋችው‹‹….ወይኔ አላመንኩም…በቃ እኮ ባልና ሚስት መሆናችን ነው››አለችኝ ሳቅ በሳቅ ሆና..ዊልቸሬን ወደ አልጋው አስጠጋችና ጎንበስ ብላ ጫማዬን ከእግሬ ላይ አወለቀችልኝ… ቀስ ብላ ወደ አልጋው ገለበጠችኝ… ቀና ልትል ስትል በዛችው ብርቅ የሆነችውን ግራ እጄን አንቀሳቀስኩና የለበሰችውን የቲሸርት እጅጌ ጨምድጄ በመያዝ ወደ ራሴ ስቤ አስቀረዋት
‹‹….እንዴ!!! አንተ ጉዳኛ..ምን ፈለክ..?››መጎተቴን ቀጠልኩ
‹‹እሺ እሺ….መሳም አምሮህ ነው አይደል..? ብላ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀችብኝ…. የፈለኩት ነገር ስለነበረ ዘና ብዬ እመጠምጣት ጀመር…መሳሞን ሳታቋርጥ ቀስ ብላ በአንድ እጇ ተራ በተራ ጫማዋን አወለቀች…እናም ወደ አልጋ ሙሉ በሙሉ ወጣች..ቀኝ እጆን አንገቴ ስር አሾልካ አስገባችና ግራ እጆን ጭንቅላቴ ላይ አድርጋ ፀጉሬን እያሻሸችልኝ ልዩ ገነታዊ ወደሆነ አለም ውስጥ ከተተችኝ..ምን እንደሚሰማኝ ሙሉ በሙሉ ለመናገር ሁሉ አልችልም…እንደምንም ከንፈሯን ከከንፈሬ አላቃ ግንባሬን እየሳመች ..ጉንጬን እየሳመችኝ …አንገቴን እየሳመቺኝ….‹‹ታፈቅረኛለህ አይደል..?››ስትል ጠየቀችኝ
ግራ እጄን ወደ ቀኝ ጡቷ ልኬ ጠንከረ አድርጌ ጨመኳት‹‹አዎ በጣም..እጅግ በጣም አፈቅርሻለው››ማለቴ ነው…እስቲ በእግዚያብሄር ጡት መጭመቅ እና አፈቅርሻለው የሚለው ቃል በምንኛ ነው የሚገናኘው..?
እሷ ግን የልብ አውቃ ነች..ወዲያው ነው የተረደችኝ‹‹ያን ያህል ነው ምታፈቅረኝ..?››
ግራ እጄን ወደ ግራ ጡቶ አዘዋወርኩና ይበልጥ ጠንከር ባለ ኃይል ጨመቅኳት‹‹ወይኔ ታድዬ ብላ ወደ ከንፈሬ ተመለሰችና ስትመጠኝ … ያለንበት ክፍል በራፋ ተንኳኳ…
ደንግጣ በተለየ ቅልጥፍና ከተኛችበት ተነሳችና ከአላጋው በመውረድ ‹‹ማነው..? ››አስትል ጠየቀች
‹‹እኔ ነኝ…ተኛችሁ እንዴ..?››የሀርሜ ድምፅ ነበር
‹‹እንዴ እቴቴ…አንቺ ነሽ....?አልተኛንም››ይሄንን የምታወራው… ቀሚሶን ወደ ታች እየጎተተች..የተዛነፈው ቲሸርቷን እያስተካከለች ነው….፡፡ቁልቁል እኔን እያች ..በማፈር እና በድንጋጤ መካከል ሆና በራፍን ልትከፍትላት እርምጃ ከጀመረች ብኃላ መልሳ ወደ እኔ በመምጣት አልጋ ልብሱን ከባዶ የአልጋው ክፍል ሰብስባ ከወገቤ በተች ያለውን ሰውነቴን አለበሰችኝና….‹‹ይሄንን ብልግናህን እናትህ ማየት የለባትም›› ብላ ዝቅ ባለ ድምጽ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ ነገራኝ ወደ በራፉ ሄደች…ለምን አልጋ ልብሱን እንዳለበሰቺኝ ገባኝ…የተቀሰረ ብልቴን እናቴ እንዳታይ መከለሏ ነው….የደስታ ፈገግታ ፈገግ አልኩ…..
‹‹ግን እናቴ ምን ነካት....?ከእንዲህ አይነት ታሪካዊና ወሲባዊ ቁርኝታችን እንዴት ታናጥበናለች....?ምን ፈልጋ ነው የምታንኳኳው...?እንዴ ምን ነካኝ …..?እኔ እኮ እድሜ ዘመኔን ሙሉ የእናቴን ኮቴ እንደሞዛር ሙዚቃ ሳጣጥም የኖርኩ ሰው ነኝ..እኔ እኮ የእናቴን ወደእኔ አካባቢ የመቅረብ ሽታ ልክ እንደናርዶስ ሽቶ ወደ ውስጤ ..ነፌሴ ድረስ ዘልቆ እንዲሰማኝ በመሳብ ስረካና ስደሰት የኖርኩ ሰው ነኝ….እኔ እኮ እድሜ ልኬን የእናቴን ወደ እኔ ክፍል የመምጣት የሚያበስረውን ድምጾን ስሰማ ለእምዬ ማርያም ከመላአኩ ገብርኤል መንፈሳዊ አንደበት የወጣ የብስራት ድምጽ በደረሳት ጊዜ እንደተሰማት አይነት ደስታ ሲሰማኝ የኖርኩ ሰው ነኝ..እና ለምንድነው ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቴን ድምጽ መስማቴ በውስጤ ቅሬታ የፈጠረብኝ…...?እንዴት የእናቴ ወደ እኔ ክፍል ለመግባት መፈለጓ ደስ ሳያሰኘኝ ቀረ…..?
ብቻ በራፉን ከፈተችላትና እናቴ ወደ ውስጥ ገባች….
‹‹ምነው እቴቴ ሰላም ነው..?››
‹‹አይ ሰላም ነው..ግነ ሀሳቤን ቀይሬ ነው››ይሄንን የምትናገረው በራፉን አልፋ ወደ ውስጥ ዘልቃ ፊት ለፊት ቆማ ሁለታችንንም እያፈራረቀች እያየችን ነው..ደግሞ በሁለት እጆቾ ሁለት የተለያዩ በፔስታል የተጠቀለለ ዕቃ ይዛለች
‹‹ምን ይሆን..?››
‹‹የትኛውን ሀሳብ….?››
‹‹ይገርምሻል… ማክዳ አልተኛም ብላ የምታስቸግር መስሎኝ ነበር..አሁን ስለደከማት መሰለኝ ገና ጎኗ አልጋው ላይ ከማረፉ ነው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት…››
እናቴ ምን እያለች እንደሆነ አልገባኝም…
‹‹አሪፍ ነው ››ትርሲት መለሰች ግራ መጋባቷን በሚሳብቅ ድምፅ ቅላፄ
‹‹ስለዚህ አታስቸግርሽም ማለት ነው...››
‹‹ማ..? ማክዳ እኔን..?››
‹‹አዎ ሰለተኛች አታስቸግሪሽም… ስለዚህ ሂጂና ከእሷ ጋር ተኚ››
‹‹ከእሷ ጋር…ለምን .?አንቺስ..?››ጥያቄዋን አግተለተለች
‹‹እንዴ እኔማ እዚህ ተኛለው..ከልጄ ጋር››ኮስተር ብላ መለሰች
ፈክቶ የነበረው ፊቴ ሲጨልም ለእኔ ለራሱ ይታወቀኛል….በፍትወት ስሜት ግሎ የነበረው ሰውነቴ አሁን በንዴት ኩምሽሽ ማለት ጀመረ…እንዴ ሀርሜ ምን ነካት…..?ለእሷስ ቢሆን እድሜ ልኳን ከእኔ ጋ መተኛት አይሰለቻትም…...?ቅድም ሀይቁ ዳር ቁጭ ብለን በተመስጦ ና በፅሞና ስንዝናና ያየውት በቅርብ እርቀት የነበረ አንድ ሽበታምና ደንደን ያለ ሙሉ ሰው ትዝ አለኝ….ለምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ.? …እናቴ ላይ አፍጧባት ነበር….አይኖቹን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻለም ነበር…ደግሞ እራት ስንበላም በአቅራቢያችን ሲያንዣብብ አይቼዋለው..እሷም አንድ ሁለቴ በመገላመጥ ስታየው እና በመገረም ስትሸረድደው ታዝቤለው…እና ምን አለ አሁን ማክዳ ከተኛችላት ወጣ ብትል….?እርግጠኛ ነኝ አሁን ካለንበት ክፍል በአስር ሜትር እርቀት አይጠፋም…እና ከእሱ ጋር ዘና ለማለት ብትሞክር መቼስ እናቴን ገና ጮርቃ ልጅአገረድ ነች ባልላችሁም በእሷ ዕድሜ አካባቢ ያለን ማንኛውንም ወንድ ማማለል
👍10
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-ሰባት
:
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...በውበት እና በፍቅር ያሸበረቁ ሁለት የእረፍት ቀናቶችን በሶደሬ አሳልፈን ወደ ቤት ከተመለስን ሶስት ቀናቶችን ሆኗናል፡፡ከረፍት እንደተመለስን እናቴ አንዳንድ ስር ነቀል የሆኑ ለውጦችን በቤት ውስጥ አካሄዳለች..በመጀመሪያ ያደረገችው ለቤቱ ሌላ ሰራተኛ መቅጠር ነው ይሄን ስትሰሙ መቼስ ሳትደነግጡ አትቀሩም ትርሲትስ ምን ልትሆን ነው…?ከእናትህ ተጣላች እንዴ…?ወይስ በቃኝ ወደ አሜሪካ ልብረር አለች..?ይሄ በውስጣቹሁ ሚመጣ ወይም የሚፈጠር ጥያቄ ነው..ግን ሌላ ሰራተኛ ያስፈለገው ትርሲትን ሙሉ በሙሉ ከስራ ጫና ለማላቀቅ ነው..ይሄ የሀርሜ ውሳኔ ነው..በቃ ያንቺ ዋና ስራ ፀግሽን መንከባከብ ብቻ ነው ተብላለች፡፡
ሌላው የተወሰደው ስር ነቀል ለውጥ እኔ መኝታ እድሜ ልኬን ከተዳበልኳት ከእናቴ መኝታ በመነጠል ወደ ትርሲት መኝታ ቤት ተዘዋወርኩ…ይሄም ቀጥታ በእናቴ ትዕዛዝ የሆነ ነው….
ሌላው ሁል ግዜ አንቴ ከስራዋ እንደመጣች ትርሲትን ከእኔ ነጥላ ወደ ክፍሎ ትወስዳትና ለአንድ ሰዓት ያህል ታወራታለች…ምን እንደምታወራት በጣም ለማወቅ ብጣጣርም እየደጋገምኩ ብጠይቃትም ትርሲትም ፍንክች ልትልልኝ አልቻለችም…ግን በእናቴ ተመክራ ከመጣች ብኃላ በየቀኑ አንድ የተለየ እና ዓዲስ ነገር በእኔ ላይ ታደርጋለች….ሰውነቴን ማሸት….እግሮቼን ማንቀሳቀስ…የእጆቼን ጣቶች ማነቃነቅ …ደግፋኝ መቆም ..በእየእለቱ የምታደርገው ነገር ነው ፡፡
ይሄንን ነገር ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ፕሮፌሽናል በሆኑ ቴራፒስቶች ጋር ሞክሬው ተስፋ የለሌውና አበሳጭ ሁኔታ ብቻ ሆኖብኝ የተውኩት ነገር ነው..አሁን ግን በአማተሯ ፍቅረኛዬ ባልጠና ሁኔታ እየተከወነ ቢሆንም ግን ደስ እያለኝ ነው የማደርገው…እያንዳንዶን የሰውነቴን ክፍል ስትነካኝና ስታነቃንቀው የሆነ የዘመናት ድንዛዜዬ ከውስጤ ቀስ በቀስ ሲተን ይታወቀኛል… እየታየኝ ነው እና አርግ ያለችኝን ሁሉ ማድረግ ቢያቀቅተኝ እንኳን ቢያንስ በሀሳቤ እሞክራለው..እርግጥ ለማድረግ የምትጥረው ጥረት በሙሉ የእሷ ሀሳብ እንዳልሆነ ከገባኝ ከራርሞል ..ከጀርባው የሀርሜ ምክር አለበት…የእሷ ስልጠና አለበት…የእሷ ጉጉት አለበት….ሀርሜ ይህቺን ትርሲት ለእኔ ዕፀ ድህነቴ እንደምትሆን ተስፋ ማድረግ እና ማመን ከጀመረች ሰነባብታለች..ይሄንን ደግሞ ከንግግሯ ከሁኔታዋ እና ከአይኖቾ ውስጥ በየቀኑ አነበዋለው…..እኔ ግን ባለው ነገር ደስተኛ ነኝ…አሁን በውስጤ በሚሰማኝ ነገር ደስተኛ ነኝ..በውስጤ በሚዘንበው የፍቅር ዝናብ መላ ውስጠቴ ደስታ እየረሰረሰ ነው…ለምን ተፈጠርኩ ብዬ ለዓመታት ፈጣሪን ስጠይቅና ስወቅስ የኖርኩት ልጅ አሁን እንኳንም ፈጠርከኝ ለማለት በቅቼያለው…ትርሲትን ከምነግራችሁ በላይ አፍቅሬያታለው…ለደቂቃም ከፊቴ ዞር ስትል በድቅድቅ ጨለማ መብራቱ እንደጠፋበት ቤት ውስጤ ጭልም ይልብኛል..ወደ ውጭ የሆነ እቃ ልግዛ ብላ ስትወጣ ተመልሳ የምትመጣ አይመስለኝም….ከእኔ የተሸለ ሎጋ ወጣት ቢለክፋትስ…?ከእኔ የተሸለ ዘናጪ ቢጠልፋትስ…?
የምትፈልገውን የሚሰጣት..የሚያምራትን ቀሚስ የሚገዛላት…ትልቅ ሆቴል ወስዶ የሚጋብዛት ብታገኝስ..?ልግባሽ የሚላት ባለቤትና መኪና ቢያማልላት እና ቢወደስድብኝስ.?በውስጤ እየተንፈራገጠ የሚያሰቃኝ ስጋት ነው….ይሄንን ሳስብ በተአምርም ቢሆን መዳን እንዳለብኝ ይሰማኛል…ጤነኛ ሆኜ በእግሮቼ መራመድ እንዳለብኝ …እጆቼን አንቀሳቅሼ መስራትና መብላት..በእሷ እጅ መጎረስ ብቻ ሳይሆን እሷንም ማጉረስ እንዳለብኝ ወስናለው…አንደበቴ ተላቀው ቃላት ማውጣት ..ከውስጤ ስለእሷ ምን እንደሚሰማኝ ..ምን ያህል እንደማፈቅራት..ላገባትም እንደምገፈልግ በጆሮዋ ልነግራት እፈልጋለው..አዎ መዳን አለብኝ..ዉሳኔዬ ነው..ግን እንዴት ነው በሀያ ሶስት አመት ሙካራ ያልተሳካልኝን የመዳን ጥረት በሳምንታት ውስጥ ተስፋ ማድረግ የቻልኩት፡፡
አሁን ያለውት ሳሎን ውስጥ ነው ፡፡ማታ ነው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ..ቀስ በቀስ የቤቱ ሰዎች ሁሉ መጥተው ሳሎኑን አድምቀውታል…ውጭ የቀረው የቤቱ አባል መሀሪ ብቻ ነው..የእኔዋ ትርሲት ፊት ለፊት አጠር ያለች ኩርሲ ላይ ተቀምጣ ትታየኛለች..ከፊት ለፊቷ በመለስተኛ ረከቦት ላይ እንደ ሰለጠነ ሰራዊት በተርታ የተሰለፉ አስር የሚሆኑ ነጫጭ ሲኒዎች ከረከቦቱ ጎን ጥቁር ጀበና ከፊት ለፊቱ የእጣን ጢስ የሚትጎለጎልበት ጊርጊረ ይታያል…አያችሁ ይህቺ ልጅ ምን ያህል ቀልቤን እንደተቆጣጠረችው..አሁን እንኳን ስለቤታችን ሁኔታ ስገልጽላችሁ ከሷው ነው የጀመርኩት..
ለማኝኛውም ቀጠልኩ…እናቴ ከእኔ ያለውበት ሶፋ ላይ ነው የተቀመጠቸው ጭኗ ላይ ጭንቅላቴን አንተርሳ ፀጉሬን እየዳበሰችልኝ….ከእኛ በቅርብ እርቀት እናትና ልጅ ተቃቅፈው ይታዩኛል ፌናን እና ማክዳ …ከነሱ ፈንጠር ብላ ሮሚ አቀርቅራ ካልኩሌተረ እየጠቀጠቀች ማስታወሻ ደብተሯ ላይ ትሞነጫጭራለች…አዲሷ ሰራተኛ ፊት ለፊት የለችም… ማአድ ቤት ስራ እየሰራች ሳይሆን አይቀርም
‹‹ፌን መች ነው ምርቃታችሁ››እናቴ ነች ጠያቂዋ
‹‹ሀያ ቀን ቀርቶታል››
ልትገላገይ ነዋ››አለቻት ሮሚ የምትሰራውን የሂሳብ ስራ አቋርጣ
-ምን መገላገል አለው…ስኮላር ሺፕ እሞከርኩ ነው..ከተሳካልኝ ወደ ውጭ ሄጄ ትምህርቴን ቀጥላለው››
-ቀጥላለው..››በመደነቅና በመንገሽገሽ ጠየቀቻት
‹‹ምነው አዎ ቀጥላለው››
-ትቀልጂያለሽ እንዴ..ሰባት አመት እኮ ነው የተማርሺው..አሁንም ቀጥላለው ስትዪ ትንሽ አይደብርሽም››
-ለምን ይደብራታል››እናቴ ጣልቃ ገባች
እንዴ እሺ ትምርቱ አይሰልቻት..ደሞዝ መብላት አያምራትም››
-ያምረኛል..ግን ገንዘብ ከመልመዴ በፊት ትምህርቴን ያሰብኩት ቦታ ማድረስ አለብኝ››
-አረ አትጃጃይ. ያንቺ ትምህረት መድረሻው አይታወቅምና…እድመሜሽን ወረቀት በማገላበጥ ትጨርሺዋለሽ..›
አየሽ ለአንቺ ሰባት አመት መማር የሰማይ ያህል ከባድ መስሎ ሊሰማሽ ይችላል..ግን ስለሰው ልጅ ጤና ነው የምንማረው..ህይወትን ስለማዳን ነው የምንማረው..ለዛ ደግሞ በቂ አይደለም.አሁን አጠቃላይ ሀኪም ሆኜ ነው የተመረቅኩት ግን ስፔሻላይዝድ ማድረግ እፈልጋለው..
ጎሽ ልጄ ..እሷን አትስሚያት…ለመሆኑ ከቀናሽ በምንድነው ስፔሻላይዝድ ማድረግ የምትፈልጎው››
በትክክል በዚህ ብዬ አልወሰንኩም ፡፡ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ..በቀጣይነት ምማረው የህክምና ትምህርት ውንድሜ ጤና ላይ ቅንጣትም ቢሆን ለውጥ እንዳመጣ የሚያግዘኝ መሆን አለበት..ቀኝ እጁን ማንቀሳቀስ እንዲችል ብረዳው…ወይንም የእግሮቹን ጣቶች እንዲታዘዙለት ማድረግ ብችል..ከላሆነ አንደበቱ ተላቀው ቃላት እንዲያወጣ ልረዳው ብችል..አዎ እድሉን ባገኝ ይንን ብቃት የሚሰጠኝን ትምህርት ነው የምማረው..ለዛ ደግሞ አልሰለችም…ከአሁን ቡኃላ 19 ዓመት እንኳን ቢወስደብኝ አይሰለቸኝም… እማራለው…ያንን ማደረግ ስችል ነው የእውነት እንደተማርኩ የሚሰማኝ……
ይሄንን ስትናገር እናቴ እንባዋ መንጠባጠብ ጀምራ ነበር..ትርሲትም እሷን ተከትላ መነፍረቅ ጀመረች.. ሮሚ እንኳን የጀመረችውን ክርክር ትታ በሀዘኔታ አፍጥጣ ስታያት ቆየችና ከተቀመጠችበት በመነሳት ልጆን አቅፋ ወዳለችው ፊናን በመሄድ አቅፋ ግንባሯን ሳመቻትና ‹‹የእኔ እህት በእውነት ሀሳብሽ ድንቅ ነው..በጣም ነው ስሜቴን የነካሽው..››ግን ለፀግሽ የአንቺ እንደዚህ ህይወትሽን ከባድ በሆነ ሁኔታ ከወረቀት ጋር መታገል የለብሽም››
‹ለምን የለብነኝም››በቁጣ ጠየቀቻት
‹አትቆጬ ..ለወንድሜ እኔ አለውለት ፣፣ሁለት አመት ብቻ ስጡኝ …ሁለት አመት ከዛ ቡሃላ ታይላንድ ሆነ ሆላንድ፤ ደብብ አፍሪካ ሆነ
👍16
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል- 8

:
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...አሁንም ዙሪያዬ በብርሀን እንደታጠረ ነው ..ውስጤ በፍቅር እንደተጥለቀለቀ ነው፡፡ውስጤ ይራመዳል..ውስጤ ይሮጣል…ዉስጤ በትርሲት ልብ ውስጥ ይጋልባል፡፡በመንፈሳዊያን ስሌት ሰው ሁለቴ ይወለዳል..አንድም ከወላጆቹ በስጋ ..ከዛ ከአምላኩ በመንፈስ…እኔም አሁን ሁለተኛ እንደተወለድኩ እየተሰማኝ ነው.ከትርሲት ንጽህ እና የጠራ ልብ ውስጥ በፍቅር እንደተወለድኩ…፡፡አዎ ለዛ ነው መቼም ተስምቶኝ የማያውቀው ሙሉነት እየተሰማኝ ያለው ፡፡ልክ ንፁህ ዘይት እንደተቀየረለት ሞተር ደሜ በእያንዳንዷ ህብረሰረሰሬ ..በእያንዳንዷ የሰውነቴ ቅንጣ ሲራወጥ እና ሲብላላ ይታወቀኛል፡፡ፍፅም ሰላም እና ፍፅም ጤንነት ይሰማኛል፡፡
እንደተለመደው ዊልቸሬ ላይ ቁጭ ብዬ በፅሞና የጥዋት ፀሀይ እየሞቅኩ ነው..ለስለስ ያለች ስሜት ነዛሪ ሙቀት ያላት ፀሀይ ነች፡፡ሰዓቱ ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡እናቴም መደገፊያ ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ከጎኔ ተቀምጣ ትካዜ ይሁን ተመስጦ ባለየውት ዝምታ ውስጥ ተውጣለች..በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከተቀመጥን አንድ ሰዓት አልፎናል፡፡አንድ ሰዓት በየራሳችን ሀሳብ ውስጥ ተሸሽገን….
ቅድም ሲንጫጩ እና ሲዘምሩ የነበሩት ባለ አስደማሚ ህብረ ቀለም ወፎች አሁን ፀሀዬ ጠንከር እያለች ስትሄድ መሰለኝ አይታዩም…..ግቢ ውስጥ ማንም አይታይም .እቤት ውስጥ ግን የእኔዋን ትርሲትን ጨምሮ ቢያንስ 3 ሴቶች እንዳሉ አውቃለው፡፡ግን አይታዩንም….
ድንገት እናቴ ሰትመጣ ከነበረችበት የደበተ ስሜት እንደመባነን ብላ ታወራኝ ጀመር‹‹…የእኔ ፀጋ ዛሬ የሚገርም ህልም ነው ያየውት…እዚህ እተቀመጥንበት ቦታ ላይ ትልቅ በጥላው ግቢውን የሚያለብስ ዋርካ በቅሎ አየው… ብታይ ሚገርም ዛፍ ነው…እንዴ …?ከየት የመጣ ዛፍ ነው……?ማን ተከለው…..…? መች አደገ ……?ተገርሜ ጠይቃለው ፡፡ሌላ ሰው አጠገቤ ኖሮ ሳይሆን እንዲሁ ከመገረሜ ብዛት ከራሴ ጋር ነበር እያወራው የነበረው..ግን ሌላ የሚያስደምም ነገር አጋጠመኝ..አንድ ፍም የመሰለ ቀይ አዛውንት ..አንደ በረዶ የነጣ ትከሻው ላይ የተንዛፈፈ ሉጫ ፁጉር ያለው መልከ መልካም ብርሀናማ ዓይኖች ያሉት አዛውንት ከላይ ሰማዩን ሰንጥቆ እየተምዘገዘገ መጣና በሁለት ሜትር እርቀት ፊቴ ቆመ‹‹ልጄ ለጥያቄሽ መልስ ልሰጥሽ ነው የመጣውት››
ለየትኛው ጥያቄዬ››ስል መልሼ ጠየቅኩት
‹‹ስለዚሁ ግዙፍ ዛፍ እየጠየቅሽ ስላለው ጥያቄ››
‹‹እሺ እንዴት ሆነ …?ይሄ ዛፍ ከየት መጣ..…?››
‹‹አይ ድሮም የነበረ እኮ ነው… እራስሽ ነሽ ወጣት እያለሽ የተከልሽው…. ግን እስከዛሬ በስህተት ወደ ታች ነበር ሲያድግ የነበረው..››
እና እንዴት በአንዴ ይሄን አክሎ ላየው ቻልኩ…?››
‹‹አሁን የመስተካከያው ጊዜ ስለደረሰ ነው..አየሽ የተጣመመው የሚቃናበት… የተደፋው ሚታፈስበት…የወደቀው የሚነሳበት…የተሰበረው ሚጠገንበት የሄደው ሚመለስበት…የጠፋው ሚገኝበት…የጨለመው ሚነጋበት ለሁሉም የራሱ የሆነ ጊዜ አለው…መሆን የሚገባው ነገር ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ መሆኑ የማይቀር ነው…ካልሆነ ደግሞ መጀመሪያውኑ መሆን የማይገባው ነገር ይሆናል…. ስለዚህም ይሄም ዛፍ ወደ ታች ማደጉንና መስፋፋቱን አቁሞ እንዲህ ከመሬት በላይ ግርማ ሞገሱን ጠብቆ ለመታየተ አሁን ጊዜው ስለሆነ ነው ያስተካከልነው…አሁን አንቺም ልጆችሽም በጥላው ትጠለላላችሁ….በውበቱ ትደመማላችሁ….እላዩ ላይ ጎጆቸውን ቀልሰው ዝማሬ በሚዘምሩ አዕዋፋት ትዝናናላችሁ…እላዩ ላይም የንብ ቀፎ ሰቅላችሁ ወለላ የማር እሼት እየቆረጣችሁ ልትመገቡም ትችላላችሁ›› ብሎ አብራራልኝና እንደ ደመና እየተበታተነ ቅርፁን በማጣት ከአየሩ ጋር ተዋሀደ…እና ነቅቼም እንኳን ሽበታሙ አዛውንት ሆነ ግዙፍ ዋርካ ከአዕምሮዬ ሊጠፋ አልቻሉም..እና የዚህ ህልም ፍቺ ጥሩ ይሁን መጥፎ አላውቅም …ግን አንድ ታአምር በቤታችን የሚፈጠር ይመስለኛል..አዎ በዛ እርግጠኛ…..
ሀርሜ- ንግግሯን ሳትጨርስ የውጩ በራፍ ተንኳኳ… ሀርሜ ወሬዋን አቆርጣ እንደመባነን አለችና በዝግታ ከተቀመጠችበት ወንበር በመነሳት ቆመች….እግሯን አፍታታች….ሳስበው የደነዘዛት ይመሰለኛል፡፡በእርጋታ ወደ በራፉ ስትሄድ እያየዋት ነው ..ደረሰችና የወጩን በራፍ ከፈተች…..ገርበብ አድርጋ በልኩ…. ወዲያው ግን ሊገመት በማይችል የድንጋጤ ይሁን የፍራቻ ስሜት ድምጽ አውጥታ በመጮህ መልሳ በራፉን ደረገመችው…አይኖቾ በድንጋጤ ተበለቀጡ… እንዴ ምን ነካት..?እብድ ነው እንዴ በራፉን ያንኳኳው?››እራሴን ጠየቅኩ..
ሀርሜ በራፉን ቀርቅራ ተደግፋዋለች .. በድንጋጤ እየተንቀተቀጠች ያለችም ይመስለኛል….እጆቾን አፏ ላይ ከድናለች….አሁንም በራፉ መንኳኳቱን ቀጠለ…..እናቴ የሚያንኳኳው ሰው በራፉን ገንጥሎት ወደ ውስጥ እንዳይገባባት የፈራች ይመስል በራፍን መልሳ ዘግታ እላው ላይ በሙሉ ኃይሏ በመደገፍ ወጥራ ይዘዋለች..በዚህ ጊዜ ከኃላ ድምጽ ተሰማኝ…‹‹እንዴ እማ ማነው?››የሮሚ ድምጽ ነው፡፡….ከቤት ወጥታ እናቴ ወዳለችበት እየተጠጋች…
‹‹ እማ ምን ሆንሽ..?ማን ነው የሚያንኳኳው…?.››ከሀርሜ መልስ የለም…
‹‹ብቻ ፃረ-ሞት ያየ ሰው መስላለች››….ከውጭ ማንኳኳቱ ቀጥሎል…
ሮሚ ሀርሜ ያለችበት ቦታ ደረሰች‹‹እማ !!እስቲ ዞር በይ… ማን ነው…?››
‹‹ተይ ልጄ ተይ….ማንም አይደለ››በራፍ እንዳይከፈት አጥብቃ ተከላከለች
‹‹እንዴ እየተንኳኳ ?እይሰማሽም .. …?››
‹‹ተይ ይቅርብሽ ልጄ››ተማፀነቻት
ሮሚ ለደቂቃዎች የእናቷን ጤንነት የተጠረጠረች ይመስለኛል .አዎ አስተያቷ እንደዛ ነው ሚመስለው..እናቴን አፍጥጣ አየቻትና እንደምንም ጎትታ ከበራፍ ላይ ዞር አደርጋት…. በራፉን በከፊል ከፈተችው
ጤነኛ ሰው ነው የሚታየኝ …. ፀዳ ያለ ልብስ የለበሰ…የተመቸው አይነት ሰው
እሮማን የከፈተችውን በር በአንድ እጆ እንደያዘች ‹‹አቤት ምን ነበር…?››ብላ ፊት ለፊቷ ያለውን ሰው ጠየቀችው. ሰውዬው እንደእናቴ ፈዟል..ድንገት የህይወቱ ህልም የሆነችውን ልጅ መንገድ ላይ አይቶ በፍቅር እንደነሆለለ እርብትብት ጓረምሳ ሮሚ ላይ አፍጥጦባታል…
‹‹አቤት !!!ማንን ፈልገው ነው…?››ደግማ ጠየቀችው
‹‹እርግቤ…በጣም አድ…ገ….ሻል..ትልቅ ልጅ ሆነሻል››
‹‹ዋት….እርግቤ…››በታላቅ መገረም መልሳ ጠየቀችው
በዚህ ጊዜ የእኔም ሰውነት መንቀጥቀጥ ጀመረ..አዎ ሮሚን እርግቤ ብሎ ይጠራት የነበረው አንድ ሰው ነው..ሮሚን ብቻ ሳይሆን ፌናንንም በተመሳሳይ ስም…ሁለቱ አንድ ላይ ሲሆኑ ደግሞ እርግቦቼ ይላቸው ነበር…. ይሄንን ታሪክ በተደጋጋሚ ጊዜ ሰምቼዋለው ከእናቴ ሰምቼዋለው‹‹..ሰውዬው መጣ ማለት ነው……?አሁን የእናቴ የድንዛዜ ምክንያት በግልጽ ፍንትው ብሎ ገባኝ….
‹‹አባዬ..››ሮማን እጆቾን በድንግጤ ጭንቅላቷ ላይ ጭና…
‹‹አዎ አባትሽ ነኝ..ልጄ››ዘላ ተጠመጠመችበት…ወገቧን አቅፎ በአየር ላይ አሽከረከራት…ፀጉሯ በንፋሱ ብትንትን አለ ከውጭ ለሚታዘባቸው በፊልም ላይ ደገግመን የምናያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች ላይ የሚሰሩ ፍቅረኛሞች ይመስላሉ..አንገቷ ስር ገብቶ ሲስማት ይታየኛል..አዎ እያለቀሰም መሰለኝ..እሷም እያለቀሰች ነው..እናቴ ደንዝዛ ከቆመችበት ቦታ በደመነፍስ ለቃ ወደእኔ መራመድ ጀመረች …አዎ ፊቷ ግርጥት ብሏል..ሰው እንዴት በደቂቃ እንዲህ ቅይርይር ይላል…?፡፡ሰሬ ደረሰችና ቅድም ተቀምጣበት የነበረበት ወንበር ላይ ተቀመጠችና በጣም በደከመ እና በሰነፈ ድምፅ ‹‹አባትህ መጥቷል›› በአለችኝ
አይኔን በንዴት እና በጥላቻ አጉረጠረጥኩት….ሮሚ ገረመችኝ..ልክ ለአንድ ሳምንተ ለቫኬሽን
👍10
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-ዘጠኝ

:
:
ደራሲ- ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ሳምንት ቢያልፈውም የተአምራዊው ቀን አንጎበር ዛሬም ድረስ ከቤታችን
አልጠፋም…አብላጫውን ደስታ ነው..ሳቅና ፈንጠዝያ ነው..ይሔ ደስታ ደግሞ
በእኔ አካል ላይ የታየ አዲስ ለውጥን ተከትሎ የተከሰተ ነው..የቀኝ እጄ
ለአእምሮዬ መታዘዙን ተከትሎ…ይሄ ማለት ምን ያህል ከባድና ሊታመን
የማይችል ተአምራዊ ክስተት መሆኑን የምናውቀው እኔና ቤተሰቦቼ ብቻ ነን…
መከራውን ለሃያ ምናመምን አመት ተሸክመን የኖርነው፡፡ደግሞ ሌላም
አስተውለን የማናውቀው ግን ቀን በቀን ኢምንት ያህል ለውጥ እያሳየ የነበረ
የአካሌ ክፍል እንዳለ መረዳት ችያለው..የአንገቴ ነገር..፡፡አንገቴ እንደ ድሮው ወደ
ዞረበት ክንብል ብሎ የሚደፋ አቅመቢስ አይደለም…ከአንዱ አቅጣጫ ወደ
ሌላው አቅጣጫ ለመዞር የሚፈጅበት የጊዜ ስሌት በ50 ፐርሰንት ማፍጠን
ችሏል፡፡ ይሄም ድንቅ ነው…..ዘንድሮ እኔን በተመለከተ መንገዶች ሁሉ ወደ ተስፋ እያመሩ
ያሉ ይመስለኛል..ደግሞም እንደዛ ነው….፡፡
ሌላው ከደስታችን ጋር የተቀየጠ የሆነ የታፈነ ጭንቀትም በቤታችን አለ …
ሰውዬውን በተመለከተ አሁንም ደጅ እንደፀና ነው…፡፡ልጆቹን በጠቅላላ ማሳመን
እና ከጎኑ ማሰለፍ ችሏል..፡፡ለዛውም በቀላሉ..፡፡ሌላው ይቅረ መፈጠሩንም
የማታውቀው ትንሻ ማክዳ እንኳን እላዩ ላይ ስትንጠለጠል ሳይ በግርምት አፌን
እይዛለው…እስከአሁን እኔና እናቴን ነው ያልቻለው…እናቴ አንዴ የሰጠችውን ቃል
ልትቀይር ፍቃደኛ አይደለችም…ጉዳዩን ወደ እኔ መርታዋለች..እኔ ደግሞ አይኑን
ሳይ እራሱ ያቅለሸልሸኛል…ሲሸማቀቅ ሳይ ውስጤ ይረካል….
አሁን መኝታ ቤቴ ተኝቼ ስለዚሁ ጉዳይ እያሰላሰልኩ ሳለው በሩ በስሱ ተንኳኳና
ተከፈተ‹‹ይህቺ እብድ ልትሸውደኝ ነው ..ብዬ አንገቴን ወደ በሩ አዞርኩ..ትርሲት
መስላኝ ነበር፣ግን አይደለችም ፤ወንድሜ ነው
‹‹…ይቅርታ አረበሽኩህም አይደል?››እያለ ወደ እኔ መጣና አልጋው ጠርዝ ላይ
ተቀመጠ…….
‹‹ወንድሜ አንድ ነገር ላወራህ ፈልጌ ነው…››አይኔን በማርገብገብ እንዲቀጥል
አበረታታውት
‹‹ስለአባቴ ነው ላወራህ….››ንግግሩን ሳይጨርስ እጄን አፉ ላይ ከደንኩበት…
በዚህ ርዕስ ላይ ከማንም ጋር ማውራት እንደማልፈልግ በደንብ እንዲያውቅ
ስለፈለግኩ
እሱም እጄን ከአፉ ላይ አንስቶ ወደ ቦታው በመመለስ ንግግሩን
ቀጠለ‹‹..ወንድሜ የምትወደኝ ከሆነ የግድ ልታዳምጠኝ ይገባል..እምልልሀለው
ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ነው የማናግርህ..የምወድህ ታላቅ ወንድሜ ነህ ስለዚህ
ባትወደውም እንድታዳምጠኝ እፈልጋለው..ውስጤ ያለውን ስሜት ለመጨረሻ
ጊዜ አውጥቼ ልነግርህ እፈልጋለው…ምንም እንድታደርግ አልፈልግም
እንድታዳምጠኝ ብቻ ነው የምፈልገው……››
ምንም ማድረግ አልቻልኩም …ይሄንን ተማፅኖውን አሻፈረኝ ልለው አልችልም
ስለዚህ ቢጓመዝዘኝም ተረጋግቼ ላዳምጠው ወሰንኩ …..
‹‹እሺ ሳለፈቀድክልኝ አመሰግናለው..ፀግሽ ምን መሰለህ…እርግጥ አንተ ምን
እንደሚሰማህ አውቃለው …በእሱ ምክንያት ከሁላችንም በላይ ያንተ ልብ ነው
የቆሰለው…በአንተ ምክንያት ነው ፍቅሩንም ቤቱንም ልጆቹንም ጥሎ
የሄደው…..ይሄ ደግሞ እሱን ለመጥላት እሱን ይቅር ላለማለት ከበቂ በላይ
ምክንያት ነው..ግን ምን መሰለህ አሁን ስለእሱ እኔን ብትጠይቀኝ ምንም እንኳን
በዛን ወቅት የሰራውን ታሪክ ሳስታውስ በጣም ብረበሽና ቅሬታ የሚሰማኝ
ቢሆንም በጥላቻ የተጋረደ እይታ ግን የለኝም፡፡አውለው…ይሄ ቤተሰብ በጣም
ብዙ መከራ አሳልፎል…በተለይ እናታችን ይሄን ሁሉ ልጅ ለብቻዋ አባትም እናትም
ሆነ አሳድጋለች…ግን ቢሆንም ያው ጉድለቱን ሙሉ በሙሉ ልታጠፋው አልቻለችም…
አንዳንዴ አባት እና እናት ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ግንኑነት ከሆነ ነገር ጋር
የተገናኘ አይመስለኝም…ማለቴ ከእነሱ ጥሩነት እና መጥፎነት ጋር… ከእነሱ
ሀብታም መሆንና ድህነት ጋር….ከእነሱ የትምህርት ደረጃቸው ጋር አዎ ከእነዚህ
ሁሉ ነገር ጋር የተገናኘ አይደለም..ዝም ብሎ ምከንያት አልባ ነው… ተፈጥሮዊው
ብቻ…በደም ትስስር እና በነፍስ ቁርኝት የተገመደ ዝም ብለህ የምትቀበለው
ሚስጥራዊ ጥምረት ነው..ለዛ ነው ሁለችንም ሳናስበው በዚህ ፍጥነት
የተቀበልነው…በዚህ ፍጥነት ይቅር ያልነው..፡፡
ካንተ በስተቀር ሁላችንም ጋር ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነው..እርግጥ የእኛን ካንተ
ጋር ማወዳደራችን አይደለም …ግን ያው አባትነቱ ለሁላችንም እኩል ነው…አየህ
አሁን እሱን ይቅር ብለነው ወደ ህይወታችን እንዲቀላቀል ካልፈቀድንለት
ወደፊትም ባለው ሙሉ ህይወታችን ስለአባት ያለን ትዝታ ባዶና ጥቁር ብቻ
ሊሆን ነው…ለልጆቻችንስ ምን እንነግራቸዋለን….?ስለአባታችን ሲጠይቁን
ምንም የምንላቸው ነገር አይኖረንም..ይሄ ቀላል ይመስልሀል ?›››
ቀኝ እጅን ከግራ ወደ ቀኝ በማወናጨፍ ፈጽሞ ይቅር ልለው እንደማልችል ደግሜ
አስረዳውት
እሱም የማሳመን ጥረቱን ቀጠለ‹‹አይ እኔ ምንም እንድትለኝ አልፈልግም….
ስለውሳኔህ እንድትነግረኝ አልፈልግም…እኔ እንዳልኩህ የውስጤን ነግሬህ ብቻ
መሄድ ነው የምፈልገው…..
አየህ አብዛኛውን ነገር ነግሬሀለው ግን አንድ ነገር ይቀረኛል..እናቴን በተመለከተ
..እናቴ እሱ ላይ እርግጠኛ ሁን ጥላቻ የላትም..ያን ያህል ቢበድላትም ግን
አሁንም ይቅር ልትለው ትፈልጋለች..እንደውም በውስጧ ድሮ ገና ድሮ ይቅር
ያለችው ይመስለኛል..አሁን እሷ ላይ የሚታው ንዴት ነው…ከፍተኛ ንዴት…አየህ
ቅድም እንደነገርኩህ ከሁላችንም በላይ አንተን ጎድተቶሀል አቁስሎሀል..ግን ያ
እውነት የሚሆነው ከእኛ ከልጆቹ ጋር ሲነፃጸር ብቻ ነው..ከእናታችን ጋር ሲነፃፀር
ግን በአንተ ላይ ያደረሰው በደል ትንሽ ነው…አየህ ፍቅሯን ነው የነጠቃት… አራት
ልጆቾን ነው ብቻዋን እንድታሳድግ በትኖባት የሄደው..ያለ ባል ነው ይሄን ሁሉ
አመት እንድትኖር የፈረደባት…ሌላ ወንድ ላፍቅር ብትል እንኳን አትችልም.. ማን
ነው አራት ልጆች ያሏትን ሴት ሚስቴ ብሎ የሚቀበለው..
..አልፎ አልፎ ነበር የእሱ አለመኖር በውስጣችን የፈጠረው ሽንቁር
የሚታወቀን፣ምክንያም እሷ ለደስታችን በየእለቱ ትፈለምልን ነበር …ለሳቃችን
በየደቂቃው ትዋደቅልን ነበር…ሀዘኑን ሁሉ ለብቻዋ ውጣ ወደ እኛ እንዳይደርስ
ግድግዳ ሆና ትከላከልልን ነበር….ችግር ወደቤታችን እንዳይገባ በፅናት
ስትታገል ነው የኖረችው…
እሷ ግን ይሄንን ሁሉ አመት በሀዘን እንደተለበለበች ነበር….ግማሽ እድሜዋን
በፍቅር ክህደት የተጎዳ ልቧን እየመረቀዘባት ..ከምርቅዙ የሚመነጨውን መግል
እየጠረገችና እያስታመመች የኖረች ሚስኪን ሴት ነች..ለልጆቾ ስትል መስዋዕት
የሆነች ሴት …በተለይ ለአንተ ስትል መስዋዕት የሆነች ዕንቁ እናት ነች..እና አሁን
እኔ አንተን ብሆን ለእሷ ስል መስዋዕት እሆን ነበር….›› ግራ ጋባኝ አባባሉ እንዴት ነው?እንዴትስ ነው ለእናቴ ስል መስዋዕት ልሆን
የምችለው..?እርግጥ ነው ለእናቴ ጥቂት ደስታ ማምጣት ከቻልኩ ህይወቴን
እንኳን በመስጠት መስዋዕት ለመሆን አላቅማማም ምክንያም ይህ ህይወቴ
ይሄን ሁለ ዘመን በዚህ ምድር የኖረው በእናቴ ብርታትና ጥንካሬ ነው፣..ሀርሜ
የህልውናዬ መሰረት ሁሉ ነገሬ ነች…
ወንድሜ ቀጥሏል‹‹አየህ ከልብህ እንኳዋን ባይሆን አባትህን ይቅር ብትለው
ለእናታችን ትልቅ ነገር ይመስለኛል አየህ አንተ ይቅር ማለትህን ካወቀች እሷም
ይቅር ማለት አይከብዳትም ያንን ደግሞ እንደምታደርግ በቃሏ
አረጋግጣልናለች አንተ ከእሱ ጋር መቀራረብ ብትጀምር እሷም ሁሉን ነገር ረስታ
እንደአዲስ ትቀርበዋለች..እና ደግሞ በሂደት አንተ ከእሱ ጋር አንድ ላይ መኖር ብትፈቅድ
👍31
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-አስር

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

....ትርሲት ‹‹ሰውዬውን ማናገር ፈልጋለው ››የምትለዋን ወረቀት እንደሰጠዋትን
ወረቀቱን አንጠልጥላ ከመኘታ ቤታችን እየጮኸች ስትወጣ እኔ ግን በውስጤ
መራገም ጀምሬ ነበር..ምን አለ አሁን የሆነ ተአምር ቢፈጠር …ምን አለ አሁን
ይሄንን ሰውዬ ፊቴ ከመቀረብ በፊት እነዛ ማሰር የሚወዱት ሰዎች አንጠልጥለው
ማአከላዊ ወይም ቂሊንጦ ቢወረውሩልኝ፡፡እወነቴን ነው እዛ ባህር ማዶ ሆኖ
ከስልጣን ልቀቁ..ሀገር አትዝረፉ… ህዝብ አታስለቅሱ እያለ በየሶሻል ሚዲያው
ሲዘበዝብ አይደለ የኖረው… እርግጥ አውቃለው በየፌስብኩ ላይ በፅሁፍ
ከመዋጋት ያለፈ ሌላ መሬት የወረደ የትግል ታሪክ እንደሌለው አውቃለው..ይሄ
ታዲያ ሀሳብን በነጻ የመግለፅ ህገ -መንግስታዊ መብቱ ነው ልትሉኝ
ትችላላችሁ…ግን እኮ አሁን እስር ቤቱን በከፊል የሞሉት እኮ ይሄንን ህገ
መንግስታዊ መብታቸውን ሲጠቀሙ የነበሩ ግን በፀረ-ሽብር ህጉ የተጠለፍ
ናቸው ..እና በነካ እጃቸው ይሄን ሰውዬም ቢጠልፉልኝ እፎይ እል አልነበር…?
ለማንኛውም ሀሳቤን ሳልቋጭ ነው መአት የእግር ኮቴ ከወደ ሳሎን አካባቢ ወደ
እኔ ሲርመሰመስ የተሰማኝ..አንዷ በአንዷ ላይ እየተተረማመሱ ወደ እኔ ክፍል
ገቡና ወረሩኝ …ሮሚ.. ማክዳ..ትርሲት ‹‹‹ፀግሽ አሪፍ ውሳኔ ነው…ደስ ብሎናል…
>>አንዷ በቀኝ አንዷ በግራ አልጋው ላይ በመውጣት ጉንጬን አጣብቀው
ይሱሙኝ ጀመር ….ሁለቱ እህቶቼ ሲስሙኝ ፊት ለፊቴ የቆመችው ትርሲት
በመጎምዠት የገዛ ከንፈሩን በስሜት ስትስም ሾፍኮት ...... እናም ታዘብኮትና
ፈገግ አልኩ ‹‹ይሄ ጉድ ደስታ እንደአዲስ አስደመመኝ .… በቃ ይሄ ሰውዬ የቤቱን
ልብ ሁሉ በቀላሉ ተቆጣጥሮታል ማለት ነው…ግን እሱ የሰራውን በደል የሰራ
አንድ ጭርቁስቁስ ያለ አባት ሆኖ ከደንበጫ ወይም ከአሶሳ መጥቶ ቢሆን
እንዲህ ሰፍ ብለው ይቀበሉታል……?እኔ እንጃ ጥርጣሬ አለኝ ..!!አዎ አሁን አባት
ብቻ ስለሆነም አይመስለኝም ዲያስፖራ ነው… ወደ ቤታችን ሲመጣ እራሱ ይዞት
የሚመጣት መሃና ታፈዛለች፡፡
ከግርግሩ ቡኃላ ሁሉም ጥለውኝ ወጡ…በቤቱ ተተረማምሶል ..… በቃ ሰርግ
በሉት የሰርግ ዝግጅት…ትርሲት ወደ መኝታ ክፍል መጣችና ‹‹በል ተነስ ሻወር
እንወሰድ›› ብላኝ እየረዳችኝ ወደ ዊልቸሩ አሸጋገርኩ..አሁን ከአልጋዬ ወደ
ዊልቸሬ መሸጋገር በዙም ከባድ አይደለም..ሁለቱንም እጆቼን በትክክል
መጠቀም ስለጀመርኩ ጥቂት እገዛ ብቻ ነው የምፈልገው ..ደገፋችኝ እና
ከዊልቸሬ ወደ ሻውሩ መቀመጫ አጋላበጠችኝ…እንደገባን ዘጋችው ….
እንደዘጋቻም ቀድማ የራሷን ልብስ ውልቅልቅ አደረገች ፣..ሳቅኩባት ‹‹ምን
ያስቅሀል..…?ምን ሚያስቅ ነገር አለ …?ይሄን የመሰለ ውብ ገላ ያስጎመዣል
እንጂ ምኑ ያስቃል…?›› አለችኝ ሌጣ መቀመጫዋን ፊቴ እያገላበጠች…
እኔ ግን መሳቄን አላቆምኩም …የሳቁኩት እኔን ልጠብህ ብላ ወስዳ ተስገብግባ
የራሷን ልብስ ቀድማ ማውለቋ ነው…. እንጂማ ይሄንን ሰውነት አሁን
ለምጄዋለው… የገዛ የራሴ ሰውነት እስኪመስለኝ እያንዳንዷን ጉብታ፣እያንዳንዷን
ሸለቆ ..እያንዳንዷን ሽፋታ… እያንዳንዷን ጭረት አውቃላው..እንደበቱ የእሷን
እገዛም ሳልፈልግ ከላይ ለብሼ የነበረውን ቲሸርት አወለቅኩት….‹‹ውይ ያንተን
ለካ አለወለቅኩልህም ››አለችን ወደ እኔ ተጠግታ ሱሬዬን እንዳወልቅ
አገዘቺኝ፣አሁን ሁለታችንም ራቁታችንን ነን፡፡ከዊልቸሩ ወደ ሻወሩ አስጠጋቺኝ
‹‹ቆይ መጀመሪያ ከመታጠባችን በፊት ይሄንን የአማዞን ደን የመሰለውን
ጭገርህን ልመንጥርልህ …አለችና የሳሙና ማስቀመጨው ላይ አስቀምጣ
የነበርውን መለጫ ይዛ ፊት ለፊቴ በርከክ አለችና እግሬን ወዲና ወዲያ ከፍታ
ጭኔ መካከል ገባች..እኔም በሁለት እጆቼ ጭኖቾን ፈለቀቅኩና ሸለቆዋን
የከበበውን ጭገር ጨምድጄ በመያዝ እስጮህኮት..‹‹ስለሰው ታወሪያለሽ
የራስሽን እስቲ እይው›› ማለቴ ነው
‹‹አንተ አሳመመምከኝ እኮ… በጣም ባልገሀል ››እያለች ከእጆቼ አላቀቀችና
..ያለችውን ደን በጥንቃቄ መነጠረችው…ወደ ራሷ ስትሸጋገር ጎተትኩና
ተቀበልኮት …..ፊቴ እንድትቆም አድርጌ ልክ ከበድን ድንጋይ ውስጥ ምርጥ
ምስል ጠርቦ እንደሚያወጣ አርቲስት እኔም በፅሞና እና በጥንቃቄ
አፀዳውላት…. ለዛውም ጥበባዊ በሆነ ሁኔታ በልብ ቅርፅ ….እንዴት
እንደምወዳት ለመግለፅ የተጠቀምኩበት ነው…ይህ ደግሞ እንደገመትኩት
እሷንም በጣም ነው ያስደሰታት….ከመደሰቷ የተነሳ የብለቷን ምስል ወዲያውኑ
ነበር በሞባያሏ በማንሳት መልሳ ስታየው ነበረው……ብቻ ከዛ ሻወር ቤት
ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ ነው የወሰደብን….ከዛም ወደ መኝታ ቤታችን
መልሳኝ ዝንጥ ብዬ እንድለብስ አደረገችና ወደ ሳሎን ወሰደችኝ፡፡
የተለመደው ሶፋ ላይ ተመቻችቼ ጋደም አልኩ… ሳሎኑ በምግብ ሽታ ታውዷል፡፡
በራፉ ጥግ ያለ አንድ ገዘፍ ያለ ጠረጰዛ ላይ አስራ ምናምን አይነት ወጣ ወጥ
የያዙ ሰሀኖች ይታየኛል….ሰርግ ያለበት ቤት ነው ያስመሰሉት..ይሄን ሁሉ ምግብ
በዚህ አጭር ጊዜ እንዴት አድርገው ሰሩት በጣም የገረመኝ ነገር ነበር…ደግሞ
አዘናነጣቸው..እሱ ገዝቶላቸው ይሆን …አዳዲስ አይቼ የማላውቀው ልብስ ነው
የለበሱት ከእናቴ በስተቀር..የእኔዋ ትርሲትንም ጭምር፡፡ስድስት ሰዓት ሲሆን
የሳሎኑ በር ተንኳኳ..ሁሉም ለመክፈት ስትራኮት በቆሪጥና በትዝብት እያዋቸው
ነው…ግን ትንhን ማክዳ የቀደማት አልነበረም..ከፍታ መጀመሪያ ያየችው ታናሽ
ወንድሜን ነው …..እሱን ተከትሎ ሰውዬው አለ:: ተጠመጠመችበት ወደ ላይ
አንጠልጥሎ ጉንጮቾን አገላብጦ ከሳማት ቡኃላ መልሶ አስቀመጣት..እንግዲህ
ለእሷ የአባቷንም ቦታ የአያትነቱንም ድርሻ ለመወጣት እየሞከረ መሆኑ ነው፡፡
ከሁሉንም ጋር በመተቃቀፍ ሰላምታ ከተለዋወጠ ቡኃላ እኔና እናቴ ስንቀረው
መሀል ሰሎን ላይ ተገትሮ ቆመ ቁጭ በል ያለውም የለ እሱም ምን ማድረግ
እንዳለበት ግራ የገባው ይመስለኛል፡፡እናቴም በተቀመጠችበት አንዴ እሱን
ደግሞ እኔን እያፈራረቀች ታየኛለች..እህቶቼም ሆኑ ወንድሜ ወደ መሬት
እንዳቀረቀሩ ናቸው…
እንደምንም እግሩን የመጎተት ያህል እያንቀሳቀሰ ወደ እኔ ተጠጋ..በደንብ ተጠጋ
..ከዛ ወለል ላይ በርከክ ብሎ እጁን ወደ ሰውነቴ መዘርጋት ጀምሮ መሀከል ላይ
አቆመው…. የበቀደምለታው ትዕይንት ትዝ ያለው ይመስለኛል..እሱ ብቻ ሳይሆን
እናቴም በተቀመጠችበት ስትሸማቀቅ አየዋትና ሰውዬውን ለማበረታታት ፊቴን
በተጠና ፈገግታ አደመቅኩት…ያልጠበቀው ነገር ነበርና እጁን እጄ ላይ አሳርፎ
ጭንቅላቱን ደረቴ ላይ ደፍቶ
‹‹ልጄ እባክህ ይቅር በለኝ…በቃ በእናት እማፀንሀለው..በእህቶችህና
በወንድምህ እማፀንሀለው..ይቅር በለኝ….፡››ያልቀባጠረው ነገር
የለም….ከንግግሩም በተጨማሪ ከአይኖቹ የሚፈሱት የእንባ እርጠበት ለደረቴ
ደረሰው..ግን አላሰሳዘነኝም..አሁንም አንጀቴ ለእሱ እንደደነደነ ነው…ግን ቢሆንም
ሰላም ለመፍጠር ወስኜያለው እጄን ወደ ግንባሩ ላኩና ቀና አደረግኩት…
ጭንቅላቴን በማነቃነቅ ይቅር እንዳልኩት ሳረጋግጥለት ቤቱ በእህቶቼ የደስታ
እልልታ ተናጋ … ሁሉም እርስ በእርስ መተቃቀፍ ጀመረ››
ሰውዬውም እጆቼን እየሳመ ግንባሬን እየሳመ ‹አመሰግናለው
ልጄ..አመሰግናለው››እያለ ከለበት ተነሳና አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ እናቴ
ተስፈነጠረ..እግሯ ስር ከመደፋቱ በፊት ቀልጠፍ ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና
በአየር ላይ ቀለበችው ተጠመጠመባት ….ተጠመጠመችበት..በቃ ከዚህ
በላይ ያለውን ትዕይንት እናቴን መታዘብ ስለሚሆንብኝ አልነግራችሁም ….

ከሳምንት ቡኋላ
👍9
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል- #አስራ_አንድ #የመጨረሻ_ክፍል

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ሁሉ ነገር በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ተቀያየረ …..በቤተሰቡ ውሳኔ ትርሲትን
በቋሚነት እናቴን ደግሞ በተመላላሽነት አስከትዬ በአባቴ ወደተዘጋጀልኝ መኖሪያ
ቤት ገብቼያለው…አያችሁ ሰውዬው ማለት ትቼ አባቴ እያልኩኝ ነው…ያ ማለት እኔም እየተቀየርኩ ሳይሆን አይቀርም…? በቀላል ሂሳብ የእኔንም ልብ
እየተቆጣጠረው ነው…የእናቴንማ ቆየ …መቀጣጠር፤ መገባበዝ፤ እንደ አዲስ
ፍቅረኛሞች መጎነታተል ጀምረዋል…እና በቅርብ የድሮ ፍቅራቸው ያገረሻባቸዋል
ብዬ በደንብ አሰባለው….
አባቴ ያዘጋጀልኝ ቤት ሆኜ አባቴ ባዘጋጀልኝ የህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ
ሙከራው በከፍተኛ ጥረት እየተከናወነ ነው ..የመጣው ሽማግሌ የፈረንጅ
ዶክተር በሳምንት ሁለት ቀን ወደ ሆስፒታል ወስዶኝ ከሌሎች ዶክተሮች ጋር
በመሆን በተለያዩ ዘመን አመጣሽ የህክምና ማሽኖች በመታገዝ እንድመረመር
ያደርገኛል…ያው ይመራመሩብኛል ማለት ይቀላል..ወጣቷም ቴራፒስት በልዩ
እንክብካቤ እና ጥንቃቄ ስራዋን እየሰራች ቢሆንም ከትርሲት ግን ይሁንታን
ሳላላገኘች የእሷን ማመናጨቅና ግልምጫ አማሯታል…ቢሆንም ተስፋ
አልቆረጠችም….ይሄም ፍሬ እንደሚያፈራ ፍንጭ እያሳየ ነው..የእግሮቼ ጣቶች
ተራ በተራ መንቀሳቀስ ጀምረዋል…
ዛሬ እማዬም ሆነ ትርሲት አብረውኝ ናቸው …ጊዜው መሽቷል …..ተከታታይ ፊልም
ስናይ ስለቆየን ሳናስበው ነው አምስት ሰዓት የሆነው..እናም ሁላችንም ተዳክመናል…
‹‹በሉ ተነሱ እንተኛ ››አለች እናቴ ..ትርሲት በፊቱኑም እናቴ እንደዛ እስክትል
እየጠበቀች ያለ ይመስል ቶሎ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ጋደም ብዬበት
ከነበረው ሶፋ ወደ ዊልቸሬ አዘዋወረቺኝና እየገፋች ወደ መኝታችን አመራን …
እናቴም ከተቀመጠችበት ተነስታ ከኃላ ስትከተለን ይሰማኛል…ከዛ ሌለኛው
መኝታ ክፍል ውስጥ ገባች፡፡ እኔና ትርሲትም መኝታ ቤታችን እንደገባን
አወላልቀንና ተቃቅፈን ለመተኛት የአስር ደቂቃ ጊዜም አላባከንም…እኔ የምጠቀምበት መኝታ ክፍል በጣም ሰፊና ሁለት አልጋ ማዶና ማዶ ሁለቱን ትይዩ ግድጋዳዎች ተጠግቶ የተዘረጋበት ነው፡፡
ሀኪሞቹ ቀኑን ሙሉ ከወዲህ ወዲያ ሲያንገላቱኝ ድክም ብሎኝ ስለነበር
ወዲያው ነው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደኝ…ብቻ ከምን ያህል ሰዓት ቡኃላ
እንደሆነ አላውቅም ኃይለኛ የበር መንኳኳት አረ ከመንኳኳትም አለፍ ያለ
የመንጎጎት አይነት ድምጽ ነበር ከእንቅልፌ ያባነነኝ….አይኔን ስገልጥ ትርሲትም
በድንጋጤ እና በመበርገግ ‹‹ማነው… ?ምንድነው ? ››እያለች በስስ ቢጃማ
የተሸፈነ ሰውነት እያምታታች ከአልጋው ዘላ ስትወርድ የመኝታ ቤታችን በራፍ
ተበርግዶ ሲከፈት ጥቁር ጭንብል የለበሱ ሁለት ወጠምሻ ሰዎች እናቴን
ከግራና..:
ከቀኝ አንጠልጥለው እየገፈታተሩ ይዘዋት ወደ ውስጥ ገቡ..ሶስተኛ
ጓደኛቸው በአንድ እጁ ሽጉጥ በአንድ እጅ ደግሞ የሚያብረቀርቅ ጩቤ ወድሮ
ይከተላቸዋል…
‹‹ እኔን እንደፈለጋችሁ ..ልጆቼን አንዳትነኩብኝ..ልጆቼ ጫፍ
እንዳትደርሱ….››እያለች ትማፀናቸዋለች ‹‹ምንድነው ምትፈልጉት …እናቴን
ልቀቋት …የፈለጋችሁትን ይዛችሁ ውጡ››ትርሲትም እየተርበተበተች መለፍለፍ
ጀመረች…..እኔ በተኛውበት ድንዝዝ እንዳልኩ ነው …የማየው ነገር በህልም
ይሁን በእውን እርግጠኛ መሆን አቃቶኛል..እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ …?
ግቢውን ሚጠብቅ ዘበኛ አለ እሱን እንዴት አለፉት….?
‹‹አትለፍልፊብን››ብሎ አንዴ በጥፊ አላሳት ትርሲትን…ፀጥ አለች….
‹‹በል እሰራት›› አለው… ሽጉጥና ጩቤ የደገነው ባዶውን ያለውን ጎደኛውን
‹‹መጀመሪያ ጎረምሳውን ባስረው አይሻለም…?››ጠየቀ ወደ እኔ እጠቆመ
‹‹ምኑን ታስረዋለህ .. ?ፈርቶ ከአልጋው ላይ መንቀሳቀስ አቅቶት በድን ሆኖ
እያየህ››መለሰለት በእኔ በማፌዝ
‹‹አረ እግዚያብሄርን ፍሩ… ልጄ መንቀሳቀስ የማይችል ዊልቸር ተጠቃሚ
ነው…››እናቴ ነች ተናጋሪዋ፡፡
‹‹አሀ እንደዛ ነው..?ስራ ቀለለልና….››አለ አንድ ሌላው እንደተባለው ከሰፊ
የጃኬት ኪሱ ውስጥ ገመድ አወጣና የትርሲትን እጆች ወደኃላ ጠምዝዞ አንድ
ላይ በማጣመር ጠፈነጋትና ከአልጋው የራስጌ ብረት ጋር አሰራት ‹‹እሷንም
ልሰራት?››ጠየቀ እናቴን እያየ..
‹‹አይ መጀመሪያ እሷኑ አፎን ክደንልኝ… አትለፍልፍብኝ ››ከአልጋው ላይ ለብሰን
የነበረውን አንሶላ መዥርጦ አወጣና በጩቤው የሚበቃውን መጠን ያህል
መጥኖ ሸረከተውና ለጓደኛው አቀበለው..
እሱም የትርሲትን አፍ በጨርቁ ጠቀጠቀና ..እናቴንም በተመሳሳይ ሁኔታ
አሰራት… በል አንተ ጠብቃቸው እኛ የሚጠቅም ዕቃ ከቤት ውስጥ እንምረጥን
በመኪናችን እንጫን …ስንጨርስ መጥተን እንነግርሀለን››ብለውት ሁለቱ
ተያይዘው ወጡ…የቀረው ጩቤውንም ሽጉጡንም በእጆቹ እያሽከረከረ የመኝታ
ቤቱን በራፍ ከውስጥ ቀረቀረና ፊት ለፊት ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጠና
ሶስታችንንም በማፈራረቅ መመልከት ጀመር..የተቀመጠበት መቀመጫ እኔ
ከተኛውበት አልጋ የሁለት ሜትር ያህል እርቀት አለው….ሰውዬው ሲታይ
ወጠምሻ እና አስፈሪ ነገር ነው..ምንም እንኳን በለበሰው ጭንብል ምክንያት ፊቱ
ባይታየኝም የሆነ ጥቁርና አሳፈሪ እንደሆነ እንዲሁ መገመት ችያለው
..ቀስ በቀስ እይታውን ከማፈራረቅ ወደ ማተኮር አሸጋገረው..አዎ ዓይኖቹን
ትርሲት ላይ እንደሰካ ፈዞ ቀረ …አዎ የሚያየው ደግሞ የተጋለጠ ገላ
..ስትንፈራገጥ ቢጃማዋ ወደ ላይ ስለተሰበሰበ የተራቆተ ጭኖን ነው…ድሮም
ለአመል ያህል ስውነቷን ይሸፍንላት የነበረውን ቢጃማ አሁን ጭረሽ ወደ ላይ
ተሰብስቦ ከውስጥ የለበሰች ሰማያዊ ፓንት እስኪታይ ድረስ ለእይታ
ተጋልጣለች…ትዝ ይለኛል አሁን የለበሰችውን ፓንትም ሆነ ቢጃማ የገዛችላት
እናቴ ነች.. ፡፡
ሶደሬ ሄደን በነበረበት ቀን …አሁን በዚህ ሰአት ይሄንን ማሰብ ምን ይሉታል …?
ሰውዬው በተቀመጠበት በመቁነጥነጥ ምራቅ እየዋጠ ነው..ምኑም
አላመረኝም..፡፡ቀስ ብሎ ተነሳና ቆመ‹‹አንቺ እንዴት አባሽ ታምሪያለሽ?››አለ የዛን
ጊዜ የሶስታችንም አይን በድንጋጤ ፈጠጠ..መላ ነገራችን በስጋት ታፈነ…
‹‹ይሄን ገላማ ጎደኛቼ እኪመጡ ዘና ልበልበት››
‹‹የፈራውት ደረሰ ..››አልኩ በልቤ አሁን እንዴት ነው ሚሆነው…?በምንስ ተዐምር
ነው ከዚህ ጉድ የምንወጣው…?እንዲህ ማፈቅራትን ሴት እንዴት ፊቴ
ይደፍራታል…?ከዛስ ብኃላ ሕይወታችን እንዴት ይቀጥላል…?ለመጀመሪያ ጊዜ
ያለውበትን ሁኔታ አምኜ መቀበል አቃተኝ….፡፡ ውስጤ በቁጣና በንዴት ከውስጥ
ይቀጣጠል ጀመረ … ሰውዬው በሀሳቡ እንደገፋበት ነው…የያዘውን ጩቤ ወንበር
ላይ እንዳስቀመጠ ሽጉጡን ብቻ በአንድ እጁ ቀስሮ ወደ ትርሲት ሄደና እጆቾን
ፈታቻው…እጆን አንጠለጠለና ወደ ሌለኛው አልጋ እየጎተተ ይዞት ሄደ …እጆቼን
እና አንገቴን እያወራጨው የሆነ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ቢሆንም እሱ ግን
ነገሬም አላለኝ..እናቴም እጆቾም አፎም ስለተለጎመ አቅመ ቢስ ሆናለች….
ትርሲትን አልጋው ላይ ዘራራትና አንደኛው እጆን የአንዱ አልጋ ጫፍ ብረት ጋር
ሌለኛውን እጆን ከሌለኛው ብረት ጫፍ ሰትሮ አሰራት… ከዛ ደግፎ ሙሉ በሙሉ
ወደ አልጋው አወጣትና ዘረራት…እሷ በታሰረችበት በፍርሀት ጉንጮቾ ቀልተው
ፊ.ቷ በእናባ እየታጠበ… በአይኖቾ ስትለማመጠውና ስትለምንው ሳይ ውስጤ
ተገለባበጠ..ምንው አምላክ ለ5 ደቂቃ በተአምሩ ጤነኛ ቢያደርገኝ…?በዚህ
ሰዓት የመፅሀፍ ቅዱሱ ሳምሶን ነው ትዝ ያለኝ… በፍቅረኛው ደሊላ ተታሎ
ኃይሉን አጥቶ በጠላቶቹ እጅ ወድቆ በነበረበት በዛ ክፉ ደቂቃ የተሰማው ስሜት
ነው አሁን እኔንም እየተተሰማኝ ያለው.
👍7
እኔም በአሁኑ ሰአት አምላክን የምለምነው ለእሱ የሰጠውን የመጨረሻ ሰከንድ ዕድል እንዲሰጠኝ ነው አሁን
እየለመንኩት ያለውት ..አንድም እንደዚህ የምወዳቸውን ሁለት ሴቶች
የማድንበትን ኃይል እንዲሰጠኝ.. ያ ካልሆነ ደግሞ እነዚህን ወንጀለኞች አጥፍቼ
የምጠፋበትን ኃይል…..ይባስ ብሎ ሰውዬው ያያዘውን ሽጉጥ ከጩቤው ጎን
ወንበሩ ላይ አስቀመጠና ልብሱን ማውለቅ ጀመረ.፡፡ጃኬቱን አወለቀ….ሸሚዙንም አወለቀ..ከዛ ሱሪውን ሊያወልቅ ቀበቶ በመፍታት ላይ ሳለ
የመኝታ ቤቱ በራፍ ተንኳኳ…
‹‹ ተመስጌን ››አልኩ… አዎ ያንኳኳት የገዛ ጎደኞቹ እንደሆኑ ባውቅም ቢያንስ
እንዲህ አይነት ፀያፍ ድርጊት እንዲሰራ አይፈቅዱለትም ..››ስል ገመትኩም
ተመኘውም….፡፡
‹‹ጨረሳችሁ እንዴ…? ››እያለ በሩን ከፈተላቸው
‹‹አዎ ጨርሰናል እንሂዲ..››
‹‹እንግዲያው ትንሽ ጠብቁኝ ይህቺን እንብጥ አንዴ ላስደስታት››
ይቃወሙታል ብዬ ስጠብቅ በተቃራኒው‹‹አይ ችግር የለም ተደሰት
እንጠብቅሀለን›› ብለው አንዴ ወደኋላ ሲመለስ..ሌለኛው‹‹.እንዴ እኛስ
አያምረንም እንዴ?››ስል በቆመበት ጠየቀው
‹‹ካመረህ ተራህን ጠብቃ››
‹‹አይ ለተራማ ሰዓት የለንም… እዚሁ ስንርመጠመጥ ፖሊስ ቢከበንስ?››
‹‹እና ታዲያ?›››
‹‹እናማ አንተ እንቡጧን እንደጀመርክ ቀጥል…እኔ አሮጌቷን ልሞክር..ጠፈፍ ያለ
እኮ ጣዕሙ ልዩ ነው››
‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው››አለው
‹‹ከዛ አዲስ መጤው ወደእናቴ መራመድ ጀመረ… ከታሰረችበት ፈታትና
እየገፈታተረ ይዟት ከመኛታ ቤት ወጣ… በራፍ ተዘጋ ፡፡
ክፍል ውስጥ ሶስታችን ቀረን…ሰውዬው ቀበቶውን መፍታት ቀጠለ…የሱሪውን
ቁልፍ ሲከፍት አየውት …የሱሪውን ዚፕ ወደ ታች ተረተረው…ምን አይነት ሲኦላዊ
ስቃይ ነው..?ከወደ ውጭ ሀርሜ እያጎራች ነው…..የማደርገው ግራ ገባኝ …
በሶስት ሜትር እርቀት ሹጉጡም ጩቤውም ይታየኛል …ሽጉጡ እጄ ቢገባ ይሄን
ሰውዬ እደፋው ነበር…አዎ ደፋዋለው…፡፡
ሰውዬው ሱሪውን ሙሉ በሙሉ አወለቀና በፓንት ብቻ ቀረ..የእናቴ ማጎራት እና
የሆነ የዕቃ መሰባበረ ድምጽ ከውጭ ይሰማኛል….በህይወቴ ሙሉ እንደዛሬው
አይነት ፈተና ውስጥ ገብቼ አላውቅም… በአሁኑ ሰዓት በህይወቴ ውስጥ
ከምንም በላይ ከራሴም በላይ ብል ማጋነን ባለሆነበት ሁኔታ የማፈቅራቸው
ሁለት ሰዎች በከፋተኛ መከራ ውስጥ ነው ያሉት… በአውሬ መንጋጋ ውስጥ
ገብተው በአስፈሪ ስል ጥርሶቹ ሊዘነጣጠሉ ነው…ስለዚህ የግድ አንድ ነገር
ማድረግ አለብኝ…ደግሞ ክፋቱ ዊልቸሬ ከእኔ ርቀት በተቃራኒው ግድግዳ
ተደግፈ ነው ያለው….፡፡ተንቀሳቀስኩ..በእጆቼ የለበስኩትን ብርድልብስ ከላዬ ላይ
ገፈፍኩት….እንደመንሳፈፍ አይነት ከወገቤ ብድግ እልኩና ቁጭ አልኩ…ከዛ
በቀኝ እጄ ቀኝ እግሬን አነሳውና ጎትቼ ወደ መሬት አወረድኩት..

ግራ እግሬን አስከተልኩት…፡፡ ከዛ አልጋውን ተደግፌ ቆምኩ …፡፡
ሰውዬው ፊቱን ወደ ፍቅሬ ትርሲት ጭን አዙሮ ፓንቱን እያወለቀ ነው…ወደ በራፉ
ድንገት ሳይ ቀይ ደም እየተንኳለለ በበራፍ የታችኛው ስንጥቅ ወደ አለንበት
ክፍል ሲገባ ተመለከትኩ… እናቴን ገድለዋት እንዳይሆን… ?ሀርሜ ኮን አጣዋት
ማለት ነው..፡፡
ከዛ ግድግዳውን በእጆቼ ተደግፌ እየተሳብኩ እንደመንሳፈፍ ብዬ ወንበሩ ጋር
ደረስኩ… ይሄ እንግዲህ በህይወቴ በራሴው ጥረት ራሴን ችዬ የተጓዝኩት
ሪከርድ የሰበረ ርቀት መሆኑ ነው.. ሽጉጡ ጋር ደረስኩ ..አነሳውትና ወደ ሰውዬው
ቀሰርኩ…እንዴት እንደሚተኮስ ባለዋውቅም ደቅኜበታለው.. ‹‹ተ.ተተ..ተተ
..››ከአንደበቴ መሽሎክ የቻለ ብቸኛው ተደጋጋሚ ፊደል ነበር….ቢሆንም
የሰውዬውን ትኩረት ለመሳብ በቂ ነበር..ዞር አለና.
.‹‹እንዴ ጎረምሳው….!!!መራመድ አትችልም አላሉም እንዴ?››እያለ ብዙም
ፍርሀት በማታይበት ሁኔታ ወደ ታች እየሳበ የነበረውን ፓንት ወደ ላይ መልሶ
በመልበስ ሙሉ በሙሉ ወደ እኔ ዞረ…..
‹‹መራመድ ትችል ነበር .. ?መቆምስ ትችል ነበር?››ጠየቀኝ በድጋሜ…
በጥቂቱም ቢሆን ያለውን ነገር ሳስብበት ግራ ተጋባው..እንዴት ነው የቆምኩት ?
እርግጥ ግድግዳውን ተደግፊያለው ቢሆንም እግሮቼ ግን መንቀሳቀስ ችለዋል…
ቀጥ ብዬም በጥንካሬ መቆም ችያለው….የእግዚያብሄር ተአምር ይሆናል?
በሰከንዶች ሽርፍራፊ ውስጥ ፀሎቴን መልሶልኝም ይሆናል..?ቢሆንም አሁን ይሄን
ለማሰብ ጊዜው አይደለም….እጣቴን የሽጉጡ ምላጭ ላይ አሳረፍኩና በደረቱ
አቅጣጫ አነጣጥርኩ….ተጫንኩት….ቧ ወይም ዷ የሚል የተኩስ ድምጽ
እሰማለው ብዬ ስጠብቅ ቀጭ የሚል የክሽፈት ድምጽ ሰማው …ደገምኩት
ተመሳሳይ ነው፡፡
ሰውዬው ፈገግ አለ ..ሱሬውን ከወደቀበት አነሳና መልበስ ጀመረ…ቲሸርቱንም
መልበስ ቀጠለ…ግራ ተጋባው እኔም ብቻ ሳልሆን እጆቾ የተጠፈነጉባት አፎ
የታፈነባት ፍቅሬ ትሪሲትም ግራ ማጋባቷ ከፊቷ ይታያል…..ግን የመደመሞ
ምንጭ በእኔ ይመስላል….
በእኔ መቆም በእኔ እግሮቼን በዚህ መጠን በማንቀሳቀሴ … እርግጠኛ ነኝ አፎ
መታፈኑ እንጂ እሪታዋን ታስነካው ነበር …ሰውዬው ለብሶ ጨረሰ….ወደ እኔ
ከመንቀሳቀሱ በፊት አንድ ሌላ ነገር መሞከር አለብኝ ጥቅም የሌለውን ሽጉጥ
ወዲያ አሸቀንጥሬ አጠገቤ ካላው ወንበር ላይ ጩቤውን አነሳው ……አዎ
ከተጠጋኝ ሰካበታለው..ወይንም ወርውሬ ግንባሩ ላይ ሰነቅርበታለው….››ከውጭ
የሚመጣው ደም ተንኳሎ እግሬ አጠገብ ደርሶል..እንደማጥወልወን እያደረገኝ
ነው..እራሴንም ልስት ሰከንዶች ብቻ የቀሩኝ ይመስለኛል፡፡
ሰውዬው የሆነ የተለየ ነገር እያደረገ ነው …የትርሲትን እጆች ይፈታላት ጀመር
..ምን እያደረገ ነው..?አፎ ውስጥ ጠቅጥቆት የነበረውን ጨርቅ አወጣላት… ነጻ
አደረጋት ..፡፡የእኔን ጩቤ ወድሮ እሱን ለማጥቃት መዘጋጀት ከመጤፍም
ሳይቆጥረው ወደ በራፍ በመሄድ ከፈተው..ወለል አድርጎ
….የባሰ አስገራሚ ነገር ….እናቴ በራፍ ላይ ሙሉ ጤነኛ ሆና በአድናቆት አይኖቾን
አፍጥጣ ታየችኝ …. በእጆቼ ጩቤ ወድሬ በትክክል ቀጥ ብዬ ቆሜ ስታዬኝ
እሪታዋን እያስነካችው ወደእኔ ተንደርድራ ተጠመጠመችብኝ፣‹‹…..ልጄ ያሰብኩት
ተሳካልኝ…እቅዴ ሰራልኝ›› እያለች እየሳመችኝ እያቀፈችኝ ምትሆነውን ጠፍቶታል
..ትርሲትም ከድንጋጤዋ ባትነቃም መጥታ ተቀላቅላናለች… ሶስታችንም ተቃቅፈናል
‹‹እቴቴ ምንድ ነው..?ሰዎቹስ?››ጠየቀቻት ትርሲት
‹‹አይዞሽ ምንም የሚያስጨንቅሽ ነገር የለም.?.እነሱ ስራቸውን ጨርሰው
በሰላም ሄደዋል››
‹‹የምን ስራ…?ብዙ ዕቃ ዘረፍን እንዴ..?አንቺን የጎዱሽ እኮ መስሎኝ ነበር››
‹‹አይዞሽ ..ምንም ጉዳት አላደረሱብኝም ፣ምንም አልዘፈረፉንም..አሁን ልጄ
ደክሞሀል ተቀመጥ›› ብላ ወንበሩ ላይ እንድቀመጥ አደረገችኝና ሁለቱም
ከግራና ከቀኜ ቆመው ንግግራቸውን ቀጠሉ
‹‹ትሪሲት ይሄን ቀስ ብዬ አስረዳችኋለው..ሌቦች አይደሉም ..ልጄን ለማዳን
ያደረግኩት ነገር ነው..እናም ተሳክቶልኛል..ቀጥ ብሎ መቆም ችሎል..እግሮቹን
ማንቀሳቀስ ችሏል..እኛን ለማዳን እኔ እና አንቺን ለማዳን ምንም ነገር ከማድረግ
አንደማይሰንፍ አውቅ ነበር..ተዓምር ፈጥሮም ቢሆን ሊያድነን እንደሚጥር
እገምት ነበር..እናም ትክከል ነበርኩ››አለች
የአናቴን ንግግር..የሀርሜን ዘዴ….ጥረቷንና እና ጥበቧን ሳስብ ሁሉ ነገር
ከአዕምሮዬ በላይ ሆነብኝ..በቃ ሀርሜ !!! ህይወቴ ነች..ሁለ
መላዬ…..እስከመጨረሻው ጠብታ ተስፋ ማትቆርጥብኝ….
እናቴ ..ሀርሜ -

💫💫💫 ተፈፀመ 💫💫💫

#ሀርሜ_ኮ እንዴት ነበር ? ተመቻቹ እንደተለመደው ሀሳባችሁን በ @atronosebot ግለጹልኝ..ድርሰቱ የተመቸዉ 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
👍12😱2🥰1